You are on page 1of 80

ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት


ነገረ መጽሐፍ ቅዱስ
አራተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት


ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀ 2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ያግኙን

Email
office@eotc-gssu.org
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCZl-
WxxCvV2UzcSz1Qxh6UAg
Facebook
http://facebook.com/EOTC.GSSU
Telegram
https://t.me/EOTCNSSU
Website
https://eotc-gssu.org/a/
Twitter
https://twitter.com/tibeb_felege

Copyright ©
2015 E.C

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

መክሥተ ርዕስ (ማውጫ)


ምዕራፍ አንድ ነገረ መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስ የስሙ ትርጉም ለምን ቅዱስ እንደተባለ
መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?
መጽሐፍ ቅዱስ መቼ ተጻፈ?
መጽሐፍ ቅዱስ የት ቦታ/ሀገር/ ተጻፈ?
መጽሐፍ ቅዱስ በምን ቋንቋ ተጻፈ?
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅም
ምዕራፍ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል እና ስርጭት
የቅዱሳት መጻሕፍት አከፋፈል
የሁለቱ ኪዳናት ግንኙነት
መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም መድረክ
መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ክብር በቤተክርስቲያን
ምዕራፍ ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ (የቅዱሳት መጻሕፍት) ንባብ ሥርዓት
ምዕራፍ አራት የመጽሐፍ ቅዱስ መልክአ ምድር
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችና ሀገሮች
ሀገረ እስራኤል የሚገኙ ከተሞችና መንደሮች
ሌሎች ከሀገረ እስራኤል ውጭ ያሉ ሀገሮችና ከተሞች
ምዕራፍ አምስት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ የውሃ አካላት እና የየብስ ምድር
ባህሮች
ወንዞች
ምንጮች
ተራሮች
ሜዳዎች
ስምጥ ሸለቆዎች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል
ምዕራፍ ስድስት የሥራ መስክ እና መገበያያ በመጽሐፍ ቅዱስ
ገበሬ
ነጋዴ
ሐኪም
ቀራጭ
የገንዘብ መስፈሪያ
የጦር መሣሪያ
ምዕራፍ ሰባት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንስሳት እና እጽዋት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንስሳት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ እጽዋት
ምዕራፍ ስምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች (የመጽሐፍ ቅዱስ ኮዴክስ)
የዕብራይስጥ የመጽሐፍት ቅጂዎች
የካይሮ ቅጂ
ፒተርስ በርግ ቅጂ
የአልፎኔስ ቅጂ
የሎንደኒሲስ ቅጂ
የሪዮቺላኒየስ ቅጂ
የኢርፋተኔሲስ ቅጂ
የግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ
የአሌክስንደርያ ቅጂ
የቫቲካን ቅጂ
የሲናቲክስ ቅጂ
የኤፍሪም ሪስክሪፕተስ ቅጂ
ቢዛኢ ቅጂ
የፓፒረስ የመጽሐፍ ቅዱስ
የሙት ባህር ጥቅሎች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል
የትምህርት አጠቃላይ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ተምረው እንደጨረሱ
1. ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጠቅላላ መግቢያ ይረዳሉ
2. መጽሐፍትን በማንበብና በማጥናት የእግዚአብሔርን ቃል መማር እና
እግዚአብሔርን በማወቅ በመንፈሳዊ ሕይወት መዳበር ያሳያሉ።
3. መጽሐፍ ቅዱስን በየጊዜው ያነባሉ።
4. የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን አከፋፈልና የተጻበትን ምክንያት ለይተው
መግለጽ
ይችላሉ፡፡
5. በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን መካከል ያለውን ግንኙነት ይተነትናሉ፡፡
6. የመጽሐፍ ቅዱስን መልክዓ ምድር ፣ የሥራ መስክ ፣ በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ
የተጠቀሱ እንስሳትና እጽዋትን ያውቃሉ።
7. ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎችን ያውቃሉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ምዕራፍ አንድ
ነገረ መጽሐፍ ቅዱስ

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ለምን ቅዱስ እንደተባለ የሚሰጠውን


ጥቅም እና እነማን እንደጻፉት ያውቃሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

፩- መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው?


፪- መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ የተባለበት ምክንያት ምንድን ነው?
፫- መጽሐፍ ቅዱስ ለምን ለምን ይጠቅማል?


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

1.1 መጽሐፍ ቅዱስ የስሙ ትርጉም ለምን ቅዱስ እንደተባለ


መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በአንድ ጥራዝ የሚገኝ የብዙ መጻሕፍት ሰብስብ
የሆነ የተለየ፣ የተቀደሰ፣ ጽሑፍ ማለትነው። በውስጡም ከኢየሱስ
ክርስቶስ በፊት የተጻፈ ብሉይ ኪዳንና ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ
የተጻፈው አዲስ ኪዳን ተብለው የተከፈሉ መጻሕፍትን የያዘ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሰ የተባለበት ምክንያት ከሌሎች መጻሕፍት የተለየ


በመሆኑ ነው፡፡ የተለየ የሆነው በሚከተለው ምክንያቶች ነው ፡-
1. በመጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ የሚገኙት ጽሑፍች ከቅዱሱ ከእግዚአብሔር
የተገኙ እና የእግዚአብሔር ቃል የያዙ ስለሆኑ፡፡
2. መጽሐፉ ቅድስና ምን እንደሆነ፣ ስዎች ቅዱሱን እግዚአብሔር
በቅድስና እንዲመስሉ የሚመክሩ የሚያስተምሩ ታሪኮችን እና ምክሮችን
የያዘ መጽሐፍ በመሆኑ እና
3. መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነቡትን፣ የሚሰሙትን ፣ የሚያምኑበትና
የተሳለሙትን ሁሉ የሚቀድስ፣ የሚባርክ ስለሆነ ቅዱስ ተብሏል።
4. ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ
5. የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ሁነት እና ወደፊት
የሚፈጸሙትን በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ፤

1.2 መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?


መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በተለያዩ ጊዜ እና ቦታ በነበሩ ከተለያዩ የሥራ
መስክ በተሰማሩ ከ፵ በላይ በሚሆኑ ቅዱሳን ስዎች ሲሆኑ የመጽሐፍ
ቅዱስ ጸሐፊያን እንዲጽፉ ያደረጋቸው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር
መጽሐፍቱን እንዲጽፉ ያደረገበት ምክንያትም ሰዎች በእግዚአብሔር
እንዲያምኑና ሕጉን እና ትእዛዙና አክብረው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው፡
፡ በሌላ በኩልም መጽሐፍ ቅዱስ የጻፉትን ሰዎች የመረጠቸው እርሱ
እግዚአብሔር ነው ሲመርጣቸውም ከተለያዩ ሙያ የነበራቸው ሰዎች
ነው፡፡ እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፉት መካከል የተወስኑት እንመለከት፦

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ፦


ኤርሚያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዘካሪያስ ካህናት ሲሆኑ
ኢሳይያስ፣ ዳንኤልና ሆሴዕ ደግሞ ከነቢያነት
ቅዱስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን ደግሞ ከነገሥነት
ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው አሞፅ ከእረኛነት ነበረ
ከሐዲስ ኪዳን ጽሐፊዎች ደግሞ
ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ የሐንስ፣ ቅዱስ ያዕቆብ እና ቅዱስ እንድርያስ
ከአሳ አጥማጅነት፣ ማቴዎስ (ሌዊ) ከቀራጭነት በመመረጥ መጽሐፍትን
እንዲጽፉ አድርጓቸዋል።

1.3 መጽሐፍ ቅዱስ መቼ ተጻፈ?


• እግዚአብሔር ዘላለም የሚኖር አምላክ በመሆኑ በተለያዩ ዘመናት የነበሩ
ሰዎች በመምረጥ ያጻፈው መጽሐፍ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፉን
የጻፉት ስዎች የኖሩበት ዘመን የተለያየ በመሆኑ መጽሐፍቱም
የተጻፉበት ዘመንም እንዲሁ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ለመመለከት ያህል፦
• እንደ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በመጀመሪያ የተጻፈው
መጽሐፈ ሄኖክ ነው። መጽሐፈ ሄኖክ ዓለም ከተፈጠረ በ1486
ዓ.ዓ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ
በፊት 4014 ቅ.ል.ክ ገደማ ተጽፏል፡፡ ከዚህም ቀጥሎ ሌሎች
• የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ1500 ዓ.ዓ–300 ዓ.ዓ (ዓመተ ዓለም)
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ በፊት
ያለው ጊዜ እና አሁን ያለንበት ዓመት ማለት ነው
• ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐርገ በኋላ ከ45ዓ.ም–
100ዓ.ም ዓመተ ምሕረት ፤ ባሉትነ ጊዜያት ውስጥ ተጽፏል።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

1.4 መጽሐፍ ቅዱስ የት ቦታ/ሀገር/ ተጻፈ?


መጽሐፍቱ በተለያዩ ዘመናት ከመጻፋቸው ባሻገር የተጻፉባቸው ቦታዎች
እንዲሁ የተለያዩ ናቸው።
ለምሳሌ፡- የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ብንመለከት
• አምስቱ የሙሴ መጽሐፍት በሲና ምድረ በዳ
• አሥራ ሁለቱ የታሪክ መጽሐፍት በኢየሩሳሌም
• በባቢሎን የሕዝቅኤልና የዳንኤል በባቢሎን የተጻፉ ሲሆን

የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ስንመለከት ደግሞ፡-


ሐዋርያው ማቴዎስ የጻፈው የማቴዎስ ወንጌል በምድረ ፍልስጤም
፣ የማርቆስ እና የሉቃስ ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል ደግሞ በሮም ሀገር
የተጻፈ ሲሆን የቅዱስ ጳውሎስ እና የቅዱስ ዮሐንስ መልእክታት
በታኛሿ እስያ እና በሮም ግዣት ባሉ ቦታዎች መልእክታት ተጽፈዋል።

1.5 መጽሐፍ ቅዱስ በምን ቋንቋ ተጻፈ?


መጽሐፍቱ በተለያዩ ዘመናት፣ ቦታ እንደ ተጻፉ ሁሉ የተጻፉበትም
ቋንቋ እንዲሁ የተለያዩ ናቸው። ለምሳሌ
• ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት በመጀመሪያ
በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፉ ሲሆን ጥቂት ክፍሎች ግን በአረማይክ
ቋንቋ እንደተጻፉ ሊቃውንት አባቶች ይናገራሉ።
• የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ደግሞ የማቴዎስ ወንጌል በዕብራይስጥ፣
የማርቆስ ወንጌል በሮማይስጥ /ላቲን/፣ የሉቃስ ወንጌል የተጻፈ
ሲሆን የቀሩት ግን በዘመኑ ሥልጣኔ የአብዛኛው ሕዝብ መነጋገሪያ
በሆነው በግሪክ /በጽርዕ/ ቋንቋ ተጽፈዋል።

1.6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅም


መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትሮ የሚያነብ ስው ሕይወቱን በእግዘአብሔር
ቃል መምራት ያስችለዋል ይኸውም የእግዚአብሔር ሕግጋትና ትዕዛዝት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

እንዲከብር ይረዳዋል በተጨማሪም አባት እና እናትን ማክብርን፣ ለስዎች


ሁሉ በጎ ማድረግን የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆኑትን እንስሳትን እና
እጽዋትን መንከባከብ እንዳለበት ሁሉ ለማውቅ ይጠቅማል።

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትክክል የሆነውን እውነት ትክክል ያልሆነውን ደግሞ ሐሰት
በማለት መልሱ።

፩- መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ቅዱሳን ሰዎች ናቸዉ።


፪- መጽሐፍ ቅዱስ ማለት የተለየ መጽሐፍ ማለት ነው።
፫- መጽሐፍ ቅዱስ ስያሜውን ያገኘው አስገኝው እግዚአብሔር ስለሆነ
ነው።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ምዕራፍ ሁሉት
የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈልና ስርጭት

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈልን ፣ የሁለቱ ኪዳናት ግንኙነትን እንዲሁም


መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም መድረክ እና በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል
በቤተ ክርስቲያንችን የሚሰጠውን ክብር ጨምረው ይረዳሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

፩- መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ መጻሕፍት በስንት ይከፈላሉ?


፪- የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ከምንላቸው መካከል የምታውቋቸውን
መጻሕፍት ተናገሩ?
፫- የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ከምንላቸው መካከል
የምታውቋቸውን ተናገሩ።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

2.1 የቅዱሳት መጽሐፍት አከፋፈል


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ መጽሐፍት የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን
መጽሐፍት ተብለው ይከፈላሉ፡፡
የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት የምንላቸው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
ሰው መሆን በፊት ቅዱሳን ሰዎች የጻፏቸውን መጻሕፍት ነው፡፡ እነዚህ
መጻሕፍት የፍጥረታትን አፈጣጠር፣ ስውና መላእክት በተለየ ክብር
ስለመፈጠረቸው የስውን ልጅ መፈጠር፣ ከአዳም በኋላ ስለተነሱ ስዎች
ደግነትና ክፍት የሚተረኩ እግዚአብሔር ከቀደሞት አባቶች ከአዳም ፣
ኖህ፣ አብርሃም እና ከአብርሃም ልጆች ያደረገው ቃል ኪዳን እና ለሰው
ልጆች የስጣቸውን ተስፋ የሚገልጹ መጽሐፍት ናቸው፡፡
የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ከተጻፉበት ጊዜ፣ በያዙት ሐሳብና ከአጻጻፋቸው
ሁኔታ አንጻር በአራት ምድቦች ይከፈላሉ ። እነርሱም፦
1.የሕግ (የኦሪት) መጽሐፍት፦
መጽሐፍት ኦሪት ቃሉ የሱርስት ሲሆን ትርጒሙም
ሕግ ማለት ነው። ብዛታቸው አምስት መጻሕፍት ነው።
2. የታሪክ መጽሐፍት፦
መጽሐፍት ብዛታቸው ዐሥራ ሰባት ነው። በአብዛኛው
የእስራኤልን ሕዝብና የነገሥታቱን ታሪክ በሰፊው ይተርካሉ።
3.የመዝሙርና የጥበብ መጽሐፍት፦
መጽሐፍት መዝሙር ማለት ምስጋና ማለት
ነው። ጥበብ ማለት ደግሞ ማስተዋል ፣መንፈሳዊ ዕውቀት ማንኛውንም
ነገር ለማግኘት የመመርመር ችሎታ ማለት ነው። ስምንት መጽሐፍትን
ይዟል።
4.የትንቢት መጽሐፍት፦ ዐሥራ ስድስት መጽሐፍትን ይዟል።
የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት በኋላ
የተጻፉ፣ መወለዱን በአይሁድ መካከል እየተዘዋወረ ያስተማራቸውን
ትምህርቶች ያደረጋቸውን ታምራቶች እኛን የስው ልጆች ለማድን መከራን
መቀብሉን መሰቀሉን መሞቱን፣ ሞትን ድል አድርጉ መነሳቱንና የአዳም
ልጆች በእርሱ አምነን ተጠምቀን ትእዛዙን እየፈጸምን የምንድንበትን
መንገድ ማበጀቱን የሚናገሩ መጻሕፍቱን ናቸው፡፡ በተጨማሪም ቅዱሳን
ሐዋርያት እና እነርሱ የሰበሰቧትን የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ
እነዚህን ክርስቲያኖችን ለማጽናት ያላሙኑትንም ለማሳመን ሐዋርያት
አባቶቻችን የጻፏቸውን መልእክታትንም ያጠቃልላሉ፡፡
የአዲስ ኪዳን በመጽሐፍት በአምስት ክፍሎች ይከፈላሉ። እነርሱም፦
1. የወንጌል ክፍል፦
ክፍል ወንጌል “ኢቫንጌልዮን” ከሚለው የግሪክ ቃል ተወሰደ
ሲሆን ትርጒሙም ስብከት፣ የምሥራች ማለት ነው። የሚናገረውም
ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የወንጌል መጽሐፍት
የሚባሉትም የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዎቹ ወንጌል የተሰኙት ዐራት
መጽሐፍት ናቸው።
2. የታሪክ መጽሐፍት ክፍል፦
ክፍል ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ ቅዱስ
ጳውሎስ ወደ ሮም እስከ ገባበት ጊዜ ድረስ ያለውን የመጀመሪያይቱን
ቤተክርስቲያን ታሪክ የሚናገር ክፍል ነው። ይኽም ታሪክ ከ፴፬ ዓ.ም
እስከ ፷፬ ዓ.ም ያለው የ፴ዓመት አጠቃላይ የቅድስት ቤተክርስቲያን
መሠረታዊ ታሪክ ነው። ይህንንም ታሪክ የያዘው መጽሐፍ አንድ ሲሆን
እርሱም “የሐዋርያት ሥራ” የተባለው መጽሐፍ ነው።
3. የመልእክት መጽሐፍት ክፍል፦
ክፍል ሐዋርያት ቀደም ሲል ላስተማሯቸውም
ሆነ በዐይን ላዩዋቸው ምዕመናን ከሌላ ቦታ ሆነው የጻፏቸው ናቸው።
ከ፪፭ቱ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት መካከል ሃያ አንዱ መልእክታት
ናቸው። ፲፬ቱ መልእክታት ደግሞ በቅዱስ ጳውሎስ የተጻፉ ሲሆኑ ሰባቱ
መልእክታት የተጻፉት ደግሞ በጴጥሮስ/2/፣ በዮሐንስ/3/፣ በያዕቆብ/1/
እና በይሁዳ/1/ ናቸው።
4. የትንቢት መጽሐፍት ክፍል፦
ክፍል ወደ ፊት የሚሆኑ ድርጊቶችን የሚገልጽ
የትንቢት ቃል ስለ ያዘ ነው። አንድ መጽሐፍ ብቻ የያዘ ሲሆን እርሱም
የዮሐንስ ራእይ ነው።
5. የሕግ (የሥርዓት) መጽሐፈት ክፍል፡-
ክፍል ቤተ ክርስቲያን የምትተዳደርበትን
የአስተዳደር ሥርዓትን የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ የመጻሕፍቱም ብዛት
ስምንት ናቸው።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

2.2 የሁለቱ ኪዳናት ግንኙነት


የሁለቱ ኪዳናት (የብሉይና የሐዲስ) አስገኝ እግዚአብሔር በመሆኑ
ዓላማቸውም አንድ ነው። ብሉይ ኪዳን መነሻ ሐዲስ ኪዳን መድረሻ
ነው ።ሐዲስ ኪዳንን ለማስተማር ብሉይ ኪዳን ይጠቀሳል። ብሉይን
ለመቀጠል ፍጻሜው ሐዲስ ኪዳን ያስፈልጋል። ስለዚህ ያለ ብሉይ ኪዳን
ሐዲስ ኪዳን ያለ ሐዲስ ኪዳን ብሉይ ኪዳን ጎደሎ ወይም ያልተሟላ
ይሆናል። የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት አንድነት በጥቂቱ
ለመመልከት ያህል፡-
• የሁለቱም ኪዳናት መጽሐፍት ዘመን የማይሽራቸው ናቸው፡ “ሣሩ
ይደርቃል፣ አበባውም ይረግፋል የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም
ጸንታ ትኖራለች”/ኢሳ ፵ ፡8/
• የሁለቱም ኪዳናት መጽሐፍት የተጻፉት በአንድ በእግዚአብሔር
መንፈስ አነሳሽነት በተለያዩ ዘመናት ባስነሳቸው ቅዱሳን ላይ በጸጋ
አድሮ የሚጽፉትን እያመለከታቸው የተጻፉ ናቸው። /ዘጸ17፥14፣
ኤር3፥62፣ 30፥2፣ 2ኛጴጥ1፥20፣ ራእ1፥11/
• የሚታየውንና የማይታየውን ፍጥረት የፈጠረ እግዚአብሔር እንደሆነ
ዓለምን ከመፍጠሩ በፊትም ሆነ በኋላ በክብር በአንድነት በሦስትነት
እንዳለ ይገልጣሉ። /ዘፍ1፥2፣ 11፥7፣ ማቴ28፥19፣ ዮሐ1፥1-4
• የሁለቱም ኪዳናት መጽሐፍት የእግዚአብሔርን ባሕርይና ዘላለማዊ
ፈቃዱ ምን እንደ ሆነ አውቀን እንደ ፈቃዱ እንድንመራ ያደርጋሉ።
/ሮሜ 15፥4/
• የሰው ልጅ ትእዛዙን በመጠበቅ በሃይማኖትና በምግባር ሲኖር
የእግዚአብሔርን ርስት የመውረስ ተስፋ እንዳለው ያስረዳሉ።
• መጽሐፍ ቅዱስ (ብሉይና ሐዲስ) የሚያነቡትን፣ የሚሰሙትን ወደ
ቅድስና ስለሚመራ በቅድስና ዓላማው አንድ ነው። /ዘሌ19፥2/


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ
2.3 መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም መድረክ
መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ980 አካባቢ
ወደ ግእዝ ተተርጒሟል። ምንም እንኳን ቅዱሳት መጽሐፍት በመጀመሪያ
የተተረጎሙት ወደ ጽርዕ /ግሪክ/ ቋንቋ ነው የሚሉ ቢኖሩም፤ ሰባው
ሊቃውንት ቅዱሳት መጽሐፍቱን የተረጎሙት ከክርስቶስ ልደት በፊት
በ284 ዓመት ላይ በበጥሊሞስ ዘመነ መንግሥት ነው። በዚህ መሠረት
ወደ ግእዝ ቋንቋ ከተመለሰበት ጋር ሲነጻጸር በመካከላቸው የ696 ዓመት
ልዩነት ይታያል። ስለዚህ የግሪኩ ትርጒም ሁለተኛ መሆኑ ግልጽ
ነው። በሁለቱ መካከል የተተረጎመ የለምና። የግሪኩ ትርጒም ሴፕቱ
አጊንት /የሰባው ሊቃናት ወይም የሰባው ሊቃውንት ትርጒም/ በመባል
ይታወቃል።
ከጌታችን ልደት ወዲህ የግሪኩን ሴፕቱ አጊንት ትርጒም ለማቅናት
በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡት ሲማኩስ፣ አኪላ እና በሦስተኛው
መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ሉቅያኖስ ይጠቀሳሉ።
ከዚህም በኋላ ኑን ክሉስ እና ዮናታን የተባሉ የታወቁ የአይሁድ
ሊቃውንት ብሉይ ኪዳንን ወደ አረማይክ ቋንቋ መልሰዋል። በጌታችን
መዋዕለ ስብከት በእስራኤል የሚነገረው ቋንቋ አረማይክ ነበር። በዚህም
ቋንቋ ጌታችን አስተምሯል።
ምንም እንኳን አንዳንድ መጽሐፍት አስቀድመው በላቲን ቋንቋ
ተተርጒመው እንደበር ቢነገርም በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን (በሄሬዲሞስ
ዘመነ መንግሥት በ366 እ.ኤ.አ) የተነሳው ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት
አባ ጄሮም ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ለ40 ዓመታት የዕብራይስጥና
የግሪክ ቋንቋዎችን በሚገባ በማጥናት መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ቩልጌት
ተርጒሞታል። ትርጒሙም ቩልጌት በመባል ይታወቃል። ቩልጌት በሮም
ይኖሩ የነበሩ “ቩልገስ” እየተባሉ የሚጠሩ ሕዝቦች ቋንቋ ነው። አባ
ጄሮም /ሄሮኒመስ/ ከቩልገስ ቋንቋ ወደ ላቲን እየተረጎመው ሳለ አረፈ።
ይህን የእርሱን ትርጒም ከእርሱ በኋላ የተነሡ ሰዎች እንዳጠናቀቁት
ይነገራል።
፲፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ከዚያም ከላቲን ወደ ጥንታዊ የጀርመኖች ቋንቋ “ጎቲክ” ተተረጎመ።


በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተነሣው ማርቲን ሉተር አልቀበልም ያለው
ይህን ከአባ ጀሮም ትርጒም የተመለሰውን የጎቲክ ትርጒም ነው።
ሶርያ በሱርስት ቋንቋ የተተረጎሙ በርካታ ቅዱሳት መጽሐፍት
እንደነበሯት ይነገራል። በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሮሐ ኤጲስቆጶስ
የሆነው ራቡላ እና የመንበግ ኤጲስቆጶስ የሆነው ፊልክስዮስ ፤ በ7ኛው
መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ ቶማስ ዘሄራክሊያ ለሀገራቸው በሶርያ የነበሩትን
ትርጒሞች በማቅናት ይታወቃሉ። በአርማንያ ቅዱስ ሚስሮኝና ቅዱስ
ሳህክ ከሦስተኛው እስከ ዐራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅዱሳት መጽሐፍትን
ወደ አርመን ቋንቋ መልሰዋል።
የፕሮቴስታንት መሥራች ማርቲን ሉተር የአባ ጀሮምን ትርጒም
አልቀበልም በማለት በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስን በራሱ
አመለካከት ወደ ጀርመንኛ ተረጎመ። ከዚያም በ1525/26 እ.ኤ.አ ቴንዳሌ
በተባለ እንግሊዛዊ የተወሰኑ መጽሐፍት ወደ እንግሊዘኛ ተተረጎመ። ዛሬ
በዓለም ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ከ2123 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉሞ
ተሰራጭቷል።

2.4 መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ


ሕገ ኦሪት እና ወንጌልን በመቀበል ከእስራኤል ቀጥላ አሚነ እግዚአብሔርን
እንደያዘች መጽሐፍ ቅዱስ የሚመሰክርላት ኢትዮጵያ ነች። (1ኛነገ 10፥1-
12፣ሐዋ 8፥26፣መዝ 67፥31) በዚህ እግዚአብሔር በሰጣት የሃይማኖት
ታሪክ የእግዚአብሔርን ቃላት የያዙት ቅዱሳት መጽሐፍትም በየጊዜው
ወደ ሀገር ውስጥ ተተርጉመዋል።
እነዚህም ፦
ሀ. ብሉያት ፦ የብሉይ ኪዳን የሆኑትና አብዛኞቹ ከንጉሥ ሰሎሞን
በፊት የተጻፉት አብዛኞቹ መጽሐፍት በቀዳማዊ ምንሊክ ከክርስቶስ
ልደት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከዚያም ከንጉሡ ጋር የመጡት
ሌዋውያን ካህናተ ኦሪት ግእዝን ተምረው መጽሐፍቱን ወደ ግእዝ
፲፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ተርጉመዋል። ከቀዳማዊ ምንሊክ በኋላም መጽሐፍቶቹ በሚከተሉት


መንገድ ገብተዋል።
ኢየሩሳሌም ለመሳለምና ለንግድ በሄዱ አበው (ጃንደረባው ባኮስ) ሐዋ
8፥26
ከምድረ ከንዓን (እስራኤል) በተሰደዱ አይሁድ በነገሥታት መጻጻፍ።
በኢትዮጵያዊው እና የይሁዳው ዘሩባቤል ተጻጽፈዋል። (ሲራክ ወሰሎሞን
ትርጓሜ)
ከባቢሎን ምርኮ በኋላ ቅዱሳት መጽሐፍትን እንደተለዋወጡ (ሲራክ
ወሰሎሞን መግቢያ ትርጓሜ) ያስረዳል።
ለ. ሐዲሳት ፦ ከክርስትና መግባት በኋላ ደግሞ ብሉይ ከሰባ ሊቃናት
ትርጒም ጋር በማዛመድና የሐዲስ ኪዳንን መጽሐፍት በመጨመር
ወደ ግእዝ የተረጎሙት ቅዱሳን ሊቃውንት ብዙ ናቸው። ከእነኝህም ፦
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ ፍሬምናጦስ 328ዓ.ም በእስክንድርያ
ፓትርያርክ በአትናቴዎስ እጅ ተሹሞ ጃንደረባው በመሠረተው ላይ
ክርስትናን ከማጠናከሩም በተጨማሪ ቅዱሳት መጽሐፍትን ከሱርስት
ከዕብራይስጥና ከጽርእ ቋንቋ መልሷል።
በቢዛንታይን መንግሥት ስቃይ የበዛባቸው ዘጠኙ ቅዱሳን መነኮሳት
ከታናሹ እስያ እና ከሶርያ ተሰደው በ480ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት
የሀገሪቱን የግእዝ ቋንቋ ተምረው አያሌ መጽሐፍትን ከሱርስትና ከጽርእ
ቋንቋ ወደ ግእዝ ከመመለሳቸው በተጨማሪ የሰባው ሊቃውንትን
መጽሐፍት ይዘው መጥተዋል።
በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባ ሰላማ ካልዕ (መተርጒም) ሐዲስ ኪዳንን
ከተለያዩ ቋንቋዎች ወደ ግእዝ ተርጒመዋል። አባ አብርሃም (ግብጾች
አባ ሮሜ ይሏቸዋል) የተባሉት ኢትዮጵያዊ ሊቅ ከጎንደር ተነስተው ወደ
ግብጽ በመሄድ የተለያዩ ቋንቋዎችን በማጥናት ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን
ወደ አማርኛ ተርጒመዋል። ይሄን ትርጒም በእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ
ማኅበር በ1816 ዓ.ም አራቱን ወንጌላት በ1821 ዓ.ም ሐዲስ ኪዳንን
በ1832 ዓ.ም ደግሞ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ታትሞ ወጥቷል። ከዚያ
፲፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ወዲህ በ1878 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሊቃውንት የዕብራይስጡን እና ግሪኩን


ቋንቋ ከሚያውቁ የውጭ ሀገር ዜጎች ጋር በመሆን (ለምሳሌ ማርቲን
ፍላድ) እንደገና በማገናዘብ እንዲታተም አድርገዋል። በ1921ዓ.ም
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተቋቋመው “መጽሐፍ ቅዱስ ትርጒም ኮሜቴ
”የተጀመረው በቤተክርስቲያን ሊቃውንት የማዘጋጀት ሥራ በጣልያን
ወረራ ቢስ ተጓጎልም በሎንዶን በኦፍሴት ታተመ።
1832ዓ.ም የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ያሳተመው የአባ አብርሃም
ትርጓሜ ላይ ማሻሻያ ተደርጎ እና ቤተክርስቲያን የምትቀበላቸው የብሉይ
ኪዳን መጽሐፍት ተካተውበት በ1947 ዓ.ም ተሰራጨ። በ1980ዓ.ም
ከመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር የ1947ዓ.ም እትም እንደገና
ታትሟል።
ከዚያም የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጒምና
ኅትመት ሥራዎችን ያከናወነ ሲሆን መነሻቸው የውጪ ስለነበር እና
66ቱ ብቻ ስለሆነ ቤተክርስቲያን እርምት እንዲሰጥበት ማሳሰቢያ እና
መረጃ ከመስጠት ጋር 27ቱን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት በግእዝና አማርኛ
በ1975ዓ.ም አሳተመች።
በመጨረሻም በ1986ዓ.ም “የቅዱሳት መጽሐፍት ዝግጅት ጉባዔ” ተቋቁሞ
ግእዙን መሠረት ያደረገና ጥንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች ዘርእ
ጠብቆ በአማርኛ 46ቱ ብሉያትና 27ቱን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት
በ2000ዓ.ም ቤተክርስቲያናችን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳትማለች።
በአለቃ ዘነበ ከዚያም በኋላ በአናሲሞስ ነሲቡ በ1899 ዓ.ም ወደ ኦሮምኛ
ቋንቋ ተተረጎመ። በአለቃ ተክለ ወልድ መድኅን ገብሩ በ1948 ዓ.ም ወደ
ትግርኛ ተተርጒሟል። ቅዱሳት መጽሐፍትን ከስር ከስር የተቀበለች
በመሆኗ ለሁለቱም ኪዳናት ብቸኛ ባለቤት የሆነችው ሀገራችን ለሰማንያ
አሐዱ ቅዱሳት መጽሐፍት ብቸኛ ባለቤት ናት።

፲፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

2.5 የመጽሐፍ ቅዱስ ክብር በቤተክርስቲያን


ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለመጽሐፍ ቅዱስ ታላቅ ክብር ትሰጣለች።
በየዕለቱ በሚቀደሰው ቅዳሴ ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጡ ምዕራፎች
ይነበባሉ። ወንጌል ከመነበቡ በፊት የዳዊት መዝሙር በዜማ ይሰማል።
ወንጌል እየተነበበ ሳለም ሁለት ዲያቆናት የእግዚአብሔር ሕግ ለእግራችን
መብራት ለመንገዳችን ብርሃን ነው። የሚል ምስጢር ያለው የጧፍ
መብራት ይዘው ይቆማሉ። ከዚህም በላይ የብርሃናችን ብርሃን የዐይናችን
ብርሃን የእግዚአብሔር ቃል ነው ሲሉ ነው። ወንጌሉን ለመስማት
በሚደረገው ጸሎትም ካህኑ “እኛንም እንደ እነርሱም ወንጌልህን ሰምተን
ለመሥራት የበቃን ታደርገን ዘንድ በቅዱሳን ጸሎት እንለምንሃለን”
ይላል። መጀመሪያውኑ ወንጌልን ለመሥማት የበቃን የተዘጋጀን መሆን
አለብን። ነገር ግን እኛ በራሳችን የበቃን አይደለንምና የቅዱሳን ጸሎት
ያስፈልገናል። ዲያቆኑም “ስለ ወንጌል ጸልዩ” ብሎ ሲያውጅ ሕዝቡ
“ወንጌልህን ለመስማት የተዘጋጀን አድርገን” ይላል። ሕዝቡ ሁሉ
ለወንጌል ከሠጠው ክብር የተነሳ ወንጌል ሲነበብ አይቀመጥም። የወንጌል
ቃል ለዓለም ሁሉ መዳረስ ሲያመለክት ካህኑም ወንጌሉን ከራስ በላይ
ከፍ አድርጎ በመያዝ መንበሩን ይዞራል።

የቤተክርስቲያናችን ስብከት ፣ ማንኛውም መንፈሳዊ ትምህርት በሙሉ


የተመሠረተው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው። ቤተ ክርስቲያን ለትውፊትም
በምትሠጠው ተመሳሳይ ትልቅ ግምት ውስጥም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር
የሚጻረር አንዳችም ነገር አይገኝም። ይልቁንም እያንዳንዱ የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍል በትውፊት የተደገፈ ፣ ትውፊትም በመጽሐፍ ቅዱስ መልቶ
የሚገኝ ነው እንጂ።
በጸሎት ቅዳሴም ይሁን በማኅበር ምንጸልያቸው ጸሎቶች ሁሉ ውስጥ
የምናገኘው በመንፈስ ቅዱስ ያገኘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ፍሬ ነው።
በየሰዓቱ የምንጸልየው ጸሎትም ከዳዊት መዝሙርና ከወንጌል የተወሰደ
ስለሆነ ለኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ጸሎቱ መጽሐፍ ቅዱስን የሚማርበት
፲፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ሌላው መንገድ ነው።


ቤተ ክርስቲያን ምስጢራትን ለመፈጸምም የምትጠቀመው መጽሐፍ
ቅዱስን ነው። ለምሳሌ በምስጢረ ቀንዲል አፈጻጸም ላይ ለሚደረጉት
ሰባቱ ጸሎቶች ሰባት የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎች ይነበባሉ።
በጥምቀትም ለውኃው በሚደረገው ጸሎት ቡራኬ በርካታ ምዕራፎች
ከትንቢት ከመዝሙር፣ ከወንጌልና ከመልእክታት ይነበባሉ።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርአያ በሆነን መሠረት፣
የእግር መተጣጠቡ ሥርዓት በሚፈጽምበት፣ በሕማማቱ ሳምንት ሐሙስ
ዕለት፣ ህማሙን፣ ሥቃይ፣ መከራውን፣ ትኅትናውን የሚናገሩ የብሉይ
ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ይነበባሉ። አዲስ የተሠሩ አብያተ
ክርስቲያናት ለመባረክ፣ ቤቶችን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለመለየት፣
ሥርዓተ ምንኩስናን ለመፈጸም ቤተክርስቲያን የምትጠቀመው መጽሐፍ
ቅዱስን ነው።
ይህ ሁሉ የሚያሳየው ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል ለመጻሕፍ ቅዱስ
የምትስጠው ክብር የሚያሳይ ነው፡፡

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትክክለኛውን መልስ መልሱ።

፩- የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት የሚባሉት በስንት ይከፈላሉ? ዘርዝሯቸው።


፪- መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተተረጎመው ወደ የትኛው ቋንቋ
ነው?
፫- ቤተ ክርስቲያናችን ለመጽሐፍ ቅዱስ የምትሰጠውን ክብር ዘርዝሩ።

፲፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ምዕራፍ ሦስት
የመጽሐፍ ቅዱስ (የቅዱሳት መጽሐፍት) ንባብ ሥርዓት

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማንበብ እንደሚገባቸው አውቀው መጽሐፍ


ቅዱስ የማንበብ ልምድን ያዳብራሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

መጽሐፍ ቅዱስን ከማንበባችሁ በፊት ምን ምን ዝግጅት


ታደርጋላችሁ?

፲፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

3.1 መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ልምድ


መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ሌሎች መጽሐፍት በተገኘው አጋጣሚ፣ ቦታና
ጊዜ የሚነበብ አይደለም። (2ኛጴጥ1፥20) ነገር ግን አንባቢው አንብቦት
ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ እንዲሆን ፣መንፈሳዊውን ትምህርት
ለመማር፣ ራስን ለመገሠጽና ልቡናውን አቅንቶ በጽድቅ ሥራ የተጋ
ይሆን ዘንድ ልዩ የሆነ ውስጣዊና አፍአዊ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል።
2ኛጢሞ3፥16

1.ጸሎት ማድረግ
በባለፈው ትምህርታችን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት በስፋት ተመልክተን
ነበር ከዛም መካከል እግዚአብሔር በዘመኑ በነበሩ ቅዱስን ስዎች
አማካኝነት ለእኛ የጻፈው መጽሐፍት እንደሆነ ገልጸን ነበር በመሆኑም
መጽሐፍ ቅዱስ ለማንባብም ለማጥናትም የእግዚአብሔር ረዳትንና
አገዥነት ያስፈልገናል፡፡ ምክንያቱም ለቅዱሳን መጻሕፍትን እንዲጽፉ
ምስጢርን ስለገለጸላቸው ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ የስው ልጆችን
የሚመክር የሚያስተምር መጽሐፍ እንዲጽፉ አስችሏችአል። አሁንም
እኛም እግዚአብሔር እኛን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹትን ታሪኮች
ሕግች ተግሳጽ እና ምክሮች ምስጢር እንዲገልጽልን እግዚአብሔርን
በጸሎት ልንጠይቅ ይገባል፡፡

2.መምህራን በመጠየቅ እና በማንባብ


ኢትየጵያዊውን ጃንዳረባ ‹‹በውኑ የምትነበውን ታስተውለዋለህን? ብሎ
በጠየቀው ጊዜ ‹‹የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንደምን ይቻላኛል?›› በማለት
በመለሰለት ጊዜ ፊሎጶስ ያነበው የነበረውን የነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ
ተርጉም እንዳስረዳውና ጃንዳረባውም አምኖ እንደተጠመቀ ተጻፏል፡
፡ እኛም መጽሐፍ ቅዱስን ማንባብ እና ያልተተረዳናውን መምህራን
በመጠይቅ መረዳት እንደሚገባን ይህ የጃንደረባው ታሪክ ያስተምረናል፡፡

፲፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ
3.በቤተ ክርስቲያን በምትሰጠው አገልግሎት ውስጥ በመሳተፍ
ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል ከዓመት እስከ ዓመት የሚነገርባት
የእግዚአብሔር ቤት ናት በመሆኑም በዓውደ ምሕረት በሚሰጡ የሰርክ
ጉባኤ በመገኘት፣ በቅዳሴ ሥርዓት በመሳተፍ፣ በሚከበር በዓለት በመገኘት
እና በስንበት ትምህርት ቤት በሚስጡ ተከታታይ ትምህርት በመከታተል
መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንችላለን።

4.ማስታወሻ ማዘጋጀት
አንባቢው ያነበበውን እንዳይረሳ ከሚያነበው ውስጥ የሚገነዘበውን
የሚጽፍበት ማስታወሻ ማዘጋጀትም ይኖርበታል። “ለሚጠይቋችሁ ሁሉ
መልስ ለመስጠት ዘውትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ” 1ኛጴጥ 3፥1

የመልመጃ ጥያቄዎች

ትክክለኛውን መልስ መልሱ።


፩- መጽሐፍ ቅድዱስን ለማንበብ ማድረግ የሚገቡ ዝግጅቶችን ዘርዝሩ።

፲፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

የተግባር ልምምድ

ተማሪዎች አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ወይንም


የአንድ ቅዱስ አባትን ስም አጥንታችሁ በመምጣት
ያጠናችሁትንም ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ምዕራፍ አራት
የመጽሐፍ ቅዱስ መልክዐ ምድር

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የመጽሐፍ ቅዱስ ምልክዐ ምድርን በመረዳት ዓበይት ታሪኮች


የተፈጸመባቸውን ቦታዎችን ያውቃሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሰፊው ተጠቅሰው የሚገኙ


የምታውቋቸውን ሀገራትን ተናገሩ?

፳፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ድርጊቶች የተፈጸሙባቸው ሕዝቦች፣ ሀገሮች፣


ባሕሮች፣ ወንዞች፣ ተራሮች... ወዘተ ይገኛሉ። እነዚህ ሁሉ ግን በየራሳቸው
የየራሳቸው ታሪክ፣ ምሳሌና ትርጒም አላቸው። ይህንን ለመረዳት ይቻል
ዘንድ ደግሞ መጠነኛ ግንዛቤ በዚህ ክፍል እናገኛለን። በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ የምናገኛቸው ታሪኮች አምላካዊ ሥራዎች፣ የቅዱሳን ገድላት...
በጊዜና በቦታ የተከናወኑ ናቸው። እግዚአብሔር ሥራውን የሠራባቸው
ቦታዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሰዋል። ቦታዎቹ ከጥቃቅን ምንጮች
እስከ ታላላቅ ውኃማ አካሎች፣ ከጎድጓዳማ ሸለቆዎች እስከ ሰማይ
ጠቀስ ተራራዎች፣ ከጥቃቅን ዕፅው እስከ ረጃጅም ዝግባዎች... ያሉትን
ያጠቃልላሉ።
በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን የተጠቀሱ መልክአ ምድሮች በሁለት
ይከፈላሉ። እነዚህም የእሥራኤል የቃልኪዳን ሀገር በሆነችው በከንዓን
የሚገኙና ከከንዓን ውጪ ያሉትን ያጠቃልላሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ
የተጠቀሱ ቦታዎች ከሮም እስከ ኢትዮጵያ፣ ከምድረ ዐረብ እስከ ሊቢያ
ያሉትን ሀገሮች ያካትታሉ። አዳም ከተፈጠረባት ኤልዳ ከምትባለው
ምድር ሐዋርያት ለስብከት እስከ ወጡባቸውና እስከ ወረዱባቸው
መንደሮችና ከተሞች ያሉት ቦታዎች እንደ የአስፈላጊነታቸው በመጽሐፍ
ቅዱስ ተጠቅሰዋል። እነዚህን ቦታዎች ማወቅና ማጥናት የእግዚአብሔርን
ሥራ፣ አበው ቅዱሳን ሐዋርያትና ልጆቻቸው የእግዚአብሔርን ወንጌል
ለዓለም ዞረው ለመስበክ በየቦታው ያደረጉትን መንፈሳዊ ተጋድሎዎች
እንድናስተውል ያደርገናል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት መልክአ ምድሮች /ቦታዎች/ ብዙ
ከመሆናቸው የተነሳ በተቻለ መጠን ዐበይት የሆኑትን ብቻ ለመመልከት
እንሞክራለን።

፳፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ
4.1 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችና ሀገሮች
ከተማ ማለት ብዙ ሰዎች አንድ ላይ ተሰባስበው የሚኖሩበት ቦታ
ነው። በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ከተማ ሄኖሕ ትባላለች። ይህች ከተማ
የተሠራችው በቃየን ሲሆን የተሰየመችውም በቃየን የመጀመሪያ ልጅ ስም
እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል።“... ከተማም ሠራ። የከተማይቱንም
ስም በልጁ ስም ሄኖሕ አላት” ዘፍ 4፥16-17 ከዚያም ወዲያ ሰዎች
በአንድነት ለመኖር ሲፈልጉ ውኃ በሚገኝበትና ለምሽግ በሚያመች አምባ
ወይም ተራራ ላይ ቤቶችን በመሥራት ከተማን ይመሠርቱ ነበር።

4.2.1 በሀገረ እስራኤል የሚገኙ ከተሞችና መንደሮች


1. በገሊላ አውራጃ የሚገኙ ከተሞችና መንደሮች
ይህ አካባቢ በምሥራቅ ከሶርያና ከገሊላ ባሕር፣ በሰሜን ከሶሪያ እና
ከሊባኖስ በምዕራብ ደግሞ ከፊንቄ ሀገር ይዋሰናል። የእስራኤል ሰሜናዊ
ጫፍ ነው። ከእስራኤል ምርኮ በኋላ አሕዛብ ወደ ገሊላ ገብተው መኖር
ጀመሩ። 2ኛነገ15፥ 29፣17፥24 በገሊላ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን
አይሁድ ይንቋቸው ነበር። ይህም ሃይማኖታቸው ከአሕዛብ ጋር
የተቀላቀለ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነበር። ዮሐ1፥47፣ዮሐ7፥52 ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌሎች በተለየ በገሊላ አካባቢ ብዙ ጊዜ
አስተምሯል። ተአምራትንም ፈጽሟል። ጌታችን በሚያስተምርበት ወቅት
ሄሮድስ የገሊላ ገዥ ነበር። ሉቃ3፥1፣13፥ 31 ጌታችን ሁለት ጊዜ እንጀራ
አበርክቶ ያበላው እንዲሁም የተራራው ላይ ስብከት የተካሄደውም በገሊላ
አውራጃ ነው። ማቴ14፥16-21፣ 15፥32-39

ሀ) ናዝሬት
ነጭ ድንጋይ ማለት ነው። በገሊላ አውራጃ በስተ ደቡብ ምዕራብ ከገሊላ
ባሕር በስተምዕራብ 24 ኪ.ሜ ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት። የእመቤታችንና
የዮሴፍ የትውልድ ሥፍራ ናት። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን
ያበሠረው በዚህች ሥፍራ ነው።
፳፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ለ) ቃና
ከናዝሬት ከተማ በስተ ሰሜን ምሥራቅ በቅርበት የምትገኝ መንደር
ናት። በብሉይ ኪዳንም የምትታወቅ ከተማ ናት። ኢያ19፥28 ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእመቤታችን አማላጅነት የመጀመሪያውን
ተአምር በዶኪማስ ቤት የፈጸመባት ክብርት ቦታ ናት። ዮሐ2፥1-11
ሐዋርያው ናትናኤል የተወለደው በቃና ነው። ጌታችን ውኃውን ወደ
ወይን የለወጠባቸው ስድስቱ ጋኖች ዛሬም ይጎበኛሉ።

ሐ) ቅፍርናሆም
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጒሙም የናሆም መንደር ማለት ነው።
በገሊላ ባሕር በስተ ሰሜን የምትገኝ የወደብ ከተማ ናት። የታወቀች የዓሣ
ማጥመጃ ሥፍራ ናት። ጌታችን የምኩራብ አለቃውን የኢያኤሮስን ሴት
ልጅ “ጣቢታ ቁሚ” ብሎ ከሞት ያስነሣት በዚህች ቦታ ነው። ማር 5፥22
ትርጒሙም ‘አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ’ማለት ነው። በዚህች ከተማ
ምኩራብ ስለ ነበር ጌታችን ብዙ ጊዜ አስተምሮባታል። ማር 1፥21 ጌታችን
ከአህዛብ ሀገር የነበረውን የመቶ አለቃውን ልጅ ከሽባነቱ የተረተረባት
ማቴ8፥5፣ አጋንንት ያደረባቸውን ሰዎች የፈወሰባት ማቴ8፥16፣ የቅዱስ
ጴጥሮስን አማት ከንዳድ በሽታ ያዳነበት ፣ማቴ8፥ 14፣ እንዲሁ ከ12
ዓመት ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረችውን ሴት ያዳነባት ማር5፥25-
34 ሥፍራ ናት። ይሁን እንጂ በውስጧ የነበሩት ሰዎች ይህን ሁሉ
ተአምራት ቢያዩም አላመኑም ነበር። ማቴ11፥23-25 በዚህም ምክንያት
ጌታችን ስለረገማት ከተማይቱ ጥፍታለች። በመሬት መንቀጥቀጥና
በጦርነት እንዳልነበር ሆናለች። ቅዱስ ማቴዎስ ከመመረጡ በፊት ቀረጥ
ይቀርጥባት የነበረች ሥፍራ ናት። ማቴ9፥ 9-13፣ ማር2፥13-17

መ) ቤተ ሳይዳ
የዓሣ አጥማጅ ቤት ማለት ነው። በኢየሩሳሌም ከተማ በበጎች በርከ
ምትገኘው ቤተ ሳይዳ የተለየች ናት። በገሊላ የባሕር ወደብ በስተሰሜን
፳፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ
ጫፍ ሆና የተሠራች ናት። የቅዱስ ጴጥሮስ፣ የወንድሙ የእንድርያስ እና
የፊልጶስ የትውልድ ቦታ ናት። ዮሐ1፥45፣ዮሐ12፥21 ጌታችን አምስቱን
እንጀራ እና ሁለቱን ዓሣ አበርክቶ ያበላው ከቤተሳይዳ አጠገብ በሚገኘው
ምድረ በዳ ነው።ሉቃ 9፥10-17 ጌታችንም ዕውር የነበረውን ሰው ያዳነውም
በዚህች ከተማ ነው። ማር8፥22-26 እንደዚህ ዓይነት ታላላቅ ተአምራት
ቢደረግባትም ነዋሪዎቿ ግን የጌታን አምላክነት ሊቀበሉ ባለመቻላቸው
በስተሰሜን ምሥራቅ ከምትገኘው ኰራዚን ጋር በአንድ ላይ ተረግመው
ከምድረ ገጽ ጠፍተዋል ።ማቴ 11፥20-21

ሠ)ጌርጌሴኖን
የገሊላ የባሕር ወደብ ሆና ከባሕሩ በስተምዕራብ አዋሳኝ ያለች ከተማ
ናት። ጌታችን በዚህች ከተማ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ፈውሷል።
ነዋሪዎቹ ግን አልተቀበሉትም። ይልቁንም ከሀገራችን ውጣልን
ብለውታል። ማቴ 8፥28-34

የተግባር ልምምድ
.ተማሪዎች ሌሎች በገሊላ አውራጃ ከሚገኙ ከተሞች ውስጥ
ቤቴል፣ ጌልጌላ፣ ጊብዓ፣ ገባዖን፣ ፊልጶስ ቂሣርያ እና
ዓይነከርም ስለ ተሰኙ ከተሞች አጠር ያለ ጽሑፍ ይዛችሁ
በመምጣት ለመምህራችሁ እና ለተማሪዎች በክፍል ውስጥ
አንብቡላቸው።

፳፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

2. በይሁዳ አውራጃ የሚገኙ ከተሞች


የእስራኤል ደቡባዊ ክፍል ነው። በስተ ምሥራቅ የዮርዳኖስ ወንዝ
እየከበበው ከወረደ በኋላ ለሙት ባሕር ይለቅለታል። የእስራኤል ልጆች
ከባቢሎን ምርኮ ተመልሰው ወደ አገራቸው ሲገቡ አብዛኞቹ ከይሁዳ ወገን
ስለነበሩ በከንዓን ሀገር የተቀመጡባት ሥፍራ ይሁዳ ተብሎ ተሰየመ።
ሰዎቹም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አይሁድ ተባሉ። ዕዝ 5፥8 በጌታችን መዋዕለ
ሥጋዌ ጲላጦስ የይሁዳ ገዥ ነበር። ሉቃ3፥1

ሀ) ኢየሩሳሌም
በይሁዳ ኰረብታዎች ላይ ተንጣልላ የምትገኝ በዓለም ላይ የሚኖሩ የብዙ
ሰዎችን ቀልብየ ምትስብ ታሪካዊትና ቅድስት ከተማ ናት። በዕብራይስጥ
“የሩሻላይም” /yerushalayim/ ትባላለች፤ ትርጒሙም የሰላም ከተማ
ማለት ነው። ዐረቦች ግን የተቀደሰች ሲሉ ኤልኩድስ /elkuds/ ይሏታል።
በአራት ተራሮች የተከበበች ከተማ ናት። እነዚህም፦ የሞሪ ተራራ፣ የጽዮን
ተራራ፣ የጋሬብ ተራራ /ኤር31፥39/ እና የቤዜታ ተራራ ናቸው። ከባሕር
ወለል በላይ 750 ሜትር ከፍ ትላለች። ጥንታዊ ስሟ ሳሌም ነበር።
ዘፍ14፥ 18፣ ቀጥሎም ኢያቡስ ተባለች። ኢያ15፥63፣18፥16 ፣ጽዮን
እየተባለችም ተጠርታለች። መዝ136፥1፣ ቅድስቲቱ ከተማ በመባልም
ትታወቅ ነበር። ነህ11፥1 ቅዱስ ዳዊት ኢያቡሳውያንን ድል ካደረጋቸው
በኋላ የይሁዳ ዋና ከተማ አደረጋት። 2ኛሳሙ5፥6-14 ከተማይቱ በተለያዩ
ጦርነቶች ሰባት ጊዜ ፈርሳለች። ጌቴሴማኒ፣ ጐልጐታ እና ጽርሐ ጽዮን
የሚገኙት በኢየሩሳሌም ውስጥ ነው።
ጐልጐታ
የምትገኘው በኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ነው። በዕብራይስጥ የራስ
ቅል ማለት ነው። ጥንት አጽመ አዳም የተቀበረባት ኋላም ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለባት ቅድስት ቦታ ናት።

፳፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ
ጽርሐ ጽዮን
የምትገኘው በጽዮን ተራራ ነው። በጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ለደቀ
መዛሙርቱ ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተባት፣ እግራቸውን ዝቅ ብሎ
ያጠበባት፣ ከትንሣኤውም በኋላ ሁለት ጊዜ የተገለጠባት፣ ቅዱስ ቶማስ
“ጌታዬ አምላኬም” ብሎ የተናገረባት፣ በበዓለ ጰራቅሊጦ ስለ ሐዋርያት
ጸጋ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠባት ቅድስት ቦታ ናት። እመቤታችን ለአሥራ
አራት ዓመታት ተቀምጣበታለች።

ለ) ኬብሮን
የቃሉ ትርጒም ኅብረት ማለት ነው። ከሙት ባሕር በስተ ምዕራብ
ከኢየሩሳሌም ደግሞ በስተደቡብ 30ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ
ከተማ ናት። ከባሕር ወለል በላይ 297 ሜትር ከፍታ አላት። የጥንት
ስሟ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር። ዘፍ23፥2፣ዘፍ35፥27 መቃብረ
አበው እና/ ወይም የመድፌላ ዋሻ እየተባለች ትጠራለች። ዘፍ29፥1-
35፣49፥31፣50፥13 ቅዱስ ዳዊት በእስራኤል ላይ ለ40 ዓመታት ሲነግስ
ሰባቱን ዓመታት ኬብሮንን ሠላሳ ሦስቱን ዓመታት ደግሞ ኢየሩሳሌምን
ዋና ከተማው አድርጎ ነግሧል። 2ኛሳሙ2፥1-5

ሐ) ቤተልሔም
የእንጀራ ቤት ማለት ነው። ጥንት በያዕቆብ ዘመን ኤፍራታት ባል
ነበር። ትርጒሙም የፍሬ መያዣ ማለት ነው። ከብታ እየተባለችም
ትጠራለች። ትርጒሙም ቤተ ስብሐት ማለት ነው። ለዚህ ሥፍራ
ሦስቱን ስም የሰጠው ካሌብ ነው። የቅዱስ ዳዊት የትውልድ ሥፍራ
ናት። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባት ሥፍራ
ናት። ጌታችንም በተወለደ ጊዜ እንስሳት ትንፋሻቸውን የገበሩላት፣ ሰውና
መላእክት በአንድነት ያመሰገኑባት ሰብአ ሰገልን ይመራቸው የነበረው
ኮከብ የቆመባት ቅድስት ከተማ ናት።

፳፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

መ) ቢታንያ
ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በኩል3 ኪሎ ሜትር ርቃ በደብረዘይት
ተራራ ምሥራቃዊ ቁልቁለት ላይ ያለች ኮረብታማ ከተማ ናት። ዛሬ
የዐረቦች መንደር ስትሆን ኤልአዛርያ /የበለስቤት/ ትባላለች። የአልአዛር
፣የማርታና የማርያም ቤት በዚህች ከተማ ነበር። ዮሐ 11፥1፣17፣12፥1-
2 በስምዖን ቤት ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው በዚህች ከተማ ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው በቢታንያ ነው። ሉቃ 24፥50-51

ሠ) ኢያሪኮ
የጨረቃ ከተማ ማለት ሲሆን በጨረቃ የሚያመልኩ ሰዎች ስለነበሩባት
የተሰጣት ስያሜ ነው። በዐርብኛ ደግሞ ሪሃ ትባላለች። ትርጉሙም ሽቱ
ማለት ነው። የቴምር ዛፍ በብዛት ስለሚገኝባት የቴምር አገርም ተብላለች።
እስራኤል ከግብጽ ወጥተው በመጀመሪያ የያዟት ታላቅ ከተማ ናት።
ኢያ6፥1 -21 በኢያሪኮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ይዞታ አላት። ከባሕር ጠለል በላይ 250 ሜትር ከፍታ አላት። ዘኬዎስ
ጌታችንን ለማየት የበቃውና ወደቤቱ አስገብቶ ያስተናገደውም በዚህች
ከተማ ነው። ሉቃ19፥1-10 በርጤሜዎስም ከዕውርነት የተፈወሰው
በኢያሪኮ ነው። ማር10፥46-52

ረ) ጌቴ ሴማኒ
በአረማይክ የዘይት መጭመቂያ ማለት ሲሆን በግእዝ ደግሞ አፀደ ሐመል
ትርጒሙም የአትክልት ቦታ በመባል ይታወቃል። ጌታችን በሰቃዮች
እጅ አልፎ ከመሰጠቱ በፊት በዚህች ሥፍራ ጸልዮአል። ማር14፥32-42
ጌታችን የተያዘውም በዚህች ሥፋራ ነው። የእመቤታችን፣ የእናትና
አባቷ (ሐና እና ኢያቄም) የጠባቂዋ የጻድቁ ዮሴፍ መቃብር የሚገኘው
በዚህ ሥፍራ ነው።

3. በሰማርያ አውራጃ የሚገኙ ከተሞች


፳፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

በስተ ምዕራብ በኩል በሜድትራንያን ባሕር ተገድቦ ከገሊላ በስተ ደቡብ


ከይሁዳ በስተ ሰሜን የሚገኝ አውራጃ ነው። ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን ከሞተ
በኋላ ራሱን በቻለ መንግሥት ይተዳደር ነበር። 1ኛነገ 13፥32፣አሞ3፥9
በሰማርያ የሚኖሩ ሰዎች ሳምራውያን ይባላሉ። አይሁዳውያን ይንቋቸው
ስለ ነበር አይዋደዱም። ዮሐ4፥9

ሀ)ቂሣርያ
በሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ ያለች ከተማ ስትሆን በብሉይ ኪዳን ታሪክ
የላትም። በሐዲስ ኪዳን ግን በይሁዳ ላይ የሚሾሙ የሮማ ገዥዎች
ይቀመጡባት የነበረች በታላቁ ሄሮድስ ዘመን የተሠራችው ከተማ ናት።
ከፊልጶስ ቂሣርያ ትለያለች። ቅዱስ ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስን ከእነ ቤተሰቡ
ያጠመቀው በቂሣርያ ነው። ሐዋ10፥1-48 ቅዱስ ጳውሎስ በቂሣርይ
ለሁለት ዓመታት ታስሯል። ሐዋ24፥27 የሐዋርያው ፊልጶስ ቤትም
በቂሣርያ ነበር። እነ ባስልዮስ ዘቂሣርያን የመሰሉ አባቶች ተገኝተውባታል።

ለ)ሰማርያ
ትርጒሙ የጠባቂ ግንብ ማለት ነው። ከተማዋም አውራጃዋም በዚሁ
ስም ይጠሩታል። ከሰሜን በስተ ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ከኢየሩሳሌም
በስተ ሰሜን 65 ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በሳምርስም ሰማርያ ተብላ
ተጠራች። 1ኛነገ 16፥24 ከተማዋን የመሠረታት ግን ንጉሡ ዘንበሪ ነው።
ዘንበሪ ከሳምር ላይ ተራራውን ሁለት መክሊት በሚመዝን ብር ገዝቶ
ከተማዋን ሠራ። መጥምቁ ዮሐንስ የታሠረውና አንገቱ የተቆረጠው
በሰማርያ ነው።

4.2.2 ሌሎች ከሀገረ እስራኤል ውጭ ያሉ ሀገሮችና ከተሞች


ሀ) ፍልስጤም
በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ
ከእስራኤል በስተ ደቡብ ምዕራብ የሚገኝ ቦታ ሲሆን ሜድትራንያንን በስተ
፳፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ምዕራብ አፍሪካ በተለይም ግብጽን በስተ ደቡብ አዋሳኝ አድርጎ የሚገኝ


አካባቢ ነው። ኢያ13፥3 አባታችን አብርሃም በረሃብ ምክንያት በተሰደደ
ጊዜ ወደ ፍልስጤም ሄዶ ተቀምጧል። ዘፍ20፥1-18 በፍልስጤም የሚኖሩ
ሰዎች ፍልስጤማውያን ይባላሉ። የካም ነገዶች ናቸው። ዘፍ 10፥6-14
እስራኤላውያን ከግብጽ ሲወጡ ፍልስጤማውያንን ፈርተው አቋራጩን
መንገድ ትተው በረዥም መንገድ ተጉዘዋል። ዘጸ13፥17 የማኑሄ ልጅ
ሶምሶን ተነስቶ ድል እስኪ ያደርጋቸው ድረስ እስራኤልን ለ40 ዓመታት
ገዝተዋል። ፍልስጤማውያን ከጥንትም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው።
በተለይም ሦስት የታወቁ ጣዖታት ነበሯቸው።
1) ዳጎን፦ በአዛጦን...1ኛሳሙ5፥2
2) አስታሮት፦ የሴት አምላክ...1ኛሳሙ31፥10
3) ብዔልዜቡል፦ በአቃሮን...2ኛነገ1፥2የዝንብ ጌታ ማለት ነው።

ለ) ኢትዮጵያ
በመጽሐፍ ቅዱስ ከ40 ጊዜ በላይ ስሟ ተጠቅሷል። በመጽሐፍ ቅዱስ
ኢትዮጵያ የሚለው በሰሜን ግብጽ በምሥራቅ ደግሞ የሕንድ ውቅያኖስ
የሚያዋስኑትን ቦታ ሁሉ የሚያካልል ነው። ሀገሪቱ ብዙ መለያዎች
አሏት። ለአብነትያህል፦
የኢትዮጵያ የስም አመጣጥ ይች ሀገር የደረገችው በጌታ ልደት ጊዜ
በንጉሥ ሰለሞን ጊዜ እና ጌታም የመሰከረላት ሀገር መሆኑ
1. በአምልኮተ እግዚአብሔር፦ ዘኁ12፥1
2. በማዕድን ሀብቷ፦ ኢዮ28፥19
3. በተዋጊነቷ፦ 2ኛነገ19፥9፣ 2ኛዜና19፥9፣19፥8፣ ኤር46፥9፣
ዘጸ18፥1፣2፥21፣ ዘኁ12፥ 1፣ ዘጸ18፥12፣ ዘጸ18፥13-27፣ ኤር38፥7-12፣
ኤር39፥15-18፣ ተረፈ ኤር9፥1፣ኤር13፥23፣ አሞጽ9፥7፣ መዝ71፥9-10፣
መዝ67፥31፣ 1ኛነገ10፥1-13፣ 2ኛዜና9፥1-12፣ ማቴ 12፥42፣....
ከኢየሩሳሌም ውጪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
በአራት የተለያዩ ቦታዎች ይዞታዎች አሏት።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

በቤተልሔም፦ መካነ ሰላም የተሰኘ የኢየሱስ ቤተመቅደስ የያዘ ገዳም


ይገኛል።
በቢታንያ፦ /ቤተ አልአዛር/ በስተ ምሥራቅ በአቡነ ተክለሃይማኖት
ስም አንድ ቤተ ክርስቲያን አለ። በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
ለመቃብርነት ይጠቀሙበታል።
በኢያሪኮ፦ “ቤተ አማረች”በተሰኘ ገዳም ውስጥ ወ/ሮ አማረች ዋለለ
የተባሉ ኢትዮጵያዊት ገዝተው የሰጡትና ብጹዕ አቡነ ታዴዎስ ያሠሩት
የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አለ።
በዮርዳኖስ፦ ማኅበረ ሥላሴ ይባላል። በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም በእቴጌ
መነን የተመሠረተ ገዳም ነው።

ሐ) ግብጽ
በብሉይ ኪዳን በጣዖት አምላኪነት ከሚታወቁት ሀገሮች አንዷ ናት።
ነገሥታቶቹ “ፈርዖን” በሚል ማዕረግ ይጠሩ ነበር ። የእስራኤላውያን
የረሃብ ጊዜ የስደት ሀገር ነበረች። አብርሃም በረሃብ ጊዜ ወደ ግብጽ
ተሰዷል። ዘፍ12፥10፣ ያዕቆብና ቤተሰቦቹ በረሃብ ምክንያት ወደ
ግብጽ ተሰደዋል። ዘፍ 48፥27 ፣ ዮሴፍ ተሸጦ ወደ ግብጽ ሄዷል።
ዘፍ 39፥21 ፣እስራኤላውያን በባርነት ለ430 ዓመታት ኖረውባታል።
ዘፍ15፥13 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ክርስቶስን ይዛ
ከጠባቂዋ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደዋል። ማቴ2፥14-
15፣ሆሴ11፥1በሐዲስ ኪዳን ቀድመውክርስትናን ከተቀበሉት ሀገሮች
አንዷ ናት።ኢሳ 19፥21፣ሐዋ2፥10

መ) ባቢሎን
የዛሬዋ ኢራቅ ስትሆን በዕብራይስጥ “ባብኤል” ይሏታል። ትርጒሙም
ድብልቅልቅ ማለት ነው። ጥንት ሰናኦር ይባል የነበረው አካባቢ ነው።
ዘፍ11፥9 በጣዖት አምልኮ ከታወቁት ሀገሮች አንዷ ናት። እግዚአብሔር
ተግሣፅ ቢሰጣትም በእንቢተኝነት ጸንታ ቀርታለች። ከክርስቶስ ልደት በፊት
፴፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ከ 605 – 562 ናቡከደነፆር የተባለው ኃይለኛ ንጉሥ በባቢሎን ነግሧል።


ናቡከደነፆር ማለት ናባው ሥልጣኑን ጠበቀ ማለት ነው።ናባው ከባቢሎን
ጣዖታት አንዱ ነው።ኢሳ46፥1 የኢየሩሳሌምን ከተማና የእስራኤልን ቤት
ያቃጠለ ጨካኝ ሰው ነው። 2ኛነገ25፥8-10 ባቢሎን የክፉ ሥራ ምሳሌ
ናት። ኤር51፥9፣ራእ18፥4፣ኢሳ48፥20 አርጤክስ የተባለው የፋርስ ንጉሥ
በተነሣ ጊዜ ባቢሎንን ቅኝ ግዛት አድርጓታል።

ሠ) ፋርስ
ከጤግሮስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ የነበረች ሀገር ናት። መንግሥቷ ሲስፋፋ
ሱሳ መናገሻ ከተማ ሆነ። የዛሬዋ ኢራን ናት። በንጉሧ አርጤክስ ዘመን
ከኢትዮጵያ እስከ ሕንድ የሚደርስ ግዛት የነበራት ታላቅ ሀገር ነበርች።
ቂሮስ እስራኤላውያንን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ቤተመቅደስ እንዲ
ሠሩ ፈቀደ። ዕዝ 1 የፋርስ ንጉሥ አርጤክስስ አስቴርን አገባ። ስለ አይሁድ
ሕዝብ የለመነችውንም ልመና ተቀበል። (መጽሐፈ አስቴርን ይመልከቱ)
ዕዝራም ብዙ ሰዎችን አስከትሎ ወደ አየሩሳሌም እንዲ መለስና ሕጉን
እንዲያስተምር ፈቀደለት። (ዕዝ7፥8) እንደገናም ተለምኖ የእስራኤልንም
ቅጥር እንዲሠራ ነህምያን ላከው። ነህ2፥1-8 የፋርስ መንግሥት ለረጅም
ዓመታት በገናናነት ቆይቷል። ኋላ ግን ከጌታችን ልደት 330 ዓመታት
አስቀድሞ የተነሣው የግሪኩ ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ድል አድርጎታል።

ረ) ግሪክ
ከጥንቷ ታናሽ እስያከ ዛሬዋ ቱርክ /በመካከል ታላቁ ባሕር ቢኖርም/ በስተ
ምዕራብ የምትገኝ ሀገር ናት። በስተ ደቡብ፣ በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ
የሜዲትራንያን ባሕር ያዋስኗታል። በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ዳንኤል ባየው
ራእይ ውስጥ ተጠቅሳለች። ዳን8፥21 በማርቆስ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው
ልጇ ንጋኔን ያሰቃይባት የነበረችው ሴት ግሪካዊ ናት። ማር 7፥26 የግሪክ
ሰዎች ሐዋርያው ፊልጶስን ወደ ጌታ እንዲያቀርባቸው በጠየቁት ጊዜ
ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አቅርቧቸዋል። ዮሐ12፥20 ግሪካውያን ቋንቋቸው
፴፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ጽርዕ ወይም ግሪክ ይባላል። ብዙዎች የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት የተጻፉት


በግሪክ ነው። የግሪክ ሰዎች ጥበበኞች /በሥልጣኔ ያደጉ/ ነበሩ። ሮሜ1፥14
በሐዲስ ኪዳን ግሪካውያን ክርስትናን ቶሎ ከተቀበሉት ሕዝቦች መካከል
ናቸው። ሐዋ 14፥1፣17፥4፣18፥4፣20፥2፣ዮሐ12፥30 አቴና የግሪክ ዋና
ከተማ የነበረች ስትሆን ተሰሎንቄ፣ ፊልጵስዮስ፣ ቤርያ እና ኒቆጵልዮን
ሁሉ የግሪክ ከተሞች ነበሩ። ቅዱስ ጳውሎስ በሁለተኛውና በሦስተኛው
ጉዞው በግሪክ ሀገር እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥቱን አዳርሷል።

ሰ) ሶርያ
ከገሊላ ወይም ከእስራኤል በስተ ሰሜን በኩል ያለች ሀገር ናት። ዛሬ
የምትጠራው በጥንቷ ስሟ ነው። የሴም ልጅ የአራም ሀገር ናት። ዘፍ
10፥22-23 በአራምም ቋንቋቸው አረማይክ ተብሏል። ከጥንት ከክርስቶስ
ልደት 2000 ዓመት በፊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ዋና ከተማዋ ደማስቆ
ናት ። ሶርያውያን ከክርስቶስ ልደት 850 ዓመት አካባቢ በፊት አዴር
ለሚባል ጣዖት ይሰግዱ ነበር። ብዙ ጊዜ ከእስራኤል ጋር ስትዋጋ ኖራለች።
በንጉሡ በዳዊት ዘመን በጦርነት ተሸንፋለች። 2ኛሳሙ10፥6-19
በሰሎሞን ጊዜ ግን በእስራኤል ላይ አመፀችና ነፃ ወጣች። 1ነገ11፥23-
25 ባኋላ ደግሞ ለበርካታ ጊዜያት በእስራኤል ላይ ጦርነት እያወጀች
በጦርነት ቆይታለች። 2ኛነገ5፥7፣8፥12-13፣ 2ኛዜና16፥10፣20፣28፣27
በሐዲስ ኪዳንም በመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ክርስትና ከተሰበከባቸው
ሀገሮች አንዷ ናት። ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ክርስትና
የተጠራውና የተመለሰው ወደ ደማስቆ ከተማ ሲጓዝ ነው። ሐዋ9፥1-18
ወንጌልን ማስተማር የጀመረውም በደማስቆ ነው። አባናና ፋርፋ የተባሉ
ወንዞች በደማስቆ ዙሪያ ይፈስሳሉ። ደማስቆን በ628ዓ.ም እ.ኤ.አ ግን
ሙስሊሞች በጦርነት ከተማዋን ከያዙ በኋላ የትምህርታቸው ማስፋፊያ
አደረጓት። ነገር ግን ዛሬም በርካታ ተጽዕኖዎችን ተቋቁመው በሶሪያ
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ይገኛሉ። አንጾኪያና ሴሌውቅያ
የተባሉት ከተሞች በሶርያ ይገኛሉ። አንጾኪያ ከክርስቶስ ልደት 301
፴፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ዓመት አስቀድማ የታነጸች ከተማ ናት። ከቅዱስ እስጢፋኖስ መወገር


በኋላ ወደ አንጾኪያየ ተሰደዱ ክርስቲያኖች ነበሩ። እነርሱም በዚያ
ሲያስተምሩ አንድ ዓመት ያክል ከቆዩ በኋላ ደቀመዛሙርት በመጀመሪያ
በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ። ሐዋ 11፥19-26 ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ
በርናባስ በአንጾኪያ አስተምረዋል። ሐዋ 15፥35፣ ሐዋ 13፥1-3

የመልመጃ ጥያቄዎች

ትክክለኛውን መልስ መልሱ።


፩- በይሁዳ አውራጃ የሚገኙትን ከተሞች ዘርዝሩ።
፪- ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምን በምን ትታወቃለች?
፫- ጌታችን የተወለደበት ስፍራ የት ነው?

፴፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ምዕራፍ አምስት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ የውሃ አካላት እና የየብስ
ምድር

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የመጽሐፍ ቅዱስ ምልክዐ ምድርን በመረዳት ዓበይት ታሪኮች


የተፈጸመባቸውን የውሃ አካላትን እና የየብስ ክፍሎችን ያውቃሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እና ወንድሙ


ያዕቆብ ዓሳ ያጠምዱበት የነበረው ባሕር ምን እየተባለ
ይጠራል?

፴፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ባሕሮች
በሀገረ እስራኤል ሁለት ታላላቅ ባሕሮች ይገኛሉ። አንደኛው የገሊላ
ባሕር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሙት ባሕር ነው።

የገሊላ ባሕር
ዛሬ ጥብርያዶስ እየተባለ የሚጠራው ነው። ዮሐ21፥1 የጌንሳሬጥ ባሕርም
ይባላል። ማቴ4፥18፣ሉቃ5፥1 ጥብርያዶስ እና ጌንሳሬጥ በባሕሩ ወደብ
የሚገኙ ከተሞች ናቸው። ሄሮድስ አንቲጳስ በገሊላ ባሕር ምዕራባዊ ዳርቻ
ከተማ ከመሠረተ በኋላ በጢባርዮስ ቄሣር ስም ጥብርያዶስ ብሎ ሰየማት።
የባሕሩ ርዝመት 4.5 ኪ.ሜ ሲሆን ወርዱ ደግሞ 8ኪ.ሜ ነው። የባሕሩ
ጥልቀት በአማካይ ከ208.5ሜትር እስከ 213ሜትር ከባሕር ጠለል በታች
ነው። የመጨረሻው ጥልቅ ቦታ ግን ከባሕር ጠለል በታች እስከ 254
ሜትር ይጠልቃል። በባሕር ውስጥ 25 የዓሣ ዓይነቶች ስለሚገኙ በዓሣ
ምርት የታወቀ ነው። በዚህ ባሕር ላይ ጌታችን ለማስተማር ብዙ ጊዜ
ተመላልሷል። ብዙ ተአምራትንም አድርጎበታል።

የጴጥሮስን መረብ እስኪ ቀደድ ድረስ በዓሣ ሞልቶታል። ሉቃ5፥1-11


ዓሣው በባሕሩ ውስጥ እያለ የእነ ስምዖን ጴጥሮስ መረብ ግን ባዶ ሆነ።
ጌታችን ሲመጣ ግን ዓሣና መረብ ተገናኙ። እግዚአብሔር ያልገባበት
ኑሮና ሥራ ሁሉ እንዲህ ነው። ገንዘብ ይዞ መራብ ፣መታመምና
መሰቃየት ይኖራል። እግዚአብሔር ግን ጥቂቱ ይበዛል። የተጣላው
ይታረቃል፤ የተራራቀው ይቀራረባል።
ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚህ ባሕር በታንኳ ሲጓዝ ተነሥቶ
የነበረውን የማዕበል ንውጽውጽታ ፀጥ አድርጎታል። ማቴ 8፥23
ለአምላክነቱ አልገዛም የሚል ፍጥረት የለምና። ጌታችን በባሕሩ ላይ
በእግሩ ተራምዷል። ማቴ 14፥22-23 ቅዱስ ጴጥሮስ ከጌታችን ታዝዞ
ለተጠየቁት ግብር የሚከፍሉትን ሁለት እስታቴር ያገኘበትን ዓሣ
አጥምዶ ያወጣው በዚህ ባሕር ነው። ማቴ17፥24-27 በዚህ ባሕር አጠገብ
፴፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ጌታችን ከትንሣኤ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ ተገልጧል። ያጡትንም ዓሣ


ሰጥቷቸዋል። አብሯቸውም ተመግቧል። ዮሐ21፥1-14 ቅዱስ ጴጥሮስ“
ግልገሎቼን አሠማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጎቼን አሠማራ” የተባለው
በገሊላ ባሕር አጠገብ ነው። ዮሐ21፥15-17

ሙት ባሕር
ጨው ይበዛበታልና “ጨው ባሕር” ተብሏል። ከባሕሩ 3 ኪሎ ውኃ
ውስጥ 1ኪሎ ጨው ይወጣል። “ሙት ባሕር” ይባላል ። የባሕሩ ዙሪያ
በድኝና በቅጥራን (ዝፍት) የተከበበ ስለሆነ ሕይወት ያለው ነገር ፈጽሞ
አይገኝበትም። ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በ ኢያሪኮ በስተደቡብ የሚገኝ
ባሕር ነው። 88 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ከባሕር ወለል በታች
467 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ታች እየወረደ
ነው ይባላል። “ባሕረ ሎጥም” ይባላል። ሰዶምና ገሞራ ከመጥፋታቸው
በፊት የብስ የነበር ቦታ ነበር። ዘፍ19፥1-29 የዮርዳኖስ ወንዝ በየቀኑ
6 ሚሊዮን ቶን ውኃ ለባሕሩ ይገብራል። ሌሎችም ወንዞች ወደ ባሕሩ
፴፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

የሚገብሩ አሉ።
ባሕረ ኤርትራ
እስያና አፍሪካን የሚለያይ ባሕር ነው። ርዝመቱ 2175ኪ.ሜ ሲሆን ስፋቱ
ደግሞ 370ኪ.ሜ ነው። በአንዳንድ ቦታዎች የ1830 ሜትር ጥልቀት
አለው። ወደ ባሕሩ የሚገባ ምንም ዓይነት ወንዝ የለም። እስራኤላውያን
ከግብጽ ባርነት ነጻ ሲወጡ በዚህ ባህር ውኃው እንደ ግንብ ቆሞ መሀሉ
ደረቅ መሬት ሆኖ ተሻግረው ሀገራቸው ገብተዋል ።ዘጸ14፥15-31
በባሕረ ኤርትራ እና በሜዲትራን ያን መካከል የስዊዝ ቦይ (Suez Ca-
nal) በመባል የሚታወቅ ሰው ሠራሽ ልሳነ ምድር ይገኛል። ይህ ምግብ
ጽና እስራኤልን በደረቅ መሬት የሚያገናኘው ቦታ ነው።

ወንዞች
ወንዝ ማለት ከአንድ ቦታ ተነሥቶ ወደ ሌላ ስፍራ የሚፈስ (ፈሳሽ) ውኃ
ነው። ሁለት ዓይነት ወንዞች አሉ።ክረምት ከበጋ የማይደርቁ ወንዞች እና
በዝናብ ጊዜ ብቻ የውኃ ፈሳሽ የሚገኝባቸው ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ የታወቁ ወንዞች አሉ። እነዚህ ወንዞችም በእስራኤል ምድርና
፴፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በሚያነሣቸው ሀገሮች ይገኛሉ።


የዮርዳኖስ ወንዝ
ከአርሞንኤም ተራራ ግርጌ ተነሥቶ በገሊላ ባሕር በማለፍ ወደ ጨው
ባሕር ይፈሳል። የወንዙ ስፋትና ጥልቀት እንደ ዝናቡ መጠን ይለዋወጣል።
ይኸውም ከአንድ ሜትር እስከ ሦስት ሜትር ጥልቀትና እስከ ሠላሳ
ሜትር ስፋት የሚደርስበት ወቅት ይኖራል። በዮርዳኖስ ወንዝ በተለያዩ
ጊዜያት ገቢረ ተአምራት ተፈጽመውበታል።
የቃልኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ወደዮ ርዳኖስ ወንዝ ሲገቡ
የሞላው ውኃ ከሁለት ተከፍሎ በሩቅ በመቆሙ እስራኤል በኢያሱ
መሪነት በደረቅ ተሻገሩ።

ነቢዩ ኤልያስም በመጎናጸፊያው ከፍሎት ተሻግሯል። 2ኛነገ2፥8


ነቢዩ ኤልሳዕም በኤልያስ መጎናጸፊያ ከፍሎት ተሻግሯል። 2ኛነገ2፥14
ንዕማን የተባለ የሶርያ የሠራዊት ዓለቃ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ
፴፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ከለምጽ ነጽቷል።2ኛነገ5፥10-14
ታላቁ የእግዚአብሔር ሰው ኢዮብ በሰውነቱ ላይ ከወጣበት ደዌ የተፈወሰው
በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ነው።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ አርአያ ሊሆነን ና የጥምቀትን ሥርዓት
ሊሠራልን ምስጢረ ሥላሴንም ሊገልጥልን የተጠመቀው በዚህ ወንዝ
ነው።ማቴ3፥13-17

ግዮን
በኢትዮጲያ የሚገኝ ወንዝ ነው። የጣናን ሐይቅ ከሁለት ከፍሎ ይጓዛል።
በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የዓባይ ወንዝ ተብሎ ተጠቅሷል።
ኢሳ19፥7-8፣23፥3 በበረሃማው የግብጽ ምድር የዓባይ ወንዝ የሚያልፍበት
ቦታ ሁሉ ለምለም ነው። ሱዳንና ግብጽን አጠጥቶ ወደ ሜዲትራንያን
ባሕር ይገባል። ከመነሻው እስከ መድረሻውያለው ርቀት 6470 ኪሎ
ሜትር ያህል ነው። የሙሴ ወላጆች ከፈርዖን ትእዛዝ የተነሣ ሙሴ
እንዳይሞትባቸው ከዓባይ ወንዝ ዳር ሸሽገውታል።ዘጸ2፥1-10 ፈርዖን
እስራኤልን አልለቅም ብሎ ልቡን ባጸናበት ወቅት ከእግዚአብሔር
በታዘዘው መሠረት በግብጽ ምድር ብቻ የዓባይ ውኃ ወደ ደምነት
ተቀየረ። ዘጸ7፥20-21

ተራሮች
ተራራው ከሜዳውና ከደልዳላው መሬት ከፍ ያለ የመሬት ክፍል ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስም ብዙ ተራሮች ተጠቅሰው ይገኛሉ።

1. ደብረ ሲና
ደብር ማለት ተራራ ማለት ነው። ደብረ ሲና ማለት የሲና ተራራ ማለት
ነው። ኮሬብ እየተባለም ይጠራል። ዘጸ3፥1 ፣ዘዳ4፥ 9-10 የእግዚአብሔር
ተራራም ይባላል። ዘጸ3፥1 ፣1ኛነገ19 ፥8 ከግብጽ በስተ ምሥራቅ
ከእስራኤል ደግሞ በስተ ደቡብ ይገኛል። እግዚአብሔር ለሊቀ ነቢያት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ሙሴ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጠለት በዚህ ተራራ ነው። ዘጸ3፥2-1 2


እግዚአብሔር በሙሴ በትር አማካኝነት ከዓለት ውኃ አፍልቆ ለሕዝበ
እስራኤል ያጠጣው በኮሬብ ተራራ አጠገብ ነው። ዘጸ17፥5-7 እግዚአብሔር
በዚህ ተራራ ለሙሴ በደመና በነጎድጓድና በመብረቅ ተገልጦለታል።
ዘጸ 19፥16-25 በሁለት የድንጋይ ጽላት የተጻፉት ዐሥርቱ ትእዛዛት
ለሙሴ የተሰጡት በዚህ ተራራ ነው። ዘጸ 34፥28 ለሁለተኛ ጊዜ ጽላቱን
ለመቀበል ወደ ተራራው ወጥቶ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በጾም ቆይቷል።
ዘጸ34፥28 በዚህ ሥፍራ ግሪኮች “ቤተክርስቲያን” ሠርተዋል።

2.ሞሪያ
ከኢየሩሳሌም ከተማ በስተ ምሥራቅ ይገኛል። አብርሃም በስተርጅና
ያገኘውን ልጁን ሊሠዋበት የሄደበት ተራራ ነው። ዘፍ22፥2 ጠቢቡ
ሰሎሞንም በዚህ ተራራ ቤተ መቅደሱን እንደሠራ መጽሐፍ ቅዱስ
ይናገራል። 2ኛዜና3፥1

3. ደብረ ታቦር
ከገሊላ ባሕር በስተ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት
ላይ ከናዝሬት ደግሞ በስተ ምሥራቅ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብ
የሚገኝ ተራራ ነው። ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ከፍታ አለው።
የዛብሎንን ፣ የይሳኮርን ና የንፍታሌምን ርስት ያዋስናል ።እንግልጣሮች
(እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች) Transfiguration Mount ይሉታል። ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደ ገለጠበት
ሲያጠይቁ ነው። ዐረቦች ደግሞ ጀበልቶር (DjebolTor=Mountainoft-
hebull) ይሉታል። በዚህ ተራራ ባርቅና ዲቦራ የእስራኤል ጠላት ሆኖ
የተነሣውን ሲሣራን ድል አድርገውበታል። መሳ4፥4-2 4 በልምላሜ
የተሞላ ተራራ መሆኑ ይነገርለታል። በሐዲስ ኪዳን ስሙ አይጠቀስ
እንጂ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ረጅም ተራራ የተባለው
እርሱ ነው። ማቴ17፥1- 9፣ መዝ88፥ 12 በዚህ ምክንያት ሊቀ ሐዋርያት
፵፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ቅዱስ ጴጥሮስ“ ቅዱስ ተራራ” ብሎታል። 2ኛጴጥ 1፥18 በደብረ ታቦር


ግሪኮችና ላቲኖች (ሮማውያን) በ1923 ዓ.ም እ.ኤ.ዕ “ቤተክርስቲያን”
ሠርተዋል።

4.ደብረ ዘይት
የዘይት ታራራ ማለት ሲሆን በወይራ ዛፍ የተሸፈነ በመሆኑ የተሰጠው
ስያሜ ነው። 800 ሜትር ያህል ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ አለው።
ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በቅርብ የሚገኝ ቦታ ነው። ጌታችን ቀን
ቀን ኢየሩሳሌም ከተማ ሲያስተምር ውሎ ወደ ማታ በደብረ ዘይት ተራራ
በኩል ወደ አልዓዛር ቤት ቢታንያ ለማደር ይሄድ ነበር። ማር11፥ 19፣
ማቴ21፥17 ከተራራው ግርጌም ቤተፋጌና ቢታንያ የሚባሉ መንደሮች
ይገኛሉ። ከፍታ ያለው ተራራ በመሆኑ ከጫፉ ላይ ሆኖ ኢየሩሳሌምን፣
፵፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ኤዶምያስን፣ ሞዓብንና አሞንን ማየት ይቻላል። ጌታችን ማታ ማታ


ያድርበት የነበረ ሲሆን ጥንት መቃብረ ነቢያት እንደ ነበር ይነገራል።
ጌታችን ስለ ነገረ ምጽአት ያስተማረው በዚህ ተራራ ነው። ማቴ 24፥3
፣ 25፥31-46 ቅድስት ቤተክርስቲያንም ጌታችን በደብረዘይት ዓለምን
ሊያሳልፍ እንደሚመጣ ተስፋ ታደርጋለች። ዘካ 14፥4 ጌታችን በሆሳዕና
ዕለት በአህያ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ከዚህ ተራራ ተዳፋት ተነሥቶ
ነው። ማር 11፥1 ጌታችን የተያዘውም ከተራራው ግርጌ በምትገኘው
ጌቴሴማኒ ነው። ማቴ 26፥30-36 ጌታችን ወደዚህ ዓለም የመጣበትን
የቤዛነት ሥራ ከፈጸመ በኋላ ያረገው በዚህ ተራራ ነው። ሉቃ24፥51-52
፣ ሐዋ 1፥12 ዛሬ ግን ቦታው በመሐመዳውያን እጅ ይገኛል። ጌታችን
አቡነ ዘበሰማያትን (አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት) ያስተማረው በዚህ
ሲሆን ዛሬ ግን በ35 ቋንቋዎች ጸሎቱ ተጽፎ ይገኛል። ከእነዚህም
ቋንቋዎች አንዱ ግእዝ ነው።

፵፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ምንጮች
ትናንሽ የሆኑና ለመጠጥነት የሚያገለግሉ ውኃማ ቦታዎች ምንጮች
ይባላሉ። የአጋር ምንጭ የሣራ አገልጋይ የነበረችው አጋር ከአብርሃም
እንዳረገዘች ባየች ጊዜ ሣራን ናቀቻት። በዚህ የተነሣ ከአብርሃም ቤት
ተባርራ ወጣች ፤ በምድረ በዳ ውኃ ጥም ጸንቶባት በተቸገረችና ባለቀሰች
ጊዜ መልአከ እግዚአብሔር ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ
ባለች ምንጭ ጎን ተገለጠላት። የዚያችም ምንጭ ስም ብኤርለሃይሮኢ
ተባለ። ዘፍ 16፥1-14

የያዕቆብ ምንጭ
ሲካር በምትባለው የሰማርያ ከተማ ትገኛለች። ሲካርም ከሴኬም በስተ
ደቡብ በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች። የዕቆብ
ከአጎቱ ሀገር ከሶርያ ሲመለስ በከንዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም
ከተማ መጣ። ድንኳኑን ተክሎበት የነበረውን የእርሻ ማሳ ከሴኬም አባት
ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛ። በዚያም ያዕቆብ ለራሱ ያስቆፈራት
ምንጭ ነበረች። ያዕቆብ ና ቤተሰቦቹ ሁሉ ከዚያች ምንጭ ሲጠጡ ኑረዋል
። ዘፍ 33፥18-20 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁዳን
ትቶ ወደ ገሊላ በሔደበት ወቅት በሰማርያ ወደ ምትገኘው ወደ ሲካር
መጣ የሥጋን ገንዘብ ባሕርይው አድርጓልና ከመንገዱ ርዝመት፣ ከዋዕዩ
ብርታት የተነሣ ደከመው፤ ተጠማም በሲካር ወደምትገኘው የያዕቆብ
ምንጭ ቀርቦ ከአንዲት ሳምራዊት ሴት ውኃ ለመነ። እርሱ የሕይወት
ውኃ እንዳለውና እርሱ ከሚሰጠው የሕይወት ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ
ማይጠማ አስተማራት። የተሠወረ ሕይወቷን ገልጦ በማስተማሩም
ሳምራዊቷ ሴት በእርሱ ከማመኗም በላይ የከተማውን ሰው በሙሉ
ጠርታ ከእርሱ ተምረው አምነውበታል። ይህ ሁሉ የተከናወነው በያዕቆብ
ምንጭ አጠገብ ነው። ምንጩ 32 ሜትር ያህል ጥልቀት አለው።
ዮሐ4፥1-32

፵፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ሜዳዎች
ሜዳዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዛት ተጠቅሰው አይገኙም።
የሰናዖር ሜዳ
በባቢሎን ዙሪያ ያለ ሰፊ ሜዳ ሲሆን ከኖኅ ዘመን የጥፋት ውኃ በኃላ
የተነሡ ሰዎች ግን በመገንባት የጀመሩት በዚህ ሜዳ ነው። የሰው ልጆች
ቋንቋ የተለያየበት (የተደበላለቀበት) ስለሆነ ባቢሎን ተብሏል። ባቢሎን
ማለትም ድብልቅልቅ ማለት ነው። ዘፍ11፥1-9

የአርማጌዶን ሜዳ
ከቀር ሜሎስ ተራራዎች በስተ ደቡብ ከደብረ ታቦር ተራራዎች ፊት
ለፊት የሚገኝ ሜዳ ነው። ቀድሞ በቀርሜሎስ ተራራዎች ከሰሜን ወደ
ደቡብ ጋዛንና ደማስቆን የሚያገናኘውን መንገድ ለመጠበቅ የተመሸገ
ከተማ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ሜዳ ሰዎች አይኖሩበትም። ዲቦራና
ሲሣራን ድል ያደረገችው፣ ፈርዖን ኒካውም ኢዮስያስን የገደለው በዚሁ
፵፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

በአርማጌዶን ሜዳ አጠገብ ነው። መሳ5፥ 19፣ 2ኛነገ 23፥29-30 የዓለም


መጨረሻ ምልክት የሚሆን ጦርነት ይደረግበታል። ራእ16፥12-16
አርማጌዶን ማለትም መካነ ድምሳሴ (የመደምሰሻ ቦታ) ፣መካነ ስራዌ (
የማነቂያ ቦታ) ማለት ነው። ዘካ12፥11-14

ሸለቆዎች
ሸለቆ ማለት ጎድጓዳ የሆነና የሚሞቅ፣ ሐሩር የበዛበት ቦታ ማለት ነው።

የሄኖም ሸለቆ
ስያሜውን ሄኖም ከተባለው ሰው እንዳገኘው ይነገርለታል። ከቄድሮስ
ወንዝ በታች ከጥንታዊው የኢየሩሳሌም ከተማ በምዕራብና በደቡብ በኩል
ይገኛል። ይሁዳና ብንያም በዚህ ሸለቆ ይዋሰናሉ። ኢያ15፥8 ከኢዮስያስ
በፊት የነበሩ ነገሥታት በሄኖም ሸለቆ የጣዖት መስገጃዎችን ሠርተው
ሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸውን ሳይቀር ይሠዉቡት ነበር። ኤር19፥1-9 ፣
2ኛ ዜና28፥1-4፣ 2ኛዜና33፥1 7 ፣ 2ኛነገ16፥3 ይሁን እንጂ ኢዮስያስ
በነገሠ ጊዜ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር መንገድ በመሔዱ
በሄኖም የነበሩ የማምለኪያ አፀዶችንና መሠዊያዎችን አጠፋቸው።
2ኛነገ23፥10-14

የኢዮሳፍጥ ሸለቆ
ኢዮሳፍጥ ከ870 እስከ 845 ከክርስቶስ ልደት በፊት በይሁዳ የነገሠ
አራተኛው ንጉሥ ነው። እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያሸንፍ ዘንድ ኃይል
ስለሰጠውና ጠላቶቹንም ድል ስላደረጋቸው፣ ምርኮአቸውንም ከወሰደ
በኋላ በዚህ ሸለቆ ፈጣሪውንም ስላመሰገነበት የኢዮሳፍጥ ሸለቆ ተባለ።
የኢዮሳፍጥ ሸለቆ በኢየሩሌምና በደብረ ዘይት መከከል የቄድሮን ወንዝ
ይፈስበታል። በአሁኑ ጊዜ ብዙ የአይሁድና የእስላም መቃብር ይገኝበታል።
ነቢዩ ኢዩኤል በኢዮሳፍጥ ሸለቆ በሕዝብና በአሕዛብ ላይ እግዚአብሔር
የሚፈርድባቸው መሆኑን ተናግሯል። ኢዩ3፥2-12 በኢየሩሳሌም ነግሠው
፵፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

የነበሩ ነገሥታት ሥጋ በዚሁ ሸለቆ የተቀበረ መሆኑም በተለያዩ


መጽሐፍት ተገልጧል።

ዋሻዎች
ዋሻ ማለት በተፈጥሮም ሆነ በሰው ኃይል የተቦረቦረ፣ የተፈለፈለ
መሬት ቋጥኝ ነው። ብዙውን ጊዜ ዋሻ መናንያን ገብተው ይጸልዩበታል።
ስደተኞች ይጠጉበታል። አራዊትም ይኖሩበታል። በመጽሐፍ ቅዱስም
የተለያዩ ዋሻዎች ተመዝግበዋል።

የኤልያስ ዋሻ
በይሁዳ በረሃ ይገኛል። በዐረብኛ ዋዲከልት ይባላል። ነቢዩ ኤልያስ
ለእግዚአብሔር ቀንቶ አምልኮቱን የዘነጉትን አክዓብንና ኤልዛቤልን
ከነሠራዊታቸው ለመቅጣት ሲል ሰማይ ዝናብ ለዘር ፣ ጠል ለመከር
እንዳትሰጥ ለጎመ። በዚህ የተነሣ አክዓብ እንዳይገድለውና በረሃብም
እንዳይጎዳ ልዑል እግዚአብሔር “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሒድ
፣ በዮርዳኖስም ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸገ። ከወንዙም
ትጠጣለህ ቁራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ” አለው።
እንደተናገረውም ቁራዎች በጠዋትና በማታ ኅብስትና ሥጋ እያመጡ
ኤልያስን ይመግቡት ነበር። ያቺ ኤልያስ የተሸሸገበት ፈፋ (ዋሻ) የኤልያስ
ዋሻ ትባላለች። 1ኛ ነገ 17፥1-7

፵፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

የመልመጃ ጥያቄዎች

በ “ሀ” ረድፍ ያሉትን በ “ለ” ረድፍ ካሉት ጋር አዛመዱ።


ሀ ለ
1. የኤርትራ ባህር ሀ. ኢትዮጵያ
2. ዮርዳኖስ ለ. ጌታ የተጠመቀበት ወንዝ
3. ግዮን ወንዝ ሐ. ሙሴ እስራኤላውያን ያሻገረው
4. ደብረ ዘይት መ. ጌታችን ያስተማረበት ቦታ
5. ሞሪያም ተራራ ሠ. አብረሃም መስዋዕት ያቀረበበት
ቦታ

፵፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ምዕራፍ ስድስት
የሥራ መስክ እና መገበያያ በመጽሐፍ ቅዱስ

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች


የተሰማሩባቸውን የሥራ መስክ እና የሚገበያዩበትን መገበያያዎች
ለይተው ያውቃሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምታውቋቸውን ሀኪም ፣ ዓሳ


አጥማጅ ፣ ድንኳን ሰፊ ፣ ቀረጥ ሰብሳቢ ፣ ገበሬ ወዘተ
ሰዎችን ጥቀሱ።

፵፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

የሥራ መስክ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለያዩ የሥራ መስኮች ተጠቅሰው ይገኛሉ።
አዳም “በሕይወት ዘመንህ ሁሉ በድካም ከእርሷ ትበላለህ ”ከተባለበት ጊዜ
ጀምሮ የሰው ልጅ ኑሮውን ለማሸነፍ በተለያዩ የሥራ መስክ እየተሰለፈ
ኖሯል። ዘፍ 3፥17 የሰው ልጅ እንደተፈጠረ ሥራ እንዲሠራ ተደርጓል።
ዘፍ 2፥15 ከአስርቱ ትእዛዛት መካከልም አንዱ ሥራ መሥራት እንደሚገባ
የሚናገር ነው። ዘጸ 20፥9

ቅዱስ ጳውሎስ በተሰሎንቄ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ሠርተው እንዲኖሩ


መክሯቸዋል። 1ኛ ተሰ 4፥12 “ሊሠራ የማይወድ አይብላ” 2ኛተሰ 3፥14
ሥራ እንድንሠራ የታዘዝን ቢሆንም ሥራችንን ሁሉ እንዲያቃናልን
ፈጣሪያችንን መማጸን ይኖርብናል። “በቃል ቢሆን በሥራ የምታደርጉትን
ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉት” ቆላ 3፥17
ዋናው ቁም ነገር ሥራን ሳይንቁ በሥራ ተሰማርቶ መገኘት እና ረድኤተ
እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግ ነው። የሥራ ዘርፎች ከጥንት ጀምሮ
ነበሩ። ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰዋል።
ግብርና ፦ እርሻን ፣ ከብት እርባታንና አደንን የሚያጠቃልል የሥራ
መስክ ነው። ገበሬ የሚለው በአብዛኛው የእርሻ ሥራን ሲያመለክት
ይገኛል።

እርሻ ፦ በሀገረ እስራኤል እንደ ወይን ፣ስንዴ ፣ የወይን ዛፍ ፣ ተምር


እና በለስ የመሳሰሉት ይመረታሉ። የእርሻ ሥራ ከአዳም ጀምሮ ተያይዞ
የመጣ ነው። ዘፍ 4፥2 ኖኅም በእርሻ ሥራ ይተዳደር ነበር። ዘፍ 9፥20
አበ ብዙሀን አብርሃምም ገበሬ ነበር። “አብርሃም በቤርሳቤህ የተምር
ዛፍን ተከለ ”ዘፍ 21፥33 ነቢየ እግዚአብሔር ኤልሳዕም ከመጠራቱ
በፊት በአሥራ ሁለት ጥማድ በሬ የሚያርስ የሚያጎርስ ገበሬ ነበር።
1ኛ ነገ19፥19 ኤልዛቤል በቅናት ያስገደለችው ኢይዝራኤላዊው ናቡቴም
የወይን እርሻ የነበረው ገበሬ ነበር። 1ኛነገ20፥1 ጌታችን መድኃኒታችን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ኢየሱስ ክርስቶስም የሰውን ልብ በእርሻ መስሎ አስተምሯል። ማቴ13፥1-


49

ከብት እርባታ ፦ በእስራኤል ጥንታው ያን ከሆኑት የሥራ መስኮች ዋነኛው


ነው። አቤል በግ ጠባቂ ነበር። ዘፍ4፥2 እስራኤላውያን በከፍተኛ ደረጃ የበግ
እርባታን ያከናውናሉ። እስከ ዛሬም ድረስ ይታወቁበታል። አብርሃምና
ሎጥም ከብት አርቢዎች እንደ ነበሩ ተጽፏል። ዘፍ12፥5፣ ዘፍ13፥5-8
ታላቁ ያዕቆብም ለረጅም ዓመታት ከብት ጠባቂ ሆኖ ቆይቷል። ዘፍ
30፥29 በግብጻውያን ዘንድ በግ ጠባቂ እንደ ርኩስ ይቆጠር ነበርና ዮሴፍ
ቤተሰቦችን ፈርዖን ቢጠይቃችሁ ከብት አርቢዎች ነን በሉት አላቸው።
ዘፍ 46፥34 ቅዱስ ዳዊትም ወደ መንበረ ሥልጣን ከመውጣቱ በፊት
፶፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

በግ ጠባቂ ነበር። 1ኛሳሙ 16፥11 ነቢዩ አሞጽም ለነቢይነት ከመጠራቱ


በፊት በከብት አርቢነት ሥራ ተሰማርቶ ይኖር ነበር። አሞ1፥1 እረኞች
በጥንት ጊዜ በፈረቃ ይጠብቁ ነበር። በጌታችን ልደት ጊዜም የተጠሩት
እረኞችም ፈረቃቸው በሌሊት ስለ ነበር በዚያው መንጎቻቸውን ሲጠብቁ
ብሥራቱን ለመስማት ታድለዋል። ሉቃ2፥8 ጌታችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን በእረኛ መስሎ ተናግሯል። “መልካም እረኛ እኔ
ነኝ” እንዳለው ዮሐ10፥11 ላይ። ካህናትም በእረኞች ይመሰላሉ። “እረኞች
ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ” ሲል ካህናትን ነው። ሕዝ34።7
ጌታችንም ስምዖን ጴጥሮስን “ግልገሎቼን አሰማራ ፣ ጠበቶቼን ጠብቅ
በጎቼን አሰማራ እያለ እንደ ቅደም ተከተሉ አዝዞታል። ዮሐ21፥ 15-17
አደን፦ በዱር ውስጥ የሚኖሩ እንሰሳትን አስድዶ መያዝ ወይም መግደል
አደን ይባላል። “ዔሳውም አደን የሚያውቅ የበረሀ ሰው ሆነ” ሲል አደን
እንደ አንድ የሥራ መስክ ይወሰድ እንደነበር ያሳያል። ዘፍ25፥27

፶፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ንግድ በጥንት ጊዜ ንግድ ታላቅ የሥራ መስክ ነበር። ታላቁ አባት


ንግድ፦
አብርሃም ከእርሻና ከከብት እርባታ በተጨማሪ የንግድ ሥራንም ያከናውን
ነበር።“ አብራምም በከብት፣ በብርና በወርቅ በለጠገ” ዘፍ13፥ 3 ይኖርባት
የነበረችው በከለዳውያን ምድር የምትገኘው ዑርበ ንግድ የገነነች ሀገር
ነበረች።
ግብጽም የንግድ መናኽሪያ ነበረች። ቀደም ሲል የባሪያ ንግድ ከተስፋፋባቸው
ሀገሮች አንዷ በመሆኗም ዮሴፍ ተሸጦባታል። እርሱንም የሸጡት ወደ
ግብጽ ይወርዱ የነበሩ ነጋዴዎች ናቸው። ዘፍ37፥30
ሀገረ እስራኤልም ታላቅ የንግድ መናኽሪያ ከመሆኗ የተነሣ ጠቢቡ
ሰሎሞን በጊዜው ከተለያዩ ሀገራት ይመላለሱ ከነበሩት በርካታ ነጋዴዎች
ግብር ይቀበል እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል።1ኛነገ10፥ 11 ነቢዩ
ዮናስ ወደ ተርሴስ ለመጓዝ የተነሣው በነጋዴዎች መርከብ ተሳፍሮ ነበር።
ይህም የባህር ንግድ ተስፋፍቶ እንደነበር ያመለክታል። በተለይ ጢሮስ
ከፍተኛ የንግድ ሀገር ነበረች። “በእንጨት፣ በሸራ፣ በሐር ፣በቆርቆሮ፣
በእርሳስ፣ በብርና በብረታ ብረት፣ በዝሆን ጥርስ፣ በወርቀ ዘቦ፣ በዞጲ፣
በቅመማ ቅመም.. .ንግድ እጅግ የከበረች ነበረች ”ሕዝ27፥1-25
ንግድ በተስፋፋት ወቅት የዕቃ በዕቃ ለውጥ (Bartering) አንዱ የመገበያያ
መንገድ እንደሆነ ተጽፏል። “ይለውጡ ዘንድ የዝሆን ጥርስና ዞጲአ
መጡልሽ” ሕዝ27፥15 አብርሃም እና ያዕቆብ በከብት ቦታ ገዝተዋል።
ዘፍ21፥28፣33፥18-20
ጌታችን በተወለደበት ዘመን እስራኤል የተለያዩ ሀገሮችን የምታገናኝ
ታልቅ የንግድ ሥፍራ ነበረች። ሐዋ16፥13-15 ጌታችን እንደ ሌሎቹ
ሥራዎች ሁሉ በንግድ እየመሰለ አስተምሯል። ማቴ25፥14-30 “ደግሞም
መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች።
ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ ባገኘ ጊዜ ሔዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ
ገዛት” በማለት አስተምሯል። ማቴ13፥45-46 ነጋዴው የምዕመናን፣
ያለውን ሁሉ መሸጡ ራሱን የመካድ ምሳሌ ናቸው።
በሐዲስ ኪዳን ነጋዴዎች ለንግድ ወደ ተለያዩ ሀገሮች ሲጓዙ ወንጌልን
፶፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

አስተምረዋል። ምሳሌ፦ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ወደ


ኢትዮጲያ አስተምረዋል ። ንግሥተ ሳባስ ለጠቢቡ ሰሎሞን በጥንቃቄ
የተረዳችውን ታምሪን ከሚባል ኢትዮጲያዊ ነጋዴ መሆኑንም ነጋዴያን
ምን ያህል ቃለ እግዚአብሔርን ለማስፋፋት ምን ያህል የተመቻቸ ሁኔታ
እንደ ነበራቸው ያመለክታል።
ሕክምና ፦ መጽሐፍ “ወይስ በዚያ ሐኪም የለም?” ሲል ሕክምና ጥበብ
የነበረ መሆኑን ያመለክታል። ኤር 8፥22 “ ዮሴፍም ባለ መድኃኒቶች
አገልጋዮቹ አባቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ።” ተብሎ እንደ ተነገረ
የሕክምና ሥራ ከጥንት ጀምሮ አለ። ዘፍ50፥ 2 እንዲሁም ንጉሡ
አሳ እግሩን በታመመ ጊዜ“ ባለመድኃኒቶች እንጂ እግዚአብሔርን
አልፈለገም። ”2ኛዜና16፥12 ባለመድኃኒቶች የተባሉ ሐኪሞች ናቸው።
አባታችን ጻዲቁ ኖኅ ከእግዚአብሔር በተገለጠለት ጥበብ የመጀመሪያው
ሐኪም ነው። እግዚአብሔር ከተለያዩ ዕፆች ወይም ዕፅዋት ብዙ ዓይነት
መድኃኒት ሊሠራ እንደሚችል አሳይቶታል።
ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊው “ባለመድኃኒቱ” ተብሎ የተጠራው ሐኪም
በመሆኑ ነው። ቆላ 4፥14፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረችው
ሴትም ከክርስቶስ አስቀድሞ ከብዙ ባለ መድኃኒቶች ጋር ተገናኝታ ነበር።
ማር5፥26

አናጺነት በአሁኑ ወቅት አናጺ የሚለው ቃል የተወሰነ የሥራ መስክን


አናጺነት፦
ብቻ ያመለክታል። እርሱም ከእንጨት ሥራዎች ጋር ብቻ የተያያዘ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን አናጺነትን ከመኃንዲስነት ሥራ ጋር ያመላክታል።
ሕዝ40፥3፣ ራእ21 ፥15 ስለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ“ የእግዚአብሔር ጸጋ
እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሀተኛ የአናጺ አለቃ መሠረት መሠረት
ሁሌ ላውም በላዩ ላይ ያንጻል። ”ሲል የተናገረው። 1ኛቆሮ3፥10
አናጺዎች የፈረሱ ቤቶችን ይጠግኑ ነበር። 2ኛዜና34፥11 አረጋዊው ዮሴፍ
የአናጺነት ሙያ ነበረው። ማቴ13፥15 ጌታችንም በልጅነቱ በአናጺነት ሥራ
ዮሴፍን ይረዳው ነበር። ጠቢቡ ሰሎሞን ታላቁን ቤተ መቅደስ ያሠራው
፶፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

የእንጨት ሠራተኞችን (አናጺዎችን) ከጢሮስና ከሲኖዳ አስመጥቶ ነው።


በእነዚህ ሀገሮች ታዋቂ አናጺዎች ነበሩ። 2ኛ ዜና1፥3-14

ግንበኝነት ፦ የሰናዖርን ግንብ ከተሰሡት ሰዎች ጀምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ


በሰፊው ተጠቅሶ የሚገኝ የሥራ መስክ ነው። ዘፍ11፥1-9 እስራኤላውያን
በዚህ ሥራ የታወቁ ነበሩ። በተለይም ወደ ግብጽ በተሰደዱበት ጊዜ
ዓለም የሚያደንቃቸውን ፒራሚዶች እንደሠሩ ይነገራል። ምክንያቱም
በኦሪት የተጻፉት ታሪኮች ከዚህ ጋር የተያያዙ ናቸው። ጡብ በመሥራት
ለፈርዖን ፊቶም ና ራምሴ የተባሉ ጽኑ ከተማዎችን እንደ ከተሙ
ተጽፏል። ዘፍ1፥8-14
ጌታችን“ ግንበኞች የናቁት ድንቃይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ” ተብሏል።
ማቴ 21፥ 42“ እንሆ የተመረጠና የተከበረ የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን
፶፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” ተብሎ ተጽፏል። ሮሜ9፥23


ዕብራውያን ለበርካታ ጊዜ በተካሄዱ ጦርነቶች ወደ ተለያዩ አገሮች
ሲሰደዱ እንደ መኖራቸው ከልዩ ልዩ ሕዝቦች የተግባረ ዕድ ጥበብን
ቀስመዋል። 2ኛ ነገ18፥1-7፣ 1ኛዜና 24፥5
በተግባረ ዕድ /በእጅ ሥራ/ የተሰማሩ ሰዎች ጥንት በባልጩት /ስለታም
ድንጋይ/ እና በናስ ሥራዎቻቸውን ማከናወን ጀመሩ። ዘፍ4፥22 ከዚያም
ብረትን ማቅለጥ እና መቀጥቀጥ ሲቻል የተለያዩ መሳሪያዎች ተገኙ።
ከእነዚህም መሳሪያዎች የሚከተሉት ይገኛሉ። መራጃ፣ መጥረቢያ፣
መቅረጫ፣ መዶሻ፣ መጋዝ፣ ምሳር፣ ቢላዋ፣ ካራ፣ማጭድ፣ማረሻ፣
ወስፌ፣መርፌ...ወዘተ። 1ኛነገ6፥7፣ ኢሳ44፥13፣ መሳ5፥26፣
2ኛሳሙ12፥31፣ ዘዳ19፥5፣ 2ኛነገ6፥5፣ ዘፍ22፥6፣ ምሳ30፥ 14 ኢሳ2፥4፣
ዘጸ21፥6፣ ማቴ19፥24

የተግባር ልምምድ
ተማሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጎላ ብሎ ከተነገረላቸው
/ከተጻፈላቸው/ የሥራ መስኮች መካከል አንጥረኝነት እና
ቀጥቃጭነት፣ ልብስ ሥራ፣ ሸክላ ሥራ፣ ሽቱ ቀማሚነት፣
ቁርበት ፋቂ እና ቀንድ አንጣጭ ይገኛሉ። ስለ እነዚህ
የሥራ መስኮች በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን ጽፋችሁ
በመምጣት ለተማሪዎችና ለመምህሩ ያንብቡላቸው።

፶፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

መስፈሪያ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የርዝመት /Length/ ፣ የክብደት
/Weight/ እና ይዘት /Volume/ መስፈሪያዎች /MeasuringUnits/
አሉ። እነዚህም ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ናቸው። “በፍርድ በመለካትም ፣
በመመዘንም ፣ በመስፈርም አመፃ አታድርጉ።” ዘሌ 19፥36-37

የደረቅ ነገር መስፈሪያ ፦ ለደረቅ ነገሮች የይዘት መለኪያ ነው። እነዚህም


ቆሮስ ፦ በዛ ያለ የእህል ሸክም የሚሰፈርበት መስፈሪያ ነው። ዘሌ 27፥16
፣ ወደ 400 ሊትር አካባቢ ነው።
ኢፍ ፦ ዐሥር የኢፍ መስፈሪያ አንድ ቆሮስ የሚያህል ነው። ወይም
አንድ ቆሮስ አንድ ዐሥረኛ ሲሆን ይህም 40 ሊትር ይሆናል። ሕዝ
45፥11
ጎሞር ፦ ዐሥር የጎሞር መስፈሪያ አንድ ኢፍ ይመዝናል። ይህም ዐራት
ሊትር ነው። ዘጸ 16፥16-36

የፈሳሽ ነገር መስፈሪያ ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሦስት ዓይነት የፈሳሽ


መለኪያዎች ይገኛሉ። አብዛኛውን ጊዜ ውኃ ፣ ወይን እና ዘይት ይገኛሉ።
ባዶስ ፦ ባዶስና ኢፍ እኩል ይዘት አላቸው። የቆሮስ አንድ ዐሥረኛ ክፍል
ነው። ሕዝ 45፥11፣14 አንድ ባዶስ የ40 ሊትር ይዘት አለው።
ኢን ፦ የባዶስ አንድ ስድስተኛ ክፍል ነው። 6 ሊትር ተኩል አካባቢ ነው።
ሕዝ 4፥1 ፣ ዘጸ 29፥40 ፣ ዘሌ 23፥13
ሎግ ፦ የባዶስ አንድ ዐሥራ ሁለተኛ ወይም የኢን አንድ ሁለተኛ ክፍል
ነው። 3 ሊትር አካባቢ ነው። ዘሌ 14፥10

የክብደት መለኪያ ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ሰባት ዓይነት የክብደት መለኪያዎች


ተጠቅሰዋል። እነዚህም ፦
ምናን ፦ አንድ ምናን ከ500 እስከ 700 ግራም ክብደት እንዳለው ይነገራል።
ዕዝ 2፥69 ፣ 1ኛ ነገ 10፥17
፶፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ዳሪክ ፦ ለቤተ እግዚአብሔር መስሪያ የተበረከተው ወርቅ የተለካው


በዳሪክ ነው። “ስድሳ አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ” እንዲል። ዕዝ 2፥69
ሰቅል ፦ ከ12–14 ግራም ያህል ክብደት አለው። ጎልያድ የለበሰው
የነሐስ ጥሩር 5000 ሰቅል ያኽል ነበር። 1ኛ ሳሙ 17፥5 ይህም ወደ
65 ኪሎግራም አካባቢ ይመዝን ነበር። “አብርሃም በ400 ሰቅል ለሣራ
መቃብር በኬብሮን ገዛ” ዘፍ 23፥1-16 ፣ 1ኛ ነገ 10፥16
የንጉሥ ፣ የመቅደስና የሕዝብ የሚባል ሰቅል እንደነበር በመጽሐፍ
ተገልጧል። 2ኛ ሳሙ 14፥26 ዘጸ 30፥12-14
አቦሊ ፦ አንድ አቦሊ የሰቅል አንድ ሃያኛ ነው። ዘጸ 30፥14
መክሊት ፦ አንድ መክሊት ሠላሳ ኪሎግራም ነው። 2ኛ ነገ 18፥14 ፣
1ኛ ነገ 10፥14 እና 15
ንጥር ፦ አንድ ንጥር 327.45 ግራም አካባቢ ይመዝናል። ዮሐ 19፥39
ታላንት ፦ አንድ ታላንት 3 ፈረሱላ አካባቢ ወይም 50ኪ.ግ ያህል
ይመዝናል።

የርቀት /የርዝመት/ መለኪያ


ዘንግ ፦ ቁመቱ 2.7 ሜትር እና ከዚያም በላይ ሲሆን እንደ ሸምበቆ ካለ
እንጨት የሚሠራ ነው። ሕዝ 40፥5 ፣ ራእ 21፥15-16
ክንድ ፦ 50 ሴ.ሜ ወይም ግማሽ ሜትር ያህላል። ዘዳ 3፥11 ፣ ዘጸ
25፥10-11 ፣ 1ኛ ሳሙ 17፥4
ጋት ፦ አውራ ጣትን ሳይጨምር የአራት እጅ ጣቶች ነው። ውፍረትንም
ለመለካት ይጠቅም ነበር። ዘጸ 25፥25 ፣ 1ኛ ነገ 7፥26
ስንዝር፦ የእጅ ጣቶችን በተለይም በተለይም አውራ ጣትንና መካከለኛ
ስንዝር
ጣትን በተቃራኒ አቅጣጫ በመወጠር /በመቀሰር/ ከአንዱ ጫፍ እስከ
ሌላው ጫፍ ያለው ርቀት ወይም ርዝመት ስንዝር ይባላል። ዘጸ 28፥16
ይህ መለኪያ የክንድ ግማሽ ነው። አንድ ስንዝር 25 ሳ.ሜ አካባቢ ነው።
ምዕራፍ ፦ አንድ ምዕራፍ 200 ሜትር ያህላል። ሉቃ 24፥13
የሰንበት መንገድ ፦ 6 ምዕራፍ ወይም 1200ሜ/ 1.2ኪ.ሜ ያህል ነው።
፶፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

በብሉይ በሰንበት ቀን ከዚህ ርቀት በላይ መጓዝ አይፈቀድም ነበር። ዘጸ


16፥29 ፣ ሐዋ 1፥12
የሰው ቁመት ፦ አራት ክንድ ወይም ስድስት ጫማ ያህላል። ለባሕር
ጥልቀት መለኪያም ይውል ነበር። ሐዋ 27፥28

ገንዘብ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገንዘብ የሚለው ቃል ሁለት ዓይነት አገባብ
አለው። አንደኛው ለመገበያያ ይሆን ዘንድ ከተለያዩ ዓይነት ማዕድናት
/ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ እና ከነሐስ/ በተለያየ መጠን የሚሠራውን
ሲያመለክት፣ ሁለተኛው ደግሞ በአጠቃላይ ሀብትን ወይም ንብረትን
ያመለክታል። ሆኖም የመጀመሪያውን የገንዘብ ዓይነት በተመለከተ
፶፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

መጽሐፍ ምን እንደሚል እንመለከታለን።


ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ 700 ዓመት ድረስ ምን ዛሬ ያለው ገንዘብ
እንዳልነበር ብዙዎች ይስማማሉ። ሆኖም ግን ከወርቅ ፣ ከብር ፣
ከመዳብ እና ከነሐስ የተሠሩ ልዩ ልዩ የግሪክና የሮማውያን ገንዘቦች
በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ የታወቁ መገበያያዎች እየሆኑ መጡ።
ጌታችን “ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ…. አታግኙ ያለው
ከእነዚህ መዓድናት የተሠሩ ገንዘቦች እንደ ነበሩ ያመለክታል። ማቴ
10፥9 አይሁድም በግሪኮችና ሮማውያን ቅኝ ግዛት ሥር ሆነው ስለነበር
የእነዚህን መንግሥታት ገንዘቦች ጥቅም ላይ አውለዋል። እነዚህም
ገንዘቦች፡

የግሪክ ገንዘቦች
1. መክሊት፦ የወርቅ መሐለቅ ነው። በእስራኤል ዘንድ የታወቀ የመገበያያ
ገንዘብ ነው። ጌታችንም እየመሰለ በተናገረባቸው አንዳንድ ቦታዎች ላይ
ተጠቅሞበታል። ማቴ18፥24፣ ማቴ25፥14-15 አንድ መክሊት 2100
የኢትዮጲያ ብር ያህል ይመነዘራል።
2. ምናን፦ 35 የኢትዮጲያ ብር ያህል ይመነዘራል። ጌታችን በማቴዎስ
ወንጌል ላይ በመክሊት መስሎ ያስተማረው በሉቃስ ወንጌል ደግሞ በምናን
ተተክቶ መነገሩ ሁለቱም የገንዘብ መጠን መናገሪያዎች በመሆቸው
ነው። ሉቃ 19፥13-27
3. ድራክማ፦ ድሪም እየተባለ በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው
ገንዘብ ነው። ዲናር ተብሎ የሚጠራው የሮማውያንን ገንዘብ ያህል ዋጋ
አለው። ዕድሜው ከሃያ ዓመት በላይ የሆነው አይሁዳዊ ሁሉ በየዓመቱ
ለቤተ መቅደስ ሁለት ሁለት ድሪም /ድራክማ/ ግብር ይከፍል ነበር።
ሉቃ15፥8


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

የሮም ገንዘቦች
1.ዲናር፦ የብር መሐለቅ ነው። አንድ ዲናር የአንድ ቀን ሠራተኛ ዋጋ
ነበር። ማቴ 20፥9-10 በጌታችን መዋዕለ ስብከት በዲናሩም ላይ የሮማ
ነገሥታቶች /ቄሣሮች/ ምስል ይታተምበት ነበር። ማር12፥15-17 ፣ ሉቃ
10፥35
2. እስታቴር፦ አንድ እስታቴር ዐራት ዲናር ያህል ነው።ማቴ17፥
3. አሣርዮን፦ የቄሣር መልክ ያለበት የመዳብ ገንዘብ ነው። በአማርኛው
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምስት ሳንቲም የተባለው አንድ አሣርዮን ነው።
“ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ” ማቴ1 0፥29
4. ካድራንስ፦ የአሣርዮን ሩብ ነው። ይህም በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ
አንድ ሳንቲም የተባለው ነው። ማር 12፥ 42
5. ሌፕቶን፦ እስካሁን ከተጠቀሱት ሁሉ የሚያንስ ሲሆን የኳድራንስ
፷፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ግማሽ ነው። በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ግማሽ ሳንቲም ተብሎ


የተጠቀሰው ነው። ሉቃ 12፥59፣ ማቴ5፥26፣ ማር 12፥42

የጦር መሣሪያ
የሰው ልጅ እርስ በእርሱም ሆነ ከአራዊት ጋር መታገል ከጀመረበት ጊዜ
አንስቶ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሲገለገልባቸው ኖሯል ። ከድንጋይ
ጀምሮ እስከ አጥንት፣ እሳትና የተለያዩ ብረታ ብረቶች ሁሉ በጥንት
ጊዜ እንደ ጦር መሳሪያ አገልግለዋል። የመጀመሪያው ሟች አቤልም
የሞተው በድንጋይ ነው። ዘፍ4፥8 ሶምሶም ፍልስጤማው ያንን ሸነፋቸው
በአንድ የአህያ መንጋጋ ነው። መሳ15፥15 ከዚህ ቀጥሎ በመጽሐፍ ቅዱስ
የተጠቀሱትን አንዳንድ የጦር መሳሪያዎች እንመለከታለን።
ወንጭፍ፦ በዘመነ መሳፍንት እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅመውበታል።
መሳ20፥16 ቅዱስ ዳዊትም ጎልያድን አሸንፎበታል። 1ኛሳሙ17፥40-49፣
1ኛዜና12፥2
ጦር ፦ ጎልያድ ዳዊትን ለመግደል ጦር ይዞ ወጥቶ ነበር። ከጦሩም ጋር
አብሮ ጭሬ ይዞ ነበር። 1ኛሳሙ 17፥6-7 ጭሬ ቀጭንና አጭር ጫፉ
ጠባብ የሆነ የጦር ዓይነት ነው። ሳዖል ባይሳካለትም ዳዊትን ለመግደል
ጦር ወርውሯል። 1ኛሳሙ18፥ 11 ሌንጊኖስ የተባለው የሮማውያን
፷፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

ወታደር የጌታችንን ጎን የወጋው በጦር ነው። ዮሐ19፥34፣ ዮሐ18፥3


ሰይፍ፦ በሁለት በኩል የተሳለ ከብረት የሚሠራ የጦር መሣሪያ ዓይነት
ሰይፍ
ነው። ከጎራዴ የሚለየው በሁለት በኩል የተሳለ እና አጠር ያለ በመሆኑ
ነው። በአንድ በኩል ብቻ የተሳሉ አንዳንድ ሰይፎችም ይኖራሉ።
1ኛሳሙ13፥19-22 ፣ ሉቃ22፥53 ጌታችን በተያዘ ጊዜም ቅዱስ ጴጥሮስ
የሊቀ ካህናቱን የቀያፋን ባሪያ /የማልኮስን/ ቀኝ ጆሮ በሰይፍ መትቶ
ቆርጧል። ዮሐ18፥10 ቃለ እግዚአብሔር በሰይፍ ይመሰላል። “የመንፈስን
ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።” ኤፌ6፥1 7፣ ዕብ 4፥12
፣ መዝ149፥6

ጥሩር ከአንገት እስከ ጉልበት የሚጠለቅ ከቆዳ ወይም ከተለያዩ ብረታ


ጥሩር፦
ብረት የሚሠራ መከላከያ ነው። 1ኛሳሙ1 7፥38- 39፣ 1ኛነገ22፥34፣
ነህ4፥16 ጥሩር የጽድቅ ምሳሌ ነው።“ የጽድቅ ጥሩር ለብሳችሁ”
ኤፌ6፥13-15
ጋሻ ፦ ከብረት ፣ ከናስ ወይም ከቆዳ የሚሠራ በእጅ የሚያዝ ለሚወረወርም
ሆነ ለሚሰነዘር የጦር መሳሪያ መከላከያ ወይም መመከቻ የሚውል
ነው። ነህ 4፥16 ጋሻ በእምነት ይመሰላል። “እናንተ መሳፍንት ሆይ
ተነሡ፣ ጋሻውን አዘጋጁ” ኢሳ 21፥5“የእምነት ጋሻ አንሱ” ኤፌ6፥ 16፣
መዝ34፥2፣ ዘፍ15፥1
፷፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

ቁር
ቁር፦ በራስ ላይ የሚጠለቅ ከናስ፣ ከብረትና ከሌላም ቁሳቁስ ሊሠራ
የሚችል የጦር መከላከያ ነው። “በራሱም ላይ የጦር ቁር ደፋለት።
1ኛሳሙ17፥38፣ ቁር የመዳኛ ምሳሌ ነው።“ የመዳንንም ራስ ቁር
የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ” ኤፌ6፥17
ቀስትና ፍላፃ፦
ፍላፃ ቀስት ከእንጨት ወይም ከሌሎች ብረታ ብረት
የሚሠራ እንደ ደጋን ያለ ቅርጽ ያለው ሲሆን ከአንዱ ጫፍ እስከ
ሌላው ጫፍ ከጅማት ወይም ከጭራ የተገመደና የተወጠረ ክር ያለው
መሣሪያ ነው። ፍላፃ ደግሞ በቀስቱ አማካኝነት እንዲፈናጠር ሆኖ ዘንጉ
ብረት ወይም እንጨት የሆነ ጫፉ ግን ሹል ብረት ያለው መሣሪያ
ነው።ዘፍ21፥20፣1ኛዜና5፥18፣1ኛዜና12፥2

፷፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

፷፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

፷፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

፷፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል

፷፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ

፷፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አራተኛ ክፍል


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
የሰንበት ት/ቤት አመራር እና መምህራን
እንዲሁም ተማሪዎችና ወላጆች በመጽሐፉ ላይ
ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት እና ግብዓት
በሚከተለው አድራሻ ላኩልን

office@eotc-gssu.org
https://t.me/GSSUCurricu-
lum_bot

You might also like