You are on page 1of 12

«

እውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዱአቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም» (ማቴ.፲፩፥፲፩)

በዘመነ ሥጋዌ ንጉሥ ሄሮድስ ሲሞት ሦስቱ ልጆቹ ሄሮድስ ፍሊጶስ ዳግማዊ፣ አርኬላዎስ እና ሄሮድሰ
አንቲጳስ መንግሥቱን ለሦስት ተካፈሉት፡፡ ሄሮድስ ፍሊጶስ ዳግማዊ ሄሮድያዳ የምትባል ሚስትና ሰሎሜ
የምትባል ልጅ ነበሩት፡፡ ይህች ሄሮድስን ባሏን ትታ መጥታ የገሊላ ገዥ የነበረውን የባሏን ወንድም ሔሮድስ
አንቲጳስን አገባች፡፡ በዚህን ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ «የወንድምህን የፍልጶስን ሚስት ማግባት
አይገባህም» እያለ በድፍረት ይገስጸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት አሲዞ ወደ እስር ቤት አስገባው፤ ሊገድለው
ቢፈልግም ሕዝቡ እንደ ነቢይ ይመለከተው ነበርና ተቃውሞ እንዳይነሳበት ፈርቶ ተወው፡፡ (ማቴ.፲፬÷፬)

ቅዱስ ዮሐንስ በእስር ቤት ሳለ ጌታ በእርሱ እጅ ከተጠመቀና ዓርባ መዓልትና ዓርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ
በማድረግ ላይ ያለውን ነገር /ትምህርቱን፣ ተአምራቱን/ በሰማ ጊዜ በደቀመዛሙርቱ አማካኝነት ወደ
ጌታችን መልእክት ላከ፤ እንዲህ ሲል፡- «የሚመጣው አንተ ነህ? ወይስ ተስፋ የምናደርገው ሌላ
አለ?» ጌታችንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ እንዲህ በማለት በምሥጢራዊ ዘይቤ የአዎንታ
መልስ ላከለት፡ «ሂዳችሁ ያያችሁትንና የሰማችሁትን ለዮሐንስ ንገሩት፡፡ ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶችም
ይሄዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎችም ይሰማሉ፤ ሙታንም ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል
ይሰበካል፡፡ በእኔም የማይሰናከል ብፁዕ ነው፡፡» (ማቴ.፲፩፥፭) መልእክተኞቹ ከሄዱ በኋላም ጌታ አብረውት
ለነበሩት ሕዝቦች ቅዱስ ዮሐንስን «እውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዱአቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ
የሚበልጥ አልተነሣም» እያለ አመስግኖታል፡፡ (ማቴ.፲፩፥፲፩)

ቅዱስ ዮሐንስ ታሥሮ ከጳጉሜን ፪ ቀን እስከ መስከረም ፪ ቀን በእስር ቤት ቆየ፡፡ ያሳሰረው ሔሮድስ
አንቲጳስ መስከረም ሁለት ቀን የልደት በዓሉን ያከብር ነበር፡፡ በዚህ ዕለት የሆነውን ነገር ቅዱስ ማቴዎስ
በወንጌሉ በምዕራፍ ፲፬ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡

«
የሄሮድስም የልደቱ ቀን በሆነ ጊዜ የሄሮድያዳን ልጅ /ሰሎሜ/ በመካከለቸው ዘፈነችለት፤ ሄሮድስንም ደስ
አሰኘችው፡፡ ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ ሊሰጣት ማለላት፡፡ እርሷ ግን አስቀድማ በእናቷ ዘንድ አውቃ
ነበርና የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጪት ስጠኝ» አለችው፡፡ (ወጭት እንደ ጎድጓዳ ሳህን ያለ ዕቃ ነው)
ንጉሡም አዘነ፤ ነገር ግን ስለ መሐላው፣ አብረውት በማዕድ ተቀምጠው ስላሉት ሰዎች የዮሐንስን ራስ
ቆርጠው ይሰጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ልኮም በግዞት በእስር ቤት ሳለ የዮሐንስን ራስ አስቆረጠው፡፡ ራሱንም
በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጧት፤ እርስዋም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች፡፡ ደቀመዛሙርቱም መጡ፤
በድኑንም ወስደው ቀበሩት መጥተውም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ነገሩት፡፡» /ማቴ.፲፬፥፭-፲፪/

የመጀመሪያ ባሏን ሄሮድስ ፊሊጶስን ትታ የባሏን ወንድም ያገባችው ሄሮድያዳ «የወንድምህን ሚስት


ልታገባ አይገባህም» በሚለው በቅዱስ ዮሐንስ ግሣጼ ትበሳጭ ስለነበር የምታጠቃበትን መንገድ ሁልጊዜ
ትፈልግ ስለነበር ለልጇ ለሰሎሜ እንዲህ ያለ ምክር መክራ የቅዱስ ዮሐንስ አንገት እንዲቆረጥ አደረገች፡፡
ሄሮድስ አንድ ጊዜ በሰዎች ፊት ቃል ስለ ገባ እንጂ በውሳኔው ደስተኛ አልነበረም፤ አዝኗል፡፡ ምክንያቱ
ሁለት ነው፡፡
የመጀመሪያው አስቀድመን እንደጠቀስ ነው፤ ሕዝቡ ቅዱስ ዮሐንስን ይወዱትና ይቀበሉት ስለነበር
እንዳይቃወሙት ፈርቶ ነው፡፡ ሁለተኛው የቅዱስ ዮሐንስን ሕይወትና ትምህርት እያስተዋለ ሲሔድ ቅዱስ
ዮሐንስ በእውነትም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መሆኑን ስላወቀ ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ዮሐንስን አንገቱን
ካስቆረጠው በኋላ ጌታችን ያደርጋቸው የነበሩትን ተአምራት በሰማ ጊዜ «ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤
እርሱ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶአል፤ ስለዚህ በእርሱ ተአምራት ይደረጋል» በማለቱ ይታወቃል፡፡
(ማቴ.፲፬፥፪)

የመስከረም ሁለት ስንክሳር በዚህ ላይ ተጨማሪ አስደናቂ ነገር ይነግረናል፡፡ «በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ
ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋጼ ሆነ፡፡ ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን
ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮህ ዘልፋዋለችና» (ስንክሳር ዘወርኃ መስከረም) ነቢዩ ሚልክያስ
ስለ ቅዱስ ዮሐንስ መምጣትና መንገድ ጠራጊነት ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ «እነሆ ታላቁና የምታስፈራው
የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ቴስቢያዊውን ኤልያስን እልክላችኋለሁ፡፡ … እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ
ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል፡፡» (ሚል.፬፥፭-፮)
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም የቅዱስ ዮሐንስን መወለድ ለአባቱ ለዘካርያስ በቤተ መቅደስ ሲያበሥረው
እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ «… እርሱም የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓድያንንም ዐሳብ ወደ ጻድቃን ዕውቀት
ይመልስ ዘንድ፥ ሕዝብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ
ይሄዳል፡፡» (ሉቃ.፩፥፲፯) በዚህም ምክንያት ሕዝቡ ከመሲህ መምጣት በፊት የኤልያስን መምጣት ይጠብቁ
ነበር፡፡ ለምሳሌ ጌታችንን ደቀመዛሙርቱ «ጻፎች ኤልያስ አስቀድሞ ይመጣ ዘንድ አለው ለምን
ይላሉ?» ብለው ጠይቀውት ነበር፡፡ (ማቴ.፲፯፥፲፣ ማር.፱፥፲፩)

ጌታችንም ኤልያስ ይመጣል ተብሎ የተነገረው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መሆኑን እንዳስረዳቸው እነርሱም
እንደተረዱ ቅዱስ ማቴዎስ ይነግረናል፤ «ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለችው «አዎን፥ ኤልያስ
አስቀድሞ ይመጣል፥ ሁሉንም ያቀናል፡፡ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ፈጽሞ መጥቶአል፤ የወደዱትንም
ሁሉ በእርሱ ላይ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ …» ከዚህም በኋላ ደቀመዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ
እንደነገራቸው አወቁ፡፡» (ማቴ.፲፯፥፲፩-፲፫) ከአንድ ታላቅ እና ታዋቂ ሰው በኋላ የሚነሱ ደጋግ ሰዎችን
በእዚያ በታላቁ ሰው ስም መጥራት በትንቢቶች ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ዳዊት
እሥራኤላውያን የሚወዱትና ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ንጉሣቸው ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት ካለፈ በኋላ
እግዚአብሔር ደጋግ ነገሥታትን እንደሚያስነሳላቸው ለእሥራኤል ተስፋ ሲሰጥ ዳዊትን አስነሳላችኋለሁ
ይላቸው ነበር፡፡ «ባርያዬም ዳዊት በላያቸው ላይ ንጉሥ ይሆናል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ
ይሆንላቸዋል» እና  «ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም፥ ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም
ይገዛሉ» እንደተባለው አሁንም የተደረገው ይኸው ነው፡፡ አይሁድ ኤልያስን በጣም ይወዱትና ያከብሩት
ነበር፡፡ አሁንም ድረስ ያሉ አይሁዳውያን የፋሲካን በዓል በሚያከብሩበት ዕለት ለማዕድ
ሲቀመጡ «ለኤልያስ» ብለው አንድ ቦታ ይተዋሉ፤ የወይን ጠጅ የተሞላ ብርጭቆም ያስቀምጣሉ፡፡ የቅዱስ
ዮሐንስ መጥምቅ መምጣት «ኤልያስ ይመጣል» ተብሎ የተነገረው ለዚህ ነው፡፡ «እንደ ኤልያስ ያለ
የኤልያስን ዓይነት ሥራ የሚሠራ ነቢይ ይወጣል» ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ለካህኑ ለዘካርያስ
የተናገረው ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡ «…በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ
ይሄዳል…» (ሕዝ.፴፯፥፳፬፣ኤር.፴፥፱፣ ሉቃ.፩፥፲፯)

ታዲያ ሄሮዳድያ የዮሐንስን አንገት ከልጇ ተቀብላ በጥፊ ልትመታ እጇን ሥትዘረጋ የዮሐንስ አንገት ክንፍ
አውጥታ የቤቱን ግንብ ሠንጥቃ በመውጣት አንገቱ ብቻ 15 አመት በክንፍ እየበረረች ስታሥተምር ቆይታ
ሚያዚያ 15 ቀን አርፏል፡፡
የሄሮዳድያን አሟሟት ብንመለከት እጇ ከሠውነቷ ተለይቶ መሬት ተከፍታ ዋጠቻት ልጇም አበደች ፡
የቤቱን እቃ ሁሉ ጨረሠች ሄሮድሥንም እንደ ዮሀንሥ መዘለፍ ጀመረች የወንድምህን ሚሥት ማግባት
አይገባህም እያለች እሡም በመናደዱ እንዲገድሏት አዘዘ እሡም አብዶ አሟሟታቸው በሥቃይ
ሆነባቸው፡፡
ቃሉም እንዲህ ነው የሚለው "በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በፃድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች
ድዳ ይሁኑ"መዝ 30:18

ወዮው ወዮታ አለባችሁ ቅዱሣን አያማልዱም የምትሉ ወደ ልባችሁ ተመለሡ፡፡ የሄሮዳዲያ ሞት


ያሥተምራችሁ

ቅዱስ ዮሐንስ ዛሬ እኛን እግዚአብሔር ለወዳጆቹ በሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት በጸሎቱ ከእግዚአብሔር
ያማልደናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ዘወትር «ሰአል ለነ ዮሐንስ» «ዮሐንስ ሆይ ለምንልን» ትለዋለች፤ «በአንተ
ዮሐንስ መጥምቅ መሐረነ» «ስለ ዮሐንስ ስትል ማረን» እያለችም ትጸልያለች፡፡ እኛም ገድሉንና፣ መልኩን
በመጸለይ፣ መታሰቢያው በሚደረግበት ጊዜም በስሙ ዝክር በመዘከር፣ ቸርነት በማድረግ በረከትን
ለማግኘት ልንተጋ ይገባናል፡፡ «ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ በደቀ መዝሙሬ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ
የሚጠጣ፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም» /ማቴ.፲፥፵፪/
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለመጥምቁ ዮሐንስ የሰጠው ልዩ ቃልኪዳን፡-

1. ‹‹…ከሚበላውና ከሚጠጣው ከፍሎ በስምህ ለነዳያን ለሰጠ ሥጋዬን ደሜን እሰጠዋለሁ፤ በሃይማኖት ፀንቶ፣
በምግባር ሠፍቶ ሥጋዬን ደሜን እንዲቀበል አደርገዋለሁ፤ ለሥጋዬ ለደሜ የሚያበቃ ሥራ እንዲሠራ
አደርገዋለሁ፤ እስከ ሃምሣ አምስት ትውልድም ድረስ እምረዋለሁ፡፡››
2. ‹‹ሰው ሁሉ ወደ ሥጋዊ ተግባርም ሆነ ወደ መንፈሳዊ ተግባርም ቢሆን ሲሄድ ‹ይህ የመጥምቀ መለኮት
ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ነው› ብሎ ቅጽሩን፣ ገራገሩን ቢሳለም የተሳለመው ሰው ቢኖር እኔ መንበረ መንግሥቴን
አሳልመዋለሁ፡፡ የገድልህንም መጽሐፍ የተሳለመ ቢኖር እኔ መንበረ መንግሥቴን አሳልመዋለሁ፡፡››
3. ‹‹ከቤተክርስቲያንህ የተቀበረውን ሰው ከመከራ ሥጋ፣ ከሲኦል እሳት አድነዋለሁ፤ እኔ ከተቀበርኩበት
ኢየሩሳሌም ሄዶ ከእኔ መቃብር ውስጥ እንደተቀበረ አደርገዋለሁ፡፡››
4. ‹‹ቤተክርስቲያንህ ከታነፀችበት፣ ስምህ ከሚጠራበት፣ መታሰቢያህ ከሚደረግበት፣ የተአምርህ ዜና ከሚነገርበት፣
የገድልህ መጽሐፍ ተነቦ ከሚተረጎምበት፣ እኔ በረድኤት ከዚያ እገኛለሁ፤ ከዚያ ቦታ አልለይም፡፡ የገድልህ
መጽሐፍ ከሚተረጎምበት ቦታ አጋንንት አይደርሱም፤ ከዚያ ቦታ ሰይጣናት ይርቃሉ፡፡››
5. ‹‹የገድልህ የተአምርህ መጽሐፍ የተነበበትን ውኃ እኔ እንደተጠመቅሁበት እንደ ማየ ዮርዳኖስ አደርገዋለሁ፡፡
የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት ውኃ የተጠመቀበት ሰው ቢኖር የሰማንያ ዓመት ኃጢአቱን አስተሠርይለታለሁ፤
ወንዱን የአርባ ቀን፣ ሴቷን የሰማንያ ቀን ሕጻን አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ በተጠመቅሁበት ማየ ዮርዳኖስ
እንደተጠመቀ ሆኖለት ከኃጢአቱ ይነጻል፡፡››
6. ‹‹ሰውም ሆነ እንስሳ ቢታመም በጽኑ እምነት ይደረግልኛል ብሎ አምኖ ያለ ጥርጥር ውኃ አቅርቦ የገድልህን
መጽሐፍ በላዩ ላይ አንብቦ የተነበበበትን ውኃ ቢታጠብበት ወይም ቢጠጣ ያለ ጥፋት ፈጥኖ ከደዌው
ይፈወሳል፡፡››
7. ‹‹የገድልህ መጽሐፍ የተነበበትን ማየ ጸሎት በቤቱ ውስጥ ቢረጭ ከዚያ ቤት በረከቴን እመላበታለሁ፤
ተድላን፣ ደስታን፣ ጥጋብን በዚያ ቤት አሳድራለሁ፤ እስከ ዘለዓለም ድረስ በቤቱ ውስጥ የእህል መታጣትና
ረሀብ፣ የውኃ ጥማት፣ ተላላፊ በሽታ አይገባበትም፤ ፈጽሜም አላመጣበትም፡፡››
8. ‹‹ደስ ብሎት በተድላ በደስታ በዓለህን ያከበረውን ሰው ሁሉ በቅዱሳን መላእክቶቼና በሰማያዊ አባቴ በአብ
ማሕያዊ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ፊት እኔ ደስ አሰኘዋለሁ፡፡ እነሆ እኔም ከበዓልህ ቦታ ላይ አልለይም፤
በዓልህንም ከሚያከብሩት ጋር እኔ አብሬያቸው እቀመጣለሁ፤ እስከ ሃምሣ አምስት ትውልድም እምረዋለሁ፡፡››
9. ‹‹ለቤተክርስቲያንህ ዕጣን፣ ሻማ፣ ጧፍ፣ ልብሰ ተክህኖ፣ መጎናጸፊያ፣ መጋረጃ፣ ነጭ ስንዴ የሰጠ ሰው ቢኖር
እስከ ሃምሣ አምስት ትውልድም ድረስ እምረዋለሁ፡፡››
10. ‹‹ሥጋዬን ደሜን መቀበል ያልተቻለው ሰው ቢኖር ለመታሰቢያህ ዝክር ከተደረገው ፍርፋሪ ይቅመስ፣
ሥጋዬን ደሜን እንደተቀበለ እኔ አደርግለታለሁ፡፡ ፍርፋሪውን ባያገኝ እንጀራውና ዳቦው የተበላበትን ገበታ፣
ጠላው የተጠጣበትን ፅዋ በምላሱ ይላስ፣ እኔ ኢየሱስ ቃሌ የማያብለው ሥጋዬን ደሜን እንደተቀበለ
አደርግለታለሁ፤ ስለ እምነቱ ሥጋዬን ደሜን ለመቀበል የሚያበቃውና እውነተኛውን ምግባር የጽድቅ ሥራ
እንዲሠራ አደርገዋለሁ፡፡›› ጌታችን በቅዱስ ወንጌሉ ስለ ዮሐንስ ሲናገር ‹‹ዮሐንስ የሚያበራ መብራት ነበረ››
ነው ያለው፡፡ ዮሐ 5፡35፡፡ ዳግመኛም ክብሩን ሲገልጥለት "እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል
ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም" በማለት መስክሮለታል፡፡ ማቴ 11:11፣ ሉቃ 7:28፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ቤተሰብ


 ሕፃኑም ዮሐንስ
በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ 
ማኅፀን ሳለ  መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል። (ሉቃ ፩፥፲፭)
 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥ
ም መንፈስ  ቅዱስ ሞላባት። (ሉቃ ፩፥፵፩)
 አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ። (ሉቃ ፩፥፷፯)  

መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ታላቅ ቤተሰብ ታሪክ በሉቃስ ወንጌል ላይ ካህኑ ዘካርያስ እና ከካህኑ ከአሮን ወገን
የሆነች
ኤልሳቤጥ ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃ
ን ነበሩ በማለት ይገልፃል። የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ታሪክም እንዲህ በሚለው በቅዱስ
ገብርኤል ብሥራት
ይጀምራል፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ 
ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች 
ደስ ይላቸዋል። በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገ
ናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌ
ታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል። እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን 
ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል 
በፊቱ ይሄዳል። (ሉቃ ፩፥፲፭-፲፯)

የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሕግጋት እየጠበቀ በቅድስና ይኖር የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ከእግዚአብሔር ተልኮ
የመጣውን የቅዱስ ገብርኤል ቃል ባለመስማቱ ሕፃኑ እስከሚወለድ ድረስ ድዳ እንደሚሆን በአብሳሪው
መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተነገረው። ይወለዳል የተባለው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን የኤልሳቤጥ
መፅነስ በቤተሰቡ መካከል ለረጅም ጊዜ ይፈለግ የነበረ ስለነበር ደስታ ሲፈጥር የካህኑ ዘካርያስ ድዳ መሆን
ደግሞ ቤተሰቡን የሚያስጨንቅ ሌላ ክስተት ሆነ። ቅድስት ኤልሳቤጥም ባለመውለዷ ምክንያት በአካባቢው
ሰዎች ግን እግዚአብሔር እንዳዘነባትና ልጅ እንደከለከላት ይነገርባት ስለነበር የልምላሜዋ ዘመን ካለፈ በኋላ
መፅነስ
በመቻሏ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ 
አድርጎልኛል (ሉቃ ፩፥፳፭) በማለት ደስታዋን ገልፃለች።

አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስ የአዋጅ ነጋሪ ቃል ተብሎ እንደተነገረው የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ
ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካክሉ በማለት ፊት አውራሪ ሆኖ የሚላከውን ቅዱስ ዮሐንስን
የፀነሰችው ቅድስት ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛው ወር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን 
ልትጠይቃት ወደ እርሷ በሔደች ጊዜ እጅግ የሚያስገርም ሁኔታ ተፈጠረ። ይኸውም ቅዱስ ዮሐንስ
በማኅፀን ውስጥ ኾኖ ለቅድስት ድንግል ማርያም እና በማኅፀኗ ላለው ለዓለም መድኃኒት ለኢየሱስ
ክርስቶስ ሰግዷል (ሉቃ. ፩፥፳፮-፵፩) ።

 ሕፃኑም ከተወለደ በኋላ አባቱ ካህኑ ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንደዚህ አለ፦
ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና
፤ እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤ ይህም ከላይ 
የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፤ ብርሃኑም በጨለማና 
በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል። (ሉቃ ፩፥፸፮-
፸፱)

በዚያም ዘመን ሄሮድስ የአምላካችን፣  የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ ከሰብአ


ሰገል ሲሰማ መንግሥቴን ይወስድብኛል ብሎ በመፍራቱ የቤተልሔም ሕፃናትን መግደል የመጀመርያ
ውሳኔው ሆነ። (ማቴ. ፪፥፩-፲፮) ቅድስት ኤልሳቤጥም ልጇን ዮሐንስን ይዛ ወደ ምድረ በዳ ተሰደደች።
የአዋጅ ነጋሪው ቃል ተብሎ የተነገረለት ቅዱስ ዮሐንስ ጊዜው ሲደርስ ከነበረበት በረሐ ድምፁን እያሰማ
መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ! እያለ እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለው አገር ሁሉ ወጣ። (ሉቃ.
፫፥፫-፮) ።

በስብከቱም እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ኹሉ ይቈረጣል፤ ወደ


እሳትም ይጣላል፤ ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፤ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ፤ ከታዘዘላችሁ
አብልጣችሁ አትውሰዱ፤ በማንም ላይ ግፍ አትሥሩ፤ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፤ ደመወዛችሁም
ይብቃችሁ፤ ይል ነበር። (ሉቃ. ፫፥፯-፲፬)።

የትሕትና አባት የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ ጌታ ሊጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጣ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤
አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? በማለት የጌታችንን አምላክነት ፍጹም በሆነ ትሕትና ተናግሯል (ማቴ. ፫፥፲፬)
። ብዙ ተከታይ የነበረውና በስብከቱ የብዙ ሰዎችን ቀልብ የገዛው ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
ሲናገር ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ
ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል። (ዮሐ ፫፥፳-፱-፴)

በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የሚገባውና ከሁሉ የበለጠ ሙሽራ መሆኑን ተናግሯል። መጥምቀ መለኮት
ቅዱስ ዮሐንስ ካህን፣ መምህር፣ ሐዋርያ፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ እና ሰማዕት ነው። ሊቁም ከሰማይ
መላእክት ወገንም ሆነ በምድር ካሉ ቅዱሳን፣ ነቢያት፣ ካህናት፣ መምህራንና ሐዋርያት መካከል ማንም እንደ
ቅዱስ ዮሐንስ መለኮትን ለማጥመቅ የተመረጠ አለመኖሩን በመጥቀስ ዮሐንስ ሆይ ራጉኤል በትጋቱ፣
ኢዮብም በጽድቁ ቢመኙም ሆነ ቢጨነቁ እንደ አንተ የሚነድ እሳትን (መለኮትን) ሊያጠምቁ
አልተቻላቸውም ሲል ተናግሮለታል። (መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ) ።

ሰኔ ፴ ቅዱስ ዮሐንስ የተወለደበትን ቀን ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴ  እና ታቦት በማውጣት


ታከብራለች። በጌታ የተወደደ እና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ሆኖ አምላክን ለማጥመቅ የታደለው የቅዱስ
ዮሐንስ ረድኤት አይለየን፣ መንፈስ ቅዱስን ተሞልተው ድንቅ ያደረጉና ሕያው ምስክርነትን የሰጡት
የመላው ቤተሰብ በረከትም ከሁላችን ጋር ይሁን።
መስከረም 2- ዕረፍቱ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ!

ይኸውም ጌታችን አስቀድሞ "በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል" (ሉቃ 1:14) በማለት የመጥምቁ መወለድ
ለእኛ የደስታ ቀናችን መሆኑን ነግሮናል፡፡ ዳግመኛም ጌታችን የመጥምቁን ክብር ሲገልጥለት "እውነት እላችኋለሁ
ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም" በማለት መስክሮለታል፡፡ ማቴ
11:11፣ ሉቃ 7:28፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ገድሉ ላይ እንደተጠቀሰው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጥምቁ ዮሐንስ ዓሥር እጅግ አስደናቂ ቃል የድኅነት ኪዳኖችን እንደገባለት ከቅዱስ ገድሉ
ላይ ያገኘነውን ቀጥሎ እንናገራለን፡-
ገድለ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (በጎል ሰከበ ደብረ መንክራት ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል ማኅበረ ሰላም አንድነት
ገዳም ያሳተመው- 2003 ዓ.ም) ‹‹እግዚአብሔር ወደ በራክይ ልጅ ወደ ዘካርያስ ልጅ እንደሚወልድ ይነግረው
ዘንድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ላከው፡፡

እርሱም በመሠዊያው በስተቀኝ በኩል ተገልጦ ለዘካርያስ ታየው፡፡ ለሰይጣን ቀኝ የለውምና መልአክ ግን
ብርሃናዊ የማናዊ ነውና መልአክ እንደሆነ ለማጠየቅ በቀኝ በኩል ተገልጦ ታየው፡፡ አንድም ሰው ሁሉ ወደ
የማናዊ ግብ የሚመለስበት ዘመን ደረሰ ሲል በቀኝ በኩል ታየው፡፡ አንድም ሰውን ሁሉ መክሮ አስተምሮ ወደ
ቀኝ ወደ መንፈስ ቅዱስ ሥራ የሚመልስ ልጅ ትወልዳለህ ሲለው በቀኝ በኩል ተገልጦ ታየው፡፡››

የእግዚአብሔርን ስጦታ በልብ ብቻ በድብቅ መያዝ እንደሚገባ፡-‹‹የአካባቢዋ ሰዎችም ሁሉ መካን በመሆኗ


አልሳቤጥን ‹ጡተ ደረቅ፣ ማኅፀንሽም የተዘጋ፣ በረከትን ያጣሽ፣ መርገምንም የተመላሽ፣ የበቅሎ ዘመድ፣
ቢወልዷት እንጂ አትወልድ…› እያሉ ይሰድቧት ነበር፡፡ አልሳቤጥም ‹በዚህ ወራት መፀነሷን ባወቀች ጊዜ
ስድቤን ሁሉ ከሰው ያርቅልኝ ዘንድ እግዚአብሔር በረድኤት በጎበኘኝ ጊዜ እንዲህ አደረገኝን!› ብላ አምስት ወር
ፅንሷን ሠወረች (ለማንም አልተናገረችም)፡፡ እነርሱም ‹ይህቺ ሴት የበላችው ቂጣ ቢነፋት ፀነስኩ ትላለች›
ብለው ቢሰድቧት እንጂ ሌላ ረብ (ጥቅም) ባልነበረው ነበር፡፡ኤልሳቤጥም ስድስት ወር በሆናት ጊዜ መልአኩ
ለቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ ድንግል ማርያምም መልአኩ ስለ ኤልሳቤጥ
መፀነስ የነገራትን ለማረጋገጥ ወደ እርሷ ሄደች፡፡ እመቤታችንም ‹እንዴት ነሽ?› ስትላት ኤልሳቤጥ በሰማች ጊዜ
በማኅፀኗ ያለው ፅንስ በደስታ ሰገደ፡፡››
መንፈስ ቅዱስ የተለየው ሰው የክርስቶስን አምላክነትና የድንግል ማርያምን አማላጅነት ማወቅ አይችልም፡-
‹‹ኤልሳቤጥም ‹እንዴት ነሽ?› ስትላት የእመቤታችንን ድምፅ በሰማች ጊዜ የፈጠረው አምላክ በማርያም ማኅፀን
ውስጥ መኖሩን አወቀ፡፡ የዓለሙ መድኃኒት ፈጣሪው በድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ መኖሩን ለማየት
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዐይኖች በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ በእናቱ ማኅፀን ውስጥ የተገለጡ ሆኑ፡፡
የሁለቱም የማኅፀን መጋረጃዎች ሳይገለጡ ፈጣሪውን ለማየት የዮሐንስ ዐይኖች በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ተገልጠው
እንደ መስታዎት ሆኑለት፡፡ የሁለቱም የማኅፀን መጋረጃዎች ፈጣሪውን ለማየት የዮሐንስ ዐይኖች
አልከለከሉትም፡፡ መልአኩ ለአባቱ ለዘካርያስ ‹ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስን የተመላ ይሆናልና› ብሎ
እንደነገረው በእናቱ ማኅፀን ሆኖ በማርያም ማኅፀን ውስጥ ያለውን ፈጣሪውን አየው፡፡ ፈጣሪውንም ለመቀበል
ሰገደለት፣ እንደ እንቦሳ ጥጃም በደስታ ፈንድቆ ዘለለ፡፡ በእርሱ ላይም የመላው መንፈስ ቅዱስ በኤልሳቤጥም
ላይ መላባትና እንዲህ ብላ ተናረች፡- ‹ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ
ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድነኝ?› አለቻት፡፡››

መጥምቁ ዮሐንስ ምግቡ የበረሃ አንበጣ ነበር›› የሚለው አነጋገር ስሕተት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በተለምዶ ሲነገር
እንደምንሰማው መጥምቁ ዮሐንስ የበረሃ አንበጣ እየተመገበ ይኖር ነበር ይባላል፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ገድሉ
የሚናገረው ቅዱስ ዮሐንስ ይመገብ የነበረው ‹‹የበረሃ አንበጣ›› ሳይሆን ‹‹አንቦጣ›› ተብላ የምትጠራ
አንዲት የበረሃ ቅጠልንና የጣዝማ ማርን እንደነበር ነው፡፡ ቅዱስ ገድሉ ላይ የተጻፈውን እንይ፡- ‹‹ዮሐንስና
እናቱ ኤልሳቤጥ ወደ በረሃ ከገቡ አምስት ዓመት በሆናቸው ጊዜ እርሱ ዕድሜው ሰባት ዓመት ከመንፈቅ
ከሆነው በኋላ እናቱ ኤልሳቤጥ ሞተችበትና ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተወችው፡፡ ዮሐንስም በሰፊዋ በረሃ ውስጥ
በአራዊቶች መካክል ብቻውን ቀረ፡፡ ለዮሐንስ ግን በእርሱ ላይ ምንም መጥፎ ነገር ሳያደርጉ የቶራና የአንበሳ፣
የነብርም ልጆች እንደ ወንድምና እንደ እኅት ሆኑት፡፡ አራዊቶችም ሁሉ ወዳጅ ሆኑት እንጂ፡፡

ምግቡም የበረሃ ቅጠል ነው፤ መጠጡም ከተቀመጠባት ድንጋይ ሥር የምትፈልቀው ውኃ ነበረች፡፡ ዮሐንስ
ሰውነትን አለምልመው፣ ሥጋን አለስልሰው፣ ገጽንና ፊትን የሚያሳምሩትን የበረሃ ቅጠሎችንም አልተመገበም፡፡
አንቦጣ ከተባለችው ከአንዲት የበረሃ ቅጠልና ከጣዝማ ማር በስተቀር ከሚበሉት ምግቦች ሁሉ ዮሐንስ
ሕርምተኛ ሆኖ የተለየ ነበር›› ይላል ቅዱስ ገድሉ፡፡ እስመ ሕሩም ውእቱ ዮሐንስ እምኲሉ መባልዕት ዘእንበለ
አሐቲ ዕፅ እንተ ይእቲ አንቦጣ ወመዐረ ጸደንያ ባሕቲቱ እንዲል መጽሐፍ፡፡ ዮሐንስ ጌታችንን ሲያጠምቀው
ሁለቱ ምን ብለው እንደተነጋገሩ፡- ‹‹በዚያን ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ
ያጠምቀው ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወደ ዮሐንስ መጣ፡፡ ዮሐንስም በእርሱ ላይ አድሮበት ባለው በመንፈስ
ቅዱስ ፀጋ ጌታችን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ አሰምቶ ጮኸ፤ በታላቅ ቃልም እንዲህ አለ፡- ‹እኛን ለማዳን
የመጣው የእግዚአብሔር በግ እነሆ፡፡ ነቢያትም ስለ እርሱ ትንቢት የተናገሩለት ንጉሠ ነገሥት ይህ ነው፡፡
በዕውነት ቀዳሚና ተከታይ የሌለውና ለመንግሥቱም ፍጻሜ የሌለው አምላክ ይህ ነው፡፡› ዮሐንስም ይህን ቃል
እየተናገረ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠርቶ እንዲህ አለው፡- ‹ዮሐንስ ሆይ! ስለ እኔ የተጻፈውን ሕግ ሁሉ
ትፈጽም ዘንድ እነሆ ይገባሃል፤ እነሆ በአየኸው ሁሉ ምስክር ትሆን ዘንድ በአንተ እጅ የምጠመቅበት ጊዜ
ስለደረሰ አጥምቀኝ› አለው፡፡ ዮሐንስም ለጌታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- ‹ወደ አንተ መጥቼ መጠመቅ ለእኔ
ይገባኛል እንጂ እኔ ባሪያህ ሆኜ ሳለሁ በእኔ እጅ ትጠመቅ ዘንድ ስለምን ወደ እኔ መጣህ? አንተ ጌታ ሆነህ ይህ
ነገር ፈጽሞ አይገባም› አለው፡፡

ጌታችንም ‹ዮሐንስ ሆይ! በአንተ እጅ ስለመጠመቄ ደስ መሰኘት ይገባሃል፤ አትፍራም፡፡ አንተ እጅህን በራሴ
ላይ ታኖራለህ፤ ሰውነቴንም እኔ አጠምቃታለሁ፡፡ ዮሐንስ ሆይ! እንቢ አትበለኝ እነሆ ነቢያት ስለ እኔ የተናገሩትን
ሕግና ትእዛዝን ሁሉ ልፈጽም መጥቻሁና› አለው፡፡ ጌታችንም ይህን ቃል ለዮሐንስ ነግሮት ከጨረሰ በኋላ ወደ
ዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ገባ፡፡ ያንጊዜ ዮርዳኖስ አርባ ክንድ ወደኋላው ተመለልሶ ሸሸ፣ ውኃውም በእሳት
እንዳፈሉት ሆነ፡፡ በጸናችው የጥበቡ ኃይል አዳምን ከነልጆቹ ለማዳን ወደዚህ ዓለም ከመጣው ከጌታችን ፊት
ዮርዳኖስ ስለ መሸሿና ወደ ኋላዋ ስለ መመለሷ ነቢዩ ዳዊት ትንቢት ተናግሮአል፡- ‹አቤቱ ውኆች አዩህ፣
ውኆችም አይተውህ ፈሩ፡፡› አንቺ ባሕር የሸሸሽው፣ አንቺ ዮርዳኖስ ወደ ኋላ የተመለሽው ምን ሆናችኋል?
ጌታችንም ዮርዳኖስን እንዲህ በማለት ገሠፀው፡- ‹ዮርዳኖስ ሆይ! በጥምቀቴ ጊዜ አትሽሽ፣ ባለህበት ቦታም
ተመልሰህ ቁም› አለው፡፡ ጌታችንም ይህን ቃል በተናገረው ጊዜ የነቢዩ ዳዊት ትንቢት ይደርስ ዘንድ ውኃው
ወደ ቦታው ተመልሶ ቆመ፤ ከጌታችንም ፊት ሰገደ፡፡ ዮሐንስም ዮርዳኖስ ወደ ኋላዋ ተመልሳ መሸሿንና በጌታችን
ትእዛዝ ወደ ቀድሞ ቦታዋ ተመልሳ ከጌታችን ፊት ስትሰግድ ባየና በተመለከተ ጊዜ ፈራ፣ ደነገጠ፣ ታላቅ
መንቀጥቀጥም አደረበት፣ በፊቱም ሰገደለት፡፡

‹እነሆ አንተ ጌታዬና ፈጣሪዬና ነህ እኔ አገልጋይህ ባሪያህ ነኝ፣ አቤቱ ጌታዬ ሆይ! ይህን ሁሉ ደካማነቴን
ተመልክተህ እጁን በራስህ ላይ ያኖር ዘንድ ባሪያህን አታስገድደው› አለው፡፡ ጌታችንም ለዮሐንስ እንዲህ
አለው፡- ‹ይህ ለእኛ ተድላ ደስታ ነውና እውነትን ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና ያዘዝኩህን አድርግ› አለው፡፡
‹አንተም መጥምቀ መለኮት ተብለህ ክብርህ ይነገራልና እኔም በባሪያው እጅ ተጠመቀ ተብዬ ትሕትናዬ
ይነገራልና› አለው፡፡ ይህንንም ሲናገረው ዮሐንስ ተወው፡፡ ዮሐንስም እንዲህ አለው፡- ‹የአብ ስም በአንተው
አለ፣ የወልድ ስም አንተው ነህ፣ የመንፈስ ቅዱስም ስም በአንተው ሕልው ሆኖ አለ፡፡ ሌላውን በአንተ ስም
አጠምቃለሁ፣ አንተን ግን በማን ስም አጠምቃለሁ?› አለው፡፡ ጌታም ዮሐንስን እንዲህ እያልክ አጥምቀኝ
አለው፡- ‹እንደ መልከጼዴቅ ሹመት የዓለሙ ካህን፣ ብርሃንን የምትገልጽ፣ የአብ የባሕርይ ልጅ፣ አቤቱ ይቅር
በለን፣ የዓለምን ኃጢአት የምታስወግደው የእግዚአብሔር በግ ይቅር በለን እያልክ አጥምቀኝ› አለው፡፡ ያንጊዜ
ዮሐንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ከሌሊቱ በአሥር ሰዓት አጠመቀው፡፡››

አስቀድሞ መሐላ መማል ፈጽሞ ተገቢ እንደልሆነ፡- ‹‹የሄሮድያዳ ልጅ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ
ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገ፡፡ ‹እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን
ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡› እንዲህም እያለ
‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?› እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ
በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ልመና ከአፏ በሰማ
ጊዜ ‹የፈለግሽውን እሰጥሻለሁ› ብሎ በሕዝቡ ፊት ስለማለ ለሰው ይምሰል አዘነ፣ ተከዘ፡፡ ኃዘኑም ስለ ዮሐንስ
መሞት አይደለም፣ ዮሐንስን ሕዝቡ ይወደው ስለነበር እነርሱን ስለ መፍራቱና መሐላ ምሎ ከዳ እንዳይባል ነው
እንጂ፡፡ ስለ ዮሐንስ አዝኖ ቢሆን ኖሮ ቀድሞውንም በግፍ እንዲታሰር ባላደረገው ነበር፡፡ ወንድሞቼ እኅቶቼ
ሆይ! ከመሐላ
የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፡፡ ‹የለመንሽውን ሁሉ እሰጥሻለሁ› ብሎ ስለማለ ሄሮድስ የዮሐንስን አንገት
እንድትቆረጥ አደረገ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቅዱስ ወንጌል ‹ፈጽማችሁ አትማሉ› ብሏል፡፡ ከዚህ በኋላ
ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሄዱ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ
ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ
እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡

የሄሮድስን ቃል እንዳያቃልሉ ጭፍሮቹም የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስን አንገት ስለ መሐላው ቆረጡት፡፡ በመሐላ
ምክንያት ባይሆን ኖሮ ሄሮድስ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ባላስገደለው ነበር፡፡ ስለዚህ ወንድሞቸ እኅቶች ሆይ!
እናንተም ከመሐላ የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፣ ፈጽማችሁም መማል የለባችሁም፡፡›› ስካርና ዘፈን ከሚገኙበት
ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ አሉ፡- ‹‹ወንድሞችና እኅቶች ሆይ! አለልክ መብላና መጠጣት ካለበት ቦታ
እግዚአብሔርን መበደል፣ ማስቀየምና ማስቆጣት ይገኝበታል፡፡ ስካር ከሚገኝበት ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ
አሉ፡፡ ስካርና ዘፈን ከሚገኝበት ቦታ የእግዚአብሔር መቅሰፍት የፈጣሪያችን ቁጣና በቀል ይፈጸምበታልና፡፡
እናንተ ሕዝበ ክርስቲያኖች ሆይ! ከስካር፣ ከዘፈንና ከዝሙት መራቅ ይገባችኋል፡፡ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን
ያስገደለው ዘፈን፣ ስካርና የዘማ ፍቅር መሆኑን ልብ በማለት መገንዘብ አለባችሁ፡፡››

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተገለጠበት ልዩ ሁኔታ፡- ‹‹ንጉሥ ሄሮድስ በሞተ ጊዜ እነሆ
እግዚአብሔር መልአክ በግብፅ አገር ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ ታየው፡፡ እንዲህም አለው፡- ‹እነሆ የዚህን ሕፃን
ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ እስራኤል ተመለስ› አለው፡፡ ዮሴፍም
ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ምድረ እስራኤል ገባ፡፡ ‹ልጄ ናዝራዊ ይባላል› ተብሎ በነቢይ የተነገረው
ቃል ይደርስ ይፈዘም ዘንድ መጥቶ ናዝሬት በምትባል አገር ተቀመጠ፡፡ ለሞት ይፈልገው የነበረው የተረገመ
ከሐዲ ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ከምድረ ግብፅ ተመልሶ
በናዝሬት ተቀምጦ ሳለ እነሆ የዕድሜ ባለፀጋ የሆነችው የዮሐንስ እናት ክብርት ኤልሳቤጥ ልጇን ዮሐንስን
ይዛው ወደ ደብረሲና በረሃ ከገቡ ከአምስት ዓመት በኋላ ዐረፈች፡፡ ዮሐንስም በእናቱ አስክሬን አጠገብ ተቀምጦ
በእጅጉ እያዘነ መሪር ልቅሶንም እያለቀሰ ሳለ የተሸሸገውን ሁሉ የሚያውቅ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የኤልሳቤጥን መሞት፣ እናቱም ስለሞተችበት ዮሐንስ ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተቀምጦ እያለቀሰ መሆኑን
ዐወቀ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኤልሳቤጥን መሞት፣ የወዳጁ ዮሐንስ ኃዘንና ማልቀስ ባወቀ ጊዜ
እርሱም በናዝሬት ሆኖ ያለቅስ ጀመር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇ ወዳጅዋ ሲያለቅስ ባየችው
ጊዜ ‹ልጄ ወዳጄ ሆይ! ምን ሆንክ? ስለምንስ ታለቅሳለህ?› ብላ ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም ለቅድስት እናቱ እንዲህ
በማለት መለሰላት፡- ‹እነሆ ወገንሽ የሆነችው ኤልሳቤጥ ዐረፈች፤ ዮሐንስንም ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተወችው፡፡
ዮሐንስም ሕፃን ስለሆነ የሚያደርገውን አጥቶ በእናቱ አስክሬን አጠገብ ከፊት ለፊቷ ተቀምጦ በመረረ ኃዘን
ያለቅሳል፡፡ እናቴ ሆይ እኔም ዘመድሽ የሆነ የዮሐንስን ልቆሶ ስላወቅሁኝና የእርሱም ኃዘን ስለተሰማኝ የማለቅሰው
ስለዚህ ነው› አላት፡፡ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም
የኤልሳቤጥን መሞት በሰማች ጊዜ በጣም ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ ያንጊዜም ብርሕት ደመና መጥታ ከፊታቸው
ቆመች፤ ፈጥናም ተሸከመቻቸውና ኤልሳቤጥ ከሞተችበት ዮሐንስም ካለበት ቦታ ከደብረሲና በረሃ ውስጥ ወስዳ
አደረሰቻቸው፡፡ ዮሐንስም ባያቸው ጊዜ ደነገጠ፡፡ ከዚያ በፊት ሰው አይቶ ስለማያውቅ የእናቱን አስክሬን
ብቻውን ትቶ ወደ ጫካ ሸሸ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የዮሐንስን ፍርሃት አራቀለትና እንዲህ አለው፡- ‹እኛን
ከማየትህ የተነሣ አትፍራ፣ አትደንግጥም፤ አይዞህ እነሆ የእናትህ ዘመዶች ማርያምና ሰሎሜ በእናትህ አስክሬን
ላይ መልካም ነገር ሊያደርጉ መጥተዋልና ና ወደ እኛ ቅረብ› አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ቃል ከጌታችን አንደበት
በሰማ ጊዜ ወደኋላው ተመለሰ፡፡ ከመሬትም ላይ
ወድቆ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰገደለት፡፡ ጌታችንም እመቤታችን ማርያምንና ሰሎሜን እንዲህ ብሎ
አዘዛቸው፡- ‹በጠማው ጊዜ ለእርሷ ይጠጣ ዘንድ ለዮሐንስ በፈለቀችለት ውኃ የኤልሳቤጥን ሥጋ አጥባችሁ
ገንዙ› አላቸው፡፡ እንዳዘዛቸውም የኤልሳቤጥን አስክሬን አጥበው ገነዙት፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ
ገብርኤልን ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ፈጥነው እንደ ዐይን ጥቅሻ ከሰማይ ወርደው መጡና ከጌታችን
ፊት ቆሙ፡፡ ጌታችንም ‹የኤልሳቤጥን ሥጋ የሚቀበርበትን መሬት ቆፍሩ› አላቸው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ
ገብርኤልንም መቃብሩን ይቆፍሩ ዘንድ ጀመሩ፡፡
ጌታችን ዘካርያስንና ስምዖንን በአካለ ነፍስ ከሰማይ መጥተው በኤልሳቤጥ አስክሬን ላይ ጸሎተ ፍትሐቱን ያደርሱ
ዘንድ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም የኤልሳቤጥ አስክሬን ካለበት ቦታ ላይ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል፣
እመቤታችን ማርያምና ሰሎሜ ከጌታችን ፊት ቆመው ሳለ ስምዖንና ዘካርያስ በአስክሬኑ አጠገብ ቆመው ጸሎተ
ፍትሐቱን ያደርሱ ጀመር፡፡ ጸሎተ ፍትሐቱንም በጨረሱ ጊዜ መላእክት በቆፈሩት መቃብር ውስጥ ቀበሩዋትና
የስምዖንና የዘካርያስ ነፍስ ወደነበረችበት ቦታዋ ተመለሰች፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የኤልሳቤጥን መቃብር
በትእምርተ መስቀል አምሳል ደፈነው፡፡ ኤልሳቤጥም ያረፈችበት ዕለት የካቲት አሥራ ስድስት ቀን ሆነ፡፡

ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ትተውት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ጋር ወደ
ናዝሬት ለመመለስ ከደመናዋ ላይ ተሣፍሮ ተነሣ፡፡ ያንጊዜም ክብርት እመቤታችን ልጇን እንዲህ አለችው፡-
‹ጌታዬና አምላኬ ፈጣሪዬ ሆይ! ስለምን ዮሐንስን ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ትተወዋለህ? እንዴትስ ትተነው
እንሄዳለን? ወደዚህ ቦታ ይዛው የሸሸችው እናቱ ጥላው ሞታ በመቃብር ውስጥ ተቀብራለች ከእኛ ጋር ይዘነው
እንሂድ እንጂ› አለችው፡፡ ዳግመኛም እመቤታችን እንዲህ አለችው፡- ‹ነፍስ ያለወቀ ሕፃን ስላሆነ አራዊት
ይበሉታልና ይዘነው መሄድ አለብን› አለችው፡፡ ጌታችንም ለቅድስት እናቱ እንዲህ በማለት መለሰላት፡-
‹በመምህርነት ወጥቶ ለእስራኤል ታይቶ እስከሚያስተምር ድረስ የሰማያዊው አባቴ ፈቃድ በበረሃ ውስጥ
ብቻውን እንዲኖር ነው፡፡
አንቺ ብቻውን እንዴት ከበረሃ ይኖራል ትያለሽ፤ አራዊቶች እንዳይጣሉት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
ከእርሱ አይለይም፡፡ በፈለገው ነገር ሁሉ እንዲራዱትና እንዲታዘዙለት መላእክተ ብርሃንን አዝለታለሁ፡፡
ብርሃናዊው መልአክ ገብርኤልም ሰማያዊ ሕብስትን ለምግቡ ያመጣለታል፤ በጠማውም ጊዜ እንደ ወተት
የነጣችውን፣ እንደ ወለላ ማርም የጣፈጠችውን ውኃ ከኤዶም ገነት ያመጣለታል፡፡ ይህችንም እርሱ ካለበት
ድንጋይ ሥር የምትፈልቀውን ውኃ እንደ እናቱ ጡት ለአፉ የጣፈጠች አደርግለታለሁ፡፡ አንቺ ብቻውን እንዴት
በበረሃ ውስጥ ይኖራል ትያለሽ፤ እስከ ዛሬ ድረስም የጠበቅሁት እኔ ነኝ፣ ሌላ ማን ጠበቀው ብለሽ ነው? እኔ
አይደለሁምን? ወዳጄ ዮሐንስን ሰማያዊው አባቴ ከዚህ ዓለም ፍጥረት ሁሉ በጣም አብልጦ ይወደዋል፡፡ አባቱ
ዘካርያስም በሥጋው ቢሞት በነፍሱ ሕያው ስለሆነ ዮሐንስን ለማጽናናት በአካለ ነፍስ ከእርሱ እንዳይለየው
አደርጋለሁ፡፡ እናቱ አልሳቤጥም በሥጋዋ ብትሞት በነፍሷ ሕያዊት ስለሆነች ታጽናናው ዘንድ በነፍሷ በፍጹም
ከእርሱ እንዳትለየው አደርጋለሁ፡፡ ዮሐንስን የተሸከመች ማኅፀን ንዕድ፣ ክብርት ስለሆነች በሥጋዋ ውስጥ መጥፎ
ሽታ፣ ክፉ መዓዛ አይገኝባት፣ በመቃብሯም ውስጥ ትሎች አይገኙበት፡፡ ድንግል እናቴ ሆይ! አንቺ እኔን ፀንሰሽ
ሳለሽ ወደ ኤልሳቤጥ በሄድሽ ጊዜ በእጇ ይዛ ጨብጣ፣ በአፏ በሳመችሽ ጊዜ እንዲህ ብላ ትንቢት ተናግራለች፡፡
‹አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፤ የጌታዬ እናቱ ወደ እኔ ትመጪ
ዘንድ እኔ ምንድነኝ? ከእግዚአብሔር አግኝተው የነገሩሽን ቃል ይደረጋል ብለሽ የተቀበልሽ አንቺ ብፅዕት ነሽ፣
ክብርት ነሽ› ብላ ስላመሰገነችሽ እንኳን ሥጋዋ ሊፈርስ ይቅርና መግነዟም አይለወጥም፤ መቃብሯም አይጠፋም፤
ነፍሷንም ከሥጋዋ ጋር እንድትኖር አደርጋታለሁ፡፡› ይህን የመሰለ ነገር ስለ ወዳጁ ዮሐንስ ለድንግል እናቱ
ነግሯት ለጨረሰ በኋላ ዮሐንስን ከበረሃ ውስጥ ትተውት በደመና ላይ ተጭነው ወደ ናዝሬት ተመለሱ፡፡››

You might also like