You are on page 1of 65

/// / //

የደ ኃ ቅ ራጉኤል ቤ ክ አንቀጸ ሰ ት ቤት

ጥናታዊ ፅሁፍ ርዕስ፦የካህናት እና የምዕመናን መንፈሳዊ ግንኙነት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል

አዘጋጆች ፦አበራ ጥሩውሃ


ብሩክ ንቅበሸዋ
ሙሉቀን ሸዋረጋ
አስቴር አስፋው
ፅዮን ደስታ
ሜላት ፀጋዬ

አማካሪ ፦ብንያም አ አ.
2016 . ዓ ም
ማውጫ
ርዕስ ገፅ

ምዕራፍ 1 ...............................................................................
1.1 የጥናቱ ዳራ .........................................................................
1.2 የጥናቱ ችግር ተኮር ................................................................
1.3 የጥናቱ አስፈላጊነት .................................................................
1.4 የጥናቱ ወሰን .......................................................................
1.5 የጥናቱ ገደብ .................................................................
1.6 በጥናቱ ወቅት ሊያጋጥሙን የሚችሉ ችግሮች ...........................................
ምዕራፍ 2 ..............................................................................
የተዛማጅ ጽሑፍ ዳሰሳ ..............................................................
2.1.ክህነት ማለት ምን ማለት ነው? ክህነት ምንድን ነው
2.2 ክህነት መቼ ተጀመረ
2.3 የክህነት አገልግሎት ምንድን ነው ?ካህናት እነማን ናቸው
2.4 የካህናትን ጉዳይ ማድረግ ለምን አስፈለገ ?
2.5 ንስሐ ምንድን ነው ?
2.6 ንስሐ መቼ ተጀመረ ?
2.7 የንስሐ ጥቅም
2.8 የነፍስ አባት እዴት ይያዛል
2.9 ንስሐ ለመግባት ምን ያስፈልጋል
2.10 በንስሐ ጊዜ የካህናት ድርሻ
2.11 በንስሐ ጊዜ የምእመናን ድርሻ እና ቀኖናዎች
2.12 የንስሐ አባትና ልጅ ግንኙነት ምን ይመስላል ?
2.13 በንስሐ አባትና ልጅ ግንኙነት ላይ የሌሎች አኃት ቤተ-ክርስቲያን ተሞክሮ ምን ይመስላል
ምዕራፍ 3 .................................
የጥናቱ ዓላማ ............................................
3.1 ዐቢይ ዓላማ ..................................
3.2 ንዑስ ዓላማ ..............................................
ምዕራፍ 4 ...................................................
የጥናት ዘዴ ..........................
4.1 የጥናቱ ቦታ .........................................
4.2 የጥናቱ ጊዛ...........................................
4.3 የጥናቱ አይነት..........................
ምዕራፍ 1
መግቢያ

1.1 ጥናታዊ ዳራ
<< እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር >>አለ ሥላሤ ሰውን ከአራቱ
ባህሪያተ ስጋ ከአምስተኛ ባህሪየ ነፍስ በገቢር ፈጠሩ። ዘፍ 1፥16-31
በሳምንቱም አርብ በነገህ አዳም ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አደለም ብለው ከጎኑ አጥንትን ወስደው ሔዋንን

ፈጠሯት። ዘፍ 2፥18-23
( )
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከሌሎች ፍጥረታት ሁሉ አስበልጦ በእጁ ስራ በገቢር በመፍጠሩ የሰውን ክብር አጉልቶ
ያሳያል አንድም በምድር የተፈጠሩ ፍጥረታት ሁሉ ገዢ አድርጎ ሾሞታል ። አንድም በንፅህና፣በቅድስና፣በፀጋ በአክብሮ
የእግዚአብሔር የፀጋ ልጅነትን ሰጥቶ በመፍጠሩ አምላክ ለእኛ የሰጠንን ክብር ያሳያል። እግዚአብሔር አዳምና ሄዋንን
ሲፈጥር ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው የፈለጉትን እንዲመርጡና ለመረጡትም ነገር ሀላፊነት እንዲወስዱ ተደርገው ነው

የተፈጠሩት በዚህም አዳም በተሰጠው ነፃ ፍቃድ ተጠቅሞ <<አትብላ ከእርሱ በበላክ ቀን ሞትን ትሞታለህና
>>ያለውን ትዕዛዝ ተላልፎ ዕፀ በለስን በልቶ በገዛ ፍቃዱ ሞትን ባልንጀራ አደረገው ።አዳም በጠላት ዲያቢሎስ
አስመሳይ ቃል ተታሎ የነበረበትን የክብር ቦታ የተሰጠውን ልብስ ፀጋ አጥቶ ወደ ምድረ ፋይድ (የመከራ ቦታ)
ከተወረወረ ቡሐላ የደረሰበት የመጀመሪያ የመፍትሔ ሀሳብ ሳይለምነው የፈጠረውን ሳይጠይቅ የሰጠውን ፈጣሪውን
በሚስጢረ ንስሐ አማካይነት ይቅርታ መጠየቅ ነበር ይህ መልካም ምኞቱም ተሳክቶለት አዳም የፈፀመውን በደል
እያስታወሰ ባቀረበው የእንባ ፣የሐዘን፣የፀሎት፣የፀፀት መስዋዕት እግዚአብሔር አምላኩን እስከ ቀራንዮ አደባባይ ድረስ
በማምጣት ተባሮ ከወጣበት የክብር ሀገሩ ተመልሶ እንዲገባ በማድረግ የንስሐ መንፈሳዊ ጥቅም ተረጋግጧል።
ንስሐ ማለት ነስሐ ተፀፀተ ካለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው ንስሐ ማለት ፀፀት፣ኀዘን ፣ቅጣት፣ቀኖና ማለት ነው።ንስሐ
በሐጢአት ምክኒያት የተፃፈን ልብ አጥርቶ የሀጢአት እቅፋቶችን አስወግዶ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ ታላቅ
መንፈሳዊ በረከት ነው።

( )
ንስሐ ለገነት መንግስተ ሰማያት የሚያበቃ መሆኑ ተደጋግሞ ተገልጿል።መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ
ተብሎ የመጀመሪያውን አዋጅ የተናገረውም ስለዚህ ነው።

/ <<እንግዲህ ከጌታ
ሐዋርያው ቅ ጳውሎስም ስለ አዲስ ኪዳን ምስጢረ ንስሐ አስፈላጊነት ሲያስረዳ እንዲህ ይላል

ፊት የመፅናናት ዘመን እንዲመጣላችሁ ሀጢያታቹ ይደምሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም>>።

የሐዋ 3 19
፥ በአዲስ ኪዳን አንድ ሰው ሀጢያቱ በንስሐ ተደመሰሰለት ማለት ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀለት ርስት
መነሰግስተ ሰማያትን ለመውረስ የተዘጋጀ መሆኑን ልብ ይላል።

( )
የንስሐ አባት ማለት ለተነሳሒው ንስሐ ለሚገባው ሰው ኃጢያቱን አምኖ ለሚመጣ ሰው ''ሰው ሆኖ የማይሳሳት
እንጨት ሆኖ የማይጨስ የለም'' እንደሚባለው ኃጢአት መስራት የተጀመረው ከሰው ወገን ከመጀመሪያዎቹ ሰዎች
ከአዳምና ከሄዋን ጀምሮ በመሆኑ በእኔ ተጀመረ ብለው ተስፋ እንዳይቆርጡ አጽናንቶ ከዚያም የንስሐን ምንነት
ያስረዳቸዋል።በመቀጠልም የሚፆሙትን ፆም
የሚጸልዩትን ጸሎት የሚሰግዱትን ስግደት የሚመፀውቱትን ምጽዋት የሚሳለሙትን ገዳም ወዘተ በመስጠት ጨርሰው
ሲመጡም ከዚህ ቡሐላ ስለዚያ ኃጥያት በማሰብ ጊዜ እንዳያባክኑ መክሮአቸው ለወደፊትም እንዳይሰሩት እንዴት
እንደሚጠበቁ ይነግራቸዋል።
የንስሐ ልጅ ማለት ደግሞ በዚህ አለም ሲኖር እራሱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ አውቆ በድፍረት ሳያዉቅ በስህተት የሠራውን
ሀጢያት ካህኑን ምስክር አድርጌ ለእግዚአብሔር መናዘዝ መናገር አለብኝ ብሎ ከካህኑ ዘንድ ቀርቦ ሲሰራው ያላፈረውን
ኃጢያት የሚያውቀውን ሁሉ ሳይደብቅ አንድም ሳያስቀር የሚናገር ነው።እንዲሁም የተሰጠውንቀኖና በእምነት ተቀብሎ
ሳያጓድል የሚፈፅምና እንደተፈፀመ መጥቶ ለንስሐ አባቱ አሳውቆ እግዚአብሔር ይፍታህ ሲባል ከሀጢአቱ ተፈትቶ
ዳግመኛ የንን ኃጢአት ላለመስራት ወስኖ በተሻለ ህይወት የሚኖር ማለት ነው።
እኛም ይህን አስተምሮ ተረድተን አነሳሽ ምክኒያት አድርገን የካህናት እና የምዕመናን መንፈሳዊ ግንኙነታቸው ምን
እደሚመስል ችግሮቻቸውንና መፍትሔውን በዚህ ጥናታችን እናስቀምጣለን።

<< እንግዲህ
ንስሐ የቦታና የፆታ ልዩነት ሳይደረግ የሚፈፀም ስርዓት መሆኑን ቅዱሳት መፃህፍት ይመክራሉ ።

እግዛብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን የያዛል>>።የሐዋ 17፥30
የሰው ልጅ እግዚአብሔር ከአባትት ፍቅሩ የተነሳ ያደረገለትን ቸርነት በመዘንጋት በሀጢያት ባርነት ተይዞባቸው
የቆዩባቸው ወራቶች ያለማወቅ ወራቶች ተብለዋል ምክንያቱም በታሪክ ተደጋግሞ እንደምናነበው አንድ ሰው ሀጢያትን
መስራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አእምሮው በአለማወቅ ጥቁር መጋረጃ ይሸፈናል። የሚፈፀመው በደል ሁሉ ለእርሱ
መልካም እየሆነ
ይታየዋል ለምሳሌ ታሪኩ በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ካዕል 18 1-34
፣ የተመዘገበው የእሥራኤል ንጉሥ
አክአብ እውነተኛውን ነቢየ እግዚአብሔር ሚኪያስን ከመስማት ይልቅ አራት መቶ ነቢያተ ሐሰትን እንዲሰማና
ምክራቸውን እንዲቀበል ያደረገው አእምሮውን የጋረደው ያለማወቅና ያለማስተዋልመጋረጀሠ እንደነበር እናስተውላለን።
ስለዚህበየትያውም ክፍለ አለም በሥራና በኑሮ ምክንያት የተለያዩ የሰው ልጆች በቦታው አቀማመጥ ይለያዩ እንጅ
ሀጢአትን በመሥራት ተመሳሳይነት የሚታይባቸው ስለሆነ እነርሱ ባሉበት ሀገር እግዚአብሔር አለና በያሉበት ንስሐ
ይገቡ ዘንድ መታዘዛቸውን ያስረዳል።
ይህንም አስተምሮ ተቀብላ ቅድስት ቤተክርስቲያንም በማኅበረ ካህናትና ምእመናን መደራጀቷ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
አስተዳደር መመራቷ ከጥንት ያለ እንጂ አዲስ አለመሆኑን በቤተክርስቲያን ታሪክና በቅዱሳት በመፃህፍት የተፃፈውን
በተለይም ግብረ ሐዋርያትን መሰረት በማድረግ ተመክሮና ተወስኖ በህግና በስርዓት ይመራል።

ሰበካ ጉባኤ ስንል በአጥብያ ለተቋቋመውና ለሚቋቋመው የቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ አሰተዳደር ጉባኤ (ስራ
አስፈፃሚ ኮሚቴ ) የሚያስፈልጉትን አባላት ለመምረጥና በአባልነትም ለመመረጥ የሚችሉ ቤተክርስቲያን
በእውቀታቸው በጉልበታቸው በሃብታቸውና በአገልግሎታቸው የሚረዱ ካህናት ምዕመናን እና የሰንበት ት ቤት /
/
ወጣቶች የሚገኙበት የአጥቢያ ቤ ክ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብስብ ነው።

/ /
እኛም በዚህ ጥናታችን በደብራችን በቅ ራጉኤል ቤ ክ የሚገኙ
/
ካህናት ና ምእመናን በቃለ አዋዲ መሰረት በአንድነት የአጥቢያ ቤ ክ ሰበካ ካህናትና ምዕመናን በአንድነት የሚገኙበት
መንፈሳዊ ጉባኤ ተፈጥሮ ምዕመናን ያለምንም መድሎ በፆታ፣በእድሜ፣በዘር፣በቋንቋ፣በገንዘብ ባለመለየት ምዕመኑ

/
የተጫናቸውን የሀጢአት ሸክም በሥልጣኑ ካራገፈላቸው ቀኖና ስርአተ ቤ ክ ሚስጢረ ንስሐን ከፈፀሙላቸው ቡኃላ ቀስ
በቀስ ከሐጢአት የተለያዩ እና የሀጢያትን ምንጭ እያደረቁ በመንፈሳዊ ህይወት የሚበረቱበትና ትሩፋትን የሚሰሩበትን
መንገድ መምራት አለባቸው።
ቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ቢኖራትም በሰበካ ጉባኤ ብዙ ቢሰራበትም ዳሩ ግን በአንዳንድ

( ) ( )
የንስሐ አባት ካህናት እና ልጅ ምዕመን መካከል ባለው የግንኙነት የአገልግሎት ክፍተት ምክንያት ከቅ ቤ ክ //
ቀላል በማይባል ሁኔታ ምዕመናን ወደ ሌላ የዕምነት ተቋማት ወደ አልባሌ ሱስ ህይወት እንዲሁም ተስፋ በማጣት
በመቁረጥ ወደ ስደት ወጥተዋል ከቤተክርስቲያንም ዕርቀዋል በአለም ተወስደዋል የዚህም ችግሩን እንዲህም የሆነበት
ምክንያት ምን እደሆነ ለመረዳት ለማወቅ ይረዳን ዘንድ ከተለያዩ ምዕመናን እና ካህናት የሰበካ ጉባኤ አስተዳደሮች ጋር
በመቅረብ መረጃ በመዉሰድ ለዚህ ችግር የመፍትሔ አቅጣጫ ይህ ጥናታዊ ፅሁፋችን ያስቀምጣል።

1.2 የጥናቱ መነሻ ችግር


ሰውነታችንን መክረን አስተምረን ማኖር እንደምን ይቻለናል ብለው በትህትና በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን የሚኖሩ

ምእመናን ንዑዳን ክቡራን ናቸው ።ማቴ 5:5


የሰው ልጆች ድኩማን ናቸውና ህይወታቸውን የሚመራ መንፈሳዊ አባት ያስፈልጋቸዋል።በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን
የሚኖሩ ሰዎች ሀጢያትን ከመናዘዝ ባሻገር በስጋዊ ህይወታቸው መሪን ያገኛሉ ያለ ምክረ ካህን የሚኖር ክርስቲያን
የለቀዛፊ የሚሄድ መርከብ ነው።ብዙዎች በህይወታቸው የሚያጋጥማቸውን ችግሮች መፍታት ሳይችሉ የሚቀሩት ካህን
ስለማያማክሩ ነው ከስነ አእምሮ ጠበብት ይልቅ ብዙ ጉዳኞች የሚፈቱበት መንፈሳዊ ፀጋ ያላቸው ካህናት ናቸው።
ለምሳሌ፦ወጣቶች ከእድሜአቸው አንፃር የሚያጋጥማቸው ፈተና ብዙ ሊሆን ይችላል። ብሎም ዲያቢሎስ የብዙ

( )
ወራዞትን ወጣቶችን ልቦና ሁሉን ሁሉን ልጨብጥ ሁሉን ልያዝ በሚል ስሜትም እንዲታወክ ያደርጋል።ረጋ ብለው
ካለማሰብና በስሜትም ከመገፋፋትም ቀሪ ዘመናቸውን ሁሉ የሚፀፀቱበት ስህተት ውስጥ እንዲገቡ ይሆናል ገና ብዙ
ሳይኖሩ ህይወትን እንዲያማሩ ብሎም እራስን እስከማጥፋት ድረስ ውሳኔ ሳይቀር ይወስናሉ።
በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን አለመመራት የመጣውን ተፅእኖ ስንመለከት

- በሀጢያጥ ሲወድቁና የህይወት አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ ተስፋ ሲቆርጡ የሚታዩት የጥንቆላ ጋዜጦችን፣የስነልቦና
መፅሐፍት ቀመሮችን እያነበቡ ህይወታቸውን የሚያመሰቃቅሉት በምክረ ካህን ስለማይመሩ መምህርን ቤ/ክ
ስለማይጠይቁነው

- ምዕመኑ በራሳቸው መንገድ ከተጓዙ በኃላ በምክረ ካህን ሊታገዝ ሊለየው የማይገባውን የጮኝነት ጊዜ ሂደት ከትዳር
በፊት ከቅዱስ ቁርባኑ በፊት የማይደረግ አላስፈላጊ ግንኙነቶች ይፈጥራሉ ።
- በምክረ ካህን ያልታገዙ ምዕመናኖች ዲያብሎስ ፍሬን ከገለባ እንደሚለይ ሁሉ ምዕመኑንም ከእግዚአብሔር ደጅ
አስጋ ደሙ ይለያቸዋል።

- እነዚህ ችግሮች ካልተፈቱ ምዕመኑም በምክረ ካህን ካልታገዙ ከቅድስት ቤተክርስቲያን መራቅ ከስጋ ደሙ
መከልከልን ያመጣል ብሎም በዚህ ክፍተት ድካም ዲያብሎስም ተጠቅሞበት በመናፍቃን እና በአህዛብ እንዲወሰዱ
ያደርጋል።
እነዚህን አንገብጋቢ ችግሮች ተረድተን መፍትሄ ካላበጀንለት ምዕመኑም ወደ ሌላ ሀይማኖት መሄድ ስርአተ
ቤተክርስቲያን መጣስ የቤተክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖናዋ ተጥሶ በኢአማንያን እነድትደፈር ያደርጋል

( )
የዚህ ጥናት መነሻ ችግሩ የአጥቢያው ምዕመን ከንስሐ አባት ከካህናት ጋር ያለቻው መንፈሳዊ ግንኙነት በመዳከሙ
ምዕመኑ ከቅድስት ቤተክርስቲያን በመራቅ ግብረገብ አጥቶ ከስጋ ደሙ ርቀው አልፎም በሌላ እምነት ተቋማት
ተወስደው የሚታይ የሚገኝ በመሆኑ ነው።

1.3 የጥናቱ አስፈላጊነት


ምዕመኑ ከምክረ ካህን እርቀው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ጠፍተው በአለም እንዳይወስዱ በሀጢአት መንገድ ላይ
እንዳይመላለሱ የፅድቅን መንገድ እረስተው በአለም ከንቱ ስበት በኢአማንያን በተለያዩ ጥቅማጥቅም ማታለያ ያሉበትን
የሚከተሉትን እምነት ከኑሮ ደረጃቸው እያነፃፀሩ በተለያዩ ቁሳዊ ነገሮች እያታለሏቸው ከእምነት ጎዳና እንድሄዱ
ምዕመኑን ከቤተክርስቲያን አስተው አስወጥተው ወደ ቤተክርስቲያን እንዳሄዱ በማድረግ ያዳክማሉ።ይህን ተመልክተን
ከምዕመኑ እና ከካህናት በኩል ያለውን
ድክመት አይተን የሚያስከትሉትን በቤተክርስቲያን ላይ የሚመጡትን ጫናዎች እንዴት መፍትሔ መስጠት እንዳለብን
የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።
የቀደመችውን ቅድስት ቤተክርስቲያን ለማቆየት ስርዓቷ ዶግማዋ ቀኖናዋ ተጠብቆ ለምዕመናን ለማስተላለፍ በካህናትና
በምዕመናን መካከል ያለውን ክፍተት ተስተካክሎ ምዕመኑ ለካህናቱ ቅርብ ሆነው ካህናቱም ለምዕመኑ እረኛ ሆነው
ከቤተክርስቲያን ሳይጠፋ ስጋ ደሙን ተቀብለው በአንድነት በህብረት እንዲኖሩ አማራጭ መፍትሔ ማመላከት
ማስቀመጥ አስፈላጊተቱ የጎላ ነው።

1.6 የጥናቱ ወሰን


በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያንላይ
የተወሰነ ሲሆን በካህናቱ እና በምእመናን ላይ ያለውን መንፈሳዊ ግንኙነታቸው ላይ ያለውን ክፍተት የሚያጠና ነው

1.7 የጥናቱ ገደብ

ጥናቱ የሚካሄደው ከሀምሌ 2015 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
1.8 በጥናቱ ወቅት ሊያጋጥሙን የሚችሉ ችግሮች
የተጠና ጥናት አለመኖሩ
Ÿ ይህ ጥናት በምናጠናበት ወቅት ምዕመኑ ለመጠየቅ ፍቃደኛ አለመሆን ካህናቱ ጊዜ በቂ ጊዜ አለማግኘት
Ÿ ጥናቱን የምንሰራው ተማሪዎች ሰራተኛ ስለሆንን በቂ የተረጋጋ ጊዜ አለመኖር
ምዕራፍ 2
የተዛማጅ ጽሑፍ ዳሰሳ

1.ክህነት ማለት ምን ማለት ነው?


'' '' '' '' ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማገልገል ማለት ነው ።
በግእዝ ቋንቋ ተክህነ ፤ አገለገለ
አገልግሎቱም ለሃይማኖት ብቻ ነው ።

ክህነት የአገልግሎቱ ስም ሲሆን ፤ አገልጋዮቹ ''ካህናት '' ይባላሉ ። በዕብራዊያን ቋንቋም ስያሜው ከግእዝ ቋንቋ
ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ''ካህን'' ይሉታል ።
- ዮናናውያንም ''ኢየራቲቪን'' - ''ተክህኖ ፤ ተክህኖት'' ከሚለው አርእስት ''ኢየሬብአ'' ብለው
ያወጣሉ ፤ ትርጓሜውም በተመሳሳይ ''ካህን'' ማለት ነው ።

- ክህነት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የተቀደሰ አገልግሎት ነው ።


ሥልጣነ ክህነት :- ማለት ጳጳሳት በአንብሮተ እድ የሚያስተላልፉት ፤ የሚሾሙት የክህነት ማዕረግን ለማግኘት
የሚደረግ አገልግሎት ነው ። ይኸውም ምስጢረ ክህነት የማሰር እና የመፍታት ሥልጣን ያለው ከመሆኑ ሌላ ሌላውንም

-
ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት የሚያከብር የሚቀድስ ነው ። ይህም ማዕረግ በጳጳሱ ጸሎት በአንብሮተ እድ
ተሿሚው ካህን የሚቀበለው ጸጋ ሥልጣንም የሚገኝበት ምስጢር ነው ።

2.ክህነት መቼ ተጀመረ ?
የመጀመሪያ የእግዚአብሔር እና የሰው ልጆች አገልጋዮች
ካህናት መላእክት ናቸው፡፡

‹‹በዙፋኑ ዙሪያ ሃያ አራት ወንበሮች ነበሩ፡፡ በእነዚያ ወንበሮችም ሃያ አራት አለቆች (ካህናተ ሰማይ)
ተቀምጠዋል፡፡ ነጭ ልብስም ለብሰዋል፡፡ በራሶቻቸው ላይ የወርቅ አክሊሎች ደፍተው ነበር … በዂለንተናቸው
ዓይኖችን የተመሉ ናቸው፡፡ ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረውና ያለው፣ የሚመጣውም፤ ዂሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ›
እያሉ›› ቀንና ሌሊት አያርፉም፡፡ እነዚህ በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘለዓለም እስከዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው
ለእርሱ አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ይሰግዳሉ፡፡ እንዲህም ይላሉ፤ ‹ጌታችን እና አምላካችን ሆይ፣ አንተ
ዂሉን ፈጥረሃልና በፈቃድህም ኾነዋልና ተፈጥረውማልና ክብርና ውዳሴ ኀይልም ለአንተ ይገባል፤››› ተብሎ እንደ

( . )
ተጻፈ ራእ ፬፥፬ ፡፡
ክህነት በብሉይ ኪዳን

( )
እግዚአብሔር ሙሴን ለምስፍና ለመስፍንነት ፣ አሮንን ለክህነት መርጧቸዋል፡፡ የመረጠበት ግብርም ረቂቅ ነው፡፡
ዂሉም እስራኤል ግን መሳፍንት፣ ገዢዎች፣ መሪዎች አልነበሩም፡፡ የሌዊ ወገን ለክህነት፣ የይሁዳ ወገን ለመንግሥት

የተመረጠ ነበር (ዘኍ. ፫፥፮)፡፡ የሌዊ ነገድ ተለይተው የክህነቱን አገልግሎት፣ መሥዋዕት መሠዋት የመሳሰሉትን
ይሠሩ ነበር (ዘዳ. ፲፥፰፤ ፳፰፥፩-፵፫)፡፡ ሌሎች ነገደ ፳ኤል ድንኳን በመሸከም ልዩ ልዩ አገልግሎት ይሠጡ ነበር፡፡
ይህን የተላለፈ ፳ኤላዊ መቀሠፍቱ ከባድ ነበር፡፡ ከላይ እንደ ተመለከትነው ለክህነት መመረጥ፣ መለየት፣ መቀባት፣
መሾም፣ መቀደስ
የግድ ያስፈልጋል፡፡ ማንም ዝም ብሎ ካህን ነኝ፤ ነቢይ ነኝ ማለት አይችልም፡፡ መሥዋዕቱን ምእመናነ እስራኤል
ያመጣሉ፤ አሮንና ልጆቹ ደግሞ መሥዋዕቱን ያቀርባሉ፡፡ ሕዝቡ በጉን፣ ርግቡን፣ ዋኖሱን፣ በሬውን ያመጣሉ፤ ካህናቱ
እጃቸውን ጭነው ይጸልያሉ፤ ኀጢአትን ያስተሰርያሉ፡፡ ሕዝቡን ያስተምራሉ፤ ይመክራሉ፡፡ ሕዝቡም ይመከራል፤
ይገሠፃል፡፡

በእግዚአብሔር ሳይመረጡና ሳይሾሙ ካህን ነን ቢሉ የሚመጣው ቅጣት ከባድ ነው፡፡ ከሌዊ ወገን የተወለዱ ዳታንና

( . - )
አቤሮን የደረሰባቸው ቅጣት በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል ዘኍ ፲፮፥፩ ፶፩ ፡፡ ያልተሰጣቸውን ሽተው፣ ከህነት
ሳይኖራቸው ለማጠን ገብተው የእሳት ራት ሆነዋል፡፡ መሬት ተከፍቶ ውጧቸዋል፡፡ በሕይወት ሳሉ ተቀብረዋል፡ ለክህነት
የተመረጠው አሮንና ልጆቹ ግን አልጠፉም፡፡ ከዚህ እንዳየነው ለክህነት መመረጥ፣ መቀደስ፣ መለየት፣ መሰጠት
ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይኾን ማንም ተነሥቶ ካህን ነኝ፣ ነቢይ ነኝ ቢል ይህ ዕጣ ፋንታ ይገጥመዋል፡፡ እግዚአብሔር

አልመረጠውምና፡፡ የእነዚህ ሰዎች ዕጣን ማሳረግ(ማጠን) ለመቅሠፍት፤ የሳኦል መሥዋዕትም መንግሥትን ለማጣት
ዳርጓቸዋል፡፡ ሳኦል፣ ሳሙኤል እስኪመጣ መታገሥ አቅቶት መሥዋዕት በመሠዋቱ ነው መንግሥቱን የተነጠቀው (፩ኛ

ሳሙ. ፲፭፥፳፪፤ ፳፰፥፲፯)፡፡


ክህነት በሐዲስ ኪዳን
ክህነት በዓለመ መላእክት፣ በብሉይ ኪዳን ምን እንደሚመስል ተመልክተናል፡፡ በዓለመ መላእክት መሥዋዕቱ ምስጋና፣
ውዳሴ፣ ተልእኮ ነው፡፡ ካህናቱ መላእክት ናቸው፡፡ ቤተ መቅደሱ ዓለመ መላእክት ነው፡፡ በብሉይ ካህናቱ ከሌዋውያን
የአሮን ልጆች፣ ቤተ መቅደሱ የመገናኛው ድንኳን፣ መሥዋዕቱ ላም፣ በግ፣ ፍየል፣ ርግብ፣ ዋኖስ የእኽል አይነቶች
ናቸው፡፡ የሐዲስ ኪዳን ክህነቱም፣ መሥዋዕቱም፣ ካህናቱም ከተመለከትነው የተለየ ነው፡፡ ክህነቱና ካህናቱ ልዩ
የሚኾንበት ምክንያት መሥዋዕቱ ልዩ በመኾኑ ነው፡፡ መሥዋዕቱ በቀራንዮ ዐደባባይ ዓለም ለማዳን ሥጋውን ቈርሶ፣
ደሙን አፍስሶ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቀደም ሲል ያየነው የመላእክት መሥዋዕት ዓለምን ማዳን
አልተቻለውም፡፡ የሌዋውያንን መሥዋዕትም አንድ ኀጢአተኛ ሰው ያመጣዋል፡፡ ከመርገም ያልተለየ ካህን ይሠዋዋል፡፡
መሥዋዕቱም ሥጋዊ ይቅርታን ብቻ ያሰጥ ነበር፡፡ መሥዋዕቱ፣ በአቀራረቡም ጉድለት ነበረበት፡፡ ስርየቱ የሚያስገኘውም
ላመጣው ሰው ብቻ ነበር፡፡

የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት ግን መሥዋዕቱ ፍጹም ጉድለት የሌለበት ነው፡፡ መሥዋዕቱም፣ አቅራቢውም፣ ተቀባዩም
ኢየሱስ ክርስቶስ በመኾኑ ክህነቱም ፍጹም ነው፡፡ ይህን ፍጹም ክህነት ፍጹም የሆነውን መሥዋዕት ለሚያቀርቡ ካህናት
ሰጠ፡፡ ክህነቱን አገልግሎቱን በትህትና አሳያቸው አስተማራቸው፡፡ ክህነቱንም መሥዋዕቱንም ሰጣቸው፡፡ በዚህ የተነሳ
የሐዲስ ኪዳን ካህናት መላእክት ያልሰዉትን የብሉይ ኪዳን ካህናት ያላቀረቡትን መሥዋዕት የማቅረብ የማገልገል
ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው በመሆኑ ክህነቱ ምጡቅ ምስጢሩ ጥልቅ አገልግሎታቸውም
ረቂቅ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ‹‹ኢተአምሩኑ ከመ መላእክተ ጥቀ ንኴንን ኅድጉሰ ዘዝ ዓለም፤ የዚህን ዓለም ዳኝነት

ተዉትና በመላእክት ስንኳን እንድንፈርድ አታውቁምን ?›› ሲል እንደ ጠቀሰው፤ መምህራነ ቤተ


ክርስቲያንም ‹‹ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት፤ ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ›› በማለት

እንደሚያስተምሩን (፩ኛ ቆሮ. ፮፥፲፫)፡፡


የብሉይ ኪዳን ካህናት ሰዉን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ አልተቻላቸውም፡፡ የሐዲስ ኪዳን ካህናት ግን የጠብ
ግድግዳ ከፈረሰ፣ ልጅነት ከተመለሰ፣ ጸጋ ከተገኘ፣ ሰውና እግዚአብሔር ከተገናኘ በኋላ ስለ ተሾሙ ክህነታቸው ልዩ፣
መሥዋዕታቸው ልዩ፣ ክብራቸው ልዩ ነው፡፡ ምድራውያን ናቸው፤ ነገር ግን ሰማያዊ ሥልጣን አላቸው፡፡ የተሾሙትም
ሰማያዊውን ርስት ለመስበክ፣ ሰውን ከምድራዊ ግብር ለይተው ሰማያዊ ጸጋ አሰጥተው መንግሥተ ሰማያትን ለማውረስ
ነው፡፡ አምላክ ይህን ያደረገው በመልእክት አይደለም፤ ሰው ኾኖ መጥቶ ሥርዓቱን ሠርቶ አሳይቶ ሥልጣኑን ሰጥቶ
አገልግሎቱን መሥርቶ ነው፡፡ ‹‹ወአልቦ ዘይነስእ ክብረ ለርዕሱ ዳዕሙ ዘጸውዖ እግዚአብሔር በከመ አሮን፤ በቃሁ ነቃሁ

(እንደ አሮን በእግዚአብሔር


ብሎ ክብረ ክህነትን ለራሱ የሚያደርግ የለም፡፡ እግዚአብሔር እንደ አሮን ነው እንጂ

ከተጠራ በቀር ማንም ክብርን ለራሱ የሚወስድ የለም፤››) እንዳለ (ዕብ. ፭፥፬)፡፡

3.የክህነት አገልግሎት ምንድን ነው? ካህናት እነማን ናቸው?


ለክህነት እና ለካህናት አገልግሎት መሠረቱ ነው፡፡
‹‹በመዓልትም በሌሊትም አያርፉም›› ያለው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን የዘወትር አገልግሎት
በግልጽ ያሳያል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ምስጋናው በሰማይና በምድር የሞላ ነው›› በማለት
የምታሰመግነው በክህነት እና በካህናት አማካይነት ነው፡፡ ካህናት፣ ምድራውያን መላእክት ናቸው፡፡ መላእክት
እንደሚያመሰግኑ ያመሰግናሉ፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዲቆሙ ይቆማሉ፡፡ የክህነት አግልግሎት ከመላእክት ቀጥሎ
የተሰጠው ለሰው ልጅ ነው፡፡ ለሰው የተሰጠው ክህነት ፈጣሪውን እንዲያመሰግንበት ብቻ አይደለም፡፡ መሥዋዕት
ሊሠዋበት፣ ዕጣን ሊያሳርግበት፣ ሰውን ሊረዳበት የተሰጠ ነው፡፡ ለሰው ክህነት ተሰጠው ስንል ሰው ዂሉ ካህን ነው
ማለት አይደለም፡፡ ከሰው ልጆች ወገን ለክህነት የተመረጡ አሉ፡፡ ዂሉም ሰው ተነስቶ ካህን ነኝ ሊል አይችልም፡፡ ይህ
ማለት የአካል ክፍል እንደማጥፋት ማለት ነው፡፡ በአካል ውስጥ ዓይን፣ እጅ፣ እግር፣ አፍ፣ አፍንጫ … አሉ፡፡ ዂሉም
የአካል ክፍሎች ዓይን መኾን አይችሉም፡፡ እጅ መዳሰስ፣ እግር መሔድ፣ ዓይን ማየት፣ አፍንጫ ማሽተት፣ አፍ መጉረስ
ነው የሥራ ድርሻቸው፡፡ እጅ፣ እግር፣ አፍ፣ አፍንጫ፣ ጆሮ ካላየን ቢሉ፣ ዓይን እንኹን ብለው ቢያስቡ ወይም ነን ቢሉ

( )
ዓይን መኾን ማየት አይችሉም፡፡ ማየት የዓይን ተግባር እንደ ኾነ ዂሉ ሰዎችም ካህን ሳይኾኑ ነን በማለት መዓርገ
ክህት አይገኝም፡፡ እግዚአብሔር የመረጣቸው ካህናት ይኾናሉ እንጂ፡፡ ሥልጣነ ክህነት በጳጳሳት እጅ የሚሰጥ ሥልጣን
ነውና ማቃለል አይገባም፡፡ ካህናት የእግዚአብሔር
ዓይኖች ናቸውና፡፡ እግዚአብሔር ኀጢአተኛውን የሚያየው፣ የሚጐበኘውና ኀጢአቱን ይቅር የሚለው በእነርሱ በኩል

( . )
ነው፡፡ ‹‹ሒድ ራስህን ለካህን አሳይ›› ማቴ ፰፥፬ ተብሎ እንደ ተጻፈ ካህን አየን ማለት እግዚአብሔር አየን
ማለት ነው፡፡ ካህን የእግዚአብሔር ዓይን ነውና፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ የምንኾነውም በካህናት ተጠምቀን ነውና

(ማቴ. ፳፰፥፲፱)፡፡ በዚህ መሠረት ያለ ካህን እና ያለ መሥዋዕት የሚፈጸም አገልግሎት የለም፡፡ ቢኖርም አገልግሎቱ
የውሸት ነው፡፡ ሕሙማን በክህነት አገልግሎት ይድናሉ፡፡ ‹‹ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉ
ቀሳውስትን ወደ እርሱ ይጥራና ይጸልዩለት፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቅቡት
የሃይማኖት ጸሎት ድውዩን ይፈውሰዋል፡፡ እግዚአብሔርም ያስነሣዋል፤ ኀጢአትንም ሠርቶ እንደ ኾነ

ይሰረይለታል፤›› እንዲል (ያዕ. ፭፥፲፫-፲፮)፡፡


ካህናት ይህን ዂሉ የማድረግ ሥልጣን የተሰጣቸው የቤተ ክርስቲያን አባቶች ናቸው፡፡ በትረ ክህነት የጨበጡ፣
በእግዚአብሔር የተመረጡ፣ አጋንንትን የሚቀጡ፣ ኀጢአትን እንደ ሰም አቅልጠው የሚያጠፉ ናቸው፡፡ ሰውን ወደ
እግዚአብሔር ያቀርባሉ፤ የእግዚአብሔርን መንጋ ምእመናንን ይጠብቃሉ፡፡ በለመለመ መስክ በጠራ ውኃ ያሠማራሉ፡፡
ማለት ያልተበረዘ ያልተከለሰ ከሐዋርያት የተገኘ ንጹሕ ወንጌልን ያስተምራሉ፡፡ ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት
ወያሴስል ኃጢአተ ዓለም፤ እነሆ የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ
የእግዚአብሔር በግ›› እያሉ ሰውን ዂሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥትና ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያቀርቡ የድኅነት

በር ናቸው (ዮሐ. ፩፥፳፱)፡፡


የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ፤ የሙሴ መንፈስ በኢያሱ እንዳደረ የሐዋርያት መንፈስ ያደረበት እግዚአብሔር የመረጠው
የገለጠው ክህነት በአበው ጳጳሳት ቅባትና ጸሎት አማካይነት ይታደላል፡፡ አባቶች ጳጳሳት በአንብሮተ እድ ባርከው
በንፍሐት እፍ ብለው በእግዚአብሔር ስም ክህነቱን ካላሳደሩበት በቀር ማንም ካህን መኾን አይችልም፡፡ እግዚአበሔር
የሾመው ሐዋርያትን ብቻ አይደለም፤ ጳጳሳትንም የሾመው እርሱ ነውና፡፡ ‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ
ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ዂሉና ለራሳችሁ

( . )
ተጠንቀቁ፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈ ሐዋ ፳፥፳፰ ፡፡ ጌታችን ‹‹እውነት እላችኋለሁ፤ በምድር የምታስሩት ዂሉ
በሰማይ የታሰረ ይኾናል፡፡ በምድርም የምትፈቱት ዂሉ በሰማይ የተፈታ ይኾናል›› በማለት ለቅዱሳን ሐዋርያት የማሰር

የመፍታት ሥልጣን እንደ ሰጣቸው በማያሻማ ኹኔታ በቅዱስ ወንጌል ተቀምጧል (ማቴ. ፲፰፥፲፰፤ ሉቃ. ፳፬፥፶፤
ዮሐ . ፳፥፳፪-፳፬፤ ሐዋ. ፱፥፲፯፤ ፩ኛ ጢሞ. ፬፥፲፭)፡፡
ስለዚህ ክህነት በእግዚአብሔር ጥሪ የሚፈጸም በእግዚአብሔር ሰጭነት የሚከናወን መኾኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ
ሥልጣን እግዚአብሔር መጀመሪያ የመረጠው ቅዱሳን
ሐዋርያትን ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ የሐዲስ ኪዳን ካህናት ሐዋርያት ናቸው፡፡ የመረጣቸው፣ የጠራቸው፣ የሾማቸውም

( . )
እርሱ ራሱ ነው ማቴ ፲፥፩ ፡፡ ሥልጣኑን ያገኙት ከባለቤቱ ከኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
ሥልጣነ ክህነት ሐዋርያት ተቀብለውት የሚቀር ሳይኾን ለተመረጡ ሰዎች ሊሰጡት እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር

( . )
ነው ሐዋ ፩፥፳፬ ፡፡ በዚህ መልኩ የሚሾሙ ካህናት የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሐዋርያት ተከታዮች ሐዋርያት
ናቸው፡፡ ለእነርሱ የተሰጠውን ሥልጣን ማመን፣ መቀበልና መጠቀም ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ በየፌርማታው ነቢይ ነኝ
ካህን ነኝ ከሚሉት መጠንቀቅ ያሻል፡፡ ክህነት ዝም ብሎ በየመንገዱ የሚታፈስ አይደለም፡፡ ማንም እየተነሣ የሚዘግነው
የእድር ቆሎም አይደለምና

:-
የካሕናት አገልግሎት ፤ ኃላፊነት እና ተግባር
የካህናት ኃላፊነትና ተግባር ቀድሞ መጻህፍተ ህግጋት ሳይጻፉ በብሉይ ሆነ በሐዲስ ኪዳን ከዘመነ አበው ጀምሮ
እንደየዘመኑ አፈጻጸሙ ይለያይ እንጂ ሰፊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በመሠረቱ ክህነት፣ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ፣
በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ማገልገል፣
Ÿ የአምልኮ ሥርዓት መፈጸምና ማስፈጸም፣
Ÿ ሕዝብን መጠበቅና መምራት፣
Ÿ ስለ ራስ፣ ስለ ሕዝብና ስለ ሀገር ጸሎትና መሥዋዕት ማቅረብ፣
Ÿ ሕዝብን መጠብቅና መምራት፣
Ÿ ማስተማር፣ በአጠቃላይ የእግዚአብሔር እንደራሴ መሆን ሕዝብን ለማገልግልና ለመጠበቅ፣ ሕዝባውያን ወይም
ምዕመናን ሊፈጽሙዋቸው የማይችሉትን አገልግሎቶች ለማበርከት ከእግዚአብሔር ለተጠሩና ለተመረጡ ሰዎች የሚሰጥ
መንፈሳዊ ኃይል እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ክህነት ከምንጩ ከመሰረቱና ከመገኛው፣ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ሆኖ

ሰማያዊና ምድራዊ መግቦትን ያካተተ ሐላፊነት ነው፡፡ ግብረ 6፡1-7፡፡ 20፡28፡፡ 1 ኛ ጢሞ/4፡
16፡፡ ጴጥ፡ 5፡2-4፡፡
ክህነት ለዚህ ታላቅ ሐለፊነት ለተዘጋጀና ለተጠራ ሰው የተሰጠ ሥልጣን ከሆነ፣ ካህንም የእግዚአብሔርን ሕዝብ
ይጠብቅና ያገለግል ዘንድ ከእግዚአብሔር የተጠራ እንጂ በሰው ልዩ ፍላጎትና ኃይል የሚሾም አለመሆኑን ማወቅና
መረዳት ለአገልግሎቱም መዘጋጀት ግዴታ ነው፡፡

ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ወአንትሙኒ ጽንዑ ከመእብን መንፈሳዊ ወኩኑ ታቦተ መንፈሳዌ ለክህነት
ቅድስት ወንጽሕት ከመታቅርቡ ወታዕርጉ መሥዋዕተ መንፈሳዌ ዘይሰጠወክሙ እግዚአብሔር በእደዊሁ ለኢየሱስ

.
ክርስቶስ፡፡›› … ማለት፣ ‹‹እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ
የሚያሰኝ መንፈሳዊ መስዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ፡፡›› ያለው፣

1 ኛ ጴጥ፣ 2፡5-6፡፡
እንግዲህ ረዘም ያለ ታሪክ ያለውን ክህነታዊ የትምህርት አገልግሎት፣ በዘመነ አበው፣ በዘመነ ኦሪትና በዘመነ ሐዲስ
በሚል ርእስ ለይተን አጠር ባለ መልኩ እንደሚከተው ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

የክህነት አገልግሎት በዘመነ አበውና በዘመነ ኦሪት


በዘመነ አበው የክህነት አገልግሎት በቤተሰብ ሐላፊ አማካይንነት ይከናወን ነበር ማለትም አንድ ሰው የቤተሰብ ሐላፊ
በመሆኑ ብቻ መስዋትን የማቅረብ ሥልጣን ሲኖረው በዘመነ ኦሪት ግን የክህነት አገልግሎት፣ በተለዩና ለዚህ አገልግሎት

በተጠሩ ሰዎች ብቻ የሚከናወን ሆነ፡፡ ከኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 14 ላይ እንደምንረዳው፣ የሰላሙ ንጉሥ መልከ
ጼዴቅ ስለ አሻሿሙ ምሥጢርና በዘመኑ ይፈጸም ስለነበረው የክህናት አገልግሎት ሥርዓት በመጽሐፍ ቅዱስ በስፋት
የተጻፈ መረጃ ባይኖርም፣ የልዑል እግዚአብሔር ካህን፣ የሰያሜ ካህናት የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ እንደቀረበ ግን

14፡17-20፣ መዝ፡109/110፡4፡፡፣ ዕብ፡5፡6፡6፡20፡


እንረዳለን፡፡ ዘፍ፡

7፡1-22፡፡
መልከ ጼዴቅ ለአብርሃም የሰጠውን በረከት ስንመለከት ዛሬ ካህናት ለምዕመናን ለሕፃናት ለእናቶች የሚሰጡት በረከት
ምን መሆን እንዳለበት እንድናስብ ይጋብዘናል፣ ከጦርነት ማግስት በረከት ያገኘው አብርሃምን ስናስብ ዛሬ ሰላም
አጥተው ዕድገታቸው በሚቀጭ ሕፃናት፣ ደህንነታቸው ለማይጠብቅ እናቶች የምናቀርበው በረከት ምን እንደሚሆን
እንድናጤን
ያስገድደናል፡፡
ከላይ በተገለጸው መልኩ ያገለግል በነበረው በሥርዓተ አበው ምትክ ሥርዓተ ኦሪት በተሰራ ጊዜም ለክህነት አገልግሎት

የሚመረጡ፣ ነውረ ሥራ የሌለባቸው (ያልተገኘባቸው) የአሮን ልጆችና የልጅ ልጆች ሆኑ፡፡ ዘሌ፡21፡16-
24፡፡
የካህናተ ኦሪት፣ መደበኛ ሐላፊነት ተግባር፣ መስዋዕትን ማቅረብ ሆኖ፣ የበዓላት አከባበር ሥርዓትን መጠበቅና
ማስጠበቅ፣ መጻሕፍተ ኦሪትንና ነቢያትን ማንበብና መተርጎም ቋሚ ሥራቸው ነበር፡፡
ካህናተ ኦሪት፣ የሕዝቡን ንጽሕናና ጤንነት ማስጠበቅም ከአገልግሎታቸው ዘርፍ አንዱ ነበር፡፡

1 ኛ. ዘዳ፣ 28፡1-5፡፡ 2 ኛ. ዘኁ፡15፡40፡፡


3 ኛ. ዘኁ፡18፡5 4 ኛ. ዕዝ፡2፡63፡፡
5 ኛ. 2 ኛ፡ዜና፡መ፡15፡3፡፡ 6 ኛ. ኤር፡18፡18፡፡
7 ኛ. ሕዝ፣ 7፡26፡፡ 8 ኛ. ሚክ፡3፡11፡፡
ካህናተ ኦሪት ሊቃነ ካህናትና ሌዋውያን በሚሉ ዐበይት መደቦች የሚከፈሉ ሲሆን፣ የሥራ መደባቸውም
እንደየምድባቸው የሚከፋፈል ይሆናል፡፡
ካህናተ ኦሪት ሓላፊነታቸውና ተግባራቸው ከሁሉ የከበደ እንደሆነ ቢታወቅም ከጊዜ በኋላ ግን ዓላማቸውን ለውጠው

በሰማያዊ ክብር ፋንታ ምድራዊ ክብርን ሽተው (ታይታ) ለተርእዮ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ሆነው ተገኝተው ስለነበር
መድሐኔታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓለም በይቅርታ በጎበኘበት ወቅት የጸሐፍትንና የፈሪሣውያንን ከንቱነትና ግብዝነት ተመልክቶ

በስምንት ዓበይት ነጥቦች መስሎ ወቅሶአቸዋል፡፡ ማቴ 23፡13-36፡፡


መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ክህነታዊ ግዴታቸውን ወይንም የኖላዊነት ሓላፊነታቸውን ባልተወጡ ፈሪሣውያን
ተግሣፁን በዚህ ሥእላዊ መግለጫ አሳየ እንጂ፣ ቀደም ሲል ሥርዓተ ኖሎት ሲጓደል፣ ሕዝቡ በመንፈሳዊም ሆነ
በማኅበራዊ ሕይወቱ ሲበድል እግዚአብሔር በተለያዩ ወቅቶች ካህናቱን ገሥጾአል፡፡ በነቢዩ በሕዝቅኤል የተነገረውን
ቃል ስንመለከት ‹‹የማሠማርያዬን በጎች ለሚያጠፋና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው ይላል እግዚአብሔር፡፡ ስለዚህ
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለማይጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፡፡ በጎቼን በትናችኋል አባራችኋልም፣
አልጎበኛችኋቸውምም፡፡ እነሆ የሥራችሁን ክፋት እጎበኝባችኋለሁ ይላል እግዚአብሔር፡፡›› የሚል ሆኖ ስናገኘው፣
በሕዝቡና በካህናቱ መካከል ያለውን የመግቦትና የኖላዊነት ሥራ ሲጓድል የእግዚአብሔር ተግሣጽ ምን ያህል

እንደሚበረታ እንረዳለን፡፡ ሕዝ፡34 1-16


፡ ፡፡
የካህናት ሓላፊነትና ተግባር በአዲስ ኪዳን
ከዚህ በላይ የተመለትነው የካህናተ ኦሪትን የክህነታዊ አገልግሎት አፈጻጸምን በአጭሩ ነበረ፡፡ ቀጥሎም የካህናተ ወንጌልን
ጥሪ፣ የሥራ ሓላፊነትንና ተግባርን እንመለከታለን፡፡
የካህናተ ሐዲስ ሥልጣን እንደ ካህናተ ኦሪት በዘር የሚወረስ፣
በይገባኛል የሚገኝ መብት ሳይሆን አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከማይሰፈር ብዕሉ ለሰው ልጅ በሰጠው ጸጋ መሰረት
ጥሪውን ተቀብለው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለሚሰለፉ ሰዎች የተሰጠና የሚሰጥ፣ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ
እናውቃለን እናምናለን፡፡ ሢመተ ክህነት ከሊቀ ካህናት ከኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የተሰጠ ጸጋና ሰማያዊ በረከት
በመሆኑ፣ ድኅነተ ነፍስን ማስገኘት ካልተቻለው ከካህናተ ኦሪት የተለየ፣ ለካህናተ ኦሪት ያልተሰጠ ኃይልና ሥልጣን
የተገኘበት ሰማያዊ ሐብት ነው፡፡

ካህን፣ ጠባቂ፣ መምህር፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የሕዝብ መሪ አስተማሪ ኖላዊ
መንፈሳዊ አባት ሆኖ የዓለምን ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመጥራት የተሰለፈ የእግዚአብሔር ሕግ አስፈጻሚ
በመሆኑ ሓላፊነቱ ነፍስን የመጠበቅ ሓላፊነት ብቻ አይሆንም፣ በደዌ ሥጋ የሚፈርሰውን የእግዚአብሔርን ሕንፃ
መጠበቅም ሓላፊነቱ ነው፡፡
ካህናት፣ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኳችሁንም ሁሉ
እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡
የሚለውን አምላካዊ አዋጅ ለመፈጸም ሥልጣን የተሰጣቸው የእግዚአብሔርን መንጋ ለመጠበቅ እንዲሰለፉ፣ ደዌ ሥጋንና
ደዌ ነፍስን እንዲፈውሱ፣ ሙታነ ሥጋንና ሙታነ ነፍስን እንዲያስነሱ፣ አጋንንትን እንዲገዙ ኃይልና ሥልጣን የተሰጣቸው
የክርስቶስ እንደራሴዎች፣ ይሕይወት ጎዳና መሪዎችና የመንግስተ እግዚአብሔር በረኞች ናቸው፡፡ ማቴ፡ 19፡
19፡፡ 18፡18፡፡ 28፡19፡፡
ዛሬ የዚህ ሥልጣን በረከት ባለቤቶች የሆኑ፣ በዚህ ጸጋ የበለጸጉ ካህናት መንፈሳዊ ኃይላቸውን በሰው ሕይወት ላይ
በሰለጠኑት ደዌያት ላይ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፣ ዛሬ በሰው ልጅ ድኅነት ላይ ማነቆ ሆኖ የሚታየው የኋላ ቀርነት

( )
ቀንበር ፈቺዎች እንዲሆኑ በተስፋ የሚጠበቁ የእግዚአብሔር መንጋዎች የምእመናን በረከት ናቸው፡፡ መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ዓሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ፣ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኃይልንና
ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ የእግዚአብሔርንም መንግስት እንዲሰብኩና ደዌዎችንም እንዲፈውሱ ላካቸው፡፡ ተብሎ መጻፉን

እናውቃለንና ነው፡፡ ሉቃ፡ 9፡1-2፡፡


ካህናተ እግዚአብሔር ሰይፈ መንፈስ ቅዱስን አንግበው ቃለ ወንጌልን ተጫምተው ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ሊወጉ
የተሰለፉ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው፡፡ ካህናት፣ በእግዚአብሔር ጥበብ የሠለጠኑ ሆነው ደዌ ሥጋንና ደዌ ነፍስን
የሚፈውሱ የምዕመናን ሐኪሞች ናቸው፡፡ ወደ ዓለም የሚላኩት ካህናት ዓላማቸውን ለማስፈጸም ክህነታዊ
አገልግሎታቸውን የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ ጥበብና የውሃትን ገንዘብ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሮአቸዋል፡፡ ‹‹ወናሁ
አነ እፌንወክሙ
ከመአባግዕ ማእከለ ተኩላት፣ ኩኑ እንከ ጠቢባነ ከመአርዌ ምድር ወየዋሃነ ከመርግብ ተብሎ ተጽፏል፡፡ መቴ፡ 10፡
1፡፡ ሉቃ 10፡3፡፡
ይህን ታላቅና ከባድ ኃላፊነት የተሸከመ ካህን፣ በተኩላዎች መካከል ገብቶ፣ በጥበብና በየዋህነት እየተመራ፣
የእግዚአብሔርን መንጋ መጠበቅ
Ÿ የጠፋውን መፈለግ
Ÿ የባዘነውን መመለስ
Ÿ የደከመውን ማጽናናት
Ÿ የታመመውን ማከም
Ÿ የተሰበረውን መጠገን
Ÿ በጨለማው ዓለም የሚኖረውን ሕይወት በኢየሱስ ክርስቶስ የብርሃን ጉዳና እንዲመላለስ ማድረግ፣
Ÿ አልጫውንና መራራውን ዓለም ለውጦ ማጣፈጥ ኃላፊነቱና ተግባሩ በመሆኑ ይህን ኃላፊነት ተወጥቶ የማያልፈውን
የክብር አክሊል ለመቀዳጀት የሚያስችል ዓቅም ብቃትና ሙሉ ፍላጎት ይዞ መነሳት እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡ ሕዝ፡

34፡1-31፡፡ 1 ኛ፡ ጴጥ፡5፡2-4፡፡
Ÿ ካህን የወገኖቹን ችግር ችግሩ ኃዘናቸውንም ኃዘኑ አድርጎ ሲያዝኑ አዝኖ ሲያለቅሱ አልቅሶ ሲደሰቱ ተደስቶ በማጽናናቱ፣
በምክሩና በትምህርቱ የሻከረውን ልብ የሚያለዝብ ያዘነውንም የሚያጽናና የሥነ ልቡና መምህር ወይም ሳይኮሌጂስት

ነው፡፡ ሮሜ፡ 12፡15፡፡ መዝ፡34፡13-14፡፡


ካህን መምህረ ሕግ ወሥርዓት ከመሆኑም ሌላ ለሚጠብቀው መንጋ ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመሆኑም የሚያስበውና
የሚጨነቀው ስለሰው ልጅ መንፈሳዊ ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡ ዘእንበለ ሥጋ ኢትቀውም ነፍስ መባሉ ለእንዲያው
አይደለምና ሰው ነፍስና ሥጋውን ማኖር የሚስችለውን ጥረት ልማት እንዲያደርግ ሥጋዊና መንፈሳዊ መግባባቱን

ለማረጋገጥ ማስተማር ሓላፊነቱና ግዴታው ነው፡፡ ዘፍ፡ 2፡15፡፡ 3፡19፡፡ ኩፉ፡4፡9፡፡ 5፡7፡፡
5 13-16
ማቴ፡ ፡ ፡፡
የእውነተኛ ዕረኛ መመዘኛ ነጥቦች
የክህነት አገልግሎት ሰማያዊና ምድራዊ መግቦት ከሆነ ለዚህ ከባድ ኃላፊነት ብቁ ሆኖ ቸር ጠባቂና ታማኝ የክርስቶስ
አምባሳደር እኔ ነኝ ብሎ በልበ ሙሉነት የሚቀርቡ ሰው እሱ ማነው ቢባል ሁኔታው ከባድ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ ነገር

/
ግን ቅ ጳውሎስ በዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመሰለፍ መመኘት ከሁሉ የበለጠ መልካሙን ሥራ መመኘት መሆኑን ስለ
አንቀጸ ካህናት በጻፈው መልእክቱ፣ ‹‹እሙን ነገር ዘይፈቅድ ይሠየም ጳጳስ ሠናየ ግብረ ፈተወ፡፡›› ካለ በኋላ ለክህነት

አገልግሎት የሚሰለፍ ሰው፡ -


ዘአያደሉ ለገጽ፡፡ በፍርድ በብያኔ፣ በጸሎት፣ አይቶ የማያዳላ፡፡
Ÿ ዘኢያፈቅር ንዋየ፡፡ ኃላፊውን ነብት የማይወድ፣
Ÿ መፍቀሬ ነገድ ወዘሠናይ ምግባሩ፣
Ÿ ዘአንጽሐ ርዕሰ ጻድቅ ወኄር፣
Ÿ ዘምሁር ቃለ ሃይማኖት መምህር ወመገሥጽ በትምህርተ ሕይወት ወይዘልፎሙ ለእለ ይተዋስኡ በማለት መመዘኛዎቹን

አስቀምጦአቸዋል፡፡ 1 3 1-7
ኛ ጦሞ፡ ፡ ፡፡ ቲቶ1 5-9
፡ ፡
Ÿ የአንድ ካህን ዋና ዓላማውና ተግባሩ የወንጌል ገበሬ ሆኖ መንግስተ እግዚአብሔርን ለመስበክ መሰለፍ ነው፡፡ ስለሆነም
የሚከተሉትን መርሖች ቀዳሚና ቋሚ መርሕ አድርጎ መንቀሳቀስ፣ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

1. የወንጌል አገልግሎትን አውቆ ማሳወቅ


የወንጌል አገልጋይ፣ ሐዋርያ፣ ካህን፣ የሚል ክብር የተሰጠው ሰው፣ የወንጌልን መሠረተ ሐሳብ በሚገባ ሲያውቅ በቂ
አገልግሎት ማበርከት ይችላል፡፡ ለትምህርተ ወንጌል መስፋፋት ወሳኙ ኃይለ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኃይለ
እግዚአብሔር በሰባኪው ላይ አድሮ ሥራውን እንዲሰራ ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ከመጠየቅ ጋር ከአንድ መምህር

ወንጌል ከሚፈለጉ በርካታ ቁም ነገሮች ጥቂቶቹን ብናስታውስ፣ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡እነዚህም፡ -


የሰባኪውን ችሎታና ብቃት ማጠናከር፣
Ÿ ለመልካም ሥነ ምግባር ራስን ማስገዛት፣

Ÿ አርአያ ክህነትን ማክበር(መከተል)


Ÿ የሰማዕያንን (የተሰባክያንን) ዓቅም መመጠን፣
Ÿ ርእስን ጠብቆ ማስተማር መቻል፣
Ÿ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፣
Ÿ ምስጋናንና ተግሣጽን ለይቶ መጠቀም፣
Ÿ የሚሰጠው ትምህርት በዝግጅት ሆኖ ለሁሉም ግልጽ እንደሚሆን ማረጋገጥ፣
Ÿ ወቅትን የተከተለ ገላጭ ምሳሌን መጠቀም፣
Ÿ ቃለ ወንጌልን ከውዳሴ፣ ከንቱ፣ ከአጓጉል ነቀፋ ነፃ በሆነ መልኩ ማስተላለፍ እንጂ ጥላቻን አለመቀላቀል፣ ራስንም
አለመስበክ፣ የሚሉ ናቸው፡፡

Ÿ 2 ኛ መልካም ሥነ ምግባር፣

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣ በእያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ላይ እንዲገኝ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ከታመነበት
ይልቁንም፣ ለዚህ አብነት መሪና ፊታውራሪ ሆኖ መገኘት ያለበት መምህረ ወንጌል ነው፡፡ አንድ ሐዋርያ ወይም አንድ
ካህን አርአያነቱ ምን ያህል ለምዕመናን ጠቃሚ እንደሚሆን ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩን ጢሞቴዎስን ሲመክር
እንዲህ ብሎአል፡፡ ‹‹ከመዝ መሀር ወገሥጽ፤ ወአልቦ ዘያስተአብዳ ለውርዙትከ፤ ወኩኖሙ አርአያ ወአምሳለ
ለመሃይምናን በቃልከ፣ ወበምግባሪከ፣ በፍቅር ወበሃይማኖት ወበንጽህ፡፡ እንዋዲህ ምከር አስተምር ሕፃንነትህን
የሚንቃት አይኑር፤ በቃልህም በሥራህም ለመሃይምናን አርአያ ምሳሌ ሁናቸው፡፡

በፍቅር በሃይማኖት በንጽሕናም፡፡… ዘንተ አንብብ ወበዝ ሀሉ ከመ ይትዐወቅ ስላጤከ በኩለሄ፡፡…… . ይህን አንብብ
በዚህ
ጸንተህ ኑር፤ ፍጹምነትህ በሁሉ ይታወቅ ዘንድ፡፡ ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰማህንም ታድናለህ፡፡ 1 ኛ/ ጢሞ፡
4፡11-16፡፡ የወንጌል ዓላማዋና አገልግሎት፣ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ጨለማው ዓለም በብርሃን
እንዲመላለስ፣ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ሆኖ የእግዚአብሔርን መንግስት ወራሽነቱን እንዲያረጋግጥ ማድግ
ነው፡፡ መራራው ዓለም በቃለ ወንጌል ጣፍጦ ጣዕም እንዲኖረው ማድረግ የሚቻለው፣ በጨለማው ዓለም ብርሃን
የሚበራው፣ አልጫውን ዓለም ለማጣፈጥ የተሰጠውን ሰማያዊ ጸጋ በአግባቡ መጠቀም የሚችል ሐዋርያ ሲኖር ነው፡፡

በሰባኪውና በተሰባኪው መካከል የዓላማ አንድነት፣ መግባባትና መተማመን ሲኖር፣ የወንጌልን አገልግሎት የሰመረ
ያደርገዋል፡፡ የመምህረ ወንጌል መንገድ ቀና ከሆነ ምዕመናንም፣ ከተንኮል፣ ከቂም፣ ከበቀልና ከክፉ ነገር ሁሉ ርቀው ወደ
እግዚአብሔር በምታደርሳቸው ጎዳና የመጓዝ ዕድል ያገኛሉ፡፡ በጠባቂው በመንጋው መካከል መግባባት መደማመጥና
መተማመን ካለ ሐዋርያው፣ ነስሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት ሲል፣ ምእመናንም፣ ምንተ ንግበር ይላሉ፣ መምህረ
ወንጌሉ፣ ግብሩኬ እንከ ፍሬ ሠናየ ዘይደልወክሙ ለንስሓ ወትነሥኡ ጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ፣ ሲል ሕዝበ ክርስቲያኑም
ልባቸው ይከፈታል፡፡ ኦሆ፣ እሺ በጀ የሚለውን ቋንቋ የአፍመፈቻ ቋንቋቸው ያደርጋሉ፡፡ አንደበታቸው ለጸሎት እጃቸው
ለምጽዋት የተዘጋጀ ይሆናል፡፡ እንዲህ ሲሆንም
የወንጌል አገልግሎት የሠመረ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ግብ፡ሐዋ፡ 2፡37-40፡፡ ምዕ፡3፡19፡፡
3/ ኛ በወንጌል አገልግሎት አለማፈር
በማንኛውም ሥራ ውጤት ማስገኘት የሚቻለው አምነውበት ሲሰሩ ነው፡፡ ይልቁንም ትምህርት ወንጌል፣ ፍጹም የሆነ
መጥዎተ ርእሰን ይጠይቃል፤ ለዚሁም ቅዱስ ጳውሎስ የሚከተለውን ያስተምረናል፡፡

‹‹እስመ ኢየኃፍር ምህሮ ወንጌሉ እስመ ኃይሉ ለእግዚአብሔር ውእቱ ዘይሐይዎሙ ለእለ የአምኑ ቦቱ፡፡ ወንጌሉን
ማስተማርን አላፍርም፤ የእግዚአብሔር ኃይሉ ስለሆነ ያመኑበትን ሁሉ የሚያጽናናቸው፡፡›› ሮሜ፡1፡16፡፡

Ÿ ‹‹እስመ አኮ መንፈሰ ፍርሐት ዘወሀበነ እግዚአብሔር ዘእንበለ መንፈስ ኃይል ወንጽሕ ወተፋቅሮ ወጥበብ፡፡
እግዚአብሔር የፍርሐት መንፈስን የሰጠን አይደለም የኃይል፣ የንጽሕና የፍቅር የጥበብ መንፈስን እንጂ፡፡ እንግዲህ
ለጌታችን ስለመመስከር አትፈር፣ እኔንም እስረኛውን አታሳፍረኝ፣ በእግዚአብሔር ኃይል ለማስተማር ድከም እንጂ፡፡ ‹‹

2 ኛ/ ጢሞ፣ 1፡7-8፡፡
Ÿ 4/ ኛ የሰማዕያንን ዐቅም መመጠን
የማስተማር ዘዴ፣ ልዩ ሥልጠና የሚያስፈልገው፣ ጥልቀትና ምጥቀት ያለው ሙያ እንደሆነ ይታመንበታል፡፡ በዚህ ሙያ
የሚመደቡ መምህራንም የሥነ ልቡና ጠበብት በመባል ይታወቃሉ፡፡ ሙያቸውን በተግባር ለመተርጎም የሚጠበቅባቸው
ጥረት ልዩ ነው፡፡ ትምህርታቸውን ከሰው ኅሊና ለመቅረጽ የእያንዳንዱን ሰው ማንነት ፍላጎትና አቅም ይለካሉ፡፡ ሰውን
ወደ ትምህርት የሚያገቡት በመናገር ብቻ ሳይሆን ሰውን በመምሰል ነው፡፡ ይህንኑ ብልሃት ቅዱስ ጳውሎስም
ሲጠቀምበት እንመለከታለን፡፡

5/ ኛ የሚገባ ተግሣፅ
ብዙ ሰዎች ተግሳፅ አስፈላጊ አይደለም፣ የሚል አመለካከት አላቸው፡፡ ነገር ግን ተግሣፅና ምስጋና ጊዜያቸውን ጠብቀው
ሲነገሩ እኩል አገልግሎት አላቸው፤ምስጋና አለቦታው ገብቶ ሲነገር የሚጎዳውን ያህል ተግሣፅም አለቦታውና አለጊዜው
ሲነገር ይጎዳል፡፡ ምስጋና በሚጋባ ሲነገር የሚጠቅመውን ያህል ተግሣፅም በአግባቡ ሲነገር ጥቅሙ በእጅጉ የጎላ
ይሆናል፡፡

6/ ኛ ምእመናንን ማበረታታት
ምእመናን በሃይማኖት የጸኑ፣ በምግባር የቀኑ ይሆኑ ዘንድ በሞራል ሊገነቡ ይገባል፡፡ እንደዚህ ሲባል ግን ከላይ
እንደተጠቀሰው በእውነት ላይ የተመሰረተ ምስጋና፤ ሞራላቸውን ይገነባል ለማለት እንጂ ባልሰሩት ይመስገኑ ማለት
አይሆንም፡፡ የማይገባ ምስጋና ስድብ ነው፡፡ የሚገባ ምስጋና ግን ትልቅ ሽልማት ነው፡፡

( በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት )


* ለክህነት የማያበቁ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው ?

-
በግል ሕይወቱ ያልተመሰከረለት ፤ መንፈስ ቅዱስ ጥበብን ያልሞላበት ፣ እልከኛ የሆነ ፣ እራሱን የማይገዛ ፣ የሚሰክር ፣
አዲስ አማኝ የሆነ ፣ በማይገባ ሥራ የተሰማራ ፣ አራጣ የሚበላ ፣ በሐሰት የሚምል ፣ በጥቅምና በሌላ ሥጋዊ ነገር

በከፍተኛ ወንጀል ተከሶ በእስር ቤት የቆየ ፣ ክህነት ለመሾም በገንዘብም ሆነ በዘመድ በኃይልና ....
ወዘተ ለማሳመን
የሞከረ ። ከተጠመቀ በኋላ በዝሙት የወደቀ ፣ ከእጮኛውም ሆነ ከሌላ ሴት ጋር ከጋብቻ በፊት ሩካቤ የፈጸመ ፣

....ወዘተ ለክህነት አይበቃም ።


ብሉያትን ሐዲሳትን ያልተማረ ፣ ይልቁንም አራቱን ወንጌላዊያን ያላወቀ

/ፍት.መን.አነ. 5 ፤ 1 ጢሞ.3 : 1-7 ፤ ሐዋ 6 : 3 ፤ ጉባኤ ዘኒቂያ ቁጥር 10 ፤


ፍት.መን.አን.6 / ሌላው ተገቢ ያልሆነ ጋብቻ ለምሣል በመዘጋጃ ከሥረዓተ ቤተ-ክርስቲያን ውጪ ጋብቻውን
የፈጸመ ፤ ከአንድ ጊዜ በሌይ ያገባ ፤ የፈታች ባሏ የሞተባት ፣ በድንግልና ያልቆየች ሴትን ያገባ ፣ ዳንሰኛ ፤ ዘፋኝ የሆነች
ወይም መንፈሳዊ ሕይወትን የሚቃረኑ ሥራዎችን የምትሰራ ሴቶችን ያገባ ፣ ለክህነተ ሥልጣን አይበቃም ።

2.5.ንስሐ ምንድን ነው ?
ንስሐ '' ነስሓ '' ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ፍቺውም ሐዘን፣ጸጸት፣ ቁጭት፣ምላሽ፣ መቀጮ፣ ቅጣት

፣ቀኖና፣ የኃጢአት ካሣ ማለት ነው፡፡(ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት)፡፡ ንስሓ ማለት ተነሳሂው በሠራው ጥፋት፣
ባደረገው
ስሕተትና በፈጸመው ኃጢአት ማዘን፣ መቆርቆር፣ መጸጸት፣ ሲሰራው የነበረውን ኃጠአት መልሶ ላለመሥራት መወሰን
ማለት ነው፡፡ ንስሐ ገባ ማለት አዘነ፣ ተጸጸተ፣ተመለሰ ፣ክፉ አመሉን ተወ፣ጠባዩን ለወጠ ማለት ነው፡፡
በተጨማሪም ንስሐ ማለት የአስተሳሰብ ለውጥ ፣ ትንሳኤ ፣ የስሜት ለውጥ ተብሎ ይፈታል ። በአንድ ወቅት ፣ እለት
ሁኔታ ወይም ረዥም የዘመናችን ጉዞ ውስጥ የለመድነውን መልካም ያልሆነ ልማድ ፣ አመለካከት ፣ ስሜት ፣ ግብር ንቀን
አንቅተን ትተን ወደ ተለየ የመንፈሳዊ የሕይወት ልማድ ፣ ሥራ ፣ አስተሳሰብና ሰሜት ስንገባና ይህ ሁሉ በትህትና እና

-
በጸጸት ከምስጢረ ቤተ ክርስቲያን ጋር ሲፈጸም ንስሐ ይባላል ።

ንስሓ ሰው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርግ የእግዚአብሔር ጥሪ ነው፡፡ ይህን ጥሪ ሰምቶ የተከተለ በረከተ ሥጋ
በረከተ ነፍስን ያገኛል፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይወርሳል፡፡ ንስሓ ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡
ንስሓ ከሚደገሙት ምሥጢራትም ይመደባል፡፡ ንስሓ ምሥጢር መባሉ ኃጢአታችንን ተናዘን ቀኖናችን ሰንጨርስ
ኃጢአታችን ተደምስሶ ንጹሕ እንሆናለን፤ ይህ ሲሆን ለተነሳሂው በግዙፍ አለመታየቱ ምሥጢር ያስብለዋል፡፡

ንስሓ በሰው ሕይወት ውስጥ ሲተረጎም፡ -

1. ንስሓ ኀጢአትን ሲሠሩ ከመኖር ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር


መኖርን መመረጥ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን መምረጥ ማለት ደግሞ መንገዱን፣ ፈቃዱንና ሐሳቡንም የእግዚአብሔር
ማድረግ ማለት ነው፡፡ በእምነትና በምግባር ኖሮ የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረስ ማለት ነው፡፡ “ለእኔስ ወደ

እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፡፡“ እንዲል (መዝ፸ ፫፡፳፰)፡፡

2. ንስሓ ስላለፈው ኃጢአት ስሕተት አብዝቶ ማልቀስና የባለፈውን ኑሮ መኮነን ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ኢዩኤል
“በፍጹም ልባችሁ በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ፡፡“ የሚለው ሰው ከልቡ ሲመለስ ስለ ኀጢአቱ ያለቅሳልና ፡፡

“በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትመሰሉ፡፡“ ( ሮሜ ፲፪፡፪) የሚለውም ይህንኑ የሚያጠናክር
ነው፡፡

3. ንስሐ ከኃጠአት እንቅልፍ መንቃት ነው፡፡ ኃጢአት በመንፈሳዊ ሕይወት ማንቀላፋት ሲሆን ንስሓ ደገሞ
ከኃጠአት እንቅልፍ መንቃት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደሆነ ዘመኑን ዕወቁ“
በማለት የሮሜ ሰዎች ከኃጢአት እንቅልፍ ነቅተው ንሰሓ እንዲገቡ የሚመራ ጥሪ ነው፡፡ በኃጢአት ጠፍቶና አንቀላፍቶ
የነበረው የጠፋው ልጅም ከኃጢአት እንቅልፍ በነቃ ጊዜ ወደ አባቱ ቤት ተመልሶ ልጅ ልባል ባይገባኝም
ከባለሙያተኞች ቁጠረኝ ያለው በኃጢአት እንቅልፍ እያለ የሚያደርገውን አላወቀም ነበር ወደ ልቡ ሲመለስ ግን

አስተዋለ፤ “ወደ ልቡ ተመለሰ፡፡“ እንዲል (ሉቃ ፲፭፡፩)፡፡


4. ንሰሓ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው፡፡ ኃጠአት በነፍስ መሞት ሲሆን ንሰሓ ደግም ድኅነትን ማግኘት
ነው፡፡ “በኃጠአት ሞተን ሳለን ክርስቶስ አዳነን (ሥጋችንን ተዋሕዶ ሕያው አደረገን“ እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡(ኤፌ ፪፡

፭)፡፡ “አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስ ያበራልሃል“ ሲል የተናገረው ለዚህ ነው፡፡ “እኛ ከሞት ወደ

ሕይወት እንደተሸጋገርን እናውቃለን“ ፩ዮሐ ፫፡፲፬)፡፡ ኃጢአት ከመንፈሳዊ ሕይወት መለየት ነው፤ ንስሓ ደግሞ
የመንፈሳዊ ሕይወት ትንሣኤ ነው፡፡

5. ንሰሓ በሰው ቅን ልቡና ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ከንጹሕ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው፡፡

(ምንጭ፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ትርጉም)

ሰለ ንስሐ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ የለናል !!!


(ንስሐ_በቅዱስ_ኤፍሬም)

ወንድሞቼ ሆይ ! ጊዜ ሳለልን ንስሐ እንግባና ለንስሐ የሚገባ ፍሬ እናፍራ፡፡ ጌታችን ምን እንዳለ እስኪ አድምጡ፡-
“ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይኾናል”
/ሉቃ.15፥7/፡፡
ወንድሞቼ ሆይ ! ስለምን ታድያ በኃጢአት፣ በስንፍና፣ በንዝህላል እንደተያዘዝን እንቆያለን? ስለምንድነው ተስፋ
ቆርጠን የምንቆዝመው? በእኛ ንስሐ መግባት ምክንያት በሰማያት ታላቅ ደስታ የሚሆን ከሆነ ምንድነው

የሚያስፈራን? ቅዱሳን መላዕክት ስለ እኛ ንስሐ እጅግ ደስ የሚላቸው ከሆነ ስለምንድነው እኛ ልል ዘሊል፣ ደንታ

ቢስና ፈዛዛ የምንሆነው? የመላዕክት ጌታ ንስሐ ግቡ እያለ አስተምሮን ሳለ ምንድነው የምንፈራው? የማይከፈሉ
ሦስት፣ የማይጠቀለሉ አንድ የሚሆኑ ሥላሴ ንስሐ እንገባ ዘንድ እየጠሩን ሳለ እኛ ያለምንም የንስሐ ፍሬ እንቆይ ዘንድ

አግባብ ነውን ?

!
ተወዳጆች ሆይ በዚህ ጊዜአዊ ዓለም ርኵሰት ጣዕም አንታለል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳቱ የማይጠፋ ትሉ
የማያንቀላፋ ምረረ ገሃነም ይጠብቀናል፡፡ ስለዚህ ከዘለዓለማዊው እሳት እንድን ዘንድ አሁን ጥቂት ብናለቅስ ይሻለናል፡፡

!
ተወዳጆች ሆይ እስኪ እናስተውል፡፡ ስለምንናገረው ነገርም ችላ የሚለው ሰው ከቶ አይገኝ፡፡ ክርስቶስ ድንገት እንደ
ብርሃን ብልጭታ ይመጣልና፡፡ ክርስቶስ ድንገት በመጣ ጊዜ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦም ለሁሉም እንደየሥራው ሲከፍለው

ማየት አያስፈራምን ?
የዚያን ጊዜ ሁሉም የየራሱን ሸክም ይሸከማል፡፡እያንዳንዱ ሰው በዚህ ምድር የዘራውን
ያጭዳል፡፡ ሁሉም ዕራቆቱ ይቆማል፡፡ ሁሉም ወደ ክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ይቀርባል፡፡ የዚያን ጊዜ ማንም ማንንም
መርዳት አይችልም፡፡
ወንድም ወንድሙን ወይም ጓደኛ ጓደኛውን መርዳት አይችልም፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ልጆች
ወላጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ባሎች ሚስቶቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ሁሉም በፍርሐትና በረዐድ
በመንቀጥቀጥም የእግዚአብሔርን ፍርድ ይጠብቃል እንጂ ማንም ማንንም መርዳት አይችልም፡፡

ወንድሞቼ ሆይ ! ታድያ ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የምንሰንፈው? ለምንድነው ልል ዘሊል የምንሆነው?


ለምንድነው በምግባር በሃይማኖት የማንዘጋጀው? ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የማናስተውለው? ለምንድነው ቃለ

ሕይወትን ለመስማት የማንቻኰለው? ስለምንድነው ቃለ እግዚአብሔርን የማንሰማው? ስለምንድነው ቃለ

ክርስቶስን ችላ የምንለው? ቃሉ በዚያ ሰዓት እንደሚፈርድብን አትገነዘቡምን? ቃለ ነቢያት ቃለ ሐዋርያት በዚያ

ሰዓት እንደሚፈርድብን አታውቁምን? ካላወቃችኁ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ያላቸውን አድምጡ “የሚሰማችሁ

እኔን ይሰማል እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል” /ሉቃ.10፥16/፡፡ ዳግመኛም

በሌላ አንቀጽ እንዲህ ብሏል፡- “የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው ርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርኩት ቃል

ርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል” /ዮሐ.12፥48/፡፡ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድብን ቃሉስ የትኛው

ነው? በወንጌሉ እንዲሁም በሐዋርያትና በነቢያት አድሮ የተናገረው ቃሉ፡፡ እንኪያስ ወንድሞቼ ሆይ! ቃሉን ችላ

የምንለው አንኹን፡፡ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም” ያለውን አንርሳው /


ማቴ .24፥35/፡፡
እንኪያስ እጅግ የምወዳችሁ ሆይ ! ኑ! አስፈሪው ቀን ሳይመጣ ቃሉን ሰምተን ንስሐ እንግባ፡፡ የእግዚአብሔርን
ምሕረት እንቀበል፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ ምሕረቱን እንድንቀበል እንዲህ እያለ ያበረታታናልና፡- “እናንተ ደካሞች

ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ” ማቴ.11፡28፡፡ በዚህ ቃሉ ትዕግሥተኛው፣


አፍቃሪውና ሰው ወዳጁ ጌታ ሁላችንም እንድን ዘንድ ይጠራናል፡፡ የጠራው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ

.“
አይደለም፤ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ” ብሎ ሁላችንም እንጂ፡፡ “ባለጸጋም ቢሆን ድኻም ቢሆን ሁሉም ወደ እኔ
ይምጣ፡፡ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፡፡ ወደ እኔ የሚመጣውስ ማን ነው ትዕዛዛቴን
የሚጠብቀው፤ ቃሌን የሚሰማው፤ በላከኝም የሚያምነው፡፡” የክርስቶስን ቃል ሰምቶ ንስሐ የሚገባው ንስሐም ገብቶ
የንስሐን ፍሬ የሚያፈራ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ የማይሰማው ግን እጅግ ጐስቋላ ሰው ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ

እንደተጻፈ፡ - “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው” /ዕብ.10፥31/፡፡


2.6. ንስሐ መቼ ተጀመረ ?
ደመና ከምድር በርኅቀት ላይ ሆኖ ፀሐይ የሚወጣበትን ሰማይ ጋርዶ እንደሚታይ ፀሐይ ጽድቅ ዘበአማን የተባለ እየሱስ
ክርስቶስን የምታወጣ ዳግሚት ሰማይ እመቤታችን ድንግል ማርያም በዘመን ርኅቀት በምስጢር ርቀት ተሸፍና ኖራለች ።
በአበው ልቡና ፣ በትውልድ የዘር ገንዳ ላይ ኮለል ብላ ከአንዱ ወደ አንዱ እየተቀዳች እስከ ዘመነ ካህናት ደረሳ
በአራተኛው
( )
ዘመን በዘመነ ካህናት ሶልያና ጨረቃ የተባለች እርሷ አስቀድማ ተገልጣ በኋላ አማናዊውን ብርሃን ኢየሱስ
ክርስቶስ ወልዳልናለች ።
ንስሐም እንደ እመቤታችን ለድኅነተ አዳም ብቻ ሳይሆን ለፍጥረተ አዳምም ምክንያት ናት ። እግዚአብሔር
አምላክ የአዳምን ግብር እና መጻኢ ዕድል እንዲሁም የዲያብሎስን ተንኮል እና ጥፋት አዳም ገና ከመፈጠሩ በፊት
በአምላክነቱ ያውቀው ነበር ። አስቀድሞ በማወቁም ዲያብሎስ ቢበድል ንስሐ እንደሚገባ አውቆ ርስቲ የሆነች የገነትንና
የዕፀ ሕይወትን ጎዳናዎች በእጃቸው ውስጥ የምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍ በያዙ በሱራፌል እንዳስጠበቀለት ሊቀ ነቢያት
ሙሴ ጽፎልናል ። ስለዚህ እግዚአብሔር ለአዳም መዳኛ የሆኑ ሁለቱን ምክንያቶች ድንግል ማርያምን እና ንስሐን
ባያዘጋጅለት አስቀድሞም አይፈጥረውም ነበር ።
አሞኒዎስ እና አውሳብዮስ የተባሉት ሊቃውንት በቅድመ ወንጌል ላይ ሲያብራሩ ፤ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን
ሰለሁለት ምክንያቶች ከፍዳው ሊያድነው ወደደ ። አንደኛው ምክንያቱ አዳም አላበጀሁም አጠፋሁ እያለ ኃጢአቱን
አውቆ እግዚአብሔርንም እንደበደለ ተረድቶ እግዚአብሔር ኃጢአቱን ይቅር እንዲለው ወዶ በገነት የነበረውን ተድላ

ደስታውን በመዘንጋት ስለኃጢአቱ እና በደሉ እየተጨነቀ በማልቀሱ (ንስሐ ገንዘብ በማድረጉ) እንደሆነ መስክረዋል

/
ቅ አትናቴዎስም በቅዳሴው ፤ አዳምና ሔዋን ሆይ እናንተስ ይቅር ባይ በሆነ በጌታ ተግሳጽ ንስሐ
ገብታችኋል ፣ አዳምና
ሔዋን ሆይ በእውነት ድናችኋል ፣ በተቤዣችሁ በጌታ ደም ያለመከልከል ወደ ቀደመ ርስታችሁ ገብታችኋል በማለት
በአዳምና በሔዋን ድኅነት ውስጥ ንስሐ አንዷ መንገድ እንደነበረች ገልጦልናል ። በአዳም ኃጢአት ዓለሙ በሙሉ
እንደተጎሳቆለ በንስሐውም እርሱ ብቻ ሣይሆን ዓለሙን በሙሉ አዳነ ። ክርስቶስ ሰው የሆነው የአዳምን ንስሐ ተቀብሎ
ነውና ። አዳም እንደ ዲያብሎስ ልቡን ቢያደነድን እኛም ዘለዓለም በመከራና በሥቃይ መኖር ዕጣ ፈንታችን ይሆን ነበር

2.7 የንስሐ ጥቅም


በ 40 እና በ 80 ቀን ተጠምቀን ሀብተ ወልድ እና ስመ ክርስትና ላገኘን የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ
ከጥምቀት በማስከተል የተሰጠችን መንፈሳዊ ሀብታችን ናት ። እርሷም የእግዚአብሔርን ቸርነት ለሚሹ ሁሉ የተከፈተች
የይቅርታ በር ናት ። በእርሷም በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርብባታለን ።

( )
በኃጢአት ለተጎዱ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ደዌ ነፍስን ቁስለ ነፍስን የሚፈውስ ሥልጣነ ክህነት ባለው መንፈሳዊ
ሀኪም ካህን የሚፈጸም የኃጢአት ማስተሰረያ መንፈሳዊመድኃኒት ነው። ንስሐ ከሠሩት ኃጢአት አንጽታ ከእግዚአብሔር
በማስታረቅ ከዘላለማዊ ፍርድ የምታድን ፣ ዘማዊውን እንደ ድንግል ፣ ሌባ ቀማኛውን እንደ መጽዋች የምታደርግ
ምስጢር ነች ።

2.8 የነፍስ አባት እዴት ይያዛል


ምዕመናን መምህረ ንስሐ ይሆናቸው ዘንድ ካህን የሚመርጡበት መስፈርት የካህኑ ሃይማኖት የቀና መሆኑን እና
-
ቤተ ክርስቲያን የምታውቀው በአገልግሎት ላይ ያለ ካህን መሆኑን ነው ። እንዲሁም በሚገባ ክትትል ማድረግ የሚችል

መሆኑን አስቀድሞ የማጣራት መብት አላቸው ። ነገር ግን ''የእገሌ ምግባሩ እንዲህ ነው '' እያሉ በማይመለከታቸው
ጉዳይ ሊገቡ አይገባም ።

ተነሳሒ ( ንስሐ የሚገባ ሰው) መምህረ ንስሐው በምግባር በመንፈሳዊ እውቀትና በመሣሰሉት ሁሉ
ፍጹም እንዲሆን መጠበቅ የለበትም ። ምንም ክህን ቢሆን ሰው ነውና ድክመት አያጣውም ። አንደኛ ሁሉነ ነገር
ለማወቅ እና ለመማር ዕድሜውም አይበቃውም ። ሁለተኛ ደግሞ ብዙ የተማረ ቢሆንም እንኳን ሰው እንደመሆኑ

እውቀት ሊከፈልበት ( )
ሊዘነጋው ይችላል ። ስለዚህ ተነሳሒው ከካህኑ ሁሉንም ነገር ካላገኘሁ ማለት የለበትም ።
በየጊዜው የሚኖረውን ጥያቄ ደግሞ የመምህረ ንስሐውን የእውቀት ደረጃ እያገናዘበ ሊጠይቅ ይችላል ። ምን አልባት

-
የምናነሳው ጥያቄ በመምህረ ንስሐችን የማይመለስ ቢሆነ እንኳን ሌሎች መምህራነ ቤተ ክርስቲያንን የመጠየቅ መብት

''
አለን ። ለጠየቅሁት ነገር ሁሉ መልስ ሊሰጠኝ አልቻለምና መምህረ ንስሐ ሊሆነኝ አይችልም ''
ማለት ተገቢ
አይደለም ። እንዲሁም ደግሞ ተነሳሒው ሌሎች መምህራንን መጠየቅ ይችላል ማለት ከሌሎች እየጠየቀ መምህረ
ንስሐውን መፈታተን የበላይ ለመምሰል መሞከር ማለትም አይደለም ። እንዲህ የሚያደርግ ሰው ምንም ያህል ቢያውቅ

''ልጅ ቢሮጥ አባቱን አይቀድምም'' እንዲሉ በካህኑ ካለች ጸጋ እግዚአብሔር እና ልዕልት ሥልጣን ሊቀድም
እንደማይችል ማወቅ አለበት ።
ተነሳሒያን ምንአልባት ከመምህረ ንስሐቸው በጎ አቀባበልና አቀራረብ ባይገጥማቸው እንኳ ተስፋ መቁረጥ
የለባቸውም ። ምክንያቱም መምህረ ንስሐው ይህን የሚያደርግበትም ምክንያት ሊኖረው ይችላል ። ባይኖረውም ግን
መታገስ ይገባል ። ስለዚህ ተነሳሒው የካህኑን ቁጣና ሌላም ነገር ሁሉ እንደ ቀኖና ቆጥሮ የሥራዬ ዋጋ ነው ብሎ ታግሶ
ሥርየትን ማግኘት ይኖርበታል ። ብዙ ጊዜን በኃጢአት አሳልፎ እግዚአብሔር ታግሶ ለንስሐ ያደረሰው ሆኖ ሳለ ዛሬ

''
በንስሐ ወቅት የሚገጥመው እክል ለመታገስ ፈቃደኛ ካልሆነ የበደለኛ ጥጋበኛ ''
መሆኑ ነው ። በንስሐ ወቅት
የሚገጥሙ ሀሰናክሎች በትዕግስት ማለፍ አለመቻል ለዲያብሎስ መሸነፍ ነው ። እርሱ ተነሳሒያንን በተለያዩ ምክንያቶች
ከንስሐ ለማራቅ ይፈልጋልና ።

መምህረ ንስሐ እንዴት መለወጥ ይቻላል ?

- /
በሥረዓተ ቤተ ክርስቲያን መምህረ ንስሐን ለመለወጥ የሚያስችሉ የሚፈቀድባቸው / ሁለት ምክንያቶች አሉ ።
እነዚህም :-

1- መምህረ ንስሐው በሞት የተለየ እንደሆነ ነው ። ይህም ምንም ሥልጣኑ የማትሞት ብትሆንም ከሞት ወዲያ
ቀኖና መስጠትም ሆነ ክትትል ማድረግ አይቻለውምና ነው ።

2- በካህኑ ሕጸጸ ሃይማኖት (የሃይማኖት ጉድለት) ወይም ክህደት የተገኘበት እንደሆነ ነው ። ኑፋቄ እና ባዕድ
አምልኮ ያለበት ካህን የምግባር ሳይሆን የሃይማኖት ችግር አለበትና
እንዲህ ያለው ሰው እንኳንስ ክህነቱ ምዕመንነቱም ፈርሷልና አባት ሊሆን አይችልም ። ጌታችንም በወንጌል በምስጢር

''ለጣዖት ስገዱ የሚል አባት አይኑራችሁ , ማቴ. 23 : 9 ትርጓሜ '' ብሏልና ። ከመቀራረብ የተነሳ
'' ከርሳቸው ከምለይ'' ብሎ ቢሄድ ግን ሐሰተኛ አባት አልጣ ብሎ ሃይማኖቱን ያጣል ። ጌታችንም በቃሉ ''
አባቱንና እናቱን ያልተወ ሊከተለኝ አይችልም '' ያለው እንደዚህ ላለውም ነው ።

** በተለያዩ ማኅበራዊ ምክንያቶች ተነሳሒው ከመምህረ ንስሐው ጋር መገናኘት የማይችልበት ነገር ቢፈጠር
በቅርብ በሚገኝ ካህን ለጊዜው ''እንደ ሞግዚት አባት '' አድርጎ በመቅረብ ኑዛዜን መፈጸምና ሥጋ ወደሙን መቀበል
ይችላል ። ይህ ማለት ግን ንሰሐ አባት ለውጧል ማለት አይደለም ።
አንዳንዴ ንስሐ አባትን ለመለወጥ መፈለግ መንፈሳዊ እንክብካቤን ከማጣት ብቻም ላይሆን ይችላል ። አንዳንዶች

በኃጢአታቸው በመሰቀቅ ትዝብት ፍራቻም ''


ታጥቦ ጭቃ ''ላለመባል ሲሉ መምህረ ንስሐን ሊለውጡ ይችላሉ ፤
ይህም ሁሉን የሚያይ ፈጣሪን ከመፍራት ይልቅ ለይሉኝታ ቦታን መስጠት ነው ። የንስሐ አባትን መቀያየር በምዕመኑ
መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ዝግመትን ያመጣል ። ከሐኪም ሐኪም የሚቀያይር ሕመምተኛ እንደማይጠቀም መምህረ

''
ንስሐን የሚለዋውጥም እንዲሁ ነው ። ፊቱ ጠቆረ ቃሉ ሻከረ ፤ ይህ ይጎድለዋል ይህ ነሣኝ''
እያለና እያማረጠ
መምህረ ንስሐን የሚለዋውጥ ሰው ትዕግስት ኖሮት ዕድሜውን ሙሉ ቢፈልግ እንኳ እርሱ እንደሚፈልገው ዓይነት
የንስሐ አባት አያገኝም ።
ምክንያቱም እግዚአብሔር መርጦ የሾመውን ሲያቃልሉበት አይወድምና ነው ። መምህረ ንስሐ ለመለወጥ ቢሆን እንኳን
ለካህኑ ከነ ምክንያቱ ማሳወቅ ያስፈልጋል ።

2.9.ንስሐ ለመግባት ምን ያስፈልጋል


መፀፀት
Ÿ አንድ ክርስቲያን በድፍረትም ይሁን በስህተት “የሠራው በደል” መጻሕፍት በማንበብ ፣ ከመምህራን ተምሮ ፣ የስብከት
ካሴት አዳምጦ ፤ ህሊናው ወቅሶት ፣ ወይም በሌላ በአንድ ምክንያት ስህተት መሆኑን ከተረዳ በኋላ ተፀፅቶ ከእግዚ

( )
አብሔር ለመታረቅ በደሉን ለማስተስረይ የሚያደርገው ጉዞ ንስሐ ይባላል ። በሠራው በደል ሳይፀፀት ፤ ለጊዜው
ህሊናውን ስለረበሸው ብቻ ንስሐ የሚገባ ሰው ፤ ከስሐውን በኋላ ወደ ቀደመ ሕይወቱ ሊመለስ ይችላል ። ምክንያቱም ፡
ንስሐ የገባው ፡ በሠራው በደል ከልቡ ተፀፅቶ ሳይሆን ፤ በስሜት ተነሳስቶ ነውና ፤
ኃጢአትን መጥላት
Ÿ በበደላችን ከተፀፅትን በኋላ የሰራነውን በደል መጥላትና ወደፊትም መሥራት እንደሌለብን ራሳችንን ማሳመንና ከኃጢዓት
መንገድ መራቅ ማለት ነው ።
ከንስሐ በኋላ ስላለው ሕይወት መወሰን
Ÿ አንድ ምዕመን ንስሐ ከመግባቱ በፊት ለወደፊቱ የሚኖረውን ሕይወት አስቀ ድሞ መመርመርና መወሰን ይገባዋል

2 37
የእግዚአብሔን ቃል ስንሰማ ለጊዜው ልባችን ሊነካ ፣ ምን እናድርግ ልንል እንችላለን ። የሐ ሥ ፥ ። ነገር
ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዓለሙን ወደመምሰል እንደማንመለስ አስቀድመን ራሳችንን መመርመር አለብን ። ብዙዎቹ
በስሜት ወደ ክርስትና ከገቡ በኋላ ፤ በጊዜያዊ
ነገር ተታለው በድንገት ከሃይማኖት መንገድ ወጥተዋልና ።
አንድ ምዕመን ካለፈ በደሉ በንስሐ ታጥቦ በአዲስ ሕይወት ራሱን ለማስተካከልና ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ከወሰነ
በኋላ የንስሐ አባት ሊኖረው ይገባል ። ጌታችን “ካህናትን” ራሱን ወክለው መንጋውን እንዲጠብቁ “በምድር ያሰራችሁት

( 8 ፥ ዮሐ 21 ፥ 15 ። ማቴ 16
በሰማይ የታሰረ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሁን” ማቴ

፥19) በማለት መንጋውን እንዲጠብቁ ሾሟቸዋልና። አንድ ክርስቲያን በሕይወት ሲኖር ፤ የእግዚአብሔርን
መንገድ የሚመራው ፤ ሲሳሳት ንስሐውን ተቀ ብሎ ቀኖና በመስጠት ከእግዚአብሔር የሚያስታርቀው የንስሐ አባት
የግድ ሊኖረው ይገባል።
ንስሐ የሚገባው ምዕመን በካህኑ ፊት በሚቀርብበት ጊዜ የሚከተሉትን ማሟላት አለበት
የሠራውን ስህተት በሙሉ ማስታወስ
Ÿ ቀኖናው የሚሰጠው እንደ በደሉ ዓይነት ስለሆነ የሠራውን ማስታወስ አለበት ፤ በቃሉ የሚረሳው ከሆነም በጽሁፍ
መመዝገብ ያስልጋል ።

(
ሳይቀንሱ ሳይከፍሉ ) በሙሉ መናገር
Ÿ “ይህን ብናገር ሰው ምን ይለኛል ?” ብሎ ከባዱን (የሚያሳፍረውን) ነገር መደበቅ የለበትም። ሲሰራው
ያላሳፈረውን ሲናገረው ሊያፍርበት አይገባም። አንድ ጊዜ ተናግሮ ከህሊናው ካላስወጣው ሁሌም ሲረብ ሸው ይኖራልና።

“እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ ሸክማችሁን አራግፋለሁ” ማቴ 11 ፥ 28


ተብሏልና በትክክል አስታውሶ መናዘዝና የኃጢአትን ሸክም ማራገፍ ይገባል። ስለ በደላችን በምንናዘዝበት ጊዜ ግን ፤
ከዕገሌ ጋር ፤ በዚህ ጊዜ ፤ በዚህ ቦታ ፤ ይህን አድርጌያለሁ እያልን ፤ ቦታውን ፤
ጊዜውን የሌላ ሰው ስም በዝርዝር እንድንናገር አንገደድም ፣ የሠራነውን በደል ብቻ “ጣዖት አምልኬያለሁ ፤ ሠርቄያለሁ
፤ አመንዝሬያለሁ” በማለት በጥቅሉ መናገር እንችላለን ።

(
ኑዛዜ ራስን መክሰስ )
Ÿ በራሳችን ድካም የሠራነውን በደል “ዕገሌ አሳስቶኝ” እያሉ ሌላውን ሰው ስለ እኛ ስህተት ተጠያቂ ማድረግ ሳይሆን ፣
አንደበታችንን ከሳሽ ህሊናችን ምስክር አድርገን በመጨከን ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት መክሰስ ነው ። አምላካችን
የልባችንን መመለስ ፣ አይቶ የሰራነውን በደል ሁሉ እንዳልተሠራ አድርጎ ያነጻናል ። በደልን በንስሐ ይቅር ማለት
የእግዚአብሔር የቸርነት ሥራ ነውና።

አንድ ምዕመን ንስሐ ከገባ በኋላ የሚከተሉትን በቅደም ተከተል ማድረግ አለበት ?
የተቀበለውን ቀኖና በትክክል መፈጸም

Ÿ ቀኖና የግሪክ ቃል ሲሆን : መለኪያ ማለት ነው ። ካህኑ ለበደለው ምዕመን እንደ ሃይማኖቱ ጽናት ፣ እንደ አእምሮው
ስፋት ፤ የሠራውን በደል መጥኖ ቀኖና ከሰጠው በኋላ እንደታዘዘው መፈጸም አለበት ። የነነዌ ሰዎች ፣ ት. ዮና 3

፥1 ። ንጉሡ ህዝቅያስ ፣ ኢሳ 38 ፥ 1 ። ቅዱስ ጴጥሮስ ሉቃ 22 ፥ 54 ። እና ሌሎችም ይቅርታን


ያገኙት ፤ በበደላቸው ተጸጽተው በማልቀሳቸውና ንስሃ በመግባታቸው ነው ። በንስሐ ወቅት ፡መሬት ላይ መተኛት
ምግብ መቀነስ ፣ ከዓለማዊ ነገሮችና ለመንፈሳዊ ሕይወት ከማይመቹ ጓደኞች መራቅ ያስፈልጋል ። በንስሐ ጊዜ
እንዳናደርግ ከታዘዝነው ነገር ራሳችንን በመግዛት መቆጠብ አለብን ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ ወደ ድኅነት ከጠራን በኋላ

እንደገና ተመልሰን ወደተውነው ድካማችን መመለስ የለብንም። የጊዜውን ሳይሆን የመጨረሻውን ማሰብ አለብን ። 2
ጢሞ 4 10 ፥ ። መዝ6 6 ፥ ።
በደላችን በንስሐ እንደሚሰረይልን ማመን
Ÿ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው በደላችንን ለመደምሰስ ስለሆነ ከበደላችን ሊያነጻን የታመነ አምላክ ነው ። ከሠራነው ብዙ
ኃጢአት አንጻር የሚሰጠን ቀኖና ትንሽ መስሎ ቢታየንም ። ማሰብ ያለብን የራሳችንን በደል ሳይሆን የእግዚአብሔርን
ቸርነት ነው ። ከእኛ በደል የእግዚአብሔር የቸርነት ሥራው እጅግ ይበልጣልና የታዘዝነውን ፈጽመን የቀረውን
እንደቸርነትህ ማለት ይገባል ። “የታዘዛችሁትን ባደረጋችሁ ጊዜ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ” ተብለናልና ። ሉቃ

17 ፥ 10 ።
(
በሥጋውና በደሙ መታተም መቁረብ )
Ÿ አንድ የተራበ ሰው እጁን ስለታጠበ ብቻ አይጠግብም ። የግድ ምግብ መብላት አለበት ። ንስሐ ማለት መታጠብ ፣

(
ከእድፍ ከኃጢአት ) መንጻት ማለት ሲሆን ፤ ድኅነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት የሚሰጠውን ቅዱስ ሥጋውንና
ክቡር ደሙን በመቀበል ነው ። ዮሐ 6፥33 ። ብዙዎቹ መቁረብን እንደ ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ

(ለሽማግሌ ብቻ) አድርገው ስለሚቆጥሩት ለመቀበል ሲዘጋጁ አይታዩም ። ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ
ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል ። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና ።
ሁሌም ለንስሐ መዘጋጀት
Ÿ ንስሐ ከገባንና ከቆርብን በኋላ እንደገና በኃጢአት ልንወድቅ እንችላለን። አምለካችን “ለምን ንስሐ አልገባህም እንጅ

ለምን ኃጢአት ሠራህ ? አይልምና” ሁለተኛ ስንበድል ሀፍረት ሳይሰማንና ከኃጢአት መላቀቅ ካልቻልሁ በየጊዜው
የንስሐ አባቴን ከማስቸግር
አርፌ ብቀመጥ ይሻለኛል በማለት ፡ ሁሉንም እርግፍ አድርገን እንድተወው ፡ ክፉ ሀሳብ በአምሯችን ሊፈታተነን ይችላል

ነገር ግን ከንስሐ በኋላ እንደ መላእክት በቅድስና ብቻ እንኖራለን ማለት ሳይሆን “ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል ፤ ሰባት

ጊዜ ይነሳል” ምሳ24፥ 16 ። እንደተባለ ፡ አምላካችን ብንወድቅ ሊያነሳን ፤ ብንጠፋ ሊፈልገን ፤ ብንርቅ


ሊያቀርበን ፤ በኃጢአት ብንረክስ ሊቀድሰን (እንደ ባዘቶ ሊያጠራን) የታመነ አምላክ ስለሆነ ተስፋ ሳንቆርጥ ፤

በኃጢአታችን ሳንደበቅ ፤ ዘወትር ለንስሓ መዘጋጀት አለብን። ኢሳ 1 ፥ 18 ።

2.10 በንስሐ ጊዜ የካህናት ድርሻ


( )
ካህን ቄስ እግዚአብሔር በሰጠው ሥልጣነ ክህነት በራሱ ዘመን በትጋት አምላኩን አገልግሎ ማለፍ
ይገባዋል።ለልጆቹ ትምህርተ ወንጌልን በማስተማር ፣የተጣሉትን፣ በማስታረቅ ፣ከእግዚአብሔር የራቁትን ወደ

(
እግዚአብሔር በማቅረብ ለሰማያዊ ሽልማት አክሊል ) መትጋት፣የነፍስ ልጆቹን በአንድነት እና በተናጠል በወንጌል
( )
ትምህርት ማነጽ ማሳደግ አለበት።
የሀጢአት እስረኛ የሆነውን ሰው በተሰጣቸው መንፈሳዊ አደራ ከታሰረበት የሀጢአት እስራት ነፃ ለማውጣት መንፈሳዊ

ግዴታቸው መሆኑ ይታወቃል።በኃጢአት ምክኒያት ተስፋ የቆረጡ ቢኖሩ እንኳ <<አፅናኑ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል
አምላካችሁ >> 40 1
ኢሳ ፥
ተስፋቸው እንዳልተሟጠጠ በመግለፅ በንስሐ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ ማስተማር መጋበዝ የካህናት ትልቁ ድርሻ
ነው።
ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው መለኮታዊ አደራም ይኸው ነው ።

<<ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን የዮና ልጅ ስምኦን ሆይ ትወደኛለህን አለው >>


<<አዎ ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ >> ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስም መለሰለት <<ጠቦቶቼን ጠብቅ
በጎቼን አሰማራ>>የተሰጠው አደራ ጠቦቶቹንና በጎቹን እዲጠብቅ ነው።በጎች የባሉት ምዕመናን ጠቦቶች የተባሉት
ደግሞ የበግ ግልገሎች ወይም ከልጅ እሰሸከ ወጣት ያሉት ክርስቲያኖች መሆናቸው ይታወቃል።ጥበቃውም ከኃሰተኞች
መምህራን ሲሆን በቃሉ በኩል ነፍስን ከዘላለም ሞት መታደግ ከሥጋ ሥራ ተላቀው መንፈሳዊ ፍሬ እንዲኖራቸው
ማድረግ ነው።

ጌታችን መምህር ተብሎ መምህራን ፣ሊቀ ካህናት ተብሎ ካህናት፣እረኛ ተብሎ እረኞች የመባልን እድል መመረጥ ያገኙ
አባቶች ካህናት ናቸው።

<<የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሀለው በምድርም የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል


በምድርም ምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል>>

ማቴ 16፥19
ይህችን የቀደመችውን የህይወት መንገድ ከጥፋት መንገድ ለይቶ ማሳየት የተሻለ ትውልድ ለመተካት መጣር የነፍስ
አባቶች ሰማያዊ አደራ በመሆኑ ለትንሽ ጊዜ እንኳ ሊዘነጋ የማይገባው ነው ። ምዕመኑ ሀገሩንና ሃይማኖቱን አፍቃሪ
ብሎም ተቆርቋሪና ታማኝ ሆኖ እንዲያድግ የአባቶች ሚና በሁሉም እረገድ ወሳኝ ነው።

<<እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ


መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርሷ ላይ ሂዱ ለነፍሳቹሁ እረፍት ታገኛላችሁ>>ኤር 6፥16
የቀደመችውን መንገድ መከተል በእርሷም መሄድ እረፍትና ሰላምን በህይወት መኖርን ያስገኛል።በታሪኳ ክፉም በጎም
እየተፈራረቁባት በሀይማኖት አባቶች መንፈሳዊ ትምህርት እገዛ ጭምር መሆኑ ግልፅ ነው። ዛሬም
ሀገሩን፣ታሪኩን፣ሃይማኖቱን የሚጠብቅ በመልካም ሥነምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት የሃይማኖት አባቶች

(ካህናት) ሀላፊነት ግንባር ቀደም ሊሆን ይገባል።

2.11 በንስሐ ጊዜ የምእመናን ድርሻ እና ቀኖናዎች


አንድም ምዕመን ከነፍስ አባቱ (ከካህናቱ)ዘንድ የሚነገረውን ትምህርትም ሆነ ምክር መቀበልና መተግበር

አለበት።<<በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል>>ዩሐ 10፥3

እውነተኛ ምዕመን (የንስሐ ልጆች) የንስሐ አባቶቻቸው (ካህናት)የሚሉአቸውን በማስተዋልና በልበ ሰፊነት
ማዳመጥ መተግበር ይጠበቅባቸዋል።
እንግዲህ ንስሓ ገብተን፣ የኃጢአትን ሥርየት አግኝተን፣ ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን በጽድቅ ጎዳና ለመራመድና
በደኅንነት ጸጋ ለመኖር እንድንችል ቢያንስ ሦስት ነገሮችን መፈጸም አለብን።

የመጀመሪያው የንስሓ ኀዘን ወይም እውነተኛና ልባዊ የሆነ ጸጸት ሲሆን ይህም ስለ ክፉ ሥራችን ነው፤ ስለ መተላለፋችን
የምንጸጸትበትና በደላችንን የምናምንበት ነው። መበደላችንንና መተላለፋችንን ሳናምንና ጥፋተኝነታችንን ሳንቀበል ወደ
ሚቀጥለው የንስሓ ሥርዓት ልንደርስ አንችልም።

ሁለተኛው ኑዛዜ ሲሆን የበደልነውን በደልና ክፉ ሥራችንን ሁሉ ካህኑን


ምስክር አድርገን በእግዚአብሔር ዳኝነት ፊት የምንናዘዝበትና ራሳችንን ጥፋተኛ አድርገን የምንቀርብበት መንገድ ነው።

ሦስተኛው ደግሞ ስለ ኃጢአታችን የሚሰጠንን የንስሓ ቅጣት የሚመለከት ሲሆን የሚሰጠንን ቀኖና (ሥርዓት)
( )
መፈጸምና ከዚህ በኋላ በካህኑ በኩል የምናገኘው የፍትሐት ከኃጢአት እሥራት የመፈታት ጸጋ ነው። እግዚአብሔር
ኃጢአታችንን ይቅር እንደሚለንና ምሕረትን እንደምንቀበል ማመናችን የተሰጠንን ቀኖና በመንፈሳዊ ታማኝነትና
በእምነት በመፈጸማችን ይታወቃል።

ምእመናን በንስሓ አባታችን ዘንድ የንስሓ ልጆች እንደመሆናችን ከላይ የተመለከትናቸውን ሦስቱን ነገሮች በአግባቡ
ልንፈጽምና በሥርዓቱ ልንመላለስ ይገባል፤ እንዲሁም አንድ ሕፃን በአባቱ ፊት እንደማያፍርና እንደማይሽኮረመም

( )
ይልቅስ የሚፈልገውን ሁሉ በግልጽ እንዲናገር እኛም ለአባታችን አበ ነፍስ በደላችንን በእምነትና በነጻነት መናገር
መቻል አለብን። ነገር ግን ንስሓችንን በግልጽ ባንናገር ብንደብቅ እንደ ሐናንያና እንደ ሰጲራ እግዚአብሔርን መዋሸት
ይሆንብናል፤ ስለዚህ ሳንደብቅ ሳናስቀር መናዘዝ መቻል አለብን፤ እንዲሁም፦
የተሰጠውን ቀኖና በአግባቡ መፈጸም አለብን፤ ተነሣሒውም የተማረ እንደሆነ ቄሱ ንስሓውን ቢያሳንስለት የንስሓዬን ልክ
እኔ አውቀዋለሁ ብሎ አይጨምር። ቄሱ ከሰጠኝ ጥቂት ቢሆን እኔ ምን ዕዳዬ አይበል። የኃጢአቴን ብዛት እኔ
አውቀዋለሁ ጨምርልኝ አይበል፤ ወደ እግዚአብሔር ንስሓዬን ሳላደርስ አትግደለኝ እያለ ያመለክት እንጂ።
Ÿ ንስሓ ሲገቡ ቄስ ያዘዘውን ማድረግ ይገባል፤ ቄስ ካዘዘው ግን መውጣት አይገባም። አስቀድሞ ሲናገር ምክንያት

( )
አለመስጠት፣ ከኃጢአት አለመክፈል አለማስቀረት ፣ የሰጠውን ማድረስ ከሰጠው አለማስቀረት አለመጨመር
ይገባል።
Ÿ በጊዜው ሁሉ ያጋጠመውን ሥጋዊም ይሁን መንፈሳዊ ችግር ለንስሓ አባት ማካፈልና መፍትሔ ማግኘት ይገባል።
Ÿ ስለ ሠራው ኃጢአት ንስሓ ለመግባት ነገ ዛሬ ያለማለት መብትም ኃላፊነትም አለበት ‹‹ተቆጡ አትበድሉም ፀሐይ

( . )
ሳይጠልቅም ቁጣችሁን አብርዱ ለሰይጣንም መንገድን አትስጡት›› ተብሎአልና። ኤፌ ፬፥፳፯
Ÿ የንስሓ አባቱን ክብር የመጠበቅ ይህም ማለት ሲመጣ መነሣት ሲሄድ የመሸኘት ነው። የንስሓ ልጅ ይህንና የመሰለውን
በተግባር የመፈጸም ኃላፊነት አለበት። ‹‹ለመምህራኖቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸው፤ ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ
የሚሰጡ እንደ መሆናቸው ይህን ሳያዝኑ ደስ ብሎአቸው ያደርጉት ዘንድ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉና›› እንደተባለ መምህረ

( . )
ንስሓው ለእርሱ ነፍስ የሚጨነቀውን ያህል ልጁም ስለ መምህረ ንስሓው የሚያስብ ሊሆን ይገባል። ዕብ ፲፫፥፲፯
Ÿ በዚህም መሠረት አንድ ምእመን ንስሓውን “እግዚአብሔርን በደልኩ፤ አሳዘንኩት” በሚል ጽኑ በሆነ ኀዘንና ቁጭት

( )
ለካህን ለንስሓ አባት ይነግረዋል፤ መምህረ ንስሓውም የተነሳሒውን አቅም መዝኖ የጾም፣ የጸሎት፣ የስግደት፣
የምጽዋት ቅጣት ይሰጠዋል። ለዚህም ጊዜ ይወሰንለታል። የቀኖና ጊዜውን ከጨረሰ በኋላ ተነሳሒው ወደ መምህረ
ንስሓው ተመልሶ እንደ ትእዛዙ
መፈጸሙን ይነግረዋል። ቄሱም ፍትሐት ሰጥቶ ሥጋውን ደሙን አቀብሎ ከምእመናን ጋር እንዲቀላቀል ይፈቅድለታል።

(ኅብረ ሥርዓት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊት በመምህር አብርሃም አረጋ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ካህናት
ክንፈ ገብርኤል አልታየ፣ መጽሐፈ ምዕዳን በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን፣ ዓምደ ሃይማኖት)

2.12 የንስሐ አባትና ልጅ ግንኙነት ምን ይመስላል ?


የንስሐ አባቶችን ሚና የሚያወሱና አገልግሎታቸውን የሚዘረዝሩ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በተለይ ካህናት
ምእመናንን የመጠበቅ የእረኝነት ተግባራቸው ላይ ያተኩራሉ፡፡ ካህናት ምእመናንን ቃለ እግዚአብሔር መመገብ
አለባቸው፤ ይኸውም በአደባባይ መስበክን የሚመለከት ሲኾን ከዚኹም ጋር በግል ለእያንዳንዱ የንስሐ ልጃቸው ምክር
አዘል የኾነ ቃለ እግዚአብሔርን ማካፈልን ይጨምራል፡፡

የንስሐ አባቶች ለልጆቻቸው በግል የሚሰጡት አገልግሎት ጌታችን በወንጌል፡ -“


መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ
ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በበረኻ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ማን

ነው?” / .15 5/
ሉቃ ፡ ያለው ቃሉን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ካህናት ከእግዚአብሔር በአደራ እንዲጠብቁ
የተሰጣቸውን ኹሉንም ሳይዘነጉ እያንዳንዱን በነፍስ ወከፍ ሊጠብቁና ሊያገለግሉ ይገባቸዋል፡፡

“ሕዝብ በበዛበት በአደባባይ መስበክ ለካህኑ ዋና ተግባሩ ነው ብለን ነበር፤ ነገር ግን ይኽ ብቻ በቂ አይኾንም፤
እንዲኹ
ለእያንዳንዱ የተለየ ርዳታ የተለየ ጥበቃ ሊደረግና በግል ሊሰበክ ይገባል፡፡ ሊቀ ካህናት ክርስቶስ እንዲኹ በአደባባይ
ብቻ አያስተምርም ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ዕድሜያቸው እንደየፍላጐታቸው ለእያንዳንዱ የተለየ ርዳታ ያደርግ ነበር፡፡
ከሱም በኋላ የተነሡ መምህራን እንዲኹ ሥራቸውን በማኅበር በአደባባይ በግልም ለእያንዳንዱ ያደርጉ እንደነበር

/
የታወቀ ነው፡፡” ትምህርተ አበ ነፍስ፣ ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ገጽ 110-111/፡፡

ይኽ የንስሐ አባትነት ተግባር በዘመናችንም ያልተቋረጠ መኾኑ እሙን ነው፡፡ ችግሩ የሚነሣው የንስሐ አባቶች ከንስሐ
ልጆቻቸው ጋር የሚፈጥሩት ግላዊ ግንኙነት ከቤተሰባዊነት ያልተሻገረ ኾኖ ሲቀነጭር ነው፡፡ ብዙ ካህናት ወደ ምእመናን
ቤት መጥተው ሲያበቁ መስቀል ከማሳለምና ጠበል ከመርጨት ያለፈ አገልግሎት አይሰጡም፡፡ ካህናት ሥርዓተ ቤተ
ክርስቲያን እንዳስቀመጠላቸው ከሥራቸው ኹሉ ቅድሚያውን ሰጥተው ማስተማር፣ መምከር፣ ኑዛዜን መቀበል፣
ማጽናናትና መገሰጽ ይገባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ የንስሐ ልጃቸውን በጥንቃቄ ይዘው ለሥጋ ወደሙ ማብቃት ግባቸው
ስለኾነ ትኩረታቸው ኹሉ ወደዚኽ ዋነኛ የክህነት ዓላማቸው መሰብሰብ ይኖርበታል፡፡

በዚኽ ጽሑፋችን ካህናት ኾነው ሳለ ወደ ልዩ ልዩ ሥራዎችና አገልግሎቶች አዘንብለው የአበነፍስነት ተግባራቸውን ችላ


ያሉ ካህናትን ለማንቃት ያስችለን ዘንድ የመልካም ልምድ ባለቤት የኾኑ አባቶችን አብነት ነሥተን እናያለን፡፡ ከዚያ
ቀድመን ግን
ችግሩን በመጠኑ እንዳስሳለን፡፡

የንስሐ አባት ማግኘት

በርካታ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት በሚገኙባት አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙት ካህናት በቁጥር ምን ያኽል የበዙ
መኾናቸውን የሚያውቅ ሰው በዚኽች ከተማ ውስጥ የንስሐ አባት ማግኘት የቸገራቸው ሰዎች ይኖራሉቢባል ትልቅ
ተቃርኖ ይመስለው ይኾናል፡፡

መጋቢት 7 2005 . .
ቀን ዓ ም የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ወደ
አቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም አዘጋጅቶት በነበረው መንፈሳዊ ጉዞ ላይ አባላቱ ስለ ንስሐ አባትና ልጅ ግንኙነት ውይይት
አድርገው ከውይይቱ የተገኘው ውጤት ፍጹም ባልተጠበቀ ኹኔታ ይኽን ችግር የሚያሳይ ነበር፡፡ በተለይ የሰንበት
ትምህርት ቤቱ የመዠመሪያ ዓመት ተማሪዎች መካከል ብዙዎቹ የንስሐ አባት ማግኘት ግራ የሚያጋባ ሒደት
እንደኾነባቸው ገልጸዋል፡፡

አባት ማግኘት የቻሉት እንኳን በአጋጣሚ በጓደኛ በኵል እንዳገኙ የገለጹ ሲኾን መፍትሔውንም በተመለከተ ለቀረበው
ጥያቄ ከተሰጡት ሐሳቦች መካከል የችግሩ ሰለባ የኾነች አንዲት ወጣት ማንኛውም ክርስቲያን የንስሐ አባት ማግኘት
ሲፈልግ አገልግሎቱን የሚያገኝበት ቢሮ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሊከፈት ይገባዋል ያለችውን አወያዮቹ ያስታውሳሉ፡፡

አንድ ለስንት?
የንስሐ አባት ማግኘት ይኽን ያኽል ሲቸግር በሌላ በኵል ደግሞ አንዳንድ አባቶች የንስሐ ልጆቻቸው ቁጥር ከመጠን
በላይ ብዙ
ከመኾኑ የተነሣ የንስሐ አባትና ልጅ የመኾኑ ምክንያት ምን ይኾን ? የሚል ጥያቄን የሚያጭር ይኾናል፡፡ አንዳንድ
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከኾነ ከ 1,000 በላይ የንስሐ ልጆች ያሉዋቸው ካህናት አሉ፡፡ ይኽ ኹኔታ ምን
ችግር አስከትሏል? በሚል ሐሳብ ተነሣስተው ቀሲስ ፋሲል ታደሰ በግላቸው ባካሔዱት ጥናት መጠይቅ
ከቀረበላቸው ካህናት መካከል አንደኛው የሰጡት ምላሽ የሚያሳየው ካህኑ 500 የንስሐ ልጆች ያሉዋቸው ሲኾን

ከነዚኽም መካከል ለንስሐ ያበቁዋቸው 105 ያኽሉን ብቻ ነው

2.13 በንስሐ አባትና ልጅ ግንኙነት ላይ የሌሎች አኃት ቤተ-ክርስቲያን ተሞክሮ ምን ይመስላል


ሀገረ ሕንድ ዓለምን በሰው ልጆች ቁጥር ከቻይና ጋር እየመራች ሲሆን በውሰጧ ያሉ ወደ አንድ ቢሊዮን ሦስት መቶ
ሚሊዮን ዜጎቿም በሃያ ስምንት ግዛቶች እና በስምንት ልዩ ግዛቶች ተከፋፍለው ከሃያ ሁለት በላይ የተለያዩ ቋንቋዎችን
እየተናገሩ ከሰባት በላይ በሆኑ ሃይማኖት ሥረዓተ አምልኳቸውን እየፈጸሙ በፍቅር እና በአንድነት የሚኖሩ ለሥራ
ትጉኃን ያሉባት በኤሽያ አህጉር የምትገኝ ሰፊ ሀገር ናት ።

/
በዚህች ሀገር ከሚገኙት የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሆነችው በሐዋርያው ቅ ቶማስ እምነት ላይ ተመስርታ ጌታዬ

አምላኬም (MY LORD AND MY GOD) ብላ የምታምን

የማላንካራ ኦርቶዶክስ ሲሪያን ቤተ-ክርስቲያን (የሕንድ ቤተ-ክርስቲያን) አንዷ ነች ።


የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ በሆነው በቅዱስ
-
ቶማስ ስብከት እና ሰማዕትነት ክርስትናን የተቀበለችው የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ሲሪያን ቤተ ክርስቲያን ለኤሽያ
ላሉ በብዙ ለሚቆጠሩ ህዝቦች በበረሃ ያለች ምንጭ ሆና ለዘመናት አገልግላለች ዛሬም ላይ እያገለገለች ትገኛለች ።
በየዘመናቱ በቅኝ ገዢዎች በደረሰባት ተደጋጋሚ የመከራዎች መከራ ልጆቿን ፣ ታሪኳን ፣ ብዙ እሴቶቿን አጥታ ለዛሬ

-
ደርሳለች ። የዛሬዎቹ የማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ምንም እንኳን ትንሽ ቢሆኑ አኩሪ ታሪክ ለዘመኑ

-
ትውልድ እየሰሩ በጎቻቸውን በአግባቡ እየጠበቁ ይገኛሉ ። የማላንካራ ኦርቶዶክስ ሴርያን ቤተ ክርስቲያን 2.5
ሚሊዮን ምዕመናንን ብቻ ይዛ 30 አህጉረ ሰብከት (Dioces) አቋቁማ ልጆቿ ዘመኑን ሊዋጁት
ጊዜውን ሊቀድሙት ዕለት ዕለት ይፋጠናሉ ። ከሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ሲሪያን ቤተ-ክርስቲያን ሰፊ እና ብዙ
አገልግሎቶች መካከል ለዚህ ለያዝነው ርዕሳችን የሚሆነውን የደብሩ ካህናት በየምዕመናን ቤት በሳምንት ለሦስት ቀናት

-
በዙር የሚያደርጉት ተደራሽ የሆነ የመንፈሳዊና የማህበራዊ አገልግሎታቸው እንመለከታለን ። ቤተ ክርስቲያኗ ልጆቿን
በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊው ኑሮ የተዘጋጁ እና ብቁ እንዲሆኑ ለማስቻል ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ዘርፍ እና ተልዕኮዎች
አሏት ። ከምንም በላይ ሁሉንም ምዕመናን እና ምዕመናትን ተደራሽ ለማድረግ የዘረጋቻቸው የአገልግሎት ዘርፎች እና

''The
አደረጃጀቶች ተጠቃሽ ናቸው ። ከእነዚህ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ የሆነው

minister of Human Empowerment''(የሰው


ማብቂያሚኒስቴር) አንዱ ነው ።
- (
የዚህ የቤተ ክርስቲያኗ ሚኒስቴር መምሪያ ) ዋናው አላማ በተለያዩ መንገዶች ምዕመናኑ ጋር በመድረስ የልጆቿን
ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት እና ለማነቃቃት (explore ,enlighten

&empower) ማንቀሳቀስ ነው ። የዚህ ክፍል ዋናው ትኩረት በቤተሰብ ውስጥ ያለውን


አጠቃላይ ዕሴት መገምገም ፣ መደገፍ እና እንዲሻሻል (Evaluate, Guide, &

Enhance) ማድረግ ነው ። ይህ የቤተክርስቲያኗ ሚኒስቴር በተለያዩ የቤተሰብ ክፍሎችን (ህፃናት


፣ ወጣቶች ፣ ታላላቅ ሰዎች ፣ ለእጮኛሞች ፣ ለሴቶች) በማደራጀት እንደ ፍላጎታቸውና ዝንባሌያቸው አገልግሎቱን
ተደራሽ በማድረግና አቅማቸውን በማጎልበት በጋራ ትብብር በአንድነት ሆነው ለቤተክርስቲያኗ እና ለማህበረሰቡ እድገት
አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ድጋፍ ያደርጋል ። ይህንን ተደራሽ ለማድረግ የቤተክርስቲያኒቱን እምነት

(faithful) ተኮር ጉዳዮች በማንሳት የተለያዩ (Awareness talks


campains, Seminars, psycological,
phychological and spiritual) ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ድጋፍ
ያደርጋል ።

ከሚኒስትሩ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል :-


- Human welfare /ለሰው ልጅ ደህንነት/
- Human resource training /
- Human resource enlightenment /
- Human resource counseling /
- Human resource data bank /
ከዚህ ባሻገር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየቀረጸ የሚሰራ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ

- prject on family welfare /


- Anti-Addiction Campaign /
- Christian parenting /
- Geriatric & palliative Care /
- Women Safety & empowerment
ይገኙበታል ።

-
የማላንካራ ኦርቶዶክስ ሲሪያን ቤተ ክርስቲያን ይህን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከምትጠቀምባቸው ዘርፈ ብዙ
መንገዶች አንዱ የአጥቢያ ካህናት የዙር የየመንደሩ አገልግሎት ተጠቃሽ ነው ። ይህ መርሐ ግብር በደብሩ ካህን

,
የሚመራ ሲሆን በሳምንት ሦስት ቀናት ሰኞ ረቡዕ እና ዓርብ የሚካሄድ ነው ። ዮህ ፕሮግራም ዓመታዊ መርሐ ግብር
ወጥቶለት ለምዕመናን የሚደርስ ሲሆን ሁሌ የየሳምንቱ መረሐ ግብር በየአብያተክርስቲያኒቱ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ
የሚለጠፍ ሲሆን እሁድ ከቅዳሴ በኋለ ከማይቀሩ ማስታወቂያዎች መካከል አንዱ ነው ።
ካህኑ ቅዳሴው ተጠናቆ ከማሳረጉ በፊት ወረቀት ይዞ የዚህ ሳምንት የቤት ለቤት መርሐ ግብር እነማን ቤትና የት

አካባቢ እንደሆነ በዝርዝር ይናገራል ።''የሰኞ መርሐ ግብር የ..... አካባቢ የ.......ቤት ሲሆን የቤት
ቁጥሩ እና ቦታው ልዩ ምልክት ይህ ነው'' ይላል ። የረቡዕንም የአርብንም ፕሮግራም እንዲሁ ያስተዋውቃል ።
መርሐ ግብሩ በሚደረግበት ምዕመናን ቤት ዙሪያና በቅርበት
ያሉ አባቶች, እናቶች እና ወጣቶች በጋራ መርሐ ግብሩ ይሳተፋሉ ።
የማላንካራ እርቶዶክስ ሲሪያን ቤተ-ክርስቲያን ለምዕመናን በቤተ-ክርስቲያን ከምትሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ
ይህ ቤት ለቤት በካህናት አባቶች የሚደረገው መርሐግብር ለምዕመናን ምን ያህል ለምዕመናን ቅርብ እና ተልዕኮ ተኮር
እንደሆነች ማሳያ ነው ። ከመንበረ ፓትሪያርክ ጀምሮ እስከ ምዕመናን ቤት በሚደርስ አደረጃጀት ዘርግታ ለልጆቿ
ዘመኑን ዋጅታና ቀድማ ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች ።

-
የማላንካራ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅማ ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትሪያርክ በዘረጋችው ወጥ

(Data bank)
ሥርዓት የእያንዴንዱ ክርስቲያን እና የቤተሰብ አባላት መረጃን በመረጃ ቋት
ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ፤ ወደዚህ ዓለም ሲመጡም ሆነ ከዚህ ዓለም ሲሄዱ ልጆቿን በቀላሉ መደመር እና መቀነስ
ትችላለች ። ይህም የሆነው የተማሩ ልጆቿን በየአጥቢያው ባሉ አገልግሎቶች በማሳተፍ ከዘመኑ እኩል እንድትራመድ
አስችሏታል ።

ምንጭ :- ማላንካራዊያን(የበረሃ ምንጮች) /መኮንን ኃብተ-ሚካኤል 2013 ዓ.ም./


ምዕራፍ 3
1.4 የጥናቱ አላማ
በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አጥቢያ ያሉትን ምዕመናን እና ካህናት ያላቸው ግንኙነት ምን መምሰል
እዳለበት ማሳየት ነው።

1.5 የጥናቱ ንዑስ አላማ


በንስሐ አባቶች አያያዝ ጉድለት ከቤተክርስቲያን እየራቁ ያሉትን ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለሱ ማድረግ።
Ÿ /
የምዕመኑ አቀባበል እና የካህናቱ የማስተማሩ ሂደቱን እንዴት ዘመኑን በዋጀ ባማከለ ማሻሻል እንደሚገባ።
Ÿ ካህናት የንስሐ ልጆቻቸውን የሚያገለግሉበትን የአገልግሎት ልዩነት ማስተካከል።
Ÿ ካህናት ምዕመናንን ለቤተሰባዊ አገልግሎት የሚያደርጉትን የግንዛቤ ድጋፍን እና ክትትልን መቃኘት።
ምዕራፍ 4
የጥናቱ ዘዴ

4.1 የጥናቱ ቦታ

/// /// /
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአ አ ክ ከተማ በደ ኃ ቅ ራጉኤል ቤ ክ ላይ በሚገኙ የአጥቢያው ምዕመናን ላይ እና
የደብሩ ካህናትና ያለውን መንፈሳዊ ህይወት ላይ ትኩረት አድርገን ጥናታችንን እናካሂዳለን።

4.3 የጥናቱ አይነት


ይህ ጥናት ኩነታዊ ገላጭ የምርምር አይነት ሲሆን የካህናትና የምዕመናን መንፈሳዊ ግኑኝነት ቅርበት ደካማ ያነሰ
በመሆኑ በምዕመኑ ላይ ያመጣታው የእምነት ቸልተኝነት ደካማነት በመንፈሳዊ በምክረ ካህን የታገዘ ህይወት
ስለሌላቸው ለቤተክርስቲያንም ትልቅ ፈተና የሆነ ችግር ስለሆነ ከ አጥቢያው ምዕመኑ እና ከካህናቱ ተጨባጭ መረጃ
በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ በመግለጽ፣ ትክክለኛ መፍትሔ ወይም መደምደሚያ
በመፈልግ ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡
ምንጭ

መፅሐፍ ቅዱስ
ክብረ ክህነት፦ሄኖክ ሀይሌ
Ÿ /
የነፍስ አባትና የነፍስ ልጅ የመሆን ምስጢር ፦ቀሲስ መዘምር ወ ሩፋኤል
Ÿ የንስሐ አባትና የንስሐ ልጅ ድርሻ
Ÿ የጽሑፉ ምንጭ፡ - ሐመር መጽሔት፥ የግንቦት 2005 ዓ.ም. እትም ነው፡፡

You might also like