You are on page 1of 45

ምዕራፍ አንድ

ነገረ ማርያም

ወደ ነገረ ማርያም ትምህርት ዘልቆ ከመግባት አስቀድሞ ነገረ ማርያም ማለት ምን ማለት እንበሆነ ከማወቅ መጀመር
ተገቢ በመሆኑ የቃሉን ፍቺ በመስጠት እንጀምራለን።

ትርጉም:- ነገረ ማረያም ከሁለት ቃላት የተገኘ /የተሰናነለ/ ነው።


 ነገር:- የሚለው ቃል በቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ የአንድን ትምህርት መግለጫ አጉልቶ የሚያሳይ ሆኖ ያገለግላል።
 ማርያም:- ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የተሰጠ ክቡር ስም ነው።
ነገረ ማርያም:- ሲል በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በኩል ለሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጠውን ሁሉ
የምነማርበት ትምህርት ነው። በዚህም ትምህርትም በሰው ልጆች የመዳን ምሥጢር ውስጥ የእመቤታችን የድንግል ማርያም
አስተዋጽኦ:- ከዚህም የተነሣ የተሰጣት ጸጋ፣ ክብርና ቅድስና ስለዚህም እኛ ልናቀርብላት የሚገባን ክብር፣ ስግደት፣ ምስጋና ወዘተ
ምን እንደሆነ ተገቢ ዕውቀት እናገኛለን፤ የሚጀመረውም ከስሟ ትርጓሜ ነው።

ስመ ድንግል ማርያም ትረጓሜ በቤተ ክርስቲያናችን

ማርያም የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ማሪሃም /ሚርያም/ ሲሆን ትርጉሙም እመ ብዙኃን /የብዙዎች እናት/ ማለት እንደሆነ።
(ዘፍ. 18፥18)

ማርያም የሚለውን ስም አበው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በምሥጢራዊ ዘይቤ እንደሚከተለው አስቅምጥምጠውታል።

ሀ. ማረያም ማለት መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት /ወደ መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ/ ማለት ነው። ምክንያቱም ከሕገ
እግዚአብሔር የወጣው ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቂተው አዳም ወደ ቀደመ ክብሩ እንዲመለስ ምክንያተ ድኅነት የሆነችው
ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ናትና። ወደ መንግሥተ ሰማ መርታ የምታስግገባ ትባላለች።

የእመቤታችንን አማላጅነት ተስፋ ሳያደርግ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት የሚቻለው የለምና።

"አልባ ጸሎት፣ ወአልቦ ተነሳኤ፣ እንበሌኪ ማርያም ዘየዐርግ ሉዓሌ /ድንግል ማርያም ሆይ ያለ አንቺ አማላጅነትና
ተራዳኢነት ወደ ላይ /ወደ ሰማይ/ የሚያርግ ጸሎትና ልመና የለም" እነዳለ ሊቁ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ።

ለ. ማረያም ማለት ጸጋ ወሀብት ማለት ነው።

እመቤታችን ወላጂቿ ለጊዜው በመምከናቸው በሰው ዘንድ ተንቀውና ተዋርደው እነርሱም አዝነው ይኖሩ ከነበሩ ታላቅ ሀብት
ጸጋ ሆና ተሰጥታለች፤ ፍጻሜ ግን አማላጅነቷን አውቀው ቃል ኪዳኗን አምነው ከሚመጡ ምእመናን ሁሉ ሀብት፣ ጸጋ ሆና
ተሰጥታለች። ይህም እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው በሚለው የመልአኩ ንግግር ታውቋል። ሉቃ.1፥28-39። ምክንያቱም:-

 በበደሉ ምክንያት ከጸጋ እግዚአብሔር ተራቁቶ በእግረ አጋንንት ይጠቀጠቅ የነበረው አዳን ጸጋው ተመልሶለት ሀብተ
መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ ያደረገው ነእመቤታችን በኩል ነውና። አዳም ከገንነት በተባረረ ጊዜ ተስፋው አንቺ ነሽ ብሎ አባ
ሕርያቆስ በቅዳሴው ያመሰገናትም ለዚህ ነው።
 አሁንም በእግዚአብሔር ወልድ የባሕርይ አምላክነት የሚያምኑ ምእመናን አምላካዊ ጸጋውነና ሀብቱን ከማግኘት
መሠረት የሚያደርጉት ወላዲተ አምላክን ነው። ምክንያቱም "ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር
በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን:- አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ አላት ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩን:- እናትህ እነኋት አለው"።
ዮሐ. 19፥25 በማለት በመስቀሉ ዙፋንነት የጸጋና የሀብት ድሀ የነበረውን የሰው ልጅ ሁሉም ጸጋና ሀብት ወደ ተሰጣት
እመቤታችን እንዲመለከት የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆነ። እመቤታችንን ለዚህ ሁሉ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ያበቃት
ምንድነው ከሚል ጠያቂ የአምላክ እናት ሆና በመመረጧ ነው።(መዝ. 131፥13-14) የእግዚአብሔር ጸጋ የተገለጠው
በእርስዋ ላይ ነውና። (ሮሜ. 5፥18)

ሐ. ማረያም ማለት ፍጽምተ ሥጋ ወነፍስ / በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች፣ ፍጽምት/ ማለት ነው። ከነቢብ፣ ከገቢር፣
ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና እናትነትን ከድንግንና፣ ድንግልናን ከእናትነት ጋር አስተባብራ ይዛለችና።

እግዚአብሔር በባሕርዩ ፍጹም ስለሆነ፤ ለምሥጢረ ሥጋዌ (ለማዳን) ጉዞውም ሰው ይሆንባት ዘንድ በመለኮታዊ ጥበቡ
የመረጣት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምነት ትሆን ዘንድ ይገባልና በነስም በሥጋም ፍጽምት አደረጋት።

በመሆኑም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ማርያም የሚለውን ስመ ተጸውኦ ፍጽምተ ሥጋ ወነፍስ /በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ
ነፍስ ፍጽምት የሆነች/ ብለው ተረጎሙት። ንጽሐ ሥጋን፣ ንጽሐ ነፍስንና ንጽሐ ልቡናን አንድ አድርጋ አስተባብራ ይዛለችና።

ፍጽምት ማለት ምንም ዓይነት እንከንና ጉድነት የሌለባት ንጽሕተ ንጽሐን ቅድስተ ቅዱሳን አባማዊ በደል ያልነካት
ማኅድረ እግዚአሔር ትሆን ዘንድ የተገባት ማለት ነው።

መ. ማርያም ማለት መልዕልተ-ፍጡራን መታህተ ፈጣሪ /ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ያለች/ ማለት ነው።

 ከፍጡራን በላይ ስንል ምን ማለታችን ነው?


 ፍጡራን የምንላቸውስ ምንና ምን ናቸው?

በሥነ ፋትረት ህግ መሠረት ከዕለተ እሑድ ጀምሮ እስከ ዕለተ ዓርብ የተፈጠሩ ሁሉ ፍጡራን ይባላሉ። ከነዚህም ፍጡራን
መካከል እግዚአብሔር አክብሮና አልቆ የፈጠራቸው ሰውንና መላእክትን ነው።

እመቤታችንን ከፍጡራን በላይ ስንልም ከሰው ልጆችም ሆነ ከመላእክት የምትልቅ የምትልቅ የምትከብር ማለታችን ነው፤
ምክንያቱም በቅዱሳን መላእክትም ሆነ በቅዱሳን አባቶቻችን እግዚአብሔር በረድኤት አድሮባቸው ይኖራል።

እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ በፍጹም ተዋህዶ ዓለምን ከማዳን ምሕረቱን
የገለጠባት እመ መሐሪ በመሆኗ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ከእርሷ በቀር ማንም የለም።

 ከመላእክት እንደምተበልጥ "ጸጋን የተመላሽና የደስታ መገኛ ሆይ . . . ዓይኖቻችቸውን ብዙዎች ከሆኑ ከኪሩቤልና
ክንፎቻቸው ስድስት ከሆኑ ከሆኑ ከሱራፌል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። እነዚህያ ፊታቸውን ይሸፍናሉ። .
. . ከልጅሽ መለኮት ከሚወጣው እሳት ይድኑ ዘንድ፣ አንቺ ግን ከመለኮት ማደሪያ ሆንሽ የመለኮት ባሕርይም
አላቃጠለሽም። የእሳት ነበልባልን ተሸከምሽ።" በማለት ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድ የሰጠው ምስክርነት
ያስረዳል።
 ከሰው ልጆችም እንደምትበልጥ "ከቅዱሳን ክብር የእመቤታችን ክብር ይበልጣል አካላዊ ቃልን ለመቀበል በቅታ
ተገኝታለችና መላእክት የሚፈሩትን ትጉኃን በሰማይ የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኅፀንዋ ቻለችው።"
በማለት ቅዱሳ ኤፍሬም በረቡዕ ውዳሴ ማርያም ከመላእክትም፣ ከደቂቀ አዳምም ከፍጡራን ሁሉ በላይ መሆንዋን
መሰከረ።

ሠ. ማርያም ማለት እግዝእተ ብዙኃን /የብዙዎች እመቤት/ ማለት ነው።

 ከአዳምና ሔዋን ውድቀት በኋላ የሰው ዘር በሙሉ በዲያቢሎስ የኃጢአት አገዛዝ ቀንበር ሥር ወድቆ ነበር የዚያ
ዘመን ፍዳ መገለጫም አዳም የዲያብሎስ ወንድ ባሪያ ነው፣ ሔዋን የዳያቢሎስ ሴት ባርያ ናት የሚለው የመከራ
ማኅተም ነበር።
የዚህ ጊዜ (የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ) ፍጻሜው ሲድርስ ከመልአኩ እመቤታችን የሰማችው ድምፅ "ከሴቶች
ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና" በማለቱ በሔዋን ምክንያት
የገባ ስሕተትና መርገም ሁሉ በልጇ ይሻር ዘንድ እግዚአብሔር ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ ሰው መሆኑን ነገረን።
የሁኑም ጌታ እግዚአብሔር ከእርስዋ በመሆናቸው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እመቤታቸው ናት።

መልአኩ ቅድስ ገብርኤል እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነወና ባለው ቃል መሠረት ፍጥረትን ሁሉ ካለመኖር ወደ
መኖር አምጥቶ የፈጠረው፣ የሚመግበው፣ የሚያስተዳድረው፣ ኋላም የሚያሳልፈው አምላክ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ
በኅቱም ድንግልና ከእረስዋ ስለተወለደ የእግዚአብሔር እናት፣ የፍጥረት ሁሉ እመቤት መባል የተገባት ሆነች።

ረ. ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ማለት ነው።

አካላዊ ቃል በእመቤታችን ማኅፀን አድሮ ከሥጋዋ ሥጋ ከነ ፍስዋ ነፍስ ነሥቶ መለኮትን ከትስብእት (ከሥጋ)
ትስብእትን ከመለኮት አዋሕዶ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ሆኖ ስለተገከጠባት ከአምላክ ሰው የመሆኑ ምክንያት፣
ለሰው የመዳኑ ምክንያትናትና ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ትባላለች። የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔርንም ይቅርታ
ወደ ሰው በማድረስ ድኅነት ሥጋ ድኅነት ነፍስ፣ በረከት ነፍስ እያማለደች ታሳጣለችና።

የእመቤታችን ሌሎች ስሞች


 ጽዮን

እመቤታችንቅድስትድንግልማርያም«ጽዮን»ተብላትጠራለች።ምክንያቱም ጽዮን ማለት አምባ መጠጊያ ማለት


እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም ፦ለነፍስናለሥጋ ፥ለኃጥአንና ለጻድቃን ፥አምባ መጠጊያ ናትና።ቅዱስ ዳዊት፦እግዚአብሔር
ጽዮን መርጧታልና፥ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤መርጫታለሁና በዚህች
አድራለሁ።» ያለው እመቤታችንን ነው።መዝ136፥13።ምክንያቱም፦ለእናትነት መርጦ ያደረው በእርሷ ማኅፀን ነውና።
«ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤» ማለቱም፦እርሱ የዘለዓለም አምላክ እንደሆነ፥ እርሷም ለዘለዓለም ወላዲተ አምላክ ተብላ
እንደምትኖር የሚያመለክት ነው።በሌላ ምዕራፍም፦የወደደውን የጽዮንን ተራራ ፥መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ።
ለዘለዓለምም በምድር ውስጥ መሠረታት።» ብሏል።መዝ፸፯፥፷፰።

ጽርሐአርያም ከሰባቱ ሰማያት አንዱ ነው። በዚያ፦ኪሩቤል የሚሸክሙት፥ ሱራፌል የሚያጥኑት የእግዚአብሔር የእሳት
ዙፋን አለ። ዙፋኑም በሰባት የእሳት መጋረጃዎች የተጋረደነው።ኢሳ፮፥፩፣፪ኛሳሙ፬፥፬፣ሕዝ፩፥፭-፲፰፣ራእ፬፥፮-፱።
ቅዱስያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ድርሰቱ፦እመቤታችንን፦«በሰማይ ባለ ጽርሐአርያም ፈንታ በምድር ላይ አርያምን ሆንሽ፤
» ብሏታል።ከዚህም፦ቅዱስ ዳዊት «የወደደውን የጽዮንን ተራራ፥መቅደሱን እንደአርያም ሠራ፤» ያለው ለእመቤታችን
እንደሆነ እንረዳለን።

ድንግልናዋን በተመለከተም፦ኢየሩሳሌምሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥ጽዮንም ሆይ አምላክሽን አመስግኚ፤


የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፤» ብሏል።መዝ፩፻፵፯፥፩።ይህም፦ለጊዜው ለከተማይቱ ሲሆን ለፍጸሜው
ለእመቤታችን ነው።ይኸውም ይታወቅ ዘንድ ኢየሩሳሌም፥ጽዮን፥የተባለች እመቤታችን ቅድስትድንግልማርያም፦
በመንፈስቅዱስ ግብር አምላክን በድንግልና በፀነሰች ጊዜ፦ «ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች።ልቡናዬም በአምላኬ
በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች።» በማለት አመስግናለች። ሉቃ፩፥፵፮። የእርሷ ሰውነት፦ የሥጋን ንጽሕና፥የልብን
ንጽሕና፥ የነፍስን ንጽሕና፥ አስተባብራ አንድ አድርጋ ይዛ የተገኘችናት። «የዶጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤»
የተባለውም ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን ነው። እመቤታችን፦ ቅድመ ወሊድ፥ ጊዜወሊድ፥ ድኅረወሊድ ድንግል ናትና።
ይኽንንም ነቢዩ ኢሳይያስ፦ «እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ወንድልጅም (ወልድን) ትወልዳለች ፤ስሙንም አማኑኤል ብላ
ትጠራዋለች።» በማለት ተናግሯል። ኢሳ፯፥፲፬። ነቢዩ ሕዝቅኤልም፦ «ወደ ምሥራቅም ወደ ሚመለከተው
በስተውጭ ወዳለው በር መለሰኝ ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ
አትከፈትም፤ (ድንግል ማርያም ለዘለዓለም በድንግልና ጸንታ ትኖራለች)። ሰውም አይገባባትም፤ የእስራኤል አምላክ
እግዚአብሔር ገብቶባታልና ተዘግታ ትኖራለች። (አምላክ በማኅፀኗ ተፀንሶ፥ ከእርሷ ተወልዷልና በድንግልና ጸንታ
ትኖራለች)።» ብሏል።ሕዝ፵፬፥፩-፪።

ደብረጽዮንና ታቦተጽዮን ምሳሌዋ የሆኑላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረላት፦ ሰው
ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል። ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ድኅነተ
ዓለምን በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ፥ ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስን፦ «እነኋትእናትህ፤» ብሎታል። ዮሐ፲፱፥፳፭።

 ማኅደረ መለኰት

ማኅደር የሚለው፦ በቁሙ ሲተረጐም፦ ማደሪያ ፥ሰፈር ፥ቤት፥ በኣት፥ የመኝታ ቦታ ፥ እልፍኝ ፥በታላላቅ ቤት
ውስጥ የሚሠራ ልዩ ልዩ ክፍል ፥ ደጃፍና መስኮት ያለው ፥ድንኳን ማለት ነው። ቃሉ ማደሪያነት ላለው ቦታ ኹሉ የሚነገር
ነው።
መለኰት፦ ማለት ደግሞ፦ አምላክነት ፥ ፈጣሪነት ፥ አምላክ መኾን ፥ ፈጣሪ መኾን ፥ ወይም የአምላክ ባሕርይ
፥ ጠባይ፥ ኹኔታ ማለት ነው። በአጠቃላይ አነጋገር፦ አገዛዝን ፥ጌትነትን ፥ ባሕርይን ፥ አምላክነትን ፥ ክብርን ፥ ስምን
ያመለክታል።

አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም እመቤታችንም ማኅደረ መለኰት ሆና መመረጧን አድንቋል።«መጠንና


መመርመር የሌለበት እሳተ መለኮት በሆድሽ አደረ፤ በምድራዊ እሳት እንመስለው ዘንድ አይገባም፥ ለእሳትስ መጠን
አለው ፥ ልክም አለው፤ መለኮት ግን ይህን ያህላል ፥ ይህንንም ይመስላል ፥ ሊባል አይቻልም። ለመለኮት እንደ ፀሐይና
ጨረቃ ክበብ ፥እንደ ሰውም መጠን ያለው አይደለም ፥ ድንቅ ነው እንጂ፤ የሰው ሕሊና የመላእክትም አእምሮ
በማይደርስበት በአርያሙ የሚኖር ነው እንጂ፤ ለመለኮት ወርድና ቁመት ፥ ላይና ታች ፥ ቀኝና ግራ ያለው አይደለም ፥
ግዛቱ (ጌትነቱ) በአገሩ ሁሉ ነው እንጂ፤ ለመለኮት በላይ ጠፈር በታችም መሠረት ያለው አይደለም ፥ ጠፈሩ እርሱ
መሠረቱም እርሱ ነው እንጂ፤ ለመለኮት ከምድር ከውስጧ የሆነውን ያነሣ ዘንድ ፥ ማጎንበስ ራስንም ዝቅ ማድረግ
ያለበት አይደለም ፥ለጴጥሮስ እንዳሳየው ሁሉ በእጁ የተያዘ ነው እንጂ፤» ብሏል።ስለዚህም የመለኮት ማደሪያ ናትና
ማኅደረ መለኰት እንላታለን
 እመ ብርሃን
የብርሃን እናት ማለት ነው አምላካችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋወው ‘’እኔ የአለም ብርሃን ነኝ
ብሏል(ዮሐ 8፤12) ቅዱስ ዮሓንስ ወንጌላዊው በራእዩ ሴት ብርሃን ተጎናጽፋ ጨረቃ ተጫምታ 12 ከዋክብት የተቀረጸበት
ዘውድ ደፍታ ተገለጸችልኝ ብሏል(ራእ 12፤1)
ብርሃን የተባለ መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ስለዚህ የእርሱ እናት ደግሞ ድንግል ማርያም ናትና እመ ብርሃን
እንላታለን።
 ወላዲተ አምላክ
ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህሪይ አንድ ባህርይ የሆነ የተዋህዶ የከበረ የወልደ እግዚአብሄር የኢየሱስ ክርስቶስ
በስጋ እናት ለመሆን ከሴቶች መካከል የተመረጠች እርሷ በመሆኗ ነብዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ እንደተናገረው ከእርሷ
የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ነው።(ኢሳ 7፤14)
‘’አማኑል’’ማለትም የእግዚአብሄር መላእክ እንደተረጎመው እግዚአብሄር ከስጋችን ስጋን ከነፍሳችን ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ
ማለት ነው(ማቴ1፤23) የ እስክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ “አማኑል የ ባህርይ አምላክ እንደሆነ ንጽይት
ድንግልም አምላከን የወለደች እንደሆንች የማያምን ሰው ቢኖር የተወገዘ ይሁን’’ በማለት ካወገዘ በኋላ ‘’ዳግመኛ
በኋላ ዘመን ቅድስት ድንግል እርሱን በስጋ ወለደችው ስለ እኛ ሰው የሆነ የእግዚአብሄር’’ ስለዚህም ቅድስት ድንግል
ወላዲተ አምላክ እንላታለን በማለት ወላዲተ አምላክ መሆኗን መስክሯል።
 ኪዳነ ምህረት
ኪዳን ውል ስምምነት መሓላ የሚል ትርጉም ሲኖረው ምህረት፣ቸርነት፣ነጻ ስጦታ፣ፍቅርን የሚያመለክት ኃይለ ቃል
ሲሆን ይህ ስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታችን ከአምላካችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
ስምሽን የጠራ እምርልሻለው የሚል ስል ኃጥአን የተሰጣት የምህረት ቃልኪዳን ማሳሰቢያ ነው።(መዝ 88፤
3)ከመርጥኳቸው ጋር የምህረት ቃል ኪዳኔን አደርግሁ እንዲል።
የልደቷ ነገር
ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የነገረ ድኅነት ምሥጢር ተገልጦለት ያለፈውን ያለውን እና የሚመጣውን አገናዝቦ
ሲናገር ፡- « የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ. እንደ ሰዶም በሆንን . እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር ፡
፡ » ብሏል፡፡ ኢሳ 1.9 ፡፡ ይህም ለፍጻሜው ለእመቤታችን የተነገረ ትንቢት ነው ፡፡ ከዚህም በበለጠ ኹኔታ ትርጓሜ
የማያሻው ደረቅ ትንቢት ሲናገረም፡- « ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች. ወልድንም
ትወልዳለች. ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ፡፡» ብሏል ኢሳ 7.04 ፡፡
እነ ኢሳይያስ በጥንተ አብሶ ምክንያት ፡- « ሁላችን እንደ ርኵስ ሰው ሆነናል ፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም
ጨርቅ ነው፤ » ኢሳ 64.6፤ ቢሉም ፡- እግዚአብሔር ባወቀ ጥንተ አብሶ ፈጽሞ ባልደረሰባት በእመቤታችን ይመኩ.
ተስፋም ያደርጉ ነበር ፡፡ ለዚህም ነው፡- «እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ . . . ፤» ያሉት ፡፡ እመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ገና ከጧቱ ንጽሕት ሆና የተዘጋጀች ጥንተ መድኃኒት ናትና ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ፡-
« መመኪያ አክሊላች ጥንተ መድኃኒታችን የንጽሕናችን መሠረት ፤» እያለ ያመሰገናት ለዚህ ነው፡፡ በሌላም ስፍራ ቅዱስ
ዳዊት ስለልደቷ ነገር ሲገልጽ መሰረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው (መዝ 86፤1)ብሎ ከአዳም ጀምሮ አብርሃምን፣ዳዊትን፣
ሰለሞንን ወዘተ እስከ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷን ታሪክ ከዚህ እንደሚከተለው እንመልከታለን።
በኢየሩሳለም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ የሚኖሩ አካባቢ በቅዱስ ጋብቻ ተወስነው የሚኖሩ ጰጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ
ደጋግ ሰዎች ነበሩ።ይሁን እንጂ የሌላቸው መካኖች በመሆናቸው ያፈሩትን ሃብት የሚወርስ ልጅ ባለምመውለዳቸው
ያዝኑ ይተክዙ ነበር።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ስለሃብታቸው ብዛት በሰፊው ከተንጋገሩ በኋላ ጰጥርቃ ተስፋ በመቁርጥ ‘’እህቴ ሆይ ይህ ሁሉ
የሰበሰብነው ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን የሚወርሰን ልጅ የለንም ምክንያቱም አንቺ መካን ነሽ እኔ ደግሞ ከአንቺ
በቀር ሴት አላውቅም” አላት።ቴክታም ‘’ጌታዬ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንትም እንደኔው ትቀራለህን
ከሌላ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እርሱም’’እንዲህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንደማላስበው አምላከ
እስራኤል ያውቃል’’አላት።
ከዚህ ሁሉ ውይይት በኋላ ቴክታ ለጰጥርቃ እንዲህ አለችው። ‘’እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትናንትና
ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድና እስከ 7 ትውልድ ድረስ ሲዋለዱ
7ኛይቱ ጨረቃን ስትወለድ አየሁ’’ አለችው በዚህ ተደንቀውና እግዚአብሔርን አመስግነው ወደ ህልም ፈቺ ሄደው
የሆነውን ሁሉ ነገሩት። ያም ህልም ፈች እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷቸኋል ብሎ ህልማቸውን እንዲህ ሲል ፈታላቸው።
7 እንስት ጥጆች ትወልዳላቹ፤7ተኛይቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላዕክት የከበረች ደግ ፍጥረት
ትወልዳላቹ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም ጊዜ ይፍታው አላቸው።በዚያም ወራት ቴክታ ጸነሰች ሴት ልጅንም ወለደች
ስሟንም ሔመን አሏት በመቀጠልም የሚከተሉት በተከታታይ ተወለዱ።
ሔመን ዴርዴን ወለደች ፣ዴርዴም ቶናን ወለደች፣ቶናም ሲካርን ወለደች፣ሴትናም ሄርሜላን ወለደች፣ሄርሜላም
ማጣትን አግብታ ከ አንስተ አለም ተመርጣ የአምላክ እናት ለመሆን የበቃችውን ቅድስት ሃናን መስከርም 7 ቀን ወለደች
። ሃናም በስርዐት አደገች ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት የተወለደውን ክቡር ጻድቅ ኢያቄምን አገባች።
እነርሱም በዚህ የተቀደሰ ትውልድ አልፈው ለድህነተ አለም የመርጣትን ድንግል ማርያምን ወለዱ።እናት እና አባቷ
ጻድቃን ቢሆኑም ድሆች ግን ነበሩ።መካንነታቸውን ሰበብ አርገው ህገ ጋብቻቸውን ያላሳደፉ ንጹሃን ናቸው።
አምላካችንም ንጽህናቸውን ተመልክቶ ከብዙ ደጅ ጥናት በኋላ ድንግል ማርያምን ሰጣቸው።እመቤታችን ነሐሴ 7
ተጽንሳለች በተጸንሰች ጊዜም ብዙ ተአምራት ተደርጓል።የቅድስት ሃናን ማህጸን እየዳበሱ ዕውራን በርተዋል፣ጎባጦች
ቀንተዋል ብዙ በሽተኞች ተፈውሰዋል።ሞቶ የነበረ ሳሚናስ የሚባል የቅድስት ሃና የአጎት ልጅ የምትሆን ድንግል ማርያም
በማህጸን መላእክት ክብሯን ሲናገሩ መስማቱን መሰከረ።በዚህ ጊዜ አይሁድ ቀንተው ኢያቄምናሃና ሊገሏቸው
በጠላትነት በተነሱ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ ወስዷቸው በዚያም እመቤታችን ድንግል ማርያምን
ግንቦት 1 ቀን ተወልዳለች ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባቷ
ቅዱስ ኢያቄምናቅድስት ሃና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በንጽህና በቅድስና በቤታቸው 3 አመት ካሳደጓት
በኋላ ስዕለት ተስለው ስለነበር የወለዷት ‘’የሰጠ ቢነሳ የለበት ወቀሳ ‘’ብለው ለቤተ እግዚአብሄር የሚያስፈልገውን እጅ
መንሻ ይዘው እመቤታችንን ለቤተ እግዚአብሄር እንድታገለግል ሊሰጧት ወደ ቤተ መቅደስ አመጧት። ካህኑ ዘካሪያስም
ደውል መትቶ ህዝቡን ሰበሰባቸው።ህዝቡም ሲሰበሰብ ‘’ቀድሞ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ስዕለት ይመጣ የነበረው
ወርቅ፣ብር ፣በሬ፣በግ ነበር።አሁን ግን ሰው ነው። ይህቺን ብላቴና ተቀብለን ምን እናበላታለን?፣ምን እናጠጣታለን? የት
እናኖራታለን? ብሎ ህዝቡን ጠየቃቸው።በዚህ ነገር ሲጨነቁ አምላካችን ልዑል እግዚአብሄር መላእኩን ቅዱስ ፋኑኤልን
ኅብስት ሰማያዊ ጽዋ ሰማያዊ አስይዞ ወደ እነርሱ ላከው ከሊቀ ካህኑ ጀምሮ ሌሎች እደየማዕረጋቸው ይህንን
እንቀበላለን ብለው ሲጠጉ ለእነርሱ ስላልመጣ ከእነርሱ ራቀ።በኋላ እመቤታችንን ከሰው ለይተው ለብቻዋ ባቆሟት ጊዜ
ከሰማይ ወርዶ አንድ ክንፉን ጋርዶ እመቤቴ ደጅ ባስጠናሁሽ ይቅር በይኝ ብሎ መግቧት አርጓል።የምግቧ ነገር ከተያዘ
ከሰው ጋር ምን ያጋፋታል ቤተ መቅደስ ትኑር ብለው በታህሳስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስግብተዋል።በዚያም ህብስት
ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየተመገበች መላዕክት እያረጓጓት ሀር እና ወርቅ እያስማማች እየፈተለች ቤተ መቅደሱን
እያገለገለች 12 አመት ተቀምጣለች። አባ ህርያቆስም ይህንን ሲያጎላ በድርሰቱ በቅዳሴ ማርያም እንዲ እንዲህ ብሏል ‘’
ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ ድንግል
ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች እድፍ ጉድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንጽህና በቅድስና በቤተ
መቅደስ ኖርሽ እንጂ’’እንዲል ቅዳሴ ማርያም ።
የእመቤታችን እና የቅዱስ ዮሴፍ ዝምድና

ቅዱስ ዮሴፍ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የቅርብ ዘመዷ ነው። ቅዱስ ማቴዎስ የአበውን ልደት
እየተናገረ መጥቶ ወደ መጨረሻው ላይ፦ «አልዓዛርም ማትያንን ወለደ፤ ማትያንም ያዕቆብን ወለደ። ያዕቆብም
ክርስቶስ የተባለ ጌታ ኢየሱስ ከእርሷ የተወለደ የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።» ብሏል። ለቅዱስ ዮሴፍና
ለእመቤታችን የሥጋ ዝምድና ግንዱ አልዓዛር ነው። አልዓዛር የወለደው ማትያንን ብቻ ሳይሆን ቅስራንም ነው። ቅስራ
ቅዱስ ኢያቄምን ወለደ፤ ቅዱስ ኢያቄም ደግሞ እመቤታችንን ወለደ። ዝምድናቸው የሦስት ትውልድ ነው። ለሁለቱም
ቅድመ አያታቸው አልዓዛር ነው።

አልዓዛር፤

ማትያን ፤ ቅስራ፤

ያዕቆብ፤ ኢያቄም፤

ዮሴፍ ፤ ድንግል ማርያም፤

በዕብራዊያን ልማድ ሴትንና ወንድን ቀላቅሎ ትውልድ መቁጠር ሥርዓት አይደለም። በመሆኑም፦ ቅዱስ
ማቴዎስ «ሥርዓት አፈረሰ፤» ይሉኛል፥ ብሎ የጌታን ልደት ስለ ዝምድናቸው በዮሴፍ በኲል ቆጥሯል፥ እርሷም እንዳትቀር
በቅጽል አምጥቷታል።

እመቤታችን ለምን ለዮሴፍ ታጨች?

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዮሴፍ የመታጨቷን ነገር መናፍቃን በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ አፈታት
ፈት ተው (ተርጉመው) ስለሚያስተምሩ፦ የእንቅፋት፥ የመሰናከያ ድንጋይ ሆኖባቸዋል። ከመናፍቅነት የጸዱ ምዕመናን
ደግሞ መናፍቃኑ በሚሉት ባይስማሙም የኅሊና ጥያቄ ስለሚሆንባቸው መልስ ይፈልጋሉ። ለዚህም የማያዳግም
መልስ የሚሆ ነው፥ አባቶቻችን በአፍም በመጽሐፍም ያስተማሩት ትምህርት ነው ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ከጥንተ አብሶ ነጻ ሆና የተፈጠረችው፥ ከማኅፀን ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀችው፥ አሥራ ሁለት ዓመት
በቤተ መቅደስ የኖረ ችው፥ ሰማያዊ ምግብ የተመገበችው፥ በቅዱሳን መላእክት የተገለገለችው፥ ለአምላክ እናትነት ነው።
ይህ እንዲህ ከሆነ ለምን ለዮሴፍ ታጨች?

ኃይል አርያማዊት እንዳይሏት ነው

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፦ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን፥ ዓለምን በእጁ መዳፍ የያዘውን፥
መንበሩ እሳት፥ መጋረጃው እሳት፥ አጋልጋዮቹ እሳት፥ መለኰታዊ ባሕርዩም እሳት የሆነውን አምላክ በማኅፀኗ መሸከሟ
ከሰው አእምሮ በላይ ነው። ምክንያቱም፦ እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ፥ በተዋሕዶ ሰው ሁኖ ዓለምን
ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣልና ነው። በመሆኑም፦ «በሰው አቅም እንዴት ይቻላል? ኃያላን የሚባሉ ኪሩቤል እንኳን እሱን
ሳይሆን፥ የሚሸከሙት የእሳቱን መንበር ነው፤ ሱራፌልም የሚያጥኑት እርሱን ሳይሆን፥ የእሳቱን መንበር ነው፤ በዚህም
ላይ ፊቶቻቸውንም እግሮቻቸውንም ይሸፍናሉ፤» እያሉ፥ የእመቤታችንን ከሰው ወገን መሆን የሚጠራጠሩ፥ «ኃይል
አርያማዊት (ሰማያዊት ኃይል)» የሚሉ ሰዎች እንደሚመጡ እግዚአብሔር ያውቃል። በማወቁም፦ የሰው እጮኛ
እንድትሆን ሳይሆን እንድትባል አድርጓል። ይኸውም፦ «ለሰው መታጨቷ ከሰው ወገን ብትሆን ነው፤» ለማሰኘት ነው።
የጌታን ጽንስ ከአጋንንት ለመሰወር ነው

አጋንንት፦ የሰውን ጥፋቱን እንጂ ድኅነቱን አይሹም፤ ጥንትም፦ እግዚአብሔርን ያህል አባት፥ ገነትን ያህል ርስት
ያሳጡት እነርሱ ናቸው። የሰውን ልጅ ከአባቱ ለይተውት፥ ከርስቱ ነቅለውት፥ እስከ ልጅ ልጆቹ፥ በእጃቸው ጨብጠው፣
በእግራቸው ረግጠው በሲኦል ገዝተውታል፤ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ባለ ዕዳ አድረገው አሰቃይተውታል።
የጌታ ወደዚህ ዓለም መምጣት ደግሞ ይኽንን ሁሉ ለመሰረዝ ነው፤ የሰውን ልጅ ከአጋንንት ቁራኝነት አላቅቆ ከሲኦል
ለማውጣት፥ ከሞት ወደ ሕይወት ለማሸጋገር፥ ወደ ጥንተ ርስቱ ገነት ለመመለስ ነው።

አጋንንት፦ የጌታን በመንፈስ ቅዱስ ግብር መፀነስ ሰምተውት ወይም አውቀውት ቢሆን ኖሮ፥ «ይህ ሳይሆን
አይቀርም፤» እያሉ የብዙ ሴቶችን ጽንስ ባበላሹ ነበር። ለምሳሌ፦ በልደቱ ጊዜ፥ በሄሮድስ አድረው፥ አንድ መቶ አርባ
አራት ሺህ ሕጻናትን ያሳረዱት ከእነዚያ መካከል ሕፃኑ ኢየሱስ አይጠፋም በሚል ግምት ነው። ማቴ ፪፥፲፮። በመሆኑም
አመቤታችን የዮሴፍ እጮኛ እንድትባል አድርጎ፥ በመንፈስ ቅዱስ ግብር የሆነ ፅንሱን ከአጋንንት ሰውሮባቸዋል።

ከርስት ገብቶ እንዲቆጠርላት ነው

በእስራኤል ከርስት ገብቶ የሚቆጠረው ወንድ ብቻ ነው፥ ሴቶቹ ግን በወንዱ ሥር ሆነው ከርስት ገብተው
ይቆጠራሉ። «በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሰው ሁሉ ይቈጠር ዘንድ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣ። ቄሬኔዎስ ለሶርያ
መስፍን በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ቈጠራ ሆነ። ሰው ሁሉ ሊቈጠር ወደየከተማው ሄደ። ዮሴፍም ከገሊላ አውራጃ
ከናዝሬት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ቤተልሔም ወደምትባለው ወደ ዳዊት ከተማ ወጣ፤ እርሱም ከዳዊት ሀገርና ከዘመዶቹ
ወገን ነበርና። ፀንሳ ሳለች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይቈጠር ዘንድ ሄደ።» እንዲል፦ ከርስት ገብቶ ሊቆጠርላት
እግዚአብሔር ባወቀ እጮኛዋ ተባለ። ሉቃ ፪፥፩-፭።

በመከራ ጊዜ እንዲከተላት ነው

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፦ በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ብዙ መከራ እንደሚያጋጥማት
በእርሱ ዘንድ አስቀድሞ የታወቀ ነው። በመሆኑም በሄሮድስ አሳዳጅነት፥ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በረሀ ለበረሀ በስደት
በምትንከራተትበት ጊዜ፥ የሚከተላት፣ የሚያገለግላት ሰው ያስፈልጋታል። ይህም ሰው የሥጋ ዘመዷ የሆነ፥ እጮኛዋ
የተባለ፥ አረጋዊው ዮሴፍ ነው። «እነርሱም (ሰብአ ሰገል) ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም
ታይቶ፥ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ እስከምነግርህም
ድረስ በዚያ ኑር አለው፤» እንዲል፦ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ እርሷን እያገለገለ አብሯት ተንከራትቷል። «እርሱም በሌሊት
ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ። ከእግዚአብሔር ዘንድ፥ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት ተብሎ በነቢይ (በነቢዩ
በሆሴዕ) የተነገረው ይፈፀም ዘንድ፤ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።» ይሏል። ማቴ ፪፥፲፫-፲፭፣ ሆሴ ፲፩፥፩።

በደንጊያ ከመገደል ሊያድናት ነው

በኦሪቱ ሕግ ሴት ልጅ ከሕጋዊ ጋብቻ ውጪ ጸንሳ ስትገኝ፥ በአደባባይ ተፈርዶባት፥ በደንጊያ ተቀጥቅጣ


ትገደላለች። ወንድም ቢሆን፦ «አመነዘረ፤» ተብሎ ሕጉ ይፈጸምበታል። «ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም
ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽሞ ይገደሉ።» ይላል። ዘሌ ፳፥፲። በተጨማሪም፦
«ለወንድ የታጨች ድንግል ልጅ ብትኖር፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርሷ ጋር ቢተኛ፥ ሁለቱን ወደዚያች
ከተማ በር አውጧቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዬውም የባልንጀራውን ሚስት
አስነውሯልና በድንጋይ ወግረው ይግደሏቸው፤ እንዲሁ ክፉውን ነገር ከውስጥህ ታስወግዳለህ።» የሚል አለ። ዘዳ ፳፪፥
፳፫።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢረ ጽንሰቱን (በመንፈስ ቅዱስ ግብር መሆኑን)
ከአይሁድም ሰውሮባቸዋል። በመሆኑም፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፥ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፀንሳ
በተገኘችበት ወራት፥ በስመ እጮኛ አረጋዊ ዮሴፍ በአጠገቧ ባይኖር ኖሮ፥ ሕገ ኦሪትን ለመፈጸም ብለው በደንጊያ
ቀጥቅጠው ይገድሏት ነበር።

ከስድብ ከነቀፋ ሊያድናት ነው


በእስራኤል አንዲት ድንግል ሳትታጭ ከቆየች፥ ሁሉ ይሰድባታል፥ ሁሉ ይነቅፋታል፤ እንደ አገራችን ባሕል፦ «ቆማ
የቀረች፥ ፈላጊ ያጣች፤» ትባላለች። ምክንያቱም ለጋብቻ መታጨት፥ ለቁም ነገር መፈለግ፥ የጨዋነት ምልክት ነውና።
በመሆኑም ያጨም፥ የታጨችም በሰው ዘንድ ክብር አላቸው። እንዲህ ካልሆነ ግን በቀጥታም ሆነ በአሽሙር
የሚጐነትላቸው ይበዛል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፦ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ አድሮባት በሚኖር መንፈስ ቅዱስ ተጠብቃ፥
በእሳታውያን መላእክት ተከብባ፥ በክንፎቻቸውም ተሸፍና የምትኖር ለእግዚአብሔር እናትነት የተመረጠች፥
የተቆለፈች፥ ተቆልፋም ለዘለዓለሙ የምትኖር፥ እግዚአብሔር ብቻ ሳይከፍት ገብቶ ሰይከፍት የሚወጣባት፥ ሰው
የማይገባባት፥ የእግዚአብሔር ቤተ መቅድስ ናት። ቅዱስ ኤፍሬም፦ በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ ፣ በእሑዱ ክፍል፦
«በእግዚአብሔር ሥዕል የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ፤» ያለው ለዚህ ነው። በቅዳሜውም ክፍል፦
«የማትፈርሽ መቅደስ ነሽ፤» ብሏታል። ቅዱስ ዳዊትም፦ «እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው
ዘንድ ወድዷታልና፤ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።» በማለት ትንቢቱን አስቀድሞ
ተናግሯል። መዝ ፻፴፩፥፲፫። ነቢዩ ሕዝቅኤልም፦ «ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው ወደ መቅደሱ በር መለሰኝ፤
ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም፦ ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ አትከፈትም፤ ሰውም አይገባባትም፤ የእስራኤል
አምላክ እግዚአብሔር ገብቶባታልና ተዘግታ ትኖራለች፣አለኝ፤» ብሏል።ሕዝ ፵፬፥፩-፪። በመሆኑም፦ ሰዎች
እመቤታችንን፦ በሥጋ ምኞት እንዳያስቧት ኀሊናቸውን ጠብቆላታል። ይኽንን በተመለከተ አባ ሕርያቆስ፦ መንፈስ
ቅዱስ በገለጠለት በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ ላይ፦ «ድንግል ሆይ፥ የሚያታልሉ ጎልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም፥ የሰማይ
መላእክት ጎበኙሽ እንጂ፤ (ተድላ ዓለም ፥ ብዕለ ዓለም ፥ ያታለላቸው ፣አንድም አጋንንት በውዳሴ ከንቱ
የሚያታልሏቸው፥ አንድም በሎሚ በቀለበት የሚያታልሉ፥ አንድም ፈቃደ ሥጋቸው ያታለላቸው ወጣቶች ያረጋጉሽ
አይደለሽም፤ መላእክት ጐበኙሽ፥ አጫወቱሽ እንጂ፤» ብሏል። ቊ ፵፫። በሌላ በኩል ደግሞ፥ እንደ ሌሎች ሴቶች
መስላቸው ወደ ነቀፋና ወደ ስድብ እንዳይሄዱ፥ ዘመዷን ዮሴፍን በአጠገቧ አስቀምጦላታል። ምክንያቱም፦ «ከሴቶች
ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ፤» የሚለውን ስለማያውቁት ነው፥ አንድም እግዚአብሔር ባወቀ ስለተሰወረባቸው ነው።
የዮሴፍ እጮኝነት፥ ምሥጢር ለተሰወረባቸው አይሁድና ለአጋንንት ሌላ ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ማደሪያውን
የጠበቀበት ጥበብ ነው። ቅዱስ ዳዊት፦ እግዚአብሔርን፦ «አቤቱ ሥራህ እጅግ ታላቅ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፤»
ብሎታል። መዝ ፻፫፥፳፬። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦ «የእግዚአብሔር ባለጠግነት ፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ
ነው!» ብሏል። ሮሜ፲፩፥፴፫።
እንዲጠብቃት እንዲያገለግላት ነው

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፦ ለዮሴፍ የታጨችበት ዋናው ዓላማ እንደ አባት ሊጠብቃት፥ እንደ
አሽከር ሊያገለግላት ነው። አንድም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ድንግል ማርያምን እንዲጠብቅ እንዲያገለግል ከብዙ
አረጋውያን መካከል የተመረጠ ታማኝ አገልጋይ ነው። አባ ሕርያቆስ፥ ከላይ እንደገለጥነው፥ መንፈስ ቅዱስ ገልጦለት፥
እመቤታችንን ባመሰገነበት ድርሰቱ፥ በቅዳሴ ማርያም ላይ፦ «ድንግልሆይ፥ ለዮሴፍ የታጨሽ ለትዳር አይደለም፥ ንጹሕ
ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ፤» ያለው ለዚህ ነው። ቊ ፵፬።

ኢያሱ ወልደ ነዌ፥ ሙሴን እንዲያገለግል በመታጨቱ (በመመረጡ) እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ (ሙሴ ከዚህ ዓለም
እስኪለይ) ድረስ አገልግሎታል። በመጽሐፉ መጀመሪያ ላይ፦ «እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ
በኋላ፥ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፤» ይላል። ኢያ ፩፥፩። ኢያቡር
የተባለው የአብርሃም ሎሌ፥ ጌታውን አብርሃምን እስኪሸመገል፥ ዘመኑም እስኪያልፍ ድረስ ታጥቆ አገልግሎታል። ዘፍ
፳፬፥፩። ሌዋውያን ካህኑን አሮንን እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር መርጧቸው ነበር። «እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ
ብሎ ተናገረው፥ የሌዊን ነገድ አቅርበህ ያገለግሉት ዘንድ በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው፤» ይላል። ዘኁ ፫፥፭።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን ማገልገልን ነው፤ ይኽንንም፦ «የሰው ልጅ
(ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ) ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ ሊያገለግሉት አልመጣምና፤»
በማለት ነግሮናል። ማር ፲፥፵፭። ይኽንን በተናገረበት አንቀጽ ላይ፥ ደቀመዛሙርቱንም፦ «ነገር ግን ማንም ከእናንተ
ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤»
ብሎአቸዋል። ማር ፲፥፵፫። ከዚህም የምንማረው፥ መልዕልተ ፍጡራን ለሆነች ለአምላክ እናት ቀርቶ፥ ለሚመስለን
ወንድማችን እንኳ ባሪያ መሆን እንደሚገባ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦ «ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ
ባሪያዎች ሁኑ፤» ብሏል። ገላ ፭፥፲፫። ስለራሱም ሲናገር፦ «እኔ ከሁሉ ይልቅ ነጻ ስሆን ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት
እሰበስባቸው ዘንድ እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛሁ።» ብሏል። ፩ኛ ቆሮ ፱፥፲፱። ሐዋርያው ራሱን ባሪያ አድርጐ
ያስገዛው ከእርሱ ለሚያንሱት እንኳ ነው።

ስምዖን የተባለው ቁርበት ፋቂ ቅዱስ ጴጥሮስን በቤቱ ተቀብሎ አገልግሎታል፤ የሐዋ ፲፥፵፮። በብሉይ ኪዳን
ዘመንም እግዚአብሔር ያዘጋጃት መበለት፥ የሰራፕታዋ ሴት፥ ነቢዩ ኤልያስን አገልግላዋለች። «የእግዚአብሔር ቃል ወደ
ኤልያስ መጣ፥ እንዲህም አለው፦ ተነሥተህ በሲዶና አጠገብ ወዳለችው ወደ ሰራፕታ ሂድ፤ በዚያም ተቀመጥ፤ እነሆም፥
ትመግብህ ዘንድ አንዲት መበለት አዝዣለሁ፤» ይላል። ፩ኛ ነገ ፲፯፥፰። ሱናማዊቷም ሴት ነቢዩ ኤልሳዕን ቤት ሠርታ
እስከመስጠት ድረስ አገልግላዋለች። ሱናማዊቷ ሴት ባሏን፦ «ይህ በእኛ ዘንድ ሁልጊዜ የሚያልፈው (ነቢዩ ኤልሳዕ) ቅዱስ
የእግዚአብሔር ሰው እንደሆነ አውቃለሁ። ትንሽ ቤት በሰገነቱ ላይ እንሥራ፤ በዚያም አልጋና ጠረጴዛ፥ ወንበርና መቅረዝ
እናኑርለት፤ ወደእኛም ሲመጣ ወደዚያ ይግባ አለችው፤» ይላል። ፪ኛ ነገ ፬፥፱። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ ቅዱሳንን
ማገልገል እንደሚገባ ሲናገር፦ «ለቅዱሳን ስለሚሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት መላልሰው ማለዱን።
እነርሱ አስቀድመው በፈቃዳቸው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔርም፥ ለእኛም አሳልፈው
ሰጥተዋልና እኛ እንደአሰብነው አይደለም፤ ይህንም የቸርነት ሥራ እንደጀመረ ይፈጽምላቸው ዘንድ ቲቶን ማለድነው።
በሁሉም ነገር በእምነትና በቃል፥ በዕውቀትም፥ በትጋትም በእናንተ ዘንድ በሆነው ሁሉ እኛን በመውደዳችሁ ፍጹማን
እንደሆናችሁ፥ እንዲሁም ደግሞ ይህቺን ስጦታ አብዙ።» ብሏል። ፪ኛ ቆሮ ፰፥፬።
ዮሴፍ የተመረጠበት መንገድ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፥ ለእናት ለአባቷ የስዕለት ልጅ ናት፤ ከዚያ በፊት መሐኖች ነበሩ። በዘመነ
ኦሪት፦ የሕልቃና ሚስት ሐና፦ «ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤» ብላ
እንደተሳለች፥ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐናም ልጅ ቢሰጣቸው መልሰው ለእግዚአብሔር እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።
፩ኛ ሳሙ ፩፥፲፩። ከፍጥረት ሁሉ በላይ የከበረች ልጅ እንደሚወልዱም ሁለቱም በየራሳቸው በህልም ተረድተዋል።
እግዚአብሔርም፦ ህልማቸውን እስኪፈታላቸው፥ ስእለታቸውን እስኪፈጽምላቸው ድረስ መኝታ ለይተው ጾም ጸሎት
ይዘዋል፤ ሱባኤም ገብተዋል።

ጊዜው ሲደርስ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መኝታቸውን አንድ እንዲያደርጉ ነግሯቸው፥ ነሐሴ ሰባት ቀን
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች። ይኽንንም አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ ላይ፦ «ኦ ድንግል
አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ፥ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ። ድንግል ሆይ፥ በኃጢአት ፍትወት
የተፀነስሽ አይደለም፥ በሕግ በሆነ በሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ።» በማለት ተናግሯል። ቊ ፴፰።
የተወለደችውም ግንቦት አንድ ቀን ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሞላት፥ «አባ፥ እማ» ማለት ስትጀምር፥ ወስደው ለቤተ
እግዚአብሔር ሰጥተዋታል። ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ነበር፤ እርሱም፦ ከፀሐይ ይልቅ የጠራች፥ ከጨረቃ ይልቅ የደመቀች፥
ይህችን የመሰለች ልጅ፥ «ምን አበላታለሁ? ምን አጠጣታለሁ? ምን አለብሳታለሁ? ምን አነጥፍላታለሁ? ምንስ
እጋርድላታለሁ?» ብሎ ሰው ሰውኛውን ሲጨነቅ፥ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከሰማይ ወርዶ፥ አንድ ክንፉን አነጠፈላት፥
በአንድ ክንፉ ደግሞ ጋረዳት። ኅብስት ሰማያዊ፥ ጽዋ ሰማያዊም መገባት። ይኽንንም በተመለከተ አባ ሕርያቆስ፦ «ኦ
ድንግል፥ አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፥ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፤ ኦ ድንግል አኮ ስቴ
ምድራዊ ዘሰተይኪ፥ አላ ስቴ ሰማያዊ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድሐ፤ ድንገል ሆይ፥ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ
አይደለሽም፥ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ፥ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ
አይደለሽም፥ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤» ብሏል። ቅዳ ማርያም ቊ ፵። ይህም በግብር
አምላካዊ የተገኘ ነው። ዘካርያስም የምግቧ ነገር ከተያዘ ብሎ ወደ ቤተመቅደስ አስገብቷታል።

በቤተ መቅደስ፦ መላእክት እየመገቧትና እያረጋጓት አሥራ ሁለት ዓመት ተቀምጣለች። በዚያም በአጭር
ታጥቃ፣ ማድጋ ነጥቃ፣ ውኃ በመቅዳት፥ ሐርና ወርቅ እያስማማች በመፍተል መጋረጃ በመሥራት፥ በአገልግሎት ኖረች
እንጂ በሥራ ፈትነት አይደለም። ይህ ነገር በጎ ኅሊና የጐደላቸውን አይሁድን አላስደሰታቸውም። «ቤተ መቅደሳችንን
ታረክስብናለች፤» ብለው በቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ላይ በጠላትነት ተነሡባት። የእነርሱ ቤተ መቅደስ
የሚፈርስ ቤተ መቅደስ ነው፤ ይኽንንም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ «እውነት እላችኋለሁ፥
ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፤ (ይህ ቤተ መቅደስ እንዲህ እንዳሸበረቀ አይቀርም፥ ይፈርሳል)፤»
በማለት አድንቀው ለነገሩት ለደቀመዛሙርቱ ነግሯቸዋል። ማቴ ፳፬፥፪። እንደተናገረውም የሮም ንጉሥ ጥጦስ
ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ በ70 ዓም ፈርሷል። እመቤታችን ግን ቅዱስ ኤፍሬም በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ፥ በቅዳሜው
ክፍል እንደተናገረው፥ «የማትፈርስ ቤተ መቅደስ» ናት።

ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ፥ አይሁድ፦ «እነሆ አሥራ አምስት ዓመት ሆኗታል፥ መጠነ አንስትም አድርሳለች፥ ቤተ
መቅደስ ታሳድፍብናለችና ትውጣልን፤» እያሉ አላስቆም አላስቀምጥ አሉት። እርሷ ግን፦ ጠቢቡ ሰሎሞን፦ «ወዳጄ
ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ምንም ነውር የለብሽም።» እንዳለ፥ እድፍ ጉድፍ የሌለባት፥ ንጽሕተ ንጹሐን፥ ቅዱስተ
ቅዱሳን ናት። የረከሰውን የምትቀድስ ናት። መኃ ፬፥፯። ዘካርያስም ወደ እርስዋ ገብቶ «ምን ይበጅሻል? እንዴት
ትሆኚ?» ቢላት «ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ፤» ብላዋለች። ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት፦ «ከነገደ ይሁዳ
ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን አስቈጥረህ፥ በትራቸውን ከቤተ መቅደስ አግብተህ ስትጸልይበት እደርና አውጣው፤»
ብሎታል። እንደተባለው ቢያደርግ ከበትረ ዮሴፍ ላይ፦ «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት፥ ኢትፍራህ ነሢኦታ ለማርያም ፍኅርትከ፤
የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ እጮኛህን ማርያም ለመውሰድ አትፍራ፤» የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበት ተገኝቷል። ይኸውም፦
የነቢያት አለቃ ሙሴ፥ እግዚአብሔር እንዳዘዘው፥ በአሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ልክ፥ አሥራ ሁለት በትሮችን ሰብስቦ፥
ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ቢጸልይበት፥ በትረ አሮን ለምልማ፣ አብባና አፍርታ እንደተገኘችው ማለት ነው። ዘኁ ፲፯፥፩-
፰። ሁለተኛም፦ ነጭ ርግብ ወርዳ ከዮሴፍ ራስ ላይ አርፋበታለች፤ ሦስተኛም፦ ዕጣ ቢጣጣሉ ዕጣው ለዮሴፍ
ወጥቶለታል። ከዚህ በኋላ ለማኅደረ መለኰትነት የተመረጠች ድንግል ማርያምን ይጠብቃት፥ ይንከባከባትም ዘንድ
ወደ ቤቱ ይዟት ሄዷል።

እግዚአብሔር እሥራኤልን ማጨቱ

እግዚአብሔር እስራኤልን በማጨቱ የእስራኤል እጮኛ ተብላለች፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር፥ በነቢዩ
በሆሴዕ አድሮ ሲናገር፥ «ስለዚህ እነሆ አቅበዘብዛታለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም አወጣታለሁ፤ ለልብዋም እናገራለሁ።
ከዚያም የተገኘውን ገንዘብዋን እሰጣታለሁ። ምክርዋንም በአኮር ሸለቆ እገልጣለሁ፤ እንደ ሕፃንነትዋ ወራት፥ ከግብፅም
እንደወጣችበት ቀን ትዘምራለች። በዚያን ቀን ባሌ (እግዚአብሔር ፈጣሪዬ ነህ)፤ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ በዓሊም (ጣዖቱ
እንደማያድን እርሱም አያድንም)፤ ብለሽ አትጠሪኝም፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የበዓሊምን (የጣዖታቱን) ስሞች ከአፍዋ
አስወግዳቸዋለሁና፥ (ጣዖታቱን እንዳታመሰግን አደርጋታለሁ)፥ ስማቸውም ከእንግዲህ ወዲህ አይታሰብም። (ቤል፣ ዳጎን
እያለች ስማቸውን አታነሣም)። በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች (ከአሕዛብና ከኃያላን) ጋር ከመሬትም
ተንቀሳቃሾች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። (በጠላትነት ተነሥተው እንዳያጠፏት አደርጋለሁ)። ቀስትንና ሰይፍን፥
ጦርንም ከምድሩ እሰብራለሁ፤ (በቀስትና በሰይፍ፥ በጦርም ሊያጠፉ የሚችሉትን ሁሉ አጠፋቸዋለሁ)፤ ተዘልለሽም
ትቀመጫለሽ። (ጠላት ጠፍቶልሽ በሰላም ትኖሪያለሽ)፤» ካለ በኋላ፥ «ለዘለዓለምም ለእኔ እንድትሆኚ እጭሻለሁ፤
በጽድቅና በፍርድ በምሕረትና በይቅርታ አጭሻለሁ። (በሃይማኖት ጸንተሽ፥ ጽድቅን፣ ርትዕን፣ ጸሎትን፣ ገንዘብ አድርገሽ
ብትገኚ፥ እውነትን፣ ፍርድን፣ ምሕረትንና ይቅርታን ማጫ አድርጌ ለዘለዓለም ማደሪያዬ ልትሆኚ አጭሻለሁ)። ለእኔም
እንድትሆኚ በመታመን አጭሻለሁ፤ አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂአለሽ። (ይቅርታን ቸርነትን አድርጌልሽ ፈጣሪሽ እኔ
እንደሆንኩ ታውቂኛለሽ)።» ብሏል። ሆሴ ፪፥፲፬-፳።

እስራኤል ዘሥጋ፥ ከግብፅ ምድር በወጡ በሦስተኛው ወር፥ እግዚአብሔር ሙሴን፦ «በግብፃውያን ላይ
ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ (ንስር ፈጣን እንደሆነ ፈጥኜ እንዳወጣኋችሁ)፥ ወደ እኔም
እንዳመጣኋችሁ (በባለሟልነት እንዳቀርብኳችሁ) አይታችኋል። አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ፥ ኪዳኔንም
ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ (የታጨ) ርስት (ወገን) ትሆኑኛላችሁ፤ እናንተም የክህነት
መንግሥት፥ የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። (ካህናቱ ነገሥታቱ ከእናንተ ይወለዳሉ፥ ምግባር ሃይማኖት የሚጠብቁ
ከእናንተ ይወለዱልኛል፥ በእኔ በእግዚአብሔር ላይ የጣዖት ውሽማ የማያበጁ ከእናንተ ይገኙልኛል)፤ ብለህ ለእስራኤል
ልጆች ንገራቸው።» ብሎታል። ዘፀ ፲፱፥፫-፮። በኦሪት ዘዳግም ላይ ደግሞ፦ «ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ
ሕዝብ ነህና፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዘብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር
መርጦሃልና። እግዚአብሔር የወደዳችሁና የመረጣችሁ፥ ከአሕዛብ ሁሉ ስለበዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ
ጥቂቶች ነበራችሁና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አባቶቻችሁን መረጣቸው፤ ወደዳቸውም፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን
ዘራቸውን እንደዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መረጠ።» የሚል ተጽፏል። ዘዳ ፲፥፲፭። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦
«እኒህም፦ ልጅነት፥ ክብር፥ ኪዳን፥ ሕግና አምልኮ ያላቸው፥ ተስፋም የተሰጣቸው፥ እስራኤላውያን ናቸው። እነርሱም
አባቶቻችን ናቸው፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ ተወለደ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ ነው፤
አሜን።» ብሏል። ሮሜ ፱፥፬-፭።

ምእመናን ለክርስቶስ መታጨታቸው

የአዲስ ኪዳን እስራኤል፦ በሥላሴ ስም የተጠመቁ፥ በሜሮን የከበሩ፥ በሥጋ ወደሙ የታተሙ ምዕመናን
ናቸው። እነርሱም እስራኤል ዘነፍስ ይባላሉ። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ ቅዱስ ጴጥሮስ፦
«እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንግዲህ ምን እናገኛለን?» ብሎ በጠየቀው ጊዜ፥ «እውነት እላችኋለሁ፤ የተከተላችሁኝ
እናንተ በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ እናንተም በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ
ሁለቱም ነገደ እስራኤል ትፈርዳላችሁ።» ብሎታል። ማቴ ፲፱፥፳፯-፳፰። «በእስራኤል ትፈርዳላችሁ፤» ማለቱም
በእስራኤል ዘሥጋ በአይሁድ ብቻ ሳይሆን እስራኤል ዘነፍስ በሚባሉ በምዕመናንም ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤል ዘሥጋ ለእግዚአብሔር እንደታጩ፥ በአዲስ ኪዳን
ዘመን ደግሞ ምዕመናን ለክርስቶስ መታጨታቸውን ሲናገር፦ «በስንፍናዬ እናገር ዘንድ (በመመካት መናገሬን) ጥቂት
ልትታገሡኝ ይገባ ነበር፤ ቢሆንም በእርግጥ ታገሡኝ፤ (መመካት ሥርዓት እንደሆነ አድርጋችሁ አትያዙብኝ)፤
ለእግዚአብሔር የሚገባ ቅንዐት እቀናላችኋለሁና፤ (መንፈሳዊ ቅንዐት እቀናላችኋለሁና)፤ ወደ እርሱ አቀርባችሁ
(አዋህዳችሁ) ዘንድ ለአንዱ ንጹሕ ድንግል ለክርስቶስ አጭቻችኋለሁና።» ብሏል። ፪ኛ ቆሮ ፲፩፥፩-፪።

ጻድቁ ዮሴፍ እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን፦ ሊጠብቃት፥ ሊያገለግላትና ሊላላካት፥ በእግዚአብሔር
ፈቃድ ከካህናቱ እጅ በአደራ ተቀብሏታል። ሰው ሰውኛውን እርሱ ይጠብቃት እንጂ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ጠባቂዋ
መንፈስ ቅዱስ ነው። እግዚአብሔር ለተዋሕዶ አካላዊ ቃል የመረጣት ስለሆነ፥ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ንጽሐ ጠባይዕ
ሳያድፍባት፥ ከአዳም በዘር ይተላለፍ የነበረው የውርስ ኃጢአት ሳያገኛት፥ በመንፈስ ቅዱስ ተጠብቃ ኖራለች። አምላክን
በድንግልና ፀንሳ፥ በድንግልና እንደምትወልድ ያበሠራት መልአከ ቅዱስ ገብርኤል፦ «መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤» ያላት
ለዚህ ነው። ይህም፦ የምትፀንሺው፥ ከእናትሽ ማኅፀን ጀምሮ በጠበቀሽ፧ ለቅጽበተ ዓይን እንኳ ተለይቶሽ በማያውቅ
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ነው፥ ሲላት ነው። ሉቃ ፩፥፴፰። ምክንያቱም በውስጧ ሆኖ የጠበቃት፥ በኋላም ያዋሐደ እርሱ
ነውና።

የባሕርይ አምላክ ፥ ከሰማይ ወርዶ፥ በማኅጸነ ድንግል ማርያም በተዋሕዶ ሰው የሆነበት ምሥጢር ከሰው
አእምሮ በላይ ነው። ይህ፦ አምላክ ሰው የሆነበት ጥበብ (የመንፈስ ቅዱስ ግብር) እጅግ ጥልቅና የማይመረመር ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ
የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም።» ያለው ለዚህ ነው። ሮሜ ፲፩፥፴፫። ለልጁ ለጢሞቴዎስ በጻፈው መልእክቱም
ላይ፦ «ቤተ ክርስቲያኒቱ የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤት ናት። የዚህ የመልካም አምልኮ (አምላክ
ሰው የሆነበት ምሥጢር) ታላቅ ነውና። ይኸውም በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የተረዳ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ
ዘንድ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ ነው።» ብሏል። ፩ኛ ጢሞ ፫፥፲፮። እንኳን ይህ ታላቅ ምስጢር ቀርቶ፥
እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ሥራ ከሰው ዕውቀት በላይ በመሆኑ ከማድነቅ በስተቀር እንዲህ ነው ብሎ ለመናገር (በቃላት
ለመወሰን) አስቸጋሪ ነው። ቅዱስ ዳዊት፦ «እግዚአብሔርን ሥራህ ግሩም ነው፥ በሉት፤» ያለው ለዚህ ነው።

ቅዱስ ዮሴፍ፦ እርሱ በማያውቀው ምሥጢር እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ፀንሳ በማግኘቱ እንደ
ሰው ተቸግሯል። ምክንያቱም፦ ምንም ዓይነት ሥጋዊ ምክንያት አያገኘባትምና ነው። በውዳሴ ማርያም ትርጓሜ፥
በዓርቡ ክፍል እንደተጻፈው ቅዱስ ዮሴፍ ፦ ዮሐንስ የሚባል ፈላስፋ ወዳጅ ነበረውና በመልኳ መፅነሷን አውቆ
ነግሮታል። ይኽንን ይዞ ቢጠይቃት፦ «እኔስ መልአኩ አክብሮ ከነገረኝ በቀር የማውቀው የለም፤ በዚያውስ ላይ አዕዋፍ
እንዲራቡ (እንዲባዙ)፥ አዕዋም እንዲያፈሩ የሚያደርግ ማን መስሎሃል?» ብላዋለች። ከዚህም ጋር ከደጅ ቆሞ የነበረ
ደረቅ ግንድ አለምልማ አሳይታዋለች። ከዚህ በኋላ ለክብረ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም የሚወጡበት ጊዜ ደረሰ።

ቅዱስ ዮሴፍ በአሳብ ውጣ ውረድ ኅሊናው ተወጠረ። ከቤት ትቷት እንዳይሄድም፥ ወደ በዓሉም ይዟት
እንዳይወጣም ተቸገረ። ይኸውም አይሁድን ፈርቶ ነው። ወደ በዓሉ ይዟት እንዳይወጣ፥ ቀድሞም ሊቀ ካህናቱን
ዘካርያስን አስጨንቀው አሥራ ሁለት ዓመት ከኖረችበት ቤተ መቅደስ እንድትወጣ ያስደረጉት ለምን እንደሆነ ያውቃል።
«የፈራነው ደረሰ፤» ብለው፥ በሕግ ሽፋን ፅንሱን ቆራርጦ የሚያወጣና አንጀቷን የሚበጣጥስ፥ ማየ ዘለፋ
እንደሚያጠጧት፥ በደንጊያ ቀጥቅጠው እንደሚገድሏት ከእርሱ የተሠወረ አይደለም። ከቤት ትቷት እንዳይሄድ ደግሞ
አፋቸውን እንደ ጦር ፈራው። ከብዙ የአሳብ ውጣ ውረድ በኋላ ግን፥ በአይሁድ ፊት ተገልጣ ባላወቁት ምሥጢር
እንዳይፈርዱባት በስውር ከቤት ትቷት ወደ በዓሉ ለመሄድ አሰበ።

የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ታየው

ቅዱስ ዮሴፍ፦ ጻድቅ ሰው በመሆኑ፥ አንድም እንዲጠብቅ የተሰጠችው አደራ መትኅተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን
በመሆኗ በነገር ሁሉ ቅዱሳን መላእክት ይራዱት ነበር። በሕልም ይነጋገሩት ነበር። ለደጋግ ሰዎች ሕልም ከእግዚአብሔር
ነው። ኢዮ ፪፥፳፰፣ የሐዋ ፪፥፲፯። ያዕቆብ፦ በቤቴል ድንጋይ ተንተርሶ በተኛበት ሌሊት ጫፉ ሰማይ ደርሶ እግዚአብሔር
የቆመባት መሰላል፥ ቅዱሳን መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት (ጸሎት ሲያሳርጉባት፥ ምሕረት ሲያወርዱባት) አይቷል።
ዘፍ ፳፰፥፲-፲፪። ይህች እግዚአብሔር ተገልጦ የታየባት መሰላል፥ አምላክ ሰው ኾኖ ለተገለጠባት ለእመቤታችን ለቅድስት
ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት። ላባን ለመገናኘት በተጓዘ ጊዜም የእግዚአብሔርን መላእክት በዙሪያው ከትመው
ሲጠብቁት በገሀድ አይቷል። ዘፍ ፴፪፥፩-፪። በእግረ ሙሴ የተተካ ኢያሱ ወልደ ነዌም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘውን የሠራዊት
አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ፊት ለፊት አይቷል። ኢያ ፭፥፲፫። ጌዴዎንንም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ አነጋግሮታል። መሳ
፮፥፲፪። የሶምሶንን ወላጆች ማኑሄን እና ሚስቱንም አነጋግሯቸዋል። በፊታቸውም ተአምራት አድርጓል። መሳ ፲፫፥፩-፳።

ነቢዩ ኤልያስ መፍቀሪተ ጣዖት ኤሌዛቤል ባሳደደችው ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ኅብስት
በመሶብ ወርቅ አድርጎ መግቦታል። ኅብስት የጌታ፥ መሶበ ወርቅ የእመቤታችን ምሳሌዎች ናቸው። ፩ኛ ነገ ፲፱፥ ፩-፰።
ነቢዩ ኤልሳዕ በዶታይን የሶርያው ንጉሥ በፈረሶችና በሰረገሎች ባስከበበው ጊዜ፦ ቅዱሳን መላእክት በዙሪያው ከትመው
የእሳት አጥር ሆነው ሲጠብቁት አይቷል። ሎሌውንም፦ «ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ።»
በማለት አጽናንቶታል። በነቢዩ ጸሎት ለሎሌውም ተገልጠውለታል። ፪ኛ ነገ ፮፥፲፬-፲፯። ከዓይነ ሞት የተሰወረ ሄኖክ
ቅዱሳን መላእክትን ፊት ለፊት አይቷቸዋል፥ እነ ቅዱስ ሜካኤልም ያነጋግሩት ነበር። ሄኖ ፲፮፥፩-፵፩። ዕዝራ ሱቱኤልን
ቅዱስ ዑራኤል አነጋግሮታል፥ የጥበብንም ጽዋ አጠጥቶታል። ዕዝ ፫፥፳። ቅዱስ ሩፋኤል ደግሞ ጦቢያን እያነጋገረው
በመንገዱ ሁሉ አልተለየውም ነበር። ጦቢት ፭፥፩-፳፪፣ ፮፥፩-፲፯፣፯፥፩-፲፰።
ነቢዩ ኢሳይያስ የሱራፌልን መልካቸውን አይቷል፥ ቅዳሴአቸውንም ሰምቷል። ከሱራፌል አንዱም ከሰማይ ይዞት
በመጣው እሳት አፉን ዳስሶ ከለምጹ ፈውሶታል። ኢሳ ፮፥፩-፯። ለነቢዩ ለዳንኤል ራእዩን የሚተረጉምለት ቅዱስ ገብርኤል
ነበር። ዳን ፰፥፲፭-፳፯። በጾሙ ጊዜም እየተገለጠ ይዳስሰው፥ ያነጋግረውም ነበር። ይህ ታላቅ ነቢይ፥ «ከአለቃችሁ
ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም።» በማለት መስክሯል። ዳን ፩፥፩-፲፩። ጻድቁ ዮሴፍ፦ አባቶቹን ቅዱሳንን
በዘመነ አበው፥ በዘመነ መሳፍንት፥ በዘመነ ነገሥት፥ በዘመነ ካህናትም እየተገለጡ ያነጋገሩ ቅዱሳን መላእክት እርሱንም
አነጋግረውታል። እርሱ ሰው ሰውኛውን ሲጨነቅ መንፈሳዊውን ምሥጢር ገልጠውለታል።

«ከእርስዋ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ነው»

የእግዚአብሔር መልአክ ዮሴፍን፦ «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ኢትፍራህ ነሢኦታ ለማርያም ፍኅርትከ፥ እስመ
ዘይትወለድ እምኔሃ እመንፈስ ቅዱስ። የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን
ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።» ብሎታል። በዚህም የእመቤታችን ጽንስ በመንፈስ ቅዱስ ግብር መሆኑን
አስረድቶታል። ይህንንም፦ «መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤» ብሎ አስቀድሞ ለእመቤታችን ነግሯት ነበር። ሉቃ ፩፥፴፭።
መልአኩ ዮሴፍን፦ «የዳዊት ልጅ» ብሎ በመጥራት ንጉሡን ዳዊትን ያነሣው ያለ ምክንያት አይደለም። ይኸውም፦
«ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ፤ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ አስነሣለሁ፤
መንግሥቱንም አዘጋጃለሁ። (በዙፋንህ አስቀምጠዋለሁ)።» ተብሎ ለቅዱስ ዳዊት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን
ሲያጠይቅ ነው። ፪ኛ ሳሙ ፯፥፲፪። ይህ ትንቢት ለጊዜው ለሰሎሞን ሲሆን ለፍጻሜው ለኢየሱስ ክርስቶስ ነበረ።
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን በፍጹም ትህትና ባበሠራት ጊዜ፦ «እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን
የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል።» ያላት ለዚህ ነበር። ሉቃ ፩፥፴፪። የመጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሀንስ አባት ጻድቁ ካህን
ዘካርያስም፦ አድሮበት በሚኖር መንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ፦ «ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ
እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤» ብሏል። ሉቃ ፩፥፷፰። መልአከ
አግዚአብሔር ዮሴፍን፦ «አትፍራ» ያለው፥ «ልትጠብቃት፥ ልታገለግላት ከካህናት እጅ በአደራ እንደተቀበልካት፥
ከመንፈስ ቅዱስ እጅ መቀበልንም አትፍራ፤»ሲለው ነው። ከዚህም አያይዞ፦ «ልጅም (ወልድን) ትወልዳለች፤ እርሱ
ሕዝቡን ከኃጢአታቸው (በኃጢአት ከመጣባቸው ፍዳ) ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።» ብሎታል። በዚህም
«ኢየሱስ» ብሎ ንባቡን፥ «ያድናቸዋል፤» ብሎ ትርጓሜውን ነግሮታል። የስም ኃይሉ ትርጉሙ ነውና። ምክንያቱንም
ዘርዝሮ ሲነግረው፥ «እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም (ወልድን) ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤
ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ተብሎ ከእግዚአብሔር ዘንድ (ከእግዚአብሔር አግኝቶ) በነቢይ
የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፤» በማለት ትንቢተ ኢሳይያስን ጠቅሶለታል። በዚህም ላይ ነቢዩ በንባብ ብቻ
ያስቀመጠውን «አማኑኤል» የሚለውን ስም ተርጉሞለታል። «ወተንሢኦ ዮሴፍ እምንዋሙ ገብረ በከመ አዘዞ መልአከ
እግዚአብሔር፤ ወነሥአ ለማርያም ፍኅርቱ። ዮሴፍም ከእንቅልፉ ተነሥቶ (ነቅቶ) የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው
አደረገ፤ እጮኛውን (እንዲጠብቃት እንዲያገለግላት፥ እንዲላካት የተመረጠላትን) ማርያምንም ወሰዳት።» የወሰዳትም
ከቤቱ ወደ በዓሉ ነው።

«ብሥራተ ገብርኤል ወፅንሰት፡፡ »


ከዚህም በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ በ 3 ሰአት በቤተ መቅደስ ሀርና
ወርቅ እያስማማች ስትፈትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ወደ እመቤታችን በመጣ ጊዜ ፡
- « ደስ ያለሽ. ጸጋንም የተመላሽ ሆይ. ደስ ይበልሽ ፤ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው ፤ ከሴቶች ተለይተሸ አንቺ የተባረክሽ
ነሽ ፡፡» በማለት አመስግኗታል፡፡ ሉቃ 1.28 ፡፡ ከእርሷ በፊት ይህን በሚመስል ምስጋና የተመሰገነ ማንም አልነበረም ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ለእመቤታችን የተሰጠ ምስጋና ነው ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ ተይዛ
ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል « ጸጋን የተመላሽ ሆይ » አይላትም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጥንተ አብሶ ጸጋዋን ጐዶሎ
ያሰኝባት ነበርና ፡፡ ከላይ እንደገለጥነው እነ ኢሳይያስን ጽድቃቸውን የመርገም ጨርቅ ያሰኘባቸው ጥንተ አብሶ ነው፡፡
የቅድስናን ሥራ እየሠሩ « ሁላችንም እንደ ርኵስ ሰው ሆነናል ፤ » ያሰኛቸው ይኽው ነው ፡፡ ኢሳ 64.6 እነ ኤርምያስንም
፡- « ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም፡፡ ስንዴ ዘሩ እሾህንም አጨዱ ፤ » አሰኝቷቸዋል፡፡ ኤር 12. 13፡፡ እመቤታችን ግን
ከመጀመሪያው ንጽሕት ቅድስት በመሆኗ « ጸጋን የተመላሽ ሆይ ፤ » ተብላለች።
አንዳንዶች፡- ለእመቤታችን ጥንተ አብሶ የጠፋላት መልአኩ ባበሠራት ጊዜ ነው ይላሉ፡፡ ይህም አባባላቸው ሁለት
ጥያቄዎችን ያስነሣል፡፡ 1ኛ ፡- ከዚህ በፊት መልአክ ያበሠራቸው ማኑሄና ሚስቱ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ለምን ጥንተ አብሶ
አልጠፋላቸውም; መሳ 13.2 ሉቃ 1.8 ፤ 2ኛ ፡- ጥንተ አብሶ የሚጠፋው በብሥራተ መልአክ ቢሆን ኖሮ አካላዊ ቃል
ከሰማይ ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው መሆን . መከራ መቀበልና በመስቀል ላይ መሞት ለምን አስፈለገው;
በልዑል መንበሩ እንደተቀመጠ እልፍ አዕላፋት ወትእልፊተ አዕላፋት መላእክትን ልኮ በብሥራት ብቻ ጥንተ አብሶን
አያጠፋም ነበር;

አንዳንዶች ደግሞ « ጌታ በተፀነሰ ጊዜ በዚያ ቅጽበት ነው የጠፋላት ፤ » ይላሉ፡፡ ይህም ፡- «ጌታ የመጣው ጥንተ
አብሶን እንዴት አድርጐ ለማጥፋት ነው; » የሚል ጥያቄ ያስነሣል ፡፡ መልሱም « በመስቀል ላይ በሚፈጽመው ቤዛነት
በሚከፍለው መሥዋዕትነት ነው፤» የሚል ይሆናል ፡፡ እንግዲህ እመቤታችን ጥንተ አብሶ ነበረባት የሚሉ ከሆነ «እርሷም
በጥንተ አብሶ እንደተያዙ እንደማናቸውም ሰው ናት፤ » ማለታቸው ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ እንደማናቸውም ሰው
በመስቀል ላይ በሚፈጸም ቤዛነት ብቻ ከጥንተ አብሶ ትድን ነበር እንጂ ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት ሊሆን አይችልም፡፡
እመቤታችንም የ መላእኩን ቃል ሰምታ ደነገጠች እንዴት ያለ ሰላምታ ነው ብላ አሰበች መላእኩም መልአኩም እንዲህ
አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥
ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ አላት’’ እመቤታችን በመልአኩ አንደበት የተነገረላት በ እግዚአብሔር ፊት ሞገስ አጊኝታለች
።ከዚህም ጋ አያይዞ በድንግልና ጸንሳ በድንግልና እንደምትወለድ ነገራት።ማርያምም መልአኩን። ወንድ ስለማላውቅ
ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ
ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ
ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ’’ አለች።ቃሏን ምክያት አድርጎ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በማህጸኗ ተወሰነ።(የሉቃስ ወንጌል 1:38)
በዚህ የወንጌል ንባብ እመቤታችን በፍጹም ድንግል መሆኗን ያመለክታል።አንዳንድ ስጋውያን እንደሚሉት አረጋዊው
ዮሴፍ እመቤታችን እንዲጠብቃት እንዲያገለግላት ተሰጠችው እንጂ ለባል እና ለሚስት ደንብ አለመሆኑን
እመቤታችንም በስጋ ብቻ ያይደለ የሃሳብ ድንግል መሆኗን ማስርጃ ነው።ስለዚህ የአምላክ እናት ለመሆን ተመረጠች።
ጌታን በህቱም ድንግልና ጸንሳ በህቱም ድንግልና ታህሳስ 29 ቀን ወልዳለች ።
ቃል ሥጋ ሆነ፤ ዮሐ ፩፥፲፬
ቅዱስ ዮሐንስ፦ «ከእግዚአብሔር ተወለዱ፤» በማለት፦ ግዙፋኑ ከረቂቁ ከእግዚአብሔር በመንፈስ በረቂቅ ልደት
እንሚወለዱ የተናገረው ያለምክንያት አይደለም። ሰው ከእግዚአብሔር በመንፈስ መንፈሳዊ ልደት ተወልዶ
የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚሆን ሁሉ፦ ረቂቁ ከግዙፉ ማለትም፦ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከእመቤታችን
ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ የሰው ልጅ እንደሆነ ለመናገር ፈልጎ ነው። በመሆኑም፦ « ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤
» ያላቸው፦ እንደቀድሞው ማለትም፦ እንደ ብሉይ ኪዳን ዘመን በረድኤት ፥ በምሳሌ እንዳይመስላቸው ሲል፦ « ያ
በቅድምና ነበረ ፥ በአብ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነው፥ እግዚአብሔር ነው ፥ ወደ ዓለም የመጣ ብርሃን ነው፥» ያልኳችሁ
አካላዊ ቃል ሥጋ ሆነ ፤ በእኛም አደረ፤ ( በኲነት በመሆን በተዋሕዶ አደረ) ፤» ብሏቸዋል።

«ሆነ፤» የሚለውን ይዘው ፦ «ተለወጠ፤» እንዳይሉበትም «አደረ፤» ብሏል። «አደረ፤» የሚለውንም ይዘው «
ኅድረት ( መለኮት ሥጋንና ነፍስን አልተዋሃደም) ፤ » እንዳይሉበት «ሆነ፤» ብሎባቸዋል። «ኮነ፤» እና «ኀደረ፤» እንደ
አለቃና እንደ ጠበቃ ይጠባበቃሉ። «ኮነ፤» የሚለው ብቻ ተይዞ፦ «ተለወጠ፤» እንዳይባል፦ «ኀደረ፤» ይጠብቀዋል።
«ኀደረ፤» የሚለውም ተይዞ፦ «ኅድረት፤» እንዳይባል፦ «ኮነ፤» ይጠብቀዋል።

ቃል ከእመቤታችን የነሣው ነፍስንም ጭምር ነው

«ቃል ሥጋ ሆነ፤» የሚለውን፦ ንባቡን ብቻ በመያዝ፦ ነፍስን አልነሣም የሚሉ አሉ። ይህም በተዘዋዋሪ ሳይሆን
፥ ፊት ለፊት ከእውነት ጋር መጋጨት ፣ መጣላት ነው። እውነት ደግሞ እግዚአብሔር ነው፤ የነቢዩ የሳሙኤል እናት ሐና
፦ « ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐዳጉድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ
ይፈርዳል፤» ብላለች። ፩ኛ ሳሙ ፪፥፲።

ነፍስ ከሥጋ ጋር በተዋሕዶ ያለች በመሆኗ፦ አካላዊ ቃል በማኀጸነ ድንግል ማርያም አድሮ፦ በመንፈስ ቅዱስ
ግብር ሰው በሆነ ጊዜ ፦ ከሥጋዋ ሥጋ በነሣበት ቅጽበት ፥ ከሥጋ ጋር በተዋሕዶ ያለችን ነፍስም ነሥቷል። ደግሞም ሰው
ማለት የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ነው። ሥጋ ብቻውን ወይም ነፍስ ብቻዋን ሰው አይባሉም። ስለዚህ አካላዊ ቃል
ከእመቤታችን የነሣው ሥጋን ብቻ ቢሆን ኖሮ « አምላክ ሰው ሆነ፤» አይባልም ነበር። እርሱም፦ «የሰው ልጅ፤» ተብሎ
አይጠራም ነበር። ነገር ግን ሰው የሚያሰኘውን ሥጋን ነፍስንም ከእመቤታችን ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው በመሆኑ « የሰው
ልጅ፤» ተብሏል።

- «የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?» ማቴ ፲፮ ፥፲፫ ።


- «የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤» ማቴ ፲፮ ፥፳፯።
- «የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ፥ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክት ይመጣሉ፤» ማቴ ፳፭ ፥ ፴፩።
- «የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደተጻፈ ይሄዳል፥ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤» ማቴ ፳፮፥
፳፬።
- «ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ፤» ማቴ ፳፮ ፥፷፬።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድረ ግብፅ ስደት እያለች ፦ የእግዚአብሔር መልአክ፦ ለአረጋዊው ፥
ለዘመዷ ፥ ለጠባቂዋ ፥ ለጻድቁ ፥ ለዮሴፍ ተገልጦ፦ «የሕፃኑን ነፍሰ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ
ወደ እሥራኤል ሀገር ሂድ፤» ብሎታል። ማቴ ፪፥፳። ቃል፦ ነፍስንም ጭምር ባይነሣ ኖሮ ፦ መልአኩ፦ የሕፃኑን(የኢየሱስን)
ነፍሰ፤ » አይልም ነበር። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ አጸድ በጸለየ ጊዜ፦ «ነፍሴ እስከ
ሞት ድረስ አዘነች፤» ብሏል። ማቴ ፳፮፥፴፰። ቅዱስ አግናጥዮስ፦ ይኽንን ይዞ፦ «ነፍስን አልነሣም የሚል ፥ እንዲህም
የሚክድ ሰው ፥ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ አዘነች ፥ ያለውን የጌታችን የኢየሱስን ቃል ሰምቶ ፥ እንግዲህ ይፈር፤» ብሏል።
(ሃይ አበው ፲፩፥፲፮)። ጌታችን የሞቱንና የትንሣኤውን ነገር ባስተማረበትም ወቅት፦ «ነፍሴንም ደግሞ አነሣት ዘንድ
አኖራለሁና፤» በማለት ተናግሯል። ዮሐ ፲፥፲፯። ድኅነተ ዓለምን ፦ በመልዕልተ መስቀል በፈጸመ ጊዜ ደግሞ ፦ «ኢየሱስም
ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ፤» ይላል። ማቴ ፳፯፥፶። ጌታችን፦ ስለእኛ አሳልፎ የሰጠው ይህ ነፍስ
ከእመቤታችን የነሣው ነው። ማር ፲፭፥፴፯፣ ዮሐ ፲፱፥፴። በሉቃስ ወንጌል ላይ ደግሞ፦ « አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ
እሰጣለሁ አለ፥ ይህን ብሎ ነፍሱን ሰጠ።» ይላል። ሉቃ ፳፫፥፵፮። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፦ ቃል ሥጋንም ነፍስንም
እንደነሣ፦ በተናገረበት አንቀጽ፦ «ነሥአ እምድንግል ሥጋ ዘቦቱ ነፍሰ ነባቢት ወለባዊት፤ ከድንግል የምትናገር ፥
የምታውቅ ነፍስ ያለችው ሥጋን ነሣ፤» ብሏል። (ሃይ አበው ፷፮፥፴)። ቅዱስ ቄርሎስ ደግሞ፦ «በኋላ ዘመንም ገብርኤል
መልአክ ፥ ወደ ንጽሕት ድንግል ማርያም በተላከ ጊዜ፦ ጸጋን ክብርን የተመላሽ ድንግል ሆይ ፥ እግዚአብሔር ከሥጋሽ
ሥጋን ፣ ከነፍስሽ ነፍስን ነሥቶ ሰው ይሆናልና ፥ ክብር ላንቺ ይገባል ብሎ በነገራት ጊዜ፦ ሳይወሰን በማይመረመር ግብር
ያለዘርዐ ብእሲ (ያለወንድ ዘር) በመስማት ብቻ ቃል በማኅፀኗ አደረ፤» ብሏል። (ሃይ አበው ፸፩ ፥፫)።

የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ


ሰው ማለት፦ የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ነው ብለናል። ቅዱስ ዮሐንስ፦ «ቃል ሥጋ ሆነ፤» ያለው፦ «ሥጋን
ብቻ ነሣ፤» ለማለት አይደለም ፥ የነፍስ እና የሥጋን ተዋሕዶ በሥጋ ስም ሲጠራ እንጂ። የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ በሥጋ
ስም ወይም በነፍስ ስም ሊጠራ ይችላል።

በሥጋ ስም በሚጠራበት ጊዜ
ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት፦ በመዝሙሩ፦ «ሰማዕ ጸሎተ ኲሉ ዘሥጋ ዘመጽአ ኀቤከ፤ ወደ አንተ
የመጣውን የሥጋን ሁሉ ጸሎት ስማ፤» ብሏል። መዝ ፷፬ ፥ ፪። ይህም የነፍስንና የሥጋን ተዋሕዶ በሥጋ ስም ሲጠራ
እንጂ፦ ነፍስ የተለየው ወይም የሌለው ሥጋ ብቻውን ይጸልያል ፥ ማለት አይደለም። በመሆኑም፦ «የሥጋን ጸሎት፤»
በማለቱ፦ «ነፍስ የሌለው ሥጋ ብቻውን ጸለየ፤» አያሰኝበትም። ነፍስ የተለየው ሥጋማ ሙት ነው ፥ በድን ፥ሬሣ ፥
አስከሬን ነው። ያዕ ፪፥፳፮።

በነፍስ ስም በሚጠራበት ጊዜ
ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ፦ በግብረ ሐዋርያት መጽሐፉ ላይ፦ ስለ ዮሴፍ ወልደ ያዕቆብ ሲተርክ፦
«የአባቶችም አለቆች፦ በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብጽ ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ። ከመከራውም ሁሉ
አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በከነዓን ሀገር ረኃብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤
አባቶቻችንም የሚበሉት አጡ። ያዕቆብም በግብፅ ሀገር እህል እንዳለ ሰማ፤ አባቶቻችንንም አስቀድሞ ላካቸው፤ ወደ
ግብፅም እንደገና በተመለሱ ጊዜ ወንድሞቹ ዮሴፍን አወቁት፤ ፈርዖንም የዮሴፍን ዘመዶች አወቃቸው። ዮሴፍም አባቱን
ያዕቆብንና ዘመዶቹን ሁሉ እንዲጠራቸው ላካቸው፤ ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ነፍስ ነበረ፤» ብሏል። የሐዋ ፯፥፱-፲፬።
ይህም የሥጋን እና የነፍስን ተዋሕዶ በነፍስ ስም ሲጠራ እንጂ፦ ሥጋቸውን በከነዓን አስቀምጠው፦ በነፍስ ብቻ ወደ
ግብፅ ወረዱ ፥ ማለቱ አይደለም። ቅዱስ ዳዊትም፦ «ዐይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ፤ የሰው ሁሉ ነፍስ አንተን ተስፋ
ያደርጋል፤» በማለት የሥጋን እና የነፍስን ተዋሕዶ በነፍስ ስም ጠርቷል። መዝ ፻፵፬፥፲፭። እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያምም የሥጋን እና የነፍስን ተዋሕዶ በነፍስ ስም ስትጠራ፦ «ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤» ብላለች። ሉቃ ፩፥፵፯።

ነፍስን ጭምር እንደነሣ የሊቃውንት ምስክርነት


ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይኽንን በተመለከተ ያስተማሩት ትምህርት ሁሉ አንድ ነው። ቅዱስ ባስልዮስ
ዘቂሣርያ፦ «ወልድም ኃጢአት እንደበዛ ባየ ጊዜ ፥ በማይነገርና በማይመረመር ግብር ወርዶ ፥ በእመቤታችን በቅድስት
ድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀንም በማኅፀኗ ተወሰነ። በእርሷ አድሮ ሊዋሐደው የፈጠረውን
ፍጹም ሥጋን በአብ ፈቃድ፥ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ከእርሷ ነሣ። ከፈጣሪነት እንዳናወጣው፦ አብ ፈጠረለት ፥
አንበል፤ ሊዋሐደው እርሱ ፈጠረው እንላለን እንጂ። ከአብ ጋር በሥራው ሁሉ ( በፈጣሪነት)፦ አንድ ጌትነት ፥አንድ አገዛዝ
አለውና፤ ሰው ለመሆን በወረደ ጊዜ፥ ሥጋን ይዞ አልመጣም ፤ የሰው ዘር፦ ምክንያት ሳይሆነው፦ ከድንግል ማርያም
ሥጋን ነፍስን ነሥቶ ተዋሐደ እንጂ።» በማለት መስክሯል። (ሃይ አበው ፻፲፯፥፱)። ቅዱስ አቡሊድስም፦ «ሥጋ የሌለው
እርሱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆነ፤ እርሱን የምንመስል ሰማያውያን
ያደርገን ዘንድ፤ እርሱ ሰማያዊ ነውና።» በማለት አስተምሯል። (ሃይ አበው ፴፱፥፵፮)። የሮም ሊቀ ጳጳሳት፦
አዮክንድዮስም፦ «እግዚአብሔር ከሰማይ በወረደ ጊዜ፦ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀንም ባደረ
ጊዜ፦ ከእርሷም ሥጋን ነፍስን ነሥቶ ሰው በሆነ ጊዜ፦ ከሰማይ ሥጋን ይዞ አልመጣም፤ መለኮቱም ከምድር አልተገኘም።
» በማለት ተናጎሯል። (ሃይ አበው ፵፬ ፥፪) ቅዱስ ኤጴፋንዮስ ደግሞ የቅዱስ ዳዊትን ትንቢት ሲተረጉም፦ «ነቢዩ ዳዊት፦
ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ የባሕርይ ልጅህንም ሙስና መቃብርን ያይ ዘንድ አሳልፈህ አትሰጠውም፥ አለ። ይህም ጌታ
በተዋሐደው አካል ያለውን የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ያስረዳል፤ የቀና ልቡና፥ እውቀት ፥ በእርሱ ጸንቶ ይኖር ዘንድ ዳዊት
የተናገረው እውነት ሆነ። ነፍስ መለኰትን ተዋሕዳ ወደ ሲኦል ወርዳለችና፤ ሥጋም ሦስት መዓልት ፥ሦስት ሌሊት ፥
በመቃብር ሳለ፦ መለኮት፦ ከሥጋ አልተለየም። አምላክ ሰው የመሆኑን እውነትነት ያስረዳ ዘንድ፦ መለኮትና ነፍስ
በሲኦል ምሥጢርን ፈጽመዋልና፤ በሲኦልም በቁራኝነት አልተያዙምና።» ብሏል። (ሃይ አበው ፶፭፥፯)። በዚህም፦ «ቃል
ሥጋን እንጂ ነፍስን አልነሣም ፥ መለኮቱ እንደ ነፍሰ ሆነለት፤» የሚሉትን ፈጽሞ አሳፍሯቸዋል። ቅዱስ ኤራቅሊስም፦
«አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው አካል፦ ሥጋ ከእርሱ ጋር አንድ ሆነ፤
ከባሕርያችን ተገኝቶ ፦ አምላክ የሆነ ሥጋ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ሕይወቱ ሲሆን፦ የምትናገር የሥጋ ሕይወት ነፍስ
አለችው፤» ብሏል። (ሃይ አበው ፵፰፥፳፩)። ቅዱስ ቄርሎስም በበኲሉ፦ «ቅዱሳን አባቶቻችን፦ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ
ክርስቶስ፦ ከአብ ባሕርይ የተገኘ፦ አንድ ወልድ ፥ ቃል ፥ እንደሆነ ተናገሩ፤ ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ፥
ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፥ ሁሉ የተፈጠረበት እርሱ፦ ነፍስን ሥጋን ነሥቶ፦ ሰው ሆነ፤ ከድንግልም በሥጋ ይወለድ ዘንድ
ወደደ፥ በእኛም ባሕርይ ተገለጠ ፥ ሰው የሆነበት ባሕርይ ይህ ነው።» በማለት የእውነት ምስክር ሆኗል። (ሃይ አበው ፸፪፥
፩)

ቃል ሥጋ የሆነው ፦ ያለ ሚጠት ነው

ሚጠት፦ ማለት፦ መመለስ ማለት ነው። ይኽውም እንደ ማየ ግብፅ ፥ እንደ በትረ ሙሴ ነው። «ሙሴና አሮንም
እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን አነሣ፤ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤
የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለወጦ ደም ሆነ።» ይላል። ዘዳ ፯፥፳። የግብፅ ወንዞች ደም የሆኑት ውኃነታቸውን ሙሉ በሙሉ
ለቅቀው ነው። በመጨረሻም ደምነታቸውን ትተው ወደ ውኃነታቸው ተመልሰዋል። ባይመለሱ ኖሮ እስከዛሬም የግብጽ
ወንዞች ደም ሆነው በቀሩ ነበር። ሚጠት ማለት እንዲህ ነው።
እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ይህ በእጅህ ያለው ምንድን ነው?» አለው። እርሱም «በትር ነው፤» አለ። «ወደ
መሬትም ጣለው፤ አለው፤ እባብም ሆነ፤ ሙሴም ከእርሱ ሸሸ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «እጅህን ዘርግተህ ጅራቱን
ያዝ፤» አለው፤ ሙሴም እጁን ዘርግቶ ፥ ጅራቱን ይዞ ፥ አነሣው፤ በእጁም ላይ በትር ሆነ።የሙሴ በትር እባብ የሆነችው
እንጨትነቷን ለቅቃ ነው። በዚያው አልቀረችም ፥ ተመልሳ በትር ሆናለች። ዘፀ ፫፥፪። እንግዲህ ቃል ሥጋ ሲሆን፦
አምላክነቱን ለቅቆ ሰው የሆነ ፥ ተመልሶም ሰውነቱን ለቅቆ አምላክ የሆነ አይደለም። ቅዱስ ቄርሎስ፦ «ክርስቶስን በፊት
ሰው ሆኖ ኋላ ተመልሶ አምላክ ሆነ አንለውም፤ ቃል ጥንቱን አምላክ ነበረ እንጂ፤ እርሱ አንዱ፦ ሰው የሆነ አምላክ
እንደሆነ እናውቅ ዘንድ፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፸፪፥፭)

ቃል ሥጋ የሆነው፦ ያለ ውላጤ ነው

ውላጤ ማለት መለወጥ ማለት ነው። ይህም እንደ ብእሲተ ሎጥ እና እንደ ማየ ቃና ነው። ቅዱሳን መላእክት፦
ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል፦ ሎጥን፦ «ተነሣ፤ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ አንተም
በከተማይቱ ሰዎች ኃጢአት እንዳትጠፋ፤» ብለውት ከከተማይቱ እያቻኮሉ አውጥተውታል። ከዚህም በኋላ፦ ራስህን
አድን፤ ወደ ኋላ አትይ ፥ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም ፥ እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።» ብለውታል።
ዘፍ ፲፱ ፥፲፪-፳፰። የሎጥ ሚስት ግን ቅዱሳን መላእክት የሠሩላቸውን ሥርዓት አቃልላ በዚያ ሥፍራ ቆመች ፥ ወደ
ኋላዋም አየች። በዚህም ምክንያት ሙሉ በሙሉ ተለውጣ የጨው ሐውልት ሆና ቀርታለች።

በአዲስ ኪዳን ደግሞ፦ በቃና ዘገሊላ ሠርግ ነበረ፤ በዚህ ሠርግ ላይ፦ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ፥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና የጌታ ደቀመዛሙርት ነበሩ። እናትን ጠርቶ ልጅን ፥ ወይም ልጅን
ጠርተው እናትን፤ መምህርን ጠርተው ደቀመዛሙርትን ፥ ወይም ደቀመዛሙርትን ጠርተው መምህርን ማስቀረት
ስለማይገባ ሁሉም ተጠርተዋል። ወደ ሠርጉ የተጠሩ እድምተኞች ብዙዎች ስለነበሩ ፥ የወይን ጠጁ አልቆ ሠራተኞቹ
ተጨነቁ። ከሰው ወገን የሰው ችግር ፈጥኖ የሚገባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሳይነግሯት አውቃላቸው
አማለደቻቸው። ጌታም በስድስቱ የድንጋይ ጋኖች ያስሞላውን ውኃ በተአምር ወደ ወይን ጠጅነት ለወጠው። ዮሐ ፪፥
፩-፲፩። ውኃው ሙሉ በሙሉ ተለውጦ የወይን ጠጅ ሆኗል። ውላጤ ማለት እንዲህ ነው። «ቃል ሥጋ ሆነ፤» ማለት ግን፦
አምላክነቱን ለቅቆ ፥ ተለውጦ፥ ሰው ሆነ፤ ማለት አይደለም። ምክንያቱም ቃል እግዚአብሔር ነውና፤ ዮሐ ፩፥፪።
እግዚአብሔር ደግሞ አይለወጥም። ይኽንንም፦ «እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤» በማለት ነግሮናል። ሚል ፫፥፮።
ደግሞም ቃል ሥጋ የሆነው በመለወጥ ቢሆን ኖሮ፦ ጌታችን፦ ሰው ከሆነ በኋላ፦ «እኔና አብ አንድ ነን፤» አይልም ነበር።
ዮሐ ፩፥፴። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦ በመስቀል ላይ የፈሰሰውን ደም፦ «የእግዚአብሔር ደም፤» አይለውም ነበር።
የሐዋ ፳፥፳፰። ከዚህም ሌላ አምላክ ወደዚህ ዓለም የመጣበትን የማዳን ዓላማ መርሳት አይገባም። ለመሆኑ ጌታችን
ዓለምን ለማዳን ተለወጦ ሰው መሆን ለምን አስፈለገው? በሰማይ ዙፋን እንደተቀመጠ፦ በአንድ ነቢይ ወይም በአንድ
ሐዋርያ ደም ዓለምን አያድንም ነበር? ቅዱስ ቄርሎስ፦ «ቃል ሰው ሲሆን ከነበረበት ባህርዩ አልተለወጠም ፥ በእኛ ባሕርይ
ቢገለጥም ፦ ቃል አስቀድሞ በነበረበት ባሕርዩ ጸንቶ ኖረ፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፸፪ ፥፬) ። ዳግመኛም፦ «የማይታየው
ሳይለወጥ ሰው ሆነ፤ ከቀደሙ አበው፦ አስቀድሞ የነበረ እርሱ በሥጋ ተወለደ፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፸፪ ፥ ፲፭)።
ሦስተኛም፦ «የእግዚአብሔር ቃል ሥጋን ወደ መሆን ፥ ሥጋም መለኮትን ወደ መሆን ተለወጠ አንልም ፤ የእግዚአብሔር
ቃል አይናወጥም ፥ አይለወጥምና፤» ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፸፬፥፵) ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙም፦ «ሁሉን የፈጠረ ነው
፤ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ፥ ሰውም ሆኖ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ እግዚአብሔር ቃል ነውና፤ እርሱ
መቸም መች አንድ ነው ፤ የመለኮቱ ባሕርይ አልተለወጠም፤» ብሏል። (ሃይ ፡ ፷፥፲፯)። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ደግሞ፦ «ዳግመኛ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ፦ ጽኑዕ መለኮቱ ከባሕርዩ አልተለወጠም፤ አምላክ ለሦስትነት እንደሚገባ
ተወለደ፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፷፯ ፥፯)። ቅዱስ ኤፍሬምም በሐሙስ ውዳሴ ማርያም ላይ፦ «እምድኅረ ወለደቶ
ድንግልናሃ ተረክበ ፥ ወመለኮቱ ኢተወለጠ ኮነ ወልደ ዕጓለ እመሕያው፤ «እርሱንም ከወለደችው በኋላ ማኅተመ
ድንግልናዋ አልተለወጠም ፥ ሰውም ቢሆን ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠም፤» ብሏል።

ቃል ሥጋ የሆነው ያለ ቱሳሔ ነው

ቱሳሔ ማለት፦ ቅልቅል ፥ የተቀላቀለ ማለት ነው። ይኸውም እንደ ማር እና እንደ ውኃ ፥ እንደ ወተት እና እንደ
ቡና ነው። ማር እና ውኃ ቢቀላቀሉ፦ ስም ማዕከላዊ ፥መልክ ማዕከላዊ ፥ ጣዕመ ማዕከላዊ ፥ ይገኝባቸዋል። ስም
ማዕከላዊ የሚባለው፦ የዕለቱ ብርዝ ፥ የሰነበተው ጠጅ ይባላል እንጂ ከቀደሙት ስሞች በአንዱ ወኃ ወይም ማር
ተብለው አይጠሩም። መልክ ማዕከላዊ የሚባለው፦ ብርዙ ወይም ጠጁ፦ እንደ ማር አይነጣም ፥ ወይም እንደ ውኃ
አይጠቁርም ፥ ማዕከላዊ መልክ ይይዛል። ጣዕም ማዕከላዊ የሚባለው ደግሞ፦ እንደ ማር ሳይከብድ ፥ እንደ ውኃም
ሳይቀል መካከለኛ ጣዕም ይኖረዋል። ወተት እና ቡናም ሲቀላቀሉ እንዲሁ ናቸው። እንደ ወተት ያልነጣ ፥ እንደ ቡናም
ያልጠቆረ ማዕከላዊ መልክ ያመጣሉ፤ ጣዕማቸውም ከሁለቱም ወስዶ ማዕከላዊ ይሆናል፤ ስማቸውም፦ በማዕከላዊ
ስም፦ «ማኪያቶ» ቢባል እንጂ በቀደመ ስም ቡና ወይም ወተት ተብለው አይጠሩም።

ቃል ሥጋ የሆነው እንዲህ አይደለም፤ እንዲህ ቢሆን ኖሮ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክም ፥ የሰው ልጅም ተብሎ
አይጠራም ነበር። ነገር ግን ሰው ከሆነ በኋላ «የሰው ልጅ፤» ተብሎ ተጠርቷል። ማቴ ፲፮፥፲፫። ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
ደግሞ፦ «የእግዚአብሔር ልጅ (የአብ ልጅ ወልድ) እንደመጣ ፥ እውነተኛም የሆነውን እግዚአብሔርን እናውቅ ዘንድ
ልቡናን እንደሰጠን እናውቃለን፤ . . . እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው፤» ብሎታል። ፩ኛ ዮሐ ፭፥፳።
ይኽንን በተመለከተ፦ ቅዱስ ቄርሎስ፦ «መለኮትና ትስብእት እርስ በርሳቸው ሳይቀላቀሉ፦ መለየት በሌለበት ተዋሕዶ
ፈጽመው አንድ ሆኑ፤» ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፸፫ ፥፴)።

ቃል ሥጋ የሆነው ያለ ትድምርት ነው

ትድምርት ማለት፦ መደረብ ፥ መደመር ማለት ነው። ይህም እንደ ልብስ ፥ እንደ እንጀራ ነው። ልብስ ቢደርቡት
ይደረባል ፥ ቢነጥሉት ይነጠላል፤ እንጀራም ቢደርቡት ይደረባል ፥ ቢነጥሉት ይነጠላል። ቃል ሥጋ የሆነው እንዲህ፦
በመደረብ ወይም በመደመር አይደለም። መለኮት፦ ከሥጋ ተጠግቶ ፥ ወይም ተደርቦ፥ የኖረ፦ በኋላም ተለይቶ የሄደ
አይደለም። ቅዱስ ቄርሎስ ፦ «ሥጋንም ለእርሱ ብቻ ገንዘብ አደረገ፤ ልብስ ከአካል እንዲለይ መለኮትን ከትስብእት
አንለየውም፤ በተዋሕዶ ጸንቶ ይኖራል እንጂ፤ እግዚአብሔር እንደሆነ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ አውቀነዋል።»
ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፸፪፥፴)። በተጨማሪም፦ «መለኮትና ትስብእት አንዱ ከአንዱ ጋር በኅብረት የሚኖሩ አይደለም፤
አንዱ በአንዱ አላደረም፤ መለኮትና ትስብእት በባሕርይም በአካልም አንድ ናቸው እንጂ። ሰው የሆነ እርሱ እግዚአብሔር
ነው፤ በዚህ አንቀጽ ከሥጋ ጋር መዋሓዱን የምናገርለት፤ መለኮትን በመዋሓድም አምላክ የሆነው ሰው ነው፤» በማለት
ተናግሯል። (ሃይ፡ አበው ፷፩ ፥ ፳፩) ፡

ቃል ሥጋ የሆነው ያለ ቡዓዴ ነው

ቡዓዴ ማለት፦ መለየት ፥ አለያየት ፥ ልዩነት ፥ ማለት ነው። ለምሳሌ፦ ሁለት የተለያዩ ነገሮችን ፦ (ብረትንና
እንጨትን)፦ በብሎን ማያያዝ ፥ መልሶም መለያየት ይቻላል። የቃል ሥጋ መሆን እንዲህ አይደለም። የአንጾኪያ ሊቀ
ጳጳስ አባ ዮሐንስ፦ «ይህም ወልድ ዋሕድ ፥ እግዚአብሔር ቃልን ፦ ከወለደችው ከእመቤታችን ከንጽሕት ከቅድስት
ድንግል ማርያም የተገኘ ነው፤ ግድ ሰው ሁን ፥ ያለው ሳይኖር፦ ከእርሷ በፈቃዱ ሥጋን ነሣ፤ ለመለኮት ለትስብእት
እንደሚገባ ያለመከፈል፦ (በተዋሕዶ) የአምላክነትን ፥ የሰውነትን ሥራ ሠራ፤ እንደ ሰው አነጋገር ይናገራል፤ አምላክ
እንደመሆኑ ሙት ያስነሣል፤ ድውይ ይፈውሳል፤ መከራም ይቀበላል፤ ነገር ግን፦ ከማይነገርና ከማይመረመር ተዋሕዶ
በኋላ፦ አምላካዊነት ባሕርይ ፥ ከሰብአዊት ባሕርይ ተለይታ አይደለም፤ አነጋገሩን ፥ ሥራውን ፥ መከራውን ፥ ይህ፦
ለመለኮት ይገባል፤ ይህ፦ ለትስብእት ይገባል ፥ እያልን በየራሳቸው አንለይ፤ አንድ ባሕርይ ፥ አንድ አካል ፥ አንድ ገጽ
በመሆን (በተዋሕዶ) ሠራው እንበል እንጂ፤» ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፻፲፫ ፥፲፬)።

ቃል ሥጋ የሆነው በኅድረት አይደለም

ከላይ እንደገለጥነው፦ ቅዱስ ዮሐንስ፦ አስቀድሞ ፦ «ሆነ፤» ያለው፦ «አደረ፤» የሚለውን ይዘው ኅድረት
እንዳይሉበት ነው። «ኅድረት፤» ማለት፦ ማደር ማለት ነው። ይኸውም፦ እንደ ውኃና ማድጋ ፥ እንደ ዳዊትና ማኅደር ፥
እንደ ሰይፍና ሰገባ ነው። እነዚህ አንደኛው አካል በሌለኛው አካል እንደሚቀመጡ፦ (ኀዳሪና ማኅደር) ፦ እንደሆኑ ፥
መለኰትም ፦ ሥጋን ማኅደር አድርጎ የተቀመጠ አይደለም። ይኽንን በተመለከተ፦ ቅዱስ ቄርሎስ፦ «እርሱ አንድ ወልድ
አንድ ጌታ ነው፤ ቃል በዕሩቅ ብእሲ አላደረም ፥ በክብሩም አላስተካከለውም፤ ብዙ ሰዎች በድንቊርና አስበው
እንደተናገሩት በኅድረት የልጅነትን ክብርና አምላክነትንም አልሰጠውም ፤ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፥ ከእግዚአብሔር
የተገኘ የእግዚአብሔር ቃል፦ እርሱ ነፍስን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ሆነ እንጂ።» ብሏል። (ሃይ ፡አበው ፸፪ ፥ ፲፩)። ዳግመኛም፦
«እግዚአብሔር ቃልስ ዓለምን ሳይፈጥር አስቀድሞ የነበረ ነው፤ የተዋሓደውን ሥጋም ከሰው ባሕርይ ፈጠረው፤
ከተዋሕዶ በኋላ ለክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አሉት ብሎ የተናገረ ከእነርሱ (ከአባቶቻችን) አንድ ሰው እንኳ አለን? ወይስ
በእግዚአብሔር ፈቃድ በድንግል ማኅፀን ፍጹም ሕፃን ተፈጠረ ፥ ከዚህ በኋላ ከማርያም በተገኘው በዚያ ሕፃን
እግዚአብሔር ቃል አደረበት ብሎ የተናገረ አለን? ወይስ ከተዋሕዶ በኋላ ለአንድ ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አሉት ተብሎ
ሊነገር በውኑ ይገባልን?» ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፸፭ ፥፲፩)።

ተጨማሪ ማስረጃ ከሊቃውንት

ቅዱስ አቡሊድስ፦ «ፈጣሪ እርሱ በሰው ያደረ አይደለም፤ በነቢያት በሐዋርያት አድሮ ሥራ የሠራ፦ ፍጹም
አምላክ በሥጋ ተገለጠ እንጂ። ሰውም ቢሆን በመለኮቱ ፍጹም ነው፤ . . . ከአብ ዘንድ ብቻውን የተወለደ ፥ ከድንግልም
አንድ ብቻውን የተወለደ እርሱ አንድ ነው እንጂ። በተዋሕዶ ሰው የሆነ የባሕርይ አምላክ ነው።» ብሏል። (ሃይ፡ አበው
፴፱ ፥፲፩)። ዳግመኛም፦ «መቀላቀል ፥ ይህንንም የመሰለ ሌላ ነገር የለበትም እንላለን፤ ተዋሕዶው እውነተኛ ስለሆነ
ተቀላቀለ ማለት አይስማማውምና። የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ ዋሕድ ነፍስን ሥጋን ነሥቶ ሰው ሆነ ባልን ጊዜም፦
ስለዚህም ነገር ቢሆን እነዚያ( መናፍቃን) እንደሚያምኑ መቀላቀል የለበትም፤ የቃል ባሕርይ የሥጋን ባሕርይ ወደ መሆን
፥የሥጋ ባሕርይም የቃልን ባሕርይ ወደ መሆን አልተለወጠም፤ ሁለቱ ባሕርያት ያለመለወጥ ያለመቀላቀል ጸንተው
ይኖራሉ እንጂ።» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፵፭ ፥፭)።

ቅዱስ ፊልክስ፦ «ክርስቶስ በሐዲስ ግብር (በኅድረት በውላጤ) አልመሰለንም፤ በማይመረመር ተዋሕዶ
ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጎ ነው እንጂ። ብሏል። ቅዱስ ጎርጎርዮስም፦ «የእግዚአብሔር ቃል፦ ድንግል ማርያም
በወለደችው ሰው እንዳደረ የሚናገሩትን፦ እኔ ልበ ሰፊ በመሆን፦ የትስብእትና የመለኮት ሁለቱ ባሕርያት በተዋሕዶ
አንድ የሆኑ አይደለምን? ብዬ እጠይቃቸዋለሁ፤ በአካል ፍጹም የሚሆን የቃል ባሕርይ፦ የምታውቅና የምትናገር ነፍስ
ያለችውም የሥጋን ባሕርይ ተዋሕዷልና ፥ በሥጋም ከድንግል ተወልዷልና። ሰው ሆኖ የታየ እርሱም በፍጡራን ልቡና
ከመመርመር የራቀ ነው፤ ከመለኮትና ከትስብእት ከሁለቱ ባሕርያት ድንቅ በሚያሰኝ ምሥጢር አንድ ክርስቶስ ሆነ፤
ቅን ልቡና ያላቸው ሰዎች ግን አግዚአብሔር በሰው እንዳደረ አይናገሩም ፥ ተዋሕዶ አዲስ ሥራ ነውና ፥ ድንቅ
ምሥጢርም ነውና። . . . እኛ ግን እግዚአብሔር ቃልን ከነፍስ ከሥጋ አንለየውም፤ ከዓለም ሁሉ አስቀድሞ የነበረ፦
ቀዳማዊ ወልድ ዋሕድ መዋሓዱን እናምናለን እንጂ፤ በመዋሓዱም ከሥጋው ጋር አልተቀላቀለም፤ እኛን ለማዳን ነፍስ
ልቡና ያለው ሥጋን ከእኛ ባሕርይ ነሥቶ ተዋሐደ እንጂ።» ብሏል።(ሃይ፡ አበው ፷፮፥፪ ፣፲፮)።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፦ «ነገር ግን እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ አንድ እንደሆነ ብንናገር ፥ ወዲህም ከእኛ
ባሕርይ የተገኘ ሥጋ ያለመለየት በማይመረመር ተዋሕዶ ከቃል ጋር አንድ መሆኑን እኛ እናውቃለን፤ ሥጋ የመለኮትን
ባሕርይ እንዳልለወጠ ፥ መለኮትም እንዲሁ የሥጋን ባሕርይ አልለወጠም፤ እርሱ ወልድ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ
ነው፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፷፯ ፥፴፩)። ቅዱስ አትናቴዎስም፦ «እርሱ ሰው የሆነ አምላክ ነው፤ ስለዚህም መለኮት ሥጋን
ወደ መሆን ፥ ሥጋም መለኮትን ወደ መሆን አይለወጥም፤ እርሱ ከመለወጥ ከመለዋወጥ ሁሉ የራቀ ነው፤ ከተዋሕዶ
በኋላ ግን ፈጽሞ መለየት የለበትም፤ ሰው የሆነ ቃል፦ አንድ አካል ፥አንድ ባሕርይ መሆኑ እውነተኛ ተዋሕዶው የጸና
ነው፤ እግዚአብሔር ያደረባቸው አበው እንዳስተማሩን፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፻፮፥፲፫)። ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ደግሞ፦
«አድሮ እንደተናገረባቸው እንደ ነቢያት ሁሉ አይደለም፥ ፍጹም ሰው ሆነ እንጂ። ቃል ሥጋ ሆነ፤ አልተለወጠም ፤
መለኮቱን ሰው ወደ መሆን አልለወጠውም ፤ ከመለኮት ጋር ጽኑዕ አንድነቱን በተዋሕዶ አደረገ እንጂ።» ብሏል። (ሃይ፡
አበው ፶፯ ፥፳፰)።

ቃል ሥጋ የሆነው በተዋሕዶ ነው
አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ሰው የሆነው በተዋሕዶ ነው። ተዋሕዶውም እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ ተዋሕዶ ነው።
ነፍስ ረቂቅ ናት ፥ ሥጋ ደግሞ ግዙፍ ነው፤ ነፍስ ረቂቅነቷን ሳትለቅ ፥ ሥጋም ግዝፈቱን ሳይተው በተዋሕዶ ጸንተው
ይኖራሉ። በመሆኑም አንድ ሰው እንጂ ሁለት አይባሉም።

ቅዱስ ቄሮሎስ፦ የተዋሕዶን ነገር በብረትና በእሳት እየመሰለ አስተምሯል። «በእግዚአብሔር ቃል፦ በረቂቅ
ባሕርይ የሆነውን ተዋሕዶ አንካድ ፤ ብረት ከእሳት በተዋሐደ ጊዜ፦ ከእሳትም በመዋሐዱ የእሳትን ባሕርይ ገንዘብ
ያደርጋል፤ (ማቃጣል መፋጀት ይጀምራል)፤ ብረት በመዶሻ በሚመታበት ጊዜ፦ ከእሳቱ ጋር በአንድነት(በተዋሕዶ)
ይመታል፤ ነገር ግን ከመዶሻው የተነሣ የእሳት ባሕርይ በምንም በምን አይጐዳም፤ ሰው የሆነ አምላክ ቃልም በመለኮቱ
ሕማም ሳይኖርበት፦ በሥጋ እንደታመመ እናስተውል፤» ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፸፫ ፥፲፪)።

ቅዱስ አትናቴዎስ፦ የተዋሕዶን ምሥጢር ሲያስረዳ፦ «አሁንም በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ እንደሆነ ሰምተህ
ዕወቅ፤ አምላክ ብቻ ከሆነማ እንደምን በታመመ ነበር? ወይስ እንደምን በሰቀሉት ነበር? ወይስ እንደምን በሞተ ነበር?
ይህ ሥራ፦ (ሕማምና ሞት) ከእግዚአብሔር የራቀ ነውና፤ ዘዳ ፴፪፥፵። ሰው ብቻ ከሆነ በታመመ በሞተ ጊዜ ሞትን
እንደምን ድል ይነሣው ነበር? ይህ ከሰው ኃይል በላይ ነውና። ፩ኛ ቆሮ ፭ ፥፲፫ ፣ ዕብ ፭፥፩-፬።» ብሏል። ስለ እመቤታችን
ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲናገር ደግሞ፦ «ድንግል ወንድ ሳታወቅ ሊዋሐደው በፈጠረው ሥጋ የፀነሰችውን
ወለደች፤ ያለ ኃጢአት ያለ ምጥ ወለደችው፤ የአራስነት ግብር አላገኛትም፤ ያለ ድካም ያለ መታከት አሳደገችው፤ ያለ
ድካም አጠባችው፤ ለሥጋ በሚገባ ሕግ ምን አበላዋለሁ? ምን አጠጣዋለሁ? ምን አለብሰዋለሁ? ሳትል አሳደገችው፤»
ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፳፯ ፥፮ ፣ ፳፰፥፲፱)። በተጨማሪም፦ «ዳግመኛም በክህደታቸው አስበው፦ ማርያም የወለደችው፦
ገዥ ፥ ፈጣሪ እንዳይደለ የሚናገሩ የመናፍቃን ልጆች ፈጽመው ምላሽ ይጡ፤ እግዚአብሔር ቃል ሥጋን ካልተዋሐደ
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ እንደምን አማኑኤል ተባለ? ትርጓሜውም እግዚአብሔር
ከሥጋችን ሥጋ ፥ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ ማለት ነው። ኢሳ ፯፥፲፬ ፣ ማቴ ፩፥፲፰-፳፭።
እንኪያስ ቃል ሥጋን ካልተዋሐደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በእውነት ለዘለዓለሙ
የከበረ አምላክ ከሁሉ በላይ የሚሆን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ በሥጋ ታመመ ብሎ እንደምን ጻፈ? ሮሜ
፭፥፯-፲፪ ፣ ፱፥፩-፭፤» ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፴፭፥፲፱)።

የቅዱስ ባስልዮስ ወንድም ቅዱስ ጎርጎርዮስ፦ «ትስብእትን ከመለኮት ልዩ ነው ፥ አትበሉ፤ ከተዋሕዶ በኋላ
አይለይምና፥ አይቀላቀልምና፤ መለኮትን ከተዋሐደው ከትስብእት ልዩ ነው ፥ አትበሉ፤ በርሱ ያለውን ተዋሕዶውን እመኑ
እንጂ፤» ብሏል። (ሃይ ፡ አበው ፴፭ ፥፲፱)። በተጨማሪም፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች የጻፈውን
መልእክት በተርጐመበት አንቀጽ፦ «እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው ኢየሱስ
ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ሥራ በልቡናችሁ ዕወቁ፤ ሽቶ(ፈልጎ) ቀምቶ ከእግዚአብሔር ጋር የተካከለ አይደለም፤ ራሱን
አዋርዶ ሰው ኹኖ የተገዥን ባሕርይ ተዋሕዶ ነው እንጂ። ፊል ፪፥፭-፰። ሥጋን ከመዋሐድ የበለጠ በእግዚአብሔር ዘንድ
ምን ድህነት አለ? ነገር ግን እርሱ ነገሥታትን ፥ መኳንንትን ፥የሚገዛ ሲሆን፦ እኛን ወደ መምሰል በመጣ ጊዜ፥ የተገዥን
ባሕርይ በተዋሐደ ጊዜ ፥ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አላነሰም። ምድርን የፈጠረ እርሱን በትውልድ እንበልጣለን የሚሉ ሐና
ቀያፋ ዘበቱበት፤ ፍጥረትን ሁሉ የሚገዛ እርሱ የሚያርፍበት ቦታ አላገኘም፤ በሥጋ በተወለደ ጊዜ ላሞች በሚያድሩበት
በረት አስተኙት እንጂ። መዝ ፳፫፥፩፤፺፪፥፩፤፺፭፥፲፫፤ ማቴ ፰፥፳፣ ሉቃ ፪፥፩-፯። የማይለወጥ ንጹሕ ቃል የሚለወጥ
የሰውን ባሕርይ ተዋሐደ፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፴፭፥፳፱-፴፫)።

ቅዱስ አብሊድስ፦ «ዳግመኛም ቃልን ከሥጋ አዋሕደን እንሰግድለታለን፤ . . . ፍጡር ሥጋን ፈጣሪ እንደተዋሐደው
እናምናለን፤ ፈጣሪ ከፍጡር በተዋሐደ ጊዜ ፦ አንድ አካል በመሆን የጸና አንድ ባሕርይ ሆነ፤ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ
አይደለም፤ የመለኮትንና የትስብእትን ተዋሕዶ እናውቃለን፤ ባሕርያችን ሁለት (ነፍስና ሥጋ) ሲሆን አንድ ይሆናል፤ አንድ
አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ያድጋል፤ አንድ ሰውም ይባላል፤ ዘፍ ፩፥፳፮፣ ዕብ ፪፥፲፬።» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፴፱፥፳፩-
፳፬) ። በተጨማሪም፦ «ከአብ ጋር አንድ ነው፥ እንዳልነው ሁሉ ሥጋን በመዋሐድ ከሰው ጋር አንድ ነው፥ እንላለን፤
መለኮትም ለሰው የሚገባ ስምን ገንዘብ ያደርጋል፤ ሥጋን በመዋሐድ ከእኛ ባሕርይ ጋር አንድ ስለሆነ ከእርሱም ጋር
አንድ ስለአደረገው። ኢሳ ፱፥፮ ፣ ማቴ ፩፥፳፪ ፣ ፊል ፪፥፭። ከተዋሐደው ከሥጋ ባሕርይ ምንም አልተለወጠም፤ አንድ
መሆንም ሰውን ወድዶ ስለ መዋሓዱ የመለኮት ባሕርይ እንዳልተለወጠ መጠን ፥ ከእርሱ ጋር አንድ ከሚሆን
ከእግዚአብሔር ጋር ገንዘቡ የሚሆን መተካከል ያለበት ስም ነው። ማቴ ፳፰፥፲፱ ፣ ሉቃ ፩፥፴፪ ፣ ዮሐ ፩፥፩ ፤ ፲፥፴ ፣ ፩ኛ
ቆሮ ፰፥፮፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፵፥፲፮)።

ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ደግሞ፦ «በዘመኑ ሁሉ የማይለያዩትን የአምላክነትን የሰውነትን ግብራት በተዋሕዶ አጸና፤
ክርስቶስ በመለኮቱ ያይደለ በሥጋ አንደታመመ ተናገረ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደተናገረ መለኮት ከትስብእት
አልተለየም፤ መለኮትና ትስብእት አንድ ባሕርይ በመሆን ተዋሓዱ እንጂ። ፩ኛ ጴጥ ፫፥፲፰ ፣፬-፩። ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስም ፦ መለኮትንና ትስብእትን አንድ አድርጎ እርሱን የክብር ባለቤትን ባልሰቀሉትም ነበር ብሎ ተናገረ፤ ፩ኛ ቆሮ
፪፥፰።» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፶፯ ፥ ፴፮)።

ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም፦ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን ሰዎች የጻፈውን መልእክት በተረጎመበት
እንቀጽ፦ «የተዋሐደውን ሥጋ ከመላእክት ባሕርይ የነሣው አይደለም ፥ ከአብርሃም ባሕርይ ነሣው እንጂ። ዕብ ፪ ፥ ፲፯።
ለዚህ ታላቅ ፍቅር አንክሮ ይገባል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ወገን ለተደረገ ለማይመረመር ለዚህ ፍቅር አንክሮ
ይገባል፤ ይህ ለመላእክት ያላደረገው ነው። የተደረገውን አስተውል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ባሕርይ የተዋሐደው ተዋሕዶ
ጥቂት ክብር አይምሰልህ፤ ይህንን ለመላእክት አላደረገውምና ፥ የመላእክት ባሕርይ አልተዋሐደችውምና ፥
የተዋሐደችው የእኛ ባሕርይ ናት እንጂ። ባሕርያችንን ተዋሕዷል እንጂ። ከባሕርያችን ከፍሎ ተዋሐደ ለምን አላለም?
ወዳጁ እንደኮበለለ እስኪያገኘውም ድረስ እንደሄደና እንዳገኘው ሰው የእኛ ባሕርይ እንደዚህ ከእግዚአብሔር ተለይታ
ነበርና፤ ከእርሱም ፈጽማ ርቃ ነበርና፤ ሥጋ በመሆን ገንዘብ እስኪያደርጋት ድረስ ፈጥኖ ፈለጋት ፤ እርሷም ተዋሐደችው፤
ይህንንም ተዋሕዶ እኛን በመውደድ እንዳደረገው የታወቀ ነው። መኃ ፫፥፬ ፣ ማቴ ፲፰፥፲፪ -፲፬፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው
፷፫፥፪-፭)። በተጨማሪም፦ «ተዋሕዶንም አስረዳለሁ፤ እግዚአብሔር ቃል በአካሉ ፍጹም የሚሆን ነፍስ ፣ ዕውቀት ያለው
ሥጋን ከእኛ ባሕርይ ነሥቷልና፤ እርሱንም ተዋሕዷልና፤ ስለዚህም ነፍስን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል
አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ እንናገራለን፤» ብሏል። (ሃይ፡ አበው ፷፯፥፴)።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፦ ጌታን፦ በድንግልና መውለዷ በራሱ ምሥጢረ ተዋሕዶን ያስተምረናል።
ይኸውም፦ በመንፈስ ቅዱስ ግብር በድንግልና የጸነሰችውን አምላክ በድንግልና የወለደችው፦ መለኮት ከእርሷ የነሣውን
ሥጋና ነፍስ በመዋሐዱ ነው። ምክንያቱም፦ በተዋሕዶ የመለኮት ገንዘብ ለሥጋ፥ የሥጋም ገንዘብ ለመለኮት ሆኗልና።
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል፦ እመቤታችንን ባበሠራት ጊዜ፦ «ከአንቺ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፤
(የእግዚአብሔር አብ ልጅ፦ እግዚአብሔር ወልድ ነው፥ ከሦሥቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው) ፤ ማለቱም ለምሥጢረ ተዋሕዶ
ምስክር ነው። ሉቃ ፩፥፴፭። ምክንያቱም መለኮት በማኅፀን ነፍስን እና ሥጋን ባይዋሐድ ኖሮ ከእመቤታችን
የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ፥ ከሦስቱ ቅዱስ(ከሥላሴ) አንዱ ቅዱስ ነው ፥ አይባልም ነበር።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ በመዋዕለ ሥጋዌው ያደረጋቸው ተአምራትም ምሥጢረ
ተዋሕዶን የሚያሳዩ ናቸው። ለምሳሌ፦ ሁለት ማየት የተሳናቸውን ሰዎች በእጆቹ በዳሰሳቸው ጊዜ፦ ተፈውሰዋል። ይህም
ሊሆን የቻለው መለኮት በተዋሐዶ ከሥጋ ጋር ስለነበረ ነው። ማቴ ፱፥፳፯-፴፩። ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ፦ ዓይነ ስውር
የነበረውንም ብላቴና በምራቁ አፈሩን ለውሶ በዚያ ፈውሶታል። ምራቅ የሥጋ ነው፤ ነገር ግን መለኮት ሥጋን
ስለተዋሐደው ፥ ከተዋሕዶ በፊት የሥጋ ብቻ የነበረ ምራቅ የብላቴናውን ዓይን አብርቶለታል። ዮሐ ፱፥፩-፲፪።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው፦ መግነዝ ሳይፈታለት ፥
መቃብር ሳይከፈትለት ነው። ሥጋ በራሱ መቃብር ሳይከፈትለት መውጣት አይችልም ። መለኮት ግን የሚያግደው
የለም። በመሆኑም፦ መለኮታዊ አካልና ባሕርይ ፥ ከሥጋ አካልና ባሕርይ ጋር ተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ
በመሆኑ፦ ልዩነት ሳይኖር መቃብሩ እንደታተመ ከመቃብር ወጥቷል። ከትንሣኤው በኋላም በሩ ሳይከፈት
ደቀመዛሙርቱ ወደነበሩበት ቤት ገብቷል። ደቀመዛሙርቱ፦ ይህ ምሥጢር ረቅቆባቸው፦ በእርሱ አምሳል ምትሐት
የሚያዩ መስሏቸው ነበር። እርሱ ግን፦ « ምን ያስደነግጣችኋል? በልባችሁስ እንዲህ ያለ ሐሳብ ለምን ይነሣሣል? እጄንና
እግሬን እዩ፤ ዳስሱኝም፤ እኔ እንደሆንሁም ዕወቁ፤ በእኔ እንደምታዩት ለምትሐት አጥንትና ሥጋ የለውምና፤» ብሎ
ተዳሰሰላቸው። ይህ የዳሰሱት አካል ነው፥ መዝጊያው ሳይከፈት የገባው። ምክንያቱም መዝጊያና ግድግዳ የማያግደው
መለኮት እንደ ነፍስና ሥጋ ተዋሕዶታልና። ማቴ ፳፰፥፩-፲ ፣ ሉቃ ፳፬፥፲፮ ፣ ዮሐ ፳፥፲፱።

ጌታችን፦ በዝግ ቤት ለደቀመዛሙርቱ በተገለጠላቸው ጊዜ ቶማስ አልነበረም። የሆነውን ሁሉ በነገሩት ጊዜ፦


«የችንካሩን ምልክት በእጁ ካላየሁ ፥ ጣቴንም ወደተቸነከረበት ካልጨመርሁ ፥ እጄንም ወደጎኑ ካላገባሁ አላምንም፤
አላቸው። ከስምንት ቀን በኋላም በሩ እንደተዘጋ ፥ ቶማስ ባለበት ተገልጦላቸው፦ «ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ »አላቸው።
ከዚህም በኋላ ቶማስን ፦ ጣትህን ወዲህ አምጣና እጆቼን እይ ፤ እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ
ተጠራጣሪ አትሁን፤» አለው። ቶማስም ፦ ከዳሰሰ በኋላ፦ «ጌታዬ አምላኬም» ብሎ መለሰ። የዳሰሰው አካል፦ እሳተ
መለኮት የተዋሐደው በመሆኑ እጁን ፈጅቶታል። በመሆኑም ቢዳሰስለት፦ «ጌታዬ» ቢፈጀው፦ «አምላኬ» ብሏል። ዮሐ
፳፥፳፰።

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊም፦ አይታይ አይዳሰስ የነበር መለኮት የሚታይ የሚዳሰስ ሥጋን ተዋሕዶ በሰውነት (
ነፍስንም ጭምር በመዋሐድ) በመገለጡ፦ «ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያ የነበረውንና በጆሮአችን የሰማነውን ፥
በዓይኖቻችንም ያየነውን፥ የተመለከትነውንም ፥ እጆቻችንም የዳሰሱትን እንነግራችኋለን። ሕይወት ለእኛ ተገልጻለችና
አየናት ፥ ምስክርም ሆንን፤ ለእናንተም ከአብ ዘንድ ያለችውንና ለእኛ የተገለጠችውን የዘለዓለምን ሕይወት
እንነግራችኋለን፤» ብሏል። ፩ኛ ዮሐ ፩፥፩።

የእመቤታችን ስደት

እመቤታችን ጌታን ከወለደችው ግዜ ሰብአ ሰገል ከሩቅ ምስራቅ( ባቢሎን) ወደ ኢየሩሳሌም አደረሳቸው።
ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ተሰወረባቸው።እነርሱም የተወለደው የ አይሁድ ንጉስ ወዴት ነው?ብለው ሲጠይቁ በጊዜው
የነበረው ንጉስ ሄሮድስ ከሰራዊቱ ጋር ይህንን ሰምቶ ደነገጠ።ካህናተ አይሁድን ንጉስ የት እንደሚወለድ ጠየቀ እነርሱም ቤቴልሄም
እንደሆነ ነገሩት እርሱም ሰብአ ሰገል ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ ጠየቃቸው እነርሱንም 2 አመት እንደሆነው ነግሩት።
እነርሱንም ወደ ቤቴልሄም እንዲሄዱ ላካቸው።ኮከቡም ተገለጠላቸው፤ቤቴልሄም ደርሰው ህጻኑን ከእናቱ ማርያም ጋር
አገኙት።ሳጥናቸውንም ከፍተው ወርቅ እጣን ከርቤ እጅ መንስሻ አገቡለት።ከዛም የጌታ መልአክ በ ሌላ መንገድ 40ኛው
ቀን ወደ ሀገራቸው አስገባቸው።(ማቴ 2፣1_13) እነርሱም ከሄዱ በኋላ የጌታ መልአክ በህልም ተገልጾ ህጻኑን ከእናቱ ጋር
ይዞ ወደ ግብጽ ወርዳለች(ተሰዳለችና)፣በስደቷ ወራት ስለ ልጇ ስትል ተርባለች ተጠምታለች፣የእመቤታችን ስደት ለ3
አመት ከ6 ወር ነበር። ሄሮድስም ጌታን የሚያገኝ መስሎት በርከት ያለ ቁጥር ያላቸውን የቤቴልሄም ህጻናት በግፍ
እንዲጨፍጨፉ አድርጓል።(ማቴ 2፣13_21፤ራእ 12፣12፤ኢሳ 19፣1፤ሆሴ11፣1)

የእመቤታችን እረፍት፣ትንሳኤ እና እርገት

እመቤታችን በእናት በአባቷ ቤት 3 ዓመት በቤተ መቅደስ 12 ዓመት ጌታን ጸንሳ 9 ወር ከ5 ቀን ጌታን በድንግልና
ወልዳ ከጌታ ጋር 33 ዓመት ከ 3 ወር አብራ አልተለየችም ጌታን በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሳለ ከእግረ መስቀሉ ሥር
አብራ ነበረች ። ጌታም ለሚወደው ደቀመዝሙር ለቅዱስ ዮሃንስ አደራ ሰጣት ቅዱስ ዮሃንስም ወደ ቤቱ ወሰዶ
አገለገላት ።(ዮሓ19፤26) በድምሩ 24 ዓመት በድምሩ 64 ዓመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን 49 ዓ.ም ገደማ ከዚህ አለም
ድካም አርፋለች ።

በ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚተረከው የእመቤታችን እረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያት


የእመቤታችን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኔ መካነ መቃብር ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅናት መንፈስ ተነሳስተው ቀድሞ
ልጇን በ 3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ በ 40ኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረግ እንደገናም ይህን አለም ለማሳለፍ የመጣል
እያሉ በማስተማር ህዝቡን ፈጽመው ወስደውታል።አሁንም ዝም በለን ብንተዋት እርሷም እንደልጇ አረገች እያሉ
በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን ብለው ኑ! ተሰብሰቡና በ እሳት እናቃጥልጥ ብለው ተማክርው ከመካከላቸው
ታውፋንያ የተባለ ጎበዝ አይሁዳዊ ተመርጦ ሄደ የእመቤታችንንም ሥጋ የተሸከመበትን አልጋ ሸንኮር ያዘ የአልጋውም
ሸንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሄር መልአክ በ እሳት ሰይፍ ሁለቱን እጆቹን ስለቆረጣቸው ተንጠልጥለው ቀሩ።ነገር ኝ
ታውፋኛ በ ፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በ ኅኑዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደቀድሞውው
አድርጋ ፈውሳቸዋለች።

በዚያን ጊዜም መልአከ እግዚአብሄር የእመቤታችንን ሥጋ ከሐዋርያው ከዮሃንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ ከ ገነት እጸ
ህይወት ስር አስቀመጠው ፤ቅዱስ ዮሃንስም ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችንን ሥጋ በ ገነት
መኖሩን ነገራቸው።ሐዋርያትም የእመቤታችንን ሥጋ አግኝተው መቅበር በነበራቸው ምኞት እና ፍላጎት ነሓሴ 1 ቀን
ሱባኤ ጀምረው ከ 14 ወይም ሁለት ሱባኤ እንደጨረሱ ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ አስክሬን አምጥቶ
ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ እና ውዳሴ በጽኑዕ ምሕላ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀ መካነ እረፍት ጌቴሴማኔ ቀበሯት ።

የእመቤታችን የቀብር ስነስርዐት በተፈጸመ ጊዜ ከ12 ሐዋርያት የሆነው ቅዱስ ቶማስ አልነበረምና ከ ሃገረ ስብከቱ
ከ ሕንድ በ ደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በ 3ኛ ቀን እንደ ልጇ ተነስታ ሲታርግ
ያገኛታል። በዚያን ጊዜም ትንሳኤዋን ሌሎቹ ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረ መስሎት ተበሳጭቶ በልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ
ቀረው ብሎ ከማዝኑም ከደምና ተወርውሮ ሊወድቅ ቃታው።በዚህ ጊዜ እመቤታችን ከእርሱ በቀር ሌሎች ሐዋርያት
ትንሳኤዋን እንዳላዩ ነግራው ቅዱስ ቶማስ አጽናናችው።ሄዶም ለወንድሞቹ ለ ሐዋርያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራቸው
አዘዘችው።ለምልክት ምስክር የሆን ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው በመላእክት ታጅባ እየተመሰገነች ወደ ሰማይ አርጋለች።ሐዋርያ
ቅዱስ ቶማስም ሐዋርያት ወደ አሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት እርሱም አውቆ
ምስጢሩን ደብቆ አይደረገም ሞት በ ጥር ነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል አላቸው ።አንተ ቀድሞ የጌታን ትንሳሴ
ተጠራጠርክ በለው በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ወደ እመቤታችንመካነ እረፍት ይዘውት ሄደው ሊያሳዩት ቢከፍቱት
የእመቤታችንን ሥጋ ስላጡ ደነገጡ።ቅዱስ ቶማስም አታምኑኝም በዬ እንጂ እመቤታችንማ ተነስታ አርጋለች ብሎ
የሆነውን ሁሉ ነገራቸው።ለምስክርም ይሆን ዘንድ ሰበኗን አሳያቸው።እነርሱም ሰበኗን ቆራጠው ከተከፋፈሉ በኋላ ወደ
አህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል።

በአመቱ ትንሳኤሽን ቶማስ አይቶ እኛ እንዴት ይቅርብን ብለው ነሐሴ 1 የጀመሩ በ 16ኛው ቀን ጌታችን
የለመኑትን ልመና ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር፣ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ(ረዳት) ቄስ፣እስጢፋኖስ ገባሬ ሰናይ(ዋና
ዲያቆን)አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም ከአቆረባቸው በኋላ የእመቤታችንን ትንሳኤዋን እና ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል።
የእመቤታችን የ ቅድስት ድንግል ማርያም ትንሳኤ እና እርገት በትንቢተ ነብያት የተነገረ ነበር።መዝ 131፤8/መኃ 2_5)

"ዕርገተ ማርያም!" በመጻሐፍ ቅዱስ

"ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።" ዮሐ3፣13

እርሱ በማለት በመዉጣት እና በመዉረድ እንድዉም \\ የሰዉ ልጅ \\ ተብሎ የተነገረዉ ወልደ አምላክ እርሱ ራሱ
አምላክ የሆነ \\1ኛዮሐ5፣20 ‹ዮሐ1፣1\\ ጌታችን ክርስቶስ ነዉ:: ሥጋን በመዋሀዱ በመዉጣት በመዉረድ ተነገረለት
እንጅ እርሱ ከዓለም አስቀድሞ የነበረ ፡፡ \\ ዮሐ1፣1\\ ለእስራኤል ዘሥጋ ( በብሉይ ለነበሩ ሕዝበ እግዚአብሔር) ማደርያ
ይሆን ዘንድ መቅደስ ስሩልኝ

አላቸዉ (ዘፀ25፣8) ነገር ግን አምላክነቱ በምድር በሰማይ የሞላ መሆኑን ልያሳስባቸዉ ( ሰማይ ዙፋኔ ነዉ፣ ምድርም
የእግሬ መረጌጫ ናት እናንተ የምትሰሩልኝ ቤት ምን አይነት ነዉ?) \\ኢሳ66፣1\\ እንዲሁም (ሰማይ ከሰማይ በላይ
ያለዉ ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም) \\1ኛነገ8፣27\\ በብዙ ክፍሎች
ላይም የእግዚአብሔርን ምድር መሸከም እንደ ማትችል ይነገራል ከፍና ዝቅ፣ መዉጣትና መዉረድ ለሰዉ ልጅ የሚነገር
ነዉ፡፡ በመጽሐፈ ነገስት ላይ ሰዉ የሆነ ኤልያስ በዐዉሎ ንፋስ ወደ ሰማይ ወጣ ይለዋል \\2ኛነገ2፣11\\፣ እንዲሁም
ሄኖክን \\ዘፍ5፣24\\ (አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋረ ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሔር ወስዶታል፡፡) እኝ ቅዱሳን አረጉ
ስንል አካሄዳቸዉ ከእግዚአብሔር

ጋር አደረጉ እርሱ ሰወራቸዉ ማለታችን እንደሆነ ግልፅ ነዉ፡፡ ከእግዚአብሔር ዉጪ በራሳቸዉ አረጉ ማለት አይደለም፡፡

ጌታችን መዳንታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ይይዘዉ ዘንድ የማይቻለዉ አምላክ ነዉ፡፡ \\ሐዋ2፣24.. 2ኛጢሞ1፣10\\
የሕይወት ጌታ ሕይወትን የሰጠን፣ የትንሳኤ ጌታ ትንሳኤን የሰጠን \\ዮሐ11፣25\\ በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት
ተወስኖ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

ከሥጋዋ ሥጋ ከነብሷ ነብስ ነስቶ ተወለደ፡፡ \\ገላ4፣4..ሉቃ1፣31-32\\ ከእርሳም የነሳዉን ሥጋና ደም ሥጋየን የበላ
ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለዉ\\ዮሐ5፣53\\ ብሎ ተናገረ ፣መለኮት ሥጋና ደም የለዉም እርሱ ሰዉ ከመሆኑ
በፊት መለኮት ነዉ፤ የዘላለም ሕይወት የሚናገኝበትን ሥጋና ደም የሕይወት ጌታ ከእመቤታችን ነሳ፡፡ እርሱ በእዉነት
ሕይወት ነዉ፤ የእዉነተኛ ሕይወት እመቤታችን የእርሱ እናት ናትና የሕይወት እናት እንላታለን፡፡

ንፁሁ የሆነዉ ጌታችን ስለሰዎች ሲል አጥያት የሌለበት፣ አምላክ እንዲ ነዉ ተብሎ በአፍ ከመነገር በልብ ከመዘከር በላይ
የሆነ አምላክ ይህን ያህላል በዚህ አለ ተብሎ የማይነገርለት በአንዲት ንፅህት ቅድስት ድንግል ብላቴና ማህፀን ተወሰነ ፣
ይህ ማህፀን በእዉነት እንዴት ያለ ነዉ? በዉስጡ ስብሐቴ (ምስጋና) እግዚአብሔር የምቀርብበት እዉነትም ለዚይህ
ማህፀን አንክሮ

ይገባል፡፡ ተወለደ ጌታ እንደ ህፃን ድሆ፣ለእናቱ እየታዘዘ፣ቀስ በቀስ እንደ ሰዉ አደገ፣ የሰዉ ልጅ ድኅነት ከፅንስ እስከ
መስቀል ፈፀመ፣ ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለምና የማይሞተዉ ሞተ(ዕብ9፣-) ሰዉን ልያድን ፡፡

ሰዉ ሞትን የሞተዉ በሀጢያቱ ነዉ፡፡ እርሱ ግን ንፁ ነዉ፣ አሰቀድሞ አንፅቶ ለዓለም ድኅነት የመረጣት የድኅነታችን
መጀመርያ ያደረጋት እመቤታችን ናት (ንፅህተ ንፁሀን ) ሰዉ ቢሞት በሀጢያቱ ነዉ፡፡ ጌታም ቢሞት የሰዉን ልጅ ለማዳን
(የሰዉን ሁሉ ሀጢያት ተሸክሞ)ነዉ፣ እርሱ ካልሞተ ድኅነት የለም፡፡

እርሷ ግን (እመቤታችን) ንፅህት ስትሆን ለምን ሞተች ይህን ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር (ለሟች ሁሉ ሞት
ይገባዋል የእመቤታችን ሞት ግን ያስገርማል ብሏል) የሕይወት እናት ሆና በመሞቷ ተደንቆ፣ መሞቷ ሰዉ መሆኗን
ያመለክተናል፡፡ ቅ.ጳዉሎስ( ሮሜ6፣5 ||ሞትን በሚመስል ሞቱ ከተባበርነዉ

ትንሳኤዉን በሚመስል ትንሳኤ እንተባበራለን||) እንለዳዉ በልጇ ፍቃድ ሞታለች፣ትንሳኤዉን በሚመስል ትንሳኤ
በእርሱ ፍቃድ እንደ ልጇ እርሷም በሶስተኛዉ ቀን ተነስታለች፡፡ አስቀድሞ የእናቱንና የእርሱን እርገት በትንቢት አናግሯል
ሊቃዉንተ ቤተ-ክርስቲን የማረጓን ነገር በትንቢተ ነቢያት የተነገረዉን ሚስጥር ተርጉመሁልናል ይህም ቃል
\\መዝ131(2):8 አቤቱ ወደ እረፍት ተነስ አንተና የመቅደስ ታቦት \\ ቅዱስ ዳዊት በአማረ ቤት ዉስጥ እኔ ተቀምጨ

የእግዚአብሔር ታቦት እንዴት በድንኳን ታድራለች ብሎ ከነቢዩ ናታን ጋር ሱባኤ ገባ፡፡ ምድራዊዉን የእግዚአብሔር
ማደርያ(ቤተ-መቅደስ) ሲለምነን ለነቢዩ ናታን ምድራዊዉን ቤተ-መቅደስ እርሱ መስራት እንደማይችል ልጁ ሰለሞን
እንደሚሰራዉ ገለፀለት፡፡ ቤተ-መቅደሱን የሰራዉ ልጁ ሰለሞን ነዉ፡፡ ለቅዱስ ዳዊት ግን የልደቱን ሚስጥር ገለጠለት
አማናዊቷ ቤተ-መቅደስ ከእርሱ አብራክ እንደምትወጣ ገለጠለት ለዚህ ነዉ፣ ከምዕራፉ መጀመርያ ጀምሮ ስንመለከት

ወደ ቤቴም አልገባም ፣ ለዓይኖቼም መኝታ ለጉንጮቼም እረፍት የላቸዉም እግዚአብሔር ማረፍያ ለያዕቆብ አምላክ
ማደረያ እስከ አገኝ ድረስ \\መዝ131(132)\\ ይህ ፀሎቱ ነዉ፡፡ ወረድ ስንል እነሆ በኤፍራታ ሰማነዉ በዱር ዉስጥ
አገኘነዉ(የጌታ ልደት ተገልጦለት)፡፡ ሲል እንመለከታለን ከዚያም (አቤቱ ወደ እረፍት ተነስ አንተ እና የመቅደስ ታቦት )
በማለት ወደ ጥልቁ ሚስጥር ሲገባ እንመለከታለን፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር አብን መቅደስ የተባለዉ ልጅህን እና
የልጅ(የክርስቶስ) ማደርያ ታቦትን ይዘህ ወደ ሰማይ አርግ ማለት ነዉ፡፡

በዝርዝር ስናየዉ \\ታቦትና መቅስ\\ የሚሉ ሁለት ወሳኝ ቃላት አሉ፡፡ መቅደስ የተባለዉ የጌታችን ሰዉነት ነዉ፣
\\በዮሐ2፣19\\ ይህ ቤት መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛዉም ቀንም አነስዋለዉ አላቸዉ እርሱ ግን ስለ ሰዉነቱ ቤተ-
መቅደስ ይል ነበር፡፡\\ዮሐ2፣21\\ ይላል ስለዚህ ጌታችን መቅደስ ይባላል፡፡ ታቦት የእመቤታችን ምሳሌ ነዉ፣ አማናዊቷ
ታቦት እርሷ ናት፡፡ ታቦት ማለት ማደርያ ማለት ነዉ፡፡ እመቤታችን ታቦት የተሰኘችበት ምክንያት ታቦት ዉስጥ ያለዉ
የእግዚአብሔር ቃል ነዉ፡፡ \\ዘፀ25(ዘፀ31)(ዘፀ32)\\ አማዊቷ ታቦት እመቤታችን ናት ቃል የተባለዉን ወልድ ኢየሱሰ
ክርስቶስ በማህፀኗ የያዘች ናት፡፡

ታቦት በዉስጥም በዉጭም በወርቅ እንድለብጠዉ ሙሴን እግዚአብሔር አዞታል፡፡ \\ዘፀ25፣11\\ ወርቅ የንፅህና
ምሳሌ ነዉ እርሷም በዉስጥም በዉጭም ንፅህት ናት \\ሉቃ1፣34\\(ማርያምም መልአኩን፡፡ ወንድ ስለማላዉቅ ይህ
እንዴት ይሆናል? አለችዉ፡፡ ) ወደፊትም ልጅ የመዉለድ ሀሳብ የሌላት፣ሀሳብ ቢኖራት ኖሮ ልክ ነህ ወደፊት ጎጆ ቀልሸ
እወልዳለዉ ባለች ነበር፡፡ ንፅህተ ህልና እራሷን ለእግዚአብሔር ያጨች አማናዊት ሙሽራ ናት፣ ስለዚህ በታቦት
ትመሰላለች፡፡

ታቦቱን ለማጠን (ለማገልገል) ካህኑ አሮን የተመረጠዉ፣ ከተመረጡት ሰዎች በትር መሀከል የአሮን በትር ለምልማ
በመገኘቷ ምክንያት ነዉ፡፡ \\ዘኁ17፣8\\ ቅዱስ ዮሴፍም እመቤታችን ለመጠበቅ(ለማገልገል) የተመረጠዉ ከተመረጡት
በትር መሀከል የእርሱ በትር በመለምለሟ ምክንያት ነዉ፡፡\\ታምህረ ማርያም\\ ስለዚህ በታቦት ትመሰላለች፡፡

ታቦተ ጽዮን በፍልስጤማዉያን ተማርካ ድል አድርጋ ወደ አገሯ ስትመለስ መዝሙሬኛዉ ዳዊት (የእግዚአብሔር ታቦት
እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?)\\2ኛሳሙ6፣9 ብሏል ይህንኑ ቃል በሐድስ ኪደዳን ለእመቤታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ
ስትናገር እንመለከተታለን፡፡(የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል ? )ሉቃ1፣43 ስለዚህ በታቦት
ትመሰላለች፡፡

የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በገባ ጊዜ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ይዘልል ነበር፡፡2ኛሳሙ6፣14 (ኤልሳቤጥም
የማርምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማህፀንዋ ዉስጥ ፅንሱ በደስታ ዘለለ) ሉቃ1፣41 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ (እንደ
ዮሐንስ በማህፀን ሆነን ማመስገን( በደስታ ዘለለ ) ቢያቅተን እንዴት እንደ ዳዊት ከተወለድን በኃላ ማመስገን ያቅተናል፡
፡) ተመለሰች፡፡ ) (ሉቃ1፣56) እኝህ ሁሉ ከላይ ያየናቸዉ አማናዊቷ ታቦት እመቤታችን መሆኗን እንገነዘባለን፡፡በብሉይ
ወደ ቤተ-መቅደስ ስንገባ ኪሩብን(የእግዚአብሔርን መንበር የምሸከሙ) እንመለከታለን የአዲስ ኪዳን ኪሩብ
እመቤተታችን ናት፣ ዛሬ ወደ ቤተ-መቅደስ ስንገባ እመቤታችንን ነዉ የምንመለከተዉ፡፡(አቤቱ ወደ እረፍት ተነስ )
ተብሎ የተነገረዉ ለእግዚአብሔር አብ ነዉ፣ መቅደስ የተባለዉን የባሕርይ ልጅህን የወልድ ማኅደር(ማደርያ) ታቦቱን
እመቤታችንን ይዘህ ወደ መንግሥተ ሰማይ ተነስ የሚል ፍች አለዉ፡፡
መነሳትስ ለእመቤታችን ትልቅ ነገር አይደለም፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነዉ እንጅ እኛም እንነሳለን፡፡ ወደ ሰማይ አርጋለች ስንል ልጇ
አሳርጓታል ማለታችን እኮ ነዉ፡፡ በስንት ጊዜ አንዴ ሀሳባችንን ሰብስበን የሚንፀልይ ሰዎች፣ እንደዚ የከበረች የሆነች እናት
እንዴት ቀደመችን? ማለት በፍፁም የማይወን ነዉ !!! ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነዉ፣ እርሷ ግን በሕይወት
ዘመኗ ከእርሱ ጋር ስትነጋገር የኖረች እኮ ናት !!! ለዚይህ አንክሮ ይገባል፡፡ ባይሆን ሊያስጨንቀን የሚገባዉ በሰማይ ምን
አይነት አቀባበል ተደርጎላት ይሆን ? የሚለው ነዉ!፡፡

ዳዊት በታቦት ፊት ዘለለ፣ በምድር የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል ያለች ኤልሳቤጥ ተናገረች ፣
ቅዱሳን ሁሉ፣ መላዕክት የጌታቸዉ እናት ስትመጣ እንዴት ተቀበሏት!፣ (ሉቃ16፣16-) ላይ አላዘር መላዕክት ወደ
አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ይላል እመቤታችንን ምን ያህል መላዕክት ናቸዉ የወሰዷት ?፣ ጠቢቡ ሰሎሞን እናቱ ቤርባቤኤ
ስትመጣ ከመንግስተ ወንበሩ

ተነስቶ ተቀብሏታል በቀኙም አስቀምጧታል \\1ኛነገ2፣19\\ ሰዉ በቻለዉ አቅም እናቱን በምድር ላይ ያከብራል
የሰማይ እና የምድር ጌታ የሆነ ጌታ አምላክ እናቱን እንደት ይቀበላት ይሆን? በእዉነት ሃይማኖታዊ ጥያቄስ ከሆነ እንዲ
ነዉ የሚጠየቀዉ ! እንጅ ይህ በፍፁም አይሆንም እንዴት ታርጋለች የሚል ካለ ለምሳሌ- ሄኖክ እና ኤልያስ በሕይወት
ሳሉ አርገዋል፣ ሐሳዊ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይገደላሉ 3ቀን በድናቸዉ በጎዳና ከቆየ በኃላ ከእግዚአብሔር የወጣ

የሕይወት መንፈስ ገባባቸዉ በእግራቸዉ ቆሙ ----- በሰማይም ወደዚህ ዉጡ የሚላቸዉን ታላው ድምፅ ሰሙ፡፡
\\ራዕ11፣10-12\\ እኝ ቅዱሳን በአካለ ሥጋ ካረጉ የእናታችን የቅድስተ-ቅዱሳን ማረግ ትልቅ ነገር ሊባል አይችልም!፡፡

በወንጌል ጌታ እራሱን መንግስተሰማይ ብሎ ጠርቷል (ሉቃ17÷21) እመቤታችን ወደ መንግስተሰማይ ማረግ ቢቻ


ሳይሆን መንግስተሰማይ የሆነ እርሱ ልጇ እኮ በሆዷ ነዉ!!! በእዉነት መንግስተሰማይ ሆይ እንኳን ደስ አለሽ ካንች
የበለጠሰማይ ስላየሽ ልንላት ይገባል !!!ለዚህ ማህፀን በእዉነት አንክሮ ይገባል --- !!!የእናታችን ፍቅሯ አይለየን!!!

ምዕራፍ ሁለት

ክብረ ድንግል ማርያም


እመቤታችን ከሁሉ ይልቅ ወላዲተ አምላክ በመሆኗ ከፍጥረት ሁሉ የከበረች ናት። ይህ ከእግዚአብሔር
የተስጣት ክብር ድግሞ በተለያዩ መንገዶች ይግልጣል:- የሚከተሉት እመቤታችንን ክብር ከሚያሳዩት ማካከል
የሚጠቀሱ ናቸው።

ሀ. ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከተለዩት የተለየች ከከበሩት የከበረች የሚያደርጋት ማኅተመ ድንግልናዋ
ሳይለወጥ አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷ ነው። (ማቴ. ፩፥፲፰-፳)

እምቤታችን ጌታን ከመፅንሷ በፊት ፣ በፀነች ጊዜ ፣ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፣ በወለደች ጊዜ ፣ ከወለደች
በኋላ ድንግል ናት። እመቤታችን ከሌሎች ሴቶች ተለይታ እግዜብሔር ከፈጥራት ጀምሮ በሀሳብ ፣ በመናገርና
በመሥራት ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት ንጽሕት ድንግል ናት።
ድንግል የሚልው ቃል በርግጥ ቅድስናዋን ንጽሕናዋን ብቻ ሳይሆን ልዩ መሆንዋንም ያመለክታል። በዓለም
ከሚኖሩ ሴቶች እንደ እመቤታችን ድንግልናን ከእናትነት እናትነትን ከድንግልና አስትባብራ የተገኘች ሴት የለችም።

እመቤታችን የዘለዓለም ድንግል ናት (መኃል. ፬፥ ፲፭) ነብዩ ሕዝቅኤል የተመለከተው ራዕይም እመቤታችን እናትና
ድንግል መሆኗን ነው። (ሕዝ. ፵፬፥፫)

ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስም "ቅዱስ ገብርኤል ወደ አንዲት ድንግል ትላከ የዚያችም ድንግል ስም ማርያም ነው"
በማለት ስለድንግልናዋ ተናግሯል። (ሉቃ. ፲፪፥፯)።

ነቢዩ ኢሳያስም "እንሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" (ኢሳ.፯፥፲፬) በማለት ስምዋን እስከ ግብሯ
ድንግል ብሏታል። ወንጌላዊያን ማቴዎስና ሉቃስም ከላይ የተነገሩት ትዕንቢቶች እንዴት በተግባር እንደተተረጎሙ
መስክርዋል(ማቴ.፩፥፲፰ ፣ ሉቃ.፪፥፴-፴፭) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በድንግልናዋ ፀንታ የኖረች የአምላክ
እናት ናት እንጂ ሌሎች ልጆችን የወለደች አይደለችም። የተመረጠችውም ለአምላክ እናትነት ብቻ ነውና።

በማቴዊስ ወንጌል ፩፥፳ እና በሉቃስ ወንጌል ፩፥፳፯ ላይ እመቤታችን የዮሴፍ እጮኛ ስትባል ከቆየች ብኋላ በማቴዎስ
ወንጌል ፪፥፲፫ ፣ ፲፬፥፳ እና ፳፩ ላይ የዮሴፍ እጭኛ መባልዋ ቀርቶ ሕፃኑን ከእናቱ ጋር መባል ተጀመረ። ለምን?

ዮሴፍ እመቤታችንን ወደ ቤቱ እንዲወስዳት የታዘዘው እንዲጠብቃት እንጂ እንዲያገባት አይደለምና፣

ምንም እንኳን የመልአኩን ብስራት ከመስማቷ በፊት እመቤታችን የዮሴፍ እጮኛ የነበረች መሆኗ ቢገልጥም
መልአኩ ቅድስ ገብርኤል ወንድ ልጅ ትወልጃልሽ ብሎ ባበሰራት ጊዜ “እኔ ድንግል ነኝ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብላ
መጠየቅዋ በድንግልና ለመኖር የነበራትን ቁርጥ ሀሳብ ያረጋግጣል።”

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ በድንግል መውለዷ ታላቅ ትምህርታዊ ምሥጢር አለው።
ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘር በሩካቤ ቢወለድ ኖሮ ዕሩቅ ብእሲ ነው ባሉት ነበርና ነው።

ሌላው ደግሞ ትንቢቱና ምሳሌውን ለመፍጸም ነው። ትንቢቱ ምንድነው ቢሉ "ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ
ልጅም ትወልዳለች" ተብሎ ይትንግረው ይፍጸም ዘንድ (ኢሳ.፯፥፲፬) ነው።

ምሳሌውም ድግሞ ቀዳማዊ አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል። ይህም የክርስቶስ ምሳሌ ነው። ምክንያቱም ከኅቱም
ማኅፀነ ድንግል ተገኝቷልና ነው። የቀደመው አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል ዳግማይ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ድንግል
ካልሆነች ቢገኝ የቀደመው ከኋላኛው ይበልጣል ያሰኛል። ይህ ደግሞ የሚያንሰው የሚበልጠውን ሊያድን አይችልምና
"አልዳንም" ወደሚል ክህድት ያድርሳል። ስለዚህ እመቤታችን ከዚያችኛዋ ኅቱም ምድር የምትበልጥ ፍጹም
ድንግልናት።

ስለ ወላዲተ አምላክ ዘላለማዊ ድንግልና ስናነሳ ለማመን የሚቸግሩ አንዳንድ ሰዎች የሚያነሱት ጥያቄ ከዚህ ጋር
አያይዘን በጥቂቱ እንመልከት :-

ሀ. በሉቃስ ወንጌል (፪፥፯) ላይ የበኩር ልጅዋን ወለደች መባሏ ሌሎች ልጆች ያሉዋት መሆኑን ያመለክታል ይላሉ።

ለ. በማቴዎስ ወንጌል (፩፥፳፭) ላይ የበኩር ልጅዋን እስከምትወልድ አላወቃትም መባሉ ከወለደች በኋላ አውቃት
ለማለት ነው የሚሉ አሉ።
ሐ. በተከያዩ ቦታዎች የጌታችን ወንድም ወይም ወንድሞች ተብሎ መጠቀሱ እመቤታችን ሌሎችን ለመውልዷ
ማስረጃ ነው ብለው ይከራክራሉ ፤ ነገር ግን ቅዱሳን መጻሕፍት ለዚህ አባባል መልስ አላቸው።

የበኩር ትርጉም:-

የበኩር ልጅዋን ወለደችው የሚለው ቃል ብዙ ሰዎችን አሳስቱዋል ይህም ሊሆን የቻለው በተለምዶ የበኩር ልጅ
የሚባሉ የግድ ተከታታይ ያላቸው መሆን አለባቸው የሚል አስተሳሰብ በእያንዳድዱ ህሊና ስለተቀረጸ ነው መጽሃፍ
ቅዱስ ግን የበኩርን ትርጉም ብዙሃኑ ከተረዳው ለየት ባለ አተረጋጎም ይተረጉመዋል እግዚአብሄር ሙሴን እንዲህ ብሎ
ተንናገረው በኦሪት ዘጸአት ፲፫፥፪ ላይ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንሳትም ማኅፀን የሚከፍተውን በኩር ሁሉ
ለእሌ ቀድስልኝ የእኔ ነው ተባለ እንጂ በኩር የመባሉ ምሥጢር አመጣጡ ልዩ በመሆኑ ነው።

በመጽሃፍ ቅዱስ እንደትገለጸው በኩር የሚባሉት ለመጀመሪያ ጊዜ ከእናታቸው ማህጽን የወጡ መሆናቸውን
እንጂ የግዴታ ተከታታይ ሊኖራቸው እንደማይገባ ይገልጻል አንድም ብቻም ቢሆን የእናቱን ማህጸን ለመጀመሪ ጊዜ
ከፍቶ ከወጣ ተከታይ ባይኖረውም በኩር ነው። የክርስቶስ በኩርና ግን በዚች ብቻ የሚፈታ አይደለም ክርስቶስ በኩር
መባሉ የእመቤታችንን ብቸኛ ልጅ መሆኑን ለመግለጽ ብቻም አደለም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለውን የአብ የባህረይ ልጅ
መውለዳዋን ለመግለጽ ወንጌላዊው ማቴዎስ የበኩር ልጅዋን ብሉዋል በተጨማሪም ክርስቶን በመጽሀፍ ቅዱስ
ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በኩር ተብሎ ተጠርቷል ጥቂቶቹን እንመልከት።

1. ቆላ፩÷፲፯ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው ሁሉ በእርሱ እና ለእርሱ ተፈጥሮአል እርሱም ከሁሉ በፊት ነው እዚህ
ላይ በኩር የሚለው ቃል ተወዳዳሪ ላላቸው ነገሮች የሚጠቀስ ሆኖ ከቀረበ ጌታን ፍጡር አድርጎ ከፍጡራን ጋር
አነጻጽሮ እርሱን ከፍጥረታት በፊት ቀደም ብሎ የተፈጠረ ፍጡርነው እንደ ማለት ይሆንና። ይህ ደግሞ
የክርስትናን ትምህርት ስር መሰረት የሚያናጋ የተፃፈ አርዮሳዊያን ትምህርት ስለሆነ ከቅድስት ቤተክርስቲያን
እምነት ውጪ ነው አባባሉ የገባው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍጥረታት በፊት ያለፍጥረታትንም አሳልፎ
የሚኖር መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው መሆኑን ፈጣሪነቱን ለመግለጥ የተጠቀሰ ነው።

2. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልዕክቱ(፩፥፮) እንደጠቀሰው እግዚአብሔር ወልድ የእግዚአብሔር አብ


የበኩር ልጁ መባሉ ለአብ ከወልድ ሌላ ልጅ አለው ማለት እንዳልሆነ ይታወቃል። ዕብ. 1፥18 ላይ መቼም ቢሆን
እግዚአብሄርን ያየው አንድስንኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ነገረን ብሎ ወልድ ብቻ የአብ የባህርይ
ልጁ እንደሆነ አስረግጦናል። እንግዲህ የበኩር ልጅዋን መባሉ መጽሀፍት በኩር ብለው የተናገሩለት ዓለም
ከመፈጠሩ በፊት የነበረ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ፍጥበታትን የፈጠረ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው አምላክ
አዶናይ ልዑል ባህርይን ወለደች ለማለት ተፈልጎ ነው።
3. የክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና መወለድ የተለየ ልደት በመሆኑ በኩር ተባለ እንጂ እመቤታችን
ሌሎች ልጆች አሉዋት ማለት አይደለም።
4. የክርስቶስ ሞቱ የተለየ በመሆኑ ማለት ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው የሚለየው በፍቃዱ ስለሆነ ተባለ።
(ዮሐ፰፥፲፯)።
5. ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው በሥልጣኑ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በመሆኑ (መዝ.፷፯፥
፷፭) በኩር ተብሏል እንጂ ባሕር የሚለው ቃል ለእመቤታችን ሌላ ልጅ መውለዷን መጠቆሙ አለመሆኑን
እንገነዘባለን።

የጌታችን ልደቱ፣ ሞቱ ፣ ትንሣኤው "በኩር" በሚሉ ቃላት የሚገለጡት የእርሱን በመሰለ ልድት የተወለደ፣
የእርሱን ሞት የመሰለ (በራስ ስልጣን መሞት) ሞት የሞተ፣ የእርሱንም ትንሣኤ በምትመስል ትንሣኤ የተነሣ ስለሌለ
ስለማይኖር ጭምር ነው። ስለዚህ በኩረ አብ፣ በኩረ ሙታን ፣ በኩረ ትንሣኤ ስንለው ተመሳሳይ አለው ላለማለት
እንደሆነ ሁሉ በኩረ ማርያምም ስንል ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልዩ ማለታችን ነው።

እስከ:- የሚለው ደግሞ ሁለት ዓይነት አግባብ አለው ፍጻሜ ያለው እስከ እና ፍጻሜ የሌለው እስከ። በሌላ አንጻር
እስከን ተገን አድርገው እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም የሚለውን እስከን ፍጻሜ ላለው ነገር አስገብተው ከዚያ በኃላ
በግብር አወቃት የሚል ትርጓሜ ቢሰጡትም የተሳሳቱ መሆናቸውን ራሱ መፅሃፍ ቅዱስ ይነግራቸዋል እስከ ፍጻሜ
ላለው ነገረ እንደሚግባ ሁሉ ፍጻሜ ለሌለው ነገርም ይገባል የሚከተሉት ከመፅሐፍ ቅዱስ የወጡ ሲሆን የእስከን
አገባብ ግልጽ ያደርጉታል።

 ፍጻሜ የሌለው:- በሁለተኛ ሳሙኤል ፮፥፳፫ "የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከሞትች ድረስ ልጅ አልወለደችም ሲል
እስከ መቼም ድረስ አለመውለድዋን እንጂ ከሞተች በኋላ ወለደች ለማለት አይደልም"

በማቴዎስ ወንጌል ፳፥፳፰ ላይ "እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ" ሲል ከዓለም ፍጻሜ በኋላ
ከእነርሱ ጋር መሆኑ ቀረ ማለት አይደለም።

ኢሳያስ ፳፪፥ ፲፬ ይህም ነገር በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ እስከ ሞቱም ድረስ ይህ በደል በእውነት
አይሰረይላችሁም ይላል ከሞቱ በኋላ ይሰረይላቹሃል ማለት ይሁን የዚህ የትርጉሙ ለዘላለምለ ማለት ነው።

ሮሜ ፬፥፲፬ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሰ ይላል ከሙሴ በኋላ ሞት ቀረ ማለቱ ነውን አይደለም
ሞት ሆይ መውጊያህ የታለየ ተባለው ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ነው።

መዝሙር ፻፲፥፩ እግዚአብሔር ጌታዬን ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ
አለው ሲባል ጠላቶቹን ካሸነፈ በኋላ በቀኜ መቀመጡ ቀረ ማለት አደለም ወደ ቆላስያስ ሰዎች በተላከው በሐዋርያው
የጳውሎስ መልእክትም

እንግዲህ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በማቴ ፩፥፳፭ የተጠቀሰው ፍጻሜ የሌለው እስከ መሆኑን ያስረዳናልና፡፡
ስለዚህም ዮሴፍ እመቤታችንን እስከ ፍጻሜው በግብር አላወቃትም የሚል ትርጉምን ይሰጠናል፡፡

አላወቃትም

አላወቃትም የሚለውን ቃል አንድ ትርጉም ብቻ ሰጥቶት ያስተምራል ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት
መተርጎም የሚገባቸውን እንደ አረፍተ ነገሩ ይዘት ነው፡፡ ለምሳሌ የአስራ ሁለት አመት ልጅ በሆነ ጊዜ እንደ በዓሉ
ስርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮስፍም እናቱም አላወቁም ነበር /ሉቃ.2፡41-43/ የሚለው ቃል እንደ
ሄልፊደስብን ተረጉመው በቀጥታ ስህተት ውስጥ እንወድቃለን፤ ነገር ግን እንደ አረፍተነገሩ ይዘት ከትረጎምነው
ትክክለኛ ፍቺ ይሰጠናል፡፡
እንደዚሁ እስከ ትውልድ ድረስ አላውቃትም ማለቱ ድንግል ማርያም የጌታችንን ወልዳ የሰማይ መላእክት
ሲያመሰግኑት፣ ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ይዘው ሲሰግዱለት፣እረኞች የምስራቹን ቃል ሰምተው ለምስጋና እስኪሲታደሙ
ድረስ ዮሴፍ በነብዩ የተነገረላት ድንግል እርሷ መሆኗን በቅጡ አልተረዳም ለማለት ፈልጎ ነው።እንደህም ሲል እምነቱ
ፍፁም ሆነለት ማለቱ ነው።ከመስማት ማየት ይበልጣልና ስለዚህም ወንጌላዊው "አላወቃትም " አለ ።

የጌታወንድሞችናእህቶች

ሀ. "ገናለሕዝቡ እንሆ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋግሩት ፈልገው በውጪ ቆመው ነበር።” / ማቴ.፲፪፥፵፮/

ለ. "ከዚህ በኃላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀመዛሙርቱ ወደ ቅፍርያኖስ ወረደ። " /ዩሐ.፪፥፲፪/

ሐ. "እንግዲህ ወንድሞቹ ደቀመዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ስራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሳና ወደ ይሁዳ


ሂድ…ወንድሞቹስ እንኳ አላመኑበትም ነበር።" /ዩሐ.፯፥፫-፭/

መ. "ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር። እንዲህም አሉ ይህን ተአምራት
እና ጥበብ ከወዴት አገኘው? ይህ የፀራቢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ
ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እህቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን?" / ማቴ.፲፫፥፶፬-፶፭/

ሠ. "እነዚህ ሁሉ ከሴቶች እና ከኢየሱስ እናት ማርያም ከወንድሞቹ ጋር በአንድ ልብ ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር። "

ረ. "ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ ከሐዋሪያት ሌላ አላገኘሁም" / ገላ.፩፥፲፱/

ሰ. "ልበላና ልጠጣ መብት የለኝምን? እንደ ሌሎች ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደኬፋም እህታችንን ይዘን
ልንዞር መብት የለንምን? "

መናፍቃን እነዚህ የጌታ ወንድሞች የተባሉት በትክክል የድንግል ማሪያም ልጆች መሆናቸዉን የሚያረጋግጡልን
እነዚህ ናቸው ብለው ከታች የተዘረዘሩትን ጥቅሶች ይተቅሳሉ። እነዚህ ማርያም የያዕቆብና የዮሳ እናት እንደሆነች
ይገልጻሉ ብሎ ይከራከራል።

ሀ. "ኢየሱስን አያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ። ከእነርሱም መቅደላዊት
ማርያም የዘብዴዎስም ልጆች እናቱ ነበሩ።" / ማቴ.፳፯፥፶፭-፶፮/

ለ. "ሴቶችም ደግሞ በሩቁ ሆነው ይመለከቱ ነበ ምር ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መቅደላዊት
የታናሹ የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም ነበሩ።" / ማር.፲፭፥፵-፵፩/

ሐ. "ይህንንም ለሐዋሪያት የነገረቻቸው መቅደላዊት ማርያምና የዮሳና የያዕቆብ እናት ማርያም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።"

መናፍቃን እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ጥቅሶች መሰረት አድርገው እንደሚሉት ከሆነ ድንግል ማርያም
በስቅለቱ ጊዜ ከነመቅደላዊት ማርያም ጋር ነበረች። ወንጌላውያኑም እርሷን የያዕቆብና የዮሳ እናት ብለው ጽፈዋታል።
ይህም ድንግል ማርያም ሌላ ልጅ እንዳላት ማረጋገጫ ነው ብለው ይከራከራሉ። የሚገርመው ግን እርሱ የሚረታበትን
ወንጌላዊው ዩሐንስ የጻፈውን ሊገልጽ አለመዉደዱ ነው። ኃይለቃሉም፦

"ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፣ የእናቱም እህት የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፣ መቅደላዊት
ማርያምም ቆመው ነበር።" /የሐ. ፲፱፥፳፭/ የሚለዉን ነው።
በዚህ ጥቅስ ዉስጥ ወንጌላዊው ድንግል ማርያምን እናቱ ብሎ ሲጠራት ከእርሷ ጋር ሌሎች ሴቶችም እንዳሉ
ጠቅሶልናል። ከእነዚህም ሁለት ሴቶች መካከልም የድንግል ማርያም እህት የምትባል የቀለዮጳ ሚስት የሆነች ማርያም
የተባለች ሴት እንዳለች ገልጾልናል። ይህቺ ናት ታዲያ የያዕቆብ፣ የዮሳ፣ የይሁዳ እናት የተባለችው። ይህ ግልጽ እንዲሆንልን
ከታች ያለዉን ማብራሪያ በእርጋታ እናንብበዉ።

ወንጌላዊው ማርቆስ የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብን ታናሹያዕቆብ ብሎ ይጠራዋል። /ማር.፲፭፥፵-፵፩/ ይህም


የዘብዴዎስ ልጅ ከሆነዉ ከዮሐንስ ወንድም ሐዋሪያው ያዕቆብ ለመለየት ብሎ የተጠቀመበት ቃል ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስም ከሐዋሪያት ጋር ለመገናኘት ወደ እየሩስአሌም በሄደ ጊዜ መጀመሪያ የተገናኘው


ከታናሹ ያዕቆብ ጋር ነበር። ታላቁ ያዕቆብ ግን በጊዜው ሞቶ ነበር፤ ገዳዩም ሄሮድስ ነወ። /የሐዋ. ፲፪፥፪/

ቅዱስ ጳውሎስም "ከዚያ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን ልጠይቅ ወደ እየሩስአሌም መጥቼ ከእነርሱ ጋር
ዐሥራ አምስት ቀን ሰነበትኩ፣ ነገር ግን ከጌታ ወንድም ያዕቆብ በቀር ከሐዋሪያት ሌላ አላገኘሁም።" /ገላ. ፩፥፲፱/

በማለት የጌታ ወንድም የተባለውንና በ ቅዱስ ማርቆስ ታናሹ ያዕቆብ የተባለውን ሐዋርያ ብሎ መጥራቱን
እንመለከታለን።እርሱን ቅዱስ ጳውሎስ ከነጴጥሮስ ከነዮሃንስ ጋር አዕማድ ተብሎ መጠራቱን እናስተውላለን።

መፅህፍ ቅዱስ ደግሞ ሁለት ያዕቆብ ሚባሉ ሐዋርያት እንዳሉ ይገልጻል።(ማቴ ፲÷፫-፭) አንደኛው የዘብድዮስ ልጅ
የዮሃንስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ ነው። ከእነዚህ ውጭ ያዕቆብ ሐዋርያ
የለም።3ኛ አለ ምንል ከሆነ ኝ ቅዱስ ማርቆስ የጌታ ወንድም የተባለውን ያዕቆብ ታናሹ ያዕቆብ ማለት ባላስፈለገው።
ታናሽ እና ታላቅ የሚለውን ለ 2 እንጂ ለሶስት ነገር አንጠቀምባቸውም።ስልዚህ በሐዋርያት ዝርዝር ውስጥ
የተካተተውብ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ የተባለው ያዕቆብ አባቱ እልፍዮስ እናቱ የ እመቤታችን እህት የተባለችው ፣
በመስቅሉም ስር የነበረችው የያዕቆብና የይሁዳ (ማቴ ፳፯፤፶፭-፶፮) እናት ማርያም ናት ማለት ነው። ወንጌላዊው
ዮሃንስም ቀልዮጳ ያለው እልፍዮስን መሆኑን በዚህ ማረጋግጥ እንችላለን።አንድን ሰው ከ ሁለት እና ከእዛ በላይ አውጥቶ
መጥራት በ ዕብራውያን ባህል የተለመደ ነው።በዚህም መሰረት ቀልዮጳ የ እልፍዮስ ሌላኛው ስሙ እንደሆነ
እናረጋግጣለን።

ለምሳሌ፡ የሙሴ አማት የነበርው ራጉኤል ሌላ ጊዜ ዮቶር (ዘጸ ፲፰÷፮/ዘኁ ፲÷፳፬)ተብሎ ተጠርቶ እንመለከታለን።

፡ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስምኦን እና ኬፋ ተብሎ ተጠርቷል።በዚህም መሰርት መጻህፍ ቅዱስም


እንደሚያስርዳን የጌታ ወንድሞች የተባሉትየእልፍዮስ ወይም የቀልዮጳ እና የድንግል ማርያም እህት የትናለችው ልጆች
ሲሆኑ ለጌታ ደግሞ የአክስት ልጆች እንደማለት ነው።በ አይሁድ ለማድ ደግሞ የአክስት ልጆችን ወንድም ብሎ መጥራት
የተለመደ ነው።ይህም በ ሃገራችንም ጭምር የሚታይ ነው።

መጻህፍ ቅዱስ 4 አይነት ወንድምነት እንዳለ ይገልጽልናል

1. በመወለድ_ እንዲህ አይነቱን ወንድምነት ከ1 እናት እና አባት መወለድን በእናት ወይም በአባት አንድ መሆንን
ይጠይቃል።ለምሳሌ ያዕቆብ እና ኤሳው/ዘፍ ፬፣፩-፪/ 12ቱ የያዕቆብ ልጆች/ዘፍ ፴፬÷፳፫ / ወዘተ
2. የወገን ወንድምነት _እንዲህ አይነቱን ወንድምነት በወገን አንድ መሆንን ይጠይቃል። አይሁድ ከአብርሃም ወገን
ስለሆኑ ወንድምማማቾች ተብለዋል። ለምሳሌ " አንተም ወንድምህን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዛ
ስድስት ዓመት ያገልግሉህ፤ በሰባተኛውም ዓመት ከአንተ ዘንድ አርነት አውጣው።"(ኦሪት ዘዳግም ፲፭:፲፪)
" አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ
ታነግሣለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም።
(ኦሪት ዘዳግም ፲፯÷፲፭)
(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. ፱)
---ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤
ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ
የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና።
3. በሥጋ ዝምድና ወንድምነት የቅርብ የሥጋ ቁርኝት ካለ ወንድምማማቾች ተብለው ይጠራሉ ።ለምሳሌ ሎጥ የ
አብርሃም የ ወንድም ልጅ ነው፣ማለትም የአብርሃም አጎቱ ነው። ነገር ግን ወንድሜ ብሎ ጠርቶታል።/ዘፍ ፲፪፤፫-
፭/ ፲፫÷፰/፲፬÷፲፬/
እንደዚሁ ሓዋርያው ታናሹ ያዕቆብ፣ይሁዳ፤ስምኦንና ዮሳ የ እመቤታችን እህት የተባለችው የ ማርያም ልጆች
በመሆናቸው ለ ጌታችን የአክስት ልጆች ናቸው።
4. የፍቅር ወንድምነት መንፈሳዊ አንድነትን የሚጠቁም ነው።ለምሳሌ " ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥
መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።"
(መዝሙረ ዳዊት ፻፴፫÷፩)
" ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፥ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።"
(መዝሙረ ዳዊት ፳፪÷፳፪)
" አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም
ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል
እንኳን አትብሉ።"
(፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፭÷፲፩)

በመሆኑም ወላዲተ አምላክ የአምላክ ማደሪያ ለመሆን የተመረጠች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች
ንጽሕተ ሥጋ፣ ንጽሕተ ነፍስና ንጽሕተ ልቦና በመሆኗ አምላክን በድንግልና ለመውልድ ተመረጠች። በዚህም
ምሥጢር መሠረት "የበኩር ልጅዋን እስከምትውልድ ድረስ አላወቃትም" የሚለው ዓረፍተ ነገር ላይ ያለው
"እስከ" ፍጻሜ የሌለው ነው።

ለ. ወላዲተ አምላክነዋ

ማንኝኛውም ክርስቲያን ነኝ የሚል ሰው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪይ አምላክ መሆኑን
ሊጠራጠር አይገባውም። እርሱም በቤተልዬም ከቅድስት ድንግል ማሪያም መወለዱ የታወቀ ነው። ስለዚህ
እመቤታችንም የአምላክ እናት መሆኗ የሚካድ አይደለም። ክርስቶስን አምላክ ብሎ ወላዲተ አምላክ የግድ ነው።

1. “ከአንቺ የሚወለድው ቅዱስ የእግዜብሔር ልጅ ይባላል። (ሉቃ.፩፥፵፩)


2. "አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ
እንዴት ይሆንልኛል” (ሉቃ. ፩፥፵፩)

"ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዜብሔር ልጁን ላከልን እርሱም ከሴት የተወለደ ለሕግም ታዛዥ ሆነ”(ገላ.
፬፥፬) የመሳሰሉት ምሥክሮች የእመቤታችንን የአምላክ እናትነት ያስረዳሉ።
ሐ. ንጽሕናዋና ቅድስናዋ

"እኔ ቅዱስ እንደሆንሁ እናተም ቅዱሳን ሁኑ" በማለት ልዑል እግዚአብሔር እንደተንናገረው (29፥2) በፈጣሪው
አርአያና አምሳል ለተፈጠረው የሰው ልጅም በቅድስና የፈጣሪውን አርአያ መከተል ሃይማኒታዊ ግዴታው ነው።

ይህን ግዴታ ለመፈጸም በቀና እምነትና ብጎ ምግባር ለብፅዕና ለቅድስና የበቁ የብሉይና የሐዲስ ምእምናን ቁጥር
በፈጣሪ እንጂ በፍጡር አእምሮ ተደምሮና ተባዝቶ የሚደረስበት አይደለም። ሆኖም ከዚህ ዓለም ቅዱሳንና ቅዱሳት
መካከል እንደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ያለ፣ በእርሷ መጠን ጸጋን የተመላ በንጽሕናና ቅድስና የተዋበ
የመንፈስ ቅዱስ ማድሪያ የሆነና በልዑል ኃይል የተጠበቀ ሰውነት ያለው የለም። (ሉቃ. ፩፥፳፰-፴፮)

ይሄውም እመቤታችን ለአምላክ እናትነት የተመረጠችው ድንግል በመሆንዋና የአምላክ እናት እንድመሆንዋ መጠን
በሐልዮ፣ በነቢብና በገቢር ሁሉ ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት ቅድስትና ቡርክት በመሆንዋ ነው።

ስለዚህ ራስዋ ወላዲተ አምላክ አስቀድማ በወንጌል ቃል እንደተናገረችው ትውልድ ሁሉ "ቅድስት ወብፅዕት" እያሉ
ሲያመሰግኗት ይኖራሉ።

በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ማረጋገጥ እንደሚቻለው ለሕይወት ዓለም እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነው ረድኤተ
እግዜብሔር በዘመነ ፍዳና በዘመነ ኩነኔ ከዓለም ሊርቅና ሊነሣ የቻለው በዓመፃና ክፋት ብዛት ነበር።

የሰው ልጅ ያን ጊዜ በበረከተ ሥጋና በበረከተ ነፍስ እጦት ይሰቃይ የነበረውም በዚሁ ምክንያት ሲሆን ያጣውን ሁሉ
አግኝቶ እንደገና ለመክብር የበቃውም ደግሞ በፍፁም ተስፋ ይጠበቅ የነበረው የዓለም መሢሕ ከእመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማሪያም ከተወለደ ወዲህ ነው።

ስለሆነም የሰው ልጅ ንጽሐ ጠባይዕ በድቀተ ኃጢአት ምክንያት ከማደፉ በፊት የነበረው የተፈጥሮ ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ
ነፍስና ንጽሐ ልቡና ወይም የሐለዮ፣ የነቢብና የገቢር ንጽሐና የቱን ያህል እንደ ነበረ ማረጋገጥ የተቻለውም
በእመቤታችን ንጽሕናና ቅድስና ነው።

ይኸውም እመቤታችን ከፈጣሪዋ በተሰጣት ምሉዕ ጸጋ መሠረት በውስጥ በአፍአ የነበራትን ነጽሕናና ቅድስና ሁሉ
ፍጹም ስለሆነ ነው። እኛም አሁን ከእመቤታችን ረድኤትና በረከት እንዲከፍለን ወደ ውድ ልጅዋ የምንማፀነው
በእርስዋ ከተሰጠው የንጽሕናና የቅድስና በረከት እንድናገኝ ነው።

"ወብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ዘነገሩኪ ቃለ እምኀበ እግዚአብሔር ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነው እውነተኛ ቃል
ሲናገርሽ ሳትጠራጠሪ አምነሽ የምትቀበይ አንቺ ብፅዕት ነሽ።" (ሉቃ. ፩፥፵፭)።

እውነትን ከሐሰት በመለየት ፈጥኖ ለመቀበል መብቃት ራሱ ታላቅ ብፅዕና ነው። እመቤታችን የመላአኩ የቅዱስ
ገብርኤልን እውነተኛ ብስራት እንደ ዘካሪያስ ሳትጠራጠር አምና በመቀበሏ ቅድስት ብፅዕት ተበላ የተመሰገነች
በሚገባ ነው።

አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማሪያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት (ጥንተ
አብሶ) ያላገኛት $ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት$ ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ሕሊና ታስባ ትኖር
የነበርች፣ በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ አሳብና ፈቃድ የተጠበቀች፣ ከተለዩት የተለየች ንጽሕት ቅድስተ
ቅዱሳን ናት። (መኃል. ፬፥፯)።
"ምልዕተ ጸጋ ምልዕተ ክብር ሆይ ደስ ይበልሽ" ተብላ በቅዱሳን መላእክት አንደበት በቅድስናዋ ተመስግናለች። (ሉቃ.
፩፥፳፰)።

እመቤታችን በውስጥ በአፍአ በነብስ በሥጋ ቅድስት ስለሆንች እግዚአብሔር ለልጁ ማደሪያ መርጦአታል።
ማኅድረ መለኮት እንድትሆን አድርጓታ። አምላክን ለመውለድ ያስመረጣትና ያበቃት ንጽሕናዋ ቅድስናዋ ነው። (አባ
ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም) መዝ. ፻፴፪፥፲፫ ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና ለእመቤታችን ገንዘቦቿ ናቸው።

መ. አማላጅነትዋ

ትርጉም:- ተንበ ለመነ፣ ተንባሊ የሚለምን፣ የሚጸልይ አማላጅ ማለት ሲሆን አማላጅ በሁለት ወገኖች መካከል
በመግባት አንዱን ስለሌላው የሚማልድ ማለት ነው።

በመንፈሳዊ መንገድ ስንመለከተው ደግሞ የሚለመነው ልዑል እግዚአብሔር ሲሆን የሚያማልዱት በእግዚአብሕሔር
ዘንድ የተጠሩና የተመረጡ ቅዱሳን ናቸው።

ምልጃ የታዘዘውና የተፈቀድው (ያስፈልገው) እግዚአብሔር ከኃጥአን ይልቅ የጻድቃንን ጸሎት የበለጠ ስለሚሰማ ነው።
"እግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸው" (መዝ. ፴፥፲፭) ተብሎ ተጽፏልና።

አማላጅት የእግዚአብሔር የቸርነት ስጦታ ነው። ምክንያቱም ምግባራቸው የደከመና ጽሎታቸው እንደርሱ ፈቃድ
ያልሆነ ተነሳሕያን ኃጥአን የእርሱን ፈቃድ በሚያውቁና በሚፈጽሙ በምግባር በበለጽጉ ጻድቃን እንዲረዱ ማድረጉ
የቸርነቱ መግለጫ ነው።

ለምሳሌ:- አቤሜሌክ ንጉስ ጌራራ (የጌራራ ነጉሥ) በፈጸመው ስሕተት እግዚአብሔርን በማስቀየሙ ይቅርታ ያገኝ
ዘንድ የተላከው ወደ አብርሃም ነው "ነብይ ነውና ስለአንተ ይጸልያል ትድናለህም” (ዘፍ. ፳፥፩-፯) በማለት። ለቅዱሳን
አባቶቻችን ይህን ያህል አማልዶ የማስታረቅ ሥልጣን ከተሰጠ ለወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምማ እንዴት
የበለጠ ሀብተ ምልጃ አይሰጣትም። ምክንያቱም ምልዕተ ጸጋ ናትና።

ወላዲተ አምላክ ማርያም የምእምናን ሁሉ እናት ሆና መሰጠቷን በተለያዩ ቦታ ተመልክተናል። የእናት አማላጅ ደግሞ
አያሳፍርም ምክንያቱም የሰራፕታዋ መበለት ልጅ ቢሞትባት ለእግዚአብሔር ሰው ለኤልያስ ነግራ (አማልዳ) ከሞት
እንዲነሣ አስደርጋለች። (፩ነገ. ፲፯፥፲፯-፳፬)።

ከነብያት ወገን የሆነች አንዲት ሴት እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያመልክ ባልዋ ከመሞቱ በፊት ተበድሮት በነበረው
ዕዳ ምክንያት አበዳሪው ልጆቹን ሽጦ ገንዘቡን ለመውሰድ በቀረበ ጊዜ እርስዋ ግን አይሆንም ብላ ለእግዚአብሔር
ሰው ለኤልሳዕ በመንገር በእግዚአብሔር ቸርነት በነቢዩ ኤልሳዕ አማላጅነት ልጆቿ ከሞት እንዲተርፉ አስደርጋለች። ፪ነገ.
፬፥፳፭።

 በመስቀሉ ሥር የተረከብናት እናታችን ድንግል ማርያም በምልዕተ ጸጋነቷ፣


 በተሰጣት የአማላጅነት ቃል ኪዳን መሠረት ለሚተማመኑ ሁሉ የእናት አማላጃቸው ናት።

ቤተ ክርስቲያን ስለ እመቤታችን አማላጅነት የምታስትምረው በቅዱሳት መጻሕፍት በተጻፈው ቃልና ፍፁም በሆነ
ሐዋርያዊ ትውፊት መሠረት ነው።
እመቤታችን የእናትነት ክብርና የአማላጅነት ቃል ኪዳን ከልጅዋ ከጌታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ተቀብላለች በቃና ዘገሊላ
ሠረግ ቤት ልጅዋ መድኃኒ ዓለም ክርስቶስ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦ የመጀመሪያውን ተአምር ያደረገው
በእመቤታችን አማላጅነት መሆኑ የታመነ ነው።( ዮሐ. ፪፥፩-፭)።

እናት ወልዳ ማስገኘት ብቻ ሳይሆን ልጇን የማዘዝ መብትም አላት። በተለይ ወላዲተ አማላክ (የአምላክ እናት)
የመሆና ትልቅ ምሥጢርም የማዳን ሥራው ተካፋይ መሆን ነውና።

በቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ትምህርት ድንግል ማርያም ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ከስመ ሥላሴ ቀጥሎ ሰሟ
የሚጠራ ስለሆነ ታማልዳለች ብለን ማመናችን ቢያንስ እንጂ ሊበዛ አይችልም።

 እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁሉ ቃል ኪዳናቸውን በመጠበቅ ከእነርሱ ጋር ለዘለዓለም ይኖራልና (መዝ.


፹፰፥፫) የማማለድ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።
 ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻልና አትፍሪ ብሎ መልአኩ በክብር እንዳበሰራት እንረዳለን
(ሉቃ. ፩፥፳) ሞገስ የሚለው ቃል ባለሟልነት፣ ክብር፣ ተሰሚነት፣ ማማለድ፣ ማስታረቅ የሚሉትን ያብራራል።
ይህ ሁሉ ለእመቤታችን የተሰጠ ጸጋ ነው።

የእመቤታችን አማላጅነት እንደ እንግዳ ደራሽ አዲስ ነገር አይደለምና ነቢዩ ዳዊት በትንቢቱ "በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና
ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” (መዝ. ፵፬፥፱)። ሲል ቀድሞ ተናግሯልና።

ንግስቲቱ ወላዲተ አምላክ በንጽሕና በቅድስና አጊጣ በወልደ እግዚአብሔር ቀኝ (ሥልጣን) የኃጥአን አማላጅ ሆና
እንደምትቆም ያስርዳል።

ነገረ እግዚአብሕርን በሚገባ ለሚያዉቅና ለሚጠነቅቅ ሰዉ የአማላጅነት ትምህርት የሚያስደንቀዉና


የሚያጠራጥረዉ ሊሆን አይገባም፡፡ የአማላጅነት ትምህርት ከጊዜ በኋላ ድንገት የመጣ ሳይሆን በዘመነ አበዉ በህገ
ልቦና በዘመነ ኦሪት በመፅሐፍተ ሐዲሳት የነበረና አሁንም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ነዉ፡፡

ነገር ግን መናፍቃን ለፍጡር የተሰጠዉን የማማለድ ጸጋ ለፈጣሪ ሰጥተዉ ጌታችንን ወደ ፍጡርነት (ሎቱ ስብሐት)
ደረጃ ዝቅ ለማድረግ ይሞከራሉ፡፡ለኢየሱስ ክርስቶስ ማማለድ የሚለዉ ቃል መቀጸል ባልተገባዉም ነበር በሥጋዌዉ
እኛን ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን ይባላል እንጂ አማለደን አይባልም፡፡ ምክንያቱም ማማለድ ዝቅ ብሎ መለመንን
የሚያሳይና ተማላጁ እንቢ ቢል እንኳን ጉዳዩ ላይፈጸም የሚችል ነገርን ሲያመለክት ጌታ ግን በራሱ ፍቃድ በአብ
ፍቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፍቃድ ከባህርይ አባቱ( በስልጣን እኩል ከሚሆነዉ) አስታርቆናልና ነዉ፡፡

ስለዚህ ያ የማስታረቅ ስራዉ አንድ ግዜ በመስቀል ላይ የተፈጸመ ስለሆነ ዛሬም ነገም ያስታርቀናል የሚባል እንዳልሆነ
ልብ ልንል ይገባናል (፪ቆሮ. ፭-፲፯-፳)

የበለጠ የሚያስገርመው ደግሞ ግማሾቹ በአጠቃላይ አማላጅነትን ሲቃወሙ ሌሎቹ ደግሞ በአጸደ ነብስ ያለዉን
ማማለድ ብቻ የማይቀበሉ መሆናቸዉ ነዉ፡፡ ካለማስተዋል ወይም መፅሐፍ ቅዱስን ካለማዎቅ ካልሆነ በስተቀር
ቅዱሳን በአፀደ ሥጋ እያሉ እንደሚያማልዱ በዘ ፲፰-፲፮-፳፩ ዘፀ ፴፪-፯-፲ ኤር፯-፲፮ ማቴ፲፭-፳፩-፳፫ ፪ኛ ቆሮ፯-፲፬
እንዲሁም ደግሞ በአፀደ ነፍስ ሳሉ እንደሚያማልዱ ዘፍ ፬-፱-፲ ሉቃ.፲፮-፲፱ሔኖክ.፮-፳፮-፳፲ ባሉት ጥቅሶች
መመልከት ይቻላል፡፡
ደግሞም ቅዱሳን ከሞት በኃላ ደገሞም እንደማያማልዱ በአጠቃላይ ምንም እንደማያዉቁ ማድረግ እግዚአብሕርን
የሙታን አምላክ ማድረግ መሆኑን ማዎቅ ያስፈልጋል እኔ የእነ አብርሐሃም የእነ ያእቆብ አምላከ ነኝ እንጂ የመዉታን
አምላከ አይደለሁም፡፡ማር፲፪-፳፯

ይህንን ሁሉ ከተመለከትን ዘንዳ ቅዱሳን ይህን ያህል ክብርና አማላጅነት ካገኙ የእመቤታችን ማርያምን ያህል ይሆን
እንድንል ያደርገናል፡፡ ምክንያቱም እመአምላክ የእግዚአብሔርን ቃል ለመቀበል በተገባ የተገኘች ምልዕልተ ፍጡራን
በመሆንዋ ነዉ፡፡ ልጅ ምንም ያህል ትልቅና የከበረ ቢሆን የእናቱን ልመናና ቃል አይተላለፍም ደግሞም “አክብር አባከ
ወእምከ”(ዘፀ.፳፥፲፪) ብሎ ትዕዛዝ የሰራ አምላክ የእናቱን ልመናና አማላጅነት አይቀበልም ብሎ ማሰብ ስንፍና ነው።
ይህንንም በዮሐ፪-፩-፲፩ ባለዉ ላይ እንረዳለን፡፡

ለባለ ሰርጉ ዶኪማስ በአፍላ ድግስ ላይ የሚጠጣዉ ነገር ባለቀበት ግዜ ማንም ሳይነግራት ጭንቀቱን በመረዳት ለልጇ
ነግራ ከዐፍረት አድናዋለች፡፡ የሰባቱ ሀብታት ባለቤት ዳዊትም በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግስቲቱ በቀኝ ትቆማለች ካለ
በኋላ የምድር ባለጠጎች አህዛብ በፊትሽ ይማልላሉ፡፡ (መዝ ፵፬(፵፭)፱-፲፫) በማለት ፍጥረት በሙሉ ከእግዚአብሔር
ምህረትን ይቅርታን እንድታሰጠን በፊቷ የምንወድቅ የምንለምን መሆኑን ገልጿል፡፡ የወርቅ ልብስ የተባለው ንጽሐ
ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ሲሆን ከጌታ ቀኝ በመሆን በእርሷ ለሚተማመኑ ለምኝልን ኃጥያታችንን አስተስርይልን ለሚሉ
የቃልኪዳን ልጆቿ አማላጅ መሆንዋን ያሳያል፡፡

ጌታችን በመልዕልተ መስቀል ላይ ሆኖ ለወዳጁ ቅዱስ ዮሃንስ እነኋት እናትህ በማለት የሰጠዉም ለዚህ ነዉ(ዮሐ ፲፱፳፥
፯) እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የተሰጣትን ቃልኪዳነ እና በአማላጅነትዋ የሰራችውን የበለጠውን ሁሉ ደግሞ
ከነገረ ማርያም ከሰኔ ጎልጎታና ከታምረ ማርያም ተመልክቷል፡፡

እንዲሁ ልበአምላክ ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደዋላቸዉም ይመለሱ (መዝ፻፳፰(፰፻፳፱)፥፩) እንዳለ
መንፈስ ጽርፈት (ስድብ) አድሮባቸዉ ዲያቢሎስ ሔዋንን ባሳተበት ምላስ በሐሰት ትምህርት የሚማሩ የቅዱሳንን
የመላእክትን የእመቤታችንን ስምና ቅድስና የሚያጎናጽፉ የጌታችን መለኮታዊ ብርሃን ሳይበራላቸዉ በሻማ
ድንግዝግዝ የሚጓዙ የሽንገላ አንደበት በማስመሰል የአፍ ለምድ ተጀቡነዉ ውስጣቸው ግን ነጣቂ ተኩላዎች የሆኑ
ተረፈ አርዮሳዉያን መናፍቃን ሊአፍሩ ይገባቸዋል። ይልቁንስ ስህተትን አምኖ በንስሃ መመልስ ከጥበብ ሁሉ የበለጠ
ነውና ወደልባቸዉ እንዲመለሱ የሁላችንም ጸሎት ነዉ፡፡(፲፩-፲፩-፴፪) እኛ ግን የተዋህዶ ልጆች ጽዮንን ክበብዋት
በዙሪያዋም ተመላለሱ ግንቦችዋን አስቡ ለሚመጣዉ ትዉልድ ትነግሩ ዘንድ (መዝ ፵፯-፰፰)-፲፪) እንደተባልን ጽዮን
የተባለች እናታችን ማርያምን አንድም ቅድስት ቤተክርስቲያን ከብበን ንጹህ ነገረ ሃይማኖትን በመማር ራሳችንን
ከሚነፍሰዉ የጥርጥር ክህደት ከሚወረወረው የኑፋቄ ቀስት ከሚሰነዘረው የክደት ፍላጻ ሁሉ መጠበቅ መቻል አለብን
የትዉልድ ባላደራዎች ነንና፡፡

ቅዱስ ጳዉሎስ “ልዩ ልዩ በሆነ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬም እስከዘላለም ያዉ
ነዉ፡፡(ዕብ፲፫-፱) በማለት እንዳስተማረን በአንዲት ርትዕት ሐይማኖት (ኤር፮-፲፮) እንድንጓዝ እግዚአብሕር ይርዳን፡፡

ይህም በሰዉ ፍቃድ ሳይሆን በአምላክ ቸርነት የሚሆን ነውና እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆችዋ
ስለሆንን (ዮሐ ፲፱-፰፮-፳፯) በአማላጅነትዋ በጸሎትዋ የኃጥያት የክደት አዝመራ ከሚሰበሰብበት ዓለም ትጠብቀን
ከፊት ትምራን ከኋላ ትከተለን ከቀኝ እና ከግራ ትደግፈን ትከተለን ከቀኝ ትምራን ከኋላ ትከተለን ከቀኝና ከግራ
ትደግፈን ለዘለዓለምም በህይዎታችንና በእረፍታችን ግዜ አትለየን አሜን!
ሠ. ስግደት የሚገባት መሆኗ

በቤተክርስቲያናችን ለፈጣሪአችን ለእግዚአብሔር የአምልኮት ለቅዱሳኑ ደግሞ የጸጋ ስግደት እንሰግዳለን። እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ ከቅዱሳኑ መካከል ከመሆኗም በላይ መትኃተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ቅድስተ
ቅዱሳን በመሆኗ ከተሰጣት ጸጋ የተነሣ የጸጋ ስግደት እንሰግድላታለን። የአምላክ እናት፣ ማኅደረ መለኮት ለመሆን
የሚያበቃ ልዩ ጸጋ ተሰጥቷታልና።

አስቀድሞ በነብዩ " ወንዶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ።
ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል።" (ኢሳ. ፵፱፥፳፪)። በማለት ተነግሮላታል። ይኸው
የእግዚአብሔር ነቢይ "የእግሬንም ሥፍራ አከብራከሁ የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ድፍተው ወደ አንቺ
ይመጣሉ። የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ።" በማለት በድጋሚ ተናግሮታል። ኢሳ. ፷፥፲፫።

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ የተመላ ስለነበር የእመቤታችን ድምፅ
ለኤልሳቤጥ በተሰማበት ቅጽብት ለድንግል ማርያም የጸጋ ስግደት ሰግዷል። ሉቃ. ፩፥፵፬።

ከዚህም በመነሣት ማኅደረ መለኮት እመ አመላክ ለመሆን የተመረጠች ቅድስት ድንግል ማርያም ከተሰጣት ሰማያዊ
ክብር የተነሣ የጸጋ ስግደት ሊሰግድላት ይገባል። ከወንጌል እንደተማርነውም ዮሃንስ በማኅፀን ሳለ በደስታ በፍሰሐ
የአምላክ እናት መጣች ብሎ እንዲሰግድ ያደርገ መንፈስ ቅዱስ ነው። ዛሬም ቢሆን የእግዚአብሔር መንፈስ
ያልተለያቸው ሁሉ ለእመቤታችን የጸጋ ስግደት ይሰግዳሉ። ሰለክብሯም በፊትዎ ይንበረከካሉ።

ምዕራፍ ሶስት

የእመቤታችን ምሳሌዎች
በቅዱስ መጽሐፍስ ለጌታ ስለእመቤታችን ስለ ቤተክርስቲያን ወዘተ የተመሰሉ ምሳሌዎች አያሌ ናቸው አስተዋይ
የሆነ ትርጓሜአቸውን በመረዳት ይጠቀምባቸው፡፡በመጽሐፍ ቅዱስ ስለእመቤታችን የተነገሩትን ምሳሌዎች
በመመርመር ተርጓሜያቸውን እንድናስተውል ያስፈጋል፡፡በተለይ የብሕንሳውኤ ጲስቆጶስ አባታችን አባሕርያቆስ
በመንፈስቅዱስ ተቐኝቶ በቅዱስመጽሐፍ የተጻፈውን የእመቤታችንን ምሳሌ በመግለጽ እመቤታችንን አመስግኗታል፡፡
ስለዚህ እኛም ለትምህርታቸን የተወሱኑ ጥቂት ምሳሌዎችን ተርጉመን እንመለከተለን፡፡እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ
ምስጢሩን ማስተዋሉን ይገለጽልን አሜን፡፡

 የኖህመርከብ (ዘፍ 7፡2-23)

ኖህ በእግዚአብሄር ትዕዛዝ ሊመጣ ካለው ጥፋት ለመዳን መርከቡን አዘጋጀ እርሱ ሚስቱ እ ሴም ካምያፌት የተባሉ
ልጆቹ ከነሚስቶቻቸው ከየወገኑም የተመረጡ እንስሳት ሁሉ ወደ መርከቡ ገቡ በዚህም ከጥፋት ውሃ ዳኑ፡፡ዘፍ 72-
27˝ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተሰቦቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፡፡ዕብ
11፡7 እንዲል ኖኅ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘ በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበር፡፡አካሄዱንም ከእግዚአብሔር
ጋር በማድረጉ ፈጣሪው የሚድንበትን መንገድ አሳየው በዚያም ተጠቀቅሞ 3 ክፍል ባላት መርከብ ለመዳን በቃ፤
በኖኅ ያላገጡ በተዘጋጀው መርከብ እንድናለን ብለው ያላመኑ ጠፉ ይህ እንግዲህ ምሳሌ ነው፡፡

የምሳሌውም ትርጓሜ ከዚህ እነደሚከተለውነው፡፡


የኖኅመርከብ፡-የእመቤታችን ምሳሌ ናት ሶስት ክፍል እንደነበራት እመቤታችን ቅድስት ድንግልማርያምም
የአብሙሽራው የወልድእናቱ የመንፈስቅዱስ ንጽህት አዳራሽ ናትና አንድም እመቤታችን በንጽሐ ሥጋ በንጽሐ ነፍስ
በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ቅድስተ ቅዱሳን የመሆኗ ምሳሌ ነው፡፡

ኖኅ፡-የጌታ ምሳሌ

የጥፋት ውሃ፡-የምልአተ ኃጢያት ምሳሌ አንድም፡የሲኦልምሳሌ

ከመርከብ ውስጥ ሆነው ከጥፋት የዳኑ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቃልኪዳን እና አማላጅነት ያመነ
በእርሷም ምልጃ ከጥፋት የዳኑ ከሲኦል የሚድኑ ነፍሳት ምሳሌ ነው፡፡

ከመርከቡ በአፍ አውጭ የቀሩትና የጠፉት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያን ቃልኪዳን እና አማላጅነት ሳያምኑ
በኃጢአት በሲኦል ውስጥ የሚጠፉት ነፍሳት ምሳሌ ነው፡፡ከኖኅ ሕይወት የምንማረው ነገር አለ እርሱም ጻድቅ ፍጹም
እነደሆነ እየተመሰከረለት ነገርግን አምላካቸን እግዚአብሔር ለመዳን የሚሆንለትን መርከብ እንዲያዘጋጅ ሲየዘው
አልተከርከረውም በእምነት መርከብ ሰርቶ በመርከብ ከጥፋት ዳነ እንጂ ስለዚህ በእኛ ዘመን አንዳንድ ሰዎች
በሌላቸው ጽድቅ እየተመጻደቁ የእመቤታችንን ቃልኪዳን እና አማላጅነት አያስፈልግም በማለት ሲንቁ ይታያል
እኛኦርቶዶክሳውያን ግን እንደ ኖህ አባታችን የተሠጠችንን የመዳን ምክንያት እመቤታችንን ማለትም አማላጅነቷን
በሕይታችን ሁልጊዜ ልንተቀምበት ያስፈልጋል፡፡

 የሲና ሐመልማል ዕፀ ጳጦስ (ዘፀ 1፡6)

ሙሴም የምድያምን ካህን በጎች ይጠብቅ ነበር ወደ ምድበዳም ዳርቻ በጎቹን እየነዳ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ
ኮሬብ መጣ የእግዘአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቁጥቋጦ መካከል ታየው እነሆም ቁጥቋጦ ውስጥ
ለምን አልተቃጠለም ይህ ታላቅ ራዕይ ልይ አለ እግዚአብሔር እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደመጣ ባየጊዜ
እግዚአብሔርከ ቁጥቋጦ ውስጥ እርሱን ጠርቶ ሙሴ ሙሴ ሆይ አለ እርሱም እነሆኝ አለ ወደዚህ አትቅረብ አንተ
የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ አለው ደግሞም እኔ የአባትህ አምላክ
የአብርሀም አምላክ ይስሐቅም አምላክየ ያዕቆብም አምላክ ነኝ አለው ሙሴም እግዚአብሔርን ያይ ዘንድ ፈርቷልና
ፊቱን ሸፈነ፡፡ዘጸ 3፤1-6 በዚህ ንባብ በምሳሌነት የእመቤታችን ነገር እንማራለን፡፡

 ዕፀጳጦስ (ሲናሐመልማል)፡-የአመቤታችን ምሳሌ

ነበልባል፡- የመለኮት የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ

ሐመልማል፡-(የትስዕት) የሥጋ ምሳሌ

ነበልባሉ እና ሐመልማሉ ተዋሕደው ሙሴ መመልከቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን በድንግልና
ፀንሳ በድንግልና የመውለዷ ምሳሌ፡፡

ደብረሲና ፡-የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ሙሴ ጫማህን አውልቅ እንደ ተባለ ወደ ቤተክርስቲያን ጫማ አድርጎ
መግባት አይገባም ሲልነው፡፡
 የጌድዮን ፀምር

ጌድዮነን እግዚአብርን እንደተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደሆን በአውድማው ላይ የተባዘተ የበግ
ጠጉር አኖራለሁ፡፡በጠጉሩ ላይ ብቻ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን እንደተናገገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ
እጅ እንድታድናቸው አውቃለሁ፡፡እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት እንዲሁ አደረገ በማለት ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል፡፡
መጻ መሳ 5፡36-40፡፡

ፀምር የእመቤታችን፣ ጠል የጌታችን ምሳሌ ነው፡፡ጠል በፀምሩ ላይ መውረዱ ከሦስቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር
ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በማኅፀኗ ማደሩንና ሥጋን
ተዋሕዶ ሰው መሆኑን ያጠይቃል፡፡

ጠል በምድር ላይ አለመውረዱ ሌሎች ሴቶች ለዚህ ታላቅ ክብር አለመብቃታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ሁለተኛም ጠል
በምድር ላይ ሆኖ በጸምሩ ላይ አልወረደም፡፡ይኸም በሌሎች ሴቶች ላይ ያለ መርገምና ኃጢአት ያላረፈባት
እመቤታችን ከአንስተ ዓለም የተለየች የተባረከች መሆኗን ያስረዳል፡፡እግዚአብሔር ባወቀ ሁለቱንም ምሳሌዎች
በወቅቱ ገለጣቸው፡፡

 በትረ አሮን /የአሮን በትር/

በኦሪት ዘኁልቊ 16፡8-11 ላይ የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ተወካዮች ከነበሩት በትሮች መካከል የአሮን በትር ብቸ
ሳይተክሏት ተተክላ ውኃ ሳያጠጧት አቆጥቁጣ፤ ለምልማና አብባ የበሰለ ለውዝ አፍርታ መገኘቷ ተገልጧል፡፡

የአሮን በትር የእመቤታችን ፣ ለውዝ የጌታችን ምሳሌ ነው፡፡የአሮን በትር ሳይተክሏትና ውኃ ሳይጠጧት አብባና
አፍርታ እንደተገኘች እመቤታቸንም ያለ ዘርዐ ብእሲ በማይመረመር ምሥጢር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በኅቱም
ድንግልና ወልዳለችና፡፡

ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ኤፍሬምም እመቤታችንን ባመሰገነበት ድረሰቱ ክርስቶስ አምላካችንን
የወለድሽልን አንቺ ሳይተክሏት እንደበቀለቸው፣ ውኃ ሳያጠጧት ለምልማና አብባ እንዳፈራችው የአሮን በትር ነሽ
በማለት ምሳሌነቷን ገልጧል፡፡/ውዳሴ ማርያም ዘሰንበተ ክርስቲያን/፡፡

የያዕቆብ ምሥጢር

ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳው ጋር ተጣልቶ ወደ አጎቱ ወደ ላባ በሚሄድበት ወቅት መንገድ ላይ መንጋቸውን እየጠበቁ
ከውኃው አፍ ላይ የተገጠመውን ድንጋይ የሚያነሳላቸው አጥተው በችግር ላይ የነበሩት እረኞችን እንደአገኘኛ ራሔል
ከመጣች በኋላ ያን ታላቅ ድንጋይ ከጉድጓዱ ውኃ አፍ ላይ አንስቶ በጎቻቸውን እንዳጠጣላቸው ቅዱስ መጽሐፍ
ይናገራል፡፡ዘፍ 29፡1-11

ምሥጢራዊ ምሳሌውም ውኃ የማየ ሕይወት፣ ድንጋይ የመርገም፣ አናግዕ/በጎች/ የምእመናን፣ ኞሎት /እረኞች/
የነብያት፣ ራሔል የእመቤታችን፣ ያዕቆብ የክርስቶስ ነው፡፡

እረኞች በጎቻቸውን ለማጠጣት ድንጋዩን ማንሳት አልቻሉም፡፡

ነቢያትም በትምህርቶቻቸው በተጋድሎአቸው መርገምን አርቀው ማየ ሕይወትን ለማጠጣት አልቻሉም፡፡እረኞች


ራሔል እስክትመጣ ድረስ እንደጠበቁ ሁሉ ነብያትም በትንቢታቸው የእመቤታችንን መምጣት ይጠባበቁ ነበር፡፡
ራሔል በመጣች ጊዜ ብዙ እረኞች ማንሣት ያልቻሉትን ድንጋይ ያዕቆብ ብቻውን አንስቶ በጎቹን እንዲጠጡ አደረገ፡፡
እመቤታችንም ከተወለደች በኋላም ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነብያት በተገድሎአቸው ሊያርቁት
ያልቻሉትን መርገም በፈቃዱ በተቀበለው ፀዋትወ መከራ አራቀው አባግዕ ምእመናንንም ከማየ ሕይወት አጠጣ፡፡ዮሐ
4፤7

 ዕፀ ሳቤቅ

መፍቀሬ እግዚአብሔር አብርሃም በትዕዛአ እግዚአብሔር ልጁ ይስሐቅን ለመሰዋት ሞርያ ተራራ ላይ ከደረሰና ቅድመ
ዝግጅቱን ከአጠናቀቀ በኋላ በእግዚአብሔር መልአክ እጅ የተያዘ በዕፀሳቤቅ ሐረግ የታሰረ በግ እንዲሰዋ እንጂ ልጁ
ይስሐቅን እንዳይሠዋ ተነገረው፡፡

አብርሃምም ዐይኑን አነሣ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዕፀሳቤቅ ተይዞ አየ አብርሃምም ሔደ በጉንም ወሰደው
በልጁም ፈንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው ዘፍ9፡17፡፡ እንዲል ይህም ምሳሌ ነበረ

ምሳሌውም

 ይስሐቅ- የአዳምና የዘሩ


 በጉ - የመድኅኒ ዓለም ክርስቶስ
 ሰይፉ- የሥልጣነ እግዚአብሔር
 ዕፀ ሳቤቅ -የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም
 በጉ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ በዱር መገኘቱ- ጌታችን ከድንግል ማርያም ተወልዶ በሥጋ በመገለጡ በበረት ተኝቶ
የመገኘቱ ምሳሌ ነው፡፡
 የያዕቆብ መሰላል

ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ፡፡ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አረፈ በዚያም
ስፍራ ድንጋይ አነሳ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ፡፡ሕልምም አለመ እነሆ መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ
ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ እነሆም እግዚአብሔር በላይ ቆሞባት ነበር፡፡ዘፋ 28፡1-20

ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራዕይ ያያት መሰላል የእመቤታችን

የተንተራሰው ድንጋይ የትንቢተ ነብያት (እመቤታችን በትንቢተ ነብያት ጸንታ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው)፡፡

መሰላልዋ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ ማይቱ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው ጥላቻ ተወግዶ ምድራውያን
ሰዎችና ሰማያውያን መላእክት፤ እግዚአብሔር ወልድ ሥጋዋን ለመዋሐድ የወረደና ያረገባት የቅድስት ድንግል
ማርያም ምሳሌ ነው፡፡

 ቀስት ደመና

እግዚአብሔርም ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ። እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በኋላ ከሚመጣው ከዘራችሁ
ጋር አቆማለሁ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ዳግመኛ አይጠፋም:- እግዚአብሔርም አለ በኔና በናተ መካከል ከእናንተም ጋር ባለው
በህያው ነፍስ ሁሉ መካከል ለዘላለም የሚያደርግው የቃልኪዳን ምልክት ይህ ነው። "ቀስቴን በደመና አደርጋለሁ
የቃልኪዳኑንም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል ይሆናል" ዘፍ. 9፥8-15
ቀስተ ደመናው የይቅርታ ምልክት ነው ናኅ የተሰጠውን የይቅርታ ምልክት በእምነት ተቀብሎ ከመከራ ሥጋ መዳኑ
አዳም ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔርና በሰው ዘር መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ የሚያፈርስ እና ዓለመ
ዳግመኛ ጥፋት የሌለበትን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ለማግኘት መልከት ሆና በራሱ በእግዚአብሔር ፍቃድ
ለተሰጠችው ለወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነበር፤ አምላክን በድንግልና ጽንሳ መውለዷ
የመዳናችን ምልክት ነውና።
"ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች።
" እንዲል ኢሳ. 7፥14።

 የመጀመሪያይቱ ምድር
" እግዚአብሔር ምድርን ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ
ዛፍን ታብቅል አለ። እንዲሁም ሆነ ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ አበቀለች" ዘፍ. 1፥11።
1. የምውጀመሪያይቱ ምድር ለሰው ሕይወት የሆነውን ፍሬ ያበቀከቸው ምነም ዓይነት ዘር ሳይዘራባት በእግዚአብሔር
ቃለ ብስራት ምክንያትነት ብቻ ነው።
ወላዲተ አምላክ ቅዱስት ድንግል ማርያምም ለመድኃኒተ ዓለም ወደዚህ ዓለም የመጣውን ክርስቶስን
የወለደችው ያለዘርዐ ብእሲ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ቃል ነው።
2. አዳም የተገኘው ከኅቱም ምድር /ያላባት ያለ እናት/ ነው "እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው"
እንዲል። ዘፍ. 2፥7። ወልደ እግዚአብሔርም ቅዱመ ዓለም ከአብ ያለእናት እንደተገኘ ሰው የሆነውም በሁለት ወገን
ድንግል ከሆነች ከእመቤታችን ያለአባት ነው።
ምንም እንኳን እመቤታችን በመጀመሪያይቱ ምድር ብትመሰልም ከምድሪቱ ትበልጣለች ምክንያቱም ከምድሪቱ
የተገኘው ምግበ ሥጋ ሲሆን ከእመቤታችን የተገኘው ግን ለመንግሥተ ሰማያት የሚያበቃ ምግብ ሕይወት፣ ምግበ ነፍስ
ነውና።
ይህንኑ ታላቅ አባት ቅዱስ ኤፍሬም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም "ዘር ያልተዘራባሽ እራሻ አንቺ" በማለት ገለጠው። ነቢዩ
ዳዊትም በመንፈስ ቅዱስ ተመስጦ የእግዚአብሔር ወልድን ከሰማያት መውረድና ከእመቤታችን መውለድ የገለጸው
ሰማይና ምድር በማለት ነበር።
ምህረትና እውነት ተገናኙ፣ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ። እውነት ከምድር በቀለች ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች" መዝ.
84፣10-13 በማለት በምሥጢራዊ ትንቢቱ ስለ እመቤትውችን ተናገረ። ነገር ግን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰማያትና
ምድር ከመፈጠራቸው በፊት በአምላክ ልቡና ታስባ ነበረች። ምክንያቱም እግዚአብሔር በባሕርዩ ሁሉን አዋቂ ነውና
"ኢየሱስመ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር ስለስሙም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና" ዮሐ. 2፥25

ተፈፀመ

You might also like