You are on page 1of 8

ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት

“ስለ ጽድቅኽም ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንኻው።” መዝ. ፻፲፰÷፻፷፬ በማለት በቀን ሰባት ጊዜ
ይጸልይ እንደነበር ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ተናግሯል። በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስትያን ስርዓት መሰረት በአንድ ቀን ውስጥ የተመደቡ የጸሎት ጊዜያት ሲኖሩ እነርሱም ሰባት
(፯) ናቸው። አንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው ቢችል በአንድ ቀን ዉስጥ
ሰባቱንም ጸሎታት ማድረስ ይኖርበታል፣ በስራ ወይም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ሳይመቸው ቢቀር
ቢያንስ በጸሎቱ ሠዓታት ሚታሰቡትን ነገሮች አስቦ ማሳለፍ ይኖርበታል። ነገር ግን እናመሰግነው
ዘንድ ለፈጠረን አምላክ በስራስ ቦታ ቢሆን የሁለት እና የሦስት ደቂቃ ጊዜ እነዴት እናጣለታለን? እና
ከቻልን አቡነ ዘበሰማያት (አባታችን ሆይ) የምትለዋን አጭር ጸሎት ብናደርስ ይመረጣል። ያንንም
እናደርግ ዘንድ እግዚአብሄር ይርዳን!

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ስለ ጽድቅኽ ፍርድ በቀን ሰባት (፯) ጊዜ አመሰግንኻለኑ ብሎ
አምላኩን በቀን ሰባት(፯) ጊዜ እንዳመሰገነ እና እንደጸለየ ሁሉ እኛም አባቶች በጉባኤ በደነገጉት እና
ባፀኑት ሕግ መሠረት የአባቶቻችንን መንገድ ተከትለን በቀን ውስጥ ሰባት (፯) ጊዜ እራሳችንን
ለእግዚአብሔር በማስገዛት ለጸሎት እንተጋለን። ሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ከዚህ በታች በዝርዝር
ተቀምጠው እናገኛለን። እነሱም ነግኅ፣ ሠለስት፣ ቀትር፣ ተሰዓት፣ ሠርክ፣ ንዋም እና መንፈቀ-ሌሊት
ናቸው።

፩. ነግኅ (ማለዳ ጧት)


“በማለዳ ድማፄን ትሰማለህ በማለዳ በፊትኽ እቆማለሁ።” መዝ. ፭÷፫ ብሎ ነብየ እግዚአብሔር
ለጸሎት እና ለምሰጋና በፊቱ እንደቆመ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር ሌሊቱን በሰላም እና
በምህረት ጠብቆ የማለዳውን ብርሃን እንድናይ ስለረዳን እናመሰግነዋለን። አንድም፤ አባታችን አዳም
የተፈጠረበት ሰዓት ማለዳ ነውና (ዘፍ. ፩÷፳፮) በአምላካችን አርአያ እና አምሳል በመፍጠራችን
አማላካችን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን። አንድም፤ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና አምላካችን
ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት ቆሞ የተመረመረበት ሰዓት ነውና፤ ፈጣሪው እና መርማሪው አምላክ ለእኛ
ለባሪያዎቹ ብሎ በፍጡር አንደበት ተመርምሯል። በዚህም ምክንያት ስለእኛ የሆነልንን ነገር በማሰብ
በዚህ ሰዓት በጸሎት እንተጋለን። (ማቴ. ፳፯÷፩)

፪. ሠለስት (ሦስት ሰዓት)


በዚህ ሰዓት የሁላችንም እናት ሔዋን የተፈጠረችበት ሰዓት ነውና (ዘፍ. ፪÷፳፩-፳፬) እናቶቻችን፣
የትዳር አጋሮች፣ እህቶች፣ ሴት ልጆች የማግኘታችን መሠረት ነውና በዚህ ሰዓት እግዚአብሔር
አምላካችን እናታችን ሔዋንን ስለፈጠረልን እናመሰግነዋለን። አንድም፤ ነብየ እግዚአብሔር ዳንኤል
በዚህ ሰዓት መሰኮቶቹን ወደ ኢየሩሳሌም አንፃር በመክፈት ይጸልይ ነበር። (ዳን. ፮÷፲) አንድም፤
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤል ብስራት የሰማችበት እና አምላካችንን
የጸነሰችበት ሰዓት ነው። (ሉቃ. ፩÷፳፮) አንድም፤ ክብር ይግባውና ጌታችን በጲላጦስ ፊት
የተገረፈበት ሰዓት ነው። (ማቴ. ፳፯÷፳፮) አንድም፤ በጽርያ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት
የወረደበት ሰዓት ነውና በነዚህ ሰዓቶች (ከጠዋቱ ፫ ሰዓት) እግዚአብሔርን በጸሎት እናመሰግነዋለን።

፫. ቀትር (ስድስት ሰዓት)


በዚህ ሰዓት ፀሐይ ስትበረታ ሰውነታችን ሲዝል አዕምሮአችን ይሰንፋል እና አጋንንት ይበረታሉ።
በዚህም ምክንያት ሰውነታችንን አበርትተን ህሊናችንን ሰብስበን ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን።
(መዝ. ፶፬÷፲፯ ፤ ፺÷፮) አንድም፤ አዳም አባታችን እፀ በለስ በልቶ ከክብሩ የተዋረደበት ሰዓት ነውና
ወደ ፈተና እንዳንገባ እንጸልያለን። (ዘፍ. ፫÷፮) አንድም፤ የአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሔኖክ
ቤተ-መቅደስን ያጠነበት ሰዓት ነው። (ኩፋ. ፭÷፴፪) አንድም፤ አምላካችን ክርስቶስ ክብር ይግባውና
ለኛ ለባርያዎቹ ድህነት ይሆነን ዘንድ በዕለት አርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ሰዓት ነው። (ዮሐ.
፲፱÷፩፬)

፬. ተሰዓት (ዘጠኝ ሰዓት)


በዚህ ሰዓት ቅዱሳን መላዕክት የሰው ልጅ የጸለየውን ጸሎት፣ ልመና፣ እጣን እና የሠራውን ሥራ ሁሉ
የሚያሳርጉበት ሰዓት ነው። (የሐዋ. ፲÷፫) አንድም፤ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ ለጸሎት ወደ
ቤተ መቅደስ ይወጡበት የነበረበት ሰዓት ነው። (የሐዋ. ፫÷፩) አንድም፤ አምላካችን በዘመን ሁሉ
ምስጋና ለዕርሱ ይሁንና ለኛ ለደካማ ልጆቹ ድህነት ይሆነን ዘንድ በዚህች ሰዓት ቅድስት ነፍሱን
ከክብር ሥጋው የለየበት ሰዓት ነው። ይህም ቀን ዕለተ አርብ ከቀኑ ዘጠኝ (፱) ሰዓት አምላካችን
ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ያረፈበት ሰዓት ነው።

፭. ሠርክ (ዐሥራ አንድ ሰዓት)


በዚህ ሰዓት ላይ ሰው ሁሉ ሥራ ሠርቶ ከሥራው የሚያርፍበት እና ዋጋውን የሚቀበልበት ሰዓት
ሲሆን እኛም ምግባር ቱሩፋት ሰርተን ዋጋችንን ከአምላካችን የምንቀበልበት ሰዓት ነው። (ማቴ.
፳÷፩-፲፮) አንድም፤ ነብየ ዳዊት እንዳለ “ጸሎቴን በፊትህ እንደዕጣን ተቀበልልኝ፤ እጅ መንሣቴም
እንደ ሠርክ መስዋዕት ትሁን” (መዝ. ፻፵÷፪) በማለት ይህች ሰዓት ታላቅ የጸሎት ሰዓት መሆኗን
ያስተምረናል። አንድም፤ ነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ በዚህች ሰዓት የሰዋው መሰዋትእና ያቀረበው
ጸሎት በቅድስት ሥላሴ ዘንድ ተወዶለታል። (፩ኛ.ነገ ፲፰÷፴፮) አንድም፤ አባታችን ዕዝራም በዚህች
ሰዓት ጸሎት አቅርቦበታል። (ዕዝ. ፱÷፭) አንድም፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም
አጠራሩ ክብር ይግባውና እኛን ከሞት እና ከሲኦል ያወጣ ዘንድ በሥጋው ወደ ከርሠ መቃብር በነፍሱ
ደግሞ ወደ ሲኦል የወረደበት ሰዓት ነው። (ማቴ. ፳፯÷፵፭ - ፷፩)
፮. ንዋም (የመኝታ ሰዓት)
በዚህ ሰዓት ቀኑን ሙሉ ስንወጣ ስንወርድ የጠበቀንን አምላክ አመስግነን፤ ዳግመኛም የሌሊቱን ሰዓት
ባርኮ የሰላም እንቅልፍ ይሰጠን ዘንድ ለጸሎት እንቆማለን። አንድም፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በጌቴሴማኒ ሥርዓተ-ጸሎትን ያስተማረበት ሰዓት ነው። (ማቴ. ፳፮÷፴፮)

፯. መንፈቀ ሌሊት
ይህ ሰዓት ታላቅ ሰዓት ነው። አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት፣
ሙታን መካከል ተለይቶ የተነሣበት፣ ዳግመኛም በህያዋን እና በሙታን ለመፍረድ የሚመጣባት ሠዓት
ስለሆነች ይህን ሁሉ በማሰብ እና እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ያደረገዉን ነገር ሁሉ በማሰብ
የሚጸለይበት ሠዓት ነው። (ሉቃ. ፪÷፯-፰፣ ዮሐ. ፳÷፩፣ ማቴ. ፳፭÷፮፣ ማር. ፲፫÷፴፭) በዚህም
ምክንያት አምላካችን ለእኛ የሆነውን እና ያደረገውን ሁሉ በማስተዋል እንጸልያለን። አንድም፤
ቅዱስ ጳውሎስ እና ደቀመዝሙሩ ሲላሰ በእሥር ቤት ውስጥ እያሉ በዜማ አሸናፊ ልዑል
እግዚአብሔር ያመሰገኑበት ሰዓት ነው። (የሐዋ. ፲፮÷ ፳፭)

በነዚህ የጸሎት ሰዓቶች ውስጥ እግዚአብሔር በረዳን መጠን በጸሎት ልንተጋ ይገባል። እነዚህን
የጸሎት ሰዓቶች በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነን መተግበር ቢያቅተን እንኳን ጠዋት
ከመኝታችን ስንነሳና ማታ ወደ መኝታችን ስናመራ መጸለይ ይገባናል ከዚህ ውጭ በገዳም ተወስነው
ዳዋ ጥሰው ጤዛ ልሰው ቁርበት ለብሰው ድንጋይ ተንተርሰው ድምፀ-አራዊቱን ግርማ ሌሊቱን ፀብና
አጋንንቱን ታግሰው የሚኖሩ ገዳማውያን መነኮሳት አባቶቻችን እና እናቶቻችን እነዚህ ከላይ
በዝርዝር ያየናቸውን ሰባቱን የጸሎት ሰዓታት ለአይን ጥቅሻ እንኳ ለምታክል ጊዜ እንኳ ሳያስታጉሉ
እስካሁን ፀንተው ኖረዋል፤ ወደፊትም ይኖራሉ።

ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን


አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባለችን በዚህች አጭር የእግድነት ዘመናችን በጸሎት
እድንተጋ ይርዳን፤ አለማመናችንን ይርዳው አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለወላዲቱ
ድንግል፤ ወለመስቀሉ ክቡር።
የዘወትር ጸሎት

አማርኛ ግዕዝ

፩. ገጼን እና ኲለንታዬን በትእምርተ መስቀል አአትብ ገጽየ ወኲለንታየ በትእምርተ መስቀል


አማትባለሁ (፫ ጊዜ በል)። በስመ አብ ወወልድ (፫ ጊዜያተ በል)። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ
ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ በቅድስት ሥላሴ ቅዱስ አሐዱ አምላክ በቅድስት ሥላሴ እንዘ
እያመንኩ እና እየተማፀንኩ፣ በዚች በእናቴ አአምን ወእትመሐፀን እክሕደከ ፀርየ ሰይጣን
በቤተክርስቲያን ፊት ቆሜ ጠላቴ ሰይጣንን በቅድመ ዛቲ እምየ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
እክድሃለሁ። ለዚህም ምስክሬ ማርያም ጽዮን ናት እንተ ይእቲ ስምዕየ ማርያም ጽዮን ለዓለመ
ለዘለዓለም። ዓለም።

፪. አቤቱ እናመሠግንሃለን፤ አቤቱ እናከብርሃለን፤ ነአኵተከ እግዚኦ ወንሴብሐከ ንባርከከ እግዚኦ


አቤቱ እንገዛልሃለን፤ አቤቱ ቅዱስ ስምህን ወንትአመነከ። ንገኒ ለከ እግዚኦ ወንትቀነይ
እናመሰግናለን፤ ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ አቤቱ ለስምከ ቅዱስ። ንሰግድ ለከ ኦ ዘለከ ይሰግድ
እንሰግድልሃለን፤ አንደበትም ሁሉ ለአንተ ይገዛል፤ ኲሉ ብርክ ወለከ ይትቀነይ ኲሉ ልሳን። አንተ
የአምላኮች አምላክ፣ የጌቶች ጌታ የንጉሦችም ውእቱ አምላከ አማልክት ወእግዚኣ አጋዕዝት
ንጉሥ እንተ ነህ። የሥጋም የነፍስም ፈጣሪ አንተ ወንጉሠ ነገሥት አምላክ አንተ ለኲሉ ዘሥጋ
ነህ። እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ ወለኵላ ዘነፍስ ወንጼውዐከ በከመ መሐረነ
ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን ቅዱስ ወልድከ እንዘ ይብል አንትሙሰ ሶበ
እንጠራሃለን። ትጼልዩ ከመዝ በሉ።

፫. አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፤ ትምጻእ
መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ፤ በከመ በሰማይ
እንዲሁም በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ከማሁ በምድር ሲሳየነ፤ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም፤
ስጠን ዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛ ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ
የበደሉንን ይቅር እንደምንል፤ አቤቱ ወደ ለዘአበሰ ለነ፤ ኢትኣብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት
ፈተናምም አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ፤ ኣላ አድኅነነ፤ ወባልሐነ እምኵሉ እኩይ፤ እስመ
መንግሥት ያንተ ናትና ኃይል እና ስብሃሃት ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ
ለዘለዓለሙ፤ አሜን። ዓለም፤ አሜን።
፬. እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ
በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ ማርያም ሰላም ለኪ፤ ድንግል በኅሊናኪ
በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። ወድንግል በሥጋኪ፤ እመ እግዚአብሔር ጸባዖት
የአሸናፈ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ሰላም ለኪ፤ ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ
ላንቺ ይገባል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ ፍሬ ከርሥኪ፤ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ
የተባረክሽ ነሽ የማኀፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ፤ ሰአሊ ወጸልዪ ኀበ
ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይሥረይ
ከአንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ለነ ኃጣዊኢነ።
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርከቶስ ዘንድ
ይቅርታን ለምኝልን ኃጥያታችንን ያስተሠርይልን
ዘንድ ለዘለዓለሙ፤ አሜን።

፭. ሁለን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ


በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ሰማይና አኃዜ ኩሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ
ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን ወዘኢያስተርኢ ወነአምን በአሐዱ እግዚእ
ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ ኣብ ዋሕድ ዘሀልው
ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም።
እናምናለን።
ብርሃን ዘእምብርሃን አምላክ ዘእምአምላክ
ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ ዘበአማን። ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ዘዕሩይ
የተገኘ አምላክ፤ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ምስለ አብ በመለኮቱ። ዘቦቱ ኵሉ ኮነ
በባሕርይው ከአብ ጋር የሚስተካከል ሁሉ በእርሱ ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ
የሆነ በሰማይ ካለው በምድርም ካለው ያለእርሱ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ።
ምንም የሆነ የለም።
ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ
ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ እምሰማያት ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ወእማርያም እምቅድስት ድንግል ኮነ ብእሲ
ፍጹም ሰውን ሆነ ደግሞም ስለእኛ ተሰቀለ። ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ
በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ጰንጤናዊ። ሐመ ወሞተ ወተቀበረ ወተንሥአ
ተቀበለ፤ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን እሙታን አመ ሣልስት ዕለት በከመ ጽሑፍ
ከሙታን ተለይቶ ተነሳ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት ዐርገ በስብሐት
እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማኑ አቡሁ ዳግመ
በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፤ ዳግመኛም በሕያዋንና ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ
በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል፤ ወኣልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ።
ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፤ እርሱም ጌታ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ
ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ፤ ከአብና ከወልድ ዘሠረጸ እምአብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ
ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን፤ ምስለአብ ወወልድ ወነበበ በነቢያት። ወነአምን
እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው። በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ
ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት ጉባዔ ዘሐዋርያት። ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት
በአንዲት ክብርት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ለሥርየተ ኃጢአት ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን
ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም።
እናምናለን። የሙታንንም መነሣት ተስፋ
እናደርጋለን፤ የሚመጣውንም ሕይወት
ለዘለዓለሙ፤ አሜን።

፮. አሸናፊ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚብሔር ጸባዖት ፍጹም
ተብለህ ትመሰገናለህ። ምስጋናህም በሰማይና ምሉዕ ሰማያት ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
በምድር የሞላሞላ ነው። ክርስቶስ ላንተ ንስግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ
እንሰግድልሃለን፤ ከሰማያዊው ከቸር አባትህ ጋር፤ ወመንፈስከ ቅዱስ ማኅየዊ እስመ መጻእከ
አዳኝ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ወአድኃንከነ።
እንሰግድልሃለን፤ ወደዚህ ዓለም መጥተህ
አድነኸናልና።

፯. ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት
ለመንፈስ ቅዱስ (፫ ጊዜ በል)። አምላክን ለመንፈስ ቅዱስ (፫ ጊዜያተ በል)። ስብሐት
ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
ምስጋና ይገባል። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ
መስቀልም ምስጋና ይገባል። ክርስቶስ በምህረቱ በምሕረቱ ይዘከረነ። አመ ዳግም ምጽአቱ
ያስበን፤ ዳግመኛም በመጣምም ጊዜ አያሳፍረን፤ ኢያስተኀፍረነ። ለሰብሖተ ስሙ ያንቅሀነ፤
ስሙን ለማመስገን ያንቃን፤ በእርሱ አምልኮትም ወበአምልኮቱ ያጽንአነ። እግዝእትነ ማርያም
ያጽናን። እመቤታችን ጸሎታችንን አሳርጊልን፣ አዕርጊ ጸሎተነ ወአስተሥርዪ ኃጢአተነ ቅድመ
ኃጢአታችንንም አስተሥርይልን፤ በጌታችን መንበሩ ለእግዚእነ ለዘአብልዐነ ዘንተ ኅብስተ
መንበር ፊት ጸሎታችንን አሳርጊልን። ይህንን ወለዘአስተየነ ዘንተ ጽዋዓ ወለዘሠርዐ ለነ ሲሳየነ
ኀብስት ላበላን ይህንንም ጽዋ ላጠጣን፤ ወአራዘነ ወለዘተዐገሠ ኵሉ ኃጢአተነ
ምግባችንንና ልብሳችንን ላዘጋጀልን፤ ወለዘወሀበነ ሥጋሁ ቅዱስ ወደሞ ክቡረ
ኃጢአታችንንም ሁሉ ለታገሠልን፤ ክቡር ደሙን ወለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት።
ቅዱስ ሥጋውን ለሰጠን፤ እስከዚችም ሰዓት
ላደረሰን።
፰ ለልዑል እግዚኣብሔር ፍፁም ምስጋና ይገባል፤ ነሀብ ሎቱ ስብሐተ ወአኰቴተ ለእግዚአብሔር
. ለድንግል እናቱ እና ክቡር መስቀሉም ምስጋና ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል። ወለመስቀሉ ክቡር
ይገባል። የእግዚአብሔር ስሙ ፈጽሞ ይመስገን ይትአኰት ወይሰባሕ ስሙ ለእግዚአብሔር
ዘወትር በየጊዜያቱና በየሰዓቱ። ወትረ በኲሉ ጊዜ ወበኲሉ ሰዓት።

፱. ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ማርያም እምነ
እናታችን ማርያም ሆይ እንማልድሻለን ከአዳኝ ናስተበቊዐኪ። እምአርዌ ነዓዊ ተማኅፀነ ብኪ።
አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል ስለ እናትሽ በእንተ ሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ ማኅበረነ
ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ዮም ድንግል ባርኪ።
ድንግል ማኀበራችንን ዛሬ ባርኪልን።

፲. ማርያም አለችች፦ ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ወትቤ ማርያም፦ ተዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር
ታደርገዋለች። መንፈሴም በመድኃኒቴ ወትትሐሠይ መንፈስየ በአምላክየ እስመ ርእየ
በእግዚአብሔር ደስ ይላታል። የባሪያይቱን ሕማማ ለአመቱ። ናሁ እምይእዜሰ
መዋረድ አይቷልና፤ እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ያስተበፅፅዑኒ ኲሉ ትውልድ እስመ ገብረ ሊተ
ሁሉ ብርክት ይሉኛል፤ እርሱ ብርቱ የሚሆን ኃይለ ዐቢያተ ወቅዱስ ስሙ፤ ወሣህሉኒ
ታላቅ ሥራን ለእኔ አድርጓልና፤ ስሙም ቅዱስ ለትውልደ ትውልድ ለእለ ይፈርህዎ ወገብረ
ነው። ለሚፈሩትም ምሕረቱ ለልጅ ልጅ ነው። ኃይለ በመዝራዕቱ። ወዘረዎሙ ለእለ ያዐብዩ
ኃይልን በክንዱ አሳይቷል፤ በልባቸው አሳብ ኅሊና ልቦሙ ወነሠቶሙ ለኃያላንያላን
የሚኮሩ ትዕቢተኞችን በታተናቸው፤ እመናብርቲሆሙ ኣዕበዮሙ ለትሑታን
ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን። ወፈነዎሙ
የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ዕራቆሙ ለለብዑላን ወተወክፎ ለእስራኤል
የተራቡትንም በቸርነቱ አጠገባቸው፤ ቍልዔሁ ወተዘከረ ሣህሎ ዘይቤሎሙ ለአቢዊነ
ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው፤ ለአብርሃም ወለዘርዑ እስከ ለዓለም።
ምሕረቱን እንዲያስብ እስራኤል ባሪያውን
ተቀበለ። ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩም
እስከዘለዓለሙ ድረስ እንደተናገረው።

የመቁጠሪያ ጸሎት

መቁጠሪያ በትኩረትና በተመስጥኦ አምልኮ የሚቀርብበት እንዲሁም ትሩፋት የሚሰራበት ንዋየ


ቅዱስ ነው። ምዑመናን መቁጠሪያን ተጠቅመው ጽሎትን በማቅረብ፣ ስግደትን በመስገድ፣ አፈር
የሆነውን ኃጥያተኛ ስጋቸውን በመጎሰምም አምልኮ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ፵፩ የመቁጠሪያ ፍሬዎች
ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል የተገረፋቸውን ፴፱ ግርፋት፤ ፩ም በጦር የተወጋውን ጎኑን፤
፩ም በእራሱ ላይ የተጫነውን የእሾህ አክሊልን ተደምረው ያመላክታሉ። መቁጠሪያ ከዚህ ተጨማሪ
፷፬ ፍሬዎች የእመቤታችንን እድሜ ለማመላከት ወይም ፻፳ ፍሬዎች የኃዋርይቱን ቤተሰብ ቁጥር
ለማመላከት ሊኖረው ይችላል። ከዝህም በላይ እጥፍ ፍሬዎች ያላቸውን መቁጠርያ በአብያተ
ክርስትያናት እና በገዳማት ያሉ መነኩሳን ተጠቅመው ይዘክሩበታል። እንግዲህ በ ፵፩ ፍሬ መቁጠሪያ
መቅረብ የሚችሉት የተመስጦ እና የምጻኔ ጸሎታት ይህንን ይመስላሉ፦

፩. አባታችን ሆይ ከእመቤታችን ሆይ ጸሎት ጋር (የዘወትር ጸሎት ፫ እና ፬)፦ ፲፪ ጊዜ

፪. ሰላም ለለኪ ከጸሎተ እግዚተነ ማርያም ጋር (የዘወትር ጸሎት ፱ እና ፲)፦ ፯ ጊዜ

፫. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ (አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ)፦ ፲፪ ጊዜ

፬. በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ (በእመቤታችን ማርያም ስም፤ ክርስቶስ ሆይ


ማረኝ)፦ ፵፩ ጊዜ

፭. ኪርያላይሶን (አቤቱ ጌታዬ ሆይ ማረኝ)፦ ፵፩ ጊዜ

፮. አምስቱን ቅንዋተ መስቀል (ችንካረ መስቀል) እያሰቡ ፵፩ ጊዜ ማለት። እነሱም፦


● ሳዶር(ቀዳማዊ)፦ አምላካችን ክርስቶስ በተሰቀለበት መስቀል መሃል ላይ በቁም እና

በአግድም ያሉትን እንጨቶች የቸነከሩበት ቅንዋት(ችንካር) ነው።


● አላዶር(ሁለተኛ)፦ አምላካችን ክርስቶስ ቀኝ እጁ የተቸነከረበት ነው።

● ዳናት(ሦስተኛ)፦ አምላካችን ክርስቶስ ግራ እጁ የተቸነከረበት ነው።

● አዴራ(ዐራተኛ)፦ አምላካችን ክርስቶስ ሁለቱ እግሮቹ በአንድ ላይ የተቸነከሩበት ነው።

● ሮዳስ(አምስተኛ)፦ ጲላጦስ በማላገጥ የአምላካችን ክርስቶስ መስቀል አናት ላይ “እየሱስ

ናዝራዊ፤ ንጉስ አይሁዳዊ” ብሎ ያጻፈው ጽሁፍ የተቸነከረበት ነው።

፯. ኦ አምላክ፦ ፵፩ ጊዜ

፰. ኦ ክርስቶስ፦ ፵፩ ጊዜ

፱. ኤሎሄ (አምላኬ)፦ ፵፩ ጊዜ

፲. እግዚኦ ከመአቱ ሰውረን በምህረትህ ታደገን፤ በእንተ ማርያም ወዲተ፦ ፵፩ ጊዜ

፲፩. ስማአነ አምላክነ ወመዳኒነ (ስማኝ አምላኬ እና መድሃኒቴ)፦ ፵፩ ጊዜ

፲፪. ዬዬ አምላክ ሆይ ተመልከተኝ ታረቀኝ፦ ፵፩ ጊዜ

፲፫. አምለክ ሆይ፤ እንደምህረትህ እንጂ እንደ ህጥያታችን አይሁን፦ ፵፩ ጊዜ

፲፬. እግዚኦ ተዘከረነ በውስትከ መንግሥትከ (ጌታ ሆይ በመንግሥትህ ውስጥ አስበን)፦ ፵፩ ጊዜ

You might also like