You are on page 1of 5

የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕማማቱ ፣የሞቱ፣የትንሣኤውና

የዕርገቱ ታሪክ በአራቱ ወንጌላት


የኢየሱስ ክርሰቶስ ሕማማት

በጲላጦስ ዘመን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፤ ትንቢቱም
ይፈጸም ዘንድ መከራን ተቀበለ፤ ጲላጦስ በ፫ ሰዓት ይሰቅል ዘንድ ሲፈርድበትም፤ ‹‹መስቀሉንም ተሸክሞ
በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ›› (ዮሐ.፲፱፥፲፯) የራስ ቅል ስፍራ ቀራንዮ-ጎልጎታ
አዳም ዐጽም የተቀበረበት ቦታ ነበር፡፡ በዚያም የአዳም መቃብር የሆነች ዋሻ አለች፤ የመስቀሉንም እንጨት በዚያ
በምድር መካከል አይሁዶች ተከሉት፡፡ የአዳም አጽም ቀድሞ ከአዳም ትውልዶች ሲተላለፍ ከኖኅ ደርሷል፤ ኖኅም ወደ
መርከብ እንደታቦት አስገብቶት በኋላ መልከጼዴቅ ቀብሮታል፡፡ ጌታችንም ከአዳም የራስ ቅል በላይ ሊያድነው መስቀል
ተሸከሞ ተንገላታ፤ አይሁዶችም የቀራንዮን ዳገት እየገረፉ ከወደ ጫፍ አደረሱት፤ሁለቱንም እንጨት አመሳቅለው
ዐይኖቹ እያዩ እጆቹንና እግሮቹን ቸነከሩት፤ በዕለተ ዐርብ ቀትር ፮ ሰዓት ላይም ተሰቀለ፡፡

ጌታችን የተሰቀለበት ሰዓት ፀሐይ በሰማይ መካከል በሆነ ጊዜ የጥላ መታየት በሚጠፋበት፤ ወደ ሰው ተረከዝም
በሚገባበት ነበር፡፤ ከ፮ ሰዓት ጀምሮ እስከ ፱ ምድር ጨለመች፤ ፀሐይ፤ጨረቃ፤ከዋክብት ብርሃናቸውን ከለከሉ፤
ምክንያቱም የፈጣሪያቸውን ዕርቃኑን ይሸፍኑ ዘንድ ነበር፤ ‹‹ቀትርም በሆነ ጊዜ ፀሐይ ጨለመ፤ምድርም ሁሉ እስከ
፱ ሰዓት ድረስ ጨለማ ሆነ›› ማር.፲፭፥፴፫፡፡

በ፱ ሰዓት በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ስለ ጌታችን በሰማይ ፫ት በምድር ፬ት ተአምራትን ሲያደርጉ አይቶ በእውነት
አምላክ እንደሆነ አመነ፤ ‹‹አቤቱ በመንግሥት በመጣህ ጊዜ አስበኝ›› ባለ ጊዜ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ግን ‹‹እስቲ
አምላክ ከሆነ እራሱን ያድን›› ብሎ ተዘባበተ፡፡ ፍያታዊ ዘየማን ግን ‹‹እኛስ በበደላችን ነው የተሰቀልን፤ እርሱ ግን
ምንም ሳይበድል ነው፤ እንዴት በአምላክ ላይ ክፉ ነገርን ትናገራለህ›› ብሎ ገሰጸው ፤ፍያታዊ ዘየማንም ጌታችን
በጌትነት መንበረ ጸባዖት(መንግሥት) ሆኖ ታየው፤እርሱንም አይቶ ‹‹ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ›› ቢለው
ጌታችን ‹‹ዮም ትሄሉ ምስሌየ ውስተ ገነት›› ብሎ ደመ ማኅተሙን ሰጥቶታል፤ በኋላ ገነት ሲገባም መልአኩ አንተ
ማነህ፤ አዳም ነህ፤ አብርሃም ወይንስ ይስሐቅ? እያለ ጠይቆታል፡፡ መልአኩ ሳያውቅ የጠየቀ ሆኖ አይደለም፤እንኳን
በመጨረሻ የጸደቀ ፍያታዊ ቀርቶ በዘመናቸው የኖሩ ጻድቃንን ያውቃል፤ አዳምን ፤አብርሃምን፤ይስሐቅን ሳያውቅ
ቀርቶም አይደለም፡፡ ነገር ግን ሊቃውንት ሲተረጉሙት ‹‹አዳም ነህ›› ማለቱ የአዳምን ያህል ሥራ አለህን?
አብርሃም ነህ ሲለው ደግሞ የአብርሃምን ያህል ሥራ አለህን ? ለማለት ነው፡፡ ‹‹በጌታችን ኢየሱስ መስቀል አጠገብም
እናቱ፤ የእናቱም እኅት፤ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፤መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር›› (ዮሐ.፲፱፥፳፭)
‹‹እነርሱም ማርያም መግደላዊት፤ የታናሹ ያዕቆብ እና የዮሳ እናት ማርያም፤ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ሰሎሜም
ነበሩ›› (ማር.፲፭፥፵)፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከተናገራቸው የአደራ ቃላት አንዱ እመቤታችን ለቅዱስ ዮሐንስ መሰጠቷ
ነው፤ ለወዳጁ ዮሐንስ ከስጦታ ሁሉ ስጦታ የሆነች እናቱን እናት ትሁንህ ብሎ ሰጠው፤‹‹እነኋት እናትህ፤ እነሆ
ልጅሽ›› (ዮሐ.፲፱፥፳፮)፡፡ በኋላ ወደ ቤቱ ወስዷት ፲፭ ዓመት ኖራለች፤ በዚህም የዮሐንስ ቤት በአቢዳራ ቤት
ተመስላለች፤እመቤታችንም የሚያጽናናትን ወዳጁ ዮሐንስን ሰጥቷታል፡፡ የእመቤታችን ለዮሐንስ መሰጠት ቀድሞ
በሙሴ አንጻር ጽላቷ ለሕዝቡ ሁሉ እንደተሰጠች፤በዮሐንስ አንጻርም እመቤታችን ለሁላችን ለምእመናን
ተሰጥታናለች፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት
፱ ሰዓት በሆነ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ፤አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ›› ብሎ
በታላቅ ቃል ተናገረ፤(ማር.፲፭፥፴፬)፡፡ በዚያም ቆመው የነበሩት ‹‹አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ፤›› የሚለውን
ድምጽ የሰሙ ኤልያስን ይጣራል እያሉ አሙት፤ ክህደትንም ተናገሩ፤ ያንጊዜ አንዱ ወታደር ሮጦ ሆምጣጤ የመላበት
ዕቃ ተቀምጦ ነበርና በሰፍነግ መልቶ በሂሶጽም አድርጎ በአፉ ውስጥ ጨመረለት፡፡
በመስቀል ላይ ሳለ ጌታችን ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ሁሉ ተፈጸመ አለ፤ (ማር. ፲፭፥፴፯)፤ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ
ሥጋው በፈቃዱ ለየ፡፡ አይሁድም እኒህ ሰዎች እንደተሰቀሉ አይደሩ፤ ምክንያቱም ቀጣዩ ቀን ሰንበት ነውና ጭናቸውን
ሰብረው ያወርዷቸው ዘንድ ጲላጦስን ጠየቁት፤ እርሱም ፈቀደላቸው፡፡ የሁለቱ ወንበዴዎች፤ ፈያታይ ዘየማንንና
ፈያታይ ዘጸጋምን አብረው አወረዷቸው፤ ከጌታችን ዘንድ ቢቀርቡ ፈጽሞ ሞቶ አገኙት፤ በዚህም ጭኑን ሳይሰብሩት
ቀሩ፡፡ ሌላው ግን የተመሰለው ምሳሌ ፍጻሜ ሲያገኝ ነው፤ የፋሲካውን በግ ‹‹አጥንቱን ከእርሱ አትስበሩ›› የተባለው
አሁን ተፈጸመ፤(በዘፀ.፲፪፥፲)፡፡ ከጭፍሮቹም አንዱ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው እንዲል ከወታደሮቹ አንዱ የሆነው
ለንጊኖስ የጌታችንን ጎን ቢወጋው ትኩስ ደምና ቀዝቃዛ ውኃ ፈሷል፡፡ ለንጊኖስ ጥንተ ታሪኩ አንድ ዐይኑ የጠፋ ሲሆን
ጌታችን በተሰቀለበት ጊዜ ወደ ጫካ ሸሽቶ ርቆ ነበር፤ ምክንያቱም ከዚህ ሰው ሞት አልተባበርም በማለት ነው፡፡
አመሻሹ ላይ የአይሁድ አለቆች ሲመለሱ ከመንገድ አገኘቱ፤ስለምን ከመሢሑ ሞት አልተባበርክም አሉት ? እርሱም
ምንም ስላላገኘሁበት አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ እንደሕጋቸው እንደሚቀጡት ቢነግሩት እየሮጠ ሔዶ የጌታችንን ጎን
ሲወጋው ደሙ በዐይኑ ላይ ፈሰሰ፤ ያን ጊዜ ዐይኑ በራለት፤ከጌታችን ጎን የፈሰሰው ደም እንደ " ለ" ቅርጽ ሆኖ በሁለት
ወገን ደምና ውኃ ሆነ፡፡(ዮሐ.19፥34)
ከጌታችንም የፈሰሰውን ትኩስ ደም መላእክት በጽዋ ቀድተው በዓለም ላይ ረጩት፤ ይህ መሠረት ሆኖ ዛሬ ቤተ
ክርስቲያን የሚታነጸው የጌታችን ደም የነጠበበት ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ
ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን
ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ
ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤
ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡

ቅዱስ ዳዊት፡- “ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትም” ያለው ይኽንን
ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡፡ /መዝ ፲፭፥፲/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ክርስቶስ ደግሞ ወደ
እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ
በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው
ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ
(መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤” ብሏል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ

ጌታችን በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ “ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች”
የሚለው ቃለ ትንቢት የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው፡፡ /መዝ ፲፭፥፱/፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም “ወደ መቃብር
የወረደ ሥጋዬ በተስፋ ትንሣኤ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፤” ማለት ነው፡፡ ተስፋ ትንሣኤውም
በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር የወረደ መለኰት ነው፡፡ ነቢዩ ሆሴዕም፡ - “ኑ÷ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤
እርሱ ሰብሮናልና÷ (በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን ጨምሮ የፈረደብን እርሱ ነው)÷ እርሱም ይፈውሰናል፤ (መርገመ
ሥጋን መርገመ ነፍስን አስወግዶ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋግረናል )፤ እርሱ መትቶናል÷ እርሱም ይጠግነናል፡፡ ከሁለት
ቀን በኋላ ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፡፡” በማለት ትንሣኤ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን መሆኑን
አረጋግጧል፡፡ /ሆሴ ፮፥፲፪/፡፡ ይልቁንም ጌታችን ራሱ በመዋዕለ ሥጋዌው፡- ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች
ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ በግልጥ
ነግሯቸዋል፡፡ /ማቴ ፲፮፥፳፩/፡፡ በገሊላም ሲመላለሱ፡- “ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ
ዘንድ አለው÷ ይገድሉትማል÷ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” ብሏቸዋል፡፡ /ማቴ ፲፯፥፳/፡፡ ጻፎችና ፈሪሳውያንም
ምልክት በጠየቁት ጊዜ፡- “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል÷ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት
አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ፥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ÷ እንዲሁ የሰው ልጅ (ወልደ ዕጓለ
እመሕያው ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል፡፡” ብሏቸዋል፡፡ /ማቴ ፲፪፥፴፰-፵/።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በከረሰ መቃብር የቆየው እንዴት
ነው?

ጌታ በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ ይኽንንም ለመረዳት ዕብራውያን ዕለታትን እንዴት
እንደሚቆጥሩ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ እኛ በሀገራችን የሌሊቱን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ከዋዜማው ከምሽቱ
አንድ ሰዓት ነው÷ የቀኑን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ደግሞ ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ የሌሊቱ ሰዓት
የሚያልቀው ከማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን፥ የቀኑ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ነው፡፡ የቀኑም
የሌሊቱም ሰዓት ተደምሮ ሃያ አራት ሰዓት ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰዓት ዕለቱን ይወክላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እሑድ ዕለት
ከሃያ አራቱ ሰዓት በአንዱ ቢወለድ እሑድ ተወለደ ይባላል÷ቢሞትም እሑድ ሞተ ይባላል፡፡ ዕለቱ በሚጀምርበትም
ሰዓት ሆነ፥ በሚያልቅበት ሰዓት፥ ድርጊቱ ቢፈጸም ያ ሰዓት እንደ አንድ መዓልትና እንደ አንድ ሌሊት ይቆጠራል፡፡
አውሮፓውያን አንድ ብለው ሰዓት መቁጠር የሚጀምሩት በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ነው፡፡ እስከ ሃያ አራት
ይቆጥሩና በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን ይጨርሳሉ፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ሲሆን ዜሮ ይሉና እንደገና አንድ
ብለው መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ከሌሊት እስከ ሌሊት ይቆጥራሉ፡፡ አሜሪካውያን ደግሞ በእኛ ከሌሊቱ
ሰባት ሰዓት ሲሆን አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ከዚያም
በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እንደገና አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት
ብለው ይጨርሳሉ፡፡

ዕብራውያን ግን ዕለትን መቁጠር የሚጀምሩት ከዋዜማው ማለትም በአውሮፓውያን ከአሥራ ሰባት ሰዓት÷
በአሜሪካውያን ከአምስት ሰዓት (P.M.) ÷ በእኛ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ
እስከ ቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ሃያ አራት ሰዓት ቆጥረው አንድ ቀን ይላሉ፡፡ ከላይ እንደተገለጠው እያንዳንዱ
ሰዓት የዕለቱን መዓልትና ሌሊት ይወክላል፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ከመስቀል ወርዶ የተቀበረው ዓርብ ቅዳሜ
ከመግባቱ በፊት ነው፡፡ ዓርብ ዕለቱ የሚጀምረው ከዋዜማው ሐሙስ በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ
ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ የተቀበረው በዓርብ ሃያ አራት ሰዓት ክልል ውስጥ በመሆኑ እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ዓርብ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ሦስተኛው
ደግሞ ቅዳሜ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ እሑድ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የሰኞ
ምሽት ይገባል፡፡ ጌታ የተነሣው በሦስተኛው ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት ነው።

እንዴት ተነሣ?

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ነው፡፡ ይህ
ኃይልና ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ ይኽንንም፡- “ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ (ሰውነቴን ከሞት አነሣት ዘንድ)
አኖራለሁና (በፈቃዴ እሞታለሁና)፤ ስለዚህ አብ ይወደኛል፡፡ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ (ነፍሴን በፈቃዴ ከሥጋዬ
ለይቼ በገነት÷ ሥጋዬንም በመቃብር አኖራቸዋለሁ እንጂ) ከእኔ ማንም አይወስዳትም፡፡ (ያለ እኔ ፈቃድ የሚፈጸም
ምንም ነገር የለም)፡፡ ላኖራት (ነፍሴን በገነት÷ ሥጋዬን በመቃብር ላኖራቸው) ሥልጣን አለኝ፤ ደግሞም ላነሣት
(ነፍሴን ከሥጋዬ አዋሕጄ ላነሣት) ሥልጣን አለኝ” በማለት አስቀድሞ ተናግሮታል፡፡ /ዮሐ ፲፥፲፯-፲፰/፡፡ክርስቶስ
በኃይሉ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጐ÷ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሥቷል፡፡ እርሱ የትንሣኤና የሕይወት ባለቤት
ነውና፡፡ /ዮሐ ፲፩፥፳፭/፡፡

ጌታችንን ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘው ከቀበሩት በኋላ፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተመልሰው፡ - “ጌታ
ሆይ÷ ያ ሰው (ክርስቶስ)፥ ገና በሕይወቱ ሳለ፥ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፥ እንዳለ ትዝ አለን፡፡ እንግዲህ
ደቀመዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ ÷ የኋለኛይቱ ስሕተት
ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት፡፡ ጲላጦስም፡–
ጠባቆች አሉአችሁ፥ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ” አላቸው፡፡ እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው
መቃብሩን አስጠበቁ” /ማቴ ፳፯፥፷፫-፷፮/፡፡ በታላቅ ድንጋይ የተገጠመው መቃብር፥ ድንጋዩ እንደታተመ፥ ክርስቶስ
ሞትን ድል አድርጐ ተነሥቷል፡፡ ይኸውም፦ ምንም የማያግደው መለኰት በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር በመቃብር ስለነበረ
ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ እንደተናገረው፥ በተዋሕዶ፥ የቃል ገንዘብ ለሥጋ፥ የሥጋም ገንዘብ ለቃል በመሆኑ ነው፡፡
ለምሳሌ፦ አይሁድ ብዙ ጊዜ በድንጋይ ቀጥቅጠው ሊገድሉት ሲፈልጉ፥ እያዩት ይሰወርባቸው ከእጃቸውም ይወጣ
ነበር፡፡ በመካከላቸው አልፎ ሲወጣ አያዩትም ነበር፡፡ /ዮሐ ፰፥፶፱፤ ፲፥፴፱/፡፡ ይህም የሆነው፥ እንደ ነፍስና ሥጋ
ተዋሕዶ፥ መለኰት ሥጋን በመዋሐዱ ነው፡፡ ከትንሣኤው በኋላም ከአንዴም ሁለት ጊዜ ከተዘጋ ቤት በሩ ሳይከፈት
የገባው ለዚህ ነው፡፡ /ዮሐ ፳፥፲፱፤ ፳፮/፡፡ በልደቱም ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና
እንደታተመች የተወለደው ለዚህ ነው፡፡ /ኢሳ ፯፥፲፬፣ ማቴ ፩፥፳-፳፫፣ ሉቃ ፪፥፮-፯/፡

መቃብሩን ማን ከፈተው?

ጌታችን የተነሣው መግነዝ ፍቱልኝ፥ መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ከሆነ፥ “መቃብሩን ማን ከፈተው? ለምንስ
ተከፈተ?” የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል፤ በወንጌል እንደተጻፈው፥ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜ ካለፈ በኋላ፥ እሑድ
በማለዳ፥ ፀሐይ ሲወጣ፥ መግደላዊት ማርያም÷ የያዕቆብም እናት ማርያም ሶሎሜም ሽቱ ሊቀቡት ወደ መቃብሩ
መጥተው ነበር፡፡ ትልቁ ጭንቀታቸው “ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?” የሚል ነበር÷ ድንጋዩ
እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደነበር ተመለከቱ፡፡ ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ
ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ፡፡ በጐልማሳ አምሳል የተገለጠላቸው የጌታ መልአክ
ነው፡፡ እርሱ ግን፡- “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ አውቃለሁ፤ ተንሥቷል በዚህ
የለም” አላቸው፡፡ /ማር ፲፮፥፩-፮/፡፡ ጌታችን በዝግ መቃብር ከተነሣ በኋላ ባዶ የነበረውን መቃብር የከፈተው ይህ
የጌታ መልአክ ነው፡፡ የከፈተበትም ምክንያት በእምነት የመጡ እነዚህ ሴቶች ያልተነሣ መስሏቸው ዘወትር
በመመላለስ እንዳይቸገሩ ነው፡፡ አንድም ትንሣኤውን እንዳይጠራጠሩ ነው፡፡ በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌልም “በሰንበትም
መጨረሻ የመጀመሪያው ቀን ሲነጋ፥ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡ እነሆም
የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ፡፡ መልኩም
እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፡፡ ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ፡፡ እንደ ሞቱም ሆኑ፡፡
መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው፥ እናንተስ አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ አውቃለሁና፤ እንደ
ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም” የሚል ተጽፏል፡፡ /ማቴ ፳፰፥፩-፮/፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በእርግጠኝነት ትንሣኤውን
ያመኑት መልአኩ ወደ ከፈተው መቃብር ገብተው መግነዙን ካዩ በኋላ ነው። /ዮሐ ፳፥፯/።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለባሕርይ አባቱ፥ ለአብ ለእናቱ ለድንግል ማርያምም የበኵር
ልጅ ነው። ሉቃ. ፪÷፯፡፡
ለበጎ ነገርም ሁሉ በኵር በመሆኑ የትንሣኤያችንም በኵር እርሱ ነው፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት


“ዕርገት” የሚለው ቃል “ዐርገ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከታች ወደ ላይ መውጣት፣ ክፍ
ከፍ ማለት፣ ማረግ ማለት ነው፡፡ ዕርገት (Ascension) ሲባልም ማረግን፣ ከፍ ከፍ ማለትን፣ ወደ ላይ መውጣትን
ያመለክታል፡፡ ዕርገት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የነበረውን የማዳኑን ሥራ ጨርሶ ወደ ላይ
መውጣቱና በቀደመ ክብሩ በአብ ቀኝ መቀመጡ የሚነገርበት ነው፡፡
አምላካችን ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላ እና በሁሉም ቦታ የሚኖር) ነዉ። ስለዚህ ጌታችን በባሕርይው መውጣት
መውረድ የለበትም:: ‘ወረደ፣ ተወለደ’ ሲባል ፍጽም ሰው መሆኑን የትህትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ
ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም ከሰማያዊዉ ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም :: በምድር
ላይ ሊሰራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ:: እንዲሁም ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተክርስቲያን
የተለየበት ጊዜ የለም። ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋዉ የተደረገዉን ዕርገቱን ያመለክታል። ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋዉ
በምድር የስበት ቁጥጥር (Gravitational force) የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ አምላካዊ
ስልጣኑን ያሳያል።
ዕርገቱም የተፈጸመው ስለ ምጽአቱ ባስተማረበትና ዳግም ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት በደብረ ዘይት ተራራ ነበር፡፡
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ይህንን “እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም
ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ” (ሉቃ ፳፬፡፶)
ቅዱስ ማርቆስ የጌታችንን ዕርገት በገለጸበት አንቀጽ “ጌታችን ኢየሱስም ከተነጋገራቸዉ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፥
በአባቱም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡” (ማር. ፲፮፡፲፱) ብሏል፡፡ “ወደ ሰማይ” የሚለው ቃል ወደ ሰማየ
ሰማያት ማለት ነው ። “ዐረገ” የሚለውም ( መላእክት አሳረጉት አላለም) በራሱ ኃይል ሥልጣንና ማረጉን ያሳያል፡፡
ከጌታችን በቀር በራሱ ኃይል ያረገ የለም። ሌሎች ቅዱሳን፡ ለምሳሌ ኤልያስ እና ሄኖክም ቢሆኑ እግዚአብሔር
ዐሳረጋቸው እንጂ በራሳቸው ስልጣን ዐላረጉም ።

"ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በዃላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።"(ማር.፲፮፥፲፱)


ጌታችን በዕርገቱ “በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ” መባሉ ለእግዚኣብሔር ግራና ቀኝ ፥ታችና ላይ ኖሮት ሳይሆን
ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን በስልጣን እኩል መሆናቸዉን የሚያስረዳ ነው፡፡
ጌታችን በሥጋዌው ራሱን በፈቃዱ ዝቅ አደረገ እንጅ በክብር ከአብ ከመንፈስቅዱስ እንደማይለይ ያስረዳናል፡፡
በቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት በአብ ቀኝ ተቀመጠ ማለት በሥልጣን አንድ መሆንን ያሳያል፡፡ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ስንል በክብር በልዕልና ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው።
ይህም ከተዋሕዶ በፊት ደካማ፣ በደለኛ እና ውርደት ይስማማው የነበረው የእኛ ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ ጸጋን
የሚያድል፣ እውነተኛ ፍርድን የሚያደርግ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ሥልጣን ያለው እውነተኛ ፈራጅ
አምላክ እንደሆነ ለመግለጽ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብ ሥልጣን ዝቅ ያለበት የዐይን ጥቅሻ ያህል ጊዜ እንኳ የለም።
“ቀኝ” የሚለው ቃል ኃይልን ቅድስናን ወይም ክብርን የሚያመለክት ነው ።

You might also like