You are on page 1of 31

ምዕራፍ አንድ(፩)

፩. የነገረ ማርያም ትምህርት መሠረታውያን


መግቢያ፡-
 ይህ የነገረ ማርያም(Mariology) ትምህርት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ
ያለውን የሕይወቷን ታሪክ ብቻ የሚያጠና ሳይሆን ፣ስለ አምላክ እናትነቷ(እግዚአብሔር ወልድ ተወለደ፣ሰው
ሆነ ስንል እንዴት ሰዉ ሆነ የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ) ፣ ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ፣ በነገረ ሥጋዌ (በነገረ
ድኅነት ትምህርት ዉስጥ ) ስላላት ድርሻ ፣ ስለ ንጽሕናዋ ፣ቅድስናዋ፣ስለተሰጣት ክብር ጨምሮ የሚያጠና
የሚያካትት የሃይማኖት ትምህርት ክፍል ነው፡፡ ነገረ ማርያም የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የነገረ ድኅነት
አስተምህሮ አካል ነዉ፡፡

የትምህርቱ አጠቃላይ ዓላማዎች:-


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 እመቤታችን አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ከመውለድ ጀምሮ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ለሰው ልጆች
ባደረገው የማዳን ሥራ ውስጥ ያላትን ድርሻ ተገንዝበው ሃይማኖታቸውን ያጸናሉ፡፡
 የእመቤታችን ትወልድ ፣የዘር ሐረግና አስተዳደግ እንዲሁም ቅድስና ፣ድንግልና እና አማላጅነት ተረድተው
ተገቢውን አክብሮት ይሰጣሉ፡፡
 ስለ እመቤታችን በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገሩትን ትንቢቶችና ምሳሌዎች እንዲረዱት፡፡

ከተማሪዎች አጠቃላይ የሚጠበቅ ብቃት/ውጤት፡- ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ካጠናቀቁ በኋላ፡-


 የነገረ ማርያምን መሠረታዊ ጽንሰ ሀሳብ ይረዳሉ፡፡
 ነገረ ማርያም ምን ማለት እንደሆነ ይገነዘባሉ፡፡

፩.፩ ትርጉም፡-
ነገረ ማርያም ማለት ምን ማለት ነው ?
ነገረ ማርያም ከሁለት ቃላት የተገኘ /የተሰናሰለ/የተያያዘ/ነዉ፡፡
 ነገር፡- የሚለዉ ቃል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የአንድን ትምህርት መግለጫ አጉልቶ የሚያሳይ ሆኖ
ያገለግላል/እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ”ትምህርት” ማለት ነው/፡፡
 ማርያም ፡- ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የተሠጠ ክቡር ስም ነዉ፡፡
 ነገረ ማርያም ፡- ሲል በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በኩል ለስው ልጅ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጠዉን
ሁሉ የምንማርበት ትምህርት ነዉ፡፡
 አንድም በአምላክ ሕሊና ታስባ እንደምትኖርና ከጽንሰቷ እስከ ዕርገቷ ያለዉን የምንማርበት ትምህርት ነዉ፡፡
 ነገረ ማርያም ፡- የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ፤የስብከተ ሐዋርያት መነሻ፣የሊቃዉንተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢር
ነዉ፡፡
 ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ክርስቶስን(Chiristology) መናገር አይቻልም፡፡

፩.፪ ነገረ ማርያምን መማር ለምን አስፈለገ?


ሀ. ክርስትናን በአግባቡ ለመረዳት፡-
 ክርስትና ልዑል እግዚአብሔር የሰውን ሥጋ ለብሶ ክርስቶስ መባል በምድር ላይ ተመላልሶ ያሳየንን የእርሱን ፍለጋ
ተከትለን እርሱን መስለን የምንኖረዉ ኑሮ ነዉ፡፡
 ይህንን በአግባቡ ለመረዳት የእርሱን ሥጋ የመልበሱን ነገር በደንብ መረዳት ያስፈልገናል፡፡
 ሥጋን ለበሰ ስንል እንዴት ? ከማን ? የሚሉትንና ሥጋ ለብሶ ምን አደረገ የሚለው ነገር ወሳኝ ነው፡፡
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓለም ሁሉ ለዳነበት ምስጢር መፈ
ጸሚያ መቅደስ ለመለኮት ማደሪያ እነድትሆን ተመርጣለች።

ገጽ 1
 በሰዎች ላይ ሰልጥኖ የነበረው የጨለማው ገዢ ዲያብሎስ ድል የተነሳበት አዳም ከጨለማ ግዞት ነፃ የወጣበት
አማናዊ ብርሃን ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘባት ምስራቅ የድህነታችን መሰረት የመዳናችን ምክንያት
በመሆኗ ነገረ ማርያምን ትምህርት መማር አስፈልጓል።
ለ. ስለ እመቤታችን ጸጋ እና ክብር ለማወቅ
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላካችን ከልዑል እግዚአብሔር በተሰጣት ጸጋ ከነገደ መላእክትም ሆነ
ከደቂቀ አዳም በክብር የሚመስላት በጸጋ የሚተካከላት የለም ፡፡ በጥቅሉ ከ፳፪ቱ ፍጥረት በላይ ናት፡፡
 ይኸውም ከፍጡራን መካከል ተለይታ የአምላክ እናት ለመሆን የተመረጠች አምላክን በህቱም ድንግልና ፀንሳ
በህቱም ድንግልና የወለደች ሁሉን የሚመግበውን አምላክ ጡቶቿን አጥብታ ያሳደገች ፣ በጀርባዋ ያዘለች ፣ ስለ
ልጇ የተሰደደች በማለት በማስተማር ዘመኑ ከጌታችን ጋር የነበረች እስከ እግረ መስቀል ያልተለየች በመሆኗ ስለ
እርሷ ስለተሰጣትም ፀጋ እና ክብር ለማወቅ አውቆም ለማክበር ነገረ ማርያም ትምህርት መማር ያስፈልጋል።
ሐ. በሕይወታችን መጠቀም እንድንችል ፡-
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጣት የከበረ ቃል ኪዳን አላት፡፡“ስምሽን
የጠራ ዝክርሽን ያዘከረ በቃል ኪዳንሽ የተማመነዉን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ በረከተ
ሥጋ በረከተ ነፍስ እሰጠዋለሁ፡፡” የሚል ነው፡፡
 ይህ ቃል ኪዳን በህይወታችን እንዲሰራ በነፍስም በሥጋም ከኃጢአት በስተቀር የምንፈልገውና የሚገባን
(የሚጠቅመን) ነገር እንዲፈፀምልን ይህንን የምናውቅበትን እና የምንረዳበትን ትምህርት ነገረ ማርያምን መማር
ያስፈልጋል።
መ. ከቅዱሳን ጋር ባለሀገሮችና ቤተሰቦች በመሆናችን (ኤፌ ፪÷፲፱) እና ሌሎችም ፡-
 የቅዱሳን እናት ስለሆነችው ስለ እመቤታችን ማወቅ በክርስትና ስላገኘነዉ ሰማያዊ ቤተሰብ መረዳትና ማወቅ
ነዉ፡፡“ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ፡፡” ኤፌ ፪÷፲፱

፩.፫ የስመ ድንግል ማርያም ትርጓሜ በቤተ ክርስቲያናችን


ማንኛውም የሚታይና የማይታይ ነገር የሚጠራበትና የሚታወቅበት መጠሪያ “ስም” ይባላል፡፡ በዚህ መሠረት ግብርን
፣ጠባይን እና ሁኔታን የሚገልጡ ስያሜዎች ለሰዎች እና ለቦታዎች ይሰጣሉ፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ የምናገኛቸው የሰው እና
የቦታ ስሞች አብዛኛዎቹ ከመጠሪያ አገልገሎታው ባሻገር ብዙ ትርጉም አላቸው፡፡
በዚህ ንዑስ ርዕስ ስለ ስም አሰያየም ያነሳነው የእመቤታችን ወላጆች ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና
እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ቸርነት ለመግለጥ ለእመቤታችን ያወጡላትን ስም ለመመልከትና መናፍቃን የተሳሳተ
መረዳት ስላላቸው ብዥታቸውን ለማጥራት ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም የእመቤታችንን መሠረተ ንጽሕ /የንጽሕና
መሠረት/ ድንግል፣ርኅርኅተ ልቦና አማላጅ መሆኗን ለመግለጥ ከጥቅል ስሟ ጀምረው በስሟ ውስጥ የተካተቱትን
ቀለማት/ኆሄያት/ዘርዝረው በመጻፍና በመተርጎም ያስተምራሉ፡፡

 ማርያም የሚለዉ ቃል በዕብራይስጥ ማሪሃም ሲሆን ትርጉሙም እመ ብዙኃን/የብዙዎች እናት /ማለት ነዉ፡፡
ዘፍ ፲፯÷፭ አብርሃም ማለት አበ ብዙኃን /የብዙዎች አባት/ ማለት እንደሆነ ፡፡ (ዘፍ ፲፰÷፲፰)
 ማርያም የሚለዉን ስም አበዉ ሊቃዉንተ ቤተ ክርስቲያን በምስጢራዊ ዘይቤ እንደሚከተለዉ
አስቀምጠዉታል፡፡

ሀ. ማርያም ማለት መርሕ ለመንግስተ ሰማይ ማለት ነዉ፡፡


(ወደ መንግስተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነዉ፡፡)

ሰዎችን ወደ መንግስተ እግዚአብሔር መምራት የእግዚአብሔር አግልጋዮች የዘወትር ተግባር ነው፡፡በዘመነ ብሉይ የእነ
ሙሴ መሪነት እስራኤልን ወደ ተስፋቱ ምድር ማድረስ ነበር፡፡ በዘመነ ሐዋርያትም የቅዱሳን ሐዋርያት ተልእኮ ሰዎችን
አሳምኖ ወደ መንግስተ ሰማያት መምራት ነው፡፡

በሰዎች የድኅነት ጉዞ ውስጥ ከሰው ወገን የመጀመሪያውን ስፍራ የምትይዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡
ምክንያቱም ፡-
 ከሰው ሁሉ አስቀድማ የአዳምን የልጆች የመዳን ዜና የሰማች እመቤታችን ናት፡፡ በመሆኑም ”መርሕ
ለመንግስተ ሰማያት“ ትባላለች፡፡

ገጽ 2
 አባታችን አዳም ወደ ቀደመ ክብሩ እንዲመለስ ምክንያተ ድኅነት የሆነችዉ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም
ናትና፡፡
 የእመቤታችንን አማላጅነት ተስፋ ሳያደርግ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት የሚችለዉ የለም፡፡ “ድንግል
ማርያም ሆይ ያለ አንቺ አማልጅነትና ተረዳኢነት ወደ ሰማይ የሚያርግ ጸሎትና ልመና የለም” እንዳለ
ሊቁ አባ ጽጌ በማሕሌተ ጽጌ ድርሰቱ ::

ለ. ማርያም ማለት ጸጋ ወሀብት ማለት ነዉ፡፡

እመቤታችን ወላጆቿ ለጊዜዉ በመምከናቸዉ በሰዉ ዘንድ ተንቀዉና ተዋርደዉ እነርሱም አዝነዉ ይኖሩ ለነበሩ ታላቅ
ሀብት ፀጋ ሆና ተሠጥታለች ፡፡ ፍፃሜዉ ግን አማላጅነቷን አዉቀዉ ቃል ኪዳኗን አምነዉ ለሚመጡ ምእመናን ሁሉ ሀብት
፤ፀጋ ሆና ተሠጥታናለች፡፡ ይኸም ትርጉም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እውነት ነው፡፡ “እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር
ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው” ይላል፡፡ (መዝ ፻፳፮፥፫)፡፡ በእርግጥ በመጀመሪያ እመቤታችን ለእናት ለአባቷ
የተሠጠች ጸጋ ናት፡፡ ሊቃውንቱም ” ፀጋ ወሀብት” ብለው ስሟን መሰየማቸው መጽሐፍ ቅዱስን በቀና ልቦና የሚያነብን
አንባቢ አይጎረብጥም፡፡
 የአዳም ፀጋዉ የተመለሠዉ በድንግል ማርያም ነዉ፡፡
 እመቤታችን በዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ አማካኝነት ለዓለም የጸጋ እናት ሆና ተሰጥታለች፡፡ ”እነኋት እናትህ ፣እነኆ
ልጅሽ፡፡”ዮሐ ፲፱÷፳፭

ሐ. ማርያም ማለት ፍጽምተ ሥጋ ወነፍስ ማለት ነዉ፡፡


(በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ፍጽምት)ማለት ነዉ፡፡

 ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለስመ ማርያም ትርጉም ሲሰጡ ”ማርያም ማለት “ፍጽምት” ማለት ነው፡፡ ለጊዜው
መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ከንጽሐ ነፍስ ድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ
አስተባብራ ተገኝታለችና“ ይላሉ፡፡
 ከነቢብ፣ከሐሊዮ፣ከገቢር ኃጢአት ንፅሕት ናትና እናትነትን ከድንግልና፤ድንግልናን ከእናትነት ጋር አስተባብራ
ይዛለችና፡፡
 ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ምርያም ድርሰቱ እመቤታችንን ሲያመሰግን ”የንጽሕናችን መሠረት“ ብሏታል፡፡
 ጠቢቡ ሰሎሞንም እመቤታችን ሥጋ ለብሳ በንጽሐ ሥጋ በንጽሐ ነፍስ በንጽሕና ያጌጠች ብቸኛ ፍጥረት መሆኗን
ሲያስረዳ “አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ ፤ባንቺ ላይ ምንም ነውር የለብሽም ” መኃ ፬፥፯
ብሏታል፡፡
 እንኳን እመቤታችን በቅድስናቸው በእግዚአብሔር አፍ የተመሰከረላቸው ፍጹማን ሰዎች መኖራቸውን መጽሐፍ
ሲመሰክር ”ኖኅ በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ነበር ፡፡” (ዘፍ ፮፥፱ )

መ. ማርያም ማለት መልዕልተ-ፍጡርን ምትህተ ፈጣሪ ማለት ነዉ፡፡


(ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ያለች)ማለት ነዉ፡፡
 መልዕልተ ፍጡራን ከፍጡራን በላይ ስንል ከ ፳፪ቱ ሥነ ፍጥረት ማለታችን ነው።
 እመቤታችንን ከፍጡራን በላይ ሰንል ከሰዉ ልጆችም ሆነ ከመላዕክት የምትልቅ የምትከብር ማለት ነዉ፡፡
ምክንያቱም እግዚአብሔር በቅድሳን ላይ ቢያድር በፀጋ ነዉ በእመቤታችን ግን በፍፁም ተዋህዶ ነዉ፡፡
 የእመቤታችን ክብር ከፍጡራን ክብር እንደሚመልጥ ፡-

 ቅድስ ያሬድ፡- “ጸጋን የተሞላሽና የደስታ መገኛ ሆይ … ዓይኖቻቸዉ ብዙዎች ከሆኑ ከኪሩቤልና
ክንፎቻቸዉ ስድስት(፮) ከሆኑ ከሱራፌል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ”
 ቅዱስ ኤፍሬም:- “የዐቢ ክብራ ለማርያም እምኩሎሙ ቅዱሳን” የማርያም ክብር ከቅዱሳን ክብር
ይበልጣል። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች…… .ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ለአንዱ
(ለእግዚአብሔር ወልድ) ማደሪያ ሆናለችና ብሏል። በውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ

ሠ. ማርያም ማለት እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነዉ፡፡


(የብዙዎች እመቤት)ማለት ነዉ፡፡
ገጽ 3
 እመቤት ማለት በአንድ ቤተሰብ መካከል አስተዳዳሪና ኃላፊ የሆነች ታላቅ ሴት ማለት ነዉ፡፡ እንዲሁም በክርስቶስ
የባሕርይ አምላክነት ያመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ በክርስቶስ አንድ ቤተሠብ በመሆናቸዉ እናቱ ቅድስት ድንግል
ማርያም እመቤታችን ናት፡፡

ረ. ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ማለት ነዉ፡፡


 አካላዊ ቃል በእመቤታችን አድሮ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፈስዋ ነፍስ ነስቶ መለኮትን ከትስብእት (ከሥጋ) ትስብእትን
ከመለኮት አዋሕዶ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ ስለተገለጠባት ለአምላክ ሰው የመሆኑ ምክንያት ለሰው
የመዳኑ ምክንያት ናትና “ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብዕ” ትባላለች።
 የሰዉን ልመና ወደ እግዚአብሔር ፤የእግዚአብሔርን ይቅርታ ወደ ሰዉ በማድረስ ድኅነተ ሥጋ ድኀነተ ነፈስ ፤በረከተ
ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለደች ታሰጣለችና ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ትባላለች፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስሞች እንዳሉ ሆነው ሌላ ምስጢራዊ ወይም
ዘይቤያዊ/የክብር/ ስሞችም አሏት፡፡ እነርሱም፡-

ሀ. እመ ብርሃን፡-
 የብርሃን እናት ማለት ነዉ፡፡ ነው።ጌታችን እና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው
(በማስተማር ዘመኑ) “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ብሏል ( ዮሐ ፰÷፲፪):: ስለዚህ የእርሱ እናት ደግሞ ድንግል ማርያም
ስለሆነች ይህ እመ ብርሃን የተሰኘው ስም ይገባታል።
ለ. ወላዲተ አምላክ፡-
 የአምላክ እናት ይህ ስም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የሚገባ ነው፡፡ ጌታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ
ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗልና፡፡ (ኢሳ ፮÷፱፣ ማቴ ፩÷፳፫)
 ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ የሆነ በተዋሕዶ የከበረ የወልደ እግዚአብሔር የኢየሱስ
ክርስቶስ በሥጋ እናት ለመሆን ከሴቶች መካከል የተመረጠች ናት፡፡
 ነቢዩ ኢሳይያስም በትንቢቱ እንደተናገረው ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ መካር ኃያል
አምላክ ነው።(ኢሳ ፱፥፮)።
 በሌላም ሥፍራ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የምትወልደው አምላክ ስሙ አማኑኤል ተብሎ እንደሚጠራ
ተናግሯል።(ኢሳ ፯፥፲፬)። “አማኑኤል” ማለትም የእግዚአብሔር መልአክ እንደተረጐመው እግዚአብሔር
ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ ሰው ሆነ ማለት ነው።(ማቴ ፩፥፳፫)።
 የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባታችን ቅዱስ ቄርሎስ፡- “አማኑኤል የባሕርይ አምላክ እንደሆነ ንጽሕት ድንግልም
አምላክን የወለደች እንደሆነች ሰው የሆነ የእግዚአብሔርንም ቃል እንደወለደች የማያምን ሰው ቢኖር የተወገዘ
ይሁን” በማለት ከአወገዘ በኋላ “ዳግመኛ በኋላ ዘመን ቅድስት ድንግል እርሱን በሥጋ በወለደችው ስለእኛ ሰው
የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ወለደችው።” ስለዚህም ቅድስት ድንግልን ወላዲተ አምላክ እንላታለን። ሰው ሳይሆን
ሰውም ከሆነ በኋላ አንድ ወልድ አንድ ክርስቶስ ነው።ከእግዚአብሔር አብ የተገኘ ቃል ሌላ አይደለም ከቅድስት
ድንግል የተወለደውም ሌላ አይደለም የምናምንበት ከዓለም አስቀድሞ የነበረ ከድንግል በሥጋ የተወለደ ይህ አንድ
ወልድ ነው እንጂ (ሃይ.አበ. ገጽ ፪፻፸፯-፫፻፭) በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ
መሆኗን መስክሯል።

ሐ. ኪዳነ ምሕረት፡-
 ኪዳን ውል ስምምነት መሓላ የሚል ትርጉም ሲኖረው ምሕረት፣ቸርነት፣ ነፃ ስጦታ፣ፍቅርን የሚያመለክት ኃይለ
ቃል ሲሆን ይህ ስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ
ክርስቶስ ስምሽን የጠራ እምርልሻለሁ የሚል ስለ ኃጥአን የተሰጣትን የምሕረት ቃል ኪዳን ማሳሰቢያ
ነው።“ከመረጥኳቸዉ ጋር የምሕረት ቃል ኪዳንን አደረግሁ፡፡” እንዲል፡፡ (መዝ ፹፰÷፫)
 እመቤታችን አውነተኛ የምሕረት አማላጅ ናትና ኪዳነ ምሕረት ትባላለች፡፡

መ. ሰዓሊተ ምሕረት
 ምሕረትን ለሰው ወገን መለመን/መጠየቅ/ ማለት ነው፡፡ የድንግል ማርያም አማላጅነት ደግሞ የወዳጅነት ብቻ
ሳይሆን የእናትነትም ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ “ማርያም ንጽሕት ድንግል ወላዲተ

ገጽ 4
አምላክ ማእምንት ሰዓሊተ ምሕረት ለውሉደ ሰብዕ -ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን
የወለደች ናት፤ ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት” /ውዳሴ ማርያም ዘአርብ ቁ.፮/
ሠ. ቤዛዊተ ዓለም
 እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ስላት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ”በእንተ
ሔዋን ተአጽወ ኆኅተ ገነት ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርኅወ ለነ ዳግመ ከፈለነ ንብላእ እመ ዕፀ ሕይወት -
በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ፤ በድንግል ማርያም ምክንያት ዳግመኛ ተከፈተልን፤ከዕፀ ሕይወት እንበላ
ዘንድ አደለን“/ቅዱስ ኤፍሬም ፤ ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ፤ቁ.፪/በማለት በድኅነተ ዓለም ውስጥ ያላትን ሚና
ገልጸዋል፡፡ በሔዋን ስሕተት ምክንያት ያጣነውን ጸጋ በእመቤታችን በኩል መከፈሉን ለማስታወስ ሊቃውንተ ቤተ
ክርስቲያን ያጣነውን ጸጋ ደግሞ የተካሰንብሽ አንቺ ነሽ ለማለት “ቤዛዊተ ዓለም” በሚል ስያሜ ይጠሯታል፡፡
 እመቤታችን በዚህ ስም መጠራቷ በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ስፍራ ያሳያል፡ እንጂ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል
የተፈጸመልንን የቤዛነት ሥራ አይሻማም፡፡ ምክንያቱም እመቤታችን በነገረ ድኅነት ውስጥ ቀጥተኛ ሱታፌ
እንዲኖራት የተመረጠችው በእግዚአብሔር ነውና፡፡
ረ. መራሒተ ፍኖት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሕይወት መንገድ ሲያስተምር ”እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ
በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም“ ብሏል(ዮሐ ፲፬፥፮)፡፡ ጌታችን እውነተኛ መንገድ ነው፡፡ቀድመው የነበሩ መንገዶች ለድኅነት
የሚያበቁ አልነበሩም፡፡ ከቀድሞው መንገድ እርሱ የተለየ መሆኑንም እዉነትን በመጨመር ነግሮናል፡፡በመንገድ
ከተመሰለው ወይም ወደ እውነተኛው መንገድ የመራችን መንገዱን ያስተዋወቀችን መንገድን፤ሕይወትን እና እውነትን
የወለደች ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ እመቤታችን ከላይ እንደተብራራው “መራሒተ ፍኖት”
መባሏ የመንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት በመሆኗ ነው፡፡
ሰ. ምዕራገ ጸሎት
 ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ክብረ ቅዱሳንን ሲገልጥ “አዕቲሁ ለእግዚአብሔር ኀበ ጻድቃኑ ወእዝኑሂ ኀበ
ስእለቶሙ-የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸው፡፡” ብሏል/መዝ
፴፫፥፲፭/፡፡
 እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ለመስማት ጆሮዎች ከሚከፍላቸው ቅዱሳን ጻድቃን ሁሉ እመቤታችን ቅደስት ድንግል
ማርያም በክር ትበልጣለች፡፡ ይህንን ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሲመሰክር ”ምልእተ ክብር ሆይ ከቅዱሳን ይልቅ
ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳት አንቺ ትበልጫለሽ ከነቢያትም ትበልጫለሽ “ ብሏል፡፡
 ሊቁ እንደገለጸው የእመቤታችን ክብር ከሁሉም ቅዱሳን በላይ ነው፡፡ ይሄንን ልዩ ክብሯን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል
ሲመሰክር ”በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻል“ ብሏል /ሉቃ ፩፥፴/፡፡
 በመሆኑም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እመቤታችን ልዩ ሞገስ የተቸረች ክብርት እናትነቷን ለሰው ወገን ሁሉ
አማላጅነቷን ለመግለጽ ”ምዕራገ ጸሎት“ ይሏታል፡፡

ሌሎች ሊቃውንት አባቶቻችን ለእመቤታችን ያላቸዉን ፍቅር ሲገልጡ የስሟን አራት ቀለማት/ኆኄያት / እንዲህ ብለዉ
በዚህ መሠረት ተርጉመዉታል፡፡
‹‹ማ›› “ማኅደረ መለኮት”( የመለኮት ማደሪያ)
‹‹ር›› “ርግብዬ ይቤላ” (ሰሎሞን ርግብዬ ይላታልና) መኃ ፮÷፱
‹‹ያ›› “ያንቃዐዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት ” (ፍጥረት ሁሉ ለምኝልን እያሉ ወደ አንቺ ያንጋጥጣሉ)
‹‹ም›› “ምስጋድ ወምስአል ወመስተሥራየ ኃጢአት” (መማጸኛ ፤መስገጃ፣፣የኃጢአት ማስተሰርያ)

፩. ፬ የነገረ ማርያም ትምህርት ምንጮች


የነገረ ማርያም ትምህርት ልብ ወለድ ፈጠራ ሳይሆን ምንጭ አለዉ፡፡የነገረ ማርያም ትምህርት ምንጮች ምን እንደሆነ
ከዚህ በታች የተገለጹት ናቸው፡፡

ገጽ 5
 መጽሐፍ ቅዱስ ፡- ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን
 ሃይማኖተ አበዉ፡፡
 አዋልድ መጽሐፍት፡- አዋልድ መጽሐፍት የሚባሉትም ፡-
 ተአምረ ማርያም፣
 የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች( አንቀጸ ብርሃን፣ ድጓ፣ጾመድጓ ፣መዋሥእት፣ምዕራፍ ወ.ዘ.ተ)
 የአባ ጊዮርጊስ ድርሰቶች( ሰዓታት ዘመዓልት ወዘሌሊት፣ኖኅተ ብርሃን /ከመጽሐፈ አርጋኖን ጋር አብሮ
ታትሟል/፣ውዳሴ መስቀል፣ቅዳሴ፣ ውዳሴ ሐዋርያት፣አርጋኖነ ውዳሴ፣ ፍካሬ ሃይማኖት፣ መጽሐፈ
ምሥጢር፣ ውዳሴ ስብሐት፣እንዚራ ስብሐት፣ ሕይወተ ማርያም፣ተአምኖ ቅዱሳን፣መጽሐፈ ብርሃን፣ጸሎት
ዘቤት ቤት)
 የቅዱስ ኤፍሬም ድርሰቶች (ዉዳሴ ማርያም ፣ወ.ዘ.ተ)
 አባ ሕርያቆስ ድርሰቶች( ቅዳሴ ማርያም.. ወ.ዘ.ተ)
 የአባ ጽጌ ድርሰቶች (ማኅሌተ ጽጌ ፣ወ.ዘ.ተ) ናቸዉ፡፡

እነዚህን ድርሰቶች ያስደረሳቸዉ(ያጻፋቸው) እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ነገር የገለጸላቸዉ ያደረባቸው
እና የመረጣቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡መንፈስ ቅዱስ ያላደረበት የእመቤታችንን ክብር ገልጾ መናገር
አይችልምና፡፡ (ሉቃ ፩÷፴፱) “በኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስ መላባት ድምጿን ከፍ አድርጋ የጌታዬ እናት ወደ እኔ
ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? አንቺ ከሴቶች ተለይተሸ የተባክሽ ነሽ የማኅፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው….፡፡
አለች” እንዲል፡፡

ምዕራፍ ሁለት(፪)
፪.የእመቤታችን ታሪክ

፪.፩ የእመቤታችን የዘር ሐረግ እና የልደቷ ታሪክ

“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር”። (ኢሳ ፩፥፱) ነቢዩ
በመንፈስ ቅዱስ ተቀኝቶ እንደተናገረ ስለ አዳም ልጆች መዳን ያስቀራት ንፅሕት ዘር ማለትም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ
የሌለባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ፡፡

 ስለ እመቤታችን የትዉልድ ሐረግ ስናነሳ መነሻችን አበዉ ቅድሳን ናቸዉ፡፡ ቅዱስ ደዊት በመዝ ፹፮÷፩ “መሠረታቲሃ
ውስተ አድባር ቅዱሳን - መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸዉ፡፡” እንዳለ፡፡ቅዱስ ጳዉሎስም በዕብ ፪÷፲፮ “የአብርሃምን
ዘር ይዟል እንጂ የያዘዉ የመላዕክትን አይደለም”፡፡
 የእመቤታችን የዘር ሀረግ ከአዳም ጀምሮ እስከ ኢያቄምና ሐና ድረስ በተቀደሱ አባቶችና እናቶች በኩል ስትወርድ
እንደመጣች ሊቃዉንተ ቤተ ክርስቲያን ይመሰክራሉ፡፡ ይህም
- ከአዳም ልጆች በሴት በኩል
- ከኖህ ልጆች በሴም በኩል
- ከአብርሃም ልጆች በይስሐቅ በኩል
- ከያዕቆብ ልጆችበይሁዳና በሌዊ በኩል
- ከዳዊት ልጆች በሰሎሞን በኩል በተመረጡና በተቀደሱ አባቶችና እናቶች በኩል በጥበብ እግዚአብሔር
ስትወርድ ከመጣች በኋላ ከቤተ ሌዊ ከነገደ አሮን ከካህናቱ ወገን ከሆነች ከቅድስት ሐናና ከነገደ ይሁዳ
ከነገሥታቱ ወገን ከሆነዉ ከቅድስ ኢያቄም እንደምትወለድ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበር፡፡ “ማርያምሰ
ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ - ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም
ባሕርይ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለችና” ይላታል ቅድስ ያሬድ በድጓዉ፡፡

የእመቤታችን ቅደመ አያቶች-ጴጥርቃ እና ቴክታ


፩. ጴጥርቃ የእመቤታችን ወንድ ቅድመ አያት
፪. ቴክታ የእመቤታችን ሴት ቅድመ አያታ
- በእግዚአብሔር ያመኑ የተወደዱ ጻድቃን ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡
- በሰውም በእግዚአብሔርም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ፡፡
ገጽ 6
- ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም ፤ መካን ነበሩ፡፡
- ከዕለታት አንድ ቀን ጴጥርቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ ደብዳቤውን አይቶ ሀብቱን ሰፍሮ ቆጥሮ ከቤት
ሔዶ እኅቴ ሆይ ሀብታችን ስፍር ቁጥር የለውም ይህን የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ?
የሚወርሰን ልጅ የለን፡፡ አንቺ መካን እኔ ከአንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡
- እርሷም አቤቱ ጌታዬ ሆይ አምላከ ፳ኤል/እስራኤል/ ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደ እኔ ትቀራለህን ? ከሌላ
ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው ፤
- እርሱም እንዲህ ያለ ነገር እንኳን እኔ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ ፳ኤል ያውቃል አላት፡፡
- እንዲህ እያሉ ሲያዝኑ ቴክታ ህልም አየች
 ጴጥርቃና ቴክታ ያዩት ሕልም፡-
 ቴክታ ለጴጥሪቃ እንዲህ አለችው፤“እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ
በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማኅጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድና እስከ ሰባት ትውልድ
ድረስ ሲዋለዱ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አየሁ” አለችው፡፡ ወደ ሕልም
ፈቺ ሔደውም ነገሩት፡፡ ያም ህልም ፈቺ፡-
 ሰባት እንስት ጥጆች መውለዳችሁ ወይም ሲወለዱ ማየታችሁ ፡- ሰባት ሴት ልጆች ትወልዳላችሁ፡፡
 ሰባተኛይቱ ጨረቃን መውለዷ- ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ፡፡
 የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጠልኝም ጊዜ ይፍታው አላቸው፡፡ በዚህም ወራት ቴክታ ፀነሰች ሴት ልጅ ወለደች
ስሟን ሄሜን ብለው አወጡላት፡፡ በመቀጠልም፡-
- ሔሜን ዴርዴንን ወለደች፤
- ዴርዴም ቶናን ወለደች
- ቶናም ሲካርን፤
- ሲካርም ሴትናን
- ሴትናም ሄርሜላን፤
- ሄርሜላም ማጣትን አግብታ ሐናን መስከረም ፯ ቀን ወለደች
- ሐናም ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስታደርስ ከቤተ መንግስት የተወለደውን ክቡር ጻድቅ
ኢያቄም የሚባለውን ባል አጋቧት፡፡

እነዚህም ኢያቄምና ሐና ባንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሄደው ሲጸልዩ
ሲያዝኑ ዋሉ ፡፡ሐዘናቸውስ እንዴት ነው ቢሉ ?
 ኢያቄም ”አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሀለሁ አትጣለኝ፣አትናቀኝ፣ጸሎቴን ስማኝ
፣ፈቃዴን ፈጽምልኝ ለዓይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ“ ብሎ ሲለምን ዋለ፡፡
 ሐናም በበኩሏ ”አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሀለሁ አትጣለኝ፣አትናቀኝ፣ጸሎቴን
ስማኝ ፣ፈቃዴን ፈጽምልኝ ለዓይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከች ሴት ልጅ ስጠኝ“ብላ ስትለምነው
ዋለች፡፡
 እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሐና ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ ”አቤቴ ጌታዬ ለዚች ግዕዛን
ለሌላት እንሰሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለእኔ ልጅ ነሳኸኝ ?“ ብላ ምርር ባላ አለቀሰች፡፡
 እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቃነ ካህናቱ ሄደው ”አቤቱ ጌታችን ሆይ ፣ወንድ ልጅ
ብንወልድ ተምሮ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፡፡ ሴት ልጅ ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶበ ወርቅ
ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን” አሉት፡፡
 ዘካርያስም ”እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማላችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻሕቀ ልቡናችሁን ይፈጽምላችሁ“
ብሎ አሳረገላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ እንዲህ ብለው ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩስ እንዴት ነው
ቡሉ ?
 ኢያቄም፡- “፯ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ
“አላት፡፡
- ወፍ የተባለው ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
- ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፡፡
- ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በላዬ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱም፡ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ
እንዳደረገው ዕወቅ ሲል ነው፡፡
- “፯ቱ ሰማያት የተባሉት፡ የጌታችን ምልዓቱ ስፍሐቱ ርቀቱ ልዕልናው ዕበዩ መንግስቱ ናቸው፡፡
ገጽ 7
 ሐናም ፡- “እኔም አየሁ”አለች፡፡ ”ምን አየሽ ?“ አላት፡፡“ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ በራሴ ላይ ወርዳ
በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ”አለችው፡፡
- ርግብ የተባለች እመቤታችን እግእዝትነ ማርያም ናት፡፡
- ነጭነቷ ንጽሕናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡
- ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ፡
ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን እግእዝትነ ማርያም ጌታችንን መፅነሷ ነው፡፡
 ይህንንም ራእይ ያዩት ሐምሌ ፴ ዕለት ነው፡፡
 እነሱም እንዲህ ያለ ራእይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገኛኙም፡፡ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን
አዳምና ሔዋንን ብዝኁ ወተባዝኁ ወምልእዋ ለምድር/ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት/ብሎ ያበሰረ አምላክ ለእኛስ
ይልክልን የለምን ? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ፯ ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡
 ነሐሴ ፯ ቀን ”ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ጠጉር የማያህል
ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ ብሏችኋልና ጌታ“ ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና
ነገራት፡፡
 በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን እግእዝትነ ማርያም እሁድ ተፀነሰች፡፡
 እመቤታችን እግእዝትነ ማርያም የተፀነሰች እለት ጀምሮ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው፡፡ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ ?
የሐና የአጎቷ ልጅ ሳሚናስ ሞቶ ሳለ ሐናም ከዘመዶቿ ጋር እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ከሞት ስለተነሳና
ስላመሰገናት ቀንተው ነው፡፡
 በተፀነሰች ጊዜ በማህፀነ ሐና እያለች የቤርሳቤህን ዓይን አብርታለች፡፡
 ግንቦት ፩ ቀን ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራና መወደድ ያለባት ወላዲተ አምላክ በሊባኖስ ተራራ ተወለደች፡፡
 እመቤታችን በሊባኖስ ተራራ የመወለዷ ምክንያት አይሁድ ቢሆኑም ምስጢሩ ግን የተነገረዉ ትንቢት
እንዲፈፀም ነዉ፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች የሚል ትንቢት ነበርና፡፡ መኃ ፬÷፰ ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱ
ሰማይም ፀሐይን ወለደች፡፡
 የእመቤታችንን ትዉልድ ሀረግ ወንጌላዊ ማቴዎስ በማቴ ፩÷፩-፳፩ ከአዳም እስከ ራስዋ ቤተሰብ ድረስ ሲያያዝ
የመጣዉን የዘር ሀረግ በመዘርዘር የፃፈዉን መመልከት ነዉ፡፡

ከላይ በሥዕላዊ መግለጫዉ እንደተመለከትነዉ ወንጌላዊው ማቴዎስ የጌታን ልደት ሲፅፍ ከአብርሃም ጀምሮ እሰከ
አልዓዛር ከደረሰ በኃላ ቅስራ፤ኢያቄም፤ድንግል ማርያም በማለት አልፃፈም፡፡ ነገር ግን አልዓዛርን ጠቅሶ ማታን ፤
ያዕቆብ፤ዮሴፍ ብሎ ቆጠረ፡፡ ይህም ያለምክንያት አይደለም፡፡ ቅድስ ማቴዎስ የጌታን ልደት በእመቤታችን በኩል ቢቆጥር
ኖሮ በአይሁድ ልማድ ትዉልደ አበዉ የሚቆጠረዉ በወንድ በኩል ስለሆነ አቀላቅሎ ፃፈ ብለዉ ባልተቀበሉት ነበር፡፡

፪.፪ በዓታ ለማርያም (የእመቤታችን ዕድገት)


 እመቤታችን በእናትና አባቷ ቤት ለ፫ ዓመት ያህል ከቆየች በኋላ በነቢዩ ቃለ ትንቢት መሠረት (መዝ ፷፰÷፲፫) ሐናና
ኢያቄም አስቀድሞ በገቡት ብፅኦት መሰረት የ፫ ዓመት ልጃቸዉን ደስ እያላቸዉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፡፡
 እግዚአብሔር የሰጣቸዉን መልሰዉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፡፡ “በህዝብ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር
እፈፅማለሁ፡፡” ተብሎ ተፅፏልና (መዝ ፻፲፭÷፱)
 ዕለቱ ታህሳስ ፫ ቀን ነበር፡፡
 ስትመገብ የነበረዉም ሰማያዊ ህብስት ስትጠጣ የነበረውም ሰማያዊ ጽዋ ነዉ፡፡
 “ልጄ ሆይ ስሚ ልብ ብለሽ አድምጪ ወገንሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ ንጉስ ስነ ቅድስናሽን ወዷልና፡፡ መዝ ፵፬÷፲
 ለ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ማይ እየቀዳች ሐርና ወርቅ እያስማማች ስትፈትል ኖረች፡፡
 እመቤታችን ከቤተ መቅደስ ወጥታ በዮሴፍ ቤት ቆየች ምክንያቱም በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የምትወልድበት
ጊዜ ስለደረሰ ከቤተ መቅደስ ወጥታ በአረጋዊ ዮሴፍ ቤት እንድትቆይ ተደረገ፡፡
ገጽ 8
የዚህ ዓቢይ ምክንያት፡-
 አንዲት ብላቴና ፀንሳ ብትገኝ በህግ ተላላፊነት በድንጋይ ተደብድባና በእሳት ተቃጥላ እንደምትሞት የኦሪት ህግ
ስለሚያዝ፤
 ከእርሷም የሚወለደዉ ህፃን ማንነት ከሚያሳስባቸዉ ሄሮድሳዊያን ፊት ለመሸሽ ስትል በሚደርስባት የስደት
የጭንቀት ወቅት የቅርብ ረዳቷና ጠባቂዋ ሆኖ እንዲጠብቃት ፈቃደ እግዚአብሔር በመሆኑ ፡፡ ማቴ ፩÷፲፮-፳፪

፪.፫. እመቤታችንና የዮሴፍ ጠባቂነት


እመቤታችን አይሁድ ከቤተ መቅደስ መዉጣት አለባት ባሉ ጊዜ ሊቀ ካህኑ ከእመቤታችን ዘንድ ገብቶ እንደምን ትሆኝ ብሎ
ጠየቃት፡፡ ወደ እግዚአብሔር አመልክትብኝ አለችዉ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸዉ
የሞቱባቸዉን አስቆጥረህ በትራቸዉን ከቤተ መቅደስ አስገብተህ ፀልይበት ምልክትም እሠጥሃለሁ አለዉ፡፡ ሊቀ ካህናቱም
በትራቸዉን ሰብስቦ ከቤተ መቅደስ አስገብቶ ሲፀልይበት አድሮ ሲያወጣቸዉ ከበትረ ዮሴፍ ላይ “ዮሴፍ ሆይ እጮኛህን
ማርያምን ለመዉሰድ አትፍራ፡፡” የሚል ፁሑፍ ተቀርጾ ተገኝቷል፡፡ ዕጣም ቢያወጡ ለእርሱ ወጣ፡፡ ዮሴፍ በወቅቱ
ዕድሜዉ የገፋ አረጋዊ /ሽማግሌ/ ነበር ፡፡ ዘኁ ፲፩ ÷፰

እመቤታችን ለዮሴፍ ለምን ታጨች?


 ሴት ልጅ ጠባቂ ያስፈልጋታልና በእጮኛ ስም እንዲጠብቃት ነዉ፡፡
 ጌታችን ያለ ወንድ ዘር መወለዱን ተመልክተዉ እመቤታችንን ከሠማይ የመጣች ኃይል ናት እንጂ የአዳም ዘር
አይደለችም እንዳይሉ፡፡
 አገልጋይዋ ተላላኪዋ እንዲሆነዉ፡፡

፪.፬ የቅዱስ ገብርኤል ብስራት


እግዚአብሔር ዘመኑ ሲፈፀም መልዐኩ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ላከዉ “በስድስተኛዉ ወር
መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደ ምትባል ገሊላ ከተማ ከዳዊት ወገን ለሆነዉ ዮሴፍ ለሚባለዉ ሰዉ ወደ ታጨች ወደ
አንዲት ደንግል ከእግዚከብሔር ዘንድ ተላከ፡፡ የድግሊቱም ስም ማርያም ነበር፡፡ ሉቃ ፩÷፳፮ ሲል ገልፆታል፡፡ ስለ ወላዲተ
አምላክ በመልአኩ መበሰር በሊቃዉንተ ቤተ ክርስቲያን ይተረካል፡፡

፪.፭ ልደተ ክርስቶስ (የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ)


 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን ዮሴፍ በተወለደባት ሀገር በኢየሩሳሌም በከብቶች በረት
ወለደችዉ ሉቃ ፪÷፩-፯
በመወለዱ ምክንያት፡-
- ብርሃን አበራ የእግዚያብሔር መልዓክ ታየ፡፡
- ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች የሚል ቃለ ትንቢት ተፈፀመ፡፡
ኢሳ ፯÷፲፬ ማቴ ፩÷፳፫
- የአዳም ልጅ ፍዳ ዘመኑ አለቀለት ኢሳ ፱÷፪
- ጌታችን በመንፈስ ቅዱስ ግብር/ተኣምር/ ያለ ወንድ ዘር የተወለደ መሆኑ በተግባር ተገለጠ፡፡

፪.፮ ስደታ ለማርያም/ የእመቤታችን ስደት/


ስለ እመቤታችን ከሚነገሩ ታሪኮች አንዱ የስደቷ ነገር ነዉ፡፡ ታሪኩን ማቴ ፪÷፲፫-፳፩ ተመልከት፡፡
 ለምን ተሰደደች
ሀ. ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ፡፡(ማቴ ፪÷፲፭)
ለ. ክርስቶስ ያለ ጊዜዉ ደሙን ስለማያፈስ
ሐ. ስደትን ለቅዱሳን ባርኮ ለመስጠት
- ስደቷን ለማሠብ “ሰቆቃወ ድንግል” የተባለ መፅሐፍ ያንብቡ፡፡
እመቤታችን በጌታችን የማስተማር ዘመን
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን የማስተማር ዘመን አብራ አልተለየችም፡፡ በዮሐ ፪፡፩-፲፩ ላይ በቃና
ዘገሊላ የመጀመሪያው ተአምር ሲፈፀም ውሃው ወደ ወይን ጠጅነት ለመቀየሩ ምክንያት የእመቤታችን አማላጅነት
እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ገጽ 9
 ጌታችን ዙሮ ካስተማረ በኋላ በመልዕልተ መስቀል ሲሰቀል ከእግረ መስቀሉ አብራ ነበረች፡፡ዮሐ ፲፱፡፳፮
 በዮሐንስ አማካኝነት እኛ የድንግል ማርያም የፀጋ ልጆች መሆናችን ድንግል ማርያም ደግሞ የፀጋ እናታችን መሆኗ
በዚህ ተረጋግጧል፡፡

እመቤታችን ከሐዋርያት ጋር
• ወንጌላዊው ዮሐንስ እመቤታችንን ወደ ቤቱ ወሰዳት ሲባል ወደ መጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ወደ ማርቆስ እናት
ቤት ወደ ማርያም ቤት አመጣት ማለት ነው፡፡ በዚያ ሐዋርያት ይሰባሰቡ ነበር፡፡ ሐዋርያትም ከጌታ ሞት እና ትንሳኤ
እንዲሁም እርገት በኋላ የሚሰጣቸውን ፀጋ መንፈስ ቅዱስን ተስፋ አድርገው ድንግል እመቤታችንን ማርያምን ከበው
ፀሎት ያደርጉ ነበር፡፡ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ተቀብሎ ከሞት በተነሳ በ፶ኛው ቀን በክብር ባረገ በ
፲ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸው ፸፪ ቋንቋ ተገልፆላቸው መከራውን ሁሉ ታግሰው ዓለምን ዙረው አስተምረዋል፡፡
• አባቶቻችንም ይህንን ታሪክ መነሻ አድርገው እመቤታችንን ሲያመሰግኗት ሞገስ ስብከቶሙ ለሐዋርያት-
የሐዋርያት የስብከታቸው ሞገስ አንቺ ነሽ ብለው አመስግነዋታል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል
እመቤታችንን ከበው መፀለያቸው እንደጠቀማቸው እኛም በእመቤታችን ተማፅነን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ
እንድናገኝ ያስፈልጋል፡፡ ሐዋ ፩፥፲፪-፲፬፣ ሐዋ ፪፥፩

፪.፯ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም(የእመቤታችን የማርያም ጸሎት)

ስለ ድንግል ማርያም ተናግሮ በወንጌል ስለሚገኘዉ ፀሎቷ ሳይናገሩ ማለፍ አይቻልም በአጭሩ ማቅረብ ተገቢ ነዉ ተብሎ
ስለታመነበት እንደ ሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
፪.፯.፩ ሰዉነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች :: (ሉቃ ፩÷፵፮)
 እመቤታችን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ተለይታ ንፅሐ ሥጋና ፤ንፅሐ ልቦናን ፤ ንፅሐ ነፍስን ገንዘብ
በመድረግ ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች ማለቷ እዉነት ነዉ፡፡
፪.፯.፪ መንፈሴም በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች::
 ሐሴት ማለት ታላቅ የደስታ ምልክት ነዉ፡፡ የእመቤታችን ደስታም በዚህ አለም በሚገኝ ሀብትና ስልጣን አይደለም
፡፡ ደስታዋ በልዑል እግዚአብሔር ነዉ፡፡ መልአኩ እንዲህ እንዳለ “እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነዉ ፡፡” ሉቃ ፪÷፲
፪.፯.፫ የባርያዉን ትህትና ተመልክቷልና ፡፡
 የእኔን የእናቱ እና የአገልጋዩን የገረዱን ትህትና ተመልክቷልና ተመልክቶ ከእኔ ተወልዶ አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ያድን
ዘንድ ፈቃድ ሆኗልና ልቡናዬ በፈጣሪዬ ደስ ይላታል አለች፡፡
፪.፯.፬ ከእንግዲህ ወዲህ ትዉልድ ሁሉ ያመስግኙኛል፡፡
 እመቤታችን በአንድ ሠማያዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤልና በአንዲት ምድራዊት እናት ቅድስት ኤሌሳቤጥ አንደበት
ብቻ ምስጋናዋ የሚገታ ባለመሆኑ በአጠቃላይ ፍጥረታት ያመሰግኑኛል ስትል ነዉ፡፡
፪.፯.፭ ብርቱ የሆነ እርሱ ለእኔ ታላቅ ስራ አድርጓልና::
 ደግ ስራ ሠርቶልኛልማለት ነዉ፡፡ ምክንያቱም ብርቱ የሆነ እርሱ ታላላቅ ነገስታትን የመታ፤ብርቱዎችን ነገስታት
ገደለ፤ እኛንም በመዋረዳችን ያሰበን ልዑል እግዚአብሔር መዝ ፻፴፭ ÷ ፲፮ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ
ከእመቤታችን በተዋህዶ ከድንግል እንዲወለድ ፈቃዱ ስለሆነ ታላቅ ስራ አድርጓልና በማለት መሰከረች ፡፡
፪.፯.፮ ስሙም ቅዱስ ነዉ::
 የእግዚአብሔር ስም ቅዱስ ነዉ ታላቁ አባት ነብዩ ዳዊት “በቅዱስ ስሙ ታምነናልና ” በማለት እግዚአብሔር
የሚለዉ ቅዱስ የሚለው ስም የሰዉ ልጆች መታመኛ መሆኑን ይገልፃል፡፡ መዝ ፴፪÷፳፩
 ወላዲተ አምላክ በጸሎቷ ዉስጥ ድንቅ ስራዉን ብቻ ሳይሆን ለቅዱስ ስሙም የሰጠችዉን ክብር
እንመለከታለን፡፡ እንደ አባቶቿ ነቢያት የፈጣሪዋን ስም ቅዱስ ነዉ ብላ መስክራለችና፡፡
፪.፯.፯ ምህረቱም ለሚፈሩት እስከ ትዉልድና ትዉልድ ይኖራል::
 የእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ለሚፈሩት ነዉ ያዉም ለልጅ ልጅ የሚዘልቅ ምህረትና ቸርነት መዝ ፻፪÷፲፯
እመቤታችንም እግዚአብሔር ለእባቶቿ የገባዉን ኪዳን በእርሷ ፈፅሞ በዘለአለማዊነት እንደሚያፀናዉ
ስለምታወቅ ነዉ፡፡
፪.፯.፰ በክንዱ ኃይል አድርጓልና::
 እግዚአብሔር አብ በልጁ እግዚአብሔር ወልድ በኢየሱስ ክርስቶሰ እንዲሁም እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ
ክርስቶስ በስልጣኑ ታላላቅን ደጋግ ተአምራትን አደገን ማለት ነዉ፡፡
 ክንዱን በመስቀል ላይ ዘርግቶ አጋንንትን አስጨነቀ

ገጽ 10
 ክንዱን በሲኦል ዘርግቶ ነፍሳትን አወጣ በመሆኑም በክንዱ ኃይልን አደረገ በማለት አመሰገነች፡፡
፪.፯.፱ ትዕቢተኞችን በልባቸዉ አሳብ በትኖአል::
 የእግዚአብሔር ጠላቶች ተብለዉ ከሚታወቁት ፍጡራን መካከል የመጀመሪያዎቹ ትዕቢተኞች ናቸዉ፡፡
የመጀመሪያዉ ጠላት ድያብሎስ የወደቀዉ በትዕቢት ስለሆነ ትዕቢተኞች ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን በተናቸዉ፡፡
 ራሳቸዉን በማፅደቅ ሌላዉን ይንቁ ነበርና :: ማቴ ፱÷፲፩
 አጋንንትን በተናቸዉ የትዕቢት መሠረቶች ናቸዉና ፡፡ ዮሐ ፰÷፵፬
፪.፯.፲ ገዥዎችን ከዙፋናቸዉ አዋርዶአል ::
 በወቅቱ ኃያላን ነን ይሉ የነበሩ ፀሐፍት ፈሪሳዊያንን ከነበራቸዉ ሹመታቸዉ ሻራቸዉ ፤ከክብራቸዉ
አዋረዳቸዉ፡፡
 በሰዉ ልጅ ላይ ሰልጥነዉ የነበሩ አጋንንትን ከማደሪያቸዉ ከሰዉ ልጆች ለያቸዉ /ኃይላቸዉን በመስቀሉ
ቀጠቀጠዉ/
፪.፯.፲፩ ትሁታንንም ከፍ አድርጓል፡፡
 በእግረ አጋንንት ይረገጡ የነበሩ ትሑታን ነፍሳትን በልዕልና ነፍስ ሰጥቶ አከበራቸዉ /ገነት መንግስተ ሰማያት
እንዲገቡ ፈቀደላቸዉ/
 ትሑታን የነበሩ ሐዋርያትን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ሠጥቶ /አድሎ/ አከበራቸዉ ::
 አስራቱን ፤በኩራቱን ቀዳምያቱን ሰጥቶ ልጆች አደረጋቸዉ፡፡ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሠጣል:: (ያዕ ፬÷፮)እንዲል
፪.፯.፲፪ የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸዉ ::
 ከእግዚአብሔር አምላካቸዉ ተለይተዉ በረሀበ ነፍስ ይሰቃዩ የነበሩ ነፍሳትን ቅዱስ ሥጋዉና ደሙን ሰጥቶ
አጠገባቸዉ፡፡
፪.፯.፲፫ ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸዉን ሰዶአቸዋል ::
 ጸሐፍት ፈሪሳዉያንን ከአስራት ፣ከበኩራት ቀዳምያት ለይቶ ባዶ እጃቸዉን አሰቀራቸዉ፡፡
 በሰዉ ላይ ሠልጥነዉ የነበሩ አጋንንትን ከሰዉ ለይቶ ባዶ እጃቸዉን ሰደዳቸዉ፡፡ መዝ ፵፬÷፲
፪.፯.፲፬ ለአባቶቻችን እንደተናገረዉ ለአብርሃም ለዘሩ የዘለዓለም ምሕረቱን አስቦ እስራኤል ብላቴናዉን
ረድቶአልና ::
 እመቤታችን በጸሎቷ ማጠቃለያ የአባቶቿንና የእግዚያብሔር ቃል ኪዳን መደምደሚያ አደረገች፡፡ ወላዲተ
አምላክም የእነዚህ ደጋጎች አባቶች ልጅ በመሆኗ ልዑል እግዚአብሔር ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ አምላክ
በተዋሕዶተ ሥጋ አለምን ለማዳን የመጣዉ የድኅነት ሥራዉን የፈፀመዉ ከአባቶች ጋር የገባዉን ኪዳን አስቦ
መሆኑን በፀሎቷ መጨረሻ ላይ መጠቀሱ ለምእመናን አብነት ይሆን ዘንድ ነዉ፡፡

የእመቤታችን እረፍት፣ትንሣኤ እና ዕርገት


 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታ ጋር ፴፫ ዓመት ከ፫-ወር አብራ አልተለየችም ጌታችን በመልዕልተ መስቀል
ተሰቅሎ ሳለ ከእግረ መስቀሉ ሥር አብራ ነበረች። ጌታም ለሚወደው ደቀ መዝሙር ለቅዱስ ዮሐንስ አደራ ሰጣት
ቅዱስ ዮሐንስም ወደ ቤቱ ወስዶ አገለገላት።(ዮሐ ፲፱፥፳፮)። እመቤታችንም በዮሐንስ ቤት ለ፲፭ ዓመት ተቀምጣለች
በድምሩ ፷፬ ዓመት ሲሆናት ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓ.ም ገደማ ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች።

 የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ (አስክሬን)
ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ መካነ ዕረፍት (የመቃብር ቦታ) ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንአት ኑ! ተሰብሰቡና በእሳት
እናቃጥላት ብለው ተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋንያ የተባለ ጎበዝ አይሁዳዊ ተመርጦ ሄደ
የእመቤታችንን ሥጋ (አስክሬን)የተሸከመበትን አልጋ ሸንኮር ያዘ የአልጋውን ሸንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ
በእሳት ሰይፍ ሁለት እጆቹን ስለቆረጣቸው ከአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ።

 በዚያን ጊዜም መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ (አስክሬን) ከሐዋርያው ከዮሐንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ በገነት
ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው ቅዱስ ዮሐንስም ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችን ሥጋ
(አስክሬን) በገነት መኖሩን ነገራቸው ሐዋርያትም የእመቤታችንን ሥጋ (አስክሬን) አግኝተው ለመቅበር በነበራቸው
ምኞትና ጉጉት የተነሣ ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው ሲጾሙና ሲፀልዩ ከሰነበቱ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን (በሁለተኛው ሱባኤ
መጨረሻ)ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ አስክሬን አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ በውዳሴና በጽኑ ምሕላ
ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀ መካነ ዕረፍት በጌቴ ሴማኒ ቀበሯት።

ገጽ 11
 የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ አልነበረምና
ከሀገረ ስብከቱ ከህንድ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ
ትንሣኤ ተነስታ ስታርግ ያገኛታል። በዚያ ጊዜም ትንሣኤዋን ሌሎቹ ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት
ተበሳጭቶ ፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይለዋል ማለትም በፊት የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ
ቀረሁ ብሎ ከማዘኑ የተነሣ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ከእርሱ በቀር ሌሎች
ሐዋርያት ትንሣኤዋን እንዳላዩ ነግራው ቅዱስ ቶማስን አፅናናችው ሄዶም ለወንድሞቹ ለሐዋያት የሆነውን ሁሉ
እንዲነግራቸው አዘዘችው ለምልክት ምስክር ይሆነው ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው በመላእክት ታጅባ
እየተመሰገነች ወደ ሰማይ ዐርጋለች።

 በዓመቱ ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛ እንዴት ይቅርብን ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ በሱባኤው
መጨረሻም በነሐሴ በ፲፮ኛው ቀን (ነሐሴ ፲፮) ቀን ጌታችን የለመኑትን ልመና ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር፣ቅዱስ
ጴጥሮስን ንፍቅ (ረዳት) ቄስ፣ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ ዋና ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም ከአቆረባቸው በኋላ
የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል።የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤ እና ዕርገት በትንቢተ
ነቢያት የተነገረ ነበር።(መዝ ፻፴፩፥፰፣መኃ ፪፥፲-፲፭)።

ምዕራፍ ሦስት(፫)
፫.ነገረ ማርያም በነገረ ድኅነት

በዚህ ዓቢይ ርዕስ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በሰው ልጆች መዳን ያላትን ሱታፌ (ድርሻ)
የምንመለከትበት ነው።

፫.፩.ኪዳነ አዳም

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ሥነ-ፍጥረትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) አምጥቶ በቸርነቱ
ሲፈጥራቸው የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ “ሰው” (አዳም) ነው።ምክንያቱም በመልኩ በአርአያው በምሳሌው ፈጥሮታልና
ከፈጠረው በኋላም ሕግ ሰርቶለታል ይህችውም የመታዘዝ ሕግ የመጠበቅ ምልክት ዕፀ በለስን እንዳይበላ መጠበቅ ነው።

ይህንን ህግ ለ፯ ዓመት ከ፫ ወር ከ ፲ ቀን ጠብቆ ከኖረ በኋላ በምክረ ከይሲ በዲያብሎስ ምክር ተታሎ አምላክነት ሽቶ
(ተመኝቶ) ዕፀ በለስን በበላ ጊዜ “ኮናኔ በርትዕ ፈታሔ በጽድቅ” የሆነ እግዚአብሔር አምላክም የምትሞት ትሞታለህ ብሎ
እንደነገረው ፍርዱንም ፈረደበት ከገነትም አባረረው አባታችን አዳምም ከገነት ከወጣ በኋላ እግዚአብሔርን ፍፁም
እንደበደለው አውቆ ንስሐ ገባ የስንዴ ፍሬም ከደሙ ጋር ቀላቅሎ ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጐ አቀረበ አምላካችን
ልዑል እግዚአብሔርም የአሁኑን ተቀብዬልሃለሁ ዓለም የሚድነው በአንተ ደም ሳይሆን በእኔ ልጅ ደም ነው አምስት ቀን
ተኩል ሲፈፀም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በሜዳህ ድሄ በመስቀል ሞት አድንሀለሁ ብሎታል።

በዚህ የአዳም ቃል ኪዳን ልጅህ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው አንቲ
ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እም ገነት ትርጉም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ብሏታል አምስት
ቀን ተኩልም የተባለው አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ነው ይህ እንደተፈፀመም ቅዱስ ጳውሎስ ሲያረጋግጥ እንዲህ
ብሏል ነገር ግን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ።(ገላ
፬፥፬)።

• የዘመን ፍፃሜ ብሎ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመንን


• ሴት ብሎ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን
• ልጅ ብሎ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስን አነሳ።

ገጽ 12
፫.፪.ነገረ ንጽሐ ጠባይዕ ወጥንተ አብሶ
ንጽሐ ጠባይዕ

 ንጽሐ ጠባይዕ ማለት በጥንተ ተፈጥሮ ከንጽሐ ባሕርይ ከእግዚአብሔር ያገኘናት ሀብታችን ናት፡፡ እግዚአብሔር
ንጹሐ ባሕርይ ነው፡፡
 የሰው ባሕርይ ሰውነት ነው፡፡ አራቱ ባሕርያተ ጥንታት ፍጥረቱ ናቸው፡፡ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ
ተብለው መጠራታቸውም ሰውነትን ያስገኙት የእነዚህ ውሕደት ስለሆነና የሰውነት መገለጫዎቹም እነዚህ ስለሆኑ
ነው፡፡

ጥነተ አብሶ

 ጥንተ አብሶ ማለት የመጀመሪያ (የጥንት) በደል ፣የውርስ ኃጢአት ማለት ነው ፡፡


 ይህም ከአዳም መረገም የተነሳ በሰው ልጆች ከአንዱ ወደ አንዱ በዘር የሚወረስ ቁራኝነት ነው ፡፡
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ከዚህ ሁሉ ማለት በዘር ከሚሆነው ኃጢአት እግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስ ጠብቋታል ፡፡ “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እም ከርሰ እማ” እንዲል ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፡፡ ይህንንም ነቢዩ
ኢሳይያስ ሲያረጋግጥ እንዲህ ብሏል ”እግዚአብሔር ፀባኦት እመ ኢያትረፈ ለነ ዘርዐ ከመ ሰዶም እም ኮነ
ወከመ ገሞራ እመሰልነ ፡፡ ትርጉሙም ፦ አሸናፊ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም
በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር” በማለት እንደተናገረ ፡፡ (ት.ኢሳ ፩፥፱)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም በአምላክ ጥበብ ከእናቷ ማሕፀን ጀምራ በአዳም በደል ከመጣው ከመርገመ ሥጋ እና ከመርገመ ነፍስ
ተጠብቃ ያለች ንጽህት ዘር መሆኗን ትንቢት ተናግሮለታል።
 ሰው ከባሕርይ ንጽሐ ወደ ባሕርይ መጎስቆል የመጣበት ሰውና እግዚአብሔር፣ሰውና መላእክት፣ነፍስና ሥጋ
፣በኋላም ሕዝብና አሕዛብ እንዲለያዩ ያደረገ ይህ የመጀመሪያ (የጥንት) በደል ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ በደል
ከልብሰ ብርሃን መራቆትን፣የልጅነት ጸጋን ማጣትንና መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አስከትሏልና፡፡
 “በአንድ በአዳም ምክንያት ኃጢአት ወደዚህ ዓለም ገባ በዚህችም ኃጢአት ምክንያት በሰው ሁሉ ተፈረደ፡፡” (ሮሜ
፭፥፲፪)፡፡ በዚህም ሰው ሁሉ እንደተጎዳበት ለምልአተ ኃጢአትም መነሻው መሠረቱ ጥነተ አብሶ እንደሆነ ሲናገር
”ኃጢአትም ሰውን ኃጥእ አሰኘችው“ አለ፡፡
 ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት በእመቤታችን የተፈፀመ ማለትም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፈስ የሌለባት
መሆኑን ቅዱስ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ መስክሯል። ”ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምልዕተ ፀጋ
እግዚአብሔር ምስሌኪ፤ ትርጉሙም ፡- ፀጋን የተመላሽ ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው፡፡ ቡርክት
አንቲ እምአንስት -አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ። ሉቃ ፩፥፳፰ ። በማለት መልአኩ ምስክርነቱን
ሰጥቷል።

ይህንን የነቢዩ የኢሳይያስንና የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤልን ምስክርነት በመያዝ በርካቶች ቅዱሳን አባቶችም ቅድስት
ድንግል ማርያም በአምላካዊ ጥበብ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ (በጥንተ አብሶ) ተጠብቃ የኖረች ንጽህት ዘር ስለ
መሆኗ በስፋት መስክረዋል፡፡

ስምዐ ሊቃውንት ወመጻሕፍት -የሊቃውንትና የመጽሐፍት ምስክርነት


፩. ዕንቈ ባሕርይ ፀዐዳ

በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ለዚህ ምሥጢር ተቀዳሚ ተጠቃሽ ሊሆን የሚገባው “ማርያምሰ ተሐቱ እምትካት
ውስተ ከርሡ ለአዳም ከመባሕርይ ፀዐዳ- ትርጉሙም ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ
ነጭ ዕንቁ ታበራ(ትፍለቀለቅ) ነበር” ብሎ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በድጓ ድርሰቱ
(ድጓ ገጽ ፸፱) ያስቀመጠው ሊሆን ይገባል ፡፡

ፅንቈ ባሕርይ ክርስቶስን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች አዲስ መዝገብ የተባለች ቅድስት ድንግል ማርያም አዳም
አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስን በመብላቱ ምክንያት ከመጣበት የሥጋና የነፍስ መርገም በጌታ ጥበብ ተጠብቃ የኖረች
መሆኑን ሲገልጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች ብሏል።

ገጽ 13
 ዕንቈ መገኛው ከአፈር ነው፡፡ ተፈጥሮውም ከአፈር ነው፡፡ ነገር ግን ተፈጥሮው ከአፈር ይሁን እንጂ የአፈርን ገፀ
ባሕርይ የሚገልፅ ገፀ ባሕርይ የለውም ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የተገኘችው ቅዱሳንና ከሰው
ወገን/ምድራዊ ከሆኑ ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐና ነው፡፡ ነገር ግን የውርስ ኃጢአት ካለባቸው እናት እና
አባቷ ትወለድ እንጂ ጥንተ አብሶ /የውርስ ኃጢአት ፈጽሞ አላገኛትም፡፡በመንፈስ ቅዱስ ተጠብቃ ኖረች
እንጂ፡፡“መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እም ከርሰ እማ” እንዲል ፡፡ (አባ ጊዮርጊስ አርጋኖን ዘእሑድ)
 ዳግመኛም ዕንቈ ጽሩይ/የጠራ/ ነው፡፡ ከጽሩይነቱም የተነሳ ቀረብ ብሎ ወደ ዕንቈ ሲመለከቱ መልክን ቁልጭ
አድርጎ ያሳያል፡፡ እመቤታችንም እንደ ቅዱስ ያሬድ በሃይማኖት በትህትና ሆኖ ለሚያያት መልክአ ተፈጥሮአችንን
የምናይባት ፣ያላደፈውን ንጽሐ ጠባያችንን የምናስተውልባት ድንቅ መስታዎታችን ናትና፡፡
 ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም ፡፡መኃ ፬፥፯፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም መንፈስ ቅዱስ
የእመቤታችን ነገር እንደገለጠለት ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም ብሎ ተናገረ ለጊዜው መልክ ከደም
ግባት ጋር አስተባብራ በመገኘቷ ይህ ተነግሮላታል ለፍፃሜው ግን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጥንተ አብሶ
የሌለባት ንፅህት መሆኗን የሚያስረዳ ኃይለ ቃል ነው።

፪. ጽሩይ እምጽቡር

 ሊቁ ቅዱስ ኤራቅሊስ፡- “ወእምጽቡር ጽሩየ ገብራ-ከጭቃ መካከል ጽሩይ ወርቅ አድርጎ ፈጠራት”፡፡ ይህን በቅጥነተ
ልብ (በጣም በመራቀቅ) ሊያዩት የሚገባ ምሥጢር ነው፡፡ እንደ ሊቁ አገላለጽ ጭቃ አይደለችም ወርቅ ናት ፤መገኛዋ
ግን ጭቃ ነው ማለት ነው፡፡ እነደዚህ ማለቱ እመቤታችን መርገም ካለባቸው የአዳምና የሔዋን አካል ክፋይ ብትሆንም
ግን የአዳምና የሔዋን መርገም በፍጹም የለባትም ማለቱ ነው፡፡ ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተጠብቃለችና ”አልብኪ
ነውር ወኢምንትኒ በላእሌኪ - ምንም ነውር ነቀፋ የለብሽም ” መኃ ፬፥፯፡፡
 ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፡- ”ንጽሕት ኩሎ ጊዜ -ሁል ጊዜ ንጽሕት የሆንሽ የንጽሕና መሠረት”
 ሊቅ ቅዱስ ቴዎዶጦስ(ሃይ.አበ ፶፫፥፳፪)፡- ”ወኢሊኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል
በሥጋሃ -ከፈጠራት ጀምሮ በምንም ምን ነውር አልተገኘባትም በሕሊናዋም በሥጋዋም ንጽሕት ድንግል ናት እንጂ” ፡፡
 ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (ሃይ.አበ ፷፮፥፲፬)፡- ”ወሶበ ለከበ ሥጋሃ ቅዱሰ ወነፍሳ ቅድስተ ፈጠረ ሎቱ በመንፈስ
ቅዱስ ሕያወ መቅደሰ-የዚህችን ድንግል ነፍሷንም ሥጋዋንም ነጹሕ ሆኖ ቢያገኘው በመንፈስ ቅዱስ የሚናገር
መቅደሱን(ትስብእትን) ለራሱ ፈጠረ ፣አዘጋጀ” ሊል ይገልጻታል፡፡

፫. ጽጌ በማዕከለ አሥዋክ

 ”በማዕከለ አሥዋክ ዘጸገየት ጽጌ ሃይማኖት ዘበአማን-በእሾህ መካከል ያበበች(የፈነደቀች ) የሃይማኖት


አበባ” በማለት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ድጓ በተሰኘ ድርሰቱ ከጽጌረዳ ምሣሌ ነስቶ(ወስዶ) ሦከ ኃጢአት
የኃጢአት እሾህ) ያልደረሰባት መሆኗን አመሥጥሮ አመሥግኗታል ፡፡ (ድጓ ገጽ ፸፭ )
 ጽጌረዳ ከአበባዎች ሁሉ የተለየ መዓዛ ያላት ለየት ያለች አበባ ናት፡፡ ከማዕዛዋ ማማርም የተነሳ ካህናት
አባቶቻችን ከዕጣኑ ጋር እየጨመሩ በማዕጠንት ጊዜ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ያውሉታል፡፡

፬. የሲና ምድረ በዳ
 ዘፍ ፫፥፲፯ “ምድር ካንተ የተነሳ የተረገመች ትሁን፡፡
 ዘጸ ፫፥ ፭ “አንተ የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ፡፡”

፫.፫.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታ ጽንሰት እስከ ቀራኒዮ ያደረገችው አገልግሎት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ተመርጣ እናት እንደምትሆነው በነቢያት በተነገረው ትንቢት
መሰረት አምላክ ዓለሙን ለማዳን የቀጠሮው ጊዜ ሲደርስ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ እመቤታችን ላከው እርሷም ሀርና ወርቅ
እያስማማች ስትፈትል ልብሱን እየታጠቀ እየፈታ ለእርሷ የሚገባውን ክብር ሰጥቶ እያመሰገናት ለእግዚአብሔር እናት
እንድትሆነው መመረጧን ነገራት እርሷም እኔ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? ብላ ጠየቀችው እርሱም
“ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም” አላት እመቤታችንም እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ (ገረድ) ነኝ እንደ ቃልህ
ይደረግልኝ አለችው። በዚህ ጊዜ አካላዊ ቃል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ
ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በተለየ አካሉ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የዕለት ፅንስ ሆኗል። ሉቃ
፩፥፳፮።

ገጽ 14
 የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አገልግሎት ከዚህ ይጀምራል። እግዚአብሔር ዓለሙን ለማዳን በወደደ ጊዜ
እሺ ብላ እመቤታችን ፈቃደኛ በመሆኗ ከእርሷ ሰው ሆኗልና አባቶቻችን በነገረ ማርያም እንደሚያስተምሩት
እመቤታችን በቤተ መቅደስ ሳለች መጽሐፈ ኢሳይያስ ስትመለከት ከትንቢተ ኢሳይያስ ምዕ ፯፥፲፬ ላይ ”ድንግል
በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል።” የሚለውን ስታነብ ከዚች ድንግል ከዘመኗ
ደርሼ እንጨት ሰብሬላት ውሃ ቀድቼላት ገረድ ሆኜ ባገለገልኳት ብላ ተመኝታ ነበር፡፡ አምላካችን ልዑል
እግዚአብሔርም ትህትናዋን ተመልክቶ ለበለጠው አገልግሎት ለእናትነት መረጣት እርሷም በኅቱም ድንግልና ፀንሳው
በኅቱም ድንግልና ወልዳዋለች።

 ጌታችን በተወለደ ጊዜ ሰብአ ሰገል ለጌታችን የሚሆነውን እጅ መንሻ ይዘው ከሩቅ ምሥራቅ መምጣታቸውን ተመልክቶ
በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ ጌታችንን ሊገድለው በምቀኝነት ተነሳበት ፡፡ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ
ለአረጋዊ ዮሴፍ በህልም ተገልፆ ህፃኑን ከእናቱ ጋር ይዞ ወደ ግብፅ እንዲሰደድ አዘዘው ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ህፃን ልጇን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለ ፫ ዓመት ከ፮ ወር በግብፅ
በርሃ ተንከራታለች።

 በዚህ የመከራ ዘመንም ስለ ልጇ ስትል ተርባለች ፤ ተጠምታለች፣ ሽፍቶች አስደንግጠዋታል ፣የተለያዩ ብዙ መከራዎችን
ተቀብላለች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ወቅት አገልግሎቷ መከራ በመቀበል ነበር ፡፡ ቅዱስ ወንጌል
ምስክር እንደሆነ ማቴ ፪፥፲፫-፲፱ ፣ራዕ ፲፪፥፩ ከዚያም ሄሮድስ ከነ ክፋቱ ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለአረጋዊ
ዮሴፍ በህልም ተገልፆ የሕፃኑን ነፍስ የሚሹት ሞተዋልና “ህፃኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለስ” ብሎ
አዘዘው፡፡ እነርሱም፦ማለትም እመቤታችን ጌታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰዋል። በኢየሩሳሌም
ናዝሬት በተባለ ቦታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን በዚያ አሳድጋዋለች። ማቴ ፪፥፳፪-፳፫ ፣ ሉቃ
፪፥፶፩-፶፪ ፡፡ ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስ በሃይማኖተ አበው ይህንን ነገር አጉልቶ ሲናገር እንዲህ ብሏል ”ድንግል
ወንድ ሳታውቅ ሊዋሀደው በፈጠረው ሥጋ የፀነሰችውን ወለደች ያለ ሀጢአት ያለ ምጥ ወለደችው
የአራስነት ግብር አላገኛትም ያለ ድካም ያለ መታከት አሳደገችው ያለ ድካም አጠገባቸው ለሥጋ በሚገባ
ሕግ ምን አበላው ምን አለብሰው ሳትል አሳደገችው” ሃይ.አበ ገጽ ፹፮፥፲፱።
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማስተማር ዘመኑም ከጌታችን አልተለየችም፡፡ በቅዱስ ወንጌል
“የመጀመሪያው ተአምር” ተብሎም የተመዘገበው ተአምር የተከወነው በእመቤታችን ምልጃ ነው።ይኸውም የውሃው
ወደ ወይንነት መለወጥ ነው።ዮሐ ፪፥፩-፲፩።
 በስተመጨረሻም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለድህነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል በተሰቀለ ጊዜ ከመስቀሉ ስር
ነበረች ልብን በሚያቃጥል እንባ እያለቀሰች ታዝን ነበር ከእርሷ ጋር እነ ሰሎሜ፣ እነ ማርያም መግደላዊት ፣ ሌሎችም
ሴቶች ፣ ከደቀ መዛሙርቱም ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ቁመው አብረው ያለቅሱ ነበር፡፡ ጌታችንም ለድንግል ማርያም
ዮሐንስን እነሆ ልጅሽ አላት ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን ደግሞ ድንግል ማርያምን “እናትህ እነኋት” አለው።ደቀ መዝሙሩ
ዮሐንስ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ዮሐ ፲፱፥፳፮። ይህ እንዲህ ለጊዜው በዮሐንስ አማካኝነት እመቤታችን ለሐዋርያት በእናትነት
መሰጠቷን እርሷም እነርሱን በፀጋ ልጅነት መቀበሏን ያሳያል።ለፍጻሜው ግን እኛን ሁላችንን በፀጋ ልጅነት
ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም መሰጠቱን እና ለእኛ ለሁላችን ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያምን በፀጋ እናት አማላጅ አድርጎ መስጠቱን የሚያመለክት ኃይለ ቃል ነው።

ሐዋርያትም ከጌታችን ሞት እና ትንሣኤ እንዲሁም በ፵ኛው ቀን ማረግ በኋላ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ
ክርስቶስ ተስፋውን እንደሰሙ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በማርቆስ እናት ቤት ዘግተው ደጅ ሲፀኑ (ሲፀልዩ) በመካከላቸው
እመቤታችን አብራ እንደነበረች ቅዱስ ሉቃስ በግብረ ሐዋርያት መፅሐፍ ምስክር ሁኗል ። ዮሐ ሥራ ፩፥፲፬።

“እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለፀሎት ይተጉ ነበር” እንዲል።
ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሊሰብኩት በየአህጉረ ስብከታቸው ሲፋጠኑ እመቤታችን አልተለየቻቸውም
ነበር።ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ድርሰቱ “ሞገሰ ስብከቶሙ ለሐዋርያት” ብሏታል።ትርጉሙም የሐዋርያት
የስብከታቸው ሞገስ አንቺ ነሽ ማለት ነው።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን አገልግሎት ለመግቢያ ያህል ጠቀስን እንጅ
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አገልግሎት ከነቢያት ከሐዋርያት ከቅዱሳን ሁሉ የበለጠ በፍፁም እምነት ከእናንት
ፍቅር ጋር ልዑል እግዚአብሔርን ያገለገለች እናት ናት።

ገጽ 15
፫.፬. የእመቤታችን ምልጃ በነገረ ድኅነት

“ድኅነት” ስንል በሀጢአት ምክንያት የወደቀውና የጎሰቆለው የሰው ልጅ ከደረሰበት ድቀትና ሞት ሙሉ በሙሉ ነፃ
መውጣቱን እና አጥቶት የነበረውን ፀጋ ማግኘቱን መጀመሪያ ከመበደሉ በፊት ወደ ነበረበት ሀኔታ (ከዚያም ወደ በለጠ
ደረጃ) መመለሱን ማለታችን ነው። “የሰው ልጅ ዳነ” ስንል ተፈርዶበት የነበረው የሞት ፍርድ ተወገደለት ተነስቶት
(ተወስዶበት) የነበረው ሕይወት ተመለሰለት ማለታችን ነው።ይህ ድኅነት የተፈፀመው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር
ፈቅዶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በህቱም ድንግልና ተፀንሶ በህቱም ድንግልና ተወለዶ በ፴ ዘመኑ ተጠምቆ
ዙሮ አስተምሮ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ሞቶ ተቀብሮ በ፫ኛው ቀን ተነስቶ በክብር አርጐ
ደግሞ ሰው ፍፁም ካሳ ከተደረገለት በኋላ የድህነቱ ማረጋገጫ የሚሆን ጥምቀትን ቁርባንን ሥጋ ወደሙን ቤተ
ክርስቲያንን ሰጥቷል።

ይህ ሁሉ ግን ለሰው የተደረገለት ከሰው በጎ ሥራ የተነሣ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
እንዲህ ብሏል “እኛ ሁላችን ደግሞ የሥጋችንን ፈቃድ እያደረግን በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎችም
ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ፀጋ ስለሆነ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ
በበደላችን ሙት እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን በፀጋ ድናችኋልና።”ኤፌ ፪፥፫-፰ እንዲል በሌላም ሥፍራ
“ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደድ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት
በሚሆነው ጥምቀትና በመንፈስ ቅዱስ ኪዳንን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም። ቲቶ ፫፥፫-፭
ብሏል።

ከዚህ ሁሉ ጋር ሰው በምግባር ጉድለት ቢገኝበት የመዳን ምክንያት እንዲሆንለት ቅዱሳንን በቃል ኪዳን አክብሮ ሰዎችን
እንዲያማልዱ ፈቃዱ ሆኗል።ማቴ ፲፥፵፩ “ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል ፃድቅንም በፃድቅ ስም
የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል”እንዲል፡፡ ከቅዱሳን ሁሉ የበለጠ ክብር ያላት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም
የተሰጣት ቃል ኪዳን እና ምልጃም አንዱ ነው ይህም የመዳን ምክንያት ነው።

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ወፍ ዘራሽ ብቅ ያለ አይደለም። ትንቢት
የተነገረለት ምሳሌ የተመሰለለት በሐዲስ ኪዳን አማናዊ ሁኖ የተገለጠ ነው።

የተመሰለ ምሳሌ

 ዘፍ ፯. “በጥፋት ውሃ ዘመን ኖህ እና ቤተሰቦቹ እንዲሁም እንስሳቱ እና አራዊቱ በመርከብ ውስጥ ሆነው ከጥፋት
ውሃ ድነዋል ከመርከቡ ውጭ የነበሩ ፍጥረታት ግን ተደምስሰዋል።ይህም ምሳሌ ነው በመርከቡ ውስጥ የነበሩ
የዳኑ ነፍሳት የእመቤታችን አማላጅነት ቃል ኪዳን አምነው የዳኑ የሚድኑ ነፍሳት ከመርከቡ ውጭ ሁነው (የጠፉ)
በእመቤታችን ምልጃ የማያምኑ የሚጠፍ (የጠፉ) የመናፍቃን ምሳሌ የጥፋት ውሃ የሲኦል ምሳሌ ነው።
 የእመቤታችን ምልጃ በዚህ ምሳሌ እንደተገለፀ ልብ ይሏል።

የተተነበየ ትንቢት

 መዝ ፵፬፥፱ “በወርቅ ልብስ ተጐናፅፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች”

• ንግሥቲቱ ወላዲተ አምላክ በንፅሕና በቅድስና አጊጣ አንተ በሰጠሀት ክብር በወልደ እግዚአብሔር ቀኝ
(ሥልጣን) የኃጥአን አማላጅ ሆና ለጥብቅና እንደምትቆም የሚያስረዳ የትንቢት ሀይለ ቃል ነው።

እንግዲህ ከላይ ለማየት እንደሞከርነው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በምሳሌ እና በትንቢት
የተነገረ ነው።አማላጅነትን በአጠቃላይ ስንመለከት ትርጓሜው የሚለምን፣ የሚፀልይ፣አማላጅ የሚሆን ማለት ሲሆን
በሁለት ወገኖች መካከል በመግባት አንዱን ስለሌላው የሚማልድ ማለት ነው።በመንፈሳዊ መንገድ ስንመለከተው ደግሞ
የሚለመነው ልዑል እግዚአብሔር ሲሆን የሚያማልዱት በእግዚአብሔር የተጠሩና የተመረጡ ቅዱሳን ሁሉ ይልቁንም
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።ምልጃ የታዘዘውና የተፈቀደው ያስፈለገው እግዚአብሔር ከኃጢአን ይልቅ
የጻድቃንን የእመቤታችንን ፀሎት የበለጠ ስለሚሰማ ነው። መዝ ፴፫፥፲፭ ። የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ፃድቃን ጆሮዎቹም
ወደ ጩኸታቸው ናቸው። እንዲል

ገጽ 16
አማላጅነት የእግዚአብሔር የቸርነት ስጦታ ነው።ምክንያቱም ምግባራቸው የደከመና ፀሎታቸው እንደርሱ ፈቃድ ያልሆነ
ተነሳሕያን ኃጥአን የእርሱን ፈቃድ በሚያውቁና በሚፈጽሙ በምግባር በበለፀጉ ፃድቃን እንዲረዱ ማድረግ የቸርነቱ
መግለጫ ነው። ዘፍ ፳፥፩-፯ “ነቢይ ነውና ስለ እናንተ ይፀልያል” ትድናለህም።እንዲል አቤሜሌክ ንጉሠ ጌራራ በፈፀመው
ስሕተት እግዚአብሔርን በማስቀየሙ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ የተላከው ወደ ቅዱሱ አብርሃም ነው። ለቅዱሳን አባቶቻችን ይህን
ያህል አማልዶ ማስታረቅ ሥልጣን ከተሰጠ ለወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም እማ እንዴት የበለጠ ሀብተ ምልጃ
አይሰጣት ምክንያቱም ምልዕተ ፀጋ ናትና።ሉቃ ፩፥፳፰

እመቤታችን የእናትነት ክብርና የአማላጅነት ቃል ኪዳን ከልጅዋ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለች
በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት ልጅዋ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ወኃውን ወደ ወይን ለውጦ የመጀመሪያውን ተአምር ያደረገ
ው።በእመቤታችን አማላጅነት መሆኑ የታመነ ነው።ዮሐ ፪፥፩-፲፩ ፡፡ እናት ወልዳ ማስገኘት ብቻ ሳይሆን ልጇን የማዘዝ
መብትም አላት። በተለይ ወላዲተ አምላክ (የአምላክ እናት) የመሆኗ ትልቁ ምስጢርም የማዳን ሥራው ተካፋይ መሆን
ነውና ከዚህ የተነሳ አባቶች በብሒላቸው “የእናት አማላጅ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ ሲሆን በውድ ያለበለዚያ
በግድ”። ይላሉ። ስለዚህ በእመቤታችን ቃል ኪዳን እና አማላጅነት በህይወታችን ተጠቃሚዎች ልንሆን ያስፈልጋል።

ምዕራፍ አራት(፬)
፬. ክብረ ቅድስት ድንግል ማርያም(ክብረ ድንግል)
 እመቤታችን ከሁሉ ይልቅ ወላዲተ አምላክ በመሆኗ ከፍጥረታት ሁሉ የከበረች ናት፡፡ የሚከተሉት እመቤታችንን
ክብርት ከሚያሰኟት መካከል የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡

፬.፩.የአምላክ እናት መሆኗ


 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗ ቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረ ነው።ነቢየ እግዚአብሔር
ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ እንዲህ ብሎ ተናግሯል “ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶልናልና አለቅነትም
በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።ኢሳ ፱፥፮
ይህም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ” ተብሎ የተነገረለት የባህርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።እርሱን የወለደች
ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ::
 በሌላም ሥፍራ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ብሏል “ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል
ተብሎ ይጠራል”።ኢሳ ፯፥፲፬ “አማኑኤል” ማለትም የእግዚአብሔር መልአክ እንደተረጐመው እግዚአብሔር ከሥጋችን
ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ ማለት ነው ይህም የባህርይ አምላክ ነው በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችው
ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ስለዚህ የአምላክ እናት መባል ይገባታል።ማቴ ፩፥፳፫።
 ቅድስት ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተመልታ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗን ስትመሰክር የጌታዬ እናት
ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል ብላለች።ሉቃ፩፥፵፫። ድንግል ማርያም በቅድምና ለነበረ አካላዊ ቃል
ለእግዚአብሔር ወልድ እናቱ ናት።ዮሐ ፩፥፩-፲፬ ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው።የሐዋ.ሥራ
፳፥፹። ስለዚህም ነው የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ የምንላት በዘመኑ ፍጻሜ ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ
ክርስቶስ የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ አምላክ ወልደ አምላክ ነው።ገላ ፬፥፬፣ሮሜ ፩፥፫-፬ ስለዚህም እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ትባላለች።
 በብሉይ ኪዳን ነቢያት “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” እያሉ የተናገሩት ትንቢት በኢየሱስ ክርስቶስ መፈፀሙ የኢየሱስ
ክርስቶስን እግዚአብሔርነት የባህርይ አምላክነት የሚያረጋግጥ ነው።ኢዮ ፪፥፴፪፣የሐዋ ፪፥፳፩-፴፰፣ሮሜ ፲፥፱-፲፫፣ኢሳ
፵፥፫፣ማር ፩፥፩-፫ እነዚህን ማመሳከሩ ብቻ በቂ ነው።ይህንን ሁሉ ይዘን ድንግል ማርያም ለአምላክ እናትነት ብቻ
የተፈጠረች የእግዚአብሔር እናት ናት እንላለን።
 በተጨማሪም የእስክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ አባታችን ቅዱስ ቄርሎስ “አማኑኤል የባሕርይ አምላክ እንደሆነ
ንጽሕት ድንግልም አምላክን የወለደች እንደሆነች ሰው የሆነ የእግዚአብሔርንም ቃል እንደወለደች
የማያምን ሰው ቢኖር የተወገዘ ይሁን” በማለት ካወገዙ በኋላ ዳግመኛ በኋላ ዘመን ቅድስት ድንግል እርሱን በሥጋ
ወለደችው ስለ እኛ ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ወለደችው ስለዚህም ቅድስት ድንግልን ወላዲተ አምላክ
እንላታለን። ሃ.አበው ገጽ 277-305 በማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መባል
እንደሚገባት አስረግጦ ተናግሯል።
፬.፪. ቅድስናዋ

ገጽ 17
- ቅድስተ ቅዱሳን ከተለዩ የተለየች ትባላለች።አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም
ቅዱሳን ሁኑ።ዘሌ ፲፱፥፪
- ከዚህ ዓለም ቅዱሳን እና ቅዱሳት መካከል እንደ እመቤታችን ያለ በእርስዋ መጠን ፀጋን የተመላ በንጽሕናና
በቅድስና የተዋበ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነና በልዑል ኃይልም የተጠበቀ ሰውነት ያለው የለም።ሉቃ ፩፥፳፰-
፴፮።
- በሐልዮ ፣በነቢብ ፣በገቢር ንፅሐ ጠባይ ያላደፈባት ቅድስትና ቡርክት በመሆኗ ነው ስለዚህ ራስዋ ወላዲተ አምላክ
አስቀድማ በወንጌል ቃል እንደተናገረችው ትውልድ ሁሉ “ቅድስት ወብፅዕት” እያሉ ሲያመሰገኗት ይኖራሉ።ሉቃ
፩፥፵፰።
- አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ
ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) አላገኛትም፡፡ መኃ ፬፥፯።
- “ምልዕተ ጸጋ ምልዕተ ክብር ሆይ ደስ ይበልሽ”ተብላ በቅዱሳን መላእክት አንደበት በቅድስናዋ
ተመስግናለች።ሉቃ ፩፥፳፰
- “እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ ምሥራቁን እና ምዕራቡን ሰሜኑን እና ደቡቡን ዳርቻዎችን ሁሉ ተመለከተ
እንደ አንቺ ያለ አልተገኘም ያንቺን ንጽሕና ወደደ ደም ግባትሽን ወደደ የሚወደውን ልጁን ወደ አንቺ ሰደደ። ”
ቅዳሴ ምርያም
- በመዝ ፻፴፩፥፲፫ “እግዚአብሔር ፅዮንን መርጧታል ማደሪያው እንድትሆን አስጊጧታል።”
፬.፫ ድንግልናዋ
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከተለዩ የተለየች ከከበሩት የከበረች የሚያደርጋት ማኅተመ ድንግልናዋ
ሳይለወጥ አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መዉለዷ ነዉ፡፡ ማቴ ፩÷፲፰-፳
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት፣በፀነሰች ጊዜ፣ከፀነሰች በኋላ፣ከመውለዷ
በፊት፣በወለደች ጊዜ፣ከወለደች በኋላ ድንግል ናት እመቤታችን ከሌሎች ሴቶች ተለይታ እግዚአብሔር ከፈጠራት
ጀምሮ በአሳብ በመናገርና በመሥራት ንጽሐ ጠባይ ያላደፈባት ንጽሕት ናት።
 “ድንግል” የሚለው ቃል በርግጥ ቅድስናዋን፣ንጽሕናዋን ብቻ ሳይሆን ልዩ መሆኗንም ያመለክታል በዓለም
ከነበሩና ከሚኖሩ ሴቶች እንደ እመቤታችን ድንግልና ከእናትነት፣ እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የተገኘች ሴት
የለችም ::
 እመቤታችን ለዘለዓለም ድንግል ናት፡፡ ”እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ
ናት።” (መኃ ፬÷፲፭)
 ነቢዩ ሕዝቅኤል የተመለከተዉ ራዕይም እመቤታችን እናትና ድንግል መሆኗን ነዉ፡፡ ”ወደ ምሥራቅም
ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር።እግዚአብሔርም።
ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር
ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።” ሕዝ ፵፬÷፩-፫
 ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስም “ቅድስ ገብርኤል ወደ አንዲት ድንግል ተላከ የዚያችም ድንግል ስም ማርያም
ነዉ” በማለት ስለድንግልናዋ ተናግሯል :: ሉቃ ፪÷፯
 ነቢዩ ኢሳይያስም “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች።”ኢሳ ፯፥፲፬። በማለት ስምዋን እስከ
ግብሯ ድንግል ብሏታል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልናዋ ፀንታ የኖረች የአምላክ እናት ናት፡፡
ነቢያት የተናገሩት ትንቢትም በእመቤታችን የተፈፀመ እርሷም ዘለዓለማዊ ድንግልና ያላት መሆኗን ወንጌላዊው
አረጋግጦ ፅፎታል።ማቴ ፩፥፲፰፣ሉቃ ፪፥፴፬-፴፭።
 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ “ሥጋ የሌለው እርሱ ሥጋዋን ተዋሕዶ እንደ ሰው ሁሉ ዘጠኝ ወር ከአምስት
ቀን በጌትነቱ ሳለ በማኅፀኗ ተወሰነ።ከዚያ በኋላም የሚወለድበት ቀን ሲደርስ በማይመረመር ግብር
በኅቱም ድንግልና ተወለደ ማኅተመ ድንግልናዋም አልተለወጠም ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ
ተወለደ እንጂ ” ብሏል ፡፡ ሃይ.አበ ገፅ ፪፻፲፪
 አባታችን የአንፆኪያው ሊቅ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ “አምላክን የወለደች ማርያም ለዘለዓለሙ ድንግል
እንደሆነች መውለዷም የማይመረመር ድንቅ እንደሆነ ከወለደችም በኋላ በድንግልና ፀንታ እንደኖረች
አስረዳ” ሲል ተናገረ፡፡ ሃ.አ.ገፅ ፫፻፸፭።

ገጽ 18
 ቅድስት ድንግል ማርያም መድኃኒታችንን ከወለደች በኋላ ድንግል አይደለችም ለሚሉ መናፍቃን መልስ በሰጠበት
ድርሳኑ ቅዱስ ጀሮም “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተዘጋው በር እንዴት እንደገባ ይንገሩኝና ቅድስት
ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን እነግራችኋለሁ” ብሏል።(St.mary in the
orthodox concept by Tadros malaty).

፬.፬ የክብረ ድንግል መገለጫዎች


• ክብር የሚለው ቃል ጌትነትንና ከፍተኛነትን የሚያሳይ ነው።ከሁሉ በላይ ክብር ያለው እግዚአብሔር ነው::
ክብሩም በሥራው ይታያል።መዝ ፲፰፥፩ ፣ ዘፀ፲፮፥፯ ፣ ኢሳ ፮፥፫ ። እግዚአብሔር ክቡር በመሆኑ የአሸናፊ
የእግዚአብሔር እናት ቅድስት ድንግል ማርያም አንዳች ያልጎደለባት ምልዕተ ጸጋ ስለሆነች እግዚአብሔርም ከእርሷ
ጋር ስለሆነ ክብርት ናት።እንኳን መልዕልተ ፍጡራን የሆነች እርሷ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ክቡር ነው።ሉቃ
፪፥፱ ፣ ፩ቆሮ ፲፩፥፯ ፣ ፩ቆሮ ፲፭፥፵፩።
• አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብሩን በተአምራቱ በደብረ ታቦር በትንሣኤውና በዕርገቱ
ገልጧል።ዮሐ ፪፥፲፩ ፣ ማቴ ፲፯፥፩ ፣ ፩ጴጥ ፩፥፳ በኋላም በዳግም ምጽአቱ ይገለጣል።ማር ፰፥፴፰። የእናቱ የቅድስት
ድንግል ማርያም ክብር ደግሞ የተገለጠው አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና በመውለዷ ነው።ይህ ክብር ልዩ
ነው።ምክንያቱም ከእርሷ በቀር የአምላክ እናት የሆነ የለምና ወደ ፊትም አይኖርም።
• “ፀሐይን ተጐናፅፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋ ላይ አሥራ ሁለት ከዋክብት የሆነላት”። በማለት
ክብሯን በሰማይ ከፍ ብሎ በማየቱ አክብሯታል።ከነቢያት ለመጥቀስ ያህል ንግሥቲቱ በወርቅ ልብስ ተጐናፅፋና
ተሸፋፍና በቀኝህ ትቆማለች ያለው የእመቤታችንን ክብሯን ሲገልጥ ነው።ራዕ ፲፪፥፩ ፣ መዝ ፵፬ ፥፱።
• በረቡዕ ውዳሴው “ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ
ተገኝታለችና።መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማህፀኗ
ተሸክማዋለች እርሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች ከሱራፌልም ትበልጣለች ከቅድስት ሥላሴ ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና
የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህቺ ናት።ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት ሲል የተሰጣትን ክብር ገልጧል
እኛም ቅዱስ ኤፍሬምን አብነት አድርገን እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናከብራታለን።

፬.፬.፩ ስግደት ለእመቤታችን

 ለእመቤታችን የፀጋ ስግደት መስገድ እንዲገባ ቅዱሳት መጻሕፍት ተባብረው አስረግጠው ተናግረዋል።ኢሳ ፵፱፥፳፪።
“ወንዶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሟቸዋል። ነገስታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ። እቴጌዎቻቸውም
ሞግዚቶችሽም ይሆናሉ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል የእግርሽን ትቢያ ይልሳሉ”። ብሎ
ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ አስቀድሞ ተናግሯል በሌላም ስፍራ ነቢዩ እንዲህ ብሏል “የእግሬን ሥፍራ እሰብራለሁ
የአስጨናቂዎችም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ
የእግዚአብሔር ከተማ የእሥራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።ኢሳ ፷፥፲፫።
 የፀጋ ስግደት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የአምልኮት ስግደት በማኅፀነ ድንግል ላለው ጌታ ለኢየሱስ
ክርስቶስ ሰግዷል ሉቃ ፩፥፲፭ ፣ ሉቃ፩፥፴፱-፵፮።

፬.፬.፪.ምስጋና ለእመቤታችን

 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ስለሆነች ምስጋና ይገባታል፡፡ ምስጋናም
እንዲገባት ከዚህ እንደሚከተለው መጽሐፍ ቅዱስን የተመረኮዘ አስረጂ እንገልጻለን፡፡
 መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “ደስ ይበልሽ ፀጋ የመላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው አንቺ ከሴቶች መካከል
ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ” ብሎ የአመስጋኞች ጀማሪ ሆኖ ምስጋናዋን ተናግሯል፡፡ እንዲህ ባለ ምስጋናም
የተመሰገነ ማንም አልነበረም ሉቃ ፩፥፳፰።

ገጽ 19
 ቅድስት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝታ ”አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህፀንሽ
ፍሬም የተባረከ ነው” አለች አመስግናታለች።(ሉቃ ፩፥፴፱-፵፭)።
 ራሷ እመቤታችን ከእንግዲህ ወዲህ ከዛሬም ጀምሮ በአንድ መልአክ በአንዲት ሴት ብቻ አልመሰገንም
ፍጥረቱ ሁሉ ትውልዱም ሁሉ ያመሰግኑኛል ስትል “ከእንግዲህ ወዲህ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል’’ ብላ
ተናግራለች (ሉቃ ፩፥፵፰)።
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሰባቱ ቀናት ዑደት ከዓመት እስከ ዓመት ለዘለዓለም ስትመሰገን ትኖራለች
፡፡ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬምንም ውዳሴዋን ስታስደርሰውም ከሰባት ከፍላ አስደርሰዋለች፡፡ “ለምን?” ቢሉ በሰባቱ ዕለታት
መመስገን ፈቃድዋ ስለኾነ /ሉቃ.፩፡፵፰/፤ አንድም ሰባቱ ዕለታት ምሳሌዋ ናቸውና፡፡ ይኸውም፡-
 በዕለተ እሑድ አሥራወ ፍጥረታት አራቱ በሕርያት (እሳት፣ ውሃ፣ ነፋስና መሬት) ተገኝተዋል /ዘፍ.፩፡፩፣
ኩፋ.፪፡፰/፡፡ ከሷም ለዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ የሚባለው፣ ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ፣
ያለ እርሱ ቃልነት ያለ እርሱ ሕልውና ምንም ምን የተፈጠረ የሌለ፣ አምጻኤ ዓለማት ፈጣሬ ዓለማት ፤ በአጭር
ቃል አሥራወ ፍጥረት ጌታችን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተገኝቷል/ዮሐ.፩፡፫/፡፡
 በዕለት ሰኞ የብርሃን ማኅደር የኾነው ጠፈር ተገኝቷል /ዘፍ.፩፡፮-፯/፡፡ ከእርሷም ብርሃን ክርስቶስ ተገኝቷል
/ዮሐ.፩፡፭-፱/፡፡
 በዕለተ ሠሉስ ምድር ገበሬ ሳይጥርባት፣ ሳይደክምባት፣ ዘር ሳይወድቅባት በቃሉ ብቻ በእጅ የሚለቀሙ
አትክልት፣ በማጭድ የሚታጨዱ አዝርእት፣ በምሳር የሚቆረጡ ዕፅዋት ለሥጋውያን ምግብ የሚኾኑ ተገኝተዋል፡፡
ከእሷም የወንድ ዘር ሳይወድቅባት ዕፀ ሕይወት፣ ፍሬ ሕይወት (የመንፈሳዊያን ምግብ) የሚኾን ጌታ ተገኝቷል፡፡
 በዕለተ ረቡዕ “ለይቁሙ ብርሃናት በገጸ ሰማይ” ባለ ጊዜ የተሠወረውን የሚገልጡ፣ የጨለመውን የሚያስለቅቁ
ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ተገኝተዋል /ዘፍ.፩፡፲፬-፲፱/፡፡ ከእሷም በብርሃኑ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት፣ ጠፈር ደፈር
የማይከለክለው፣ መዓልትና ሌሊት የማይፈራረቀው፣ የጽድቅ ፀሐይ (ለመንፈሳዊያን ምግብ) የሚኾን ጌታ
ተገኝቷል፡፡
 በዕለተ ሐሙስ “ለታወጽእ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት” ባለ ጊዜ በልባቸው የሚሳቡ፣ በእግቸው የሚሽከረከሩ፣
በክንፋቸው የሚበሩ፣ በደመ ነፍስ ሕይወት ሕያዋን ኹነው የሚኖሩ ደመ ነፍስ ከሌለባት ከባሕር ተገኝተዋል፡፡
ዘርዐ ብእሲ፣ ሩካቤ ብእሲ ከሌለባት ከእመቤታችንም ለምእመናን ምክንያተ ሕይወት የሚኾን ያውም ከጐኑ
በፈሰሰ ውሃ ተጠምቀው ምእመናን ሕያዋን የኾኑለት ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷል፡፡
 በዕለተ ዐርብ በኩረ ፍጥረት አዳም ከድንግል መሬት ተገኝቷል፡፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምም
ዳግማዊ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷልና፡፡
 በዕለተ ቀዳሚት ሥጋዊ ዕረፍት ተገኝቷል፡፡ ከእርሷም የመንፈሳውያን ዕረፍት ጌታ ተገኝቷልና ነው /ማቴ.፲፩፡፳፰-
፴/፡፡

እመቤታችንን ከአመሰገኑ ሊቃውንት መካከል፡-


• አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
• አባ ሕርያቆስ
• ቅዱስ ኤፍሬም
• ቅዱስ ያሬድ
• አባ ጽጌ ድንግል

 አምላካችን እግዚአብሔር ለወዳጁ ለአብርሃም “ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፣እባርክሃለሁ፣ ስምህንም አከብረዋለሁ።


ለበረከትም ሁን የሚባርኩህንም እባርካለሁ፣የሚረግሙህንም እረግማለሁ የምድር ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።ዘፍ
፲፪፥፩-፫።

ገጽ 20
፬.፬.፫. የእመቤታችን ቃል ኪዳን አማላጅነት እና መታሰቢያ (ዝክር)
በዚህ ክፍለ ትምህርት ሦስት ዓበይት ርዕሶችን ይዞ እንመለከታለን እነርሱም
ሀ. የእመቤታችን ቃል ኪዳን
ለ. የእመቤታችን አማላጅነት
ሐ. በእመቤታችን ስም (ዝክር) መታሰቢያ ማድረግ

ሀ. የእመቤታችን ቃል ኪዳን

 “ቃል ኪዳን” ትርጓሜው ውል ስምምነት መሓላ የሚል ሲሆን በቃል ኪዳን ውስጥ ቃል ኪዳኑን ሰጪ፣ቃል ኪዳኑን
ተቀባይ፣በቃል ኪዳኑ ተጠቃሚ የሚሆኑ እንዳሉ ያስረዳል ይህን ሀሳብ ግልፅ ለማድረግ ቃል ኪዳን ሰጪ አምላካችን
ልዑል እግዚአብሕር ሲሆን ቃል ኪዳኑን ተቀባይ እመቤታችን እና ሌሎችንም በተጋድሎ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙ
ቅዱሳን ናቸው በቃል ኪዳን ተጠቃሚ የሚሆኑት ደግሞ በቅዱሳን በእመብታችን ቃል ኪዳን ይሆንልኛል ብለው
ያመኑ ሁሉ ናቸው ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ።መዝ ፹፰፥፫ እንዲል።
 እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረቱ ቁጣውን በትዕግስቱ በመግታት የሰውን ሕይወት ለዘለዓለሙ
ለመጠበቅ ሲል በመጀመሪያ በስሕተቱ ከተፀፀተው ከአዳም ቀጥሎ በፃድቅነቱ ከጥፋት ውኃ ለመዳን ከቻለው
ከኖህ ከዚያም በእምነቱ በምግባሩ ቀናነት የእግዚአብሔር ወዳጅ ተብሎ ከተሰየመው ከአብርሃም ጋር ለመላው
የሰው ዘር ሁሉ የሚሆን የምሕረትና የበረከት ቃል ኪዳን ገብቷል።ዘፍ ፱፥፲፩-፲፯ ፣ ዘፍ ፲፪፥፩።
 ከዘመነ ብሉይና ከዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን መካከል ከፍተኛው ፀጋና ክብር የተሰጠውም የአምላክ እናት ለሆነችውና
በዚህም “ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች” እየተባለች ለምትጠራው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለሆነ
ሌሎች የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ቅዱሳንና ቅዱሳት ከተሰጠው ቃል ኪዳን ይልቅ ለእመቤታችን የተሰጠው ከሁሉም
በላይ የበለጠ /የላቀ/ነው።
 “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ”የሚለው የምሕረት ቃል ኪዳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአዳም
የቃል ኪዳን ልጅ መሆኗን የሚያረጋግጥ ሲሆን መስቀሉን በሞቱ አዳምን ለማዳን ከአዳም የልጅ ልጅ የተወለደው
መሢህ ኢየሱስ ክርስቶስ በልደቱ በሞቱ ዓመተ ኩነኔን በዓመተ ምሕረት ለመተካት አስቀድሞ የገባውን ቃል ኪዳን
ፈፅሞአል።
ስለሆነም ምን ጊዜም ምእመናን ቅድስተ ቅዱሳን ለሆነችው እናቱ የሰጠውን የምሕረት ቃል ኪዳን በማሰብ በምሕረትና
በቸርነቱ ይጎበኛቸው ዘንድ በወላዲተ አምላክ ስም ይማፀናሉ::

• በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ


• እመቤታችን ሆይ ወደ እኛ ተመልከች የልጅሽ ቸርነት ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ
• ቅድስት ሆይ ለምኝልን
• ስለ እናቱ ስለ ወላዲተ አምላክ ብሎ በቸርነቱ ከመዓቱ ይሠውረን እያልን እንማጸናለን የተሰጣትን ኪዳን መማፀኛ
እናደርጋለን።

ለ. የእመቤታችን አማላጅነት
 የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ በልብ ወለድ የሚነገር
ሳይሆን መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው።መዝ ፵፬፥፱። “ንግስቲቱ ወርቅ ዘቦ ግምጃ ደርባ እና ተጎናጽፋ በቀኝህ ትቆማለች
በማለት ተናገረ ትቆማለች ማለቱ ለአማላጅነት ነው።ምዕመናን ምግባር ጎድሎባቸው በልጇ ፊት የሞት ሞት
የሲኦል ፍርድ እንዳይፈረድባቸው ልጄ ማርልኝ የገባህልኝን ቃል ኪዳን አስብ እያለች በቀደመ ልመናዋ
የምታሰማራቸው (የምታማልዳቸው) መሆኑን መናገሩ ነው።
 የእመቤታችንም ሆነ የቅዱሳን ምልጃ የታዘዘውና የተፈቀደው (ያስፈለገው) እግዚአብሔር ከኅጥአን ይልቅ
የፃድቃን ፀሎት የበለጠ ስለሚሰማ ነው። የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ፃድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው
ናቸው።መዝ ፴፫፥፲፭።ተብሎ ተፅፎአል አማላጅነት የእግዚአብሔር የቸርነት ስጦታ ነው::ምክንያቱም ምግባራቸው
የደከመና ፀሎታቸው እንደርሱ ፈቃድ ያልሆኑ ተነሳሕያን ኃጥአን የእርሱን ፈቃድ በሚያውቁ እና በሚፈፅሙ
ገጽ 21
በምግባር በበለፀጉ ቅዱሳን ይልቁንም በእናቱ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በኩል እንዲረዱ ማድረግ
የቸርነቱ መገለጫ ነው።
 ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የምእመናን ሁሉ “እናት” ሁና መሰጠቷን ቅዱስ ወንጌል ምስክር
ሆኗል።ዮሐ፲፱፥፳፮። የእናት አማላጅ ደግሞ አያሳፍርም :: ምክንያቱም የሰራኘታዋ መበለት ልጅ በሞተባት ጊዜ
ለእግዚአብሔር ሰው ለኤልያስ ነግራ (አማልዳ) ከሞት እንዲነሳ አደረገች።፩ነገ ፲፯፥፲፯-፳፬።
 ሌሎችም ብዙ እናቶች ለልጆቻቸው ብዙ ነገር አድርገዋል ርብቃ ለያዕቆብ በጥበብ የአባቱን በረከት
አሰጥታዋለች።ዘፍ ፳፭፥
 ከነቢያት ወገን የሆነች ሴት ባሏ በዕዳ የተበደረውን ሳይከፍል ቢሞት ልጆቿ በባርነት እንዳይያዙባት ለነቢየ
እግዚአብሔር ለኤልሳዕ ነግራ ጥቂቱን ዘይት አበርክቶላት ያንን ሽጣ ዕዳዋን ከፋላ ልጆቿን ከባርነት ነፃ
አውጥታለች ፪ነገ ፬፥፳፭።
 በከነዓን ትኖር የነበረችው ሴትም ልጇ እንድትፈወስላት ለጌታችን ነግራ ለዚያውም ጌታችን “በውሻ” መስሏት ግን
በትህትና ቃል “ውሾችም ከጌታቸው ማዕድ የሚወድቀውን ፍራፋሬ ይመገባሉ::” በማለት የሚያራራ የልመና ቃል
አቅርባ ልጇ እንድትፈወስላት ሆናለች።አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው እንደ እምነትሽ ይደረግልሽ ባላት ጊዜ ልጇ
ተፈወሰች።እንዲል ማቴ ፲፭

ስለዚህ ከእንተም የምትበልጥ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምንም ምሳሌ የማይገኝላት እመቤታችን
ታማልደናለችና በህይወታችን በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ ልንጠቀም ያስፈልጋል::በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት ልጅዋ መድኀኔዓለም
ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦ የመጀመሪውን ተአምር ያደረገው በእመቤታችን አማላጅነት ነው።ዮሐ ፪፥፩-
፲፩። ውሃ ጣዕም መልክ የለውም በእመቤታችን አማላጅነት ግን ወይን ሆኖ መልክ ጣዕም አመጣ እንደዚሁ ሁሉ የክርስትና
መልክ የክርስትና ጣዕም በህይወታችን እንዲኖር የእመቤታችን ምልጃ ወሳኝ ነገር መሆኑን የዚህ ክፍለ ንባብ ታሪክ
ያስረዳናል።

በቤተ ክርስቲያናችን እምነት እና ትምህርት ድንግል ማርያም ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ከስመ ሥላሴ ቀጥሎ ስሟ
የሚጠራ ስለሆነ ታማልዳለች ብለን ማመናችን ቢያንስ እንጂ ሊበዛ አይችልም።
• እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁሉ ቃል ኪዳናቸውን በመጠበቅ ከእነርሱ ጋር ለዘለዓለም ይኖራልና (መዝ
፹፰፥፫።)የማማለድ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።
• ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻልና አትፍሪ ብሎ መልአኩ በክብር እንዳበሰራት
እንረዳለን።ሉቃ፩፥፳፰-፴። “ሞገስ” የሚለው ቃል ባለሟልነት፣ ክብር፣ ተሰሚነት፣ ማማለድ፣ ማስታረቅ
የሚሉትን ያብራራል:: ይህ ሁሉ ለእመቤታችን የተሰጠ ፀጋ ነው።
እንግዲህ ከብዙው በጥቂቱ ስለ እመቤታችን አማላጅነት ለመግቢያ ያህል ከላይ የተዘረዘሩትን ከተመለከትን ትልቁና
ዋነኛው ነገር በዕለት ተዕለት ኑሮአችን በአጠቃላይ በህይወታችን በእመቤታችን አማላጅነት የበለጠ ተጠቃሚዎች ለመሆን
ልንተጋ ያስፈልጋል።አባቶቻችን በብሒላቸው የእናት አማላጅ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ ሲሆን በውድ አለበለዚያ
በግድ ይላሉ እና በእመቤታችን አማላጅነት የልጇ ቸርነት እንዲደረግልን ልንተጋ ያስፈልጋል።

ሐ. በእመቤታችን ስም (ዝክር) መታሰቢያ ማድረግ


በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የክብር መገለጫ ከሆኑት ነገሮች
መካከል በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ሥም ዝክር መዘከር ነው:: “ዝክር” ትርጓሜው መታሰቢያ ማለት ሲሆን
ይህ ዘለዓለማዊ መታሰቢያ ለወዳጆቹ ለቅዱሳን ይልቁንም ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም እንዲደረግ የፈቀደ
አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ነው። “እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል
ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላል::በቤቴና በቅጥር ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ
መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ ኢሳ ፶፮፥፬ እና ፭ እንዲል።
ጌታችንም በቅዱስ ወንጌል “ፃድቅን በፃድቅ ስም የተቀበለ የፃድቁን ዋጋ ያገኛል እውነት እላችኋለሁ በቀደ መዝሙሩ
ስም ቀዝቃዛ ፅዋ ውሃ የሰጠ ዋጋው አይጠፋበትም” ማቴ ፲፥፵፩ :: ብሎ እንደተናገረ በፃድቃን በቅዱሳን ስም የተመፀወተ
(የተሰጠ) የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ዋጋ የሚያሰጥ ከሆነ የፃድቃን የቅዱሳንን አምላክ የወለደች የእመቤታችንን ስም ለሚጠራ
የሚመፀውትማ የበለጠ ዋጋ ይሰጠዋል ማለት ዋጋው አይጠፋበትም።

ገጽ 22
፬.፬.፬.የእመቤታችን በዓላት

በዓል ማለት የአንድ መንፈሳዊ ነገር መታሰቢያ ማለት ነዉ፡፡ የፃድቅ ሰዉ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል በማለት ነቢዩ
ዳዊት ገልፆታል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት በመቀጠል የቅድስት ድንግል
ማርያም በዓላት ታከብራለች፡፡ እነርሱም በወርና በዓመት በዓላት የተከፈሉ /የተለያዩ/ ናቸዉ፡፡
ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በተአምረ ማርያም መቅድም እንደተጻፈ በሕግ የተወሰኑ ፴፫ በዓላት
አሏት::እነዚህን በዓላት ምክንያት አድርገን በስሟ የተራበ ልናበላ የተጠማ ልናጠጣ የታረዘ ልናለብስ የተጨነቀ ልናረጋጋ
ለቤተ ክርስቲያን ዕጣን ጧፍ፣ዘቢብ የተለያዩ ንዋየ ቅድሳት ልንሰጥ በአጠቃላይ በጎ ሥራ ልንሰራ ያስፈልጋል:: ይህንን በጎ
ሥራችንን ወደ ልጇ አቅርባ የኃጢአት ሥርየት ታሰጠናለች:በኋላም እረፍት መንግስተ ሰማያት ታኖረናለች።
ጌታችን በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ብላል “ምሳ ወይ እራት ባደረግህ ጊዜ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ
ብድራትህንም እንዳይመልሱልህ ወዳጆችህና ወንድምችህን ዘመዶችህንም ባለጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ ነገር ግን
ግበዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ
ትሆናለህ በፃድቃን ትንሣኤ ይመለስልሀልና።”ሉቃ ፲፬፥፲፪-፲፬።እንዲል።

የወር በዓላት በየወሩ በ፳፩ ቀን የሚከበረዉ የእመቤታችን በዓላት በድምሩ ፲፪ ናቸዉ፡፡ ከመስከረም እስከ ነሐሴ ማለት
ነዉ፡፡
በአመት አንድ ጊዜ በታላቅ ድምቀት የሚከበሩት በዓላት ደግሞ የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
 ፅንሰታ ለማርያም ---------------------------------- ነሐሴ ፯ ቀን
 ልደታ ለማርያም ----------------------------------- ግንቦት ፩ ቀን
 በአታ ለማርያም------------------------------------ ታህሳስ ፫ ቀን
 ኪዳነ ምሕረት-------------------------------------- የካቲት ፲፮ ቀን
 አስተርእዮ ማርያም(የእመቤታችን ዕረፍት)------------- ጥር ፳፩ ቀን
 ፍልሰታ ለማርያም ----------------------------------- ነሐሴ ፲፮ ቀን

ምዕራፍ አምስት (፭)


፭. እመቤታችን በአበው ቀደምት የተመሰለላት ምሳሌ እና እመቤታችን በቅዱሳን
ነቢያት የተነገረላት ትንቢትና እመቤታችን በሊቃውንት ትርጓሜ

፭.፩ ወላዲተ አምላክ በዘመነ አበው/በሕገ ልቦና/

ሀ. የመጀመሪያቱ መሬት(ምድር) ዘፍ ፩÷፲፩


“እግዚአብሔርም ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን
የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፡፡ እንዲህም ሆነ ምድርም ዘርን የሚሠጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ አበቀለች ”
ዘፍ ፩÷፲፩
 የመጀመሪያይቱ መሬት ለሰዉ ህይወት የሚሆነዉን ፍሬ ያበቀለችዉ ምንም ዓይነት ዘር ሳይዘራባት በእግዚአብሔር
ቃል ብስራት ምክንያት ብቻ ነዉ፡፡
 ድንግል ማርያምም ክረስቶስን የወለደችዉ ያለ ዘርዓ ብዕሲ በመልአኩ ቃል ነዉ፡፡
 አዳም የተገኝዉ ከኅቱም ምድር /ያለ አባት ያለ እናት/ ነዉ፡፡
 ወልደ እግዚአብሔርም ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደተገኝ ሰዉ የሆነዉም በሁለት ወገን ድንግል
ከሆነች ከእመቤታችን ያለአባት ነዉ፡፡
 እመቤታችን በመጀመሪያይቱ ምድር ብትመሰልም ከምድሪቱ ትበልጣለች፡፡ ምክንያቱም፡-
 ከምድሪቱ የተገኘው ምግበ ሥጋ ሲሆን፣ ከእመቤታችን የተገኘዉ ግን ለመንግስተ ሰማያት የሚያበቃ
ምግበ ህይወት ምግበ ነፍስ ነዉ፡፡
ለ. የአቤል ደግነት፡፡ (ዘፍ ፬÷፬)
 እግዚአብሔር የመረጣት ንጽህት ቅድስት ድንግል ማርያም በአቤል ደግነት ትመሠላለች፡፡
ገጽ 23
 እግዚያብሔር የአቤልን መስዋዕት የተቀበለዉ ደግነቱን ተመልክቶ ነዉ፡፡ እመቤታችም የአምላክ እናት ለመሆን
የተመረጠችዉ በደግነቷ ነዉ፡፡ “የአቤል የዋህቱ አንቺ ነሽ” እንዳለ አባ ሕርቆስ

ሐ. የኖኅ መርከብ (ሐመረ ኖኅ)፡፡ ዘፍ ፰÷፩-ፍጻሜ


 ኖኅ በእግዚያብሔር ትዕዛዝ ሊመጣ ካለዉ ጥፋት ለመዳን መርከብን አዘጋጀ፡፡
 ኖኅ የሰራት መርከብ ፫ ከፍል አላት/ነበረት/፡፡
 መርከብ የእመቤታችን፣
 ኖኅ የጌታ፣
 መርከቢቱ ባለ ሦስት ክፍል መሆኗ ለእመቤታችን ንፅሐ ስጋ ንፅሐ ነፍስና ንፅሐ ልቦና/ህሊና/ምሳሌ ነዉ፡፡
 ወደ መርከቢቱ ገብተዉ የዳኑት በእመቤታችን ቃል ኪዳን፣ አማላጅነት አምነዉ ከመከራ ሥጋወነፍስ
ለዳኑት ምሳሌ ነዉ፡፡
 ከመርከቢቱ በዉጭ በኩል የቀሩት የከሃድያንና የመናፍቃን ምሳሌ ናቸዉ፡፡

መ. ሰላማዊ ርግብ፡፡(ዘፍ ፰÷፰-፲፩)

 ርግብ ሰላም አብሳሪ ነች፡፡


 ርግብ በጥፋት ዉኃ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ማረፊያ በማጣቷ ወደ መርከቢቱ ተመለሰች በ፪ኛ ጊዜ የወይራ
ዝንጣፊ ይዛ በመመለስ በምድር ላይ ሠላም መሆኑን የጥፋት ዉኃ መድረቁን አበሰረች ፡፡
 ኖኅና ቤተሰቡም ከነበሩበት ጭንቀት አረፋ፡፡
 ኖኅና ቤተሰቦቹ የምዕመናን
 የጥፋት ዉኃ የኃጢአት
 ርግብ የእመቤታችን
 የወይራ ዝንጣፊ ከእመቤታችን የተወለደዉ በጌታችን የተገኘዉን ሠላም ያመለክታል፡፡
“ሠላማዊት ርግብ ድንግል ማርያም ሆይ ሠላምታ ይገባሻል”፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
“እህቴ ወዳጄ ርግቤ መደምደሚያዬ” መኃ ፭÷፪

ሠ. ቀስተ ደመና፡- (ዘፍ ፱÷፰-፲፭)

 ቀስተ ደመናዉ የይቅርታ ምልክት ነዉ፡፡ ኖኅ የተሰጠዉን የይቅርታ ምልክት በእምነት ተቀብሎ ከመከራ ሥጋ
መዳኑ አዳም ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔርና በሰዉ ዘር መካከል የነበረዉን የጥል ግድግዳ እንዲፈርስና
ዓለም ዳግመኛ ጥፋት የሌለበትን ተስፋ መንግስተ ሰማያት ለማግኘት ምልክት ሆና በራሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ
ለተሠጠችዉ ለወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግለ ማርያም ምሳሌ ነበር፡፡
 አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መዉለዷ የመዳናችን ምልክት ናትና፡፡ ኢሳ ፯÷፲፬

ረ. ዕፀ ሳቤቅ (ዘፍ ፳፪÷፱-፲፫)

“አብርሃምም ዓይኑን አነሳ በኋላም እንሆ አንድ በግ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ አብርሃምም ሔዶ በጉንም ወሰደዉ
በልጁም ፋንታ መስዋዕት አድርጎ ሰዋዉ፡፡ ዘፍ ፳፪÷፱-፲፫ እንዲል ይህም ምሳሌ ነበረ፡፡
ምሳሌዉም፡-
 ይስሐቅ የአዳምኛ የዘሩ፣
 በጉ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ፣
 ሰይፋ የስልጣነ እግዚአብሔር
 ዕፀ ሳቤቅ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
 በጉ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ በዱር መገኘቱ ከድንግል ተወልዶ በሥጋ በመገለጡ በበረት ተኝቶ የመገኘቱ ምሳሌ ነዉ፡፡

ሰ. የያዕቆብ መሰላል:: (ዘፍ ፳፰÷፲-፳)

ገጽ 24
“ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ ፡፡ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አረፈ
በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚህ ስፋራ ተኛ፡፡ ሕልምም አለመ እንሆ መሠላል
በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደረሶ እነሆም እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር ፡፡ ” ዘፍ ፳፰÷፲-፳

 ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራዕይ ያያት መሠላል የእመቤታችን


 የተንተራሰዉ ድንጋይ ትንቢተ ነቢያት (እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ፀንታ ለመገኘቷ ምሳል ነዉ፡፡)
 መሠላል ከምድር እስከ ሠማይ ደርሶ ማየቱ በሰዉና በእግዚአብሔር መካከል የነበረዉ ጥላቻ ተወግዶ
ምድራዊያን ሠዎችና ሰማያዊያን መላዕክት እግዚአብሔር ወልድ ስጋዋን ለመዋሐድ የወረደና ያደረባት የቅድስት
ድንግል ማርያም ምሳሌ ነዉ፡፡

የያዕቆብ ምሰጢር፡፡ ዘፍ ፳፱÷፩-፲፩

ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳዉ ጋር ተጣልቶ ወደ አጎቱ ወደ ላባ በሚሄድበት ወቅት መንገድ ላይ መንጋቸዉን እየጠበቁ
ከዉኃዉ አፍ ላይ የተገጠመዉን ድንጋይ የሚያነሳላቸዉ አጥተዉ በችግር ላይ የነበሩት እረኞችን እንደ አገኘና ራሔል
ከመጣች በኋላ ያን ታላቅ ድንጋይ ከጉድጓድ ዉኃ አፍ ላይ አንስቶ በጎቻቸዉን እንደ አጠጣላቸዉ ቅዱስ መፅሐፍ
ይናገራል፡፡ ዘፍ ፳፱÷፩-፲፩

ምስጢራዊ ምሳሌዉ፡-
 ዉኃ - የማየ ሕይወት
 ድንጋይ- የመርገም
 አባግዕ/በጎች/- የምዕመናን
 ኖሎት/እረኞች/-የነቢያት
 ራሔል- የእመቤታችን
 ያዕቆብ-የክርስቶስ
 እረኞች በጎቻቸዉን ለማጠጣት ድንጋዩን ማነሳት አለመቻላቸዉ ነቢያትም በትምህርታቸዉ በተጋድሏቸዉ መርገምን
አርቀዉ ማየ ህይወት ለማጠጣት አልቻሉም፡፡
 እረኞች ራሔል እስክትመጣ ድረስ እንደጠበቁ ሁሉ ነቢያትም በትንቢታቸዉ የእመቤታችንን መምጣት ይጠባበቁ
ነበር፡፡
 ራሔል በመጣች ጊዜ ብዙ እረኞች ማንሳት ያልቻሉትን ድንጋይ ያዕቆብ ብቻዉን አንስቶ በጎቹ እንዲጠጡ አደረገ፡፡
 እመቤታችን ከተወለደች በኋላም ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነቢያት በተጋድሎአቸዉ ሊያርቁት
ያልቻሉትን መርገም በፍቃዱ በተቀበለዉ ፀዋትወ መከራ አራቀዉ:: አባግፅ ምእመናንም ከማየ ህይወት አጠጣ (ዮሐ
፬÷፯)

፭.፪ ወላዲተ አምላክ በዘመነ ኦሪት


ሀ. የሲና ሐመልማል(ዕፀ ጳጦስ) (ዘጸ ፫÷፩-፮)
“ሙሴም የምድያምን ካህን በጎች እየጠበቀ ባለበት ወቅት ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ በጎቹን ነዳ ወደ
እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ እነሆም ቁጥቋጦዉ በእሳት ሲነድ ሐመልማሉም ሳይቃጠል አየ” ዘጸ
፫÷፩-፮
 ሙሴ ያያት ዕፅ የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡
 ሐመልማሉ የትስብእት፣ ነበልባል የመለኮት ምሳሌ ነዉ፡፡ እመቤታችን ጌታችንን ስትፀንስ የመለኮት ባሕርይ
ሳያቃጥላት ትሰብእትና መለኮት በእርሷ ማሕፀን ተዋሕደዋልና ዕፀ ጳጦስ ዘሲና ትባላለች ፡፡ ዘጸ ፫÷፩-፬

ለ. የቃል ኪዳኑ ታቦት፡፡ ዘፀ ፳፭÷፲-፳፪

የቃል ኪዳን ታቦት ከማይነቅዝ እንጨት የተሠራና ከዉስጥም ከዉጭም በወርቅ የተለበጠ መሆኑን ከቅዱሳን መጻሕፍት
እንረዳለን፡፡ ዘፀ ፳፭÷፲-፳፪
 ከማይነቅዝ እንጨት መሰራቱ ዘላለማዊ ቅድስናዋን ያመለክታል፡፤
 በዉጭም በዉስጥም በወርቅ የተለበጠ መሆኑ ደግሞ የእመቤታችንን ክብርና ንፅህና የሚያመለክት ነዉ፡፡
ገጽ 25
 በታቦቱ ላይ ከሠማይ የወረደ መና መቀመጡ በእመቤታችን ማሕፀን በተዋህዶ ሰዉ የሆነዉን አማናዊ መና
መድሃኔ ዓለምን የሚያመለክት ነዉ፡፡
 በታቦቱ ዉስጥ ቃለ እግዚአብሔር የተፃፈበት ፅላተ መኖሩ በማሕፀነ ማርያም ቃለ እግዚአብሔር ለማደሩ ምሳሌ
ነዉ፡፡ ዉዳሴ ማርያም ዘሰንበት

ሐ. በትረ አሮን/የአሮን በትር/፡፡ ዘኁ ፲፯÷፰-፲፩

በኦሪት ዘኁልቁ ፲፯÷፰-፲፩ ላይ የ፲፪ቱ የእስራኤል ነገድ ተወካዮች ከነበሩት በትሮች መካከል የአሮን በትር ብቻ ሳይተክሏት
ተተክላ ዉኃ ሳያጠጧት አቆጥቁጣ ለምልማና አብባ የበሠለ ለዉዝ አፍርታ መገኘቷ ተገልጧል፡፡
 የአሮን በትር የእመቤታችን፤
 ለዉዝ የጌታችን ምሳሌ ነዉ፤
 የአሮን በትር ሳይተክሏትና ዉኃ ሳያጠጧት አብባና አፍርታ እንደተገኘች እመቤታችንም ያለ ዘርዓ ብእሲ
በማይመረመር ምስጢር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና ወልዳለችና፡፡ ዉዳሴ ማርያም ዘእሁድ

መ. የገዴዎን ፀምር፡፡ መ.መሳ ፭÷፴፮-፵

“ጌዴዎንም እግዚአብሔር እንደተናገርህ የአስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደሆነ በአዉድማዉ ላይ የተባዘተ የበግ
ጠጉር አኖራለሁ፡፡ በጠጉሩ ላይ ብቻ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን እንደተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ
እንድታድናቸዉ አዉቃለሁ፡፡
እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት እንዲህ አደረገ በማለት መፅሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ መ.መሳ ፭÷፴፮-፵
 ፀምር የእመቤታችን ፤ጠል የጌታ ምሳሌ ነዉ፡፡
 ጠል በፀምሩ ላይ መዉረዱ ከ፫ቱ አካልnወልድ ከሰማያት ወረደ ከድንግል ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ
በማህፀኗ ማደሩና ሥጋን ተዋህዶ ሰዉ መሆኑን ይጠይቃል፡፡
 ጠል ምድር ላይ አለመዉረዱ ሌሎች ሴቶች የዚህ ታላቅ ክብር አለመብቃታቸዉን የሚያሳይ ነዉ፡፡
 ሁለተኛው ጠል በምድር ላይ ሆኖ በፀምሩ ላይ አልወረደም ይኸዉም በሌሎች ሴቶች ላይ ያለ መርገምና ኃጢአት
ያላረፈባት እመቤታችን ከአንስተ ዓለም የተለየች የተባረከች መሆኗን ያስረዳል ፡፡ እግዚአብሔር ባወቀ ሁለቱንም
ምሳሌዎች በወቅቱ ገለጣቸዉ፡፡

ሠ. ደመና ኤልያስ(የኤልያስ ደመና)፡፡ ፩ነገ ፲፰÷፵፩-፵፫

ነብዩ ኤልያስ ከመምላኬ ጣኦት (ከጣኦት አምላኪዉ አክአብ ጋር በተጣለ ጊዜ ሰማይን ዝናም ለዘር ጠል ለመከር እንዳይሰጥ
ምድርንም የዘሩባትን እንዳታበቅል የተከሉባትን እንዳታፀድቅ አድርጎ ፫አመት ከ፮ ወር በኃይለ ፀሎቱ ለጉሞ ከቆየ በኋላ
ከአክአብ ጋር በተደረገዉ ስምምነት ነቢያተ ሀሴትን አስገድሎ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ በጉልበቱ መካከል በግንባሩ
ተደፍቶ ሲፀልይ እነሆ የሰዉ ልጅ የምታህል ደመና ከባህር ወጣች ብሎ ደቀ መዝመሩ እንደነገረዉና ከጥቂት ቆይታ በኋላ
ብዙ ዝናም እንደዘነበ መጽሐፍ ቅድስ ይነግረናል፡፡ ፩ነገ ፲፰÷፵፩-፵፫
 ይህች ትንሽ ደመና የተባለችዉ የእመቤታችን ምሳሌ ስትሆን
 ዝናም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነዉ፡፡
 ትንሿ ንጽህት ደመና ምድርን ያረካ ዝናም እንደተገኘባት ሁሉ እመቤታችንም ድንግል ማርያም ዝናበ ምህረት
ኢየሱስ ክርስቶስን በመዉለድ ሰላምን ተርቦ ምህረት ቸርነትን ተጠምቶ የነበረዉ የሰዉ ልጅ በበረከተ ሥጋ
ወነፍስ በመጥገቡና በመርካቱ እመቤታችን በደመና ኤልያስ ትመሰላለች፡፡ ዉዳሴ ማርያም ዘማክሰኞ

ረ. የኤልያስ መሰበ ወርቅ፡፡ ፩ነገ ፲፱÷፩-፰


ነቡዩ ኤልያስ ከንጉስ አክአብና ከንግስት ኤቤዛቤል በተጣለ ጊዜ ነፍሱን ለማዳን አንድ ቀን የሚያህል መንገድ ሄዶ በምደረ
በዳ በክትክታ ስር ተኝቶ መልአኩ የተጋገረ እንጎቻና በማስሮ ዉሃ አምጥቶ ሁለት ጊዜ እንደመገበዉና በዚያም ኃይል አግኝቶ
እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ ፵ ቀን ፵ ሊሊት ተጓዘ ፡፡ ፩ነገ ፲፱÷፩-፰
 ኤልያስ የአዳም መሶብ የእመቤታችንን መሳሌዎች ናቸዉ፡፡ የህይወት እንጀራ ኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘዉ በመሶበ
ወርቅ ከተመሰለችዉ ከእመቤታችን ነዉ፡፡ከሠማይ የወደረ እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ዮሐ ፮÷፶፩
 ኤልያስ ዳግመኛ በተመገበዉ ምግብ ኃይል አግኝቶ እስከ እግዚአብሔር ተራራ አስከ ኮሬብ እንደተጓዘ ሁሉ የሰዉ
ልጅም ዳግመኛ በተሠጠዉ የሕይወት ምግብ በሥጋዉና በደሙ ኃይል አግኝቶ ወደ መንገስተ ሰማያት የመግባቱ
ምሳሌ ነዉ፡፡

ገጽ 26
ሰ. የኤልሳዕ ማሰሮ ፪ነገ ፪÷፲፱-፳፩
“የከተማይቱም ሠዎች ኤልሳዕን እነሆ ጌታችን እንደምታያት የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነወ፡፡ ዉኃዉ ግን ክፉ ነዉ፡፡
ምድሪቱም ፍሬዋን ታጨነግፋለች አሉት እርሱም አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ ጨዉም ጨምሩበት አለ፡፡ ያንንም አመጡለት
ዉኃዉ ወደ አለበት ምንጭ ወጥቶ ጨዉ ጣለበትና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ይህን ዉሃ ፈዌሸዋለሁ ከዚህም በኋላ
ሞትና ጭንገፋ አይሆንበትም አለ ኤሌሳዕም እንደተናገረዉ ነገር ዉኃው አስከ ዛሬ ደረሰ ተፈዉሷል ”:: ፪ነገ ፪÷፲፱-፳፩
በዚህ ምሳሌ

 አዲስ ማሰሮ የተባለችዉ እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡


 ያልተነካችና ያልተሰራባት አዲስ ማሰሮ መሆኗ በድንግልና በንፅህናዋ እድፍ ጉድፍ የሌለባት ከጥንት አብሶ የነፃች
የመሆኗ ምሳሌ ነዉ፡፡
 በዉስጧ የነበረዉ ጨዉ ዓለምን በቤዛነቱ ያጣፈጠዉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ፡፡
 መርዝ የኃጢኣት ምሳሌ ነዉ፡፡
 ዉኃዉ ደግሞ አለም ነዉ
 ዉኃዉ መመረዙ ዓለም በኃጢአት ምክንያት ተመርዞ በሰዉ ልጆች ላይ ሁሉ በማህፀን ያሉት ሳይቀሩ በሞት እጅ
በፍርድ ቅጣት ስር ወድቀዉ እንደነበር ሲያመለክት
 ከማሰሮ የተገኘዉ ጨዉ ዉኃዉን መፈወሱ ደግሞ ከድንግል ማርያም የተወለደዉ መድሃኒዓለም ዓለሙን
በደሙ መቀደሱን ሞትን ማጥፋቱን፣ፍርድን ማስወገዱን እና ማዳኑን ያመለክታል፡፡

፭.፫ ወላዲተ አምላክ በትንቢተ ነቢያት


ታላቁ የቤተ ክርሰቲያን አባት አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም “ድንግል ሆይ ነቢያት ትንቢት የተናረጉልሽ ምሳሌ የመሠሉልሽ
አንቺ ነሽ” በማለት ምስጢሩ በአምላካዊ ዕዉቀት የታቀደ በነቢያት የተነገረ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ስለዚህ በዚህ ክፍል ስለ
ድንግል ማርያም የተነገሩ ቃላት ትንቢትን እንመለከታለን፡፡

ሀ. ጽዮንን ክበቡአት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፤ግንቦችዋንም ቁጠሩ፣ በብርታትዋም ልባችሁን አጉሩ፣ አዳራሽዋን
አስቡ፣ለሚመጣዉም ትዉልድ ትነግሩ ዘንድ ፡፡ መዝ ፵፯÷፲፯

 ጽዮን የሚለዉ ቃል ስለ አራት ነገር ተፅፏል፤


 ታቦተ ጽዮን (፪ሳሙ ፮÷፰-፲፭)
 የዳዊት መናገሻ ከተማ (፪ሳሙ፭÷፮-፲)
 ሕዝበ እስራኤል (መዝ ፻፳፭÷፩)
 ኢሩሳሌም ሰማያዊት ፡፡በምስጠር እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ናት፡፡
 ጽዮንን ክበብአት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፡- ማለቱ በአማላጅነቷ፤በረድኤቷ፤በበረከቷ መጠቀምን ያሳያል፡፡
 ግንቦቿና ብርታቷ፡- ማለቱ ምልዕተ ፀጋ (የሁሉም ፀጋዎች ባለቤት መሆኗን በፀጋዋ መጠቀም እንደምንችል
ያሳያል፤
 አዳራሽዋን አስቡ፡- ማለቱ ድንግልናዋን፤ንፅህናዋን፤ብፅዕናዋን፤ቅድስናዋን አስተዉሉ ሲል
 ለሚመጣዉ ትዉልድ ትነገሩ ዘንድ ፡- ማለቱ ትንቢቱ እስኪፈፀም ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንደሚተላለፍ
ያስረዳል፡፡

ለ. ሰዉ እናታችን ፅዮን ይላል በዉስጧም ሰዉ ተወለደ፡፡ መዝ ፹፮÷፭


 ነብዩ ዳዊት ወላዲተ አምላክን እናታችን አላት፡፡ ምክንያቱም እነኋት እናትህ(እናታችሁ እንኋት ተብላ የምትሠጠን
ስለሆነ፡፡(ዮሐ ፲፱÷፳፯)
 እግዚአብሔር ወልድን ሰዉ አለዉ፡፡ በዳዊት ከተማ ጌታችን ተወልዷልና ሉቃ ፪÷፲፩

ሐ. እግዚአብሔር ማደሪያዉን ቀደሰ(ለየ) እግዚአብሔር በመካከልዋ ነዉና አትናወጥም ፤ እግዚአብሔር ፈፅሞ


ይረዳታልና ፡፡ መዝ ፵፭÷፬
 እግዚአብሔር ማደሪያዉን ቀደሰ ፡- የሚለዉ ቃል እመቤታችንን ለአምላካነቱ ማደሪያ ትሆነዉ ዘንድ የመረጠ
እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን የሚያስረዳ ነዉ፡፡

ገጽ 27
 እግዚአብሔር በመካከልዋ ነዉና አትናወጥም ፡- የሚለዉ እግዚአብሔር ከሥጋዋ ሥ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ከመፀነሱ
በፊት፣ በፀነሰች ጊዜ ፣ከተፀነሰ በኋላ ከመወለዱ በፊት፣ በተወለደም ጊዜ ከተወለደም በኋላ በድንግልና ፍፅምት
ጽንእት መሆኗን ይጠይቃል፡፡
 እግዚአብሔር ፈፅሞ ይረዳታል፡- ይህ ሁሉ አምላካዊ ፈቃድ እስከ ዘላለሙ ከእመቤታችን አለመለየቱን
ያረጋግጣል፡፡ ምክንያቱም፡-

 ሦስቱ አካላት ስለ ሦስት ነገሮች አድረዉባታል፡-


 እግዚአብሔር አብ ለአጽንኦ/ለማጽናት/ ያለ እግዚአብሔር ፀጋ የሚቻል የለምና፡፡
 እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ለመዋሐድ
 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ
መ. የወደደዉን የፅዮንን ተራራ መቅደሱን እንደ አርያም ሰራ ለዘላለም በምድር ዉስጥ መሠረታት፡፡
መዝ ፸፯÷፷፰

 የወደደዉን የፅዮንን ተራራ የተባለች ወላዲተ አምላክ ናት፡፡


 መቅደሱን እነደ አርያም ሰራ ያለዉም አርያም ሥሉስ ቅድስ የሚገለጡበት የተለየ የክብር ቦታ እንደሆነ ሁሉ
በእመቤታችንምሥሉስ ቅደስ የተገለጡባት ዳግማዊት አርያም ዘበምድር ናት፡፡
 ለዘለዓለም በምድር ላይ መሰረታት የተባለዉም እመቤታችንን በንፅህና፤በቅደስና ፈጠራት ድንግልናዋና
አማላጅነቷም ዘለዓለማዊ ነዉ ማለት ነዉ፡፡

ሠ. እግዚአብሔር ፅዮንን መርጦአታል ማደሪያዉም ትሆነዉ ዘንድ ወደአታልና ይህች ለዘለዓለም ማደሪያዬ
ናትና፡፡ መዝ ፻፴፩÷፲፫
 ይህ ቃለ ትንቢት በወቅቱ የተነገረዉ ለኢየሩሳሌም ነዉ፡፡ የትንቢቱ ፍጻሜ ግን ልዑል እግዚአብሔር ከሴቶች ሁሉ
ለይቶ እመቤታችንን የመረጣት መሆኑንና ማደሪያዉም ትሆነዉ ዘንድ የወደዳት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነዉ፡፡
 ሲያጠቃልለዉም ይህች የዘለዓለም ማደሪያዬ ናት ብሎ ነዉ፡፡ እግዚአብሔርም ለዘለዓለም ከእርሷ ጋር ነዉና
የእመቤታችን ድንግልና ፤ቅድስት እና ብፅዕና ዘለዓለማዊ ነዉ፡፡

ረ. ከነብዩ ዳዊት በተጨማሪ ነብዩ ኢሳይያስ እንደሚከተለዉ ገልፆታል፡፡


“እግዚአብሔር በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶ ነበር ፡፡” ኢሳ ፮÷፩
በማለት ራዕዩን ይገልፃል፡፡
 ረጅምና ከፍ ያለ ዙፋን የተባለችዉ እመቤታችን ስትሆን
 የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር የተባለዉም በመለኮታዊ ክብሩ ከአባቱ ዕሪና (እኩልነት ) ሳይጎድልና
ሳይጨመር እግዚአብሔር ወልድ በማኅፀነ ድንግል ማደሩንና ረቂቁ አምላክ በገሃድ መገለጡን ያመለክታል፡፡

ሰ. በሌላ በኩልም ነብዩ ኢሳይያስ ስለ ድንግል ማርያም ምልክትነት ሲናገር “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት
ይሠጣችኃል እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች :: ” ኢሳ ፯÷፲፬
በማለት አስረግጧል፡፡
ሸ. ከእሰይ ሥር በትር ትወጣለች አበባዋም ከእርስዋ ይወጣል::” ኢሳ ፲፩÷፩
 የትንቢቱ ዓላማ እግዚአብሔር ሠዉ የመሆኑን ምስጢር መግለፅ ነዉ፡፡
 ከንጉሱ ከዳዊት ዘር የምትገኘዉ አባበ/እመቤታችን/ከእርሷ የሚወለደዉ ፍሬ / መድኃኔአለም በቅድስ ሥጋዉ
በቅዱስ ደሙ ዓለሙን የሚያድንበት ምስጢረ ሥጋዌ መሆኑን ነብዩ ለማስረዳት በትርና አበባ ብሎአቸዋል፡፡
 አበባን ያስገኘች በትር፤ፍሬን ያስገኛት አበባ ናትና ፡፡

ቀ. “ የአስጨናቂዎችሽ ልጆች አንገታቸዉን ደፍተዉ ወደ አንቺ ይመጣሉ፡፡ የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ


ይሰግዳሉ ፡፡ የእግዚአብሔርም ከተማ የእስራኤል ቅድስ የሆንሽ ፅዮን ይሉሻል ፡፡” ኢሳ ፷÷፲፬

 እዚህ ላይ ነብዩ በመጀመሪያ በኢየሩሳሌም ዙሪያ መሽገዉ ያስችግሩ ለነበሩ ነገስተ አህዛብ ማስጠንቀቂያ ቢሆንም
ፍፃሜዉ ግን፡

ገጽ 28
 ከአዳም እስከ ክርስቶስ በሲኦል ነፍሳትን ያስጨነቁ የነበሩ አጋንንት በመስቀሉ ስር መዉደቃቸዉን ያመለክታል፡፡
ምክንያቱም በመስቀሉ ላይ ዉሎ አጋንንትን በመስቀሉ የቀጠቀጠዉ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ከእመቤታችን
የነሳዉ ነዉ፡፡
 ለፀሐፍት ፈሪሳዊያን
 ለመናፍቃን
“የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማልላሉና:: ” መዝ ፵፬÷፲፪

በ. ስለ እመቤታችን ድንግልና ቅድስና ክብር ከተናገሩ ነቢይ መካከል ነብዩ ሕዝቅኤል ተጠቃሽ ነዉ፡፡
ቃሉም እንዲህ ይላል፡- “ወደ ምስራቅም ወደ ሚመለከተዉ በስተዉም ወደ አለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ
ተዘግቶም ነበር እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይሆራል አንጂ አይከፈትም ሰዉም አይገባበትም የአስራኤል
አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፡፡” ሕዝ ፵፬÷፩-፲፪
ነቢዩ፡-
 ምስራቅ ያላት እመቤታችንን ነዉ፡፡
 መቅደስ ያለዉ ማኅፀንዋን ነዉ፡፡
 የተዘጋዉ በር ያላት ማኅተመ ድንግልናዋን ለመግለፅ ነዉ፡፡
 ተዘግቶ ነበር የሚለዉ ቃል ጌታን ከመዉለዷ በፊት ድንግል እንደነበረች
 ተዘግቶ ይኖራል አይከፈትም የሚለዉ ቃልም መድኃኔዓለም ክርስቶስን ከወለደች በኋላ ዘላለማዊ ድንግል
መሆኗን ያስረዳል፡፡
 ሰዉም አይገባበትም የእስራኤል አምልክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና የሚለዉም ወላዲተ አምላክ እግዚአብሔር
ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግልና ከወለደች በኋላ በድንግልና እንደምትኖርና ከእርሱ በቀር ሌላ ልጅ አንደሌላት
በማያሻማ ቋንቋ ያረጋገጠዉ ትንቢታዊ መነፅር ነዉ፡፡

ተ. ከነቢያተ እግዚአብሔር አንዱ የሆነዉ ነብዩ ዳንኤልም “ … እጅ ሳይነካዉ ድንጋይ ከተራራዉ ተፈንቅሎ
ከብረትና ከሸክላ የሆነዉን ምስሉን ሲመታና ሲፈጭ አየሁ ፡፡ በዚያን ጊዜም ብረቱ፤ ሸክላዉ፤ናሡና ብሩ
ወርቁም አንድነት ተፈጨ …ምስሉንም የመታ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈፅሞ ሞላ፡፡” ዳን ፪ ÷፴፩-
፴፭ በማለት ተናግሯል፡፡
 ይህ የሚያሳየዉ በወቅቱ ኃያል የነበረዉን ምድራዊ መንግስት የናቡከደነጾርን መንኮታኮት ነበር፡፡ ዋናዉ የትንቢት
/የራዕዩ/ ምስጢር ግን፡-
 በተራራ ተመሰለችዉ ወላዲተ አምላክ በድንጋይ የተመሰለዉ ክርስቶስ በመወለዱ በምድር ላይ በሰዉ ልቦና
ሠልጥነዉ የነበሩት አጋንንትን በመስቀሉ ላይ በፈፀመዉ ቤዛነት የቀጠቀጣቸዉና ያደቀቃቸዉ መሆኑን
የሚያለመክት ነዉ፡፡
 ድንጋይ ላይ የወደቀም ሆነ ድንጋይ የወደቀበት ዕድሉ መሰበር እንደሆነ :- በእግዚአብሔር ወልድ የባሕርይ
አምላክነት የማያምንም ሆነ እርሷን ወላዲተ አምላክ የማይል ዕጣዉ አንድ መሆኑንም ያመለክታል፡፡ መዝ
፻፲፯÷፳፪ ፤ ማቴ ፳፩÷ ፵፬ ፤፩ቆሮ፲÷፬ ተመልከት፡፡

ቸ. በነቢዩ ሚክያስም ወላዲተ አምላክ እንደሚከተለዉ ተነግራለች፤


“አንቺም ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ አእላፍ መካከል ትሆኝ ዘንድ ታነሽ ነሽ፡፡ ከአንቺ ግን አወጣጡ
ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል ፡፡ ” ሚክ ፭÷፪
ቤተልሔም ኤፍራታ ከሌሎች ክፍላተ ሀገር ያነሰች ብትሆንም በሌሎች ክፍላተ ሀገር ያልተፈጸመ ገቢረ ተአምር

በልደተ ክርስቶስ ጊዜ አይታለች፡፡
 እመቤታችንም “ይህ ነገር እንደምን ይንልኛል” በማለት ታናሽነቷን በትህትና እየገለፀች ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለአለም
የሆነዉን ክርስቶስን ለመዉለድ የበቃች መሆኑን አመለከተ፡፡
 ኤፍራታ ማለት ጸዋሪተ ፍሬ/ፍሬን የተሸከመች /ማለት ሲሆን እዉነተኛ ፍሬ ህይወት የተገኘባት ዕፀ ህይወት
ወለዲተ አምላክ ናትና፡፡
ቤተልሔም ማለትም ቤተ ህብስት ቤተ እንጀራ ማለት ነዉ፡፡ እመቤታችንም “እኔ እዉነተኛ እንጀራ ነኝ” የለጌታ ያስገኘች
እዉነተኛ ቤተልሔም ናት፡፡

ገጽ 29
፭. ፬ እመቤታችን በሊቃውንት ትርጓሜ
ንባብ ይገድላል ትርጓሜ ያድናል እንደተባለዉ አበዉ ለቃዉንት ስለ እመቤታችን የተናገሩትን ደረቅ ምንባባት
በትርጓሜአቸዉ ጠርበዉና ቀርፀዉ ህይወትን የሚሠጡ አድርገዋቸዋል፡፡ በመሆኑም በተሠጣቸዉ ሀብተ ዉዳሴ
እንደሚከተለዉ በምስክርነት እማኝነታቸዉን አስቀምጠዋል፡፡

ሀ. አባ መቃርስ ፡-

የእስክንድርያ ሊቀ ዻዻስ ሲሆን ስለእመቤታችን ሲናገር፡- “ከማይመረመር ልደቱ በኋላ ማኀተመ ደንግልናዋ አልተለወጠም
ስለዚህ ወላዲተ አምላክ እንደሆነች አመንን ህፃን ሆኖ ተወለደ በጨርቅም ተጠቀለለ በጎል ተጣለ፡፡ ይህን ጊዜ ተገኘ
የማይባል ከአብ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር የነበረ ያለ ለዘለዓለም እርሱ ዘመን ተቆጠረለት፣ ጊዜ ተነገረለት እርሱ አንድ ወልድ
ሲሆን በየጥቂቱ አደገ” ኢሳ ፱÷፮-፯ ፤ ዕብ ፲፫÷፰፣ ሃይማኖተ አበዉ ዘመቃርስ ፺፰÷፲፫(ገፅ ፬፻፴፯)
ለ. ቅድስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡-
የቁስጥንጥንያ ሊቀ ዻዻስ ሲሆን ስለእመቤታችን ሲናገር “የማይወሰን እግዚአብሔር በድንግል ማኅፀን እንደተወሰነ ማን
አየ? ማን ሰማ? ሰማያት ለማይወስኑት ለእርሱ የድንግል ማኅፅን አልጠበበዉም ባሕርዩ ሳይለወጥ ከእርስዋ ተወለደ እንጂ”
(አበዉ ምዕራፍ ፷፮ ክፍል ፭) (ገፅ ፪፻፴፮ / እያለ አመሠገነ፡፡

ሐ. ቅደስ ቴዎዶጦስ የዕንቆራ ኤዺሳቆዾስ፡-


“ዛሬ እግዚአብሔር ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ታየ፡፡ ድንግልም እንደ ቀድሞዋ በድንግልና ፀንታ ኖረች እናትም
ተባለች ህይወትን የሚለዉጥ በድንግል ተፈትሖ ማኅፀንን አላመጣም” ( ሃይማኖተ አበዉ ገፅ ፻፸፪ ም. ፶፫÷፫)

ሠ. ቅድስ ሳዊሮስ የአንፆኪያ ሊቀ ዻዻስ፡-


“አምላክን የወለደች ማርያም ለዘለዓለም ድንግል እንደሆነች በመዉለዷም የማይመረመር ድንቅ እንደሆነ
ከወለደችዉም በኋላ በድንግልና ፀንታ እነደኖረች አስረዳ” (ሃይማኖተ አበዉ ም ፸፯÷፲፬) ገፅ ፫፻፹፭
ረ. የእስክንድሪያዉ ሊቀዻዻስ ቅዱስ ቄርሎስ፡-
“ዳግመኛም በኋላ ዘመን ቅድስት ድንግል እርሱን በሥጋ ወለደችዉ ስለ እኛም ሰዉ የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችዉ
ስለዚህም ቅድስት ድንግልን ወላዲተ አምላክ እንላታለን” (ሃይማኖተ አበዉ ም ፸፰÷፱) ገፅ ፫፻፭

ሰ. የሶሪያዉ ቅዱስ ኤፍሬም፡-


 “ንፅህት ድንግል በእዉነት አምላክን የወለደች እንዶሆነች እንናገራለን እግዚአብሔር ቃል ከእርስዋ ሥጋን
ተዋህዷልና” (ሃይማኖተ አበዉ ም ፹፮÷፰) ገፅ ፫፻፸፪
 “የድንግል ገናነቷን ሊናገሩት አይቻልም ጌታ መርጧታልና (ዉዳሴማርያም ዘሰሉስ)
 “ከቅዱሳን ክብር የማርያም ከብር ይበልጣል የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና” (ዉዳሴ ማርያም ዘዕቡዕ)
 “የመመኪያችን ዘዉድ ፤የደህንነታችን መጀመሪያ የንፅህናችን መሠረት” (ዉዳሴ ማርያም ለሰሉስ)
ሸ. አባ ሕርያቆስ የብሒንሳዉ ኤዺስ ቆዾስ
“የቀደሙት ሰዎች እነ አብርሃም ከሞት ወደ ህይወት ከሲኦል ወደ ገነት የተሸጋገሩብሽ ድልድይ አንቺ ነሽ ከምድር እስከ
ሰማይ ደርሳ ያለች መሠላል አንቺ ነሽ” (ቅዳሴ ማር ገፅ ፷፰)

ቀ. ሊቁ ጎርጎርዮስ፡
እመቤታችን በእዉነት አምላከ ቃልን የወለደች እንደሆነች ሰው ቢኖር ዉጉዝ ይሁን ከእግዚአብሔርም የራቀ ነዉ በማለት
አባታዊ ምክሩን ሰጥቷል፡፡ ሃይማኖተ አበው ገጽ ፬፻፴፬ ም. ፻፯

ገጽ 30
ዋቢ መጽሐፍት

 ነገረ ማርያም አዲሱ የግቢ ጉባኤ ኮርስ ማስተማሪያ/ማኅበረ ቅዱሳን-2010ዓ.ም/


 ነገረ ማርያም ነባሩ የግቢ ጉባኤ ኮርስ ማስተማሪያ/ማኅበረ ቅዱሳን - 2006ዓ.ም/
 www.betedejene.com/ነገረ ማርያም፡- ከክፍል ፩-፳፬/
 ሐውልተ ስምዕ/መምህር ኃይለማርያም ላቀው-2004 ዓ.ም/
 ሕይወተ ማርያም ድንግል/ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መላክ-2007ዓ.ም/
 ክብረ ድንግል/ሊቀ ሥልጣናት ሀብተማርያም ወርቅነህ(አባ መልከ ጼዴቅ)-1955ዓ.ም/
 ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ፩ እና ፪/መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ-በ2002 እና በ2004 ዓ.ም/
 ታኦዶኮስ/መምህር በጽሐ ዓለሙ-2010ዓ.ም/
 መድሎተ ጽድቅ ቅጽ ፩/ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ-2007 ዓ.ም-ክፍል ፪-ገጽ 266-325/

ገጽ 31

You might also like