You are on page 1of 186

የቤተ ክርስቲያን

ምሥጢራትና ሥርዓት

በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ


ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ
አገልግሎት ዋና ክፍል የተዘጋጀ

አዘጋጅ፦መምህር ፈቃዱ ሣህሌ

፳፻፯ ዓ.ም
1
መቅድም
ቅድስት ቤተክርስቲያን ለልጆቿ ቅዱስ ቃሉን እየመገበች ምሥጢራትን
እየፈጸመችና በሥነ ምግባራት ሠናያት እያነፀች ባሕረ ዓለምን ቀዝፋ ወደ ዕረፍት ወደብ
የምታሻግር /የምታደርስ/ መንፈሳዊት መርከብ ናት፡፡ በኢየሩሳሌም (በጸኑት)፣ በይሁዳ
(አምነው፤ እየወደቁና እየተነሡ በሚታገሉት)፣ በሰማርያ (አምነው በካዱት) ና በምድር
ዳርቻ (ፈጽመው ባላመኑት) መካከል በምታደርገው ሐዋርያዊ አገልግሎት የምትመራበት
መንፈሳዊ ሥርዓትም ባለቤት ናት።(ሐዋ፩፥፰)።

እግዚአብሔር አምላካችን በሰዎች መካከል ማደር በፈለገ ጊዜ በሰማይ ባለ መቅደሱ


አምሳል ደብተራ ኦሪትን እንዲሠራ ሙሴን አዘዘው። (ዘጸ፳፭፥፰፳፰)፡፡ ንዋያተ ቅድሳቱና
ሥርዓተ ደብተራ ኦሪቱም በዚያው አምሳል የተከናወነ እንዲሆን ፈቀደ፡፡ “ፊተኛይቱም
ደግሞ የአገልግሎት ሥርዓትና የዚህ ዓለም የሆነው መቅደስ ነበራት” (ዕብ ፱፥፩)፡፡ በማለት
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ይህንኑ የሚያጸና ትምህርት ነው፡፡ መቅደሰ
ሰሎሞንም በደብተራ ኦሪት አምሳል ሲሠራ ድንኳኑ ሕንፃ ከመሆኑ በስተቀር ንዋየ
ቅድሳቱና ሥርዓቱ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ በተፈጸመበት ወቅት ንጉሥ
ሰሎሞን የእስራኤልን ጉባኤ በመረቀበት አንቀጽ “በመንገዱም ሁሉ እንሄድ ዘንድ
ለአባቶቻችንም ያዘዛትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን እንጠብቅ ዘንድ ልባችንን ወደ እርሱ
ይመልስ።”(ነገ ቀዳ ፰፥፶፰) ማለቱን እናነባለን:: ይህም በመቅደሰ ሰሎሞን ይፈጸም
የነበረው ሥርዓተ አምልኮ አባቶቻቸው በደብተራ ኦሪት ይፈጽሙት በነበረው ሁኔታ
መቀጠሉን ያሳያል።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤት”


ብሎ የጠራት (፩ጢሞ፫፥፲፭) ቤተክርስቲያንም በመቅደሰ ሰሎሞን አምሳል ተሠርታለች።
ይህም ውጭያዊ የሕንፃ አሠራሯን ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ የአምልኮ ሥርዓቷን ሁሉ
የተመለከተ ነው። (፩ቆሮ ፲፬፥፵)፡፡ ከሥርዓት ውጪ እንዳሻቸው በመሄድ ቤተ
ክርስቲያንን የሚያውኩትንም “ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው”፤ (፩ተሰ፭፥፲፬)።
“ወንድሞቻችን ሆይ፥በሠራንላችሁ ሥርዓት ሳይሆን በተንኮል ከሚሄዱት ወንድሞች
ሁሉ፥ትለዩ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን።”(፪ተሰ፫፥፮)።በማለት
ማስተማሩን ማስተዋል ይገባል ደገኛውን ሥርዓት ይዞ መጓዝ እንደሚገባም ”አሁንም
ወንድሞቻችን ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ፤በቃላችንም ቢሆንወይም በመልእክታችን
ያስተማርናችሁንና የሠራንላችሁን ሥርዓት ያዙ” (፪ተሰ ፪፥፲፭)በማለት አሳስቧል።

ቤተክርስቲያን በየጊዜው የፈጸመችውና የምትፈጽመው መንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ


ሥርዓትን በመከተል የተከናወነና የሚከናወን መሆኑ ግልጽ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱ
ሁለንተናዊ ሕይወት የሆነው ይህ ሥርዓተ አምልኮ ሳይበረዝና ሳይከለስ፣ሳይጨመርበትና
ሳይቀነስለት እንዲጓዝ ለማድረግ ካህናትና ምእመናን የበኩላቸውን (የድርሻቸውን)
ማበርከት ይጠበቅባቸዋል። የዚህ ጽሑፍ አንባብያንም ከዚች አነስተኛ መጽሐፍ መንፈሳዊ
ዕውቀትን እየገበዩና ራሳቸውን እየገመገሙ የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተሳታፊዎች
ለመሆን ይነሣሣሉ ተብሎ ይታመናል።በመንፈሳዊ ቅንዓት እየተቃጠሉ ቤተ
2
ክርስቲያናቸውን፣ ሥርዓታቸውን፣ ንዋያተ ቅድሳታቸውንና የተቀደሰ ትውፊታቸውን
ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንዲወስኑና እንዲጋደሉ መሠረታዊ መነሻ ይሆናል።

ስለዚህ አንባብያን መጽሐፍ ቅዱስ በመያዝ የመጽሐፉን ምሥጢራት በጸሎት መንፈስ


በርጋታ እንዲያነቡ ይመከራሉ፡፡ መምህራንንም እየጠየቁ ያልተፍታታውንና የተቋጠረውን
እያላሉ /እያለሰለሱ/ እንዲመገቡት እንጋብዛለን፡፡ በየምዕራፉ ግርጌ በዋቢነት የተጠቀሱ
ቅዱሳት መጻሕፍትን በተቻለ መጠን እየፈለጉ ማንበብ በየርእሰ ጉዳዩ ዙሪያ የተሻለ
ግንዛቤ ለማግኘት እንደሚያግዝ ለመጠቆምም እንወዳለን።

3
መክሥተ አርእስት

ርእሰ ጉዳይ

ተ/ቁ ገጽ

፩. የቤተ ክርስቲያን ጽንሰ አሳብ (ነገረ ቤተ ክርስቲያን)፤

፩.፩. የቤተ ክርስቲያን ትርጉም፤

፩.፪. የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት፤

፩.፫. የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት፤

፪. ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ከነገረ ድኅነት ጋር ያላቸው


ግንኙነት፤

፪.፩. ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ምንድናቸው? እነማን ናቸው?

፪.፪. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያ ምንድነው?

፪.፫. የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጮችና ታሪክ፤

፪.፬. ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ከነገረ ድኀነት

ጋር ያላቸው ግንኙነት፤

፫. ምሥጢራተ ጥምቀትና አፈጻጸሙ፤

፫.፩. አመሠራረት፤

፫.፪. አስተምህሮ፤

፫.፫. አፈጻጸም ፤

፫.፬. የሚያስገኘው ጸጋ፤

፬. ምሥጢረ ሜሮንና አፈጻጸሙ፤

፬.፩. አመሠራረት፤

፬.፪. አስተምህሮ፤

4
፬.፫. አፈጻጸም፤

፬.፬. የሚያስገኘው ጸጋ፤

፭. ምሥጢረ ቁርባንና አፈጻጸሙ፤

፭.፩. አመሠራረት፤

፭.፪. አስተምህሮ፤

፭.፫. አፈጻጸም፤

፭.፬. ቅዳሴ፤

፭.፭. የሚያስገኘው ጸጋ፤

፮. ምሥጢረ ክህነትና አፈጻጸሙ፤

፮.፩. አመሠራረት፤

፮.፪. አስተምህሮ፤

፮.፫. አፈጻጸም፤

፮.፬. የሚያስገኘው ጸጋ፤

፯. ምሥጢረ ንስሐና አፈጻጸሙ፤

፯.፩. አመሠራረት፤

፯.፪. አስተምህሮ፤

፯.፫. አፈጻጸም፤

፯.፬. የሚያስገኘው ጸጋ፤

፰. ምሥጢረ ተክሊልና አፈጻጸሙ፤

፰.፩.አመሠራረት፤

፰.፪. አስተምህሮ፤

፰.፫. አፈጻጸም፤

፰.፬. የሚያስገኘው ጸጋ፤

፱. ምሥጢረ ቀንዲልና አፈጻጸሙ፤

፱.፩. አመሠራረት፤

፱.፪. አስተምህሮ፤

5
፱.፫. አፈጻጸም፤

፱.፬. የሚያስገኘው ጸጋ፤

፲. በዓላት፤

፲.፩. የበዓላት ጽንሰ አሳብ፤

፲.፪. የበዓላት ታሪክ፤

፲.፫. የበዓላት አከባበር፤

• በዋዜማ፤

• በዕለቱ (ፍጻሜ)፤

፲.፬. ዋና ዋና በዓላት፤

፲.፭. ሥርዓተ ዑደት፤

• የቤተ መቅደስ ዑደታት፤

• በጥምቀት የታቦታቱ መውረድ፤

• ንግሥ፤

፲፩. ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ንዋያተ ቅድሳት፤

፲፩.፩. የቤተ ክርስቲያን ሥሪት፤

፲፩.፪. ቅዱሳት ሥዕላት፤

፲፩.፫. ንዋየ ቅድሳት፤

፲፩.፬. ዜማ፣ መዝሙርና የዜማ መሣሪያዎች፤

፲፩.፭. ዕጣን፤

፲፩.፮. ታቦትና ጽላት፤

6
መግቢያ
ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር አምላካችን የጸጋው ግምጃ ቤት
በሆነችው ቤተ ክርስቲያን በኩል የሚያድላቸው የድኅነትና የአገልግሎት ሥጦታዎች
ናቸው፡፡ እነዚህም ሰዎችን ለመዳን ማለትም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ
የሚያበቁ፣ ቀጣይነት ላለው ክርስቲያናዊ ሕይወት መጠናከር የሚያስፈልጉ፣ በቤተ
ክርስቲያን አገልግሎት የሚያጸኑና ፈውስ ሥጋ፣ ፈውስ ነፍስ የሚያሰጡ ናቸው።

የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ማከናወኛና የመንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ ማስፋፊያ


ሕግ ወይም ደንብ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ይባላል። ይኸውም እግዚአብሔር ከጥንት
ጀምሮ በወደዳቸው አበውና ሊቃውንት ሁሉ እያደረ የሠራው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት
መመሪያ ነው።የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሁሉ ማለትም ምሥጢራቱ፣ ጸሎቱ፣ ቅዳሴው፣
ማኅሌቱ፣ መዝሙሩ፣ ሰዓታቱና የመሳሰሉት ሁሉ በጋራ /በኀብረት/ የሚከናወኑ መንፈሳዊ
ተግባራት ናቸው።

ማኀበረ ካህናቱና ማኀበረ ምእመናኑ የድኀነት ጸጋን የሚያገኙባቸው ምሥጢራተ ቤተ


ክርስቲያን የታወቀና የተረዳ የአፈጻጸም ሥርዓት አላቸው፡፡ ከታቦተ ሕጉ ጀምሮ ያሉ
ንዋያተ ቅድሳትም የአቀማመጥና የአጠቃቀም መመሪያ ተወስኖላቸዋል፡፡ በጥቅሉ ሥርዓተ
ቤተ ክርስቲያን ማለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሕንፃ ዐቅድ አሠራር፣ አደረጃጀትና
አከባበር ጀምሮ አምልኮተ እግዚአብሔርን የምታስፈጽምባቸው መንገዶች ናቸው።

በዚህ መጽሐፍ አሥራ አንድ ምዕራፎች፣ ፴፯ ንዑሳን ክፍሎችና ዝርዝር ማብራሪያዎች


ሰፍረዋል።ዐበይት ምዕራፎቹም የሚከተሉት ናቸው፦

• የቤተ ክርስቲያን ጽንሰ አሳብ፤

• ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

ከነገረ ድኅነት ጋር ያለው ግንኙነት፤

• ምሥጢረ ጥምቀትና አፈጻጸሙ፤

• ምሥጢረ ሜሮንና አፈጻጸሙ፤

• ምሥጢረ ቁርባንና አፈጻጸሙ፤

7
• ምሥጢረ ክህነትና አፈጻጸሙ፤

• ምሥጢረ ንሰሐና አፈጻጸሙ፤

• ምሥጢረ ተክሊልና አፈጻጸሙ፤

• ምሥጢረ ቀንዲልና አፈጻጸሙ፤

• በዓላትና

• ሕንፃ ቤተክርስቲያንና ንዋያተ ቅዱሳት የሚሉትን ያጠቃልላል፡፡

የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትና ሥርዓት በሚል ገዢ ርእስ በአዲስ መልክ የተዘጋጀው


ይህ የመማሪያ መጽሐፍ ማኀበረ ቅዱሳን አዲስ በከለሰው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት
የተሰናዳ ነው።አገልግሎቱ በዋናነት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላሉት የግቢ ጉባኤያት
ተማሪዎች ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ለሆኑ ምእመናን
በሙሉ ከፍተኛ ጥቅም ሊሰጥ እንዲችል ሆኖ ተዘጋጅቷል።

በቀደመው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ግቢ ጉባኤያት ተከታታይ ትምህርት


ሲቀስሙባቸው የነበሩ ሦስት የመማሪያ መጻሕፍት በዚህ መጽሐፍ ተጠቃለው
ቀርበውበታል። እነዚህም፦

• ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣

• ሥርዓተ ቤተክርስቲያንና

• ቤተክርስቲያንህን ዕወቅ የሚሉት ናቸው።

እነዚህን መጻሕፍት በአንድነት ማቅረብ ያስፈለገበት ምክንያት ምግቡን፣


መመገቢያውንና አመጋገቡን በማገናኘት ለተመጋቢው ማቅረብ የተሻለ ሆኖ ስለተገኘ
ነው። ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን እንደ ምግብ፣ ቤተክርስቲያን እንደመመገቢያ፣ ሥርዓተ
ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንደ አመጋገብ ስልት (መመሪያ) እንዲሁም እንደተመጋቢው
(ክርስቲያኑ) ሆኖ ይመሠጠራል። አንባቢው (ተመጋቢው) አንዱን ይዞ አንዱን ፍለጋ
እንዳይደክም ወይም አጥቶት ዕውቀቱ በተከፍሎ እንዳይቀር ይረዳ ዘንድ ወገን ከወገኑ
ተገናኝቶ እንዲቀርብ ተደርጓል።

8
ምዕራፍ አንድ፡-

የቤተ ክርስቲያን ጽንሰ አሳብ (ነገረ ቤተ ክርስቲያን)

መግቢያ

በክርስቶስ ደም የታነፀችውና በቅዱስ ጴጥሮስ የምስክርነት ቃል ዐለት ላይ


የተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ከእግዚአብሔር ጋር የምታገናኝ
መድረክ (ድልድይ) ናት። የቅድስናዋ ምንጭም በስሙ የተጠራችበት ክርስቶስ ነው።
ሐዋርያት በፈቃደ እግዚአብሔር በፊልጵስዩስ ከሠሩዋት የመጀመሪያይቱ ሕንፃ ቤተ
ክርስቲያን ጀምሮ በመላው ዓለም በጥፋት ውኃ ውስጥ ያሉትን ለመዋጀት የድኅነት ወደብ
መርከብ ሆና ተገልጣለች። ሐዋርያትም አንተ ዐርጋለሁ ብለኸናልና ቤተ ክርስቲያን
የምትተዳደርበት ንገረን ብለው ጠይቀውት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አስተምሮዋቸዋል፡፡
እነሱም እንዳንድ ልብ መካሪ እንዳንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ወስነው ለቀሌምንጦስ
ሰጥተውታል፡፡ከዚያም ለቤተ ክርስቲያን አባቶች በቃልም በድርጊትም አስተምረው
አኖሩት። (ዲድስቅሊያ-ታሪክ)

በዚህ ምዕራፍ የዚች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትርጉም፣ አመሠራረትና ባሕርያት


ተገልጸዋል። ምሥጢራቷንና ሥርዓቷን ከማወቅ ቀድሞ የምሥጢራቱና የሥርዓቱ ባለቤት
የሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማወቅ ለክርስቲያኖች ሁሉ ተገቢ መሆኑ ከማንም
የሚሰወር አይሆንም።

ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ካጠናቀቁ


በኋላ፡-

• የቤተ ክርስቲያንን ትርጉም ይረዳሉ፡፡

• የቤተ ክርስቲያንን አመሠራረት ይገነዘባሉ፡፡

• የቤተ ክርስቲያንን ባሕርያት መዘርዘር ይችላሉ፡፡

፩.፩ የቤተ ክርስቲያን ትርጉም


የተከበሩ አንባቢ በቅድሚያ ይህን ጥያቄ ካለዎት የቀደመ ግንዛቤ በመነሣት ለራስዎ
ለመመለስ ይሞክሩ፡፡

9
❖ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?

ቤተ ክርስቲያን ስለሚለው ድርብ ቃል እያንዳንዱ ምእመን የራሱ የሆነ ግንዛቤ


ይኖረዋል፡፡ ቃሉ ሲጠራ በብዙዎቻችን ሕሊና ወዲያውኑ የሚከሰተው አምልኮተ
እግዚአብሔር የሚፈጸምበት ቅዱስ ቤት /ሕንፃ/ ነው፡፡ነገር ግን “ቤተ ክርስቲያን” የሚለው
ቃል ሰፋ ያለ ትርጉም አለው ይህንንም እንደሚከተለው እናብራራለን።

ሀ/ “ቤተ ክርስቲያን”፦ የሚለው ቃል መሠረቱ የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ ቃሉን ለሁለት


ከፍለን ለየብቻ ተርጉመን ስናገናኘው የሚከተለውን ትርጉም ይሰጠናል፡፡ “ቤተ”-ኖረ፣ አደረ
የሚል ፍቺ ሲኖረው “ቤት”-መኖሪያ፣ማደሪያ የሚል ትርጓሜ የሚይዘው በዚሁ መሠረት
ነው፡፡ “ክርስቲያን የሚለው” ቃል ደግሞ የክርስቶስ ተከታይ፣ በስሙ የተጠራ ማለትም
ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና (ልጅነት) ያለው ማለት ነው፡፡ በተገናኘ (በአንድነት)
ሲፈታም የክርስቲያን መኖሪያ፣ ማደሪያ፣ የክርስቲያን ቤት ማለት ይሆናል፡፡

ስለዚህ “ቤተ ክርስቲያን” ክርስቲያኖች የሚሰባሰቡበት፣ ቃለ እግዚአብሔርን


የሚሰሙበት፣ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት፣ ምግባር ትሩፋት
የሚሠሩበት፣ ስለኃጢአታቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት፣ ንስሐ የሚገቡበትና ሥጋ ወደሙን
የሚቀበሉበት ቤቱ /ሕንፃው/ ነው ማለት ነው፡፡ የተቀደሰው ቤት /ሕንፃ/ በምንልበትም ጊዜ
ባዶ ቤት /አዳራሽ/ ማለታችን እንዳልሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡

• የተወደዱ አንባቢ ሆይ!

❖ የእኛ ቤተ ክርስቲያንን ሌሎች የእምነት ተቋማት ቤተ ክርስቲያን ከሚሉት


ባዶ አዳራሽ የሚለያት ምንድነው? የጥያቄውን መልስ እራስዎ ያቅርቡ።

በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፩ ቁጥር ፩ ላይ ስለ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ የሚል ተጽፎ


እናገኛለን፡፡ “ቤተ ክርስቲያን ግን የጸሎት ቤት ናት፡፡ ”ይህም የጌታችንን ትምህርት
መሠረት ያደረገና ቃል በቃል ያሰፈረ ኃይለ ቃል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ (ማቴ. ፳፩፥፲፫
ማር.፲፩፥፲፯) በዚህ የጸሎት ቤትም ካህናትና ምእመናን የሚገለገሉባቸውና
የሚያገለግሉባቸው በርካታ ቅድሳት ንዋያት፣ ምሥጢራት፣ አገልግሎትና አገልጋዮች
እንደሚከተለው ተገልጸዋል።እነዚህም ቤተ ክርስቲያንን ከባዶ አዳራሽ ልዩ የሚያደርጓት
የቅድስናዋ መገለጫዎች ናቸው።

➢ በተቀደሰው ቤት የሚኖሩ የተቀደሱ ንዋያትም፡-

• ታቦተ እግዚአብሔር፣

• መስቀለ ክርስቶስ፣

• ቅዱሳት መጻሕፍት፣
10
• ቅዱሳት ሥዕላት፣

• ንዋያተ ቅዱሳት፣

• የማኅሌት/ዝማሬ ንዋያትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

➢ በተቀደሰው ቤት የሚፈጸሙ ምሥጢራት፡-

• ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን

➢ በተቀደሰው ቤት የሚቀርበው አገልግሎት፡-

• ማኅሌት፣

• ሰዓታት፣

• ኪዳን፣

• ቅዳሴ፣

• መዝሙር፣

• ቅኔ፣

• ስብከተ ወንጌልና የመሳሰሉት ሁሉ ናቸው፡፡

➢ በተቀደሰው ቤት የሚኖሩ አገልጋዮች፡-

• ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣

• ሊቃነ ጳጳሳት፣

• ጳጳሳት (ኤጲስ ቆጶሳት)፣

• ቀሳውስት፣

• ዲያቆናት፣

• ዘማርያን፣

11
• ሰባክያን፣

• አንባብያንና

• ምእመናን ሁሉ ናቸው፡፡

እነዚህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ካህናትና ምእመናን በቤተ ክርስቲያን አንድ ሆነው
እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፡፡ ቀሪዎቹም እሱን የማመስገኛ መንገዶች መሣሪያዎችና ጸጋ
እግዚአብሔርን የሚሳተፉባቸው መድረኮችና ምሥጢራት ናቸው። ይህቺ ቤት ከባዶ
አዳራሽ የምትለይበት ዋናው ምሥጢርም እነዚህን ሁሉ የሠራና የፈቀደ ያዘዘም
እግዚአብሔር በረድኤት ስለሚኖርባት ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ “የዘገየሁ እንደሆነ ግን


የእግዚአብሔርን ቤት እንዴት እንደምታስተዳድር ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ ቤተ
ክርስቲያኒቱ የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤት ናት የዚህ የመልካም
አምልኮ ምሥጢር ታላቅ ነውና” (፩ጢሞ ፫፥፲፭-፲፮)።በማለት የሕያው እግዚአብሔር ቤት
መሆኗንና በውስጧ የሚከናወነው ሥርዓተ አምልኮ ደገኛ (መልካም) መሆኑን
መስክሮልናል።

ለ/ቤተ ክርስቲያን፦ የሚለው ቃል ምሥጢራዊ /ፍካሬያዊ/ በሆነ መንገድ ሲፈታ ደግሞ


የክርስቲያንን ሃይማኖት የሚያመለክት ይሆናል፡፡ የክርስትና እምነትን የተቀበሉ
ምእመናን በጉባኤ /በጋራ/ና በተናጠል የሚጠሩበት ስያሜ ሆኖ ይፈታል፡፡ ይህ የበለጠ
ሲተነተን ደግሞ ቤተ-ወገን፣ ዘር፣ የክርስቲያን ትውልድ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ይህም
ለምሳሌ “ቤተ-ያዕቆብ” ሲል የያዕቆብ ወገን፣የያዕቆብ ዘር፣የያዕቆብ ትውልድ፣ተብሎ
ይተረጐማል።ከዚሁ በመነሣት ቤተ ክርስቲያንም የክርስቲያን ወገን፣ የክርስቲያን
ዘር፣ትውልድ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ይህም ከላይ እንደገለጽነው በተቀደሰው ቤት
የተቀደሰውን አምልኮና አገልግሎት የሚፈጽመውንና የሚፈጸምለትን አካል የሚያመለክት
ይሆናል፡፡ ይህ የትርጓሜ ስልት አብሮን የኖረና የተለመደ አካሄድ ነው፡፡ ከላይ ካየነው
በተጨማሪ ቤተ እስራኤል፣ ቤተ ዳዊት፣ ቤተ ክህነት፣ ቤተ መንግሥት የሚለውን ማየት
ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር ቤተ
መነግሥት እንዲሁም የጸጋው ግምጃ ቤት ናት፡፡ ይህችውም የክርስቶስ አካሉ ስትሆን እሱ
(ክርስቶስ) ደግሞ ራሷ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተመዝግቦናል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ሲያብራራ “ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን


ራስዋ፣አዳኝዋም እንደሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነው።”(ኤፌ ፭፥፳፫) እዚህ ላይ ቤተ
ክርስቲያን አካሉ ስትሆን ክርስቶስ ራስዋ መሆኑ ተገልጿል።አካል ከራሱ ተለያይቶ መኖር

12
እንደማይችል ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ ተለይታ መኖር አትችልም መስቀለ
ክርስቶስን ከአናቷ ላይ ጉልላቷ ላይ በክብር የምታስቀምጠውም ለዚህ ነው እያንዳንዱ
ክርስቲያን የክርስቶስ አካ በመሆኑ ነው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበትም
አላውል ብሎ ለሚያሳድዳቸው ለሳውል ጳውሎስ ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ አንተ
የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ (ሐዋ ፱፥፬-፮)።በማት ጌታችን የጠየቀውና
የመለሰለት።

• የተከበሩ አንባቢ በቅድሚያ መጽሐፍ ቅዱስ አዘጋጁና

• የሚከተሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች መርምረው ከየትኛው የቤተ ክርስቲያን


ፍቺ ጋር እንደሚገናኙና(ትርጉም) ማስረጃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለራስዎ መርምረው
ለማገናዘብ ይሞክሩ፡፡

• ማቴ. ፲፰፥፲፭-፲፯ - ፩ቆሮ ፫፥፲፮-፲፯ - ሐዋ. ፳፥፳፰

• ማቴ. ፰፥፳ - ፪ጴጥ. ፭፥፲፫ - ኢሳ. ፶፮፥፭-፯

• መዝ. ፵፬፥፰ - መዝ-፻፲፯፥፫ - ኤር. ፯፥፲‐፲፩

• ጦቢ. ፰፥፱ - ሐዋ. ፲፰፥፴፪ - ማቴ. ፳፩፥፲፫

• ፩ነገ. ፱፥፫

• ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው


ነው።ለአጠቃላይ ዕውቀትም የሚከተለውን መመልከት ይቻላል፡፡ በግሪኩ ኤክሌስያ
(Ecclessia) በሚል ቃል ነው የሚታወቀው።ይህ ቃል በቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት
፷፪ ጊዜ፣በሐዋርያት ሥራ ፳፫ ጊዜ፣ በዮሐንስ ራእይ ፳ ጊዜ፣ በማቴዎስ ወንጌል ፫
ጊዜና በሌሎች መልእክታት ፮ ጊዜ በድምሩ ፻፲፬ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጾ
እናገኘዋለን፡፡ይህም ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛ የትኩረት ነጥብ
መሆኑን ይጠቁመናል።

❖ ቤተ ክርስቲያን መቼ፣ እንዴትና የት ተመሠረተች?

13
፩.፪ የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት

• የተከበሩ የዚህ መጽሐፍ ተከታታይ በቅድሚያ ለራስዎ፦ይህን ጥያቄ ለመመለስ


ይሞክሩ።

❖ ቤተ ክርስቲያን መቼ፣ እንዴትና የት ተመሠረተች?

ቤተ ክርስቲያንን የመሠረታት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡


በቂሳርያ ሳሉ ደቀመዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” በማለት
በጠየቃቸው ጊዜ ሐዋርያት እንደገለጹት ሰዎች ስለእሱ ማንነት የሰጡት መልስ
ትክክለኛ አልነበረም፡፡ “እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ?” በማለት ደቀ
መዛሙርቱ ሲጠየቁ ግን ቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠው ፈጣን መልስ የክርስቶስን ማንነት
በሚገባ የገለጠ ነበር፡፡ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” የሚለውን
ምላሽ ሰጠ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “… አንተ ዓለት ነህ፤ በዚች
ዓለትም ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እመሠርታታለሁ፡፡” (ማቴ. ፲፮፥፲፫-፲፰)። በማለት
ቃል ኪዳን ገባ፡፡ይህም ማለት በማይናወጽ ጽኑ መሠረት ማለትም ወልድ ዋሕድ
በምትል እምነት /ትምህርት/ ላይ የክርስትና ሃይማኖትና ቤተ ክርስቲያን
መታነፅዋን ያሳያል፡፡ በዓለት ላይ የተመሠረተ ቤት በንፋስ በጎርፍና በልዩ ልዩ
ፈተና እንደማይፈርስ ሁሉ በቅዱስ ጴጥሮስ የምስክርነት ቃል ላይ ክርስቶስ
የመሠረታት ራሱን አሳልፎ የሰጠላት ቤትም በኑፋቄ ነፋስና በክህደት ጉርፍ
የማትንበረከክ ልዩ ልዩ የፈተና ማዕበላትን ተቋቁማ ልጆቿን ወደ ዕረፍት ወደብ
መንግሥተ ሰማያት የምታደርስ መሆኗን ያስገነዝበናል።(ማቴ ፯፥፳፬-፳፮)።

❖ ቤተ ክርስቲያን የማን ነች?ለማን ተሰጠች?

ከላይ እንደገለጽነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ፣ ደሙን


አፍስሶ፣ አሮጌውን የምሥጢር ሥርዓት አድሶ በቅዱሳን ነቢያት ትንቢትና በቅዱሳን
ሐዋርያት ትምህርት፣ የክህነት ሥልጣንና አገልግሎት /ሥራ/ ላይ ቅድስት ቤተ
ክርስቲያኑን መሥርቷታል፡፡ (ሐዋ. ፳፥፳፰ ኤፌ. ፪፥፳) ዮሐ. ፳፥፳፩-፳፪ ማቴ.
፲፰፥፲፰)። ክርስቲያን ልጆቻቸውም በዚህች ቤተ ክርስቲያንም ጥላ ሥር ለቅዱሳን አበውና
እማት አንድ ጊዜ የተሰጠች ሃይማኖትን አጽንተው እየተጋደሉ ይኖሩባታል።(ይሁ ፫.)
በኋላም ወደ መንግሥተ ሰማያት ይሸጋገሩባታል፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ሀብተ ወልድና
ስመ ክርስትና ላላቸው ክርስቲያኖች ሁሉ ቤታቸው ናት፡፡ ማናቸውም ዓይነቶች ምድራዊ
ልዩነቶች በቤተ ክርስቲያን አባልነት፣ በክርስቶስም አካልነት ጣልቃ የመግባት አቅም
14
አይኖራቸውም፡፡ የፖለቲካ፣ የብሔር (ብሔረሰብ)፣ የቋንቋ፣ የቀለም፣ የጤና፣ የኢኮኖሚ፣
የሥልጣንና የመሳሰሉት ልዩነቶች ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም።
ቤተክርስቲያን በሁሉም ያለች፣ የሁሉምና ለሁሉም ናት፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርት
እስካመነ ድረስ በሌሎች ልዩነቶች ምክንያት ለይታ የምታቀርበውና የምታርቀው የተለየ
ወገንና አባል የላትም።

፩.፫ የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት


የተከበሩ የዚህ መጽሐፍ አንባቢ በቅድሚያ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመረዳትና
ለመመለስ ይሞክሩ

❖ “ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቡዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ


ክርስቲያን እናምናለን፡፡” የሚለውን የጸሎተ ሃይማኖት ክፍለ ንባብ እንዴት
ይገልጹታል?
❖ የቅዱስ ሲኖዶስን መከፈል፣ አንዳንዶችም በአገር ውስጥ “የነፍጠኛ
ሃይማኖት፤” በውጪውም “የነ እገሌ ቤተ ክርስቲያን፤” የሚለውን ወቅታዊ
ተግዳሮት ከቤተ ክርስቲያን ባሕርያት አንጻር እንዴት ያዩታል?

የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት ማለት የእውነተኛው ቤተ ክርስቲያን መታወቂያ (መገለጫ)


የሆኑ ምልክቶቿ ናቸው፡፡ በአንቀጸ (ጸሎተ) ሃይማኖት ከሠፈሩት አስተምህሮዎችና
ውሳኔዎች መካከል አንዱ የቤተ ክርስቲያንን ባሕርያትና ደረጃዎች በግልጽ
የሚያስቀምጠው ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ ይህም “ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት
በሰበሰቡዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡፡” የሚለው ነው።ከዚህ ክፍለ
ንባብ በመነሣት የቤተ ክርስቲያንን ባሕርያት እንደሚከተለው እናብራራለን፡፡ በዚህ
ዐረፍተ ነገር /ኃይለ ቃል/ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት በተሟላ መንገድ በሥርዓት
ተሰድረውና ተሟልተው እናገኛቸዋለን፡፡ እስቲ አንድ ባንድ ባጭሩ እንዳሳቸው፦

የተወደዱ አንባቢ በቅድሚያ የሚከተሉትን ጥያቄ ለራስዎ ይመልሱ

ሀ/ አንዲት፡- ይህ ቃል ለቤተ ክርስቲያን ሲቀጸል መሠረታዊ መገለጫዋ ሆኖ


ይቀርባል፡፡ እንደሚታወቀው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረታት ቤተ ክርስቲያን
አንዲት ናት፡፡ እርሷንም በደሙ ዋጅቶ በመመሥረት የራሱ አካል አደረጋት፡፡
በየማዕዘናቱና በየአህጉራቱ ያቋቋማቸው ልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት የሉትም፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እውነት የገለጠው “በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ አንድ
አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” (ኤፌ.፬፥፬-
፭) በማለት ነው፡፡ ይህም አንዲቱ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ተስፋ የተጠራች፣ የክርስቶስ
አንዲት አካል የሆነች በአንድ የእግዚአብሔር መንፈስ የምትንቀሳቀስ (የምትመራ)፣ አንድ
ጌታ ያላት፣ አንድ ሃይማኖት የያዘች፣በአንዲት ጥምቀት የተወለደች ምእመናንንም
ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ የምትወልድ አንዲት ማኅደረ እግዚአብሔር
መሆኗን ይነግረናል፡፡

15
ለአምልኮተ እግዚአብሔር እንዲመች በየሀገሩ፣ ምእመናን እየበዙ፣ ሕንፃ ቤተክርስቲያን
እየተሠራ ቤተክርስቲያን በየወገኑ ተስፋፍታ ቅርንጫፎቿ ቢበዙም፤ በቦታና በጊዜ
ቢራራቁም በብሔርና በቋንቋ ቢለያዩም ግንዷና መሠረቷ፣ እምነቷና ሥርዓቷ ታሪኳና
ትምህርቷ፣ መመሪያና ትውፊቷ አንድ ነው፡፡ ይህም በአንድ የወይን ግንድ ላይ በቅለው
በአንድነት አንድ ዓይነት ምግብ እየተመገቡ እንደሚያድጉ የወይን ቅርንጫፎች ማለት
ነው፡፡ (ዮሐ. ፲፭፥፩-፯)፡፡ እኛ ክርስቲያኖችም የአንዲቱ አካል የቤተ ክርስቲያን አባሎች፣
የክርስቶስ አካሎች ነን፡፡ በአንድ እግዚአብሔር በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
የተጠመቅን፣ የአንድ የክርስቶስን ሥጋና ደም የተቀበልን በመሆናችን አንድ የክርስቶስ
አካልም ነን፡፡ (፩ቆሮ. ፲፥፲፮-፲፯)፡፡ በዚህም ሁላችንም አንድ የክርስቶስ አካል (ሥጋ)
በመሆናችን አንድ ቤተሰብ፣ አንዲትም ቤተ ክርስቲያን ነን ማለት ነው፡፡

❖ አምስቱ እኅት አብያተ ክርስቲያናት አምስት ሲሆኑ እንዴት አንዲት ቤተ


ክርስቲያን ሊባሉ ይችላል?

ለዚህም ትምህርተ ሃይማኖታቸው አንድ የሆነውን አምስቱን እኀትማማች አብያተ


ክርስቲያናትን አብነት ማድረግ እንችላለን።በተለያየ ፓለቲካዊና መልክዓ ምድራዊ
አቀማመጥ እንደመገኘታቸው አምስቱም ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መጠነኛ
ልዩነት ያለው የአፈጻጸም ሥርዓት አላቸው፡፡ ይህም ወደ ክርስትና የመጡበትን የቀደመ
የአምልኮ ሕይወት መሠረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ የክህነት መሠረታቸው ከክርስቶስ
የተገኘ አንድ ሐዋርያዊ ሥልጣንና መንበር ነው፡፡ ትምህርታቸው በነቢያት ትንቢት፣
በክርስቶስ ፈጻሚነትና በሐዋርያት ስብከት ላይ የተመሠረተ አንድ ነው፡፡ በመጽሐፍ
ቅዱስ ያለውን እውቀት በመቀበል፣ በመመስከርና በመኖር በምሥጢራትም ጸጋ
እግዚአብሔርን በማደል አንድ ናቸው። በየጊዜው የተነሱ ልዩ ልዩ ኑፋቄያትን
በመቃወምና መናፍቃንንም በማውገዝ ልዩነት የለባቸውምና የአንዲት ቤተ ክርስቲያን
ቅርንጫፎች ናቸው።

የተወደዱ የዚህ መጽሐፍ ተከታታይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማጤን ለመመለስ


ይሞክሩ።

❖ አንዳንድ ምእመናን የአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ብልሹ ሥነ


ምግባር በማየት ዳግመኛ ቤተ ክርስቲያን ላለመሔድ ይወስናሉ፡፡ እርስዎ
ይህን ውሳኔ እንዴት ይገመግሙታል? የአገልጋዮች መጥፎ ሥነ ምግባር
በቤተ ክርስቲያን ቅድስና ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ይኖራልን?
❖ አንድ ሰው የቤተ ክርስቲያን አባል የክርቶስም አካል ሆኗል የሚባለው
እንዴት ነው?

ለ/ ቅድስት፡- በአንቀጸ ሃይማኖት የሰፈረው ሁለተኛው የቤተ ክርስቲያን መገለጫ


ቅድስት የሚለው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረታት፣ በተቀደሰው ደሙ ያነጻት ክርስቶስ
ቅዱስ ስለሆነ ማደሪያውም በእውነት ቅድስት ናት፡፡ (ኤፌ. ፭፥፳፮)፡፡ በበዓለ ሃምሳ
ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነውን (የቅድስና ባለቤት) መንፈስ ቅዱስን በተቀበለች ጊዜም
16
ፈጽሞ ቀድሷታል፡፡ የቅዱስ እግዚአብሔር የተቀደሰች ማደሪያው በመሆኗም የቅድስናና
የጸጋው ሁሉ መዝገብ ለመሆን ችላለች፡፡ የአገልጋዮቿ (የአባላቷ) በኃጢአት መሰነካከል
ቅድስናዋን አያረክሰውም፤ መንፈሳዊ ውበቷንም አያቆሽሸውም ፡፡ ይልቁንም እነሱን
በንስሐ አንጽታ ወደ ቀደመ ክብራቸው እንዲመለሱ በቅድስና ታከብራቸዋለች፡፡ ለእርሷ
የሚቀርበው መሥዋዕትና አገልግሎት ሁሉ የተቀደሰ ነው፡፡ “እርሱ አካሉ የሆነች ቤተ
ክርስቲያን ራስ ነው፤” (ቈላ. ፩፥፲፰)። ተብሎ እንደተጻፈው ራሷ ቅዱስ በመሆኑ አካሉ
የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ቅድስት ነች፡፡ “ነገር ግን የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እንዲሁ
እናንተም በአካሔዳችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፡፡ “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ” የሚል
ተጽፏልና፡፡” (፩ጴጥ. ፩፥፲፭-፲፯) በማለት ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተላለፈልን መልእክት
ፍጻሜውን ሊያገኝ የሚችለው በዚችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል ብቻ ነው። ለዚህ
የተጠሩ የምድራውያን (በአጸደ ሥጋ ያሉ) ክርስቲያኖችና የሰማያውያን (በአጸደ ነፍስ ያሉ)
ቅዱሳን ኅብረት መሆኗም የቅድስናዋ ሌላው መታወቂያዋ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የናቁና
በብልሹ ሥነ ምግባር በድፍረትም የተመላለሱ ቢገኙ እንደ ዳታን አቤሮንና ቆሬ (ዘኁ
፲፮)፣ እንደ ሐናንያና ሰጲራም (ሐዋ ፭፥፩-፲፭)፣ በእግዚአብሔር ቸርነትና ትዕግሥት
ከተጎበኙ በኋላ ይቀጡና ይወገዳሉ እንጂ ቤተ ክርስቲያን በኃጢአታቸው አትረክስም፡፡
አንድ አካባቢ ያለች አንዲት አጥቢያ ለሌላው ተግሣጽ ብትጠፋም እንኳን ቤተ ክርስቲያን
ግን የሲኦል አበጋዞች ሳያሸንፏት በቅድስናዋ ትቀጥላለች።(ማቴ ፲፮፥፲፰)።

ሐ/ ኩላዊት፡- ሦስተኛው የቤተ ክርስቲያን መታወቂያ በአንቀጸ ሃይማኖት “ከሁሉ በላይ


በምትሆን” ተብሎ የተገለጸው ኩላዊነቷን የተመለከተ አንቀጽ ነው፡፡ ይህም ቤተ ክርስቲያን
ምንም ዓይነት የቀለም፣ የጤና ሁኔታ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የቋንቋ፣ የጾታ፣ የሀብት፣
የመልክአ ምድርና ማንኛውም ልዩነት ሳያግዳት በየትኛውም ሀገር የምትገኝ ዓለም
አቀፋዊት ቤተ እግዚአብሔር መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሐዋርያትን” “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤
በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፤ በሰማርያና እስከምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቼ
ትሆኑኛላችሁ፡፡” (ሐዋ. ፩፥፰)፡፡ በማለት የሰጠው አምላካዊ መመሪያ ይህንኑ የቤተ
ክርስቲያንን ድንበር የለሽ አገልገሎት ማለትም ኩላዊነት አጉልቶ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም
ማቴ. ፳፰፥፲፱ ሚል. ፩፥፲፩ ዮሐ. ፫፥፲፮-፲፰ ማር. ፲፮፥፰ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ
ኃይለ ቃላት ብንመለከታቸው ይህንኑ ርእሰ ጉዳይ የሚያጠናክሩ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
“በእርሱ ዘንድ አይሁዳዊ፣ ግሪካዊ፣ የተገዘረ፣ ያልተገዘረም፣ አረመኔም፣ ባላገርም፣ ቤተሰብ
እና አሳዳሪ ማለት የለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ለሁሉ በሁሉም ዘንድ ነው፡፡” (ቈላ. ፫፥፲፩)
በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ያስተላለፈልን ትምህርትም ሌላው የቤተ ክርስቲያን
ኩላዊነት ዋነኛ ማረጋገጫ ነው፡፡የቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፋዊነት (ኩላዊነት) ከቦታ
አንጻር ብቻ የሚታይ ሳይሆን ከጊዜም አንጻር የሚብራራ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን በቦታ ብቻ ሳይሆን በጊዜም የማትወሰን በመሆኗ በብሉይ ኪዳን


የነበሩትን አበውና እማት ጨምሮ ከሐዋርያት ጀምሮ እስከ ምጽአት ያሉትን ምእመናን
ልጆቿን ሁሉ አካታ /ሁሉንም በማጠቃለል/ የያዘች እናት ናት፡፡ ይህ ጉዳይ በሌላ
መንገድ ሲገለጽ ቤተ ክርስቲያን በአጸደ ሥጋና በአደጸ ነፍስ ያሉ ምእመናን አንድነት
17
(ሕብረት) ናት፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባሎቿ በሁለት ይከፈላሉና፡፡ የመጀመሪያዎቹ
በአጸደ ሥጋ ያሉት ተዋጊዎች፣ ሰልፈኞች የሆኑት ሲሆኑ፤ ሁለተኞቹ ደግሞ በአፀደ
ነፍስ የሚገኙ አሸናፊዎች፣ ድል አድራጊዎች የሆኑት ናቸው፡፡ እነዚህም ከላይ
የክርስቲያን ዘር፣ የክርስቲያን ወገን፣ የክርስቲያን ትውልድ ያልናቸውን አጉልተው
የሚያሳዩ ናቸው። በዚህም መሠረት የቤተ ክርስቲያን ኩላዊነት በሰማይም በምድርም፣
በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም ያሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል መሆኑን ማስተዋል
ይገባል፡፡

ከላይ እንደገለጽነው የቤተ ክርስቲያን መሥራቿና ራሷ ክርስቶስ በሰማይ፣ በምድርና


በሁሉም ቦታ ይኖራል፡፡ እሱ የሌለበትና የማይኖርበት ቦታ እንደሌለ (እንደማይኖር)
ሁሉ አካሉ ቤተ ክርስቲያንም የሌለችበትና የማትኖርበት ቦታ አይኖርም፡፡ ኩላዊነቷ
(ዓለም አቀፋዊነቷ) የሚመነጨው ከዚህ እውነት ነው፡፡ በአጸደ ነፍስ ያሉት በሰማያዊ
ስፍራ ከክርስቶስ ጋር የሆኑትን ያህል በአጸደ ሥጋም ያሉት በልባቸውና በመንፈሳዊው
ሕይወታቸው ከጌታቸውና ከሚወዱት ከክርስቶስ አምላካቸው ጋር በሰማይ ናቸውና፡፡
ምንም እንኳን በዚህ ምድር ላይ በታላቅ መከራ፣ በስደት፣ በጉስቁልናና ተዋርዶ ውስጥ
ቢኖሩም ክርስቶስ በሰጣቸውና ተዘጋጅቶላቸው ባለ ተስፋ በመጽናናት ይኖራሉ፡፡
ኩላዊነት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ የሁሉ እናት ሆና በሞት የለያዩትን፣ በቦታና በጊዜ
የተራራቁትን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አቀራርባ በአንድ ጊዜና ቦታ
እንደምታድማቸው፤(እንደምትሰበስባቸው) የሚያሳይ ምሥጢራዊ ቃል ነው።

ዓለም አቀፋዊነት ሙሉ ለሙሉ ምድራዊ የሆነችውን የዚችን መሬት (ዓለም) ዜጎች


የሚያቅፍ የምድራዊ ሕብረት መገለጫ ሲሆን ኩላዊነት ግን ምድራውያንና ሰማያውያን
የቤተ ክርስቲያን አባላት (የቅዱሳንን አንድነት) ጨምሮ የሚያቅፍ ላቅ ያለ ትርጉም
ያለው የቤተ ክርስቲያን አንዱ ባሕርይ (መገለጫ) መሆኑን ማስተዋል ይገባል።

ውድ አንባቢ ሆይ የሚከተሉውን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ

• የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊነት እንዴት ይገለጻል?

መ/ ሐዋርያዊት፡- በአንቀጸ ሃይማኖት “ሐዋርያት በሰበሰቧት” ተብሎ መገለጹ ቤተ


ክርስቲያን ሐዋርያዊት መሆኗን የሚያስረዳ ኃይለ ቃል ነው፡፡ ከላይ አመሠራረቷን
በተመለከተ እንደገለጽነው ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኑን የመሠረታት በቅዱስ ጴጥሮስ
የምስክርነት ቃል ላይ ሲሆን የመሥራቿ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በሆኑ በቅዱሳን
ሐዋርያት የማይቋረጥ /ዘላለማዊ/ የክህነት ሥልጣንና አገልግሎት ላይ አጽንቷታል፡፡
አምላካችን ክርስቶስ ያወቁትን፣ ያመኑበትን፣ ያዩትን፣ የሰሙትን፣ በእጆቻቸው የዳሰሱትን
ለዓለም እንዲያስተምሩና እንዲመሰክሩ የቤተ ክርስቲያንን ተግባርና ሓላፊነት ለቅዱሳን
ደቀ መዛሙርቱ ሰጥቷቸዋል፡፡ (፩ጢሞ፩፥ ፭)፡፡ እነርሱን የሰማ እርሱን እንደሚሰማ፤
እነርሱን እንቢ ያለም እነርሱን እንቢ እንደሚል ገልጾ በቤተ ክርስቲያን ላይ ባለ ሙሉ
ሥልጣን አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡ (ማቴ. ፲፥፵። ማር. ፱፥፴፯ ሉቃ. ፲፥፲፮ ዮሐ. ፲፫፥፳)፡፡

18
እነርሱም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት እየፈወሱ ዓለምን ዕጣ
በዕጣ ተካፍለው በወንጌል መረብነት ምእመናንን በውቅያኖስ ከተመሰለው ዓለም ሰበሰቡ፡፡
አንዲት፣ ቅድስትና ኩላዊት የሆነች ቤተ ክርስቲያንንም በመላው ዓለም አስፋፉ፡፡ ክርስቶስ
የእርሱ የባሕርይ ገንዘቦች የሆኑትን ሀብታት በጸጋ አጎናጽፏቸዋልና፡፡ (ማር. ፲፮፥፲፭-፲፱
ዮሐ. ፳፥፳፪-፳፫።፳፩-፲፭-፲፰)፡፡ “ሐዋርያዊት” የሚለው ቃል ለእውነተኛይቱ ቤተ
ክርስቲያን መገለጫ ባሕርይዋ፣ አርማና ምልክቷ ነው፡፡ ትውፊቷ፣ ትምህርቷ፣ ሥርዓቷና
ሥልጣነ ክህነቷ ከአባቶቻችን ከሐዋርያት ተያይዞ የመጣና ሰንሰለቱ ያልተቋረጠ፣ ዛሬ ከኛ
ዘመን የደረሰና ነገም እስከምጽአት የሚጓዝ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት
ተብላለች፡፡ እነዚህን የቤተክርስቲያን ባሕርያት ማወቅ ምእመናን በቤተክርስቲያን
እንዲኖሩ ኋላም የመንግሥተ ሰማያት እድምተኞች እንዲሆኑ ያነሳሳቸዋል።ሐዋርያዊ
ትውፊት፣ ትምህርት፣ ሥርዓትና ሥልጣነ ክህነት ሳይኖር ቤተ ክርስቲያን ልትኖር
አትችልምና።

ማጠቃለያ፦
የቤተ ክርስቲያንን ፍቺ ከሕንፃውና ከምእመናን ጉባኤ አንጻር ብናስቀምጠውም የተለያዩ
ናቸው ማለት እንዳልሆነ መታወቅ ይኖርበታል። ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ያለ ምእመናን
ጉባኤ (ማኅበረ ካህናት ወማኅበረ ምዕመናን) ቤተ ክርስቲያን ሊባል አይችልም፡፡ የማኅበረ
ካህናትና የማኅበረ ምእመናን ጉባኤም ይነስም ይብዛም ያለ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
ሊታሰብና ሊነገር አይችልም፤ መጀመሪያውኑም ያለ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳውያን
ዜጎችና ክርስቲያኖች የመንግሥተ ሰማያት ዕድምተኞች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ አንዱን
ስናነሣ ሁለተኛውም አብሮት እንዳለ መረዳት ጠቃሚ ይሆናል። በውስጡ የሚከናወን
አገልግሎት፣ ሥርዓት፣ ምሥጢራት፣ ንዋያተ ቅዱሳትና አገልጋዮቹ ለብቻቸው መቆም
የሚችሉ ሳይሆኑ የተሰናሰሉ ናቸው። ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ
ክርስቶስ ያነፃት (የሠራት) ሕይወት አካሉ ናት፡፡ በቅድስና ያጌጠ (የተሸለመ)ና
ከሐዋርያት የተገኘ አንድ መሠረት፣ አንዲት ሕንፃ፣ አንድ ሥርዓት፣ አንድ ትውፊት፣
አንድ ትምህርተ ሃይማኖትና አንድ የሥልጣነ ክህነት መስመር ስላላት በምንም ዓይነት
ምድራዊ መለኪያ ልትመዘንና ልትከፋፈል የማትችል ናት፡፡ የሰውን ልጆች ሁሉ ወደ
ድኅነት ወደብ የምትጠራ፣ የምትቀበል፣ የምትመግብ፣ የምታሳድግና ለፍሬ የምታበቃ እመ
ብዙኅን (የብዙዎች እናት) ናት፡፡ በምድር ያለች የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት
ስለሆነችና ሰማይና ምድርን የምታገናኝ በመሆኗ ኩላዊት ናት:: የቤተ ክርስቲያን ልጅ
የሆነ ሁሉ እንደ ቤተ ክርስቲያን አባልነቱ የቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ (ዓላማ) ከዳር
ከማድረስ (ከማስፈጸም) አኳያ የድርሻውን ሱታፌ ማበርከት ይኖርበታል።

ዋቢ መጻሕፍት

• ቀሲስ ዶ/ር ሰሙ ምትኩና መ/ር ቸሬ አበበ፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቁጥር፩፤


ማኅበረ ቅዱሳን፤ ፳፻ አ/አ።

19
• ዲ/ን ያሬድ ገ/መድኅን፤ ኆኅተ ሰማይ፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፮፤ አ/አ።
• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫፤ አ/አ።
• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤ ሥርዓተ
ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤አ/አ።
• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፤
፲፱፻፺፤ አ/አ።
• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።
• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤EAMERSEN፤2000፤ አ/አ።
• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት፤ ማኀበረ
ቅዱሳን ፤1996፤ አ/አ።
• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ
ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኅበረ ቅዱሳን፤ 1999፤ አ/አ።
• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፣ መጽሐፈቅዳሴ፣ ትንሣኤማሳተሚያድርጅት፣ ፲፱፻፹፰፣ አዲስ አበባ።

20
ምዕራፍ ሁለት
ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ከነገረ
ድኅነት ጋር ያላቸው ግንኙነት (፩ ሰዓት)
መግቢያ
ነገረ ድኅነት በክርስቶስ ሰው መሆንና ቤዛነት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲያው በነጻ
የተሰጠ የሕይወት ፈቃድ ነው። ይህን የሕይወት ፈቃድ ለሰው ልጆች ሁሉ እንድትናኝ
(እንድትሰጥ) ሥልጣንና ሓፊነት የሰጠው ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ
ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ከነገረ ድኅነት ጋር ያላቸው
ትስስር (ግንኙነት) ተገልጧል። በዋናው ርእስ ሥርም፡-

• የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ምንነት፤

• የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትርጉም፤

• የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነትና ምንጮች፤የሚሉት ንዑሳን አርእስት


ተብራርተዋል።

ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምረው


ሲያጠናቅቁ፡-

• ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ከነገረ ድኅነት ጋር ያላቸውን ግንኙነትና አስፈላጊነት


ይረዳሉ፤ ያስረዳሉ፡፡

• የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንነት ተገንዝበውና ለነገረ ድኅነት ያለውን ጠቀሜታ


አምነው ሕይወታቸውን ይመረምራሉ፡፡

21
፪.፩ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን እነማን ናቸው?
ውድ አንባቢ ሆይ፦

በክፍለ ትምህርቱ የተጠየቀውን ዐቢይ ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት የሚከተለውን ጥያቄ


ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ ምሥጢር የሚሰኙት እንዴት ነው?

ምእመናነ ክርስቶስ ሁለት ልደታት አሏቸው፡፡ እነዚህም ሥጋዊና መንፈሳዊ ልደት


በመባል ይታወቃሉ፡፡ ለሥጋዊው ልደት ዕድገትና ሌሎች ተያያዥ ነገሮች እንዳሉት ሁሉ
መንፈሳዊውም ልደት ዕድገትና ሌሎች ጉዳዮች ይከታተሉታል፡፡ አንድ ሰው መንፈሳዊ
ልደት የሚያገኘው በእምነትና በጥምቀት ሲሆን በተከታታይ (በአንድ ዕለት) ምሥጢረ
ሜሮንና ምሥጢረ ቁርባን ተፈጽመውለት ልደቱን ፍጹም በማድረግ ለዕድገቱም መሠረት
ይሆኑታል፡፡ በዚህም ልደቱ አዲስ ሆኖ ይፈጠራል፤ ይወለዳል፤ ማለትም የክርስቲያናዊ
ሕይወት ባለቤት ይሆናል፡፡ በቀሪ የሕይወት ዘመኑና በክርስቲያናዊ ሕይወቱ ክርስቶስን
ወደ መምሰልሚያድግ፣ ለክብር የሚበቃ፣ በሰማያዊው የእግዚአብሔር መንግሥትም
የሚታደም ይሆናል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ከማኅፀነ ዮርዳኖስ፣ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ምእመናንን ወልዳ በማሳደግ


ለክብር የምታበቃባቸው መንገዶች ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በመባል ይታወቃሉ፡፡
ከእነዚህ ምሥጢራት ውጪ ልደት መንፈሳዊም ሆነ ዕድገት ሰማያዊ ፈጽሞ የማይታሰብ
ነው፡፡ ይህም በምእመናን ክርስቲያናዊ ሕይወት (በሥራ) ተገልጦ ይታያል፤ድምፁም
ይሰማል፡፡ ማለትም ሌሎች ሰዎች በልብ ዓይን ዓይተው፣ በልብ ጆሮ ሰምተው፣ በልብ
እጅም ዳሰው ይረዱታል፡፡ በእምነት ከመቀበል ውጪ ልደቱም ሆነ ዕድገቱ በሥጋ ዓይን
የማይታይ፣ በሥጋ ጆሮ የማይሰማ፣ በሥጋ እጆችም የማይዳሰስ በመሆኑ ምሥጢር ሊባል
ችሏል፡፡(፪ቆሮ ፭፥፯)፡፡ አዕማደ ምሥጢራት ሰዎች ይድኑ ዘንድ ሊያውቁትና ሊያምኑበት
የሚገባውን ትምህርተ ክርስትና /የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ/ ይዘው የቀረቡ ሲሆኑ
ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ግን ተግባራዊ የሆነውን የክርስትና ሕይወት በመንፈሳዊ
ሥርዓት የሚያሳዩ፣ የአማኞችንም ቀጥተኛ ሱታፌ የሚጠይቁ ናቸው፡፡ በዚህ ክፍለ
ትምህርት የምንማረው እያንዳንዳችን ያጣጣምነውን፣ በተግባር ያየነውን፣ በቅርበት
የምናውቀውንና ከዕለት ተዕለት ኑሮዋችን ጋር በጥብቅ የተያያዘውን ጉዳይ መሆኑን
መረዳት ይገባል፡፡ ስለዚህም “ምን ያህል አውቄዋለሁ?” በማለት ብቻ ሳይሆን “ምን ያህል
የምሥጢራቱ ተሳታፊ ነኝ (ሆኛለሁ)?” ብሎ ራስን በመጠየቅ ክርስቲያኖች በዘመናት ሁሉ
የሚማሩበት የሕይወት ትምህርት መሆኑን መርሳት አይገባም።

ውድ አንባቢ ሆይ፥

❖ ለመሆኑ እነዚህን ምሥጢራት ምን ያህል ያውቋቸዋል?


22
እነማንስ ናቸው? የሚያስታውሱትን ያህል በማስታወሻዎ ላይ ያስፍሩ።

አንድ ያመነ ሰው ክርስቲያን ለመባል የግድ ሊፈጽማቸው የሚገቡ ምሥጢራት የትኞቹ


ናቸው?

❖ እርስዎ የትኞቹ ምሥጢራት ተፈጽሞልዎታል?


❖ የትኞቹን ምሥጢራት ሳያቋርጡ ቀጥለዋል?
❖ የትኞቹን ምሥጢራት ነው እስካሁን ያልፈጸሙት? ለምን?ወደፊትስ ምን
አቅደዋል?

እንደሚታወቀው ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በቁጥር ሰባት ናቸው፡፡ ቁጥራቸውና


ዝርዝር ማብራሪያቸው ከአፈጻም መመሪያው ጋር በሚቀጥሉት ምዕራፎች የሚቀርቡ
ይሆናል።ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ሜሮን፣ ምሥጢረ ቁርባን፣ ምሥጢረ
ክህነት፣ ምሥጢረ ንስሓ፣ ምሥጢረ ተክሊልና ምሥጢረ ቀንዲል ናቸው፡፡

የእነዚህ ምሥጢራት ሰባት መሆን በመጽሐፈ ምሳሌ እንደሚከተለው ተገልጿል


“ጥበብ ለራስዋ ቤቷን ሠራች ሰባቱንም ምሰሶዎቿን አቆመች፤ ፍሪዳዋን አረደች፤
የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች፤ ማዕድዋን አዘጋጀች፤ አገልጋዮቿን ልካ
በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕዷ ጠራች፤ እንዲህም አለች፡- አላዋቂ የሆነ ወደ እኔ ይምጣ፤
አእምሮ የጎደላቸውንም እንዲህ አለች፡- ኑ እንጀራዬን ብሉ፤ የጠመቅሁላችሁን የወይን
ጠጅም ጠጡ፤ ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፤ በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን
ፈልጉ፤ በመረዳትም ዕውቀትን አቅኑ፤” (ምሳ.9፡1-3)፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ስለነዚህ
ምሥጢራት ጠቢቡ የተናገረው ትንቢት ነው። ኃይለ ቃሉ የምሥጢራቱን ሰባትነት
ብቻ ሳይሆን የምሥጢራቱ ሁሉ መክብባቸው ስለሆነው ስለ ምሥጢረ ቁርባን በጉልህ
ይናገራል፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በቅዳሴው ጥበብ የተባለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ መሆኑን
ተርጉሞልናል፡፡ ከዚህ በመነሣት የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን መሥራች ክርስቶስ
እንደሆነና ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ ለቤዛ ዓለም መስጠቱን እንማራለን፡፡ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮቹ ሐዋርያትንና ሰብአ አርድእትን ወደ ዓለም ሁሉ ልኮ
የመንግሥትን ወንጌል እንዲሰብኩ ቤተ ክርስቲያን በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
አማካኝነት ወደምታድላቸው ጸጋዎች ወደ ዘላለማዊ ድኅነት እንዲጠሩ መላካቸውን
ይነግረናል፡፡ በስብከታቸው ያመኑ በጥምቀት በር የገቡና በሜሮን የታተሙ ሥጋውን
በልተው ደሙን ጠጥተው እንዲድኑ መጠራታቸውን ያስተምረናል።

23
፪.፪ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንድነው?
የተከበሩ አንባቢ ሆይ፦ በምዕራፍ አንድ የተማሩትን ያስታውሳሉን? እስቲ ከዚህ በታች
የቀረቡትን ጥያቄዎች በማሰላሰል ለመመለስ ይሞክሩ፡፡

❖ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?


❖ እንዴትና ማን መሠረታት?
❖ በስንት ዓይነት መንገድ ትገለጻለች? (ባሕርይዋ ምንድነው?)

ሥርዓት የሚለው ቃል “ሠርዐ-ሠራ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ስም ነው፡፡ ትርጉሙም


ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ሆኖ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲባልም የቤተ ክርስቲያን
ሕግ፣ ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር፣ ዐቅድ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህም መሠረት በዚህ
ክፍለ ትምህርት አንዲቷ፣ ሐዋርያዊቷና ኩላዊቷ (ዓለም አቀፋዊቷ) ቅድስት ቤተ
ክርስቲያን ከመሥራቿ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለችውን የክህነት አገልግሎት
አፈጻጸም እናያለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሥርየተ ኃጢአት፣ የኖላዊነት (እረኝነት)፣
የማስተማር፣ የማስተዳደርና ምሥጢራትን የመፈጸም ሥራ ለማከናወን የምትችልበት
ሥርዓትም ባለቤት ናት፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በምንልበትም ጊዜ በተቀደሰው ቤት
(ሕንፃ) ለሚከናወነው አገልግሎት፣ በምእመናን ጉባኤ ለሚተገበረው መንፈሳዊ ሥራና
በእያንዳንዱ ምእመን ሕይወት ከልደት እስከ ዕረፍት ለሚፈጸመው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ
ሁሉ መመሪያ የሚሆነውን ማለታችን ነው፡፡

፪.፫ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነትና ምንጮች


ይህን ርእሰ ጉዳይ ከማየታችን በፊት የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማሰላሰል በኀሊናዎ
ለመመለስ ይሞክሩ፤

❖ “ሥርዓት ነጻነትን ያሳጣል፤መታሰር ነው፤ሕዝቡን ልቀቁት፤ፍቱት” የሚሉ


አንዳንድ ሰዎች አሉ።ይህን አባባል እንዴት ያዩታል?
❖ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ለምን ያስፈልጋል? (ጠቀሜታው ምንድነው?)
❖ በዓለም ላይ ያለ ሥርዓት የሚጓዙ ዓለማዊም ሆኑ መንፈሳዊያን ተቋማት
ይኖራሉ ብለው ያስባሉ?

ሀ/ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነት


የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት (ሥራ) ይቅርና ማንኛውም በዚህ ዓለም ውስጥ
የሚከናወን ተግባር ያለ ሥርዓት ሊጀመር፣ ሊሠራና ሊፈጸም አይችልም፡፡ ሥርዓተ ቤተ
ክርስቲያን ካለ ዘንድ ጠቀሜታውን ማወቅ፣ ማክበርና ለተፈጻሚነቱ ሁሉም የድርሻውን
24
ማበርከት ይጠበቅበታል፡፡ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነት በሚከተለው መልኩ
ሊገለጽ ይችላል፡፡

፩ኛ. የቤተ ክርስቲያንን ልጆች በአንድ መስመር ለመምራት፣ ወጥና ዘላቂ በሆነ መንገድ
እንዲጓዙ ለማስቻል ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ፡- ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ክፍለ
ዓለም ብትታነፅም /ብትሠራም/፣ በየትኛውም ዓይነት ቋንቋ ብትገለገልም፣ አገልግሎቷን
ለየትኛውም ዓይነት ሕዝብ ብታቀርብም መሠረተ እምነቷ፣ የምሥጢራት አፈጻጸሟና
ሁለንተናዊ አገልግሎቷ ወጥና ዘላቂ (የማይቀያየር) በሆነ ሥርዓት መመራቱ የግድ ነው፡፡
ይህ ካልሆነ ግን አስተማሪውና ተማሪው፣ ተናጋሪውና ሰሚው፣ ቀዳሹና አስቀዳሹ፣
አገልጋዩና ተገልጋዩ፣ እረኛውና በጉ፣ ጀማሪውና ተከታዩ … ወዘተ ስለማይታወቅ
የተደበላለቀ (ውጥንቅጡ የወጣ) ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን ሁሉን
በአገባብና በሥርዓት አድርጉ፤” (፩ቆሮ ፲፬፥፵) በማለት ያስተማረው፡፡

፪ኛ. የክርስቶስ አካላት፣ የቤተ ክርስቲያንም አባላት የሆኑት ካህናትና ምእመናን አንድ
ልብና አንድ አሳብ ለመሆን የሚችሉት አንድ ዓይነት ሥርዓት ሲኖራቸውና ሲመሩበት
ነው፡፡ አለበለዚያ አንዱ ሲያስተምር አንዱ የሚዘምር፣ አንዱ ሲጀምር አንዱ የሚጨርስ፣
አንዱ ሲያበራ አንዱ የሚያጠፋ፣ አንዱ ሲከፍት አንዱ የሚዘጋ … ወዘተ ይሆንና ቤተ
ክርስቲያን ትርምስና ሁከት መለያየትም የሚነግሥባት ቤት ትሆናለች:: ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስ “የተጻፈው ሁሉ በመታገሳችንና መጻሕፍትን በማመናችን ተስፋችንን እናገኝ
ዘንድ እኛ ልንማርበት ፤ የትዕግስትና የመጽናናት አምላክ እግዚአብሔር እንደ ኢየሱስ
ክርስቶስ ፈቃድ እርስ በርሳችን አንድ ሀሳብ መሆንን ይስጠን፤ ሁላችን አንድ ሆነን
በአንድ አፍ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን እናመሰግነው ዘንድ፡፡” (ሮሜ
15-4-7) በማለት እንደተናገረው ክርስቲያኖች አንድ ሀሳብ መሆንና አንድ ሆነው በአንድ
አፍ እግዚአብሔርን ማመስገን የሚችሉት ወጥ በሆነ ሥርዓት መመራት ሲችሉ ነው፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ይህን ስለተረዱ ነው በእግዚአብሔር መንፈስ ተቃኝተው ስምንቱን
የሥርዓት መጻሕፍት የሠሩልን፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ሉቃስ “ያመኑትም ሁሉ አንድ ልቡና
አንዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡” (ሐዋ 4፡32) በማለት የጻፈልንን ብንመረምረው አንድ
ልብና አንዲት ነፍስ የመሆን ምሥጢሩ በሥርዓት መመራት መተባበርም መሆኑን
ለመረዳት አያዳግትም፡፡

፫ኛ. የሃይማኖትን ምሥጢራት ለመፈጸም የሚቻለው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲኖር ብቻ


ነው፡፡ ሥርዓት የሃይማኖት መግለጫ ነውና፡፡ ሥርዓት የሌለው ሃይማኖት ፈጽሞ ሊኖር
አይችልም፡፡ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት የሚከናወንበት የራሱ የሆነ ሥርዓት አለው፡፡ በመሠረተ እምነት ደረጃ
የምናምነውን በተግባር የምንገልጸው ሥርዓት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ
ጥንትም በብሉይ ኪዳን ኋላም ሰው ሆኖ ቤተ ክርስቲያኑን በመሠረታት ጊዜ ያለ ሥርዓት
ያከናወነውና እንድናከናውንም ያዘዘን አንዳች ነገር የለም፡፡ ለምሳሌ ከብሉይ ኪዳን
የፋሲካውን በግ በተመለከተ የተጻፈውን ብንመለከት ጠቦቱ የሚያዝበት ወሩና ቀኑ፣ የተመጋቢዎች
ቁጥር፣ የጠቦቱ ዓይነትና መጠኑ፣ የሚታረድበት ሰዓት፣ ደሙ የሚቀባበት ቦታና አቀባቡ፣ የምግቡ

25
አዘገጃጀት፣ የመብሊያው ሰዓት፣ የአመጋገቡ ሂደትና የተመጋቢዎቹ ዝግጅት በዝርዝር መታዘዙ
ሥርዓት መሆኑንና አዛዡም እግዚአብሔር መሆኑን ማስተዋል ይገባል፡፡ (ዘፀ 12፡6-15)፡፡

በሐዲስ ኪዳንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ፤


በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን ያስተማርናችሁንና የሠራንላችሁን ሥራዓት ያዙ፡፡”
(2 ተሰ. 2፡15)፡፡ በማለት ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት የሚበጅ ሥርዓት መሥራታቸውንና
ክርስቲያኖችም ይህን ሥርዓት መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝቧል፡፡ በሥርዓት መመራት
እስረኝነት ሳይሆን ያመኑበትንና ያወቁትን በተግባር ለመግለጽ የሚያስችል ነጻነት ነው፡፡
ከላይ ለማየት እንደቻልነው እግዚአብሔር በመረጣቸው ቅዱሳን በኩል ያዘዘው፣ ሰው ሆኖ
በተገለጸ ጊዜ የሠራውና በመንፈስ ቅዱስ ተረድተው አባቶች የሠሩልን ነው፡፡ ለማሳያ
ያህልም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የምጽዋት፣ የጸሎትና የጾም
ሥርዓትን እንደሠራልን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ (ማቴ 6፡1-19)፡፡ እግዚአብሔር
የፈጠረው ሥነ ፍጥረት እንኳን በዚህ ዓለም የሚመላለሰው በተሠራለት ተፈጥሮአዊ
ሥራዓትና ሕግ ነው፡፡ “በሥርዓትህ ለሚኖሩ እንስሳ ሁሉ ታጠግባለህ፡፡” (መዝ 144፡16)
እንዲል፡፡ በዓለማዊው ስብሰባ እንኳን ሥርዓት ባይኖር ኖሮ የመናገር ነጻነትና መደማመጥ
ወዴት በተገኘ ነበር፡፡

ለ/ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጮች


ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁ በዘፈቀደ በሰዎች ፍላጎትና አሳብ የተጀመረ (የመጣ)
አይደለም፡፡ ይልቁንም ከላይ እንደገለጽነው የቤተ ክርስቲያኒቱ መሥራችና ራስ በሆነው
በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ የተሠራና ለቤተ ክርስቲያንም
መተዳደሪያ ይሆናት ዘንድ የተሰጠ ታላቅ ሀብት ነው፡፡ በዋናነት የሥርዓተ ቤተ
ክርስቲያን ምንጭ ነው ብላ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረው መጽሐፍ ቅዱስን ነው፡፡
ይህም ዘርዘር ተደርጎ ሲገለጽ፦

• መጻሕፍተ ብሉያት፣

• መጻሕፍተ ሐዲሳት፣

• የሐዋርያት ሲኖዶሳት፣

• ሥርዓተ ጽዮን፣

• አብጥሊስ፣

• ትእዛዝ ፣

• ግጽው፣

• ዲድስቅልያና
26
• ቀሌምንጦስ የሚባሉትን ያካትታል፡፡

በተጨማሪም

• ፍትሕ መንፈሳዊና

• የሦስቱ ጉባኤያት ውሳኔዎች የሥርዓተ ቤተ ክርሥቲያን ምንጮች ናቸው፡፡

በሌላ መንገድም የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ሥርዓተ ቤተ መቅደስ ሲሆን፤


የሥርዓተ ቤተ መቅደሱ መሠረት ደግሞ ሥርዓተ ደብተራ ኦሪቱ ነው፡፡ የሥርዓተ
ደብተራ ኦሪት መሠረቱ ደግሞ ሥርዓተ መቅደስ ሰማያዊ መሆኑን እግዚአብሔር ራሱ
ነግሮናል፡፡ “በተራራው እንዳሳየሁህ ሁሉ፣ እንደ ማደሪያው ምሳሌ፣ እንደ ዕቃውም ሁሉ
ምሳሌ ለእኔ ትሠራለህ፤ እንዲሁ ትሠራለህ፡፡” (ዘጸ. ፳፭፥፱ ፣ ፳፮-፴፣ ፳፯፥፰)፡፡
በማለት ሙሴን እንዳዘዘው የተጻፈው የሚገልጽልን ይህንኑ እውነታ ነው፡፡ ይህን
ሰማያዊ መቅደስ ዮሐንስ ወንጌላዊም በራእዩ ማየቱን ነግሮናል፡፡ “ከዚህም በኋላ
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የእግዚአብሔር የሕጉ ታቦትም
በመቅደሱ ታየች፤” (ራእ. ፲፩፥፲፱) እንዲል፡፡ ሙሴ ወደ ተራራው በወጣ ጊዜ
እግዚአብሔር ሰማያዊውን የብርሃን መቅደስ” ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ንዋየ ቅዱሳትንና
የአገልግሎቱን ሥርዓት እንዲያይና እንዲሰማ ፈቅዶለታል፡፡ ለዚህም ነው በተደጋጋሚ
“በተራራው ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ፡፡” እያለ የሚያሳስበው፡፡ ቅዱስ
ዮሐንስ ወንጌላዊም “ሰማይ ተከፈተ” በማለት ዓይነ ልቡናው በርቶለት ምሥጢራትም
ተገልጠውለት ሰማያዊን የብርሃን ቤተ መቅደስ ከታቦተ እግዚአብሔርና ንዋያተ
ቅዱሳት ጋር ማየቱን ነው የገለጠልን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መቅደሱንና ታቦተ
እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን ያየው የካህናተ ሰማይ የቅዱሳን መላእክትን የአገልግሎት
ሥርዓትም ነው፡፡ (ራእ. ፰፥፩-፮)፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ቢሆኑ በአገልግሎት ዘመናቸው
ይህንኑ ሰማያዊ የአገልግሎት ሥርዓት እግዚአብሔር በገለጠላቸው መጠን ማየትና
መስማት ችለዋል፡፡ (ኢሳ. ፮፥፩-፮፡፡ ሕዝ. ፩፥፩-ፍጻ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትን
የምትፈጽምበትና አገልግሎቱን የምታከናውንበት ሥርዓት በቀጥታ ከሰማያዊው
የብርሃን መቅደስ የተገኘ (የተቀዳ) መሆኑን ማስተዋልና ሥርዓቷን አክብሮ መጓዝ
ይገባል፡፡

27
፪.፬.ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
ከነገረ ድኅነት ጋር ያላቸው ግንኙነት
ቃለ ወንጌልን በመስማት የሚጀምረው የሰው ልጆች ድኅነት በእምነት የሚመሠረት
ቢሆንም የተሟላ የሚሆነው ግን ምሥጢራትን በመፈጸም ነው፡፡ ይህም ድኅነት በአንድ
ጊዜ ተጀምሮ የሚያልቅ ባለመሆኑ በሰው ልጆች ምድራዊ ሕይወት ሁሉ ከሰይጣን፣
ከእኩያት ኃጣውእና ከፍትወታት እኩያት ጋር በሚደረግ ረጅም መንፈሳዊ ተጋድሎ
የሚረጋገጥ ነው፡፡ በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ውስጥ ሁሉ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ መሠረት አንድ ሰው መዳን ከፈለገ ቃለ
እግዚአብሔርን መስማት፣ ማመን፣ መጸለይ፣ ሌሎች ትእዛዛትን መፈጸምና የምሥጢራተ
ቤተ ክርስቲያን ተካፋይ መሆን ይኖርበታል፡፡ “… በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ሆናችሁ
ለድኅነታችሁ ሥሩ፡፡” (ፊልጵ. ፪፥፲፪፡፡) እንደተባለ፤ ሁላችንም የምሥጢራተ ቤተ
ክርስቲያን ተሳታፊ ለመሆን መትጋት ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ
እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ፡፡” (ያዕ. ፩፥፳፪፡፡) ተብሎ
ተጽፏልና፡፡ ክርስቶስን ማመናችንና መቀበላችን የሚረጋገጠው፣ በጸጋው መዳናችንም
የሚታወቀው ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በመፈጸም ብቻ መሆኑን ማመን ይኖርብናል፡፡
ይህንንም የምናገኘው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ ስንሆን ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ
መሆንና ራስን በራስ ግላዊ አስተያየትና ፍልስፍና ከቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ገለልተኛ
ማድረግ ከድኅነት መስመር መራቅ ነው፡፡

ነገረ ድኅነትና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸው፡፡ ያለ


ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ድኅነት ፈጽሞ አይታሰብምና፡፡ ለማሳያ ያህልም ብንመለከት
“ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡” (ማር. ፲፮፥፲፮፡፡) “ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ
የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በኋለኛይቱ ቀን አነሳዋለሁ፡፡” (ዮሐ. ፮፥፶፬፡፡) ለመዳንና
የዘላለም ሕይወት ባለቤት ለመሆን የምንችለው ምሥጢረ ጥምቀትን ቁርባንን ስንፈጽም
መሆኑን ከጥቅሶቹ መልእክት እንማራለን።

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንንም ከነገረ ድኅነት አንጻር ብንመረምር በተመሳሳይ ሁኔታ


ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው እንገነዘባለን፡፡ ያለ ሥርዓት የሚፈጸሙ የቤተ ክርስቲያን
ምሥጢራት የሌሉ እንደመሆኑ መጠን ያለ ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው
ድኅነትም የለም፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለድኅነተ ዓለም የተጓዘባቸው መንገዶችና
የመሠረታቸው ምሥጢራት ሁሉ የተከናወኑት በዘፈቀደ ሳይሆን በአገባብና በሥርዓት
መሆኑ ይታወቃል፡፡ የአዲስ ኪዳን መሥዋዕት የሆነውን የቅዱስ ቁርባንን አመሠራረት
ለአብነት ብናይ የሥርዓትንና የነገረ ድኅነትን ቀጥተኛ ግንኙነት መረዳት እንችላለን፡፡
መጀመሪያ ኅብስቱን መባረኩና መቁረሱ ይበሉም ዘንድ አስቀድሞ ራሱ በልቶ ለደቀ
መዙሙርቱ መስጠቱ፣ ወይኑንም አክብሮ ጠጥቶ ማጠጣቱ ራሱን የቻለ ታላቅ ሥርዓት
ነው፡፡ በዚህ ረገድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ድረስ የምትፈጽመው የቁርባን (የቅዳሴ)
ሥርዓት ይህን መሠረት ያደረገ እንደሆነ ማስተዋል የክርስቲያኖች ሁሉ ተግባር ነው፡፡

28
ማጠቃለያ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመንፈሳውያን ልጆቿና በጥላዋ ሊጠለሉ ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ
የምትፈጽመው አገልግሎት አላት፡፤ አዳዲስ አማንያንን የቤተ ክርስቲያን አባል፣ የክርስቶስ
አካል የምታደርግባቸው ምሥጢራት አላት፡፡ ነባር ልጆቿን በመንፈስ የምትመግብበት
በሃይማኖትም የምትጠብቅበት ምሥጢራትም ገንዘቦቿ ናቸው፡፡ ሁሉንም በቅዱሳት
መጻሕፍት አስተምህሮ መሠረት የምታከናውንበት እንከን የለሽ ሥርዓት ባለቤትም ነች፡፡
ለዘላለማዊ ሕይወት የተጠሩ ሁሉ ያለእነዚህ ምሥጢራት ሊድኑ እንደማይችሉ ቤተ
ክርስቲያን አስተምራለች፡፡ በምዕራፍ ሁለት ሥር የሰፈረው ርእሰ ጉዳይና ዝርዝር
ማብራሪያዎች ይህንኑ እንዲገልጡ ሆነው የተዘጋጁ ናቸው፡፡

ዋቢመጻሕፍት
• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫
አ/አ።

• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ


ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

29
ምዕራፍ ሦስት፡-

ምሥጢረ ጥምቀትና አፈጻጸሙ /1፡30 ሰዓት/


መግቢያ
አበው በምሳሌ፤ ነቢያትም በትንቢትና በብዙ ኅብረ አምሳል ቀድመው ካዩዋቸውና
ከተናገሩላቸው የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት መካከል የመጀመሪያው ምሥጢረ ጥምቀት
ነው። በዚህ ምዕራፍ ሥር፡-

• የምሥጢረ ጥምቀት አመሠራረት፣

• አስተምህሮ፣

• አፈጻጸምና

• ምሥጢረ ጥምቀት የሚያስገኘው ጸጋ /ክብር/ የሚሉ አራት ዝርዝር አሳቦች


ተብራርተው ቀርበውበታል።

ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምረው


ሲያጠናቅቁ፡-

• የምሥጢረ ጥምቀትን አመሠራረት፣ አስተምህሮና አፈጻጸም ይገነዘባሉ፡፡

• ምሥጢረ ጥምቀት የሚያስገኘውን ጸጋ አምነው ይቀበላሉ፡፡

የምሥጢራት ሁሉ መግቢያ በር የሆነው ምሥጢረ ጥምቀት የራሱ የሆነ አመሠራረት፣


አስተምህሮና የአፈጻጸም ሥርዓት አለው፡፡ ወደዚህ ዝርዝር ማብራሪያ ከመግባታችን በፊት

፫.፩ የምሥጢረ ጥምቀት አመሠራረት


ክርስቶስ አምላካችን የዕዳ ደብዳቤያችንን ያስወገደበትና እንደገና እኛን በልጅነት
ያከበረበት ምሥጢር እንደመሆኑ መጠን መሥራቹም ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው፡፡ እከብር አይል ክቡር፣ እቀደስ አይል ቅዱስ የሆነ አምላካችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በሰላሳ ዓመቱ በማየ ዮርዳኖስ፣ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ምሥጢረ ጥምቀትን በይፋ
መሠረተልን፡፡ እኛም ደፍረን እንጠመቅ ዘንድ አብነት ሆነን፡፡ ሰው ከውኃና ከመንፈስ
ቅዱስ ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንደማይችል
ያረጋገጠልንም ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ
30
ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም፡፡… እውነት እውነት
እልሃለሁ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር
መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነውና ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ
ነውና፡፡” (ዮሐ. ፫፥፫-፮፡፡) እንዲል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባልነትና የመንፈስ ቅዱስ ሱታፌ
የሚገኘውና የእግዚአብሔር ልጅነት የሚረጋገጠው የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ
መቅድማቸው በሆነው ምሥጢረ ጥምቀት በርነት በመግባት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ምሥጢረ
ሜሮንና ቁርባን በዛው ቀን ሌሎቹ ምሥጢራትም እንደአስፈላጊነቱ ጊዜው ሲደርስ
የሚፈጸሙለት ይሆናል ማለት ነው፡፡

፫.፪ አስተምህሮ
• ጥምቀትን የመሠረተው ጌታችን ነው፡፡ ጌታችን የተጠመቀውም በ፴ ዘመኑ ነው፡፡
የእኛ ቤተክርስቲያን ግን ሕፃናትን ታጠምቃለች ፤ ይህ ልክ (ትክክል) ነውን?
እንዴት?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቲያስ በ፴ ዓመቱ በዮርዳኖስ ወንዝ ፥በእደ ዮሐንስ


ተጠምቆ ምሥጢረ ጥምቀትን የመሠረተበት መሠረታዊ ምክንያት አለው፡፡ የዚህም
ምክንያቱ አዳም የ፴ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ ሳለ በድሎ ገነትን ያህል ቦታ፣
እግዚአብሔርን ያህል ጌታ አጣ። በዚህም በደል ምክንያት ከክብሩ ተዋርዶ ነበርና ወደ
ቀደመ ክብርህና አገርህ መለስኩህ ሲል አዳም በተፈጠረበት ዕድሜ ተጠምቆ እንደካሰለት
ለማጠየቅ በ፴ ዓመቱ ተጠመቀ። በዚህም መሠረት ከሱ ጀምሮ ዘሩን (ትውልዱን) በሙሉ
እንዳዳናቸው ለማረጋገጥ ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ ለቤተ ክርስቲያን ሰጠ፡፡ ቤተ
ክርስቲያንም መጽሐፈ ክርስትና ደግማና ሥርዓተ ቅዳሴ አድርሳ አዳዲስ አማንያንንና
ሕፃናትን በጥምቀት በማክበር ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ታሰጣቸዋለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ አድርጋ


ሕፃናትን በሙሉ ማለትም ወንዶችን በተወለዱ በ፵ ቀናቸው ሴቶችን ደግሞ በተወለዱ
በ፹ ቀናቸው ታጠምቃለች፡፡ ይህም ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ
ያልተገኘ አዲስ ሥርዓት አይደለም፡፡ አዳም በተፈጠረ በ፵ኛው ቀን ሔዋንም በተፈጠረች
በ፹ኛው ቀን በይባቤ መላእክት ታጅበው ገነት መግባታቸውን መሠረት ያደረገ ሥርዓት
ነው እንጂ፡፡ (ኩፋ. ፬፥፱-፲፬፡፡) በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላካችን ሴት ልጅ ከሕርስ
ስለምትነጻበት፣ ወደ መቅደስ ስለምትገባበትና የተወለደውን/ችውን/ በእግዚአብሔር ፊት
ማቆም ስለሚችሉበት ጊዜ ሲናገር ለወንድ ልጅ ፵ ቀን ለሴት ልጅም ፹ ቀን መቆየት
እንደሚያስፈልግ ሥርዓት ሠርቷል።(ዘሌ. ፲፪፥፩-ፍጻሜው፡፡)

ቀደም ብሎም የእግዚአብሔር ወገን የመሆን የቃል ኪዳን ምልክት የሆነው ግዝረት
ሕፃናት በተወለዱ በስምንተኛው ቀን ይፈጸም ነበር፡፡ (ዘፍ. ፲፯ ፥፩‐ፍጻሜው፡፡ ቈላ.
፪፥፲፩‐፲፬፡፡)

31
በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትም የሕፃናትን ጥምቀት በተመለከተ በርካታ ማስረጃዎች
አሉ፡፡ ሐዋርያት አባቶቻችን አማኞችን ባጠመቁ ጊዜ እንደ ክርስቶስ ፴ ዓመት
እስኪሞላቸው የሚጠብቁ አልነበረም፡፡ ሁሉንም (ሕፃናትንም ጭምር) በተገኙበት ዕድሜ
በማጥመቅ ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያሰጧቸው ነበር እንጂ፡፡ እዚህ ላይ ሕፃናት
ባመኑ ወላጆቻቸው እምነት አብረው ይጠመቁ እንደነበር ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ (ሐዋ.
፲፥፵፯-ፍጻሜ፤ ፲፩፥፲፬፤ ፲፮፥፲፭፡፴-፴፬፤ ፩ቆሮ. ፩፥፲፮፡፡) ከዚህም በተጨማሪ ጌታችን
ኢየሱስም “ሕፃናትን ተውአቸው፤ ወደ እኔም ይመጡ ዘንደ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ
ሰማያት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና፡፡” (ማቴ. ፲፱፥፲፬-፲፮፡፡) በማለት አዝዞናል።

እሱ ከፈቀደላቸው በኋላ እግዚአብሔር የተቀበላቸውን “ዕድሜያችሁ ገና ነውና ዘወር በሉ!”


በማለት እኛ ልንከለክላቸው አንችላለንን? እግዚአብሔር የተቀበላቸውን እኛ መከልከል
እንደማንችል መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሕፃናት ሳያውቁ ከእናት አባታቸው በሥጋ
እንደተወለዱ ሁሉ እንደዚሁም ሳያውቁ (ሳያምኑ) በወላጆቻቸው እምነት መንፈሳዊ ልደትን
በጥምቀት ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ አለማወቅና ሕፃንነት እግዚአብሔር የሚሰጠውን ድኅነተ
ሥጋ፣ ድኅነተ ነፍስ ሊገድበው አይችልም፡፡ ሌላው ቀርቶ እግዚአብሔር ሕፃናትን
ከእናታቸው ማኅፀንም ሳይቀር እንደሚመርጣቸውና እንደሚቀድሳቸው መጽሐፍ ቅዱስ
ይነግረናል፡፡ (ኤር. ፩፥፭፡፡ ሉቃ. ፲፥፵፬፡፡)

ከዚህም ሁሉ ጋር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትን


ክርስትና ስታነሣ ከወላጆቻቸው በተጨማሪ ለወንዶቹ የክርስትና አባት፣ ለሴቶቹም
የክርስትና እናት ተቀብላ በክርስትና ሃይማኖት ኮትኩተው እንዲያሳድጓቸው አደራ
(ሓላፊነት) ሰጥታና ቃል አስገብታ ነው፡፡ ይህንንም ሓላፊነት ለምእመናን የማሳወቁና
ከተጠያቂነት የማዳኑ ተግባር የካህናተ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ
፫፥፳-፳፮)። በቤተ ክርስቲያናችን ሌላው ቀርቶ ሕጻናት ፵ እና ፹ ቀናቸው ሳይሞላ ለሞት
የሚያሰጋ ሕመም ቢታመሙ በሞግዚት ቤተ ክርስቲያን ወስደው እንዲያጠምቋቸው
ታዟል፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፫፥፴፬)። ቢሞቱም ባገኙት ልጅነት ይድናሉ፤ ቢድኑም
ጥምቀት አንዲት ስለሆነች በዚያው ከብረው ይኖራሉ፡፡ ይህንንም አውቆ የማሳወቁ ተግባር
የመምህራንና የካህናት አባቶች መሆኑ መዘንጋት የለበትም።

ውድ አንባቢ ሆይ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ፡፡

• አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ አምኖ ሳይጠመቅ ቢሞት መንግሥተ


ሰማያት ሊገባ ይችላልን?

አንድ ሰው በክርስትና ሃይማኖት አምኖ ካልተጠመቀ (ዳግመኛ ካልተወለደ)


እንደማይድንና መንግሥተ እግዚአብሔርን እንደማይወርስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
አስተምሮናል፡፡ (ማር. ፲፮፥፲፭-፲፮ ዮሐ. ፫፥፩-፯ ሮሜ. ፮፥፫-፭)። እምነት ከሁሉ ነገር
ቢቀድምም አዲስ የሆነውን ክርስቲያናዊ ሕይወት ለማግኘትና ለመዳን ጥምቀት ደግሞ
32
ከምሥጢራት ሁሉ ቀድሞ ለአዲሱ አማኝ ይፈጸምለታል፡፡ ምሥጢረ ሜሮንና ምሥጢረ
ቁርባንም በዕለቱ (ወዲያወኑ) ተፈጽመውለት ተጠማቂው ሰው የክርስቶስ አካል፥ የቤተ
ክርስቲያን አባል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ አንድ ሰው በክርስቶስ አምኛለሁ፣
አመልከዋለሁም እያለ ጥምቀት አያስፈልገኝም ቢል ሊድን አይችልም፡፡ በክርስቶስ ያመነ
ሰው ትምህርቱን ሁሉ መቀበልና መፈጸም ይጠበቅበታልና፡፡ “ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ
ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡” (ዮሐ.3፡5፡፡)
በማለት ያስተማረን ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ ይህን አምላካዊ መመሪያ
ሳይፈጽሙ በክርስቶስ አምናለሁ ማለት ፈጽሞ አብሮ ሊሔድ አይችልም፡፡ ስለዚህ
በክርስቶስ ያመነ እወደዋለሁም የሚል ሰው ትእዛዛቱን በመፈጸም እንደሚድን መርሳት
አይኖርበትም፡፡

፫.፫ አፈጻጸም
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀትን አምነው ሊጠመቁ ለሚቀርቡ ሁሉ
የምታጠምቅበት የተቀደሰ ሥርዓት አላት፡፡ በዚህም መሠረት አዳዲስ ተጠማቂያን ሀብተ
ወልድና ስመ ክርስትና እንዲያገኙ ታደርጋለች።

ውድ የዚህ መጽሐፍ አንባቢ ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ።

• የክርስትና አባት/እናት ሆነው ካወቁ ወይም ሥርዓተ ጥምቀት ሲፈጸም በሚገባ


ተመልክተው ከሆነ የጥምቀት አፈጻጸም ሥርዓቱ በቅደም ተከተል እንዴት ነበር?

• አይተው የማያውቁ ከሆነ ደግሞ በዓላማ ሄደው በማየት ያዩትንና የሰሙትን


በማስታወሻዎ ላይ ጽፈው ለቤተሰብዎ ያንብቡላቸው /ያስረዱዋቸው/።

ምሥጢረ ጥምቀት የሚፈጸመው በቤተ ክርስቲያንና በካህናት አማካኝነት ብቻ ነው፡፡


አጥማቂው ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ሲሆን ዲያቆናት ደግሞ በተራዳኢነት ይፋጠናሉ፡፡
(ፍትሐ ነገሥት ፫፥፳፩፡፡) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አስቀድሞ ወንጌለ መንግሥትን
እያስተማሩ አሕዛብን ሁሉ እንዲያስተምሩና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
እንዲያጠምቋቸው ሐዋርያትን ማዘዙ ይታወቃል። እንዲህ ሲል “እንግዲህ ሂዱና በአብ
በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አህዛብን ሁሉ አስተምሩ ያዘዛኋችሁንም
እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋር
እኖራለሁ::” (ማቴ፳፰፥፲፱፣፲፱፥፳፡፡) በዚህም የአጥማቂነት ሥልጣን ለቅዱሳን ደቀ
መዛሙርቱና በእነሱም አማካኝነት እስከ ዓለም ፍጻሜ ለሚነሡ ካህናት ሁሉ የተሰጠ
መሆኑን እንረዳለን፡፡ በተጨማሪም ጥምቀት በሥላሴ ስም መሆን እንደሚገባውም በዚሁ
አንቀጽ አስተምሮናል፡፡

ዋና ዋናዎቹ የምሥጢረ ጥምቀት አፈጻጸም ሥርዓትን የሚመለከቱ ነጥቦች ከዚህ በታች


የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

33
፩. ንዑሰ ክርስቲያን የሚጠመቁት የትንሣኤ ዕለት ከሆነ ተገቢውን ትምህርት ቀድመው
ተምረውና ንስሐ ገብተው በሰሙነ ሕማማት ሐሙስ ልብሳቸውን አዘጋጅተውና
ሰውነታቸውን ታጥበው በመጾም ቅዳሜ ሌሊቱን እሑድ ይጠመቃሉ፡፡ በሌላ ቀን ከሆነ
ደግሞ በዋዜማው ታጥበውና ጾመው ይዘጋጁና የመቁረቢያ ልብሳቸውን በንጽሕና
አዘጋጅተው በዕለቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደው ይጠመቃሉ፡፡

፪. ኤጲስ ቆጶሱ (ቄሱ) የሚጠመቁትን ሰብስቦ ራሳቸውን ወደ ምሥራቅ እንዲያዘነብሉ


ያዛቸዋል፡፡ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ ይጸልይላቸዋል፡፡

፫. መሐላውን አስምሎ ማለትም ሰይጣንን እስክዶና ክርስቶስን አሳምኖ ከፈጸመ በኋላ


በዐራቱም መዓዘን ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሰግዶ በፊታቸው ላይ እፍ
ይልባቸዋል፡፡ አካላቸውንም አማትቦ ይባርካል፡፡

፬. ጥምቀቱ በትንሣኤ ከሆነ በዶሮ ጩኸት ጊዜ፤ በሌላ ቀንም ከሆነ መጠመቂያው ሰዓት
ሲደርስ ተጠማቂዎችን በመካነ ጥምቀቱ ያቆማቸዋል፡፡ ያውም ካልሆነ ካህኑ ማዩን
በብርት አድርጎ ሥርዓተ ጸሎቱን ያደርሳል፡፡

፭. ከሰይጣን ቁራኝነት በሚለይበት በቅብዓ ቅዱሱ ላይ ጸልዮ ለተራዳኢው ቄስ ይሰጥና


ከተጠማቂዎች በስተግራ ያቆመዋል፡፡

፮. ልጅነት በሚያሰጠውና መንፈስ ቅዱስን በሚያሳድረው በሜሮኑ ላይ ይጸልይና


ለሁለተኛው ቄስ ሰጥቶ ከተጠማቂዎች በስተቀኝ ያቆመዋል፡፡

፯. ተጠማቂዎችን በማዘዝ ፊታቸውን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ


ይመልሳቸውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ማመናቸውን ያረጋግጣል::

፰. አንዱ ቄስ የተጠማቂዎችን እጅ እየያዘ ሕፃናትም ከሆኑ ዲያቆኑ (ቄሱ) አቅፎ


ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ይመልሳቸዋል፡፡ ይህም ሰይጣንን ክደው በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም ማመናቸውን በምሳሌ የሚያረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡ ምዕራብ
የማኅደረ ዲያብሎስ ምሥራቅም የማኅደረ ሥላሴ ምሳሌዎች ናቸውና፡፡

፱. ከዚህ በኋላ ቅብዐ ቅዱሱን ቀብቶ ያጠምቃቸዋል፡፡ ሲያጠምቃቸውም ልብሳቸውንና


ማንኛውንም ጌጣ ጌጥ አውልቀውና ሴቶችም ሹርባቸውን ፈትተው ነው፡፡ ከዚያም
በመጠመቂያው ፫ ጊዜ ብቅ ጥልቅ ያደርጋቸዋል፡፡ ምቹ መጠመቂያ ከሌለም ማዩን
በላያቸው ላይ ሦስት ጊዜ እያፈሰሰ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አጠምቅሃለሁ/ሻለሁ/፤ እያለ ያጠምቃቸዋል:: ከመጠመቂያው በወጡም ጊዜ በንፍሐት
ልጅነትን ያሳድርባቸዋል፡፡

፲. ሴት በምትጠመቅበት ዕለት የወር አበባ (ግዳጅ) ከመጣባት እስክትነጻ ሳትጠመቅ


ትቆያለች፡፡

34
፲፩. ተጠማቂዎች መናገር ከቻሉ ራሳቸው፤ ካልቻሉም የክርስትና አባት (እናት) የሆኑት
ክርስቲያኖች የተጠማቂውን አውራ ጣት ይዘው ጸሎተ ሃይማኖትን በማንበብ
ሃይማኖታቸውን ይመሰክራሉ፡፡

፲፪. ሥርዓተ ቅዳሴውን አድርሰው፣ መጽሐፈ ክርስትናውን ደግመው ማዩን ከባረኩ በኋላ
ነው ማጥመቅ የሚጀምሩት፡፡ የ፵ እና የ፹ ቀን ሕፃናት ከተጠመቁ በኋላ ንዑሰ
ክርስቲያን ወንዶችና ሴቶች ይጠመቃሉ፡፡

በሚያጠምቁበትም ጊዜ “አጠምቀከ/ኪ በስመ አብ፣ አጠምቀከ/ኪ በስመ ወልድ፣


አጠምቀከ/ኪ በስመ መንፈስ ቅዱስ፤ ስምከ/ኪ ይኩን እገሌ/ሊት” በማለት ሲሆን
አስቀድመው መስቀል ግንባሩ ላይ አድርገው የሰየሙትን ስመ ክርስትና የሚያጸኑት
በዚያው ሰዓት ነው ማለት ነው፡፡

፲፫. ከተጠመቁ በኋላ ካህኑ ሜሮን ይቀባቸዋል፡፡ የተዘጋጀላቸውን ነጭ ልብስ ለብሰው


ቅዳሴ አስቀድሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉ፡፡ በሜሮን ከከበሩም በኋላ ሦስት ኅብረ
ቀለማት ያሉት ማተብ ይታሰርላቸዋል፡፡ ኅብረ ቀለማቱም ነጭ፣ ቀይ፣ ጥቁር(ቢጫ)
ናቸው፡፡

፲፬. የክርስትና አባት/እናት አብረው ጾመውና ተገቢውን ዝግጅት አድርገው በዕለቱ


ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉ፡፡

፲፭. በዕለቱ ክርስትና የተነሡ (የተጠመቁ) ሕፃናትና ንዑሰ ክርስቲያን የነበሩ አዳዲስ የቤተ
ክርስቲያን ልጆች ከሌሎች ቆራብያን አስቀድመው ቅዱሱን ቁርባን ይቀበላሉ፡፡

፲፮. ወንዶች ሴቶችን፣ ሴቶችም ወንዶችን ክርስትና አያነሡም፡፡

፲፯. የምትጠመቀዋ ንዑሰ ክርስቲያን ሴት ከሆነች ቅብዓ ቅዱሱንም ሆነ ሜሮኑን ኤጲስ


ቆጶሱ/ቄሱ/ ልብስ እንደለበሰች ከአንገት በላይ ከቀባት በኋላ ዓይኑን ተሸፍኖ ወይም
በመጋረጃ ተጋርዶ ዲያቆናዊት ማለትም ዕድሜዋ የገፋ ከስልሳ ዓመት በላይ የሆነችና
የምታገለግል መነኩሲት እጁን ይዛ እየመራቸው ሌሎቹን ሕዋሳት ይቀባታል፡፡

፲፰. የተጠማቂዎችን ራስ የሚያጠልቅ ማይ (ውኃ) በቤተ ክርስቲያን የማይገኝ ከሆነ ማዩን


በእጁ እየታፈነ (እየዘገነ) በሥላሴ ስም ያጥምቃቸዋል፡፡

፫ ምሥጢረ ጥምቀት የሚያስገኘው ጸጋ /ክብር/


በጸሎተ ሃይማኖት “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት፤ ኃጢአት
በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡” ተብሎ እንደተገለጸው በጥምቀት የሚገኘው
ጸጋ የኃጢአት ሥርየትን የሚያስገኝና የእግዚአብሔር ልጅነትን የሚያሰጥ ነው፡፡ ኃጢአቱ
35
ከተሠረየለት በኋላም ተጠማቂው መንፈሳዊ ልደትን /ልጅነትን/ በማግኘት ሀገረ ሕይወትን
መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የተዘጋጀ ይሆናል፡፡ (ዮሐ. ፫፥፫-፯፤ ሕዝ. ፴፮፥፴፭-፳፱፤
ሐዋ. ፪፥፳፰። ፩ቆሮ. ፮፥፲፩፡፡)

ከላይ እንደገለጽነው አንድ ሰው “አምስቱን አዕማደ ምሥጢራት አምኛለሁ ለመዳን ይህ


ይበቃኛል ብሎ አልጠመቅም፡፡” ቢል ለመዳን አይችልም፡፡ ለመዳን ማመን ብቻ ሳይሆን
መጠመቅም የግድ አስፈላጊ ነውና፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ያመነ የተጠመቀም
ይድናል፡፡” (ማር. 16፡16፡፡) በማለት ያስተማረን ለዚህ ነው፡፡ በምሥጢረ ጥምቀት
ከእግዚአብሔር ያገኘነው የመዳን ጸጋ (ስጦታ) በመሆኑ በሕጻንነታችን በቤተሰቦቻችን
እምነት፤ ካደግን በኋላም ተምረንና አምነን በመጠመቅ ድህነታችንን ማረጋገጥ
ይኖርብናል፡፡

ማጠቃለያ
በርሰ ጉዳዩ ሥር ስለ ምሥጢረ ጥምቀትና ዝርዝር አፈጻጸሙ እንዲሁም ስለሚያስገኘው
ጸጋ በመጠኑ ተረድተናል፡፡ ምሥጢረ ጥምቀትን በማስመልከት የሚነሡትን አንዳንድ
ወቅታዊ ጥያቄዎች ለመመለስም ተሞክሯል፡፡ ይህም ግንዛቤያችንን በማስፋት
ትክክለኛውን የአፈጻጸም ሥርዓት ተከትለን እንድንጓዝ፣ በልምድ ያጣመምናቸውን
አቃንተንና ያጐደልናቸውንም ሞልተን እንድናገለግልና እንድንገለገል ይረዳናል፡፡ በዚህም
መሠረት ከራሳችን ተርፈን ለሌሎች ወገኖቻችንም የቀናውን ክርስቲያናዊ አስተምህሮ፣
ትውፊት፣ ሥርዓትና ታሪክ ማድረስ (ማስተላለፍ) ይጠበቅብናል።

ዋቢ መጻሕፍት
• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫፤
አ/አ።

• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

36
• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ
ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን
1999፤ አ/አ።

ምዕራፍ ዐራት

ምሥጢረ ሜሮንና አፈጻጸሙ


መግቢያ
ምሥጢረ ሜሮን ከምሥጢረ ጥምቀት ቀጥሎ ወዲያውኑ የሚፈጸም ማኅተመ መንፈስ
ቅዱስ ነው፡፡ በተጨማሪም የአጠቃቀም ሥርዓቱና ጸሎቱ የተለየ ሆኖ ቅብዓ ሜሮን
ለምሥጢረ ክህነትና ለምሥጢረ ተክሊል ማክበሪያነት ያገለግላል፡፡ በዚህ ምዕራፍ ሥር፡-
አመሠራረት፣ አስተምህሮ፣አፈጻጸምና የሚያስገኘው ጸጋ በሚሉ ንዑሳን አርእስት መነሻነት
ማብራሪያዎች መቅረባቸውን ለአንባብያን መጠቆም እንወዳለን።

ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምረው


ሲያጠናቅቁ፡-

• የምሥጢረ ሜሮንን ምንነትና አመሠራረት ይገነዘባሉ፡፡

• የምሥጢረ ሜሮንን አፈጻጸምና የሚያስገኘውን ጸጋ ይረዳሉ፡፡

ውድ የዚህ መጽሐፍ አንባቢ በቅድሚያ የእነዚህን ጥያቄዎች አሳብ ይረዱና ለመመለስ


ይሞክሩ።

❖ የምሥጢረ ሜሮን አመሠራረት እንዴት ነው?


❖ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንፈስ የሚቀበሉት እንዴት ነው?
37
ከዚህ በላይ ላሉት ጥያቄዎች መልስዎን በጽሑፍ አስፍረው ለራስዎ ደጋግመው ያንብቡትና
ከተሰጠው ማብራሪያ ጋር ያገናዝቡ።

፬.፩ አመሠራረት
ሜሮን ማለት ቅብዐ ቅዱስ፣ የተባረከ ሽቱ፣ ብፁዓን ጳጳሳት ከበለሳንና ከዕፀወ ዕጣን
ከአስጳዳቶስ ከሌላም ከብዙ ዓይነት ሽቱ፣ ተገቢውን ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመው የሚያወጡት
ነው፡፡ (መጽ. ሰዋ. ወግስ መመዝ. ቃላት ሐዲስ ገጽ ፮፻፰፡፡)

ምሥጢረ ሜሮን ከጥምቀት ጋር ተያይዞ ከጥምቀት ቀጥሎ የሚፈጸም፣ መንፈስ ቅዱስን


የሚያሳድር፣ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቃችንን፣ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለዳችንን
የሚያረጋግጥልን ታላቅ ምሥጢር ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ
ዮርዳኖስ፣ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ሲወጣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ
ባረፈ ጊዜ የአብ የባሕርይ ልጅነቱ በባሕርይ አባቱ ምስክርነት ተረጋግጧል፡፡ እንደዚሁም
ሁሉ አማኞች ተጠምቀው ሲወጡ በቅዱስ ቅብዐት በሜሮን ከብረው የጸጋ ልጅነት
ማግኘታቸው ይረጋገጣል፡፡ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ መወለዳቸው
ይታወቃል፡፡

ምሥጢረ ሜሮንን የመሠረተልን ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡


መጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስ “እኔ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን
ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ
በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤” (ማቴ. ፫፥፲፩፡፡) በማለት እንደመሰከረለት
በመንፈስ ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቅ እሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
ለሐዋርያትም ተስፋ እንዳደረገላቸው በበዓለ ሃምሳ ከአብ የሠረፀ መንፈስ ቅዱስን
ላከላቸው፤ በመንፈስ ቅዱስ አጠመቃቸው፡፡ (ሐዋ. ፩፥፭፤ ፪፥፩-፲፬፡፡) በደቀ መዛሙርቱ
ላይ እፍ ባለባቸው ጊዜ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀበሉ፡፡ (ዮሐ. ፳፥፳፩-፳፬፡፡)
ከዕርገቱ በፊትም ደቀ መዛሙርቱን እስከ ቢታንያ አውጥቶ እጁን አንሥቶ በላያቸው ጭኖ
ባርኳቸዋል:: (ሉቃ. @4÷%ÝÝ::) በዚሁ መሠረትም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቀበሉትን የመንፈስ
ቅዱስ ጸጋ ለተከታዮቻቸው በአንብሮተ ዕድ ያድሉ ነበር፡፡ አዳዲስ ተጠማቂዎችም
በሐዋርያትና በተከታዮቻቸው አንብሮተ እድ እየተደረገላቸው በልጅነት ይከብሩ ነበር።
(ሐዋ. ፰፥፲፬-፲፯፤ ፲፱፥፭-፮::) ከጊዜ በኋላ ተጠማቂዎች እየበዙ ሲመጡ ለአባቶቻችን
እግዚአብሔር ገልጾላቸው ቅብዐ ሜሮኑን በአንብሮተ እድ እያከበሩ ለአብያተ
ክርስቲያናት በማከፋፈል ምሥጢረ ሜሮን በአንብሮተ እድ ምትክ እንዲፈጸም ማድረግ
ጀመሩ፡፡ ይህንንም የቤተ ክርስቲያን አባቶች በሎዶቅያ ጉባኤ ወስነው አጸኑ፡፡

4.፪ አስተምህሮ

38
የሐዲስ ኪዳን ሥርዓተ ሜሮን መነሻውና ምሳሌው የብሉይ ኪዳን ቅብዐ ዘይት ነው፡፡
የተከበሩ አንባቢ ሆይ፦ ዘጸ ፴፥፳፪-፴፰ ያለውን ጥቅስ (ኃይለ ቃል) አንብቡና ፍሬ
አሳቡን በማስታወሻዎ ላይ አስፍሩ፡፡ የአዲስ ኪዳኑ ቅብዐ ሜሮን መነሻው ከላይ
እንደገለጽነው ይህ የብሉይ ኪዳኑ ቅብዐ ዘይት አጠቃቀምና አገልግሎት ነው፡፡ ፈቅዶና
መመሪያ ሰጥቶ ያስጀመረውም ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ በዚህ ክፍለ ንባብ
እንደተብራራው በተጠቀሰው ኃይለ ቃል ውስጥ የከበረው የቅብዐት ዘይት፡-

• ከምን ከምን እንደሚሠራ፣

• እንዴት እንደሚሠራና

• ለምን አገልግሎት እንደሚውል ወይም እነማን እንደሚከብሩበት በሚገባ ታትቷል፡፡


በዚህ የንባብ ክፍል ቤተ መቅደሱ፣ ካህናቱ፣ የምስክሩ ድንኳንና ለልዩ ልዩ
አገልግሎት የሚውሉ ንዋየ ቅዱሳቱ ቅዱሱን ዘይት ተቀብተው ቅዱሰ ቅዱሳን
እንደሚሆኑና የሚነካቸውና የሚነኩት ሁሉ የተቀደሰ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
የብሉይ ኪዳኑ ሥርዓተ ቅብዐ ዘይት ይህን ያህል የከበረና የቅድስና ክብርንም
የሚያድል ከሆነ የአማናዊቷና ፍጽምት ሕግ የሆነች የወንጌል ሥርዓተ ሜሮንማ
ምን ያህል የከበረና ቅድስናንም የሚያድል ይሆን?!

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በሐዲስ ኪዳን በቅብዐ ሜሮን የሚታደለውን የመንፈስ ቅዱስ
ስጦታ በተመለከተ ሲያብራራ “እናንተስ ከቅዱሱ ያገኛችሁት ቅብዐት አላችሁ፤ ሁሉንም
ታውቃላችሁ፡፡ እውነትን የምታውቁ ስለሆናችሁ፣ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ
ስለምታውቁ እንጂ እውነትን እንደማታውቁ አድርጌ አልጽፍላችኁም፡፡” (፩ዮሐ. ፪፥፳-
፳፪፡፡) በማለት አስተምሮናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ከዚህ አሳብ ጋር ተመሳሳይ
የሆነ መልእክት “ከእናንተ ጋር በክርስቶስ ስም የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፡፡
ደግሞም ያተመንና የመንፈስ ቅዱስን ፊርማ በልቦናችን የሰጠን እርሱ ነው::” በማለት
አስተላልፎልናል፡፡ (፪ ቆሮ. ፩፥፳፩-፳፫፡፡)

የቅብዐ ሜሮን አገልግሎት ለአንድ ዓይነት ተግባር ብቻ አይደለም፡፡ በብሉይ ኪዳን


እንዳየነው ሁሉ በሐዲስ ኪዳንም ቅብዓ ሜሮን ሦስት ዓይነት አገልግሎቶች አሉት፡፡
እነዚህም፡-

፩ኛ. ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል፡- አዳዲስ አማንያን (ተጠማቂዎች) ከተጠመቁ


በኋላ በሜሮን ተቀብተውና ከብረው ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንዲያድርባቸው ያደርጋል፡፡

፪ኛ. የእግዚአብሔር አገልጋዮች (ካህናት)ን ለመሾም፡- ካህናት አባቶች


የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ወይም ሕዝብ ለማገልገል የሚችሉበትን ሥልጣን

39
(ሹመት)፣ ማስተዋል (ጥበብ)፣ ኃይል ብርታት)፣ ትዕግሥትና ጽናት የሚያጎናጽፋቸውን ጸጋ
መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል እንዲችሉ በሚሾሙበት ጊዜ በሜሮን ይቀባሉ (ይከብራሉ)፡፡

፫ኛ. ለአዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ለንዋየ ቅድሳት ማክበሪያ፡- አዲስ ሕንፃ


ቤተ ክርስቲያንና ንዋየ ቅድሳቱ የእግዚአብሔር ገንዘቦች እንዲሆኑ በሜሮን ተቀብተው
እንዲከብሩ ይደረጋል፡፡

❖ ውድ አንባቢ ሆይ፦ ተጠማቂዎች ሜሮን ሲቀቡ አይተው ያውቃሉ? አይተው


ከሆነ እስቲ ያዩትን በቅደም ተከተል በኅሊናዎ ለማሰላሰል ይሞክሩ።
የሚቀቡት የተጠማቂዎች አካላት ምን ምን ናቸው?

፬.፫ አፈጻጸም
ምሥጢረ ሜሮን እንደሌሎቹ ምሥጢራት ሁሉ የራሱ የሆነ የአቀባብ (የአፈጻጸም)ሥርዓት
አለው፡፡

ቅብዐ ሜሮን በዋነኛ ምሥጢራዊ አገልግሎቱ ከምሥጢረ ጥምቀት አፈጻጸም አይለይም፡፡


በዚህም መሠረት የተወሰኑትን የአቀባብ ሥርዓቶች ከምሥጢረ ጥምቀት ጋር አብረን
ገልጸናቸዋል፡፡ ቀሪዎቹን ዝርዝር የአፈጻጸም ሥርዓቶች ደግሞ ከዚህ በታች
እናቀርባቸዋለንና ይከታተሉ::

• በዕለተ ጥምቀት ሜሮን በጳጳሳት ከተባረከ በኋላ ለአገልግሎት የተሰየመው ቄስ በእጁ


ይዞ ይጸልይበታል፡፡ መጽሐፈ ክርስትናንም ይደግማል (ያነባል)::

• የተጠማቂውን ፴፮ ሕዋሳት በታዘዘው መሠረት ክፍል ክፍሉን እየለየ ይቀባል፡፡


ቅብዐ ሜሮኑን በአውራ ጣቱ እየጠቀሰ (እያስነካ) በትእምርተ መስቀል አምሳል
እቀብዐከ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እያለ ተጠማቂውን ይቀባዋል፡፡

• በሥርዓተ ጥምቀት እንደገለጽነው ንዑሰ ክርስቲያን ሴት ከሆነች ልብስ ለብሳ


ከአንገቷ በላይ ኤጲስ ቆጶሱ (ቄሱ) ይቀባታል::በኋላም ከአንገት በታች ያሉትን ቀሪ
ሕዋሳት ጳጳሱ ወይም ቄሱ ተጋርዶ (ተሸፍኖ) ዲያቆናዊት የቄሱን እጅ ይዛ
እየመራች ይቀባታል፡፡

40
• የተጠማቂው ፴፮ቱ ሕዋሳት በሜሮን ሲከብሩ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን የአቀባባቸው
ቅደም ተከተል የታወቀ ነው፡፡ ከላይ እንደገለጽነው ሁሉም በትእምርተ መስቀል
አምሳል የሚታተሙ (የሚቀቡ) ናቸው።

• ግንባሩን ግራና ቀኝ ሁለት ቦታ ይቀባና በፊቱ ላይ እፍ ይልበታል ……….1

• ሁለቱን የአፍንጫ በሮች፣ ……………………………………………………2

• ሁለቱን ከናፍር፣ ……………………………………………………………..2

• ሁለቱን ጆሮዎች፣ …………………………………………………………….2

• ሁለቱን ዓይኖች፣ ……………………………………………………………..2

• ደረቱን ፣……………………………………………………………………....1

• ልቡን፣ ………………………………………………………………………..1

• ከመሐል አናት እስከ ወገብ ያለውን አካል፣ ………………………………….1

• መሐል ጀርባውን፣ ……………………………………………………………1

• እንብርቱን፣ ……………………………………………………………………1

• ሁለቱን እጆች፣ ……………………………………………………………….2

• የእጆቹን መገናኛዎች፣ ………………………………………………………..2

• ትከሻዎቹን፣……………………………………………………………………2

• ማጅራቱን፣………………………………………………………………………1

• አንገቱን፣ ………………………………………………………………………1

• ክርኖቹን፣ ………………………………………………………………………2

• የእጆቹን ውጪያዊ ክፍሎች (መዳፎች)፣ ………………………………………2

• የእጆቹን ውስጣዊ ክፍሎች (መዳፎች)፣ ………………………………………..2

41
• የእግር መገናኛዎቹን (መዳፎች)፣ ………………………………………………2

• ጉልበቶቹን፣ ……………………………………………………………………..2

• የእግሮቹን ውጪያዊ ክፍሎች (ጣቶች)፣ ……………………………………….2

• የእግሮቹን ውስጣዊ ክፍሎች (ጣቶች)፣ …………………………………………2

በድምሩ 36 ሕዋሳት ይሆናሉ፡፡

እነዚህን ሕዋሳት በቅደም ተከተል ከቀባ በኋላ በተጠማቂው ላይ እጁን ጭኖ “በሰማያውያን


በረከት የተባረክህ ሁን” እያለ ይባርከዋል፡፡ ሠላሳ ስድስቱ የተጠማቂው ሕዋሳት በዚህ
መልክ በቅብዐ ማሮን ታትመው የእግዚአብሔር ገንዘቦች (ማደሪያዎች) ይሆናሉ፡፡

የተከበሩ የዚህ መጽሐፍ ተጠቃሚ

❖ ከተጠማቂዎች ሌላ በሜሮን የሚከብሩ ምን ምን ናቸው? የሚከብሩበት


ጊዜስ መቼ ነው? እስቲ ይህን ጥያቄ በተማሩት መሠረት ለመመለስ
ይሞክሩ::
❖ ከአገልግሎት በፊት በሜሮን የሚከብሩ ንዋየ ቅድሳት ምን ምን እንደሆኑ
ያውቃሉ? የቻሉትን ያህል በማስታወሻዎ ላይ ይዘርዝሩአቸው፡፡ ከዚያም
ከተሰጠው ማብራሪያ ጋር ያነጻጽሩት።

ከተጠማቂዎች ሌላ ቅብዐ ሜሮን ለሁለት ምሥጢራት ማክበሪያነት (ማተሚያነት)


ያገለግላል፡፡ እነዚህም ምሥጢረ ክህነትና ምሥጢረ ተክሊል ናቸው፡፡ በምሥጢረ
ክህነት ካህናት ከቄሱ ጀምሮ ወደ ላይ ያሉት ማለትም ጳጳስና ቄስ በቅብዐ ሜሮን
ከብረው ካህናተ እግዚአብሔር ይሆናሉ፡፡ ይህም በብሉይ ኪዳን “እኔንም በክህነት
እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ የቅብዐትንም
ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈሰዋለህ፤ ትቀባውማለህ፡፡ ልጆቹንም ታቆርባቸዋለህ፤
ቀሚሶችንም ታለብሳቸዋለህ፤ በመታጠቂያም ታስታጥቃቸዋለህ፤ ቆብንም
ታደርግላቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል፡፡ እንዲሁም የአሮንና
የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ፡፡ (ዘፀ. @9÷1--- 8፡፡ÝÝ) የተባለውን መሠረት ያደረገ
ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ካህናትን በቅብዐ ሜሮን አክብሮ ሥልጣነ ሐዋርያትን
ማስተላለፍ ጥንታዊ የተለመደና የከበረ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ነው፡፡
42
በምሥጢረ ተክሊልም ሙሽራውና ሙሽሪት በቅብዓ ሜሮን ታትመው
ይከብራሉ፡፡ በመጽሐፈ ተክሊል ከሌሎቹ የሥርዓተ ተክሊል አፈጻጸሞች ጋር
የአቀባብ ሥርዓቱና በቅብዐ ሜሮኑ ላይ የሚጸለየው ጸሎት ሠፍሮ ይገኛል:: ከዚህም
በተጨማሪም አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከጽላቱ ጀምሮ መስቀሉ፣
ጽንሐው፣ ከበሮው፣ ሰኑ፣ ብርቱና የመሳሰለው ሁሉ በሜሮን ከከበረ በኋላ
ለአገልግሎት ይውላል::

፬.፬ የሚያስገኘው ጸጋ
❖ በምሥጢረ ሜሮን የሚገኘው ጸጋ ምንድነው?

በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው ምእመናን በጊዜ ጥምቀት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ


የሚያገኙት በምሥጢረ ሜሮን ነው፡፡ አካሉ አንድ ሲሆን ስጦታው ልዩ ልዩ (ብዙ) የሆነ
መንፈስ ቅዱስ (፩ቆሮ. ፲፪፥፬፡፡) ምእመናንን ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚያዘጋጃቸው በዚሁ
ዕለት በሜሮን አማካኝነት በሚቀበሉት (በሚያድርባቸው) የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ነው፡፡
(፩ቆሮ. ፲፪፥፳፯-ፍጻ፡፡) በጥምቀት የሚሰጠውን ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና የሚያጸናው
ማኅተም ሜሮን ነው፡፡ በጥምቀት የሚጀመረው መንፈሳዊ ልደት (ልጅነት) በምሥጢረ
ሜሮን ይታተማል፡፡ (ሐዋ. ሥራ ፰፥፲፬-፲፰)። አዲሱ ተጠማቂ የቤተ ክርስቲያን ልጅ፣
የእግዚአብሔር ማደሪያ ስለሚሆንም ለተፈጠረበት ዓላማ የሚሠራ ሆኖ ይዘጋጃል፡፡
የክርስቶስ አካልነቱ የቤተ ክርስቲያንም አባልነቱ የተረጋገጠ ክርስቲያን ይሆናል፡፡
የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ በምሥጢረ ሜሮን የተቀበሉ ምእመናን ከእግዚአብሔር በመንፈስ
ይወለዳሉ፣ በክርስቶስ ጸጋ ያድጋሉ፤ ይህም ጸጋ የሃይማኖትን ፍሬ ያፈሩ ዘንድ
ያበቃቸዋል፡፡ (ገላ. ፩፥፳፪-፳፭፡፡ ኢሳ. ፳፩፥፪፡፡)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሥጋችሁም ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤


እግዚአብሔርም ለሥጋችሁ ነው፡፡ … ሥጋችሁ የክርስቶስ አካል እንደሆነ አታውቁምን?
እንግዲህ የክርስቶስን አካል ወስዳችሁ የአመንዝራ አካል ታደርጉታላችሁን? አይገባም፡፡
ከአመንዝራ ጋር የተገናኘ ከእርስዋ ጋር አንድ አካል እንዲሆን አታውቁምን? መጽሐፍ፣
“ሁለቱ አንድ አካል ይሆናሉ” ብሎአልና፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የተዋሐደ ግን ከእርሱ ጋር
አንድ መንፈስ ይሆናል፡፡ … ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር ለተቀበላችሁት በእናንተ አድሮ ላለ
ለመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን? ለራሳችሁ አይደላችሁም፡፡ በዋጋ
ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን በሥጋችሁ አክብሩት፡፡” (፩ቆሮ. ፮፥፲፫-ፍጻ፡፡)
በማለት ያስተማረን ይህን የሚያጎላና ሌሎች ምሥጢራትንም አካቶ የያዘ ነው፡፡

የተከበሩ አንባቢ ሆይ:- ከላይ ያሰፈርነውን የሐዋርያውን የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት


ሁላችንም ማስተዋል ይገባናል፡፡

❖ በ፵ እና በ፹ ቀናችን ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ (ዮሐ. ፫፥፭፡፡) ተወልደን ማኅደረ


እግዚአብሔር ከሆንን በኋላ ከማ ጋር እየኖርን ነው? የክርስቶስ አካል የከበረ
ሥጋችንን ምን እየሠራንበት ነው? የክርስቶስ አካል ሰውነታችንን ለማ አሳልፈን

43
ሰጠነው? ማንን አሠለጠንንበት? ክርስቶስን ወይስ ቤልሆርን? ለሚሉት ጥያቄዎች
ለራሳችን ምላሽ መስጠትና ራስን መመርመር ይገባል፡፡

ከማኅፀነ ዮርዳኖስ፥ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልደን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ


መሆን የጀመርነው ከተጠመቅንበትና በሜሮን ከከበርንበት ዕለትና ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡
በመቅደስ ሰውነታችን አድሮ የነበረውን አምላክ አሳዝነን አስወጣነው ወይስ አስደስተን
እስካሁን ከኛ ጋር አቆየነው? የሚለው ጥያቄም መመለስ ያለበት መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡

የእግዚአብሔርን የክብር ዕቃ፣ ማደሪያ መቅደሱንም በጥንቃቄ የማይዙና የሚያቃልሉ ሁሉ


የሚቀጡ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የመቅደሱ ባለቤት እግዚአብሔር ለቤቱና
ለሥርዓቱ ቀናዒ ነው፡፡ መቅደሱ የኃጢአት ሸቀጥ ማራገፊያና መነገጃ ሲሆን ዝም ብሎ
አያይም፡፡ (ማቴ. ፳፩፥፲፪-፲፰፡፡) ንጉሡ ብልጣሶር ያደረገውንና የሆነበትንም ክፉ ነገር
አልሰሙምን? አባቱ ናቡከዳናፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ማርኮ በቤተ መንግሥቱ ዕቃ
ቤት በክብር ያኖራቸውን ንዋያተ ቅድሳት አስመጥቶ በማቃለል ጣዖታትን እያመለኩ
እንዲበሉባቸውና እንዲጠጡባቸው አደረገ፡፡ እንዲህ አድርጎ በንዋየ ቅድሳቱ በተሳለቀባቸው
ዕለትም ተገድሎ አደረ፡፡ (ዳን. ፭፥፩-ፍጻ፡፡) እግዚአብሔርንና የሱ የሆኑትን ሁሉ
የማያከብሩ ሰዎች ለማይገባ አዕምሮ ተላልፈው እንደሚሰጡ ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ (ሮሜ.
፩፥፳፩-ፍጻ፡፡) እግዚአብሔር ያከበራቸውን ማቃለል እግዚአብሔርን ማቃለል ነውና። (ሉቃ
፲፥፲፮፡፡) የሱ ማደሪያ ይሆን ዘንድ የከበረ የተለየ ሰውነትንም በማቃለል የኃጢአት
መሣሪያና ማደሪያ የሚያደርጉም ሰዎች መቀጣታቸው እንደማይቀር ይህ የላይኛው ታሪክ
ያስተምረናል::

ማጠቃለያ

ቤተ ክርስቲያናችን ከምትፈጽማቸው ምሥጢራት መካከል ሁለተኛው ምሥጢረ ሜሮን


ነው፡፡ ምንጊዜም ከምሥጢረ ጥምቀት ቀጥሎ ወዲያውኑ ይፈጸማል:: ሜሮን የሚፈላው
/የሚዘጋጀው/ በጳጳሳት ጸሎትና ቡራኬ ብቻ ሲሆን በሚመለከተው ጳጳስ አማካኝነት በየሀገረ
ስብከቱ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በነጻ ይታደላል:: ከዚህ ውጪ ከአታላዮች በስመ
ሜሮን ወይም ቅብዐ ቅዱስ እየገዙ ለምሥጢረ ሜሮን መፈጸሚያነት መጠቀም ሕገ ወጥ
ተግባር ነው፡፡ ማንኛውም ደብር ከማለቁ በፊት ከሊቀ ጳጳሱ ጠይቆ በመውሰድ
መጠቀምና የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ጠብቆ ማስጠበቅ በተለይ ከካህናት አባቶች ሁሉ
የሚጠበቅ ነው፡፡ ምእመናም ቢሆኑ የአታላዮችን ድርጊት በመቃወምና ለካህናት ትክክለኛ
አገልግሎት አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት የበኩላቸውን ሁሉ መወጣት ይኖርባቸዋል::

• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫


አ/አ።

• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።
44
• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ
ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ


ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፹፰፤ አዲስ አበባ።

• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን
1999፤ አ/አ።

45
ምዕራፍ አምስት
ምሥጢረ ቁርባንና አፈጻጸሙ (፪ ሰዓት)
መግቢያ
ምሥጢረ ቁርባን የምሥጢራተ ቤተክርስቲያንና የአገልግሎቶች ሁሉ የማረጋገጫ ማኅተም
ነው፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም ምሥጢር በቤተክርስቲያን ከተፈጸመ በኋላ በምሥጢረ
ቁርባን ካልተፈጸመ (ካልታተመ) የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ሊባል አይችልም፡፡
በተጨማሪም በቤተክርስቲያን የሚከናወኑ አገልግሎቶች ሁሉ ማለትም ማኅሌቱ፣ ሰዓታቱ፣
መዝሙሩ፣ ቅኔው፣ ኪዳኑና የመሳሰሉት ሁሉ ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት በቅዳሴ ነው፡፡
ቅዳሴውም የምሥጢረ ቁርባን መክበሪያ የጸሎታት ሁሉ ቁንጮ የሆነ፤ የምስጋናና የጸሎት
ሥርዓት ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ሥር የምሥጢረ ቁርባን አመሠራረት፣ አስተምህሮ፣
አፈጻጸም፣ ቅዳሴውም ከዝርዝር ክፍሎቹና አፈጻጸሞቹ ጋር እንዲሁም በመጨረሻ
የሚያስገኘው ጸጋ የሚሉት የተብራሩበት ነው::

ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምረው


ሲያጠናቅቁ፡-

• የምሥጢረ ቁርባንን አመሠራረትና ምንነት ይገነዘባሉ።

• የምሥጢረ ቁርባንን አፈጻጸምና የቅዳሴን ምንነት ይረዳሉ::

• ቅዱስ ቁርባን ያለውን ጥቅምና የሚያስገኘውን ጸጋ ይገነዘባሉ፡፡

• ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል መደረግ ያለባቸውን ነገሮች ይረዳሉ፡፡

ቁርባን የሚለው ቃል መሠረቱ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የመጣ ሲሆን “ስጦታ” የሚል ትርጉም
ይኖረዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት የተወደደ ስጦታ

46
መሥዋዕትና ቁርባን ይባል ነበር፡፡ ከእንስሳት (ሥጋና ደም) የሚቀርበው መሥዋዕት፤
ከእህል ወገን የሆነው ደግሞ ቁርባን ይባል ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ግን አማናዊው ቁርባን
(መሥዋዕት) ሰዎች የሚያቀርቡት (የሚሰጡት) መባዕ ሳይሆን መድኃኔዓለም ክርስቶስ
ዓለሙን ለማዳን በቀራንዮ አደባባይ በአባቱ ፈቃድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ፣ በራሱም
ፈቃድ በመስቀል ላይ ለዓለሙ ሁሉ ያቀረበው (የሰጠው) ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ
ነው፡፡ ይህም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካህናት በቅዳሴ ጊዜ የሚያቀርቡት ኅብስት
የክርስቶስ ሥጋ፥ወይኑም የክርስቶስ ደም በመሆን የሚፈተት የሚቀዳ አማናዊ የአዲስ
ኪዳን ቁርባን ነው፡፡

፭.፩ አመሠራረት
ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተልን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን
የመሠረተበት ዕለትም በስቅለቱ ዋዜማ ጸሎት ሐሙስ በሚባለው ዕለት ነበር፡፡ የኦሪትን
መሥዋዕትና ቁርባን አሳልፎ (ሽሮ) የወንጌልን መሥዋዕት (ቁርባን) የመሠረተልን
በአልዓዛር ቤት ነበር፡፡ (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፰፡፡)ከንጹሕ ስንዴ የተዘጋጀውን ኅብስትና
ከንጹሕ ወይን የተጨመቀውን ጽዋዕ እውነተኛ ሥጋውና ደሙ አድርጎ በመስጠት ነው
የመሠረተልን፡፡ (ዮሐ. ፮፥፴፭፡፡) በዕለተ ዓርብ የቆረሰውን ሥጋ፣ ያፈሰሰውንም ደም
አስቀድሞ በዋዜማው ኅብስቱንና ወይኑን ለውጦ ኅብስቱን ፲፫ ቦታ ፈትቶ (ቆራርሶ)፣
አብነት ለመሆንና ለማስደፈር ራሱ በራሱ እጅ ተቀብሎ ለቀደ መዛሙርቱ አቀበላቸው፡፡
በመስቀል ላይ ለአንዴና ለዘለዓለሙ የፈጸመው ይህ አምላካዊ የማዳን ሥራ እስከምጽአት
ድረስ ለዓለሙ ሁሉ በሥርዓተ ቅዳሴ ከብሮ እንዲታደልም (እንዲዳረስም) ሐዋርያት
አባቶቻችንን አዘዛቸው፡፡ በምሥጢረ ክህነት እንዳየነው የምሥራቹን ቃል እንዲያስተምሩ፣
በስሙ ሥርየተ ኃጢአትን እንዲሰጡና ሌሎች ምሥጢራትንም እንዲፈጽሙ የሚያስችል
ሥልጣነ ክህነትን ሰጣቸው፡፡ (ማቴ. ፳፰፥፲፱-፳፡፡ ሉቃ. ፳፪፥፲፬-፳፤ ፳፬፥፵፬-፶፡፡ ፩ቆሮ.
፲፩፥፳፫-፳፯፡፡) በዚሁ መሠረትም ሐዋርያት ቃሉን አስተምረው ካሳመኑ በኋላ
እያጠመቁና በአንብሮተ እድ መንፈስ ቅዱስን እያሳደሩ ምሥጢረ ቁርባንን እየፈጸሙ
በማቁረብ ተተኪዎቻቸውንም በዚሁ ሥርዓት በማጽናት ቤተ ክርስቲያንን እንዲህ
በማስፋፋት ኖሩ፡፡ የዚህ ሥልጣን አገልግሎትና ሓላፊነት ባለቤትም ቅድስት
ቤተክርስቲያን ብቻ ናት፡፡ ይህንንም አውቃ ስትፈጽመው ኖራለች፤ እየፈጸመችም
ትገኛለች፤ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስም ስትፈጽመው ትኖራለች::

፭.፪ አስተምህሮ
የተከበሩ አንባቢ ሆይ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እየሞከሩ ራስዎን ይገምግሙ::

47
❖ እኛ በዚች ዓለም ላይ ስንኖር እሱን የምንፈልግበት ዕቅድና ዓላማ ከሱ አምላካዊ
ዕቅድና ዓላማ ጋር የተነናኘ ነው ብለው ያስባሉ? እንዴት?

❖ የምንወጣውና የምንወርደው፣ ማለትም ሙሉ ጊዜ ሰጥተን የምንደክመው ለየትኛው


መብል ነው? ለሥጋዊው ወይስ ለመንፈሳዊው?

እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች በአይሁድ ሕይወት አንጻር ራሳችንን የምናይባቸውና


ለማስተካከልም የምንነሣባቸው መሠረታዊ ነጥቦች ናቸው፡፡ ጥያቄዎቹን በግልዎ ይሥሩና
በታማኝነት ራስዎ አርመው ውጤቱን በእግዚአበሔር ፊት ያስቀመጡ፡፡ ፈተናውን
የምያልፉ ይመስልዎታል? በቀጣይስ ምን ዓይነት ሕይወት ሊኖረኝ ይገባል ይላሉ?

የምሥጢረ ቁርባን አስተምህሮ በስፋት ከቀረበባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል


የዮሐንስ ወንጌል ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በዚሁ ወንጌል ምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፳፮ ጀምሮ ምሥጢረ ቁርባንን በተመለከተ ለጊዜው
ለቤተ አይሁድ ለፍጻሜውም ለዓለሙ ሁሉ የሚሆን ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥቷል፡፡ በወቅቱ
አይሁድ ባሕር እስከማቆራረጥ (እስከመሻገር) ደርሰው ጌታችንን የፈለጉበት ዓላማ ሥጋዊ
ነበር፡፡ ይህን ጠንቅቆ ያወቀው የባሕርይ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት
እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለበላችሁና ስለጠገባችሁ ነው እንጂ
ተአምራት ስላያችሁ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላዓለም ሕይወት ለሚኖር
መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ
አትሞታልና፡፡” (ዮሐ. ፮፥፳፮-፳፰) በማለት የፍለጋቸው ዓላማ እሱ ሰው ሆኖ የጠፋውን
የሰው ልጅ ለመፈለግ ከመጣበት ዓላማ ጋር እንደማይገናኝ ነግሯቸዋል፡፡

ቤተ አይሁድም “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ሥራ እንሠራ ዘንድ ምን እናድርግ?” (ዮሐ.


፮፥፳፰)። ሲሉ ላቀረቡት ጥያቄ “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ
ነው” (ቁ. ፳፱)። በማለት ነው ጌታችን የመለሰላቸው፡፡ ይህ የሰጠው መልስ የክርስቲያናዊ
ሕይወት ማዕከል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ በክርስቶስ ማመን ነው ማለት በትምህርቱ፣
በተአምራቱ፣ በድርጊቱ ማለትም በጥምቀቱ፣ በሕማሙ፣ በመስቀሉ፣ በቆረሰው ሥጋና
ባፈሰሰው ደሙ፣ በሞቱ፣ በትንሣኤው፣ በዕርገቱና በዳግም ምጽአቱ … ማመን ማለት ነው፡፡
እንደገለጽነውም ከነዚህ መካከል አንዱ የምሥጢራት ሁሉ መክበባቸውና ማረጋገጫቸው
የምሥጢረ ቁርባንን አማናዊነት ማመንና ተሳታፊ መሆን ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላው ዝርዝር ማብራሪያ የሰጠበት አንቀጽ ደግሞ አይሁድ
ላቀረቡት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ መነሻነት የቀረበ ተጨማሪ ትምህርት ነው፡፡ በክርስቶስ
ለማመን እንዲችሉ ሙሴ ያደረገውን ዓይነት መና አውርዶ እንዲያሳያቸው ማለትም

48
ተአምር /ምልክት/ ማየት እንደሚሹ ጠየቁት፡፡ አምስቱን የገብስ እንጀራና ሁለቱን
ዓሣዎች አበርክቶ ካበላቸው በኋላ ይህን ድንቅ ተአምር ወደጎን ጥለው ሌላ ምልክት
እንዲያሳያቸው ጠየቁት፡፡ ጌታችንም ላባቶቻቸው በምድረ በዳ መና ያወረደላቸው ሙሴ
ሳይሆን እግዚአብሔር መሆኑን አስረግጦ ነገራቸው። በማስከተልም “የእግዚአብሔር እንጀራ
ከሰማይ የሚወርድ፤ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነው፡፡” (ዮሐ. ፮፥፴፫)።በማለት ከሰማይ
የወረደ እንጀራ ከፈለጉ አማናዊው የሕይወት እንጀራ እሱ ራሱ መሆኑን አረጋገጠላቸው፡፡
እነሱም ያንን እንደጀራ እንዲሰጣቸው ለመኑት፡፡ ቤተ አይሁድ አሁንም ሥጋዊ ከሆነው
አመለካከታቸውና መንገዳቸው ባለመመለሳቸው ሳይሠሩ ዘወትር እያፈሱና እየለቀሙ
የሚበሉትን የአባቶቻቸውን ዓይነት መና ነው እየለመኑ ያሉት፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ
ግን ስለሕይወት እንጀራ ማለትም ስለ ሥጋውና ደሙ መንገሩን በመቀጠል ዓይናቸውን
ወደ እውነተኛው የሕይወት እንጀራ (ምግብ) እንዲያዞሩ አሳሰባቸው፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “ዐሳቤ እንደ ዐሳባችሁ፣ መንገዴም እንደመንገዳችሁ


አይደለምና፣ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ፣ እንዲሁ መንገዴ
ከመንገዳችሁ፣ ዐሳቤም ከዐሳባችሁ የራቀ ነው፡፡” (ኢሳ. ፶፭፤፰-፲፡፡) በማለት እንደተናገረው
የአይሁድ ዐሳብና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐሳብ ፈጽሞ የተራራቀ ነበር፡፡ እርሱ
ሰማያዊውን፣ ዘላለማዊውንና መንፈሳዊውን የሕይወት እንጀራ እንዲቀበሉ
ያስተምራቸዋል፡፡ እነሱ ደግሞ ምድራዊውን፣ ጊዜያዊውንና ሥጋዊውን እንጀራ
ይለምናሉ፡፡ ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ የሰፈረ የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር ያደረገው እጅግ
አስገራሚው ቃለ ምልልስ ነው። የእኛስ ዐሳባችንና መንገዳችን ከእግዚአብሔር ዐሳብና
መንገድ ጋር የተገናኘ ይሆንን? ክርስቲያኖች ሁሉ መሠረታዊውን ሥራ መሥራት
ያለባቸው እዚህ ጋ ነው።

“ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” የሚለውን እውነት አይሁድ መቀበል


ስላልፈለጉ (ስላልቻሉ) አንጐራጐሩ፡፡ የአንደበቱን ትምህርት የእጁንም ተአምራት
ሰምተውና አይተው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን ማለትም
ሰው የሆነ አምላክ መሆኑን ማመን አቃታቸው። ቅድመ ዓለም ከአብ ያለእናት፣ ድኅረ
ዓለም ማለትም አምስት ሺ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም ከእመቤታችን ከቅድስት
ድንግል ማርያም ያለ አባት መወለዱን በመካዳቸው “እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል?”
አሉ፡፡ ጌታችንም የአብ የባሕርይ ልጁ መሆኑን ገልጾ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ
እሱ መሆኑን ዳግም አስረግጦ ነገራቸው:: አባቶቻቸው በምድረ በዳ ከበሉት መና ጋር
ሲነጻጸር ያለውን ልዩነትም አስረዳቸው፡፡ (ዮሐ. ፮፥፵፩-፶፪፡፡) “ከሰማይ የወረደ የሕይወት
እንጀራ እኔ ነኝ” ያላቸውን እየተረጎመ ማስረዳቱንም ቀጠለ፡፡ “እንጀራ” እያለ ሲገልጸው
የቆየው የሕይወት እንጀራ የሆነውን ቅዱስ ሥጋውን እንደሆነም ገለጸ፡፡ በዚህ ጊዜ የበለጠ
መደናገርና ማጉረምረም በአይሁድ መካከል ተፈጠረ፡፡

የተከበሩ የዚህ ትምህርት ተከታታይ፦

❖ ለአንድ ሰው መዳን (መንፈሳዊ ድኅነት ማግኘት) ቁርባን የግድ ነውን? ለምን?

49
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ፣ ደሙን አፍስሶ ከመስጠቱ፣ በስቅለቱም ዋዜማ
ምሥጢረ ቁርባንን ከመመሥረቱ አስቀድሞ በጎላ በተረዳ መንገድ ስለ ቅዱስ ቁርባን
አስተማረ፡፡ አይሁድም “ይህ እንበላ ዘንድ ሥጋውን ሊሰጠን እንዴት ይችላል?” ብለው
እርስ በርሳቸው ተከራከሩ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤
የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፣ ደሙንም ካልጠጣችሁ የዘላለም ሕይወት የላችሁም፡፡
ሥጋዬን የሚበላ÷ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በኋለኛይቱ ቀን
አነሣዋለሁ፡፡” (ዮሐ. ፮፥፶፫-፶፭፡፡) በማለት የተብራራ÷ የተረዳ÷ ሕይወትም የሆነ ቃሉን
ነገራቸው፡፡ ይህንና ይህን የመሰለውን እውነተኛ ትምህርት በጨመረና ባስተማረ ቁጥር
አይሁድ የበለጠ እየታወኩና እየተደናገሩ በክህደትም ልቡናቸውን እያጸኑ ሔዱ፡፡ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገልጸውን እውነትና ሕይወት የሆነውን ትምህርት መሸከም የተሳናቸው
አይሁድ ወደኋላቸው ተመልሰው ሸሹ፡፡ ይከተሉት ከነበሩት ብዙዎቹ “ይህ የሚያስጨንቅ
ንግግር ነው፣ ማንስ ሊሰማው ይችላል?” (ዮሐ. ፮፥፷ ፤፤) እያሉ አንጐራጐሩና ወደ ኋላቸው
ተመለሱ፡፡ ጌታችንም ከአምስት ገበያ ሕዝብ መካከል ከእርሱ ጋር ጸንተው የቆዩትን
ዐሥራ ሁለቱን ደቀመዛሙርት “እናንተ ደግሞ ልትሔዱ ትሻላችሁን?” (ቁ. ፷፯) በማለት
ጠየቃቸው:: ለዚህም ጥያቄ ስምዖን ጴጥሮስ “አንተ የዘላለም የሕይወት ቃል እያለህ ወደ
ማን እንሄዳለን? እኛስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ እንደሆንህ አምነናል፤
አውቀናልም፡፡” (ቁ. ፷፰-፷፱፡፡) በማለት ለእውነተኛ ክርስቲያኖች ሁሉ የሕይወት
መመሪያ የሚሆን መልስ ሰጠ፡፡

ከዚህ ምዕራፍ በግልጽ ለመረዳት እንደቻልነው አንድ ሰው አምኛለሁ ቢልም፣ የፈለገውን


ያህል ምግባር ቢሠራና ቢያገለግል በሥጋውና ደሙ እስካልታተመ ድረስ የሕይወት
ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ለሰው ልጆች ድኅነት ምሥጢረ ቁርባን የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
አስቀድመንም ከምሥጢረ ጥምቀትና ሜሮን ጋር ምሥጢረ ቁርባንም ለድኅነት የግድ
አስፈላጊ መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

የተከበሩ አንባቢ ሆይ:- ለጥቂት ደቂቃዎች በሚከተሉት ጥያቄዎች ራስዎን ይመርምሩና


በክርስትና ሕይወትዎ ያሉበትን ቦታ ይፈልጉ፡፡

❖ ከሥጋ ወደሙ ከተለያዩ (ከተራራቁ) ስንት ዓመት ሆነዎት?

❖ እንደ ሐዋርያት ከክርስቶስ ጋር አብረው ከቆሙ(ሲቀበሉ ከኖሩ) በኋላ ዳግመኛ


እንደ አይሁድ የኋሊት ገፍቶ የወሰደዎት ነገር ይኖርን ? (ካልሆነ ለምን አፈገፈጉ?)

❖ የዘላለም ሕይወት ከሚያገኙበት ከዚህ ቅዱስ ምሥጢር ርቀው የሚኖሩት እስከመቼ


ድረስ ነው?

እነዚህ ጥያቄዎች በአንደበት ብቻ ሳይሆን በተግባርም ፈጣን ምላሽ የሚሹ ናቸው፡፡ ከሥጋ
ወደሙ መራቅ ከመስቀሉ መራቅ ነው፡፡ ከመስቀሉ መራቅ ደግሞ ከክርስቶስ መራቅ ነው፡፡
በጥቅሉ ከእግዚአብሔር መለየት ከዘለዓለማዊ ሕይወትም ወጥቶ ወደ ዘለዓለማዊ ሞት
50
መነዳት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነውና።
ከሥጋ ወደሙ ለመራቃችን ምንም ዓይነት ምክንያት ብንደረድር በክርስቶስ ፊት አሳማኝ
ሊሆን እንደማይችል መርሳት የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅርና የከፈለውን
ውለታ ሊያስረሳና ሊሸፍን የሚችል የቱንም ያህል ምክንያትና ችግር ሊኖር አይችልም፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ነውን? ኀዘን ነውን? ስደት
ነውን? ራብ ነውን? መራቆት ነውን? ጭንቀት ነውን? ሾተል ነውን?” (ሮሜ ፰፥፴፭፡፡)”
በማለት ያስተማረን ከላይ የገለጽነውን ቁም ነገር የሚያጠናክርልን ነው፡፡

❖ ቁርባን በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ልዩነቱና አንድነቱ ምንድነው?

ይህን ጥያቄ እስቲ ለመመለስ ይሞክሩ::

በብሉይ ኪዳን ታሪክ መሥዋዕትና ቁርባን ለእግዚአብሔር ማቅረብ የተጀመረው


ከአባታችን ከአዳም ጀምሮ ነው፡፡ በዘመነ አበው የነበሩ አባቶች እስከሙሴ ድረስ በሕገ
ልቡና መርምረው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አቅርበው ተመስግነውበታል፡፡
ያማረ የተወደደ መሥዋዕት ማቅረብ ያልቻሉ ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት
ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ (ዘፍ. ፬፥፫-፮፡፡) ከሙሴ ጀምሮ ባለው ዘመን ደግሞ እግዚአብሔር
በሙሴ አማካኝነት እስራኤልን ባዘዘው መሠረት ከሥጋ (ከእንስሳ) ወገን የሆነውን
መሥዋዕት፣ ከአዝርዕትና ከአትክልት ወገን የሆነውን ደግሞ ቁርባን እያሉ በመጥራት
ለእግዚአብሔር ያቀርቡት ነበር፡፡ መሥዋዕቱና ቁርባኑም የዘወትር፣ የመባቻ፣ የሰንበት፣
የበዓል፣ የፈቃድ፣ የምስጋና፣ የመድኃኒት፣ የንስሐ፣ የብፅዓት፣ የቅንዓት እየተባሉ ይጠሩ
ነበር፡፡ (ዘኁ@8÷1-ፍጻ፣@9÷1ፍጻ፡፡) የዘወትሩን መሥዋዕት ካህናት፣ የዓመቱን መሥዋዕት
ደግሞ ሊቀ ካህናት፤ ያቀርቡት ነበር፡፡ ካህናቱም አስቀድመው ስለራሳቸው በደል
በመቀጠልም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር፡፡
ከመጋረጃ ውጪ በቅድስት ካህናቱ መሥዋዕት ሲያቀርቡ ሊቀ ካህናቱ ግን ከመጋረጃ ውስጥ
በዓመት አንድ ቀን በቅድስተ ቅዱሳን መሥዋዕቱን ያቀርብ ነበር፡፡ መሥዋዕቱም ሆነ
ቁርባኑ ከሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቀርብና ጊዜያዊ ኃጢአትን ለማስተሥረይ ብቻ
የሚችል ነበር፡፡ (ዕብ 9÷፮-፰፡፡) የሐዲስ ኪዳኑ መሥዋዕት ግን አስቀድመን እንደገለጽነው
እግዚአብሔር ዓለሙን ሁሉ እስከ ሞት ድረስ የወደደበትና ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ
የፍቅር ስጦታ ነው፡፡ (ዮሐ ፫፥፲፮፡፡) በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ አበው ሁሉ ያቀረቡት
መሥዋዕትና ቁርባን፣ በአዳምና በሔዋን በደል በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ተፈርዶ የነበረውን
መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ሊያስወግድ አልቻለም ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን
ይህንን መርገም ያጠፋበት፤ የጥሉንም ግድግዳ ያፈረሰበት አማናዊ መሥዋዕት ክርስቶስ
በመስቀል ላይ የቆረሰውና ያፈሰሰው ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ መሆኑም ይታወቃል፡፡
የሁለቱ ኪዳናት መሥዋዕት አንድነታቸው ካህናት በቤተ መቅደስ ስለራሳቸውና ስለሰዎች
በእግዚአብሔር ፊት የሚያቀርቡት መሆኑ ነው፡፡

51
፭.፫ አፈጻጸም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣
የሠራውንና ሐዋርያትና፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያቆዩትን የተቀደሰ ሥርዓት ተከትላ
/መሠረት አድርጋ/ ምሥጢረ ቁርባንን ትፈጽማለች፡፡ በምትፈጽምበትም ጊዜ “ንዜኑ
ሞተከ ወትንሣኤከ ቅድስት ሞትህን የተቀደሰች ትንሣኤህን እንመሠክራለን፡፡” (ፍሬ
ቅዳሴ) እያለች ትዘምራለች፡፡ የምሥጢረ ቁርባን አፈጻጸም ከቅዳሴ ተለይቶ የሚታይ
ባለመሆኑ ከዚህ በታች ከቅዳሴው ሥርዓት ጋር አብረን በዝርዝር የምንመለከተው
ይሆናል፡፡

፭.፬ ቅዳሴ
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ቃሉ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በተባለው
መጽሐፋቸው “ቅዳሴ” የሚለውን ቃል “መቀደስ፤ አቀዳደስ፤ ቅደሳ፤ ቡራኬ፤ ምስጋና፤
የቁርባን ጸሎት “በማለት ይፈቱታል፡፡ (ገጽ ፯፻፹፬፡፡) ቅዳሴ ከምሥጢረ ቁርባን ጋር
በቀጥታ የተያያዘ ሲሆን ለሌሎቹ ምሥጢራትም የምሥጢርነታቸው ማረጋገጫ ማኅተም
ነው፡፡ ያለ ሥጋ ወደሙ ምሥጢራቱ በራሳቸው ምሉዕ ሊሆኑ አይችሉምና፡፡

አጠቃላይ ሥርዓተ ቅዳሴው በሦስት ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነዚህም ክፍሎች የዝግጅት


ቅዳሴ፣ የንባብ /ትምህርት/ ቅዳሴና ፍሬ ቅዳሴ በመባል ይታወቃሉ፡፡ በዝርዝር ለማየትም
ያህል ከዚህ የሚከተለውን እንከታተል:

፩ የዝግጅት ቅዳሴ
የዝግጅት ቅዳሴ በሌላ መጠሪያው ግብዓተ መንጦላዕት ይባላል፡፡ በዚህ ክፍል የሚቀርበው
ጸሎት ከመቅደስ በአፍአ (ከመጋረጃ ውጪ) የሚጸለይና ወደ መጋረጃው ውስጥ /መቅደስ/
ለመግባት አሐዱ ብሎ ለመቀደስም የሚያስችል ነው፡፡ ይህም “ሚ መጠን ግርምት ዛቲ
ዕለት-ይህች ዕለት ምንኛ የምታስፈራ ናት…” እስከሚለው ድረስ ያለውን የሚያካትት
ነው፡፡

ካህኑ ዝግጅቱን የሚጀምረው ወደ መቅደስ ገብቶ በታቦተ እግዚአብሔር ፊት በመስገድ


ነው፡፡ ይኸውም ከመጋረጃው በአፍአ (ውጪ) አንድ ጊዜ ከመጋረጃው ውስጥ ሦስት ጊዜ
በመስገድ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በሚያጠይቅ (በሚያስተምር) መንገድ የሚፈጸም
ነው፡፡ ከዚያም ካህናቱንና ዲያቆናቱን እጅ በመንሳት (ሰላም በማለት) ተረኛነቱን
ይገልጽላቸውና በጸሎት እንዲያስቡት ይማጸናል፡፡ ይህም አገልግሎቱ የፍቅርና የመተሳሰብ
መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ በመቀጠል ሳይረዝም ወይም ሳያጥር ልኩ የሚሆነውን ልብስ
መርጦ ከሱ የሚበልጥ ካህን (ጳጳስ) ካለ አስባርኮ ከሌለም ራሱ ባርኮ የክህነት
(የአገልግሎት) ልብሱን ይለብሳል፡፡አንዴ ከለበሰ በኋላ አገልግሎቱ ሳይፈጸም አውልቆ
መቀየር አይቻልም።

52
ልብሰ ተክህኖ ከለበሰ በኋላ ቀጥታ የሚያመራው ቀደም ብለን እንደገለጽነው ወደ መቅደስ
ለመግባት የሚያስችለውን ጸሎት ወደ ማቅረብ ነው፡፡ ይህም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ
ማደሪያ ለመግባት የሚደረገውን ጥንቃቄ ያሳያል የጸሎቶቹ ዝርዝር መገለጫም
እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

በመጀመሪያ ጸሎቱ የሚካተቱ፡-


• ካህኑ ፊቱን ወደ ሕዝቡ አድርጎ ለራሱና ለምእመናኑ የሚጸልየው ጸሎት እንደ
መጀመሪያ የቅዳሴ ጸሎት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይህም ምዕዳን /ምክር/ ጭምር የያዘ
ነው።

• የንስሐ ጸሎት (ካህኑ ቀዳሾቹን በሙሉ ይዞ በሕዝቡ ፊት ቆሞ የሚጸልየው) ሲሆን


ይህም ለቅዳሴው ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት ንጹሐን ሆነው መቅረባቸውን
ማረጋገጫ ነው፡

• ልዩ ልዩ የቅዱስ ዳዊት መዝሙራትን ማለትም፡-

፳፬ኛውን፣ ፷፰ኛውን፣ ፻፩ኛውን፣ ፻፪ኛውን፣ ፻፳፱ኛውንና ፻፴ኛውን ይደግማል፡፡


በማከታተልም፡-

• “እግዚአብሔር አምላክነ አንተ ውእቱ ባሕቲትከ ቅዱስ…፤ እግዚአብሔር አምላካችን


ሆይ አንተ ብቻ ልዩ፣ ምስጉን፣ ክቡር ነህ” የሚለውን፣

• “እግዚአብሔር አምላክነ ዘተአምር ኵሎ ኅሊና ሰብእ…፤ የሰውን ሁሉ ዐሳብ


የምታውቅ እግዚአብሔር አምላካችን” የሚለውን የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያን
ጸሎት (ይህ ጸሎት ከመቅደሱ ገብቶ፥ ከመንጦላዕት ውጪ ሆኖ የሚቀርብ ነው፡፡)

• ካህኑ “እግዚአብሔር አምላክነ ወፈጣሪነ…፤እግዚአብሔር አምላካችንና


ፈጣሪያችን…” የሚለውን (ከመቅደስ ገብቶ፣ መንጦላዕቱን አልፎ፣ ከመንበሩ ፊት
ቁሞ ከሰገደ በኋላ የሚጸለይ ነው) ይህን እየጸለየ መንበሩን በመክፈት ንዋያተ
ቅዱሳቱን እያወጣ በየቦታቸው ያስቀምጣል፡፡

• በመቀጠልም “ኦ እግዚእነ ወአምላክነ መወድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአንሣእከነ


እምድር…፤ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኛን
ከምድር ያነሣኸን …” የሚለውን

53
• በመጨረሻም “እግዚአብሔር አምላክነ ዘይነብር መልዕልተ ኩሉ…፤ ከሁሉ በላይ
ያለህ /የምትኖር/ እግዚአብሔር አምላካችን” የሚለውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን
ጸሎት ሦስት ጊዜ ሰግዶ ይጸልያል፡፡

በሁለተኛ ጸሎቱ የሚካተቱ፡-


ከላይ የገለጽናቸው ጸሎታት ሲፈጸሙ ንዋያቱን በቡራኬ ያከብራቸዋል፡፡ ይህም ከብሉይ
ኪዳን መሥዋዕት ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ለሐዲስ ኪዳኑ መሥዋዕት የምትሰጠውን ፍጹም
ክብር የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ጸሎታት ያቀርባል፡፡

• “እግዚአብሔር አምላክነ ኄር ወመሐሪ ወቅዱስ…፤ ቸር፣ ይቅር ባይ፣ ልዩ፣ ምስጉን፣


ክቡር አምላካችን እግዚአብሔር” የሚለውን፣

• በማኅፈድ፣ በጻሕል፣ በጽዋዕ፣ በዕርፈ መስቀል፣ በሞሰበ ወርቅ ላይ የተሠራውን


ጸሎት ጸልዮ ከባረካቸው በኋላ መንበሩን፣ ጻሕሉንና ጽዋውን በማልበስ በየቦታቸው
ያኖራቸዋል፡፡

• “እግዚአብሔር ማእምረ ልብ…፤ በልብ ውስጥ ያለውን ሁሉ የምታውቅ


እግዚአብሔር” የሚለውንና “ሃሌ ሉያ ወአንሰ በብዝኃ ምሕረትከ እበውእ ቤተከ…፤
ሃሌ ሉያ (እግዚአብሔርን አመስግኑ) በቸርነትህ ብዛት ወደ ቤትህ (መቅደስህ)
እገባለሁ” የሚለውን ጸልዮ ወደ መንጦላዕት (መቅደስ) ይገባል፡፡ (ሥርዓተ ቅዳሴ
ክፍል 1-9)

፪ የንባብ ወይም የትምህርት ቅዳሴ


የዝግጅት ቅዳሴ ልዑካኑን (ሰሞነኞቹን) ብቻ የሚመለከት ሲሆን ይህኛው ክፍል ደግሞ
ምእመናንን የሚያሳትፍ ጸሎት ነው፡፡ ይህ ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት
የሚቀርቡበትና ትምህርተ ወንጌልም የሚሰጥበት ነው፡፡

የተከበሩ ውድ አንባቢ ሆይ የማስቀደስ ልምድዎን በመጠቀም የሚከተሉትን ተያያዥ


ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ፡፡

❖ ኅብስቱና ወይኑ የሚዘጋጀው የት ነው? ወዴት ይወሰዳል? የሚያዘጋጃቸው ማነው?


የሚወሰዱት በምንድን ነው?

• ዲያቆናት በቤተልሔም አዘጋጅተው ኅብስቱን በሞሰበወርቅ ወይኑን በጽዋዕ


አድርገው የቀራንዮ አምሳል ወደሆነችው ቤተ ክርስቲያን ያገቡታል፡፡ ንፍቁ ቄስ
54
በማዕጠንት አጅቦ፣ ቃጭል (መረዋ) እየተመታ፣ ደወልም እየተደወለ በክብር
እየዘመሩ ያስገቡታል፡፡ እንደጊዜው ሁኔታ “እምነ በሀ፤ ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ፤ ሃሌ
ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ፤ መስቀል አብርሐ በከዋክብት፤” ከሚሉት ጸሎታት መካከል
ለዕለቱ ቅዳሴ የታዘዘውን እየጸለዩ ወደ መቅደስ ይገባሉ፡፡

• በዚህ ጊዜ ካህኑ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ “ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት”


የሚለውን ዐዋጅ ያውጃል፡፡ ሕዝቡና ካህናቱ ባንድነት “እመቦ ብእሲ እምእመናን
ዘቦአ ቤተ ክርስቲያን … ከምእመናን ወገን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ሰው
ቢኖር…” የሚለውን የሐዋርያት ሲኖዶስ ትእዛዝ ያውጃሉ።

• ቀዳስያኑ በኅብረት መንበሩን ይዞራሉ፤ ካህኑም “ተዘከር እግዚኦ እለ አቅረቡ ለከ…፤


አቤቱ ላንተ ያቀረቡልህን አስባቸው፤” የሚለውን እየጸለየ አብሯቸው ይዞራል፡፡

• ቀዳስያንና አስቀዳሾች ባንድነት “አንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ እንተ ውስቴታ
መና ኅቡዕ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወሀቤ ሕይወት ለኵሉ ዓለም፤ ለዓለሙ
ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ከሰማያት የወረደ የተሰወረ መና ያለባት የወርቅ መሶብ
አንቺ ነሽ” እያሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ኅብስቱን በያዘችው
መሶበ ወርቅ ምሳሌነት (አንጻር) ያመሰግኗታል፡፡ በዚህን ጊዜ ገባሬ ሠናዩ ቄስ
(ካህን) “እግዚአብሔር አምላክነ ዘተወከፍከ ቁርባነ አቤል ጻድቅ በውስተ በድው…፤”
እግዚአብሔር አምላካችን በምድረ በዳ የሠዋውን የአቤል መስዋዕት የተቀበልክ”
የሚለውን እየጸለየ መብራት የያዘው ዲያቆን ከፊቱ፣ ያልያዘው ከኋላ ሆነው
መንበሩን አንድ ጊዜ ይዞራሉ፡፡ ዲያቆኑም “እግዚአብሔር ይሬእየኒ…፤
እግዚአብሔር ይጠብቀኛል” (መዝ. ፳፪፥፩፡፡) የሚለውን ይደግማል፡፡

• ካህኑ በመቀጠል “ክርስቶስ አምላክነ ዘበአማን እግዚእነ ዘሖርከ ውስተ ከብካብ አመ


ጸውዑከ በቃና ዘገሊላ…፤ አቤቱ የባህርይ አምላክ የምትሆን ጌታችን ክርስቶስ
የገሊላ አውራጃ በምትሆን በቃና ወደ ሠርግ ቤት ተጠርተህ የሄድክ…” የሚለውን
በመጸለይ ቡራኬ ይጀምራል፡፡ እጁን አመሳቅሎ የሚፈጽመው ቡራኬውም “ቡሩክ
እግዚአብሐር አብ አኀዜ ኵሉ ዓለም አምላክነ፤ ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ
ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒነ፤ ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንኢ
ወመንጽሔ ኵልነ…፤ ሁሉን የሚገዛ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር አብ ምስጉን ነው፣

55
ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ምስጉን
ነው፣ መጽንዒ መንጽሒ የሚሆን መንፈስ ቅዱስም ክቡር ምስጉን ነው…፤“
የሚለውንና ተመሳሳዩን ጸሎት እየጸለየ መጀመሪያ ኅብስቱን በማስከተልም ወይኑን
፤ በመጨረሻም ለሦስተኛ ጊዜ ያንኑ ጸሎት እየጸለየ ኅብስቱንና ወይኑን ባንድነት
ይባርካል፡፡ ሕዝቡም “አሜን፤ አሜን፤ አሜን” ይላሉበመቀጠልም እየሰገደ
“ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ፤ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሥሉስ
ዕሩይ ኵሎ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን፡፡ በዘመን በክብር አንድ፤
በአካል ሦስት ለሚሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል
ዛሬም ዘወትርም ለዘለአለሙ አሜን፡፡” በማለት ቡራኬውን ይፈጽማል፡፡

• በመጨረሻም ካህኑ ስለራሱና ስለ መሥዋዕቱ ሁሉም እንዲጸልዩለት “ጸልዩ አበውየ


ወአኃውየ ላዕሌየ ወላዕለ ዝንቱ መሥዋዕት፤ አባቶቼ ወንድሞቼ ከቀሳፊ መልአክ
እንዲሰውረኝ መሥዋዕቴን እንዲለውጥልኝ /እንዲቀበልልኝ/ ጸልዩልኝ በማለት
ይማጸናል፡፡ አቡነ ዘበሰማያትም ይደገማል፡፡ ወደ ንፍቁ ቄስም ፊቱን አዙሮ
“ተዘከረኒ ኦ አቡየ ካህን በጸሎትከ ቅድስት፤ አባቴ ካህን ሆይ በጸሎትህ አስበኝ”
በማለት በትሕትና ይለምነዋል፡፡ ንፍቁም ካህን “እግዚአብሔር ክህነትህን ይጠብቅ፤
መሥዋዕትህንም፣ (ቁርባንህንም) በብሩህ ገጽ ይቀበልልህ፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ
ታድነን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፡፡” በማለት ይጸልይለታል፡፡

ከዚህ በኋላ ያሉትን ጸሎታት ደግሞ ዝርዝር ማብራሪያውን ተወት አድርገን በጥቅል
በጥቅሉ እንደሚከተለው የምናያቸው ይሆናል፡፡ በቅድሚያ ግን የሚከተለውን ጥያቄ
ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ ባስቀደሱባቸው ጊዜያት ሁሉ ከሚያስታውሷቸው ጸሎታት መካከል ዋናው የቅዳሴ


መጀመሪያ ተደርጎ የሚታየው ቀጣዩ ጸሎት ምን የሚለው ነው? ትርጉሙስ
ምንድን ነው?

የሃይማኖት ምስክርነት
ብዙዎቻችን የቅዳሴ መጀመያ አድርገን የምንመለከተው ጸሎት ገባሬ ሠናዩ ካህን እጅቹን
ዘርግቶ፣ ዐይኖቹን አቅንቶ በዐቢይ ዜማ የሚያዜመው የሃይማኖት ምስክርነት ነው፡፡
ይኸውም “አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤
ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል በግብር ልዩ የሆነ አብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ
ጋር በመለኮት÷ በባሕርይ÷ በሕልውና አንድ ነው፡፡ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ በስም፣
56
በአካል፣ በግብር ልዩ የሆነ ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት÷ በባሕርይ÷
በሕልውና አንድ ነው፡፡ ከአብ ከወልድ በስም፣ በአካል፣ በግብር ልዩ የሆነ መንፈስ ቅዱስም
ከአብ ከወልድ ጋር በመለኮት÷ በባሕርይ÷ በህልውና አንድ ነው፡፡” በማለት ምሥጢረ
ሥላሴን እንደ ሸማ ጠቅሎ፣ እንደ ወርቅም አንከብሎ የሚያመሠጥርበት የቅዳሴው ዐቢይ
አንቀጽ ነው፡፡ ይህን የቅዳሴ መጀመሪያ አድርጎ መመልከት ግን ከዚህ በፊት ያሉትን
ጸሎታት ከቅዳሴው የወጡ ያስመስላቸዋልና ጥንቃቄ ያሻል፡፡ ካህኑን ይህን ምስክርነት
ለመስጠት የሚያበቁት የቀደሙት ጸሎታት ናቸውና፡፡

በዕለቱ ቅዱስ ቁርባን ሊቀበሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን የገቡት ምእመናንም “በአማን አብ


ቅዱስ፣ በአማን ወልድ ቅዱስ፣ በአማን ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” እያሉ ሃይማኖታቸውን
ከካህኑ ጋር አንድ ሆነው ይመሰክራሉ፡፡ ትርጓሜው “በእውነት” የሚለውን “በአማን”
ለሚለው ከመተካት በስተቀር ሌላው ሁሉ እንደላይኛው (እንደ ካህኑ) ነው፡፡

ጸሎተ አኰቴት (የምሥጋና ጸሎት)


ይህንን ጸሎት የደረሰው ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው፡፡ ጸሎተ
አኰቴት ሰባቱም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በሚፈጸሙበት ጊዜ ሁሉ ይጸለያል፡፡
በተጨማሪም ለጸሎተ ፍትሐት ይጸለያል፡፡ በሥርዓተ ቅዳሴም በዚህ በሁለተኛው ክፍል
ይጸለያል፡፡ ይህም “ነአኵቶ ለገባሬ ሠናያት…፤ ሥራዎቹ መልካም የሆኑ እግዚአብሔርን
እናመስግነው…” ከሚለው ጀምሮ እስከ ፍሬ ቅዳሴ የሚጸለየውን ጸሎት የያዘ ነው፡፡
የሚጀምረውም “ተንሥኡ ለጸሎት፤ ለጸሎት ተነሡ፤” ብሎ ዲያቆኑ በሚያውጀው ዐዋጅ
ነው፡፡

ጸሎተ መባዕ
ይህ ጸሎተ መባዕ ማለትም ጧፍ፣ ሻማ፣ ዘይት፣ ዕጣን፣ ዘቢብ፣ መጋረጃ፣ ምንጣፍ፣
አልባሳት፣ መጻሕፍትና የመሳሰሉትን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለሚያገቡ
(ለሚሰጡ) ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ነው፡፡ የሚጸለየውም በጸሎተ አኰቴት
(በምስጋና ጸሎት) መካከል ነው፡፡ ይህም ጸሎት እንደ ላይኛው “ተንሥኡ ለጸሎት፤
ለጸሎት ተነሡ፤” በሚለው ይጀምራል። ካህኑ የሐዋርያትን የመባዕ ጸሎት የሚያደርስበት
ወቅት ሲደርስ ዲያቆኑ “ጸልዩ በእንተ እለ ያበውኡ መባዐ፤ መባ ስለሚያገቡ ሰዎች
ጸልዩ፤” ብሎ ያዝዛል፡፡

ሕዝቡም “ተወከፍ መባዖሙ ለአኃው ወተወከፍ መባዖን ለአኀት ለነኒ ተወከፍ መባዐነ
ወቁርባንነ፤ የወንድሞችን፣ የእኅቶችን መባቸውን ተቀበልላቸው እንዲሁም የእኛንም
ቁርባናችንን ተቀበልልን፡፡” እያሉ ይጸልያሉ፡፡ ካህኑም የሰጡትን ብቻ ሳይሆን ሊሰጡ
ያሰቡትን ሁሉ እንኳን ሳይቀር እንደሰጡ እንዲቆጥርላቸው ወደ እግዚአብሔር
ይጸልይላቸዋል፡፡

ጸሎተ ዕንፎራ /አንፎራ/

57
“ዕንፎራ” የሚለውን ቃል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በጽርዕ “አናፎራ” ይባላል ብለው
ትርጉሙን ደግሞ “አኰቴት፣ ኅብስተ መሥዋዕት” በማለት ያስቀምጡታል፡፡ (ገጽ. ፮፻፺፱)
ይህ ጸሎትም እንደትርጉሙ ሁሉ ስለኅብስቱና ስለወይኑ ክብር በተለይ የሚጸለይ፣ ቡራኬ
የሚተላለፍበትና እማሬ /ምልከታ/ የሚደረግበት ጸሎት ነው፡፡ ካህኑ “ኦ ሊቅየ ኢየሱስ
ክርስቶስ…፤ ጌታዬ ኢሱስ ክርስቶስ…፤” የሚለውን ጸሎተ ዕንፎራ /አንፎራ/ በሚጀምርበት
ጊዜ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የቤተ ክርስቲያን አባቶች
ይመክራሉ፡፡

፩ኛ. እማሬ /ምልከታ/፡- እማሬ የሚል ቃል በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ካህኑ በዐይኑ


እየተመለከተ፣ በእጁም እያመለከተ ልቡንና አንደበቱን አንድ አድርጎ መጸለይ አለበት፡፡
ይህን የመሰሉ ትእዛዛት በየክፍሉ አሉ፡፡ በጥቅሉ እማሬያት ፲፩ ሲሆኑ ሲተነተኑም በዚህ
በጸሎተ ዕንፎራ ፪፣ ይረስዮ ሲል ፪፣ በሥጋ በደሙ ላይ ፯ ጊዜ ናቸው፡፡

፪ኛ. ቡራኬ፡- ይህን ቃል ካህኑ በሚመለከትበት ጊዜ ሁሉ እንደትእዛዙ ፩ ወይም ፫ ጊዜ


በኅብስቱና በወይኑ ላይ መባረክ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ ማንበቡን ትቶ የቡራኬውን ቃል ብቻ
እየደገመ በዓይኑ እየተመለከተ በእጁ መባረክ አለበት፡፡ በመላው ቅዳሴ ውስጥ ያሉ
ቡራኬያት ፵፪ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ፳፩ዱ የአፍአ /የውጭ/፣ ፳፩ዱ ደግሞ የውስጥ
ቡራኬያት ተብለው ይጠራሉ፡፡ የአፍአ ቡራኬያት ለሕዝቡ ማክበሪያ ሲሆኑ፣ የውስጥ
ቡራኬያት ደግሞ ለቁርባኑ ማክበሪያነት የሚውሉ ናቸው፡፡ በኅብስቱና በወይኑ ላይ ቡራኬ
ከታዘዘ መባረክ እንጂ ማመልከት የተፈቀደ አይደለም፡፡ ካህኑ በመስቀልኛ ምልክት
እያመሳቀለ በታዘዘው መሠረት መባረክ ይጠበቅበታል፡፡

ጸሎተ መግነዝ
ጸሎተ መግነዝ ማለት የመገነዣ ጸሎት ማለት ነው፡፡ ካህኑ ይህን የሚጸልየው በማኅፈድ
ኅብስተ ቁርባኑንና ጽዋውን ሲሸፍን ነው፡፡ ኅብስቱንና ወይኑን የመሸፈኑ ምክንያትም
ጌታችን የመገነዙ ምሳሌ ነው፡፡ ካህኑ “አንበርነ ዲበ ዝንቱ ጻሕል ቡሩክ በአምሳለ
መቃብር…፤ ፫ መዓልት፣ ፫ ሌሊት ባደርህበት መቃብር አምሳል ክቡር በሚሆን በዚህ
ጻሕል ላይ አኖርን::” እያለ በመጸለይ ኅብስቱንና ጽዋውን በማኅፈድ ይሸፍናል፡፡ በአንድ
ላይም መጎናጸፊያ ያለብሳቸዋል፡፡ ምሳሌነቱም ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታን ገንዘው
የመቅበራቸው ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ ሕዝቡ መልሶ “ሰው በልቡናው ቂምንና በቀልን
ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ፣ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ” በማለት አስጠንቅቆ
“ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት፤ ለእግዚአብዘሔር በፍርሐት ስገዱ፤” በማለት ያውጃል፡፡
ምእመናን በፍርሃት ለእግዚአብሔር እንዲሰግዱና ስለኃጢአታቸው ሥርየት ካህኑ
የሚጸልይላቸውን የፍትሐት ጸሎት እንዲያደምጡ ትእዛዝ ያስተላልፋል፡፡ ሕዝቡም “አቤቱ
ባንተ ፊት እንሰግዳለን እናመሰግንህማለን፡፡” በማለት ታዛዥነታቸውን በተግባር
(በመስገድ) ይገልጣሉ፡፡

58
በዚህ ጊዜ አንዳንዶች ካህናትና አስቀዳሽ ምእመናን ራስን ዝቅ በማድረግ ጉልበትና
ግንባር ምድር በማስነካት ለእግዚአብሔር ሊቀርብ የሚገባውን ስግደት ባለማወቅ ወይም
ከምንም ባለመቁጠር የዕረፍት፣ ተቀምጦ የማንቀላፊያ፣ የመዝናኛና የወሬ ማውሪያ ጊዜ
ሲያደርጉት ይስተዋላሉ፡፡ እኛ ግን እንደ ትእዛዙ መሬት በመውደቅ፣ የኃጢአታችንን
ሥርየት መለመንና የጸሎቱን ሒደት ከልብ መከታተል ይኖርብናል፡፡

ጸሎተ ፍትሐት ዘወልድ


ከላይ እንደገለጽነው ይኽ ጸሎት ምእመናን ሰግደው ሳለ ንፍቁ ቄስ ለሥርየተ ኃጢአት
እንዲሆን የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ በዚሁ ጊዜ ቡራኬ በሚያስፈልግበት ቦታ ሁሉ
ሠራዒው ቄስ በመስቀል ምልክት ይባርካል፡፡ በመቀጠልም በእንተ ቅድሳትን ዲያቆን
(ቄስም ቢሆን) እያነበበ ምእመናን “አሜን ኪሪያላይሶን” ወይም “አሜን እግዚኦ ተሠሃለነ”
እያሉ ይማጸናሉ፡፡

ጸሎተ ዕጣን
ይህ ጸሎት ካህኑ ዕጣኑን ለማክበርና ለመባረክ በዕጣኑ ላይ የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡
አምስት ቆቀር ዕጣን ተመርጦ ይቀርብና ካህኑ በዕጣኑ ላይ ጸሎቱን አድርጎ ይባርከዋል፡፡
ሦስቱን ቆቀር ዕጣን ወዲያው እንደባረከው በማዕጠንቱ ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ አንዱን
በጸሎተ ወንጌል ጊዜ፤ አንዱን ደግሞ “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤ አቤቱ
በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበን፤” በሚባልበት ወቅት ይጨምረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ
ሰግደው የነበሩ ሁሉ ይነሣሉ፤ ጳጳስ ካለ ጳጳሱ ከሌለም ቀዳሹ ቄስ ዕጣኑን ይባርካል፤
ያከብራል፡፡ ይህንንም ጸሎት የሚያደርግ ካህን ሌሊቱን፣ መዓልቱን፣ ዕለቱን፣ ወርኁን፣
ዓመቱን፣ ወንጌላዊውን ቀምሮ (አስልቶ) ማውጣት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
በመቀጠል ባለው ጸሎት ውስጥ “እማሬ” ሲል በጥንቃቄ እያመለከተ፤ “ቡራኬ” ሲልም
እየባረከ ይጸልያል፡፡ ሠራዒ ቄስና ዲያቆን ከንፍቅ ዲያቆን ጋር ሁነው መንበሩን
ይዞራሉ፡፡ ከዚያ በኋላ “ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን …” የሚለውን ጸሎት ዲያቆኑ
አሰምቶ ከጸለየ በኋላ “ንስግድ” የሚለውና ቀሪ ጸሎታት በቅደም ተከተላቸው ይቀርባሉ፡፡

የሐዲስ ኪዳን ምንባባት


ውድ የዚህ ጽሑፍ ተከታታይ

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማስተዋል መርምረው ይመልሱ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ ከልዑካኑ መካከል፦

❖ ወንጌልን ፣የሐዋርያት ሥራን፣ የቅዱስ ጳውሎስን መልእክትና ሌሎቹን


መልእክታት የሚያነባቸው ማነው?

59
በዚህ ክፍል ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምንባባት በልዑካኑ በየተራቸው፣ በየአባባላቸውና
በየቦታቸው ሆነው ይነበባሉ፡፡ ገባሬ ሠናይ ዲያቆን የቅዱስ ጳውሎስን፣ ንፍቅ ቄስ
የሐዋርያት ሥራን፣ ገባሬ ሠናዩ ካህን ወንጌልንናንፍቅ ዲያቆን ቀሪውን መልእክት
ያነባሉ፡፡ ሁሉም በዜማ የሚደርስ የራሳቸው የሆነ የመግቢያና የመሰናበቻ ምስጋና
(መርገፍ) ስላላቸው ከንባብ በፊትና በኋላ በዜማ ይቀርባሉ፡፡ እነዚህም መርገፎች ራሳቸውን
የቻሉ ሃይማኖታዊ ምስክርነት ያላቸው ናቸው፡፡ በየመሐሉ “ተንሥኡ ለጸሎት” የሚለውና
“ሰላም ለኵልክሙ” በማለት የሚቀርበው የበረከት ቃል በየቦታቸው በቅብብሎሽ ይባላሉ፡፡
“ዝ ውእቱ ጊዜ ባርኮት..፤ ይኽ የቡራኬ (ምስጋና) ጊዜ ነው…፤” የሚለውን፤ በበዓለ ሃምሳ
ከሆነ ደግሞ “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት…፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ
ሞቶ ሞትን ቀማው…፤” የሚለውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡

ጸሎተ ኪዳን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዕለተ ዓርብ ያስተማረው ወንጌል፣ ከትንሣኤው እሰከ
ዕርገቱ ያስተማረው ደገሞ ኪዳን ይባላል፡፡ ይህም ጸሎት የዚሁ አካል የሆነ በመጽሐፈ
ኪዳንም ሰፍሮ የሚገኝ ነው፡፡ ለጸሎት የተለዩ ሰባት ኪዳናት ሲኖሩ አንዱ ይህኛው ነው፡፡
የኪዳን አዳራረስ ሥርዓት በሦስቱ ጊዜያት ማለትም በሌሊት፣ በነግህና በሠርክ የተከፋፈለ
ሲሆን በሥርዓተ ቅዳሴ የሚደረሰው የነግሁ በነግህ፣ የሠርኩም በሠርክ ነው፡፡ “ቅዱስ”
ተብሎ የሚጀምረው ጳጳስ ካለ ጳጳስ ከሌለም ሠራኢው ካህን ነው፡፡ የሚቀርብበት ዜማ
በአራራይ ነው፡፡ ሕዝቡም ኪያከ ንሴብህ (ንዌድስ)እግዚኦ፤ አቤቱ አንተን እናመሰግናለን”
እያለ በየክፍሉ ከካህናት ጋር አብሮ ተሰጥዖውን በመቀበል ያመሰግናል፡፡

ጸሎተ ወንጌል
የኪዳን ጸሎት ተፈጽሞ አቡነ ዘበሰማያት ከተደገመ በኋላ ቀጣዩ የቅዳሴ ሥርዓት ወንጌል
የሚነበብበት ክፍል ነው፡፡ ጸሎተ ወንጌል ደግሞ ካህናትና ምእመናን በአንድነት ሆነው
የወንጌልን ቃል በንቃት የሚያዳምጡበትና የሚያስተውሉበት ኃይል እንዲያገኙ ቅድመ
ወንጌል የሚጸለይ ጸሎት ነው፡፡ ጸሎቱ እንደተለመደው ዲያቆኑን፣ ሕዝቡንና ካህኑን
የሚያሳትፍ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡

ዲያቆን፡- ፊቱን ወደ ሕዝቡ መልሶ “ጸልዩ በእንተ ወንጌል ቅዱስ፤ ስለ ቅዱስ ወንጌል
ጸልዩ” በማለት ያዝዛል፡፡

ሕዝቡ፡- በያለበት በንቃት ቆሞ በአንድ መንፈስና ድምፅ “ረስየነ ድልዋነ ለሰሚዓ ወንጌል
ቅዱስ፤ ቅዱስ ወንጌልን ለማዳመጥ (ለማስተዋል) የተዘጋጀን (የተገባን) አድርገን” በማለት
እግዚአብሔርን ይለምናሉ፡፡

60
ካህኑ፡- ከቅዱሳት መጻሕፍት እያውጣጣና እየመሰከረ የሚነበበው ወንጌል ከሰሚዎቹ ጋር
እንዲዋሐድ ሰሚዎቹም እንዲዘጋጁ እንዲህ በማለት ይጸልያል፤ አምላካችንና
መድኃኒታችን ሰውንም የምትወድ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱሳን የሚሆኑ ደቀመዛሙርትህንና
አገልጋዮችህን ንጹሐን ሐዋርያትን ወደ ዓለም ዳርቻ የሰደድሃቸው አንተ ነህ፡፡
የመንግሥትህን ወንጌል ይሰብኩና ያስተምሩ ዘንድ በሕዝብህም ውስጥ ያለውን ደዌውን
ሁሉ በሽታውንም ሁሉ ያድኑ ዘንድ፤ ከዓለም አስቀድሞ የነበረውን የተሰወረውን
ምሥጢርህንም ያስተምሩ ዘንድ፤ አሁንም ጌታችን አምላካችን ሆይ ብርሃንህንና ጽድቅህን
ላክልን፤ ያሳባችንንና የልቡናችንን ዓይኖች አብራልን፤ የከበረ የወንጌልን ቃል በመጨከን
እንሰማ ዘንድ የበቃን አድርገን፤ የምንሰማ ብቻ አይደለንም እንደሰማን ልንሠራም ነው
እንጂ። ስለ አንዱ ፈንታ ሠላሳና ስልሳ መቶም ያማረ ፍሬ በላያችን ያፈራ ዘንድ
የወገኖችህን ኀጢአት ታስተሠርይ ዘንድ በመንግሥተ ሰማያትም የበቃን እንሆን ዘንድ።”

ከዚህ በኋላ ዲያቆኑ ከቅዱስ ዳዊት መዝሙር ለዕለቱ የተወሰነውን አባቶቻችን በመጽሐፈ
ግጻዌ ቀምረው ባዘጋጁት መሠረት ሦስቱን ስንኞች በዐቢይ ዜማ ያዜማል (ያቀርባል)፡፡
ሕዝቡም ተሰጥኦውን እየተቀባበሉ ሁለት ሁለት ጊዜ፤ ሦስተኛውን ደግሞ በጋራ (በኀብረት)
ይዘምራሉ (ያቀርባሉ)፡፡ ካህኑ በዚህ ጊዜ አራቱን መዓዘን “እግዚአብሔር ልዑል ይባርክ
ላዕለ ኵልነ ወይቀድሰነ በኵሉ በረከት፤ እግዚአበሔር ልዑል ሁላችንንም ይባርከን፤
በመንፈሳዊ በረከትም ያክብረን” እያለ ይባርካል፡፡ ከዚህ በማስከተል አብሮ (ተያይዞ)
የቀረበውን ጸሎት ከጸለየ በኋላ በመሠዊያው ዙሪያ እያጠነ አብሪ ዲያቆን ከፊት፣ ንፍቅ
ካህን ወንጌሉን ይዞ አብሪውን ዲያቆን እየተከተለው መሐል ላይ ሠራኢው ካህን፣ ከኋላውም
ሠራኢው ዲያቆን መስቀሉን ይዞ፣ በመጨረሻም ጥላ (ድባብ) የያዘው ዲያቆን ሆነው
በመሠዊያው (በመንበሩ) ዙሪያ ዑደት ያደርጋሉ፡፡ ይህም ምሳሌ አለው፤ ንፍቅ ዲያቆን
(አብሪ) የነቢያት፣ ንፍቅ ቄስ የመጥምቁ ቅ/ዮሐንስ፣ ሠራኢው ካህን የጌታ፣ ሠራኢ ዲያቆን
የቅ/እስጢፋኖስ ምሳሌዎች ናቸው፡፡

በማስከተልም ቀሪ የጸሎተ ወንጌሉ አካላት ተጸልየው ሠራኢው ዲያቆን ወንጌል ከመነበቡ


በፊት “ሃሌ ሉያ ቁሙ ወአጽምኡ ወንጌለ ቅዱሰ ዜናሁ ለእግዚእነ ወመድኃኒነኢየሱስ
ክርስቶስ፤ የንጉሥን ዐዋጅ ወንጌለ መንግሥትን ቁሙና አድምጡ፤ እርሱም የጌታችን
የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራን የሚያበስር የምስራች ነው፡፡” በማለት በማስቀደስ
ላይ ያሉትን ሁሉ ያነቃቸዋል፡፡ ካህኑም “እግዚአብሔር ምስለ ኩልክሙ፤ እግዚአብሔር
በረድኤት አይለያችሁ” በማለት ወንጌሉን በሚሰሙበት ጊዜ ጸጋ እግዚአብሔር
እንዳይለያቸው ይባርካቸዋል፤ (ይመርቃቸዋል)፡፡ ከዚህ በኋላ በዐቢይ ድምፅ “ወንጌል
ቅዱስ ዘዜነወ (ዘሰበከ) …” እያለ ለዕለቱ እንደታዘዘው የወንጌሉን ስም እያከለ
(እየጠራ)ያዜማል፡፡ ሕዝቡም በበኩሉ “ስብሐት ለከ ክርስቶስ እግዚእየ ወአምላኪየ ኵሎ
ጊዜ፤ ይህን ቅዱስ ቃል የምታሰማኝ ጌታዬና አምላኬ ክርስቶስ ሁልጊዜም ለአንተ ምስጋና
ይገባል፡፡” በማለት የክርስቶስን ውለታ እያስታወሰ ያመሰግናል፡፡

ወንጌል ከመነበቡ በፊትና በኋላ እንደየጊዜው ሁኔታና እንደወንጌሉ ዓይነት በዜማ


የሚቀርብ ልዩ ልዩ መርገፍ አለው፡፡ ይህም ምስጋና፣ የትምህርተ ሃይማኖት ምስክርነትን

61
የያዘ ነው፡፡ “ወንጌል ቅዱስ” ብሎ ወደ ቅድስት ከወጡ በኋላ በመጀመሪያ ሠራኢው ካህን
“ነዋ ወንጌለ መንግሥት” ጌትነቱን የምትናገር ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ ወንጌል
ይህቺ ናት::” በማለት ለንፍቁ ካህን ይሰጠዋል፡፡ ንፍቁ ካህን ደግሞ “መንግሥቶ ወጽድቆ
ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ፤ ጌትነቱን ቸርነቱን የምትናገር ቄሱ የሰጠኝን ወንጌልን ሰጠሁህ”
እያለ ለዲያቆኑ ይሰጣል፡፡ ዲያቆኑ ደግሞ “ነስሑ ወእመኑ እስመ ቀርበት ይእቲ
መንግሥተ ሰማያት፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በማወጅ ለካህኑ
አመቻችቶ ይይዝለታል፡፡ ይህም ለጊዜው “ወንጌል የምትነገርበት ጊዜ ቀርቧልና
ነቅታችሁ÷ ተግታችሁ ስሙ፤” ማለት ሲሆን ለፍጻሜውም “ልጅነት፣ መንግሥተ ሰማያት
የምትሰጥበት ጊዜ ቀርባልና ንስሐ ግቡ፤” ማለት ነው:: ሠራኢው ካህን ፊቱን ወደ
ምሥራቅ መልሶ የዕለቱን ወንጌል ጎላ ባለ ድምፅ ያነባል፡፡

ወንጌል ተነቦ ሲያበቃ አስቀድመን እንደተናገርነው መርገፉ በዜማ ከቀረበ በኋላ


አማናዊውን ሰላም የምትሰብክ ወንጌል ናትና ሰላማውያን ክርስቲያኖች ከካህናቱ ጀምሮ
ምእመናኑ ሁሉ ይሳለሟታል፤ ይስሟታል፡፡

የተከበሩ አንባቢ ሆይ አሁን ደግሞ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ

❖ በቅዳሴ ጊዜ (መሐል) ቅዱስ ወንጌል ሲነበብ እንዴት ሆነው ነው የሚያዳምጡት?


(ምን ያህል ትኩረት ይሰጡታል?)

ስለ ክብረ ወንጌልና ስለጠቅላላው ጸሎተ ቅዳሴ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያስተላለፉልን


ቃለ ምዕዳን የሚለውን እስኪ እንስማ!

“በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃላት ሲነበቡ የሰማያውዊን ንጉሥ የተከበረ


የወንጌሉን ቃል ለመስማት ከመጀመሪያቸው እስከ መጨረሻቸው ድረስ ከማመስገንና
ከመቀደስ በቀር ማድነቅና ጸጥታ ሊሆን ይገባል፡፡ የምድራዊ ንጉሥ ደብዳቤ ሲነበብ አንድ
ሰው እንኳን ለመናገር የማይደፍር ከሆነ፤ ቢናገርም ግርፋትና ቅጣት የሚያገኘው ከሆነ፤
የሰማያዊ ንጉሥ ደብዳቤ የምትሆን ወንጌል ስትነበብማ ቢናገር እንደምን ያለ ቅጣት (ፍዳ)
ያገኘው ይሆን?”

ወንጌል ከተነበበ በኋላ ካህኑ የተነበቡትን መጻሕፍተ ሐዲሳትና ምስባኩን በማብራራት


አጠር አድርጎ ለአስቀዳሹ ሕዝብ ያስተምራል፡፡ በዕውቀት እንዲታነፁና በእምነት እንዲጸኑ
እስከዚህ ሰዓት ድረስ በቅኔ ማኅሌቱ በተፈቀደላቸው ቦታ ሆነው ያዳምጡ የነበሩ ንዑሰ
ክርስቲያኖች “ጻኡ ንዑሰ ክርስቲያን፤ የክርስቲያን ታናናሾች ውጡ” ተብሎ ሲታወጅ
ይወጡና በተሰጣቸው በአት ይቆያሉ፡፡ የፍሬ ቅዳሴ መጀመሪያው ነውና ምሥጢረ
ቁርባንንም ሊቀበሉ ገና አይችሉምና፣ ተምረው፣ መስክረውና ተጠምቀው ከምእመናን
አንድነት እስኪቆጠሩ፥ ምሥጢራትንም ለመቀበል እስኪፈቀድላቸው ድረስ ፍሬ ቅዳሴውን
አይሳተፉም፡፡

62
ጸዋትው
ይህ ጸሎት ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ካህናትና፣ ስለ ማኅበረ ምእመናን ካህናት ወደ
እግዚአብሔር የሚያቀርቡት ነው፡፡ ጸዋትው ማለት የምእመናን ወገኖች ማለት ነው፡፡ ስለ
ጾታ ምእመናን ስለሚጸለይ ጸዋትው ተብሏል፡፡ ስለ አንዲቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ፍጹም ሰላምና አነድነት፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ ስለ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን
ሕይወት፣ ጤንነትና ሰላም፣ አንድነት ሠራኢው ካህንና ዲያቆኑ እያስተዛዘሉ ወደ
እግዚአብሔር ምልጃ የሚያቀርቡበት ክፍል ነው፡፡ ካህኑ “ኵሎ ሕዝበ ወኵሎ መራእየ
ባርኮሙ፤ ሕዝቡንና መንጋውን ሁሉ ባርክ” እያለ የሚባርክበት፣ ሕዝቡም ኪሪያላይሶን
(አቤቱ ይቅር በለን!) እያለ የሚማፀንበትና ቡራኬውን የሚቀበሉበት የሥርዓተ ቅዳሴ አንዱ
አካል ነው፡፡ ዲያቆኑ “ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወማኅበርነ ዘውስቴታ፤
ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በውስጧም ስለሚገኙ ማኅበር (ስለ ምእመናን
አንድነት) ጸልዩ” ባለ ጊዜም ሕዝቡም “ማኅበረነ ባርክ ዕቀብ በሰላም፤ ማኅበራችንን
ባርክልን፣ በሰላምም ጠብቅልን” በማለት እምነቱን፣ ፈቃዱንና ፍላጎቱን የሚገልጽበት ጸሎት
ነው፡፡

ጸሎተ ሃይማኖት
❖ ጸሎተ ሃይማኖትን በቃልዎ መድገም ይችላሉን? በቃልዎ እያነበቡ በማስታወሻ
ደብተርዎ የቻሉትን ያህል ለመጻፍ ይሞክሩ፡

ጸሎተ ሃይማኖት የሃይማኖት ምስክርነት ነው፡፡ ምእመናን ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና


ሲቀበሉ ዐዋቂዎቹ (በዕድሜ) ተምረውና አምነው ምስክርነታቸውን የሚሰጡበት፤ ሕፃናት
ደግሞ በክርስትና አባቶቻቸው /እናቶቻቸው/ በኩል ተመስክሮላቸው የሚከብሩበት ጸሎት
ነው፡፡ ጸሎተ ሃይማኖት አምስቱን አዕማደ ምሥጢራት ሰብስቦ የያዘ፤ ሊቃውንት
አባቶቻችን ምሥጢር አደላድለው፣ አንቀጽ አውጥተው፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አልበው፣
ጉባኤ ሠርተው፣ መናፍቃንን ረትተውና ሃይማኖት አቅንተው የሠሩልን መሠረተ እምነት
ነው፡፡ ማንኛውም ምእመን በሕይወቱ ሁሉ የሚጸልየው (የሚያነብበው)፣ በጸሎተ ቅዳሴም
አንድ ሆኖ የሚዘምረው የክርስቲያናዊነቱ መታወቂያ ነው፡፡ በዕለቱ የታዘዘው ቅዳሴ
የሊቃውንት ከሆነ የሚጸለየው ጸሎተ ሃይማኖት ነው፡፡ ቅዳሴ ሐዋርያት፣ ቅዳሴ እግዚእ፣
ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድና ቅዳሴ ማርያም ከሆነ ደግሞ “አመክንዮ ዘሐዋርያት”
ሕየንተ ጸሎተ ሃይማኖት (በጸሎተ ሃይማኖት ምትክ) ይጸለያል፡፡

የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ በመሞከር ራስዎን ይገምግሙ፡፡

❖ ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ “ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል፤ ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል፤


ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል፣ በልቡናው

63
ቂምን የያዘ ልዩ አሳብና ዝሙትም ያለበት ቢኖር አይቅረብ፡፡” በማለት
የሚያውጀውን ዐዋጅ እንዴት ያዩታል?

ጸሎተ ሃይማኖት ከተደገመ በኋላ ካህኑ እጁን ሲናጻ (ሲታጠብ) የሚከተለውን ትእዛዝ
ያስተላልፋል፡፡ “ዘኮነ ንጹሐ ይንሣእ እምቁርባን፤ ወዘኢኮነ ንጹሐ ኢይንሣእ ከመ ኢየዐይ
በእሳተ መለኮት ዘተደለወ ለሰይጣን ወለመላእክቲሁ፤ ዘቦ ቂም ውስተ ልቡ ወዘቦ ውስቴቱ
ኅሊና ነኪር ወዝሙት ኢይቅረብ፤- ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል፤ ንጹሕ ያልሆነ ግን
አይቀበል፤ ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል፤
በልቡናው ቂምን የያዘ ልዩ አሳብና ዝሙትም ያለበት ቢኖር አይቅረብ፡፡” በሂደት ለማወቅ
እንደተቻለው ይህን አንቀጽ ብዙዎች ምእመናን ይፈሩታል፡፡ አንዳንዶችም “ሰው ወደ
ሥጋ ወደሙ እንዳይቀርብ ካህናት ምእመናንን የሚያስፈራሩበት መሣሪያ ነው፡፡”
እስከማለትም ይደርሳሉ፡፡ የዚህ አንቀጽ /ክፍለ ንባብ/ ዋነኛ መልእክት ግን እንደተባለው
ሳይሆን ምእመናን ንስሐ ሳይገቡ በድፍረትና በግዴለሽነት ወደ ሥጋውና ደሙ
እንዳይቀርቡ ማድረግ ነው፡፡ የተጣሉ ታርቀው፣ የቀሙ መልሰው፣ የበደሉ ክሰውና ንስሐ
ገብተው ወደ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ እንዲቀርቡ የሚያሳስብ ትምህርት ነው፡፡ በርግጥ ከዚህ
ውጪ በድፍረትና በማንአለብኝነት (ንስሐ ሳይገቡ) ተንደርድረው የሚቀርቡ ካሉ
መቀጣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህም በድፍረትና ባለማወቅ ምእመናን እንዳይጎዱ
ለመጠበቅ እንጂ በማስፈራራት ለማራቅ አለመሆኑ መታወቅ አለበት።

ካህኑ ከላይ የተናገርነውን እውነት እጁን ተናጽቶ ሲያበቃ በእፍኙ የያዘውን ማይ ወደ


ሕዝቡ እየረጨ ይመሰክራል፡፡ እንዲህ ሲል፡- “በከመ አንጻሕኩ እደውየ እምርስሐት
አፍአዊ ከማሁ ንጹሕ አነ እምደመ ኵልክሙ፤ በድፍረትክሙ ለእመ ቀረብክሙ ኀበ
ሥጋሁ ወደሙ ለከርስቶስ፤ አልቦ ላዕሌየ ትኅላፍ ለተመጥወትክሙ እምኔሁ፤ ንጹሕ አነ
እምጌጋይክሙ፣ ኃጢአትክሙ ዳዕሙ ይገብእ ዲበ ርእስክሙ ለእመ በንጹሕ
ኢቀረብክሙ፤- እጄን ከአፍአዊ እድፍ ንጹሕ እንዳደረግሁ እንዲሁም ከሁላችሁ ደም ንጹሕ
ነኝ፤ ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከእርሱ ለመቀበላችሁ መተላለፍ
የለብኝም፤ በደላችሁ በራሳችሁ ይመለሳል እንጂ፣ በንጽሕና ሁናችሁ ባትቀርቡ እኔ
ከበደላችሁ ንጹሕ ነኝ፡፡”

የተከበሩ አንባቢ ሆይ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው ይህ ምስክርነት አሁንም ቢሆን


ማስፈራሪያ ወይም ማባረሪያ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እንወዳለን፡፡ ምእመናን ንስሐ
ሳይገቡ በድፍረት በመቅረብ ሊመጣባቸው ከሚችል አምላካዊ ቅጣት መጠበቂያ (መከላከያ)
ነው እንጂ፡፡ መፍትሔውም ኃጢአትን ለመምህረ ንስሐ በመናገር የሚሰጠውን ቀኖና
ፈጽሞ በትሕትና ቀርቦ ሥጋውንና ደሙን መቀበል ብቻ ነው፡፡ ካህኑ እጁን የሚታጠብበት
ምክንያትም ከዚህ ወዲያ ወደ ፍሬ ቅዳሴው የሚገባ ስለሆነ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ሥጋውና
ደሙን ከመባረክና ከመዳሰስ ውጪ ምንም ነገር አይነካምና ነው፡፡ ይህም አይሁድ “ስቅሎ፣
ስቅሎ፤ ስቀለው፣ ስቀለው” ብለው ክርስቶስን ለሞት አሳልፈው በሰጡት ጊዜ መስፍኑ
ጲላጦስ “ከደሙ ንጹሕ ነኝ! (በክርስቶስ ሞት አልተባበርኩም)” በማለት በአደባባይ እጁን
መታጠቡን የሚያዘክር (የሚያስታውስ) ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ካህኑ እጁን መታጠቡ
64
ንስሐ ሳይገቡ፣ ከበደላቸውም ሳይነጹ የሚቀርቡ ካሉ በደማቸው የማይገባ (የማይጠየቅ)፣
በኃጢአታቸውም (በድፍረታቸው) የማይተባበር መሆኑን መግለጹ ነው፡፡ ዲያቆኑም ከካህኑ
ጋር አንድ ሆኖ “ይህን የካህኑን ቃል ሰምቶ ያፌዘ፣ የሣቀ፣ ዋዛ፥ፈዛዛ የተነጋገረ ቢኖር
ጌታን እንዳሳዘነው፣ እጁንም በእርሱ ላይ እንዳነሣ ይወቅ ይረዳ፤ በቡራኬ ፈንታ
መርገምን፣ በኃጢአት ሥርየትም ፈንታ ገሃነመ እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል፡፡”
በማለት ገልጦ ያውጃል፤ ያስጠነቅቃል፡፡

ጸሎተ አምኃ ቅድሳት


ይህ ጸሎት በጊዜ ቅዳሴ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ካህናትና ምእመናን
በየጾታቸው ማለትም ካህናት ከካህናት ጋር፤ (ቀሳውስት ከቀሳውስት፣ ዲያቆናት ከዲያቆናት
ጋር) ወንዶች ከወንዶች ጋር፤ ሴቶችም ከሴቶች ጋር፤ ከይሁዳ ሰላምታ በተለየች
(በተቀደሰች ሰላምታ) ሰላም እንዲባባሉ (እጅ እንዲነሳሱ) ዲያቆኑ የሚያውጅበት ክፍል
ነው፡፡ ዲያቆኑ “ተንሥኡ ለጸሎት” ብሎ ሕዝቡ ተሰጥኦውን ከመለሰ በኋላ ካህኑ
“እግዚአብሔር ዐቢይ ዘለዓለም…፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ታላቅ /ከፍ ከፍ ያለ/ ነው…፤”
የሚለውን ጸሎት ይጸልያል፡፡ በማስከተልም ቅዱሳን መላእክት ጌታችን በተወለደ ጊዜ
ያቀረቡትን ምስጋና “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ”
የሚለውን በዜማ ያቀርባል፡፡ ሕዝቡም እንደካህኑ ይዘምራሉ፡፡ ከዚያም ዲያቆኑ “ጸልዩ
በእንተ ሰላም ፍጽምት ወፍቅር ተአምኁ በበይናቲክሙ በአምኃ ቅድሳት፤ በፍጹም ሰላምና
ፍቅር እርስ በርሳችሁ ሰላም ተባባሉ” በማለት ያዝዛል፡፡ ሕዝቡም “ክርስቶስ አምላክነ
ይረስየነ ድልዋነ ከመ ንትአማኅ በበይናቲነ በአምኃ ቅድሳት፤ ክርስቶስ አምላካችን
በተቀደሰች (ልዩ በሆነች) ሰላምታ እርስ በርሳችን ሰላም እንድንባባል (ለመባባል)
የተዘጋጀን ያድርገን፤” እያሉ እጅ ይነሳሳሉ::(ሰላም ይባባላሉ)፡፡

ፍሬ ቅዳሴ
የአጠቃላዩ ሥርዓተ ቅዳሴ የመጨረሻ ክፍል ፍሬ ቅዳሴ ነው፡፡ ይህ ክፍል ኅብስቱና ወይኑ
ወደ ሥጋ ወደሙ የሚለወጥበትን ጊዜ የሚመለከት ጸሎትና ቡራኬ የያዘ ነው፡፡ ከላይ
እንደተገለጸው መረሳት የሌለበት ጉዳይ ኅብስቱና ወይኑ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔርና ደመ
ወልደ እግዚአብሔር ወደመሆን የሚለወጠው በአንድ ክፍለ ጸሎት ብቻ አለመሆኑን ነው፡፡
የኅብስቱና የወይኑ የክርስቶስን ሥጋና ደም ወደ መሆን መለወጥ የአጠቃላዩ የሥርዓተ
ቅዳሴው /ሥርዓተ ጸሎት/ ውጤት ነው፡፡

አኰቴተ ቁርባን (የቁርባን ምስጋና)


በቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ላይ የዋሉ ፲፬ ቅዳሴያት አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን
ከወቅቱና ከዕለቱ በዓል ጋር እየመረመረች መጽሐፈ ግጻዌ በሚባል መጽሐፍ ምንባባትንና
መዝሙራትን ወጥ አድርጋ ስትሠራ በዕለቱ የሚቀደሰውንም ቅዳሴ ምሥጢር በማስማማት
ለይታ አብራ ሠርታለች፡፡ አባቶቻችን ቁርባንን በሚያቀርቡበት ጊዜ ለአምላካቸው
የሚያቀርቡት ምሥጋና መሆኑን ለመግለጥ “አኰቴተ ቁርባን” ብለውታል፡፡ ሁሉም
65
ቅዳሴያት ሲጀምሩ አኰቴተ ቁርባን ዘቅዱስ…………. በረከተ ጸሎቶሙ/ ጸሎቱ ወበረከቱ/
የሃሉ ምስለ…………፤” በማለት ይጀምራሉ፡፡ ቅዳሴ እግዚእ “እመጽሐፈ ኪዳን ዘነግሮሙ
እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቲሁ ንጹሐን…፤ ጌታችንና መድኃታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ለንጹሐን ሐዋርያቱ የነገራቸው የኪዳን መጽሐፍ…..፡” ብሎ ያስቀድምና
ምዕራፍ ፪ ላይ እንደሌሎቹ ሁሉ “አኰቴተ ቁርባን ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ
ኢየሱስ ክርስቶስ በረከተ ሣህሉ የሃሉ ምስለ…….፤” በማለት ይቀጥላል፡፡ በተመሳሳይ
ሁኔታ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስም “ጸልዩ በእንተ አበዊነ ጳጳሳት፣ ወአበዊነ ኤጲስ ቆጶሳት፣
ወአበዊነ ቀሳውስት፣…፤ ስለ አባቶቻችን ጳጳሳት፣ ስለ አባቶቻችን ኤጲስ ቆጶሳት፣ ስለ
አባቶቻችንም ቀሳውስት ጸልዩ…፤” የሚለውን ያስቀድምና ቁጥር ፫ ላይ እንደሌሎቹ ሁሉ
“አኰቴተ ቁርባን” በማለት ያስተካክላል፡፡ ሌሎቹ ቅዳሴያት ግን ከላይ በገለጽነው መሠረት
የሚጀምሩ ናቸው::

ከዚህ በታች የምናየው የፍሬ ቅዳሴ ክፍል ለማሳያ ያህል የአባቶቻችን የሐዋርያትን
ይሆናል፡፡ በጥቅሉ የፍሬ ቅዳሴው ክፍል በውስጡ በስማቸውና በአፈጻጸማቸው ልዩ ልዩ
የሆነ በዛ ያሉ ንዑሳን ክፍሎችን ይዞ ይገኛል፡፡ ዐሥራ ዐራቱ ቅዳሴያት በዝርዝር ሲታዩ፡-
ቅዳሴ እግዚእ፣ ዘሐዋርያት፣ ቅዳሴ ማርያም፤ ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፣ ዘጎርጎርዮስ፣
ዘአትናቴዎስ፣ ዘቄርሎስ፣ ዘሠለስቱ ምዕት፣ ዘባስልዮስ፣ ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ዘኤጲፋንዮስ፣
ዘዲዮስቆሮስ፣ ዘያዕቆብ ዘስሩግ፣ ዘጎርጎርዮስ ካልዕ በመባል የሚታወቁ ናቸው፡፡

ቅዳሴ ሐዋርያት በውስጡ ምሥጋናና ልመና፣ ብዙዎች ትእዛዛትም በብዛት የሚገኙበት


ቅዳሴ ነው፡፡ ሌሎቹን ቅዳሴያት ለማጥናት እንደመሠረት የሚሆን በመሆኑ ለምሳሌነት
(ለማሳያነት) ተመርጧል፡፡ ሌሎቹ ጥቂት ለውጥ ወይም ጭማሬ ከሚኖርባቸው በቀር በዚህ
መሠረትነት የሚጓዙ ናቸው፡፡ ቅዳሴውን አባቶቻችን ሐዋርያት እንደ አንድ ልብ መካሪ፣
እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው የተናገሩት፣ ያመሰገኑት ምሥጋና፤ የለመኑትም ልመና
(ጸሎት) ነው፡፡ አስተጋባዒው (አደራጅቶ የጻፈው) ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ነው፡፡
ሲጀምርም “አኰቴተ ቁርባን ዘአበዊነ ሐዋርያት በረከተ ጸሎቶሙ የሃሉ ምስለ ፍቁሮሙ
(እገሌ) ለዓለመ ዓለም” ይላል፡፡ ትርጉሙም “ከልመናቸው የተነሣ የሚገኝ በረከታቸው
ይደርብንና ካህናት ሥጋውን በጻሐል፣ ደሙን በጽዋዕ አድርገው ወደ መንበር
የሚያቀርቡት አኰቴት፣ የሚለውጡት፣ የሚያከብሩት፤ አንድም በክብር በባለሟልነት ወደ
እግዚአብሔር የሚያቀርብ፤ አንድም የሚቀበሉት የሚያቀብሉት አኰቴት ፲፪ቱ ሐዋርያት
የተናገሩት ቅዳሴ ይህ ነው፡፡” የሚል ነው፡፡

ይ.ካ፡- እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ /እግዚአብሔር አድሮባችሁ ይኑር/፤

ይ.ሕ፡- ምስለ መንፈስከ /እንደቃልህ ይደረግልን (ከመንፈስህ ጋር)/፤

ይ.ካ፡- አእኩትዎ ለአምላክነ /ፈጣሪያችንን አመስግኑት/፤

ይ.ሕ፡- ርቱዕ ይደሉ /ምስጋናው እውነት ነው፤ ይገባል፡፡/፤

66
ይ.ካ፡- ነአኵተከ እግዚኦ በፍቁር ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ፤ አቤቱ ልጅህ ወዳጅህ ኢየሱስ
ክርስቶስ ለምስጋናው አብነት ሁኖን፣ በልጅህ በወዳጅህ ባደረግኸው ቸርነት
እናመሰግንሃለን፡፡”

የፍሬ ቅዳሴ ውስጣዊ ክፍሎች በአጫጭሩ

ጸሎተ አስተብቍዖት
ይህ የጸሎት ክፍል “ጸሎተ አስተቍዖት፤ የምልጃ ጸሎት” ይባላል፡፡ ይህም ፍሬ ቅዳሴ
እንደተጀመረ አብሮ ይጀምራል፡፡

ይ.ዲ፡- “በእንተ ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ (እገሌ)፤ ንዑድ፣ ክቡር ስለሚሆን
ስለ ሊቀ ጳጳሱ አባ (እገሌ)” በማለት በጊዜው የተሰየመውን ፓትርያርክ ስም አስገብቶ
ይጸልያል፤ ይማጸናል፡፡ በዚህ ክፍል አሁን በቤተ ክርስቲያን በአገልግሎት ላይ (በአጸደ
ሥጋ) ካሉት ጀምሮ እመቤታችንን፣ ወንጌላውያንን፣ ሐዋርያትን፣ አርድዕትን አንድ ባንድ
እያነሣ፤ ቅዱስ እስጢፋኖስን፣ ካህኑ ዘካርያስን፣ መጥምቁ ዮሐንስን…. በአጸደ ነፍስ ካሉ
ቅዱሳን ዋና ዋናዎቹን ስማቸውን እየጠራ “ስለነሱ ብለህ ማረን” እያለ ይማጸናል፤
ይማልዳል፡፡ በዚህ ወቅት በቤተ ክርስቲያን የኖሩትንና ያረፉትን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ
ክርስቲያን ታላቅ ሥራ የሠሩትን አባቶች ሁሉ በጸሎት ያስታውሳቸዋል፡፡

ጸሎተ ቡራኬ
ይህ የቡራኬ ጸሎት ነው፡፡ ንፍቁ ካህን ቅዱስ ባስልዮስ የተናገረውን የቡራኬ ጸሎት
ይጸልያል፡፡ ሠራኢው ካህን ደግሞ ንፍቁ ካህን “ባርክ” በሚልበት ጊዜ በሕዝቡና
በሚጠራው ሁሉ ላይ ይባርካል፡፡ በዚህም ቡራኬና ጸሎት የሚደረግላቸው ሕዝቡ፣ ቤተ
ክርስቲያን፣ ሕሙማን፣ መንገደኞች፣ ነጋዴዎች፣ ነፋሳተ ሰማይ፣ ዝናማት፣ የምድር ፍሬ፣
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ነገሥታትና የሀገር መሪዎች፣ ነፍሳተ ሙታን፣ ለቤተ
ክርስቲያን መባዐ የሚሰጡ፣ የተጨነቁ ነፍሳት (ሰውነት)፣ እስረኞች (ታራሚዎች)፣ በጽኑ
አገዛዝ (በምርኰ) የተያዙ፣ የተሰደዱ (ስደተኞች)፣ በጸሎታችሁ አስቡን ብለው የተማጸኑ
ምእመናንና አገልጋይ ካህናቱ ሁሉ ናቸው፡፡

ዲያቆኑም “መሐሮሙ እግዚኦ ወተሠሃሎሙ ለሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣


ቀሳውስት ወዲያቆናት ወኵሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን-ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣
ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትንና ምእመናንንም ሁሉ ማራቸው፤ እዘንላቸው፤ ይቅርም በላቸው፡፡”
ይላል፡፡ ካህኑም የጠራቸውንና ያልጠራቸውን ሁሉንም ባንድነት እግዚአብሔር ያረፉትን
እንዲምራቸው ያሉትን እንዲጠብቃቸው ይማፀናል፡፡

ከዚህ በመቀጠል ዲያቆኑ ምእመናኑን ደግሞ ደጋግሞ ያነቃቸዋል፡፡ በቅዳሴ ጊዜ


የተቀመጡ ካሉ እንዲነሡ ያሳስባቸዋል፡፡ የዚህም ምሥጢሩ ሕሊናቸው በሌላ ዐሳብ
የተያዘና ከቆሙበት መንፈሳዊ ዓላማ የራቁ ካሉ ወደ ኅሊናቸው እንዲመለሱ፣ ነቅተው
ቅዳሴውን እንዲከታተሉና ለቅዱስ ቁርባን እንዲዘጋጁ ማድረግ ነው፡፡ ከዚያም
67
“ወደምሥራቅ ተመልከቱ” ይላቸዋል፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት
ምሥራቅ ማኅደረ እግዚአብሔር፤ ምዕራብ ደግሞ ማኅደረ ዲያብሎስ ስለሆነ ነው፡፡
“ከሰይጣንና ከሰይጣናዊ አስተሳሰብ ተለይታችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመልከቱ” ሲል ነው፡፡
በሌላ መንገድም “ምሥራቃዊት በሆነች ወንጌል፤ ምሥራቃውያን ሰብአ ሰገል ባመኑባት
ወንጌል (ባመኑበት ጌታ) እመኑ” ማለቱ ነው፡፡ እንደገናም “ሕማመ ክርስቶስን፣ ሞተ
ክርስቶስን፣ መስቀለ ክርስቶስን እያሰባችሁ ኑሩ” ማለት ነው፡፡

የተከበሩ አንባቢ ሆይ ጥቂት ደቂቃዎችን ተጠቅመው ለሚከተሉት ጥያቄዎች


መልስ ለመስጠት ይሞክሩ::

❖ የሰጎን ዕንቁላል ከቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በመስቀሉ ዙሪያ የሚደረገው ለምን


ይመስልዎታል?
❖ ይህ ምልክት ከያዝነው ርእሰ ጉዳይ ጋር የሚያገናኘው ነጥብ ይኖራል ብለው
ያስባሉ? ካለ ምንድነው?

በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት የሰጎን እንቁላል በቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ


ሲደረግ ነው የኖረው፡፡ አሁን አሁን የሰጎን እንቁላል ማግኘት ስለማይቻል ምልክቱን
በጥንትና በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጉልላት ላይ ብቻ ለማየት ተገደናል፡፡ ምሥጢሩም
(ምሳሌያዊ ትርጉሙም) የሚከተለውን ይመስላል ሰጎን እንቁላሏን በአሸዋ ውስጥ ቀብራ
እንዲፈለፈል የምታደርገው ትክ ብ፣ላ በማየት ነው፡፡ ለአፍታ እንኳን ማየቷን ካቋረጠች
ይለወጥባታል፤ ማለት ይበላሽና አይፈለፈልላትም፡፡ ምግቧን ለመፈለግ እንኳን ወንዱን
ተክታ ነው፡፡ የዚህም ምሳሌነቱ ምእመናንም ጉልላቱ ላይ በክብር የተቀመጠውንና በሰጎን
ዕንቁላል የተከበበውን መስቀል በዓይነ ሥጋ፤ በላዩ ላይ ተሰቅሎ ዓለሙን ያዳነውን ጌታ
ክርስቶስን በዓይነ ኀሊና እንደያዩ ያሳስባል፡፡ ከመስቀሉ ዓይናቸውን የሚነቅሉ /የሚያነሡ/
ሁሉ መፈልፈል እንደማይችለው የሰጎን እንቁላል ሕይወት እንደማይኖራቸው ያጠይቃል፡፡
በሕይወት ይኖሩ ዘንድም መስቀሉን እያሰቡ፣ በመስቀሉም እየተባረኩና ለመስቀሉ የፀጋ
ስግደት እየሰገዱ እንዲማፀኑበት ያመለክታል::

ዲያቆኑ “እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ የተቀመጣችሁ ተነሡ፤” ካለ ጊዜ ጀምሮ ሠራኢው ካህን


“ለከ ንሰግድ ለዘይቀውሙ ቅድሜከ አዕላፈ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት ቅዱሳን
መላእክት፤ ብዙ፣ የብዙ ብዙ የሚሆኑ ክቡራን መላእክት፣ ክንፋቸው ፮ የሚሆን ኪሩቤልና
ሱራፌል ከፊትህ ለሚቆሙልህ ላንተ እንሰግድልሃለን፤” “እያለ የሥላሴን ክብር፣
የሠራዊቱንም ተፈጥሮና አገልግሎት እየመሰከረ ይጓዛል፡፡ በዚህ ልዑል ምስክርነት ወቅት
አሁንም ዲያቆኑ ምእመናንን ማንቃቱን ይቀጥላል፡፡ “ንነጽር፤ ይህን (ምስክርነቱን)
እናስተውል” ይላል፡፡ ካህኑ የቅዱሳን መላእክቱን የማያቋርጥ ምሥጋና ገልጾ “እኛም ከነሱ
68
ጋር፤ (እንደነሱ) እናመሰግንሃለን” ይላል፡፡ ከዚያም “ዓዲ ተወከፍ ዘዚአነሂ ቅዳሴ፤
የመላእክትን ምስጋና እንደተቀበልህላቸው እኛም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ
እግዚአብሔር…እያልን የምናቀርብልህን ምስጋና (ጸሎት) ተቀበልልን፤” በማለት
ይማፀናል፡፡

ዲያቆኑም በዚህ ጊዜ “አውስኡ፤ ካህኑ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ… ብሎ እንዳመሰገነ እናንተም


አመስግኑ (ተሰጥዎውን መልሱ)” ይላል፡፡ የዚህን ጊዜ ሕዝቡም የዲያቆኑን ትእዛዝ
ተቀብሎ “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ…” የሚለውን ምስጋና ያቀርባል፡፡ ይህን ምስጋና
በመጀመሪያ ለእግዚአብሔር ያቀረቡት ቅዱሳን መላእክት ለመሆናቸው በቅዱሳት
መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ (ኢሳ. ፮፥፩-፬፡፡ ራእ. ፬፥፰፡፡) በዚህም መሠረት
በቅዳሴው ጸሎት በሰዓታትና በማኅሌት እንዲሁም በኪዳን “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ
እግዚአብሔር” ስንል ከመላእክት ማኀበር ምስጋና ጋር መተባበራችንን የምንረዳበትና
የምንመሰክርበት መሆኑን መረዳት ይገባል::

ሠራኢው ካህን ከዚያ አያይዞ ከርደቱ ጀምሮ እየተረከና ስለወልደ እግዚአብሔር ሰው


መሆን እየመሰከረ ምሥጢረ ሥጋዌን እያብራራ ያመሰግናል፡፡ ሕዝቡም “ተዘከረነ እግዚኦ
በውስተ መንግሥትከ፤ ኋላ በጌትነትህ ለጻድቃን ልትፈርድላቸው፣ በኃጥአንም
ልትፈርድባቸው በምትመጣ ጊዜ አንድም በመንግሥተ ሰማያት አስበን፤” እያሉ
ይማፀናሉ፡፡

የተከበሩ የዚህ መጽሐፍ አንባቢ ሆይ:-ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የሚከተሉትን ጥያቄዎች


ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ ከሰው ልጆች መካከል ይህን ልመና ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረበው ማነው?

❖ የትና መቼ ነው ያቀረበው?

❖ ለልመናው ማን፣ ምን ዓይነት መልስ ሰጠው?

“ተዘከረነ” የሚለውን ጸሎት ካህኑና ሕዝቡ እየተቀባበሉ ሲጸልዩ ንፍቁ ካህን ደግሞ ዕጣን
ያሳርጋል (ያጥናል)፡፡ ሠራኢው ካህንም የዕጣኑን ጭስ በእጁ እየታፈነ ፫ ጊዜ ከኅብስቱ፣ ፫
ጊዜ ከወይኑ ያደርገዋል /ያሳርጋል/፡፡ይህን ምስጋና ከሰው ልጆች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ
ያቀረበው በክርስቶስ ቀኝ የተሰቀለው ሽፍታ /ፊያታዊ ዘየማን/ ጥጦስ የሚባለው ነው፡፡
ይህም ወንበዴ ተሰቅሎ በታላቅ መከራ ውስጥ እያለ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ
ዐስበን በማለት ለመነው፡፡ ጓደኛው /በግራ የተሰቀለው/ ወንበዴ በክርስቶስ ላይ
በሚሳለቅበት ጊዜ እርሱ አምላክነቱን አምኖ ግሩም ጸሎት አቀረበና ለምእመናን ሁሉ
አብነት ምሳሌ ሆናቸው፡፡ በመከራ ሰዓት ወዴትና እንዴት መጸለይ እንዳለብን አሳየን፡፡
መድኃኔዓለም ክርስቶስም “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ፤”
(ሉቃ፳፫፥፵፪-፵፬፡፡) በማለት የይቅርታ ድምፁን አሰማው፡፡

69
ዲያቆኑ በመቀጠል “አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስት፤ ሠራዒው ካህን ኅብስቱን፣ ንፍቁ ካህን
ማኅፈዱን ለማንሣት እጆቻችሁን አንሡ” በማለት ያሳስባል፡፡ ይህም የትንሣኤ ክርስቶስ
ምሳሌ ነው፡፡ ሠራዒው ካህን ኅብስቱን ከጻሕሉ ላይ ማንሣቱ፡- ክርስቶስ ሞትን ድል
አድርጎ የመነሣቱ፤ ንፍቁ ካህን ማኅፈዱን ማንሣቱ፡- በመቃብር ላይ የተገጠመችውን
ድንጋይ መልአከ እግዚአብሔር የማንከባለሉ ምሳሌ ነው፡፡ በመቀጠልም ካህኑ ክርስቶስ
በተያዘባት በዚያች ዕለት ቀደም ብሎ ኅብስቱንና ወይኑን አክብሮ ሥጋውን ደሙን አድርጎ
መስጠቱን ይመሰክራል፡፡ ሕዝቡም “ነአምን ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን፤ የተነሣው
ይህ እንደሆነ፤ አንድም ይህ አሁን ካህኑ የሚያከብረው ኅብስትና ወይን እንደያኔው
በእውነት በዕለተ ዓርብ የቆረስከውን ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር፣ ያፈሰስከውንም ደመ
ወልደ እግዚአብሔር እንደሆነ እናምናለን” እያለ ሥጋ ወደሙን ደጅ ይጠናል፤
ይጸልያልም፡፡ ሕዝቡም የካህኑን ምስክርነት እያዳመጠ የሃይማኖቱን ማረጋገጫ መስጠቱን
ይቀጥላል፡፡ ካህኑ በቃል የሚናገረው ምስጋናና ጸሎት በድርጊትም የሚገልጠው ምሥጢር
ጠቅላላ የዕለተ ዓርቡን ሕማማተ መስቀል የሚያዘክር (የሚያስብ) ነው፡፡ በማስተዋል
የሚከታተለው ክርስቲያን ቢኖር ክርስቶስ በቀራንዮ በተሰቀለ ጊዜ በቦታው ተገኝቶ
በዓይኖቹ ያየ እስኪመስለው ድረስ ልቡ በሐዘን ጦር ይወጋል፡፡ ሕዝቡ “ንዜኑ ሞተከ
እግዚኦ፣ ወትንሣኤከ ቅድስተ፣ ነአምን ዕርገተከ፣ ወዳግመ ምጽአተከ፣ ንሴብሐከ
ወንትአመነከ፤ አቤቱ ሞትህን፣ ልዩ የሚሆን ትንሣኤህንም እንመሰክራለን (እንናገራለን)፤
ዕርገትህንና ዳግመኛ ዓለምን ለማሳለፍ መምጣትህን እናምናለን፤ አምነንም
እናመሰግንሃለን።” እያሉ ከቄሱ ጋር አብረው ቅድስት የሆነች እምነታቸውን ይመሰክራሉ፡፡

ውላጤ ኅብስት ወወይን


ካህኑ “ይእዜኒ እግዚኦ፣ ንዜከር ሞተከ፣ ወትንሣኤከ ንትአመነከ፤ አቤቱ አምነን ሞትህን
ትንሣኤህን እንናገራለን፡፡ እያመሰገንህ የሞትህ መታሰቢያ የሚሆን ይህን መሥዋዕት
እናቀርብልሃለን፤” እያለ ያመሰግናል፡፡ ከዚህ በኋላ “መሥዋዕቱን (ኅብስቱንና ወይኑን)
ራርተህ ይቅር ብለህ መንፈስ ቅዱስን አሳድርበት፤ ሥጋህና ደምህ ወደመሆን ይለውጣቸው
ዘንድ” እያለ ይለምናል፡፡ በነዚህ ጊዜያትም እማሬና ቡራኬ አለው፡፡ በመቀጠልም “ይረስዮ
ሥጋሁ ወደሞ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ኅብስቱን ለውጦ ሥጋ
መለኰት፣ ወይኑን ለውጦ ደመ መለኰት ያደርገው ዘንድ፤ አንድም የጌታችን
የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ወደ መሆን ይለውጠው”
ይላል፡፡ በዚህም ጊዜ “ሥጋሁ” ሲል “ሥጋውን”፣ “ወደሞ” ሲል ደሙን፣ “ለእግዚእነ” … ሲል
ሁለቱንም አንዳንድ ጊዜ ይባርካል፡፡ ሕዝቡም “አሜን እግዚኦ መሐረነ፣ እግዚኦ መሐከነ
እግዚኦ ተሣሃለነ፤ አሜን በእውነት ይለውጠው፤ አንድም በእውነት ቅዱስ መንፈሱን
ይላክልን (ይስደድልን)፤ አንድም በእውነት ማረን፣ ራራልን፣ ይቅር በለን” ይላሉ፡፡

ዲያቆኑ ከዚሁ ጋር አያይዞ “በኵሉ ልብ ናስተብቁዖ ለእግዚአብሔር አምላክነ ኅብረተ


መንፈስ ቅዱስ ሠናየ ከመ ይጸግወነ፤ በፍጹም ልቡናችን በመንፈስ ቅዱስ አንድ መሆንን
ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው፤ አንድም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ያደርገን
ዘንድ አንድ አድርገን ብለን እንለምነው፤” በማለት ያሳስባል፡፡ ሕዝቡም “በከመ ሀሎ ህልወ
70
ወይሄሉ ለትውልደ ትውልድ ለዓለመ ዓለም፤ በቅድምና የነበረ፤ ዛሬም ያለ፤ ለዘለዓለሙ
የሚኖር እሱ ነው” በማለት ይመሰክራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ሠራዒው ካህን ደሙን ባውራ ጣቱ
ጠምቶ (ነክሮ) በደሙ ሥጋውን ያትማል፡፡ ከላይ ወደታች፣ ከታች ወደላይ፣ ከቀኝ ወደግራ፣
ከግራ ወደቀኝ ያትመዋል፡፡ ይህም ሥጋውን ከደሙ፣ ደሙንም ከሥጋው ጋር አነድ
እንዳደረገው ለማጠየቅ ነው፡፡ አንድም መላእክት በዕለተ ዓርብ ደሙን በጽዋዕ ብርሃን
ተቀብለው ጽንፍ እስከ ጽንፍ ለመርጨታቸው ምሳሌ ነው፡፡

ካህኑ ስለ ምእመናን ሕይወት ጸሎቱን ይቀጥላል፡፡ “ደሚረከ ተሀቦሙ (ሀቦሙ) ለኵሎሙ


ለእለ ይነሥኡ እምኔሁ፤ ለሚቀበሉት ሁሉ ሥጋህን ከደምህ፣ ደምህን ከሥጋህ ጋር አንድ
አድርገህ ስጣቸው” በማለት ተማኅጽኖውን ያቀርባል፡፡ ከዚህ አያይዞም “ሀበነ ንኅበር
በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስ ወፈውሰነ በዝንቱ ጵርስፎራ” ከመ ብከ ንሕየው ዘለኵሉ ዓለም
ወለዓለመ ዓለም፤ ባንተ ህልውና ባለ መንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ አንድ መሆንን
ስጠን፤ አድርግልን፡፡ በዚህ በሥጋ ወደሙ ከደዌ ነፍስ አድነን፡፡ ባንተ ሕያውነት ሕያዋን
ሁነን እንኖር ዘንድ፤ ለዘለዓለም” ብሎ ይጸልያል፡፡ ሕዝቡም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደ ቄሱ
ተሰጥዎውን በመቀበል ጸሎት ያቀርባሉ፡፡

ካህኑ በመቀጠል ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን ጠቅሎ የያዘ ምስክርነትና


ምስጋና ያቀርባል፡፡ “ቡሩክ ስሙ ለእግዚአብሔር፣ ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ
እግዚአብሔር፣ ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ፣ ለይኩን፣ ለይኩን፣ ቡሩከ ለይኩን፤
እግዚአብሔር አብ ክቡር ምስጉን ነው፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ፣ እግዚአብሔር ነኝ
ብሎ የሚመጣ፣ እግዚአብሔር “ይህ የምወደው ልጄ ነው” ብሎ መስክሮለት የሚመጣ ወልድ
ክቡር ምስጉን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም ክቡር ምስጉን ነው፡ ይሁን፣ ይሁን፣ ይደረግ፣
ይጽና፡፡” በማለት ነው በምሥጢር የሚያመሰግነው፡፡ ሕዝቡም ካህኑን ተከትሎ እንደካህኑ
በተመሳሳይ ምሥጢርና ዜማ ያመሰግናል፡፡ እንደገናም ካህኑ “ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ
ላዕሌነ፤ በሥጋ በደሙ ምክንያት መንፈስ ቅዱስን አሳድርብን፡፡” ይላል፡፡ ሕዝቡም
እንደእሱ አብረው ይለምናሉ ያመሰግናሉም፡፡

ጸሎተ ፈትቶ
ይህ ጸሎት ካህኑ ሥጋውን እየፈተተ የሚጸልየው ነው፡፡ ይኸውም፡- “ከወዳጁ ከአልዓዛር
ቤት ግብር አግብቶ ሳለ ለበረከት ካመጡለት ከኅብስቱና ከወይኑ ከፍሎ “ዝ ውእቱ ሥጋየ፤
ዝ ውእቱ ደምየ፤ ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው፡፡” ብሎ አክብሮ ለውጦ ትኩስ ሥጋ
ትኩስ ደም አድርጎ ሰጣቸው፡፡ የፍታቴው ሥርዓትም ከክርስቶስ /ከምሥጢረ ሥጋዌ/ ሙሉ
ጉዞ ጋር የተሰናሰለ ምሳሌነት ያለው ነው፡፡ አሁን በዚህ ቦታና ጊዜ ግን ልንገልጸው
አይቻለንም፡፡ ከዚህ በመቀጠል ዲያቆኑ “ጸልዩ” ብሎ ሲያዝ ሕዝቡ ከካህናቱ ጋር በጋራ
“አቡነ ዘበሰማያት”ን በዜማ ይደግመዋል፡፡ አያይዞም “በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ
በከመ አበሳነ፤ አቤቱ ሥጋህን ደምህን መስጠትህ እንዳንተ እንደቸርነትህ ነው እንጂ እንደ
ኃጢአታችን አይደለም፡፡ እንደ ኃጢአታችንማ ባልተገባንም ነበር፡፡ አንድም
ኃጢአታችንን ይቅር የምትለን እንዳንተ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደኛ እንደ
ኃጢአታችን አይደለም፡፡ እንደ እኛስ እንደ ኃጢአታችን ባልተገባንም ነበር፡፡ አንድም
71
መከራውን የምታመጣብን ቅሉ እንዳንተ እንደቸርነትህ ነው እንጂ፤ እንደኛ እንደ
ኃጢአታችን አይደለም፡፡ እንደ እኛስ እንደ ኃጢአታችን ቢሆን ኖሮ ፈጥኖ፣ በዝቶ
በተደረገብን ነበር፡፡” የሚለውን ጸሎት ሦስት ጊዜ መላልሰው እየተቀባበሉ ያደርሱታል፡፡
ይህም በራሱ ምሥጢረ ሥላሴን ያሳያል፡፡

❖ ከዚህ በላይ የቀረበው ሥርዓተ ጸሎት ምሥጢረ ሥላሴን እንዴት ሊገልጽልን


ይችላል ብለው ያስባሉ?

“አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይደለም፤” የሚለው ሦስት


ጊዜ መደጋገሙ እግዚአብሔር በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት መሆኑን ሲያመለክት፤
የምስጋናው ቃል /ዐረፍተ ነገሩ/ እና ምሥጢሩ አንድ ዓይነት መሆኑ በመለኮት፣ በባሕርይ፣
በህልውና አንድ መሆኑን በማመልከት ምሥጢረ ሥላሴን ያስተምራል ማለት ነው

ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው ምስጋናና ጸሎት “ሠራዊት” ይባላል፡፡ “ሠራዊተ መላእክቲሁ”


በማለት ይጀምራልና፡፡ ካህናቱ (ልዑካኑ) ይህን ሲያቀርቡም ከመንጦላዕት በአፍአ፣
(በውጪ) ከመንጦላዕት በውስጥ ሆነው ነው፡፡ ንፍቅ ካህንና ንፍቅ ዲያቆን በአፍአ (በውጪ)
ይሆናሉ፤ ምሳሌነታቸውም የነቢያት ነው፡፡ ሠራዒው ካህን፣ ሠራዒው ዲያቆንና አብሪ ካህን
(ዲያቆን) ደግሞ በውስጥ ይሆናሉ፡፡ ምሳሌነታቸውም የሐዋርያት ነው፡፡ ምስጋናውም
የሚከተለውን ይመስላል፡፡

• ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔዓለም ዬ ዬ ዬ ይቀውሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔዓለም።

-የመድኃኔዓለም አገልጋዮች ሠራዊተ መላእክት ወዮ ወዮ ወዮ ከሞት ደረስህ እያሉ


ከፊቱ ይቆማሉ።

• ወይኬልልዎ ለመድኃኔዓለም ዬ ዬ ዬ ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔዓለም

-መላእክት የሚጋርዱት፣ የሚያመሰግኑት የመድኃኔዓለም ሥጋውና ደሙ ይህ ነው፡፡


እያመሰገኑ ከፊቱ ቆመው ይጋርዳሉ፤ ወዮ ወዮ ወዮ ከሞት ደረስህ እያሉ
ያመሰግናሉ፡፡

• ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔዓለም ዬ ዬ ዬ በአሚነ ዚአሁ ለክርስቶስ ንገኒ


/ሐዋርያት ተለዉ አሠሮ/፤

-መላእክት ከፊቱ እንደሚቆሙ ከፊቱ እንቆም ዘንድ፣መላእክት በቧለሟልነት


እንዲያመሰግኑት እናመሰግነው ዘንድ ወዮ ወዮ ወዮ ከሞት ደረስህ እያልን ወደሱ
እንቅረብ፤ እሱን በማመን ጸንተን በጸሎት በአምልኮት ለክርስቶስ

72
እንገዛለን፡፡/ሐዋርያት በሱ አምነው ቤታቸውን፣ ንብረታቸውን ጥለው
እንደተከተሉት፤ አንድም በመስቀል ተሰቅለው እንደመሰሉት እንመስለው ዘንድ፡፡/

ንፍቅ ዲያቆን ከመንጦላዕት (ከመጋረጃ) በአፍአ ነበርና ወደ ውስጥ ለመግባት “አርኅዉ


ኆኃተ መኳንንት፤ አናጉስጢሳውያን ደጆችን (በሮችን) ክፈቱ” ይላል፡፡ የአናጉስጢሳውያን
መዓርግ በመኳንንት ይመሰላልና፡፡ የመንጦላዕት መገለጥ የበሮችም መከፈት ምሥጢሩ
ግን ጌታችንን ሁሉ እንዲያየው ብለው በገበያ ቀን ሰቅለውት ነበርና የዚያ ምሳሌ ነው፡፡
ሠራዒው ዲያቆን ደግሞ ከውስጥ ሆኖ “እለ ትቀውሙ አትሕቱ ርእሰክሙ፤ ከዚህ
የቆማችሁ ርእሰ ልቡናችሁ ዝቅ ዝቅ አድርጉ፤ አንድም ልቡናችሁን ከትዕቢት አዋርዱ፡፡”
ይላል፡፡ ይህም ዝቅ ዝቅ ማለት የአካል ሳይሆን የሕሊና ነው፡፡

❖ ለጥቂት ደቂቃዎች ወደ ኋላ ሄደው ያስታውሱ! በምያስቀድሱበት ጊዜ


እዚህኛው የምስጋና ሰዓት ሲደርሱ እንዴት ነበር የዲያቆኑን ዐዋጅ
የሚፈጽሙት? ወደፊትስ?

በተገለጸው መሠረት ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ ለሚያደርጉት ምእመናን ሠራዒው ካህን


“እግዚአብሔር ዘለዓለም ማዕምር ዘኅቡዕ ወዘገሀድ ቅድሜከ አትሐቱ ርእሶሙ ሕዝብከ
ወለከ አግረሩ ቀፈተ ልብ ዘሥጋ፤ ርኢ ዘእምድልው ማኅደርከ፤ ባርክ ኪያሆሙ ወኪያሆን፤
አጽምፅ ሎሙ ዕዝነከ ወስምዖሙ ጸሎቶሙ፤ አጽንዕ በኃይለ የማንከ፤ ክድን ወርዳዕ
እምሕመሜ እኩይ፤ ዓቃቤ ሎሙ ኩን ለሥጋነሂ ወለነፍስነሂ፤ ወስክ ሎሙሂ ወሎንሂ
ሃይማኖተከ ወፈሪሆተ ስምከ በ፩ዱ ወልድከ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ
ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም፡፡

አቤቱ ቅድመ ዓለም የነበርህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር፤ የተሰወረውንና የተገለጸውን


(ረቂቁን ግዙፉን) አንድም ቅድመ ዓለም የነበረውን፣ ድኅረ ዓለም ያለውን የምታውቅ፤
ርእሰ ልቡናቸውን ዝቅ ዝቅ ያደረጉ ወገኖችህን፣ ልቡናቸውን ከትዕቢት ያዋረዱትን፣
ከጽርሐ አርያም ሁነህ (ከማደሪያህ ሁነህ) ጠብቃቸው፡፡ ወንዶቹንም ሴቶቹንም በረከተ
ሥጋ፣ በረከተ ነፍስ ሰጥተህ አክብር፡፡ ልመናቸውን ፈጥነህ ስማቸው፤ ኃይልን
በምትገልጽበት ሥልጣንህ አጽናቸው፤ ከመከራ ጠብቃቸው፤ ከደዌ ነፍስ፣ ከክፉ ነገር
አድናቸው፡፡ ለሥጋችንም ለነፍሳችንም ዓቃቤ ሥራይ ዘነፍስ (የነፍስ ሐኪም) ሁነን፤
ለወንዶቹም ለሴቶቹም ሃይማኖተ ሰሚዕን ከሃይማኖተ ርዕይ አድርስልን፡፡ አንተን
መፍራትን አሳድርብን፡፡ …” በማለት ይጸልይላቸዋል፡፡

የተከበሩ የዚህ ጽሑፍ ተከታታይ፦

❖ ይህ ጸሎትና በረከቱ ይደርሰን ዘንድ በቅዳሴ ጊዜ እንዴት ባለ ሰብእና


መቆምና ማስቀደስ ይኖርብናል ይላሉ?

73
ዲያቆኑ፦ “ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት፤ በፈሪሃ እግዚአብሔር ሁናችሁ ስገዱ፡፡”
ይላል፡፡ ጸሎተ ንስሐ ሊደገምላቸው ስለሆነ ሰግደው እንዲያስደግሙ እያዘዛቸው ነው፡፡
አስቀድሞ ፍትሐት ዘወልድንና በእንተ ቅድሳትን ወድቀው እንዳስደገሙ፡፡ ሕዝቡም
“ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ፤ አቤቱ ወድቀን (ሰግደን) እናመሰግንሃለን፤
(እያመሰገንህ እንሰግዳለን)፤” እያሉ ይሰግዳሉ፡፡

ጸሎተ ንስሐ
ዲያቆኑ፦ ስገዱ ካለና ሕዝቡም ከሰገዱ በኋላ ሠራዒው ቄስ (ካህን) ጸሎተ ንስሐ
ይደግምላቸዋል። ከዚህ ጸሎት የሚገኝ ጥቅም ብዙ ነው፡፡ ጸሎቱ “በደልን፣ ተመለስንም”
ላሉ ሁሉ የሚጸለይ ነው። ስለዚህም ጸሎቱ መናዘዣ ነው። ተናጋሪውም ቅዱስ ባስልዮስ
ነው። “እኔ ከንሰሐ ሕይወት ውጪ ነኝ” ብሎ ወድቆ (ሰግዶ) የማያስደግም ምእመንም ሆነ
ካህን ሊኖር አይችልም።

የተከበሩ አንባቢ ሆይ የሚከተለውን ጥያቄ በማስተዋል ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ በንስሐ ጸሎት የተካተቱ ዐበይት ቁም ነገሮች ምንድናቸው ?

ጸሎተ ንስሐ በይዘቱ በርካታ መንፈሳዊ ቁም ነገሮችን የያዘ ነው አጠር አድርገን


እንደሚከተለው ማየት እንችላለን ምሥጢረ ሥላሴና ምሥጢረ ሥጋዌን በተመለከተ፣
ኃጢአትን የሚደመስስ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን፣ ለሐዋርያት (ለካህናት) የማሰርና
የመፍታት ሥልጣን እንደተሰጣቸው፣ በቅ/ ጴጥሮስ መሠረትነት (የምስክር ቃል) ላይ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለመመሥረቷ፣ ስለ ራሱና (ሠራኢው ካህን) ስለሁሉም ሥርዓተ
ኃጢአት ልመና፣ ስለ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ስለ ጳጳሳቱ፣ ስለ ልዑካኑ፣ ስለ ሀገር መሪዎች፣
ስለ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ስለ መነኮሳት፣ ረዳት ስለሌላቸው፣ ስለ ምዕመናንም ሁሉ
የሚቀርብ ማሳሰቢያ፤ በቀናች ሃይማኖት ሆነው ስላረፉ ነፍሳተ ሙታን ሥርየት የሚቀርብ
ልመና፣ ከኃጢአት፣ ከክህደት፣ በሐሰት ከመማል፣ ሃይማኖት ከመለወጥ፣ ከሰይጣንና
ከሥራዎቹ ስለመራቅና ፈርሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ ስለማድረግ፣ ሰማያዊውን መንግሥተ
እግዚአብሔር ተስፋ ስለማድረግ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በመሐሉም ፊቱን ወደ
ምዕራብ (ሕዝቡ) መልሶ ሦስት ጊዜ ይባርካቸዋል።

ካህኑ ጸሎተ ንስሐ ከደገመ በኋላ ዲያቆኑ “ነጽር፤ አስተውል” ይላል ካህኑም “ቅዱሳት
ለቅዱሳን፤ ሥጋ ወደሙ የተሰጠ ከኃጢአት ለነጹ ለበቁ ነው፤ በቅቻለሁ የሚል ይምጣ
ይቀበል።” በማለት ያውጃል ፡፡ሕዝቡም “አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ
ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ይመልሳል።

ይህን ጽሑፍ በመከታተል ላይ የሚገኙ የተከበሩ አንባቢ ሆይ አሁን ደግሞ የሚከተሉትን


ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ “ቅዱሳት ለቅዱሳን፤ የተቀደሰው ለተቀደሱ ነው፡፡” የሚለው የካህኑ ዐዋጅ ምእመናን


ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዳይቀርቡ ይከለክላልን?
74
❖ የሕዝቡ ምስክርነት (ተሰጥዖ) ምን ማለት ነው?

ሥጋውና ደሙ የተቀደሰ የሕይወት ምግብ በመሆኑ ራሳቸውን በንስሐ አዘጋጅተው


የሚቀበሉትን ሁሉ ይቀድሳቸዋል፡፡ “የተቀደሰው ሥጋውና ደሙ ለቅዱሳን ነው‹” ማለት
“ሥጋውና ደሙን መቀበል የሚችሉት ንስሐ የገቡ ናቸው፡፡” ማለት ነው፡፡ ንስሐ ኃጥኡን
ፈጽሞ ስለሚያነጻው መላ ሰውነቱ የተቀደሰና ለሥጋ ወደሙ የተገባ ይሆናል፡፡ ኃይለ ቃሉ
ንስሐ ሳይገባ ማንም በድፍረት ወደ ምሥጢረ ቁርባን እንዳይቀርብና እንዳይጎዳ
የሚጠብቅ እንጂ አስፈራርቶ የሚያባርር አይደለም፡፡ ሕዝቡም በባሕርይ በህልውና ከወልድ
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሚሆን ወልድ ንጹሕ ነው፤ ካልነጹ አያድርም፤ ሲሉ ነው
የሚመሰክሩት፡፡ “ካልነጹ” ሲልም “ንስሐ ካልገቡ፤ ሥጋ ወደሙ ቢቀበሉት አይጠቅምም፤
አይዋሐድም፤ እግዚአብሔርም በዚያ ሰው አያድርም፤” ማለት ነው

ሠራዒው ካህን “እግዚአብሔር ምስለ ኩልክሙ” እግዚአብሔር አድሮባችሁ ይኑር።” ይላል


ሕዝቡም “ምስለ መንፈስከ፤ እንደ ቃልህ ይደረግልን፤ (ከመንፈስህ ጋራ)፤” በማለት
ይመልሳሉ። ከዚያም ሠራዒው ካህን መላውን ኅብስት በእጁ ከፍ አድርጎ ይዞ (የዕርገቱ
ምሳሌ ነው።) “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ፤ አቤቱ ክርስቶስ ማረን፣ እዘንልን፣ ይቅር በለን፣”
የሚለውን ጸሎት በዐቢይ ዜማ ፳፩ ጊዜ ይጸልያል። ሕዝቡም በተመሳሳይ ዜማ ፳ ጊዜ
በመቀበል ይማጸናሉ፤ በድምሩ ፵፩ ጊዜ ይሆናል።

በመቀጠል ዲያቆኑ “እለ ውስተ ንስሐ ሀለውክሙ አትሕቱ ርእሰክሙ፤ በደልን፤ ተመለሰን
በማለት ያላችሁ ርእሰ ልቡናችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ፤” በማለት በድጋሚ ያዝዛል። ካህኑም
እግዚአብሔር ልቡናቸውን ያዋረዱትን ሁሉ እንዲምራቸው ይጸልይላቸዋል።

ምስክርነት
ሠራዒው ካህን በዚህ ክፍለ ጸሎት ስለ ምሥጢረ ተዋሕዶ (ሥጋዌ) በተለይም ስለ ቅዱስ
ሥጋውና ደሙ የሃይማኖት ምስክርነት ያቀርባል። በዚህ ምስክርነትም እማሬዎች አሉበት።
ምስክርነቱም ፦

• ንጹሕ የክርስቶስ (አማኑኤል) ሥጋና ደም መሆኑን ፣

• ለሚቀበሉት የኃጢአት ማሥተስረያ፣ ሕይወተ ሥጋና ሕይወተ ነፍስ እንደሚሆን፣

• ሥጋው ከደሙ፣ ደሙም ከሥጋው ጋር አንድ መሆኑን፣

• ይህ ሥጋና ደም ንዕድ ክብርት ከምትሆን ከእመቤታችን የነሳው የጌታ ሥጋውና


ደሙ እንደሆነ፣

• ከባሕርየ መለኮቱ ጋር አንድ ያደረገው ሥጋና ደም መሆኑን፣

• የሥጋና የመለኮት ተዋሕዶ ያለመቀላቀል (ያለመጣፋት)፣ ያለመለወጥ፣ ያለ መለየት


እንደሆነ፣

75
• ክርስቶስ ወዶና ፈቅዶ በጲላጦስ ፊት በእውነት (ለእምነት) የመሰከረ ስለመሆኑ፣

• ለሕማም ለሞት የተሰጠልን ክርስቶስ ለኛ ሕይወት መድኃኒት አድርጎ ሥጋውን


ደሙን የሰጠን መሆኑን “አምናለሁ፤ አምናለሁ፤አምናለሁ፤ በእውነት፤ እታመናለሁ”
የሚል ነው።

ምእመናንም (ካህናትም ጭምር) እንደ ካህኑ “አሜን፣ አሜን ፣አሜን ፤ነአምን” በማለት
ሃይማኖታዊ ምስክርነታቸውን በተመሳሳይ ሁኔታ ይሰጣሉ።

ውድ አንባቢ ሆይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ “ክርስቲያን ሁሉ አስቀዳሽ፣ አስቀዳሽም ሁሉ ቆራቢ ነው፤” በሚለው አባባል


ይስማማሉ? እንዴት? ለምን?

❖ ከላይኛው አሳብ ድምዳሜ አኳያ ወቅታዊው የቅዳሴና የምሥጢር ቁርባን


ሕይወትዎ ምን ይመስላል? ወደ ፊትስ እንዴት መጓዝ አስበዋል?

❖ በቀራኒዮ ክርስቶስ የቆረሰው ሥጋ ፣ያፈሰሰውም ደም በዚህ ቅዳሴ ከከበረው ሥጋና


ደም ጋር ያለው አንድነትና ልዩነት ምንድነው?

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሥርዓት መሠረት


ክርስቲያን ሁሉ በተለይ በሰንበትና በዐበይት በዓላት ሊያስቀድስ፤ ያስቀደሰም ሁሉ
ቅዱስ የሆነውን ቁርባን ሊቀበል ይገባዋል፡፡ በዚህ ዓለም እንኳን ወደ ድግስ ወይም
ግብዣ ቦታ የሄደ ሰው ከተዘጋጀው መብልና መጠጥ ሳይሳተፍ /ሳይበላና ሳይጠጣ/
አይመለስም፡፡ ሳይመገብ ቢመለስ ግን ከባለ ድግሱ ጋር መጣላቱ አይቀሬ ነው፡፡
እንደዚሁም ሁሉ መንፈሳዊው የሕይወት ምግብ ዘወትር የሚዘጋጅባት ቅድስት ቤተ
ክርስቲያንም ዘላለማዊ ሕይወት የሚያድለውን ፍሪዳ አርዳ አወራርዳ የወይን
ጠጇንም ቀድታ በቅዳሴ ጊዜያት ሁሉ ትጋብዘናለች፡፡ የድግሱ ባለቤት
እግዚአብሔር ስለሆነ ይህንን የሕይወት ምግብ ሳይመገብ የሚመለስ ክርስቲያን
ቢኖር ከፈጣሪው ጋር መጣላቱ አይቀሬ ነው፡፡

ካህናት በቅዳሴ የሚያከብሩት ሥጋና ደም በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ከቆረሰው


ሥጋውና ካፈሰሰው ደሙ ጋር ፍጹም አንድ መሆኑን የነገረን ራሱ ክርስቶስ ነው፤፤
በስቅለቱ ዋዜማ በዕለተ ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ሲመሠርት “ሲበሉም ጌታችን
ኢየሱስ ኅብስቱንአንስቶ፣ ባረከ፤ ቈረሰ፤ ለደቀ መዛሙርቱም “ይህ ሥጋዬ ነው እንኩ
ብሉ” ብሎ ሰጠ፡፡ ጽዋዉንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው፤ እንዲህም አለ፣ “ሁላችሁ ከእርሱ
ጠጡ፡፡ ኀጢአትን ለማሥተሰረይ፤ ስለ ብዙዎች የሚፈስ፣ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡” (ማቴ.26፡26-29) ይህ
የሚያሳየን በቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለት የሚቀርበው ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከቆረሰው ቅዱስ ሥጋና
ካፈሰሰው ከቡር ደም ጋር ፈጽሞ ተመሳሳይ መሆኑን ነው፡፡

ለቁርባን መዘጋጀት

76
ከዚህ ቀጥሎ ያለው የቅዳሴ ክፍል ያስቀደሰ ሁሉ ቁርባን ለመቀበል የሚዘጋጅበት ክፍል
ነው። ካህኑ “እግዚአብሔር አምላኪየ ናሁ ሥጋ ወልድከ መሥዋዕት ዘያሠምረከ፤ ፈጣሪዬ
እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያሰኝህ መሥዋዕት የልጅህ ሥጋ እነሆ” በማለት ይጀምርና
ኃጢአቱን (የራሱን)ይቅር ይልለት ዘንድ ሥጋ ወደሙን እያማፀነ ይጸልያል። ከዚህ
በማያያዝ ምእመናንም ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላቸው በፊት ሊጸልዩት የሚገባ ጸሎት
ይደገማል ።”ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አኮ ዘይደልወኒ ትባዕ ታሕተ ጠፈረ ቤትየ
ርኩስት፤ አቤቱ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥በኃጢአት በተታታ ሰውነቴ ማደር
የሚገባህ አይደለም”። የሚለውን ጸሎት ምእመናን እየደገሙ ይቀበላሉ።

በጊዜ ቁርባን ቆራብያን የሚያቀርቡት ቀሪው የጸሎት ክፍልም የሚከተለውን ይመስላል።

“አሳዝኜሃለሁና፤ በፊትህ ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና፤ በምሳሌህና በአርአያህ የፈጠርኸውን


ሰውነቴን ሕግህን በማፍረስ በኃጢአት አሳድፌያለሁ። በጎ ሥራም የለኝም። ነገር ግን
ስለፈጠርኸኝ፣ እኔን ለማዳን ሰው ስለሆንህ፤ አንድም ሰው ሆነህ ስላዳንኸኝ፣ ክቡር ስለሆነ
ስለ ስቅለትህ /መስቀልህ/፣ ስለ ሞትህ፣ በሦስተኛው ቀን ስለተነሣህ /ስለመነሣትህ/
እለምንሃለሁ። አቤቱ ከኃጢአት፣ ከመርገም፣ ከክህደት ታድነኝ፣ ታነጻኝ ዘንድ አድነኝ፥
አንጻኝ ብዬ እለምንሃለሁ፤ እማልድሃለሁ። ሥጋህን ደምህን በተቀበልሁ ጊዜ መወቀሻ፥
መከሰሻ አይሁንብኝ፤ የሚፈርድብኝም አይሁን፤ ወደ እኔ ኑ!” ከሚባሉት ጋር ይደምረኝ
እንጂ። በሥጋው በደሙም ኃጢአቴን አስተሥርይልኝ፤ ሕይወተ ነፍስንም ስጠኝ። አቤቱ
የድኅነት መገኛ በወለደችህ፥ ንዕድ፥ ክብርት፥ በነፍስ በሥጋ ድንግል በምትሆን
በእመቤታችን አማላጅነት፤ በመጥምቁ ዮሐንስ አማላጅነት፤ ንዑዳን ክቡራን በሚሆኑ
በመላእክት አማላጅነት፤ ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃን፣ በሰማዕታት አማላጅነት ሥጋህን
ደምህን ስጠኝ (እንድቀበል ፍቀድልኝ)። ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን!

ውድ አንባቢ ሆይ በቅድሚያ መጽሐፍ ቅዱስ ያዘጋጁና የሚከተሉትን ጥያቄዎች


ለመመለስ ጥረት ያድርጉ።

❖ ይህ ጸሎት በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፰ ላይ ካለው ኃይለ ቃል ጋር


ያለው አንድነት ምንድነው?

❖ ትሕትና፣ ተአምኖ ኃጣውእ፣ ምልጃ፣ ነገረ መስቀል፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ መላእክት፣
ነገረ ቅዱሳንና ክብረ ሥጋ ወደሙ ከዚህ ጸሎት አንጻር የሚገኙበትን አንቀጽ
ለማዛመድ ይሞክሩ።

ከዚህ በኋላ ቀሪ ጸሎታት ተሟልተው ከቀረቡ በኋላ ሰዓቱ ሲደርስ ከሠራዒው ጀምሮ
ልዑካኑ ካህናቱና ምእመናኑ በየተራቸው ቅዱሱን ቁርባን ይቀበላሉ። ልዑካኑ እንደተቀበሉ
ሃይማኖተ አበው ይነበባል፡፡ ከዚያም ስለ ሥጋውና ደሙ ክብር የተዘጋጀው መልክዐ
ቁርባን በዜማ ይደርሳል። የዚህ ጸሎት መጀመሪያ “ሰላም ለኪ” የሚለው ነው።የቆራቢያን
የአቆራረብ ቅደም ተከተልም እንደሚከተለው ነው፦

• ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ሊቃነ ጳጳሳት ፣ጳጳሳት ፣(ኤጲስ ቆጶሳት)፤


77
• ቀሳውስት ወዲያቆናት፤

• ወንዶች በየመዓርጋቸው፤

• ሴቶች በየክብራቸው፤

• በ፵ እና በ፹ ቀናቸው የተጠመቁ ሕፃናት ከምእመናን ቀድመው ይቆርባሉ፤

• ለወንዶች የ፵ ቀን ሕፃናት የመጀመሪያ ናቸው፤

• ንዑሰ ክርስቲያን ተጠማቂዎች እንደየ ዕድሜያቸው ከትንሽ ወደ ትልቅ ፤

• በድንግልና ኑረው የመነኮሱ መነኮሳት፤

• ፳ ዓመት በላይ የሆናቸው መነኮሳት (ከመነኮሱ)፤

• ንፍቀ ዲያቆናት፣ አናጉንስጥሳውያን፣ መዘምራን ዓፀወተ ኃዋኅው ፤

• በሕግ ኑረው የመነኮሱ መነኩሳት፤

• በሕግ ጸንተው ያሉ ሕጋዊያን፤

• በንስሐ ተመልሰው የመነኮሱ መነኮሳት፤

• ንስሐ የገቡ ሕዝባዊያን በየማዕረጋቸው፤ቅዱሱን ቁርባን ይቀበላሉ፡፡

• ለሴቶቹ የ፹ ቀን ተጠማቂ ሕጻናት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፤

• ንዑሰ ክርስቲያን ተጠማቂዎች በየዕድሜያቸው ቅደም ተከተል (ከትንሽ ወደ


ትልቅ)፤

• በድንግልና ኑረው የመነኮሱ ደናግል፤

• የቀሳውስት ሚስቶች፤

• በሕግ ኑረው የመነኮሱ መነኮሳት፤

• የዲያቆናት ሚስቶች፤

• በንስሐ ተመልሰው የመነኮሱ መነኮሳት፤

• የንፍቅ ዲያቆናት፤ የአናጉስጢሳዊያንና የመዘምራን ሚስቶች፤

• በሕግ ጸንተው ያሉ ሕጋውያን፤

• ንስሐ የገቡ ሕዝባውያን ሴቶች (ሚስቶች)፤

በየመዓርጋቸው ቅዱሱን ምሥጢር (ሥጋ ወደሙን) ይቀበላሉ።


78
አኮቴተ ቅድሳት (የተለየ ምስጋና)
ቅዱሱን ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ በአፍ ውስጥ እያለ በሕሊና የሚጸልዩት ጸሎት
የሚመሰክሩት ምስክርነት፣ የሚያመሰግኑት ምስጋና የሚከተለው ነው።

“ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ሥሉስ ዘኢይትነገር፤ ሀበኒ ከመ እንሣዕ ለሕይወት ዘንተ ሥጋ


ወደመ ዘእንበለ ኩነኔ። ሀበኒ እግበር ፍሬ ዘያሠምረከ፤ ከመ አስተርኢ በስብሐቲከ፤
ወእሕየው ለከ እንዘ እገብር ዘዚአከ ፈቃደ። በተአምኖ እጼውአከ አብ ወእጼውዕ
መንግሥተከ። ይትቀደስ እግዚኦ ስምከ በላዕሌነ። እስመ ኃያል አንተ እኩት ወስቡሕ፤
ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም፡፡” የሚለውን ጸልየው ይላኩት (ይዋጡት)። ትርጉሙም፦

“የማይመረመር ልዩ ሦስት ሳይፈረድብኝ ይህን ሥጋውን ደሙን ሕይወተ ሥጋ ሕይወተ


ነፍስ ሊሆነኝ እቀበል ዘንድ መቀበሉን ፍቀድልኝ፤ ስጠኝ (አዋሕድልኝ)፤ ደስ የሚያሰኝህ
ፍሬ ሃይማኖት አፈራ ዘንድ፤ ምግባረ ነፍስ እሠራ ዘንድ መሥራቱን ስጠኝ (ፍቀድልኝ)።
በጎ ሥራ ሠርቼ በክብርህ ከብሬ እታይ ዘንድ (አመሠግንህ ዘንድ)፤
ሕያው ሆኜ ላንተ ምግባረ ነፍስ እየሠራሁ ምስጋና ሳቀርብ እኖር ዘንድ (አመስግኜህ እኖር
ዘንድ)። አምኜ አቡነ ዘበሰማያት ብዬ እለምናለሁ (እጠራሃለሁ)። ጌትነትህንም
እለምናለሁ፤ መንፈስ ቅዱስ ይምጣልኝ ብዬ (ትምጸአ መንግሥተከ ብዬ) እለምንሃለሁ።
አቤቱ ስመ አምላክነትህን ግለጽልን፤ (ስመ ወላዲነትህን፥ ተወላዲነትህን፥ሠራፂነትህን
ግለጽልን)። ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተህ የፈጠርክ፤ ከመኖርም ወደ
አለመኖር የምታሳልፍ ኃያል ከሃሊ አንተ ነህና እኩት ስቡሕ ተብለህ ትመሰገናለህ። ላንተ
ክብር ምስጋና ይገባሃል።” የሚል ነው።

ቆራቢያን ቅዱሱን ቁርባን በተቀበሉ ጊዜ እጃቸውን ካፋቸው ላይ ማኖር ይኖርባቸዋል።


ይህም ለጥንቃቄ፣ እንዳይነጥብ ነው። ከአፍ ያለውን ተልኮ (ቀስ በቀስ ውጦ) እስኪያበቃ
ድረስ ነው። ከጥርስ፥ ከትናጋ፥ ከምላስ ተጣብቆ (ተላኮ) እንዳይቀርና እንዳይነጥብ ነው።
ሥጋ ወደሙ በጥርስ አይላመጥም።

ቆራቢያን ሥጋውን ተቀብለው ወደ ደሙ ሲሔዱ በሕሊናቸው “ፈጽሞ ደስ ብሎኝ በነፍስ


በሥጋ እንዳመሰግንህ አድርገኝ፤ መለኮት የተዋሐደውን ሥጋውን ደሙን ከመቀበሌ
የተነሣ፤” ይላሉ። ደሙን ሲቀበሉ ደግሞ “እውነት ነው! ከሰማይ የወረደ የክርስቶስ ደሙ
ነው፤ ይላሉ። ደሙን ከተቀበሉ በኋላ ደግሞ በሕሊናቸው የሚጸልዩት ይህ ነው “አቤቱ
ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ በሥጋ ለሠራሁት ኃጢአት ማስተሠሪያ ይሆነኝ ዘንድ
ንጹሕ ክቡር የሚሆን ሥጋህን ደምህን እነሆ ተቀበልሁ”። ተቀዳሚ ተከታይ የሌለህ ሰው
ወዳጅ የምትሆን ወልድ ምስጋናህን እናገር ዘንድ እንዳመሰግንህ አድርገኝ። አምስት ሺህ
አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ሰው የሆንህ አንተ ነህና በሥጋ የተመሰገንህ (የተገለጽህ)።
እስከ ዘለዓለሙ ታድነኝ ዘንድ ክቡር ጽኑ በሚሆን ስምህ ስላመንሁ (ስለተጠራሁ) አቤቱ
ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ላንተ ክብር ምስጋና ይገባሃል። ባገልጋይህ (በስመ ክርስትናው
የገባሬ ሠራዩን ቄስ ስሙን ጠርቶ) እጅ ሥጋህን ከደምህ፤ ደምህን ከሥጋህ አንድ አድርገህ
የሰጠኸኝ ከምእመናን ጋራ አንድ ታደርገኝ ዘንድ ፈጽሜ እለምንሃለሁ። በረድኤት
79
ተቀበለኝ። የቀደመውን ኃጢአቴን አትዘከርብኝ (አታስብብኝ)፤ ይቅር በለኝ፤ የሰጠኸኝ
ጸጋህን በእኔ አድራ ያለች ረድኤትህንም አመሰግናለሁ።” ይላሉ።

ከዚህ በኋላ ካህኑም፣ዲያቆኑም፣ሕዝቡም በቅብበሎሽ የሚያቀርቡት ምስጋናና ጸሎት አለ።


ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሚያቀርቡት ቅኔ (ክብር ይእቲ፤ እጣነ ሞገር) የሚዘምሩት
ዝማሬ አለ። ሁሉም ግን ስለ ሥጋውና ደሙ ክብር በተመለከተ የሚቀርብ በመሆኑ
ምሥጢሩ ምሥጢረ ሥጋዌን በተለይም ምሥጢረ ቁርባንን የሚያዘክር ነው የሚሆነው።

ሠርሆተ ሕዝብ
በሥርዓተ ቅዳሴው መጨረሻ ላይ ራሱን የቻለ የመሰናበቻ ሥርዓትና ጸሎት አለ። ቀደም
ብሎም ሐዳፌ ነፍስና አንብሮተ እድ የሚባሉ ስለ ሁሉም የሚቀርቡ ጸሎታትና
ምስጋናዎች ይቀርባሉ። ካህኑ የማሰናበቻውን ጸሎትና ቡራኬ ከፈጸመ በኋላ ዲያቆኑ እትዉ
በሰላም ብሎ ሕዝቡን ያሰናብታል፡፡ ዲያቆኑ ከማሰናበቱ በፊት ንፍቁ ቄስ እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያምን ፣ሊቃነ መላእክትን ፣ዐርባዕቱ እንስሳን ፣አርእስተ አበውን፣
መጥምቀ መለኮትን፣ ዐርባዕቱ ወንጌላዊያንን፣ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያትን፣ ጻድቃን
ሰማዕታትን፣ እያማፀነ በነሱ ጸሎት፣ በነሱ ምልጃ ጠብቃቸው እያለ ይለምናል፡፡
በመቀጠልም “አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ፤ በፈጣሪያችን
በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ፤” በማለት ዲያቆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑን
ለቡራኬ ያዘጋጃቸዋል። ከቡራኬ በኋላም “እትዉ በሰላም፤ በሰላም ግቡ፤” ብሎ
ያሰናብታቸዋል። “በሕይወት በጤንነት እሾህ ሳይወጋችሁ፥ እንቅፋት ሳይመታችሁ፤ወደ
ቤታችሁ ግቡ፤” ይላል። ምሥጢሩ ግን ሥጋውን ደሙን በመቀበላችሁ ኃጢአታችሁ
ተሠረየላችሁ፤ ባንድነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ግቡ፤” ማለቱ ነው። “ዕትዉ” የ “ንዑ
ኃቤየ” ምሳሌ ነውና።

ለመቁረብ የሚደረግ ጥንቃቄ /ዝግጅት/


❖ የተከበሩ አንባቢ ሆይ ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል አንድ ምእመን ማድረግ
የሚጠበቅበትን ጥንቃቄ ምንድነው?

ምእመናን ሥጋ ወደሙን ለመቀበል በሚፈልጉበት ወቅት ሊፈጽሟቸው የሚገቡ ዝግጅቶች


አሉ። ሥጋዊ ማዕድስ እንኳን ከመበላቱ በፊት የራሱ የሆነ ዝግጅት አሉት። ሰማያዊው
ማዕድማ ምን ያህል ጥንቃቄ ይፈልግ ይሆን!? /ማቴ ፳፪፥፲፪፡፡/ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በሰርግ ቤት ምሳሌነት በርካታ ትምህርቶችን አስተምሯል። ካስተማራቸው ትምህርቶች
መካከል በተጠቀሰው ወንጌልና ምዕራፍ ከቁጥር ፩ ጀምሮ የሰፈረውን ታሪክ ስናነበው
ከርእሰ ጉዳያችን ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ነጥቦች እናገኛለን።

“መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች፤” በማለት ይጀምራል። ወደ


ሰርጉ ከታደሙት መካከል አንደኛው ለሰርጉ ቤት ክብር የሚመጥን ዝግጅት ሳያደርግ
በዘፈቀደ በመግባቱ የደረሰበት ችግርና ቅጣት ቁጥር ፲፪ ጀምሮ ስናነብ የምናገኘው ነው።
ንጉሡ ተጋባዦችን ሊጎበኝ /ሊያይ/ ወደ ሰርጉ ቤት በገባ ጊዜ ያ ሰው የሰርግ ልብስ

80
ሳይለብስ በመገኘቱ ነው ተግሣጹም ቅጣቱም ያገኘው። ይህም ምድራዊው ሰርግም እንኳን
ቢሆን የራሱ የሆነ የአለባበስ፣ የአቀማመጥ፣ የአመጋገብና የክንውን ሥርዓትና ጊዜ
እንዳለው ያሳየናል።

የሰርጉ ቤት የቤተ ክርስቲያንና የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ሲሆን የሰርጉ ባለቤት ደግሞ
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ታዳሚዎቹም የምእመናነ ክርስቶስ ምሳሌዎች
ናቸው። ድግሱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጸሎተ ቅዳሴ በየጊዜው የምታዘጋጀው ቅዱስ
ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው። ይህም ዝም ተብሎ በዘፈቀደ ማንም ባሻው ጊዜ እየተነሣ
ያለምንም ዝግጅት የሚመገበው ተራ ምግብ አይደለም። ተግሣጹም ሆነ ጽኑዕ ቅጣቱ
እንዳያገኘን ባግባቡ ተዘጋጅተን በካህናት እጅ የሚሰዋውን መሠዋዕተ ሐዲስ መቀበል
ይኖርብናል፡፡ ዋና ዋናዎቹ የዝግጅቱ አካላትም የሚከተሉት ናቸው።

• ባለፈ ኃጢአት መጸጸት፣ መናዘዝና ቀኖና ተቀብሎ በትሕትናና በፍቅር መፈጸም፤


ዳግም ላለመበደልም ወስኖ መጋደል፤

• ወደ ልባችን የኃጢአትን አሳብ እንዳያስገቡ አካላዊ ስሜቶችን ሁሉ መግዛት፤

• ሰውነትን /አካልን/ በዋዜማው በአግባቡ መታጠብና አቅም በፈቀደ መጠን ተገቢውን


ልብስ (ከተቻለ ነጭ) አዘጋጅቶ መልበስ፤

• ለ፲፰ ሰዓታት ከምግበ ሥጋ መከልከል፣

• በዋዜማው ቀለል ያለ ምግብ መመገብ ፣

• ሕጋዉያን (ባለ ጋብቻ) ቆራቢያን ከሩካቤ ሥጋ ለ፫ ቀናት መታቀብ፣

• ከሕልመ ሌሊትና ከወር አበባ እንዲሁም ከሚደማና ከሚያዥ ቁስል ነጻ መሆንን


ማረጋገጥ፣

• በወሊድ ጊዜ ሴቶች ለወንድ ልጅ ፵ ቀን ለሴትም ልጅ ፹ ቀን የሞላቸው መሆኑን


መገንዘብ፣

• ሥርዓተ ጸሎተ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት መድረስ የሚሉትና የመሳሰሉት ዝግጅቶች


አስፈላጊ ናቸው። ከጤንነት ጋ በተያያዘ የጾም ሰዓትን በተመለከተ ከመምህረ ንስሐ
ጋር በመመካከር በፈቃደ ካህን የሚስተካከል ይሆናል።

ቅዱስ ቁርባንን ከተቀበሉ በኋላ የሚደረግ ጥንቃቄ


❖ የተከበሩ አንባቢ ሆይ ቅዱስ ቁርባንን ከተቀበሉ በኋላ የማይፈቀዱ ተግባራት
ምን ምን ናቸው?

81
በዕለቱ ቆራቢያን እንዲፈጽሟቸው የማይፈቀዱ ተግባራት በከፊል ከዚህ በታች የቀረቡት
ናቸው፡፡

• ገላን (ሰውነትን) መታጠብ፣

• ከልብስ መራቆት፣

• መስገድ መንበርከክ፣

• ምራቅን እንትፍ ማለት፣

• መበጣት መቆረጥ፣

• መታገም መተኮስ፣

• የእጅና ይእግር ጥፍር መቆረጥ፣

• ፀጉርን መላጨት፣

• ሩቅ መንገድ መሔድ፣

• መፍረድ፣ መክሰስ፣ መካሰስ፣

• ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድና መታጠብ፣

• ያለ መጠን መብላት፣ መጠጣት፣

• ለሦስት ቀናት ያህል ግብረ ሥጋ /ሩካቤ/፣

• ይህን የመሳሰሉትን ሁሉ ማድረግ አይገባም፡፡

፭.የሚያስገኘው ጸጋ
❖ ውድ ተሳታፊ ሆይ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ለምን ለምን ይጠቅማል?

የሚታየው ኅብስትና ወይን በክርስቶስ ቃል ኪዳን፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ በካህኑ ጸሎትና
በጸሎተ ቅዳሴ ነፍስ የተለየው፣ መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ወልደ እግዚአብሔርና ደመ
ወልደ እግዚአብሔር ወደ መሆን ይለወጣል። ምእመናን ይህን አምነውና ንስሐ ገብተው
ሲቀበሉ በወንጌል የተጻፈውን የማይታይ ጸጋ ለማግኘት ይችላሉ። እነዚህም፦

• ሥርየተ ኀጢአት፣ (ማቴ፳፮፥፳፮-፳፰፡፡)

• የዘላለም ሕይወት፣ (ዮሐ ፮፥፶፬፡፡)

• የኃጢአት ልጓም ሆኖ ማገልገል፣ (ዮሐ ፮፥፴፭፤፶፭፡፡)

• ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን፣ (ዮሐ ፮፥፶፫፡፡)


82
• ፍትወታትን ድል መንሳት፣ (ያዕ ፬፥፯፡፡)

• ፍላጎትን ለመቆጣጠርና ራስን መግዛት፣ (፪ጢሞ፥፩፥፯፡፡)

• የፍቅር ሰዎች መሆን፣ (፩ ዮሐ፬፥፯‐ፍጻሜው፡፡)

• የትዕግሥትን ጸጋ ለመቀበል፣ (ዕብ ፬፥ፍጻሜው፡፡)

የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል የሚገኙ ጸጋዎች (ጥቅሞች) ናቸው።


የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ማኀተም ምሥጢረ ቁርባን መሆኑ የታወቀ ነው።
ሁሉም በቅዱስ ሥጋውና ደሙ ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ። ምሥጢረ ቁርባን የምሥጢራተ
ቤተ ክርስቲያን አክሊል ነው የተባለውም በዚህ ምክንያት ነው።

ማጠቃለያ
ምሥጢረ ቁርባን የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ ማረጋገጫ ማኅተም ነው፡፡ ለዚህም
ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ ሥጋ
ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠታችሁ የዘላለም ሕይወት የላችሁም፤ ሥጋዬን የሚበላ
ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በኃለኛይቱ ቀን አነሣዋለሁ፡፡”
በማለት በግልጽ ያስተማረን፡፡ (ዮሐ 6፥%3-%5ÝÝ፡፡) ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን ርእሰ
ጉዳይ በተመለከተ ቆም ብለው በርጋታ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ክርስቲያኖች ተብለው
በስሙ መጠራታቸው ብቻውን የሕይወት ባለቤት ሊያደርጋቸው አይችልም፡፡
መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንዳስተማረን እሱ የወይን ግንድ ክርስቲያኖችም
ቅርንጫፎቹ ናቸው፡፡ ከግንዱ ከክርስቶስ የተወለደ ሆኖ ሳለ የቃለ እግዚአብሔር
እንዲሁም የሥጋውና የደሙ ምግብ የተቋረጠበት ቅርንጫፍ /ክርስቲያን/ ደግሞ
ጠውልጎ መድረቁ አይቀርም፡፡ ከደረቀና ከግንዱ ተቆርጦ ከተጣለም ለእሳት
የተዘጋጀ ይሆናል፡፡ በሕይወቱ እንዳይጠወልግ፣ እንዳይደርቅና እንዳይቃጠል
የሚፈልግ ምእመን ሁሉ ከግንዱ ጋር ሊኖር፤ ከግንዱ ከክርስቶስ የሚገኘውን
የሕወት ምግብም ሳያቋርጥ ንስሐ እየገባ ሊመገብ ያስፈልገዋል፡፡ እያስቀደሱ
ጥቂቶች ብቻ ማዕዱን ከበው ሲመገቡ ማየት ብቻውን ለተራበች ሰውነት /ነፍስ/
የሚፈይደው አንዳች ቁም ነገር የለውም፡፡ (ዮሐ 05፥1-0፡፡Ý) በዚህ ምዕራፍ
ያነበብነውን ሁሉ ከራሳችን ተግባራዊ ሕይወት ጋር በማመዛዘን ወደ ቅዱስ ቁርባን
ለመቅረብ የምንችልበት መሣሪያ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

ዋቢ መጻሕፍት
• ዲ/ን ያሬድ ገ/መድኅን፤ ኆኅተ ሰማይ፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤
፲፱፻፺፮፤ አ/አ።

• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫


አ/አ።
83
• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ


ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፹፰፤ አዲስ አበባ።

• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን
1999፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ


ድርጅት፤ ፳፻፬፤ አ/አ፤

84
ምዕራፍ ፮
ምሥጢረ ክህነትና አፈጻጸሙ
መግቢያ
ከ@2ቱ ፍጥረታት መካከል የፍጥረታት ሁሉ ዘውድ የሚባለው የሰው ልጅ ነው፡፡ ከሰው
ልጆች መካከልም እግዚአብሔር የተወሰኑትን መርጦ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ ዕጣን
እንዲያሳርጉና በመቅደሱ እንዲያገለግሉ አደረገ፡፡ እነዚህ ሰዎችም ካህናት /አገልጋዮች/
ተብለው ይጠራሉ፡፡ እግዚአብሔር ሙሴን “አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር
ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ በክህነት ያገለገሉኝ ዘንድ ወደ አንተ
አቅርብ፡፡” በማለት ያዘዘውን ማየት ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ
ኪዳን የክህነት መሠረቱ የእግዚአብሔር ጥሪ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ በዝርዝር
የምንመለከተው ምሥጢረ ክህነትን ነው፡፡ በምዕራፉ ሥርም አመሠራረቱን፣
አስተምህሮውን፣ አፈጻጸሙንና የሚያስገኘውን ጸጋ በተገቢው ሁኔታ ለማብራራት
ተሞክሯል፡፡

ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት፤ይህንን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-

• የምሥጢረ ክህነትን አፈጻጸምና አስተምህሮ ይገነዘባሉ፡፡

• በምሥጢረ ክህነት የሚገኘውን ጸጋ በመረዳት በርሱ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን


ግንዛቤ ያዳብራሉ።

85
፮.፩ አመሠራረት
አማናዊው የሐዲስ ኪዳን ክህነት ከመጀመሩ በፊት በብሉይ ኪዳንም ክህነትና
አገልግሎቱ በስፋት ይታይ ነበር። በሕገ ልቡና ዘመን ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ
ድረስ የተመረጡ አበው ለቤተሰቦቻቸው የክህነትን ተግባር ይፈጽሙ ነበር። ክህነት
እግዚአብሔር የሚገለገልበት ልዩ ጥሪና ስጦታ እንደመሆኑ መጠን እነዚህ አባቶች
ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በማገናኘት ይህን አገልግሎት
ይፈጽሙ ነበር። ለማስረጃ ያህልም የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል።

• “በዚያችም ቀን አዳም ከኤዶም ገነት ሲወጣ ለበጎ መዓዛ ነጭ ዕጣን፣ ቀንዓትና


ልባንጃ ስንቡልም ኀፍረቱን በሸፈነበት ቀን በጥዋት ፀሐይ ሲወጣ ዐጠነ።” (ኩፋ.
፭፥፩፡፡) ይህም አባታችን አዳም በተፈጠረበት ወቅት እግዚአብሔር ካሳደረበት ፯ት
ሀብታት አንዱ ሀብተ ክህነት መሆኑን የምንረዳበት አንዱ ማስረጃ ነው፡፡”

• “አቤልም ደግሞ ከበጎቹ መጀመሪያ የተወለደውንና ከሰቡት አቀረበ፤


እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤” (ዘፍ፬፥፬፡፡)

• “ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠዊያውን ሠራ፤ከንጹሕም እንሰሳ ሁሉ፣ ከንጹሕም ወፎች


ወሰደ፤ በመሠዊያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም አምላክም
መልካሙን መዓዛ አሸተተ፡፡” (ዘፍ፰፥፳‐፳፩፡፡)

• “እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።”


አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠዊያውን
ሠራ፡፡… በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፡፡”
(ዘፍ፲፪፥፯‐፱፡፡)

• ስለ ይስሐቅም “በዚያም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤


የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፡፡” ተብሏል። (ዘፍ ፳፮፥፳፭፡፡)

• ስለ ያዕቆብ ደግሞ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለ፤ “በዚያም መሠዊያውን ሠራ፤


የዚያንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፡፡’’ (፴፭፥፯፡፡)

በዘመነ አበው ከነበሩት የክህነት አገልግሎቶች ላቅ ያለ ስፍራ የሚሰጠው


የመልከጼዴቅ ክህነትና አገልግሎት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ እርሱ የተጻፉት
ኃይለ ቃላት እንዲህ ነው የሚሉት፡፡

• “የሳሌም ንጉሥ መልከጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል


እግዚአብሔር ካህን ነበረ፡፡” (ዘፍ፲፬፥፲፱፡፡)

• “እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት፥ አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ


አይጸጸትም፡፡” (መዝ ፻፱፥፬፡፡)

86
ይህም ኀይለ ቃል መልከጼዴቅ የልዑል እግዚአብሔር ካህን ብቻ ሳይሆን የወልደ
እግዚአብሔርም ምሳሌ መሆኑን ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ኀይለ ቃል
ሲያብራራ እንዲህ ነበር ያለው፤ “የሳሌም ንጉሥ፣ የልዑል እግዚአብሔርም ካህን
የሆነ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብርሃም ነገሥታትን ድል ነስቶ በተመለሰ ጊዜ ከእርሱ
ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው፤… ክህነቱ
የወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል።” (ዕብ፯፥፩‐፬፡፡) ለጊዜው
ይህን ያህል ጠቀስን እንጂ ሙሉው ምዕራፍ የመልከ ጼዴቅን ክህነትና ክብር
ከክርስቶስ ጋር እያነጻጸረ ያቀረበበት ክፍል ነው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስም
በቅዳሴው ምዕራፍ ፫ ላይ በሰፊው ያቀረበውን ምስክርነት መመልከት ይቻላል።

የተከበሩ አንባቢ ሆይ፦

❖ ቅዱስ ጳውሎስ “የአባቶች አለቃ አብርሃም ከምርኮው ሁሉ የሚሻለውን


ዐሥራት የሰጠውን የዚህን ካህን ክብር ታያላችሁን?” (ዕብ ፯፥፬) ከሚለው
ኃይለ ቃል ምን ትረዳላችሁ?

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ የሆነ መልከጼዴቅ አበ ብዙኃን ከተባለ


ከአብርሃም ዐሥራት መቀበሉ፤ አብርሃምም ዐሥራት መስጠቱ ታላቅነቱንና
ክብሩን ያሳያል፡፡ ይህም ምሳሌነት ወልደ እግዚአብሔር ክህነት
በመልከጼዴቅ ክህነት ዘምሳል ጸንቶ መኖሩን ያሳያል፡፡ መልከጼዴቅ
በስንዴና በወይን ቁርባን ማመስገኑ (ማስታኮቱ)፣ ሹመቱን ከእገሌ ተሾመው
መባል አለመቻሉና ሹመቱ ለእገሌ አለፈ አለመባሉ የትውልድ ቁጥር
ካለመኖሩ ጋር ተደምሮ ክርስቶስን አስመስሎታል፡፡ ርእሰ አበው የተባለ
አብርሃምም ለሱ አሥራት አውጣጥቶ ማቅረቡ የምእመናን ምሳሌ
ያደርገዋል፡፡ ህ ታሪክ ደገኛ ምሳሌ ሆኖ አማናዊቱን የአዲስ ኪዳን ክህነት
ክብር ከማሳየቱም በላይ ምእመናን ለካህናት አባቶች መታዘዝ
እንደሚገባቸው ያስተምራል፡፡ (ትርጓሜ ዕብራውያን ምዕራፍ ፯)

ከሙሴ ጀምሮ ባለው ዘመነ ኦሪትም እግዚአብሔር ከአሥራ ሁለቱ ነገዶች


መካከል አንዱ በክህነት እንዲያገለግለው መምረጡን እንረዳለን። (ዘጸ
፳፱፥፩‐፲፡፡ ዘሌ፰፥፲፪‐፲፬፤ ፳፩፥፩‐ፍጻሜ፡፡ ዘኁ፩፥፶‐፶፪፤ ዘኁ፩፥፶‐፶፪፤
ዘኁ፫፥፩‐፲፬፡፡) ከተመረጠው የሌዊ ነገድ መካከልም አሮንና ልጆቹን የበለጠ
አክብሮና አቅርቦ በክህነት እንዲያገለግሉት መፍቀዱን ከላይ የጠቀስናቸው
ማስረጃዎች ይነግሩናል። አሿሿማቸውን፣ ዝርዝር አገልግሎታቸውንና
መሥዋዕታቸውን በተመለከተም በኦሪት ዘጸአት ፳፰፡፳፱፣ ዘሌዋዉያን ፰፡፲
እና ዘኁልቁ ምዕራፍ ፫‐፬ ተጽፎ እናገኛለን፡፡

እንደሚታወቀው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጊዜያዊውን


የብሉይ ኪዳን አገልግሎት (ክህነት) እና መሥዋዕት አሳለፈው። እርሱ ራሱ
መሥዋዕት፣ መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህንና መሥዋዕት ተቀባይ አምላክ
87
ሆኖ የሐዲስ ኪዳኑን አማናዊ ክህነት መሠረተልን። በአዲስ ሥርዓት፣
መሥዋዕትና ኪዳን የመሠረተው ይህ ምሥጢረ ክህነት ምእመናንን ወደ
እግዚአብሔር መንግሥት የሚያቀርብ (የሚያስገባ) ሆነ፡፡ ለደቀ መዛሙርቱ
የሰጣቸው የማስተማር፣ የማጥመቅ፣ የማቁረብ ኃጢአትን የማስተስተሥርይ፣
ሥልጣን በደሙ የመሠረታትን ቤተክርስቲያን ማለትም ምእመናንን
እንዲጠብቁለትና እንዲመሩለት ነው፡፡ (ሐዋ.፳፥፲፯-፳፰፡፡ ዮሐ፳፩፥፲፭‐፳፡፡)

፮.፪.አስተምህሮ
የተከበሩ አንባቢ ሆይ-upÉT>Á የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ፡፡

❖ ክህነት ምንድነው? ዐበይት ተግባራቱስ ምን ምን ናቸው?

❖ ቤ/ክ ለልጆቿ ከምትሰጣቸው ሰፋፊ አገልግሎቶች አንዱ እረኞችን /የንስሐ


አባቶችን/ ማሠማራቷ ነው። የንስሐ አባትዎ (መንፈሳዊ እረኛዎ) በመንፈሳዊ
ሕይወት ጉዞዎ ምን ጥቅም /አጋዥነት /ይኖራቸዋል?

ክህነት መንፈሳዊ አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱም በሰውና በእግዚአብሔር


መካከል የሚፈጸም ነው። የክህነት ሥልጣን ምድራውያን መሪዎችና ዳኞች የማይሾሙትና
የማይሽሩት ሰማያዊ ሹመት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የማሰርና
የመፍታት ሥልጣን በመስጠት ነው ምሥጢረ ክህነትን ያጸናው። ቤተክርስቲያን
የምሥራቹን ቃል ለዓለም በማዳረስ ምእመናንን የምትጠራቸው በካህናት አማካኝነት ነው።
ምሥጢራቷን የምታከናውነውና የእግዚአብሔር ጸጋ ለሚገባቸው ሰዎች የምታድለው
በሐዲስ ኪዳን ካህናት በኩል ነው፡፡ የካህናት አገልግሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመሠረተው (በሠራው) ሥርዓት መሠረት የሚጓዝ ነው።

የካህናት ዐበይት ተግባራት ሦስት ናቸው።

እነዚህም፦

፩/ ለጸሎት መትጋትና ትምህርተ ወንጌልን ለመላው ዓለም ማዳረስ፤ (ማቴ፳፰፥፲፱‐፳፡፡


ማር፲፮፥፲፭፡፡ ሐዋ፩፥፰፤ ፮፥፩‐፬፡፡)

፪ኛ/ የሕዝቡን ኃጢአት ማስተሥረይና ወደ ቅድስና ጎዳና መምራትና፤ /ዮሐ፳፥፳፫፡፡/

፫ኛ/ መንጋውን /ምእመናነ ክርስቶስን/ የመጠበቅና የማስተዳደር ሥራ ነው።


(ዮሐ፳፩፥፲፭‐፲፰፡፡ ፩ኛጴጥ ፭፥፩‐፭፡፡)

88
እነዚህንም ተግባራት የሚያከናውኑት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን
ከመፈጸምና ከማገልገል ጋር ነው።

❖ ሁሉም ክርስቲያን ካህን መሆን ይችላልን? ወይም ሁሉም ለክህነት


ተጠርቷልን? ለምን? እንዴት?

ምንም እንኩዋን ለሐዲስ ኪዳን ክህነት እንደ ብሉይ ኪዳን ለክህነት አገልግሎት
የተለየ ዘርና ነገድ ባያስፈልገውም ሁሉም የሰው ዘር ካህን ሊሆን እንደማይችል ግልጽ
ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይከተሉት ከነበሩት ፭ ገበያ ሕዝብ
መካከል ለክህነት አገልግሎት መጀመሪያ የመረጣቸው አስራ ሁለቱን ሐዋርያት እንጂ
ሁሉንም ተከታዮች አልነበረም። (ማቴ ፲፥፩‐፭፡፡ ማር፫፥፲፫‐፲፱፡፡ሉቃ፮፥፲፪‐፲፮፡፡)

እዚህ ላይ ልንመለከተው የሚገባን በብሉይ ኪዳን ለቤተ እስራኤልና በሐዲስ ኪዳን


ለክርስቲያኖች የተሰጠ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ቃልኪዳን አለ፡፡ ይህንንም በንጽጽር
እንደሚከተለው እናየዋለን ።

• “ለያዕቆብ ቤት እንዲህ በል፤ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ንገር፤… አሁንም ቃሌን


በእውነት ብትሰሙ፥ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ
የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤ እናንተም የክህነት መንግሥት፤ የተቀደሰም
ሕዝብ ትሆናላችሁ፡፡” (ዘፀ፲፱፥፫‐፯፡፡)

• “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትነግሩ


የተመረጠ ትውልድ፥ የመንግሥትና የክህነት ወገን፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱም
የተለየ ወገን ናችሁ፤ እናንተ ቀድሞ ወገኖች አልነበራችሁም፤ አሁን ግን
የእግዚአብሔር ወገኖች ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን
ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።” (፩ኛ ጴጥ፪፥፱‐፲፩፡፡) ቀደም ሲልም “በሰው ወደ
ተናቀ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው
ድንጋይ ወደ እርሱ ቅረቡ። ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ በኢየሱስ
ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ
ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ፡፡ (፩ጴጥ፪፥፬‐፮፡፡)
እነዚህ ከላይ እንደገለጥነው ተመሳሳይ ምሥጢር የያዙ ኃይለ ቃላት ሆነው
እናገኛቸዋለን ።

• “ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለአባቱም ለእግዚአብሔር ነገሥታትና


ካህናት ላደረገን ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤
አሜን፡፡ (ራእ፩፥፭‐፯፡፡)

• “ከእነርሱም ለአምላካችን ነገሥታትና ካህናትን ሾምህ፤ በምድርም ሁሉ ይነግሣሉ፡፡”


(ራእ፭፥፲፡፡) የሚሉትም ከላይኞቹ ኃይለ ቃላት ጋር የተዛመዱ ናቸው፡፡

89
በኦሪቱ እንደተጻፈ መልእክቱ ለቤተ እስራኤል ሁሉ ነው፡፡ በካህናት አገልግሎት
ለምትወደስ፣ ለምትመሰገን የእግዚአብሔር መንግሥት መመረጣቸውን፤ ካህናት ከእነሱ
ማኅፀንና አብራክ እንደሚወለዱና ከሌላው የዓለም ሕዝብ ሁሉ ተለይተው የእግዚአብሔር
ማደሪያዎች እንደሚሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሁሉንም እስራኤላዉያን ካህናት
ናቸው ማለቱ አልነበረም፡፡ ይህማ እንዳይሆን ከመካከላቸው የሌዊን ነገድ በተለይም ደግሞ
አሮንንና ልጆቹን በክህነት እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር መምረጡን ባልነገረንም ነበር።

በሐዲስ ኪዳንም ያሉት ከላይ የጠቀስናቸው ማስረጃዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ሁሉም


ክርስቲያኖች ካህናት ናቸውና ካህናት አያስፈልጉም ለማለት የተጻፉና የተነገሩ አይደሉም።
የእግዚአብሔርን አምላክነትና ቸርነት ለሚያምኑ ሁሉ ለመንገር፣ በሕይወትም ለመመስከር
የተጠሩ አገልጋዮች መሆናቸውን ነው የሚናገሩት። ክርስቲያኖች የተመረጡ የመንግሥተ
እግዚአብሔር ዜጎችና በካህናት ጥበቃ (እረኝነት) ሥር ያሉ መንጎች /ወገኖች/ መሆናቸውን
ነው የሚናገሩት። የክርስቲያኖች አገልግሎትም የተቀደሰ እና በእግዚአብሔር ዘንድ
የተወደደ መሆኑን እንጂ ሁሉም ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን የሚፈጽሙ የቤተ ክርስቲያን
የውስጥ አገልጋዮች ናቸው ማለት አይደለም፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን በሙሴ ምስፍናና በአሮን ክህነት ላይ የሚያጉረመርሙ፤ “ሁሉም


ቅዱሳን ናቸውና እናንተ አበዛችሁት” የሚሉ ተቃዋሚዎች ተነሥተው ነበር። (ዘኁ
፲፮፥፩‐ፍጻሜ፡፡) በምዕራፉ ውስጥ በግልጽ እንደተቀመጠው ከእግዚአብሔር የተከፈለው
የተቃዋሚዎች ዕጣ ፈንታ “ትክክል ናችሁ!” የሚል መልስና “በረከት” ሳይሆን ታይቶ
የማይታወቅ ጥፋትና ጉስቁልና ነበር። ዳግመኛ ተመሳሳይ መገዳደር በካህናት ላይ
እንዳይነሣ ለማድረግም እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ፲፪ ቱንም ነገዶች የሚወክሉ
የአባቶቻቸውን በትር ስማቸውን ጽፎ ወደ መቅደስ እንዲያስገባ አደረገ። እስራኤላውያን
ሁሉም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሆነው ሳለ አሁንም ክህነትን ለአሮንና ለአባቱ ለሌዊ ቤት
ማጽናቱን በተዓምር መሰከረ። ቀድሞ በሰጠው ምልክት መሠረትም የአሮን ስም የተጻፈባት
የአባቱ የሌዊ በትር አቆጥቁጣ /ለምልማ/ ፣አብባና የበሰለ ለውዝ አፍርታ ተገኘች። መላው
የእስራኤል ልጆችም አዩና አመኑ። (ዘኁ ፲፯፥፩‐፲፡፡) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ
አዘዘው፤ “ማጉረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ፥ እነርሱም እንዳይሞቱ፥ ለማይሰሙ
ልጆች (ለሚያምፁብኝ) ምልክት ሆና ትጠበቅ ዘንድ የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አኑር።”
(ዘኁ፲፯፥፲፡፡) ሊቀ ነቢያት ሙሴና አሮንም እንደታዘዙት ያችን የለመለመች በትር በቤተ
መቅደስ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳን አኖሯት፡፡ ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ ምስክርና
ተግሣጽ ይሆነን ዘንድ ሲተርክልን ይኖራል። (ሮሜ ፲፭፥፬፡፡)

ከዚህ በላይ የቀረበው ማብራሪያ ለሚያስተውሉ ሁሉ በቂ መልስ ቢሆንም ጥቂት


እናክልበት። በራእይ ዮሐንስ ፩፥፭‐፯ የሰፈረውን መልእክት ብናይ “ነገሥታትና ካህናት
አደረገን” ይላል። ይህ ማለት ግን ሁላችንም ነገሥታት፤ ሁላችንም ካህናት ነን ማለት
አይደለም። የመንግሥተ እግዚአብሔር ታዳሚነታችንን እንዲሁም “ተክህነ‐አገለገለ” ማለት
እንደሆነ ሁሉ እግዚአብሔርን ለማገልገል መጠራታችንን የሚያሳይ መሆኑን ማስተዋል
ያስፈልጋል።

90
በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ክህነት መካከል ያለ ልዩነት
ተራ.ቁ የብሉይ ኪዳን ክህነት የሐዲስ ኪዳን ክህነት
፩ ጊዜያዊ ነበር። ዘላለማዊ ነው፡፡

፪ ከእስራኤል መካከል ለአንድ ነገድ ብቻ -ብቁ ሆነው ለተገኙ የሰው ልጆች


የተሰጠ ነበር። ሁሉ የተፈቀደ ነው።

፫ - አገልግሎቱ በቤተ እስራኤል ብቻ -አገልግሎቱ ለመላው የሰው ልጆች


የተወሰነ ነበር፡፡ ሁሉ ነው።

፬ - ሥጋዊ ፈውስ ብቻ ይሰጥ ነበር -ፈውሰ ሥጋ ወነፍስ የሚሰጥ ነው።

፭ - ጊዜያዊ የኃጢአት ሥርየትን ያሰጥ ፍጹም የሆነ ሥርየተ ኃጢአትን


ነበር፡፡ ያሰጣል።

፮ - መሥዋዕቱ የእንሰሳ ሥጋና ደም -መሥዋዕቱ የዘለዓለም ሕይወት የሆነ


ነበር፡፡ የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው።

፯ - ሌዊንና አሮንን መሠረት ያደረገ -ክርስቶስን መሠረት ያደረገ ነው።


ነበር።

-ለአዲስ ኪዳን ክህነት አምሳልና ጥላ -አማናዊ ነው፡፡


፰ ነበር፡፡

91
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታወቁ ሦስት የክህነት ሥልጣን ደረጃዎች አሉ።እነዚህም
ጵጵስና ፣ቅስናና ድቁና ናቸው። እነዚህ የሥልጣን ደረጃዎችም ከየትም የተገኙና የተፈጠሩ
ሳይሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆናቸውን እንደሚከተለው እናያለን፡፡

፩.ጵጵስና /ኤጲስ ቆጶስና /


ይህ መዓርገ ክህነት ለከፍተኛው የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሚሰጥ ሥልጣን ሲሆን
የመዓርጉ ባለቤት ኤጲስ ቆዾስ /ጳጳስ/ ይባላል። ቅዱሳት መጽሐፍት ይህን መዓርገ ክህነት
በተመለከተ ምን ይላሉ?

• “ጵጵስናን /ኤጲስ ቆጶስነትን/ ሊሾም የሚወድ መልካም ሥራን ወደደ።”


(፩.ጢሞ.፫፥፩‐፪፡፡)

• “አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ
ተጠንቀቁ።” (ሐዋ ፳፥፳፰፡፡)

• “ጳጳስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋል።” (ቲቶ ፩፥፯፡፡)

• “ኤጲስ ቆጶስ ሆይ በሥራው ሁሉ ራስህን በንጽሕና አጽና። የሹመትህንም መዓርግ


እወቅ። በሕዝቡ ዘንድ በሹመትህ እንደ እግዚአብሔር ነህና። ለሕዝቡ፣ ለነገሥታት
ሁሉ፣ ለመኳንንቱ፣ ለካህናቱ ለአባቶችና ለተማሩት ልጆቻቸው፣ ከትእዛዝህ በታች
ላሉት ሁሉ፣ አለቃ ሁነሃልና። በቤተክርስቲያን ተቀመጥ። በቃልህም አስተምር።
(ፍት.ነገ አን፭፥፻፲፰)

• “ስለ ኤጲስ ቆጶስም፣ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ የሚሾመው


የምእመናን ጠባቂ፣ ነውር የሌለበት፣ ንጹሕና ቸር፣ የዚህንም ዓለም ጭንቀት
የማያስብ፣ ፶ ዓመት የሞላው፣ የጎልማሳነት ኀይልን ያለፈ፣ ነገር የማይሠራ፣
በወንድሞችም መካከል ሐሰትን የማይናገር ይሆን ዘንድ እንደሚገባው በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰማን። (ዲድስቅልያ ፬፥፩፡፡)

፪.ቅስና፦
ይህ ከመዐርጋተ ክህነት አንዱ ሲሆን ባለሙያውና ተሿሚው ቄስ ወይም ቀሲስ ይባላል።
ትርጓሜውም የቤ/ክ አገልጋይ ማለት ነው። ቅስናን በተመለከተም ቅዱሳት መጻሕፍት
የሚሰጡት ምስክርነት ብዙ ነው። ጥቂቶቹን ብቻ እንደሚከተለው እናያለን።

• “ለቤተ ክርስቲያንም ቀሳውስትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለዩም፤ ለሚታመኑበት


ለእግዚአብሔርም አደራ ሰጡአቸው። (ሐዋ ፲፬፥፳፫፡፡) “ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ
ጊዜም ምእመናንና ሐዋርያት ቀሳውስትም ተቀበሏቸው።” (ሐዋ፲፭፥፬፡፡)

92
• ”በየከተማውም ሲሄዱ ሐዋርያትና ቀሳውስት በኢየሩሳሌም ያዘዙትን ሥርዓት
አስተማሩአቸው። አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ጸኑ፤ ዕለት ዕለትም
ቁጥራቸው ይበዛ ነበር።” (ሐዋ፲፮፥፬‐፮፡፡) በመልካም የሚያስተዳድሩ ቀሳውስት
ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።”
(፩ጢሞ፭፥፲፯፡፡)

• “ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተክርስቲያን ያሉ ቀሳውስትን ይጥራና


ይጸልዩለት።” (ያዕ፭፥፲፬፡፡)

• “መልካም የሆኑትን የአምላክን መጻሕፍት ነገር፣ ይልቁንም አራቱን ወንጌላት


ያላወቀ አንዱ ስንኳ ቄስ አይሁን፤ አምስት ሰዎች ያልመሰከሩለት አንዱ ስንኳ ቄስ
አይሁን።” (ፍት.ነገ.አነ.፮፥፪፻፲፪፡፡)

፫.ድቁና፦
ይህ የመጨረሻው (ታችኛው) መዓርግ ክህነት ነው። ቃሉ “ዲያኮንያ” ከሚለው የግሪክ
ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ረዳት፣ አገልጋይ” ማለት ነው። ይህንንም መዓርገ ክህነት
በተመለከተ ቅዱሳት መጻሕፍት ምን እንደሚሉ ደግሞ እንመለከታለን ።

• “ከኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ


ከቀሳውስት፣ ከኤዺስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ቅዱሳን
ሁሉ።” (ፊልጵ.፩፥፩፡፡)

• “እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፣ ቃላቸው የማይለወጥ፣….” (፩ጢሞ፫፥፰፡፡)


ዲያቆናትም ልጆቻቸውንና የቤታቸውን አስተዳደር በመልካም እየገዙ፣እያንዳንዳቸው
የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።” (፩ጢሞ፫፥፲፪፡፡)

• “ዲያቆናት መልካም ሥራን በመዓልትም በሌሊትም በቦታው ሁሉ የሚሠሩ


ይሁኑ።” (ፍትነገ.አን.፯፥፪፻፶፰፡፡) ከዚህም በተጨማሪ ሐዋርያት ሰባቱን ዲያቆናት
በፈቃደ እግዚአብሔር እንደሾሙ ተገልጾልናል። እነዚህ ሁሉ ምስክሮች መዐርጋተ
ክህነት፣ ተፈላጊ ሥነ ምግባራትና ሥርዓተ ክህነትን የተመለከቱ ምሥጢራት ሁሉ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆናቸውን ማሳያ ናቸው። ከተጠቀሱት ውጪ በተገለጹት
ዐበይት የክህነት ደረጃዎች ሥርና መካከል ሌሎች በቤተክርስቲያናችን አገልግሎት
የታወቁ ንዑሳን የሥልጣን መዓርጋት አሉ፡፡ ለማስታወስ ያህልም እንደሚከተለው
ቀርበዋል

• ዲያቆናዊት፣

93
• ንፍቅ ዲያቆን፣

• አናጉንስጢስ /አንባቢ/፣

• መዘምር፣ ዘማሪ /ማኅሌታዊ/፣

• ዐጸውተ ኀዋኅው፣

• ሊቀ ዲያቆን፣

• ቆሞስ፣

• ሊቀ ጳጳስና

• ፓትርያርክ የሚባሉት ናቸው።

የሦስቱ ዐበይት መዓርጋት ክህነት ዋና ዋና የሥራ ድርሻዎች


ኤጲስ ቆጶስ/ጳጳስ/ ቄስ ዲያቆን
‐ ቀሳውስት፣ ዲያቆናትንና ሌሎች አገልጋዮችን -ማስተማር፤ ‐መላላክና መራዳት፤
መሾም፤ -ማጥመቅ፤ ‐ሕሙማንን
‐ ማስተማርና መገሠጽ፤ -ማቁረብ /መቀደስ/፤ መጎብኘት፤
‐ ቀድሶ ማቁረብ፤ -መባረክ፤ ‐የምእመናንን ችግር
‐ ማጥመቅ፤ -ማሰርና መፍታት፤ ለቄሱ ወይም ለጳጳሱ
‐ሁሉንም ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን -መናዘዝ፤ ማቅረብና መጸለይ፤
ማስተዳደር፤ -ምእመናንን መጠበቅ፤ ‐ምእመናንን
‐ለነዳያንና ለሕሙማን ለችግረኞችም ሁሉ -ሕሙማንን መጠየቅ፣ መፈወስ፤ ለመልካምሥራ
መራራት፤ ማጽናናት፤ ማነሣሣትና
‐መባረክ፣ ማሰርና መፍታት፤ -እሱራንን መጠየቅ፤ ማጽናናት፣ ማስተባበር፤
‐ቤተክርስቲያንን በሥጋ በነፍስ መመገብ፤ -ሐዘንተኞችን ማረጋጋት፤ ‐በቅዳሴ ጊዜ
‐ነውር የተገኘባቸውን ቀሳውስትና ዲያቆናት -የተጣሉትን ማስታረቅ፤ ምእመናንን
መክሮ ፣ገሥጾ፣ አልመለስ ካሉ መሻር /መለየት/ -የተለያዩትን አንድ ማድረግ፤ መቆጣጠርና
፤ -ምስጢራትን ከምሥጢረ ክህነት ማስተናበር፤
‐ምእመናንን ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር በስተቀር መፈጸም፤ ‐ደመ ክርስቶስን
ማስታረቅ፤ ለቆራቢያን ማቀበል
‐መልዕክታተ
ሐዋርያትን ማንበብ፤

፮.፫. አፈጻጸም
94
ምሥጢረ ክህነት እንደሌሎቹ ምሥጢራት ሁሉ ራሱን የቻለ የአፈጻጸም ሥርዓት አለው።
ይህንንም በሦስቱ ዐበይት የክህነት ደረጃዎች አንጻር ብቻ እንመለከታለን።

❖ ኤጲስ ቆጶስ የሚመረጥባቸው መስፈርታት ምንድናቸው? “አንዲት ሴት


ያገባ” የሚለው መስፈርት አሁን ሲፈጸም የማይታየው ለምንድነው?

ሀ.ሥርዓተ ሲመተ ኤጲስ ቆጶስ


መስፈርታት/መመዘኛዎች/

“ጵጵስና ሊሾም የሚወድ መልካም ሥራን ወደደ የሚለው ቃል የታመነ ነው፤ ነገር ግን
ጵጵስናን የሚሾም እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፡፡

• የማይነቀፍ፤

• አንዲት ሴት ያገባ፦ ይህ እስከ ኒቂያ ጉባኤ ድረስ የተተገበረ ሲሆን በ3)08ቱ


ቅዱሳን አባቶች ጉባኤ ጳጳስ ድንግላዊ እንዲሆን በመወሰኑ አሁን እየተፈጸመ ያለው
ይህኛው /ድንግላዊ የሚለው/ ነው። ሌሎቹ መስፈርቶች ግን ሳይለወጡ እንዳሉ
የቀጠሉ ናቸው፡፡ ባለትዳሩ ድንግላዊ በሆነው የተቀየረበትም ምክንያትም
የሚከተለው ነው፡፡ ካህኑ ባለትዳር በመሆኑ ምክንያት ሙሉ ጊዜውንና ትኩረቱን
ለቤተ ክርስቲያን ማድረግ እያቃተው በመምጣቱ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሥራ
በሙሉ ልብ፣ ትኩረትና ጊዜ ሊሠራ የሚገባው በመሆኑ በተለይ በመሪነት ያሉት
ጳጳሳት ይህን ያሟሉ እንዲሆኑ በማስፈለጉ በ፫፻፳፭ ዓ.ም የቤተ ክርስቲያን አባቶች
በኒቂያ ጉባኤ ጳጳሳት ድንግላውያን እንዲሆኑ ወሰኑ፡፡ ለዚህም ውሳኔያቸው፡- “ነገር
ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ፡፡ ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንደሚያሰኘው
የጌታን ነገር ያስባል፤ ያገባ ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንደሚያሰኛት የዓለምን ነገር
ያስባል፤ ልቡም ተከፍሏል፡፡” (፩ቆሮ ፯፥፴፪-፴፬) በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ያስተማረውን ትምህርት መሠረት አድርገዋል፡፡ ካህኑ በሚስቱ ላይ ልጆች
ሲጨመሩበት ልቡን ምን ያህል ሊከፍልበት እንደሚችል ተረድተው መላ ዘመኑን
በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እግዚአብርሔርን እንዴት ሊያስደስተው እንደሚችል
እንዲያስብና የሚያስጨንቀው የአብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ብቻ እንዲሆን
ለማስቻል ይህን ወስነዋል፡፡ (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፰፡፡)

ትጉህ፤ ብልህ፤ እንደሚናገረው የሚሠራ፤ እንግዳ ተቀባይ፤ ራሱን የጠበቀ፤


የሚያስተምርና የሚገሥጽ፤ የማይሰክር፤ ለመማታት /ለማውገዝ/ እጁን /አንደበቱን/
የማያፈጥን፤ ትዕግሥተኛ፤ የማይጣላ፤ ገንዘብ የማይወድ፤ ቤቱን በመልካም
የሚያስተዳድር፤ በፍጹም ንጽህና የሚታዘዙ ልጆች ያሉት፤ አዲስ አማኝ
/ክርስቲያን/ ያልሆነና መልካም ምስክር ያለው ሊሆን እንደሚገባ ተጽፏል። (፩ጢሞ
፫፥፩‐፰፡፡)

95
“ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ የሚሾመው የምእመናን ጠባቂ ሆኖ
ነውር የሌለበት፤ ንጹሕና ቸር፤ የዚህን ዓለም ጭንቀት የማያስብ፤ ፶ ዓመት የሞላው፤
የጎልማሳነት ኃይልን ያለፈ፤ ነገር የማይሠራ፤ በወንድሞች መካከል ሐሰትን የማይናገር
ይሆን ዘንድ እንደሚገባው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰማን (ዲድስቅልያ
፬፥፩፡፡) የሚማር ይሁን፤ ሰላምን የሚያደርግ ይሁን፤ ቂም ክፋትና ዐመፅ የሌለበት ልበ
ንጹሕ ይሁን፤ በጎ ሥራን ለመሥራት ትጉህ መንፈሳዊ ይሁን፤ የማይሳሳት፤
የማይቆጣ፤ የማይበቀል፤ ጸብና ክርክር የሌለው፤ የማይኮራ፤ ገንዘብ የማይወድ፤
የማይሳደብ ይሁን፤ በዚህ ዓለም ጉዳይና በሥጋው ነውር የሌለበት ይሁን፤ የሚራራና
የሚመጸውት ይሁን፤ ሰውን ወዳጅ የሆነ፤ እንግዳን የሚቀበል፤ ፊት አይቶ የማያዳላ፤
እውነተኛ ፈራጅ የሆነ፤ ጥበብ ያለው፤ ለመስጠት እጁን የሚዘረጋ፤ ረዳት የሌለውን
የሚቀበል፤ ድሆችን፥ ደሀ አደጎችንና ባልቴቶችን የሚወድ ይሁን”። (ዲዲስቅልያ
፬፥፰‐፲፭፡፡)

የአሿሿም ሥርዓት

ኤጲስ ቆጶስ በዕለተ እሑድ ይሾም። በሚሾምበትም ቀን ካህናትና ምዕመናን ይገኙ


ሕዝቡና ካህናቱም መክረውለት ይሾም፤ እጃቸውን በእርሱ ላይ ሊያኖሩ የመጡ ኤጲስ
ቆጶሳቱም “እኛ በዚህ በተመረጠ በእግዚአብሔር ባሪያ ላይ እጃችንን እናስቀምጣለን፤ እያሉ
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እጃቸውን ያስቀምጡ።

ነውር በሌለባትና አንዲት በሆነች በማይገለጥ በሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በጸናች


ሥርዓት ይጸና ዘንድ፣ የቀና ፍርድን ለመፍረድ፣ ምስጋናን፣ ለመግለጥ ልጅነትን
ለማሰጠት፣ ለታመነች ትምህርት፤ ይኸውም ነገረ መስቀሉን ለማስተማር ከሥሉስ ቅዱስ
ዘንድ በጉባኤ በቤተክርስቲያን የተሾመ ነው። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ቀዳሚ የሆነው ኤጲስ
ቆጶስ እጁን ይጫንበት የሹመቱንም ጸሎት ያድርስ፤ ሕዝቡም “አሜን” ይበሉ። ከዚህ በኋላ
ኤጲስ ቆጶሳቱ እጅ ይንሡት ሕዝቡና ካህናቱም ይገባዋል! ይገባዋል! ይበሉ። ሁሉም እጅ
ይንሱት። በእንተ ሰላምን ይጸልዩለት ከዚህ በኋላ ሊነበብ የሚገባውን ክፍለ መጽሐፍ
ቅዱስ ያንብቡ፡፡ አከታትለውም ቅዳሴውን ይፈጽሙ አስቀድሞ እርሱ ሥጋውንና ደሙን
ይቀበል። ከዚያም በየማዕረጋቸው ለሁሉም ሥጋውና ደሙን ያቀብላቸው። በሰላምም
ያሰናብታቸው። እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ በጌታ ትንሣኤ አምሳል ፫ ቀን መንፈሳዊ በዓል
ያክብሩ።

ሁሉም ከተመረጡ በኋላ ሕዝቡና ቀሳውስቱ ዲያቆናቱ ኤጲስ ቆጶሳቱም በዕለተ እሑድ
ይሰብሰቡ። ከእርሱ የሚበልጠው “አለቃ ይሆናችሁ ዘንድ የመረጣችሁት ይህ ነውን?” ብሎ
ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን ይጠይቃቸዋል። አዎን ቢሉ “የከበረችው ሹመት ለዚህ
ትገባዋለችን?” ይበል፤ “በሚገባና በተረዳ ሥርዓት አኗኗርን አጽንቷልን? ምንም በደል
አልተገኘበትምን?” ይበል እነርሱም መልሰው እንደዚህ እንደሆነ ቢናገሩ በማድላት ያይደለ
በእውነት ሹመት ይገባዋል፡፡ በሦስተኛውም ደግሞ “ለዚህ ሹመት በእውነት ይገባዋልን?”
96
ብሎ ይጠይቃቸው። ነገር ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ይጸናልና በሦስተኛውም
ጊዜ ይገባዋል ቢሉ ሁሉም እጃቸውን ዘርግተው ያጨበጭባሉ። ይህንንም በስምምነት
ካደረጉ በኋላ ጸጥታ ይሁን። ዲያቆናትም ቅዱሳት ወንጌላትን ገልጠው በተሾመው ራስ ላይ
ይያዙ፤ ኤጲስ ቆጶሳትም ለርሱ በሚገባው ወምበር ያስቀምጡት፤ ሁሉም ከተቀበሉት
እግዚአብሔርም ይቀበለዋል።

በሦስት ኤጲስ ቆጶሳት ይሾም፤ እንደዚህ ይሾም። በራሱ ላይ ወንጌልን ተሸክመው የበለጠው
ኤጲስ ቆጶስ እንደዚህ (ለሲመቱ የተዘጋጀውን ጸሎት) ይጸልይ። ጸሎቱን ከጨረሰ በኋላ
እጁን ይጫንበት። ይሳለመውም። መንፈስ ቅዱስም ይመላበት (ያድርበት) ዘንድ በፊቱ
ላይ እፍ ይበልበት። ከዚህ በኋላ የቀሩት ካህናት ሁሉ እጅ ይንሱት:: ሕዝቡ ግን እጁን
ይሳሙት:: ከዚህ በኋላ ቅዳሴውን ይፈጽሙ። (ፍት.ነገ .አንቀጽ፭፥፻፳‐፻፮፡፡)

ከዚህ በተጨማሪ

• ኤጲስ ቆጶሳቱ አዲሱን ኤጲስ ቆጶስ ከመሾማቸው በፊት እጃቸውን ይታጠባሉ።


/ፍትነገ .አን፬፡፡/

• ተሿሚውን ኤጲስ ቆጶስ መስቀል ያስይዙታል።

• ኤጲስ ቆጶስ ከአንድ ኤጲስ ቆጶስ አይሾምም። ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር ሁለት
ወይም ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት /ጳጳሳት/ አንብሮተ እድ በማድረግ ይሾማሉ። /አብጥሊስ
፪፡፡/

• ኤጲስ ቆጶስ የሚሾመው በሚሾምበት ሀገር ካህናትና ምእመናን ምርጫና በርእሰ


ሊቃነ ጳጳሳቱ ፈቃድ ነው። /አብጥሊስ ፪፡፡/

• መራጮችም (ቢያንስ) 30 ዘመን (ዓመት) የሆናቸው ናቸው።

ለ.ሥርዓተ ሲመተ ቀሳውስት


መመዘኛዎች

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለጊዜው ለረድኡና ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ለሾመው ለቲቶ
ለፍጻሜው ደግሞ ለቤተክርስቲያን መመሪያ እንዲሆን ያስቀመጠው /ያስተላለፈው/
የቀሳውስት መስፈርት የሚከተለውን ይመስላል::

የአንዲት ሚስት ባል፤ የማይነቀፍ፤ የሚያምኑ ልጆች ያሉት፤ ስለመዳራት ወይም


ስለአለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር ሹመው (ቲቶ ፩፥፭‐፯) በተጨማሪም በፍትሐ
ነገሥት አባቶቻችን (የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት) በጉባኤ የወሰኑአቸው መመዘኛዎች
ቀርበዋል ጥቂቶቹን እነሆ፦ በራሱ ፈቃድ የሚኖር አይሁን፤ ቂመኛ፣ አብዝቶ፣ የሚጠጣ፣
ለመማታት (ለመገዘት) እጁን (አንደበቱን) የሚያፈጥን አይሁን፤ እንግዳ መቀበልን
የሚወድ፤ በጎ ሥራን የሚወድ፤ ንጹሕ፥ ጻድቅ፥ ቸር የሆነ፤ ከፍትወታት ሰውነቱን ወስኖ

97
ገትቶ የያዘ፤ የሃይማኖት ትምህርት ነገርን በማስተማር የሚተጋ፤ ያልታዘዘ ትርፍን
የሚወድ አይሁን። የእውነት ትምህርትን በማስተማር ማረጋጋት የሚችል፤ የሚክዱትንና
የሚተናኮሉትን የሚከራከራቸው ይሁን እንጂ፤ ሠላሳ ዓመት የሆነው፤ መልካም የሆኑትን
የአምላክ መጻሕፍትን ነገር ይልቁንም አራቱን ወንጌላት ያወቀ፤ አምስት ሰዎች
የመሰከሩለት፤ (ፍት.ነገ.አነ ፮፥፪፻፲‐፪፲፫፡፡)

አፈጻጸም
በዚሁ መመዘኛ መሠረት በፍትሐ ነገሥት ስለቀሳውስት የአሿሿም ሥርዓት የሚከተለው
ሰፍሮ ይገኛል።

• ኤጲስ ቆጶሳት አንብሮተ እድ ይሾማሉ፤

• ቀሳውስት ዙሪያቸውን ከበው ይዳስሷቸዋል፤

• ለኤጲስ ቆጶስ ሹመት እንደተነገረው ይጸልዩለት::(ፍት.ነገ.አን ፮፥፲፫፡፡)

ሐ. ሥርዓተ ሲመተ ዲያቆናት


መመዘኛዎች

ዲያቆናትን ለመሾም የሚቻልባቸው መመዘኛዎች በቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ውስጥ


በሰፊው ሰፍረዋል። ለማሳያ ያህል የሚከተለውን መመልከት እንችላለን::

እንዲሁም ዲያቆናት:- ጭምቶች፤ ቃላቸው የማይለወጥ፤ የወይን ጠጅ መጠጣትን


የማያበዙ፤ ከንቱ ትርፍንም የማይወድዱ ይሁኑ፤ የሃይማኖትንም ምሥጢር በንጹሕ ልብ
የሚጠብቁ ሊሆኑ ይገባል፤ እነርሱም አስቀድመው ይፈትኑአቸው ከዚህም በኋላ ያለነቀፋ
ከሆኑ ያገልግሉ፤ የአንዲት ሴት ባሎች የሆኑ፤ ልጆቻቸውንና የቤታቸውን አስተዳደር
በመልካም የሚገዙ በማለት ይዘረዝራል። “በመልካም ለሚያገለግሉት ከፍተኛውን ሹመት
ይስጧቸው፤ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ብዙ ባለሟልነት አለና”። (፩ጢሞ፫፥፰‐፲፩፡፡)
በማለት ያጠቃልላል።

በፍትሐ ነገሥትም ከቀረቡት መመዘኛዎች መካከል ለየት ያሉ የሚመስሉትን ብቻ


መርጠን እናቀርባለን። ርኩስ የሆነውን የትርፍ ድርሻ አይውደዱ፤ የሚራሩ፣ የዋሃን፣
የማያንጎራጉሩ ይሁኑ፤ ቁጡዎች አይሁኑ፤ ለባለጸጎች ፊት የሚያደሉ ነዳያንን
የሚያሳዝእኑ ወይን አብዝተው የሚጠጡ አይሁኑ፤ ስለበጎ ምሥጢራት ምርመራ
የሚሰንፉ አይሁኑ ፤ከሶስት ሰዎች የተመረጡና የተመሰከረላቸው ይሁኑ፤ ሃያ አምስት
ዓመት የሆናቸው፤ (ፍት.ነገ. ፯፥፪፻፴፱‐፪፻፵፮፡፡)

አፈጻጸም

98
የዲያቆናትን ሹመት በተመለከተ ፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ተጽፏል::

“ዲያቆኑን በምትሾምበት ጊዜ በእርሱ ላይ እጅህን አኑርና (አስቀምጥና) ጸልይ። ሁሉም


ቀሳውስትና ዲያቆናት ቁመው ሳሉ አስቀድመን እንደተናገርንና እንዳልን ይመረጥ። ከዚህ
በኋላ ኤጲስ ቆጶሱ ብቻ እጁን ይጫንበት። ቀሳውስት የሚተባበሩበትን ቅስና ይህ ዲያቆን
ይቀበል ዘንድ አይሾምምና፤ የኤጲስ ቆጶሱን ትእዛዝ ይሠራ ዘንድ ነው እንጂ።
(ፍት.ነገ.አን.፯፥፪፻፵፱፡፡)

፬.የሚያስገኘው ጸጋ፦
የተከበሩ አንባቢ ሆይ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ

❖ ሴቶች ለምን ካህናት አይሆኑም?

በገሃድ እንደሚታወቀው ሥልጣነ ክህነት ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ወንዶች እንኳን


ቢሆን አይሰጥም። በብሉይ ኪዳን ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መካከል የክህነት
አገግሎት ለሌዊ ነገድ፤ ከዚያም ለአሮንና ለልጆቹ የተፈቀደ ሲሆን ሌሎቹ ግን መቅደሱን
እንዳይዳፈሩ ተከልክለዋል:: ክህነትን በዐመፅ ለመቀማት ያሰቡት ቆሬ ዳታንና አቤሮን
ከነቤተሰቦቻቸውና ንብረታቸው ጥፋትን መጎናፀፋቸው ይታወሳል። (ዘኁ ፲፮፥፩‐ፍጻሜ፡፡)
እግዚአብሔር አምላካችን ሙሴን የአሥራ ሁለቱንም ነገድ አባቶች በትር ማታ ወደ
ቤተመቅደስ አግብቶ ጠዋት እንዲያወጣ አዘዘው:: በክህነት ያገለግለው ዘንድ የመረጠው
በትር ላይ ምልክት እንደሚያሳየውም አክሎ(ጨምሮ) ነግሮታል። ቀደም ብለን
እንደገለጽነውም የአሮን በትር ለምልማ አብባና አፍርታ በመገኘቷ የእስራኤል
ማጉረምረማቸው ለጊዜውም ቢሆን ጸጥ ብሎ ነበር። ያቺ የአሮን በትርም
ለማጉረምረማቸው ምስክር ትሆን ዘንድ በምስክሩ ታቦት አጠገብ እንድትቀመጥ መታዘዙም
ይታወቃል:: (ዘኁ ፲፯፥፩‐፲፪፡፡) በዚህ ሁሉ የክህነት አገልግሎት ታሪክ ውስጥ ሴቶች
ሱታፌ እንዳልነበራቸው መረዳት ተገቢ ነው።

በአዲስ ኪዳንም ቢሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክህነትን ምሥጢር በመሠረተ ጊዜ


የማሰርና የመፍታት ሥልጣንን ሰጥቶ ምሥጢራትን እንዲፈጽሙ የፈቀደላቸው
ከተከተሉት መካከል ወንዶች ማለትም ቀደም ብሎ ፲፪ቱ ሐዋርያት፤ ከዚያም ፸፪ቱ
99
አርድዕትና የመሳሰሉት ናቸው። ለሁሉም አማኝ ማለትም ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች
አለመፈቀዱን ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ይነግሩናል:: ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ
ጢሞቴዎስን ፈጥኖ እጁን በመጫን ካህናትን እንዳይሾም ማስጠንቀቁ ለዚህ አንድ ማሳያ
ነው:: ሁሉም ካህናት መሆን የሚችሉ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ያለ ማስጠንቀቂያና ትምህርት
አይሰጥም ነበር (፩ጢሞ ፭፥፳፪፤ ፫፥፩‐፲፬፡፡) ከላይ እንደገለጽነው የሐዲስ ኪዳን ትምህርት
ከብሉይ ኪዳን ክህነት የሚለየው የዘር ተከፍሎ ስለሌለበት ነው። ውድ አንባቢ ሆይ እዚህ
ላይ መረዳት ያለብን እግዚአብሔር ከወንዶች መካከል እሱ ባወቀ በመረጣቸው ብቻ
ሥልጣነ ክህነትን ፈቅዶ ሌሎችን የከለከለበት ምክንያት የማይታወቅ መሆኑን ነው።
እግዚአብሔርን “ይህን ለእገሌ ፈቅደህ ይህንን ለነእገሌ ለምን ከለከልክ?” ማለት የማይቻል
መሆኑ መረሳት የለበትም:: (ኢሳ ፵፥፲፩‐፲፭፡፡) የሥልጣነ ክህነት አለመፈቀድ ማለት
የቅድስና ሕይወትና የመንግሥተ ሰማያት በር መዘጋት ወይም መከልከል ስላልሆነ
በተሰጠውና በተፈቀደው የአገልግሎት መስመር እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን ተግቶ
ማገልገል ለቅድስና ሕይወት እንደሚያበቃ ማወቅ ይገባል። ከዚህ ውጪ “ሴቶች ክህነት
ለምን ተከለከሉ?” በማለት እግዚአብሔርን መሞገት ምንም ዓይነት ዕርባና የለውም።
(ኢሳ፵፥፱‐፲፩፡፡) ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚያስገቡ መንገዶች በርካታ
መሆናቸውንና እነዚህም ለሴቶችም ጭምር የተፈቀዱ የአገልግሎት መስመሮች
መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም።
(፪ቆሮ፲፪፥፩‐ፍጻሜው።)

❖ አንድ ሰው የክህነት ሥልጣን ሲሰጠው የሚያገኘው ጸጋ ምንድነው?

ጳጳሳት አባቶቻችን በሚያደርጉት ጸሎትና አንብሮተ እድ በካህናት በኩል የሚተላለፈው


ጸጋ እግዚአብሔረ በእጅጉ ታላቅ ነው:: በሚታየው አገልግሎት የማይታየው ጸጋ በሦስቱም
የክህነት ደረጃዎች እንደየአቅማቸው ይሰጣል። (፪ጢሞ፩፥፮፤ ፩ጢሞ፬፥፲፬፡፡) በካህኑ ላይ
የሚያድርበት ይህ ጸጋ እግዚአብሔር ሥልጣንና ተግባሩን የሚያስፈጽምለትና ለምእመናን
የሚያበረክተውን አገልግሎት የሚያሠምርለት ነው:: ካህናት እንደ ነቢያት ቃለ
እግዚአብሔርን የማስተማር፣ እንደ ካህንነታቸውም ኃጢአትን የማስተሥርይና
ምሥጢራትን የመፈጸም እንዲሁም እንደ ንጉሥ /መሪ/ የክርስቶስን መንጋ የመጠበቅና
የማስተዳደር ሥልጣን አላቸው። በጥቅሉ ለካህናት አባቶቻችን ክርስቶስን የሚመስሉበት
ታላቅ የአገልግሎት ሕይወት የሚያጎናጽፋቸው ነው። ምክንያቱም፦

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንደ አናጉንስጢስ በቤተ መቅደስ መጻሕፍትን


አንብቧል። (ሉቃ ፬፥፮፡፡) እንደ አጻዌ ኀዋኅው የቤተ መቅደስን በሮች ጠብቋል።
(ማቴ፳፩፥፲፪፡፡) እንደ ዲያቆን ዝቅ ብሎ ታዟል፤አገልግሏል። (ዮሐ ፲፫፥፭፱፡፡
ማቴ፳፥፳፱፡፡ ሉቃ፳፪፥፳፮፡፡) እንደ ሊቀ ዲያቆን አገልጋዮችን አስተባብሯል፤
አሰማርቷል። (ማቴ፲፥፮‐፭፡፡ ማር፲፮፥፲፭፡፡) እንደ ካህን /ቄስ/ ሥጋ ወደሙን
ፈትቶ ቆርቦ አቁርቧል። (ማር፲፬፥፳፪‐፳፮፡፡) እንደ ጳጳስ ሕዝቡን ሰብስቦ
አስተምሯል፤ የተበታተኑትን ሰብስቧል። (ማቴ ፱፥፴፮‐፴፰፡፡ ዮሐ፰፥፰፩‐፰፯፡፡)
100
እንደ ፓትርያርክ እጁን ጭኖ ሥልጣነ ክህነት ሰጥቷል።(ሉቃ፳፬፥፶፡፡
ዮሐ፳፥፳፪‐፳፫፡፡ ማቴ፲፰፥፲፰፡፡)

በዚህ መሠረት ክርስቶስን ከመምሰል የሚበልጥ ምንም ጸጋ ፈጽሞ ስለሌለ ለካህናት


የተሰጠ ጸጋ ለአማኞች ሁሉ ከተሰጠ የልጅነት ጸጋ ይበልጣል:: ከልጅነት ጸጋ በተጨማሪ
ለጨለማው ዓለም ብርሃን፣ ለአልጫው ዓለም ጨው በመሆን የተለያየውን ዓለም በክርስቶስ
አንድ እንዲያደርጉ ተመርጠዋልና። ካህናት ድውያኑን እንዲፈውሱ። የታሰረውን እነዲፈቱ
ኃጢአትን እንዲያስተሠርዩና ምሥጢራትን ሁሉ እየፈጸሙ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ
የተሾሙ ናቸው።

ማጠቃለያ:-
ቅዱሳት መጻሕፍት የካህናትን ሥራ በእረኝነት ተግባር መስለው ያስተምራሉ፡፡ የእረኛው
መዘናጋት በጎችን ለተኩላዎችና ለቀበሮዎች የተጋለጡ እንደሚያደርጋቸው ሁሉ የካህናት
መዘናጋትም በበግ የተመሰሉ ምእመናንን ለክህደትና ለኑፋቄ የተመቻቹ ያደርጋቸዋል፡፡
ሕዝቡ በኃጢአቱ ቢፈረድበትም ካህናትም ተጠያቂ መሆናቸው አይቀርም፡፡ መንጋው
የአራዊት ንጥቂያ ቢሆን፣ አለቅት ቢይዘው፣ ሳይጠግብ ቢመለስ፣ ከሌላ ማሳ ገብቶ ቢያጠፋ
በዚህም ምክንያት ወቀሳና ክስ ቢከተል፣ /ቢመጣ/ ዋናው ተጠያቂ እረኛው መሆኑ የታወቀ
ነው፡፡ በምእመናን ጥፋት፣ ክህደት፣ ሥርዓት የለሽ መሆን፣ ንስሐ አለመግባትና ከቅዱስ
ቁርባንና ከመልካም ምግባራት ሁሉ መራቅ ቀጥተኛ ተጠያቂው ካህኑ ስለሆነ ካህናት
እንዲጠነቀቁና ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ እነዚሁ መጻሕፍት ያስጠነቅቃሉ፡፡ (ሕዝ
፴፫፥፯‐፲፤ ፴፬፥፩‐ፍጻሜ፡፡) በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት ቤተ
ክርስቲያን ናት፡፡ አስተናጋጆች /አስተናባሪዎች/፣ መጋቢዎች፣ መሳፍንትና መኳንንት
ይሆኑት ዘንድ ንጉሡ እግዚአብሔር የሾማቸው ደግሞ ካህናትን ነው፡፡ በምድር ላይ ከዚህ
የተሻለ ቀርቶ የሚወዳደር ምን ዓይነት ሥልጣን ይኖራል? ካህን ሆኖ ከመሾምስ
የሚበልጥና የሚወዳደር ምን ዓይነት ሥራና አገልግሎት አለ? በእውነቱ ካህናት በምድር
ላይ ያሉ የእግዚአብሔር መላእክት ናቸው፡፡ እነሱን ማክበር መውደድና መታዘዝ
እግዚአብሔርን የሚያስደስት መሆኑን መረዳት ከምእመናን ይጠበቃል፡፡ ካህኑ ክህነቱ
ሲያቃልላት ከእግዚአብሔር እንደሚለይ ሁሉ ምእመናንም ካናትን ሲያቃልሉ
ከእግዚአብሔር ይጣላሉ::

ዋቢ መጻሕፍት

• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫


አ/አ።
101
• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ


ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን
1999፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ


ድርጅት፤ ፳፻፬፤ አ/አ፡፡

102
ምዕራፍ ሰባት
ምሥጢረ ንስሐና አፈጻጸሙ
መግቢያ
እግዚአብሔር አምላካችን ለሰው ልጆች ሥጋዊ ደዌ ሕመም ፈውስ የሚሆኑትን መፈወሻ
መድኃኒት እንደሰጠን ሁሉ የነፍስ ደዌ ኃጢአትን የሚያርቅና ከሕመሙ የሚፈውስ
መድኃኒት ንስሐን ሰጥቷቸዋል:: ደዌ የሆነው ኃጢአት በምድራዊ ኑሮአችው ሁሉ አብሮ
እንደሚኖር የታወቀ በመሆኑ መድኃኔዓለም ክርስቶስ መድኃኒቱንም አብሯቸው ይኖር
ዘንድ ከሐኪሞች ከካህናት ጋር በመካከላችው አኖረው::

በዚህ ምዕራፍ ሥር ይህን ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ መሠረታዊ የሆኑ ነጥቦችን


በማብራራት እናያለን፡፡ በዋናነትም አመሠራረቱንና አስተምህሮውን፤ አፈጻጸሙንና
የሚያስገኘውን ጸጋ እንዳስሳለን፡፡ ክቡር የዚህ መጽሐፍ አንባቢ ሆይ በየንዑስ ክፍሉ
የቀረቡትን ማብራሪያዎች በማስተዋል /በማንበብ/ ከዕለት ተዕለት ክርስቲያናዊ ሕይወትዎ
ጋር እያጣጣሙ ለክርስቲያናዊ ስኬት እንዲጠቀሙበት እንመክርዎታለን::

ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ተምረው


ሲፈጸሙ፡-

• የምሥጢረ ንስሐን ምንነትና አፈጻጸም ይገነዘባሉ።

• ሕይወታቸውን በንስሐ ለማደስና ሌሎችንም ለማነጽ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ


ያዳብራሉ።

103
፯∙፩ አመሠራረት
የምሥጢረ ንስሐን አመሠራረት ከማየታችን በፊት ምነነቱን ባጭሩ እንገልጻለን።
ንስሐ ማለት ከጥምቀት በኋላ በሠሩት ኃጢአት ከልብ ማዘን፣ ወደ መምህረ ንስሐ
ሄዶ መናዘዝ (ኃጢአትን መናገር)፣ ጥፋትን ላለመድገም መወሰንና በእግዚአብሔር
ቸርነት፥ በካህኑም የማሰር የመፍታት ሥልጣን አምኖ አነሰ፣ በዛ ሳይሉ የተሰጠውን
ቀኖና በደስታና በምስጋና ተቀብሎ መፈጸም ነው። ከላይ በተገለጸው መሠረት
ምሥጢረ ንስሐ ምእመናን ከኃጢአት ቁራኝነት የሚላቀቁበትና አዲስ ሕይወትን
የሚያገኙበት የድኅነተ ነፍስ መንገድ ነው፡፡ ሥርወ ቃሉ “ነስሐ” የሚለው የግእዝ
ቃል ሲሆን ትርጉሙም ንስሐ ገባ፣ ዐዘነ፣ ተጠጠተ፣ ተመለሰ፣ ክፉ ዐመሉን ተወ፣
ጠባዩን ለወጠ፣ ማለት ነው። (ኪ.ወ.ክፍሌ ገጽ ፮፻፶፭፡፡)

ንስሐ ለምን ያስፈልጋል?


ምሥጢረ ንስሐን የመሠረተው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::
በሞቱ ሞትን አጥፍቶ የዕዳ ደብዳቤያችንን ደምሰሶ ነጻ ካወጣን በኋላ ዳግመኛ በኃጢአት
መተዳደፋችን እንደማይቀር ስለሚያወቅ የንስሐን ምሥጢር መሠረተልን። “ሸማ ሲያድፍ
በውሃ፤ ሰውነት ሲያድፍ በንስሐ” እንዲሉ:: ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና የተቀበለ ሰው
ከቀደመ ኃጢአቱ በጥምቀት ቢነጻም በቀረ ዘመኑ ከሚሠራቸው ጥፋቶች በምሥጢረ ንስሐ
እንዲነጻ ክርስቶስ ፈቀደለት:: አስቀድሞ ለሐዋርያት ከዚያም ቀደም ባለው ምዕራፍ
እንዳየነው በተዋረድ ለተነሡና ለሚነሡ አገልጋዮች (ካህናት) ኃጢአትን ይቅር የሚሉበትና
የሚይዙበት /የሚፈቱበትና የሚያስሩበት/ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ (ዮሐ፳፥፳፩‐፳፫፡፡
ማቴ፲፰፥፲፰፡፡) ይህም ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአትን የሚያስተሰርዩበትን
ጸጋ፣ መንግሥተ ሰማያትንም ከፍተው የክርስቶስን መንጋ የሚያስገቡበት ቁልፍ ለካህናት
አባቶቻችን ሰጥቷቸዋል። ”… የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር
የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት
የተፈታ ይሆናል” በማለት እንደገለጸልን፡፡ (ማቴ፲፮፥፲፮‐፳፡፡)

፯.፪. አስተምህሮ
❖ (በሉቃ ፲፭፥፬-ፍጻሜው) ስናነብ ከምናገኛቸው ሦስቱ የጠፉ ነገሮች መካከል
ከርስዎ ሕይወት ጋር የሚመሳሰለውን ለይተው ለማወቅ ይሞክሩ ።

በሉቃስ ወንጌል ምዕ፲፭፥፬- ፍጻሜው ያለውን ታሪክ ስንመለከት ከመንጋው ተነጥሎና


ባዝኖ በምድረ በዳ የጠፋውን በግ፣ በቤት ውስጥ የጠፋውን ድሪምና ከቤተሰቡ ተለይቶ
ወጥቶ የጠፋውን ታናሹን ልጅ እናገኛቸዋለን። ባለበጎቹ፣ ባለድሪሟና፣ የልጁ አባት
በጠፋባቸው ነገር እጅግ እንዳዘኑ፣ የጠፋባቸውን አጥብቀው እንደፈለጉና ባገኙትም ጊዜ
ፍጹም ደስ እንዳላቸው እናነባለን:: እነዚህ ተገናዛቢ ታሪኮች ሁሉም የንስሐን ክብር፣

104
ኃይልና ምሥጢር ያሳዩናል:: ከሀገርና ከወገን ተለይቶ፤ ከሃይማኖት፣ ከምግባር ምድረ በዳ
በሆነ ቦታም መጥፋት አለ:: በቤት ውስጥ ሆኖ የትም ሳይወጡ ባሉበት ሁኔታ መጥፋት
አለ:: ከሞላ ከተትረፈረፈ፥ ሰላምና ፍቅር ከሰፈነበት ቤት አሻፈረኝ ልቀቁኝ ብሎ ወጥቶም
መጥፋት አለ፡፡ ባለንብረትና ወላጅ አባት የሆነ ሰው ደግሞ ያ ነገር የጠፋበትን መንገድና
ሁኔታ እያሰላሰለ ከመናደድ ይልቅ የሚገኝበትን መንገድ በማሰብ ፍለጋው ላይ ተግቶ
ይሠራል:: ባገኘው ጊዜ ደግሞ ባለው ነገርና አቅም ሁሉ ደስታውን ይገልጻል። በመንፈሳዊ
የሕይወት ጉዞም ሰዎች በተመሳሳይ እይታ በልዩ ልዩ መንገድ ከእግዚአብሔር እጅ
ሊወጡ፤ ከመንፈሳዊት ቤታቸውም ሊኮበልሉ /ሊጠፉ/ ይችላሉ:: እግዚአብሔር አምላካችን
ግን የኀጥኡን ሰው ሞቱንና ጥፋቱን አይሻም፤ መመለሱን እንጂ። “በውኑ ኃጢያተኛ
ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገድ ሊመልስና በሕይወት
ይኖር ዘንድ አደለምን?” እንዲል፡፡ (ሕዝ ፲፰፥፳፫፡፡)

ከላይ የጠቀስነውን ምሳሌያዊ ትምህርት ያስተማረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ


ክርስቶስ ነው። በዋናነት የጠፋውን በግ አዳምን የፈለገውና ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት
በትከሻው የተሸከመው እሱ ክርስቶስ ነው። (መቅድም ማርያም፡፡) ምሳሌዎቹም ይህን
የምሥጢረ ሥጋዌ ታሪክ አጉልተው የሚናገሩ ናቸው:: በተጨማሪም ምሳሌዎቹ በማወቅም
ይሁን ባለማወቅ ከሀገር ወጥተውም ሆነ በሀገር ቤት /በቤት /ውስጥ/፣ በቤተሰብ ቁጥጥር
ሥር ሆነውም ይሁን ከቤት ወጥተው /ከቤተሰብም ተለይተው/ በኃጢአት የጠፉትንና
የሚጠፉትን ሁሉ ይናገሯቸዋል፡፡ እነዚህ የጠፉ አካላት ራሳቸውን ፈልገው እንዲያገኙና
በሕይወት እንዲኖሩ ይጋብዟቸዋል። ሌሎች ስለጠፉት የሚገዳቸው ክርስቲያኖች ሁሉና
የሚመለከታቸው አካላትም የጠፉ ወገኖቻቸውን ፈልገው እንዲያገኟቸውና ሐሴት
እንዲያደርጉ ይጎተጉቷቸዋል:: በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የጠፉበት ምክንያት፣
የጠፉበት ቦታ፣ የጠፉበት ሁኔታና የጠፉበት ጊዜ ሚዛን የሚደፋ ጉዳይ አይደለም። ሚዛን
የሚደፋውና በሁሉም ዘንድ በእጅጉ የሚፈለገው የጠፋው ነገር ፍለጋ፣ መገኘትና ወደ
ቀደመ መኖሪያና ቦታው መመለሱ ነው። በግልጽ አነጋገር ለክርስቲያኖችና ለቤተ
ክርስቲያን መሠረታዊው ጉዳይ ኀጥአን በንስሐ የመመለሳቸው ነገር ነው።

የቀደመ በደልና ኀጢአት ይደመሰስ /ይሠረይ/ ዘንድ ንስሐ በእጅጉ አስፈላጊ ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ዼጥሮስ በበዓለ ሃምሳ በጽርሐ ጽዮን ዙሪያ ተሰብስበው ለነበሩ እጅግ
በርካታ ሕዝቦች የድኅነትን ትምህርት አስተማራቸው:: በትምህርቱ የተመሰጡት እነዚያ
ሰዎችም “ምን እናድርግ?” ባሉ ጊዜ የተመለሰላቸው መልስ ከንስሐ ሕይወት ጋር የተያያዘ
ነበር። (ሐዋ.፪፥፲፬‐፵፩፡፡) በቤተ መቅደስ በር ላይ ይቀመጥ የነበረውን ድውይ /መሔድ
የተሳነውን ሕሙም/ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስ በክርስቶስ ስም በፈወሱት ጊዜ
መገረምና መደነቅ የሞላባቸው አይሁድ ብዙ ነበሩ። ቅዱስ ጴጥሮስ ለእነዚህም በሥጋ
ስለተገለጠው አምላክ ካስተማራቸው በኋላ አለቆቻቸው በዓለማ ክርስቶስን በካዱትና
በገደሉት ጊዜ ተባባሪዎቻቸው የሆናችሁት እናንተ እንግዲህ ኀጢአታችሁ ይሰረይላችሁ
ዘንድ ንስሐ ግቡ፤ ተመለሱም፤ (ሐዋ. ፫፥፲፱፡፡) መባላቸውን እናነባለን። እነዚህ ሁለት
ተያያዥ ኃይለ ቃላት (ነጥቦች) የንስሐን አስፈላጊነት የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ንስሐ
የማንኛውንም ምእመን ቁስለ ነፍስ የሚፈውስ መንፈሳዊ መድኃኒት ነው::
105
ንስሐን ስናስብ ምንጊዜም ኀጢአትን ማሰባችን አይቀርም:: ምክንያቱም አንድ ሰው
የሠራው ኀጢአት በእግዚአብሔር በሌሎች፣ በራሱና በቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጸመ
ጥፋት ነውና:: ኀጢአት ባይኖር ኖሮ ንሰሐ ባላስፈለገም ነበርና:: ኀጢአትን በምናስብበት
ጊዜ ደግሞ ምንጩን መነሻውንና የሚያባብሱትን ነገሮች መመርመራችን የግድ ነው::
ይህም መንፈሳዊ ሕይወታችንን እንዳያውክብን ቀድመን ለመጠንቀቅ ማለትም አርቆ
ለማጠር ይጠቅመናል፡፡ ኀጢአት ከ፯ ዓመት ጀምሮ በማንኛውም የዕድሜ ክልል
ይፈጸማል:: በተለይ ደግሞ በሃይማኖት መኖርን እንደ እስረኝነት በሚቆጥር፣ አዳዲስ
ነገሮችን ሁሉ ለመሞከር በሚደፍርና ሌላው ያየውን ካላየ ሞቶ የሚያድር የሚመስለው
ትውልድ የኃጢአት ተጋላጭነቱ ከፍተኛ ነው:: ለዚህ ተጋላጭ የሆነው ወጣት ስሜቶቹን
መፈተሽ ይኖርበታል። ስሜቶቹ በምን እንደተቃኙና እንዳሻቸው ቢለቀቁ ውጤታቸው ምን
ሊሆን እንደሚችል ማስተዋል በእጅጉ ይጠቅመዋል፡፡ መረን መለቀቅ (ዝርው መሆን)
ከመንፈሳዊ ሕይወት አንጻር ሲመዘን ምን ሊባል እንደሚችል ቀድሞ ማሰብ ይገባዋል::
ይህን ማድረጉ ከኃጢአት ተላቆ ወደ ጽድቅ ከተማ የሚያደርገውን ጉዞ ያቀላጥፋለታል::
ያዘነበት፣ የተጸጸተበት፣ የተናዘዘበትና የተሠረየለት ኀጢአት ዳግመኛ ደጁን እንዳያንኳኳ፤
ቢያንኳኳም እንኳን አስተናጋጅ እንዲያጣ፤ ቢሰናከልም ፈጥኖ የሚፀፀትበትንና
የሚናዘዝበትን ኃይል ያደርግለታል:: በዚህም ምክንያት የኀጢአት ምንጮቹንና
የሚያባብሱ ጉዳዮችን ለይቶ (አውቆ) መጋደል /መዋጋት/ በክርስቲያኖች መንፈሳዊ ጉዞ
ውስጥ የንስሐ ሕይወት አካል ይሆናል ማለት ነው።

፯∙፫∙ አፈጻጸም
❖ አንድ ወጣት ከአንዲት ተማሪ ጋር ድቀት አገኘውና ልጅቱ ፀነሰች፤መፅነሷን
ሲሰማ ባደረገው ነገር እጅግ ተጸጽቶ ቤ/ክ ሄደና ለእግዚአብሔር አየተናዘዘ
አለቀሰ:: ይህ ልጅ ንስሐ ገባ ማለት ይቻላልን? ለምን? /እንዴት?

የእግዚአብሔር ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር በሚያደርጉት የማያቋርጥ ትግል ውስጥ


መውደቅና መነሣት ያለ ነው። /ምሳ፳፬፥፲፮፡፡/ ንስሐም የመላ ሕይወት ዘመን ባልንጀራ
ሆኖ አብሮን የሚዘልቅ እንዲሆን ተደርጎ መሠራቱ ለዚህ ነው። በኃጢአት መውደቅ
በተከሰተ ጊዜ ለመነሣት የሚቻለው ደግሞ በዘፈቀደ ሳይሆን በተፈቀደውና ቤተ ክርስቲያን
በሠራቸው የአፈጻጸም ሥርዓት ውስጥ በመጓዝ ነው:: በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን
ማንኛውም መንፈሳዊ እንቅስቃሴ (ሥራ) እንደየዘመኑ ነባራዊ ሁኔታ እግዚአብሔር ባዘዘው
መንገድ ይፈጸም ነበር:: በቅድሚያ ለአብነት ያህል የብሉይ ኪዳኑን የንስሐ አፈጻጸም
መመልከት እንችላለን:: (ዘሌ ፭፥፩‐ፍጻሜው):: የበለጠ ፍሬ ነገሩን በግልጽ ለማሳየት ያህል
ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ እግዚአብሔርም አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን
ቢተላለፍ፥ ቢታወቀው፣ ኃጢአት ስለሆነችበትም ንስሐ ቢገባ፣ ነውር የሌለበትን በሰቅል
የተገመተውን አውራ በግ ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣዋል፤ ካህኑም
ሳያውቅ ስለሳተው ስሕተት ያስተሰርይለታል። ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል፣ እርሱ
በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ ገብቷልና፡፡ (ዘሌ፭፥፲፯‐ፍጻሜው፡፡) በዚህ ሂደት ውስጥ
ኀጢአተኛው፣ መሥዋዕቱ፣ ካህኑና አቀራረቡን እናያለን። ሙሴን እንዲህ እንዲፈጸም
106
ያዘዘው እግዚአብሔር ነው:: ኅጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ
ካህኑንና ኀጢአተኛው አፈጻጸሙን ተከትለው እንዲቀርቡ ማዘዙን ልብ ማለት ይገባል።

በሐዲስ ኪዳንም ተነሳሒውና ካህኑ ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥርየተ ኃጢአት /የንስሐ/


አፈጻጸም መንገዶች ተመቻችተውልናል። የቤተክርስቲያናችን የምሥጢረ ንስሐ አፈጻጸም
ሥርዓት የተነሳሒውን ድርሻ፣ የካህኑን ሐላፊነት የቀኖናውን ዓይነትና የመሳሰሉትን
የሚያካትት ነው። ይህን በተመለከተ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ የንስሐ አፈጻጸም
ደረጃዎችን በሦስት ከፍለው አስተምረዋል:: የንስሐ የመጀመሪያ ደረጃ ኀጢአትን መተው
ሳይሆን ንስሐ ለመግባት ማሰብ ወይም መፈለግ ነው:: ይህ ኀጢአትን ከመተው የሚቀድም
ነው፡፡ ሰዎች ንስሐ ለመግባት ባልፈለጉና ባላሰቡ መጠን በኃጢአት እየተደሰቱ ኃጢአትን
እየሠሩ ይኖራሉ። በእነርሱ አመለካከትም የያዙት የኀጢአት ኑሮአቸው መልካም
ስለሚመስላቸው አይለወጡም። የዚህ ምዕራፍ አንዱ ዓላማ አንባቢያን በቅድሚያ ንስሐ
ለመግባት ማሰብና መፈለግ ቀዳሚው ክርስቲያናዊ ተግባር መሆኑን መረዳት እንዲችሉ
ማሳየት ነው።

በንስሐ ሂደት ሁለተኛው ደረጃ ኀጢአትን መተው ነው። ኀጢአትን መተው ሲባልም
የኀጢአትን እርሾ ከኅሊናና ከልቡና ጨርሶ /ፈጽሞ/ ማጥፋት ነው፡፡ ይህም ኀጢአትን
ከማሰብ መለየት ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ምንም እንኳን ኀጢአቱን በገቢር
/በተግባር/ ባይፈጽምም በልቡ ፍቅረ ኀጢአት ከነገሠ/ /ኀጢአት በልቡ ከተመላለሰ/ ንስሐ
አያስፈልገውም አይባልም። ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ሕግ ለመጠበቅ ብሎ ኀጢአትን
በገቢር ባይሠራም ኀጢአትን አልጠላምና ኀጢአትን ትቷል ሊባል አይችልም፡፡ በልቡናው
የኀጢአት ፍቅርና ቅሪት ስላለ ፀፀቱና ንስሐው ልቡናው ከኀጢአት እስኪነጻ መሆን
አለበት።

የመጨረሻው የንስሐ ደረጃ ኀጢአትን መጥላት ነው:: ይህም ኀጢአትን በፍጹም ልብ


መጥላት፣ አለማሰብና የኀጢአት ተገዢ አለመሆን ነው:: ይህ ከፍተኛው የንስሐ ደረጃ ሲሆን
እዚህ ደረጃ ለመድረስ በክርስትና ሕይወቱ የሚገለጡለትን ረቂቃን /ጥቃቅን/ ኀጢአቶች
ከዚያም ከፍተኛውንና ዋነኛውን ኀጢአት እስኪረሳ ድረስ መሆን አለበት።

በሌላም መንገድ የንስሐን አፈጻጸም ስንመለከት ንስሐ የሚገባ ሰው በመጀመሪያ


የፈጸመውን ኀጢአት ማመን አለበት:: ይህ የመጀመሪያው የለውጥና የንስሐ መንገድ ነው::
ይህንንም እያንዳንዱ ምእመን ዘወትር ሊፈጽመው የሚገባ ተግባር ነው:: ከዚህ ዓለም
ሰዎች ከእመቤታችን በስተቀር “ኀጢአት አልሠራሁም፤ ንጹሕም ነኝ፤” ሊል የሚችል
የለምና:: /፩ዮሐ፩፥፰፡፡/ ኀጢአቱን ካመነ በኋላም እውነተኛውን ደስታ ለማግኘት
ኃጢአቱን እያስታወሰ፣ ሰውንና ፈጣሪውን መበደሉን እያሰበ እውነተኛ የልብ ሐዘን ሊያዝን
ይገባዋል:: ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ በጻፈላቸው መልእክት መነሻነት ተገቢውን የንስሐ /ልባዊ/
ሐዘን በማዘናቸው በቆሮንቶስ ምእመናን መደሰቱን የገለጸው ለዚህ ነው፡፡ ስለ
እግዚአብሔር ብለው አዝነዋልና። (፪ቆሮ፯፥፰‐ፍጻሜው፡፡) “ወአልቦ ካልዕ ሕሊና ላዕለ
አዳም ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ፤ በኃጢአቱ ከማልቀስ በቀር በአዳም ሌላ አሳብ
/ፍላጎት/ አልነበረውም፤” ተብሎ የተገለጸው ለዚህ ነው:: አዳምን የቤተ ፊተ ልማድ
107
አላገኘውም። የቤተ ፈት ልማድ የተባለውም “በዚህ ጊዜ እበላ፥ እጠጣ፥ እደሰት ነበር፥
ይህ ሁሉ አሁን ቀረብኝ፤” በማለት መፀፀትና ማዘን ነው፡፡ የአዳም ሐዘን አንዲህ ዓይነት
አልነበረም፡፡ ያዝን የነበረው “ያልተሰጠኝን ተመኝቼ፣ የእግዚአብሔርን ሕጉን ትእዛዙን
ጥሼ አሳዘንኩት።” በማለት ነበርና። ከፈጣሪው ቃል ኪዳን ተቀብሎ በጊዜው ጊዜ የዳነው
በተገቢው መንገድ በማዘኑ ነው:: (መቅድመ ወንጌል ሦስተኛ ጉባኤ)

❖ አንድ ሰው ንስሐ ሲገባ የሠራውን ኃጢአት ለንስሐ አባቱ ይናገራል። በዚህ


ድርጊት ተነሳሂው የሚያገኘው ጥቅም ምንድነው? ይልቁንም የራሱን
ምሥጢር ለሌላ ሰው በመናገሩ ሥጋት ሊይዘው አይችልምን?

በምሥጢረ ንስሐ አፈጻጸም መምህረ ንስሐ ከመያዝ የሚቀድም ተግባር የለም፡፡


የምእመናን የመጀመሪያ ተግባር በአጥቢያቸው ከሚገኙ ካህናት /ቀሳውስት/ መካከል
መርጦ የንስሐ አባት መያዝ ነው። ካህኑም /ቄሱም/ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ከንስሐ ልጁ
አይለይም። ነቅቶና ተግቶ እንደ እረኝነቱ ከነጣቂ ተኩላ፥ ከኃጢአት አሽክላ ምእመናንን
/የንስሐ ልጆቹን/ ይጠብቃቸዋል:: መንፈሳዊውን የሕይወት ምግብ እየመገበ፣ መንፈሳዊውን
የሕይወት መጠጥ እያጠጣ ልጆቹን ወደ እገዚአብሔር መንግሥት ይመራቸዋል፡፡
በዋነኛነትም ወደ መንግሥተ ሰማያት በሚያደርጉት መንፈሳዊ ጉዞ የሚገጥማቸውን
መሰናክል /ኃጢአት/ ለማስወገድ ከእግዚአብሔር ጋር ይሠራል:: ምእመናንም ኀጢአት
በሠሩ ጊዜ ወደ መምህረ ንስሐቸው በመሔድና በመናዘዝ ከማእሰረ ኀጢአት ይላቀቃሉ።
በሚሠሩት ሥራ ሁሉ በመንፈሳዊ አባታቸው ፈቃድና ምክር ይመራሉ።

ከላይ እንደገለጽነው ኃጢአቱን /በደሉን ያመነ/ ሰው ከልቡ እያዘነ ወደ መምህረ ንስሐው


ይሔዳል። በመቀጠልም ተነሳሒው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሠራውን ኀጢአቱን
ሳይደብቅ /ሳይሰውር/ ይናዘዛል። (ምሳ ፳፰፥፲፫):: ኀጢአትን መናዘዝ የሚጠቅመው እጅግ
አስፈሪ ከሆነው የዘለዓለም ሞት ለመዳን እስከሆነ ድረስ የተፈጸመው ምንም ዓይነት
ኀጢአት ቢሆን ሳያፍሩና ሳይፈሩ መናዘዝ ይገባል:: “ምን ይሉኛል?” ብሎ አፍሮና ፈርቶ
ባለመናዘዝ የሞት ሞት ከመሞት ሰዎች “ያሉትን ይበሉ!” ብሎ በድፍረት በመናዘዝ ራስን
ከገሃነም እሳት ማዳን አማራጭ የሌለው መንገድ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ካህናት
ምሥጢር የመጠበቅ ታላቅ ሓላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት አይገባም። “ለንስሐ አባቴ
ብነግራቸው ምሥጢሬን ለሰው ሊያወሩብኝ ይችላሉ፤” በማለት መፍራት አይገባም፡፡ ይህን
የመሰለ ነውር እንዲያደርጉ የክህነታቸው ሥነ ምግባር አይፈቅድላቸውም:: አባቶቻችን
ለዚህ ነው “ለካህን የተነገረ ነገር ፥ ከባሕር የተወረወረ ጠጠር፤” በማለት
የሚያመሠጥሩት፡፡ አንዳንድ ከክህነት ሥነ ምግባር ውጪ የሆነ ቄስ ቢያጋጥምም እንኳን
ምሥጢር ባለመጠበቁ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ዘንድ ይጠየቅበታል፤ ይቀጣበታል።

ምእመናን በሚናዘዙበትም ወቅት “ቀን ጥሎኝ /ጎድሎብኝ/፣ ሰይጣን አሳስቶኝ፣


እግዚአብሔር አዞብኝ፣… ኀጢአት ሠራሁ።” ብሎ መናዘዝ ተገቢ አይደለም:: የእነዚህ
አባባሎች መልእክትም “ኃጢአት ያሠራኝ /የሠራው/ ቀኑ (ጊዜው) ነው እንጂ እኔስ ንጹሕ
ነኝ፤ ኀጢአቱን የሠራው ሠይጣን ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።” ማለት ነው።
እግዚአብሔር አዞብኝ ማለትም ይቅር ባይ ቸር ርኅሩኅ አዛኝ የሆነ እግዚአብሔርን
108
ኀጢአት ወዳጅ ማድረግ ነው:: ይልቅስ መባል ያለበት በአፍ ብቻ ሳይሆን በልብም ጭምር
እንዲህ ነው።

“ሥጋዬን ወድጄ፥ ነፍሴን ጠልቼ፥ ኀጢአት ሠራሁ፥ የእግዚአብሔር ሕጉን፥ ትእዛዙን


በመጣስ በደልሁ፥ አጠፋሁም፥ ፈጣሪዬንም አሳዘንሁ።” በማለት በፍርሐትና በፍጹም
ትሕትና እውነቱን ተናግሮ ራስን መክሰስና ከልብ ማዘን ይገባል፡፡ ኑዛዜውም ተነሳሒው
በዓይነ ሥጋ በሚያየው በአባቱ በካህኑና በዓይነ ሕሊና በሚያየው በአባቱ በእግዚአብሔር
ፊት ነው።

ቀጣዩ ተግባር ተነሳሒው ከካህኑ ምክርና ተግሣጽ የሚያገኝበት፤ ቀኖና /የንስሐ ቅጣት/
የሚቀበልበትና ካሣ /መቀጫ/ የሚከፈልበት ክፍል ነው፡፡ ካህኑ የሚሰጠው ቀኖና እንደ
ኅጢአቱ መጠን ተለክቶ የተሰጠ ማወራረጃ ማካካሻ ሳይሆን እንደተነሳሒው አቅም፣ እንደ
ካህኑ ሥልጣንና እንደ እግዚአብሔር ቸርነት የሆነ የድኅነት ምክንያት ሆኖ የሚቀርብ
ነው:: ቀኖናውም የጾም፣ የጸሎት፣ የስግደት፣ የምጽዋት ሊሆን ይችላል። ቀኖናው
ከተጠቀሱት ውስጥ በከፊል፣ በተጠናጠል ወይም በጠቅላላው የያዘ ሊሆን ይችላል።
ኀጢአቱን የሚደመስሰው የቀኖናው መብዛትና ማነስ ሳይሆን በካህኑ ሥልጣን ላይ የተገለጸ
የእግዚአብሔር ቸርነትና ርኁራኄ ነው:: ቀኖናው ግን ለቸርነቱ ምክንያት የሚሆን
የተነሳሒውን ፍላጎት፣ ጥረት፣ እምነት፣ ፀፀት እንዲሁም የካህኑን ሥልጣን መሠረት ያደረገ
ነው፡፡ ቀኖናውም ለተነሳሒው የመታዘዙና የመፀፀቱ ማሳያ (መገለጫ) ተደርጎ ይወሰዳል።
የኀጢአትና የዐመፅ መሣሪያ የነበሩ ብልቶቹ የጽድቅ መሣሪያ ሆነው ለመለወጣቸውም
ማረጋገጫ ነው። ተነሳሒው በታዛዥነት ቀኖናውን ተቀብሎ ሲፈጽም፣ ልቡናው በጸጸት
ሲሰበር፣ ኃጢአትን ሲጠላና ሰይጣንን ሲክድ እግዚአብሔር ይደሰትበታል፡፡ በመጨረሻም
ቀኖናውን ፈጽሞ ለመምህረ ንስሐው ንስሐውን በመንገር ፍትሐት ዘወልድ ተደግሞለት
ካህኑ “እግዚአብሔር ይፍታህ!” ሲለው ከኃጢአት የተፈታና ነጻ የወጣ ይሆናል፡፡
ወዲያውኑም ሥጋውን በልቶ፣ ደሙንም ጠጥቶ ከማኅበረ ምእመናን ይቀላቀላል። ቀደም
አድርገን እንደገለጽነውም ልቡ በጥልቅ ሐዘን በተሰበረና በተፀፀተ ጊዜ ለመናዘዝ የተነሣው
ዳግመኛ ያንን ኃጢአት ላለመሥራት ወስኖ ነው:: ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ከማኅበረ
ምእመናን ከተቀላቀለ በኋላ በእግዚአብሔር አጋዥነት ውሳኔውን ለማስከበር ይታገላል።
አሁንም ዳግመኛ ከተሳሳተ ከላይ የተመለከትነው የንስሐ ሂደት ዳግመኛ ይቀጥላል::
ኃጢአት መሥራቱ በድፍረት አይሁን እንጂ ኃጢአት ምንጊዜም በንስሐ ይሰረያል።

፯∙፬ የሚያስገኘው ጸጋ
❖ ደግሜ ያንን ኃጢአት ልሠራው ስልምችል ላለመሥራት እንዴት
እወስናለሁ? ኃጢአት ላለመሥራት መወሰን ይቻላልን?

በንስሐ ሕይወት መመላለስ በተነሳሕያን ሕይወት የሚታዩ ጉልህ ፍሬዎች አሉት::


የአፈጻጸም ሥርዓቱን ጠብቆ በተገለጸው መሠረት የተገበረ ሰው ከምንም በላይ ታስሮበት
ከነበረው ኃጢአት የተፈታ ይሆናል፡፡ ይህ ነጻነት በምሥጢረ ንስሐ የሚገኝ ፍሬ (ጸጋ)
ነው። ተነሳሒው በኑሮው ሁሉ ትሑት እንዲሆንም ይረዳዋል። በዚህም ከትዕቢት ተላቆ
109
ራሱን በማዋረድ ክርስቶስን ወደሚመስልበት ሕይወት ለማደግ ይችላል:: ሌላው ተነሳሒው
የሚያገኘው ጥቅም ኀጢአትን የሚጸየፍበትና የሚጠላበትን ኃይል መጎናጸፍ ነው፡፡ ከዚሁ
ጋር በተያያዘ ኃጢአተኞችን ግን የሚወድበት ስለ እነርሱም የሚያለቅስበት ጸጋ ያገኛል::
ይህም በሌሎች ኀጢአት (ላይ) በመፍረድ ከሚመጣ አምላካዊ ፍርድ ለመዳን ያስችለዋል።
በራሱ ኀጢአት ከልቡ ያዘነና የተጸጸተ ሰው ለኀጢአተኞች ከማዘን ውጪ በእነርሱ ላይ
የማይጠቅሙ (የፍርድ) ቃላትን ሊያስብና ሊናገር አይችልምና።

ንስሐ የገባ ሰው ስለኃጢአቱ የሚያዝነው ሐዘን ከላይ እንደገለጽነው እንደ ቤተ ፈት “በዚህ


ጊዜ ተሾሜ ይህን እበላ፤ ይህንንም እጠጣ ነበር፤ ወይኔ ዛሬ ግን ይኼ ሁሉ ቀረብኝ፤”
እንደሚለው ያለ አይደለም። እንደ አባታችን አዳም “የእግዚአብሔር ሕጉን አፍርሼ፥
ፈጣሪዬን አሳዘንኩት።” እያለ ነው የሚያዝነው። እንዲህ ያለው ሰው ከንስሐ በኋላ ዘወትር
ጭምትና ሰላማዊ፣ የማይከራከርና ዝምተኛ በመሆን ሕገ እግዚአብሔርን እያሰላሰለ
የሚኖርበትን ጸጋ ያገኛል ሕይወቱንም ወደ ተሻለ መንፈሳዊ ደረጃ ከፍ ማድረግ
በሚያስችል ፍቅረ እግዚአብሔር እርከን ላይ ያወጣል:: በፍቅረ እግዚአብሔር የተቃኘ ሰው
ደግሞ በንስሐ መመላለስን ስለማይሰለችና ስለማይዘናጋ የበዛ ኃጢአቱ ይሰረይለታል፡፡
(ሉቃ ፯፥፵፯፡፡) የበዛ ኃጢአቱ የተሰረየለት ምእመንም ሳይገባው የተደረገለትን ይቅርታ
ዘወትር ስለሚያስብ ልቡ በፍቅረ እግዚአብሔር እሳት እየጋመ መሔዱ አይቀሬ ነው።
ንስሐ የገባ ሰው ዓይኖቹ አጥርተው ስለሚያዩ ቀድሞ በኃጢአቱ ምክንያት ማየት
ያልቻለውን የተከፈተ የገነት ደጅ ይመለከታል:: ይህ በራሱ በንስሐ አማካኝነት የተገኘ ጸጋ
ነው:: በተጠረገለት የንስሐ ጎዳና ስለሚጓዝም አዲስ የመንፈሳዊ ሕይወት ምዕራፍ
ይጀምራል። በዚህም ለራሱም ጭምር ሊረዳው ወደማይችል ጥልቅ ተመስጦ የሚያስገባ
አዲስ መንፈሳዊ ዓለምን ማጣጣም ይከፈታል። በዚህም ምክንያት የመንፈሳዊ ጽናቱ
/ጥንካሬው/ ምንጭ በንስሐ ሕይወት መመላለሱ እንደሆነ ማስተዋል ይጀምራል:: ከዚያም
ንጽሕናን ገንዘብ ለማድረግ እየታገለ በተቀደሰ ሕይወት ለመኖርና ከንስሐ ሕይወት
ሰገነት ላለመውረድ እየታገለ ይጓዛል።

ማጠቃለያ

ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በፍርድ ቀን በአምላኩ ፊት ሲቀርብ ለስንፋናው ምላሽ አጥቶ ዝም


እንዲል የሚያደርገው በተሰጠው የንስሐ ድል አለመጠቀሙ ነው ለምን ኃጢአት ሠራህ
ሳይሆን ለምን ንስሐ አልገባም የሚለውን ጥያቄ በምክንያት አስተካክሎ ማለፍ አይቻልም
ጊዜ፣ ውኃ፣ ሳሙና፣ አጣቢ፣ የማጠቢያ ሥፍራና ዕቃ የተማላለት ሰው “ለምን ልብስህን
ሳታጥብ መጣህ?” ተብሎ ቢጠየቅ ምን ዓይነት ምላሽ ሊያቀርብ ይችላል? ክርስቲያኖችም
የንስሐ ዘመን፣ ካህን፣ ሥርዓተ ንስሐ፣ ቤተ ክርስቲያን እያላችው ንስሐ አለመግባታቸውን
በምን አመካኝተው ሊያመልጡ ይችላሉ? ምንም ዓይነት የማምለጫ መንገድ አይኖርም፡፡

ስለዚህ እግዚአብሔር በዕድሜያችን ላይ የሚጨምራትን እያንዳንዷን ሰከንድ፣ ደቂቃ


በከንቱ የሚያባክኑ ጉዳዮችን ማስወገድና ለቅዱስ ቁርባን መብቃት ይኖርብናል፡፡
ከተጠያቂነት የሚያድነን ብቸኛው መንገድ ይህ ብቻ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
ከኃጢአት ደዌና ከተያያዥ ስቃይ ነጻ የሚያወጣው ፍቱኑ መድኃኒት ንስሐ መግባት ብቻ
ነውና::

110
ዋቢ መጻሕፍት

• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫


አ/አ።

• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ


ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን
1999፤ አ/አ።

111
ምዕራፍ ስምንት
ምሥጢረ ተክሊልና አፈጻጸሙ
መግቢያ
ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ለእግዚአብሔር መንግሥት ለመብቃት በሚያደርጉት መንፈሳዊ
ጉዞ ሁለት የኑሮ አማራጮች አቅርባላቸዋለች፡፡ አንደኛው ፍጹም የሆነ የድንግልና
ሕይወትን ጠብቆ በመኖር የሚገባበትና በተጋድሎ የሚኖርበት የምንኩስና ሕይወት ሲሆን
ሁለተኛው በተቀደሰ ጋብቻ ክብደ ዓለምን በመቋቋም እየተጋገዙ የሚጓዙበት ሕይወት ነው::

በዚህ ምዕራፍ ሥር ሁለተኛውን አማራጭ ማለትም በጋብቻ መኖርን በተመለከተ


ቤተክርስቲያን የምትመራበትንና ምእመናንን የምታስተናግድበትን ሁኔታ ለማቅረብ
ተሞክሯል:: በተጠቀሰው ርእሰ ጉዳይ ሥር የምሥጢረ ተክሊልን አመሠራረት፣
አስተምህሮ፣ አፈጻጸምና የሚያስገኘውን ጸጋ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል::
በየአንቀጹ የቀረቡ ጥያቄዎችን ከራስ ልምድና ሕይወት አኳያ ለመመለስ በመሞከር
ከተሰጡ ማብራሪያዎች ጋር እያገናዘቡ እንዲያነቡ እንመክራለን::

➢ ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ይህንን ምዕራፍ ካጠናቀቁ በኋላ


ተማሪዎች፦

• የምሥጢረ ተክሊልን አመሠራረትና አስተምህሮ ይገነዘባሉ።

112
• የምሥጢረ ተክሊልን አፈጻጸምና የሚያስገኘውን ጸጋ ይረዳሉ።

፰.፩. አመሠራረት
በጋብቻ አመሠራረት ሂደት “እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ
መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።” (ዘፍ ፪፥፲፰፡፡) የሚለው
ኃይለ ቃል መነሻና መሠረት ነው። ይህም የጋብቻ መሥራቹና ፈቃጁ እግዚአብሔር
መሆኑንና የተመሠረተውም በመጀመሪያዎቹ አባታችንና እናታችን /በአዳምና በሔዋን/
መካከል እንደነበር ያስረዳል:: “ምሥጢረ ተክሊል”

በሐዲስ ኪዳን የተሰጠው መጠሪያ ስም ነው። ተክሊል “ከለለ” ከሚለው የግእዝ ግስ


የሚወጣ /የሚገኝ/ ሲሆን ትርጉሙም ጋረደ ፣አጠረ፣ ከበበ፣ አከበረ፣ አጀበ፣ ፈጽሞ አስጌጠ፣

ሸለመ፣ አክሊል አቀዳጀ፣ ማለት ነው። ምሥጢረ ተክሊል በሰፊው ሲብራራ ደግሞ
የሙሽራውንና የሙሽራይቱን የጋብቻ ቃል ኪዳን በሃይማኖት የሚያጸና፣ የጋብቻ ግዴታን
ለመወጣት የሚያስችል፣ በፍቅር የሚያስተሳስርና ዘላቂ አነድነትን የሚያስገኝ የጸጋ
ምሥጢር ነው፡፡ የሚሰጠውም ምንጊዜም ቢሆን እንደሌሎቹ ምሥጢራት ከቅዱስ ቁርባን
ጋር ነው። ይህ የጋብቻ ሥርዓት፣ የጋብቻ ኪዳን፣ ስምምነትና ውል በታወቀ በቂ ማክንያት
ካልሆነ በቀር ፈጽሞ የማይፈርስ ጽኑዕ አንድነት ነው። ቅድስት ቤተክርስቲያን ለሙሽራው
/መርዓዊ/ እና ለሙሽሪት /መርዓት/ የምትፈጽመው ይህ መንፈሳዊ የጋብቻ ሥርዓት
በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ላለው ጽኑዕ አንድነትና ዘላለማዊ ፍቅር ምሳሌ
የሚሆን /የሆነ/ ታላቅ ምሥጢር ነው። (ኤፌ ፭፥፴‐፴፫፡፡) በሐዲስ ኪዳንም ዘመን
መጀመሪያ አካባቢ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ ቃና በተዘጋጀው የጋብቻ ሥርዓት
ላይ በመገኘት ክርስቲያናዊ ጋብቻን አክብሯል። በዶኪማስ ቤት ከእናቱ ከእመቤታችን
ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከደቀ መዛሙርቱ ከሐዋርያት ጋር ተገኝቶ ጋብቻን ፈጽሞ
ባርኮታል። የታወቀና የተገለጠ የመጀመሪያ ተአምሩንም በእመቤታችን ምልጃ የፈጸመው
በዚሁ ሰርግ ቤት መሆኑ ይታወቃል። (ዮሐ ፪፥፩‐፲፪፡፡)

፰∙፪∙ አስተምህሮ
ከላይ የምሥጢረ ተክሊል አመሠራረት ላይ እንዳየነው እግዚአብሔር አምላካችን ጋብቻን
በአዳምና በሔዋን መካከል ሲመሠርት አንድ ወንድ ላንዲት ሴት፥ አንዲት ሴትም
ለአንድ ወንድ ብቻ መሆኑን በተግባር ገልጾልናል፡፡ ይህም ለክርስቲያናዊ ጋብቻ ቋሚ
የዘለዓለም መመሪያ መሆኑን በሚገባ ማስተዋል ይገባል። ጋብቻውም የተመሠረተው
113
በተመሳሳይ ጾታ መካከል ሳይሆን በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች መካከል መሆኑንም ያሳየን
ራሱ እግዚአብሔር ነው። /ዘፍ፪፥፲፰-ፍጻሜ፡፡) ግብረ ሰዶማውያን ለሚያነሱት መሠረት
የለሽ ጥያቄ ይህን ከሰብአዊ ተፈጥሮአችን አኳያ መመርመር በራሱ መልስ ይሰጣል።

የጋብቻን መሠረታዊ ዓላማዎች የተመለከትንም እንደሆነ ሦስት መሠረታዊ (ዐበይት)


ነጥቦችን ያስታውሰናል። ይህ የተቀደሰ የጋብቻ ሥርዓት /ምሥጢረ ተክሊል/
ሙሽራይቱንና ሙሽራውን ከሥጋዊ ሕይወት ለመውጣትና ወደ መንፈሳዊ ሕይወት
ለመድረስ የሚያደርጉትን ጉዞ የተቃና በማድረግ ሦስቱን ዓላማዎች ጠብቀው እንዲጓዙ
ያስችላቸዋል። አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ይህ ምሥጢር ለሙሽራይቱና ለሙሽራው
ጊዜያዊ የሆነ ሥጋዊ ፍላጎት መፈጸሚያ፣ ለሰው ፊት መታያና ለቀረፃ ማሳመሪያ የሚውል
የካሜራ ፍጆታ አይደለም፡፡ ዕጮኞሞች ሳይገባቸውና ሳይገባቸው (“…ገባ…”አንዱ ጠብቆ
አንዱ ላልቶ ይነበብ) ከማን አንሼ በማለት የሚገቡበት ኑሮም አይደለም። ተገቢውን
የክርስትና ትምህርት የወሰዱ ወደፊት የምንገልጠውን የጋብቻ መስፈርት የሚያሟሉና
ሦስቱን የጋብቻ ዓላማዎች ተረድተውና አምነው የወሰኑ ዕጩዎች /ጥንዶች/ የሚፈጽሙት
አንድነት ነው።

የጋብቻ ዓላማዎች
❖ እግዚአብሔር ጋብቻን ፈቅዶ ለሰው ልጆች የሰጠበት ምክንያት (ዓላማ)
ምንድን ነው?

እግዚአብሔር አምላክ ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ ጋብቻን ለሰው ልጆች ባርኮ የሰጠበት
መሠረታዊ ዓላማ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሀ. ዘር መተካት፦
እግዚአብሔር አምላክ ባዘዘው (በፈቀደው) መሠረት የመጀመሪያው የጋብቻ ዓላማ ልጆችን
መውለድ ዘርን መተካትና ማብዛትና ትውልድ እንዲቀጥል /እንዳይቋረጥ/ ማድረግ ነው።
(ዘፍ፩፥፳፯፡፡) አዳምን ያለዘርና ያለልደት ከዐራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባሕርያተ
ነፍስ የፈጠረው እግዚአብሔር ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ነሥቶ ፈጠራት ቀጣዩ የሰው
ልጅ ትውልድ ግን ከጋብቻ ፍሬ (ከዘር ከሩካቤ በሚገኝ ውጤት) ላይ የተመሠረተ እንዲሆን
ፈቀደ። በዚህም መሠረት ጥንዶቹ (ወላጆች) ልጆችን በመውለድ የእግዚአብሔር ሥራ፣
ፈቃድና ትእዛዝ ተባባሪዎችና ፈጻሚዎች ይሆናሉ ማለት ነው። ትዳርን አማራጫቸው
ያደረጉ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህንን ትእዛዘ እግዚአብሔር ማክበር ይኖርባቸዋል።

ለ.እርስ በርስ መረዳዳት፦


ሁለተኛው የጋብቻ ዓላማ (አስፈላጊነት) ባለ ትዳሮቹ በኑሮአቸው ሁሉ እርስ በርሳቸው
መረዳዳት እንዳለባቸው የሚገልጸው ነው። ይህንንም ትእዛዝ የሰጠው እግዚአብሔር
አምላካችን ነው፡፡ (ዘፍ፪፥፲፰‐፳፭፡፡) ሔዋንን ከመፍጠሩ በፊት የተናገረው ኃይለ ቃል
የአዳምና የሔዋን ተግባር አንዱ ለሌላው ምቹ ረዳት መሆን እንደሚገባው የተገለጸበት
114
ነው። እሱ እግዚአብሔር የባረከው ትዳር ስለሆነም አዳምና ሔዋን በዘመናቸው ሁሉ
እየወደቁ እየተነሡም የሚረዳዱና የሚደጋገፉ ሆነዋል: :ባለትዳሮች እርስ በርሳቸው
በመረዳዳትና በመደጋገፍ ካልኖሩ የዚህን ዓለም ከባድ የኑሮ ቀንበር መሸከም አይችሉም።
በዚህ ዓለም የሚፈራረቀው ውጣ ውረድ፣ መከራም ሆነ ደስታ በተናጠል አይገፋም። ጋብቻ
የመሠረቱ ክርስቲያኖች ሁሉ ቅድስናቸውን ጠብቀው በረድኤተ እግዚአብሔር፣ በድንግል
ማርያም አማላጅነትና በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ተጠብቀው በፍቅርና በአንድነት ጸንተው
እየተረዳዱ መኖርን መዘንጋት የለባቸውም። ጋብቻ ያልመሠረቱ ክርስቲያን ወጣቶችም
ዓላማው ገብቷቸውና በዚህ መንፈስ ተቃኝተው ከወዲሁ ራሳቸውን ለቅዱስ ጋብቻ
ማዘጋጀት አለባቸው።

ሐ.ከዝሙት ጠንቅ ለመዳን፦


ጋብቻ ቅድስናውን ጠብቆ እንዲዘልቅ የሥጋ ፍትወትን (ፍላጎትን) መቆጣጠር ወሳኝነት
አለው። ይህ ደግሞ የጋብቻ ዓይነተኛ ዓላማ ነው። በዝሙት ጠንቅ ከሚመጣው የሥጋ ደዌ
/በሽታ/፣ የመንፈስ ጭንቀት፣ የትዳር መናጋትና የልጆች መበተን የሚዳነው ይህን ዓላማ
በአግባቡ በመረዳትና በማስተናገድ ነው፡፡ ስለዚህም ፈቃደ ሥጋ ከጥንዶቹ በአንዳቸው
በጸና (በተነሣ) ጊዜ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው በጸሎት ለመትጋት
እንዲቻል ለጊዜው በመስማማት ካልሆነ በስተቀር እርስ በርሳቸው እንዳይከላከሉ ቤተ
ክርስቲያን ታስተምራለች። (፩ቆሮ፯፥፩‐፯፡፡) በዚሁ በተጠቀሰው ምዕራፍ ውስጥ
የምንማረው ሌላው ቁም ነገር በምኞት ከመቃጠል እና ተያያዥ ከሆኑ ችግሮች ሁሉ
ለመዳን ጋብቻ ፍቱን መድኃኒት መሆኑን ነው። ጋብቻ በመሠረቱ ጥንዶች መካከል
የሚደረግ ተራክቦም ከጋብቻ በፊትና ከጋብቻ ውጪ እንደሚደረገው ግብረ ሥጋ ግንኙነት
የረከሰና ፈጻሚዎቹንም የሚያረክስ አይደለም። (ዕብ፲፫፥፫‐፬፡፡) በጋብቻ ውስጥ ግብረ
ሥጋ ግንኙነት እንዳይፈጸምባቸው ቤተ ክርስቲያን የምትከለክላቸው ቀናትም የሚከተሉት
ናቸው።

• በአራስነት ወቅት (ለወንድ ፵፣ ለሴት ፹ ቀናት እስኪሞላ ያሉት ቀናት)፤

• የወር አበባ ጀምሮ እስኪጠራ (ሰባት ቀናት)፤

• ሥጋ ወደሙ ከመቀበል ቀድሞ ያሉ (ሦስት ቀናት)፤

• ሥጋ ወደሙ ከተቀበሉ በኋላ (ሦስት ቀናት)፤

• ሁለቱ ሰናብት (ሰንበቶች)፤

• ዐበይት በዓላት (ዓመታዊ የቤተ ክርስቲያን በዓላት)፤

• በየወሩ በ፲፪፣ በ፳፩ እና ፳፱ ያሉ (የግዝት በዓላት)፤

• እርግዝና ሲገፋ፤

115
• ቢቻል በሰባቱ አጽዋማት፤ በተለይ ግን በዐቢይ ጾም፤ (ፍት.ነገ
፳፬፥፱፻፳፩‐፱፻፳፬፡፡) ከዚህ ውጪ፤ እንግዳ ክስተቶች ሲፈጠሩ ከንስሐ አባት ጋር
መነጋገርና መጨረስ ይገባል።

የተከበሩ የዚህ ጽሑፍ ተከታታይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ::

❖ ብዙ ሰው ጋብቻውን መፈጸም ሲያስብ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በሆነ ዓለማዊ


ሥርዓት ማድረግ ይፈልጋል:: ይህ ለምን ይመስልዎታል? በቤተ ክርስቲያን
ማድረግ ስለማይፈልግ ነውን?

ወጣቶች ለአቅመ አዳምና ሔዋን ደርሰው ማግባት ከፈለጉ የምሥጢረ ተክሊልን ጋብቻ
መምረጥ ለሥጋም ለነፍስም እንደሚበጅ መረዳት አለባቸው። አባቶቻችንና እናቶቻችን
በፈቃደ እግዚአብሔር በመታገዝ ከማግባታቸው በፊት ድንግልናቸውን ጠብቀው ማለትም
ታቅበው ይኖሩ ነበር:: ከዚያ በኋላ በድንግልና በመጋባት የተባረከ የትዳር ጊዜን እንዳሳለፉ
መርሳት አይገባም። በፈቃደ እግዚአብሔር የሚመራ ሰው እግዚአብሔር መንገዶቹን ሁሉ
ስለሚያቃናለት አይቸገርም:: የምትሆነውን የትዳር አጋር በወላጆቹ፣ በራሱና በወደደው ላይ
አድሮ ስለሚመርጥለት ባትመቸኝስ፥ ባይመቸኝስ በሚል ስጋት አይጨነቅም። ቀድሜ
መሞከር አለብኝ በሚል ድፍረትም ክብሩን የሚያሳጣውንና የሚያስቀጣውን ኃጢአት
አይሠራም። በማያዋጣ ሥጋዊ ጥበብ ሽፋን ሥጋዊ ፍትወቱን ከማርካት ይልቅ በጸሎት
ፈጣሪውን ወደ መጠየቅ ስለሚያዘነብል የተመካበት እግዚአብሔር ጎዶሎውን ሁሉ
ይሞላለታል። የሚመቻትን ረዳት እንደሚሰጠው ስለሚያምን እግዚአብሔር ይደሰትበታል።
ክርስቲያኖች ሁሉ ዓለማዊውን ፍልስፍናና ሙከራ (ትግበራ) ትተው በተወክሎ
እግዚአብሔር የትዳር አጋራቸውን መፈለግ፣ መምረጥ፣ ከእግዚአብሔር እጅ መቀበልና
ትዳርን መመሥረት ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም ሁለቱ እጮኛሞች በድብቅ ስለቆረቡ
ወይም ምናልባትም የንስሐ አባታቸው /ካህኑ/ ከተጠቀሰው ሥርዓት ውጪ ስላማማላቸው
ሥርዓተ ተክሊል እንደተፈጸመና በሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንደተጋቡ እንደማይቆጠር
ማስተዋል ያስፈልጋል። ብዙዎች ግን ስለማይተማመኑና በተክሊል መጋባትን
እንደመታሰር ስለሚቆጥሩት ከተቀደሰው የጋብቻ ሥርዓት ይርቃሉ፡፡ በተጨማሪም ስለ
ቅዱስ ጋብቻ (የተክሊል ጋብቻ) አስፈላጊነት፣ አፈጻጸምና ክብር ባለማወቅም ዓለማዊውን
ጋብቻ የሚመርጡ አሉ፡፡

፰∙፫ አፈጻጸም
የተከበሩ አንባቢ ሆይ ይህን ርእስ ከማብራራታችን በፊት የሚከተሉትን ጥያቄዎች
ለመመለስ ይሞክሩ?

❖ ምሥጢረ ተክሊል ሲፈጸም አይተው ካወቁ ትዝ የሚልዎትን ያህል የአፈጻጸም


ቅደም ተከተሉን ዘርዝሩ?

116
❖ ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸመው ሁለቱም ደናግል ሆነው ሲገኙ ነው።
ድንግልናቸውን በልዩ ልዩ ሁኔታ ላጡ ወጣቶች /ወንዶችም ሴቶችም/ ቤተ
ክርስቲያን የምታስተናግድበት መንፈሳዊ ሥርዓት አላትን? ካለ ምንድነው?

ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸመው በሁለቱ ተጋቢዎችና በወላጆቻቸው /አሳዳጊዎቻቸው/ ፈቃድ


መሠረት ነው:: የሚጋቡትም ወንዶችና ሴቶች ለአካለ መጠን የደረሱና ማለትም ለወንድ
ሃያ ዓመት (20)፣ ለሴት አስራ አምስት (15) ዓመት ከሆናቸው ጀምሮ ያሉ እና በሃይማኖት
የተካከሉ /የተመሳሰሉ/ መሆን ይገባቸዋል:: ሥርዓተ ተክሊሉ የሚፈጸመውም በድንግልና
ለተወሰኑ እጮኛሞች ነው። ሥርዓቱ የሚፈጸመው ካህናትና ምእመናን በተሰበሰቡበት
በጉባኤ ነው እንጂ በስውር በድብቅ አይደለም። ከዚህ ውጪ የሚፈጸም የተክሊል ጋብቻ
የለም። የጋብቻው ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ቢፈጸምም በቅዱስ ቁርባን ያልታተመ ከሆነ
የተክሊል ጋብቻ ተፈጸመ ሊባል አይቻልም። የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ሁሉ
ማኅተማቸውና መክብባቸው ምሥጢረ ቁርባን ነውና። /ፍት.ነገ.፳፬፥፰፻፺፰‐፱፻፡፡) ጋብቻ
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቃል ኪዳንና በቡራኬ፣ በጸሎተ ተክሊልና በቅዱስ ቁርባን
ሲፈጸም ምሥጢርነት ይኖረዋል። /ኤፌ. ፭፥፴፪፡፡/ በሚታዩ የአፈጻጸም ሥርዓቶችና
ምልክቶች የማይታይ ጸጋ እግዚአብሔ ይገኝበታልና።

ምሥጢረ ተክሊል ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በምንም ዓይነት መንገድና በየትኛውም ቦታ


አይፈጸምም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ከወጣ ካህናት ቢኖሩም እንኳን በየትኛውም ቦታ
አይፈጸምም:: ቤተክርስቲያን ሳታውቀው የሚፈጸም ጋብቻ መንፈሳዊ ጋብቻ ሊባል
አይችልም:: ሥርዓተ ተክሊሉ በሚፈጸምበት ዕለት የሚኖረው አፈጻጸም የሚከተለውን
ይመስላል፡፡ ሙሽራው ከሚዜዎቹና ከዘመዶቹ ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ በሰሜናዊው
ማዕዘን ይቆማል። ሙሽሪትም ከሚዜዎቿና ከዘመዶቿ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ገብታ
በደቡባዊ ማዕዘን ትቆማለች፡፡ ከዚያም በንስሐ አባታቸውና በሊቀ ዲያቆኑ አስተናባሪነት
በቅድስት በተዘጋጀላቸው የክብር ወንበር ላይ ይቀመጣሉ:: ከእግራቸው ሥር ልዩ የክብር
ምንጣፍ ይነጠፋል:: ካህናቱ ከፊት ለፊታቸው ካለው ጠረጴዛ ላይ በአንድነት የሚለብሱትን
ነጭ ልብስ፣ ካባ፣ መጎናጸፊያ፣ ተቀብተው የሚከብሩበትን ቅብዓ ቅዱስ፣ (ሜሮን)
የሚቀዳጇቸውን አክሊላት፣ የሚያጠልቁትን ቀለበትና የሚጨብጡትን መስቀል ያኖራሉ፡፡
ቀጥለውም ሥርዓተ ተክሊሉን አድርሰው ቃልኪዳን በመገባባት እንደ ትእዛዙ
ይፈጽሙላቸዋል። በመጨረሻም ቅዳሴ አስቀድሰው ሥጋውን ይበላሉ፤ ደሙንም ይጠጣሉ::

እስቲ ደግሞ የሚከተለው ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ::

❖ በሥርዓተ ተክሊል አፈጻጸም ወቅት የሚታዩ የምልክቶች ምሳሌያዊ ትርጉም


ምንድነው?

በአፈጻጸም ሒደት የሚታዩ ምልክቶች ሁሉ መንፈሳዊ ትርጉም አላቸው፡፡ ለማሳያ ያህልም


የሚከተሉትን ማየት እንችላለን፡፡

ሀ. መስቀል /ወንጌል/ ጨብጠው ቃል ኪዳን መግባታቸው

117
-በሃይማኖት ጸንተው ለመኖር በሚያደርጉት ግብግብ የሚቀበሉትን ፈተና ያመለክታል::
በመስቀሉ /በወንጌሉ/ ኃይልም ፈተናውን ድል እንደሚያደርጉት ያሳያል። መስቀልና
ወንጌል የድል አድራጊነት /የአሸናፊነት/ ምልክት ነውና።

ለ. አንድ ነጭ መጎናጸፊያ መጎናፀፋቸው፤

ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያላቸው የሥላሴ ልጆች መሆናቸውን ያጠይቃል። አንድ


ልብስ ለብሰው አንድ ክብር ወርሰው በዚህ ዓለም የመኖራቸውና በወዲያኛውም ዓለም
አንዲት ርስት መንግሥተ ሰማያትን ወርሰው ከክርስቶስ ጋር የሚኖሩ መሆኑን
ያመለክታል:: ነጭ ልብስ /መጎናጸፊያ/ ክብርን፣ ትንሣኤንና የሚቀበሉትን የመንፈስ
ቅዱስ ጸጋ የሚያስረዳ ነውና::

ሐ አንድ በሆነ ምሳሌያዊ ቀለበት የሁለቱንም አውራ ጣቶች ባንድ ማጣመራቸው፤

ቀለበቱ የሃይማኖት ምሳሌ ነው:: ቀለበት በክብነቱና ፍጻሜ የለሽ በመሆኑ በቃል ኪዳን
የጸናው የተክሊል ጋብቻም ከሕይወት ፍጻሜ በስተቀር ማንም የማይለያየው መሆኑን
ያሳያል። በአንዲት ርትዕት ሃይማኖት የማይናወጽ መሠረት ላይ የታነጸ እንደመሆኑ
የጠላት ነፋስ፣ የፈተና ጎርፍና ልዩ ልዩ ወቅታዊ የስሜት ማዕበላት የማያናዋውጡት
/የማያፈርሱት/ መሆኑን ያመለክታል።

መ. በቅብዓ ቅዱስ (ሜሮን) ተቀብተው መክበራቸው

ቅብዐ ሜሮን በምሥጢረ ሜሮን እንዳየነው የመንፈስ ቅዱስ ማሳደሪያ ነው:: በዚህም
መሠረት ረድኤተ መንፈስ ቅዱስ በትዳራቸው ዘመን ሙሉ የማይለያቸው መሆኑን
ያጠይቃል።

ሠ. አክሊል መቀዳጀታቸው

አክሊል የድል አድራጊነት ምልክት እንደመሆኑ ድል አድራጊነታቸውን ያመለክታል።


እስከ ጋብቻቸው ዕለት ባሉት አፍላ የወጣትነት ቆይታዎች በርካታ ውጣ ውረዶችን
በረድኤተ እግዚአብሔር አልፈው፤ ድንግልናቸውን ጠብቀው፤ ለዚያች ዕለት በመድረሳቸው
ቤተ ክርስቲያን የምትሸልማቸው የክብራቸው መገለጫ ነው:: በቀጣይ የሕይወት ዘመናቸው
ደግሞ በጾም፣ በጸሎት፣ በንስሐ፣ በሥጋ ወደሙና በመልካም ምግባራት ሁሉ ጸንተው
እንዲኖሩ ያስችላቸዋል። ትዳራቸውን በፈቃደ እግዚአብሔር ጠብቀው ከተጓዙ
ሰማያዊውን የክብር አክሊል የሚቀዳጁ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን በምሥጢር
የምታበሥርበት ሥርዓት ነው። በተጨማሪም በተስፋ ልጆቿን የምታጸናበት የሕይወት
መንገድ ነው።

እስኪ ደግሞ የሚከተለውን ጥያቄ ከሕይወት ልምድዎ ካዩትና ከሰሙት ተነሥተው


ይመልሱ::

118
• በጋብቻ ሕይወት ውስጥ ከባድ ፈተና ነው ብለው የሚያስቡት ምንድነው? እንዴት?

ቤተ ክርስቲያን በተክሊል ተጋብተው በታወቀ ምክንያት ጋብቻቸው ለፈረሰባቸውና


በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ድንግልናቸውን ላጡ /ላልጠበቁ /ምእመናን ልጆቿ በቅዱስ
ቁርባን የምታጋባበት ሥርዓት አላት። ይኸውም በንስሐ ታርመውና ተስተካክለው
ለተመለሱ ክርስቲያኖች ከተክሊል ጋብቻ የተቀደሰ ሥርዓት ጎን ለጎን በተለየ ሁኔታ
የምታጋባበት መንፈሳዊ ሥርዓት ነው። በሥርዓተ ጸሎቱ፣ አክሊል ባለመቀዳጀታቸውና
ቅብዐ ሜሮን ባለመቀባታቸው ከሥርዓተ ተክሊል አፈጻጸም ይለያል። የንስሐ ጸሎት
ተደግሞላቸው የታዘዘው ሥርዓትም ተፈጽሞላቸው ሥጋ ወደሙ ተቀብለው ይከብራሉ::
በንስሐና በሥጋ ወደሙ ይባረካሉ። በዓለማዊ ጋብቻ የተጋቡ ክርስቲያኖችም ጋብቻቸውን
/ትዳራቸውን/ በንስሐና በሥጋ ወደሙ የሚያስባርኩበት መስመር አለ፡፡ ቤተክርስቲያን
ሁሉም ልጆቿ የቅድስናን ሕይወት የሚያጣጥሙበት፣ በዚህ ዓለም ባመኑበት እምነት
በሠሩትም ሥራ ከብረው መንግሥተ ሰማያትን የሚወርሱበት መንገድ ባለቤት ነች። በዚህ
መሠረት መጓዝን ትተው ድንግልና የሌላቸው ሰዎች ለሰው ይምሰልና ለታይታ ብለው
ለደናግል ብቻ የተፈቀደውን ሥርዓተ ተክሊል ቢያስፈጽሙ ከበረከት ይልቅ መርገምን
ይቀበላሉ:: ልብንና ኩላሊትን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን ማታለል ሞክረዋልና
ሳይቀጡ አይቀሩም። እግዚአብሔር አምላካችን ከሁሉም አዋቂነቱ ጋር ለቤቱና
ለሥርዓቱም ቀናዒ፣ ፈራጅና ተበቃይም ነውና።

፰∙፬ የሚያስገኘው ጸጋ
❖ በምሥጢረ ተክሊል ተጋቢ ጥንዶቹ የሚያገኙት ጸጋ ምንድን ነው?

በተቀደሰው መንፈሳዊ ጋብቻ ያለፉና የሚያልፉ ተጋቢዎች የሚያገኟቸው በርካታ ጸጋዎች


አሉ። ምክንያቱም ደጋግመን ለመግለጽ እንደሞከርነው ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ሁሉ
ምእመናን ከእግዚአብሔር የማይታየውን ጸጋ የሚቀበሉባቸው መንፈሳዊ መንገዶች
ናቸውና። ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ያህልም፦

ሀ.ሥጋዊና መንፈሳዊ አንድነት

ሁለቱ ተጋቢዎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ከሁለትነት ወደ አንድነት


የሚመጡት በቅዱስ ጋብቻ /በምሥጢረ ተክሊል/ ነው:: ይህ ጥምረት /አንድነት/ በጥበበ
እግዚአብሔር የሚከናወን ስለሆነ ሰዎች ሊለዩት እንዳይሞክሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ::
/ማቴ ፲፱፥፮፡፡/ ይህም አንድነት በሥጋ ዓይን የሚታየው ሁለትነት ሳይጠፋ የሚከናወን
የባልና ሚስት ተዋሕዶ ስለሆነ ታላቅ ምሥጢር ነው። /ኤፌ ፭፥፴፪፡፡/ ይህም የአሳብ
አንድነትና የጋራ መተሳሰብን በማምጣት ይታወቃል። ጋብቻው በፈቃደ እግዚአብሔር
ስለሚመራም ተጋቢዎች የተረጋጋ ሕሊናና ሰላም ይኖራቸዋል፡፡ ማኅበረሰቡም ይህን
በመረዳቱ “ባልና ሚስት ከአንድ ባሕር ይቀዳሉ፤” እያለ አንድነታቸውን በሥነ ቃል
ሲያውጅላቸው ይኖራል።

ለ/ እውነተኛና ዘላቂ ፍቅር


119
በባልና ሚስት መካከል የሚኖረው መተሳሰብ መቻቻልና ሰላም ሌላው የቅዱስ ጋብቻ ፍሬ
ነው:: የአንድነቱ መሠረት የሆነው እውነተኛ ፍቅር በተጋቢዎች መካከል ካለ ለጋብቻው
ዘላቂነት ታላቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል:: ጋብቻው የታነጸበት /የተመሠረተበት/ ሃይማኖት
መሠረቱ የማይነቃነቅ እምነት ሲሆነ የእውነተኛ ፍቅራቸውም መገኛ እሱው ነው::
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረንም በባልና ሚስት መካከል ሊኖር የሚገባው
እውነተኛ ፍቅር በፍትወት እንስሳዊት የተቃኘ አይደለም:: በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን
መካከል ካለው ጽኑ ፍቅር የተቀዳ ነው እንጂ፡፡ (ኤፌ፭፥፳‐፴፪፡፡) ይህም እውነተኛ ፍቅር
በፈሪሐ እግዚአብሔርና በመተማመን ላይ የተመሠረተ ሆኖ አንዱ ላንዱ ራሱን መሥዋዕት
አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ የሚያበቃ መሆኑን ያስገነዝበናል። ይህ እውነተኛ ፍቅር
ጋብቻቸውን በተቀደሰው ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ፈጽመው በቅዱስ ቁርባን ለታተሙ
ባልና ሚስት እንዲሁም በንስሐና በሥጋ ወደሙ ትዳራቸውን ላስባረኩ ጥንዶች መሆኑን
ማስተዋል ያስፈልጋል።

ሐ.የተባረኩ ልጆች

እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች በመንገዶቹም የሚጓዙ ሰዎች ምስጉኖች (ብፁዓን)


እንደሚባሉ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል:: መገለጫዎቹንም ሲያብራራ እንዲህ ይላል:‐
“የድካምህን ፍሬ ትመገባለህ፣ ብፁዕ ነህ፣ መልካምም ይሆንልሃል። ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ
ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ
ተክል ይሆናሉ፤ እነሆ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል:: እግዚአብሔር
ከጽዮን ይባርክህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፤ የኢየሩሳሌምን መልካምነት ታያለህ፤
የልጆችህንም ልጆች ታያለህ፤ በእስራኤልም ላይ ሰላም ይሁን።” (መዝ፻፳፮፥፩‐ፍጻሜው፡፡)

ይህንን ክፍለ ንባብ ከተነሣንበት ርእሰ ጉዳይ ጋር ስናጣጥመው በተቀደሰው ሥርዓት


ጋብቻቸውን የሚፈጽሙ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው:: እነዚህም በመንገዶቹ
የሚጓዙ ማለትም በሃይማኖት ጸንተው፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ጠብቀው ምሥጢራትን
የሚፈጽሙ /በምሥጢረ ተክሊል የሚያገቡ/ ናቸው። በዚህም ምክንያት ብፁዓን
/የተመሰገኑ/ ተብለው ይጠራሉ:: ትዳራቸውና መንፈሳዊ ሕይወታቸው የተቀደሰ መሆኑም
የሚታወቀው በራሳቸውና በትዳር አጋራቸው ቅድስናና ፍሬያማነት፣ በልጆቻቸውም ሥነ
ምግባር መልካምነት ነው:: እግዚአብሔርም በጽዮን ቤተክርስቲያን፣ በጽዮን እመቤታችን
ቅድስና ይባርካቸዋል:: የሕይወት ዘመናቸው ሁሉ የተባረከ ይሆናል፤ ዛሬም በቅድስና
የተባረኩ ሆነው በቤተ ክርስቲያን ይኖራሉ፤ መልካምነቷን ያያሉ፤ ይነግራሉ በኋላም ተስፋ
የሚያደርጓትን ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ወርሰው መልካምነቱን ያያሉ፤ በመልካምነቷ
ይኖራሉ:: እግዚአብሔርም እነዚህን ሰዎች ልጆቻቸውን ብቻ ሳይሆን በእውነት የተተኩ፣
የልጅ ልጆቻቸውንም በማሳየት ያስደስታቸዋል:: ለዚህም ቅዱስ ዳዊት “እነሆ ልጆች
የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የሆድም ፍሬ የእነርሱ ዋጋ ነው፡፡ (መዝ፻፳፮፥፫፡፡) በማለት
ዘምሯል። ለሀገር፣ ለማህበረሰብና፣ ለቤተሰብ ሸክም የሆኑና ራሳቸውንም ለአልባሌ ነገሮች
የሸጡ ልጆች እንዳይወለዱ ጋብቻን በተቀደሰው መስመር መፈጸም ይገባል:: ብዙ ጥቅም
የሌላቸው ክፉዎች ልጆች ከመውለድ ሳይወልዱ መሞት እንደሚሻል ቅዱሳት መጻሕፍት
ይናገራሉና፡፡ (ሲራ፲፮፥፩‐፭፡፡)
120
ማጠቃለያ
ብዙዎች መንፈሳዊ ዕሴቶቻቸውን እየጣሉ በምዕራባውያን የረከሰ ባህል በመዋጣታቸው
ለድንግልናና ለቅዱስ ጋብቻ የነበራቸው ክብር እየተሟጠጠ ይገኛል:: ከዚህም በላይ የተጋቡ
ባለትዳሮች ልጅን የሚጸየፉ ማለትም በመውለድና በማሳደግ ሂደት ያለውን ውጣ ውረድ
ለመጋፈጥ የሚፈሩ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ አልፎ ተርፎም አባቶቻችንና እናቶቻችን በእጅጉ
ይጠሉትና እንደ ነውር ይቆጥሩት የነበረውን ፍቺ በዚሁ ምክንያት ሲፈጽሙ እንደጀብዱ
የሚቆጠሩ ክርስቲያች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው::

ከዚህ መንፈሳዊ ድቀት የሚበልጥ ተግዳሮት ለቤተ ክርስቲያን አይኖራትም:: ክርስትና


በክርስቲያኖች ሕይወት የሚንጸባረቅ የዕለት ተዕለት ተግባራዊ መንፈሳዊ ጉዞ የመሆኑን
ያህል ኢ-ክርስቲያናዊነትም በግልባጩ በዓለማዊነት ጎዳና የሚደረግ ሥጋዊ ሩጫ ነው፡፡
በተለይ በዚህ የሉዓላዊነት /ግሎባላይዜሽን/ ዘመን የምንገኝ ክርስቲያኖች ለተቀደሰ
የተክሊል ጋብቻ ለመብቃትም ሆነ የተመሠረተውን ጋብቻ ጠብቆ ለመጓዝ የሚገጥሙን
ፈተናዎች ቀላል የሚባሉ አይሆኑም፤ በረድኤተ እግዚአብሔር ተቋቁሞ ለማለፍ በቂ
ግንዛቤ መያዝ በራሱ ታላቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል:: በዚህም ረገድ ከዚህ ምዕራፍ
ያገኘነውን ዕውቀት ይዘን በማስፋፋት ለተግባራዊ ሕይወት ግብአት አድርጎ መጠቀም
የሚገባ መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም::

ዋቢ መጻሕፍት
• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫
አ/አ።

• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ


ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

121
• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤
1999፤ አ/አ።

ምዕራፍ ዘጠኝ
ምሥጢረ ቀንዲልና አፈጻጸሙ
መግቢያ:‐
ይህ ምሥጢር በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት ከቁጥር ሟሟያነት የዘለለ
ተግባራዊ አፋጻጸም የማይታይበት ነው፡፡ የቀደሙ አባቶቻችን ይህንንም ምሥጢር እንደ
ሌሎቹ ምሥጢራት በአግባቡ ይፈጽሙት እንደ ነበር ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ::
የቤተ ክርስቲያን አባቶች በፈቃደ እግዚአብሔር የሠሩት የምሥጢረ ቀንዲል አፈጻጸም
ከአመሠራረቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና የሚያስገኘው ጸጋም በዚህ ምዕራፍ
ተብራርቶ ቀርቧል፡፡ ከሰባቱ የቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች ወይም ምሥጢራት ይህም እንደ
ስድስቱ ሁሉ ጸንቶ እንዲቆም በማድረግ ሒደት አንባቢያን ሁሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ
ይህ ጽሑፍ አስተዋጽዖ ያበረክታል ተብሎ ታምኖበታል::

• ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ተማሪዎች ይህንን ትም/ት ከተማሩ


በኋላ፦

• ስለ ምሥጢረ ቀንዲል ምንነትና አመሠራረት ይገነዘባሉ፡፡

• ምሥጢረ ቀንዲል የሚያሰጠውን ጸጋና ትክክለኛ አፈጻጸሙን ይረዳሉ፡፡

፱∙፩ አመሠራረት

122
ካንድል /Candle/ የሚለውን የላቲን ቃል መሠረት ያደረገው “ቀንዲል” ትርጉሙም
“መብራት” ነው። ምሥጢረ ቀንዲል ማለት ካህኑ ለታመሙ ክርስቲያኖች በሚያደርገው
ጸሎት፣ በሚሰጠው ቡራኬና በሚቀባውም ዘይት /ቅብዐ ቅዱስ/ አማካኝነት በእግዚአብሔር
ቸርነት የሚገኘውን የሥጋና የነፍስ ድኅነትና ፈውስ የሚያመለክት ምሥጢር ነው።
መጽሐፈ ዘይት፣ ጸሎተ ዘይት፣ ቅብዐ ድውያን ማለትም ይሆናል:: ስሙን ከድርጊቱ
አግኝቶታል። ጸሎቱ ሲፈጸም መብራት አብርቶ ነውና::

የምሥጢረ ቀንዲል መሥራች ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይኸውም


ለቅዱሳን ሐዋርያቱ ድውያንን እንዲፈውሱ፣ ሙታንን እንዲያስነሡ፣ ልሙፃንን እንዲያነጹ፣
አጋንንትን እንዲያወጡና ኃጢአትን ሁሉ እንዲያስተሠርዩ ሥልጣንን በሰጣቸው ጊዜ ነው።
“ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ ጠርቶ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤ በርኩሳን መናፍስት
ላይም ሥልጣን ሰጣቸው፤ ወጥተውም ሁሉ ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰበኩ፤ብዙ አጋንንትንም
አወጡ፤ ብዙ ድውያንንም ዘይት እየቀቡ ፈወሷቸው።” (ማር፮፥፯‐፲፬፡፡) እንዲል:: ከሰባቱ
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ለመሆን የበቃበት ምክንያት በሚታይ አገልግሎት
ከሚታይ ፈውሰ ሥጋ ጋር የማይታይ ፈውሰ ነፍስም ስለሚገኝበት ነው:: ከእናንተ የታመመ
ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉ ቀሳውስትን ይጥራና ይጸልዩለት፤ በጌታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቅቡት፤ የሃይማኖት ጸሎትም ድውዩን ይፈውሰዋል፤
እግዚአብሔርም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደሆነ ይሠረይለታል። (ያዕ
፭፥፲፬‐፲፮፡፡) በማለት ቅዱስ ያዕቆብ ምስክርነቱን የሰጠን ለዚህ ነው።

❖ ፱∙፪. አስተምህሮ
ይህ ምሥጢር ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያን ይፈጸም እንደነበር የታወቀ ነው:: ከላይ
እንዳየነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን፣ ሐዋርያትም ተከታዮቻቸውን፣ አዘዋቸው
ነበርና። ኢጶሊጦስ ዘሮም የተባለው አባት /፫መ/ክ/ዘ/ “ሐዋርያዊ ትውፊት” በተባለው
መጽሐፉ በምሥጢረ ቀንዲል አፈጻጸም ጊዜ ይጸለይ የነበረውን ጸሎት አስፍሮታል:: ይህም
የሚያመለክተው ምሥጢረ ቀንዲል በቤተ ክርስቲያን ይፈጸም የነበረው ከጥንት
/ከምሥረታዋ/ ጀምሮ መሆኑን ነው።

በጸሎት ድዉያንን የመፈወስ ተግባር በብሉይ ኪዳን ዘመንም እንደነበር ቅዱሳት


መጻሕፍት ምስክሮቻችን ናቸው። (ዘሌ. ፲፫፥፩‐ፍጻሜው፡፡) በድፍረት የእግዚአብሔር
አገልጋይ በሆነው በወንድሟ በሙሴ ላይ ካህኑ አሮንን በማስተባበር ሐሜት በመሰንዘሯ
በለምጽ በሽታ የተመታችው ማርያም እኅተ ሙሴ የዳነችው በወንድሟ በሊቀ ነቢያት
ሙሴ ጸሎት ነበር። “ሙሴም ወደ እግዚአብሔር እየጮኸ አቤቱ እባክህ አድናት አለው።”
/ዘኁ ፲፪፥፩‐፲፮፡፡/ “የተባለው ይህንን ያረጋግጥልናል። የቀንዲል መብራቶችም በደብተራ
ኦሪት እንደነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ዘጸ ፵፥፬፡፡) እነዚህ ሁሉ አማናዊ ለሆነው
ምሥጢረ ቀንዲል ምሳሌዎችና መነሻዎች መሆናቸውን ማስተዋል ይገባል::

ከምሥጢረ ቀንዲል ጋር ፈጽሞ የሚስማማ ሌላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃም አለ:: ይህን


አስመልክቶ መጽሐፈ ሲራክ ላይ እንዲህ የሚል ተጽፏል። “…ልጄ ሆይ በሽታህን ቸል
123
አትበል፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸልይ፤ እርሱም ይፈውስሃል:: ኃጢአትን ተዋት፣ እጅህን
አቅና፣ ልቡናህንም ከኃጢአት ሁሉ አንጻ፤ መባህን አግባ የመታሰቢያውንም የስንዴ ዱቄት
ስጥ።” (ሲራ. ፴፰፥፩‐፲፮፡፡) ከእግዚአብሔር የምትገኝ ፈውሰ ሥጋን ለማግኘት ንስሐ
መግባትና ለእግዚአብሔር መባዕ ማስገባት እንደሚገባ ልብ ይሏል፡፡

፱∙፫. አፈጻጸም
❖ ቤተክርስቲያን ምሥጢረ ቀንዲል የምትፈጽምላቸው ሕሙማን ምን ዓይነት ሕመም
ለታመሙት ነው?

የተከበሩ የምዕራፉ አንባቢ ሆይ:‐ የዚህን ጥያቄ መልስ በማስታወሻዎ ለመጻፍ ይሞክሩ

ቀንዲል:‐ ቅብዓ ቅዱስ /የተለየ የከበረ ዘይት (ቅባት) እየተባለ ይጠራል። ይህም ከወይራ
ዛፍ በጸሎት በመታገዝ በረድኤተ እግዚአብሔር የሚዘጋጅ /የሚወጣ /ዘይት ነው።
በተዘጋጀለት የክብር ዕቃ /ብልቃጥ/ ተደርጎ በከርሰ መንበር ወይም በዕቃ ቤት በክብር
ይቀመጣል። የቀንዲሉ አዘጋጅና ባለቤት ምሥጢሩንም ፈጻሚዋ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
ከምእመናን ወገን የታመሙ ሲኖሩ ወደ ቤተክርስቲያን ወደ ካህኑ ይመጣሉ። የማይችሉ
የሆኑ እንደሆነ ካህኑን /ካህናቱን/ ወደ ቤታቸው ይጠራሉ፡፡ ካህኑ /የንስሐ አባቱ/ ሕሙሙን
ምእመን በማጽናናት ኃጢአቱን እንዲናዘዝ/ ንስሐ እንዲገባ/ ያደርገዋል:: በመቀጠልም
ባቅሙ የሚችለውን ቀኖና እንዲፈጽም ያዘዋል:: ከዚያም ካህኑ /የንስሐ አባቱ/ ከሌሎች
ካህናት ጋር ሆኖ ምሥጢሩን ለታማሚው ለመፈጸም ይዘጋጃል፡፡ ከዚያም ቀንዲሉን
/መብራቱን/ አብርቶ መጽሐፈ ቀንዲልን በመጠቀም የታዘዘውን ጸሎት ይጸልዩለታል።
በጸሎቱ ፍጻሜም የሕመምተኛውን ሕዋሳት በተለይ የታመመውን ክፍል በተጸለየበት ቅብዐ
ቅዱስ በመስቀል አምሳል /ምልክት/ ይቀቡታል:: በመጨረሻም ከማእሰረ ኃጢአት
የሚፈታበትን ሥርዓት /ኑዛዜ/ ይፈጽሙለታል። ይህም ለታመመው ምእመን ፈውሰ ሥጋ፣
ፈውሰ ነፍስን ያድለዋል።

ለማብራራትም ያህልሥርዓተ ቀንዲልን የሚፈጽሙት ሰባት ኤጲስ ቆጶሳት ወይም


ቀሳውስት ሆነው ነው። እነዚህ ሰባት መሆናቸው ሰባት ቁጥር በዕብራውያን ፍጹም ቁጥር
እንደመሆኑ በምሥጢረ ቀንዲል ፍጹም ሥርየትና ፈውስ መገኘቱን ለማጠየቅ ነው።
እነሱም /ካህናቱ/ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ያያቸው የሰባቱ የወርቅ መቅረዞችና መብራቶች
ምሳሌ ናቸው። (ራእ፩፥፳፡፡) ከላይ እንደገለጽነው ኃጢአቱን ለተናዘዘው ምእመን በቀረበው
ንጹሕ ዘይት ላይ የታዘዘው ጸሎት ይደረሳል። ሰባቱም ካህናት በየተራ በታመመው ራስ
ላይ የታዘዙትን የወንጌል ክፍላት ያነባሉ ወንጌል ከተነበበ በኋላም ሰባቱም እጃቸውን
በሕመምተኛው ላይ ጭነው የታዘዙትን ጸሎታት ይጸልዩለታል::

በመጨረሻም አስቀድመን እንደተናገርነው በሰባት እንጨቶች ጫፍ ላይ ጥጥ በመጠምጠም


ተራ በተራ በተጸለየበት ቅብዐ ዘይት እየነከሩ አምስቱን የስሜት ሕዋሳት /ዓይኑን፣
ጆሮውን፣ አፍንጫውን፣ አፉንና እጁን በመስቀል ምልክት ይቀቡታል:: የዚህም ምክንያት
በዓይኑ አይቶ፣ በጆሮው ሰምቶ፣ ባፍንጫው አሽትቶ፣ በአፉ ተናግሮና በእጁ ዳሶ ለሠራው

124
ኃጢአት ሥርየት እንዲሆነው ነው። አእምሮ የሚገኝበት የአምስቱ የስሜት ሕዋሳት
ማዕከልና የማስተዋል /የማሰብ/ ኃይል የሚገኝበት ክፍል ነውና፤ በዋናነት ግንባርም
ይቀባል:: የልብ ማረፊያ ነውና ደረቱም ይቀባል፡፡ ሰውነቱን ሁሉ ሊበክል የሚችል
የርኩሰት ቁስል /ቁስለ ነፍስ/ የሚመነጭ ከሱ ነውና ፈጽሞ እንዲፈወስ እነዚህ ሁሉ
ይቀባሉ፡፡ ከቀሳውስት በታች ያሉ ዲያቆናት ግን ለካህናት ከመታዘዝና ከመራዳት
በስተቀር ይህንን ምሥጢር መፈጸም እንደማይችሉ የታወቀ ነው።

ስለዚህ የሚመለከታቸው የቤ/ክርስቲያኒቱ አባቶች ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ


ሆኖ ስለሚቆጠረው ምሥጢረ ቀንዲል ተፈጻሚነትና ቀጣይነት አንድ መላ ማለት
(መፍትሔ መፈለግ) አለባቸው:: በጽሑፍና በቃል ከመቆጠር ባለፈ እንደ ስድስቱ
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በተግባር ተፈጽሞ እንዲታይ ማድረግ ይገባል:: ምእመናንም
ይህን ምሥጢርና አፈጻጸሙን በማወቅ ለተግባራዊነቱ የድርሻቸውን ማበርከት አለባቸው።

❖ በአንዳንድ ሰዎች በየብልቃጡ እየተሞላ የሚሸጠው “ዘይት” ምስጢረ ቀንዲልን


ይተካልን? ለምን?

ይህ ምሥጢር በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት እየተፈጸመ አይደለም::


አስተምህሮው እንዲህ ነው፣ እንዲህ ይደረጋል፣ ከማለት ውጪ ሲተገበር አይታይም::
በምትኩም ከአስተምህሮአችን ውጪ የሆኑ ተግባራት ሲፈጸሙ ይታያል:: “ከኢየሩሳሌም
የመጣ፣ ባህታዊ እገሌ የጸለዩበት፣ አጥማቂ እገሌ የባረኩት፣…ቅብዓ ቅዱስ ነው፤ ወዘተ”
እየተባለ በየስፍራው የሚቸበቸብ ዘይት ማየት የተለመደ ሆኗል:: ይህንንም እንዳንድ
ግንዛቤ የሌላቸው ምእመናን እየገዙ “ቅብዓ ቅዱስ” በማለት በራሳቸው ጊዜ በቤታቸው
እያኖሩ የሚቀቡ በዚህም ምክንያት ከፈውስ ይልቅ ተጨማሪ ደዌ የሚሸከሙ ሆነዋል፡፡
እነዚህ ሰዎች ከትክክለኛው መስመር ያፈነገጡ በመሆናቸው በነፍሳቸው ከበረከት ይልቅ
መርገምን ተከናንበው ድርብ ጉዳት የሚጎዱ ከመሆናቸውም በላይ ከክርስቲያን
ትምህርትም የራቁና የወጡ ሆነዋል:: ይህ ግን በእውነቱ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ
የሆነ ጸያፍ ተግባር መሆኑን በመረዳት የሳቱ ሰዎች ወደ እውነተኛው የቤተ ክርስቲያን
ትምህርትና ሥርዓት መመለስ ይኖርባቸዋል። በምንም አይነት ሁኔታ በየቦታው በቤተ
ክርስቲያን ግቢም እንኳን ቢሆን የሚሸጡ ዘይቶች ይህን ቅዱስ ምሥጢር መተካት
አይችሉም፡፡ ደጋግመን እንደተናገርነው ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ በገንዘብ
የሚሸጡና የሚገዙ አደሉም፡፡

፱∙፬. የሚያስገኘው ጸጋ
❖ በምሥጢረ ቀንዲል የሚገኘው ጥቅም ምንድን ነው?

ምሥጢረ ቀንዲል እንደሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ በሚታይ አገልግሎት፣


አገልጋይና መገልገያ ንዋያተ ቅዱሳት የማይታየውን ጸጋ እግዚአብሔር ያስገኛል።
እነዚህንም ጸጋች በሁለት ከፍለን እናያቸዋለን። ምሥጢሩ የሚፈጸምላቸው ህሙማን

125
የሥጋና የነፍስ ደዌ ያላባቸው በመሆናቸው ፈውሱም የሥጋና የነፍስ ተብሎ በሁለት
ይከፈላል፡፡

ሀ. ፈውሰ ሥጋ ፦
ሰው ማለት ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ የተፈጠረ እንደመሆኑ በዚህ
ዓለም ሲኖር በሥጋውና በነፍሱ የሚቀበላቸው ሕማማት አሉ። ያንዱ መታመም
ሌላኛውንም ይጎዳል፤ ማለትም የሥጋ መታመም ነፍስን፣ የነፍስም መታመም ሥጋን
ስለሚያውከው ቤተክርስቲያን መንፈሳዊውን ሕክምና በተናጠል አትፈጽምም:: አንዱ
ተፈውሶ አንዱ ከታመመ ከላይ እንደገለጽነው የተፈወሰውም ታማሚ መሆኑ አይቀርምና
ምእመናን ይህን ድርብ ሕክምና ታክመው ፈውሰ ሥጋ፣ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙ
የምታደርግበት መንገድ ምሥጢረ ቀንዲል ይባላል።

ከላይ በአፈጻጸሙ እንደገለጽነው ምሥጢረ ቀንዲል በታዘዘው መሠረት የተፈጸመለት


ታማሚ ምእመን ከሕማመ ሥጋው ይፈወሳል። ሁሉንም ልጆቹን እንዳይታመሙ
የሚጠብቃቸው፣ በሆነ ምክንያት በታመሙም ጊዜ የሚፈውሳቸው እግዚአብሔር ነው።
“አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፣ በፊትህም መልካምን
ብታደርግ፣ ትእዛዙንም ብታደምጥ፣ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፣ በግብፃዊያን ላይ
ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ::” (ዘጸ፲፭፥፳፮፡፡)
እንደተባለ:: ሰው ሆኖ በዚህ ዓለም ላይ የሚመላለስ ክርስቲያን ሁሉ ሥጋዊ ጤንነቱ
በበሽታ በተናጋ ጊዜ ድውያንን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ካህናት
ቀርቦ መታከም ይኖርበታል:: “እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋር
እኖራለሁ::” (ማቴ. ፳፰፥፳፡፡) ብሏቸዋልና። መድኃኔዓለም ክርስቶስ በሰጣቸው ሥልጣን
መሠረት ሕመምተኛውን ይፈውሰዋል:: በተለይም በክርስቲያናዊ ሕይወቱ ጠንክሮ
እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚተጋ ሰው ካለ ደዌው እንዳይጸናበትና እንዳያስመርረው
እግዚአብሔር ከሱ ጋር ሆኖ ያቀልለታል:: አስፈላጊ በሆነ ሰዓትና ቦታም በምሥጢረ
ቀንዲል ይፈውሰዋል:: /መዝ ፵፥፩‐፭፡፡/ ይህ ምሥጢር በፍጹም እምነት “ይደረግልኛል!”
ብሎ በማመን ከተፈጸመ ሕሙማንን ከደዌ ዳኛ ከአልጋ ቁራኛ ይገላግላቸዋል።

ፈውሰ ነፍስ
በምሥጢረ ቀንዲል የሚገኝ ሁለተኛው ጸጋ ፈውሰ ነፍስ ነው:: የሚታመመው ሥጋ ብቻ
ስላልሆነ /ነፍስም ስለምትታመም/ እንደ ሥጋ ሁሉ እሷም ፈውስ ያስፈልጋታል። ነፍስን
የሚያቆስላትና የሚያሳምማት ደግሞ ኀጢአት ነው። ከላይ እንደገለጽነው አንዱ አካል
ተፈውሶ ሌላኛው አካል በሽተኛ ከሆነ ሰውየው ጤነኛ ሆነ ማለት አይቻልምና፤ ሁለቱንም
እንደ ሕመማቸው ዓይነትና ጽናት ተመጣጣኝ የሆነ ሕክምና ሰጥቶ መፈወስ ይገባል።
ስንዱዋ ቤተክርስቲያን የአካለ ሥጋና የአካለ ነፍስ ውሑድ የሆነውን /ሰውን/ በጠቀስነው
መሠረት እያከመች ኖራለች፤ ትኖራለችም:: መንፈሳዊ ሐኪሞቿም ካህናት ናቸው፡፡
ሥልጣናቸው የሁለቱንም አካላት (የሥጋንና የነፍስን) ሕመም ለማከም የሚያስችል ሀይል
ያለው ነውና::
126
ሕመምተኛው ሰው የእግዚአብሔርን ቸርነት አምኖ ኀጢአቱን በተናዘዘ ጊዜ ኃጢአቱ
መክሰም ትጀምራለች። ካህኑ በሚሰጠው መንፈሳዊ ትምህርት መሠረት ከኃጢአት ጋር
ያለውን ሰንሰለት ቆርጦ በጣለና እግዚአብሔርን ኃጢአት እየሠራ ላለማሳዘን በወሰነ ጊዜ
ደግሞ በምሥጢረ ንስሐ እንደገለጽነው ከማእሰረ ኃጢአት የተፈታ ይሆናል:: የንስሐው፣
የኑዛዜዉና የቀኖናው አስፈላጊነትም ለፈውስ ነፍስ ነው:: እግዚአብሔር አምላካችን
የነፍሳችንን ድኅነትና ፈውስ ከሥጋችን ድኅነትና ፈውስ የበለጠ ስለሚፈልግ ለፈውሰ ነፍስ
ከፍተኛ ትኩረት እንድንሰጥ ይፈልጋል። ቅዱስ ጴጥሮስም “ክርስቶስ ስለ እኛ በሥጋው
ከተሰቀለ እናንተም ይህቺን ዐሳብ ጋሻ አድርጋችሁ ኑሩ፤ በሥጋው መከራ የተቀበለ
ከኃጢአት ድኖአልና።” (፩ጴጥ፬፥፩፡፡) በማለት የተናገረው ከያዝነው ፍሬ አሳብ ጋር
የተጣጣመ መልዕክት ያለው ነው። ይህም ምሥጢር የሚስማማው የሥጋን ሕመምና
መከራ እንደጸጋ ቆጥረውና ተቀብለው ለሚታገሡት ነው። የምሥጢረ ቀንዲልም ዋናው
ትኩረት የሥጋ ፈውስ መስጠት አለመስጠት ላይ ሳይሆን ሕመምተኛው ፈውሰ ሥጋ
እንኳን ባያገኝ በሽታውን በአኮቴት /በትዕግሥትና በምስጋና/ ተቀብሎ ከነፍስ ሕማምና
ከሥጋ ሞት እንዲድን ማድረግ ላይ ነው ።

ማጠቃለያ
የዚህ ዓለም መንግሥታት ለሚያስተዳድሩት ሕዝብ ይበጃል ያሉትን ሁሉ ከማድረግ
ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ለምሳሌ የሕዝቡን ጤና በተመለከተ በርካታ የጤና ተቋማት በየጊዜው
እየገነቡ አገልግሎታቸውን የተሟላ ለማድረግ ሲጣጣሩ ይታያል:: የፀጋው ግምጃ ቤት
የሆነች ቤተ ክርስቲያንም የምእመናንን አጠቃላይ ምድራዊ ኑሮ የምታስተናግድባቸው
የምትመራባቸውና የምታስተዳድርባቸው የጠሩና የበቁ ምሥጢራት አሏት፡፡ ከነዚህ ውስጥ
አንዱ ምሥጢረ ቀንዲል ሲሆን ይህም ከላይ እንደተገለጸው ቤተክርስቲያን የምእመናንን
ሥጋዊና መንፈሳዊ ጤንነት የምትጠብቅበት የተቀደሰ መንገድ ነው:: ይህን ምሥጢር
በተሟላ ሁኔታ በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ተደራሽ እንዲሆን (እንዲሰጥ) ማድረግ
ይገባል:: ይሁን እንጂ ይህ ሲተገበር አይታይም ቤተ ክርስቲያን ከዓለማውያኑ የዚህ ዓለም
መንግሥታት ታንሳለችን? አታንስም፤ ትበልጣለች እንጂ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ታላቅነቷንና
ብልጫዋን እንደቀድሞው አገልግሎቷን የተሟላ በማድረግ ማሳየት ይጠበቅባታል፡፡ ለዚህም
የተለየ ክፍልን ብቻ ተጠያቂ ሳናደርግና ሳንጠብቅ ሁላችንም በጋራ በመንቀሳቀስ ይህን
ምሥጢር በታዘዘው መሠረት እውን ለማድረግ መነሣት አለብን::

ዋቢ መጻሕፍት
• ማ/ቅ፤ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፫፤
አ/አ።

• ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየና ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔ፤


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፯፤ አ/አ።

127
• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ
ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ


ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ 1996፤ አ/አ።

• አባ በትረ ሃይማኖትና ዲ/ን ዮሐንስ መኰንን፤ ሰባቱ ምሥጢራተ


ቤተ ክርስቲያን፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፰፤ አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፹፰፤ አዲስ አበባ።

• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤
1999፤ አ/አ።

128
ምዕራፍ አሥር
በዓላት
ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ካጠናቀቁ በኋላ ፦

• የቅድስት ቤተክርስቲያንን በዓላት ምንነት፣ታሪክና አከባበር ይረዳሉ።

• ዋና ዋና የቤተክርስቲያን በዓላትን አውቀው በሥርዓት ማክበር ይችላሉ።

መግቢያ:‐ ዘመንኩ ባዩ ዓለም የእግዚአብሔርና የቅዱሳኑ መታሰቢያ የሆኑ በዓላትን


የሚጠላ ሆኗል:: በጣም የሚገርመው ግን እዚህ ግባ ለማይባሉ ነገሮች እንኳን ሳይቀር
መታሰቢያ ሲያቆምላቸው መታየቱ ነው፡፡ እምነት የለሹ ይህ ዓለም እግዚአብሔርንና
የእግዚአብሔር ገንዘቦች የሆኑትን ሁሉ የሚቃወም በመሆኑ መንፈሳዊያት በዓላትን
ቢቃወምና ሊያጠፋ ቢጣደፍ ከዓላማው አንጻር ለምን ሊባል አይገባውም::

የቤተ ክርስቲያን ልጆች በዚህ ፀረ ክርስትና አስተምህሮ ተወናብደው እንዳይስቱ


ግብራቸውን ሁሉ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ማለት
በእምነት ይፈጽሙት የነበረውን በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ መሠረት በማጠናከር
ከቀሳጥያን ማታለል ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው፡፡

በዚህ ምዕራፍ ሥር በዓላትን በተመለከተ

• የበዓላት ፅንሰ አሳብ ምንነት


• የበዓላት ታሪክ
• የበዓላት አከባበር
• ዋና ዋና በዓላት
• ሥርዓተ ዑደት
129
• መንፈሳዊና ሥጋዊ ጠቀሜታዎችና
• የበዓል አከባበር ተግዳሮቶች የሚሉትን ንዑሳን አርእስት መነሻ በማድረግ ዘርዘር
ያሉ ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡ በማስተዋል ማንበብ ጥያቄዎችን ለመመለስ
መሞከርና ለተግባራዊ ምላሽ ራስን ማዘጋጀት ከእያንዳንዱ አንባቢ የሚጠበቅ
ይሆናል::

፲∙፩∙የበዓላት ፅንሰ አሳብ


የተከበሩ አንባቢ ሆይ:‐ስለ በዓላት ማብራሪያ ከመስጠታችን በፊት የሚከተለውን ጥያቄ
ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ በዓል ለእርስዎ ምንድነው? እንዴት ይተረጉሙታል? ወደ ቀጣዩ ምንባብ ከማለፍዎ


በፊትመልስዎን በጽሑፍ ያስፍሩ፡፡

በዓላት ምንድን ናቸው?


በዓል “አብዐለ” አከበረ÷ አበለጠ÷ ዕለትን በዓል አደረገ ከሚለው ግስ የወጣ ስም ነው።
በቁሙ ሲፈታም የደስታ፥የዕረፍት ቀን ፥በዓመት በወርና በሳምንት የሚከበር፥ ያለፈ
ድርጊት የሚታወስበትና ምእመናን የበዓሉን ምሥጢር እያሰቡ ሐሴት የሚያደርጉበት
ነው:: ዘርዘር ተደርጎ ሲታይም ምእመናን መደበኛ ሥራቸውን ትተው ለበዓሉ ይገባዋል
የሚሉትን ተግባር የሚፈጽሙበት የበዓሉን ባለቤት እግዚአብሔርንና የበዓሉን ምክንያት
እያሰቡና እያመሰገኑ ደስ የሚሰኙበት ዕለት ነው። ቅዱስ ዳዊት “….በዓልን የሚያደርጉ
ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ:: ”(መዝ ፵፩፥፬፡፡) እንዳለው ማለት
ነው። በዓላት የዕረፍት ቀናት ናቸው ማለት ከሥጋዊ ወይም ምድራዊ (ዓለማዊ) ሥራዎች
የሚያርፉባቸው ናቸው ለማለት ነው። በአንጻሩ ግን መንፈሳዊ ሥራዎች ሁሉ እንደየችሎታ
የሚከናወንባቸው መሆናቸው መረሳት የለበትም፡፡ እነዚህ ዕለታት እግዚአብሔር በራሱ
ወይም በቅዱሳኑ አድሮ ለሠራቸው ድንቅ ሥራዎች (ተአምራት) መታሰቢያዎች ናቸው።
(መዝ፻፲፥፬)፡፡ ፻፲፩፥፮፡፡ ሉቃ፳፪፥፲፱፡፡)

በዚህም መሠረት እግዚአብሔር ለድንቅ ሥራዎቹና ለቅዱሳኑ ከሰጣቸው መታሰቢያዎች


አንዱ በዓል መሆኑን እንረዳለን :: በዓላት እግዚአብሔር እንደወደደ (እንደቸርነቱ)
የሚሠራቸው ድንቅ ሥራዎች የሚገለጡባቸውና የቅዱሳኑ ተጋድሎ፣ ድል አድራጊነትና
እግዚአብሔር የሰጣቸው ቃል ኪዳን የሚዘከርባቸው (የሚታሰብባቸው) ዕለታት ናቸው።
እግዚአብሔር አምላክ “ሰንበታቴንም ቀድሱ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንኩ
130
ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሁኑ፤” በማለት (ሕዝ ፳፥፳፡፡)
እንደተናገረው በዓላት እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል የመሆኑ ማረጋገጫዎች ናቸው።

፲∙፪∙ የበዓላት ታሪክ


❖ በሰው ልጆች አኗኗር ውስጥ የበዓላት አስተዋጽዖ እንዴት ይገለጻል?

የበዓላትን የት መጣ በተመለከተ የምንጀምረው “ሰማይና ምድር ዓለማቸውም ሁሉ


ተፈጸመ። እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በስድስተኛው ቀን ፈጸመ፣ እግዚአብሔርም
በሰባተኛው ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። እግዚአብሔርም ሰባተኛዋን ቀን ባረካት፤
ቀደሳትም፤ ሊፈጥረው ከጀመረው ሥራ ሁሉ በእርስዋ ዐርፎአልና። (ዘፍ፪፥፩‐፬)።” በማለት
እግዚአብሔር ከተናገረው ክፍለ ንባብ ነው። ይህቺ ዕለት ቀዳሚት ሰንበት ትባላለች
አክብሮና ቀድሶ ለሰው ልጆች የዕረፍት ቀን ትሆን ዘንድ የሰጠውም ራሱ እግዚአብሔር
ነው፡፡ በዚህም የሥራ ቀናትና የዕረፍት ቀን ለየብቻ ተለይተው መገለጻቸውን ልብ ማለት
ያስፈልጋል። በዚህም ሠርቶ ማረፍ፣ ዐርፎም መሥራት በሰው ልጆች የሕይወት ጉዞ ውስጥ
የማያቋርጥ ዑደት ሆኖ የኖረ ያለና የሚኖር መሆኑን እንረዳለን::

ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላክ እስራኤል ዘሥጋ ሊያከብሯቸው የሚገቡትን


በዓላት ከአከባበር ሥርዓታቸው ጋር ለሙሴ ነግሮታል:: ለማሳያ ያህል በኦሪት ዘሌዋውያን
ምዕራፍ ፳፫፥፩-ፍጻሜው ድረስ ያለውን ማስተዋል ይገባል። የብሉይ ኪዳን በዓላት ጥንት
መጀመሪያ ከሆነችው ከቀዳሚት ሰንበት ጀምሮ በዓለ ፋሲካና በዓለ ናዕት (የቂጣ በዓል)፣
በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል)፣ በዓለ መጥቅዕ፣ ዕለተ (በዓለ) አስተርዮ፣ የዳስ በዓል ዋና ዋናዎቹ
ሃይማኖታዊ በዓላት ናቸው። ሌሎች በዓላትንም እንደ ቀዳሚነት ሰንበት ሁሉ ሰንበት ብሎ
የጠራበት ሁኔታም አለ። (ዘሌ፳፫፥፴‐፴፫፡፡) ከዚህም ሰንበታትም ይሁኑ ሌሎች
የእግዚአብሔርና የቅዱሳን በዓላት ሥጋዊ ዕረፍት የሚደረግባቸውና እግዚአብሔርን
እያመሰገኑ በደስታ የሚያከብሯቸው ቀናት በመሆናቸው በስያሜ ደረጃ ቢለያዩም
በሚከበሩበት ዓላማና ሁኔታ ተመሳሳይነት እንዳላቸው እንማራለን። ሌላው ቀርቶ በየ፯
ዓመቱ የሚከበር የምድር ሰንበትና (ዘሌ ፳፭፥፩‐፰፡፡) ሰባት የዓመታት ሰንበቶች፥ ሰባት
ጊዜ ሰባት ተቆጥሮ አርባ ዘጠኝ ዓመት ከሞላ በኋላ በአምሳኛው ዓመት የሚከበር ዓመተ
ኢዮቤልዩ (ዘሌ፳፭፥፰‐፲፰፡፡) እንደነበራቸው ከእስራኤላውያን የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ
ታሪክ እንረዳለን።

የበዓላትን ጉዞ በሐዲስ ኪዳን የተመለከትን እንደሆነ ደግሞ ጌታችንና መድኃኒታችን


ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን በሚቆጠርለት ሥጋ ተገልጦ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሞላው ጊዜ
ካከበረው በዓል ይጀምራል። “ዘመዶቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ
ነበር። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሞላው ጊዜ እንደ አስለመዱ ወደ ኢየሩሳሌም ለበዓል
ወጡ። ሥራቸውንም ጨርሰው ተመለሱ፤ ሕፃኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን
በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮሴፍና እናቱም አላወቁም ነበር፤
በመንገዱም ከሰዎች ጋርያለ መስሏቸው ነበር:: ያንድ ቀን መንገድም ከሄዱ በኋላ ዕለቱን
ከዘመዶቹ፤ከሚያውቁትም ዘንድ ፈለጉት። ባላገኙትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም
131
ተመለሱ። ከዚህም በኋላ በሦስተኛው ቀን በቤተመቅደስ በሊቃውንት መካከል ተቀምጦ
ሲሰማቸውና ሲጠይቃቸው አገኙት። ”(ሉቃ ፪፥፵፩‐፵፯፡፡) ከሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ
አንቀጽ ውስጥ ሳንወጣ በዓልን እንደሰውነቱ አክብሮ እንደ አምላክነቱም ባርኮ ምእመናን
እንዲያከብሩ የሰጠው መድኃኔዓለም ክርስቶስ መሆኑን እንረዳለን።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያበላሹትን የበዓል አከባበርና የመቅደሱን


ሥርዓት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳስተካከለውም ነግሮናል። “የአይሁድም
የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር። ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን፣ ርግቦችንም የሚሸጡትን፥ ገንዘብ ለዋጮችንም
ተቀምጠው አገኘ:: የገመድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎችንና በሬዎችን፥ ሁሉንም ከቤተ መቅደስ
አስወጣ፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ። ርግብ ሻጮችንም “ይህን
ከዚህ አውጡ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ አላቸው።” (ዮሐ.፪፥፲፫‐፲፯፡፡)
የሚለው አንቀጽ ላነሣነው ነጥብ ሁነኛ ማስረጃ ነው።
ጸሐፍት ፈሪሳውያን በሙሴ አማካኝነት እግዚአብሔር ያዘዘውን የበዓል አከባበር ሥርዓት
ወደ ጎን ብለው ሥጋዊ ጥቅማቸውን ብቻ ሊያስከብርላቸው የሚችል አዲስ ነገር ቀላቅለው
ስለነበር ነው ተግሣጽ የደረሰባቸው:: ይህም የጸሐፍት ፈሪሳውያን ነቀፋና ተግሣጽ ብቻ
ሳይሆን ለሐዲስ ኪዳን የበዓል አከባበርም የተሰጠ አምላካዊ መመሪያ መሆኑን መገንዘብ
ይገባል:: አሁን ደግሞ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ።

፲.፫. የበዓላት አከባበር


የተከበሩ የዚህ ጽሑፍ ተከታታይ፦

❖ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታትን በ፮ ቀናት ፈጥሮ /ሥራ ሠርቶ/ በዕለተ ሰንበት


/ቀዳሚት ሰንበት/ ዐርፏል:: ይህን መሠረት በማድረግ ሳይሠሩ ማረፍ /በዓል
ማክበር/ አይገባም የሚል አሳብ አለ:: እርስዎ ይህ አሳብ ትክክል ነው ይላሉ?
እንዴት? ለምን?

❖ በቤተ ክርስቲያን በዓላት ሲከበሩ ካዩና ከሰሙ ትዝ የሚልዎትን ያከባበር ሥርዓት


ይዘርዝሩ። እስካሁን እንዳዩት አብዛኛው ምእመን የቤተ ክርስቲያን በዓላትን
ሲያከብር ከሥጋዊውና ከመንፈሳዊው ዝግጅት ለየትኛው ነው ከፍተኛ ትኩረት
የሚሰጠው?

በቅድሚያ ከዚህ በላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ:: በመቀጠልም


የተሰጡትን ማብራሪያዎች በማንበብ ለጥያቄዎቹ ከሰጧቸው መልሶች ጋር ያነጻጽሩ።

በብሉይ ኪዳን ይከበሩ የነበሩ በዓላትን የአከባበር ሥርዓት በዝርዝር ሳይሆን በጥቅል
በማየት እንጀምራለን። በዚህ ዘመን በዐላት እንዲከበሩ ያዘዘው እግዚአብሔር ሲሆን
ለያንዳንዱ ክብረ በዓል የአከባበር ሥርዓቱንም ደንግጎ ሰጥቷል። ዋና ዋናዎቹ
ትእዛዛትም ተግባረ ሥጋን መተው (ዘሌ፳፫፥፫‐፴‐፴፪፡፡) ተገቢ መሥዋዕት ማቅረብ
(ዘኁ ፳፰፥፩-ፍጻሜው፡፡) በተለይ በሦስቱ ዐበይት በዓላት (የቂጣ፣ የመከር፣ የአዝርዕት
132
መክተቻ (የዳስ በዓል) ወደ ቤተ መቅደስ መውጣትና በዚያም ባዶ እጅ አለመታየት
(ዘጸ፳፫፥፲፬‐፲፰፡፡ ዘዳ፲፮፥፲፮‐፲፰፡፡) ምስጋና ማቅረብ (፩ኛ ዜና መዋ ፲፮፥፩‐፴፯፡፡
መዝ ፹፥፩‐፭፡፡) እና የመሳሰሉት ናቸው።

❖ ከአቅም በላይ ባልሆነ ምክንያት አንድ ሰው የቤተ ክርስቲያን በዓል በሚከበርበት


ዕለት በዓሉን ሳያከብር ከሥራ በኋላ ሠርክ ጉባዔ ቢማርና መዝሙር ቢዘምር በቂ
አይደለምን?

የሐዲስ ኪዳን በዓላትንም በተመለከተ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ብንመረምር እንደ


ብዛታቸው ሁሉ የአከባበር ሥርዓታቸውም ልዩ ልዩ ሆኖ እናገኘዋለን። ከዚህ የተነሣ በዚህ
መጽሐፍ የምንገልጸው በበዓላቱ ላይ በዋናነት በማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምእመናን በጋራ
የሚፈጸመውን አጠቃላይ የአከባበር ሥርዓት የተመለከተውን ብቻ ነው:: ምእመናን
በዓላቱን በሚያከብሩበት ጊዜ ሁልጊዜም ባይሆን ባብዛኛው የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት
አለባቸው። አንድ ክርስቲያን ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሳይደርስበት የዕለቱን በዓል
ማክበር እየቻለ በዓላት በሚከበሩባቸው ዕለታት ከቤተ ክርስቲን መቅረት የለበትም፡፡ ዳሩ
ግን በግዴለሽነት ከቤተ ክርስቲያን ቀርቶ በበዓሉ ዕለት ሠርክ ጉባዔ በመማርና በመዘመር
ብቻ በዓልን በአግባቡ እንዳከበረ መቁጠር የተሳሳተ ነው፡፡ በዓላትን በአግባቡ ማክበሩን
ለማረጋገጥ የፈለገ ክርስቲያን የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋል ይኖርበታል፡፡

በዓል የሚያከብር ሰው፡-

• ሥጋዊ ያልሆነና ፈሪሐ እግዚአብሔር ባልተለየው ደስታ ምስጋና ማቅረብ፤


(ፍ.ነገ ቁጥር ፯፻፲፱‐፯፻፳፩፡፡ መዝ፪፥፲፩፤፻፲፯፥፳፬‐፳፰፡፡)

• እንደ አይሁድና እንደ አሕዛብ ሳይሆን እንደ ክርስቲያን ማክበር


(ፍ.ነቁጥር.፯፻፲፫-፯፻፲፭፡፡)

• በቤተ ክርስቲያን መሰብሰብ፤ (ፍ.ነቁጥር.፯፻፲፯‐፯፻፲፱፡፡)

• ምሕረት ማድረግ፤ (ማቴ፮፥፲፭፤ፍ.ነ.ቁጥር፯፻፲፮፡፡ ፯፻፵፩‐፯፻፵፫፡፡)

• ከግብረ ኃጢአት መራቅ፤

• በተለይ ለማለት ያህል እንጂ ከኃጢአት መራቅስ ምን ጊዜም ቢሆን


ለክርስቲያን ሁሉ የሚገባ የዘወትር ተግባሩ ነው። ለምሳሌ ያህልም፦

• በልቶ ጠጥቶ ከልክ ማለፍ /መስከር፣…./

• ሐሜት፣ ዋዛ ፈዛዛ፣

• ክርስቲያናዊ ያልሆነ አለባበስ፣

133
• ክርስቲያናዊውን ባህል ማጣጣልና የመሳሰሉት ሁሉ
የማይገቡ ናቸውና ክርስቲያኖች ከነዚህ መራቅ
ይኖርባቸዋል።

• ተጋድሏቸውን ማሰብ /በዓሉ የቅዱሳን ከሆነ/፣ (፩ተሰ.፭፥፲፪‐፲፭፡፡)

• ንስሐ ገብቶ ቅዱሱን ቁርባን መቀበል (ዮሐ ፮፥፶፫‐፶፭፡፡)

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትንና የመሳሰሉትን በማሳያነት መመልከት ይቻላል።


የመንፈሳዊ በዓላት አከባበር እንደገለጽነው እንደየበዓሉ ዓይነት ልዩ ልዩ ቢሆንም በቀጣይ
ደግሞ በብዙዎቹ በዓላት አከባበር የጋራ የሆነውን የአፈጻጸም ሥርዓት ከዋዜማው ጀምረን
እንደሚከተለው ባጭር ባጭሩ ለመግለጥ እንሞክራለን።

ዋዜማ
ዋዜማ ሁለት ተያያዥ የሆኑ ፍቺዎች አሉት::

፩.በቁሙ፤ መጀመሪያ ዜማ፤ ከበዓሉ በፊት ማታውን የሚዜምና የሚመራ መዝሙር፤ ቅኔ።

፪.ድራር፤ ንዑስ በዓል፤ ማኅትው የሚቆምበት፤ ዋዜማ የሚመራበት ቀን፤ (ማኅትው የነግህ
መዝሙር ነው። (ኪ.ወ.ክ. ገጽ፬፻፲፰፡፡)

ሥርዓተ ዋዜማውም በቁጥር አንድ ትርጉም ላይ እንደተቀመጠው ከበዓሉ በፊት


ለዕለቱ የተሠራውን የምስጋና ቃል እየመሩ፣ እየተመሩ፣ እያነሡ፣ እየዘመሙ፣ መስተብቁዕ
እየደገሙ፣ እያመረገዱ፣ እያመለጠኑ፣ እየጸፉ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ውዳሴ
(ምስጋና) ነው:: የጋራ የሆኑት ሥርዓቶች ደግሞ የሚከተሉትን ይመስላሉ። ሲጀመር
አሥርቆት ተደርጎ (ዕለቱ ወሩና ዓመቱ በፀሐይና በጨረቃ አቆጣጠር ተሰልቶ) በአቡነ
ዘበሰማያት ይታረጋል። በመቀጠልም በግእዝ ዜማ “ቅዱስ” ብሎ የሠርክ ኪዳን የምስጋና
ጸሎት በንባብ ወይም በዜማ ይቀርባል:: እንደተለመደውም ጸሎተ ኪዳኑ በአቡነ
ዘበሰማያት ይታሰራል:: ከዚያም ሰላም ለኪ ተብሎ አንቀጸ ብርሃን ይደገምና በአቡነ
ዘበሰማያት ይታረጋል፤ (ይደገማል።) ከዚህ በኋላ ነው ከላይ ለመግለጽ እንደ ሞከርነው
ለበዓሉ የተሠራው ለየት ያለ ምስጋና የሚቀርበው የዋዜማንና የአንቀጸ ብርሃንን ቋሚ
ተዛምዶ በተመለከተ መምህር መንግሥቱ ገብረ አብ “ምዕራፍ ዘቅዱስ ያሬድ” በሚለው
መጽሐፋቸው ያሰፈሩትን ማስታወስ እንወዳለን። ቅዱስ ያሬድ በቅድስት አክሱም ጽዮን
ሳለ ፫ ሰዓት ሲሆን “ሃሌ ሉያ ለአብ፥ ሃሌ ሉያ ለወልድ፥ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፤”
ብሎ “ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ፣ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን አዘጋጀ (ዘረጋ)” አዜመ።
በ፱ ሰዓት ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ሳለ ከቆመበት አንድ ክንድ ወደ
ላይ መጥቆ የአንቀጸ ብርሃንን ዘርና ዜማን ተናገረ። አያይዞም “ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ
እመላእክት ቅዱሳን”፤ በሰማይ ከቅዱሳን መላእክት (አንደበት) የሰማሁት ምስጋና ምንኛ
ድንቅ ነው!” የሚለውን ደረሰ /አዜመ/። “ዋይ ዜማ” የተሰኘውን ቃል በአርባዕቱ እንሰሳ
134
(ኪሩቤል) ክብረ በዓል (ኅዳር ፰ ቀን) ምስጋና ውስጥ ከሚገኘው ከዚሁ ዋይ ዜማ ከሚለው
ቃል የተወሰደ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ በዋይ ዜማ (ዋዜማ) ቁመት ጊዜ አንቀጸ ብርሃንና
ዋዜማ ተከታትለው ለመባላቸው ማስረጃው ይህ ነው።”(ገጽ ፪፻፵፱)

በዕለቱ
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የበዓላቱ አከባበር እንደየበዓላቱ ዓይነት ልዩ ልዩ ነው።
ለዋዜማው የሚቀርበውን ስብሐተ እግዚአብሔር ለሁሉም በጋራ የሚደረስና እንደ በዓሉ
ሁኔታ ልዩ ልዩ የምስጋና ስልትና ሥርዓት እንዳለው ባየነው መሰረት ማለት ነው።
ሥርዓተ በዓላትን በጥቅሉ ስናያቸው በዕለቱ ያላቸውን አከባበር በሁለት ከፍለን ማየት
እንችላለን ።

ሀ.ታቦት በማውጣት፦ ይህ በበዓሉ ባለቤት ስም ለመታሰቢያነት የተሰየመውን ታቦተ


/ጽላተ/ እግዚአብሔር በማውጣት የሚከበረው ነው። ከዋዜማው ቀጥሎ ካለው ቀዳማይ ሰዓተ
ሌሊት ጀምሮ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ማኅሌት በመቆምና ሞልጣን በማመልጠን
እግዚአብሔርንና በደረጃው ያለ የበዓሉን ባለቤት ሲያመሰግኑ ያድራሉ። ቅዳሴው ጠዋት
ከሆነ ቅዳሴውን እንደሥርዓቱ ፈጽመው በሊቃውንቱ፣ በሰ/ት/ቤት፣ ወጣት ዘማርያንና
በምእመናን የተባበረ ምስጋና ዝማሬና ዕልልታ ታጅቦ ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ተነሥቶ
ይወጣል። የበዓሉ ታዳሚዎች በሙሉ ለታቦተ እግዚአብሔር እየሰገዱ ተገቢውን ክብርና
ምስጋና ያቀርባሉ። ዑደቱ፣ ውዳሴው፣ ትምህርቱ /ስብከቱ/ እና ቃለ ምዕዳኑ ከቀረበ
/ከተሰጠ/ በኋላ በበዓሉ ላይ በተገኘው ታላቅ /በማዕረግ/ አባት አቡነ ዘበሰማያት ተሰጥቶ
ታቦቱ በታላቅ ክብር ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል፡፡ የበዓሉም ፍጻሜ ይሆናል። ቅዳሴው
ከሰዓት ከሆነ ደግሞ ማኅሌቱና ምልጣኑ እንዳበቃ ከላይ በጠቀስነው መሠረት ሥርዓተ
ዑደቱ ትምህርቱ ምስጋናና ቃለ ቡራኬው ተፈጽሞ ቅዳሴው የበዓሉ ማሰሪያ ይሆናል።

ለ.ልዩ ልዩ መታሰቢያ በማድረግ፦ የአንድ በዓል ባለቤት መታሰቢያ የሆነ ታቦት


(ጽላት) በሌለባቸው ወይም እያለ በማይከብርባቸው አጥቢያዎች የጌታችን፣ የእመቤታችንና
የቅዱሳን በዓላት ታቦተ እግዚአብሔር ሳይወጣም በልዩ ልዩ መታሰቢያዎች ይከበራሉ::
በየሳምንቱ የምትመጣው ሰንበተ ክርስቲያንም በተመሳሳይ ሁኔታ በየአብያተ ክርስቲያናቱ
በልዩ ልዩ መንገድ ትከበራለች። እነዚህ በዓላት ከሚከበሩባቸው መንገዶች መካከልም
የሚከተሉትን መግለጽ ይቻላል::

• በማሕሌት፣ በዝማሬ፣ በሽብሸባና በዕልልታ፣ በቅኔና በደስታ በልዩ ልዩ መባልዕትም


ሁሉ፤

• በሰዓታት፣ በጾምና በጸሎት፤

• በሐዘን፣ በለቅሶ፣ በስግደት፣ በምጽዋትና በዝክር፣ እንዲሁም በጉባዔና በቅዳሴ በዓላቱ


ይከበራሉ።

፲.፬. ዋና ዋና በዓላት
135
ክቡር አንባቢ ሆይ፦

ይህንን ርእሰ ጉዳይ በዝርዝር ከማየታችን በፊት የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ።

❖ በቤተ ክርስቲያን ስንት ዋና ዋና በዓላት አሉ?

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምታከብራቸውና እንድናከብራቸው ያዘዘቻቸው በዓላት ልዩ


ልዩ ናቸው፡፤ በፈቃደ እግዚአብሔር በኒቂያ የተሰበሰቡ ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ
ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሠሯቸው የታወቁ በዓላትን በሚከተለው መልኩ መዘርዘር
ይቻላል።

ዐበይት የጌታ በዓላት


ተ.ቁ የበዓላት ዝርዝር የክብር ቀን የሚከብርበት ምክንያት
1 ትስብእት መጋቢት 29 ጌታ ስለተፀነሰበት
2 ልደት ታኅሣሥ 29 ጌታ ስለተወለደበት
3 ጥምቀት ጥር 11 ጌታ ስለተጠመቀበት
4 ደብረ ታቦር ነሐሴ 13 ጌታ ኪቢሩን ስለገለጠበት
5 ሆሣዕና ቋሚ ቀን የለውም በሕፃናት አፍ ስለተመሰገነበት
6 ስቅለት ቋሚ ቀን የለውም ተሰቅሎ ዓለምን ስላዳነበት
7 ትንሣኤ ቋሚ ቀን የለውም ሞትን ድል አድርጎ ስለተነሣበት
8 ዕርገት ቋሚ ቀን የለውም ወደ ሰማይ ስላረገበት
9 ጰራቅሊጦስ ቋሚ ቀን የለውም መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት ስለወረደበት

ሀ. ንዑሳት የጌታ በዓላት


1.ስብከት

2.ብርሃን

3.ኖላዊ

4.በዓለጌና

5.ግዝረት

6.ልደተ ስምኦን

7. ቃና ዘገሊላ

8. ደብረ ዘይት

9.መስቀል
136
ለ.የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም ፴፫ ዓመታዊና ወርኃዊ በዓላት አሏት።(መቅድመ ተአምረ ማርያም፡፡)
በዚህ ጽሑፍ ከነዚህ በዓላት መካከል ዋና ዋና የሚባሉ አምስቱን ብቻ እንዘረዝራቸዋለን ።

1. ልደቷ (የተወለደችበት)፡- ግንቦት ፩ ቀን፤

2. ዕረፍቷ፡- ጥር ፳፩ ቀን፤

3. ኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ቃል ኪዳን ከልጇ) የተቀበለችበት፡- የካቲት ፲፮ ቀን፤

4.ቅዳሴ ቤቷ፡- ሰኔ ፳፩ ቀን፤

5.ፍልሰተ ሥጋዋ (ዕርገቷ) ፡- ነሐሴ ፲፮ ቀን፤

ከነዚህ በዓላት በተጨማሪ ለሁሉም ክርስቲያን የጋራ የሆኑ የግዝት በዓላት አሉ።እነዚህም
ከእመቤታችን በተጨማሪ ወር በገባ በ፲፪ የቅዱስ ሚካኤልና በ፳፱ የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ ናቸው:: በየአጥቢያዎቹ የሚከበሩ ልዩ ልዩ ተጨማሪ በዓላትም
አሉ።እነዚህ ግን በአጥቢያው ካህናትና ምእመናን ደረጃ ብቻ የተወሰኑ ናቸው። ከነዚህ
ውጪ የሆኑት በዓላት ሁሉ ምእመናን በግላቸው (በፈቃዳቸው) ከተደረገላቸው ድንቅ ሥራ
ተነሥተው በፍቅርና በፍላጎት የሚፈጽሙት መሆኑ መታወቅ አለበት:: እነዚህን
ቤተክርሰቲያናችን ምእመናን በግድ እንዲያከብሯቸው ያላዘዘቻቸው (በግዝት
ያልሠራቻቸው) ናቸው።

፲∙፭∙ ሥርዐተ ዑደት


❖ ዑደት ሲደረግ የርስዎ ተሳትፎ ምን ይምስል ነበር?

ይህ ሥርዓት ዓመታዊ የሆኑ የጌታችን፣ የእመቤታችን፣ የሐዋርያት፣ የመላእክት፣ የጻድቃን፣


የሰማዕታት፣ መታሰቢያ በዓላት የሚከበሩበትና የሚከናወኑበት ነው። በነዚህ ዓመታዊ
የንግሥ በዓላት ታቦታትን አክብሮ ዑደት ማድረግ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ
በእግዚአብሔር ትእዛዝና ፈቃድ ይከናወን የነበረ ጥንታዊ ሥርዓት ነው።
(ኢያ፮፥፩‐ፍጻሜው፡፡)

ዑደት ታቦተ እግዚአብሔር እንደ ዕለቱ በዓል ማንነት ከመንበረ ክብሩ እየተነሣ በታላቅ
ክብርና ምስጋና ቤተ መቅደሱን የሚዞርበት እግዚአብሔርም ህዝቡን የሚባርክበት ሥርዓት
ነው። በዑደቱ ጊዜም ከልሂቅ እስከደቂቅ የተማረ ያልተማረ ሳይባል ሁሉም እንደ ችሎታው
እግዚአብሔርንና መታሰቢያ የተደረገለትን ቅዱስ ያመሰግናል::በዓላትን በዑደት የማክበር
መሠረታዊ ዓላማውም ምእመናን በቅዱሳን አማካኝነት የሚታደለውን በረከተ እግዚአብሔር
እንዲያገኙና ለመንግሥተ እግዚአብሔር የሚያበቃቸውን ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩ
ለንስሐም እንዲዘጋጁ ማድረግ ነው።ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ በመዞርም ምሥጢረ

137
ሥላሴን ይሰብካሉ ሦስት ጊዜ መሆኑ የሦስትነት ግብሩ (ድርጊቱ) አንድ ዓይነት መሆኑ
(አለመለወጡ) ያንድነት ምሳሌ ሆኖ ይመሠጠራልና።አፈጻጸሙም ቀደም ብለን ባጭሩ
በገለጽነው መሠረት ይሆናል።

አከባበሩ ይህን የሚመስል ሆኖ ሳለ በአንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ያለው ድርጊት አሳሳቢ


እየሆነ መምጣቱ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ የተቀደሰ ሥርዓት ሽፋን ከቤት ወጥቶ መደባደብ፣
መጨፈር፣ መዳራት፣ ማመንዘር፣ መስረቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ ተግባራት መፈጸም
ክርስቲያናዊ ያልሆነ አሕዛባዊ ልማድ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ስለዚህ በማወቅም ይሁን
ባለማወቅ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑትን በመምከር ማስተካከል የክርስቲያኖች ሁሉ
ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው፡፡

ጥምቀት (ኤጲፋንያ)
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት እንደ ደመራ
(መስቀል) በዓል ሁሉ በዓለ ጥምቀትም የአደባባይ በዓል ነው:: በሁለቱ መካከል ያለው
ልዩነት የአከባበሩ ሥርዓት ልዩ ልዩ ውበት ያለው መሆኑና በደመራ በዓል ካህናቱ ይዘው
የሚወጡት መስቀል ሲሆን በጥምቀት (ኤጲፋንያ) ደግሞ ወደ ጥምቀተ ባሕር ይዘው
የሚወርዱት በየአጥቢያው የሚገኙ ታቦታትን መሆኑ ነው። መስቀል ወደ አደባባይ
የሚወጣው በበዓሉ ዋዜማ በደመራው ዕለት ከሰዓት በኋላ እንደሆነ ሁሉ ታቦታቱም
ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት በበዓሉ ዋዜማ በከተራ
ነው:: ሌላው የሚያመሳስላቸው ነጥብ ደግሞ ሁለቱም በዓላት የሚከበሩት እንደ ሌሎቹ
የጌታ በዓላት ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ ለመመስከር መሆኑ ነው።

ምእመናን በታላቅ ጉጉት ከሚጠብቋቸው በዓላት አንዱ በሆነው በዚህ በዓል ታቦታቱ
በምስጋና፣ በዕልልታ፣ በሆታ ታጅበው ወደ ባሕረ ጥምቀት ይወርዳሉ:: አስቀድሞ በባሕረ
ጥምቀቱ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ዳስ ተጥሎ ወይም ድንኳን ተተክሎ እና ከተራ
ተከትሮ /ውሃ ተገድቦ/ ይጠብቃል። ታቦታቱ ከዛ ሲደርሱ ቀሪው የምስጋናና የልመና
(የምህላ) ሥርዓት ይፈጸማል። በመቀጠልም በተዘጋጀው ጊዜያዊ ማረፊያ (መቅደስ)
ታቦታቱና ንዋያተ ቅድሳቱ እንዲገቡ ይደረጋል። ይህ ዕለትና ቦታ በዓመት ውስጥ
ቤተክርስቲያን ከመደበኛው ቦታዋ ውጪ ሥርዓተ ቅዳሴ የምታከናውነበትና ምሥጢራትን
የምታድልበት ብቸኛና ልዩ ዕለትና ቦታ ነው።

ልዩ የዑደት ሥርዓት
በአክሱም ጽዮን ማርያም ከጥንት ጀምሮ የነበረና አሁንም ያለ ልዩ የዑደት ሥርዓት እዚህ
ላይ መጠቀስ ይኖርበታል ብለን እናምናለን:: ይሀ ሥርዓተ ዑደት የሚከናወነው በየወሩ ለ፯
ተከታታይ ቀናት ከመባቻ (፩) እስከ ሥላሴ (፯) ድረስ ነው። ከሌሊቱ ፲፩ ሰዓት ጀምሮ
የአክሱም ከተማ ካህናትና ምእመናን በብዛት ወጥተው ጧፋ እያበሩ ታቦተ እግዚአብሔርን
የሚያከብሩበትና የሚባረኩበት ልዩ የዑደት ሥርዓት ነው። ከመቅደሱ የወጣው ታቦትም
በካህናቱ ከብሮ የከተማውን እምብርትና ዋነኛ ክፍል እየባረከ ዞሮ የሚመለስበት በየወሩ

138
ለ፯ ቀናት የሚከናወን አስደሳች ሥርዓት ነው። የዑደቱ መሠረታዊ ዓላማ እመቤታችንን
ድንግል ማርያምንና በእሷም በኩል እግዚአብሔርን በምህላ (እግዚኦታ) መማፀን ነው።
በግራና በቀኝ እየተቀባበሉ (እያስተዛዘሉ) ከተለመደው አደባባይ ደርሰው ምህላውን በልዩ
ልዩ ጸሎታት አጠናክረው በአቡነ ዘበሰማያት ያሳርጋሉ። በዚያም ትምህርተ ወንጌል
ተሰጥቶ በታላቅ ክብር ወደ ቤተክርስቲያን ይጓዛል። ቀሪውን ዑደት በቤተ ክርስቲያኒቱ
ዙሪያ ከፈጸሙ በኋላም ታቦቱ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል:: ይህም ከላይ እንደገለጽነው
በአክሱም ጽዮን ከዓመት ዓመት የማይታጎል (የማይቋረጥ) ሥርዓተ ዑደት ከጥንት ጀምሮ
የነበርና ዛሬም በመፈጸም ላይ ያለ ክርስቲያናዊ ዕሴትና ሥርዓተ አምልኮ ነው። አንዳንድ
ገዳማትና አድባራትም ይህን ትውፊት ይዘው ታቦት አውጥተው ዑደት ባያደርጉም በየወሩ
ለ፯ ቀናት ምህላ ያደርጋሉ።

የተከበሩ አንባቢ ሆይ:‐


❖ ከላይ ከተጠቀሰው ሥርዓተ ዑደት አኳያ ከአክሱም ጽዮን ማኀበረ ካህናትና ማኀበሩ
ምእመናን የምንማረው ዐቢይ ቁም ነገር ምንድነው ብለው ያስባሉ?

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል ባንድ ወቅት አክሱማውያን “እኛ የዓለም
ቅርስ ጠባቂዎች ነን።” ያሉትን መነሻ ማድረግ ይኖርብናል። አዎ በእውነቱ ከሆነ
አክሱማውያን ዓለም በመላው ዓይኑን አቅንቶ ጆሮውን ከፍቶና ልቡን አጓጉቶ
የሚጠብቃትን ታቦተ ጽዮንን ከሙሉ ታሪኳና ሥርዓቷ ጋር እየጠበቁ ያሉ ቀናዕያን
ክርስቲያኖች ናቸው። በሌላ አነጋገር እነሱ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ መንፈሳዊ
ቅርሶች ባለቤቶች ብቻ ሳይሆኑ ተገቢውን ክብር በመስጠት ከእግዚአብሔር ጋር
የኖሩና የሚኖሩም ናቸው። እነሱ የቤተ ክርስቲያንና የእግዚአብሔር አደራ
ተቀባዮች፣ ተንከባካቢዎች፣ ጠባቂዎችና ለተተኪው ትውልድ አስተላላፊዎች ናቸው።
ከነዚህ ከተቀበሏቸውና ከጠበቋቸው ቅርሶችና ዕሴቶች መካከልም አንዱ ከላይ
የገለጽነው ሥርዓተ ዑደት ነው።

ከነዚህ ወገኖቻችን ታማኝነትን፣ ጽንዓትን፣ ትጋትን፣ ቀናዒነትን፣ ሥርዓት


ጠባቂነትንና አክባሪነትን እንማራለን።

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ በቅድሚያ እርስዎን ልጠይቅዎ፡-

❖ እስከዛሬ ከተገኙባቸው የንግሥ በዓላት ምን የተጠቀሙ ይመስልዎታል? ማኅበራዊ


ጠቀሜታቸውስ ምንድነው? ያሰተዋሏቸው ችግሮች (ተግዳሮቶች) ምንድናቸው?
መልሱን ከሰጡ በኋላ ንባባን ይቀጥሉ፡፡

የኢትዮጲያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታቦት አውጥታ ሥርዓተ ዑደት ፈጽማ


የምታከብራቸው የንግሥ በዓላት ለሀገርና ለወገን /ለሕዝብ/ ሳይቀር በርካታ ጠቀሜታ
አላቸው፡፡እነዚህን ጠቀሜታዎች ባጭሩ እንደሚከተለው በሁለት ከፍለን
እንመለከታቸዋለን።

ሀ.መንፈሳዊ ጠቀሜታዎች
139
• ከበዓሉ ባለቤት (ከቅዱሱ፣ ከቅድስቷ) የቃል ኪዳን በረከትና ረድኤት ለማግኘት፤
/መዘ ፻፲፩፥፮። ምሳ፲፥፯፡፡/

• ከቅዱሳኑ ተጋድሎ ጽናትን፣ ትዕግሥትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ተስፋንና፣


የመሳሰሉትን ለመማር፤ (ዕብ፲፪፥፫፤ ፲፫፥፯፡፡)

• ከቤተ ክርስቲያን መምህራን ቃለ እግዚአብሔርን ለመማር፤ ( ሮሜ፲፥፲፬-፲፰፡፡)

• አምልኮተ እግዚአብሔርን በሥርዓት ለመፈጸምና እምነትን ለመግለጥ፤


(ማቴ፳፪፥፴፰‐፵፡፡)

• የቤ/ክርስቲያንን አንዲትነትና የሥርዓቷን ወጥነት ለማሳየት፤ /ኤፌ ፬፥፫‐፮፡፡/

• ለሰው ልጆች አስፈላጊ የሆነው ዕረፍት (ሥጋዊና ሕሊናዊ ዕረፍት) ስለሚገኝበት፤


ይህንና ይህን የመሳሰሉ መንፈሳዊ ጠቀሜታዎች አላቸው። /ዘፀ፳፥፰‐፲፪፡፡/

ለ.ማኀበራዊ ጠቀሜታዎች
• የሀገርና የዜጎችን መልካም ገጽታ ለመጠበቅና ለማዳበር፤

• ዘመድ ከዘመድ ለመጠያየቅና ለመረዳዳት፤

• ብሔራዊ የገቢ ምንጭን ለማሳደግ /የውጪ ምንዛሬ/፤

• በምእመናን መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይኖር ደስታን በእኩልነት


ለማጣጣም፤

• ባህልንና ማንነትን ጠብቆ ለመኖር፤

• ማኅበረሰባዊ መቻቻልን፣መከባበርንና ፍቅርን ለማዳበርና ለመሳሰሉት ከፍተኛ


ጠቀሜታ ያበረክታሉ።

የበዓል አከባበር ተግዳሮቶች


እየታዩ ካሉና ሊስተካከሉ ከሚገባቸው የበዓል አከባበር ተግዳሮቶች መካከል የሚከተሉትን
ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

• በዓሉ በሚከበርበት ቤተክርስቲያን አካባቢ ማዕከላዊነት የጎደለው የስብከት


አገልግሎት መታየቱ፤

• የበዓሉ አካባቢ በልዩ ልዩ ሸቀጦች መሞላቱና ገበያ መሆኑ፤

• ከቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሮች በቤተክርስቲያን


አባቶች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ማግኘታቸው፤

140
• በብዙ ወጪና ድካም ከበዓሉ ቦታ ደርሰው ቅዳሴ ሳያስቀድሱና ሥጋ ወደሙ
ሳይቀበሉ የሚመለሱ “እግረኛ ምእመናን” በብዛት መታየታቸው፤

• በአንድ ዓይነት በዓል የቤተክርስቲያንን አንድነት ሊገልጽ የማይችል ልዩ ልዩ


/የተዘበራረቀ/ የበዓል አከባበር በልዩ ልዩ አጥቢያዎች መታየት መጀመሩ፤

• በዓላትንና አከባበራቸውን ከገንዘብ ማግኛ መንገድነታቸው አንጻር ብቻ የሚቃኙ፣


የሚሠሩና መንፈሳዊ ዕሴቶቻቸውን ፈጽመው የሚረሱ አካሄዶች እያቆጠቆጡ
መምጣታቸውንና እነዚህን የመሳሰሉትን ለይቶ ማጥናት ይቻላል። እነዚህ አደገኛ
አዝማሚያዎች ቤተ ክርሰቲያኒቱን ወዴት ሊመሯት እንደሚችሉ ከወዲሁ መገመት
አዳጋች አይሆንም:: ስለዚህም የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ወገናችን ሆይ ተግዳሮቶቹን
ቢቻል ለማጥፋት ባይቻልም ለመቀነስ የበኩልዎን ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅብዎ
ማስታወስ እንሻለን።

ማጠቃለያ
ከቀረበው ማብራሪያ ቅዱሳት በዓላትን በተመለከተ በቂ ማብራሪያ እንዳገኙ እምነታችን
ነው፡፡ አንዳንዶች እንደሚመስላቸው የድህነት መንስኤ ሳይሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች
ያሉት መሆኑን ለማሳየት ተሞክ…ል፡፡ ከምንም በላይ ሰው ሠራሽ ሳይሆኑ እግዚአብሔር
ፈቅዶ የሠራልን ለመሆናቸው በሰፊው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ያላቸው የማይዳሰሱ
መንፈሳዊ ቅርሶች ናቸው፡፡ በቅዱሳት በዓላት ስንፍናቸውን ለመሸፈን በዓል አክባሪ
መስለው ሥራ ፈተው የሚውሉ አንዳንድ ግለሰቦች ቢኖሩ (ካሉ) የግላቸው የግንዛቤ ችግር
ከመሆን አልፎ ቤተ ክርስቲያንን አያስጠይቅም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የምትጠየቀው ልጆቿን
ካላስተማረች ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እያስተማረች ምእመናን በራሳቸው መንገድ
እየተÕዙ በዓላትን የስንፍና መሸሸጊያ ካደረጉ ደግሞ ተጠያቂዎቹ እነሱው ስለሆኑ
በፈጣሪያቸው ዘንድም የሚቀጡ ይሆናሉ:: በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት በዓላትን
በአግባቡና በሥርዓቱ የሚያከብሩት ደግሞ ዋጋ የሚያገኙበትና የሚከበሩበት ይሆናል::

የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በአግባቡ የተማሩ ምእመናን ሥጋውያን በሚያቀርቡ


መሠረተ ቢስ ትምህርትና በቤተ ክርስቲያን ጠላቶች በሚያቀርቡት ክስ አይወናበዱም፡፡
ጠያቂዎች ካሉም በተገቢው ሁኔታ በጥበብ በመመለስ ራሳቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን
ይጠብቃሉ፡፡ ከዚህ ጽሑፍ አንባቢም የሚጠበቀው ይኸው ነው:: ከዚህ ጽሑፍና ከዋቢ
መጻሕፍት ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን
ፀረ ቅዱሳት በዓላት በመሆን ከሚንቀሳቀሱ ከሀድያን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ በዚህም መሠረት
የክርስትና ሃይማኖትና የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ በመሆን የክህደቱን ማዕበልና የኑፋቄውን
ጎርፍ ለመከላከል ግንባር ቀደሙን ሚና የሚጫወቱ ይሆናሉ ተብሎ ይታመናል::

ዋቢ መጻሕፍት፦

• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

141
• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ
ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ፤ በዓላት፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፱፤ አዲስ


አበባ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፈዲድስቅልያ፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ


ድርጅት፤ ፳፻፬፤ አ/አ፡፡

• ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ፤ ይትበሃል ዘጎንደር ዘውእቱ ሥርዓተ


ማኅሌት፤ አ/አ፤ ፳፻፬ ዓ.ም::

142
ምዕራፍ ፲፩
ሕንጻ ቤተክርስቲያንና ንዋያተ ቅድሳት
መግቢያ
በዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ስለ ቤተ ክርስቲያን በቂ መረጃ
ማግኘት የሚያስችል ጽሑፍ ማቅረባችን ይታወሳል በዚህኛው ምዕራፍ የምናየው
የዚያኛውን አሳብ በመድገም ሳይሆን ቀጣይ የሆኑ ጉዳዮችን በማንሳት ይሆናል
ከላይ በጠቀስነው ዋና ርእስ ሥር

- የቤተ ክርስቲያን ሥሪት (ገጠር፣ ደብር፣ ገዳም)፤


- ቅዱሳት ሥዕላት፤
- ንዋየ ቅድሳት፤
- ዜማና መዝሙር የዜማ መሣሪያዎች፤
- ዕጣን፤
- ታቦት ጽላትና

መስቀል የተባሉ ንዑሳን አርእስትን ከዝርዝር ማብራሪያዎችቸው ጋር ይዘን ቀርበናል፡፡


በዚህ ምዕራፍ የተብራሩት ነጥቦች ከዕለት ተዕለት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችንና
አምልኮታችን ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን የሃያ አራት ሰዓት
አገልግሎትና የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጻጸም በቀጥታ በዚህ ምዕራፍ በተገለጹት
መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ እነዚህን መማራችንም የቤተ ክርስቲያንን
አገልግሎት እንድንወደውና እንድናከብረው የሚረዳን ብቻ ሳይሆን የድርሻችንን ሱታፌ
እንድናበረክት ያዘጋጀናል:: እንደምታስታውሱት በምዕራፍ ፩ ትምህርታችን፦የቤተ
ክርስቲያን ትርጉም፤ የቤተክርስቲያን አመሠራረትና የቤተክርስቲያን ባሕርያት የሚሉትን
መሠረታዊ ነጥቦች መዳሰሳችን ይታወቃል፡፡ በዚህ ምዕራፍ የምንዳስሰው ከቤተ ክርስቲያን
ጋር የተያያዙ ቀሪ ነጥቦችን በማንሳት ይሆናል።

143
ከተማሪዎች የሚጠበቅ አጠቃላይ ውጤት፦
ተማሪዎች ይህን ትምህርት /ምዕራፍ/ ካጠናቀቁ በኋላ፦

• የሕንጻ ቤተክርስቲያንን አሠራርና የቤተክርስቲያንን ሥሪት ይገነዘባሉ።

• የቤተ መቅደስ ንዋያተ ቅዱሳትን ዓይነት'አገልግሎትና ጥቅም ይረዳሉ።

• የቤተ ክርስቲያንን የዜማ መሣሪያዎችና መዝሙር በመረዳት


አገልግሎታቸውን ይፈትሻሉ።

፲፩.፩፦ የቤተ ክርስቲያን ሥሪት /ገጠር፣ ደብር፣ ገዳም/


ሀ. የሕንጻ ቤተ እግዚአብሔር አጀማመር
እግዚአብሔር አምላካችን በዘመናት ሁሉ በወደደው ቦታና ሁኔታ መመስገን ፈቃዱ
ነው። እስራኤልን ከግብጽ ምድር እንዲያወጣ በመረጠውና ታላቅ ነቢይ በሆነው በሙሴ
በኩል “መቅደስ ትሠራልኛለህ በመካከላቸውም አድራለሁ። በተራራው እንዳሳየሁህ
ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ፥ እንደዕቃውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠራለህ፤ እንዲሁ
ትሠራለህ።” /ዘጸ ፳፭፥፰‐፲፡፡/ የሚል መመሪያ አስተላልፏል። በዚህ መመሪያ መሠረት
ነቢዩ ሙሴ ደብተራ ኦሪትን ለመሥራት እንደቻለ የታወቀ ነው፡፡ በአሠራር ሒደቱም
ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ እግዚአብሔር አምላክ ለሙሴ በተደጋጋሚ “በተራራው ላይ
እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ!” የሚል ኃይለ ቃል ይናገረው ነበር።
/ዘጸ፳፭፥፵፤ ፳፮፥፴፤ ፳፯፥፰።/ ይህም ደብተራ ኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ በደብረ
ሲና ተራራ ላይ ባሳየው መቅደሰ ብርሃን (የብርሃን (ሰማያዊ) መቅደስ ሥርዓትና
አምሳል (ምሳሌ) የተዘጋጀች መሆኗን ያረጋግጥልናል። በዚህ መሠረትነትም መቅደሰ
ሰሎሞን በደብተራ ኦሪት አምሳልና ሥርዓት፣ ቤተክርስቲያንም በመቅደሰ ሰሎሞን
አምሳልና ሥርዓት የተሠሩ (የተዘጋጁ) መሆናቸውን እንረዳለን። ይህም በመንፈሳዊ
ስሌት ሲሰላ ቤተክርስቲያን ራሷ በሰማያዊው (ብርሃናዊው) መቅደስና ሥርዓት አምሳል
የተሠራች፥ በምድር ላይ ያለች አማናዊት የእግዚአብሔር መንግሥት እንደሆነች
አጉልቶ ያሳያል። (ራእይ ፲፩፥፲፱፤፰፥፫‐፭፡፡)

ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርና የክርስቲያኖች የጋራ ቤት ስለሆነች ምእመናን


በዚያ ከፈጣሪያቸውና ከአባታቸው ከእግዚአብሔር ጋር ይገናኛሉ። ቤተ ክርስቲያን
እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል በረድኤቱ፣ በፍቅሩ፣ በቸርነቱና በአካሉ /ሥጋ ወደሙ/
ሊያድርባት የመረጣት ናትና። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ይህንኑ እውነታ
በሚያጎላ መልኩ “የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፣ የጸና ተራራና
የለመለመ ተራራ ነው። የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ? እግዚአብሔር ያድርበት
ዘንድ የወደደው ተራራ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያድርባቸዋልና። የብዙ
ብዙ ሺህ የእግዚአብሔር ሰረገላዎች ደስተኞች ናቸው። እግዚአብሔር በመቅደሱ በሲና
በመካከላቸው ነው።” /መዝ፷፯፥፲፭‐፲፰፡፡/ ብሏል። በተጨማሪም ስለ ሕዝቡ “ወደ
144
መቅደሱ ተራራ ወሰዳቸው፥ ቀኙ ወደ ፈጠረችው ተራራ፤” (መዝ፸፯፥፶፬፡፡) በማለት
ተናግሯል። ደብረ ሲና ሰማያዊው ንጉሥ እግዚአብሔር በሰማያዊው መቅደስና ሥርዓት
ሆኖ ለሙሴ የታየባት፣ ያስተማረባትና ከሕዝቡ ጋር መሆኑን ያረጋገጠባት መቅደሱ
ነበረችና። ቤተክርስቲያንም ከመቅደሰ ሰሎሞንም ሆነ ከደብተራ ኦሪት በእጅጉ
የምትከብርና የምትበልጥ መሆኗን ማወቅና እስራኤል ዘሥጋ ለመቅደሱ ይሰጡ
ከነበረው ክብር (ጥንቃቄ) የበለጠ (የተሻለ) ጥንቃቄ የተሞላው ክብር መስጠት
እንደሚገባ መረዳት ይገባል። /፪ቆሮ፫፥፯‐፲፪፡፡ ዕብ ፰፥፩‐ፍጻሜው።/

ለ. የቤተ ክርስቲያን ሥራ ፈቃድና ዐቅድ (ፕላን፣ ዲዛይን)


እያንዳንዳንዱ መንፈሳዊ ሥራ በእግዚአብሔርና ለዚያ ሥራ የበላይ አድርጎ በሾማቸው
ባለሥልጣናት ፈቃድና ትእዛዝ ይሠራል። ቤተ ክርስቲያንም በዚሁ መሠረት
እግዚአብሔር ይመግቧት ይመሯትና ያስተዳድሯት ዘንድ በሾማቸው ጳጳሳት ፈቃድና
ቡራኬ ትታነጻለች። የክፍሉ (የሀገረ ስብከቱ) ጳጳስ ሳያውቀውና ሳይፈቅድ የሚሠራ
ሕንጻ ሁሉ ምንም እንኳን አሠራሩና ቅርጹ ያማረ ቢሆን “ቤተክርስቲያን” የሚለውን
ስያሜ ማግኘት አይችልም። /ፍት.መን.፩፥፪፡፡/ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቤት
እንደመሆኗ መጠን በግለሰቦች ፈቃድ፣ ፍላጎትና ስምምነት ልትተከልና አገልግሎት
ልትሰጥ አትችልም:: ከላይ የገለጽነው የመጽሐፍ ክፍል “ያለ ኤጲስ ቆጶሱ ትእዛዝ ቤተ
ክርስቲያንን አይሥሩ። አንድ ሰው ስንኳ ደፍሮ ከዚህ ውጪ ቢሠራ በውስጧ እስከ
ዘለዓለም ቁርባን አይቀበል፤ ቄሱም ይህን ተላልፎ ቁርባንን ቢያቀርብ ይሻር፤” በማለት
ያስጠነቀቀው ለዚህ ነው።

የተከበሩ አንባቢ ሆይ፦

❖ ሦስቱ የቤ/ክ የውስጥ ክፍሎች ምንምን ናቸው? አገልግሎታቸውስ ምንድነው?

የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ሥራ ፈቃድ ከሚመለከተው መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን አባት


/የሀረገ ስብከቱ ጳጳስ/ ከተገኘና ቦታው ከተባረከ በኋላ ሕንጻ ቤ/ክርስቲያን ለመሥራት
ተገቢውን ጥናት በማድረግ ዐቅዱ /ፕላኑ-ዲዛይኑ/ ይዘጋጃል::

በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረትም ሦስት ዋና ዋና


የቤተ ክርስቲያን አሠራር ዓይነቶችን /ቅርጾችን ወይም ዐቅዶችን/ ማየት ይቻላል።
እነዚህም፦

፩. ክብ ቅርጽ፦ ይህ የአሠራር ዓይነት በቀደመው ጊዜ ማለትም በአባቶቻችንና


በእናቶቻችን ዘመን በብዛት፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በተለይ በገጠራማው የሀገራችን
ክፍል በከፊል የሚዘወተረው ነው፡፡ የዚህ አሠራር ሌላኛው ስሙ “ቤተ ንጉሥ”
ቅርጽ ይባላል:: ይህም አንዳንድ ነገሥታት ቤተክርስቲያንን በራሳቸው
ቤተመንግሥት አምሳል ስለሠሯት ከዚያ የተወሰደ ስያሜ ነው:: ይህች

145
ቤተክርስቲያን ዙሪያዋ ክብ ሆኖ (ሙሉ ክብ ወይም ማዕዘናማ ክብ) ባለ አንድ
ጉልላት ናት። በፊልጵስዩስ ከተማ ሰኔ ሃያ ቀን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ
ተአምር በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም የተመሠረተችው
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ክብ ቅርጽ እንደነበራት የቤተክርስቲያን ታሪክ
ያስረዳል። ይህች ቤተ ክርስቲያን በተሠራች ማግስት ሰኔ ሃያ አንድ ቀን በጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረች መሆኗም ይታወቃል:: በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ
መሠረት የቤተክርስቲያን ክብነት ፍጹምነቷን የሚያመለክት ነው። ይህ ማለትም
የእምነቷን፣ የአስተምህሮዋን፣ የሕጓን፣ የሥርዓቷንና የአገልግሎቷን ፍጹምነትና
ልጆቿን ለፍጹምነት ማዕረግ የምታበቃ መሆኗን የሚያመለክት ነው። ይህችኛዋ ቤተ
ክርስቲያን ሦስት ክፍሎችና ሦስት በሮች ያላት ስትሆን ሦስቱን የመላእክት ዓለም
(ኢዮር፤ ራማ፤ ኤረር)፣ ሦስቱን መዐርጋተ ክህነት (ጳጳስ፤ ቄስ፤ ዲያቆን)፣ ሦስቱን
ጾታ ምእመናን (ካህን፤ ወንድ፤ ሴት) እና ሦስቱን የገነት በሮች የሚያመለክቱ
አማንያን (እውነተኛ) ምሳሌዎች ናቸው።

ሦስቱ ክፍሎችም ውስጠኛው ክፍል መቅደስ (ቅድስተ ቅዱሳን) መንበረ ታቦትና


ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት የሚገኙበት፣ ልኡካኑ የሚያገለግሉበትና ምሥጢረ ቁርባን
የሚፈጸምበት ክፍል ነው፡፡ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሱ ጀምሮ ሥዩማን ካህናት ሁሉ
ከቅዱሱ ምሥጢር የሚካፈሉበት ነው፡፡ ሦስት በሮች ያሉት ሲሆን ለእያንዳንዱ በር
መንጦላዕት መጋረጃ ይደረግለታል፡፡ ሁለተኛው ክፍል ቅድስት ይባላል፡፡ የቤተ
ክርስቲያኑ ማዕከላዊ ሥፍራ ሲሆን ቆራቢያን ወንዶችና ሴቶች አስቀድሰው ሥጋ
ወደሙን ይቀበሉበታል፡፡ ከሥርዓተ ጥምቀትና ንስሐ በስተቀር ሌሎች ምሥጢራት
የሚፈጸሙበት ነው፡፡ ይህ ክፍል አራት በሮች በአራቱም አቅጣጫዎች አሉት፡፡ ቅኔ
ማኅሌት እንደ ስሙ ሥርዓተ ማኅሌት የሚቀርብበት ትልቁ ሰፊው ክፍል ነው፡፡
አባቶች ካህናት ሰዓታት፣ ጸሎተ ኪዳን የሚያደርሱበትና “ፃዑ ንዑሰ ክርስቲያን”
እስኪባሉ ድረስ ንዑሰ ክርስቲያን የሆኑ ሥርዓተ ቅዳሴውን የሚከታተሉበት ባለ
ሦስት በሮች ክፍል ነው::

፪. ሰቀላማ ወይም ሞላላ ቅርጽ፦ ይህኛው ቤተክርስቲያን አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው፣
ሞላላ የሆነና ከፍ ብሎ የሚታነፅ ነው። ይህ ዓይነቱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ
በተለይ በከተሞች በከፍተኛ ደረጃ በመስፋፋት ላይ ያለ ሲሆን አሠራሩም የተወሰደው
ንጉሥ ሰሎሞን ካሠራው ቤተ መቅደስ ነው። ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይህን ዓይነቱን
የቤተ መቅደስ አሠራር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ
የፈጸመውን የድኅነት ሥራ የሚያዘክር ነው ይላሉ። አሠራሩን ብዙ ጊዜ መሠረቱን
በመስቀል ቅርጽ አውጥተው ግድግዳውንም በዚያው ላይ በመገንባት መስቀልኛ
ቤተክርስቲያን የሚያደርጉት ለዚህ ነው። ይህ ዓይነቱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ከ፩ በላይ
ጉልላትና ከሦስት በላይ በሮች ይኖሩታል። ውስጣዊ ክፍሎቹ የሚከፋፈሉት ደግሞ
በመጋረጃ ይሆናል።

146
፫. ዋሻ ቅርጽ፦ ከዓላውያን ነገሥታት ስቃይና መከራ ለማምለጥ በየዘመኑ የተነሡ
ክርስቲያኖች በየዋሻውና በየፍርኩታው ይሸሸጉ ነበር፡፡ በዚያን ዘመን አምልኮአቸው
እንዳይቋረጥ በየዋሻው ይማማሩና መሥዋት ይሠው ነበር:: በዚህ ሁኔታ የተጀመረው
የዋሻ ቤተክርስቲያን ምንም ጉልላት የለውም:: እንደ ሰቀላማው የቤተክርስቲያን ቅርፅ
ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች የሚለዩት በመጋረጃ ነው፡፡ አንዳንድ ተፈጥሮአዊ
የዋሻ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም በሀገራችን በብዛት ተመዝግበው የሚገኙት በእነ
ቅዱስ ላሊበላ የተሠሩ ሰው ሠራሽ (ፍልፍል) የዋሻ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

• ውድ አንባቢእርስዎ የኖሩበት (የሚኖሩበት) አካባቢ (ወረዳ) ውስጥ ያሉትን


አብያተ ክርስቲያናት በዝርዝር በመጻፍ እያንዳንዱ በየትኛው ዓይነት ቅርጽ
እንደተሠራ ይግለጹ፡፡

ሐ. የቤተክርስቲያን ሥሪት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለአምልኮተ እግዚአብሔር
የምትገለገልባቸው አብያተ ክርስቲያናት ሥሪት በሦስት ምድብ /ክፍል/ የታወቁ
ናቸው። እነርሱም፦

፩. ገዳም
ገዳም የታላቁን ነቢይ የኤልያስንና (፩ነገ.፲፯፥፩‐፰፡፡) የመጥምቁ የቅዱስ ዮሐንስን
(ማቴ፫፥፬፡፡) አኗኗርና ሕይወት አርአያ አድርገው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፍለጋ
(ማቴ፬፥፩‐፲፪፡፡) የተከተሉ መናንያን መነኮሳት የሚጋደሉበት የተቀደሰ ቦታ ነው።
ትምህርተ ክርስቶስን መሠረት አድርገው (ማቴ፲፥፴፯‐፵፡፡) እንደ ሐዋርያት
(ማቴ፲፱፥፳፯‐ፍጻሜው፡፡) ሁሉን ትተው የተከተሉት እነዚህ መናንያን መነኮሳት በጾም፣
በጸሎት፣ በስግደትና በልዩ ልዩ ተጋድሎ ጸንተውና ከዓለም ርቀው ይኖሩበታል። በገዳም
የሚኖሩት መነኮሳትና መነኮሳይያት እንዲሁም በአመክሮ ላይ ያሉ ጥቁር ራሶች ብቻ
ናቸው:: መናንያን ከፈተና ይጠበቁ ዘንድ የወንዶችና የሴቶች ገዳም ብዙውን ጊዜ
የተለያየ ነው:: አንዳንድ ገዳማት ብቻ ሁለቱንም ጾታዎች በአንድነት የያዙ ሆነው
ይገኛሉ::

በገዳም ተወስነው የሚኖሩ መነኮሳት ገዳሙ የሚያዛቸውን ከመፈጸም ውጪ የኔ


የሚሉት ንብረት የሌላቸውና በራሳቸውም እንኳን ሊያዝዙ ከቶ አይችሉም። የምናኔ
መመሪያቸውም “ነፍሴን ለእግዚአብሔር፤ ሥጋዬን ለማኅበር አስገዛለሁ (ሰጥቻለሁ)፤”
የሚል ነው፡፡ የገዳሙ መምህር ወይም አበምኔት ወይም አስተዳዳሪ የሚሾመው በዕድሜ፣
በመልካም ጠባይ፣ በገድል፣ በትሩፋትና በመሳሰሉት የተሻለው አባት ከመነኮሳቱ
መካከል ተመርጦ ነው:: በአንዳንድ ጥንታውያን ገዳማት የገዳሙ መምህር “የአጎዛ
መምህር” (ዕብ፲፩፥፴፯) በመባል ይጠራል።በሴቶች ገዳም የምትሾመው የመነኮሳይያቱ
የበላይ ተጠሪ ደግሞ “እመ ምኔት” ትባላለች ።

147
የአበምኔቱ ረዳቶች አፈመምህር፣ መጋቢ፣ እጓል መጋቢ፣ ሊቀ ረድእ፣ ሊቀ ዲያቆን
…ወዘተ በመባል ይጠራሉ። ገዳማውያን መነኮሳት/ይያት/ በማኅበር እየሠሩ፣ እየጸለዩ፣
እየተመገቡ፣ አንድ ዓይነት ልብስ እየለበሱ ወዘተ በመኖር የሚጋደሉ ናቸው። ቤተ
ክርስቲያን ልዩ ለሆነ አገልግሎት ካልጠራቻቸው ወይም ገዳሙ ለተለየ ተልዕኮ፣
ለተወሰነ ጊዜ ካላካቸው በስተቀር መነኮሳት በአታቸውን ጥለው ከገዳማቸው እንዲወጡ
አይፈቀድላቸውም። እነርሱም ይህ የምናኔ ዓላማ ገብቷቸውና ፈቅደው ስለሚመነኩሱ
በአታቸውን ጥለው ለመውጣት አይፈልጉም። በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን አባ ጳኩሚስ
ባዘጋጁት ሥርዓተ ምንኩስና /ገዳም/ መሠረት በመጋደል የሚኖሩ መናንያነ ዓለም
ናቸውና።

፪. ደብር፦
ደብር ከፍ ያለ ቦታ፥ ተራራ፥ ኮረብታ ማለት ነው። ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር ብዙ
ጊዜ በተራራ ላይ ራሱንና ምሥጢራቱን ለወደዳቸውና ለመረጣቸው ሰዎች ይገልጥ
ነበር። (ዘጸ፲፱፥፩‐ፍጻሜው፤ ፳፬፥፩-ፍጻሜው። ማቴ፲፯፥፩‐፲፤ ፳፬፥፫፡፡) ተራራ
በቅዱሳን አበውና እማት፣ በጻድቃን በሰማዕታትም ሁሉ ይመሰላል። የእመቤታችንን
የዘር ግንድ (ሐረግ) በተመለከተ ነቢዩ ዳዊት ሲናገር “መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች
ናቸው፡፡” (መዝ፹፮፥፩፡፡) በማለት የተናገረው ለዚህ በቂ ማሳያ ነው። ጌታችንም ከላይ
እንዳየነው በተራራ ላይ ይጸልይ፤ ክብሩን ይገልጥና ምሥጢራትን ለደቀ መዛሙርቱ
ይነግር ነበር። ይህንና ይህን ከመሳሰሉት መነሻዎች አኳያ ቤተ ክርስቲያን አንደኛውን
ሥሪት ደብር ብላ ጠርታዋለች።

ደብር ከሌሎቹ አገልግሎቶች በተጨማሪ ከዓመት እስከ ዓመት ስብሐተ


እግዚአብሔር ማለትም ስብሐተ ነግህ፣ መዝሙርና ቅዳሴ የማይቋረጥበት ነው።
በደብርም በልዩ ምክንያት ከተፈቀደላቸው መነኮሳት ጀምሮ ሕጋውያኑ ካህናት
ያገለግሉበታል። ደብር በዓለም ውስጥ በተለይም በከተማ አካባቢ የሚተከል እንደመሆኑ
ምእመናን ዘወትር ያገለግሉበታል፤ ይገለገሉበታል። የደብር አስተዳዳሪ አለቃ
ይባላል። የሚሾመውም እንደ አድባራቱ ሥርዓት ከመነኮሳት ወይም ከሕጋዊያን
ቀሳውስት ወይም ከመምህራን ነው:: የደብር አስተዳዳሪ የሆነው አባት እንደ ደብሩ
ስያሜ ንቡረ እድ፣ ሊቀ ሥልጣናት፣ ሊቀ ሊቃውንት፣ መልአከ ገነት፣ መልአከ
ፀሐይ፣…. ወዘተ እየተባለ ይጠራል። አጠቃላይ አገልግሎቱ በሰበካ ጉባኤ ይመራል፡፡

፫. ገጠር
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ዙሪያና በፍልስጥኤም ባሉ ገጠሮችና
መንደሮችም እየተዘዋወረ ያስተምር ነበር። ከነዚህም መንደሮች የተውጣጣ ፭ ገበያ
ያህል ሕዝብ ይከተለው ነበር። (ማቴ፲፬፥፲፫‐፳፪፡፡) ሐዋርያትንና ሰባ ሁለቱን
አርድዕትም የመንግሥትን ወንጌል ያስተምሩና ድውያኑን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ በምድረ
148
እስራኤል ሁሉ ልኳቸዋል። (ማቴ ፲፥፭‐፯፡፡) (ሉቃ፲፥፩፡፡) ይህንን መሠረት በማድረግ
ወንጌልን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ለማድረስና ምሥጢራትንም በመፈጸም አማንያንን
የሥላሴ ልጆች ለማድረግ ይቻል ዘንድ በየገጠሩ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ታንጿል፤
ይታነፃልም። እንዲህ ያለችው ቤተ ክርስቲያን “ገጠር” የሚል መጠሪያ ተሰጥቷታል።

የገጠር ቤተክርስቲያን መገለጫ የቦታው ገጠርነት (ከከተማ ወጣ ማለቱ) ብቻ ሳይሆን


ከላይ በደብር የጠቀስናቸው አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ ዘወትር የማይሰጡባት መሆኑ
ነው፡፡ እነዚህም በዕለተ ሰንበት፣ በወርኃዊና ዓመታዊ በዓላት ብቻ የሚቀደስባቸው
ናቸው። የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እንደ ችሎታውና ዕውቀቱ አለቃ፣ መሪጌታ፣
ወይም ገበዝ ይባላል። እንደ ደብር ይህም በሰበካ ጉባኤ ይመራል፡፡

፲፩፥፪. ቅዱሳት ሥዕላት


❖ ቅዱሳት ሥዕላት ምንድናቸው? ማንም ሙያ ያለው ሰው ሊሥላቸው ይችላልን?

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ቅዱሳት ሥዕላት


መሳክወ ገነት /የገነት መስኮቶች/ በመባል ይታወቃል። እነዚህም የቤተ ክርስቲያንን
ሰማያዊነትና መንፈሳዊ ውበት በትክክል የሚያንጸባርቁ ናቸው። ቅዱሳት ሥዕላት
በማንኛውም ባለሙያ በዘፈቀደ የሚዘጋጁ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ሳይሆኑ ቀኖና
ቤተክርስቲያንን ተከትለው የሚሣሉ የከበሩ ንዋያተ ቅዱሳት ናቸው። ቅዱሳት ሥዕላት
እውነተኛ እምነት፣ የተስተካከለ ክርስቲያናዊ ሕይወት፣ ሙያ፣ ተሰጥኦና ፈቃደኝነት
ባላቸው ሠዓሊያን ተሥለው ለምእመናን አምልኮተ እግዚአብሔር መግለጫነት
የሚያገለግሉ የቤተክርስቲያን ሀብቶች ናቸው። በእግዚአብሔር ትእዛዝና ፈቃድ ተሥለው
የእግዚአብሔር ስም በሚጠራበትና ክብሩም በሚገለጥበት ቦታ ይቀመጣሉ (ይሰቀላሉ)፡፡
እነዚህም በአብያተ ክርስቲያናት በሮች፣ ግድግዳና ጣሪያ ላይ፣ በሸራ፣ በብራና፣ በወረቀት፣
በጨርቅና በመሳሰሉት ሰሌዳዎች ላይ በቀለም የሚሳሉና ከእይታ በስተቀር በመዳሰስ
ሊታወቁ የማይችሉ ናቸው።

ቅዱሳት ሥዕላት ከቅርጽና ከምስል ፈጽመው የተለዩ ሲሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቅርጽና ምስል
(በዳሰሳ የሰው ልጅ ሊረዳቸው የሚችል) ተቀባይነት የላቸውም። ተቀባይነት ያላቸው
ቅዱሳት ሥዕላት ሲሆኑ ምእመናን በሥርዓተ አምልኮ ከሥዕሉ ባለቤት በረከትንና
ተራዳኢነትን እንዲያገኙ ይረዳሉ። የልዑል እግዚአብሔርን፣ የእመቤታችን፣ የቅድስት
ድንግል ማርያምን፣ የቅዱሳን መላዕክትን፣ የሐዋርያትን፣ የነቢያትን፣ የጻድቃንንና
የሰማዕታትን ማንነት፣ ሕይወትና የቃል ኪዳን በረከት የሚገልጹና የሚያስተላልፉ ናቸው።
ቅዱሳት ሥዕላት በፈቃደ እግዚአብሔር መንፈሳዊና ሰማያዊ ውክልና ስላላቸው ምንም
መንፈሳዊ መልእክት ከሌላቸው ከሥጋዊው ዓለም ቅርጾች፣ ምስሎችና ሥዕላት ፈጽመው

149
የተለዩ ናቸው። ምክንያቱም የቆሙለት ውክልና /የሚወክሉት አካል/ ቅዱስ በመሆኑና ስለ
እግዚአብሔር የሚመሰክሩ የረቀቁ መምህራን በመሆናቸው ነው።

በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት የቅዱሳት ሥዕላትን አመጣጥ ስናጠና ፍጹም


መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሆኖ እናገኘዋለን። ከእነዚህም መካከል የተወሰኑትን ለአብነት ያህል
እንደሚከተለው እናያቸዋለን።“ ኦርቶዶክሳውያን የሥነ መለኮት ሊቃውንት እንደሚያትቱት
የሰው ልጅ ራሱ የእግዚአብሔር መልክ የተሣለበት በምድር ላይ ያለ ሕያው
የእግዚአብሔር ሥዕል ነው።” በመሆኑም የሰው ልጅ የእግዚአብሔር መልክ የተቀረጸበት፣
መለኮታዊ ውበት የተገለጠበትና አምላካዊ ክብር የተንጸባረቀበት ክቡርና ሕያው ፍጡር
ነው። (ዘፍ፩፥፳፮፡፡ማቴ፳፭፥፵፮፡፡)

ከዚህ በማስከተል ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ የሰፈሩ ጥቂት


ማስረጃዎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

• “ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም


ግምጃ ዐሥር መጋረጃዎችን ሥራ፥ ኪሩቤልም በእርሱ ላይ ይሁኑ፥
እንደሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።” (ዘጸ፳፮፥፩‐፴፩፤ ፴፮፥፰፡፡)

• “ሙሴም ወደ ምስክሩ ድንኳን እርሱን ለማነጋገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት


ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው በላይ ከኪሩቤልም መካከል የእግዚአብሔርን
ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ይናገር ነበር።” (ዘኁ፯፥፹፱፡፡
ዘጸ፳፭፥፲፰‐፳፪::)

• “ሁለቱንም ሣንቃዎች ከወይራ እንጨት ሠራ፤ የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ፥


የፈነዳም አበባ ሥዕል ቀረጸባቸው፤ በወርቅም ለበጠባቸው፣ ኪሩቤልንና
የዘንባባውን ዛፍ በወርቅ ለበጠ።” (፩ነገ፮፥፴፪፤ ፯፥፴፮፡፡ ፪ዜና፫፥፰‐፲፬፡፡)

• “ከሰማያዊውም፥ ከሐምራዊውም፥ ከቀዩም ሐር። ከጥሩም በፍታ መጋረጃውን


ሠራ፤ ኪሩቤልንም ጠለፈበት።” (፪ዜና፫፥፲፬፡፡)

ከዚህ በላይ የጠቀስናቸው ማስረጃዎች የሚያሳዩት በብሉይ ኪዳን ዘመን በደብተራ ኦሪትም
ሆነ በመቅደሰ ሰሎሞን ሥዕለ ኪሩብ በየመጋረጃው ላይ ሳይቀር ይጠለፍ ይቀረጽ እንደነበር
ነው። በዚህ መልክ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ከፍተኛ ጠቀሜታ እየሰጡ ከዘመናችን
ደርሰዋል። በሐዲስ ኪዳንም ቅዱሳት ሥዕላት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በስፋትና
በብዛት ለአምልኮተ እግዚአብሔር መግለጫ እንዲሆኑ ተደርገዋል። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ
እንደተገለጸው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለሮሙ ንጉሥ ለጢባርዮስ ቄሳር የጌታችንን ሥነ-
ስቅለት ሥሎ እንደሰጠውና እንደተጽናናበት ታውቋል። ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ ደግሞ
“ምስለ ፍቁር ወልዳ” በመባል የሚታወቀውን የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን
ሥዕለ አድኅኖ በመሣል ለሐዲስ ኪዳን የቅዱሳት ሥዕላት አገልግሎት ፈር ቀዳጆች
ለመሆን እንደቻሉ ታውቋል።

150
ከሁሉ የሚቀድመውና ለቅዱሳት ሥዕላት አሣሳል የመድኃኔዓለም ፈቃድ ተደርጎ ሊወሰድ
የሚችለው ክርስቶስ በመከራው ሰዓት በድንቅ ተአምር በጨርቅ ላይ ያተመው ሥዕል ነው።
ይህም ያገለግሉትና ይከተሉት ከነበሩት ደናግል (ቅዱሳት አንስት) አንዷ ቤሮኒካ ከራሱ
የሚወርደው ደሙ ፊቱን ቢሸፍነው እንዲጠርግበት በሰጠችው የሐር ጨርቅ (መሐረም) ላይ
ፊቱን በጠረገበት ጊዜ የታተመው ሙሉ የፊቱን ገጽታ የሚያሳየው ሥዕል ነው። “ቅዱሱ
ፊት” በመባል የሚታወቀው ይህ ሥዕል የሰው እጅ የሠራው አይደለም። በሌላ ታሪክም
የኤዴሳው ንጉሥ አብጋር ታሞ ሳለ ጌታችን መጥቶ እንዲፈውሰው መልእክተኛ ቢልክ
ጌታችን በሐር ጨርቅ የፊቱን መልክ አትሞ (በተአምር ሥሎ) የላከለት እንደሆነ
ሊቃውንት ያስተምራሉ፡፡ ፲፪ ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረችው ሴት (ማር.፭፥፳፭‐፴፭፡፡)
ከተፈወሰች በኋላ ለጌታ ውለታ መታሰቢያ እንዲሆንላት በግቢዋ ያቆመችው ከነሐስ
የተሠራ ሥዕልም ሌላው ማረጋገጫ እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊያን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥዕል (አሣሳል)


ልዩ ባሕርያት
ቤተ ክርስቲያናችን እንደሌላው አገልግሎት ሁሉ በሥዕል ረገድም የራሷ የሆኑ የአሣሳል
ስልትና ቅዱሳት ሥዕላት አሏት። የእነዚህንም መገለጫ ባሕርያት አጠር አጠር አድርገን
በሚከተለው ሁኔታ ለማብራራት እንሞክራለን።

የተከበሩ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ሆይ፡-

❖ ቅዱሳት ሥዕላትን ሲገዙ ሠርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቁ መሆናቸውን በምን


ያረጋግጣሉ?

ሀ.ትምህርተ ሃይማኖትን መጠበቅ

ቅዱሳት ሥዕላት በራሳቸው አስተማሪዎች ስለሆኑ የሚያስተላልፉት መልእክት በመጽሐፍ


ቅዱስ ላይ የተመሠረተውን የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ (ትምህርተ ሃይማኖት) የጠበቁ
ናቸው::ከዚህ መስመር ከወጡ ቅድስናቸውንና የቤተ ክርስቲያን ሀብት መሆናቸውን
ያጣሉና ።

ለ.መልክእ

የቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት የባለ ሥዕሉን እውነተኛ መልክእ የሚያሳዩ ሳይሆኑ


ወክለው (በውክልና) የሚቀርቡ በእምነትም የምንቀበላቸው ናቸው። ቤተክርስቲያን
የምታከብራቸው በነፍሳቸው ባገኙት ክብር እንጂ በአካላዊ ቁመናቸው፣ ግዝፈታቸው፣
መልክእ እና ሥጋዊ በሆኑ መገለጫዎቻቸው አይደለም። በተጨማሪም፦

• በሥዕሉ ባለቤት አናት /ራስ/ ዙሪያ አክሊለ ብርሃን ይደረጋል። ይህም ሰማያዊ
ክብራቸውን ያሳያል፡፡ (ሠራዊተ መላእክት በብዛት ሲሣሉ ላይደረግ ይችላል።)
151
• ዐይናቸው የጎላና ወደ አንድ አቅጣጫ የሚመለከት ይሆናል። ይህም የጎላች፣
የተረዳች ርትዕት (ቀጥተኛ) የክርስትና ሃይማኖትን ያለ ጥርጥር መቀበላቸውንና
ማቀበላቸውን ያመለክታል።

• መናፍቃንና ከሀድያን ሲሣሉ መጠናቸው ያንስና በግማሽ ፊትና በአንድ ዐይን


ይገለጣሉ፡፡ ይህም በአንጻሩ እምነተ ጎዶሎ መሆናቸውን ያሳያል።

ሐ.ቀለም

በቤተ ክርስቲያናችን የሥዕል አሣሣል ጥበብ መሠረት ቅዱሳት ሥዕላትን ለመሣል ጥቅም
ላይ የሚውሉ /የሚታዩ/ ቀለማት በአብዛኛው የሚከተሉት ናቸው::

፩.ሰማያዊ፦ ሰማያዊ ሕይወትንና በፈቃደ ነፍስ መመራትን ያመለክታል።

፪.ቀይ፦ የሰማዕትነት፣ የነጻ አውጪነት፣ የመሥዋዕትነት፣ ምልክት ነው።

፫. ነጭ፦ ድል አድራጊነትን፣ ንጽሕናን፣ ፍጹምነትን ያመለክታል::

ከነዚህም ሌላ ቤተክርስቲያን ሌሎች ቀለማትን እንደአስፈላጊነታቸው ትጠቀምባቸዋለች

ለምሳሌ፦.ቢጫ አክሊለ ብርሃንን ለመሣል ትጠቀምበታለች።

ለአብነት ያህል በቀለም አጠቃቀም ሂደት የእመቤታችንን ሥዕል አሳሣል ከምሥጢራዊ


ትርጓሜያቸው ጋር በአጭሩ ብንመለከት፦

ሀ. ከውስጥ ቀይ ትለብሳለች፦ ይህም አረጋዊው ስምዖን “በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ባንቺ ግን


በልብሽ ፍላጻ ይገባል።” (ሉቃ ፪፥፴፭፡፡) እንዳላት ሁሉ ጌታን አዝላ የተሰደደች፣ እስከ
ቀራንዮ /መስቀል/ ድረስ ስለልጇ ልዩ ልዩ መከራን የተቀበለች፣ የሰማዕታት እናት መሆኗን
ለማመልከት ነው።

ለ. ከውጭ ሰማያዊ ትጎናፀፋለች፦ ይህም ንጽሐ ሥጋን ከንጽሐ ነፍስ ጋር አስተባብራ


የተሸለመች፣ እንደ ሰማያውያን መላእክት በፍጹም ቅድስና ያጌጠች፣ የመላእክት
እኅታቸው፣ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በማኀፀንዋ የተሸከመች ዳግሚት አርያም
/ሰማይ/ መሆኗን ለመግለጥ ነው።

የቅዱሳን ሥዕላት ጠቀሜታና ክብር


የቅዱሳት ሥዕላት ጠቀሜታ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት በጣም ብዙ ነው:: ዋና
ዋናዎቹን ጠቀሜታዎች ለመግለጥ ያህልም የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል።

• ለማስተማር ክርስቲያኖች ዐላውያን ነገሥታትን በመፍራት በየዋሻውና ፍርኩታው


በተሸሸጉባቸው ዘመናት ክርስቲያኖችን ለማጽናናት ወንጌል ይሰበክ የነበረው
በቅዱሳት ሥዕላት አማካኝነት ነበር::

152
• ለማስታወስ አንድ ወቅት የተከናወነው ክርስቲያናዊው ክስተት ከምእመናን ልቡና
እንዳይጠፋና በወቅቱ ያሉ ያህል ሆኖ እንዲሰማቸው ለማድረግ ቅዱሳት ሥዕላት
ከፍተኛውን ሚና ሲጫወቱ ኖረዋል፤ ይኖራሉ።

• ከሥዕሉ ባለቤት /ቅዱስ/ ጋር በእምነትና በመንፈሳዊ ሕይወት ለመገናኘት፤


ማለትም ከቅዱሳን ጋር መንፈሳዊ ኅብረትና አንድነት ለመመሥረት፤

• ቅዱሳኑን በእምነት እንድንመስላቸው /እንድንከተላቸው/ ለማበረታታት፤

• ከሥዕላቱ በሚገኘው መንፈሳዊ ልምምድ ራስን ለማነጽና ለመቀደስ፤በቅዱሳኑ


ረድኤት መጎብኘት ሰውነትን ንጹሕ፣ ልቡናን ንቁህ፣ ኅሊናንም ብሩህ ያደርጋልና፤

• የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ውበት በማጉላት የሥርዓተ አምልኮን ሂደት ፍሬያማ


ለማድረግ፤

• ከባለ ሥዕሉ የቃል ኪዳን በረከትና ምልጃን ወይም ምሕረትንና ይቅርታን


ለማግኘትና ለመሳሰሉት ቅዱሳት ሥዕላት ለክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሕይወት
መጠንከር በእጅጉ ይጠቅማሉ::

ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ የቅዱሳት ሥዕላትን ጠቀሜታና ክብር አስመልክቶ


“ለቅዱሳት ሥዕላት የምንሰጠው ክብር ለባለ ሥዕሉ ያለንን ፍጹም የሆነ ልባዊ ፍቅርና
አክብሮት ለመግለጽ በመሆኑ ከባለ ሥዕሉ ረድኤትና በረከት ተካፋዮች ነን እንጂ
እንዲያው ተመልካቾች ብቻ አይደለንም “ብሏል:: ከዚህም ኃይለ ቃል ለሥዕል የምንሰጠው
ክብር ለተሣለበት ሰሌዳ፥ ቀለም ወይም ሌላ ግዑዝ ነገር ሳይሆን በዚያ ውስጥ ለተገለጠው
ቅዱስ/ስት መሆኑን እንረዳለን።

በሁለተኛው የኒቂያ ጉባኤም “ለሥዕል የሚሰጠው ማንኛውም አክብሮት በቀጥታ ለባለ


ሥዕሉ የሚቀርብ ነው።” ተብሎ መወሰኑም ይህንኑ እውነታ ለማረጋገጥ ነው፡፡ በዚህ ውሳኔ
መነሻም ፀረ-ቅዱሳት ሥዕላት የሆኑ መናፍቃን እስከ ፰ኛውና ፱ኛው መ/ክ/ዘ ድረስ
ምእመናንን ያደናግሩ ስለነበር ነው:: በተቃዋሚዎች አሳብ ላይ ተወያይቶ ቅዱሳት
ሥዕላትን በተመለከተ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ መወሰን ስላስፈለገ በ787 ዓ.ም
በኒቂያ ከተማ ፪ኛ ጉባኤ ተካሂዷል:: በዚህ ጉባኤ የተሰበሰቡ አባቶችም ተቃዋሚዎች
ቅዱሳትን ሥዕላት ከጣዖታት ጋር ለመደመር /ለመቁጠር/ ያነሧቸውን ጥቅሶች በመተንተን
ተቃውሞአቸው መሠረተ ቢስ መሆኑን አትተው የቅዱሳት ሥዕላትን ቀኖና ደንግነዋል::
ተቃዋሚዎችንም ከክህደታቸው ባለመመለሳቸው አውግዘዋቸዋል:: የተለያዩ የቤተ
ክርስቲያን ተቃዋሚዎች በነበሩባቸው ዘመናት ሁሉ የቅዱሳት ሥዕላት ጠበቆች የሆኑ የቤተ
ክርስቲያን አባቶችም ነበሩ:: ለአብነት ያህልም ዮሐንስ ዘደማስቆን /650-730ዓ.ም፡፡/
ቴዎዶር ዘእስቱዳይትን /759-826ዓ.ም/ እና ፓትርያርክ ኒሲፎረስን /750-828ዓ.ም/
ማንሣት/መጥቀስ/ እንችላለን።

153
፲፩.፫ ንዋየ ቅድሳት
የተከበሩ አንባቢ ሆይ፡-

❖ በቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ሥርዓትን ለመፈጸምየሚያገለግሉ ንዋያተ ቅድሳትን


በማስታወሻ ድበተርዎ ላይ ይዘርዝሯቸው፡፡

ንዋይ የሚለው ቃል ዕቃ ማለት ሆኖ ይተረጎማል። ቅድሳት ደግሞ የተቀደሱ፣ የተለዩ፣


የከበሩ፣ የተመረጡ ማለት ይሆናል። በተገናኝ ሲፈታም የተቀደሱ፣ የተከበሩ፣ የተመረጡ፣
የተለዩ የቤተ ክርስቲያን ዕቃዎች ማለት ይሆናል። በቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ሥርዓትን
ለመፈጸም የሚያገለግሉ ንዋየተ ቅድሳትን በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች መድበን ማየት
እንችላለን፡፡ እነዚህም በቤተ ክርስቲያንና በዙሪያዋ የሚገኙ ንዋየተ ቅድሳትና የቅዳሴና
የሌሎች ተዛማጅ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች ማከናወኛ ንዋየተ ቅድሳት የሚባሉት
ናቸው:: በመቀጠል ደግሞ እነዚህን ሁለት ዋና ክፍሎች ለየብቻቸው ከንዋያተ ቅድሳት
ዝርዝርና ምሳሌያዊ ትርጉማቸው ጋር አጠር አጠር አድርገን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

ሀ.በቤተ ክርስቲያንና በዙሪያዋ የሚገኙ /የማይንቀሳቀሱ/ ንዋያተ


ቅድሳት
፩.አዕማድ /ምሰሶዎች/ እነዚህ በቤተክርስቲያን ውስጣዊ ክፍል ተተክለው ጣሪያውን
በመሸከም ግድግዳውን የሚያግዙ ናቸው።

ምሳሌነታቸው ሌሊትና ቀን ሳያርፉ በእግዚአብሔር ፊት ለምስጋና የሚቆሙ ቅዱሳን


መላእክትን ያሳስባሉ። /ራእ ፬፥፰‐፲/።

2.በአገልግሎት ጸንተው እግዚአብሔርን ሌሊትና ቀን ሳያርፉ ያገለገሉትንና ደስ ያሰኙትን


ሐዋርያት ያሳያሉ። /ገላ ፱/።

154
፪.ጉበን ወይም ደረጃ

ጉበን ወይም ደረጃ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚያደርስ /የሚያገባ/ ከፍ ከፍ እያለ


የሚጓዝ መንገድና መግቢያ ነው።

ምሳሌነቱ፦ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ


የሚመጣ የለም።” /ዮሐ፲፬፥፮፡፡/ ብሎ የተናገረ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህም
እኔን የባህርይ ልጅ /ተወላዲ/ ሳይል አብን የባሕርይ አባት /ወላዲ/ ሊለው የሚችል የለም፤
ማለቱ ነው። እርሱን አርአያና አብነት አድርገን የምንኖር ከሆነ ወደ ሰማያዊ መንግሥቱ
ያገባናል።

፫.የቤተ ክርስቲያን ክዳን ሣር መሆኑ

ምሳሌነቱ፦

• ሄሮድስ በጭካኔ ያስፈጃቸውን የቤተልሔም ሕፃናት ያመለክታል፡፡ /ማቴ


፪፥፲፮‐፲፱፡፡/ የሣር ክዳን መጠኑ ይህን ያህላል የማይባል ብዙ እንደሆነ ሁሉ
ሕፃናቱም ምንም እንኳን ለመቆጠር ቢችሉም እጅግ ብዙ ናቸውና። በዚህ
ተመስለዋል::

የቤተ ክርስቲያን ቅጽር /የግቢው ከለላ/ አጥር፦

• ምሳሌነቱ ረድኤተ እግዚአብሔርን ያመለክታል:: አጥር ከልዩ ልዩ ሥጋዊ


ጥቃት ለጊዜውም ቢሆን እንደሚከላከል ሁሉ ረድኤተ እግዚአብሔር ደግሞ
ቤተ ክርስቲያንንና አባሎቿን ከፀብአ አጋንንት /ከጠላት ፍላፃ/
የሚጠብቃቸው መሆኑን ያስገነዝባል።

፭.ዕፅዋት፦

ምሳሌነቱ፦ በመዓልትም በሌሊትም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የማይለዩትን ቅዱሳን


መላእክት ያሳስባል:: ዕፅዋቱ በቤተክርስቲያን ግቢ በብዛት እንደሚታዩ በቤተ ክርስቲያን
የሚኖሩ ቅዱሳን መላእክትም እጅግ ብዙ ናቸው:: ዕፅዋቱ አምረውና ተውበው ለቤተ
ክርስቲያን ሞገስ ሆነው እንደሚታዩ ሁሉ ቅዱሳን መላእክትም የቤተ ክርስቲያንና
የምእመናን መንፈሳዊ ሞገሶች ናቸው። /መዝ፺፥፲፩፡፡/ እንደዕፅዋቱ የምእመናን ጥላ ከለላ
መሆናቸውን ያሳያል።

፮.ማገር፦

ምሳሌነቱ፦

የቅድስት ሥላሴ ነው:: ማገር የሕንፃውን ግድግዳና ጣሪያ አገናኝቶና አጽንቶ


እንደሚያቆመው ቅድስት ሥላሴም ቤተ መቅደስ በሆነው የክርስቲያን ሰውነት ላይ አድረው
በሃይማኖትና በምግባር አጽንተውት እንደሚኖሩ ያመለክታል።
155
፯.ግድግዳ

ምሳሌነቱ፦

የነቢያት ነው:: ግድግዳ ለቤተክርስቲያን ውስጣዊ ክፍሎች መለያና ከአንዱ ወደ አንዱ


መሸጋገሪያ እንደሆነ ሁሉ ነቢያትም ከዘመናት ወደ ዘመናት /ከዓመተ ፍዳ ወደ ዓመተ
ምሕረት/ ለተደረገው ሽግግር ትንቢት ተናጋሪዎች መሆናቸውን ያሳያል። /ማቴ፫፥፩‐፯፡፡/

፰.የተጠረቡ ድንጋዮችና የለዘቡ እንጨቶች

ምሳሌነታቸው ፦

የሰማዕታት ነው። ደንጊያዎችና ዕንጨቶች ተወቅረውና ተጠርበው ለቤተ ክርስቲያን


መሥሪያ እንደሚውሉ ሁሉ ሰማዕታትም በእሳት እየተፈተኑ በስለት እየተመተሩ
ለመንግሥተ እግዚአብሔር የበቁ፥ ለምእመናንም የሚተርፉ እንደሆኑ ያመለክታል፡፡ /ዕብ
፲፩፥፴፮‐፴፱፡፡/

፱.ጉልላት

ምሳሌነቱ፦

የቀራኒዮ ነው:: ጉልላትንና ከላዩ ላይ ያለውን መስቀል ለሚመለከት ጌታችን ኢየሱስ


ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ለድኀነተ ዓለም በቀራኒዮ ኮረብታ /አደባባይ/ መሰቀሉን እንዲያስብ
ያደርገዋል። /ዮሐ ፲፱፥፲፯፡፡/

፲.በጣሪያው ዙሪያ ያሉ ሻኩራዎች

ምሳሌነታቸው፦

የቅዱሳን መላእክት ነው:: ሻኩራዎች ሌሊትና ቀን በነፋስ እየተወዛወዙ ድምፅ


እንደሚሰጡ ቅዱሳን መላእክትም በአጸደ ቤተክርስቲያን ሌሊትና ቀን ያሸበሽባሉ፤
ይዘምራሉ:: /ዘፍ፳፰፥፲፩‐፲፰፡፡/

፲፩. የሰጎን እንቁላል

ይህ አሁን ከችግር አኳያ እየቀረ የመጣ ቢሆንም በጥንታውያኑና ገጠራማ አካባቢ በሚገኙ
አብያተ ክርስቲያናት የተለመደ ነው:: በጉልላቱ ላይ በሚቆመው መስቀል ዙሪያ የሰጎን
እንቁላል ይደረጋል።

ምሳሌነቱ /ምሥጢራዊ ትርጉሙ/፦

ሰጎን እንቁላሏን ለመፈልፈል የምታበቃው በመታቀፍ ሳይሆን ሳታቋርጥ /ሳትንቀሳቀስ/


በማየት ነው። ምግብ ሲያስፈልጋት እንኳን ወንዱን በቦታዋ ተክታ ነው። የቤተክርስቲያን
ጉልላት ላይ እንቁላሏ መሰቀሉ ሰጎን ያለማቋረጥ እንቁላልዋን እንደምትመለከት

156
እግዚአብሔርም ፍጥረቱን የማይረሳ በጸጋውና በረድኤቱ ከፍጥረቱ የማይለይ መሆኑን
ያመለክታል። እንቁላሉ በእግዚአብሔርና በምእመናን መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት
ያስረዳል /፪ዜና ፯፥፲፮፡፡ ኢሳ፵፱፥፲፭፡፡/

ሰጎኗ ዓይኗን ለአፍታም ያህል እንኳን ካነሳች፥ እንቁላሉ ይለወጣል፤ ማለትም ይበላሻል፤
አይፈለፈልም:: እንደዚሁም እግዚአብሔር መግቦቱንና ጠብቆቱን /ረድኤቱን/ ለአፍታም
ያህል ቢያቋርጥ ምእመናን /የሰው ልጆች/ ሕይወት አይኖራቸውም:: አንድም ታሪኩ
ምእመናን እንደ ሰጎን ዓይነ ልቦናቸውን ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ቤተክርስቲያን፣ ወደ
መስቀሉ፣ ወደ እመቤታችን፣ ወደ ቅዱሳኑ ሁሉ እንዲያደርጉ ይጋብዛል። ዓይነ ልቡናቸውን
ከእግዚአብሔር፣ ከቤተ ክርስቲያን፣ ከቅዱስ መስቀሉ፣ ከእመቤታችን፣ ከቅዱሳኑ ሁሉ ላይ
ካነሡ /ከነቀሉ/ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንደሚበላሽ ፍጻሜያቸውም እንደማያምር
ያሳያል። /ዮሐ ፲፱፥፳፭‐፳፰፡፡/

፲፪. ሦስቱ በሮች

እነዚህ በሮች ወደ ቤተክርስቲያን የሚያስገቡና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ የሚገኙ


ናቸው። በምሥራቅ ካህናት፣ በሰሜን ወንዶችና በደቡብ ሴቶች ይገቡባቸዋል።

፲፫. ቤተልሔም

ከቤተ ክርስቲያን በስተምሥራቅ የሚሠራው ይህ ቤት መሥዋዕተ ወንጌል (ሥጋውና ደሙ


ማትም ኅብስቱና ወይኑ የሚዘጋጅበት ክፍል ነው::

ምሳሌነቱ፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተወለደበት ዋሻ /ጎል/ ነው።

፲፬. ቤተ ምርፋቅ

ይህ ክፍል ከአገልግሎት በኋላ ካህናት ዕረፍት አድርገው እህል ውሃ የሚቀምሱበት ነው።


ይህም በልማዳዊ አጠራር ደጀ ሰላም የሚባለው ነው።

ምሳሌነቱ፦ የገነት ነው:: ገነት ለቅዱሳን ጊዜያዊ የዕረፍት ቦታ /የነፍስ ማረፊያ/


እንደሆነች ሁሉ ቤተ ምርፋቅም ለአገልጋይ ካህናት ጊዜያዊ የዕረፍት ክፍል መሆኗን
ያሳያል።

ለ.የቅዳሴና የሌሎች ተዛማጅ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ማከናወኛ ንዋያተ ቅድሳት

ሀ. ቃጭል /መረዋ/፦ከብረት፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከነሐስና ከመሳሰሉት ማዕድናት የሚሠራ


ንዋየ ቅዱስ ነው። ከደወል በመጠን በጣም ያነሰ ካህናት ቅዳሴንና እግዚኦታን ለመሳሰሉ
የቤተ ክርስቲያን የውስጥ አገልግሎት የሚጠቀሙበት ንዋይ ቅዱስ ነው፡፡ ደወል ከውጪ

157
ቃጭል /መረዋ/ ደግሞ ከውስጥ በቅዳሴ ሰዓት በመናበብ /አንዱ አንዱን በመከተል/
አገልግሎት ይሰጣሉ።

ምሳሌነቱ፦

1. መጥምቀ መለኮት ቅ/ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ።”


(ማቴ፫፥፫፡፡) በማለት ለጮኸው ድምጽ ነው::

2. በተጨማሪም በእግረ መስቀል ሆኖ ያለቀሰው የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ልቅሶ ምሳሌ


ነው።

3. ቃጭል /መረዋ/ እየተመታ ከቤተልሔም ወደ ቤተ ክርስቲያን /መቅደስ/ መገባቱ ፲፪ቱ


ሐዋርያት ከጌታ ዕርገት በኋላ በየሀገረ ስብከታቸው “ሥጋውን ብሉ፣ ደሙን ጠጡ፤” እያሉ
የማስተማራቸው ምሳሌ ነው።

4. አንድም “አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ።” ያለው የቅ/ገብርኤል ብሥራት ምሳሌ


ነው። በዚህም የጌታችን ዜና ልደቱ ይታሰብበታል።

የተከበሩ አንባቢ ሆይ፥


❖ በቅዳሴ ጊዜ ቃጭል /መረዋ/ የሚመታው በምን ጊዜ ነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ
ይችሉ ዘንድ የቅዳሴ ልምድዎትን እያስቡ ጊዜያቱን ለማስታወስ ይሞክሩ።

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት፡-

• ቀዳስያን /ልዑካን/ ከቤተልሔም ወደ መቅደስ ሲገቡ፣

• ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን /የክርስቲያን ታናናሾች ውጡ/

• ድርገት (ስጋውና ደሙ ሊሰጥ) ሲወርድና

• በእግዚኦታ ጊዜ ቃጭል/መረዋ/ ይመታል::

ለ. ሰን ወይም መቁረርት /ኩስኩስት/፦ “ቈረ፡-ቀዘቀዘ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን


ቆሪር በራድ ማለት ይሆንና መቁረርት፣ ማቁረሪያ፣ ማብረጃ፣ ማቀዝቀዣ የሚል ትርጉም
ይሰጠናል። ሥጋ ወደሙ የተቀበሉ ምእመናን በጥርሳቸውና በትናጋቸው እንዳይቀርና
እንዳይነጥብ ከአፋቸው ለቅልቀው /ጠርገው/ የሚያወርዱበት ቅዳሴ ጠበል ስለሚሰጥበት
ይህን ስያሜውን አግኝቷል:: ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ እጁን የሚያነጻበትም /የሚታጠብበትም/
ነው። በብሉይ ኪዳንም ለመቅደስ አገልግሎት ከዋሉ ንዋየ ቅዱሳት መካከል አንዱ
የመታጠቢያ ሰን ነበር:: /ዘፀ ፴፥፲፮‐፳፪፡፡/

ምሳሌነቱ፦

158
1. በቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ አገልግሎት ገባሬ ሠናይ ካህን ቄሱ “ከደማችሁ ንጹሕ ነኝ!”
እያለ መናጻቱ ጲላጦስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊት “እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹህ ነኝ!”
በማለት ለመናገሩ ምሳሌ ነው::

2. በጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ላጠበበት ሰን


ምሳሌም ይሆናል::

ሐ. ብርት፡- እንደሰኑ ከተመሳሳይ ማዕድን ተሠርቶ ለተመሳሳይ አገልግሎት የሚውል ማይ


ማጠራቀሚያው ሣህን ነው::

መ. ጽንሐሕ፦ ይህ የዕጣን ማጠኛ ቅዱስ ንዋይ ነው። በብሉይ ኪዳንም በአሠራር ደረጃ
ልዩነት ቢኖረውም የዕጣን መሠዊያ ከማይነቅዝ ዕንጨት ተሠርቶ በወርቅ ተለብጦ
አገልግሎት ይሰጥ ነበር። /ዘጸ፴፥፩‐፲፩፤ ፴፯፥፳፭‐፳፱፡፡/

ምሳሌነቱ፦ ማዕጠንት /ጽንሐሕ/:- የእመቤታችን፤

• የተለበጠበት ወርቅ፦ የንጽሕናዋ /የቅድስናዋ/፤

• ዕጣኑ፦ የትብስእት /የሥጋ/፤

• ፍሕም፦ የመለኮት፤

• የወርቅ ዘንግ /ማዋሐጃው/:- የመንፈስ ቅዱስ፤

• በመሠዊያው አራት ማዕዘኖች ላይ ያሉት አቅርንት /ቀንዶች/:- የሥልጣነ


እግዚአብሔር ሙዳይ የሚመስለው ፍህሙና ዕጣኑ የሚቀመጥበት ክፍል የማኅፀነ
ማርያም፤ ሙዳይ መሰሉን ንዋይ የሚከድነው (መክደኛው) በአናቱ ላይ ካለው
መስቀል ጋር የቀራኒዮ፣ መካከለኛው ዘንግ (ከመክደኛውና አናቱ ላይ ካለው መስቀል
ጋር የተያያዘ ነው።):- የቅድስት ሥላሴ (የአንድነታቸው)፤

- ይህ ዘንግ ዝቅ ማለቱ (መውረዱ):- ወልደ እግዚአብሔር ሰው የመሆኑ፣


- የመሰቀሉና የሞቱ፤ ከፍ ማለቱ /መውጣቱ/:- ወልደ እግዚአብሔር የመነሣቱና
የማረጉ፤

• ሻኩራዎችን የየያዙ ሦስቱ ዘንጎች:- የእግዚአብሔርን የአካል፣ የግብር፣ የስም፣ የኩነት


ሦስትነት፣

• ሻኩራዎች ብዛታቸው ፲፪ (፳፬) መሆኑ:- የ፲፪ቱ ሐዋርያት፣ የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ፤

- የሚያሰሙት ድምፅ፦ የስብከታቸው የምስጋናቸው፤

ሠ. ሙዳይ፡- ይህ በእናቶቻችን አማካኝነት የሚሰፋ ለዕጣን ማኖሪያ የሚያገለግል በመጠን


ያነሰ የአገልግል ዓይነት ነው።

159
ምሳሌነቱ ፦

• ሙዳዩ የእመቤታችን፤

• ዕጣን የጌታ፤

• ካህኑ ከቅዳሴ በፊት መርጦ የሚያስቀምጠው ፭ ቆቀር /ፍሬ/ ዕጣን:- የ፭ቱ ኪዳናት
ማለትም የቁርባነ አቤል፣ የመሥዋዕተ ኖኅ፣ የኂሩተ አብርሃም፣ የመብዐ ይስሐቅ፣
የተልእኮተ ሙሴ ወአሮን ምሳሌ ነው፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ ገጽ ፴፪ ቁጥር ፳፩ እና
ገጽ ፮ ቁጥር ፵፩-፵፫፡፡)

ረ. መሶበ ወርቅ፦ ይህ መሥዋዕቱ (ኅብስቱ) ከቤተልሔም ወደ መቅደስ የሚገባበት የከበረ


ንዋይ ነው:: በብሉይ ኪዳንም አገልግሎት ይሰጥ ነበር። /ዘፀ፲፮፥፴፫፡፡/ አሠራሩ እንደ
ሙዳዩ ነው::

ምሳሌነቱ ፦መሶብ:- የእመቤታችን፤

• የተለበጠበት ወርቅ፦ የንጽሕናዋ፥ የቅድስናዋ፤


• መና /ኅብስት/፦ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ (የእሑድ ውዳሴ ማርያም፡፡)

በሌላ በኩል ደግሞ ሌላው እንደላይኛው ሆኖ ኤልያስ ለምእመናን ምሳሌ ይሆናል። (፩ነገ
፲፱፥፬‐፱፡፡ ቅዳሴ ማርያም፡፡)

ሰ. ጻሕል፦ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከብረት፣ ተሠርቶ ከከበረ በኋላ በታቦቱ ላይ ሆኖ


በቅዳሴ ጊዜ የጌታችን ሥጋ የሚሠዋበት ነው።

ምሳሌነቱ፦ ጌታችን ለተወለደበት በረት፤ አንድም ለእመቤታችን ነው።

ቀ. ዕርፈ መስቀል፦ ዲያቆኑ ደሙን ለምእመናን የሚያቀብልበት ንዋይ ቅዱስ ነው።

ምሳሌነቱ፦ ለንጊኖስ የጌታችንን ጎን ለወጋበት ጦር፤ (መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜ


፡፡)

:-ጉጠት፦ የዕርፈ መስቀል ምሳሌ /ኢሳ ፮፥፮-፰፡፡/

ሸ. ጽዋዕ:-ዲያቆኑ የጌታችንን ክቡር ደም የሚያቀብልበት ክቡር ንዋይ ነው::

ምሳሌነቱ:-የተወጋ የጌታችን ጎን፣አንድም የእመቤታችን፤አንድም በዕለተ ዓርብ ጌታ


በተሰቀለ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ደሙን የተቀበሉበት የብርሃን ጽዋዕ፤ ምሳሌ ነው።

ጽዋው የሚሸፈንበት ልብስ ፊቱን ሲጸፉት(በጥፊ ሲመቱት) ለመሳለቅ ዐይኑን ለሸፈኑበት


ጨርቅ ምሳሌ ነው።

በ. ዐውድ፦ ትርጉሙ አደባባይ ሆኖ በድርገት ጊዜ ጻሕሉ የሚቀመጥበት ሰፋ ያለ ትልቅ


ሣህን መሳይ ቅዱስ ንዋይ መጠሪያ ነው።
160
ምሳሌነቱ፦ አይሁድ በጌታችን ላይ እንዲሞት ለመከሩበት አደባባይ፤

ተ. አጎበር፦ ከብረት ወይም ከዕንጨት ተሠርቶ በድርገት ጊዜ በዐውዱ ላይ የሚደፋ ሦስት


እግሮች ያሉት ንዋይ ቅዱስ ነው።

ምሳሌነቱ ፦የማኅተመ መቃብር /የመቃብር መክደኛ (መዝጊያ)፤

- ሦስት እግሮች:- የቅድስት ሥላሴ /የሦስትነት/፤

ቸ. አትሮንስ፦ የቅዱሳት መጻሕፍት ማንበቢያ ነው::

ምሳሌነቱ፦ የእመቤታችን፤

- ቅዱስ መጽሐፍ፦ የጌታችን፤

ኀ. ማኅፈዳት፦ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያላቸው፣ ለመጠቅለያነት የሚያገለግሉ ፭ የሐር


ጨርቆች (ልብሶች) ናቸው:: ብዙ ጊዜ ጥቁር ቀለም ያላቸው ይሆናሉ::

አንደኛው፦ በጻሕሉ ሥር በዐውዱ ላይ ይነጠፋል::

ሁለተኛው፦ ከጻሕሉ ላይ ይነጠፋል፤ ኅብስቱ የሚጠቀለልበት ነው።

የቀሩት ሦስቱ:- በአጎበሩ ላይ ይነጠፋሉ።

ምሳሌነቱ ፦

- ዐውዱ፦ የቤተልሔም
- ዐውዱ ላይ የሚነጠፈው ማኅፈድ:- እመቤታችን ጌታን በወለደች ጊዜ ያለበሰችው
ቈጽለ በለስ፤
- ጻሕል፦ ጌታ የተወለደበት የከብቶች በረት፤

:- የእመቤታችን የሰውነቷ፤

- በጻሕሉ ላይ የተነጠፈው ማኅፈድ:-የድንግልናዋ፤


- ሦስቱ ማኀፈዳት:-የቅድስት ሥላሴ (የሦስትነት)፤

• እመቤታችን ጌታን በፀነሰች ጊዜ አብ ለማጽናት፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን


ለመዋሐድ፣ መንፈስ ቅዱስ ድንግልናን ከማጣት ዘርንም ከመቀበል ሊጠብቃት
/ለማንጻት/ እንዳልተለዩዋት ያመለክታል።

አንድም፦

ዐውድ፦ የጎልጎታ

ጻሕል፦ የመቃብረ ክርስቶስ

161
የታችኛው ማኀፈድ፦ የመግነዝ፤

የላይኛው ማኀፈድ፦ የሰበን፤

አጎበር፦ የማኀተመ መቃብር ምሳሌዎች ናቸው::

ነ. ጃንጥላ (ጥላ)፦ የሚዘረጋው መቼ መቼ ነው? ቢሉ:- መሥዋዕቱን ለማክበር ወደ


ቤተልሔም ሲወርዱ፤

- መሥዋዕቱን አክብረው ሲመለሱ፤


- ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ተነሥቶ ሲወጣ፤
- በቅዳሴ ጊዜ ለማዕጠንት ሲወጡ፤
- ወንጌል ቅዱስ ሲነበብና፤
- ለልዩ ልዩ አገልግሎት መስቀል ሲወጣ ተዘርግቶ ይይዛል። የሚዘረጋውም ለታቦቱ፣
ለመሥዋዕቱ፣ ለወንጌሉና ለመስቀሉ ክብር ነው።

ምሳሌነቱ፦ እስራኤልን በበረሃ የጋረደ ደመና /የረድኤተ እግዚአብሔር/፤

ሙሴን በደብረ ሲና የሸፈነ ደመና፤

ኘ. ተቅዋመ /መቅረዝ/፦ ይህ የቀንዲል፣ የሻማ፣ የመብራት ማብሪያ ንዋይ ቅዱስ ነው።


/ዘካ ፬፥፪። ዘጸ ፳፭፥፴፩-ፍጻሜው፡፡ ፴፯፥፲፯‐፳፭፡፡/

ምሳሌነቱ፦ ተቅዋም፦ የዘመን፤

• ተቅዋም፦ የእመቤታችን፤

• ብርሃን፦ የጌታችን /ውዳሴ ዘሰንበተ ክርስቲያን

• ሌሎችም ንዋየ ቅድሳት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን


አስተምህሮ መሠረት መንፈሳዊ ትርጓሜና ምሳሌነት ያላቸው ናቸው። ይህም
ንዋያተ ቅዱሳቱ በራሳቸው ላስተዋላቸው አስተማሪዎች መሆናቸውን ያስገነዝበናል።
ንዋያተ ቅድሳቱም በምዕራፍ ሦስት ለመግለጽ እንደሞከርነው በአዲስነታቸው ወደ
ቤተክርስቲያን ሲገቡና ለአገልግሎት ሲዘጋጁ ይባረካሉ። /በቅብዓ ሜሮን
ይከብራሉ/።

አ. ደወል /መጥቅዕ/

ደወል የሚደወልባቸው ምክንያቶች

ሀ. የተጋብኦ ደወል

ካህናትና ምእመናን ለልዩ ልዩ አገልግሎት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲሰበሰቡ


የሚጠራ የቤተ ክርስቲያን በሮች ከመከፈታቸው በፊት የሚደወል ነው።

162
ምሳሌነቱ፦ የትንቢተ ነቢያት ነው:: ደውሉ ካህናትና ምእመናንን ቀስቅሶ
ለአገልግሎት /ለጸሎት/ እንደሚዘጋጅ፤ ነቢያትም የሕዝቡን ልብ እየቀሰቀሱ፤
ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሱ፤ ለአዲስ ኪዳን
አገልግሎት እንዲዘጋጁ ያደርጉ እንደነበር ያሳያል።

ለ.የቅዳሴ መግቢያ ደወል፦

ይህ ደወል ካህናት መሥዋዕቱን አክብረው ከቤተልሔም ወደ መቅደስ ሲጓዙ


የሚደወል ነው፡፡
ምሳሌነቱ፦
1. የብስራተ ገብርኤል ነው፤ አንድም
2. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እነሆ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር
በግ (ዮሐ ፩፥፪፱፡፡) በማለት የጮኸው /የተናገረው/ ድምፅ ነው።

ሐ. የወንጌል ደወል

ይህ ደወል “ፃኡ” በሚባልበት የቅዳሴ ክፍል መካከል የሚደወል ነው።

ምሳሌነቱ፦
የስብከተ ዮሐንስ፣ የሐዋርያትና የሰብአ አርድዕት ልቅሶ ነው። (ሉቃ፫፥፫‐፯፡፡) ይህ
ደወል ከተደወለ በኋላ ያለው የቅዳሴ ክፍል ፍሬ ቅዳሴ ይባላል:: ይህም መሥዋዕተ
ወንጌል የሆነው የክርስቶስ ሥጋውና ደሙ የሚቀርብበት ነው:: ደወሉ ሐዋርያትና
አርድእት ቅዱሳት አንስትም ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ያዘኑትን ሐዘን፥ ያለቅሱትንም
ለቅሶ፣ ያፈሰሱትንም ዕንባ የሚያስታውስ ነው።

መ.የእግዚኦታ ደወል

በቅዳሴ ጊዜ መጨረሻ አካባቢ ካህናትና ምእመናን በቅብብሎሽ /በማስተዘዘል /፵፩፥


፵፩/ ጊዜ እግዚኦታ ያደርሳሉ:: በዚህን ጊዜ ከላይ የገለጽነው ደወል ይደወላል::
ምሳሌነቱ፦
ከመስቀሉ አጠገብ ያልተለዩ የክርስቶስን መከራ አይተው ያለቀሱ የእመቤታችንና
የቅ/ዮሐንስ ወንጌላዊ የልቅሶ ድምፅ ነው:: /ዮሐ ፲፱፥፳፭‐፳፰፡፡/

ሠ.የድርገት ደወል

ሥጋ ወደሙ ለቆራብያን ለሰጥ (ሊታደል) ልዑካኑ ከመቅደስ ወደ ቅድስት ሲወጡ


የሚደወል ነው።
ምሳሌነቱ፦ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በገነዙት ጊዜ ያለቀሱት ልቅሶ ነው:: አንድም
የሐዋርያትና የሰብአ አርድእት ትምህርት ነው:: ዮሴፍና ኒቆዲሞስ የጌታችንን ሥጋ
በገነዙበት ጊዜ እያለቅሱ ነፍስ የተለየውን፣ መለኮት የተዋሐደውን የጌታችንን ሥጋ
ገንዘው ባዲስ መቃብር “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር…” ብለው እንዳኖሩት፤

163
ካህናትም በቅዳሴ ጊዜ ነፍስ የተለየውን መለኮት ያልተለየውን (የተዋሐደውን)
የክርስቶስን ሥጋና ደም እንዲያቀብሉ ደወል ይደወላል:: ሐዋርያትና ሰብአ
አርድእት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ወንጌልን በመላው ዓለም አስተምረዋል፤
ሰብከዋል። ዞረው ማስተማራቸውንና በስብከታቸው የሰው ልጆች ሁሉ ከሞት ወደ
ሕይወት መሸጋገራቸውን ለማሰብና ምእምናንም ዛሬ በደወሉ ድምፅ የዘለዓለም
ሕይወት ወደሚያገኙበት፥ የክርስቶስ ሥጋና ደም እንደሚቀርቡ ለማመልከት ነው::

፲፩.፬. ዜማና መዝሙር /የዜማ መሣሪያዎች/


መዝሙር የሚለው ቃል “ዘመረ‐አመሰገነ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም
ምስጋና ማለት ነው። በቤተክርስቲያን የዝማሬ ሥርዓት መሠረት ለእግዚአብሔር በዜማ
የሚቀርብ ምሥጋና ማለት ነው።

ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ የሚከተለውን ጥያቄ ለማብራራት ሞክሩ::

❖ ምስጋና /ዝማሬ/ መቼ፣ እንዴት? በማን ተጀመረ?

ከ፳፪ቱ ሥነ ፍጥረታት መካከል ቅዱሳን መላእክትና የሰው ልጆች የእግዚአብሔር


ስሙን ቀድሰው ክብሩን እንዲወርሱ የተፈጠሩ ናቸው። “የመላእክትን እንጀራ የሰው
ልጆች በሉ።” (መዝ ፸፯፥፳፭፡፡) የሚለውን የቅዱስ ዳዊት ምስጋና የተመለከትን
እንደሆነ ምስጋናቸውን ምስጋና በማድረግ /አብሮ በማመስገን/ መተባበራቸውን
የሚያመለክት እንደሆነ ሊቃውንቱ ይነግሩናል። የቅዱሳን መላእክት ምግባቸው፣
መጠጣቸው፣ ልብሳቸውና ዕረፍታቸው “ቅዱስ፤ ቅዱስ፤ ቅዱስ፤” እያሉ /ኢሳ፮፥፫። ራእ
፬፥፰፡፡/ እንደነቅዐማይ (የውሃ ምንጭ) እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ማመስገናቸው
ነውና:: ሳያርፉ ያመሰግናሉ፤ ሲያመሰግኑም ያርፋሉ፤ ስለዚህም ያለማቋረጥ
ያመሰግናሉ። በሐዲስ ኪዳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ
ተለያይተው የነበሩ ቅዱሳን መላእክትና የሰው ልጆች አንድ ላይ ሆነው አዲሱን ዝማሬ
ዘምረዋል:: አዲሱንም ቅኔ ተቀኝተዋል። /ሉቃ ፪፥፰‐፲፭፡፡/ በመቅድመ ወንጌልም “ዮም
አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ በቃለ አሚን።
ቅዱሳን መላእክትና የሰው ልጆች ክርስቶስን በእምነት ቃል ያመሰግኑት ዘንድ ዛሬ
አንድ መንጋ (ማኀበር) ሆኑ።” (መቅድመ ወንጌል፡፡) የተባለው የምስጋናውን አንድነት
ያሳያል:: ይህም በሰው በደል ተቋርጦ የነበረ የቅዱሳን መላእክትና የሰው ልጆች
የተባበረ ምስጋና በክርስቶስ ልደት ዳግም መጀመሩ የተረጋገጠበት ነው።

የመዝሙር ጥቅም
ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ጉልህ ሥፍራ ያለው መዝሙር
/በዜማ ስልት በወጉ የተዘጋጀ ምስጋና/ በርካታ ጥቅሞች አሉት:: ከምንም በላይ
እግዚአብሔር አምላክንና በእርሱ ፈቃድም ለመረጣቸው ቅዱሳንና ቅዱሳት ሁሉ ምስጋና
164
በማቅረብ መባረክ /መቀደስ/ ዋናው ጥቅም ነው። በተጨማሪም ለማሳያ የሚሆኑ ጥቅሶችን
ብንጠቅስ፦ደዌያት እንዲከለከሉ /እንዲገሠጹ/፤ /፩ሳሙ ፲፮፥፳፩‐ ፍጻሜው፡፡/ የጠላት
ወጥመድ እንዲበጣጠስ፣ እግር ብረቶችና ሰንሰለቶች እንዲወላልቁና እስረኞችም ነጻ
እንዲወጡ፤ /ሐዋ፲፮፥፳፭‐፴፭፡፡/ መዝሙር በምእመናን የዕለት ተዕለት ክርስቲያናዊ
ሕይወት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር ይነግረናል።

ቅዱስ ያሬድና ዜማው


የተወደዱ የክርስቶስ ቤተሰብ ሆይ፦

❖ ከተጠቀሱት ነጥቦች ሌላ መዝሙር ለመንፈሳዊ ሕይወት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ


ምንድነው?

❖ ምን ዓይነት መዝሙር ይወዳሉ? ለምን?

❖ ስለ ቅዱስ ያሬድ ታሪክ ምን ያውቃሉ?

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ ።

በ505 ዓ.ም በአክሱም የተወለደው ቅ/ ያሬድ በዚች ምድር ላይ የኖረባቸውን ፶፭ ዓመታት


ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፈና ለተፈጠረበት ቅዱስ ዓላማ የኖረ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ
አባት ነው። የልጅነት የአብነት ትምህርት ቤት ሕይወቱ አዳጋች የነበረ ቢሆንም ከአንዲት
ትል ተፈጥሮአዊ አኗኗርና ውጣ ውረድ (ትግል) ተስፋ አለመቁረጥን ተማረ። በዚህም የ፯
ዓመቱን መልክአ ፊደል (የፊደል መልክ) ያለመለየት ጉዞ በረድኤተ እግዚአብሔር
ለመቀየር ተዘጋጀ:: በማስተዋሉም የሥነ ፍጥረትን መምህርነት የተረዳ ትጉህ ካህን ሆነ::
እግዚአብሔርም ቁርጥ ውሳኔውንና ፍላጎቱን ምክንያት አድርጎ ዓይነ ልቡናውን ብሩህ ዕዝነ
ልቦናውንም ንቁሕ አደረገለት:: ከዛ በፊት ለምድራውያን ያልተገለጠ ሰማያዊ
ምሥጢርንም ገለጠለት:: ግእዝ፥ ዕዝልና አራራይ የተባሉ ሦስቱን ዜማዎች ከቅዱሳን
መላእክት /ከካህናተ ሰማይ/ እንዲማር ፈቀደለት። በቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜና በቅኔ
ችሎታው ወደር የማይገኝለት እስከ መሆን የደረሰው ይህ አባት በስሙ የተሰየመውን
ሰማያዊ ዜማ በአሥሩ የዜማ ምልክቶች ቀምሮ ቅዱስ እግዚአብሔርን፣ ቅድስት ድንግል
ማርያምን፣ ቅዱስ መስቀሉን፣ ቅዱሳን መላእክትን፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትንና
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባቸው በተገለጠለት መጠን ያመሰገነ ታላቅ የዜማ
አባት ነው::

የቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት


የተከበሩ የዚህ መጽሐፍ አንባቢ ሆይ:-

❖ የቅዱስ ያሬድን የዜማ መጻሕፍት ያውቋቸዋል? አስቲ ለመዘርዘር ይሞክሩ፡፡


165
የቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት አራት ናቸው:: አንዳንዶች ጾመ ድጓን ራሱን አስችለው
በመቁጠር አምስት ናቸው ይላሉ:: ጾመ ድጓ የድጓ አንድ ክፍል እንጂ ራሱን ችሎ
የሚቆጠር አይደለም:: እነዚህም የዜማ መጻሕፍት ከ፹፩ ዱ ቅዱሳት መጻሕፍትና አዋልድ
መጻሕፍት አውጣጥቶ በራሱ የዘይቤ አገላለጥ አጣፍጦና በሰማያዊው ዜማ አስውቦ
ያቀረባቸው ናቸው፡፡ እነርሱም ድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋሥዕትና ምዕራፍ በመባል ይታወቃሉ
ከዚህ በመቀጠል አጠር አጠር አድርገን እያንዳንዳቸውን ለማየት እንሞክራለን።

፩ መጽሐፈ ድጓ፦
ይህ የምስጋና መጽሐፍ በዓመቱ ውስጥ ያሉ የበዓላትና የሰናብት መዝሙራትን ሰብስቦ
የያዘ ነው:: ድጓ ማለትም እስትጉቡእ /ስብስብ/ የቤተ ክርስቲያን ድግ /ትጥቅ/ ከቅዱሳት
መጻሕፍት ተለቅሞ የወጣ ድርሳን፣ መዝሙረ ሐዲስ ማለት ነው:: ድጓ በውስጡ አራት
ታላላቅ ክፍሎች አሉት:: እነርሱም:-

ሀ/ የዮሐንስ ድጓ፤

ለ/ የአስተምህሮ ድጓ፤

ሐ/ ጾመ ድጓና

መ/ የፋሲካ ድጓ ተብለው ይጠራሉ።

ምሳሌነታቸው፦

➢ የአራቱ ክፍላተ ዘመን ማለትም “መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት” ለሚባሉት ነው፡፡
እንዲሁም:-
➢ በብሉይ ኪዳን የነበሩ የአራቱ ክፍላተ ዘመን፣ “ዘመነ አበው፣ ዘመነ መሳፍንት፣ ዘመነ
ነገሥታትና ዘመነ ካህናት” ይሆናሉ፡፡ አንድም:-
➢ በሐዲስ ኪዳን የነበሩና ያሉ ያራቱ ክፍላተ ዘመን ዘመነ “ሐዋርያት፣ ዘመነ
ሐዋርያውያን አበው፣ ዘመነ ሰማዕታት እና ዘመነ ሊቃውንት” እንዲሁም
➢ የአራቱ ወንጌላውያን “ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ” ነው።

፪/መጽሐፈ ዝማሬ፦
ዝማሬ ዘመረ አመሰገነ ከሚለው የግእዝ ቃል የሚወጣ ስም ነው:: በነጠላው መዘመር፣
አዘማመር፣ ዝመራ፣ ዜማ፣ የኅብረት ምስጋና፣ የሚል ፍቺ ይኖረዋል:: አገልግሎቱ ሥርዓተ
ቅዳሴ በሚፈጸምበት ወቅት ከድርገት በኋላ የሚቃኝ፣ የሚዜም፣ የሚዘመርና የቅዳሴውን
አካሄድና ዓላማ ተከትሎ የሚጓዝ ምስጋና ነው:: የሚዘመረውም በሳምንት (ሰንበት)፣ በወርና
በክብረ በዓላት ወቅት ነው:: አከፋፈሉንም በተመለከተ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች
ይመደባል። እነርሱም፦ዝማሬ፣ አኮቴትና ምሥጢር ይባላሉ:: በውስጡም ሦስት ንዑሳን
ክፍሎች አሉት:: እነርሱም በበኩላቸው ኅብስት ጽዋዕና መንፈስ በመባል ይታወቃሉ:: ቅ/
ያሬድ በሦስት ክፍላት /አርእስት/ የዘመረበት የራሱ የሆነ ምሥጢራዊ ፍቺም አለው፡፡
166
ምሳሌነቱ፦ ጌታችን ፫ መዓልት፣ ፫ ሌሊት በከርሰ መቃብር ለማደሩ ነው።

፫.መጽሐፈ መዋሥዕት
የቃሉ ትርጉም በሁለት መንገድ ሊገለጥ (ሊፈታ) ይችላል። ይኸውም በአንድ በኩል:-

ሀ. ”አውሥአ‐መለሰ” ካለው የግእዝ ግስ ወጥቶ ምልልስ የሚል ትርጉም ይኖረዋል።

ለ. ሁለተኛው ፍቺ ደግሞ ሰዋሰወ ነፍሰ (የነፍስ መሸጋገሪያ) መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት


(ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚመራ) ማለት ይሆናል።

መዋሥዕት ቀድመን እንዳየናቸው እንደ ሁለቱ የዜማ መጻሕፍት አከፋፈል የለውም::


በውስጡ በዋናነት የጌታችንን ልደት፣ ጥምቀት፣ ትንሣኤና ዕርገት የሚገልጡ ምሥጢራትን
ይዟል፡፡ በመቀጠልም የእመቤታችንን አማላጅነትና ክብር አጉልቶ አቅርቧል:: ከዚያም
የጻድቃን የሰማዕታትን፣ የደናግላንንና የመነኮሳትን ጥብዓትና ተጋድሎ የመላእክትን
ተራዳኢነት የሙታንን ጸአተ ነፍስና ዕረፍተ ነፍስ አጠቃሎ ይዟል።

፬.መጽሐፈ ምዕራፍ
ማረፊያ ወይንም ማሳደሪያ የሚል ትርጉም የሚኖረው ይህ መጽሐፍ የዘወትርና የጾም
ተብሎ በ ፪ ታላቅ ክፍሎች የቀረበ ምስጋና ነው። የሁለቱም ክፍሎች መሠረታቸው የቅ/
ዳዊት መዝሙርና የራሱ የቅ/ ያሬድ ድጓ ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ ባሉት ሳምንታትና በዓላት
እግዚአብሔርን ለማመስገን አገልግሎት ላይ የሚውለው የዘወትር ምዕራፍ ነው:: የጾም
ምዕራፍ ደግሞ በጾመ ሁዳዴ /ዐቢይ ጾም/ እና በረቡዕና ዓርብ ጾም እንዲሁም በምሕላ
ቀኖች እግዚአብሔርን መለመኛና ማመስገኛ ነው።

ምዕራፍ የተባለበትን ምክንያት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሲያብራሩ ቅዱስ ያሬድ ፳፪


ዓመታት ሙሉ ጸዋትወ መከራውን ታግሦ ፈጣሪውን በተገለጠለት ሰማያዊ ዜማ ካመሰገነና
ተተኪዎችንም ለቤተ ክርስቲያን ካፈራ በኋላ የዕረፍቱ ቀን በደረሰበት በመጨረሻይቱ ሰዓት
/ወቅት/ ስለደረሰው ነው ይላሉ።

የቅ/ያሬድ የዜማ ምልክቶች


እስቲ ደግሞ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ

• የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

• የዜማ ዓይነቶቹና ምሳሌነታቸው እንዴት ይገለጻሉ?

• የቅዱስ ያሬድ ዜማ ልዩ ጠባያት /ከሌላው ዜማ የሚለዩበት/ ምን ምን ናቸው?


167
• የዘመኑን መዝሙራት ከቅዱስ ያሬድ ዜማ አኳያ እንዴት ይገመግሙታል?

፩/ድፋት / / ፦ የጌታችንን ከሰማየ ሰማያት መውረድና ከድንግል ማርያም መወለድ


የሚያስረዳ ነው።

፪/ሒደት / / ፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረ እስራኤል ተዘዋውሮ ማስተማሩን፣


በአይሁድ የሐሰት ክስ መሠረትም ከሐና ወደ ቀያፋ፣ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ መመላለሱን
ያጠይቃል።

፫/ቅናት / /፦ አይሁድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋዊ ቅናት


ተመቅኝተው እንደሰቀሉት ያሳያል።

፬/ይዘት / / ፦ አይሁድ ጌታን በሐሰት ከሰው /ወንጅለው/ እንደያዙት ያመለክታል።

፭/ቁርጥ / /፦ ጌታችን አዳምንና ልጆቹ ለማዳን በመልዕልተ መስቀል ለመሞት


መቁረጡን (መወሰኑን) ያጠይቃል።

፮/ጭረት / /፦ ጌታ በዕለተ ዓርብ በሰውነቱ ላይ በደረሰበት ግርፋት የታየውን የሰንበር


ምልክት ያመለክታል።

፯/ርክርክ / /፦ ጌታችን በዕለተ ዓርብ በደረሰበት ጸዋትወ መከራ ከሰውነቱ


የተንጠባጠበውን ደም ያመለክታል።

፰/ደረት / / ፦ የጌታን ዕርገት ያሳያል።

፱/ድርስ /ስ/ ፦ ጌታችን ስለሱ የተነገሩትን ትንቢተ ነቢያት መፈጸሙን (ትንቢቱ


መድረሱን) ያጠይቃል።

፲/አንብር /ር/፦ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ በማረግ በአባቱ ዕሪና
/ክብርና ትክክልነት/ መቀመጡን ያስረዳል።

እነዚህ የዜማ ምልክቶች በንባቡ ላይ እየተመለከቱ /በሚዜመው ሆሄ ላይ ምልክት


እየተደረጉ/ ማንኛውም የዜማ ተማሪ ሙያውን ጠንቅቆ እንዲማርባቸውና ከተማረም በኋላ
እያዜመ ፈጣሪውን እንዲያመሰግን ይረዱታል። በዚህም መሠረት ላለፉት ፲፭፻ (አንድ
ሺህ አምስት መቶ) ዓመታት የቤተ ክርስቲያን ዜማ ሳይፋለስና ሳይዛባ ማንኛውም ሥጋዊ
ፍላጎትም ሳይጨመርበትና ሳይቀላቀልበት የቤተ ክርስቲያናችን የአምልኮተ እግዚአብሔር
መሣሪያና ዋነኛ መገለጫ ሆኖ ኖሯል፤ ይኖራልም:: ይህንን መንፈሳዊ ሀብት ጠብቆና
አስጠብቆ መኖር ደግሞ የወጣቱ ትውልድ ሓላፊነት መሆኑን መረዳትና አስፈላጊውን ሁሉ
ለማድረግ መትጋት ይገባል። ምክንያቱም ይህን ታላቅ የቤተክርስቲያን፣ የሀገርና የዓለም
ሀብት የሆነ ያሬዳዊ ዜማ ለመበረዝና ለማጥፋት የሚታገሉ ሥጋውያን ሰዎች ተመሳስለው
ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋልና።

የቅ/ ያሬድ የዜማ ዓይነቶች


168
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የቅ/ያሬድ የዜማ ዓይነቶች በቅድስት ሥላሴ
አምሳል ሦስት ናቸው። እነዚህን የዜማ ዓይነቶች ከአጫጭር መግለጫዎች ጋር
እንደሚከተለው እናቀርባለን።

ሀ/ ግእዝ ዜማ ፦ ግእዝ ማለት በመጀመሪያ የተገኘ ማለት ነው። በዜማነቱ ሲተረጎምም


የዜማ ስልቱ የቀና፣ ርቱዕ፣ ቀጥ ያለ፣ ጠንካራ ማለት ይሆናል። ከዜማው ጠንካራነት የተነሣ
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “ደረቅ ዜማ” ብለውታል።

ምሳሌነቱ፦ የአብ ነው።

ለ/ ዕዝል ዜማ፦ ከግእዙ ዜማ ጋር ተደርቦ ወይም ታዝሎ የሚዜም በመሆኑ ይህንን


መጠሪያውን አግኝቷል:: ዜማው ለስላሳ ሲሆን ዕዝል ማለትም “ጽኑዕ ዜማ” ማለት
ይሆናል።

ምሳሌነቱ፦ የወልድ ነው፤ ወልደ እግዚአብሔር ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን
ለማዳን ጽኑዕ መከራ በመቀበሉ ተመስሏልና::

ሐ/ አራራይ ዜማ፦ ይህ ዜማ የሚያረጋጋ ፣የሚያራራ የሚያሳዝንና ልብን የሚመስጥ


“ቀጠን ያለ ዜማ” ነው።

ምሳሌነቱ፦ የመንፈስ ቅዱስ ነው።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በአገልግሎቶቿ ሁሉ /ቅዳሴ፣ ማኅሌት፣ ሰዓታት፣ ኪዳን…./


የምትጠቀምበት የዜማ ስልት ከነዚህ ከሦስቱ የዜማ ዓይነቶች አይወጣም። ይህም በቅዱስ
ያሬድ በኩል ከእግዚአብሔር የተሰጣት መንፈሳዊና ሰማያዊ ሀብት ነው። እግዚአብሔርና
ቅዱሳኑ የሚመሰገኑበት ይህ ሰማያዊ ዜማና ዓለም ለልዩ ልዩ ፍጆታዎች የምታውለው
ሥጋዊ ዜማ ፈጽሞ የተለያየ መሆኑንም መረዳት ይገባል። ቅዱስ ዳዊት እስራኤላውያን
ወገኖቹ ተማርከው በባቢሎን የሚደርስባቸውን መከራ በትንቢት መነጽር አይቶ ተናግሯል።
በዚህ ትንቢቱ ውስጥም ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ምስጋና ከአለማዊው ሙዚቃ ፈጽሞ
የተለየና መንፈሳዊው ዝማሬ በተቀደሰው ምድር በክብር የሚዘመር መሆኑን ገልጿል።
የእግዚአብሔር ዝማሬ ለአሕዛብ መሳለቂያና መዝናኛነት የሚቀርብ አለመሆኑንም አብሮ
እንዲህ በማለት አስቀምጦታል። “በባቢሎን ወገዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም
ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። በአኻያ ዛፎችዋ ላይ በገናዎቻችንን ሰቀልን፤ የማረኩን በዚያ
የዝማሬ ቃል ጠይቀውናልና፤ የወሰዱንም፤ የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን::
የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ
ቀኜ ትርሳኝ:: ባላስብሽ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን
ባልወድድ።” /መዝ፻፴፮፥፩‐፯፡፡/

ይህን አስተውሎ የሚያነብ ሰው የቤተ ክርስቲያን ዝማሬ የእግዚአብሔር ዝማሬ እንደሆነ


ይረዳል። ማንም ይሳለቅበት ዘንድ በባዕድ ምድር፣ ጣዖት በሚመለክበት ቦታ የከበረው ይህ
የእግዚአብሔር ዝማሬ እንደማይዘመርም ያስተምረናል፡፡ ኢየሩሳሌም የተባለች

169
ቤተክርስቲያንን፣ ትምህርቷን፣ ዜማዋን፣ ቅርሷን፣ ታሪኳንና ትውፊቷን፣ መርሳት /መተው/
እንደማይገባና ከዚህ ዓለም ጥቅሞች፣ ከሥጋዊ ፍላጎቶችና ከደስታዎች ሁሉ በላይ
ቤተክርስቲያንንና የጠቀስናቸውን መንፈሳዊ ሀብቶች መውደድ እንደሚገባ ከዚህ ኃይለ
ቃል መረዳት ይችላል።

የቅዱስ ያሬድ ዜማ ልዩ ጠባያት

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የቅ/ ያሬድ ዜማ ሰማያዊ ነው። እንዲህም በመሆኑ


ሕሊናን የመሰብሰብና የመመሰጥ ከሥጋዊ ፍላጎትና ከኃጢአት ወጥመድ የመጠበቅ፣
መንፈሳዊውንና ሰማያዊውን ድንቅ የምስጋና ምሥጢር የማሳወቅ ኃይልና ብቃት አለው።
እንደተገለጠውም ማለዳ ማለዳ ሳይለወጥ፣ ሳያረጅና ሳይሰለች አዲስ በመሆን
እየተመሰገነበት ፲፭ መቶ ክፍላተ ዘመናትን መሻገር ችሏል። የእግዚአብሔር ስጦታ
መሆኑ ከሚታወቅባቸው መንገዶች አንዱ ይኸው ዘወትር አዲስነትና አይጠገብነት
የሚታይበት መሆኑ ነው ።

ከሌሎች ዜማዎች የሚለይባቸውን ጥቂት ዋና ዋና ነጥቦች ብቻ ብንመለከት እንኳን


ከላይ የገለጽነውን ያጎላልናል።

ሀ. ዜማው በዘፈቀደ እንደተገኘ የሚዜም ሳይሆን በአዝማናት ተለይቶ በወቅቶች


ተከፋፍሎ መዜሙ የመጀመሪያው ነው።

ለምሳሌ፦ ከቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶች ዋናውን ድጓን ብንመለከት በ፬ ወቅቶች /ክፍለ
ዘመናት/ ተከፋፍሎ መዜሙን እንረዳለን። እነሱም፦

1.ዮሐንስ:- የመጥምቁ ዮሐንስን ክብር፣ ቅድስናና አገልግሎት በመግለጥ የሚጀመር

2.አስተምህሮ:- ክርስቶስ ያስተማረውን ትምህርት አጉልቶ የሚያሳይ፤

3.ጾመ ድጓ:- ጾመ ክርስቶስን መሠረት አድርጎ ስለ አጽዋማት የሚያትት፤ /በዓቢይ ጾም


የሚዘመር /

4.ፋሲካ፡- የክርስቶስን ስቅለትና ትንሣኤ የሚገልጥ፤ በመባል ይታወቃሉ። እነዚህም


ዓመቱን ለ፬ ተካፍለው በታመቀ ምሥጢራቸው ወቅታዊውን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ
እየመሰከሩ ይዜማሉ።

ለ. የተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ያለው መሆኑ ሁለተኛው ነው::

ሐ. በጥቅሉ ያሬዳዊ ዜማ የሰሙትን ሰዎች በመንፈስ እንዲመላለሱ የሚያደርግ፤ በአንጻሩ


ደግሞ ከሥጋ ፈቃድና ወጥመድ መንጭቆ የማውጣት ኃይል ያለው መሆኑ ሦስተኛው
ጠባዩ ነው::

170
መ. ዜማው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ምሥጢር የተሞላ መሆኑ ሌላው ልዩ ጠባዩ ነው።
የዜማው መሠረቶችም፦ መጻሕፍተ ብሉያት፣ መጻሐፍተ ሐዲሳት፣መጻሕፍተ
ሊቃውንት፣መጻሕፍተ መነኮሳት፣አዋልድ መጻሕፍትና ትውፊት ናቸው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመዝሙር /ዜማ/መሣሪያዎችና


ምሥጢራዊ ትርጉማቸው

የተከበሩ የዚህ ጽሑፍ ተከታታይ /አንባቢ/ በተቻለ መጠን የሚከተሉትን ጥያቄዎች


ለመመለስ ሞክሩ::

❖ የሚያስታውሷቸውን የቤተ ክርስቲያን የዜማ መሣሪያዎች ከምሥጢራዊ ምሳሌያዊ


ትርጉማቸው ጋር በማስታወሻ ደብተርዎ ላይ ይጻፉ::
❖ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወንጌልን አትሰብክም የሚል ትችት
ቢሰሙ ከያዝነው ርእሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምን ብለው ሊመልሱ ይችላሉ?

በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት እንደማኅሌት ያሉ አገልግሎቶችና የዑደት


ወረቦች ከተዘጋጁላቸው መሣሪያዎች ጋር ተስማምተው ይዜማሉ:: ዜማው ብቻ ሳይሆን
የዜማ መሣሪያው እና አጠቃቀሙ የቤተክርስቲያኒቱን ትውፊትና ሥርዓት የጠበቀ መሆን
ይኖርበታል። ቤተክርስቲያን የሥጋ ስሜትን በመከተል የሚፈጸምና በዘፈቀደ የሚጓዝ
ምንም ዓይነት አገልግሎት የላትም። እያንዳንዳቸው የዜማ መሣሪያዎቿም መጽሐፍ
ቅዱሳዊ መነሻና መልእክት የአጠቃቀም ሥርዓትም አላቸው። በመዘምራኑ አንደበት
ከሚገለጠው ሥልታዊ ዜማ ጋር መሣሪያዎቹ የሚያወጡት ሥርዓት ያለው ድምጽ ተደምሮ
እዝነ ልቡናን ወደ ሰማየ ሰማያት ነጥቆ ያወጣል:: ሰማዕያኑም በተቀደሰው ዜማ ተስበው
ከአምላካቸው ጋር ይገናኛሉ። ሰማያዊውን ምሥጢር እየተማሩ በሕይወታቸው ሁሉ
የተባረኩ ይሆናሉ።

የመዝሙር /የዜማ/ መሣሪያዎቻችን አስቀድመን ለመጠቆም እንደሞከርነው የየራሳቸው


የሆነ መንፈሳዊ ትርጉምና ምሳሌነት አላቸው:: እነዚህንም በአጭሩ እንደሚከተለው
እንገልጣቸዋለን።

፩ መሰንቆ ይህ የዝማሬ አገልግሎት መስጫ መሣሪያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻ ያለው


ነው። በአሉታዊ መልኩ በመጠቀም እግዚአብሔርን የማያስቡትን /የማያመሰግኑትን/
በመንቀፍ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ትንቢት ተናግሯል:: “በጥዋት ወደ መሸታ ቤት
ለሚገሰግሱና በመጠጥ ቤት ለሚውሉ ወዮላቸው! ወይኑ ያቃጥላቸዋልና። በመሰንቆና በበገና
በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን
አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።” /ኢሳ ፭፥ ፲፩‐፲፫፡፡/ በማለት በጻፈው
አንቀጽ ውስጥ መሰንቆም ተጠቅሶ እናገኘዋለን። መሰንቆ ከበገና ጋር ከመጀመሪያዎቹ
አባቶቻችን ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ የዜማ መሣሪያ ነው። /ዘፍ ፬፥፳፩፡፡/
እግዚአብሔርን ማመስገኛ የዜማ መሣሪያ መሆኑንም ቅዱስ ዳዊት ራሱ አመስግኖበትና
ከብሮበት መስክሮልናል። /መዝ፵፪፥፬።/፺፩፥፫፡፡/ ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔርን
እንድናመሰግንበትም አዞናል። /መዝ፹፥፪፤ ፻፵፮፥፯፡፡/ በቀረው ደግሞ ቀጣዮቹን ጥቅሶች
171
ከርእሰ ጉዳዩ ጋር በተያያዘ እናንተው አገናዝቡት። /ኢሳ. ፲፮፥፲፩፤ ፳፬፥፰፡፡ ፩ ሳሙ.
፲፥፭፡፡/

ምሳሌነቱ፦

ሀ/ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ነው። /ቅዳሴ ማርያም/ የመሰንቆ ጭራው


በዕጣነ ካልታሸ ድምጽ አይሰጥም።

- ዕጣን፦ የጌታ
- ጽምፅ፦ የምስጋናዋ፤ የመስንቆ ጭራ (ክር) በዕጣን ታሽቶ ድምጽ እንደሚሰጥ፣
እመቤታችንም ጌታን ወልዳ ወላዲተ አምላክ ለመባል በቅታለች። ጌታን ፀንሳ
ሳለችም “ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል።” (ሉቃ፩፥፵፰፡፡) በማለት
ተናግራለች::

ለ/ የሃይማኖት ምሳሌ ነው። በመሰንቆ አገልግሎት ሂደት ድምፅ የሚሰጠው ፩ ክር ብቻ


ነው። ይህም አንድ ድምፅ “ወልድ ዋሕድ” ብላ የተዋሕዶን የእምነት ድምፅ የምታሰማ
አንዲት ሃይማኖትን ያመለክታል። /ቅዳ. አት. ፶፱፡፡/

ሐ/ የመስቀል ምሳሌ ነው። በመሰንቆው ጫፍ ላይ የድኅነታችን ምልክትና የነጻነታችን


ዓርማ የሆነው መስቀል አለበት፡፡ ሁለቱ ክሮች /የመሰንቆውና የመምቻው/ የመስቀል
ምልክት እየሰጡ ነው ድምጽ የሚፈጥሩት:: ስለዚህ በመሰንቆ በዘመርን ጊዜ ሁሉ በእግረ
ሕሊና ቀራንዮ ሄደን የተዋለልንን ውለታ እንድናስብ ያደርገናል ማለት ነው::

መ/ የመሰንቆው መምቻ የኪዳነ ኖኅ ምሳሌ ነው። /ዘፍ ፱፥፲፩-፳፡፡/ የመሰንቆ መምቻ


ቀስተ ደመናን ይመስላል፤ በመሰንቆ መዘመር /ማመስገን/ “ኪዳነ ኖኅን አስበህ ማረን”
የሚል አቤቱታን /መልእክትን/ የያዘ ነው ማለት ነው። በሌላም በኩል አባታችን ኖኅ
ከነቤተሰቡ የዳነብሽ አማናዊቷ መርከባችን ድንግል ማርያም ሆይ፥ የኃጢአት ማዕበልና
የፈተና ሞገድ ገፍቶ በክህደትና በጥርጥር ገደል እንዳይጥለን ዛሬም ለኛ ፈጥነሽ ድረሽልን
በማለት እመቤታችንን መለመናችን ነው።

፪ መለከት፦ ጥንታዊያን ከሆኑ የዜማ መሣሪያዎች አንዱ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ


በተደጋጋሚ አገልግሎት ላይ መዋሉ ተገልጿል። /ኢያ ፮፥፳፡፡ ፪ሳሙ፮፥፲፭።
፪ዜና፭፥፲፫፡፡ መዝ፹፥፫፡፡/

ምሳሌነቱ፡- የጌታ ዳግም ምጽአት ምሳሌ ነው:: /ማቴ ፳፬፥፴፩፡፡ ፩ተሰ፬፥፲፮


፡፡ ፩ቆሮ፲፭፥፶፪፡፡/

፫. በገና ከመጀመሪያዎቹ የዝማሬ መሣሪያዎች አንዱ ነው፡፡ /ዘፋ ፬፥፳፩፡፡/ ቅዱስ ዳዊት
በገና እየደረደረና እግዚአብሔርን እያመሰገነ ንጉሥ ሳኦልን ከደዌው /ከያዘው ርኩስ
መንፈስ/ ይገላግልበት የነበረ የዜማ መሣሪያ ነው። /፩ሳሙ፲፮፥፲፮፡፡/ ካህናተ ሰማይ
ቅዱሳን መላእክት የቅዱሳን ጸሎት ከሆነ ዕጣን ከሞላበት የወርቅ ዕቃ /ጽናሐሕ/ ጋር በገና
ይዘው በአዲስ መዝሙር ሲያመሰግኑ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ አይቷቸዋል። /ራእ
172
፭፥፰‐፲፡፡/ ይህም የዚህን የዝማሬ መሣሪያ ሰማያዊ ክብርና ተቀባይነት የሚያጎላልን
ይሆናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ መዋሉ ተመዝግቧል:: /፩ ዜና ፲፭፥፳፩፡፡
፪ ዜና ፳፱፥፳፭‐፳፰። መዝ ፴፪፥፩‐፬፤ ፺፩፥፩‐፫፡፡/

ምሳሌነቱ፦ ዐሥሩ አውታሮች------------------------------------------------ የዐሥሩ ትእዛዛት፤

- ሁለቱ የዳርና ዳር እንጨቶች--------------- የብሉይና የሐዲስ ኪዳናት፤


- ብርኩማው ------------------------------------- የደብረ ሲና፤

፬. መቋሚያ፦ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ወቅት ለካህናትና ምእመናን መደገፊያነት


ከሚጠቅመው በላይ ጥልቅ ሃይማኖታዊ ምሥጢር ያለው ንዋየ ማኅሌት ነው።

ምሳሌነቱ፦ የተስፋ አዳም፤ የመስቀል፤ አንድም ሙሴ ባሕረ ኤርትራን የከፈለበት በትር


/የበትረ ሙሴ/ ነው። /ዘጸ ፲፬፥፲፮‐ፍጻሜው፡፡/

• መዘምራን ሲወርቡ በትከሻቸው ተሸክመው ማሸብሸባቸው፦ ጌታችን “የሚወደኝ


ቢኖር መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ።” ያለውን ቃል እያሳሰቡ ማመስገናቸውን
ያመለክታል። /ማቴ ፲፥፴፰፡፡ሉቃ፲፬፥፳፭‐፳፰፡፡)

• መዘምራኑ መቋሚያውን በእጃቸው ይዘው ወደ ቀኝና ግራ መዝመማቸው ጌታችን


ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘ ጊዜ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ፣ ከሐና ወደ ቀያፋ መመላለሱን
ያጠይቃል:: /ሉቃ፳፫፥፩‐፲፫፡፡ ዮሐ፲፰፥፲፪‐፲፭፡፡/

• መዘምራኑ መቋሚያውን ወደ ላይ እያነሡ መልሰው ወደ መሬት በማውረድ


መደሰቃቸው /ወለሉን መምታታቸው/ አይሁድ ጌታችንን በያዙት ጊዜ በገመድ
አስረው መሬት ለመሬት መጎተታቸውንና በመሬት ላይ ይጥሉት እንደነበረ
ያሳስባል። /ድርሳነ ማኅየዊ፡፡/

በመረግድ ጊዜም መዘምራኑ መቋሚያውን ተሸክመው ክብ ሠርተው እያመሰገኑ


መዞራቸው ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ቀራኒዮ ተራራ መውጣቱን
ያመለክታል። /ዮሐ ፲፱፥፲፯፡፡/

፭.ጸናጽል፦ከንዋያተ ማኅሌት አንዱ ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስም ከቅዱስ ዳዊት የአገልግሎት


ዘመን ጀምሮ ጥቅም ላይ እንደዋለ ማወቅ ይቻላል። /፪ኛ ሳሙ ፮፥፭። ፩ ዜና ፲፫፥፰፤
፲፭፥፲፮፤ ፲፱፥፳፰፤ ፲፮፥፭፤ ፵፪፥፳፭፥፩‐፮። ፪ኛ ዜና ፳፱፥፳፭። ዕዝ. ፫፥፲፡፡ ነህ
፲፪፥፳፯፡፡ መዝ ፻፶፥፭፡፡/ ከዚህም ሁሉ ጋር በጸናጽልና በተጠቀሱት የዜማ ንዋያት
የሚዘመረውን ዝማሬ እግዚአብሔር እንደሚወድደውና እንደሚቀበለው የሚያመለክት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አለን። “መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ ከአሳፍና ከኤማን
ከኤዶትምም ልጆች ጋር ወንድሞቻቸውም ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና ከበሮ፣ መሰንቆም
እየመቱ በመሠውያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር። መለከቱንም የሚነፉ
መዘምራኑ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ፥ “እግዚአብሔር ቸር
ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤” እያሉ በአንድ ቃል
173
ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል፥ በዜማም ዕቃ ሁሉ
እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር የክብሩ ደመና የእግዚአብሔርን ቤት
ሞላው። የእግዚአብሔርንም ቤት የእግዚአብሔር ክብር ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ከደመናው
የተነሣ መቆምና ማገልገል አልተቻላቸውም። / ፪ ዜና ፭፥፲፪‐ፍጻሜው፡፡/

ምሳሌነቱ፦ የኪዳነ ኖኅ ነው። /ዘፍ ፱፥፲፪‐፲፰፡፡/ የጸናጽሉን የሁለት ዘንግ ጫፎች


ያገናኘው ደጋን የመሰለ መስመር ቀስተ ደመና ይመስላልና። በተጨማሪም፦

• ሁለቱ ዓምዶች፦ /ግራና ቀኝ ያሉት/:- የሁለቱ ኪዳናት /ብሉይና ሐዲስ/፤

• ሁለቱ ሻኩራዎችን የሚይዙ ዘንጎች /ጋድሞች/:- ያዕቆብ በሎዛ ያየው የብርሃን


መሰላል፤

• ሁለትነታቸው:- የፍቅረ ቢጽና የፍቅረ እግዚአብሔር፤

-የደቂቀ አዳምና የነገደ መላእክት፤

-ብሉይና የሐዲስ ኪዳን፤

• ሻኩራዎች /ቅጠሎች/:- የቅዱሳን መላእክት፤

• የሚያሰሙት ድምፅ፡- የቅዱሳን መላእክት ምስጋና፤

• የሻኩራዎቹ ቁጥር፦

፭ ከሆነ የ፭ቱ አዕማደ ምሥጢራት፤

፮ ከሆነ የ፮ቱ ቃላተ ወንጌል፤

፯ ከሆነ የ፯ቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፤ ምሳሌዎች በመሆን ነገረ እግዚአብሔርን


ይሰብካሉ:: በዚህም ቤተክርስቲያን እንኳን በመጻሕፍቷና በሊቃውንቷ አስተምህሮና
ሕይወት ይቅርና በአገልግሎቷና በንዋያተ ቅድሳቷ ሁሉ ወንጌልን ስትሰብክ የኖረች፥
በመስበክ ላይ ያለችና የምትኖር መሆኗን ማስተዋል ተገቢ ነው።

፮.ከበሮ፦

ይህ የማኅሌትና የዝማሬ /የመዝሙር/ መሣሪያ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው።


በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክም እስራኤል የኤርትራን ባሕር ከተሻገሩበት ጊዜ ጀምሮ ጥቅም
ላይ መዋሉን መረዳት ይቻላል። /ዘጸ ፲፭፥፳፡፡/ ከዛም በፊት ቢሆን ይጠቀሙበት
እንደነበር የላይኛውን ጥቅስ ስናነብ መገንዘብ እንችላለን። “የአሮን እኅት ነቢይቱ
ማርያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤” የሚለው ኃይለ ቃል ከዛም በፊት ከበሮን ይጠቀሙበት
እንደ ነበረ በሚገባ ይጠቁመናል፡፡ በተጨማሪም ለማሳያ ያህል የሚከተሉትን ማየት
እንችላለን። (መሳ ፲፩፥፴፬፡፡ ፪ ሳሙ ፮፥፭። ፪ ዜና ፲፫፥፰። መዝ ፷፯፥፳፬‐፳፯።
፹፩፥፩‐፭። ፻፵፱፥፫። ፻፶፥፬፡፡) ቀሪዎቹን ጥቅሶች በማንበብ በከበሮ መዘመር
174
በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅነትና ተቀባይነት ያለው መሆኑን ጸናጽል በሚለው ሥር
የተጻፈውን ማስረጃና ማብራሪያ ማገናዘብ የተሻለ ይሆናል።

ከበሮ ከዝማሬ መሣሪያነቱ በተጨማሪ እንደሌሎቹ ንዋያት ሁሉ ከፍተኛ መንፈሳዊ


ትምህርት የሚሰጥ ሰባኪ ነው። ይህንንም ለመረዳት ከዚህ በታች የቀረበውን መግለጫ
ለአብነት ይሆን ዘንድ መመልከት ይገባል።

• ከበሮ የክርስቶስ ምሳሌ ይሆንና፤

• ከበሮ የሚለብሰው ቀይ ጨርቅ፦ አይሁድ በዕለተ ዓርብ ጌታችንን ያለበሱትን


ከለሜዳ፤

• ሁለቱ የከበሮ አፎች የተወጠሩበት ጥልፍልፍ ጠፍር፤ ጌታ ሲገረፍ በሰውነቱ ላይ


የታየውን ሰንበር፤

• ትንሹ የከበሮ አፍ:- የትስብእት፤ /የለበሰውን ሥጋ ውስንነት፤/

• ትልቁ የከበሮ አፍ:- የመለኮት፤ /የመለኮትን ስፋሕነትና ምሉዕነት፤/

• ሁለቱ አፎች በጠፍሩ አማካኝነት ተይዘው /ተጠፍረው/ አንድ ከበሮ


ማስገኘታቸው፦ መለኮትና ትስብእት በተዋህዶ አንድ አምላክ የመሆናቸው፤

• ጠፍሩ - የተዋሕዶ፤

• የከበሮው ማንገቻ /ማንጠልጠያ/፦ ጌታችን በዕለተ ዓርብ የተገረፈበትና የግንግሪት


/የፊጥኝ/ የታሰረበት ገመድ፤

• ከበሮ በቀስታ ተጀምሮ በፍጥነት መመታቱ፦ የጌታን በጥፊ መመታትና ግርፋት፤


/በርጋታ አርባ ሊገርፉት ጀምረው ስድስት ሺ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጊዜ
ለመግረፋቸው/….ምሳሌዎች ናቸው።

ይህም በጥቅሉ ከበሮ የክርስቶስን ሕማማተ መስቀል የሚያሳስብና የሚሰብክ ከከበሩ


ንዋየ ቅድሳት አንዱ መሆኑን ያመለክታል። እነዚህም ከዚህ በላይ የዘረዘርናቸው የዜማ
መሣሪያዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንግዲህ ለ፪ሺ ዓመታት አገልግሎቷን


የፈጸመችውና የምትፈጽመው በዚህ ሁኔታና መንገድ ነው። ከዚህም በመነሣት
የቤተክርስቲያን የዜማ አገልግሎትና የዜማ መሣሪያዎቿ ፍጹም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑና
በቀደሙት አባቶች የአገልግሎት ሕይወት መሠረት ላይ የቀጠሉ መሆናቸውን መገንዘብ
ይገባል። ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነው ሰማያዊ አገልግሎት ላይ ዓለማዊና የሰዎች
ሥጋዊ አሳብ የፈጠረውን አካሄድ መከተል እንደማይጠቅምም ያሳያል። ለመንፈሳውያን
ሰዎች እግዚአብሔር የወደደውን፣ ክብሩንም የገለጠበትን መንገድ ከመከተልና ሳያዛቡ
ከመተግበር የበለጠ ምን ደስታ ይኖራል?!
175
፲፩.፭. ዕጣን

በቤተክርስቲያን አገልግሎት ከፍተኛ ጠቀሜታ ካላቸው መባዎች አንዱ ዕጣን ነው።


/ዘፀ ፳፭፥፮፡፡/ ዕጣንን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ በጣም ብዙ ማስረጃዎችን
ይሰጠናል:: ዕጣንን ከደብተራ ኦሪት ጀምሮ ካህናት እንዲያጥኑ ያዘዛቸው፣ የመሠውያውን
አሠራርና የዕጣኑንና ዓይነት የነገራቸው ራሱ እግዚአብሔር ነው። /ዘፀ ፴፥፩‐፲፤
፴፬‐ፍጻሜው፡፡/ ሙሴና ካህናቱ የዕጣኑን መሠውያ፣ ዕጣኑንና በጥቅሉ የደብተራ ኦሪትን
ሥራ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ፈጽመው ዕጣኑን መሥዋዕቱን ባቀረቡ ጊዜ እግዚአብሔር
በሥሙር ገጽ እንደተቀበለላቸው መገንዘብ ተገቢ ነው። /ዘፀ ፵፥፳‐ፍጻሜው፡፡/ የዕጣን
መሥዋዕት እግዚአብሔር በመረጠውና በሾመው ካህን ካልሆነ በቀር ካህን ባልሆነ ሰው
በድፍረት መቅረብ እንደማይገባውም ቅዱስ መጽሐፍ አስጠንቅቆናል። /ዘኁ ፲፮፥፬‐፵፩፡፡/
በዚህ ድፍረታቸው እግዚአብሔር ተቆጥቶ ዐመፀኞችን መቅጣት በጀመረበት ጊዜ
እስራኤል በእግዚአብሔርና በአገልጋዮቹ ሙሴና አሮን ላይ አጉረምርመው ዐመፁ::
ከእግዚአብሔርም መቅሠፍት ታዞ ብዙዎችን መግደል ሲጀምር በሙሴ ጸሎትና ምልጃ፥
በእግዚአብሔር ፈቃድ መቅሠፍቱ ተከለከለ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሾመው ካህን
አሮን በመካከላቸው የከበረውን ዕጣን እያጠነ ኃጢአታቸውን አስተሰርዮላቸው ነበርና።
ካህኑ አሮን በሕያዋንና በሙታን መካከል በቆመና ዕጣን እያጠነ ባገለገለ ጊዜም መቅሰፍቱ
መከልከሉን እንረዳለን። /ዘኁ. ፲፮፥፵፩‐ፍጻሜው፡፡/ የእግዚአብሔርን ፍርዱንና ሕጉን
ማስተማር፣ በፊቱ በማዕጠንት ዕጣንን ማጠን /መሠዋት/ እና የሚቃጠል መሥዋዕትን
ማቅረብ በእግዚአብሔር ፊት ያማሩና የተወደዱ ነበሩ፤ ዛሬም ናቸው። /ዘዳ ፴፫፥፲። ፪
ዜና ፪‐፭፡፡ መዝ ፷፮፥፲፭፤ ፻፵፥፪፡፡/

በሐዲስ ኪዳን ዘመንም በልደቱ ጊዜ በጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) እጅ መንሻ


ከቀረቡት መባዎች አንዱ ዕጣን ነው። /መዝ ፸፩፥፲፡፡ ኢሳ፷፥፮፡፡ ማቴ. ፪፥፲፩፡፡/ ለካህኑ
ዘካርያስ መልአከ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤል የተገለጠለትና የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅን
መወለድ /ልደት/ ያበሰረው በቤተመቅደስ ዕጣን በሚያጥንበት ጊዜ ነበር። /ሉቃ
፩፥፰‐፲፰፡፡/ ቅዱሳን መላእክት የቅዱሳንን ጸሎት መሥዋዕትና ዕጣን ወደ ልዑል
እግዚአብሔር የሚያሳርጉት በዕጣን ነው። (ራእ፰፥፫‐፭፡፡) ለልዑል እግዚአብሔር ስምና
ክብር ንጹሕ ዕጣን በመላው ዓለም በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንደሚታጠንም ነቢዩ
ሚልክያስ አስቀድሞ ትንቢት መናገሩ ተገልጿል። /ሚል. ፩፥፲፩፡፡/ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ
ጥቀሶች የዕጣንን ጥቅምም የሚነግሩን መሆናቸውን ማገናዘብ እንችላለን፡፡

የዕጣን ምሳሌያዊ ትርጉም

ሀ. የዕጣኑ ጢስ በደመና ስለሚመሰል እግዚአብሔር ከቤተ ክርስቲያኑ /ከምእመናን/ ጋር


የመሆኑ ምሳሌ ነው።

ለ. የቅዱሳን ሕይወት፤ ቅዱሳን ራሳቸውን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው


የማቅረባቸው ምሳሌ ነው።

176
ሐ. የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ መውጣት በቤተክርስቲያን የሚቀርበው ጠቅላላ አገልግሎትና
ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የማረጉ (የመቅረቡ) ምሳሌ ነው።

መ. ለጌታችን ዳግም ምጽአት ምሳሌ ይሆናል:: ጌታችን ዳግም ለፍርድ የሚመጣው


በደመና ስለሆነና የዕጣኑም ጢስ በደመና ስለሚመሰል ማለት ነው።

፲፩∙፮. ታቦት /ጽላት/

ውድ የዚህ ምዕራፍ አንባቢ ሆይ:- በቅድሚያ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክሩ::

❖ ታቦት ማለት ምን ማለት ነው? ጽላትስ?

❖ ከሌሎች ኦርቶዶክስ እኅት አብያተ ክርስቲያናት ተለይታ ቤተክርስቲያናችን


ታቦትን በአደባባይ የምታከብረው ለምንድነው?

❖ በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ጽላት (ታቦት) መካከል ያለው አንድነትና ልዩነት
ምንድነው?

ታቦት
ሥርወ ቃሉን ስንመለከት ቤተ-አደረ ከሚለው ግስ ይወጣና ታቦት ማለት የጽላቱ
ማደሪያ፥ መኖሪያ የሚል ይሆናል። ይኸውም የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ፥ የክብሩም
ዙፋን ነው:: በአሁኑ (አዲስ ኪዳን) የቤተ ክርስቲያን አጠቃቀም ታቦት ስንል ጽላት
ማለታችን ነው። ታቦት ወጣ ማለትም የጽላት ማደሪያው ወጣ ማለት አይደለም፡፡ ስመ
አምላክ የተጻፈበት አማናዊው የሐዲስ ኪዳን መሠውያ፣ የሥጋ ወደሙ ማክበሪያ፣ የጻሕሉና
የጽዋው ማኖሪያ የሆነው ጽላት ወጣ ማለታችን ነው እንጂ፡፡ ከዚህ በታች ታቦት እያልን
ስንጽፍም ጽላት ማለታችን እንደሆነ በመረዳት እንዲያነቡ እንጠይቃለን:: ታቦት
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ /የመሆኑ/ ምልክት ነው። /ዘፀ ፳፭፥፩-፳፪፡፡/

ታቦት በብሉይ ኪዳን


በብሉይ ኪዳን ዘመን ታቦቱ ከላይ እንደገለጽነው የጽላቱ ማደሪያ ነው:: አስቀድሞ
በግብረ እግዚአብሐር የተገኙ ፪ቱ ጽላት ለሙሴ ተሰጥቶት ነበር:: ጽላቱ ቢሰበሩ ደግሞ
በፈቃደ እግዚአብሔር በታላቁ ነቢይ በሙሴ ተዘጋጅተው ፲ቱ ቃላት በእግዚአብሔር
ጣቶች የተጻፈባቸው ጽላት ያድሩበት ነበር:: ጽላተ ኪዳኑም ማኅደረ እግዚአብሔር
(የእግዚአብሔር ማደሪያ) ነው። ይህ ታቦት ከእስራኤል የነጻነት ሕይወት ጋር የተያያዘ
ታሪክ አለው፡፡ ከግብጽ ወጥተው ወደ ምድረ ርስት ሲገሠግሱ ደብረ ሲና ደረሱ። በዚያም
ሙሴ ወደ ተራራው ወጥቶ ፵ ቀንና ሌሊት በመጾም ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት
ለመነጋገር በቃ፡፡ ከእግዚአብሔርም እጅ ሁለቱን ጽላት ተቀብሎ ወረደ:: በጉዞአቸውም
እግዚአብሔር በታቦቱ /ጽላቱ/ ላይ ክብሩን እየገለጠ ጠላቶቻቸውን እያጠፋላቸውና

177
እስራኤልን እየታደጋቸው፤ መንገዳቸውንና ማደሪያቸውንም እያዘጋጀላቸው ተጉዘዋል።
/ዘኁ፲፥፴፫፡፡ ኢያ፫፥፩-ፍጻሜው፤ ፮፥፩-ፍጻሜው፡፡/ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሁሉ
የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት /ጽላት/ እየተባለ ይጠራ ነበር። /ዘዳ ፲፥፰፤
፴፩፥፱‐፳፭፡፡/

የቃል ኪዳኑ ታቦት ያደረገውን ድንቅ ተአምር በተመለከተም መታሰቢያ እንዲያቆሙና


ለትውልድ ሁሉ እንዲነግሩም ታዘው ነበር። /ኢያ. ፬፥፩‐፲፡፡/ በእስራኤል ዘንድ
እግዚአብሔርን በለቅሶ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ መሥዋዕት በማቅረብ፣ የተቸገሩትን እና
የሚሹትን መጠየቅ የተለመደ ነበር። ይህንንም በክብሩ ዙፋን በታቦቱ ፊት ያደርጉት
እግዚአብሔርም በታቦቱ አድሮ ይመልስላቸው ነበር። /ኢያ፰፥፳፮-፳፱፡፡/ ነቢዩ ሳሙኤል
የነቢይነት ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ስለ ካህናቱ አፍኒንና ፍንሐስ ስለመሰሎቻቸውም
ኃጢአት የቃል ኪዳኑ ታቦት ከጦር ሜዳ ተማርኮ ነበር። ይሁን እንጂ በታቦቱ ላይ አድሮ
ያለ (የሚኖር) እግዚአብሔር አሕዛብንና ምድራቸውን በመቅሠፍት መታ፡፡ በዚህም
ምክንያት ከታላቅ እጅ መንሻ ጋር በድንቅ ተአምራት የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ እስራኤል
በክብር ተመልሷል። /፩ሳሙ፬፥፮/። ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ለቅዱስ ጊዮርጊስ
መታሰቢያነት የተሰየመውን የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ዐደዋ የዘመቱትና በዘመናዊ
የጦር መሣሪያ ተደራጅቶ የመጣውን የጣልያን ጦር በኃይለ እግዚአብሔር ጦርና ጎራዴ
ይዘው ድል ያደረጉት ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ተከትለው እንደሆነ ልብ ማለት
ይገባል። በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት መቆም፣ መሥዋዕት ማቅረብ፣
እግዚአብሕርን ማመስገንና የፈለጉትን መለመን የተለመደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጉዞ እንደሆነ
የታወቀ ነው። /፩ነገ፫፥፲፭። ፰፥፳፪‐፷፪፡፡/ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት
በዝማሬና በዜማ መሣሪያዎች ማመስገንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት /ውርስ/ ነው።
/፩ዜና፲፭፥፳፭-፳፱፤ ፲፮፥፬‐፯፣፴፯፥፵፡፡/ ለቃል ኪዳኑ ታቦት ተገቢውን ክብር ያልሰጡ
ሰዎች መቀጣታቸውንም መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። /፪ሳሙ፮፥፮‐ፍጻሜው፡፡/

በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ስለ ታቦት የተጻፉት በብዛት መሠውያ እየተባሉ የተገለጡት


ናቸው። የሐዲስ ኪዳን መሠዊያ ታቦቱ /ጽላቱ/ ነውና፡፡ ለምሳሌ ያህልም ብንመለከት
“መባህን በመሠውያው በምታቀርብበት ጊዜ ፥ በዚያም ሳለህ የተጣላህ ወንድምህ እንዳለ
ብታስብ መባህን ከዚያ በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድና አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር
ታረቅ፤ ከዚህም በኋላም ተመልሰህ መባህን አቅርብ።” /ማቴ፭፥፳፫‐፳፭፡፡/ በዚህ አንቀጽ
መሠዊያ እየተባለ የተገለጸው ታቦቱ መሆኑን አንባቢ ያስተውል:: በተጨማሪም /ማቴ
፳፫፥፲፰‐፳፫‐፴፭፣(፩ ቆሮ ፲፥፲፰፣ዕብ፲፫፥፲)።ያሉትን ጥቅሶች በማንበብ የመጀመሪያውን
አሳብ ማጠናከር ይቻላል።

ይህ መሠውያው በሰማያዊው መቅደስም እንኳን አለ። /ራእ ፮፥፱፤ ፰፥፫፤ ፲፩፥፩፡፡/ በራእ.
፲፩፥፲፱ ላይ ያለው ደግሞ በግብሩ ብቻ እንደላይኞቹ መሠውያ እያለ ሳይሆን እንደ
ፊተኛው /በብሉይ ኪዳን ይጠራ እንደነበረው/ በመጥራት ወንጌላዊው ዮሐንስ ያየውን
እንዲህ በማለት አስፍሮታል። “ከዚህም በኋላ በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ
ተከፈተ፣ የእግዚአብሔር የሕጉ ታቦትም በመቅደሱ ታየች፤ የመብረቅና የነጎድጓድ ድምፅ፥

178
የምድር መናወጥና ታላቅ በረዶም ሆነ።” እንዲል:: ምሥጢሩ ግን ያው እንደላይኛው
መሠውያ ማለትን ያስተረጉማል:: ለታቦትም ሲሰገድ፣ በታቦቱ አድሮ ድንቅ ሥራ
ለሚሠራው፣ ሥጋውንና ደሙን ለሚያምኑበት ሁሉ መድኃኒት አድርጎ ለሰጠው
ለእግዚአብሔር ነው የምንሰግደው፡፡ በሐዲስ ኪዳን ታቦት በምንልበት ጊዜ አማናዊት
ታቦት እመቤታችን ድንግል ማርያም አብራ ትዘከራለች። /መዝ ፻፴፩፥፰፡፡/ የብሉይ ኪዳን
መጻሕፍት ትርጓሜያት ታቦት የእመቤታችን ጽላት የልጇ (የክርስቶስ) በማለት
የሚያመሠጥሩትም ለዚህ ነው።

ሌሎች እኅት የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም የግብፅ፣ የሶሪያ፣ የአርመንና


የሕንድ ወገኖቻችን ወደ ክርስትና የመጡት በቀጥታ ከአሕዛባዊ ሕይወትና አኗኗር ነው::
ማንኛውንም የብሉይ ኪዳን ሕግ ትእዛዝና የቤተ መቅደስ አገልግሎት አያውቁም ነበር::
ወደ ክርስትና ሲገቡም በክርስትና ሕግና ትእዛዝ ጸንተው ወደፊት እንዲጓዙ ብቻ እንጂ
የኦሪትን ሕግና ሥርዓት እንዲጠብቁ ሐዋርያት አላዘዟቸውም፡፡ ተመረው ወደ ኋላ
እንዳይመለሱ በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ካራቱ ወሳኝ ሕግጋት በስተቀር እንዲተገብሩ
አልታዘዙም፡፡ (ሐዋ. 15) የአዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት (ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን)
ቅዱስ መሠውያ ብለው በመንበሩ ላይ ይሠዋሉ:: ምሥጢሩ ያው እኛ ታቦት (ጽላት)
ካልነው ጋር አንድ ነው:: በዚሁ መሠረት ታቦትንም እንደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
ሊከብሩበትና ሊያከብሩት አልቻሉም:: ዳሩ ግን እንደ መናፍቃን አያቃልሉትም፡፡ ከብሉይ
ኪዳን ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ በታቦት ተቀድሳና ዛሬም ትውፊቷን ይዛ በመገኘቷ
ያደንቃሉ እንጂ።

፲፩•፯ መስቀል

መስቀል የክርስቲያኖች የነጻነት ዓርማ፣ የድኅነትም መገኛ ነው:: ቀድሞ የእርግማን


ምልክትና የወንጀለኞች መቅጫ /ዘፍ፵፥፲፱፡፡/ የነበረው መስቀል ጌታችን በመስቀል
ተሰቅሎ በላዩ ላይ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ካከበረው በኋላ የሕይወትና የድኅነት
ምልክት ሆኖ ለሚቀበሉት የሰው ልጆች ሁሉ ተሰጠ። /መዝ ፶፱፥፬፡፡/ በዚህም መነሻነት
“መስቀል ኃይላችን ነው፤ መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው።…” /የዘወትር ጸሎት፡፡/ እያሉ
በማማተብ ምእመናን ይጸልዩበታል፡፡ የሰይጣንንም ወጥመድ ያከሽፉበታል። ክርስቶስ
አምላካችን የሐሰት አባት፣ ነፍሰ ገዳይና የዓመፃ ሁሉ መገኛ የሆነ ዲያብሎስን ቀጥቅጦ
ያስወገደው በመስቀል ነው:: በዚህም ምክንያት የቤተክርስቲያን ልጆች በእምነት ጸንተው
በመስቀል ምልክት ሲያማትቡና ስመ ሥላሴን መስቀሉን ሲጠሩ ሠራዊተ ዲያብሎስ
ይሸበራሉ፤ ከአካባቢያቸውም ፈጥነው ይሸሻሉ።

የተመሳቀለ እንጨት ወይም ብረት ሁሉ በየሜዳው ቢሠራና ቢተከል በክርስቶስ መስቀል


አምሳል የተቀደሰ መስቀል ሊሆን አይችልም:: የተቀደሰ መስቀል ይሆን ዘንድ
ቤተክርስቲያን ባባቶች ቡራኬ ካከበረችው በኋላ ነው ኃይለ እግዚአብሔር የሚገለጥበት
179
ቅዱስ መስቀል የሚሆነው፡፡ አባቶች ካህናትም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ምእመናን
እየገዙ /እያሠሩ/ የሚሰጡትን መስቀል በቅብዓ ሜሮንና (ዘይት) በጸሎት እያከበሩ
ለአገልግሎት የሚያዘጋጁት ለዚህ ነው፡፡ ታቦቱም እንኳን ቢሆን ቤተክርስቲያን
በፈቀደችለት አካል ከተዘጋጀ በኋላ በተመሳሳይ መልኩ በሊቃነ ጳጳሳት ከብሮ ነው ቅዱስ
መሠዊያ የሚሆነው፡፡ ምእመናንም የአንገት ማተባቸውንና መስቀላቸውን በካህናት
ማስባረክ እንዳለባቸው ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረው ለዚህ ነው።

ውድ አንባቢ ሆይ:- እስቲ ደግሞ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ

❖ መስቀሉን እንዴት ባሉ ቃላት ልትገልጹት ትችላላችሁ?

❖ ስንት ዓይነት መስቀል ታውቃላችሁ ምን? ምን?

❖ በጸሎት ወቅት በመስቀል ምልክት የምናማትበው መቼ መቼ ነው?

❖ መስቀሉን ስናይ አብሮ የሚታየን (የሚታወሰን) ምንድነው?

በአጠቃላይ መስቀል

፩. ምእመናነ ክርስቶስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የሚያስቡበት ነው::


/፩ዮሐ፫፥፲፮፡፡/

፪. ዲያቢሎስ ተመትቶ የተሸነፈበት የድል ዓርማ ነው። /፩ቆሮ፲፭፥፶፬‐፶፰።


ቆላ፪፥፲፬‐፲፮፡፡/

፫. ቅዱስ ሥጋው የተፈተተበት ክቡር ደሙም የተቀዳበት /የፈሰሰበት/ አማናዊ የዕለተ


ዓርብ መሠውያ ነው:: /ማቴ ፳፮፥፳፮‐፴፡፡/

፬. የጌታችንን ውለታ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለክርስቲያኖች ሁሉ እናት


ሆና መሰጠቷን የምናስብበት ነው:: /ዮሐ ፲፱፥፳፭‐፳፰፡፡/

፭. በሰው በደል ተዘግቶ የነበረው የገነት ደጅ የተከፈተበት የምሥጢር ቁልፍ ነው።


/ዘፍ፫፥፳፪‐ፍጻሜው። ሉቃ፳፫፥፵፫፡፡/

፮. ካህናትና ምእመናን መንፈሳዊ ኃይል የሚያገኙበት የክርስቶስ ስጦታ ነው።


/፩ቆሮ፩፥፲፰፡፡/

፯. አዳም ከነልጆቹ ከሲዖል ረግረግ ነጻ የወጣበት የሕይወት መሰላል ነው። /ኤፌ ፪፥፲፬፡፡/

፰. የክርስቲያኖች ሁሉ ምርኩዝ፣ የዚህን ዓለም የፈተና ማዕበል የሚሻገሩበት አስተማማኝ


(መርከብ) ድልድይ ነው። /ገላ፮፥፲፬፡፡/

180
፱. ካህናትና ምእመናን መውጣት መግባታቸውን (መንገዳቸውን)፣ ምግባቸውንና
መጠጣቸውን፣ ሥራቸውንና ኑሮአቸውን ሁሉ የሚያስባርኩበት መንፈሳዊ መሣሪያና
የመጽናናት ምልክት ነው።

ይኸውም፦

ሀ. ስመ እግዚአብሔርን “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ” እያሉ


በመጥራት በመስቀል ምልክት በጣታቸው እያማተቡ የሚጠቀሙበት መንፈሳዊ መሣሪያ
ነው:: በዚህም ምሥጢረ ሥላሴን ከነገረ መስቀሉ ጋር አገናዝበው መመስከራቸውን
ያሳያል። በጸሎትም ወቅት ጸሎታቸውን ሲጀምሩ፣ የመስቀሉን ስም ከሚያነሣ አንቀጽ
ሲደርሱ፣ ሕሊናቸውን የሚረብሽ ክስተት ሲገጥማቸውና ጸሎቱን ሲያጠቃልሉ በመስቀል
ምልክትና በስመ ሥላሴ ያማትባሉ።

ለ. በመስቀል ምልክት እያማተቡ ነገረ ድኅነትን /ምሥጢረ ሥጋዌን/ ይመሰክሩበታል።


ከላይ ወደታች እያማተቡ ሲወርዱ ወልደ እግዚአብሔር በተለየ አካሉ፣ በተወላዲነት ግብሩ
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም መወለዱን፤

ከግራ ወደ ቀኝ ሲያማትቡ ከሲኦል ባርነት መውጣታቸውን ወደ ገነት መግባታቸውን


ይመሰክሩበታል።

ሐ. መስቀል ከሰይጣን ፍላፃ ለመዳን፣ ሰይጣንን ለማራቅና በረከትን ለማሳደር


ከእግዚአብሔር የተሰጠ ምልክት በመሆኑ እያማተቡ ይባርኩበታል። /ዘፍ ፵፰፥፰‐፲፮፡፡
መዝ፶፱፥፬።/

የመስቀል ዓይነቶች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት መስቀልን


ከአገልግሎቱ አንጻር ከፋፍለን ስናየው የሚከተለውን ይመስላል።

፩. የመጾር መስቀል፦ በቅዳሴና በማዕጠንት (ጸሎተ ዕጣን) ጊዜ ሠራዒው ዲያቆን


የሚያገለግልበት /የሚይዘው/ ነው።

፪. የእጅ መስቀል፦ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳትና ቀሳውስት ዘወትር
የሚይዙትና ምእመናንን የሚባርኩበት ነው።

፫. የአንገት መስቀል፦ ምእመናን በአንገታቸው አስረው ነገረ መስቀሉንና የክርስቶስን


ፍቅር የሚስቡበት (የሚዘከሩበት) ነው።

፬. እርፈ መስቀል፦ ሠራዒው ዲያቆን ክቡር ደሙን ለቆራቢያን የሚያቀብልበት ነው።

ከሚሠሩበት ንዋይ አንጻር ሲታይ ያለው ምሥጢር

181
የእንጨት መስቀል፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ፯ ዓይነት ዕፅዋት
በተዘጋጀ መስቀል የመስቀሉ መታሰቢያ ነው::

የብረት መስቀል፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአምስት የብረት ቅንዋት


(ችንካር) ማለትም ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራና ሮዳስ የመቸንከሩ መዘከሪያ ነው።

የብር መስቀል፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይሁዳ በ፴ ብር ለአይሁድ አሳልፎ የመሸጡ


(የመስጠቱ) መታሰቢያ ነው።

የወርቅ መስቀል፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንጽሐ ባሕርይ አምላክ የመሆኑ ማዘከሪያ
ነው።

የመዳብ መስቀል፦ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ መፍሰስ ዓለምን የማዳኑ
/መዳብ ቀይ ነውና/ ማስታወሻ ነው።

መስቀል ከቅርጹ አንጻር ሲታይ በቤተ ክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ ጥቅም /አገልግሎት/
ላይ የዋሉ የመስቀል ዓይነቶች ደግሞ እንደሚከተለው ሆነው ሊዘረዘሩ ይችላሉ።

• ቀርነ በግዕ መስቀል፣

• ዕፀ ሳቤቅ መስቀል፣

• አርዌ ብርት መስቀል ፣

• ጽጌ ደንጎላ መስቀል፣

• ቀራንዮ /ሐዋርያ/ መስቀል፣

• ዓምደ ዓለም መስቀል፣

• ልሳነ ከለባት መስቀል፣

• ትእምርተ ክዋክብት መስቀል፣

• ትምእርተ ንትፈት መስቀል፣

• እሳተ ገቡእ መስቀል፣

• ዕፀ ስርናይ መስቀል፣

• ለንጊኖስ መስቀል፣እና

• ሐረገ ወይን መስቀል በመባል ይታወቃሉ።

በእንደዚህ ያለ ኅብሩና ዓይነቱ /ቅርጹ/ በበዛ ሁኔታ መስቀልን እያዘጋጁ መጠቀማቸው ግን


ነገረ መስቀሉን /ሕማማተ መስቀሉን/ በልዩ ልዩ መንገድ ለማሰብ መሆኑ ልብ ሊባል
182
ይገባዋል። ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረውም በዓይነ ሥጋ መስቀሉን፣ በዓይነ ሕሊና ደግሞ
የተሰቀለውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን እያየን በመስቀሉ ፊት እንሰግዳለን። “እንግዲህስ
ወደ እግዚአብሔር ማደሪያዎች እንገባለን፤ የጌታችን እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ
እንሰግዳለን።” /መዝ ፻፴፩፥፯፡፡/ በማለት የገለጸው ይህን ያጠይቃል። የእግዚአብሔር
ማደሪያዎች ያለው አብያተ ክርስቲያናትን ሲገልጽ የጌታችን እግሮቹ የሚቆሙበት ቦታ
የተባለው መካነ ስግደት ደግሞ የክርስቶስ አካሉ የሆነች ቤተክርስቲያንንና /ኤፌ ፭፥፳፫፡፡/
ሥጋውን ለቆረሰበት ደሙንም ላፈሰሰበት መስቀል /ቆላ፩፥፳፡፡/ ሆኖ ይተረጎማል::
ምእመናን በቤተ ክርስቲያንና በመስቀሉ ፊት ለእግዚአብሔር የባሕርይ፤ ለቤተ
ክርስቲያንና ለመስቀሉ ደግሞ የጸጋ ስግደት ያቀርባሉ። መስቀል ታላቅ የፍቅር ምልክት
በመሆኑ ጌታችን ደጋግሞ ክርስቲያኖች መስቀሉን ተሸክመው እንዲከተሉት አስተምሯል።
/ማቴ ፲፮፥፳፬‐ፍጻሜው፡፡/ ሐዋርያት፣ ሐዋርያውያን አበው፣ ቅዱሳን የቤተክርስቲያን
ጠበቆችና ሊቃውንት እንዲሁም ጻድቃንና ሰማዕታት ሁሉ ይህን አምላካዊ የፍቅርና
የሕይወት ጥሪ ተቀብለው (መስቀሉን ተሸክመው) በመጋደል ከብረውበታል።

ማጠቃለያ
በዚህ ዓለም ላይ አንድ ሰው የወላጆቹ ልጅ መሆኑ ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ
የወላጆቹን አኗኗራቸውን በወጉ የተረዳ መሆኑና የውጪውንና የውስጡን ንብረታቸውን
ሰፍሮ ቆጥሮ ማወቅ፣ መጠበቅና መጠቀም ሲችል ነው፡፡ ወላጆቹ እስካሉ አብሮአቸው
ይጠቀማል፤ ባረፉ ጊዜም እንዳየና እንደሰማ ሕይወታቸውንና የእነሱ የሆነውን ሀብታቸውን
ወርሶ ይኖራል፡፡

የቅድስት ቤተክርስቲያን አባል የክርስቶስ አካል የተባሉ ክርስቲያኖችም ቤተ


ክርስቲያናቸውንና የቤተ ክርስቲያን የሆኑትን መንፈሳውያን ሀብቶቿን ከባሕሪያቸው
ከአጠቃቀምና አፈጻጸም ሥርዓታቸው ጋር ጠንቅቀው ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንንም
ከቅዱሳት መጻሕፍት ገበታዎች (ሠሌዳዎች) እና በቤተ ክርስቲያን አባቶች እግር ሥር
በመቀመጥ ከአንደበታቸው መማር ይችላሉ፡፡ እስካሉ ድረስ ከእነሱ ጋር አምላካቸውን
እያመለኩ ይኖራሉ፡፡ በዚህ ረገድ ይህንን ምዕራፍ ያነበቡ ወገኖች ቤተ ክርስቲያናቸውን
ከሀብቶቿ ጋር ለማወቅ የሚያስችል ዕውቀት እንዳገኙባት ይታመናል፡፡ ቀሪው ጉዳይ
በተገኘው መንፈሳዊ ዕውቀት መሠረት ራስን ማስተካከልና ትክክለኛውን መንፈሳዊ ኑሮ
ለመኖር መታገል ለሌሎችም መመስከር መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን::

183
ዋቢ መጻሕፍት
• የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜው፤ትንሣኤ
ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፺፤ አ/አ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ


ማኀበር፤ ፳፻፤ አ/አ።

• ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፤ EAMERSEN፤


2000፤ አ/አ።

• ዲ/ን ሰሎሞን ወንድሙ፣ መሪጌታ ዘወንጌል ገ/ኪዳንና ዲ/ን ዝናዬ


ኃ/ማርያም፤ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ፤ ማኀበረ ቅዱሳን፤ ፲፱፻፺፮፤
አ/አ።

• ሊ/ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኘ፤ ሥርዓት ወምሥጢራት ዘቤተ


ክርስቲያን ተዋሕዶ፤ 2006፤ አዲስ አበባ።

• የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ ትንሣኤ


ማሳተሚያ ድርጅት፤ ፲፱፻፹፰፤ አዲስ አበባ።

184
• ክርስቲን ሻዮ፤ መ/ሰ ዳኛቸው ካሳሁን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤ/ክ ትውፊትና መንፈሳዊ ሕይወት፤ ማኅበረ ቅዱሳን
1999፤ አ/አ።

• መምህር አንዱዓለም ዳግማዊ፤ ነቅዐ ሕይወት፤ ሚያዝያ 2002


አ.አ።

ማጠቃለያ ፦
ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራኒዮ አደባባይ ሥጋውን ቆርሶ ፥ ደሙን
አፍስሶ ዓለሙን ሁሉ አዳነ። በመዋዕለ ሥጋዌው ድውያነ ሥጋን በተአምራት ፥ ድውያነ
ነፍስን ደግሞ በትምህርት እየፈወሰ በምድረ እስራኤል ተመላለሰ። በዚህም ምሥጢራትን
በመመሥረት ሥርዓታቸውንም አከናውኖ ቤተ ክርስቲያንን አደራጀ። ከትንሣኤው በፊት
ያስተማረው ትምህርት፣ የሠራው ተአምራት “ወንጌል” ሲባል ከትንሣኤው በኋላ ያስተማረው
ትምህርት ደግሞ “ኪዳን” ይባላል። ሞትን በሞቱ አጥፍቶ ከሲዖል ባርነት ከሠይጣንም
ቁራኝነት የሰውን ልጅ ነጻ ቢያደርገውም “ነጻ ወጥቻለሁ!” ብሎ እንዳሻው እንዲኖር ግን
አልተፈቀደለትም።

መድኃኔዓለም ክርስቶስ የሰውን ልጅ በቤዛነቱ ሲያድነው በአርአያነቱ (ሠርቶ በማሳየቱ)


ደግሞ በክርስትና ሕይወት እንዴት መመላለስ እንዳለበት አሳይቶታል። ቅድስት
ቤተክርስቲያናችን ክርስቲያኖች የክርስቶስ አካል፥ የቤተ ክርስቲያን አባል እንዴት
እንደሚሆኑ፣ መቼ እንደሚሆኑ፥ የት እንደመሚሆኑ፥ ለምን እንደሚሆኑ… ወዘተ የታወቀና
የተረዳ ትምህርት አላት። “ስንዱ እመቤት” ከሚያሰኟት ቁም ነገሮች አንዱም ይህ ነው።
ክርስቶስ የሠራት መንፈሳዊት ቤት እንደማንኛውም ተራ (ባዶ) አዳራሽ ዓይነት
አይደለችም። “ቤተክርስቲያኒቱ የእውነት ዐምድና የሕያው እግዚአብሔር ቤት ናት።”
185
(፩ጢሞ ፫፥፲፭) ፍሪዳዋ (ክርስቶስ) በፈቃዱ የተሠዋላት፣ ሥጋውን አወራርዳ፣ ደሙንም
ቀድታ ለልጆቿ ያዘጋጀች ጠንቃቃ እመቤት ነች። (ምሳ ፬፥፩-፫፡፡)

ይህች ቅድስት ቤተክርስቲያን አገልጋዮቿን ልካ ከማዕዷ ይበሉ ዘንድ፥ ከወይን


ጠጇም ይጠጡ ዘንድ ዘወትር የሰው ልጆችን ሁሉ ትጋብዛለች። በጥላው ሥር እንዲጠለሉ፣
ለድካማቸውም ሰባቱን ምሰሶዎች (ምሥጢራት) እንዲደገፉና እንዲያርፉ ትጣራለች።
እንዲህ እያለች:- “አላዋቂ የሆነ ወደ እኔ ይምጣ” አእምሮ የጎደላቸውንም እንዲህ አለች፦
“ኑ እንጀራዬን ብሉ፤ የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ፤ ስንፍናን ትታችሁ
በሕይወት ኑሩ፥ በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን ፈልጉ፥ በመረዳትም ዕውቀትን
አቅኑ።” (ምሳ ፱፥፫‐፯፡፡)

የተከበሩ የዚህ መጽሐፍ አንባቢ ሆይ እንዳዩትና እንዳነበቡት ሁሉ ይህ መጽሐፍም


ይህን የቤተክርስቲያን ተልዕኮና ጥሪ የተሸከመ ነው። መጽሐፉ የቤተ ክርስቲያንን
ሁለንተናዊ (የውጪና የውስጥ) ማንነትና አገልግሎት ለማሳየት ሞክሯል። በየምዕራፎቹ
ዐቢይ ዓላማዎች ለመግለጽ እንደተሞከረው መጽሐፉን አንበው ከጨረሱ በኋላ ሦስት
መሠረታዊ ለውጦችን አሳይተው እንደሆነ ራስዎን ይጠይቁ። እነዚህም የሚጠበቁት
ውጤቶች የዕውቀት፣ የአመለካከትና የክህሎት ለውጦች ናቸው። እግዚአብሔር
አምላካችን በሚገባ ዐውቀንና በቀና አመለካከት ታንፀን እንድንመለስና የተማርነውን ሁሉ
በሕይወት እንድንኖረው ይፈልጋል:: በዚህ መስመር ብቻ ነው የመንግሥቱ ወራሾች፥
የርስቱም ተቋዳሾች መሆን የምንችለው። አምላካችን ደግሞ ከሰማያዊ መንግሥቱ ውጪ
እንድንሆንበት አይፈልግም።

ስለዚህ ከላይ እንደተናገርነው መጽሐፉንና በዋቢነት የተጠቀሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን


ደጋግመን በማንበብና ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን (ከመምህራን) በመማር “የቀረኝ
የጎደለኝ ምንድነው?” እያሉ ራስን መመርመር አስፈላጊ ነው። የቀረውን /የጎደለውንም/
ጊዜ ሳይሰጥ በፍጥነት ማስተካከልና ማሟላት ከአንባቢያን ይጠበቃል። አበው እንደሚሉት
“ከብዙ ቃል (ዕውቀት) ይልቅ አንዲት ተግባር /ሥራ/ የበለጠ መጮህ ትችላለች።” እና
በታወቀውና በተረዳው መጠን እየኖሩ ለማደግ መታገል ይገባል። መረሳት የሌለበት ጉዳይ
ሰው የሚድነው ቅዱስ ቃሉን በመስማት አምኖ፤ ምግባራት ሠናያትን በመሥራትና
የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተሳታፊ በመሆን ነው። እግዚአብሔር አምላካችን በዚህ
መስመር በመጓዝ፣ ስሙን በመቀደስ፣ ክብሩንና መንግሥቱን እንድንወርስ የበቃን
ያድርገን፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳንና አማላጅነት የቅዱሳን
ሁሉ በረከትና ረድኤት በሕይወት ዘመናችን ሁሉ አላባሽ ጋሻ ይሁነን ለዘለዓለሙ አሜን።

186

You might also like