You are on page 1of 4

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የመረጃ ሥራ አመራር ባለሙያ I የመረጃ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ


VIII 01 16 01

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 ለተቋሙ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በመሰብሰብ ለቀጣይ ሥራ ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡
2.2. የሥራ መደቡ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡ መረጃዎችን ማሰባሰብና ማደራጀት፣
 መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ መረጃ የሚሰበሰብባቸውን ጉዳዮች(Variables) እና አመልካቾችን (Indicators) ይለያል፣
ለሚመለከተው ይሰጣል፣
 መረጃዎችን ከተለያዩ የሥራ ዘርፎችና ተጠሪ ተቋማት ይሰበስባል፣
 የተሰበሰቡ መረጃዎች በቅጹ መሰረት ስለመሞላታቸው ያመሳክራል፣
 በተቋሙ የተለያዩ ዘርፎች ላይ ተፅዕኖ ሊያስርፉ የሚችሉ መረጃዎቸን ለውሳኔ በሚረዳ መልኩ ያደራጃል፤
 የተቋሙን ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላትን የሚመለከት ኘሮፋይሎችን በማሰባሰብ ያደራጃል፣ ወቅታዊ
ያደረጋል፤
 መረጃዎችን ወደ መረጃ ቋት ኮድ በማድረግ ያስገባል፣
 የተደራጁ፣የተጠናቀሩ፣ የተተነተኑ የንግድ መረጃዎች እና ሪፖርቶች ለተጠቃሚ በወቅቱ ያደረሳል፣
 ዓመታዊ የስታትሰቲክስ መጽሄቶች፣ በራሪ ጽሁፎች፤ ኒውስ ሌተሮች፤ ብሮሹሮች፤ያሰራጫል፤
 ሌሎች ከተቋሙ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሰነዶች ያሰራጫል፤
 መረጃ በማሰባሰብ ሂደት ከሚያጋጥሙ ችግሮችን መነሻ በማድረግ መረጃ ለማሰባሰብ የተዘጋጁ ቅጾችን
ያሻሽላል፣
 ከመረጃ አሰባሰብ እስከ ጥንቅር ያሉትን ተግባራት ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር ለማድረግ እንዲሁም ለሚፈጠሩ
ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት በሚደረጉ ጥናቶች ላይ ይሣተፋል፣

1
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 የሥራ ክንውን ሪፖርት ያቀርባል፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች፤


3.1. የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች መሰብሰብን፣ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ መረጃ የሚሰበሰብባቸውን ጉዳዮች
(Variables) እና አመልካቾችን (Indicators) መለየት፣ በተቋሙ የተለያዩ ዘርፎች ላይ ተፅዕኖ ሊያስርፉ የሚችሉ
መረጃዎቸን ለውሳኔ በሚረዳ መልኩ ማደራጀት፣ መረጃዎችን ወደ መረጃ ቋት ኮድ በማድረግ ማስገባት የሚጠይቅ
ሲሆን በሥራው ክንውን ወቅት መረጃዎቹ የሚመጡበት ቅጽ አለመመሳሰልና የመረጃ ምንጮች የሥራ ባህሪ መቀያየር፣ መረጃዎች
በሚፈለገው አይነት፣ ጥራትና ጊዜ ያለማግኘት፣ መረጃዎች በየጊዜው መለዋወጥ፣ የመረጃ ተጠቃሚዎች ፍላጎት በየጊዜው መቀያየር
የሚያጋጥሙ ችግሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ቅጾቹ ተሻሽለው እንዲዘጋጁ ለሚመለከተው አካል በማመላከትና መፍትሄዎችን
በማፈላለግ፣ መረጃዎቹን ተከታትሎ በማሰባሰብ ወቅታዊ በማድረግ፣ መረጃዎን ለሚደሰጡ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
በመስጠት ይፈታሉ፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው ከቅርብ ኃላፊው በሚሰጠው ዝርዝር መመሪያ መሰረት ይከናወናል፡፡
3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው በተሠጠው ዝርዝር መመሪያ መሠረት ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊው ክትትልና ድጋፍ ይደረግበታል፡፡
3.3. ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት
 ሥራው መረጃዎቹን መሰብሰብ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ተግባር በአግባቡ ባይከናወን መረጃዎቹን ተከትሎ በሚሰሩ ቀጣይ
የሥራ ክፍሉ ሥራዎች ላይ መስተጓጎልን ይፈጥራል፡፡
3.3.2. ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 ሥራው ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎቹን ሰነዶች መያዝ አይጠይቅም፡፡
3.4 ፈጠራ
 ሥራው በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጾች መሠረት በማድረግ መሰብሰብ የሚጠይቅ ሲሆን በመረጃ መሰብሰቢያ ቅጾች
ላይ ቀላል/ መሠረታዊ ያልሆኑ/ የማሻሻያ መነሻ ሃሰብ ማቅረብ ይጠይቃል፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት፣
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው በመ/ቤቱ ውስጥ ከቅርብ ኃላፊው፣ ከሥራ ባልደረቦቹና ከሌሎች የሥራ ክፍል ሠራተኞች እንዲሁም ከመ/ቤቱ ውጭ
መረጃ ከሚሠጡ ተቋማትና ከመረጃ ተጠቃሚዎች ጋር ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

2
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ


 መረጃ ለመሰብሰብና ለመስጠት፣ አመራር ለመቀበልና ሪፖርት ለማቅረብ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ሥራው መካከለኛ 30 በመቶ የሆነ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በሀላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 በሥሩ የሚመራቸውና የሚያስተዳደራቸው ሠራተኞች የሉም፡፡
3.6.1.2 የኃላፊነት አይነት ና ደረጃ
 የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 ሥራው ገንዘብ የመያዝ ወይም የማዘዝ ኃላፊነት የለበትም፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራው ለቢሮ መገልገያነት የተሰጡትን ወንበር፣ ጠርጴዛ፣ መደርደሪያ ና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር በኃላፊነት መያዝን የሚጠይቅ
ሲሆን የነዚህ መሣራያዎችም ዋጋ አስከ 40,000 ብር ይገመታል፡፡

3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች መሰብሰብን፣ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ መረጃ የሚሰበሰብባቸውን ጉዳዮች (Variables)
እና አመልካቾችን (Indicators) መለየት፣ በተቋሙ የተለያዩ ዘርፎች ላይ ተፅዕኖ ሊያስርፉ የሚችሉ መረጃዎቸን
ለውሳኔ በሚረዳ መልኩ ማደራጀት፣ መረጃዎችን ወደ መረጃ ቋት ኮድ በማድረግ ማስገባት አእምሮን የሚያደክሙ
ተግባራት ሲሆኑ እነዚህም ተግባራት ከሥራ ሰዓቱ 30% ይወስዳሉ፡፡
3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት
 መረጃዎችን በማሰባሰብ ሂደት መረጃ ሰጪ አካላት ፍቃደኛ አለመሆን የሚያጋጥም ሲሆን ይህም አልፎ አልፎ ስነ
ልቦናን ይፈታተናል፡፡ ይህም ስሜትን በመቆጣጠርና በትዕግስት የመረጃ ሰጪ አካላትን ማግባባትና መረጃዎችን
በአግባቡ መሰብሰብን ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
4. ወደ ኮምፒዩተር መረጃዎችን መሙላትና ማማሳከር እይታን የሚያደክም ተግባራ ሲሆን ይህም ከስራ ሰዓቱ 25 % ይወስዳል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
5. ሥራው ከስራ ሰዓቱ 80% በመቀመጥና 20% በመንቀሳቀስ ይከናወናል፡፡
3.8. የሥራ አካባቢ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ

3
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

6. ሥራው ለአደጋ ተጋላጭነት በሌለበት ሁኔታ ይከናወናል፡፡


3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ፣
7. በምቹ የሥራ አካባቢ ሁኔታ የሚከናወን ነው

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
የመጀመሪያ ዲግሪ በስታትስቲክስ፣ በ MIS፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሥራ አመራር፣
3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
0 ዓመት
የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like