Professional Documents
Culture Documents
ስልጠና
February 2021
Asella
2. የመመርያው አላማ
አዘጋጅ፡ ABDI@H Page 1
ይህ መመርያ አሰልጣኞች የንግድ ስራ ክህሎ እና አንትረትረነርሽፕ ስልጠናን ለሰልጣኞች በተዘጋጀው
የስልጠና ማንዋል መሰረት
መስጠት እንዲችሉ ያግዛቸዋል፡፡
3. የስልጠናው ተጠቃሚዎች
ይህ ስልጠና በፕሮጀክቱ ተመዝግበው ያሉ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ያማከለ ነው ፡፡
4. የስልጠናው ግብ
የዚህ ስልጠና ዋና ዋና ግቦች የሚከተሉት ናቸው፡
በንግድ ክህሎት ላይ መወረታዊ የሆነ እውቀት ያስጨብጣል
ሴቶች በንግድ ሰራቸው ውጤታማና ምርታማ እንዲሆኑ የንግድ ስራ አመራር ክህሎቶችን
እንዲያዳብሩ ማስቻል
ኢንትረፕረነርሽፕ ክህሎታቸው እንዲዳብር ማስቻል
ነባራዊ ሁኔታው ግምት ውስጥ በማስገባት አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን ማመንጨት እና
ተግባራዊ በማድረግ ንግዳቸውን
ማስፋፋት የሚያስችል ክህሎት እንዲያዳብሩ ማስቻል
ስልጣኞች በስርዓተ ፆታ ላይ የሚደርስባቸውን ጫና ተቋቁመው በንግዳቸው ውጤታማ
እንዲሆኑ ማስቻል፡፡
ትርፍ
ደንበኛ
ፈጠራ
ግዥ
ስኬት ግብ
ተወዳዳ
ሪ
የንግድ
ሀሳብ
የንግድ ክህሎት
የንግድ
ስልት
ተነሳሽነት
መልካም
ግንኙነት
በራስ
መተማመን
ገበያ
የአሰልጣኙ ማስታወሻ 2፡ አነስተኛና ጥቃቅን ቢዝነሶች፡ አነስተኛና ጥቃቅን ቢዝነሶች ለአንድ ሀገር
የምጣኔ ሀብት እድገት መሠረት ናቸው፡፡
አነስተኛና ጥቃቅን ቢዝነሶች በተለይ እንደ ኢትዮጵያ አይነት ድሀ ሀገር ውስጥ ለእድገት መሰረቶች
ናቸው፡፡ በተጨማሪም የውድድር
መንፈስ በመፍጠር ተጠቃሚዎች ዕቃዎችን/አገልግሎቶችን በተሻለ ዋጋ ማግኘት ያስችላሉ፡፡ ነገር ግን
ያላቸዉ ሚና ከሚጠበቀዉ በታች
ነዉ፡፡ ይህም በመሆኑ ከፍተኛ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ዋና ዋናዎቹ እገዛዎች የስለጠና አገልግሎት፡
የማማከር አገልግሎት፡ መረጃ
የመስጠት፡ የቴክኖሎጅ ማስፋፊያና ስርጭት እና የንግድ ትስስርን ለመፍር የሚያስችል እገዛ ማድረግ
ናቸዉ፡፡ ይህ ስልጠናም ከነዘህ
ድጋፎች አንዱ መሆኑን ተረድተው ሰልጣኞች እንዲጠቀምበት ያበረታቷቸው፡፡
4. ያልታሰበ እድገት፡ እድገት የተፈጥሮ ባህሪ ስለሆነ ይፈለጋል፡፡ ይሁን እንጂ የቢዝነሱ እድገት
በጣም ከፈጠነ ለማስፋፋት
ከምንችለው በላይ አቅም ይጠይቀናል በዚህ ጊዜ ያለን ልምድና ተሞክሮ ከዕድገቱ ጋር አብሮ
ሥለማይወነጨፍ ለውድቀት
እንዳረጋልን፡፡ ምክንያቱም የሰው ኃይል አስተዳደር፣ የገንዘብ ፍሰቱና ቁጥጥር ከምናስብው በላይ
ይወሳሰብል፡፡
5. ትክክል ያልሆነ ቦታ፡ ቦታ ለአንድ ቢዝነስ ጤናማ ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ በትክክልና ጊዜ ወስደን ቢዝነሱ
ምን ዓይነት ቦታ (ሥፋቱን
ጭምር)፣ ደንበኞቻችን የት ነው የሚኖሩት፣ የኪራዩ ዋጋ ሥንት ነው ብለን ካላጠናነው ውድቀታችን
የከፍ ይሆናል፡፡ ሥለዚህ
ክፍት ቦታ (በርካሽ ዋጋ) ሥለተገኘ ብቻ ሥራ መጀመር ተመካሪ አይደለም፡፡
6. ደካማ የዕቃዎች ቁጥጥር ለሽያጭ/ለአገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ብዙውን ገንዘባቸውን እንደሚይዙ
ይታወቃል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ደንበኞቻችን የሚፈልጉትን ዕቃ ገዝተን ልናስቀምጥ እንችላለን ሌላ ጊዜ ደግሞ ደንበኞቻችን
የሚፈልጉት ዕቃ በሙሉ ሊያልቅ
ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ስንጠይቅ መልሳችን ዕቅድ የለንም ይሆናል፡፡ ደንበኛ በእኛ እርካታ ያጣና ወደ
ተፎካካሪያችን በመሔድ
አገልግሎቱን/ዕቃውን ያገኛል፡፡ ሽያጭ አጣን ማለት ትርፍ የለም፡፡
የገንዘብ ስኬት
ማህበራዊ ስኬት
የሚያረካቸው
የሚያረካቸው
የግል ስኬትን አጥብቀው
ከፍተኛ መነሳሳት
የሚፈልጉ
እና የፈጠራ
ክህሎት
ታታሪዎች
ከግለኝነት አመለካከት
ት
የጸዱ
ከውይይታቸው በመነሳት ሊኖራት የሚገባውን የባህሪ ክህሎቶችን በማቅረብ የማጠቃለያ ሀሳብ ይስጡ፡፡
ከታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋና
ነጥቦች ማየት ይቻላል፡፡
የአሰልጣኙ ማስታወሻ 1
የአሰልጣኙ ማስታወሻ 2
ለምን እንቆጥባለን?
የወደፊት ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት
የተወሰነ ፍላጎትን ለማሟላት
እሴት ወይም ከምንፈልገው በላይ የሆነውን ለማስቀመጥ
ህግ ስለሚያስገድደን
መች እንቆጥባለን?
በኢኮኖሚ ለማደግ ገንዘብ ፈሰስ ማድረግ ስንፈልግ
ወደፊት ፍላጎት ይፈጠራል ብለን ስናስብ
ስንገደድ
ማን መቆጠብ አለበት?
1. ለማደግና ለመስፋፋት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው
2. ድሀ - ሀብት በማጠራቀም የድህነት አዙሪትን ሰብሮ ለመውጣት
3. ሀብታም - ሀብታቸውን ለማስፋት
4. አገሮች - የህዝብ ሀብትን ለማሳደግ
የቁጠባ ጥቅሞች
በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ለማዋል
አንገብጋቢ የሆኑ የወደፊት ፍላጎቶችን ለማሟላት
በወለድ ለሌሎች ለማበደር
1. የራስ ምንጮች
2. ስጦታዎች
3. ብድሮች (ከጓደኞች፤ ከባንክ እና ከማህበራት)
4. ከአቅራቢ ዱቤዎች
5. የተጠራቀመ ትርፍ
6. አክሲዮኖች በመሸጥ /ወለዶችክፍል 3፡ የንግድ ክህሎትን ማሳደግ
የአሰልጣኙ ማስታወሻ
አባክዎ አሰልጣኝ ተሳታፊዎች ስልጠና ማንዋሉ ላይ የቀረቡትን መልመጃዎች በቅደም ተከተል እንዲሰሩ
ያድርጓቸው፡፡ የተወያዩበትን ዋና
ዋና ነጥብ ለክፍሉ በሚያካፍሉበት ጊዜ የሃሳብ ፍጭቶቹ ትኩረት ያደረጉባቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች
በመለየት የማጠቃለያ ሃሳቡን
ተሳታፊዎች ራሳቸውን ብዙ ጥያቄ እንዲጠይቁ በሚያደርግና የበለጠ ሊያወያያቸው በሚችል መልኩ
ከላይ የተጠቀሱት ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሁኑ ወጭዎች ተደምረው የማምረቻ ዋጋን ይሰጡናል፡፡ ማለትም
የማምረቻ ዋጋ ቀመር
1. የሽያጭ እና
አስተዳደራዊ
ወጭዎች
2. የፋብሪካ
ጭዎች
3. ቀጥተኛ
5. መሰረታዊ
የጉልበት የማምረቻ ዋጋ 6. ተመርቶ የሙሉ
(3 + 4) እስኪወጣ የምርት ዋጋ
ወጭዎች
የፈጀው ዋጋ
(2+5) (1+6)
የንግድ እድገት
• ንግድ የሚያድገው የንግዱ ባለቤቷ የምታገኘውን ትርፍ መልሳ ለስራ ስትጠቀምበት ሲሆን ይህም
የበለጠ ገቢና እንቅስቃሴ
እንዲኖራት ያስችላታል።
ለእድገት እንቅፋቶች:
1. አነስተኛ የገበያ እድል
2. የገንዘብ እጥረት
3. አነስተኛ የቴክኖሎጂ ደረጃ
4. የባለሙያ እጥረት
5. የአመራር ስልት ድክመት
6. ለእድገት የአስተሳሰብ መድከም
7. ደካማ የአመራር ክህሎት
8. ፈጠራ የተሞላበት አስተሳሰብ ማነስ
9. ምርትና አገልግሎትን ለማሻሻል አቅም ማጣት
10. ለማስተዋወቅ የሀብትና የክህሎት ማነስ
11. ህግ ነክ እንቅፋቶች
12. ውድድር
13. የትራንስፖርት ዋጋ ከፍ ማለት
የእድገት ስልቶች:
• ሌላ የንግድ ድርጅትን በመግዛት እና ተጨማሪ አቅም በመፍጠር
• ከሌሎች የስራ ፈጣሪዎች ጋር አብሮ መስራት የሚቻልበትን ሁኔታ በማመቻቸት
• ከአከፋፋዮች እና ከአገናኝ ወይም ኮሚሽን ድርጅቶች ጋር ስምምነቶች በመፍጠር
• አዳዲስ የገበያ ስልቶቸን በመከተል
• የዘርፍ ማህበራት እና ሌሎች ስብስቦችን በመቀላቀል
• አክሲዮን ለህዝቡ በመሸጥ
• በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፎችን በመክፈት
• ደንበኞችን ለመድረስ ሌሎች አካላቶችን መጠቀም
• እና ሌሎች ስልቶችን በመከተል፡
ንዑስ ክፍል 5፡ የንግድ እንቅስቃሴን መገም
የነኝህ ጥያቄዎች የጨረሻ መልስ የስራ ዕቅዱ ይሆናል ማልት ነዉ:: ዕቅድዎ እየሰራ
እንደሆነ ለማዎቅ፤ የንግዱን ሁኔታ በየጊዜው
በመገምገም ጤናማ እና ጠንካራ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል።በእቅዱ ሂደት ውስጥ ግዕቦችን
ማስቀመጥ ያስፈልጋል።ግብ በመጨረሻ
ማሳካት የምፈልጉት ውጤት ነዉ።እነዚህን ግዕቦች በአጭር እና በረጅም ጊዜ ማሰቡ ጠቃሚ
ነው።በዚህ መንገድ በትክክለኛው መንገድ
ላይ ስለመሆንዎ ወይም ከሚፈልጉት አቅጣጫ መዉጣትዎን መከታተል ይችላሉ።
ምንም እንኳን እነዚህ ምሳሌዎች SMART ግቦች ቢሆኑም፤ የበለጠ ተጨባጭ ወይም ዉስን
በማድረግ ማሻሻል ይችላሉ፡፡
ለእያንዳንዱ የንግድ ግቦች በድጋሜ በማየት ያቅዱ። ግቦቹን በቀጣዩ ገጽ በሚገኘው ሰንጠረዥ
በቅደም ተከተል ይዘርዝሩ። ይህ የደረጃ
አሰጣጥ ግብዓቶች በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ግቦች ቅድሚያ እንዲሰጡ ያደርጋል፤ ብዙም
ትኩረት የማይሰጣቸው ግቦች ግን አነስተኛ
ቅድሚያ እንዲሰጡ ያደርጋል።
አጠቃላይ ሀሳብ፡ ማርኬቲንግ እያንዳንዱን የእለት ከለት እንቅስቃሴያችን ውስት ጉልህ ሚና አለው፡፡
ምክንያቱም በእያንዳንዱ ቀን ወይ
እንሸጣለን አሊያም እቃዎችን /አገልግሎቶችን እንገዛለን፡፡ በመሆኑም ማርኬቲንግ ብዙ ውሳኔዎቻችን ላይ
ተጽኖ ያመጣል እንደ ገዥ
ወይም እንደ ሻጭ፡፡ ስለዚህ ማርኬቲንግ ክህሎት ሊኖረን ይገባል፡፡
ለምሳሌ እንደ ደንበኛ እዚህ ስልጠና ቦታ ለመምጣት የመጓጓዣ ዘዴ መምረጥና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን
ለመመለስ ወይም እነዚህን
ውሳኔዎች ለመወሰን ማርኬቲንግ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
የማርኬቲንግ ተግባራት
1. ምርት/ አገልግሎት
የማርኬቲንግ የመጀመሪው ተግባር ደንበኛ የሚፈልገውን ምርት /አገልግሎት ለይቶ ማወቅ እና
ለማምረት መዘጋጀት ለማምረት
የሚያስፈልጉ ግብይቶችን ለይቶ ማወቅና ማቅረብ ነው፡፡ እዚህ ጋር የሚነሳዉ ትልቁ ጉዳይ
1. ምን አይነት ምርት/አገልግሎት ደንበኛው ይፈልጋል
2. ቀለም፡ መጠን ወ.ዘ.ተ
3. የምርቱ ስም መለያ ምልክት
4. የምርቱ የጥራት ደረጃ
5. ዋስትና የሚሰጥ መሆኑንና አለመሆኑን
2. ዋጋ መተመን /pricing/
ከላይ ያነሳናቸውን ከምርት ጋር የተያያዙ ጉዳዬች ከመለስን በኋላ የምርታችንን/ አገለግሎታችንን ዋጋ
መተመን ይኖርብናል፡፡ ዋጋ
ስንተምን በዘፈቀደ መሆን የለበትም ብዙ ነገሮችን ከግምት ማስገባት ይኖርብናል፡፡ ከነዚህም ውስጥ
1ኛ. የማምረቻ ወጭ
2ኛ. እቅዳችን - የረጅም ጊዜ ትርፍ እቅድ
- የአጭር ጊዜ ትርፍ እቅድ
- በቶሎ ወጭን መመለስ
5. ስራ ፈጣሪው / person/
የንግዱ ባለቤት ለንግዱ ስኬት በጣም አስፈላጊ ከሚባሉ ነገሮች ሁሉ የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል፡፡
በመሆኑም ግለሰቡ / ግለሰቧ
ወይም የጋራ ንግድ ከሆነ ባለቤቶች የሚከተሉትን ክህሎቶች ሊያዳብሩ/ ሊኖሯቸው ይገባል፡፡
ሀ. ተግባራዊ የማምረት ክህሎት
ለ. የንግድ አስተዳደር ችሎታ
ሐ. ታታሪነት ለስራ ተነሳሽነት ቁርጠኝነት
መ. ውሳኔ ሸጭነት ባህሪያት
- ደስተኛ ደንበኛ
- ብዙ ሽያጭና
- ተደጋጋሚ ግዥ ናቸዉ፡፡
አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ የተደሰተ አንድ ደንበኛ ስለ ድርጅቱ ወይም ምርቱ ለ 4 ሰዎች የሚናገር
ሲሆን ያልተደሰተ ደንበኛ ግን
ከ 11-20 ሰዎች የሚናቨር መሆኑን ነው፤ ከዚህ ጥናት ውጤት ምን እንማራለን?
2. ተወዳዳሪ
ሁሉም የንግድ ሰራዎች ማለት ይቻላል ተወዳዳሪ አላቸው ፡፡ በመሆኑም ሁሉም ስራ ፈጣሪዎች ጠንካራ እና
ደካማ ጎናቸውን አውቀው
ጠንካራ ጎናቸው ላይ መሠረት አድርገው ተወዳዳሪ ሊያደርጋቸው የሚችሉ ስልቶችን መንደፍ
ይገባቸዋል፡፡ መረጃ መሰብሰብ በጣም
አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ - ተወዳዳሪዎቻችን እነማን እንደሆኑ መለየት እና የነሱን ጠንካራ ጎን ማወቅ፡፡
3. ዋጋ
ዋጋን በተመለከተ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ስልት ዋጋ መቀነስ ሲሆን በጥንቃቄ ልናየው ይገባል፡፡
ምክንያቱም ከተገቢው በታች ዋና
መቀነስ ወይም መጨመር የራሱ የሆነ ጉዳት አለው፡፡ በጣም ከቀነሰ ንግዱ ኪሳራ ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡
5. የምርት ማሸጊያ
የምርት ማሸጊያ ለአንድ የንግድ ስራ ስኬት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ጥሩ ማሸጊያ መጠቀም
ደንበኛን ለመሳብና ሽያጭን
ለመጨመር አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳ ምርቱ እንዳይበላሽ እንዳይፈስ ወይም እንዳይሰበር ማሸጊያ
አስፈላጊ ነው፡፡
ምን አይነት ማሸጊያ ነው የሚያስፈልገን? ከወረቀት የተሠራ ወይም ከፕላስቲክ / ከአልሙኒየም ሊሆን
ይችላል፡፡ ማስጊያ ከፍተኛ የሆነ
የአሰልጣኙ ማስታወሻ
የምርት ሂደት ምንድን ነው? የምርት ሂደት ምርትና አገልግሎትን እውን ለማድረግ የሚድረግ ክንውን
ነው፡፡
የስራ ቦታ፡ ምርትና አገልግሎቶች የሚመረቱበት ቦታ በአጠቃላይ የስራ ቦታ በመባል ይጠራል፡፡ ምርትና
አገልግሎቶች በጥሩ ሁኔታ
እንዲመረቱ በስራ ቦታ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
የመሳሪያዎች አያያዝና አቀማመጥ
የስራ አካባቢ
ምርታማ ማሽኖች
የጎጂ ንጥረ ነገሮች ቁጥጥር
ብርሀን
የመሳሪያ ደህንነት
ግቢው
የመሳሪያ አቀማመጥና አያያዝ
ቦታ እንዳይዙ
የመሳሪያዎችን ብልሽት ለመቀነስ
የሚጠፋ ጊዜን ለመቀነስ
አደጋዎችን ለመቀነስ
አዘጋጅ፡ ABDI@H Page 21
የስራ አካባቢዎች:
የስራ አካባቢያችሁን ለብክነት በማያጋልጥና ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ አዘጋጁ፡፡
• ኤሌክትሪክን፤ የማሽን ማብሪያ ማጥፊያን፤ መሳሪያዎችን እና መቆጣጠሪያዎችን ሰራተኞች
በቀላሉ በሚደርሱበት መልኩ
ማደራጀት
ከሰራተኞች የሚጠበቀውን ጥረት ለመቀነስ የእቃ ማንቀሳቀሻ ማሽኖችን መጠቀም
ለእያንዳንዱ የስራ አካባቢ ቋሚ ቦታ መስጠት
ስራ እየተሰራ ባለበት ወቅት ማጥበቂያውችን፤ ማሰሪያዎችን እና ሌሎች መሰል መሳሪያዎች መጠቀም
የመሳሪያዎችን ከፍታ ማስተካከል፤ አጎንብሶና ተንጠራርቶ መስራትን ማስወገድ
ሰራተኞች በምርጫቸው ቆመው ወይም ተቀምጠው መስራት እንዲችሉ የስራ ዘዴን መቀየር
ወንበሮች ወይም ትክክለኛ ከፍታና የእጅ ማሳረፊያ ያላቸውን አግዳሚ ወንበሮች ማቅረብ ።
የተግባር ልምምድ
• በሰልጣኝ ማኑዋል ላያ ያለውን መልመጃ በትእዛዙ መሰረት አሰራቸው፡፡
• እንዴት ዋጋን፤ ጥራትን እና እደላን መደራደር እንደሚችሉ ግንዛቤ ፍጠሩላቸዉ፡፡
አዘጋጅ፡ ABDI@H Page 22
• ለንግድ የሚሆኑ አቅርቦቶችን ለመግዛት ምን አይነት ሂደት እንደሚከተሉ አወያያቸዉ፡፡
• በተቀመጠዉ የግዢ ፎርም መሰረት ግዢ እንዴት መፈጸም እንደሚችሉ ግንዛቤ ፍጠርላቸው፡፡
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች
• ፓርከር
• ፍሊፕ ቻርት
• የማስተማሪያ ስነ-ዘዴ
• አንድ ቢዝነስ መሰረት በማድረግ እና አዳዲስ ሀሳብን በማንሳት ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን
እነዲዘረዝሩ
ማድረግ፡፡
• ሰልጣኞች ግዥ እንዴት እንደሚፈፅሙ እና የተለያዩ ግዢዎችን ፎርም እንዲሞሉ ያደርጋል፡፡
በማሰልጠኛው ማንዋል ላይ
ያለውን ማስታወሻ እንዲያነቡ እና ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ያድርጉ፡፡
• የግዥ እቅድ እንዲያዘጋጁ ያድርጉ፡፡ንዑስ ክፍለ 4: የመዝገብ አያያዝ
የአሰልጣኙ ማስታወሻ 1
እባክዎ አሰልጣኝ ተሳታፊዎች በመዝገብ አያያዝ ዙሪያ በደንብ ልምምድ እንዲያደርጉ ከሁለተኛው
የስልጠና ቀን ጀምሮ ወጪና
ገቢያቸውን የሚመዘግቡበት የሂሳብ መዝገብ ይዘው እንዲመጡ በማድረግ ስልጠናው በሚቆይባቸው
ቀናት ያለውን የቢዝነሳቸውን
የገንዘብ ልውውጥ (ገዢ ሺያጭ) እንዲመዘግቡ ያርጓቸው፡፡ በየቀኑ መጀመርያ ላይ ያለፈውን ቀን
የገንዘብ ልውውጥ በምን መልኩ
እንደመዘገቡት ይዩላቸውና አስተያየት ይስጧቸው፡፡ መመዝገብ ለሚቸገሩ ተሳታፊዎች ልዩ ድጋፍ
ያርጉላቸው፡፡
እነዚህንና ሌሎች ተመሳሳ ጥያቄዎች የሚያሳዩን በተገቢው መልኩና ሁኔታ መረጃዎችን መዝግቦ
አለመያዝ ሊያስከትል የሚችለውን
ችግሮች ውስብስብ እንደሆኑ ያመላክታል፡፡
የመዝገብ አያያዝ ጥቅሞች
የመዝገብ አያያዝ የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት
1ኛ. የጥሬ ገንዘብ ፍሰትን ለመቆጣጠር ይረዳል
2ኛ. የንግዱ እንቅስቃሴ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ያሳየናል
3ኛ. ለሌሎች አካላት የንግድ እንቅስቃሴያችን ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መረጃ ይሠጣል፡፡
4ኛ. ለወደፊት እቅድ እንደመነሻ ያገለግላል፡፡ ያለፈ ጊዜ ድክመቶችንና ጠንካራ ጎኖችን በግልጽ
ስለሚያሳይ ለነገ ጥሩ እቅድ
ለመንደፍ ያስችላል፡፡
ስለዚህ የንግድ እንቅስቃሴያችን የተቃና ለማድረግ ጥሩ የመዝገብ አያያዝ ክህሎት ሊኖረን ይገባል፡፡
የአነስተኛ እና ጥቃቅን ንግድ ተቋማትን አላማ ከግብ ለመድረስ ያለውን የሰው ሀይል በአግባብ መጠቀም ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ በዘህ
የውድድር ዘመን ትክክለኛውን ሰው ማለትም በችሎተው የተመሰከረለት፣ ጥሩ ባህሪ ያለው፣ ታታሪ፣ ታማኝ ወ.ዘ.ተ እና በሚፈለገው
ብዛት ያለው ሰው ማግኘት ከባድ እየሆነ ሆኗል፡፡ ለዚህም የተቋማቱ ባለቤቶች የሰው ሀይል አስተዳደር ክህሎት ሊያዳብሩ ይገባል፡፡
የምልመላ ዘዴዎች
ማስታወቂያ
በሌሎች ሰዎች ጥቆማ
የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ተቋማት
ሌሎች አማራጮች
ጊዜዊ ሰራኛ መቅጠር
የስራችንን የተወሰነ ክፍል ለሌሎች ሰዎች ወይም ተቋማት መስጠት/Subcontracting
የሰራተኛ ውሰት
የሰራተኛ ቅጠር
ከላይ በተጠቀሱት የምልመላ ዘዴዎች አማካኝነት ካመለከቱት አመልካቾች ውስጥ ለስራው ብቁ የሆነውን
ለመምረጥ የሚከተሉትን
በጥንቃቄ ማከነወን ተገቢ ነው፡፡
የትምህርት ማስረጃዎቸን እና የስራ ልምድ እንዲሁም ሌሎች የተያያዙ ሰነዶችን በትንቃቄ
መመርመር እና የተሻሉትን
መምረጥተ፡፡
አዘጋጅ፡ ABDI@H Page 25
ለተመረጡት አመልካቾች የስራ ፈተና መስጠት
ቃለ መጠይቅ ማካሄድ
የተሻለ ውጤት ያመጣውን/ችውን መምረጥ እና ፈቃደኝነታቸውን ማወቅ
የጤና ምርመራ ማድረግ
የቅጥር ደብደቤ መስጠት
2. ስራውን እና የስራ ቦታውን ማስተዋወቅ
3. ስልጠና መስጠት
4. የስራ ግምገማ ማድረግ
5. ተገቢውን ጥቅማጥቅም መክፈል
6. በተገቢው የስራ መደብ መመደብ
7. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሰራተኛ አዋጁ በሚፈቅው መሰረት ማሰናበት፡፡