Professional Documents
Culture Documents
መሥሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
በዌብ ሳይት የሚጫኑ ይዘቶች ዝግጅት፣ስጭትና ክትትል ደረጃን በጠበቀ መልኩ የሚከናወንበት ሁኔታን ያጣናል፣
ከተለያዩ አገሮችና ድርጅቶች ተሞክሮዎችን ይቀምራል፣ አሠራሮችን ያጠናል፣ አዳዲስ ሃሳቦችን የሚያካትት ረቂቅ
መመሪያ ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተው ያቀርባል፤
የአገሪቱን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና የልማት ዕንቅስቃሴዎች በበጎ ጎኑ ከሚመለከቱና ከሚደግፉ የተለያዩ ድህረ-ገጾች ጋር
ግንኙነት ይፈጥራል፣ በአገራዊ አጀንዳ ዙሪያ ያሰባስባል፣ ከተቋሙ ዌብ-ሳይት ጋር ያስተሳስራል፣
በተቋሙ ዌብ-ሳይት በሚጫኑ ይዘቶች ዙሪያ መልእክቶችን እንዲደግፉና እንዲጋሩ /Like, Share, Subscribe
እንዲያደርጉ/ ደጋፊዎችን ይጋብዛል፣ በመልእክቶቹ ዙሪያ ያከራክራል፣
የተቋሙን ዌብ-ሳይት ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ዌብ-ሳይቶት ጋር ያስተሳስራል፣ መረጃዎችን መለዋወጥ
የሚቻልበትን ሁኔታን አጥንቶ ለውሳኔ ያቀርባል
የተቋሙ የውስጥ ተገልጋዮች በተቋሙ ውስጥ በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በኢንተራኔት/interanet/ መረጃ
የሚለዋወጡበትን ሁኔታ አጥንቶ ለውሳኔ ያቀርባል፣ ስፈቀድም ሙያዊ ሥራን ያከናውናል፣
የፌዴራል፣ የክልልና የተቋሙን ሃላፊዎችና፣ ኮሙዩኒኬተሮችና ሠራተኞች የድህረገጽ ስልጠና ፍለጎት ዳሰሳ ጥናት
ያደርጋል፣
የቡድኑ እቅድ ሲዘጋጅ ግብዓት ይሰጣል፣ ከቡድኑ ዕቅድ በመነሳት የስራ ዕቅዱን አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ በዕቅዱ
መሠረት ሥራዎችን ያከናውናል፣
በየወቅቱ ስለ ስራው ክንውን ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ያቀርባል።
ውጤት 2፡ የዌብ-ሳይት ይዘቶችን በማዘጋጀት ማሰራጨት ፤
የመንግሥት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ ዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮችን፣ የመንግሥት ተቋማት እቅድ
አፈጻጸሞችን፣ ሀገራዊና ከሀገራችን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ
ለሀገራዊ የጋራ መግባባትና ገጽታ ግንባታ የሚሆኑ ይዘቶችን/መልእክቶችን/ ጽሁፎችን፣ ምስሎችን፣ቪዲዮዎችን፣
የመሳሰሉትን/ ያዘጋጃል፣ የአርትኦት ሥራ ይሰራል፣ በተቋሙ ዌብ-ሳይት ይጭናል፣
ከሌሎች ባለድርሻ አካላት/ከተለያዩ ፌዴራልና ክልል ተቋማትና ግለሰቦች/ ተዘጋጅተው የሚደርሱትን ይዘቶች ከሀገሪቱ
ፖሊሲዎች፣ ስትራተጂዎች፣የአፈጻጸም መመሪያዎችና ሌሎች ህጎች አንፃር የተቃኙ መሆናቸውን አረጋግጦ
በተቋሙ ዌብ-ሳይት ይጭናል፣ መስተካከል የሚገባቸው ይዘቶችን ለይቶ ያቀርባል፣
አከራካሪ የሆኑ፣ ጥንቃቄ የሚሹና በህግ የሚያስጠይቁ ጉዳዮችን የያዙ መረጃዎችን ለይቶ ለቅርብ ኃላፊ ያቀርባል፣ ማስተካከያ
ሲደረግባቸው በተቋሙ ዌብ-ሳይት ይጭናል፣
ከአገራችን ጋር ተያያዥነት ያላቸው አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁነቶች፣ ኮንፍረንሶችና መግለጫዎች ሲኖሩ
ይዘቶችን በተለያየ አግባብ ሳቢና የጥራት ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ያዘጋጃል፣ የአርትኦት ሥራ ይሰራል፣ በተቋሙ
ዌብ-ሳይት ላይ ይጭናል፣
በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የፌዴራል መንግስትና የክልል መስተዳድሮች ፖሊሲዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና
መመሪያዎች ወዘተ ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው የዌብሳይት ሰታንዳርድን መሠረት በማድረግ ይዘቶችን
ያዘጋጃል፣ የአርኦት ሥራ ይሰራል፣ በተቋሙ ዌብ-ሳይት ላይ ይጭናል፣
በፌዴራልና ክልል የመንግሥት ተቋማት ዌብሳይቶች የሚጫኑ መረጃዎችን ከሀገራዊ ፈይዳ አኳያ በመቃኘት
አሻሽሎ በተቋሙ ዌብ-ሳይት ይጭናል፣
የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች የሚያደርጋቸውን የሥራ እንቅስቃሴዎች /ጉብኝቶች፣ መግለጫዎችና ማብራሪያዎች
እንዲሁም በተቋማዊ፣ አገራዊ፣ አከባቢያዊ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጓቸው ውይይቶችና
ስምምነቶች፣ የመሣሰሉት/ ዙሪያ በቅርበት በመከታተል መልዕክቶችን ለዌብ-ሳይት በሚመጥን መልኩ በተለያየ
አግባብ/ዜና፣ ፊውቸር አርትክል፣ በዶክመንትሪ፣ በፎቶና በመሳሰሉ/ ያዘጋጃል፣ የአርትኦት ሥራ ይሰራል በተቋሙ
ዌብ-ሳይት ይጭናል፣
ውጤት 3፡- የዌብ-ሳይት ይዘቶችን መከታተልና መተንተን
በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ድረ-ገጾች የሚጫኑ መረጃዎችን ይዘት የመንግስት አቋምንና አቅጣጫን
የሚያንጸባርቁና ለአገር ገጽታ ግንባታና አገራዊ የጋራ መግባባት ከሚኖራቸውን ፋይዳ አንጻር ያላቸውን ጠቀሜታ
ለዌብ-ሳይት በሚመጥን መልኩ ተዘጋጅተው መጫናቸውን ይከታተላል፣ ይተነትናል፣ ክትትልና ድጋፍ
ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እንዲሁም አገራዊ ፋይዳ ያላቸውና ለተቋሙ ዌብ-ሳይት ግብዓት የሚሆኑ
መረጃዎችን ይለያል፣ ለሚመለከተው ያቀርባል፣
አገራችን አስመልክቶ በተለያዩ ዌብ-ሳይቶች የሚሰራጩ መረጃዎችን ከአገራችን ነባራዊና ተጨባጭ ሁኔታ
አገናዝቦ ይከታተላል፣ ይዘታቸውን ይተነትናል፣ ፈጣን አጸፋዊ ምላሽ /በጽሑፍ፣ በፎቶና በቪዲዮ/ ያዘጋጃል፣
ይጭናል፣ በሌሎች ምላሽ ልሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ይለያል፣ ለቅርብ ኃላፊ ያቀርባል፣ በአዎንታዊነት
የሚወሰዱትን ለይቶ በግብዓትነት ይጠቀማል፣
በመስሪያ ቤቱ ድረ-ገጽ የሚጫኑ መልዕክቶች ዙሪያ የሚሰነዘሩ አስተያየቶችን/ግብረመልሶችን/ ይከታተተላል፣
ይዘታቸውን ይተነትናል፣ ይገመግማል፣ ምላሽ ለሚያሻቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ፈጣን አጸፋዊ ምላሽ ይሰጣል፣
ሌሎች ምላሽ እንዲሰጡበት የሚገቡ ጉዳዮችን ለይቶ ለቅርብ ኃላፊ ያቀርባል፣ አዎንታዊነት የሚወሰዱትን
በግብዓትነት ይጠቀማል፣
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
3.1. የሥራ ውስብስብነት
ሥራው የዌብ-ሳይት ተሞክሮዎችን የመቀመር፣ ረቂቅ የአሰራር ስርዓት መመሪያ የማዘጋጀት፣ ለሀገራዊ የጋራ
መግባባትና ገጽታ ግንባታ የሚሆኑ መልእክቶችን በተለያዩ አግባቦች የማዘጋጀት፣ የአርትኦት ሥራን የመስራት፣
አገራዊና ከአገራችን ጋር ተያያዥነት ያላቸው አለም አቀፋዊ ሁነቶችን መሠረት በማድረግ መልእክቶችን
በተለያየ አግባብ አጭር፣ ግልጽ፣ ሳቢና የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ አድርጎ የማዘጋጀትን፣ የዌብ-ሳይት ይዘትን
የመከታተልና የመተንተን፣ የዌብ-ሳይት ግንኙነቶችን የማጠናከር ተግባራትን ማከናወን ነው።
በሥራ ክንውን ወቅት ተሞክሮ ለመቀመርና ረቂቅ የአሰራር ሥርዓት መመሪያ ለማዘጋጀት ዌብ-ሳይት በአገራች
ተጨባጭ ሁኔታ ገና ያልተስፋፋ መሆኑ፣ ዌብ-ሳይት በባህሪው አለም አቀፋዊ ይዘት ያለው መሆኑ፣ በስራው ሂደት
የቴክኖሎጂ ተለዋዋጭ መሆን የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲሆኑ ችግሮችን ለመፍታት በዌብ-ሳይት አጠቃቀም
ተሞክሮ ካላቸው ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶችና ካደጉት ሃገሮች ስልጠናዎችን መውሰድና ልምዶችን በመቅሰም፣
በአዳዲስ ቴክኖሎጂ በመታገዝ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመምረጥ የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድ እና
የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ትንተና በማድረግ ችግሮቹን መፍታትን ይጠይቃል፡፡
3.2. ራስን ችሎ መስራት
ሥራው ሀገር አቀፍ የድረ-ገጽ/ ፖርታል/ ፖሊሲና የአፈጻጸም መመሪያን መሠረት በማድረግ ይከናወናል፡፡
3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
ሥራው ውጤትን ከማምጣት አንጻር ከስራው ልዩ ባህሪይ ጋር ተያይዞ ለሚዲያ ክትትል ሥራ ፈጣን ምላሽ
ከመስጠት አኳያ እንደ አስፈላጊነቱ ተከታታይ የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፣ በቅርብ ኃላፊው በመጨረሻ አጠቃላይ
ግምገማ ይደረግበታል፡፣
3.3.ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /
ሥራው የዌብ-ሳይት ተሞክሮዎችን የመቀመር፣ ረቂቅ የአሰራር ስርዓት መመሪያ የማዘጋጀት፣ ለሀገራዊ የጋራ
መግባባትና ገጽታ ግንባታ የሚሆኑ መልእክቶችን በተለያዩ አግባቦች የማዘጋጀት፣ የአርትኦት ሥራን የመስራት፣
አገራዊና ከአገራችን ጋር ተያያዥነት ያለቸው አለም አቀፋዊ ሁነቶችን መሰረት በማድረግ መልእክቶችን በተለያየ
አግባብ አጭር፣ ግልጽ፣ ሳቢና የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ አድርጎ የማዘጋጀትን፣ የዌብ-ሳይት ይዘትን የመከታተልና
የመተንተን፣ የዌብ-ሳይት ግንኙነቶችን የማጠናከር ተግባራትን በሚጠበቀው የጥራት ደረጃ እና በአግባቡ ባይከናወን
ወይም በስራ ክንውን ወቅት የሚከሰቱ ችግሮች በወቅቱ ባይታረሙ ተቋሙ ለሌሎች ተገልጋዮች የሚሰጠውን
አገልግሎት ያስተጓጉላል፣ ተቋሙ ከተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ያለውን ግንኙነት
ያሻክራል፣ በጎ ገጽታ ግንባታ ውጤታማ እንዳይሆን ምክንያት ይሆናል። በአጠቃላይ የዌብ-ሳይት ስራን
በማስተጓጎል በዳሬክቶሬቱ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።