You are on page 1of 4

መግቢያ

ይህ መፅሐፍ በሕይወትህ ውስጥ ተዓምራዊ ለውጥ እንዴት ሊያመጣ ይችላል;

በዓለም ዙሪያ ባሉ በማንኛውም ማህበራዊ መደብ በሚካተቱ ሰዎች ዂሉ ሕይወት ላይ


ተዓምር ሲፈጠር አይቻለሁ፡፡ የውስጠ ሕሊናህን ኃይል ከተጠቀምክበት በአንተም ሕይወት
ተዓምር ይከሰታል፡፡ የዘወትር አስተሳሰብህ እጣ ፈንታህ ቀራፂ መሆኑን ማስተማር ነው የዚህ
መፅሐፍ ዋና ዓላማ ፤ ሰው የሚሆነው የሚያስበውን ነውና፡፡

ምላሾቹን ታውቃቸዋለህ?
አንዱ ደስተኛ ሲሆን ሌላው ለምን የተከፋ ይሆናል? አንዱ ሐብታም ሌላው ደሀ፣ ኑሮው በችጋር
የተተበተበ ለምን ይሆናል? አንዱ በፍርሃትና በሥጋት የተቆራመደ ሌላው ደግሞ በዕምነትና በራስ
መተማመን የተሞላ ለምን ይሆናል? አንዱ የተሳካለት ሌላው ደግሞ ዂሉ ነገር የሚከሽፍበት
የሚሆነው ለምንድን ነው? አንዱ በቀላል በሽታ ሲሞት ሌላው ለምን ‹‹አይድኑም›› ከሚባሉ
ሕመሞች በቶሎ ያገግማል? ኢ-ሞራላዊና ኃይማኖት የለሽ የሆኑ ሰዎች የሚበለፅጉትና ጤናማ
የሚሆኑት ለምንድን ነው?
ለእነዚህ ጥያቄዎች በአዕምሮህም ሆነ በውስጠ ሕሊናህ ምላሽ ታገኝላቸዋለህ? በሚገባ፡፡

ለዚህ መፅሐፍ መዘጋጀት ምክንያቶች


ከላይ ለተዘረዘሩትና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ነው መፅሐፉ የተሰናዳው፡፡ ስለ
አዕምሮአችን ኃያልነት በተቻለ መጠን ቀላል በሆነና በሚገባ ቋንቋ ለማስረዳት ሞክሬያለሁ፡፡
ይህን መፅሐፍ የሚያነብ ሰው በመፅሐፉ ውስጥ የተቀመጠውን ቁም ነገር በሚገባ መርምሮና
አገናዝቦ ፍሬ ነገሩን እንዲረዳ አሳስባለሁ፡፡ ይህ ሲሆን ከግራ መጋባት፣ ከችግር፣ ከሐዘንና
ከውድቀት ሊያነሳ የሚችለውን ተዓምራዊ ኃይል መጠቀም እንደምትጀምር
ይሰማኛል፤ይገባኛልም፡፡ ይህ ተዓምራዊ ኃይል የተተበተብክበትን ችግር ይፈታልሃል፣ ከትክክለኛ
ሥፍራህ ያደርስሃል፣ ነፃነትን፣ ደስታን የአዕምሮ ሰላምን ያጎናፅፍሃል፡፡
ይህ ተዓምራዊ የውስጠ ሕሊና ኃይል ከሕመም ይፈውስሃል፡፡ ይህንን ተዓምራዊ ኃይል መጠቀም
ስትችል ቅዱስ ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጆች በመሆን እንደሚገኝ የገለፀውን ስብሐት
የተሞላበት የነፃነት ሕይወት መምራት ትጀምራለህ፡፡

ተዐምር ፈጣሪውን ኃይል ገቢራዊ ማድረግ/ማመንጨት

III
ግላዊ መዳን ለውስጠ ሕሊናችን ኃያልነት የበለጠ አሳማኙ ምክንያት ነው፡፡ ከአርባ ሁለት
ዓመታት በፊት ‹‹ሳርኮማ›› ከተባለ አደገኛ በሽታ ፈጥሮ በሚያኖረኝ ውስጠ-ሕሊናዬ ኃይል
አማካይነት መዳን ችያለሁ፡፡ የተጠቀምኩበት የመዳን ዘዴ በዚህ መፅሐፍ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፣
ሌሎችም የተቀበረውን የውስጠ ሕሊናቸውን ያልተገደበ የማዳን ኃይል እንዲረዱና ለውጥ
እንዲያመጣላቸውም እንዲያምኑ እንደሚረዳ አምናለሁ፡፡ ጥንታዊው አባባልስ ‹‹ሐኪም ቁስሉን
ያሽጋል፤ የሚያድነው ግን እግዚአብሔር ነው›› አይደል የሚለው!
በአግባቡ ከጸለይክ ተዓምራትን ታያለህ
ሳይንሳዊ ጸሎት በሳይንሳዊ መንገድ ለአንድ ዓላማ አዕምሮና ውስጠ ሕሊና ሕብር ፈጥረው
የሚዋሃዱበት ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ በአንተ ውስጥ ያለውን ገደብ የለሽ ኃይል ልጓም አበጅተህለት
በሕይወት የምትፈልገውን ለማግኘት ያስችልሃል፡፡ ደስታ የተሞላበት የተድላ ሕይወት ነው
የምትፈልገው፡፡ ስለዚህ በዚህ መፅሐፍ ምዕራፎች ውስጥ የቀረቡትን የውስጥ ሕሊናን ተዓምራት
በጥንቃቄ መርምረህ ተረዳ፡፡
ጸሎት ለዂሉም
ውጤታማ ጸሎት እንዴት እንደሆነ ታውቃለህ? ከጸለይክ ምን ያክል ጊዜ ሆኖሀል? በድንገተኛ
አደጋ ጊዜ፣ ችግር ሲገጥምህ፣ በሕመም ስትወድቅ ሞት ሲቃረብ ጸልይ፡፡ ዕለታዊ ጋዜጦችህን
አንብባቸው እስኪ፤ በማይድን ደዌ ለተለከፉ ሕፃናት፣ ለዓለም ሕዝቦች ሰላም እንዲሆን፣
በማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ ለተቀበሩ ሠራተኞች ደህንነት ጸሎት እንደተደረገ ይዘግባሉ፡፡
ኋላ ላይም ማዕድን ቆፋሪዎቹ ሲተርፉ እንዲ ባለሁኔታ እንዳይሞቱ ሲጸልዩ እንደነበር ይገልፃሉ፡፡
በእርግጥም በችግር ጊዜ ጸሎት መታደጊያ ነው፡፡ ነገር ግን ጸሎት የሕይወት አንድ አካል እንዲሆን
ችግር እስኪገጥምህ ድረስ መጠበቅ የለብህም፡፡
በሥራዬ የተነሳ ሰዎች ተግባራዊ የሚያደርጓቸውን የተለያዩ የጸሎት አቀራረቦች ለማጥናት
ችያለሁ፡፡ በገዛ ሕይወቴም የጸሎትን ኃያልነት ተገንዝቤያለሁ፡፡ እንዲሁም ከጸሎት መልካም
ውጤት ማግኘት ከቻሉ ሰዎች ጋር በቅርበት ሰርቼያለሁ፤ ተነጋግሬያለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ችግር
የሚሆነው ለሌሎች እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው መንገሩ ነው፡፡ በችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች
በአግባቡ ለማሰብና ሚዛናዊ ሆነው ለመተግበር ይሳናቸዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች ለመከተልና
ለመተግበር ቀላል የሆነ ቀመር ነው የሚያስፈልጋቸው፡፡
የመፅሐፉ ልዩነት
የዚህ መፅሐፍ ልዩነቱ መሬት ላይ ወርዶ ተግባራዊ መሆን መቻሉ ነው፡፡ በዕለት ተዕለት ሕይወትህ
ውስጥ ተግባራዊ የምታደርጋቸው ቀላልና ጠቃሚ ዘዴዎች ቀርበውልሃል፡፡ እነዚህን ቀላል ዘዴዎች

IV
በዓለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች አስተምሬያለሁ፡፡ በቅርቡ ደግሞ በሎስ አንጀለስ ከዂሉም የዕምነት
ተከታዮች ለተውጣጡ ሰዎች ከመፅሐፉ እየጠቀስኩ ልዩ ትምህርት ሰጥቻለሁ፡፡ ብዙዎቹ እስከ
ሁለት መቶ ማይልስ ርቆ ከሚገኝ አካባቢ እየመጡ ነበር ትምህርቱን የሚከታተሉት፡፡ የመፅሐፉ
ልዩ ገፅታዎች የሚገለጡልህ ብዙውን ጊዜ ከፀሎትህ በተቃራኒ ያልፈለከው ለምን
እንደሚደርስብህ የሚያስረዱ በመሆናቸው ነው፡፡ እጅግ አያሌ ሰዎች ‹‹ብጸልይ፣ ብጸልይ ምላሽ
የማላገኘው ለምንድን ነው?›› ሲሉ በተደጋጋሚ ጠይቀውኛል፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ከመፅሐፉ
ታገኛለህ፡፡
ምን ታምናለህ?
የምታምነው አይደለም ለጸሎትህ ምላሽ የሚያስገኘው፡፡ ለጸሎት ምላሽ የሚያመጣው የግለሰቡ
ውስጠ ሕሊና በአዕምሮው ውስጥ ላለው ምስል ከሚሰጠው ምላሽ ነው፡፡ ይህ ሕግ በዂሉም
ሀይማኖቶች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡
ቡድሂስቱ፣ ክርስቲያኑ፣ ሙስሊሙ እና አይሁዱ ለጸሎታቸው ምላሽ የሚያገኙት
ከሀይማኖታቸው፣ ከሚፈፅሙት ሥርዓት፣ ከሚያቀርቡት መስዋዕት የተነሳ ሳይሆን ለሚጸልዩት
ነገር ካላቸው ፅኑና አዕምሯዊ እምነት ወይም አዕምሯዊ ቅበላ የተነሳ ነው፡፡
የሕይወት ሕግ የእምነት ሕግ ነው፡፡ እምነት ደግሞ በአዕምሮ ውስጥ ያለ ሐሳብ ነው፡፡ አንድ ሰው
ሲያስብ፣ ሲሰማው እና ሲያምን የአዕምሮውን፣ የአካሉንና የአጠቃላይ ኹኔታው ኑባሬ በዚህ
ይቃኛል፡፡
ምን እያደረግህ እንደሆነና ለምን እያደረግከው መሆኑን መገንዘቡ በሕይወት ውስጥ ያሉ መልካም
ነገሮች በሙሉ በውስጠ ሕሊናህ ውስጥ እንዲቀረፁ ለማድረግ ያስችልሃል፡፡
መሻትም ጸሎት ነው
ማንኛውም ሰው የተሟላ ጤና፣ ደስታ፣ ደህንነት፣ እና የአዕምሮ ሰላም ይሻል፡፡ አንድ የዩኒቨርስቲ
መምህር በቅርቡ ‹‹አስተሳሰቤን ባስተካክልና ስሜቴን መቆጣጠር ብችል የሚያሰቃየኝ የውስጥ
ደዌ እንደሚድን አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ዘዴውን አላውቀውም፡፡ አዕምሮዬ በብዙ
ችግሮች ተተብትቧል፡፡ ደስታ ርቆኝ ሽንፈትና ጭንቀት ነው የሚሰማኝ›› ሲል አዋይቶኛል፡፡ ይህ
ፕሮፌሰር ለተሟላ ጤንነት መሻት አለው፡፡ የሚያስፈልገው ይህን መሻቱን እውን ለማድረግ
ይቻለው ዘንድ አዕምሮውን የሚያሰራበት እውቀት ነው፡፡ እኔ ያካፈልኩትን፣ በዚህ መፅሐፍ
የተጠቀሱትን የፈውስ ዘዴዎች ተግባራዊ በማድረግ መሻቱን እውን አድርጓል፡፡

V
የውስጠ ሕሊናችን ተዓምራዊ ኃይል እኔም ሆንኩ አንተ ከመወለዳችን በፊት በምድር ላይ የነበረ
ነው፡፡ ታላቅ የሆኑት ዘለዓለማዊ እውነታዎችና የሕይወት መርሆዎች ከዂሉም ሀይማኖቶች
ቀድመው የነበሩ ናቸው፡፡

VI

You might also like