You are on page 1of 10

¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

12 ኛ
ትምህርት ከታህሳስ
ከ 4 – 10
1 2007 ዓ.ም

ጸሎት፣ ፈውስ እና መመለስ


(ወደ እውነት)

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ያዕ. 5፡13-20፣ 1ዮሐ. 514፣
1ቆሮ. 15፡54. ዕብ. 12፡13፣ ዮሐ. 8፡43-45፣ ምሳ. 10፡12፡፡

መታሰቢያ ጥቅስ፡- “ስለዚህ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ


ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ
ለሌላው ይጸልይ፡፡ የጻድቅ ሰው
ጸሎት ኃይል አለው፤ ታላቅ ነገርም
ያደርጋል” (ያዕ. 5፡16)፡፡

ብ ዙ ሰዎች በተአምራት እና አስማት አጥብቀው ይሳባሉ፡፡ ወደነዚህ ነገሮች


የመሳባቸው መንስዔ የተለዩ ክስተቶችን በመነጽር ውስጥ ለመመልከት ባላቸው
ጉጉት ነው፡፡ የሱስ ለመዝናኛ በሚመስል መልኩ ተአምራት እንዲያደርግ
ተጠይቆአል (ሉቃ. 23፡8-9) ወይም መሲህ መሆኑን የሚያረጋግጥ ምልክት እንዲያሳይ
(ማቴ. 12፡38-41) ወይም ደግሞ ለእራሱ የሚያስፈልገውን ሟሟላት የሚያስችለውን
ተአምራት እንዲያደርግ (4፡2-4) ቢጠየቅ የሱስ ግን ተቃወመ፡፡ የሱስ እንደ ባለ ሥልጣን
የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም
115
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ያስተማረበት እና ተአምራዊ ፈውስ ያደረገበት መንፈስ ከንቱ ጥቅም ላይ የሚውል ኃይል


አይደለም፡፡ እኛ በእጆቹ የምንገኝ መሣሪያው ልንሆን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር የታመሙትን
ሁሉ በደስታ የሚፈውስ ቢሆንም፤ ከዚያ በላይ በሆነ ፈውስ ግን ይበልጥ ደስተኛ ነው፡፡

በዚህ ጽንሰ ሃሳብ


ብ ዙሪያ አንዳንድ
ን አስፈላጊ
ስ ላ ጥያቄዎችን
ቄ እንመልከት፡
ን ከ -- በያዕቆብ መልእክትእ
የታመሙትን
ታ ት ስለ መፈወስ የቀረበውን
ቀ ን ሃሳብ
ብ እንዴትት እናስተውለዋለን?
እ ስ ለ ከጸሎት
ከጸ መልስ
መል
አኳያ በፈውስ እና በኃጢአት ይቅርታ መካከልመካከ ግንኙነት
ኙ አለ? ክህደት
ህ ት ከዳር እስከ
ስ ዳር
ተንሰራፍቶቶ በነበረበት
በ ት ወቅትቅ ኤልያስ
ል ስ ብርቱ የጸሎት
ሎ ምሳሌ
ም ሆኖ
ሆ እናገኘዋለን፡፡
ኘ እስራኤልን

ወደ
ደ እግዚአብሔር
ግ እናና ወደ እውነተኛ
ተ አምልኮ ከመመለስ
ከ አኳያ
አ ያ ከጸሎትት ህይወቱ
ህ ምንን
መማር እንችላለን?
እ ለ

እሑድ ታህሳስ
ታ ስ5

ከክርስቲያኖች
ያ ሊለይ የማይገባ ትጥቅ
ይህን ጥቅስስ ያንብቡ፡
ያ ያዕ.
ዕ. 5፡13፡፡ ምን ዓይነት
ነት ንጽጽር
ንጽ አቅርቦአል?
ቅ ል ማሳሰቢዎቹን
ማ ሰ ቹን
በተሞክሮአችን
ሞ ላይይ የምናክላቸው
የ ክላ እንዴት
እ ት ነው?

------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------------------------

ከሁለት የተለያዩ ነገሮች ጋር መጎዳኘታችንን (መከራ እና ደስታ) ያዕቆብ ከጸሎት እና


ምስጋና ጋር ያስተሳስራቸዋል --መከራ ሲደርስብን መጸለይ ደስ ሲለን ደግሞ ማመስገን፡፡
አብዛኞቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የምስጋና መዝሙሮች ጸሎት በመሆናቸው እነዚህ ሁለቱ
መንገዶች የተለያዩ አይደሉም፡፡ ያዕቆብም ቢሆን በመልእክቱ መጀመሪያ እንዲህ ብሎአል
“ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፤ ምክንያቱም የእምነታችሁ
መፈተን ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ ” (ያዕ. 1፡2-3)፡፡ ነገሩን ጠቅለል አድርገን
ስናስብ የጸሎት እና የምስጋና ጊዜ ይበልጥ የተሳሰሩ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

116 የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም


¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

“መከራ” (ያዕ. 5፡10) --በአካልም ሆነ በአእምሮ የሚደርስ ሥቃይ ሊሆን ይችላል


“የጦርነትን ገፈት ተከትሎ የሚመጣ አደጋ እና ፍዳ” Ceslas Spicq, Theological Lexi-
con of the New Testament, vol. 2, p. 239) በተጨማሪ እጅግ አድካሚ የጉልበት ሥራ
እና ብርቱ ጥረት ሊሆን ይችላል፡፡ ቃሉ በ 2ጢሞቴ. 2፡9 እና 4፡5 የሚከተለውን ሃሳብ
ለመግለጽ ተጠቅሶአል “በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ወይም ሥቃይ ተስፋ የማይቆርጥ
የሐዋርያ አገልግሎት” —Theological Lexicon of the New Testament, vol. 2, p.
240. እንደ ክርስቲያንነታችን በመከራ ወቅት ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር እንመልሳለን፡፡
አስቸጋሪ ሁናቴዎች ሲገጥሙን በተለይ ጸሎት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ መዘመርና መንፈሳዊ
ሙዚቃ መጫወትም እንዲሁ ጠቃሚ ነው፡፡

“መዘመር እንደ ጸሎት ሁሉ እግዚአብሔርን የምናመልክበት መንገድ ነው፡፡ በእርግጥ


አብዛኛው መዝሙር ጸሎት ነው”—Ellen G. White, Education, p. 168. በድብርት እና
ብቸኝነት ስሜት ውስጥ ሆነን የመዝሙር ቃላት ወደ አእምሮአችን ሲመጡ የማንነቃቃ
ስንቶቻች ነን? በጸሎት እና መዝሙር ቢጎበኙ የሚነቃቁ፣ የሚበረታቱና ደስተኞች የሚሆኑ
አያሌ ወገኖች በመከራ ውስጥ አሉ፡፡ “ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም
ጋር እዘኑ” (ሮሜ 12፡15፡፡

ለእርዳታ ወዴት መሄድ እንዳለብን ግራ መጋባት ሲይዘን በተለይ የመዝሙር መጽሐፍ


መንፈሳዊ መነሳሳትና መነቃቃት የሚፈጥር የጸሎት እና መዝሙር ክምችት ነው፡፡

መከራ ምምን ያያህል


ል ወደ ጌታ ሊያቀርበን
በ እንደሚችል እና እንዴት ወደ ጸሎት
ሎ እንደሚመራን
ጠንቅቀን
ቅ እናውቃለን፡፡
ና ቃ ፡ ነገሮች ች በመልካም
መል ሁኔታ ሲሄዱልን
ል ሊከተሉሉ የሚችሉ መንፈሳዊሳ
አደጋዎች
ደ ች ምንድን ድ ናቸው?? በተለይ
በ ይ በእነዚህ
እ ወቅቶች
ወ ማመስገን አስፈላጊ የሆነው
ነ ለምንድን
ለ ን
ነው??

ሰኞ ታህሳስ
ሳ 6

ለታመሙት
ሙ መጸለይ
የሚከተሉትን
ት ጥቅሶች
ሶ ያንብቡ፡
ቡ፡ ያዕ.. 5፡14-
5፡ -14፡፡፡ ያዕቆብ
ዕቆብ ለታመሙ
ታመ ዘይት ቀብቶ
ብ ለመጸለይ

አስፈላጊ
ስ ላ አድርጎ
ድ ጎ የሚያስቀምጣቸው
የ ቸ ነገሮች ምንድን ናቸው? ቸ በጥቅሶቹ መንፈሳዊ
ሳ ይዘት
የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም
117
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ያላቸው
ያ ነገሮች
ገ ምንድን
ን ናቸው?
ና ?
-----------------------------------------------------------------------------------------------

የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ወደ ታመመው ሰው መጥተው “በጌታ ስም ዘይት ቀብተው”


እንዲጸልዩለት ማድረግ ግለሰቡ ለመዳን ያለውን መንፈሳዊ ፍላጎት እና መለኮት ጣልቃ
ገብቶ ግለሰቡን እንዲፈውሰው የሚደረግን የህብረት ልመና ያሳያል (ማር. 6፡13)፡፡ ስለ
ኃጢአት ይቅርታ የተሰጠ ማጣቀሻ እንደሚያሳየው ህመምተኛው ከአካላዊው በተጨማሪ
መንፈሳዊ ፈውስ ለማግኘት ምኞት ከሌለው በቀር በኃይማኖታዊ ልምድ ፈውስ ማግኘት
አይችልም፡፡ “የጤና ህውከት ገጥሞአቸው በጸሎት ፈውስ የማግኘት ምኞት ያላቸው
ወገኖች ተፈጥሮአዊውንም ሆነ መንፈሳዊውን የእግዚአብሔር ሕግ መጣስ ኃጢአት
መሆኑና የእርሱን በረከት ለመቀበል ኃጢአትን መናዘዝ እና መተው የግድ መሆኑ ግልጽ
ሊሆንላቸው ይገባል፡፡”—Ellen G. White, The Ministry of Healing, p. 228.

መለኮታዊውን ጣልቃ ገብነት መለመን እና የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችን መጥራት


የግለሰቡን ህመም አሳሳቢነት የሚያሳይ እንደመሆኑ፤ ምናልባትም ከመደበኛው የቤተ
ክርስቲያን ጉባዔ ጋር ትስስር መፍጠርን ጨምሮ በአስቸኳይ መከናወን ሊኖርበት ይችላል፡፡
ከታመሙ ጋር በተያያዘ ሁሉት ዓይነት የግሪክ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ የመጀመሪያው
ቃል --astheneō (በቁ. 14 ላይ የምናገኘው) ሲሆን በተጨማሪ በሐዋ. 9፡37 ታማ
የሞተችው ዶርቃ ታሪክ ላይ ተጠቅሶአል፡፡ ሁለተኛው kamnō (በቁ. 15 ላይ የምናገኘው)
አጠቃላይ ከታማሚ ጋር ለተያየዘ ጉዳይ እንዲሁም በሞት አፋፍ ላይ ያሉን ለመግለጽ
ጥቅም ላይ ውሎአል፡፡ “በእምነት የቀረበ ጸሎት” ተአምራዊ ፈውስ በማምጣት ምላሽ
ማግኘት ይችላል፡፡ ይኸውም ፈውስ ኖረ ወይም አልኖረ እንደ ፈቃዱ በመለመን ነው
(1ዮሐ. 5፡14)፡፡ እንዲሁም “ነፍሱን ከሞት ያድነዋል” (5፡20) የሚለው ሃረግ የተሟላውን
ፈውስ --ትንሳኤን ያመለክታል “የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተውም የማይሞተውን
በሚለብስበት ጊዜ. . . ” (1ቆሮ. 15፡54)፡፡

አብዛኞቻችን
ቻ ን ለለታመሙ ዘይት ቀ ቀብቶ የመጸለይለ አገልግሎትን
ል ሎ ን እ እናውቃለን
ው ወይም

የአገልግሎቱ
ል ተካፋዮች
ካፋ ልንሆን እንችላለን፡፡
ን ን ላ ን፡ በዚህ አገልግሎትት ምናልባትም
ት ህመምተኛው
ሳይፈወስ
ፈ ስ የቀረበት
ቀ በ ወይም
ይ የሞተበትን
ተ ን አጋጣሚ
ጋ ትውስታ
ት ታሊሊኖረንን ይችላል፡፡
ላ ፡ ታዲያ በጥቅሱ
የቀረበው
በ ትንሳኤ ብቸኛው ተስፋችን ይሆንን?

የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም


118
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ማክሰኞ
ኞ ታህሳስ
ሳ 7

የነፍስ ፈ
ፈውስ
ከአካላዊው ፈውስ ይልቅ በእጅጉ አስፈላጊው የነፍስ ፈውስ ነው፡፡ ዓላማችን ሰዎችን
ጤነኛ ኃጢአተኞች ማድረግ ሳይሆን በየሱስ ወደ ተመሰረተው ዘላማዊው ሕይወት
ማመላከት ነው፡፡ ከቁ. 13-15 ከቀረቡት ይልቅ ስለ ፈውስ ብቸኛ ግልጽ ማጣቀሻ የሆነው
የዚህ ሳምንት ጥናታችን መታሰቢያ ጥቅስ (ቁ. 16) ላይ የምናገኘው ፈውስ የሚለው ቃል
የተተረጎመው (iaomai) ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፤ ቃሉ ከአካላዊ ፈውስ ባሻገር
ያለውን ደኅንነት ያመለክታል (የሚከተለውን ጥቅስ ይመልከቱ፡ ማቴ. 13፡15)፡፡ ቀደም
ብሎ በቁ. 15 ስለ ፈውስ የተሰጠውን ሰፊ ሃሳብ (ትንሳኤ) መሰረት በማድረግ ያዕቆብ
በህመም እና በኃጢአት መካከል ያለውን ግንኙነት ያሳየናል፡፡ አባባሉ ለእያንዳንዱ ህመም
መንስዔ ከበስተኋላው እራሱን የቻለ ኃጢአት አለ ለማለት ሳይሆን ብርቱ ችግሮቻችን
የሆኑት ህመም እና ሞት ኃጢአተኛ የመሆናችን ውጤት ናቸው የሚል አንደምታ አለው፡፡

የሚከተለውን ው ጥቅስ በማንበብ


ማ በቅንፍ
በ ፍ ከተቀመጡት
ከ ት ጋር ያስተያዩ፡
ያ ፡ ማር. 2፡1-
1 12
1 (ዕብ.
122፡12፣
፡ 13፣3፣ 1ጴጥ.
1 . 2፡24-225))፡፡ ጥቅሶቹ
ቅ የሚገልጹት
ል ምንን ዓይነት
ይነ ፈውስ ነው? የፈውሱ ው
መሰረትስረ ምንድንን ነው??

------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------------------------

በየሱስ ላይ የሚኖር እምነት በመንፈሳዊ ድካም እና ኃጢአት ላይ ፈውስ ያስገኛል፡፡ ከዚህ


አኳያ የሱስ የፈጸመው እያንዳንዱ ፈውስ የሰዎችን አትኩሮት ጥልቅ ወደ ሆነው የደኀንነት
ፍላጎት ለመሳብ ታልሞ የተደረገ ነበር፡፡ በማርቆስ ምዕ. 2 ላይ በምናገኘው የሽባው ሰው
ታሪክ መንፈሳዊ ፈውስ ለእርሱ ከሁሉ በላቀ የሚያሳስበው ጉዳይ እንደነበር
እንመለከታለን፡፡ ስለዚህ ኃጢአቱ ይቅር መባሉን የሱስ ወዲያውኑ አረጋገጠለት፡፡ “ግለሰቡ
ከአካላዊ ፈውስ ይልቅ ከኃጢአት ሸክም ተገላግሎ እፎይታ የሚያገኝበትን መንገድ አጥብቆ
ተመኝቶ ነበር፡፡ የሱስን በዐይኖቹ ማየት ቢችል፣ የኃጢአት ይቅርታ ማረጋገጫ እና
ሰማያዊውን ሰላም ቢያገኝ ከዚህ በኋላ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቢኖር ወይም ቢሞት

የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም


119
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ደስታው ነው”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 267. እግዚአብሔር የፈውስ


ጥበብ የሰጣቸው ሐኪሞች ህመምተኛውን ለማዳን ማንኛውንም የህክምና መሣሪያ
ይጠቀማሉ፡፡ ፈውስ በዚህ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ለዘላለማዊውም ይሆን ዘንድ ተገቢው
ጥረት መደረግ ይኖርበታል፡፡

ፈውስ የእርስ በርስ ግንኙነታችንን የሚያካትት ሲሆን “ስለዚህ ኃጢአታችሁን እርስ


በርሳችሁ ተናዘዙ” (ያዕ. 5፡16) ይኸውም የበደልናቸውን ወይም ያሳዘንናቸውን ይቅርታ
መጠየቅን ይመለከታል (ማቴ. 18፡15፣21-22)፡፡ የኃጢአት ይቅርታ መጠየቅ ለኃጢአት ሞቶ
ክርስቶስን መልበስ እንደመሆኑ --የጌታ በረከት በእኛ ላይ ያርፋል፡፡

ረቡዕዕ ታህሳስ 8

የጸሎት
ጸሎ ተምሳሌቶች

ይህን ጥቅስ
ቅ ያንብቡ፡
ያ ቡ ያዕ. ዕ. 5፡17-
5፡17-18
18፡፡ ስለ ጸሎት
ት ከኤልያስ
ከ ል ስ ምሳሌ
ሳ ምን
ም እንማራለን??
ከፈውስ፣ ይቅርታ እና ደኅንነት ጋር ያለው
ያ ው ትስስር
ስ ምን ይመስላል?
ይመስ

------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------------------------

“. . . የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል” (ያዕ. 5፡16) ጥቅሱ
በቁጥሩ መጨረሻ ላይ የተሰጡንን ማረጋገጫዎች ያሳያል፡፡ ኤልያስ “ጻድቅ” ብቻ ሳይሆን
ወደ ሰማይ የተነጠቀ ሰው ጭምር ነበር፡፡ ከዚህ ውጪ ሱፐርማን አልነበረም፡፡ ኤልያስ
በእኛ ያለውን ጥልቅ ስሜት የሚጋራ ሰው እንደ ነበረ ሁሉ፤ እግዚአብሔር የእርሱን ጸሎት
የመሰማቱ እውነታ የእኛም እንደሚሰማ የሚያበረታታን ሊሆን ይገባል፡፡ ያዕቆብ ሲናገር
ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ “አጥብቆ ጸለየ” ይለናል (ዝርዝሩ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
አልተጠቀሰም) ሆኖም ይህ ልመናው ከዘዳግ. 11፡13-17 ፍጻሜ ጋር ተያያዥነት አለው፡፡
(ያዕ. 5፡18 ቀጥታ ባልሆነ መልኩ ዘዳግም ላይ የሚገኘውን መልእክት ይጠቅሳል)፡፡

በዘዳግም መጽሐፍ በትንቢት እንደተቀመጠው እስራኤላውያን የማዕበልና ነጎድጓድ አምላክ


ብለው የሚጠሩትን በዓል ማምለካቸው በዝምታ የሚታለፍ አልነበረም፡፡ ምንም እንኳ
ኤልያስ ጸሎቱ ሳይሰማ ምን ያህል ጊዜ እንደቆየ ባናውቅም ልመናዎቹ በእግዚአብሔር ቃል
የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም
120
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ላይ ያነጣጠሩ፣ በጥንቃቄ የተሞሉ ጥናቶችን መሰረት ያደረጉ እና እርሱ የሚገኝበትን


ነባራዊ ሁናቴ ያገናዘቡ ነበሩ፡፡ ዳንኤል ለኢየሩሳሌም የጸለየው ጸሎት በኤርምያስ ትንቢት
ላይ በነበረው ጥናት ላይ የተመሰረተ እንደነበረ ሁሉ (ዳን. 9፡2-3) በዘዳግም የሚገኘውን
ትንቢት የጸሎቱ አንዱ ክፍል አድርጎ መጥቀሱ ይሆናል፡፡ የምንገኝበትን ነባራዊ ሁናቴ
ከእግዚአብሔር ቃል ብርሃን አኳያ አያይዘን የምናቀርብ ከሆነ እኛም ጸሎት ይበልጥ
ውጠታማ ይሆናል፡፡

ዝናብ ለሦስት ዓመት ተኩል ሳይዘንብ መቆየቱ (በተጨማሪ በሉቃ. 4፡25 ተጠቅሶአል)
በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናገኘው ብርቱ የፈተና ወቅት ነበር፡፡ (እንደ ግማሽ ሳምንት
ትንቢታዊ ጊዜ ወይም በዳን. 9፡27 የተጠቀሰው ሦስት ዓመት ተኩል የሚፈጀው የየሱስ
አገልግሎት እንዲሁም “እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኩሌታ” (ሦስት ዓመት ተኩል)
በክርስትና ላይ የሚፈጸመው ክህደት ዳን. 7፡25 ፣ ራእ. 12፡14)፡፡ ሕዝቡ የሚገኝበትን
የክህደት ጥልቀት ያስተውል ዘንድ በጊዜው መጨረሻ ላይ የመነቃቃትና የተሐድሶ ሥራ
ለመጀመር እግዚአብሔር ኤልያስን ተጠቀመበት፡፡ ሥራው መጥምቁ ዮሐንስ ለክርስቶስ
የመጀመሪያ ምጽአት የጌታን መንገድ የማዘጋጀት አገልግሎት ለመጀመሪያው ክፍለ ዘመን
እስራኤላውያን ከሰጠው እና እግዚአብሔር ዛሬ የምትገኘው ትሩፋን (ቅሬታዋ) ቤተ
ክርስቲያኑ ሕዝቦችን ለዳግም ምጽአቱ የማዘጋጀት ሥራ እንድትሠራ ከሰጣት ኃላፊነት ጋር
ተመሳሳይ ነው (ሚልክ. 4፡5-5፣ ማቴ. 11፡13-14)፡፡

እንደ
ን ቤተ ክርስቲያን
ክ ቲ ---ተሐድሶ
ሐ እና መነቃቃት
መነ ማግኘት
ግኘ ፍላጎታችን
ፍ ጎ ን ቢሆንም
ን ነገር
ገ ግን ይህ
መጀመር
መር ያለበት
ያ በ ዕለት ዕለት፣
ት በግል፣
በ በገዛ ራሳችን
ራ ሕይወት ውስጥ ነው፡፡ እርስዎ
ር ብቻ፣፣
የህይወትዎን አቅጣጫ
አ እና
እ መዳረሻ ሊወስን
ሊወ የሚችል
ሚች ምን ዓይነትነት ምርጫ መምረጥ ጥ
ይችላሉ?
ይችላሉ?

ሐሙስ
ሙ ታህሳስ
ሳ 9

መመለስ
መ ስ እና ይቅር ማለት
የእግዚአብሔር መንፈስ በእስራኤል እና በራሱ በኩል ያለውን ግንኙነት ለማደስ በኤልያስ
ሠራ፡፡ ሆኖም አብዛኛው የኤልያስ ሥራ በቀርሜሎስ ተራራ ብቻ የተገደበ አልነበረም፡፡ ያ
በእርግጥ ጅማሬ ነበር! ኤልያስ ይህን ሥራ ወደ አነስተኛ መንደሮች፣ ቤቶች ብሎም
የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም
121
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

የወደፊቶቹ መንፈሳዊ መሪዎች ሠልጥነው ወደ ሚወጡባቸው የነቢያት ትምህርት ቤቶች


በማሰራጨት የመነቃቃት እና የተሐድሶ ሥራውን በብዙ እጥፍ አበዛው፡፡

የሚከተለውንው ጥቅስ ያንብቡ፡


ያ ቡ ያዕ. 5፡19-
5፡19-20፡፡ በዚህ ስፍራ
ስ ያለው
ያ ሥራ ከኤልያስ፣፣
ከመጥምቁ ዮሐንስ ን እና ከሌሎች ጋር
ጋ ሲነጻጸር ጻ ር እንዴት ይገለጻል?
ለ ል ሉቃ.
ቃ 1፡16-
፡ -177፣
ሐዋ. 3፡19፡፡

-------------------------------------------------------------------------------------------------
-------------------------------------------------------------------------------------------------

ኤልያስ በየዓመቱ በፍቅር እና በትዕግሥት ሲሠራ የኖረውን ሥራ የዘነጋን እንመስላለን፡፡


መጥምቁ ዮሐንስም እንዲሁ ሕዝቦችን ወደ ንስሐ ጥምቀት በመምራት ወደ እውነት
የሚመለሱበት ሥራ ላይ ትኩረት አድርጎ ሠራ፡፡ የሱስ የሠራውን ሥራ ተመሳሳይ በሆነ
አነጋገር ሲገልጽ ይስተዋላል --ሰዎችን ከስህተት አውጥቶ ወደ እውነት መመለስ (ዮሐ.
8፡43-45)፡፡

በያዕ. 5፡19-20 በቀረበው ንድፈሃሳባዊ አገላለጽ ከእውነት መሳት ወይም ክህደት ምናልባት
ሊሆን ቢችል በሚል ተቀመጠ እንጂ በፍጹም ይከሰታል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ከእውነት
መሳት ኃይማኖታዊው አስተምህሮ ላይ ብቻ ሳይሆን አኗኗራችንም ላይ ማፈንገጥ ወይም
ክህደት መፈጸም ነው --የመጀመሪያው ስህተት ወደ ሁለተኛው ይወስደናል! ጥርጣሬ
በእምነታችን ላይ መፈጠር ሲጀምር ሁለት ልብ መሆን ይመጣል፤ በስተመጨረሻም ወደ
ለየለት ክህደት ልንገባ እንችላለን “ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ ሰው
ነፍሱን ከሞት ያድነዋል” (ያዕ. 5፡20)፡፡ ያዕቆብ ቀደም ብለው የቀረቡትን ሃሳቦች በአንድ
ላይ ጠቅለል አድርጎ በማቅረብ በቤተ ክርስቲያን ያሉ ወንድሞች ኤልያስ ካደረገው
በተመሳሳይ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር የመመለስ ሥራ እንዲሠሩ ይማጸናል፡፡

ይህ ሥራ መጠነ ሰፊ ትዕግሥት፣ ርኅራኄ፣ ፍቅር እና እራስን ዝቅ ማድረግ ይጠይቃል፡


“ወንድሞች ሆይ አንድ ሰው በኃጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ
እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል፡፡ ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን እራስህን
ጠብቅ” (ገላ. 6፡1)፡፡ የኤልያስ ሥራ የሰዎችን ልብ ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ሕዝቦቹ
መመለስ እንጂ በተቃራኒው ማራቅ አልነበረም፡፡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ኃጢአታቸውን
በሚገባ ቢያውቁትም እንዲገለጥባቸው ግን አይፈልጉም፡፡ አብልጦ የሚያስፈልገን ነገር
122 የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ቢኖር በየሱስ እና በሞቱ የተሰጠን የይቅርባይነት ምሳሌ ነው፡፡ ነፍስን ከሞት ማዳን
የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ኃጢአትን “በመክደን” ወንጌልን በሕይወታችን ላይ ተግብረን
የምህረት መሣሪያ መሆን ስንችል ነው (ምሳ. 10፡12)፡፡

የከፋ ስህተት
ተ ሠርቶ ስህተቱን
ተ ስለሚያውቅ
ሚያ ቅ ሰውው ያስቡ፡፡
ስ ፡ ይህን
ይ ሰው
ሰ ወደ ጌታ
ጌ ለመመለስ
መመለ
ምን ማድረግ ይችላሉ?
ላ ምንም ሊሉትስ
ት ይችላሉ?

አርብ
ር ታህሳስ
ሳ 10

ተጨማሪ
ጨ ጥናት፡-
ጥናት፡-
ጥና Ellen G. White, “Prayer for the Sick,” pp. 225–
233, in The Ministry of Healing; “Snares of Satan,” pp. 518–523, in The
Great Controversy.

“ክርስቶስ . . . በማዳን ሥራ ከእርሱ ጋር እንድንተባበር በመጠየቅ ‘በነፃ የተቀበላችሁትን


በነፃ ስጡ ይለናል’ (ማቴ. 10፡8)፡፡ ኃጢአት ከክፉ ነገር ሁሉ የከፋ ነው፤ ስለዚህ
ለኃጢአተኛው የማዘን እና ኃጢአተኛውን የመርዳት ኃላፊነት አለብን፡፡ ስህተት የሚሠሩና
በስህተታቸው የሚያፍሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የማበረታቻ ቃል ይፈልጋሉ፡፡ ስለ
ስህተታቸው በማሰብ ተስፋ ወደ መቁረጥ ይደርሳሉ፡፡ እነዚህን ነፍሳት ችላ ማለት
የለብንም . . .

“ለቆሰሉት እንደ ፈውስ ዕጽ የማዳን ኃይል ያለው የእምነት እና የማደፋፈሪያ ቃል


ንገሩአቸው” (የዘመናት ምኞት ገጽ፡ 521-522)፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች፡-
ያ ዎች

በኃጢአትዎ
ኃጢ ት ምክንያት
ክ ያ እራስዎን፣
ራስ ሌሎችንም
ሎ ን ሆነ ጌታን የጎዱበትን
የ ዱ ጊዜ ያስቡ፡፡

ምንም
ም እንኳ
ንኳ የፈጸሙትን
ጸ ት ድርጊት
ር እንዳልተከሰተ
እ ል ተ አድርገው
ድ ባያስቡም
ቡም የሆነው

ሆኖ
ኖ እርስዎንን ለማበረታታት
ማ ታ እና መንፈስዎንን ከፍ ለማድረግ
ለ የሚሠሩ
ሚሠ ሰዎችን
ሰ ን
ማግኘትዎ
ት ለእርስዎስ ምን
ም ያህል ትርጉም
ት አለውው? ሰለነዚህ ተሞክሮዎች
የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም
123
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

አብልጠው
ብ ጠ የሚያስታውሱት
የ ው ት ምንድን
ንድ ነው?? እነዚህ
እ የሚያስታውሷቸው
የ ው ነገሮች
በተመሳሳይ
ተ ከበድ
ከ ያለ ስህተት የሠራን
የ ን ሰው ለመርዳት
መር ት እንዴት
እ ት ሊረዱዎት
ይችላሉ??

ይህንን ጥቅስ
ቅ በጸሎት
ጸ መንፈስ
መን ሆነው
ሆ ው ያንብቡ፡፡ ያዕ. 5፡16፡፡
6 በመልእክቱ ምን
ዓይነት
ት አስፈላጊ
ስ ላ መንፈሳዊ ትምህርት እናገኛለን?
ና ስለለ ጸሎትሎ ኃይል እናእ
ለመንፈሳዊ
መን ዊ ህይወታችን ስላለው
ን ለ አስፈላጊነት
ስ ላ ት ምን ይነግረናል?
ና ምንም እንኳ

ጸሎት
ሎ በእጅጉ
በ የግል
የ ጉዳይ ቢሆንም ለእርስዎ
ለ ስ ውጤትው ስላመጡ
ላ ልመናዎች
እንዲሁም
ን እርስዎ
ስ በፈለጉት
ፈ ጉ መንገድ
መን መልስ ባላገኘው
ባ ገ ጸሎትዎ
ሎ እንዴት በጌታ

መታመን
መን እንደተማሩ
እ ተ በክፍል
ክ ተወያዩ፡፡
ተ ዩ ፡ በመጨረሻ
መጨ “ጸሎት ኃይል አለው”
አ ው
ሲል
ል ምን
ም ማለቱ ቱ ነው?

124 የያዕቆብ መልእክት 4ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ.ም

You might also like