Professional Documents
Culture Documents
ማኅበረ ቅዱሳን
የወላይታ ሶዶ ማዕከል
ምስጋና (Acknowledgement)
በቅድሚያ በጅማሪም በፍጻሜ የማይለይ እንዲሁም ያለተለየኝ የምሥጢራት እና የሥርዓት ሁሉ
መሠረት እና ባለቤት፤ ከሃያ ሁለቱ ሥነ- ፍጥረታት አልቆ፣ አስውቦ፣ ለርስቱ ለመውረስ
ከሰባቱ ባሕርያት ለፈጠረው ለሰው ልጅ ምሥጢራትና ሥርዓትን ያደለ ለልዑል እግዚአብሔር
አምጣ ወልዳ እርሷም አሳድጋ ብርሃን የሰጠችን የድነታችን መሠረት፣ የብርሃን መገኛ ምሥራቅ
ለንጽሕተ ንጽኋን፣ ለቅድስተ ቅዱሳን፣ ወላዲተ አምላክ፣ ለቅድስት ድንግል ማርያም
የእኛን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የእግዚአብሔርን ምኅረት ወደ እኛ የሚያመጡ ቅዱሳን በሙሉ
ደከመኝ ሰለችኝ ሳይሉ ቤታቸውን ጥለው ከእኛ ጎን በመሆን በሀዘን በደስታችን ላልተለዩን
ምክራቸውንና ተግሳጻቸው ዘወትር ለሕይወታችን ብርሃን ለሆነው ለዋዱ ቁስቋም ማርያም
ቤተክርስቲያን አባቶች ካህናት በሙሉ
ወጣቱን በነጣቂ ተኩላዎች እንዳይበላ ግቢ ጉባያትን በማቋቋም ዘወትር ጠዋትና ማታ መንፈሳዊ
ማዕድን በመዘርጋት ሌተ ቀን ለሚተጋው ማኅበረ ቅዱሳን
ዘወትር ስብከትን በማዘጋጀት እና መጽሐፍትን በመጻፍ፣ በጉባኤ፣ በማኅበራዊ ሚዲያና እና
ድረገጾች ለምታስተምሩ እና አፋጣኝ ምላሽ ለምትሰጡ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን
መግቢያ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ነገር ቢኖር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና
ትምህርቴን ስከታተል ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በዓለም ወጥመድ ገብቼ እንዳልቀር እና ሰው
መሆኔን እንዳልረሳ በዋናው ግቢ ጉባኤ በዋዱ ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ
ሕይወትን እየመገቡኝ ቆይቻለሁ፡፡ በዚህም ቆይታዬ መካከል በአገልግሎት ተመሳስለውን የነበሩ ነገር
ግን ከኛ የተለዩ ወገኞች በሥርዓተ እና በምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ዙርያ የማደናገርያ ጥያቄዎች
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንቁ ፍሬዎች ሲጠይቋቸው እና ብዙዎቹም በጥያቄያቸው እየተደናገሩ
ሃይማኖታቸውን ሲክዱና ሲቀይሩ በመመልከቴ፡፡ አንድም ምዕመናንም ሥርዓተ እና ምሥጢራተ
ቤተክርስቲያንን ባለመጠንቀቅ (ባለማወቅ) ሲስቱ በመመልከቴ፡፡ በተጨማሪም በ2011ዓ.ም ለሁለተኛ
ዓመት ለዩኒቨርስቲ ለአሮቶዶክስ ተዋሕዶ ተማሪዎች የቤተክርስቲያን ምሥጢራት እና ሥርዓት
የሚለው ኮርስ እያስተማርኩኝ ነበርና ኮርሱ በሀንዳውት መልክ ለማዘጋጀት አስቤ ነው፡፡ በተለይ
ደግሞ ብዙዎች ወቅታዊ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ የያዙ መጽሐፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ እና
በፈለጉት ቦታ ባለማግኘታቸው መልስ ለመስጠት እየተቸጋገሩ ስለሆነ ምንአልባት ልታግዛቸው
ትችላለች በሚል አስተሳሰብ ለማዘጋጀት ተነሳሳሁኝ፡፡ ለዚህም እንዲረዳኝ በማኅበረ ቅዱሳን
የተዘጋጀው የኮርሱ መጽሐፍ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ በተለያየ ቦታ አና ጊዜ ለሚነሱ ጥያቄዎች
መልስ ይሆን ዘንድ ከቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ካስተማሯቸው መጻሕፍቶች፣ ከሰበኳቸው ስብከቶች
እና ከለቀቋቸው ከድረገጽ ጹሑፎች እንዲሁም ከተለያየ ጊዜ ከተማተርኳቸው ኮርሶች መካከል
ወሰድኩኝ፡፡ በተጨማሪም መንፈሳዊ ወንድሜ ወንድማገኝ ጥላሁንን በመጠየቅ ይህን ጽሑፍ ወደ
ተንቀሻቃሽ ስልክ መተግበሪያ (Mobaile APP) ቀይሮልኛል፡፡ ስለሆነም ውድ አንባቢያን ሆይ በዚህ
ጹሑፍ ብቻ ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ ላታገኙ ትችላላችሁና የተለያዩ የሊቃውንት እና የመምህራነ
ቤተክርስቲያን መጽሕፍትን ለይተን በመመልከትና በማንበብ እንድታዳብሩ በተለይ ደግሞ በአሁኑ
ሰዓት የቤተ ክርስቲያን የብብት እሳት የሆኑባትን ተሐድሶ መናፈቃን አና የአሕዛብ ጥያቄ መልስ
በመስጠት እንድትመክቱ እያልኩኝ በእግዚአብሔር ስም እማጸናችኋለሁ፡፡ በቀጣይ የቅዱሳን አምላክ
ቅዱስ እግዚአብሔር ዕውቀት፣ ጥበብና ማስተዋሉን ቢገልጽልን ወላዲተ አምላክ ጥላ ከለላ ብትሆነን
በሌላ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በሰፊው እንገኛኛለን ብዬ አስባለሁኝ፡፡ አስከዛው ሠላመ እግዚአብሔር
አይለየን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ይህ ጽሑፍ ግድፈት፣ ደሀጸ ብታገኙበት ፈጥኜ ስጽፈው ስቼ ነውና አርሙኝ፡፡ ሐሳብ
አስታያት ጥያቄ ካላችሁ በአድራሻዬ አግኙኝ፡፡
መልካም ንባብ!!!
አዘጋጅ ዲያቆን አሸናፊ ወልደኢየሱስ
መቅድም (Abstract)
“አንተም ሁነህ አስተካክለው” (አቡነ ጎርጎርዮስ) ቅድስት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም
ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ ለልጆቿ ቅዱስ ቃሉን እየመገበች ምሥጢራትን እየፈጸመችና
በሥነ ምግባራት ሠናያት እያነፀች ባሕረ ዓለምን ቀዝፋ ወደ ዕረፍት ወደብ እያሻገረች
/እያደረሰች/ የምትገኝ መንፈሳዊት መርከብ ናት፡፡ ይኽችም በኢየሩሳሌም (በጸኑት)፣ በይሁዳ
(አምነው፤ እየወደቁና እየተነሡ በሚታገሉት) ፣ በሰማርያ (አምነው በካዱት) እና በምድር
ዳርቻ (ፈጽመው ባላመኑት) መካከል በምታደርገው ሐዋርያዊ አገልግሎት የምትመራበት
መንፈሳዊ ሥርዓትም ባለቤት ናት። እግዚአብሔር አምላካችን በሰዎች መካከል ማደር
በፈለገ ጊዜ በሰማይ ባለ መቅደሱ አምሳል ደብተራ ኦሪትን እንዲሠራ ሙሴን አዘዘው።
(ዘጸ፳፭፥፰፳፰) ንዋያተ ቅድሳቱና ሥርዓተ ደብተራ ኦሪቱም በዚያው አምሳል የተከናወነ
እንዲሆን ፈቀደ፡፡ “ፊተኛይቱም ደግሞ የአገልግሎት ሥርዓትና የዚህ ዓለም የሆነው መቅደስ
ነበራት” (ዕብ ፱፥፩) መቅደሰ ሰሎሞንም በደብተራ ኦሪት አምሳል ሲሠራ ድንኳኑ ሕንፃ
ከመሆኑ በስተቀር ንዋየ ቅድሳቱና ሥርዓቱ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ
በተፈጸመበት ወቅት ንጉሥ ሰሎሞን የእስራኤልን ጉባኤ በመረቀበት አንቀጽ “በመንገዱም
ሁሉ እንሄድ ዘንድ ለአባቶቻችንም ያዘዛትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን እንጠብቅ ዘንድ ልባችንን
ወደ እርሱ ይመልስ።” (ነገ ቀዳ ፰፥፶፰) በመቅደሰ ሰሎሞን ይፈጸም የነበረው ሥርዓተ
አምልኮ አባቶቻቸው በደብተራ ኦሪት ይፈጽሙት በነበረው ሁኔታ መቀጠሉን ያሳያል።
ቤተክርስቲያንም በመቅደሰ ሰሎሞን አምሳል ተሠርታለች። ይህም ውጭያዊ የሕንፃ
አሠራሯን ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ የአምልኮ ሥርዓቷን ሁሉ የተመለከተ ነው። ከሥርዓት
ውጪ እንዳሻቸው በመሄድ ቤተ ክርስቲያንን የሚያውኩትንም “ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን
ገሥጹአቸው” ፤ (፩ተሰ፭፥፲፬)። “ወንድሞቻችን ሆይ በሠራንላችሁ ሥርዓት ሳይሆን በተንኮል
ከሚሄዱት ወንድሞች ሁሉ፥ ትለዩ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን። በማለት
ማስተማሩን ማስተዋል ይገባል ደገኛውን ሥርዓት ይዞ መጓዝ እንደሚገባም” አሁንም
ወንድሞቻችን ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን
ያስተማርናችሁንና የሠራንላችሁን ሥርዓት ያዙ” (፪ተሰ ፪፥፲፭) በማለት አሳስቧል።
ቤተክርስቲያን በየጊዜው የፈጸመችውና የምትፈጽመው መንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ
ሥርዓትን በመከተል የተከናወነና የሚከናወን መሆኑ ግልጽ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱ
ሁለንተናዊ ሕይወት የሆነው ይህ ሥርዓተ አምልኮ ሳይበረዝና ሳይከለስ፣ ሳይጨመርበትና
ሳይቀነስለት እንዲጓዝ ለማድረግ ካህናት ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን የበኩላቸውን
(የድርሻቸውን) ማበርከት ይጠበቅብናል፡፡ ምክንያቱም ዲያቆኑ ሀቢብ ጊዮርጊስ ፓትርያሪኩን
አቡነ ሺኖዳን አስገኘቷልና፡፡
ማውጫ
ምስጋና (Acknowledgment) ........................................................................................ II
መቅድም (Abstract) .................................................................................................... III
1. አንቀጸ መድኃኒት ቤተ ክርስቲያን .............................................................................. 1
1.1 የቤተ ክርስቲያን የቃሉ ትርጉም .......................................................................... 1
1.2 የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት .............................................................................. 2
1.3 የቤተ-ክርስቲያን ዓላማ ........................................................................................ 3
1.4 ቤተ ክርስቲያን የማን ነች? ለማን ተሰጠች? ......................................................... 3
1.5 የቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊነት .......................................................................... 3
1.6 ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ዕምነቶች የሚለያት ......................................................... 4
1.7 የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት ................................................................................... 4
1.8 የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በሐዲስ ኪዳን .................................................................. 9
1.9 የሕንጻ ቤተ እግዚአብሔር አጀማመር ................................................................. 10
1.10 የቤተክርስቲያን ሥሪት .................................................................................... 11
1.11 የሕንጻ ቤተክርስቲያን አተካከል ........................................................................ 14
1.12 የሕንጻ ቤተ-ክርስቲያን አሰራር (ዲዛይን) ........................................................... 14
1.13 የቤተ መቅደስ ክፍሎች.................................................................................... 15
1.14 በቤተ ክርስቲያንና በዙሪያዋ የሚገኙ /የማይንቀሳቀሱ/ ንዋያተ ቅድሳት ............... 16
1.15 በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰሩሌሎች ቤቶች.................................................... 18
1.16 ቤተ ክርስቲያን ስትባረክ .................................................................................. 18
1.17 ለምን ወደ ቤተክርስቲያን እንሔዳለን? .............................................................. 19
2. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ......................................................................................... 21
2.1 ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የቃሉ ትርጉም ............................................................. 21
2.2 የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት .................................................................... 21
2.3 የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነት ................................................................ 22
2.4 የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጮች ................................................................... 23
2.4.1 መጽሐፍ ቅዱስ .......................................................................................... 23
2.4.2 ሐዋርያት የሠሯቸዉ የሥርዓት መጻሕፍት ................................................. 28
2.5 Passion week ሰሙነ ሕማማት ...................................................................... 30
2.6 በበዓለ ሃምሳ ንስሓ ለምን ተከለከለ? .................................................................. 32
2.7 የሰሙነ ሕማማት ሥርዓት ............................................................................... 34
2.8 የዐብይ ጾምሥራዓት ከሌሎች አፅዋማት ለምን ተለየ? .......................................... 36
9.4 በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ክህነት መካከል ያለ ልዩነት ................................ 162
9.5 የክህነት ሥልጣን ደረጃዎች ............................................................................. 162
9.6.1 ሥርዓተ ሲመተ ኤጲስ ቆጶስ ..................................................................... 164
9.6.2 ሥርዓተ ሲመተ ቀሳውስት ........................................................................ 167
9.6.3 ሥርዓተ ሲመተ ዲያቆናት ........................................................................ 168
9.7 የቤተ ክርስቲያን አባቶች አገልግሎታቸውን በአግባቡ እንዲፈጸሙ ...................... 169
9.8 የቤተ ክርስቲያን አባቶች በፈተና ቢወድቁስ? ..................................................... 170
9.9 ሊቀ ካህናት አለን ሲል ምን ማለቱ ነው ........................................................... 173
9.10 ሴቶች ለምን ካህናት አይሆኑም? ................................................................... 174
9.11 ምሥጢረ ክህነት የሚያስገኘው ጸጋ................................................................ 175
10. ምሥጢረ ቀንዲል .............................................................................................. 177
10.1 የምሥጢረ ቀንዲል የቃሉ ትርጉም ................................................................ 177
10.2 የምሥጢረ ቀንዲል አመሠራረት .................................................................... 178
10.3 የምሥጢረ ቀንዲል አፈጻጸም ........................................................................ 179
10.4 በየብልቃጡ እየተሞላ የሚሸጠው “ዘይት” ምስጢረ ቀንዲልን ይተካልን? .......... 180
10.5 ምሥጢረ ቀንዲል የሚያስገኘው ጸጋ .............................................................. 180
ማጠቃላያ (ምክረ አበው) ........................................................................................... 183
በአጠቃላይ ቤተ-ክርስቲያን፡-
በክርስቶስ ደም በቅዱስ ጴጥሮስ የምስክርነት ቃል ዐለት ላይ ተመስርታለች
በምድር ያለች የእግዚአብሔር ቤተ-መንግስትና የፀጋዉ ግምጃ ቤት ናት
ምዕመናንን ከእግዚአብሔር ጋር የምታገናኝ ድልድይ ናት
ለመጀመሪያ ጊዜ በፊልጵስዮስ የተመሰረተች ናት
ከመላዉ ዓለም በጥፋት ዉስጥ ያሉትን የምትዋጅ የድነት ወደብ መርከብ ናት
ለሰው እምነቱ የማያድነው ከሆነ ደግሞ እምነቱ ትክክል አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ
ትክክለኛው እምነትና ትክክለኛው አምልኮተ እግዚአብሔር የቱ ነው ወይም የኦርቶዶክሳዊነት
መገለጫዎች ምን ምን ናቸው የሚለውን ጥያቄ እንድናነሣ ቤተ ክርስቲያን ተብላ
የምትጠራው አካለ ክርስቶስም እነዚህን ማሟላት አለማሟላቷን ለመመርመር እንገደዳለን፡፡
ለምን ይህ ከሌለ ያች ቤተ ክርስቲያን አካለ ክርስቶስ ሳትሆን እንደ ማንኛውም ሰዎች
የሚያቋቁሟቸው ተቋማት ድርጅት ብቻ ትሆናለችና፡፡ ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን
ስንል ኦርቶዶክሳዊነትን ገንዘብ ያደረገች አካለ ክርስቶስ ማለት ነው፡፡ አካለ ክርስቶስ ከሆነች
ኦርቶዶክሳዊ ናት፤ ኦርቶዶክሳዊ ሆና አካለ ክርስቶስ ያልሆነች የለችም፤ ልትኖርም
አትችልም፡፡
በበዓለ ሃምሳ ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነውን (የቅድስና ባለቤት) መንፈስ ቅዱስን
በተቀበለች ጊዜም ፈጽሞ ቀድሷታል፡፡ የቅዱስ እግዚአብሔር የተቀደሰች ማደሪያው
በመሆኗም የቅድስናና የጸጋው ሁሉ መዝገብ ለመሆን ችላለች፡፡ የአገልጋዮቿ (የአባላቷ)
በኃጢኣት መሰነካከል ቅድስናዋን አያረክሰውም፤ መንፈሳዊ ውበቷንም አያቆሽሸውም ፡፡
ይልቁንም እነሱን በንስሐ አንጽታ ወደ ቀደመ ክብራቸው እንዲመለሱ በቅድስና
ታከብራቸዋለች፡፡ ለእርሷ የሚቀርበው መሥዋዕትና አገልግሎት ሁሉ የተቀደሰ ነው፡፡ “እርሱ
የቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፋዊነት ኲላዊነት ከቦታ አንጻር ብቻ የሚታይ ሳይሆን ከጊዜም
አንጻር የሚብራራ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በቦታ ብቻ ሳይሆን በጊዜም የማትወሰን በመሆኗ
በብሉይ ኪዳን የነበሩትን አበውና እማት ጨምሮ ከሐዋርያት ጀምሮ እስከ ምጽአት ያሉትን
ምእመናን ልጆቿን ሁሉ አካታ /ሁሉንም በማጠቃለል/ የያዘች እናት ናት፡፡ የቤተ ክርስቲያን
አባሎቿ በሁለት ይከፈላሉና፡፡ የመጀመሪያዎቹ በአጸደ ሥጋ ያሉት ተዋጊዎች፣ ሰልፈኞች
የሆኑት ሲሆኑ፤ ሁለተኞቹ ደግሞ በአፀደ ነፍስ የሚገኙ አሸናፊዎች፣ ድል አድራጊዎች
የሆኑት ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት የቤተ ክርስቲያን ኲላዊነት በሰማይም በምድርም፣
በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም ያሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል መሆኑን ማስተዋል ይገባል፡፡
ከላይ እንደገለጽነው የቤተ ክርስቲያን መሥራቿና ራሷ ክርስቶስ በሰማይ፣ በምድርና
በሁሉም ቦታ ይኖራል፡፡ እሱ የሌለበትና የማይኖርበት ቦታ እንደሌለ (እንደማይኖር) ሁሉ
አካሉ ቤተ ክርስቲያንም የሌለችበትና የማትኖርበት ቦታ አይኖርም፡፡
፩. ገዳም
፪. ደብር፦
፫. ገጠር
የቤተ መቅደስ ክፍሎች ቅኔ ማህሌት፣ ቅድስትና መቅደስ ሲባሉ እነዚህ ክፍሎች ጎልተው
የሚታዩት ክብ ቅርጽ ባላቸው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም የቤተክርስቲያን
የውስጥ ክፍሎች ሦስት ናቸው ፡፡ የእነዚህም ምሳሌነታቸው
ሐ. መቅደስ፡- በብለይ ኪዳን ቅድስተ ቅደሳን ከሚባለው ጋር የሚነጻር ነው፡፡ የቃል ኪዲኑ
ታቦት በክብር ያርፍበታል፡፡ ሌሎች ነዋያተ ቅድሳት ይቀመጡበታል፡፡ ስልጣነ ክህነት
ካላቸው በስተቀር ማንም መግባት አይችሉም፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዓን
ሊቀጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ያስቀድሱበታል፡፡ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ሶስት በሮች
ሲኖሩት እያንዳንዱ መንጦላዕት አለው፡፡ በምስራቅ አቅጣጫ የማይከፈት መስኮት
ይበጅለታል፡፡ ለእመቤታችን የድንግልናዋ ምሳሌ ነው፡
፲፩. የሰውን እንቁላል፡- ይህ አሁን ከችግር አኳያ እየቀረ የመጣ ቢሆንም በጥንታውያኑና
ገጠራማ አካባቢ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተለመደ ነው: በጉልላቱ ላይ በሚቆመው
መስቀል ዙሪያ የሰጎን እንቁላል ይደረጋል። ምሳሌነቱ /ምሥጢራዊ ትርጉም/፦ የሰጎን
እንቁላሏን ለመፈልፈል የምታበቃው በመታቀፍ ሳይሆን ሳታቋርጥ /ሳትንቀሳቀስ/ በማየት
ነው። ምግብ ሲያስፈልጋት እንኳን ወንዱን በቦታዋ ተክታ ነው። የቤተክርስቲያን ልደት ላይ
እንቁላሏ መሰቀሉ ሰጎን ያለማቋረጥ እንቁላልዋን እንደምትመለከት እግዚአብሔርም
ፍጥረቱን የማይረሳ በጸጋውና በረድኤቱ ከፍጥረቱ የማይለይ መሆኑን ያመለክታል።
እንቁላሉ በእግዚአብሔርና በምእመናን መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ያስረዳል /፪ዜና ፯፥
፲፮፡፡ ኢሳ፵፱፥፲፭፡፡/
ሰጎኗ ዓይኗን ለአፍታም ያህል እንኳን ካነሳች፥ እንቁላሉ ይለወጣል፤ ማለትም ይበላሻል፤
አይፈለፈልም: እንደዚሁም እግዚአብሔር መግቦቱንና ጠብቆቱን /ረድኤቱን/ ለአፍታም ያህል
ቢያቋርጥ ምእመናን /የሰው ልጆች/ ሕይወት አይኖራቸውም: አንድም ታሪኩ ምእመናን
እንደ ሰጎን ዓይነ ልቦናቸውን ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ቤተክርስቲያን፣ ወደ መስቀሉ፣ ወደ
እመቤታችን፣ ወደ ቅዱሳኑ ሁሉ እንዲያደርጉ ይጋብዛል። ዓይነ ልቡናውን ከእግዚአብሔር፣
ከቤተ ክርስቲያን፣ ከቅዱስ መስቀሉ፣ ከእመቤታችን፣ ከቅዱሳን ሁሉ ላይ ነህ /ከቀይ/
መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንደሚበላሽ ፍጻሜያቸውም እንደማያምር ያሳያል። /ዮሐ ፲፱፥፳፭/
ታቦቱም ሲቀረጽ ከላይ አልፋ፣ ቤጣ፣ የውጣ፣ ወኦ/ወዖ/ ይቀረጻል። ቀጥሎ እመቤታችንን፣
ከእመቤታችን ቀጥሎ ዮሐንስን፣ ቀጥሎ ቤተ ክርስቲያኑ የሚተከለው ታቦት መልአክም
ቢሆን፣ ሰማዕትም ቢሆን፣ ጻድቅም ቢሆን ይቀረጻል። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ካልተሟሉ
ታቦቱን ሊቀድሱበት አይገባም።
ከቤተ ክርስቲያን የገባ ዕቃ የወርቅ፣ የብር፣ ፃሕል ጽዋእ እርፈ መስቀል ቢሆን ንዋየ
ቅድሳት ነው ተብሎ አቡነ ዘበሰማያት ከተደገመበት በኋላ ከቤታቸው ወስደው በፃሕሉ
ፈትፍተው ሊበሉበት በጽዋው ቀድተው ሊጠጡበት አይገባም። ደፍረው ቢያደርጉ ሥርዓት
ማፍረስ ነውና ይህን ያደረገ ቢኖር በአንድ ሁለት ተቀጥቶ ንሰሐውን እሰኪፈጽም
ከምዕመናን ይለይ። /ዳን. ፭፥፩-፴፩/።
2. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
2.1 ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የቃሉ ትርጉም
ሥርዓት ማለት “ሠርዐ-ሠሪ” ከሚዉ የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙ ደንብ፣ ሕግ፣
አሰራር፣ መርሐግብር፣ ዕቅድ፣ ሕገ፣ ደንብ ማለት ነዉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሥርየተ
ኃጢአት፣ የኖላዊነት (እረኝነት)፣ የማስተማር፣ የማስተዳደርና ምሥጢራትን የመፈጸም
ሥራ ለማከናወን የምትችልበት ሥርዓትም ባለቤት ናት፡፡ ይህም አንዲቷ፣ ሐዋርያዊቷና
ኩላዊቷ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ከክርስቶስ የተቀበለችዉን የክህነት አገልግሎት አፈጻጸም
ማለትም የሥርየተ ኃጢአት፣ የኖላዊነት (እረኝነት)፣ የማስተማር፣ የማስተዳደርና
ምስጢራትን የመፈጸም ሥራ ማከናወን የምትችልበት እና በምዕመናን የሚተገበር መንፈሳዊ
ሥራና የእያንዳንዱ ምዕመናን መንፈሳዊ ሕይወት ከልደት እስከ ዕረፍት…… ደንብ፣
አሠራር፣ መርሐግብር፣ ሕግና፣ መመሪያ ማለት ነዉ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊም “ሰማይ ተከፈተ” በማለት ዓይነ ልቡናው በርቶለት ምሥጢራትም
ተገልጠውለት ሰማያዊን የብርሃን ቤተ መቅደስ ከታቦተ እግዚአብሔርና ንዋያተ ቅዱሳት
ጋር ማየቱን ነው የገለጠልን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መቅደሱንና ታቦተ እግዚአብሔርን ብቻ
ሳይሆን ያየው የካህናተ ሰማይ የቅዱሳን መላእክትን የአገልግሎት ሥርዓትም ነው፡፡ (ራእ.
፰፥፩-፮)፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ቢሆኑ በአገልግሎት ዘመናቸው ይህንኑ ሰማያዊ የአገልግሎት
ሥርዓት እግዚአብሔር በገለጠላቸው መጠን ማየትና መስማት ችለዋል፡፡ (ኢሳ. ፮፥፩-፮፡፡ ሕዝ.
፩፥፩-ፍጻ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትን የምትፈጽምበትና አገልግሎቱን የምታከናውንበት
ሥርዓት በቀጥታ ከሰማያዊው የብርሃን መቅደስ የተገኘ (የተቀዳ) መሆኑን ማስተዋልና
ሥርዓቷን አክብሮ መጓዝ ይገባል፡፡
፩ኛ. የቤተ ክርስቲያንን ልጆች በአንድ መስመር ለመምራት፣ ወጥና ዘላቂ በሆነ መንገድ
እንዲጓዙ ለማስቻል ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ፡- ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ክፍለ
ዓለም ብትታነፅም /ብትሠራም/፣ በየትኛውም ዓይነት ቋንቋ ብትገለገልም፣ አገልግሎቷን
ለየትኛውም ዓይነት ሕዝብ ብታቀርብም መሠረተ እምነቷ፣ የምሥጢራት አፈጻጸሟና
ሁለንተናዊ አገልግሎቷ ወጥና ዘላቂ (የማይቀያየር) በሆነ ሥርዓት መመራቱ የግድ ነው፡፡
ይህ ካልሆነ ግን አስተማሪውና ተማሪው፣ ተናጋሪውና ሰሚው፣ ቀዳሹና አስቀዳሹ፣
አገልጋዩና ተገልጋዩ፣ እረኛውና በጉ፣ ጀማሪውና ተከታዩ … ወዘተ ስለማይታወቅ
የተደበላለቀ (ውጥንቅጡ የወጣ) ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን ሁሉን
በአገባብና በሥርዓት አድርጉ፤” (፩ቆሮ ፲፬፥፵) በማለት ያስተማረው፡፡
፪ኛ. የክርስቶስ አካላት፣ የቤተ ክርስቲያንም አባላት የሆኑት ካህናትና ምእመናን አንድ ልብና
አንድ አሳብ ለመሆን የሚችሉት አንድ ዓይነት ሥርዓት ሲኖራቸውና ሲመሩበት ነው፡፡
አለበለዚያ አንዱ ሲያስተምር አንዱ የሚዘምር፣ አንዱ ሲጀምር አንዱ የሚጨርስ፣ አንዱ
ሲያበራ አንዱ የሚያጠፋ፣ አንዱ ሲከፍት አንዱ የሚዘጋ … ወዘተ ይሆንና ቤተ ክርስቲያን
ትርምስና ሁከት መለያየትም የሚነግሥባት ቤት ትሆናለች፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
“የተጻፈው ሁሉ በመታገሳችንና መጻሕፍትን በማመናችን ተስፋችንን እናገኝ ዘንድ እኛ
ልንማርበት፤ የትዕግስትና የመጽናናት አምላክ እግዚአብሔር እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ
እርስ በርሳችን አንድ ሀሳብ መሆንን ይስጠን፤ ሁላችን አንድ ሆነን በአንድ አፍ በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን እናመሰግነው ዘንድ፡፡” (ሮሜ 15-4-7) በማለት
በዲያቆን አሸናፊ ወልደኢየሱስ (በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ ግቢ ጉባኤ ትምህርት ክፍል)
ገጽ | 22
የቤተክርስቲያን ምስጢራትና ሥርዓት የኮርስ ሃንዳውት 2011 ዓ.ም
ደግሞ የተለየ፣ የተከበረ ማለት ነው፡፡ አንድም መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በአንድ ጥራዝ
የተሰበሰበ የተለየና የተከበረ ፅሁፍ ማለት ነው፡፡ ስለምን ቅዱስ ተባለ ትሉኝ እንደሆነ፡-
8. ድካምን ማራቅ፡- ከሥራ ብዛት፣ ከጤና መታወክ የተነሳ የአእምሮም ሆነ የስጋ ድካም
የሚፈጠርበት ወቅት አለ፡፡ በዚህ ወቅት ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ ከመቅረብ ይልቅ
የሚሰማውን ድካም ዕረፍት በመውሰድ ማሳለፍ ይገባል፡፡
3. አሪት ዘሰባው ሊቃናት፡- ቅደመ ልደተ ክርስቶስ በ275 ክፍለ ዘመን በንጉስ በበጥሊሞስ
አማካይነት ከኢብሩ ወደ ግሪክ አስተርጉሟል፡፡
4. ቭልጌት ትራንዜሽን፡- ቅደመ ልደተ ክርስቶስ በ481 ክፍለ ዘመን ጄሮም ወደ ላቲን
የተረጎመበት ነው፡፡ ወደ ላቲን ሲተረጉም ቆርጦ ይጥላል፡፡ ለምን ቢባል ከ63 እስከ 68
መ/ክ/ዘ በክርስቲያኖች ላይ በነበረው ስድት ምክንያት አይሁድ በጉባኤያቸው (በሸንጓቸው)
ተሰባስበው የክርስቶስ ሰም ያለበትን በሙሉ ቆርጠው ጣሉት፡፡ ለዚህም ነው ጄሮም አይሁድ
ስላልተጠቀሙበት ቆርጬ ጥዬዋለው ያለው፡፡ ዛሬም በፕሮቴስታንቱ ዓለም የሚያራምዱትና
የሚቀበሉት ይህንኑ ነው፡፡
5. ዴልስ ክሮስ፡- ይህም ከልደተ ክርስቶስ በኋላ 1949 አስከ 1956 በውጮች አቆጣጠር
በሙት ባሕር ዳርቻ የተገኙ ናቸው፡፡ ይህም የሙሴ አሪት፤የሰማርያውያን ኦሪት፣የሰባው
ሊቃናት ትርጓሜ እንዲሁም የሔኖክም መጽሐፍ ጭምር የያዘ ነው፡፡
ሌላኛው ስልሳ ስድስቱ ብቻ እንቀበላለን የሚሉ ከሆነ ጥያቄ ያስነሳብናል፡፡ ለምሳሌ ጥቂቶቹን
ብንመለከት፡- መላዕክት መቼ ተፈጠሩ፣ ዲያብሎስ ከየት መጣ እንዴትስ ሳተ፣ቃዬል ከየት
አምጥቶ ሚስት አገባ፣ማቴ 27፡9 ያለው በ30 ብር እንደሚሸጡት የነብዩ የኤርምያስ ትቢት
የት ነው ያለው፣ይሁዳ 1፡14 ላይ ያለው የሔኖክ ትንቢት የት ነው ያለው፡፡ እነዚህ በስልሳ
ስድስቱ የሉም ነገር ግን የሚገኙት 81 ላይ ነው የሚገኘው፡፡
1. ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ያሉት ሳትነጣጥል በአንድ ዓይነት ትቀበላለች፡፡
ምክንያቱም በማኅፀነ ብሉይ የነበረው በሐዲስ ኪዳን ተዋልዷል፡፡ አንድም ብሉይኪዳን
የሐዲስ ኪዳን መንገድ ይጠርግ ነበር፡፡ ገላ 4፡4 ፣ሲራ 4፡፡ እንዲሆም አዲስ ኪዳን ክርስቶስ
መጥቶ የመሰረታት ሳትሆን የገለጣት ናት፡፡ ዘፍ 3፡20 አዳም መልካሙና ደጉን ያውቅ
በዲያቆን አሸናፊ ወልደኢየሱስ (በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ ግቢ ጉባኤ ትምህርት ክፍል)
ገጽ | 27
የቤተክርስቲያን ምስጢራትና ሥርዓት የኮርስ ሃንዳውት 2011 ዓ.ም
ዘንድ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፡፡ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ማለቱ ወልደ እግዚአብሔር የስውን
ስጋ እንደሚለብስ ሲገልጽ ነው፡፡ ዮሐ1፡1 በመጀመርያ ቃል ነበር፡፡ በተጨማሪም ምስጢሩን
ለመረዳት ብሉይኪዳን ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ለአዲስ ኪዳን መሠረት
ስለሆነ፡፡
2.. መጽሐፍ ቅዱስ የምንለካበት መንገድ ምስጢረ ስጋዊና ምስጢረ ስላሴ ነው፡፡ ስላሴ
ማለት ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ቅድስት ስላሴ ማለት ደግሞ ልዩ የሆነች ሦስትነት ማለት
ነው፡፡ ምክንያቱም በሦስትነት ውስጥ አንድነት ስላለባት ይህም በአብ ልብነት ሦስቱም
ያስባሉ ፣በወልድ ቃልነት ይናገራሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ሕያው ይኖራሉ፡፡ ዕብ
1፡2 እግዚአብሔር ዘመናትን በፈጠረበት (በተናገረበት) በልጁ ተናገረን፡፡ መለኮት ማለት
መለከ ገዛ፣ ግዛት ማለት ነው፡፡ ዮሐ 15፡26 ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ መንፈስ
በመጣ ጊዜ ስለኔ ይመሰክራል፡፡
2.. መጽሐፈ ግጸዉ፡- ሐዋርያት ለቀለሜንጦስ የሰጡት ሁለተኛ መጽሐፍ ነዉ፡፡ ምልክቱ
ረስጠጅ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ህልዉና ከማስረዳት ጀምሮ ስለ ምስጢረ ሥጋዌ፣ አጠቃላይ
ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ስለ ማስተማሩና ስለ ሠራቸዉ ሥራዎች ይናገራል፡፡ 27
ያህል አንቀጾች አሉት፡፡ ረስጠጅ 30 ስለ መስዋዕትና አቀራረቡ የናገራል
5. መጽሐፈ ኪዳን፡- ኪዳን ማለት በቁሙ ዉል፣ ስምምነት፣ የፍቅርና የአንድነት መሐላ፣
ሰላማዊ ሕግ፣ ትምህርት፣ ምስጋና ማለትም ሁለቱን ወገን (እግዚአብሔርና ሰዉ ሰዉና
ሰዉን) የሚያደርግ ነዉ፡፡ ለሰዉ ረብና ጥቅም የሚሆን በተስፋ የቆሙ ቢጠብቁት በረከት
የሚያሰጥ ቢያፈርሱት ጉዳትና ጠብ የሚያመጣ ብዙ በረከት የሚያሰጥ ነዉ፡፡ መጽሐፈ
ኪዳን ኢሱስ ክርስቶስ የሐዋሪያት ቃል ከትንሳኤ እስከ ዕርገት ያስተማራቸዉ እየጠቁት
የመለሰላቸዉ ነዉ፡፡ ይህንንም ከዕርገት በኋላ በጥንታ…. ሐዋርያት ጽፈዉታል፡፡
5.1 መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ፡- ዮሐንስ፣ ጴጥሮስና ማቴዮስ ጌታችን እያጻፋቸዉ ጽፈዉታል፡
፡ 59 አንቀጾች አሉት፡፡ ስለ ሥርዓተ ቤተ-ክረስቲያን፣ የዘወትር ኪዳናት፣ ትምህርተ
ኅቡአት፣ እግዚአብሔር ዘብርሃናት፣ቅዳሴ እግዚእ፣ በእንተ ቅድሳት ያተተ ነዉ፡፡ ይዘቱ
ሥርዓተ ጸሎትና ሥርዓተ ቅዳሴ ነዉ፡፡ዘጠኙ ኪዳናት የምንላቸው፡-
ከሦስተኛው መቶ አጋማሽ እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በጾም ወቅት ከሥጋ መታቀብ
እንዳለብንና ዓርብንና ቅዳሚት ስዑርን ፍጹም ጾም እንድንጾም ታዟል። ይህ ማለት አኹን
ሥጋ ተፈቅዷል ለማለት ሳይኾን ጥንትም ጀምሮ በጾም ሥጋን መብላት የተከለከለ ነው
ከጠዋት እስከ ምሽት ይጹሙ በዚህ ቀን ከክርስቶስ ጋር መከራ የሚቀበል ክርስቲያን ብፁዕ
ነው። "አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ሲል የተቀበላቸውን መከራዎች
የምናስብበትን ሳምንት እንዴት ልናከብር እንደሚገባ ገለጸልን።
የሐዋርያት ቀኖናም በዚህ ሳምንት ውስጥ ያሉትን ሥርዓቶች አስመልክቶ እንዲህ ይላል
«ይልቁንም በእነዚህ በስድስቱ ቀኖች መጾም የሚችል ቢኖር ሁለት ሁለት ቀን ይጹም፡፡
የማይችል ግን አንድ አንድ ቀን ይጹም፡፡ ሌሎችን ቀኖች እስከ ዘጠኝ ሰዓት ይጹሙ፤
እችላለሁ የሚል ግን ፀሐይ እስኪገባ ይጹም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብስባችሁ
መጻሕፍተ ኦሪትን እና መጻሕፍተ ነቢያትን፣ የዳዊትንም መዝሙር እያነበባችሁ በምስጋና
በጸሎት ዶሮ እስከሚጮኽ ድረስ የሌሊቱን ሰዓት ጠብቁ፡፡ ባለመፍራት እንዳይጠፋ ውስጣዊ
ሰውነቱን ይመርምር፡፡ ጾምን ከመፍታታቸው በፊት ገላቸውን ይታጠቡ፤ ሁሉም መብራት
የሚያበሩ ይሁኑ፡፡ የቻለ ዓርብ እና ቅዳሜ ሁለት ቀን ይጹም፤ ሁለት ቀን መጾም የማይችል
በሽተኛ ቢሆን ግን ቀዳም ሥዑርን ይጹም፡፡ የኀዘን ቀን ስለሆነች፡፡ እንጀራ እና ጨውም
አይቅመስ፡፡
ስለዚህ በእነዚህ ቀናት መጾም፣ መስገድ "መንግስተ ሰማያት ውስጥ ከገቡ በሁዋላ ድካም፣
መውጣት መውረድ አለ" ያሰኛልና ነው:: በዚያውም ላይ "ኢታጹርዎሙ ጾረ ክቡደ (ከባድ
ሸክም አታሸክሙ)" የተባለ ትዕዛዝ አለና ቅዱሳን አበው በጾም የተጐዳ ሰውነት ካልጠገነ
ወጥቶ ወርዶ : ሠርቶ መብላት ይቸግረዋልና ሰውነታችን እንዲጠገን : ይህንን በፈሊጥ
ሠርተዋል:: ስለዚህም:- "ሐጋጌ አጽዋም እምስቴ:: ወሠራዔ መብልዕ በዸንጠኮስቴ::" እያልን
አበውን እናከብራለን:: (አርኬ) ስለዚህ በበዓለ ሃምሳ ጾም፣ ስግደት፣ ንስሃ፣ ሐዘን፣ ልቅሶ፣
የለም::
50ውን ቀናት ጥሬ የሚበሉ አሉ፣ ጠዋት ተመግበው ከ24 ሰዓት በሁዋላ ጠዋት የሚመገቡ
አሉ፣ መጥነው ጥቂት በልተው አምላካቸውን የሚያመሰግኑ አሉ፣ ነዳያንን አጥግበው
እነርሱ ከነዳያን ትራፊ የሚቀምሱ አሉ:: እኛም ከእነዚህ መካከል የሚስማማንን መርጠን
ልንከውን በተለይ ደግሞ በጸሎት ልንተጋ ይገባል:: አልያ ብሉ ተብሏል ብለን ያለ ቅጥ
ብንበላ : ብንጠጣ እኛው ራሳችን የሰይጣን ራት መሆናችን ነውና ልብ እንበል::
ማስተዋልንም ገንዘብ እናድርግ:: "እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና:: እንደ
መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ:: ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና:: ስለ
መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው:: ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል
ነውና:: ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና:: መገዛትም ተስኖታል:: በሥጋ ያሉትም
እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም::" (ሮሜ. 8:5)
አይደለም ለማለት እንዳይደለ የታወቀና የተረዳ ስለኾነ አንዳንድ የሐዲስ ኪዳን ሥርዓቶች
ሲደረጉ ብናይ እንዴት ልንል አይገባንም።
በዚህ ታላቅ ሳምንት ውስጥ የክርስቶስን መከራ በማሰብ ገጹ የጠቆረውን ዮሐንስ ወንጌላዊን
ወደ መምሰል ማደግና ከኹሉም አብልጣ በስቃዮቹ ውስጥ በእናትነት ፍቅሯ እየደማች
የተሰቃየችውን ንጽሕትና ቅድስት እናታችን ድንግል ማርያምን መርሳት አይገባንም። ወደ
ክርስቶሰ የሕማማቱ ቤት መግቢያ በሮች እኚህ ናቸውና። በዚህ ሳምንት ውስጥ ክፉ ሥራ
የማይወዳጁትን አይሁድ ከሮማዊያን ጋር አወዳጅቶ በአምላካችን ላይ ስቃይን እንዳደረሱበት
እያሰብን ክፉ ከተባለው የክፋት ምንጭ (the father of evil) ጋር ተወዳጅተን የክርስቶስን
ስቃይ የረሳንባቸውን ጊዜያት በማዘከር ልናነባ ይገባናል። በዚህ ሳምንት ውስጥ ጌታን
አሳልፎ ከሰጠው ከይሁዳ ወገን እንኾን? ወይንስ ይህን ሰውዬ አላውቀውም ካለው ከጴጥሮስ?
የፈጸማቸውን ድንቅ የአምላክነት ሥራውን በትዕቢት ዕውርነት ምክንያት ከሚመለከቱት
አይሁድ ወገን እንኾን ወይስ ጌታን ለመስቀል ከወደዱት ከሮማዊያን ወታደሮች? በእርግጥ
በኖርንባቸው የዕድሜ ልኬታችን ውስጥ በጌታችን ላይ ከተነሣሡትና መከራን ካደረሱበት
ሰዎች አንዱን መኾናችንን መርምረን ይኾን? አምላካችን እግዚአብሔር በሕማማቱ ወደ
ፍቅሩ ይክተተን፡፡
በእየለቱ፣ ሠለስት በእየሠዓቱ ነው፡፡ ቅዳሴው ግዕዝ ነው፣ ሌሊት ሠዓታት ይቆማል፣
ስብሐተ ነግህ አይቋረጥም በተጨማሪም የገዳም አባቶች ወደ ዋሻ (ወደ ባዕታቸው) ገብተው
ይጾሙታል፡፡ በዚህ ጾም ወቅት የሚውሉ በዓላት ተለዋጭ ይደረግላቸዋል ምክንያቱም
በበዓል ፍስሐ ደስታ ስለሚደረግ እና በዐብይ ጾም ግን በሐዘን እንድንጾማ ስለታዘዝን ነው፡፡
፩ ወንድ የሴትን ልብስ አይልበስ ሴትም የወንድን ልብስ አትልበስ። ወንድ የራሱ የኾነ
ልብስ አለው፤ ሴትም የራሷ የኾነ ልብስ አላት፤ በመኾኑም አንዱ የአንዱን ልብስ አይልበስ
የሚለው ቃል ከእግዚአብሔር የተሰጠ በመኾኑ ከእግዚአብሔር አልፎ መልካም የኾነውን
ማወቅ የሚችል ስለሌለ፤ ትዕዛዙን ከልብ ኾነን ልንቀበል ይገባናል። ክርስቲያን የኾነ ኹሉ
ተቃራኒ ልብስ አይልበስ፤ ይህ ከአምላኩ የሚለየው ነውና። እዚህ ጋ በጣም የሚያስደንቀው
ብዙ ሴቶች ሱሪ ማድረግ ምን ችግር አለው ይላሉ፦ ግን በቅንነት ኾነን ብናስብ ሱሪ
የወንዶች ልብስ መኾኑ በኹሉ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እውነታ ነው።
ይህ በሕገ ልብና ነው። ወንዶችን በተለይ ካህናት ሱሪን ይልበሱ የሚል ምስክር ግን አለ ዘጸ
፴፱፥፳፰። ከዚህም ካህናት ወንዶች ስለኾኑ ሱሪ እንዲለብሱ ከተባለ ሴቶች ሴት በመኾናቸወ
፬ የሴት የወንድን ልብስ ካልለበስኩ ባይነትና የወንድ የሴትን ልብስ መልበስ የፓጋንነት
መለያ ነውና ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ ወንድም እንዲሁ። በዘመነ ነቢያት የነበሩ ሰዎች
ከእግዚአብሔር ሕግ በመውጣት ከአምልኮታቸው ጋር በተያያዘ መልክ ለሚያመልኩት ጣዖት
ወንዶች የሴቶችን ልብስ በመልበስ፤ ጠጉራቸው በማሳደግ፤ ሴቶችም የወንድን ልብስ
በመልበስ ይታዩ ነበር። ከዚህ ከጣዖታዊ ሥርዐት ጋር በተያያዘ መልኩ ሴቶች የወንድን
ልብስ በመልበስ ወንዶችም የሴቶችን ልብስ በመልበስ ይዘፍኑ ይጨፍሩ ነበር።
መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብሉይም ሆነ በሀዲስ ኪዳን አንድ ሴት ሰበከች ተብሎ አልተፃፈም
ጌታም እንዲሰብኩ የመረጠው ከ 12ቱ ሐዋርያት ውስጥ ሴት የለችም እንደውም ሐዋርያቱ
በይሁዳ ፋንታ እጣ ሲያወጡ ማቴዎስ ሲደርሰው በእጣው ሴት አልተካተተችም
ወንጌላቱንም ሆነ መልእክታቱን የጻፉት ወንዶች ናቸው የጻፉትም የሰበኩትን ነው አንድም
ቦታ ሴት ስትሰብክ አልታየም ሴት የራሷ አገልግሎት ነበራት ለምሳሌ ሊዲያ የቅዱስ
ጳውሎስን መልእክታት ለተፃፈበት አገር ይዛ ትሔድ ነበር ይህም ድንቅ አገልግሎት ነበር
በመዝሙር በምስጋና ይሳተፋሉ በገንዘብም ቤተክርስቲያንን ይረዱ ነበር፡፡ ቅድስት
ቤተክርሰቲያናችንም መፅሐፍ ቅዱስን አብነት አድርጋ ሴት ልጅ እንድትሰብክ አትፈቅድም፡፡
1ኛ ጢሞ 2፥11 "ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር" 1ኛ ቆሮ 14፥35 "ለሴት
በዲያቆን አሸናፊ ወልደኢየሱስ (በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ ግቢ ጉባኤ ትምህርት ክፍል)
ገጽ | 39
የቤተክርስቲያን ምስጢራትና ሥርዓት የኮርስ ሃንዳውት 2011 ዓ.ም
በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን
ይጠይቁ።" ይህ ሴት እህቶቻችን መስበክ የሌለባቸው በጉባኤ /በአውደምህረት/ወንዶች
ባሉበት በአካል እንደሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉ
የብልቶቹም ሥራ አንድ እንዳይደል ሁሉ ወንድና ሴትም በአንድ አካል ያሉ የተለያዩ
ብልቶች ናቸው። አገልግሎታቸውም /የሥራ ድርሻቸውም እንዲሁ የተለያየ ነው። ወንድ
ራስ ሲሆን ሴት ደግሞ ልብ ትሆናለች ሴቶች የራሳቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆች ያስተምሩ
ዘንድ ችሎታው አላቸው።
3. ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙን መቀበል፡፡ ዮሐ 6፡54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ
የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሰዋለው
ፍቅርን የሰጠ አምላክ ስለሆነ አዳምን የሚጎዳ ነገር አያስቀምጥበትም፡፡ ማቴ 7፡11 እናነተ
ክፍዎች ስትሆኑ ለልጆቻቹን መልካም ስጦታን መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው
አባታችሁን ለሚለምኑት እንዴት አብዝቶ መልካም ነገርን ይሰጣቸው ይሆን ፡፡ ስለዚህ ዕፀ
በለስ የተፈጠረችው ለመልካም ነገር ነበር፡፡ ነገር ግን አዳምና ሔዋን እግዚአብሔር አምላክ
የሰጣቸውን ትዕዛዝ ትተው በዲያብሎስ ባዶ ስብከት ተታለው እግዚአብሔር የሚያህል
አምላክ ትተው ዲያብሎስን አምነው ሕጉንና ትዕዛዙን ጣሱ (አፈረሱ)፡፡ በኋላ የሰው
ውድቀት መጣ ፡፡ እንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ሰው መሆን ያስፈለገውም የሰው ልጅ
ውድቀት ነው፡፡
ምክንያቱም አምላክ ቃሏን ጠብቆ ነውና ያደረባት፡፡ ታዳያ ከዚህ ምን እንረዳለን እንደቃል
ይሁንልኝ የሚለውን የልመና ቃሏ ከፍጥረት መዳን ጋር የሚገናኝ ከሆን መላኩም
ሲያበስራት ካንቺ የሚወለደው ከሦስቱ አካል አንዱ ቅዱስ ነው፡፡ የዓለም መዳኃኒት ኢየሱስ
ይባላል፡፡ እንደ ቃልህ ይሁንና አምላክ ከእኔ ተወልዶ፣ ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ሰውን ከዲያብሎስ
ቁራኝነት ያለቀው፣ በልጁ ብርሃንነት የ5500 ዘመን ድቅድቅ ጨለማ ይገፈፍ ፣ነፍሳት
ከሲኦል ወደገነት ይመልስ የሚል መልዕክት ያለው የምልጃ ቃል ለደቂቀ አዳም አቀረበች፡፡
ገና በቤተ መቅደስ ሳለች የነብዩ የኢሳያስ ትንቢት አንብባ የተመኘችውን እናትነት ሳይሆን
ባርያ መሆንን ነበር፡፡ ዓላማዋ ፍላጎቷ ሰው አንዲድን እንጂን ክብርን እንድታገኝ እንዳል
አለሆኑን በዚሁ ይታወቃል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር ትህትናዋ አይቶ መረጣት፡፡ እርሷም
ፍጥረት ከዳነልኘማ ይሁን አድርገው ብላ አምላክን ጠየቀች፡፡ ልክ ልጇ በጌቴ ሴማኒ በጸለየ
ጊዜ ይህች ጽዋ በእኔ ትለፍ ብሎ የሞትን ጽዋ ከአዳም ዘር ሁሉ እንዳሳለፈ እናቱም ከእኔ
ተወለድና ጽዋን ከሰው ልጆች ሁሉ አሳልፍ ብላ በመማለድ ሲጠባበቅ የነበረውን ቃሏን
ሰጠቸው፡፡ ታዲያ ያለዚህ ምልጃ ያለዚህ ፈቃድ የክርስቶስ ልደት የሰው ልጆች ድኅነት
እርግጥ ይሆን ነበር? ስለዚህ ያለድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም ሁሉ አይድንም፡፡
4. ምሥጢረ ጥምቀት
4.1 የምሥጢረ ጥምቀት የቃሉ ትርጉም
ጥምቀት እንዲሆን ያደረገ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦
እውነት እውነት እልኻለሁ ማንም ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር
መንግሥት ይገባ ዘንድ አይችልም። (ዮሐ. ፫፡፭) እንግዲህ ሂዱና በአብና በወልድ በመንፈስ
ቅዱስ ስም አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፤ አጥምቋቸውም። (ማቴ. ፳፰፡፲፱) ያመነ የተጠመቀ
ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። (ማር. ፲፮፡፲፮) ከእግዚአብሔር መወለዳችን
የእግዚአብሔርን ርስት መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ነው።
ሆኖናል (ማቴ 3፡13)፡፡ ሁለተኛም በትምህርቱ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር 16፡16)
እንዲሁም “እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔር
መንግሥት ሊያይ አይችልም” (ዮሐ 3፡3-6) በማለት ጥምቀት ለድኅነት አስፈላጊ መሆኑን
አስተምሯል፡፡ ሦስተኛም ለቅዱሳን ሐዋርያት በሰጣቸው ትዕዛዝ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን
ሁሉ በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው”
(ማቴ 28፡19-20) በማለት ምስጢረ ጥምቀትን መስርቶልናል።
3. ንዕማን ሶርያዊ ተጠምቆ ከለምጽ መዳኑ (2ነገ. 5፡14)፡- ይኸውም ምእመናን ተጠምቀው
ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ የመዳናቸው ምሳሌ ነው፡፡
4. የኖኅ መርከብ (ዘፍ. 7፥13)፡- ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “ጥቂቶች ማለት
ስምንት ነፍሳት በውኃ የዳኑባትን መርከብ ሲሠራ በኖኅ ዘመን የእግዚአብሔር ትዕግሥት
በዘገየ ጊዜ ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ሰበከላቸው፡፡ አሁንም እኛን በዚያው አምሳል በጥምቀት
ያድነናል ሥጋን ከዕድፍ በመታጠብ አይደለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመነሣቱ
በእግዚአብሔር እንድናምን መልካም ግብርን ያስተምረን ዘንድ ነው እንጂ” (1ጴጥ. 3፥20)
በማለት ገልጾታል፡፡ የጥፋት ውሃ በኖኅ ዘመን በበደላቸው ተጸጽተው ንስሓ ያልገቡ
ሰዎችንና (ከኖኅና ቤተሰቡ እንዲሁም ለዘር እንዲቀሩ ከተደረጉት ፍጥረታት በቀር) በምድር
የሚኖሩትን ሁሉ ያጠፋው ማየ አይኅ(የጥፋት ውሃ) የጥምቀት ምሳሌ ሲሆን ፤ ከጥፋት
ውሃ የዳኑት ኖኅና ልጆቹ ፤ ከክርስቶስ ጎን ለጥምቀታችን በፈሰሰው ትኩስ ውሃ በጥምቀት
ከእግዚአብሔር ተወልደው ከፍርድ ለሚድኑ ምዕመናን ምሳሌ ነው።
6. የእስራኤል የኤርትራ ባህርን (ቀይ ባህርን) መሻገር (ዘፀ 14፡21፣ 1ቆሮ 10፡1)፡- ሙሴ
የክርስቶስ፤ ባህሩን የከፈለባት በትር የመስቀል፤ ባሕረ ኤርትራ የፍርድና የሲኦል፤
በተከፈለው ባሕር የተሻገሩት እስራኤል በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ በጥምቀት ከእግዚአ
ብሔር ተወልደው ባሕረ ኃጢአትን የሚሻገሩ ምዕመናን ምሳሌ ነው። ኢያሱ የዮርዳኖስን
ባሕር ክፍሎ እስራኤል መሻገራቸውም እንዲሁ የጥምቀት ምሳሌ ነው (ኢያ 3፡14 4፡15)።
ኢያሱ የክርስቶስ፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት፤ ዮርዳኖስን የተሻገሩ እስራኤል በክርስቶስ አምነው
በመጠመቅ የዳኑ ምዕመናን ምሳሌ ነው።
7. የዮሐንስ ጥምቀት (ማቴ 3፡1)፡- ዮሐንስ ህዝቡን የንስሓ ጥምቀት እያጠመቃቸው ከቆየ
በኋላ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ ግን እነሆ የእግዚአብሔር በግ በማለት ወደ ጌታ መርቷቸዋል
ስለዚህ የዮሐንስ ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ለአማናዊዉ የጌታ ጥምቀት የሚያዘጋጅ ነው፡፡
1. የንስሓ ጥምቀት
የንስሓ ጥምቀት ልጅነትን ላገኙ ሰዎች ሕይወት ፈተና ለሚደርስባቸው ድካምና ጉስቁልና
ፈውስ እንዲሆን የሚሰጥ ሊደጋገምም የሚችል የጥምቀት ዓይነት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ
መጥምቅ ያጠምቀው የነበረ ጥምቀት የንስሓ ጥምቀት ማሳያ ነው፡፡ ምንም እንኳን ዮሐንስ
ጥምቀትን ያጠምቅ የነበረ ቢሆንም የዮሐንስ ጥምቀት ልጅነትን የሚያሰጥ ጥምቀት
አልነበረም፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት የንስሐ ጥምቀት ነበር፡፡
2. የደም ጥምቀት፡-
3. የልጅነት ጥምቀት
በውኃ መጠመቅ እየቻሉ መጠመቅን እንደተራ ነገር አድርገው የሚያቃልሉ ሰዎች ኤሳው
እንዳቃለላት ብኩርና ባለማወቅ የእግዚአብሔርን ጸጋ ያቃልላሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ በፍጹም
ልብ የክርስትናን ትምህርት አምነው ከመጠመቃቸው በፊት በሰማዕትነት የሚያርፉ
ሰማዕታት እግዚአብሔር ባወቀ የልጅነትን ጥምቀት ከመንፈስ ቅዱስ ወይም ከእሳት
ይቀበላሉ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማለት ደግሞ በውሃ ሳንጠመቅ እግዚአብሔር በፍቃዱ
ጸጋውን በመላክ የሚሰጠን ልደት ነው። ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን ቅዱሳን ሐዋርያት
የተጠመቁት ጥምቀት ነው (ሉቃ 3፡16 ፡ ሐዋ 1፡5 ፡ ሐዋ 2፡1-4 ፡ 1ኛ ቆሮ 12፡13)፡፡
እምነት ከሁሉ ነገር ቢቀድምም አዲስ የሆነውን ክርስቲያናዊ ሕይወት ለማግኘትና ለመዳን
ጥምቀት ደግሞ ከምሥጢራት ሁሉ ቀድሞ ለአዲሱ አማኝ ይፈጸምለታል፡፡ ምሥጢረ
ሜሮንና ምሥጢረ ቁርባንም በዕለቱ (ወዲያወኑ) ተፈጽመውለት ተጠማቂው ሰው የክርስቶስ
አካል፥ የቤተ ክርስቲያን አባል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ አንድ ሰው በክርስቶስ
አምኛለሁ፣ አመልከዋለሁም እያለ ጥምቀት አያስፈልገኝም ቢል ሊድን አይችልም፡፡
በክርስቶስ ያመነ ሰው ትምህርቱን ሁሉ መቀበልና መፈጸም ይጠበቅበታልና፡፡ “ዳግመኛ
ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡”
(ዮሐ.3፡5፡፡) በማለት ያስተማረን ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ ይህን አምላካዊ
መመሪያ ሳይፈጽሙ በክርስቶስ አምናለሁ ማለት ፈጽሞ አብሮ ሊሔድ አይችልም፡፡ ስለዚህ
በክርስቶስ ያመነ እወደዋለሁም የሚል ሰው ትእዛዛቱን በመፈጸም እንደሚድን መርሳት
አይኖርበትም፡፡
ሥጋዌ ልደት ከወንድና ከሴት እንደሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ልደትም ከዉኃና ከመንፈስ ቅዱስ
ነዉ፡፡ በዚህም የመንፈስ ቅዱስ ልጆች እንባላለን እንጅ የዉኃ ልጆች አንባልም፡፡ ምክንያቱም
የምንከብረዉ ከዉኃዉ ሳይሆን በመንፍስ ቅዱስ ስለሆነ ነዉ፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ሕጻናትን በ40 እና በ80 ቀን ስታጠምቅ ምስጢራትን፣ ምሳሌዎችን፣
ትውፊትን እንዲሁም የጌታንና የሐዋርያትን አስተምህሮ መሠረት አድርጋ ነው፡፡ ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅም እንደሚናገረው ቤተ ክርስቲያን ሕጻናትን የምታጠምቀው ኃጢአት በደል
አለባቸው ብላ ሳይሆን ከለጋነት ዕድሜያቸው ጀምረው ፍቅሩን እያጣጣሙ እንዲያድጉ
የሚያስችላቸውን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን ጸጋ ልትሰጣቸው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን
ሕጻናትን የምታጠምቀው ያውቃሉ ወይም አያውቁም ብላ አይደለም፡፡ የቤተሰቦቻቸውን
እምነትና ፈቃድ ምስክር በማድረግ ነው እንጂ፡፡ በተጨማሪም ቤተክርስቲያን ሕጻናትን
የማጥመቋ ዋነኛ ምክንያቷ መጽሐፍ ቅዱስን መርኅ (መሠረት) አድርጋ ነው፡፡ ለምሳሌ
ያህል ብንመለከት፡-
አዳምና ሔዋን በተፈጠሩ በ40 እና በ80 ቀናቸው ወደ ገነት መግባታቸው (ኩፋ 4፡9)
እስራኤል መስዋዕት ይዘው በ40 እና በ80 ቀን ወደ ቤተመቅደስ እንዲመጡ
መታዘዛቸው (ዘሌ 12፡1-8)
በኦሪቱ ሕፃናትም አዋቂዎችም ተገርዘው የተስፋው ወራሾች ነበሩና ይህም የጥምቀት
ምሳሌ ነው (ዘፍ 17፡1-5 ቆላ 2፡11-12)
በባህረ ኤርትራ የተሸገሩት ሕፃናትም ጭምር ነበሩና ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው
(1ኛ ቆሮ 10፡1-2)፡፡
ወደ ኖኅ መርከብ የገቡት መላው ቤተሰብ ነውና ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው (ዘፍ
7፡1-17 1ኛ ጴጥ 3፡20-22)፡፡
ሕፃናት በማኅፀን ሳሉ መንፈስ ቅዱስ ከሞላባቸው ሲወለዱ እንዳይጠመቁ
የሚከለክለቸው ምንድን ነው (ሉቃ 1፡15 ኤር 1፡4-5)፡፡
ሐዋርያትም ካስተማሩ በኋላ ቤተሰቡን ሙሉ ያጠምቁ ነበር (ሐዋ 10፡44-48 11፡
13-14 16፡15 16፡43)፡፡
ጌታችንም “ሰው ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ…” ያለው ሕፃናትንም
ይመለከታል (ዮሐ 3፡8)፡፡
ጌታችንም “ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው” ብሏል (ማቴ 19፡14)፡፡
ጥምቀት የማትደገም፣ የማትከለስ አንዲት ናት፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ልጅነትን
የምናገኝባት ጥምቀት የማትደገምና የማትከለስ አንዲት ብቻ መሆንዋን ሲያስተምር ‹‹አንድ
ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…አለ›› ብሏል (ኤፌ.4÷5)፡፡ ሃይማኖታቸው የቀና
318ቱ ሊቃውንትም ‹‹ኃጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡›› ብለው
አስተምረዋል፡፡ “ኃጢአት በሚሠረይባት አንዲት ጥምቀት እናምናለን” እንዲል፡፡ ከወላጆቻችን
በሥጋ የምንወለደው አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ሁሉ ከውሃና ከመንፈስም ከእግዚአብሔር
የምንወለደውም (የምንጠመቀው) አንድ ጊዜ ብቻ ነው። የጥምቀት ምሳሌ የነበረው ግዝረት
አንድ ጊዜ ብቻ እንደነበረ ሁሉ ጥምቀትም አንድ ጊዜ ነው (ቆላ 2 ፥ 11)። ከጌታ ሥጋና
ደም የምንሳተፍበት ምሥጢር በመሆኑ ጌታም የሞተውና የተነሳው አንድ ጊዜ ነውና አንድ
ጊዜ ብቻ እንጠመቃለን (ሮሜ 6፡3)።
በበዓለ ሃምሳ ከየሃገሩ የተሰበሰቡት አይሁድ ከጥንት ጀምሮ በነቢያት አንደበት ይወርዳል
ይወለዳል እየተባለ የተነገረለትን መሲሕን ተስፋ ያደርጉ ነበር፡፡ ሐዋርያውም ያ የተስፋው
ቃል ዛሬ መፈጸሙንና በተስፋው ቃል መሠረት ከድንግል ማርያም በሥጋ ተወልዶ 33
ዓመተ ከ3 ወር በምድር ላይ ተመላልሶ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሰውን ልጅ በደሙ የዋጀው
ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት የተነገረለት ሱባዔ የተቆጠረለት መሆኑን አምነው በሰው
ካልተጠመቁ በስተቀር አብርሃም አባታችን እግዚአብሔር አምላካችን በሚለው እምነት ብቻ
አምነው ጌታን በሰቀሉት አይሁድ መንገድ የሚጓዙ ከሆነ እንደማይድኑ በመሲሕ አምነው
በስሙም ከተጠመቁ ግን እንደ ሚድኑ ሊያስተምራቸው ስለፈለገ የጌታን ስም ለይቶ ጠራ፡፡
በዚህም የጌታን አዳኝነትና መሲሕነት አምነው እንዲቀበሉ በአጽንዖት መናገሩ ነው፡፡
በአራቱም ወንጌላት የጌታችን ጥምቀትም በውኃ ውስጥ ገብቶ በመውጣት መሆኑ ተጽፏል፡፡
“ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ
የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ (ማቴ 3፡16)”
በሚለው ቃል ውስጥ “ከውኃ ወጣ” የሚለው የጌታችን ጥምቀት የተከናወነው በመነከር
እንደነበር ያሳያል፡፡ በተጨማሪም በሥጋ መወለድ በእናት ማኅፀን ውስጥ ቆይቶ መውጣትን
የሚያመለክት እንደሆነ ሁሉ “ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድም” እንዲሁ ውኃ ውስጥ
ገብቶ መውጣትን (መነከርን) ይጠይቃል፡፡ ስለዚህም ነው ጥምቀት “ዳግመኛ መወለድ”
የተባለው (ዮሐ 3፡3)፡፡ ዋና ዋናዎቹ የምሥጢረ ጥምቀት አፈጻጸም ሥርዓትን የሚመለከቱ
ነጥቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
፬. ጥምቀቱ በትንሣኤ ከሆነ በዶሮ ጩኸት ጊዜ፤ በሌላ ቀንም ከሆነ መጠመቂያው ሰዓት
ሲደርስ ተጠማቂዎችን በመካነ ጥምቀቱ ያቆማቸዋል፡፡ ያውም ካልሆነ ካህኑ ማዩን ቸቸ
በብርት አድርጎ ሥርዓተ ጸሎቱን ያደርሳል፡፡
፲፩. ተጠማቂዎች መናገር ከቻሉ ራሳቸው፤ ካልቻሉም የክርስትና አባት (እናት) የሆኑት
ክርስቲያኖች የተጠማቂውን አውራ ጣት ይዘው ጸሎተ ሃይማኖትን በማንበብ
ሃይማኖታቸውን ይመሰክራሉ፡፡
፲፪. ሥርዓተ ቅዳሴውን አድርሰው፣ መጽሐፈ ክርስትናውን ደግመው ማዩን ከባረኩ በኋላ
ነው ማጥመቅ የሚጀምሩት፡፡ የ፵ እና የ፹ ቀን ሕፃናት ከተጠመቁ በኋላ ንዑሰ
ክርስቲያን ወንዶችና ሴቶች ይጠመቃሉ፡፡
፲፫. ከተጠመቁ በኋላ ካህኑ ሜሮን ይቀባቸዋል፡፡ የተዘጋጀላቸውን ነጭ ልብስ ለብሰው ቅዳሴ
አስቀድሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉ፡፡ በሜሮን ከከበሩም በኋላ ሦስት ኅብረ ቀለማት
ያሉት ማተብ ይታሰርላቸዋል፡፡ ኅብረ ቀለማቱም ነጭ፣ ቀይ፣ ጥቁር(ቢጫ) ናቸው፡፡
ምሳሌነት አለው በአንድ መገመዱ የሥላሴን አንደነት ሦስተ መሆኑ……
፲፬. የክርስትና አባት/እናት አብረው ጾመውና ተገቢውን ዝግጅት አድርገው በዕለቱ ሥጋውን
ደሙን ይቀበላሉ፡፡
፲፭. በዕለቱ ክርስትና የተነሡ (የተጠመቁ) ሕፃናትና ንዑሰ ክርስቲያን የነበሩ አዳዲስ የቤተ
ክርስቲያን ልጆች ከሌሎች ቆራብያን አስቀድመው ቅዱሱን ቊርባን ይቀበላሉ፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በውኃ ነው እኛም እርሱን አብነት በማድረግ በውኃ
ልንጠመቅ ይገባናል (ማቴ.3÷13-16)፡፡
ጌታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ
እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም›› ስላለ እኛም የጌታን ትእዛዝ ለመፈጸም በውኃ
እንጠመቃለን (ዮሐ.3÷5)፡፡
ሐዋርያት ከጌታ በተማሩት መሠረት ያጠመቁት በውኃ ነው፡፡ ጴጥሮስም መልሶ ‹‹እነዚህ እንደ
እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን
ነው? አለ›› (የሐዋ.10÷46ና 47)፡፡ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ
አጠመቃቸውም (የሐዋ.8÷28)፡፡
ውኃ የሰውነትን እድፍ እንደሚያጠራ ሁሉ እንዲሁም ጥምቀት የነፍስን እድፍ ያስወግዳል
ውኃ መልክን ያሳያል እኛም በመጠመቅ የሥላሴን ምሥጢር በዓይነ ኅሊናችን እናያለን፡፡
ለንጊኖስ የተባለው ሐራዊ (ወታደር) የጌታን ቀኝ ጎን በጦር በወጋው ጊዜ ትኩስ ደምና ውኃ
ባንድነት ፈሷል (ዮሐ. 19÷34)፡፡ ደሙ ለመጠጣችን፣ ውኃው ለጥምቀታችን መሆኑን ሲያጠይቅ
ነው፡፡ ይህንንም ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ገልጾታል ‹‹በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው፡፡
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡የሚመሰክሩት መንፈሱና
ውኃው ደሙም እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡ የሚመሰክሩተ መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት
ናቸውና፡፡ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ›› (1ዮሐ.5÷6-8)፡፡
ውኃ በሁሉም ቤት ይገኛል፡፡ በሀብታሙም በድኃውም ጥምቀትም ላመነ ሁሉ የተፈቀደ መሆኑን
ለማጠየቅ በውኃ ሆኗል፡፡ ስለዚህም በውኃ ብቻ እንጠመቃለን፡፡ ሥርዓተ ጥምቀቱን የሚፈጽመው
ካህን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በእግዚአብሔር
ቃል ሲባርከው ውኃው ተለውጦ በዕለተ ዓርብ ከጌታችን ቀኝ ጐን የፈሰሰውን ውኃ ይሆናል፡፡
ተለውጦ እስራኤል መባልን አግኝቷል፡፡ "ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ
ያዕቆብ አይባል፡፡" ዘፍ 32:28 በአዲስ ኪዳንም መድኃኒ ዓለም ክርስቶስ የዮና ልጅ
ስምዖንን ጴጥሮስ ብሎታል፡፡ ማቴ 16:18 ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ስለ ተሰጠው ኀላፊነት
የሚገልፅ ነውና፡፡ በቀደመ ግብሩ ክርስቲያኖችን ያሰድድ የነበረው ሳውል ስሙ ተለውጦ
ጳውሎስ ተብሏል፡፡ ሐዋ 13:7 ነቢዩ ኢሳይያስም "በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ሴቶች
ልጆች የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፡፡ የማይጠፋ የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ፡፡"
ኢሳ 56:5 እንዳለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህን አማናዊ ቃል መሰረት አድርጋ ከምዕመን
ክርስቲያን እስከ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በቅዱሳን ስም እንዲጠራ ታደርጋለች፡፡
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከኒቂያ ጉባኤ በኋላ ከተነሱት አባቶች አንዱ “በፊተኛው
ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም”
(ራእይ20:6) የሚለውን የወንጌላዊው ዮሐንስን አባባል በተረጎመበት የእግዚአብሔር ከተማ
በሚለው መጽሐፉ ላይ “ፊተኛው ትንሣኤ” የተባለው ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና
የምናገኝበት ጥምቀት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ክርስቶስን መሠረት ያደረገ እምነት ሁሉ “ሰው
ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” (ዮሐ. 3፡3)
የሚለው የጌታ ትምህርት መመሪያው ሊሆን ግድ ነው፡፡ ጌታችን እንዳስተማረውም
ያለጥምቀት ድኅነት የለም፡፡ በምስጢረ ጥምቀት በሚታየው አገልግሎት የሚገኘው
የማይታይ ጸጋ ግን ብዙ ነው፡፡ የሚከተሉት በጥምቀት የሚገኙ የማይታዩ ጸጋዎች ናቸው፡፡
1. ድኅነት
መዳን ስንል የእግዚአብሔርን መንግሥት ወርሶ የዘላለም ሕይወት ባለቤት መሆን ማለት
ነው፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የሌሊት
የትምህርት መርኃ ግብር ትምህርቱን በተመስጦ ኅሊና በሰቂለ ልቡና ይከታተል ለነበረው
ለኒቆዲሞስ የድኅነት በሩ ጥምቀት እንደሆነ ገልጾለታል “እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው
ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ ይችልም” (ዮሐ.3፡
5)፡፡ ይህ ታላቅ ቃልም ጥምቀት ለድኅነት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከጌታችን ጎን
በተገኘዉ በዉኃዉና በደሙ ልጅነትና ሥርየት ኃጢአት እናገኛለን፡፡ በማየ ገቦዉ
ጥምቀትን ዳግም ልደት ያስባለው ከሥጋ ልደት የተለየ በመሆኑ ነው፡፡ በአዳምና በሔዋን
ስህተት ምክንያት አጥተነው የነበረውን የልጅነት ጸጋ የምናስመልሰው በውኃ በምናደርገው
ጥምቀት ነው፡፡ ዳግም ከሥላሴ የምንወለደው በውኃ በምናደርገው ጥምቀት ነው፡፡
ምክንያቱም በጥምቀት የሚገኘዉ ልደት የማይጠፋና የማያዳግም ዘልዓለማዊ የልጅነት
ማኅተም ነዉ፡፡ 1ኛ ጴጥ 1÷23 “ዳግኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፣ በሕያዉና
ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነዉ እንጂ፡፡” ገላ 4÷6-7 “ልጆችም
ስለሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባትብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ዉስጥ ላከ፡፡
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ አንጅ ባሪያ አይደለህም፡፡” ሮሜ 8÷15-17 “አባ አባት
ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን
መንፈስ አልተቀበላችሁምና የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ
ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል፡፡”
4. ሥርየተ ኃጢአት:
5. ክርስቶስን መምሰል
“ጥምቀት የክርስቶስ አካል መሆናችን የሚረጋገጥበት ነው” (ገላ 3፡27) በዘመነ ብሉይ
የአብርሃም ወገኖች የአብርሃም ልጆች መሆናቸው ይረጋገጥ የነበረው በግዝረት ነበር፡፡
ግዝረት በኦሪቱ የእግዚአብሔር ሕዝብ መለያ ነበር፡፡ ያልተገረዘ ሁሉ ከሕዝቡ ተለይቶ
እንዲጠፋ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነበር (ዘፍ. 17፡14)፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ
በአምሳልነት ሲፈጸም የኖረው ግዝረት በዘመነ ሐዲስ በጥምቀት መተካቱን “በክርስቶስ
ገዛሪነት የኃጢአትን ሕዋስ ሰንኮፍ ቆርጦ በመጣል ሰው ሰራሽ ያይደለ ግዝረትን
የተገዘራችሁበት፤ በጥምቀት ከእሱ ጋር ተቀበራችሁ ከሙታን ለይቶ ባስነሣው
በእግዚአብሔር ረዳትነትም በሃይማኖት ከእሱ ጋር ለመኖር በእስዋ ተነሣችሁ” (ቆላ. 2፡11-
12) በማለት አበክሮ ያስገነዝባል፡፡ ግዝረት ለሕዝበ እግዚአብሔር የአብርሃም የቃል ኪዳን
ተሳታፊዎች የመሆናቸው መለያ ምልክት እንደነበር ሁሉ ጥምቀት ደግሞ በጌታ በኢየሱስ
ክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ የጸጋው ግምጃ ቤት ከሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ
የሚገኘው ጸጋ ተሳታፊ ያደርጋቸዋል፡፡ በጥምቀት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ
እንሆናለን፡፡ “ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን
ለብሳችኋልና” (ገላ. 3፡27) በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው በጥምቀት
ከእግዚአብሔር ጋር አንድ እንሆናለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ያደሰውን አዲሱን ሰውነት
የምንለብሰውና የክርስቶስ ተከታዮች የምንሆነው በጥምቀት ነው፡፡
5. ምስጢረ ሜሮን
5.1 የቅብዓ ሜሮን ትርጉም
ሜሮን ማለት የጽርዕ ቋንቋ ነው ትርጉሙም መዓዛ ያለው የሚያውድ ፣ የሚጣፍጥ፣ ልብ
የሚመስጥ ፣ ጣዕም ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት ነው፡፡ በግሪክ ሲሆን ደግሞ ትርጉሙም
ቅብዕ ማለት ነው፡፡ በግዕዝ ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ አንድም ሜሮን ማለት ቅዱስ
ቅብዕ / ዘይት ማለት ነው ፡፡ ቅብዐ ቅዱስ፣ የተባረከ ሽቱ፣ ብፁዓን ጳጳሳት ከበለስንና ከዕፀወ
ዕጣን ከአስጳዳቶስ ከሌላም ከብዙ ዓይነት ሽቱ፣ ተገቢውን ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመው
የሚያወጡት ሲሆን በሚመለከተው ጳጳስ አማካኝነት በየሀገረ ስብከቱ ላሉ አብያተ
ክርስቲያናት ሁሉ በነጻ የሚታደል ነው፡፡ ይህም ለመንፈሳዊ አገልግሎት ብቻ የሚውል
የተቀደሰ ቅባት ነው። (መጽ. ሰዋ. ወግስ መመዝ. ቃላት ሐዲስ ገጽ ፮፻፰፡፡) ስለ ቅብዐ
ሜሮን ቅዱስ መጽሐፍን የፃፉ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዐት ይሉታል፡፡ 2ቆሮ 1፡
21 ዮሐ 2፡20 ቅብዕን በመንፈስ ቅዱስ ማህተምን ይሉታል፡፡ ኤፊ 1፡13 ፣4፡30 ይህ ቅብዓ
ማህተመ ሕይወት በመሆኑ ለአገልግሎት ይውላል፡፡
ዘንድ ሜሮን የሚፈላው በጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቅዳሴ ላይ ነው፡፡ ግሪኮች የቁስጥንጥንያ
መንበር ለማክበር ሲሉ ጳጳሶቻቸውን ወደ ቁስጥንጥንያ ልከው በዚያ ፍልሀተ ሜሮን
ያደርጋሉ፡፡
የአዲስ ኪዳኑ ቅብዐ ሜሮን መነሻው ከላይ እንደገለጽነው ይህ የብሉይ ኪዳኑ ቅብዐ ዘይት
አጠቃቀምና አገልግሎት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ለታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ይውል
እንደነበረው የተቀደሰ ቅብዓት በሐዲስ ኪዳንም መንፈሳዊ ዓላማውን ሳይለቅ አገልግሎቱ
ቀጥሏል ። 1 ዮሐ 2፥17 ፈቅዶና መመሪያ ሰጥቶ ያስጀመረውም ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
ካህናትን በቅብዐ ሜሮን አክብሮ ሥልጣነ ሐዋርያትን ማስተላለፍ ጥንታዊ የተለመደና የከበረ
የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ነው፡፡ በምሥጢረ ተክሊልም ሙሽራውና ሙሽሪት በቅብዓ ሜሮን
ታትመው ይከብራሉ፡፡ በመጽሐፈ ተክሊል ከሌሎቹ የሥርዓተ ተክሊል አፈጻጸሞች ጋር
የአቀባብ ሥርዓቱና በቅብዐ ሜሮኑ ላይ የሚጸለየው ጸሎት ሠፍሮ ይገኛል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በሐዲስ ኪዳን በቅብዐ ሜሮን የሚታደለውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ
መሆኑን “እናንተስ ከቅዱሱ ያገኛችሁት ቅብዐት አላችሁ ሁሉንም ታውቃላችሁ፡፡ እውነትን
የምታውቁ ስለሆናችሁ፣ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን
እንደማታውቁ አድርጌ እጽፍላችኁም፡፡” (፩ዮሐ. ፪፥፳-፳፪፡፡) በማለት አስተምሮናል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ከዚህ አሳብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ መልእክት “ከእናንተ ጋር
በክርስቶስ ስም የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፡፡ ደግሞም ያተመንና የመንፈስ
ቅዱስን ፊርማ በልቦናችን የሰጠን እርሱ ነው፡፡” በማለት አስተላልፎልናል፡፡ (፪ ቆሮ. ፩፥፳፩-
6. ምስጢረ ቁርባን
6.1 የምስጢረ ቁርባን የቃሉ ትርጉም
ቁርባን የሚለው ቃል መሠረቱ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የመጣ ሲሆን “ስጦታ” የሚል ትርጉም
ይኖረዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ
የክርስቶስ ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር
ይመለከተዋል፡፡ ይህም ማለት እንደ ኦሪቱ ቁርባን ሰው ለእግዚአብሔር ያቀረበውን ስጦታ
ብቻ የሚያመለክት ሳይሆን እግዚአብሔርም በተለየ ሁኔታ ለሰዎች ደኅንነት ለዓለም ሁሉ
የሰጠውን በሥጋና በደም የመጣውን የልጁን ስጦታ ያስገነዝባል። ስለዚህም ለዓለም
መድኃኒት ሆኖ የተሰጠው በጸሎተ ኀሙስ ማታ ወደ ጌታ ሥጋና ደም የተለወጠው
ኅብስትና ወይን ዛሬም በጸሎተ ቅዳሴ የጌታን ሥጋና ደም ሆኖ የሚቀርበው ቅዱስ ቁርባን
ይባላል። እርሱም ከእግዚአብሔር የተሰጠ የተቀደሰ ስጦታና መሥዋዕት ነው።
ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን
ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ
አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳሌ ሆነው አልፈዋል፡፡ በሐዲስ ኪዳን
ግን አማናዊው ቊርባን (መሥዋዕት) ሰዎች የሚያቀርቡት (የሚሰጡት) መባዕ ሳይሆን
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ዓለሙን ለማዳን በቀራንዮ ዐደባባይ በአባቱ ፈቃድ፣ በመንፈስ ቅዱስ
ፈቃድ፣ በራሱም ፈቃድ በመስቀል ላይ ለዓለሙ ሁሉ ያቀረበው (የሰጠው) ቅዱስ ሥጋውና
ክቡር ደሙ ነው፡፡
ጠጡ ብሎ ሰጣቸው፤ ሉቃ. ፳፪፥ ፲፱–፳ ማቴ. ፳፮፥ ፳፮ ማር. ፲፬፥ ፳፪ የኦሪትን መሥዋዕት
አሳልፎ መሥዋዕተ ወንጌልን መሥርቷል።
“ኢየሱስ እንጀራና ኅብስትን አንስቶ ባረከ። ቆርሶ ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና እንካቹ ብሉ፤ ይህ
ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው። እንዲህም አለ ሁላችሁም
ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው”
በማለት ምሥጢረ ቁርባንን መሠረተ /ማቴ ፳፮፣፳፮-፳፰/። ኪዳን ማለት ከእግዚአብሔር ጋር
የምንገባው ቃል ኪዳን የሚያመለክት ነው። “እውነት እውነት እላችኋለሁ እውነተኛ እንጀራ
ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤
የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው።
ዮሐ. ፮፥ ፴፪–፴፫
በመቀጠልም ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ
ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም
ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።
ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን
እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡ ዮሐ. ፮፥ ፶፭–፶፰ ጌታችን ይህን ነገር በቃሉ
ሲነግራቸው መጀመሪያ ለሰሙት ሰዎች በሥራ እስኪያሳያቸው ድረስ ሊታመን የማይችል
ረቂቅ ነገር ነበር። ኋላ ግን ሠርቶ ባሳያቸው ጊዜ ተረድተው አምነውበታል። በዕለተ ዓርብ
የቆረሰውን ሥጋ፣ ያፈሰሰውንም ደም አስቀድሞ በዋዜማው ኅብስቱንና ወይኑን ለውጦ
ኅብስቱን ፲፫ ቦታ ፈትቶ (ቆራርሶ)፣ አብነት ለመሆንና ለማስደፈር ራሱ በራሱ እጅ ተቀብሎ
ለቀደ መዛሙርቱ አቀበላቸው፡፡ በመስቀል ላይ ለአንዴና ለዘለዓለሙ የፈጸመው ይህ
አምላካዊ የማዳን ሥራ እስከምጽአት ድረስ ለዓለሙ ሁሉ በሥርዓተ ቅዳሴ ከብሮ
እንዲታደልም (እንዲዳረስም) ሐዋርያት አባቶቻችንን አዘዛቸው፡፡
በምንጣፍ አንድ ከመሆን መታቀብ፡- በዕለቱ (ሌሊት) ለነፍስ ፈቃድ ሥጋን ማስገዛት፡፡ ምሳ
12÷13 "ለሰዉ የከበረ ሃብት ትጋቱ ነዉ" በተራክቦ የደከመና የዛለ አዕምሮ የዞ ወደ ቤተ
መቅደስ መግባት አይገባም፡፡ 1ኛ ቆሮ 7÷5 "ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜዉ
ካልሆነ በስተቀር እርስበርሳችሁ አትከላከሉ፡፡" ፍት. ነገ 24÷7 "እግዚአብሔርን ለማገልገል
ከሆነ ግን በምንጣፍ በአልጋ አንድ ከመሆን (የአካል ተዋሕዶ) ከመፈጸም መጠበቅ አለብን፡፡"
ወርሃዊ ልማደ አንስት በተከሰት ጊዜ መታቀብ፡- ፍት. ነገ አንቀጽ 5631 "እናቶችና እህቶች
ወርሃዊ ልማደ አንስት በተከሠተ ጊዜ ወደ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ዉስጥ በመግባት ራስን
ማብቃትና ለጸሎት ለቅዳሴ እንዲሁም ሥርዓተ አምልኮ ለመፈጸም ራስን ማዘጋጀት አግባብ
አየደለም፡፡" ልማደ አንስት እንደ ብሉይ ኪዳኑ መርገም አይደለም፡፡ "ዲያቢሎስ ያሳሳታት
በቅዳሴ ጊዜ የሚስቅ ሰው ቅዱስ ባስልዮስ በጻፈው በ፸፪ኛው አንቀጽ ካህን ቢሆን የሚያቀብል
ነውና ሥጋ ወደሙን ከተቀበለና ካቀበለ በኋላ ወጥቶ አንድ ሱባዔ ይቀጣ ይጹም ይስገድ፣
የሳቀው ሕዝባዊ ቢሆን ግን ሥጋ ወደሙን ሳይቀበል ያን ጊዜ ፈጥኖ ይውጣ ይላል። ምነው
ፍርድ አበላለጠ ካህኑን ተቀብሎ ወጥቶ ይቀጣ አለ፤ ሕዝባዊውን ሳይቀበል ወጥቶ ይሂድ
አለ ቢሉ ካህኑ የሚቆመው ከውስጥ ነው ሲስቅ የሚያየው የለም። ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ
ቅዳሴውን ጥሎ ወጥቶ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ቄስ እገሌ አባ እገሌ በመሥዋዕቱ ምን
አይተውበታል ብለው መሥዋዕቱን ሳይቀር ይጠራጠሩታል፤ ስለዚህ ነው። ምዕመኑ ግን
ሲስቅ ሁሉ ያየዋልና ለሌላ መቀጣጫ እንዲሆን፤ በቤተ መቅደስ የማይወደድ ሌላ ነገር
አይናገር፤ በቤተ መቅደስ ጭንቅ፣ ደዌ ሳያገኘው አንዱን ስንኳ ምራቁን እንትፍ አይበል።
ነገር ግን ደዌ ቢያስጨንቀው ድምፅ ሳያሰማ ምራቁን በመሐረቡ ተቀብሎ ያሽሸው።
መስሎ የሚቀርብ በመሆኑ ነው። አንድም በመሰረቱ ግብሩ የሥጋ እንደመሆኑ መጠን
ስለሚቀበሉት ምስጢር ክብር መንፈሳዊ ጥንቃቄ ለማድረግ ነው።
ለዐሥራ ስምንት ሰዓታት መጾም፦ ጌታ በምሴተ ሐሙስ በሦስት ሰዓት በአይሁድ ጭፍሮች
ተይዞ እስከ አርብ 9 ሰዓት ድረስ ያለውን ጊዜ በማሰብ 18 ሰዓታት የተመገቡት ከሆዳቸው
ጠፍቶ ለአፋቸው ምረት፣ ለሆዳቸው ባዶነት እስኪሰማቸው እንዲጾሙ ቤተክርስቲያን
ታስተምራለች። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች ከቅንነት አንጻር ይህን ያህል ሰዓት መቆየት
ባለመቻላቸው ሥጋደሙን ለመቀበል ቤተክርስቲያን መጥተው ሲታመሙ እና ራሳቸውን
ስተው ሲወድቁ ይታያል። እንዲህ አይነቱን ችግር ለማቃለል ከንስሐ አባታቸው ጋ
በቅድሚያ ሊማከሩበት ይገባል። "ጴጥሮስ በሁለተኛው ቀሌምንጦስ በ46ኛው አንቀጽ ጠንቅቆ
ሳይጾም ማንም ማን ሥጋ ወደሙን አይቀበል። ከወንዶችም ከሴቶችም ወገን ማንም ምን
የቀመሰ ቢኖር፣ ከቀመሰ በኋላ ሥጋውን ደሙን ቢቀበል፣ ተደፋፍሮ ይህንን ቢያደርግ
ለዘለዓለም ከምዕመናን በውግዘት ይለይ።"
በቤተ ክርስቲያን ውስጥም አፍን ለማደፍ ዘቢብ ወይም ሌላ ማናቸውንም ነገር እንዲበሉ
ሥርዓት ያስቀመጠ መጽሃፍ የለም፡፡ ቅዳሴ ጠበሉ እሱ አፍ ማደፊያ ነው፡፡ ምእመናን
ምእመናት አባቶችን አብነት ለማድረግ ሲገባቸው በራሳቸው መንገድ ከሥርዓት የወጣ ነገር
መፈጸም አይገባቸውም፡፡ ቤተሰቦቻቸውም ማደፊያ የሚሆን ነገር ይዘው ውጪ
እንዲጠብቋቸው አልያም በእናቶች የሚታደለውን ዳቤና ንፍሮ ተቀብለው አፋቸውን ማደፍ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ይህን ዓይነቱን ስህተት የሚፈጽሙ ሰዎች ሊታረሙ ይገባል፡፡
ሰ. ከቂም በቀል ያለበት የዝሙትና የስካር መንፈስ ያለበት ሰዉ የህን ሁሉ በንስሐ ሳያርቅ
መቀበል አይገባዉም፡፡
የሰርጉ ቤት የቤተ ክርስቲያንና የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ሲሆን የሰርጉ ባለቤት ደግሞ
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ታዳሚዎቹም የምእመናነ ክርስቶስ ምሳሌዎች
ናቸው። ድግሱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጸሎተ ቅዳሴ በየጊዜው የምታዘጋጀው ቅዱስ
ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው። ይህም ዝም ተብሎ በዘፈቀደ ማንም ባሻው ጊዜ እየተነሣ
ያለምንም ዝግጅት የሚመገበው ተራ ምግብ አይደለም። ተግሣጹም ሆነ ጽኑዕ ቅጣቱ
እንዳያገኘን ባግባቡ ተዘጋጅተን በካህናት እጅ የሚሰዋውን መሠዋዕተ ሐዲስ መቀበል
ይኖርብናል፡፡ ዋና ዋናዎቹ የዝግጅቱ አካላትም የሚከተሉት ናቸው።
በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ አበው ሁሉ ያቀረቡት መሥዋዕትና ቁርባን፣ በአዳምና በሔዋን
በደል በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ተፈርዶ የነበረውን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ሊያስወግድ
አልቻለም ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ይህንን መርገም ያጠፋበት፤ የጥሉንም ግድግዳ
ያፈረሰበት አማናዊ መሥዋዕት ክርስቶስ በመስቀል ላይ የቆረሰውና ያፈሰሰው ቅዱስ ሥጋው
የብሉይ ኪዳን ታቦት በይዘቱ ትልቅ የሆነና አራት መያዣዎች ያሉት ሲሆን በአራት ሰዎች
የሚያዝ ነው። አገልግሎቱ ደግሞ አሰርቱ ትእዛዛት የተጻፈባቸውን ሁለት ጽላቶች
ለማስቀመጫነት የሚጠቅም ነው። ታቦት የሚለው ቃል ማደሪያ የሚል ትርጉምንም ያገኘው
ከዚሁ ይሰጥ ከነበረው የማደሪያነት አገልግሎት አንጻር የተሰጠ ስያሜ ነው። ይህንን የከበረ
የሕግ ማደሪያ(ታቦት) ይሰሩና በወርቅ ይለብጡት ዘንድ ለሙሴና ለአሮን ያዘዛቸው ራሱ
እግዚአብሔር ነው። ዘፀ 25፥8 እግዚአብሔር ያለ ዓላማና ያለ ምክንያት አንዳችም ነገር ሰዎች
ይሰሩ ዘንድ አያዝም።
በዘመነ ብሉይ የታቦቱ መኖር ታላቁ ዓላማ እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው ወደ ከነዓን ሲጓዙ
መንፈስ የሆነውንና በሥጋዊ ዓይን የማይታየውን እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ
ለማምለክ የእምነት ደረጃቸውና የአምልኮ ልምምዳቸው ገና ስለነበር በሚታየው ታቦት ፊት
የማይታየውን እግዚአብሔርን ያመልኩት ዘንድ አዕምሯቸውን የሚያግዝ በፊታቸው
የሚያልፍ፣ የሚታይና ግዘፍ ያለው ነገር መኖር ስለነበረበት እግዚአብሔር ታቦት በመካከላቸው
ይኖር ዘንድ ወደደ። የሰው ልጅ አእምሮ በሃይማኖት አድጎና በእምነት ጎልምሶ በመንፈስ
ማምለክ እስካልጀመረ ድረስ ከኅሊና በላይ ረቂቅ የሆነውን እግዚአብሔርን ለማምለክ በዓይኑ
ፊት የሚታዩና የሚዳሰሱ ኅሊናውን ለአምልኮ የሚያግዙ መንፈሳዊ ንዋያት ያስፈልጉታል።
በዚህም ምክንያት ነበር የሕጉ ማደሪያ በሆነው በታቦት ላይ የሠራዊት ጌታ ራሱን በክብር
እየገለጠ ኃልዎቱን በማሳየት ለክብር የመረጠው ሕዝብ እግዚአብሔር የሚባል አምላክ እንዳለ
በእርግጠኝነት እንዲያምንና ለእርሱ በፍቅር እየተንበረከከ የእጆቹን በረከት እንዲመገብ
እንዲሁም ከአሕዛብ ጣዖታት ራሱን እንዲጠብቅ ያደርግ የነበረው።
ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የአዲስ ኪዳን ታቦት በይዘትና በመጠን በአገልግሎት እና በዓላማ
እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሳይሆን የከበረውን የክርስቶስ ሥጋና ደም በከበረ ቅዱስ ንዋይ ላይ
ለመፈተት የምንጠቀምበት ክቡር ምስዋዕ ነው። በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው
በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዌ በኩል ነው ። መልአኩ ለቅድስት ድንግል ከአንቺ
የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ካበሰረ በኋላ ባሕርያችንን ባሕርይው አድርጎ
በአጭር ቁመትና በጠባብ ደረት ተወስኖ በምድራችን በሥጋ የተገለጠው ቅዱሱ የእግዚአብሔር
ልጅ ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት በላቀ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ክብር ገልጦልናል፣በአባቱ እቅፍ
ያለው የበኩር ልጅ አባቱን ተርኮልናል።
"መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ
ተረከው።" (የዮሐንስ ወንጌል 1:18) ሌላው የብሉይ ኪዳን ታቦት አገልግሎት ሕጉ ለተጻፈበት
ጽላት ማደሪያ ነበር ዛሬ የአዲስ ኪዳን ታቦት ላይ በየቤተ ክርስቲያኑ ስመ እግዚአብሔር
ይጻፍበታል እንጂ አስርቱ ትእዛዛት አይጻፍበትም ምክንያቱም ሕጉን በልባችን ላይ እንደ
ሚጽፈው በቅዱስ ቃሉ አስረግጦ ነግሮናል። ክርስትና ደግሞ ከፊደል ሕግ በላይ በመንፈስ ሕግ
የምንኖርበት የቅድስና ሕይወት ነው። "እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም
አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ
የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።" (2ቆሮ3:3)
የከበረው የክርስቶስ ደምና ሥጋ ለሚቀርብበት ቅዱስ መሰዊያማ የበለጠ ክብር ልንሰጥ ይገባል።
አንዳንዶች እኛ ኢትዮጵያውያን ከሌላው የዓለም ማኅበረሰብ ይልቅ በልዩ ሁኔታ ከታቦት ጋር
ያለንን ልዩ ሕብረት በመመልከት ሌሎች ሀገሮች የማይጠቀሙትን እናንተ ኦርቶዶክሳውያን
እንዴት ትጠቀማላችሁ ይሄ ወንጌልን አለመረዳት ኦሪታዊነት ነው ይላሉ በጣም ስህተት ነው።
ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን በንን የሚለያይ ነው፡፡ ከዚህም በጥልቀት ልናጠና ይገባል ሌሎች
ሀገራት ክርስትናን የተከተሉትና ወንጌልን የተቀበሉት ቀድሞ ከነበሩበት ከጣዖት አምልኮ
በሐዋርያት ስብከትና በብዙ ድንቅ ተአምራት ተላቀው ወጥተው ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን
ወደ ሕገ ወንጌል የተሻገርነውና ክርስትናን የተቀበልነው ቀድሞ ከነበርንበት ከሕገ ኦሪት ወጥተን
ነው። ታሪክ በግልጽ እንደሚያስረዳን ከእስራኤል ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን ሕግና መንፈሳዊ
ሥርዓት እግዚአብሔርን ስታመልክ የኖረች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች ። ሌላው ዓለም
(ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት
የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን
ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡ የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር
የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት አንዱ "ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ
ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ
ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ
እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን
ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው
የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of
God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ
‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ
ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው
የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ
ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ
ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡››
ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ
ሲናገሩ፡፡
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን
ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ
ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና
ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን
ያዋረዱ የሚመስላቸው፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት
ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ
ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚፈተትበትና ስለ ሚሠዋበት
የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ
የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡
ስለዚህ ሁሉን በሩቅ አጥሮ መያዝ ስለሚገባ አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያቆዩልንን
መንፈሳዊ ክብራችንን፣ሥርዓትና አምልኳችንን ሁሉ ጠንቅቀን ልንጠብቅ ይገባል። ክብራችንን
እያቀለልን ወንጌል ገብቶኛል ማለት ፍጹም የተሳሳተ አመለካከትና ፍጻሜው የማያምር ሕይወት
ነው። አንዳንዶች አለቦታው የሚጠቀስ ጥቅስ በመጥቀስ ታቦት ተሽሯል ሲሉም እንሰማለን ።
ይህ የሚያሳየው የግለሰቦቹ በዘመንና በትርጉም ተከፍሎ የሚጠናውን መጽሐፍ ቅዱስ
በጥልቀት አለማጥናታቸውን ነው። ቃሉ እንዲህ የሚል ነው። "በበዛችሁምጊዜ በምድርም ላይ
በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን።
በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ጎንደር በሚገኙ 21 ወረዳዎች ከ2117 ያላነሱ ገዳማትና አብያተ
ክርስቲያናት ሲኖሩ በዋና ከተማዋ ደግሞ ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ በአብነት
ት/ቤት ረገድም የመጻሕፍት ጉባዔያት፣ የአቋቋም ምስክር፣ የቅኔ አብያተ ጉባዔያት እንዲሁም
የዜማ ት/ቤቶች በከተማዋ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ
ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም በአብዛኛው ስማቸው ደጋግሞ የሚነሳው የ44ቱ ብቻ
ነው፡፡ አንዳንዳን ሰዎች በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙት የአብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ስያሜ
ብዛት ሲመስላቸው ሌሎች ደግሞ በጎንደር በጥምቀት በዓል ወደ ጥምቀተ ባህር የሚወርዱትን
ብቻ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር ከቤተ መንግሥቶቹ በተጨማሪ ታሪካዊዋ
ጎንደር የምትታወቅበት ቅርስ ነው፡፡
ጎንደር ከተማ በአፄ ፋሲል የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የአካባቢው ነዋሪዎች
ተክለዋቸው የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ቀሐ ኢየሱስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ አበራ
ጊዮርጊስ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከሆነችበት እስከ ጎንደር ዘመን
ማክተሚያ ፈፃሜ መንግሥት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ 18 ነገሥታት የነገሱ
ሲሆን እነዚህም አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተዋል፡፡ እንግዲህ 44 የሚባሉት
አብያተ ክርስቲያናት ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የተተከሉበትን ጨምሮ
እስከ ፈፃሜ መንግሥት ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ የተተከሉትን ብቻ ሲሆን
ቁጥራቸውም 44 ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ ከዘመነ መሳፍንት እስከ አሁን የተተከሉ በርካታ አብያተ
ክርስቲያናት ቢኖሩም ከ44ቱ የሚቆጠሩ አይደሉም፡፡
በአጠቃላይ አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር በጎንደር ዘመን በጎንደር ከተማና አካባቢው የሚገኙና
የነበሩ 44 አብያተ ክርስቲያናት ጥቅል ስም ነው፡፡ ስለዚህ አርባ አራቱ ታቦት ሲባል ይህን
ታሪክ ተከትሎ የመጣ ስያሜ እንጂ በቤተ-ክርስትያናችን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ታቦታት ነው
ያሉት! ምክንያቱም ሁልጊዜም አዲስ ቤተ ክርስቲያን በሚሰራበት ጊዜ ታቦት ተቀርጾ በላዩ ላይ
"ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋ ኦሜጋ" ተብሎ ይጻፍበታል። ኢየሱስ ፊተኛውና ኃለኛው፤
መጀመሪያውና መጨረሻው ማለት ነው ፡፡ ይህ ቃል ከተጻፈበት በኋላ በሊቀ ጳጳስ እጅ ተባርኮና
ሜሮን ተቀብቶ በመንበሩ ይሰየማል (ይቀመጣል)፣ በቅዳሴም ጊዜ ሕብስቱና ወይኑ ወደ ቤተ
መቅደስ ሲገባ ቄሱ ሥርዓተ ቅዳሴውን የሚያከናውነው ሕብስቱን ሥጋ መለኮት፣ ወይኑን ደመ
መለኮት ወደ መሆን የሚለውጠው በዚህ በታቦቱ ላይ አክብሮ በሚጸልየው ጸሎት ነው ፡፡
ሥጋዬን ብሉ ደሜንም ጠጡ እያለ ያመኑትን ሁሉ የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ)
ነው፡፡ ታቦት በሐዲስ ኪዳን እውነተኛው የሕይወት ምግብ የክርስቶስ ሥጋና ደም
የሚቀርብበትና የሚፈተትበት መሠዊያ ነው። ስለዚህ ታቦት በአርባ አራት ቁጥር ብቻ
የሚወሰን ሳይሆን እልፍ አዕላፍ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል! "ለሚጠይቋቹ ጥያቄ ሁሉ
እንዴት መልስ መመለስ እንዳለባቹ ታውቁ ዘንድ ንግግራቹ ሁል ጊዜ በጨው እንደተቀመመ
በፀጋ ይሁን" ቆላስይስ 4:6 ብዙ ጊዜ ከኦርቶዶክስ እምነት ውጪ ያሉ ሰዎች የሚያነሱት ጥያቄ
እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ጽላት እንዲያስቀምጥበት ሥራ ያለው ታቦት አንድ ብቻ ነው
ዛሬ ግን በጣም ብዙ ነው ለምን ይሄ ሆነ? ይላሉ። ለዚህ ጥያቄ ምላሻችን ሁለት ነው።
አንደኛ እግዚአብሔር በሙሴ ዘመን ሰጥቶት የነበረው ጽላት በጊዜው ለነበረው ሕዝብ
ማምለኪያ ነው። በአንድ በተወሰነ ቦታ ተሰብስቦ በሙሴና በአሮን መሪነት ያመልክ ለነበረው
የተወሰነ ሕዝብ አንድ ታቦት በቂው ነበር። ሕዝብ ሲበዛና እግዚአብሔርን የሚያመልከው አማኝ
በየቦታው ሲሰፋ ግን ጽላቱን ማብዛት የግድ ነው።ለዚህም ነው እግዚአብሔር ለሙሴ እኔ
የሰጠሁህን ዓይነት ጽላት ቅረጽ ብሎ ፈቃድ የሰጠው ዛሬም እንደ ሙሴ ያሉ የሃይማኖት
አባቶች ይህንን ቅዱስ ንዋይ ያዘጋጃሉ። "ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም
በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።" (ኦሪት ዘጸአት 32:16) "
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ።"
(ኦሪት ዘጸአት 34:1)
በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ በዓለም ዙሪያ ተባዝቶ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ ለምን በዛ?
የሚል ጠያቂ ካለ መልሱ አጭርና ግልጽ ነው። እግዚአብሔርን የሚያመልከው ሕዝብና በቃሉ
ሕይወት ማግኘት ያለበት አማኝ ስለበዛ መጽሐፉም ተባዝቷል። ይህንን ማድረግ ደግሞ ምንም
ስህተት የሌለበት የተቀደሰ ተግባር እንደሆነ ሁሉ። ታቦታት ቢብዙና እግዚአብሔርን
የሚያመልከው ሕዝብ ባለበት፣ አብያተ ክርስቲያን በታነጸበት ቦታ ሁሉ ቢቀመጥ ስህተት
አይደለም። ታቦት አይመለክም የምናመልከውና የምንሰግደው በታቦቱ ላይ ለተጻፈው አልፋና
ኦሜጋ ለሆነው በደሙ ቤዛ ለሆነን ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
7. ምሥጢረ ተክሊል
መግቢያ
ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም
ተከተል መሰረት በመተጫጨት እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡
ቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡
ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡
ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡
27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን
የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን
ልናረጋግጥ ይገባል፡፡
በጋብቻ አመሠራረት ሂደት “እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም
አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።” (ዘፍ ፪፥፲፰፡፡) የሚለው ኃይለ ቃል መነሻና
መሠረት ነው። ይህም የጋብቻ መሥራቹና ፈቃዱ እግዚአብሔር መሆኑንና የተመሠረተውም
በመጀመሪያዎቹ አባታችንና እናታችን /በአዳምና በሔዋን/ መካከል እንደነበር ያስረዳል፡፡
“ምሥጢረ ተክሊል” በሐዲስ ኪዳን የተሰጠው መጠሪያ ስም ነው። ተክሊል “ከለለ” ከሚለው
የግእዝ ግስ የሚወጣ /የሚገኝ/ ሲሆን ትርጉሙም ጋረደ ፣አጠረ፣ ከበበ፣ አከበረ፣ አጀበ፣ ፈጽሞ
አስጌጠ፣ ሸለመ፣ አክሊል አቀዳጀ፣ ማለት ነው።
በሐዲስ ኪዳንም ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ ቃና በተዘጋጀው
የጋብቻ ሥርዓት ላይ በመገኘት ክርስቲያናዊ ጋብቻን አክብሯል። በዶኪማስ ቤት ከእናቱ
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከደቀ መዛሙርቱ ከሐዋርያት ጋር ተገኝቶ ጋብቻን
ፈጽሞ ባርኮታል። የታወቀና የተገለጠ የመጀመሪያ ተአምሩንም በእመቤታችን ምልጃ የፈጸመው
በዚሁ ሰርግ ቤት መሆኑ ይታወቃል። (ዮሐ ፪፥፩‐፲፪፡፡)
ሀ. ለመረዳዳት፡- “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ አግባብ አይደለም የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት
። ዘፍ 2 ፥ 18 ።” ብሎ እግዚአብሔር እንደተናገረ ፤ ሰው በኑሮው ሁሉ እንዳይቸገር
የውስጡን ሀሳብ የሚያካፍለው ፣ ችግሩን የሚጋራውና ራሱን የሚወክልለት የህይወት አጋሩን
እየመረጠ ጋብቻ ይመሠርታል ።
ሀ. ዘር መተካት፦
ጋብቻ ቅድስናውን ጠብቆ እንዲዘልቅ የሥጋ ፍትወትን (ፍላጎትን) መቆጣጠር ወሳኝነት አለው።
ይህ ደግሞ የጋብቻ ዓይነተኛ ዓላማ ነው። በዝሙት ጠንቅ ከሚመጣው የሥጋ ደዌ /በሽታ/፣
የመንፈስ ጭንቀት፣ የትዳር መናጋትና የልጆች መበተን የሚዳነው ይህን ዓላማ በአግባቡ
በመረዳትና በማስተናገድ ነው፡፡ ስለዚህም ፈቃደ ሥጋ ከጥንዶቹ በአንዳቸው በጸና (በተነሣ) ጊዜ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው በጸሎት ለመትጋት እንዲቻል ለጊዜው በመስማማት
ካልሆነ በስተቀር እርስ በርሳቸው እንዳይከላከሉ ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች። (፩ቆሮ፯፥፩‐፯፡፡)
በዚሁ በተጠቀሰው ምዕራፍ ውስጥ የምንማረው ሌላው ቁም ነገር በምኞት ከመቃጠል እና
ተያያዥ ከሆኑ ችግሮች ሁሉ ለመዳን ጋብቻ ፍቱን መድኃኒት መሆኑን ነው። ጋብቻ በመሠረቱ
ጥንዶች መካከል የሚደረግ ተራክቦም ከጋብቻ በፊትና ከጋብቻ ውጪ እንደሚደረገው ግብረ
ሥጋ ግንኙነት የረከሰና ፈጻሚዎቹንም የሚያረክስ አይደለም። (ዕብ፲፫
በወጣትነት ሁሉም ነገር ያምራል ሀብት፣ ትዳር፣ ትምህርት፣ መታወቅን 1ጲጥ 4፡1-2 እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፡፡ በወጣትንነት ጊዜ ያሉ ለውጦች
ስንመለከት ጠባያዊ ለውጦች፣ የአስተሳሰብ፣ የስሜት፣ የሀሳብ፣ የፍላጎት ለውጦች ይይዛል፡፡
በተጨማሪም ለተቃራኒ ጾታ የሚኖረው ፍላጎት (አመለካከት) ጎልቶ ይታያል፡፡ እነዚህ
ስሜቶችም ይሁን ለውጦች በራሳቸው ችግር አይደሉም ስነ ተፈጥሯዊ ናቸውና ነገር ግን ሰው
አካላዊ ዕድገቱን ከወጣትነት ደረጃ ደርሶ እነዚህ ለውጦች ላይ ሲደርስ መንፈሳዊ ዕድገቱን
ቀጫጫ ከሆነ(ከተመናመነ) ወይም አካላዊ እድገቱን በአግባቡ መምራት የሚችልበት ደረጃ
ካልደረሰ ሰው ሰውነቱ ቀርቶ እንስሳዊ ወደ መሆን ደረጃ ላይ ይደርሳል ማለት ነው፡፡ አንድም
በሁለቱም ጾታዎች ውስጣዊ ተግዳሮቶች መካከል ደግሞ የሚከተሉትን የጠባይ ለውጦች
በእዚህ በወጣትንት እድሜ ይከሰታሉ፡፡
በዚህ ጊዜ
በቂ እረፍት ስፈልጋታል፡፡
ቀልጣፋ የተግባርና የእንቅስቃሴ ሰዉ ሆኖ መገነት ያስፈልጋል
ትዝብት ላይ እስከ መዉደቅ የሚያደርስ መቅበጥበጥ
የመደበር፡- በቀላሉ በሆነ ባልሆነ መከፋት
በወር አበባ ላይ የሚገኙ ሴቶችን በሚገባ መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡
ዘፍ 31÷35 "ላባ የተባለ ሰዉ የጥፋት ዕቃ በሚፈልግበት ጊዜ በወር አበባ ላይ ትገኝ
የነበረችዉን ልጅ ራሔልን ከተቀመጠችበት ቦታ ላለማስነሣት የተቀመጠችበትን ስፍራ
ከመበርበር ተቆጥቧል፡፡ ምክንያቱም "በፊትህ ልቆም ስላልቻልኩ አትቆጣብኝ በሴቶች
የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛል""
እነዚህም የሌሎች ልጆች በጥምቀት ክርስትና የተነሱ ናቸዉ፡፡ ኒቂያ 23÷25 "ክርስትና
አንሺዉና ተነሺዉ ከሁለተኛዉ ጋር አይጋቡ ወላጆቹም፣ወነወድሞቹም፣ልጆቹም፣ልጅ ልጆቹም
የሚስቱ ከሌላ ልጆችም ወገን ንዱ ልጆች ከሁለተኛ ልጁ ጋራ አይጋቡ ሴት ልጆን ባሏ
ክርስትና ላነሳዉ ወንድ አታግባ" ወንድም እንደዚሁልጁን ሚስቱ ክርስትና ላነሳችዉ ወንድ
አያጋባ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በመካከላቸዉ መንፈሳዊ ተዛመዶ ሆኗል፡፡
ማጨት ቃልኪዳን መግባት ከጋብቻ የሚቀድም ተስፋ ነዉ፡፡ በደኩም ያለ ደብዳቤ ሊሆን
ይችላል፡፡ ዕድሜዉ ከ7 ዓመት ላለፈ ሕፃን አይጩለት፡፡ የወንዶች አካለ መጠን ፍጻሜ 20
ዓመት ያም ባይሆን 25 ዓመት ነዉ፡፡ የሴቶችም 12 ዓመት ያም ባይሆን15 ዓመት፡፡ የጋብቻ
አንድነት ግን በካሕናት መኖር በላያቸዉ በሚጸልትጸሎት ካልሆነ በቀር አይሆንም ኤፈጸምም፡፡
አንድ አካል እንደ ሆኑ ቅዱስ ቁርባን ያቀብላቸዋል፡፡ ሁለተኛ የሚያገቡ ወንዶች ካሕናት ቢሆኑ
ከሹመታቸዉ ይሻሩ፡፡ ከዚያም በኋላ ቢደግሙ የረከሱ ይሆናሉ፡፡ 1ኛቆሮ 7÷39"ሴት ባሏ
በሕይወት እያለ በሕግ የታሰረች ናት ባሏ ቢሞት ግን ነፃ ናት፡፡
እግዚአብሔርን ከሚያምኑ ወገን የወደደችዉን ልታገባ ይገባታል፡፡ በምክሬ ብትፀና ብፅዕት ናት፤
መታገስ ሲሳናት ግን ታግባ፡፡" የሚጋቡ ፈቶች ቢሆኑ ተክሊል አያድርጉላቸዉ፡፡በረከተ ተክሊል
ለድንግል ወንድና ለድንግል ሴት የገባልና፡፡ ሮሜ 7÷3"ሴት ባሏ በሕይወት ሳለ ሌላ ሰዉ
ብታገባ ሴሰኛ ሕግ አፍራሽም ሆነች፡፡" ያመነች ሴት ያለመነ ወንድ ብታገባ ከምዕመናን ትለይ፡፡
1ኛቆሮ 6÷12-15"ያላመነች ሚስት ያለችዉ ወንድም ቢኖር ከእርሱ ጋር ልትኖር ብትወድ
አይፍታት ያመነች ሴትም ያለመነ ባል ቢኖራት እርሱም ከእርሷ ጋር ሊኖር ቢወድ ባሏን
አትፍታዉ ያላመነ ወንድ ባመነች ሴት ይከብራልና፡፡ እንደዚሁም ያላመነች ሴት ባመነ ወንድ
ትከብራለች፡፡ ያላመነዉ መለየትን ቢወድ ግን ይለያይ፡፡"
7.9 የእጮኝነት ጊዜ
የእጮኝነት ጊዜ የጋብቻ ጊዜ እንዳለመሆኑ መጠን የተቃራኒ ጾታ ግንኙነትን ሳናደርግ በሐሳብ
የምንግባባበት ጠባይ ለጠባይ የምንጠናናበት በማናቸውም ጉዳዮች ሳንተፋፈር የምንነጋገርበት
ጠንከርም ሲል ቤተሰቦቻችንን የምናስተዋውቅበት የቅድመ ጋብቻ አንዱ ክፍል ነው በመሆኑም
ቅድስናን (ክብረ ንጽሕናን) የሚያሳጡንን የረዘመ የእጮኝነት ጊዜ ማስቆጠር በምንገናኝበት ጊዜ
ከሰው የተደበቀ ቦታን መምረጥ እንዲሁም ሕይታችንን የሚያለመልመውን ቃለ እግዚአብሔር
በሕብረት አለመመገብ ናቸው፡፡ ሌላውና የመጨረሻው የእጮኝነት ጊዜአችንን የተሳካ
የሚያደርግልን እና ለቅዱሱ ጋብቻ የሚያበቃን
2ኛ. የሚገባን ልብስ ማድረግ አካልን የሚግልጥ ልብስን አለማድረግ፡፡ 2ሳሙ 13፡19 ከጋለሞታ
ልብስ የተለየ ምሳ 7፡10 ባትን ከሚያሳይ ልብስ የተለየ ኢሳ 47፡2፤ የተገባ አለባበስ ጌጠኛ
(ንጹሕ) እና ደገኛ ልብስ ኢሳ 52፡1 ነብዩ ኤርሚያስ ሴቶች ስለምን የተገላለጠ ልብስ
እንደሚያደርጉ ሲገልጥ "በልብሽም እንዲህ ያለ ነገር ስለምን ደረሰብኝ ብትይ ከኃጢአትሽ ብዛት
የተነሳ የልብስሽ ዘርፍ ተገልጦአል ተረከዝሽም ተገፍፏል፡፡" ኤር13፡22
4ኛ. የዝሙት ጾርን በጾምና በጸሎት ማሸነፍ የእጮኝነት ጊዜአችንን የተሳካና ጣፋጭ
እግዚአብሔር ያለበት ያደርግልናል፡፡
2. በእጮኝነት ወቅት ለፈቃደ ስጋ ሳይሸነፉ ለሌላ ወገንም ፈተና (መሰናኪያ) ሳይሆን እንዴት
ባለ ጥንቃቄ ያሳልፋል፡፡ ሌላኛው ነገር ከራሳቸውም ሆነ ከአካባቢ ለሚመጣው ፈተና መቋቋም
ያለባቸው ብቻቸውን አለመገናኘት አለመሆን የጋብቻውን ጊዜ በትግስት በጾም በጸሎት በስግደት
መጠበቅ ና ንስሐ አባት መያዝና ሁሉንም ማመከር ነው፡፡ መተጫጨታቸውን ግልጽ በማድረግ
ሳይጠጋጉ በጣምም ሳይራራቁ ምልክት ሳያሳዩ በእሀትነትና በወንድምነት ደረጃ መጓዝ መኖርም
ነው፡፡ከዚህ በተረፈ ስለማይመለከተው ሌላ ሰው ብዙ አለመጨነቅ ወሳኝ አቋም ነው፡፡
ለዚህ ስህተት የሚዳረጉትን ሰዎች በተመለከተ፡- "...ከእነርሱም ወገን ስለ ገንዘብ ብዛት ጋብቻን
የሚሻ አለ፡፡ ... ስለዚህም ስለ ገንዘብ ፍቅር የሚስቱን መልከ ጥፉነት የሚታገሥ አለ፡፡..."
(ፍት.ነገ. ትርጓሜ አን.24፡839 ገጽ211) ካስተዋልን ግን ገንዘብ እኮ ድግስን እንጂ ጋብቻን
አያሳካም ፍቅርን አይገዛም ይልቁንም ደገኛ ሀብት ቢኖረን ባለጸጋውን አምላክ እንደማምለካችን
መመካታችን በእርሱ ብቻ ይሆን ዘንድ ልባችን ቢመካ ሰላማችን እንደ ወንዝ በሆነ ነበር፡፡
ምክንያቱም ብንመካበት የተገባ የዘላለም መኖሪያች እና የሕይወታችን ትርጉም፤የመኖራችን
ዋስትና የሚሆን እንደ እግዚአብሔር ያለ ለእኛ ማንም የለም፡፡ ዘዳ 33፡26 መመካት
በእግዚአብሔር መሆን እንዳለበት ነብየ እግዚአብሔር ኤርሚያስ እንዲህ በማለት ያመጣዋል ፡-
"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ባለ ጠጋም
በብልጥግናው አይመካ ነገር ግን የሚመካው ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ
ወጪያዊ ውበት ተክለ ሰውነት ፡- ነገር ግን ይህን ብቻ እንደ መስፈርት በመቁጠር ስንቱን
ቆንጆ ላናገባቸው በእጮኝነት ጊዜ አስነወርናቸው? አንገታቸውን አስደፋናቸው? አላማውያን
የማያደርጉትን ነውር እርም የሆነ ነገር ፈጸምን? ጋብቻን ለመመስረትም ለመተጫጨትም
ተክለ ሰውነት አይከለከልም፤በተክለ ሰውነትም ምክንያት ጋብቻ አይፈርስም፡፡ ምሳ31፡30
ሁሉም ውብ ነው፤በእግዚአብሔር ጣቶች የተዘጋጀ የእግዚአብሔር ውጤት ነው፡፡ በዝሙት
የምናይ ከሆነ"ቆንጆና እሸት አይታለፍም" እያልን ካገኘነው ጋር አንሶላ እየተጋፋን
እግዚአብሔርን እናሳዝናለን፤ባለማስተዋል እንዲህ የምናደርግ ይህ የእግዚአብሔር ድምጽ ነውና
ንሠሐ ገብተን ሰው ልንሆን ይገባናል፡፡
ጋብቻ የአካልና የመንፈስ አንድነት ነው። "ሁለት አካል አንድ ልብ" የሚሆኑበት
ድንቅና ሰማያዊ ምስጢር እንጂ በአካልም በመንፈስም የተለያዩ ሰዎች በአንድ ላይ የሚኖሩበት
የደባልነት ኑሮ አይደለም። ቅድመ ጋብቻ የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ዝሙት በመሆኑ
ከእግዚአብሔር ይለየናል። ማመንዘር ደግሞ ከእግዚአብሔር መንግስት የሚለይ ነው።
"አመንዝሮች...የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም" 1ኛ. ቆሮ 6:9 እንዲል። ቅዱስ ዮሐንስ
ወንጌላዊም "የሴሰኞች እድላቸው በዲንና በእሳት የሚቃጠል ባሕር ነው ይሀውም ሁለተኛ ሞት
ነው።" ራዕ. 20:8 በማለት ያስጠነቅቃል። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጋብቻ የቡራኬ ስርዓት
ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ዘፍ. 1:28 ከሚለውና የመጀመርያው ቡራኬና ከቃና ሰርግ ቤት
ምስጢር ወስደው በጋብቻ በዓል ጊዜ የሚፈጸም ልዩ የቡራኬ ጸሎት ሰርተዋል።
ቅዱስ አግናጥዮስ የተባለው የቤተ ክርስቲያን አባት የክርስቲያኖች ጋብቻ በኤጲስ ቆጶሱ ፈቃድ
ኤጲስ ቆጶሱ ባለበት እንዲፈጸም ስርዓት ሰርቷል። ሊቁ ጠርጡለስም ይህንን ትምህርት
በመደገፍ "የክርስቲያኖች ጋብቻ አማናዊ የሚሆነው በኤጲስ ቆጶስ ፈቃድ የሆነ እንደሆነ ነው።
ያለበለዚያ ግን ጋብቻ አይባልም።" ብሏል። እንዲያውም ይሀው ሊቅ "ቤተ ክርስቲያን
ሳታውቀው የሚፈጸም ጋብቻ ሁሉ ዝሙት እንጂ ጋብቻ አይባልም።" ብሏል።
ድንግልና ማለት ደግሞ ወንድ የማታውቅ ከወንድ ጋር ሩካቤ ፈጽማ የማታውቅ ጥብቅ
ልጃገረድ ሴት ወይም ሴትን በምንጣፍ ተገናኝቶ የማያውቅ ወንድ ማለት ነው። በሰው ልጆች
ዘንድ ካለ ዘር መቀበል ማቀበልና ሰስሎተ ድንግልና (የድንግልና መወገድ) መኖሩ የታወቀ
ነው። ይህ ስለታወቀ ብቻ ሩካቤ ከተፈጸመ ማሕተመ ድንግልና አይኖርም ድንጋሌ ስጋ ካለ
ደግሞ ሩካቤ አልተፈጸመም በማለት ድምዳሜ ላይ አያደርስም።
ሩካቤን ፈጽመው የማያውቁ ሴቶች ሲወለዱ ጀምሮ ማሕተመ ድንግልና የሌላቸው ሊሆኑ
ይችላሉ። ወይም ከጊዜ በኋላ በከባድ የአካል እንቅስቃሴ፣ በአደጋ በሕክምና ወይም በእድሜ
ብዛት ምክንያት ማሕተመ ድንግልናቸው ሊፈርስባቸው ይችላል። እንዲህ ያሉ ሴቶች ማሕተመ
ድንግልናቸውን ቢያጡም ሩካቤ ፈጽመው እስካላወቁ ድረስ ደናግል መባላቸው የተጠበቀ ነው።
በሌላ በኩል ወንዶች ሩካቤ ፈጽመው ሳለ እንደ ሴቶች የሚገሰስ ማሕተመ ድንግልና
ስለሌላቸው ድንግልናቸው አልፈረሰም እንደማይባል ሁሉ ሴቶች ሩካቤ ስጋ እየፈጸሙ በልዩ
ልዩ ምክንያት ማሕተመ ድንግልናቸው ባይገሰስ መደበኛ ሩካቤ እስከፈጸሙ ድረስ ደናግላን
ሊባሉ አይችሉም። ለምሳሌ: - የሚያይ የሚመስል ዓይን እያላቸው በመፍዘዙ ምክንያት የማያዩ
ሰዎች የዓይን ምልክታቸው (ዓይን የሚባለው ሕዋስ ወይም መልክ) ጨርሶ ስላልጠፋ ብቻ
ዓይን አላቸው ይባላልን? እንደዚሁም ሁሉ ሩካቤ ፈጽመው ሳለ ማሕተመ ድንግልናቸው
ባለመጥፋቱ ብቻ ደናግል ሊባሉ አይችሉም። (ሕይወተ ወራዙት: 122-125)
2. እንደ መላዕክት ንጹሕ ሆኖ ለመኖር፡-2ጢሞ 1፡7 የሥጋ ፈቃድ ማሸነፍና መግታት መቻል
ሌሎችንም ፈተናዎች መታገስ የሚቻልበትን መንፈሳዊ ኃይልን ብርታትን ያጎናጽፋልና፡፡
እንደ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ድንግልና በሁለት ዓይነት መልኩ እንዳለ በተለያዩ ሉቃውንተ
ቤተክርስቲያን የብዕር ውጤቶቻቸው በስፋት ተገልጧል፡፡ ድንግልናን የሥጋ እና የነፍስ በማለት
በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን፡፡ የደናግላን ምሳሌ የሆነች እመቤታችን ድንግል ማርያም
በሥጋም በነፍስም ድንግል ናት፡፡ አንዳንዴም የሕሊና ድንግልና የነፍስ ድንግልና ተብሎ ሊገለጽ
ይችላል፡፡ የ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፡ -“ድንጋሌ ሥጋ ለድንግሌ
ነፍስ መገለጫ፣ ጥላ ወይም አምሳል ነው፡፡” በማለት የሥጋ እና የነፍስ ድንግልና ያላቸውን
ትስስር በሚገባ ገልጽዋል፡፡ ይኸውም፡- ድንጋሌ ሥጋ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በመራቅ
የምንኖረው የቅድስና ሕይወት ሲሆን፤ ድንጋሌ ነፍስ ደግሞ ኃጢአታችንን ለካህናት አባቶቻችን
በመግለጽ በንሰሐ እየተመላለስን የምንኖረው ሰማያዊ ሕይወት ነው፡፡ እዚህ ላይ ከድንግል
ማርያም በስተቀር ሰው በሕሊናው ይበድላልና ዕለት ዕለት ንሰሐ ካልገባ በዚህ ንጹሕ ይሆን
ዘንድ የሚችል የለም፡፡
7.11 በጋብቻ ጊዜ
በውሳኔ መጽናት የሁለቱም ወገን ዘመዶችና ጓደኞች የራሳቸው ፍላጎት እንዲሆንላቸው በማሰብ
ስለ ሠርጉ ፕሮግራም በማውጣት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ እንዲደረግ ወይም ደግሞ በሁለቱም
በቤተ ክርስቲያንም (በሥርዓተ ተክሊል እንዲፈጸም በመዘምራን እንዲታጀቡ) እንደገናም
በዓለማዊ ሠርግ (በቬሎ እንዲወጡ፣ በባንድ እንዲታጀቡ) በማዋከብ ግራ ሊያጋቡ ይችላሉ ።
ነገር ግን የሚጋቡት አጃቢዎቹ ስላልሆኑ፣ መወሰን ያለበት በሙሽሮቹ ነው። ሙሽሮቹም
በውሳኔያቸው መጽናት አለባቸው። በውስጣቸው ያልተቆረጠ ዓለማዊ ፍላጎት ስላላቸውና
ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ለቤተሰቦቻቸው ምክርና ትእዛዝ ክብር በመስጠት ሠርጉ
የተደበላለቀና ቅጥ ያጣ ብዙ ሰዎችንም የሚያሰናክል ሊሆን አይገባም ።
ጋብቻው በቅዱስ ቁርባን መሆን አለበት ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸምላቸው የሥጋ ድንግልና
ላላቸው ሲሆን ሌሎችም ክርስቲያኖች ጋብቻቸውን በቅዱስ ቁርባን ማድረግ ይችላሉ።
ክርስቲያናዊ ጋብቻ ያለ ቅዱስ ቁርባን አይደረግም። አንዳንድ ሰዎች ለፎቶ ግራፍና ለቪዲዮ
ሲሉ ብቻ ጋብቻቸውን በሥርዓተ ተክሊል ለማድረግ ያስባሉ፣ ይህ ተገቢ ስላልሆነ አስቀድመው
ስለ ጋብቻ ትምህርት በሚገባ መማርና ምርጫቸውን ከወዲሁ ማስተካከል ይገባቸዋል ።
ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቃል ኪዳንና በቡራኬ፣ በጸሎተ ተክሊልና በቅዱስ ቁርባን
ሲፈጸም ምሥጢርነት ይኖረዋል። /ኤፌ. ፭፥፴፪፡፡/ በሚታዩ የአፈጻጸም ሥርዓቶችና ምልክቶች
የማይታይ ጸጋ እግዚአብሔ ይገኝበታልና። ምሥጢረ ተክሊል ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በምንም
ዓይነት መንገድና በየትኛውም ቦታ አይፈጸምም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ከወጣ ካህናት ቢኖሩም
እንኳን በየትኛውም ቦታ አይፈጸምም፡፡ ቤተክርስቲያን ሳታውቀው የሚፈጸም ጋብቻ መንፈሳዊ
ጋብቻ ሊባል አይችልም፡፡ ሥርዓተ ተክሊሉ በሚፈጸምበት ዕለት የሚኖረው አፈጻጸም
የሚከተለውን ይመስላል፡፡
ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያላቸው የሥላሴ ልጆች መሆናቸውን ያጠይቃል። አንድ ልብስ
ለብሰው አንድ ክብር ወርሰው በዚህ ዓለም የመኖራቸውና በወዲያኛውም ዓለም አንዲት ርስት
መንግሥተ ሰማያትን ወርሰው ከክርስቶስ ጋር የሚኖሩ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ነጭ ልብስ
/መጎናጸፊያ/ ክብርን፣ ትንሣኤንና የሚቀበሉትን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያስረዳ ነውና፡፡
ቀለበቱ የሃይማኖት ምሳሌ ነው፡፡ ቀለበት በክብነቱና ፍጻሜ የለሽ በመሆኑ በቃል ኪዳን የጸናው
የተክሊል ጋብቻም ከሕይወት ፍጻሜ በስተቀር ማንም የማይለያየው መሆኑን ያሳያል።
በአንዲት ርትዕት ሃይማኖት የማይናወጽ መሠረት ላይ የታነጸ እንደመሆኑ የጠላት ነፋስ፣
የፈተና ጎርፍና ልዩ ልዩ ወቅታዊ የስሜት ማዕበላት /የማያፈርሱት/ መሆኑን ያመለክታል።
ቅብዐ ሜሮን በምሥጢረ ሜሮን እንዳየነው የመንፈስ ቅዱስ ማሳደሪያ ነው፡፡ በዚህም መሠረት
ረድኤተ መንፈስ ቅዱስ በትዳራቸው ዘመን ሙሉ የማይለያቸው መሆኑን ያጠይቃል።
ሠ. አክሊል መቀዳጀታቸው
በባልና ሚስት መካከል የሚኖረው መተሳሰብ መቻቻልና ሰላም ሌላው የቅዱስ ጋብቻ ፍሬ ነው፡፡
የአንድነቱ መሠረት የሆነው እውነተኛ ፍቅር በተጋቢዎች መካከል ካለ ለጋብቻው ዘላቂነት
ሐ. የተባረኩ ልጆች
እንጅ ለመቀበል ድርድር ውስጥ አይገባም። ከእኛ በፊት የተደረጉ ነገሮችን በሙሉ አምነን
እንድንቀበል ተፈጥሮ ያስገድደናል። ትዳር ግን ተስማምቶ፣ ወዶና፣ ፈርሞ የሚገባበት ዘላቂ
ሕይወት ስለሆነ፣ ስምምነቱ እስከ ሕይወት ፍጻሜ የጸና ነው። “ሰው እናትና አባቱን ይተዋል
ወደ ሚስቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ይሆናሉ። ዘፍ 2፡24 ማቴ 19፡4” ባለው አምላካዊ ቃል
መሠረት በትዳራቸው ውስጥ ማንም ሊገባ አይፈቀድለትም። ወላጆችም ቢሆኑ ልጆቻቸው
ባይስማሙ ያስታርቃሉ፣ ይመክራሉ እንጅ ለእነሱ ስላልተስማማቸውና ግላዊ ጥቅማቸው
ስለቀረባቸው ብቻ ፍታት፣ ፍቺው እያሉ የልጆቻቸውን ትዳር መበጥበጥ የለባቸውም የብዙዎች
ትዳር የሚበተነው በቤተሰብ ጣልቃ ገብነት በመሆኑ ባለትዳሮች ይህን ጉዳይ አስቀድመው
ሊረዱት ይገባል ።
4. ዝሙት ከሁለቱ አንዳቸው በዝሙት ከወደቁ ንጹሁ ሰው ትዳሩን መፍታት ይችላል። ነገር
ግን ወሬ በመስማትና በጥርጣሬ ሳይሆን በተጨባጭ ከተገኘ መሆን አለበት። ማቴ 5፡32
የቤትን ገመና ለውጭ ማውራት ነገረ ሰሪ የሆኑ ሰዎችን ሊያስገባ ይችላልና መጠንቀቅ
ያስፈልጋል። የትዳር መሠረቱ በእውነት መግባባትና መተማመን ስለሆነ በሁኔታዎች
መጠራጠርና መጨቃጨቅ አያስፈልግም። ባልና ሚስት በትዳራቸው በሚኖረው ማንኛውም
ዓይነት ኑሮ በመመካከርና በመወያየት መወሰን አለባቸው ።
ትዳር የሁለቱም የጋራ ሕይወት ስለሆነ ፤ መመሪያ አውጪና ተቀባይ መሆን የለባቸውም ።
ገቢያቸውም ሆነ ወጪያቸው በጋራ መ ወሰን አለበት። ትዳሩ እውነት የሚሆነው እነዚህ
ሲሟሉ ነውና ። የባለትዳሮችን አንድነት የበለጠ የሚያረጋግጡት የሚወልዷቸው ልጆች ናቸው
ልጆች የሁለቱም እኩል ሀብቶች ስለሆኑ ያቀራርቧቸዋል። ትዳራቸውንም ማክበር ያለባቸው
የሚወዷቸው ልጆቻቸው እንዳይበታተኑባቸው በማሰብ ጭምር መሆን አለበት። በመካንነት
ምክንያት መውለድ ያልቻሉት ባለትዳሮችም እግዚአብሔር ለእነሱ የወሰነላቸው የተሻለ መሆ
ኑን በማሰብ ማመስገን ይገባቸዋል እንጅ በአምላክ ሥራ ገብተው ማማረር አይገባቸውም።
የተወለደውም ቢሆን ካልተባረከ ሊሞት ወይም መጥፎ ልጅ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር
8. ምሥጢረ ንስሓ
መግቢያ
ንስሐ ማለት ከጥምቀት በኋላ በሠሩት ኃጢአት ከልብ ማዘን፣ ወደ መምህረ ንስሐ ሄዶ
መናዘዝ (ኃጢአትን መናገር)፣ ጥፋትን ላለመድገም መወሰንና በእግዚአብሔር ቸርነት፥ በካህኑም
የማሰር የመፍታት ሥልጣን አምኖ አነሰ፣ በዛ ሳይሉ የተሰጠውን ቀኖና በደስታና በምስጋና
ተቀብሎ መፈጸም ነው። ከላይ በተገለጸው መሠረት ምሥጢረ ንስሐ ምእመናን ከኃጢአት
ቁራኝነት የሚላቀቁበትና አዲስ ሕይወትን የሚያገኙበት የድኅነተ ነፍስ መንገድ ነው፡፡ ሥርወ
ቃሉ “ነስሐ” የሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ንስሐ ገባ፣ ዐዘነ፣ ተጠጠተ፣ ተመለሰ፣
ክፉ ዐመሉን ተወ፣ ጠባዩን ለወጠ፣ ማለት ነው። (ኪ.ወ.ክፍሌ)
ንስሐ የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ጸጸት ነው፡፡ ጸጸትነቱ ሰው በሠራው ኃጢአት ተጸጽቶ
ኃጢአቱ ይሰረይለት ዘንድ እግዚአብሔርን በሐዘን በለቅሶ ሲለምን እንጂ የጐልማሳ ሚስት
ሳልቀማ፣ የሰው ገንዘብ ሳልሰርቅ ቀረሁ … በማለት የሚጸጸተው ጸጸት አይደለም፡፡
ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት። በጥምቀት ከእግዚአብሔር
የምትገኝ የልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ ናት፡፡ በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው የመንግሥተ ሰማያት
አራቦን ማለትም መግዣ ናት። ንስሐ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት፡፡ በንስሐ
በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን።
ምሥጢረ ንስሐን የመሠረተ ራሱ ጌታችን ነው። ለሰው ልጆች አዛኝ የሆነው መፍቀሬ ሰብ
ክርስቶስ የኛን ኃጢአት ሁሉ በሰውነቱ ተሸክሞ በሕማምና በሞቱ አንድ ጊዜ አድኖናል።
ይህንንም ጸጋ በምሥጢረ ጥምቀት አግኝተነዋል። ከዚህ በኋላ ለምንፈጽመው በደል ማስተስረያ
እንዲሆነን ለሐዋርያትና እነሱን ለሚከተሉት ካህናት ሥልጣንን በመስጠት ምሥጢረ ንስሐን
መሥርቶልናል። ኃጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን የእግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ለእኛ ጥቅምና
ደህንነት ሲል ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለጴጥሮስና ለሐዋርያት ተከታዮች ሰጥቷል። ቅዱስ
ጴጥሮስ ስለ እውነተኛ እምነቱ ከመሰከረ በኋላ ሥልጣነ ክህነትን ማለትም የመንግሥተ
ሰማያትን ቁልፍ ክርስቶስ ሰጥቶታል። እንዲህም ብሎታል «የመንግሥተ ሰማያትንም
መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም
የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል» ማቴ. ፲፮፥፲፱
የቀደመ በደልና ኀጢአት ይደመሰስ /ይሠረይ/ ዘንድ ንስሐ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ሐዋርያው
ቅዱስ ዼጥሮስ በበዓለ ሃምሳ በጽርሐ ጽዮን ዙሪያ ተሰብስበው ለነበሩ እጅግ በርካታ ሕዝቦች
የድኅነትን ትምህርት አስተማራቸው፡፡ በትምህርቱ የተመሰጡት እነዚያ ሰዎችም “ምን
እናድርግ?” ባሉ ጊዜ የተመለሰላቸው መልስ ከንስሐ ሕይወት ጋር የተያያዘ ነበር። (ሐዋ.፪፥
፲፬‐፵፩፡፡) በቤተ መቅደስ በር ላይ ይቀመጥ የነበረውን ድውይ /መሔድ የተሳነውን ሕሙም/
ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስ በክርስቶስ ስም በፈወሱት ጊዜ መገረምና መደነቅ የሞላባቸው
“ሸማ ሲያድፍ በውሃ፤ ሰውነት ሲያድፍ በንስሐ” እንዲሉ:: ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና
የተቀበለ ሰው ከቀደመ ኃጢአቱ በጥምቀት ቢነጻም በቀረ ዘመኑ ከሚሠራቸው ጥፋቶች
በምሥጢረ ንስሐ እንዲነጻ ክርስቶስ ፈቀደለት፡፡ አስቀድሞ ለሐዋርያት ከዚያም ቀደም ባለው
ምዕራፍ እንዳየነው በተዋረድ ለተነሡና ለሚነሡ አገልጋዮች (ካህናት) ኃጢአትን ይቅር
የሚሉበትና የሚይዙበት /የሚፈቱበትና የሚያስሩበት/ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ (ዮሐ፳፥፳፩‐፳፫
ማቴ፲፰፥፲፰) ይህም ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአትን የሚያስተሰርዩበትን ጸጋ፣
መንግሥተ ሰማያትንም ከፍተው የክርስቶስን መንጋ የሚያስገቡበት ቁልፍ ለካህናት አባቶቻችን
ሰጥቷቸዋል።” የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ
በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” በማለት
እንደገለጸልን፡፡ (ማቴ፲፮፥፲፮‐፳፡፡)
በሉቃስ ወንጌል ምዕ፲፭፥፬- ፍጻሜው ያለውን ታሪክ ስንመለከት ከመንጋው ተነጥሎና ባዝኖ
በምድረ በዳ የጠፋውን በግ፣ በቤት ውስጥ የጠፋውን ድሪምና ከቤተሰቡ ተለይቶ ወጥቶ
የጠፋውን ታናሹን ልጅ እናገኛቸዋለን። ባለበጎቹ፣ ባለድሪሟና፣ የልጁ አባት በጠፋባቸው ነገር
እጅግ እንዳዘኑ፣ የጠፋባቸውን አጥብቀው እንደፈለጉና ባገኙትም ጊዜ ፍጹም ደስ እንዳላቸው
እናነባለን፡፡ እነዚህ ተገናዛቢ ታሪኮች ሁሉም የንስሐን ክብር፣ ኃይልና ምሥጢር ያሳዩናል፡፡
ከሀገርና ከወገን ተለይቶ፤ ከሃይማኖት፣ ከምግባር ምድረ በዳ በሆነ ቦታም መጥፋት አለ፡፡ በቤት
ውስጥ ሆኖ የትም ሳይወጡ ባሉበት ሁኔታ መጥፋት አለ:: ከሞላ ከተትረፈረፈ፥ ሰላምና ፍቅር
ከሰፈነበት ቤት አሻፈረኝ ልቀቁኝ ብሎ ወጥቶም መጥፋት አለ፡፡
ባለንብረትና ወላጅ አባት የሆነ ሰው ደግሞ ያ ነገር የጠፋበትን መንገድና ሁኔታ እያሰላሰለ
ከመናደድ ይልቅ የሚገኝበትን መንገድ በማሰብ ፍለጋው ላይ ተግቶ ይሠራል:: ባገኘው ጊዜ
ደግሞ ባለው ነገርና አቅም ሁሉ ደስታውን ይገልጻል። በመንፈሳዊ የሕይወት ጉዞም ሰዎች
8.4.2 ኑዛዜ
ከዚህ ቀጥሎ ተነሳሒው ኃጢአቱን ሥልጣነ ክህነት ላለው ካህን ይናዘዛል። ኑዛዜ ማድረግ
በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘ ነው። «ከነዚህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ቢሆን፥ የሠራውን ኃጢአት
ይናዘዛል። ስለሠራው ኃጢአት ለእግዚአብሔር የበደልን መስዋዕት ያመጣል፤ … ካህኑ
ስለኃጢአቱ ያስተሰርይለታል። … እርሱም ይቅር ይባላል።» /ዘሌ. ፭፥፭-፮፣፲/። ከዚህ ጥቅስ
የኃጢአትን ስርየት ለማግኘት ለካህን መናዘዝ እንደሚገባ እንማራለን። ስለዚህ ኃጢአታችንን
ለአናዛዡ ካህን ከበደሉ ዓይነትና ሁኔታ ጋር ማስረዳት ይገባናል። ስንናዘዝም ከእንባና ከጸጸት
ጋር ሆነን ከካህኑ ጋር አብሮ እግዚአብሔር እንደሚሰማን አምነን በእውነት መናገር
ያስፈልገናል።
በሽታውን የሰወረ መድኃኒት አያገኝም ተብሏልና ለነፍስ ቁስል ሐኪም ለሆነው ለካህኑ
ኃጢአታችንን ከሰወርን ለነፍስ የሚሆነውን ፈውስ ለማግኘት አንችልም።«ኃጢአቱን የሚሰውር
ምንም እንኳን ተነሳሒው ከዘላለም የሞት ቅጣት ቢድንም ዓይነቱና መጠኑ የተለያየ ጊዜያዊ
ቅጣት መቀበል ይገባዋል። ይህም የንስሐ ቀኖና ይባላል። ጊዜያዊ ቅጣት ወይም ቀኖና
ያስፈለገበት ምክንያት ኃጢአትን መሥራት ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ለተነሳሒው ለማሳሰብና
ዳግመኛ እንዳይበድል ለማስጠንቀቅ እንዲሁም ደግሞ ሥጋን በመገሰጽ ለነፍሱ የጽድቅንና
የደህንነትን ጎዳና ለማስተማር ነው። ምንጊዜም ፍቅሩና ምሕረቱ ከኛ ጋር ቢሆንም
እግዚአብሔር በአባትነቱ ላጠፋነው ጥፋት በጊዜያዊ ቅጣት ይቀጣናል። መልካም አባት ልጁን
እንደሚገስጽና እንደሚቀጣ ዓይነት ይቀጣናል። /ዕብ. ፲፪፥፭-፲፩/። እንግዲህ ያልተገራ ልቦና ካለን
ለእግዚአብሔር በማስገዛት የኃጢአታችንንም ቅጣት በደስታ በመቀበል የበለጠ ጸጋና ረድኤትን
እናገኛለን። «በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፣ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ እኔ
በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና የሚሰጠው እንደ ተነሳሒው የኃጢአት ዓይነትና ሁኔታ ታይቶ
ነው። ካህኑ የተነሳሒውን የኑሮ ሁኔታና ያጋጠመውን ፈተና በማስመልከት ምክርና ትምህርት
ይሰጠዋል። እንደመልካም የነፍስ ሐኪምም እንደበሽታው ሁኔታ ካህኑ አስፈላጊውን የነፍስ
መድኃኒት ይሰጠዋል። የቀኖና አሰጣጥ መንገዱና ዓይነቱ ብዙ ነው። ለአንዳንዱ ተነሳሒ የቃል
ምክርና ተግሳጽ ብቻ የሚበቃው አለ። ለሌላው ጾም ብቻ ወይም ከስግደት ጋር ቀኖና
ይሰጠዋል። ልዩ የንስሐ ጸሎት፣ ምጽዋት፣ ለተበደለው ወገን ካሳ መክፈል፣ ለችግረኞች
አገልግሎት መስጠት አስፈላጊም ከሆነ ለተወሰነ ጊዜ ከቁርባን መለየት ወይም ልዩ ልዩ
አስቸጋሪ ነገሮችን መፈጸም ወይም ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ኑሮ የሚጠቅሙ
የጉልበትም ሆነ የአዕምሮ ሥራ መሥራትና የመሳሰሉት ሁሉ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን
ይቆጠራሉ።
8.5 የሚያስገኘው ጸጋ
በንስሐ ሕይወት መመላለስ በተነሳሕያን ሕይወት የሚታዩ ጉልህ ፍሬዎች አሉት:: የአፈጻጸም
ሥርዓቱን ጠብቆ በተገለጸው መሠረት የተገበረ ሰው ከምንም በላይ ታስሮበት ከነበረው ኃጢአት
የተፈታ ይሆናል፡፡ ይህ ነጻነት በምሥጢረ ንስሐ የሚገኝ ፍሬ (ጸጋ) ነው። ተነሳሒው በኑሮው
ሁሉ ትሑት እንዲሆንም ይረዳዋል። በዚህም ከትዕቢት ተላቆ ራሱን በማዋረድ ክርስቶስን
ወደሚመስልበት ሕይወት ለማደግ ይችላል:: ሌላው ተነሳሒው የሚያገኘው ጥቅም ኀጢአትን
የሚጸየፍበትና የሚጠላበትን ኃይል መጎናጸፍ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኃጢአተኞችን ግን
የሚወድበት ስለ እነርሱም የሚያለቅስበት ጸጋ ያገኛል:: ይህም በሌሎች ኀጢአት (ላይ)
በመፍረድ ከሚመጣ አምላካዊ ፍርድ ለመዳን ያስችለዋል። በራሱ ኀጢአት ከልቡ ያዘነና
የተጸጸተ ሰው ለኀጢአተኞች ከማዘን ውጪ በእነርሱ ላይ የማይጠቅሙ (የፍርድ) ቃላትን
ሊያስብና ሊናገር አይችልምና።
9. ምሥጢረ ክህነት
9.1 የምሥጢረ ክህነት የቃሉ ትርጉም
ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ 18 1ቆሮ 4፡1 ማር
28፡20 ክህነት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የተቀደሰ አገልግሎት ማለት ነው፡፡ የክህነት
አገልግሎት የተጀመረው በላይ በሰማይ ነው ፡፡ ክህነት የአገልግሎት ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን
ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡ ሃያ አራቱ መላእክት (ካህናተ ሰማይ) የእግዚአብሔር
አገልጋዮች ይባላሉ፡፡ ያለ እረፍት ‹ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረና ያለ የሚመጣው ሁሉንም
የሚገዛ› እያሉ ሲያመሰግኑ ይኖራሉ፡፡ አንድም ክህነት መንፈሳዊ አገልግሎት ነው፡፡
አገልግሎቱም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የሚፈጸም ነው። የክህነት ሥልጣን ምድራውያን
መሪዎችና ዳኞች የማይሾሙትና የማይሽሩት ሰማያዊ ሹመት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለደቀ መዛሙርቱ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን በመስጠት ነው ምሥጢረ ክህነትን ያጸናው።
ቤተክርስቲያን የምሥራቹን ቃል ለዓለም በማዳረስ ምእመናንን የምትጠራቸው በካህናት
አማካኝነት ነው። ምሥጢራቷን የምታከናውነውና የእግዚአብሔር ጸጋ ለሚገባቸው ሰዎች
የምታድለው በሐዲስ ኪዳን ካህናት በኩል ነው፡፡ የካህናት አገልግሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመሠረተው (በሠራው) ሥርዓት መሠረት የሚጓዝ ነው።
እግዚአብሔር አዳምንም ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል
ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው
ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ)
በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት
ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ
ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ
ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ 20፡22 ማሬ 18፡
ኦሪት ከተሰጠች በኋላ የመጀመሪያው ካህን ሆኖ የተሾመው አሮን ይባላል፡፡
እውነተኛውን( አማናዊውን) ክህነት የመሰረተው ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፡
፡ ዕብ 6፣26-28 ‹‹ካህኑ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልክተኛ ነውና ከከንፈሮቹ (ከአንደበቱ)
ዕውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል ፤ ሰዎችን ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል፡፡››
“በዚያችም ቀን አዳም ከኤዶም ገነት ሲወጣ ለበጎ መዓዛ ነጭ ዕጣን፣ ቀንዓትና ልባንጃ
ስንቡልም ኀፍረቱን በሸፈነበት ቀን በጥዋት ፀሐይ ሲወጣ ዐጠነ።” ኩፋ. ፭፥፩ ይህም
አባታችን አዳም በተፈጠረበት ወቅት እግዚአብሔር ካሳደረበት ፯ት ሀብታት አንዱ ሀብተ
ክህነት መሆኑን የምንረዳበት አንዱ ማስረጃ ነው፡፡”
ስለ ያዕቆብ ደግሞ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለ፤ “በዚያም መሠዊያውን ሠራ፤ የዚያንም ቦታ
ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፡፡’’ (፴፭፥፯፡፡)
እግዚአብሔር ካህን ነበረ፡፡” (ዘፍ፲፬፥፲፱) ፣ “እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት፥ አንተ ለዘለዓለም ካህን
ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም፡፡” (መዝ ፻፱፥፬፡፡) ይህም ኀይለ ቃል መልከጼዴቅ
የልዑል እግዚአብሔር ካህን ብቻ ሳይሆን የወልደ እግዚአብሔርም ምሳሌ መሆኑን
ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ኀይለ ቃል ሲያብራራ እንዲህ ነበር ያለው፤ “የሳሌም
ንጉሥ፣ የልዑል እግዚአብሔርም ካህን የሆነ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብርሃም ነገሥታትን ድል
ነስቶ በተመለሰ ጊዜ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ
ሰጠው፤… ክህነቱ የወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል።” (ዕብ፯፥፩‐፬፡፡)
ለጊዜው ይህን ያህል ጠቀስን እንጂ ሙሉው ምዕራፍ የመልከ ጼዴቅን ክህነትና ክብር
ከክርስቶስ ጋር እያነጻጸረ ያቀረበበት ክፍል ነው።
ከሙሴ ጀምሮ ባለው ዘመነ ኦሪትም እግዚአብሔር ከአሥራ ሁለቱ ነገዶች መካከል አንዱ
በክህነት እንዲያገለግለው መምረጡን እንረዳለን። (ዘጸ ፳፱፥፩‐፲ ዘሌ፰፥፲፪፤ ፳፩፥፩‐ፍጻሜ፡፡ ዘኁ፩፥
፶‐፶፪፤ ዘኁ፩፥፶‐፶፪፤ ዘኁ፫፥፩‐፲፬፡፡) ከተመረጠው የሌዊ ነገድ መካከልም አሮንና ልጆቹን የበለጠ
አክብሮና አቅርቦ በክህነት እንዲያገለግሉት መፍቀዱን ከላይ የጠቀስናቸው ማስረጃዎች
ይነግሩናል። አሿሿማቸውን፣ ዝርዝር አገልግሎታቸውንና መሥዋዕታቸውን በተመለከተም
በኦሪት ዘጸአት ፳፰፡፳፱፣ ዘሌዋዉያን ፰፡፲ እና ዘኁልቁ ምዕራፍ ፫‐፬ ተጽፎ እናገኛለን፡፡
ምንም እንኳን ለሐዲስ ኪዳን ክህነት እንደ ብሉይ ኪዳን ለክህነት አገልግሎት የተለየ ዘርና
ነገድ ባያስፈልገውም ሁሉም የሰው ዘር ካህን ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይከተሉት ከነበሩት ፭ ገበያ ሕዝብ መካከል ለክህነት
አገልግሎት መጀመሪያ የመረጣቸው ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያት እንጂ ሁሉንም ተከታዮች
አልነበረም። (ማቴ ፲፥፩‐፭፡፡ ማር፫፥፲፫‐፲፱፡፡ሉቃ፮፥፲፪‐፲፮፡፡) እዚህ ላይ ልንመለከተው የሚገባን
በብሉይ ኪዳን ለቤተ እስራኤልና በሐዲስ ኪዳን ለክርስቲያኖች የተሰጠ ተመሳሳይ ይዘት ያለው
ቃልኪዳን አለ፡፡ ይህንንም በንጽጽር እንደሚከተለው እናየዋለን ።
በብሉይ ኪዳን ዘመን በሙሴ ምስፍናና በአሮን ክህነት ላይ የሚያጉረመርሙ፤ “ሁሉም ቅዱሳን
ናቸውና እናንተ አበዛችሁት” የሚሉ ተቃዋሚዎች ተነሥተው ነበር። (ዘኁ ፲፮፥፩‐ፍጻሜ፡፡)
በምዕራፉ ውስጥ በግልጽ እንደተቀመጠው ከእግዚአብሔር የተከፈለው የተቃዋሚዎች ዕጣ
ፈንታ “ትክክል ናችሁ!” የሚል መልስና “በረከት” ሳይሆን ታይቶ የማይታወቅ ጥፋትና
ጉስቁልና ነበር። ዳግመኛ ተመሳሳይ መገዳደር በካህናት ላይ እንዳይነሣ ለማድረግም
እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ፲፪ ቱንም ነገዶች የሚወክሉ የአባቶቻቸውን በትር ስማቸውን
ጽፎ ወደ መቅደስ እንዲያስገባ አደረገ። እስራኤላውያን ሁሉም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሆነው
ሳለ አሁንም ክህነትን ለአሮንና ለአባቱ ለሌዊ ቤት ማጽናቱን በተዓምር መሰከረ። ቀድሞ
በሰጠው ምልክት መሠረትም የአሮን ስም የተጻፈባት የአባቱ የሌዊ በትር አቆጥቁጣ /ለምልማ/
አብባና የበሰለ ለውዝ አፍርታ ተገኘች። መላው የእስራኤል ልጆችም አዩና አመኑ። (ዘኁ ፲፯)
፭ ጊዜያዊ የኃጢአት ሥርየትን ያሰጥ ነበር ፍጹም የሆነ ሥርየተ ኃጢአትን ያሰጣል
መስፈርታት /መመዘኛዎች/
“ጵጵስና ሊሾም የሚወድ መልካም ሥራን ወደደ የሚለው ቃል የታመነ ነው፤ ነገር ግን
ጵጵስናን የሚሾም እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፡፡
1. የማይነቀፍ፤
2. አንዲት ሴት ያገባ፦ ይህ እስከ ኒቅያ ጉባኤ ድረስ የተተገበረ ሲሆን በ318ቱ ቅዱሳን አባቶች
ጉባኤ ጳጳስ ድንግላዊ እንዲሆን በመወሰኑ አሁን እየተፈጸመ ያለው ይህኛው /ድንግላዊ
የአሿሿም ሥርዓት
ኤጲስ ቆጶስ በዕለተ እሑድ ይሾም። በሚሾምበትም ቀን ካህናትና ምዕመናን ይገኙ ሕዝቡና
ካህናቱም መክረውለት ይሾም፤ እጃቸውን በእርሱ ላይ ሊያኖሩ የመጡ ኤጲስ ቆጶሳቱም “እኛ
በዚህ በተመረጠ በእግዚአብሔር ባሪያ ላይ እጃችንን እናስቀምጣለን፤ እያሉ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም እጃቸውን ያስቀምጡ። ነውር በሌለባትና አንዲት በሆነች በማይገለጥ
በሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በጸናች ሥርዓት ይጸና ዘንድ፣ የቀና ፍርድን ለመፍረድ፣
ምስጋናን፣ ለመግለጥ ልጅነትን ለማሰጠት፣ ለታመነች ትምህርት፤ ይኸውም ነገረ መስቀሉን
ለማስተማር ከሥሉስ ቅዱስ ዘንድ በጉባኤ በቤተክርስቲያን የተሾመ ነው።
ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ቀዳሚ የሆነው ኤጲስ ቆጶስ እጁን ይጫንበት የሹመቱንም ጸሎት
ያድርስ፤ ሕዝቡም “አሜን” ይበሉ። ከዚህ በኋላ ኤጲስ ቆጶሳቱ እጅ ይንሡት ሕዝቡና ካህናቱም
ይገባዋል! ይገባዋል! ይበሉ። ሁሉም እጅ ይንሱት። በእንተ ሰላምን ይጸልዩለት ከዚህ በኋላ
ሊነበብ የሚገባውን ክፍለ መጽሐፍ ቅዱስ ያንብቡ፡፡ አከታትለውም ቅዳሴውን ይፈጽሙ
አስቀድሞ እርሱ ሥጋውንና ደሙን ይቀበል። ከዚያም በየማዕረጋቸው ለሁሉም ሥጋውና
ደሙን ያቀብላቸው። በሰላምም ያሰናብታቸው። እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ በጌታ ትንሣኤ
አምሳል ፫ ቀን መንፈሳዊ በዓል ያክብሩ።
ሁሉም ከተመረጡ በኋላ ሕዝቡና ቀሳውስቱ ዲያቆናቱ ኤጲስ ቆጶሳቱም በዕለተ እሑድ
ይሰብሰቡ። ከእርሱ የሚበልጠው “አለቃ ይሆናችሁ ዘንድ የመረጣችሁት ይህ ነውን?” ብሎ
ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን ይጠይቃቸዋል። አዎን ቢሉ “የከበረችው ሹመት ለዚህ ትገባዋለችን?”
ይበል፤ “በሚገባና በተረዳ ሥርዓት አኗኗርን አጽንቷልን? ምንም በደል አልተገኘበትምን?”
ይበል እነርሱም መልሰው እንደዚህ እንደሆነ ቢናገሩ በማድላት ያይደለ በእውነት ሹመት
ይገባዋል፡፡ በሦስተኛውም ደግሞ “ለዚህ ሹመት በእውነት ይገባዋልን?” ብሎ ይጠይቃቸው።
ነገር ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ይጸናልና በሦስተኛውም ጊዜ ይገባዋል ቢሉ ሁሉም
እጃቸውን ዘርግተው ያጨበጭባሉ። ይህንንም በስምምነት ካደረጉ በኋላ ጸጥታ ይሁን።
ኤጲስ ቆጶሳቱ አዲሱን ኤጲስ ቆጶስ ከመሾማቸው በፊት እጃቸውን ይታጠባሉ። /ፍትነገ.
አን፬፡፡/
ተሿሚውን ኤጲስ ቆጶስ መስቀል ያስይዙታል።
ኤጲስ ቆጶስ በአንድ ኤጲስ ቆጶስ አይሾምም። ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር ሁለት ወይም
ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት /ጳጳሳት/ አንብሮተ እድ በማድረግ ይሾማሉ። /አብጥሊስ ፪፡፡/
ኤጲስ ቆጶስ የሚሾመው በሚሾምበት ሀገር ካህናትና ምእመናን ምርጫና በርእሰ ሊቃነ
ጳጳሳቱ ፈቃድ ነው። /አብጥሊስ ፪፡፡/
መራጮችም (ቢያንስ) 30 ዘመን (ዓመት) የሆናቸው ናቸው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለጊዜው ለረድኡና ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ለሾመው ለቲቶ ለፍጻሜው
ደግሞ ለቤተክርስቲያን መመሪያ እንዲሆን ያስቀመጠው /ያስተላለፈው/ የቀሳውስት መስፈርት
የሚከተለውን ይመስላል፡፡ የአንዲት ሚስት ባል፤ የማይነቀፍ፤ የሚያምኑ ልጆች ያሉት፤
ስለመዳራት ወይም ስለአለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር ሹመው፡፡ (ቲቶ ፩፥፭‐፯)
በተጨማሪም በፍትሐ ነገሥት አባቶቻችን (የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት) በጉባኤ የወሰኑአቸው
መመዘኛዎች ቀርበዋል፡፡ ጥቂቶቹን እነሆ፡- በራሱ ፈቃድ የሚኖር አይሁን፤ ቂመኛ፣ አብዝቶ፣
የሚጠጣ፣ ለመማታት (ለመገዘት) እጁን (አንደበቱን) የሚያፈጥን አይሁን፤ እንግዳ መቀበልን
የሚወድ፤ በጎ ሥራን የሚወድ፤ ንጹሕ፥ ጻድቅ፥ ቸር የሆነ፤ ከፍትወታት ሰውነቱን ወስኖ ገትቶ
የያዘ፤ የሃይማኖት ትምህርት ነገርን በማስተማር የሚተጋ፤ ያልታዘዘ ትርፍን የሚወድ
አይሁን። የእውነት ትምህርትን በማስተማር ማረጋጋት የሚችል፤ የሚክዱትንና
የሚተናኮሉትን የሚከራከራቸው ይሁን እንጂ፤ ሠላሳ ዓመት የሆነው፤ መልካም የሆኑትን
የአምላክ መጻሕፍትን ነገር ይልቁንም አራቱን ወንጌላት ያወቀ፤ አምስት ሰዎች የመሰከሩለት፤
(ፍት.ነገ. አነ ፮፥፪፻፲‐፪፲፫)
አፈጻጸም
አፈጻጸም
ያሸነፉትን ጠቅሰን ተናገርን እንጂ፡፡ በዚህ ፈተና ድል የሚነሱ፣ መንጋው ይበተን ዘንድ
ዲያብሎስ መትቶ የሚጥላቸው፣ ከዚያም በኋላ ከራሳቸው አልፎ ምዕመናንንም
የሚያሰናክልባቸው አባቶችም ጥቂት አይደሉም፡፡
የአባቶች በፈተና መውደቅ ክብደቱ የተለያየ ነው፡፡ አባቶቻችን እንደኛው ሥጋ ለባሽ ፍጡር
ናቸውና የጋራ ድካማችን ይጋራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በየዕለቱ ጥቃቅን ስህተቶችን
መፈጸማቸው አይቀርም፡፡ ቅዱሳን አባቶች እንደሚሉት «ማንም በዚህች ምድር ላይ ለአንድ ቀን
ቢውል እግዚአብሔርን ሳይበድል የሚውል የለም»፡፡ ስለዚህ አባቶችም በፈተና ቢወድቁ
አይገርምም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ንስሓን ለሁሉም ትፈቅዳለች፡፡ እያንዳንዳቸው ካህናት
አባቶች ለሌሎች የንስሐ አባት ቢሆኑም ለራሳቸው ደግሞ የንስሐ አባት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
ስለዚህ አባቶቻችን በትንሽም በትልቅም ኃጠአት ቢወድቁ ንስሐቸውን እግዚአብሔር ይቀበላል፤
ምዕመናንም የኃጢአትን አስቸጋሪነት እያወቁ ያዝኑላቸዋል ይጸልዩላቸዋል እንጅ
አይፈርዱባቸውም፡፡ ነገር ግን ክህነትን የሚያስነጥቁ ኀጢአቶች አሉ፡፡
አባቶች በእነዚህ ኃጢአቶች ቢወድቁና ንስሐ ቢገቡ ኃጢአታቸው ይቅር ይባላል፤ ክህነታቸው
ግን አይመለስም፡፡ በእነዚህ ኃጢአቶች የተሰነካከሉና ንስሐ የገቡ አባቶች እንደምዕመናን ሆነው
ወደ ቅድስና የማደግ ፀጋ ሳይነፈጋቸው በቤተ ክርስቲያን በጾም በጸሎት በሰላም ይኖራሉ፡፡
ከዚህ የከፋው የአባቶች ፈተና ግን ታላላቅ ኃጢአቶችን /ለምሳሌ፡- እንግዳ ትምህርት
ማስተማር፣ ምንፍቅና፣ ዝሙት.../ ሰርተው ንስሐ አለማግባት ነው፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው
የተወሰኑ የዋሃን ምዕመናንን ተከታይ በማድረግ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚያውኩ በቤተ
ክርስቲያን ታሪክ ይታወቃል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የከፋፈሉት ታላላቆቹ መናፍቃን በቤተ
ክርስቲያን የክህነት ማዕርግ የነበራቸው /አርዮስ ቄስ ነበር፤ ንስጥሮስ የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ
ነበር.../ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ናቸው፡፡
በህዝበ እስራኤል ኃጢአት ታቦተ ጽዮን ተማርካ እንደነበር፣ ነቢያቱም በባቢሎን ተማርከው
እንደነበረ አሁንም አባቶቻችን የተማርኩት በእኛ ኃጢአት ምክንያት ይሆንን? ብሎ ራስን
መጠየቅ ይገባል፡፡ አባቶች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩበት፣ ገዳማት ተጠናክረው
ለጸሎትና መልካም አባቶችን ለማፍራት እንዲተጉ ረድተናቸዋል ወይ? አባቶች በፈተና ሲወድቁ
እጃችን በእነርሱ ላይ የምንቀስር ሁላችን ወደ ፈተና እንዳይገቡ በምን ረዳናቸው? በጸሎታችን
እናስባቸዋለን ወይ? አስራት በኩራት እናወጣለን ወይ? «የሚያስተምሩንና አርአያ የሚሆኑን
አባቶች ብናገኝ እናደርግ ነበር» ልንል እንችላለን፡፡ ነገር ግን ይህ ግማሽ ምክንያት እንጅ ሙሉ
ስላልሆነ እኛም እነርሱም /ካህናቱም/ ከበደል አናመልጥም፡፡«ሁላችንም በድለናል»ማለት
ይሻለናል።
2. መፍረድ አይገባም
«እንዳይፈረድብህ አትፍረድ» ይላል /ማቴ 7፥1/ ለመፍረድ ማንም ስልጣን አልሰጠንም፡፡ ኧረ
ለመሆኑ አባቶች የተሸከሙትን ፈተና ሞክረን አይተነዋል ወይ? እኛ ብንሆን እንደነርሱ
እንደማንሆን ምን ማረጋገጫ አለን? አባቶቻችን ዓለምንና ክብርን ንቀው፣ ራሳቸውን
ለምንኩስናና ራስን የመካድ ኑሮ አሳልፈው ሰጡ፡፡ ከእነርሱ መካከል የተውትን ክብር የናፈቁ፣
የካዱት እኔነታቸው እያሸነፋቸው ይኖራሉ፡፡ በእነዚህ አባቶች ላይ እጆቻችን የምንቀስር
ስንቶቻችን ይህንን ክብርንና ራስን የመካድ ኑሮ ሞክረነው እናውቃለን፡፡ አብዛኞቻችን
የምዕራባውያንን የተንደላቀቀ ኑሮ የለመድን፣ የምንኩስናንና የተጋድሎን ኑሮ እንኳን
የምንሞክረው ቀርቶ ስንሰማው የሚያንገሸግሸን፣ አንዳንዴም የምንቀላለድበት አይደለምን?
ታዲያ እንዴት ሞክረውት የተሸነፉትን ለመውቀስና ለመኮነን እንፈጥናለን?
ነበር። ያቺ የአሮን በትርም ለማጉረምረማቸው ምስክር ትሆን ዘንድ በምስክሩ ታቦት አጠገብ
እንድትቀመጥ መታዘዙም ይታወቃል፡፡ (ዘኁ ፲፯፥፩‐፲፪፡፡) በዚህ ሁሉ የክህነት አገልግሎት ታሪክ
ውስጥ ሴቶች ሱታፌ እንዳልነበራቸው መረዳት ተገቢ ነው።
በአዲስ ኪዳንም ቢሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክህነትን ምሥጢር በመሠረተ ጊዜ የማሰርና
የመፍታት ሥልጣንን ሰጥቶ ምሥጢራትን እንዲፈጽሙ የፈቀደላቸው ከተከተሉት መካከል
ወንዶች ማለትም ቀደም ብሎ ፲፪ቱ ሐዋርያት፤ ከዚያም ፸፪ቱ አርድዕትና የመሳሰሉት ናቸው።
ለሁሉም አማኝ ማለትም ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች አለመፈቀዱን ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ
ይነግሩናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ ጢሞቴዎስን ፈጥኖ እጁን በመጫን ካህናትን
እንዳይሾም ማስጠንቀቁ ለዚህ አንድ ማሳያ ነው፡፡ ሁሉም ካህናት መሆን የሚችሉ ቢሆን ኖሮ
እንዲህ ያለ ማስጠንቀቂያና ትምህርት አይሰጥም ነበር (፩ጢሞ ፭፥፳፪፤ ፫፥፩‐፲፬፡፡) ከላይ
እንደገለጽነው የሐዲስ ኪዳን ትምህርት ከብሉይ ኪዳን ክህነት የሚለየው የዘር ተከፍሎ
ስለሌለበት ነው። ውድ አንባቢ ሆይ እዚህ ላይ መረዳት ያለብን እግዚአብሔር ከወንዶች መካከል
እሱ ባወቀ በመረጣቸው ብቻ ሥልጣነ ክህነትን ፈቅዶ ሌሎችን የከለከለበት ምክንያት
የማይታወቅ መሆኑን ነው። እግዚአብሔርን “ይህን ለእገሌ ፈቅደህ ይህንን ለነእገሌ ለምን
ከለከልክ?” ማለት የማይቻል መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ (ኢሳ ፵፥፲፩‐፲፭፡፡) የሥልጣነ ክህነት
አለመፈቀድ ማለት የቅድስና ሕይወትና የመንግሥተ ሰማያት በር መዘጋት ወይም መከልከል
ስላልሆነ በተሰጠውና በተፈቀደው የአገልግሎት መስመር እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን
ተግቶ ማገልገል ለቅድስና ሕይወት እንደሚያበቃ ማወቅ ይገባል። ከዚህ ውጪ “ሴቶች ክህነት
ለምን ተከለከሉ?” በማለት እግዚአብሔርን መሞገት ምንም ዓይነት ዕርባና የለውም። (ኢሳ፵፥
፱‐፲፩) ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚያስገቡ መንገዶች በርካታ መሆናቸውንና እነዚህም
ለሴቶችም ጭምር የተፈቀዱ የአገልግሎት መስመሮች መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም።
(፪ቆሮ፲፪፥፩‐ፍጻሜው)
በጸሎት ድዉያንን የመፈወስ ተግባር በብሉይ ኪዳን ዘመንም እንደነበር ቅዱሳት መጻሕፍት
ምስክሮቻችን ናቸው። (ዘሌ. ፲፫፥፩‐ፍጻሜው፡፡) በድፍረት የእግዚአብሔር አገልጋይ በሆነው
በወንድሟ በሙሴ ላይ ካህኑ አሮንን በማስተባበር ሐሜት በመሰንዘሯ በለምጽ በሽታ
የተመታችው ማርያም እኅተ ሙሴ የዳነችው በወንድሟ በሊቀ ነቢያት ሙሴ ጸሎት ነበር።
“ሙሴም ወደ እግዚአብሔር እየጮኸ አቤቱ እባክህ አድናት አለው።” /ዘኁ ፲፪፥፩‐፲፮፡፡/
“የተባለው ይህንን ያረጋግጥልናል። የቀንዲል መብራቶችም በደብተራ ኦሪት እንደነበሩ መጽሐፍ
ቅዱስ ይነግረናል። (ዘጸ ፵፥፬፡፡) እነዚህ ሁሉ አማናዊ ለሆነው ምሥጢረ ቀንዲል ምሳሌዎችና
መነሻዎች መሆናቸውን ማስተዋል ይገባል::
ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ
ቀንዲል ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው
የሚሰቃዩ ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች
ሥርዓተ ቀንዲልን የሚፈጽሙት ሰባት ኤጲስ ቆጶሳት ወይም ቀሳውስት ሆነው ነው። እነዚህ
ሰባት መሆናቸው ሰባት ቁጥር በዕብራውያን ፍጹም ቁጥር እንደመሆኑ በምሥጢረ ቀንዲል
ፍጹም ሥርየትና ፈውስ መገኘቱን ለማጠየቅ ነው። እነሱም /ካህናቱ/ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ
ያያቸው የሰባቱ የወርቅ መቅረዞችና መብራቶች ምሳሌ ናቸው። (ራእ፩፥፳፡፡) ከላይ እንደገለጽነው
ኃጢአቱን ለተናዘዘው ምእመን በቀረበው ንጹሕ ዘይት ላይ የታዘዘው ጸሎት ይደረሳል። ሰባቱም
ካህናት በየተራ በታመመው ራስ ላይ የታዘዙትን የወንጌል ክፍላት ያነባሉ ወንጌል ከተነበበ
በኋላም ሰባቱም እጃቸውን በሕመምተኛው ላይ ጭነው የታዘዙትን ጸሎታት ይጸልዩለታል፡፡
ቅብዓ ቅዱስ በማንኛውም ዓይነት በሽታ በተለይ በቁስል ለተመቱና ጆሯቸው ለታመመባቸው
ሰዎች እንዲሁም ደዌ ነፍስ ላደረባቸውና ረድኤተ እግዚአብሔር አጋዥ እንዲሆናቸው ፣
ከኃጢአታቸውም እንዲነጹ የፈለጉ ምዕመናን ካህኑ ጸሎተ ቀንዲል ጸልዮ በሚቀባቸው ጊዜ
ከነበረባቸው የሥጋና በሽታና የነፍስ ደዌ (ኃጢአት) ይፈወሳሉ። ነገር ግን በሚቀቡበት ጊዜ
ሀ. ፈውሰ ሥጋ ፦
ሰው ማለት ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ የተፈጠረ እንደመሆኑ በዚህ
ዓለም ሲኖር በሥጋውና በነፍሱ የሚቀበላቸው ሕማማት አሉ። ያንዱ መታመም ሌላኛውንም
ይጎዳል፤ ማለትም የሥጋ መታመም ነፍስን፣ የነፍስም መታመም ሥጋን ስለሚያውከው
ቤተክርስቲያን መንፈሳዊውን ሕክምና በተናጠል አትፈጽምም፡፡ አንዱ ተፈውሶ አንዱ ከታመመ
ከላይ እንደገለጽነው የተፈወሰውም ታማሚ መሆኑ አይቀርምና ምእመናን ይህን ድርብ ሕክምና
ታክመው ፈውሰ ሥጋ፣ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙ የምታደርግበት መንገድ ምሥጢረ ቀንዲል
ይባላል።
ለ. ፈውሰ ነፍስ