You are on page 1of 13

ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?

ZïC KLL mNGST db#B nU¶T Uz@È


DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTHERN NATIONS,
NATIONALITIES AND PEOPLE’S REGIONAL STATE

›mT q$_R bdb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLልE Year No


መንግሥት Mክር b@T ጠባቂነት የወጣ
Hêœ mUb!T 01 qN ፪¹!፯ ›.M Hawassa /2015
ዋጅ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ደንብ ቁጥር
124 /2007

መግቢያ
የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ተደራሽነት የሚያረጋግጥ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት
በማስፈለጉ፣

በክልሉ መንግስት የበጀት ዋስትና የአፈር ማዳበሪያ በግዥ ቀርቦ ለተጠቃሚዎች እጅ በእጅ ክፍያ እና በብድር የሚሰራጭ
በመሆኑ የማዳበሪያ አያያዝና አጠባበቅ፣ የሽያጭ ገንዘብ አሰባሰብና የብድር አመላለስ በተወሰነ ህጋዊ አካል በባለቤትነትና
ተጠያቂነት በሚያሰፍን አግባብ ማከናወን በማስፈለጉ፣

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና
ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፴፫/፪፻፻፫ አንቀጽ ፵፬ ንዑስ አንቀጽ ፩ በተሰጠው
ስልጣን መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1. አጭር ርዕስ

1
ይህ ደንብ “የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት
ደንብ ቁጥር 124/2007 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጓሜ የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ መሠረት፡-

1) “ክልል” ማለት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ነው፤

2) “ግብርና ቢሮ” TKƒ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የግብርና ቢሮ እና
በተዋረድ የሚገኝ የግብርና ሴክተር መዋቅር ነው፤

3) “ግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ” ማለት በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት
ግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ እና በተዋረድ የሚገኝ የግብይትና ኅብረት ሥራ ሴክተር መዋቅር ነው፤

4) “ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ” በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት
በተዋረድ የሚገኝ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሴክተር መዋቅር ነው፤

5) “ፋይናንስ ተቋም” ማለት የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ነው፤

6) “ባንክ” ማለት በክልሉ መንግስት የበጀት ዋስትና ለማዳበሪያ መግዣ የሚሆን ገንዘብ አበዳሪ የሆነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፤

7) “ዞን” ማለት በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የተዋቀረ የዞን የአስተዳደር እርከን ነው፤

8) “ወረዳ ወይም ልዩ ወረዳ አስተዳደር” ማለት እንደቅደምተከተሉ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና


ሕዝቦች ክልል የተዋቀረ የወረዳ ወይም ልዩ ወረዳ አስተዳደር እርከን ነው፡፡

9) “ቀበሌ” ማለት በገጠር ወረዳ ወይም በከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ ዝቅተኛው የአስተዳደር
መዋቅር ነው፡፡

10) “ልማት ቡድን” ማለት በገጠር ቀበሌ አስተዳደር ስር የሚገኝ የግብርና ኤክስቴንሽን አደረጃጀት ነው፤

11) “ፌደሬሽን” ማለት የደቡብ ክልል የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌደሬሽን ነው፤

12) “ዩኒየን” ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት ህብረት የተቋቋመ
የህግ ሰውነት ያለው ተቋም ነው፤

2
13) “መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር” ማለት በአባላት ነጻ ፍላጎት የተቋቋመ የህግ ሰውነት ያለው ማህበር
ነው፤

14) “ኤጀንት” ማለት በቀበሌ ደረጃ የቁጠባና ብድር አገልግሎት የሚሰጥ የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም
ተቀጣሪ ሰራተኛ ነው፤

15) “ተበዳሪ” ማለት የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ
ተቋም ብድር የተመቻቸለት ተበዳሪ አርሶ አደር ነው፤

16) “ማዳበሪያ” ማለት ለተክሎች ለምግብነት አስፈላጊ የሆነ ንጥረ-ነገር የያዘ ሰው ሰራሽ ቁስ ሲሆን
ድብልቅን፣ አካላዊ ድብልቅንና ወደ አንኳርነት የተለወጠ የማዳበሪያ ድብልቅን ይጨምራል፤

17) “የብድር ዋስትና” ማለት ተበዳሪ ከፋይናንስ ተቋም ለሚወስደው ብድር ለዋስትና የሚቀርብ መያዣ
ነው፤

18) “የቡድን ዋስትና” ማለት የአፈር ማዳበሪያ በብድር ለመውሰድ የተፈቀደላቸው አርሶ አደሮች
በማይከፋፈል ሃላፊነት የአንድነት እና የነጠላ ዋስትና ለፋይናንስ ተቋሙ የሚገቡበት አሰራር ነው፤

19) “ወለድ” ማለት በውል ስምምነት መሰረት ለአበዳሪ ባንክ ወይም ለፋይናንስ ተቋሙ በዓመት ወይም
በቆይታ ጊዜ በመቶኛ ተሰልቶ የሚከፈል ገንዘብ ነው፤

20) “የአገልግሎት ክፍያ” ማለት የፋይናንስ ተቋም፣ ዩኒየኖች፣ ፌደሬሽን እና መሠረታዊ ኅብረት ሥራ
ማህበራት በማዳበሪያ አያያዝና አጠባበቅ፣ ስርጭት፣ ሽያጭና ብድር አመላለስ ላይ በውል ስምምነት
መሠረት ለሰጡት አገልግሎት ተሰልቶ የሚከፈል ክፍያ ነው፤

21) “ኩፖን” ማለት በፋይናንስ ተቋሙ የሚዘጋጅ ሆኖ አርሶ አደሩ ወይም ተጠቃሚው በከፈለው ወይም
በተበደረው ገንዘብ ልክ የአፈር ማዳበሪያ መጠን ተጽፎበት የሚሰጠው የማዳበሪያ መረከቢያ ሰነድ
ነው፤

22) “ምክረ-ሀሳብ” ማለት አንድ አርሶ አደር ባለው ማሳ መጠቀም የሚገባውን የግብአት ዓይነትና መጠን
በባለሙያ ተሰልቶ የሚሰጥ ሙያዊ አስተያየት ነው፤

23) “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤

24) የፆታ አገላለጽ በዚህ ደንብ ውስጥ በወንድ የተገለፀው አነጋገር ለሴትም ያገለግላል፡፡

4. የተፈጻሚነት ወሰን

3
ይህ ደንብ በክልሉ አስተዳደር ወሰን ስር በሚተዳደሩ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች፣ ወረዳዎችና የከተማ
አስተዳደሮች ውስጥ በሚኖሩ የአፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት
የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ ስርጭትና ብድር አመላለስ ሥርዓት

5. የአፈር ማዳበሪያ ዕቅድ ስለማዘጋጀት


1) በየደረጃው የሚገኝ የግብርና ልማት መዋቅር በምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ በተጠቃሚ
ብዛት፣ በመሬት መጠን፣ በሰብል ዓይነት በኃላፊነት በመለየት በየደረጃው በሚገኝ የአስተዳደር ምክር ቤት
ያስወስናል፣
2) የክልል ግብርና ቢሮ የፀደቀ የዘመኑን የአፈር ማዳበሪያ በመጠንና በዓይነት፤ በዞን፣ በወረዳ፣ በልዩ ወረዳ እና
በከተማ አስተዳደር ለይቶ ለግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ ያስተላልፋል፣

6. የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት አሰራር


1) በታቀደው የዘመኑ የአፈር ማዳበሪያ መጠንና አይነት ላይ በመመስረት የግዢና ስርጭት ዋጋ በማጥናት
የብድር ፍላጎት በዞን፣ በወረዳ፣ በልዩ ወረዳ፣ በከተማ አስተዳደር ይዘጋጃል፣ በመስተዳደር ምክር ቤት
ይወሰናል፣
2) በየደረጃው የሚገኝ የአስተዳደር ምክር ቤት የምርት ዘመኑን የማዳበሪያ ዕቅድና የብድር መጠን በዓመቱ
መጀመሪያ ለምክር ቤት አቅርቦ ይፀድቃል፣
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት የጸደቀ የማዳበሪያ መግዣ የገንዘብ ብድር በበጀት ዋስትና
እንዲፈጸም ለክልል ምክር ቤት ቀርቦ እንዲጸድቅ ይደረጋል፡
4) የዞንና የልዩ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ለጸደቀ የማዳበረያ መጠን
መግዣ የሚሆን ብደር የበጀት ዋስትና ስምምነት ለክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ይሰጣሉ፣
5) በክልል መስተዳድር ምክር ቤት በኩል የብድር ጥያቄ ለአበዳሪው ባንክ እና የበጀት ዋስትና ለገንዘብና
የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ይቀርባል፣
6) በክልል መስተዳደር ም/ቤት ውክልና የተሰጣቸው አካላት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት
ለተፈቀደ ብድር ከአበዳሪ ባንኩ ጋር የብድር ውል ስምምነት ይፈጽማሉ ፤
7) በምርት ዘመኑ ለክልሉ የሚያስፈልግ የአፈር ማዳበሪያን ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር በመወያየት
ከውጭ ወይም ከአገር ውስጥ በግዢ ለሚያቀርብ አካል ውክልና ይሰጣል፣ ከአበዳሪ ባንኩ ጋርም
የሦስትዮሽ ውል ይፈፀማል፣
8) ከውጭ ወይም ከአገር ውስጥ ተገዝቶ የሚቀርብ ማዳበሪያ ተረክቦ ለስርጭት ጣቢያ የማጓጓዙን ሥራ
በኃላፊነት የሚሠሩ የህብረት ሥራ ማህበራት በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች ወይም በከተማ አስተዳደር
ውክልና እንዲሰጥ ይደረጋል፣ የሁለትዮሽ የውል ስምምነት ይፈፀማል፤

4
9) መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት በወረዳዎች ወይም ከተማ አስተዳደር ውክልና መሠረት የሁለትዮሽ
ውል ስምምነት ይፈጽማሉ፣ ማዳበሪያ ተረክበው እንዲያሰራጩ ይደረጋል፣
10) ከማዕከላዊ መጋዘን ወደ ስርጭት ጣቢያ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶች በመንግሥት የግዢ ደንብና
መመሪያ መሠረት በህብረት ሥራ ማህበራት ተሳትፎ በውድድር ይመረጣሉ፣ ውል ይገባል፣ የስምሪት
ትዕዛዝ ይሰጣል፣
11) ከውጭ አገር ወይም ከአገር ውስጥ ውክልና በተሰጠው አካል በግዢ የሚቀርብ ማዳበሪያ በክልሉ
ማዕከላዊ መጋዘኖች የተወከሉ የህብረት ሥራ ማህበራት ይረከባሉ፣ ለተለዩ የስርጭት ጣቢያዎች ያጓጉዛሉ፣
7. የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ ስሌትና የስርጭት አሰራር
1) የአፈር ማዳበሪያ የመሸጫ ዋጋ የሚሰላው የማዳበሪያ መግዣ ዋጋ፣ የአገር ውስጥ የትራንስፖርት፣ የባንክ
ወለድና ኢንሹራንስ፣ የአገልግሎት ክፍያና ተዛማጅ ወጪዎችን በማስላት በያንዳንዱ የሽያጭ ጣቢያ
ይሆናል፣
2) የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ወይም ለተጠቃሚው የሚሰራጨው በሚከተለው የሽያጭ አማራጭ
ይሆናል፡፡
ሀ. የአፈር ማዳበሪያ እጅ በእጅ ክፍያ ተጠቃሚዎች በምክረ-ሀሳቡ መሠረት በማሳቸው መጠንና
በሰብሉ ዓይነት ተሰልቶ የሚያስፈልጋቸውን ማዳበሪያ ሙሉ ክፍያ በመፈፀም እንዲወስዱ
ይደረጋል፡፡
ለ. የአፈር ማዳበሪያ እጅ በእጅ ግዢ ለመፈፀም አቅም የሚያንሳቸው አርሶ አደሮች በአንድ
ለአምስት አደረጃጀታቸውና በልማት ቡድናቸው ተለይተው በምክረሀሳቡ መሠረት በማሳቸው
መጠንና በሰብሉ ዓይነት ተሰልቶ ቅድመክፍያ ከፍለውና የቡድን ዋስትና አሟልተው
እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡
3) የአፈር ማዳበሪያ የእጅ በእጅ ሽያጭ፣ የቅድመ ክፍያና የብድር ተመላሽ ገንዘብ የሚሰበሰበው
በፋይናንስ ተቋሙ ለዚሁ ተግባር በታተመ ህጋዊ ደረሰኝና በሥሩ በሚገኙ ባለሙያዎች ብቻ
ይሆናል፡፡
4) የአፈር ማዳበሪያ እጅ በእጅ ሽያጭም ሆነ በቅድመክፍያና በብድር ሽያጭ የሚከናወነው
በፋይናንስ ተቋሙ ለዚሁ ተግባር ተብሎ በተዘጋጀው ደረሰኝና ኩፖን ብቻ ሆኖ በተጻፈበት
ገንዘብ ልክ የሚመጣጠን ማዳበሪያ ከመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት ይወሰድበታል፡፡
5) በብድር ተጠቃሚ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የቡድን ዋስትና የገቡ የአንድ ለአምስት ወይም
የልማት ቡድን አባላት በውል ስምምነታቸው መሠረት ለሰጡት ዋስትና በቡድንና በግል
ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
6) በፋይናንስ ተቋሙ በብድር የተሰራጨ የማዳበሪያ ገንዘብ በውሉ መሠረት በወቅቱ ተሰብስቦ
ለባንክ ገቢ ይደረጋል፤ የተሰራጨውን ብድር በወቅቱ ካልተመለሰ በውል ስምምነቱ መሰረት

5
በህግ አግባብ የማስመለሱ ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ የባንክ ወለድን በማካተት ከፋይናንስ
ተቋሙ ሂሳብ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡

8. የማዳበሪያ ተጠቃሚ ወይም ገዢ መብት


1) ማንኛውም የማዳበሪያ ተጠቃሚ ለከፈለው ገንዘብ ለዚሁ ተግባር የታተመ ደረሰኝ የማግኘት፣
2) የአፈር ማዳበሪያ ክፍያውን ወይም የተፈቀደለትን ብድር ስምምነት በፈጸመ ቢበዛ በሁለት ቀናት ውስጥ
ማዳበሪያውን የማግኘት፣
3) ስለማዳበሪያው ወይም ሽያጭ ዋጋና የብድር አመላላስ መረጃዎችን የማግኘት፣
4) ስለማዳበሪያው ወይም ሽያጭ ዋጋና የብድር አመላላስ መረጃዎችን የማግኘት፣
9. የማዳበሪያ ተጠቃሚዎችና ዋስትና ሰጪዎች ግዴታዎች

1) በምርት ዘመኑ የሚያለማውን መሬት በግብርና ባለሙያ ወይም በቀበሌው በሰለጠኑ ቀያሾች
በሚታወቅ መለኪያ በማስለካት የሚያስፈልገውን የማዳበሪያ መጠን ብቻ የማሳወቅ፣
2) የብድር ተጠቃሚ ከሆነ፡-
ሀ) የፋይናንስ ተቋሙ የሚጠይቀውን የቡድን ዋስትና ወይም የንብረት ዋስትና የማቅረብ፣
ለ) የልማት ቡድኗ የወሰነችውን የቅድመ ክፍያ የመክፈል፣
ሐ) የወሰደውን ማዳበሪያ ለሌላ ወገን አሳልፎ ያለመስጠት፤
መ) የወሰደውን የማዳበሪያ ገንዘብ በውል ስምምነቱ መሠረት በወቅቱ የመክፈል፤
3) የተበደረውን ብድር በውሉ መሠረት ባይከፍል ዋስትና የወሰደው ቡድን ዕዳውን ይከፍላል፤
4) ዋስትና የወሰደው ቡድን ዕዳውን ከፍሎ አግባብ ባለው ህግ በመጠየቅ ከነወለዱና ቅጣቱ
የማስከፈል፣
10. የአፈር ማዳበሪያ በብድር ለሚወስዱ የብድር መጠን አወሳሰን

1) የልማት ቡድኑ የምርት ዘመኑን ከሰብል ልማት ዕቅዱ መነሻ ማዳበሪያ እጅ በእጅ የመግዛት አቅም
የሌላቸውን አርሶ አደሮች ይለያል፣
2) የግብርና ባለሙያው የብድር ጠያቂውን አርሶ አደር ማሳ በመለካት ከሚያለማው ሰብል
ዓይነት በምክረሀሳቡ መሠረት የሚያስፈልገውን የማዳበሪያ መጠን በኃላፊነት ወስኖ
ለልማት ቡድኗ ያቀርባል፤
3) ማዳበሪያ በብድር እንዲወስድ የተፈቀደለት አርሶ አደር የሚከፍለውን የቅድመክፍያ መጠን በልማት
ቡድን የሚወሰን ሆኖ መጠኑም ከጠቅላላ ዋጋ ከ 25 በመቶ ማነስ የለበትም፡፡ ሆኖም በተለየ የሰው ሰራሽ
እና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የሚወሰን ውሳኔ በሚያስፈልግበት ጊዜ ጥያቄው ለወረዳ
አስተዳደር ቀርቦ ይወሰናል፡፡

6
4) የአፈር ማዳበሪያ በብድር ለሚወስድ አርሶ አደር የቡድን ዋስትና የሚወስዱ የልማት ቡድኗ
አባል አርሶ አደሮች ብዛት ተበዳሪውን ጨምሮ ከ 3 እስከ 5 ሊሆኑ ይገባል፤
5) የልማት ቡድኑ በዘመኑ ዕቅድ ላይ ተመስርቶ እጅ በእጅ የሚገዙትንና የተበዳሪዎችን ስም ዝርዝር፣
የማዳበሪያና የቅድመ-ክፍያ መጠን ውሳኔ ለቀበሌ አስተዳደር ያስተላልፋል፤ የቀበሌ አስተዳደርም
መርምሮ በማጽደቅ ለቀበሌው የኦሞ ኤጀንት እና ለወረዳ አስተዳደር ያስተላልፋል፣

ክፍል ሶስት

የአስፈጻሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

11. በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች


1) የምርት ዘመኑን የማዳበሪያ ዕቅድና የብድር መጠን ማጽደቅ፣
2) የማዳበሪያ ብድር አመላለስ መገምገም፣ ድጋፍ ማድረግ፣
12. በየደረጃው የሚገኝ የአስተዳደር ምክር ቤት
1) የምርት ዘመኑን የማዳበሪያ ዕቅድና የብድር መጠን መወሰን፣
2) ለማዳበሪያ ግዢና ተዛማጅ ወጪዎች የሚውል የባንክ ብድር በበጀት ዋስትና ይሰጣል፣
3) የማዳበሪያ አጠቃቀሙንና የብድር አመላለሱን መከታተልና መገምገም፣
4) የቀበሌ አስተዳደር ከልማት ቡድን የተበዳሪ አርሶ አደር ዝርዝር፣ የማዳበሪያ መጠንና ዓይነት፣ የቅድመ ክፍያ
መጠን፣ የብድር መጠን ተቀብሎ የመወሰን፣ ውሳኔውን ለፋይናንስ ተቋሙ ከዘር ጊዜ ቢያንስ ከአንድ
ወር በፊት ማስተላለፍ፣
5) የቀበሌ አስተዳደሩ በቀበሌው መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ከሌለ የማህበሩን ተግባርና ኃላፊነት
ይወጣል፣

13. በየደረጃው የሚገኝ የግብርና ቢሮ መዋቅር


1) በዓመቱ የሚያስፈልግ የማዳበሪያ መጠን በዓይነት ለይቶ ማቀድ፣
2) የማዳበሪያ አቅርቦትና አጠቃቀም ይከታተላል፣ ያለአግባብ የሚያድር ማዳበሪያ ካለ ኃላፊነት
ይወስዳል፣
3) የማዳበሪያ ጥራት መቆጣጠር፣ አያያዝና ዝውውርን መከታተል፣
4) ፈጻሚና የባለድርሻ አካላትን ያስተባብራል፣ ያቀናጃል፣ ይደግፋል፣
14. በየደረጃው የሚገኝ የግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ መዋቅር
1) በቀረበ የማዳበሪያ ፍላጎት መረጃ መሰረት የብድር ጥያቄ ማዘጋጀት፣ በመስተዳድር ምክር ቤት
ማስወሰን፣

7
2) ከአበዳሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተፈቀደው ብድር አጠቃቀምና አመላለስን በተመለ l ከተ
ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር በመሆን የሦስትዮሽ ውል ይፈጽማል፣ ያስፈጽማል፣
3) በውጭ አገር ወይም በአገር ውስጥ ለሚፈፀም የማዳበሪያ ግዢ ውክልና ይሰጣል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣
4) ማዳበሪያ ተረክቦ የሚያሰራጭ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር፣ ዩኒየን፣ ፌደሬሽን ወይም
መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር በሌለበት የቀበሌ አስተዳደር በመለየት፣ መወሰን፣ ማስወሰን፣
5) ከወደብ የሚቀርብ ማዳበሪያ የሚራገፍባቸው ማዕከላዊ መጋዘኖችና የማሰራጫ ጣቢያዎች በመለየት
እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
6) ከማዕከላዊ መጋዘን ወደማሰራጫ ጣቢያዎች ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ ማውጣትና ስርጭት
መምራት፣
7) የማዳበሪያ መሸጫ ዋጋ እና የአገልግሎት ክፍያዎችን መወሰን፣ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ፣
8) በየምርት ዘመኑ የማዳበሪያ ዕዳ ማስገቢያ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ያዛል፣ ለፋይናንስ ተቋሙና
ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ፣ የባንክ መረጃ የሚከታተል ባለሙያ የመወከል፤
9) ለማዳበሪያ ግዢ፣ የአገር ውስጥ ማጓጓዣ፣ የአገልግሎትና ሌሎች ተዛማጅ ክፍያዎችን መፈፀም፣
10) የማዕከላዊ መጋዘንና የስርጭት ጣቢያ መጋዘን የማዳበሪያ ወቅታዊ ሚዛን መከታተልና ዓመታዊ ቆጠራ
ማካሄድ፣
11) የማዳበሪያ ብድር አመላለስ መከታተል፣ ሪፖርት በየደረጃው ለሚገኝ የአስተዳደር መዋቅር ማቅረብ፣
12) ማዳበሪያ መረከቢያና ማሰራጫ ደረሰኞችን ማሳተም፣
15. በየደረጃው የሚገኝ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ መዋቅር
1) በዓመቱ ለአፈር ማዳበሪያና ለምርጥ ዘር ግዢና ተዛማጅ ወጪዎች የሚያስፈልግ ብድር ሲፈቀድ ከግብይትና
ኅብረት ሥራ ቢሮና ከአበዳሪው ባንክ ጋር የሦስትዮሽ ውል መፈጸም፣
2) ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በምርት ዘመኑ ለሚቀርብላቸው ማዳበሪያ የበጀት ዋስትና ስምምነት እንዲሰጡ
ያደርጋል፣
3) በሚደረግ ስምምነት መሰረት የግብይትና ህብረት ስራ ቢሮን የብድር አጠቃቀም፣ የግዢና ክፍያ ሚዛን፣
የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋምን የማዳበሪያ ሽያጭና የባንክ ብድር አመላለስ፣ የህብረት ሥራ
ማህበራትን የማዳበሪያ ገቢና ስርጭት ሚዛን በወረዳ፣ በዞንና በክልል በየወቅቱ ኢንስፔክሽንና
በየዓመቱ ኦዲት ያደርጋል፤ በየደረጃው ለሚገኝ የአስተዳደር ም/ቤት የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
16. በየደረጃው የሚገኝ የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም
1) ተጠቃሚዎች ለሚከፍሉት ገንዘብ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀ ደረሰኝና ማዳበሪያ መረከቢያ ኩፖን
ማዘጋጀት፣
2) የማዳበሪያ ሽያጭ ለማከናወንና ገንዘቡን ለባንክ በወቅቱ ገቢ ለማድረግ የሦስትዮሽ ውል ከግብይትና
ህብረት ሥራ ቢሮ፣ ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር ይዋዋላል፡፡

8
3) ከቀበሌ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በሚቀርብ የአፈር ማዳበሪያ ተበዳሪዎች ስም ዝርዝር፣
የማዳበሪያ መጠንና ዓይነት፣ የቅድመ ክፍያና የብድር መጠን መሰረት እንደአስፈላጊነቱ
ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ቅድመክፍያ በመቀበል የብድር ውል ስምምነት ይፈጽማል፡፡
4) ከተጠቃሚዎች ለተከፈለ የማዳበሪያ ክፍያ ወይም በውል ስምምነት መሠረት ለተፈፀመ ብድር፡-

ሀ. እጅ በእጅ ለሚሸጥ ማዳበሪያ አርሶ አደሩ ለከፈለው ገንዘብ ደረሰኝ እና ማዳበሪያ መረከቢያ ኩፖን በኤጀንቱ
አማካይነት ይሰጣል፡፡

ለ. የብድር ሽያጭ ሲሆን አርሶ አደሩ ለከፈለው ቅድመክፍያ ገንዘብ ደረሰኝና በብድር ስምምነቱ እና
በተከፈለው ቅድመክፍያ ገንዘብ ልክ ማዳበሪያ መረከቢያ ኩፖን በኤጀንቱ
አማካይነት ይሰጣል፡፡

5) እጅ በእጅ ከተሸጠና በቅድመክፍያ የተሰበሰበ ገንዘብ በአስር ቀናት ውስጥ በወረዳው ስም በተከፈተ
የዘመኑ የማዳበሪያ ዕዳ ማስገቢያ የባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ ኮፒ ለወረዳ
ግብይትና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ያቀርባል፤
6) በብድር ከተሰራጨ ማዳበሪያ ገንዘብ ከአርሶ አደሩ በተሰበሰበ በአስር ቀናት ውስጥ ከላይ በተገለፀው
አግባብ ለባንክ ገቢ ይደረጋል፤
7) በፋይናንስ ተቋሙ የተሰበሰበ የሽያጭ ገንዘብ በወቅቱ ባንክ ባይደርስ እንዲሁም ከአርሶ አደሩ ብድር
ባለማስመለስ በውል በተጠቀሰው ጊዜ ለባንክ ያልተመለሰ ገንዘብን ከነወለዱ የመክፈል
ኃላፊነት አለበት፡፡ ዕዳውን ከተበዳሪ አርሶ አደሮች በዋስትናው መሠረት እንዲመለስለት
ያደርጋል፣
8) በየወሩ የማዳበሪያ ሽያጭና የገንዘብ አመላለስ ሪፖርት በየደረጃው ለሚገኝ የግብይትና ኅብረት ሥራ
ተቋም ያቀርባል፤
9) የገቢና ወጪ ሂሳቡን ለብቻ በማደራጀት በተፈለገ ጊዜ ያስመረምራል፣
10) ከወረዳ ግብይትና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ማዳበሪያ
የተሰራጨበትን ኩፖን ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ለመሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራት
የአገልግሎት ወጪ ይከፍላል የራሱንም ቀንሶ ያስቀራል፤
11) የብድር መመለሻ ወቅት ከመድረሱ በፊትና አርሶ አደሩ ገቢ የሚያገኝበትን ወቅት ለይቶ
ከቀበሌና ከልማት ቡድን አመራሮች ጋር ስለብድር አመላለስ የግንዛቤ ማዳበሪያ ሥራ ይሰራል
ወቅቱ ሲደርስም ብድሩን ያስመልሳል፤
12) አርሶ አደሮች በፋይናንስ ተቋሙ ለግብርና ግብዓት መግዣ የሚሆን የቁጠባ ባህል እንዲዳብር
የማበረታቻ ስልት ቀይሶ ይንቀሳቀሳል፣ ያበረታታል፣
17. የኅብረት ሥራ ዩኒየኖች ወይም ፌደሬሽን

9
1) በዞን ወይም በልዩ ወረዳ ውክልና መሠረት የአፈር ማዳበሪያ ለመረከብና ለማጓጓዝ
ከግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ ጋር ውል ይገባል፣
2) በማዕከላዊ ቦታዎች ደረጃውን የጠበቀ የማዳበሪያ መጋዘን ማዘጋጀት፣ መረከብ፣ ወደ
ስርጭት ጣቢያዎች ማጓጓዝ፣
3) የግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ በሚያወጣው የትራንስፖርት ጨረታ ይሳተፋል፣ ከአሸናፊው
የትራንስፖርት ድርጅት ጋር ውል በመዋዋል ስምሪት ይሰጣል፣
4) ማዳበሪያውን ለመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት በግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ በታተመ
ህጋዊ ሰነድ እንዲረከቡ በማድረግ ለተሰጠ የትራንስፖርት አገልግሎትና ተዛማጅ ወጪዎች
በውል ስምምነት ታሪፍ መሠረት ክፍያ ይቀበላል፣ ይፈጽማል፣
5) ከውጭ አገር የገባ ወይም የተረከቡትን ወደ ሽያጭ ጣቢያ የተጓጓዘ ማዳበሪያ ሚዛን
በጣቢያ፣ በወረዳ እና በዞን በማደራጀት ለግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ በየሣምንቱ ሪፖርት
ያቀርባል፣
18. የመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት
1) በወረዳ ወይም ልዩ ወረዳ አስተዳደር በሚሰጠው ውክልና መሰረት ውክልና ለተሰጠባቸው
ቀበሌያት የሚሆን ማዳበሪያ ስለመረከብ፣ ስለመጠበቅ፣ ስለስርጭትና የአገልግሎት ክፍያ
አስመልክቶ ከወረዳ ወይም ልዩ ወረዳ ግብይትና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ጋር ውል
መግባት፣
2) የአፈር ማዳበሪያ ለማከማቸት ደረጃውን የሚያሟላ መጋዘን ያዘጋጃል፣ የሚቀርብ ማዳበሪያን
በግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ ለማዳበሪያ አገልግሎት ብቻ በታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ተረክቦ
ጥበቃ ያደርጋል፣ በሚቀርብ ኩፖን መሰረትም ማሰራጨት፣
3) የማዳበሪያ መጋዘን በማንኛውም የሥራ ሠዓት ለተጠቃሚው ክፍት ሆኖ አገልግሎት እንዲሰጥ
ያደርጋል ፣
4) በተረከበው ማዳበሪያ መጠን በውል ስምምነቱ በተገለፀው መሠረት ተሰልቶ በየ 3 ወሩ ወይም
እንደአስፈላጊነቱ ባነሰ ጊዜ ከግብይትና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት እንዲታዘዝ በማድረግ የአገልግሎት ክፍያ
ይቀበላል፣
5) ከፋይናንስ ተቋም በተላከ ኩፖን መሰረት የተሰራጨ ማዳበሪያ ለማገናዘብ የአርሶ አደሮችን
ስም ዝርዝር፣ የኩፖን ቁጥር እና የማዳበሪያ መጠን እንዲሁም የቀሪ ማዳበሪያ ሚዛን የያዘ
መረጃ በየሣምንቱ ለወረዳው ግብይትና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤትና ለፋይናንስ ተቋሙ
ማቅረብ፣

ክፍል አራት
የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭትን የሚመራ አስተባባሪ ኮሚቴ

10
19. መቋቋም
ተጠሪነቱ በየደረጃው ለሚገኝ አስተዳደር ወይም መስተዳደር ምክር ቤት የሆነ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ ስርጭት፣
ሽያጭና ብድር አመላለስ ተግባርን የሚከታተልና የሚመራ አስተባባሪ ኮሚቴ (ከዚህ በኋላ “አስተባባሪ
ኮሚቴ” እየተባለ የሚጠራ) ከክልል እስከ ቀበሌ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል፡፡
20. የቀበሌ አስተባባሪ ኮሚቴ
1) የቀበሌ አስተዳዳሪ---------------------------------------------------------------ሰብሳቢ
2) የቀበሌ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ--------------------------------------------ፀሐፊ
3) የቀበሌ ሥራ አስኪያጅ------------------------------------------------------------አባል
4) የህብረት ሥራ ልማት ባለሙያ ባለበት---------------------------------------አባል
5) የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኤጀንት---------------------------------------አባል
6) የቀበሌ ሴቶች ጉዳይ ተወካይ--------------------------------------------------------አባል
21. የወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴ
1) የወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ---------------------------------------- ሰብሳቢ
2) የወረዳ ግብይትና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ-------------------------ፀሐፊ
3) የወረዳ የህብረት ሥራ ልማት ሥራ ሂደት አስተባባሪ ------------------አባል
4) የወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ --------------------አባል
5) የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ-------------------------------------------------አባል
6) የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ----አባል
7) በወረዳ ማዕከል ላይ የሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ------------------------------------------አባል
22. የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ
1) የግብርና መምሪያ ኃላፊ---------------------------------------------------------- ሰብሳቢ
2) የግብይትና ኅብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ------------------------------------------ፀሐፊ
3) የህብረት ሥራ ልማት ሥራ ሂደት አስተባባሪ--------------------------------- አባል
4) የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ--------------------------------------አባል
5) የዞን ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ---------------------------------------------------------አባል
6) የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ----------------አባል
7) ለዞኑ ማዳበሪያ የሚያቀርብ ዩኒየን ወይም ፌደሬሽን ሥራ አስኪያጅ----------አባል
23. የክልል አስተባባሪ ኮሚቴ
1) የግብርና ቢሮ ኃላፊ-------------------------------------------------------------ሰብሳቢ
2) የግብይትና ኅብረት ሥራ ቢሮ ኃላፊ---------------------------------------ምክትል ሰብሳቢ

11
3) የኅብረት ሥራ ልማት ሥራ ሂደት ባለቤት-----------------------------------ፀሐፊ
4) የግብርና ግብአት አቅርቦት ዋና ስራ ሂደት ባለቤት ………………….. አባል
5) የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ---------------------------------------አባል
6) የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ-------------------------አባል
7) የርዕሰ መስተዳድሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዋና አማካሪ ------------------------አባል
8) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃዋሳ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ-------------------አባል
9) የደቡብ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌደሬሽን ሥራ አስኪያጅ----------------- አባል

24. የአስተባባሪ ኮሚቴዎች የወል ተግባርና ሀላፊነት


1) በዚህ ደንብ መሰረት የተቋቋሙ አስተባባሪ ኮሚቴዎች የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ ስርጭት፣ ሽያጭና
ብድር አመላለስ ተግባርን በበላይነት ይከታተላል፤ ይመራል፣ ይደግፋል፡፡
2) የአፈጻጸም ሪፖርት በየደረጃው ለሚገኝ አስተዳደር ም/ቤት ሪፖርት በየወሩ ያቀርባል፡፡
3) የአፈር ማዳበሪያ ገንዘብ ለአበዳሪ ባንክ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡
4) የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ ስርጭት፣ ሽያጭና ብድር አመላለስ ተግባር አፈጻጸምን ይከታተለል፣
የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
25. የኮሚቴው የስብሰባ ጊዜና የውሣኔ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት
1) የኮሚቴው የመደበኛ ስብሰባ ጊዜ በወር አንድ ጊዜ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ አስቸኳይ ስብሰባዎችን
በሰብሳቢው ወይም በፀሐፊው አማካይነት ሊጠራ ይችላል፣
2) ከኮሚቴው አባላት መካከል ሁለት ሶስተኛው በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልአተ-ጉባኤ ይሆናል፡፡
3) የኮሚቴው ውሣኔ በድምጽ ብልጫ ይፀድቃል፡፡ ሆኖም ድምጹ እኩል ከሆነ ሰብሳቢው የሚደግፈው የውሳኔ
ሀሳብ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

ክፍል አምስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

26. የመተባበር ግዴታ


ማናቸውም ሰው ደንቡ በተሟላ መልኩ እንዲተገበር አስፈላጊውን ድጋፍ የመስጠትና የመተባበር
ግዴታ አለበት፡፡
27. የወንጀል ተጠያቂነት
በዚህ ደንብ የተሸፈኑ ጉዳዮች ተጥሰው ሲገኙ አጥፊው እንደጥፋቱ ዓይነት አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡
28. ተፈጻሚነት የሌላቸው ህጎች

12
ይህንን ደንብ የሚቃረን ማንኛውም ደንብና መመሪያ ወይም የአሠራር ልምድ በዚህ ደንብ የተሸፈኑ
ጉዳዮችን በሚመለከት ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
29. መመሪያ የማውጣት ሥልጣን
በዚህ ደንብ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ ስርጭትና ብድር አመላለሰን በተመለከተ ተግባርና ኃላፊነት
የተሰጧቸው የክልል አስፈጻሚ አካላት በተናጠል የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት ለማስፈፀም
የሚረዱ መመሪያዎችን ሊያወጡ ይችላሉ፡፡
30. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ ደንብ ከፀደቀበት ከዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ደሴ ዳልኬ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት
ፕሬዝዳንት
ሀዋሳ

13

You might also like