You are on page 1of 10

“አመራር ለስኬት ቁልፍ ነው፡፡”

ራስን መምራት
The Leader
In You
Dale Carnegie

ትርጉም፡-ኤፍሬም ዓለሙ
© የአሳታሚው መብት በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

የመጀመሪያ ሕትመት፡- ታህሳስ 2008 ዓ.ም.

ዋና አከፋፋይ
ዩኒቲ መጻሕፍት መደብር
ኮሜርስ ከቴሌ ባር አጠገብ
ስልክ፡- 0912 02 87 94
፡- 0911 66 99 46
የመ.ሳ.ቁ. 4143
የሚከተሉትን በከፍተኛ ደረጃ የተሸጡ የዴል ካርንጌን መጻሕፍት በገበያ ያገኛሉ!

How to Develop Self-Confidence & Influence People by Public Speaking

How to Enjoy your Life & your Job

How to Stop Worrying & Start Living

How to Win Friends & Influence People

The Quick & Easy Way to Effective Speaking

በትክክል መሪ መሆን ይፈልጋሉ

አንዳንድ የቢዝነስ መሪዎች ስለዚህ The Leader in You ስለተሰኘው መጽሐፍ የሚሉትን
እነሆ፤

በዚህ መጽሐፍ ላይ አንድም ውስብስብ፤ ምሥጢራዊ ወይንም ለመረዳት አዳጋች ሆኖ የቀረበ


ነገር አላየሁም፡፡ ይሁን እንጂ በዚህች አስቸጋሪ፤ ውስብስብ አንዳንዴም ደግሞ ምሥጢራዊ
በሆነች ዓለም ውስጥ ውጤታማ መሪ ሊያደርግዎ የሚችል መርህ ነው በሥራው የቀረበው፡፡
አመራር ለስኬት ቁልፍ ነው፡፡

--በርት ማኒንግ፤

የ J. Walter Thompson ሊቀመንበር እና ዋ/ሥ/አስፈጻሚ


ዴል ካርንጌ ቀደም ሲል ይታወቅበት የነበረውን ዘይቤ ቀጥሎበት ሰዎች ውጤታማ የሆነ
የአመራር ክህሎትን በቀላሉ ማዳበር እንደሚችሉ አሳይቷል፡፡ ብዙ ሰዎች ይኼ ክህሎት
በውስጣቸው አለ፡፡ ብዙ በሥራው ዓለም የሚገኙ ሰዎች እርግጠኛ ካልሆኑበት ከዚህ ዓለም
ተነስተው ወደ ስኬት ያመሩ ዘንድ መርሁ ይጠቅማቸዋል፡፡

--ዶ/ር ኢርዊን ኤል. ኬልነር

በ Chemical Banking Corp. ዋና ኢኮኖሚስት

ምርጥ ከሆነው የተለያየ የሰዎች ተሞክሮ ለመማር የሚጠቅም እና ወደር-የለሽ ዕድልን


የሚፈጥር መጽሐፍ፡፡ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሉ እና ውጤት ያመጡ ሰዎች የግል
ተሞክሯቸውን እና ለስኬት እንዳበቋቻ ያረጋገጧቸውን ስትራቴጂዎች ያጋሩናል፡፡ በእውነት እኔ
ለዚህ መጽሐፍ የመጨረሻውን ትልቁን ነጥብ ሰጥቼዋለሁ!

--ሜሪ ሉ ሬተን

በመሠረቱ አመራር ማለት ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ነገር ትክክለኛ በሆነ ጊዜ በጉጉት እና በራስ
መተማመን ለመከወን ያላቸው ችሎታ ነው፡፡ ይህ ጉጉትን የሚያጭር፤ ተነባቢ እንዲሁም
በከፍተኛ ደረጃ ጠቃሚ የሆነው The Leader in You የተሰኘው መጽሐፍ አሁን ያለንበት
ሙያና ሁኔታ ምንም ይሁን ምን የአመራር እምቅ ኃይላችንን እንዴት ልናሳድግ እንደምንችል
ይነግረናል፡፡

---ሎረን ቦሰን

የ SGS-Thompson Microelectronics Inc. ፕሬዚዳንት እና ዋ/ሥ/አስፈጻሚ

Dale Carnegie & Associates, Inc., ሶስት ትላልቅ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተሸጡ
መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል፡፡ እነዚህም How to Win Friends & Influence People,
How to Stop Worrying & Start Living እና How to Enjoy Your Life & Your Job
የተባሉት መጻሕፍት ሲሆኑ ከ 30 ሚልዮን ቅጂዎች በላይ እስከዛሬ ድረስ ቀርበዋል፡፡
በዓለማችን የተለያዩ አገራት በየሳምንቱ ከ 3,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የዴል ካርንጌን ኮርሶች
ለመውሰድ ይመዘገባሉ፡፡ እነዚህ ደግሞ
በየጊዜው ተደማምረው እስከዛሬ ድረስ ከዚህ
ራስን በማሻሻልና በማሳደግ ረገድ ጥሩ
ሥልጠና ከሚሰጠው ተቋም ተመርቀው
የወጡትን 3.5 ሚልዮን ሰዎች ቁጥር
የትለየለሌ ያደርሰዋል፡፡
ስቱዋርት አር. ሌቪን

እኚህ ሰው የ Dale Carnegie &


Associates, Inc., ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዚህ ኩባንያ
የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የሥራ አስፈፃሚ
አባልም በመሆን አገልግለዋል፡፡ ሌቪን በ New
York ስቴት ዋና ገዢ በተቋቋመው የ
Excelsior Award የግብረ ኃይል ላይም አባል
ናቸው፡፡

ማይክል ኤ.
ክሮም
የ Dale Carnegie Centers of Excellence ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የኩባንያውን
የክልላዊና የውጭ አገር ቅርንጫፎች በተለመከተ ሙሉ ኃላፊነቱን ይዘዋል፡፡ ፤ ምሥጢራዊ
ወይንም መረዳት አዳጋች ሆኖ የቀረበ ነገር አላየሁም፡፡ የዚህ ኩባንያ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና
የሥራ አስፈፃሚ አባልም በመሆን አገልግለዋል፡፡

በዚህ በ 21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አማካዩ የሥራ ቦታና ሁኔታ ከመቼውም የቀደመ ጊዜ ይልቅ
ፈታኝ ሆኗል፡፡ በመሆኑም የወደፊት ጊዜያችንን ብሩህና ፍሬያማ ለማድረግ ዛሬ ላይ መዋዕለ-
ንዋይ እናፍስስ፡፡

The Leader in You 

ከ Dale Carnegie & Associates, Inc., የሚወጡ በርካታ ቃላት ለዘመናት ያህል ወደ ስኬት
ሰዎችን ሲመሩ ታይተዋል፡፡ በሚልዮን የሚቆጠሩ ምሩቃን ይኼንን ማየታቸውን መስክረዋል፤
በሳምንት ከዓለም ዙሪያ 3,000 ያህል ሰዎች ጓጉተው መመዝገባቸው ሌላው ማረጋገጫ ነው፡፡
How to Win Friends & Influence People የተባለውን ጨምሮ ሌሎች መጻሐፍት ከ 30
ሚልዮን ቅጂዎች በላይ እስከዛሬ ድረስ ቀርበዋል፡፡

በዚህ አሁን በቀረበው እና The Leader in You በተሰኘው ሥራ ላይ ስቱዋርት አር. ሌቪን እና
ማይክል ኤ. ክሮም ኩባንያው አመንጭቷቸው ዘመን-ተሻጋሪና አዋጪ መሆናቸው
የተረጋገጠላቸውን መርሆዎች ከተጠቀመ ማንም ሰው ቢሆን የቱንም ዓይነት ሥራ ቢሰራ
የፈጠራ ክህሎት እና ጉጉትን በመጠቀም ይበልጥ ምርታማ ሊሆን እንደሚችል በተለይም የ
1990 ዎቹን ተሞክሮዎች በመጥቀስ አመላክተዋል፡፡

በኮርፖሬት፤ መዝናኛ፤ ስፖርት፤ ትምህርት እና ፖለቲካ መስኮች ካሉ የዳበረ ልምድና ተሞክሮ


ካላቸው ሰዎች ግብዓቶችንና ምሳሌዎችን በመጥቀስ ደረጃ በደረጃ ወደ ስኬት ሊያደርሱን
የሚችሉ ነገሮችን አቅርበዋል፡፡ ከጠቀሷቸው ስትራቴጂዎች መካከልም፤

 የአመራር ጥንካሬዎቻችንን መለየት


 ግቦቻችንን መቀዳጀት እና በራስ-መተማመናችንን ማጎልበት
 የ ‹እኛ እና እነሱ› ዓይነት ተጻራሪነት ስሜትን ማስወገድ
 የቡድን ተጫዋችነትን በማጎልበት በሥራ ባልደረቦች መካከል የሚደረግን ትብብር
ማጠንከር
 በሥራ እና በመዝናናት መካከል ተገቢ መመጣጠን መፍጠር
 ጭንቀቶቻችንን በመቆጣጠር ሕይወታችንን ጉልበት ያለው እንዲሆን ማድረግ
 እንዲሁም ሌሎች በርካቶች

በውስጣችን ያለውን የመሪነት እምቅ ክህሎት ለማውጣት የሚሆነውን ቁልፍ በዚህ The
Leader in You በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ጊዜያችንን፤ ትኩረታችንን እና ጥቂት ገንዘባችንን
በማዋል እናውጣው፡፡
በትክክል መሪ መሆን
ይፈልጋሉ
ማውጫ
መግቢያ፡ 11

የሰው-ለሰው ግንኙነት አብዮታዊ ለውጥ

1. በውስጥዎ ያለውን መሪ ማግኘት 21

2. የኮምዩኒኬሽን መጀመሪያ 31

3. ሌሎች እንዲነሳሱ ማድረግ 42

4. በሌሎች ላይ እውነተኛ ፍላጎት እንዳለን መግለጽ 50

5. ነገሮችን በሌሎች እይታ አንጻር መቃኘት 59

6. ማድመጥን መማር 70

7. ለነገ መቧደን 80

8. የሌሎችን ክብር መጠበቅ 96

9. ዕውቀና፤ ምስጋና እና ሽልማት 114

10. ስህተቶችን፤ ሮሮዎችን እና ትችቶችን ማስተናገድ 129

11. ግቦችን ማስቀመጥ 142


12. ትኩረት እና ዲሲፕሊን 157

13. ሚዛንን ማግኘት 169

14. ቀና አስተሳሰብ እንዲኖረን ማድረግ 179

15. አለመጨነቅን መማር 191

16. ጉጉት 208

ማጠቃለያ፡
እውን ማድረግ 218

You might also like