You are on page 1of 16

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ተጠንቶና ተገምግሞ የቀረበ የቁጥጥር ሥርዓት ሪፖርት

መግቢያ

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በመ/ቤቱ ሥጋት ያለባቸውን የሥራ ዘርፎች አስተዳደር የቁጥጥርን እና የሥራ አመራር ውጤታማነት በመገምገም እና
በማሻሻል ለመ/ቤቱ ሰፋ ያለ የሥራ ድርሻ የሚያበረክት ሲሆን የተሻሻለው የመንግስታዊ የአሰራር ዘዴ እና የሥራ ክንውን እንዲኖር ከፍተኛ ኃላፊነት
ያለበት የሥራ ክፍል ነው፡፡የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት የውስጥ ቁጥጥር የአሰራር ሥርዓት ከማረጋገጥ አንፃር፣የመንግስት መ/ቤቱ የሥራ አካል ቁጥጥርን
የሚያስፈቱት እና የሚያሳድግ መሆኑን፣ተጨባጭ የተፈፀሙ ዓላማና ግቦች መቀመጣቸው፣ያልተፈቀዱ አሰራሮችን የሚዘረዝሩ እና ተሰርተው ሲገኙ
የሚወሰደው እርምጃ የሚያብራሩ በፁሑፍ የተዘጋጁ ፖሊሲዎች (ለምሳሌ የሥነ-ምግባር ድንጋጌ መኖራቸው፣ክፍያ ለመፍቀድ የሚያስችል ተገቢው
የውክልና ስልጣን መኖሩንና የተቋሙን ተግባር ለመከታተል እና በተለይ ከፍተኛ ሥጋት ባለባቸው አካባቢዎች የንብረቶችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ
ፖሊሲዎች የአሰራር ልምዶች፣ ሥርዓቶች ፣የሪፖርት አቀራረብ ዘዴዎች ተዘጋጅተው በሥራ ላይ መዋላቸውን፣በተቋሙ ውስጥ የተዘረጉ የግንኙነት
ሥርዓቶች ለተቋሙ ሥራ አመራር በቂ እና አስተማማኝ መረጃ የሚያስገኙ መሆኑን እንዲሁም በተቋሙ ውስጥ የሚፈፀመውን የማጭበርበር ተግባር
መከላከል የሚያስችል ወጪን ከውጤት ጋር ያገናዘበ ሥርዓት እንዲዘረጋ አስተያየት የሚሰጥ የሥራ ክፍል ነው፡፡

የኦዲቱ ዓላማ፡- የመንግስት ሥራ በተደራጀ አኳኃን በሥነ-ምግባር ኢኮኖሚያዊ ውጤታማና ብቃት ባለው መንገድ ለሚከናወኑ የተጠያቂነትን ግዴታዎችን
ለማሟላት፣አግባብነት ያላቸውን ህጎችና ግዴታዎችን ተከትሎ መሥራት፣ሀብትን ከስርቆት፣አለአግባብ ከመጠቀምና ከብልሽት እንዲጠበቅ ከማድረግ
አንፃር ጥናት ተደርጎ የማሻሻያ ሀሳብ ለቢሮ አመራር ሪፖርት ለማቅረብ ነው፡፡

የኦዲት ስልት(ዘዴ)

የተወሰኑ፣ የቢሮ ከፍተኛ፣መካከለኛ እና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን ባለሙያዎች ጥያቄ በማዘጋጀት በጥያቄ ምልሽ እንዲሰጡ በማድረግ ነው፡፡

የኦዲቱ ወሰን የ 2011 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት ይሆናል፡፡

ለውስጥ ቁጥጥሩ ሥርዓት ለአመራሩና ለባለሙያዎች በመጠይቁ መሠረት የቀረበ ጥያቄና የተሰጡ ምላሾች በተመለከተ፡

1. መ/ቤቱ መንግስታዊ አወቃቀሩ ወቅታዊና በግልፅ የተቀመጠ ስዕላዊ መግለጫ አለን ? አመራሩና የሚመለከታቸው አካላት መኖሩን ያውቃሉን? ተብሎ
ለተጠያቂው ጥያቄ 6/አምስት/ አመራር የለም በማለት የመለሱ ሲሆን 5 አመራር ደግሞ አለን በማለት ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
2. በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎች ሚናና ኃላፊነት በሰነድ ተቀምጧልን ? በተጨማሪም ሁሉም እንዲያውቁት ተደርጓልን? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ 4
አመራርና አይደለም የሚል ምላሽ ሲሰጡ 6 አመራር ደግሞ አለ የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
3. ውክልና ሲሰጥ ኃላፊነትና ተጠያቂነት አብሮ ይታያልን? ይህንን በተገቢው መንገድ እንዲወጣ የሚደረግ የከትትል ሥርዓት አለን? ተብሎ ለቀረበው
ጥያቄ 7 አመራር አዎ የሚል ምላሽ ሲሰጥ 4 አመራሮች አይደለም የሚል ምልሽ ሰጥቷል፡፡
4. በሶስተኛወገን ለሚሰሩ ስራዎች/ለተደረጉ አገልግሎቶች/ ለምሳሌ የባንክ አድቫይስ፣የባንክ ማስታረቂያ፣ኢንሹራንስ፣የተለያዩ ጨረታዎች
በተመለከተ ሲሆን አገልግሎት የተሰጠበት የተደረጉ ስምምነቶች ሰነዶች በወቅቱ ስለመድረሳቸውና የሥራው ደረጃ የደረሰበት የቢሮው አመራሩ በትክክል
እንዲያውቅ ይደረጋልን? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ 7 አመራር አዎ ብሎ ሲመልስ 6 አመራር አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
5. መ/ቤቱ የሥነ-ምግባር አሰራር አለን ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ የተጠየቁ አመራሮች ሁሉም አዎ የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
6. በሥራ አመራሩ በፁሑፍ የተቀመጠ የሠራተኞች የሥነ-ምግባር ደንብ ስለመኖሩ ለቀረበው ጥያቄ 7 አመራር አዎ የሚል ምላሽ የሰጠ ሲሆን 6
አመራሮች የለም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
7. የሥራ አመራሩ የበጀት ዕቅድ ቁጥጥርን እና የተቋሙ ስጋቶችን የሚቆጣጠርበት እና ሊያግዝ የሚችል ሥርዓት ዘርግቷል፡፡ወይ ? ዕቅድና በጀት
ይጣጣማል ወይ? ተብለው ለቀረበው ጥያቄ 8 አመራር አዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን 5 አመራር አናውቅም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
8. የባለፈው ዓመት የሂሳብ መግለጫዎች በወቅቱ ለፋ/ኢ/ል/ቢሮ ቀርቧል?አስፈላጊ ማስተካከያ ያስፈልገዋል ተብሎ በተሰጠው አስተያየት መሠረት
መገለፁን አመራሩ አውቆ ክትትል የሚያደርግበት ሥርዓት አለን? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ 8 ምላሽ አዎ የሚል ሲሆን 3/ሦስት መልሶች አይደለም በሚል
ተሰጥቷል፡፡
9. መ/ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ የሂሳብ ሪፖርቶችን አሟልቷል ወይ?ለምሳሌ የወጪ፣የተሰብሳቢ፣የተከፈለ፣እና ሌሎች ቅፆች ወዘተ የተሞላ መሆኑን እና
ለአመራሩ ሪፖርት በየጊዜው እየቀረበ አውቆት የሥራ ክትትል የሚያደርግበት ሥርዓት አለን ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ 6 ምላሽ አዎ የሚል ሲሰጥ 7
ምላሽ አልቀረበም በሚል ተሰጥቷል፡፡
10. ሀ.የሰው ኃይል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ዕድገትንና ማበረታቻን /ማካካሻን/ለማስተናገድ የወጣ አሰራር ተከትሎ ለመስራት በሚያስችል አግባብ
የተለዩ አመራሮችና ባለሙያዎች

ለ. በቅጥር ወቅት ክህሎት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ሠራተኞች መመደብ የሚለውን አሰራር ተከትሎ የሚፈፀም ስለመሆኑ፡፡

ሐ. የዳሰሳ ጥናት ተደርጎ ክህሎትና ብቃት ያላቸው ሠራተኞችን የማቆየት ሥራ መሰራቱን፡፡ በሥራ አመራሩ የፀደቀ ደንብና መመሪያ አለን ተብሎ
ለቀረበው ጥያቄ 6 ምላሽ አዎ በሚል የተሰጠ ሲሆን 7 ምላሾች አይደለም በሚል ተሰጥቷል፡፡
11. ሀ. ለሁሉም ሠራተኞች የቅጥር የሥራ ውል አለን?
ለ. ለእያንዳንዱ ሥራ የሥራ ዝርዝር አለን? ተብሎ ለቀረቡ ጥያቄዎች 8 ምላሽ አዎ ሲባል 5 ምላሽ አይደለም በሚል ተሰጥቷል፡፡
12. በዕቅድ ክለሳ ወቅት ያልተሰሩ ሥራዎች ተለይተው ምክንያቱ ታውቆ እርምጃ ይወሰድባቸዋል? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ 8 ምላሽ አዎ ተብሎ
ሲሰጥ 5 ምላሽ ግን አይደለም በሚል ተሰጥቷል፡፡
13. በሥራ ክፍሎች ውስጥ በቂ በሆነ የሰው ኃይል መሟላቱንና ክፍት የሥራ ቦታ በሚኖረው ጊዜ በወቅቱ እንዲሞላ ይደረጋልን ? ተብሎ ለቀረበው
ጥያቄ 8 ሰው አዎ በሚል ምላሽ የሰጠ ሲሆን 5/አምስት/ ሰው አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
14. ባለፈው ጊዜ ኦዲተሮች እንዲገለጽላቸው የተጠየቁት መረጃዎችና ሰነዶች በሥራ አመራሩ ተአማኒ የሆኑ ምላሾች ተሰጥቷቸዋልን ?4 ሰው አዎ
የሚል መልስ የሰጠ ሲሆን 3 ሰው አይደለም በሚል ምላሽ የሰጠ ሲሆን 6/ስድስት/ አመራር ደግሞ አናውቅም በሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
15. በሥራ አመራሩ በኩል መልካም የሆነ የሥራ ግንኙነት ያለመኖሩን የሚጠቀሱ ሁኔታዎች አለን ? ካሉ በሥራ አመራሩ በኩል የተፈታበት አግባብ
አለን? ተብሎ ለተጠየቀ ጥያቄ 5 አመራር አዎ በሚል የተሰጠ ሲሆን 8 መልሶች አይደለም በሚል ተሰጥቷል፡፡
16. በስራ አመራሩ በአሰራር ላይ የሚያጋጥሙ ስጋቶች ተለይተውና ሲያጋጥሙም በመረጃ ተመዝግበው የተያዘ መመሪያ አለን ? ተብሎ ለተጠየቀው
ጥያቄ 6 አመራር አዎ በሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን 7 አይደለም በሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
17. በየጊዜው የሥጋት ዳሰሳ (Risk Assesment) መሠራቱን የሚገልፅ መረጃ አለን? ለተጠየቀው ጥያቄ ሁሉም መልስ የሰጡ አካላት አይደለም
የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
18. በስጋት ዳሰሳ/ወቅት/
ሀ. የንብረት አስ/ር
ለ. የወጪ አስተዳደር
ሐ. የሰው ሃይል አስተዳደር
መ. ማጭበርበርና
ሠ. አገልግሎት አሰጣጥ ተለይተው ታይተዋልን? ተብሎ ለቀረቡ ጥያቄዎች ሁሉም ተጠያቂዎች ምላሽ አልሰጡም፡፡
19. ሥራ አመራሩ ስለ ስጋት ግጭት አስቀምጧልን? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ሁሉም ምላሽ የሰጡ አካላት አይደለም በሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
20. ሥራ አመራሩ ለተለዩ ስጋቶች ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መከላከያ ስልት አለን? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ 4/አራት/አመራር አዎ ሲሆን
9/ዘጠኝ/አመራር አይደለም በሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
21. የአመራሩ የመረጃ ሥርዓትና ግንኙነት በተመለከተ (Ineformation system and (commicat የሥራ ኃላፊዎች ዋና ዋና በሆኑ ኦዲት በሚደረጉት
የሂሳብ አይነቶች ቁጥጥር በሰነድ የተደገፉ ህግና ደንብ እንዲሁም የተጠናከረ የተደገፉ ህግና ደንብ እንዲሁም የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት
በሚከተሉት ማለትም
ሀ. ገቢ
ለ. ወጪ
ሐ. የሠራተኛ ጥቅማጥቅምና ደመወዝ
መ. ንብረትና ሀብት
ሠ. ዕዳዎች
ሸ. ዋና ዋና አገልግሎቶች ላይ አለን? ተብለው ለተጠየቁ ጥያቄዎች መሠረት 4 ተጠያቂ አዎ በሚል ምላሽ የሠጠ ሲሆን 7 አመራር አናውቅም
በሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
22. ሀ. ሰነድ የሚያዘጋጅና ሪፖርት የሚያቀርቡ ሠራተኞች ሚናና ኃላፊነት
ለ. የሠራተኛ ሚናና ኃላፊነት በግልፅ የተለየ የሥራ ክፍፍል አለን?
ሐ. የተሳሳተ አሰራር ለማስተካከል የተቀመጠ የአሰራር ዘዴ አለን?
መ. የተጣሱ የሥራ አካሄዶችን በምን ሁኔታ እንደሚታይና ተጠያቂነታቸው ጭምር የሚያሳዩ አሰራር ተዘርግቷል ? ወይም ይህንን የሚያሰገድድ
ህግና ደንብ አለን ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ 9 ምላሽ አዎን የተባለ ሲሆን 4 አመራር አይደለም በሚል መልስ ተሰጥቷል፡፡
23. ደንብና መመሪያ በሚዘጋጅበት ጊዜ ከህግ አንፃር ያለውን ሁኔታ የሥራ ኃላፊዎች ከህግ አማካሪ መማከራቸውን ማረጋገጥ የሚችሉበት አሰራር አለን
ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ 7 አመራር አዎን የሚል ምላሽ ሲሰጥ 6 አመራር አይደለም የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
24. የመ/ቤቱ ሠራተኞች ማወቅ ያለባቸውን ደንብና መመሪያዎች እንዲያውቁ ይደረጋልን ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ? 7 አመራር አዎ የሚል ምላሽ
ሲሰጥ 6 ሰው አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
25. የደንብና መመሪያ መተላለፉን በተመለከተ ለሚወስድ የዲስፒሊን ቅጣቶች ተገቢነታቸውንና ወጥነት (ተመሳሳይነት) ሥርዓት አለን? ተብሎ
ለተጠያቂው ጥያቄ ሁሉም ተጠያቂዎች አዎን የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
26. የቁጥጥር ሥራዎችን(Control Activitis) በተመለከተ አመራሩ
ሀ. በቂ የሆነ የንብረት ጥበቃ አለን?
ለ. በእያንዳንዱ የኦዲት ኡደት እንደየሂሳብ እንቅስቃሴያቸው በተለያዩ ሰዎች መሰራታቸውን የሚያረጋግጥ፣
ሐ. ፈቃድ (ማረጋገጫ) መስጠትና ሂሳብ የማጽደቅ ተግባር፣ምዝገባና የመመዝገብ ተግባርና ንብረት የመጠበቅ ተግባር የሥራ ክፍል የተደረገበትና
ቁጥጥር በአመራር የሚደረግበት መሆኑ ተብሎ ለተጠያቂው ጥያቄ 4 አመራር አዎ የሚል ምላሽ ሲሰጥ 9 አመራር አናውቅም/አይደለም/የሚል
ምላሽ ሰጥቷል፡፡
27. የመ/ቤቱ ኃላፊዎች የውስጥ ኦዲት ክፍል ሪፖርቶችን ለክትትልና ግምገማ ይጠቀሙባቸዋል? ተብሎ ለሚቀርበው ጥያቄ 9 አመራር አዎ የሚል
ምላሽ ሲሰጡ 4 አመራር ግን አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
28. ሀ. የንብረት መዝገቡን ከንብረት ደረሰኞችና ከቢን ካርድ ጋር ማስታረቅ፣
ለ. የንበረት ቆጠራን ከምዝገባ ጋር ማስታረቅ፣
ሐ. የተለያዩ ኮምፒዩተር የምዝገባ ሥርዓቶችን /ሂደቶችን/ማስታረቅ እንዲሁም የባንክ ማስታረቂያ በየወሩ በወቅቱ መሠረታቸውን ካልተሰሩም
ችግሮችን በመለየት አሰራሩ የተስተካከለና መመሪያን የተከተለ እንዲሆን የሚሰራበት አሰራር ተዘርግቷል ? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ 5 አመራር
አዎ ተብሎ ሲሰጥ 6 አመራር ግን አይደለም (አናውቅም) የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
29. በውስጥ እና በውጪ ኦዲተር የተሰጠ ዋና ዋና የማሻሸያ ሀሳቦች በወቅቱ ተግባራዊ መደረጋቸውን/መታረማቸውን/ ክትትል የደረጋልን? ተብሎ ለቀረበ
ጥያቄ 6 አመራር አዎ ተብሎ የተመለሰ ሲሆን 7 አመራር አይደለም የሚል መልስ ተሰጥቷል፡፡
30. የሥራውን ሂደት ለማስተግበር እና ህግና ደንብ እንዲከበር የተሰጡ የማሻሸያ ሃሳቦች በአመራሩ ተለይተው ተቀምጧል? ተብለው ለተጠየቁ
ጥያቄዎች 6 አመራር አዎ የሚል ምላሽ ሲሰጡ 6 አመራር ግን አይደለም የሚል ምላሽ ተጥቷል፡፡
31. በውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቱ ከህግና ደንብ ወጪ የተሰሩ ሥራዎች ተጓዳኝ የሆኑ ማስተካከያዎች በመ/ቤቱ ኃላፊዎች ተለይተዋልን? በዚሁ
መሠረት ማሻሸያ መጥቷልን? ተብሎ ለተጠየ ጥያቄ 7 አመራር አዎ የሚል ሲሆን ነገር ግን 6 አመራር የሰጡ ሰዎች አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የቢሮው የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በአካባቢያዊ ቁጥጥር ሁኔታ(Control enviroment)፣የተቋሙ በስጋት ዳሰሳ ሂደት (Risk
Assesment)፣በመረጃ ስርዓትና ግንኙነት (Information system and communication)፣እና በክትትል (mactring) በቀረቡ ጥያቄዎችና
ከተሰጡ ምላሾች እና ጭብጦች መነሻ በማድረግ እንዲሁም አዋጆች፣ደንቦችና፣መመሪያዎች፣የአሰራር ማኑዋሎች ተከትሎ የሚከተለውን የጥናቱን
/የግምገማ/ የውሳኔ ሀሳብና አስተያየት አቅርቧል፡፡

በቃለ መጠይቅ ትኩረት የተሰጠባቸው ርዕሶች በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ሲሆኑ ይህም በፋይናንስ ቁጥጥሮች ማለትም የበጀት፣የሂሳብ ምዝገባ፣የክፍያ
ስርዓት፣የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር እና የንብረትና ግዥ አፈፃፀም ሥርዓት ሲሆን፣የሥራ አመራር ቁጥጥሮች ማለትም የተቋሙ ዕቅድ ሥራን ተቀናጅቶ
ሥራ ላይ ያሉትን አሰራሮችና አሰራሩን በብቃት ሊወጣበት እችላለሁ ብሎ መ /ቤቱ የሚሰራበትን ፖሊሲ በማጠናከር ሥራ ላይ የሚያውልበትን አሰራር
ተከትሎ በመፈፀም እንዲሁም የመ/ቤቱን ዕቅድ አፈፃፀም ተግባርና ኃላፊነትን እያንዳንዱ የሥራ ክፍል የሪፖርት ተጠሪነትና አቀራረብ ለይቶ በማወቅ
አንፃር የስልጣን ውክልና ሲሰጥ ኃላፊነትን ከተጠያቂነት አንፃር መሆኑ ለኃላፊዎችና ለሠራተኞች የሥራ ድርሻ ተለይቶ በፁሑፍ የተሰጠ ስለመሆኑ
አንዲሁም ሁሉም አካላት ከተሰጣቸው ኃላፊነት ጋር የሚመጥን ችሎታ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ቁጥጥር ተዘርግቶ እየተሰራበት ስለመሆኑ የመረጃ
ግንኙነትና በአጠቃላይ የቁጥጥር እና ክትትል ሥራ ጤናማ መሆን ያለመሆኑን ያለማ የቁጥጥር ሥርዓት ግምገማ ወይም ጥናት ሲሆን

የክልሉ መንግስት እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ ዘላቂና ተቋማዊ ለማድረግ እንዲሁም የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎችን በብቃት
ለመወጣት የሚያስችል አሁን ከተደረሰበት ደረጃ አንፃር የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት፣ሥልጠና ተግባር መወሰኛ አዋጅ በተመለከተ በ 2011 በጀት ዓመት
ቢሮው የሚኖረውን ኃላፊነትና ሥልጣን ሁሉም የሚመለከታቸው በየደረጃው የሚገኑ ኃላፊዎች ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ እንዲፈጥር እና
እንዲያውቁ ከማድረግ አንፃር ኃላፊነትን እና የሥራ ድርሻ /ዝርዝር/ እንዲያውቁ ከማድረግ አንፃር አመራሩ ይህን በተገቢው መንገድ ተደራጅቶ ምላሽ
ለመስጠት የሙከራ ቢሆንም ነገር ግን ቀላል የማይባል አመራር ደግሞ ያለማወቁን ምላሽ የሰጠ በመሆኑ በቀጣይ የሁሉም የሥራ ድርሻ ከኃላፊነትና
ተጠያቂነት አንፃር የሥራ ድርሻ ከኃላፊነትና ተጠያቂነት አንፃር ምን ሊሰራ እንደሚችል በፁሑፍ እንዲያውቅ የማድረግ ሥራ ሊሰራ የሚገባ እና ወደፊት
ይህ የማስተካከያ እርምጃም ስለመውሰድ አመራሩ ተቀናጅቶ ክትትል ሊያደርግ ይገባል የሚል አስተያየት እንሰጣለን፡፡

ከሦስተኛ ወገን ምን አይነት ማስረጃ ሊገኝ እንደሚችል ለምሳሌ የተሰብሳቢ ሂሳቦችን ዝርዝር ለባለዕዳዎች በደብዳቤ /በማስታወቂያ/ እንድያረጋግጡ
ከማድረግ አንፃር የባንክ ሂሳብ ሚዛን፣ሚዛን ከማድረግ አንፃር፣ደብዳቤዎችና የባንክና አድቫይሶች እና የባንክ ማስታረቂያ እየተዘጋጀ አመራሩ በየወሩ
ሪፖርት እንደ ሂሳብ እየገመገመ ከመሄድ አንፃር፣ ምርመራ ከሚደረግበት ኃላፊዎች መረጃና ማብራሪያ አመራሩ ጠይቆ ከሚደርሰው አስተማመኝ እና
ተአማኒ ሪፖርት መሠረት ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ ከመውሰድና ክትትል ከማድረግ አንፃር የቁጥጥር ሥርዓት ክፍተት መኖሩ ከቀረቡ ምላሾች
የተረዳን ስለሆነ በቀጣይ ከላይ በተጠቀሱ ውስንነቶች ተገቢው ግንዛቤ እንዲፈጥርና ከሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት እያገኘ አሰራሩን በየወቅቱ
እየገመገመ እንዲሄድ አስተያየት እንሰጣለን፡፡

በስራ አመራሩ በፁሑፍ የተቀመጠ የሥራተኞች የስነ-ምግባ ደንብ በተመለከተ የቢሮው አመራር የሴክተር ሠራተኞች የስነ -ምግባር የዕሴትና የእምነት
ግንባታ አፈፃፀም መመሪያ ማለትም የሴክተሩ ሠራተኞች በክልሉ ልማት የመልካም አስተዳደርናየዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ላይ የጎላ ሚና
መጫወት እንዲችሉ የተቋማዊ መልካም ስነ-ምግባር፣ዕሴትና እምነት የተነሳ አስተሳሰብ ባለቤት እንዲሆን ለምሳሌ፣

ሀ. የሴክተሩ መሠረታዊ እሴቶችና እምነቶችን በተመለከተ

 የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስተር ፖሊሲዎችና ስትራቲጅዎች የዕቅዶቻችን ማጠንጠኛዎች ከማድረግ አንፃር ሁሉም ግንዛቤ እንዲኖር
ለማድረግ አሰራር በማዘርጋት፣
 ፍትሃዊ፣አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ማለትም የሴክተሩ አመራር አካላትና ሠራተኞች ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈፃፀም ባለው ሂደት
ላይ ያለምን ልዩነትና አድሎ ሀሳባቸውን በነፃነት እያንሸራሸሩ የሚሳተፉበት አገልግሎት ተቀባዮችም ያለ ልዩነት የሚስተናገዱበትን እንዲሁም
የመ/ቤቱ ሠራተኞች ዕድገት፣ሽልማት፣ቅጣት በሥራ አፈፃፀማቸው ብቻ አየታየ ተፈፃሚ የሚሆንበት አሰራር ከመተግበር አንፃር አሁን በሴክተሩ
የተጀመሩ ተግባራት እሰይ የሚያስብል በመሆኑ የቁጥጥር ስርዓቱ ክትትል የበለጠ እንዲጠናከር ማድረግን የሚጠይቅ መሆኑ?
 ሀገራችንና ክልላችን ካሉት ሀብት ዋንኛው የሰው ሀብት በመሆኑ መንግስት ምንም ያህል ጥሩ የሚባል የልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ ቢኖረውም ያንን
ወደ ልማት መለወጥ የሚችል የሰለጠነ የሰው ኃይል ከሌላ በልማት ስኬት ማስመዝገብ አዳጋች ስለሚሆን ማንኛውም የልማት እንቅስቃሴ የሰው
ኃይል መሠረት ለማድረግ ሴክተሩ ያለውን የስልነ የሰው ኃይል ከሌላ በልማት ስኬት ማስመዝገቡ አዳጋች ስለሚሆን ማንኛውም የልማት
እንቅስቃሴየሰው ኃይል መሠረት ለማድረግ ሴክተሩ ያለውን የስልጠና የሰው ኃይል ለፈጣን ልማት ለማዋል የማስፈፀም አቅሙን በተከታታይ
ስልጠና በማብቃትና የሥራ አካባቢውን ምቹ በማድረግ ሙሉ ኃይሉን በፍቃደኝነትና በተነሳሽነት መንፈስ ለሀገሪቱ ልማት እንዲውል ከማስቻል
አንፃር የተሻሉ ተግባር እየፈፀመ የሚሄድ መሆኑን እውን ቢሆንም ከስልጠና ከሚያገኘው ዕውቀት መሰረት ሁሉም ፈጣን የሆነ ልማት ቀጣይነት
ያለው ዕድገት እንዲያስመዘግብ ከማድረግ አንፃር የቁጥጥር ሥርዓት ሊጠናከር ይገባል፣
 ሥርዓታችን የጋራ አመለካከትና ግንዛቤ ከመፍጠር መጀመር መቻል አለብን ማለትም ከላይ አመራር እስከታችኛው ሠራተኛ ድረስ ያለው የሰው
ኃይል በመ/ቤቱ ዕቅድ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ማን ምን፣ለምን፣እንዴትና መቼ መፈፀም እንዳለበት የአሰራር ስርዓት ክትትል እየተደረገ ሊጠናከር
ይገባል፣
 ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን መሆናቸውን አውቀን ከተገልጋዮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በአክብሮት ተቀብለን በአፋጣኝ በማጣራት ወቅታዊ
ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ሊበጅ የሚገባ መሆኑን፣
 ቀጠሮ ማክበርና ማስከበር ባህላችን በማድረግ አመራሩ ቀድሞ ወደ ሥራ ከመግባትና ለተገልጋዩ በተያዘለት ጊዜና በተቀመጠለት ስታንዳርድ መሠረት
ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለሚመራው ሠራተኛ መልካም አርአያ በመሆኑ ሠራተኛው ፍላጎቱን በመከተል ለተገልጋዩ ፍትሃዊ ቀልጣፋ
አገልግሎት የመስጠት ባህሉ እንዲያድግ የአሰራር ሥርዓት ሊበጁ የሚገባ መሆኑን፣
 ሥራችን አለቃችን በመሆኑ እንዲሁም የመኖራችን ዋስትና ስለሆነ የሌላ አካል ትዕዛዝ ሳንጠብቅ ኃላፊነታችንን በአግባቡ በመወጣት
የምናስመዘግበው ውጤትተጠቃሚዎች እኛው እራሳችን ስለምንሆን በየቀኑ ሥራችንን አክብረን የመስራት ባህል እንዲዳብር የአሰራር ሥርዓት
ቢበጅለት በተጨማሪም የስነ-ምግባር መርሆች እና የጋራ ሥርዓቶቻችን የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የሥነ-ምግባር ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የክልሉ
የመንግስት ሠራተኞች የስነ-ምግባር ደቡብ ውስጥ የተካተቱ 12 መርሆች አንፃር ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ፡-
1. የሥራ ሰዓት አከባበር
2. የሥራ ቦታ አለባበስ ሁሉን የሚያካትት ቢሆንም ግን የአትክልተኞች ፣የጥበቃ፣ የመልዕከተኞች፣ የፅዳት፣የቤተ መፅሐፍት፣ የመዝገቤት ቤት፣ የማባዣና
ፎቶኮፒ፣ የንብረት አስተዳደርና ግምጃቤት ሠራተኞች እንደ ሥራ ባህሪያቸው ከጨርቅ አመራረጥና ስፊት ጀምሮ የመንግስት ፋይናንስ የሲቪል
ሰርቪስ ደንብና መመሪያ ተከትሎ እንዲፈፀም የቁጥጥር ሥርዓት ቢኖር የተሻለ ነው፣
3. የባጅ አጠቃቀም የሴክተሩ ኃላፊና ሠራተኞች በስራ ሰዓት አዘወትሮ ስሙንና የስራ ኃላፊነቱን የሚገልጽ ባጅ ለተገልጋዩ በግልፅና በቀላሉ ሊታይ
በሚችል መልኩ የመጠቀም ሁኔታ የቁጥጥር ሥርዓት ቢኖር የተሻለ ነው፣
4. የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀም በንጽህና እና በጥንቃቄ መጠቀም እንዲችል የቁጥጥር ሥርዓት ቢዘረጋ፣
5. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች አጠቃቀም
6. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች አጠቃቀም
7. የቢሮ ውስጣዊ አጠቃቀም
8. የህንፃውን ደህንነትና መብት መጠበቅ በተመለከተ ሁሉም አመራርና ሠራተኞች የሚያከብሩበት የቢሮ አመራር የሴክተር ሠራተኞች የስነ -
ምግባር፣የዕሴትና የእምነት ግንባታ የአፈፃፀም መመሪያ ወጥቶ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ቢዘረጋ የተሻለ ነው የሚል አስተያየት እንሰጣለን፡፡

ከጥያቄ ቁጥር 7- 39 የተጠየቁ ጥያቄዎች የሚመሰክሩና የተያያዙ በመሆናቸው የተሰጡ ምላሾች ጥቂት አመራር የሚያውቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው
አመራር የሚያውቁ በማለት የተሰጠ ሲሆን ይህን በተመለከተ ከመመሪያዎች አንፃር ሲፈተሽ፡-

 የበላይ አመራሩና ለመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ አመራሮች ሠራተኞች በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሠረት ወቅታዊ እና አግባብ ያለው አስተማማኝ
የፋይናንስ መረጃ ትንታኔ ማዘጋጀቱንና መሰራጨቱን የሚያረጋግጥ መሆኑ
 የክፍያ ገደብን በተመለከተ በአዋጁ ላይ ከአንቀጽ 23 እስከ ቁጥር 16 በተደነገገው መሠረት ካልሆነ በስተቀር በአንድ በጀት ዓመት ውስጥ በበጀት አዋጁ
ለተመለከቱት የመንግስት መ/ቤቶች እንዲከፈል ተለይቶ ከተፈቀደው የገንዘብ መጠን በላይ ክፍያ መፈፀም የማይቻል መሆኑን የውስጥ ቁጥጥር
ሥርዓት ክትትል እንዲኖር ማድረግ፣
 በአዋጁ አንቀጽ 54 የንብረት ጥበቃና ቁጥጥር በሚመለከት የቢሮው የበላይ ኃላፊዎች፡-
1. ንብረት በሚገባ የተመዘገበና የክትትል ሥርዓ የተዘረጋለት መሆኑ፣
2. ተገቢው ጥንቃቄና እንክብካቤ የተደረገለት መሆኑን፣
3. አገልግሎት የማይሰጥ ሆኖ ሲገኝ በወቅቱ እንዲወገድ የተደረገ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኃለፊነት ያለባቸው መሆኑን በዚሁ መሠረት ስለመፈፀሙ
የቁጥጥር ሥርዓት ማድረጉን፣
 የመንግስት ገንዘብ በአግባቡ ስለመጠቀም በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የፋይናንስ ኃላፊነት መመሪያ ቁጥር 12/2005 መሠረት
ሀ. የመንግስት መ/ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች የመንግስት ገንዘብ ለፀደቀው ዓላማና በተፈቀደው መጠን ብቻ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ለማናቸውም
የተሰበሰበው ወይም ወጪ የተደረገ ገንዘብ በህግ ወይም በሌላ አኳኃን የተሰጠ ተገቢ ሥልጣን መኖሩ በማረጋገጥ ረገድ ኃላፊነት አለባቸው የሚል በመሆኑ
የተቀመጠው የቁጥጥር ሥርዓት መሠረት ሊጠናከር የሚገባ መሆኑን

 የፋይናንስ ማረጋገጫ ሪፖርት አቀራረብን በተመለከተ የሥራ አመራሩ መከተል የሚገባው የቁጥጥር ሥርዓት በተመለከተ
1. የተመዘገበው ሀብትና ዕዳ ሁሉ በእርግጥ በአሁኑ ሰዓት አለ ወይ ? የሚለውን በሪፖርቱ መሠረት ከሚመለከተው ሥራ ክፍል ቀርቦ ገምግሞ
አቅጣጫ የማስቀመጥ ህጉን ተከትሎ የመፈፀም ኃላፊነት ያለበት መሆኑን፣
2. የተመዘገቡ ገቢና ወጪ ሂሳቦች በበጀት ዓመቱ የተፈፀሙ መሆናቸውን እያንዳንዱ የሥራ ኃላፊ መጠቀሙን የማረጋገጥ ኃላፊነት የቁጥጥር
ሥርዓት መኖሩን፣
3. በበጀት ዓመቱ ሀብትና ዕዳ፣ገቢና ወጪ ሙሉ በመሉ በሂሳብ እንቅስቃሴ የተመዘገበ መሆኑን ቁጥጥር የማድረግ ኃላፊነት መኖሩን፡፡
4. የተመዘገበው ገቢና ወጪ ሂሳቦች የዋጋ ግምት በመንግስት ሂሳብ አያያዝ ፖሊሲ መሠረት በትክክል የተሰራ መሆኑን የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት
የማድረግ ተግባር ያለበት መሆኑን፣
5. በጥሬ ገንዘብ አስተዳደር መጠሪያ ቁጥር 8/2005 በገፅ 18 ተራ ቁጥር 1 መሠረት ማንኛውም የመንግስት መ/ቤት የባንክ ሂሳብ በመ/ቤቱ የበላይ
ኃላፊ ወይም እርሱ የፋይናንስ ስራ ለመንቀሳቀስ ውክልና በሚሰጠው ሰው ለመንቀሳቀስ ውክልና በሚሰጠው ሊንቀሳቀስ ይችላል በዚህ መሠረት
ውክልና የተሰጣቸው ኃላፊዎች ለባንክና ለፋ/ኢ/ል/ቢሮ መተላለፍ ያለበት መሆኑን የቁጥጥር ሥርዓት ያለበት መሆኑን ሥርዓቱን ተከትሎ
ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መውጣታቸው የክትትል ሥርዓት ሊኖር የሚገባ መሆኑ፣
6. እያንዳንዱ ሀብትና ገቢና ወጪ በትክክል የተመደበ መሆኑን የቁጥጥር ሥርዓት ክትትል የማድረግ ሁኔታ የተጠናከረ ስለመሆኑ፣
 የፋይናንስ ሪፖርት መግለጫዎች አቀራረቡ በአግባቡ ስለመሆኑ ለምሳሌ፡-
 ህጎች ደንቦች መመሪያዎች መከበራቸውን ፣
 ለወጣው ወጪ ተገቢው አገልግሎት ተሰጥቷል ወይም ዕቃዎች ገቢ ማድረግ ኃላፊዎች የማረጋገጥ ስርዓት ያለበት መሆኑን፣
 ወጪው የተፈቀደው ከተፈቀደው በጀት መሆኑን ወጪው የተፈቀደው በወጡት ደንቦች መመሪያዎች ህጎች መሆኑን የሚያረጋግጥ
ኃላፊነት ያለበት መሆኑን፣
 ወጪው ከተፈቀደው በጀት በላይ ያለመሆኑን ሥራውን ከሚሰራው ሥራ ሂደት (ዳይሬክቶሬት) ታአማኒነት ያለው የፋይናንስ መግለጫና
ሪፖርት ቀርቦ በሁሉም አመራር ተገምግሞ ማስተካከያ ካለ እንዲታረም የማድረግ የቁጥጥር ሥርዓት መኖሩን ማረጋገጥ የሚያስፈልግ
መሆኑን፣
 የቢሮው አመራሮች በፋይናንስ አስተዳደሩ የተዘረጉ የውስጥ ሥርዓቶች

ሀ. በእጅ የሚገኙና በባንክ ያለ ጥሬ ገንዘብ አስተዳደሩ፣

ለ. ለጥቃቅን ወጪ የሚያዝ የገንዘብ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት፣

ሐ. የተሰብሳቢ ሂሳብ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት፣

መ. የተከፋይ ሂሳብ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት፣

ሠ. የገቢ ሂሳብ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት፣

ረ. የወጪ/ክፍያ/ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት

ሸ. የግዥና ክፍያ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት፣

ቀ. በግንባታ ውል መሠረት በየጊዜው የሚፈፀም ክፍያ ካለ የክፍያ ቁጥጥር ሥርዓት፣

በ. የተሸከርካሪ ጥገና ክፍያ /ወጪ/ ቁጥጥር ሥርዓት፣

ተ. የደመወዝ ክፍያ ቁጥጥር ሥርዓት፣

ቸ. የስልጠና (የስብሰባ አበልና ትራንስፖርት ክፍየያ ቁጥጥር ሥርዓት፣

 የበጀት ቁጥጥር ሥርዓት፣


 የንብረት ቁጥጥር ሥርዓት፣ የንብረት ገቢ፣ወጪ፣ምዝገባ፤አቀማመጥና ጥበቃ የንብረት ቆጠራ፣ የቋሚ ንብረት ማስወገድ የቁጥጥር ሥርዓቶች
የተዘረጉ ስለሆነ አመራሩ የተዘረጉ የቁጥጥር ሥርዓቶች ቢያንስ በየሩብ ዓመቱ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት በሚቀርቡ
ሪፖርቶች መነሻ መሠረት አቅጣጫ እያስቀመጡ መሄድ የሚገባ መሆኑን፣
 በውጪና በውስጥ ኦዲት ወቅት በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር አፈፃፀም ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ ዋና ዋና ግኝቶች ከለፈው የኦዲት ውጤት መነሻ
ለማንሳት ያህል
1. የጥሬ ገንዘብና ባንክ በተመለከተ
 ገንዘብ ያዥ አልፎ አልፎ በካዝና መቆጣጠሪያ መዝገብ ገቢ፣ወጪ፣ከወጪ ቀሪ እንዲመዘገብ ያለማድረግ፣
 በየጊዜው የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ በማድረግ ከተያዘው የመዝገብ ከወጪ ቀሪ ጋር እንዲመሳከር አለማድረግ፣
 አንዳንድ ጊዜ የባንክ ሂሳብ ሌጀር አለመያዝና በየወሩ በባንክ ከሚላከው ጋር የሂሳብ መግለጫ አለማስታረቅ፣

የተሰብሳቢ ሂሳብ በተመለከተ

 የሥራ ማስኬጃ የሰነድ ሂሳብ በመመሪያ መሰረት እንዲወራረድ ያለማድረግ፣


 የሰነድ ሂሳብ ያለባቸው ሠራተኞች ሲለቁ ወይም ሲዘዋወሩ ሂሳባቸውን ሳያወራርዱ ክሪላንስ መስጠት
 በርካታ ዓመታት ያስቆጠሩ የሰነድ ሂሳብ እንዲሰበሰብ ወይም እንዲሰረዝ አለማድረግ
 ከተከፋይ ሂሳብ ያልተቀነሰ የቅድሚያ ገቢ ግብር የሚገኝ መሆኑን፣

የሂሳብ አያያዝና አመዘጋገብ በተመለከተ

 የገቢ ደረሰን የተቆጠረለት ሂሳብ አለመመዝገብ፣


 የገቢና የወጪ ማስረጃዎች ከያዙት ገንዘብ መጠን በላይ እና በታች መመዝገብ፣
 የገቢና ወጪ ሂሳብ በድጋሚ መመዝገብ እና በሌጀር ላይ የተመለከተውን በትክክል አለመመዝገብና ከሌጀር ሪፖርት በትክክል ያለመውሰድ፣
 የገቢና የወጪ ሂሳቦችን በትክክለኛ የሂሳብ ስርዓት ያለመመዝገብ፣
 ማስረጃ የቀረበለት የገቢና ወጪ ሂሳብ ያለመመዝገብ፣
 ማስረጃ ሳይቀርብ የወጪ ሂሳብ ማመሳከሪያ ማዘጋጀትና መመዝገብ፣
 ማስረጃ ለቀረበለት የወጪ ሂሳብ የወጪ ሂሳብ አለመመዝገብ፣

የወጪ ሂሳብ በተመለከተ

 በዋጋ ማቅረቢያ መፈፀም የሚገባው ግዥ ያለውድድር ግዥ መፈፀም፣


 በሚመለከተው ኃላፊ ሳይፈቀድ፣ክፍያ መፈፀም፣ወጪውን የሚያጸድቀው ኃላፊም መረጃዎቹ የተሟላ መሆኑን አለማረጋገጥ፣
 መስክ ሳይወጣ የውሎ አበል ክፍያ መፈፀም፣
 ለአንድ ጊዜ የመስክ ስራ ከተለያዩ ቦታዎች ውሎ አበል ክፍያ መፈፀም፣
 የጥራት ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቀ/ንብረት ገዝቶ ገቢ ማድረግ፣

የተሰብሳቢ ሂሳብ በተመለከተ

 በአጠቃላይ የሂሳብ ሌጀር ካርድ የሚታይ የተሰብሳቢ ሂሳብ ሚዛን ከማን እንደሚፈለግ የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ ያለማዘጋጀት ተቀፅላ የሂሳብ
ሌጀር በተሟላ ሁኔታ አለመያዝ ተአማኝነት ያለው ሪፖርት ለአመራሩ ለውሳኔ አለማቅረብ፣

የተከፋይ ሂሳብን በተመለከተ

 በአጠቃላይ የሂሳብ ሌጀር ካርድ የሚታይ የተከፈለ ሂሳብ ሚዛን ለማን እንደሚከፈል የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ የተከፋይ ሂሳብ ሌጀር
አለመያዝ የተሟላ ሪፖርት ለአመራሩ ለውሳኔ አለማቅረብ፣

የበጀት አስተዳደር በተመለከተ

 ክፍያ ከተፈቀደ በጀት በላይ እንዳይሆን ለመቆጣጠር የሚያስችል የባጀት ሌጀር ካርድ በመቋቋም በጀትን አለመቆጣጠር፣
 በሂሳብ መደቡ ከተፈቀደው በጀት በላይ መጠቀም፣

የንብረት አያያዝና አስተዳደር በተመለከተ

 በንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ ንብረት ለቆጠራ አመቺ በሆነ መልኩ በዓይነትና በአገልግሎታቸው ላይቶ ያለማስቀመጥ፣
 የዓመታዊ የቋሚና አላቂ ዕቃዎች ቆጠራ ተደርጎ ከመዝገብ ከወጪ ቀሪ ጋር አለማስታረቅ፣
 ለቋሚ ዕቃዎች የመለያ ቁጥር አለመስጠት፣

የዋና ዋና ግኝቶች መንስኤ ናቸው ተብለው የተጠኑ

 የፈፃሚዎች ዕውቀትና ክህሎት ማነስ፣የክህሎት ማሻሻያ ሥልጣናዎችን የተሰጡ ቢሆንም ችግር ሊፈቱ በሚችሉ አግባብ አለመሰጠት፣የተሰጡ
የክህሎት ማሻሻያ አፈፃፀምን በማሻሻል ረገድ ያስገኙትን ፋይዳ በአመራሩ አለመገምገም፡፡
 በኃላፊዎች ዘንድ በመንግስት ተቀርፀው የተዘረጉትን የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቶች ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በሚያዙት መሰረት
ለመፈፀም የሚያስችል በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣
 በመንግስት የወጡ ህጎች፣ደንቦችና መመሪያዎች ሆነ ብሎ መጣስ እና ድርጊቱ በሚፈፅሙት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀልጣፋና
አስተማሪ ያለመሆን፣

በጥናቱ መሠረት ለመፍትሔ ይሆናሉ ተብሎ የቀረቡ የመፍትሔ ሃሳቦች በተመለከተ

1. በመንግስት የተዘረጋው የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ህጎች ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም በቢሮ አመራር የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተቀመጡ
የማሻሻያ አቅጣጫዎች በኃላፊዎች በሠራተኞች እንዲታወቁና ሥራ ላይም ማዋሉን ማረጋገጥና በየጊዜው ወቅታዊ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
የሚያስፈልግ መሆኑን
2. አሁን ተገምግሞና ተጠንቶ በቀረበው የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት መሠረት በቀረቡ ጥያቄዎችና ምላሾችን መነሻ በማድረግ የውስጥ ቁጥጥር
ባልተዘረጋባቸው አፈፃፀሞች በአመራሩ የውስጥ ቁጥጥር የመዘርጋት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን፣
3. የውስጥ ኦዲተሮችና ሠራተኞች ለሚመደቡበት ሥራ ተመጣጣኝ ሥልጣና እንዲያገኙና ለሥራው ተገቢ የሆኑ ህግና መመሪያዎችን
እንዲያውቁና የሥነ-ምግባር ደንብ አክብረው እንዲሰሩ ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑን፣
4. ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለተመደቡበት ሥራ ኃላፊነት ዝርዝር የሥራ ተግባር በፁሑፍ እንዲያውቁ ማድረግ ሪፖርት ማን ለማን እንዴት መቼ
እንደሚቀርብ እንዲያውቁ ማድረግ፣
 አመራሩ በኦዲት ሥራ የተገኙና ሪፖርት የተደረጉ ግድፈቶች ላይ ወቅታዊ እርምጃ መውሰድ፣ ለህግ ማቅረብ ያለባቸውን ለህግ
ማቅረብ፣ማስተካከያ ሊደረጉ የሚገባቸውን ተስተካክለው ለወደፊቱ ተመሳሳይ ስህተቶችን /ግድፈቶችን/እንዳይከሰቱ መከላከልና የተሰጡ
ማሻሻያ ሀሳቦችን በትክክል ተግባራዊ ማድረግ፣
 የሚሰሩ ሥራዎች ህግን መሠረት ያደረጉ በእቅድ የሚመሩና የመ/ቤቱን ዓላማ ለማሳካት በሚረዱ መልኩ ማከናወን፤የሂሳብ ሰነዶች የአፈፃፀም
መረጃዎች አደራጅቶ መያዝ፣ለኦዲት ሥራ በሚፈለጉበት ጊዜ ማቅረብ፣ ለኦዲት ግኝቶች በቂ ማብራሪያ ወይም ሰነድ ማቅረብ የሚያስችል
የቁጥጥር ሥርዓትና ክትትል በአመራሩ የቁጥጥር ሥርዓት ክትልል መደረግ ያለበት መሆኑን፣
 የቁጥጥር ሥርዓት ግምገማ ወይም ጥናት ለማድረግ ዋና ዋና ጉዳዮች ወደ 39 ጥያቄ ያካተተ ዝርዝር የያዘ 66 ጥያቄዎችን የያዘ ቃለ መጠይቅ
ለቢሮ ም/ኃላፊዎችና በስራቸው ለሚገኙ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በቀረበው መሠረት በሰንጠረዡ በተገለጸው መሠረት ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

ተ. በዋና ዋና ጉዳዮች በዋና ዋና ጉዳዮች በዋና ዋና ተግባራት ሥር በቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት ምላሽ የሰጡ የዘርፉ
ቁ ከተጠየቀው 39 ከተጠየቀው 39 በዝርዝር በተጠየቁ 66 /ኤጀንሲ/ጽ/ቤት ዳይሬክቶሬት ስም ዝርዝር
ጥያቄ ውስጥ አዎ ጥያቄ ጥያቄዎች መሠረት
በማለት ምላሽ አይደለም/የለም/ መረጃ እንደሌላቸው
የሰጡ ብለው ምላሽ እንደማያውቁ ምላሽ
የሠጡ የሰጡ
1 12 2 52 ዕቅድ በጀት ዝ/ክ/ግ/ዳይሬክቶሬት
2 27 12 10 የመሬት ልማት ኤጀንሲ
3 35 4 12 ከመሬት ልማት ኤጀንሲ ከአንዱ ዳይሬክቶሬት
4 17 22 31 ከቤቶች ልማት አስ/ር ኤጀንሲ
5 20 19 38 ከቤቶች ልማት ዳይሬክቶሬት
6 26 13 28 ፕላን ኢንስቲትዩት
7 17 22 42 ከፕላን ኢንስቲትዩት ከአንድ ዳይሬክቶሬት
8 27 12 16 ከግ/ፈ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት
9 16 23 42 ከሰው ሀብት ልማት አስ/ር ዳሬክቶሬት
10 26 13 26 ከቢሮ ጽ/ቤት
11 26 13 26 ከአስ/ፋይ/ዘርፍ
12 25 14 32 ከማስፈጸም አቅ/ግ/የአካ/ልማት ዘርፍ
13 19 20 21 የህብተረሰብ ተሳ/ አካ/ ልማት ዳዳዳይረክቶሬት
ማሳሰቢያ
ከጥያቄ ምላሽ እንደተገነዘብነው የዘርፉ፣የኤጀንሲ፣የኢንስቲትዩት ኃላፊዎች ከሥራቸው ካሉ ኃላፊዎችና ከሌሎች
ቢሮ ስራ አመራር ጋር በቅንጅት ከመስራት አንፃር ክፍተት መኖሩን እንዲሁም ህግ፣ደንብና መመሪያን አውቆ
የቁጥጥር ሥርዓት ክትትል ከማድረግ አንፃር ያሉት ክፍተቶች በርካታ ስለሆነ በቀጣይ በጥያቄ የተጠቀሱ ጉዳዮች
ሙሉ በሙሉ ሁሉም አመራር፣የቢሮው ሠራተኞች በግልፅ አውቀው እና ተረድተው የሴክተሩን ዓላማ፣ግቦች እና
እሴቶች ላይ የላቃ ውጤት እንዲመጣ ይደረጋል የሚል እምነት ይኖረናል፡፡
 በመጨረሻም መንግስት በየዓመቱ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚመደበው በጀት ሕግ፣ደንብና
መመሪያን ተከትሎ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋል ስለሚገባው በተለይም በአሁኑ ወቅት መንግስት ያወጣውን
የዕድገትና ትራንፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ከላይ የተመለከቱ ችግሮች በመፍታት በመፍትሔ ዙሪያ በተሰጡ
የውሳኔ አስተያየቶች መሰረት እንዲተገበር እያልን በመጨረሻም ይህን ግምገማ /ጥናት/ እንዲሳካ ያደረጉ
የሥራ ኃላፊዎችን ለማመስገን እንወዳለን፡፡

“ከሠላምታ ጋር”

ኦዲተሮች

1. ሙሴ ፎንጣ
2. እምነት ተሻለ

15
16

You might also like