You are on page 1of 107

የባለቤትነት መብት

ይህንን መጽሐፍ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል አባዝቶ ለተለያየ አገልግሎት መጠቀም የሚቻል

ሲሆን በሽያጭ የሚገኝ ገቢ ካለ ግን ለቤተ ክርስትያን ብቻ ገቢ መደረግ ይኖርበታል።

©© 2007 ዓም

i
ምስጋና
የዚህን መጽሐፍ መነሻ ሃሳብ በእንግሊዘኛ ያዘጋጁትና በመነሻነት እንድጠቀምበት
የፈቀዱልኝ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ታምራት ላይኔና ባለቤታቸው ወ/ሮ
ሙሉ ግርማይ፣ እንዲሁም ፓስተር ላሪ ጄ ዊክስና ፓስተር ጆኒ ዊክስ ናቸው። “ሰው ባይረዳን
የጠራንና የሚመራን ጌታ አውቆን ታድጎናልና ሌላ ምን ያሻናል” ሲሉ የሚደመጡት እነዚህ
ቤተሰቦች በጸሎት ምሽጋቸው ለሀገራቸው ሲማልዱና ሲያነቡ ላየ የጌታን የፍቅሩን ጉልበት
መረዳት ያስችለዋል። እውነተኛው መምህር በየዕለቱ በሕይወታቸው ጣልቃ እየገባ ታማኝ
ወዳጅነቱን ገልጦላቸዋልና፣ ይህ ጽሁፍ እንዲወለድና ጌታ በብዙ እንዲመለክ ስለሚተጉ
እድሜያቸው ይርዘም ። ስለ መልካም ፈቃዳቸው እግዚአብሔር አብዝቶ ልባቸውን፣
አዕምሯቸውን እና ጓዳቸውን ይባርክ።
ሰው በአንደበቱም ሆነ በተግባሩ በሌላው ላይ የሚያሳድረው አዎንታዊ አልያም አሉታዊ
ተፅዕኖ ይኖራል። ሐዋርያው ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ለጢሞቴዎስ በላከው መልዕክቱ “በቃልና
በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን
አይናቀው።” (1ኛ ጢሞ 4፥12) እንዳለው፣ ዶ/ር ቄስ ገመቺስ ደስታ በቅርብ በሚያውቋቸው
ክርስቲያኖች ሕይወት፣ አመለካከት እና እምነት ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድሩ
ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት ከጌታ
ነውና በአፋችን ላይ እጅን ከመጫን በላይ ምን ልንል ይቻለናል?! በፍቅር የተሞሉ፣ ሰጥተው
የማይረኩ፣ ተናግረው የማይጠገቡ መልካም መምህር መሆንዎን የሚያውቁ ሁሉ ይመሰክራሉ።
ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልዎት።
በጽሁፍና በቃል በሚያስተምሩት ትምህርት ለሕይወት የሚጠቅም ምክር ለጋሽ ነዎት፤
በተለይ በግለ ታሪክዎ ላይ በማተኮር የጻፉት መጽሐፍ ላይ ስለ ዕድሜዎ ያስቀመጡት
ትንቢታዊ መልእክት ይህ ጽሑፍ ፈጥኖ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ጋሽ በቄ እርሶ ወደ ጌታ
ከመሄድዎ በፊት ይችህን ጽሑፍ እንዲያነቡ በመሽቀዳደም የተሰራች ናት። በእግዚአብሔር
እርዳታ 75 ዓመት ሳይሞላዎ ለንባብ በመብቃቷ ምስጋና ለአምላክ ይሁን። የእግዚአብሔር
ሰላምና ፍቅር ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሕይወትዎም እንደ ምንጭ ዳር ቄጠማ የለመለመችና
ያማረች ትሁንልዎት።

ii
እስከ ዛሬ ድረስ ክርስቲያኖች ወንጌልን በቤተክርስቲያንም ሆነ በግለሰብ ደረጃ፣
ለሚያምኑትም ይሁን ለማያምኑት፣ በቃላቸው እንጂ በሕይወት ኖረው ሲመሰክሩ እምብዛም
አይታይም። ይህ ደግሞ ለብዙዎች እውነተኛውን ኑሮ እንዳይኖሩ መሰናክል ሲሆን ቆይቷል።
በዘመናችን እንደ ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ፣ ለብዙዎች መዳን ምክንያት የሆነ
የእግዚአብሔር ሰው ማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜ የተገኘህ በመሆንህ አምላክ ዘመንህን
ይባርክ ለማለት እወዳለሁ። መጋቢ መስፍን ሙሉጌታ ሕይወትህ ብዙ ታስተምራለች።
የምትናገረውን ሕይወት ኖረህ እውነትን ስላሳየኸን ምስጋና ይገባሀል። እግዚአብሔር
የአገልግሎትህን ዘመን ይባርክ። ጸጋህንም ይጠብቅልህ።
የወንጌልን አገልግሎት፣ ከእግዚአብሔር “እንዲህ ብለህ ተናገር” የተባልነውን መናገር
ነው። ሌሎችን ላለማስከፋት ወይም ተወዳጅነትን ለማትረፍ የም ንቀንሰው ወይም
የምንጨምረው የራሳችን የሆነ ሀሳብ ሊኖር ባልተገባ ነበር። ነገር ግን በቤተክርስቲያን አድር
ባይ ሰባኪዎችና የሀሰት ነቢያት መብዛታቸው የሚያሳዝን ቢሆንም የመጨረሻው ዘመን ፍሬ
ነውና አያስደነግጠንም። ውድ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁንና ፓስተር ማሙሻ ፈንታ እውነትን
በታማኝነት፣ በድፍረት እና በንጽህና የመግለጽ ጸጋችሁ በጣም የሚደነቅ ነው። በተለይ እውነት
በእውቀት ሲገለፅ ያለውን ውበት ማሳየት የቻላችሁ ድንቅ መምህራን ናችሁ። ለዚህ መጽሐፍ
ለንባብ መብቃትም የእናንተ ቆራጥ የሆነ አቋምና እውነተኛ አስተምህሮ ከፍተኛ አስተዋፅዖ
እንዳለው ልገልጽላችሁ እወዳለሁ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ! የነፍስ አገልግሎታችሁ ዘመን
የረዘመች ትሁን።
ገንዘባችሁን፣ እውቀታችሁን፣ እንዲሁም ጊዜያችሁን ሳትቆጥቡ ለዚህ መፅሐፍ ውልደት
ልዩ ድጋፍ ያደረጋቸሁ እናንተ የጌታ ውድ ስጦታዎች ድካማችሁ ለፍሬ በቅቷልና እንኳን ደስ
ያላችሁ። በቅንነትና በትጋት ታዛችኋልና ብድራቱ ከእርሱ በብዙ ይከፈላችሁ።

“እውነት ለሕዝቡ በዚህ መልክ ይገለጥ ዘንድ ለወደደው ድንቅ፣


መካር፣ ኃያል እንዲሁም የሰላም አምላክ ክብርና ውዳሴ ይሁን።”
አሜን።

iii
መቅድም
መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ ሂደቶቹ እየዳበረ የመጣ፣ ረዥም ዕድሜን
ያስቆጠረ እና በዓለም ላይ በበርካታ ሀገራት ቋንቋ ተተርጉሞ የተሰራጨ፣ የእውቀትና ጥበብ
ምንጭ የሆነ አንጋፋ መጽሐፍ ነው። ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ከማጥናት ይልቅ ከሰዎች
በቁንፅል በማድመጥ ባልተሟላ መረዳት ግራ ሲጋቡ ይስተዋላል። ለዚህ ግራ መጋባት ኃላፊነቱን
የሚወስደው በርካታ አካል ቢሆንም የእውቀት ሁሉ ምንጭ የሆነውን ቃል በጥልቀት ከማጥናት
ይልቅ ከራስጌ መብራት ጎን በማስቀመጥ አማኝ የመምሰል አባዜ ከጥበብ አርቆናል። ሀሳቡን
በትክክል ባለመረዳታችን ግራ መጋባት ውስጥ እንወድቃለን። ለዚህ ግራ መጋባት ተጠያቂው
አንባቢው ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የእምነት ድርጅቶች አንዱን የአምላክ ቃል በተለያዩ መልኩ
በመተርጎሙና ተከታዩንም የዚህ አስተሳሰብ ተገዢ ማድረጉ ጭምር ነው። በዚም ምክንያት
በርካታ ሰው ስለ አዲሱ ፍጥረት ያለው ዕውቀት እጅግ አናሳ ከመሆኑ የተነሳ በአምላክ አምሳል
መፈጠሩን ዘንግቶ በአሮጌው አዳማዊ ባህርይ ሲመላለስ ይስተዋላል። በቤተክርስቲያንም
በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ ዓይነቱ ችግር በተደጋጋሚ ሲከሰት ይታያል። በዚሁ መሰረት
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሊታወቁ የሚገባቸውን እውነቶች ሊያሳይ የሚችልና አነስተኛ ግንዛቤ
ሊያስጨብጥ በሚችል መልኩ ይህ መጽሐፍ ተዘጋጅቶ በእያንዳንዱ ነጥቦች ላይ ማብራሪያ
ለመስጠት ሙከራ ተደርጓል።
መጽሐፉ በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀትና መረዳት ለማደግ ለሚፈልግ ለማንኛውም
ክርስቲያን፣ ለአገልግሎት ለሚዘጋጁ ወንድሞችና እህቶች፣ በግል ሕይወታቸውም ሆነ
በአገልግሎታቸው ሊጠቀሙበት የሚችሉ ወገኖችን ሁሉ የሚያገለግል ቅዱሳዊ መረጃ የያዘ
መጽሐፍ ነው። ስለዚህ በዋናነት በቤተክርስቲያን የሚያገለግሉ፣ በአባልነት የታቀፉ እና ገና
ወደ ጌታ መጥተው የክትትልና የደህንነት ትምህርት የሚማሩ ሁሉ ይህን መጽሐፍ በመጠቀም
ሕይወታቸውን ትክክለኛ አቅጣጫን ማስያዝ ይችላሉ።
የእግዚአብሔር ቃል “አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።” (ሮሜ
15፥4) እንደሚል በመጽሐፉ ውስጥ በርካታ ትምህርት ሰጪ የሆኑ ቁምነገሮች ሰፍረው
ይገኛሉ። እነዚህን ቁምነገሮችና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸውን ዓበይት የሆኑ መሰረታዊ
ትምህርቶችን በሚገባ ለመረዳት የዚህች መጽሐፍ ጠቀሜታ ጉልህ ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትና ከሕይወታችንም ጋር ልናዋህደው መሞከር የእውቀት
ሁሉ መጀመሪያና የበላይ ነው። ምክንያቱም በ2ኛ ጢሞ 2፥15 ላይ “የእውነትን ቃል በቅንነት
የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።”
በማለት ይመክራል። በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያላቸውን ትምህርቶች በራሳችን
ሃሳብ ከመተርጎምና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቱን በለቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ
መሰረታዊ እውነቱን ተረድተን ከሕይወታችን ማዛመድ ለግል ሕይወታችንም ሆነ ለሌሎች
እውነተኛውን የሕይወት መንገድ የምናሳይበትና የምንመራበት መንገድ መሆን አለበት።

iv
በምድር ላይ ስንኖር እውነተኛውን ሕይወት እንዳንኖር የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች
አሉ። ከእነዚህ ምክንያቶች አንዱ ለምን እንደምንኖር አለማወቅ ነው። እግዚአብሔር ወደዚህች
ምድር ሲያመጣን በሕይወታችን ላይ ትልቅ ዓላማ ኖሮት ነው። ዓላማችንን አለመረዳታችን
ወዴት መሄድ እንዳለብን እንዳናውቅ ያደርገናል። ተልዕኳችንን አለመረዳታችን የመኖራችንን
ግብ ሳንፈጽም ሕይወታችንን በዋዛ ፈዛዛ እንድናሳልፍ ያደርገናል። ተልዕኳችንን እንድንረዳ
ስለ ተልዕኮው የሚያስረዳን ያስፈልገናል። ይህንን መረዳት የምናገኘው ደግሞ ዘወትር
ከእግዚአብሔር ቃል በመማር ነው። እያንዳንዱን ቀን ከትላንት ይልቅ እግዚአብሔርን
የሚያስከብር ሕይወት ለመኖር ዘወትር ከቃሉ መማር አለብን። ለዚህ ደግሞ ይህች መጽሐፍ
በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ያለውን ነገርና በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ የአማኝን ስልጣን
በማሳየት ጉልህ ሚና ትጫወታለች።
እውነተኛ ሕይወት በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረታዊ አስተምሮዎች ላይ መመስረት አለበት።
በመሆኑም በዚህ መጽሐፍ ወደ ስድስት የሚጠጉ ርዕሰ ጉዳዮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ በውስጣዊ
ማስረጃዎች እየተመሳከሩ በሰፊ ርዕሰ ጉዳዮች ተዳሰዋል። ስለ አዲስ ሕይወት፣ መንፈሳዊ ውጊያ
እና ለተሰበረ ልብ ፈውስ ማግኘት ስለሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች በሰፊው ማብራሪያ ስለተሰጠባቸው
ይህንን መጽሐፍ የሚያነብ ሁሉ ለሕይወቱ እንዲሁም ለአገልግሎቱ ጠቃሚ አቅጣጫ ይይዛል።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያንም ያገኛል ።

“እግዚአብሔር የምናነበውን እንረዳ ዘንድ መረዳቱን ይስጠን፤”


አሜን!!

v
መግቢያ
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከእርሱ ጋር በሕብረት እንዲኖር በመልኩና በአምሳሉ ለራሱ
ክብር እንደፈጠረው የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ በእግዚአብሔር
አምሳል የተፈጠረው ሰው በምድር ላይ እንዲበዛና ምድርን እንዲሞላ የተባረከ ሲሆን ምድርን
እንዲጠብቃትና እንዲንከባከባት ኃላፊነትም ተሰጥቶት ነበር። ሰው ግን በማልማት ፈንታ
በማውደም፣ የእግዚአብሔርን መልክ ከማሳየት ይልቅ ክፋትን በምድር ላይ በማምጣት ምድር
እንድትረገም ምክንያት ሆነ። በነፍሱም ሟች በመሆኑ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ተለየ።
እግዚአብሔር ግን ይህ ሟች የሆነውንና ከእርሱ የተለየውን ሰው ወደ ራሱ ለማምጣት
ወይም ለመመለስ አዲስ የመዳን መንገድ አዘጋጀ። ይህም የመዳን መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ
ነው። በእግዚአብሔር ዕቅድ መሰረት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለና
የሕይወቱ ጌታ አድርጎ የወሰነ ሁሉ ወደ ቀድሞ ማንነቱ እንደሚቀየር እንዲሁም አሮጌው ማንነቱ
እንደሚወገድ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። መጽሐፉ በአብዛኛው የሚዳስሰው ይህንኑ እውነታ
ነው። መጽሐፉ በስድስት ዋና ዋና ምዕራፍ የሚከፈል ሲሆን እያንዳንዱ ተያያዥነት ያላቸውንና
ቅደም ተከተላቸውን የጠበቁ ርዕሶችን ይዟል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ ውስጥ አዲሱን ሰው ስለመረዳትና ሰው በእግዚአብሔር መልክና
አምሳል እንደተፈጠረ በሰፊው ያብራራል። መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ስለ አዲሱ ፍጥረት
የሚናገር ቢሆንም በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ ስለ አዲስ ፍጥረት በሰፊው የተብራራ ትንቢት
ሰፍሯል። በዚህ ክፍል የተነገረው ትንቢታዊ ቃል በመጽሐፉ ውስጥ በስፋት ተዳስሶ እናገኛለን።
ስለ ነፍስ፣ መንፈስ እና ስለ አካል ባህርያት በተጨማሪም ስለ አሮጌው ሰውና አዲሱ ሰው
ምንነት፣ አንድነት እና ልዩነት በጥልቀት በምዕራፍ አንድ ውስጥ ተዳስሶ እናገኘዋለን።
በሽታ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ካሉ የኑሮ ሰንኮፋዎች አንዱ ነው። በምድራችን
ላይ መድኃኒት የሚገኝላቸው በሽታዎች እንዳሉ ሁሉ መድኃኒት የማይገኝላቸው በሽታዎችም
አሉ። መድሀኒት አልባ ከሆኑ በሽታዎች የልብ ስብራት አንዱ ነው። ይህ በሽታ ወደ ሰው ልጆች
ሕይወት ውስጥ የመጣው ከእግዚአብሔር በተለየባት ሰከንድ ነው። በሽታው እንደ አጥንት
ስብራት በወጌሻ ወይም በሕክምና ማዳን የሚቻል አይደለም። የስብራቱ መድኃኒት ኢየሱስ
ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። የዚህ መጽሐፍ ሁለተኛው ምዕራፍ
ስለዚህ ስብራት እንዲሁም ስብራቱ የሚጠገንበትን ብቸኛ መንገድ በተመለከተ ከመጽሐፍ
ቅዱስ አንፃር ያትታል።

vi
እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ በልዩ ሁኔታ የተፈጠረው ሰው ሕግን
መተላለፉ ከእግዚአብሔር ከፈጣሪው ስለለየው ሰው በስጋውና በመንፈሱ ሟች ሆነ። ራሱን
ማዳን የማይችል ልፍስፍስ ከመሆኑም ባሻገር በሰማይም ሆነ በምድር ሊያድነው የሚችል
አካልም አልነበረውም። ምንም እንኳን እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ በመፍጠሩ
የተጸጸተ ቢሆንም ለዚህ ድንቅ ፍጥረት ካለው ፍቅር የተነሳ የመዳን መንገድ ሲያዘጋጅ
እንመለከታለን። ዮሐ 3፥16 “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ
እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንዲያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” ይላል።
ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ታላቅ ፍቅር ነው። ከፍቅሩ የተነሳ ኢየሱስ
ክርስቶስ ከገባንበት አዘቀጥ ሊያነሳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ራሱን አዋርዶ እና የሰውን ስጋ
ለብሶ እኛን ነፃ አወጣን። በዚህ መጽሐፍ ምዕራፍ ሶሰት የምናገኘውም ይህንኑን እውነት
ነው። ኢየሱስ ነፃ አውጪአችን መሆኑን ይገልጽና ከምንና እንዴት ነፃ እንደወጣን ያብራራል።
በክርስቶስ ነፃ በመውጣታችን የልጅነት ስልጣን እንዳገኘን የዮሐ ወንጌል 1፥12 ላይ “ለተቀበሉት
ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው”
በማለት ያረጋግጥልናል። በዚሁ መሰረት በክርስቶስ ነፃ አውጪነት ያገኘነውን ስልጣን በዝርዝር
በማብራራት ያስረዳል።
ሐዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ በምዕራፍ 6፥10 ላይ ስለ መንፈሳዊ
ውጊያ በዝርዘር ገልጾላቸዋል። ውጊያውም ከደምና ከስጋ ጋር እንዳልሆነና በሰማይ ካለው
ከርኩሳን መናፍስት ጋር እንደሆነ ይናገራል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ለተከታዮቹ “በዓለም
ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌአለሁ” (ዮሐ 16፥33) ብሎ
ሲመክራቸው እናያለን። ይህ ምክር የሚያሳየው በምድር ላይ ስንኖር ከሰይጣንና ከጭፍሮቹ
ሁልጊዜ ውጊያ እንዳለብንና ዘወትር በመዘጋጀት ድል መንሳት እንዳለብን ነው። ይህንን እውነት
በሰፊው ለማብራራት የውጊያን ምንነት፣ የሰይጣንና የጭፍሮቹ ባህርያት፣ ውጊያው የት እና
መቼ እንደሚካሄድ በምዕራፍ አራት ላይ በዝርዘር ተቀምጧል። ይህንን ምዕራፍ በማንበብ
ሁልጊዜ የተዘጋጀን እንድንሆንና የመንፈሳዊ ውጊያን ምንነት ተረድተን እንድንኖር መጽሐፏ
ጠቃሚ ምክሮችንና መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረጉ አስተምህሮዎች ይዛለች።

vii
እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ የሰጠው የልጅነት ስልጣን አለ። ይህንን ስልጣን
ለመቀማት ሰይጣን ሁልጊዜ በክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ ጦርነት ይከፍታል። የሚመጣውን
ጦርነት ለመዋጋት ክርስቲያኑ መንፈሳዊ ጦር እቃዎችን መያዝ እንዳለበት የእግዚአብሔር ቃል
ያስተምራል። የጦር ሜዳውንና የውጊያውን ስልት አውቀን መዋጋት ከክርስቲያኖች ይጠበቃል።
የእውነተኛ ሕይወት ጅማሬ ውጊያን ድል በማድረግ እና የልጅነትን ስልጣን ለማንም አሳልፎ
ካለመስጠት የሚጀምር ነው። የመዳን ራስ ቁር፡ ይህ ልጅ ስለሆንን እግዚአብሔርን ከማመስገን
የሚጀምር ሲሆን በመዳናችን ምክንያት የክርስቶስ ልብ እንዳለን የሚያሳይ ነው። 1ኛ ቆሮ2፥16
የጽድቅ ጽሩር፡ ይህ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን እንዲመረምር ከልመና የሚጀምር ነው።
መዝ 139፥23-24 የእውነት መታጠቂያ፡ ለራስና ለእግዚአብሔር እውነተኛ ከመሆን የሚጀምር
ሲሆን ስሜቶችን በመቆጣጠር እውነትን መያዝን ያጠቃልላል። ያዕ4፥3 የመዘጋጀት ጫማ፡
ይህ የውጊያ መሳሪያ ከዝግጅት የሚጀምር ሲሆን ወንጌልን ለጠፉት በማካፈል መማለድንም
የሚያጠቃልል ነው። 1ኛ ጢሞ 2፥1-4 የመንፈስ ሰይፍ፡ ይህ የጦር መሳሪያ ቃሉን ከማወቅ
የሚጀምር ነው። በቃሉ መሰረት መጸለይ፣ በቃሉ መሰረት መኖር እና ቃሉን የሕይወት መመሪያ
ማድረግን የሚያጠቃልል ነው። ዕብ 4፥12 ሌላኛው የመንፈሳዊ ውጊያ መሳሪያ ጸሎት ነው።
አማኞች የሰይጣንን ጦርነት ለማሸነፍ ዘወትር በጸሎት የሚጋደሉበት ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል።
ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ በእነዚህ የጦር መሳሪያዎች ዙሪያ የቀረቡ ዝርዝር ሀሳቦች በመኖራቸው
መጽሐፉን የሚያነብ ሁሉ በምድር ላይ ሲመላለስ ለሚገጥመው ጦርነት በቂ ዝግጅትና ትጥቅ
እንደሚኖረው ሙሉ በይታመናል።
የሰው ልጅ ዘረ-መሉ ምን እንደሆነ ማወቁ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። ዋነኛ ማንነታችንን
ከሚገነቡትና ከሌሎች ሰዎችና ፍጥረታት ከሚለዩን ነገሮች የመጀመሪያው ዘረመል (DNA)
ነው። በዓለም ላይ ያለን ፍጥረታት በሙሉ የራሳችን ብቻ የሆነ ዘረ-መል አለን። ይህ ዘረመል
የማንነታችንን ዕድገት፣ ባህርይ እና አሠራራችን ይለያል። ዘረመል ከወላጆቻችን ከተወጣጡ
የበራሂ (genes) ድብልቅ የሚመጣ ሲሆን ለእኛ የተለየ ማንነት የሚሰጥ የንድፍ መዋቅር
ነው። ከእናትና አባታችን የምንወርሰው የዘረመል ክፍልፋዮች በትንሹ ቢያመሳስለንም
ፍፁም የሆነ ልዩነትም ይሰጠናል። ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር አባታችን ሰውን በመጀመሪያ
ሲፈጥር የተነፈሰበት የሕይወት እስትንፋስ መንፈሳዊ ዘረመላችንን በእርሱ አምሳል እንዲገነባ
አድርጎታል። ይህም ማንነታችን መንፈሳዊ ዕድገታችንን፣ ስራችንን፣ የግል ባህርያችንን
በአጠቃላይ ዓላማችንን የሚወስንልን ክፍል ነው። መንፈሳዊ ዘረመላችን በእግዚአብሔር
አምሳል የተገነባ ነበር። ነገር ግን ይህን ዘረመል በኃጢአት ምክንያት ተበላሽቷል። ስለዚህ
በኃጢአት የተበከለውን መንፈሳዊ ዘረመላችንን ለማንጻት በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን
ያስፈልጋል። ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው። (2 ቆሮ 5፥17)

viii
“የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።”
ኢዮ 33፥4። በመሆኑም የመጽሐፉ የመጨረሻ ምዕራፍ የሚያስረዳን ይህንኑን እውነት ነው። ይህ
በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው ሰው እንዴት እንደተበከለና እንዴት የዓመፅ ምንጭ እንደሆነ
የዓመፅ ውጤቱን በመግለጽ እንዴት ከውስጣችን አስወግደን እውነተኛውን ሕይወት መኖር
እንደም ንችል ያስረዳል።
በመሆኑም ይህንን መጽሐፍ በማንበብ በግል ሕይወታችንና በአገልግሎታችን እንዴት
እውነተኛውን ሕይወት መኖር እንደምንችል የሚያስረዱ ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
መሰረት ያላቸው መመሪያዎች እና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንዲሁም
ማስረጃዎች ያላት መጽሐፍ መሆኗን ለማስገንዘብ እፈልጋለሁ። ሁላችንም ከመጽሐፏ ጠቃሚ
የሚሆኑ ምክሮችንና ተግሳጾችን ስለምናገኝ ጌታ እስኪመጣ ድረስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎቹን
ተግባራዊ እያደረግን በድክመታችን ደግሞ እርሱ እንዲረዳን በመፍቀድ እንድንኖር ወንድማዊ
ምክሬን አስተላልፋለሁ። የእውነተኛ ሕይወት መንገድ ጠፍቶብን በመጨረሻው ቀን ከሕይወት
መዝገብ እንዳንታጣ የአዲሱ ሰው ባህርይን ተላብሰን፣ የሚመጣውን ጦርንት በመንፈሳዊ ውጊያ
ተዋግተን፣ እንዲሁም የተሰጠንን የልጅነት ስልጣን እስከመጨረሻው ይዘን መቆየት እንድንችል
ተግተን እንጸልይ።

የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ፤ ይብዛልን፤ አሜን !!

ix
ርዕስ ማውጫ
ምዕራፍ 1 አዲሱን ፍጥረት መረዳት 4
1.1 ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል 6
1.2 ስለ አዲስ ፍጥረት የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ቃል 9
1.3 ለምን እንታገላለን? 10
1.4 ነፍሳችንና መንፈሳችን 11
1.5 የነፍስ ባህርያት 11
1.6 የነፍስ ተፅዕኖ 11
1.7 የስጋ ወይም የአካል ባህርያት 12
1.8 አሮጌው ሰውና አዲሱ ሰው 12
1.9 አዲሱን ፍጥረት መረዳት 13
1.10 ደህንነታችንን ማስፈፀም 13
1.11 አሮጌውን ሰው ማስወጣት 14
1.11.1 ስለዚህ እንዴት አሮጌውን ማንነት ማስወገድ እንችላለን? 15
1.12 በክርስቶስ ያለን አዲስ ቦታ (ማንነት፥ ስለራሳችን ያለን
አመለካከት) 16
1.13 ቃል ኪዳኑን መተግበር 17
1.14 ማጠቃለያ 17

ምዕራፍ 2 የተሰበረውን ልብ መፈወስ 19


2.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስብራትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ
ምን እንደሆነ ይነግረናል 19
2.2 ስብራት ምንድን ነው? 20
2.3 ልብ ምንድን ነው? 21
2.3.1 ልብ እንዴት ይሰበራል? 21
2.4 በሕይወታችን ያለውን ስብራት ማስተዋል 23
2.4.1 የስብራት ባህርያት 23
2.4.2 በሁለት ሃሳብ መሆንvv 23
2.4.3 በሁለት ነፍስ መሆን 23
2.5 ለልባችን ቁስል እንዴት ፈውስን ማግኘት እንችላለን? 25
2.5.1 የልብ ስብራት ፈውስን መቀበል መማር 25
2.5.2 ሌሎችን ማፅናናት 27
ምዕራፍ 3 ኢየሱስ ነፃ አውጪያችን 28
3.1 በኢየሱስ ነፃ መውጣት ማለት ምን ማለት ነው? 29
3.2 ኢየሱስ ከምንና እንዴት ነፃ እንዳወጣን 29
3.2.1 ከምን ነፃ ወጣን? 30
3.3 በክርስቶስ ኢየሱስ ነፃ የወጣ ሰው የተሰጠው ስልጣን 32

ምዕራፍ 4 መንፈሳዊ ውጊያ 41


4.1 የመንፈሳዊ ውጊያ ጭብጥ 41
4.2 የሰይጣንና ጭፍሮቹ ማንነትና ባህርያት 42
4.3 መንፈሳዊ ውጊያ የት፣ መቼ እና እንዴት ይካሄዳል? 46
4.3.1 ጠላት ዲያብሎስ ክርስቲያኖችን ለማጥመድ የሚጠቀምባቸው
ስልቶች 47
4.3.2 ነፍሳችን ሕይወታችንን እንድትመራ በመፍቀድ 48
4.3.3 ለገንዘብ ጤናማ ያልሆነ ፍቅር እንዲኖረን በማድረግ 48
4.4 እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች 49
4.4.1 በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር 54
4.4.1.1 መሪዎችና እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች 54
4.4.1.2 ዲያብሎስ የራሱን ባህርይ በመጠቀም 55
4.4.1.3 በዓመፅ በተያዙ ሰዎች አማካኝነት 55
4.4.2 የጥንቆላ መንፈስና ቤተክርስቲያን 56
4.4.2.1 የጥንቆላን ጥቃት መረዳትና መለየት 58
4.4.2.2 አስማት 59
4.4.3 በጥንቆላ መንፈስ ላይ ድልን መቀዳጀት 60
4.4.4 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማያከብሩ የሚደርስባቸው ችግሮች 63
4.4.5 የህቡዕ ድርጅት አደገኛነት 65
4.5 የዲያብሎስን ሥራ ማጋለጥና ማፍረስ 65
ምዕራፍ 5 የአማኞች ስልጣንና የመውጊያ
መሳሪያዎች
5.1 የአማኞች ስልጣን 70
5.2 መንፈሳዊ ማሰልጠኛ 73
5.2.1 ክርስቶስ ከጠላት ጋር እንድንዋጋ ያሰተምረናል፤ ያሰለጥነናል 73
5.2.2 ክርስቶስ በማበረታታት ያግዘናል 73
5.2.3 መልካሙን ጦርነት እንድንዋጋ ያስችለናል 74
5.3 ከእግዚአብሔር የሆኑ መንፈሳዊ የጦር እቃዎች 75
ምዕራፍ 6 መንፈሳዊ ዘረመልን መረዳት
(SPIRITUAL DNA) 84
6.4 መንፈሳዊ ዘረመል ምንድን ነው? 84
6.5 አሉታዊ/የተበከለ ዘረመል፥ ዓመፅ 84
6.2.1 የዓመፅ ፅንሠ ሀሳብ/የዓመፅ ምንነት 84
6.2.2 የዓመፅ ምንጭና ባህርይ 86
6.2.3 ዓመፅ የሚያስከትለው መዘዝ 88
6.6 ደህንነት/በክርሰቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን በእግዚአብሔር
አምሳል ዘረመልን መልሶ መገንባት 90
6.3.1 ዓመፅን ማስወገድ 90
6.7 በደልና የሰው መንፈስ፥ 92
6.4.1 የሰውን መንፈስ መረዳት 92
6.4.2 የመንፈሳችን አዕምሮ 93
6.8 ሕይወትን እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ መምራት 97
ምዕራፍ 1
አዲሱን ፍጥረት መረዳት

♥♥ «ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ነገር አልፏል፤ እነሆ ሁሉም አዲስ
ሆኗል።» 2ቆሮ 5፥17
አብዛኞቻችን አዲስ ነገርን እንወዳለን። በተለይ ደግሞ ጥቅም የሚሰጥ አዲስ ነገርን። ዘወትር
አዲስ መኪና፣ አዲስ ልብስ፣ አዲስ ቤት ወዘተ እንዲኖረን እንሻለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተለይ
በአዲስ ኪዳን ላይ “አዲስ” የሚለው ሀረግ በተደጋጋሚ የወንጌልን የተለያዩ ፈርጆች ለማስረዳት
ጥቅም ላይ ውሏል። አዲሱ ውል፣ አዲሱ ፍጡር፣ አዲስ ትዕዛዛት፣ አዲስ ገነት እና አዲስ ምድርን
በአብነት መጥቀስ ይቻላል። (ኢሳ 65፥17-20፣ 66፥22፣ ዕብ 12፥26-28፣ ራዕ 21፥1-4)
†† ለመሆኑ “አዲስ ፍጥረት መሆን” ማለት ምን ማለት ነው? ጳውሎስ ስለ አዲስ ፍጥረት
በቆላስያስ 1፥26-27 ላይ “በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ የሕይወታችን መሰረት ነው፤”
ሲል ፅፏል። ይህም ለረዥም ዘመናት ከሰው ዘር ልቦና ጠፍቶ የነበረ እውነት ነበር።
አዲስ የሚለው ቃል በፊት ያልነበረን ነገር ወደ ማኖር ማምጣትን ያመለክታል። አዲስ
ፍጥረትም በፊት የሌለ ህልውናን ወደ መኖር ያመጣዋል። የነበረን ነገር ወደ አዲስ ለመቀየር ደግሞ
ወይም ፈርሶ መሰራት አለበት አልያም ቀድሞ የሌለውን ነገር ጨምሮ መታደስ አለበት። በእርግጥ
እንደሰውኛ የሰው ልጅ አዲስ ፍጥረት መሆን አለበት ሲባል በስጋዊ አካሉ ሞቶ መነሳት ወይም ወደ
እናቱ ሆድ ተመልሶ ገብቶ በድጋሜ መወለድ አለበት ማለት ሳይሆን ሲፈጠር ከነኃጢአቱ የነበረውን
መንፈሱን ለክርስቶስ ተገዢ በማድረግ፣ እግዚአብሔር በላከው በአንድያ ልጁ በማመንና ከኃጢአት
በመራቅ እንዲሁም ከቀድሞ የተለየ አተያይና የአኗኗር ዘዬ መከተልን የሚያሳይ ሀሳብ ነው።
♥♥ “ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ
ተገልጦአል።ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት
ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ
መሆኑ ነው።” ቆላ1፥26-27
4
†† እንደ አማኝ ሕይወታችን የሚመሰረተው አዲስ ፍጥረት በመሆናችን ላይ ነው፤
ምክንያቱም ክርስቶስ በእኛ ዘንድ አለ።
♥♥ “የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን
መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ
ይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም
ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” 1ቆሮ3፥10-11
†† አንድ ሰው ክርስቶስን ሳይቀበል የሚያሳልፈው የሕይወት ዘመን በሙሉ ባረጀና
በቆሸሸ ማንነት የሚጓዝበት ዘመን ለመሆኑ አጠራጣሪ አይደለም። በዮሐንስ ወንጌል
ላይ ክርስቶስን ለሚፈልጉት ሁሉ እንደመጣ በመናገር፣ ማመን የክርስቶስ ልጅ ሆኖ
በአዲስ ማንነት መገለጥ ማለት እንደሆነ ይገልፃል።
♥♥ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ
ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ
ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።” ዮሐ 1፥12-13
እዚህ ጋር ለአብነት ያህል ጌታ በገሊላ ቃና ሰርግ ላይ ተገኝቶ ያደረገውን ተአምር
ብናይ መልካም ነው። ውኃውን ወደ ወይን ጠጅነት ሲቀይር በመጀመሪያ ያዘዘው ከገንቦው
ውስጥ ያለውን አሮጌ የወይን ጠጅ እንዲያወጡና ንፁህ (አዲስ) ውኃ እንዲጨምሩበት ነበር።
በመቀጠልም ከገንቦው ውስጥ ውኃውን እየቀዱ ለእንግዶቹ እንዲያድሏቸው አዘዛቸው።
አስተናጋጆቹ ወይን ጠጁን ቀድተው ለእንግዶቹ ሲሰጡ ቀድሞ ከነበረውና ለብዙ ቀናት
ከተጠመቀው የወይን ጠጅ እጅግ የላቀ ጣዕም ያለው ሆነ ተገኘ። የዛኔ የቀድሞው የወይን ጠጅ
መናኛ (የማይረባ) ተባለ። ጣዕም ያልነበረው ውኃ ጣዕም ተሰጠው፤ ሽታ ያልነበረው ውኃ
ባለ መዓዛ ሆነ፤ መልክ ያልነበረው ውኃ ባለ ቀለም ሆነ። አዲስ ሰው መሆንም ልክ እንደዚሁ
ነው። የክርስትና ሕይወታችን ጣዕም አልባ ቢሆን፣ ሽታው ቢከረፋ፣ መልከ ጥፉ ቢሆን
ጌታን ስንቀበልና ውስጣችንን በመንፈሱ ሲሞላው ሁሉ ነገር ይቀየርና ተቃራኒውን ክብር
እንጎናጸፋለን። ቀድሞውንም መሆን የነበረብንን ሰዎች እንሆናለን። ከራሳችን አልፎ በዙሪያችን
ላሉ ሰዎች ሰላም እንሆናለን። (ዮሐ 2፥1-11)
ብዙ ሰዎች በኃጢአተኛ ተፈጥሯዊ ማንነት እንደምንወለድ አያምኑም። ነገር ግን
ከአዳምና ሄዋን ዘር የወጣ የሰው ልጅ ሀረግ ሁሉ የኃጢአት ውርስ እንዳለበት ቅዱስ ቃሉ
ያስተምራል። እንደተወለድን ብንሞት እንኳ የውርስ ማንነታችን አብሮን አለ። ይህ ኃጢአተኛ
ማንነትም ከአባታችን ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የገደበው
ነበር። ኃጢአትን ለማሰረይ በየጊዜው በሚደረግ የደም መስዋዕት የነበረው ስርዓት በአንድያ
ልጁ የመጨረሻ መስዋዕትነት ሲዘጋ እግዚአብሔር ልጆቹ ወደ ፊቱ ያለመከልከል እንዲቀርቡ
በማሰብ ነው። ይህንንም በማመን ልጆች ለአባታቸው ጥሪ ምላሽ ሲሰጡ የድሮ ማንነታቸውን
በመግደል አዲስ ማንነትን ይቀበላሉ። ክርስቶስ የእኛን ኃጢአት ለማሰረይ የመጣ አንዱና ብቸኛ
መንገድ መሆኑን ከተረዳንና ካመንን ያኔ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን።

5
ጳውሎስ በመልዕክቱ መሰረታዊ እውነት የሆነውን ክርስቶስን፣ አዲስ ፍጥረት መሆናችንን
እና አሮጌው ነገር እንዳለፈ ሁሉም ነገር አዲስ እንደሆነ ያስተምራል። በዓለም፣ በስጋ እና
በሰይጣን ላይ የተቀዳጀነው የድል ምክንያቱ በክርስቶስ እንደ አዲስ መሰራታችንና መሰረታችን
እርሱ መሆኑ ነው።
በመሆኑም በተፈጥሯዊ ማንነታችንና በክርስቶስ በማመናችን ም ክንያት በተሰጠን
የክርስቶስ ልብ መካከል ያለ ልዩነት አለ። በክርስቶስ አምነን ዳግም ስንወለድ አዲስ ማንነት፣
አዲስ ተፈጥሮ እና የክርስቶስ ልብ ተሰጥቶናል። ማንነት፥ ራስን የመሆን ሁኔታ፣ የእኛነታችን
መገለጫዎች ወይም ስለራስ የሚኖር ግንዛቤ ነው። በክርስቶስ አምነን ዳግም ስንወለድ
በተፈጥሮ ውርስ በሚገኝ ማንነት ውስጥ እናገኛለን። ውርስ የአንድን ነገር ወይም የአንድን ሰው
ባህርይ መያዝ ሲሆን በአዲስ ተፈጥሯዊ ባህርይ እንደገና ተወልደናል፤ የእግዚአብሔር ተፈጥሯዊ
ባህርይ ወራሾች ሆነናል የሚለውን እውነታ የሚያረጋግጥልን ነው። በክርስቶስ አምነን ዳግም
ስንወለድ የክርስቶስ ልብ ተሰጥቶናል። እርሱ የሚያስበውን የማሰብ ብቃትና የመለኮትን
ምስጢር የመረዳት አቅም አለን።

1.1 ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል


♥♥ «እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት
አድርጎ ፈጠራቸው።» ዘፍ 1፥27
ሁላችንም “በእግዚአብሔር አምሳል” መፈጠራችንን ከልጅነት እስከ እውቀት ስንሰማው
የቆየነው ጉዳይ ነው። በእውነቱ ይህ መልካም ሀሳብ ነው። ምናልባትም የሰው ልጅ ለራሱ
የሚሰጠውን ግምት ለማስታወስ ሲያስብ በአዕምሮው የሚከሰት የመጀመሪያ ሀሳብ ሊሆን
ይችላል። ነገር ግን እኛ ሰዎች በራሳችን የፊታችን ገፅታ በመልክ ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን ጥቁር፣
አንዳንዶቻችን ነጭ፣ ገሚሶቻችን ደግሞ ጠይም ስንሆን በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶቻችን
የረዘምን የተቀረነው ደግሞ አጠር ያልን፣ አንዳንዶቻችን ወፍራም ሌሎቻችንም ቀጭኖች ነን።
ታዲያ እኛ ራሳችን ሳንመሳሰል ጌታን እንዴት ልንመስለው እንችላለን? እውነት “በእግዚአብሔር
መልክ መፈጠር ማለት ምን ማለት ነው?”
የልጆችን ባህርይና እንዴት ቤተሰቦቻቸውን እንደሚመስሉ በመመልከት በእግዚአብሔር
አምሳል መፈጠር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተሻለ መልኩ መረዳት እንችላለን። ልጆች
ራሳቸውን ሆነው እያለ ወላጆቻቸውን በአካልና በባህርይ መስለው ይወለዳሉ። አብዛኛውን ጊዜ
ህፃናት ከወላጆቻቸው አንዳቸውን በመልክ ሲመስሉ ድርጊታቸው ደግሞ እንደ ሌላኛው ወላጅ
ሊሆን ይችላል፤ ይህንንም በማንሳት ህፃናት የቤተሰቦቻቸውን ባህርይና አገላለፅ ወርሰዋል
ሲባል ይስተዋላል።
ሁላችንም ለወላጆቻችን ልዩ የሆነ የራስ ማንነት ያለን ግለሰቦች ነን። የእግዚአብሔር ልጅ
ስንሆንም በተለያየ መልኩ የእርሱን ባህርይ አገላለፅ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እናሳያለን።
እግዚአብሔር አዳምና ሄዋንን በአምሳሉ ሲፈጥር የሰው ዘር የእርሱን መለኮታዊ ማንነት፣
ዝንባሌና የአስተዳደሩን ስርዓት በምድር ሁሉ ላይ እንዲያሰፍን ነው።
6
እኛ ሰዎች በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተሰርተናል። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጠር
እርሱን የሚመስልበትን የዘላለማዊነትን፣ የእውቀትን፣ የመልካምነትን እና የገዢነትን መንፈስ
(እስትንፋስ) እፍ አለበት። ይህ እስትንፋስ ለየትኛውም ፍጥረት አልተሰጠም (ለመላእክትም
ቢሆን)። የእግዚአብሔር የሆነው መንፈስ በእስትንፋሱ ውስጥ ባህርዩን በውስጣችን
አኑሮልናል። ሰውንና እግዚአብሔርን ያመሳሰለውና ያገናኘው ይህ በውስጣችን ያለው
የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው። እግዚአብሔር፥ መንፈስ ነፍስና (እሳቤ፣ ስሜት እና ፈቃድ)
መንፈሳዊ አካል ያለው አምላክ ነው። ሰው መንፈስ ያለው ራሱን የሚገልጥበት ነፍስ ያለው
ሲሆን በስጋዊ አካል ይገለጣል።
♥♥ “የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ ስጋችሁም
ጌታችን ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ያለነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።” 1ኛ ተሰ 5፥23

የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት የእግዚአብሔርን ማንነት፣ ፍጥረት እና ስልጣን የሚገልጥ


ማንነት ነበረው። በገላ 5፥22 የተዘረዘሩት የመንፈስ ፍሬ የእግዚአብሔር ባህርያት ናቸው።
እነኚህን የመንፈስ ፍሬ መለማመድና ለዓለም መግለጥ ከእኛ ከአዲስ ፍጥረቶች የሚጠበቅ ነው።
♥♥ “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣
ራስን መግዛት ነው።” ገላ 5፥22
†† በ1ኛ ቆሮ 13 የተፃፈውን የፍቅር ትርጉም በማንበብ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ምንነትና
የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት ስለነበረው ማንነት በይበልጥ መረዳት እንችላለን።
♥♥ “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤
የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤
ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን
ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።” 1ኛ ቆሮ 13፥4-7
ከአዳምና ከሄዋን ውድቀት በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ረገመ። ከዛን ጊዜ ወዲህ የዚህ
እርግማኑ ውጤት የሆኑ ብዙ ለውጦች ተስተናግደዋል። እሾህና አሜኬላ የተባሉ የተፈጥሯችን
ያልሆኑ የአኗኗርና የባህርይ ለውጦች ፍጹም ወደተለየ ማንነት መርተውናል። ንፁህ፣ ፃድቅ
እና ቅዱስ የነበረው የሰው ልጅ ተፈጥሮ በኃጢአትና በዓመፅ ተበክሏል። ለዘላለማዊነት
የተፈጠረው ፍጡር ለሞት ተገዢ ሆኗል። ከዚህ ማንነት የተነሳ ምድርን በመግዛት ፈንታ
ለምድራዊ ነገር ተገዢ ለመሆን ተገዷል። ንፁህ ልብ ሆኖ የተፈጠረው የሰው ዘር እንደ ቃየን
7
ወንድሙን የሚገድል (ዘፍ 4)፣ እንደ አምኖን እህቱን የሚደፍር (2 ሳሙ 13)፣ እንደ ኢዮብ
ሚስት አምላክህን ስደብና ሙት የሚል (ኢዮ 2)፣ እንደ ይሁዳ ወዳጁን የሚሸጥ (ሉቃ 22)፣
እንደ አይሁድ ቅዱሱን ሰቅለህ ወንበዴውን ፍታ የሚል ሆኗል (ማቴ 27)።
♥♥ “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥
በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ
ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው።በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ
ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር
ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።” ኤፌ 2፥1-3
♥♥ ለ̋ ሴቲቱም አለ፥- በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም
ወደ ባልሽ ይሆናል እርሱም ገዢሽ ይሆናል። አዳምንም አለው፥- የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና
ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝኩህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ካንተ የተነሳ የተረገመች ትሁን፤
በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ። ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ
ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህና።” ዘፍ 3፥16-19
ነገር ግን ኢየሱስ የሰው ልጆች በውስጣቸው አዲስ ባህርይ ኖሯቸውና በድጋሚ ተወልደው
አዲስ ፍጥረት እንዲሆኑ መንገድ ለመክፈት ወደዚህ ምድር መጥቷል። የጠፋውንም ሊፈልግ
ወደ መሬት ወርዷል። በእርሱ መምጣትም ይህች በክፋት የቆሸሸች ዓለም ተቃራኒ በሆነ
ማንነትና አዲስ በሆነ ምላሽ ተቀይራለች። የኃጢአት ብርድ ላንቀጠቀጣት ዓለም እርቃኑን
በመሰቀል የጸጋውን ኩታ አልብሷታል። ለማየት በሚከብድ አሰቃቂ መንገድ ለሚወግሩት
አካላት “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት ቂም የነገሰበት ልብን ሰብሮ
ፍቅርን አስርጾበታል፤ ሞትን ድል አድርጎ በመነሳት ዘላለማዊነቱን መልሶለታል። እነዚህም ሁሉ
በኃጢአት ምክንያት መስመሩን የለቀቀው የሰዎች ማንነት በክርስቶስ አዲስ አቅጣጫ መያዙን
ያመለክታል።
♥♥ “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌው ነገር አልፏል፤ እነሆ ሁሉም
አዲስ ሆኗል።” 2ኛ ቆሮ 5፥17
♥♥ “በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ
አይጠቅምምና።” ገላ 6፥15
†† ጳውሎስ አዲስ ፍጥረት የመሆን አስፈላጊነትን እንዲህ ሲል ይናገራል። ኢየሱስ አዲስ
የሰውን ዘር ጅማሬ ሊቀይስ ወደዚህ ምድር መጣ፤ በመንፈሱም የተወለዱ ወንዶችና
ሴቶች ልጆቹ በውስጣቸው የእግዚአብሔር ባህርያዊ ማንነት አለ።
♥♥ “እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ
በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን
ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ
ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።” ኤፌ 2፥15-16
♥♥ “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤
ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” ገላ 3፥28-29
†† ክርስቲያን መሆን ማለት አንድን የእምነት አቋም ማራመድ ሳይሆን በክርስቶስ መሆን
ማለት ነው። ዋናው ጥያቄ “በክርስቶስ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?” የሚለው ነው።
8
1.2 ስለ አዲስ ፍጥረት የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ቃል
†† በሕዝ 36፥26-27 ላይ ዳግም ስንወለድ ስለሚሆነው ነገር ምስል ከሳች በሆነ ትንቢታዊ
ቃል አስቀምጦታል።
♥♥ “አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ
ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ
በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።” ሕዝ 36፥26-27
እግዚአብሔር ከሰውነት አካላት ሁሉ ዋነኛ የሆኑትን አዲስ ልብንና አዲስ መንፈስን
አጎናፅፎናል። የነገሮች ሁሉ ምንጭ ልብ (አዕምሮ) ነውና። አንዲት መኪና ሌላው አካላቷ
በሙሉ አዲስ ሆነው ሞተሯ ግን ያረጀ ከሆነ ምንም አትጠቅምም። ምክንያቱም የመኪናዋ
ሁለንተና በሞተሩ ጉልበት ይወሰናልና። መላ አካላቷ ቢቆሽሽ ምንም ችግር ላይኖረው ይችላል።
ሞተሩ ከቆሸሸ ግን መኪናዋ መንቀሳቀስ ያቅታታል። የሰው ልጅ ልቦናም እንደመኪናዋ
በመሆኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ “…ልብህን ጠብቅ፤” በማለት ይናገራል። የሰው ልብ ከቆሸሸ ወይም
ካረጀ መልካም አይደለም። ምክንያቱም ልባችን የማንነታችን መገለጫ ነውና ። ነፍሳችን
የምትገኘው ልባችን ውስጥ ሲሆን የአስተውሎታችንና የስሜታችን ውህድ ናት። ልባችን
ደግሞ መንፈሳችንና ነፍሳችን የሚገኙበት ቦታ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኛችን
አድርገን ስንቀበል በእርግጥ እንደገና ተወልደናል ማለት ነው። አንድ ነገር ተወለደ ሲባል
ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰትን ያመለክታል። የሕዝቅኤል መጽሐፍ (36፥26-27) እግዚአብሔር
አዲስ ልብና አዲስን መንፈስ እንደሚሰጠን ሲናገር የቀድሞ ልባችንን እንደገና እንደሚሰራው
ሳይሆን የሚያመለክተው፣ አልገዛ ያለውን ልባችንን አውጥቶ ከዚህ በፊት ያልነበረንን አዲስ
ልብን እንደሚሰጠን ነው። ኃጢአታችንን ከመንፈሳችን አላጠበልንም፤ ነገር ግን መንፈሱን
በውስጣችን አደረገ። ከዚህ በፊት በውስጣችን ያልነበረን አዲስን መንፈስ ሰጠን። እንደገና
ተወልደናል፤ በመንፈሳችን አዲስ ሆነናል፤ አዲስ ልብ ተሰጥቶናል። ስለዚህ በክርስቶስ አዲስ
ፍጥረት ሆነናል። አዲስ ፍጥረት ስለሆንን አሁን አዲስ ማንነት አለን። (2ኛ ቆሮ 5፥17)
†† ብዙ ሰዎች ስለ ልብ ሲናገሩ የኤርሚያስን መጽሐፍ በተሳሳተ መንገድ ይጠቅሳሉ።
ትንቢተ ኤርሚያስ ምዕራፍ 17 ቁጥር 9 ላይ “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛና
እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?” በማለት የሰውን ማንነት አስቀምጦታል። እዚህ
ጋር አንድ የተረሳው ነገር መጽሐፉ የተፃፈው ላልተለወጠ ማንነት መሆኑን ነው።
♥♥ “ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ
ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” ዮሐ 3፥5-7
†† የእግዚአብሔር አምሳያ ነን (2ኛ ጴጥ 1፥4)፤ በክርስቶስ አንድ መንፈስ መሆን ችለናል
(1ኛ ቆሮ 6፥17)፤ የመንፈስ ፍሬ ተሰጥቶናል (ገላ 5፥22-23)፤ ፅድቅ አግኘተናል (2ኛ ቆሮ
5፥19፣ ሮሜ 5፥17-18)፤ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለው ሆነናል (ቆላ 1፥21-22)፤ ለዘላለም ፍፁም
ሆነናል (ዕብ 10፥14)፤ የክርስቶስ ልብ ተሰጥቶናል (1ኛ ቆሮ 2፥16)፤ እነዚህም ከተሰጡን
አዳዲስ ማንነቶች መሀከል መጠቀስ ይችላሉ።

9
1.3 ለምን እንታገላለን?
እስካሁን ያልነው ሁሉ እውነት ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እኛ የሚናገረውን መሆን ለምን
አልቻልንም? ከስጋዊ ኃጢአት ጋር ለምን በየእለቱ እንታገላለን? ሰይጣን እንዴት አካላዊና ስነ
ልቦናዊ ችግር ሊፈጥርብን ቻለ? እንዴት በእኛ ውስጥ ያለውን የክርስቶስ መለኮታዊ ባህርይ
ተካፋዮች መሆን እንችላለን?
ከላይ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች መልስ ሊሆን የሚችለው እኛ ዳግም የተወለድነው
ከመንፈሳችን የተነሳ አዲስ ልብ ተሰጥቶናል። ነገር ግን ነፍሳችን ዳግም አልተወለደችም።
መጽሐፍ ቅዱስ ፍጥረት ስጋ፣ መንፈስ እና ነፍስ እንዳለው ያስተምራል። በአንዳንድ ቦታዎች
ላይ መንፈስንና ነፍስን እየቀያየረ ቢጠቀምም በሌሎች ቦታዎች ላይ ግን እንደሚለያዩ በግልፅ
አስቀምጧል። በዕብራውያን 4፥12 ላይ እንደተገለፀው ከሰው አዕምሮ በላይ ሊሆን የሚችል ነገር
ግን ግልፅ የሆነ ልዩነት በመንፈስና በነፍስ መካከል አለ።
በክርስትናው ዓለም የሰው ልጅ ከምን እንደተሰራ ከሚንፀባረቅባቸው የተለያዩ
አመለካከቶች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት የ“ዳይኮቶሚ”ና የ“ትራይኮቶሚ”
ዶክትሪኖች ናቸው።
†† የዳይኮቶሚ አስተምህሮ የሰው ልጅ በስጋና በነፍስ ብቻ የተዋቀረ ነው የሚል ሲሆን
ሰው በስጋው ከቁሳዊው ዓለም ጋር መገናኛ እንደሆነና መንፈስ ግን ከመንፈሳዊው
ዓለም ጋር (ከእግዚአብሔር ጋር) የሚያገናኝ የነፍስ አንድ ክፍል እንደሆነ ይገልፃል።
(ዘፍ 2፥7፣ መክ 125፥7፣ ማቴ 10፥28፣ 2ኛ ቆሮ 5፥1-10)
†† የትራይኮቶሚ አስተምህሮ የሰው ልጅ በስጋ፣ በነፍስ እና በመንፈስ የተዋቀረ ነው
የሚል ነው። የሰው ልጅ ስጋዊ አካል ከቁሳዊው ዓለም ጋር ሲያገናኘው ነፍስ ደግሞ
የማንነት/የሀለወት ምንጭ እንደሆነ እንዲሁም መንፈስ ደግሞ ከአምላክ ጋር የሚያገናኝ
እንደሆነ ይገልፃል። በዚህ አስተሳሰብ መሰረት ሶስቱም የራሳቸው ማንነት እንዳላቸው
ያስቀምጣል። በዚህም ምክንያት ያልዳነ ሰው መንፈሳዊ ሞትን እንደሚሞት ይታመናል።
(1ኛ ተሰ 5፥23፣ 1ኛ ቆሮ 15፥44፣ ሉቃ 10፥27፣ ኤፌ 2፥1፣ቆላ 2፥13፣ ሉቃ 1፥46-47፣
ኢሳ 26፥9)

10
1.4 ነፍሳችንና መንፈሳችን
በነፍሳችንና በመንፈሳችን መካከል ያለውን ልዩነት ስናውቅ እኛና ሌሎች አማኞች
ለምን ከእግዚአብሔር መንገድ የራቀ ድርጊትን እንደምናደርግ መረዳት አንችላለን። ጳውሎስ
ሁላችንንም ስለሚገጥመን ስለዚህ ትግል በ ሮሜ 7፥19 ላይ እንዲህ ሲል አስፍሯል።
“የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎ ነገር አላደርገውም።”
በመንፈሳችን ዳግም ብንወለድ እንኳን ነፍሳችን ዳግም ስላልተወለደች በሁለቱ መካከል
ያለውን የፈቃድ ልዩነት እንድናውቅ የእግዚአብሔር ቃል እውቀትና የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ
ያስፈልገናል።
♥♥ የእግዚአብሔር ቃል ህያው ነውና የሚሰራም ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው
ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለያይ ድረስ ይወጋል የልብንም ስሜትና
ሃሳብ ይመረምራል፤ ዕብ 4፥12-13
†† ያዕቆብ በመልእክቱ ስለ ነፍስና ስለ መንፈስ ልዩነት ፅፏል፤ (“ስለዚህ ርኩሰትን ሁሉ
የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም
የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።” ያዕ 1፥21)

1.5 የነፍስ ባህርያት


ነፍሳችን የተፈጥሮ አካል ስትሆን የተፈጠረችበት ዓላማም የእግዚአብሔርን ማንነት፣
ባህርይውን እና ስልጣኑን ለዓለም ሁሉ እንድትገልጥ ነው። ችግሩ ግን የነፍሳችን ስሜትና ሀሳብ
የተሰራው በዚህ በወደቀው ማንነት ነው። ነፍሳችን በአዕምሮ፣ በስሜት እና በፈቃድ የተዋቀረች
ነች። አዕምሮ፥ መረዳታችን፣ ስሜት ፈቃድ፥ ምርጫችንን የምናውቅበት ኃይል ነው።
†† የነፍስ ባህርይ የተገነባው በኃጢአት በተበከለ መንፈስ፣ መልካም ባልሆነ ማንነት፣
በአምስቱ የስሜት ህዋሶች፣ በቤተሰቦቻችንና በባህላችን ወዘተ… ነው።

1.6 የነፍስ ተፅዕኖ


♥♥ ከእግዚአብሔር እንደሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን። 1ኛ ዮሐ 5፥19
†† ነፍሳችን ጠላት የተሳሳተ አመለካከትን ምሽግ የሚሰራበት (2ኛ ቆሮ 10፥3-5)፣ ስጋዊ
ልማዶች የሚመነጩበት (ገላ 5፥19-21)፣ የሰው ጥበብ መነሻ (1ኛ ቆሮ 2፥4)፣ ራስን
መፈለግ፣ ራስን መውደድ፣ ራስን ማፅደቅ የሚያድግበት “አንተ የምታደርገውን ነህ”
የሚለው የተሳሳተ አመለካከት የሚመነጭበት ነው።

11
በነፍስ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ነገሮች

1.7 የስጋ ወይም የአካል ባህርያት


አካላችን አምስት ስሜቶችን የያዘ ሲሆን ማየት፣ መዳሰስ፣ መቅመስ፣ ማሽተት እና ማድመጥ
ናቸው። እነኚህ ስሜቶች በሰው ምክንያታዊነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን የሚያመጡ ከመሆናቸውም
በላይ ተፈጥሯዊውን ግዛት ለመረዳት ዋና ምንጮች ናቸው። ተፈጥሯዊው ሰውና ስጋዊው ክርስቲያን
የሕይወት ውሳኔን ለመወሰን በዋናነት የሚጠቀሙት ከአምስቱ ስሜቶች የሚያገኙትን መረጃ ነው።

1.8 አሮጌው ሰውና አዲሱ ሰው


ሐዋሪያው ጳውሎስ በክርስቶስ የሆነውን አዲሱን ሰውና አሮጌውን ሰው ያነፃፅራል።
ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆኑ ስለሚገጥማቸው የዕለት ተዕለት ተግዳሮት ለኤፌሶን
ሰዎች በላከው መልእክት ላይ በምዕራፍ 4 በቁጥር 22-24 በግልፅ ጽፏል። 22- ፊተኛ ኑሯችሁን
እያሰባችሁ 23- በአዕምሯችሁ መንፈስ ታደሱ፣ 24- ለእውነትም በሚሆኑ ፅድቅና ቅድስና እንደ
እግዚአብሔር ምሳሌ እያለ ተናግሯል።
12
♥♥ “በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤ ፊተኛ ኑሯችሁን
እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአዕምሯችሁም
መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን
አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥21-24

1.9 አዲሱን ፍጥረት መረዳት


ለበርካታ አመታት የአዲስ ፍጥረት ምንነትን አብዛኛው ክርስቲያን በጥልቀት ያልተረዳው ጉዳይ
ነበር። አብዛኞቻችን የምናስበው ኃጢአተኞች እንደነበርን ነገር ግን በጸጋው እንደዳንን ነው። ከቅርብ
ጊዜያት ወዲህ በክርስቶስ ያለንን እውነተኛ ማንነት ለማወቅ ጥሩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው።
እንደ አማኝ የሚገጥመን ተፃራሪ ሀሳብ አለ። እየሆንን ያለነው የነበርነውን ነው። እንደ አማኞች
ቅዱስ ወይም ፃድቅ ለመሆን ባህርያችንን በራሳችን መቀየር አንችልም። ነገር ግን ባህርያችን በበጎ
መልኩ ልንቀይር የቻልነው አዲስ ፍጥረት ስለሆንንና ክርስቶስን ስንቀበል ቅዱስና ፃድቅ ተደርገን
እንደገና ስለተፈጠርን ነው። ይህንን የእድገት ሂደት ለመረዳት አዲስ ከተወለደ ልጅ ጋር እናነፃፅረው።
አንድ አዲስ ለተወለደ ህፃን ልጅ ወንድነት ወይም ሴትነት፣ ማንነት፣ የመጣበት ቤተሰብ ምንም
ትርጉም አይሰጠውም። ነገር ግን ወደማንነቱ ማደግና መብሰል እንዳለበት ጥያቄ የማያስነሳ ጉዳይ
ነው። ዳግም ለተወለድነው ለእኛም ይህ ምሳሌ ይሰራል። ሁላችንም በእግዚአብሔር ቤተሰብ
ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ያለው ክርስቶስን እንድንመስል በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ
እያሳደገን ነው። እየሆንን ያለነው የሆነውን ነው። የታየልን ማንነታችን ላይ በፅድቅ መንገድ ማደግ
እንጀምራለን።

1.10 ደህንነታችንን ማስፈፀም


“ማስፈፀም” ማለት በውስጥ ያለን ነገር ወደውጭ ማውጣት፣ የነበረውን ነገር ወደ መሬት
ማውረድ ወይም በተግባር ላይ እንዲውል ማድረግ ማለት ነው። በሕይወታችን ላይ የእግዚአብሔር
ማንነት(ተፈጥሮ) እንዲታይ የሚያደርገው በውስጣችን ያደረው እግዚአብሔር ራሱ ነው። ይህ አዲስ
የሆነ ማንነት በሕይወታችን መንሰራፋት ሲጀምር አሮጌው ፍጥረት፣ ኃጢአት፣ ቁጣ፣ ፍርሀት፣
መስገብገብ፣ የመሳሰሉት ሁሉም ስጋዊ ማንነቶች ከሕይወታችን መገፋትና መውጣት ይጀምራሉ።
ይህንን ሂደት ካልተረዳን ለጠላት ክስ ተጋላጮች እንሆናለን።
♥♥ “ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን
አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ ስለበጎ ፈቃዱ መፈለግንም
ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።” ፊል 2፥12-13
እኛ የክርስቶስ አማኞች በክርስቶስ ዘንድ ስለፀደቅን ከፍርድ የዳንን ነን። በድካማችን ምክንያት
ፈተናዎች ሊገጠሙን ወይም ወደ ፈተና ልንገባ እንችላለን። በራሳችን ምኞትና ፍላጎት ወዳልተገባ
መንገድ መሳብና መታለላችን የስጋ ድካማችን መገለጫዎች ናቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን
ባህርያችንን እንደሞተ ሰው እንድንተወው ይፈልጋል:: በዚህ ሂደት ምሽጎች ይጋለጣሉ። በመንፈስ
ቅዱስ እርዳታ እነኚህን ምሽጎች ማፍረስና ክርስቶስን ወደ መምሰል እናድጋለን።

13
♥♥ “እግዚአብሔር በማንኛውም ሁኔታ አይፈትነንም። ማንም ሲፈተን፥ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ
አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም። ነገር ግን
እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።” ያዕ 1፥13-14

የእግዚአብሔር ቃልኪዳንና በመንገዳችን ላይ ያሉ የጠላት ምሽጎች


♥♥ “ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን።” መዝ 103፥7

1.11 አሮጌውን ሰው ማስወጣት


ንጉስ ዳዊት ልጁን ሰለሞንን ሲመክረው “ልጄ ሆይ ሰው ሁን” አለው (1ኛ ነገ 2፥2)። የአብራኩን
ክፋይ “ሰው ሁን” ያለው ሰው የመሆን ትርጉሙ ምን ቢሆን ነው? መልሱ ግልጽ ሲሆን መልእክቱም
እግዚአብሔር ያዘዘህን ፈፅም፤ ራስህን ከኃጢአት መንገድ አርቅ፤ ያደፈው ማንነትህን ትተህ
የፈጠረህን አምላክ የሚገልፀውን አዲሱን ሰው ሁን ማለቱ ነው። ስለዚህ ሰው የመሆን ትርጉሙ
በሁለት እግር ቀጥ ብሎ መራመድ መቻል፣ በሁለት እጅ ስራዎችን መፈጸም እና ማሰብ መቻል ብቻ
ሳይሆን ሌላ ሁኔታም እንዳለ ያሳያል። አሮጌውን ማንነት አውልቀን ስንጥለው ሰው እንሆናለን። ሰው
ደግሞ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው።
♥♥ “ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር
እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።” ሮሜ 6፥6
♥♥ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤” ሮሜ 3፥23

14
†† የአሮጌው ሰው ልማድና አመለካከት መሰረት ያደረጋቸው ስጋዊነት፣ ራስን የመውደድ
ዝንባሌ እና ባህርይ ናቸው።
♥♥ “የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥
ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥
ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው።” ገላ 5፥19-21
♥♥ “መራርነትና ንዴት፥ ቁጣም፥ ጩኸትም፥ መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ
ይወገድ።” ኤፌ 4፥31

1.11.1 ስለዚህ እንዴት አሮጌውን ማንነት ማስወገድ እንችላለን?


ሰዎች በመጀመሪያ አስተሳሰባችን፣ ስሜታችን እና ባህርያችን የፈለጉትን ቢሉን ያ አሮጌው
ማንነታችን ከክርስቶስ ጋር መሰቀሉን ማመን አለብን። እኛ ደግሞ በጥምቀት አማካኝነት
የሞቱ ተካፋዮች ሆነናል። ጥሩው ዜና አሮጌው ሰውነታችን ሞቷል። ይህ ማንነታችን የሞተው
ልክ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል ነው። የዚህ ማንነት ኃይል የተወገደው
በማመናችንና በጥምቀት አማካኝነት ነው። መሞታችን የአዲሱ ማንነታችን አካል ሆኗል። ከዚህ
በኋላ የኃጢአት ባሪያ ሳንሆን የእግዚአብሔር ውድ ልጆች ነን። አሮጌው ማንነታችንን አሽቀንጥሮ
ለመጣል ግን በፍጹም ልብ በአምላካችን መታመን ይገባናል። የወርቅ ቅብ የሆነ ብረት ወርቅን
መሆን እንደማይችል ሁሉ “አማኝ ነኝ” የሚል ነገር ግን በልቡ ጌታን የሚክደው ቢኖር አዲስ መሆን
አይችልም። ልብ በእምነት ለጌታ መንፈስ ሲከፈት መታደስ ይሆንለታል።
♥♥ “እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። ለኃጢአት
የሞትን እኛ ወደፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ
እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደጠመቅን አታውቁም ን?”
ሮሜ 6፥1-3
♥♥ “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤
አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ
እምነት የምኖረው ነው።” ገላ 2፥20
በውልደት የምናገኘው ማንነትና ተፈጥሯዊ ባህርይ ክርስቶስን ስንቀበል እንደሞተ እናውቃለን።
ስለዚህ በአዲሱ ተፈጥሯችን መኖር እንችላለን። በዚህም የመለኮታዊ ባህርይ ተካፋዮች እንሆናለን።
በቃሉ እምነት መለኮታዊ ማንነቱን እንካፈላለን።
†† በክርስቶስ ያለን አዲስ ማንነት:
•• ከመንፈስ የተወለድን መሆኑን (ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
ዮሐ 3፥6)፣
•• በመንፈሳችን ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆንን (ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።
1ኛ ቆሮ 6፥17)፣
•• በክርስቶስ የፀደቅን መሆኑን (ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን
በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው። 1ኛ ቆሮ 1፥30፤ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር
ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛ ቆሮ 5፥21)፣
15
•• ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለብን፣ ምግባረ መልካም መሆናችን (እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና
ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ
በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።
ቆላ 1፥21-22)፣
•• ለዘላለም ፍፁም መሆናችን (አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።
ዕብ 10፥14)፣
•• የመንፈስ ፍሬዎች ባለቤት መሆናችንን ያሳየናል። (የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥
ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውኃት፥ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል
ሕግ የለም። የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ገላ 5፥22)
ከአዲሱ ተፈጥሯችን ጋር አዲስ የሕይወት ለውጥ ይመጣል። ከዚህ የተነሳ አዲስ የሆነ ማንነት
መመስረት እንችላለን።

1.12 በክርስቶስ ያለን አዲስ ቦታ (ማንነት፥ ስለራሳችን ያለን


አመለካከት)
በክርስቶስ ያለን አዲስ ቦታ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት መሸጋገር ነው። በክርስቶስ ደም
የኃጢአት ስርየትን አግኝተናል። በቤዛነቱ ከእስራት ነፃ ወጥተናል። በመንግስተ ሰማይ ከእርሱ
ጋር ሆነናል፤ ፀድቀናል፤ ተቀድሰናል፤ ለተለየ ዓላማ ተመርጠናል፤ በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል፤
የመንግስተ ሰማይ ዜጎች ሆነናል፤ የክርስቶስ እንደራሴዎች ሆነናል፤ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን።
♥♥ “እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም፥ እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ
ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።” ቆላ 1፥13-14
♥♥ “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም
የበደላችን ስርየት።” ኤፌ 1፥7
♥♥ “ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።” ኤፌ 2፥6
♥♥ “ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።” ቲቶ 3፥6-7
♥♥ “በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።” ዕብ 10፥10
♥♥ “ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።” 2ኛ ቆሮ 1፥22
♥♥ “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ
ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤” ፊል 2፥20
♥♥ “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤” 2ኛ ቆሮ 5፥20
†† ስለዚህ አሮጌውን ማንነት አውጥተን አዲሱን ማንነት ለብሰን እንዴት እንደ አዲስ ፍጥረት
መጓዝ እንችላለን? ለሚለው ጥያቄ መልስ እነሆ፦
♥♥ “እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤ በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም
በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት
የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአዕምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ

16
ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ስለዚህ ውሸትን
አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን
ተነጋገሩ። ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም
ፈንታ አትስጡት። የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው
የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ
ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ
ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ
ይቅር ተባባሉ።” አፌ 4፥20-32

1.13 ቃል ኪዳኑን መተግበር


የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን በሕይወታችን ውስጥ መተግበር ከምንችልባቸው መንገዶች
የመጀመሪያውና ዋነኛው እግዚአብሔርን በማምለክና በማመስገን ነው።
♥♥ “ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ
እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።” መዝ 100፥4-5
በቀጣይነት የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳንና የቃሉን እውቀት በሕይወታችን ላይ ማወጅ ኪዳኑን
ለመተግበር ያስችለናል።
♥♥ “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።” ምሳ 18፥21
♥♥ “ነገርንም ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።” ኢዮ 22፥28

ምሳሌያዊ ጸሎት
ጌታ ሆይ በአንተ አዲስ ፍጥረት ስለሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ አከብርሃለሁ። በመንፈስ ከአንተ
ጋር አንድ ስለሆንኩ የመለኮታዊ ባህርይህ ተካፋይ ሆኛለሁ፤ ስለዚህም አመሰግንሃለሁ። ጌታ ሆይ
በፊትህ ፃድቅ፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለብኝ እንድሆን ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ። ክርስቶስ በከፈለው
መስዕዋትነት ለዘላለም በደሙ እንከን የለሽ ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ። የክርስቶስን ልብ ስለሰጠኸኝ
አመሰግንሃለሁ።

1.14 ማጠቃለያ
በሚቀጥሉት ትምህርቶች በመንፈስ እንድንጓዝና በሕይወታችን የእርሱን ማንነት እንድንለማመድ
መሰናክል የሆኑብንን ነገሮች እንመለከታለን። ከመሰናክሎቹ መካከል ስብራትና የነፍስ እስራቶች፣
ከጠላት ውሸት ጋር የምንፈፅመው ስምምነትና ከጠላት ውሸት ጋር የምናደርገው በደል ይጠቀሳሉ።
♥♥ “የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።” 1ኛ ተሰ 5፥23

17
መንፈሳዊ ሰው ስጋዊ ሰው/ የሰው ምክንያታዊነት

ነፍስ አካል
መንፈሰ ያዕ 1፥21 5ቱ የስሜት ህዋሳት
♥♥ በክርስቶስ አዲስ
ፍጥረት መሆን
2 ቆሮ 5፥17
♥♥ አዲስ ግዛት ቆላ
1፥26-27
♥♥ አዲስ ሕይወት
ዮሐ 6፥63
♥♥ ዳግም ውልደት
ዮሐ 3፥5-7 የስጋ ሰው ጥቂት ባህርያት
♥♥ መለኮታዊ •• ማንነት ንጉስ ነው፣ የሰው ስጋዊ ባህርይ እኔነት ዋና ቦታውን
ተፈጥሮ ይዟል፣
2ጴጥ 1፥4
•• ውሳኔዎች የሚደረጉት በሰው ምክንያታዊነት ነው።
♥♥ የመንፈስ ፍሬዎች
ገላ 5፥22-23 •• የራስን ብቻ መፈለግ፣ ራስ ላይ ማተኮር፣ ራስን መውደድ፣

♥♥ ከክርስቶስ ጋር •• ስጋዊ ኑሮ፣


አንድ መሆን •• በሰው ልማድ መመላለስ፣
1ኛ ቆሮ 6፥17
•• ኩራት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ክፉ ምኞት፣ ቁጣ፣ ፍርድ፣ መታበይ፣
♥♥ በክርስቶስ
ተቀባይነትን •• ተስፋ መቁረጥ፣ መደንገጥ፣ ደካማ መሆን/መዛል
ማግኘት ኤፌ •• ከእምነት ጋር መታገል፣
1፥6
•• ስለ እግዚአብሔርና ስለራስ የተዛባ አመለካከት፣
♥♥ ፅድቅ 2ቆሮ 5፥21
•• ጥልና ቁጣ የሞላበት ሕይወት
♥♥ ቅዱስ፣ ነቀፋ
የሌለበት፣ ፃድቅ •• የሕይወት ዋስትና ማጣትና ፍርሃት
ቆላ 1፥21-22
♥♥ ፍፁም ዕብ
10፥14
♥♥ የክርስቶስ
አዕምሮ
1ኛ ቆሮ 2፥16

18
ምዕራፍ 2
የተሰበረውን ልብ መፈወስ
♥♥ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም
መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነፃ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም
የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። …” ሉቃ 4፥18
†† በዚህ ክፍል በሕይወታችን ያለውን የስብራት ምሽግ እንዴት እንደምናፈርስና ሌሎችም
ገብቷቸው እንዴት ማፍረስ እንደሚችሉ እናያለን።
•• ስብራትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ፥
•• ስለ ልብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ገለፃ፥
•• እንዴት ልባችን ይሰበራል?
•• ስብራት ሲከሰት እንዴት ማወቅ እንችላለን?
•• ለልባችን ቁስል እንዴት ፈውስን ማግኘት እንችላለን?

2.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስብራትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ


ምን እንደሆነ ይነግረናል
በዓለማችን ላይ ብዙ ዓይነት የአካል ስብራት ይከሰታሉ። ቢሆንም አብዛኛው የአካል ስብራቶች
በተለያዩ ባለሙያዎች የሚጠገኑ ናቸው። በሀገራችን ሊጠገኑ የማይችሉ ስብራቶች በውጪ
ባለሞያዎች መፍትሔ ሊገኝላቸው ይችላል። የመንፈሳዊ ልብ ስብራት ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር
በማንም ሊጠገን የማይችል ነው። “ምን ሆነህ ተሰበርክ?” ብሎ የማይጠይቅ፣ “እኔ ስላልቻልኩ
ሂድና ዶክተር እገሌ ጋር ታይ” የማይል፣ “ብቸኛ ነኝና አጋዥ ዶክተር ይመደብልኝ የማይል” ነው።
እግዚአብሔር ሁልጊዜም ልባቸው የተሰበረ ሰዎችን ሲጣራ ድምፁ ይሰማል።
♥♥ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ማቴ 11፥28
†† ይህ ፍጹም ፍቅርን የተላበሰ ጥሪ የገባቸው እንደ መግደላዊት ማርያም ያሉ ሰዎች “ዛሬ
ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል (ሉቃ 7፥48)”፤ በጎልጎታ ላይ በቀኝ እንደተሰቀለው ወንበዴ “ዛሬ
ከኔ ጋር በገነት ትሆናለህ (ሉቃ 23፥43)” ተብለዋል።
i. ኢየሱስ ሰዎች ወደ እርሱ ቢመጡ እንደሚፈውሳቸው ለደቀመዛሙርቱ ተናግሯል፤
♥♥ “ከእርሱም ኃይል ወጥቶ ሁሉን ይፈውስ ነበርና ሕዝቡ ሁሉ ሊዳስሱት ይሹ ነበር።” ሉቃ 6፥19
♥♥ “እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ ሰምቶ ልጁ ሊሞት ስላለው ወደ እርሱ ሄደ
ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው።” ዮሐ 4፥47

19
♥♥ “በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሯቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም
እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሯቸውም ደንቁሯል ዓይናቸውንም
ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።” ማቴ 13፥15
ii. ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሁ ሲመጣ የተሰበረን ልብ እንደሚፈውስ(እንደሚጠግን)
ተናግሯል።
♥♥ “የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር
ቀብቶኛልና ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነፃነትን ለታሰሩትም መፈታትን
እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን
እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ
ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ
የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።”
ኢሳ 61፥1-3
†† በሉቃ 4፥18-21 ኢየሱስ ከኢሳ 61፥21 ላይ ያነበበው ትንቢት በእርሱ በኩል እንደተፈፀመም
ተናግሯል። መጽሐፍ ቅዱስ የተሰበረን ልብ መጠገን (መፈወስ) የእግዚአብሔር ፈቃድ
እንደሆነ ይነግረናል።
♥♥ “…እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።”
መዝ34፥18
♥♥ “…ልባቸውን የቈሰሉትን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።” መዝ 147፥3

2.2 ስብራት ምንድን ነው?


I. የስብራት ምንነት
ስብራት ብለን የምንገልፀው የስሜት ዓይነት ውስጣችን ካልጠበቅነው ነገር የተነሳ በጣሙን
ሲያዝን የሚሰማንና ምንም ዓይነት የማፅናኛ ቃላት ወይም ማንኛውም ዓይነት ሰው ሊያስረሳን
የማይችለው የሀዘንና የመጎዳት ድብልቅ የሆነ ስሜት ነው።
†† ኢየሱስ ሊፈውሰው ከመጣው የስብራት አይነቶች አንዱ በሕይወታችን በሚገጥሙን
መረሳቶችና መገለሎች ምክንያት የሚመጣውን ስብራት ነው።
II. አሳዛኝ አጋጣሚዎችና መገለሎች ልባችንን ሊሰብሩ ይችላሉ
•• ነውር (ከባህልና ከተለመደው ሁኔታ ውጪ እንደ አፀያፊ ተግባር የሚቆጠሩ ነገሮች)
•• የቃል፣ አካላዊና፣ ፆታዊ ጥቃቶች
•• መተው/መጣል
•• አዕምሯዊና ስሜታዊ ጥቃት
†† ኢየሱስ የተሰበረ ልባችንን ሊፈውስ መጣ ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ
ነው።

20
2.3 ልብ ምንድን ነው?
የዕብራይስጥ ቋንቋ ልብን “ሌብ (labe)” ይለዋል። ይህም የህያውነታችን፣ የአዕምሯችን፣
የእሳቤያችን እና የስሜታችን መካከለኛ (inner man, mind, will, heart) ሲሆን የግሪኩ (kar-
dee”-ah) - ነፍስ፣ ልብ፣ ሃሳብ፣ የስሜት መካከል ይለዋል (the heart; mind, character, inner
self, will, intention, center) ። (Strong”s Concordance፣ Bible Hub)
2.3.1 ልብ እንዴት ይሰበራል?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የህያውነታችን፣ የነፍሳችንና የአዕምሯዊ ስሜቶታችን መካከለኛ
እንደሆነ ተገልጧል። በአዲስ ኪዳንም ሆነ በብሉይ ኪዳን ላይ ብዙ ክፍሎች የልብን ባህርይ የሚገልፁ
የጥቅስ ክፍሎች አሉ። ለምሳሌ ያህል ልብ ያዝናል (ሕዝ 13፥22፣ ይታለላል (ኢሳ 44፥20፣ ሮሜ 16፥18)፣
ክፋትን ያስባል (ማር 7፥21)፣ ይመኛል (2ኛ ጴጥ 2፥14)፣ ያስተውላል (ዘዳ 29፥4፣ ኢዮ 38፥36)፣
ያውቃል (2ኛ ዜና 26፥5፣ ኤር 24፥7)፣ ይፈራል (ኢሳ 35፥4) እና ሌሎች ብዙ በልብ የሚደረጉ
የሕይወት ጉዞዎች ተጽፈዋል። በአብዛኛው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ልብ አድርግ” የሚለው ሀረግ
ሲገኝ ይህም የማስተዋልንና አመዛዝኖ የመጓዝ ጥበብ በልብ ውስጥ እንደተቀመጠ ያሳየናል።
ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የልብ ስብራት የሚመነጨው ከጠበቅነውና ካሰብነው ውጤት
ውጪ ሌላ ውጤት ሲከሰትና አሉታዊ ተፅዕኖን ሲያመጣብን ነው። በተጨማሪም የልብ ስብራት
ብዙውን ጊዜ በፍፁም ማንነታችን ያመንነው ነገር ፈርሶ ስናየው የሚደርስብን ከባድ የሆነ ሀዘንን
ይገልፃል። ብቸኝነት፣ በሰው ዘንድ መጠላት፣ መረሳት፣ አፅናኝ ማጣት እና ሌሎችም የልብ ስብራትን
ከሚያስከትሉ ምክንያቶች ተርታ ተሰላፊ ናቸው።
•• ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልባቸው ከተሰበሩ ሰዎች መሀከል ዳዊት አንዱ ነበር፤
†† የእግዚአብሔር ኃያል ተዋጊ (ጦረኛ) የሆነው ንጉስ ዳዊት ሰለራሱ የተሰበረ ልብ እያሰበ
ሲናገር እናያለን።
♥♥ “አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው። ነፍሴ
ስድብንና ኃሣርን ታገሠች አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም ። የሚያጽናናኝም አጣሁ።”
መዝ 69፥19-20
†† ዳዊት ስድብ፣ እፍረትና ነውር ልቡን እንደሰበሩትና ብቸኝነት የሚሰማው፣ ሀዘንተኛ፣
የተገለለ፣ የተጠላ(የተተወ) በማለት ራሱን ይገልፃል።
†† ነብዩ ሳሙኤል ወደ ዳዊት ቤተሰብ ሲመጣ ዳዊት በመረሳቱ ምክንያት እንዴት የዳዊት ልብ
እንደተሰበረ በ1ኛሳሙ 16፥5-11 መመልከት እንችላለን።
•• ሳሙኤል እሴይን ለንጉስ በሚደረገው ምርጫ ላይ ዳዊት ከወንድሞቹ ጋር እንዲካተት ማሳመን
ነበረበት። ሌላው ዳዊት በሕይወቱ የደረሰበት እፍረት ለወንድሞቹ ምግብ ለማድረስ በሄደበት
ወንድሙ ኤልያብ በአደባባይ በኩራቱና በብልግናው በወቀሰው ጊዜ ነው።
♥♥ “ታላቅ ወንድሙም ኤልያብ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰማ የኤልያብም ቍጣ በዳዊት ላይ ነድዶ፥
ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂቶች በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውኃቸው? እኔ ኵራትህንና
የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል አለው። ዳዊትም፦ እኔ ምን አደረግሁ?
ይህ ታላቅ ነገር አይደለምን? አለ።” 1ኛ ሳሙ 17፥28-29

21
†† የዳዊት መንቋሸሽና መወገዝ ጎልያድን ሊገጥም በተነሳ ጊዜም ቀጥሏል። በሌሎች ፊት
በውሸት(በሃሰት) ተከሷል፤ ተትቷል፤ በአባቱም ዘንድ ተቀባይነትም አጥቷል፤ ስለዚህ ዳዊት
ልቡ ከመሰበር በላይ ሆኗል።
• በ2ኛ ሳሙ 13፥1-20 የዳዊት ቤተሰቦች እንዴት አስደንጋጭና አግባብ ባልሆነ
መንገድ ልባቸው እንደተሰበረ እንመለከታለን።
ለንጉስ ዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የተባለች የተዋበች እህት ነበረችው። ከሌላ የተወለደው
ወንድሙም ከትዕማር ኃያል ፍቅር ይዞት ነበርና በጓደኛው ምክር ትዕማርን ወደ ቤቱ አስመጥቶ
በግድ አስነወራት። ምንም እንኳን በተቻላት መጠን ብትከላከለውም ካስገደዳት በኋላ ቀድሞ
ከሚወዳት ይልቅ ስለጠላት ከቤቱ አባረራት። (2ኛ ሳሙ 13፥1-18)
♥♥ “ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም
በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች። ወንድምዋም አቤሴሎም፥ ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር
ነበረን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ ወንድምሽ ነው ይህን ነገር በልብሽ አትያዢው አላት።
ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት ብቻዋን ተቀመጠች።” 2ኛ ሳሙ 13፥19-20
†† የዳዊት ልጅ ትዕማር በወንድሟ ተደፍራለች፤ ተጠልታለች፤ አፍራለች፤ ብቻዋን ተጥላለች።
በዚህ ምክንያት በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ያለ አንዳች ደስታ፣ በብቸኝነት እና ተስፋ በመቁረጥ
በወንድሟ ቤት ለመኖር ተገዳለች።
†† በ2ኛ ሳሙ 16 ላይ ንጉስ ዳዊት ከዙፋኑ ወርዶ ስደት ላይ በነበረ ወቅት የሳዖል ዘመድ
የነበረ የጌራ ልጅ ሳሚ ንጉሱን እየተከተለ በሰደበው ጊዜ፣ ንጉሱ ከማዘኑ የተነሳ ተከታዮቹ
እንግደለው ሲሉት እንኳን ፈቃደኛ አልነበረም። (2ኛ ሳሙ 16)
♥♥ “ዳዊትም አቢሳንና ባሪያዎቹን ሁሉ፥ እነሆ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል ይልቁንስ ይህ
የብንያም ልጅ እንዴት ነዋ? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ። ምናልባት በዚህ ቀን
መከራዬን አይቶ ስለ እርግማኑ መልካም ይመልስልኛል አላቸው።” 2ኛ ሳሙ 16፥11-12
†† ልክ በዳዊት ሕይወት ላይ እንደሆነው ሁሉ የጠላት ዓላማ ሕይወታችንንና ከእግዚአብሔር
ጋር የሚኖረንን ኅብረት ማበላሸት ነው። ጥሩው ዜና ግን ኢየሱስ የጠላትን ስራ ለማፍረስና
የተሰበረውን ልባችንን ለመጠገን መጥቷል።
♥♥ “ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።”
1ኛ ዮሐ 3፥8
በሰዎች ዘንድ መጠላታችን አልያም መተዋችን በአስተሳሰባችን፣ በስሜታችንና በምንወስደው
የውሳኔ እርምጃ ላይ ተፅዕኖ ያመጣል። ሆኖም ግን ከዚህ የልብ ስብራት እኛን ሊፈውስ ኢየሱስ
ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጣ። ኢየሱስ ይህንን የተሰበረውን ልባችንን እንዲፈውስልን መጀመሪያ
ስብራታችንን ማወቅና ማስተዋል አለብን። በመቀጠልም የልባችንን ጉዳትና ስብራት እንዲፈውስልን
መጠየቅ እንችላለን።

22
2.4 በሕይወታችን ያለውን ስብራት ማስተዋል

2.4.1 የስብራት ባህርያት


ጳውሎስ ስብራትን የምናሰተውልበት ቁልፍ ሃሰቦችን ሰጥቶናል።
♥♥ “የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱን
አላደርገውም። የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር
አላደርገውም። የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም፥
በእኔ የሚኖር ኃጢአት ነው እንጂ።” ሮሜ 7፥15፣19-20
የስብራታችን ህመም በስሜቶቻችን እንድንመራ ሊያደርገን ይችላል። ፍርሀት፣ ቁጣ፣ ቅንአት፣
ምቀኝነት፣ የተለያዩ ችግሮች የስብራት ውጤቶች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴ ለነገሮች የምንሰጠው
ምላሽ ተገቢ ላይሆን ይችላል። ጰውሎስ እንዳለው የምናደርገው የምንፈልገውን ሳይሆን ማድረግ
የማንፈልገውን ነው። የማንፈልገውን ነገር ስናደርግ ለምን የምንፈልገውን ማድረግ እንደማንችል ግራ
ይገባናል፤ (ውስጣችን ይወቀሳል)፤ ይህ ስብራት በሕይወታችን የሚንሰራፋበት አንዱ መንገድ ነው።

2.4.2 በሁለት ሃሳብ መሆን


በልብ ስብራት ምክንያት በሁለት ሃሳብ የሚዋዥቁ ሰዎች በእሳቤአቸውና በስሜታቸው
ሲወጠሩ ራሳቸውን ያገኛሉ። እነኚህ ሰዎች በሕይወት ጉዟቸው የተረጋጉ አይደሉም። ገለባ ወደ
ንፋስ አቅጣጫ እንደሚንሳፈፍና “የእኔ” የሚለው አቅጣጫ እንደሌለው ሁሉ በሁለት ሀሳብ
የሚዋልሉትም ባመኑበት ነገር ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች ይመራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ
አካላት ሲናገር እንዲህ ይላል፤
♥♥ “ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ
አይምሰለው።” ያዕ 1፥7-8
†† በሁለት ሃሳብ የሚዋዥቁ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ጥሩ እምነት ይኖራቸዋል፥
ሌላ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ፍቅር ይጠራጠሩታል።
†† በሁለት ሃሳብ መሆን በግሪኩ dipsuchos (dip»-soo-khos) ሲሆን ትርጉሙም ሁለት
ነፍስ (of two souls, of two selves), double-minded, wavering) መሆን ማለት ነው።
(ምንጭ፤ Strong»s Concordance/biblehubcom)

2.4.3 በሁለት ነፍስ መሆን


ነፍሳችን ከአዕምሯችንና ከስሜታችን እንዲሁም ከፈቃዳችን እንደተሰራች ስንረዳ ስብራት
ሲከሰት ስለሚኖረው ሁለት ነፍስ ለመረዳት ያን ያክል ከባድ አይሆንም።
ልባችን እንዲሰበር የሚያደርግ መጠላት ሲገጥመን የተሰበረው ወይም የተጎዳው ልባችን
ለሰውየውና ስብራቱ እንዲከሰት ላደረገው ሁናቴ ተገዢ ስለሚሆን በሁለት ሀሳብ መዋዠቀን
ያስከትላል። ስብራቱ ውስጥ ህሊናችን እንደሚገኝ ላናስተውለው እንችላለን፤ ስለዚህ አሰተሳሰባችን
23
ላይ፣ ከሰዎችና ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ኅብረት ላይ ተፅዕኖን ያመጣል። በሁለት ሃሳብ
መዋዠቃችንም ለልባችን ስብራት ተገዢዎች የመሆናችን ውጤት ነው።
†† አዕምሯችን ዛሬ ባለውና ቀድሞ በነበረው እውነታ በሁለት ተከፍሏል። ባደገው ማንነታችን
(አስተሳሰባችን) እግዚአብሔርን ማመንና በእርሱ መመካት እንችላለን፤ ግን ለስብራት
ተገዢ በሆነው ማንነታችን ምክንያታዊነታችን እንደተጎዳ ልጅ ይሆናል። በሁለት ሃሳብ
የመሆን ባህሪዎች፦
•• ስብራት በሁለት ሃሳብ ለመሆናችን፣ በኃጢአተኛ ማንነት ውስጥ እንድንሆን እና የማንፈልገውን
ነገር እንድናደርግ ምክንያት ይሆናል።
•• በእግዚአብሔርና በሌሎች ሰዎች ላይ እምነት እንዳይኖረን እንቅፋት ይሆናል።
•• ከእግዚአብሔር መንገድ ያፈነገጠ ሕይወት እንድንመራ ያደርገናል።
•• ፀሎታችን እንዳይሰማ ያደርጋል።
በሁለት ሃሳብ የሆነ ሰው ከእግዚአብሔር ምንም ነገር አይቀበልም ማለት እግዚአብሔር ምንም
ነገር ሊሰጠን ፈቃደኛ አይደለም ማለት ሳይሆን በሁለት ሀሳብ ስለሆንን እኛ ራሳችን መቀበል
አንችልም ማለት ነው። ከእግዚአብሔር የሚሰጠንን ማንኛውምንም ነገር መቀበል የምንችለው
በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ እምነት ሲኖረን ብቻ ነው። በልባችን ስብራትና በሁለት የሃሳብ መንገድ
ተጓዥ መሆናችን ማንነታችን በእምነትና በጥርጣሬ መካከል እንዲዋልል እድል ይከፍትለታል።
በሁለት ሃሳብ የተወጠሩ ሰዎች አንድን ነገር ብቻ በትጋት ለማድረግ ሲጥሩ ይስተዋላሉ። በነገሩ
መጨረሻ ግን ሀሳባቸውን ይቀይራሉ አልያም የጀመሩትን ስራ ሳይጨርሱ ያቋርጣሉ። አልበገር
ባይነትና ቁጥጥር መፈለግ በሁለት ሀሳብ የሚዋልል ሰው ዋና መገለጫ ባህርያት ናቸው። እነኚህ
ልባቸው በተለያየ ምክንያት የተሰበረ ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከልና በድጋሚ ላለመጎዳት የአልበገር
ባይነት ባህሪን ያዳብራሉ። በተቃራኒው ደግሞ ከልብ የሚንከባከባቸውና ጥሩ የፍቅር ማንነትን
የሚያሳያቸው ሰው ካገኙ የመለወጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
•• ቀጣዩ ምስል የተሰበረን ሰው ልብንና በሁለት ሃሳብ መሆን በሙላት ከመኖር እንዴት
እንደሚከለክለን ያሳያል።
በውስጣችን ያለው የመወሰን ብቃት በአብዛኛው በሕይወታችን ውስጥ በሚያጋጥሙን ነገሮች
ላይ የተመሰረተ መሆኑ አያጠያይቅም። በፊት ካጋጠሙን ነገሮች ተነስተን ዛሬ ላይ የምንወስናቸው
ጥሩም ሆነ መጥፎ ውሳኔዎች በአዕምሯችን ውስጥ የሚሰማንን የስሜት አቅጣጫ ይውስኑልናል።
ያለን የመወሰን ድምፅ ሲወጣ ወደ ሀዘን ወይም ፀፀት ውስጥ የሚያስገባ ውጤትን ካመጣ ይህ
ችሎታ የመጠራጠርን ስሜት ይወልዳል። ከነበረን ልምድና በድግግሞሽ ከምናውቃቸው ነገሮች
የተነሳ የመጠራጠር ስሜት ይከሰታል። ልባችን በተከሰተው ነገር ማዘን ይጀምራል። በየዋህነትና
በትህትና ያምን የነበረው ንፁህ ልባችን በጥርጣሬ ይደነድናል። ይህም “እንዲህ ቢሆን እንዲህ
ይሆናል፤ እንዲህ ቢሆን እንደዚያ ይሆናል” የሚል አሉታዊ ስሌት ውስጥ ይከተናል። የፍርሀት
ድምፅም እያደገ በመምጣት ከልባችን በመጀመር መላ አካላታችንን ያሽመደምደዋል። መልካም
ፈቃዳችንንም በመንጠቅ፣ ባለማመን ተከበን የውሳኔ ሰዎች እንዳንሆን እንዲሁም በብዙ ሀሳቦች
መካከል እንድንዋትት ያደርገናል።
24
ፍርሀትም አዕምሯችንን ይይዛል። አዕምሯችን ደግሞ የሰውነታችንን ስሜት የሚቆጣጠርልን ክፍል
እንደመሆኑ መጠን የሚሰማንን ሕመም ልክ እንደፈቀድንለት መጠን ያስተላልፍልናል። ፈቃዳችን
በተስፋ መቁረጥ፣ “ሰዎች ምን ይሉኛል” በሚል ሀፍረት እና ልባችንን በማደንደን በምንይዘው
መንገድ ይመራል ማለት ነው። ይህም የትኛው ምርጫ ትክክለኛ እንደሆነ ከማየት ይጋርደናል።
ጠንክረን ካለንበት አረንቋ መውጣት እንዳለብን ቢሰማንም ሕመማችንን ማስታመም ይቀለናል።
የተሰበርንበትን ነገር ወደ ኋላ ትተን ወደፊት ከመሄድ ይልቅ ባለንበት በሁለት ሀሳብ መካከል
እንዋዥቃለን።

2.5 ለልባችን ቁስል እንዴት ፈውስን ማግኘት እንችላለን?


ለልባችን ቁስል በተለያየ መልኩ ፈውስ ማግኘት እንችላለን። የልብ ስብራት ፈውስን መቀበል
መማርና ሌሎችን ማፅናናት ዋና ከሚባሉ መንገዶች መካከል ይጠቀሳሉ።

2.5.1 የልብ ስብራት ፈውስን መቀበል መማር


በሀዘናችን ጊዜ መቼም የምንፅናና አይመስለንም። ይህ ደግሞ አብዛኛው ሰው የሚያስተናግደው
እንግዳ ያልሆነ ስሜት ነው። ዘለዓለም የምናዝንና የምንከፋ፣ ስብራታችን ሁሌም አብሮን የሚኖር
ይመስለናል። ዳግመኛ ለመሳቅ ተዓምር የሚሆን፣ ከሀዘናችን በኋላ ምንም ነገር ሊያስደስተን
እንደማይችል እናስባለን። ነገር ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው።
25
ወደ ደስታ መንገድ ቀስ በቀስ መጓዝ፣ ተስፋ፣ ፍቅርና ደስታ በውስጣችን እንዲያድጉ መፍቀድ
እንዲሁም የተጎዳንበትንና ያዘንበትን ነገር በሚገባ ማወቅ (“ምንድን ነው? ከየት መጣ? ከዚህ
በኋላ ምን ላድርግ?” ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት መሞከር) ለመፈወስ የምናደርገው
ጉዞ የተዋጣ እንዲሆን ያደርገዋል። የተጎዳውን ስሜታችንን የምንገልፅበት መሪር ሀዘን ከአስቀያሚ
የመንፈስ ቁስል እንድንድን የሚያደርግ ተፈጥሯዊና ጤናማ ሒደት ነው። እዚህ ጋር የዳዊትን ታሪክ
ማንሳት ብዙ የሚያስተምረን ነገር አለ። ዳዊት የሚወደውና የሚሳሳለት ልጁ በጠና ታመመ።
በሞትና በሕይወት መካከል ሲያጣጥር አይቶ ነፍሱ እጅግ ተጨነቀች። በመሆኑም አምላኩ ልጁን
ይፈውስለት ዘንድ ከንግስና ወንበሩ ወርዶ፣ የንግስና ልብሱን አውልቆ፣ ከምግብና ከውኃ ተከልክሎ፣
በራሱ ላይ ትቢያ እየነሰነሰ እና በእንባ እየታጠበ አምላኩን ልጄን አድንልኝ እየለ ይጠይቀው ነበር።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሳይፈቅድ ቀርቶ ልጁ ሞተ። አገልጋዮቹም “ገና ልጁ ሳይሞት ራሱን እንደዚያ
የጎዳ መሞቱን ስንነግረው መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል” ብለው የልጁን መሞት ይነግሩት ዘንድ
እጅግ ፈሩ። እውነቱን የነገሩት ጊዜ ግን የተፈጠረው ነገር ከሃሳባቸው ተቃራኒ ነበር። ንጉሱ ከትቢያ
ላይ ተነሳ፣ እንባውን ጠራርጎ ተጣጠበም፣ የንግስና ልብሱን ለብሶ የሚመገበውን እንዲሰጡት አዘዘ።
የዚህ ሁኔታ ግራ የገባቸው አገልጋዮቹ አንድ ጥያቄ ጠየቁት። “ልጅህ ታሞ ሳለ አይሆኑትን ሆንክ
መሞቱን ስንነግርህ በራስህ ላይ ጉዳት ታደርሳለህ ብለን ስንጠብቅህ አንተ ግን ተነሳህ፤ ፊትህንም
ተጣጥበህ ተቀባባህ፤ የንግስናህን ልብስም ለብሰህ በላህ፤ ሚስጥሩ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት
እሱም እንዲ ሲል መለሰላቸው፤ “ልጄ በሕይወት ሳለ ቢምርልኝ ብዬ ተጎዳሁ። ከሞተ በኋላ ግን
ለምን?” አላቸው።
እግዚአብሔር ልጆቹን ያፅናናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ትዕግስተኛው ኢዮብ
በዙሪያው ከነበረው ነውጥ ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቆ ነበር።
የዳዊት ቅድመ አያት የነበረችው ኑኃሚን ወደ ሞዓብ ሔዳ ያላትን ነገር ሁሉ አጥታ ስትመለስ
የነበረባትን ሀዘን ለመርሳት ስሟን እስከማስለወጥ ደረጃ አድርሷት ነበር። ነገር ግን በሀዘን ጊዜ ከጎኗ
ያልተለየቻት ሩት ከአፅናኝነቷ በላይ በረከት ሆናላታለች።
†† በዮሐ 11 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እምነትንና ሀዘንን በአንድ
ላይ ያዋሀደበት ምዕራፍ እንደሆነ ማየት እንችላለን። አልዓዛርን ከሞት እንደሚያስነሳው
ቢያውቅም ከአልዓዛር እህቶች ማርያምና ማርታ ጋር ከልቡ አልቅሷል። (ዮሐ 11፥35)
†† ክርስቶስ ኢየሱስ ሀዘናችንና ስብራታችን እንደሚገባው በማወቅ መፅናናት እንችላለን። አዲስ
ሰው ከሆንን በኋላ የእርሱ መንፈስ በእኛ ውስጥ ስላለና ስሜታችን ከስሜቱ ጋር የተዋሀደ
ስለሆነ የሚሰማንን ያውቃል። ማጣታችን፣ መከዳታችን፣ መጣላታችንን እና መሞታችንን
ይረዳል። እንደ አዳኛችንና እንደ ነፃ አውጪያችን ለእኛ ይጠነቀቃል። የክርስቲያን
ስብራትም ቀለል እንዲል ከሚያደርገው አንዱ በክርስቶስ ያለን ተስፋ ነው። በለመለመ
መስክ ያሳድረናል፤ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብንሔድ እርሱ ከኛ ጋር ነው፤ ብርሃናችን
ነውና። (መዝ 23)።
♥♥ “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥…” 2ኛ ጴጥ 3፥9።
♥♥ “ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።…ለማልቀስ ጊዜ አለው፥
ለመሳቅም ጊዜ አለው ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው…” መክ 3፥1-4።
26
†† በስብራት ወቅትም መንፈስ ቅዱስ፣ አፅናኙ የእግዚኣብሔርን ሰላም ይሰጠናል።
(ዮሐ 14፥15-16፣ 26)
†† ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች የተላከውም መልእክት ይህንኑ ያጠናክርልናል። ከሁኔታዎች ይልቅ
ወደ አምላካችን ይበልጥ ስንጠጋ የእግዚአብሔር ሰላም ውስጣችንን ያሳርፈዋል።
♥♥ “ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን
አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።አዕምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና
አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።” ፊል 4፥6-7
†† ስብራት ሀሳባችን፣ ባህርያችን፣ ስሜታችን፣ ግንኙነታችን እና ጤናችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ
ያመጣል። በሀዘን ጊዜ ከከባድ ነገሮች አንዱ ዕክሉን ካስከተለው ነገር ጋር ተለያይቶ አዲስ
የሚመስል ኑሮን መጀመር ነው። ነገር ግን እምነታችንን በእግዚአብሔር ላይ መጣልን
መልመድ ለዚህ ሁኔታ ከፍተኛ አስተዋዕፆ አለው።
♥♥ “ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ
ነው።” ኢሳ 55፥9
በእግዚአብሔር ላይ ምንም ያህል ጥያቄ ቢፈጠርም በስተመጨረሻ እሱ ስለእኛ እንደሚያስብና
የሚሆነውን እንዲሁም መሆን ያለበትን እንደሚያውቅ ማመን አለብን። እንደሚረዳን በማሰብ
የእርሱን ማፅናናት ለመቀበልም ዝግጁ መሆን መቻል አለብን። በጸሎትና ቃሉን በማሰላሰል ለእኛ
ያለውን የእግዚአብሔርን ሰላም ተቋዳሾች መሆን እንችላለን።
•• (መዝ 16፣23፣34፣91፣ ዮሐ 14፥1-27፣ 2ኛ ቆሮ 5፥1-9፣ ፊል 4፥6-13፣ 1ኛ ተሰ 4፥13-18፣
ራዕ 21፥1፣ 22፥5)

2.5.2 ሌሎችን ማፅናናት


እኛ ካለን ልምድ በመነሳት ለሌሎችም መፍትሔ መሆን እችላለን። እግዚአብሔር ያስተማረንን
ነገር ወደ ጎን ከማለትና ከማማረር አልፈን ሌሎችን መርዳት እንችላለን። ምናልባት በዛ ውስጥ
ያልተቀረፈ ሀዘን ካለን ለማንሳትና ለማደግ ይጠቅመናል። ይህንንም በጸሎት ከእግዚአብሔር
ጋር በመገናኘት፣ ሌሎች ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ በማበረታታት፣ በሰው ላይ ቀድሞ
አለመፍረድና ልምድን በማካፈል (ሮሜ 12፥15)፣ በቶሎ ወደ ነበረው ሕይወታቸው እንዲመለሱ
ባለመገፋፋት እንዲሁም እግዚአብሔር ለእኛ ከጎናችን እንደነበር እኛም ከነሱ ጎን መሆናችንን በትንሽ
ነገር በማሳየት፣ ሰዎች ተገቢውን ሀዘን አልፈው ለፈውሳቸው እንዲዘጋጁና በጊዜው ተቀብለው ወደ
ጤናማ ኑሯቸው እንዲመለሱ ማድረግ እንችላለን።
የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለ ስብራትና መፅናናት የሚናገሩት ነገር አለ።
•••• መዝ 13፣ 23፥1-6፣ 30፥11-12፣ •• 2ኛ ቆሮ 1፥3-4
56፣ 34፥18፣ 73፥26፣ 139፥2
•• 1ኛ ተሰ 4፥13
•• መክ 3፥1-14
•• 1ኛ ጴጥ 5፥7
•• ዮሐ 16፥16
•• ራዕ 21፥4

27
ምዕራፍ 3
ኢየሱስ ነፃ አውጪያችን

♥♥ “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው
ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።” 2ኛ ጢሞ 2፥19
♥♥ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው
ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” ሮሜ 3፥23-24
የግሪኩ ቃል ነፃ መውጣትን “አፖሉኦትሮሲስ” ሲለው ትርጉሙንም አንድን ነገር ዋጋ በመክፈል
ማስለቀቅ ወይም መቤዠት ይለዋል። የዕብራይስጡ ቃል ደግሞ “ጋዋል” የሚል መጠሪያ ሰጥቶታል።
ትርጉሙም መልሶ መግዛት ወይም ነፃ አውጪ ማለት ነው።
ሰው ሁሉ ነፃ መውጣት ያስፈልገዋል። ስንወለድ ጀምሮ የነበረን ማንነት በክርስቶስ መታደስ
አለበት። የክርስቶስ ነፃ ማውጣት ከኃጢአትና ከጥፋት ማላቀቅ ነው።
የሰው ልጅ ሁሉ ነፃ መውጣት ያስፈልገዋል። ነፃ ለመውጣት ደግሞ ስንወለድ ጀምሮ የነበረን
ማንነት በክርስቶስ መታደስ መቻል አለበት። በክርስቶስ ነፃ መውጣት ማለት ከምድራዊ ኃጢአትና
ጥፋት መላቀቅን ያመለክታል። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ሰውን ሁሉ ሊያድንና ከአብ
ጋር ሊያስታርቀን ሲሆን ድምፁን ለሚሰሙትም ይህ ይሆንላቸዋል። በዚህ ምዕራፍ ስር “ኢየሱስ
ነፃ አወጣን” ስንል ምን ማለት እንደሆነ፣ ነፃ የወጣ ሰው ባህሪው ምን መምሰል እንዳለበት እና
በክርስቶስ ውስጥ የሚኖር ሰው ያለው ስልጣንን በጥቂቱ ለመመልከት እንሞክራለን። ክርስቶስ
በሞቱ ሞታችንን፣ በቁስሉ ቁስላችንን፣ በደዌው ህመማችንን እንደፈወሰልንና የመወለዱ ምክንያት
በጸጋውና በፍቅሩ ኃጢአታችንን ሰርዞ የእግዚአብሔር ልጆች ሊያደርገን እንደመጣ በደንብ ማወቅና
ማስተዋል ይኖርብናል።
28
3.1 በኢየሱስ ነፃ መውጣት ማለት ምን ማለት ነው?
♥♥ “እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥ይህ ቁርበቴም
ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።” ኢዮ 19፥25-26
ነፃ መውጣት ከያዘ ባርነት መላቀቅ እንዳለ ያሳያል። እንደ ክርስቲያኖች ነፃ ወጣን ስንል በላያችን
ሰልጥኖ ወይም ነግሶ የነበረን ሰይጣናዊ ግዞትና በላያችን ያኖረው ቀንበር ተወገደ ማለት ነው። ነፃ
ማውጣት ማለት ደግሞ የተከፈለን ነገር መኖሩን ያሳያል። በዋጋ፣ በገንዘብ፣ በስራ፣ በመሳሰሉት
ምክንያቶች አንድን ነገር ከተያዘበት ነገር ማውጣትን ወይም መለየትን ያመላክታል። በኢየሱስ ነፃ
መውጣትም እንደዚሁ ሰው ከነበረበት የኃጢአት እስራት፣ በፍቅሩ ዋጋ በሞቱ ትንሳዔ መቤዠት
በክርስቶስ ወደ ነፃ ዓለም መመለስን ያመላክታል።
♥♥ “መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም
የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነፃ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።” ቲቶ 2፥14
ከእግዚአብሔር ጋር ያለያየን ኃጢያት በክርስቶስ ስናምንና የክርስትናን መንገድ ስንከተል
ይሰረዛል። በዚህም ከጌታችን ጋር አዲስ የሆነ ንፁህ ግንኙነት ያንሰራራል። የክርስቶስን ይቅርታ
ለማግኘት የሚጠበቅብን ስለኃጢያታችን ስርየትን መጠየቅ ብቻ ነው። ክርስቶስን እንደግል አዳኛችን
ስንቀበልና በስሙ ስንጠመቅ ዓመፃችንን ሁሉ ትተን፣ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ውኃው ውስጥ
ቀብረን፣ በደሙ ታጥበን አዲስ ሰው መሆናችንን ያመለክታል። በውስጣችን መኖር በሚጀምረውም
መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መታረቅ ይሆንልናል። ይህም የኢየሱስን ነፃ ማውጣት ይመሰክርልናል።
ከኃጢአት ቀንበር፣ ከጨለማ ወደ ነፃነትና ወደ ብርሀን መንገዳችንን ለውጦታል። ፍቅር ወደሞላበት
ወደ ቅዱስ ሕይወት ይመራናል።
ክርስቶስ እኛን ከሰይጣን አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በደሙ ዋጋ ከፍሎልናል፤ የኃጢአታችንን
ቅጣት እርሱ ወስዶልናል። የመስቀሉ ሞት የትንሳዔውን ክብር እንድናስተውል አድርጎናል።
በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሊቆም ራሱን በመስጠት ስለ እኛ በደል ተሰቃየ፤ ሞቱም
የማስታረቂያ ድልድይ ሆነ፤ ፍፁም ሰው ስለነበረ የነበርንበትንና የምንሆነውን ያውቃል። ስለዚህም
የጠፉትን በጎች መንገድ ሊያሳይ፣ ዳግመኛ ወደቤታቸው ሊመልሳቸውና ከጠላት እጅ መንጭቆ
ሊያወጣ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጠ። ራሱን በመሰዋቱና በክብር ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ አማኞች
ዛሬ በነፃነት በምርጫችን ወደንና ፈቅደን እንድንከተለው አድርጎናል።

3.2 ኢየሱስ ከምንና እንዴት ነፃ እንዳወጣን


ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ዋና ዓላማ በኃጢአት ምክንያት በእኛና በእግዚአብሔር
መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ እኛን ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያደርሰውን መንገድ
ለማደስ ነው። ከዚህም ባለፈ ኃጢአተኞችን ሊያድን፣ በዓለም ላይ ያጠላውን ጨለማ ሊገፍ፣ ከሞት
እጅ ሊያወጣን እንዲሁም የዲያብሎስን ስራ ሊገልጥ መጥቷል።
♥♥ “…የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና አለው።” ሉቃ 19፥10
29
♥♥ “የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፥ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ
ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን
እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነፃ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ
ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።” ሉቃ 4፥17-19
3.2.1 ከምን ነፃ ወጣን?
የእግዚአብሔር መንፈስ የእግዚአብሔር ልጆች መሆን ለምንወድ ሁሉ ከቀንበሮቻችን
እንዲያላቅቀን ተልኮልናል። ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተገልፀዋል።
ሀ) ከኃጢአት
♥♥ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎሏቸዋል።” ሮሜ 3፥23
የእኛ ሀጥያት የታጠበው በሳሙናና በውኃ አይደለም። ነገር ግን ለዓለም ሁሉ ያለ ምንም በደል
በፈሰሰ ንጹህ ደም እንጂ። የኃጢአት መዝገብ በደልን ሁሉ ትቶ ስለበደሉት ሰዎች ራሱን መስዋዕት
ባደረገ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ተዘግቷል። ያመኑበት ሁሉ ለፍርድ የሚያቆም የክስ ፋይል
የለባቸውም።
♥♥ “ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥” ራዕ 1፥4-5
♥♥ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” ሮሜ 3፥23-24
♥♥ “እርሱም እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።” መዝ 130፥8
ለ) ከህግ ባርነት/ከህግ እርግማን
♥♥ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ
ከሕግ እርግማን ዋጀን፤” ገላ 3፥13፤
♥♥ “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች
የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።”
ገላ 4፥4-5
ሐ) ከባዶ ሃይማኖት
♥♥ “ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሯችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥
ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።”
1ኛ ጴጥ 1፥18
♥♥ “እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች
ነበርን፤” ገላ 4፥3
♥♥ “ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት
ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነፃ ይሆን?” ዕብ 9፥14
መ) ከሰይጣን ኃይል/ከጨለማ አሰራረር
የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማ ብሎ ከገነት ከተባረረ ወዲያ በሀሳብም ሆነ በአኗኗር
የሰይጣን ተገዢ ሆኗል። ዓለምም ለጨለማው አሰራር ተላልፋ ተሰጥታለች። ሰውም ጣዖትን
የሚያመልክና ለተቀረጹ ምስሎች የሚሰግድ ሆነ። አምላኩን ረስቶ ሁለመናውን ለጨለማው ንጉስ
ባርነት አስረከበ።
30
ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዲያብሎስ ቀንበር ፈትቶናል። ኃይሉንም ነጥቆ በጠላት ላይ
ኃይል እንዲኖረን አድርጎናል።
♥♥ “እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ
ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።” ቆላ 1፥13-14
♥♥ “የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ
ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥
ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።” ሐዋ 26፥18
♥♥ “ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን
ራሱን ሰጠ።” ገላ 1፥4
ሰ) ከሚመጣው ፍርድ/ቍጣ
♥♥ “እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና
ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን
ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት
ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።” 1ኛ ተሰ 1፥9-10
♥♥ “ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።” ሮሜ 5፥9
♥♥ “እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው
እንጂ።” 1ኛ ተሰ 5፥9
ረ) ከሞት (ከዘላለም ሞት/ከመንፈሳዊ ሞት)
የእግዚአብሔር ቃል የኃጢአት ደሞዝ ሞት እንደሆነ ይናገራል። አዳምም “ይህቺን እጸ በለስ
በበላህ ጊዜ ትሞታለህ” ተብሎ የተነገረውን ፍሬ በበላ ጊዜ በስጋው ሟች ከመሆኑም ባሻገር
በመንፈሱም ሞተ። የእርሱም ኃጢአት በዘሩ ሁሉ የሚተላለፍ ነበር። ምንም እንኳን ጻድቅ ቢሆን
ጽድቅ እንደ መርገም ጨርቅ ሆነ። የበጎችና የዋኖሶች ደም የማያጥበው ከባድ ኃጢአትን የሰው ልጅ
ተሸከመ። (ኢሳ 64፥6)
♥♥ “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት
እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ
የነበሩትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” ዕብ 2፥14-15
♥♥ “ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ ሞት ሆይ፥ ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል
ሆይ፥ ማጥፋትህ ወዴት አለ? …” ሆሴ 13፥14
ሠ) አሁን ካለው/ከጠላት አሰራር
ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ የጠላት ተቃውሞ
ያጋጥመናል። ሰይጣን አርፎ አይቀመጥም። ብዙውን ጊዜ ክርስቲያኖች ውጊያ ሲበዛብን ለጠላት
ሀሳብ ቶሎ እጅ እንሰጣለን። አንድ ሁለቴ ከመጸለይ ባላለፈ ጥርጣሬንና ተስፋ መቁረጥን
እናንፀባርቃለን። እግዚአብሔርም በዚህ ደስተኛ አይሆንም።
♥♥ “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ
እጠላሃለሁ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።” ሆሴ 4፥6
31
†† ይህ ደግሞ የጠላት ሀሳብ ነው። ጠላት እኛን ከእግዚአብሔር ለማራራቅና ለማጣላት
የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ለዚህ ነው ክርስቲያኖች በጌታ እንድንበረታና ለጠላት ሀሳብ
እጅ እንዳንሰጥ ማስተዋል ያለብን።
♥♥ “በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።” 2ኛ ቆሮ 2፥11
በአጠቃላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ለክርስቲያኖች በስሙ እንድናገለግል ስልጣን ሰጥቶናል። ልክ
አዲስ ሰዎች ስንሆን ይህ ስልጣን በእጃችን ገብቷል። በስሙ ከተደረጉልን ጥቂት ነገሮች ውስጥ
ኃጢአታችን ይቅር መባሉ፣ እኛን ዳግም ልጆቹ ማድረጉ፣ በጸሎት እንድናነጋግረው ስልጣን
መስጠቱ፣ ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንደምንኖር መፍቀዱ ይገኙበታል። የክርስቶስ ልጆች ስንሆን ሁሉ
በእጃችን አለ። አንዳንዴ ግን ይህንን እየረሳን በሽንፈት እንኖራለን።

3.3 በክርስቶስ ኢየሱስ ነፃ የወጣ ሰው የተሰጠው ስልጣን


♥♥ “ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ
ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን
ሊያደርግ አይችልም።” 1ኛ ዮሐ 3፥9
ሀ) ዲያብሎስንና ስራውን ለማውደም (ለማጥፋት)
የክርስቶስ ኃይል ከሰይጣንና ከጨለማ መናፍስት ይበልጣል። ይህንንም ስልጣን ለኛ
ለተከታዮቹ አካፍሎናል።
♥♥ “አሥራ ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ ደዌንም ይፈውሱ
ዘንድ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤” ሉቃ 9፥1
እግዚአብሔር የእርሱን ኃይል ስጥቶናል። በክርስቶስ አምነን መንፈስ ቅዱስን ስንቀበል
ኃይልንም እንቀበላለን። እዚህ ላይ ልብ ማድረግ የሚገባን የእኛ ኃይል ሳይሆን የእግዚአብሔር ኃይል
መሆኑን ነው። በእርሱ ኃይል የተሰጠንን ስልጣን መለማመድ እንችላለን። በመናፍስት ላይ ኃይልና
ስልጣን ተሰጥቶናል።
•• ሉቃ 10፥1፣17-19፤ ዮሐ 14፥13-14
መፅሐፍ ቅዱስ “የተሰጠን ኃይል” ብሎ ያስቀመጠው ቃላቱን በማለት ውስጥ ሳይሆን የክርስቶስ
ስም የሚያመላክተውን ነገር በመረዳትና በማመን ውስጥ ነው። ስሙም በመስቀል ላይ የሰራውን
ስራ፣ የእግዚአብሔርን ዓላማና ቃልኪዳን (ነፃ የማውጣት ቃል)፣ በኃጢአት ላይ ድልን መቀዳጀት፣
ሞትን እና የሰይጣንን ግዛት ድል መንሳቱን ያመላክታል። የክርስቶስ ስም ሲጠራ እግዚአብሔር
በፍቅሩ የሰጠንን ስልጣን በሙሉ ይይዛል።
•• (ኤፌ 1፥21 ፊል 2፥9-10 ዕብ 1፥3-4፣ ሉቃ 10፥17፣ 10፥18-20፣ ማር 16፥17)
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የእስራኤላውያን ሕዝብ ጠላቶቻቸውን እንዲያጠፉ ሲነግራቸው
እንደነበረ እንመለከታለን። ኢየሱስም የዲያብሎስን ስራ ሊያፈርስ ወደዚህ ምድር መጣ።
♥♥ “መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥የዘላለም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ
አውጥቶ፥ አጥፋው ይላል።” ዘዳ 33፥27
32
♥♥ ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።” 1ኛ ዮሐ 3፥8
†† ማውደም ወይም ማጥፋት የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን በስድስት የግሪክ ቃላት ተተርሟል፤
• Strong”s 3089-“luo” ሎ- መለቀቅ፣ ማፍረስ፣ መስበር፣ ማጥፋት
♥♥  ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።” 1ኛ ዮሐ 3፥8
• Strong”s #2637-“Katargeo” ጥቅም የሌለው ማድረግ፣ ማስወገድ

♥♥ “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት
እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥” ዕብ 2፥14
• Strong”s #622-“phtheiro” መጣል፣ ማፍረስ፣ ማስወገድ
♥♥ “ማንም የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር
ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” 1ኛ ቆሮ 3፥17
• Strong”s #622-“apollumi”

♥♥ “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም


በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።” ማቴ 10፥28
• Strong”s #2647-“kataluo” ሙሉ ለሙሉ ማውደም፣ መሻር

♥♥ “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።”
ማቴ 5፥17
• Strong”s #1331-“diaphtheiroerio”
♥♥ “…ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” ራዕ 11፥18
እኛ ሰዎች ሰይጣንን በግላችን ማጥፋት አንችልም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ስልጣን
የተረገጡትን አጋንቶች ምን ሊያደርጋቸው እንደሚፈልግ እርሱን መጠየቅ አለብን።
♥♥ “በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።” አፌ 6፥10
†† በየዕለቱ በክርስቶስ ያለንን ስልጣን ማስታወስ አለብን። ይህ ስልጣን የራሳችን ሳይሆን ጌታ
ኢየሱስ የሰጠን ስልጣን ነው።
♥♥ “እነሆ፥እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን
ሰጥቻችኋለሁ፥የሚጐዳችሁም ምንም የለም።” ሉቃ 10፥19
♥♥ “የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” ሮሜ 16፥20
ለ) ጠላትን/አጋንንትን ለማስወጣት
♥♥ “እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር
መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።” ማቴ 12፤28

33
መናፍስት ለክርስቶስ ስልጣን አገልግሎትና ለቤተክርስቲያን ተገዢዎች ናቸው። የጠላት
ሠራዊት ሁሉ በክርስቶስ ስልጣን ስር ናቸው። ለእርሱም ተገዢዎች ናቸው። እርሱ የፈቀደውን ብቻ
ያደርጋሉ፤ ለእርሱም ይታዘዛሉ። ከቃሉም የተነሳ ይበተናሉ።
የክርስቶስ ስምም በመናፍስት ላይ ስልጣን አለው። ደቀ መዛሙርቱ በጠላት ላይ በተሰጣቸው
ስልጣን መሰረት ሰይጣንን ለመገሰፅ ስሙን ተጠቅመዋል። ይህ አገልግሎት በክርስቶስ ዘመን
ቢጀመርም በአሁኑም ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይሰራል።
ነፃ የማውጣት አገልግሎትን በሁለቱም ጎኑ እንደተሳለ ሰይፍ መመሰል ይቻላል። የሰይጣንን
ኃይል በመንፈስም በስጋም ያስወግዳል።
•• ዲያብሎስ ያልተፈወሰ ስብራታችንንና ከጠላት ጋር ባደረግነው ስምምነት ላይ በመመስረት
በአማኞች ሕይወት ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ ይችላል።
•• “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ
ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” ሮሜ 12፥2
•• ጠላት በድካማችን ሊገባ ይችላል።
♥♥ “ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም
ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ፈወሳቸውም።”
ማቴ 4፥24
♥♥ “ኢየሱስም ገሠጸው ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፥ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።”
ማቴ 17፥18
†† የአማኞች ስጋዊ ማንነት ከክርስቶስ ጋር ካልተሰቀለ ጠላት በስጋ ምኞት አማኞችን
ሊያባብል ይችላል።
♥♥ “ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር
እንደተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና። ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ
ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤” ሮሜ 6፥6-7
♥♥ “ፊተኛ ኑሯችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥
በአእምሯችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር
ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22-24
♥♥ “የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። በመንፈስ ብንኖር
በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።” ገላ 5፥24-25
ከነፃ መውጣት በሚገኘው ሁሉን አቀፍ ድል ምክንያት ጠላት ይህንን ነፃ መውጣት
ሊከፋፍለው ይፈልጋል። መንፈሳችን ብቻ ነፃ ወጥቶ ነፍስና ስጋችን ከተረሱ ነፃ በወጣው ሰው ላይ
ጠላት ስራውን መስራት ይቀጥላል።
ሐ) ጠላትን ለማሰርና ለመፍታት
♥♥ “እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደሆንኩ ትላላችሁ? አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ
ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ
ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።እኔም
34
እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም
አይችሉአትም።የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ
በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” ማቴ
16፥15-19
•• አለቱ መሲሁ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ነው።
•• ይህ የክርስቶስ ማንነት መገለጥ ቤተክርስቲያን የምትመሰረትበት ምሰሶ ነው።
•• ዲያብሎስ ሰዎች ይህንን መገለጥ እንዳያስተውሉ ያደርጋቸዋል።
•• የጠላት ኃይል ይህንን የመገለጥ እውነት ሊቋቋም አይችልም።
†† በዚህ መገለጥ ኃይል ለመሄድ ቁልፉ መንገድ ኢየሱስ የሰጠንን የመንግስቱን ኃይል
መጠቀም ነው፤ ይህም ማለት በሰማይ የታሰረውን በምድር ማሰር በሰማይ የተፈታውን
በምድር መፍታት ነው።
መ) ኃይለኛውን አስሮ ኃይለኛውን ለመበዝበዝ
ሰይጣን በተለያዩ ወጥመዶች የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወደ ሲኦል በምታመራ መንገድ ላይ
አሰማርቷቸዋል። ቅንና ዘላለማዊ በምትመስል ነገር ግን ወደ ሞት የምታመራ መንገድ ላይም
ለዓላማው አሰልፏቸዋል። (ምሳሌ 14፥12፣ 16፥25) ምርኮውንም አፅንቷል። እኛ የክርስቶስን ስምን
የያዝን ግን በሚያበረታንና ጉልበት በሚሆነን በእርሱ የእግዚአብሔር የሆኑትን ከኃይለኛው እጅ
ላይ ፈልቅቀን እንድንወስድ ስልጣኑን ተቀብለናል። ይህን የሚያደርገው በውስጣችን የሚሰራው
ቅዱስ መንፈሱ እንጂ እኛ አይደለንም።
♥♥ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።”
ዮሐ 15፥5
• ክርስቶስ ባለሙሉ ስልጣን እንደሆነ ማመን ማለት ለሰይጣን እኛ ራሳችን
ስልጣን ካልሰጠነው በስተቀር ምንም ስልጣን እንደሌለው ማመን እንደሆነ
ከስር የተቀመጡት ጥቅሶች ያለመክታሉ።
♥♥ “ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።”
ማቴ 28፥18
♥♥ “አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።” ቆላ 2፥15
• ከኢየሱስ ከተቀበልነው ስልጣን የተነሳ በሰይጣን ላይ ብርቱ መሆናችንን
መቀበል።
♥♥ “በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ
በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ሞልታችኋል።” ቆላ 2፥9-10
• መንፈስ ቅዱስ ሰይጣን የሚጠቀምባቸውን ማንነቶች ማለትም ኃጢአት፣
በደል፣ ይቅር ማለት፣ አመፀኝነትና ስብራት እንዲሁም የነፍስ እስራት ላይ
ከሰይጣን ጋር የተስማማነውን ስምምነት እንዲገልጥልን መጠየቅ።
35
♥♥ “በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።” አፌ 4፥27
• ማናቸውም መወገድ፣ መጥፋት ያለባቸውን የዲያብሎስ አሰራሮችን
እንዲገልጣቸው መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ።

• ሰይጣን በውስጣችን ባስቀመጣቸው ማንነቶች ፈንታ ምን ማስቀመጥ


እንሚፈልግ መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ

♥♥ “ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።” መዝ 107፥20


• እግዚአብሔርን ስላደረገልን ነገር ማመስገንና ማክበር።

♥♥ “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን
ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።” 1ኛ ቆሮ 10፥31
ለመሆኑ ኃይለኛው ሰው ማነው?
♥♥ “ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት
ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።” ማቴ 12፥29
†† በኃይለኛ ሰው የተመሰለው ሰይጣን ነው። (ኢሳ 49፤ 24-25) ይህንንም የተባለበት
ምክንያት የድካም መንፈስ ካልተፈጠረባቸውና የረሀብ መንፈስ ከሌላቸው መላእክት አንዱ
ከመሆኑም ባሻገር በሰዎች ላይ በተለይም ባላመኑት ላይ ጠንካራ ተፅዕኖ ማድረግ የሚችል
በመሆኑ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ስሞቹም ይህንኑ ያሳያሉ።
†† እንደሚያገሣ አንበሳ (1ኛ ጴጥ 5፥8)፣ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ
እርሱም የቀደመው እባብ (ራዕ 12፥9)፣ ሌዋታን (ኢሳ 27፥1)፣ ጥልቅ መልአክ (ራዕ 9፥11)፣
የብርሃንን መልአክ የሚመስል (2ኛ ቆሮ 11፥14)፣ ክፉ (ማቴ 13፥39)፣ የዚህ ዓለም አም ላክ
(2ኛ ቆሮ 4፥4)፣
ኢየሱስ ግን ብርቱ ስለሆነ አሸንፎታል። ከእጁ ሰዎችን አስለቅቋል። ሲኦልን መዝብሮ ነፍሳትን
ነፃ አውጥቷል። ሰዎችን በማንቃት፣ አይኖቻቸውን በመክፈት ቅድስና እና ሞገስን በልብ በማስቀመጥ
ለእግዚአብሔር መንፈስ ምቹ ማደሪያ እንዲሆን በማዘጋጀት ጠላትን ድል ነስቷል።
ማቴ 12፥29ን ስናነብ በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ አንድ ጠንካራና ልጓም ሊበጅለት
የሚያስፈልገው ሰው እንዳለ ኢየሱስ ሲናገር ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን ኢየሱስ ምን ማለት ፈልጎ
እንደሆነ ሰፋ ያለ ጥናት ያስፈልጋል። ፈሪሳውያን ኃይለኛ ሰው የሚለውን አባባል በኢሳ 49፥24-25
ባለው አገባብ ይረዱታል።
♥♥ “በውኑ ብዝበዛ ከኃያል እጅ ይወሰዳልን? ወይስ የጨካኙ ምርኮኞች ያመልጣሉን? እግዚአብሔር
ግን እንዲህ ይላል። በኃያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፥ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል ከአንቺ ጋር
የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፥ ልጆችሽንም አድናለሁ።” ኢሳ 49፥24-25
ኃይለኛው ሰው የሚለው ቃል ኃያል ተብሎ በኢሳ 49፥24 በተገለፀው ቃል መረዳት እንችላለን።
ኃያል የሚለው ቃል በዕብራይስጥ የሚገልፀው መለኮታዊ ወይም አጋንንታዊ ኃይልን ሲሆን
36
የሚያመለክተው ደግሞ ብዙ ኃይላትን ነው። በኢሳ 49 ላይ ያለው ቃል በሰዎች እስራት ምክንያት
ከሰብዓዊ ባህርይ ውጭ የሆነ ግጭትን ያመለክታል። እዚህ ጋር ኢየሱስ እየተናገረ ያለው አንድ
ኃይለኛ ሰው በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ እንዳለ ሳይሆን አንድን ሰው የሚያስሩ ብዙ ማንነቶች
በሕይወቱ ውስጥ እንዳሉ ነው።
• አጋንንት የሚሰሩት በስልጣን ተዋረድ ነው፤
♥♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ
ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
አፌ 6፥12
ከዚህ ማየት የምንችለው በአንድ ሰው ውስጥ ያለ ጠንካራ (ኃይለኛ ማንነት) በስልጣን ስርዓት
ውስጥ እንዳለ ነው። ይህ ማለት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ካለው አጋንንት እስከ ዝቅተኛ ስልጣን ያለው
አጋንንት ድረስ መስራት ይችላሉ ማለት ነው። አንድ ሰው ሙሉ ለሙሉ ነፃ ለመውጣት እነኚህ ሁሉ
መወገድ አለባቸው።
የኃይለኛው ሰው ቤት ምንድን ነው ?
“የሱ ቤት”- የሚለው ቃል በእርሱ ስር የሚገዛቸውን በሙሉ ይገልፃል። ዓለምን፣ የአየር ላይ
ልዑል፣ ከስራው አንፃር በሰዎች ላይ ያለው ተፅዕኖና መንፈሳዊ ፈቃድ በተሰጠው ላይ እንዲሁም
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ባለው ሰው ላይ ያለውን ስልጣን ያሳያል።
በማቴ 12፥29 “ቤት” የሚለው ቃል ከሁለት የግሪክ ቃላት የመጣ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን
ኦኪያ (oikia) ወይም ኦኪዮሰ የሚለው ቃል የሚያመለክተውም መኖሪያን፣ ቤተሰብን፣ ቤትን፣
መጠለያንና መቅደስን ነው። የጥቅሶቹን አገባብ በመመልከት ኢየሱስ የሰውን አካል የኃይለኛው
ሰውና በእርሱ ስር ያሉት መኖሪያ ቤትነት ለመግለፅ እንደፈለገ እንረዳለን። የሁለቱን የግሪክ ቃላት
ሙሉ ትርጉም በጥምረት በመመልከት ኢየሱስ በተጨማሪ ለመግለፅ የፈለገው አንድን ቤተሰብ
መሆኑን መረዳት ይቻላል። የእግዚአብሔር በረከት ወይም እርግማን ለግለሰብ ብቻ ሳይሆን
ለትውልድም ነው ።
♥♥ “ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም
ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።” ዘፍ 17፥7
♥♥ “ሰባት ቀን በዳሶች ውስጥ ትቀመጣላችሁ ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች
በዳስ ውስጥ እንዳስቀመጥኋቸው የልጅ ልጆቻችሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእስራኤል ያሉት የአገር ልጆች
ሁሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።” ዘሌ 23፥43
♥♥ “አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ
ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ
ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።”
ዘፀ 20፥5-6
የኃይለኛው ሰው እቃዎች
♥♥ “ሌዋውያን ሆይ፥ ስሙኝ ተቀደሱ፥ የአባቶቻችሁንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ቀድሱ ርኩሱን
ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።” 1ኛ ዜና 29፥5

37
ከዚህ ጥቅስ አኳያ የኃይለኛው ሰው እቃዎችን አጋንንታዊ እቃዎች ብለን ልንጠራቸው የምንችል
ሲሆን የሰው ልጅ ኢየሱስን ከማወቁ በፊት ጠላት በሰው ሕይወት ውስጥ የሚያስቀምጣቸው
ቆሻሻዎች ናቸው። ይህንንም የሚያደርገው አጋንንት በአማኞች ሕይወት ውስጥ ያለውን መልካም
ገፅታ በጠላት ቆሻሻ እንዲነትብና በእርሱ ተፅዕኖ ውሰጥ እንዲወድቁ ከመሻት ነው። ኢየሱስ
እንዳለው ከኃይለኛው ሰው ቤት መውጣትና መፍረስ ያለባቸው ማንነቶች አሉ። (ማቴ 12፥29)
♥♥ “ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል ነፍሱን ለሞት አሳልፎ
ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ
ዓመፀኞችም ማለደ።” ኢሳ 53፥12
የአጋንንት ባህርይ መስረቅ፣ መግደልና ማጥፋት ነው። በዚህ ምክንያት ኢየሱስ በግልፅ
የሚናገረው የኃይለኛውን ሰው እቃ መውረስ አንደኛው የነፃ ማውጣት አካል ነው።
♥♥ “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው
እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” ዮሐ 10፥10
አጋንንት በእያንዳንዱ የሰው ሕይወት ላይ የሚያመጣው ማንኛውም ነገር ለሰውየውና
ከሰውየው ጋር የደም ትስስር ባላቸው ሰዎች ላይ ጥፋት የሚያመጣ ሲሆን ሰውየውም ቢሆን
ቤተሰቦቹ በአጋንንት ስልጣን ስር እንዲወድቁ በር ይከፍትላቸዋል። በዚህ መንገድ የሚመጡ የባዕድ
መንፈሳዊ መሳሪያዎች፣ ሰዎች በራሳቸው ኃጢአትና በጣዖት አምላኪነታቸው ከትውልድ ወደ
ትውልድ እንዲተላለፉ ያደርጋሉ።
ለጠላት መጠቀሚያ እቃዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች፦
• የጨለማው አሰራር
የጨለማ አሰራር ማለት ሰዎች በተገለጠ ብርሃን እንዲጓዙ ከማድረግ ይልቅ በድቅድቅ ጨለማ
እንዲደናበሩ ማድረግን የሚመለክት ሲሆን ከሌሎች ተሸሽጎ እንደ ዘረፋ፣ ድብደባ እና ዝሙት ያሉ
ድብቅ ኃጢአቶችን መስራት ማለት ነው።
ማንም በጨለማ የሚጓዝ ቢኖር ውስጡ በፍርሀት ይጨነቃል። በጉዞውም ደህንነት
አይሰማውም። በጨለማ ውስጥ የተደበቀ ጠላት ክፉ ተግባር ይሰነዝርበታልና። ከጨለማ ወደ
ብርሀን ስንወጣ ግን በግልፅ እናያለን። ስለዚህ ደህንነትም ይሰማናል። በመንፈሳዊ ሕይወታችንም
የጽድቃችን ፀሃይ በሆነው ጌታ ባበራልን ብርሃን ልንጓዝ ይገባናል።
♥♥ “ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣቸው፥ እስራታቸውንም ሰበረ። ”̋ መዝ 107፥14
• ቀንበር
ሰይጣን የሰው ልጆች በኑሯቸው እንዳይደሰቱና አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር እንዳያደርጉ
ብዙ ቀንበሮችን አድርጎባቸዋል። ስለዚህ ስለ ዘላለማዊ ሕይወታቸው ከማሰብ ይልቅ በሕይወታቸው
ውስጥ የሚያጠነጥነውን ችግር በመፋቅ ብኩን እንዲሆኑ አድርጎዋቸዋል።
♥♥ “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር
ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?”
ኢሳ 58፥6
♥♥ “ባሪያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ
38
የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።” ዘሌ 26፥13
እነኚህንና እነኚህን የመሳሰሉ መንፈሳዊ መሳሪያዎች ከሰው ሕይወት ካልተወገዱ ጠላት በሰው
ሕይወት ውስጥ ስልጣኑን ያሰፋል። አጋንንታዊ እቃዎችንና መጠቀሚያዎች መለየት የምንችለው
መንፈስቅዱስ እንዲገልጣቸውና ከተገለጡ በኋላ ምን መደረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔርን
ስንጠይቅ ብቻ ነው።
• አይነ-ርግብ

♥♥ ስለአይነ-ርግብ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት


በመከዳችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀድዳታለሁ፥ እንደ ወፍም የምታጠምዱአቸውን
ነፍሳት እለቅቃለሁ። ሽፋኖቻችሁን ደግሞ እቀድዳለሁ ሕዝቤንም ከእጃችሁ አድናለሁ፥ ከዚያም
ወዲያ በእጃችሁ ለመታደን አይሆኑም እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። እኔም
ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገድ
እንዳይመለስ የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና።” ሕዝ 12፥20-22
ሰ) ሰዎችን ከእስራት ነፃ ለማውጣት
♥♥ “ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ
ዘላለም ድረስ ይሁን፤አሜን።” 1ኛ ጢሞ 1፥17
ሰዎችን ከእስራት ነፃ የማውጣት ዓላማ ኢየሱስ እንዲከብርና ስላደረገልን ነገር እንዲመሰገን
ነው። ሰዎች ነፃ እንዲወጡ የምንፀልየው ኢየሱስ የሰው ልጆችን ስለሚወድና ለነፃነታችን እስከ
ሞት ድረስ ዋጋ ስለከፈለ ነው። የእርሱ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን ደግሞ የእርሱን ፈለግ
ልንከተል ይገባል። በመሆኑም በሞት ጥላ ስር ላሉ መፈታትን፣ በባእድ አምልኮ ለተጠመዱ
የሕይወት መንገድን፣ በጨለማው አሰራር ተሰናክለው ለወደቁት ዳግም መነሳትን፣ በተስፋ መቁረጥ
ረመጥ ውስጥ ላሉ ተስፋን፣ መንፈሳዊ አይናቸው ታውሮ በስጋ መንፈስ ብቻ ወደሞት የሚጓዙትን
የወንጌሉን ብርሃን እየሰበክን ከዲያብሎስ ምርኮ ነፃ ማውጣት ከጌታ የተቀበልነው ኃላፊነታችን
ነው።
†† የመጽሐፍ ቅዱስ አዲሱ ትርጉም ሉቃ 4፥18 በሚከተለው መንገድ ይተረጉመዋል።
♥♥ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው ለድሆች ወንጌልን እንድሰብክ ቀብቶኛልና ለታሰሩት መፈታትን
ለታወሩት ማየትን እንዳውጅ የተጨነቁትን ነፃ እንዳወጣ የተወደደችውን የጌታ አመት እንዳወጅ
ልኮኛል።”

39
ምዕራፍ 4
መንፈሳዊ ውጊያ

መንፈሳዊ ውጊያ ለክርስቲያኖች የሕይወት አንዱ ክፍል ነው። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ
አምነን ከተጠመቅንባት ጊዜ አንስቶ የመንፈስ ውጊያ ወታደሮች ነን። በምድራዊው ዓለም ላይ ሳለን
ሀገራችንም ሀሳባችንም ሰማያዊ ነው። ሰይጣን የምድራዊው መንግስት ገዢ ነውና ሰማያዊ ዜግነትን
ሽተን የምድራዊ ዜግነትን መናቃችን ለእርሱ ሕመሙ ነው። በመሆኑም በእኛና በሰይጣን መካከል
“ከግዛቴ አትወጡም”ና “እንወጣለን” በሚል ምክንያት ጦርነት ይፈጠራል። ይህ በጠላት ጭፍሮችና
በክርስቶስ ኢየሱስ አማኞች መካከል የሚደረገው ውጊያ መንፈሳዊ ውጊያ የሚል መጠሪያ አለው።
መንፈሳዊ ውጊያ ሰው በራሱ ፈልጎ የሚያመጣው ሳይሆን ክርስቲያን በመሆኑና የጠላትን መንገድ
አልፈልግም ብሎ በመካዱ ምክንያት የሚመጣ የሰይጣን የበቀል እርምጃ ነው። መንፈሳዊ ውጊያ
አንድ አማኝ ጌታን ከተቀበለ በኋላ የሚያጋጥመውን እንቅፋት የሚወጣበት ስልትም ነው።
ይህ ምዕራፍ አንድ አማኝ ጌታን ከተቀበለ በኋላ የሚያጋጥመውን ከጠላት የሆነ እክል በመንፈስ
ቅዱስ አማካኝነት እንዴት የጠላትን ግዛት በራሱ ሕይወትም ሆነ በአካባቢው ላይ ማፈራረስ
የሚችልበትና ከጠላት ስልታዊ ጥቃቶች እንዴት መከለል እንዳለበት በጥቂቱ በመግለፅ የሚያዘጋጅ
ነው።

4.1 የመንፈሳዊ ውጊያ ጭብጥ


በወደቀው ዓለም ውስጥ እስካለን ድረስ መንፈሳዊው ውጊያ እየተፋፋመ የሚቀጥል እንጂ
ማቆሚያ ያለው አይደለም። ሰይጣንና የወደቁት ተከታዮቹ ግዛታቸውን ከእግዚአብሔር ግዛት
ለማስጠበቅ ሌት ተቀን ይተጋሉ። ይህም ተጋድሎ ሰዎች የመዳንን ነፃነት እንዳያገኙ በማሳወር የጠፉ

40
ነፍሳትን ለራሱ መንግስት በማስገዛትና ቅዱሳን ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግስት እንዳያስፋፉ
በዓላማና ዕቅድ የሚያሰናክልበት መንገድ ነው።
ለአዲስ አማኞች መንፈሳዊው ውጊያ ይበረታባቸዋል። በእምነት የጎለበቱትም ቢሆኑ
ከውጊያው የሚያመልጡ አይደሉም። በክርስቲያኖች ላይ ውጊያ የሚበረታው ከእግዚአብሔር ወገን
በመሆናችን ነው። ሁልጊዜም ውጊያ ሲካሄድ ሁለቱ አካላት ከአንድ ወገን እንዳልሆኑ የታወቀ ነው።
ከዲያብሎስና ከወገኖቹ ጋር የሚካሄደው ውጊያም የዚህ ልዩነት መገለጫ ነው። ከተማረከ ሰራዊት
ጋር ማንም እንደማይዋጋ ሀቅ ነው። ጌታ ይህን አስቀድሞ ስለተናገረን ተዘጋጅቶ መቆም ተገቢ ነው።
በመንፈሳዊ ውጊያ ሂደት ውስጥ ነፃ የወጣን ሰዎች በየጊዜው እንፈተናለን፤ በጌታ መታመናችንና
በእርሱ ላይ ብቻ መደገፍ እንድንጀምር እንማርበታለን።
የመንፈሳዊ ውጊያ ውጤት በገሃዱ ዓለምም የሚታዩ ተግዳሮቶች አሉት። በቅዱሳን መላእክትና
በጠላት ጭፍራዎች መካከል የሚደረገው ትግል ፈለግነውም አልፈለግነውም እኛን ይመለከታል።
በተለይ አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን የጠላት ጠላት ስለሚሆንና ሰይጣንም የአማኝ ዋጋ ምን ያህል
እንደሆነ ስለሚያውቅ ይህ ተጋድሎ ይበልጥ ይበረታል።
♥♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ
ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
ኤፌ 6፥12
የጠላትን ስራ ለማጋለጥ በመጀመሪያ ማወቅ ያለብን ነገሮች አሉ፤ መንፈሳዊ ውጊያ
በእግዚአብሔር ኃይላት (ማለትም ቅዱሳን መላእክትና የዳኑ ሰዎች) እንዲሁም በሰይጣንና
በተከታዮቹ መካከል የሚደረግ ውጊያ ነው። ይህም ውጊያ የጠፉትን ነፍሳት ወደ መዳን እንዲመጡ
የሚያደርግ ነው። ሰይጣን ብዙ ሰዎች እንደጠፉ እንዲቀሩ ይፈልጋል። የክርስቲያኖች ዓላማ ደግሞ
በጠላት ግዛት ላይ ሕይወትን በሚለውጠው ወንጌል አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር መንግስት
የጠፉትን መሰብሰብ ነው።

4.2 የሰይጣንና ጭፍሮቹ ማንነትና ባህርያት


♥♥ “በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን
በግሪክም አጶልዮን ይባላል።” ራዕ 9፥11
•• ሰይጣን አፈጣጠሩ እንደ መልአክ ነበር። የተፈጠረበትም ዓላማ እንደሌሎቹ ቅዱሳን መላእክት
የእግዚአብሔር አገልጋይ እንዲሆን ነበር።
♥♥ “አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ በእሳት
ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።” ሕዝ 28፥14
ነገር ግን ሰይጣን ለፈጠረለት ዓላማ ከመኖር ይልቅ ባልተፈጠረለት ዓላማ ጌታ መሆንን
ሻተ። ጌትነቱንም መላእክቱ ያምኑለት ዘንድ ሰበካቸው። በመሆኑም ያመኑት ሌሎች መልአክትም
ነበሩት። ሰይጣን የነበረው የመላእክነት ስልጣኑ ተገፎ ወደ ምድር ሲጣል ያመኑበት ሁሉ አብረውት
ተጥለዋል። ከዛን ጊዜ የጀመረ ክፋቱ ዛሬም ድረስ በሰዎች ሕይወት ውስጥ መሰናክሎችን እያስቀመጠ
እንዲወድቁ ያደርጋል።
41
♥♥ “ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ
ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።” ራዕ 12፥4
♥♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ
ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
ኤፌ 6፥12
♥♥ “እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን
ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8፥44
†† ጠላታችን ይህ ሰይጣን ሲሆን እርሱም የወደቀው መልአክ፣ ሲሶ (1/3) መላእክት ያሳተና
ፈጣሪያቸውን ትተው እርሱን የመረጡ ተከታዮች ያሉት፣ እግዚአብሔርን ባለመታዘዙ
ምክንያት በወደቀው የሰው ማንነት ላይ ጥፋትን የሚያመጣ ማንነት ያለው መንፈስ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰይጣንን ሊገልፁ ከሚችሉ ስሞች መካከል ጥቂቶቹ እነሆ፦
ሌባ፤ አጥፊና ገዳይ
ሰይጣን ብዙ ጊዜ የሚጠራባቸው ስሞች ምግባሩን የሚገልፁ ናቸው። ከመጥፎ ምግባሮቹ
መካከል ሌብነት አንዱ በመሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሌባ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት እናገኘዋለን።
♥♥ “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው
እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” ዮሐ 10፥10
ሰይጣን ከሰዎች ላይ የሰረቃቸው አካላዊ ነገሮች እንዳሉ ሆነው የሰረቃቸው መንፈሳዊ ነገሮች
ግን በሰዎች ላይ ይበልጥ ጉዳትን አስከትለዋል። ሰዎች ከተሰረቁባቸው መንፈሳዊ ነገሮች መካከልም
ሰላም፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ ጤና፣ አንድነት፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ ንጹህ ልብ፣ የገዢነት ስልጣን፣
ጥንካሬ እና ሌሎች ቆጥረን የማንጨርሳቸው ነገሮች ናቸው። የሰው ልጆች ጸጋ የነበሩ እነዚህን ሁሉ
መንፈሳዊ ሀብቶች አጥፍቷቸዋልና አጥፊ የሚለው ስያሜም ተሰጥቶታል።
ውሸታምና ወንጀለኛ
ውሸት የሰይጣን መገለጫ ነው። ይህ ውሸት የሰው ልጆችን ከገነት ያባረረና ብዙ መላእክትንም
ወደ ጥልቁ ያስጣለ ሲሆን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንም ጭምር በኃጢአት ለመጣል በፈተና መልክ
የቀረበ ነው። በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሲሉ የሀሰት መዓት ይደረድራሉ።
ይህንንም ሲያደርጉ ዕቅዳቸውን ከመፈፀም ባሻገር የሰይጣናዊ ባህርይ እያጎለበቱ እንደሆነ
አይገነዘቡትም።
♥♥ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ
ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር
ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8፥44
ተንኮለኛና አታላይ
ተንኮል የሚሰራው በሌላው ስህተትና ውድቀት ለመደሰት ሲሆን ተንኮሉ ለተሰራበት አካል
ጉዳት በተቃራኒው ደግሞ ተንኮሉን ላደረገው አካል መዝናኛ ነው። ሰይጣን በሰራው ተንኮል የሰው
42
ልጆች ከገነት ሲባረሩ ማየቱ ደስታው ነበረ። የሰይጣን ተንኮል አሁንም ቢሆን የሰው ልጆችን እየጣለ፣
ከእውነተኛው መንገድም እያሳታቸው ይገኛል። ዓለም አወቅኩ የምትላቸው ነገሮች በእግዚአብሔር
ዘንድ ያላዋቂነት ምልክቶች ናቸው፤ ዓለም ሰለጠንኩ የምትልባቸው መንገዶችም ከእግዚአብሔር
የሚያርቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ዓለም የምትነግረን በምንም ሁኔታ ቢሆን ትርፍ እንድናተርፍ ሲሆን
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ኪሳራ ነው። ለዚህም ነው ክርስቶስ “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ
ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል” ማር 8፥36 ያለው። እነዚህ ሁሉ ሰይጣን ዓለምን ወደ
ስህተት የሚመራባቸው የተንኮል ወጥመዶቹ ናቸው። በተጨማሪም አዳምንና ሄዋንን አታሎ ከጌታ
መንግስት ከማባረሩም ባሻገር አሁንም ዓለምንና አሸንክታቦቿን የሚያምሩ በማስመሰል ወደሞት
የሚመራ ነውና አታላይ ተባለ።
♥♥ “ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ ሀሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና
ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።” 2ኛ ቆሮ 11፥13
♥♥ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው
እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።” ራዕ 12፥9
ከሳሽ
♥♥ “ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም
የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ
ተጥሎአልና።” ራዕ 12፥10
የሚያገሳ አንበሳ
♥♥ “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና”
1ኛ ጴጥ 5፥8
የፍርሃት መንፈስ
የሰው ልጅ ሲፈጠር የሚፈራው አንዳች ነገር አልነበረውም። ታዲያ የፍርሃትን ስሜት በሰው
ልጆች ሕይወት ውስጥ ማን ዘራው? ሀሳቡስ እንዴት ተሳካለት? የፍርሃት ስሜትን ወደ ሕይወታችን
ያስገባው የሰው ልጅ ሁሉ ጠላት የሆነው ዲያብሎስ ነው። ሀሳቡ ሊሳካለት የቻለውም የሰው ልጅ
በአምላኩ ላይ የነበረውን እምነት ከውስጡ ሸርሽሮ ስለወሰደበት ነው። የሚያምን አይፈራም፤
አይጠራጠርምም። የሚያምን ቢኖር ግን እንደ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ወደ እሳት ቢጣል
እንኳን በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ሳይሆን እስከሞት ድረስ በመታመን ነው። እንደ ሰማዕቱ
እስጢፋኖስም ከሚወረወርበት ድንጋይ ይልቅ ነፍሱ የምታርፍበትን የሰማይ ደጅ ተከፍቶ ያያል።
ስለዚህ አይፈራም።
♥♥ “ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤
የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።” 1ኛ ዮሐ 4፥18
የብርሃን መላእክት መሰል
የዲያብሎስ አሰራር ሰዎች በስህተት መንገድ እንዲሰለፉ ያደረገ ነው። ማንም ሰይጣንን በጸብና
በክርክር ብቻ የሚገለጽ ነው ብሎ የሚያምን ከሆነ ስህተት ነው። ሰይጣን አማኞችን የሚዋጋው
ጦርን በመሰበቅ ብቻ ሳይሆን የብርሀን መልአክ በመምሰል የክርስቲያኖች ስብስብ መካከል
43
ላይ በመገኘት ነው። እንደ አገልጋይም በመሆን መድረክ ላይ በመውጣትና የሌሎች ኃጢአትን
በመዘርዘር ለሌሎች መሰናክል ይሆናል። የጌታን ቃል ገልጦ የአሮጊቶችን ተረት ተረት ያወራል።
የኢየሱስ ክርስቶስን ቃልና ትምህርት በማጣመም የሀሰት ትምህርትን በማሰራጨት ብዙዎችን ወደ
ስህተት መንገድ ይመራል። ለእምነታቸው የቀኑ መስሏቸው የሚያመልኩትን አምላክ ሳያውቁት
እንዲክዱ ያደርጋቸዋል።
♥♥ “ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።” 2ኛ
ቆሮ 11፥14
♥♥ “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች
ነቢያት ተጠንቀቁ።” ማቴ 7፥15
ፈታኝ
የሰይጣን ፈተና ትኩረት የሚያደርገው ሰዎችን ከትክክለኛው መንገድ በማሳት ላይ ነው።
ብዙ ጊዜ የሚፈትነን ደግሞ ከሁሉ አብልጠን በምንወዳቸው ነገሮች ነው። ይህ ደግሞ ለብዙ
ሰዎች ፈተናውን እንዳናልፍ ምክንያት ይሆናል። ገንዘብን አብልጠን የምንወደውን በገንዘብ፣ ዝናን
የምናፈቅረውን በዝና፣ ቤተሰባችንን አብልጠን ለምንወድ ደግሞ በቤተሰብ ፈተናውን ያዘጋጃል።
እንደ ልቤ የተባለው ንጉስ ዳዊት የተሸነፈበት ፈተና በሴት ልጅ ውበት ነበር። የጌታ ደቀመዝሙር
የነበረው ይሁዳ ደግሞ የተሸነፈው አዕምሮውን ጠፍሮ በያዘው የገንዘብ ፍቅር ነበር።
ትዕግስተኛው ኢዮብ ግን ምንም እንኳን በምንወዳቸው ነገሮች የሚመጡብን ፈተናዎች
ቢበዙብንም ከአምላካችን ጋር እንዳይስተካከሉብን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባን ያሳየናል። ኢዮብ
አምላኩን እንዲክድ በሚወዳቸውና በሚያፈቅራቸው ነገሮች በሙሉ ተፈትኗል። ከተፈተነባቸው
ነገሮች መካከል ያሉት ንብረቶች በሙሉ ወደሙበት። ይህ በመሆኑ ግን በአምላኩ ላይ የስድብም
ሆነ የማማረር ቃል አልተናገረም። ቀጥሎም የተፈተነው ከንብረቱ በላይ በሚሳሳላቸው ውድ ልጆቹ
ነበር። እነዚህ ልጆች የቤቱ ማዕዘን ተደርምሶባቸው በአንድ ላይ ማለቃቸውን ሲነገረው እንኳን
የማማረር ቃል አልተሰማበትም ነበር። ይልቁኑም “እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ነሣ፤ (ኢዮ
1፥21)” በማለት ለአምላኩ ያለውን ፍቅር በቁስ አካላት እንደማይለካ አረጋገጠ እንጂ። በመቀጠልም
በጤናው፣ ከዛም በገዛ በሚስቱና ጓደኞቹ ተፈተነ። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ቢያፈቅራቸውም ነገር ግን
ከአምላኩ ጋር ሊስተካከሉለት አልቻሉም። በመሆኑም ፈታኙ ሰይጣን በፈተናው ተሸነፈ። እኛም
በምን አይነት ፈተና እየተፈተንን እንዳለን መገንዘብ አለብን። እምነታችን የሚለካው በሱ ነውና።
♥♥ “ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ። ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል
ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።” 1ኛ ተሰ 3፥5
ክፉ
ክፉ የምንለው በሌሎች ላይ እኩይ የሆነ ድርጊትን የሚፈጽም አካልን ነው። የክፋቱ ዓላማም
በሌሎች ሀዘን ለመደሰት እንዲሁም መሰናክልን በማድረግ ካሰቡበት ስፍራ ለማስቀረት ሊሆን
ይችላል። ሰይጣን በፈጣሪው ላይ በማመጽ የጀመረው ክፋት የሰው ልጆችንም ትእዛዝ አለማክበርን
በመስበክ ባህሪያቸው እንዲቆሽሽ፣ የጸጋ ልብሳቸው እንዲገፈፍና ከገነት ወደ ምድር እንዲጣል፣
በኑሮው ውስጥም እሾክና አሜኬላ እንዲያበቅል አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪም አዳምን ከገነት
እንዲባረር ያደረገ፣ ለቃየን ድንጋይ በማቀበል በወንድሙ ላይ ግድያ እንዲፈጽም፣ በአሁኑም ጊዜ

44
ጎሳ በጎሳ ላይ፣ ሀገርም በሀገራት ላይ ጦር እንዲሰብቁ በማድረግ የክፋትን ባህርይ ከራሱ አልፎ
በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠረው የሰው ዘርም አውርሶታል።
♥♥ “የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል
በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።” ማቴ 13፥19
♥♥ “…እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም
መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።” ማቴ 13፥39
†† አዳምን እና ሄዋንን አታሎ ከጌታ መንግስት ከማባረሩም ባሻገር አሁንም ዓለምን እና
አሸንክታቦቿን የሚያምር በማስመሰል ወደሞት የሚመራ ነውና አታላይ ተባለ።
♥♥ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው
እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።” ራዕ 12፥9
ዘንዶ
♥♥ “ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት
በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥” ራዕ 12፥3
የዚህ ዓለም ገዢ
ሰይጣን የዚህ ዓለም ገዢ ተብሏል። ገዢ የተባለበትም ምክንያት ሰዎችን ከእግዚአብሔር
መንገድ ውጪ በማድረግ ለገዛ ሀሳቡ ተገዢ ስለሚያደርጋቸውና ለፍላጎቱም ስለሚያሰልፋቸው
ነው። የአገዛዝ ስርዓቱ ደግሞ “በምድር ላይ ሳለህ አንተን ብቻ ደስ ይበልህ” የሚል መርህን
ይከተላል። ይህንንም ደስታ ለማግኘት ስረቅ፤ ዝረፍ፤ ዘሙት፤ ጨፍር፤ ደንስ፤ ሌላውን አሸንፈህ
አንተ ብቻ የበላይ ሁን እንጂ ማንም ካንተ የበላይ አይሁን፤ አንተ ለማለፍ ከፈለግክ ሌሎቹን ጣል፤
መከበርንም ከፈለግክ ሌሎቹን አዋርድ የሚል ነው። ነገር ግን ክርስቲያኖች የምንመራው በዚህ
ዓለም ገዢ ሳይሆን በእግዚአብሔር ነው። በመሆኑም እነዚህን የጠላት አገዛዝ ስርዓቶችን በሙሉ
እንቃወማለን።
♥♥ “ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም
አንዳች የለውም” ዮሐ 14፥30

4.3 መንፈሳዊ ውጊያ የት፣ መቼ እና እንዴት ይካሄዳል?


(ኤፌ 6፥12፣ 1ኛ ቆሮ 4፥14)

እግዚአብሔር በሚሰራበት በማንኛውም ቦታ መንፈሳዊ ውጊያ አለ። የክፉ ሀሳብ


የእግዚአብሔርን ልጆች ከመልካም መንገድ መመለስና ወደ ጥፋት መንገድ ማስገባት ነው።
በማይታየው መንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ይህ ውጊያ በቤታችን ውስጥ፣ በስራችን ቦታ፣
በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ይካሄዳል። መንፈሳዊ ውጊያ በሰማያዊ ግዛት ላይ የሚካሄድ ሲሆን
የጦር ሜዳውም የሰዎች አዕምሮ ውስጥ ነው።

45
መንፈሳዊ ውጊያ መቼ ይካሄዳል?
ይህ ውጊያ የጀመረው መላእክት ሲወድቁ ሲሆን ወደ ምድር የመጣው ደግሞ አዳምና ሔዋን
ከገነት ሲባረሩ ነው። ሰዎች ወደ ክርስቶስ መንገድ ሲመጡ ከሰይጣን ቁጥጥር ውጪ ይሆናሉ።
የዚህን ጊዜ ጠላት ታላቅ ውጊያ ይጀምራል። ሰይጣን ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚሰጠው ቦታ እጅግ
ከፍተኛ ነው። ወደ ዓለም ፍፃሜ እየተቃረብን በመጣን ቁጥር ኃይሉን እያጠናከረ ይገኛል። ኃጢአትን
ለማድረግ ስናስብ፣ የስጋ ባህርያትን ስናሳይ፣ ከሰው ጋር ተጣልተን ልባችን ሲሰበር፣ መንፈሳችን
ሲወድቅ፣ በእነዚህ ሁሉ ጊዜ መንፈሳዊ ውጊያን እየተዋጋን ነው። ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ወጥተን ጌታ
ወደሚፈልገው ቦታ ለመድረስ ከፍተኛ ትግል ሊጠብቀን ይችላል። እግዚአብሔርን መታመናችንና
የዳንበትን ዓላማ በደንብ ማወቅ አሸናፊዎች ያደርገናል።
•• መንፈሳዊ ውጊያ እንዴት ይካሄዳል? (ኤፌ 6፥12፣ ዳን 10)
ሰይጣን በመንፈሳዊና በገሃዱ ዓለም ጦርነት ይከፍታል። በመንፈሳዊው ዓለም በሰዎች ልብና
አዕምሮ ውስጥ ይህ ውጊያ ሲካሄድ በተጓዳኙ በገሃዱ ዓለም ደግሞ የመሬትን ይዘት በመያዝ በሚታዩ
ዕንቅፋቶች በጭፍራዎቹ አማካኝነት ያካሄዳል። ሰይጣን ኃይሉን በሙሉ አሟጦ ክርስቲያኖችን
ሊያጠፋና ዓላማቸውንም ሊያስት ይታገላል። ነገር ግን መንፈሳዊ ውጊያን ስንዋጋ መጠንቀቅ ያለብን
ነገር ብቻችንን አለመሆናችን ማረጋገጥ ነው። የክርስቶስን ስም ስለጠራን ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል።
ከኢየሱስ ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ሲኖረን ስሙን ስንጠራ ኃይልና ስልጣን ይኖረናል።
ብላቴናው ዳዊት በእስራኤላውያን ዘንድ ይፈራ የነበረውን ጎልያድን መትቶ የጣለው በወንጭፍ
በተወረወረች አንዲት ጠጠር መስሎ ከተሰማን ተሳስተናል። ዳዊትም ያለው “አንተ በኃይልህ እና
በጉልበትህ ስትመጣ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሀለሁ (1ኛ ሳሙ 17፥45)” ነው።
እንደዚህ በእግዚአብሔር ኃይል ላይ ለመደገፍ ደግሞ እርሱን ማወቅ ይገባናል።
4.3.1 ጠላት ዲያብሎስ ክርስቲያኖችን ለማጥመድ
የሚጠቀምባቸው ስልቶች
አንዳንድ ሰዎች ዲያብሎስን የሚስሉት መልኩ ጥቁር፣ ጥፍሮቹ የሾሉ፣ ጥርሱ ያገጠጠ፣ አይኑ
ደም የመሰለ እና እርቃነ ስጋውን እደሚጓዝ ፍጡር አድርገው ነው። የብርሃን መልአክ እስከሚመስል
ድረስ ራሱን እንደሚለውጥ አይገነዘቡም። ስለዚህ ራሱን ቆንጆ አድርጎ ከመጣ በውጊያ ላይ መቆየት
ይሳናቸዋል። ሁለመናቸውን ለሀሰተኛው አባት ምርኮኛ አድርገው ያስገዛሉ። ከዚህም ሌላ ልናውቅ
የሚገባን ነገር መልካም ሆኖ እንዲሁም ተለሳልሶ በመቅረብ ብዙ ክርስቲያኖችን ራሳቸውን ምርኮኛ
አድርገው እንዲያስገዙለት የማድረግ መንገድም መከተሉን ነው። ጠላታችን ዲያብሎስ ለውጊያው
የሚጠቀምበት የተለያዩ ስልቶችና የጦር ሜዳዎች ሲኖሩት በዋነኛነት ሶስት የጦር ሜዳዎችን
ይጠቀማል፤ እነሱም የነፍስ የጦር ሜዳ፣ የዲያብሎስ የጦር ሜዳ እና የሰዎች የጦር ሜዳ ስልቶች
ናቸው።

46
4.3.2 ነፍሳችን ሕይወታችንን እንድትመራ በመፍቀድ
ነፍሳችን የአዕምሯችን፣ የፈቃዳችን፣ የስሜታችን ውቅር ናት። የነፍስ ትስስር የማይታይ
ነገር ግን የአንድ ሰው ነፍስ ከሌላ ሰው ነፍስ ጋር ሲዋሃድ (ሲጣጣም) የሚፈጠር ነው። ነፍሳችን
ሃሳባችንን፣ ስሜታችን እና ፈቃዳችንን አካታለች። ለምሳሌ ያህል ዳዊትና ዮናታን በ 1ኛ ሳሙኤል
በምዕራፍ 18 ቁጥር 1 ላይ እንደተገለፀው ነፍሳቸው እንደተሳሰረና እስከሞት ድረስ ይዋደዱ እንደነበር
ይታወቃል። የነፍስ ትስስር ከጥልቅ ፍቅር የሚመነጭ ሲሆን ማንኛውንም መሰናክል የሚያሳልፍ
ኃይል ይሰጣል።
የነፍስ የጦር ሜዳ በነፍሳችን ውስጥ የሚካሄደውን ሙግት ያመላክታል። የሰዎችን ባህርይ
የነፍስ ሙግት ውጤት ነው ልንለው እንችላለን። በጎው ጎናችን ከስጋዊ ፍላጎታችን ጋር ይዋጋሉ፤
ከዛም አንዱ ያሸንፋል። ስጋ ሲያሸንፍ ሰዎች ክፋት የነገሰባቸው፣ በሌሎች ሃዘን የሚደሰቱ፣
ራስ ወዳድ እና በሁለት ሀሳብ ወላዋይ ይሆናሉ። በወንድሞቻቸው ላይ እንኳን ሳይቀር የክፋት
ሰይፋቸውን ይመዛሉ። ነገር ግን ሰላም ከሕይወታቸው ይርቃል። በመሆኑም የሚኖሩባት ዓለም
የምታሳድዳቸው እስኪመስላቸው ድረስ ጥላቸውን እንኳን ማመን ይሳናቸዋል። (ዘፍ 4)
በጎ ጎናችን ሲያሸንፍ ደግሞ የእግዚአብሔር ሰላም በውስጣችን ይሞላል። ለወንድሞች አዛኝ፣
ቅን፣ ደስተኛ እንሆናለን። የዲያብሎስን አሰራር አሸንፈን እንደ እግዚአብሔር ውጥን መኖር ይቻለናል።
እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ ለመኖር የጦርነቱ ውጤት በመልካሙ ጎናችን አሸናፊነት መጠናቀቅ አለበት።
♥♥ “ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ
በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤”
ሮሜ 8፥6-7
♥♥ “በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና፤ ፈቃድ አለኝና፥ መልካሙን ግን ማድረግ
የለኝም። የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደርገውም።”
ሮሜ 7፥18-19
♥♥ “ነገር ግን በብልቶቼ ከአዕምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ
የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ። እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን
ያድነኛል?” ሮሜ 7፥23-24
4.3.3 ለገንዘብ ጤናማ ያልሆነ ፍቅር እንዲኖረን በማድረግ
ገንዘብ ለሰው ልጆች መገልገያ ተደርጎ የተፈበረከ ቢሆንም በተቃራኒው ብዙ ጊዜ ሰዎች ገንዘብን
ሲያገለግሉ ይታያሉ። ሰይጣን የሰው ልጆችን ከሚያጠምድበት ወጥመዶች መካከል ዋነኛው ገንዘብ
ነው። ይህንን ስትራቴጂ በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንም ቢሆን ለመፈተን
ተጠቅሞበታል። በረሃቡ ጊዜ በእንጀራ ሊያጓጓው ያልተሳካለትና አምላኩን እንዲፈታተን ያቀረበው
ሀሳብ ውድቅ የሆነበት ዲያብሎስ በመጨረሻ ግን ዋናውን ፈተና ፈተነው። ወደ ተራራ ወስዶ
የተዋበ ዓለምን አሳየው። እናም ለኔ ከሰገድክልኝ ይህንን የምታየውን ዓለም እሰጥሀለው አለው።
ብዙውን ጊዜ እኛ ሰዎች ይቺን ፈተና ማለፍ ከባድ ይሆንብናል። ለዛም ነው ሰይጣን ዋናውንና
የመጨረሻ ከባድ የሚለውን ፈተና በጌታ ላይ የተገበረው። “ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ
ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና” ብሎ ሲመልስለት እንደማይሸነፍ አወቀ። በጌታ
ፊት መቆምም ተሳነው። (ማቴ 4፥1-10፤ ሉቃ 4፥1-13)
47
በገንዘብ የሚመጣብንን ውጊያ ማሸነፍ ትልቅ ድል ነው። ምክንያቱም ገንዘብን መውደድ
የኃጢአት ሁሉ ስር ነውና (1ኛ ጢሞ 6፥10)። ወንድም ወንድሙን የሚያስገድልበት፣ የሚዋደዱ
ጓደኛሞችን ፍቅር የሚያስፈትንበት፣ ሀገርና ወገንን አስክዶ የራስን ጥቅም ብቻ የሚያሳድድበት፣
ክብርን አሳልፎ ሰጥቶ ስጋን የሚያሸጥ፣ ሰብዓዊነት ተዘንግቶ ድሆችን እንደ ርኩስ የሚያስቆጥርበት
የገንዘብ ልክፍት እውነትም የኃጢአት ሁሉ ስር ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ለሁለት ጌቶች ልትገዙ አትችሉም ብሎ ወይ አምላክን አልያም ደግሞ
ገንዘብን እንድንመርጥ ይነግረናል (ሉቃ 16፥13)። እዚህ ጋር የሚገርመው ነገር ገንዘብም እንደ አምላክ
ጌታ መባሉ ነው። በአንዳንድ ሰዎች ሕይወት ላይ ከአምላክም በላይ ገዝፎ ይታያል። ስንት ዘማሪ
የነበሩ ወንድምና እህቶቻችን ለገንዘብ ሲሉ በዘመሩበት አንደበታቸው ዘፈኑበት? ስንቱ ቃሉን
ለዓለም እንዲሰብኩ የተሰጣቸው ለገንዘብ ሲሉ ጸጋቸውን ችላ አሉ? ስንት የቃሉን ማዕድ አብረውን
ይቋደሱ የነበሩ ዛሬ ቃሉን ለመቋደስ ጊዜ አጡ? ታዲያ በላያችን ላይ ገንዘብን ከጌታም በላይ ጌታ
አደረግነው ማለት አይደለምን?
የጌታ ደቀመዝሙር የነበረው ይሁዳ ከአልባሌ ቦታ አንስቶ ለክብር ያበቃውን ጌታውን የሸጠው
ለገንዘብ ሲል ነው። አዎ! ገንዘብ አብዛኛው ክርስቲያን ተወግቶ የወደቀበት የሰይጣን ዋነኛው
የውጊያ መሳሪያ ነው። ለዛም ነው ባለጸጋ ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ
ብትሾልክ ይቀላል የተባለው (ማቴ 19፥24፤ ማር 10፥25፤ ሉቃ 18፥25)። የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ገንዘብ
አይጠቅምም ለማለት አይደለም። ባለጸጋ አትሁኑ ለማለትም አይደለም። ነገር ግን በፍቅረ ነዋይ
ተወግተን የሰይጣናዊ አሰራር ምርኮኛ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን።

4.4 እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች


♥♥ “አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።” ምሳ 4፥23
•• እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች እንዴት ይፈጠራሉ?
♥♥ እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች የሚፈጠሩት ከሚጎዱና በኃጢአት የተሞላ ኅብረት
ከሌሎች ጋር ስናደርግ ነው። “ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው፥ አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ
ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።” 2ኛ ጴጥ2፥19
በእኛ ላይ የሚደረጉ ኃጢአታዊ ስራዎች ለምሳሌ የንግግር፣ የፆታዊና አካላዊ ጥቃቶች
ሲገጥሙን እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ ወይንም ጤናማ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች ሊገጥሙን ይችላሉ።
በሕይወታችን የሚገጥሙን እነኚህ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ከሚጎዱን ሰዎች ጋር በነፍስ እንድንተሳሰር
ያደርጉናል። ሰዎች እንደማንረባና እንደማንጠቅም ሲነግሩን ወይንም በሌሎች መገለልና መጣል
ሲደርስብን የሚፈልጉን ከሚመስሉን አጉል ነገሮች ጋር ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስርን
ሊፈጥርብን ይችላል። በጣም ልንገለል ወይንም ብቸኝነት ሊሰማን ይችላል። ይህንን ለመከላከል
በስሜታዊነት ለሌሎች ሰዎች ባሮች ወይንም ተገዢዎች ልንሆን እንችላለን። ከሰዎች ጋር
የተለማመድናቸው መጥፎ የሆኑ የነፍስ ትስስሮች አሁን ልንመሰርት ያለውን አዲስ ኅብረት እነኚህ
መጥፎ በሆኑት ልምምዶች መነፅር እንድንመለከት እንገደዳለን።
•• እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች እንዴት ይጠነክራሉ?

48
ምንም እንኳን ጥቃቱ ቢቆምም፣ ኃጢአታዊ ማንነቶች ቢያበቁም የነፍስ ትስስር በቀላሉ
ላይወገድ ይችላል። በተለያዩ ምክንያቶች ለሌሎች ተገዢ ልንሆን እንችላለን፥ ለምሳሌ በጥቃት፣
በኃጢአት፣ በቤተሰብ ችግር፣ ሀሺሽ፣ ይቅር አለማለት፣ ቁጣ፣ በአስማት መሳተፍ፣ ዝሙት፣
ማመንዘር፣ ስካር እና ሌሎች በገላ5፥19-21 የተጠቀሱት የስጋ ሥራዎች ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።
ግጭትና ብስጭት
አንድ ሰው ከትዳር አጋሩ ጋር ከእግዚአብሔር ያልሆነና ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር
በመካላቸው ሊኖር ይችላል። ይህ ትስስር ሊፈጠር የሚችለው የትዳር ጥንዶች በተለያየ የሕይወትና
መንፈሳዊ ልምምድ ስለሚኖራቸውና አመለካከታቸውም ያንኑ ያህል የተለያየ ሊሆን ስለሚችል
ነው። ይህንን ልዩነት ባለመረዳትና አቻችሎ ለመሄድ ፈቃደኛ ባለመሆን ጥንዶቹ እርስ በእርሳቸው
ልብን የሚጎዱ ንግግሮችን ሊነጋገሩ ይችላሉ። ይህ ሁኔታ በጊዜው በመነጋገርና በይቅርታ ሊፈታ
ካልተቻለ ግን በመካከላቸው ከእግዚአብሔር ያልሆነ ትስስርን ይፈጥራል። ይህንን ከእርሱ
ያልሆነውን ትስስር እንዲበጥስ በጸሎት ካልጠየቁ በቀር በብስጭት ይሞላሉ። ዲያብሎስም
በሕይወታቸው ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እድል ፈንታ ያገኛል። የክፋት ምክሩንም ለሁለቱም
ማማከሩን ይጀምራል። “እንዲህ፣ እንዲህ በይው፤ እንዲህ በላት፤ እንዲህ አድርጊው፤ እንዲህ
አድርጋት፤” በማለት የሚሰጣቸውን የክፋት ምክር በመቀበል ሰብዓዊ ያልሆኑ ስራዎችን እስከ
መስራት ድረስ ያደርሳቸዋል። ይህ ሁሉ ጉዳት ሊመጣ የሚችለው ሁለቱም ወይም ከሁለቱ አንዱ
ልባቸውን እልከኛ በማድረጋቸው ነው። ሰይጣን እድል ያገኘበት ትዳር ውስጥ “የትዳር ጓደኛዬ
አትወደኝም” ወይም “አይወደኝም” የሚል ዕሳቤን እንዲያዳብሩ ያደርጋቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ
በኤፌሶን መጽሐፍ እንዲህ ይገልፀዋል፦
♥♥ “ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።”
ኤፌ 4፥26-27
ይህ ካልሆነ ልብ በይቅር ባይነትና በእረፍት ፋንታ በሚቀጥለው ጊዜ ግጭት ሲፈጠር ትዕግስት
ማጣት ይከሰታል። ይህ የነፍስ ትስስር ስህተትን የምንቀበል ሳይሆን ፈራጆች እንድንሆን ያደርገናል።
በዚህ ጊዜ ችግርን ተቀብሎ ይቅር ከመባባል ይልቅ የእርስ በእርስ አልበገር ባይነት ይዳበራል፥
ምክንያቱም ሰይጣን የልብን ዙፋን ይቆናጠጣል። ከእግዚአብሔር የሆነ የነፍስ ትስስር ቢኖረንም
እንኳን ጠላት እኛን ለመከፋፈልና ለትዳር አጋሮቻችን የሚኖረንን አስተሳሰብ በጎ ባልሆነ መልኩ
እንድንቀይር ሊፈትነን ይችላል። ከጠላት ሃሳብ ጋር ስንስማማ ጠላት ትዳራችንን እንዲበጠብጥ
ህጋዊ ፈቃድ ሰጠነው ማለት ነው።
ቀድሞ የነበረን መልካም ያልሆነ የጓደኝነት(የእጮኝነት) ጊዜ አሁን ባለንበት እጮኝነት ላይ
ተፅዕኖ የሚያመጣ ከሆነ ጠላት ቀድሞ የነበረብንን ብስጭት አሁን ባለው ሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ
እንዲያመጣ እድልን ሰጥተነዋል ማለት ነው።
ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት ከሌሎች ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ከነበራቸው በሚመሰርቱት
ትዳር ላይ ተፅዕኖ እንደሚያመጣ የታወቀ ነው። ስለዚህ ከእነኚህ ሰዎች ጋር የነበራቸው የነፍስ
ትስስር መሰበር አለበት። እግዚአብሔር ምህረት እንዲያደርግና ይህንን የነፍስ ትስስር እንዲሰብረው
ካልጠየቁ በስሜታቸው ብስጭት ይከማቻል።

49
ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር ቀላል በሚመስሉ ስምምነቶች ሊፈጠር ይችላል። ከእግዚአብሔር
ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች በፍቅር የተሞላን ከእግዚአብሔር የሆነን የነፍስ ትስስር አያጠፋም። ነገር
ግን ብስጭት በሕይወት እንዲሆን በማድረግ ለወደፊቱ የሚጎዳ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋሉ።
ማሽኮርመምና መዳራት
አብዛኛው ሰው ማሽኮርመምን ሰይጣን ሰዎችን በዝሙት ለመጣል የሚጠቀምበት መሳሪያ
መሆኑን ሳያውቁ እንደጨዋታ ይቆጥሩታል። ማሽኮርመም ማለት የወሲብ ስሜትን ለማነሳሳት
የሚደረግ የንግግር ወይም የእንቅስቃሴ ድርጊት ነው። ለእንደዚህ አይነቱ ድርጊት ተመሳሳዩ መዳራት
ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ማሽኮርመም የሚናገር ሲሆን ምን ማለት እንደሆነና ፍሬዎቹን በግልፅ
ያስቀምጥልናል። ምሳ 6፥24-26 እና ምሳ7፥5 ስለ ማሽኮርመምና የሚዳሩ ሰዎች ስለሚጠቀሟቸው
ቃላት ይገልፃል። ወንዶችና ሴቶች እርስ በራሳቸው ሲሽኮረመሙ የተዳሪዎችን ተግባር ያደርጋሉ።
የከፋው ነገር የመዳራትና የማሽኮርመም ፍሬ የነፍስ ትስስርን ያስከትላል። ይህም ያንን ሰው
እንድንመኝ ያደርጋል፤ በትዳር ውስጥ ችግር ካለ የተሻለ ነገር ለማግኘት መመኘት ይጀመራል።
†† መዳራት ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስርን ያመጣል። በመጀመሪያ አስተሳሰብን
ያስራል። በመቀጠል ስሜትን በመጨረሻም ፈቃድን ያስራል። ጠላት በኢንተርኔት በሚታዩ
ወስባዊ ምስሎችና ወሲብን በተመለከተ የሚደረጉ የአጫጭር መልእክት ልውውጦች
እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች በሰዎች ላይ ለማድረግ ይጠቀምበታል። በዚህ
ቅፅበት ልባችን ይረታል። ለዚህ ነው ኢየሱስ ማንም ወደ ሴት ያየ በልቡ አመንዝሯል
የሚለው (ማቴ 5፥28)።
ፆታዊ የስጋ ትስስር ኃጢአት
በኃጢአት ከሌሎች ሰዎች ጋር መሳተፍ ከእግዚአብሔር ያልሆነ የመንፈስ መተሳሰርን
ያመጣል። አዲስ ኪዳን ፆታዊ ኃጢአትን በሁለት ይከፍለዋል። እነሱም ማመንዘርና መዘሞት
(ዝሙት መፈፀም)ናቸው።
ማመንዘር ማለት አንድ ባለትዳር የሆነ ሰው ከትዳሩ ውጪ ወሲብ ሲፈፅም ወይም አግባብ
ያልሆኑ ፆታዊ ባህርይዎችን ሲለማመድ ነው። መዘሞት ማለት አግባብ ያልሆነ ፆታ ባህርይ ሲሆን
ማመንዘርንም ያካትታል። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ሁለቱም ድርጊቶች የስጋ ስራ ናቸው።
♥♥ “የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥
ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥
ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው።” ገላ 5፥19
ጊዜው ይለያይ እንጂ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥረው ወንድና ሴት አድርጎ ነው።
ይህንን ያደረገበትም ምክንያት እርስ በእርስ እንዲረዳዱ፣ አብረው ደስ እንዲላቸው እንዲሁም
ዓለምን እንዲሞሏት ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሀሳብ ወይም ዓላማ እውን የሚሆነው የሰው ልጅ
ከተፈቀደለትና በትዳር ከተሳሰረው አንድ ሰው ጋር ብቻ ነው። ለዚህም ነው በመጽሐፍ ቅዱስ
ላይ “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤” ዕብ 13፥4 በማለት የሚናገረው።
ማንኛውም ከትዳር ዉጪ የሚደረግ ፆታዊ ግንኙነት (ወሲብ) ኃጢአት ሲሆን ይህንን ከምናደርገው
ሰው ጋር ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስር እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል። እንዲህ ዓይነት
50
ፆታዊ ኃጢአት በጣም የጠነከረ የነፍስ ትስስርን ሲፈጥር በተጨማሪም ለጠላት ስቃይ ያጋልጣል።
ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ 6፥18 ላይ በማንኛውም የፆታዊ ኃጢአት ላይ ስንሳተፍ በገዛ አካላችን
ላይ ኃጢአት እንደምንሰራ ይነግረናል።
♥♥ “ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፥ ዝሙትን የሚሠራ ግን
በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።” 1ኛ ቆሮ 6፥18
ሌላው ከእግዚአብሔር ያልሆነ ጾታዊ ትስስር ግብረ ሰዶማዊነት ነው። ይህ ተግባር
እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሙሉ ለሙሉ በመቃወም የሚደረግ ርኩሰት ነው። ቃሉም
“ስለዚህ እርስ በእርሳቸው ስጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኩሰት
አሳልፎ ሰጣቸው።” ሮሜ 1፥24 እንዳለ ይህ ተግባር ቅጣትን የሚያስከትልና ክፉ የሆነ የስጋ ትስስር
ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰዶምና ገሞራ ሰዎች በዚህ ኃጢአት የተበከሉ እንደነበሩ እናውቃለን።
እርስ በእርሳቸው የሚያደርጉት በደል አልበቃ ብሏቸው ሎጥ ቤት እንግዳ መስለው በመጡ
መላእክት ላይ እንኳን ይህንን ድርጊት ለመፈጸም ተሰባስበው እንደመጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።
(ዘፍ 19፥1-25) በአሁኑ ወቅትም ቢሆን ይህ ድርጊት በድብቅ ከመሰራትም አልፎ በአንዳንድ
ሀገራት ላይ እንደ መብት ተደርጎ በህጋቸው አጽድቀውት ይገኛሉ። ነገር ግን ይህ የኃጢአት ተግባር
ለሰዶማውያን ሕዝብ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር እንደሆነ ዓለማችን የተረዳች አትመስልም።
በስመ ስልጣኔ ጠላት ይህንን አፀያፊ ልማድ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ እየዘራ ይገኛል። ሀገራችንን
ጨምሮ “ክርስቲያን ነን” በሚሉ ሀገራት ውስጥ ይህ የጥፋት መንገድ ከምንጊዜውም በላይ በፍጥነት
እየተገነባ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ማንነታችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆነ ይነግረናል። በዚህ ቤተ
መቅደስ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚገባቸው ነገሮች ሁሉ ለአምላክ መታጠንና መቅረብ የሚችሉ መሆን
አለባቸው። ለዚህም ነው የአማኞች አካል የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንጂ ኃጢአት የሚፈፀምበት
አይደለም የሚባለው። ፆታዊ ኃጢአት በሕይወታችን ሰይጣን እንዲገባ መንገድ ይከፍትለታል።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችን ቀርቶ የሰይጣን ማረፊያ እስክንመስል ድረስ ለበለጠ
የድፍረት ኃጢአት የተለማመድን እንድንሆንም ያደርገናል። በመሆኑም ከዳንን በኋላ የሚኖረንን
ነፃነት ለማጣጣም በፊት በነበሩን ፆታዊ ግንኙነቶች አማካኝነት የነበሩን የነፍስ ትስስሮች መቆም
አለባቸው። ነገር ግን እነኚህ ትስስሮች በጸሎትና ከጠላት ጋር ያለ ስምምነት ካልፈረሰ በትዳር
አልጋ ላይ በሀሳብ፣ በስሜት፣ በመንፈስ ሊገለጡ ይችላሉ። ይህ ደግሞ አካላዊና መንፈሳዊ ጉዳት
ሊያስከትል ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ ጠላት እነኚህን የነፍስ ትስስሮችን ትዳርን ለማፍረስ መሰረት
አድርጎ ይጠቀምባቸዋል።
ፖርኖግራፊ
የግሪኩ ቃል ፖርኒያህ ሲለው ትርጓሜውም ዝሙት ወይም ማመንዘር ማለት ነው።
ፖርኖግራፊ የወሲብ ስሜትን የሚያነሳሱ ነገሮችን ማለትም ፎቶግራፎች፣ የተለያዩ እርቃነ-ስጋን
የሚያሳዩ ስዕሎች እንዲሁም ቪዲዮችን (ከትዳር አጋር ውጪ የሚደረጉ ግንኙነት፣ ሰዶማዊ
ግንኙነት ወዘተ) በመመልከት ትክክለኛ ወዳልሆነ ፆታዊ ግንኙነቶች እንድናመራ የሚያደርግ፣
የሰውን አዕምሮ የሚይዝ መንፈስ ነው። በአሁኑ ጊዜ ፖርኖግራፊ በወንድም በሴትም እየጨመረ
ያለ ችግር ነው። በዚህ ጊዜ የነፍስ ትስስር የሚኖረው ሰዎች ከማያውቋቸው ሰዎች፣ በልብወለድ፣
51
በኢንተርኔት በሚታይ ለወሲብ በሚያነሳሱ ፊልሞች፣ በመጽሐፍት እና መፅሄቶች ላይ አንድን
ገፀ ባህርይ ወክለው ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ነው። ሰይጣን ፖርኖግራፊን በተለያዩ የዓለም ክፍል
ያሉ ወጣቶችን የስጋዊ ፍላጎታቸውን በማነሳሳት በምክንያታዊነት ሳይሆን በጭፍን ስጋዊ ስሜት
እንዲመሩ ያደርጋቸዋል። ብዙ ተፈጥሯዊ ያልሆኑና ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ እንደ ሰዶማዊ
ያሉ ተራክቦዎችን ያስተምራቸዋል። ያስተማራቸውንም ተግባር ላይ እንዲያውሉ በመገፋፋት
ርካሽ ለሆነ ድርጊት ይዳርጋቸዋል። በድርጊታቸው እንዳይጸጸቱ እንኳን የስልጣኔ ትርጉም ይህ ነው
ይላቸዋል።
በሁለተኛ ቆሮንቶስ 10፥3-5 የጠላት ምሽግ በውስጣችን የሚፈጠረው በአዕምሯችን ካሉ
መጥፎ እሳቤዎች እንደሆነ ተገልጿል። ጠላትም አሁን ከምንጊዜውም በላይ ፖርኖግራፊን እንደ
አንድ መሳሪያ ይጠቀማል።
♥♥ “በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር እቃችን
ሥጋዊ አይደለምና፥ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን፤ ለክርስቶስም ለመታዘዝ
አዕምሮን ሁሉ እንማርካለን፥” 2ኛ ቆሮ 10፥3-5
አዕምሯችንና እሳቤአችን በምንመለከታቸው ወሲባዊ ስዕሎች ይበከላል። ፖርኖግራፊ ወንዶችና
ሴቶችን ለፆታ ግንኙነት የተፈጠሩ እቃዎች ያደርጋቸዋል። ይህንን ፖርኖግራፊ የተመለከቱ ሰዎች
ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስርን የፈጠሩ ሲሆን ከዲያብሎስ ጋር ሰዎችን ለራስ እርካታ
ሲባል መጠቀም ምንም ችግር እንደሌለው ስምምነት አድርገዋል። ከእግዚአብሔር ያልሆኑ የነፍስ
ትስስሮች መበጠስ አለባቸው። በተጨማሪም ከዲያብሎስ ጋር የተደረጉ ስምምነቶች መፍረስ
አለባቸው።
የልብ ወዳጅ ምርጫ
የልብ ወዳጅ ስንመርጥ መጠንቀቅ አለብን። ሰይጣን ከአማኞች መልካምን ነገር ለመስረቅ
አንዱ የሚጠቀመው መንገድ እኛን ለመጉዳትና ለመጠቀም የሚፈልጉ ሰዎችን በማምጣት ነው።
እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች ትክክለኛ ካልሆኑ ጓደኞች ጋር በምናደርገው የተመቻቸ
ግንኙነት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ አምኖን ከኢዮናዳብ ጋር
የመሰረተው ያልተገባ ጓደኝነት ነው። አንዳንድ ጓደኞች ያለብንን መንፈሳዊ ድክመት እንድንቀርፍ
ከማገዝ ይልቅ ስህተት በሆነ መንገዳችን እንገፋበት ዘንድ በል በል ይሉናል። አምኖንም በእህቱ
ፍቅር መጠመዱን ለጓደኛው ኢዮናዳብ በነገረው ጊዜ ይህ ሃሳብ ካንተ ይራቅ ብሎ እንደመምከር
አሞኛል ብለህ ወደ ቤትህ ጥራት እሷም ወንድሟ ነህና ስትሮጥ ትመጣለች። የዛኔ ስሜትህን
ንገራት። አምኖንም የተባለውን ፈጸመ። ለእህቱ ልብ መሰበር ምክንያትም ሊሆን በቃ (2ኛ ሳሙ
13)። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው መልካም ባልሆነ ጓደኛነት ምክንያት ነው። ከቀድሞም ቢሆን ከአሁን
የሚኖሩን እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች ካልተወገዱ ሁልጊዜ ወደ ስህተት ማምራታችን
አይቀርም። ለዛም ነው የእግዚአብሔር ቃል “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ
ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?” 2ኛ ቆሮ 6፥14
ያለው። ምንም እንኳን በመጥፎ ጓደኛችን መጥፎ አካሄድ ተፅዕኖ ስር አንወድቅም ብለን ብናስብም
ቀስ በቀስ ባላወቅነው መንገድ በመጥፎ ስራቸው ልንወሰድ እንችላለን።
♥♥ “አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን ዓመል ያጠፋል።” 1ኛ ቆሮ 15፥33
52
ነገር ግን መልካም ጓደኛ ወደ ሕይወት መንገድ እንድናቀና ያደርጋል፤ ለችግር መፍትሔ
ይኖረዋል። ለመንፈሳዊ ሕይወት መጎልበት ይረዳል። ያለብንን ድክመት እያረመ ለሰይጣናዊ ስራ
የማንመች ያደርጋል።
♥♥ “ጻድቅ ለባልንጀራው መንገዱን ያሳያል የኀጥኣን መንገድ ግን ታስታቸዋለች።” ምሳ 12፥26
♥♥ “ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥በዋዘኞችም ወንበር
ያልተቀመጠ።” መዝ 1፥1

4.4.1 በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር


በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር ማለት አንዳንድ ሰዎች በተለየ መንገድ የማይገባንን ቦታ
ሲሰጡን የሚፈጠር ነው። ማንኛውም ሰው በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር ሊገጥመው ይችላል፤
ነገር ግን በአመራር ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ስለዚህ የነፍስ ትስስር ንቃት ሊኖራቸው ይገባል።
በአንድ በኩል የሆነን የነፍስ ትስስር መለየት
ትክክለኛ ባልሆነ መልኩ በሌሎች ሰዎች የምንፈለግ ከሆነ ይህ ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር
መሆኑን መረዳት እንችላለን። አንዳንድ ጊዜ ዝሙትን ያካተተ የነፍስ ትስስር ካለባቸው ሰዎች
ጋር ጊዜ ስናሳልፍ ወቃሽ ስሜት ሊሰማን ይችላል። ማለትም በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር
መንፈሳችንን ሊያወርድ ይችላል። እነኚህ ሰዎች በእጃችን ቢሆኑም እንኳን እነሱን ከሕይወታችን
ለማስወገድ ልንቸገር እንችላለን። የሚፈጁብን ጊዜ ግድ ሳይላቸው ሙሉ አትኩሮት እንድንሰጣቸው
ይፈልጋሉ። በሕይወታቸው ለሚፈልጉት ነገር እግዚአብሔርን ከመጠየቅ ይልቅ እኛን ጣዖታቸው
አድርገው ፍላጎታቸውን እንድናሟላ ይፈልጋሉ። በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስሰር ምሳሌ፦ጥገኞች
የሆኑ ሰዎች፣ ፍርሃት ያለባቸው፣ ሰውን እንደ ራሳቸው ጀግና የሚቆጥሩ፣ ለፆታዊ ግንኙነት ሰዎችን
የሚፈልጉ ወዘተ…ይጠቀሳሉ።
አንድ ሰው የራሱን መንፈሳዊና ስሜታዊ ፍላጎት ለማሟላት ጥገኛነትን የሚያዳብር ከሆነ
ይህ ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር መወገድ አለበት። በተጨማሪም ራሳችንን ከዚህ እስራት ነፃ
ለማውጣት በሕይወታቸው የማይገባንን ቦታ ከሰጡን ሰዎች ነፃ ለመውጣት መጸለይ ያስፈልጋል።

4.4.1.1 መሪዎችና እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች


በአመራር ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር ሊገጥማቸው ይችላል። ይህንን
አይነት የነፍስ ትስስር ሊፈጥሩ የሚፈልጉት አካላት በስራቸው ሳይሆን ከመሪው ጋር በሚኖራቸው
የኃጢአት ግንኙነት ብቻ ተቀባይነትንና ስልጣንን የሚያገኙ በሚመስላቸው ክፍሎች ናቸው።
መሪዎቻቸውን ከማክበርም ባለፈ ማምለክ ደረጃ ይደርሳሉ። ስለዚም አድርጉ ለተባሉት ማንኛውም
መጥፎ ስነምግባር ራሳቸውን ከማሰለፋቸውም ባሻገር መሪውንም ጭምር ወዳላሰበው መጥፎ
ድርጊት የመምራት ዝንባሌ አላቸው። ከዚህም በተጨማሪም ቅናተኞችና ተፎካካሪ ሰዎች መሪዎች
የያዙትን ስልጣን በመፈለግ ከእግዚአብሔር ያልሆነን የነፍስ ትስስር ሊፈጥሩ ይችላሉ። በአንዳንድ
ሰዎች አካባቢ ስንሆን የማይመች ወይንም ጥሩ ስሜት የማይሰማን ከሆነ ሰዎቹ ከእግዚአብሔር
ያልሆነን የነፍስ ትስሰር ከእኛ ጋር ሊኖራቸው ይችላል።

53
4.4.1.2 ዲያብሎስ የራሱን ባህርይ በመጠቀም
ቀደም ብሎ ያየናቸው የውጊያ ስልቶች በሌሎች አካላት አማካኝነት የሚደርሱብን የሰይጣን
ፈተናዎች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ከውጪ መልካምና አስደሳች የሚመስሉ ናቸው። ስለዚም በጦርነት
ውስጥ እንዳለን እንኳን ሳንረዳ እንዲሁም ራሳችንን ለውጊያው ዝግጁ ሳናደርግ የሚጥሉ ክስተቶች
ናቸው። ይህኛው የዲያብሎስ የጦር ሜዳ ግን የጠላት ባህርይ በጣሙን የሚታይበት ሲሆን ራሱ
በሕይወት መንገዳችን ላይ መሰናከያዎችን እያስቀመጠ አምላክን እስከምናማርር ድረስ ወይም
መኖሩን እስከምንጠራጠር ድረስ የሚዋጋበት መንገድ ነው። በኑሯችን ውስጥም ምንም አይነት
ምቾት እንዳይሰማን እያደረገ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ሳይሆን በሚኖሩብን የዕለት ችግር ላይ
ብቻ ትኩረት እንድናደርግ ማድረግ የዚህ የውጊያ ስልት ዋነኛ ዓላማ ነው። ይህም ከአሕዛብ በላይ
በአማኞች ላይ ይበረታል። ለዛም ነው የእግዚአብሔር ቃል “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ
ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤” 1ኛ ጴጥ 5፥8 እያለ የሚመክረን።
እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ ሁሌም በጸሎት መትጋት ይገባናል። እንደ ትእግስተኛው
ኢዮብም በነገሮች ሁሉ “እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን” በማለት ከደረሱብን ችግሮች ይልቅ
የሚደርስልን አምላክ እንደሚበልጥ ማሳየት አለብን። መብለጡንም በአንደበታችንና በህሊናችንም
ልንመሰክር ይገባናል።
የዲያብሎስ የጦር ሜዳ የጠላት ባህርይ በጣሙን የሚታይበት ሲሆን ራሱ የሚያስቀምጣቸውን
ዕንቅፋቶች ያካትታል። የዲያብሎስ ባህርይ መግደል፣ መዋሸት፣ ማጭበርበር፣ መክሰስ፣ መስረቅና
ማጨንገፍ ነው። ይህም ከአሕዛብ በላይ በአማኞች ላይ ይበረታል።
♥♥ “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤”
1ኛ ጴጥ 5፥8
♥♥ “ደግሞም፦ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሓን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን
ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው፥ ወደ አዕምሮ ይመለሳሉ
ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።” 2ኛ ጢሞ 2፥25-26

4.4.1.3 በዓመፅ በተያዙ ሰዎች አማካኝነት


(አስማተኞች፥ መተተኞች፥ መናፍስት ጠሪዎች፥ ጠንቋዮች፥ …)
ይህ ወጥመድ በክርስቲያኖች ላይ በኃጢአት ተፅዕኖ ስር ባሉ ሰዎች በኩል የሚደረግ ውጊያን
የሚያመላክት ሲሆን አስማት፣ ጥንቆላ፣ የመሳሰሉትን የኤልዛቤል መንፈሶችን ያካትታል። በዚህም
ጠላት ዋነኛ ተጠቃሚ ነው። ሶስተኛው የጦር ሜዳ ውስጥ በዓመፅ ተፅዕኖ ስር ያሉ ሰዎች
የክርስቲያኖችን ሕይወት ለመቆጣጠር ዓላማ ካደረጉ ጋር የሚደረግ ጦርነት ይካሄድበታል።
እግዚአብሔር ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር ኅብረት እንዳናደርግ አጥብቆ ያዘናል።
♥♥ “ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።”
1ኛ ዮሐ 3፥8
♥♥ “ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ?” ገላ 5፥7
♥♥ “የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ
ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?” ገላ 3፥1
54
♥♥ “አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት
ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ
ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥
ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር
ፊት የተጠላ ነው ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል። አንተ ግን
በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን። የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና
ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ አንተ ግን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከልክሎሃል።”
ዘዳ 18፥9-14

4.4.2 የጥንቆላ መንፈስና ቤተክርስቲያን


አብዛኛው ሰው ወዶ የጥንቆላን ስራ ላይከተል ይችላል። ነገር ግን ሁሌም ከጌታ መንገድ
ሊያወጣን የሚተጋው ሰይጣን በብዙ መልኩ በማስጨነቅ ወደ አሰራሩ ስርዓት እንድንገባ ግፊት
ያደርግብናል። ራሱ ለፈጠረው ችግር መፍትሔው እሱ ጋር ያለ በማስመሰል ይጠራቸዋል።
ጥሪውን ሰምተው ለሄዱ ሰዎች ደግሞ ዳግም እንዲመጡ የሚገፋፋ መንፈስን አስርፆ ከመላኩም
ባሻገር ሌሎችም ወደእርሱ እንዲመጡ መንገዱን ጠራጊ ያደርጋቸዋል። በእምነት ያሉትንም ቢሆን
“አምላካችሁ መቼ ይሰማችኋል? እርሱ ይዘገያልና ዛሬውኑ መፍትሔ የሚሰጣችሁ አካል ጋር ሂዱ፥
ዳግም በዚህ ችግር መጨነቃችሁ ይብቃ፤” በማለት እግዚአብሔርን ተንበርክከው የልባቸውን
ባማከሩት ማግስት ለጥንቆላ እንዲንበረከኩ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን እኛ እንደ ክርስቲያን በገባን
እውነት እግዚአብሔርን ከመታዘዝ በቀር በማንኛውም የጥንቆላ ስራ ውሰጥ መሳተፍ የለብንም።
በሀገራችን ለጥንቆላ መንፈስ የተሰጠች አንዲት ስም አለች። እሷም “አዋቂ” የምትል ናት። እዚህ
ጋር አንድ ክርስቲያን ወንድም ሲናገር የሰማሁትን ገጠመኝ ባስገባት ለሁላችን መማሪያ ልትሆን
የምትችል ታሪክ ትመስለኛለች። ነገሩን ሲያጫውተኝ፣ “በሰፈራችን ያለ አንድ ጠንቋይ ነበረ። ታዲያ
አንዲት ሴትዮ ዝናውን ሰምታ ከሌላ ሀገር ትመጣለች። እኔንም ከቤት ስወጣ ታገኘኝና “እባክህን
የአዋቂውን ቤት ታሳየኛለህ?” በማለት ጠየቀቺኝ” አለ። “ሴቲቱ ልትጠይቀኝ የፈለገችው ምን
እንደሆነ ቢገባኝም “አዋቂ” በማለት ስለጠራችው ግን ቅሬታ ተሰማኝና ጣቴን ጌታን እንድታስታውስ
ወደ ሰማይ እያሳየዋት “የአዋቂው ቤት እዛ ነው አልኳት”።” እኔም “ለምንድን ነው አዋቂ ስላለችው
ቅሬታ የተሰማህ? ስሙ ማንም ቢሆን ስራውን እኮ ነው ልንቃወመው የሚገባው” ባልኩት ጊዜ
የመለሰልኝ መልስ እንዲ የሚል ነበር። “ለምን አዋቂ እንለዋለን? የእርሱ ትክክለኛ ስሙ ጠንቋይ
ነው። ይህ ስም ትክክለኛ ምግባሩን ይናገራል። ትርጉሙም ስለ ጠንቅ ወይም ስለ ክፋት የሚውል
ማለት ነው” አለኝ። የዛን ጊዜም “ሰዎች ወደዚህ አካል የሚሄዱት ስሙ እንኳን ስለ ጠንቅ የሚውል
መሆኑን እንደሚናገር ገብቷቸው ይሆን?” ብዬ ራሴን ጠየቅኩ።
ሙሴ በትሩን እባብ ባደረገ ጊዜ የግብፅ አስማተኞችና ጠንቋዮችም ከእርሱ እኩል
በትራቸውን እባብ ማድረግ መቻላቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ነገር ግን ሰይጣናዊ ድግምት
በእግዚአብሔር ሰው ፊት ለፊት ምንም አቅም የለውም። ለዚህም ነው የሙሴ እባብ የመተተኞቹን
እባብ መዋጥና ስፍራ እንዳይገኝላቸው ማድረግ መቻሏ። ስለዚም እኛ እንደክርስቲያን በገባን እውነት
እግዚአብሔርን ከመታዘዝ በቀር በማንኛውም የጥንቆላ ስራ ውሰጥ መሳተፍ የለብንም።

55
ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔር የሆነው ዓይን ሲበራላቸው በጥንቆላ መንፈስ የተነዱበት እድሜ
ምን ያህል የባከነ እንደነበር ይረዱታል። ቤታቸው አስቀምጠው ቅቤ የሚያጠጧትን ጨሌ
አውጥተው ጥለው ሁለመናቸውን ለጌታ ያስገዛሉ።
♥♥ “አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።
ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም
ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።” ሐዋ 19፥18-19
በጥንቆላ መንፈስ ውስጥ ያሉ ክርስቲያን ነን ባዮች በክፉ መንፈስ ስለመያዛቸው እውቀቱ
አይኖራቸውም። እውነታውን እንዳያውቁ ታውረዋል። ጥንቆላዎች በሕይወታችን ቦታ የሚያገኙት
ራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ከመስጠት ይልቅ ከአጋንንት ጋር ስምምነት ስናደርግ ነው።
♥♥ “ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደማምለክ ነው
የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።” 1ኛ ሳሙ 15፥23
የጥንቆላ መንፈስ ራስ ወዳድና ዋጋ የሚያስከፍል ነው። በዚህ መንፈስ የሚሰሩ ሰዎች አዛዦች፣
በዝባዦችና ጥቅም ፈላጊዎች ሲሆኑ እነርሱ ከማንም በላይ ራሳቸውን እንደ ጥሩ መንፈሳዊያን
ሰዎች በመቁጠር በትዕቢት የተሞላ መንፈሳዊ የበላይነትን ለማግኘት ይሞክራሉ። ጸሎት
እንዳንፀልይ፣ ከአማኞች ጋር በኅብረት እንዳንሆን፣ ወደ ቤተክርስቲያን በሰዓት እንዳንሄድ እና
ከነጭራሹም እንድንቀር ሊያደርጉን ይችላሉ። ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን መንፈሳዊ ኅብረት
እንድናዳብር ከማበረታታት ይልቅ ለመንፈሳዊ ምሪትና ለጸሎት ወደ እነርሱ እንድንሄድ ይፈልጋሉ።
እግዚአብሔራዊ ያልሆነ የመንፈስ እስራት በውስጣችን እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ከእነዚህ አብዛኞቹ
በራሳቸው ሐዋሪያት ወይም ነብያት እንደሆኑ ያወጁ ናቸው፤ ነገር ግን ትንቢታቸው ከመንፈስ ቅዱስ
ያልሆነ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚፃረር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለን ትንቢቶችን መርምረን
ከእግዚአብሔር እንደሆኑና እንዳልሆኑ ማወቅ አለብን።
♥♥ “ነቢያትም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ ሌሎችም ይለዩአቸው፤” 1ኛ ቆሮ 14፥29
ትንቢት የሚናገሩ ጠንቋዮች ከላይ ተገልፀዋል። በዚህ መንፈስ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ሰዎች
ሌሎች ሰዎችን በኃጢአት ተፅዕኖ ውስጥ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። ይህ መንፈስ የሚቆጣጠራቸው
ሰዎች ዘመናቸው በከንቱ ያልቃል፤ ምክንያቱም ሰዎች ኃጢአታቸውን አውቀው ነፃ ለመውጣት
እንዲሞከሩ አያበረታታም።
♥♥ “በሰማርያ ነቢያት ላይ ስንፍናን አይቻለሁ በበኣል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤል
ያስቱ ነበር።” ኤር 23፥13
የጥንቆላ መንፈስ ቤተክርስቲያንና ከቤተክርስቲያን ጋር የሚኖረንን ግንኙነት የሚያጠቃ
የቅንዓት፣ የፉክክር እና ነፍስ የማጥፋት መንፈስ ነው። የሚሰራውም በስጋ ነው። የጥንቆላ መንፈስ
ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠንን ቅባትና ስጦታ አይወድም። ይህ መንፈስ በእኛ፣ በመጋቢዎች፣
በአገልጋዮች እንዲሁም በቤተክርስቲያን ውስጥ በአመራር ቦታ ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ያለውን የመንፈስ
ቅዱስ ቅባት ሊያጠፋና ሊገድል ይፈልጋል።

56
4.4.2.1 የጥንቆላን ጥቃት መረዳትና መለየት
ጥንቆላ ምስጢራዊ ሲሆን ዋና ስራውም በድብቅ ወይም በጨለማ የሚሰራ ነው። በሰዎች
የሚሰሩ የሚመስሉ ነገር ግን በአምስቱ ስሜቶቻችን ልንረዳቸው የማንችላቸው በሰይጣናዊ ኃይሎች
የሚሰሩትን ስራዎች ያጠቃልላል። ከጥንቆላ በስተጀርባ ያለው ኃይል እግዚአብሔርን የማይወድ
ሰይጣናዊ ኃይል ነው። ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ካለማወቅ የተነሳ ለችግሮቻቸው ሌሎች
አማራጮችን ይፈልጋሉ። በደመነፍስ ዝም ብሎ ከመኖር አዋቂ የሚመስሉ ስዎች ጋር ይጠጋሉ።
ከእነዚህም መካከል ጠንቋዮች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ። እነርሱም ከጠላት በመሆናቸው እውቀት
የላቸውም።
♥♥ “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ
እጠላሃለሁ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።” ሆሴ 4፥6
የሰዎች ሕይወት በሀሜት፣ በረሃብ፣ በበሽታ፣ በመከፋፈል እና በጭንገፋ ምክንያት እየጠፋ
ነው። ይህም የሚሆነው ጠንቋዮች በሰው ሕይወት ላይ የሚያደርጉት ተፅዕኖ ችላ ስለሚባል
ነው። በአስማት ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች የሰይጣንን ዓላማ በድግምትና በእርግማን በመሳሰሉት
አጋንንታዊ ተልዕኮዎች ቀውስን ያመጣሉ። ይህ ደግሞ አለመስማማትን፣ መከፋፈልንና ጭንገፋን
ያስከትላል።
†† የጠንቋይ ወይም የመተተኛ ስራዎች ሁሉ ከሰይጣን መሆናቸውን ሊያሳዩ የሚችሉ ብዙ
ምልክቶች አሉ። ከምልክቶቹም መካከል ለሰዎች እርስ በእርስ መባላት ትልቁ ምክንያት
መሆናቸው ነው። “ያንቺ ጠላት/ያንተ ጠላት እከሌ ነው፤ ስለዚህ ይህንን ድግምት
ወስደህ እንደዚህ አድርግ። እኔ ሕይወቱ እንዲበጠበጥ አደርጋለሁ” ይላሉ። የሰዎችን
ሕይወት መበጥበጥ ደግሞ የሰይጣን ባህሪ ነው። ከዚህም በተጨማሪም ወደ እርሱ ሄደው
ፍላጎታቸውን እንዲያሟላላቸው የሚጠይቁ ሰዎች ራሳቸው “እከሌን ግደልልኝ፤ አጥፋልኝ፤
አሳብድልኝ፤ ደሀ አርግልኝ፤ አፍዝልኝ” እና የመሳሰሉትን የክፋት ጥያቄዎች መጠየቃቸው
የቦታውን ሰይጣናዊነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። በዚም ምክንያት ሰይጣን በሰዎች ሕይወት
እያመጣ ያለው ችግር እጅግ ብዙ ነው። ስንቱ የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል? በቤታቸውስ ሰላም
አጥተው ስንቱ የፍቺ ጥያቄ ለፍርድ ቤት ያስገባል? ስንቱስ በአፍዝ አደንግዝ በሕይወት
ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነዋል? ሳዖል በክፉ መንፈስ ተጠቅቶ እንደነበረ በ1ኛ ሳሙ
16፥14 ተገልጿል። በዳዊት ላይ የእግዚአብሔር ቅባት ስለነበር ሳዖል ከዳዊት ጋር መፎካከርና
በዳዊት ላይ መቅናት ጀመረ። ሳዖል ከቅናቱ የተነሳ ዳዊትን በተደጋጋሚ ሊገድለው እንደፈለገ
እንመለከታለን። ከዚህም በተጨማሪ ሳዖል የእግዚአብሔርን ድምፅ ችላ በማለት ጠንቋይ
ጋር በመሄድ እግዚአብሔርን ይበልጥ አሳዝኗል። በዚህም ምክንያት ሕይወቱ አልፏል።
(1ኛ ዜና 10፥13-14)
ስለዚህ ሰይጣን ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸውን ቅርበት ለማዳከም ጥንቆላን
ይጠቀማል። ክርስቲያን የሆኑ ሰዎች በጥንቆላ ተፅዕኖ ውስጥ ሲሆኑ ሊገጥማቸው ከሚችሉ ነገሮች
መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተገልፀዋል። (ዘዳ 28፣ ዘዳ 32 ይነበብ።)

57
•• ግጭትና ሰላም ማጣት፥ ይህ ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ካለማወቅና ካለማመን የሚመጣ
ነው።
♥♥ “እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ
ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።” 1ኛ ቆሮ 14፥33
•• ቀርፋፋና ድንጉጥ መሆን
♥♥ “እኔን ስለ ተውኸኝ፥ ስለ ሥራህ ክፋት፥ እስክትጠፋ ፈጥነህም እስክታልቅ ድረስ በምትሠራው
ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር መርገምን፥ ሽሽትን፥ ተግሣጽን ይሰድብሃል።…እግዚአብሔር በዕብደት፥
በዕውርነት፥ በድንጋጤም ይመታሃል።” ዘዳ 28፥20-28
•• ከእግዚአብሔር ለመስማት መታገል
•• በዚህ ተፅዕኖ ውስጥ ያለ ሰው በአካላዊም በመንፈሳዊም ሁኔታ ከወደፊት ራዕያቸው ጋር መገናኘት
አይችሉም። ለአትኩሮት ይቸገራሉ።
•• ለነገሮች የሚኖራቸው ተነሳሽነት ዝቅ ያለ ወይንም እስከ አለመኖር ሊደርስ ይችላል።
•• ራሳቸውን ያገልላሉ።
•• ኃጢአተኛ እንደሆኑና ትክክለኛ እንዳልሆኑ ይሰማቸዋል(ተስፋ አስቆራጭ የሆነ መጥፎ ወቀሳ)።
•• ክርስቲያን የሆኑ ሰዎች በእርግማን ሲያዙ ስሜታቸው እጅጉን ይጎዳል ወይንም በስሜታቸው
ደካማ ይሆናሉ።
•• በመንፈሳዊ እርግማን የተያዙ ሰዎች ጨለማና ድብርት በገፅታቸው ላይ ይነበባል። ከመገኘታቸው
የተነሳ መንፈሳዊው አየር ይለወጣል።
•• በጭንቅላታቸው አካባቢ የሚሰማቸው ስሜት ይኖራል ይህን ልክ እንደ ራስ ምታት ልንመስለው
እንችላለን።
•• ጠላት በሚያጠቃቸው ጊዜ አካላዊ ህመም ለምሳሌ ድንገተኛ ማቅለሽለሽ፣ ራስ ምታት፣ አፍንጫ
ላይ የሚኖር ችግር፣ ድብርት፣ መንቀጥቀጥና የትንፋሽ ችግር የመሳሰሉት በአጠቃላይ አካላዊ
በሽታዎች ሊገጥማቸው ይችላል።
•• በተጨማሪም ድብርት፣ ተስፋ ማጣት፣ ልፍስፍስነት፣ ፍርሀት፣ ሃዘን፣ ቁጣ እና ከልክ በላይ
ማውራት ሊገጥማቸው ይችላል።
•• በብዛት ከጥንቆላ ጋር የተያያዙ እርግማኖች ትክክለኛ ያልሆኑ አዕምሮን የሚረብሹ ፍርሃቶች
እንዲከሰቱ ሊያደርጉ ይችላሉ።
እኛ ክርስቲያኖች ግን ለዚህ ክፉ ስራ ተባባሪ አይደለንም። እንዲሁም እነርሱ ጋር ካለው እኛ ጋር
ያለው ይበልጣልና የድግምትና የመተት ስራ በእኛ ላይ አንዳች የለውም። ይልቁኑም በዚህ መንፈስ
የተያዙትን ስለ እውነተኛው መድሀኒትና ስለ እውነተኛው አዋቂ በመስበክ ካሉበት ሰይጣናዊ
እስራት ነፃ ልናወጣቸው ይገባል።

4.4.2.2 አስማት
በማንኛውም የአስማት ስራ ውስጥ መሳተፍ ከጠላት ጋር የነፍስ ትስስርን ሊፈጥር ይችላል።
ጥንቆላ ሰይጣን ሰዎችን ለመማረክና ነፍሳትን ለማደን የሚጠቀምበት አንዱ መንገድ ነው።
58
♥♥ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፥ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና?
ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?” 1ኛ ቆሮ 6፥14
♥♥ “እንዲህም በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ነፍስን ለማጥመድ ለእጅ ድጋፍ ሁሉ መከዳ
ለሚሰፉ ለሰውም ሁሉ ራስ እንደ እየቁመቱ ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ
ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን?” ሕዝ 13፥18
♥♥ “የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ
ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?” ገላ 3፥1

4.4.3 በጥንቆላ መንፈስ ላይ ድልን መቀዳጀት


ክርስቲያኖች የጥንቆላ ስራ መኖሩን አንክድም። ነገር ግን ይህ ሰይጣናዊ ድርጊት በእኛ ላይ
ምንም ስልጣን ይኖረው ዘንድ የተገባ አይደለም። ምክንያቱም እኛ ጋር ያለው ከእልፍ አእላፋት
መናፍስት ይበልጣል። ሰዎች በተለይም ለዚህ ክፉ መንፈስ ስራ ተገዢ የሚሆኑት ከእግዚአብሔር
ጋር ካላቸው የላላ ግንኙነት ምክንያት ነው። የሚሰራባቸውም ድግምትና ማንኛውም ክፉ ድርጊት
የሚደርስባቸው መከላከያ የሚሆንላቸውን መንፈሳዊ ጋሻ ባለመያዛቸው እንዲሁም “እጠቃለሁ”
በሚል ፍራቻቸው ነው። ይህ ፍራቻ ሰዎች በአምላካቸው ላይ ያላቸውን መተማመን ስለሚቀንሰው
ለሰይጣናዊ ስራ መግቢያ ቀዳዳን ያበጁለታል። ክርስቲያኖች ሁሉ ለእሳት ተላልፈው ከተሰጡት
ከነሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ትምህርት መውሰድ ይገባናል።
ትምህርት አንድ፥ በእኛ ሕይወት ውስጥ የሚመላለሱ የተለያዩ አካላት (ናቡከደነጾር) ምስልን
ወይም የባእድ አምልኮ መገለጫን ፊት ለፊታችን አቁመው “ስገዱ፤ ካለበለዚያ ግን በሚንቀለቀል
እሳት ውስጥ ትጣላላችሁ” ይሉናል። ይህ ሁለት የተለያዩ ጽንፍ የያዘ ምርጫ ነው። አንደኛው ምርጫ
“አምላክህን ክደህ ለቆመልህ ምስል ስገድ፤ በሰላምም ትኖራለህ” ሲሆን ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ
“አምላኬን አልክድም፤ ላቆማችሁትም ምስል አልሰግድም” በማለት የሚመጣብንን ማንኛውንም
ነገር ለመቀበል ራስን ዝግጁ ማድረግ ነው።
ትምህርት ሁለት፥ ከእነዚህ ሰዎች የምንማረው ሁለተኛው ትምህርት ደግሞ በአምላካችን ላይ
ያለንን ፍጹም የሆነ መተማመን በአንደበታችን መግለጽ ይሆናል። ስለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ
“ካነደድከው እሳት የምናመልከው አምላክ ያድነናል” በማለት ነበር። ይህ እምነት በሁላችንም ማንነት
ወስጥ ሊገነባ የሚገባ እምነት ነው። የምናመልከው አምላክ ሰይጣን የሚቃጣብንን መከራ ሁሉ
በመመከት ያድነናል። እዚህ የእምነት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ብዙ ሰዎች ለሰይጣን ፉከራና ሸለልቶ
ድንጉጥ ይሆናሉ። በመጨረሻም አምላካቸውን በመካድ ለቆመላቸው ምስል ይሰግዳሉ።
ትምህርት ሶስት፥ እነዚህ ሶስት ሰዎች በአምላካቸው ላይ ያላቸውን ሙሉ እምነት ከገለጹ
በኋላ የተናገሩት አንድ ነገር ነበረ።” አምላካችን ከዚህ እሳት ባያድነን እንኳን አንተ ላቆምከው
ምስል አንሰግድም።” አምላካችንን የምናመልከው በሰዓቱ ከተቃጣብን መከራ ስለሚያድነን ብቻ
ሊሆን አይገባውም። ምክንያቱም በደረሰብን ትንሽ ችግር “አምላክ ለካ የለም” ወደሚል ድምዳሜ
ላይ ያደርሰናልና። እምነታችን ላይ ቅድመ ሁኔታ ልናስቀምጥ አይገባንም። የቀረበልንን ሰይጣናዊ
ማስፈራሪያ ችላ ብለን “አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም” በማለት እምነታችንን ማፅናት አለብን።
እነዚህ ሶስት ሰዎች ምርጫው በቀረበላቸው ጊዜ የትርዒቱን ታዳሚዎችን በሙሉ ያስገረመና
ያስተማረ መልስ መልሰዋል። ለእኛም ምሳሌ የሚሆን ውሳኔን ወስነዋል።
59
ትምህርት አራት፥ እነ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ በተጋረጠባቸው ፈተና ላይ ድልን
ተቀዳጁ። የተቀዳጁትን ድል በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን። አንደኛ በራሳቸው ላይ የተቀዳጁት
ድልና ሁለተኛ “ለባእድ አካል ስገዱ” እያሉ በሚያስገድዱት አካላት ላይ የተቀዳጁት ድል ናቸው።
በመጀመሪያ በራሳቸው አካል ላይ የተቀዳጁትን ድል እንመልከት። ማንም ሰው ትሞታለህ ሲባል
የማይፈራ የለም። ላለመሞት የማያምንባቸውን ብዙ ነገሮች ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም።
እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች የነፍስና የስጋ ሙግት የሚካሄዱባቸው አጣብቂኝ ጊዜ ናቸው። በዚህ
አጣብቂኝ ጊዜ አብዛኛውን ጊዜ ስጋ ነፍስን ታሸንፋታለች። እነዚህ ሰዎች ግን ዘላለማዊ ሕይወትን
በማስቀደም “ከፈለክ ግደለን” ማለታቸው አምልኮታቸውን እንከን አልባ አድርጎታል። ሁለተኛው
ድል ደግሞ በሌሎቹ ላይ ያስመዘገቡት ድል ነው። ንጉሱን “አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም”
በማለታቸው በብዙ ታዳሚዎች ፊት ለሌሎቹ መቀጣጫ ይሆኑ ዘንድ ወደ እሳቱ ተጣሉ። ነገር ግን
ሶስት ሆነቀው ተጥለው አራት ሆነው ይታዩ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ መልአኩን ልኮላቸው
እሳቱ ቢንበለበልም አላቃጠላቸውም ነበር። ይህንን ሁኔታ የተመለከቱ ሁሉ ልባቸው ተሰበረ።
ሰዎች ለዘረጉት የአምልኮ ስርዓት ተገዝቶ በሕይወት ከመኖር ይልቅ በአምላክ ተማምኖ ወደ እሳቱ
መጣል የበለጠ መሆኑን ተረዱ።
ጥንቆላ መኖሩን የማናውቅ ወይም የማንቀበል ከሆነ በመንፈሱ ላይ ድልን መቀዳጀት አንችልም።
ጳውሎስ በቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ የሰይጣንን ስራ ችላ ማለት እንደሌለብን ይነግረናል። እውነታን
ካልተቀበልን የምንታለልበትን መንገድ እንከፍታለን። ሁላችንም በበጎ መልኩ ተፅዕኖ እንድናደርግ
በእግዚአብሔር የተሰጠን ስልጣን አለ። ተፅዕኖ የምናደርገው ቤተሰቦቻችን ላይ፣ አገልግሎታችን ላይ
እና ማናቸውም ተፅዕኖ ማምጣት የሚገቡን ቦታዎች ላይ ሊሆን ይችላል።
♥♥ “እኛ ግን እግዚአብሔር እንደወሰነልን እስከ እናንተ እንኳ እንደሚደርስ እንደ ክፍላችን ልክ እንጂ
ያለ ልክ አንመካም። ወደ እናንተ እንደማንደርስ አድርገን ከመጠን አናልፍምና፥ የክርስቶስን
ወንጌል በመስበክ እስከ እናንተ እንኳ ደርሰናልና፥ በሌሎች ድካም ያለልክ አንመካም፥ ነገር ግን
እምነታችሁ ሲያድግ ከእናንተ ወዲያ ባለው አገር እስክንሰብክ ሥራችንን እየጨመርን፥ በክፍላችን
በእናንተ ዘንድ እንድንከብር ተስፋ እናደርጋለን፤ በሌላው ክፍል ስለ ተዘጋጀው ነገር አንመካም።”
2ኛ ቆሮ 10፥13-16
እግዚአብሔር እኛን የጠራን ድል አድራጊዎች እንድንሆን እንጂ ተጠቂዎች (ድል ተደራጊዎች)
እንድንሆን አይደለም። እኛ የሰይጣን ወይም በእርሱ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥገኛ አይደለንም።
በእነኚህ መናፍስት እንድንታለልና እንድንገዛ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም። መልካሙ ዜና
በጥንቆላ መንፈስ ላይ ሙሉ ስልጣን አለን። እግዚአብሔር የጥንቆላን መንፈስ የምንዋጋበት ስልጣን
ሰጥቶናል።
♥♥ “በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር እቃችን
ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ
በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም
ለመታዘዝ አዕምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ
ልንበቀል ተዘጋጅተናል።” 2ኛ ቆሮ 10፥3-6
†† ጥንቆላ እግዚአብሔር የሰጠን መንፈሳዊ የጦር እቃ እውነት እንዳልሆነ ሊነግረን ይችላል።
በዚህ ምክንያት እኛን በጠላት ላይ ያለንን ስልጣን ሙሉ ለሙሉ እንዳንጠቀም ሊያደርገን
ይችላል። እግዚአብሔር የጥንቆላን መንፈስ የምናሸንፍበት ቃሉንና ቅባቱን በመንፈስ ቅዱስ
አማካኝነት ሰጥቶናል።
60
ጥንቆላን የሚቃወም ምሳሌያዊ ጸሎት
ጥንቆላና ከጠላት ጋር የተያያዙ ነገሮች ከእግዚአብሔር እንደሚያጣሉን ካወቅን ቀጣዩ እርምጃ
መሆን ያለበት ከጠላት እጅ ፈልቅቆ ያወጣንን አምላክ መታመንና በእርሱ ትዕዛዛት መንገድ
መጓዝ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ በመሰጠት በጸሎት ፊቱ መቅረብ አለብን። እግዚአብሔርን
ከተማመንን ደግሞ እንደ እርሱ ፈቃድ በስሙ የምንጠይቀውን ሁሉ ሊያደርግልን የታመነ ነው።
ከዚህ በታች ያለው ምሳሌያዊ ጸሎት እንዴት መጸለይ እንደምንችል ያሳያል።
“ነገርንም ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።” ኢዮ 22፥28
♥♥ “የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ
ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” ማቴ 16፥19
†† በሰማይ ያለህ አባት ሆይ በአጋንንት ላይና በጥንቆላ መንፈስ ለይ ስለተሰጠኝ ስልጣን
አመሰግንሃለሁ። በሕይወቴ ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም የጥንቆላ አሰራሮች በክርስቶስ
ኢየሱስ ስም አስወግዳለሁ። የክርስቶስን ደም በስሜቴ ላይ፣ በፈቃዴ ላይ፣ በአካሌ ላይ
አውጃለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ እንደሆነና ማንም በእኔ ላይ ጌታ ሊሆን እንደማይችል
አውጃለሁ። በቃልህ እንደተናገርከው “በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም
በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ
ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር” ኢሳ 54፥17) ርስቴ አንተ
ነህና ከአንተ ውጪ ማንም አይገዛኝም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ መላእክትህን ልከህ መልካም
ያልሆነ መንፈስን ወደ እኔ የሚያስተላልፉትን እንድታስወግዳቸው እፀልያለሁ። በእኔ
ላይ የተደረጉትን አስማቶች ሁሉ እሰብራለሁ። በእኔ ላይ የሚደረገውን የጥንቆላ ኃይል
በክርስቶስ ደም ሰብሬዋለሁ። በጥንቆላ መንፈሰ የተያዘውን አዕምሮዬን አስለቅቃለሁ።
በቃሉ እንደተጻፈው ከማንኛውም የጥንቆላ ኃይል ነፃ እንደሆነኩ አውጃለሁ (እንግዲህ ልጁ
አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ። ዮሐ 8፥36)። አንተ ብቻ በእኔ ላይ
ጌታ እንደሆንክና ማንም በእኔ ላይ ጌታ ሊሆን እንደማይችል አውጃለሁ።
†† በዙሪያዬም ያሉት ሰዎች በእኔ ላይ አንተ ብቻ ስልጣን እንዳለህ እንዲያውቁ እርዳቸው።
በታመነው ቃልህ መሰረት በእነኚህ ሰዎች የተደረገ ማንኛውም ሕይወቴን የሚያበላሸውን
ነገር ሁሉ በክርስቶስ ስም አፈርሳለሁ። ወደ እኔ መንፈስን ሊያስተላልፉ ያሉ ሰዎችን
ከልክላቸው። የክርስቶስን ደም በእኔና መንፈስን ሊያስተላልፉ ባሉ ሰዎች መካከል
አደርጋለሁ። እነኚህ ሰዎች በማንኛውም መንገድ ወደ እኔ እንዳይመለሱ እከለክላለሁ።
በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ስልጣንና በደሙ ጉልበት በሕይወቴ ላይ የተደረጉ የኮከብ
ቆጠራ ስራዎችን እደመስሳለሁ። በሰዎች አማካኝነት በእኔ ላይ አስማትን ወይም ጥንቆላን
ሊያደርጉ የተነሱ አጋንንት ስልጣናቸውን አስወግዳለሁ። እነኚህን አጋንንት በደሙ ጉልበት
አጠፋቸዋለሁ። የክርስቶስን ደም በእኔና በእነርሱ መካከል አደርጋለሁ። የሰይጣንን
ማንነትና አንተ ለእነርሱ ያለህን ፍቅር ገልጠህላቸው ከአጋንንት መንፈስ ነፃ ይወጡ ዘንድ
እፀልያለሁ።

61
†† በሕይወቴ ያለውን ማንኛውም ትምክህት፣ ዓመፅ፣ ኃጢአት፣ አለመታዘዝ እናዘዛለሁ።
ከዲያብሎስ ጋር በማንኛውም ሁኔታ ስምምነት አድርጌ ከሆነ ይቅር እንድትለኝና
ስምምነቶቹ ከሚያመጡት ችግር እንድታነፃኝ እፀልያለሁ።
†† አባት እግዚአብሔር ሆይ በማንኛውም ሁኔታ የአንተ ካልሆኑና መንፈስን ከሚያስሩ ሰዎች
ጋር ኅብረት አድርጌ ከሆነ ይህንን እንድትገልጥልኝ እፀልያለሁ። በሕይወቴ ጤናማ ባልሆነ
መንገድ ከሌሎች ጋር ስምምነት ፈጥሬ ከሆነ ይቅር በለኝ።
†† የተሰጠኝን መብራት አበራለሁ። ይህንን መብራት ከፍ አድርጌ በማብራት ጨለማን ሁሉ
እንዲያስወግድ አደርጋለሁ። ወደ ምድር ወርደህ የሰይጣንን ስራ ስላፈረስክ አመሰግንሃለሁ።
ጉልበት ሁሉ በሰማይም በምድርም ሊንበረከክለት፣ ሁሉም ምላስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ
ሊመሰክር እንደሚገባ አውጃለሁ። አሜን!!

4.4.4 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማያከብሩ የሚደርስባቸው ችግሮች


መታዘዝ ከሰነፎች መስዋት እንደሚሻል የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። በመሆኑም
ሕይወታችን ሙሉ የበረከት ፍሬዎችን እንድንለቅም የመታዘዝን አስፈላጊነት መገንዘብ አስፈላጊ
ነው። በመውጣታችን እንባረካለን፤ ስንገባም እናባረካለን፤ በአህዛብ መካከል የተደሰተ ሕዝብ አድርጎ
ያቆመናል። ለተቸገሩ እንድናበድር ኪሳችንን ሙሉ፣ እጃችንንም ለመርዳት የተፈታ ያደርገዋል።
እርሱ ከሚሰራልን መስመር ቀኝም ግራም አንልምና ኑሯችን ሁሌም በለመለመው መስክ ይሆናል።
(ዘዳ 8)። ነገር ግን እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ልቡንም ስለክፋት የሚያደነድን ቢኖር የሚከተሉት
እርግማኖች ይደርሱበታል።
ሀ) ድህነት
ድህነት ከቁሳዊነቱ ይልቅ መንፈሳዊነቱ ያመዝናል። አንዳንድ ሰዎች እጅግ ብዙ የሚባል ገንዘብ
በካዝናቸው ውስጥ ቢኖር እንኳን የድህነት መንፈስን ከውስጣቸው ይፍቁት ዘንድ ይሳናቸዋል።
እነዚህ ሰዎች የቁስ ባለጸጋ ቢሆኑም እንኳን ሁሌም ገንዘብን ይጠሟታል። በሕይወት ዘመናቸው
ሁሉ ያገለግሏታል እንጂ አይገለገሉባትም። በመሆኑም በኑሯቸው ውስጥ ምንም እርካታ
ከማጣታቸውም ባሻገር ገንዘባቸው የሚያተርፍላቸው ጭንቀትን ብቻ ነው።
♥♥ “ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን
ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል። በከተማ ርጉም
ትሆናለህ፥ በእርሻም ርጉም ትሆናለህ። እንቅብህና ቡሃቃህ ርጉም ይሆናል።” ዘዳ 28፥15-17
እንዲሁም ሃብቱ ሁሉ የተረገመና ወዳሚ ይሆናል። ይህ ቃል የሚያሳየን ቁም ነገር የሌማት
መሙላት ብቻ የህሊናን ፍላጎት አያጠግበውም። ስለዚህ ኃጢአተኞች ምንም እንኳን ባለጸጋ ቢሆኑ
የእግዚአብሔር ክብር ጎሏቸዋልና ፍሬውን እንዳይበሉ ይሆናሉ። ቢበሉ እንኳን የማይረኩ ይሆናሉ።
ብዙ ጊዜ በየሆስፒታሎቹ የተለያዩ ባለጸጋዎች ከምግብ አንፃር እንኳን “ከአንድ ምግብ ዓይነት ውጪ
ከበላህ ትሞታለህ” ሲባል ይሰማል። እንደዚህ የተባሉ ሰዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር አልታዘዝ ያሉ ናቸው
ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር ያዘነባቸው ሰዎች እንደዚህ አይነት ችግርን ሊያስተናግዱ ይችላሉ።

62
♥♥ “የምድርህን ፍሬ ድካምህንም ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል አንተም ሁልጊዜ የተጨነቅህ
የተገፋህም ትሆናለህ። እጅግ ዘር ወደ እርሻ ታወጣለህ አንበጣም ይበላዋልና ጥቂት ትሰበስባለህ።”
ዘዳ 28፥33ና 38
ለ) አቅመ ደካማነት
ሰዎች በራሳቸው ደካማ ናቸው። ነገር ግን በሚያበረታን በእግዚአብሔር መከራንም ቢሆን፣
ችግርንም ቢሆን የምንወጣበት አቅም ይኖረናል። ማዕበል የሚያላጋው የባህር ዳር ድንጋይ
እንደሚያብረቀርቅ ሁሉ ለአማኞች ፈተና በበለጠ ድል የሚያንጸባርቁበት አጋጣሚ ይሆንላቸዋል
እንጂ ወድቀው አይቀሩም። መሰናክሎችንም ቢሆን በጥንካሬ ያልፋሉ። ነገር ግን ማንም ከጌታ
ፈቃድ ቢያዘነብል “እንደራሴ ፈቃድ እንጂ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አልኖርም” ቢል የጥንካሬው
መንፈስ ከእርሱ ጋር አይደለምና ደካማና ልፍስፍስ ይሆናል። በማያልቅ የችግር ውርጂብኝ ውስጥ
ይኖራል። በመከራዎቹ ውስጥ አብሮት የሚቆምና አይዞህ የሚለው ክፍልም አይኖርም።
♥♥ “እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።በቀትርም ጊዜ ዕውር በጨለማ እንደሚርመሰመስ
ትርመሰመሳለህ፥ መንገድህም የቀና አይሆንም በዘመንህም ሁሉ የተጨነቅህ የተዘረፍህም
ትሆናለህ፥ የሚያድንህም የለም።” ዘዳ 28፥22ና 29
ሐ) ዕብደት
ዕብደት ማለት መደበኛ ሁኔታ ላይ አለመሆንና የህሊና ክፉ እና ደጉን የማመዛዘን አቅምን
ማጣትን ያሳያል።እነዚህ ሁኔታዎች የሚሳዩት ደግሞ ዕብደት ማለት የግድ ጨርቅን መጣል ብቻ
አለመሆኑን ነው። ነገር ግን በህብረተሰብ ዘንድ አሳፋሪ የሚባሉና የተናቁ ስራዎችን መስራት፣ ግራ
መጋባት፣ ጭንቀት፣ መርሳት፣ ደግ እና ክፉን አለመለየት፣ ያለምክንያት ከሰዎች ጋር መጣላት፣ ራስን
መጥላት፣ የልብ አለመረጋጋት እና የመሳሰሉት የዚህ እርግማን ውጤቶች ናቸው።
♥♥ “እግዚአብሔር በዕብደት፥ በዕውርነት፥ በድንጋጤም ይመታሃል።” ዘዳ 28፥28
በምሳሌ 26፥2 ላይ እንደሚታየው እርግማን ያለምክንያት ሰው ላይ ተፅዕኖ ሊያመጣ
አይችልም። በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ እንዲያመጣ የሚያደርጉት ይቅር አለማለት፣ ኃጢአት፣
በዘር ውስጥ ያለ በደል፣ እምነት ማጣት፣ ፍርሃት፣ አለመታዘዝ፣ ስርቆት እና ከሰይጣን አገልጋዮች
የሚመጣ እርግማን ምክንያቶች ይሆናሉ።
ሕዝቅኤል በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደረገው ጥንቆላ ይናገራል፤ (ሕዝ 13)። ጠንቋዮች
አማኞችን እንዲወጉ ወይም እንዲያጠፉ መንገድ ከሚከፍትላቸው ዘዴዎች መካከል እጅን በመጫን
የሰይጣንን መንፈስ ማስተላለፍ፣ የሰዎችን የወደፊት ሕይወት ለማወቅ የሚደረግ ኮከብ ቆጠራ፥
አስማት (ከሰው አዕምሮ በላይ የሆነን ነገር ማድረግ)፣ የደረቅ መርፌ ህክምና፣ እኛ ወይም ዘሮቻችን
ዓለም አቀፍ ህቡዕ ድርጅት አባል መሆንና መሳተፍ ተፅዕኖ እንዲያመጡ ሊያደርጋቸው ይችላል።
(ህቡዕ ድርጅት ምስጢራዊ ድርጅት ሲሆን ከላይ ሲታይ የሚጎዳ የማይመስል ነገር ግን ስለ
እግዚአብሔር ያለው እምነትና አስተምህሮ ከትክክለኛው አስተምህሮ የሚፃረር ነገር ያለበት ድርጅት
ነው። ህቡዕ ድርጅት የሚያሰተምረው አንድ እግዚአብሔር እንዳለና በሁሉ ሃይማኖት የሚገኝ ሰው
አንድ እግዚአብሔርን በተለያየ ስም እንደሚያመልክ ነው።)

63
♥♥ “ስለዚህም ጌታ፥ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም
የሚገዛ ጌታ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና
ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።” 2ኛ ቆሮ 6፥17-18
በህቡዕ ድርጅት ውስጥ አባላት የሆኑ ሰዎች አባልነታቸውን በውጪ ካሉ ሰዎች መደበቅ አልያም
መካድ እንዳለባቸው አንዳንድ ፅሁፎች ያስረዳሉ። የድርጅቱን ምስጢር በመሀላ እንዲጠብቁም
ይደረጋሉ። ህቡዕ ድርጅቶች በውስጣቸው የተለያዩ ዓይነት ስርዓታዊ አከባበር ሲኖራቸው ጉዳት
ከማያመጣው የቡድን ስብስብ በዓለም ሁኔታ ላይ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እስከሚችሉ የሰዎች ስብስብ
ሊደርስ ይችላል። በአብዛኛው ጊዜም እነዚህ ትልልቅ የሚባሉ ድርጅቶች የሰይጣን አስተሳሰብንና
አምልኮትን እንደሚከተሉ የተለያዩ ማስረጃዎች አሉ።
ህቡዕ ድርጅት የሀይማኖት ድርጅት እንዳልሆነ ሲነገር፣ ነገር ግን የራሱ የሆነ መመሪያ
መጽሐፍ ያለው፣ የተለያዩ አማልክትን የሚያመልኩ እና በጥምቀት የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ
ነው። መጽሐፉም እንደሚገልፀው ዘላለማዊ ሕይወት አንዱ የሃይማኖቱ መሰረት እንደሆነ ነው።
አብዛኛው የህቡዕ ድርጅቶች አባላት በለጋ እድሜአቸው ሲሞቱ ቤተሰቦቻቸው ደግሞ ለመናፍስት
በሚያደርጉት ስለትና መሃላ በተለያዩ በሽታዎች እንዲሰቃዩ አድርጓቸዋል።
አብዛኞቹ የህቡዕ ድርጅቶች አባላት የሆኑ ሕዝብ ጥሩ ሰዎች ቢሆኑም በእርግማን የታሰሩ
ናቸው። ብዙ ሰው በዙሪያቸው ያሉ የህቡዕ ድርጅት አባላት በባህርያቸው ጥሩ ስለሆኑና ጥሩ ነገር
ስለሚያደርጉ ስለድርጅቱ ማንነት በትክከል አይረዱም። በዚህ ምክንያት ይህን ቡድን መቀላቀል
መልካም እንደሆነና እንደማይጎዳቸው ያስባሉ። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ሲሆን የህቡዕ ድርጅት
መሰረቱ የተለያዩ ጣዖቶች በመሆኑ ይዞት የሚመጣው መዘዝ ከፊት ለፊት አይታወቅም። እነኚህ
የትውልድ በደሎች የደም ትስስር ባላቸው ሰዎች ያልፋሉ፤ በደሎቹ ለትውልድ እርግማን በር
ይከፍታሉ። ከህቡዕ እምነትና እርግማን ለመውጣት ሰዎች በክርስቶስ ደም መታጠብና መንፃት
አለባቸው።

4.4.5 የህቡዕ ድርጅት አደገኛነት


†† ደህንነትን ለመቀበል ወደ ፈጣሪ የሚያደርሱ ብዙ መንገዶች አሉ የሚለው የማታለል
አስተምህሮ
†† ጥሩ ስራ በመስራት ብቻ ደህንነት ይገኛል የሚለው አስተምህሮ
†† ለአማልክቶች የሚደረግ ስለትና መሀላ
†† ወደፊት የሚመጡ ትውልዶች ለእጅ ስራ የተሰጡ ናቸው
†† የድርጅቱ መሰረት ጥንቆላ መሆኑ

4.5 የዲያብሎስን ሥራ ማጋለጥና ማፍረስ


የዲያብሎስ ስራዎች ጨለማ ውስጥ ባሉ ሁኔታዎች ይመሰላሉ። ፍራቻ፣ ተንኮል፣ የሚሄዱበትን
አለማወቅ፣ ደባ፣ ርኩሰት፣ መሰናክል፣ ዝሙት፣ ስርቆት እና የመሳሰሉት የሚሰሩት በጨለማ

64
ነው። እነዚህን ስራዎች ስናፈራርስበት ግን የሰይጣን ምሽግ የሆነው የጨለማ ሕይወት በብርሀን
ይጥለቀለቃል። ለዲያብሎስም ራሱን የሚያስጠጋበት ስፍራ አይገኝለትም።
♥♥ “ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለ
ሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ
ብርሃን ነውና።” ኤፌ 5፥11-13
•• ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው እነዚህን የጨለማ አሰራር በሕይወት ቃሉና ወደር
አልባ በሆነ ፍቅሩ ሊያፈርስ ነው።
♥♥ “ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።” 1ኛ ዮሐ 3፥8-9
ጸሎት
ጸሎት የግል ስሜት ብቻ የምናንጸባርቅበት ሁኔታ አይደለም። አንዳንድ ክርስቲያኖች
የእግዚአብሔርን ቃል ባለመረዳት የሚጸልዩት ችግር ሲደርስባቸውና የዲያብሎስ ውጊያ
ሲበረታባቸው ብቻ ነው። በመሆኑም ጸሎት ብሶትንና ሀዘንን ብቻ ማካፈያ መንገድ አድርገው
ያስቡታል። ለምስጋና የሚሆን ጊዜ የላቸውም። የዕለት ቆይታን ሪፖርት የሚያቀርቡ ይመስል
ስለደረሰባቸው ችግርና ስላጋጠማቸው ፈተና ብቻ ይናገራሉ። ስለዚህ በጸሎት ውስጥ ከመናገር
በቀር መስማትን አይለማመዱም። ነገር ግን ስንጸልይ ከጌታ ጋር አብረን እንደሆንን ልናስብ
ይገባናል። ለጸሎት ስንንበረከክ አባታዊ ምክሩና ቡራኬውን ለመቀበል ከእግሩ ስር እንዳለን ሊሰማን
ይገባል። አጥንትን የሚያለመልም እንዲሁም ውስጥን በሀሴት በሚሞላ ቃላት ሲያናግረን በጥሞና
መስማት ይኖርብናል። የዛኔ ሰይጣን ከእኛ ጎን መቆም ተስኖት ሲርቅ ውስጣችንም በመንፈሳዊ
ጉልበት ሲታደስ ይሰማናል። ይህ ነው ዲያብሎስን ድል እንድንነሳው የሚያስችለን የመውጊያው
ጦር፤ ይህ ነው ከሚቃጡብን የዲያብሎስ ፈተናዎች የምንሻገርበት ድልድይ።
♥♥ “በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤” አፌ 6፥18
በሕይወታችን ላይ የክርስቶስ ኢየሱስን ደም ማወጅ
የጌታችን ደም መድኃኒት ሊሆነን እንጂ እንዲሁ በከንቱ የፈሰሰ አይደለም። የሰው ልጆችን
ኃጢአት ሊያነፃ የሚችል፣ መድኃኒትም የሆነ በነፃ የሚገኝ ውድ ፈሳሽ ነው። ለዛም ነው “የዓለሙን
ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” የተባለው። ይህ ደም መድኃኒት የሚሆነው
ለተቀበሉት ብቻ ነው እንጂ ለማያምኑት አይደለም። ሰይጣን በክርስቶስ ደም መዋጀታችንን
አይወደውም። ምክንያቱም ይህ ደም ግዛቱ የሆነችውን ሲኦልን ባዶ ያስቀረ፣ የማረካቸውንም ነፍሳት
የነጠቀ ነውና። ዛሬም “እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት (ራዕይ
12፥11)” በማለት በክርስቶስ ደም ዲያብሎስን ድል እንደምንነሳ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል።
በእግዚአብሔር ቃል መበርታትና መቆም
የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና መስማት በመጀመሪያ በትዕቢትና በሰይጣናዊ ስሜት የደነደነ
ልብ ይሰብራል፤ ይቀድስማል። ቃሉን ከሕይወታችን ጋር በማዋሀድና እንደ ሃሳቡም በመኖር
አሸናፊዎች እንሆናለን።

65
♥♥ “በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን
የእምነትን ጋሻ አንሡ፤የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር
ቃል ነው። በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለቅዱሳን ሁሉ
እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤” አፌ 6፥16-18
♥♥ “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ
ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና
አሳብ ይመረምራል፤” ዕብ 4፥12
እግዚአብሔርን ከማወቅ የሚያግዱ ሃሳቦችን ማስወጣት (መተው)
ያወቅነውንና የተቀበልነውን አምላክ እግዚአብሔርን እንድንረሳ የሚያደርጉንን ሁኔታዎች
መተው መቻል አለብን። እግዚአብሔርን እንድንረሳ ከሚያደርጉን ሁኔታዎች አንዱ ለሰዎች
የምንሰጠው ትክክል ያልሆነ ግምትና ክብር ነው። የምናደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ “ሰዎች
ይደሰቱበታል ወይስ አይደሰቱበትም?” ማለት እንጂ “እግዚአብሔር ይደሰትበታል ወይስ
አይደሰትበትም?” የሚል ሀሳብ ውስጥ እንድንገባ እንሆናለን። ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች ዝሙትን
ለመስራት፣ ጉቦ ለመቀባበል፣ ሰውን ለመግደል፣ እንዲሁም ሌሎች የኃጢአት ስራዎችን ለመስራት
ማንም ሰው የማያይበትን አሳቻ ቦታና ጨለማን የሚመርጡት። “ሰው አየኝ አላየኝ” ከማለት ባሻገር
“እግዚአብሔር አየኝ አላየኝ” የሚለው ሀሳብ በህሊናቸው ውስጥ አይመላለስም። ብላቴናው ዮሴፍ
በዚህ ረገድ ሊያስተምረን የሚችል ታሪክ አለው። ይህ ሰው የእግዚአብሔር ክብር አብሮት ስለነበር
በባእድ ሀገር በንጉሱ ዘንድ ክብርን ተጎናጽፎ ነበር። በመሆኑም ንጉሱ ወደ ሌላ ቦታ በሄደ ጊዜ
በስልጣኑና በንብረቱ ላይ ወክሎት ሄዶ ነበር። ታዲያ የዚያ ንጉስ ሚስት በዮሴፍ ላይ የዝሙት
መንፈስ አድሮባት ነበርና “አብረኸኝ ተደሰት፤ ከአልጋዬም ላይ ውጣ በማለት” ትጋብዘዋለች።
ዮሴፍ ግን “በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?” (ዘፍ 39) በማለት መለሰላት።
ይህንን አይነት ልምምድ እኛም ብንሆን ማዳበር ያለብን ነገር ነው። ከሰዎች ተደብቀን የምንሰራቸው
ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ግልጽ መሆናቸውን ማወቅ መልካም ነው። በመሆኑም
“ይህንን አስጸያፊ ድርጊት በአምላኬ ፊት አልፈጽምም” በማለት መተው አለብን።
♥♥ “የጦር እቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤
የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን
ለክርስቶስም ለመታዘዝ አዕምሮን ሁሉ እንማርካለን፥” 2ኛ ቆሮ 10፥4-5
ቃል ኪዳንን የራስ ማድረግ
♥♥ “የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ
ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን
መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን
ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም።” ዘኁ 33፥52-53
♥♥ ራስን አለማግለልና በቤተክርስቲያን ውስጥ መሳተፍ
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ሰጥቶናል። ለአንዳንዶቻችን በዝማሬና
በምስጋና እንድናገለግል፣ ለሌሎቻችን ቃሉን እንድንሰብክ፣ ለአንዳንዶቻችን እንድንመክር፣
ለአንዳንዶቻችን እንድንመራ፣ ለአንዳንዶቻችን በጽሁፍ እንድናገለግል የተለያዩ ጸጋዎች

66
ተሰጥተውናል። በእነዚህ በተሰጡን መክሊቶች ልናተርፍባቸው እንጂ ልንቀብራቸው አይገባም።
ምክንያቱም በትንሹ መታመን በትልቁ ለመሾም ምክንያት ነውና። በመሆኑም ራስን ከማግለል
ይልቅ የተሰጡንን ጸጋዎች ለመተግበር ዘወትር መትጋት ይገባናል።
♥♥ “ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ
እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ
እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።” ዕብ 10፥24-25
የሰዎችን የጸጋ ስጦታ ሳይሆን የሕይወታቸውን ፍሬ መመልከት
ምልክትን እያዩ መጓዝ ብዙ ችግሮች አሉት። ሰዎች ስለፈወሱና ድንቅ ድንቅ ነገሮችን
ስላደረጉ ብቻ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አስማተኞችም
ድንቅ ድንቅ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉና። ሙሴ በትሩን እባብ ሲያደርግ አስማተኞቹም ይህንን
ማድረግ እንዳልተሳናቸው ማስታወስ ይገባል። በመሆኑም የሕይወታቸውን ፍሬ ማየት ተገቢ
ነው። የእግዚአብሔር ቃልም እንድንጠነቀቅ ይመክረናል። የጌታ የሆኑት ግን ነገሮችን ሁሉ በፍቅር
ያደርጋሉ።
♥♥ “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች
ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?”
ማቴ 7፥15-16
♥♥ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”
ዮሐ 13፥35
እጅን ጭኖ ስለሚፀልይልን ሰው በሚገባ ማወቅ(መጠንቀቅ)
ተአምራትን ሲሰሩ ስላየናቸው ብቻ ሰዎችን በላያችን ላይ እጃቸውን ጭነው እንዲጸልዩ
ልንፈቅድላቸው አይገባም።
♥♥ “በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፥ በሌሎችም ኃጢአት አትተባበር፥ ራስህን በንጽህና
ጠብቅ።” 1ኛ ጢሞ 5፥22
እኛን ለመቆጣጠር የሚፈለጉ ነገሮችን ማስወገድ
ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ምንም ነገር ቢሆን ሊቆጣጠረን አይገባም። እንደ ሲጋራና
መጠጥ ያሉ ሱሶች ውስጥ ካለን ፈጥነን መውጣት ይገባናል። ሰው ለዛውም የእግዚአብሔር ድንቅ
ስራ ነውና አካልንም መንፈስንም በሚያቆሽሽ ግዑዝ ነገር ቁጥጥር ውስጥ መውደቅ አይገባውም።
ካልገዛው እያለ ፈተናውን በሚያበዛብን የስጋ ፍላጎትም ቁጥጥር ስር መውደቅ የለብንም። ስጋችንን
እየጎሸምን ልንኖር ግድ ነው፤ አለበለዚያ እንደስጋ ፈቃድ ወደ ፈለግንበት አቅጣጫ ስንነዳ እይታችን
ከአምላካችን ላይ ይነቀላል። ልባችንን ሕይወት ለሚሆናት ከእግዚአብሔር ሀሳብ በቀር ለጊዜያዊ
ምቾትና ደስታ ተገዢ አናድርጋት። ሌሎች በእኛ ላይ የሚተገብሩት ሰይጣናዊ ተግባርም ቢሆን
እንዳይሰራ እንዲሁም መሰናክል እንዳይሆንብን ልባችን በአምላካችን ላይ ፍጹም የሆነ እምነት
ሊኖረው ይገባል።
♥♥ “አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።” ምሳ 4፥23

67
♥♥ “በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም በፍርድም በሚነሣብሽ ም ላስ ሁሉ
ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል
እግዚአብሔር፦” ኢሳ 54፥17
አመፀኛ ሰዎችን መለየት
ዓመፀኞችን በእግዚአብሔር ቃል ልንለውጣቸው ከቻልን መልካም ነው። የክርስትና ሕይወት
ትርጉሙ በዓመፃ ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎችን መልሶ ለእግዚአብሔር ተገዢ ማድረግ ነው።
በጸሎታችን ማሰብ፣ የሕይወት ቃልንም ልንመሰክርላቸው ይገባል። የምንሄድበትን የሕይወት
መንገድ ለእነርሱም ይሆን ዘንድ ሰላማችንንና ፍቅራችንን እንግለጽላቸው። ነገር ግን አንዳንዶች
የምንነግራቸውን ቃል እንደ ሞኝነት ይቆጥሩታልና ሰምተው ለመቀበል ይከብዳቸዋል። ይልቁንም
እኛም የጊዜውን ፍልስፍና ተከታይ እንድንሆንና የክርስቶስን ሞትና ትንሳዔ ዜና እንዳናወራ
ማሰናከያዎችን ይፈጥራሉ። በመንገዳቸው ተስበን እንዳንቀር ሊቀየር የማይፈልግ የዓመፅን ሰው
መለየት አለብን።
♥♥ “ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው
የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።” 1ሳሙ15፥23
♥♥ “እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ወደ
እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት
አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።” ያዕ 4፥7-8

68
ምዕራፍ 5
የአማኞች ስልጣንና የመውጊያ መሳሪያዎች

♥♥ “እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥


የሚጐዳችሁም ምንም የለም።” ሉቃ 10፥19
ሰው ክርስቶስ አዳኙና ጌታው መሆኑን አምኖ ከተቀበለ በኋላ ለሚኖረው ሕይወት ምሉዕነት
የእግዚአብሔር ኃይል በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ደጋፊው ይሆናል። ይህም በተሰጠው ስልጣን
መሰረት በሕይወቱ ውስጥ ሊያጋጥመው የሚችለውን መንፈሳዊ ውጊያ ለመቋቋም እንዲችል
ያደርገዋል።
†† ይህ ምዕራፍ አንድ አማኝ የተሰጠውን ስልጣን ምን እንደሆነ እንዲያውቅና ስልጣኑን
በእምነት ተቀብሎ እንዴት መጠቀም እንዳለበት በጥቂቱ ያሳያል።
5.1 የአማኞች ስልጣን
ሀ ፍጥረታትን በሙሉ እንዲያስተዳድሩ
አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ባህርይ በእስትንፋሱ አማካኝነት አስተላልፎልናል። በመሆኑም
ፍጥረታትን የመምራት ባህርይን ከእግዚአብሔር ተጋርተናል። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ
የነበረው የመጀመሪያው ዓላማ ምድርን እንዲገዛ ነበር። ወንድና ሴት አድርጎ ከፈጠራቸው በኋላ
የሰጣቸው ትእዛዝ በምድር ላይ ያሉትን ፍጥረታት በሙሉ እንዲያስተዳድሩ ነበር። እግዚአብሔር
ሰውን በአምሳሉ ሲፈጥር የእግዚአብሔርን ምስል እንዲያሳይ ብቻ ሳይሆን በተሰጠው ስልጣን
በተፅዕኖ ምድርን እንዲመራ ነበር። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመስማታቸው ግን የዘላለም ሞት
ሲፈረድባቸው ዳግመኛ ወደነበሩበት ቦታ እንዲመልሳቸው ተሰፋን በመስጠት ነበር። ይህም ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣቱና ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት ራሱን መስዋዕት በማድረጉ ሲፈፀም የሰው
ልጆች የተቀማነውን ስልጣን በእርሱ በማመን መልሰን ማግኘት እንችላለን። ከእነዚህም ስልጣናት
መካከል አንዱ ጠላታችን ዲያብሎስንን የምንወጋበት ነው። እንደ ቃሉ በእምነት ከክርስቶስ ጋር
በመንግሰተ ሰማይ በስልጣኑ ከእርሱ ጋር ተቀምጠናል፤ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ምድርንም
እንመራለን።
69
♥♥ “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና
የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድ እና ሴት አድርጎ
ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም
ሙሉአት፥ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ
ግዙአቸው።” ዘፍ 1፥26-28
ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመስማቱ ግን የዘላለም ሞት ተፈርዶበታል። ከእርግማኑም
የተነሳ ምድርና ሌሎች ፍጥረታት ከሰው ልጆች ጋር የነበራቸው ተፈጥሯዊ መስተጋብር ልዩ የሆነ
አቅጣጫን ለመያዝ በቅቷል። የምድር እሾህና አሜኬላን ማብቀልና የእንስሳትም በሰው ልጆች ላይ
ማመጽ የዚህ እርግማን ነጸብራቅ ናቸው። የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታይ ማንነት
ባይኖረነም እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ የበደሉን እዳ በልጁ ሞት ተክቶልናል።
♥♥ “የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው። መሬታዊው እንደሆነ
መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው፥ ሰማያዊው እንደሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ
እንዲሁ ናቸው።” 1ኛ ቆሮ 15፥47-49
♥♥ “የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ታስበው
ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው? ከመላእክት እጅግ ጥቂት
አሳነስኸው በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።  በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው ሁሉን
ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥” መዝ 8፥3-6
♥♥ “የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።” መዝ 115፥16
♥♥ “ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ
ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም
ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ
ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴ 28፥18-20
♥♥ “ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና
በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ
በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል።”
ኤፌ 1፥20-21
♥♥ “በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን
ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር
አስቀመጠን።” ኤፌ 2፥6
•• ክርስቶስ በማንኛውም ነገር ላይ ሙሉ ስልጣንና ሙሉ ኃይል አለው።
♥♥ “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም
ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና
ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሯል። እርሱም ከሁሉ በፊት ነው
ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።” 1ኛ ቆላ 1፥15-17
♥♥ “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ
ያለው ታላቅ ነውና።” 1ኛ ዮሐ 4፥4

70
ለ) በአጋንንት ሁሉ ላይ ስልጣንና ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ
አጋንንትና ጭፍሮቻቸው በሰዎች ልጆች ላይ ምንም ዓይነት ስልጣን የላቸውም። የአጋንንት
አሰራር በእኛ ላይ ምንም ጉልበት የለውም። ይልቁኑም እኛ በክርስቶስ ስም ለምናምን እንደ ሀሳቡም
ለተጠራን የአጋንንትና የጭፍሮቻቸውን ስራ እናፈራርስ ዘንድ ስልጣኑ ተሰጥቶናል። ዳንኤል
በበደሉ ሳይሆን በጸሎት ከአምላኩ ጋር በመተዋወቁ ጠላቱ ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል
ቢያስፈርድበትም ይህ የእግዚአብሔር ሰው ግን ከአንበሶቹ ጋር ያለምንም ችግር ማደር መቻሉ
ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው።
♥♥ አሥራ ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ ደዌንም
ይፈውሱ ዘንድ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤ ሉቃ 9፥1
እኛ የክርስቶስ አካሎች ነን። ለዛም ነው ራሱ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎቼ
ናችሁ (ዮሐ 15፥5)” ብሎ የተናገረው። የታላቁ ንጉስ አካላት መሆናችን የእርሱን ኃይል እንድንላበስ
ያደርገናል። የጌታ ኃይል በመስቀል ላይ ተገልጿል።
♥♥ “እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል። አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል
በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።” ቆላ 2፥14-15
እኛንም በጠላት ኃይል ላይ ድልን እንድንጎናጸፍ ሲነግረን እንዲህ ይላል፤
♥♥ “እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥
የሚጐዳችሁም ምንም የለም።” ሉቃ 10፥19
♥♥ “በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ
በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።” ቆላ 2፥9-10
እርግጥ ነው ኃይላችንና ጉልበታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። እኛ በራሳችን ምንም ጉልበት
የሌለን ልፍስፍሶችና ደካማዎች ነን። አንድ ቅርንጫፍ ከዋናው ግንድ ተለይቶ እሳት ማቀጣጠያ
ከመሆን በቀር ምን እርባና አለው? መልሱ ምንም ነው። እኛም ከወይኑ ግንድ የተለየን ቅርንጫፎች
ከሆንን እንደዚሁ ነው። በጠላት ኃይል ላይ ድልን ልንጎናጸፍ አንችልም። ይህ እውነታ የተገለጠለት
ነብዩ ዳዊት “አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሀለሁ (መዝ 18፥1)” ብሎ አመሰገነ። የእኛ ጉልበትና ኃይል
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ነው።
♥♥ “የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” ሮሜ 16፥20
♥♥ ይህ ጸጋ ከእኛ ጋር ሲሆን ጦራችንና ጋሻችን ይሆናል። “በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ
ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ
አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።” ኢሳ 43፥2

71
ሐ ማሰርና መፍታት
♥♥ “ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት
ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።” ማቴ 12፥29
♥♥ “የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ
ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” ማቴ 16፥19

5.2 መንፈሳዊ ማሰልጠኛ


አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወቱ ውስጥ የሚያጋጥመውን ችግሮችና ውጊያዎች በድል
ለማለፍ መበርታት አለበት። ለመበርታት ደግሞ ከማን ጋር እንደምንዋጋና እንዴት እንደምንዋጋ
ማወቅና መሰልጠን አለብን። ይህም ጌታን በመስማትና ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ነው።
♥♥ “እግዚአብሔር አምላኬ ይባረክ፥ ለእጆቼ ሰልፍን፥ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር…፤” መዝ
144፥1

5.2.1 ክርስቶስ ከጠላት ጋር እንድንዋጋ ያሰተምረናል፤ ያሰለጥነናል


የሰይጣን ውጊያ ስልት ልዩ ልዩ ነው። የራሳችንን ስጋዊ ስሜት በመቀስቀስ፣ ጓደኞቻችንን
በክፋት በማስነሳት፣ በስራ ቦታ በመቃወም፣ በመንገዳችን መሰናከያ በማስቀመጥ እና በምንወዳቸው
ነገሮች ሁሉ ይዋጋናል። ምናልባትም እየተዋጋን መሆኑ ሳይገባንና እየጣለን መሆኑን ሳናውቅ ወደ
ሀሳቡ ሊወስደን ይችላል። ነገር ግን በአሸናፊው በክርስቶስ በመማርና በመሰልጠን፣ አካሄዱን ሁሉ
በመረዳት ድልን እንቀዳጃለን። ለዛም ነው መዝሙረኛው ዳዊት “እግዚአብሔር ይባረክ፣ ለእጆቼ
ሰልፍን፣ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር…(መዝ 144፥1)” ብሎ ያመሰገነው።
♥♥ “ይሄዱባት ዘንድ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ወይም አይጠብቁ እንደ ሆነ እስራኤልን
እፈትንባቸው ዘንድ፥ ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው አሕዛብ አንዱን ሰው እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ
ከፊታቸው አላወጣም። እግዚአብሔርም እነዚህን አሕዛብ አስቀረ፥ ፈጥኖም አላወጣቸውም፥
በኢያሱም እጅ አሳልፎ አልሰጣቸውም።”መሳ 2፥21-23
♥♥ “ከከነዓናውያንም ጋር መዋጋት ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ፥ በፊትም
ሰልፍን ያልለመዱ የእስራኤል ልጆች ትውልድ መዋጋትን ያውቁና ይማሩ ዘንድ እግዚአብሔር
ያስቀራቸው አሕዛብ እነዚህ ናቸው።” መሳ 3፥1-2

5.2.2 ክርስቶስ በማበረታታት ያግዘናል


እግዚአብሔር የሰይጣን ውጊያ ሲበረታ እንዳንደክም የሚያበረታን መንፈሱን ልኮልናል። ንስር
ያረጀ አካሉን በአዲስ እንደሚተካ እኛም ዘወትር በእርሱ ቅዱስ መንፈስ እንበረታለን፤ ጉልበታችንንም
እናድሳለን። የሚከብደንም ነገር አይኖርም።
♥♥ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።” ፊል 4፥13

72
እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው ወደ ከነዓን ሲጓዙ የእግዚአብሔር እርዳታ ተለይቷቸው
ቢሆን ኖሮ ተመልሰው ራሳቸውን ለፈርዖን አሳልፈው በሰጡ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን
እውነታ ስለሚያውቅ ከፊት ለፊታቸው ጥልቅ የሆነና በሰፊው የተንጣለለ ውኃ በገጠማቸው ጊዜ
ውኃውን ልክ እንደ ግድግዳ ለሁለት ከፍሎ በደረቅ እንዲሻገሩ በማድረግ እንዲሁም የፈርዖንን
ሰራዊት በዚያ ውኃ ውስጥ በማስጠም ሲያድናቸው፣ በዚያ እልም ባለው በረሀ ከደረቅ ድንጋይ
ውስጥ ውኃ እያፈለቀ እያጠጣቸው፣ መናን እያወረደ እየመገባቸው፣ ወደፊት ይጓዙ ዘንድ
እያበረታቸው፣ እሱን ብለው የወጡ ሕዝቡን በሰላም እንዲሄዱ አስችሏቸዋል።
♥♥ “እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ፥ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።
እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፤ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።” 2ኛ ሳሙ 22፥34-35
በክርስቶስ ስናምንና ከእርሱ ጋር አንድ ስንሆን በሰማያዊ ቦታ በስልጣን እንቀመጣለን። ሁሉ
ነገራችንን በአዲስ ሁኔታ መመልከት እንጀምራለን። የደከሙ የሚመስለን ማንኛውንም አካላት
ያበረታልናል። ለአብነት ያህል እጆች፥ ጥንካሬን ይወክላሉ፤ ነሀስ ደግሞ የእግዚአብሔርን ፃድቅ
ፈራጅነት ይወክላል። ኢየሱስ በጠላት ስራ ላይ በሙሉ ስልጣን እንድንፈርድ ስልጣን ሰጥቶናል።
እርሱን በምንታዘዝበት ጊዜ ደግሞ ይህ ስልጣን መስራት ይጀምራል። በክርስቶስ በኩል ትክክል
ባልሆኑ ነገሮች ላይ በፅድቅ እንድንፈርድ ስልጣን ተሰጥቶናል።
♥♥ “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ
ካህናት የለንም።” ዕብ 4፥15

5.2.3 መልካሙን ጦርነት እንድንዋጋ ያስችለናል


እርግጥ ነው በዓለም ላይ መልካም ጦርነት እንዲሁም መጥፎ ሰላም ኖሮ አያውቅም። ለዛም
ነው ሀገራት ሁሉ ወደ ጦርነት ላለመግባት የሚደራደሩትና አስታራቂ መፍትሔን የሚያፈላልጉት።
ከሰይጣን ጋር ጦርነት ላለማድረግ ግን መደራደሪያው አንድና አንድ ብቻ ነው። እሱም የጥፋት ልጅ
መሆን። እኛ የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችን ወደ ጦርነት መግባት አማራጭ የሌለው ነው። የዚህ
ጦርነት መልካም የመባሉም ምክንያት የጦርነቱ አካል መሆን ነፍስን የሚያጠፋ ሳይሆን የሚያተርፍ
በመሆኑ፣ የሚሰብር ሳይሆን የሚጠግን በመሆኑ፣ የሚያከስር ሳይሆን የሚያተርፍ በመሆኑ፣
የሚያደክም ሳይሆን የሚያበረታ በመሆኑ እና መሸነፊያ ሳይሆን ድልን መቀዳጃ በመሆኑ ነው።
♥♥ “ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለአንተ እንደተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ
ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ።” 1ኛ ጢሞ 1፥18
ስለዚህ ማንም ቢሆን ለዚህ መልካም ጦርነት ታጥቆ መነሳት ይኖርበታል። ነገር ግን “እኔ
ደካማ ነኝ፥ ሰይጣንን ታግዬ መጣል አይቻለኝም” አይበል። ምክንያቱም የመውጊያ ጦራችን ስጋዊ
አይደለምና። አዎ! እኛ የምንዋጋው የሰይጣንን ስራ ልክ እንደ ሸክላ የሰባበረው ሲኦልንም መዝብሮ
ባዶ ማድረግ በቻለው በክርስቶስ ደምና ጸጋ ነውና።
♥♥ “የጦር እቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ
ነው፤  የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ
እናፈርሳለን ለክርስቶስ ለመታዘዝ አዕምሮን ሁሉ እንማርካለን፥” 2ኛ ቆሮ 10፥4-5።
♥♥ “እነርም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከሞት
ድረስ አልወደዱም።” ራዕ 12፥11
73
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በመመስረት ብዙውን ጊዜ ስለ መልካሙ ውጊያ ስናወራ ይበልጥ ስለ
እምነት አብሮ ይነሳል። ክርስቶስ የጴጥሮስን የልብ እምነት በማየቱ ጴጥሮስ ካሰበው በላይ ባርኮታል።
አማኞች እግዚአብሔርን ባመንን ልክ ስልጣናችንም ያንን ያህል ነው። የክርስትና ሕይወት እረፍት
የለሽ የትግል ኑሮ በሆነበት በዚህ ዘመን እምነት የክርስቶስ ወታደሮች ሆነን በፅናት እንድንቆም፣
ሊለካ የማይችል ቦታ ይይዛል። ተስፋ መቁረጥና የክርስቶስ ቅንዓት አለመኖር ከኢየሱስ ቤተሰቦች
መካከል መወገድ ስንፍናዎች ናቸው። በመጨረሻ ወደ ሰማያዊው ቤታችን ብንሔድ ከመቆጨት
ያድነናል። ክርስቶስ እምነታችን ነው። እምነታችንን በሙሉ በእርሱ ላይ ከጣልን እንደ እርሱ ፍላጎት
ትግላችንን በድል እንጨርሳለን።

5.3 ከእግዚአብሔር የሆኑ መንፈሳዊ የጦር እቃዎች


የእግዚአብሔርን የጦር እቃዎች (ክርስቶስንም ጨምሮ) በመልበስ ራሳችንን ማዘጋጀት
አለብን። በተጨማሪም እኛ የእግዚአብሔር መሳሪያዎች ነን፤ እግዚአብሔር ጠላትን የምንዋጋበት
ሙሉ ትጥቅ ሰጥቶናል። መንፈስ ቅዱስ የሰይጣንን ስራ ለማፍረስ ቃሉን ወደ ሚያስፈልገው መሳሪያ
መቀየር ይችላል።
♥♥ “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።
መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ
ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” ኤፌ
6፥11-12
♥♥ “አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ በአንቺም መንግሥታትን
አጠፋለሁ።” ኤር 51፥20
♥♥ “በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር፦”
ኤር 23፥29
†† በኤፌ 6፥14-18 እንዲሁም በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ እንደ ጦር እቃዎች
ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ነገሮች ተፅፎልናል፦
i. የእውነት ቀበቶ፥
እውነትን ተናጋሪዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው። ከሀሰተኛ ጋር አይተባበሩም። ጌታ
ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ
የለም። (ዮሐ 14፥6)” ብሏል። በተቃራኒው ዲያብሎስ የሀሰት አባት ተብሏል (ዮሐ 8፥44)። ስለዚህ
እውነትን የታጠቀ ዲያብሎስ የካበውን የሀሰት ካብ የሚያፈራርስበትን መዶሻ ይዟል ማለት ነው።
ከአምላካችን ከእግዚአብሔር በቀር ማንንም አምላክ ነው ቢሉን ይህንን የእውነት ቃል በእምነት
መናገር እንችላለን።
♥♥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም ከእኔም በቀር አምላክ የለም በፀሐይ መውጫ
እና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን
አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።” ኢሳ 45፥5
ii. የፅድቅ ጥሩር፦ ኢየሱሰ ፅድቃችን ነው።
74
iii. እኛ በራሳችን ጽድቅ የለንም።
♥♥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የሚያስመካ ስራን አልሰራንም። ነገር ግን ከነጉድለታችን የሚቀበለን
የጽድቃችንን መመኪያ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም የፈሰሰልን ንጹህ ደሙ የጽድቃችን
ማህተም ነውና እሱን መያዝ አለብን። “እግዚአብሔር የጽድቅ ጋሻዬ ነው…” መዝ 7፥10
♥♥ “ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፥ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቍር አደረገ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፥
በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ።” ኢሳ 59፥17
iv. በሰላም ወንጌል መጫማት፥
†† ወንጌልን ስንጫማ ጥሩ ተዋጊዎች መሆን እንችላለን። ነገር ግን ወንጌልን መጫማት
ቃሉን ማወቅን የሚያካትት ቢሆንም ቃሉን ልንለብሰው ወይም ልንዋሀደው ካልቻልን
ግን ጥቅም አልባ ይሆንብናል። ምክንያቱም ቃሉንማ ሰይጣንም ቢሆን ጌታን ለማሳሳት
ሲሞክር ተጠቅሞበታል። ዛሬም ቢሆን እኛን ለማሳትና ለመጣል ይጠቀምበታል። ስለዚህ
ቃሉ በውስጣችን እንዲሰራ መፍቀድ ይኖርብናል። ለዛም ነው ቃሉ “ይህንን መጽሐፍ ብላ“
ያለው።
♥♥ “ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ
ያቀናል።” ሉቃ 1፥79
v. የእምነት ጋሻ
†† ብዙ ጊዜ ሰዎች እምነት የሚለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ይተረጉሙታል። ለመሆኑ
እምነት ምንድነው? እምነት ማለት የድርጅት አባል መሆን ማለት አይደለም። ክርስቶስ
ለእኛ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደም መቀበል ማለት ነው። ሕይወት የሚጀምረው ከዚህ
ነው። በሰማይም በምድርም እናምንበት ዘንድ ያለን አንድ ብቻ ነው። ከእርሱ በቀር ሌላ
እምነትን የሚያመጣ ቢኖር እርሱ የሞት አገልግሎትን ያገለግላል።
♥♥ “እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ለአንተ ዛሬ እነሆ አስታወቅሁህ።” ምሳ 22፥19
♥♥ “በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና።” መዝ 4፥8
♥♥ እምነት በአንደበት ብቻ የሚገለጥ ሳይሆን የምናምንበትን ነገር ወደ ውስጣችን ማስረጽ ነው። ይህ
እምነታችን ከዲያብሎስ ፍላጻ የምንሸሸግበት ጋሻችን፣ ራስ ራሱን የምንቀጠቅጥበት ጫማችን፣
ከክርስቶስ ቤተሰቦች ጋር አንድነትን የምንመሰርትበት ማህበር፣ ከአምላካችን ጋር የምንገናኝበት
መስመር፣ ከውድቀታችን የምንነሳበት ምርኩዝ፣ ያላየናትን መንግስተ ሰማይ የምናይበት መነጽር፣
የዲያብሎስን ስራ የምናፈራርስበት መሳሪያችን ነው። “በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን
የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ።” ኤፌ 6፥16
♥♥ “የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።” መዝ 33፥4
♥♥ ማንም ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ኑሮውም የምድራዊ ስኬትን ጫፍ ቢነካ ነገር ግን እምነት አልባ
ቢሆን ምን ይጠቅመዋል? ጠቢቡ ሰለሞን እንደተናገረው “ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ
መከተል ነው።” መክ 1፥14
♥♥ “በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ
ተቃወሙት።” 1ኛ ጴጥ 5፥9

75
vi. የመዳን ራስ ቁር
†† የራስ ቁር ሰዎች በተለያየ ምክንያት ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው
ለመከላከያ ተብሎ የሚሰራ፣ ጭንቅላትን ከጉዳት የሚጠብቅ ብረት ለበስ መከላከያ ነው።
የክርስትናው የራስ ቁርም ይህንን ገላጭ ምሳሌ በመከተል መንፈስ ለሆነው ጠላታችን
መንፈሳዊ የራስ ቁር መከላከያ እናጠልቃለን። ይህ መንፈሳዊ መሳሪያ የዲያብሎስ ጦር
ቢወጋን እንኳን እንዳይጥለን ይጠብቀናል።
♥♥ “እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን
በመጠን እንኑር፤” 1ኛ ተሰ 5፥8
vii. የመንፈስ ሰይፍ፥-
†† ዲያብሎስ መንፈስ እንደመሆኑ መጠን የሚዋጋንም በመንፈስ እንጂ ስጋዊ ጦር በማዝመት
አይደለም። ስለዚህ የእኛም የጦር እቃ ቁሳዊ ጋሻና ቁሳዊ ጦር አይደሉም። ረቂቅ የሆነውን
የዲያብሎስን ጦሮች የሚያይ መነጽር፣ ወደ እኛ የሚወነጨፉትን የርኩሳን መናፍስት ጦሮች
የሚመክት መንፈሳዊ ጋሻ እንዲሁም ድል የምናደርግበት መንፈሳዊ ጦር ያስፈልገናል።
እሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
♥♥ “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ
ነው።” ዕብ 4፥12
viii. የእግዚአብሔር ክብር
†† ክብር ከማፍቀር ይጀምራል። ያለ ፍቅር ግን ክብር የለም። ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር
የሚገለጸው ደግሞ አብረውን ያሉ እህት ወንድሞቻችንን በማፍቀር፣ መጠጊያ አልባ ለሆኑ
ሰዎች መጠጊያ በመሆን፣ ለፍጥረት ርህራሄ ሲኖረን፣ ጭካኔንን ከሕይወታችን ስናርቅ
ነው። “ሰው አያየንም” ብለን የምንሰራቸውን የክፋት ስራዎችና ኃጢአት “በአምላኬ
በእግዚአብሔር ፊት እሰራ ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ” በማለት ነው። ይህ ክብር የሰይጣን ደባ
በእኛ ላይ አቅም እንዳይኖረው ዋስትናችን ነው።
♥♥ “የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።” ኢሳ 58፥8
♥♥ “እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና…” ኢሳ 52፥12
ix. የብርሃን ጋሻ ጦር
†† ጨለማ በብርሀን ይገፈፋል። ስለዚህ የጨለማውን አሰራር ልንገልጥ እንዲሁም በመንፈሳዊ
ብርሃን ልንተካው የብርሃንን ጋሻ መያዝ ይገባናል። ጌታ ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ያለ
እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም (ዮሐ 8፥12፣ 9፥5)” እንዳለ የጨለማን ስራ የምናፈራርስበት
የብርሃን የጦር እቃችን ጌታ ነው።
♥♥ “በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።” ዮሐ 12፥4

76
♥♥ “እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።” 1ኛ ዮሐ 1፥5
♥♥ “ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር
እንልበስ።” ሮሜ 13፥12
♥♥ “ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ
ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው
ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።” 1ኛ ቆሮ 4፥5
♥♥ “ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፥ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም
በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።” 1ኛ ዮሐ 1፥5
x. የእግዚአብሔር ቃል (ኢየሱስ)
†† ቃሉ ለመንገዳችን መብራት፣ የሕይወት እንጀራ፣ መዶሻ፣ እሳት እና ሰይፍ በመባል
ተገልጿል። እግዚአብሔር በቃሉ አማካኝነት ጠላት ላይ አዋጅ እንድናወጣና ጠላትን
እንድናዝ ስልጣን ሰጥቶናል።
♥♥ “ነገርንም ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።” ኢዮ 22፥28
(1) ቃሉ ሕይወት ነው
†† የእግዚአብሔር ቃል እንደ ዓለማዊ መጽሐፍ በምድር ላይ ስለሚቀርና ስለሚያልፍ እውቀት
የሚነግረን አይደለም። ልብ ወለድ ተብለው እንደሚጻፉትም ጊዜያዊ ደስታ ወይም ሽብር
እንዲሰማን አድርጎ የሚያልፍም አይደለም። እንደ ነገስታትና መሳፍንት ቃልም በሹመት
ዘመን የሚከበር ሲወርዱ ደግሞ አብሮ የሚወርድ አይደለም። ሕይወት ነው፤ ለዛውም
ዘላለማዊ የሆነ። የሚያምኑበትና እንደ ሊድያ (ሐዋ 16) ልቦናቸውን ክፍት አድርገው
የሚሰሙት ሁሉ ሕይወትን ያገኛሉ።
♥♥ “ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው ሥጋ ምንም አይጠቅምም እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው
ሕይወትም ነው” ዮሐ 6፥63
(2) የሚያጠግብ እንጀራ
†† የእግዚአብሔር ቃል የሚያጠግብ እንጀራ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው? የዚህ አባባል
ትርጉም ስጋ የሚያመጣብንን ውጊያ እንድንንቅ ያደርገናል ማለታችን ነው። ብዙ ሰዎች
የሚወድቁበት የውጊያ ስፍራ ሆድ ነው። ከአዳም ጀምሮ የነበረው መሰናክል ዲያብሎስ
ኢየሱስ ክርስቶስን እንኳን ሳይቀር በራበው ሰዓት በእንጀራ ፈትኖታል። ኢየሱስ ክርስቶስ
ግን የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቃል ሲኖር የስጋ ጊዜያዊ መራብ ምንም እንዳልሆነ
ተናግሯል። የእግዚአብሔር ቃል በመንፈሳዊ እርካታና ጥጋብ ያኖረናል። ቃሉን ለሚቀበሉት
ሁሉ ለዓለማዊ ምግብና መጠጥ ብለው አምላካቸውን እንዳይተዉ የሚያደርግ መንፈሳዊ
እርካታ ነው ልንለው እንችላለን። በሰማርያ ሊያልፍ ግድ የሆነበትና ለሳምራዊቷ ሴት በቃሉ
ስለሚገኝ ዘላለማዊ የሕይወት ውኃ የነገራት እረፍትን እንድታገኝ ነበር።
♥♥ “ኢየሱስም፦ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ
መለሰለት። ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት
አሳየው። ዲያብሎስም፥ ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም
77
እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው።
ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።”
ሉቃ 4፥4-8
♥♥ “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”
ዮሐ 1፥1
♥♥ “የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።” ኤፌ 6፥17
(3) ሰይፍ ነው
†† የእግዚአብሔር ቃል ሰይፍነቱ በሁለት መልኩ ነው። የመጀመሪያው ሰይፍ ራስን
ከዓለማዊነትና ከረከሰ መንገድ በመቁረጥ የሚነጥል መሆኑ ነው። ክርስቲያኖች ምንም
እንኳን በዓለም ላይ የምንኖር ብንሆንም ዓለም ከምታሰናዳው የዓመፅ ድግስ ግን የተለየን
ነን። ከማያምኑና ለስጋቸው ብቻ ከአደሩ አካላት የለየንና ወደ እግዚአብሔር ማህበር
ያሰባሰበን የቃሉ ሰይፍ ነው። ሰይፍ የተባለበት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሰይጣንን
ተዋግተን አሸናፊ የምንሆንበት በመሆኑ ነው።
♥♥ “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ
ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና
አሳብ ይመረምራል” ዕብ 4፥12
♥♥ “በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።” ራዕ 19፥13
xi. የእግዚአብሔር ስም
†† የእግዚአብሔር ስም ከስሞች ሁሉ የበላይ የሆነ ስም ነው። ይህ ማለት በስሙ ብቻ
ታላቅና ድንቅ የሚሰራበት የተመረጠ ስም ነው። ብቸኛና ታላቅ ስም ነው። የታዋቂ
ሰዎችም ስምም ሆነ የነገስታት ስም ምንም ያህል ገናና ቢሆን እንኳን ስማቸው ምንም ነገር
ሊያደርግ አይችልም። የገናናው አምላክ ስም ግን አጋንንትን አቅማቸውን የሚሰልብ ነው።
የእግዚአብሔር ስም ለሚደገፉት ደጋፊ ነው፤ ለሚያምኑት ሰላም ነው፤ ተስፋ ለሚያደርጉት
እረፍት ነው፤ ለሚጠሩት ሁሉን ቻይ ነው።
♥♥ “ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፥ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት።”
ሉቃ 10፥17
†† ይህ ስም ጎባጦችን ያቀና፣ ዕውራንንም ያበራ፣ ሙታንንም ያስነሳ ስም ነው። በሐዋ 3፥6
ላይ ስናነብ ጴጥሮስ መንገድ ዳር ቁጭ ብሎ የሚለምነውን ሰው “የምሰጥህ ገንዘብ የለኝም
በጌታ ስም ተነስና ተመላለስ” ብሎ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ የነበረውን ሰው ዘሎ እንዲቆም
አስችሎታል። ቃሉ እንደሚናገረው ወዲያው ቁርጭምጭሚቱም በረታ፤ ዘሎም ቀጥ ብሎ
ቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ወዲያና ወዲህም እየሄደ እየዘለለም የእግዚአብሔርን ስም
እንዳመሰገነ እንረዳለን። ይህንን ያክል ታላላቅ ተአምራትን የሚያደርግ ስም አንድ ብቻ ነው፤
እሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው።
♥♥ “በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።”መዝ 44፥5
♥♥ “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ
78
እባቦችን ይይዛሉ፥” ማር 16፥17
♥♥ “ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥”
ፊል 2፥10
xii. የኢየሱስ ደም
♥♥ “እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት
ድረስ አልወደዱም።” ራዕ 12፥11
♥♥ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው።
እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል። አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል
በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።” ቆላ 2፥14-15
xiii. የእግዚአብሔር እሳት
†† እሳት ለሰው ልጆች ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ግኝቶች አንዱ ነው። እሳት
ከብርሃንነት አንስቶ ምግብን እስከማብሰል ድረስ ጥቅም ይሰጣል። ሲበዛም ያቃጥላል።
ማቃጠሉም በሁለቱም ጎኖች፣ በጥቅምም በጉዳትም ሊገለፅ ይችላል። በዓለም አብዛኛው
ክፍል ላይ ሰዎች እሳትን ቁስል እንኳን እንዲድን ይጠቀሙበታል። የእግዚአብሔርም
እሳት እንደዚሁ ነው። የእግዚአብሔር እሳት ለእኛ ክርስቲያኖች ብርሃን ከመሆን ባሻገር
ፍቅሩን፣ አዳኝነቱን፣ ጥበቃውን፣ ሁሉን ቻይነቱን፣ ልጆቹን ማንፃትና መቀደሱን ሲያመላክት
ለኃጢአተኞች ደግሞ ማስፈራቱን፣ ቁጠኝነቱን እንዲሁም ቅጣቱን ይገልፃል።
♥♥ “የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ፥ እጄም ፍርድን ትይዛለች፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥
ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ።” ዘዳ 32፥41
♥♥ “እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።” መዝ 97፥3
♥♥ “እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ
የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።  በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም
በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥
ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፦” ኢሳ 54፥16-17
♥♥ “ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ
ውስጥ ቃሌን እሳት ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸውማለች።” ኤር 5፥14
♥♥ “በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር፦”
ኤር 23፥29
♥♥ “እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ…” ዘካ 2፥5
xiv. አምልኮና ምስጋና
†† ዓለማችን በፍላጎቶች የተሞላች ናት። አንዱን ስናሳካ ሌላው ይጎድልብናል። ስለሆነም ያሉንን
ወይም የተሰጡን ብዙ ነገሮች ሳሉ ትኩረታችን የሌለን ነገሮች ላይ ይሆናል። ስለዚህ ጸሎት
ሰንፀልይ ከልመና በቀር የማመስገን ልምድ እንዳናዳብር እንሆናለን። እዚህ ጋር ማንሳት
ያለብን ጥያቄዎች አሉ። “ጌታን ተመስገን ልንል ምን ምክንያት አለን? ጤነኛ እጅና እግር
አለን? ውስጣችን ጤናማ ነውን? ሕይወታችንስ እጅግ የተጎሳቆለ፣ ለእኛ የሚሆን ትንሽ
79
ነገር ያጣን ነን? የሚወዱን ቤተሰቦችና ጓደኞችስ አሉን? የምንበላው አጥተን ጾማችንን
እናድራለን? የምንለብሰው አጥተን ራቁታችንን እየሄድን ነውን? የሚጠለሉበትን አጥተው
የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑትን ስናይ ምን ይሰማናል? የዓይናቸውን ብርሃን አጥተው ቀኑ
ጨለማ የሆነባቸውን ስናይስ ስለራሳችን ምን እናስባለን? በእውኑ እግዚአብሔርን ይህንን
አድርገህልኛልና አመሰግንሃለሁ ለማለት ምክንያት እናጣለን? ከቃላት ባለፈ ማመስገንና
መዘመር በራሱ በጠላቶቻችን ላይ ድልን እንድንቀዳጅ እንደሚያስችል እናውቃለን?”
♥♥ “ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞዓብ ልጆች
በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦርን አመጣባቸው እነርሱም ተመቱ።” 2ኛ
ዜና 20፥22
♥♥ “ቅዱሳን በክብር ይመካሉ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። የእግዚአብሔር ምስጋና
በጕሮሯቸው ነው ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው፥ በአሕዛብ ላይ በቀልን በሰዎችም
መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ
ዘንድ የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።” መዝ
149፥5-9
xv. የመንፈስ ቅዱስ ቅባትና ስጦታዎች
†† የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የተለያዩ ናቸው። በመድረክ ላይ ቆሞ የሚሰብክ ሰባኪ፣
ግለሰብን ቀርቦ የሚመክር መካሪ፣ ተስፋ በመቁረጥ ላይ ላለ ሰው የተስፋን መንገድ
የሚያሳይ ምእመን፣ ባለው ጸጋ ቤተክርስቲያንን የሚመራ ምሁር፣ እንደ ልድያ የልቡን
ደጅ ወለል አድርጎ ከፍቶ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ግለሰብ፣ ዘወትር ለአገልግሎት
ራሳቸውን የሚሰጡ ዲያቆናት፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ጸጋን ተቀብሏል። ከስጦታዎችም
መካከል የተሸበረና ያዘነ ልብን ማጽናናት አንዱ ነው። ምንም እንኳን ጠላት የሚውጠውን
ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችን ቢዞርም መንፈስ ቅዱስ ያጽናናናል፤ ያበረታታናል።
ሌላው በመንፈስ ቅዱስ የምናገኘው ስጦታ ፈተናን የምናልፍበትና ጠላትን የምናሸንፍበት
ኃይልን ነው።
♥♥ “መልሶም፥ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና
በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦” ዘካ 4፥6
♥♥ “እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም
መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።” 1ኛ ቆሮ 2፥4
♥♥ “…መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥” ሐዋ 1፥8
♥♥ “እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥
ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤” ሮሜ 8፥26
†† ሌሎች ድንቅ ድንቅ ነገሮችን የምናደርግበትን ጥበብም ይሰጠናል።
♥♥ “ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር
ይሰጠዋል፥ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥
ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥  ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥
ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤”
1ኛ ቆሮ 12፥8-10
80
♥♥ “እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ
በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥…” ይሁ 1፥20
xvi. ጾም
†† ጾም ስጋን እያደከምን ሕይወታችንን የምንገነባበት መሳሪያ ነው። በመንፈሳዊ ሕይወታችን
ውስጥ የሚታየውን መዛል በአዲስ ጥንካሬ የምናድስበት ነው። ስለዚህ መጾማችን
ከምግብና ከውኃ ብቻ ሳይሆን ከክፋትም ጭምር ሊሆን ይገባል። ነገር ግን የኃጢአትን
ሃሳብ ሳናጠፋ ጾም እስኪያልቅ ብቻ በይደር ማቆየት የለብንም። አንዳንድ ሰዎች “አሁን
ጾም ላይ ስላለሁ ነው እንጂ አንተን ፈርቼ እንዳይመስልህ” በማለት እየጾሙ እንኳን የጸብ
መንፈስን እንዳላስወገዱ አመላካች ንግግርን ይናገራሉ። ይህንን ዓይነቱን ሁኔታ ጾም ሳይሆን
የረሃብ አድማ ብንለው የተሻለ ይገልፀዋል። ለነፍስ የሚሆን በረከትም አይገኝበትም።
♥♥ “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር
ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?”
ኢሳ 58፥6
†† ጾም ጸሎት ይዘን በምንፀልይ ጊዜ ፀሎታችን ከምድራዊ መረዳት ያለፈና በጠላት ላይ
መለኮታዊ ሽብርን ያመጣል። ጾም ጸሎት መንፈሳዊ መረዳታችንን በማሳደግ ከእግዚአብሔር
ቃል ጋር ጊዜ እንድንወስድና ድምፁን መስማት እንድንችል ይረዳናል። ጾም ለችግሮቻችን
ሁሉ መፍትሔ የምናገኝበት፣ በጠላቶቻችን ላይ ሁሉ ድልን የምንቀዳጅበት፣ ዲያብሎስንና
ጭፍራዎቹን ጅራፍ ሳናነሳ የምንገርፍበት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በ2ዜና 20፥1-30
ላይ ንጉስ ኢዮሳፍጥ ጠላቶች ሊወሩት በመጡ ጊዜ በሀገሩ ይሁዳ ሁሉ ጾም አውጆ ነበር።
በመጨረሻም ሰይፍን ሳያነሳ ጠላቶቹ እርስ በእርስ እንደተገዳደሉ እናያለን።
†† በአስቴር መጽሐፍ አይሁዶች ላይ የወጣውን ፍርድ ለማስቀየር ንግስት አስቴር
እግዚአብሔር እንዲያግዛት ጾም አውጃ ነበር። በመጨረሻም አይሁዳውያን እንደዳኑና
የአይሁድ ጠላት ሀማ ራሱ ባዘጋጀው መስቀያ ላይ እንደተሰቀለ ይናገራል።
†† በማቴ 4፥1-11 ኢየሱስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከፆመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ
ሲፈትነው ፈተናውን ያለፈው የእግዚአብሔርን ቃል በመናገር ነበር።
†† ጾም ጠላትን ለመውጋት ኃይል ያለው መሳሪያ ሲሆን በጠላት ላይ ድልን እንድንቀዳጅ
ይረዳናል። ጾም ስለ ሕዝብ ሰላምን ለመለመን እንዲሁም ራስንም ልክ እንደ መቅደላዊቷ
ሴት ከጌታ እግር በታች ዝቅ አድርጎ ምህረት ለመለመን ያገለግላል። ከዚህ በተጨማሪም
በጉዟችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ሀሳብና ፍላጎት ለመረዳትም ይጠቅማል። ሰው ከዓለም
የኃጢአት ጉዞ ጋር እንዳይተባበርና እንዳይረክስም ጭምር በጾም መትጋት ይገባዋል። ነገር
ግን በጾም ጊዜ የምንሰራው መልካም ስራ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ድርጊታችን በጾም
ጊዜ ብቻ የተወሰነ ካልሆነ ብቻ ነው። ከአሰብነው የጾም ጊዜ ቀጥሎ በሚኖሩት ጊዜያትም
ውስጥ ድርጊታችንን መቀጠል ከቻልን ብቻ ነው። ጾማችንን እግዚአብሔር እንደሚያየው
ያለነቀፋ የምንጾም ከሆነ ከመብልና መጠጥ ብቻ ሳይሆን ከሚያረክሰው ክፉ መሻትና
ከዓለማዊነት ሕይወት ልንርቅ ይገባናል። ዛሬ ላይ ጾማችን መጨከን ካልቻለ ጾማችን ገና
ሌላ እውነተኛ ጾም፣ ሌላ እውነተኛ ጸሎት፣ ሌላ እውነተኛ ንስሐ ያስፈልገዋል። ዋጋቸውን
በሰው ፊት እንደተቀበሉት ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ሳይሆን ሙሉ ዋጋቸውን በሰማያት
81
ባለው አባታችን ፊት እንደተቀበሉ ቅዱሳን ተግተን ከጸሎት ጋር ጾማችንን በመንፈስ ቅዱስ
ጉልበት መጾም አለብን።
“አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎና!!”
የውጊያ ጸሎት
†† በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣንና በደሙ ጉልበት በቃሉ በተጻፈ መሰረት ቤቴ እንደተባረከ
አውጃለሁ።
♥♥ “የእግዚአብሔር መርገም በኃጥእ ቤት ነው፥ የጻድቃን ቤት ግን ይባረካል።” ምሳ 3፥33
♥♥ “ኀጥኣን ይገለበጣሉ፥ ደግሞም አይገኙም የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።” ምሳ 12፥7
♥♥ “በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ኃይል አለ የኃጥእ ሰው መዝገብ ግን ሁከት ነው።” ምሳ 15፥6
♥♥ “ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ በታመነም ቤት በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል።” ኢሳ 32፥18
†† በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣንና በደሙ ጉልበት በቃሉ በተፃፈው መሰረት ልጆቼ
መባረካቸውን አውጃለሁ።
♥♥ “በተጠማ ላይ ውኃን በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና መንፈሴን በዘርህ ላይ
በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥” ኢሳ 44፥3
♥♥ “ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።” ኢሳ 54፥13
♥♥ “የእግዚአብሔር ምሕረት ግን ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ
ነው።” መዝ 103፥17
♥♥ “ክፉ ሰው እጅ በእጅ ሳይቀጣ አይቀርም የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።” ምሳ 11፥21

82
ምዕራፍ 6
መንፈሳዊ ዘረመልን መረዳት (SPIRITUAL DNA)

6.4 መንፈሳዊ ዘረመል ምንድን ነው?


ዋነኛ ማንነታችንን ከሚገነቡትና ከሌሎች ሰዎችና ፍጥረታት ከሚለዩን ነገሮች የመጀመሪያው
ዘረመል (DNA) ነው። በዓለም ላይ ያለን ፍጥረታት በሙሉ የራሳችን ብቻ የሆነ ዘረመል አለን።
ይህ ዘረመል የማንነታችንን ዕድገት፣ ባህርይና አሠራራችን ይለያል። ዘረመል /DNA/ ከወላጆቻችን
ከተወጣጡ የበራሂ (genes) ድብልቅ የሚመጣ ሲሆን ለእኛ የተለየ ማንነት የሚሰጥ የንድፍ
መዋቅር ነው። ከእናትና አባታችን የምንወርሰው የዘረመል ክፍልፋዮች በትንሹ ቢያመሳስለንም
ፍፁም የሆነ ልዩነትም ይሰጠናል። ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር አባታችን ሰውን በመጀመሪያ
ሲፈጥር የተነፈሰበት የሕይወት እስትንፋስ መንፈሳዊ ዘረመላችንን በእርሱ አምሳል እንዲገነባ
አድርጎታል። ይህም ማንነታችን መንፈሳዊ ዕድገታችንን፣ ስራችንን፣ የግል ባህርያችንን ባጠቃላይ
ዓላማችንን የሚወስንልን ክፍል ነው። መንፈሳዊ ዘረመላችን በእግዚአብሔር አምሳል የተገነባ ነበር።
ይህ በእግዚአብሔር አምሳል የተገነባው ዘረመላችን በኃጢአት ምክንያት ተበክሏል፤ በኃጢአትና
በበደል ተሸፍኗል፤ ወደ አሉታዊ ዘረመል ተቀይሯል። ስለዚህ በኃጢአት የተበከለውን መንፈሳዊ
ዘረመላችንን ለማንጻት በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆንን የግድ ይላል። ማንም በክርስቶስ ቢሆን
አዲስ ፍጥረት ነው። (2 ቆሮ 5፥17)
♥♥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።”
ኢዮ 33፥4።

6.5 አሉታዊ/የተበከለ ዘረመል፥ ዓመፅ


6.2.1 የዓመፅ ፅንሠ ሀሳብ/የዓመፅ ምንነት
ዓመፅን ማወቅና እንዴት በሕይወታችን እንደሚሰራ መረዳት እንደ አማኝ ልናውቀው የሚገባ
አስፈላጊ እውነት ነው። በሕይወታችን ያለ የበደልን ምሽግ ማፈራረሳችን የሰይጣንን የጭቆና አገዛዝ
ከሕይወታችን ለማስወገድና ከስጋ ፈተናዎች ነፃ ለመውጣት ይረዳናል።
83
የዕብራይስጡ ቃል ዓመፅን መርድ /marad/rebel፣ ፓሻ /pasha/transgression/ እንዲሁም
arown በሚባሉት ቃላት ሲገልፀው የግሪኩ ደግሞ አፖስትሬፎ /apostrepho /turn away፣
አኑፖትአክቶስ /anupotaktos /rebellion ወይም anomia ይለዋል። ትርጉሙም ጠማማ፣
መጥፎ ተነሳሽነት፣ የተቆላለፈ፣ የማይታዘዝ፣ መተላለፍ እና የተረገመ የሚሉትን ቃላት ይወክላል።
ዓመፅ ለጠላት እስራትና ለሰይጣናዊ አገዛዝ በር ይከፍታል። ይህንን ዘረመል በሰው ልጆች ንጹህ
ማንነት ውስጥ ያስቀመጠው ጠላት ዲያብሎስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ከዓመፅ እንድንርቅ
ይመክረናል። ዓመፅ የሚያስከትለው መዘዝም እጅግ የከፋ ነው።
†† እግዚአብሔር አዳምና ሄዋንን ሲፈጥር ዓላማው ፍሬያማ እንዲሆኑና በእግዚአብሔር
አምሳል የተፈጠረውን የሰው ዘር በምድር ሁሉ ላይ እንዲያበዙ እንዲሁም ቤተሰብ
እንዲሆኑ ነው። የእስራኤልን ነገዶች ስንመለከት ለእያንዳንዱ ነገድ እግዚአብሔር ዓላማ
ነበረው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገድ ዓላማ እንደነበረው ለቤተሰባችንም በስጋ
ለምንገናኝ ዘመዳሞችም ዓላማ አለው። ነገር ግን በቤተሰብ ውስጥ በሚኖረው ጣዖት
አምላኪነትና በዓመፅ ምክንያት የእግዚአብሔር ፈቃድ ተቀይሯል። (ዘፍ 49 ያንብቡ።)
ስለ ዓመፅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ የተነገረ ሲሆን በመጀመሪያው የሳሙኤል
መጽሐፍ ላይ ከሟርተኝነት ጋር አንድ ያደርገዋል። በተጨማሪም ጥንቁልናንም የሚያጠቃልል
ቃል ነው። ሁለቱም ከፍተኛ የጠላትን ኃይል በመጠቀማቸው አደገኞች ናቸው። የሰው ልጆች
በእግዚአብሔር ፊት ከሚያቀርቡት መስዋዕትና መባ ይልቅ ልባቸውን ንጹህ ማድረጋቸው የበለጠ
የተወደደና የተመረጠ ነው።
♥♥ “ሳሙኤልም በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና
በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ
ከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን
እንደ ማምለክ ነው የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።”
1ኛ ሳሙ 15፥23
♥♥ “ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ
ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።” ሐዋ 16፥16
በዓመፅ መንፈስ የተያዘ ማንነት ብዙ ነገሮችን አያገናዝብም። ለማይጠቅምና ለማይረባ
አዕምሮም ተላልፎ ይሰጣል። በሕይወቱ ውስጥ ምንም ጥቅም በሌላቸው ነገሮች ላይ ጊዜውንና
ኑሮውን ያባክናል። ከእርሱ በታች ለሆነ ቢጮህ ለማይሰማው የተቀረጸ ምስል ያወራል። ድርጊቱንም
ለማይመለከተው ግዑዝ ነገር ጉልበቱን ያንበረክካል።
♥♥ “ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ምሕረትህ ስለ እውነትህም
ምስጋናን ስጥ።አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? አይበሉ።  አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው
በሰማይም በምድርም የፈቀደውን ሁሉ አደረገ። የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ
ሥራ ናቸው። አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤
አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤
በጕሮሯቸውም አይናገሩም። የሚሠሯቸውም የሚያምኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።”
መዝ 115፥1-8

84
የምናምናቸውና የሚያገለግሉን ነገሮች እንደ ጣዖት ሊሆኑብን ይችላሉ። በሰው ልጅ ሕይወት
ውስጥ ጣዖት የሆኑ የተቀረጹ ምስሎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ሕይወቱን የተቆጣጠሩ ማንኛውንም
ነገሮች ያጠቃልላል። አንዳንድ ሰው የያዘው ስልጣን ጣዖት ይሆንበታል። ነገሮቹን ሁሉ የሚያስበው
ከእግዚአብሔር ሀሳብ አንጻር ሳይሆን ከስልጣኑ አንጻር ነው። በመሆኑም ስልጣኑን ተገን አድርጎ
በበታቾቹ ላይ በደልን ይፈጽማል። ሌላውም ደግሞ አምላኩ የፈጠረለት ውበት ጣዖት ይሆንበታል።
ውበቱን በመጠቀም ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት በመጣር ሂደት ውስጥ አምላክን የሚያሳዝን እንደ
ዝሙትና መዳራት ያሉ ኃጢአቶችን ይፈጽማል። ሌላው ደግሞ ያለው ሀብትና ንብረት ጣዖት
ይሆንበታል። አምላኩንም ፈጽሞ እንዳያስብ አዕምሮው በገንዘብ በሚገኙ ገጸ በረከቶች ላይ ብቻ
ትኩረት ያደርጋል። የኃጢአትና የበደል መፍለቂያም ይሆናል። ስለዚህ የበለጠ ያልተገባ ገንዘብ
ለማግኘት ብሎ መዋሸት፣ ማጭበርበር እንዲሁም መግደል ውስጥ ይገባል። ይህ ድርጊት አምላክን
አስክዶ ወደራሱ መሳብ ችሏልና ጣዖት ሆኖበታል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለመዝናናት ብለው
በቀልድ የጀመሩት አልኮል ጣዖት ይሆንባቸዋል። ቀስ በቀስ በተደረገ ልምምድ ሱስ ይሆንባቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ አጉል ባህርያት ቁጣ፣ ፍርሃት፣ ማመንዘር፣ በአስማት መሳተፍ፣ እንዲሁም
ማናቸውም የሥጋ ሰራዎች ባህሪው ሊሆኑ ይችላሉ።
ክርስቲያኖች ሕይወታችን ውስጥ ጣዖት ሊሆኑ የሚችሉ ማንኛውንም ነገሮች ማስወገድ
ይኖርብናል። ጣዖትን ማምለክ ለዲያብሎስ በር ከፍቶ መንፈሳችንን እንዲበክል ፈቃድ መስጠት
ነው። የዲያብሎስ የሀሰት ማታለያዎቹ ናቸውና። ክርስቶስ እኛን መቅደሶቹ እንሆን ዘንድ የቀባን
ስለሆንን ከእነዚህ ክፉ ጣዖታት እንድንለይ የእግዚአብሔር ቃል ይመክረናል።
♥♥ “እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ ምናምን ነው እላለሁን? ወይስ ጣዖት ምናምን እንዲሆን
እላለሁን?” 1ኛ ቆሮ 10፥19-20
♥♥ “ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር
ቤተ መቅደስ ነንና” 2ኛ ቆሮ 6፥16
♥♥ “እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም
እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።” 2ኛ ቆሮ 7፥1
6.2.2 የዓመፅ ምንጭና ባህርይ
የዓመፅ ምንጩ የሉሲፈርን ሀሳብ ማስተናገድና መቀበል ነው። አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ
ተላልፎ መልካምና ክፉውን የሚያሳውቀውን የዛፍ ፍሬ በበላ ጊዜ ዓመፅ (እርግማን) ወደ ሰው
ልጆች ገባ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሰው ተፈጥሮ ተለወጠ፤ ሰው ከዲያብሎስ ጋር መስማማትና መጓዝ
ጀመረ። ዓመፅ የእርግማንና የክፉ ተነሳሽነት መገኛ ነው። ሰዎች ከመዳናቸው በፊትም ሆነ ከዳኑ
በኋላ በእግዚአብሔር መንገድ እንዳይጓዙ የሚያደርግ ነው።
♥♥ “አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ በእሳት
ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ። ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ
ፍጹም ነበርህ።” ሕዝ 28፥14-15
♥♥ “በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ
በታላቅም በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።” ኢሳ 27፥1
85
†† የዓመፅም ባህርይ ይህን ይመስላል። በውስጣችን ያለውን የድሮ ማንነት በማስታወስ ወይም
ካለን ማንነት ውስጥ ከአዲሱ ማንነታችን ባህርይ ውጪና ባልተለመደ መንገድ እንድንኖር
ያደርገናል። ይህም ዓመፅ እየሰፋና እያደገ በሄደ ቁጥር ትርምስን፣ ረብሽን፣ ብጥብጥን
እና በመጨረሻም ሞትን ያስከትላል። ሰው እግዚአብሔር ለርሱ ያለውን ዓላማ መረዳት
ሲያቆም ወይም ሳይረዳ ሲቀር ማመፅ ይጀምራል። በዚህም ምክንያት ከመንፈስ ቅዱስ
ቁጥጥር ውጪ መሆን ይጀምራል።”
♥♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ
ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
ኤፌ 6፥12
ዓመፅ የኃጢአት ስር ነው። ዳዊት በመዝሙር 51፥5 እናቱ በዓመፅ እንደፀነሰችው ይናገራል።
ኃጢአትን ስናደርግ የኃጢአቱ ምንጭ የሰው ልጅ ልብ ከአምላኩ መንገድ ውጪ መሆኑ ነው።
ልብንም በማደንደን ለእግዚአብሔር ምክር ልቡን ማደንደን ይጀምራል። በዚህም ዓመፅ የክፋት
መሰረት ይሆናል። ዓመፅ ለኃጢአት ከትውልድ ወደ ትውልድ የመተላለፍ መሰረታዊ ምክንያት
ነው። የዘር ሀረግን ይረብሻል። ከእግዚአብሔር ባልሆኑ ምርጫዎች፣ ጤናማ ባልሆኑ ባህርይዎች
ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻችን ይገባል። የክርስቶስን አዳኝነትና በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ
እንዳናስተውልና እንድንክድ ያደርጋል። ለምሳሌ ያህል በስርቆት፣ በስግብግብነት፣ በዝሙት፣
በአስማት በመሳተፍ በመሳሰሉት ስራዎች ዓመፅ ይበልጥ ያድጋል።
መጽሐፍ ቅዱስ ዓመፅን የኃጢአት ስጋ ይለዋል። ዓመፅ በሁሉም በሰው ዘር መንፈሳዊ አካል
ውስጥ አለ። የኃጢአት ስጋ መነሻው የሰው ውድቀት ሲሆን የሰውን አዕምሮ፣ ስሜት፣ ፈቃድ እና
አካላዊ ማንነቱን በክሏል። በዓመፅ ምክንያትም ጠላት ሰዎችን በእርግማንና በበሸታ ለመምታት
የሚጠቀምበት መንገድ ተከፍቶለታል።
♥♥ “ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር
እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።” ሮሜ 6፥6
♥♥ “ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን
በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።” ያዕ 1፥21
ዓመፅ አሉታዊ የሆነ መንፈሳዊ ዘረመል ሲሆን በቤተሰብ የዘር ግንድ እና ከትውልድ ወደ
ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል ነው።
♥♥ “እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥
በደለኛውንም ከቶ የማያነፃ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም
በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ። ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ
እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።  በላይ በሰማይ
ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥
የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ
ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ…” ዘፀ 20፤1-5

86
6.2.3 ዓመፅ የሚያስከትለው መዘዝ
ዓመፅ ወደ ሰዎች ሕይወት ከሚገባባቸው ምክንያቶች እንደዋና ከሚጠቀሱት መካከል የሰው
ልብ እልከኝነትና ትምክህተኝነት ሲሆኑ ልብ እንዲጠጥር ደግሞ የተለያዩ መንስዔዎች መጥቀስ
ይቻላል። ለምሳሌ ሌሎች ሰዎች የሚጎዳን ነገር በሚያደርጉብን ጊዜ በምንሰጠው ምላሽ፣ አካላዊና
ፆታዊ የቃላት ጥቃት፣ ሰው ስለ እኛ በሚያወራው ነገር፣ የእምነት ማጣት የመሳሰሉት ናቸው።
በእነዚህም ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን ግንኙነት ይቋረጣል። ዓመፅ እግዚአብሔርን
ያስቆጣዋል፤ እግዚአብሔርም ዓመፅን የሚያደርጉትን እንደጠላቶቹ ይቆጥራቸዋል፤ ጨካኝ መልአክ
ይላክበታል፤ በምድረ በዳ ለብቻ ያስቀራል።
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲወስዳቸው
የገባላቸው አንድ ቃል ነበረ። እሱም በአርባ ቀናት ውስጥ ወደ ስፍራው እንደሚደርሱ ነው። ነገር
ግን ሕዝቤ የሚላቸው እስራኤላውያን በየቦታው በእግዚአብሔር ላይ ያምፁ ነበር። ሙሴ ከአምላኩ
ጋር ሊነጋገር እንዲሁም የቃል ኪዳኑን ታቦት ሊያመጣ ወደ ተራራ በወጣ ጊዜ እስራኤላውያን ግን
ከወርቅና ከነሀስ የተቀረጸ ምስል አቁመው እየጮሁ ያመልኩ ነበር። በዚህ ድርጊታቸው አምላካቸው
እግዚአብሔር እጅግ አዝኖ ተቆጥቶም ነበር። ሙሴም ያመጣውን ታቦት ወርውሮ እስኪሰብረው
ድረስ በሚመራቸው ሕዝብ ድርጊት ተቆጥቶ ነበር (ዘፀ 32)። እስራኤላዊያን በየመንገዱ የዓመፅና
የትዕቢት ቃላት ይናገሩ ነበር። ከሰማይ መናን እያወረደ ቢመግባቸው “መና ሰለቸን፤ የግብፅ
ሽንኩርት ደግሞ ናፍቆናልና እንመለስ” ብለውትም ያውቃሉ (ዘፀ 16፣ 17)። በግዞት ለብዙ ዘመናት
ያሳለፉት የችግርና የስቃይ ጊዜ ተረስቷቸው በበረሀ ማለቅ አንፈልግምና ወደ ግብፅ እንመለስ
በማለትም አጉረምርመዋል። ታዲያ ለዚህና ላልተጠቀሱት በደሎች እግዚአብሔር ሲቀጣቸው
እንመለከታለን። ከቅጣታቸውም መካከል ብዙዎቹ ሕዝብ በበረሀ በሞት ተቀጥተው አልቀዋል።
በመሆኑም ከግብፅ ከወጡት ሕዝብ ሁለት ሰው ብቻ ወደ ተስፋይቱ ምድር ገቡ። በረከታቸውን
በመታዘዝ በአርባ ቀን መቀበል እየቻሉ በዓመፃቸው ምክንያት አርባ ዓመት ተራዝሞ ሳያዩት እንኳን
አልፈዋል (ዘኁ 14)። እግዚአብሔር ጣዖትን የሚያመልኩ ሰዎችን እንደ ጠላቶቹ ይቆጥራቸዋል።
♥♥ “የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል የበደላቸውንም መቅሠፍት
በፊታቸው አቁመዋል እኔስ ከእነርሱ ልጠየቅን? ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ሁሉም በጣዖቶቻቸው ከእኔ ተለይተዋልና የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዝ ዘንድ ከእስራኤል
ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ
በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ ብለህ ንገራቸው።” ሕዝ
14፥3-6
♥♥ “በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት ዐጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ
ስፍራ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።” 2ኛ ዜና 34፥25
በቀላሉ ጣዖትን ማምለክ ማለት ከአንዱ እግዚአብሔር ሌላ በሰዎች፣ በእቃና በመሳሰሉት
ዋስትናን መፈለግ ነው። አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር ከእግዚአብሔር አብልጠን ስንታመንና
ፍላጎታችንን ለማሟላት ራሳችንንም ጨምሮ በሰዎች መመካትና በሌላ ነገር መደገፍን ያመላክታል።
አንድን ነገር ያለማቋረጥ ማሰላሰል/obsession/ ጣዖት ሊሆንብን ስለሚችል መጠንቀቅ አለብን።

87
♥♥ “አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ
የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ
ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና” ዘፀ 20፥5
♥♥ “ተመልከተኝ ስማኝም፤ በኀዘኔ ተቅበዘበዝሁ ተናወጥሁም ከጠላት ድምፅ ከዓመፀኛም ግፍ
የተነሣ ዓመፃን በላዬ ጥለውብኛልና፥ በቁጣም ጠልተውኛልና።ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞት
ድንጋጤም ወደቀብኝ።” መዝ 55፥2-4
♥♥ “ክፉ ሰው ዓመፃን ብቻ ይሻል ስለዚህ ጨካኝ መልአክ ይላክበታል።” ምሳ 17፥11
†† ዓመፅ ሰውን ከእግዚአብሔር ያቆራርጠዋል። በምድረ በዳ ለብቻ ያስቀራል።
♥♥ “እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል ዓመፀኞች ግን
በምድረ በዳ ይኖራሉ።” መዝ 68፥6
መጽሐፍ ቅዱስ አመፀኛ ሰው ልቡና አረማመዱ ከእግዚአብሔር ጋር እንዳልሆነ ይናገራል።
በዚህም ምክንያት ፍርድ ይመጣበታል። ዓመፅ ልብን ያሸፍታል፤ ያደነድናል። ሰይጣንም ይህንን
በመጠቀም መንፈሳዊ ዓይንን ያሳውራል። የልብ ዓይን ሲታወር ደግሞ ምርጫችንን በጣም
ያበላሸዋል። የምርጫ መበላሸት ለወደፊት ሕይወት መመሳቀልና የፀፀት ኑሮ እንዲመራ ያደርጋል።
♥♥ “እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ጠማማና የምታስመርር ትውልድ፥ ልብዋን ያላቀናች ትውልድ፥
ነፍስዋ በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነች።” መዝ 78፥8
አታድርጉ የተባልነውን ማድረግ የዓመፅ መገለጫ እንደሆነ ሁሉ አድርጉ የተባልነውንም
አለማድረግ የዓመፅ አንዱ ክፍል ነው። በትንቢተ ዮናስ ላይ እንደ ምንመለከተው እግዚአብሔር
ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ሲልከው ዮናስ ግን ይህንን ጥያቄ አለመቀበሉን እንመለከታለን።
ከእግዚአብሔርም ፊት ኮብልሎ ወደ ተርሴስ በመርከብ ሲሄድ እግዚአብሔር በባህሩ ላይ ታላቅ
ማዕበልን እንዳስነሳ፣ መርከቢቱን እጅግ እንዳንገላታት፣ ዮናስም ወደ ባህሩ እስኪጣል ድረስ ከፍተኛ
ጭንቅን በመርከቢቱ ላይ እንደሆነ እናያለን። ዮናስ ባህር ውስጥ በተጣለ ጊዜ ታላቅ አሳ እንደዋጠው
ሳያኝከው ሶስት ቀን ሙሉ በሆዱ ይዞ አቆየው። በመጨረሻም በባህሩ ዳርቻ ወስዶ ተፋው።
(ዮና 1፣ 2)
የዮናስ ታሪክ እኛንም ብዙ ያስተምረናል። እግዚአብሔር አድርጉ ያለንን ባለማድረግ ስንት ጊዜ
የዓመፅ ተግባር ፈፀምን? እግዚአብሔር በተለያዩ መንገዶች እናደርግ ዘንድ የሚፈልጋቸውን ነገሮች
ሲያዘን ኖሯል። በውስጣችን ካለው መንፈስ ቅዱስ ድምፅ አንስቶ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በሰባኪያን እና
በተለያዩ አገልጋዮች በኩል ትእዛዝን አስተላልፎልናል። ነገር ግን እነዚህን ትዕዛዛት በእንቢተኛነት
ካልፈጸምን የዓመፅ አንዱን አይነት በሕይወታችን ላይ እየተገበርን መሆኑን መረዳት አለብን።
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እያመፁ መሆናቸው ሳይገባቸው በተደጋጋሚ በዚህ ክፉ ተግባር
ተሳታፊ ይሆናሉ። ይህኛው አይነት ዓመፅ ደግሞ ቀናኢ የሆኑ መስሏቸው ነገር ግን ሰዎች ወደ
እግዚአብሔር መንግስት እንዳይገቡ ደንቃራ መሆንን ያመለክታል። ክርስቲያኖች የምናምነው
አምላክ እግዚአብሔርን ነው። የሀይማኖታችን መሰረት ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረው
የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህንን ቃል “አልቀበልም” የሚል ወይም “ለእምነቴ በሚመች መንገድ
ይህንን ቃል እተረጉማለሁ” የሚል ማንም ቢኖር ዓመፅን እየተገበረ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል።

88
ሐዋርያው ጳውሎስም በአንድ ሰሞን በዚህ ሆን ተብሎ በማይተገበረው ወይም ከእውቀት ማነስ
የተነሳ በሚመጣው የዓመፅ ተግባር ላይ ተሳትፎ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ሐዋ 7፣ 8)
አመፀኛነት የሰይጣንን ሀሳብ ወደ ሕይወታችን ከምንጋብዝበት መንገድ አንዱ ነው። ነገር ግን
ንሰሀ በመግባትና ኃጢአትን በመናዘዝ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ይቻላል። ዓመፅ ከሰይጣን
የጀመረ ነው። እግዚአብሔር ምድርን ከመፍጠሩ በፊት መላእክትን ፈጥሮ ነበር። የራሳቸውም
ምርጫ ነበራቸው። ከእነሱም አንዱ በእግዚአብሔር ላይ አመፀ (ኢሳ 14፥12-14፣ ሕዝ 28፣12-19)።
ከእሱም ጋር የነበሩትን አሳምፆ ከተፈጠሩበት ዓላማ ወደ ራሱ ፈቃድ አስወጣቸው። ወደ ምድር
ከተጣለ በኋላም የሰዎችን ሕይወት የማመሳቀልና የመበጥበጥ ስራውን በትጋት እየተወጣ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎችን ወደ ራሱ ሀሳብ እያፈለሰ እንደሚጠቀምባቸው
ይታያል። ይህንንም ስራውን በአሁኑ ጊዜ በግልፅ ሁኔታ በሰፊው እያከናወነ ነው።
ሉሲፈር ትምክህተኝነቱ አሸንፎት ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቷል። ከእግዚአብሔር ዙፋን
ፊት መባረሩም ሌሎች የዓመፅ ፍሬዎችን ከማፍራት በላይ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑትን ሁሉ
ለማጥፋትና ከእጁ እንዲገቡ አድርጎታል።
♥♥ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ
ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር
ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8፥44 (በተጨማሪ ራዕ 12፥4-9 ይነበብ።)

6.6 ደህንነት/በክርሰቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን በእግዚአብሔር


አምሳል ዘረመልን መልሶ መገንባት
ከላይ ያየናቸውን የእግዚአብሔር የሆነውን ዘረመል ያቆሸሹና በኃጢአት የተበከለ ዘረመልንም
ወደ ሕይወታችን የጋበዙ ድርጊቶችን በሙሉ ከማንነታችን ውስጥ አውጥተን መጣል ይኖርብናል።
እርግጥ ነው የሰው ልጅ ከኃጢአት የነፃና ፍጹም ይሆን ዘንድ አይቻለውም። ይህንን እውነታ
መረዳት በተለያዩ ጊዜያት ሳናውቅ በምንፈጽማቸው ስህተቶች ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል።
ሁልጊዜም የቆሸሸው ማንነታችንን የምናጠራው በተሰበረ ልብና በንስሀ ዘወትር ወደ አምላካችን
በመቅረብ እንጂ ፍጹም በመሆን አይደለም። እስከ አሁን ስለ ዓመፅ ስናይ ደህንነታችንን ለማስፈፀም
እየሞከርን እንዳልሆነ መረዳቱ ተገቢ ነው። መዳናችን የተፈፀመው በክርስቶስ ነው።
6.3.1 ዓመፅን ማስወገድ
ዓመፅን ስናስወግድ በእግዚአብሔር ሀሳብ ውስጥ የታየልንን ማንነታችን በውስጣችን መስራት
ይጀምራል። ይህ የቀድሞ ማንነት ፍቅር፣ ሰላም፣ መታዘዝ፣ መከባበር፣ መተጋገዝ፣ እግዚአብሔርን
በፍጹም ልብና በፍጹም ሀሳብ መውደድ እንዲሁም ሌሎች መልካምነትን የሚያሳዩ ተግባራትን
መፈጸምን ያጠቃልላል። ሌላው ከዓመፅ ነፃ ስንሆን በመንጋ ማሰባችንና ከመንጋው ጋር ለኃጢአት
ማበራችን ይቀራል። ራሳችንንም ለክርስቶስ የተለየ አድርገን ማቅረብ እንችላለን።

89
አብዛኛውን ጊዜ በኃጢአትና በዓመፅ ምክንያት የሚመጡ ባህሪዎች ተመሳሳይ ሊመስሉ
ይችላሉ። ዓመፃችንን ለመናዘዝ መንፈስ ቅዱስ ዓመፃችንንና ኃጢአታችንን እንዲለይልን
መጸለይ ያስፈልጋል። ኃጢአታችንን ብቻ ተናዘን ዓመፃችንን ካልተናዘዝንና ካልተውን ሰይጣን
በሕይወታችን ስራውን መስራቱን ይቀጥላል።
ምሳሌ የሚሆነን ፖርኖግራፊ ነው፤ በፖርኖግራፊ በመሳተፋችን ኃጢአታችንን መናዘዝና
እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በመጸለይ ከኃጢአት ልንነፃ እንችላለን። ነገር ግን ዓመፃችን ከነ ሰንኮፉ
ስላልተነቀለ ተመልሰን ወደ ነበርንበት እንመለሳለን። ብዙ ጊዜ በደል ወይም ዓመፅ በቤተሰብ
ሊደበቅ ወይም ግልፅ ላይሆን ስለሚችል መንፈስ ቅዱስን መጠየቁ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው።
†† በደልን ለማወቅ መጀመሪያ የምንሰራውን ኃጢአት ማወቅ አለብን። ስለ ኃጢአት ያለን
እውቀትና ግንዛቤ መመርመር አለበት።
•• ምን ዓይነት ኃጢአት የመስራት ልማድ አለን?
•• በቤተሰባችን ያለው ኃጢአት ምነድነው?
•• ወደ እኛ የተሸጋገረው ምንድነው?
†† በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል መመልከት አለብን።
♥♥ “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
ትዕቢተኛ ዓይን፥ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልም
ጠብን የሚዘራ፤” ምሳ 6፥16-19
†† እነኚህ በአዳምና በሄዋን ውድቀት ምክንያት ወደ ሰው ዘር የገቡ ማንነቶች ናቸው። ስለዚህ
ከሕይወታችን እንዲወገዱ መጸለይ አለብን።
†† መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአትን እንዴት ማስወገድ እንዳለብን በግልፅ አስቀምጦልናል።
†† ኃጢአትን ስንናዘዝ ከኃጢአታችን እንነፃለን። በደልና መናዘዝና ድካማችንን ከሕይወታችን
ማስወገድ አስፈላጊ ነው።
♥♥ “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ
ነው።” 1ኛ ዮሐ 1፥9
♥♥ “በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም
ኃጢአት ይናዘዛሉ።” ዘሌ 26፥40
†† ከበደልና ከበደል ኃይል ለመላቀቅ የራሳችንንና የዘርማንዘሮቻችንን በደል እንድንናዘዝ
እግዚአብሔር ይፈልጋል።
ኃጢአት እንዳለብን አውቀን ኃጢአታችንን መናዘዝ ከእኛ አልፎ ትውልዳችንን ያድናል።
ከጠላት እስራት ለመፈታት ማንነታችንን ለሱ ማቅረብ አለብን። እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳችን
እኛን ለማውጣት ሁሌም ዝግጁ ነው። ወደ እቅፉ በመግባት የሰላም ኑሮን መምራት እንችላለን
ለሌሎችም መዳን ምክንያት እንሆናለን።

90
†† በመጽሐፍ ቅዱስ ስለበደል የተፀለዩ ፀሎቶች መልስ አግኝተዋል
•• ሙሴ ለእስራኤል ይቅር መባል የፀለየው ጸሎት፤
♥♥ “አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነውና ጌታዬ በመካከላችን
ይሂድ ጠማማነታችንንና ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ ለርስትህም ተቀበለን አለ” ዘፀ 34፥9
♥♥ ነህ 1፥1-11
•• ለእስራኤል በደል የዳንኤል ጸሎት፤
♥♥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ኃጢአታችንና ስለ አባቶቻችን በደል ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ላሉት
ሁሉ መሰደቢያ ሆነዋልና እንደ ጽድቅህ ሁሉ ቍጣህና መዓትህ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም ከቅዱስ
ተራራህ እንዲመለስ እለምንሃለሁ።” ዳን 9፥16

6.7 በደልና የሰው መንፈስ፥


በክፍል አንድ እንደተማርነው ሰው በመንፈስ፣ በነፍስና በስጋ የተዋቀረ ነው። እግዚአብሔር
ነፍስን የሰጠን በምድራዊ አካላችን ስንኖር የራሱን መንፈስ ለሌሎች እንድንገልጥ ነው። ልክ አዳምና
ሄዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተላልፈው መልካምና ክፉውን የምታሳውቀውን ፍሬ በበሉ ጊዜ
ኃጢአት ወደ ሰው ዘር ገባ ።
♥♥ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ
ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤” ሮሜ 5፥12
†† አዳም ከዲያብሎስ ጋር ለመስማማት ሲመርጥ ድካም ወደ ሰው ዘር በመግባቱ የሰው
ተፈጥሮ ሙሉ ለሙሉ ተለወጠ።
♥♥ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ
ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር
ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8፥44
♥♥ “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥
በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን
እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን
ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ
ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።” ኤፌ 2፥1-3

6.4.1 የሰውን መንፈስ መረዳት


ሰው መንፈስን፣ ደመነፍስን፣ እንዲሁም ህሊናን ያካትታል። ከደህንነት በፊት መንፈሳችን
በኃጢአት ምክንያት የሞተና የክፉ መኖሪያ ነበር። ከደህንነት በኋላ መንፈሳችን በድጋሚ ስለተወለደ
የእግዚአብሔር ማደሪያ ሆኗል።

91
አንድነት
•• በክርስቶስ አንድ የምንሆንበት
•• አዲስ ፍጥረት የሚመሰረትበት
•• የእግዚአብሔርን ድምፅ የምንሰማበት
•• ከነፍሳችን ጋር የምንገናኝበት
ደመነፍስ
†† ዌብስተር የተባለው መዝገበ ቃላት ደመነፍስን ያለምንም ምክንያት (ምንጭ) የሚገኝ
እውቀት ይለዋል። ስድስተኛው የስሜት ህዋስ በመባልም ይታወቃል።
•• በደመነፍስ የምናገኘው እውቀት በዙሪያችን ማየት የማንችለውን ነገር ግን እየተደረገ ያለን ነገር
እንድናውቅ ይረዳናል።
•• ደመነፍሳችን መንፈሳዊውን ማንነታችንን ከተፈጥሯዊ ማንነታችን ጋር የሚያገናኝ አንቴና ነው።
•• ለምሳሌ፥ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ይደውላሉ ብለን አስበን የሚደውሉበት ጊዜ አለ፤ ወይም መጥፎ
ነገር ሊከሰት እንደሆነ ሊሰማን ይችላል።
•• ደመነፍስ መንፈስ ቅዱስ የትንቢትን ስጦታና የቃሉን እውቀት የሚያስቀምጥበት ቦታ ነው።
ህሊና
†† ህሊና ማለት አንድን ሰው ትክክል ነው ትክክል አይደለም ብሎ መልካሙን ነገር እንዲያደርግ
ሰውየው ላይ ግፊት የሚፈጠር የአዕምሮ ስሜት ነው።
•• ህሊና ፈሪሀ እግዚአብሔርና ጥበብ የሚገኝበት ነው።
•• ህሊና መጽሐፍ ቅዱስ ሳናነብ ወይንም ሳይነገረን ክፉና ደጉን የምንለይበት ቦታ ነው።
†† ነገር ግን ህሊናችን በተደጋጋሚ በምናደርገው ዓመፅና ኃጢአት ሊደነዝዝ ይችላል።
♥♥ “ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ
ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው
ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።” ሮሜ 2፥14-16

6.4.2 የመንፈሳችን አዕምሮ


†† ይህ ከዚህ በፊት ያልተማርነውን መለኮታዊ እውቀት የምንቀበልበት ነው::
♥♥ “የክርስቶስ አዕምሮ ስላለን ስለ እግዚአብሔር መንፈስ የበለጠ መረዳት እንችላለን “መንፈሳዊ ሰው
ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን
አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።” 1ኛ ቆሮ 2፥15-16
♥♥ “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ
እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን
በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ
የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤” ኤፌ 1፥17-20

92
የኃይል መቀመጫ
†† በእግዚአብሔር አምሳል ስለተፈጠርን በውስጣችን ያለው መንፈሳችን በኃይል የተሞላ ነው።
በጌታ ኢየሱሰ አምነን መንፈስ ቅዱስን በተቀበልን ጊዜ ደግሞ መንፈሳችን በእግዚአብሔር
ኃይል ይሞላል። በዚህም ምክንያት ፈውሶች፣ ተአምራት እንዲሁም የተለያዩ አስደናቂ
ምልክቶች የሚታወጁበት ቦታ ነው
♥♥ “እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ
አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥…” አፌ 3፥20
♥♥ “ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ።”
ቆላ 1፥29
♥♥ “አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ
የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ
ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና” ዘፀ 20፥5
♥♥ “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው
ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።” 2ኛ ጢሞ 2፥19
ነገር ግን ውዱ አምላካችን እግዚአብሔር ልጆቹን በምንም ምክንያት ማጣት አይፈልግም።
ስለዚህም እስከመጨረሻው ድረስ አይለቀንም። ነገር ግን በኃጢአታችን ምክንያት ያዝናል።
ምርጫችንን ባይወደውም ይመክረናል፤ ይታገሰናል፤ ከዓመፃችን እስክንመለስ ይጠብቀናል። በንስሐ
ስንመለስ ደግሞ እጆቹን ዘርግቶ ይቀበለናል።
♥♥ “ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና
ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች
አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ።” ሮሜ 6፥19
♥♥ “በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፋት
ይመለሳል።” ምሳ 16፥6
♥♥ “እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።” ዮሐ 8፥32
♥♥ “እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም ከቶ
የሚያነፃ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ
ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን።” ዘኁ 14፥17-18
♥♥ “እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነፃቸዋለሁ እኔንም የበደሉኝን ያመፁብኝንም ኃጢአታቸውን
ሁሉ ይቅር እላለሁ።” ኤር 33፥8
♥♥ “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ
ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” ኢሳ 53፥5
♥♥ “እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ
እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።” ኢሳ 53፥6

93
♥♥ “ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል ነፍሱን ለሞት አሳልፎ
ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ
ዓመፀኞችም ማለደ።” ኢሳ 53፥12
†† በደልን ከሕይወታችን ስናስወግድ ከኃጢአት ነፃ መሆንና ከዚህ በፊት ተለማምደነው
በማናውቀው መልኩ የመንፈስ ፍሬዎች በሕይወታችን መገለጥ ይጀምራሉ።
♥♥ “ሆኖም፥ ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ
የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል። ትልቅም ቤት የእንጨትና
የሸክላ እቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር እቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥
እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነፃ፥ ለክብር የሚሆን
የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ እቃ ይሆናል።” 2ኛ ጢሞ 2፥19-21
†† ኤፌ 4፥1-14 በክርስቶስ የሆነ ማንኛውም ሰው አንድ አካልን ለመገንባት እንደሚያስፈልግና
እንደተሰጠው ጸጋ እንዲሰራ ይናገራል። ምንም ነገር ሲሰራ ጠንካራ መሰረት ሊኖረው
ይገባል አለበለዚያ ትንሽ ነገር ሲገፋው ይወድቃል። አንድ ቤት ሲገነባ በማይገጥም ድንጋይ
ወይም በበሰበሰ እንጨት ከተሰራ መጨረሻው መውደቅ ነው። ልክ እንደዚህ የክርስቶስን
አካል ለመገንባት ኃጢአት አይገጥምም። አመፀኛ ልብ ከጌታ አካል ጋር አይገጥምም፤
መጨረሻውም ስለማይጠቅም መጣል ይሆናል።
♥♥ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ
ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም
ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።” ዮሐ 1፥12-13
የዘላለምን የሕይወት ስጦታ ክርስቶስን በመቀበል ስናገኝና በመንፈስ እንደ አዲስ ሰው ዳግም
ስንወለድ ሰመያዊውን ዘረመል እንቀበላለን። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችን ካለው
መንፈስ ጋር አንድ ይሆናል። በዚህም ምክንያት መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ማንነታችንን ማሳደግ
ይጀምራል። እለት በእለትም እግዚአብሔርን እየመሰልን እናድጋለን።
በሳይንሳዊው ዓለም ከወላጆቻችን ጋር የሚያመሳስለንን ዘረመል ማቋረጥ/መስበር አንችልም።
ልክ እንደዚያው የጌታ ልጆች ከሆንን በኋላ ይህንን ግንኙነት ማቋረጥ አንችልም። ነገር ግን በበሽታ
ምክንያት ዘረመላችን ሊበላሽ ይችላል። እንደዚሁም በኃጢአት በሽታ ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር
ያለንን ግንኙነት ልናዛባው እንችላለን። ዓመፅም ይህንን ዘረመል ከሚበክሉት ኃጢአት አንዱ ነው።
በዓመፃችን ፊታችንን ስናዞርበት ከአባታችን ጋር ያለንን ዝምድና እናበላሸዋለን። ወላጅን የመካድ
ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ቢችሉም ያለንን ቁርኝት ግን መለወጥ አይቻልም።
♥♥ “እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም ከቶ
የሚያነፃ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ
ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን።” ዘኁ14፥18
♥♥ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን
እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ
ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። ዮሐ 10፥27-29
†† ዳንኤል ኦሲቤ (Daniel Osigbe) የተባለው ፀሐፊ “The Secret Rebellion” በሚባል
መጽሐፉ ላይ እንደዚህ ዓይነት ሀሳብን አስቀምጧል።
94
“የቤተ-ክርስቲያን ዕድገትና ቅርፅ በመንፈስ ቅዱስና በእግዚአብሔር ቃል የሚመራ ነው።
የክርስቶስ ሰውነት ማንነት ባለን በመንፈሳዊ በራሂ አካል /spiritual gene/ ይመሰረታል። ከአዳም
እስከነኃጢአታችን ብንመጣም በክርስቶስ በማመናችን በደሙ አዲስ ፍጥረት ሆነናል። በዚህም
ምክንያት አዲስ መንፈሳዊ ዘረመል ተሰጥቶናል። በአዲሱ ማንነታችንም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት
እንድናድግና የመንፈስ ፍሬዎችን እንድናፈራ ሆኗል።”
♥♥ “እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን
መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።”
2ኛ ቆሮ 3፥18
♥♥ “ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም
አንዳች የለውም፤ ዮሐ 14፥30
♥♥ “የዚያን ጊዜም አለቆችና መሳፍንቱ ስለ መንግሥቱ በዳንኤል ላይ ሰበብ ይፈልጉ ነበር ነገር ግን
የታመነ ነበረና፥ ስሕተትና በደልም አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ
አልቻሉም።” ዳን 6፥4
♥♥ “በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።” ኤፌ 4፥27
ልክ እንደ ኢየሱስ ዓላማችን መሆን ያለበት ጠላት በራሳችን ኃጢአት፣ ሌሎች በእኛ ላይ
ለሚያደርጉት በደል በምንሰጠው ምላሽ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በደል በእኛ
ላይ ምንም ቦታ እንደሌለው እርግጠኛ መሆን ነው። ጳውሎስ በጢሞቴዎስ መልዕክቱ ላይ ከበደል
እንድንለይ ይመክረናል።
♥♥ “እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነፃ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም
ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ እቃ ይሆናል።” 2ኛ ጢሞ 2፥21
ይህንን ስናደርግ የክብር አቃዎች፣ ለጌታችን ጠቃሚዎች ለመልካም ስራ የተዘጋጀን እንሆናለን።
•• ዓመፅን እንደሚገባ ያልተረዳነውና በቂ ትምህርት ያላገኘንበት ምክንያት በደል፣ መተላለፍ እና
ኃጢአት በአንድ ላይ ተጨምቀው ተመሳሳይ ትርጉም ስለሚሰጣቸው ነው።
•• ዓመፅ ምን እንደሆነና በሕይወታችን ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያመጣ በጥልቀት ስንመለከት
በደል፣ ኃጢአት እና መተላለፍ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ኅብረት እንዴት እንደሚያበላሹ
ማወቅ እንችላለን። ሶስቱም የተለያየ ትርጓሜ አላቸው።
ኢየሱስ ለበደላችን፣ ለመተላለፋችን ዋጋ ከፍሏል።
♥♥ “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ
ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” ኢሳ 53፥5
♥♥ “እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ
እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።” ኢሳ 53፥6
♥♥ “ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል ነፍሱን ለሞት አሳልፎ
ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ
ዓመፀኞችም ማለደ።” ኢሳ 53፥12

95
• ኃጢአት፥ እግዚአብሔርንና ሌሎችን የሚያሳዝን ድርጊት ነው (መተላለፍ)።
• ዓመፅ፥ ልብን በማደንደን ከእግዚአብሔር መቃረን ነው (መቃወም)።
• በደል፥ ጠማማነት የሚያስከትል ድካም፣ ከእግዚአብሔር ዞር ማለት፣
ዓመፅ ነው (ማስከፋት)።
†† ንጉስ ዳዊት በኃጢአት፣ በዓመፅ እና በመተላለፍ መካከል ያለውን ልዩነት ተናግሯል።
♥♥ “አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። ከበደሌ
ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ
ነውና። አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም
ንጹሕ ትሆን ዘንድ። እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።” መዝ 51፥1-5
♥♥ ለሙሴ እንደተናገረውም፦“እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን
ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነፃ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ
ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ።” ዘፀ 34፥7
†† እግዚአብሔር በኃጢአት፣ በዓመፅና በመተላለፍ ምክንያት ልዩነትን ካደረገ እኛም በእርሱ
መንገድ መሄድ አለብን። በዚህ መረዳት ካልኖርን ኃጢአታችንን ብቻ ተናዝዘን የበደል
ምሽግ ግን በሕይወታችን ይኖራል።

6.8 ሕይወትን እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ መምራት


በምድር ላይ እንድንኖርበት በተሰጠን ጊዜ እግዚአብሔርን አስከብሮ መኖር የክርስቲያን ዋና
ዓላማና የኑሮ ግብ መሆን አለበት። እንደተሰጠን ስልጣንና የልጅነት መብት ጨውና ብርሃን የመሆን
ኃላፊነት አለብን። ይህም እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ያስቀመጠውን ሀሳቡን አሳክተን እንድናልፍ
መውሰድ ካለብን ጥቂት እርምጃዎች መካከል ከዚህ በታች የተገለፁት ይገኛሉ።
•• ቃሉን መብላት፤
•• መዘመር፤ መጾምና መጸለይ፤
•• ወንጌልን መመስከር፤
•• አጋንንትን ማውጣት፤
•• እግዚአብሔርን ማመስገንና ማምለክ፤
•• ትኩረትን በምድራዊ ነገር ላይ ሳይሆን በመንፈሳዊ ነገር ላይ ማድረግ፤
•• ለጌታ የሚገባውን መስጠት (መባ፣ አስራት እና በኩራት ከጌታ አለመስረቅ)
•• እንደቃሉ መኖር
•• ወዘተ

96
ማጠቃለያ
በእግዚአብሔር መልክና አምሳል መፈጠራችን የእርሱን ባህርይ እንድንላበስ አድርጎናል።
የእግዚአብሔር መልክ ቁሳዊ ባልሆነው በማይሞተው የሰው ማንነት ላይ ተንፀባርቋል። አዳምና
ሄዋን የተከለከሉትን በማድረግ ኃጢአትን ወደ ገነት ካስገቡ በኋላ መንፈሳቸው ተበክሏል። ይህንንም
ኃጢአት ለማጥራትና የነበረውን ጥምረት ሊመልስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቷል። የተበላሸውን
ገጽታ በከፈለው ውድ መስዋዕትነት ወደ ሚገባው ፅድቅ መልሶታል።
ጠላት የተቀደደውን ጥቁር መጋረጃ ሊሰፋ በብዙ ይሞክራል። ከእውነተኛ ክርስቲያኖች
ጋር የበረታ ውጊያን ይፈጥራል። በሚታይና በማይታይ ቁሳዊና መንፈሳዊ በሆነ የማጥቂያ ስልት
በእግዚአብሔር ልጆች ላይ እንቅፋት ያስቀምጣል። የድሮ ማንነትን በማስታወስ፣ በሕይወታችን ላይ
ተፅዕኖን በመፍጠር፣ ልባችንን በመስበር፣ ተስፋ በማሳጣት፣ ማስተዋላችንን ለመጋረድ ይተጋል።
በዓለም ላይ ላሉ ለሌሎች ሰዎች ብርሃንና ጨው መሆን ሲገባን በድቅድቅ ጨለማ ጣዕመ-ቢስ
የሆነ ኑሮን እንድንገፋ ቀን ከሌት ይጥራል።
ክርስቶስን አምነን ሕይወቱን መኖር ስንጀምር የክፉ አሰራር በእጥፍ ጨምሮ ወደ ሕይወታችን
ያመራል። በጌታ በኢየሱስ ነፃ የወጣ ነፍስ አሮጌ ማንነቱን ቆርጦ በመጣል ጠላት ለሚያዘጋጅልን
ወጥመዶች አስቀድሞ ማየት የሚችል የተከፈቱ አይኖች እንዲኖሩን ያደርጋል። መንፈሳዊ ውጊያን
ስንዋጋ ከማን ጋር እንደምንዋጋ፣ ለምን እንደምንዋጋ እንዲሁም እንዴት እንደምንዋጋ በማወቅ
ራሳችንን ሁልጊዜ ዝግጁ አድርገን መገኘት አለብን። በዓለም ላይ ስንኖር ከስጋ ስራዎችና
ከኃጢአት በመራቅ “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ” (ማቴ 10፥16) ይላልና።
ጠላት የሚሰራባቸውን መንገዶች በመለየት የተጠራንበትን ዓላማ ግቡን እንዲመታ ግለ-ድርሻችንን
መወጣት ይጠበቅብናል።
አማኝ በምድር ላይ የሚኖረው ቆይታ በዓላማ መሆን አለበት። የክርስቲያን ሕይወት
እግዚአብሔርን በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ መግለጥ መቻል አለበት። ይህም ጸጋ ከእግዚአብሔር
የሚገኝ ብቻ ነው። መንገዱም ከሰማያዊው አባታችን ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት በማድረግ ነው።
አማኞች ችላ ብለን የምናልፋቸውን ሁኔታዎች ለማስታወስና ከብዙው በጥቂቱ መወሰድ ያለባቸውን
እርምጃዎች ለማመላከት በተዘጋጀው በዚህ ፅሁፍ እንደተገለገላችሁ ተስፋዬ የላቀ ነው። የጥበብ ሁሉ
ምንጭ የሆነው አምላካችን ውስጣዊ እይታችንን ይግለጥልን፤ ከጠላት ቀስትም ይጠብቀን። አሜን።

97

You might also like