You are on page 1of 80

ጥናት እና ሥልጠና ንዑስ

ክፍል

የአገልግሎት ስልጠና ማንዋል


የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህር ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ትምህርት ማሰልጠኛ
ማንዋል
መቅድም

ይህ የስልጠና መምሪያ ተማሪዎች የመንፈሳዊ አገልግሎት ምንነትን እንዲያውቁ ማድረግ፣ መንፈሳዊ


አገልግሎት የሚለይባቸውን ልዩ ባሕርያት ማሳወቅ እንዲሁም መንፈሳዊ አገልግሎት ያለውን ሁለንተናዊ

ጥቅም እንዲረዱ ማስቻል፣ አገልጋዮች በአገልግሎት የሚያጋጥማቸውን ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ማሳወቅ

እና ምንጮቹን እንዲለዩ ማስቻል ፈተናዎቹን ማለፊያ መንገዶች መጠቆም የአገልጋዮን አዕምሮ ከ secular

አስተሳሰብ ነፃ ማውጣትና መወሰን የሚፈልገውን የህይወት አማራጭ ውሳኔ ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን

ፍፁም ማንነት ጋር እንዲጣጣምና ትግል እንዲጀምር ማስቻል እንዲሁም የቀደሙ የአባቶቻውን ታሪክ

በመረዳት ዛሬ ላይ ፍልሚያ እንዲጀምሩ ማድረግን አላማ አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡የስልጠና መምሪያው

በአምስት ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን የመጀመሪው ክፍል ስለ አገልግሎት፣መንፈሳዊነት እንዲሁም ስለ

መንፈሳዊ አገልግሎት የያዘ ነው፡፡ሁለተኛው ክፍል ደግሞ በመንፈሳዊ አገልግሎት ስለሚያጋጥሙን ፈተናዎች

እና መፍሄትዎቻቸው የተዳሰሰበት ነው፡፡ በሦስተኛው ክፍልም ስለ ቀደምት ኢትዮጵያ ታሪክ ፣ስለ ወርቃማ

ዘመናቿ እንሁም ስላጋጠሟት ፈተናዎች ተፅፏል፡፡በአራኛው ክፍልም ዛሬ ላይ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

ፈተና የሆኑት ነገሮች ቀርበዋል፡፡አምስተኛው እና የመጨረሻው ክፍል ላይም የሰንበት ትምህርት ቤት

አመሰራረት ታሪክ እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ምን እንደሚመስል ለማየት ተሞክሯል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 1


መግቢያ

“እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባረጋችሁ ግዜ የምንጠቅም ባሪያዎች ነን ልናደርገው የሚገባንን


አድርገናል በሉ!”

ሉቃ 17፡10

“አገልግሎት” የሚለውን ቃል ሰዎች ለእግዚአብሔር ወይም ለሰው የሚሰሩት ሥራ ነው በማለት

ልንተረጉመው እንችላለን፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው አገልግሎት ደግሞ ከዚህ ትርጉም በተጨማሪ

“አምልኮት ነው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች በአገልግሎታቸው ለአምላካቸው

ክብርና ምስጋና ይሰጣሉ፣ ተገዢነታቸውን ያሳያሉ ብሎም ልጅነታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ፍጥረታት ሁሉ

አገልጋዮች ናቸው፡፡ ቅድስት ሥላሴ አንዱንም ፍጥረት ካለዓላማ እንዲሁ በዘፈቀደ አልፈጠሩምና ይልቁንስ

አበው እንዳስተማሩት ሰውና መላእክትን እንዲያመሰግኑ ሌሎቹን ፍጥረታት ደግሞ ለአንክሮ' ለተዘክሮ

'ለምስክርነት ፈጥርዋል፡፡ ስለዚህ ላያገለግል የተፈጠረ ፍጥረት የለም ፡፡ ካልእ ፍጥረታት የሰው ልጅ

አገልግሎቱን በዘነጋ ጊዜ ስለ አምላክ እየመሰከሩ ሰውን ወደተፈጠረበት ዓላማ (አገልግሎት) ለመመለስ

በመጣር አገልግለዋል ፡፡ የበለዓም አህያ (ዘፍ 22) እና የቢታኒያ ድንጋዮች (ሉቃ 19)ለዚህ ምስክሮች ናቸው፡፡

እግዚአብሔር አምላክ እስራኤላዊያንን ከዘመናት የግብፅ ስደት ወደ ምድረ ርስት የመመለሻው ወቅት በደረሰ

ጊዜ በሙሴ በኩል ፈርኦንን እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ (ዘፀ 7፤16) ብሎታል፡፡ የእስራኤላዊያን ከስደት

መመለስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ነው ፡፡ በሌላ አነጋግር ከስደት የመፈታታቸው ዓላማ አገልግሎት ነው፡፡ ከስደት

ተመልሶ እግዚአብሔርን የማያገለግል በስደት ቢኖር ይሻለዋል፡፡ “እንዲያገለግሉኝ” ብሏልና፡፡ በተመሳሳይ የሰው

ልጅ የመፈጠሩ ዓላማ ሃይማኖት እንደመሆኑና ሃይማኖት ደግሞ የማመንና የመታመን ጉዳይ በመሆኑ'

እንደዚሁም መታመን በመንፈሳዊ አገልግሎት ስለሆነ እግዚአብሔር የማያገለግል ሰወ የመፍጠሩን ዓላማ

ዘንግቷል፡፡ የመንፈሳዊ አገልግሎት መሰረቱ በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድና ፈቃዱን

ለመፈጸም የሚያተጋን አምላካዊ መመሪያ ነው፡፡ ከዘመነ አበው ጀምሮ፣ በዘመነ ኦሪትም በቅዱሳን አባቶችና

ነቢያት አድሮ የመንፈሳዊ አገልግሎት ተልዕኮንና መመሪያን የሰጠው በፍፁም አንድነትና በልዩ ሦስትነት

የሚመሰገን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከሦስቱ አካላት አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ

ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ግዕዘ ህፃናትን ሳያፋልስ በትህትና አድጎ፣

መንፈሳዊ አገልግሎት ምን መምሰል እንዳለበት በተግባር አስተምሮ ለቅዱሳን ሐዋርያት አብነት የሆነ

የአገልግሎት ተልዕኮና መመሪያ ሰጥቷቸዋል፡፡ አብነት የሆነው ተልዕኮ ‹‹እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 2


እልካችኋለሁ›› የሚለው ሲሆን መሪ መመሪያው ደግሞ ‹‹ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብ የዋሆች

ሁኑ›› የሚለው ታላቅ ቃል ነው (ማቴ 10፡16)፡፡ ጌታችን ይህንን ተልዕኮና መመሪያ የሰጠው ለጊዜው ለደቀ

መዛሙርቱ ሲሆን ኋላም በእነርሱ እግር ተተክተው በመንፈሳዊ አገልግሎት ለሚሳተፉ ሁሉ ነው፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 3


ክፍል 1

የስልጠናው አላማ

 ተማሪዎች የመንፈሳዊ አገልግሎት ምንነትን እንዲያውቁ ማድረግ፣


 መንፈሳዊ አገልግሎት የሚለይባቸውን ልዩ ባሕያት ማሳወቅ እንዲሁም
 መንፈሳዊ አገልግሎት የለውን ሁለንተናዊ ጥቅም እንዲረዱ ማስቻል፡፡

የስልጠናው ይዘት

1.መንፈሳዊ አገልግሎት

1.1 መንፈሳዊነት

1.2 አገልግሎት

1.3 መንፈሳዊ አገልግሎት

1.3.1 የመንፈሳዊ አገልግሎት ምንነት

1.3.2 የመንፈሳዊ አገልግሎት ባህርያት

1.3.3 የመንፈሳዊ አገልግሎት ረብ/ጥቅም

1.4 መንፈሳዊ አገልጋይ

1.4.1 መንፈሳዊ አገልጋይ መንፈሳዊ አገልጋይ ማን ነው?

1.4.2 መንፈሳዊ አገልጋይ ምን ያስፈልገዋል?

1.4.3 መንፈሳዊ አገልጋይ እና ዘመናዊነት

1.4.4 መንፈሳዊ አገልጋይ በማህበራዊ ህይወት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 4


1.1 መንፈሳዊነት ምንድን ነው?

መንፈሳዊነት የእግዚአብሔርን መንገድ መምረጥ ፣መከተል፣በፈቃደ እግዚአብሔር መኖር ማለት ነው፡፡

የመንፈስ ቅዱስን/መንፈሳዊ/ ስራ መስራት ወይም የእግዚአብሔር መልዕክተኛ መሆን ማለት ነው፡፡

መንፈሳዊነት ሰው የእግዚአብሔርን መንግስት እንዲወርስና በህጉና በስርዓቱ እንዲኖር ለማድርግ የሚያስችን

መንፈሳውዊ ስራ መስራት ነው፡፡

በጸጋ እግዚአብሔር፤በእግዚአብሔር ቤት መኖር ማለት ነው፡፡ መዝ 121÷1‹‹ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ

ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ›› መዝ 26÷4‹‹እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንኩት እርስዋንም እሻለሁ በሕይወቴ

ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ›› የመንፈስ ቅዱስ

ማደሪያ /የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ/ መሆን ማለት ነው፡፡1 ኛ ቆሮ 3÷16 በእግዚአብሔር ፍቅር፤በቅድስና

ሕይወት መኖር ማለት ነው፡፡ሮሜ 6 ÷6፣1 ኛ ዮሐ 3 ÷9፣1 ዮሐ 2 ÷5-6

በቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ የተቃኘ ኑሮ ፡ፈቃደ ሥጋ ወይም የሥጋ ፍላጎት ፈጽመው ቢከተሉት

ከእግዚአብሔር ሊያርቅ፣ ከሕግ ከሥርዓት ሊያናውጽ የሚችል ነው፡፡ ይህ ፈቃድ ለጊዜው ብቻ ይድላኝ፣

ይመቸኝ፣ የሚያሰኝ ሲሆን የወደፊቱንና ዘላለማዊውን የማያገናዝብ ነው፡፡ ይኸው ፈቃድ ሙሉ በሙሉ

ሰውነትን ሲቆጣጠር፣ ኅሊናን ሲይዝ ከእግዚአብሔር ያርቃል ፡፡

ፈቃዳችንን ለፈቃደ እግዚአብሔር የምናስገዛበት ሕይወት ነው፡፡ ከአርአያ እግዚአብሔር ወደ ወደ አምሳለ

እግዚአብሔር (From Image to Likeness) ማደግ ነው::

‹‹… በመንፈሳዊ ክብር ትከበር ዘንድ ሥጋዊ ክብርን ጥላ ›› ማር ይሳሐቅ

1.2 አገልግሎት

አገልግሎት ገለገለ ካለው ግስ ይነሳል፡፡ ገለገለ - ሎሌ ቀጠረ፣ አሽከር አሳደረ ሲሆን አገለገለ - ደግሞ ቀደሰ
፣አወደሰ፣ አመሰገነ፣ ረባ፣ ጠቀመ የሚል ትርጉም ይይዛል፡፡ አገልጋይ -ያገለገለ፣ቅን ሎሌ ሲሆን አገልግሎት
ማንያውም ስጋዊና መንፈሳዊ የማገልገል ስራ ነው፡፡1 ስለዚህ አገልግሎት ማለት መታዘዝ፣ መገዛት፣ መረዳት
መጥቀም... ማለት ይሆናል፡፡ ማንኛውንም ሥጋዊና መንፈሳዊ ሥራ አገልግሎት ነው፡፡ ለመንግሥት የሚሰራ
የመንግሥት አገልጋይ፣ ለግለሰብ የሚሠራ የግለሰብ አገልጋይ፣ ለእግዚአብሔርም የሚሠራ የእግዚአብሔር
አገልጋይ ነው፡፡

1
ደስታ ተክለ ወልድ፡ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበቃላት፡ 1921-1950 ዓ.ም ፡ ገፅ 260
የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 5
ስለዚህ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ እግዚአብሔር ሰዎችን ለአገልግሎት ሲመርጥ ሲጠራ ነበረ፡፡ «ማን ይላክልናል፤
ማንን እልካለሁ›› ኢሳ.6፡8 በማለት ኢሳይያስ እንደተናገረው ዛሬም እግዚአብሔር ሰዎች ያገለግሉት ዘንድ
በዚህም የፍቅሩ፣ የበረከቱ ተሳታፊዎች ይሆኑ ዘንድ ይጣራል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢሳይያስን ለአገልግሎት ከመጥራቱና የሚላክለት ሰው እንዳጣ ከመናገሩ በፊት ግሩም
የሆነውን ሰማያዊ የምሥጋና ሥርዓት ከሁሉም በላይ የርሱን ክብርና ልዕልና አሳይቶታል፡፡
«ማንን እልካለሁ፤ ማን ይላክልኛል›› ብሎ የተናገረውም ንግግር ኢሳይያስ ከዚህ የምሥጋና ምሥጢር ተሳታፊ
ይሆን ዘንድ እግዚአብሔርን በማገልገል ሱራፌልና ኪሩቤል ያገኙትን ጸጋ ያገኝ ዘንድ እንጂ ቸግሮት እንዳልሆነ
ይረዳ ዘንድ አስቀድሞ ያንን አሳየው፡፡የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማለት የዚህ ጥሪ ተሳታፊ መሆን ማለት
ነው፡፡

ኢሳይያስ « ከንፈሮቼ የረከሱብኝ በመሆኔ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ
የሠራዊት ጌታን ንጉሡን እግዚአብሔርን ስላዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ›› በማለት ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔር
ኢሳይያስን ሲጠራው ምስጢሩንም ሲያሳየው ከንፈሮቹ በለምጽ መመታታቸውን ያውቅ ነበር፡፡ኢሳ. 6፡8

ዛሬም እግዚአብሔር ለአገልግሎት የጠራን ኃጢአተኝነታችንንና በደለኛነታችንን እያወቀ እንጂ ንፁሐን


ስለሆንን አይደለም፡፡ ይልቁንም በቤቱ ያለውን ምሥጢር አይተንና ተረድተን ከኃጢአታችን እንነፃ ዘንድ
እንጂ፤ፀሐይ በሆነው እድሜያችን(በወጣትነት ጊዜያችን) ለቤ/ክናችን ልናበረክትላት የሚገባውን አገልግሎት
በትጋትና በታማኝነት እንድንፈጽምና በኋላም የመንግስቱ ወራሾች እንድንሆን እንጂ፡፡ አበው ከተሳተፉት
ሰማያዊ ፀጋ እነርሱ ከገቡበት ማኀበር ይደምረን ዘንድ እንጂ፡፡ስለዚህም እግዚአብሔር በደካሞቹ በእኛ
ሊገለገል፣ በዚያም የምናገኘውን የማይጠፋ እድፈት የሌለበት የማያልፍ ርስት ይሰጠን ዘንድ የጠራን ሁላችን
ተስፋ የተደረገልንን በረከት ለማግኘት እስከ መጨረሻው መጽናት ይገባናል፡፡

1. አገልግሎት ከእግዚአብሔርን ጋር አንድነት ለመፍጠር መጠራት ነው፡፡ አገልግሎት እግዚአብሔር ለሕዝቡ


ሊያደርስ የፈለገውን መልእክት ለማስተላፍ ዝግጁ ሆኖ መገኘት ነው፡፡ በአካል፣ በኅሊና፣ በሥነ ልቡና፣ በስሜት
መዘጋጀት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመላእክትን አገልግሎት ባስረዳበት አንቀጽ እንዲህ ብሏል፡-
“ሁሉስ መዳንን ለመውረስ ያላቸውን ለማገዝ የተላኩ አይደሉምን” ዕብ 1፤14/ ይላል፡፡

2. አገልግሎት መሠረቱን የሚያደርገው የእኛን አቅም ፣ ጉልበት፣ ዕውቀት፣ ችሎታ፣ ክህሎት አይደለም
የመንፈስ ቅዱስን ኃይልን እንጂ፤ ከእኛ የሚጠበቀው ቅንነት፣ ቅናትና ታማኝነት ለአገልግሎትም ታዛዥ
መሆንና መፋጠን ነው፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥበብን የሚሰጥ የጥበብ መንፈስ፣ ዕውቀትን የሚያደል
የዕውቀት መንፈስ፣ ለልግስናው ወደር የሌለው፣ የኃይል መንፈስ ነው፡፡ ጥበብን የሚመላብን የምንናገረውንም
የሚሠጠን እርሱ ነው፡፡ የአገልግሎት ጸጋ ብርታትም ገንዘብም እርሱ ነው፡፡

3. አገልግሎት የክርስቶስ መልእክተኛ መሆን ነው፡፡ መልእክተኛ በሁለንተናዊ ባህርዩ የላከው ማንነት
የሚያስረዳ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ እርሱ ቅዱስ ስለሆነ ቅድስናን ፣ እርሱ ፍቅር ስለሆነ ፍቅርን፣ እርሱ ትሑት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 6


ስለሆነ ትሕትናን ገንዘብ ያደረገ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ
ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን እንማልዳችኋለን”/ 2 ኛቆሮ 5፥20

4. አገልግሎት የአንድ አገልግሎት ማኅበር አባል ነኝ ብሎ መናገር ወይም ማስመሰል አይደለም በእግዚአብሔር
ቃል መኖር ነው እንጂ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል መኖር ስንጀምር ከራሳችን አልፈን የሌሎች ወገኖችን ጭንቀት
የምንካፈል እንሆናለን፡፡ ለሌሎች መኖርንም እንጀምራን፡፡ ክርስቲያን ስለ አራት ነገሮች መኖር ይጠበቅበታል
የመጀመሪያው ለራሱ ነው፡፡ ሰው ለራሱ ማሰብ ሲችል ለራሱ መኖር ይጀምራል፡፡ ለራሱ መኖር የጀመረ ሰው
ቀጥሎ ቤተሰቡን ሊመለከት ይገባዋል፤ ምክንያቱም ቤተሰብ ልዑል እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ትንሹ ቤተ
ክርስቲያን ነውና፡፡ ቀጥሎ በዙሪያው ስለሚገኙ ሰዎች ይኖራል፡፡ አራተኛው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን መኖር
ነው፡፡

5.ሌሎችን ማገልገል ከመጀመራችን በፊት ራሳችንን ማገልገላችንን አለመንዘንጋት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ
መጥምቅ ራሱን ሰላሣ ዘመን ከሰው ተለይቶ አገለገለ፡፡ ሌሎችን ያገለገለው ስድስት ወራትን ብቻ ነበር፡፡ ነገር
ግን አገልግሎቱ ምን ያህል የሰመረ እንደሆነ መመልከት እንችላለን፡፡ ተራራው ዝቅ እንዲል፣ ሸለቆውንም ሜዳ
አደረገ፡፡ ሁሉንም ለክርስቶስ እንዲዘጋጁ አደረገ፡፡ ራሳችን ቃሉ በእኛ ሳይኖር እንደምን ለሌሎች መስጠት
ይቻለናል) እኛ ሕጉንና ትእዛዛቱን ሳንጠብቅ ሌሎችን እንደምን ጠብቁ ማለት ይቻለናል) 6. አገልግሎት
ከእግዚአብሔር ጋር መሆን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ጊዜ የሚወሰንለት ሳይሆን ሁሉንም ጊዜ/የወጣትነት፣ ጎልማሳነት፣
የአረጋዊነት ዕድሜ/ ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡ ከእውነተኛው የሕይወት ምንጭ ጋር መሆን ነው፡፡ ክርስቶስ
የሰላም ፣ የደስታ፣ የበረከት አምላክ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር መሆን ደስታን ያጎናጽፋል፡፡ ሐዋርያት ጌታ ለእኛ በዚህ
መሆን መልካም ነው የማለታቸው ምስጢርም ይኼው ነው፡፡ በሕይወታችን እውነተኛ በረከት ሽልማትም
ነው፡፡ ስለዚህም ነው ጌታ ለደቀመዛሙርቱ እውነት እውነት እላችኋለሁ ስለእኔ ብሎ አባትን ወይም እናትን፣
ወይም ወንድምን፣ እኅትን፣ ልጆችን የተወ በሚመጣው ዓለም መቶ እጥፍን የማይቀበል ማንም የለም /ሉቃ
18፡29-30/ በማለት የተናገረው፡፡

7. ትንሽ መስሎ ቢታይ እንኳን እግዚአብሔር ለእርሱ ተብሎ የሚሠጥን የአገልግሎት ሰዓት ይባርካል፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር በመኖራችንና በመስራታችን መባረክ ነው፡፡

8. የምናገልግል ከሆነ አገልግሎት በሕይወታችን ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባ መሆኑን
አንዘንጋ፡፡ በልባችን ልንገድበው የሚገባ ስፍራ አይኖርም፡፡ አገልግሎትና አገልግሎት ብቻ የምንመካበት ከሆነ
ከእግዚአብሔር የምናስቀድመው ወገን አይኖርም፡፡ የምንኖረው በዓለም ደረጃ ከሆነ የምናስቀድመውም ነገር
በዚሁ መጠን የሚለይ መሆኑን አንዘንጋ፡፡ ስለዚህም ነው ዓለሙንና በዓለሙም ያሉትን አትውደዱ የመባላችን
ምስጢር፡፡ ማንም ዓለሙን ቢወድድ የአባት ፍቅር በእርሱ የለም፡፡/1 ኛ ዮሐ 2፡15/

1.3 መንፈሳዊ አገልግሎት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 7


1.3.1 የመንፈሳዊ አገልግሎት ምንነት

መንፈሳዊ አገልግሎት

መንፈሳዊ አገልግሎት ምንድን ነው የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ መመለስ በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ
የሚኖረንን ሚና ለማወቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ‹‹መንፈሳዊ (Spiritual)›› እና
‹‹አገልግሎት (Service)›› የሚሉትን ቃላቶች የያዘ ሲሆን ‹‹መንፈሳዊ›› የሚለው ገላጭ የአገልግሎቱን
ዓላማና መሪ የሚያሳይ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው የሰው ልጆች ድኅነት ነው፡፡ መሪውም መንፈስ
ቅዱስ ነው፡፡ የክህነት አገልግሎትን ጨምሮ ሰው በመንፈሳዊ ሕይወቱ ስለ ጸጋ /በጎ ዋጋ/ ብሎ የሚያደርገው
በጎ ነገር ሁሉ አገልግሎት ሊባል ይችላል፡፡በአጠቃላይ የሰው ልጆች ለመንግስተ ሰማያት እንዲበቁ የሚደረግ
ማንኛውም እንቅስቃሴ ‹‹መንፈሳዊ አገልግሎት›› ሊባል ይችላል፡፡ ይህም የሕይወትን ቃል ያላወቁ ወገኖች
እንዲያውቁና እንዲያምኑ ማድረግ፣ ያመኑት ደግሞ እንዲጸኑና መንፈሳዊ ትሩፋትን እንዲሠሩ ማድረግን
ያካትታል፡፡

ለዚህ የሚስማማ አንድ የግሪክ ቃል አለ «ዲያኮንያ (Diaknia) ይሉታል::2 በቤተክርስቲያን ሱታፌ ማድረግ፣
አንድ ቦታ መያዝ መንፈሳዊ አገልግሎት ይባላል፡፡

መንፈሳዊ አገልግሎት በሰውና በእግዚአብሔር እንዲሁም የእግዚአብሔር ከሆኑ ቅዱሳን ሰማዕታት ጋር

ቅዱሳት ነብያት ሐዋርያት ጋር እንዲሁም በቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳት በኩል በሃይማኖት የሚደረግ

ግንኙነት እና ስርአተ አምልኮ ነውመንፈሳዊ አገልግሎት የምንለው የእግዚአብሔር የሆነውና መንፈሳዊ ዓላማን

መሠረት በማድረግ የሚገለገለውን ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎትን ከሌሎች አገልግሎቶች/ ሥራዎች የሚለዩት

በርካታ ጠባያት አሉ፡፡ ትልቁና መሠረታዊው ልዩነት ዓላማው ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ የመንፈሳውያን

ሰዎችና የሰማያውያን መላእክት ረቂቅ ኅብረትና አንድነት የሚገለፅበት በማይታይ ፀጋ ወደ ክርስቶስ

በእውነትና በፍቅር የሚሳድግ (ኤፌ. 4፡15) የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ስንተረጉም ማንኛውም ሥራ ሠርቶ

ጌታውን ደስ ማሰኘት ነው ካልን መንፈሳዊ አገልግሎትም ጌታው እንደእግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔርን ደስ

የሚያሰኝ ማንኛውንም ሥራ መሥራት ነው፡፡ (ሮሜ. 12፡1)እግዚአብሔር ደስ ማሰኘት የሚቻለው ደግሞ

በዕምነት ብቻ በመሆን (ዕብ. 11፡6)መንፈሳዊ አገልግሎት የመታመን ሥራ ነው፡፡ ሃይማኖት ማለት ማመንና

መታመን ማለት እንደመሆኑ አምላክን አምነን የምንታመነው በመንፈሳዊ አገልግሎት መሆኑን መገንዘብ

ያስፈልጋል፡፡

2
Diakonia is a Christian theological term from Greek that encompasses the call to serve the poor
and oppressed.

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 8


1.3.2 የመንፈሳዊ አገልግሎት ባህርያት

 አገልግሎቱ፦ሠማያዊ ዋጋ፥ ታስቦ የሚደረግ ነው። የሚመራውምበመንፈስ፣ የሚሠራውም በመንፈስ


ከኾነ ነው
"መንፈሳዊ አገልግሎት" የሚባለው።ምድራዊ ዋጋ ታስቦ የሚደረግ ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግሎት" አይደ
ለም፤ ይኼ ሥራ ነው።
 አገልግሎቱ፦
መሥዋዕትነት ካለበት ነው፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት"አገልግሎት የሚባለው። ያ የሚያገለግለው ሠው እ
ራሱ መሥዋዕት እየኾነ የሚያገለግለውከኾነ ነው። ሌላውን እየሰዋ የሚያገለግለው ከኾነ፣ ወይም ደግሞ
ምንም ዐይነትመሥዋዕትነት የማይከፈልበት ከኾነ አገልግሎቱ፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው ማለትአይ
ቻልም
 አገልግሎቱ፦ በትህትና ከኾነ ነው። ከትዕቢት፣ ከሥልጣን፣ ከክብር፤ እነዚህን ከመሳሰሉት ነገሮች የራቀ
ከሆነና በትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ የሚሆን ከሆነ ነው፡፡ "መንፈሳዊ አገልግሎት"ምድራዊ ክብርን
የሚያመጣ
ምድራዊ ሥልጣንን የሚያመጣና በምድር ሠዎችን በጣምከፍ የሚያደርጋቸው ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግ
ሎት" መኾን አይችልም። "መንፈሳዊአገልግሎት" ኾኖ ቢጀመር እንኳን "መንፈሳዊ አገልግሎት" ኾኖ አ
ያልቅም።
 አገልግሎቱ፦መሥዋዕትነት ካለበት ነው፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት"አገልግሎት የሚባለው። ያ የሚያገለግ
ለው ሠው እራሱ መሥዋዕት እየኾነ የሚያገለግለውከኾነ ነው። ሌላውን እየሰዋ የሚያገለግለው ከኾነ፣
ወይም ደግሞ ምንም ዐይነትመሥዋዕትነት የማይከፈልበት ከኾነ አገልግሎቱ፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት"
ነው ማለትአይቻልም፡፡
 አገልግሎቱ፡- ሰው ያየኛል ተብሎ ሳይሆን እግዚአብሔር ያየኛል ብሎው ሲያገለግሉ ነው፣ ስው ያየኛል
እያሉ ማገልገል ወደ ከንቱ ውዳሴ ይወስዳል፡፡

አስረጂ፡- ‹‹… ውዳሴ ከንቱ መሻት የገሃነመ እሳት እናት ናት ፡፡ ውዳሴ ከንቱ መሻት እሳቱ ለማይጠፋው ትሉ
ለማያንቀላፈው ዓለም መጋቢዋ ናት ፡፡ ›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈውርቅ

1.3.3 የመንፈሳዊ አገልሎት ረብ/ጥቅም

ሀ/ ምድራዊ በረከትን ያሰጣል

 እግዚአብሔር ሰውን ለአገልግሎት ሲጠራው ከሰው የሚፈልገው ስጦታ በመኖሩ አይደለም፤ይልቁንም


የሚጎድለንን ሊሞላ እንጂ፡፡ እኛ ጥሪውን ሰምተን ስንከተለው እሱ የኛን ሥራ ይሠራል፡፡ በነበረን
ጥቂት ነገር ላይ በረከቱን ያበዛልናል፡፡ በአምስት ኀብስትና በሁለት ዓሣ አምስት ሺህ ሕዝብ መግቦ
አሥራ ሁለት መሶብ እንዲተርፍ ያደረገ አምላክ ነውና፡፡ ማቴ. 14፤13-21፡፡እየበሉ መራብ፤እየጠጡ
አለመርካትም የሚመጣው የእግዚአብሔርስም ከማይጠራበት ማዕድ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማመን
ስሙን መጥራት ፤እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔርነቱ ማምለክ ግን የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 9


እግዚአብሔር ለማገልግል መጠራት ደግሞ የበለጠ ዕድለኛ መሆን ነው፡፡ ‹‹…እሺ ብትሉ ለእኔም
ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ…››ኢሳ.1፤18 እግዚአብሔርን የሚያምን ሰው በድካሙ
ከሚያገኘው ብዙ ሀብት ይልቅ እግዚአብሔር ባርኮ ቀድሶ የሚሰጠው ጥቂት ሀብት ይበልጣል፡፡ የሰውን
ሕይወት ወደ መልካም መንገድ የሚያመጣ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ የሰው ዕውቀት አይደለም፡፡

 እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ሰዎች በሕይወታቸው የሚወስኑትን ጉዳይ ከሱ ፈቃድ ጋር


ስለሚያስማሙ ምድራዊ ኑሮአቸው በበረከት የተሞላ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔርን ከእግዚአብሔር
በተሰጠው ውስጣዊና አፍአዊ ሀብቱ የሚያገለግል ሰው ጥቂት ዘርቶ ብዙ ያጭዳል፣ ያበድራል እንጂ
አይበደርም፡፡ ዕድሜው በምድር ይረዝማል፡፡ በሰው ዘንድ ይከበራል፡፡

ለ/ ሰማያዊ ጸጋን ያጎናጽፋል

 እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ አገልግሎት ሲጠራ በአገልጋዩ አድሮ ሥራ ለመሥራት ነው፡፡ ስለ


እግዚአብሔር ሲሉ የጽድቅን ሥራ በመሥራት የፀኑ ሰዎች የመልካም ሥራቸው ዋጋ በምድር ብቻ
የሚቀር ሳይሆን በወዲያኛው ዓለምም ይከተላቸዋል፡፡ከሃይማኖት የተነሣ ሰዎችን ለማገልገል መልካም
ገድልን የተጋደሉ ቅዱሳን በእግዚአብሔር መንግስት እንደ ፀሐይ ያበራሉ፡፡

 ስለእግዚአብሔር ሲሉ የጽድቅን ሥራ በመሥራት የጸኑ የመልካም ሥረዎች ዋጋ በምድር ብቻ


የሚቀር ሳይሆን በወዲያኛው ዓለምም ይከተላቸዋል፡፡ ከሃይማኖት የተነሣ ሰዎችን ለማገልገል
መልካም ገድልን የተጋደሉ ቅዱሳን በእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ፡፡ ጌታችን
መድኀኒታችን ኢሱስ ክርስቶስ “ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ
እናንተ ደግሞ በዐሥራ ሁለቱ የእሰራኤል ነገድ ሰትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ
“ያለው ላገለገሉት ነው፡፡ማቴ 19፡28-29

ሐ/ ታሪካዊ ሕይወት ያስገኛል

 እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙት ቅዱሳን በዚህ ዓለም በሚታይ እና በምንረዳው መንገድ የዘላለም


መታሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ /ኢሳ. 56፤6

 በዚህ ዓለም ሲኖሩ መልካም ያደረጉ ሁሉ ስማቸውና መልካም ሥራቸው ሲወሳ ይኖራል፡፡ በሰው ፊት
የተመሰገነ ሥራው ይረሳ ይሆናል፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የሚያስመሰግን ሥራ የሠራውን ግን ሰው
ቢረሳው እንኳን እግዚአብሔር አይረሳውም፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎችም አይረሱትም፡፡ ይልቁንም
ሥራውን ምሳሌ አድርገው ሲያወሱት ይኖራሉ፡፡ «ኤልያስ አንደ እኛ ሰው ነበረ ዝናብም እንዳይዘንብ
አጥብቆ ጸለየ . . . » ተብሎ የተጻፈውም ይህን ያሳያል፡፡ ያዕ. 5፤17

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 10


መ. የእግዚአብሔር ፍቅር በሰዎች ልቡና ዘልቆ እንዲገባ

ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የታለ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ዓለሙን እንዲሁ ወድዋልና፡፡ዮሐ 3፣16
የአገልጋይ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ባሕርይ ፍቅረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔርን የምንወደው ከሆነ
ፈተናው፣ ችግሩ ፣ ተግዳሮቱ፣ ማስፈራራቱ፣ ራቡ፣ ጥሙ፣ ስደቱ መከራው አይከብደንም፡፡

ሠ. ተልዕኮ ቤተክርስቲያን ለማስፈጸም

ይህ ማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወይም ልጀ ነኝ የሚል ስው ሊፈጽመው የሚገባ ነው ፡፡

የቤተክርስቲያን ተልዕኮ

1. ያላመኑትን ማሳመን

2. ያመኑትን ማጽናት

3. አምነው ገና በአረማዊ ጠባይ ያሉትን ማነጽ

4. አምነው በምግባር የጸኑትን መጠበቅ ናቸው

ረ. ለቤተክርስቲያን ተተኪ እና ጠበቃ የሚቆሙ ምዕመንን ማፍራት

ለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዋስ ጠበቃ የሚሆኑ ምዕመናን ማፍራት አንዱ እና ዋነኛው የአገልግሎት ዓለማ
ነው ፡፡ ቤተክርስቲያን ተስፋ የሌለው ወጣት በወጣቱም ተስፋ የሌላት ቤተክርስቲያን እንዳናይ ጠንክረን
በምግባር በሃይማኖት የጽና ትውልድን ማፍራት አለብን ፡፡

1.4 መንፈሳዊ አገልገይ

1.4.1 መንፈሳዊ አገልጋይ ማን ነው

ፍጥረታት ሁሉ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ቅድስት ሥላሴ አንዱንም ፍጥረት ካለዓላማ እንዲሁ በዘፈቀደ

አልፈጠሩምና ይልቁንስ አበው እንዳስተማሩት ሰውና መላእክትን እንዲያመሰግኑ ሌሎቹን ፍጥረታት ደግሞ

ለአንክሮ፣ ለተዘክሮ፣ ለምስክርነት ፈጥረዋል፡፡ ስለዚህ ላያገለግል የተፈጠረ ፍጥረት የለም፡፡ ካልእ ፍጥረታት

የሰው ልጅ አገልግሎቱን በዘነጋ ጊዜ ስለ አምላክ

እየመሰከሩ ሰውን ወደተፈጠረበት ዓላማ (አገልግሎት) ለመመለስ በመጣር አገልግለዋል፡፡ የበለዓም አህያ (ዘፍ

22) እና የቢታንያ ድንጋዮች (ሉቃ 19) ለዚህ ምስክሮች ናቸው፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 11


ስለ ቅዱሳን መላእክት መንፈሳዊ አገልጋይነት በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ ተጽፏል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ

በዕብራውያን መልእክቱ ምዕራፍ 1 ቁጥር 14 ላይ ‘ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ

የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?’ በማለት ከርቀታቸው (ረቂቅነታቸው) የተነሳ መናፍስት ብሎ

የሚያገለግሉ ያላቸው መላእክትን ነው፡፡ ልበ አምላክ ዳዊትም ‘መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዮቹንም

የእሳት ነበልባል’ በማለት (መዝ 103፡4) ይህንኑ አጠናክሯል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስና ነባቤ መለኮት ዮሐንስም

የምስጋና አገልግሎታቸውን በራእይ ተመልክተው ጽፈውታል፡፡ (ኢሳ. 6፡1-6፣ ራዕ. 4፡5-8)

የሰው ልጅ የመፈጠሩ ዓላማ ሃይማኖት እንደመሆኑና ሃይማኖት ደግሞ የማመንና የመታመን ጉዳይ በመሆኑ፣

እንደዚሁም መታመን በመንፈሳዊ አገልግሎት ይገለጣል፡፡ መንፈሳዊ አገልጋይ ማለት እራሱን ለመንፈሳዊ ስራ

ወይም አገልግሎት የለየ፤ የእግዚአብሔርን መንገድ የመረጠና የሚከተል ማለት ነው፡፡ ማቴ 19÷27-30 «እነሆ

እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንኪያስ ምን እንናገኝ ይሆን »፣መዝ 118፤105‹‹ሕግህ ለእግሬ መብራት

ለመንገዴብርሃንነው፡፡››፣ መዝ 118፤113 ‹‹ሕግህን ወደድሁ››

መንፈሳዊ አገልጋይ በተሰጠው ጸጋ የሚያገለግልና ፈቃደኛ የሆነ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው፡፡ 1 ኛቆሮ 12

÷4-7 «የጸጋ ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው አሰራር

ልዩ ልዩ ነው…» ኢሳ 6፤8 መንፈሳዊ አገልጋይ ሕያው መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ተንቀሳቃሽ ቤተ ክርስቲያን

ነው፡፡መንፈሳዊ አገልጋይ የሚናገር ብቻ ሳይሆን ህጉና ስርዓቱ የሚፈጸበት የሚነበብ ፊደል ነው፡፡ 1 ኛ ጢሞ

4፤12 መንፈሳዊ አገልጋይ የክርስቶስ መዓዛ ነው፡፡ 2 ኛቆሮ 2 ÷15

መንፈሳዊ አገልጋይ ያለ ማቋረጥ ወደ እግዚአብሔር የሚጓዝ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በልቡ ውስጥ ስላለ

እያንዳንዱን ሰው ወደ እግዚአብሔር ለማሸጋገርና ለሌሎች ብርሃን ለመስጠት ሲል እንደ ሻማ ይቀልጣል፡፡

መንፈሳዊ አገልጋይ ሁልጊዜ ተማሪ ነው፡፡ሁል ጊዜ ያነባል፣ይዘጋጃል፣ በሚያገለግልበት ሁሉ በሚያየውና

በሚሰማው ነገር ይማራል፡፡ሉቃ 10፤42 ፣1 ኛ ጢሞ 4፤16 መንፈሳዊ አገልጋይ ሁልጊዜ ይሰራል፡፡ዮሐ 5፤17

‹‹አባቴ እስከ ዛሬ ይሰራል እኔም ደግሞ እሰራለሁ…››ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን

በማስተማር ሌሊት ደግሞ በጸሎት ይተጋ ነበር ይህ እኛን ለማስተማር ነው ማቴ 26፤36፡፡አንድም ሁል ጊዜ

በእግዚአብሔር ይሰራል(ይስተካከላል)፡፡የሚሰራውም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንጅ በእራሱ ኃይል አይደለም፡፡

መንፈሳዊ አገልጋይ የመንፈስ ፍሬዎች የተባሉትን የሚያደርጋቸው ነው፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 12


አንዳንድ ጊዜ «መንፈሳዊነት» ከ«መንፈሳይነት» ጋር እየተመሳሰለ የምንቸገር እንቸገራለን፡፡

መንፈሳዊነት መሆን እንጂ መምሰል አይደለም፣መንፈሳይ ሲል መንፈሳዊ መሳይ ለማለት ነው፡፡በዱርዬና


በሴተኛ አዳሪዎች ዘንድ ያለውን ፈሪሃ እግዚአብሔር በአገልጋዮች ዘንድ የለም ይሄ ደግሞ የሚሆነው
አንዳንዶች በአገልግሎት እየበረቱ ሲሄዱ ከመንፈሳዊነት ወደ መንፈሳይነት ስለሚለወጡ ነው፡፡ ለማስመሰል
በመንፈሳዊነት የሚኖር ሰው ደግሞ አንድ ቀን የውስጥ ማንነቱ ያሸንፍና እንደ ዴማስ ያስኮበልላቸዋል፡፡

1.4.2 መንፈሳዊ አገልጋይ ምን ያስፈልገዋል

በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሠጥ ሰው አስቀድሞ ራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ «የልብ
መዘጋጀት ከሰው ነው የምላስ መልስ ግን ከእግዚአብሔር ነው፡፡» /ምሳ.16፤1/ ምክንያቱም

በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ተስፋ የምናደርገውን ሰማያዊ ጸጋ ለማግኘት ስንጥር ፈተና ይገጥመናልና ነው፡፡
ይህንንም አልፎ ለክብር ለመብቃት መዘጋጀት የግድ ያስፈልጋል፡፡

አንድ ሰው የጀመረውን የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት እስከ መጨረሻው ለመጠበቅና ከዘራው


መንፈሳዊ ዘር በመከር ወቅት ፍሬውን ለመሰብሰብ ይችል ዘንድ የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ሀ/ ፈቃደኝነት

እግዚአብሔር የሚሰጠውን የጸጋ ስጦታ ተቀብሎ ማገልገል እንደሚገባ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል፡፡
/1 ኛቆሮ.12፤11/ለአገልግሎት የተጠራ ሰው ጥሪውን በፈቃደኝነት መቀበልና ለዚህ አገልግሎትም የጠራው
እግዚአብሔር መሆኑን መገንዘብና ማመን አለበት፡፡2 ኛ ዜና 11፣29 እግዚአብሔርንና ቤቱን ማክበር፣ ራስንም
ዝቅ ማድረግ ይገባል፡፡ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተማርነውም ይህንኑ ነው፡፡ «እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ
እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁ » ዮሐ. 13፤15

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 13


ቅዱሳንም በሕይወታቸው ያስተማሩን ይህንኑ መንገድ ስለሆነ ልጅ አባቱን መስሎ ለማገልገል የአገልግሎት
ፈቃደኝነት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰው ሲሳሳት፣ ሲያጠፋ ለመመለስ የተዘጋጀ ልብ ያለው ነውና
ለአገልግሎት ሲጠራ ፈቃደኛ መሆን ጥቅሙ ለራሱ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ቅዱስ ጳውሎስ «እንግዲህ
ምሕረት እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው እንቅረብ » /ዕብ. 4፤16/
እንዳለን ዕለት ዕለት እግዚአብሔርን በጸሎት እየጠየቅን በአገልግሎት ልንተጋ ያስፈልጋል፡፡

ለ/ የዓላማ ጽናት

አንድ ሰው ረዥም ጉዞ ሲጀምር ካሰበው ሳይደርስ የሚጥሙትን ችግሮችና ፈተናዎች ማለፍ የሚችለው
ዓላማ ሲኖረው ነው፡፡ዓላማ የሌለው ሰው ወደየት እንደሚሔድ አያውቅም፡፡ ዓላማ ያለው ሰው ግን መንገዱን
ያውቃል፡፡ መንፈሳዊ አገልጋይም ዓላማው ምን እንደሆነ በአንክሮ ተረድቶ ፣ለምን እንደሚያገለግልና በየት
በኩል እንደሚጓዝ አውቆ ያገለግላል፡፡

መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው እግዚአብሔርን ማግኘት ከእርሱም ጋር መኖር ነው፡፡ በራሱም ሆነ በሌላው
ሕይወት ውስጥ የመንፈስን ፍሬ ማፍራት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ያለ እግዚአብሔር አጋዥነት ሊሆን አይችልም፡፡
«ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም» ብሏል፡፡ ዮሐ.15፤5 ስለዚህ አገልጋይ የሆነ ሰው ለሥራው መነሻ፣
መገስገሻና መድረሻ የሚያደርገው ዓላማ ሊኖረው ይገባል፡፡

ከዓላማ የሚያርቁ ቀዳዳዎችን መድፈን ከመሳት ይጠብቃል፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት የአንድ ሰሞን የስሜት
ሩጫ ሳይሆን እስከመጨረሻው ድረስ የሚሮጡት ሩጫ ነው፡፡ «እሰከሞት ድረስ የታመንክ ሁን» እንደተባለ፡፡
ራእ.2፤10

ሐ/ አርአያነት

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሕዝቡ አርአያና ምሳሌ እንዲሆኑ ከዓለም ለይቶ የጠራቸውን ቅዱሳን
ሐዋርያትን ለሥራ ያዘጋጀው በምሳሌነትና በቃሉ ትምሕርት ነው፡፡ ኑ ተመልከቱኝ እንዳላቸው የሚሠራውን
እያዩ ጸንተው ኖሩ፡፡ዮሐ 1፣44

የእግዚአብሔርን ፍቅርና ከእርሱ ጋር የመኖርን ጣዕም ያወቀ አገልጋይ በመከራ፣ በችግር፣ በስደት እና
በብቸኝነቱ ጊዜ በሃይማኖቱ በመጽናት ለሕዝቡ ምሳሌ ይሆናል፡፡«እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደአሳቡም
ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን» ተብሎ የተጻፈውም ለዚሁ ነው፡፡ /ሮሜ 8፤28/

አንድ አገልጋይ የምንነግራችሁን እንጂ የምንሠራውን አትዩ እያለ ቢያገለግል የማንንም ሕይወት አያንጽም፡፡
ስለሆነም ራሱን ከነውርና ከነቀፋ ለይቶ ሊኖር ግድ ነው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ «ወንድሞች ሆይ
ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ
በእግዚአብሔር ርኀራኄ እለምናችኋለሁ፡- እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው» በማለት
የተናገረው ሮሜ 12፤5 አንድ ሰው ለሌሎች አርአያ ሆኖ ሲያገለግል በውጤቱ ይደሰታል፣ እግዚአብሔርንም
ያስመሰግናል፡፡ራስህ ስትገል ያየህ ሁሉ ሞቷል እንደሚባለው….

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 14


መ/ለአገልግሎቱ በቂ ጊዜ መመደብ/መስጠት

ማንኛውም ነገር የሚከናወነው በጊዜ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎትም የሚፈጸመው ለአገልግሎት


በምንመድበው በቂ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ጊዜ ከሌላው የሚለየው እግዚአብሔር የሚገኝበት፣ ከሱ ጋር ሆነን
የምናገለግልበት በመሆኑ ነው፡፡ለመንፈሳውያን ከእግዚአብሔር ጋር እንደመኖር የሚናፈቅ ሌላ ነገር
የላቸውም፡፡ በመሆኑም ለአገልግሎት የሚውል ጊዜ ያስደስታቸዋል፡፡ለመንፈሳዊ አገልግሎት ጊዜ መመደብ
ለአምላካችን ያለንን ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ነው፡፡ ለዚህም ነው አገልጋዮች በሚሰጡት ጥቂት ጊዜ
እግዚአብሔር ብዙ እንዲያከናውኑ የሚያደርገው፡፡

ጊዜን ወደ ኋላ መጠቀም አይቻልም፤ቆጥቦ በባንክ ማጠራቀምም እንደዚሁ፡፡ ስለዚህ ጊዜን የምንጠቀመው


አስቀድሞ በማቀድ ነው፡፡ጊዜያችንን በከንቱ የምናሳልፍ ከሆነ ዛሬ ባለን ጊዜ ያልሠራናቸው ሥራዎች የነገውን
ጊዜያችንን ይሻሙብናልና ይህ እንዳይሆን ጊዜን ለተገቢው እና ቅድሚያ ለሚሰጠው ተግባር መመደብ
የአገልጋዮች ሓላፊነት ነው፡፡ Time is precious, we must not be wested!! Time is life for Ethiopian
Christians /sprituals/, but money for foreigners. Time has value just like as currency. በአግባቡ
ካልተጠቀምንበት ጊዜ ጨካኝ ነው፤በክፉ ቀን ድረስልን ብለን ብንጮህ አይሰማንም፡፡ምክንያቱም ወርቅ
በገንዘብ ይገዛል፣ ጊዜን ግን መግዛት አይቻልምና የጊዜ ውድነት ከሁሉም የበለጠ ነው፡፡

ጊዜ የጌታ የመሆንንም/የህይወትንም/ የዲያቢሎስ የመሆንንም/የሞትንም/ዕጣ ፈንታችንን ይወስናል፡፡

 ለምሳሌ ፡- 1. ፈያታዊ ዘየማንን/ጥጦስን/ ለህይወት ፈያታዊ ፀጋማይን /ዳክርስን/ለሞት ተላልፎ


የመሰጠት ዕጣ ፈንታ የተወሰነው በጊዜ ነበረ፡፡

 2. ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ክዶ ሲያበቃ ወዲያው በዶሮው ጩኸት ነቅቶና ወደ ልቡ ተመልሶ ንስሐ ገብቶ
ለትልቅ ማዕረግ ሲበቃ ጊዜውን በአግባቡ ያልተጠቀመውና ማስተዋል የተሳነው የአስቆሮቱ ይሁዳ
የሕይወት ሞትን እንዲሞት ሆኖአል፡፡

 3.ቅዱስ ዳዊት የኦርዮንን ሚስት በመቀማቱ ሐጢአት መስራቱ ሲነገረው ወዲያው ንስሐ ገብቶ
ከአምላኩ ታርቆ ልበ አምላክ እስኪሰኝ ድረስ በእግዚአብሔር መወደድ ችሎአል፡፡ቆሬና ዳታን
ከወገኖቻቸው ጋር የጠፉት እናንተ ማጠን አትችሉም ፤አልተመረጣችሁም ፤ተብለው በሙሴና በአሮን
ሲገሰጹ አልሰማ በማለታቸውና ፈጥነው ንስሐ ባለመግባታቸው ነበረ፡፡

ሠ/ የሚከሰቱ ፈተናዎችን ለመቋቋም ራስን ማዘጋጀት

ለአገልግሎት የተጠራ ሰው ልዩ ልዩ ዓይነት ፈተናዎች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ መገንዘብ አለበት፡፡ፈተና


መኖሩን ብቻ ሳይሆን መምጫ መንገዱንም ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ አገልጋይ ከአገልግሎት አስቀድሞ ፈተና
መኖሩን ማወቅ አለበት ፡፡ «በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፣ ነገር ግን አይዞአችሁ፣ እኔ ዓለምን
አሸንፌዋለሁ» ተብሎ የተመከረ አገልጋይ ዮሐ. 16፤33 ፡፡ እግዚአብሔር ዘወትር ከእርሱ ጋር እንዳለ በማመን
እያገለገለ በሕይወት እየበረታ ሲሔድ ወደታላቅ አገልግሎት ይሸጋገራል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 15


ረ/ በአገልግሎት የሚገኘውን ዋጋ ተስፋ ማድረግ

የመንፈሳዊ አገልግሎት ዋጋ፡-አሁን ተከፍሎ አሁን በሁዋላ እንደሚያጡት ምድራዊ ደመወዝ አይደለም
የሚከፈለው ቃሉ በማይለወጠው አምላክ በልዑል እግዚአብሔር ነው ፡፡ ብልና ነቀዝ የሚያበላሸውና ታይቶ
የሚጠፋ ያይደለ ከሰው አሳብ በላይ የሆነ ስጦታ ነው፡፡አገልጋዮች ተስፋ ሊያደርጉት የሚገባ ደመወዝም ይህ
ነው፡፡ «ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፡፡ ይህንንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ
ያስረክባል፡፡ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም ፡፡» 2 ጢሞ. 4፤8

ሰ/ ለአገልግሎት የሚያበቃ ዕውቀት ማግኘት

የእግዚአብሔር አገልጋዮች ከሁሉ የሚያስቀድሙት መሠረታዊ የሆነውን መንፈሳዊ ዕውቀትን ነው፡፡


አባቶቻችን የዕድሜያቸውን እኩሌታ ያሳለፉት የእግዚአብሔርን ቃል በመማርና ለማወቅ ባደረጉት ጥረት
ነው፡፡ከማገልገል ዕውቀት እንደሚቀድም የሚያሻማ ባይሆንም ለአገልግሎት የሚያስፈልገው ዕውቀት እንደ
የአገልግሎት ድርሻው ይለያያል፡፡ አንድ አገልጋይ ስለተሰጠው የአገልግሎት ድርሻ በማወቅ ምን እንደሚሠራና
የሚሠራበትንም መንገድ ከመገንዘብ ባሻገር አገልግሎቱ የሚጠይቀውን መሥዋዕትነት እንዲገነዘብ ይረዳዋል፡፡

የተጀመረ አገልግሎት ዳር እንዳይደርስ ከሚያደርጉ መሠረታዊ ምክንያቶች የመጀመሪያው በቂ ዕውቀት


አለመያዝ ነው፡፡የመማር /የማወቅ/ ፍላጎት የሚመነጨውም ከአገልጋዩ አእምሮ ነው፡፡ የማወቅ ፍላጎት
የሚመጣው ከውስጥ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ለተዘጋጀ ሰው እግዚአብሔር ዕውቀቱን ይገልጽለታል፡፡
በኰኲኀ ሃይማኖት መጽሐፍ መግቢያ እንደተገለጸው «ሳይማር የሚያስተምር ከተሳዳቢ ይቆጠራል፡፡»
አበውም «ከመጠምጠም መማር ይቅደም» ይላሉ፡፡አገልግሎት ማስተማር ብቻ አይደለም፡፡ በተለያዩ የሥራ
ዘርፎች መታዘዝም ጭምር እንጂ፡፡በየአገልግሎት ክፍሎች የተዘጋጁ መመሪያዎችን፣ የሥራ ዝርዝሮችን
ለማወቅ ጥረት ማድረግ የአገልጋዮች ድርሻ ነው፡፡

ሸ/ በሚሰጡት አገልግሎት ደስተኛ መሆን

ከመንፈሳዊ አገልግሎት የምናገኘው ደስታን ነው፡፡በአገልግሎቱ እየተማረረ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሰው


ስህተት ይሠራል፡፡በአገልግሎት ደስተኛ እንድንሆን ከማያደርጉን ምክንያቶች አንዱ በራሳችን ዕውቀትና ፈቃድ
ስንጓዝ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ በእንደዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ ሆነን ከምናገለግል አስቀድመን ደስተኛ
እንዳንሆን ያደረጉንን ሰንካላ ምክንያቶች ለይተን በማውጣት የየራሳቸው መፍትሔ በመፈለግ እውነተኛውን
ደስታ የምናገኝበትን መንገድ ልንይዝ ይገባል፡፡

ቀ/ ፍቅር

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 16


የአገልግሎት መሠረት ፍቅር ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን አሳልፎ የሰጠው ለሰው ልጆች
ባለው ፍቅር ነው፡፡ የሰውን ልጅ ያገለገለውም በዚህ ፍቅሩ ነው፡፡የአገልግሎት መነሻው እግዚአብሔርንና
የእግዚአብሔር የሆኑትን መውደድ ነው፡፡ የሰውን ልጅ ሁሉ መውደድ ደግሞ እግዚአብሔርን ከመውደድ
ይመነጫል፡፡ ቤተክርስቲያንንና ሀገርን መውደድ ሌላው የፍቅር ፍሬ ነው፡፡አምላክ እስከሞት ድረስ የወደደውን
የሰውን ልጅ ወደ ድኀነት ለመጥራት የሚቻለው ሰውን ሁሉ በማፍቀር ነው፡፡ ነጭ፣ ጥቁር፣ ድሀ፣ ሀብታም፣
የተማረ፣ ያልተማረ ሳይል ሰውን ሁሉ በእኩል ያፈቀረ አምላክ ያስተማረን ይህንኑ ነው፡፡ሰውን ሁሉ እኩል
ማየት ከአንድ አገልጋይ ይጠበቃል፡፡ የዘረኝነት /ሰውን ከሰው የማበላለጥ/ መንፈስ በሕይወቱ ካለ አገልግሎቱ
ስኬታማ አይሆንም፡፡

1.4.3 መንፈሳዊ አገልጋይ እና ዘመናዊነት

ዘመናዊ የሚለው ቃል ቀጥታ ትርጉሙን ስንመለከት፣ “ዘመን” ማለት ዓመትን ወይም ጊዜን የሚያመለክት
የግእዝ ስም ሲኾን ዘመናዊ የሚለው ቅጽልም “ዘመኑ ሲሄድ፣ ሲጨምር ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ፤
በቀድሞው ዘመን ላይ ተኝቶ ኋላቀር ያልኾነ፤ ዕድገቱ ያላቋረጠ፤ ባለፈው ዘመን ከነበረበት ከፍ ብሎ
ከዘመኑ/ከጊዜው እኩል ያደገ” እንደማለት ነው፡፡ ለኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች መዘመን የጊዜ እሳቤ ሳይሆን
የማንነት ጥበቃና ያንን ማንነት ሉላዊ የማድረግ ፍላጎት በመሆኑ፣ የዘመናዊ ሳይንስ ውጤት አጠቃቀም
ከዚህ ዓላማ በሚስማማ መሆን ይገባዋል፡፡

ዘመናዊነት በሶስት መልክ ለየብቻውና ሶስቱም በአንድነት ይለካል ይተነተናል፡-

1. በአስተሳሰብ (አእምሮአዊና መንፈሳዊ)፣

2. በአኗኗር፣

3. በአምሮአዊ ጥበብ በሚገኝ ቁሳዊ ውጤት መራቀቅ፡፡

ያለፈውን ትቶ (አዲስና በዘመኑ በተለያየ ዘርፍ የበላይነት ካላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚስማማ)፣
አዲስ የመጣ (የተቀዳ) ወይንም የተፈጠረ አስተሳሰብን መቀበልና የተቀበሉትን አስተሳሰብ የሚያንፀባርቅ
አነጋገር፣ አሠራር፣ እምነት፣ ባህል ወዘተ ማሳየት የሚሉት ፅንሰ ሀሳቦች መዘመንን ሊገልፁ ይችላሉ፡፡በፍልስፍና
ክርክርና የኅብረተሰብ ትምህርት ለውጥ ምክኒያት የተወሰነው አይነት አስተሳሰብ አይሎ ብዙሃንና የተለያየ
አቅም ያላቸውን ክፍሎችን ማስከተል ሲችል የአዲሱ አስተሳሰብ ተከታዮች የዘመኑ፣ የተሻሻሉ
ይባላሉ፣ተቃራኒዎቹ ኃላቀር፣ ጎታች፣ ጎጂዎች ይሰኛሉ፡

 ሥልጣኔ ፣ እድገት፣ መሻሻል፣ ማወቅ፣ ሰው መሆን ሁሉ በሴኩላር ሂዩማኒዝም ማእቀፈ እሳቤ የሚመራ
በመሆኑ መደበኛ ትምህርት፣ ዘመናዊው ሥርዓተ መንግሥት፣ የማኅበራዊና ኢኮኒሚያዊ ሥርዓት ፣
የአስተዳደር መመሪያ ሁሉ በሴኩላር ሂዩማኒዝም መሥፍርት የሚመዘን ነው፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 17


 መንፈሳዊ አገልጋዮች ዘመኑን በመዋጀት ሊያገለግሉ ይገባል እንጂ ዘመናዊነት ተብለው በሚመጡ
እሳቤዎች ጥገኛ መሆን የለባቸውም፡፡ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም አገልግሎትን
መፋጠን እንጂ ከአገልግሎት ለመትፋ ምክንያት እንዲሆኑ መፍቀድ የለባቸውም፡፡

1.4.4 መንፈሳዊ አገልጋይ በማህበራዊ ህይወት

“……በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፣በትምህርትህም ደህንነትን


ጭምትነትን ፣ጤናና የማይነቀፍ ንግገርን ግለጥ!” ቲቶ 2፤8 መንፈሳዊነት እና ማኅበራዊ ህይወትን ለያየቶ
ለመመልከት መሞከር አስቸጋሪ ነው፡፡ ሀያማኖታዊነትን የማሳየት ምስጢር ሲኖረው ምህበራዊነት የሚለው
ደግሞ የሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ስራውን የሚገልጥበት ሰው የመሆን ግዴታውን የሚወጣበት ተግባር ነው፡፡3
ሁለቱም የሚገለጡትበአንድነት፣ በአንድ ግዜና በአንድ ቦታ ነው፡፡ይህ የሚሆነው ግን በማህበራዊ ህይወታችን
የምናከናውናቸው ተግባራት መንፈሳዊነትን የተላበሱ ከሆነ ነው፡፡

መንፈሳዊ አገልጋይ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በአገልግሎቱ ውስጥ ምሳሌና በረከት ነው፡፡አገልጋይ ለሚያገለግለው
ሕዝብ ምሳሌና በረከትይሆናል፤ ለእራሱም ከእግዚአብሔር በረከትን ያገኛል፡፡ታዲያ የአገልጋዮች መንፈሳዊነት
በማህበራዊ ህይወት እንዴት ሊገለጥ ይችላል

በቤተክርስቲያን

ቅድስት ቤተክርስቲያን የመንፈሳ ህይወት መገለጫ መሆኗ ይታወቃል፡፡በቤተክርስቲያን አካባቢ የሚከናወኑ


ማህበራዊ ህይወቶች መንፈሳነትን ካልተላበሱ ስራ ብቻ ሆነወ ይቀራሉ፡፡

በስራቦታ

የስራ ቦታ ሰዎች ስራ በመስራ የሚውሉበት ቦታ ነው፡፡እዚያ ቦታ ለምን እንደተቀመጡ እንደ ክርስቲያን ማሰብ
ካልተቻለ ያ ቦታ ደሞዝ የሚገንበት ብቻ እንጂ ሰዎችን የሚረዱበትና የሚገለግሉበት መሆኑን ይረሱታል፡፡
በተሰጠን የሥራቦታ በታማኝነት፣ በታታሪነት፣በርህራሄ፣የግለሰቦችን ችግር እንደራስ በመቁጠር ሃላፊነታችንን
የማንወጣ ከሆነ ከመንፈሳዊነት እየራቅን ነው ማለት ነው፡፡መንፈሳዊ ህይወት በመስሪ ቤት ሲገለጥ
ከአድሎኣዊነት፣ ከዝምድና፣ ከሙስና፣ ከግዴለሽነት፣ ከራወዳድነት፣ ከሌሎችም ስጋዊ አመለካቶች የፀዳ ሆኖ
ይታያል፡፡ይህ መንፈሳዊ ህይወት በመንፈሳዊም ሆነ በስጋዊ መስሪያ ቤቶች ስራ ላይ ከዋለ አገርም ምድርም
የተባረከ፣ ህዝብም የተከበረ ይሆናል፡፡

በትምህርት ቤት

ሰው መልካም ስብዕና ኖሮት እንዲቀረጽባቸው ቦታዎች አንዱና ዋነኛው ትምህርት ቤት ነው፡፡ት/ቤቶች


የሚስጨብጡን ዕውቀት ነው፤መንፈሳዊ ህይወት ደግሞ ዕውቀትን ለመልካም ነገር እንድንጠቀምበት
የማድረግ ኃይል አለው፡፡የቀደሙ አባቶች ዘመናዊውንና መንፈሳዊውን ዕውቀት በማገናኘት ለመልካም ነገር
3
አገልጋይ በመንፈሳዊና በማህበራዊ ህይወት መካከል፣ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን እና አዱኛ ማእምር፣ ማህበረ ቅዱሳን 1998 ዓ.ም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 18


በማዋላቸው ለዚህች አገርና ቤተክርስቲያን የፈጸሙት አኩሪ ተግባር ለትውልዱም እየተቀመው ይገኛል፡፡
መንፈሳዊ ህይወት የሌለው ዕውቀት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

በጎረቤት

ማንኛውም መንፈሰዊ ህይወት ከግል ህይወት ጀምሮበቤተሰብ አልፎ እስከ ጎረቤት እየተጠናከረ ሄዶ አለም
አቀፍ ደረጃ ይደርስና ፀጋን ያጎናጽፋል፡፡በመንፈሳዊ ህይወት የሚመራ አገልጋይ የጎረቤቶቹንም አኗኗረ
ይመለከታል፡፡ምናልባት የማይለምኑ ግን የሚራቡ፣የሚታመሙ ግን መታከሚያ የሌላቸው፣ የሚማሩ ግን
ወደስጋወ ደሙ ያልቀረቡ መኖራቸወን በመገንዘብና የሚችሉትን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ይህን ያላገናዘበ
መንፈሳዊ ህይወት የነዌ ህይወት መሆኑ ነው፡፡መንፈሳዊ ህይወት ከራስ ባሻገር የሌሎችን ችግር መረዳት
የሚጀምር መሆን አለበት፡፡

በቤተሰብ

ቤተሰብ የማህበረሰብ መቅጃ ምንጭ ነወ፡፡ ምንጭ ደግሞ በጥንቃቄ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡ ቤተሰብ
የሚገባውን ህይወት ሳያገኝ መንፈሳዊ ህይወትን በርቀት መጀመር ችግኙን እየረገጡ ዛፉን መንከባከብ ነው፡፡
እንክብካቤ ከችግኝ ከተጀመረ የተዋጣለት ዛፍ ማግኝ ይቻላል፡፡4

በግል ሕይወቱ

አንድ አገልጋይ ጥሩ መንፈሳዊ ሕይወትን መምራት ከቻለ የሰማያዊውን ሕይወት በምድር ላይ የተለማመደ

ብቻ ሳይሆን ራሱን በሥነ ምግባር ያነጸ ምርጥ ዜጋም ይሆናል፡፡ ስለሆነም በቤትና በትምህርት ቤትም ሆነ

በሥራ ቦታ ለቀረቡት ሁሉ በማንነቱ ክርስቶስን ያሳያል፡፡ በአነጋገሩ፣ በአመለካከቱና በአካሄዱ አምላኩን

ይሰብካል፡፡ እንዲህ አይነቱ አገልጋይ በኑሮው በማይመች አካሄድ ያልተጠመደ፣ ክፉ ባልንጀርነትን ያራቀና

የዋዘኞችን መንገድ /መንበር/ የናቀ ነው፡፡

4
አገልጋይ በመንፈሳዊና በማህበራዊ ህይወት መካከል፣ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን እና አዱኛ ማእምር፣ ማህበረ ቅዱሳን 1998 ዓ.ም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 19


ክፍል 2

የምዕራፉ አላማ

 ተማሪዎች የመንፈሳዊ አገልግሎት ምንነትን እንዲያውቁ ማድረግ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት


የሚለይባቸውን ልዩ ባሕርያት ማሳወቅ እንዲሁም መንፈሳዊ አገልግሎት ያለውን ሁለንተናዊ ጥቅም
እንዲረዱ ማስቻል፡፡
 አገልጋዮች በአገልግሎት የሚያጋጥማቸውን ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ማሳወቅ እና ምንጮቹን
እንዲለዩ ማስቻል
 ፈተናዎቹን ማለፊያ መንገዶች መጠቆም
 የአገልጋዮን አዕምሮ ከ secular አስተሳሰብ ነፃ ማውጣትና መወሰን የሚፈልገውን የህይወት አማራጭ
ውሳኔ ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ፍፁም ማንነት ጋር እንዲጣጣምና ትግል እንዲጀምር ማስቻል

የት ቆመናል? ወዴትስ መድረስ እንፈልጋን ? እንዴት?

የምዕራፉ ይዘት

2.መንፈሳዊ አገልግሎትና ተግዳሮቶቹ


የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 20
2.1 በመፈሳዊ አገልግሎት ፈተና ለምን ያጋጥመናል?

2.2 የፈተናዎቹበ ምንጮች የትኛቹ ናቸው?

2.2.1 ውስጣዊ ፈተናዎች

2.2.2 ውጫዊ ፈተናዎች

2.3 ዐበይት ፈተናዎች

2.3.1 ዓላማን መሳት

2.3.2 የግዜ አጠቃቀም

2.3.3 ከንቱ ውዳሴ

2.3.4 ትዕግስት ማጣት

2.4 ፈተናዎቹን ለማለፍ የመፍትሄ አቅጣጫዎች

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 21


2. በመንፈሳዊ አገልግሎት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈተናዎች

የአገልግሎት ሕይወት የተሳካ እንዳይሆን የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች ሰዎች
በራሳቸው ደካማነት ያመጧቸው ወይም የነበሩበት አካባቢና ማኅበረሰብ ያደረሰባቸው ተጽዕኖና ከሌሎች
ሰዎች አልያም ደግሞ ከርኩሳን መናፍስት የሚመጣ ውጤት ይሆናል፡፡

2.1 በመንፈሳዊ አገልግሎት ፈተና ለምን ያጋጥመናል

መጋደላችን ከስጋና ከደም ጋር ስላልሆነ ነው፡፡ ኤፌ 6፤12 “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥
ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን
ሠራዊት ጋር ነው እንጂ….እንዳለ ሐዋርያው! በምድር በሚኖረን አገልግሎት ሁሉ የመልካም ነገሮች ጠላት
የሆነው ዲያብሎስ አርፎ አይተኛምና በፈተና እንድንፈተን ያደርገናል፡፡

ከምናገለግላቸው ሰዎች የተሻለ መንፈሳዊ ሀይወት ስለሌለን ነው፡፡በእምነትም በእውቀትም ከምናገለግላቸው


ሰዎች ሰዎች የተሸለ መንፈሳዊ ህይወት ስለሌለን፣ ራሳችንን ለአገልግሎት የሚያበቃ መንፈሳዊ እውቀት
እንዲኖረን ስለማንሰራ እና በፆም፣ፀሎት ስግደት አና በመሳሰሉት መንፈሳዊ ተግባራት ሱታፌ ስለሌለን
በቀላሉ በፈተና እንወድቃን፡፡ትልቁ የአገልግሎት ግብ ራስን መጠበቅ ነው፡፡ ራስህን ስትገል ያየህ ሁሉ ሞቷል!
እንደሚባለው ራስ እየሞቱ ሌላውን ማገልገል አይቻልም፡፡

አገልግሎታችን በፍቅር ሳይሆን በቸልተኘነት ስለሆነ

በተጨማሪም መንፈሳዊ አገልግሎታችንን ከተግባር ይልቅ በማውራት ስለምንገልፀው እንዲሁም አገልግሎትን


በስሜታዊነት ከመጀመር ባለፈ ቁርጠኝነት ስለሌለን እንፈተናን፡፡

የኛ ዘመን የክርስትና ተጋድሎ ከሌላው ስለሚለይ…

እንዴት?

ኃጢአት የመንግስት ጥበቃ ይደረግለታል፤ ለምሳሌ ሰው ግብረሰዶማዊነትን ለማስፋፋት ፈቃድ ይጠይቃል


መንግስትም ይፈቅዳል፡፡

ዶግማ በአክራሪነት ይከሰሳል፣ንዝህላልነት በስልጣኔ ይመዘናል፤ለምሳሌ ረጅም ቀሚስ በነጠላ አድርጋ


የምንመለከታን እህት አብዛኞቻችን ውይ እሷ አክራሪ ናት እንላለን፣በአንጻሩ ደግሞወጣ ያለ አለበባስን
ከሰልጣኔ ጋር እናያይዘዋለን፡፡

ሰው በተለያዩ መዝናኛዎች የህይወትን ትርጉም distort እያደረገው ነው፤ ሁልግዜ ማስተዋል ያለብን
ለኦርቶዶክስ ከመስቀል የሚያርቀው ነገር ሁሉ ውበት የለውም!

ሮሜ 7፡14 እኔ ግን ለኃጢኣት የተሸጥሁ ስጋዊ ነኝ የማደርገውንም አላውቅምና የምወደውን ያንን ምንም


አላደርገውም፣ያንን የምጠላውን ብቻ እሰራለሁ እንጂ…….

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 22


የዘመናችን ውጤቶች የሆኑት ሉላዊነት፣ ዘመናዊነት፣ አለማዊነት የመሳሰሉትም ከክርስትና እሴት በተራቆተ
ፍልስፍና እንድንመራ እና ለፈተና ተጋላጭ እንድሆን ይሄ ነው የማይባል አስተዋፅኦ አላቸው፡፡

2.2 የፈተናዎቹ ምንጮች

በአገልግሎት ለሚነሱ ፈተናዎች ምንጮች የሚሆኑት ከሁለት ነገር የሚነሱ ናቸው፡፡እነሱም ውስጣዊእና
ውጫዊ ናቸው፡፡

2.2.1 ውስጣዊ

ከአገልጋዩ ከውስጥ ከራስ የሚመነጭ ፣የሌላ የውጭ አካል ጣልቃገብነት እና ጫና ሳይኖር የሚፈጠር ነው፡፡

 ቤ/ክንን ራሱ ይጠብቃታል/ ለውጥ አላመጣም የሚል እሳቤዎች ሐዋ 20፡28 ፣1 ኛቆሮ 3፡6

ሁሉን የሚያከናውን እግዚአብሔር ቢሆንም ሰዎች የድርሻቸውን ሊሰሩ ግድ ነው፡፡ፅድቅን የሚያጎናፅፍ ግን


እግዚአብሔር ነው፡፡ሐዋ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። 1 ኛቆሮ 3፡6 እኔ
ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ . . . ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።”

 ምቹ ሁኔታዎችን መፈለግ

በተመቻች ቦታ ማገልገል ለሁሉም ሰው ቀላ ነው፡፡ለአገልግሎት የተጠራ ሰው ሁሌ ማስተዋል ያለበት ልዩ ልዩ


ፈተናዎች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ ነው፡፡ለአገልግሎት የተጠራ ሰው ሁሌ ማስተዋል ያለበት ልዩ ልዩ
ፈተናዎች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ ነው፡፡አብዛኛውን ግዜ ለአገልግሎት ምንፈልጋቸው ምቹ ሁኔታዎች
የሥጋ ጠባያትን የሚያንጸባርቁ ሆነው ይገኛሉ፡፡በስጋዊ ስሜት ስለምንጓዝ ከግዜ ጋርየሚልፉትን ጉዳዮች
መቋቋም ያቀተናል፡፡ አገልግሎትን ከምቾት ጋር ካያያዝነው ኦርቶዶክስ መሆን አይቻልም፡፡

አገልገሎት በሚመቸውም በማይመቸውም ጠመዝማዛ መንገድ ወጥተን ወርደን አንድ ውጤት ማሳየትን ግድ
ይላል፡፡በአገልግሎት ውስጥ የሚከሰቱ ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ማገልግል በፈቃዳችን የተቀበልነው
ኃላፊነት ነው፡፡ ይህ ከሆነ የአገልግሎትን ጣዕም እናውቃለን፡፡ፈተናዎችን ለማቃለል ባደረግነው ውጣውረድ
ብዙ እንማራለን፡፡አገልግሎት የማያቋርጥ ሂደት በመሆኑ የሚገጥሙን ችግሮችና ፈተናቸውን አይነትና
መልካቸውን እየለዋወጡ ይከሰታሉ፡፡

 በተስፋ ከሚናፈቅ ፍፁም ረፍት ይልቅ ግዚያዊ ድሎትን መመኘት

የመንፈሳዊ አገልግሎት ዋጋ አሁን ተከፍሎ አሁን እንደሚያወጡት ደሞዝ አይደለም፡፡የመንፈሳዊ አገልግሎት


ዋጋ የሚከፈለው በባለቤቱ በልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡አገልጋዮች ተስፋ ሊያደርጉት የሚገባው ደሞዝም
ይኸው ነው፡፡በአገልግሎት ከመሳተፍ የበለጠና የተሸለ ዋጋ ያለው ስራ በዚህ አለም እንደሌለ ተገንዝቦ ማገልገል
የሚያስገኘው ዋጋ እጥፍ ድርብ መሆኑን መገንዘብ የአገልጋጭ ድርሻ ነው፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 23


ተግሳፅ 22 በምግባር በትሩፋት የሚገኘውን ዋጋ እናዳናጣ ተድላ ደስታን መተው ይገባል፡፡ መዝ 126፡5 በለቅሶ
የሚዘሩ በደስታ ያጭዳሉ ፣ ተስፋችን ብልና ነቀዝ የማያበላሸው ታይቶ የሚጠፋ ያይደለ ከሰው ሁሉ ሀሳብ
በላይ የሆነ ስጦታ ነውና፡፡

 ግድየለሽነት እና ቸልተኛነት

It isn't that they can't see the solution. It is that they can't see the problem.” G.K. Chesterton

ቸልተኝነት በግዛቱ ስር እየጣለን ሲመጣ ከግል ሥጋዊና መንፈሳዊ የህይወት ዘይቤ አውጥቶን ብቻ ዝም
አይልም፡፡ለቤተክርስቲያንና ለማህበረሰባችን የምንተርፍበትን እግዚአብሔር ለህዝቦቹ የሚኖረውን ፈቃድ
የምንፈጽምበትን አገልግሎታችንንም እንዳንወጣው ያደርገናል፡፡ልንሸፍነው የሚገባን የቤተክርስቲያን ቀዳዳ
እያለ ተገንዝበን ፀጋዬ ነው አይደለም ብሎ መመንታት የተረበ ሰው አይቶ እንጀራ ልስጠው ወይስ ዳቦ እያለ
የሚያማርጥ ሰውን ይመስላል፡፡

አስረጂ፡- በየ 10 አመታት ልዩነት በሚደረገው የህዝብ ቆጠራ የኦርቶዶክሱ ቁጥር ምን ያህል እያሽቆለቆለ
እንደሆነና የሌሎች ቤተእምነቶች ቁጥር ደግሞ ምን ያህል እያሻቀበ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በእርግጥ ይሄ ጠፍቶን
ሳይሆን እንዳላየ እንዳልሰማ በቸልተንነት ስለምናልፈው እንጂ….

ምሳ 1፡32 ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋል

60.0
54.0
50.6
50.0
43.5

40.0
32.9 32.8 33.9

30.0

18.6
20.0

10.2
10.0 6.6
5.5 5.6
3.3
1.0 0.9 0.7
0.0
Orothodox Protestant Catholic Muslim Others

1984 1994 2007

 የስሜት ጫና

የሰው ልጅ የሦስት ነገሮች ውጤት ነው፣

አስረጂ፡-

ስሜታዊው ክፍል በሌሎች በሁለቱ ሲሰለጥን ሰው ነገሮችን ሳያገናዝብ ያደርጋል፣ይቸኩላል ውሳኔዎችንም


ካደረጋቸው በኋላ ይፀፀታል ማስተዋል ማገናዘብ ይጎደልዋል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 24


አዕምሮኣዊው ክፍል በሌሎቹ ሲሰለጥነ ደግሞ ሰው ነገሮችን አገናዝቦ ያደርጋል ነገር ግን ለውሳኔ በጣም ሊዘገይ
እና ሀገሮች ካለፉ በኋላ ሊፀፀት ይችላል፡፡

መንፈሳዊው የበላይ ገዢ ሲሆን ግን ሳይፈጥንም ሳይዘገይም በአስተውሎት እንዲራመድ ያደርገዋል፡፡በእኛ


ህይወትስ የበላይ ገዢው የቱ ነው? በአገልግሎት እየኖርን እንኳን ነገሮችን አገናዘበን እንዳናደርግ
አስተውሎታችንን በስሜት ጫና እንነጠቃለን፡፡

Emotional
ስሜ ታ ዊ
Intellectual
አዕም ሮ ኣዊ
Spiritual
መን ፈ ሳ ዊ

 የመንፈስ ዝለት

መንፈሳዊ እንደሆንን እያሰብን እና እየተሰማን ነገር ግን ቀድሞ የነበረንን ብርታት በመተው የሚሰማን
የድካምና የመሰልቸት ስሜት ነው፡፡ተራ፣አንፃራዊ ወይም አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡

ዝለት በጥልቀት ሳይገቡ ከእግዚአብሔር ጋር ከላይ ከላይ የሚደረግ ውጫዊ ግንኙነት ነው፡፡ መንፈሳዊ
እንደሆንን እያሰብን እና እየተሰማን ነገር ግን ቀድሞ የነበረንን ብርታት በመተው የሚሰማን የድካምነሰ
የመሰልቸት ስሜት ነው፡፡ሂደቱም ከፍቅር ወደ ወረት፣ ከመንፈሳዊነት ወደ ዓለማዊነት፣ ከመንፈሳዊ ተግባር
ወደ ዓለማዊ ተግባር፣ስለእግዚአብሔር ከማሰብ ስለሰው ማሰብ፣ወዘተ የሚወስድ ነው፡፡

ራዕ 3፡15 በራድ ወይም ትኩስ ሳትሆን ለብ ያልክ ሆነሃልና ልተፋሀ ነው፡፡

የዝለት መንስኤዎች

መንፈሳዊ ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ሊዝል ወይም ሊደክም ይችላል፡፡ሰው በተፈጥሮው የሥጋ ድካም ያለበት
በመሆኑ፡ ይህ ድካም በራሱ ስህተት የመጣ ሳይሆን በአካሉ ወይም በህሊናው የተወሰነ ድካም ወይም በስራ
ብዛት ሲጠመድ የሚመጣ ነው፡፡”መንፈስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው፡፡” ማቴ 26፡41 ይህ የአካል ድካም
ለመንፈሳዊ ሥራ እንቅፋት ሆኖ መንፈሳዊ ዝለትን ያመጣል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 25


 በፈተናዎች መብዛት/ ፈተናዎች ሲገጥሙ/፡ መንፈሳዊ ሰው ሊገጥመው የሚችለውን ፈተና
አስቀድሞ ካላወቀ ፈተናዎች ሲገጥሙት መፍትሔዎችን ከመፈለግ ይልቅ ይሰናከላል፡፡
ሐሜት፣ማዳላት ፣መጎሻሸም…ወዘተ በመንፈሳውያን መካከል ሲመለከት መሰናከልና መዛል
ይጀምራል፡፡
 የመንፈሳዊነትን/የክርስትናን አላማ ሲረሳ/ አንድ መንፈሳዊ ሰው ዋና ዓላማውን እረስቶ በምድራዊ
ጥቅምና ምድራዊ በሆነ አገልግሎት ሲጠመድ መንፈሳዊ ዝለት ያጋጥመዋል፡፡ ለምሳሌ ውዳሴ ከንቱን
መሻት ፣ለአገልግሎቱ ክፍያ ሲፈልግ፣ፈልጎት የሄደውን ሲያገኝ ወዘተ ዝለት ያጋጥመዋል ፡፡
 እራሱን ከሌሎች ሰዎች ጋር ማመሳሰል /ማነፃፀር/ሲጀምር፡ አንድ መንፈሳዊ ሰው እራሱን ከሌሎች
ሰዎች ጋር ማመሳሰል /ማነፃፀር/ ሲጀምርና ደካሞችን ሲመለከት እራሱን የበቃና ጻድቅ ሰው አድርጎ
በመቁጠር እርሱ ብቻ ያለ ይመስለዋል፤እኔ ብቻ ነኝ ያለሁ ብሎ ማሰብ ይጀምራል፡፡በዚህም ዝለት
እየተሰማው ኃጢአት መሥራት ይጀምራል፡፡ይህ ቀስ በቀስ ውድቀትን ያመጣል፡፡
 የጭንቀት መብዛት፡ መንፈሳዊ ሰው ሸክሙን በእግዚአብሔር ላይ ከመጣል ይልቅ በጥቃቅን ነገር
ሁሉ የሚጨነቅ ከሆነ እምነቱ እየቀነሰ መንፈሳዊነቱ እየቀዘቀዘ ይሄዳል፡፡ማቴ 14፡31 ለምሳሌ የኑሮ
ውድነት፣ስራ አጥነት፣… ለዚህ ምሳሌ ናቸው፡፡
 የሥራ ሁኔታና የዓለሙ ጫና/ከእግዚአብሔር ጋር በማያገናኙ ስራዎች መጠመድ/፡ በአለንበት ዘመን
የሥራ ቦታና የስራው ዓይነት ፣ አብሮት የሚውለው ሰው ሁኔታና የሚጠቀመው ቴክኖሎጅ፣
ዓለሙ/ሉዑላዊነት/ እየፈጠረው ያለው ጫና ለመንፈሳዊነት ዝለት ብሎም መጥፋት ተጠቃሽ ነው፡፡
 ሰዎችን መከተል /ለሕይዎት ወሳኝ አካል ማድረግ/: ሰው ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰዎችን ዓላማ
አድርጎ የሚንቀሳቀስ አገልጋይ ውድቀቱ የከፋ ነው፡፡ ለምሳሌ ዘማሪያንን፣ሰባኪያንን …መከተል
 መንፈሳዊ አገልግሎትን እንደ ተራ ተግባር ማሰብ/በልማድ ማገልገል/: አገልግሎትን በተመስጦና
በጥልቀት ከመፈጸም ይልቅ በልማድ ፣በዘፈቀደ ና በቸልተኝነት ማድረግ በሂደት ዝለትን ይፈጥራል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ሰዎች መንፈሳዊ ሕይወትን የሚመለከቱት እንደቀላል
ጸሎት፣ጾም፣ንስሓ፣ቁርባን፣ጉባኤና አገልግሎት በመሆኑ የሚፈጽሙት ለእነርሱ ሕሌና በሚመች
መንግድ ብቻ ነው፡፡
 የምቾት/የተድላ ደስታ መብዛት/ : ሰው ምቾት ወይም ደስታ ሲበዛለት
ለጾም፣ጸሎት፣ለንስሓ፣እራስን ለማየት ወዘተ የሚሰጠው ጊዜ በጣም አናሳ በመሆኑ መንፈሳዊ ዝለት
ይሰማዋል፡፡
 ከንስሓ ሕይወት መራቅ ንስሓ በተገቢው ወይም በጠንካራ መሰረት ላይ ካልተመሰረት ዝለት
ያጋጥማል፡፡
 በአገልግሎት አለመርካትና የድርሻየን ተወጥቻለሁ ብሎ ማሰብ፤ አገልጋዮች በሚያገለግሉበት ጉዳይ
የሚጠበቀውን ለውጥ ካላገኙ ወይም በአገልግሎቴ ጥሩ ውጤት አምጥቻለሁ ብለው ካሰቡ ወይም
ምድራዊ እርካታ ሲያገኙ ለመንፈሳዊ ዝለት ይዳረጋሉ፡፡

ለመንፈሳዊ ዝለት ምልክቶች

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 26


 ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር/ ጸሎት ፣ስግደት ፣ጾም ፣ምጽዋት…/ ይቀንሳል፡፡የሚያደርገውንም በልማድ
ያደርጋል፤ ከጥልቀትና ተመስጦ ይልቅ ለፍጥነትና ለደንብ ትኩረት ይሰጣል፡፡
 እንፀልያለን ግን በተመስጦ አይደለም
 በቅዳሴው፣በመንፈሳዊ አገልግሎት እንሳተፋለን በህይወታችን ለውጥ የለም
 በፀሎታችን ስለብዛቱ እንጂ ስለጥራቱ አንጨነቅም፤ ቅ.ይስሐቅ- በእግዚኣብሔር ፊት የቆምኩት
ቃላትን ልቆጥር አይደለም እንዳለ!
 ከእግዚአብሔር ጋር በማያገናኙን ጉዳዮች ባተሌ መሆን
 አገልግሎትን ወደ ተራ ስራነት ተቀይሮብን ልንወጣ እንደሚገባ ግዳጅ ማየት
 ለምናጠፋቸው ጥፋቶች መንፈሳዊ የሚመስሉ ምክንያቶች መስጠት
 ሌሎችን ሰዎች መንቀፍ ይጀምራል፤ለአገልግሎቱ መቀነስ ምክንያት ሰወችና በኃላፊነት ላይ ያሉት
እንደኑ አድርጎ በመቁጠር እነርሱን ይኮንናል፡፡
 ጉባኤያትን መካፈል፣መዝሙር ማዳመጥ ፣ ቅ/መጻሕፍትን ማንበብ ይቀንሳል ወይም ያቆማል፡፡
የሚያነበውም ሆነ የሚሰማው በልማድ ነው፡፡
 በስውር ኃጢአት መሥራት ይጀምራል፤ለሚሠራው ኃጢአት ሁሉ ምክንያት ይሰጣል ፡፡ እንደ ሔዋን
እባብ አሳሳተኝ ያበዛል፡፡
 ለአገልግሎት ትኩረት የማይሰጥ/መንፈሳዊ ቅንዓት/ የሌለው ግድ የለሽ ይሆናል፡፡ለበዓላት የነበረው
ጉጉት ይቀዘቅዛል፣ራስን ማዋረድና የንስሓን ለመምራት የነበረው ኃይል እየሳሳ ይመጣል፡፡

አቡነ ሺኖዳ; እንዲህ አይነቱን አገልጋይ የቤ/ክ ደወል ይሉታል፡፡ሁሌ ሰው የሚቀሰቅስ ራሱ


ማይነቃ፣ሁሌ ሌላውን የሚጠራ ራሱ ማይሰማ ቅ.አምብሮስ; ኖኅ ያችን መርከብ ሲሰራ ምስማርና
እንጨት የሚያቀብሉ ሰዎቸ ቀጥሮ ነበረ፡፡እነዚህ ሰዎች ከጥፋት አልዳኑም ፡፡ቤ/ክ ሰርቶ አገልገሎ
መሞትም አለ፡፡

2.2.2 ውጫዊ

በሌላ የውጭ አካል ጣልቃገብነት እና ጫና እንዲሁም ግፊት አማካኝነት ከመንፈሳዊ አገልግሎት የሚያርቅ
ነው፡፡

 በአገልግሎት አለመናበብ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 27


በአገልግሎት የሚታዩት ተና ያለመስራት ችግሮች ወጥ ለሆነው የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚያስከትሉት
ጉድለቶች በጣም ብዙ ናቸው፡፡አንድ የአገልግሎት ክፍል ከሌላው ወይም አንድ ንኡስ ክፍል ከሌላው ክፍል ጋር
በመናበብ የሚፈጽትአገልግሎት ውጤቱ የጎላ፡፡ስለዚህ አገልጋዮች በመናበብ ማገልገል ይጠበቀባቸዋል፡፡

አስረጂ፡ ሐዋ 15፡36 “በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤
ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም
ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና።ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም
ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ
አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ”

 በአሳብ መለያየት

በአገልግሎት ውስጥ የሚሰበሰቡ ሰዎች የየራሳቸው ጠባይና አስተዳደግ ሁኔታ ያላቸው ናቸው፡፡ ሰዎች
በመንፈሳዊ ህይወት ያላቸው የብስለት ደረጃም እንደዚሁ ይለያያል፡፡በመሆኑም ስለ ችግሮችም ሆነ ስለሌሎች
ጉዳዮች ያላቸው የግንዛቤ ደረጃም ይለያያል፤ ቸግሮች ስለሚፈቱበት ስልትና ስለአፈፃፀማቸው የሚኖራቸው
ግንዛቤ ይለያያል፡፡

በመጀመሪያ በሰዎች መካከል የአሳብ ልዩነቶች መኖሩ ከሚያስከትለው ችግር ይልቅ ጠቃሚ ጎኑ ያመዝናል፡፡
የተለያዩ ስብባዎች መኖራቸው ያስፈለገው የብዙ ሰዎችን አሳብ ወደ አንድ ለማምጣት ነው፡፡ አንዳንድ ግዜ
በአገልግሎት ወቅት ተግባብተን የማናገለግል ከሆነ የሰራን እየመሰለን እናፈራሳለን እና በፍቅር እና በ መግባባት
ማገልገል ያስፈልጋል ፡፡

አስረጂ፡- በአገልግሎት በሚነሱ የሀሳብ መለየየቶች ሀሳቦቻን ይጋጩ እንጂ እኛ አንጋጭ!

 የጓደኛ ግፊት (peer influence)

ወጣቶች በቅድሚያ አብረዋቸው የሚውሉ ጓደኞቻቸውን ከመንፈሳዊና ትምህርታዊ ዓላማቸው አንጻር

ሊፈትሹና ሊመርጡ ይገባል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ በባልንጀራቸው ምክንያት የተጠቀሙ እንደተገለጹት ሁሉ

በመጥፎ ባልንጀራቸው ምክንያት ወደ ክሕደትና ኃጢአት ያመሩ ሰዎች ጉዳይም በስፋት ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡

ስለዚህ ወጣቶች ባልንጀራዬ ማነው? ብለው ራሳቸውን መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች

ጓደኞቻቸውን መምረጥ እንኳን ቢከብዳቸው መጥፎ የአቻ ግፊትን በመከላከል ለፈቃደ እግዚአብሔር እና

ለሕይወት ግባቸው ቅድሚያ በመስጠት በንቃትና በቆራጥነት ለመጥፎ ተጽዕኖዎች አይሆንም እምቢ ማለትን

ሊለማመዱ ይገባል፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ ወምስለ ብእሲ ንጹሕ ንጹሐ ትከውን

ወምስለ ጠዋይ ትጠዊ፤ ከጻድቅ ሰው ጋር ጻድቅ ትሆናለህ፤ ከቅን ሰው ጋርም ቅን ትሆናለህ፤ ከንጹሕ ሰው ጋር

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 28


ንጹሕ ትሆናለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ትሆናለህ፡፡” (መዝ፲፯፥፳፬) በማለት እንዳስረዳን ማንኛውም ሰው

ውሎውን ካላስተካከለ አወዳደቁ የከፋ ይሆናልና ጓደኞቻችንን መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ በጓደኛ ተጽዕኖ

ሕይወታቸው የተበላሸባቸው በርካታ ምሳሌዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከነዚህም መካከል

አምኖን ከኢዮናዳብ ጋር፣ ሶምሶን ከደሊላ ጋር ያደረጉት ጓደኝነት ሕይወታቸውን እንደጎዳው ተጠቃሽ ነው፡፡

1 ኛቆሮ 15፡33፣ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋዋል!

 ሉላዊነት (Globalizatin)

አንድ እሳቤ፣ አንድ ፍልስፍና፣ አንድ አሠራር፣ አንድ እምነት፣ አንድ ሂደት፣ አንድ አመለካከት፣ አንድ ሕግ
አለም አቀፋዊ እንዲሆን የሚሠራ ነው፡፡

አላማው ሰውን ወደአለማዊነት መውሰድ ነው፡፡በዚህም ሰው ኃጢኣትን እንዲለማመድ እና ራስ ወዳድ


እንዲሆን ማድረግ Justifying and normalizing sin… አንድ ሊቅ” Secularisim, I submit, above all is
negation with worship.”

“Today I resigned from the staff of IMF after over 12 years … hawking your medicine and your
bag of tricks to governments and to peoples in Latin America and the Caribbean and Africa. To
me resignation is a priceless liberation, for with it I have taken the first big step to that place
where I may hope to wash my hands of what in my mind’s eye is the blood of millions of poor
and starving peoples. … The blood is so much, you know, it runs in rivers. It dries up, too; it
cakes all over me; sometimes I feel that there is not enough soap in the whole world to cleanse
me from the things that I did do in your name.”5

ሉላዊነት ለቤተክርስቲያን ሥጋት የመሆኑን ያህል መልካም አጋጣሚዎችንም የፈጠረ በጎ ጎን አለው፡፡ ለስብከተ

ወንጌል እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ያለውን ሰው እንደ ጥንቱ በእግር ሐዋርያነት ብቻ ሳይኾን ፈጣንና ቀላል

በሆኑት የሥነ ዝማኔ/ቴክኖሎጂ/ ውጤቶች በመጠቀም ወንጌልን ማስፋፋት ተችሏል፡፡ ሆኖም በምዕራቡ ዓለም

የሚሠራው ሁሉ ዘመናዊነት የሚመስለው ወጣት ሁሉ በሥነ ዝማኔው ውጤቶች የአውሮፓውያኑና

የአሜሪካውያኑ ድርጊት እና ሁኔታ በደቂቃ ልዩነት እየተነገረው እንደነሱ ለመሆን ሲሻ ከማንነቱ ተራርቆ

በአስከፊ ጥገኝነትና የማንነት እጦት እንዲሁም የመንፈስ ድርቀት ውስጥ ይገኛል፡፡የመገናኛ ብዙኃኑም በዚሁ

5
D. L. Budhoo, Enough is Enough: Dear Mr Camdessus … Open Letter of Resignation to the
Managing Director of the IMF (New York, New Horizons Press, 1990)

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 29


ተጠቅተው ዜናው ሁሉ እገሌ ይህን ለበሰ፣ እገሌ ይህን ሆነ፣እገሌ እንዲህ አለ በማለት የነጮችን ሥራ

በማራገብ ኋላቀርነት ተራቁተዋል፡፡

 ሴኩላር ሂዩማኒዝም ዓለማዊነት

ሴኩላሪዝም የመንግሥትና የሃይማኖትን መለያየት የሚሰብክ ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡ እሳቤው በብዙ መልኩ

ቤተክርስቲያንን ጎድቷታል፡፡ ይዞታዎችዋና ቅዱስ ትውፊቷ ላይም ከባድ ተጽእኖን አሳርፏል፡፡ ጽንሰ ሐሳቡ

ዘመን አመጣሽና ዘመናዊ ነው በማለት ብዙ ምእመን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ክርስትናንበትምህርት ቤትና

በመሥሪያ ቤት የሌላውን መብት ሳይረግጥም ቢሆን እንዳይተገብር ፈተና ሆኗል፡፡ በጽናት የሚተገብሩትም

በሹፈትና በማላገጥ እንዲሸማቀቁ አስተዋጽኦን በማበርከቱ ከዕለት ዕለት የጠንካራው አማኝ ቁጥር ቀንሷል፡፡

እንደውም ሃይማኖታዊነትን መመስከር ሞኝነትና ኋላቀር እንዲመስልና ዘመናዊነት ከሃይማኖት እጅግ የራቀ

ሆኖ እንዲታሰብ አድርጓል፡፡6

እዚህ ጋር ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ሴኩላሪዝም በአሁኑ ጊዜ የመንግሥትና የሃይማኖትን መለያየት

የሚሰብክ ጽንሰ ሐሳብ ብቻ አለመሆኑን ነው። በሌላ አገላለፅ የሃይማኖት ፀር ነው። ለዚህም 'ሴኩላሪስት'

የሚለውን ቃል ትርጉም ከመዛግብተ ቃላት መመልከት በቂ ነው። ቃሉን ብዙዎች ፀረ-ሃይማኖታዊነት ብለው

ይገልፁታል። ከዚህ በመነሣትም 'ሴኩላራይዜሽን'ን ሃይማኖትን የማጥፋት ሒደት ፣ 'ሴኩላሪዝም'ን

የመንግሥትና የሃይማኖት መለያየት ሳይሆን የፀረ-ሃይማኖታዊነት ስያሜ ፣ 'ሴኩላር' የሚለው ደግሞ የኢ-

አማኒ ቅጽል እንደሆኑ ይብራራሉ።በእግዚአብሔር መኖር ከማያምን ማእቀፈ እሳቤ የሚመነጭ ፣ “ለሰው
ልጅ አዳኙ ራሱ የሰው ልጅ ነው፣ ሌላ ከዚህ ዓለም ውጭ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል የለም፣ መንፈሳዊ ዓለም
የለም” ባይ ነው፡፡ No regard to spiritual, religious, or ecclesiastical doctrines, beliefs, or power
structures.If God does not exist, then He cannot establish an absolute moral code. Humanist
Max Hocutt says that human beings "may, and do, make up their own rules... Morality is not
discovered; it is made.” 7

ሴኩላሪዝም አላማው እና ውጤቱ

 Emptying God from the world


 Machiaveli-ስኬታማ መሆን ከፈለክ፣ጥሩ መምሰል እንጂ መሆን አይጠበቅብህም

6
ዘመናዊነትና ክርስትና በሚል የተፃፈ ፅሁፍ፣ ዲ/ን ህሊና በለጠ
7
Max Hocutt, "Toward an Ethic of Mutual Accommodation," in Humanist Ethics, ed. Morris B. Storer , Buffalo:
Prometheus Books, 1980), p. 137.

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 30


 Survival of the fittest
 ከሆድ ሌላ ጌታ
 ከአለም ሌላ ሀገር
 ፍትወትን ከማጥገብ ሌላ የደስታ ምንጭ
 ከማሸነፍ ሌላ ታላቅነት
 ከዝናና በሌላ ፍጡር ከመከበር ሌላ ልዕልና
 በስጋ ኃያል ከመሆን የተሸለ የደስታ መለኪያ የለም
 ዘመናዊነት ቆላ 4፡5

Modern of relating to the present or recent times, characterized by or using the most up-to date
techniques.8 Modernity is development without dependency.9

ዘመናዊነት ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ ሁለንተናዊ እድገት ጥገኝነት የሌለበትን መሆን አለበት እኛ ግን አድርጉ

የሚሉንን መጥፎም ይሁን ጥሩ እንቀበላለን…. ክርስትናም ሆነ ቤተክርስቲያን ዘመናዊነት ከሚለው

መለኪያም በላይ መሆናቸውን አንድ አገልጋይ/ክርስቲያን መረዳት ይገባዋል፡፡ ክርስትና በዘመን ውስጥ ሳይሆን

ዘመን ስለ ክርስትና ተፈጥሯልና /ዘመን/ በክርስትና ውስጥ ንዑስ ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡ ለክርስትና መገለጫ

የሆኑት ምግባራትም ሆነ ሥርዓቶች፣ አለባበስም ሆነ ንዋያት ምንም እንኳን በዓለሙ መስፈርት ሞኝ

ቢያሰኙም ከዚያም በላይ መሆናቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ዘመናዊ መሳይ የሆኑና አገልጋዮችን

የሚያሸማቅቁ ጉዳዮችም ከዚህ በታች እንደሆኑ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ዘመናዊነት ማለት 'ዕድገት ካለ ጥገኝነት' ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ለመንፈሳዊነት ዕድገቱ ኢክርስቲያናዊ ነገሮች

ላይ ጥገኛ ከሆነ መንፈሳዊነቱንም ሆነ ዘመናዊነቱን ያጣል፡፡ ስለዚህ እንደ ክርስቲያን በሚገባው ሁሉ ካለ

ጥገኝነት ኹለንተናዊ ዕድገትን ማደግ አለበት፡፡ ኹለንተናዊ ዕድገት የሚለውን ወደ ግለሰብዕ ካመጣነው

እንደሚከተለው ነው፡፡ የሰው ልጅ ኹለንተናዊ ዕድገትን ዐደገ ስንል በአካሉ /በሥጋው ፣ በስሜቱ/ ፣

በነፍሱ/በዕውቀቱ፣ በለብዎቱ/ እና በመንፈሱ/በመንፈሳዊነቱ/ ዐደገ ማለታችን ነው፡፡ ሦስቱም ዕድገቶች

ካልተመጣጠኑ መልካም አይሆንም፡፡

2.3 ዐበይት የፈተናዎቹ ምንጮች

8
Merrium Webster dictionary
9
The muse of modernity: essays on the culture as development in Africa:Altbach, Phillip G, Hssan, Salah M.

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 31


1. ዓላማን መሳት፡- አገልግሎት ትርጉም የሚኖረው በዓላማ ሲፈፀም ነው፡፡አላማውን የዘነጋ አገልጋይ
በአገልግሎት አይሰነብትም፣የቆመ ቢመስለው ይወድቃል፡፡አገልጋይ የሆነ ሁሉ የየራሱ ኃላፊነት አለወ ወደ አንድ
ግብ የሚደርስ አላማን ለማሳካት የሚሰጥ ኃላፊነት ትልቅ ትንሽ የለውም፡፡አላማውን የረሳ አገልጋይ እንጇንስ
በፈቃዱ ኃላፊነትን ሊቀበል ይቅርና የእርሱም ህይወት እንደ ሎጥ ሚስት በመንገድ ላይ መቅረት ይሆንበታል፡፡

2. የግዜ አጠቃቀም ፡-ግዜ ሀብት ነው፡፡ ሀብተ እግዚአብሔር በሆነው ሰዓትም የትኛውን ሰዓት በየትናው ሥራ
ላይ ማዋል እንዳበት ለሰው ልጅ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ቤተክርስቲን ለዚህ አብነታችን ናት፡፡ ም/ም
የሰዓታት ግ፣ የኪዳን ግዜ፣ የክርስትና ማንሳት ግዜ፣ የትምሀርት ግዜ፣ የግል የፀሎት ግዜ መድባ በመንቀሳቀሷ
አገልግሎቷ ኤይቋረጥም፡፡10 ለመንፈሳዊያን አገልጋዮች ከእግዚአብሔር ጋር እንደመኖር የሚናፈቅ ነገር
የላቸውም፡፡ ግዜ ሀብትህ ስለሆነ የት እንደምታውለው ካንተ ጋር ተመከካር፡፡መንፈሳዊነትህንና አገልሎትህን
የሚያዳክሙ ነገሮችን መመጠን ይገባል፡፡የማሀበራዊ ሚድያ አጠቃቀም፣ለፊልም፣ ለመጽሐፍት ነብብ
፣ለአገልግሎት የምትመድበው ግዜ ይኑርህ፡፡

3. ከንቱ ውዳሴ፡- ከንቱ ውዳሴን የሚያመጣው ለታይታ ማገልገል ነው፡፡በአገልግሎት ውስጥ ለታይታ የሚሆን

ቦታ የለም፡፡ አገልጋይ ታይታ የሚወድድ ከሆነ ወደ ውድቀት ያመራል፡፡ አደገኛ በሽታም ነው፡፡ ታይታ ለውጫዊ

እንጂ ለውስጣዊ ማንነት አለመጨነቅ ነው፡፡ በውጭ ሲመለከቱን ጻድቅ በውስጥ ግን ግዴለሽ የመሆን ዝንባሌ

ነው፡፡

ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው፡፡አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደህንነት
በሚሰማህ አሳቻ ሳታውቀው ያዘርፍሀል፣ይገድልህማል እንዲል ቅ.ጎርጎርዮስ ፣ “ሰዎች ሁሉ መልካም
ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው፤ ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና።” ሉቃ. 6:26

4. ትዕግስት ማጣት፡- በአገልግሎት ውስጥ ሁልግዜ ደስታ ሁልግዜ መከራ የለም፡፡ሁልግዜ ማጣት ሁልግዜ
ማግኘት፣ ሁልግዜ ጤንነት ሁልግዜ ሕመም የለም ፡፡አንዱ ባንዱ እየተተካ ጉዞው ይቀጥላ፡፡ አገልግሎት ያለ
ትዕግስት አይታሰብም ክርስትና ሩጫ ነው ሐዋርያት በብዙ መከራ እያለፉ በትዕግስት ዝም ያሉት የሚጠብቁት
ነገር ስለነበር ነው፡፡

የትዕግስት በረከት ለተጋድሎ ለመከራ መቀበያ መሳሪያ ብቻ አይደለም፡፡አገልጋዩ በተገልጋዩ፣ደናግሉ በንጽህናው


ህይወት፣ተጋቢዎች በጋብቻቸውና በልጆቻው አስተዳደግ፣ መምህሩ በተማሪው ውጤታማነት ተናጋሪው

10
አገልጋይ በመንፈሳዊና በማህበራዊ ህይወት መካከል፣ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን እና አዱኛ ማእምር፣ ማህበረ ቅዱሳን 1998 ዓ.ም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 32


በሰሚዎቹ እይታ በአጠቃላይ አንዱ ሌላውን የሚያስተናግድበት የክርስትና መመዘኛም ነው፡፡ነብዩ ሙሴ
የሕዝበ እራኤልን ቁጣ የሚሸከምበት የትዕግስት ትከሻ ባይኖረው ኖሮ አደራን ባለመወጣቱ ይጠየቅ ነበር፡፡11

2.4 ፈተናዎቹን ለማለፍ ምን እናድርግ (መፍትሄዎች)

1. አላማን አለመርሳት፡- መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው እግዚአብሔርን ማግኘት ከእርሱም ጋር መኖር ነው፡፡
ከአላማ የሚርያቁ ቀዳዳዎችን መድፈን ከመሳት ይጠብቃል፡፡ስለዚህ አንድ አገልጋይ አላማውን ሁልግዜ ማሰብ
አለበት፡፡መንፈሳዊ አገልግሎት የአንድ ሰሞን የስሜት ሩጫ ሳይሆን እስከመጨረሻው ድረስ የሚሮጡት ሩጫ
ነው፡፡እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን እንደተባለ………ራዕ 2፡10

አላማ ርዕይ ተኮር እንጂ ክስተት (ግለሰብ) ተኮር አይደለም Being objective not subjective. አባቶቻችን
ጉዳይ ተኮር እንጂ ግለሰብ ተኮር አልነበሩም፡፡ሰዎችን ከስህተት ማውጣትና ከእውነት ጋር ማሰለፍ የቻሉት
ለዚህ ነበር፡፡

2. ትህትና፡- ትሕትና የአገልግሎት መሠረት ነው፡፡ሌሎችን አገልግሎቶች የሚያቃና ትሕትና ነው፡፡ የትሕትና
መጉደል አገልግሎትን ያጠፋል፡፡ በአገልገሎት ላይ የማሰናከያ ድንጋይ ይሆናል፡፡ በአገልግሎት ትሑት ለመሆን
ማን እንደሆንን፣ ከየት እንደመጣን ወዴትም እንደምንሄድ ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡

ምሳ 22፡4 ትህትና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነትም ሀይወትም ነው፡፡ካለትህትና የሚሆን አገልግሎት


ፍሬን የሌለው መኪና እንደመንዳት ነውምሳ 22፡4 ትህትና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነትም ሀይወትም
ነው፡፡

 ካለ ትህትና የሚሆን አገልግሎት ፍሬን የሌለው መኪና እንደመንዳት ነው

እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብም ልባም ሁን (Innocence+Intellegence)

 እንደ ርግብ የዋህ መሆን (innocence)፡-ጌታችን እንደ ርግብ የዋህ ሁኑ ሲል ለመንፈሳዊ አገልግሎት
ተልዕኮ ታመኑ (የቁራ መልእክተኛ እንዳትሆኑ)፣ በመንፈሳዊ አገልግሎት ሰላምን ስበኩ (ጥልና ክርክር
ከእናንተ ይራቅ)፣ በመንፈስ ቅዱስ ተመሩ (የራሳችሁን ፍላጎት ግቱ)፣ ሰው የሚፈልገውን ሳይሆን
ለሰው የሚያስፈልገውን በመስበክ አስፈላጊ ሆኖም ሲገኝ መስዋዕትነት ክፈሉ ማለቱ ነው፡፡ ነገር ግን
‹‹እንደ ርግብ የዋህ ሁኑ›› አለ እንጂ ‹‹ርግብ ሁኑ›› አላለም፡፡ ርግብን መምሰል ያለብን በሦስት ነገሮች
ነው፡፡

በርህራሄ ፡- ይቅር የምንልና በሌሎች ላይ ቂም የማንይዝ በመሆን

በየዋህነት፡- የማናታልል የማንጎዳ በመሆን (ርግብ አትዋጋም፣ አትናከስም፣ ግን ትበራለችና)

በንጽህና ፡- ራሳችንን ከኃጢአት በመጠበቅና በንስሐ ሕይወት በመኖር

11
አገልጋይ በመንፈሳዊና በማህበራዊ ህይወት መካከል፣ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን እና አዱኛ ማእምር፣ ማህበረ ቅዱሳን 1998 ዓ.ም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 33


 እንደ እባብ ብልህ መሆን (intelligence)፡- አገልጋይ ሲያገለግል ዋናውን እንዳያጣ (ራሱን
እንዲጠብቅ)፣ ለሌሎች እንቅፋት እንዳይሆን፣ በሌሎች ክፋት ተስቦ እንዳይፈተንና ካለው መንፈሳዊ
ጽናት እንዳይወድቅ ለማስገንዘብ ነው፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባን ነጥብ አለ፡፡ ጌታችን
‹‹ብልህ/ልባም›› እንጂ ‹‹ብልጥ ሁኑ›› አላለም፡፡ ሌላውን እንዳንጎዳ ‹‹እንደ እባብ ልባም ሁኑ›› አለ
እንጂ ‹‹እባብ ሁኑ›› አላለም፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ከራስ ይልቅ ሌላውን ማስቀደም ይጠይቃልና፡፡

ፈጣን ዐይኖች (sharp eyes) ፡- ዐይኖቻችንን በእውቀት በማብራት ፈጣን መሆን

የማይደለሉ ጆሮዎች (Focused ears) ፡- በአስመሰዮች አሉባልታና በወሬ የማይታለሉ፣ የማይረቱ ጆሮዎች
እንዲኖሩን

በጥበብ መኖር (Wisdom) ፡- ራስን በመጠበቅ እምነታችንን በማጽናት መኖር

 ቅዱሳን አባቶቻችን መቼም ቢሆን ራሳቸውን ከፍ አላደረጉም፣ አንሳሳትም ብለውም አላሰቡም፤


ይልቁንም በታላቅ ትሕትና ደካማነታቸውን በመግለጥ እነርሱ ያጠፉት ካለ ሌሎች እንዲያስተካክሉት
ይማጸኑ ነበር፡፡

3. ፅናት፡- ክርስትና በቦታና በግዜ የሚወሰን ሳሆን እስከ መጨረሻው የምንጸናበት ምስጢር በመሆኑ
ተጋድሎውም የሚገለው በምናሳየው ብርታና ፅናት ይሆናል፡፡የተገድሎ መጀመሪያህን ራስን በማሸነፍ ከሆነ

4. ትጋት፡- ከዘመነ አበው ጀምሮ የእግዚአብሔር ወዳጆች እየተባሉ የሚጠሩ ሁሉ የፍቅረ እግዚአብሔር
መግለጫቸው ትጋታቸው ነበር፡፡ የመጨረሻው ደሞዝ የሚከፈለው ከጥዋት እስከ ማታ በስራ ገበታቸው ላይ
ለተገኙ ሰራተኞች መሆኑን ስታይ የመንፈሳዊ ህይወት መታወቂያው ትጋት መሆኑን ያመለክታል፡፡ማቴ 20፡1-
12 ራስህን ከማገልገል ጀምር፣ 2 ኛ ጴጥ 5፡7 ፣1 ኛ ቆሮ 9፡27

ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ በበጎነትም እውቀትንራስን


መግዛትም…..2 ና ጴጥ 5፡7፣ 1 ኛ ቆሮ 9፡27 ለሌሎች ከሰበኩ በኃላ እንዳልወድቅ ራሴን እጎስማለሁ!

5.መንፈሳዊነትን መላበስ ፡-ፆም ፣ፀሎት ፣ስግደት የተባ መንፈሳዊ የጦር እቃዎችን ልበስ፡፡

አንድ አገልጋይ ከሚመራቸው ሰዎች በላይ የሆነ መንፈሳዊ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆን ይገባዋል፡፡ ጹሞ ጹሙ
የሚል፣ ጸልዮ ስለጸሎት ጠቃሚነት የሚያስረዳ፣ የፍቅር ሰው ሆኖ ፍቅርን የሚሰበክ፣ አትዋሹ ብሎ የማይዋሽ
ሰው መሆን አለበት፡፡

“ያለ ጸሎት ከሚደረግ አገልግሎት ያለ አገልግሎት የሚደርግ ጸሎት እርሱ ይበልጣል ፡፡” አቡነ ሺኖዳ

6.ሁልግዜም ራስህን ፈትሽ፡- በአገልግሎቱ እየተማረረ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሰው ስህት ይሰራል፡፡


በምክንያተኝነት የሚቀርቡ ሀሳቦችን ብንመረምራቸው ደስተኛ የማንሆነው በራሳችን ዕውቀትና ፍቃድ
ስንጓዝ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡በአገልግሎታችን ደስተኛ እንዳንሆን ያረጉንን ምክንያቶች ለይተን በማውጣት
የየራቸውን መፍትሄ በመፈለግ ማገልግል ይገባናል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 34


አስረጂ፡- ገላ 2፡1-10 ምናልባትም በከንቱ እንዳለሮጥ ወይም በከንቱ ሩጬ እንዳልሆነ በአህዛብ መካከል
የምሰብከውን ወንጌል አስታወኩዋቸው፡፡ሉቃ 15፡1

7.ፍፁም እስክሆን ጠብቄ አገለግላለሁ አትበል ፡-በፍቅረ እግዚአብሔር መሞላትና ጣፋጩን እግዚአብሔርን
ማወቅ እንጂ ዛሬ በደለኛ ነኝ፣ ሃጢአተኛ ስለሆንኩ ስስተካከል አገለግላለሁ አትበል፡፡ መቼም ፍፁም አትሆንም
እና ባለህ ነገር ሁሉ አገልግል፡፡

አስረጂ፡ -አቡነ ሺኖዳ

“እኔ ራሴን አስተካክዬ ጥሩ ስሆን አገለግልሀለሁ,ጥሩ ስሆን አገለግልሀለሁ? መቼም ጥሩ አትሆንም ራስህን ጥሩ
አድርገህ ወደእኔ ከምትመጣ ወደእኔ ናና ጥሩ አደርግሃለሁ፣እኛ ምን እንላለን እኔ ቤትህ የማልገባበት ም/ት
ንፁህ ስላልሆንኩ ነው፣አይደለም ወደ እኔ ና አፀዳሃለሁ፣ እኔ ቤትህ የማልገባበት ም/ት ጥሩ ሰው ስላልሆንኩ
ነው፣አይደለም ወደ እኔ ና ጥሩ ሰው ትሆናለህ፣ለምንድን ነው ብቻህን መስራት የምትፈልገው እስቲ የማዳን
ስራውን ተመልከት፣ለምፃሙ የሄደው እንዲፀዳ፣በሽተኛው የሄደው እንዲድን ሽባውም የሄደው ደጋሜ
መመሄድ እንዲችል ነው፡፡እኔም እንደዛው ነኝ በሉትወዳንተ የምመጣው በመላ ደካማነቴ፣በመላ ጉድለቴ፣በመላ
አወዳደቄ፤ልክ እንደጠፋው ልጅ ወደአባቱ ሲመለስ ከነቆሻሻው እንደተመለሰው፡፡እና እግዚአብሔር ካንተ ጋር
እንዲሰራ ሞክር ከእግዚአብሔር ረህ ራስህን ለማስተካከል አትሞክር በፍፁም አትችልም !”

8.ፍቅር ፡- የአገልሎት መሰረቱ ፍቅር ነው፡፡መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን አሳለፎ የሰጠወ ለሰው
ልጆች ባለው ፍቅር ነው፡፡ የአገልግሎት መነሻው እግዚአብሄርንና የእግዚአብሔር የሆኑትን መውደድ ነው፡፡
የሰወን ልጅ ሁሉ መውደድ እግዚአብሄርን ከመውደድ ይመነጫል፡፡ቤተክርስቲንንና ሀገርነ መውደድ ሌላው
የፍቅር ፍሬ ነው፡፡

እኔ እጠቀምበት ብለህ የምትሰራው ደሞዝ እንጂ ፍቅር አይደለም፣ ፍቀር ሳትቀበል የምትሰጠው ነው፡ማንም
ከእናንተ ወገን ይህች ፍቅር ደክመን የምንሰራውን ያለድካም እንዲሆን ታደርጋለችና እሱዋን እሹዋት፡፡”
ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፣1 ኛጴጥ 4፡8

 ለእኛስ የፍቅር ጥግ መለኪያችን እግዚአብሔር አምላክ ነው፡፡ያለመንም ቅድመሁኔታ እንዲሁ


የወደደን

9.ዋጋ የሚከፍል ትውልድ ለመሆን ተዘጋጅ፡-ዋጋ ለመክፈል ያልተዘጋጀ ትውልድ ውጤት ማግኘት አይችልም፡፡
ይህንንም ማድረግ የምችለው መጀመሪያ ለአገልግሎት የሚያበቃ እውቀተ እንዲኖረን ራሳችን ላይ በመስራት
ነው፡፡አንድ አገልጋይ ስለተሰጠው የአገልግሎት ድርሻ በማወቅ ምን እንደሚሰራና የሚሠራበትንም መንገድ
ከመገንዘብ ባሻገር አገልግሎቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት እንዲረዳው ረዳዋል፡፡ከመጠምጠም መማር
ይቅደም እንዲሉ አበው ሳይማሩ ማስተማርም ከተሳዳቢነት ይቆጠራል፡፡12

10.ኦርቶዶክሳዊ ሰብዕና እና ማንነት ይኑርህ፡-ነገሮችን እንዳለ ከኦርቶዶክሳዊ እይታ አንፃር የምታስተውላቸው


ሁን፡፡

12
ኰኲሐ ሃይማት፣ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣የካቲት 1989 ዓ.ም አዲስ አበባ
የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 35
 ክርስትናን ህይወት እንጂ ሆቢ አታድርገው

 ሁለገብ የሆነ ሰው

 የቤ/ክ ጠበቃ መሆን

 Apostolic Succession(ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ)መጠበቅ

 ከሌላው አለመጠበቅ፣የራስን ድርሻ መወጣት

1 ኛ ሳሙ 14፡6-23፣2 ኛ ሳሙ 9፡10

 ቤ/ክ የእውቀት ልዕልና እንዲኖራት መስራት

 ሲኦል መንገዱ እንጂ ውስጡ ደስ አይልምና አትብቀህ ራቀው፡፡

ክፍል 3

የስልጠናው አላማ

 የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ያሳለፈቻቸውን ወርቃማ ዘመናትእንዲሁም የፈተና ግዜያት


ማሳየት
 በወቅቱ የነበሩ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ሕይወት፣ብርታ እና ጥንካሬ አንፃር ተማሪዎች
እንዲመለከቱት ማድረግ
 የአገልጋዮች ብርታት እና ቅድስና ለቤተክርስቲኒቱ ያመጣውን መልካም ውጤት ማሳየት እንዲሁም
ከመከራ ቤተክርስቲያንን እንዴት እንዳሻገሯት ማሳወቅ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 36


የስልጠናው ይዘት

3. የአትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትናንት

3.1 ክርስትና በኢትዮጵያ አጀማመር

3.2 የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ወርቃማ ዘመናት

3.2.1 ጥንታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ታሪክ

3.2.2 ዘመነ ዛጉዌ

3.2.3 መካከለኛው ዘመን

3.2.4 ዘመነ ጎንደር

3.3 የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ዐበይት የፈተና ዘመናት

3.3.1 ዘመነ ዮዲት ጉዲት

3.3.2 ዘመነ ግራኝ አህመድ

3.3.3 ዘመነ ካቶሊክ

3.3.4 የቅባትና የጸጋ መነሳት

3.3.5 ዘመነ መሳፍንት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 37


3. የአትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትናንት

3.1 ክርስትና በኢትዮጵያ አጀማመር

ጥንታዊ የግሪክ ባለ ቅኔዎች፣ ገጣሚዎችና የታሪክ ጸሐፊዎች ስለኢትዮጵያ ብዙ ጽፈዋል፤ ከነዚህ መካከል

ሆሜር ስለአገሪቱና ስለሕዝቧ ሲገልጽ “በጉልበት ሃያላን፣ በውበት የተደነቁና በጠባይ ጭምቶች፣ትህትናን

የተሞሉ እንከን የሌለባቸው ዘሮች” ሲል በ 490 ከጌታ ልደት በፊት የነበረው ምዕራባውያኑ የታሪክ አባት

የሚሉት ሔሮዶቱስ አትዮጵንና አትዮጵያውያንን ባነሳበት መፅሀፍ አትዮጵያውያን በውበት፣ በቁመትና

በኃይል ከሰዎች ሁሉ የሚበልጡ ናቸው ብሏል(ሔሮዶቶስ ፫ኛ መፅሐፍ፣ ምዕራፍ 20)፡፡13

በብሉይ ኪዳን ንግሥተ ሳባ ንጉሥ ሰለሞንን ለመጎብኘት ወደ የኢየሩሳሌም ያደረገችውን ጉዞ በ 1 ኛ ነገ.

10፥1-13 ተጽፎ ሲገኝ በኢትዮጵያውያንም ዘንድ ይህ ጉዞ ብሉይ ኪዳን በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ያደረገና፤

የንጉሥ ሰለሞንና የንግሥት ሳባ ልጅ የሆነው ቀዳማዊ ምኒሊክ ጽላተ ሙሴን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ያደረገ

ነው ተብሎ ይታመናል። ከዚያን ጊዜ በኋላ የአይሁድ እምነትና ሥርዓተ አምልኮ የሕዝቧ እምነትና የቀን ተቀን

ኑሮ መመሪያ ሆኗል። በቀዳማዊ ምኒሊክ የተመሰረተው የአክሱም ሥርወ መንግሥት ተብላ ትታወቅ ነበር።

የክርስትና እምነት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በሐዋርያት ዘመን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑና ሌሎች ታሪካዊ

ማስረጃዎች ይመሰክራሉ። (ሐዋ. 8፥26-36) ላይና በአራተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ታላቁ የቤተ ክርስቲያን

ታሪክ ጸሐፊ አውሳቢዮስ “የኢትዮጵያው ጃንደረባ ጥምቀት በዓለም የመጀመሪያው የክርስትና እምነት

ፍሬ፣ለወገኖቹ ኀዋርያ ሆነ ፣ ከቤተ እስራኤል ውጭ የአካላዊ ቃልን ምስጢር ለመቀበል የመጀመሪያወ

ነው፣በአለም የወንጌል ፍሬ በመሆንና ወደ አገሩም ተመልሶ በማስተማር በዓለም የመጀመሪያው ነው፣በዚህም

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተባለው ተፈፀመ፤ So that through him in truth the
propicency obtained itsfulfilment ,which declares that :Ethiopia streatches out her hand unto

GOD”ብሎታል 14 በተጨማሪም ሩፊኖስ ቀጥሎም በቴዎድሬት፣ሶቅራጦስና ሶዝሜን ታሪክ ዘጋቢዎች ይህንን

ታላቅ ሁኔታ ዘግበውታል። ይኸውም የሕንደኬ ጃንደረባ ኢየሩሳሌም ደርሶ በኦሪቱ ልመድ የፋሲካን በዓል

አክብሮ በጋዛ በኩል ሲመለስ ፊልጶስ ጃንደረባውን የ ትንቢተ ኢሳይያስ ክፍል እንዲገባው አስረድቶት

በክርስትና አጠመቀው። ካንደረባውም ከፊሊጶስ የተማረውን ክርስትና ትምህርት ዜና ለኢትዮጵያ ህዝብ

አሰማ፡፡የሊጰን ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ሄሬኒዎስ ጃንደረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ ያላል፡፡ “But again: Whom

13
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቀ ጳጳ፣ሰኔ 1974 ዓ.ም
14
Ecclesiastical History(History of the church), Eusebius the Caesarea,Book II,ch1, No 13.

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 38


did Philip preach to the eunuch of the queen of the Ethiopians, returning from Jerusalem, ... and,
immediately requesting to be baptized, he said, "I believe Jesus Christ to be the Son of God."
This man was also sent into the regions of Ethiopia, to preach what he had himself believed." 15

ከ 4 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ እስከ 5 ኛው መቶ ክፍለዘመን መጀመሪያ የኖረው ሩፊኖስ የተባለው የቤ/ክ

ታሪክ ፀሐፊ ስለ ክርስትና እምነት ወደ ኢትዮጵያ መግባ ይህንን ፅፏል፤ ”በ 4 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አብርሃና

አፅበሀ(ክርስትናን ከመቀበላቸው በፊት ኢዛናና ሳይዛና ይባሉ ነበር) የተባሉ ወንድማማቾች አክሡም ነግሰው

ሳለ ከአጎቱ ከፈላስፋው ከመሮፔዎ ጋር ህንድን ለመጎብኘት ሲጓዝ መርከባቸው ስለሰጠመች ከወንድሙ

ከሲድራኮስ ጋር ከሞት ተርፎ መፅዋ አጠገብ የተገኘው የጢሮስ ተወላጅ ግሪካውው ፍሬሚናጦስ ከህፃንነቱ

ጀምሮ ወንጌልን እየተማረ ያደገ ስለነበር ፤ከኦሪቱ ሊቀካህናት ከእንረም ጋር ተመከክሮ የሚያስተምር

የሚያጠምቅና የሚያቆርብ ጳጳስ ከእስክንድርያ ለማጣት ተላከ፡፡ የእስክንድርያው ፓትርያርክ አትናቴዎስም

የኢትዮጵያን ቋንቋና ልማድ ስለምታውቅ አንተው ጳጳስ እና ሐዋርያ ሁን ብሎ ሰላማ በሚል መዓርገ ጵጵስና

ሰጥቶ በ 330 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ሰደደው፡፡”16ንጉሥ ኢዛና በገንዘቦቹ ላይ የነበሩትን የጨረቃ ሥዕልን ቀይሮ

የመስቀል ምልክት በማድረግ በዓለም ከነበሩት ነገሥታቶች መካከል ቀድምትነትን ቦታ አግኝቷል።17

3.2 የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዐበይት የፈተና ዘመናት

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ሃይማኖቱን መስክሮ መጠመቅ በሯን ለክርስትና የከፈተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሐዋርያት ስብከት ተጀምራ ከዚያም በመንበረ ጵጵስና ራሷን ችላ ወንጌልን
እየሰበከችና ምሥጢራትን እየፈጸመች ከዛሬ ደርሳለች፡፡በአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ጳጳስነት፣በቅዳሳን ነገሥታት
በአብርሃና አጽብሐ አስተባባሪነት፣ በሌሎች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሠራተኛነት ወንጌል በአራተኛው መቶ
ዓመት በተለያዪ አቅጣጫዎች ተሰበከ፤ ክርስትናም ተስፋፋ፡፡ ብዙ መጻሐፍት ተተረጎመ፡፡ነገር ግን
ቤተከርስጢያን በወርቃማ ግዜያት እንደሳለፈችው ሁሉ የደረሱባ ዐበይት ፈተናዎችም ነበሩ፡፡እነዚህንም ከዚህ
ቀጥለን ለማየት እንሞክራለን….

3.3.1 የዮዲት ጉዲት መነሣት ( 9 ኛው ክ/ዘመን)

15
Ireanaeus of Lyons : Adversus Hæreses Book III. Ch. 12. 8
16
የቤተክርቲያን ታሪክ በሉሌ መልአኩ፣ 1986 አዲስ አበባ
17
የኢትዮጰያ የ የ 5 ሺህ አመት ታሪክ ከኖህ-ኢህአዴግ፣ፍስሐ ያዜ፣ 2003 አዲስ አበባ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 39


ከቀዳማዊ ምኒሊክ ዘመን ጀምረው በየጊዜው ከፍልስጥኤም እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ እስራኤላውያን

ብዙዎች ክርስትናን ሲቀበሉ ጥቂቶቹ ደግሞ አንቀበልም ብለው በሀገሪቱ ተራራማና ቆላ ቦታዎች ይኖሩ ነበር፡፡

እነዚህም በሌላው ሕዝብ ዘንድ ፈላሾች እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ስደተኞች ማለት ነው፡፡ የሚያስተዳድራቸውም

ጌዴዎን የሚባል ሹም ነበር፡፡ እሱም ዮዲት የምትባል ልጅ ነበረችው ፡፡መልከ መልካምና ኃይለኛ ነበረች፡፡

በ 624 ዓ.ም ገደማ ዮዲት አክሱም ከተማ ገብታ ወረራዋ አደረገች፡፡ በክርስቲያኖች ላይ ከአባቷ የወረደ ጥላቻ

ስለነበራት የክርስቲያኖች ቅርስ የነበረውን ሁሉ አቃጠለች፡፡

ያደረሰው ተፅዕኖ

 በአብርሃና አብጽሐ የተሠራችውን በኢትዮጵያ የመጀመሪያዪቱን የድንግል ማርያምን

ቤተክተርስቲያን አቃጠለች፤

 መጽሐፍት፣ ንዋያተ ቅዱሳት ተቃጠሉ፤

 አያሌ ክርስቲያኖችና ካህናትም ከቤተክርስቲያን ጋር አብረው ተቃጠሉ

ከ 40 ዓመት የመከራና የስቃይ አገዛዝ በኋላ ጉዲት ሞተች፡፡

3.3.2 የግራኝ አህመድ ወረራ (16 ኛው ክ/ዘመን)

በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ወሰን ላይ የተወለደው ግራኝ አህመድ ከቱርክ ባለስልጣናት

ጋር እየተላላከ የኢትዮጵያን ሕዝበ ክርስቲያን ለመደምሰስና ሀገሪቱንም ለቱርክ ለማስረከብ ተነሳሳ፡፡ 15

ዓመት ሙሉ በኢትዮጵያ ላይ ዘመቱ፡፡ ከዮዲት ወረራ ተርፈው የቀሩትና ከርሷም በኋላ የተተኩት የክርስቲያን

ቅርሶች በግራኝ ወረራ ጨርሰው ወደሙ፡፡

ያደረሰው ተፅዕኖ

 በወርቅ በብር የተሠሩ ገዳማትበእሳት ተቃጥለዋል፡፡ለምሳሌ፡-የወረኢሉ መካነ ስላሴ ገዳም፣የደብረ

ሊባኖስ ገዳም…

 የሃይማኖት መጽሐፍት የታሪክ ሰነዶች ተቃጥለዋል፡፡

 ምዕመናን በሰይፍ እየተገደዱ የእስልምና ሃይማኖት እንዲቀበሉ ተደርገዋል፡፡

 የቤተ ክህነት የሙያ ደረጃ ዝቅ ማለት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 40


 ያለ ካህን ፈቃድ ማግባት (ዕቁባት ማስቀመጥ)

 ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች መውለድ

 ህዝቡ ለወንጌል ትምህርት አና ሃይማቱን ለማወቅ የሚሰጠው ግምት መውረድ

 ኢ-ክርስቲያናዊ የሆኑ ልማዶች መስፋፋት ለምሳሌ ዛር

 ቤ/ክ ይዞታዎች የስምና የቦታ ተፋልሶ ለምሳሌ ባሌ የነበረው በአቡነ አኖሬዎስ ስም ይጠራ የነበረ ቦታ

ዛሬ ኑር-ሁሴን ነው የሚባለው

3.3.3 የካቶሊክ ሚሲናውያን መነሳት (16 ኛው ክ/ዘመን)

ኢየሱሳውያን የሚባሉት ካቶሊኮች ውስጥ ውስጡን ሲሄዱ ቆይተው በይፋ የተከሠተው በዐፄ ሱስንዮስ ዘመነ

መንሥት ነው፡፡ዐፄ ሱስንዮስም ከፖርቹጋል መንግሥት የጦር መሣርያ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ በ 1626 ዓ.ም

የካቲት 11 የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሮም ሥር እንድትተዳደር እንዲሁም፡-

 ክርስቲያኖች እንደገና እንዲጠመቁ፤

 አብያተ-ክርስቲያናቱም እንደገና በሮማውያን እንዲከብሩ፤በውስጣቸው ያለው ቅዱሳን

ስዕላት ከድንጋይ በተጠረበ(የተቀረፀ ምስል)እንዲቆም

 የሮማውያን የቅዳሴ ሥርዐትና የቀን መቁጠሪያ በኢትዮጵያ እንዲሠራበት፤

 ዓርብና ዕረቡ መጸም ቀርቶ ቅዳሜ እንዲጾም፤የቅዳሜ ሰንበትነት እንዲሻር፤

ወደ ካቶሊክ እምነት ያልገባና ይህንን ሕግ ያላከበረ የአካል ቅጣት እንዲፈጸምበት የሚል አዋጅ እንዲታወጅ

ትዛዝ ሰጡ፡፡አልፎን ሱሜንዴዝ እና ንጉሡ ከመሰሎቻቸው ጋር የካቶሊክን ሃይማኖት ለማስፋፋት ሲጥሩ

ጳጳሱ አቡነ ስምዖን ደግሞ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተቆርቋሪ የሆኑትን ይዘው ከንጉሱ ጋር ጦርነት ገጠሙ፡፡

በጦርነቱ ላይ ድሉ የዐፄ ሱስንዮስ ሆነ፡፡ በዚህም ከጎጃም፣ ከበጌ ምድር፣ ከትግራይና ከላስታ ሰማዕትነት

እንዳያመልጣቸው በማለት እየተጠራሩ ከ 8 ሽህ በላይ ሕዝብ ረገፈ፡፡ በዚህ የተነሣ ለሰባት ዓመታት ያህል

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጦርነት ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ዐፅም ከያለበት እየወጣ ተቃጠለ፣ ብዙ ካህናት፣

መነኮሳት እና ምዕመናን ብዙ ስቃይ ደረሰባቸው፡፡ ዐፄ ሱስንዮስም በነገሡ በ 27 ኛ ዓመታቸው ታመው

አንደበታቸውም ተዘጋ፤ ልጃቸው ዐፄ ፋሲል ነገሰ፡፡

ያደረሰው ተፅዕኖ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 41


 ከ 1 ሚሊዮን በላይ ኢትዪጵያዊያን በካቶሊኮች ጦር ማለቃቸው

 በግራግ የሰለሙት ወገኖች የሚደርስላቸው አጥተው ሞታቸውን እያወረሱ ሞቱ

 ዘመነ መሳንትን አስከተለ

3.3.4 የቅባትና የጸጋ መነሳት(በ 17 ኛው ክ/ዘመን)

አልፎንሱ በድብቅ የቅባት ትምህርትን(ባህል) ለኤዎስጣቴዎስ ዘሳንኳ እንዲሁም የጸጋን ትምህርት(ባህል)

ለተክለሃማኖት ዘሸዋ አስተማራቸው፡፡ቅባት እና ጸጋ በንባብ እንጂ በምሥጢር አንድ ናቸው፡፡ ሁለቱም የሮማ

ካቶሊክ ሁለት ባሕርይ ዘውግ ናቸው፡፡

የቅባትና የጸጋ አዲስ ትምህርት ሆነ ተብሎ ለማለያየት የተተከለ እሾህ ስለሆነ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ካህናት ብቻ

ሳይሆን ሕዝቡን ከመንግሥት፣ መንግሥትን ከሕዝቡ መለያየቱ ቀጠለ፡፡ ከዐፄ ፋሲል ጀምሮ የሚነግሡ ነገስታት

አንዱ አንዱን ሲደግፉና ሲከራከሩ ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል፡፡ ለምሳሌ፡-በዐፄ ዳዊት የደረሰው እልቂት

3.3. 5 ዘመነ መሳፍንት (በ 18 ኛው -በ 19 ኛው ከ/ዘመን)

ከ 1769-1855 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያ በመሳፍንት አገዛዝ እንደ ቅርጫ ሥጋ ተከፋፈለች፡፡ በዚህ ጊዜ

ቤተክርስቲያን እየተዳከመች ሄደች፡፡ መኳንንቱ እና መሳፍንቱ እርስ በእርስ ስለማይስማሙ አንዱ ሌላውን

ለማጥፋት ከውጪ ሀገር መሣሪያ በማስገባት ለሚስዮኖቹ ሃይማኖታቸውን ለማሠራጨት ምቹ ጊዜ ነበር፡፡

ያደረሰው ተፅእኖ

 የደቡብና የምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ብዙውን ወደ እስልምና ወደ አረማዊነት

ተለወጠ፡፡

 በመሀል ሀገር ያለውን ምዕመን ለመከፋፈል የሮማ ፖፖ የነበሩት ጎርጎርዮስ ብዙ ሚስዮኖችን ላኩ፤

ሚስዮኖችም በከፋና በአንዳድ የደቡብ ኢትዮጵያ ግዛቶች እየተዘዋወሩ ማስተማር ጀመሩ፤

 ብዙ የቤተክርስቲያን ቅርሶች ጠፍተዋል፤ ለምሳሌ፡- በኢየሩሳሌም ከነበሩን አያሌ ቦታዎች

ብዙዎቹ ተወስደዋል፡፡

 ውስጥ ባለው ብጥብጥ በየዓመቱ ለትንሣኤ ወደ ኢየሩሳሌም ይደረግ የነበረው ጉዞ ተቋርጧል፡፡

 በ 1921 የጣልያን ወረራ እና የካቶሊክ (ቫቲካን) ቤ/ክ ሚና

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 42


ሞሶሎኒ አትዮፕያን ሲወር የኢ.በ/ክ ወደ ካቶሊክ ለመለወጥ ምቹ ጊዜ እንደሆነ በማሰብ የሮማው ፖፕ

ጦርነቱን ቅ.ዘመቻ በማለት የሞሶሎኒን ጦርና መድፍ ባረኩ፡፡ፖፑና የኢጣሊያ ካርዲናሎችም ለጦርነቱ ብዙ

ርዳታ አደረጉ፡፡

ያደረሰው ተፅዕኖ

 ቤ/ክ ተንከባክባና ጠብቃ ያቆየቻቸው የታሪክና የሀይማት ቅርሶች ተዘርፈው ለቫቲካን ተሰጡ

 በተ.መ.ድስታስቲክስ ክፍል እንደተመዘገበው 2000 አብያክርስቲያናና ገዳማት ተቃጥለዋል

 ከ 1 ሚሊዮን በላይ ምዕመና ተገድለዋል

 በየአድባራ ገዳማቱ በደ/ሊባኖስ፣ በላሊበላ፣ አክሱም፣ ጎንደርና ዝቋላ ብዙ ካህናትና ምዕመናን ተገለዋል

 ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ አንዳንድ ባህሎች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ለምሳሌ ሀውልቶችን በቤ/ክ

ማቆም፣የመቃብር ሀውልት ማነፅና ማስጌጥ

ክፍል 4

የምዕራፉ አላማ

 ተማሪዎች ዛሬ ላይ ቤተክርስቲን እያጋጠሟት ያሉ ችግሮችን በመረዳት ለእና ቤተክርስቲያን መፍሄ


እንዲሆኑ ማስቻል

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 43


የምዕራፉ ይዘት

4. የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ

4.1 የፈተናዎቹ ምንጮቸ

4.1.2 ውስጣዊ ፈተናዎች

1. የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግሮች

2. በአገልጋዮች እና ምዕመናን የሚታዩ ችግሮች

4.1.3 ውጫዊ ፈተናዎች

1. ዳርዊኒዝም (Darwinism)

2.ሉላዊነት (Globalization)

3. ሴኩላር ሂዩማኒዝም (ዓለማዊነት Secularism-Consumerism)

4. ሊበራሊዝም (Liberalism)

5.የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ

6.ተሐድሶ

7.አክራሪእስልምና (Fundamentalism)

. 8 ፖለቲካዊ ጉዳዮች እና በዘር መከፋፈል

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 44


4. የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ

በ 20 እና 21 ኛው ከ/ዘመን የኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያን ያጋጠሙዋት ፈተናዎች ከውስጥ እና ከውጭ በሚነሱ

ምክንያቶች ነው፡፡ለዚህም ደግሞ ትልቁን ሚና ይጫወት የነበረው የፖለቲካው እንቀስቃሴ ነበር፡፡በደርግ ዘመነ

መንግስት ቤተክርስቲያኗ ብዙ የሚባሉ ፈተናዎችን አሳልፋለች፡፡ለዚህም ዋነኛ ምክያት የነበረው ደርግ ይከተል

የነበረው የሶሻሊዝም ርዕዮተ አለም መሆኑ ነበር፡፡ይህ የሶሻሊዝም ርዕዮተ አለም የሩሲያ ኦርቶዶክስ

ቤተክርሰቲያንን በእጅጉ የፈተናት እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ፡፡በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክም የሆነው

ከዚህ የተለየ አልነበረም፡፡

 እግዚአብሔር የለም የሚል እሳቤ ነበር

 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ ከማለት ይልቅ በስመ ማርክሲዝም በስመ ሌኒኒዝም ይሉ

ነበር(ማርክሲስት ሌኒን የዚህ የሶሻሊዝምን ፅንሰ ሀሳብ ያመጣ ሰው ነበር)

 እንዴት አደራችሁ ሲባል እንኳን እግዚአብሔር ይመስገን ማለት የማይቻልባቸው ሁኔታዎች ነበሩ

 ባለስልጣናት ልጆቻቸውን እንዳያስጠምቁ ይከለከሉ ነበር

 በካህናት እና ጳጳሳት ላይ አሰቃቂ ግፍ ተፈፅሟል(የነ አቡነ ቴዎፍሎስ ማለፍ)

 ማህሌት ሰዐታት እና ቅዳሴ በማይክ ጮሀችሁ እየተባለ በለሆሳስ እንዲሆን ይገደዱ ነበር

 ባለስልጣናት ረቡዕ እና አርብ የጾም ምግቦችን እንዲመገቡ ይደረግ ነበር

4.1.1 ውስጣዊ ፈተናዎች

1. የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግሮች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ራስዋን የቻለች ዓለም አቀፍ ተቋም መሆኗ እንዲሁም

ቀኖናዊነትን አጽንቶ የዛሬውን ትውልድ ለመምራት ጥብቅና ዘመናዊ አስተዳደር እንደሚያስፈልጋት

ይታወቃል፡፡ ይህ አለመሆኑ በየአጋጣሚውና በሚገባውም በማይገባውም እየተመካኘ እየተነቀፈችበት እንዳለ

እሙን ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ አመራሩና ምእመኑ የሚፈልገውን መንፈሳዊ ዓላማ ለመፈጸምና ለማስፈጸም

ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ አቅም ማከናወን ሲቸገሩ ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህን እንደሽፋን ሊጠቀምባት

የሚፈልግ የተለየ የእምነት፤ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅም ፍላጎት ያለው ሁሉ ለራሱ ጥቅም እየገባ ያሻውን

እንዲያደርግ ምቹ ሆኖ ቆይቶር ፡፡እነዚህ ሁሉ ችግሮች በአንድነት ሲጠቃለሉ የመልካም አስተዳደር ችግር

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 45


የሚለውን ይገልፁልናል፡፡በቤተክርስቲያኒቱ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዛሬ ላ ቤተክርስቲያናችን

የምትፈተንበት ትልቁ ችግር ነው፡፡እነዚህ ችግሮችም

 የቤ/ክ የገንዘብ አጠቃቀም ግልፅነት የጎደለው መሆን፣የአንደነድ ደብር አስተዳደር አካላት ለዚህም

ያመቻቸው ዘንድ ምንም አይነት የስራና የሂሳብ ሪፖርት አለማቅረብ፣ቢቀርብም አጥጋቢ ያልሆነ ነገር

ማቅረብ

 የቤተክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል፤(በአሁን ሰዓት እንደውም G+ ቤትና መኪና የሌለው

የደብረ አለቃ ማግኘት እጅግ የሚያስደንቅበት ግዜ ሆኗል)

 ለቤተክርስቲያኒቱ ጥቅም እና ልማት ነው የሚል ምክንያትን በመደርደር ቤተክርስቲያኒቱን የሸቀጥ

መለዋወጫ ቦታ ማድረግ፤ይህን ስል ታዲያ ሙሉ በሙሉ ጉዳት አለው ሳይሆን የእውነት

ለቤተክርስቲያኒቱ ጥቅም እና ልማት ከሆነ መልካም ነበር ነገር ግን ሀሳባችን በሙሉ ገንዘብ፣ጥቅም እና

ልማት ላይ ሆኖ ለምዕመኑ ተደራሽ መሆን የነበረበት የድህነቱ ጉዳይ እየተረሳ ይመስላል

 የቤተክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል

 ዘረኝነት እና ሙስና

 የቤተክርስቲያኒቱ መደበኛ አገልጋዮች አና የአስተዳደር አካላት ዘወትር በስራ ገበታቸው ላይ

ያለመገኘት

 ምዕመናን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በሚያነሱበት ግዜ ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ ምእመኑን

ማስፈራራት እና ቤተክርስቲያኒቱን በተመለከተ ሀሳቡን በነፃነት እንዳይገልፅ መገደብ

 በሰንበት ትምህርት ቤቶች የውስጥ አስተዳደር ላይ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት እንዲሁም ሰንበት

ትምህርት ቤቱ ከሚወክለው የሰበካ ጉባኤ ተወካይ ጋር ተናቦ ያለመስራት፣ለመስራት ፈቃደኛ

አለመሆን

 የአስተዳደር አካት በተሐድሶ ምንፍቅና መዘፈቅ

 በቤተክርስቲያን ዕድሳት፣ በአብነት ትምህርት ቤቶች እና በገዳማት ስም፣ ገንዘብ እየሰበሰቡ ኦዲት

የማይደረጉ ማሕበራት የሚሰበስቡት ገንዘብ

በቤ/ክ ውስጥዝርፊያን የሚያበረታቱ 5 ክፍተቶች

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 46


1. መንፈሳዊ ተግባርን ከወንጀል ድርጊት የማይለይና ከቀሳጥያን የወገነ መንግሥታዊ ሥርዓት በገቢር መስፈኑ፣

2. የጀመረውን ሳይቋጭ በሆታና በወረት ተጩዋጩሆ ሲያበቃ ተመልሶ ወደአርምሞ የሚገባ ወረተኛ
ምዕመንና ተቆርቋሪ መበርከት፣

3. ከአገልግሎት ዋስትና ማጣት የተነሣ ፈሪና ድንጉጽ ካህን መፈጠሩ፣

4.ከመግለጫና የይምሰል የቃላት ጋጋታ (lipservice) በቀር ገቢር የማያውቅ ልምሾ አስተዳደር መሥፈኑና

ከእርሱም ብሶ ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክና ቋሚ ሲኖዶስ በኔትወርክና የጎሰኝነት ውድድር የተዘፈቀ

አስተሳሰብ አንግሦ በገዥነት መንሠራፋቱ

5.ሥራዎች የሚመሩበት የጨረታ፣ የግንባታ፣ የኪራይ፣ የሽያጭ፣ ሕግ፤ እንዲሁም የአገልጋይና አስገልጋይ

ግንኙነት የሚዳኝበትና አስተዳደራዊ ፍትሐ ብሔራዊና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ሕግ አለመኖሩ ከመንበሯ

ላይ በኔትወርክ ተደራጅቶ ፊጥ በማለት ኪሷን የዳበሰ ሁሉ ወርቅ ይዞ ያለጠያቂ የሚወጣባት አሳዛኝ ቤ/ክ

ፈጠረ፡፡

2. በአገልጋዮች እና ምዕመናን የሚታዩ ችግሮች

የአመለካከት

 ዘምሮ እና አገልግሎ ከመለያየት በዘለለ ቤተክርስቲያኔ ከኔ ምን ትፈልጋለች ብሎ አርቆ ያለማሰብ


 አገልግሎታችን ሁሉ የታይታ እንዲሆን መፈለግ እራሱን ማሳየት የሚወድ ሁሉ ውዳሴ ከንቱን ፈላጊ

ነው ውዳሴ ከንቱን የሚወድ ሰው ጾሙ ያለ ዋጋ ጸሎቱም ፍሬ ቢስ ነው!“18 ይህንን በመዘንጋት

የአገልጋዮች በውዳሴ ከንቱ መጠመድ ዋጋ እያስከፈለን ነው፡፡

 ለመደራጀት ለመሰባሰብ እና ቢያንስ ለሃይማኖት ጉዳይ አንድ ላይ ለመቆም ያለመፈለግ የድሮን

ታሪክ ብቻ በማንሳት አሁን ላይ እንኳን የተቀናጀ አደረጃጀት ሊኖር ቀርቶ ህዝበ ክርስቲያኑም እርስ

በእራሱ ለሃይማኖት ሲል አንድ መሆን አቅቶታል (ቸልተኛሆነናል)፤ ጊዜውን በደንብ የተረዳነው

አይመስለኝም

 ዘመናዊነት ለሚያመጣቸው ነገሮች በጅምላ ተገዢ የመሆን፤ ያለመጠየቅ እና ያለማሰተዋል

 መንደርተኝነት (ከተራ አገልጋይ እስከ ጳጳሳት በማህበሩ ትልቅ ቦታ ያላቸውንም ጨምሮ)


18
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ምዕራጋትና ድርሳናት፣መ/ር ሳሙኤል ፈቃዱ
የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 47
 እኛ ያልነው ካልሆነ፣ እኛብቻ ነን አዋቂዎቹ አይነት አስተሳሰብ

 ህዝብን መጠቀምያ አድርጎ ማየት

 ንዝህላነትና ቸልተኝነት

 በፈተና ያለመፅናት በአሳብ መለያትን እና በአገልግሎት አለመናበብን ምክንያት እያደረጉ መሸሽ

ብሎም ከቤተክርስቲያኒቱ መለየት ዞሮመረ ደግ መሳደብ

የክህሎት

 እርስ በእርስ ተግባብቶ የመስራት ክፍተት፤ የመደማመጥ ችግር

 የመምራት እና የማስተዳደር ክፍተቶች "አሁንም እመክርሐለሁ ቃሌን ስማ……… ሕዝቡንም

አስተምራቸው………… የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው" ዘዳ 18.15 እንደተባለ ጥሩ

ኦርቶዶክሳዊ የመምራት እና የማስተዳር ክሂሎት ያለው አገልጋይ ያስፈልገናል፣ይህንንም

በስልጠናዎች ማዳበር ያሻል

 የግዜ አጠቃቀም እና በዕቅድ ያለመመራት ችግር፡በተለይም አሁን ላይ ያለን አገልጋዮች ለወደፊት

ማሰብ አቁመናል ዕቅዶች ቢወጡም ተፈፃሚታቸው ግን አጠያያቂ ነው “Plan ahead: it wasn’t


raining when Noah built the ark.”- Richard Cushing
 ትዕግስት ማጣት፡ አገልግሎት ያለ ትዕግስት አይታሰብም በአገልግሎት የተለያዩ አለመግብብቶች

እንዲሁም የሚያበሳጩ ነገሮች ሲከሰቱ የምናስተናግድበት መንገድ “Just as athletes win crowns
by their struggles in the arena, so are Christians brought to perfection by the trial of their
temptations, if only we learn to accept what is sent us by the Lord with becoming
patience, with all thanksgiving. All things are ordained by the Lord’s love. We must not
accept anything that befalls us as grievous, even if, for the present, it affects our
weakness.19
 ፅናት ማጣት አገልግሎት መንገዱ ከባድ ቢሆንመም በከባድ ቦታ ሆኖ መራራ ህይወት ማሳለፍ ዋጋን

ከፍ ያደርጋል ስለሆነም ሁሌ በፈተና ግዜ ማስተዋል ያለብን ድሮም ልናገለግል የመጣነው ሰዎችን

እንጂ መላእክትን አይደለም የሚለውን መሆን አለበት፡፡የኛ አካሄድ ግን በተቃራኒው

ስለሆነቤተክርስቲኒቱ በፈተና ሰዓት የሚቆምላት ቁርጠኛ አገልጋይ እንዳታጣ ያሠጋል


19
St.Basil the Great, Letter CI

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 48


የእውቀት

 ከእውቀት ይልቅ በልምድ መነዳት

 የሃይማኖቱን ትምህርት ከግል አስተሳሰብ እና አረዳድ አንፃር የመተንተን

4.1.2 ውጫዊ ፈተናዎች

1.ዳርዊኒዝም (Darwinism):

የዳርዊን ትምህርት የእግዚአብሔርን ህልውና የማይቀበል ፣በመሆኑም የሰው ልጆችን የእግዘአብሔር

አምሳልነትን ከአንድ የዘር ግንድ መገኘታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባነው፡፡ የዳርዊን የዝግመተ ለውጥ

መላምቶችን ወደ ፍጹም ሳይንሳዊ ግኝት ለማድረስ የሚጥር የትምህርት መሥመር ነው፡፡ ሰውንም የዝንጀሮ

ውልድ ነው ብሎ የሚያምንና የሚያስተምር ሲሆን በዘመናች ያሉት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሳይንሶች ሁሉ

በዚህ ማእቀፈ እሳቤ የተዋጡ ናቸው፡፡

2.ሉላዊነት (Globalization)

አዲሱ የዓለም ሥርዓትና የሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐቢይ ክሥተት ነው እየተባለ ብዙ የሚባልለት

ሉላዊነት (Globalization - ግሎባላይዜሽን) ዓለምን በሙሉ በድንበር የለሽ አንድ የምጣኔ ሀብት ሥርዓት ጥላ

ሥር ለማድረግና ነጻ የካፒታል፣ የሸቀጥ፣ የሰው ኃይል፣ የአገልግሎት ወዘተ ዝውውር እንዲኖር ለማድረግ

የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡

 ሉላዊነት - አንድ እሳቤ፣ አንድ ፍልስፍና፣ አንድ አሠራር፣ አንድ እምነት፣ አንድ ሂደት፣ አንድ አመለካከት፣

አንድ ሕግ አለም አቀፋዊ እንዲሆን የሚሠራ ነው፡፡

 ሉላዊነት ዓላማው ዓለምን ለጥቂት ሀብታም ኮርፖሬሽኖች (በተለይም ለአሜሪካ ግዙፍ ኮርፖሬሽኖች)

ማመቻቸት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ሉላዊነትን Operation Corporate - ዘመቻ ኮርፖሬሽን ይሉታል፡፡

 የሰው ልጆች መታሠረዊ ፍላጎት ማሟያ ምንጭ የሆኑትን የተፈጥሮ ሀብት /በተለይ የእፅዋትና እንስሳትን

ዝርያዎችን/ የበሽታ መከላከያ መድ`ኒቶችን በጥቂት አሸናፊዎች ቁጥጥር ኝር ማዋል

በ 3 የፖሊሲ ዘርፎች ይሠራል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 49


1. የኢኮኖሚ ፖሊሲ፡- ሀገራት የምዕራባውያን ጥገኛ እንዲሆኑና ገበያቸውንና ሁለንተናቸውን ለእነርሱ

ክፍት እንዲያደርጉ በተለያዩ መንገዶች ይሠራሉ፡፡ጆን ፐርኪንስ የተባለው ሰው ሁለት ዋና ዋና ዘዴዎች

መኖራቸውን ጠቁሟል፡፡ እነዚህም፡-

 አንደኛው በ(IMF) እና በ(World Bank) አማካይነት ያች ሀገር ከመጠን በላይ እንድትበደር

ማደፋፈርና በዚህም ብድሩ ከሀገሪቱ የመክፈል ዓቅም በላይ ሲሆንባት የኢኮኖሚ ነጻነቷንና

ሁለንተናዋን ለአበዳሪዎቿ አሳልፋ እንድትሰጥ በማድረግ ነው፡፡

 ሌላው ደግሞ ሚሲዮናውያንን በመላክ በሃይማኖት ሽፋን ገብተው ለኮርፖሬሽኖቹ የኢኮኖሚ ዘመቻና

ወረራ ዋና መንገድ ጠራጊዎች ሆነው እንዲያገለግሉ በማድረግ ነው፡፡ ሚሲዮናውያኑ ወንጌል

እንሰብካለን በሚል ሽፋን ያን ኅብረተሰብ የራሱን ባህልና ሁለንተናዊ ማንነት በማስጠላት፣

ምዕራባውያን ኮርፖሬሽኖች ቢመጡለት በአንድ ጊዜ እንደሚበለጽግ፣ ሀብታም ለመሆንም

ፕሮቴስታንት መሆን አማራጭ የሌለው መንገድ እንደ ሆነ ይሰብኩታል፡፡

2. የፖለቲካ ፖሊሲእና

3. የሃይማኖትና ባህል ፖሊሲ ናቸው፡፡

ሉላዊነቱ እያሣደራቸው ያሉ ተፅዕኖዎች

 የመገናኛ ቴክኖሎጂ ማደግና ግንኙነትን ማቃለል፣

 ዓለማችንን ወደ አንዲት ትንሽ መንደርነት እየለወጠ ያለ

 ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር፣

 ነፃ የድንበር ዘለል ንግድና ካፒታል ዝውውር፣


 የባሕል ወረራ
 እንደ ዘፋኝነት፣ ዝሙትና ሃይማኖት አልባነት ያሉት የሥጋ ተግባራት የዘመናዊነት መገለጫ እየተደረጉ

መወሰዳቸው ይጨምራል፡፡

 አስረጂ፡-የኢንተርኔት ዓለም አቀፍ ተደራሽነት እንደ ማሳያ ከዓመት በፊት ከ 100 የዓለም ሰው 40 ው

ኢንተርኔት ይጠቀማል በ 1995, ተጠቃሚው 1% ብቻ ሲሆን በ 1999 እና 2013 መካከል በ 10

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 50


እጥፍ አድ ¹ ል በ 2005 ዓ.ም. 1 ቢሊዮን ሰው ተዳረሰ፣ 2 ኛው ቢሊዮን 2010 ፣ 3 ኛው ቢሊዮን
2014.

በ 2014 …. በ 1 ደቂቃ ውስጥ

 204 ሚሊዮን (ኢሜይል) ይላካል

 61,000 ሰዓት ርዝመት ያለው ሙዚቃ በ Pandora ላይ ይደመጣል

 20 ሚሊዮን ፎቶ ተከፍቶ ይታያል

 100,000 ቲዊት tweets

 277,000 በፌስ ቡክ ላይ Logins ይደረጋል

 ከ 2 ሚሊዮን በላይ ጎግል ይደረጋል

3. ሴኩላር ሂዩማኒዝም /ዓለማዊነት (Secularism-Consumerism)፡- መሠረቶቹ

1. በእግዚአብሔር የማያምን (Atheist) ነው፡-በእግዚአብሔር መኖር ከማያምን ማእቀፈ እሳቤ የሚመነጭ ፣

“ለሰው ልጅ አዳኙ ራሱ የሰው ልጅ ነው፣ ሌላ ከዚህ ዓለም ውጭ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል የለም፣ መንፈሳዊ

ዓለም የለም” ባይ ነው፡፡

2. ጸረ ሃይማኖት (non-religious/anti-religious) ነው፤No regard to spiritual, religious, or


ecclesiastical doctrines, beliefs, or power structures.

3. ዳርዊኒስት - ኢቮሉሺኒስት ነው፡፡

4. ሰውን የሚያየው እንደ ሥነ ሕይወታዊ ዕቃ (Biological instrument) ነው፡፡

Humanist Max Hocutt says that human beings "may, and do, make up their own rules... Morality
is not discovered; it is made.”20

አስረጂ፡-

20
Max Hocutt, "Toward an Ethic of Mutual Accommodation," in Humanist Ethics, ed. Morris B. Storer , Buffalo:
Prometheus Books, 1980, p. 137.

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 51


 በ 2050 ዓ.ም. 1.2 ቢሊየን የዓለማችን ሕዝብ ሃይማኖት የሌለው እንደሚሆን ይገመታል

 ሰው ክርስትናን ይረሳል፡፡ ጾም፣ጸሎት፣ስግደት፣ጽድቅ፣ኩነኔ የሚባሉ የክርስትና ዐበይት ሕግጋት ስላሉት

ምንአልባትም ይጠላዋል፡፡

 የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ-በ 2050 ከሮቦቶች /SexRobots/ ጋር ጋብቻ ሕጋዊ ሊሆን ይችላል

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 52


4. ሊበራሊዝም (Liberalism) ፡- የሊበራሊዝም ዋና ዋና መሠረታዊ መመሪያዎችና መርሆዎች የሚከተሉት

ናቸው፡-

• የሃይማኖት መሠረት አምላካዊ መገለጥና በመጽሐፍ ቅዱስና በቤ/ክ ያለው እውነት ሳይሆን በሰው

አእምሮና ተሞክሮ ተፈትሾ ነጥሮ መውጣት ሲችል ነው ይላል፡፡

• መጽሐፍ ቅዱስ የማይሳሳት የሆነ አምላካዊ መገለጥን የያዘ ነው የሚለውን አይቀበልም፡፡

• የሰው ልጅ አእምሮና አመክንዮ የመጨረሻው ወሳኝ አካልና የእውነታ ሁሉ መለኪያና መዳረሻው እርሱ

ነው ይላሉ፡፡

• የእግዚአብሔር መንግሥት የሚገለጠው በዚህ ዓለም በሚደረግ ሳይንሳዊ ምርምራና ዕድገት ከሚመጣ

የኑሮ መሻሻል ነው ይላል፡፡

• ማንኛውም ሰው ከእርሱ ውጭ ካለ ነገር ነጻ ነው (ከእርሱ በላይና ሕዝብ መርጦ ሥልጣን ከሰጠው

አካል ሌላ ኃይልና ሥልጣን ያለው የለም)

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 53


• ክርስትናን የሚመለከተው ከብዙ ሃይማኖቶች እንደ አንዱ አድርጎ ነው፡፡ ሁሉም ሃይማኖት

ከተመሠረተበት ጊዜ ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ፍጹም፣ የመጨረሻና ብቸኛው የሚባል ሃይማኖት የለም

ይላል፡፡

• በተለየ ሁኔታ ጥሩ ወይም መጥፎ የሚባል እምነት (አንቀጸ እምነት) የለም፣ እያንዳንዱ የመረጠው

እምነት እኩል ትክክል ነው ባይ ነው፡፡

• ማመንም ሆነ አለማመን የግለሰቡ አመለካከትና መብት ብቻ ናቸው፡፡ ይህንም በሐሰት የበጎ አድራጎት

ተግባራት ሽፋንና በሐሰት ነጻነት በተባለ ከለላ ያራምዳሉ፡፡ መቻቻል የሚሉትም የዚሁ አካል ነው፡፡

• የሊበራሊዝም መርሆዎችና አስፈጻሚዎች ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች ርእዮታቸውን ለማስፈጸም

ይሠራሉ - በፖለቲካው፣ በማኅበራዊው፣ በኢኮኖሚው፣ በባህላዊው፣ ወዘተ

• በዋናነት ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘውን የሃይማኖት ድልድይ ሰብረውና አጥፍተው በሰው

ነጻነት ላይ ብቻ የተመሠረተ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ይሞክራሉ፡፡

5.የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ

“ሚሽነሪዎች ለአውሮፓውያን ግዛት ወረራ እንደ መንገድ ጠራጊ ወይም ፍታውራሪ በመሆን አገልግለዋል” 21

የመንግሥትን ሓላፊነት በመያዝ ሥልጣናቸውን ያለምንም ይሉኝታ ለሃይማኖታቸው ዓላማ መጠቀም ፣

ቦታና ጊዜ በማይመረጥበት ስብከት ለመስፋፋት መጣር፣ የክህደት ጽሑፎችን በማስፋፋት፣በማበራዊ

አገልግሎት ሽፋን ስር ሃይማኖታዊ ተፅእኖ በመፍጠር ፣መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለምሳሌ ክሊኒክ፣

ት/ቤት….. በመገንባት እና ቀጥተኛ እርዳታ በመስጠት ዕየሰሩ ይገኛሉ፡፡በኢትዮጵያ ያሉት በየአዳራሾቻቸው

ከሚሠሩት በላይ በብሮድካስትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየሠሩ ነው፡፡ ሕገወጥና ከሞራል ተቃራኒ

የሆኑ ጉዳዮችን የሚፈጽሙ ፓስተሮች በዝተዋል፡፡ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ በግልጽ የሚነቅፉና የሚተቹ

ፓስተሮች አሉ፡፡ ኢትዮጵያን ፕሮቴስታንት ለማድረግ ከ 2007 ዓ.ም ጀምሮ የሃያአምስት ዓመታት ስልታዊ

ዕቅድ ነድፈዋል፡፡ ዕቅዱን ለማሳካት አራት ማስተባበሪያዎች ከፍተው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ የዕቅዱ ባለቤት

የምሥራቅ ኢትዮጵያ ክልል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትነው፡፡

ከለውጡ ጋር ተያይዞ ፕሮቴስታንት መሆን የሰውነት ውኃ ልክ እንደሆነ መናገር ጀምረዋል፡፡ ዘኢኮኖሚስት ላይ

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ሊያበለጽጋት ስለ ፈለገ ፕሮቴስታንት መሪ ሰጣት ተብሎ ተዘግቦ ነበር፡፡ በአንዳንድ
21
Donald Crummey, Priests and Politicians, p. 2
የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 54
ቦታዎች በተለይም ደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ጊዜው የእኛ ነው በሚል በኦርቶዶክሳውያን ላይ ጫና

እያሳደሩ ነው፡፡

6. ተሐድሶ

6.1 የተሐድሶ አጀማመር በኢትዮጵያ

 በ 19 ኛው መ/ክ/ዘ መጨረሻ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት 10 ሚሲዮናውያን ድርጅቶች መካከል በአፄ


ምኒልክ ፈቃድ ካገኘው ድርጅት የስዊድን ወንጌላዊት ሚሲዮን በስተቀር ሁሉም ሚሲዮናውያን
ድርጅቶች ፈቃድ ያገኙት በራስ ተፈሪ የሥልጣን ዘመን ነበር፡፡ባይብል ቸርች ሚሽናሪ ማኅበር (BCMS)
የሚባል ቡድን በኬንያ በኩል በ 1925 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጥናቱን አጠናቀቀ፡፡
 በ 1927 በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቱ ተከፍቶ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊሠማሩ የሚችሉ
ሰዎችን ማሰልጠን ጀመረ፡፡
 የተመረቁትም “ሠራዊተ ክርስቶስ” የሚባል ማኅበር አቋቋሙ፡፡ መሠረት ስብሐት ለአብና መሰሎቹ
በፈጸሙት ሥራ የተደሰተው አሰማሪያቸው የሆነ ጉስታቭ ኦሬን በ 1950 ዓ.ም. አካባቢ በጻፈው ሪፖርት
ላይ፡-“ሚሲዮኑ የተለየ ቤተ ክርስቲያን የማቋቋም ዓላማ የለውም፡፡ ነገር ግን የኦርቶዶክስ ቤተ
ክርስቲያንን መንፈሳዊ ሕይወት ለማደስ ይተጋል፡፡” ብሎ እንደ ነበር ተዘግቧል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 55


 በ 1950 ዎቹ በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተመሥርቶ የነበረው “የሃይማኖተ አበው የተማሪዎች
ማኅበር” ከቤተ ክርስቲያን እያፈነገጠ በመሄዱ ደግሞ ሌላ የሠራዊተ ክርስቶስ ማኅበር ደጋፊ ተገኘ፡፡
 አባሎቻቸው በናዝሬት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን፣ በአ_አበባ ልደታ ቤተ ክርስቲያን፣ በቅድስት
ሥላሴ ካቴድራል ሰንበት ት_ቤቶች ኑፋቄ ማስተማር ጀመሩ (ቀድሞ የአማኑኤል ማኅበር) መጽናናት
ገጽ 25
 ከሁሉም በላይ በናዝሬት የሠራተኞች መንፈሳዊ ጉባዔ በሚል በእነ ዳንኤል አሁን “ፓስተር ዳንኤል”
ተመሥርቶ ብዙዎችን ከቤተ ክርስቲያን አስኮበለሉ፡፡
 በዚህ መልኩ በምስራቁ የሃገራችን ክፍል እንቅስቃሴውን ያስፋፋው ተሐድሶ ወደ መካከለኛው፣ ደቡብ፣
ምዕራብና ሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ተዛመተ፡፡
 ይሁን እንጂ አስቀድሞም ሃይማኖታዊ ዓላማ የላቸውምና በራሳቸው ጊዜ በሚፈጥሩት ግጭቶች
መገነጣጠል ጀመሩ፡፡
 ከቤተ ክርስቲያን ወደ ፕሮቴስታንቶች አዳራሾች መሄድ እንደ ቀላል እየተለመደ የመጣው በተለይ
ሃይማኖተ አበው በሠራው ከፍተኛ የውስጥ አርበኛነት ሥራ ነው፡፡

6.2 የተሐድሶ መናፍቃን ስልቶች በኢትዮጵያ በየአዝማናቱ፡-

 አጠቃላይ አቅጣጫዎችና ስልቶች

1 ኛ. እስከ 1950 ዓ.ም. ድረስ

2 ኛ. ከ 1950 – 1990 ድረስ

3 ኛ. ከ 1990 ወዲህ ናቸው፡፡

1 ኛ. እስከ 1950 ዓ.ም. ድረስ፡- “ትክክሉየፕሮቴስታንት አስተምህሮ ነው፡- "Protestant is right”

2 ኛ. ከ 1950 – 1990 ድረስ፡-“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስህተት ናት - Orthodox is not the


right church”

 ዋና ስልት፡- ምእመኑን ከቤተ ክርስቲያን በሰበብ በአስባቡ አጋጣሚዎችን በመጠቀምና በመፍጠር


ማስደንበርና ማስወጣት፣ ከዚያም መቀሰጥ (መዝረፍ) ነው፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 56


 በግልፅ ፕሮቴስታንት ሆኖ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እየወቀሱና አበሳዋን እያበዙ
ማሳየትና “ቤተ ክርስቲያኗ ትክክል አይደለችም” በማለት ግራ በማጋባት፣ በእምነቱ ላይ ጥርጣሬ
እንዲያድርበትና ወደ ፕሮቴስታንት ጎራ እንዲቀላቀል ማድረግ

 ኦርቶዶክሳዊ ሳይሆኑ ሳይመስሉም ይልቁንም ኦርቶዶክሳዊ መገለጫዎችን በማጥላላትና


በመንገሽገሽ፣
◦ በነጠላ ሳይሆን በሱፍና በክራቫት
◦ በከበሮ ሳይሆን በጊታር፣ በአኮርዲዮን …

3 ኛ. ከ 1990 ወዲህ

 ፓውል ባሊስኪ (Paul Balisky) የተባለ “የዓለም አቀፍ ተልእኮ ማኅበር” የኢትዮጵያ ዳይሬክተር
በ 1992 ዓ.ምየደከሙት ድካምና ያወጡት ገንዘብ ሁሉ ወደ ጠበቁት ግብ እንዳላደረሳቸው፡-
 “ይህ ሁሉ ጥረት ቢደረግም ወንጌላውያኑ አሁን በማደግ ላይና በመካከለኛ ኑሮ ላይ ያለውን
የከተማውን ኅብረተሰብ መቀየር አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም የተማረና ቤ/ክንን ለማገልገል ከፍተኛ
ቅንዓት ያለው የወጣቶች ኃይል ማኅበረ ቅዱሳን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በ 21 ኛው መ/ክ/ዘመን
ዘልቃ መጓዝ ትችል ዘንድ እየተጋደለ ነውና፡፡”(The Christian Science Monitor, 8 June, 2000)

 ስለሆነም ከዚያ በፊት ያደርጉት እንደ ነበረው በውጭ ሆኖ ምእመናንን ለመንጠቅ በመሥራት ብቻ
ካሰቡት ቤተ ክርስቲያኒቱን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት ግብ ለመድረስ ቀላል እንዳልሆነ ተረዱ፡፡
 ስለዚህ አዲስ ስልት መቀየስ አስፈለጋቸው፡፡ ይህም “እናድሳለን” በሚል ሽፋን ከውጭ ወደ ውስጥ
ሠርጎ በመግባት ምእመኑን እስከ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የመረከብ ስልት ነው፡፡
 ይህንም ኬንያ ውስጥ የሚታተመው “The Horn of Africa, Challenge and Opportunity”
የተባለው መጽሔት “The objective is not to set up a new church as such but to introduce
reforms within the church22 - ዓላማው አዲስ ቤተ ክርስቲያን መመሥረት አይደለም፤ ቤተ
ክርስቲያኗን (ኦርቶዶክስን) መለወጥ (ፕሮቴስታንት ማድረግ) እንጂ” በማለት ገልጾ

22
The Horn of Africa, Challenge and opportunity, p. 6

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 57


 የተሐድሶዎች የማንሸራተቻ ስልቶች (ከ 1990 ዎቹ በኋላ)

1. ምንጮችን መለየትና ስስ ብልቶችን መምረጥ

ቤተክርስቲያንን ፕሮቴስታንት ለማድረግ ወራጁ ውኃ ላይ (ሕዝቡን መውሰድ) ሳይሆን ምንጩ ላይ መሥራት


የሚል ነው፡፡እነዚህ ምንጮችም

 ገዳማት እና አብነት ት/ ቤቶች፣


 የቴዎሎጂ ት/ቤቶች፣ ደቀ መዛሙርትና መምህራን ፣
 ሰንበት ት/ቤቶች፣
 ዩኒቨርስቲዎችና ግቢ ጉባኤያት፣
 የቤተ ክህነት አስተዳደር፣
 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት፣
 ጽዋ ማኅበራት

2. ሠርጎ መግባት እና ተአማኒነት መፍጠር፡-በእነዚህ ምንጮች ውስጥ ኦርቶዶክሳዊ በመምሰል ሰርጎ


መግባትና ለሥራ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው፡፡

 እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊና የቤተ ክርስቲያን ጠበቃና ተቆርቋሪ መስሎ መታየት፣


 ኦርቶዶክሳዊውን ዶግማ፣ ቀኖናና ሥርዓት ለጊዜው አለመንቀፍ
 ተአማኒነትን ለማግኘት ማንኛውንም መንገድ መጠቀም፣
 የአገልግሎት መድረክ መያዝ - ኃላፊነት፣ ሥልጣን መያዝ፣
 በሕዝብ ልብ ውስጥ ለማደር መሥራት

3.አስተምህሮን መቀየር፡-ስልቶቹም፡-

 የቤተ ክርስቲያኒቱን የትምህርት ጉባዔያት ይዘት መቀየር፣


 “ክርስቶስን አስኳል አድርገን እንሰብካለን” ማለት፣
 “ኦርቶዶክስ እውነተኛ ቤተ ክርስትያን ነበረች፣ ግን በየጊዜው የተጫኑባት ገለባዎች አሉ፣ ቤተ
ክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል፣ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን መመለስ አለብን” ወዘተ እያሉ
ደጋግሞ መስበክ እንዲቀበለው ወይም ተቃውሞውን እንዲያለዝብ ማድረግ፣

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 58


 ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ ስለ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ማርያም፣ ጾም፣ ጸሎት፣
ስግድት ወዘተ አስመልክቶ አለ ማስተማር፣ ማስረሳት፣ በዚህ ዙሪያ ማስተማር ለሕይወት
የማይጠቅም ርባና የለሽ እንደ ሆነ ማስወራት፣
 “ተሐድሶ” የሆኑ ሰዎች (ማኅበር ወይም ማኅበራት) የፈጠሩት ጉዳይ ብቻ ተደርጎ እንዲታሰብ
ማድረግ/

4.ተቆጣጣሪ የሌላቸውን መስመሮች መዘርጋት፡-

 ማኅበራትን በሕዋስ (cell) መልክ ማደራጀት፣


 ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ጉባዔያትን ማስለመድ፣
 የርቀት ትምህርት አገልግሎት መስጠት፣
 ባለቤት የሌላቸው በራሪ ወረቀቶችን፣ መጻሕፍትን፣ VCD, CD, DVD ማሰራጨት፣
 በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ስም ራስን ማደራጀት፣
 አብያተ ክርስቲያናትን ከደብር ወደ ገዳምነት መቀየር፣
 የገንዘብ ችግር ስላለባቸው ነፃ ርዳታ መስጠት አንዱ ስልት ነው፡፡

5.ማስጠላት እና ድንበር ማፍረስ፤ ስልቶቹም፡-

 የቤተ ክርስትያኒቱ መገለጫ የሆኑትን ነገሮች (Icons) ማስረሳት፣ ማስጠላት (ጾም፣ ጸሎት፣
ስግደት፣ ሲኖዶስ፣ ጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ ሰንበት ት/ቤቶች … )፣
 የባህል፣ የአስተምሮ፣ የቀኖና ፣ የዶግማ እና የሥርዓት ድንበር ማጥፋት፣
 ምዕመኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር፣ በአባቶች፣ በገንዘብ አያያዝ፣ በምግባር፣ በመሳሰሉት
የተነሣ ቤተ ክርስቲያንን እንዲጠላ ማድረግ፣
 ቤተ ክርስቲያንን ያረጀች ያፈጀች “አሮጊቷ ሣራ’’ አድርጎ መሳል

6.ተሐድሶ እንኳን እንደ ሆነ የማያውቅ ግን ተሐድሶ የሆነ ትውልድ መፍጠር እና ሳያውቀው የሚደግፍ ቲፎዞ
ማፍራት፤ ስልቶች፡-

 ተቆርቋሪ በመምሰል፣ ገንዘብና እርዳታ በመስጠት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማትና ሕዝቡን


መያዝ እና ቲፎዞ እንዲሆን ማድረግ፣

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 59


 ኦርቶዶክስን የማያውቅ፣ ፕሮቴስታንት የሆነ፣ ነገር ግን ተሐድሶ (ፕሮቴስታንት) መሆኑን እንኳ
የማያውቅ ምዕመን ማፍራት፡፡

7.አክራሪእስልምና (Fundamentalism)፡-

ውሀቢዝም በ 18 ኛው መ/ክ/ዘመን የተጀመረ የእስልምና አካል ሲሆን መስራቹም መሐመድ ኢብን አብደል

ወሃብ (1703-1791) በዛሬዋ ሳዑዲ አረቢያ አካባቢ ነው፡

የእስልምናን እድገት የቀበረች ኢትዮጵያ ናት፡፡ስለዚህ አድስ ኢትዮጵያ ታስፈልገናለች የሚል እሳቤ ይዘው

ተነስተዋል፡፡

ለዚህም በጉልበት ማስለም፣ቅ.ጦርነት(ጅሀድ)፣ሴቶችን ማግባትየሚሉትን ስልቶች ይጠቀማሉ፡፡

ወደ ቅዱሱ ጦርነት የሚያደርሱ ደረጃዎች

1. በፍጥነት መዋለድ

2. መገናኛ ብዙሃንን በደንብ መጠቀም

3. ታሪክ መከለስ፣የታሪክ አሻራዎችን ማጥፋት

4. ምጣኔ ሀብታዊ ቁጥጥር(በተለይም ነዳጅ)

5. አካላዊ ግፊያ ማሸበር

6. ህግን አጣሞ መጠቀም

7. ርዳታ ለነሱ ብቻ እንዲያገኙ ማድረግ

8. በፖለቲካ ውስጥ በመግባት የመንግስት ተቁዋማትን አላ ማሳት

9. የፖለቲካና የህግ ለውጥ ሲካሄድ የራስን ቦታ ከፍ ማድረግ

በሀገራችን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች አንዳንዴ በውጭ ሀይል ከሚጋጩት በስተቀር በስምነት ሲኖሩ ነበር፡፡

በአሁኑ ወቅት ግን ቀስ በቀስ ዝየጠነከረ የመጣው የውሃቢዝም እንቅስቃሴ ምክንያጥ ይህ ስምነት እየተቀየ

መጥቷል፡፡ክርስቲያኖች በሚያንሱበትና ሙስሊሞች በሚበዙበት በብዙ ቦታዎች ላይ በክርስቲያኖችና

በአብያተክርስቲያናት ላይ ግፍ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ችግሩ ከነዚሁ ቦታዎች አልፎ ብዙ ክርስቲያኖች ባሉበት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 60


ቦታዎችም በልዩ ልዩ መንገድ በመገለጽ ላይ ነው፡፡ይህ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ቤተክርስቲያናችን ብቻ ሳትሆን

ሀገራችንም ከፍኛ ፈተና ውስጥ ልትወድቅ ትችላለች፡፡

በሀገረ ስብከቱ 18 አብያተ ክረስቲያናት ሲኖሩ 7 አብያተክርስቲናት ሙሉ በሙሉ የተቃጠሉ ሲሆን 3 በከፊል

የአገልግሎት ሕንጻዎች ጉዳት የደርሶባቸው ሲሆን ጉዳቱን ስንዘረዘር፣

 መንበረ ጵጵስና፣አብነት ት/ቤቶች መቃጠል

 የካህናትና ምዕመናን መሞትና መፈናቀል፣

 የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል፣

 የካህናትና ምዕመናን ቤት መቃጠልና መዘረፍ

 የአገልጋዮችና የምዕመናን ስደትና የሥነልቡና ተጽዕኖ፣

 የቤተክርስቲያን መብት መጣስ፣

 መንፈሳዊ አገልግሎቱ መቋረጥና ቀጣይ አገልግሎቱን መጉዳት፣(በጅግጅጋ በ 4 ቱ አብያተክርስቲያናት

አገልግሎቱ መቆሙ፣ ወረዳዎች ላይ አገልግሎት ሙለ ሙሉ መቆሙ ፣ምዕመናን ተስፋ

መቁረጥ፣አገልጋዮች መሰደድ፣

በጅማ ሐ/ስብከት፡-

 ከመጋቢት 5፣2010 ዓ.ም .እስከ ሚያዝያ 5፣2011 ዓ.ም.ድረስ 12(አስራሁለት) ምእመናን ተገድለዋል፡፡

 በአዲስ ልማት ቀበሌም እንዲሁ የክርስቲያኖች ቤቶች ተደብድበዋል፣ ክርስቲያኖቹም ተሰድደዋል፡፡

ድሬዳዋሐ/ስብከት፡-

 በ 2011 ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያንን ታቦተሕጉን አጅበው ከባሕረ ጥምቀት በሚመለሱ

ኦርቶዶክሳውያን ላይ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 61


 አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያንን ቦታእንወስዳለን በማለት መጋቢት 2011 ጨምሮ ተደጋጋሚ

ጥቃቶች በእስላሞች ተፈጽሟል፡፡ የፖሊስ አካላት ጥቃት ፈጻሚዎቹን በማሸሽ፤ ቤተክርስቲያናችንን

አንሰጥም ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን አስሮ በመግረፍ ለጥቃቱ ታባባሪ ሆነዋል፡፡

8. ፖለቲካዊ ጉዳዮች እና በዘር መከፋፈል

የተለያዩ ሀገራተ አይናቸውን ኢትዮጵያ ላይ ጥለዋል፡፡እንቅስቃሴቸውንም

 በፖለቲከው ዘርፍ(ceneter of political ideology)

 በኢኮኖሚ ዘርፍ(Hub of Economy)

 በማህበራዊ ዘርፍ

 የሃይማኖት ቅኝትና የሞራል ስብዕናን ከመቀየር አንፃር እየሰሩ ይገኛሉ

ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን መቆጣጠር አላማቸው ያደረጉት ሀገራት በዋናኛነት በሶስት ቡድን መመልከት

ይቻላል፡፡ ምዕራባውያኑ፣ሩቅ ምስራቃውያኑ፣እንዲሁም የአረበረ ሀገራት ናቸው፡፡ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ

ስልት አድርገው የሚንቀሳቀሱት ምዕራባውያኑ እና ሩቅ ምስራቃውያኑ አለማዊነትን በማስፋፋት ሲሆን

የአረብ ሀገራት ደግሞ ማስለምን መሰረት አድርገው ነው፡፡

ምዕራባውያኑ እና ሩቅ ምስራቃውያኑ

 ኃጢአት የመንግስት ጥበቃ ይደረግለታል

 ሰው በተለያዩ መዝናኛዎች life meaning distort እያደረገው ነው N.B ለኦርቶዶክስ ከመስቀል

የሚያርቀው ነገር ሁሉ ውበት የለውም! ሮሜ 7፡14

 ዶግማ በአክራሪነት ይከሰሳል፣ንዝህላልነት በስልጣኔ ይመዘናል

 ሰው በአካል በፋሽን፣በቀለም፣በዘፈን በፊልምበመጠጥ በሱሶች እንዲጠመድ ማድረግ

 ለትዳራችን ፍቺን በመስት

 ለመሬታችን ማዳበሪያ ይሉት ነገር በማምጣት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 62


 በምድራዊው ህግ ሰማያዊው ይመዘናል

 ዘረኝነት

የሩዋንዳን ታሪክ በመመልከት የዘረኝነትን አስከፊ ገጽታዎች መረዳት ይቻላል፡፡

Refer to Immacuile Ilibagiza “Left to tell:Discovering God Amidst the Rwandan Holocust”

ስንተኛው ላይ ነን ?

1. Classification (መከፋፈል)

2. Symbolization (መገለጫ መስጠት)

3. Dscrimnation (ማግለል)

4. Dehumanization (ከሰውነት ዝቅ ማድረግ)

5. Organization (ሰዎችን ማደራጀት)

6. Polarization (በተቃራኒ ጎራ ማሰለፍ)

7. Preparation (ለጥፋት መዘጋጀት)

8. Persecution (ጭፍጨፋና ግድያ)

9. Extermination (በአንድነት ማስወገድ)

10. Denial (ክህደት)

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 63


ክፍል 5

የምዕራፉ አላማ

 ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዴት እና ለምን እንደተመሰረቱ ማሳወቅ


 ሰንበት ትምህርትቤቶች ያጋጠሟቸውንና እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችን መረዳት
 ሰንበት ትምህርት ቤቶች የቤተክርስቲያን ተልዕኮ እንዲሳካ ሊያበረክ ስለሚችለው አስተዋጽ ማሳወቅ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 64


የስልጠናው ይዘት

5.ሰንበት ትምህርት ቤቶች እና አገልግሎት

5.1 የሰንበት ትምህርት ቤት አመሰራረት ታሪክ

5.2 ሰንበት ትምህርት ቤቶች ያጋጠማቸው ተግዳሮቶች

5.3 ልማት እና በጎ አድራጎት በሰንበት ትምህርት ቤቶች

5.3.1 የልማት ጽንሰ ሀሳብ

5.3.2 የልማት አይነቶች ከምናለማቸው ነገሮች አንፃር

5.3.3 በጎ አድራጎት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 65


5.1 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አመሰራረት ታሪክ

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በጉዞዋ ሁሉ ወጣቱን ከጎልማሳውና ከአረጋውያን ጋር በማጣመር መልካምና ሀገራዊ

ልማት ስታካሔድ ኖራለች፤ The education system of the church served the nation for centuries,
preparing graduates for religious and governmental leaders.The epistemology of the education

system was faith.23 በተለይም ደግሞ በትምህርት ዘርፍ ወጣቱን ከሕፃንነቱ ጀምሮ በማስተማር ለሰው ልጅ

በሚያስፈልጉት የአእምሮና የመንፈስ እድገት የተሟላ እንዲሆኑ ስትሰራ ቆይታለች ፤ ወደፊትም ትሰራለች፤24

ዛሬ ባለው የቤተክርስቲያኗ መዋቅር ወጣቱን አሰባስቦ አደራጅቶ የማስተማር እና በአእምሮም ሆነ በመንፈስ

የጎለበተ ሆኖ እንዲያድግ በትምህርት የማሳደግ ሀላፊነት የተጣለው በሰንበት ት/ቤቶች ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች አሰራር መታየት የጀመረው በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ

ላይ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህም ዘመን የዘመናዊ ትምህርት ሐሳብ ወደ ሀገሪቷ መግባት የጀመረበት ከመሆኑ

የተነሳ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለወጣቱ የምታስተምርበት መንገድ ወደ አዲስ መንገድ እንደቀየረው

ይታያል፡፡ ቀደም ሲል መማር የፈለገ ወጣት ሁሉ በቤተክርስቲያን መስመር ውስጥ የሚያልፍበት ዘመን ነበር፤25

ለቤተክህነትም ሆነ ለቤተመንግስት አገልግሎት የሚያስፈልገውን የሙያ እውቀት ከቤተክርሰቲያን የትምህርት

ሥርዐት የሚያኙበት ዘመን ነበር፡፡ ከዚህም የተነሣ ወጣቶች ወላጆቻቸውን፤ ትተው ሙሉ ሕይወታቸውን

ሰጥተው ወደ አብነት ት/ቤት በመግባት ተጠልቆ ከሚያልቀው የእውቀት ማዕድ የቻሉትን ያህል በብዙ ድካም

ሸምተው ገሚሱ የመምህራቸውን ወንበር በመተካት አልያም በተለያዪ ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ቀጣይ

ትውልድ የማፍራት ሥራ ላይ ይሰማሩ ነበር፡፡

በ 20 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ የተከሰተው የዘመናዊ ትምህርት ሐሳብ ወደሀገራችን መምጣቱ ግን

ወጣቱን ለሁለት ከፈለው፡፡ ወላጆቹን ትቶ ‹‹በእንተ ስማ ለማርያም ››እያለ ከምዕመናን የዕለት ምግብ

እያሰባሰበ በአብነት ት/ቤት የሚማር ወጣት እና መኝታና ምግቡ በሞግዚት እየተዘጋጀለት በዐዳሪ ት/ቤት

የሚማሩ በሚል፡፡ በተለይ የዐዳሪ ት/ቤት የወጣቱን ስሜት እየሳበበ መምጣቱ ወደ አብነት ት/ቤት ከሚሔደው

ወጣት ይልቅ ወደ ዘመናዊ ት/ቤት የሚገባው ቁጥሩ እየጨመረ እንዲሄድ አድርጓል፡፡ ከዚህም የተነሣ
23
Tamene Mamo (2019), Study on the Role of Orthodox Churches in Tourism Development of Ethiopia: The
Case of Addis Alem St. Mary Church
24
Aselefech G/Kidan Tikuye (2014), The Role of Ethiopian Orthodox Church in the Development of
Adult Education: The Case of Ye’abnet Timhirt Bet
25
አለቃ ዕንባቆም፣ የኢትዮጵያ ባህል ጥናት ለማጥናት የተሰበሰቡ ፅሁፎች፤ሰለ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትምህርት፣ ሰኔ
1957፣አዲስ አበባ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 66


ቤተክርስቲያን ወጣቱን የምታስተምርበት ሁኔታ በመለወጥ በዘመናዊ ትምህርት ከሰኞ- አርብ የሚማረውን

ትውልድ በመንፈሳዊ እድገቱም የተስተካከለ ይሆን ዘንድ ፈቃደኛ በሆኑ ወጣቶችና ካህናት አነሳሽነት

የቅዳሜና እሑድ ት/ቤት በኢትዮጵያ መቋቋም የጀመረው ከ 1939 ዓ.ም ጀምሮነው፡፡ መሰረቱ የተጣለውም

በጊዜው ‹‹የተፈሪ መኮንን ት/ቤት›› በሚባለው በዛሬ ስሙ እንጦጦ ሙያ እና ቴክኒክ ት/ቤትውስጥነው፡፡

መሥራቹም ከተፈሪ መኮንን ት/ቤት እና ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዪንቨርስቲ ይማሩ የነበሩ አንዳንድ የኦርቶዶክሰ

ተዋህዶ ሃይማኖት ተቆርቋሪ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ምክንያት የሆናቸው በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአስተማሪነት

ያገለገሉ የነበሩ ‹‹ኢየሱሳውያን›› የሚባሉ ሚሲዮናውያን ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ወደ ዮኒቨርስቲው

ትምህርታቸውንማስተማር በመጀመራቸውነው፡፡

በተፈሪ መኮንን ት/ቤት የተጀመረው የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ወደ ምስካየ ኅዙናን

መድኀኔዓለም ገዳም ተዛውሮ ተምሮ ማስተማር የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር ተመስርቶ ሕፃናትና ወጣቶች

በተለያዩ የማስተማር ዘዴ ሥራውን ቀጠለ፡፡የምስካየ ኅዙናን ቤተክርስቲያን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ

በሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት የተፈሪ መኮንን እና የእቴጌ መነን ት/ቤት ተማሪዎችን በብዛት መሳብ

በመቻሉ በየሳምንቱ እሑድ ተማሪዎች በብዛት ወደ ቤ/ክ እየመጡ በመንፈሳዊ አገልግሎት ተሳታፊ ከሆኑ

በኋላ ብዙዎች በቤ/ክ እንዳንድ ሥራዎች በፈቃደኝነት መሳተፍ ጀመሩ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተማሪዎችና

በገዳሙ መካከል አንድነትን መፍጠር የሚችልና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚሰጥበት ሰንበት ት/ቤት

እንዲቋቋም ወጣቶቹ በመጠየቃቸው “ተምሮ ማሰተማር” የተባለው ታዋቂው ሰንበት ት/ቤት በ 1939 ዓ.ም

ተመሠረተ፡፡

በነበረው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ ወደቅድስት ሥላሴ፤ ታዕካነገስት፤ መንበረ መንግስት ቅዲስ ገብርኤል እና

ወደሌሎችም አከባቢዎች ለመስፋፋት ችሏል፡፡ በ 1960 ዓ.ምይህ የሰንበት ት/ቤቶች እንቅስቃሴ ለማስተባበር

ለማጠናከር ይቻል ዘንድ በጠቅላይ ቤተክህነት በስብከተ ወንጌልንና ማስታወቂያ መመሪያ ሥር ማእከላዊ

ጽ/ቤት ተቐቁሞለታል ሰያሜ የሰንበት መምህራን ጽ/ቤት ይባል ነበር፡፡በኃላ በ 1965 ዓ.ም ራሱን ችሎ ወደ

ወጣቶች ጉዳይ መምሪያነት አድጎ የተለያዪ የወጣቶችን መንፈሳዊ ማኅበራትን ያስተምር ጀመረ፡፡26

ከ 1970-1982

26
መጽሔተ ወራዙት፣ ግንቦት 25 2004 ዓ.ም፣ ልዩ እትም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 67


ይህ ምዕራፍ በኢትጵያ ሰ/ቶች ታሪክ ታላቅ ድርሻ ያለው ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ የሰንበት ት/ቤቶች ሕልውና በቅዱስ

ሲኖዶስ ደረጃ ተቀባይነት አግኝቶ ‹‹ሰንበትት/ቤት›› በሚል ስያሜ ይዞ ሕጋዊ ሆኖ እንዲቀጥል እና በሁሉም

አቢያተክርስቲያናት ውስጥ ሰንበት ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ የተቋቋሙትም እንዲጠናከሩ በ 1970 ዓ.ም

ተሻሽሎ በተዘጋጀው ቃለ ዐዋዲ ጸድቋል፡፡ በማያያዝም 1976 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ መተዳደሪያ ሕግ

እና ሥርዐተ ትምህርት ተሰጥቶታል፡፡በተጨማሪም በ 1970 ዎቹ መጨረሻ የነበረው ጦርነት እየተስፋፋመ

ሲመጣም ወጣቱ ለጦርነት ይፈለግ ስለነበር በሰንበት ት/ቤት እንደ ልብ መሰብሰብ አዳጋች ሆነ፡፡ ከዚህም የተነሳ

አብዛኛዎቹ ሰንበት ት/ቤቶች የሕፃናት እና የአሳዳጊዎች መዋያ ብቻ እንዲሆን አስገደዳቸው፡፡

ከ 1983 ዓ.ም በኋላ

ቀደም ሲል በወጣቶች ላይ የነበረው የመንግስት ተፅዕኖ በመነሳቱ የፕሮተቴስታንት መናፍቃን በወጣቱ ላይ

ያደረጉት ወረራ በፈጠረው ቁጭት እና ሌሎች በጎ አጋጣሚዎች ተጨምረው ወጣቱ ፊቱን ወደ ቤተክርስቲያን

በማዞር በወጣት የቤተክርስቲያን አገልግሎት እምርታ የታየበት ነው፡፡ቀደም ሲል እግዚአብሔር የለም በሚል

ርዕዮተ አለም የተመታው እና ፕሮቴስታንቲዝምን እንደ ስልጣኔ ይመለከት የነበረው የከፍተኛ ትምህር

ተቋማት ተማሪ ፊቱን ወደቤተክርስቲያን መመለሱ የሰንት ትምህርት ቤቶችን አገልግሎት ከፍ ወዳለ ምዕራፍ

እንዲሸጋገር አድርጎታል፡፡27 በ 1986 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ በቅዱስ ሲኖዶስ

ጸድቆ በሥራ ላይ መዋሉ፤ በመንፈሳዊ እና በብሔራዊ በዓላት እና የንግሥ በዓላት በታላቅ ድምቀት እንዲከበሩ

ሥርዓት በማስያዝ እና የዝማሬ አገልግሎት በማበርከት፤ የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ጥሪ እየደረሳቸው ወደ

ቤተክርስቲያን የሚጎርፉትን ወጣቶች መሰረታዊ የክርስትና ትምህርት መርሐ ግብር ዘርግቶ በማስተማር

በኮርስ መልክም በማሰልጠን እና የሰንበት ት/ቤት አባል በማድረግ፤ የስብከተ ወንጌል ፕሮግራም እንዲጠናከርና

እንዲስፋፋ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንሰንበት ት/ቤቶች ምንም እንኳን ከላይ የጠቀስናቸውን እና መሰል ተግባራት

እያከናወኑ ቢሆንም ከሚጠበቅባቸው አንጻር ሲታዩ ገና ያልደረሱባቸው በርካታ አዝመራዎች አሉ፡፡ ከላይ

እንደጠቀስነው ሰ/ት/ቤቶቻችን ከ 65 ዓመታት ያላነሰ ልምድ እና ተሞክሮ ቢኖራቸውም ለቤተክርስቲያን

ተተኪ አገልጋይ የሚሆን ትውልድ ከማፍራት አኳያ ብዙ አልተጓዘም፤ በየጊዜው በተለዋዋጭ መቋቋም

የሚችል በአእምሮውም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወቱ የበለጸገ ወጣት ከማፍራት አንጻር፤ በቃላዋዲውም ሆነ

27
መጽሔተ ወራዙት፣ ግንቦት 25 2004 ዓ.ም፣ ልዩ እትም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 68


በሀገር አቀፍ ደረጃበተዘጋጀው የሰ/ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተጠቀሰውን ዓላማ እና ግብ ከማሟላት

አንጻር ሲታዪ ሰንበት ት/ቤቶቻችን ገና ብዙ የሚቀራቸው መሆኑ ይታያል፡፡

5.2 ሰንበት ትምህርት ቤቶች ያጋጠማቸው ተግዳሮቶች

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሐዋርያዊት፣ታሪካዊትና ብሔራዊት ቤተክርስቲያን በመሆንዋ ከምንጊዜውም

በበለጠ መንጋዋን ለመጠበቅ ያለባት ኃላፊነትም በዚሁ መጠን ስፊና ጥልቀት ያለው መሆኑ በግልጽ ይታወቃል፡፡

በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ 37,332 አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከ 20,000,000 በላይ ወጣቶች እንዳሉ

የሚገመት ሲሆን፣ እስከ አሁን በ 8610 አብያተ ክርስቲያናት በሥርዓት ተመዝግበው አገልግሎት በማግኘት ላይ

ያሉ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ግን 2701253 እንደሚያህል ጥናቱ ያመለክታል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ገና ብዙ

መሥራት እንደምንችል ነው፡፡28

በሰንበትትምህርት ቤቶቻችን የክፍተት መፈጠር በሀገሪቱ ያሉት ሰንበት ት/ቤቶችን ወጥነት ያለው አንድ

ዓይነት አሰራር የሌላቸው መሆኑ፤ እርስበርስ ተገናኝተው አሠራርንም ሆነ ልምድን የሚለዋወጡበት መድረክ

የሌላቸው በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም ዘመኑን የዋጀ ወደሰንበት ት/ቤት የሚመጣውን ወጣት እንደ ዕድሜው እና

ዕውቀቱ መጠን ከፋፍሎ ማስተማር የሚያስችልሥርዓትባለመኖሩ፤ ሰንበት ት/ቤቶችን እንዲቋቁም፤

እንዲያደራጅ እና እንዲያስተባብር ኃላፊነት የተሰጠው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያው በሰው ኃ

ይል፣በበጀት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በበቂ ሁኔታ ያልተደራጀ መሆኑ ዋና ዋና ምክንያት ናቸው፡፡29

በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ዙርያ ካጋጠሙት ችግሮች መካከል

 እያንዳንዱ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት በሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ት/ቤት ችግር መፍታት

አለመቻል

 ከሀገረ ስብከት ጀምሮ እሰከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ያሉ አስፈጻሚ አካላት የቃለ ዓዋዲውን ሕግ

ተግባራዊ አለማድረጋቸው፤

 ወጣቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ በ 1986 ባወጣው መተዳደሪያ ደንብ ማደራጀትና መምራት አለመቻል፣

በሚደረገው እንቅስቃሴም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ሕጉን ለመፈፀም ፈቃደኝነት አለማሳየት፤

28
የኢ/ኦ/ቤ/ክ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አመሰራት ታሪክ፣ በመጋቤ ሐዲስ መኮነን ወ/ትንሳኤ
29
መጽሔተ ወራዙት፣ ግንቦት 25 2004 ዓ.ም፣ ልዩ እትም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 69


 የሰንበት ት/ቤቱ የሥራ አመራር ከአስተዳደሩ ጋር ጤናማ የሆነ የሥራ ግንኙነት አለመኖር

 በየሰንበት ት/ቤት የሚመረጡት የሥራ አመራር አባላት ብቃትና ችሎታ ማነስ

 ለሰንበት ት/ቤት በቋሚ የተመደቡ መምህራን አለመኖር፤

 የሰንበት ት/ቤቱን እንደ ትርፍ ሥራ የመመልከቱ የአንዳንድ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎችና

ሰበካ ጉባዔ አባላት ግንዛቤ ማነስ፤

 ወጣቶች ከልዩ ልዩ ገቢዎች ያሰባሰቡትን ገንዘብ ከሰበካ ጉባዔ ጋር በመተማመን ገቢና ወጪ ማድረግ

አለመቻል፤

ከገንዘብ እና በጀት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች

 ለሰንበት ት/ቤት ቋሚ በጀት ባለመኖሩ ሥራዎችን ለማስፈፀም አለመቻል፤

 የሰንበት ትምህርት ቤቶችን አስተዳደርና ፋይናስ ስርዓት ወጥ ለማድረግ መተዳደሪያ ደንቦች የሒሳብ

አሰራር ዘገባዎች አቀራረቦችን የተመለከቱ ጥልቅ ጥናቶች ያለመኖር

 ቋሚ የሆኑ የልማት(የገቢ) ምንጭ አለመኖር

 በአብዛኞቹ ሰንበት ት/ቤቶች የሚሠሩበት የልማት ሥራዎች ተመሣሣይ እና ጥቂት መሆናቸው

 የበጀት፣የሰው ሃይልና የንብረት አስተዳደር ስልጠናዎች እጥረት

 አባላት በሠንበት ት/ቤት የልማት ሥራዎች ላይ ለመሣተፍ ወደ ኋላ ማለታቸው

 ኦዲት ያለመስራት ችግር

 የሒሳብ አጠቃቀምና አያያዝ መመሪያዎች በስራ ላይ እየዋለ እንደሆነ ያለመቆጣጠር

 የልማት ሥራዎችን ለተወሰኑ አባላት ብቻ መተው

 ሥልቹነት (እንደራስ አይቶ አለመስራት)

ከጊዜ እና ዕቅድ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች

 በዕቅድና በዝግጅት አለመመራትና አለመምራት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 70


 ጥራት ያለው የዕቅድ አስተቃቀድ፣ የአፈፃፀም፣ የክትትልና ግምገማ ፎርማቶች ያለመኖር

 አባላት የተለያዩ መርሃ ግብራት ላይ በሠዓት አለመገኘት እና ከነጭራሹ መቅረት

 የተሠጡ (የሚሠጡ) ሥራዎች በታቀደላቸው ሰዓት ማጠናቀቅ አለመቻል

 በአስተዳደርና አመራር ላይ ችግሮች ሲከሰቱ የሚፈቱበትና የሚቃኑበት መንገድ፣ የጊዜ ርዝማኔ

፣የሒደታቸው መንገድ ተለይቶ እንዲቀመጥ የሚያስችል ነገር አለመኖሩ

 ወጥ የሆኑ የሥራ እቅዶችን ተከትሎ አለመስራት

 ተለያዩ የግል ሥራዎች ላይ በመጠመድ የሰንበት ት/ቤትን ሥራ በትርፍ ሰዓት የሚሰራ አድርጎ ማሰብ

 በስብሰባ ሰዓት ከተጠቀሰው በጣም ዘግይቶ መገኘት

መረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ችግሮች

 የሠንበት ት/ቤቱን አባላት ቁጥር፣ ያቋረጡትን፣ ያሉትን፣ ወደ ዩኒቨርስቲ የገቡትን፣ ያገቡ፣ ንስሃ አባላት

ያላቸውንና የሌላቸውን ብሎ የተጣራ መረጃ ያለመያዝ ችግር በአብዛኞቹ ሠንበት ት/ቤቶች የሚታይ

ችግር ነው፡፡

 አባላት ሐዘንና ደስታ ሲገጥማቸው ለሌሎች አባላት ማሳወቅ የሚቻልበት መደበኛ የሆነ መንገድ

አለመኖር

 ከሌሎች ሠንበት ት/ቤቶች ጋር የሚደረገው ግንኙነት ቋሚ አለመሆን

በሠንበት ት/ቤትና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ለሚነሡ ጉዳቶች ትጉ አለመሆን

የመፍትሔ ሀሳብ ጥቆማዎች

 እያንዳንዱ የሰ/ት/ቤት አባል በመንፈሳዊና በስጋዊ እድገቱ ውስጥ በየአመቱና በረጅም ግዜ የት መድረስ

እንደሚፈልግ፣ ምዕመንን ከቤተክርስቲያን የሚጠብቀውን ድጋፍ በመተንተን እንዲያቅድ መርዳት

 በየሀገረ ስብከቱ ያሉ የሰንበት ት/ቤት ተጠሪዎች በብቃት እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ

 ወጣቶች በየወቅቱ በዓለም ተለዋዋጭነትም ይሁን በተፈጥሮ ጠባያቸው ከዕድሜ ጋር ተያይዞ

የሚመጣውን ፈተና ጥያቄ የሚረዱበት፣ ተረድተው የሚያስተናግዱበት፣ ለክርስትና ሕይወት

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 71


እንቅፋት የሚሆነውን ሁለገብ ፈተና የሚዋጉበት አቅም ለማዳበር እንዲችሉ በየግዜው የነባራዊ

ሁኔታን ተለዋዋጭነት ዳሰሳ በማካሄድና በመተንተን ምላሽ የሚሰጡ ብቃት ባላቸው መንፋሳዊ

ትምህርትና የዘመናዊ ትምህርት ሊቃውንት ቅንጅት በማዘጋጀት መስራት

 በወረዳ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤት ተወካይ እንዲኖር ማድረግ

 በሰንበት ትምህር ቤቶች ዙሪያ ያለውን አስተዳደራዊ ችግሮች በጥናት መዳሰስና የመፍትሄ አቅጣጫ

ማቅረብ

 በሰንበት ትምህርት ቤቶችና በሰበካ ጉባዔ አመራር አባላት መካከል ግልፅ የሆነ አስተዳደራዊ ግንኙነት

እንዲፈጥሩ ማድረግ

 በየደረጃው ያሉት የሰንበት ት/ቤት መዋቅሮች በዕቅድና በዝግጅት እንዲመሩ አሰራር መዘርጋት

 በቃለ ዓዋዲው መመሪያ መሠረት በካህናትና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መካከል ጤናማ ግንኙነት

እንዲኖር የጋራ የውይይት መድረኮች ማዘጋጀት

 የበጀት፣የሰው ሃይልና የንብረት አስተዳደር ስልጠናዎችን ማዘጋጀት

 በተለያዩ በአቅም የሚበላለጡ የሰንበት ትምህርት ቤቶች መካከል የመረዳዳትና አብሮ የመደጋገፍ

ስርዓት ማበጀት

5.3 ልማት እና በጎ አድራጎት በሰንበት ትምህርት ቤቶች

5.3.1 የልማት ጽንሰ ሀሳብ

ልማት በሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ፣ ምቹ የተፈጥሮ ልማት አካባቢን


በመፍጠር፣ በጤና፣ በደህንት በትምህርት እና በመሳሰሉት ነገሮች እድገት ማምጣትን ያካትታል፡፡30 አለቃ
ኪዳነወልድ ክፍሌም በአማርኛ መዝገበ ቃላቸው “ለምኣ” የሚለውን ቃል በራ፣ ጠራ፣ ቁልጭ አለ፣
አማረ፣ተከናወነ ሲሉ ተርጉመውታል፡፡31

ልማት በቁጥር የሚለካ አመርቂ ውጤት ማምጣት ብቻ (Quantitative) ሳይሆን በቁጥሮች መለካት የሚቸግር
(Qualitative) ገፅታ አለው፡፡ እንዲያውም የልማት ዋነኛ ግብ በቁጥሮች ለመለካት አስቸጋሪ የሆነውን ደስተኛ
ማህበረሰብ መፍጠር ነው፡፡ ልማት የዛሬ ኑሮ ወይም የነገ ተስፋ ላይ ተጨባጭ አዎንታዊ ለውጥ መፍጠር ነው፡፡

30
Wikipedia
31
አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ፣

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 72


በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካሉት የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ ሰንበት ትምህርት መሆኑ በቃለ አዋዲው(አንቀፅ
፳፩) ተጠቅሷል፡፡ በወረዳ ቤተክርስቲያን፣ በሀገረ ስብከት፣ ከዚያም በመንበረ ፓትርያሪክ ደረጃ ካሉት
የቤተክርስቲያን የአገልግሎቶች መስመሮችና መዋቅሮች ሁሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ሰፊ ቦታ ተሰጥቶት
እየተሰራበት መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ከላይ እስከታች የተዘረጋው የቤተክርስቲያን መዋቅር
መልካምና ሊያሰራም የሚችል ነው፡፡ ሆኖም ግን መዋቅር ብቻውን ውጤት ሊያመጣ እንደማይችል እሙን
ነው፡፡ የመዋቅሩ ፈፃሚ አካላት ብቃትና ከኃላፊነቱ ጋር የተገናዘበ ዕውቀትና ልምድ፣ ጥሩ የሆነ የገንዘብ ልማት፣
በእቅድ መመራት እና የተሰናሰለ የመረጃ ፍሰት የሚሉት ነገሮች ተቀናጅተው መገኘት ሲችሉ እንጂ!

ኦርቶዶክሳዊ ፍቺ

ልማት የሚሆነው በፍፁም የእግዚአብሔር መውደድ ላላቸው እንዲሆን ቅዱስ ዳዊት ፅፏል፡፡መዝ 121፡6-7
“ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ፣ አንተን ለሚወዱ ሁሉ ልማት ይሁን በኃይልህ ሰላም በጌጠኛ ቤትህም ልማት
ይሁን፡፡” ስለዚህ ልማት በቤተክርስቲያናችን መጥፎ ስራዎችን አስወግደን መልካም ምግባራትን እንድናተርፍ፣
ከትናንት የተሻለ ስንቅን ለዛሬ እንዲሁም ለነገ የምናስቀምጥበት የሚያስችለን ፅንሰ ሀሳብ የያዘ ቃል ነው፡፡

5.3.2 የልማት አይነቶች ከምናለማቸው ነገሮች አንፃር

በሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ልናለማቸው የምንችላቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?

1. የሰው ሀብት ልማት (Human resource)

2. የገንዘብ ልማት (Financial resource)

3. የግዜ ልማት (Time resource)

4. የመረጃ ልማት (Informational resource)

1.የሰው ሀብት ልማት በሰንበት ትምህርት ቤቶች

እንደሚታወቀው በሰንበት ትምህርት ቤት መመዝገብ፣ ማገልገልን መገልገል ከሚገባቸው ከኦርቶዶክስ ወላጆች


ተገኝተው በቤተክርስቲያን ጥምቀተ ክርስትና ከፈፀሙት ሕፃናት እና ወጣቶች በአሁኑ ግዜ በገጠርና በከተማ፣
የሰንበት ትምህርት ቤት ከተቋቋመባቸው አጥቢያዎች ተሰበስበው የሚገኙ ሕፃናት እና ወጣቶች ቁጥር
ከመቶው እጅ በግምት ከ 13 የማይበልጡት ናቸው፡፡ በቁጥር ደረጃ ሕፃናቱን እና ወጣቶቹን መቶ በመቶ
የቤተክርስቲያን ትምህርት እና አገልግሎት ተሳታፊ አድርጎ ለማሳደግ በሀገሪቱ የሚገኙ 37,332 አብያተ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 73


ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው በግምት ከ 400 ያላነሱ ወጣቶችን ማስተማር አለባቸው፡፡ አንድ አራተኛውን
እንኳን መሰብሰብ ቢቻል 3 ሚሊዮን ወጣቶችን ማስተናገድ የግድ ሲሆን በዚህ ስልት እያንዳንዱ አጥቢያ ሙሉ
በሙሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ቢኖረው በቁጥር 50 ወጣትና ሕፃን መያዝ አለበት፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት
ያለው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ብዛት 8610 ብቻ በመሆኑ 3 ሚሊዮን ወጣት ለማስተናገድ እያንዳንዱ
ሰንበት ትምህርት ቤት በአማካኝ 350 ተማሪ መያዝ አለበት፡፡ ይህን ቁጥር ኦርቶዶክስ ሕፃናትን መቶ በመቶ
ለማድረስ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ቄጥር መጨመር ግድ ይላል፡፡32

የሰው ሀብትን በሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ለማልማት ዋነኛው ነገር ፍቅር ነው፡፡ ለዚያም ነው ሐዋርያው
ቅዱስ ዮሐንስ በመልዕክቱ ምዕራፍ ቁጥር 20 ላይ ማንም እግዚኣብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ
ሐሰተኛ ነው ያየውን መንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል ብሎ የፃፈልን፡፡
የአባላትን ቁጥር ማብዛት ብቻ ሳይሆን ያለውን አባል በትክክል አዋዋሉን፣ ምግባሩን ማወቅ በሚቻልበት
መልኩ መስራት ሲቻል እና የተማረውን የሀይማኖት ትምህርት የሚፈፀም፣ ለሰንበት ትምህርት ቤት እና
ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆር ቅኝ፣ ታዛዥ፣ ደግና ታማኝ አገልጋይ ማፍራት ሲቻል ሰው ለማ ለማለት
ያስችላል፡፡ 2 ኛ ጤሞ 2፡6 ”የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ ሊሆን ይገባዋል” እንደተባለ
ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች ቀዳሚ ተካፋይ መሆን አለብን፡፡

እያንዳንዱ አባል በመንፈሳዊና በስጋዊ እድገቱ ውስጥ በየአመቱና በረጅም ግዜ የት መድረስ እንደሚፈልግ፣
ምዕመንን ከቤተክርስቲያን የሚጠብቀውን ድጋፍ በመተንተን እንዲያቅድ በመርዳት፣ የነገረ ሃይማኖት
ትምህርት፣ የግልና የማህበር አምልኮ ሥርዓትን በሚመለከት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ከሌሎች
ምዕመናን በተሻለ መንገድ እንዲያሳዩና ምሳሌ እንሆኑ በመርዳት ፣በአሁኑ ወቅት እጅግ የተሻለ አገልግሎት
ያላቸውን ሰንበት ትምህር ቤቶች በማጥናት እና በሚቀጥሉት አመታት ሊደረስበት ይገባል ተብሎ
የሚታመነውን ግብ በማየት ያለውን የክፍተት ርቀት መገምገም ይህም የግብ ከፍታ
(benchmark)በማዘጋጀት፣ ሴኩላር ጠባይ ያላቸውን ትምህርቶች ይዘትና አሰጣጥ ከቤተክርስቲያኒቱ
አስተምህሮ አንፃር በመቃኘትና አሰጣጡን መቆጣጠር፣ለምሳሌ የፆታና ስነተዋልዶ፣ ኤች.አይቪ፣ ህገወጥ
ስደት… እንዲሁም በሰንበት ትምህር ቤቶች ዙሪያ ያለውን አስተዳደራዊ ችግሮች በጥናት መዳሰስና የመፍትሄ
አቅጣጫ በማቅረብ የሰውሀተን ማማት እንችላለን፡፡

2. የገንዘብ እና የቁሳቁስ ልማት በሰንበት ትምህርት ቤቶች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማፈራጃ መምሪያ መሪ ዕቅድ፣ 2005-
32

2010

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 74


ሰንበት ትምህርት ቤቶች የትምህርትና ስልጠና ማዕከል እንዲሁም በርካታ አገልግሎቶች የሚከናወንባቸው
እንደመሆናቸው ሁሉ እንደማንኛውም ተቋም ለስራው መሳለጥ የሚደግፉ የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ
ሁኔታዎች ሊመቻቹላቸው እና ራሳቸውን ለማስተዳደር የሚችሉበትን አቅም እያጠነከሩ ተገቢውን
አገልግሎት እንዲያበረክቱ ማስቻል ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ወጥ በሆነ ግልፅነትና
ተጠያቂነት ባለው የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ እንዲንቀሳቀሱና ደረጃውን የጠበቀ ሒሳብ ዝርዝር
እንዲኖራቸው ማስቻል፣ ዘመኑን የዋጀ የፋይናንስና የአስተዳደር ሥርዓት ቁልፍ ነገር ነው፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቶችን አስተዳደርና ፋይናስ ስርዓት ወጥ ለማድረግ መተዳደሪያ ደንቦች የሒሳብ
አሰራችና ዘገባዎች አቀራረቦችን የተመለከቱ ጥልቅ ጥናቶችን ሁሉንም ባማከለ መልኩ በማዘጋጀት ፣
የበጀት፣የሰው ሃይልና የንብረት አስተዳደር ስልጠናዎችን በማሰናዳት፣ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጥ
የፋይናንስ አሰራርን የሚያስፈልጉ ውሳኔዎችን የገንዘብና ሞያ ድጋፎችን፣ ትምህርትና አመራር ጥራት
ቁጥጥርን በሚመለከት መወጣት ያለባቸውን ግዴታዎች በግልጽ ማሳየትና አፈጻጸማቸውን ክትትል
የሚያደርግ አካል በማዘጋጀት ፣የሒሳብ አጠቃቀምና አያያዝ መመሪያዎች በስራ ላይ እንደዋለ በመከታተል
የገንዘብ ሀብ ልማተን ማሳደግ ይቻላል፡፡

3.የግዜ ልማት በሰንበት ትምህርት ቤቶች

የግዜ ልማት ስንል አንድን ተግባር ለማከናወን የሚወስድብንን ግዜ በእግብቡ መጠቀም ነው፡፡የግዜ ልማት ጥሩ
የሆነ የመርሀ ግብራት ዝርዝር ከማዘጋጀት ጀምሮ ፣ ግብን ማስቀመጥ፣ ከአንዱ ስራ የትኛው መቅደም
እንደዳለበት መለየት፣ ስራዎችን በቀላሉ መከፋፈል፣ ትኩረትን በአንድ ቦታ ሰብስቦ የተሻለ ስራ መስራት፣ጥሩ
የሆነ ዕቅድ ግብን እና አላማን ቀድሞ ማስቀመጥ ለስራዎች የመጨረሻ ቀን መቁረጥ የሚሉትን ፅንሰ ሀሳቦች
በዋነኛነት ይይዛል፡፡

የግዜ ልማት ጥቅሞች

 አባላት በቀጠሮ ትክክለኛ ሰዓት የሚገኙ (Punctual)እንዲኑ ያደርጋቸዋል

 አባላት በሁሉም አቅጣጫ የተደራጁ እንዲሆኑ

 ተግባራቸውን በግዜ ካጠናቀቁ ከጭንቀት እንዲላቀቁ

 ለወደፊት ስልታዊ ዕቅድን ለማርቀቅ ይጠቅማል

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 75


ጥራት ያለው የዕቅድ አስተቃቀድ፣ የአፈፃፀም፣ የክትትልና ግምገማ ፎርማቶችን በማዘጋጀት ፣ስልታዊ
(strategic plan) የሆነ ዕቅድን በማውጣት፣ ዕቅዱን ማውጣት ብቻ ሳይሆን በእሱ በመመራት፣ ምሳሌያዊነት
ያላቸውን እቅዶች በማዘጋጀት ማሳየትና ሰንበት ትምህር ቤቶች እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ
በሚሳተፉበት መንገድ ተመሳሳይ ዕቅዶችን ከየአካባያቸው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንያዘጋጁ በመርዳት
በአስተዳደርና አመራር ላይ ችግሮች ሲከሰቱ የሚፈቱበትና የሚቃኑበት መንገድ፣ የጊዜ ርዝማኔ ፣የሒደታቸው
መንገድ ተለይቶ እንዲቀመጥ በማድረግ የግዜ ልማትን ማድረግ ይቻላል፡፡

4. የመረጃ ልማት በሰንበት ትምህርት ቤቶች

መረጃ የተበታተነውንና ጥሬ የሆነውን ነገር እንዲሰበሰብ እና የበሰለ እንዲሆን የማድረግ አቅም አለው፡፡ አርቆ
የሚያይና ዘመኑን የሚዋጅ የመረጃ አያያዝ ለሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለቤተክርስቲያን
ሥርዓትና ለሁሉም ነገር ጠንቃቃ የሆነ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አስተዳደራዊ ሥርዓት ያስፈልገናል፡፡የመረጃ ልማት
ስንል የመረጃ አያያዝን፣ አባላት እርስ በራሳቸው ያላቸው ግንኙነት እንዲሁም አንድ ሰንበት ትምህርት ቤት
ከሌሎች ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር፣ ከምዕመናን ጋር፣ ከሰበካ ጉባኤው ጋር፣ ከማህበረቅዱሳን እነ ከሌሎች
ማህበራት ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል የሚሉትን በዋነኛነት ይይዛል፡፡

አሁን ባለው የቤተክርስቲያን መዋቅር ጊዜን፣ ገንዘብን በሚቆጥብና በአንድ ወጥ አመራ ከላይ ወደታች
የማያቋርጥ ክትትልና የወጣቶችን ፍላጎትና ተለዋዋጭ አካባቢያቸውን የሚቃኝ ከአመራር ወደ አባሉ
የሚወርድ፣ የመረጃ ፍሰት ሰንሰለት እንዲኖር መተለምና መተግበር ያስፈልጋል፡

ብቻውን የሮጠ አሸናፊ አይባልም እና ከሁሉም ሰንበት ትምህርቶች ጋር የሚደረግ የልምድ ልውውጥ (የመረጃ
መጋራት) መፈጠር አለበት፡፡ ቋሚ የልምድ ልውውጥ በማድረግ፣ በሰንበት ትምህርትቤች አንድነት በመሳተፍ
፣ከአጋር አካላት ጋር ጥሩ መስተጋብር በመፍጠር ፣ የተለያዩ የአንድነት መርሃግብራትን በማዘጋጀት እንዲሁም
በመረጃ አያያዝ ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን በማዘጋጀት የመረጃ ልማትን ማድረግ ይቻላል፡፡

5.3.3 በጎ አድራጎት

በጎ አድራጎት ማለት መልካም ነገሮችን ለመስራት ያለማንም ሰው ጫና በራስ ፍላጎትና ተነሳሽነት ለማከናወን
መፈለግና ማድረግም ጭምር ነው፡፡ 1 ኛ ተሰ 5፡15 “እርስ በእርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ማድረግ ትጉ!”

የበጎ አድራጎት ጥቅም

 ለጽድቅ

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 76


 የተበተኑትን ለመሰብሰብ

 በቋሚነትም ሆነ በግዜያዊነት ሊደርሱ ካሉ ጥፋቶች ወገኖችን ለመታደግ

 በገንዘብ (ኢኮኖሚ ችግር)ምክንያት ከሃይማኖታቸው የሚርቁ ምዕመናን ለመታደግ

 ሀይማኖታዊ እና ሀገራዊ ግዴታዎችን ለመወጣት

በጎ አድራጎትና ሰንበት ት/ት ቤቶች

ሰንበት ትምህርት ቤቶች ከሚያከናውኗቸው መንፈሳዊ አገልግሎቶች አንዱ በጎ አድራጎት ነው፡፡ነዳያንን


ከልመና እንዲወጡ ፣ እንዲወጡ የሚያደርግ ፕሮጀክት መንደፍ 1 ኛ ዮሐ 3፤17 “ነገር ግን በዚህ አለም ገንዘብ
ያለው ወንድሙም የሚያስፈለገውን ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ
እንዴት ይኖራል?” እንዲል፣ ጥቂት የነዳያንን ልጆች ሙሉ ወጪያቸውን ችሎ በመሸፈን የአስኳላ ወይም
ዘመናዊ ትምህርት እንዲማሩ በመርዳት፣ በተለያዩ በአላት የዘመን መለወጫ፣ ልደት ትንሳኤን አስመልክቶ
ችግረኞችን በማስፈሰክ እና በመመገብ፣ አባላትና ምዕመናን በማስተባበር በጠበል ቦታዎች የሚገኙ ህሙማንን
እንዲሁም አረጋዊያንን እና ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት መሪጃ ተቋማት በመሔድ እና በመጠየቅ
እንዲሁምዕብ 12፡12 “ስለዚህ የሰለሉትን እጆች አቅኑ” እንደተባለ ቃለ እግዚአብሔርን በማሰተማር፣ ከአቻ
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመሆን አቢያተ ከክርስቲያናትን በማነጽ፣ ለተለያዩ ገዳማት እና አድባራት
የጧፍ፣ የዕጣን እና የንዋየ ቅድሳት አስተዋፅኦ በማድረግ. የገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማትን መርጃ
ማጠናከር፣የተለያዩ የተራድኦ እና እንክብካቤ ስራዎችን በመለየት እና በማዘጋጀት እንዲሁም ሕብረተሰቡን
የሚጠቅሙ የተለያዩ ስራዎችን ከተለያዩ ግብረሰናይ የመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር
በማከናወን የበጎ አድራጎት ስራዎቻችን ማሳደግ ይገባል፡፡

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 77


ማጣቀሻዎች

1. መጽሐፍ ቅዱስ

2. ደስታ ተክለ ወልድ፡ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበቃላት፡ 1921-1950 ዓ.ም

3. አገልጋይ በመንፈሳዊና በማህበራዊ ህይወት መካከል፣ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን እና አዱኛ ማእምር፣

ማህበረ ቅዱሳን 1998 ዓ.ም

4. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ምዕራጋት እና ድርሳናት፡ በመ/ር ሳሙኤል ፈቃዱ

5. ኰኲሐ ሃይማት፣ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣የካቲት 1989 ዓ.ም አዲስ አበባ

6. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቀ ጳጳ፣ሰኔ 1974 ዓ.ም

7. የቤተክርቲያን ታሪክ በሉሌ መልአኩ፣ 1986 አዲስ አበባ

8. የኢትዮጰያ የ የ 5 ሺህ አመት ታሪክ ከኖህ-ኢህአዴግ፣ፍስሐ ያዜ፣ 2003 አዲስ አበባ

9. ትንሳኤ መፅሔት ቁጥር 34፣ ሐምሌ 1972 ዓ.ም

10. መፅሐፈ ድጓ

11. ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት በገብረእግዚአብሄር ኪደ፤ 2009 ዓ.ም አዲስ አበባ

12. የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ 2000 ዓ.ም

13. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲን ወርቃማ ዘመናት በዲ/ን ሰሎሞን ዮሐንስ፣ መጋቢት 21 2001 ዓ.ም አዲስ

አበባ

14. ገድለ አቡነ ኢየሱሰ ሞዓ

15. የቤተክርስቲያን አስተዋፅኦ ለኢትዮጵያ ስልጣኔ

16. አለቃ ዕንባቆም፣ የኢትዮጵያ ባህል ጥናት ለማጥናት የተሰበሰቡ ፅሁፎች፤ሰለ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን

ትምህርት፣ ሰኔ 1957፣አዲስ አበባ

17. መጽሔተ ወራዙት፣ ግንቦት 25 2004 ዓ.ም፣ ልዩ እትም

18. አትሮንስ መጽሔት መስከረም 2009 ዓ.ም

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 78


19. የኢ/ኦ/ቤ/ክ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አመሰራት ታሪክ፣ በመጋቤ ሐዲስ መኮነን

ወ/ትንሳኤ

20. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መሪ

ዕቅድ፣ 2005-2010

21. አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ፣ መፅሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዘገበ ቃላት


English Books and Journals
1. D. L. Budhoo, Enough is Enough: Dear Mr Camdessus … Open Letter of Resignation to
the Managing Director of the IMF (New York, New Horizons Press, 1990)
2. Max Hocutt, "Toward an Ethic of Mutual Accommodation," in Humanist Ethics, ed.
Morris B. Storer , Buffalo: Prometheus Books, 1980),.
3. Merrium Webster dictionary
4. The muse of modernity: essays on the culture as development in Africa:Altbach, Phillip G,
Hssan, Salah M.
5. St. Basil the Great, Letter VIII

6. Ecclesiastical History(History of the church), Eusebius the Caesarea,Book II


7. Ireanaeus of Lyons : Adversus Hæreses Book III.
8. St.Basil the Great, Letter CI

9. Immacuile Ilibagiza “Left to tell:Discovering God Amidst the Rwandan Holocust


10. Tamene Mamo (2019), Study on the Role of Orthodox Churches in Tourism Development
of Ethiopia: The Case of Addis Alem St. Mary Church
11. Aselefech G/Kidan Tikuye (2014), The Role of Ethiopian Orthodox Church in the
Development of Adult Education: The Case of Ye’abnet Timhirt Bet

የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የአገልግሎት ማሰልጠኛ ማንዋል ገጽ 79

You might also like