You are on page 1of 10

አገልጋይ እና አገልግሎቱ

የአገልግሎት ምንነት ማወቅና መኖር


መግቢያ
1.የትምህርቱ አስፈላጊነት
ትምህርቱ ለምን አስፈላጊ ሲባል መንፈሳዊ ሕፃንነት በተለይም የአገልግሎት ምንነትና ትርጉም በትክክል ያለማወቅ፤ አውቆም በትክክል
ያለመኖር ችግር ጎልቶ እየታየ ስላለ በአገልግሎት ምንነት ዙሪያ በተወሰነ መልክ ግንዛቤ ለመስጠት ነው።

✍️1ኛ ቆሮንቶስ 3፥1


“እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ
ልናገራችሁ አልቻልሁም።”

✍️ዕብራውያን 5፥12-14
"ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት
እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። ወተት የሚጋት ሁሉ
ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው
ለፍጹማን ሰዎች ነው።
2.የትምህርቱ ዓላማ
የትምህርቱ ዓላማ፦ እያንዳንዱን አገልጋይ ከመንፈሳዊ ሕፃንነትን በማላቀቅ ወደ መንፈሳዊ ብስለት ማሸጋገርና የአገልግሎትን ትክክለኛ
ምንነትና ትርጉም በሚገባ እንዲረዱ ማድረግ ነው።
3.የትምህርቱ ግብ
የትምህርቱ ግብ፦ እያንዳንዱ አገልጋይ ከመንፈሳዊ ሕፃንነት ተላቆ የአገልግሎትን ትክክለኛ ምንነትና ትርጉም በሚገባ ተረድቶ እውነተኛ
አገልጋይ ሆኖ ሲገን ማየት ነው።
1. የአገልግሎት ምንነት
✍️2 ዜና 29፥11 “ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር
መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።”

️️ መንፈሳዊ አገልግሎት ከመንፈሳዊ ሕይወት አይበልጥም።


️️ አገልግሎት በሕይወት ተጨምቀው የሚወጣው ጁስ ነው።
️️ በሕይወታችን ኢየሱስ ማሳየት ቀዳሚ አገልግሎት ነው።
️️ ከአገልግሎት በፊት ሰውነትን ሕያውና ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ይቀድማል።
👉አገልግሎት ምንድነው?
◆አገልግሎት፦
👉ሌሎችን መረዳት ነው።
️️የእግዚአብሔር ትዕዛዝ መፈጸም ነው።
️️እግዚአብሔር ማስደሰት ነው።
️️የተጠራንበት ሁለተኛው ዓላማ መፈጸሚያ ነው
1.አገልግሎት እድል ነው።
◈አገልግሎት የሰማይና የምድር ጌታ የሆነውን ታላቁን እግዚአብሄርን ለማገልገል የተሰጠ እድል ነው፡፡
✍️ዘኍልቁ 16፥9
“የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እንድታገለግሉአቸውም
በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁ አይበቃችሁምን?”
✍️2 ዜና 29፥11
“ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል
አትበሉ።”
◈ስለዚህ ሁልጊዜም እግዚአብሔርን ልናገለግል ስንነሳ ከምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች በሙሉ በመለየት እግዚአብሔርን እናገለግለው
ዘንድ እድሉን እንዳገኘን ማሰብና መቁጠር አለብን፡፡ ለአገልግሎት ስንነሳም ራሳችንን ትልቅ እጣ እንደወጣለት እድለኛ ሰው መቁጠርና
ማየት አለብን፡፡
✍️ገላትያ 1፥15-16
"ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን
በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥"
2. አገልግሎት ስራ ነው።
◈አገልግሎት የሰማይና የምድርን ጌታ ከሆነው ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ለተመረጡት ወይም እድለኛ ለሆኑት የተሰጠ መንፈሳዊ ስራ
ነው።
✍️ፊልጵስዩስ 2፥25፤30 “ነገር ግን ወንድሜንና ከእኔ ጋር አብሮ ሠራተኛ ወታደርም የሚሆነውን፥ የእናንተ ግን መልእክተኛ የሆነውና
የሚያስፈልገኝን የሚያገለግለውን አፍሮዲጡን እንድልክላችሁ በግድ አስባለሁ፤ ....በእኔ ዘንድ ካላችሁ አገልግሎት እናንተ ስለሌላችሁ
የጎደለኝን እንዲፈጽም፥ በነፍሱ ተወራርዶ ከጌታ ሥራ የተነሣ እስከ ሞት ቀርቦአልና።”
✍️ፊልጵስዩስ 2፥30 (አዲሱ መ.ት)
“እርሱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለማሟላት ሲል ለሕይወቱ እንኳ ሳይሳሳ፣ ለክርስቶስ ሥራ ከሞት አፋፍ ደርሶ
ነበርና።”
✅አገልግሎት ስራ ነው ሲባል ዕለታዊ እንጀራ ለማግኘት ብቻ ወይም ሰዎች ስላዘዙ ብቻ ወይም ሰዎች ስለፈለጉ ብቻ ወይም ደግሞ
መርሐ ግብር ፕሮግራም ለመፈጸምና ለማስፈጸም ያህል ብቻ የምንሰራው ስራ አይደለም።
✅አገልግሎት ስራ ነው ሲባል፦
➤ ከእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት የተነሳ ጌታን እንደ ግል አዳኛቸው አድርጎ የተቀበሉት እንዲሠሩት የተሰጠ መንፈሳዊ ስራ ነው።
➤ በአማኞች በጎ ፈቃደኝነት ላይ ተሰማርቶ የምሠራ መንፈሳዊ ተግባር ነው።
➤ አማኞች ገና እንዲባረኩ ሳይሆን ስለተባረኩ የሚሠሩት ቅዱስ ተግባር ነው።
➤ የአገልግሎቱ ባለቤት ታማኝ አድርጎ በቆጠራቸው ላይ ጌታ ያኖረው ውድና ክብር መንፈሳዊ አደራ ነው።
➤ አገልጋዩ ተልዕኮውን የሚፈጸምበትና ጸጋውን ለሌሎች የሚያስተላልፍበት መንገድ ነው።
✅አገልግሎት በውስጡ ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን አሉት፡፡ በመሆኑም ይህንን የእግዚአብሄር ስራ በኃላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ
ሳንታክት በኃይልና በብርታት እንዲሁ በትጋት መስራት ወይም ማገልገል ያስፈልጋል፡፡
✍️“2 ኛ ቆሮ 4፥1
ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም።”
◈መንፈሳዊ አገልግሎት ከመንፈሳዊ ሕይወት አይበልጥም።
◈አገልግሎት በሕይወት ተጨምቀው የሚወጣው ጁስ ነው።
◈በሕይወታችን ኢየሱስ ማሳየት ቀዳሚ አገልግሎት ነው።
◈ከአገልግሎት በፊት ሰውነትን ሕያውና ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ይቀድማል።
👉አገልግሎት ምንድነው?
◆አገልግሎት፦
ሌሎችን መረዳት ነው።
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ መፈጸም ነው።
እግዚአብሔርና ሰዎችን ማስደሰት ነው።
የተጠራንበት ሁለተኛው ዓላማ መፈጸሚያ ነው።
3.አገለግሎት ውጊያ ነዉ
◈አገልግሎት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነን፥ መከራ የምንቀበልበት፣ ስለ ክርስቶስ የምንዋጋበት መንፈሳዊ ውጊያ ነው
✍️2 ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።
² ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።
³ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።
⁴ የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።
⁵ ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።
⁶ የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።
⁷ የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ።

¹⁵ የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
✍️2 ኛ ጢሞቴዎስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም።
⁶ በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል።
⁷ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤
◈አገልግሎት ውጊያ የሚሆነው እንዴት ነው ሲባል በጎች ሆነን ወደ ተኩላዎች መካከል ስለምንላክ ነው።
✍️ማቴዎስ 10፥16-19
"እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ
ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ
እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።"
◈አንድ አገልጋይ በአገልግሎት ዘመኑ ከሦስት ነገሮች ጋር ውጊያ ይገጥማል። እነርሱ ከሰይጣን፣ ከራስ ማንነትና ከራስ ሰዎች
(ቤተሰብ፣ጓደኛ) ጋር ነው። አንድ አገልጋይ እነዚህ ጠላቶችሁን ማሸነፍ አለበት።
4.አገልግሎት አምልኮ ነው።
◈አገልግሎት አምልኮ ነው፡፡
አምልኮ ደግሞ ለእግዚአብሄር ብቻ የሚሰጥና ሰው የተጠራበት ትልቁ ዓላማ ነው።
✍️“ዘጸአት 4፥23
"እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ”
✍️ዘጸአት 7፥16
“እንዲህም ትለዋለህ፦ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።”
✍️ዘጸአት 8፥1
“እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፦ ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን
ልቀቅ።”
6. አገልግሎት ፍቅር ማሳያ መድረክ ነው።
◈አገልግሎት ለእግዚአብሄር ያለንን ፍቅር፣ ለእግዚአብሄር ያለንን መውደድ የምንገልጥበት መድረክ ነው፡፡
ኢሳይያስ 56፥6 “ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ
2. የአገልጋይ ምንነት
✅የአገልጋይ ጥሬ ትርጉም ባሪያ፣ ታዛዥ ወይም አሽከር የሚል ሲሆን በእግዚአብሔር ቃል አንጻር አገልጋይ ማለት፦
1 ኛ. በእግዚአብሔር የተመረጠና ለመንፈሳዊ ሥራ ላይ የተወከለ መንፈሳዊ ሰው ነው።
2 ኛ. የእግዚአብሔር አሳብ፣ ዓላማና ፕሮግራም የሚከናወንበት መጠቀሚያ ዕቃ ነው።
3 ኛ. እግዚአብሔር ራሱን ለሰዎች የሚገልጥበት መሣሪያ ነው።
4 ኛ.ጌታው ለእርሱ የከፈለው መሥዋዕትነትና ውለታ አስበው ጌታ የሚያዘውን በታማኝነት ለመታዘዝ የተሾመ ሰው ነው።
5 ኛ. በጌታ ቤት ወይም በቅዱሳን መካከል የጌታ ሥራ እንዳይቀዘቅዝና እንዳያቋርጥ የተቻለውንና ተገቢውን ጥረት የሚያደርግ የጌታ
ታማኝ ባሪያ ነው።
የእግዚአብሔር መሳሪያ ወይም ትጥቅ ምንድነው?
3.የአገልግሎት ትጥቅ፦
1. ጸምና ጸሎት
✍️የፈተናዎች እና የአደጋዎች መቋቋሚያ ነው
️️2 ዜና 32
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ንጉሡም ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ጸለዩ፥ ወደ ሰማይም ጮኹ።
²¹ እግዚአብሔርም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ሰደደ። የአሦርም ንጉሥ
አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።

²³ ብዙዎቹም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፥ ለይሁዳም ንጉሥ ለሕዝቅያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤
እርሱም ከዚህ ነገር በኋላ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።
️️ኢሳይያስ 62
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፥
ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።

¹⁰ እለፉ፥ በበሮች በኩል እለፉ፤ የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፥ ጐዳናውን አዘጋጁ፥ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓለማ
አንሡ።
የእግዚአብሔር ቃል
✍️የህብረት ማጠናከሪያ
️️ ዘኍልቁ 7፥89

“ሙሴም ወደ መገናኛው ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም
መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር፤ እርሱም ይናገረው ነበር።”
✍️አገልጋይ ለሚያገለግሉ ህዝብ መፀለይ አለበት
“ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥
ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም፤”
️️— ቆላስይስ 1፥9
“ደግሞ መልካሙንና ቅኑን መንገድ አስተምራችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ
ይራቅ።”
️️️— 1 ኛ ሳሙኤል 12፥23
✍️አገልጋይ የጸሎት ህይወት ሊኖረው ይገባል
✍️የሚያንዣብበውን የክፉ ሀይል መስበሪያ
2 ኛ ቆሮ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እኔም ራሴ ጳውሎስ፥ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ግን ብርቅ የምደፍራችሁ፥ በክርስቶስ የዋህነትና
ገርነት እመክራችኋለሁ፤
² በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ አምኜ ልደፍር አስባለሁ፥ በዚያ እምነት ግን ከእናንተ ጋር ሆኜ
እንዳልደፍር እለምናችኋለሁ።
³ በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤
⁴ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤
⁵ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን
ሁሉ እንማርካለን፥
⁶ መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።
✍️የአስተዋዮችና ያደጉ አገልጋዮች የሚፈፅሙት ነው።
ዳንኤል 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በከለዳውያን መንግሥት ላይ በነገሠ፥ ከሜዶን ዘር በነበረ በአሕሻዊሮስ ልጅ በዳርዮስ በመጀመሪያ ዓመት፥
² በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት እኔ ዳንኤል የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት፥ እግዚአብሔር በቃሉ ለነቢዩ
ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋልሁ።
³ ማቅ ለብሼ በአመድም ላይ ሆኜ ስጾም እጸልይና እለምን ዘንድ ፊቴን ወደ ጌታ ወደ አምላክ አቀናሁ።
⁴ ወደ አምላኬም ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፥ ተናዝዤም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሚወድዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ጋር ቃል
ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና የምታስፈራ አምላክ ሆይ፥
⁵ ኃጢአትን ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፋትንም አድርገናል፥ ዐምፀንማል፥ ከትእዛዝህና ከፍርድህም ፈቀቅ ብለናል፤
⁶ በስምህም ለነገሥታቶቻችንና ለአለቆቻችን ለአባቶቻችንም ለአገሩም ሕዝብ ሁሉ የተናገሩትን ባሪያዎችህን ነቢያትን አልሰማንም።
✍️የመንፈሳዊ ቅዱስ ኃይል
ኢሳይያስ 61
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን
እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
² የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤
³ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥
በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
⁴ ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን
ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።
⁵ መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፥ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይም ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል።
✍️የእግዚአብሔር ቃል
ኤርምያስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
⁵ በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።
⁶ እኔም። ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ።
⁷ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ። ወደምሰድድህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና። ብላቴና ነኝ አትበል።
⁸ እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና ከፊታቸው አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፦
⁹ እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ
¹⁰ እነሆ። ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ አድርጌሃለሁ
አለኝ።
✍️የአገልግሎት ሸክም
3. ከአንድ አገልጋይ ምን ይጠበቃል?
1 ኛ. የተለወጠ ማንነት
✅መለወጥ ሲባል ከአሮጌው አዳማዊ ባሕሪያችንና ሥራችን መላቀቅ እንዲሁም ከልጅነት ፀባይ፣ አስተሳሰብና አመለካከት መውጣት
ማለት ነው።
ሮሜ፡12፡1-3
ፊልሞና 1፥10-11
“አስቀድሞ ስላልጠቀመህ፥ አሁን ግን ለእኔም ለአንተም ስለሚጠቅም በእስራቴ ስለ ወለድሁት ስለ ልጄ ስለ አናሲሞስ እለምንሃለሁ። ”
2 ኛ. ፍቅርና ቅድስና
✅ፍቅርና ቅድስና ትልቁና ዋነኛው የአገልጋይ ባሕርይ/ quality ነው። ፍቅርና ቅድስና የአገልግሎት መሠረት ናቸው። ከሁለቱ ውጭ
የሆነ የትኛውም አገልግሎት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ከንቱ አገልግሎት ነው።
3 ኛ. ትሕትና መታዘዝ
✅ትሕትና መታዘዝ ሌላው ወሳኝ አገልጋይ ባሕርይ ነው። ትህትና መታዘዝም ልክ እንደ ፍቅርና ቅድስና የአገልግሎት መሠረት ነው፡፡
ከሁለቱ ውጭ የሆነ ማነኛውም አገልግሎት በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ቢስ የሆነ እንዲሁም ዋጋ የሚያስከፍል አደገኛ አገልግሎት ነው።
4 ኛ. ኃላፊነት ወይም ሸክም
✅አንድ አገልጋይ ለአገልግሎቱ ሸክም ያለው ኃላፊነት የሚሰማው፣ ለአገልግሎቱ ግድ የሚለው መሆን አለበት። ይህ ባሕርይ የሌለው
ማለትም ለአገልግሎት ምንም ሸክም የማይሰማው፣ አገልግሎቱን በግራ እጅ የሚይዝ ግድየለሽ የሆነ አገልጋይ በእግዚአብሔር ዘንድ
የተጣለ፤ በአገልግሎቱም መርገምን እየሰበሰበ ያለ አገልጋይ ነው።
2 ኛ ቆሮ 11፥28 “የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
5 ኛ. መሰጠት
✅እግዚአብሔር ከአንድ አገልጋይ በጣም የሚፈልገው ነገር ቢኖር መሰጠት ነው። መሰጠት ሲባል አጠቃላይ ሁለንተናን ለእግዚአብሔር
መሰጠት ነው።
2 ኛ ቆሮ 8፥5 “አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም።”
✅ለእግዚአብሔር በሙሉ ማንነት ያልሰጠ አገልጋይ መስቀሉን ተሸክሞ ዘወትር ኢየሱስን መከተል አይችልም። እንድ ዓይነት አገልጋይ
ደግሞ ለጌታ ልሆን አይገባውም።
ማቴዎስ 10፥38 “መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።”
6 ኛ. ትጋት
✅የአንድ አገልጋይ ትልቁ መለያ ትጋት ነው። ትጋት የሌለው ወይም የማይተጋ ሰነፍና እንቅልፋም አገልጋይ፤ አገልጋይ መሆን ይቅርና
አገልጋይ ልባልም አይገባም።
ቆላስይስ 3፥23-24 "ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት
እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና።"
7 ኛ. ታማኝነት
✅ከአንድ አገልጋይ እግዚአብሔር ታማኝነት ይፈልጋል። አንድ አገልጋይ ለአገልግሎቱ ለሾመው ደግሞ ታማኝ አድርጎ ለቆጠረው
ለእግዚአብሔር (“ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥"1 ኛ ጢሞቴዎስ 1፥12) ለሁሉም አቅጣጫ ታማኝ መሆን አለበት፤
እንዲሁም ለሰው ታማኝ መሆን አለበት። አለዚያ ለእግዚአብሔር የሚያሳፍር ሠራተኛ ይሆናል። ለዚህ ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ ልጁን
ጢሞተዎስን በ 2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፥15 ላይ፤ “የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን
ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።” የሚለው።
◆የአገልግሎት እንቅፋት

✍️ቸልተኛ መሆን
✍️ጸጋውን አለማወቅ
✍️ኃጢአት
✍️የአገልግሎት ስምሪት ማጣት
✍️አገልግሎት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ አለመሆን ወይም ትዕግሥት አለመሆን
✍️ሩቅ ያለውን ብድራት ቅርብ አድርጎ ማየት
✍️ብድራት መኖሩን ጭምር አለማወቅ
✅የአገልግሎት ክብር ምንድነው?

◆የአገልግሎት ክብር፦
የእግዚአብሔር መገኘት
የአገልግሎት ማእከል ምንድነው?
◆የአገልግሎት ማእከል፦
ኢየሱስ ክርስቶስ
የአገልግሎት Scope እስከየት ነው?
◆የአገልግሎት Scope (መጠን ራዕይ)፦
እስከ ዓለም ዳርቻ
የአገልግሎት ፈተና ምንድነው?
◆የአገልግሎት ፈተኛ፦
ትዕቢት
ልምምድ፦ የእግዚአብሔርንና አገልግሎትን መለማመድ
ምድራዊ ጥቅምን ማሳደድ
ተቃራኒ ፆታ
ያለመዘጋጀት፦ አለማንበብና አለመጸለይ
አድሎ ወይም ማዳላት
ዘር፣ ጎሳ ፣ አከባቢውነት
◆የአገልጋይ ባሕርይ፦
[ ] የአገልጋይ ባሕርይ ምንድ ነው?
1. ኢየሱስን መምሰል
2. መታዘዝ
3. መንፈሳዊ ፍሬ
4. ትህትና ፍቅር
◆የአገልግሎት ግብ፦
[ ] የአገልግሎት ግብ ምንድነው?
1. የነፍሳት መዳን
2. የእግዚአብሔር መንግስትን ማስፋፋት
3. የእግዚአብሔር ክብርና ሽልማት ማግኘት

You might also like