You are on page 1of 8

በስመ አብ ወወሌዴ ወመንፈስ ቅደስ አሏደ አምሊክ አሜን!!!

ድግማ እና ቀኖና

በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ትምህርት በኹሇት ትምህርቶች የሚጠቃሇሌ ነው፡፡

1. ድግማ እና
2. ቀኖና

1. ድግማ
ድከይን ከሚሇው የግሪክ ቃሌ የተገኘ ሲኾን በጥሬው አመሇካከት፣ አስተሳሰብ፣ አዋጅ ማሇት ቢኾንም
በምሥጢራዊ ማሇትም በቤተ ክርስቲያናዊ ትርጓሜው ግን ሃይማኖት (የእምነት መሠረት) ማሇት
ነው፡፡ በመኾኑም ድግማ የተዯነገገ ሳይኾን የተገሇጠ ነው፡፡ መገኛውም እግዚአብሔር ነው፡፡ ከሰው
ሉፈጠር አይችሌም፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠ እውነት ነው፡፡ በማኝኛውም አካሌ (በሲኖድስም
ጭምር)፣ በየትኛውም ዘመን፣ በየትኛውም ኹኔታ (በሞትም በሕይወትም) የማይሇወጥ ማንነት
አሇው፡፡
ድግማ የቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት ነው ብሇናሌ፡፡ ስሇ ቅዴስት ሥሊሴ፣ ስሇ
ምሥጢረ ሥጋዌ (ክርስቶስ ፍጹም አምሊክ ፍጹም ሰው መኾኑን፣ ከእመቤታችን ከቅዴስት ዴንግሌ
ማርያም በዴንግሌና ተጸንሶ በዴንግሌና እንዯተወሇዯ፣ እንዯ ተሰቀሇ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን
ተሇይቶ እንዯተነሣ፣ ዲግመኛ በክበበ ትስብእት እንዯሚመጣ)፣ ስሇ መንፈስ ቅደስ፣ ስሇ ምሥጢረ
ጥምቀት፣ ስሇ ምሥጢረ ቁርባን፣ ስሇ ቤተ ክርስቲያንና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ ስሇ ክብረ
ዴንግሌ ማርያምና ክብረ ቅደሳን የምንማው እንጂ ማናችንም ሌናሻሽሇው አንችሌም፡፡ እንኳንስ አንዴ
ግሇሰብ ይቅርና ሲኖድስም ቢኾን አሇመሇወጡን፣ አሇመፋሇሱን ይመረምራሌ እንጂ መጨመር ወይም
መቀነስ አይችሌም፡፡ ሏዋሪያው ቅደስ ጳውልስ፡- “ነገር ግን (ሏሳባችንን ቀይረን) እኛ ብንኾን ወይም
ከሰማይ መሌአክ ከሰበክንሊችኁ ወንጌሌ የሚሇይ ወንጌሌን የሚሰብክሊችኁ የተረገመ ይኹን” ያሇውም
ስሇዚኹ ነው /ገሊ.1፡8/፡፡

2. ቀኖና
ቀኖና ማሇት ሕግ፣ ሥርዓት፣ ዯንብ፣ ፍርዴ፣ ቅጣት፣ መጠን፣ ሌክ ማሇት ነው /ኪዲነ ወሌዴ ክፍላ (አሇቃ)፣
መጽሏፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃሊት ሏዱስ፣ ገጽ 799/፡፡ በግሪኩ ካኖን ሲኾን በዕብራይስጡ ቃኒህ ይለታሌ፡፡
ይኸውም አንዴን ነገር ሇመሇካት፣ ሇመመዘን፣ ትክክሌ መኾኑንና አሇመኾኑን ሇመሇየት፣ መጠኑን
ሇማወቅ የሚያገሇግሌ መሇኪያ ወይም መስፈርት ነው፡፡
ማኅበረ ሰብእ እስካሇ ዴረስ ሕግ አሇ፡፡ ሕግ እንዱኖር የኹሇት ሰዎች በአንዴ ሊይ መኖር በቂ ነውና፡፡
ቤተ ክርስቲያን ዯግሞ “አሏቲ ጕባኤ” እንዱሌ የምእመናን ስብስብ ስሇኾነች የራሷ ሕግ አሊት፡፡ አባቶች
“ያሌተገራ ፈረስ የባሇቤቱን ጥርስ ይሰብራሌ” እንዯሚለት ይኽ የምእመናን ስብስብ ሰሊማዊ እንዱኾን
የሚያዯርገው የቤተ ክርስቲያን ሕግ ወይም ሥርዓትም ቀኖና ይባሊሌ፡፡

1/8
ጠቅሇሌ ባሇ መሌኩ ስንመሇከተው ሕግ ኹሇት ዓይነት ነው፤
1. ተፈጥሮአዊ ሕግና የስምምነት ሕግ፡፡ የተፈጥሮ ሕግ የምንሇው የእግዚአብሔርን ሕግ ነው፡፡ ሰዎች
ይኽን የእግዚአብሔር ሕግ ሉሇውጡት አይችለም፡፡ ሇምሳላ ወንዴ ከሴት ጋር መጋባት አምሊካዊ
ሕግ ነው፡፡ ግብረ ሰድማዊነትም ይኽን የተፈጥሮ ሕግ የሚቃረን ነው፡፡ ፈረስና አህያ ተዲቅሇው
በቅልን ይወሌዲለ፡፡ ነገር ግን በቅል ራሷን መተካት አሇመቻሎ ከሕገ ተፈጥሮ ውጪ የተወሇዯች
መኾኗን ነው የሚነግረን፡፡ ጦጣና ዝንጀሮ ተዲቅሇው የሚወሌዶቸው እንስሳትም አለ፡፡ ነገር ግን
ሌክ እንዯ በቅል ራሳቸውን መተካት አይችለም፡፡ ሇምን? ስንሌም ከሕገ ተፈጥሮ ማሇትም
ከእግዚአብሔር ሕግ ውጪ የተወሇደ ናቸውና፡፡ ስሇዚኽ ተፈጥሮአዊ ሕግጋትን ተቃርነን
የምናዯርጋቸው ነገሮች ትርፉ ዴካምና በራስ ሊይ ጉዲትን መጨመር ብቻ ነው የሚኾነው፡፡
2. የስምምነት ሕግ የምንሇው ዯግሞ በፓርሊማ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በቤተ ክርስቲያን
ዯግሞ በቅደስ ሲኖድስ የሚወጣውን ሕግ ማሇታችን ነው፡፡ ምንም እንኳን የስምምነት ሕግ ብሇን
ብንጠራውም ቅደስ ሲኖድስን የሚመራው መንፈስ ቅደስ ስሇኾነ እንዱኹ የሰዎች ስምምነት ነው
ብሇን የምንወስዯው ወይም ዝቅ አዴርገን የምንመሇከተው አይዯሇም፡፡ እነዚኽ ሕጎች ኹሇት
መሠረታዊ ጠባያት አሎቸው፡፡ ጥቅሌ ወይም ዝርዝር ሕጎች ሉኾኑ ይችሊለ፡፡
የስምምነቱ ሕግ ጊዜያዊም ሇረዥም ጊዜ የሚቇይም ሉኾን ይችሊሌ፡፡ ሇምሳላ እግዚአብሔር
በምሕረት ዓይን እንዱያየንና በቤተ ክርስቲያን እንዱኹም በዓሇም ሊይ የተጋረጡትን ችግሮች
እንዱያርቅ ቅደስ ሲኖድስ ሇኹሇት ሳምንት ጾምና ጸልት ቢያውጅ ጊዜአዊ ሕግ (ቀኖና) ይባሊሌ፡፡
በዓመት ሰባት የአዋጅ አጽዋማት መኖራቸው ግን በሕይወት እስካሇን ዴረስ የሚገዛን ቀኖና ነው፡፡
የስምምነት ሕግ የተጻፈም ያሌተጻፈም ሉኾን ይችሊሌ፡፡ ያሌተጻፈ መኾኑ ግን ሕግ ከመኾን
አይከሇክሇውም፡፡ ካሌተጻፈ ተብል አይጣስም፡፡ እያንዲንዲችን የአንዲችንን ፍሊጏት ሇመጠበቅ
ተፈጥረናሌና /ዘፍ.4/፡፡

ቀኖና ቤተ ክርስቲያን
ቀኖና የሚሇው ቃሌ እንዯ አኹኑ ሇቤተ ክርስቲያን ከማገሌገለ በፊት ሕዝቡ በማንኛውም የዕሇት
ተዕሇት ሕይወቱ የሚዲኝበት ሕግን ያካተተ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያናዊ (ክርስቶሳዊ ሕግ) እና ሕዝባዊ
(ቄሳራዊ) ሕግ ተብል የተሇየው በኋሊ ነው /The Oxford Dictionary of the Christian Church, pp 277/፡፡
ቤተ ክርስቲያንም መዠመሪያ አከባቢ ሊይ ቀኖና የሚሇውን ቃሌ ስትጠቀም የመጻሕፍቶቿን ዝርዝር፣
የሥርዓተ አምሌኮቷን አፈጻጸም፣ የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን አፈጻጸም፣ የአንዴ ክርስቲያን ሥነ
ምግባር ምን መምሰሌ እንዲሇበት ሇመግሇጥ ነበር፡፡ ይኽ ቀኖና እንዱኖራት ምክንያት የኾናትም በቤተ
ክርስቲያን ውስጥ ይከሰቱ የነበሩት አሇመግባባቶች ናቸው፡፡ በተሇይ አንዲንዴ ከእምነትም ከምግባርም
የሚወጡ ሰዎች ሲገኙ ምእመናን ግራ እንዲይጋቡ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይወጣ ነበር፡፡ እንዯ ችግሩ
መጠንም የሚወጣው ሕግ (ቀኖናው) ዲርቻው አጥቢያዊ፣ ወይም ሀገረ ስብከታዊ፣ ወይም ሀገራዊ፣
ወይም ዓሇማቀፋዊ ይዘት ሉኖረው ይችሊሌ፡፡ ሇምሳላ ትንሽ ቆየት ብሇን እንዯምንመሇስበት በጉባኤ
ኒቅያ የተዯነገጉት ቀኖናት ዓሇማቀፋዊ ይዘት ያሊቸው ቀኖናት ናቸው /Ibid/፡፡
ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊት ካሌኾነች እውነተኛ አይዯሇችም፡፡ የእግዚአብሔርን ሌጅ ማወቅ ብቻውን
ትርጕም የሇውም፤ አጋንንትም ያውቁታሌና፡፡ ትርጕም የሚኖረው ስናምንና ስንጠመቅ ነው፡፡ ይቅርታ
ሰሊምን እንዯሚሰጥ ይታወቃሌ፤ ይቅር ካሊሌን ግን ትርጕም የሇውም፡፡ በላሊ አገሊሇጽ እምነታችንን
የምናከናውንበት ዝርዝር ቀኖና ከላሇ እምነታችን ትርጕም አሌባ ነው፤ ምክንያቱም ቀኖና “እምነታችንን
እንዳት እንፈጽም?” ሇሚሇው ጥያቄ መሌስ የሚሰጥ ዝርዝር አፈጻጸም ነውና፡፡
የቤተ ክርስቲያን ቀኖናት የተሰጡት በሏዋርያት ነው፡፡ ሇሕዝቡ ያስተማሩትም እነርሱ ናቸው፡፡ በእነርሱ
ወንበር የተቀመጡት ሉቃነ ጳጳሳትም በቅደስ ሲኖድስ አማካኝነት ጊዜውን የዋጀ ቀኖና ይሠራለ፡፡
ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ከላሇ የሚሠሇጥነው ዱያብልሳዊ ሕግ ነው፡፡ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ዋና
ዓሊማም ሰዎችን ሥርዓት አስይዞ የዘሇዓሇም ሕይወት እንዱኖራቸው ማዴርግ ነው፡፡ እንዯ ምሳላ
ብንጠቅስ አርዮስን ሇመገሰፅ ቤተ ክርስቲያን 25 ዓመት ፈጅቶባታሌ፡፡ የኢትዮጵያ እስር ቤቶች እንኳን
2/8
እስከ ቅርብ ጊዜ ዴረስ ዯብረ ሏይቅ (የግራኝ መሏመዴ ወንዴም የታሰረበት)፣ ዯብረ ዲሞ፣ ሏይቅ
እስጢፋኖስ፣ ክብራን ገብርኤሌ፣ ግሸን ዯብረ ከርቤ እና ላልች ታሊሊቅ ገዲማት ነበሩ፡፡ ይኽ የኾነበት
ዋና ምክንያትም የቀኖና ዓሊማ ሰዎች እንዱታረሙ ማዴረግ እንጂ ሰውን መቅጣት ስሊሌኾነ ነው፡፡ አጼ
ቴዎዴሮስ አንዴን ላባ ያገኛለ፡፡ ይዘዉም እጁን ይቇርጡታሌ፡፡ በዚያን ጊዜ የነበሩ ታሊቁ ሉቅ አሇቃ
አካሇ ወሌዴም በቅኔ አዴርገው አጼ ቴዎዴሮስን ወረፏቸው፡፡ አሇቃ አካሇ ወሌዴ ይኽን ያዯረጉበት ዋና
ምክንያትም “ሰውዬው እጁ ስሇተቇረጠ ከዚያ በኋሊ መሥራት አይችሌም፤ የሰው ጥገኛ ነው
የሚኾነው፡፡ ቀኖና ሉሰጠው ይገባ ነበር” ሲለ ነው፤ እንዯተናገርን የቀኖና ዓሊማ ሰውን ማዲን እንጂ
ሰውን መጉዲት ወይም ጫና መፍጠር አይዯሇምና፡፡
“ሕግ ከጽዮን ይወጣሌ” /ኢሳ.2፡3/ እንዯተባሇ የሕግ ምንጭ ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡ ሕግ አውጪ ብቻ
ሳትኾን ሕግ ተርጓሚዋና ሕግ አስፈጻሚዋም ርሷ ራሷ ናት፡፡ ሕጓም ዓሇምአቀፋዊ ዲርቻ አሇው፡፡ ቤተ
ክርስቲያን ባሇችበት ኹለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንም አሇ፡፡ አትስረቅ፣ አትግዯሌ፣… የሚለት የቤተ
ክርስቲያን ሕጎች ናቸው፡፡ በመኾኑም እነዚኽ ሕጎች በማንኛውም ቄሣራዊ ሥርዓት፣ በማንኛውም
ዓይነት ቋንቋ፣ በማንኛውም ዓይነት ማኅበረ ሰብእ ውስጥ አለ፡፡ የሥሊሴ አጥር ዲር ዴንበር የሇውምና
የቤተ ክርስቲያን ሕግም ዲር ዴንበር የሇውም፡፡ ጾም የቤተ ክርስቲያን ሕግ ነው፡፡ አፈጻጸሙ ግን
እንዯየቦታውና እንዯየሰዉ ኹናቴ ሉሇያይ ይችሊሌ፡፡ ሇምሳላ በዓፋር የሚኖር ክርስቲያን እስከ ዘጠኝ
ሰዓት ካሌጾምክ ካሌነው በውኃ ጥም እንገዴሎሇን፡፡ አዱስ አበባ ሊይ የሚኖረው ክርስቲያን ዓፋር ሊይ
እንዯሚኖረው ክርስቲያን 4፡00 ሰዓት ሊይ ውኃ ሌጠጣ ቢሌ ግን የተሇየ ምክንያት ከላሇው በቀር
ተቀባይነት የሇውም፡፡ እንዱኽ ሲባሌ ግን እያንዲንደ ሰው በራሱ ሕሉና ያሇበትን ኹናቴ እያመዛዘነ
በራሱ ውሳኔ የሚያዯርገው ነው ማሇታችን አይዯሇም፡፡ እንዱኽ ዓይነት ሇየት ያሇ ቀኖና (Exceptional
Canon) የሚያወጣው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ አካሌ ብቻ ነውና “ይኼ እኮ ቀኖና ነው፤ ባናዯርገውም
ምንም ችግር የሇውም” ከሚሇው ግሊዊ አስተሳሰብ ሌንጠነቀቅ ያስፈሌጋሌ፡፡

ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የራሱ የኾነ ሌዩ ባሕርያት አለት፡፡


 ሥሌጣን ባሇው አካሌ የሚዯነገግ፣ የሚተገበር፣ የሚሻሻሌ ነው፡፡ ሲዯነገግም ሲሻሻሌም በግሇሰቦች
የግሌ ፍሊጏት ወይም ፈቃዴ የሚዯነገግ ወይም የሚሻሻሌ አይዯሇም፡፡
 ሃይማኖታዊ ይዘት አሇው፡፡ ምክንያቱም ዓሊማው ሰውን ኹለ ወዯ መንግሥተ እግዚአብሔር
ማፍሇስ ስሇኾነ ቄሣራዊ ይዘት የሇውም፡፡ ቢኖርም እንኳን አንዴ ክርስቲያን በዚኽ ምዴር
የሚኖረው ቆይታ ከሰማያዊ ሕይወቱ ጋር ሳይጣረስበት እንዳት መኖር እንዲሇበት የሚያስረዲ
ነው፡፡
 የሰው ሌጅ ከሚችሇው በሊይ ሸክምን አይጭንም፤ “ሸክሜ ቀሉሌ ነው” እንዱሌ /ማቴ.11፡29/፡፡
 የሸሊሚነትና የቀጪነት ሥሌጣን አሇው፡፡ ቄሣራዊ ሕግ የሸሊሚነት ይዘት የሇውም፡፡ በቤተ
ክርስቲያን ቀኖና ግን ሇምሳላ ተጋዴልአቸውን በዴሌ ያጠናቀቁት ክርስቲያኖች ቀን ተሇይቶሊቸው፣
ታቦት ተቀርጾሊቸው በምእመናን ዘንዴ ክብርን እስከ ማግኘት ይዯርሳለ፡፡ በእግዚአብሔር ዘንዴ
ዯግሞ የዘሇዓሇም አክሉሌ ዘውዴ አሇው፡፡
 የአምሌኮ ይዘት አሇው፡፡ በውስጡ ጾም፣ ጸልት፣ ምጽዋት እና የመሳሰለትን ኹለ ያካትታሌ፡፡
 የመመዘን ጠባይ አሇው፡፡ ሇምሳላ የቃየን መሥዋዕት ያሌሰመረችው መሥዋዕት ስሊሊቀረበ ሳይኾን
በሕጉ መሠረት አሰስ ገሰስ ኾኖ ስሇተገኘ ነው /ዘፍ.4/፡፡
 በአንዴ ጊዜ በአንዴ ቦታ የተዯነገገ አይዯሇም፡፡
 ሰዎችን ዯስ ሇማሰኘት አይወጣም፤ የሚወጣው እግዚአብሔር ዯስ ሇማሰኘት ብቻ ነው፡፡ “ሇዓሇም
ከሚመች ከንቱ ሌፍሇፋ ራቅ” እንዱሌ ሇዓሇም የሚመች ቀኖና አይወጣም፡፡ ቀኖና የሚወጣው
የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት እንዱያዴግና ምእመናን በሚኖሩበት ማኅበረ ሰብእ ውስጥ አርአያ
እንዱኾኑ ነው፡፡
 አንጻራዊ ጽዴቅ ስሇላሇ አንጻራዊ ቀኖናም የሇም፡፡ ጥቁሩን ጥቁር ነጩንም ነጭ የሚሌ እንጂ
የተዴበሰበሰ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አታወጣም፤ እንዱኽ ካሌኾነ የውጫላ ሕግ ነው፡፡ በዓሇማዊ
ሕግ የወንጀለ መጠን ይታያሌ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ግን ወንጀሌ ወንጀሌ ነው፡፡
የቀኖና ምንጮች
3/8
ዛሬ ሊሇው የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ምንጮቹ ሌዩ ሌዩ ቢኾኑም ጠቅሇሌ ባሇ መሌኩ ግን
እንዯሚከተሇው ከፍሇን ማየት እንችሊሇን፡፡

ሀ) የሏዋርያት ሲኖድስ
እነዚኽ መጻሕፍት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. 81 ተብሇው ከሚታወቁት መጻሕፍት የሚካተቱ ሲኾኑ ሏዋርያት
በየጊዜው በመንፈስ ቅደስ መሪነት እየተሰበሰቡ የዯነገጓቸው እጅግ ጠቃሚ የሥርዓት መጻሕፍት
ናቸው፡፡ እነርሱም መጽሏፈ ዱዴስቅሌያና መጻሕፍተ ሲኖድሳት (ትእዛዝ፣ ግፅው፣ አብጥሉስ፣ ሥርዓተ
ጽዮን) ናቸው፡፡ ሲኖድስ የተባሇውና አራት ክፍሌ ያሇው መጽሏፍ በውስጡ ስሇ ሥርዓተ ቅዲሴ፣ ስሇ
አገሌጋዮች ማዕረጋት ቀኖና ይናገራሌ፡፡ መጽሏፈ ዱዴስቅሌያ ዯግሞ ስሇ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እና
ሥርዓተ አምሌኮን በዝርዝር ይናገራሌ፡፡
እናስተውሌ! የጌታ ትእዛዛት በሙለ ድግማ ነው፡፡ ጾም፣ ጸልት፣ ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ንስሏ፣ ከወንዴም
ጋር መታረቅ…ወዘተ ድግማ ነው፡፡ ቀኖና የሚኾነው ዝርዝር አፈጻጸሙ ሊይ ሲኾን ነው፡፡ ቀኖና
ከሏዋርያት የሚዠምረውም ሇዚኹ ነው፡፡ በመኾኑም አንዴ ሰው ተነሥቶ ጾም አያስፈሌግም ቢሌ
የቀኖና ሳይኾን የድግማ ጥሰት ነው፡፡
ሇ) ዓሇም አቀፍ ጉባኤያት
ጉባኤያት ዓሇማቀፋውያን ጉባኤያት የሚባለት ከኹለም አብያተ ክርስቲያናት የመጡ ተወካዮች
ሲኖሩበት ነው፡፡ የጉባኤው መነጋገሪያ አጀንዲም ዓሇማቀፋዊ መኾን አሇበት፡፡ የተወሰነው (የሚወሰነው)
ውሳኔም በኹለም አብያተ ክርስቲያናት ዘንዴ ተፈጻሚ መኾን አሇበት፡፡ የነገሩ ጉዲይ ሇአንዱት ሀገር
ብቻ የሚተው መኾን የሇበትም፡፡ ሇምሳላ በ325 ዓ.ም. የተካሔዯው የኒቅያ ጉባኤ ዓሇማቀፋዊ አጀንዲን
የያዘ (ዓሇም ስሇመዲኑና ስሊሇመዲኑ)፣ ከኹለም አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች የነበሩበት፣ ውሳኔውም
በኹለም አብያተ ክርስቲያናት ዘንዴ ተፈጻሚነት የነበረው ነው፡፡
በኦሬንታሌ ኦርቶድክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንዴ ተቀባይነት ያሊቸው ዓሇም አቀፍ ጉባኤያት ሦስት
ሲኾኑ፤ ምሥራቃውያን 7፥ ካቶሉኮች ዯግሞ 20 ይቀበሊለ፡፡
ኦሬንታሌ አርቶድክሶች የምንቀበሊቸው ሦስቱም ጉባኤያት ጉባኤ ኒቅያ (በ325 ዓ.ም. የተካሔዯ)፣ ጉባኤ
ቁስጥንጥንያ (በ381 ዓ.ም. የተካሔዯ) እና ጉባኤ ኤፌሶን (በ431 ዓ.ም. የተካሔዯ) ናቸው፡፡ በእነዚኽ
ዓሇም አቀፍ ጉባኤያት ብዙ ቀኖናዎች ተዯንግገዋሌ፡፡ ሇምሳላ በጉባኤ ኒቅያ ከተወሰኑት ቀኖናት
የትንሣኤ በዓሌ እሐዴ መከበር እንዲሇበት፣ ስሇ አርዮስ ጉዲይ፣ ስሇ መጻሕፍት ጉዲይ፣ ስሇ አራቱ
መንበረ ፓትሪያሪኮች ይገኙባቸዋሌ፡፡
ሏ) ብሔራውያን ጉባኤያት
ከዓሇማቀፋውያን ጉባኤያት በተጨማሪ በየአካባቢው ጉባኤያት ሉዯረጉ ይችሊለ፡፡ ሇምሳላ በቅደስ
ያሬዴ ዜማ ሊይ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጕዲይዋ አይዯሇም፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጉዲይ አይዯሇም
ብሇን ግን በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕድ ቤተ ክርስቲያን ስር ኾነን ያሬዲዊ መዝሙር አያስፈሌገንም
ወይም በኦርጋንና በፒያኖ እንዘምር ማሇት አንችሌም፡፡ እነርሱ በያሬዲዊ መዝሙር ስሊሌዘመሩ ብሇንም
ሃይማኖታዊ (የድግማ) ወይም የቀኖና ችግር አሇባቸው አንሌም፤ ውሳኔው በብሔራዊ ጕባኤ የተወሰነ
ነውና፡፡

ከብሔራውያን ጉባኤያት በተጨማሪ ሀገረ ስብከታዊ ጉባኤም ሉዯረግ ይችሊሌ፡፡ አጥቢያዊ ጉባኤም
ሉኖር ይችሊሌ፡፡ ነገር ግን በአንዴ ሀገረ ስብከት የተወሰነው ውሳኔ በላሊ ሀገረ ስብከት ተፈጻሚ ሊይኾን
ይችሊሌ፡፡ በአንዴ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራ ቀኖናም በላሊ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሊይሠራ
ይችሊሌ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በአንዲንዴ ገዲማት ሊይ ሴቶች አይገቡም የሚባሇው የዚያ ገዲም ብቻ
ቀኖና ስሇሚኾን ነው፡፡

4/8
መ) የቅደሳን አበው ቀኖናት
እነዚኽ ቀኖናት ምንም እንኳን በግሇሰብ ዯረጃ የተወሰኑ ቢኾኑም ቤተ ክርስቲያን የእኔ ብሊ
የተቀበሇቻቸው ቀኖናት ናቸው፡፡ ሇምሳላ ሥርዓተ ምንኩስና የነ አባ እንጦንስ ወይም የእነ አባ ጳኩሚስ
ሃይማኖት አይዯሇም፤ የእነዚኽ ቅደሳን አባቶች የትሩፋት ሥራ እንጂ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ስሇ
ቅደስ ቁርባን የተናገረው ሥርዓት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ሥርዓት ኾኖ የቀረውም ከዚኽ አንጻር ነው፡፡
የቅደሳን ገዴሊትና ዴርሳናትም እንዯምንጭነት ይጠቀሳለ፡፡
የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይዘት
ቤተ ክርስቲያናዊ ቀኖና በውስጡ በጣም ብዙ ነገሮችን ያካተተ ነው፡፡ የቅደሳት መጻሕፍት ቀኖና፣
የሥርዓተ አምሌኮ ቀኖና፣ የአጽዋማት ቀኖና፣ የበዓሊት ቀኖና፣ የቅደሳን ቀኖና፣ የቅደሳት ሥዕሊት
ቀኖና፣ የአሇባበስ ቀኖና ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እስኪ ጥቂቶቹን ብቻ እንዯማሳያ በአጭር በአጭሩ ሇማየት
እንሞክር፡-
1. የቅደሳት መጻሕፍት ቀኖና
የቅደሳት መጻሕፍት ቀኖና ስንሌ የመጻሕፍቱ እውነተኛነትን፣ ቅደስነትንና አምሊካዊነትን የተመሇከተ
ማሇታችን ነው፡፡ እነዚኽን ቅደሳት መጻሕፍት ሰፍረውና ቇጥረው የሰጡንም ለተራውያን ወይም
ካቶሉካውያን ሳይኾኑ ኦርቶድክሳውያን አባቶቻችን ናቸው፡፡ በተሇይም እነ ቅደስ ሄሬኔዎስ፣ ቅደስ
አግናጥዮስ ምጥው ሇአንበሳ፣ ቅደስ አትናቴዎስ በዚኽ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

እነዚኽ ቅደሳን አባቶች የብለይ ኪዲንን መጻሕፍት ሇመቀበሌ ያስቀመጧቸው መስፈርቶች ነበሩ፡፡
ከእነዚኽም መካከሌ፡-
 ወዯ ግሪክኛ የተተረጏመ፡፡ አባቶች ይኽን ያለበት ዋናው ምክንያት አይሁዲውያኑ የጌታችንን
የባሕርይ አምሊክነት ካሇመቀበሊቸው የተነሣ ብለይ ኪዲንን ቇነጻጽሇዉት ስሇነበር ነው፡፡
ስሇዚኽ ከዚኽ ከተቇነጻጸሇው መጽሏፍ ሉመጣ ከሚችሇው ግዴፈት ሇመዲን አይሁዲውያኑ
ይኽን እንዯሚያዯርጉ አስቀዴሞ የሚያውቅ እግዚአብሔር በ285 ቅ.ሌ.ክ. ሊይ ወዯ ግሪክኛ
የተተረጏመው የብለይ ኪዲን መጽሏፍ መቀበሌ ግዴ ኾኖባቸዋሌ፡፡
 የዕብራውያን ባሕሌ ያሇበት፡፡ አባቶች መጽሏፉ የዕብራውያን ባሕሌ ያሇበት መኾን አሇበት
ያለበት ምክንያት እግዚአብሔር አስቀዴሞ ሇዕብራውያኑ በባሕሊቸው ስሇነገራቸው ነው፡፡
መጽሏፉ ዕብራዊ ባሕሌ ከላሇበት ተቀባይነት አያገኝም፡፡
 የአብርሃም እምነት ያሇበት፡፡ የአብርሃም እምነት መኾን አሇበት ሲለም ከአንዴ አምሊክ በቀር
ወዯ ባዕዴ አምሌኮ የሚመሩትን መጻሕፍት ሇመሇየት ነው፡፡
የሰባ ሉቃናት ትርጕም የምንሇውም ይኽን ቀኖና ተከትል የተሠራ ትርጕም ነው፡፡ በ2000
ዓ.ም. የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ያሳተመችው መጽሏፍ ቅደስ ትርጕሙ አብዛኛው ከዚኹ ትርጕም
የተወሰዯ ነው፡፡
እናስተውሌ! በአንዲንዴ የአማርኛ ትርጕሞች ሊይ (ሇምሳላ በ1980 ዓ.ም. እትም ሊይ) በስሕተት
ተጽፎ የምናገኘው ቢኾንም በኦርቶድክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ዳትሮካኖኒካሌ የሚባለ
መጻሕፍት የለም፡፡ ዳትሮካኖኒካሌ የሚለት ካቶሉኮች ናቸው፡፡ ይኸውም ተጨማሪ መጻሕፍት
ሇማሇት ነው፡፡ ነገር ግን እነዚኽ መጻሕፍት ከመዠመሪያውኑ የነበሩ እንጂ በኋሊ የተጨመሩ
አይዯለም፡፡ ሇዚኽ ማረጋገጫውም በ1948 ዓ.ም. ሊይ በሙት ባሕር ሊይ በተገኙት ጥቅልች እነዚኽ
ተጨማሪ ናቸው ተብሇው የታሰቡት መጻሕፍት በዕብራይስጥ ተጽፈው መገኘታቸው ነው፡፡ ስሇዚኽ
አይሁዲውያኑ በ280 ዓ.ም. ሊይ ታናክ የሚለትን የመጽሏፍ ቅደስ ክፍሌ ቀኖና ሲሠሩ የሰባ ሉቃናቱን
ትርጕም የክርስቲያኖች መጽሏፍ ነው ብሇው ስሇቇነጻጸለትና ስሇቀነሷቸው እንዯተጨማሪ መጻሕፍት
ማየት (ዳትሮካኖኒካሌ ናቸው ማሇት) በጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ያሌነበረ ነው፡፡
አኹንም እናስተውሌ! እነዚኽን መጻሕፍት እንዯ ፕሮቴስታንቱ ዓሇምም አፖክሪፋ አንሊቸውም ::
አፖክሪፋ ማሇት በግሪክኛ የተሰወረ፣ ያሌተገሇጠ፣ ከእግዚአብሔር ያሌተሰጠ ሇማሇት ነው፡፡

5/8
ፕሮቴስታንቱ ዓሇም ይኽን እንዱሌ ያዯረገው ዋናው ምክንያት ከሊይ እንዯገሇጽነው አንዯኛ የካቶሉክ
ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍቱን ተጨማሪ ናቸው ስሊሇችና እነርሱም ከካቶሉክ ቤተ ክርስቲያን ሲወጡ
ተጨማሪ የሚሇውን ቃሌ ብቻ ይዘው ተጨማሪ አያስፈሌገንም በማሇት፤ ኹሇተኛ አይሁዲውያኑ
የጌታችንን የባሕርይ አምሊክነት ሊሇመቀበሌና ሇክርስቲያኖች በነበራቸው የመረረ ጥሊቻ በተንኯሌ
የቇነጻጸለትን መጽሏፍ ያሇምንም ጥያቄ ስሇተቀበለት ነው፡፡ ስሇዚኽ ራሳችንንና ወንዴማችንን
ከእንዯዚኽ ዓይነት ኦርቶድክሳዊ ያሌኾነ ትምህርት ሌንጠነቀቅ ይገባሌ፡፡ አብዛኞቹ የእንግሉዘኛ
የመጽሏፍ ቅደስ ትርጕሞች የተተረጏሙት ከዚኹ አይሁዴ ከቇነጻጸለት ቀኖና የተወሰዯ መኾኑንም
ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ ዯኅና ነው ተብል የሚታሰበው “Revised Standard Version” የሚባሇው
ነው፡፡
ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሏዱስ ኪዲንን መጻሕፍት ሇመሇየት የተጠቀሙበት መስፈርትም አሇ፡፡
እርሱም፡-
 ሏዋርያት ወይም የሏዋርያት ዯቀ መዛሙርት የጻፉት መኾን አሇበት፤
 ከ99 ዓ.ም. በፊት መጻፍ አሇበት፡፡ ይኽን ያለበት ዋና ምክንያትም ከ105 ዓ.ም. በኋሊ
የግኖስቲኮች የክሕዯት መጻሕፍት በስርጭት ሊይ ስሇነበሩ ነው፡፡
 የክርስቶስና የሏዋርያት ትምህርት የሚገሌጽ መኾን አሇበት፡፡
አንዴ ኦርቶድክሳዊ ምእመን ቅደሳት መጻሕፍትን (አሥራውም ይኹኑ አዋሌዴ) ሲሇይ ከምንም
በሊይ ማየት ያሇበት ቁጥሩን (81፣ 66፣ 73፣ 76 የሚሇውን) ሳይኾን ኦርቶድክሳዊ ይዘታቸውን
ነው፡፡ አንዴ መጽሏፍ ኦርቶድክሳዊ ይዘት እንዲሇው የሚታወቀውም፡-
 ነገረ እግዚአብሔርን የሚያስክዴ ካሌኾነ፡፡ ሇምሳላ የጀሆቫ ዊትነስ፣ የሞርሞን አማኞች
ያዘጋጁት “መጽሏፍ ቅደስ” ፍጹም ክሕዯት ነው፡፡
 የሟርት ይዘት ከላሇው፡፡ ምንም እንኳን ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቅ ቢኾንም የዚኽ ጽሐፍ
አዘጋጅ እስከ አኹን ዴረስ ባሇው መረጃ መሠረት በሏዱስ ኪዲን ኅቡእ ስም የሇም፡፡ ምንም
እንኳን በአንዲንዴ የቤተ ክርስቲያናችን ዴርሳናት ሊይ እንዱኽ ዓይነት ጽሐፍ ብናገኝም ወዯ
ኋሊ ስንሔዴና የዚያ ዴርሳን ጥንታዊውን የብራና ጽሐፍ ስንመሇከት ግን ጸ፣ጸ፣ጸ፣ጸ፣ጸ፣ጸ፣ ጨ፣
ጨ፣ ጨ፣ ጨ፣ ገ፣ ገ፣ ገ፣ ገ፣ ገ… የሚሌ ኅቡእ ስም የሇውም፡፡ እነዚኽ ኅቡእ ስሞች በኋሊ ሊይ
በስርዋፅ የገቡ ናቸው፡፡ አኹን አኹን የሚታተመውን ዴርሳነ ሚካኤሌን እንዯ አንዴ ማሳያ
ብንወስዯው ከ15ኛ መቶ ክፍሇ ዘመን በፊት በነበረው የዴርሳነ ሚካኤሌ የብራና ጽሐፍ ሊይ
እንዱኽ ዓይነት ኅቡእ ስም የሇውም፡፡ ዘወትር ሇጸልት በምንጠቀምበት በወንጌሌ፣ በመዝሙረ
ዲዊት፣ ወይም በውዲሴ ማርያም ኅቡእ ስም የሇም፡፡ ኅቡእ ስም ተብል በብዛት የምናገኘው
በተሇይ ከቅርብ ጊዜ ወዱኽ በግሇሰቦች በሚታተሙት መጻሕፍት ሊይ ነው /የቃሌ መረጃ ከመምህር
ዲንኤሌ ሰይፈሚካኤሌ፣ በቅዴስት ሥሊሴ መንፈሳዊ ኮላጅ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን መምህር/፡፡ በመኾኑም በቤተ
ክርስቲያናችን በአዋሌዴ መጻሕፍት ቀኖና ዙርያ ብዙ የሚቀር ሥራ እንዲሇ ያመሇክታሌ፡፡
የሚመሇከታቸው ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም የዴርሻቸውን እንዯሚወጡ እምነታችን
ነው፡፡
 እምነታችንን ከእግዚአብሔር አውጥቶ ሇላሊ አካሌ አሳሌፎ የሚሰጠን ካሌኾነ፡፡ ሇምሳላ ይኽን
ቃሌ ዯጋግመኽ በሇው ካሇ፤ የፈጣሪን ሥራ በላሊ የሚቀይር ከኾነ፤ ከዚኽ ከዚኽ የሚያዴኑ
ጸልቶች የሚሌ ከኾነ፤ በትራስኽ ሊይ ብትንተራሰው ካሇ፤ ይኽን ክታብ በአንገትኽ ሊይ
ብታንጠሇጥሇው የሚሌ ዓይነት ከኾነ ያሇ ምንም ቅዴመ ኹኔታ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት
እንዲሌኾኑ ዏውቀን ሌንጥሊቸው ይገባሌ፡፡

2. የቅደሳን ቀኖና
በቀኖና ወይም በሥርዓት ዯረጃ ቅደሳንን ማክበር የተዠመረው ከኹሇተኛው መቶ ክፍሇ ዘመን አንሥቶ
ነው፡፡ ነገር ግን ይኽን ያዯረገው ቅደስ ሲኖድስ ሳይኾን ሕዝቡ ወይም ምእመኑ ራሱ ነው፡፡ በዚኽም
ቀዴመው ይታሰቡና ይከበሩ የነበሩት ቅደሳን ሰማዕታት ናቸው፡፡ ከአራተኛው መቶ ክፍሇ ዘመን
ዠምሮ ግን አንዲንዴ ሰዎች በራሳቸው እይታ ቅደስ እንዯኾነ የሚያስቡትን ኹለ ቅደስ ሇማስባሌ
ስሇተነሣሡ ቤተ ክርስቲያን በጉባኤ ዯረጃ ቀኖና ቅደሳን ማውጣት ዠመረች፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና
ቅደሳን ማውጣት ዠመረች ማሇት ግን ሇሰዎቹ ቅዴስናን ሰጠች ማሇት ሳይኾን ሇቅዴስናቸው ዕውቅናን
6/8
ሰጠች ሇማሇት ነው፡፡ ይኸውም ከትሩፋታቸው ብዙ እንዴንማር፣ በቃሌ ኪዲናቸው እንዴንጠቀም፣
አሰረ ፍኖታቸውን እንዴንከተሌ፣ አማሊጅነታቸውን እንዴንጠይቅ ነው፡፡
አንዴን ቅደስ ቅደስ ሇማሇት መስፈርቶች አለት፡፡ ጥቂቶቹን ሇመጥቀስ ያኽሌ፡-
 ከምንም በፊት ክርስቲያን መኾን አሇበት፡፡ አምኖ የተጠመቀ፣ ቅደሳት ምሥጢራትን ሲፈጽም
የኖረና ከእኩያት ጋር የተጋዯሇ መኾን አሇበት፡፡ አሇበሇዚያ ክርስቲያን ሳይኾኑ (ካቶሉክም
ፕሮቴስታንትም ጭምር) የፈሇገ ያኽሌ በጏ ምግባር ቢኖራቸውም ቅደሳን አይባለም፡፡
 በክርስቲያናዊ ምግባራቸው የታወቁ፡፡ ሃይማኖት ያሇ ምግባር የሞተ ነውና፡፡ እንዱኽ ሲባሌም
ፈጽመው ኃጢአት ያሌሠሩ ሇማሇት አይዯሇም፤ እንዱኽ ያሇ ዕሩቅ ብእሲ ከእመቤታችን በቀር
ማንም አይገኝምና፡፡
 ገቢረ ተአምራትን የፈጸሙ፡፡ እንዱኽ ሲባሌም ተአምራትን ማዴረግ ብቻውን መስፈርት ሉኾን
እንዯማይገባ ሉታወቅ ይገባሌ /ማቴ.7፡21/፡፡
 ቅደሳኑ ካረፉ በኋሊ ዓጽማቸው ሕሙማንን ከፈወሰ፤ ባረፉበት ቦታ ጠበሌ ከፈሇቀ፡፡
 ሇየት ያሇ አገሌግልት ሇቤተ ክርስቲያን ካበረከቱ፡፡ ሇምሳላ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. እነ ቅደስ ሊሉበሊ፣
እነ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ ሇኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያዯረጉትን
አስተዋጽኦ ማስታወሱ በቂ ሉኾን ይችሊሌ፡፡
እንዱኽ በቀኖናው መሠረት ቅደስ የተባሇው ታሊቅ ሰው ቅዴስና ሲሰጠው የሚከተለት ነገሮች
ይፈጸሙሇታሌ፡-
 በስሙ ቤተ ክርስቲያን ይታነጽሇታሌ፤
 ገዴሌ ይጻፍሇታሌ፤
 በዓሌ ይዯረግሇታሌ፤
 ቅዴስናውን አጕሌቶ የሚያሳይ ሥዕሌ ይሣሌሇታሌ፤
 ዏፅሙ በክብር እንዱያርፍና ምእመናን እንዱያከብሩት ይዯረጋሌ፤
 ምእመናን በስሙ ሉሰየሙና ውለዯ እግዚአብሔር ሉባለ ይችሊለ /በዓሊት ምን? ሇምን? እንዳት?፣
በዱ/ን ብርሃኑ አዴማስ፣ 2005 ዓ.ም.፣ ገጽ 144-145/፡፡

3. የሥርዓተ አምሌኮ ቀኖና


በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንፈጽመው ማንኛውም ዓይነት መንፈሳዊ ዴርጊት የአምሌኮ ባሕርይ
አሇው፡፡ ስናምን፣ ስንሰጥ፣ ስንቀበሌ ኹለ አምሌኮ ነው፡፡ ማንኛውንም ዓይነት ምሥጢር ስንፈጽም
የእግዚአብሔር መኾናችንን ነው የምንገሌጠው፡፡
ያሇ ሃይማኖት ሀብተ መንፈስ ቅደስን መቀበሌ አይቻሌም፡፡ የእግዚአብሔር ሀብት ከእግዚአብሔር ጋር
በመኾን እንጂ እንዯ ሲሞን መሠሪ የምንገዛው አይዯሇምና፡፡
ሃይማኖት መታዘዝንም ይጨምራሌና እንዯ ቀኖና ዱያቆኑን፣ ቄሱን ወይም ጳጳሱን ማክበር
ይጠበቅብናሌ፡፡ በጉዴሇት፣ በትዕቢት፣ በጭቅጭቅ የምንቀበሌ ከኾነ አሇመታዘዝ ነው፡፡ ሇምሳላ
አንዲንዴ ሰዎች ዯናግሊን ሳይኾኑ ተክሉሌ ካሌተዯረገሌን ብሇው ይጨቃጨቃለ፡፡ በዚኽም ምሥጢረ
ተክሉሌን ሲፈጽሙ አምሌኮተ እግዚአብሔር እየፈጸሙ እንዯኾኑ ይረሳለ፡፡ ከሥርዓተ አምሌኮው
ይሌቅ በቤታቸው ስሇሚሰቅለት ፎቶ ይጨነቃለ፡፡ ስሇዚኽ ቀኖናና አምሌኮ በእጅጉ የተቇራኙ
መኾናቸውን ዏውቀን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በምንፈጽማቸው መንፈሳዊ ዴርጊቶች ሊይ ሌንጠነቀቅ
ይገባናሌ፡፡

4. ሥርዓተ ሲመትን የሚመሇከት ቀኖና


በጥምቀት የተወሇዯ ኹለ አገሌጋይ ነው፤ “ያገሇግለኝ ዘንዴ ሕዝቤን ሌቀቅ” እንዱሌ /ዘጸ.8፡1/፡፡
ይኸውም አሥራቱን ቀዲምያቱን የሚያወጣ፣ የሚታዘዝ ሕዝብ ይኾነኝ ዘንዴ ማሇት ነው፡፡ ከእነዚኽ
ከተጠመቁት ተመርጠው የሚያገሇግለት ዯግሞ ስዩማነ ካህናት (የአገሌጋዮች መሪዎች) ይባሊለ፡፡
እነዚኽን ስዩማነ ካህናት ሇመሾምም የራሱ የኾነ መስፈርት አሇው፡፡ ይኽን መስፈርት ሳያሟሊ ማንም
ራሱን ሉሾም አይችሌም፡፡ ከ12ቱ ሏዋርያት አንደ ይሁዲ ሲጏዴሌ ሏዋርያት በይሁዲ ፈንታ ላሊ
አንዴን ሏዋርያ ሇመሾም ሲጾሙ፣ ሲጸሌዩ፣ ዕጣ ሲጥለ፣ እጅግ ተጨንቀው ይኽን ኹለ ሲያዯርጉ
ማየታችን ኹለም ሰው ሏዋርያ እንዲሌኾነ የሚያስረዲ ነው፡፡ በላሊ አገሊሇጽ አንዴን ክርስቲያን ስዩመ
ካህን ሇማዴረግ የራሱ መስፈርት እንዲሇው የሚያስገነዝብ ነው፡፡
7/8
በአጠቃሊይ ቀኖና እጅግ በጣም አስፈሊጊ ነው፡፡ ምክንያቱም፡-

1. የፍሊጏት ሌዩነት በሰዎች መካከሌ አይቀሬ ነው፡፡ እነዚኽን ሰዎች ወዯ ስምምነት ሇማምጣት ዯግሞ የግዴ
ሕግ ያስፈሌጋሌ፡፡ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሉኖሩ የሚችለ አሇመስማማቶችን
የሚፈታ ነው፡፡
2. በሰውነታችን ውስጥ ያለት ብሌቶች የየራሳቸው ዴርሻ አሊቸው፡፡ ብዙዎች ቢኹኑም አንዴ ሰውነት
ናቸው፡፡ ብዙዎች ኾነው ሳሇ የአንዴ ሰውነት አባሌ ኾነው መቀጠሌ የሚችለት ግን እጅ የእግርን፣
ዓይን የዦሮን ሥራ ሌሥራ እስካሊሇች ዴረስ ብቻ ነው፡፡ እንዱኽ ሕገ ተፈጥሮን ጥሶ መዘበራረቅ ካሇ
ሰውነት እንዯ ሰውነት መቀጠሌ አይችሌም፡፡ ሌክ እንዯዚኹ እኛ ክርስቲያኖችም ብዙዎች ብንኾንም
የአንዴ ክርስቶስ ብሌቶች ነን፡፡ የአንዴ ክርስቶስ ብሌቶች ኾነን የምንቀጥሇው ግን ካህኑ የክህነቱን
ምእመናንም የምእመናንን ሥራ የሠራን እንዯኾነ ብቻ ነው፡፡ አንደ ምእመን ተነሥቶ የካህኑን ሥራ
ሌሥራ ቢሌ የቤተ ክርስቲያን አንዴነት ሉጠበቅ አይችሌም፡፡ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይኽ አንዴነት
እንዱኖር ይረዲሌ፡፡
3. ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዯ ቤተ ክርስቲያን ሌጅነታችን መብታችንና ግዳታችንን ሇይቶ የሚነግረን
ነው፡፡ ሇምሳላ አንዴ ምእመን ዏሥራት በኵራት የማውጣት ግዳታ አሇበት፡፡ ሇሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
መገዛት አሇበት፡፡ ይኽን ሳያዯርግ ቀርቶ ከቤተ ክርስቲያን መጥቶ ምሥጢራትን ሌፈጽም ቢሌ
ተቀባይነት የሇውም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሕግስ ይቅርና የትራፊክ ሕግም ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡

ወስብሏት ሇእግዚአብሔር !!!

ምንጭ: http://.mekrezetewahdo.org/2014/12/blog-post_23.html#more

8/8

You might also like