You are on page 1of 3

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የመረጃ ሥራ አመራር ባለሙያ II የመረጃ ሥራ አመራር
ዳይሬክቶሬት

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
ለተቋሙ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በመሰብሰብና በማደራጀት ለጥንቅርና ለትንተና ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ፣
2.2. የሥራ መደቡ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡ ለዘርፉ የሚያስፈልጉ ወቅታዊ መረጃዎችን መሰብሰብና ማደራጀት
 ተለይተው የተሰጡ የመረጃ ምንጮችን በዝርዝር ይይዛል፣
 ከመረጃ ምንጮቹ መረጃውን ይሰበስባል፣
 የተሰበሰቡ መረጃዎች በቅጹ መሰረት ስለመሞላታቸው ያመሳክራል፣
 የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማደራጀት ለጥንቅርና ለትንተና ምቹ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
 ከተጠቃሚዎች የመረጃ ፍላጎት ጥያቄ ሲቀርብ የሚፈልጉትን ለይቶ ያቀርባል፣
 ከዘርፉ የተሰበሰቡ መረጃዎች የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ሊያስተናግድ በሚችል አግባብ ያከማቻል፣
 ከመረጃ አሰባሰብ እስከ ትንተና ያሉ ተግባራትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችሉ ጥናቶች ላ
ይሣተፋል፣ የማሻሻያ ሃሳብ ያቀርባል፣
 በየጊዜው በሚዘጋጁ ስታትስቲካል ቡሌተንስ/ መጽሄት ዝግጅት ሥራ ላይ ይሣተፋል፣
 የሥራ ሂደቱ ዕቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ሥራ ላይ ይሣተፋል፣
 የሥራ ክንውን ሪፖርት ያዘጋጃል፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች


3.1. የሥራ ውስብስብነት
ሥራው መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች ማሰባሰብ፣ ማደራጀት፣ ለተጠቃሚዎች በሚያመች መልኩ መለየትና ማከማቸ
እንዲሁም በጥናትና በስታትስቲካል ቡሌተንስ ዝግጅት ላይ መሣተፍን የሚጠይቅ ሲሆን እነዚህም ሥራዎች በሚከናወኑበ
ጊዜ ተሞልተው የሚመጡ መረጃዎች በተላከውና በሚፈለገው ቅጽ መሠረት ተሞልተው እንዲላኩ አላመድረግ፣ የመረ
ምንጮች የሥራ ባህሪ መቀያየር የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲሆኑ እነዚህንም የመረጃ ማሰባሰቢያና ማደራጃ ቅጾ
የሚሻሻሉበትን መንገድ በመጠቆምና ከዚህ በፊት የተሠሩ ሥራዎችን አሰራራቸውን በማጥናት እና የሌሎች ባለሙያዎ
ተሞክሮን በመውሰድ ይፈታሉ፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
ሥራው ከቅርብ ኃላፊው በሚሰጠው የአፈጻፀም መመሪያን መሰረት ይከናወናል፡፡

1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.2.1 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ


ሥራው በተሰጠው መመሪያ መሠረት ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊው ክትትልና ድጋፍ ይደረግበታል፡፡
3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት
ሥራው መረጃዎቹን በአግባቡ መሰብሰብ፣ ማደራጀትና ለተጠቃሚዎች በሚያመች መልኩ ማከማቸት የሚጠይቅ ሲሆ
ይህም ተግባር በአግባቡ ባይከናወን መረጃዎቹን ተከትሎ በሚሰሩ ቀጣይ የሥራ ክፍሉ ሥራዎች ላይ የሥራ መስተጓጎልን እ
በመረጃ ተጠቃሚዎች ላይ ቅሬታን ይፈጥራል፡፡
3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
ሥራው ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችና ሰነዶችን መያዝ አይጠይቅም፡፡
3.4 ፈጠራ
ሥራው የመረጃ ማሰባሰቢያ ቅጾች፣ የማደራጃና ማካመቻ ዘዴዎች የሚሻሻሉበትን ሃሳቦች ማመንጨትን ይጠይቃል፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
ሥራው በመ/ቤቱ ውስጥ ከቅርብ ኃላፊው፣ ከሥራ ባልደረቦቹና ከሌሎች የሥራ ክፍል ሠራተኞች እንዲሁም ከመ/ቤቱ ው
መረጃ ከሚሠጡ ተቋማትና ከመረጃ ተጠቃሚዎች ጋር ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ
መረጃ ለመሰብሰብና ለመስጠት፣አብሮ ለመስራት፣ አመራር ለመቀበልና ሪፖርት ለማቅረብ የሥራ ግንኙነት ማድረግ
ይጠይቃል፡፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
ሥራው መካከለኛ የሆነ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ከሥራ ሰዓቱ 30% ይወስዳል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በሀላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
በሥሩ የሚመራቸውና የሚያስተዳደራቸው ሠራተኞች የሉም፡፡
3.6.1.2 የኃላፊነት አይነት ና ደረጃ
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
ሥራው ገንዘብ የመያዝ ወይም የማዘዝ ኃላፊነት የለበትም፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
ሥራው ለቢሮ መገልገያነት የተሰጡትን ወንበር፣ ጠርጴዛ፣ መደርደሪያ ና ኮምፒዩተር በኃላፊነት መያዝን የሚጠይቅ ሲሆ
የነዚህ መሣራያዎችም ዋጋ አስከ 20,000 ብር ይገመታል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
የተለያዩ መረጃዎች ማሰባሰበ፣ መረጃዎች በአግባቡ መሞላታቸውን ማመሳከር፣ ማደራጀት፣ ተጠቃሚዎች በሚፈልጉ
መልኩ መረጃዎችን ማከማቸትና ሪፖርት ማዘጋጀት አእምሮን የሚያደክሙ ተግባራት ሲሆኑ እነዚህም ተግባራት ከሥራ ሰዓ
25% ይወስዳሉ፡፡
3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት
መረጃዎችን በማሰባሰብ ሂደት መረጃ ሰጪ አካላት ፍቃደኛ አለመሆንና ተገቢ መረጃ አለመስጠት የሚያጋጥም ሲሆን ይህ
አልፎ አልፎ ስነ ልቦናን ይፈታተናል፡፡ ይህም ስሜትን በመቆጣጠርና በትዕግስት መረጃዎችን በአግባቡ መሰብሰብን ይጠይቃል፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣

2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

በኮምፒዩተር መረጃዎችን መሙላት፣ ማመሳከርና ማደራጃት እይታን የሚያደክሙ ተግባራት ሲሆኑ እነዚህም ከስራ ሰዓ
35% ይወስዳሉ፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
ሥራው ከስራ ሰዓቱ 85% በመቀመጥና 15% በመንቀሳቀስ ይከናወናል፡፡
3.8. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
ስራው ለአደጋ ተጋላጭነት በሌለበት ሁኔታ ይከናወናል፣
3.8.2. የጤና ጠንቅ፣
ሥራው የጤና ጠንቅ በማያስከትሉ አከባቢዎች ይከናወናል፡፡

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
የመጀመሪያ ዲግሪ በስታትስቲክስ፣በ MIS፣ በኢኮኖሚክስ፣

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
2 ዓመት በስታትስቲክስ፣ በመረጃ ሥራ አመራር፣ ሥራ አመራር፣
በ MIS

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን


ቡድን -9

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like