You are on page 1of 146

Releasin

g
Your
Potential

Exposing the Hidden


You

Dr. Myles Munroe

1|Page
መታሰቢያነቱ

የማያልቅ የፍቅር ምንጭ የሆነችልኝ፤ መበርታትን እና መነሳሳትን ለሰጠቺኝ፤ በውስጤ ያለውን እምቅ-
አቅም እንዳወጣ ያደረገችኝን ውድ ባለቤቴ፡፡

ወደፊት ሙሉ እምቅ አቅማቸው ወጥቶ ለማያቸው ለሴትና ወንድ ልጆቼ ቻሪሳ እና ቻሪዮ (ማይልስ ጄ.
አር.)፡፡

በሚሊዮን ለሚቆጠሩና የጽንስ ማስወረድ ሰለባ ለነበሩ፤ ድንቅ እምቅ-አቅማቸውን የማውጣት መልካም
አጋጣሚን ያላገኙና አጋጣሚውን እንዳያገኙ ለተደረጉ ሌሎች ልጆች ሁሉ፡፡

አሁን በሚልዮን በሚቆጠሩ እናቶች ማህጸን ገና ያሉ ወደፊት ዓለም ለምትጠብቀውና ለምትፈልገው ለውጥ
ተፈጥረው እምቅ-አቅማቸውን በማውጣት አስተዋፆ ለሚያደርጉ ሁሉ፡፡

እንዲሁም በሌሎች የተዛባ አመለካከትና እኩይ ጥረት የተነሳ እምቅ-አቅማቸውና አስተዋፆአቸው በታሪክ
ለረጅም ጊዜ ተናንቆና ተረግጦ የቆየባቸው፤ ዛሬ ግን እንደ ሻማ እየቀለጡ ታምር በመስራት ላይ ለሚገኙ
የሶስተኛው ዓለም ሕዝቦች፡፡

ረጥከተሉት ሰዎች ይኼንን መጽሐፍ ለሕትመት ለማብቃት አደርግ በነበረው እልህ-አስጨራሽ ትግል ድባብ
ላይ ለውጥ በማምጣት ነገሩ ሁሉ እንዲቀለኝ በማድረግ እንደ ጅረት በዳንኪራ አብሬው ከሥራው ጋር እንደ
ጅረት ለመፍሰስ አብቅተውኛልና እስከ መቼም ለማልረሳቸው ውለታቸው እስኪ ላመስግናቸው፡፡

2|Page
ምሥጋና

እውነት ለመናገር ይኼ እናንተ ክቡራትና ክቡራን የምታነቡት መጽሐፍ እንዲህ አልቆ የወጣው በርካታ
ጭንቅላቶች ተጨምቀው በሰሩት የጥምረትና የቅንጅት ሥራ ነው፡፡ እምቅ-አቅማቸውን ባላቸው ጥልቅ
ፍላጎት የተነሳ በእኔ ውስጥ ትልቅ መነሳሳት እንዲፈጠር ላደረጉ በርካታ ትልልቅ ሰዎች ያልኝን ትልቅ ምስጋና
ላቅርብ፡፡ እነዚህ ትልልቅ ሰዎች እኔን እና ትውልዱን ለማነሳሳት የሚችል ውርስ ትተው አልፈዋል፡፡

በ Bahamas Faith Ministries International ለሚገኙ እና በጸሎት፤ በትዕግስት እና በታማኝነት


ዓላማዬን ለስኬት አበቃው ዘንድ ለረዱኝ አባላት፤ ወዳጆቼ እና የሥራ ባልደረቦቼ ያለኝ አድናቆት እጅግ ከፍ
ያለ ሲሆን በተለይም ደግሞ ዋና አስተዳዳሪዋ እና ታላቅ እህቴ የምላትን ሼይላ ፍራንሲስን ማመስገን
እፈልጋለሁ፡፡

ይህ መጽሐፍ አሁን በምታዩት መልክ ይወጣ ዘንድ፤

 ድንቅ ባለቤቴ ሩት እና ልጆቼ ላሳዩኝ ድጋፍ፤ መረዳት እና ትዕግስት፤ ብዙ ጊዜ ቤት ሳልገኝ ከአገር


ውጭ እና በመስክ ስራ ስጠመድ ጠብቀውኛል፤ አበረታተውኛልና አመሰግናቸዋለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን
ዓላማ ዳር አደርስ ዘንድ እናንተ ረድታችሁኛል፡፡

 በርካታ ወዳጆቼ፤ ፓስተሮች እና የቦርድ አባላት--ሪቻርድ ፒንደር፤ ዴቭ በሮውስ፤ ዌስሊይ ስሚዝ እና


ጄይ ሙሊንግስ (ለስለሰ ባለ አንደበቱ፤ በጸና ወዳጅነቱ እምቅ-አቅሜን አወጣ ዘንድ ስለረዳኝ)
ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ እነዚህ ሁሉ ለቆምኩለት ራዕይ ትእግስትና ታማኝነታቸውን አሳይተዋልና
እግዚአብሔር በሕይወቴ ባደረገው ነገር እነሱም ጭምር ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

 በተሰጥዖዋ እና ትጋቷ የማደንቃት ድምጽን ወደ ጽሁፍ የመቀየር ሥራ የምትሰራልኝ እና አርታኢዬ


ብሎም አማካሪዬ ካቲ ሚለር ይኼንን መጽሐፍ አብራኝ አምጣ ወልዳለች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከ
Destiny Image ማርሻ ብሌሲንግ በትዕግስት በተጣበቡ በርካታ የዓለም ዓቀፍ ጉዞዎች ውስጥ
ሆኜም ቢሆን የተቀመጡልኝን የጊዜ ገደቦች እንዳሟላ በማድረጓ ላመሰግናት እወዳለሁ፡፡

3|Page
 በወንጌል አገልግሎቱ ውስጥ ያሉና የማይረሱኝ ወዳጆቼ ተርነል ኔልሰን፤ ቤትሪል ቤርድ፤ ፒተር
ሞርጋን፤ ፉችሲያ ፒኬት፤ እዝቄል ጉቲ፤ ፍሬድ ፕራይስ፤ አለን ላንግስታፍ፤ ጄሪ ሆርነር እና
ኪንግስሊይ ኼቸርን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

 በመጨረሻም የሁሉም እምቅ አቅም ምንጭ እና አቅራቢ ለሆነው፤ ሁሉን ቻዩ ለአባታችን


እግዚአብሔር እና ለታላቅ ወንድሜ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ለግል አማካሪዬ መንፈስ ቅዱስ ዝቅ
ብዬ በክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ እናንተን እንዳገለግል ለሰጣችሁኝ ክብር ወደር-የለሽ ምስጋናዬን እነሆ!

ማውጫ

መቅድም

4|Page
መነሻው

እንደ መንደርደሪያ፡

ምዕራፍ 1 የሚያሳዝነው ሳይወጣና በጥቅም ላይ ሳይወጣ የቀረው እምቅ-አቅም. . . . .

ምዕራፍ 2 እርስዎ እንዴት ነው የሚታወሱት?. . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 3 እምቅ-አቅም ምንድነው?. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 4 እምቅ-አቅማችንን እንዴት ማውጣት እንችላለን? . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 5 መሠረት የሚጥልልን ቁልፍ. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 6 ምንጭዎን ይወቁ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 7 ሥራዎትን ይወቁ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 8 ዓላማዎትን ይወቁ. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 9 ሪሶርስዎችዎን ይወቁ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 10 ትክክለኛውን ከባቢ ሁኔታ ጠብቀው ያቆዩ . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 11 ሥራ፡ ማስተር ቁልፉ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 12 እምቅ-አቅም እና ለሥራ የምንሰጠው ቅድሚያ. . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 13 ሥራን መረዳት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

ምዕራፍ 14 ለኃላፊነት ምላሽ መስጠት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

መቅድም

ንጉሥ ሰሎሞን በ (መጽሐፈ መክብብ 12፡13) ላይ የሚከተለውን ይላል፤

5|Page
ነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ትዕዛዙንም ጠብቅ

እዚህጋ ‹ፍራ› የሚለው ቃል ለየት ያለ ትርጉም አለው፡፡ ይልቅ ‹ማክበር› የሚለውን ያሳያል፡፡ እግዚአብሔርን
ማክበርና ትዕዛዛዙን መጠበቅ የሰው ልጅ ግዴታው ነው፡፡ ሆኖም ግዴታ የሚለው ቃል በስፋት ችላ መባሉን
እናስተውላለን፡፡

ትዕዛዝ የሚለውን ቃል ስንሰማ ግብረ-ገብነት ነው ወደ አዕምሯችን ፈጥኖ የሚመጣው፡፡ እንደ አትስረቅ፤


አትዋሽ፤ አታመንዝር፤ በጎረቤትህ ላይ በሀሰት አትመስክር ወዘተ. ያሉት፡፡ በቅዱስ ቃሉ የመጀመሪያው
ምዕራፍ ማለትም ኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያቀረበውን ሀሳብ ሳይሆን ትዕዛዝ
ብዙውን ጊዜ እንዘነጋዋለን፡፡ ፈጣሪ ለሰው ልጅ በዚህ ቃሉ ትልልቅ ስኬቶቹን ዘረዘረለት፤

ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፡፡ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ


የሚንቀሳቀሱትንም ግዙአቸው፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡28)

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ የፈጠረበት ዓላማ እና ምክንያት በዚህ ጥቅስ ቁልጭ ተደርጎ ተቀምጧል፡፡ በእርግጥ
በዘመናትና በብዙ ጊዜያት እነዚህ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያስቀመጣቸው ዓላማዎች ወደ ጎን ተብለውና
ተጥሰው እናያለን፡፡ በመሆኑም ይኼንን ክስተት ‹የተዘነጋው ትዕዛዝ› ልለው ተገድጃለሁ፡፡

ማይልስ ሙንሮ በዚህ አሁን በምታነቡትና በዓላማ እና እምቅ-አቅም ላይ ትኩረቱን ባደረገው አዲሱ ሥራው
እነዚህን የተዘነጉ ትዕዛዛት በአንክሮ ይመለከታል፡፡ ልክ አስፈላጊዎቹን መሣሪያዎች ሁሉ ዝግጁ አድርጎ ለንቅለ-
ተከላ እንደተሰማራ ሐኪም ሙንሮም የተለያዩ ማስረጃዎችን በርብሮ፤ ቀዶና መርምሮ የሰው ልጅ በዚህች
ምድር ላይ ሳለ የተቀመጠለትን ዓላማ እና እምቅ-አቅሙን አዛምዶ ይመለከታል፡፡

በጥቅም ላይ ያልዋለ አዕምሮ እጅግ ያሳዝናል

ሲባል ብዙዎቻችን ሰምተናል፡፡ እውነትም ነው፡፡ ነገር ግን በጥቅም ላይ ያልዋለ ወይ የባከነ ዓላማ እና እምቅ-
አቅም ደግሞ እንደ እኔ ከሆነ ይበልጥ ያሳዝናል፤ ያስቆጫልም፡፡ ‹‹ለምን ይሆን ወደዚህች ምድር የመጣሁት
ለምንስ ነው የተፈጠርኩት ሕይወትስ አስፈላጊነቷ ምንድነው›› የሚል ጥያቄ የሚመላለስብዎ ከሆነ
እንግዲያውስ ይህ መጽሐፍ አለጥርጥር የግድ ያስፈልግዎታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በሕይወት መንገድ ላይ ዓላማዎት ምን እንደሆነ ለማወቅ እየሞከሩ ግን በጨለማ ገና
እየተደናበሩ ይሆናል፡፡ እርስዎ ያሉበት ሁኔታ ይኼ ከሆነም ይህ መጽሐፍ እጅግ በጣም ይመከራል፡፡ መጽሐፉን
ያንብቡት፤ በጥልቀት ያስቡበት እንዲሁም ቁምነገሮቹን ያብላሏቸው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ የተቀመጡትን

6|Page
ቁምነገሮች እና አስተምህሮቶች ተረድተው ለመተግበር የሚያደርጉት ጥረት በሕይወትዎ እጅግ አመርቂ
ለውጥ እንዲያመጡ ይረዳዎታል፡፡ በተጨማሪም ደግሞ ዓላማዎትን እና እምቅ-አቅምዎትን ፈልገው
በማግኘትዎ ዓለም በጣም የተሻለች ሥፍራ ትሆንልዎታለች፡፡

ዶ/ር ፍሬድሪክ ኬ.ሲ. ፕራይስ

Crenshaw Christian Center

Los Angeles, California

እንደ መንደርደሪያ

በዚህች ዓለም ላይ ከማንም በላይ ያጣና የነጣው የመጨረሻው ደሀ ማን ነው ቢባል የማያልመው ሰው
በመሆኑ ላይ ልንስማማ ይገባል፡፡ ሕልም እያለመ ነገር ግን ቅዠት ሆኖ እና ተፈጻሚ ሳይሆን የሚቀርበት ሰው
ደግሞ ከማንም በላይ በሕይወቱ ተስፋ የቆረጠና ያዘነው ነው፡፡ በዚህች ምድር ላይ ያለው እያንዳንዱ
ግለሰብ--ባሕሉ፤ ፆታው፤ ዘሩ፤ የቆዳ ቀለሙ፤ ዜግነቱ፤ የኢኮኖሚ ደረጃው--ምንም ሆነ ምን ግን ሕልም
ወይንም ሕልም ሊባል የሚችል ነገር አለው ብዬ አምናለሁ፡፡ ልጆች ሕልም እንዲያልሙ የሚያደርጋቸው
በፈጣሪ የተለገሣቸው ደመ-ነፍሳዊ ስጦታ ነው፡፡ የትም ተወለድን የት በልጅነታችን ሁላችንም የሆነ ነገር
አልመናል፡፡ ይኼ ሕልም እልም ባለ የገጠር ጫካ ውስጥ ባለም ሆነ በእብነ-በረድ በተንቆጠቆጠው ምቹ
የመሳፍንትና የጌቶች ቤት ውስጥ ይታለም ቁምነገሩ ግን የዓላማችን ነጸብራቅ መሆኑን ልናውቀው ይገባል፡፡
በእኛ ግምታዊ አፈር ላይ የተዘራ የእጣ ፈንታ ዘር ነው ብሎ መናገርም ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ
በውስጣችን የተደበቀውን ክህሎት ማውጣት እንችል ዘንድ ይኼንን የዓላማችን ነጸብራቅ የሆነውን ሕልም
እና ለዚያ የሚረዳውን የግምት ተሰጥዖ በውስጣችን አኑሯል ብዬ በጽኑ አምናለሁ፡፡ ዓላማ ማለት አንድ ነገር

7|Page
የተሰራበት ምክንያት ነው፡፡ አንድን ነገር እውን ለማድረግ በጥቅም ላይ የሚውለው መሣሪያ የሚሰራለት
ነገርና መዳረሻ ነው--ዓላማ፡፡ ለእኛ የተሟላና ስኬታማ ሕይወትም ቁልፉ ነው፡፡

ማንኛውም አምራች ቢሆን አንድን ምርት ወደ ገበያ የሚያወጣው አንድን ዓላማ ከዳር ለማድረስ እንደሆነ
ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ማንኛውም ምርት ቢሆን ዲዛይን የሚደረገው በአምራቹ አዕምሮ ውስጥ
የተፀነሰውን ዓላማ እውን ለማድረግ ሲባል መሆኑም ሊጠቀስ ይገባል፡፡ ከዚህ ተነስተን የአንድ ምርት እምቅ-
አቅም የሚወሰነው በተሰራበት ዓላማ ነው ማለት እንችላለን፡፡ ይኼ እኔን እና እርስዎን ጨምሮ
ለእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ የአንድ ዘር ዓላማ ዛፍን ማብቀል ነው፡፡ በመሆኑም ዘር
ዓላማውን የማሳካት እምቅ-አቅም በውስጡ አለ፡፡ ይሁንና ዘር ጥቅጥቅ ያለ ደን የመሆን እምቅ-አቅም
ስላለው ብቻ ያንን ያደርጋል ማለት አይደለም፡፡ በተፈጥሮ እጅግ አሳዛኝ ከተባሉት እውነታዎች መካከል አንዱ
የዘር መጥፋት ወይንም ዘር ከአፈሩ የመለየቱ ክስተት መሆኑን እናውቃለን፡፡ በዚህ የተነሳ የዘር መሞት የደን
ግብዓተ-መሬት ነው፡ ችሎታ ቢኖር ይመረጣል፤ ደስ ይላል፤ ይሁንና ችሎታን ሳይጠቀሙበት መቆየት የከፋ
ነው፡፡

ሕይወትዎ የእርስዎን ዓላማ ከዳር የማድረስ እምቅ-አቅም አላት፡፡ ይሁን እንጂ ይኼንን እምቅ-አቅም ካገቱት
ሕይወትዎን ዓላማ የማሳካት ዕድሏን ያጨናግፉባታል፤ ከስኬትም አፍነው ያስቀሯታል፡፡ እርስዎ እና በዚህች
ምድር ላይ ያሉ ሌሎች ግለሰቦች ሁሉ ድንቅ ቅርስ አላችሁ፡፡ ግን በየዕለቱ ከዚህ ድንቅ ቅርስ እጅግ የበዛው
ይቀበራል--ምንም ሳይነካና ሳንጠቀምበት፡፡ ጥቂት ድፍረት በማጣት ብቻ ብዙ ታለንት፤ የፈጠራ አቅም እና
ክህሎት ይባክናል፡፡ በጣም ብዙ፤ ዕልፍ-አዕላፍ የሆኑ የማይታወቁ ሰዎች ወደ ዘለዓለም ሕይወት
ያልተጠቀሙበትን አቅም ይዘው ይሄዳሉ፡፡ ከክህሎት ጋር መኖር ኃላፊነትን ያጎናጽፋል፡፡ ክህሎት ይዞ መሞት
ኃላፊነትን አለመወጣትን ያሳያል፡፡

ማንኛውም ፍጥረት በመቀበል እና መስጠት ቀላል መርህ ይጠቀም ዘንድ ነው ዲዛይን የተደረገው፡፡ ሕይወትም
በዚህ መርህ ላይ የተንጠላጠለች ናት፡፡ ለምሳሌም እንበልና ተክሎች በውስጣቸው ያለውን ንጹህ አየር፤
አልያም ደግሞ እኛ የሰው ልጆች ደግሞ የምናመነጨውን ቆሻሻ አየር ለመልቀቅ እምቢ ብንልስ ያኔ ምድር
ባጠቃላይ በታላቅ ቀውስ ውስጥ ትወድቃለች፤ ሞትም ይንሰራፋል፡፡ ያልተጠቀምንበት እምቅ-አቅም ዋጋ-ቢስ
ብቻ ሳይሆን አደገኛም ጭምር ነው--ሊያወጣው ላልፈለገውም ሆነ አብሮት ለሚኖረው ሁሉ፡፡ ያንቀላፋና
የማይንቀሳቀስ እምቅ-አቅም ጤናማ፤ ጥቅም ያለው፤ አስተማማኝም ሆነ ውጤታማ አይደም፡፡ በመሆኑም
እርስዎ ትልቁ የእምቅ-አቅም ክምችትዎ የተሰጠዎ የሌሎችን ሕይወት እንዲያዳብሩበት መሆኑን ሊረዱት
ይገባል፡፡ እምቅ-ኃይል አለጥቅም ሲቀመጥ ራስን ያጠፋል፡፡

ለእኔና ለእርስዎ የተሰጠን ድንቅ እምቅ-አቅም በውስጣችን እንዳለ የሚወጣበትና በጥቅም ላይ የሚውልበትን
አጋጣሚና ጥያቄ ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህች ዓለም የተሻለ ነገር እንፈጥርበት ዘንድ በውስጣችን

8|Page
ያስቀመጠውን አውጥተን የመጠቀም ኃላፈነት አለብን፡፡ ብዙዎቻችን በውስጣችን ያለውን ክህሎት
እናውቃለን ሆኖም ያንን ችሎታ ለማውጣት ከዚህ ቀደም ሞክረን አልሳካ ስላለን ተስፋ ቆርጠናል፡፡
አንዳንዶቻችን ለዚህ ታሪካዊ ሁኔታዎችን ነው ተጠያቂ የምናደርገው፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ በማኅበረሰቡ ውስጥ
ባለን ደረጃ ላይ ጣታችንን እንቀስራለን፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ ብዙ ሰው ከሚመኘው እና ምርጥ ከሚባለው
የተለየ ሕይወት መኖራችንን እና መደበኛ ትምህርት አለማግኘታችንን ለዚህ ተጠያቂ እናደርጋለን፡፡

በበርካታ ዓመታት ጊዜ ውስጥ የደረስኩበት ድምዳሜ ቢኖር እግዚአብሔር በውስጣችን ያኖረውን የዘር
እምቅ-አቅምዲህ አልቆ የወጣው በርካታ ለማጥፋታችን ምንም ዓይነት ምክንያት ብንደረድር ተቀባይነት
የሌለው መሆኑን ነው፡፡ ቀድሞውንም እንድንሆነው የተፈጠርነውን ሰው ልንሆነው እንችላለን፡፡ እርስዎን
ማቆም የሚችሉት እርስዎ ብቻ ነዎት፡፡ የሚኖሩበት አካባቢ ምንም ሆነ ምን አመለካከትዎን እና ውስጣዊ
ከባቢ ሁኔታዎን ለዘርዎ ዕድገት ምቹ በሆነ መልኩ የመቀየር ችሎታ ግን አለዎት፡፡ ይህ መጽሐፍ እምቅ-
አቅምዎን አውጥቶ ለመጠቀም የሚረዱ መርሆዎችን መረዳት እና ወደ ተግባር ለመቀየር የሚረዱዎትን
መርሆዎች ለእርስዎ ለማሳየት ተዘጋጅቷል፡፡ እስከ ዛሬ እምቅ-አቅማቸውን ሳይጠቀሙ በመቃብር ቦታዎች
የተከማቹት ይበቃሉ--እርስዎ በአዲስ ጎዳና መጓዝ አለብዎት፡፡ እርስዎ ድንቅ እምቅ-አቅምዎን ካወጡት
ቀጣዩ ትውልድ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ዓለም ለቀጣዩም ሆነ ለዚህ ትውልድ ጥቅም እግዚአብሔር ያኖረልዎትን
እምቅ-አቅም አውጥተው በሚገባ መጠቀምዎን ይፈልጋል፡፡

ያለ ጥቅም ተቀምጦ ያለውን ይበጥቡጡት፡፡ ክምችቱን ያውጡት፡፡

9|Page
መግቢያ

በታሪካዊቷ የሎንዶን ከተማ በሚያንዘፈዝፍ፤ ጭፍግግ ባለና በዝናብ በታጀበ አንድ የወረሐ መስከረም እሁድ
ቀን ከቀትር በኋላ ነው፡፡ አንድ ወዳጃችን ቤት ሄደን የቀረበልንን ጣፋጭ ምግብ አጣጥመን እንደጨረስን
ጋባዣችን ጭር ባለው እና ደስ በሚለው የመኖሪያ አካባቢ ትንሽ በእግር ሸርሸር እንድንል ሀሳብ አቀረበ፡፡ እኔ
እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ለስምንት ቀናት ያህል በጣም የተጣበበ ጉዞ እና ሌሎች ፕሮግራሞች ኖረውብኝ
ተወጣጥሬ ነበረና ዕድሉ ሲገኝ በጽጥታ በእግር ሸርሸር የማለትን ዕድል በደስታ ተቀበልኩት፡፡

እጅግ በንጽህና እና ማራኪ በሆነ ሁኔታ ተይዞ ባለው የመኖሪያ መንደር ስንንጎራደድም ልክ እንደ እኛው
ዓይነት ሀሳብ ያላቸው ብዙ ሰዎች መሆናቸውን ተረዳን፡፡ ጋባዣችን በርካቶቹን አዕዋፋት፤ ተክሎች፤ አበቦች
እና አረንጓዴ መገለጫቸው የሆኑ ፍጡራንን ሲያሳየኝ ደስ ብሎታል፡፡ ትንሽ ሄድ እንዳልን አንድ በዕድሜ የገፉ
ሰው ጋባዣችንን ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥተውት ማውራት ሲጀምሩ ጉብኝቱ ተቋረጠ፡፡ ጋባዤ ከሰውየው ጋር
አስተዋውቆኝ ሁለቱ ወሬ ጀመሩ፡፡ እኔም ያኔ የቋመጥኩለትን ብቻዬን በዚያ ጭር ባለ የመኖሪያ ሥፍራ
የመንጎራደድ ፍላጎቴን እውን የማደርግበትን አጋጣሚ ነጠል በማለት አጣጣምኩት፡፡ ሆኖም ጥቂት በደስታ
እንደተጓዝኩ ቀጠን ያለው መንገድ ወደ አንድ ዕድሜ-ጠገብ መቃብር መግቢያ አደረሰኝ፡፡ ለታሪክ ያለኝ
ፈጽሞ የማይሞት ፍላጎት የመቃብሮችን ታሪካዊ ተፈጥሮ እንዳይ ገፋፋኝና አብሬ በመቃብሮቹ ላይ
የሰፈሩትን የተለያዩ መረጃዎችም አነበብኩ፡፡ በእውነት የሚገርም ተሞክሮ ነበረ--በነዚያ ቃል በማይወጣቸው
ድንጋዮች ላይ የተጻፉትን ስሞች፤ ቀኖች ወዘተ. ማንበቡ፡፡ ለምሳሌም ‹‹ጆን ሂል በ 1800 ተወልደው በ 1864
አረፉ›› ወይንም ‹‹ኤልሳቤት ሮቢንሰን በ 1790 ተወለዱ፤ በ 1830 አረፉ›› የሚሉትን ሳነብ የተቀበሩ
የእንግሊዝ ታሪኮችን ነው ማሰብ የጀመርኩት፡፡

በመቀጠል ደግሞ አንድ ትንሽ ምናልባትም ከሶስት ጫማ ቁመት የማይበልጥ መቃብር አየሁ፡፡ ‹‹ማርከስ
ሮጀርስ በ 1906 ተወለዱ፤ በ 1910 አረፉ›› ይላል፡፡ ከዚህ አሳዛኝና ልብን እጅግ ከሚነካ መረጃ ስር፤
‹‹ብትሄድም የማንረሳህ›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ በዚህ መልኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ መቃብሮችን እና መረጃዎችን
ከተመለከትኩ በኋላ ግን ዓይኔ አሁንም በሕጻኑ መቃብር ላይ ተመልሶ አረፈ፡፡ ጥልቅ ሐዘን ወደ ውስጤ ገባ፡፡
ወዲያው ደግሞ በሁሉም መቃብር ላይ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ፤ ‹‹ነፍስሽን/ህን በገነት ያኑር!››
የሚለው ጽሁፍ አለ፡፡ ያን ጊዜም በርካታ ጥያቄዎችና ሀሳቦች በአእምሮዬ ተመላለሱ፡፡ ለመሆኑ የዚህ ልጅ
ቤተሰቦች እነማን ይሆኑ የሕጻኑ ሞት መንስዔስ ምን ነበረ ምን እንዲያከናውን ይሆን የተወለደው ፈጽሞ
ያልታዩትና ማንም ያልተጠቀመባቸው የዚህ ልጅ የተለዩ ታለንቶች እና ተሰጥዖዎች ምን ይሆኑ ከዚህ ህጻን
ልጅ ጋር ምን ያህል የጥበብ ሥራዎች፤ መዝሙሮች ወዘተ. አብረው ተቀበሩ ይሆን

10 | P a g e
መልሱ ፀጥታ ሲሆን እኔም የሕጻኑን መቃብር ከበው በሚገኙት የሌሎች በርካታ ሰዎች መቃብሮች ላይ
ጥያቄዎቹን አንከባለልኩ፡፡ በእርግጥ ዕድሜዎቹ ይለያዩ እንጂ ለ 40፤ 50፤ 60 ወይ 70 እና ከዚያ በላይ
የሚቆጠሩ ዓመታትን በሕይወት የቆዩ ሰዎች መሆናቸውን ተረዳሁ፡፡ ሆኖም በዚህች ምድር ለመቆየታቸው
ማስረጃው፤ ‹‹ነፍስህን በገነት ያኑርልን›› የሚለው ጽሁፍ ብቻ ሆነ፡፡ ወዲያውኑ ግን እንዲህ የሚል ጥያቄ
በአዕምሮዬ መጣ፤ አንድ ሰው እምቅ-አቅሙን በሙሉ ይዞት መቃብር እየገባ እንዴት ነው ነፍሱን በገነት
አምላክ እንዲያኖርለት የሚጠየቀው ያ በጉም መሰል ጢስ የታጀበውና በብርድ የሚያንዘፈዝፈው ዝናብ
በጉንጮቼ ላይ ጠብ ጠብ ማለት ሲጀምር እንዲህ እያልኩ በማሰብ መጓዝ ጀመርኩ፤ አንድ ሕጻን አንዱንም
እምቅ-አቅሙን ማወቅና ማውጣት በዚህ ጨቅላ ዕድሜው ሲሞት ምንኛ ያሳዝናል!

ወዲያው አንድ ዝግ ያለ ድምጽ በአዕምሮዬ ውስጥ አቃጨለ፡፡ ሕጻኑስ መቆጣጠር በማይችለው ሁኔታ ይኼንን
ሳያደርግ አልፏል፡፡ ነገር ግን ሸብተውና ዕድሜ ጠግበው ግን ምንም ተሰጥዖዋቸውን ሳያወጡና ሳይጠቀሙ
መቃብር የሚወርዱት ሰዎች ይበልጥ አያሳዝኑም እንግዲህ እርስዎም ቢሆኑ በውስጥዎ ያለውን፤ ገና
ያላወጡትን እምቅ-አቅም ለመቃብር አሳልፈው እንደማይሰጡት ተስፋዬን እየገለጽኩ መግቢያዬን ለቀጥል፡፡

በምድራችን ላይ የኗሪው ቁጥር ይኸው አሻቅቦ ሰባት ቢልዮን ደርሷል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ለየት ያለ፤
ኦሪጅናል እና ትልቅ ዋጋ ያለው ነው፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ በጂን የሚለያይ እና አሻራው እንኳ ፈጽሞ ሊባዛ
የማይችል መሆኑን ለዚህ በማስረጃነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዛሬ በዚህች ምድር ላይ የእርስዎ ባሕሪና ክህሎት
በትክክል ያለው ማንም የለም፡፡ ማናችንም--ጥቁር ሆንን ነጭ፤ አጭር ሆንን ረጅም፤ ሀብታም ሆንን ደሀ--
በዕጣ ፈንታ ተጸንሰን፤ በዓላማ ተሰርተን ትርጉም ያለው ሕይወት እንኖር ዘንድ እምቅ-አቅም ተሰጥቶናል፡፡
በእርስዎ ውስጥ ጥልቅ ቦታ ላይ ለመባዛት እየጠበቀ ያለ የትልቅነት ዘር ተዘርቷል፡፡ እርስዎ በተፈጥሮ ታለንት፤
ተሰጥዖ፤ መሻት እና ሕልሞች የታደሉ ነዎት፡፡ በማንኛውም ባሕል፤ ዘር እና ማኅበረ-ኢኮኖሚ ደረጃ ውስጥ
የሚገኝ የሰው ልጅ ሁሉ ይኼንን እምቅ-አቅም የማሳየት ደመ-ነፍስን ይዞ ይኖራል፡፡

ፍጥረት ሁሉ ይኼንን የእምቅ-አቅም መርህ ይጠቀማል፡፡ ማንኛውም ፍጡር ቢሆን ችሎታውን የማውጣት
ተፈጥሯዊ ደመ-ነፍስ አለው፡፡ ፈጣሪ ማንኛውንም ነገር በዚህ የእምቅ-አቅም መርህ ዲዛይን ያደረገው ሲሆን
ይኼም በዘር ጽንሰ-ሀሳብ ቀለል ብሎ ቀርቧል፡፡ በቅዱስ ቃሉም ላይ፤

ምድርም ዘርን የሚሰጥ፤ ሣርን እና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን
እንደ ወገኑ አበቀለች፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡12)

ይለናል፡፡ እንግዲህ መሠረታዊ የሆነውን እውነታ ስንመለከት ማንኛውም ፍጡር ዓላማውን ለማሳካት እና
አሁን ካለው በላይ ለመስራት እምቅ-አቅሙ ተሰጥቶታል፡፡
11 | P a g e
አንድ ማስተዋል የሚገባዎት ነገር አለ፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር ምድርን ፈጥሮ የሰውን ልጅ ደግሞ በኤደን
ገነት ባኖረው ጊዜ ለሰው ልጅ ያለቀለት ነገር እንዳልሰጠው ነው፡፡ እግዚአብሔር ምንም እንኳ ሰው ምግብ፤
መጠለያ፤ ልብስ፤ መጓጓዣ እና ሌሎች ምቾቱን የሚጠብቁለትም ነገሮች እንደሚያስፈልጉት ቢያውቅም
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ግን ባንድ ጊዜ ለሰው ልጅ ዝርግፍ አድርጎ አላቀረበም፡፡ ይልቅ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ
አዘዘው፤

ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፡፡ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር


ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ግዙአቸው፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡28)

እነዚህ ትዕዛዛት እያንዳንዳቸው የሰው ልጅ የመብዛት፤ የመባዛት፤ ምድርና በውስጧ ያሉትን ሁሉ የመግዛት
ገና ያልወጣ፤ በጥቅም ላይም ያልዋለ እምቅ-አቅም አለው በሚለው እሳቤ ላይ ነው የተመሠረቱት፡፡ ይህ
ትዕዛዝ ከዚህም በተጨማሪ ፍሬያማነት (ማለትም የተደበቀ ሕይወትን ማውጣት) እንዲሁም መብዛት
(የተደበቀ ሕይወት መባዛት) በእግዚአብሔር ላይ ሳይሆን ዘሩን በያዘው ሰው ላይ የተንጠላጠሉ ነገሮች
መሆናቸውን ጭምር ይጠቁማል፡፡

እርስዎ እግዚአብሔር አምላክ የሰጠዎትን ሁሉ ለማሳካት የሚያስፈልገው ክህሎት አለዎት፡፡ ፈጣሪ ይኼንን
ውድ ዘር በማውጣት የሱን ትዕዛዝ ለመፈጸም እንጠቀምበት ዘንድ ይፈልጋል፡፡ እምቅ-አቅምን ማውጣት
ደግሞ የእግዚአብሔር ሳይሆን የእርስዎ ፈንታ ነው፡፡

ሄንሪ ፎርድ ባንድ ወቅት፤

ለእኔ ከሁሉም የሚበልጥብኝ ወዳጅ ማለት በውስጤ ያለውን ምርጡን የሚያወጣልኝ ነው

ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በዙሪያችን ላሉት ሁሉ እና ለመላው ዓለም ጥቅም ስንል በውስጣችን


የተደበቀውን አቅም ማውጣት እንችል ዘንድ ተመራጩና ከማንም የበለጠው ወዳጃችን ይሆናል የሚል
ተስፋዬን እገልጻለሁ፡፡

ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የራሴን እና የሌሎችን እምቅ-አቅም በመረዳት፤ በማሰራት፤ በማውጣት እና
በመጠቀም አሳልፌያለሁ፡፡ በዚህ ጥረቴ ውስጥ ትልቅ ቦታና ግምት የሚሰጠው ደግሞ በዚህች ዓለም ላይ በዚህ
ረገድ ተምሳሌት የሚሆኑንን በርካታ ሰዎች ተሞክሮዎች መመልከትና ማኅበረሰባቸው ላይ ምን ተጽዕኖ
እንዳሳረፉ መረዳት ይገኝበታል፡፡ በዚህም የተነሳ ማንኛውም ግለሰብ ቢሆን ብቃቱን ለመለካት ከሚደረግ
ከማንኛውም ሙከራ በጣም ከሚልቅ እምቅ-አቅም ጋር እንደተፈጠረ አምናለሁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
ግለሰቡ የሚኖርበት ውጫዊ ከባቢ ሁኔታ ምንም ሆነ ምን ይኼ እምቅ-አቅም ግን ዋጋ እንዳለው ጭምር

12 | P a g e
እምነቴ ነው፡፡ ያደረግኳቸው ጥናቶች እና ተሞክሮዬም እንደሚያሳዩኝ ከሆነ ይኼ እምቅ-አቅም ከዚህ ቀደም
እግዚአብሔር በውስጣቸው ያስቀመጠውን ሁሉ አሟጠው በመጠቀም የሚታወቁ ሰዎች የተጠቀሙባቸውን
መርሆች ተግባራዊ በማድረግ ይበልጥና በተሻለ ሁኔታ ሊወጣ ይችላል፡፡ ሰዎቹ ምንም ዓይነት ዘር፤ ቋንቋ፤
ባሕል፤ የኢኮኖሚ ሁኔታ፤ አኗኗር ወዘተ. ቢኖራቸውም መርሆቹ ግን በሁሉም ውስጥ ታይተዋል፡፡

ማንኛውም ሰው ቢሆን ትልቅ እምቅ-አቅም እና ይኼንን አቅም የሚያወጣበት ክህሎት እንዳለው የገለጽኩ
ቢሆንም በሌላ በኩል ግን ሁሉም ሰው ደግሞ ፈጣሪ የፈለገውን ያህልና ሁሉ ሆኖ እንደማይገኝ ስገልጽ
በሀዘኔታ ነው፡፡ ዛሬ በርካታ ሰዎች የሚኖሩበት ከባቢ ሁኔታ ሰለባዎች በመሆናቸው የተነሳ በሌሎች
አስተያየትና አስተሳሰብ ራሳቸውን በገዛ እጃቸው ጠልፈው ጥለዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በራሳቸውና በሌሎች
የተጣሉባቸውን ገደቦች ለማለፍና እምቅ-አቅማቸውን ለማጎልበት ወኔው የላቸውም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በየትኛውም ዕድሜና ሁኔታ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ቢሆን ከፈለገ ራሱን ሊቀይር
ይችላል፡፡ ያሉትን ማነቆዎች ለማለፍ እና እግዚአብሔር ባስቀመጠን ልክ ለመገኘት ከፈቀድን ቀድሞውንም
እንድንደርስ የተፈለግንበት መድረሳችን አይቀርም፡፡ የሚጎዳን የማናውቀው ሳይሆን የተሳሳተውና
የምናውቀው ነው፡፡

ይህ መጽሐፍ ለዘመናት የኖሩባቸውን፤ የተቀረጹባቸውን እና ትክክል ናቸው ብለው ሲያምኑባቸው


የቆዩዋቸውን አመለካከቶች ማጥራት ነው፡፡ በውስጥዎ ያለውን ጥልቅ ክህሎት፤ ጓደኞችዎ እና አቻዎችዎ
ፈጽሞ ያላዩዋቸውን እና ክምችት ውስጥ ያሉ ነገሮችን እንዲያወጡ ማደፋፈር እና ልውጣ እያለ
የሚጨቀጭቅዎትን ጸጥ ያለ ግን የተትረፈረፈ የእምቅ-አቅም ሀብት እንዲያወጡ ማደፋፈር ትልቁ ዓላማዬ
ነው፡፡ ይኼንን መጽሐፍ አንብበው ሲጨርሱ የተገለጸው እውነታ የተፈጥሯዊ አስተሳሰብዎ አካል እስኪሆን እና
እምቅ-አቅምዎን መረዳት እና ማውጣት ቀድሞም ልክ እግዚአብሔር ይፈልገው እንደነበረው ራስን መሆን
እስኪሆን ድረስ ጭምር መደጋገምዎን ይቀጥሉ፡፡ተአምራጨምቀው በሰሩት ውነት ለመናገር ይኼ እናንተ
ለሚያምነው ምንም የማይቻል ነገር የለም፡፡

ዘር እስኪወጣ ድረስ ዛፍ ይበቅላል


ከሚል ተስፋና ቃል የዘለለ አይደለም፡፡

13 | P a g e
ምዕራፍ 1

____________________ _____________________

የሚያሳዝነው፤ ያልወጣና በጥቅም ላይ ያልዋለ እምቅ-አቅም

የአንድ ዘር ሞት የደን ግብዓተ-መሬት ነው፡፡

ለአሥር ሰዓታት ያህል በሰማይ እንደ አሞራ ያደረግነው ጉዞ እየተጠናቀቀና ቁልቁል እየወረድን መሆናችንን
የሚያበስረው ድምጽ በኢንተር-ኮም ሲሰማ ወሰድ-መለስ ሲያደርገኝ ከነበረው እንቅልፍ ባነንኩ፡፡
የሚጠብቀኝን በማሰብ ለማረፍም ተዘጋጀሁ፡፡ ወደ ደቡብ አሜሪካዋ ታላቅ አገር ብራዚል ገና ለመጀመሪያ
ጊዜ ነበረ የምጓዘው፡፡ የምሄድበት ዓላማ በቁጥር እስከ አስር ሺህ ለሚደርስና መሪዎችና ተራውን ሕዝብ የያዘ
ተጋባዥ ፊት ንግግር ለማድረግ ነበረና ከበድ ያለ ኃላፊነት ተሰማኝ፡፡ በዚህች በኅብረ-ብሔራዊነት እና
ውስብስብ ባሕሎች ብሎም አኩሪ ቅርስ በምትታወቀዋ አገር ያደረግኩት ቆይታ በሰው ልጅ አንድነት ላይ
ትልቅ ትምህርትን ሰጠኝ፡፡ አንዳንድ አነስተኛ ልዩነቶች ይኑሩን እንጂ ሁላችንም የሰው ልጆች አንድ
የመሆናችንን እውነታ አረጋገጠልኝ፡፡

14 | P a g e
ለሰባት ቀናት ያህል ከቆየን በኋላ እንግዳ ተቀባይ ሆኖ አብሮኝ የቆየው እና አስተርጓሚዬ ውቧን የብራሲሊያ
መዲና አስጎበኘኝ፡፡ እጅግ ያማረችውን፤ በብዙ ሕንጻዎቿ የምትታወቀውን ከተማ ተዘዋውረን ከጎበኘን በኋላ
ሁሌም ስጓጓለት ወደነበረው ሥፍራ አቀናን--ብሔራዊ ሙዚየም፡፡ የጥበብ እና የታሪክ አድናቂ በመሆኔ እንዲህ
ዓይነት ጉዞ በየአገሩ ማድረግ እወዳለሁ፡፡

በዚያች ቀን በብራሲሊያ ያደረግኩት ጉብኝትም በዚህ መልኩ የተደረገ ነው፡፡ ለዚህች ውብ ምድር እና
ስዘዋወር ላየኋቸው ቅርሶች ትልቅ አድናቆት ተሰማኝ፡፡ እጹብ-ድንቅ የሆኑ ታሪካዊ ዳራዎችን እና የዚህችን
አገር የቀድሞ እና ወቅታዊ ዝና የሚያንጸባርቁ በምንም ዓይነት ዋጋ ሊተመኑ የማይችሉ ትሩፋቶችን
ስመለከት እያንዳንዱ ሥዕል፤ ቅርጻ-ቅርጽ እና ታሪክ ፈጽሞ የማይዘነጋው ግለሰብ አንድ ሰው እምቅ-አቅሙን
የማውጣቱ ውጤቶች መሆናቸውን ተረዳሁ፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ የጥበብ ሰዎች በሕይወት ባይኖሩም
ሥራዎቻቸው ግን ሕያው ናቸው፡፡ ከአንድ ሥራ ወደ ሌላው በተሻገርኩ ቁጥር ተቀብሮ ያልቀረን እና የወጣን
የጥበብ ሰዎች እምቅ-አቅም አስተዋልኩ፡፡ በውስጣቸው ተደብቆ የነበረውን ታለንት ለማውጣት
በመቁረጣቸው ዛሬ እኔና ብዙዎች ከታላቅ ግምታዊ ክህሎት በመነጩት ሥራዎቻቸው እንደሰታለን፤
እናደንቃለን እንዲሁም እንደመማለን፡፡

በታሪክ ውስጥ የግለሰቦች ትንንሽም ይሁኑ ትልቅ ሥራዎች--ሥዕሎች፤ መጻሕፍት፤ ሙዚቃ፤ ግጥም፤
ድራማ፤ ሥነ-ሕንጻ ወይንም የልማት ሃልየቶች--የብዙዎች ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ፈጥረዋል፡፡
የማኅበረሰባችንን ዕጣ ፈንታ በመቅረጹ አስተዋፆ የነበራቸው--እኛን ያስተማሩን እና ያነሳሱን ሁሉ--በታላቅ
ፍላጎት እምቅ-አቅማቸውን የተጠቀሙ ሲሆን ሁኔታዎች የወደፊት ጊዜያቸውን እና ዕጣ ፈንታቸውን
እንዳይወስኑባቸው የሚችሉትን ሁሉ አደረጉ፡፡ በብራዚል የጎበኘሁት ሙዚየም ልክ በመላው ዓለም
እንደሚገኙ ሙዚየሞች ሁሉ አንድ በወቅቱ በሕይወት የነበረ ሰው ሞት በእምቅ-አቅሞች ላይ የመጨረሻውን
ውሳኔ እንዳያሳልፍ አልፈቅድም ስለማለቱ ያስታውሰኛል፡፡ የእነዚህ ሰዎች የወጣና በጥቅም ላይ የዋለ እምቅ-
አቅም የዓለም ውርስ ነው፡፡

እኔ በተጨማሪም ምድር ራሷ ሙዚየም መሆኗን አምናለሁ፡፡ እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው


አንድ የምንፈጽመው ዓላማ ተቀምጦልን ነው፡፡ እግዚአብሔር የወደፊቱ ትውልድ ይማርበት እና ይነሳሳበት
ዘንድ እንድንተው አንድ ነገር ሰጥቶናል፡፡ እነዚህን ኃላፊነቶች የመወጣት እና ዳር የማድረስ ክህሎት
በእያንዳንዳችን ውስጥ አለ፡፡ ለዚህ የሚጠቅሙ መሣሪያዎች ደግሞ ተፈጥሯዊ ታለንቶቻችን፤
ተሰጥዖዎቻችን እና ምኞቶቻችን ናቸው፡፡

እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው አንድ የምንፈጽመው ዓላማ ተቀምጦልን ነው፡፡

15 | P a g e
በውስጥዎ ተኝተው እና ተቀብረው ያሉ ክህሎቶችን የማነሳሳት ኃላፊነትዎን ካልተቀበሉ ቀጣዩ ትውልድ ወደ
ሕይወት ሙዚየም ገብቶ በምድር ማሳያው ላይ ባዶ ነገር ማየቱ አይቀሬ ነው፡፡ ከምድር ማሳያ ቦታው ስር
የሚለጠፈው ጽሁፍም፤

ዓላማው ሳይሳካ፤ እምቅ-አቅሙም ሳይወጣ የቀረ

የሚል ይሆናል፡፡

 የክህሎት ውርጃ 

የትልቅነት ዋጋ ኃላፊነት ነው

እነዚህን ቃላት የተናገሩት ዊንስተን ቸርችል ነበሩ፡፡ በዚህ አባባል ውስጥ የተካተቱ እውነታዎች ልንጠብቃቸው
እና ልንጠነቀቅባቸው ይገባሉ፡፡ ዛሬ በየመቃብሩ ለትልቅነታቸው ኃላፊነት ባለመስጠታቸው የተነሳ ትልቅ
መሆን ሳይችሉ ቀርተው በመከኑ ሰዎች ነው በአመዛኙ የተሞሉት፡፡ ይኼ ያልተጠቀምንበት ክህሎት እምቅ-
አቅም ይባላል፡፡ እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የምንመጣው ፈጽሞ ገደብ-የለሽ እምቅ-አቅምን ታጥቀን
ነው፡፡ በመሆኑም ዛሬ ከሆንነው እና ከምናከናውነው በላይ ማከናወን የምንቸል ነን፡፡ ይሁን እንጂ በውስጣችን
ያለውን እስካላወጣን ድረስ እምቅ-አቅማችን መክኖ ይቀራል፤ ውርጃ ይፈጸምበታል፡፡

ዛሬ በየመቃብሩ ለትልቅነታቸው ኃላፊነት ባለመስጠታቸው የተነሳ ትልቅ መሆን ሳይችሉ


ቀርተው በመከኑ ሰዎች ነው በአመዛኙ የተሞሉት፡፡

እንግዲህ ሁላችንም እንደምናውቀው የጽንስ መቋረጥ ወይንም ውርጃ እጅግ አወዛጋቢ ከተባሉ የዘመናችን
ጉዳዮች ተርታ ይመደባል፡፡ በበርካታ አገራት ውስጥም ለሥልጣን ሽኩቻም ሆነ ለወንበር በሚደረግ ፉክክር
የተሟሟቀ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ውርጃ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በማኅበረሰባችን ውስጥ አቧራን ያስነሳ
ጉዳይ ይሁን እንጂ ፊትም ቢሆን የነበረ አወዛጋቢ ጉዳይ መሆኑ ግን ሊጠቀስ ይገባል፡፡ እንዲያውም ውርጃ
የሰውን ልጅ ዕድሜ ያህል ቦታ ነው በታሪክ ውስጥ ይዞ የሚገኘው፡፡

ነገር ግን ውርጃ በሰው ልጅ ጽንስ ማቋረጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ የመጀመሪያው የማስወረድ ተግባር
የተፈጸመው በኤደን ገነት ሲሆን አዳም ማለትም የመጀመሪያው ሰው መላውን የሰው ዘር በወገቡ ተሸክሞ
የመሄድ ኃላፊነት ተሰጠው፡፡ ይህም ማለት በአዳም ውስጥ የመላው ሰው ሁሉ ዘር እና ጥንካሬ ተቀምጦ ነበረ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ በወቅቱ ለአዳም የሰጠው ትዕዛዝ ቀላልና ግልጽ እንደነበረ መመልከት ይቻላል፤

16 | P a g e
ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምን እና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፡፡
ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 2፡16-17)

እንግዲህ በእርግጠኝነት መሞት ማለት በውስጡ ያለውን ፍሬያማነት መግደል እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡
ሞት እጅግ ቀለል ባለው ገጽታው እንመልከተው ከተባለ የእምቅ-አቅም መቋረጥ መሆኑን እናያለን፡፡ ማቋረጥ
ማለት ሕይወትን ሙሉ እምቅ-አቅሟ ሳይወጣ፤ ማለትም ተክሉ፤ እንሰሳው ወይ ሰውየው ወዘተ. ሙሉ
አቅሙን ለመጠቀም ዕድሉ ከመሰጠቱ በፊት መግደልን ያመለክታል፡፡

ሞት እጅግ ቀለል ባለው ገጽታው እንመልከተው ከተባለ የእምቅ-አቅም መቋረጥ መሆኑን


እናያለን፡፡

እግዚአብሔር ማንኛውንም ፍጡር ወደዚህች ምድር ሲያመጣ በፍጡሩ ውስጥ የተደበቀ እና ለስኬት
የሚያበቃ ክህሎት እንዲኖረው አድርጎ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጠው የፍጥረት ታሪክ
የማንኛውም ነገር ዘር እንደ ወገኑ እንዲያበቅል የታቀደ መሆኑን እንመለከታለን (ኦሪት ዘፍጥረት 1፡2 ን
ይመልከቱ)፡፡ ይኼም ማለት ማንኛውም ፍጡር የታቀደለትን ሁሉ የመሆን ድብቅ ችሎታ አለው፡፡

 በማንኛውም ዘር ውስጥ ዛፍ አለ
 በማንኛውም ዓሣ ውስጥ ትምህርት ቤት አለ
 በማንኛውም ወፍ ውስጥ የአዕዋፋት መንጋ አለ
 በማንኛውም ላም ውስጥ የላም መንጋው አለ
 በማንኛዋም ሴት ልጅ ውስጥ ትልቅ ሴት አለች
 በማንኛውም ወንድ ልጅ ውስጥ ትልቅ ሰው አለ
 በማንኛውም ሰው ውስጥ ሕዝብ አለ

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲጠቅስም ሆነ ሲያነጋግር በወገቡ እንዲሸከም ከታሰበው ሕዝብ አንጻር እንደሆነ
መረዳት ይኖርብናል፡፡ በእግዚአብሔር የሕይወት ስሌት መሠረት አንዱ ከብዙዎች ጋር እኩል ነው፤ ትንሹ
ከብዙ ጋር እኩል ነው፡፡ በመሆኑም ዘርን ማቋረጥ ማለት ደንን መግደል፤ ላምን ማቋረጥ መንጋውን መግደል፤
አንድን ልጅ ማቋረጥ ሰውን መግደል፤ አንዲት ሴት ልጅን ማቋረጥ ሴትን መግደል ወዘተ. የሆነው፡፡ በታሪክ
የታላቁ ጳጳስነትን ሥፍራ ላገኘው አብረሐም እግዚአብሔር የሚከተለውን አለ፤

17 | P a g e
ታላቅ ሕዝብም አደርግሀለሁ፤ እባርክሀለሁ፤ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፡፡
የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ ባንተ
ይባረካሉ፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 12፡ 2-3)

የጽንስ ማቋረጥ ወይንም ውርጃ (ከላይ በጠቀስነው መልኩ የቀረበው) እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ ሕይወት
መሠረቷን፤ የወደፊቱ ጊዜ ደግሞ ዋጋውን እንዲያጣ ያደርገዋል፡፡

 በቸልተኝነት የሚፈጠረው ውርጃ 

ጽንስን ማቋረጥ ማለት ኃላፊነትን መዘንጋት እንዲሁም ግዴታን መካድ ነው፡፡ ጽንስን መግደል ማለት
ፍሬያማነትን እየገደሉ የራስን ምቾት መጠበቅ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ማንኛውም ጽንስ-ማቋረጥ
ኃላፊነትን መስዕዋት ማድረግ መሆኑ ነው፡፡ እምቅ-አቅምን መግደል የወደፊቱን ጊዜ መኮነንና ማበላሸትን
ያመለክታል፡፡ ይኼ እውነታ ነው አንድ የሳይንስ ዲሲፕሊን እንዲጎለብትና እንዲያቆጠቁጥ የረዳው፡፡ ሥነ-
ምህዳር እና የአካባቢ ጥናት የተባሉት ዲሲፕሊኖች መሠረታዊው መነሻ ሀሳባቸው መጥፋት (extinction) ጋር
የቶራኘ ነው፡፡ መጥፋትን፤ አንድ ፍጡር ራሱን ወደ ስኬት ለማድረስ ያለውን የእምቅ-አቅም ኃይል ማቆም
ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡

ጽንስን ማቋረጥ ማለት ኃላፊነትን መዘንጋት እንዲሁም ግዴታን መካድ ነው፡፡

እኔን ሁልጊዜ የሚያስደምመኝ እውነታ ቢኖር የሰው ልጅ በቢልዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እያፈሰሰ
እንስሳትን፤ ተክሎችን፤ ደንን እና የኦዞን ሌየርን ለመከላከል በማሰብ ሲያፈስ ስለ ራሱ ብዙ የውስጥ ጉዳዮች
ግን ምንም አለማድረጉ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዓሣ ነባሪን፤ ጉጉትን፤ ዛፎችን እና ዓሣን ለመከላከል ጠንክሮ
ቢሰራም በሌላ በኩል ግን የገዛ ፍጡሩንና ዘሩ የሆነውን ልጁን ግን በጽንስ ውርጃ ለማስወገድ የሚታገል አለ፡፡
ምናልባትም ይኼንን ነገር ለማስቆም ከሁሉም በላይ ይረዳል ብዬ የምተማመንበት ከእያንዳንዱ አሰቃቂ ቀዶ-
ጥገና በፊት ይኼንን የሚሰራውን ሐኪም ይኼንን ቀዶ-ጥገና የማድረግ አጋጣሚው የራሱ መሆኑን፤ ለዚህ
ደግሞ ምክንያቱ የገዛ እናቱ እሱን በጽንስ ማቋረጥ ስላልገደለችው መሆኑን ማስታወስ ይሆናል፡፡

የውርጃ ችግር ከዚህ አንጻር ሲታይ ሕይወትን የማጥፋት ችግር ብቻ አይደለም---የመጨረሻው እና እጅግ
ጎጂው ውጤቱ እሱ ቢሆንም፡፡ ይልቅ ውርጃ በዓለማችን ላይ እየተንሰራፋ ያለው የእምቅ-አቅምን መርህ

18 | P a g e
ያለመረዳት እና ችላ የማለት ችግር ውጤት ነው፡፡ በየዓመቱ እንደ ቅጠል በሞት የሚረግፉት እምቅ-አቅም
ለገዛ ሕይወታቸው ያለውን መሠረታዊ ጥቅም ባለመረዳታቸው በውርጃ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

እምቅ-አቅምን ማምከን የወደፊቱን ጊዜ መግደል ነው፡፡ ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላው ውጤቱ እየቀጠለ
ይሄዳል፡፡ አዳም የእግዚአብሔርን ሕግ ሲጥስ ተሰጥቶት የነበረው ዘር እንዲሆን ተፈልጎ የነበረውን ሁሉ
የመሆን እምቅ-አቅሙን ገደለ፡፡ በታሪክ ውስጥም ሰዎች የአምላክን እውነተኛ ባሕሪ መሠረት ሳይረዱ
እንደቆዩ እንመለከታለን፡፡ የአምላክን እውነተኛ ባሕሪ ሳይረዱ መቅረት ማለት ደግሞ ከእምቅ-አቅማችን
በታች ሆነን መቆየትን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔርም ሐጢአት የሚለው ሌላ ሳይሆን ይኼንኑ ነው፡፡ ሐጢአት
በመሠረቱ ባሕሪ አይደለም፤ ይልቅ የአስተሳሰብ ደረጃ እንጂ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ከታወቁ ታላላቅ ጸሐፊዎች
አንዱ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፤

ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።

(ሮሜ 8፡ 17-18)

ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መረዳት የምንችለው የሰው ልጅ ውድቀት የገዛ እምቅ-አቅሙ ሙሉ በሙሉ
እንዳይገለጽ እና እንዳይወጣ እንቅፋት መሆኑን ነው፡፡ በሰው ልጅ ሐጢአት ፍጥረት ሁሉ ነው የተጎዳው፡፡
የፍጥረት ዕጣ ፈንታ ከሰው ልጅ ጋር የተሳሰረ ነውና የእግዚአብሔር ፍጡራን በሙሉ የሰው ልጅ ሙሉ እምቅ-
አቅም እስኪወጣ ድረስ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የውርጃ ተግባር--የሕልም፤ የራዕይ፤
የጥበብ፤ የሙዚቃ፤ የጽሁፍ፤ የቢዝነስ፤ የአመራርም ሆነ የፈጠራ--በሰው ልጅ ባሕሪ ላይም ሆነ በትውልዶች
ላይ ነው ተጽዕኖ የሚፈጥረው፡፡ ለመሆኑ እርስዎ ሳይጽፉት የቀሩትን መዝሙር ስንት ገና ያልተወለዱ ልጆች
ወደፊት ይዘምሩት ይሆን

አዳም እግዚአብሔር በልቡ ያስቀመጠውን ራዕይ ሲገድል እና የአምራቹን ትዕዛዛት ሲጥስ በጀርባው ተሸክሞት
የነበረውን የሰው ልጅ ሁሉ ዕጣ ፈንታ ቀየረው፡፡ አሁንም ወደ (ሮሜ ሰዎች) ተመልሰን እንሂድና፤

ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ
ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤ ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት
አይቈጠርም፤

ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት
ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።

19 | P a g e
ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን
የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።

አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው
ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ።

በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።

እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት
ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።

(ሮሜ 5፡ 12-17)

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የቀረበውን እና የታየውን መርህ መረዳት እጅግ ጠቃሚና ወሳኝ ነው፡፡ የእርስዎ
እምቅ-አቅም ካልወጣና ጥቅም ላይ አለመዋሉ ይኼንን ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ትወልዶችንም ይጎዳል፡፡
ፍጥረትም እኮ በእርስዎ ላይ ትመሰክራለች፡፡ እምቅ-አቅምዎን ከገደሉት ቀድሞውንም ለዓለም ሊያካፍሉት
የመጡትን በውስጥዎ ያሉትን ድንቅ ቅርሶች ዓለም እንዳይጠቀማቸው በማድረግዎ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
እርስዎ መፈጠርዎ እግዚአብሔር በውስጥዎ ያለውን እምቅ-አቅም ምድር ፈልጋለች ብሎ ለመወሰኑ ማስረጃ
ነው፡፡

እምቅ-አቅምዎን አይግደሉት፡፡ በውስጥዎ ያለውን እና ሊቀበር የሚችለውን የእምቅ-አቅም ሀብት


ይጠቀሙበት፡፡ የእምቅ-አቅምዎን ምስል በታሪክ ግድግዳ እና በምድር ሙዚየም ላይ ትተው ይለፉ፡፡

 መርሆች 

1. የእርስዎ የወጣና በጥቅም ላይ የዋለ እምቅ-አቅም የዓለም ውርስ ነው

2. እርስዎ ወደዚህች ምድር የመጡት ፈጽሞ ገደብ-የለሽ እምቅ-አቅምን ይዘው ነው

3. እርስዎ እስከዛሬ ካከናወኑትና ዛሬ ላይ ከሆኑት በላይ መከወን ይችላሉ

4. የፍጡራን ዕጣ ፈንታ ከእርስዎ እምቅ-አቅም መውጣት ጋር የተያያዘ ነው

5. እርስዎ መፈጠርዎ እግዚአብሔር በውስጥዎ ያለውን እምቅ-አቅም ምድር ፈልጋለች ብሎ ለመወሰኑ


ማስረጃ ነው፡፡

20 | P a g e
ምዕራፍ 2

_____________________ _____________________

እርስዎ በምን መልኩ ይታወሳሉ

ችሎታን እውቅና መስጠት ለኃላፊነት ጥሩ መንደርደሪያ ነው፡፡

እስኪ ወደ እኔ ልክ በሚወዱት ሰው ቀብር ላይ ለመገኘት እንደሚሄዱ እየገመቱ ይምጡ፡፡ እስኪ በሀዘን ስሜት
ተውጠው፤ ዓይኖችዎ አብጠው፤ ከለቀስተኛው ጋር በእንጉርጉሮ ተውጠው ቀብር ቦታ ደርሰው ቤተክርስትያን
ደጃፍ ተሳልመው ሲገቡ ያስቡ፡፡ የአበባ ጉንጉን፤ ነጠላ ያደረጉ ሴቶች ጋቢ ጣል ያደረጉ የቅርብ ቤተሰብ አባላት
ከበው ይሳሉ፡፡ የዘመድ፤ ወዳጅን ፊት ይመልከቱ፡፡ ይኼ ሁሉ ሰው የሚወደውን አንድ ሰው ተነጥቋልና ሐዘን
ውጦታል፤ ዋይታው ቀልጧል፡፡

21 | P a g e
የእርስዎ ቀብር ነው ብልዎትስ ይኼ ሁሉ ሰው የተገኘው እርስዎን ለመቅበር ነው፡፡ አይበለውና ከአምሥት
ዓመት በኋላ ነው ይኼ ክስተት፡፡ እርስዎ በሕይወትዎ የሰሩትን፤ ማንነትዎን እና ሁሉንም ነገር ለማስታወስ
ነው ሕዝብ ቤተክርስትያን የተሰበሰበው፡፡ አምሥት ሰዎች ንግግር ያደርጋሉ፡፡ የመጀመሪያው ተናጋሪ
የቤተሰብዎ አባል ስትሆን የወንድሞች፤ እህቶች፤ አክስቶች፤ አጎቶች ወዘተ. ስሜት ወክላ ትናገራለች፡፡
ሁለተኛው ተናጋሪ ደግሞ ከቅርብ ጓደኞችዎ አንዱ ሲሆን በግለሰብነትዎ የነበረዎትን ሚና እና ባሕሪ
ያስታውሳል፡፡ ሶስተኛዋ የሥራ ባልደረባዎት ፤ አራተኛው ደግሞ ከዕድር የመጣ ተወካይ ነው፡፡ የመጨረሻዋ
ተናጋሪ ባለቤትዎ ናት፡፡

እስኪ አሁን በጥልቀት ያስቡ፡፡ እያንዳንዳቸው ስለ እርስዎ ምን እንዲሉ ይፈልጋሉ ምን ዓይነት ጓደኛ፤
የቤተሰብ አባል፤ የሥራ ባልደረባ እና ባለቤት ተደርገው መሳልን ይፈልጋሉ ምን ዓይነት የአክስት ወይ የአጎት
ልጅ ነበረ ምን ዓይነት ወንድም ነበረ ምን ይባልልዎት ምን ዓይነት ሰው ሆነው መታየትንስ ይመኛሉ

ከዚህ በላይ ከማንበብዎ በፊት እነዚህን ጥያቄዎች በሚገባ ያስቡባቸው፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ሞት
ሳይሆን ዓላማውን ያላሳካ እና እምቅ-አቅሙን ያልተጠቀመ ሕይወት ነው እጅግ ልብ ሰባሪና አሳዛኙ፡፡

ሞት ሳይሆን ዓላማውን ያላሳካ እና እምቅ-አቅሙን ያልተጠቀመ ሕይወት ነው እጅግ ልብ ሰባሪና


አሳዛኙ፡፡

 ውጤታማ የሆነ ኑሮን መምራት 

በዚህ መጽሐፍ አማካይነት በውስጥዎ ያሉትን ድንቅ ቅርሶች--ማለትም እምቅ-አቅምዎን--እንዲያውቁ


እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ ውጤታማ የሆነ ነሮን መምራት በሚለው ጉዳይ ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠርን ሕዝብ
አነጋግሬያለሁ፡፡ በሕይወት ኖሮ ነገር ግን የታቀደን ዓላማ እውን ካለማድረግ ይልቅ ሞት ይሻላል ብዬ
ተናግሬያለሁ፡፡ ይህንን እውነታ በ (መጽሐፈ መክብብ 6፡ 3-6) ላይ ተቀምጦ እንመለከታለን፡፡

ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፤ ዕድሜውም እጅግ አመት ቢሆን፤ ነፍሱም
መልካምን ባትጠግብ መቃብርንም ባያገኝ፤ እኔ ስለ እሱ፤ ከእርሱ ጭንግፍ ይሻላል አልሁ፡፡

በከንቱ መጥቶአል በጨለማ ይሄዳል፤ ስሙም በጨለማ ይሸፈናል፡፡

ደግሞም ፀሐይን አላየውም አላውቀውምም፤ ለዚህም ከዚያ ይልቅ ዕረፍት አለው፡፡

ሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕይወት ቢኖር መልካሙንም ባያይ፤ ሁሉ ወደ አንድ ሥፍራ የሚሄድ አይደለምን 

ይህ ጥቅስ ከምንም በላይ የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ የፈለገውን ያህል ዕድሜ ሰጥቶትና ምንም ያህል
ወልዶ፤ ከብዶ ግን የተሰጠውን ዓላማ ሳያሳካ ከሚኖር ይልቅ ባይወለድ ይሻላል ነው የሚለው፡፡ በመሠረቱ

22 | P a g e
እርስዎ በውስጥዎ ያለውን እምቅ-አቅም ሲያውቁ ይኼንን ሀብት በዙሪያዎ ላለው ዓለም የማውጣት ግዴታ
አለብዎ፡፡

ችሎታ እና ኃላፊነት 

ከኋላዎ ያለው ታሪክ፤ ከፊት ለፊትዎ ያለው ደግሞ የሚጠብቅዎ ነው፡፡ ይሁንና እነዚህ ሁለቱም ቢሆኑ
በውስጥዎ ካለው ጋር ሲነጻጸሩ ኢምንት ናቸው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ ያለፈው ያለፈና ሊቀይሩት
የማይችሉት፤ የወደፊቱ ደግሞ ገና ያልተኖረ ይሁን እንጂ አሁን ያለዎት ነገር ግን ሕይወትዎን ለማጎልበት እና
በውስጥዎ ያለውን ክህሎት ለማሳደግ ዕድል ይሰጥዎታል፡፡ ለችሎታዎ ኃላፊነት መውሰድ አለብዎ---ይኼንን
ሌላ ማንም ሊያደርግልዎት አይችልም፡፡

ለችሎታዎ ኃላፊነት መውሰድ አለብዎ

እርስዎ የሚኖሩት ምን ዓይነት ሕይወት ነው ለሕይወትዎ የተሰጠዎትን ዓላማ እያጨነገፉት ነው አሁኑኑ
ለችሎታዎ ኃላፊነት እንዲወስዱ አበረታታዎታለሁ፡፡ ለቀጣዩ ትውልድ ጥቅም ሲሉ እምቅ-አቅምዎን
ለማንቀሳቀስ፤ ለማውጣት እና ለማጎልበት አሁኑኑ ይወስኑ፡፡ በታሪክ አሸዋ ላይ የእግር አሻራዎን ለአገርዎና
ሕዝብዎ ሲሉ ይተዉ፡፡ የማይቆጭ አሟሟት እንዲኖረዎ የተሟላ ኑሮን ይኑሩ፡፡ ሕይወትዎ የሞትዎን ንግግር
ትጻፍልዎ እና እምቅ-አቅምዎን እግዚአብሔር ሐሴት ያደርግ ዘንድ ለሰው ልጅ ያበርክቱ ፡፡ አንድ ነገር
ያስታውሰ--‹‹በደምብ የተገለጸ›› ከሚባለው ይልቅ ‹‹በደምብ የተሰራ›› ይበልጣል፡፡ ራዕይዎ፤ ሕልምዎ እና
ሀሳብዎ ስለሚሆነው ነገር በማውራት ብቻ አይወሰኑ፡፡ ይልቅ ካሉበትና ከታጠሩበት ወጥተው እውን
ያድርጓቸው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ያከናወኑትና ያሳኩት ሊያሳኩት ከሚችሉት አንጻር ኢምንት መሆኑን በድፍረት
ማመን ይኖርብዎታል፡፡ ከተለመዱት እና ከሚያውቋቸው የአኗኗር ዘይቤዎች ወጣ በማለት በውስጥዎ ሊሟሉ
እና ሊሳኩ እየጠበቁ በሚገኙ እቅዶች ላይ ያተኩሩ፡፡

ችሎታዎችዎ ለዓለም ይሆናሉ

ለመውጣት እና በጥቅም ላይ ለመዋል እየጠበቀ የሚገኝ ድንቅ እምቅ-አቅም በእርስዎ ውስጥ ይገኛል፡፡ ነገር
ግን ይኼንን እምቅ-አቅም ለማውጣት እስከዛሬ ያገኙትን እና ያሳኩትን መተው ይጠበቅብዎታል፡፡ ያኔ ነው
ይዘውት የተፈጠሩትን እና አሁን ዕዳ ሆኖ ያለውን ትልቅ አቅም መጠቀም የሚችሉት፡፡ እምቅ-አቅም ትልቅ
እና ገና ሲፈጠሩ እርስዎ ያላወቁት የበርካታ ሪሶርሶች ክምችት በመሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ ያሳኩትና ያከናወኑት
እምቅ-አቅምነቱ አብቅቷል፡፡ እምቅ-አቅምዎን ማውጣት ይቻላል ብለው ከሚያስቧቸው እና
ካስቀመጧቸው ገደቦች ማለፍን ይጠይቃል፡፡

23 | P a g e
እምቅ-አቅም ለማውጣት እስከዛሬ ያገኙትን እና ያሳኩትን መተው ይጠበቅብዎታል፡፡

አዳዲስ ነገሮችን ከሞከሩ እና አድማስዎን የሚያሰፉ ምርጫዎችን ካደረጉ ደስ በሚል ጎዳና ይጓዛሉ፡፡
እግዚአብሔር እንዲሆኑ አድርጎ የፈጠረዎትን ድንቅ ስብዕና ይመለከቱታል--ይቻላል ብለው ከገመቱት በላይ
ክህሎትን ያዳበረ ሰው፡፡ ጉዞው የሚጀምረው ታዲያ እምቅ-አቅም ምን እንደሆነ እና እንዴት ሊያወጡት
እንደሚችሉ መረዳት ሲችሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠዎትን ሀብት መረዳት ከጀመሩ በኋላ ግን እግዚአብሔር
የሰጠዎትን በትጋት እና በንቃት ከመጠቀም መሸሽ እምቅ-አቅምን የሚገድል እና እርስዎም እግዚአብሔር
ያስቀመጠልዎትን ዓላማ ለማሳካት አሻፈረኝ እንዳሉ የሚያሳይ ይሆናል፡፡ ለራስዎ፤ ለሌሎችና ለትውልዶች
ሲሉ መጠቀም ያልቻሏቸውን ነገሮች ማወቅ ለወደፊቱ የሚጠየቁበትና የሚዳኙበት ይሆናል፡፡ እምቅ-አቅም
እንዲጠቀሙበት እንጂ ሊባክን አልተሰጠም፡፡

እንዳንድ ሰዎች የሚፈልጉትን ለማድረግ የሚችሉበት አንድ ምክንያት ብቻ


ሲያስፈልጋቸው እነሱ ግን ላለማድረጋቸው ሺህ ምክንያቶችን ይደረድራሉ

 መርሆች

1. እግዚአብሔር በእርስዎ ውስጥ እምቅ-አቅምን ያስቀመጠው ዓለምን ይጠቅሙበት ዘንድ ነው


2. እምቅ-አቅም ትልቅ እና ገና ሲፈጠሩ እርስዎ ያላወቁት የበርካታ ሪሶርሶች ክምችት ነው
3. እምቅ-አቅም በጥቅም ላይ ሊውል ይገባል፤ አለዚያ ግን ይባክናል
4. በስኬት መርካት እምቅ-አቅምን ይገድላል

24 | P a g e
ምዕራፍ 3

______________________ ____________________

እምቅ አቅም ምንድነው

እምቅ-አቅምን ማጨናገፍ የወደፊት ብሩህ ጊዜን መግደል ነው፡፡

25 | P a g e
እምቅ-አቅም ማለት. . .

. . .ገና ይፋ ያልወጣ ችሎታ፤ በጥቅም ላይ ሳይውል ያለ ክህሎት፤ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ጥንካሬ፤


ያልተጠቀምንበት ስኬት፤ የተደበቁ ታለንቶች፤ ተከድኖ ያለ ችሎታ፤

ሊሆኑት የሚችሉት ነገር ግን ገና ያልሆኑት፤ ሊያደርጉት የሚችሉት ግን ገና ያላደረጉት፤ ሊደርሱበት


የሚችሉት ግን ያልደረሱበት የመጨረሻው ደረጃ ፤ ሊቀዳጁት የሚችሉት ግን ገና ያልተቀዳጁት

በመሆኑም እምቅ-አቅም ማለት ገና ወደፊት ሊገልጹትና ሊያወጡት የሚጠበቅ የእርስዎነትዎ የድምር


ውጤት ነው፡፡ ለመውጣት እና ይበልጥ ተጠናክሮ በጥቅም ላይ ለመዋል እየጠበቀ ያለም እንደሆነ መረዳት
ያስፈልጋል፡፡ እርስዎ አሁን ከሚያስቡት፤ ከሚገምቱት፤ ከሚያደርጉት ወይንም ከሆኑት በላይ መሆንም
ማድረግም ይችላሉ፡፡ ያ ነው እምቅ-አቅምዎ፡፡ ከፍ ያለ ነገር ላይ ለመድረስ፤ ርቀው ለመሄድ፤ ተንጠራርተው
ለማየት እና ከሚያውቁት የሰፋና የጠለቀ ነገር ለማወቅ ይሞክሩ፡፡ ያን ጊዜ እምቅ-አቅምዎን ያገኙታል፡፡

እርስዎ አሁን ከሚያስቡት፤ ከሚገምቱት፤ ከሚያደርጉት ወይንም ከሆኑት በላይ መሆንም


ማድረግም ይችላሉ፡፡

 የእምቅ-አቅም መርህ

እስኪ እንበልና እኔ እና እርስዎ በአንድ ሰፊና ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ ቆመን የሚያዩትን እንዲገልጹልኝ
ጠየቅኩዎት፡፡ ነፍሳት፤ እንስሳት፤ ቅጠሎች፤ ዛፎች፤ ቁጥቋጦዎች፤ አዕዋፋት፤ አበቦች ወዘተ. አየሁ ሊሉኝ
ይችላሉ፡፡ ይሁንና እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የሚያዩት ያንን ብቻ አይደለም፡፡ ለምን ቢባል በእነዚህ
በእያንዳንዳቸው ውስጥ ለበለጡ ዛፎች፤ ተክሎች፤ አበቦች፤ ነፍሳት፤ አዕዋፋትና እንስሳት የሚሆኑ ዘሮች
አሉ፡፡ የእምቅ-አቅም መርህ የምንለው ይኼንኑ ነው፡፡ በመሆኑም የእርስዎ እይታ ጥሬ ሃቅ እንጂ እውነታው
ግን አይደለም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በእጄ ፖም ይዤ ቢሆን ከአንድ በላይ ዘር ነው የያዝኩት፡፡ በእያንዳንዱ ዘር ውስጥ ዛፍ ያለ
ሲሆን በእያንዳንዱ ዛፍ ውስጥ ደግሞ ዘር ያለው ፖም አለ፡፡ በዘሮቹ ውስጥ ደግሞ የበለጡ ዛፎች፤ ፍሬዎች
ወዘተ. አሉ፡፡ በመሆኑም እውነታውን እንመልከት ካልን በእጄ ሙሉ የአትክልት ቦታ ነው የያዝኩት፡፡

 እምቅ-አቅምን መረዳት

26 | P a g e
እግዚአብሔር አምላክ ሁሉንም ነገር ሲፈጥር ከእምቅ-አቅም ጋር መሆኑን ገልጫለሁ፡፡ በ ኦሪት ዘፍጥረት 1፡
2 ላይ እግዚአብሔር እንዴት ተክሎችን እና ዛፎችን እንደፈጠረ እና እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን
የሚያፈራ እንዲሆን አድርጎ እንደሰራቸው ገለጠ፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ የአዕዋፋት፤
የባሕር ላይ እንሰሳት፤ የቀንድ ከብት፤ የተሳቢዎች እና የአውሬዎችን ጭምር ፍጥረት የተመለከተ ረጅም ገለጻ
ቀርቧል፡፡ እነዚህ እያንዳንዳቸው ሁሉ እንደ ወገናቸው ዘራቸው ያለበትን ፍሬ እንዲያፈሩ ችሎታው
ተሰጥቷቸዋል፡፡ በመሆኑም የእግዚአብሔር ፍጡር የሆነው ሁሉ በእምቅ-አቅም ተባርኳል፡፡ እያንዳንዱም
ቢሆን ዛሬ እና በአንድ ወቅት ላይ ከሆነውና ከሚታየው በላይ መሆን እንዲችል እምቅ-አቅም ይዟል፡፡
እያንዳንዱ የወደፊት የአዕዋፍ፤ ዛፎች፤ ተክሎች፤ አበቦች፤ እንስሳት ወዘተ. የሚጠሩበትን ዘርም ጭምር
ይዟል፡፡

የእግዚአብሔር ፍጡር የሆነው ሁሉ በእምቅ-አቅም ተባርኳል፡፡

እግዚአብሔር ከዚህ በተጨማሪም በማንኛውም ወቅት ከሆኑት በላይ መሆን የሚችሉበትን ክህሎት
ሰጥቶዎታል፡፡ እርስዎም ልክ እንደ ፖም ዘር የተደበቁ ክህሎቶችና ሪሶርሶች በውስጥዎ አሉ፡፡ እግዚአብሔር
ሲወለዱ በውስጥዎ ካስቀመጠው እምቅ-አቅም ውስጥ አብዛኛው እርስዎ ሳይጠቀሙበት እና ሳይታይ
አሁንም በውስጥዎ አለ፡፡ እኔ እርስዎን በማንኛውም ጊዜ ሳገኝዎት የማየው ሊሆኑ የሚችሉትን ሁሉ ሆነው
አይደለም፡፡

 የሁሉም እምቅ-አቅም ምንጭ 

ዛሬ ያለውም ሆነ የነበረው ሁሉ በእግዚአብሔር ውስጥ የነበረ ነው፡፡ ከዚህ እንደምንረዳው እግዚአብሔር


በውስጡ የሰራውን ሁሉ ለመስራት የሚሆን እምቅ-አቅም ነበረው፡፡ ዛሬ በእግዚአብሔር ውስጥ ቀድሞውንም
ያልነበረ አንዳችም ነገር የለም፡፡ ከሁሉም ነገር የሚቀድመው እግዚአብሔር በመሆኑ እግዚአብሔር የሕይወት
ሁሉ ምንጭ ነው፡፡

ዛሬ በእግዚአብሔር ውስጥ ቀድሞውንም ያልነበረ አንዳችም ነገር የለም፡፡

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡1)

እንግዲህ ሁሉም ነገር ከመጀመሩና ከመፈጠሩ በፊት በእግዚአብሔር ውስጥ እንደነበረ እንረዳለን፡፡ ኦሪት
ዘፍጥረት የሚጀምረው ከ ኦሪት ዘፍጥረት 1፡0 ቢሆን ኖሮ እንዲህ ሊል ይችል እንደነበረ እገምታለሁ፤

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነበረ፤ ከዚያ ፍጥረት ተጀመረና ፈጣሪም ነበረ፡፡

27 | P a g e
ከምንም ነገር በፊት የነበረው እግዚአብሔር ነበረ፡፡

እግዚአብሔር ራሱ የመጣው ወይንም የጀመረው የመጀመሪያው የምንለው ጊዜ ላይ አይደለም፡፡ እሱ


የመጀመሪያው የምንለው ከመጀመሩ በፊትም መጀመሪያ ነበረ፡፡

በመጀመሪያው ቃል ነበረ፡፡ ቃልም በእግዚአብሔር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

(የዮሐንስ ወንጌል 1፡1)

ዛሬ በዓለም ላይ የምናውቀውና ያለው፤ የነበረው ሁሉ መጀመሪያ ከመታየቱ በፊት በእግዚአብሔር ውስጥ


ነበረ፡፡

ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እሱ አልሆነም፡፡

(የዮሐንስ ወንጌል 1፡3)

በመሆኑም እግዚአብሔር የሁሉም እምቅ-አቅም ምንጭ ነው፡፡ እስከዛሬ ያላየነው ነገር ሁሉ ምንጭም
እንደሆነ እናስታውስ፡፡

ይኼንን የእግዚአብሔርን ባሕሪ ስንገልጽ እሱ ሁሉን-ቻይ (omnipotent) ነው እንላለን፡፡ Omni የሚለው ቃል


‹‹ሁልጊዜ›› የሚለውን ትርጉም ይዟል፡፡ በመቀጠል የምናገኘው የእንግሊዝኛው ቃል potent ማለት ደግሞ
‹‹በኃይል የተሞላ›› ማለት ነው፡፡ እናም እግዚአብሔር ሁልጊዜ በኃይል የተሞላ ነው የሚለውን ትርጉም
እናገኛለን፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜምና በማንኛውም ጊዜ እስከ አሁን ካደረገው በላይ ሊያደርግ ይችላል፡፡

 የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ ሂደት 

እግዚአብሔር ዓለምን በፈጠረ ጊዜ አካሄዱና ዘይቤው ትኩረትን የሚስብ ነበረ፡፡ በቅድሚያ እግዚአብሔር
ሊፈጥረው የፈለገው አቀደ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ፍጡሩ ከምን ንጥረ-ነገርና ግብዓት ሊሰራ
እንደሚችል ወሰነ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ እግዚአብሔር ከንጥረ ነገሩ ጋር የተነጋገረ ሲሆን አራተኛ ላይ ደግሞ
የተናገረው ራሱ ከተናገረው ንጥረ-ነገር መነጨ፡፡

በመሆኑም እግዚአብሔር አትክልቶችን መፍጠር ሲፈልግ መሬትን አነጋገረ፤ ለዚህ ምክንያቱ ለአትክልት
መሬት ግብዓቱ በመሆኑ ነበረ፡፡ እንስሳትን መፍጠር በፈለገ ጊዜ እንስሳት ከአፈር እንዲሰሩ በመፈለጉ አሁንም
መሬትን አነጋገረ (ኦሪት ዘፍጥረት 1፡24)፡፡ ዓሣ እግዚአብሔር ባሕርን ሲያነጋግር ነበረ የተፈጠረው (ኦሪት

28 | P a g e
ዘፍጥረት 1፡24)፡፡ ፀሐይ፤ ጨረቃ እና ክዋክብት በሰማይ ላይ የታዩት ሰማይን ባነጋገረ ጊዜ ነበር (ኦሪት
ዘፍጥረት 1፡ 14-17)፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ፍጡር የመጣው እግዚአብሔር ፍጡሩ የተሰራበትን ግብዓት
ካነጋገረው በኋላ ነው--በዕቅዱ መሠረት፡፡ እግዚአብሔር ዓለምንም በተመሳሳይ ሂደት ፈጠራት፡፡

 እግዚአብሔር እምቅ-አቅምን ሰጠዎት 

እግዚአብሔር የሰው ልጅን በፈጠረ ጊዜ ራሱን ነበረ ያነጋገረው፡፡ እርስዎ ከእግዚአብሔር የተፈጠሩት
እግዚአብሔር ልክ እንደ ራሱ ሁሉ የሰው ልጅም መንፈስ መሆን አለበት ብሎ በማቀዱ ነበረ፡፡ ዛሬ በጣም ብዙ
ሰዎች እግዚአብሔር እነሱን የፈጠረበትን ዓላማና ምክንያት አይረዱም፡፡ ለሕልውናቸው ምክንያት ሊሆን
ይችላል ያሉትን ነገር ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ ሌላ ቦታ ላይ ሁሉ ይፈልጋሉ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ሕይወት ሙሉ
አይደለም፤ እምቅ-አቅማቸውም ባክኗል፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች በመመልከት በብክነታቸው ያዝናል፡፡
‹‹አዬ! ምነው ማን መሆናችሁን፤ ማድረግ የምትችሉትን፤ ለምን ሕይወት እንደሰጠኋችሁ ብታውቁ!››
ይላል፡፡

አንድ ነገር ያስታውሱ--በቅልጥፍና እና ክህሎት ስንታገዝ ጥቂት ነገሮች ካልሆኑ የማይቻል አይኖርም፡፡ ትልቅ
ሥራ በጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በጽናትም ጭምር ይሳካል፡፡ እግዚአብሔር እርስዎን የፈጠረዎት ከእምቅ-አቅም
ጋር ነው፡፡ በሰጠዎ እጅግ ድንቅ ተሰጥዖ ምን እንደሚያደርጉ ለማየት ይፈልጋል፡፡

 መርሆች 

1. እምቅ-አቅም ማለት ገና ሊሆን የሚችለው ነው


2. እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከእምቅ-አቅም ጋር ፈጠረው
3. እግዚአብሔር የሁሉም እምቅ-አቅም ምንጭ ነው
4. እግዚአብሔር ያቀደው ካነጋገረው ግብዓት መንጭቷል
5. እግዚአብሔር እርስዎን ሲፈልግ ራሱን አነጋገረ

ምዕራፍ 4
29 | P a g e
_____________________ ____________________

እምቅ-አቅምዎን እንዴት ማውጣት ይችላሉ

እስኪ ተሸክመውት ከሚንቀሳቀሱት የእምቅ-አቅም


መቃብር ይዛቁ፤ ይውሰዱ፡፡

ይኼንን መጽሐፍ እያነበቡ አራተኛው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋልና አሁን የእምቅ-አቅምን ዝርዝር ምንነት፤
ብሎም በውስጥዎ ያለውን የእርስዎን እምቅ-አቅም እንዴት አውጥተው መጠቀም ይችላሉ ስለሚለው በቂ
ግንዛቤ አግኝተዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ለማንኛውም ዓይነት እምቅ-አቅም መሠረታዊ
የሆኑ ስድስት ዋና ዋና መርሆችን እና በውጤታማ መንገድ እምቅ-አቅምዎን ለመጠቀም ስለሚረዱ ዐሥር
መስፈርቶች እንማራለን፡፡

 እምቅ-አቅምን የሚመሩ መርሆች 

የእምቅ-አቅምዎን መጠን እና ተፈጥሯዊ ባሕሪ ከመረዳትዎ በፊት ሁሉንም እምቅ-አቅም የሚመለከቱ


ሕግጋቶችን ማወቅ ይጠበቅብዎታል፡፡ እግዚአብሔር ቢኖርም ገና የማይታይ የነበረውን እንዲታይ ለማድረግ
ሲል የፈጠራ ክህሎቱን ሲጠቀም ነበረ እነዚህን ሕግጋት ያወጣው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ
ምዕራፎች ላይ እግዚአብሔር በውስጡ የነበረውን እምቅ-አቅም እንዴት አድርጎ እንዳወጣ ነው
የምንመለከተው፡፡

30 | P a g e
መርህ # 1 እግዚአብሔር የሚያናግረው የፍጥረቱን ምንጭ ነው

የእግዚአብሔርን የፍጥረት ሂደት ስንመለከት እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ ቀደም ሲል ከምንጩ ጋር


ካደረገው ንግግር እንደመጣ እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔር ያነጋገረው ማንኛውም ነገር አስቀድሞ ሊፈጥረው
ያቀደው ነገር ሁሉ ምንጭ ሆኗል፡፡ እግዚአብሔር ተክሎችን መፍጠር በፈለገ ጊዜ አፈርን አነጋገረ (ኦሪት
ዘፍጥረት 1፡ 11-12)፡፡ እንስሳትን መፍጠር በፈለገ ጊዜ እንስሳት ከአፈር እንዲሰሩ በመፈለጉ አሁንም
መሬትን አነጋገረ (ኦሪት ዘፍጥረት 1፡24-25)፡፡ ዓሣ እግዚአብሔር ባሕርን ሲያነጋግር ነበረ የተፈጠረው (ኦሪት
ዘፍጥረት 1፡20-21)፡፡ ፀሐይ፤ ጨረቃ እና ክዋክብት በሰማይ ላይ የታዩት ሰማይን ባነጋገረ ጊዜ ነበር (ኦሪት
ዘፍጥረት 1፡ 14-17)፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ፍጡር የመጣው እግዚአብሔር ፍጡሩ የተሰራበትን ግብዓት
ካነጋገረው በኋላ ነው--በዕቅዱ መሠረት፡፡ እግዚአብሔር ዓለምንም በተመሳሳይ ሂደት ፈጠራት፡፡

መርህ # 2 ማንኛውም ፍጡር ከምንጩ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ዘርፍ እና መሠረታዊ ባሕሪ አለው

እግዚአብሔር በፍጥረት ሂደት ወቅት ያነጋገረው ምንጭ የፍጥረቶች ሁሉ የመጨረሻው መገኛ ሆኗል፡፡
የእግዚአብሔር ፍጡራን ሲሞቱ ቀድሞውንም ወደመጡበት ወደዚህ ምንጭ ይመለሳሉ፡፡ በመሆኑም ከአፈር
የመጡት ተክሎች ወደ አትክልት ይመለሳሉ፡፡ እንስሳት ከመሬት መንጭተዋልና በሞት ጊዜ መገኛቸው መሬት
ይሆናል፡፡ ዓሦች ከባሕር በመምጣታቸው ወደዚያው በሞታቸው ጊዜ ሲመለሱ ክዋክብት ወደ ሰማይ
ተመልሰው ይገባሉ፡፡ ይኼ ሊሆን የቻለው ማንኛውም ፍጡር ዘርፉና ባሕሪው ቀድሞውንም ከመጣበት
ምንጭ ጋር አንድ ዓይነት በመሆኑ ነው፡፡ ተክልን ወይንም እንስሳን በልተን በማጉሊያ መነጽር ብንመለከተው
ተክሎችም ሆኑ እንስሳት መቶ በመቶ ከአፈር መሠራታቸውን እንመለከታለን፡፡ ለዚህ ምክንያቱ አፈር
ቀድሞውንም ምንጫቸው መሆኑ ነው፡፡

መርህ # 3 ማንኛውም ፍጡር በመጣበት ምንጭ አማካይነት ተጠብቆ ሊቆይ ይገባል

የእግዚአብሔር ዓለም እግዚአብሔር የሚፈጥረው ማንኛውም ነገር በመጣበትና ቀድሞውንም በተፈጠረበት


ምንጭ አማካይነት ተጠብቆ ሊቆይ እንደሚገባ ይነግረናል፡፡ ከመሬት የተነቀሉ ተክሎቸ ይሞታሉ፡፡ ተክሎችን
መመገብ ያቆሙ እንስሳትም ሕይወታቸው ያልፋል፡፡ ከውሃ የወጣ ዓሣም ምን እንደሚሆን ይታወቃል፡፡
ከምንጫቸው የተነቀሉ አበቦች ካልተነቀሉት ጋር ሲነጻጸሩ ብዙም ሳይቆዩ ይጠወልጋሉ፡፡ በመሆኑም
ማንኛውም ሕያው ፍጡር ከምንጩ የተለየ ጊዜ ይሞታል፡፡ የሞትና የመበስበስ ምልክቶች ወዲያውኑ ግልጽ
ሆነው ላይታዩ ቢችሉም መሞታቸው ግን እርግጥ ነው፡፡ ማንኛውም የእግዚአብሔር ፍጡር ያለ ምንጩ እና
በስሪቱ አማካይነት እሱን ለማቆየት ከሚለገሠው ምግብ ውጭ ፈጽሞ አይኖርም፡፡

መርህ # 4 የማንኛውም ፍጡር እምቅ-አቅም ከምንጩ ጋር የተያያዘ ነው

31 | P a g e
ሁሉም ነገሮች በምንጫቸው አማካይነት የተሰሩ በመሆናቸው ልክ የምንጫቸውን ያህል እምቅ-አቅም ነው
ያላቸው፡፡ የእንስሳት እምቅ-አቅም ከተሰሩበት አፈር እምቅ-አቅም አያንስም፤ አይበልጥምም፡፡ ተክሎችም
የተሰሩበትን አፈር ዓይነት እምቅ-አቅም ነው ያላቸው፡፡ አፈሩ ንጥረ-ነገር ከጎደለው ወይንም ውሃ መቋጠር
የማይችል ከሆነ ከሱ ጋር የተያያዙት ተክሎች በአፈሩ የጥራት ደረጃ በጣም በከፍተኛ ደረጃ ተጽዕኖ ውስጥ
ይወድቃሉ፡፡ በተመሳሳይ መንገድም ጤናማ ባልሆነው አፈር ላይ የሚያድጉትን ተክሎች የሚመገቡት እንስሳት
ከጤናማ አፈር ላይ ከበቀሉ ተክሎች ከሚመገቡ አቻዎቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ ጤናቸው ባነሰ ደረጃ ብቻ
አስተማማኝ ነው፡፡

ማንኛውም የምርት ውጤት ቢሆን ከመጣበት ምንጭ ይበልጥ ኃይል የለውም፡፡ የእንጨት ሥሪት የሆነን
ጠረጴዛ በምሳሌነት ብንወስድ የቤት እቃ አምራቹ ከተጠቀመበት ግብዓት ከሆነው እንጨት ጥንካሬ በላይ
ሊኖረው አይችልም፡፡ ከበሰበሰ እንጨት ጠረጴዛ ብንሰራ ያው የበሰበሰ ጠረጴዛ ነው የሚኖረን፡፡ ከጽድ የተሠራ
ጣውላ ከባሉጥ የተሠራውን ያህል ዘላቂ ዕድሜ አይኖረውም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ጽድ ከባሉጥ ጋር ሲነጻጸር
ለስለስ ያለ መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም ጣውላው የሚሠራበት ግብዓት የሆነው እንጨት ዓይነት የመጨረሻውን
ጣውላ ጥራትና ዘላቂነት ይወስነዋል፡፡

ማንኛውም የምርት ውጤት ቢሆን ከመጣበት ምንጭ ይበልጥ ኃይል የለውም፡፡

በዚህ የተነሳ የማንኛውም ምርት ጥራት ምርቱን ለመስራት በግብዓትነት አምራቹ በተጠቀመበት ግብዓት
ጥራት ላይ የተመሠረተ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ የአንድ ነገር እምቅ-አቅም በተሰራበት ምንጭ እምቅ-
አቅም ላይ የተንጠላጠለ ነው፡፡ ምንም ነገር ከምንጩ ሊበልጥ አይችልም፡፡

መርህ # 5 በሕይወት ያለ ማንኛውም ፍጡር ዓላማውን የማሳካት እምቅ-አቅም አለው

የአንድ ነገር ዓላማ ነገርየውን ከፈጠረው ሰው እቅድና ፍላጎት ጋር ይያያዛል፡፡ በመሆኑም የማንኛውም ምርት
ዓላማ ሌላን ሰው ሳይሆን አምራቹን በመጠየቅ ይታወቃል፡፡

የማንኛውም ምርት ዓላማ ሌላን ሰው ሳይሆን አምራቹን በመጠየቅ ይታወቃል

በተመሳሳይ መልኩ አንድ ምርት የተሰራበትን ዓላማ ለማሳካት ያለው እምቅ-አቅም በምርቱ ላይ ዲዛይን
ይደረጋል፡፡ መቼም ማንም አምራች ቢሆን ልብስ እንዲያጥብ ብሎ ዲዛይን ያላደረገውን ምርት፤ ‹‹ልብስ
ያጥቡበታል›› ብሎ አያቀርብም፡፡ በሌላ በኩል እኔ ደግሞ ልብስ ያደርቅ ይሆናል ብዬ በመገመት ብቻ ስሞክረው
አላደርቅ ስላለኝ ማሽን ለሻጩ ባማርር አምራቹ፤ ‹‹ነገር ግን ይኼ ማሽን እኮ ልብስ እንዲያደርቅ አልነበረም
የተሰራው፡፡ ልብስ ይጠቡበት፤ በደምብ ይሰራልዎታል›› ነው ሊል የሚችለው፡፡ ‹‹ልብስ ያደርቅልኝ ግን

32 | P a g e
አይበሉ፤ ምክንያቱም ለሱ አልተሰራም፡፡›› አምራች የምርቱን ዓላማ እና ዓላማውን ለማሳካት እንዴት
በጥቅም ላይ እንደሚውል ይወስናል፡፡

መርህ # 6 እምቅ-አቅም የሚወጣውና የሚወሰነው በፈጣሪው በሚቀርብለት ጥያቄ ነው

አንድ ምርት ለመስራት ያለው እምቅ-አቅም ቀደም ሲል አምራቹ ምርቱን ሲያወጣ የፈለገውና ያሰበው
ዓላማን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ እምቅ-አቅም አምራቹ በምርቱ ላይ ባለው እምነት እና ምርቱ ያመጣልኛል
ብሎ በጠበቀው ለውጥ ላይ የተንጠላጠለ ነው፡፡ ለምሳሌም እንበልና የአንድ አነስተኛ የጭነት መኪና ሰሪ
ግማሽ ቶን ያህል ይሸከምልኛል ብሎ ምርቱን አውጥቶ ከሆነ አንድ ሙሉ ቶን ይጭናል ብሎ ግን
አያስተዋውቀውም፡፡ ለምን መኪናው ሲመረት አምራቹ ያወጣለት ዲዛይን እና ዝርዝር አድርጎ
ያስቀመጣቸው ደረጃዎች አንድ ቶን እንዲጭን የማፈቅዱለት በመሆናቸው፡፡ሆንመማለት ገና ወደፊት
ሊገልጹትና ሊያወጡት የሚጠበቅ የእርስዎነትዎ የድምር ውጤት ነው፡፡ ለመውጣት እና ይበልጥ ተጠናክሮ
በጥቅም ላይ ለመዋል እየጠበቀ ያለም እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እርስዎ አሁን ከሚያስቡት፤
ከሚገምቱት፤ ከሚያደርጉት ወይንም ከሆኑት በላይ መሆንም ማድረግም ይችላሉ፡፡

እምቅ-አቅም አምራቹ በምርቱ ላይ ባለው እምነት እና ምርቱ ያመጣልኛል ብሎ በጠበቀው ለውጥ


ላይ የተንጠላጠለ ነው፡፡

አምራቹ ምርቱ ዲዛይን ከተደረገበት አቅም በላይም ሆነ በታች እንዲያምርት አይጠይቀውም፡፡ አምራቹ
ምርቱ አንድ የሆነ አቅም ያህል አገልግሎት እንዲሰጥ ቢፈልግ ቀደም ብሎ በምርቱ ውስጥ ለዚያ አቅም
የሚሆን ነገር ማስቀመጡን እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡

 እምቅ-አቅምን ለማውጣት የሚረዱ ቁልፎች 

በአንድ ምርት ላይ እምቅ-አቅንም ፈጠርን ማለት እምቅ-አቅሙ የግድ ይወጣል ማለት አይደለም፡፡ አንድ ዘር
ጥሩ በሚባለው ሁኔታ ውስጥ ከሆነ በሳምንቱ ወይንም በሁለት ሳምንቱ ነው የሚራባው፡፡ በእነዚህ ቀደም ባሉ
የዕድገት ሳምንታት ወቅት ጥሩ እንክብካቤ አስፈላጊ መሆኑ ባያጠያይቅም ኮትኳቹ ግን የአትክልቶቹን ሙሉ
እምቅ-አቅም ማደግ እስኪጀምሩ ድረስ አያየውም፡፡

እኛ የሰው ልጆች ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር በውስጣችን ያስቀመጠውን እምቅ-አቅማችንን ቅንጫቢ በማየት


እንኳ በደስታ እንፍነከነካለን፡፡ ኢየሱስ በልባችን እንዲገባ ከጋበዝንባቸው የመጀመሪያ ሳምንታት እና ወራት
በኋላ ጊዜያችንን መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ፤ በጸሎት፤ አምልኮ እና የቃል ጥናት እናሳልፋለን፡፡ በዚህ ወቅት
አሁን ከምንገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ አሻግረን ወደፊት በመመልከት አዲሱን የእምነት ዓለም እናያለን፡፡ በዚህ
ጊዜ በየዕለቱ ራሳችንን እግዚአብሔር ላስቀመጠልን ዓላማዎች እና ምክንያቶች ስንከፍት በውሳኔያችን

33 | P a g e
እግዚአብሔር እንዲመራን እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሔር የሚያዘንብልንን ብዙ ምርቃትና ባረኮት
እንደሰትበታለን፡፡ በተቻለ መጠን ራሳችንን በማስተካከል ሕልሞቻችን እና ሀሳቦቻችን ፍጻሜ የሚያገኙበትን
መንገድ እንፈልጋለን፡፡ ይሁን እንጂ ጊዜ ባለፈ ቁጥር የእምቅ-አቅማችን ጫካ ቀደም ባሉት ጊዜያት የነበረውን
አዲስነት እና ጥንካሬ ቀስ በቀስ እያጣ የተለያዩ ሁኔታዎች እና ኃላፊነቶች በውሰጥጣችን ተደብቆ የነበረውን
የግምት ኃይል እና መልካም አጋጣሚ የሚፈልግ እምቅ ነገር ያፍኑብናል፡፡

ምናልባትም እርስዎ እግዚአብሔር በውስጥዎ ካስቀመጠው ሀብት የተወሰነውን ለዓለም ጥቅም ሲሉ


እያዋሉት ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ ያለዎት ግስጋሴና አካሄድ ግን ዘገምተኛ ወይንም ሊቆም የደረሰም ሊሆን
ይችላል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ያቀረብኳቸው ደረጃዎች እግዚአብሔር በውስጥዎ ያስቀመጠውን እምቅ-አቅም ነጻ
ሲያወጡ የሚጠቀሙባቸው ቁልፎች ናቸው፡፡

ቁልፍ # 1 እምቅ-አቅምዎን ማዳበር አለብዎት

ልምድ ያዳበሩ አትክልተኞች አረም ከአትክልት ፈጥኖ እንደሚያድግ ያውቃሉ፡፡ አንድ አትክልተኛ ለረጅም
ሳምንታት ያህል ጊዜ ከአትክልቱ ርቆ ቢሄድ ሲመለስ የተበላሸ፤ ዕድገቱ የተገታ፤ ጥቂት ብቻ ወይንም ምንም
ፍሬ የማያበቅል የአትክልት ቦታ ነው የሚጠብቀው፡፡ ይኼ የሚሆነው አረሞች ቀስ ብለው እየወጡና እያደጉ
የነበሩትን ተክሎች ስለሚያፍኗቸውና ስለሚቀጯቸው ነው፡፡ በመሆኑም እንክብካቤ ለጤናማ እና ምርታማ
ዕድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡

እምቅ-አቅም በባሕሪው ልክ እንደ ዘር ነው፡፡ የተደበቀና የተቀበረ ግን መውጣት የሚገባው ኃይል ነው፡፡
ለእምቅ-አቅማችን ጥሩ የሚያበረታታ ሁኔታና አካባቢ ያስፈልጋል፡፡ እርስዎ መቅረብና መፈለግ ያለብዎት
ቀና እና አበረታች የሆኑትን ሰዎች ነው፡፡ ወደ ቀድሞ ዓይነት ሕይወትዎ እንዲመለሱና ተንሸራተው እንዲገቡ
የሚያደርጉዎትን፤ የሚገፋፉዎትን ሰዎች በተቻለ መጠን ይራቁ፡፡ ይልቅ ምንጭዎትን በመቅረብ እምቅ-
አቅምዎን አሟጠው ከመጠቀም ከሚያግዱዎ ነገሮች ነጻ እንዲያወጣዎ ይፍቀዱለት፡፡ ብዙ እያቆጠቆጠ
የሚገኝ እምቅ-አቅም እንክብካቤ በማጣት ይሞታል፡፡ ያለዎትን የእምቅ አቅም ሀብት በተቻለ መጠን
መጠበቅና ማቆየት አለብዎ፡፡

ቁልፍ # 2 እምቅ-አቅምዎን መጠበቅ አለብዎት

በጣም በርካታ አትክልተኞች በጥንቃቄ ያሳደጉት እና የኮተኮቱት አትክልት በጥንቸል፤ ተባይ እና አእዋፍ
ሲበላሽ ሲያዩ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ አትክልቶቻቸውን ከእንዲህ መሰል ጥፋት ለመከላከል ሲሉ የሚረጩ
መድኃኒቶችን፤ አጥሮችን እና እንስሳትን ለማስፈራራት የሚያገለግሉ ቋሚ ነገሮችን ይጠቀማሉ፡፡

34 | P a g e
ሰይጣን የእኛን እምቅ-አቅም ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቷል፡፡ ችሎታዎቻችን ተቀብረው እንዲቀሩ የተለያዩ
ሁናቴዎችን፤ ባሕሪያትን፤ አመለካከቶችን፤ ነገሮችን እና ሰዎችን ጭምር በመሳሪያነት ይጠቀማል፡፡ የተደበቀ
ሀብትዎን ካልጠበቁት በቀር ምናልባትም እንጥፍጣፊውን ካልሆነ በጥቅም ላይ ሲውል አያዩትም፡፡ ሙሉ
እምቅ-አቅምዎን ማውጣት የሚችሉት ሕልሞችዎን፤ እቅዶችዎን እና ፈጠራዎችዎን በተቻለ መጠን
ሲንከባከቡ፤ ከበርካታ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ሲጠብቁ ነው፡፡

ቁልፍ # 3 እምቅ-አቅምዎን ለሌሎች ማጋራት አለብዎት

አትክልተኝነት የጋራ ጥረት ነው፡፡ አትክልተኛው መሬትን ሲያርስ፤ ዘር ሲዘራ፤ አረም ነቅሎ ሲያወጣ
ቢቆይም እንኳ ንቦች እንቡጦቹን አበቦች ካልቀሰሟቸው፤ ጸሐይ መሬትን ካላሞቀች እና ዝናብ ደግሞ አፈር
ንጥረ-ነገሮቹን በመታጠብ እንዲያወጣ ካላደረገው በቀር በቀር ተክሎች ሊያድጉ አይችሉም፡፡

የእኛን እና በዚህች ምድር ላይ የሚቆጠሩ የሌሎችን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕዝቦችን እምቅ-አቅም


ማዳበርም የጋራ ጥረት ነው፡፡ እምቅ-አቅም ለጋራ እንጂ ለግለሰባዊ ጥቅም ሲባል አልተሰጠም፡፡ ሙዚቀኞች
ተባብረው የተለያዩ ታለንታቸውን ለጋራ ጥቅም በማውጣት የማይጫወቱት ከሆነ ግጥምና ዜማ ሲደረድሩ
መዋል ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ሙዚቃውን የመጫወት ልምድም ሙሉ እርካታን ሊሰጥ የሚችለው ያንን
የሚቀበልና የሚያደንቅ ተመልካች በኮንሰርት አዳራሹ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡

እምቅ-አቅም ለጋራ እንጂ ለግለሰባዊ ጥቅም ሲባል አልተሰጠም፡፡

እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን የፈጠረው ከራሱና እና ከሌሎች ጋር በወዳጅነት ይኖሩ ዘንድ እንደሆነ
ይታወቃል፡፡ ፍቅር-አልባ የሆነ እና ስኬትን ለራሱ ብቻ አድርጎ የሚቆይ ሕይወት እምቅ-አቅሙን የማውጣት
ተነሳሽነቱን ብዙም ሳይቆይ ያጣል፡፡ ተሰጥኦዋችንን፤ ምኞታችንን እና ክህሎታችንን በነጻ ብንሰጥ እምቅ-
አቅማችን ይጎለብታል፡፡

ቁልፍ # 4 የገደብ ሕግጋትን መረዳት እና ማወቅ ይኖርብዎታል

ማንኛውም ልምድ ያዳበረ አትክልተኛ ቢሆን የአንድን አትክልት ቦታ አጠቃላይ ዕድገት ወይንም ውድቀት
የሚወሰኑ ሕግጋቶችን ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ለስለስ ያሉ ተክሎች ለምሳሌም ድብን ባለ የቀትር ፀሐይ ላይ
ቢተከሉ እንደሚጠወልጉ ይታወቃል፡፡ በጣም አናሳ ወይንም ተክል-አልባ የሆነ ውጤት የሚገኘው ውሃ
በሚገባና ተከታትሎ ካለማጠጣት ነው፡፡ ከአረም ነጻ በሆነ ከባቢ ሁኔታ ውስጥ የሚያድጉ ተክሎች በአረም

35 | P a g e
ውስጥ ከሚያድጉት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ምርትና ውጤት አላቸው፡፡ አትክልተኛው እነዚህን ሕግጋቶች ችላ
ማለት ቢችልም በዚህ ውሳኔው የተነሳ የሚመጣውን ግን ማስቀረት አይችልም፡፡

እምቅ-አቅም ላይም ይኸው ተመሳሳይ መርህ ነው የሚሰራው፡፡ እግዚአብሔር እምቅ-አቅማችንን


ለማጎልበት የሚሆን ነጻነት ሰጥቶናል፡፡ አምላክ ከዚህ በተጨማሪም እምቅ-አቅማችንን ለመጠበቅና
ለመከላከል ሲል ትዕዛዛትን እና ሕግጋቶችን ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህን ሕግጋቶችና ትዕዛዛት የማክበርም ሆነ
ያለ ማክበርን ነጻነት አለገደብ ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሔር እንድናልም፤ እንድንመኝ እና እንድናቅድ እንዲሁም
እነዚህን ሕልሞቻችንን ለማሳካት ደግሞ የሚያስፈልገውን ኃላፊነት ጭምር በውስጣችን አኑሯል፡፡ ነጻነት
ያለ ሕግ ሲሆን ዓላማ-ቢስነቱ አያጠያይቅም፡፡ ሥልጣንም ያለ ኃላፊነት ውጤታማ አይሆንም፡፡ አንዱ ሌላው
ጥፋትን ይከላከልለት ዘንድ የግድ ያስፈልገዋል፡፡ አንዱ ያለ ሌላው አይሄድም፡፡ እንግዲህ ሙሉ እምቅ
አቅማችንን ለማውጣት ከፈለግን እግዚአብሔር ይኼ አቅማችን በተሟላ ሁኔታና ተሟጦ ይወጣ ዘንድ
ይረዳሉ ብሎ ያስቀመጣቸውን ሕግጋትና ትዕዛዛት ሳናዛንፍ ማክበር አለብን፡፡

 እምቅ-አቅምን ለመቆጣጠር የሚረዱ መርሆች 

1. እግዚአብሔር የሚያነጋግረው የፍጡሩን ምንጭ ነው


2. ሁሉም ነገሮችምቅ-አቅም ለጋራ እንጂ
3. ሁሉም ነገሮች በመጡበት ምንጭ አማካይነት ተጠብቀው መቆየት አለባቸው
4. የማንኛውም ፍጡር እምቅ-አቅም ከመጣበት ምንጭ ጋር ይያያዛል
5. በሕይወት ያለ ማንኛውም ፍጡር ዓላማውን ለማሳካት የሚሆን እምቅ-አቅም አለው
6. እምቅ-አቅም የሚወሰነው በፈጣሪው አማካይነት በሚቀርብለት ጥያቄ ነው

 እምቅ-አቅምን ለማውጣት የሚረዱ ቁልፎች 

1. እምቅ-አቅምዎን ማዳበር አለብዎት


2. እምቅ-አቅምዎን መጠበቅ አለብዎት
3. እምቅ-አቅምዎን ለሌሎች ማጋራት አለብዎት
4. የገደብ ሕግጋትን መረዳት እና ማወቅ ይኖርብዎታል

36 | P a g e
5. ትክክለኛው ከባቢ ሁኔታ ሊኖርዎ ይገባል
6. እምቅ-አቅምዎን መጠቀም ይኖርብዎታል

 መርሆች 

1. እርስዎ የመጡት ከእግዚአብሔር ነው


2. የእግዚአብሔርን ተፈጥሯዊ ባሕሪና መሠረት ይጋራሉ
3. ከእግዚአብሔር ጋር ትስስር እስከሌለዎት ድረስ ሟች ነዎት
4. እምቅ-አቅምዎ በእግዚአብሔር እምቅ-አቅም ይወሰናል
5. እግዚአብሔር እምቅ-አቅምዎን የመጠቀም ክህሎትን ሰጥቶዎታል
6. እግዚአብሔር የሚፈልግብዎትን ማድረግ ይችላሉ ምክንያቱም ቀድሞውንም ያንን ለማድረግ የሚያስችለውን አቅም በውስጥዎ
አኑሯል

ምዕራፍ 5

_____________________ _____________________

37 | P a g e
መሠረት የሚጥልልን ቁልፍ

እርስዎ የእግዚአብሔርን እምቅ-ኃይል ያወጡ ዘንድ ተፈጥረዋል፡፡

የአንድ ሪሶርስ ምንጭ እምቅ-አቅሙን ይወስነዋል፡፡

ለት እምቅ-አቅም በፈጣሪው አማካይነት በሚቀርብለት ጥያቄ መጠን ይወሰናል፡፡ እነዚህ የሚቀርቡ


ጥያቄዎች ደግሞ አምራቹ ምርቱን ለመፍጠር በተጠቀመባቸው ዲዛይኖችና ክፍሎች ይወሰናሉ፡፡ በመሆኑም
አንድ የምርት ፈጣሪ ምርቱ አንድን ነገር እንዲያደርግለት ሲፈልግ አስቀድሞ በምርቱ ውስጥ ካስቀመጠው
ችሎታ በላይ ምርቱ እንዲጠቀም አይጠብቅም፤ አይፈልግምም፡፡

 ምንጭ በእምቅ-አቅምዎ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ 

ተቻለ እግዚአብሔር እምቅ-አቅምዎን በተቻለ መጠን እንዲጠቀሙ እና እንዲያጎለብቱት ነው ወደዚህች


ምድር እርስዎን ያመጣው፡፡ ይኼ ሊሆን የሚችለው ግን እርስዎ ከምንጭዎ ጋር ትስስር ያለዎ እንደሆነ ብቻ
ነው፡፡ ለምን ምክንያቱም የአንድ ነገር ምንጭ እምቅ-አቅሙን ይወስናል፡፡ ከምንጩ ውጭ ግን አንድ ምርት
ምን እንደሚሰራም ሆነ እንዴት እንደሚሰራው አያውቀውም፡፡ የእኛ የሁላችንም ምንጭ/ፈጣሪ የሆነው
እግዚአብሔር ከመወለዳችን በፊት ማንነታችንን፤ እንዴትና ምን ማድረግ እንዳለብን፤ ለምን ሲል ሕይወት
እንደሰጠን እና የተሟላ እና ምርታማ ሕይወትን ለመምራት ምን እንደሚያስፈልገን ወስኗል፡፡ ከእሱ ውጭ
እምቅ-አቅምዎን አይረዱም ወይንም አያወጡም ለምን ቢባል እምቅ-አቅምዎ ከእሱ ጋር የተሳሰረ ነውና፡፡

 እምቅ-አቅምዎ ማንነትዎን ይወስናል 

የክርስትና እምነትን ሲቀበሉ እግዚአብሔር ስምዎትን ቀየረ፡፡ በወቅቱ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ ‹‹አንተ
እንደ ልጄ እንደማትንቀሳቀስና እንደማታደርግ አውቃለሁ፡፡ ግን ልጄ ነህ፡፡ አሁን ያለህበት መከራም ችግርም
ጊዜያዊ ከመሆን አያልፍም፡፡ የእኔ እና የአንተ መንፈስ የተቆራኙ ናቸውና ባሕሪህ ከተፈጠርክበት ዓላማ ጋር
እንዲገናኝ በውስጥህ መስራት እጀምራለሁ፡፡ እስከ አሁን የነበረህ ማንነት አጠቃላይ እና ሊኖርህ የሚችለው
ማንነትህ አይደለም፤›› ሲል ተናገረ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ መዝሙረ ዳዊት ላይ ይኼንኑ የሚያረጋግጥ ነገር እናገኛለን፤

38 | P a g e
አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፡፡

እግዚአብሔር ደረጃችንን ከፍ ሊያደርግ በመፈለጉ አማልክት ናችሁ አይለንም፡፡ ይልቅ ጥሬ ሃቅ ነው የገለጸው፡፡


ሐዋርያው ጴጥሮስ በሁለተኛው ደብዳቤው ይኼንኑ ጽንሰ-ሀሳብ ያጠናክረዋል፤

የመለኮቱ ኃይል፤ በገዛ ክብሩ እና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፤ ለሕይወት እና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን
ነገር ሁሉ ስለሰጠን በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ፡፡

ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕሪ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ በእነዚያ
ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋ ሰጠን፡፡

(2 ኛ ጴጥሮስ 1፡ 3-4)

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥር መለኮታዊ ተፈጥሮውን እና ባሕሪውን እንድንጋራው በማሰብ ነበረ፡፡


የሰው ልጅ ከዚያ በኋላ ይኼንን ተስፋ በሐጢአቱ ቢያደበዝዘውም እግዚአብሔር ግን አሁንም ፍላጎቱ ያ ነው፡፡
በመሆኑም ጴጥሮስ እንደ እግዚአብሔር ተፈጥሯዊ ባሕሪ እንድንሄድ ያበረታታናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ይኼንን
ብናደርግ በየዕለቱ የሚመጡብንን ፈተናዎችና ማዘናጊያዎች በቀላሉ ማለፍ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር
ቅዱስ፤ መልካም እና ምህረትን አድራጊ እንድንሆን ይፈልጋል---እነዚህ ባሕሪያቶቹ በመሆናቸውና እኛም
ስለምንጋራቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ዳግም ትስስርን ስንፈጥር እሱ የሆነውን ሁሉ ለመሆን ኃይሉ ይኖረናል፡፡

ለመሆኑ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ምድር ላይ በነበረበት ታሪካዊ ወቅት ከኃይማኖት መሪዎች ጋር
ያጋጨው ምን እንደነበረ ያውቃሉ ምክንያቱም በእነሱ አረዳድ እጅግ የበዛ ተፈጥሯዊነት ነበረው፡፡
የአይሁዳውያን መሪዎች መንፈሳዊነትን በሚለኩባቸው ሕግጋቶችና ደምቦች ሁሉ አልተመራም፡፡ እንዲህም
ሆኖ ግን፤ ‹‹እኔ እና እግዚአብሔር ጥብቅ ትስስር አለን፤›› ለማለት ድፍረቱ ነበረው፡፡ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር
ምልከታ አንጻር ነበረ ነገሮችን የሚረዳው፡፡

እርስዎም የምንጭዎን ተፈጥሯዊ ባሕሪ ይይዙ ዘንድ ይጠበቃል፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከተፈጥሮ በላይ
ሳሆን በተፈጥሮ አኳኋን እንድንኖር ነው የሚጠብቁብን፡፡ የክርስትና እምነት ተከታይ ከሆኑ እርስዎ ከሱ
የመነጩ በመሆንዎ የእግዚአብሔር ተፈጥሯዊ አሠራር ይኖርዎታል፡፡ በተጨማሪም ደግሞ ምርት ሁልጊዜም
የምንጩ ባሕሪ አለው፡፡ ለዚህ ነው ቢጾሙ፤ ቢፀልዩ; ቢለግሱ፤ ራስዎን ከክፉ አስተሳሰቦች ቢያፀዱ፤ ከአደንዛዥ
እጽና ሌሎች ሱሶች ነጻ ቢሆኑ እግዚአብሔር የማይገረመው፡፡ እግዚአብሔር ምንጭዎ/ፈጣሪዎ በመሆኑ እና
ልጁም በመሆንዎ እንደ እሱ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡

39 | P a g e
የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከተፈጥሮ በላይ ሳሆን በተፈጥሮ አኳኋን
እንድንኖር ነው የሚጠብቁብን፡፡

 ምንጭዎ/ፈጣሪዎ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይወስናል 

ማድረግ የሚችሉት ነገር ከምንጭዎ ጋር ይያያዛል፡፡ እግዚአብሔር፤ ‹‹ያለ እኔ ምንም መስራት አትችይም››
ሲል ትርጉሙ ያ ነው፡፡ ይኼ የመንፈሳዊነት ጉዳይ ሳይሆን በትክክል አሠራሩን የሚገልጽ እንደሆነ መረዳት
ያስፈልጋል፡፡ እሱ እርስዎን ፈጠረ፤ ሰራዎት፡፡ በመሆኑም የእርስዎ ችሎታ ጥራት ከሱ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምን
ማድረግ እንደሚችሉ ማወቅ ከፈለጉ እግዚአብሔር መስራት የሚችለውን በቅድሚያ ይወቁ፡፡

ሁሉን-ቻይ የሆነው እግዚአብሔር እርስዎን ወደዚህች ምድር ያመጣው እምቅ-አቅሙን ይጋሩለት ዘንድ ነበረ፡፡
እግዚአብሔር እርስዎን በራሱ አምሳያ ሲፈጥር እዚያው በዚያው ነበረ የፈጠራ ክህሎትን በውስጥዎ
ያስቀመጠው፡፡ እርስዎ ሕልምን ወደ እውነታ ለመቀየር የእግዚአብሔርን የማቀድ እና ዲዛይን የማድረግን
እምቅ-አቅም ይጋራሉ፡፡ እግዚአብሔር እርስዎም ሆኑ ሌላ ማንም ሰው ከሚገምተው በላይ ምኞቶችና
ፕሮጀክቶችን በውስጡ ይዟል፡፡ የማይቻሉ ነገሮች አምላክ ነው፡፡ ሆኖም የእምቅ-አቅሙን መገለጽ ከእኛ
ሕልም፤ ምኞት እና ጸሎት ጋር አስተሳስሯል፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር አዘውትሮ የማይቻለውን እንሞክር
ዘንድ የሚወተውተን፡፡ የሚቻለውማ እሱን ምንም አይመስጠውም፡፡ ያንን ካደረገው ቆየ፡፡ እግዚአብሔር
ዓለም ገና ያላሳካቻቸው ዕቅዶች፤ ሐሳቦችና ዓላማዎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

እግዚአብሔር የእምቅ-አቅሙን መገለጽ ከእኛ ሕልም፤ ምኞት እና ጸሎት ጋር አስተሳስሯል፡፡

እርስዎ ለእግዚአብር የፈጠራዊ ገለጻ ቁልፍ ሚና አለዎት፡፡ ፈጣሪዎ በእርስዎ ውስጥ ካስቀመጠው በላይ
ፈጽሞ ስለማይጠብቅብዎት የሚጠይቅዎትን ማንኛውንም ነገር መፈጸም ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር ለእርስዎ
እንዲህ ይላል፤ ‹‹የፈለግከውን ተመኝ፡፡ እኔ የሌለኝን ልታቅድ አትችልም፡፡ እኔም የግምት ችሎታህን
ስለማውቅ ነው ይኼንን አቅድ የምልህ፡፡ ያንተ እምቅ-አቅም ከእኔ እምቅ-አቅም ጋር የተሳሰረ ሲሆን እኔ
ደግሞ ሁሉን-ቻይ ነኝ፡፡››

 ምንጭዎ/ፈጣሪዎ እንዴት እንደሚሰሩ ይወስናል 

40 | P a g e
ራዕይ ማለት እግዚአብሔር ሌላ ማንም ሰው ሊከውነው የማይችለውን እና ለእኛ የተለየውን ነገር እንድንሰራ
ሲጠይቀን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከዚህ ቀደም ሲሰራ ያየነውን ነገር መጠየቀ ችግር የለውም፡፡ ግን
እግዚአብሔር ከዚያ በላይ መስራትን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር እምነትን ይወዳል፡፡ የእሱ አሰራር እንደዚያ
ነው፡፡ ለነገሩ የእርስዎም ነው፡፡ እግዚአብሔር ልክ እንደ እሱ ይንቀሳቀሱ ዘንድ ነው ዲዛይን ያደረገዎት፡፡
እምነት ማለት ሌላ ማንም ሰው ያላየውን ግን በውስጡ ያለውን እንዲያወጣ እኛ ስንጠይቀው ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ከዚህ ቀደም ሲሰራ ያየነውን ነገር መጠየቀ ችግር የለውም፡፡ ግን እግዚአብሔር ከዚያ
በላይ መስራትን ይፈልጋል፡፡

ለመሆኑ እርስዎ ከዚህ ቀደም ማንም ገብቶ ወጥቶበት የማያውቅ ችግር ውስጥ ተዘፍቀዋል ማንም
ሊፈታው ያልቻለው ችግር ገጥሞዎታል ሙሉ በሙሉ ግራ ያጋባዎትና የት መሄድ ይኖርብኝ ይሆን እንዲሉ
ያደረገዎት ፈተና ውስጥ ወድቀዋል የሆነው ሆኖ ግን እግዚአብሔር ፀጋውን ለመግለጽ ትክክለኛ ምርጫው
አድርጎዎታል፡፡

ከዚህ ቀደም፤ ‹‹ለሷ አድርጎላታል እኮ፤ ታዲያ ለእኔም በእርግጠኝነት ያደርግልኛል›› እል ነበረ፤ አሁን ይኼንን
አባባል አሽቀንጥሬ ከጣልኩ ቆየሁ፡፡ እግዚአብሔር ከዚህ ቀደም አድርጎት የማያውቀውን አንድ ነገር ለእኔ
እንደሚያደርግ አውቃለሁ፡፡ የእግዚአብሔር እምቅ-አቅም ሀብት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ ያለ እሱ አንድም የተፈጠረ
ነገር የለም፡፡

እግዚአብሔርን አድርግልን ብለን ስንጠይቀው ደስታን ያገኛል፡፡ እግዚአብሔርን ማስደሰት ከፈለጉ ከዚህ
ቀደም አድርጎት የማያውቀውን ይጠይቁት፡፡ እምነትዎን ያሳዩት፡፡ እንዲህ ነው እሱ የሚሰራው፡፡ ያለ እምነት
እግዚአብሔርን ማስደሰት አንችልም (ዕብራውያን 11፡ 6)፡፡

 ምንጭዎ/ፈጣሪዎ ለምን በምድር ላይ እንደሚኖሩ ይወስናል 

እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠረዎት ካላወቁ ዓላማዎትንም አያውቁትም፡፡ የእርስዎን ዓላማ የሚያውቀው


እግዚአብሔር ብቻ ነው--ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ እርስዎን ሲፈጥር ዓላማዎትን ወስኖታልና ነው፡፡ እርስዎ
በአጋጣሚ አይደለም ወደዚህች ምድር የመጡት፡፡ መዝሙር 139 ላይ እግዚአብሔር ገና የመጀመሪያ
እስትንፋስዎን ሳይተነፍሱ ጊዜዎትን እንደወሰነው እና ባልተፈጠረው ገላዎ ላይ ሥራውን እንደጨረሰ ያሳያል፡፡
እናም እግዚአብሔር ገና እርስዎን ሳይፈጥር ምን እንዲሰሩለት እንደሚፈልግ ወስኗል፡፡

ስኬታማ እና እርካታን የሚያጎናጽፍ ሕይወትን ለመምራት መከተል የሚያስፈልግዎ አቅጣጫ በቤተሰብዎ


አባላት፤ በመምህራን፤ በአለቆችዎ፤ በነፍስ ወይንም ንሥሀ-አባትዎ አልያም በሥራ ባልደረቦችዎ አይወሰንም፡፡

41 | P a g e
እነሱም ልክ እንደ እርስዎ ሁሉ ፍጡራን ናቸው፡፡ እግዚአብሔር መንፈስን በውስጥዎ ሲያኖር አልነበሩምና
የተወለዱበትን ምክንያት እነዚህ ሰዎች ሁሉ ሊነግሩዎ አይችሉም፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሀሳብም
ሆነ እቅድ የማወቅ ልዩ ተሰጥዖና ጥቅም የላቸውም፡፡ በመሆኑም እርስዎ ዓላማዎን ሊያውቁ የሚችሉበት
ብቸኛው መንገድ ከፈጣሪዎ ከእግዚአብሔር ጋር አስተማማኝ ግንኙነት በመፍጠር ነው፡፡ እግዚአብሔር
ለእርስዎ ያሰበው ነገር እምቅ-አቅምዎን ይቀርጻል፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በጥንቃቄ ፍላጎቱን
እንዲያሟሉለት ዲዛይን ያደረገዎ መሆኑ ነው፡፡ እርስዎ እምቅ-አቅምዎን እንዲያወጡ በየጊዜው
እግዚአብሔርን መፈለግ እና በአዕምሮዎም እቅድ ሲያወጣ ምን ፈልጎ እንደነበረ መረዳት ይኖርብዎታል፡፡

 ምንጭዎ/ፈጣሪዎ በከፍተኛ ደረጃ ለመፈጸም


የሚያስፈልጉዎትን ሪሶርሶች ይወስናል 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጉዘ ያደርግ ስለነበረ አንድ ሰው የተናገረው ታሪክ አለ፡፡ ይህ ሀብታም የነበረ እና
በሥሩ አገልጋዮች የነበሩት ሰው ለጉዞው ከቤት ከመውጣቱ ቀደም ብሎ ከነበረው ሀብት ላይ ይመሩበት ዘንድ
ለሠራተኞቹ ያከፋፍላል፡፡ ጉዞውን አጠናቆ ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜም እያንዳንዳቸውን በመጥራት የሰሩትን
እንዲያወራርዱ ይጠይቃቸዋል፡፡ በተመለሰ ጊዜ ሁሉም ሠራተኛ እኩል የሆነ ሪሶርስ እጁ ላይ ይኖራል ብሎ
ባይጠብቅም አጠቃላይ ሀብቱን በሚጨምር መልኩ የሰሩት ሥራ ግን ይኖራል ብሎ ገምቷል (ማቴዎስ 25፡ 14-
30)፡፡

እግዚአብሔር እርስዎ ደስተኛ እና የበለፀገ ሕይወት እንዲኖርዎ የሚያስፈልጉዎትን ሪሶርሶች ወስኗል


ምክንያቱም ቀደም ሲል ከእርስዎ የፈለገውን ለማሟላት ይችሉ ዘንድ ምን ያህል እንደሚያስፈልግዎት
የሚያውቀው እሱ ብቻ በመሆኑ፡፡ እርስዎ ሪሶርሶችዎን ከሌሎች ሰዎች ሪሶርሶች ጋር ሁሌ የሚያነጻጽሩ
ቢሆን እግዚአብሔር በሰጠዎ ሪሶርስና መስራት በሚጠበቅብዎ ነገር ብቻ ታውረው ይኖራሉ፡፡ እርስዎ ሙሉ
እምቅ-አቅምዎን ማውጣት ይችሉ ዘንድ ሕይወትዎን በጥንቃቄ በመፈተሽ እግዚአብሔር የሰጠዎትን ብዙ
ሀብቶች እና የሰጠበትን ምክንያት መመርመር ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር የሰጠዎትን ሪሶርስ በብልሀት
መጠቀምዎን ሳያረጋግጥ ተጨማሪ ሪሶርሶችን አይሰጥዎትም፡፡

እግዚአብሔር የሰጠዎትን ሪሶርስ በብልሀት መጠቀምዎን ሳያረጋግጥ ተጨማሪ ሪሶርሶችን


አይሰጥዎትም፡፡

 ምንጭዎ/ፈጣሪዎ በከፍተኛ ደረጃ ለመፈጸም


የሚያስፈልጉዎትን ሁኔታዎች ይወስናል 

42 | P a g e
ፈጣሪዎ/ምንጭዎ ለእርስዎ ከፍተኛ ክንዋኔ አስፈላጊ የሆነውን ከባቢ-ሁኔታ በብቸኝነት ይወስናል፡፡ ይኼንን
የሚያደርገው ደግሞ በሕግጋቶቹ እና ትዕዛዛቱ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሔር ሕግጋቶች
ለእርስዎ እጅግ ተመራጭ በሚባለው ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ግብዓቶች ከመወሰንም አልፎ ተከታታይ፤ ጤናማ
ዕድገት እንዲኖርዎ የሚጠበቁ ቅድመ-ሁኔታዎችንም ጭምር ይወስናል፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት
አካባቢዎትን ተንከባክበው እንዲቆዩ ያስችላሉ፡፡ እነዚህ ትዕዛዛትና ሕግጋት የእርስዎን አስተሳሰብና ጤናም
ጭምር ይወስናሉ፡፡ የእርስዎ ደኅንነት የእግዚአብሔርን ሕግጋቶች በመረዳትዎ ላይ ይወሰናሉ፡፡ አለመታዘዝ
የተበከለ አካባቢን ይፈጥራልና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት አለማክበር ትልቅ ጉዳት ያደርስብዎታል፡፡ ይኼ
ደግሞ ዞሮ ዞሮ እምቅ-አቅምዎን የሚያፍን መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

እርስዎ ለእግዚአብሔር ሲሉ ረጅም ርቀት ለመጓዝና ብዙ ነገሮችን ለመከወን እምቅ-አቅም አለዎት፡፡ ይሁንና
አስፈላጊ የሆነውን ከባቢ ሁኔታ ጠብቆ በማቆየቱ ረገድ ከደከሙ በሐይወትዎ አንዳችም ነገር ሳይፈጠር
ይቀራል፡፡ እርስዎ ስለሚችሉት፤ ወይ ስለሚፈልጉት ወይ ስለሚመኙት ነገር ምን ያህል ያወራሉ የሚለው
ብዙም ዋጋ የለውም፤ ይኼንን ሁሉ ሲያደርጉ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ካልጠበቁ ግን እውነተኛው ማንነትዎ
ሳይወጣ ይቀራል፡፡

 ምንጭዎ/ፈጣሪዎ እምቅ-አቅምዎን እውን የሚያደርጉበትን


(ማለትም አስቀድሞ ዲዛይን በተደረጉበት መልክ)
ዘዴ ይወስናል 

እግዚአብሔር ለሕይወትዎ ያስቀመጣቸውን ዕቅዶች ለእርስዎ ማጋራት መፈለግ ብቻ ሳይሆን እነዚህን


እቅዶች እውን ለማድረግ ይችሉ ዘንድ የሚያስፈልጉዎትን የተለያዩ ተሞክሮዎችም ጭምር እንዲረዱ
ጭምር ይሻል፡፡ ዛሬ ብዙ ሰዎች የሕይወትን ትርጉም ብናገኝ ብለው ከአንዱ ወደ ሌላው በመዳከር ብዙ
ነገሮችን ሲሞክሩ ይስተዋላሉ፡፡ ከአንድ ሥራ ወደ ሌላው፤ ከአንድ አጥቢያ የአምልኮ ቦታ ወደ ሌላው፤ ከአንድ
ከተማ ወደ ሌላው፤ ባል ወይ ሚስት በመቀያየር ሁሉ ይቅበዘበዛሉ፡፡ ታዲያ በሕይወት መንገድ ላይ አቀበቱ
ሲበዛባቸው አንዱን የተሰማሩበትን እና የያዙትን ትተው ወደ ሌላ ይሄዳሉ፡፡ በተሰማሩበት በማንኛውም ነገር
ላይ ለውጥ ሊያመጡ በሚችሉበት ሁኔታ ፀንተው አይቆዩም፡፡

43 | P a g e
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ ሉቃስ ወንጌል 15፡ 8-10 ላይ ድሪም ጠፍቶባት እስክታገኘው ድረስ ቤቷን ጠርጋ
እና እቃ መነቃቅራ ስለፈለገች፤ ኋላም ድሪሟን ማግኘት ስለቻለች ሴት ታሪክ ይነግረናል፡፡ የሚመለከቱ
ሕግጋቶችን ማወቅ ይጠበቅብዎታል፡፡ ያስቀመጥኩት ሳንቲም ጠፋብኝ ብላ ሙሾ አላወረደችም፤ እጆቿን
በማወናጨፍ ተቀምጣ ስድብና እርግማን አልገባችም ይቺ ሴት፡፡ ይልቅ ተነስታ ለፍታ ፈልጋ ግን ከገባበት
አገኘችውና እፎይ አለች፡፡ እንግዲህ ይኼ የአንድ ሰው ፍላጎት ወደ እቅድ ሲያመራ ነው የሚያሳየን፡፡ ዕቅዱ
ወደ ትግበራ ተቀየረ፡፡ እምቅ-ኃይላችን ከተደበቀበት ይወጣ ዘንድ አንድን ነገር ዳር እስኪደርስ ድረስ መከታተል
አለብን፡፡ እግዚአብሔር ከሕይወታችን ምን እንደሚፈልግ ማሰላሰሉና ማውጣት ማውረዱ ብቻውን በቂ
አይደለም፤ ይልቅ ወገብን ጠበቅ አድርጎ ወደ ሥራ መግባት ነው የሚበጀው፡፡

ሥራ እግዚአብሔር እምቅ-አቅሙን ለማውጣት ያስቀመጠው ዘዴ እንደሆነ እንወቅ፡፡ በፍጥረት ታሪክ ላይ


እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር በጣም ባተሌ እንደነበረ እንረዳለን፡፡ እናም ሲጨርስ በጣም ደከመው፡፡
እርስዎም የእግዚአብሔር ፍጡር በመሆንዎ በውስጥዎ የተደበቁትን የሚያማምሩ ጌጣጌጦች ለማውጣት
ጠንክረው መሥራት ይጠበቅብዎታል፡፡ ለፍተው፤ ጥረውና ግረው እምቅ-አቅምዎን ያወጡ ዘንድ ነው
እግዚአብሔር እርስዎን ዲዛይን ያደረገዎት፡፡

 ከ SONY የተገኘ ትምህርት 

ሶኒ እንደሚታወቀው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን አምራች የጃፓን ፋብሪካ ነው፡፡ ከ SONY ዕቃ ሲገዙ


በማኑዋሉ ላይ፤ ‹የአሠራር መመሪያዎች› የምትል ጽሁፍ ያገኛሉ፡፡

ይኼንን ማሽን ከመፈታታትዎ እና በጥቅም ላይ ከማዋልዎ በፊት እነዚህን


መመሪያዎች በጥንቃቄ ያንብቡ

እንግዲህ SONY ከምርቱ ትልቁንና የመጨረሻውን አገልግሎት እናገኝ ዘንድ ማሽኑን ከመጠቀማችን በፊት
ስለ ክህሎቱና አገልግሎቱ ጥራት አብጠርጥረን እንድናውቅ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማኑዋሉን አስቀድመው
ካላነበቡት ኩባንያው በማሽኑ ውስጥ ያኖረውን የላቀ አገልግሎት እምቅ-አቅም አይገነዘቡትም፡፡

እግዚአብሔር በአምሳያው የፈጠረውና እጅግ ውስብስቡና የተራቀቀው ሰው የተባለ እንሰሳ እምቅ-አቅም


መርህም ከዚህ አይለይም፡፡ እርስዎም ቢሆኑ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የማይገነዘቡ ከሆነ እውነተኛ እምቅ-
አቅምዎ ላይ አይደርሱም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለእኛ ያስቀመጠው ማኑዋል ነው፡፡ እግዚአብሔር
በውስጥዎ ያኖረውን ሁሉ በሚገባ እስኪያውቁ ድረስ በትክክል መስራት አይችሉም፡፡

44 | P a g e
በ SONY ማኑዋል የመጀመሪያ ገጾች ላይ ከሰፈሩት መረጃዎች መካከል አንዱ ከላዩ ‹‹የተጠቃሚው ሪከርድ››
ይላል፡፡ በዚህ ገጽ ላይ እርስዎ እንደ ተጠቃሚ የማሽኑን የሴሪ ቁጥር እንዲያገኙ ይጠይቅዎታል በመቀጠልም
ከታች በተዘጋጀው ቦታ ላይ ቁጥሩን እንዲጽፉት ይጠይቃል፡፡

የአንድ ምርት የሴሪ ቁጥር በተመሳሳይ ሞዴል ከተሰሩና ዲዛይን ከተደረጉ ሌሎች ምርቶች ሁሉ ይለየዋል፡፡
እርስዎ ጌታ ኢየሱስን ወደ ውስጥዎ ይገባ ዘንድ በጋበዙባት ቅጽበት እርስዎ እንጂ ሌላ ማንም የማይሄበትን
መንገድ ጀምረዋል፡፡ የግል ባሕሪያቶችዎ እና የሕይወት ተሞክሮዎችዎ ከዚያች ክርስቶስ ወደ ውስጥዎ ከገባ
በኋላ ውሳኔዎችዎ ላይ አስተዋፆ አድርገዋል፡፡ ማንም ሌላ ሰው ቢሆን እርስዎ በሚያደርጉበት ተመሳሳይ
መንገድ የእሱን መኖርና ምህረት አድራጊነት አያጣጥምም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስዎ ፊት ለፊት የዳኑባትን ያቺን
ቀን ሁሌም ያስታውሷት፡፡ የሴሪ ቁጥርዎንም ተከታትለው ይያዙ፡፡

በ SONY አማካይነት በምትወጣው ትንሽ መጽሔት የመጀመሪያዎቹ ገጾች ላይ፤ “specifications”


ተብለው የተቀመጡ ነገሮችም አሉ፡፡ በዚህ ክፍል ላይ የእቃው ወይንም ማሽኑ እያንዳንዱ ክፍል ተለይቶ
የተቀመጠ ሲሆን አንድ ክፍል በሌላ መተካት ቢኖርበት ለዚያ መመሪያ የሚሆኑ ነገሮች ሰፍረዋል፡፡ እነዚህ
ትዕዛዛት ሁልጊዜም፤ አገልግሎት ማግኘት ከፈለጉ ትክክለኛ የ SONY ዕቃዎችን ወደሚጠቀም ወኪልዎ
ይውሰዱት ወይንም ይላኩት የምትል አባባል አለች፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ደግሞ ለእርስዎ የተሰጡ ዝርዝር መመሪያዎች አሉ፡፡ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ
ይሞሉ ዘንድ ነው እርስዎን ዲዛይን ያደረገው፡፡ በዲያብሎስ ወይንም ሌላ ዓይነት የተበላሸ መንፈስ ቢሞሉ
የእግዚብሔርን ዕቅድ ሊያሟሉ አይችሉም፡፡ ለዚህ ነው የሰው ልጅ አለእግዚአብሔር አደገኛ ነው የሚባለው፡፡
ይህ ሰው በደምብ ራሱን ስቷል፡፡ የሰው ምግባሮች ጥሩ ሊሆኑ ቢችሉም እንኳ ባሕሪው ግን መንፈሱን
ማንጸባረቁ ላይ አንጨቃጨቅም፡፡

የሰው ልጅ አለእግዚአብሔር አደገኛ ነው

ጽድቅን ጽድቅ ካልሆነ መንፈስ መጠበቅ ጅልነት ነው፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር ወደ እሱ ሲመለሱ መንፈሱን
የሰጠዎት፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ ትክክለኛና ተገቢ ባሕሪ ሊኖረን አይችልም ምክንያቱም የእኛ ተግባር
ከመንፈሳችን ይመነጫልና፡፡ እርስዎ በፍቅር መስራት ከፈለጉ የፍቅር ምንጭ የሆነው መንፈስ ሊኖረዎ
ይገባል፡፡

የ SONY ዝርዝር መመሪያ ከዚህ በተጨማሪ ኩባንያው በመሣሪያው ውስጥ ያስቀመጣቸውን የተለያዩ አካላት
ይዘረዝራል፡፡ ለምሳሌም በ SONY አማካይነት የተሠራ ቴፕ የመቅጃ ሲስተም፤ ተጨማሪ የድምጽ ማጉያ
ገመድ፤ ባለ አራት ምንጭ የሆነ የኃይል አቅርቦት እና ወደኋላ ማጠንጠንን፤ ወደፊት ማሳለፍን፤ ማቆምን፤
መቅዳትን የመሳሰሉ ትዕዛዛት ለመስጠት የሚያስችል አሠራርንም ያካትታል፡፡

45 | P a g e
እግዚአብሔር እርስዎን ሲፈጥር በኦፕሬሽን ማኑዋል ላይ ባስቀመጣቸው እና ግልጽ ባደረጋቸው የተወሰኑ
ክፍሎች አማካይነት ነው፡፡ በመሆኑም እኛ የሰው ልጆች አካል፤ ነፍስ እና መንፈስ አለን፡፡ በሙሉ እምቅ-
አቅምዎ መስራት ከፈለጉ እግዚአብሔር እነዚህን እያንዳንዳቸውን ክፍሎች እንዴት ዲዛይን እንዳደረገ ማወቅ
ይኖርብዎታል፡፡ እያንዳንዱን ባሕሪ የሚመሩ የተወሰኑ ሕግጋት አሉ፡፡ እነዚህን ሕግጋቶች ከተዉና አልታዘዝም
ካሉ በትክክል እና በአግባቡ ሊሄዱ አይችሉም፡፡

SONY ከዚህም በተጨማሪ ዕቃውን ስንጠቀም የሚያስፈልጉንን ጥንቃቄዎች ይዘረዝርልናል፡፡ ከቴፕ ሪከርደሩ
ትልቁን ግልጋሎትና ሙሉ አቅም መጠቀም ከፈለግን ልናደርግ የሚገባንን በሌላ በኩልም ደግሞ ማድረግ
የሌሉብንን ነገሮች የሚዘረዝር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌም ቴፕ ሪከርደሩ አልሰራ ሲል ዕቃውን በመፍቻ መበታተን
ፈጽሞ የማይመከር መሆኑ ይገለጻል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ነገሮች ማሽኑ በተገቢው ሁኔታ
እንዳይሰራ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ነገርም ይገለጻል፡፡

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥር በውብ ገነት ውስጥ አስቀመጠውና በገነቲቱ ውስጥ ባለው ነገር ላይ ሁሉ
ኃላፊነትን ሰጠው፡፡ ነገር ግን ወዲያው ከተል አድርጎ ጥንቃቄዎችን ነገረው፡፡ ሕይወትዎ ያመጣውን ልዩነትም
ይመዝግቡ፡፡ በዚህ መሠረትም ከሁሉም ዛፎች መብላት ሲፈቀድለት ከአንዷ ክፉና ደግን ከምትለየዋ ዛፍ ግን
እንዳይበላ በግልጽ ተከለከለ፡፡ እግዚአብሔር ይኼን ማድረግ የፈለገው የሰውን ልጅ ከሐጢአት እና ሞት
ለመከላከል በማሰብ ነበረ፡፡ የሰው ልጅ ግን ይኼንን የጥንቃቄ መመሪያ ወደ ጎን ተወ፤ ጣሰ፡፡ በዚህ የተነሳ ዛሬም
ድረስ ከአልታዘዝ ባይነቱ መዘዝ ጋር አብሮ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

እግዚአብሔር ማሳሰቢያና ማስጠነቀቂያ ከሰጠዎት ባላከብረው ምን ይደርስብኝ ይሆን ብለው አይሞክሩት፡፡


የጥንቃቄ መመሪያዎች ሁልጊዜም ቢሆን የተከለከሉ ድርጊቶችን የማድረግን ውጤት ይገልፃሉ ፡፡ አለመታዘዝ
ሁልጊዜም ቢሆን ቅጣትን በመገምገም ይታጀባል፡፡

የኦፕሬሽን ማኑዋሉ በመጨረሻ አምራቹ የሚሰጠውን ዋስትና ይገልጻል፡፡ ይኼ ዋስትና ምርቱ በጊዜ
በተቀመጠ የተወሰነና የሚታወቅ ገደብ ውስጥ ብልሽት ቢያጋጥመው ለጥገና ወደ አምራቹ መውሰድ
እንደሚቻል ያረጋግጥልናል፡፡ ነገር ግን እንበልና እርስዎ በገዙት ቴፕ ላይ በ SONY አማካይነት ተቀምጦ
የነበረውን የነጻ ጥገና ቅድመ-ሁኔታ እና ገደብ ቢጥሱ ኩባንያው ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ እነዚህ ገደቦች
ከምርቱ ኦፕሬሽን፤ ከባቢ ሁኔታ እና ጥገና ጋር ይያያዛሉ፡፡

የእግዚአብሔርን ዋስትና ስንመለከት ደግሞ በውስጡ ስለ ፀጋ የሚያትት አንቀጽ እናገኛለን፡፡ እግዚአብሔር


እርስዎን እንደተበከሉ፤ እንደተበላሹ ይቀበለዎትና ሰይጣን እርስዎን ለማበላሸት ሲል የተከላቸውን ነገሮች
በሙሉ ያጠፋልዎታል፡፡ ምንም እንኳ ጊዜ ይውሰድ እንጂ እግዚአብሔር በአዕምሮዎ ባንክ ላይ አጠቃላይ
የአዕምሮ ፈውስ እና ለውጥ እስኪመጣ ድረስ መስራቱን ይቀጥላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለጸጋው

46 | P a g e
ይመስገን፡፡ እግዚአብሔር ወደ ትክክለኛው ወኪሉ ይሂዱ እንጂ የጥገና ወጪውን በሙሉ ይሸፍናል፡፡ ወደ
ሰይጣን ለጥገና ከሄዱ ግን እግዚአብሔር ይኼንን እንዲያደርግ መጠበቅ አይችሉም፡፡

ወደ ሰይጣን ለጥገና ከሄዱ እግዚአብሔር ይኼንን እንዲያደርግ መጠበቅ አይችሉም

SONY በኦፕሬሽን ማኑዋሉ ላይ የሚገልጽልዎ ሌላው ጉዳይ ቢኖር ማኑዋሉን ወደፊት ለተለያዩ ጥያቄዎችዎ
እና ከምርቱ ጋር የተያያዙ ገጠመኞችዎ ሊያዩት ስለሚፈልጉ እንዲያስቀምጡት ነው፡፡ እርስዎም በሕይወትዎ
የሚገጥሙዎትን የኦፕሬሽን እንቆቅልሾች ለመመለስ የእግዚአብሔርን ማኑዋል ጠብቀው ማስቀመጥ
ይኖርብዎታል፡፡ እርስዎ አሁን እየሰሩ ካሉት ሶስት ሺህ ጊዜ በተሻለ ብቃት መስራት የሚችሉበት ጊዜ ላይ
ሊደርሱ ይችላሉና የእግዚአብሔርን ማኑዋል አይጣሉት፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለተሟላ እና ምርታማ የሆነ
ሕይወት ጠቃሚ የሆኑ ምላሾች ተቀምጠዋል፡፡

ሁሉን-ቻዩ እግዚአብሔር ምንጫችን/ፈጣሪያችን ነው፡፡ በእግዚአብሔር የመመሪያ ማኑዋል ላይ


ለሕይወታችን መሠረታዊ የሆኑ መስፈርቶች፤ ትዕዛዛት እና ማስጠንቀቂያዎች ሰፍረዋል፡፡ የእግዚአብሔር
ሕይወት በእኛ ላይ የሚንጠላጠል አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ውጭም አለ፡፡ የእርስዎ ሕይወት ግን
በእግዚአብሔር ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ እውነተኛ ሕይወትን ለማግኘት እግዚአብሔር የግድ ያስፈልግዎታል፡፡
በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚመሰረት ግንኙነት ወደተሻለ እና የተሟላ
ሕይወት የሚያሸጋግረን ድልድይ መሆኑን እንረዳ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እምቅ-አቅማችንን ለመረዳትና
ለማውጣት የመሠረት ቁልፉ ነው፡፡ እሱንና ዕቅዶቹን ማወቅ ለተሟላ እና ውጤታማ ሕይወት መሠረት
እንደሆነም ጭምር መረዳት ያስፈልጋል፡፡

 መርሆች 

1. እግዚአብሔር መለኮታዊ ተፈጥሯዊ ባሕሪውን እንዲጋሩት ይፈልጋል


2. እርስዎ ለእግዚአብሔር የፈጠራ ክህሎት መገለጽ ምሳሌ ነዎት
3. ከእግዚአብሔር በእምነት እንዲንቀሳቀሱ እርስዎን ዲዛይን አድርጎዎታል

47 | P a g e
4. እግዚአብሔር ለሕይወትዎ የሚሆን ዕቅድ አለው
5. ዓላማዎትን ማወቅ ይችሉ ዘንድ ከፈጣሪዎ ጋር ግንኙነት መመስረት ያስፈልግዎታል
6. ለእግዚአብሔር ትልልቅ ነገሮችን ለማድረግ እምቅ-አቅም አለዎት
7. ሥራ እግዚአብሔር የእርስዎን እምቅ-አቅም ለማውጣት ያስቀመጠው ዘዴ ነው
8. መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በእርስዎ ዙሪያ ያስቀመጠው ማኑዋል ነው፡፡ እርስዎም የተቀመጡትን መስፈርቶች፤ መመሪያዎች
እና ማስጠንቀቂያዎች ማወቅና ማክበር ይጠበቅብዎታል፡፡

ምዕራፍ 6

_____________________ ___________________

48 | P a g e
ምንጭዎትን ይወቁ

የእርስዎ ክህሎት ለእግዚአብሔር ክህሎት

በሚሰጡት አጸፋ ይወሰናል፡፡

በማንኛውም ነገር እምቅ-አቅም ላይ የሚሰራው መርህ በእርስዎ-እምቅ አቅም ላይም ይሰራል፡፡


ፈጣሪዎ/ምንጭዎ እግዚአብሔር የእርስዎን እምቅ-አቅም ይከላከላል፡፡ እርስዎ ከእግዚአብሔር የመነጩ እና
መሠረቶቹን እና ግብዓቶቹን የሚጋሩ በመሆኑ እሴቶችዎን እና እምቅ-አቅምዎን የሚያውቅ እሱ ብቻ ነው፡፡

 የእርስዎን ዋጋ እና እምቅ-ኃይል የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው

በሰው ልጅ የታሪክ ሂደት ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር በገዛ ሐጢአታችን የተነሳ ወደ ድንቁርና እንዳንገባ
ሲከላከል ነበረ የቆየው፡፡ እኛ የገዛ ፍጡራኑ እምቅ-አቅማችንን ስናራክስ እና እሱ የሰጠንን ዋጋ ስንጠራጠር
በሐዘን ይመለከታል፡፡ እሱ እንዲሆኑ በማለት የፈጠራቸው ዓይነት ሰዎች መሆናቸውን የሚያረጋግጥባቸውን
በርካታ መንገዶች በመሳት የወደቀ አካሄድ ሲሄዱ አብሯቸው ያዝናል፡፡

እግዚአብሔር በእርስዎ በኩል ሊያደርጋቸው የሚችላቸው ነገሮች ምን ድረስ ይሄዳሉ የሚለው ከመወለድዎ
ከረጅም ጊዜ በፊት ነበረ የተወሰነው፡፡ እርስዎ ገና አንዷን ቀን እንኳ በዚህች ምድር ላይ ሳይኖሩ እግዚአብሔር
አቅዶት ጨርሷል (መዝሙረ ዳዊት 139፡ 160 ን ይመልከቱ)፡፡ እግዚአብሔር ራስዎን እና ክህሎቶችዎን እሱ
በሚያይበት መንገድ እንዲመለከቱ ይፈልጋል፡፡ እሱ በእርስዎ ላይ ትልቅ ተስፋን የጣለ ሲሆን ከታለንትዎ እና
ክህሎትዎት እንጥፍጣዋን ለመጠቀም በሚያደርጉት ጥረትም ቢሆን ከጎንዎ ይቆማል፡፡ እግዚአብሔር
በእርስዎ ያምናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እርስዎ ግላዊ ዕድገት እና ልዩ ክህሎቶችዎ ብዙ የሚለው አለ፡፡

እግዚአብሔር በእርስዎ ዋጋ ላይ ምን ይላል

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ጋር ስነበረው ግንኙነት ይተርክልናል፡፡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ


የገባቸውን ቃሎች ብሎም ደግሞ ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ለፈቀዱ ደግሞ ያስቀመጣቸውን
ትዕዛዛትና ይነግረናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሌላው የሚተርክልን ደግሞ እግዚብአብሔር የሰው ልጆችን እና
ችሎታቸውን እንዴት እንደሚመለከት ነው፡፡ እግዚአብሔር ልጁን ወደዚህች ምድር በመላክ ለእኛ የሰጠውን

49 | P a g e
ዋጋ አሳይቷል፡፡ ኢየሱስ ምድር ድረስ ወርዶ ለሐጢአታችን በሞት ዋጋ እንዲከፍል ማድረጉ ለእኛ የሰጠውን
ትልቅ ዋጋ በሚገባ ያንጸባርቃል፡፡

አንድን ምርት ለመግዛት ወደ መደብር ስንሄድ በምርቱ ላይ ዋጋ አናስቀምጥም፡፡ ማለትም የዚያ ምርት ዋጋ
እኛ ግዢውን ከመፈጸማችን ረጅም ጊዜ በፊት ነው የተቀመጠው፡፡ የዓለም ችሎት ለሰው ልጅ ዋጋ
ያስፈልጋል ሲል ያ የሰው ልጅ ነፍስ ዋጋ ግን ከእግዚአብሔር ሞት ጋር እኩል ሆነ፡፡ ነገር ግን እዚህጋ
ያስተውሉ--የእግዚአብሔር ሞት ከሰው ልጅ ነፍስ ጋር እኩል ነው አላልኩም፡፡ ያልኩት የሰው ልጅ ነፍስ
ከእግዚአብሔር ሞት ዋጋ ጋር እኩል ሆነ ነው፡፡ በሌላ አባባል እግዚአብሔር፤ ‹‹በእኔና በሰው ልጅ መካከል
የነበረውን መልካም ግንኙነት ለመመለስ ያለው ዋጋ ምን ሆነ ምንም እከፍላለሁ!›› አለ፡፡ ለአንድ ነገር ዋጋ
የሚሰጠው የሚከፈለው ሳይሆን የተቀመጠለት ነው፡፡

ለአንድ ነገር ዋጋ የሚሰጠው የሚከፈለው ሳይሆን የተቀመጠለት ነው፡፡

ለመሆኑ እርስዎ ዋጋዎ ስንትና ምን ያህል እንደሆነ ያውቃሉ የምንጭዎን ዋጋ ያህል ነዎት፡፡ እርስዎ
የፈጠረዎን እግዚአብሔር ያህል ዋጋ አለዎት፡፡ ሌሎች ሰዎች ስለ እርስዎ ዋጋ በሚሰነዝሯቸው የተለያዩ
አስተያየቶች መከፋትዎን ያቁሙ፡፡ እርስዎ ልዩ ነዎት፡፡ ስለ እርስዎ ሌሎች ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው ይገባል፡፡
እርስዎ ልጅዎ፤ መምህርዎ ወይንም አለቃዎ የሚልዎት አይደሉም፡፡ እርስዎ እግዚአብሔር የሚለውን ያህል
ችሎታ፤ ዋጋ አለዎት፡፡ ሙሉ እምቅ-አቅምዎን ማውጣት ከፈለጉ እግዚአብሔር በእርስዎ ላይ ያስቀመጠውን
ዋጋ ብሎም ያለውን እምነት መቀበል ይኖርብዎታል፡፡

እግዚአብሔር በእርስዎ እምቅ-አቅም ላይ የተናገረው

የእርስዎን ዋጋ የወሰነው እግዚአብሔር እንደመሆኑ መጠን የእምቅ-አቅምዎን ትክክለኛ ደረጃ ለመወሰን


ብቸኛው ተገቢነት ያለው እሱ ነው፡፡ በእርስዎ ውስጥ ያሉት መልካም አጋጣሚዎች በእግዚአብሔር ላይ
የተመረኮዙ ናቸው ምክንያቱም የአንድ ነገር እምቅ-አቅም ሁልጊዜም ቢሆን በመጣበት ምንጭ ይወሰናልና፡፡
የአንድ የእንጨት ጠረጴዛ እምቅ-አቅም ከተሰራበት ዛፍ ጥንካሬ እንደሚወሰን ሁሉ የእርስዎ እምቅ-አቅምም
በእግዚአብሔር ይወሰናል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ እርስዎ ከእገዚአብሔር የመጡ መሆኑ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል
ላይ እምቅ-አቅማችንን በተመለከተ ያደረገውን ግምገማ በግልጽ የሚያስቀምጡ አባባሎችን እናገኛለን፡፡

 እርስዎ መንፈስ በመሆንዎ ከእግዚአብሔር መደብ ነዎት

50 | P a g e
እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበትን ሂደት ያስታውሱታል እግዚአብሔር በቅድሚያ ለመፍጠር የፈለገውን
አቀደ፡፡ በመቀጠል ያንን ከምን ምንጭ ሊሰራው እንደሚችል ወሰነ፡፡ ሊሰራበት የወሰነውን ግብዓት
ያነጋግረዋል፡፡ ለምሳሌም እግዚአብሔር እንሰሳን መፍጠር ሲፈልግ አፈርን አነጋገረ፤ ምክንያቱም ምንጫቸው
አፈር ነውና፡፡

እግዚአብሔር እኔ እና እናንተ ከአፈር ወይ ጭቃ እንድንሰራ ፍላጎቱ አልነበረም፡፡ ለምን ቢባል መሬትን፤ አየርን
ወይንም ውሃን አላነጋገረም፡፡ እሱ መንፈስ ነውና ራሱን ነው የሚያነጋግረው፡፡

እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ
ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26)

እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ ያነጋገረው ምንጭ እሱን እንድንሆን መፈለጉን ያሳያል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፎች አንድና ሁለት ላይ የተዘረዘረውን የሰውን ልጅ ፍጥረት
ብንመለከት እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር የሰራቸውን ኦፕሬሽኖች ማየት እንችላለን፡፡ እነዚህም ነገሮችን
የሰራባቸው እና የፈጠረባቸው አሠራሮች ናቸው፡፡ በዕብራይስጥኛ ቋንቋ ‹መሥራት› የሚለው ቃል ትርጉም
asha ነው፡፡ ይኼ ደግሞ ‹ከነበረ አንድ ነገር ላይ አውጥቶ መስራት› የሚል ትርጉም አለው፡፡ ሌላውና brera
የሚለው የዕብራይስጥኛ ቃል ‹መፍጠር› የሚል ትርጉም አለው፡፡ በ ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 ላይ የተጠቀሰውን
መመልከት እንችላለን፡፡

እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ
ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26)

ከዚህ የሰው ልጅ ፍጥረት ሂደት ሁለት ነገሮች እንደነበሩት እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ከምንም
ማለትም ከራሱ ፈጠረውና ከዚያም ቤቱን ደግሞ ከአፈር ሰራለት፡፡ የሰው ልጅን መኖሪያ ካበጀ በኋላ
እግዚአብሔር የፈጠረውን ወስዶ በውስጡ አኖረው፡፡ በመሆኑም የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የወጣ ሲሆን ልክ
የእግዚአብሔር ያህል መንፈስ ነው፡፡ የእኛ አካል የሆነው ቤት መጨረሻ ላይ ይበሰብስና ወደተፈጠረበት አፈር
ይመለሳል፡፡ እውነተኛ መሠረታችን የሆነው መንፈስ በመሠረቱ መንፈስ ስለማይሞት ዘለዓለም ይኖራል፡፡
እርስዎ የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ መንፈስ ሲጋሩ ከእነ ሕልሞቹ፤ ምኞቶቹ እና መሻቶቹ ነው፡፡

51 | P a g e
 እርስዎ እግዚአብሔር እንደሚንቀሳቀሰው ነው የሚንቀሳቀሱት

እግዚአብሔር በተጨማሪም ልክ እሱ እንደሚንቀሳቀሰው እንድንንቀሳቀስ ይፈልጋል፤

እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ
ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26)

አዳም እና ሔዋን ከእግዚአብሔር ጋር ከነበራቸው ግንኙነት ባፈነገጡ ጊዜ መጀመሪያ የተቀመጠላቸውን


አሰራር ሳቱ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሰው ልጆች እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ሁሌም ግራ እንደተጋቡ ነበረ
የሚቆዩት፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ከመተባበር ይልቅ ሰይጣናዊ ኃይሎች የፈጠሩብን ተጽዕኖ አይሎ እሱን
ስንቃወም እንገኛለን፡፡

እግዚአብሔር እንዴት ነው የሚሰራው

እግዚአብሔር በእምነት ይሰራል፡፡ ጨለማ ውስጥ የነበረው ብርሐን እግዚአብሔር እስኪጠራው ድረስ
አልታየም፡፡ ይሁን እንጂ ብርሐን በጨለማ ለመኖሩ እግዚአብሔር እምነቱ ነበረው፡፡ እንዲታይ ነገረው፡፡
እምነት ማለት በጨለማ መዝለል ግን አይደለም፡፡ ይልቅ በብርሐን መራመድ ነው፡፡ እምነት ግምት አይደለም--
ማወቅ እንጂ፡፡

እምነት ማለት በጨለማ መዝለል ግን አይደለም፡፡ ይልቅ በብርሐን መራመድ ነው፡፡ እምነት ግምት
አይደለም--ማወቅ እንጂ፡፡

እግዚአብሔር እርስዎን ዲዛይን ያደረገው በእምነት እንዲንቀሳቀሱ ነው፡፡ የማይታየው ሊታይ እንደሚችል
እንዲያምኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር በእርስዎ ሕይወት ውስጥ አለ የሚለው ላይታይዎት ይችላል፡፡ ሆኖም ይታያል
ብለው እንዲያምኑ ግን ይጠብቅብዎታል፡፡ እንደ እግዚአብሔር የማይንቀሳቀሱ ከሆነ ዓላማዎን ስተዋል፡፡
ማኑዋሉ ይኼንን ይላል፤

ጻድቅ በእምነት ይኖራል

52 | P a g e
(ሮሜ 1፡17)

የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ሐጢአት ነው፡፡

(ሮሜ 14፡23)

 ምድርን መሙላት፤ መግዛት እና በቁጥጥርዎ ሥር ማድረግ ይችላሉ

እግዚአብሔር በእምቅ-አቅማችን ዙሪያ ካስቀመጣቸው ነገሮች መካከል አንዱ ምድርን መሙላት፤ መግዛት
እና በቁጥጥራችን ሥር ማድረግ መቻላችንን ነው፡፡

እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ
ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26)


ለመሆኑ ምድርን መግዛት ማለት በትክክል ምን ማለት ነው ምድር እኛን ልትቆጣጠረን ወይንም የበላይ
ልትሆንብን አይገባም የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ለምሳሌም የሲጃራ ሱሰኛ የሆነ ሰው የቅጠል ተገዢ
መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ የአልኮል ሱስ ካለብዎ ደግሞ የጥራጥሬ ተገዢ ሆነዋል ማለት ነው፡፡ ቅጠልና ጥራጥሬ
ምድር ናቸው፡፡ በመሆኑ እግዚአብሔር እርስዎ ምድርን ይገዙ እንጂ በምድር ቁጥጥር ሥር ይሆኑ ዘንድ
አልፈጠረዎትም፡፡ እርስዎ በማንኛውም ልማድ ቁጥጥር ሥር ከሆኑ እግዚአብሔር የበላያቸው እንዲሆኑ
በፈለጋቸው ነገሮች እየተገዙ ነው ማለት ነው፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያስቀመጠውን ዕቅድ በሚከተለው መልኩ አረጋግጧል፤

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ፡፡

(1 ኛ ቆሮንጦስ 9፡27)

እዚህጋ ሐዋርያው ጳውሎስ አዕምሯችንን እንድናሰራ ነው የሚነግረን፡፡ በዚህች ምድር ላይ አካላችንን


እንዲቆጣጠሩ ከፈቀድንላቸው የሚገዙን ነገሮች አሉ፡፡ ጳውሎስ ይኼንኑ መርህ በ 1 ኛ ቆሮንጦስ 6፡12 ላይ
የሚነግረን፡፡

53 | P a g e
ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛ፤ ሁሉ ግን አይጠቅምም፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ
አይሠለጥንብኝም፡፡

 መብዛትና መባዛት ይችላሉ

እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፡፡ ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፡፡


የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ግዙአቸው፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፡28)

እግዚአብሔር ልጅ የመውለድ ችሎታ የሰጠን መሆኑ የታወቀ ቢሆንም አሁን እግዚአብሔር እየነገረን ያለው
ግን ልጆች ለማፍራት ካለን ችሎታ የሚበልጥ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሰዎች በአምሳያቸው ዘር
እንዲተኩ እምቅ-አቅንም ሰጥቷቸዋል፡፡ እኛ ቀጣዩን ትውልድ እየፈጠርን ነው፡፡

ነገር ግን ምን ዓይነት ልጆች ነው እርስዎ የሚወልዱት እዚህጋም እግዚአብሔር ልጆችዎን በጥሩም ሆነ


በመጥፎ መንገድ የመቅረጽ እምቅ-አቅምን ሰጥቶዎታል፡፡ ቀጣዩ ትውልድ ጠጪ፤ አጫሽ፤ ወንጀለኛ፤
ያልተማረ ይሆናል ወይንስ አምላክን አክባሪ፤ ታዛዥ እና ቅን ለማንኛውም ግን የእርስዎን ሕይወት
የሚያንጸባርቁ ልጆችን የመፍጠር ችሎታን ተለግሰዋል፡፡

 ምንም ነገር ለማድረግና ለመሆን ማቀድ ይችላሉ

እግዚአብሔር ከላይ ከተመለከትናቸው በተጨማሪም የሰው ልጅ ማንኛውንም ነገር ገምቶ፤ አልሞና አምኖ
ወደ እውነታ ሊቀይረው የሚችልበትን ክህሎት ለግሶታል፡፡ ይኼ እውነት ለመናገር ድንቅ እምቅ-አቅም ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ባብል ግንብ መገንባት ባወሳበት ክፍል ላይ ይኼንኑ ኃይል ይገልጻል፤

እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም
ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።

(ኦሪት ዘፍጥረት 11፡6)

ጌታ በሌላ በኩል እንዲህ ነው ያለው፤ ‹‹እኔ ጣልቃ ካልገባሁበት የሰው ልጅ የሚያስበውን እና የሚያቅደውን
ምንም ነገር እውን ማድረግ ይችላል፤››

54 | P a g e
በእርግጥ ሰዎች የባብለን ግንብ በሰሩ ጊዜ ጣልቃ ገብቷል--ከማሰብ ግን አላቆማቸውም፡፡ እግዚአብሔር ጣልቃ
ገብቶ ያደረገው እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ አንዱ ሌላው የማያውቀውን ቋንቋ እንዲናገሩ ነበረ፡፡ እርስዎ
ማንኛውንም ዕቅድዎን ለማሰብ፤ ለመገመት እና በዝርዝር ለማዘጋጀት እምቅ-አቅሙ አለዎት፡፡ ከሀሳብ ወደ
ተግባር የሚያሸጋግሩት ማንኛውም ነገር በውስጥዎ ያለ ነው፡፡

 የማይቻሉትን መፈጸም ይችላሉ

የሰው ልጅ ቀደም ሲል ከላይ እንደተመለከትነው ዕቅዶችን በማውጣት ለፍጻሜ ማብቃት ከመቻሉ ጋር


የሚያያዘው የማይቻል ተደርጎ የሚታየውን የማሳካት ችሎታው ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በክፉ መንፈስ
ተይዞ ለነበረ ልጅ አባት እንዲህ ማለቱን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፤
ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል።

(የማርቆስ ወንጌል 9፡23)

ይኼ ክህሎት የሰው ልጅ እንደ እግዚአብሔር የመስራት እምቅ-አቅሙ መገለጫ ነው ብለን ማስቀመጥ


እንችላለን፡፡

በማቴዎስ ወንጌል ላይ ከኢየሱስ ደቀ-መዝሙራን አንዱ የማይቻለውን ስለከወነበት የእምነት ታሪክ


እንማራለን፡፡ ጴጥሮስ ከሌሎች ደቀ-መዛሙርት ጋር በገሊላ ወንዝ ላይ በጀልባ ሆኖ እየተጓዘ ሳለ ኢየሱስ
በወንዙ ላይ ተራምዶ ወደ እነሱ መጣ፡፡ ደቀ-መዝሙራኑ ጣዕረ-ሞት መጣ ብለው በፍርሀት ጮሁ፡፡ ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነቱን እንዲለዩ ካደረጋቸው በኋላ ችኩሉ ጴጥሮስ እንዲህ አለው፤

ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ።

(የማቴዎስ ወንጌል 14፡28)

እንግዲህ እኔም ሆንኩ እናንተ አንባቢያን እንደምናውቀው የተፈጥሮ አካላዊ ሕግጋት ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ
እንዳይሄድ ይከለክሉት ነበረ፡፡ ነገር ግን የእምነት ሕግጋት ደግሞ የተለዩ ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ እንዲመጣ
ሲነግረው ጴጥሮስ ከጀልባው ወርዶ በቀጥታ ወደሱ ተራመደ፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ ነፋስ እና ሞገዶችን ሲፈራ
ነበረ መስመጥ የጀመረው፡፡

ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና። አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ? አለው።

(የማቴዎስ ወንጌል 14፡31)

55 | P a g e
እርስዎ የእምነት ሰው ከሆኑ በእምት ሕግጋት በመጠቀም ድንቅ ኃይልዎን ማውጣት ይችላሉ፡፡

 ነገሮችን በሰማይም በምድርም ተጽዕኖ ሊያደርጉባቸው ይችላሉ

የሰው ልጅ ድንቅ እምቅ-አቅም አካላዊም ሆኑ መንፈሳዊ ነገሮች ላይ ተጽዕኖ ማድረግን ያካትታል፡፡ ይኼ


ክህሎት አልፎ አልፎ ብቻ ካልሆነ የማንጠቀምበት እጅግ ግዙፍ ኃይል ነው፡፡ ጴጥሮስ ለኢየሱስ፤

ብሎ ከተናዘዘ በኋላ ኢየሱስ ይኼንን ኃይል ጠቁሟል፤

ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።

(የማቴዎስ ወንጌል 16፡16)

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን
አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን
እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር
የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

(የማቴዎስ ወንጌል 16፡17-19)

እንግዲህ ጌታ ኢየሱስ ከአካላዊ የሕይወት ገጽታችን በማለፍ ወደ መንፈሳዊው ገጽታ እነድንገባ ነው


እየገፋፋን የሚገኘው፡፡ እርስዎ በአሁን ሰዓት ሥጋዎን የተመለከቱ ነገሮች ላይ ብቻ እያተኮሩ ከሆነ ትልቁን እና
ዋናውን ነገር ረስተውታል ማለት ነው፡፡ በሥራዎት፤ በትዳርዎት ወይ ከጓደኞችዎ እና ከአምልኮ ቦታዎ ጋር
በተያያዘ ከገጠመዎ ጭንቀት ወይ ችግር አለፍ በማለት በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ውስጥ ሊነሳ በመንፈሳዊው
ዓለም እንዲሆን የሚፈልጉትን ይበሉት ማለተ ነው፡፡ በሁለቱም ዓለማት ላይ ተጽዕኖዎትን ማሳረፍ የእርስዎ
ፋንታ ነው፡፡ በሰማይም ሆነ በምድር ላይ ያለ ሥልጣን ሁሉ የጌታ ኢየሱስ በመሆኑ እርስዎም በእግዚአብሔር
መንግሥት ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስፈልግዎን ቁልፍ ይዘዋል (ማቴዎስ ወንጌል 28፡18)

እርስዎ በአሁን ሰዓት ሥጋዎን የተመለከቱ ነገሮች ላይ ብቻ እያተኮሩ ከሆነ ትልቁን እና ዋናውን
ነገር ረስተውታል ማለት ነው፡፡

56 | P a g e
 የጠየቁትን ሁሉ መቀበል ይችላሉ

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የጠየቁትን ሁሉ ማግኘት እንደሚችሉ ነገራቸው፡፡

ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።

(የማርቆስ ወንጌል 11፡ 24)

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ
ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።

(የዮሐንስ ወንጌል 15፡ 7-8)

ጌታ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በሕይወታቸው ላለው ፍሬ ትልቁ ማስረጃ ራሱ ከሱ ጋር ያላቸው ግንኙነት


መሆኑን ጠቁሟል፡፡ የሕይወት ፍሬያቸውን ማስቀጠል የሚችሉት ደግሞ ከእርሱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት
በማስቀጠል መሆኑንም ጭምር ነግሯቸዋል፡፡ እርስዎም ከፈጣሪዎ/ምንጭዎ ጋር ባለዎ ግንኙነት ፀንተው ከቆዩ
የፈለጉትን ሁሉ የመጠየቅ እና የጠየቁትን ሁሉ የማግኘት ኃይል ይኖርዎታል፡፡ እግዚአብሔር የእርስዎን
እምቅ-አቅም በተመለከተ ይኼንን ነው ቃል የገባው፡፡ ጠልቀው እና ዘልቀው በመግባት ቃሉ በሕይወትዎ
እንዲሰራ እስከፈቀዱ ድረስ የጠየቁትን ለመስጠት አምላክ ይጠብቃል፡፡

 ጌታ ኢየሱስ ካከናወናቸው የሚልቁ ነገሮችን የመስራት ኃይል አለዎት

ጌታ ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረባቸው የመጨረሻዎቹ ቀናት ከደቀ-መዝሙራኑ ጋር በመጸለይ፤ እነሱን


በማስተማር እና በሱ ኃይል እንዲኖሩ በማበረታታት ነበረ ጊዜውን ያሳለፈው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ
አባቱ ስለመመለሱ ሲናገር በምድር ላይ በሰጠው አገልግሎት በሱ ውስጥ ያዩት ያው ኃይል በውስጣቸው
በመኖሩ ደቀ-መዝሙራኑ የጀመረውን ሥራ እንደሚቀጥሉ አረጋገጠላቸው (የሐዋርያት ሥራ 1፡8 ን
ይመልከቱ)፡፡

እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥
በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤

57 | P a g e
አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ
አደርገዋለሁ።

(የዮሐንስ ወንጌል 14፡ 11-14)

እዚህጋ ትልቁ ችግር እኛ የሰው ል እነዚህን ሥራዎቻችንን የምናነጻጽረው ከጥቂት ቅሪት እንዴት ብዙዎችን
መገብን ወይንም ምን ያህል ጠለቀ በሚል ባሕር ላይ ተረማመድን በሚል መሆኑ ነው፡፡ ይኼም ሲባል የጌታ
ኢየሱስን ቃል (አደረግኩ የሚለውን ሁሉ) ስናነብ እኛ የበለጠ እናደርጋለን በሚል የተሳሳተ ትርጓሜ
እንሰጣለን፡፡

ጌታ ኢየሱስ በዚህች ምድር ላይ በቆየበት ጊዜ በውስጡ የእግዚአብሔር መንፈስ የነበረው እና በአንድ ሥጋ


የነበረ አንድ ሰው ነበረ፡፡ በሚያስተምርበት ጊዜ በአካል፤ በታሪክ ውስጥ ባለ ጊዜ እና እንደ ግለሰብ ሊፈጽመው
ስለሚችለው ነበረ ያተኮረው፡፡ ኢየሱስ ከሞተና ሞትን ድል አድርጎ በመነሳት ወደ እግዚአብሔር አባቱ
በተመለሰ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ከአንድ ሰው ወጥቶ በሚልዮን ለሚቆጠሩ ሁሉ በነጻ የሚገኝ ሆኗል፡፡ በ
ሐዋርያት ሥራ ላይ ይኼ መንፈስ በጥንታዊ ቤተክርስትያን ላይ ስለመውረዱ እንረዳለን፡፡

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ-መዝሙራቱ እሱ ከሰራውም የሚልቅ ሥራ እንደሚሰሩ አስቀድሞ ሲተነብይ


የመንፈስ ቅዱስን መጠመቅ እና ከዚህም የሚፈልቀው ኃይል ወደ ውስጣቸው እንደሚገባ መጠቆሙ ነበረ፡፡
እርስዎ ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝዎ አድርገው ከተቀበሉ እና መንፈስ ቅዱስም በውስጥዎ ከሰራ
ቤተክርስትያን ክርስቶስ ከሰራው በላይ ለመስራት በምታደርገው ጥረት ተጋሪ ለመሆን እምቅ-አቅሙ
አለዎት፡፡ በመሆኑም ክርስቶስ ከሰራው በላይ ሲባል በጥራት ሳይሆን በመጠን የሚበልጥ ለማለት መሆኑን
መረዳት እንችላለን፡፡ እነዚህ ስራዎች ደግሞ በአንድ ግለሰብም ሆነ ቦታ የተወሰኑ ሳይሆኑ በመላው ዓለም
የተስፋፉ ስለመሆናቸው መናገር እንችላለን፡፡ ምንኛ ድንቅ እምቅ-አቅም ነው!

 የእርስዎ እምቅ-አቅም በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር ሰዎች ሥራዬን ይጋሩኛል፤ ይወስዱብኛል ብሎ የሚፈራ ይመስላቸዋል፡፡


ለእግዚአብሔር ልንሰራ ስላሰብነው ወይንም ደግሞ ለመስራት ስለምንመኘው ነገር ስናወራ አንዳንድ ሰዎች፤
‹‹አንተ ከአምላክ ጋር ራስህን አታነጻጽር!›› ብለው ሊያስፈራሩ ይሞክራሉ፡፡ በእርግጥ ከምንጭዎ ሊበልጡ
አይችሉም፡፡ ከእግዚአብሔር የሚበልጥ ማቀድም ሆነ መገመት አይችሉም ለምን ቢባል እግዚአብሔር
የዕቅድዎ ምንጭ ነውና፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር እርስዎን ከውስጡና በራሱ አምሳያ ሲፈጥር ከሰፊውና

58 | P a g e
የማያልቀው እምቅ-አቅሙ የተወሰነውን በውስጥዎ አኑሯል፡፡ ልክ ብዙ ፊቸሮችና ግልጋሎቶች ያሉት የ
SONY ካሴት ድምጽ መቅረጫ እንደመያዝ ማለት ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ የፈለገ አገልግሎት ቢኖረው በሶኬት
ከምንጩ ጋር ካልተያያዘ ምንም ሊሰራ አይችልም፡፡ ለእያንዳንዱ ሰውም ይኼ እውነት ነው፡፡ ከምንጩ ጋር
ሳይያያዝ ሰውም ምንም ሊሰራ አይችልም፡፡

በመሆኑም እርስዎ የእግዚአብሔርን ባሕሪያት እና ለሰው ልጅ የሰጣቸውን ነገሮች፤ ብሎም ደግሞ እንዲከውኑ
ሲሉ ወደዚህ ዓላማ የመጡበትን ዓላማ ቢረዱ ጠቃሚ ነው፡፡ እምቅ-አቅምዎን የማውጣት ችሎታዎ በቀጥታ
ስለ እግዚአብሔር ካለዎት እውቀት እና ከሱ ጋር ለሚኖረዎ ግንኙነት ሲል ባስቀመጣቸው ማዕቀፎች ውስጥ
ለመቆየት ባለዎ ፈቃደኝነት ላይ ይወሰናል፡፡

 የእግዚአብሔርን ባሕሪያት እና መለያዎች መረዳት ይኖርብዎታል

እንግዲህ ጥራት ወይንም መለያ (በተሻለ መልኩ quality በሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ይገለጻል) ስንል አንድን
ምርት ከሌላው የተሻለ እንዲሆን የሚያደርገው ወይንም የሚያስበልጠው የደረጃው መሠረታዊ ባሕሪዊን
ያመለክታል፡፡ የአንድ ምርት ጥራት ከምንጩ ጥራት ደረጃ ፈጽሞ የተሻለ ሊሆን አይችልም፡፡ ለምሳሌም
የበሰበሰ ፖም ተጠቅሞ ጣፋጭ የአፕል-ፓይ ማዘጋጀት አይቻልም! ፓዩ የፖሙን መበስበስ ማጋለጡ
ስለማይቀር!

የአንድ ምርት ጥራት የምርቱን መሠረታዊ ባሕሪ የሚወስኑት ዋና ዋና ነገሮችን ይመለከታል ብለን
ማስቀምም እንችላለን፡፡ እነዚህ መሠረታዊ ባሕሪያት ደግሞ ከምርቱ ምንጭ ነው የሚፈልቁት፡፡ ምናልባት
ይኼንን በሌላ መንገድ እንግለጽ ከተባለ በአንድ ምርት ላይ ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ የሚንጸባረቁት ነገሮች
ምርቱ በተሰራበት ዓይነት ወይንም ቅርጹ ላይም ይታያሉ፡፡

እርስዎ የእግዚአብሔር ስሪት እንደመሆንዎ መጠን የእግዚአብሔር ደረጃዎች የእርስዎ ብልጫ


የሚወሰንባቸው መለኪያዎች ናቸው፡፡ በተመሳሳይ መንገድም የእግዚአብሔርን መሠረታዊ ተፈጥሮ
የሚያንጸባርቁት ባሕሪያት የእርስዎን መሠረታዊ ባሕሪም ያሳያሉ፡፡ ለሕይወትዎ የተቀመጡትን ደረጃዎች
ማወቅ ከፈለጉ የእግዚአብሔርን ደረጃዎች ያጣሩና ይመልከቱ፡፡ ምን ዓይነት ባሕሪያት በእርስዎ ላይ
ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ እንደሚንጸባረቁ ማወቅ ከፈለጉ የእግዚአብሔርን ባሕሪያት ይመልከቱ፡፡
እግዚአብሔር የሚያሳየው አንድ ባሕሪ ካለ ያ የእርስዎ ሕይወት አካልም ነው፡፡

ለምሳሌም እግዚአብሔር የእምነተኝነት ባሕሪ አለው፡፡ በመሆኑም እርስዎም የእምነት ሰው ለመሆን


ችሎታው አለዎት፡፡ እግዚአብሔር ማለት ፈጽሞ በቅድመ-ሁኔታ ያልተገደበ ፍቅር በመሆኑ በእርስዎ ላይ ጎላ
59 | P a g e
ብለው ከሚታዩ ጥላቻዎች ስርም ቢሆን የፍቅር ባሕሪ ተደብቆ አለ፡፡ እግዚአብሔር መሀሪ እና ቻይ በመሆኑ
እርስዎም እነዚህ ባሕሪያት በውስጥዎ አሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ማንነት እና ሥራ የሚወስኑ ባሕሪያት እና
መገለጫዎች ሁሉ በተመሳሳይ መንገድ የእርስዎንም ይጠቁማሉ፡፡ የእግዚአብሔር መለያዎች የእርስዎ መለያ
መሠረትም በመሆናቸው የእርስዎ እምቅ-አቅም በሱ ጥልቅ አቅም ውስጥ ታቅፏል፡፡ የእግዚአብሔርን
መሠረታዊ ባሕሪያት ሲረዱና ሲቀበሉ ብቻ ነው ተፈጥሮአዊ ባሕሪዎን መረዳት የሚችሉት፡፡

የእርስዎን ባሕሪ እና ደረጃ ከሚያመለክቱ ነገሮች አንዱ በእግዚአብሔር ትዕዛዛት ውስጥ ተገልጧል፡፡ ለዚህ
ነው የእግዚአብሔር መመሪያ ማኑዋል፤

ትዕዛዛቱም ከባድ አይደሉም።

(1 ኛ ዮሐንስ 5፡ 3)

ይላል፡፡

 የእግዚአብሔርን ሕግ መረዳት እና ትዕዛዛቱንም ማክበር አለብዎት

በ ኦሪት ዘፍጥረት ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ እግዚአብሔር አዳም በኤደን ገነት ከሚገኙ ዛፎች ጋር ስላለው
ግንኙነት ሕግ አስቀመጠ፡፡

ነገር ግን መልካም እና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ትሞታለህና፡፡

(ኦረት ዘፍጥረት 2፡ 17)

ከዚህ ሕግ ተነስቶ እግዚአብሔር ለአዳም ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካም እና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 2፡ 16-17)

አዳም ይኼንን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ በጣሰ ጊዜ እግዚአብሔር ቀደም ሲል ለትዕዛዙ ማጠናከሪያ ሲል


ያስቀመጠው ሕግ ተፈጻሚ ሆነበትና ሞቱን በገዛ እጁ አመጣ፡፡

60 | P a g e
በእርግጥ በ ኦሪት ዘፍጥረት ላይ ግልጽ እንደተደረገልን አዳም ያቺን የተከለከለውን ፍሬ ከሔዋን ጋር በበላበት
ቅጽበት በአካል አልሞተም፡፡ እንዲያውም 930 ዓመታትን ኖሯል፡፡ ይልቅ ግን አለመታዘዙ መንፈሳዊ ሞትን
አስከተለበት፡፡

ያረጀ ዛፍን ሞት ብንመለከት የአዳምን ሞት ለመረዳት ዓይነተኛ ምሳሌ ይሆነናል፡፡ አንድ ትልቅ ዛፍ በአውሎ
ንፋስ ቢመታና ቢወድቅ ለሳምንታት ያህል እዚያው ባለበት ይቆያል፡፡ የዛፉ ሥር ከመሬት ተነቅሎ ለነፋስ
የተጋለጠ ቢሆንም ቅጠሎቹ ግን ተመትቶ እንደወደቀ ቀለማቸው ወደ ሻጋታነት ተቀይሮ አይረግፉም፡፡ ይልቅ
ከምንጩ ከመሬት ወደ ስሩ ገብቶ የነበረው ጉልበት ወደ ግንዱ ብሎም ወደ ቅርንጫፎቹ እና ቅጠሎቹ
ስለሚሸጋገር ቶሎ ዛፉ አይሞትም፡፡ ነገር ግን ያ ጉልበት ሲጠፋ ቅጠሎቹ መሻገት ይጀምራሉ፡፡ ሆኖም ሃቁ ግን
ዛፉ የሞተው ገና በአውሎ ነፋስ ተመትቶ የወደቀ ጊዜ እንጂ ቅጠሎቹ በጉልበት መጥፋት የተነሳ የሞት
ምልክቱን ቀለማቸው ተቀይሮ ሲያሳዩ አይደለም፡፡

አዳምም ስር የሌላቸውን እና ከመሬት የተነቀሉ አረንጓዴ ቅጠሎች ይዞ ብዙ ዓመታትን ኖረ፡፡ አካሉ የሞቱን
ማስረጃ ማሳየት ከመጀመሩ ከረጅም ጊዜ ቀድሞ ግን አዳም ሞቷል፡፡ እኛ የሰው ልጆችም የአዳምን ሞት
እንጋራለን፡፡ የእርስዎ ሕይወትም ቢሆን እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመሰዋት
ካመጣው መዳን ጋር ካልተቆራኘች በቀር ዘለዓለማዊ ሞት አይቀርልዎትም፡፡ ያ የእግዚአብሔር ሕግ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ሕግጋት ብዙ ሲሆኑ ተፈጥሯዊ ተፈጻሚነት አላቸው፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ሕግጋቱን


እንዳንጥስ የተሰጡ በመሆናቸው ለእኛው ጥቅም ነው የወረዱት፡፡ አዳም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ሲጥስ
የእግዚአብሔር ሕግ ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ተፈጻሚ ሆኖበታል፡፡

የእግዚአብሔርን ሕግ ስንታዘዝ ባረኮቱን እናገኛለን፡፡ በ ኦሪት ዘዳግም ሁለተኛው ምዕራፍ ላይ እግዚአብሔር


በሙሴ አማካይነት ትዕዛዛቱን ላከበሩ የሚሰጣቸውን ባረኮት ገልጧል፡፡

እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፤ ዛረም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ብትጠብቅም አማላክህ
እግዚአብሔር ከምድር አህዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሀል፡፡

የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሀል፤ ያገኙህማል፡፡


(ኦሪት ዘዳግም 28፡ 1-2)

የእግዚአብሔርን ሕግጋት እና ዓላማዎች እስከተረዱ እና ዕውቀትዎን ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ እስከተጠቀሙበት


ድረስ እምቅ-አቅምዎ ገደብ-የለሽ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

61 | P a g e
በመጽሐፍ ቅዱስ ዳንዔል 11፡32 ላይ፤

አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፤ ያደርጋሉም፡፡

(ትንቢተ ዳንዔል 11፡32)

ይኼ እውነት የሚሆንበት ምክንያት የእርስዎ እምቅ-አቅም ከእግዚአብሔር አቅም ጋር የተያያዘ በመሆኑና


እሱ ደግሞ ሁሉን-ቻይ በመሆኑ ነው፡፡ ሁሉን-ቻይ የሚለው ቃል በዋናነት እግዚአብሔር በኃይል የተሞላ
መሆኑን ይገልፃል፡፡ ወይንም በሌላ መንገድ እናስቀምጠው ከተባለ ሁሉም እምቅ-አቅም በእግዚአብሔር አለ፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር አድርጉልኝ ብሎ የሚጠይቃቸውን ነገር ሁሉ መያዙን የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ
ትልልቅ ነገሮችን ማድረግ አያስፈራቸውም፡፡ በእግዚአብሔር ተመርተው ትልልቅ ነገሮችን ለመከወን
የሚያበቃዎት ምን ያውቃሉ የሚለው ሳይሆን ማንን ያውቃሉ የሚለው ነው፡፡

እግዚአብሔር እምቅ-አቅሙን ለመጠቀም ወሰኑም አልወሰኑም ዞሮ ዞሮ ግን እግዚአብሔር ነው፡፡ የእርስዎ


ከሱ ጋር ለመኖር ወይንም ላለመኖር መወሰን ማንነቱን እና ሊያደርግ የሚችለውን ነገር ፈጽሞ
አይቀይረውም፡፡ በሌሎች ምንጮች ሊተኩት ሲሞክሩ እሱ ዋጋውም ሆነ ማንኛውም ነገሩ አያንስም፡፡
እግዚአብሔር መቼም ቢሆን እምቅ-አቅምዎን ሙሉ ለማድረግ የሚፈልጓቸውን ነገሮች ይዟል፡፡

እግዚአብሔር እምቅ-አቅሙን ለመጠቀም ወሰኑም አልወሰኑም ዞሮ

ዞሮ ግን ያው እግዚአብሔር ነው፡፡

እግዚአብሔር ሁሉን-ቻይ ስለመሆኑ ያለዎትን ዕውቀት እርስዎ በእግዚአብሔር ያሉ ከመሆንዎ ዕውቀትዎ ጋር


ሲያጣምሩት እርስዎን ለማሸነፍ እና እምቅ-አቅምዎን ለማጥፋት ከሚጥሩ ነገሮች ሁሉ ራስዎን መጠበቅ
ይችላሉ፡፡ እርስዎ ብርቱ መሆንና ትልልቅ ነገሮችን መከወን ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር የእምቅ-አቅምዎ ምንጭ
ነው፡፡ እሱ እንዲፈጽሙ የሚፈልጋቸውን ነገሮች እንዲሰሩለት ከጥልቁና ሰፊው አቅሙ እንዲጠቀሙ
ለማድረግ እየጠበቀዎት ይገኛል፡፡

 ከእግዚአብሔር ጋር ባለዎ ግንኙነት መጽናት አለብዎ

በመጽሐፍ ቅዱስ ቆላስይስ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚከተለው መልኩ ተገልጾ እናገኛለን፤

62 | P a g e
እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፡፡ የሚታዩትና የማይታዩትንም ዙፋናት ቢሆኑ ወይንም ጌትነት ወይም
ስልጣናት፤ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፡፡ ሁሉ በእርሱና
ለእርሱ ተፈጥሯል፡፡

(ቆላስይስ 1፡15-16)

በሌላ በኩል በ ዕብራውያን 1፡3 ላይ ደግሞ፤

እርሱም የክበሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፤ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ፤ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ
በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፡፡

ተብሎ ተጽፏል፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል በቃሉ ስንፀና ነው አብሮን የሚቆየው፡፡

እግዚአብሔር ተክሎችን ሲፈጥር ከአፈር የጠራቸው ሲሆን ይኼንን በማድረጉ ተክሎች ከአፈር ይመነጫሉ
የሚለውን ሕግ አጠናከረም፡፡ ማንኛውም ተክል ቢሆን ከዚህ ትዕዛዝ ቢወጣ ይሞታል፡፡ በመሆኑም
እግዚአብሔር ተክሎችን በቃሉ ይጠብቃቸዋል፡፡ ተክሉ እግዚአብሔር በፍጥረት ጊዜ ባወጣው ሕግ እስከተመራ
ድረስ ያድጋል፤ ይፋፋልም፡፡ ተክሉ ያንን ሕግ ከጣሰ ግን ሞት አይቀሬ ይሆናል፡፡

የእኛም ሕይወት በዚህ መርህ መሠረት ትመራለች፡፡ ከራሱ በማውጣት እግዚአብሔር ሕይወታችን በሱ
የሚወሰን መሆኑን አወጀ፡፡ የእግዚአብሔርን መስፈርቶች እስካሟላን ድረስ ኃይሉ በውስጣችን ይሰራል እኛም
የተትረፈረፈ ሕይወት ይኖረናል፡፡ ለዚህ ነው የ ዕብራውያን ጸሐፊ ኢየሱስን፤ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል ኃይል››
በማለት የሚገልጸው፡፡ እኛ እስከጠበቅነው ድረስ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ኃይል አለ፡፡ ጌታ ኢየሱስ እስከ
ሞት ድረስ ቃሉን በመታዘዙ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚሰጠንን የእግዚአብሔርን ቃል አመጣልን፡፡

ጌታ ኢየሱስ ይኼንኑ ኃይል ለየት ባለ መንገድ መመልከቱን በ ዮሐንስ ወንጌል 15 ኛ ምዕራፍ ላይ


እንመለከታለን፡፡ እዚያ ላይ ኢየሱስ ራሱን እንደ ወይን ተክል፤ ደቀ-መዛሙርቱን ደግሞ እንደ ቅርንጫፎቹ
አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ ወይንን የመረጠው በቅርንጫፎቹ ላይ ሕይወት የሌለው ብቸኛው ተክል በመሆኑ ነው፡፡
የሎሚን ወይንም የጽጌሬዳን ቅርንጫፍ ቆርጠን በአፈር ላይ ተክለን አስፈላጊውን እንክብካቤ ብናደርግለት
አዲስ ሕይወት ይጀምራል፤ ያድጋል፡፡ የወይን ተክል ላይ ግን ይኼ አይሰራም፡፡ የወይን ተክል ቅርንጫፍ ሕይወት
የለውም፡፡ የቱንም ያህል አረንጓዴና የፋፋ ቢመስልም እንኳ ከግንዱ ተነጥሎ ግን ሕይወት ሊኖረው
አይችልም፡፡

በ እኔ ኑሩ እኔም በእናንተ፡፡ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፤ እንዲሁሱም የማ
እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም፡፡

(ዮሐንስ 15፡4)

63 | P a g e

እርስዎም ከእግዚአብሔር የተለዩና የተቆራረጡ ከሆኑ እምቅ-አቅምዎ ያበቃለታል፡፡ የቱንም ያህል ጠንክረው
በሌሎች ድርጅቶች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ ራስዎን ለማስረግ ቢሞክሩም እንኳ ‹‹ሞተዋል››፡፡ ራስዎን
በሃይማኖት ውስጥ ቢያስገቡም እግዚአብሔርን እስካላወቁ እና ንጥረ-ነገሮችዎን ከእሱ እስካላገኙ ድረስ
ሞተዋል፡፡

እግዚአብሔርን መፈለጋችን አማራጭ ወይንም የምርጫ ጉዳይ አይደለም ፡፡ ልክ እንደ ተክሎቹና እንስሳት ሁሉ
(ያለ አፈር ሊሰሩ እንደማይችሉት) እኛም ያለ እግዚአብሔር ሕይወት ሊኖረን አይችልም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በ ዮሐንስ 14፡6 ላይ፤ እኔ መንገድና ሕይወትም ነኝ ሲል ያንን ቃል አልተጠቀመም፡፡ በእግዚአብሔር ስረ-
መሠረት ላይ የሚገነባ ሕይወት አስፈላጊ ነው፡፡ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ለአንድ ተክል፤ ‹‹ከዚህ ከስርህ ተነቅለህ
በማስቀመጫ መስኮት ላይ ትሆናለህ፤›› ብንለው ተክሉ አማራጭ አይኖረውም፡፡ መስኮት ላይ ቢሆን
ይሞታል፡፡ የሰው ልጅም ከእግዚአብሔር ውጭ እንዲሁ ነው፡፡

እርስዎ በጌታ ቃል ውስጥ ቢቆዩ ቃሉ በልብዎ መሠረት ይዞ ይጠናከራል፡፡ እርስዎ በቃሉ ለመጽናት
በሚያደርጉት ጥረት ኃይሉ እውን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ለመውጣት ቢወስኑ ምርታማነትዎን
ነው የሚዘጉት፡፡ ልክ እንደ መጽሐፍት፤ ትምህርት፤ ሰዎች ወዘተ. በራስዎ ዛቢያ ብቻ የሚሄዱና የተገደቡ
ይሆናሉ፡፡

ሐሴት ማድረግን ይፈልጋሉ ከሆነ ወደ እግዚአብሔር ይቅረቡ፡፡ ሰላምንስ ይሻሉ ራስዎን በእግዚአብሔር
ቃልና ኃይል ውስጥ አጠናክረው ያስገቡ፡፡ ንዴትዎን ወይንም ስሜትዎን ለመቆጣጠር እርዳታ ያሻዎታል
ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ያሳልፉ፡፡

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤

በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉም ይቻላል፡፡

(የማቴዎስ ወንጌል 19፡26)

ይለናል፡፡

 ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትብብር ማድረግ አለብዎ

የእግዚአብሔር እምቅ-አቅም እንዲያደርግልን ልንጠይቀው ከምንችለው ማንኛውም ነገር በላይ ነው፡፡ ዛሬ


የሚታየው ማንኛውም ነገር ከእሱ መንጭቷል፡፡ ገና የምናየው ነገር ሁሉም ቢሆን በሱ ውስጥ አለ፡፡

64 | P a g e
ከእግዚአብሔር የተፈጠርን በመሆኑ ያ በሱ ውስጥ ያለው እምቅ-አቅም እኛ ውስጥም ተቀምጧል፡፡ ሆኖም
ተቀምጧል ማለት እንደፈለግን እንጠቀምበታለን ማለት አይደለም--የእግዚአብሔርን እምቅ-አቅም
መጠቀም ከመቻላችን በፊት ኃይሉ በውስጣችን እንዲሰራ ማድረግ አለብን፡፡

እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ
ለሚቻለው፤ ለእርሱ በቤተክርስትያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን፡፡

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡20-21)

ኢየሱስ ደቀ-መዛሙርቱን ሊሄድ እንደሆነ በነገራቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እስከዘለዓለሙ አብሯቸው


እንደሚሆን ገልፆላቸዋል (ዮሐንስ ወንጌል 14፡16 ን ይመልከቱ)፡፡ ወደ ሰማይ ከማረጉ ከጥቂት ደቂቃዎች ቀደም
ብሎ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ደቀ-መዛሙርቱን መልዕክተኞቹ ሆነው በምድር ብዙ ለመስራት
እንደሚያስችላቸው ቃል ገብቶላቸዋል (የሐዋርያት ሥራ 1:8 ን ይመልከቱ)፡፡

ለመሆኑ መንፈስ ቅዱስ በሕይወትዎ አለ እርስዎስ ያለዎትን ዕቅድ፤ ሕልም እና ውጥን ሊያዳብር በሚችል
መንፈሳዊ ግንኙነት ውስጥ ነዎት ወይንስ ትልልቅ ነገሮችን ያለ መንፈስ ኃይል ለመከወን ይፈልጋሉ

ሰማይ-ጠቀስ ህንጻ፤ የሕዋ መንኮራኩር ወይንም እጅግ የመጠቀና በሕልሙ ዓለም ካልሆነ የሌለ የሚመስል
ቅንጡ ኮምፒውተር ተመልክተን፤ ‹‹እንዴ! ይኸው የሰው ልጅ እኮ እየፈጠነና እየሰራ ነው›› ልንል እንችል
ይሆናል፡፡ መንፈስ ደግሞ እንዲህ ይልዎታል፤ ‹‹ይኼ የሰው ልጅ ሊሰራው ከሚችለው ጋር ሲነጻጸር ምንም
ማለት አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ያለ እኔ ይኼንን ነው የሚሰራው፡፡ እኔ እርስዎ ሰዎች ያለ እኔ ካልሆነ ሊሰሩት
የማይችሉትን በእኔ እንዲሰሩ እፈልጋለሁ፡፡ ሰዎችን እንዲገነቡ እፈልጋለሁ፡፡ ሰዎች አዲስ መሠረት ላይ
እንዲቆሙ እና አዲስ ሕይወትን ማየት የሚችሉበትን መስኮት ይከፍቱ ዘንድ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ
መስኮት አለኝ፡፡ እኔ ከላይ ጫፍ ሆነው የእግዚአብሔር እይታ እንዲኖርዎና ሕይወትን እንዲመለከቱ
እፈልጋሁ፡፡›› ታዲያ ደስ የሚል እና ድንቅ ኃይል አይደለምን እርስዎም ለእግዚአብሔር ትልልቅ ነገርን
መስራት ከፈለጉ በውስጥዎ ሊኖርዎ የሚገባው ኃይል ይኼ ነው፡፡

ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚያደርጉት ትብብር እግዚአብሔር እርስዎን ለመስራት የተጠቀመበትን ግብዓት


የሚገልጽበት ነው፡፡ እርስዎ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ተጣጥመው ሲሄዱ ይህች ዓለም ፈጽሞ አይታው
የማታውቀውን ነገር መከወን ይችላሉ፡፡ ኃይል አለ--ያንን ኃይል እንዲወጣ ማድረግ ግን የእርስዎ ፈንታ ነው፡፡
ያ ኃይል በእርስዎ ውስጥ እየሰራ ካልሆነ እምቅ-አቅምዎ እየባከነ እንደሆነ አይጠራጠሩ፡፡

 የክርስቶስን ጥንካሬ መጠቀም አለብዎ

65 | P a g e
በ ፊሊጲሲውስ 4፡13 ላይ ጳውሎስ፤

ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡

ይላል፡፡ እርስዎ ሁሉንም ነገር ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ይልቅ ችሎታን በሚሰጠዎ ክርስቶስ አማካይነት ግን
ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ለሰዎች፤ ‹‹ማድረግ እችላለሁ፤›› ብለው መናገር ቢችሉም እግዚአብሔር ግን፤
‹‹ለመሆኑ በክርስቶስ ነዎት›› ሲል ይጠይቅዎታል፡፡ ምክንያቱም ካልሆኑ ዕቅዶችዎ፤ ውጥኖችዎም ሆኑ
ምኞቶችዎ እንደ በጋ ጉም ከመትነን አይዘሉምና፡፡ ያለ ክርስቶስ ጥረትዎ ሁሉ መና ይቀራል፤ እርስዎም
ለብስጭትና ተስፋ መቁረጥ ይዳረጋሉ፡፡

በ ሮሜ 8፡31 ላይ ትልቅ ማበረታቻ እናገኛለን፤

እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል

የዚህ አባባል ትርጉምም እግዚአብሔር ለእርስዎ የሚሰሩለትን አንድ ሥራ ሰጥቶዎት ከእርስዎ ጎን ከቆመ
ይኼንን እንዲሰምር የሚፈልገውን ነገር ሊያስቆም የሚችል ሰውም ሆነ ሌላ ምንም ኃይል የለም ነው፡፡

እምቅ-አቅምዎን የሚያወጡ ከሆነ ከጎንዎ የቆመውን እንጂ የሚቃወመዎትን አይደለም መመልከት ያለብዎ፡፡
የፖለቲካ ጥቃት፤ በአለቆችዎና ሥራ ባልደረባዎችዎ መገለል፤ ከባለቤትዎ፤ ከዘመድ አዝማድ፤ ጓደኞችዎና
ማኅበረሰቡ ግፊት ወዘተ. ሊደርስብዎ ቢችልም እነዚህ ግን አይደሉም በሕይወትዎ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች፡፡
ሁለት አማራጭ አለዎት፡፡ አንዱ ከላይ የተጠቀሱትን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥሮ ከእነሱ ጋር በመፋለም
ሕይወትዎን መግፋት ሲሆን ሌላኛውና የተሻለው ግን እግዚአብሔር አብሮዎት እንዳለ በመረዳት እነዚህን
እንደ ጊዜያዊ እንቅፋቶች ቆጥሮ በዓላማዎ መቀጠል ነው፡፡ እግዚአብሔር ከጎንዎ ከቆመ እርስዎን
የሚከሱዎትም ሆኑ የሚያንገላቱዎ በእርስዎ ላይ ሥልጣን አይኖራቸውም፡፡

ይህ ሳምንት ለእርስዎ ጥሩ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም የእርስዎ ከለላ ከሳሾችዎ ባላቸው ሥልጣን ላይ
ሳይሆን በክርስቶስ ሥልጣን ላይ የተንጠላጠለ ነውና፡፡ ኢየሱስ በእሱ ጥንካሬ እና ኃይል ላይ እምነት ካደረግን
ሰላምና ድልን እንደምንጎናጸፍ ቃል ይገባልናል፤

በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሀሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤ አሜን፡፡

(የዮሐንስ ወንጌል 16፡33)


66 | P a g e
እግዚአብሔር የአርስዎ ምንጭ ነው፡፡ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት
ካላደረጉ እምቅ-አቅምዎን ያባክናሉ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝዎ አድርገው ካልተቀበሉ
የሚከተለውን ፀሎት ይፀልዩ ዘንድ አበረታታዎታለሁ፤

የሰማዩ ጌታ አባት ሆይ!

አንተ አባቴ ምንጬ እና የሕይወት ፈብራኪ የመሆንህን ዕውነታ እረዳለሁ፤


እቀበላለሁም፡፡ አንድ ተክል የመጣበትና ምንጩ የሆነውን አፈር ለሕልውናው
እንደሚፈልገው ሁሉ እንደምታስፈልገኝም ጭምር እረዳለሁ፡፡ በመሆኑም አንተ
ለአገናኝነት ሥልጣል ለሰጠሀቸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ ራሴን
በመስጠት የዘላለም ሕይወትን ሙሉ ዋስትና እና የእምቅ-አቅሜን ወደ ተግባር መቀየር
በማግኘቴ ሐሴትን አደርጋለሁ፡፡ በዚህም አመሰግንሀለሁ አባቴ፡፡

በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም

አሜን

 መርሆች 

1. እግዚአብሔር በእርስዎ እና በችሎታዎ ይተማመናል


2. እርስዎ እግዚአብሔር የሚለውን ያህል ዋጋ እና ችሎታ አለዎት
3. እርስዎ የእግዚአብሔር ተፈጥሯዊ ባሕሪና መለያዎች አሉዎት
4. የፈለጉትን እና የተመኙትን ማንኛውንም ነገር ከውጥን ወደ ፍጻሜ ማሸጋገር ይችላሉ
5. እግዚአብሔር የውጥንዎና ሀሳብዎ ምንጭ በመሆኑ ከሱ በላይ የሆነ ነገር ፈጽሞ መገመትም ሆነ ማቀድ አይችሉም

67 | P a g e
6. ከእግዚአብሔር መንገድ ከወጡ ሞተዋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ማለት ያለ አንዳችም ቅድመ -ሁኔታ በግድ የሚያስፈልግዎት
አፈር ነው፡፡

ምዕራፍ 7

_____________________ _____________________

ዓላማዎትን ይወቁ

68 | P a g e
ራዕይ ማለት ብዙሀኑ ከሚያዩትና ከሚረዱት በላይ ለማየት መቻል ነው፡፡

የሰው ልጅ እጽዋት እና እንስሳት እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ በመመራመርና ብዙ ነገሮችን በርብሮ በማውጣት


ሊቅ ሆኗል፡፡ አንዱን ዘር ከሌላው በማዳቀል ይበልጥ ብርቱ፤ ጠንካራ፤ የሚያማማሩ እና ልዩ የሆኑ
ፍጡራንንም አሳይቷል፡፡ በመጠን ይበልጥ የሚያድጉና በዕድሜም ረዘም የሚሉ አዳዲስ ዝርያዎችን የሰው
ልጅ አፍርቷል፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር አምላክ ራሱን እንዴት እንዲንቀሳቀስ አድርጎ እንደፈጠረው በመረዳት
ረገድ ግን የሰው ልጅ ዛሬም እጅግ የሚያሳፍርና ብዙ ይቀረዋል የሚባል ደረጃ ላይ እየተንደፋደፈ ይገኛል፡፡
ከመንፈስ ይልቅ አካላችን ላይ ነው ትኩረታችን፡፡ ይኼ ሁኔታ እምቅ-አቅማችንን ለማውጣት በእጅጉ
ይገድበናል፡፡

 ለዘለዓለማዊ ሕይወት ዲዛይን የተደረገ 

እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በፈጠረ ጊዜ የሰው ልጆች ልክ የሱን ያህል መንፈስ ይኖራቸው ዘንድ በማለት
ነበረ፡፡ የሰው ልጆች ዕውቀቱን እና ጥበቡን እንዲጋሩት ብሎም ደግሞ ውጥኖቸን እና ዓላማዎቹን መረዳት
ይችሉ ዘንድ በማሰብ እንደነበረም እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔር ከዚህ በተጨማሪም ለሰው ልጆች ከእምቅ-
አቅሙ የተወሰነውን ለሰው ልጆች ሰጥቷል፤ ምክንያቱም ዘለዓለማዊ ዕቅዶችና መንፈስን እንዲያገኙ
አድርጓል፡፡

ሆኖም ሞት እና አፈር የሕይወታችን አካል ሆነዋልና ነጻ፤ የተትረፈረፈ እና ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚለውን
ጽንሰ-ሀሳብ አንረዳም፡፡ ሞት ተፈጥሯዊ እንደሆነ እግዚአብሔርም ሐጢአት ተፈጥሯዊ በሆነበት ዓለም
የምንኖር ይመስለናል፡፡ ሃቁ ግን እግዚአብሔር በቅድስና ለዘለዓለም እንድንኖር ሲል ዲዛይን ያደረገን መሆኑ
ነው፡፡

 ያለመታዘዝ ውጤት 

የአዳም አለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ዕቅድ ያበላሸ ሲሆን እግዚአብሔርና የሰው ልጆችንም አራራቀ፡፡ የሰው
ልጅ ከምንጩና ከፈጣሪው ውጭ በመንቀሳቀሱ መንፈሱ ሞቶ አካሉም ራሱን የማጠናከርና የማብቃት
ችሎታውን አጣ፡፡ በመሆኑም መንፈሳዊ ሞትን ያመጣው ሐጢአት አካላዊ ሞትን በማያስገርም መልኩ
አመጣ፡፡

የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የፀጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡

69 | P a g e
(ሮሜ 6፡23)

በዚህ በሙት ኑሮ ውስጥ ሆኖ ሕይወቱን የሚገፋው ሰው የእግዚአብሔርን ውጥን እና ዓላማ መረዳትም


አልቻለም፡፡ ከመንፈስ ይልቅ የነፍሰ ተገዢ ሆነና መረጃ ፍለጋ አካባቢውን ይቃትት ጀመር፡፡ እንግዲህ ከዚህ
ሰው ያለ እግዚአብሔር በቆሻሻ ውስጥ የሚዳክር እና በቁሙ የሞተ መሆኑን እንረዳለን፡፡

ሰው ያለ እግዚአብሔር በቆሻሻ ውስጥ የሚዳክር እና በቁሙ የሞተ ነው፡፡

ከአዳም በኋላ ሰዎች ሁሉ ሐጢአትን ስለሚሰሩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል (ሮሜ 3፡23)፡፡

ሰራል፤ የሰው ልጆች በነፍሳቸው፤ በአካላቸው እና በመንፈሳቸው ጭምር ያለመታዘዝን ቅጣት ይዘዋል፡፡
እርስዎ ገና ሲፈጠሩ የመንፈስ ሙት ሆነው ወይንም ስንኩል ሆነው ሲሆን አካልዎም ቀስ በቀስ ያንን
የሚያረጋግጠውን ሞት ይሞታል፡፡ የእርስዎ አዕምሮ ከእግዚአብሔር ውጭ እርስዎን ከሚያስተምሩዎ
ወይንም ከሚያነቧቸው መጻሕፍት የበለጠ መረዳት አይኖረውም፡፡

 ትቢያ 

አካልዎ ለመኖር እግዚአብሔር አያስፈልገውም፡፡ የመጣው ከአፈር ነውና የአፈር ውጤቶች እስካሉ ድረስ
ሕልውናው ይጠበቃል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፈሪሳውያን ባደረገው የሚከተለው ንግግር ይኼንኑ ጠቁሟል፤

እናንተ ደግሞ እስከ አሁን የማታስተውሉ ናችሁን ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል

አትመለከቱንም ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው የ ነው፡፡ ከልብ ክፉ አሳብ፤ መግደል፤
ምንዝርነት፤ ዝሙት፤ መስረቅ፤ በውሸት መመስከር፤ ስድብ ይወጣልና ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፡፡

(የማቴዎስ ወንጌል 15፡16-20)

በመሠረቱ ወደ መንፈስዎ የሚገባው ነው የሚያጠፋዎት፡፡ ካንሰር አካልዎን እንጂ መንፈስዎን አይነካም፡፡


እርግጥ ነው በካንሰር በመያዝዎ እና ካንሰር በአካልዎ ላይ በሚፈጥረው ተጽዕኖ የተነሳ መንፈስዎ ይጨነቃል፡፡
ሆኖም መንፈስዎ ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት እስከፀና ድረስ ግን ምንም አይሆንም፡፡ በእግዚአብሔር
ላይ ማመጽ አደገኛ የሚሆነውም ለዚህ ነው፡፡ እርስዎ ራስዎን ከምንጭዎ ሲነጥሉ የመንፈስ ሰውነትዎ
ይሞትና ዘለዓለማዊ ስንኩል ይሆናል፡፡ በዚህም ከእግዚአብሔር እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ግንኙነት
ያጣል፡፡ ከዚያ የቀረው ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደ ቅጠል የሚረግፍና ጊዜውን የሚጠብቅ ሙት አካል ብቻ ይሆናል፡፡
በአካል መኖር ለሞት ይዳርጋል፡፡

70 | P a g e
ለመስረቅ ወይንም ለመወስለት ፍላጎት የሚቀሰቀስብን በአካላዊ ዓይኖቻችን በምናየው ነው፡፡ ወሲባዊ
ስሜትም በተመሳሳይ መንገድ ይቀሰቀስብናል፡፡ አካላዊ ኑሮ አክብሮትን የማያበረታታ እና ሰዎችን በቁጥጥር
ስር መደረግ እንዳለባቸው ሸቀጦች ወይንም መሣሪያዎች አድርገን እንድንመለከት ይገፋፋል፡፡ የሰው ልጆችን
ክብር እንደሚገባቸው በጌታ አምሳል የተፈጠሩ አድርጎ ከመመልከት ይልቅ በፈለግነው መልኩ
ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ምርቶች አድርገን የመመልከት ፈተና ሁሌም ተደቅኖብን እንዳሸነፈን
እንገኛለን፡፡

እግዚአብሔር ከሱ ተነጥለው በሥጋ ብቻ ለሚኖሩት ስም አውጥቷል--ትቢያ ይላቸዋል፡፡ ይኼ ስድብ ነው፡፡


ትቢያ ሲል ተራ ማለቱ እንደሆነ ከተመለከትን ከሱ የራቀና ወደ ሥጋው ያደላ ሁሉ ተራ ሰው መሆኑን
እንረዳለን፡፡ ተራ የሆነ ሰው ነገሮችን ፍጹም ተፈጥሯዊ ከሆነው መንገድ ውጭ ያደርጋል፡፡ ፈጣሪያቸውን እና
ወደዚህች ምድር የመጡበትን ዓላማ ባለመረዳታቸው እግዚአብሔር አቅዶት ከነበረው መንፈሳዊው
ማንነታቸው ይልቅ ሥጋዊ ማንነታቸውን ያስቀድማሉ፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ዲዛይን እንዳደረጋቸው
ባለመረዳት ራሳቸውን እና ሌሎችን አለአግባብ ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ፡፡ ሞትና ትቢያ የእነዘህን ሰዎች
ሕይወት በሚገባ ይገልጻሉ፡፡

 እግዚአብሔር እኛን ለመካስ ያወጣው ዕቅድ 

እኛ ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኖረን ዘንድ ዲዛያን ያደረገን እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ከእኛ ጋር እንዲኖረው
የፈለገውን ጥብቅ ግንኙነት አሁንም ይፈልገዋል፡፡ ዘለዓለማዊ ሕይወት የእኛ ይሆንና የሐጢአት መሠረትም
ይወገድ ዘንድ በማሰብ ልጁን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህች ምድር ላከ፤

እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ
ከሐጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና፡፡

(ሮሜ 8፡1-2)

የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የፀጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡

(ሮሜ 6፡23)

እግዚአብሔር የራሱን ፍላጎት ለማሟላት ብቻ ቢሆን ኖሮ እኛን ከሐጢአትና ሞት ማዳን በላስፈለገው ነበረ፡፡
እግዚአብሔር እኛ ከመፈጠራችን በፊትም ቢሆን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያስባቸውን እየፈፀመ ይገኝ ነበረ፡፡
ወደፊትም ቢሆን እኛ ከሱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ኖረን ምን በዚያ ሁኔታ መቀጠሉ አያጠያይቅም፡፡

71 | P a g e
እግዚአብሔር ለእኛ በሚያስፈልገን ነገር ነው የተነካው፡፡ እርስዎ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ለእግዚአብሔር
ሳይሆን ለእኛው ጥቅም መሆኑን ስንረዳ ነው የሱ ፀጋ ትርጉም የሚሰጠን፡፡ ጸጋ ማለት ሌላ ምንም ሳይሆን
እግዚአብሔር በሐጢአት ለወደቀው የሰው ልጅ ዘር ዳግም መዳን ያወጣው ዕቅድ ነው፤

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖረል እንጂ
ሕይወትን አያይም፡፡

(የዮሐንስ ወንጌል 3፡36)

 የመንፈሳችን ካሣ 

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህች ምድር የመጣው በሥጋችን ፍላጎት፤ ጥቅም እና ኃይል ላይ ከተመሠረተው
ሕይወት ነጻ በማውጣት በእግዚአብሔር ላይ ወደተመሠረተ አዲስ ሕይወት ሊመራን ነበረ፡፡ እግዚአብሔር
ወደ እኛ ዘንድ ኢየሱስን የላከው እንድንካስ እና መንፈሳችን ከሱ መንፈስ ጋር ትስስር ፈጥሮ እምቅ-
አቅማችንን ማውጣት እንችል ዘንድ ነው፡፡

መካስ የሚለው ቃል፤ ‹‹በድጋሚ መግዛት›› የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ለምሳሌም እርስዎ ዘመናዊ
ተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎ ቢጠፋብዎት እና አንዷ ብታገኝልዎት ለዚያ ላገኘችበት $20 ዶላር ልታስከፍልዎ
ትችላለች፡፡ ይኼ $20 ዶላር ለጠፋብዎት ዕቃ የካሣው ዋጋ ሲሆን ገዝተውት የነበረውን እና የራስዎ ሆኖ
የነበረን ነገር በድጋሚ ከመግዛት ድነውበታል፡፡

እርስዎ እንደ አዳም ዘርነትዎ በቅድሚያ የእግዚአብሔር ንብረት የነበሩ ቢሆንም ሰይጣን ግን ነጠቀዎት፡፡
ኢየሱስ ደግሞ ወደ ምድር በመውረድና በመስቀል ላይ በመሰቀል ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኖርዎ ዘንድ ካሳ
ከፈለ፡፡ ኢየሱስ ከሐጢአትና ሞት ሲያድንዎ መንፈስ ቅዱስ ከእርስዎ መንፈስ ጋር ትስስር በመፍጠር እምቅ-
አቅምዎን ማነሳሳት እንዲችል ነው ያደረገው፡፡ በኢየሱስ አማካይነት እግዚአብሔር መንፈሳዊ ሕይወትዎን
አድሶ ነፍስዎን ከራሱ የጥበብ እና የእውቀት ምጥማቅ ጋር አገናኝቶታል፡፡

 የሥጋችን ካሣ 

ኢየሱስ መንፈሳችንን ካሣ ቢሰጠውም አካላችን ግን ገና ካሣን አላገኘም፡፡ ጌታ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ


ከተነሣ በኋላ አካላችንን ካሣ ሊያጎናጽፈው እንደሚመለስ ቃል ገብቷል፡፡

አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን
በሰው በኩል ሆኖአልና።እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት

72 | P a g e
ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበት ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ
እኛም እንለወጣለን።

(1 ኛ ቆሮንጦስ 15፡20-21፤ 51-52)

የእግዚአብሔር ፍላጎት እና ዕቅድ ሥጋችን ዘለዓለም እንዲኖር ነበረ፡፡ ለዚህ ሁለት ነገሮችን በምሳሌነት
መጥቀስ እንችላለን፡፡ አንደኛው የጣታችን ከቃጠሎ በኋላ ለመፈወስ መቻል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከቀዶ
ጥገና በኋላ ያ ቀደዳ የተካሄደበት አካላችን መዳንና መፈወስ መቻሉ ናቸው፡፡ እነዚህ በአካላችን ውስጥ ቀደም
ሲል ታስቦለት ከነበረው ዘለዓለማዊ እምቅ-ኃይል የቀረ እንጥፍጣፊ እንዳለ ነው የሚያሳዩት፡፡ እግዚአብሔር
አሁንም ቢሆን ሀሳቡ እና ፍላጎቱ ዘለዓለማዊ አካል ይኖረዎ ዘንድ ነው፡፡ አካልዎ ሞትን ድል አድርጎ እንደሚነሳ
ቃል ገብቷል፡፡ የእርስዎ ከሞት የተነሳ አካል ልክ አዳም ሐጢአት ከመስራቱ ቀደም ብሎ እንደነበረው አካል
ይሆናል፡፡ አዲሱን ሰውነትዎትን መዳሰስ ይችላሉ፤

እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ
እዩ አላቸው።

(የሉቃስ ወንጌል 24፡39)

አሁን ባሉበት ሕይወት ግን ሥጋዎ እንቅፋት ሆኗል፡፡ መቀጥቀጥ ይደርስበታል፤ ይዝላል፤ ይታመማል ወዘተ.
ዕድሜዎ ሲጨምር ደግሞ ብዙ አስታሙኝ ይላል፡፡ ለዚህ ነው በማኅበረሰባችን ውስጥ በዕድሜ ባለጸጎች ዘንድ
ዳግም ወጣት የመሆን እና የመምሰል ፍላጎት እንዲህ ንሮ የምናየው፡፡ በዕድሜ በጣም የገፋ አይፈለግም፡፡
ወጣትነት ደግሞ ዋጋው የትየለሌ ሆኗል፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሕዝብ በጻፈው ሁለተኛው መልዕክት የተናገረው ይመስጠኛል፤

ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።

(2 ኛ ቆሮንጦስ 4፡16)

እውነት እውነት እልዎታለሁ፤ እግዚአብሔር አለ በተባለ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሊያገኙ የማይችሉትን አዲስ
መልክ ይሰጥዎታል፡፡ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ብቸኛ ነገር ቢኖር የተሸበሸበ
ቆዳን በተን ማድረግና መጠጋገን ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን አዲስ አካል ሊሰጥዎ ነው የተዘጋጀው፡፡ በመሆኑም
አሁን ያለዎ ሰውነት እና ገጽታ የፈለጉትን ያህል ባይሆን አይጨነቁ፡፡ መጠጋገኑ፤ ማስዋቡ እና ማሰማመሩ

73 | P a g e
ይኑር፡፡ ብቻ ዋንኛውና ትልቁ አደጋ ግን ሕይወትዎን ከሥጋዎ እኩል አድርገው መመልከት ነው፡፡ ይኼንን
ፈጽሞ አያደርጉ፡፡ እግዚአብሔር በውስጥዎ ቀድሞውንም ያስቀመጠውን ነገር ያወጣዋል፡፡ አሁን ባለን አካል
ላይ እምቅ-አቅምዎን እንዲያወጡ እና ይኼ ሥጋዎ ከበሰበሰም በኋላ ዘለዓለማዊ ክህሎቶችዎን እየተጠቀሙ
እንዲቀጥሉ ይፈልጋል፡፡ እርስዎ ከጎደሎውና እያሽቆለቆለ ከሚገኘው አካልዎ እጅግ በጣም በላይ ነዎት፡፡

 የእግዚአብሔር የአሠራር-ስምነት 

እግዚብአብሔር እርስዎን ፍጹም ገደብ-የለሽ ይሆኑ ዘንድ ነው ዲዛይን ያደረገዎት፡፡ ሁሉን-ቻይ ከሆነው
ማንነቱ እርስዎን በመፍጠር የእምቅ-አቅሙን የተወሰነ ቅሪት ወደ እርስዎ አስተላለፈ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
ልክ እንደ እሱ ይከውኑ ዘንድ አሠራር ቀየሰ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለዎት እምነት አማካይነት
ከእግዚአብሔር ጋር ዳግም ትስስር ሲፈጥሩ አስቀድሞ ወደታሰበልዎትና ከሱ ጋር ተመሳሳይ ወደሆነው
አሠራርዎ ይመለሳሉ፡፡

እግዚአብሔር እስከ አሁን ያልተፈጸሙ ነገሮችን ከእምቅ-አቅም አንፃር ነው የሚለካው፡፡ ከሚታየው ይልቅ
በማይታየው ግን እንዳለ በሚያውቀው ነገር ላይ ያተኩራል፡፡ እስከዛሬ በተሰራው ነገር አይደነቅም፡፡

አንድ ነገር አከናውነው ከሆነ ይደሰቱበት፤ ይቀበሉትም፡፡ ሆኖም ሰርቻለሁ ብሎ አጉል መኩራራትና ቀሪውን
መርሳት ግን አይመከርም፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ይኼንን በሚከተለው መልኩ ይገልጸዋል፤

ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ
ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን
እፈጥናለሁ።

(ፊሊጲሲውስ 3፡13-14)

ሐዋርያው ጳውሎስ ባገኘውና እስከዚያ ድረስ ባሳካው ነገር አልረካም፡፡ ሁልጊዜም ቀጣዩን እርምጃ ነበረ
የሚያስበው፡፡ ለምን ምክንያቱን ያለፈው ነገር አያነሳሳምና፡፡ ያልተጠቀምንበትን ታለንት እና ክህሎቶች
ማውጣት የምንችለው የወደፊቱን ከእነ ፈተናዎቹና ከሚጠበቁብን ግዴታዎች አንጻር አሻግረን እና ጓጉተን
ስንመለከት ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔር አንድ ነገር ነዎት ወይንም አለዎት ካለ በውስጥዎ ያ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች
የማይታያቸው የሚታየው ሲሆን የሚናገረው ደግሞ የሚያየውን ነው፡፡ እግዚአብሔር እርስዎ የተደቀነብዎን
አሸንፈው መሄድ ይችላሉ ካለ ይችላሉ፡፡ እርስዎ አሸንፎ ከሚሄድ ይልቅ ተጠራጣሪና ፈሪ መሆንዎ በውስጥዎ
የአሸናፊነት እምቅ-አቅም የመኖሩን ዕውነታ ፈጽሞ አይለውጠውም፡፡ እግዚአብሔር ካለው እውነት ነው፡፡

74 | P a g e
እግዚአብሔር እምቅ-አቅምዎ እስኪወጣ እየጠበቀ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይለናል፤

‹‹እርስዎ አሁን እንደሚያደርጉት እና እንደሚሆኑት ብቻ አይደሉም፡፡ ልጄ በመሆንዎ አሁን ከሚያደርጉት እና


ከሚሆኑት እጅግ የተሻለ ለመሆንና ለማድረግ እምቅ-አቅሙ አለዎት፡፡ የእኔ እምቅ-አቅም ከእኔው ወደ እርስዎ
ይፈሳል፡፡››

 ከመንፈስ ወይንስ ከሥጋ የመነጨ ሕይወት 

ብዙዎቻችን እምነት የሚሰራበትን አኳኋን እና ሁኔታ እንኳ መቀበል አንፈልግም፡፡ በምንዳስሰው፤ በምናየው
እና በምንሰማው በጣም በመመካታችን እና በመላመዳችን ወደ እምነት ንፍቀ-ክበብ መንቀሳቀስን አንወድም፡፡
ለምሳሌም አንድ ሰው፤ ‹‹እንዴት ነህ›› ብሎ ሲጠይቀን ውቅና አካላችን እና ነፍሳችን ከሚገኙበት ሁኔታ
መሠረት አድርገን መመለስ ነው የሚቀናን፡፡ ወይ ስለ ሕመማችን ወይንም ስለ ጭንቀታችን (እነዚህ
ስለሚጫኑን) እናወራና እግዚአብሔር ያደረገልንን በርካታ ባረኮቶች ግን እንዘነጋቸዋለን፡፡ እኛ ምልከታችን
ተሳስቶ እንጂ ከእግዚአብሔር ቃል የተገቡልን እነዚህ ነገሮች ከጊዜያዊ ጭንቀቶቻችን እና አካላዊ ሁኔታችን
እጅግ ይልቃሉ፤ ያሳስባሉም፡፡

ከዚህ በኋላ አንድ ሰው ያንን ጥያቄ ቢጠይቅዎ፤ ‹‹ይመስገን፤ ባርኮኛል›› ብለው መመለስን ይማሩ፡፡ እርስዎ
ተቀበሉትም አልተቀበሉትም የእግዚአብሔር ምርቃትና ባረኮት ግን በውስጥዎ አንድ የሆነ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡
ተባርኬያለሁ ባሉ ቁጥር ደግሞ በውስጥዎ ያለው ባረኮት ያድጋል፡፡ ቀስ በቀስም የሚሉት እና የሚመለከቱት
መጣጣም ይጀምራል፡፡

እምነት ገና ያልታየንና ያልተገለጠን ነገር ያሳየናል፡፡ ያለ ነገር ግን ገና የማይታይን ነገር ያሳየናል፡፡ አንድ ነገር
በግልጽ ሲታይ እምነት አያስፈልገውም፡፡ ለምን ቢባል እምነት ማለት ማመን፤ መረዳት እና የምንፈልገውን
እስክናየው መሻታችንን መግለጽ ነውና፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፤ የማናየውንም የሚያስረዳ ነው፡፡

(ወደ ዕብራውያን 11፡1)


 የእምነት ሂደት 

እምነት ይሆናል ብሎ በመቀበልና እውነት ነው ብሎ በማሰብ ይጀምራል፡፡ አንድ ነገር ይሆናል ወይንም አለ
ብሎ ለማመን ስለዚያ ግለሰብ ወይንም ነገር መኖር ወይንም ነው ብለን የምናምነውን ለመሆኑ ያለ አንዳች
ጥርጣሬና ማስረጃ ፍለጋ ማመንን ይመለከታል፡፡ በእንግሊዝኘው አዲስ ኪዳን ላይ ለእምነት የተቀመጠው ቃል

75 | P a g e
pistos ማለት፤ ‹‹በሌላ ሰው ምስክርነት ማመን›› የሚለውን ትርጓሜ ይሰጠናል፡፡ በመሆኑም በእምነት ፀንተን
እና እውነት ነው ብለን ተቀብለን መቆየትን እንጂ ቀድመን ማረጋገጥ ወይ ማየት አይደለም የሚጠበቅብን፡፡

በእምነት ፀንተን እና እውነት ነው ብለን ተቀብለን መቆየትን እንጂ ቀድመን ማረጋገጥ ወይ


ማየት አይደለም የሚጠበቅብን፡፡

ነገር ግን ይኼ ሲሉት ይቀል እንደሆነ እንጂ ለመተግበር ግን ፈተና አለው፡፡ ያም እምነት ሥጋችንን
በመንፈሳችን ቁጥጥር ሥር ማድረግን ከመጠየቁ ጋር ይያያዛል፡፡ ሥጋችን፤ ‹‹አይ፤ ካላየሁ አላምንም!››
ይለናል፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ፤ ‹‹እንደ እኔ መንቀሳቀስ የምትፈልግ ከሆነ እስክታምን ድረስ አታየውም!››
ይለናል፡፡ ዓለም ደግሞ፤ ‹‹እኔ በእርስዎ ኩባንያ አክስዮን የምገዛው ዕድገቱን ሳይና ሳረጋግጥ ብቻ ነው፤››
ይለናል፡፡ እግዚአብሔር ግን፤ ‹‹የእርስዎን ቢዝነስ በቅድሚያ ተባብረን እናሳድግ፤›› ይላል፡፡ አንዱ በማየት፤
ሌላኛው በእምነት፡፡

በእምነት መኖር ከዚህ በተጨማሪም ነፍሳችንን በመንፈሳችን ቁጥጥር ሥር ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ነፍስዎ
ስሜትዎን፤ መልካም ፈቃድዎን እና አዕምሮዎን ትቆጣጠራለች፡፡ ለነፍስዎ ሲኖሩ ለውሳኔ ከሥጋ
የሚቀበሉትን መረጃ ነው መሠረት የሚያደርጉት፡፡ ነፍስዎ እንዲህ ትላለች፤ ‹‹የሕይወቴ ውጫዊ ገጽታ እኔ
እንደምፈልገው ባለመሆኑ ደስተኛ አይደለሁም፤›› እግዚአብሔር የሚልዎት ስለማይሰማዎት ብቻ
ስለሚናገረው ጠንቅቆ ማወቁን እና እርግጠኛ መሆኑን አይጠራጠሩ፡፡

እግዚአብሔር ቃል የገባልዎትን ካመኑ ግን ማየት (መረዳት) መጀመር አለብዎ፡፡ ማየት እና መመልከት የተለያዩ
ነገሮች ናቸው፡፡ መመልከት ሲባል ውጫዊ ገጽታ ላይ የተንጠላጠለ ሲሆን ማየት ግን የማይታዩ ነገሮች
መኖራቸውን ያምናል፡፡ ብዙዎች ይመለከታሉ፤ ጥቂቶች ብቻ ግን ያያሉ፡፡ እነን እንድንንቀሳቀስ ይፈልጋል፡፡

አንድን ነገር ማየት ከቻልን በኋላ ግን ያየነውን ማውጣት አለብን፡፡ በ ኦሪት ዘፍጥረት ላይ እግዚአብሔር
ከጨለማ ብርሐንን መመልከቱን እንረዳለን፡፡ ብርሐን የነበረ ቢሆንም እግዚአብሔር እስኪያነጋግረው ድረስ ግን
ራሱን አልገለጠም ነበረ፡፡ መልዓኩ ገብርዔል የጎበኛት ወጣት ሴትም ላይ ተመሳሳይ ነገር ነበረ የተከሰተው፡፡
ለመጋባት የታጨች ቢሆንም ገና ወንድ አታውቅም፡፡ መልዓኩ ገብርዔል ፀንሳ ወንድ ልጅ ወልዳ ስሙንም
ኢየሱስ እንደምትለው ሲነግራት የቱን ያህል እንደምትገረም አስቡት፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፤ ‹‹ይኼማ
እንዴት ይሆናል›› ብላ ሙግት መግጠም ትችል የነበረ ይሁን እንጂ እሷ ግን ፍጹም ተረጋግታ ነበረ፤

ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?

(የሉቃስ ወንጌል 1፡34)

ያለችው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም የመላኩ ገብርዔልን ቃላት አምና ተቀብላለች፤

76 | P a g e
መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ
የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

ዛሬም እግዚአብሔር ከምንጠብቃቸውና ይሆናሉ ብለን ከምናምናቸው ነገሮች ተጻራሪ ስለሆኑ ነገሮች
ሊነግረን መላዕክትን ይልካል፡፡ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! ሕልሞቻችሁ እውን ይሆናሉ!›› ይለናል፡፡ ከዚያ
እስክናረጋግጥለት ይጠብቃል፡፡ ‹‹አምላክ ሆይ! አንተ እንዳልከው ይሆናል!›› እስክንለው ያየናል፡፡ ነገር ግን
ከመናገርም ባሻገር ልናምን ይገባናል፡፡ ቃላት በራሳቸው ኃይል የላቸውም፡፡ ቃላት ከእምነት ጋር የተጣመሩ
እንደሆነ ብቻ ነው የእግዚአብሔር ምኞት በሕይወታችን እውን እንዲሆን ምክንያት የሚሆኑት፡፡ ሐዋርያው
ጳውሎስ በልቡ ስለነበረው በሚከተለው መልኩ በተናገረ ጊዜ ይኼንኑ ነበረ የገለፀው፤

ነገር ግን አመንሁ፡፡ ስለዚህም ተናገርኩ ተብሎ እንደተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፤ እኛ ደግሞ
እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፡፡ ጌታን ኢየሱስን ያስነሳነው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሳን ከእናንተም
ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና፡፡

(2 ኛ ቆሮንጦስ 4፡13-14)

አግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚፈልጉ ሁሉ እምነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በ ዕብራውያን 11፡6 ላይ፤

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ


እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና፡፡

ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በ ሮሜ 1፡17 ላይ ደግሞ፤

ጻድቅ በእምነት ይኖረል

ተብሎ ተቀምጦ እናገኛለን፡፡ እኛ የሰው ልጆች በእምነት እንድንኖር ነው የተፈጠርነው፡፡ እግዚአብሔር የሰው
ልጆች ከኃይሉ ጋር የሚገናኙት በእምነት ብቻ እንዲሆን አስቀድሞ ወስኗል፡፡ እምቅ-አቅም እምነትን
ይጠይቃል፡፡ እምነትም በተራው እምቅ-አቅም ይወጣ ዘንድ ይፈልጋል፡፡

እምቅ-አቅም እምነትን ይጠይቃል፡፡ እምነትም በተራው እምቅ-አቅም ይወጣ ዘንድ ይፈልጋል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ፤ ‹‹ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ፈጥሮ የፍሬው ተቋዳሽ መሆን›› በሚል
ትርጓሜ ተሰጥቶት የምናየው ጽድቅነት እግዚአብሔር በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ባዘጋጀልን መዳን ካልሆነ
በቀር አይሳካም፡፡ ጌታ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለእኛ ሲል በመሰዋት የሐጢአታችን ቅጣት ከነበረው ዘለዓለማዊ
ሞት አድኖናል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት አዲስ ሕይወትን ላገኙ እግዚአብሔር፤ ‹‹ጥፋተኛ አይደሉም››
የሚል ፍርድ ይሰጣል፡፡

77 | P a g e
 እምነት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው 

ለክርስትያን እምነት በፍጹም የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቅ ግዴታ መሟላት አለበት፡፡ እግዚአብሔር
ተንቀሳቀሱ ካለ ለእኛ ይበልጥ የሚያሳምነን እና መንቀሳቀስ እንዳለብን የሚነግረን ሌላ ማስረጃ እስክናገኝ
ቆመን መጠበቅ ፈጽሞ የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ተንቀሳቀሱ ካለ የፈለገ ቢሆን በድፍረትና ምንም ዓይነት
የሚያስከትለው ነገር ቢኖር እንኳ እሱን አምነን ልናደርገው ይገባል፡፡

እውነት ለመናገር እምነት በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሁሉ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡ ከእምነት ውጭ ምንም
ቢኖረው የሰው ልጅ የጭንቀት ሕይወት ነው የሚመራው፡፡ በአካባቢው እና በሚገኝበት ሁኔታ ከሚገባው በላይ
ተጠምዶና ተጨንቆ የሚኖር በመሆኑ በውስጡ ያለውን እምቅ-አቅም ማውጣት የማይችል ይሆናል፡፡ እምነት
የተስፋ ምንጭ ሲሆን ማንም ሰው ደግሞ ያለ ተስፋ ሊኖር አይችልም፡፡ ተስፋ የወደፊቱ አቀጣጣይ እና ትልቅ
ነገርን ለመጠበቅ ገልበት የሚሆነን ስንቅ ነው፡፡

 እምነት ነገሮች እንዲሆኑ ያደርጋል 

ዛሬ ብዙ ሰዎች ያለ እምነት ለመኖር ስለሚሞክሩ ሕይወታቸው ተበላሽቷል፡፡ ነገር ግን በቅዱስ ቃሉ ደግሞ


የምንመኘውን፤ የምንጠይቀውን እና የምንጠብቀውን ለማግኘት እምነት መሠረት መሆኑ በማያሻማ መልኩ
ተቀምጧልና የእነዚህ ሰዎች አካሄድ ያሳዝናል፤

ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።

(የማርቆስ ወንጌል 11፡24)

እምነት ነገሮች እንዲሆኑ የሚያደርግ አፋጣኝ ነገር ነው፡፡ እምነት ከውጫዊ የሕይወትዎ ገጽታ በላይ እርስዎን
ከፍ በማድረግ ለጨለማው ብርሐን እንዲሰጡ ያደርግዎታል፡፡ የሚጠይቁትን ሁሉ እንደሚያገኙ ያስታውሱ፡፡
ችግር ይመጣል ብለው ከጠበቁ ችግርን ያገኙታል፡፡ በእግዚአብሔር አምነው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለእርሰዎ
የተሻለውን ለማምጣት እንደሚሰራ ካመኑ ይዘግይም ይፍጠንም ዞሮ ዞሮ ግን በእርስዎ ሕይወት በጠበቁት
መልኩ እየሰራ ለመሆኑ ማስረጃ ያገኛሉ፡፡

ሕይወት ሁልጊዜ የምትመስለውን አይደለችምና ያለ እምነት እንግፋሽ ካልናት ራሳችንን ነው የምናሞኘው፡፡


የምናየውና የሚሰማን ነገር ሁሉ ያለውና ሙሉው አይደለም፡፡ ነገሮች እንደሚሰሩልን እንመን፡፡ ዓይናችንን
ከእግዚአብሔር እንድንነቅል የሚያደርጉንን ነገሮች እንተው፡፡ ‹‹ኤዲያ! አንቺስ እምነት እምነት እያልሽ
ለየልሽ፡፡ ኪራይ እንኳ አንጠባጥበሽ የምትከፍይ ሴትዮ ጭራሽ በባንክ ብድር ቤት ልስራ ትያለሽ›› ይለናል
ምድራዊው አስተሳሰብ፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ሁሉም ይሳካል ብለን እንመን፡፡ ዕቅድ አውጥተው፤

78 | P a g e
‹‹በእግዚአብሔር ሁሉም እንደሚቻል አውቃለሁ!›› ይበሉ፡፡ በሚያዩት ብቻ ባለመኖርዎ አምላክን ያመስግኑ፡፡
ቃል የገባውን ይፈጽማል ብለው ይመኑ፤ ተራራውንም ይገፋልኛል ብለው ይጠብቁ (የማቴዎስ ወንጌል 21፡21 ን
ይመልከቱ)፡፡

ሕይወት ሁልጊዜ የምትመስለውን አይደለችምና ያለ እምነት እንግፋሽ ካልናት ራሳችንን ነው


የምናሞኘው፡፡

ነገሮች የሚሰሩልዎ ባይሆን ምናልባትም ከእምነትዎ፤ ከሚያስቡት እና ከሚናገሩት ነገር ጋር የተያያዘ ሊሆን
ይችላል፡፡ በመጥፎ ወይ ክፉ ነገሮች ተጽዕኖ ስር አይውደቁ፡፡ ሰይጣን በእምነት እንዲኖሩ ፍላጎቱ ስላልሆነ
መጥፎውን ክፉውን እንዲያስቡ ይጥራል፡፡ እርስዎ ግን እርሱን የተፈበረከ ውሸት አላምንም ይበሉ በሌሎች
በዙሪያዎ በሚገኙ የተለያዩ ሰዎች አቃቂር፤ ሽሙጥም ሆነ ትችት ተስፋ አይቁረጡ፡፡ እግዚአብሔር የሕልምዎ
ምንጭ ከሆነ ሰዎች ያንን ሊያጠፉት አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር የፈቀደውን ማድረግ ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ወደ እግዚአብሔር ቃል ይመለሱና ቃል የገባልዎን እንዲፈጽም ይጠየቁት፡፡ እምነት የዕለት ተዕለት


ሕይወትዎ መሠረት እንድትሆን በማድረግ፤ ‹‹እግዚአብሔር ስላለ እኔ አምናለሁ›› ይበሉ፡፡ ይኼንንም
በሕይወትዎ ልዩነት እና ለውጥ እስኪያዩ ይግፉበት፡፡ ከምንም በላይ ግን ተስፋ አይቁረጡ፡፡

በእምነት የሚያደረጉትን አኗኗር ውጤት ሳይውል ሳያድር ያዩታል፡፡ እርስዎ እና እግዚአብሔር በአንድ መንፈስ
በመሆን የማታሳኩት ነገር አይኖርምና ጧት ሲነሱ እንኳ ጥሩ ቀን ነው ብሎ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ይሆናል
ብለው ማመን ይጀምራሉ፡፡ ይኼንን ሳምንት የእግዚአብሔርን ቃል በማመን እና ትዕዛዛቱን በመጠበቅ አሀዱ
ይላሉ፡፡ በእምነት መኖር ማለትም ይኸው ነው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ እኛ እስካልፈቀድንና እስካላበረታታነው
ድረስ እምነት የሚያሳጣን ከቶ ምንም የለም፡፡

 እምነትን የመተው አሳዛኝ ውጤት 

ዛሬ በጣም ብዙዎቹ የሚያሳዝኑትና የወደቁት ሰዎች የወደቁበት ምክንያት ቢታይ ለማሸነፍ ቀርበው የነበረ
መሆኑ ነው፡፡ እርስዎ ፈጽሞ ይህ በራስዎ ላይ እንዲሆን መፍቀድ የለብዎትም፡፡ እግዚአብሔር እንዲሰጠዎት
ሲጸልዩባቸው የነበሩ ነገሮች የቱን ያህል ቀርበው እንደመጡ አያውቁም፡፡ ነገሮች ለጊዜው እየተባባሱ መጡ
ማለት እግዚአብሔር ለእርስዎ የገባውን ቃል ረስቶታል ማለት ፈጽሞ አይደለም፡፡ ወደ ድል ይበልጥ በቀረቡ
ቁጥር ፍልሚያው የዚያኑ ያህል ይጠነክራል፡፡ ብዙውን ጊዜ ነገሮች ሲባባሱና ወደ ጫፍ ሲደርሱ የጠየቁትን
ለማግኘት እየተቃረቡ ነው ማለት ነው፡፡

በመሆኑም እርስዎ በሕይወትዎ ቀና የሆኑትን ነገሮች ሁልጊዜም መመልከት እና የእምነት ድምጽዎን ማደስ
ይኖርብዎታል፡፡ በራስዎት እና በእግዚአብሔር ይመኑ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ካንተ ጋር ነኝ፤ አንተም ከእኔ

79 | P a g e
ጋር ነህ›› ይበሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በስምምነት ሲሄዱ የሚበላሽና ከቁጥጥር ውጭ የሚወጣ ነገር እንደሌለ
ይቀበሉ፡፡ እግዚአብሔር ከሁሉም ካስቀደሙት የሚገባዎትን ሽልማት እንደሚሰጠዎትም ይተማመኑ፡፡
በመጨረሻም የፈለጉትን እስኪያገኙ ድረስ ይመኑ፤ ይጠይቁ፤ አይታክቱ፡፡ ይኼ ነው እግዚአብሔር
እንዲንቀሳቀሱበት የሚፈልገው መንገድ፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

(የማቴዎስ ወንጌል 6፡33)

በእምነት መኖር ብዙውን ጊዜ አቀበትና ቁልቁለት የበዛበት መንገድ ሲሆን ጽናትና ትዕግስትን ይጠይቃል፡፡
እምነት በእርካታ ለተሞላ እና የመትረፍረፍ ሕይወት መሠረት ነው፡፡ እግዚአብሔር በውስጥዎ ያስቀመጠውን
በማውጣት ለዓለምና ለመጪው ትውልድ አስተዋፆ ያበረክቱበት ዘንድ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ እምነት ማለት
በእርስዎ ውስጥ ካለው ትልቅና ሰፊ እምቅ-አቅም የሚቀዳበት ባሊ በመሆኑ እምቅ-አቅምዎ ለማደግ የግድ
እምነትን ይፈልጋል፡፡

እምነት ማለት በእርስዎ ውስጥ ካለው ትልቅና ሰፊ እምቅ-አቅም የሚቀዳበት ባሊ በመሆኑ


እምቅ-አቅምዎ ለማደግ የግድ እምነትን ይፈልጋል፡፡

80 | P a g e
 መርሆች 

1. እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እምቅ-አቅም ያለው መንፈስን ለእርስዎ ሰጥቷል

2. እርስዎ የመንፈስ ሙት ሆነው በመወለድዎ የተነሳ ሐጢአት እምቅ-አቅምዎን ወስዶብዎታል

3. እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ መስዕዋትነት ዘለዓለማዊ ለእምቅ-አቅምዎ ካሣን አስገኝቷል

4. እርስዎ በእምነት ይኖሩ ዘንድ ነው ዲዛይን የተደረጉት

5. እምነት ማለት ማየት፤ ማውጣት እና መቀበል ነው

81 | P a g e
ምዕራፍ 8

_____________________ _____________________

ዓላማዎትን ይወቁ

ዓላማ-የለሽ ሕይወት ከሙከራ ሕይወት የተለየ አይሆንም፡፡

ሳዖል እጅግ አክራሪና ስሜቱ የሚቀድመው፤ በጥንታዊዋ ቤተክርስትያን ላይ መሰደድን ያካሄደ እና


ቤተክርስትያኒቱን ለማጥፋትም የሚችለውን ሁሉ ድንጋይ የፈነቀለ አለሁ ያለ አይሁዳዊ ነበረ፡፡ ሆኖም
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሳዖል ጨርሶ ያላወቀውና ያልጠረጠረው የተለየ ዓይነት ሕይወት ነበረ የታቀደለት፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር ሳዖልን ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ ነጥሎት በፀጋውም ጠራው፤

በአህዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፤
ወዲያው ከሥጋ እና ከደም ጋራ አልተማከርሁም፡፡

(ወደ ገላቲያ ሰዎች 1፡16)

82 | P a g e
ወደ ደማስቆ ሲጓዝ ሳዖል እግዚአብሔር ካስቀመጠለት ዓላማ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጠ፡፡ አጋጣሚ የሳዖልን
ሕይወት እስከወዲያኛው የቀየረው ሲሆን ፈርዖናዊ የነበረው ሳዖል ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆን በቃ፡፡

እርስዎ ከተቀመጠልዎ ዓላማ ጋር የሚያደርጉት መፋጠጥ የሳዖልን ያህል አስደናቂ እንዲሆን ባይጠበቅም
እግዚአብሔር ለምን ሲል ፈጥሮ ወደዚህች ምድር እንዳመጣዎት ግን መረዳት ይኖርብዎታል፡፡ እኔ በሕይወቴ
ስንትና ስንት ስኬት አግኝተው ግን ያልረኩ ብዙዎችን አውቃለሁ፡፡ ግቦችን አሳክተዋል፤ በስኬት ላይ ስኬትን
ጨምረዋል፤ ነገር ግን እርካታ ስሜት የራቃቸው በመሆኑ ‹‹ምነው›› ሲሉ አጥብቀው ይጠይቃሉ፡፡ አንድ ሰው
አስቀድሞ የዓላማውን ምንነት ተረድቶ ያንን ተቀብሎ ካልተንቀሳቀሰ ስኬትን በስኬት ላይ ቢደራርብ በእርካታ
ደረጃ ገን ባዶ ከመሆን አይዘልም፡፡ ሕይወትን ያለ ሕይወት ዓላማችን መረዳት እንጓዛት ብንል ግራ መጋባትና
ባዶነት የቅርብ ጓደኞቻችን ይሆናሉ፡፡

 የዓላማ ትርጓሜ 

የአንድ ነገር ዓላማ ማለት ያ ነገር የሚፈጠርበት ምክንያት ወይንም ፈጣሪው/ሰሪው በፈበረከው ጊዜ
እንዲሰራ ያሰበው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የአንድን ነገር ዓላማና ምክንያት ለማወቅ ሌላን ነገር መጠየቅ
ምላሹን አያስገኝም፡፡ ይልቅ ፈጣሪው/ሰሪው ነው ይኼንን በሚገባ ሊመልስ የሚችለው፡፡

እግዚአብሔር የእርስዎ ምንጭ/ፈጣሪ ነው፡፡ ለምን ሕይወት እንደሰጠዎት እና ከሌሎች ሰዎች ልዩ


የሚያደርጉዎትን ስብዕና፤ ታለንት እና ምኞት ለምን እንደሰጠዎት ያውቃል፡፡ ዓላማዎን ያሳኩ ዘንድ ለምን
ወደዚህች ምድር ተፈጥረው እንደመጡ ያውቃል፡፡ የዓላማ ስሜትና በዓላማ መንቀሳቀስ ለሕይወት ትርጉምን
ይሰጣል፡፡ ከሕልውና ባለፈ ወደ ስኬታማ እና ምርታማ ሕይወት እንዲያመሩ ያደርጋል፡፡

 አስተሳሰብዎን ይቀይሩ 

ጌታ ኢየሱስ ዓላማን የተመለከተበት መንገድ ነበረ፡፡ ይኼንን መንገድ ሐዋርያው ጳውሎስ በ 1 ኛ ቆሮንጦስ 2፡
11 ላይ በሚከተለው መልኩ ገልፆታል፤

በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው  እንዲሁም ደግሞ
ከእግዚአብሔር መንፈስ ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም፡፡

እርስዎ ከእግዚአብሔር ተነጥለው የተፈጠሩ እና ከመንፈሱም ውጭ የተወለዱ በመሆኑ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ


ስለ ንሥሀ መግባት በሰበከ ጊዜ የሰውን ልጅ አለማወቅ አጉልቶ ገልጾታል ጅ እጽዋት እና እንስሳት እንዴት
እንደሚንቀሳቀሱ በመመራመርና ብዙ ነገሮችን በርብሮ በማውጣት ሊቅ ሆኗል፡፡ አንዱን ዘር ከሌላው

83 | P a g e
በማዳቀል ይበልጥ ብርቱ፤ ጠንካራ፤ የሚያማማሩ እና ልዩ የሆኑ ፍጡራንንም አሳይቷል (የማቴዎስ ወንጌል 4፡
17 ን ይመልከቱ)፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ሙሉ የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ እንደሚጠይቅ


ያውቅ ነበረ፡፡ እናም ንስሀ እንድንገባ ትዕዛዝ ሲሰጥ የእግዚአብሔርን አዲስ የፀጋ አሠራር ነው የገለጸው፡፡ ነገር
ግን ብዙሀኑ የሃይማኖት መሪዎች ይኼንን የሱን አስተምህሮት ተቃወሙ፡፡ በተለይም የእነሱ አስተሳሰብ
የተሳሳተ መሆኑን መጠቆሙን እንደ ስድብ ቆጠሩት፡፡

እውነታውና ሃቁ ኢየሱስን ከማግኘታችን ምንም ዓይነት አስተሳሰብ ቢኖረን የተሳሳተ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ያለ
እግዚአብሔር ልቦና አይኖረንምና፤

እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአዕምሯቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም
ሆኜ እመሰክራለሁ፡፡ እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳናነት ጠንቀቅ ልቦናቸው ጨለመ፤
ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፡፡

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡17-18)

ያለ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብም አይችሉም፡፡

ከእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡

(የዮሐንሥ ወንጌል 14፡6)

እግዚአብሔርን የማያውቁትን፤ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይቀበላል፡፡ ከዚያም ቀን


በቅዱሳኑ ሊከብር፤ ምስክርነታችንንም አምናችኋልና፡፡

(2 ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1፡8-9)

እግዚአብሔር እንድንጠፋ ፍላጎቱ አይደለም፡፡

. . . ነገር ግን ሁሉ ወደ ንሥሀ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሳል፡፡

(2 ኛ የጴጥሮስ መልዕክት 3፡9 ለ)

በፍቅሩና ምህረቱ የተነሳ ከጥፋት የምንድንበትን የንሥሀ አማራጭ አዘጋጅቶልናል፡፡ እግዚአብሔርን እና


ለሕይወትዎ ያሰበውን ዓላማ ችላ በማለት መጥፋትን ካልፈለጉ አስተሳሰብዎን ነው መቀየር ያለብዎ፡፡

84 | P a g e
 ዓላማን ችላ ማለት አለአግባብ በጥቅም ላይ ወደ ማዋል ያመራል 

ቸልተኝነት አለአግባብ ወደ መጠቀም ያመራልና እምቅ-አቅማችንን ያሳጣናል፡፡ አለአግባብ መጠቀም (abuse)


ላይ በተለይ የእንግሊዝኛውን ቃል የመሠረቱትን ሁለት ቃላት እንመልከት፡፡ አንደኛው abnormal ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ use ነው፡፡ አንድን ነገር ቀድሞውኑ ለምን እንደተፈጠረና እንደተሰራ፤ እንዴት ደግሞ
ለጥቅም ዲዛይን እንደተደረገ የማናውቅ ከሆነ ተፈጥሯዊ በሆነው መልኩ ልንጠቀምበት አንችልም፡፡

ሚስትዎ ለምን እንደምታስፈልግዎ የማያውቁ ከሆነ አግባብነት የሌለው አያያዝ ይይዟታል፡፡ ባልም ለምን
እንዳስፈለገ ባያውቁ ግንኙነታችሁ ባልተፈለገ መንገድ መሄዱ አይቀርም፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ
ልጆችን አምላክ ለምን እንደሚሰጥ ሳያውቁ አለአግባብ ቢይዟቸው ነው፡፡

 የፍጥረትን ዓላማ የሚያውቅ ፈጣሪው ብቻ ነው 

ወደዚህች ምድር ለምን ተፈጥረን እንደመጣን ለማወቅ ወደ ፈጣሪያችን አዕምሮ መመለስ ይኖርብናል፡፡
የማንንም ምርት (ፍጥረት) ዓላማ ማንም ይሁን ማን የፈጣሪውን ያህል ሊያውቀው አይችልም፡፡ ቀሚስ
ቢሰፉ ቀሚሱን ለምን እንደሰፉትና አጠቃቀሙን እርስዎ ብቻ ነዎት የተሻለ የሚያውቁት፡፡ ለቤት ሥራ የቆየ
የዛፍ እንጨት ቢጠቀሙ ኋላ ላይ ቀለም ስለሚቀባ ያንን እንጨት መጠቀምዎ ለእርስዎ ነው የሚታወቀው፡፡

እርስዎ ከመጡበት ምንጭ ጋር የተያያዙ ነዎት፡፡ ይኼም ማለት የፈጣሪዎን ያህል የመጡበትን ዓላማ ሌላ
ማንም አያውቀውም፡፡ አምላክም ለእርስዎ ያሰበውን እና የሕይወት ዓላማዎን እንዲያውቁ ይፈልጋል፡፡

ያለ እግዚአብሔር ለመኖር ቢሞክሩ ያለ ዓላማ የሚኖር ሕይወት አግባብነት የለውምና የተበላሸ ከመሆን
አይዘልም፡፡

ያለ እግዚአብሔር ለመኖር ቢሞክሩ ያለ ዓላማ የሚኖር ሕይወት አግባብነት የለውምና የተበላሸ


ከመሆን አይዘልም፡፡

እስኪ ዙሪያዎትን ይመልከቱ፡፡ ብዙ ሰዎች ምግብ፤ ቤተሰብ፤ ቤት፤ መኪና፤ ወዳጆች ወዘተ.ን አለአግባብ
ይጠቀማሉ፡፡ የእነዚህን ነገሮች አስፈላጊነት እና ዓላማ ባለማወቃቸው ነው እንዲህ የሚያደርጉት፡፡ የአንድን
ምርት አስፈላጊነት ካልተረዱ አምራቹን ይጠይቁ፡፡ የቤተሰብ እና የጓደኛን አስፈላጊነት ካልተረዱ ደግሞ ወደ
እግዚአብሔር ይሂዱ፡፡ ዓላማን መረዳት አለአግባብ ከመጠቀም ያድናል፡፡

 አሁን የሚያደርጉትን ለምን ያደርጋሉ 

85 | P a g e
በአንደኛ ቆሮንጦስ ምዕራፍ አሥራ-ሶስት ላይ የነገሮችን አስፈላጊነት ባንረዳ እንዴት አለአግባብ
ልንጠቀምባቸው እንደምንችል ጥሩ ምሳሌ ተቀምጦ እናገኛለን፡፡ ይኼ ምዕራፍ ከፍቅር ጋር ተያያዥነት ያለው
በመሆኑ ብዙውን ጊዜ በጋብቻ ሥነ-ሥርዓቶች ላይ ለጋቢዎች ይነበባል፡፡ ብዙ ሰዎችም ይኼንን ምዕራፍ
ይወዱታል፤ ነገር ግን እንደሚለው ሆነው መኖር ላይ ትልቀ ችግር አለባቸው፡፡ ለዚህ አንዱ ምክንያት ከዚያ
ጥቅስ ቀደም ብሎ ያለውን ጥቅስ ይዘሉታል፡፡ ማለትም ከ ምዕራፍ 13 በፊት ምዕራፍ 12 አለ፡፡ በዚህኛው
ምዕራፍ ላይ ስለመንፈስ ቁዱስ መጠመቅ ነው የምንመለከተው፡፡

የፀጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያነዳንዱ ለጥቅም
ይሰጠዋል. . .ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል . . .ፍቅር
ይታገሳል፤ ቸርነትንም ያደርጋል፡፡

(1 ኛ ቆሮንጦስ 12፡4፤7፤11፤31 ሀ፤ 13፡4 ሀ)

በሕይወትዎ መንፈስ ቅዱስ የሌለዎ ከሆነ ፍቅርን እና ሊወዷቸው የሚሹትን አለአግባብ መያዝዎ አይቀርም፡፡
መንፈስ ቅዱስ በሕይወትዎ ከሌለ ተፈላጊውን ውጤት ፈጽሞ ማግኘት አይችሉም፡፡ መንፈስ ቅዱስ
በሌለበት ብስጩ፤ ችኩል፤ ቀናተኛ፤ ርህራሄ-ቢስ፤ ጉረኛ፤ አጉል ቁንን፤ ነውረኛ፤ በራሱ የሚወጠር እና
ከፍቅረኛዎ ጋር ባለዎ ግንኙነትም በሆነው ባልሆነው የሚፈነዳ ነው የሚሆኑት፡፡ እውነት ለመናገር ፍቅር
እግዚአብሔር በሕይወታችን የፈጠረው ኃይል የዕድገት ውጤት መሆኑን ባለመረዳትዎ የፍቅር ሕይወትዎም
ለውድቀት ይዳረጋል፡፡

ያለ ዓላማ ስኬት ቢገኝ ጊዜ ማቃጠል ነው ትርፉ፡፡

የሚሰሩትን ለምን እንደሚሰሩ የማያውቁ ከሆነ ጊዜዎትን እያቃጠሉ ሲሆን ምንም ቢሰሩ ልዩነት የለውም፡፡
ለምሳሌም ለድሆች ያለዎትን ሁሉ አሟጠው ቢሰጡም ሆነ ሰውነትዎን እንደ መስዕዋትነት ቢያቃጥሉት
ለምን ያንን እንደሚያደርጉ ግልጽ የሆነና የተጨበጠ ነገር በውስጥዎ ከሌለ ያደረጉት ከማጥፋት የተለየ
አይሆንም ማራጭ ደግሞ የለውም (1 ኛ ቆሮንጦስ 13፡3 ን ይመልከቱ)፡፡ እግዚአብሔር ሃይማኖታዊ ወይንም
ግብረ-ገብ የሆኑ ነገሮችን አብዝተን ስላደረግን ብቻ አይደሰትም--ለምን እንደምናደርጋቸው ልናውቅ ግድ
ይላል፡፡

 ሰው ያለ እግዚአብሔር የጠፋ እና ግራ የተጋባ ነው 

በ መዝሙረ ዳዊት 82 ላይ የሰው ልጅ ያለ እግዚአብሔር ምን ሊሆን እንደሚችል እናያለን፡፡

86 | P a g e
አያውቁም፥ አያስተውሉም፤ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።እኔ ግን፦ አማልክት
ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤ ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፤ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ
አልሁ፡፡

(መዝሙረ ዳዊት 82፤5-7)

እኛ የሰው ልጆች ምንም እንኳ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ልጅ ብንሆንም የሱን መንፈስ እንዳልተቀበልን
ሥጋ እና ደም ብቻ እንደያዝን ሆነን ነው እየኖርን የምንገኘው፡፡ አቀጣጫና ዓላማ የሚባል ነገር ካጣን
ሰነባብተናል፡፡ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፡፡ እኛ (እና የምንኖርባት ዓለም) ከመስመር ወጥተናል፡፡ ይኼ
ደግሞ እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠራቸው የማያውቁት ዕጣ ፈንታ ነው፡፡ ሕይወታቸው በግራ መጋባት እና
አለአግባብ ነገሮችን በመጠቀም ተሞልቷል፡፡ ምናልባትም እግዚአብሔር የፈጠረዎት ጥሩ ትምህርት
እንዲያገኙ፤ ፀሎት ቤት እንዲሄዱ ወይንም ሥራ ይዘው እንዲኖሩ ይመስልዎ ይሆናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን
በራሳቸው እግዚአብሔር እርስዎን ከፈጠረበት ዓላማ ውጭ ትርጉም የላቸውም፡፡

 እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያስቀመጠው ዓላማ 

ዓላማዎትን የማያውቁ ከሆነ እውን ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ በመሆኑም እምቅ-አቅምዎን ማውጣት የግድ
እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠረዎ ማወቅና መረዳትን ይጠይቃል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እግዚአብሔር
የሰውን ልጅ ለምን እንደፈጠረ ይነግረናል፤

በ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ላይ እንዲህ ይላል፤

እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፤26)

ከእርስዎ ጋር የተያያዘ ነገር ሁሉ የተፈጠሩበት ምክንያት ነው---ቁመትዎ፤ ዝርያዎ፤ የተፈጥሮ ታለንትዎ፤


ተሰጥዖዎ፤ ጥልቅ ፍላጎትዎ ወዘተ. እግዚአብሔር በማንነትዎና በሚመስሉት ነገር በመበሳጨት ራስዎን
እስኪቀይሩ ያህል ለራስዎ ጥላቻ እንዲኖረዎ አልፈጠረዎትም፡፡ እግዚአብሔር ሲፈጥርዎ ውበት ሰጥቶዎታል፡፡
ራስዎን እንዲመስሉ ይፈልጋል፡፡ የመዋቢያ ምርቶችን፤ የፀጉር አቆራረጥ ዘይቤዎችን፤ አዳዲስ ዘዬ ያላቸውን
አለባበሶች ማንነትዎን እና እግዚአብሔር ነዎት ያሉትን መልክ ጠብቀው እስከሆነ ድረስ ቢጠቀሙባቸው
ችግር የለውም፡፡ ለመዘነጥ፤ የተሻለ ራስዎን ጠብቀው ለመታየት ፈልገው ወዘተ. ከሆነም ይኼ ይፈቀዳል፡፡
ሆኖም ሌላ ሰው መምሰል ፈልገው ከሆነ ግን ያኔ ነው ነገሩ የተበላሸው፡፡ እግዚአብሔር ሌላ ሰው እንዲመስሉ
አይፈልግም፡፡ እርስዎ ልዩ እንዲሆኑ ነው የፈለገው፡፡ እርስዎ ራስዎን እንዲመስሉና እንደ ራስዎ ሆነው
እንዲንቀሳቀሱ ፍላጎቱ ነው፡፡

87 | P a g e
እርስዎ ራስዎን እንዲመስሉና እንደ ራስዎ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ፍላጎቱ ነው፡፡

እግዚአብሔር በአምሳያው ፈጠረን ሲባል ከአድራጎታችን እንጂ አስተሳሰባችን ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡


እግዚአብሔር በባሕሪ እሱን እንድንመስል ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር እኛን ፋሽን ያደረገን ተፈጥሯዊ ባሕሪው
በእኛ ልዩ ተፈጥሮ ይታይ ዘንድ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ተፈጥሯዊ ባሕሪ መሠረት ቀደም ሲል በተመለከትነው እና ‹ፍቅር› ላይ በሚያተኩረው


የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ላይ ተገልጧል፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ምዕራፍ የገለጣቸው ድንቅ ነገሮች አሉት፤
ነውም፤

[እግዚአብሔር] ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ [እግዚአብሔር] አይቀናም፤ [እግዚአብሔር] አይመካም፥


አይታበይም፤የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ
ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።
[እግዚአብሔር] ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን
ይሻራል።

(1 ኛ ቆሮንጦስ 13፤4-8)

እንግዲህ እርስዎም የተፈጠሩት በዚህ መልኩ ይኖሩ ዘንድ ነው፡፡ እግዚአብሔር ልክ እንደ እሱ ይንቀሳቀሱ
ዘንድ ነው የፈለገው፡፡ የእግዚአብሔርን ተፈጥሯዊ ባሕሪ ስንይዝ የፍቅር ሰው በመምሰል እና በመሆን መካከል
ያለውን ልዩነት እናገኘዋለን፡፡ አንደኛው ከውጭ የሚታይ ሲሆን ሌላኛው ግን ውስጣዊና ተፈጥሯዊ ነው፡፡
አንድ ሰው ጥሩ መስሎ እየታየ በውስጡ መሰሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ዓይኖች ተወርውረው እንዲሰኩበት
የሚያደርግ አለባበስ ያላት ዘናጭ ምላሷ ግን ሰውን የሚያርቅ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ፆም፤ፀሎቱ ላይ
ማስቀደሱ፤ መሳለሙ ወንጌልን መስበኩም ላይ በጣም ያለበት ሰው በሥራው ደግሞ ሰይጣናዊ ሊሆን
ይችላል፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር ተፈጥሯዊ ባሕሪውን እንድንመስል የሚፈልገው፡፡

እግዚአብሔር አዳም አታድርግ የተባለውን ካደረገ በኋላ በቅድሚያ ያቀረበለት ጥያቄ ወዴት ነህ (ኦሪት
ዘፍጥረት 3፤9) የሚል ነበረ፡፡ እግዚአብሔር በወቅቱ ቀኑ ሲመሽ ወደ ገነት የመጣው ከፈጠራቸው ወንድና ሴት
ጋር የመባረክን ጊዜ ለማሳለፍ ነበረ፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር የስብከት ወይንም የመባረክ ጊዜ የሚያሳልፍ ማንኛውም ፍጡር መንፈስ ሊሆን ይገባል፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔር በዚህች ፕላኔት ላይ መንፈሱን አጋርቶ በራሱ አምሳያ የፈጠረው ብቸኛ ቢኖ ሰው
ነው፡፡ ሆኖም የሰው ልጅ ግን ባልተገባ መንገድ ይኼንን የእግዚአብሔርን ጓደኝነት ሐጢአት ሰርቶ አጥቶታል፡፡

88 | P a g e
በመሆኑም አሁን ላይ ማንኛውም ሰው ቢሆን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት መዳንን እስካላገኘ ድረስ
የእግዚአብሔርን ወዳጅነት ሊያገኘው አይችልም፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ሐጢያተኞች የእግዚአብሔርን
ዓላማ እና ዕቅድ መረዳት አለመቻላቸው ነው፡፡

በ ኦሪት ዘፍጥረት ላይ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ስለመፍጠሩ ሲወሳ ከዓላማዎቹ አንዱ ተደርጎ የተቀመጠው
ምድርን መሙላትና መግዛት እንደነበረ ይታወሳል፡፡

እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና
ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፤26)

እግዚአብሔር ምድርን እንድንገዛና እንድንቆጣጠር ዘንድ ነው የፈጠረን፡፡ ሆኖም ከምንጫችን ጋር ያለን


ግንኙነት ሲቋረጥ ግራ በመጋባት የተገላቢጦሽ ምድር እንድትገዛን ፈቀድንላት፡፡ ዛሬ የሚገጥመን ችግር ሁሉ
ምድርን ለመቆጣጠር ካለመቻላችን ጋር የተያያዘ መሆኑ ነጋሪ አያሻውም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብን
በሚነግሩን ቅጠላ-ቅጠሎችና አደንዛዥ እፆች ተይዘን፤ ‹‹አሁን የማጤስና የማቡነን ጊዜ ነው፤ የማመንዠክም
እንዲሁ፡፡ ያለ እኔ አትኖሩም!›› የሚለውን ድምፃቸውን ስንሰማ እጆቻችንን ዘርግተን በቁጥጥራቸው ሥር
መሆናቸውን እናሳያቸዋለን፡፡

ሆኖም በምድርና ምድራዊ ነገሮች ቁጥጥር ስር ከመዋላችንም በላይ የሚያሳዝነው መታለላችን ነው፡፡
በሚገርም ሁኔታ ነው እኛ የሰው ልጆች ራሳችንን ምናሞኘው፡፡ ብዙ ሰዎች መጠጥ ሲጀምሩ በተለምዶው
‹ማኅበራዊ› ለመባል የበቁ ጠጪዎች እንደሚሉት፤ ‹‹በቃኝ፤ የግድ ገንዘብ ማጥፋት የለብኝ፤ ጤናዬንም
እፈልገዋለሁና ሁለተኛ አላስቀዳም በቃኝ›› ይላሉ፡፡ ሃቁ ግን ኋላ ወደ ሌላ የሚዞሩ መሆኑ ነው፡፡

በቁጥጥራችን ስር ልናውላቸው የሚገቡ ነገሮች እኛኑ በቁጥጥራቸው ሥር ሲያውሉን ሁሉም ነገር ይበላሻል፡፡
የምንኖርባት ዓለም ከዛፍ በሚሰራው ወረቀት አማካይነት በሚሰራጭ ነገር ትተራመሳለች፡፡ ገንዘብ
የሕይወታችን አዛዥ ከሆነ ቆይቷል፡፡ ያንን ወረቀት ለማግኘት ስንል እንዋሻለን፤ እንሰርቃለን፤
እናጭበረብራለን፤ እንገድላለንም ጭምር፡፡

ዓለማችን ሰዎች በምድርና ምድራዊ በሆኑ ነገሮች ሲገዙ እንደምትታመሰው ያህል ሰዎች በሰዎች ሲገዙም
እንዲሁ ውጥንቅጧ ይወጣል፡፡ ባሎች ሚስቶቻቸውን ፍፁም አግባብነት የሌለው አያያዝ ይይዛሉ፡፡ ሴቶች
ደገሞ በተራቸው ልጆቻቸውን ያሰቃያሉ፡፡ ራሳቸውን ‹የበላይ› ያሉ ዘሮች የሌሎች ዝርያ ተወላጆችን
ያገላሉ፤ አድልዖ ይፈጽሙባቸዋል፡፡ እነዚህ እና ሌሎች በርካታ ችግሮች እግዚአብሔር በምድር ላይ እንጂ
በሌሎች ሰዎች ላይ ሥልጣን እንዳልሰጠን ካለመረዳት ይመነጫሉ፡፡

89 | P a g e
የአንድን ሰው ወይንም ነገር ዓላማን አስመልክቶ ተገቢው ማስተዋልና ዕውቀት ሳይኖረን ሲቀር ወደ
ግራመጋባት እና ስቃይ እናመራለን፡፡ ከእነዚህ አስከፊ ውጤቶች መካከል በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀሰው ግብረ-
ሰዶምነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሴት ልጅ የወንድ አጋር ትሆን ዘንድ አዟል፤ ፈጥሯታል፡፡ ወንድንም
እንደዚያው፡፡ በመሆኑም ሴት ለወንድ ወንድ ደግሞ ለሴት ነው ተብሎ ታዟል፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው ማንኛውም
ነገር ግን ጤናማ አይደለም፤ ውጉዝም ጭምር ነው፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮማ ለምትገኘው ቤተክርስትያን በፃፈው መልዕክት ይኼንን እጅግ አሳፋሪና አስከፊ
ነገር ጠቅሶታል፤

እውነትን በዓመጻ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በአመፃቸው ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ


ይገለጣልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት
የሚያመካኙት አጡ፡ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር
ስለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕሪያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገቡ
ለወጡ፡፡ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕሪያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው
በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስህተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው
ተቀበሉ።

(ሮሜ 1፤18፤21፤ 26-27)

እግዚአብሔር ለተለመደው፤ ከታዘዘው ውጭ የሆነን አጠቃቀም አይወድም፡፡ ሰዶምና ገሞራን እኮ ለዚህ ነው


(ኦሪት ዘፍጥረት 18-19 ን ይመልከቱ)፡፡ ሰይጣን ግን ሐጢአትዎን፤ ‹‹ይኼ ምን ችግር አለው ተፈጥሯዊ ነው
እኮ!›› ብለው ጭራሽ ሽንጥዎን ገትረው እንዲከራከሩለት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ሐጢአትን በምንም ዓይነት
ምክንያታዊነትም ሆነ መንፈሳዊ አገለለጽ ልንታደገው አንችልም ፡፡ በስህተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው
ተቀበሉ (ሮሜ 1፤27 ለ) እውነተን ለራሳችን እኩይ ስነ-ምግባር ማሞካሻ ስንል ልንቀይረው ብንሞክር እውነትነቱ
ግን አይቀየርም፡፡

የተሰጠንን እምቅ-አቅም በጥሩ ሁኔታ ማውጣት እንችል ዘንድ እግዚአብሔር ለማን ማንን እንደፈጠረ፤ ለምን
ሲልም እያንዳንዱን እንደፈጠረ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ምድርን እንዲቆጣጠሯት ዘንድ
ፈጥሮዎታል፡፡ በሕይወትዎ በሰዎች ላይ ተቆጣጣሪ እና የላይ የሆኑበት ገጽታ ካለ ይመልከቱ፡፤ ከዚያ ንሥሀ
በመግባት ይኼንን ዐይነት የተዛነፈ ግንኙነት ይቀይሩ፡፡

እግዚአብሔር ማንኛውም ዛፍ ፍሬ ያፈራ ዘንድ ስለፈጠረው ያለ ፍሬ የሚኖር ዛፍ ፈጽሞ በምድር ላይ


እንዲኖር አይፈልግም፡፡ እግዚአብሔር ምርታማ ያልሆኑትን ገለል በማድረግ ከታታሪዎች ጋር ጉዞውን ወደፊት
የመቀጠል አሠራር አለው፡፡ ምርታማ የሚባለው ለቀረበለት ግዴታ አጸፋን በአግባቡ የሚመልስ ነው፡፡

90 | P a g e
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በ ዮሐንስ ወንጌል ላይ ፍሬ እናፈራ ዘንድ እኛ የሰው ልጆች መፈጠራችንን አስተምሯል፤

ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል፡፡ እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ


አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፤ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬያችሁም ሲኖር
ሾምኋችሁ፡፡

(የዮሐንስ ወንጌል 15፤8፤16 ሀ)

የእኛ የሰው ልጆች ፍሬያማነት ከምንመገበው ምግብ ጋር ይያያዛል፡፡ ሆኖም መንፈሳዊ ምንጫችን በጣም
የጠራ ካልሆነ ይኼ ጉድለት በምርታማነታችን ላይ ይንፀባረቃል፡፡ የትም ብንሄድ፤ ምንም ብንሰራ
እግዚአብሔር አብሮን ከሌለ ግን ከጌጥነት የማያልፍ ዛፍ ነው የምንሆነው--ፍሬ-ቢስ፡፡ እናም እኛ የሰው ልጆች
በእርግጥም የምንበላውን ነን፡፡

እግዚአብሔር በውስጣችን አስቀምጦት የነበረውን እምቅ-አቅም እንድናወጣው ይፈልጋል፡፡ የሱን ሥራ


በምድር ላይ ለብዙዎች ጥቅም ስንል እንድናጋራውም ጭምር ይሻል፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ከሰው ልጆች
የሚጠብቀው ፍሬያማነት በሕይወታችን ያለው መንፈስ ቅዱስ ነጸብራቅ ነውና የእግዚአብሔርን ጥያቄ
የመመለስ ችሎታችን ከሱ ጋር ካለን ግንኙነት ጋር በእጅጉ ይያያዛል፡፡

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፤ ደስታ፤ ሰላም፤ ትዕግስት፤ ቸርነት፤ በጎነት፤ እምነት፤ የውሃት ራስን መግዛት ነው፡፡ እንደዚህ
ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም፡፡ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ፡፡ በመንፈስ
ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ፡፡

(ወደ ገላቲያ ሰዎች 5፤22-25)

እግዚአብሔር የተትረፈረፈና በቂ ፍሬን እናፈራ ዘንድ ፈጥሮናል፡፡ ይኼ የዓላማችን አካል ነው፡፡ ታዲያ ይኼን
ዓላማ እውን ለማድረግ ከተዘጋጁልን ነገሮች አንዱና ዋንኛው የመንፈስ ቅዱስ መኖር እንደሆነ ልናጤነው
ይገባል፡፡

በመጨረሻ እግዚአብሐር እንድንበዛ እና ዘራችንን በመተካት እንድንባዛ ነው የፈጠረን (በ ኦሪት ዘፍጥረት 1፡28
ላይ እንደተቀመጠው) ታዲያ በሚያሳዝን መልኩ ይኼ ልጅ የመውለድ ችሎታ እንደ መልካም ነገር መታየት
ሲገባው እንደ እርግማን የሚቆጠርበት ጊዜም አለ፡፡ ለዚህ ዓይነቱ አሳዛኝ ስሜትና ምልከታ ደግሞ ሐጢአት
ነው መሠረቱ፡፡

እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ የመባዛት እና ምድርን የመሙላት ኃላፊነት በሰጣቸው ጊዜ አምጦ
መውለድ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ ይልቅ ሁለቱ በሐጢአት መዘፈቃቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነበረ እግዚአብሔር
ሔዋንን፤

91 | P a g e
በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እሱም ገዢሽ
ይሆናል፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 3፤16)

ሆኖም በአካል ብዙ ለመውለድ ካለን ችሎታ ይልቅ በሌሎች ውስጥ እሴቶቻችንን እና አመለካከቶቻችንን
ለማስረጽ ያለን ክህሎት ይበልጣል፡፡ የእኛ ሕይወትና አኗኗር በልጆቻችን፤ በባለቤታችን፤ በቅርብ አለቆቻችን፤
በሠራተኞቻችን፤ በወዳጆቻችን ላይ ጥሩም ሆነ መጥፎ አመለካከትን ያሳድራል፡፡

 እርስዎን ማን (ምን) ይቆጣጠርዎታል 

የእርስዎ እምቅ-አቅምዎን ማውጣት እግዚአብሔር በሕይወትዎ ያለውን ዓላማ እና እቅድ ከማወቅ፤


ከመረዳትና ለዚያ ራስዎን ከማስገዛት ጋር በቀጥታ ይገናኛል፡፡ ያንን ተግባር የመፈጸም ጥበብና ኃይል
በውስጣቸው የእግዚአብሔርን መንፈስ ለያዙ ሁሉ ተሰጥቷል፡፡በፋው አልክ እንዳለን ሀናድርገን እናስባለን፡፡
በነጻ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት የሚችሉበት እና ልብዎ እና ራዕይዎ አንድ የሚሆንበት መንገድም ጭምር
ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ውጭ የሚገፉት ሕይወት በሌሎች ነገሮች፤ ሰዎች እና መንፈሶች ቁጥጥር ውጭ የሚሆኑበት


ነው፡፡ የተፈጠሩበትን ዓላማ ደግሞ ይጋርዳል፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ ኑሮና ሁናቴ ውስጥ ደግሞ ዓላማዎም ሆነ
እምቅ-አቅምዎ ይባክናል፡፡ ብዙ ሊያበረክቱና ሊያወጡ ሲችሉ ያ በውስጥዎ እንደታመቀ ይሞታል፡፡

እስኪ ጊዜ ወስደው ሕይወትዎን ይፈትሹ፡፡ እርስዎን ማን እና ምንድነው የሚቆጣጠረዎት እግዚአብሔር


ለሕይወትዎ ያስቀመጠልዎን ዓላማ በመረዳት እምቅ-አቅምዎን እያወጡ ነው

ዓላማዎን እግዚአብሔር አስቀድሞ በውስጥዎ በማስቀመጡ ሊያሳኩት ይችላሉ፡፡ ይልቅ አሁን እግዚአብሔር
ያስቀመጠልዎን ዓላማ ፈልገው ለማግኘት ቁርጠኛ ይሁኑ፡፡

92 | P a g e
 መርሆች 

1. ዓላማ ማለት ፈጣሪ አንድን ነገር ለመስራት የተነሳበት ምክንያት ነው

2. እግዚአብሔር የእርስዎን የሕይወት ዓላማ ያውቃል

3. ያለ እግዚአብሔር የሕይወት ዓላማዎንማወቅ አይችሉም

4. ልቦና ማጣት ለብክነት ይዳርጋል

5. የሚያደርጉትን ለምን እንደሚያደርጉ ሊረዱ ይገባል

6. ራስዎን ለመንፈስ ቅዱስ ማቅረብ አለብዎ፤ አለዚያ ግን ሌላ ነገር ወይንም ሰው ይቆጣጠርዎታል

93 | P a g e
ምዕራፍ 9

_____________________ _____________________

ሪሶርሶችዎን ይወቁ

በዓለም ቁጥጥር ሥር ሆነው መቼም ቢሆን ዓለምን ሊቀይሯት አይችሉም፡፡ ማናቸውም ሪሶርሶች
ወደ መሠረታቸውና ምንጫቸው እግዚአብሔር ማምራት አለባቸው፡፡

94 | P a g e
በጣም ብዙዎቻችን በሕይወታችን ቢያንስ የተወሰኑ ጊዜያት ካለን የበለጠ ሪሶርስ በኖረን ብለን ተመኝተን
እናውቃለን፡፡ የሌላን ሀብት በማየት ቀንተን በ ‹ድህነት› አዝነንም ይሆናል፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር ድህነትና
ሀብትን የሚመለከትበት መንገድ ከእኛ ከሰው ልጆች ምልከታ ፍጹም ተቃራኒ በመሆኑ ይኼ አመለካከታችን
እምቅ-አቅማችንን እንዳናወጣ እንቅፋት ይሆንብናል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ምን ያህል አለን ከሚለው ይልቅ
ባለን ምን ሰርተናል የሚለው ይልቃል፡፡

 ድህነት እና ሀብት--መጽሐፍ-ቅዱሳዊ ምልከታ 

ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ሀብታሞችን እየደገፈ ነገሮችን ከድሆች የሚያሸሽ ይመስላቸዋል፡፡ ‹ላለው


ይጨመርለታል› የሚባለው ብሂልም ይኼንኑ ያንፀባርቃል፡፡ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ግን ይኼንን አይደለም
የሚያስተምረን፡፡ እግዚአብሔር ሀብታም፤ ደሀ ሳይል ሁሉንም ሰዎች ይወዳል፡፡

ድሀና ግፈኛ ተገናኙ፤ እግዚአብሔር የሁለቱንም ዓይን ያበራል።

(መጽሐፈ ምሳሌ 29፤13)

ለጠና ድሀ ተገናኙ፤ እግዚአብሔር የሁላቸው ፈጣሪ ነው።

(መጽሐፈ ምሳሌ 22፤2)

ከዚህ የምንረዳው እግዚአብሔር ሰዎችን ደሀ፤ ሀብታም ብሎ ስላለመፍጠሩ ነው፡፡ ይልቅ እግዚአብሔር
ሰዎችን ይፈጥራል፤ ከእነዚህ አንዳንዶቹ ሀብታም፤ ሌሎቹ ደሀ ናቸው፡፡ ቁልፉ እግዚአብሔር በሰጠን ሪሶርስ
ምን እንሰራለን የሚለው ነው፡፡

የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች።

(መጽሐፈ ምሳሌ 4፤10)

ምድሩን የሚሠራ ሰው እንጀራ ይጠግባል፤ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን አእምሮ የጐደለው ነው።

(መጽሐፈ ምሳሌ 12፤11)

ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፤ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።

(መጽሐፈ ምሳሌ 20፤13)

95 | P a g e
ድህነት የእግዚአብሔር ስጦታ ሳይሆን በራሳችን ድርጊት የምናመጣው እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ እርስዎ
የሚገኙበት የድኅነት ወይ የማጣት ደረጃ በአመዛኙ ያለዎትን ሪሶርስ እየተጠቀሙ ከሚገኙበት መንገድ ጋር
ይያያዛል፡፡ ጠንክሮና ለፍቶ፤ ያለውን በአግባቡ አብቃቅቶ የሚሰራው ሀብታም፤ ይኼንን ከማድረግ ይልቅ
የዘፈቀደ አጠቃቀምና ስንፍና ያለበት ደግሞ ለድኅነት ይዳረጋል፡፡ የእርስዎ ስኬት ባለዎት ሳይሆን ባለዎት ነገር
በሚያደርጉት ላይ ይንጠላጠላል፡፡

የእርስዎ ስኬት ባለዎት ሳይሆን ባለዎት ነገር በሚያደርጉት ላይ ይንጠላጠላል፡፡

የእርስዎ ቤተሰብ በኢኮኖሚ ደረጃው ምን ላይ ይገኛል የሚለው አያሳስብም፡፡ ይልቅ ቤተሰብዎ ባለበት
አይረግጥም ብለው ግን መወሰን ይችላሉ፡፡ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከርና ጠንክረው ለመስራትም መወሰን
አማራጭዎ ነው፡፡ እግዚአብሔር ታታሪና የሚጣጣሩ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ ካሉበት ተጨባጭ ሁኔታ አሻግረው
የሚመለከቱ ሰዎችን ይሻል፡፡

በመሆኑም የእርስዎ እምቅ-አቅም መውጣት የሪሶርሶችዎን ዓላማ እና ባሕሪያት፤ ሚመሩበትን ሕግጋቶች


ለማወቅ ባለዎ ክህሎት ላይ ይንጠላጠላል፡፡ ሪሶርሶቻችን ምን እንደሆኑ እና እንዴት አድርገው እንዲሰሩ
ዲዛይን እንደተደረጉ ካወቅን ፍጹም ገደብ-የለሽ እምቅ-አቅም ይኖረናል፡፡ ሆኖም ከታቀደውና ትክክለኛ
ከሆነው ውጭ ብንጠቀምባቸው እምቅ-አቅማችንን እናመክነዋለን፡፡

ኮኬይንን በምሳሌነት ብንወስድ በሆስፒታል ህሙማንን ለመፈወስ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሆኖም አለአግባብ
ብንጠቀምበት የማሰብ ክህሎታችንን ይጎዳዋል፤ በተጨማሪም ለእኛ አስፈላጊና ጠቃሚ የሆኑ በርካታ
ነገሮችንም እናጣለን፡፡ አስፕሪን እና ታይሊኖል ሕመምን የማስታገስ ጠቅም አላቸው፡፡ በብልቃጦቹ ላይ
የተቀመጡትን መመሪያዎች ብንከተል ጥሩ ውጤት እናገኛለን፡፡ የተሰጡትን ትዕዛዛት፤ መመሪያዎች እና
ማስጠንቀቂያዎች ችላ ካልን ግን መጨረሻችን መታመም ይሆናል፡፡

ሪሶርሶችዎን ይጠቀሙ

ለምሳሌ ቤተክርስትያን ዛሬ ዛሬ ካሉባት ችግሮች አንዱና ዋንኛው የሪሶርስ ማጣት ሳይሆን ሪሶርስን በአግባቡ
ያለመጠቀም ነው፡፡ እግዚአብሔር ለአዳም የሰጠው ሪሶርስ ሁሉ ዛሬም አለልን፡፡ ሆኖም እነሱን ሪሶርሶች ሁሉ
እየተጠቀምንባቸው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በሰጠን ነገሮች ውስጥ ምን ምን መልካም አጋጣሚዎችና
ዕድሎች እንዳሉ ከመመልከት ይልቅ ሪሶርሶቻችንን በመፈረጅ አንዳንዶቹን ዓለም እየተጠቀመችባቸው
ባለችበት መንገድ ስለምንሰጋ ለመጠቀም ፈቃደኛ እስካለመሆን እንደርሳለን፡፡

ዓለም እየሰራች ወይንም እየገነባች ያለችው አይደለም ችግሩ፡፡ ዓለማዊ የሆኑ ሰዎች ዛሬ የዓለምን ችግር
ለመፍታት በጥቅም ላይ ካዋሏቸው በላይ ሪሶርሶች የሏቸውም፡፡ ይኼ እውነታ ግን ለቤተክርስትያን

96 | P a g e
አይሰራም፡፡ ያሉንን ሪሶርሶች በተመለከተ የተሳሳተ አረዳድ ያለን በመሆኑ ቤተክርስትያን የዓለምን ችግሮች
እየፈታች አይደለችም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች መፍጠሩን ይነግረናል፡፡


ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም፡፡

(የዮሐንስ ወንጌል 1፤3)

እንግዲህ ከዚህ ለመረዳት እንደምንችለው ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በተጨማሪም፤

እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤እነሆም እጅግ መልካም ነበረ፡፡ ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኛ ቀን፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፤31)

ይኼ ማለት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ሪሶርስ ሁሉ ጥሩ እንደሆነ ይነግረናል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር ፈጣሪ፤ ሰይጣን ደግሞ የተሰራውን ለማፍረስ የሚሯሯጥ ክፉ ኃይል
መሆኑ ይነገረናል፡፡ ሰይጣን ምንም መፍጠር አይችልም፡፡ ይልቅ እግዚአብሔር የፈጠረውን ያደናቅፋል፤
ያበላሻል፡፡ የእኛ የሰው ልጆች ችግርም እዚህጋ ነው ያለው፡፡ ማጭበርበር በዓለማችን ተንሰራፍቷል፡፡ ይኼ
ሰይጣን የእግዚአብሔርን ሪሶርሶች እንድናበላሽ እና አለአግባብ እንድንጠቀምበት ተግቶ ከማስተማሩ የመነጨ
መሆኑን መረዳት ይሻል፡፡

እግዚአብሔር ሪሶርሶችን የሚሰጠዎ ወደዚህች ምድር የመጡበትን ዓላማ ማሳካት ይችሉ ዘንድ በማሰብ
ነው፡፡ በሪሶርሶቹ እንዲኖሩ እንጂ ለሪሶርሶቹ ብለው እንዲኖሩ ሲል አልሰጠዎትም፡፡ አንድ ሰው ለገንዘብ ሲል
መኖር ሲጀምር ችግር ላይ ይወድቃል፡፡ ሥራዎ የሕይወትዎ ትልቁ ነገር ሲሆን ወደ ችግር እየተንደረደሩ መሆኑ
አያጠያይቅም፡፡ አንድ ሪሶርስ ከተፈጠረለት ዓላማ በላይ ሲሆን ሪሶርሱን በአግባቡ በመጠቀም እና በማባከን
መካከል ያለውን ድንበር ጥሰነዋል ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ሪሶርሶችን የሚሰጠዎ ወደዚህች ምድር የመጡበትን ዓላማ ማሳካት ይችሉ ዘንድ
በማሰብ ነው፡፡

 ተደራሽ የሆኑ ሪሶርሶችዎ 

ስኬታማ መሆን ከፈለጉ ሊቆጣጠሯቸውና ሊረዷቸው የሚገቡ አምሥት ዓይነት ሪሶርሶች አሉ፡፡

97 | P a g e
መንፈሳዊ ሪሶርሶች

እግዚአብሔር በቅድሚያ መንፈሳዊ ሪሶርሶችን ነው የሰጠን፡፡ እግዚአብሔር በአምሳያው ስለፈጠረን እሱ


ባለው እንድንጠቀም አድርጎ ነው የሰራን፤

ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእጀራ ብቻ አይኖርም

(የማቴዎስ ወንጌል 4፤4)

ይህ መንፈሳዊ ምግብ በተለያየ መልኩ ይገኛል፡፡ በቅድሚያና ከሁሉም በበለጠ ግን ራስዎን በእግዚአብሔር ቃል
መመገብ ይኖርብዎታል፤

የእግዚአብሔር ቃል በሚሰበክባቸው መልካም ቦታዎች ይገኙ፡፡ መሄድ ብቻም ሳይሆን ደግሞ ቃሉ ሲሰበክ
በሚገባ ውስጥዎ እንዲሰርጽ ይቆዩ፡፡ በእርግጥ እንደ መንፈስ ቅዱስ ለመራመድ የሚደረገው ጥረት ከባድ ነው፡፡
በዚህ የትምህርት ሂደት መውደቅ ሊኖር ይችላል፡፡ ግን ያ መጥፎ አይደለም፡፡ አንድ ሰው መንፈሳዊ ምግብ
መመገብ እስከቀጠለ ድረስ እያደገና እየተለወጠ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ዕድገቱን ባናየውም አለ፡፡

የመንፈስ ስጦታዎችም እንዲሁ ልንመገባቸው የሚገቡ ሪሶርሶች ናቸው፡፡

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።

(1 ኛ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች 12፤7)

ከእነዚህ ሪሶርሶች መካከል የጥበብ ቃል፤ የዕውቀት ቃል፤ እምነት፤ ታምራት፤ ፈውስ፤ ልሳን፤ የልሳናት ትርጓሜ
እና ትንቢት ይጠቀሳሉ፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ድንቅ ስጦታዎች የሰጠው ቤተክርስትያንን ሊያንጽ እንደሆነ
ግልጽ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝዎ አድርገው ከተቀበሉ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በእጅዎ ናቸው፤

ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።


እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ
ተጫምተው ቁሙ፤በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን
የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። በጸሎትና
በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፤13-18)

98 | P a g e
እውነት፤ ጻድቅነት፤ ሰላም፤ እምነት፤ መዳን፤ ፀሎት፡፡ ከዚህ የበለጠ ምን ሀብት አለ! በእርግጥ እስኪ በእነዚህ
ላይ ደግሞ እንደ ፆም፤ መስጠት እና ምህረት ማድረግን እንጨምርባቸው፡፡ የእርስዎ እና የእግዚአብሔር
መንፈሶች ከገጠሙ እነዚህ ሁሉ የእርስዎ ናቸው፡፡ በመጥፎና በጥሩ ቀን፤ በዘቀጠና በስኬታማ ሕይወት መካከል
ያለውን ልዩነት ይፈጥራሉ፡፡ የሚገኙበት ሁኔታ የሚፈልጉትን ያህል ፈጥኖ ላይቀየር ይችላል ግን ምልከታዎ
እንደሚቀየር አረጋግጥልዎታለሁ፡፡

ሥጋዊ ሪሶርሶች

እግዚአብሔር ሲፈጥርዎ መንፈስዎን ፈጠረና በሥጋዎ ውስጥ አኖረው፡፡ እግዚአብሔር የሕይወትን ስጦታ
ለእርስዎ ስለሰጠዎ የእርስዎ ድንቅ፤ አካላዊ ማሽን መተንፈስ፤ መንቀሳቀስ፤ መመገብ እና መፈወስ ይችላል፡፡
ዛሬ በሕይወትዎ የሚያጣጥሟቸው አብዛኞቹ ደስታዎች የእርስዎ የሆኑት እግዚአብሔር እርስዎን ከአፈር
በእስትንፋሱ ወደ ሥጋ ቀይሮ በመስራቱ ነው፡፡ የአበቦችን ውበት፤ የጀምበር መጥለቅን ወይንም ቀስተ-ደመናን
አይተው ማድነቅ ይችላሉ፡፡ የማርን ጣፋጭነት ብሎም የተቀጠፈ ፍሬን ማጣጣምም እንዲሁ፡፡ የልጆችዎን
ፍቅርም ማግኘት፤ ማጣጣም ለእርስዎ የተሰጠ ጸጋ ነው፡፡ ልጅዎ በትንንሽ እጆቹ አቅፎ፤ ‹ማሚ እወድሻለሁ›
ሲልዎ ልብዎ እንዲያ ቅልጥልጥ ማለቱ ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር የተገናኘ ነው፡፡

ሥጋችን ድንቅ የመሆኑን ያህል ግን እንደፈለጉ አይጠቀሙበትም፡፡ እናም ለሥጋዎ ስለሚመግቡት ነገር
በጥንቃቄ ያስቡበት፡፡ ሥጋዎ ለምግብ፤ ምግብም ለሥጋዎ መሆኑን ያስቡ፡፡ ልክ እንደ ሌሎቹ ማናቸውም
የእግዚአብሔር ሪሶርሶች ሁሉ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እና ምልከታ ለጉዳትና ለብክነት ይዳርጋል፡፡

ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። መብል


ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት
አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን?

(1 ኛ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች 6፤12-13-15 ሀ)

ቁሣዊ ሪሶርሶች

እግዚአብሔር የሰጠዎ ሶስተኛው ሪሶርስ ደግሞ ቁሣዊ (material) የሚባለው ነው፡፡ እግዚአብሔር በኤደን
ገነት ለአዳም የተናገረው አዳም የሚያስፈልገይን ነገር እንዳዘጋጀለት ያሳያል፤

ከዚህ በመቀጠል ያለው ጥቅስ አዳም ለእግዚአብሔር ወርቅ፤ ሉልና የከበረ ድንጋይን ለአዳም መስጠቱን
ያመለክታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምድርን ውሃ ለማጠጣት ወንዝ ከኤደን ገነት ይወጣ እንደነበረ ተገልጧል፡፡
ከዚህም የምድር እጅግ ጥልቅና ሰፊ የከርሰ-ምድር እና መልከዓ-ምድራዊ ሀብት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ
ሕይወት መቃናት ሲል ካዘጋጃቸው ነገሮች መካከል እንደሆነ መረዳት እንችላለን፡፡

99 | P a g e
የነፍስ ሪሶርሶች

እግዚአብሔር በአራተኛ ደረጃ የነፍስ ሀብቶችን ሰጥቶናል፡፡ በ ኦሪት ዘፍጥረት 2፡7 ላይ፤

እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም
ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

ተብሎ ተነግሮናል፡፡ እርስዎ መንፈስ ነዎት፤ ነፍስ አለዎት፡፡ ከአዕምሮዎ የሚያገኙት እገዛ ማለትም በጎ
ፈቃድዎ እና ስሜትዎ እግዚአብሔር የሰጠዎ ሪሶርሶች ናቸው፡፡

ያለ እነዚህ ሪሶርሶች ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል ያስቡት፡፡ እነዚህ ሪሶርሶች ማንነታችንን


የምንገልጽባቸው ዋንኛ ነገሮች ናቸው፡፡ መንፈስዎ በነፍስዎ ላይ የሚንጠላጠል ሲሆን ይኼም ከሥጋዎ ጋር
ያመሳስለዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የነፍስ አስፈላጊነት ተገልጧል፤

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?

(የማቴዎስ ወንጌል 16፤26)

ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤

(1 ኛ የጴጥሮስ መልዕክት 2፤11)

ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።

(3 ኛ የዮሐንስ መልዕክት 1፤3)

ጌታ ኢየሱስ ነፍስን የተከተለው መንፈስ ቀላል በመሆኑ ነበረ፡፡ ሰይጣን በበጎ ፈቃድዎ፤ በስሜትዎ እና
በአእምሮዎ አማካይነት ነው ሊያጠቃዎ የሚሻው፡፡ ነፍስዎን ከጠበቁ ሥጋዎ እና መንፈስዎ ደህና ይሆናሉ፡፡
የእነዚህ የሁለቱ ሁኔታ በነፍስዎ ላይ ይንጠላጠላል፡፡ ይኼ ደግሞ በግልጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሰፍሯል፤

በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤

(መጽሐፈ ምሳሌ 23፤7)

እምነት በመንፈስ ሲካሄድ ማሰብ ግን የነፍስ ሥራ ነው፡፡ በመሆኑም የምናምነው እና የምናስበው ፍጹም
ሊለያይ ይችላል፡፡ የምናስበው የምንሆነውን እንጂ የምናምነውን አይደለም፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ንሥሀን
ይዞ የመጣው ለዚህ ነበረ፡፡ የምናስበው ልክ የምናምነውን ያህል ተጽዕኖ እንደሚያደርግብን አውቋል፡፡

100 | P a g e
ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም
መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

(የማርቆስ ወንጌል 1፤15)

ሐዋርያው ጳውሎስ ተጨማሪ ማብራሪያ በዚህ ላይ ሰጥቷል፤

እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ
ሰጣቸው፤

(ወደ ሮሜ ሰዎች 1፤28)

ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

(ወደ ሮሜ ሰዎች 8፤6)

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ
በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

(ወደ ሮሜ ሰዎች 12፤2)

ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ። በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ
እዘምራለሁ።

(1 ኛ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች 14፤13-15 ሀ)

የነፍሳችን ሀብቶች እግዚአብሔር አዕምሯችንን እንዲቀየር እስካልፈቀድንለት ድረስ አናገኛቸውም፡፡

የጊዜ ሪሶርሶች

ጊዜ እግዚአብሔር የሰጠን አምሥተኛው ሪሶርስ ነው፡፡ ጊዜ በዘለዓለማዊነት ውስጥ ያለ ጊዜያዊ መቋረጥ


መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሊገዛም ሆነ ሊሸጥ የማይችል ሸቀጥ መሆኑም እንዲሁ፡፡ ጊዜን ልንጠቀምበት ብቻ ነው
የምንችለው፡፡

101 | P a g e
ሐጢአት ጊዜን ማቃጠያ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ጫት በመቃም፤ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ በመጨለጥ፤
ኮኬይን በመሳብ ወዘተ. የሚያሳልፉትን ጊዜ ያስቡት፡፡ ሊያስተምርዎ ወይንም ሕይወትዎን በሌላ መንገድ
ሊጠቅም የሚችል ነገር መስራት ሲችሉ እርስዎ ግን አዕምሮዎን እየገደሉት ነው፡፡

ያለዎት ጊዜ አሁን ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ራስዎን ባተሌ በማድረግ የቻሉትን ያህል በአግባቡ ያሳልፉት፡፡
‹‹እግዚአብሔር ሆይ! በቀን ውስጥ ያለቺኝን እያንዳንዷን ሰዓት በአግባቡ፤ በበቂ ሁኔታ እና ገንቢ በሆነ መንገድ
አሳልፈለሁ!›› ይበሉ፡፡ ጊዜ የእግዚአብሔር ስጦታ ሲሆን እጅግ ውድ ከተባሉት ሪሶርሶቹ መካከል ይጠቀሳል፡፡
ጊዜን አለአግባብ እያጠፉ ጊዜ አነሰን ከሚሉ ብኩኖች መካከል አንዱ አልሆንም ብለው ይቁረጡ፡፡ እያንዳንዱ
ሰዓት የተቆጠረና በአግባቡ የሚጠቀሙበት ይሁን፡፡

ያለዎት ጊዜ አሁን ብቻ ነው፡፡

 ባለዎት ምን እያደረጉ ነው 

እግዚአብሔር ከመንፈስ፤ ሥጋ፤ ቁሣዊ ነገሮች፤ ነፍስ እና ጊዜ ሌላም ብዙ የእርስዎን እምቅ-አቅም


የሚፈታተኑ ሪሶርሶችን ዝግጁ አድርጓል፡፡ እርስዎስ ታዲያ እነዚህን ሪሶርሶች እንዴትና በምን መልኩ
እየተጠቀሙ ነው አልያም እነዚህ ሪሶርሶች እንዳሉዎትስ ያውቃሉ

ምናልባትም በቤትዎ ለመግዛት ሲሉ ጠንክረው የሰሩባቸው ብዙ ዕቃዎች ሞልተው ይሆናል፡፡ እና ያንን


ቤትዎን ለቤተሰብዎና ለእርስዎ መጠለያ ብቻ አድርገው ያጥሩታል ወይንስ ለሌሎች እንግዶችም ጭምር
ክፍት ነው ለመሆኑ ከእርስዎ በጣም ቀድመው የኖሩ እና ብዙ ተሞክሮ ያላቸውን አንጋፋ የቤተዘመድ አባላት
ምክር ይቀበላሉ እግዚአብሔር በሁሉም ጥረትዎ አብሮነትን እያሳዩ ይረዱዎት ዘንድ በለጋስነት የሰጠዎትን
ባለቤትዎንስ ይሰማሉ በርካታ ሙያዊ ልምድ፤ ጥቅማ-ጥቅም እና ገንዘብ የሚያስገኝልዎን ስራዎንስ
ያመሰግናሉ አለኝ ሊሉት የሚችሉት ትልቁ ነገር ገንዘብና ሌሎች ነገሮችን ለማግኘት የሚሆኑ
መሣሪያዎችንና ዘዴዎችን የሰጠዎ እግዚአብሔር ባረኮት መሆኑንስ ይገነዘባሉ በእጅዎ ከሚገኙት ሪሶርሶች
የሌሎች ፍላጎቶችን ለማሟላት ሲሉ ያጋራሉ

በመሠረቱ እግዚአብሔር ሊፈጥሩልዎ የሚችሉትን መልካም አጋጣሚዎች ለመመልከት ዓይኖዎን ከከፈተልዎ


የሪሶርሶችዎ አምቅ-አቅም ወሰን-የለሽ ነው፡፡ በመሆኑም ተትረፍርፎ ከተሰጠዎ ለሌሎች ያጋሩ፡፡ አንድን ነገር
ሲገዙ ብልሀት የተሞላበት ምርጫ ያድርጉ፡፡ ሪሶርስዎችዎን ለራስዎ ምቾትና ጥቅም ሲሉ
እንደሚያከማቿቸው ንብረቶች ሳይሆን ለእግዚአብሔር ግልጋሎት እንደሚውሉ ስጦታዎች ይመልከቷቸው፡፡
አስተሳሰብዎን ከ ‹የበለጠ ያስፈልገኛል› ከሚለው ‹አሁን ያለኝን በአግባቡ ልጠቀም› ወደሚለው ይቀይሩ፡፡

102 | P a g e
እግዚአብሔር አለኝ የሚሉትን ነገር በተመለከተ ያለዎትን እይታ ማስፋት ይፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዙሪያዎ
የከበቡዎትን ባረኮቶች እንዲያዩ ይሻል፡፡ እግዚአብሔር በቤተክርስትያን እና በተለያዩ አገልግሎቶቿ ላይ
ያስቀመጠውን ሁሉ ይመልከቱ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የዕውቀት እና የመነሳሳት ቅርስ እስኪሆን ድረስ ቅዱስ ቃሉን
በማንበብ ይጽኑ፡፡ ሕገ-መንግሥትን በማንበብ በአገርዎ በተሰጠዎ ነጻነቶች ለመጠቀም ይወስኑ፡፡ ከልጆችዎ ጋር
ጊዜን በማሳለፍ የሕይወትን ድንቅ ነገሮች በተመለከተ በልምድ የቀሰሟቸውን ብሎም የወረሷቸውን እሴቶች
በውስጣቸው ለማስረጽ ይስሩ፡፡

 ለሪሶርሶችዎ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ 

በገንዘብ የቱንም ያህል ደሀም ሆኑ ሀብታም እግዚአብሔር ለሰጠዎ እጅግ ብዙ ሪሶርሶችዎ ግን ኃላፊነት
አለብዎ፡፡ ከእግዚአብሔር እጅ የተቀበሏቸውን ውድ ስጦታዎች ፈልጎ የማግኘት፤ የማሳደግ እና የመኮትኮት
ኃላፊነት ተጥሎብዎታል፡፡ ነገር ግን ያንን ለማድረግ ሀብታም መሆንዎን መረዳት ነው የመጀመሪያው
ሥራዎ---በዓለም ሳይሆን በእግዚአብሔር ደረጃ፡፡ እግዚአብሔር በጥንቃቄ ባሕሪዎንና አመለካከትዎን
የሚያጤን ሲሆን የሰጠዎትን ሪሶርሶች በአግባቡ ወይ ያለ አግባቡ መጠቀምዎን ይገመግማል፡፡

እግዚአብሔር የሰጠዎትን ሁሉ እስከመጨረሻው እና አሟጠው ለመጠቀም አሁኑኑ ይቁረጡ፡፡ የዚህ ዓለም


ደረጃዎች እና አመለካከቶች የተሰጠዎትን ሀብት በአግባቡና በብልሀት ከመጠቀም እንዳያግዱዎ ‹እምቢ‹
ይበሉ፡፡

ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወስድበታል፡፡

(የማቴዎስ ወንጌል 25፤29)

 መርሆች 

1. እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው የሚያስፈልገውን ይሰጣል፡፡ አንዳንዶች ሀብታም ሌሎች ግን ደሀ ይሆናሉ፡፡

2. ሀብት እና ድህነት ባለን እንዴት እንጠቀማለን ከሚለው ጋር ይያያዛሉ፡፡

3. እግዚአብሔር ሪሶርሶችን የሚሰጠን ልንኖርባቸው እንጂ ለእነሱ ብለን እንድንኖር አይደለም፡፡

4. ሪሶርሶችን በአግባቡ መጠቀም እምቅ-አቅምን ያወጣል፡፡

5. ሪሶርሶችን አለአግባብ መጠቀም (ወይ ማባከን) እምቅ-አቅምን ይገድላል፡፡

103 | P a g e
6. በአሁኑ ሰዓት እየተጠቀሙባቸው ያልሆኑ ብዙ ሩሶርሶች ስሉ፡፡

ምዕራፍ 10

_____________________ _____________________

ትክክለኛውን ከባቢ ሁኔታ ጠብቀው ያቆዩ

104 | P a g e
እርስዎ የሚበሉትንም፤ ውስጥ ውስጥዎ የሚበላዎትንም ነዎት፡፡

ስለ አንድ ቤቱ ውሰጥ ውሃ በተሞላበት የመስታወት ገንዳ ውስጥ የሚርመሰመስ ዓሣውን ሊጫወትበት


ስለፈለገ ልጅ የተወራን ታሪክ ነው የምነግርዎት፡፡ እናም ልጁ በውሃ ውስጥ ወዲህ ወዲያ ሲል የነበረውን ዓሣ
አፈፍ አድርጎ ከገንዳው አውጥቶ አጠገቡ ወለል ላይ አስቀመጠው፡፡ ከዚያ የልጅ ነገር ወዲያው ደግሞ
ትኩረቱን ወለሉ ላይ ወደነበሩት እና ወላጆቹ ገዝተውለት ወደነበሩት የመጫወቻ መኪኖች አደረገ፡፡ በእነዚህ
በጣም በሚወዳቸው መኪኖች ሲጫወት ለዓሣው የሚያደርገውን አንድም ሳይቀር እየነገረው ነበረና በዚህ
ጉዳይ እጅግ በጣም ከመዘፈቁ የተነሳ ዓሣውን ጨርሶ ከነመኖሩ ረሳው፡፡ ከበርካታ ደቂቃዎች በኋላ በድንገት
ዓሣው ትዝ አለውና ዞሮ ተመለከተው፡፡ ግን ቢያገላበብጠው፤ እንደፈለገ ቢነካካው ዓሣው ግን ንቅንቅ
አይልም፡፡ በዚህ በጣም የተደናገጠው ልጅ ዓሣውን እንደያዘ ወደ እናቱ ሮጦ ሄደ፡፡

እናትየው ዓሣውን ባየች ጊዜ ፈጥና ከልጇ መንጭቃ ገንዳው ውስጥ አስቀመጠችው፡፡ ልጁም እንባ
እየተናነቀው ያ የሚወደው ዓሣ ስለሞተ ውሃው ላይኛው ጫፍ ላይ ሲንሳፈፍ ተመለከተ፡፡ እናት፤ ‹‹ምን ሆኖ
ነው ግን›› ስትል ጠየቀች፡፡ ልጅም በየዋህነት፤ ‹‹በቃ፤ መሬት ላይ አብረን ስንጫወት ድንገት ዞር ስል
ሞቷል!›› ብሎ መለሰላት፡፡

እናትም በፍፁም የርህራሄ ስሜት፤ ‹‹የኔ ቆንጆ፤ ምነው ግን ዓሣ ከውሃ ከወጣ መኖር እንደማይችል
አታውቅም ነበረ እግዚአብሔር እኮ ዓሣ በውሃ ይኖር ዘንድ ነው የፈጠረው፤›› አለችው፡፡

ከዚህ ታሪክ የምንረዳው ዋንኛው ቁምነገር የእግዚአብሔር ፍጡራን ሁሉ ለመኖር ትክክለኛው ከባቢ ሁኔታ
እንደሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ ዓሣ ለመኖርና ለማደግ ውሃ የግድ እንደሚያስፈልገው ሁሉ እኛ የሰው ልጆች
ደግሞ እግዚአብሔር ይሁናቸው ብሎ የመረጠልን አካባቢ ላይ ካልሆነ መኖር አንችልም፡፡ ሆኖም እኛ የሰው
ልጆች ብዙውን ጊዜ አካባቢ በእኛ ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ በአግባቡ አንረዳም፡፡ ልክ ዓሣው ምድር ላይ ሆኖ
እንደተገላበጠው እኘም ያለ አካባቢያችን ሄደን፤ ‹‹ምንድነው የተፈጠረው ችግር›› ማለት ይቀናናል፡፡

 በትክክለኛው እና በተመረጠው ከባቢ ሁኔታ ላይ ስንሆን


የምናገኘው የእግዚአብሔር እንክብካቤ 

105 | P a g e
እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በፈጠረ ጊዜ ትክክለኛ እና በጣም ተመራጭ የሆነውን ከባቢ ሁኔታ የሚፈጥሩ
ነገሮችን በማስቀመጥ ረገድ ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ሰርቷል፡፡ ከእነዚህ የጥንቃቄ ሥራዎች ማሳያ መካከል
መሬት ከፀሐይ በሶስት ፕላኔቶች ያህል እንድትርቅ እርጎ መስራቱ ይጠቀሳል፡፡

መሬት ከፀሐይ ጋር ያላት ግንኙነት በእውነት ይደንቃል፡፡ ፀሐይ ከምድር ገጽ ውሃ መጣ የምትወስድ ሲሆን
ይኼ ውሃ ይቀዘቅዝና ወደ ደመናነት ይቀየራል፡፡ ደመናው እየከበደና እየጠቆረ ሲሄድ ወደ ምድር ውሃው
የሚፈስ ሲሆን ይኼም ዝናም ነው፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር መጀመሪያውኑ ተጠንቅቆ መሬት እና ፀሐይን
በጥሩ ርቀት ላይ እንዲፈጠሩ በማድረጉ መሬት ከጸሐይ ጨረር በአግባቡ ከለላ ታገኛለች፤ ከፀሐይ ተመልሶ
በዝናብ መልክ የሚመጣው ውሃ ደግሞ ለተክሎች፤ እንስሳትና ሰብል ምግብ ይሆናል፡፡

 ትክክለኛ ያልሆነውን ከባቢ ሁኔታ አስቀድሞ ማወቅና መጠንቀቅ 

አካባቢን መፃረር ሁልጊዜም ለሞት ይዳርጋል፡፡ በደረቅና ውሃ በአግባቡ በማያገኝ ቦታ ላይ የተተከሉ እጽዋትና
ተክሎች ደርቀውና ጠውልገው ይሞታሉ፡፡ በድርቅ በተመታ አካባቢ የሚኖሩ የዱር እንስሳትም በረሀብ
ያልቃሉ፡፡ በተበከለ ውሃ ውስጥ የሚኖሩ ዓሣዎችም ታመው ይሞታሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይኼንን በሚገባ
የሚያንፀባርቅ ታሪክ ነግሮናል፤

በአንድ ወቅት ጌታ ኢየሱስ ልጁ ሞታበት ወደነበረ አንድ ገዢ ቤት ተጠርቶ ይሄዳል፡፡ ልክ ሲገባም አስለቃሾች
ቦታ ቦታቸውን ይዘው ሥራቸውን ጀምረው ለቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ሁሉም ለቀስተኛ መዘጋጀቱን በሚያሳይ
መልኩ ለጆሮ የሚከብዱና ልብን የሚሰብሩ የሐዘን እንጉርጉሮዎች ቤቱን ባንድ እግሩ ሊያቆት ደርሰዋል፡፡ ጌታ
ኢየሱስም ለቀስተኛውን እና አስለቃሾቹን በሙሉ አንድም ሳይቀሩ ካስወጣ በኋላ ልጅቷ ወደተኛችበት አልጋ
ሄደ፡፡ ፀጥ ባለውና መርፌ ብትወድቅ በምትሰማበት ሁኔታ ግን እጇን ይዞ ሲያነሳት ልጅቷ ነቃች፡፡ መጯጯሁ
እና እና እምነት ማጣቱ ልጅቷ ሞትን ድል አድርጋ የምትነሳበትን ዕድል ዘጋ፡፡ ኢየሱስ ይኼንን ነበረ ያስቀረው፡፡

በ ማርቆስ ወንጌል ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይሉን እንዳይጠቀም እንቅፋት ስለሆነበት አንድ ከባቢ ሁኔታ
ተጽፎ እናገኛለን፤

ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኩራብ ያስተምር ጀመር፡፡ ብዙዎችም ሰምተው ተገረሙና እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት
አገኛቸው ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው 

ይህስ ፀራቢው የማርያም ልጅ የያዕቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን  እህቶቹስ በዚህ በእኛ

ዘንድ አይደሉምን አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር፡፡ በዚያም ጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፤ ተአምር
ሊያደርግ ምንም አልቻለም፡፡

(የማርቆስ ወንጌል 6፤2-3፤5)

106 | P a g e
በዮሐንስ ወንጌል ላይ ደግሞ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈውስን ስላገኘ አንድ ዓይነ-ሥውር ታሪክ ተጽፎ
እናገኛለን፡፡ ፈሪሳውያኑ የዚህን ሰው ዓይን መፈወስን የሚያህል ነገር የፈዋሹን ኃይል እና ሥልጣን ጥያቄ
ውስጥ በመክተት ሊያጣጥሉት ሲሞክሩ ዓይኑ የበራለት ሰው ግን ከሰዎቹ የእምነት ማጣት በመነጨ ለመጡት
የተሳሳቱ አስተሳሰቦች አልገዛም ሲል እምቢታውን ገለፀ፡፡

ኃጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዕውር እንደ ነበርኩ አሁንም እንዳይ ይህን አንድ ነገር አውቃለሁ፡፡ ዕውር ሆኖ
የተወለደውን ዓይኖች ማንም እንደከፈተ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አልተሰማም፡፡ ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን
ምንም ሊያደርግ ባልቻለም ነበረ፡፡

(የዮሐንስ ወንጌል 9፡ 25፤32-33)

 ለሁሉም ነገር ትክክለኛ እና ተገቢ የሆነ ከባቢ ሁኔታ አለ 

በመሠረቱ ማንኛውም ነገር ቢሆን በተወሰነ ጤናማ እና ተስማሚ በሚባል ከባቢ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖር ነው
የተፈጠረው፡፡ የዚያ አካባቢ ሁኔታ ፍጡሩ ዓላማውን የመፈጸም ክህሎቱ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ
ዝርዝሮች ናቸው፡፡ በመሆኑም የእርስዎ እምቅ-አቅም ከአካባቢዎ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው፡፡ እርስዎ ያሉበት
አካባቢ ብቁ ካልሆነ ለማከናወን የተፈጠሩትን ሁሉ ሳያሳኩ ይቀራሉ፡፡ የሚኖሩበት ከባቢ ሁኔታ ጤናማ እና
ተመራጭ ከሆነ ደግሞ እምቅ-አቅምዎን የማሳካት መልካም አጋጣሚዎች ያልተገደቡ ይሆናሉ፡፡

አንድ ከባቢ ሁኔታ በፍጡር እድገት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን የሚይዝ በመሆኑ በእርስዎ
ዙሪያ ያለው ወይንም ዕድገትዎ ላይ አስተዋፆ የሚያደርገው ሁሉ ዓላማዎን ለመፈፀም የሚያግዝ ወይ
የሚያደናቅፍ ስለመሆኑ መፈተሽ ይኖርበታል፡፡ በእርስዎ ሕይወት የሚፈጠረው ነገር ሁሉ አብረዎት በሚኖሩ፤
ምሥጢር በሚጋሩዎት፤ ጊዜዎትን በሚያሳልፉባቸው ቦታዎች እና ለአዕምሮዎ በሚመግቧቸው ነገሮች
ይወሰናል፡፡ ውስጣዊው ከባቢ ሁኔታ ደግሞ በውጫዊው ተጽዕኖ ሥር ይወድቃል፡፡

በእርስዎ ሕይወት የሚፈጠረው ነገር ሁሉ አብረዎት በሚኖሩ፤ ምሥጢር በሚጋሩዎት፤ ጊዜዎትን


በሚያሳልፉባቸው ቦታዎች እና ለአዕምሮዎ በሚመግቧቸው ነገሮች ይወሰናል፡፡

ይኼ እውነታ ደግሞ በተለይም በቤት ከባቢ ሁኔታ ውስጥ ይንፀባረቃል፡፡ ሙሉ እምቅ-አቅምዎን መጠቀም
ከፈለጉ ከባለቤትዎ እና ከልጆችዎ ጋር ትክክለኛው ግንኙነት እንዲኖርዎ ማድረግና ይኼንንም ማስቀጠል
ይጠበቅብዎታል፡፡ በቤትዎ ውስጥ ያለው ከባቢ ሁኔታ እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ለትክክለኛው ከባቢ ሁኔታ
መስፈን ካስቀመጣቸው ሁኔታዎች ጋር ሊጣጣም ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እምቅ-አቅምዎ ይባክናል፡፡
ቀሪውን ሕይወትዎን እየመሩ በቤትዎ የሰፈነውን ነገር ችላ ብለው መቀጠል አይችሉም፡፡

107 | P a g e
እግዚአብሔር እንዲጠቀሙበትና እንዲያድጉበት ሲል የፈጠረውን አካባቢ እስኪረዱት ድረስ ቃሉን ያንብቡ፡፡
በመቀጠል ደግሞ በሙሉ የሕይወት ዘመንዎ ቀጣይ እየሆነ የሚሄድ ከባቢ ሁኔታን ያመቻቹ፡፡ እግዚአብሔር
አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ በዔደን ገነት ሲያኖራቸው አስፈላጊውን እና ተመራጩን ከባቢ ሁኔታ አመቻችቷል፡፡

እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔደን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው፡፡ እግዚአብሔር
አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል
የሕይወትን ዛፍ፤ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ፡፡ ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔደን ይወጣ
ነበረ፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበረ፡፡

(ኦሪት ዘፍጥረት 2፤8-10)

የዔደን ገነትን ገለጥ እያደረግን በዝርዝር ብንመለከት፤

1. እግዚአብሔር የዔደን ገነትን ፈጠረ

2. እግዚአብሔር ገነቱን በአትክልቶች ሞላው

3. እግዚአብሔር ገነቱን አደራጀው

4. የእግዚአብሔር መንፈስ በገነቱ ዘንድ ነበረ እና

5. እግዚአብሔር የሰው ልጅ እምነትን ጨምሮ በገነቱ ውስጥ ለመኖር ያስፈልጉት የነበሩትን ሌሎች
ነገሮች ሁሉ አቀረበ

እግዚአብሔር ለሰው ልጅ እጅግ ተመራጭ በሚባለው ከባቢ ሁኔታ እምብርት ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ነው
ሕይወት ያለ እግዚአብሔር ስኬት የሌላት እና ምርታማነት የጎደላት የምትሆነው፡፡ እግዚአብሔር ለእኔና
ለእርስዎ ሕይወትን ዲዛይን ያደረገልን የሱ መኖር ስለሚያሻን ነው፡፡

ኃይሉን ጽዋት እና እንስሳት እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ በመመራመርና ብዙ ነገሮችን በርብሮ በማውጣት ሊቅ


ሆኗል፡፡ አንዱን ዘር ከሌላው በማዳቀል ይበልጥ ብርቱ፤ ጠንካራ፤ የሚያማማሩ እና ልዩ የሆኑ ፍጡራንንም
አሳይቷል፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር በመታዘዝ እና ወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ሊመሰርቱ ይገባል፡፡


እግዚአብሔር የሚያስፈልጉትን እንደሚሰጠዎ እና በጉዞዎም እንደሚመራዎ ማረጋገጫ ማግኘት አለብዎ፡፡
የሱ ሕግጋት እና ትዕዛዛት ለእኛ ስንቅ ይሆኑናል፡፡ ከዚህ ያነሰ ማንኛውም ነገር በእግዚአብሔር ዕቅድ እና
ዓላማ መሠረት ለማደግ ያለንን ክህሎት ነው የሚያበላሸው፡፡

108 | P a g e
ከዔደን ገነት ውጭ ያለ ሕይወት እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች አይጨምርም፡፡ አዳም እና ሔዋን
በሐጢአት ከወደቁ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር መሆንና የወንድማማችነት ግንኙነትን በማግኘት ልንጠቀም
አንችልም፡፡ ከፈጠራ ክህሎቱ መቅዳትና ማግኘትም እንደዚያው፡፡ የእኛ ሕይወት በአሁን ሰዓት በእግዚአብሔር
በጥንቃቄ የተሞላ ዕቅድ ላይ በማይመራ ባዕድ አፈር ላይ ይገኛል፡፡ ትዕዛዛቱን ሳናከብር ስንቀር ነው ትርምስ
እና መዝረክረክ የሚፈጠረው፡፡ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ከባቢ ሁኔታ ውስጥ እስከሌለ ድረስ የተበላሸ ነው፡፡

የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ከባቢ ሁኔታ ውስጥ እስከሌለ ድረስ የተበላሸ ነው፡፡

 የዔደን ገነት ከባቢ-ሁኔታ ስለመቋረጡ 

ወቅታዊው ዓለም እምቅ-አቅማችንን በሚያበላሽ እና በሚያበላሽ መልኩ ነው ዲዛይን የተደረገው፡፡ ከቤትዎ


ገና እንደወጡ ለእምቅ-አቅምዎ ምንም ፍላጎት ከሌለው ዓለም ጋር ነው የሚገናኙት፡፡ ሰዎች አይወዱዎትም፤
ቦታ እንደሌለዎ እንዲሰማዎም ያደርጋሉ፡፡ የእርስዎን እሴቶች እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች
የሚያጣጥሉ ነገሮችን ሲናገሩም ይደመጣሉ፡፡ ይኼ በእርስዎ ከባቢ ሁኔታ ላይ የተቃጣው ወረራ አዳምና
ሔዋን በዔደን ገነት ተመሳሳይ ተጽዕኖና ግፊት ከደረሰባቸው በኋላ ነበረ የተጀመረው፡፡

የሰይጣን ጥቃት በአዕምሯዊ ብክለት አማካይነት ነበረ የመጣው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በእርግጥ. . . ብሏል›› ብሎ
ጠየቀ፡፡ ሴቲቱ ያንን ስትደግም እባብም አንድ ደረጃ ነገሩን ወደ ፊት በመውሰድ የሴቲቱን በእግዚአብሔር ላይ
የነበራትን እምነት የሚያበላሽ ነገር ተናገረ፤

እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም። በውኑ
እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።

(ኦሪት ዘፍጥረት 3፤1)

በዚህ ዓይነት አኳኋን እባብ ሴቲቱን አሳስቶ እምነቷን ሙሉ በሙሉ እንድታጎድል አደረገ፡፡ ያ ሔዋንን እንዲህ
ወደ ሰይጣን ሀሳብ ያስገባ ሂደት ዛሬ በእርስዎም ላይ ጥላውን አጥልቷል፡፡

እባብም ለሴቲቱ አላት። ሞትን አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም
መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 3፤4-5)

109 | P a g e
ብክለት ከዓይን ይጀምራል፡፡ ማየት ሐጢአት አይደለም፤ በመመልከቱም ሰው አይሞትም፡፡ ሆነም በማየት
ፍላጎት ይቀሰቀሳል፡፡ በመፈለግ ደግሞ ወደ ድርጊት ይኬዳል፡፡ ያየውን ሰው ይወስዳል፤ የወሰደውን ደግሞ
ይበላዋል፡፡ በመሆኑም ማየት በሐጢአተኛ ሀሳቦችና በድርጊቶች መካከል አገናኝ ድልድይ መሆኑን በቀላሉ
መመልከት ይቻላል፡፡ እናም የማይበላ ፍሬን፤ አትብላ የተባለን አለመብላት ከተፈለገ ቀድሞውንም አለማየት
ነው---ይኼ ለብዙዎች ባይጥምም፡፡

ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤

(ኦሪት ዘፍጥረት 3፤6)

የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን
ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ
እንዴት ይበረታ!

(የማቴዎስ ወንጌል 6፤22-23 ሀ)

አንድ ሰው የበለጠ ችግር ውስጥ የሚዘፈቀው የድርጊቶቹን ትክክለኛነት ወይንም ስህተተኝነት ሲያጤን እና
ከዚያ ተነስቶ የፍላጎቱን ጥቅም ማሰብ ሲጀምር ነው፡፡ ይኼ ደግሞ በተለይም እኛ ጥሩ የምንለው
እግዚአብሔር ጥሩ ከሚለው ጋር ሳይገጣጠም ሲቀር ነው የሚከሰተው፤

ፍላጎት አካባቢን ይበክላል፤ ምክንያቱም አንድን ነገር መፈለግ በየትኛውም መንገድ ቢሆን ያንን ነገር
ወደማግኘት ይመራልና፡፡ስሜቱ የሚቀድመው፤ በጥንታዊዋ ቤተክርስትያን ላይ መሰደድን ያካሄደ እና
ቤተክርስትያኒቱን ለማጥፋትም የሚችለውን ሁሉ ድንጋይ የፈነቀለ አለሁ ያለ አይሁዳዊ ነበረ፡፡ ሆኖም
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሳዖል ጨርሶ ያላወቀውና ያልጠረጠረው የተለየ ዓይነት ሕይወ የት ነበረ የታቀደለት፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር ሳዖልን ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ ነጥሎት በፀጋውም ጠራው፤

ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤

(ኦሪት ዘፍጥረት 3፤6)

የተሳሳተውና የተጣመመው ነገር ጥሩ እስኪመስለን ድረስ እንታወራለን፡፡ ፍላጎት እንዲህ ቀልባችንን


ሲቆጣጠረው የፈለግነውን ለማግኘት የምናደርገው ነገር የፈለገውን ያህል መጥፎ ውጤት ቢኖረውም ያ
የምንፈልገው ነገር ግን በአዕምሯችን ፀንቶ ቁጭ ብሎ፤ ‹አምጣ! አድርግ!›› ይለናል፡፡ የሚፋጅ ነገር እንይዝም
ይሆናል፡፡

ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤

110 | P a g e
(ኦሪት ዘፍጥረት 3፤6)

ያለንበት ከባቢ ሁኔታ ሲበከል ሐጢአት በውስጣችን የሚገባ ሲሆን ያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመጣስ
ለስብራት እንዳረጋለን፡፡ በድንገትም ችግር ውስጥ ተተት ብለን በራሳችን እንገባለን፡፡ ብቻችንንም
እንቀረቀራለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን ግንኙነት በመቋረጡ የተነሳ ለችግራችን መፍቻ በሱ ፈቃድና
ጥበብ ላይ ተስፋ ማድረግም አንችልም፡፡ በዚህ ጊዜ ጤናማ አስተሳሰባችንም ይሸሸናል፡፡ ስቃይና ራስ-ምታት
የቀኖቻችን የአብዛኛው ሰዓትን ይይዛሉ፡፡ በዚህ ዐይነቱ ሁኔታ የሀጢአትና የሰበብ ከባቢ ሁኔታችን ራሱ
ያሳብቅብናልና እግዚአብሔር እኛን በሐጢአት መክሰስ አያስፈልገውም፡፡

ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም
ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 3፤6)

የሀጢአትና የሰበብ ከባቢ ሁኔታችን ራሱ ያሳብቅብናልና እግዚአብሔር እኛን


በሐጢአት መክሰስ አያስፈልገውም፡፡

 የተሳሳተ ከባቢ-ሁኔታ የሚያስከትላቸው መዘዞች 

ከዔደን ገነት ከታገዱ በኋላ አዳምና ሔዋን እጅግ የተሳሳተችና ውጥንቅጧ የወጣ ዓለም ውስጥ ጭልጥ ብለው
ገቡ፡፡ ለዚህ በማስረጃነት የምናቀርበውና የመጀመሪያው ፍንጭ የቃየል የገዛ ወንድሙን አቤልን መግደል ነው፡፡
አቤልም ቃየልም ለአምላክ መስዕዋት ቢያቀርቡም ከቃየል ይልቅ የአቤል በአምላክ ዘንድ መወደዱ ቃየል
በቅናት እንዲቃጠል አደረገው፡፡ የዚህን የቅናት ስሜቱን ለማስታገስ ሲል ብቻ ወንድሙ ላይ ግድያ ፈፀመ፡፡

ይህ ከሆነ ከበርካታ ትውልዶች በኋላ ደግሞ የተበከለ ከባቢ-ሁኔታ የሚፈጥረውን ችግረ እንዲሁ በሌላ
አጋጣሚ እንመለከታለን፡፡ ከቃየል የዘር ግንድ ከተወለዱት አንዱ የሆነው ላሜህ ሁለት ሚስቶችን በማግባት
አመንዝራነትን አስተዋወቀ (ኦሪት ዘፍጥረት 4፤19 ን ይመልከቱ)፡፡ በኤደን ገነት አንድ ወንድ አንድ ሚስትን ያገባል
የሚለው የእግዚአብሔር ሕግ ቢሰራም ከገነት ውጭ ግን ጋብቻ የነበረውን ቅዱስ ገጽታ አጥቶና ተበርዞ የዝሙት
ማንፀባረቂያ ሆኖ ቆጭ ብሏል፡፡

በኖህ ጊዜ ደግሞ ዓለም እጅግ በጣም ከቁጥጥር ውጭ የወጣችና ልጓምም ያጣች በመሆኗ፤

እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።

111 | P a g e
(ኦሪት ዘፍጥረት 5፤6)
የሰው ልጅ ለይቶለት በሰይጣናዊ ኃይሎች የሚመራ ከመሆኑ የተነሳ የሚናገረውና የሚያስበው (ኦሪት ዘፍጥረት
11፤3-4 ን ይመልከቱ)፡፡ ራስ ወዳድነታቸው የተሳሳተ ከባቢ-ሁኔታ የሚፈጥረው መዘዝን ያሳያሉ፡፡ ሁሉንም
ነገር ለራስዎ በማሰብ፤ እግዚአብሔርንም፤ ጓደኛዎትንም ይረሳሉ፡፡

በ ኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የተጠቀሰው ክፋት ሁሉ ዛሬም በሰው ልጅ ላይ አንዣቧል፡፡ ሚስትና ልጆቹን
የሚገድል፤ የገዛ ባሏን በመጥረቢያ የምትተረክክ፤ የእግዚአብሔር ፍጡር የሆነ ጽንስን የምታስወርድ እናት፤
ለምን ሌላ ወደድክ፤ ለምን አልፈለግከኝም ብላ በኬሚካል የሰው ዓይን የምታሳውር፤ አባት ለምን እርሻ እረስ
አለኝ ብሎ ደብድቦ የአልጋ ቁራኛ የሚያደርግ. . . ኧረ ስንቱ! እነዚህና ሌሎች እኔ ያልጠቀስኳቸው ስፍር ቁጥር
የሌላቸው ክፋቶች የተዘፈቅንበትን የሙስና ሥርዓት ያንፀባርቃሉ፡፡ የሐጢአትን እጅግ አስከፊ ዋጋ ብሎም
ከዔደን ገነት ተባረን መውጣታችን ምን እንደፈጠረብን ያሳያሉ፡፡ በዚህች ከተፈጥሯዊው እና ከተለመደው
ውጭ በሆኑ ነገሮች በተሞላችዋ ዓለም ብዙ ልብ የሚሰብር ነገር ቢታይ ምን ሊገርምሳሳተ ሆነ፡፡ ሕይወት
የምትባለው ራሷ ረጅም የሐጢአትና የመርከስ ገመድ እስክትመስል ድረስ አንዱ ስህተት ወደ ሌላው፤ ከዚያ
ይኼኛውን ሐጢአት ለማረም እንደገና ሌላ ሲባል ይኸው የሰው ልጅ ጉድ ተሸክሞ ተቀምጧል፡፡ በዚህ ቅጥ
ያጣ ሁኔታ የተቆጣው እግዚአብሔርም ሰዎችን እና ምድርን አጠፋ፡፡

ይህች የምንኖርባት ዓለም በክፋት ኃይሎች ተጽዕኖ ሥር እጅጉን በመውደቋ የተነሳ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ
ይኖርባቸው ዘንድ ያቀዳቸው ሰላም እና ፍቅር በጥላቻ፤ ቅናት፤ ኢ-ግብረገባዊነት እና ንዴት ተተክተዋል፡፡ ዛሬ
ሠርጋቸውን፤ ‹‹የአብረሐም የሣራ›› እያሉና ስንቶችን ሊታደግ የሚችል ወጪ እያወጡ እየደገሱ ይኸው
ፍቺው የትየለሌ ሆኗል፡፡ ለመልሳቸው ሽር ጉድ እየተባለ ሚስት ከመኝታ ተቀርቅራ ስትቀር ምንድነው ሲባል
ዓይኗ ሥር ደህና አድርጎ በቦክስ የነረታትን ለመሸፈን እንደሆነ የሚታወቅበት፤ በሠርጉ ዕለት በደምበኛ የቃሪያ
ጥፊ የሚጠፈጠፍ ባልም አለ፡፡ የልቅ ወሲባዊነት እና አመንዝራነት አስከፊ ውጤቶች ይኸው በሰው ልጅ ላይ
አፍጥጠዋል፡፡ አካባቢያችን ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ እኛ ደካሞቹም ልጓም ልናበጅለት አቅም አጥተናል፡፡

 ግራ በተጋባንበት ወቅት እገዛ 

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህች ቅጥ አምባሯ ለጠፋ እና በሐጢአት ለተጨማለቀች ዓለም መፍትሄ ያለውን
አስቀምጧል፡፡ አባት ሁለት ልጆች አሉት፡፡ ታዲያ ከዕለታት አንድ ቀን ከሁለቱ ልጆቹ በዕድሜ አነስ ያለው
ከውርሱ ላይ የሚደርሰውን ድርሻ ይሰጠው ዘንድ ከጠየው በኋላ በዕድሜ አነስ ያለው ልጅ የደረሰችውን ይዞ
ሩቅ ቦታ ሄደና ገንዘቡን በመርጨት የለየለት የአለሌና ዱርዬ ኑሮን ተያያዘ፡፡ ዱርዬነቱና ዘሎ አልጠግብ ባይነቱ
ያለውን ገንዘብ አንድም ሳይቀር እንዲያሟጥጠው አደረገው፡፡ መጨረሻ ላይ የሚበላው ቢያጣ የዓሣሞች
ምግብ ተመኘ፡፡

112 | P a g e
ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፡፡ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው  እኔ ግን ከዚህ ከራብ
እጠፋለሁ፡፡ ተነስቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፡፡ አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በምድር በፊትህ በደልሁ፡፡ ወደ ፊትም ልጅህ
ብባል አይገባኝም ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ፡፡ እለዋለሁ፡፡ ተነስቶም ወደ አባቱ መጣ፡፡ እርሱም ገና ሩቅ ሳለ
አባቱ አየውና አዘነለት፤ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው፡፡

(የሉቃስ ወንጌል 15፤17-20)

ልጁ ድህነቱን እና ማጣቱን ተረዳ፡፡ ፍላጎቱ ሊሟላ እንደሚችልም አመነ፡፡ የአባቱን መልካምነት በማወቁ አሁን
እንደሆነው ሆኖ ሄዶ ምህረቱን ለመጠየቅም ወሰነ፡፡

በመሠረቱ እግዚአብሔር በምንኖርባት ዓለም እብደት ጉዳይ ላይ የጠለቀ እውቀት አለው፡፡ ራሱን በመፍትሄነት
አቅርቧል፡፡ በኢየሱስ በኩልም የዚያችን የዔደን ገነትን ከባቢ ሁኔታ ለእኛ በስጦታ መልክ ሰጥቷል፡፡ ሆኖም
ይኼንን ከእርሱ ጋር በወንድማማችነት፤ እና እሱን በነፃነት የምንታዘዝበትን ከባቢ ሁኔታ በግድ ተቀበሉኝ
አይልም፡፡ ልክ እንደዚያ ልጁ አልገራ ባይ አባት እግዚአብሔር በመጣን ጊዜ ሁሉ ይጠብቀናል፡፡ በዚያ ጊዜ
ሐጢአታችንን በመናዘዝ ምህረቱን በሙሉ ልባችን እስከፈልግን አምላክ በሩን አይዘጋም፡፡ ያን ጊዜ ብቻ ነው
እግዚአብሔር ዓለምን ሊረዳት የሚችለው፡፡

እግዚአብሔር በምንኖርባት ዓለም እብደት ጉዳይ ላይ የጠለቀ እውቀት አለው፡፡

እግዚአብሔር የዚህችን የተበከለች ዓለም ችግር ለመፍታት ሲል አብረሐም ሁሉንም ነገር ትቶ ይከተለው
ዘንድ ጠይቆታል (ኦሪት ዘፍጥረት 12፤1-4 ን ይመልከቱ)፡፡ ለምን እግዚአብሔር ይኼንን ያለው አብረሐም ከሱ
ጋር ያለው ግንኙነት በጓደኞች እና በቤተሰብ አባላት መጥፎ ተጽዕኖ ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል ስላወቀ
ነበረ፡፡

 እርስዎ የሚገኙበት ከባቢ ሁኔታ ምን ይመስላል 

እስኪ አሁን ደግሞ ጥቂት ጊዜ ወስደው አካባቢዎን ይቃኙ፡፡ እየተሻሻለ ወይንስ እያዘቀዘቀ ነው የመጣው
መንፈሳዊ ሕይወትዎን የሚያድስ ወይንስ የእግዚአብሔር መንፈስ በልብዎ እንዳይኖር የሚያደርግ ነው
እግዚአብሔርን መታዘዝ አብረዋቸው ጊዜዎትን ለሚያሳልፏቸው ሰዎች የተለመደ ነው ወይንስ ዓመጽና
እምቢ ባይነት ነው የእነዚህ ሰዎች ሕይወት

ሙሴ እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ያከብሩ ዘንድ አሳሰባቸው፡፡

113 | P a g e
እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ያህል ቃል በልብህ ያዝ፡፡ ለልጆችህም አስተምረው፤ በቤትህም ስትቀመጥ፤ በመንገድህም
ስትሄድ፤ ስትተኛም፤ ስትነሳም ተጫወተው፡፡ በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደ ክታብ
ይሁንልህ፡፡ በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ፃፈው፡፡

(ኦሪት ዘዳግም 6፤6-9)

እንግዲህ እርስዎም ይኼንኑ ተመሳሳይ ልምምድ ያደርጉ ዘንድ ነው ምክሬ፡፡ ለምን ቢባል እግዚአብሔርን
ማዕከል ባደረገ ልብ ውስጥ የእምነት፤ ይቅር ባይነት እና መታዘዝ ስጦታዎች እንደ ጅረት ይፈሳሉና፡፡ እነዚህ
እግዚአብሔር ዲዛይን ያደረገው ከባቢ-ሁኔታ መሠረታዊ ባሕሪያት ከእግዚአብሔር ጋር የሚፈለገውን
ወንድማማችነት እና አብሮነት ከሚያመጣልን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳው ክርስቶስ ጋር መልካም ግንኙነት
ለመፍጠራችን ማሳያ ናቸው፡፡ እምቅ-አቅማቸው መውጣት ይችል ዘንድ ቀና የሆነ ከባቢ ሁኔታን ለመፍጠር
የሚታትሩ ሰዎች ውርሶች ሲሆኑ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ግንኙነት ሁልጊዜም
ቢሆን ትክክለኛውን ከባቢ ሁኔታ ይሰጠናል፡፡

ለአካባቢያዊ ሁኔታችን የሚሆን ራሳችንን መፈተሻ ዝርዝር፤

1. ለመሆኑ ጓደኞችዎ እነማን ናቸው

2. ምን ምን ዓይነት መጻሕፍትን ያነባሉ

3. ምን ምን ዓይነት ፊልሞችን ይመለከታሉ


4. ምን ምን ዓይነት መጻሕፍት መደርደሪያዎችዎን ሞልተው ይታያሉ
5. የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎ ምን ምንድናቸው

6. የመዝናኛ እንቅስቃሴዎችዎ ምንምንድናቸው

7. የሙዚቃ ፍላጎትዎን ማን ነው የሚያረካው

8. የእርስዎ ጀግኖች እነማን ናቸው

9. መንፈሳዊ ስሜትዎን የሚያረካልዎት ማን ነው

10. በቤትዎ፤ በሥራዎ፤ በትምህርት ቤትዎ ያሉ ሁኔታዎች ለሕይወት ዓላማዎ መፈፀም ምቹ ናቸው

114 | P a g e
ከላይ የተባሉት በሙሉ በጥንቃቄ መታየት፤ መተንተን እና እምቅ-አቅምዎን በሚያዳብር፤ በሚያንቀሳቅስ
ብሎም በሚያለመልም ሁኔታ መስተካከል ይኖርባቸዋል፡፡

 መርሆች 

1. እግዚአብሔር ሁሉም ነገር በተወሰነ ከባቢ ሁኔታ እንዲሰራ ዲዛይን አድርጎታል፡፡

2. እርስዎ በትክክል የሚሰሩባቸው ሁኔታዎች

 የእግዚአብሔር መኖር

 ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ግንኙነት

 ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ወንድማማችነት

 እግዚአብሔርን የመታዘዝ ነጻነት


የመሳሰሉትን ያካትታሉ

3. እምነት፤ መታመን፤ ይቅርታ አድራጊነት እና መታዘዝ ተመራጭ ለሆነው ከባቢ ሁኔታ አስፈላጊ ናቸው

115 | P a g e
4. ትክክለኛውን ከባቢ ሁኔታ ለመፍጠር ይችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል ከአፍዎ አይነጥሉ

5. ተገቢ ያልሆነው ከባቢ ሁኔታ እምቅ-አቅምን ያበላሻል

6. ተገቢ ያልሆነን ከባቢ ሁኔታ ወይ ይተዉት አልያም ይቀይሩት

ምዕራፍ 11

____________________ ______________________

ሥራ--ማስተር ቁልፉ

116 | P a g e
አንዳንዶች ዋጋ ያለውን ነገር ሲያልሙ ሌሎች ግን

ነቅተው እነዚህን ይሰራሉ፡፡

በ Louisville, Kentuckey የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የሆነው ጂም ማይክልስ ከዕለታት ባንዱ ቀን ሀተታ


ሲያቀርብ፤

ዛሬ ዛሬ ብዙ ሠራተኛ ተግቶ በሥራው ላይ ከሚታትር ይልቅ ቤቱ የሚሄድበትን ጊዜ ይናፍቃል

አለ፡፡ አዎን፤ ሥራቸውን አሰልቺ፤ ከአንድ ዓይነት አዙሪት ያልወጣ፤ አድካሚ፤ ንዝንቅ ያለበት እና እላቸው ላይ
ለኑሮ ሲባል እንደተጫነ ዕዳ አድርገው የሚመለከቱ ብዙ ሠራተኞች ከላይ ማይክልስ ከገለጸው የተለየ
አመለካከት የላቸውም፡፡ ብዙ ሰዎች በሥራቸው ላይ የሚተክዙ፤ ቀዝቃዛ እና የድብርት ስሜት ያላቸው
መሆኑ አያስገርምም፡፡ ለብዙ ሠራተኞች ከዚህ አሰልቺ ሥራቸው የሚገላግላቸው ቤት የሚሆኑበት ወይንም
የእረፍት ጊዜ ነው፡፡

በብዙዎች ዘንድ በመካከለኛው እና ዝቅተኛው እርከን ላይ ላሉ ሠራተኞች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና


አለቆች ጥቅማ ጥቅም ከትልልቅ ደመወዝ ጋር ስላላቸው የተሻለ መነቃቃትና ፍላጎት ይኖራቸዋል የሚል
ግምት ቢኖርም ሃቁ ግን እስከ 500 እና ከዚያ በላይ ሠራተኞችን በሥራቸው የሚያስተዳድሩና በምቹ፤ ሰፊ
ቢሮ ውስጥ ሆነው ድርጅቶችን የሚመሩ ሰዎችም ከዚህ ስሜት ነጻ አይደሉም፡፡ እነሱም ስራን ልክ ነጋዴ
ታክስን እንደሚፈራው ወይ ሞት እንደሚፈራው ሁሉ ይፈሩታል፤ ይጠሉታልም፡፡

ይህ ሥራ ላይ ያለ አመለካከት ለመንግሥታት፤ ለኮርፖሬሽኖች እና ለሚዲያው ትልቅ ሥጋት እየሆነ


መጥቷል፡፡ ከሥራ ጥራት፤ የወረደ ምርታማነት እና ደካማ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮች
ኢኮኖሚው እንዲያሽቆለቁል ሲያደርጉት ማበረታቻ እና ማነቃቂያ የመስጠት ፍላጎትም በዚያው መጠን
ያድጋል፡፡ በዚህ የተነሳ እንደ ኤሮቢክስ ክፍለ-ጊዜያት፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ክፍሎች እና ለመሮጫ
የሚያገለግሉ ትራኮች በከፍተኛ ወጪ በሥራ ቦታዎች አካባቢ እየተገነቡ መጥተዋል፡፡

የአማካዩን ሠራተኛ ተነሳሽነት እና ጉጉት ለማሻሻል ከሚደረገው ከዚህ መሰሉ ጥረት ባሻገር የኮርፖሬት እና
የመንግሥት መሪዎች እጅግ ጠንካራ የተባሉትን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የምታማነት ማዕከላትን በማጥናት
ላይ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ እንዲህ ዓይነቶቹ ጥረቶች የሥራ ጥበብ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ
በዳበረባት ጃፓን ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

117 | P a g e
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጃፓን ክፉኛ ነበረ በጦርነት የተመታችው፡፡ ብዙ ሕዝብና የመሠረተ-ልማት
አውታሮች በጅምላ-ጨራሽ አቶሚክ ቦምቦች ወድመዋል፡፡ ጃፓን በዚህ ወቅት የፍርስራሽ ክምር ብቻ
የሚታይባት ሆና ቆይታለች፡፡ ሆኖም ‹ሳይደግስ አይጣላም› እንዲሉ አሜሪካ እና ሌሎች አንዳንድ አገራት
ጃፓን መልሶ ግንባታ እንድታደርግ ረዷት፡፡ ለምሳሌም አሜሪካ ጃፓናውያን በማምረቻው ዘርፍ ተቀጥረው
አሜሪካ ካሉ ሠራተኞች በጣም ያነሰ ደመወዝ እንዲያገኙ አድርጋለች፡፡ ጃፓናውያኑ በወቅቱ በጦርነት ደቀው
ገና መነሳታቸው ስለነበረ ከአሜሪካ የቀረበውን ተቀበሉ፡፡ ዛሬ ታሪኩ ተቀይሮ ጃፓን ትልቅ ኃይል ሆናለች፡፤
በእርግጥ የጃፓናውያን ኃይል ከጦር ይልቅ በኢኮኖሚ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የጃፓናውያን መሣሪያ ገንዘብ
ነው፡፡

 የእርስዎን ሕይወት የሚገዛው ምንድነው 

የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሊቆች እንደፈለጉ ነገሮችን ይሰነጣጥቁ፤ ይበልቱም እንጂ በማኅበረሰባችን ውስጥ
ያለው የኃይል ምንጮች ግን በዋናነት ወደ ሁለት ዋና ዋና ግብዓቶች ነው ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉት---
እግዚአብሔር እና ገንዘብ፡፡ እነዚህ ሁለቱ በዓለም ላይ ያሉት ዋንኛ ኃይሎች ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም
በግልጽ ከሁለቱ አንዱን እንደምናገለግል ገልጧል፤

በሕይወትዎ ያለው መሠረታዊ ኃይል የሚያነሳሳዎትን ነገር ስለሚወስን እርስዎ የሚገዙለት ከሁለቱ አንዱ
ኃይል እምቅ-አቅምዎን በማውጣት በኩል ትልቅ ሚና አለው፡፡ እርስዎን የሚያነሳሳዎት ገንዘብ ከሆነ
ስግብግብነት የድርጊቶችዎ ሁሉ ማጠንጠኛ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ኃይልን ከሰጠዎ ለሕይወትዎ
ያስቀመጣቸው ዓላማዎች እርስዎን ይቆጣጠራሉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር በቅድሚያ
ታማኝነታቸውን እና አጋርነታቸውን ለሱ ለሚሰጡት ፍላጎታቸውን እንደሚሞላ ይነግረናል፤

በመጽሐፍ ቅዱስ ከዚህም በተጨማሪ ገንዘብ ብዙ መዘዝና የገንዘብ ኪሳራ ላይ ጭምር እንደሚጥል
ያስረዳናል፤

ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤


ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም
አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤
ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት
ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

(መጽሐፈ ምሳሌ 10፤2)

በኃጢአት የተገኘ መዝገብ ጥቅም የለውም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል።

118 | P a g e
(መጽሐፈ ምሳሌ 10፤2)

ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፤ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።

(መጽሐፈ ምሳሌ 15፤27)

ክፉ ነገር ኃጢአተኞችን ያሳድዳቸዋል፤ ጻድቃን ግን መልካሙን ዋጋ ይቀበላሉ። ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል፤
የኃጢአተኛ ብልጥግና ግን ለጻድቅ ትጠበቃለች።

(መጽሐፈ ምሳሌ 13፤21-22)

ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው ፍቅረ-ንዋይ የዘቀጠ ሥነ-ምግባርን በማበረታታት ያፈነገጡ እሴቶች እንዲኖሩን
ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ምርኩዛችን እንድናደርጋቸው የሚፈልጋቸውን እውነት እና ታማኝነት ይበልጥ
ለማከማቸትና ለማካበት ያለን ጉጉት ይውጣቸዋል፡፡ አለመታመን ደግሞ የምናደርገውን እና ያንንም ነገር
እንዴት እንደምናደርገው ይወስናል፡፡

የኀጥእ ሰው ሞያ ሐሰተኛ ነው፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋ አለው።በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል


ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።

(መጽሐፈ ምሳሌ 11፤18; 28)

የጻድቅ ደመወዝ ለሕይወት ነው፤ የኃጥእ ፍሬ ግን ለኃጢአት ነው።

(መጽሐፈ ምሳሌ 10፤16)

በእግዚአብሔር እና በገንዘብ መካከል ያለው ግጭት ለሥራ አብዛኞቻችን ባለን አመለካከት ላይ ይገለፃል፡፡

 ለመሆኑ ይሠራሉ ወይንስ ገብተው በመውጣት ተወስነዋል 

ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም የሚያስገኝ ሥራ እንዲኖረን ብዙዎቻችን እንፈልጋለን--መሥራት ግን


አንፈልግም፡፡ ይኼ ማለት ገንዘብ እና ጥቅማ-ጥቅሙን ፈልገን ተገቢውን እና የሚጠየቀውን ልፋትና ጉልበት
ግን አንፈልገውም ማለት ነው፡፡ መቼም በሥራው ዓለም ላይ ተዘፍዝፎ የሚውል፤ የሚያላግጥ፤ በማቃጠር
መኖር የሚፈልግ፤ ፌስ-ቡክ እና ፊልም ላይ ተቀርቅሮ ጊዜውን የሚገድል፤ የደመወዝ ጊዜ ማንም
የማይቀድመው ደነዝ እና ሸክም ይዞ እንደመኖር እጅግ የሚያስጠላ ነገር የለም! እንዲህ ዓይነቶቹ ሥራ

119 | P a g e
አላቸው መባልን እና ከሥራቸው ጋር በተያያዘ የሚገኙ ጥቅሞችን የሚፈልጉ፤ ግን ሥራ የሚባል ነገርን
የሚጠሉ ናቸው፡፡ ጥሩ ሥራ ከመሥራት ይልቅ ወፈር፤ ጠቀም ያለ ደመወዝን ይፈልጋሉ፡፡

ይኼ ዓይነቱ አስተሳሰብ እግዚአብሔር ስለ ሥራ ካስቀመጠው ጽንሰ-ሀሳብ ጋር ሙሉ በሙሉ ይጣረሳል፡፡


እግዚአብሔር ከምናገኘው ደመወዝ፤ የቢሯችን በር ላይ ከተለጠፈው የሥራ ደረጃችን፤ ከቢሯችን ስፋትና
ጥበት ይልቅ ለሥራ ያለንን አመለካከት ያስበልጣል፡፡ እግዚአብሔር የባንክ ሂሣብ መጠንዎ እንዲጨምር
ማድረግ ይችላል ነገር ግን ስለ ሥራ ያለውን አመለካከት እንድንጋራ አያስገድደንም፡፡

 ስለ ሥራ ያለን አሉታዊ አመለካከት 

የቶማስ ኤዲሰን ድንቅ ፈጣሪ ነበረ፡፡ ዛሬ የምንጠቀምባቸው ብዙ ነገሮች--የኤሌክትሪክ መብራትን ጨምሮ--


በውስጡ የተደበቁ ክህሎቶችን እና ድንቃ-ድንቅ ነገሮችን ለማውጣት ፈቃደኛ በመሆኑ እና የሚፈለገውን
ርቀት ያህል በመሄዱ የተገኙ ናቸው፡፡ ኤዲሰን እጁን ሰብስቦ ወደ ሥራ ለመግባት አልቦዘነም፡፡ ሕይወቱም፤

ላቅ ማለት አንድ በመቶ ብቻ መነሳሳት፤ 99 በመቶ ደግሞ መጣጣር ነው፡፡

የሚለውን አባባሉን ሙሉ በሙሉ ያንፀባርቃል፡፡ ብዙውን ጊዜያችንን በሥራ ላይ ያለው ጥረት፤ ድካም እና
ችግር መልካምና ጣፋጭ ፍሬውን ይሸፍንብናል፡፡ እዚህጋ የተሳሳተው አመለካከታችን ምንጭ ሐጢአትን እና
ሥራን እኩል ማድረጋችን ነው፡፡ ሥራ ምንም እንኳ ለመኖር ሐጢአትን የማይፈልግ ቢሆንም የሥራን ሁኔታ
ግን ሐጢአት ቀይሮታል፡፡

ሥራ እግዚአብሔር እንዳቀደው ሐጢአት ገና ወደ ዓለም ሳይገባ ለሰው ልጅ የተሰጠው ነው፡፡ አዳም


ለእንስሳት ስም የመስጠትን ሥራ ያከናወነው ከሔዋን ጋር ወደ ሐጢአት ከመግባቱ ቀደም ብሎ እንደነበረ
እናስታውሳለን፡፡ እንግዲህ ሥራን ዛሬ እንደምናውቀው--ልፋቱ፤ ስቃዩ፤ ድካሙ እና ትግሉ--የአዳምና ሔዋን
አለመታዘዝ ያስከተለብን መዘዝ ሆኗል፡፡

እግዚአብሔር አዳምን ዓለምን እንዲገዛ እና በምድር ላይ የበላይ እንዲሆን ሲነግረው ሕይወት ለአዳም ገና
አዲስ የነበረች ሲሆን እግዚአብሔር በውስጡ ምን ዓይነት ኃይል እንዳስቀመጠ እንኳ አዳም ምንም
የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ እናም በዚህ ወቅት እግዚአብሔር አዳም ለእያንዳንዱ እንሰሳ የተለየ ስም
እንዲፈጥር ጠየቀው፡፡ አዳም በአየር ላይ የሚበሩትን አእዋፋት እና የጫካ ዱር እንስሳትን ስም መስጠት
ሲጀምር በውስጡ የነበረውን እምቅ-አቅም ተረዳ፡፡ በመሆኑም ሥራ በውስጥዎ ያለውን ችሎታ የሚገልጽ
ባረኮት ነው፡፡ እምቅ-አቅምዎን የሚያወጡበት ማስተር ቁልፍም ጭምር፡፡

120 | P a g e
 ሥራን የተመለከቱ የተዛቡ አመለካከቶች 

አብዛኞቻችን የሥራን ጠቃሚነት አንረዳም፡፡ ከአንድ ጥሩ የሥራ ቀን ይልቅ እረፍትና መዝናናትን


እንመርጣለን፡፡ ሆኖም እምቅ-አቅማችንን ማውጣት ካለብን ስለ ስራችን ያለንን የተዛባ አመለካከት በመረዳት
ከአሁኑ እጅግ ልቀን ልንሄድ ያስፈልጋል፡፡

የሚያሳዝነው ይኼ ማኅበረሰባችን ዛሬም ድረስ እረፍት-ዘመም መሆኑ ነው፡፡ በዓላት፤ የእረፍት ጊዜያት እና
የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ከሥራ ቀናት ይሻሉናል፡፡ በዓላት በሥራ ቀን ላይ ያልዋሉ ጊዜ እንበሳጫለን፡፡ ይኼ
እጅግ የተዛባ አመለካከት መሆኑ ግን ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡ እረፍት ከሥራ አይሻልም!

እግዚአብሔር ዓለምን በፈጠረ ጊዜ ስድስት ቀናትን በተከታታይ ሰርቶ ሰባተኛው ላይ በቻ ነበረ ያረፈው
(ኦሪት ዘፍጥረት 2፤12 ን ይመልከቱ)፡፡ እኛ የሰው ልጆች ይኼንን የእርሱን ፈለግ በመከተል ስድስት ቀናትን
ሰርተን ባንዱ ብቻ እንድናርፍ መጠየቁንም እንረዳለን (ኦሪት ዘፀዓት 23፤12 ን ይመልከቱ)፡፡ የሰው ልጅ
በሥራው ላይ የሚያሳያቸውን ባሕሪያት እና የተዛባ አመለካከቱን፤ ብሎም ስልቹነቱን ብንይ ግን ስድስቱን
አርፎ ባንዱ ቀን ብቻ ለመስራት ያለውን ፍላጎት እንረዳለን፡፡

ሥራ ከእረፍት እጅግ በተሻለ ሁኔታ ሁልጊዜም ግለሰባዊ ዕድገትን እና እርካታን ያስገኛል፡፡ የፈጠራ ክህሎትዎን
በመቀስቀስ ከተደበቀው የእምቅ፤አቅም ክምችትዎ የተወሰነውን ይጠቀማል፡፡ እርስዎ የእርካታ ማጣት ሰለባ
ከሆኑ ምናልባትም እረፍት አብዝተው ሊሆን ይችላል፡፡ ስለማይሰሩ ስልቹ ሆነዋል፡፡ አንድ ሰው ከሥራው
እየሸሸ ደስታን ሊያገኝ መጠበቅ የለበትም፡፡ ሥራ ነው እኛን ነቅተን እና ተነቃቅተን እንድንቆይ የሚያደርገን፡፡
ለሕይወት ትርጉም የሚሰጠው ግብዓት ማለት ሥራ ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ስድስት የእረፍት ሳምንታት
ቢኖረን ይኼ በምንም መለኪያ የላቀ ስኬት ማሳያ ሊሆንም ሆነ እርካታን በራሱ ሊፈጥር ከቶም አይችልም፡፡

እርስዎ የእርካታ ማጣት ሰለባ ከሆኑ ምናልባትም እረፍት አብዝተው ሊሆን ይችላል፡፡

ጡረታ መውጣት ከእግዚአብሔር ዕቅዶች መካከል አይደለም

ሥራን በተመለከተ ያለን ሁለተኛው የተፋለሰ አመለካከት ደግሞ የሥራ ግብ ሄዶ ሄዶ የሆነ ደረጃ ላይ ጡረታ
መውጣትና ማረፍ ነው የሚለው ነው፡፡ እርስዎ ግን ከሥራዎ ተሰናብተው ያርፉ ዘንድ አይደለም ዲዛይን
የተደረጉት፡፡ እርስዎ ከእግዚአብሔር ነው የወጡት፤ እግዚአብሔር ደግሞ አላረፈም፡፡ የማይታየውን ተናግሮ
እንዲታይ አድርጓል፡፡ በመሆኑም ማረፍ የእግዚአብሔር እቅድ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው
የማይሞት መንፈስ እና ዘለዓለማዊ እምቅ-አቅም ሰጥቶ በመሆኑ እግዚአብሔር ሁልጊዜም ቢሆን በሥራ
ተወጥረን እንድናሳልፍ ነው ያቀደው፡፡ ከተወሰነ ሥራ ወይ ድርጅት መልቀቅ ይቻላል፡፡ በሕይወት እያሉ ሥራን

121 | P a g e
እርግፍ አድርጎ መተው ግን አይቻልም (በሕመም ወዘተ. ካልሆነ በቀር)፡፡ መሥራት ባቆሙባት ቅጽበት መሞት
ይጀምራሉ ለምን ቢባል ሥራ የሕይወት አስፈላጊ አካል በመሆኑ፡፡

ጡረታ የወጣ ወይንም ሥራ የፈታ ነጭናጫ፤ ሕይወት የጎረበጠችው፤ የመረረው ዓይነት ሰው ያውቃሉ ያ
ሰው እንዲህ ሊሆን የቻለው ሥራ በመፍታቱ ነው፡፡ ሥራን መተው የእርካታ ስሜቱን ነጥቆት እንደሆነ ልንረዳ
ይገባል፡፡

መኪና በነዳጅ እንደሚንቀሳቀስ ሁሉ ለእኛ ለሰው ልጆችም ሥራ አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሔር በውስጥዎ
ያስቀመጠውን እምቅ ኃይል በማውጣት እርካታ እንዲያገኙ ነው ዲዛይን ያደረገዎት፡፡ የሥራዎትን ፍሬ
በማግኘት እንዲረኩ ነው ያደረገዎት፡፡

ለዚህ ነው ከሥራ ይልቅ በዋዛ በፈዛዛ ጊዜን ማሳለፍ ለጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ የሚዳርገው ፡፡ እግዚአብሔር
ቁጭ ብለን በማስካካትና ጊዜ በመግደል እንድናሳልፍ አልፈጠረንም፡፡

እግዚአብሔር እኮ ሲደክመው ነበረ ያረፈው፡፡ ያኔም ቢሆን ሥራ አላቆመም፡፡ በመሆኑም እኛን፤

እኔ ይኸው አሁንም እየሰራሁ ነው፡፡ ለምን እናንተ አትሰሩም በእናንተ አማካይነት እና በውስጣችሁ
የምፈልጋቸው ገና ብዙ ነገሮች አሉ፡››

ይለናል፡፡ እግዚአብሔር ከሥራ-ፈትነት መንፈስ ያውጣዎት፡፡ ሥራ-መፍታት ኢ-መጽሐፍ-ቅዱታዊ፤ ኢ-


መለኮታዊ እና ከመንፈሳዊነት ያፈነገጠ ነው፡፡ ሥራ መተው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ካቀደው ሙሉ
በሙሉ ውጭ ነው፡፡

በነጻ አንድ ነገር ማግኘት አይችሉም

ሶስተኛው እና ሥራን በተመለከተ ያለንን አረዳድ የሚያዛባው ደግሞ ምንም ዋጋ ሳንከፍል አንድን ነገር
ማግኘት እንችላለን የሚለው አስተሳሰብ ነው፡፡ ለዚህ አስተሳሰብ ደግሞ ትልቁ መገለጫ ሎተሪ የሚሉት
የሕልም ዓለም እንደሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ በቲቪ እና በሬዲዮ ሾዎችን እና ፕሮግራሞችን ስናደምጥ
‹ይኼንን ሞክሩት›፤ ‹ጥሩ ሽልማት አለ› የሚባሉ ነገሮች ያጨናንቁናል፡፡ የፖስታ አገልግሎት የሚሰጡ
ድርጅቶች ይበልጥ በተጠቀምን ቁጥር ማበረታቻ ሽልማቶች አሉ ይሉናል፡፡ ‹በፍጥነት ወደ ሀብት ማማ
የመውጫ መንገዶች› የሚባል ነገርን ማስተዋወቅ የብዙዎቹ አባዜ ሆኗል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የዓለም አባዜ በነጻ
ብዙ ነገርን የማግኘት አመለካከትን ያሰርጽብናል፡፡ ብዙውን ጊዜ ደግሞ የእንዲህ ዓይነቶቹ ዘዴዎች ሰለባ
መሆናችን ያሳዝናል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሳይሰሩ፤ በዕድል እና ባቋራጭ ሀብት የማካበትን አስተሳሰብ

122 | P a g e
እስካልቀረፍን ድረስ የሥራን ትክክለኛ ፍሬ መረዳት አንችልም፡፡ ሥራ ማለት እግዚአብሔር ለአርኪ እና
ትርጉም ላለው ሕልውናችን ሲል የቀየሰው ጎዳና ነው፡፡

ሥራ ማለት እግዚአብሔር ለአርኪ እና ትርጉም ላለው ሕልውናችን ሲል የቀየሰው ጎዳና ነው፡፡

ያለ ሥራ ዓላማዎትን ከዳር ማድረስ አይችሉም፡፡ ብዙ ገንዘብ በሎተሪ ዕጣ ለማግኘት መሞከር የሥራን


ጽንሰ-ሀሳብና ለፍቶ የማግኘትን ፀጋ ያሳጣል፡፡ ይኼ እንዳለ ሆኖ ሌላው ለፍቶ፤ ጥሮና ግሮ ያገኘውን ለራስ
በማድረግም እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያስቀመጠውን ማሳካት አንችልም፡፡ አብዛኞቹን የሎተሪ ባለ
ዕድሎች ማነጋገር ይቻላል፡፡ ከዚያ ዕድል በኋላ ከበፊቱ ሲነፃፀር ሕይወታቸው በቅሬታ እና በመዘዝ የተሞላ
መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ለምን ብዙዎቻችን ቀናችንን አሀዱ ብለን የምንጀምርለትን ዓላማ ያጡታልና፡፡

ሕይወት ያለ ዓላማ ትርጉመ-ቢስ ናት፡፡ እርካታ ጥረትን ስለሚጠይቅ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ቢሆንና
ብንንፈላሰስ የስኬት ስሜትን አናገኘውም፡፡ አንድ ሰው ሁለት ሚልዮን ብር የሎተሪ ዕጣ (ሙሉውን)
ቢያሸንፍና የሚቆራረጠው ተቆራርጦ የደስታ የሚመስለውን ሕይወት ቢጀምር ከዚያ ግን ወደለየለት አዘቅት
ሊያመራ ይችላል፡፡ በአካል ጥርጥር የለውም--ይለመልማል፤ ያምርበታል፤ ምቾቱ ይጠበቃል፡፡ ግን መንፈስስ
እምቅ-አቅሙ አለጥርጥር ይሞታል፡፡ የሕይወት እርካታ የሚባል ነገርም እንደ ጧት ጤዛ ይጠፋል፡፡

እግዚአብሔር ሥራን የሰጠዎት ለግላዊ ስኬትዎ መሟያ ይሆን ዘንድ ነው፡፡ አንድን ነገር በነጻ ለማግኘት
ሲሞክሩ የስኬትና እርካታ ቁልፉ ልፋት በመሆኑ ሁለቱ ስሜቶች አይገኙም፡፡ ሕይወት በብዙ መንገዶች
ይኼንን ታሳየናለች፡፡ ያለ ሥራ ጥቅምን ብናገኝ እርካታን እናጣለን ለዚህ ምክንያቱ ብዙውን ጊዜ
የምናደንቀው እና የምንቀበለው የለፋንበትን ነገር በመሆኑ ነው፡፡ አንድን የለፋንበትን ነገር ስናገኘው ያ ሁሉ
ውጣ-ውረድ፤ ልፋት፤ ያየነው መከራ ወዘተ. ትዝ ይለናል፡፡ ያንን ሁሉ መወጣታችን ከፍተኛ እርካታን
ይፈጥርብናል፡፡ ምግብ ቢታደል ለማግኘት ጥረት በማድረግ የምናገኘውን እርካታ ያሳጣናል፡፡ የዌልፌር እና
ጡረታ ትልቁ ጉዳትም ይኸው ነው፡፡ ግላዊ ኃላፊነት፤ እርካታ እና ራስን ከማሳደግና በሥራ ላይ ከማሰማራት
የሚመነጨውን የኩራት ስሜት ይነጥቀዋል፡፡

 ሥራ እና ኃላፊነት 

ከእነዚህ የተፋለሱ አመለካከቶች ራስዎን መገላገል የሚችሉት ለምርታማ ሕይወት ዋንኛው ቁልፍ ምርታማ
መሆን እንደሆነ ነው፡፡ ሥራ ከሌለን፤ አቅጣጫ ይጠፋናል እና ቀስ በቀስም ወደ ዝቅጠት እንዳረጋለን፡፡
ሕይወታችን አደጋ ላይ ይወድቃል ለምን ቢባል በርካታ የሕይወት መስኮቻችን ከዋናው ዓላማችን ያፈነገጡ
ይሆናሉ፡፡ ሥራ እጅግ በጣም የሚያስፈልገን ከመሆኑ የተነሳ የሥራ አለመኖር ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነትም
የሚያበላሽ ይሆናል፡፡

123 | P a g e
ለምሳሌም እንበልና አንድ ሰው እንዲሁ ትዳር መያዝና ከመረጣት ሴት ጋር አብሮ ከመኖር ለሚገኘው ደስታ
ሲል ቢያገባ ከትዳርና ቤተሰብ ምስረታ ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ብዙ ነገሮች--ለምሳሌም የቤት ኪራይ፤
የተለያዩ ወርሀዊ ክፍያዎች፤ የመኪና ክፍያ፤ የወር ወጪ፤ ልጅ ማሳደግ ወዘተ.--ያሉትን ሊጠላና፤ ‹ምን ውስጥ
ገባሁ!› ብሎ እስከመማረር ሊደርስ ይችላል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ገና በጋብቻ ሞቅታ ደስ ብለውት እና
ምክንያታዊ ሆነው ያገኛቸው ቤተሰብ ምሥረታ እና ጎጆ ቅለሳ ኋላ ላይ ምክንያተ-ቢስ፤ የባልነት ኃላፊነቱም
ሸክም ሊሆንበት ይችላል፡፡ ሰውየው ይኼን ጊዜ ከዚህ ፈጽሞ ሊታገሰው የሚችለው ከማይመስለው ችግር
የሚወጣበትን መንገድ ስለሆነ የሚፈልገው ያኔ ትዳሩት መታመም ይጀምራል፡፡ ለሚነዘንዙትና ከጫንቃው
አንወርድም ላሉት የበዙ ኃላፊነቶች ሚስቱን እና ልጆቹን ተጠያቂ በማድረግ ቤት መምጣትም ያስጠላዋል፡፡
‹የወር ወጪ ስጠኝ፤› ፤ ‹ቤት ኪራይ ክፈልልኝ፤›፤ ‹አብረኸኝ ኑር› ምናምን የሚባል ጥያቄ የማታመጣበትን
ሌላ ገና የተፈለቀቀ የበቆሎ እሸት የመሰለችዋን ፈልጎ እሷኑ ማሳደድ ይጀምራል፡፡

እናም ሥራ ማለት እግዚአብሔር እምቅ-አቅማችንን ለማውጣት ሲል የፈጠረው መንገድ መሆኑን መረዳት


ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር በሥራ አማካይነት ወደ ውስጠኛው ክፍላችን ያለውን በር በመክፈት የሕይወትን
ኃላፊነቶች ለመወጣት በሚያስችል መልኩ የተቀበሩ ችሎታዎቻችንን እና ታለንቶቻችንን እንዴት
እንደምንጠቀም ያሳየናል፡፡ ሥራ እና ኃላፊነትን የመሸከም ችሎታ አብረው ይሄዳሉ፤ ለምን ቢባል ሥራ
አዳዲስ ፈተናዎችን እንድንቀበል፤ ለስኬት ብለን ችሎታችንን በማውጣት መውደቅም ቢኖር እንኳ ደፍረን
እንድንሄድ ያደርገናል ብሎም ሕልማችንን ወደ እውነታ ለመቀየር የሚያስችሉንን ኃላፊነቶች እንድንወጣም
ጭምር ይገፋፋናል፡፡

እግዚአብሔር በመሠረቱ እንድንሰራ እና እንድንሆን የፈጠረንን ሁሉ እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ነው


በየጊዜው በውስጥዎ ከተደበቀው ሀብት የበለጠውን ሊያሳዩ የሚችሉ ሥራዎችን የሚሰጠዎት፡፡ እግዚአብሔር
በትንሽ በትንሽ አና ቀስ በቀስ በውስጥዎ ያስቀመጠውን ሀብት እንዲያወጡ እያደረገዎት ነው፡፡ ይህ እንዲሆን
ግን የጥረቶቹ ተባባሪ ልንሆን ይገባል፡፡ ‹በነፃ ማግኘት›፤ ‹በአቋራጭ መክበር›፤ ‹አረፍ፤ ዘና ማለት›፤ ‹የምን
ሥራ!› የሚል አባዜና ክፉ በሽታን ግን ነቅለን ከውስጣችን ልናወጣ ይገባል፡፡ የሥራ ኃላፊነትዎን ተቀብለው
እግዚአብሔር ሥራ ላይ ያለዎትን አመለካከት እንዲቀይሩ እንዲያደርግዎ ሲፈቅዱለት እግዚአብሔር ሥራን
ለሕይወታችን እርካታ ዋንኛ መንስዔ ስላደረገው በሕይወትዎ ለውጥን ያያሉ፡፡ ሥራ እምቅ-አቅምዎን
ለማውጣት ዋናው ማስተር-ቁልፍ ነው፡፡

 መርሆች 

124 | P a g e
1. እግዚአብሔር ወይንም ሕይወትዎን ይመራል

2. ከገንዘብ ጋር መወገን መንፈሳዊ፤ ሥጋዊ፤ የስሜት፤ የገንዘብ እና ማኅበራዊ መዘዞችን ያስከትላል

3. እግዚአብሔር ጥሩ ሰራተኛ እንጂ ገብተው የሚወጡ ዓይነት ተቀጣሪ ወይንም አሰሪ እንዲሆኑ አይፈልግም

4. ሥራ ማለት ልናደርገው የምንችለውን የሚገልጽ ባረኮት ነው

5. ሥራ ሁልጊዜም ቢሆን ከእረፍት ይልቅ ግላዊ ዕድገትን እና እርካታን ያስገኛል

6. ሥራን ማቆም እግዚአብሔር ለእርስዎ ሕይወት ካወጣው ዕቅድ አካል አይደለም

7. እግዚአብሔር ለግላዊ ስኬት የሚያስፈልጉዎትን ነገሮች እንዲያገኙበት ሲል ሥራን ለእርስዎ ሰጥቷል

8. እምቅ-ኃይል ይወጣ ዘንድ ሥራን ይፈልጋል

ምዕራፍ 12
125 | P a g e
_____________________ _____________________

እምቅ-አቅም እና ለሥራ የምንሰጠው ቅድሚያ

እምቅ-አቅም ያለ ሥራ ፈጽሞ ሊወጣ አይችልም፡፡

ለመሆኑ እግዚአብሔር ማንን እንደሚጠቀም አስተውለው ያውቃሉ አዎን፤ እግዚአብሔር ባተሌ ሰዎችን
ይጠቀማል፡፡ እግዚአብሔር የእነዚህ ሰዎች ባተሌነት ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸውን ያሳያል ብሎ በማመኑ
ነው ለዚህ ውሳኔው የበቃው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ይኼንኑ የአባቱን ምርጫ አንፀባርቋል፡፡
የመጀመሪያዎቹን ተከታዮቹን ሲመርጥ አራት ዓሣ አጥማጆችን ነበረ ተከተሉኝ ያለው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሥራ ያለውን ማድላት የምናይበት ሌላኛው ማስረጃ ደግሞ በገሊላ እና ይሁዳ
በየመንደሩ ሳይቀር ሲሰብክ፤ በቤተ-መቅደሶች እና ምኩራቦችም ጭምር ሳይቀር ፈውስን ሲያደርግ የነበረበት
ጊዜ ነው፡፡ እጅግ በርካታ ሰዎች ችግር ገጥሟቸው እና በእርዛት ተቀምጠው ተመለከተና እረኛ ካጣ የበግ
መንጋ ጋር አመሳሰላቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በማዘኑም ደቀ-መዛሙርቱ ሠራተኞች ፍላጎታቸው ይሟላ ዘንድ
እንዲፀልዩ አደረገ፡፡

በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ
ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፤31; 2:2)

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሠራተኞች ያስፈልጉት ነበረ፡፡ ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ያመጣ ዘንድ
በውስጣቸው ያለውን ሁሉ ለማውጣት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ፈለገ፡፡ ደቀ-መዛሙርቱም እግዚአብሔር አንድ
ይኼን የሚሰራ ሰው ይልክላቸው ዘንድ እንዲፀልዩ ነገራቸው፡፡

126 | P a g e
ዘእግዚአብሔር ዛሬም አልተቀየረም፡፡ ሥራ ዛሬ ድረስ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳዩ ነው፡፡ በአንፃሩ የዓለምም
ፍላጎት እንዲሁ ሳይቀየር ቀርቷል፡፡ በችጋር፤ በቸነፈር፤ በእርዛት፤ በድንቁርና፤ ባለማስተዋል ወዘተ. የተሰቃየ
በቢልዮን የሚቆጠር ሕዝብ እግዚአብሔር በውስጣችን ያስቀመጣቸውን በማውጣት እንረዳው ዘንድ
ይጠባበቃል፡፡

ሆኖም እኛ ግን የእግዚአብሔርን መንገድ አንቀበልም፡፡ እኛ ያለ ሂደቱ ውጤት ማግኘት የሚል አባዜ ጠፍሮ
ይዞናል፡፡ ኃላፊነት የሚባል ነገር ሳንቀበልና ሸሽተን ሹመትና ዕድገት ግን ለምን ቀረብኝ የምንል ጉዶች ሆነናል፡፡
የሥራ ጊዜ ‹ወገቤን›፤ ሹልክ ብሎ መውጣት፤ ፈቃድ ማብዛት፤ የደመወዝ ጊዜ ግን አንካሳ ዶሮ ሳይቀድመን
መምጣት. . . ይኼ ሆኗል የሰው ልጅ መገለጫ፡፡ ‹‹ኃላፊነትን ሰጥቻችኋለሁ፤ ችሎታም እንዲሁ፡፡ ይልቅ እስኪ
አሁን ምን ማድረግ እንደምትችሉ ሥራ ሰርታችሁ እዩት፤›› ያለ አምላክ ይኸው ሥራ የሚባል እንደ ጎን
ቅማል ሆኖብን ጊዜያችንን የባጥ የቆጡን በመቀባጠርና ተዘፍዝፎ በመዋል ስናሳልፍ አዝኖ ይመለከታል፡፡
ከጀርባችን ቆሞ የሚከታተል፤ ሰዓት ሰጥቶ፤ ሥራን ቆጥሮ የሚረከብ በአራዳ ቋንቋ ‹ሀርደኛ› የሚሉት ዓይነት
አለቃ ከሌለ ማሾፍ የሚለውን አባዜ እንተው፡፡ እግዚአብሔር አዳም በኤደን ገነት ውስጥ ይሰራ ዘንድ
ሲያነጋግረው ራሱ አስቦ በኃላፊነት ስሜት እንዲሰራ እንጂ ካቦ፤ ተቆጣጣሪ፤ ማኔጀር፤ የበላይ ኃላፊ ወዘተ.
አልመደበለትም፡፡

እግዚአብሔር ተፈጥሯዊ የሆነውን የመሥራት ፍላጎታችንን እንረዳው ዘንድ ይጠብቃል፡፡ ያለ ሥራ ትልቅነት


ከቶም ሊገኝ አይችልምና የሃይማኖት ተቋማትም ቢሆኑ በሰው ልጅ ዘንድ አሁን ደብዛው ሊጠፋ የደረሰ
የሚመስለውን የእግዚአብሔርን የሥራ ስሜት ለመመለስ ተግተው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ እግዚአብሔር
ስለሰራ እና እንድንሰራ ስለፈጠረን መስራት አለብን የሚባለውን እውነታ መቀበልም ይኖርብናል፡፡

 እግዚአብሔር ሰራ 

እግዚአብሔር ሥራን ቅድሚያው ያደረገው የማይታይ የነበረውን ዓለም እንዲታይ በንግግሩ ባደረገ ጊዜ ነበረ፡፡
ምንም ነገር ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ነበረ፡፡ ዛሬ የምናየው ሁሉ በእግዚአብሔር ውስጥ ነበረ--ግን
የማይታይ ሆኖ እግዚአብሔር ትዕዛዝ እስኪሰጠው ቆይቷል፡፡ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለማስጀመር
ስራውን አሀዱ ባይል ዛሬ የምናወቀው ነገር ሁሉ ጭራሹኑ ባልነበረ ነበረ፡፡ ዓለም ውስጡ ተቀብራ ትቀራለች፡፡
ሆኖም እግዚአብሔር ግን ልጆቹን በሥራ መውለድን ፈለገ፡፡ እምቅ-አቅሙን በመጠቀም እና በከፍተኛ ጥረት
በውስጡ የነበረውን ወደ እውነታ ቀየረው፡፡

እግዚአብሔር ይህችን የምንኖርባትነ ዓለም ለመፍጠር ሲል የሰራው ነገር ልናጤነው የሚገባን ነው፡፡
የክዋክብትን ቁጥር በመወሰን ስም አወጣላቸው (መዝሙረ ዳዊት 147፤4 ን ይመልከቱ)፡፡ ሰማይን በደመና
ሸፍኖ፤ መሬትን በዝናም እንድትርስ አድርጎ፤ በሜዳ ላይ ሣር እንዲያድግ አደረገ (መዝሙረ ዳዊት 147፤8 ን

127 | P a g e
ይመልከቱ) ፡፡ ተራሮችን በኃይሉ ሰራቸው (መዝሙረ ዳዊት 65፤6 ን ይመልከቱ)፡፡ የምድርን ምጥማቆች ሰራ
(መዝሙረ ዳዊት 104፤4 ን ይመልከቱ)፡፡ ጨረቃ በሱ ትዕዛዝ ወቅቶችን ታሳያለች ፀሐይ ደግሞ ጊዜን (መዝሙረ
ዳዊት 104፤19 ን ይመልከቱ)፡፡ የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ እጅግ ጥልቅ፤ ሰፊ እና ድንቅ ከመሆኑ የተነሳ
ሥራውን ካጠናቀቀ በኋላ ተመልክቶ ሁሉም ጥሩ ነው አለ፡፡

እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ
ቀን።እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 1፤31; 2:2)

እግዚአብሔር ዓለምን በምኞት፤ በማለም ወይንም በግምት አልፈጠራትም፡፡ እውነት ለመናገር እግዚአብሔር
እጅግ ተጨንቆና ተጠቦ፤ ለፍቶም ስለሰራ ማረፍ አስፈለገው፡፡

እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። እግዚአብሔርም


ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።

(ኦሪት ዘፍጥረት 2፤2-3)

እረፍት ግን በጥልቅ ከታሰበበት፤ ጊዜን፤ ጉልበትን እና የአዕምሮ ጥበብን እጅግ ከሚጠይቅ አድካሚ ሥራ በኋላ
እንጂ እዚህ ግባ የማይባል ተሰርቶ ሁሉ ማረፍ አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሔር በፍጥረት ወቅት የሰራው ግን
እጅግ ከባድ ስለነበረ እረፍት የግድ አስፈለገው፡፡

እኛ የሰው ልጆች እጅግ በሚያሳዝን እና በሚያሳፍር መልኩ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ሲባል ሥራ ከሚባል
ነገር መገላገል መስሎ ሁሉ ይሰማናል፡፡ ከዚህ በላይ ምን ስህተት አለ! እግዚአብሔር እኮ ሥራን አክብሮታል፤
ወዶታል፡፡ እግዚአብሔር ከሁሉን ቻይ ማንነቱና ውስ አዳዲስ ነገሮችን በማውጣት ሐሴት ያደርጋል፡፡ እኛ
እንድንሰራም ይፈልጋል፡፡

 እግዚአብሔር እንድንሰራ የፈጠረን ስለመሆኑ 

እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ እና የዔደን ገነትን አደራጅቶና በአታክልቶች ሞልቶ ከጨረሰ በኋላ አዳምን
በገነት አኑሮ የሚሰራውን ሥራ ሰጠው፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ከመፍጠሩ በፊትም ቢሆን በአዕምሮው
ሥራን አቅዷል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ አምላክ ሰማይንና ምድርን ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት
ይህ ነው። የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም ነበር፤ እግዚአብሔር

128 | P a g e
አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥
የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት
እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

(ኦሪት ዘፍጥረት 2፤4-7)

እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥረው በዓሦች፤ በባሕር፤ በአይ ላይ በራሪ በሆኑ አዕዋፋት እና በምድር ላይ
በሚንቀሳቀሱ እንስሳት ላይ ሁሉ የበላይ እንዲሆን ነበረ፡፡ ሆኖም የበላይ የሚለው ቃል በሥልጣን ማማ ላይ
ሆኖ ሌሎች እኛን እንዲታዘዙ በሚል ብዙዎቻችን የምንረዳው ቢሆንም እግዚአብሔር ያሰበው ግን ያ
አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር መግዛትን ወይንም የበላይ መሆኑን ከሥራ ጋር እኩል ዋጋ ይሰጠዋል፡፡ እግዚአብሔር
ለአዳም የሰጠው ሥራ ሁሉ ማለት ነው፡፡ የዔደን ገነትን መንከባከብና መጠበቅ ትልቅ ልፋትና ሥራን የጠየቀ
ነበረ፡፡ ለእንስሳት ሁሉ ስም ማውጣትም ስራ ሆነ፡፡ ምድርን መግዛትም እንዲሁ ልፋትና ሥራን የጠየቀ ነበረ፡፡
በመሆኑም ሥራ የአዳም ሕይወት ውስጥ እጅግ ትልቅና ወሳኝ ቦታ ያዘ፡፡

እንግዲህ ለእኔና ለእናንተም ይኸው እውነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘጥ ዘጥ ለማለት፤ ገባ ወጣ ለማለት፤


ለማረፍ፤ ለመዝናናት አልፈጠረንም፡፡ ፊርማ እየፈራን ሰዓት እንድንጠብቅ ወይ ደግሞ ዓይኑን
የሚያጉረጠርጥ፤ የት ገባችሁ የት ወጣችሁ የሚል አለቃ ስላለ እንድንሽቆጠቆጥም አይደለም የፈጠረን፡፡

እግዚአብሔር ጥረት አድርገው ሥራዎትን በማጠናቀቅ ስኬትን እንዲያገኙ ነው ወደዚህች


ምድር ያመጣዎት፡፡

ሥራ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠው ማንኛውም ኃላፊነት ሥራን ይጠይቃል፡፡
ኖህ መርከቧን ዝግጁ ለማድረግ መስራት ነበረበት (ኦሪት ዘፍጥረት 6 ን ይመልከቱ)፡፡ ዮሴፍ ለሰባት ዓመታት
ያህል በችጋርና ቸነፈር ለኖረው የግብጽ ሕዝብ የሚበቃውን ለማቅረብ ለፍቷል (ኦሪት ዘፍጥረት 41፤41 ን
ይመልከቱ)፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም በሥራ ነበረ ቤተ-መቅደሱን ያቆመው (መጽሐፈ ዜና ዋዕል ካልዕ 2፤4 ን
ይመልከቱ)፡፡ እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር የጠየቃቸውን በማድረግ የሕይወታቸውን ዓላማ ነው ለስኬት
ያበቁት፡፡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ለማከናወን ፈቃደኛ በመሆናቸው ለብዙዎች ባረኮትን አስገኙ፡፡

 መሥራት ያስፈልግዎታል 

ሥራ በመሠረቱ ክብር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁላችንንም ሲፈጥር ለሕይወታችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች
ሁሉ በሥራችን እናገኝ ዘንድ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ አልሰራም ሲሉ የሕይወት ዓላማዎትን የሚያሳኩበትን
መልካም አጋጣሚ ያባክኑታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ልክ እሱ እንደሚያደርገውና እንደሚሰራው እንዲሆኑ
ነው የፈጠረዎት፡፡ እምቅ-አቅምዎን ለማውጣት መስራት ግድ ይልዎታል፡፡

129 | P a g e
በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፤

ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ።

(መጽሐፈ ምሳሌ 14፤23)

የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፤ ችኵል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።

(መጽሐፈ ምሳሌ 21፤5)

እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥
በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ
እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።

(1 ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፤11-12)

ሥራ ለሰሪው የገንዘብ ኃላፊነትን እንዲወጣ በማድረግ ትርፍን ያመጣለታል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስን


በምሳሌነት ብንወስድ ድንኳን በመሥራት ነበረ ይኼንን ኃላፊነቱን የሚወጣው (አንደኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡
6-9 ን ይመልከቱ)፡፡ ጳውሎስ በሌሎች ላይ ሳይንጠላጠል በተቻለ መጠን ሰርቶ ተጠቅሟል፡፡

ይኸው ነው ለእርስዎም የሚፈለገው፡፡ በሌሎች ላይ ሸክም እንዳይሆኑ፡፡ ለራስዎትና ለቤተሰብዎ መሆን


ይችሉ ዘንድ ሥራ አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ተረጋግተው ሥራ ሊኖርዎ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ዳቦ
ለመብላት የግድ ሥራ እንደሚያስፈልግዎ ወስኗል፡፡

. . . እምቅ-አቅምን በመግለጽ

እግዚአብሔር ከዚህ በተጨማሪም ሥራ እምቅ-አቅማችንን ማሳየት እንዳለበት ወስኗል፡፡ ሁሉም ሥራ


ትርፍን የሚያስገኝ ቢሆንም የሥራ ሽልማት ወይንም ምንዳ ግን ሁልጊዜ የገንዘብ አይደለም፡፡ ለምሳሌም
በጣም እየለፉ ግን እምብዛም የገንዘብ ትሩፋት እንደሌለዎ ሊሰማዎ ይችላል፡፡ የሥራዎን ትርፍ ለማግኘት
ጠንክረው መስራትዎን ይቀጥሉ፡፡ እግዚአብሔር አይዋሽም፡፡ ማንም ገንዘብ የማይከፍልዎ ቢሆንም እንኳ ምን
ለመስራት እንደሚችሉ የሚያውቁበት በመሆኑ ሥራዎ ይከፍልዎታል፡፡ ክብር እየተገባን ባናገኘው ይሻላል--
ክብር ሳይገባን ከምናገኝ፡፡

. . . የሥራን ትሩፋቶች በመግለጽ

130 | P a g e
ሥራ ታለንቶቻችንን፤ ክህሎቶቻችንን እና ችሎታዎቻችንን ለማውጣት የሚረዳ በመሆኑ ከክብርም
ይበልጣል፡፡ ከሚከፈለን ገንዘብም በላይ ነው፡፡ ለገንዘብ መሥራትዎን ሲያቆሙ የሥራን ባረኮት በሚገባ
ይረዱታል፡፡

የሠራተኛ ራብ ለእርሱ ይሠራል፥ አፉ ይጐተጕተዋልና።

(መጽሐፈ ምሳሌ 16፤26)

. . . በስኬት ለሐሴት ለማድረግ ዕድል በመስጠት

ለሥራ ቁርጠኝነት ካለን ሰርተን በምናገኘው ክፍያ ከምንረካው በላይ እንድንደሰት የሚያደርገንን ምልከታ
እንጎናጸፋለን፡፡ በዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ክፍያችን ከምንሰራው ጋር የማይመጣጠን ቢሆንም እንኳ እንደሰታለን፡፡
አሰሪዎችና አለቆች በሥራ ለተጠመዱት ሰዎች የበለጠ ሥራን የሚሰጡት እነዚህኞቹ ለመስራት ፈቃደኛ
መሆናቸውን በማወቃቸው ነው፡፡ በመሆኑም ማደግ ከፈለጉ በሥራ ይጠመዱ፤ ምርታማም ይሁኑ፡፡ ለሻይ
እረፍት፤ ለምሳ ሰዓት እና ከሥራ ውጭ ላሉ የመዝናኛ ሰዓታት መኖርን ያቁሙ፡፡ ሥራዎትን ተቀብለው
እስከሚችሉት ድረስ ይከውኑ፡፡ ሲሰሩ ታዲያ ክፍያ ሊያገኙ ስለሆነ ሳይሆን ምን ድረስ ችሎታ እንዳለዎ
ለማወቅ ሲሉ ይሁን፡፡ በዚህ ዓይነቱ ጥረትዎ ወዲያውኑ ዓይን ውስጥ ላይገቡ ይችላሉ ሆኖም ማደግዎ ግን
የማይቀር ነው፡፡ ጥራት ያለው ሥራ ሁልጊዜም ቢሆን ሠራተኛውን ነው የሚጠቅመው፡፡

. . . ለራስ ያለን ክብር በማጎልበት

በመጨረሻ ሥራ ለራስዎት የሚሰጡትን ግምት እና ክብር በማጎልበት ትርፍ ያስገኝልዎታል፡፡ ዋጋ-ቢስ የመሆን
ስሜት ካደረብዎ ሥራ ይኑርዎ፡፡ ራስዎን በሥራ ይጥመዱ፡፡ አንድ የሚሰሩት ነገር ሲኖር ስለራስዎት ጥሩ የሆነ
ስሜት ብዙም ሳይቆይ ይኖርዎታል፡፡ ሥራ በአካል፤ በመንፈስ እና በስሜት ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡

. . . ሥራ ለሌሎች ትሩፋትን ያስገኛል

ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።

(ወደ ሮሜ ሰዎች 12፤13)

ሥራ ሌሎችን ለማገዝ የምንችልበትን መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በ ማቴዎስ ወንጌል ላይ
ሌሎችን ለመርዳት ያለን ፈቃደኝነት ለክርስቶስ ያለን ታማኝነት መለኪያ እንደሆነ ተገልፆ እናገኛለን

131 | P a g e
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25፡31-46 ን ይመልከቱ)፡፡ የቤተክርሰሐዋርያው ጳውሎስ የቆሮንጦስ
ቤተክርስትያን ለሌሎች ትናንሽ እህት ቤተክርስትያናት እገዛ ለማድረግ በመፍቀዷ ባመሰገናት ጊዜ
የማጋራትን ጥቅም አጽንዖት ሰጥቶታል 2 ኛ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች 8-9 ን ይመልከቱ)፡፡ የቤተክርስትያን ሰዎች
ቆጥበው፤ ተንሰፍስፈው ሳይሆን በለጋስነት መስጠት እንዳለባቸው ተናግሯል፡፡ ብዙ ሲሰጡ ባላቸው ላይ
እንደሚጨመርላቸውም ጭምር ገልጧል፡፡

ይህንም እላለሁ። በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።
እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።ለዘሪ
ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥
የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤ በእኛ በኩል ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ
በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ትሆናላችሁ።

(2 ኛ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች 9፤6-7፤ 10-11)

 ለመሆኑ ማን ነው ሌባው 

ሌባ ማለት ምን ዓይነት ሰው ነው የሚል ጥያቄ ባነሳልዎ ምናልባትም ቤትዎ ገብዎ አንዳንድ ነገር
የወሰደብዎትን ሰው ሊገልጹ ይችላሉ፡፡ ይኼ ትክክለኛ ትርጓሜ መሆኑ ባያከራክርም ሌባ ማለት የሱ
ያልሆነውን ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ አድብቶ የሚወስድ አይደለም፡፡

ብዙዎቻችን ሥራ እንሄዳለን፤ ግን በአለቆቻችን ላይ ማታለል እንፈጽማለን፡፡ ለምሳሌም ሥራ አርፍደን


እንገባለን፤ ለምሳሌም ለምሳ ወጥተን ዘግይተን እንገባለን፤ ከመውጫ ሰዓት ባልተገባ መልኩ ቀደም ብለን
እንወጣለን፡፡ ከዚህ ሌላ አንድ እሽግ ሙሉ ወረቀት ለግላችን ወደ ቤታችን ይዘን የምንሄድ፤ በፎቶ ኮፒ ማሽን
ለግላችን ብዙ ገጽ የምንጠቀም፤ ስልክ በውሃ የሚቆጥር ይመስል ስንንዛዛና የባጥ የቆጡን ስንቀባዥር
የምንውል፤ በሥራ ሰዓት የግል ሥራችንን የምናከናውን. . . ኧረ ስንቱ! እንዲህ ዓይነቶቹ ድርጊቶች ቤት
ሰርስሮ ከሚገባው ሌባ ድርጊት ምንም አይተናነሱም ለምን ቢባል የሱም ሆነ የኛ ሥራ ሌላ ሰው የለፋበትን
እና የራስ ያልሆነን ነገር ተጠቅሞ የራስን ጥቅም ማግኘትን ይመለከታሉ፡፡

ነገሩን ሰፋ አድርገን ስንመለከተው ሌባ ማለት የራሱን ፍላጎት ለማሟላት በራሱ የሚገባውን ለማድረግ ሰነፍ
በመሆኑ በሌላው ምርት ወይ ሀብት የሚጠቀም ነው፡፡ መስራት እየቻሉ የማይሰሩ ከሆነ ሰርተው ከሚያገኙ
ከሌሎች ይጠቀማሉ፡፡ እርስዎ ቢሰሩ የሚያገኙትን እነርሱ እንዲያመጡልን እናደርጋለን፡፡ የማይሰሩ ከሆነ ሌባ
ነዎት፡፡ በሥራ ሳይሳተፉ ነገር ግን የሥራውን ፍሬ መውሰድ ሌብነት ነው፡፡

መስራት እየቻሉ የማይሰሩ ከሆነ ሰርተው ከሚያገኙ ከሌሎች ይጠቀማሉ፡፡

132 | P a g e
ቀኑን ሙሉ ሜዳ ኳስ ሲራገጥና ፀጉሩን አንጨፍርሮ ጥርሱን እየፋቀ አላፊ አግዳሚውን ሲለክፍ የቆየ አለሌ
ጎረምሳ እናቱ ለፍተው ያፀዱትን ቤት ቢያበላሸው ይኼ ሌባ ነው፡፡ ጉልበታቸውን ሰርቋላ! በመፎረፍ እና
ትምህርቱን በሚገባ ባለመከታተል ሲወሰልት የቆየ ልጅ ድንገት ደግሞ ቤት መዋል ጀምሮ በሥራ ማንንም
ሳያግዝ ቤተሰቦቹ የለፉበትን ኩሽና ገብቶ ቢቀማምስ ይኼም ሌብነት ይባላል፡፡

ነገር ግን ሌብነት በሌሎች ጥረትና ልፋት ለመጠቀም ከመሞከርም ይዘላል፡፡ እርስዎ መወለድ ያለባቸውን
ልጆች ፀንሰዋል፡፡ እግዚአብሔር ለዓለም እንዲያጋሩ የሚፈልግብዎ ታለንቶች አሉዎት፤ ችሎታዎችም፡፡ ነገር
ግን የእግዚአብሔርን የሥራ ትርጓሜ ካልተረዱ በቀር ችሎታዎቹ አይታዩዎትም፡፡ እርስዎ ምንም ሳይሰሩ
እንዲሁ ጊዜ ከገደሉ እምቅ-አቅምዎን አያዳብሩም፡፡

 ድህነት ጠንክሮ በመሥራት ይፈወሳል 

እስኪ የሰማይ አዕዋፋትን ይመልከቱ፡፡ እግዚአብሔር የሚመገቡትን ቢያዘጋጅላቸውም እነሱ ፈልገው


አግኝተው ነው የሚመገቡት፡፡ ከመሬት ቆፍረው ያወጡታል፡፡ እርስዎምጋ እንዲህ ነው፡፡ በሕይወትዎ እርካታን
እና ስኬትን ያገኙባቸው ዘንድ ብዙ ታለንቶችን በውስጥዎ አስቀምጧል፡፡ እርካታ ግን በሥራ ነው የሚገኘው፡፡
ቁጭ ብለው እርካታ እንዲመጣ ቢጠብቁ በታአምር አይመጣም፡፡ ሥራ ማለት የተሳካ እና የተትረፈረፈ
እምቅ-አቅምዎንም የሚያወጣ ሕይወት እንድንመራ ከእግዚአብሔር የተሰጠን መሣሪያ ነው፡፡ እግዚአብሔር
እምቅ-አቅሙን ፍጥረትን ሲያደርግና ያለውን ሲያወጣ፤ አዳምም ያንኑ እንዲሰራ ሲነግረው የሥራን
አስፈላጊነት በግልጽ አስቀምጧል፡፡

133 | P a g e
 መርሆች 

1. እግዚአብሔር ሰራ፤ እርስዎም እንዲሰሩ ይፈልጋል፡፡

2. በምድር ላይ የበላይ ለመሆንና ምድርን ለመግዛት ሥራ አስፈላጊ ነው፡፡

3. አልሰራም ሲሉ እምቅ-አቅምዎን ለማሟላት ዕድሉን ያገኛሉ፡፡

4. አለመስራት ከስርቆት ተለይቶ አይታይም፡፡

5. እርስዎ በስንፍና ጊዜዎትን ሲገድሉ ራስዎን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይዘርፋሉ፡፡

6. ድህነት ጠንክሮ በመሥራት ፈውስ ያገኛል፡፡

134 | P a g e
ምዕራፍ 13

_____________________ _____________________

ሥራን መረዳት

ለስኬት መስራት ለገንዘብ ከመስራት እጅግ ይልቃል፡፡ አገልግሎት የምንሰጥበት የሥራ መስክ ዋናው
ዓላማው ሥራ እንጂ ገንዘብ አይደለም፡፡

ታሪክን የኋሊት ሄደን በሚገባ ብንመለከት በሁሉም አገሮች ማለት ይቻላል ታላላቅ ግዛቶች የተገነቡት ደምና
ላብ በፈሰሰበት ትልቅ ጉልበት ነው--ያ ጉልበት በውዴታም ይሁን በግዴታ የተገኘ ቢሆንም፡፡ የግብጽ፤ ሮማ፤
ግሪክ እና አሲሪያ ሥልጣኔ በጉልበት ሥራ እንዲሰሩ በተደረጉ ጠንካራ ሰዎች ላይ የተገነባ መሆኑን እንረዳለን፡፡
አሜሪካ በባርነት ጉልበት ነበረ የተገነባችው፡፡ ሠራተኞቹ የቱንም ያህል ተነሳሽነት ቢኖራቸው ትልቅነትና
ስኬት የሚገኘው ግን ከሥራ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

የምርታማነትን ኃይል ዛሬ ከሠራተኛ ማኅበራት መረዳት እንችላለን፡፡ ማኅበራት ሠራተኞችን ስለሚቆጣጠሩ፤


ሠራተኞች ደግሞ ምርታማነትን ይቆጣጠራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች አገርን፤ መንግሥትን ወይ ኢኮኖሚን ማድቀቅ
ይችላሉ፡፡ ምርታማነት በእጁ ያለ ሀብትንም እንደሚቆጣጠር አሌ የማይባል ሃቅ ነው፡፡

135 | P a g e
ለመሆኑ አገራት ጥንካሬና ሀብታቸውን እንዴት እንደሚለኩ ያውቃሉ እነዚህን ሁለቱን በካዝናቸው ውስጥ
ባለው ገንዘብ መጠን ብቻ ሳይሆን በጥቅል ብሔራዊ ምርት (Gross National Product) ይለኩታል፡፡
በመሆኑም የአንድ አገር አንፃራዊ ጥንካሬ ወይንም ድክመት ኢኮኖሚው ምን ያህል ሥራ ፈጠረ በሚለው እና
በአጠቃላይ ምርታማነት ነው የሚለካው፡፡ የምርታማነት ኃይል ሥራ ነው፡፡ ሰዎችን በግድ ማሰራት
ስለማይቻል አንድ አገር ሥራ የማይሰራ ሕዝብ ካለባት ዘለዓለም አለሟን ማከክ ብቻ ሳይሆን ወደ ውድቀት
አዘቅት ትገባለች፡፡ መንግሥት የፈለገውን ዓይነት ሕግ ቢያወጣ የሥራ መንፈስን ግን በማስገደድ መፍጠር
አይችልም፡፡ ሕዝብ ደግሞ በመደዳ፤ በአንድ ዓይነት ወርድና ቁመት የተሠራ የፋብሪካ ብርጭቆ ባለመሆኑ
ሳይጠይቅ፤ ሳይጠራጠርና ሳይቃወም እንዲሁ አይገዛ ነገር፡፡ ሰዎች ያለ ምንም ጥቅምና አንድ ነገር ሳያገኙ
እንደሚሰሩ ከተረዱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ማመጻቸው አይቀርም፡፡ ተስፋ ሲቆርጡም የራሳቸውን እጣ ፈንታ
በራሳቸው ለመወሰን ይሄዳሉ፡፡ በሥራ ውስጥ በመንግሥት፤ በቤተክርስትያናት
ወይንም በሌላ ማኅበራዊ ተቋም ውስጥ ካለው በላይ ኃይል አለ ለምን ቢባል ሰራተኛው ምርታማነትን
ይቆጣጠራል፤ ብሎም ደግሞ የሕዝቡን ዕጣ ፈንታ፡፡

የሙሴ እና የፈርዖን ታሪክ ይኼንኑ ዕውነታ ነው የሚያሳየው፡፡ ፈርዖን ሙሴንም ሆነ የእስራኤላውያንን


አምላክ የማይፈራ፤ ልቡ እጅግ የደነደነ ንጉሥ ነበረ፡፡ ይልቅ እሱን ያስፈራው ግዙፉን የእስራኤልን ሕዝብ
የሚያህል የሥራ ኃይል ማጣቱ ነው፡፡ በመሆኑም ሙሴ ለሶስት ቀናት ለእግዚአብሔር መስዕዋት ለማቅረብ
በበረሐ ጉዞ ይደረግ የሚል ሀሳብ ባቀረበ ጊዜ የግብፁ ንጉሥ፤

አንተ ሙሴ አንተም አሮን፥ ሕዝቡን ለምን ሥራቸውን ታስተዋላችሁ? ወደ ተግባራችሁ ሂዱ አላቸው። ፈርዖንም። እነሆ
የምድሩ ሕዝብ አሁን በዝቶአል፥ እናንተም ሥራቸውን ታስፈቱአቸዋላችሁ አለ። ፈርዖንም በዚያን ቀን የሕዝቡን
አስገባሪዎች ሹማምቶቹንም እንዲህ ሲል አዘዘ። እንደ ወትሮው ለጡብ ሥራ ደግሞ ገለባ ለሕዝቡ አትስጡ፤ ነገር ግን
እነርሱ ሄደው ገለባ ይሰብስቡ። ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ
አታጕድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ። ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ እያሉ ይጮኻሉ። እርሱንም ያደርጉ ዘንድ
በሰዎች ላይ ሥራው ይክበድባቸው፤ ከንቱ ቃልም አያስቡ።

(ኦሪት ዘፀዓት 5፤4-9)

ሕዝብ አልሰራም ቢል አገር ጀርባዋ ጎብጦ ይሰበራል፡፡ ሶቪየት ኅብረት እና ሌሎች በሶሻሊስቱ ጎራ የነበሩ
አገራት በላብ አደሩ ላይ እጅግ በመመካታቸው የቱን ያህል በወርቃማ ዘመኖቻቸው እንዳደጉ እናስታውሳለን፡፡
ዛሬ በዓለም ትልቅ ደረጃ ይዘዋል በመባል ይታወቁ የነበሩ አንዳንድ ኩባንያዎች ለመውደቃቸው ቦርድ ወይ
ፕሬዚዳንት አይደሉም ተጠያቂ፡፡ ጋሪ ገፊው፤ ሞተር አዳሹ፤ ራፖር ፀሐፊው. . . ባጠቃላይም ተራውና
ብዙውን ቁጥር የሚይዘው ሠራተኛ ነው፡፡ ሕዝብ አልሰራም በማለቱ አገሮች እየወደቁ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም
ሥራን በተመለከተ ያለንን እምነት እና አስተሳሰብ ልንቀይር ግድ ይለናል፡፡ በዚህ ረገድ ብቸኛው ተስፋችን

136 | P a g e
የእግዚአብሔርን የሥራ ትርጓሜና ምልከታ ፈልገን በማግኘት በሕይወታችን ሊያመጣቸው የሚፈልጋቸውን
ጥቅሞች መጋራት ነው፡፡

 የእግዚአብሔር የሥራ ምልከታ 

እግዚአብሔር ለሥራ የሚሰጠው ትርጉም እኛ ከምንሰጠው እጀጉን ይለያል፡፡ ሥራ መስራት ማለት የሥራ
ገበታ አለን ወይንም ተቀጠርን፤ ቢዝነስ አለን ከሚለው ይለያል፡፡ ሥራ መስራት እምቅ-አቅምን ያወጣል፡፡
ተቀጥረን ስንሰራ ወይ የራሳችን ሥራ ሲኖረን ግን ዞሮ ዞሮ ወይ ደመወዝና ጥቅማ-ጥቅም ወይ ትርፍ ነው
የምናገኘው፡፡ ሥራ መሥራት ሁሌ የገንዘብ ምንዳን አያስገኝም፡፡ ሥራ መስራት የሚመነጨው ለዓለም ሀብት
እና ደኅንነት ራሳችንን በመስጠት አስተዋፆ ለማድረግ ካለ ፍላጎት ነው፡፡ ‹‹ባልሰራ ምን ሊመጣብኝ!››
ከሚለው አስተሳሰብ እንድንወጣ ያደርገናል፡፡

ሥራ መስራት እምቅ-አቅምን ያወጣል፡፡ ተቀጥረን ስንሰራ ወይ የራሳችን ሥራ ሲኖረን ግን ዞሮ


ዞሮ ወይ ደመወዝና ጥቅማ-ጥቅም ወይ ትርፍ ነው የምናገኘው፡፡

በጣም ብዙውን ጊዜ ሥራን ከሚገባ በላይ የተራቀቀ እናደርገዋለን፡፡ የሆነው ሆኖ ግን ልፋት ያስፈልገናል፡፡
ማማጥ፤ መልፋት እና ላብ ማፍሰስን ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር፤

‹‹ስድስት ቀናት ወደ ሥራ ትሄዳላችሁ፤›› አላለም፡፡

‹‹ስድስት ቀናት ትሰራላችሁ›› ነው ያለው፡፡ ፈርሞ መግባት፤ ሻይ ሰዓት መውጣት፤ በዚያው መቆየት ወዘተ.
ምንም እንደማይጠቅም ስለሚያውቅ ነው ይኼንን ያለው፡፡ በሥራ ላይ ያለንን አመለካከት እስካልቀየርን ድረስ
የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ አንከተልም፡፡

መልፋትና መሥራት ሲባል ታዲያ ተፍ ተፍ ማለትና ነገሮችን ከማከናወን ይልቅ የተደበቀውን የውስጣችንን
ማውጣትን ይመለከታል፡፡ ያረገዙትን ካልጣሩ፤ ካላማጡና ካልወለዱ ይዞ እንደመሞት ነው--ሥራ ገብቶ
ተጎልቶና ውሎ መውጣት፤ ሱቅ ከፍቶ ዝምብ እሽ ብሎና ቆጠራ አካሂዶ ብቻ መውጣት፡፡ የፋብሪካ አዛዥ፤
የቤት እመቤት፤ የፍርድ ቤት ጠበቃ፤ መካኒክ፤ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ፤ የመረጃ ቴክኖሎጂ ባለሙያ ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ሚሊየነር፤ ብዙ ኪራይና ጥቅማ-ጥቅም የሚያገኙ ሊሆኑም ይችሉ ይሆናል፡፡ የፈለገውን ይሁኑ
እንጂ ሥራን የግድ ለሕይወትዎ አስፈላጊ እንደሆነ አድርገው ነው መስራት ያለብዎ፡፡

በእግዚአብሔር አሰራር መሠረት ሁሉም ሰው መስራት ያስፈልገዋል፡፡ እርስዎ መስራት ያስፈልግዎታል፡፡


እምቅ-አቅምዎን ለማውጣት ያለዎ ክህሎት እግዚአብሔር የሰጠዎትን ሥራዎች ለማከናወን ከሚያደርጉት
ጥረት ጋር ቁርኝት አለው፡፡ ሥራ አልሰራም ቢሉ የእግዚአብሔርን አምሳያ ለመግለጽ እና በውስጥዎ ያለውን
ፍሬ ለማፍራት ያለዎ እምቅ-አቅም ዋጋቢስ እና ተቀምጦ የሚባክን ብቻ ይሆናል፡፡ ያለ ሥራ ምንም ፍሬ

137 | P a g e
የለም፡፡ እግዚአብሔር ሊሰጠዎ የሚፈልገው ባረኮት ሁሉ ይቀርብዎታል፡፡ አልሰራም ማለትዎ ከእግዚአብሔር
የፍጥረት ሥራ ጋር ተባባሪ እና አካል ለመሆን ያለዎትን መልካም አጋጣሚ ያበላሸዋል፡፡

 የእግዚአብሔር የሥራ ምልከታ 

በመሠረቱ የእርስዎን ድኅነት ወይንም ሀብታምነት የሚወስነው ምን ያህል ሪሶርስ አለዎ የሚለው ሳይሆን
ይልቅ ባለዎ ምንም ያህል ሪሶርስ የቱን ያህል ሥራ ማመንጨት ችለዋል የሚለው ነው፡፡ የእርስዎ ለመስራት
ፈቃደኛ መሆን እምቅ-አቅምዎን በማውጣት ረገድ ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ ሥራ በሌለበት እምቅ-አቅም
ቢኖር ድኅነት ነው፡፡ ዋናውና ትልቁ ጥያቄ ምን ያህል እምቅ-አቅም አለዎት ሳይሆን እሱን ለማውጣት ምን
ያህል ሥራ ለመስራት ፈቃደኛ ነዎት የሚለው ነው፡፡ እምቅ-አቅም እኮ ማንም ዘንድ አለ--ቀደም ሲል
እንደገለጽነው ተቀምጦ ያለ ክህሎት፤ የተደበቀ ጥንካሬ፤ ያልተጠቀምንበት ሪሶርስ---ሁሉም ሰው ዘንድ አለ፡፡
ችግሩ እምቅ-አቅም ያለው ሁሉ ለማውጣት የማይሰራ ከመሆኑ ጋር ይያያዛል፡፡

ሥራ ሪሶርሶቻችንን በእጥፍ ድርብ ለመጨመርም ሆነ ለመንከባከብ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ባለችዎ ትንሽ ነገር
ታማኝ ከሆኑ እግዚአብሔር ብዙን ለመቆጣጠር ኃላፊነቱን ይሰጥዎታል፡፡ ግን ሊሰጥዎ የሚችለው እርስዎ
ለመቀበል ፈቃደኛ በሆኑት መጠን ነው፡፡ በትንሽ ነገር ታማኝ ሆኖ መገኘት የማታ የማታ በትልቅ ሪሶርሶች
ላይ ለማዘዝ መታጨትን ብሎም ዕድገትና ሹመትን ያመጣል፡፡ አንድ ሁላችንንም የሚያስማማ ነገር አለ፡፡
በደምብ ከተገለፀና ከተባለ ይልቅ በደምብ የተሰራ ሁሌም ይሻላል፡፡ እግዚአብሔር አምኖ በውስጣችን
ያኖረውን--ትልቅም ይሁን ትንሽ--ለማብዛት ሥራ ወሳኝ ሚና አለው፡፡

 ሥራ አካባቢያችንን ያስጠብቃል፤ በውስጡ ያለው እንዲወጣም ያደርጋል

ሰዎች ልክ እንደ እነሱ ከሚያስቡና ከሚያደርጉ ሰዎች ዘንድ መገኘት ደስ ይላቸዋል፡፡ ይኼ ደግሞ ሥራን
በሚሸሹ ሰዎች ይታያል፡፡ ሰነፍና በዋዛ በፈዛዛ ጊዜያቸውን መግደል የሚፈልጉ ሰዎች ክህሎታቸውን በተቻለ
መጠን ከሚጠቀሙበት ጎበዝ ሰዎች ዘንድ ብዙም መሆን አይፈልጉም---ምክንያቱም ምርታማ አለመሆናቸው
እንዳይጋለጥ ስለሚፈሩ፡፡

በመሆኑም ሥራ አዎንታዊ ከባቢ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር ቁልፍ ሚና አለው፡፡ በሥራ ቦታ፤ በሃይማኖት
ተቋም፤ በቤተሰብ ረገድ ያለብዎትን ኃላፊነት ለመወጣት ያለዎት ጽናት ሥራን የሚወዱ ሌሎች ብዙዎችን
ወደ እርስዎ ይስብልዎታል፡፡ በተመሳሳይ መንገድም ሥራ-ፈት ሆኖ ጊዜ መግደል ተመሳሳይ የስንፍና ዝንባሌ
ያላቸውን ሰዎች ወደ እኛው ስቦ ያመጣልናል፡፡ ሰነፍ ቢሆኑ ለስንፍናዎ ቅጣት የሚያገኙት በጥረትና በትጋት
ላይ የሚቀልድ ይበልጥ አሳናፊ እና ወደ መጥፎ ነገሮች የሚገፋፋ ጓደኛ ወይንም ሰዎች ወጥመድ ዒላማ
በመሆን ነው፡፡ ቀድሞውንም የሥራ ፍላጎትዎን ከውስጥዎ ያጠፋው ከባቢ ሁኔታ ዕድገትዎ የተገታ እንዲሆን

138 | P a g e
በማድረግም ትልቅ አስተዋፆ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም ለሥራ ትጋት ይኑርዎ፤ ቁርጠኝነትዎን የማይጋሩትን ሁሉ
ይራቋቸው፡፡

 እምቅ-አቅማችንን እንዴት ልንጠቀምበት እንችላለን 

አንድን ነገር ለፍፃሜ ለማብቃት ጓጉተዋል ሊፈጽሙት በጣም ከመጓጓትዎ የተነሳ ምንም የሚያደርጉለት
ራዕይስ አለዎት እንደዚያ ከሆነ ዕቅድ ያውጡና ለተፈፃሚነቱ ክትትል ያድርጉ፡፡

የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፤ ችኩል ሰው ሁሉ ግን ከመጉደል ይቸኩላል፡፡

(መጽሐፈ ምሳሌ 21፤5)

በዕቅድ እና በመቻኮል መካከል ልዩነት አለ፡፡ ችኮላ ማለት ያለ ልፋት ወይንም በቂ ጥረት አንድን ነገር ለማግኘት
መሞከር ሲሆን ወደ ድኅነትና ማጣት ያመራል፡፡ ጠንክሮ የሚሰራ ሰው ግን ዕቅድ አውጥቶ ዕቅዱ እስኪሳካ
ድረስ ጥረት ያደርጋል፡፡

ፖሊስ፤ ጠበቃ፤ ዳኛ፤ የሃይማኖት ተቋም አገልጋይ፤ ጸሐፊ፤ የሂሣብ ተቆጣጣሪ፤ ፖለቲከኛ፤ ሐኪም ወዘተ.
መሆን ይፈልጋሉ እንደዚያ ከሆነ መሆን ለሚፈልጉት ነገር ስኬት የሚገባውን ጥረት ያድርጉ፡፡ ሌሊት ብርሐን
አብርቶ ወይ ፋኖስ ለኩሶ ማንበብ ግድ ይላል፡፡ የፈለጉትን ሙያ፤ ንግድ ወይንም ሥራ ለመማር በዚያ ሥራ ላይ
የተሰማራን ሰው ፈልገው ይቀረቡ፡፡ የዕቅዶችዎ እውን መሆን ለመስራት ካለዎ ፈቃደኝነት ጋር የተቆራኘ
ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድም የእምቅ-አቅምዎ መውጣት ሀሳብዎን ወደሚታይ ተግባር ለመቀየር
በሚያደርጉት ጥረት ላይ የተንጠላጠለ ነው፡፡ በራስዎ ተነሳሽነት እና ፍላጎት መሠረት ይስሩ፡፡ ሕይወት
መስራትን አስገዳጅ እስክታደርግብዎ አይጠብቁ፡፡

ሥራ ለግል ብልጽግናዎ፤ ዕድገትዎ እና ስኬትዎ ቁልፍ ሚና አለው፡፡ ያለ ሥራ ምንንም ሊያሳኩ አይችሉም፡፡


ሥራን በተመለከተ አሉታዊና ጨለምተኛ ምልከታ ያለው ሰው ለእርካታ ማጣት እና መከፋት ይዳረጋል፡፡
በአንፃሩ አዎንታዊ የሆነ አመለካከት ለራስ የምንሰጠውን ክብር ከፍ በማድረግ ቀና፤ በራስ መተማመን ያለው
ለሰብ ያደርገናል፡፡ እግዚአብሔር የሚሰጠዎ ኃላፊነት እምቅ-አቅምዎን ለመፈተን እና እርስዎም አዳዲስ
ነገሮችን እንዲሞክሩ ለማድረግ የታቀዱ ናቸው፡፡ ሥራን የሚሸሹና ዳተኛ መሆንዎን እስካላቆሙ ድረስ
እግዚአብሔር በሥራ አማካይነት በሕይወትዎ ሊፈጥረው ያሰበውን መነቃቃት ሳያገኙት ይቀራሉ፡፡

ሥራ ለግል ብልጽግናዎ፤ ዕድገትዎ እና ስኬትዎ ቁልፍ ሚና አለው፡፡

139 | P a g e
ዛሬውኑ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያበረከተውን የሥራ ፀጋና ስጦታ ይቀበሉ፡፡ አሉታዊ የሆነ የሥራ
አመለካከት እምቅ-አቅምዎን እንዳይወስድብዎ ‹አልቀበልህም› ብለው እምቢታዎን ያሳዩ፡፡ ዎን፤
እግዚአብሔር ባተሌ ሰዎችን ይጠቀማል፡፡ ይህንን ካደረጉ የስኬትን ደስታና እግዚአብሔር በዚህች ዓለም ላይ
እንዲያከናውኑ የፈጠረዎትን በማድረግዎ በሚሰማዎ እርካታ ይጥለቀለቃሉ፡፡ ይኼን ጊዜ ሥራ በእርግጥም
ባረኮት መሆኑን ይረዳሉ፡፡

 መርሆች 

1. ትልቅ ደረጃ መድረስና ስኬትን ማግኘት ሥራን ይጠይቃል፡፡

2. ሥራ እምቅ-አቅምዎን ያወጣል፡፡

3. ሥራ. . .

የተነቃቃ ጥንካሬ እና ጉልበት


አንድን ነገር ለመከወን የሚያስችል ጥረት
ችሎታዎን እና ተሰጥዖዎችዎን አንድ ነገር ለማድረግ ሲሉ መጠቀም እና
የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት የሚያስፈልገው መሣሪያ ነው

4. እምነት ያለ ሥራ ምርታማ አይደለም፡፡

5. እግዚአብሔር በመስራት ዓላማወን እንዲያሳኩ ነው ዲዛይን ያደረገዎት፡፡

6. ሥራ ሪሶርስዎችዎ የቱንም ያህል ትንሽ ይሁኑ ብዙ ነገር ግን እንዲበዙ ያደርጋል፡፡

7. አለሥራ መቀመጥና ጊዜን መግደል ሌሎች ሰነፎችን ወደ ሕይወታችን ይጋብዛል፡፡

8. የእምቅ-አቅምዎ መውጣት የሚያስቧቸውን ነገሮች ወደ እውነታ ለመቀየር አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ ባለማድረግዎ ላይ
የተመረኮዘ ነው፡፡

140 | P a g e
ምዕራፍ 14

_____________________ _____________________

ለኃላፊነት አፀፋን መመለስ

የችሎታ ትልቁና ከሁሉም የላቀ አስፈላጊነት ኃላፊነት ነው፡፡

ወደ ሰው ልጅ ጆሮ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚገቡ ድምፆች መካከል የእንቦቃቅላ ሕጻን ገና ከማሕፀን


ሲወጣ የሚያሰማው ለቅሶ ነው፡፡ ይኼ ድምጽ የሚያምር የተባለው ገና ሕይወትን አሀዱ ያለ የሰው ልጅ አዲስ
ፍጡር የሚያሰማው በመሆኑ ነው፡፡ በቢልዮኖች የሚቆጠሩ የፕላኔታችን ኗሪዎች በዚህ ድምጽ እልል ብለዋል፤
ጨፍረዋል፤ ቦርቀዋል፤ አምላክን አመስግነዋል፡፡ ሆኖም ፈንጠዝያው እና ፌሽታው እንዳለ ሆኖ በሌላ በኩል ግን
ይኼንን ድምጽ የሚሰሙ ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች የኃላፊነትን መምጣት ይረዳሉ፡፡ ወላጆችና
አሳዳጊዎች ለልጁ ጤናማ እድገት ኃላፊነት እንዳለባቸው ሁሉ ልጁም ገና ሲፈጠር ጀምሮ በውስጡ አብሮት
ለተፈጠረው እምቅ-አቅም ተጠያቂ ይሆናል፡፡

141 | P a g e
ኃላፊነት ማለት ታማኝ፤ በተፈለገ ሰዓት ደራሽ፤ የተሰጠውን ሥራ የማያጓድል፤ ተጠሪ ማለት ነው፡፡ ኃላፊነት
ከዚህ በተጨማሪም የኮንትራት ስምምነት ወይንም ግዴታ መግባትንም ጭምር ያመለክታል፡፡ እንግዲህ ከላይ
የጠቀስናቸው ሁሉ አንዳች ዋጋ የሚሰጠው ነገር መተላለፉን የሚያመለክቱ ሲሆን እምነቱ የሚሰጠው አካል
ወይንም ሰው ደግሞ አዎንታዊ ውጤትን እንደሚያገኝ እንረዳለን፡፡ ኃላፊነት ከዚህ በተጨማሪም ራስን
መቻልን፤ ውጤታማነትን፤ ታማኝነትን እና መቻልን ያሳያል፡፡ በመሠረቱ ኃላፊነት ማለት አፀፋ መመለስ
መቻል ነው፡፡

ማንኛውም ሰው ወደዚህች ምድር ሲፈጠርና ሲመጣ እምቅ-አቅም ይዞ ነው፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ልክ እንደ
ኮምፒውተር ሁሉ የመተንተን፤ የማነጻጸር እና የመፍጠር ችሎታ አለው፡፡ ሆኖም ይህ ችሎታ በፕሮግራም
የተዋቀረ እና በየጊዜው ይወጣ ዘንድ ጥያቄ የሚቀርብለት እስካልሆነ ድረስ መኖሩ በራሱ ምንም ዋጋ
የለውም፡፡ የእርስዎ እምቅ-አቅም፤ ችሎታ እና የተፈጥሮ ታለንት የሚቀጥለው ትውልድ እምቅ-አቅሙን
መጠቀም ይችል ዘንድ በመለኮታዊ ኃይል አማካይነት ለእርስዎ ተጠቅመው እንዲያስተላልፉት የተሰጠ ነው፡፡
ማንም ሰው ቢሆን ወደዚህች ምድር ባዶ ሆኖ አልመጣም፡፡ ሁሉም ሰው አንድ ነገር ይዞ ነው የሚመጣው፡፡
ልክ አንድ ዘር በውስጡ ዛፍ የመሆን እምቅ-አቅም እንዳለ ሁሉ እርስዎም ሲወለዱ በውስጥዎ ትልቅ የመሆን
እና የማድረግ እምቅ-አቅምን ይዘው ነው፡፡

ነገር ግን የእርስዎ እና የሌሎች የሰው ልጆች አቅም በምሳሌነት ከጠቀስነው ዘር ይሻላል፡፡ እርስዎና ሌሎች
አርሶ-አደሩ ኮትኩቶ እምቅ-አቅም እስኪያወጣላችሁ አትጠብቁም፡፡ በመሆኑም የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ
በሚያሳልፈው ጊዜ ሁሉ እምቅ-አቅሙን ለማውጣት ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ የተደበቀ፤ ገና ምንም ጥቅም ላይ
ያልዋለ ችሎታን የማሳደግ ኃላፊነት የእርስዎ ብቻ ነው፡፡ የእርስዎ መወለድ ለዓለም የሚጠቅም አንድ ነገር
በውስጥዎ ስለመያዝዎ በማስረጃነት ሊወሰድ ይችላል፡፡ እስከዛሬ ምንም ሰሩ፤ አሳኩ በውስጥዎ ግን ገና ሊወጣ
የሚችል እና ተደብቆ ያለ ብዙ ነገር አለ፡፡ እርስዎ ብቻ ነዎት ይኼንን የተደበቀውን ማውጣት የሚችሉት፡፡

በመሆኑም የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ በሚያሳልፈው ጊዜ ሁሉ እምቅ-አቅሙን ለማውጣት


ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡

እኔ በግሌ ህይወት በእምቅ-አቅማችን ላይ ተደጋጋሚ ጥያቄና ጫና የሚያሳድር ከባቢ ሁኔታን በምትፈጥር


መልኩ ዲዛይን ተደርጋለች ብዬ አምናለሁ፡፡ እነዚህ ጥያቄዎችና ጫናዎች ባይኖሩ እምቅ-አቅማችን
እንደተቀበረ ነው የሚቀረው፡፡ ይኼ መሠረታዊ ሃቅ፤

ፍላጎት የፈጠራ እናት ናት

በሚለው አባባል ይረጋገጣል፡፡ ምንኛ እውነት ነው! ብዙዎቻችን ለሕይወት ፈጠራዊ በሆነ መልኩ አፀፋ
የምንመልሰው ሁኔታዎች ሲያስገድዱን ብቻ ነው፡፡ በርካቶቹ የቴክኖሎጂ፤ ሕክምና እና ማኅበረዊ ግኝቶች

142 | P a g e
በሁኔታዎች አስገዳጅነት እንደሆነ አይካድም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ላይ የሰው ልጅ በዔደን ገነት
ለመጀመሪያ ጊዜ ከተፈጥሮ ጋር ስላደረገው መፋጠጥ ይነግረናል፡፡

የሰው ልጅ ገና እግዚአብሔር በወቅቱ ሲፈጥረው መቶ በመቶ በጥቅም ላይ ያልዋለ እና ገና ያልወጣ እምቅ-


አቅም ነበረው፡፡ ሙሉ ችሎታ፤ ታለንት እና ተሰጥዖዎች የነበሩት ጎልማሳ ሆኖም ነበረ ወደዚህች ምድር
የመጣው፡፡ ሥጋዊ፤ አዕምሯዊ፤ ምሁራዊ፤ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ኃይሎቹ ሙሉ በሙሉ ጎልብተው ነበረ፡፡
ሆኖም የሰው ልጅ ኃይሎች እና ችሎታዎች ገና ምንም ያልወጡ፤ ያልታዩ እና በጥቅም ላይ ያልዋሉ
መሆናቸውም ይታወቃል፡፡ ፈጣሪ ይኼንን የተደበቀ ችሎታ ለማውጣት ያዘጋጀው እቅድ በ ኦሪት ዘፍጥረት 2፡
15፤19-20 ላይ ይገኛል፡፡

እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔደን ገነት አኖረው፡፡ እግዚአብሔር አምላክም
የምድር አራዊትን እና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳምም
ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ፡፡ አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፤ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፤
ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፡፡ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበረ፡፡

እግዚአብሔር ይኼንን ሙሉ በሙሉ አዲስ የሆነ---ገና ጡንቻዎቹን ያላፍታታ፤ አዕምሮውንም ያልተጠመበት፤


ያልተነሳሱ ስሜቶች ያሉት፤ ያላጫረው የግምት ችሎታ ያለው እና ይፋ ያልወጣ የመፍጠር ክህሎትን
የታደለ--ሰው ከፈጠረ በኋላ ያደረገው የመጀመሪያው ነገር እነዚህን የተደበቁ ችሎታዎቹን ለማውጣት
የሚረዱ ኃላፊነቶችን መስጠት ነበረ፡፡ ለአዳም ችሎታዎች ኃላፊነት በመስጠት እግዚአብሔር በአዳም እምቅ-
አቅም ላይ ጫና አሳድሯል፡፡ የእርስዎ እምቅ-አቅምም በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔር ለሕይወትዎ
ያስቀመጠውን ትልቅ ዓላማ ለማሟላት ጥያቄ ሲቀርብበት ነው፡፡ ለዚህ ነው ሥራ ቅጥር የሚባለው፡፡ እምቅ-
አቅምዎን ለማውጣት ችሎታዎትን ስለሚቀጥር፡፡

እግዚአብሔር አዳም እንዲሰራ የጣለበት ትዕዛዝ አካላዊ እምቅ-አቅሙን እንዲጠቀም ነበረ፡፡ እግዚአብሔር
አዳም የዔደን ገነትን በአበቦች እንዲያስጌጥ እና ለእንስሳት ስም እንዲያወጣ ሲያዘው የፈጠራ፤ አዕምሯዊ እና
አዕምሯዊ ታለንቶቹን እንዲጠቀም ነበረ፡፡

እግዚአብሔር የሚጭንብዎ ግዴታዎች እርስዎም አዳም እንዳደገረው እንዲያደርጉ የሚጠይቁ ናቸው፡፡


እርስዎ እምቅ-አቅምዎን ለማውጣት የመስራት ኃላፊነትን መቀበል አለብዎ ምክንያቱም ከችሎታዎች ሁሉ
ትልቁ ኃላፈነት ነውና፡፡ አንድን ነገር ለመስራት እስካልተነሳሱ ድረስ እምቅ-አቅምዎን አይረዱትም፡፡
በሕይወትዎ ትልቁ አሳዛኝ ክስተት ሞትዎ ሳይሆን አብሮዎት ሳይወጣ የሚሞተው እምቅ-አቅም ነው፡፡
እግዚአብሔር እንዲጠቀሙ የሰጠዎትን አለመጠቀም ምንኛ ያሳፍራል!

 በሶስተኛው ዓለም ላሉ የማደርሰው መልዕክት 


143 | P a g e
ታሪክ በሚገባ እንደሚያሳየን ከሆነ እምቅ-አቅማቸውን ለማውጣት፤ ለማጎልበት እና ለማንቀሳቀስ
የሚችሉባቸውን መልካም አጋጣሚዎች ሆነ ተብለው በሌሎች እንዲነፈጉ፤ እንዲነጠቁ እና እንዲያጡ
የሚደረጉ ሕዝቦች የትውልዳዊ አስተሳሰብ ጉድለት አለባቸው፡፡ በደረባቸው ጭቆና እና ረገጣ የተነሳ ስለ
ወደፊቱና አቅምን ተጠቅሞ ለትውልድ የሚጠቅም ነገር ከማስቀመጥ ይልቅ ራሳቸው ላይ ማተኮር እና ግላዊ
ደኅንነታቸው ላይ ያተኩራሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገራት ማኅበረሰቦች ውስጥ
የሚታይ ሲሆን ለወደፊት ከሚጠቅም ቅርስ ይልቅ የዛሬን እየፎከሩና በጠባብ ቅርብ ታሪክ ብቻ እየተኮፈሱ
በመኖር ይገለፃል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የተዛባ ምልከታ ደግሞ የአንድ ጎሳ አባላትን እንኳ ሳይቀር ለፍርሀት፤
ለጥርጣሬ እና ጥላቻ እንደሚዳርግ እሙን ነው፡፡

ለወደፊት በሚተላለፍ ቅርስ ላይ አለማተኮር እና በራስ ጊዜያዊ ነገሮች ላይ መጠመድ ማኅበረሰቡን ከፈጠራ
ክህሎት የራቀ፤ ግምትና ራዕይ ያጣ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በዚህ የተነሳ በእያንዳንዱ ግለሰብ ውስጥ ያለውና
ሊወጣ የሚገባው እምቅ-አቅም ባክኖ ይቀራል፡፡ በሶስተኛው ዓለም ባሉ አገራት ውስጥ የሚገኝ ማኅበረሰብ
ሁሉ ከዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ነፃ ሊወጣ ይገባል፡፡ ለልጁ እና ለልጅ ልጁ ቅርስ ለማስተላለፍ ያለበትን ኃላፊነት
ይረሳዋል፡፡ ማንም ሰው ቢሆን ካለበት ተጨባጭ ሁኔታ እና ወቅታዊ ነገር አሻግሮ ማየት እስካልቻለ ድረስ
የወደፊት ተስፋው ጨለማ ነው፡፡

የእምቅ-አቅም መሠረት ጠብቆ ማቆየት ሳይሆን ነፃ ማውጣት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ያለፈውን
መቀየር የማንችል ቢሆንም የወደፊት ዕጣችንን የመወሰን እና ለልጆቻችን እና ለልጅ ልጆቻችን የተሻለ እና
ብሩህ ነገር የመፍጠር ዕድል ግን አለን፡፡ ላለፈው ነገር ሌሎችን የመኮነን ዕድል ሁሌም አለ፤ ለሌሎች ወደፊት
ለሚመጡት ልናስተላልፍ የሚገባን ኃላፊነትና ለነሱ ያለን ተጠያቂነት ግን ያፈጥብናል፡፡ እኔ እና እርስዎ
እግዚአብሔር ለሕይወታችን ዓላማ መቃናት የሚያስፈልጉን ሁሉ ተሰጥተውናል፡፡ በቤተሰቦቻችን፤
በማኅበረሰባችን፤ በሕዝባችን እና ምናልባትም በዓለም ላይ ተጽዕኖ የመፍጠር ዕድሉ አለን፡፡

እናም ዛሬውኑ በምኞትና በታላላቅ ሕልማችን ከመጎለት ይልቅ አንድ ነገር ለመስራት እንወስን፡፡ አጉል
ማቅማማት የሚባለውን ነገር አሽቀንጥረን በመጣል እምቅ-አቅማችንን ለማውጣት ቁርጠኛ እንሁን፡፡
በምኞት ሳይሆን በጎ ፈቃድን እውን በማድረግ እንኑር፡፡ ሀሳብ ከማቅረብ በመውጣት ወደ ዓላማ ማስፈጸም
እንሸጋገር፡፡ መውተርተሩን ትተን ዛሬውኑ እናቅድ፡፡ ባዷችንን እና በውስጣችን ያለውን ሳንጠቀም ከመሞት
በመውጣት የሕይወትን ትሩፋት በጥረታችን ለማግኘት እንንቀሳቀስ፡፡ አንድ ነገር እናስታውስ፡፡ ጥቂት ነገሮች
ብቻ ጠንክሮ በመስራት ላይሳኩ እንደሚችሉ እንጂ ሌላው ሁሉ ግን በእጃችን መዳፍ እንደሆነ እናስታውስ፡፡

144 | P a g e
 መርሆች 

1. እርስዎ መፈጠርዎ ለዓለም የሚጠቅም አንድ ነገር በውስጥዎ ለመኖሩ ማስረጃ ነው፡፡

2. እግዚአብሔር ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ ትርፍ የሚያስገኝ እምቅ-አቅምን ለእርስዎ ሰጥቷል፡፡

3. የችሎታ ትልቁ ፍላጎት ኃላፊነት ነው፡፡

4. እግዚአብሔር ለችሎታችን ኃላፊነት በመስጠት በእምቅ-አቅማችን ላይ ጥያቄ ያቀርባል፡፡

5. ስኬት ከአንድ ሥራ በተገቢው መንገድ መጠናቀቅ ጋር በቀጥታ ይያያዛል፡፡

6. እግዚአብሔር በሕይወትዎ የእርሱን ዓላማ ያሳኩ ዘንድ የሚያስፈልግዎትን ሁሉ ሰጥቶዎታል፡፡

145 | P a g e
146 | P a g e

You might also like