You are on page 1of 16

ማውጫ

1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን


ታሪክ ....................................................1
2 በታሪክ .....................................................2
1.1መሠረቶች.............................................2
1.2መካከለኛዘመን.......................................4

2 ልዩ ባሕርይ .................................................5
2.1 የሚቀበሉ ቅዱሳን መጻሕፍት.................5
2.2 ልሳነ ቅዳሴና ልሳነ ስብከት....................6
2.3 ሥነሕንፃ...........................................6
2.4 ታቦት...............................................7
3. የንግስተ ሳባ ንጉስ ሰሎሞንን መጎብኘት...........14

4. የኢትዮጵያ ንጉሥ ባዜን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ


በቤተልሔም ሲወለድ ወርቅ ዕጣን ከርቤ ከገበሩለት
ሦስት ነገሥታት አንዱ ስለመሆኑ...................15

5. የኢትዮጵያ ንግሥት ህንደኬ አዛዥና ጃንደረባ ባኮስ


የኢየሩሳሌም የአምልኮ ጉዞና ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ
ስለማምጣቱ..................................................17

6. ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ.........................21

I
የኢትዮጵያ «ተዋሕዶ» ከ ልሣነ ግእዝ የመነጨ
ቃል ሲሆን፣ትርጒሙም “አንድ ሆነ”
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማለትነው።
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል
ቤተክርስቲያን ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ
ነስቶ በተዋሕዶ ከበረ ማለት ነው።
ታሪክ ለዚሁም በዐረብኛ ተመሳሳይ ቃል
ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር የምስጢር “ታውሒድ” ሲባል በአንድ አምላክ
ሀገር ናት፡፡አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ብቻ ማመን የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ
«ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ያመለክታል።
ትዘረጋለች» (መዝ. ፷፯፥፴፩) ተብሎ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ
እንደ ተነገረላት በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ክርስቲያናት ቃሉ የሚነካ የክርስቶስ
ኪዳን እንደ ማዕዘን ድንጋይ የሚታዩ ባሕርይ በ”ሰብዓዊ” እና በ”መለኮታዊ”
ታቦተ ጽዮን እና ግማደ መስቀሉን ተለይቶ ሳይሆን አንድ ብቻ እንደሆነ
እጆቿን ዘርግታ ተቀብላለች፡፡ከሌሎች የሚለው ጽኑ እምነትነው።
ክፍለ ዓለማትም ተለይታ የብሉይና በ443 ዓ.ም. (451 እ.ኤ.አ.) በሮማው
የሐዲስ ኪዳን እምነት አሻራ በጉልህ ንጉሥ መርቅያን ዘመነ መንግሥት
ይንጸባረቅባታል፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፮፻፶ ኤጲስ ቆጶሳት በተገኙበት
ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከስድስቱ የተሰበሰበው የኬልቄዶን ጉባኤ
የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ከሮማው ሊቀጳጳሳት ቀዳማዊ ልዮን
ክሪስቲያናት ማለትም “ክርስቶስ ሁለት
• ከኮፕት (ግብጽ)፣ የተለያዩ ባሕርያት አሉት” የሚል ጽሑፍ
• ህንድ፣ አቅርቦላቸው ነበር።
• ሶርያ፣ ዳሩ ግን የእስክንድርያው ፓትርያርክ
• አርመንና ቅዱስ ዲዮስቆሮስ “ጌታ ሁለት ባሕርያት
• ኤርትራ አንዷ ናት።ኢትዮጵያ አሉት” የሚለው ትምሕርት ስሕተት ነው
በመጽሐፍ ቅዱስ ከ፵ ጊዜ በላይ ብሎ ልዮንን አወገዘው።
የተነሳች ሲሆን ከክርስትና በፊት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ አብያተ
የብሉይ ኪዳንን እምነትና ባህል ተቀብላ ክርስቲያናት በእምነት ተለያዩ።
እግዚአብሔርን ታመልክ እንደነበር የቅዱስ ዲዮስቆሮስን ትምሕርት
መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። የሚከተሉ ዛሬ የአርሜኒያ፣ የሕንደኬ፣
1.በታሪክ የግብፅ፣ የሶርያ፤ የኤርትራ እና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ
መሠረቶች ክርስቲያናት ናቸው።
1 2
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ወደ ነገሥታቱም ግቢ አመጧቸውና
ቤተክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ቀስ በቀስ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለበትን
ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ደረጃን አገኙ።ንጉሥ ኢዛናን ደግሞ
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁለት ባሕርይ አንድ ወደ ክርስትና ለውጠው እንዲጠመቁ
ባሕርይ ከሁለት አካል አንድ አካል አደረጉ።ኤዛና ፍሬምናጦስን ለኢትዮጵያ
በመንሳት ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ አቡን እንዲሾም ለመጠየቅ ወደ
ማለት ነው። እስክንድርያ ላኳቸውና የእስክንድርያ
የቤተክርስቲያን መመስረት በኢትዮጵያ ጳጳስ አትናቴዎስ ፍሬምናጦስን ሾሞ
የተጀመረው በወንጌል ሰባኪ ላከው።ፍሬምናጦስ የመጀመሪያው
ቅዱስ ፊልጶስ መሆኑ ይታወሳል የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ሲሆን
(ሐዋርያትምዕራፍ፰)፦ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ
«እነሆም፥ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ አቡነ ባስልዮስ ደግሞ ፻፲፩ ኛው
ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረበ መሆናቸው ነው።
ገንዘቧም ሁሉ የሰለጠነ አንድ መካከለኛ ዘመን
የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ እስላሞች ወደ ግብጽ ከገቡ
ኢየሩሳሌም መጥቶነበር...» በኋላ ከእስክንድርያ ጋር የነበረው
በዚህ ንባብ ዘንድ ፊልጶስ ጃንደረባውን ግንኙነት ቀጥሏል።ጸሐፊው አቡ
የትንቢተ ኢሳይያስ ክፍል እንዲገባው ሳሊኅ በ፲፪ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን
አስረድቶት በክርስትና አጠመቀው። እንደገለጸው፣ፓትርያርኩ በየዓመቱ
ንግሥት ግርማዊት ህንደኬ ፯ኛ ከ ፪ ደብዳቤዎች ለኢትዮጵያና ለኖቢያ
፴፬ ዓ.ም. እስከ ፵፬ ዓ.ም. ገደማ ነገሥታት ይጽፉ ነበር።ይህንን አደራረግ
በኢትዮጵያ የነገሡ ናቸው። ግን አቡሃኪም አስቀረ። ፷፯ ኛው
በ ፬ኛው ምዕት ዘመን በወንድማማቾቹ ፓትርያርክ ቂርሎስ እንደ ኤጲስ
በንጉሥ ኤዛና እና በንጉሥ ሳይዛና ቆጶስ የላኩት ሰቨሩስ ሲሆኑ የቤተ
ዘመን በፍሬምናጦስ አማካይነት ክርስቲያንን ሥርዓት ሁሉ እንዲያስጠበቁ
ክርስትና የግዛቱ ይፋዊ ሃይማኖት ታዘዙ።
ሆነ።ይህ ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያ በ ፲፬፻፴፩ ዓ.ም. በዓጼ ዘርዐያዕቆብ
«አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን» ተብሎ ዘመን አባጊዮርጊስ ከአንድ ፈረንሳዊ
ይታወቃል። ጐብኚ ጋራ ስለ ሃይማኖት ስለ ተነጋገሩ
በወጣትነት ዕድሜው ከአጎቱ ከፈላስፋው አንድ ተልዕኮ ወደ ሮማ ተላከ።
ከመሮፔዎስ እና ከወንድሙ ከሲድራኮስ በ ፲፭፻ ዓ.ም. ደግሞ ኢትዮጵያ
ጋራ መርከባቸው ስለሰመጠች ከወንድሙ ከአዳል ጋር ስትታገል ማቴዎስ የተባለ
ጋር ከሞት ተርፈው ምጽዋ አጠገብ አንድ አርሜናዊ ወደ ፖርቱጋል ተልኮ
ተገኙ።
3 4
የፖርቱጋል ንጉሥ እርዳታን ለመነ። ይህ የቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር በቀኖና
ስለዚህ በ፲፭፻፲፪ ዓ.ም. የፖርቱጋል በ ፫፻፲፰ ቱ አበው ሊቃውንት የኒቂያ
ሚሲዮን በኢትዮጵያ ደረሰ። ገባኤ ተደንግጓል።
በሚከተለው ክፍለ ዘመን ከፖርቱጋል ልሳነ ቅዳሴና ልሳነ ስብከት
ኢየሱሳውያን የተባሉ ሚሲዮኖች
ቤተመንግሥቱን ወደ ሮማካቶሊክ
ሥነ ሕንፃ
ሃይማኖት ለማዞር ብዙ ጣሩ።
በመጨረሻ በ ፲፮፻፲፯ ዓ.ም.
ንጉሥ ሱስንዮስ ወደ ሮማ ካቶሊክ
እምነት ተቀየሩ። ዳሩ ግን የሮማ
ሃይማኖት በተዋሕዶ ፈንታ ይፋዊ
መሆኑን ሕዝቡ በጣም አልወደደምና
በ፲፮፻፳፭ ዓ.ም ሱስንዮስ ዘውዳቸውን
ለልጃቸው ለ ፋሲለደስ እንዲሰጡ
ተደረጉ።ፋሲለደስ ወዲያው አገሩን
ወደ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መለሱ። ቤተጊዮርጊስ፣ ላሊበላ
ከዚህ በላይ በ ፲፮፻፳፮ ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥነ
ፋሲለደስ ኢየሱሳውያን አገሩን ለቅቀው ሕንፃ የቤተክርስቲያናት ትውፊታዊ
እንዲሄዱ አዘዙ።በ ፲፮፻፶፰ ዓ.ም. የሥነ ሕንጻ ጥበቧ አምስት ዓይነት
መፃሕፍታቸውም እንዲቃጠሉ አዘዙ። ነው።እነርሱም
1.ክብ፥
2.ልዩባሕርይ 2.መስቀልቅርፅ፥
የሚቀበሉ ቅዱሳን 3.ዋሻ፥
መጻሕፍት 4.ፍልፍል እና
ኢትዮጵያ ብሉይ ኪዳን እና ሐዲስ 5. ስቀልማ ናቸው።
ኪዳንን በሙሉ (ከነዲዩትሮካኖኒካል ክብ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት በብዛት
መፃሕፍትጋር) በመቀበል ብቸኛ ሃገር በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን፣
ናት።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መስቀል ቅርጽ ያላቸው ደግሞ በከተማ
ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው አካባቢ ይገኛሉ።
ቅዱሳት መፃሕፍት ቁጥራቸው ፹፩ ዋሻ አብያተ ክርስቲያናት በብዛት
ሲሆን እነዚህም ፴፭ የሐዲስ ኪዳን በተራራማ አካባቢዎች ሲገኙ፣ፍልፍል
መጻሕፍትና ፵፮ የብሉይ ኪዳን አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ከአንድ
መጻሕፍት ናቸው። ቋጥኝ ተፈልፍለው የተዘጋጁ ናቸው።
5 6
ሰቀልማ የሚባለው እንደ ደብረብርሃን ይህ ዶግማ ወይም እምነት
ሥላሴ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። ይባላል። ቀኖና ግን በአምላካችን
ታቦት በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉ
ትምህርተ ሃይማኖት (የሃይማኖት ክርስቲያኖች የሚመሩበት ሥርዓት
ትምህርት) በሁለት ይከፈላል።ይኸውም፦ ስለሆነ፣ በሃይማኖት አባቶች ወይም
1ኛ) ዶግማ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት እንደ
2ኛ) ቀኖና በሚል ነው። ‘ዶግማ’ ቃሉ ጊዜው ሁኔታ የሚሻሻል በመሆኑ
የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት የሚጨመርበት፣የሚቀነስለት ነው።
ነው። ለምሳሌ ያህል እኛ ኦርቶዶክሳውያን
‘ቀኖና’ ደግሞቃሉ የግሪክ ሲሆን የምንጠመቀው ሴት በተወለደች
ሥርዓት ማለት ነው። በሰማንያ ቀን፣ወንድ በተወለደ
ከእነዚህ ከሁለቱ ዶግማ ወይም እምነት በአርባቀን ነው።
አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም የተወለዱ ሕፃናት፣ሴቷ ሰማንያ
፤አይሻሻልም፤ችግርና ፈተናም ቢመጣ ወንዱም አርባ ቀን ሳይሞላቸው
እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ቢታመሙና በሽታው አስጊ ቢሆን
ነው።ለምሳሌ ያህል፣ይህን ዓለም የግድ የተባለው ቀን ሳይጠበቅበ
ካለ መኖር ወደ መኖር አምጥቶ 10፣በ 20፣በ30… ቀናቸው
የፈጠረ፤ቢመረምር እንጂ የማይመረመር መጠመቅ ይችላሉ ቀኖና ነውና።
ሁሉን ቻይ አምላክ፤የሚሳነው ነገር በቤተክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛት
የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር መነሻው አምስት ነው።
ባለቤት፣የሠራዊት ጌታ ሕያው ምናልባት ከአምስቱ አንዱ፣ ሁለቱ፣
እግዚአብሔር ነው። ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ
እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል እስከመጨረሻ የማይገኝ ከሆነ፣ከአቅም
ሦስትነት አለው። በመለኮት ፣በመፍጠር በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ፣ሁለቱ
፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ ፣በፈቃድ እና ወይም አንዱ ብቻ ቀድሰው ማቁረብ
በመሳሰሉትግንአንድነው። በሦስትነቱ ይችላሉ፤ቀኖና ነውና።
አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ ሲባል፣ በቤተ ክርስቲያናችን ታቦት ሲከብር
በአንድነቱ አንድ መለኮት፥ አንድ ቤተክርስቲያኑን የሚዞረው ሦስት ጊዜ
እግዚአብሔር ይባላል።በአዳም ምክንያት ነው ችግር ካለ አንድ ጊዜ ብቻ ዑደት
ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ተፈጽሞ ሊገባ ይችላል።ቀኖና ነውና፤ስለ
ባርነት ነፃ የወጣነው ከሦስቱ አካላት ቀኖና (ስለ ሥርዓት) ቅዱስ ጳውሎስ
በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ፣ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ጽፏል።
በኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
7 8
1. “ነገር ግን ሁሉን በአግባብና ይዞ መጓዝ ሐዋርያትን መከተል እንጂ
በሥርዓት አድርጉ” 1ኛቆሮ. 14፥40። ወደ ኋላ ተመልሶ አይሁድን መከተል
2. “ወንድሞች ሆይ በሠራንላቸው አይደለም።
ሥርዓት ሳይሆን በተንኮል ከሚሄዱት እንግዲህ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን
ወንድሞችን ሁሉ ትለዩ ዘንድ የሚቃወሙ ሰዎች ሁሉ፣ የሚቃወሙት
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀኖና (በሥርዓት) የሚመሩትን
እናዝዛችኋለን።እኛን ልትመስሉ እንደ ክርስቲያኖች ሳይሆን የእግዚአብሔር
ሚገባችሁ እኛም በእናንተ መካከል ያለ ቃል የሆነ መፅሐፍ ቅዱስን በመሆኑ
ሥራ እንዳልኖርን ራሳችሁ ታውቃላችሁ” እንዳይሳሳቱ አደራ እንላለን።
2ኛተሰ. 3፥6-7።ቀኖና (ሥርዓት) አሁን እንግዲህ የዶግማንና የቀኖናን
የሚወሰነው በሃይማኖት አባቶች ልዩነት ከተረዳን በቀጥታ ወደ ታቦቱ
እንደሆነና ወንጌልን የሚያስተምር ጥያቄ እንሄዳለን።
ሰው ለሚያስተምራቸው ክርስቲያኖች ጥያቄ 1፦ዛሬ በእኛ ቤተ ክርስቲያን
በሃይማኖት አባቶች የተወሰነ ቀኖና ያለው ታቦት ነው? ወይስ በታቦትና
ማስተማርና ትምህርት መሰጠት በጽላት መካከል ልዩነት አለ?
እንዳለበት መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል መልስ፦ ታቦት የጽላት ማደሪያ
ያስረዳል። ነው፤ዘዳ 40፥20።ጽላት ደግሞ
“በየከተማውም ሲሄዱ፣ሐዋርያትና ቅዱስ ቃሉ የተጻፈበት ሰሌዳ ማለት
ቀሳውስት በኢየሩሳሌም ነው፤ዘዳ 34፥27-28። ስለዚህ እነዚህ
ያዘዙትን (የወሰኑትን) ሥርዓት ሁለት ነገሮች ዛሬም በሐዲስ ኪዳን
አስተማሯቸው።አብያተ ክርስቲያናትም አሉ።ሆኖም ግን አሠራሩ ሙሉ በሙሉ
በሃይማኖት ፀኑ፤ዕለት ዕለትም በዘጸ 25፥10-18 ያለውን የሙሴን
ቁጥራቸው ይበዛ ነበር” ይላልየሐዋ. ሕግ የተከተለ አይደለም። ምክንያቱም፦
16፥4-5።በዚህ የእግዚአብሔር ቃል 1ኛ፦ታቦት እንደ ሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው
መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ደርቤንና ከግራር እንጨት ሆኖ፣ርዝመቱ ሁለት
ልስጥራን በተባሉ ቦታዎች ለነበሩ ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ
ክርስቲያኖች ወንጌልን ከሰበከ በኋላ ተኩል፣ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል
ሐዋርያት የወሰኑትን ቀኖና (ሥርዓት) ይሁን ይልና፣በውስጥና በውጭም በጥሩ
እንደሰጣቸው እንረዳለን። ወርቅ ለብጠው፣በዙሪያውም የወርቅ
ስለዚህ ቀኖና ወይም ሥርዓት አክሊል አድርግለት ይላል።ደግሞም
ቤተ ክርስቲያንን ይጠቅማል እንጂ ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ
አይጎዳም።በመሆኑም ዶግማንና ቀኖናን መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ
ወይም እምነትንና ሥርዓትን ጎን ለጎን እንረዳለን።
9 10
በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት
አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ
ዘንድ አይቻልም ነበር። የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው።
ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል
ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ነው።ሲቻል ይጨመርበታል፣ሳይቻል ደግሞ
ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ይቀነስለታል።
ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና
ቀላል አይደለም። ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ
2ኛ፦ጽላት እንደ ሙሴ ሕግ ከሆነ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና
መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ አጠቃቀምን ነው።
ድንጋይ ነው።በአንድ ታቦት ውስጥም ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን
መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ
ናቸው፤ዘዳ 34፥1። 1፥31 ላይ “እግዚአብሔርም የፈጠረውን
በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም
ሥርዓት ከባድ ነው።የብሉይ ኪዳኑ እንደሆነ አየ” ስለሚልና፣እግዚአብሔር
ሥርዓትም ለሐዲስ ኪዳኑሥርዓት ጥላ የፈጠረውን ስለማይንቅ፣ከግራር
ሆኖ አልፏል፤ 2ኛቆሮ 3፥7-11፤ቆላ ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ
2፥17፤ዕብ 10፥1። እንችላለን።ቁመቱ፣ወርዱና ዙሪያውም
እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ እንደ ችሎታችን ይሆናል።
ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት በውስጥና በውጭ ስለሚሆነው የወርቅ
አሠራርና ሥርዓት ጠንቅቆና ተከትሎ ክብርም እንደ ችሎታችን ይወሰናል።
የማይሄድ ከሆነ፣ “ይህ የብሉይ ኪዳኑን ከሌለንም ወርቁ ይቀራል፣ቀኖና
የታቦትና የጽላት አቀራረጽ ሥርዓት ነውና።
ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ስለ ጽላቱም እንደዚሁ ነው፥ከቻልን
ጽላት ከየት መጣ?” የሚል ጥያቄም ከከበረ ድንጋይ፣ከዕብነ በረድ መቅረጽ
ሳያስነሳ አይቀርም። እንችላለን፤ካልቻልን ጽላቱን ከማይነቅዝ
አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው እንጨት መቅረጽ እንችላለን።
ከመግባታችን በፊት በዚህ ፅሑፍ ስለ በሌላ በኩልም ከቻልን እንደ ብሉይ
ዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ኪዳኑ በአንድ ታቦት ሁለት ጽላት
ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ማስቀመጥ እንችላለን፤ካልቻን በአንድ
ነው። ታቦት አንድ ጽላት ብቻ ይሆናል።
አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት በተጨማሪም ጽላቱን ማስቀመጫ ታቦት
ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ባይኖረን፣ጽላቱን ታቦት ብለን በመጥራት
ነው።
11 12
በጽላቱ ብቻ መጠቀም እችላለን፥ ቀኖና መልስ፦በዘዳ 32፥19 ስንመለከት
ነውና። እግዚአብሔር ራሱ አዘጋጅቶ ለሙሴ
በተጨማሪምበኤር 31፥31፤ 2ኛቆሮ የሰጠውን ሁለቱን ጽላት እሥራኤል
3፥1-3፤በዕብ 8፥8-13፣የእኛ አካልና ጣዖት ሲያመልኩ ስላገኛቸው ሙሴ
ልቡና የርሱ ታቦትና ጽላት ናቸውና ተበሳጭቶ ሰብሯቸዋል።ነገር ግን ቸርነቱ
“በሐዲስ ኪዳን ለምን ታቦትና ጽላት ለዘለዓለም የሆነ እግዚአብሔር አምላክ
አስፈለገ? ለምንስ ይህ ሁሉ ተፈጠረ?” ለሙሴ የመጀመሪያዎቹን አስመስሎ
የሚሉ አሉ። የክርስቲያኖች አካልና እንዲሠራ ነገረው፤ሙሴም አስመስሎ
ልቡና በክርስቶስ ደም ታቦት፤ጽላት፤ቤተ ሠራ።በዘዳ 34፥1-5 መሥራት ብቻ
መቅደስ መሆኑን እናምናለን ። ሳይሆን አሥሩን የቃልኪዳን ቃላትም
ቢሆንም፣ በሐዲስ ኪዳን ታቦትና በጽላቱ ላይ እንዲፅፍ ሙሉ ሥልጣን
ጽላት ያስፈለገበት ምክንያት፣ስለ ከእግዚአብሔር ተሰጠው።ሙሴም
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ተፈቅዶለታልና አሥሩን ቃላት በጽላቱ
ክርስቶስ አምላክነትና ክብር ሲባል ነው። ላይ ጻፈ።ዘዳ 34፥27-28 ከዚህ ጊዜ
ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ክብሩን ጀምሮ ጽላትንም ሆነ ታቦትን እያስመሰሉ
የገለጠበት፣ቃሉን ያሰማበት፣ሙሴን ለመሥራት ሙሉ ሥልጣንን አግኝተናል።
እንደ ባልንጀራ ያነጋገረበት የንግስተ ሳባ ንጉስ
የክብሩ ዙፋን ሆኖ፣ታቦቱ በውስጡ
ለሚቀመጠው ለጽላቱ ማደሪያ
ሰሎሞንን መጎብኘት
የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን
በመሆኑ፣በ ሐዲስ ኪዳንም የሥጋውና
ዝና፣የእግዚአብሔርንም ስም በሰማች
የደሙ የክብር ዙፋን እንዲሆን
ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ
ሲሆን ስለ እኛ በዚህ ዓለም መከራ
የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ
የተቀበለውን መድኃኔዓለም ክርስቶስን
ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ
ለማክበር ሲባል ነው።
ትፈትነው ዘንድ መጣች።ወደ
ጥያቄ 2፦ በዘዳ 31፣18፣ 32፣
ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልብዋ ያለውን
15፣ 134፥1-5፣ 2ኛዜና 5፥10
ሁሉ ነገረችው።ሰሎሞንም የጠየቀችውን
ያሉትን ጥቅሶች በመጥቀስ እግዚአብሔር
ሁሉ ፈታላት (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
ለሙሴ የሰጠው ሁለት ጽላቶችን ብቻ
፲፥፩-፲፫፤ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
ነው።ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
፱፥፩-፲፪)።
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን እልፍ
ንግስተ ሳባ ከሰሎሞን ምኒልክ የሚባል
አእላፋት ጽላት ከየት አመጣቻቸው?
ልጅ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ ወለደች፣
አራብታችሁ ቅረጹ የሚል አለ ወይ?
ልጁም አድጎ የአባቱን ሀገር
ኢየሩሳሌምን ጎብኝቶ ሲመለስ የሙሴን
13 14
ጽላትና ካህናተ ኦሪትን፣እንዲሁም ይሰግዳሉ፤ጠላቶቹም ዐመድ ይቅማሉ፤
አያሌ የብሉይ መጻሕፍትን ከሊቆቻቸው የጠርሲስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታ
ጋር ይዞ መጣ (አባ ጎርጎርዮስ ያመጣሉ፤የሳባና የዐረብ ነገሥታትም
፲፱፻፺፱)።ንግስተ ሳባ በኢትዮጵያ እጅ መንሻ ያቀርባሉ፤ነገሥታት ሁሉ
የነገሰችው ከክርቶስ ልደት በፊት ይሰግዱለታል” ብሎ (መዝ. ፸፩፥፱-
እ.አ.አ. ከ፲፻፲፫እስከ፱፻፹፪ዓ.ዓ. ፲) በተናገረው ትንቢት መሠረት
ነበር።እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ሄሮድስ በነገሠበት ዘመን የይሁዳ ክፍል
ጽላት ዛሬ በርዕሰ አድባራት አክሱም በምትሆን በቤተልሔም ጌታችን ኢየሱስ
ፅዮን ቤተ ክርስቲያን ይገኛል። ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ጥበበኞች ሰዎች
ከምሥራቅ መጡ፤ወደ ቤት ገብተው
ሕጻኑን ከእናቱ ጋር አይተው ከፈረስ
ሠረገላ ወርደው ሰገዱለት፤ሳጥናቸውን
ከፍተው ኮረጁዋቸውን ፈትተው ወርቁን
ዕጣኑንና ከርቤውን ግብር አገቡለት”
ብሎ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ
(ማቴ.፪፥፩-፲፩) እንደጻፈው ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ተወልዶ
ሳለ ወርቅ ዕጣን ከርቤ ከገበሩለት ሦስት
ነገሥታት አንዱ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባዜን
እንደነበረ ይተረካል፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ “የግመሎች ብዛት፣
የምድያምና የጌፌር ግመሎች
ይሸፍኑሻል፤ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፤ወርቅንና
ዕጣንን ያመጣሉ፤የእግዚአብሔርንም
ምስጋና ያወራሉ” (ኢሳ.፷፥፮) ብሎ
ጽዮን ማርያም በትንቢት እንደተናገረው የወርቅ እጅ
የኢትዮጵያ ንጉሥ ባዜን መንሻ ያቀረበው ኢትዮጵያዊው ንጉሥ
እንደ ነበር ይነገራል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለዚህ ኢትዮጵያ ክርስቶስን
በቤተልሔም ሲወለድ ወርቅ ያወቀችውና መባ በማቅረብ ልደቱን
ዕጣን ከርቤ ከገበሩለት ሦስት ያከበረችው ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ
ስለሆነ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ነገሥታት አንዱ ስለመሆኑ
ቀዳማዊት ቤተክርስቲያን መባሉዋ
ነቢዩ ዳዊት “ኢትዮጵያውያን በፊቱ
ትክክል ነው።
15 16
መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና “በእውኑ
የምታነበውን ስተውለዋለህን?” አለው፤
እርሱም “የተረጐመልኝ ሳይኖር
ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው፤
ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ
ፊልጶስን ለመነው፤ ያነብበውም የነበረ
የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፥ እንደ
በግ ወደ መታረድ ተነዳ፣ የበግ
ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል
እንዲሁ አፉን አልከፈተም ፤በውርደቱ
ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር
ተወግዳለችና ትውልዱንስ ማን ይናገራል”
ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ እባክህ
ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል ስለ ራሱ
ነውን ወይስ ስለሌላ አለው፤ ፊልጶስም
መናገር ጀመረ፤ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ
ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት፡፡
የኢትዮጵያ ንግሥት ህንደኬ በመንገድም ሲሔዱ ወደ ውኃ
አዛዥና ጃንደረባ ባኮስ ደረሱ፤ጃንደረባውም እነሆ ውሀ
እንዳላጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው?”
የኢየሩሳሌም የአምልኮ ጉዞና አለው፡፡ፊልጶስም “በፍጹም ልብህ
ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ብታምን ተፈቅዶአል” አለው፤ መልሶም“
ስለማምጣቱ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ
የጌታም መልአክ ፊልጶስን ተነሥተህ እንደሆነ አምናለሁ” አለ፡፡
በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፤
ወደ ሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውሀ
ሆነመንገድ ሂድ አለው፤ ተነሥቶም ወረዱ፤ አጠመቀውም፤ ከውሀውም
ሔደ፤ እነሆም “ህንደኬ” የተባለች ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን
የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ ነጠቀው ጃንደረባውም ሁለተኛ
የነበረ በገንዘቡዋም ሁሉ የሰለጠነ አላየውም ፤ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ
አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ነበርና” (የሐዋ. ሥ. ፰፡፳፮-፴፱)
ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በማለት ወንጌላዊው ሉቃስ እንደተረከው
በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን የክርስትና እምነትና ጥምቀት ወደ
ኢትዮጵያ የገባው በ፴፬ዓ.ም.
17 18
በኢትዮጵያ ንግሥት በሕንደኬ አዝመራ የሆነው ባኮስ ለኢትዮጵያ
ጃንደረባ በባኮስ አማካይነት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የእምነትና ሥርዐተ
ያጠመቀውም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት አምልኮ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይነው፡
ወንጌላዊው ፊልጶስ ነው፤ “ኢየሱስ ፡ለሐዲስ ኪዳን ኢትዮጵያም ዓለም
ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ዐቀፍ እውቅና ያገኘ የቤተክርስቲያናችን
አምናለሁ” የሚለውን የእምነት ቀመር መሥራች ነው፡፡
በመናገር የጀመረና ለዓለም ያበረከተ ባኮስ በዚህ ሃይማኖታዊ ጒዞው የሕገ
ኢትዮጵያዊው ባኮስ ነው፡፡ ኦሪትንና የሕገ ወንጌልን ጽድቅ በአንድ
ጒዞ በመፈጸም የራሱንና የአገሩን ስም
በቅዱስ መጽሐፍ ለማስጠራት በቅቷል፡
፡ባኮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ከቅዱስ
ፊልጶስ ስለ ክርስቶስ የሰማውንና
የተረዳውን ለወገኖቹ ኢትዮጵያውያን
እንደ አስተማረ የጥንት ቤተ ክርስቲያን
ታሪክ ጸሓፊ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ
ጽፎአል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
የተመሠረተችውም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ
ነው፡፡ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ
ፊልጶስ የክርስትና አባቷ ስለሆነ በስሙ
ቤተ ክርስቲያን አንፃ ጽላት ቀርፃ
ታከብረዋለች፡፡
በጸሎቱና በአማላጅነቱም ትታመናለች፤
ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ቅዱስ
ማቴዎስ፣ ቅዱስናትናኤል፣ ቅዱስ
ባኮስ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር
በርተሎሜዎስ፣ ቅዱስ ቶማስ በኑብያና
ልጅ መሆኑን አውቆና አምኖ በማሳመን
በኢትዮጵያ አውራጃዎች እየተዘዋወሩ
ለወገኖቹ ትክክለኛውን እምነት ስለሰበከ
ወንጌልን እንደ ሰበኩ የቤተ ክርስቲያን
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እስከ ዛሬ
ታሪክ ጸሐፊዎች እነ ሩፊኖስና እነ
ድረስ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር
ሶቅራጥስ መስክረዋል፡፡
ልጅ መሆኑን ታምናለች፣ትሰብካለች፤
በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት እንዲስፋፋ
ታሳምናለች፡፡
ጉልህ አስተዋጽዖ ካበረከቱ ቅዱሳን
በዘመነ ሐዋርያት የክርስትና እምነትን
መካከል ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ
በመቀበል የመጀመሪያው የወንጌል
19 20
በዚህ እትም በአጭሩ እናስተዋውቃለን። ብርሃን በሰፊው ስለገለጠ ከሣቴብርሃን
ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ተባለ፡፡
በዚሁ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
ሰላማ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም
በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን “ቅዱስና
ዐቀፍ ደረጃ የታወቀች ብሔራዊት ቤተ
ያለ ተንኰል የሚኖር ነውርም የሌለበት
ክርስቲያን ለመሆን መብቃቷን ታሪክ
ከኀጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም
ያስረዳል፡፡
ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከጥንታዊት
ይገባናል” (ዕብ.፯፣፳፮) ብሎ
የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ
ጋር የሥርዐተ እምነት አንድነትና
ሊቀ ካህናትነት እንደተናገረው ሊቀ
የእህትማማችነት ህብረት ስለነበራት
ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሾማቸው
ግብፃውያን ጳጳሳት ሥልጣነ ክህነት
ከሐዋርያት ሐረገ ክህነት ተያይዞ የመጣ
በመስጠት ብቻ ተወስነው የቀረው
የሐዋርያት ተከታይ የሆነ ሊቀ ካህናት
የአስተዳደሩና የውስጥ አመራሩ ይዞታ
ማግኘት ይገባኛል ብላ የኢትዮጵያ
ግን በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይካሄድ
ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ እንዲያስመጣላት
ነበር፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን
ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማን ወደ
በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ፣ በሥርዐተ
እስክንድርያ ላከች፡፡
ትምህርትና በባህል ራሱን የቻለ አቋም
ቅዱስ አትናቴዎስ የእስክንድርያ
የነበራትና ያላት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡
ፓትርያርክም ራሱኑ ሾሞ ላከው፡፡
ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው
ከብዙ በጥቂቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
በመጀመሪያው ምዕት ዓመት ይሁን
ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ታሪክ ይሄንን
እንጂ በሲኖዶስ ሕግ የኤጲስ ቆጶስ
ይመስላል አነሳስቶ ያስጀመረን አስጀምሮ
መንበር የተሰጣት በአራተኛው ምዕት
ያስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር
ዓመት በ፫፻፴ዓ.ም. ነው፡፡
ይመስገን።
ከኢትዮጵያ ተልኮ ሔዶ ከእስክንድርያው
ፓትርያርክ ከቅዱስ አትናቴዎስ ዘንድ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሾሞ በመጣው
በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መምህርነት
በአብርሃና በአጽብሐ ዘመነ መንግሥት
ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት በዐዋጅ
ተሰብኳል፡፡ ቅዱስ አባ ሰላማ ከዚያ
ጊዜ ጀምሮ መንበረ ጵጵስናውን አክሱም
ላይ አድርጎ በሀገራችን የወንጌልን
21 22

You might also like