Professional Documents
Culture Documents
የአካል ሶስትነት
አብ በተለየ አካሉ ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣
ፍጹም መልክእ አለው
ወልድም በተለየ አካሉ ፍጹም አካል፣ ፍጹም
ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው
መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ ፍጹም አካል፣
ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው
ይኽነንም ምስጢር ሊቁ አቡሊዲስም
“ባሕርያቸው በእውነት አንድ ሲኾን በመልክእ፣
በአካል ፍጹማን የሚኾኑ ሶስት ገጻት እንደኾኑ
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን”
በማለት በጥልቀት ገልጾታል
ልዩ ሶስትነት
የአካል ሶስትነት
የሥላሴ አካላቸው ምሉእ በኲለሄ፣ ስፉሕ፣ ረቂቅ
ሲኾን ዳር ድንበር፣ ወሰን፣ ዳርቻ የለውም
በመጽሐፈ ቀሌምንጦስም ምሉእነቱን ሲገልጽ
“ኹሉን እኛ እንሸከመዋለን እንጂ እኛን
የሚሸከመን የለም፤ ከኛ በላይ ከኛም በታች ቦታ
የለም፤ የባሕርያችን ምልአት ኹሉን ይወስናል
እንጂ የሚወስነው የለም”
ሊቁ አረጋዊ መንፈሳዊ ስለ ርቀታቸው
“የመንፈሳዉያን የኅሊናቸው ርቀት በአንተ ዘንድ
ካለው ረቂቅነት አንጻር እንደ ሥጋ የገዘፈ ነው”
በማለት አስተምሯል
ልዩ ሶስትነት
የአካል ስም ሥስትነት
አካላት በሥላሴ ዘንድ ስም አላቸው
ይኽም የሥላሴ የአካል ስም አካል ቀድሞት እንደ
ሰው ስም በኋላ የተገኘ አይደለም
“ሰብእ” (ሰው) ማለት ስሙ ከአካሉ አካሉ
ከስሙ ሳይቀድም እንደ ተገኘ የሥላሴም ስማቸው
ከአካላቸው፤ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም
ቅድመ ዓለም የነበረ ስም ነው እንጂ ድኅረ ዘመን
የተገኘ አይደለም
ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ገባሬ መንክራት "ደግሞ አብ
ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንላለን ግን አካላት
ተቀድመው ተገኝተው እሊኽ ስሞች ኋላ
የተጠሩባቸው አይደሉም፤ ሰው ማለት ኋላ የወጣ
ስም አይደለም ባሕርዩ ነው እንጂ”
ልዩ ሶስትነት
ቅዱስ አግናጥዮስም “አብም አብ ነው ወልድን
አይደለም መንፈስ ቅዱስንም አይደለም፤ ወልድም ወልድ
ነው አብን አይደለም መንፈስ ቅዱስንም አይደለም፤
መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው አብን አይደለም
ወልድን አይደለም፤ አብ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን
ለመኾን አይለወጥም፤ ወልድም አብንና መንፈስ ቅዱስን
ለመኾን አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም አብንና ወልድን
ለመኾን አይለወጥም”
የአካል ግብር ስም ሥስትነት
ቅዱስ አግናጥዮስም “አብ መቸም መች ወላዲ ነው
እንጂ ተወላዲ ሠራፂ አይደለም፤ ወልድም ተወላዲ
ይባላል እንጂ ወላዲ ሠራፂ አይባልም፤ መንፈስ ቅዱስም
ሠራፂ ይባላል እንጂ ወላዲ ተወላዲ አይባልም፤ አብ
ሠራፂ ተወላዲ ወደመሆን አይለወጥም፤ ወልድም ወላዲ
ሠራፂ ወደመሆን አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም ወላዲ
ተወላዲ ወደመሆን አይለወጥም”
የባህርይ አንድነት
ሥላሴ በባህርይ አንድ ናቸው
በሥላሴ ዘንድ መበላለጥ የለም የአንድነታቸው
ማዕከል አብ ነው
ብርሃን ከብርሃን እንደሚወለድ ይህ ዓለም
ከመፈጠሩ አስቀድሞ ወልድ ከአብ ያለ እናት
ተወለደ አባቱ አብ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ
እሱም እውነተኛ አምላክ ነው አብ ወለደው እንጂ
አልፈጠረውም አብ ብርሃን እንደ ሆነ ወልድ
ብርሃን ነው አብ ከባህርይው ወለደው ከአብ
ባህሪይ የተወለደ በባህሪይ አብን የሚመስለው
/የሚተካከለው/ ነው
የባህርይ አንድነት
ስለ ሥላሴ በባህርይ ስንናገር ግብረ ባህርይዎን
ለይተን መናገር ይገባናል
ቅዱስ ሳዊሪያኖስ ዘ ገብሎን “ሁሉን ቻይ
እግዚአብሔር አንድ ነው ፡፡ መ. ኢዮ. ፵፪፡፩-፪
‹‹ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደሆንህ
የሚሳንህም እንደሌለ ዐወቅሁ ፡፡›› ማር. ፱፡፳፫
‹‹ ቢቻልህ ብለሃል ብታምንስ ለሚያምን ሁሉ
ይቻላል ›› መ.ኢዮ. ፴፪፡፰ ‹‹ ሁሉን የሚችል
የእግዚአብሔር መንፈስም ያስተምራል ››
በማለት አንድነቱን ያስረዳል
የባህርይ አንድነት