Professional Documents
Culture Documents
መቅረዝ ዘተዋሕዶ
mekrez.blogspot.com/search
ስለ በርለዓም ሰማዕት
(1) ዛሬ ንዑድ ክቡር የሚኾን በርለዓም ወደ ቅዱስ በዓሉ ጠርቶናል፡፡ ነገር ግን እንድናመሰግነው አይደለም፤
እንድንመስለው ነው እንጂ፡፡ ሲያመሰግን እንድንሰማውም አይደለም፤ የደረሰበትን ቅድስና ዐይተን እርሱን መስለን
እዚያ የቅድስና ማዕርግ ላይ እንድንደርስ ነው እንጂ፡፡ የዚህ ዓለም ሰዎች ወደ ሥልጣን ሲወጡ ሌሎች ሰዎች ልክ
እንደ እነርሱ ታላላቅ ኾነው ማየትን በፍጹም አይወዱም፤ ቅንአት ውስጣቸውን ይተናነቃቸዋል፡፡ በመንፈሳዊ ነገሮች
ላይ ግን እንደዚህ አይደለም፤ ፍጹም ተቃራኒ ነው እንጂ፡፡ ቅዱሳን ሰማዕታት ክብራቸውን ከምንም በላይ ከፍ ብሎ
የሚያዩት ደቀ መዛሙርቶቻቸው እነርሱን አብነት አድርገው ከእነርሱ በላይ የተሻሉ ኾነው ሲመለከቱአቸው ነው፡፡
በመኾኑም አንድ ሰው ሰማዕታትን ማመስገን ቢፈልግ እነርሱን ሊመስል ይገቧል፡፡ አንድ ሰው የእምነት አትሌቶችን
ማሞገስ ቢፈልግ እነርሱን መስሎ ምግባር ትሩፋትን ሊሠራ ይገቧል፡፡ ይህ ነገርም እነርሱ ካገኙት ሹመት ሽልማት
በላይ ሰማዕታቱን ደስ ያሰኛቸዋል፡፡ በእርግጥም ያገኙትን ሹመት ሽልማት ከምንም በላይ የሚያጣጥሙትና
የተሰጣቸው ክብር ምን ያህል ታላቅ እንደ ኾነ የሚገነዘቡት እኛ እነርሱን መስለን የሔድን እንደ ኾነ ነው፡፡ ይህንንም
በማስመልከት ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ የተናገረውን አድምጡ፤ እንዲህ ያለውን፡- “እናንተ በጌታችን
ጸንታችሁ ብትቆሙ አሁን እኛ በሕይወት እንኖራለን” /1ኛ ተሰ.3፥8/፡፡ ከዚህ በፊትም ብፁዕ ሙሴ እንዲህ ብሏል፡-
“አሁንም ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር ትላቸው እንደ ኾነ ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ ደምስሰኝ”
/ዘጸ.32፥32/፡፡ እንዲህ ማለቱ ነበር፡- “እነርሱ ከተጎዱ የእኔ ክብር ምንም አይደለም፤ የምእመናን ሙላት ማለት
የአካል መገናኘትም ነውና፡፡ ታዲያ ራስ የሕይወት አክሊልን አግኝቶ እግር ቢቀጣ ምን ጥቅም አለው?”
በሥርጉተ ሥላሴ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ 07 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
https://www.printfriendly.com/p/g/rXzeUv 1/5
4/20/2021 መቅረዝ ዘተዋሕዶ
ሰማዕትነቱ
ቅዱስ አግናጥዮስ የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ በነበረበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን ከዓላውያን የሮማ ነገሥታት
ከፍተኛ መከራና ስቃይ ይደርስባት ነበር:: በድምጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ከነበረው የመከራ ማዕበል በጾም እና
በጸሎት፣ በብዙ መንፈሳዊ ተጋድሎ፥ በተለይም ምእመናን መከራውን ተሰቅቀው ከሃይማኖት እንዳይወጡ ተግቶ
በማስተማር እንደ መልካም ካፒቴን ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን መርቶ አሻግሯል:: ቅዱስ አግናጥዮስ ከትሕትናው የተነሣ
ስለ ራሱ ሕይወት እውነተኛ የክርስቶስ ፍቅር ላይ ገና አልደረስኩም፤ እውነተኛ የደቀ መዝሙርነት ፍጽምና ላይ
አልደረስኩም እያለ ያዝን ነበር:: በመሆኑም ሰማዕትነት የበለጠ ወደ እግዚአብሔር እንደሚያቀርብ በማመን
ለሰማዕትነት ክብር እንዲበቃ በእጅጉ ይመኝ ነበር::
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ 2 ቀን፣ 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ውድ የመቅረዝ ዘተዋሕዶ አንባቢያን! እንደ ምን ሰነበታችሁ? ላለፉት አምስት ሳምንታት ገደማ በመቅረዝ ላይ
አዲስ ጽሑፍ ሳልለጥፍ በመቆየቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ እንዲህ የኾንኩበት ዋና ምክንያት ግን ላለፉት ስድስት
ወራት ስተረጉመው የቆየሁትንና ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አያሌ መጻሕፍት አንዱ የኾነው የኦሪት ዘፍጥረት
የመጀመሪያ ቅጽ መጽሐፍን የመጨረሻዉን ቅርጽ ለማስያዝ ብሎም ወደ ኅትመት ለማስገባት በነበረብኝ ጫና
ምክንያት ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ በእኔ ዓቅም በብዙ ድካም የተተረጎመው ይህ አዲስ መጽሐፍ
በቅርብ ጊዜ ወደ እናንተ ይደርሳል፡፡ ለማቆያ ያህልም ከመጽሐፉ መቅድም ከዚህ በታች አቅርቤላችኋለሁ፡-
የዓርብ ፍጥረታት
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን!!!
ትምህርተ ሃይማኖት - ክፍል 18
ዓርብ ዐረበ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲኾን ተካተተ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዓርብ ማለት መካተቻ መደምደሚያ
ማለት ነው። ምዕራብ ስንል መግቢያ፣ መጥለቂያ (ለምሳሌ የፀሐይ መግቢያን ምዕራብ እንደምንለው) ማለት ሲኾን
ዐረብ ሲባልም ተመሳሳይ ነው - ከኢየሩሳሌም ምዕራባዊ አቅጣጫ ያሉ ሀገራት የዐረብ ምድር ይባላሉና። ዐርብ
የተባለበት ምክንያት በዕለተ እሑድ መፈጠር የጀመሩት ፍጥረታት ተፈጥረው ያበቁበት፣ የተካተቱበት ቀን ስለ ኾነ
ነው፡፡
በዚህ ቀን እግዚአብሔር “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትን ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም
እንደ ወገኑ ታውጣ” ብሎ አዘዘ /ዘፍ.1፥24/፡፡ በዚሁም መሠረት ልክ እንደ ሐሙስ ፍጥረታት በእግራቸው የሚሔዱ፣
በልባቸው የሚሳቡና በክንፋቸው የሚበሩ ፍጥረታት ናቸው፡፡ የሐሙስና የዓርብ መኾናቸውን የምንለየውም
በአኗኗራቸውና በግብራቸው ሲኾን የሐሙስ ፍጥረታት በባሕር፣ የዓርብ ፍጥረታትም በየብስ ይኖራሉ፡፡ በዚህ ቀን
በአራተኛ አዳምን ፈጥሯል። ይህንን በኋላ እንመለስበታለን፡፡
በሳይንሳዊ መንገድ ሔደን ምድር እነዚህን ፍጥረታት እንዴት ልታስገኛቸው ቻለች ብለን ብንጠይቅ መልስ የለውም፡፡
የተገኙት እግዚአብሔር ስላዘዘ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ምድሪቱን አዘዛት፤ እርሷም አረገዘች፤ ወለደቻቸውም፡፡
ዛሬም ይህ እውነት እንደ ኾነ የምናይበት ኹናቴ አለ፡፡ ዝናብ ወደ ሰኔ አከባቢ መዝነብ ሲጀምር አስቀድመን
ያላየናቸው ፍጥረታት ከምድር ወጥተው ሲበሩ፣ እንዲሁም እንደ እንቁራሪት ያሉ ፍጥረታት ወደ መኖር ሲመጡ
https://www.printfriendly.com/p/g/rXzeUv 2/5
4/20/2021 መቅረዝ ዘተዋሕዶ
እናያቸዋለን፡፡ አስቀድሞ ባልተጣለ ዕንቁላል የተለያዩ ዓይነት ትላትሎች ከጭቃ ውስጥ ሲፈጠሩ እናያቸዋለን፡፡
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ጥበብ ታያላችሁን?
በሥርጉተ ሥላሴ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን!!!
እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት፥ ቅዱስ አግናጥዮስ ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን ስለ ትሕትና ለማስተማር
በመካከላቸው ያቆመው ሕፃን ነው፡፡ ከዚህም የተወለደበትን ዘመን መገመት ይቻላል (30-35 ዓ.ም.)፡፡ በጌታችን ደቀ
መዛሙርት መካከል “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?” የሚል ክርክር በተነሣ ጊዜ፥ ጌታ ሕፃኑን
ቅዱስ አግናጥዮስን አቅፎ በመሳም፡- “ተመልሳችሁ፣ ከየውሀት ጠባይዓዊ ደርሳችሁ እንደዚህ ሕፃን ካልሆናችሁ
መንግሥተ ሰማያት አትገቡም” አላቸው፥ “ሕፃንንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመው እንዲህም አለ፥ እውነት
እላችኋለሁ ካልተመለሳችሁ እንደዚህም ሕፃን ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም . . . ” እንዲል /
ማቴ.18፥2-5፣ አንድምታ ወንጌል/፡፡ ሰማይና ምድርን ፈጥረው በተሸከሙ እጆች፣ ሕዝብና አሕዛብን ለማዳን ግራ
ቀኝ በተዘረጉ ቅዱሳት ክንዶች መታቀፍ ምንኛ መቀደስ ነው?! ቅዱስ አግናጥዮስ ጌታችን በመንግሥተ ሰማያት
ከሁሉ የሚበልጥ ሕፃን ብሎ እንደመሰለለት እንደዚያው እንደ ምሳሌው ሆኖ እስከ መጨረሻ ሕይወቱ በየውሀት
ጠባይዓዊ የኖረ፣ ጌታ አቅፎ እንደ ተሸከመው እርሱም ጌታውን በልቡናው የተሸከመ ቅዱስ አባት ነው፡፡ ስለዚህም
ቅዱስ አግናጥዮስ ራሱን በተደጋጋሚ ቲኦፎረስ (Theophorus - እግዚአብሔርን በልቡናው የተሸከመ፣ ለባሴ
እግዚአብሔር)፣ ክሪስቶፎረስ (Chritophorus - ክርስቶስን በልቡናው የተሸከመ፣ ለባሴ ክርስቶስ) እያለ ይጠራ ነበር፤
በጣም ደስ የሚሰኝበት ስሙም ነበር፡፡ ለዚህም ነው በመጨረሻ ለተራቡ አናብስት ተጥሎ ሰማዕትነቱን በፈጸመበት
ሰዓት አናብስት ሌላውን አካሉን በመላ ሲበሉ ልቡን መርጠው የተዉት፡፡
የሐሙስ ፍጥረታት
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 9 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ትምህርተ ሃይማኖት - ክፍል 17
ሐሙስ የሚለው ሐመሰ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲኾን አምስት አደረገ ማለት ነው። ለሥነ ፍጥረት አምስተኛ ቀን
ስለኾነ ሐሙስ ተብሏል።
በዚህ ቀን እግዚአብሔር፡- “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾችን ታስገኝ” ብሎ አዘዘ /ዘፍ.1፥20-21/፡፡
በዚሁም መሠረት በእግራቸው የሚሔዱ፣ በልባቸው የሚሳቡና በክንፋቸው የሚበሩ ሦስት ወገን ፍጥረታትን
ፈጠረ፡፡ እነዚህ ፍጥረታት ተፈጥሮአቸው ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ - ማለትም ከመሬት፣ ከውኃ፣ ከእሳትና ከነፋስ -
ሲኾን በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ደመ ነፍስ ማለትም በደም ነፍስነት፣ በደም ኃይል የሚንቀሳቀሱ፣ ደማቸው
ሲቆም ሕይወታቸውም አብሮ የሚቆም ማለት ነው፡፡ ይህም እስትንፋስ እያልን የምንጠራው ነው፡፡ ይህ እስትንፋስ -
ማለትም ደመ ነፍስ - በሰውም ዘንድ አለ፡፡
እነዚህ በዚህ ዕለት የተፈጠሩት ፍጥረታት ካለ መኖር ወደ መኖር የመጡት እግዚአብሔር ስላዘዘ እንጂ ውኃው በራሱ
ኃይል ያስገኛቸው አይደለም፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር ካልፈቀደና ካላዘዘ በስተቀር ምድር አንዲት ቡቃያስ እንኳን
ማብቀል እንደማትችለው ማለት ነው፡፡ ምድር እነዚያን ቡቃያዎች ስታበቅል አስቀድሞ ተዘርቶባት አይደለም፡፡
ውኃይቱም እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸውን ፍጥረታት ያስገኘችው አስቀድሞ እነዚህን ፍጥረታት ሊያስገኝ የሚችል
ንጥረ ነገር በውስጧ ስለያዘች ሳይኾን እንዲሁ እግዚአብሔር ስላዘዛቸውና እነዚህን ፍጥረታትንም የማስገኘት ዓቅም
ስለ ሰጣቸው እንጂ፡፡ በሌላ አነጋገር፥ የእነዚህ ፍጥረታት ዋናው መገኛቸው ቃለ እግዚአብሔር ነው፤ ቃሉ ኃይልን
የተመላና ሕይወትን የሚያስገኝ ቃል ነውና፡፡
https://www.printfriendly.com/p/g/rXzeUv 3/5
4/20/2021 መቅረዝ ዘተዋሕዶ
የረቡዕ ፍጥረታት
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ትምህርተ ሃይማኖት - ክፍል ዐሥራ ስድስት
ቸሩ እግዚአብሔር በዚህ በአራተኛው ቀን ሦስት ፍጥረታትን ማለትም፡- ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ፈጥሯል፡፡
የፀሐይ አፈጣጠር ከእሳትና ከነፋስ ሲኾን የጨረቃና የከዋክብት ደግሞ ከውኃና ከነፋስ ነው፡፡
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ምናልባት ልንጠይቀው የምንችል ጥያቄ፡- “በመጀመሪያው ቀን ላይ ብርሃን ተፈጥሯል፡፡ ሌላ
ብርሃን ታዲያ ለምን አስፈለገ?” በማለት ይጠይቅና እርሱ ራሱ እንዲህ ሲል ይመልስልናል፡- “አስቀድሞ የተፈጠረው
የብርሃን ተፈጥሮ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ቀድሞ ለተፈጠረው ብርሃን መሣሪያ ትኾን ዘንድ ፀሐይ ተፈጠረች፡፡ ኩራዝ
ማለት እሳት ማለት አይደለም፡፡ እሳት የማብራት ባሕርይ አለው፡፡ ኩራዝን የሠራነው ያ እሳት ሥርዓት ባለው መልኩ
በጨለማ ላይ እንዲያበራልን ነው፡፡ እነዚህ የብርሃን አካላትም የተፈጠሩት ልክ እንደዚሁ አስቀድሞ የተፈጠረውን
ብሩህና ጽሩይ ብርሃን መሣሪያ እንዲኾኑ ነው” /አክሲማሮስ፣ ክፍለ ትምህርት 6 ቍ. 2/፡፡
ዘመነ ጽጌ
የማክሰኞ ፍጥረታት
https://www.printfriendly.com/p/g/rXzeUv 4/5
4/20/2021 መቅረዝ ዘተዋሕዶ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 25 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን!!!
ትምህርተ ሃይማኖት - ክፍል ዐሥራ አምስት
ሦስተኛይቱ ዕለት ዕለተ ሠሉስ ትባላለች፡፡ ሠሉስ ማለት ለፍጥረት ሦስተኛ ማለት ነው፡፡ በአማርኛ ማግሰኞ
ትባላለች፤ የሰኞ ማግስት እንደ ማለት ነው፡፡ በተለምዶ ግን ማክሰኞ እንላለን፡፡ እኛም አንባብያንን ግራ ላለማጋባት
በዚህ አካሔድ እንቀጥላለን፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን ሰኞ ላይ ውኃዉን ከሦስት ከፍሎ ምድርን ግን ከውኃ እንዳልለያት ተነጋግረን ነበር፡፡ በዚህ
ዕለት ማለትም ማክሰኞ ላይ ግን በዚህ ዓለም የነበረውን ውኃ ወደ አንድ ስፍራ እንዲሰበሰብ አድርጓል፡፡ ውኃው
ሲሰበሰብም ምድር ተገልጣለች፡፡ ነገር ግን ተገለጠች እንጂ ቡቃያ አልነበረባትም፡፡ በመኾኑም በምሳር የሚቈረጡ
(እንደ ዋንዛ፣ ዝግባ፣ ወዘተ)፣ በማጭድ የሚታጨዱ፣ በጥፍር የሚለቀሙ (እንደ ሎሚ፣ እንደ ትርንጎ ያሉ)
አዝርእትን፣ አትክልትንና ዕፅዋትን እንድታስገኝ አዘዛት፡፡ ምድርም የቃሉን ትእዛዝ አድምጣ እነዚህን ሦስት
ፍጥረታትን አምጣ ወለደች /ዘፍ.1፡12-14/፡፡
https://www.printfriendly.com/p/g/rXzeUv 5/5