Professional Documents
Culture Documents
ምዕራፍ ስድስት
፩- የቅዱሳት ሥዕላት ትርጉም፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት እና ትውፊት ቅዱሳት ሥዕላት
ማለት፤ በአብያተ ክርስቲያናት ግድግዳ፡ በሸራ፡ በብራና፡ በወረቀት እና በመስቀሎች ላይ በቀለም ወይም
በጭረት ባለ ሁለት ጎን (two dimensional) ሆነው የሚሠሩ የልዑል እግዙአብሔርን፡ የእመቤታችንን፡
የቅዱሳን መላዕክትን፡ የጻድቃንን እና የሰማዕታትን ማንነት የሚገልጥ መንፈሳዊ ጥበብ ነው። ሥጋዊውን
ዓለም ከሚያንጸባርቁ መንፈሳዊ መልዕክት ከሌላቸው ሌሎች ሥዕላት ፈጽመው ስለሚለዩ ቅዱሳን
ሥዕላት ይባላሉ።
ነገር ግን በቅድስት ስላሴና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሚደረገው ፀዳለ ብርሃን የእግዙአብሔር
ቅድስና የባህርይው መሆኑን እንደሚገልፅ መረዳት ያስፈልጋል።እኔ እግዙአብሔር አምልካችሁ ቅዱስ ነኝና
እናንተም ቅዱሳን ሁኑ እንዲል። (ሌ 19፡2፣ 1ዼጥ 1፡15-16)
በአጠቃላይ ሥዕሎቻችን በኪነ ጥበብ ርፍ የተለመደውን የተለያዩ ህዋሳተ አካልን ትክክለኛ መጠን
ላይጠብቁ ይችላሉ።ይህ የሚሆነው ደግሞ ሥዕላቱ ውክልና ሃይማኖታዊ ምልክቶች በመሆናቸው፤
አንድም ሥዕላቱ የሚሳሉት ቅዱሳን ይህንን ይመስላሉ ይህንን ያክላሉ ለማለት አይደለምና ፤አንድም
የሚያስተዋዉቁን ከመንፈሳዊው ዓለምና ጣዕመ ጻጋ ጋር እንጂ ከምድራዊው ዓለም ጋር ባለመሆኑ ነው።
በመሆኑም በቅዱሳት ሥዕላቱ ላይ ሊተላለፍ የተፈለገውን ልዩና ጥልቅ መንፈሳዊ መልክእክት በመረዳት
ተገቢውን አክብሮት መስጠት ይገባል። በቤተክርስቲያናችን ቀኖና መሰረት አብዚኛውን ጊዛ
የምንጠቀማቸው ቀለማት፦ ሰማያዊ፣ቀይ፣አርንጓዴ፣ቢጫና ነጭ ሲሆኑ ቀለማቱ ራሱን የቻለ
ምስጢር ወይም ትርጉም አላቸው ።
1) ሰማያዊ፦ ሰማያዊውን ሃብት ገንብ ለማድረግ በፈቃደ ነፍስ መመራትን ለማመልከት እንዲሁም
በመንፈስ ፍሬወች ፈቃደ ሥጋን በፈቃደ ነፍስ ድል ማድረጋቸውን፤አንድም ትህትናን ያሳያል። ቅዱሳን
በትሕትና ለመኖራቸው ማሳያ ነው ።በመሆኑም ይህ ቀለም መንፈሳችን በእምነት መንገድና በትህትና
የመንፈስ ፍሬዎችን ገንብ በማድረግ እንድንጓዜ ያስታውሰናል።
2) ቀይ፦ ሰማዕትነትን ያሳያል።ይህም ቅዱሳን ነፍሳቸውን ለመከራና ለሞት አሳልፈው ስለክርስቶስና
ስለቤተክርስቲያን ብለው መስጠታቸውን ለማመልከት ይህን ቀለም እንጠቀመዋለን።የመስዋዕትነት የነፃ
አውጭነት ምልክት ነው።ጌታችን በሸንጎ ፊት ቆሞ የለበሰው ልብስ ቀይ ሐር እንደነበር። (ማር 15፡16-17፣
ኢያ2፡18)
3) ቢጫ ፦ ይህ ቀለም እውነተኛነትንና ብርሃንነትን ይገልፃል።እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ እንዲል
(ማቴ5፡14) ከዙህ በመነሳት ቤተክርስቲያን የቅድስና ማዕረግ ላይ የደረሱትን ቅዱሳት እውነተኞችና
የዓለም ብርሃን ናችሁ ስትል በራሳቸው የብርሃን አክሊል በቢጫ አድርጋ ትሥላለች።
4) አረንጓዴ፦ ከልምላሜ ከፀደይ ጋር ስለሚያያዜ መንፈስዊ ትርጉሙ መታደስን አዲስ ሕይወትን፣
ድህነትንና ተስፋን ያሳያል።በዙህ መሰረት አረንጓዴነትና ሕይወት ተወራራሽ ይሆናሉ።
5) ነጭ፦ የድል አድራጊነት የንፅህና እና የፍጹምነት ምሳሌ ነው።ቅዱሳን ዓለምንና ምኞቱን ድል ያደረጉ
ልበ ንጹሃን በመሆናቸው ነጭ ልብስ ለብሰው ይሳላሉ።ነጭ ልብስ ለብሰዋል ፤ከአለቆቹም አንዱ "እነዙህ
ነጫጭ የለበሱት እነማን ናቸው? ከየት መጡ?" አለኝ።እኔም "አቤቱ አንተ ታውቃለህ" አልኩት። እርሱም
"እኒህ ከጽኑ መከራ ነጻ የወጡ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ያነጹ ናቸው።"አለኝ። መለኮታዊ
ክብርንም ያሳያል።ለምሳሌ በደብረታቦርና በትንሳኤ ሥዕሎች ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነጭ ልብስ
ለብሶ ይሣላል።
በትውፊታዊ አሣሣል ቅዱሳት ሥዕላት ድርሰት ላይ የቅዱሳኑ አቋማቸው (በሥዕሉ ላይ የሚገኝበት
ሥፍራ)የተወሰነ ነው።ለምሳሌ የስነ ስቅለት ሥዕል ከሆነ ጌታችን ቀይ ግልድም አድርጎ፤አንገቱን ወደ ቀኝ
አንብሎ፤አክሊሊ ሦክ እንደደፋ፤በቀኙ እመቤታችን በግራው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ሆነው።በእግረ
መስቀሉ አፅመ አዳም እንዲታይ ተደርጎ ይሣላል።
ምስለ ፍቁር ወልዳ ከሆነ ደግሞ እመቤታችን ጌታን ታቅፋ ከተሳለች በኋላ በግራ በቀኝ ቅዱስ ገብር ኤልና
ቅዱስ ሚካኤል ይሣላሉ።ሆኖም ግን ይህ ሁሉም የሥዕል ድርሰት ላይ የቅዱሳን አቋማቸው የተወሰነ ነው
ማለት ግን አይደለም።ስለዙህ ቅዱሳት ሥዕላት ከላይ የተጠቀሱትን ቀኖናን ተከትለው ይሣሉ ንድ
ይገባል።
ምዕራፍ ሰባት
1. ሥርዓተ ጥምቀት
ጥምቀት የሚለውን ቃል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ሲተረጉሙ ‚ጥምቀት‛ በቁሙ፡- ‚ማጥመቅ፣
መጠመቅ፣ አጠማመቅ፣ ጠመቃ፣ የማጥመቅና የመጠመቅ ሥራ፣ ኅፅበት፣ በጥሩ ውኃ የሚፈጸም‛
በማለት ተርጉመውታል።
ጥምቀት አንድ ምዕመን እንደገና ከመንፈስ ቅዱስ ልደት የሚያገኝበትና የቤተ ክርስቲያን አባል
የሚሆንበት የመጀመሪያው መግቢያ በር ነው። ምሥጢረ ጥምቀትን የመሠረተው ጌታችን አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በሰው ልጅ ላለማዊ ድኅነት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይው ሥርዓተ ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ
ቤተ ክርስቲያን በቀዳሚነት የሚፈጸምና የማይደገም ሥርዓት ነው። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ‚አንዲት
ጥምቀት‛ በማለት የሥርዓተ ጥምቀትን አለመደገም ገልጦ ተናግሯል (ኤፌ.፬፣ ፭)።
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመዜግቦ እንደሚገኘው፥ በቁስጥንጥንያ በ ፫፻፹፩ ዓ.ም. የተሰበሰቡ ፩፻፶
የሃይማኖት አባቶቻችን ‚ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት፣ ኃጢአትን በምታስተሠርይ
በአንዲት ጥምቀት እናምናለን‛ በማለት የጥምቀትን አንድ መሆንና ኃጢአትን በደልን የምታርቅ
ስለመሆኗ በእግዙአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናግረዋል፤ ሃይማኖታቸውንም ገልጠዋል።
የሥርዓተ ጥምቀትን ትርጉምና የመሠረተው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆኑ በአጭሩ
ከገለጽን፤ ጌታችን የተጠመቀው ለምንድር ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሣ ጌታችን እርሱ ባወቀ ጥምቀትን
የፈጸመበት ዋነኛ ምክንያቶች እንደ ሊቃውንት አባቶቻችን አስተምህሮ በሦስት መንገዶች ይታያል።
እነዙህም፦
ሐዋርያውም በጥምቀት ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ አስመልክቶ ሲናገር ‚አባ አባት ብለን የምንጮኸበትን
ወይም የምንጣራበትን የልጅነትን መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ
አልተቀበላችሁምና። የእግዙአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈስ ጋር ይመሰክራል‛ ብሏል
(ሮሜ.፰፣ ፲፭-፲፮)። ጌታችንንም ለተቀበሉት ሁሉ በስሙም ላመኑበት በጠቅላላው የእግዙአብሔር ልጆች
ይሆኑ ንድ ሥልጣንን ሰጥቷቸዋል። እነርሱም ከእግዙአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ
ወይም ከወንድ ፈቃድ አለመወለዳቸው ተገልጿል (ዮሐ.፩፣ ፩-፲፫)።
ስለዙህ ጌታችን ባስተማረው መሰረት ማንኛውም ሰው ወደመንግስተ ሰማያት መግባት ይችል ንድ
በሥርዓተ ጥምቀት ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድና የእግዙአብሔር ልጅ መሆን ይገባዋል። እንግዲህ
እኛ ክርስቲያኖች ሁለት ልደታት እንዳሉን እናስብ። ይኸውም የመጀመሪያው በሥጋ ከእናትና አባታችን
የተወለድነው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከእግዙአብሔር የምንወለደው ነው፡፡ ከተወለድን በኋላ እድገታችን
በሁለቱም ወገን መሆን ያስፈልገዋል። ሰው ሥጋዊም መንፈሳዊም ነውና። እንግዲህ በጥምቀት ያገኘነውን
ጸጋና ክብር ሁላችን ልናስብ ያስፈልገናል። ይህንንም ክብራችንን መጠበቅ ያሻናል።
በኦሪት ይደረግ የነበረው ሥርዓት ለሐዲስ ምሳሌ በመሆኑ በዙሁ በኦሪት ልማድ መሰረት ልጆችም
እንደየጾታቸው በ ፵ እና በ ፹ ቀን በመጠመቅ የጸጋ ልጅነት ያገኛሉና ነው (ሌ ፲፪፣ ፩=፰፤ ሉቃ ፪፣ ፳፪)።
ሐዋርያትም በአገልግሎት መናቸው የክርስቶስን ትምህርት በመከተል የእድሜ ልዩነት ሳያደርጉ ሕዜብን
ሁሉና በአንድ ቤት የሚገኙ የቤተሰብ አባላትን በሙሉ ያጠምቁ ነበር (የሐዋ ፲፣፴፫ ፤ ፩ቆሮ ፩፣፲፮)
4. የህፃናት ጥምቀት
የሕፃናት የ40 ቀንና የ80 ቀን ጥምቀት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለሚስጥረ ጥምቀት አፈጻጸም ብርቱ
ጥንቃቄ ታደረጋለች፡፡ ሰው ሁሉ በጥምቀት አማካኝነት የሚሰጠውን ጸጋ እንዲያገኝ አሰፈላጊውን ጥረት ሁሉ
ትፈጽማለች፡፡ ሰዎች ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ በማለት ሕጻናትን የምታጠምቀው በቅዱሳት መጸሕፍት
በተረዳችው መሠረት እንደሆነ ከዙህ ቀጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡
መጽሐፈ ኩፋሌ፡- 4፡9 ከተፈጠረባት ምድር ለአዳም አርባ ቀን ከተፈጸመለት በኃላ ይገዚትም ይጠብቃትም
ንድ ወደ ገነት አሰገባው፡፡ ሚስቱንም በሰማንያ ቀን አሰገባት፡፡
ይላልና ለአዳምና ለሔዋን ንጹሕ ጠባይዕ ሳይድፍባቸው ከመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ልጅነት ተቀብለው በ40ና
በ80 ቀን ገነት እንድገቡ ዚሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እግዙአብሔር መጀመረያ በሠራው ሥራዓት መሠረት
በአዳም አለመታዜ ምክንያት የተወሰደውን ልጅነት ለማሰመለሰ ሕጻናት ወንዶችን በ40 ቀን ሕፃናት
ሴቶችን በ80 ቀን ዕድሜያቸው ታጠመቃለች፡፡
ግዜረት የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናት በተወለዱ በስምነተኛው ቀን ይገረዘ ነበር፡፡ (ፍ ፡- 17፡12)፡፡
እንግዲህ ሕፃናቱ የሚገረዘት በወላጆቻቸው እምነት እንጅ እነርሱ ዐውቀው ግረዘን ብለው አይደለም፡፡
የእስራኤል ቀይ ባሕርን ማቋረጥ የጥምቀት ምሳሌ መሆኑ በ1ቆሮ 10፡2 የተገለጸ ስሆን ባሕሩን ያቋረጡት
ዐዋቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ሕፃናትም ጭምር ናቸው፡፡ ከባርነት ከፈርዖን አገዚዜ ነፃ የወጡት ሕፃናቱም ጭምር
ናቸው፡፡ እስራኤል ከቡኩረ ሞት የዳኑበት የአንድ አምት ጠቦት በግ ደግሞ ምሳሌነቱ የጌታ መሆኑ የተወቀ
ስሆን በዙያን ጊዛ በበጉ ደም አማካኝነት ከሞት የዳኑት የታዘትን እሺ ብለው የፈጸሙት ዐዋቂዎች ብቻ
ሳይሆኑ የእነርሱም ልጆቹም ጭምር ናቸው፡፡ እንግዲህ በወላጆቻቸው እምነት ሕፃናቱ መዳናቸውን
ልናሰተውል ይገባል፡፡
ስለሆነም ቤተ ክርስቲያናችን ሕፃናትን ማጥመቋ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከቀደሙት አበው ባገኘችው ትምህርት
መሠረት ነው፡፡
1) አዳምና ሔዋን በተፈጠሩ በ40 እና በ80 ቀናቸው ወደ ገነት መግባታቸው (ኩፋ 4፡9)፡፡
2) እስራኤል መስዋዕት ይው በ40 እና በ80 ቀን ወደ ቤተመቅደስ እንዲመጡ መታዚቸው (ሌ 12፡
1-8)፡፡
3) በኦሪቱ ሕፃናትም አዋቂዎችም ተገርው የተስፋው ወራሾች ነበሩና ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው
(ፍ 17፡1-5 ቆላ 2፡11-12)፡፡
4) በባህረ ኤርትራ የተሸገሩት ሕፃናትም ጭምር ነበሩና ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው (1ኛ ቆሮ 10፡1-
2)፡፡
5) ወደ ኖኅ መርከብ የገቡት መላው ቤተሰብ ነውና ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው (ፍ 7፡1-17 1ኛ ጴጥ
3፡20-22)፡፡
6) ሕፃናት በማኅፀን ሳሉ መንፈስ ቅዱስ ከሞላባቸው ሲወለዱ እንዳይጠመቁ የሚከለክለቸው ምንድን
ነው (ሉቃ 1፡15 ኤር 1፡4-5)፡፡
7) ሐዋርያትም ካስተማሩ በኋላ ቤተሰቡን ሙሉ ያጠምቁ ነበር (ሐዋ 10፡44-48 11፡13-14 16፡15 16፡
43)፡፡
8) ጌታችንም “ሰው ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ…” ያለው ሕፃናትንም ይመለከታል
(ዮሐ 3፡8)፡፡
9) ጌታችንም “ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ንድ አትከልክሏቸው” ብሏል (ማቴ 19፡14)፡፡
በአንዳንዶች ንድ የሕጻናት ጥምቀት ለዳግም ልደት ወይስ ለጥንተ አብሶ ስርየት? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡
በዙህ ላይ የጥንተ አብሶ ትርጉም ጋር በተያያ የተለያየ አመለካከት አለ፡፡ አንዳንዶች የሕጻናት ጥምቀት
ጥንተ አብሶን ለማጥፋትና ልጅነትን ለማግኘት ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በጥንተ አብሶ ምክንያት
የተጎዳውን የሰውን ባህርይ ለመጠገንና ልጅነትን ለማግኘት ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ጥንተ አብሶ
በክርስቶስ ጠፍቶልናል፤ የሕጻናት ጥምቀት ለዳግም ልደት ብቻ ነው ይላሉ፡፡ በአጠቃላይ ግን ሕጻናት ዳግም
ልደትን ያገኙ ንድ መጠመቅ እንዳለባቸው ሁሉም ይስማማል፡፡
6. የጥምቀት አፈጻጸም
ተጠማቂው ንዑሰ ክርስቲያን ከሆነ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርቶችን ተምሮ እምነቱ የተመሰከረለት
መሆን አለበት። ሕጻናት የሆኑ እንደሆኑ ግን ለሕጻናቱ የክርስትና እናትና አባት ሊሆኑ የመጡት ሰዎች
ስለሕጻናቱ እምነት መስክረውላቸው እንዲጠመቁ ይደረጋል። በሚጠመቅበት ጊዛ በውሃ ውስጥ ሶስት ጊዛ
ብቅ ጥልቅ ማለት አለበት ፤ የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ምሳሌ ነውና። ተጠማቂው የሚጠመቀው በአብ
በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው (ማቴ 28 ፥ 19)። ተጠማቂዎች ባለትዳሮች ከሆኑና ቤተሰብም
ካላቸው ሁሉም ተምረው አምነው በአንድነት መጠመቅ አለባቸው። ከተጠመቀ በኋላ መቁረብ (ቅዱስ
ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል) ይገባል። ይህ ካልሆነ ጥምቀቱ ሕያው አይሆንም። እንዲያጠምቁ
ስልጣን ያላቸው ከክህነት ደረጃዎች ውስጥ ኢጲስቆጶስና ቀሳውስት ብቻ ናቸው፡፡ ይህም ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማጥመቅ ስልጣንን የሰጠው ለአስራ አንዱ ሐዋርያት ብቻ ስለሆነ ነው
(ማቴ 28፡19)፡፡ ዲያቆናት እንዲያጠምቁ አልተፈቀደላቸውም (ማቴ 28፡19 እና ፍት ነገ አንቀጽ 3)።
ክህነት በሌለው ሰው የተከናወነ ጥምቀት እንደ እጥበት እንጂ እንደ ጥምቀት አይቆጠርም፡፡ በዙህ
መንገድ ‚የተጠመቀ‛ ሰው ልጅነት የምታስገኘዋን እውነተኛዋን ጥምቀት መጠመቅ አለበት፡፡
12)‛ በሚለው ቃል ውስጥ መቀበር መቃብር ውስጥ መግባትን፣ ትንሣኤ ደግሞ ከመቃብር መውጣትን
እንደሚያመለክት ጥምቀትም በውኃ ውስጥ ገብቶ (በመነከር) መውጣትን ይጠይቃል፡፡
በአራቱም ወንጌላት የጌታችን ጥምቀትም በውኃ ውስጥ ገብቶ በመውጣት መሆኑ ተጽፏል፡፡ ‚ኢየሱስም
ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዙአብሔርም መንፈስ እንደ
ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ (ማቴ 3፡16)‛ በሚለው ቃል ውስጥ ‚ከውኃ ወጣ‛ የሚለው
የጌታችን ጥምቀት የተከናወነው በመነከር እንደነበር ያሳያል፡፡ በተጨማሪም በሥጋ መወለድ በእናት
ማኅፀን ውስጥ ቆይቶ መውጣትን የሚያመለክት እንደሆነ ሁሉ ‚ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድም‛
እንዲሁ ውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣትን (መነከርን) ይጠይቃል፡፡ ስለዙህም ነው ጥምቀት ‚ዳግመኛ
መወለድ‛ የተባለው (ዮሐ 3፡3)፡፡ ዋና ዋናዎቹ የምሥጢረ ጥምቀት አፈጻጸም ሥርዓትን የሚመለከቱ
ነጥቦች ከዙህ በታች የተረሩት ናቸው፡፡
1) ንዑሰ ክርስቲያን የሚጠመቁት የትንሣኤ ዕለት ከሆነ ተገቢውን ትምህርት ቀድመው ተምረውና
ንስሐ ገብተው በሰሙነ ሕማማት ሐሙስ ልብሳቸውን አጋጅተውና ሰውነታቸውን ታጥበው በመጾም
ቅዳሜ ሌሊቱን እሑድ ይጠመቃሉ፡፡ በሌላ ቀን ከሆነ ደግሞ በዋዛማው ታጥበውና ጾመው ይጋጁና
የመቁረቢያ ልብሳቸውን በንጽሕና አጋጅተው በዕለቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደው ይጠመቃሉ፡፡
2) ኤጲስ ቆጶሱ (ቄሱ) የሚጠመቁትን ሰብስቦ ራሳቸውን ወደ ምሥራቅ እንዲያነብሉ ያዚቸዋል፡፡
እጁንም በላያቸው ርግቶ ይጸልይላቸዋል፡፡
3) መሐላውን አስምሎ ማለትም ሰይጣንን አስክዶና ክርስቶስን አሳምኖ ከፈጸመ በኋላ በዐራቱም
መዓን ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሰግዶ በፊታቸው ላይ እፍ ይልባቸዋል፡፡ አካላቸውንም
አማትቦ ይባርካል፡፡
4) ጥምቀቱ በትንሣኤ ከሆነ በዶሮ ጩኸት ጊዛ፤ በሌላ ቀንም ከሆነ መጠመቂያው ሰዓት ሲደርስ
ተጠማቂዎችን በመካነ ጥምቀቱ ያቆማቸዋል፡፡ ያውም ካልሆነ ካህኑ ማዩን እንደ ገበቴ በተሰራ ብርት
አድርጎ ሥርዓተ ጸሎቱን ያደርሳል፡፡
5) ከሰይጣን ቁራኝነት በሚለይበት በቅብዓ ቅዱሱ ላይ ጸልዮ ለተራዳኢው ቄስ ይሰጥና ከተጠማቂዎች
በስተግራ ያቆመዋል፡፡
6) ልጅነት በሚያሰጠውና መንፈስ ቅዱስን በሚያሳድረው በሜሮኑ ላይ ይጸልይና ለሁለተኛው ቄስ
ሰጥቶ ከተጠማቂዎች በስተቀኝ ያቆመዋል፡፡
7) ተጠማቂዎችን በማዜ ፊታቸውን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ
ይመልሳቸውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ማመናቸውን ያረጋግጣል::
8) አንዱ ቄስ የተጠማቂዎችን እጅ እየያ ሕፃናትም ከሆኑ ዲያቆኑ (ቄሱ) አቅፎ ከምዕራብ ወደ
ምሥራቅ ይመልሳቸዋል፡፡ ይህም ሰይጣንን ክደው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ማመናቸውን በምሳሌ የሚያረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡ ምዕራብ የማኅደረ ዲያብሎስ ምሥራቅም
የማኅደረ ሥላሴ ምሳሌዎች ናቸውና፡፡ (ነጽሩ ውስተ ጽባሕ….)
9) ከዙህ በኋላ ቅብዐ ቅዱሱን ቀብቶ ያጠምቃቸዋል፡፡ ሲያጠምቃቸውም ልብሳቸውንና ማንኛውንም ጌጣ
ጌጥ አውልቀውና ሴቶችም ሹርባቸውን ፈትተው ነው፡፡ ከዙያም በመጠመቂያው ፫ ጊዛ ብቅ ጥልቅ
ያደርጋቸዋል፡፡ ምቹ መጠመቂያ ከሌለም ማዩን በላያቸው ላይ ሦስት ጊዛ እያፈሰሰ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቅሃለሁ/ሻለሁ/፤ እያለ ያጠምቃቸዋል፡፡ ከመጠመቂያው በወጡም ጊዛ
በንፍሐት ልጅነትን ያሳድርባቸዋል፡፡
10) ሴት በምትጠመቅበት ዕለት የወር አበባ (ግዳጅ) ከመጣባት እስክትነጻ ሳትጠመቅ ትቆያለች፡
11) ተጠማቂዎች መናገር ከቻሉ ራሳቸው፤ ካልቻሉም የክርስትና አባት (እናት) የሆኑት ክርስቲያኖች
የተጠማቂውን አውራ ጣት ይው ጸሎተ ሃይማኖትን በማንበብ ሃይማኖታቸውን ይመሰክራሉ፡፡
12) ሥርዓተ ቅዳሴውን አድርሰው፣ መጽሐፈ ክርስትናውን ደግመው ማዩን ከባረኩ በኋላ ነው ማጥመቅ
የሚጀምሩት፡፡ የ፵ እና የ፹ ቀን ሕፃናት ከተጠመቁ በኋላ ንዑሰ ክርስቲያን ወንዶችና ሴቶች
ይጠመቃሉ፡፡በሚያጠምቁበትም ጊዛ ‚አጠምቀከ/ኪ በስመ አብ፣ አጠምቀከ/ኪ በስመ ወልድ፣
አጠምቀከ/ኪ በስመ መንፈስ ቅዱስ፤ ስምከ/ኪ ይኩን እገሌ/ሊት‛ በማለት ሲሆን አስቀድመው
መስቀል ግንባሩ ላይ አድርገው የሰየሙትን ስመ ክርስትና የሚያጸኑት በዙያው ሰዓት ነው ማለት
ነው፡፡
13) ከተጠመቁ በኋላ ካህኑ ሜሮን ይቀባቸዋል፡፡ የተጋጀላቸውን ነጭ ልብስ ለብሰው ቅዳሴ አስቀድሰው
ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉ፡፡ በሜሮን ከከበሩም በኋላ ሦስት ኅብረ ቀለማት ያሉት ማተብ
ይታሰርላቸዋል፡፡ ኅብረ ቀለማቱም ነጭ፣ ቀይ፣ ጥቁር(ቢጫ) ናቸው፡፡ ምሳሌነት አለው በአንድ
መገመዱ የሥላሴን አንደነት ሦስተ መሆኑ……
14) የክርስትና አባት/እናት አብረው ጾመውና ተገቢውን ዜግጅት አድርገው በዕለቱ ሥጋውን ደሙን
ይቀበላሉ፡፡
15) በዕለቱ ክርስትና የተነሡ (የተጠመቁ) ሕፃናትና ንዑሰ ክርስቲያን የነበሩ አዳዲስ የቤተ ክርስቲያን ልጆች
ከሌሎች ቆራብያን አስቀድመው ቅዱሱን ቊርባን ይቀበላሉ፡፡
16) ወንዶች ሴቶችን፣ ሴቶችም ወንዶችን ክርስትና አያነሡም፡፡
17) የምትጠመቀዋ ንዑሰ ክርስቲያን ሴት ከሆነች ቅብዓ ቅዱሱንም ሆነ ሜሮኑን ኤጲስ ቆጶሱ/ቄሱ/ ልብስ
እንደለበሰች ከአንገት በላይ ከቀባት በኋላ ዓይኑን ተሸፍኖ ወይም በመጋረጃ ተጋርዶ ዲያቆናዊት
ማለትም ዕድሜዋ የገፋ ከስልሳ ዓመት በላይ የሆነችና የምታገለግል መነኩሲት እጁን ይዚ እየመራቸው
ሌሎቹን ሕዋሳት ይቀባታል፡፡
18) የተጠማቂዎችን ራስ የሚያጠልቅ ማይ (ውኃ) በቤተ ክርስቲያን የማይገኝ ከሆነ ማዩን በእጁ እየታፈነ
(እየገነ) በሥላሴ ስም ያጥምቃቸዋል፡፡
2. ሥርዓተ ሜሮን
ቅብዐ ሜሮን በዋነኛ ምሥጢራዊ አገልግሎቱ ከምሥጢረ ጥምቀት አፈጻጸም አይለይም፡፡ በእኛ
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ከላይ እንደገለጥነው የሜሮን አቀባብ ወዲያ ከጥምቀት አያይዝ
ይፈጸማል፡፡
ይህም ማለት ተጠማቂው ሰው ጥምቀት ከተፈጸመለት በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ጥምቀቱን
እንደተቀበለ ሜሮን ይቀባል፡፡ ሜሮን ሲቀባም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቁን፣ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ
መወለዱንን፣ መንፈስ ቅዱስን እንዳደረበት ይረጋገጥለታል፡፤ ተጠማቂው ተጠምቆ ሜሮን መቀባቱ
መንፈስ ቅዱስን መቀበሉን ያመለክታል፡፡
የአቀባቡም ሥርዓት የተጠመቀው ሕጻን እንደኾነ በክርስትና ዋሱ እቅፍ እንዳለ ይቀባል፡፡ አዋቂ እንደኾነ
ከማጥመቂያው ወጥቶ እንደቆመ ቄሱ ሜሮኑን በአውራ ጣቱ እየጠለፈ ‚እቀብአከ በስመ አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ እያለ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በትዕምርተ መስቀለ ያትመዋል፡፡
ቅብዐ ሜሮኑን በአውራ ጣቱ እየጠቀሰ (እያስነካ) በትእምርተ መስቀል አምሳል እቀብዐከ በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እያለ ተጠማቂውን ይቀባዋል፡፡ በሥርዓተ ጥምቀት እንደገለጽነው ንዑሰ
ክርስቲያን ሴት ከሆነች ልብስ ለብሳ ከአንገቷ በላይ ኤጲስ ቆጶሱ (ቄሱ) ይቀባታል፡፡ በኋላም ከአንገት በታች
ያሉትን ቀሪ ሕዋሳት ጳጳሱ ወይም ቄሱ ተጋርዶ (ተሸፍኖ) ዲያቆናዊት የቄሱን እጅ ይዚ እየመራች ይቀባታል፡
፡ የተጠማቂው ፴፮ቱ ሕዋሳት በሜሮን ሲከብሩ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን የአቀባባቸው ቅደም ተከተል
የታወቀ ነው፡፡ ከላይ እንደገለጽነው ሁሉም በትእምርተ መስቀል አምሳል የሚታተሙ (የሚቀቡ) ናቸው።
3. ሥርዓተ ቁርባን
ቁርባን የሚለው ቃል መሠረቱ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የመጣ ሲሆን ‚ስጦታ‛ የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡
ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ ደም ሲሆን
አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህም ማለት እንደ ኦሪቱ
ቁርባን ሰው ለእግዙአብሔር ያቀረበውን ስጦታ ብቻ የሚያመለክት ሳይሆን እግዙአብሔርም በተለየ
ሁኔታ ለሰዎች ደኅንነት ለዓለም ሁሉ የሰጠውን በሥጋና በደም የመጣውን የልጁን ስጦታ ያስገነዜባል።
ቁርባን ማለት በአንድ በኩል ለእግዙአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በሌላ በኩል ደግሞ እኛ ወደ
መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዛ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና
ለእግዙአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር፡፡ መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና
ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡
መነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው
ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት
ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳሌ ሆነው አልፈዋል፡፡ በሐዲስ ኪዳን ግን አማናዊው ቊርባን
(መሥዋዕት) ሰዎች የሚያቀርቡት (የሚሰጡት) መባዕ ሳይሆን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ዓለሙን ለማዳን
በቀራንዮ ዐደባባይ በአባቱ ፈቃድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ፣ በራሱም ፈቃድ በመስቀል ላይ ለዓለሙ ሁሉ
ያቀረበው (የሰጠው) ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡
የምሥጢረ ቁርባን አመሠራረት
ምሥጢረ ቁርባንን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕማማቱና ከሞቱ በፊት በዋዛማው ኀሙስ ማታ
መሥርቶታል፡፡ ይህም ሰዓት በአይሁድ የቀን አቆጣጠር ወደ ዓርብ ይታሰባል። መጀመሪያ የሥጋውና
የደሙን ምሥጢር ሲያሳይ እንዲህ ነበር ዓልአዚር በተባለው ሰው ቤት ጌታችን ከደቀ መዚሙርቱ ጋር
መጀመሪያ የኦሪትን መሥዋዕት ሠውቶ በልቷል።
ወዲያው የበሉትን የኦሪት መሥዋዕት በተአምራት ከሆዳቸው አጥፍቶ ሰዎች ለእራት ካመጡለት ኅብስት
አንዱን አንሥቶ ያና ወደ አባቱ ጸለየ። ኅብስቱንም በሥልጣኑ ለውጦ ሥጋውን አድርጎ ይህ ስለ እናንተ
የሚሰጥ ሥጋዬ ነውና እንኩ ብሉ ብሎ ለደቀ መዚሙርቱ ሰጣቸው መታሰቢያዬንም ይህ አድርጉት ብሎም
አስተማራቸው። ቀጥሎም ወይን በጽዋ ቀድቶ ያና ጸለየ ወይኑንም ለውጦ ደሙ አድርጎ ይህ ስለእናንተ
የሚፈስ ደሜ ነው እንኩ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው፤ ሉቃ. ፳፪፥ ፲፱–፳ ማቴ. ፳፮፥ ፳፮ ማር. ፲፬፥ ፳፪
የኦሪትን መሥዋዕት አሳልፎ መሥዋዕተ ወንጌልን መሥርቷል።
በዙያችም ምሽት የኦሪቱን በግ መሥዋዕትነት አበቃ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እውነተኛው የእግዙአብሔር በግ
ይሠዋል። እርሱም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው። ስለዙህ በማዕዱ ዘሪያ ለተሰበሰቡት ሐዋርያቱ በብሉይ
ኪዳን ምሳሌ የተመሰለለትን: ትንቢት የተነገረለትን አዲሱን ቃል ኪዳን ጌታ በራሱ ሥጋና ደም መሠረተ።
‚ኢየሱስ እንጀራና ኅብስትን አንስቶ ባረከ። ቆርሶ ለደቀመዚሙርቱ ሰጠና እንካቹ ብሉ፤ ይህ ሥጋዬ ነው
አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው። እንዲህም አለ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ
ብዘዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው‛ በማለት ምሥጢረ ቁርባንን
መሠረተ /ማቴ ፳፮፣፳፮-፳፰/።
ኪዳን ማለት ከእግዙአብሔር ጋር የምንገባው ቃል ኪዳን የሚያመለክት ነው። ‚እውነት እውነት እላችኋለሁ
እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤
የእግዙአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው። ዮሐ. ፮፥
፴፪–፴፫ በመቀጠልም ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ
ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ
ሕያው ይሆናል። ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን
እንጀራ የሚበላ ለላለም ይኖራል፡፡ ዮሐ. ፮፥ ፶፭–፶፰ ጌታችን ይህን ነገር በቃሉ
ሲነግራቸው መጀመሪያ ለሰሙት ሰዎች በሥራ እስኪያሳያቸው ድረስ ሊታመን የማይችል ረቂቅ ነገር ነበር።
4. ሥርዓተ ቅዳሴ
ቅዳሴ ማለት መቅስ፣አቀዳደስ፣ቀደሰ፣ቡራኬ፣ምስጋና የቁርባን ጸሎት ማለት ነዉ፡፡ ከምስጢረ ቁርባን ጋር
የተያያ ሲሆን ለሌሎች ምስጢራትመ የሚስጢርነታቸዉ ማረጋገጫ ማኅተም ነዉ፡፡ምክንያቱም ያለሥጋ
ወዳሙ ምስጢራቱ ምሉዕ ሊሆኑ አይችሉምና፡፡
ሥርዓተ ቅዳሴ ሦስት ክፍሎች አሉት
1. የዝግጅት (ግባተ መንጦላዕት) ፡- የሚቀርበዉ ጸሎት ከመጋረጃ ዉጭ በመቀረደስ አፍኣ
የሚጸለይ ነዉ፡፡ ሚመጠን ግርምት ዚቲ ዕለት እስከሚለዉ የሚያካትት ነዉ፡፡ የዜግያ ልዑካኑና
(ሰሞነኞቹን) ብቻ የሚመለከት ነዉ፡፡
"ዲያቢሎስ ያሳሳታት ሔዋንን ነጻ አወጣት" (የሰኞ ዉዳሴ ማርያም) "ሔዋን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ
ነፍስ ነፃ ካደረጋት ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋዉን ክብሩን
እንዳይነሳን ለምኝልን አዕምሮዉን ጥበቡን ሣይብን አሳድሪብን" ቅዱስ ኤፍሬም በቅዳሴ ጊዛ የሚስቅ
ሰው ቅዱስ ባስልዮስ በጻፈው በ፸፪ኛው አንቀጽ ካህን ቢሆን የሚያቀብል ነውና ሥጋ ወደሙን ከተቀበለና
ካቀበለ በኋላ ወጥቶ አንድ ሱባዔ ይቀጣ ይጹም ይስገድ፣ የሳቀው ሕዜባዊ ቢሆን ግን ሥጋ ወደሙን
ሳይቀበል ያን ጊዛ ፈጥኖ ይውጣ ይላል።
ምነው ፍርድ አበላለጠ ካህኑን ተቀብሎ ወጥቶ ይቀጣ አለ፤ ሕዜባዊውን ሳይቀበል ወጥቶ ይሂድ
አለ ቢሉ ካህኑ የሚቆመው ከውስጥ ነው ሲስቅ የሚያየው የለም። ካህኑ በቅዳሴ ጊዛ ቅዳሴውን ጥሎ
ወጥቶ ሲሄድ ባዩት ጊዛ ቄስ እገሌ አባ እገሌ በመሥዋዕቱ ምን አይተውበታል ብለው መሥዋዕቱን
ሳይቀር ይጠራጠሩታል፤ ስለዙህ ነው። ምዕመኑ ግን ሲስቅ ሁሉ ያየዋልና ለሌላ መቀጣጫ እንዲሆን፤
በቤተ መቅደስ የማይወደድ ሌላ ነገር አይናገር፤ በቤተ መቅደስ ጭንቅ፣ ደዌ ሳያገኘው አንዱን
ስንኳ ምራቁን እንትፍ አይበል። ነገር ግን ደዌ ቢያስጨንቀው ድምፅ ሳያሰማ ምራቁን በመሐረቡ
ተቀብሎ ያሽሸው።
እግዙአብሔር ሆነው የሚጸልዩባት የጸሎት ቦታ ናትና ቅዳሴው ሳይፈጸም አቋርጦ መውጣት አይቻልም፣
አይፈቀድም፣ በጣም ጭንቅ ምክንያት ወይም በሕመም ምክንያት ከሆን ግን ክቡር ወንጌል ከተነበበ
በኋላ ሊወጣ ይችላል።
በቅዳሴ ጊዛ ካህናት የሚቀድሱባቸው አልባሳት ነጫጭ ይሁን ነጭ ልብስ ደስ እንዲያሰኝ በሥጋ ወደሙ
የተገኘ ክብርም ደስ ያሰኛልና፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ባህርየ መለኮቱን በገለጸ ጊዛ ልብሱ እንደበረድ
ነጭ ሆኗል። መላእክትም ወርኃ ሰላም ወርኃ ፍስሐ ነው ሲሉ የልደት፣ የትንሣኤ፣ የዕርገት ነጫጭ
ልብስ ለብሰው ታይተዋል።
አንድ ሰው እንኳ ጫማ አድርጎ ከቤተ መቅደስ አይግባ ልዑል እግዙአብሔር የምትቆምባት ደብረ ሲና
የከበረች ናትና ጫማህን አውልቅ ብሎ ለሙሴ ተነግሮታልና። /ጸአት ፫-፭/። በቅዳሴ ጊዛ ተሰጥዖውን
የማያውቅ ደግሞ በአንክሮ፣ በተክሮ፣ በአንቃእድዎ፣ በንጹሕ ልቡና፣ በሰቂለ ሕሊና ሆኖ ሕሊናው
ወደ ዓለማዊ እንዳይወስደው መቆጣጠር አለበት።
ቅዱስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ ካህኑ ለሕዜቡ ተርጉሞ ይንገራቸው ያስተምራቸው እጁንም በሚታጠብበት
ጊዛ የተጣላችሁ ሳትታረቁ፣ የሰው ገንብ የወሰዳችሁትን ሳትመልሱ ሥጋ ወደሙን ብትቀበሉ ሥጋው
እሳት ሆኖ ይፈጃችኋል ደሙ ባህር ሆኖ ያሰጥማችኋል። ነገር ግን የወሰዳችሁትን የሰው ገንብ
መልሳችሁ፣ ከተጣላችሁት ታርቃችሁ ኃጢአት ብትሰሩ ንስሐ ገብታችሁ ብትቀበሉት ግን መድኃኒተ
ሥጋ መድኃኒተ ነፍስ ይሆናችኋል። በረከተ ሥጋውን በረከተ ነፍሱን ያድላችኋል ብሎ ይንገራቸው
ያስተምራቸው ይላል።
ካህኑ ሥጋ ወደሙን በፈተተበት እጁ ሕዜቡን ፊታቸውን ይባርካቸው። ቀሳውስት ግን እጅ በእጅ
ተያይው እርስ በርሳቸው ይባረኩ።
ቀዳሹ ካህን ቀሳውስትን ሲያሳልም ‚የጴጥሮስ ሥልጣን ባንተ አለ‛ ይበል፣ ተሳላሚው ቄስም
‚መንግሥተ ሰማያት ያውርስህ ከሾመ አይሻርህ‛ ይበል።
ለዲያቆናትም ‚ልዑል እግዙአብሔር ያክብርህ ይባርክህ፣ ለማስተማር ዓይነ ልቡናህን
ያብራልህ፣ ምሥጢሩን ይግለጥልህ‛ እያለ ይባርካቸው።
ለምዕመናንም ‚ልዑል እግዙአብሔር ያክብርህ፣ ይባርክህ፣ ገጸ ረድኤቱን ይግለጽልህ‛ እያለ
ይባርካቸው። ለሴቶችም ‚ልዑል እግዙአብሔር ይባርክሽ፣ ያክብርሽ ገጸ ረድኤቱን ይግለጽልሽ‛ ብሎ
በእጁ ይባርክ።
ከቅዱስ ቁርባን በፊትና በኋላ መደረግ ሥላለበት ሥርዓት
በጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደን መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ
/ዮሐ.3፥5/ የተጋጀን ክርስቲያኖች ሕያዋን እንሆን ንድ ወትር መንፈሳዊውን መብል ቅዱስ ሥጋውንና
ክቡር ደሙን መቀበል አለብን። ዮሐ.6፥26።
ሥጋዊ መብልና መጠጥ ወትር እንደሚያሻን ሁሉ አምላካችንንም ወትር እንድንሻው ቅዱስ ሥጋውንና
ክቡር ደሙን በሚበላና በሚጠጣ ሰጥቶናል። ዮሐ.6፥3 ስለዙህም ምዕመናን ወትር ከቅዱስ ሥጋውና
ከክቡር ደሙ የተለየ ሕይወት ሊኖረን አይገባም።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቀዳማዊ ቆሮንቶስ መልዕክቱ 11፥26 ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም
የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም አለበት ሰው ግን ራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ
ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባ የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና
ይጠጣልምና። በማለት እንዴት ወደ ቅዱስ ቁርባኑ መቅረብ እንዳለብን ተናግሯል። ወደ ቅዱስ ሥጋው
ክቡር ደሙ ቅድመ ቁርባን ጊዛ ቁርባንና ድኅረ ቁርባን ልንፈፅመው የሚገባውን ሥርዓት ማወቅ ተገቢ
በመሆኑ በሦስት ከፍለን እንመለከታለን።
ቅድመ ቁርባን መደረግ ያለበት ሥርዓት
ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከምንቀበልበት ሰዓት አስቀድሞ ባሉት ዐሥራ ስምንት ሰዓታት።
ልንፈፅመው የሚገባውን ሥርዓት ያሳያል።
በቅድመ ቁርባን የማፈፀሙ ሥርዓቶች፦
ከሩካቤ ሥጋ መከልከል፦ ቀዳሲያንና ሥጋውንደሙን የሚቀበሉ ምዕመናን በጋብቻ ተወስነው የሚኖሩ
ከሆነ ሥጋ ወደሙን ከመቀበላቸው ሦስት ቀናት አስቀድሞ ከሩካቤ ሥጋ መከልከል አለባቸው። "ጋብቻ
ክቡር መኝታውም ንፁሕ" /ዕብ 13፥4/ እንዳለ በሕግ የሆነ ሩካቤ ኃጢአት ሆኖ አይደለም።
ካህኑ /አቀባዩ/ ክርስቶስን መስለው ምዕመኑም /ተቀባዩም/ ሐዋርያትን መስሎ የሚቀርብ በመሆኑ ነው።
አንድም በመሰረቱ ግብሩ የሥጋ እንደመሆኑ መጠን ስለሚቀበሉት ምስጢር ክብር መንፈሳዊ ጥንቃቄ
ለማድረግ ነው።በንስሐ መታደስ፦ የሚያቀብሉና የሚቀበሉ ሰዎች ከንስሐ አባታቸው ጋር በመመካከርና
የንስሐ አባታቸውን ፈቃድ ማግኘት አለባቸው። የበደሉትን ሳይክሱ፣ የወደዱትን ሳይመልሱ፣ ከቂም
ከበቀል ሳይነጹ፣ ክፉ ኅሊናን ሳያርቁ ወደ ሥጋወደሙ መቅረብ አይገባቸውም።
ለዐሥራ ስምንት ሰዓታት መጾም፦ ጌታ በምሴተ ሐሙስ በሦስት ሰዓት በአይሁድ ጭፍሮች ተይዝ እስከ
አርብ 9 ሰዓት ድረስ ያለውን ጊዛ በማሰብ 18 ሰዓታት የተመገቡት ከሆዳቸው ጠፍቶ ለአፋቸው ምረት፣
ለሆዳቸው ባዶነት እስኪሰማቸው እንዲጾሙ ቤተክርስቲያን ታስተምራለች።
"ጴጥሮስ በሁለተኛው ቀሌምንጦስ በ46ኛው አንቀጽ ጠንቅቆ ሳይጾም ማንም ማን ሥጋ ወደሙን
አይቀበል። ከወንዶችም ከሴቶችም ወገን ማንም ምን የቀመሰ ቢኖር፣ ከቀመሰ በኋላ ሥጋውን ደሙን
ቢቀበል፣ ተደፋፍሮ ይህንን ቢያደርግ ለለዓለም ከምዕመናን በውግት ይለይ።"
ለመቀበል በተጋጁበት ዕለት ሰውነትን አለመታጠብ ፡- ምክንያቱም ሲታጠቡ ውኃ ወደ አፍ በቀላሉ
ሊገባ ስለሚችል ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ጥርስ መፋቅም መድማትን ሊያስከትል ይችላል። ስለዙህ
ሰውነትን መታጠቡ፣ ጥርስ መፋቁ፣ ጢም መላጨቱ ከመቀበሉ 18 ሰዓት በፊት ማድረግ፣
የሚለብሱትን ልብስ ንጹሕ አድርጎ ማጋጀት ይገባል።
ሓዋርያት በመጀመርያው ቀሌምንጦስ በ23ኛው ባስልዮስ በጻፈው መጻሕፍ በ99ኛው አንቀጽ ካህን
በሚያቀብልበት ጊዛ ኃጢአታችንን ለማስተስረይ ለኃጢአት ለሞት አሳልፎ የሰጠው የክርስቶስ ሥጋ ይህ
ነው ይበል፡፡ የሚቀበልም ሰው አሜን ይበል፡፡
በማለት ይኸው ሐዋርያ ያስጠነቅቀናል። ‚ስለዙህ ሳይገባው ይህን እንጀራ ኅብስት የበላ ወይም የጌታን
ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ሰው ግን ራሱን ይፈትን፣ እንዲሁም ከእንጀራው
ከኅብስቱ ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ፤ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ
ይበላልና፣ ይጠጣልምና። ስለዙህ በእናንተ ንድ የደከሙና የታመሙ ብዘዎች አሉ አያሌዎችም
አንቀላፍተዋል። ራሳችንን ብንመረመር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዛ ከዓለም
ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን‛ /፩ኛ ቆሮ ፲፩፣፳፯-፴፪/።
ለመቁረብ የሚደረግ ጥንቃቄ /ዝግጅት/
ምእመናን ሥጋ ወደሙን ለመቀበል በሚፈልጉበት ወቅት ሊፈጽሟቸው የሚገቡ ዜግጅቶች አሉ። ሥጋዊ
ማዕድስ እንኳን ከመበላቱ በፊት የራሱ የሆነ ዜግጅት አሉት። ሰማያዊው ማዕድማ ምን ያህል ጥንቃቄ
ይፈልግ ይሆን!? /ማቴ ፳፪፥፲፪፡፡/ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰርግ ቤት ምሳሌነት በርካታ
ትምህርቶችን አስተምሯል።
ይህም ዜም ተብሎ በፈቀደ ማንም ባሻው ጊዛ እየተነሣ ያለምንም ዜግጅት የሚመገበው ተራ ምግብ
አይደለም። ተግሣጹም ሆነ ጽኑዕ ቅጣቱ እንዳያገኘን ባግባቡ ተጋጅተን በካህናት እጅ የሚሰዋውን
መሠዋዕተ ሐዲስ መቀበል ይኖርብናል፡፡ ዋና ዋናዎቹ የዜግጅቱ አካላትም የሚከተሉት ናቸው።
ባለፈ ኃጢአት መጸጸት፣ መናዜና ቀኖና ተቀብሎ በትሕትናና በፍቅር መፈጸም፤
ዳግም ላለመበደልም ወስኖ መጋደል፤
ወደ ልባችን የኃጢአትን አሳብ እንዳያስገቡ አካላዊ ስሜቶችን ሁሉ መግዚት፤
ሰውነትን /አካልን/ በዋዛማው በአግባቡ መታጠብና አቅም በፈቀደ መጠን ተገቢውን ልብስ
(ከተቻለ ነጭ) አጋጅቶ መልበስ፤
በዋዛማው ቀለል ያለ ምግብ መመገብ ፣ለ፲፰ ሰዓታት ከምግበ ሥጋ መከልከል፣
ሕጋዉያን (ባለ ጋብቻ) ቆራቢያን ከሩካቤ ሥጋ ለ፫ ቀናት መታቀብ፣
ከሕልመ ሌሊትና ከወር አበባ እንዲሁም ከሚደማና ከሚያዥ ቁስል ነጻ መሆንን ማረጋገጥ፣
በወሊድ ጊዛ ሴቶች ለወንድ ልጅ ፵ ቀን ለሴትም ልጅ ፹ ቀን የሞላቸው መሆኑን መገንብ፣
ሥርዓተ ጸሎተ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት መድረስ የሚሉትና የመሳሰሉት ዜግጅቶች አስፈላጊ
ናቸው። ከጤንነት ጋ በተያያ የጾም ሰዓትን በተመለከተ ከመምህረ ንስሐ ጋር በመመካከር
በፈቃደ ካህን የሚስተካከል ይሆናል።
የማይላመጥ የአድማስ ድንጊያ ነዉ፡፡ በዙህም የሚያስከትለዉን የመከራ ጽናት ለመናገር ነዉ፡፡ የድንጊያ
ንፍሮ (የብረት ቆሎ) ማላመጥ እንደማይቻልም በአግባቡ ሆነዉ ካልተቀበሉት የሚያስከትለዉም
መከራ ጽኑዕ ነዉ፡፡
በኃጢአት ላይ ኃጢአትን የሚጨምር ከማስተስረይ ቀርቶ በደለኛ ያደርጋል፡፡
ደዌ ሥጋ ደዌ ነፍስን ያመጣል፣ በመከራ ላይ መከራን ያመጣል
እንደ ባቢሎን እሳት የሚያቃጥል የሚግጥ እሳት ይሆናል፡፡
ልቡናን በኃጢአት ያደነድናል እንደ ይሁዳ ለሌላ በደል ያጋጃል
ገላን (ሰውነትን) መታጠብ፣ ከልብስ መራቆት፣ መስገድ መንበርከክ፣ ምራቅን እንትፍ ማለት፣ መበጣት
መቆረጥ መታገም መተኮስ፣ የእጅና ይእግር ጥፍር መቆረጥ፣ ፀጉርን መላጨት፣ ሩቅ መንገድ መሔድ፣
መፍረድ፣ መክሰስ፣ መካሰስ፣ ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ፣ ያለ መጠን መብላት፣ መጠጣት፣ ለሦስት
ቀናት ያህል ግብረ ሥጋ፣ ይህን የመሳሰሉትን ሁሉ ማድረግ አይገባም፡፡
5.ሥራዓተ ተክሊል
ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ለእግዙአብሔር መንግሥት ለመብቃት በሚያደርጉት መንፈሳዊ ጉዝ ሁለት የኑሮ
አማራጮች አቅርባላቸዋለች፡፡ አንደኛው ፍጹም የሆነ የድንግልና ሕይወትን ጠብቆ በመኖር የሚገባበትና
በተጋድሎ የሚኖርበት የምንኩስና ሕይወት ሲሆን ሁለተኛው በተቀደሰ ጋብቻ ክብደ ዓለምን በመቋቋም
እየተጋገዘ የሚጓዘበት ሕይወት ነው፡፡
በመተጫጨትና በቃል ኪዳን የተመሰረተው ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱ
የሚታወቀው በተክሊልና በስጋወደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ተክሊል ማለት አከበረ ፤ ከለለ ካለው ግስ
የወጣ ቃል ነው፡፡ ይኸውም ክቡር ማለት ነው፡፡ ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቃል ኪዳንና
በቡራኬ በጸሎተ ተክሊልና በቅዱስ ቁርባን ሲፈጸም ምስጢር አለው፡፡ በሚታይ ምልክቶችና ስርአቶች
የማይታይ ጸጋ እናገኝበታለን፡፡ ኤፌ 5፤32
በጋብቻ አመሠራረት ሂደት “እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይኖር ንድ መልካም
አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።‛ (ፍ ፪፥፲፰፡፡) የሚለው ኃይለ ቃል መነሻና መሠረት
ነው። ይህም የጋብቻ መሥራቹና ፈቃዱ እግዙአብሔር መሆኑንና የተመሠረተውም በመጀመሪያዎቹ
አባታችንና እናታችን /በአዳምና በሔዋን/ መካከል እንደነበር ያስረዳል፡፡ ‚ምሥጢረ ተክሊል‛ በሐዲስ
ኪዳን የተሰጠው መጠሪያ ስም ነው። ተክሊል ‚ከለለ‛ ከሚለው የግእዜ ግስ የሚወጣ /የሚገኝ/ ሲሆን
ትርጉሙም ጋረደ ፣አጠረ፣ ከበበ፣ አከበረ፣ አጀበ፣ ፈጽሞ አስጌጠ፣ ሸለመ፣ አክሊል አቀዳጀ፣ ማለት ነው።
ምሥጢረ ተክሊል በሰፊው ሲብራራ ደግሞ የሙሽራውንና የሙሽራይቱን የጋብቻ ቃል ኪዳን በሃይማኖት
የሚያጸና፣ የጋብቻ ግዴታን ለመወጣት የሚያስችል፣ በፍቅር የሚያስተሳስርና ላቂ አነድነትን
የሚያስገኝ የጸጋ ምሥጢር ነው፡፡
በሐዲስ ኪዳንም መን መጀመሪያ አካባቢ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ ቃና በተጋጀው የጋብቻ
ሥርዓት ላይ በመገኘት ክርስቲያናዊ ጋብቻን አክብሯል። በዶኪማስ ቤት ከእናቱ ከእመቤታችን ከቅድስት
ድንግል ማርያምና ከደቀ መዚሙርቱ ከሐዋርያት ጋር ተገኝቶ ጋብቻን ፈጽሞ ባርኮታል። የታወቀና
የተገለጠ የመጀመሪያ ተአምሩንም በእመቤታችን ምልጃ የፈጸመው በዙሁ ሰርግ ቤት መሆኑ
ይታወቃል። (ዮሐ ፪፥፩‐፲፪፡፡)
ከጋብቻ በፊት እንዴት እንኑር
የጋብቻ መቅድም መተጫጨት ነው፡፡ የመተጫጨት ባህልና ሥርዓት ፍቃድና ስምምነትን ዕድሜን ፤
የስጋዊና መንፈሳዊ ዜምድናን ፤ የሃይማኖትን አንድንትን ርዜሮ ይገልጣል፡፡ ተጋቢዎች ከተዋወቁ ፣
እርስ በእርሳቸው ከተስማሙና ከተፈቃቀዱ ለወላጆቻቸው አሳውቀው ፈቃድና ስምምነትን ካገኙ በኋላ
የውዴታ ቃላቸውን በመጀመሪያ ለንስሓ አባታቸው ወይም ለቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ወይም ለክፍለ
ኤጲስ ቆጶስ በመናገር ወደ ጋብቻ ቃልኪዳን ይሔዳሉ፡፡
ዕድሜን በተመለከተ ወንዶች ከ20 ዓመት በላይ ሴቶች ከ15 ዓመት በላይ ሲሆናቸው መተጫጨትና
መጋባት ይፈቀድላቸዋል፡፡ ፍት.መን.24 ም3. ክፍል 2፡፡ በዜምድና በኩል ጋብቻን የሚከለክል ዜምንድና
ሶስት ዓይነት ነው፡፡ ስጋዊ ዜምድና ፣ የጋብቻ ዜምድናና መንፈሳዊ ዜምድና ናቸው፡፡ ስጋዊ ዜምድና
በፍትሐ ነገስት በአንቀጽ 24፡842-853 ተርዜሮ እንደተገለጸው ስጋዊ ዜምድና የሚጠበቀው እስከ ሰባት
ትውልድ ነው፡፡
ይህም በአንድ ጎን ሰባት በአንድ ጎን ሰባት ከተቆጠረ በኋላ ስምንተኛዎቹ መጋባት ይችላል፡፡ አንድ
ጥሩ መንፈሳዊ የሆነ/ች ወንድም (እህት) ጋር አብሮ ለማገልገል በእህትነትና በወንድምነት
መቀራረበን መልመድ ይኖርብናል፡፡ ነገር ግን ይህን በምናደርግበት ጊዛ የተለያዩ ክፉ ወጥመዶች
ያገኙናል ለምሳሌ፡- ክፉ ፊልሞች፣ለፈተና በሚያጋልጥ ሁኔታዎች ውስጥ መቀመጥ ፤የጓደኛ ተጽእኖ ስለ
ራሰቸው ሕይወትና ኃጢኣት ልምድ ደጋግመው በማውራት የሰዎችን ልብ መስረቅ፡፡ እኛም እነዙህ
ፈተናዎችን እንዳሉ ተመልክተን አቀራረባችንን በጥንቃቄ ማደረግ አለብን፡፡ አንድም እግዙአብሔር
ያጋጀልንን የምናገኝበት ጊዛ እስኪደርስ ድረስ ፡-
1. በትግስት መጠበቅ ዕብ 10፡36 መክ 3፡1
2. እንደ ፈቃዱ እንመላለስ 2ጢሞ 2፡22 ሮሜ 6፡12 መክ 12፡1
3. ያለ ሐሳብ እንኑር ሉቃ 21፡34 1ጴጥ 5፡6-7
4. በጾምና በጸሎት መትጋት ማቴ 26፡41 ፊል 4፡6 ዮሐ15፡14
5. ከጋብቻ በፊት ከእጮኝነት መን እንዴት እንደ ሚልቅ ማወቅ
6. ስለሚስጥረ ተክሊል እና ሌሎች ስርዓት ማወቅ
7. በትዳር ውስጥ ችግር ቢኖር እንዴት መፍታት እንደሚቻል ማወቅ
የተከለከለ ጋብቻ
1. የሥጋ መድ ጋብቻ፡-
ወደላይ፡- ወላጆች አያቶች፣ቅድመአያቶች ወደታች፡- ልጆች የልጅ ልጆች
ወደጎን፡- ያባቶች ወንድሞች፣ያባቶች ዕኅቶች የእናት እህቶችና ወንድሞች፣ወንድሞች፣ የወንድሞች ልጆች፣
ከአባቶችና ከአያቶች ስለተወለዱ የተለያዩ መዶች፡፡
የአባት ወንድም ልጅ አራተኛ ትዉልድ ናት፡፡ አባቴ እኔን ወለደ፣ሁለት አያቴ አባቴን ወለደ
አያቴ የአባቴን ወንድም ወለደ ሁለት የአባቴ ወንድም ልጁን ወለደ
2. ከህግ ወገን የመድ ጋብቻ
እነዙህም የሌሎች ልጆች በጥምቀት ክርስትና የተነሱ ናቸዉ፡፡ ኒቂያ 23÷25 "ክርስትና አንሺዉና
ተነሺዉ ከሁለተኛዉ ጋር አይጋቡ ወላጆቹም፣ወድሞቹም፣ልጆቹም፣ልጅ ልጆቹም የሚስቱ ከሌላ ልጆችም
ወገን አንዱ ልጆች ከሁለተኛ ልጁ ጋራ አይጋቡ ሴት ልጆን ባሏ ክርስትና ላነሳዉ ወንድ አታግባ"
ወንድም እንደዙሁ ልጁን ሚስቱ ክርስትና ላነሳችዉ ወንድ አያጋባ፡፡ ከእነዙህ ሁሉ በመካከላቸዉ
መንፈሳዊ ተዚመዶ ሆኗል፡፡
3. አብሮ በመኖር የተዛመዱ ሰዎች ጋብቻ
ምንመ እነርሱ በሞግዙትናት ስር ቢወጡ አሳዳጊዎቻቸዉም ቢያዩ እነዙህ ጡት መጥባትን በመሳተፉ
ወይም በልጆች መዕረግ በማሳደግ ያሉ ናቸዉ፡፡ ልጆቻቸዉም ወላጆቻቸዉም እነርሱ ቢሆኑ አባቶቻቸዉም
ያባቶቻቸዉን አባቶችም ያባቶችን ወንድሞች የእናቶቻቸዉን ወንድሞች እና እህቶች ያባት ሚስት
ያባት ሚስት (የእንጀራ እናት) አባት ልጅ ትሆናለች ብሎ ያሳደጋትን ልጅ አያግባ፡፡
4.በትዉልድ ያይደለ በግቢ ስለሚዛመዱ ሰዎች መጋባት
ያባቶች ሚስቶች፣ወንድ አያቶቻቸዉ እኅቶቻቸዉእናቶቻቸዉ ሴት አያቶቻቸዉ
የልጆች ሚሲቶች፣ልጆቻቸዉ፣እኅቶቻቸዉ፣እናቶቻቸዉ፣ሴቶች አያቶቻቸዉ
የወንድሞች ሚስቶች ልጆቻቸዉ፣እሕቶቻቸዉ፣እናቶቻቸዉ፣ሴቶች አያቶቻቸዉ
የሴት መዶች አያቷ፣እናቷ፣ያባቷ እኅት፣የእናቷ እኅት፣እኅቷ፣ልጇ፣የልጅ ልጇ ናቸዉ፡፡
5. ሊያገባት ከሾሙት ጋር አደራ ያስጠበቁት ሰዉ ጋብቻ
የኸዉም እርሱ ልጅ ወንድሙም ከገንቧ ሁሉ ጋር 26 ዓመት ከሆናት በኋላ ከሂሳብ ወገን የሚጋባ
አደራዉን ከፈጸመ በኋላ ያግባት
6. የጌታ ሚስት ባሏ ነፃ ያወጣዉ ባሪያ ሚስት ልቶን መልካም አይደለም
7. የእርሱ ወገወን ያልሆነችዉን አማኝ ያልሆነችዉን ማግባት አይገባም
8. ለጋብቻ ከሚያስፈልገዉ ሩካቤ የሚከለክል (ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ በተፈጥሮ እንደስልብ ያለ
ቢሆን) ሩካቤ የማይቻለዉ ስለሆነ ጋብቻን ይከለክላል ጃንደረባ ሆኑ የተፈጠረ
ፍናፍነታም (የወንድና የሴት አካል በአንድነት በ አንድ ቦታ ያለበት ሰዉ)
ሴትም ሩካቤ የሚከለክል ትርፍ አጥንት ያለባት ብትሆን
ስልብ፣እብድ፣የሚቆራርጡ ደዊያት እንደ ደዌ ሥጋ ያለበት ቢሆን ወይም ብትሆን
9. በዝሙት ሥራ በአግባቡ የፈረዱበትን ለመፍታት በሚገባ የፈቷትንም ማግባት
10.ሁለት (ሦስት) ጋብቻ ማግባት አይገባም
11.መነኮሳይትን ማግባት አይቻልም
12.እድሜዋ ከ60 መን ያለፈዉን ማግባት አይቻልም
13.የባሏን ሞት የሀን ወራት ያልፈጸመች ሴት ማግባት አይቻልም ሙሉ ዓመት (10 ወር) ነገር ግን
መተጫቸትና ቃል ማሰር ይቻላል
14. ከወንድና ከሴት እያንዳንዱ ካልወደዱ ሌላ ሊያገባቸዉ አይገባም
ማጨት ቃልኪዳን መግባት ከጋብቻ የሚቀድም ተስፋ ነዉ፡፡ በደኩም ያለ ደብዳቤ ሊሆን ይችላል፡፡
ዕድሜዉ ከ7 ዓመት ላለፈ ሕፃን አይጩለት፡፡ የወንዶች አካለ መጠን ፍጻሜ 20 ዓመት ያም ባይሆን 25
ዓመት ነዉ፡፡ የሴቶችም 12 ዓመት ያም ባይሆን15 ዓመት፡፡ የጋብቻ አንድነት ግን በካሕናት መኖር
በላያቸዉ በሚጸልይ ጸሎት ካልሆነ በቀር አይሆንም አይፈጸምም፡፡ አንድ አካል እንደ ሆኑ ቅዱስ ቁርባን
ያቀብላቸዋል፡፡ ሁለተኛ የሚያገቡ ወንዶች ካሕናት ቢሆኑ ከሹመታቸዉ ይሻሩ፡፡ ከዙያም በኋላ ቢደግሙ
የረከሱ ይሆናሉ፡፡ 1ኛቆሮ 7÷39"ሴት ባሏ በሕይወት እያለ በሕግ የታሰረች ናት ባሏ ቢሞት ግን ነፃ ናት፡፡
የሥርዓተ ተክሊል አፈጻጸም
ሥርዓተ ተክሊል ያለ ድንግልና የማይፈጸም ምሥጢር ነው፡፡ ስለዙህም ለተክሊል ክብር እንድንበቃ
ድንግልናችንን ልንጠብቅ ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን ራሱን የብርሐን መልአክ እስኪያደርግ ድረስ
የሚለወጠው ዲያብሎስ በልዩ ልዩ ዜንጋዬ እንድንወድቅ ያደርገናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ያለንን መንፈሳዊ
ሀብት መጠበቃችን ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑን በገለጸበት አውድ ፡- "…መልካሙን ገድል ተጋድያለው
ሃይማኖትን ጠብቄአለው…የጽድቅ አክሊል ተጋጅቶልኛል ‛2ጢሞ4፡7 እንዳለ፡፡
ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸመው ሁለቱም ደናግል ሆነው ሲገኙ ነው። ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸመው
በሁለቱ ተጋቢዎችና በወላጆቻቸው /አሳዳጊዎቻቸው/ ፈቃድ መሠረት ነው፡፡ የሚጋቡትም ወንዶችና
ሴቶች ለአካለ መጠን የደረሱና ማለትም ለወንድ ሃያ ዓመት (20)፣ ለሴት አስራ አምስት (15)
ዓመት ከሆናቸው ጀምሮ ያሉ እና በሃይማኖት የተካከሉ /የተመሳሰሉ/ መሆን ይገባቸዋል::
የጋብቻው ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ቢፈጸምም በቅዱስ ቁርባን ያልታተመ ከሆነ የተክሊል ጋብቻ
ተፈጸመ ሊባል አይቻልም። የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ሁሉ ማኅተማቸውና መክብባቸው
ምሥጢረ ቁርባን ነውና። /ፍት.ነገ.፳፬፥፰፻፺፰‐፱፻፡፡)
ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቃል ኪዳንና በቡራኬ፣ በጸሎተ ተክሊልና በቅዱስ ቁርባን ሲፈጸም
ምሥጢርነት ይኖረዋል። /ኤፌ. ፭፥፴፪፡፡/ በሚታዩ የአፈጻጸም ሥርዓቶችና ምልክቶች የማይታይ ጸጋ
እግዙአብሔ ይገኝበታልና። ምሥጢረ ተክሊል ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በምንም ዓይነት መንገድና
በየትኛውም ቦታ አይፈጸምም፡፡
መገለጫ ነው፡፡ በቀጣይ የሕይወት መናቸው ደግሞ በጾም፣ በጸሎት፣ በንስሐ፣ በሥጋ ወደሙና
በመልካም ምግባራት ሁሉ ጸንተው እንዲኖሩ ያስችላቸዋል። ትዳራቸውን በፈቃደ እግዙአብሔር ጠብቀው
ከተጓዘ ሰማያዊውን የክብር አክሊል የሚቀዳጁ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን በምሥጢር የምታሥተምርበት
ሥርዓት ነው። በተጨማሪም በተስፋ ልጆቿን የምታጸናበት የሕይወት መንገድ ነው።
በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ከድንግልና ጋር በተያያ በተክሊል ለማግባት ከሁኔታዎች አንጻር እንደ ደናግላን
በቤተክርስቲያን ምሥጢረ ተክሊል የምትፈጽምላቸው አሉ፡፡ ለምሳሌ፡-
በሕክምና ምክንያት ድንግልናቸውን ለሚያጡ፣
በተፈጥሮም ሲወለዱ ድንግልና ለሌላቸው፣
ለአቅመ ሔዋን ሳይደርሱ በመደፈር ድንግልናቸውን ላጡ
በከባድ ስራ ምክንያት የተነሳ ድንግልናቸውን ያጡ እነዙህ ያለፈቃዳቸው በመሆኑ እንደ ደናግላን
በተክሊል ማግባት ይችላሉ፡፡ፍ. ነገስት አንቀጽ 24
ፍቺ የሚፈቅድባቸው ምክንያቶች
6.ሥርዓተ ንስሓ
እግዙአብሔር አምላካችን ለሰው ልጆች ሥጋዊ ደዌ ሕመም ፈውስ የሚሆኑትን መፈወሻ መድኃኒት
እንደሰጠን ሁሉ የነፍስ ደዌ ኃጢአትን የሚያርቅና ከሕመሙ የሚፈውስ መድኃኒት ንስሐን ሰጥቷቸዋል:
ደዌ የሆነው ኃጢአት በምድራዊ ኑሮአችው ሁሉ አብሮ እንደሚኖር የታወቀ በመሆኑ መድኃኔዓለም
ክርስቶስ መድኃኒቱንም አብሯቸው ይኖር ንድ ከሐኪሞች ከካህናት ጋር በመካከላችው አኖረው፡፡
ንስሐ ፦ ነስሐ ተፀፀተ ካለው የተገኘ ሲሆን ፤ ንስሐ ማለት በሠሩት ኃጢአት መፀፀት ፣ ማን ፣ ወደ
እግዙአብሔር ለመመለስ መወሰን ማለት ነው። ንስሐ ከለዓለማዊ ፍርድ የሚያድን ፤ ማዊውን እንደ
ድንግል ፤ ሌባውን መጽዋች የሚያደርግ በፊት ከተሠራው ኃጢአት ንጹህ አድርጎ ፤ ከእግዙአብሔር ጋር
አንድ የሚያደርግ ምሥጢር ነው
የንሥሐ አፈጻጸም
እንግዲህ ንስሐ ገብተን፣ የኃጢአትን ስርየት አግኝተን፣ ከሰውና ከእግዙአብሔር ጋር ታርቀን በጽድቅ
ጎዳና ለመራመድና በደህንነት ጸጋ ለመኖር እንድንችል ቢያንስ ሦስት ነገሮችን መፈጸም አለብን።
የመጀመሪያው የንስሐ ሃን ማለትም እውነተኛና ልባዊ ጸጸት በቅድሚያ እንዲኖረን ያስፈልጋል።
ሁለተኛው ኑዚዛ ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ስለኃጢአታችን የሚሰጠንን የንስሐ ቅጣት የሚያመለክት
የቀኖናን ሥርዓት መፈጸምና እንደዙሁም በካህኑ በኩል የምናገኘው የፍትሐት ጸጋ ነው።
1. የንስሐ ሃን /ጸጸት/
ንስሐ የሚገባ ሰው በመጀመሪያ ኃጢአቱን እያስታወሰ ሰውና ፈጣሪውን መበደሉን እያሰበ የሚያደርገው
ሃን ወደ ንስሐ የሚወስድ እውነተኛ ሃን ስለሆነ ሃኑን እግዙአብሔር ይቆጥርለታል። «የሚያዜኑ
ብፁዓን ናቸው፣ መጽናናትን ያገኛሉና» /ማቴ. ፭፥፬/ የተባለው የራሳቸውንና የሌላውን ኃጢአት እያሰቡ
የሚያዜኑትን ተነሳሒያን ያመለክታል። ንስሐ ማለት ጸጸትን የሚያመለክት ቢሆንም ቁጭትና ቅንዓት
የሞላበት የዓለማዊ ጸጸት ሳይሆን እውነተኛው ሃንና መመለስ መሆኑን በቅድሚያ መገንብ
ይኖርብናል።
ስለእውነተኛው ሃን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚከተለው ያስተምረናል። «አሁን ስለንስሐ
ስላናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላናችሁ አይደለም፤ በምንም ከእኛ የተነሳ እንዳትጎዱ እንደ
እግዙአብሔር ፈቃድ አዜናችኋልና። እንደ እግዙአብሔር ፈቃድ የሆነ ሃን ጸጸት የሌለበትን፣ ወደ
መዳንን የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ሃን ግን ሞትን ያመጣል።» /፪ኛ ቆሮ. ፯፥፱-፲/።
እንግዲህ እውነተኛውን ሃን ከእንባ ጋር አድርጎ በንጹህ ልቦናና ጸሎት ለእግዙአብሔር በማቅረብ
ተነሳሒው እንደገና ላለመበደል መወሰን ይኖርበታል። ውሳኔውንም ለመፈጸም የሚያስችለውን የመንፈስ
ቅዱስን ረድኤት በማግኘት ሁልጊዛ ተግቶ መጸለይ አለበት፡፡
መፀፀት/ስንል/ምን ማለት ነው?
አንድ ክርስቲያን በድፍረትም ይሁን በስህተት ‚የሠራው በደል‛ መጻሕፍት በማንበብ ፣ ከመምህራን
ተምሮ ፣ የስብከት ካሴት አዳምጦ ፤ ህሊናው ወቅሶት ፣ ወይም በሌላ በአንድ ምክንያት ስህተት መሆኑን
ከተረዳ በኋላ ተፀፅቶ ከእግዙ አብሔር ለመታረቅ (በደሉን ለማስተስረይ) የሚያደርገው ጉዝ ንስሐ ይባላል ።
በሠራው በደል ሳይፀፀት ፤ ለጊዛው ህሊናውን ስለረበሸው ብቻ ንስሐ የሚገባ ሰው ፤ ከስሐውን በኋላ ወደ
ቀደመ ሕይወቱ ሊመለስ ይችላል ። ምክንያቱም ፡ ንስሐ የገባው ፡ በሠራው በደል ከልቡ ተፀፅቶ ሳይሆን ፤
በስሜት ተነሳስቶ ነውና ፤
በንስሐ ጊዜ
አንድ ምዕመን ካለፈ በደሉ በንስሐ ታጥቦ በአዲስ ሕይወት ራሱን ለማስተካከልና ከእግዙአብሔር ጋር
ለመኖር ከወሰነ በኋላ የንስሐ አባት ሊኖረው ይገባል ። ጌታችን ‚ካህናትን‛ ራሱን ወክለው መንጋውን
እንዲጠብቁ ‚በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሁን‛ (ማቴ 8
፥ ዮሐ 21 ፥ 15 ። ማቴ 16 ፥ 19) በማለት መንጋውን እንዲጠብቁ ሾሟቸዋልና። አንድ ክርስቲያን
በሕይወት ሲኖር ፤ የእግዙአብሔርን መንገድ የሚመራው ፤ ሲሳሳት ንስሐውን ተቀ ብሎ ቀኖና በመስጠት
ከእግዙአብሔር የሚያስታርቀው የንስሐ አባት የግድ ሊኖረው ይገባል።
2. ኑዛዜ
ከዙህ ቀጥሎ ተነሳሒው ኃጢአቱን ሥልጣነ ክህነት ላለው ካህን ይናዚል። ኑዚዛ ማድረግ በቅዱሳት
መጻሕፍት የታ ነው። «ከነዙህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ቢሆን፥ የሠራውን ኃጢአት ይናዚል። ስለሠራው
ኃጢአት ለእግዙአብሔር የበደልን መስዋዕት ያመጣል፤ካህኑ ስለኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።እርሱም ይቅር
ይባላል።» /ሌ. ፭፥፭-፮፣፲/። ከዙህ ጥቅስ የኃጢአትን ስርየት ለማግኘት ለካህን መናዜ እንደሚገባ
እንማራለን። ስለዙህ ኃጢአታችንን ለአናዚዡ ካህን ከበደሉ ዓይነትና ሁኔታ ጋር ማስረዳት ይገባናል።
ስንናዜም ከእንባና ከጸጸት ጋር ሆነን ከካህኑ ጋር አብሮ እግዙአብሔር እንደሚሰማን አምነን በእውነት
መናገር ያስፈልገናል።
በራሳችን ድካም የሠራነውን በደል ‚ዕገሌ አሳስቶኝ‛ እያሉ ሌላውን ሰው ስለ እኛ ስህተት ተጠያቂ ማድረግ
ሳይሆን ፣ አንደበታችንን ከሳሽ ህሊናችን ምስክር አድርገን በመጨከን ራሳችንን በእግዙአብሔር ፊት
መክሰስ ነው ። አምላካችን የልባችንን መመለስ ፣ አይቶ የሰራነውን በደል ሁሉ እንዳልተሠራ አድርጎ
ያነጻናል ። በደልን በንስሐ ይቅር ማለት የእግዙአብሔር የቸርነት ሥራ ነውና።
በሽታውን የሰወረ መድኃኒት አያገኝም ተብሏልና ለነፍስ ቁስል ሐኪም ለሆነው ለካህኑ ኃጢአታችንን
ከሰወርን ለነፍስ የሚሆነውን ፈውስ ለማግኘት አንችልም።«ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤
የሚናዜባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።» /ምሳ. ፳፰፥፲፫/ ተብሎ ተጽፏልና ስለዙህ እርስ
በርሳችን በቂም በቀል ሳንያያዜ የበደልነውን እየካስን፣ የበደለንን ይቅር እያልን ብንናዜና የሰማዩን
አባታችን በጸሎት ብንጠይቀው ምሕረትና ፈውስን ይሰጠናል። ነገር ግን እኛ ማንንም አልበደልንም
ኃጢአትም የለብንም ብንል እግዙአብሔርን ሐሰተኛ ማድረጋችን ስለሆነ እንጠንቀቅ።
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ እንዳለው «ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፣ እውነትም በኛ ውስጥ
የለም። በኃጢአታችን ብንናዜ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በኛ ውስጥ የለም።» /፩ኛ ዮሐ. ፩፥፰-፲/።
3. ፍትሐትና ቀኖና
እንግዲህ ተነሳሒው በእውነት ኃጢአቱን አውቆ ለካህኑና በስውር ለሚያየውና ለሚሰማው ለእግዙአብሔር
ከተና በኋላ ከካህኑ ሁለት ነገሮችን ይቀበላል። እነሱም ፍትሐትና ቀኖና ናቸው። ፍትሐት ማለት
ከኃጢአት እስራት የሚፈታበት ነው።
ቀኖና ማለት ለኃጢአቱ ምክርና ተግሳጽ የሚያገኝበትን፣ በንስሐ ቅጣት የሚቀበልበትን፣ ካሳ መቀጫ
የሚከፍልበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው። ፍትሐት የሚሰጠው ካህኑ የንስሐውን ጸሎት ሥነ ሥርዓት
ከፈጸመ በኋላ «እግዙአብሔር ይፍታህ» ሲል ተናዚዡ ወይም ተነሳሒው ከኃጢአቱ እስራት ይፈታል።
ንስሐ የገባው ሰው ከኃጢአቱ ተፈትቶ ከእግዙአብሔር ጋር መታረቁ ታላቅ ጸጋ ነው። እንግዲህ ፍትሐት
የተቀበለ ተነሳሒ ሁሉ ኃጢአቱ የተሰረየለት ስለሆነ ከላለም የሞት ቅጣት ነፃ ይሆናል።ምንም እንኳን
ተነሳሒው ከላለም የሞት ቅጣት ቢድንም ዓይነቱና መጠኑ የተለያየ ጊዛያዊ ቅጣት መቀበል ይገባዋል።
ይህም የንስሐ ቀኖና ይባላል። ጊዛያዊ ቅጣት ወይም ቀኖና ያስፈለገበት ምክንያት ኃጢአትን
መሥራት ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ለተነሳሒው ለማሳሰብና ዳግመኛ እንዳይበድል ለማስጠንቀቅ
እንዲሁም ደግሞ ሥጋን በመገሰጽ ለነፍሱ የጽድቅንና የደህንነትን ጎዳና ለማስተማር ነው። ምንጊዛም
ፍቅሩና ምሕረቱ ከኛ ጋር ቢሆንም እግዙአብሔር በአባትነቱ ላጠፋነው ጥፋት በጊዛያዊ ቅጣት
ይቀጣናል።
መልካም አባት ልጁን እንደሚገስጽና እንደሚቀጣ ዓይነት ይቀጣናል። /ዕብ. ፲፪፥፭-፲፩/። እንግዲህ ያልተገራ
ልቦና ካለን ለእግዙአብሔር በማስገዚት የኃጢአታችንንም ቅጣት በደስታ በመቀበል የበለጠ ጸጋና ረድኤትን
እናገኛለን። «በዙያን ጊዛ ያልተገረው ልባቸው ቢዋረድ፣ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ እኔ ለያዕቆብ
የማልኩትን ቃልኪዳኔን አስባለሁ … ምድሪቱንም አስባለሁ።» ተብሎ ተጽፏልና /ሌ. ፳፮፥፵፩-፵፪/።
አንድ ምዕመን ንስሐ ከገባ በኋላ የሚከተሉትን በቅደም ተከተል ማድረግ አለበት?
1. የተቀበለውን ቀኖና በትክክል መፈጸም
ቀኖና የግሪክ ቃል ሲሆን : መለኪያ ማለት ነው ። ካህኑ ለበደለው ምዕመን እንደ ሃይማኖቱ ጽናት ፣ እንደ
አእምሮው ስፋት ፤ የሠራውን በደል መጥኖ ቀኖና ከሰጠው በኋላ እንደታው መፈጸም አለበት ። የነነዌ
ሰዎች ፣ ት. ዮና 3 ፥1 ። ንጉሡ ህዜቅያስ ፣ ኢሳ 38 ፥ 1 ። ቅዱስ ጴጥሮስ ሉቃ 22 ፥ 54 ። እና ሌሎችም
ይቅርታን ያገኙት ፤ በበደላቸው ተጸጽተው በማልቀሳቸውና ንስሃ በመግባታቸው ነው ። በንስሐ ወቅት ፡
መሬት ላይ መተኛት ምግብ መቀነስ ፣ ከዓለማዊ ነገሮችና ለመንፈሳዊ ሕይወት ከማይመቹ ጓደኞች መራቅ
ያስፈልጋል ። በንስሐ ጊዛ እንዳናደርግ ከታዜነው ነገር ራሳችንን በመግዚት መቆጠብ አለብን ፤
እግዙአብሔር በቸርነቱ ወደ ድኅነት ከጠራን በኋላ እንደገና ተመልሰን ወደተውነው ድካማችን መመለስ
የለብንም። የጊዛውን ሳይሆን የመጨረሻውን ማሰብ አለብን ። 2 ጢሞ 4 ፥10 ። መዜ 6 ፥6 ።
ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው በደላችንን ለመደምሰስ ስለሆነ ከበደላችን ሊያነጻን የታመነ አምላክ ነው ።
ከሠራነው ብዘ ኃጢአት አንጻር የሚሰጠን ቀኖና ትንሽ መስሎ ቢታየንም ። ማሰብ ያለብን የራሳችንን
በደል ሳይሆን የእግዙአብሔርን ቸርነት ነው ። ከእኛ በደል የእግዙአብሔር የቸርነት ሥራው እጅግ
ይበልጣልና የታዜነውን ፈጽመን የቀረውን እንደቸርነትህ ማለት ይገባል ። ‚የታዚችሁትን ባደረጋችሁ ጊዛ
የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ‛ ተብለናልና ። ሉቃ 17 ፥ 10 ።
አንድ የተራበ ሰው እጁን ስለታጠበ ብቻ አይጠግብም ። የግድ ምግብ መብላት አለበት ። ንስሐ ማለት
መታጠብ ፣ ከእድፍ (ከኃጢአት) መንጻት ማለት ሲሆን ፤ ድኅነት የሚገኘው የለዓለም ሕይወት
የሚሰጠውን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል ነው ። ዮሐ 6፥33 ። ብዘዎቹ መቁረብን እንደ
ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ (ለሽማግሌ ብቻ) አድርገው ስለሚቆጥሩት ለመቀበል ሲጋጁ አይታዩም ።
ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል ። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን
የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና ።
ንስሐ ከገባንና ከቆርብን በኋላ እንደገና በኃጢአት ልንወድቅ እንችላለን። አምለካችን ‚ለምን ንስሐ
አልገባህም እንጅ ለምን ኃጢአት ሠራህ? አይልምና‛ ሁለተኛ ስንበድል ሀፍረት ሳይሰማንና ከኃጢአት
መላቀቅ ካልቻልሁ በየጊዛው የንስሐ አባቴን ከማስቸግር አርፌ ብቀመጥ ይሻለኛል በማለት ፡ ሁሉንም
እርግፍ አድርገን እንድተወው ፡
ክፉ ሀሳብ በአምሯችን ሊፈታተነን ይችላል ። ነገር ግን ከንስሐ በኋላ እንደ መላእክት በቅድስና ብቻ
እንኖራለን ማለት ሳይሆን ‚ጻድቅ ሰባት ጊዛ ይወድቃል ፤ ሰባት ጊዛ ይነሳል‛ ምሳ 24፥ 16 ። እንደተባለ ፡
አምላካችን ብንወድቅ ሊያነሳን ፤ ብንጠፋ ሊፈልገን ፤ ብንርቅ ሊያቀርበን ፤ በኃጢአት ብንረክስ ሊቀድሰን
(እንደ ባቶ ሊያጠራን) የታመነ አምላክ ስለሆነ ተስፋ ሳንቆርጥ ፤ በኃጢአታችን ሳንደበቅ ፤ ወትር ለንስሓ
መጋጀት አለብን። ኢሳ 1 ፥ 18 ።
ከአሮን እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ደረስ ረጅሙን የብሉይ ኪዳን መን ከአሮን ር ብቻ የሚወለዱት ቅብዓ
ክህነት እየተቀቡ በካህንነት እያገለገሉ አልፈዋል ።
ነገር ግን በር ሐረግ ላይ የተመሠረተው ክህነት ለሐዲስ ኪዳኑ ክህነት ምሳሌ ስለነበረ ፍፁምና ላቂ
አልነበረምና መስዋዕቱም ሆነ የአመራረጡ ሂደት በሌላ ተተካ ።
ክህነቱ በር ብቻ የተገደበ ስለነበረ በሐዲስ ኪዳን ህጉንና ሥርዓቱን አሟልቶ ለተገኘ ለማንኛውም
ሕዜብ የተፈቀደ ሆነ ። ክርስቶስ የመጣው ለዓለም ሁሉ ነውና ።
ጌታችን ሲያስተምር ስለ ካህናት በብዘ ቦታ ተናግሯል ። ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ ። ማቴ 8 ፥ 4 ። አንተ
ብፁዕ ነህ ፡ የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻ እሰጥሃለሁ… ። ማቴ 16 ፥ 17 ። እውነት እላችኋለሁ
በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ፣ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል ። ማቴ 18 ፥ 18 ።
ይህን የተናገረው በመዋዕለ ስብከቱ ሲሆን ከሙታን ከተነሳ በኋላም ለሐዋርያት አረጋግጦላቸዋል ። ሂዱና
በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው ። ማቴ 28 ፥ 19 ።..እፍ አለባቸውና መንፈስ ቅዱስን
ተቀበሉ ። ዮሐ 20 ፥ 22 ። በመጨረሻም ቅዱስ ዼጥሮስን ‚….ስምዖን ሆይ በጎቼን ጠብቅ ፤ (ለጊዛው አስራ
ሁለቱን ሐዋርያት ፡ ለፍጻሜው ወላጆችን) ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ ፤ (ለጊዛው ሰብዓ አርድዕትን ፡ ለፍጻሜው
ወጣቶችን) ፣ ግልገሎቼን ጠብቅ (ለጊዛው ሰላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስትን ፡ ለፍጻሜው ህጻናትን)‛ በማለት
ሐዋርያትን ዸዸሳት ፣ ቅዱስ ዼጥሮስን የመጀመሪያ ሊቀ ዻዻሳት አድርጎ ሾመው ። ዮሐ 21 ፥ 15 ። ከዙህ
ጊዛ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ዸዸስና በዸዸሳት በሚመራ መንፈሳዊ ጉባኤ (ቅዱስ ሲኖዶስ) አማካኝነት
እየተመራች አገልግሎቷን ታካሂዳለች ።
የክህነት ደረጃዎች
ሊቀ ዻሳሳት
ሊቃነ ዸሳሳት ‚ፓትርያርክ‛ እየተባለም ይጠራል ። በአንዲት ቤተ ክርስቲያን (በአንድ ሲኖዶስ) ላይ የበላይ
ሆኖ የሚሾም የሁሉም አባት ነው ። የሐዋ ሥራ 20 ፥ 28 ። በሕዜብና በካህናት ከተመረጠ በኋላ በዻሳሳት
ይሾማል ። ፍት ነገ 5 ። ረስጣ 2 ። ፓትርያርክ ያወገውን ዻዻስ አይፈታውም ። መንፈሳዊ ሥልጣኑ
ከሁሉም በላይ ነውና። (ሲኖ 51) ፓትርያርክ በመላዋ ቤተ ክርስቲያን በጸሎት ጊዛ ስሙ ይጠራል ።
ኤዺስ ቆዾስ
ዻዻስ በአንድ ሀገረ ስብከት አባት ሆኖ የሚሾም ነው ። ሲያገለግል በነበረበት አካባቢ ባሉ ምዕመናን
ጥቆማና ድምጽ በርዕሰ ሊቃነ ዻሳሳቱና በሲኖዶስ ፈቃድ ይሾማል። (ፍት ነገ 5 : አብጥ 2) በአንድ ዻዻስ
ብቻ አይሾምም። (ፍት ነገ 5 : ረስ 58 : ዲድ 34) ዻዻስ በሀገረ ስብከቱ በጸሎት ጊዛ ስሙ ይጠራል። (ፍት 5
: ክፍ 4) አዲስ ጽላት ፣ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ፣ ይባርካል ። ለቄስ ለዲያቆን ሥልጣነ ክህነት ይሰጣል ። (1
ጢሞ 5 ፥ 2 : ፍት ነገ አን 5 ክፍ 4 )
ሥርዓት ሢመት
ኤጲስ ቆጶሳቱ አዲሱን ኤጲስ ቆጶስ ከመሾማቸው በፊት እጃቸውን ይታጠባሉ። /ፍትነገ. አን፬፡፡/
ተሿሚውን ኤጲስ ቆጶስ መስቀል ያስይዘታል።
ኤጲስ ቆጶስ በአንድ ኤጲስ ቆጶስ አይሾምም። ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር ሁለት ወይም ሦስት ሊቃነ
ጳጳሳት /ጳጳሳት/ አንብሮተ እድ በማድረግ ይሾማሉ። /አብጥሊስ ፪፡፡/
ኤጲስ ቆጶስ የሚሾመው በሚሾምበት ሀገር ካህናትና ምእመናን ምርጫና በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ
ፈቃድ ነው። /አብጥሊስ ፪፡፡/
ቀሳውስት
ቅስና የሚቀበሉት በዲቁና ክህነት በማገልገል ላይ ያሉ ሲሆኑ ፤ በሁለት መንገድ ይሾማሉ ።
ካህን የመጀመሪያ ሚስቱ ከሞተችበት ፤ መነኩሴም ምንኩስናውን ከተወው በኋላ የቅስና (የክህነት) ሥራ
መሥራት አይፈ ቀድለትም ። ከማኅበረ ምዕመናን ግን አይለይም ።
ዲያቆናት
ዲያቆናት ካህናትን የሚራዱና የሚላላኩ ሲሆኑ ፤ በአገልግሎታቸው መሠረት የሚከተሉት ደረጃዎች
አሏቸው
8.ሥርዓተ ጸሎት
ጸሎት ጸለየ፡- ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዜ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል
አድርገን ስንመለከተው ከእግዙአብሔር ጋር መነጋገር እግዙአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣
መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ ‚ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዙአብሔር፡፡‛ አባታችን አዳምም ከመላእክት
ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዛ ጸሎት እያደረገ
ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡
ጸሎት ሰማእታት ከነደደ እሳት፣ ከተሳለ ስለት፣ ከአላውያን መኳንንት፣ ከአሕዚብ ነገሥታት ከዲያብሎስ
ተንኮል እና ሽንገላ ዲያብሎስ በእነርሱ ላይ ከአጠመደው አሽከላ የዳኑበት ጋሻ ነው፡፡ ኤፌ.6፥10 21 ጸሎት፣
ሰው አሳቡን ለእግዙአብሔር የሚገልጥበት እግዙአብሔርም የሰውን ልመና ተቀብሎ ፈቃዱን
የሚፈጽምበት ረቂቅ ምስጢር ነው፡፡
ጸሎተ አኰቴት
ጸሎተ ምህላ
ጸሎተ አስተብቊዖት
ጸሎተ አኰቴት፡-
ማለት እግዙአብሔርን ከሁሉም አስቀድሞ ስለተደረገልን ነገር በማመስገን የሚጀመር ጸሎት ነው ይህም
ዓይነት ጸሎት የቅዱስ ባስልዮስን የምስጋና ጸሎት የመሰለ ነው፡፡ ‚ነአኲቶ ለገባሬ ሠናያት ላዕሌነ
እግዙአብሔር መሐሪ‛
‚ለእኛ በጎ ነገርን ያደረገ ይቅርባይ እግዙአብሔር አምላካችንን እናመሰግነዋለን‛ ይልና ምክንኀያቱን ሲገልጥ
ጠብቆናልና፥ አቅርቦናልና፥ ወደ እርሱም ተቀብሎናልና፥ እስከዙችም ሰዓት አድርሶናልና‛ ይላል፡፡ /ሥርዐተ
ቅዳሴ/ ይህ ጸሎት የምስጋና ጸሎት /ጸሎተ አኰቴት/ ይባላል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን የምስጋና ጸሎት ለፊልጵስዮስ ክርስቲያኖች ሲጽፍላቸው ‚ነገር ግን በሁሉ ነገር
ጸልዩ ማልዱም እያመሰገናችሁም ልመናችሁን ለእግዙአብሔር ግለጡ‛ ይላል፡፡ ፊል.4፥6 ዳግመኛም
‚ስለእናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዙአብሔር ንድ ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ ወትር እግዙአብሔርን
አመስግነዋለሁ‛ 1ቆሮ.1፥4 ብሎ ከመለመን አስቀድሞ እግዙአብሔርን ማመስገን አስፈላጊ መሆኑን
አስተምሯል፡፡ በዙህ መሠረት ሰው የተደረገለትን በጎ ነገር ሁሉ በማሰብ ፈጣሪውን ማመስገን
ከማመስገንም ቀጥሎ የሚያስፈልገውን ከፈጣሪው መለመን አስፈላጊ ነው፡፡
ጸሎተ ምህላ፡-
ጸሎተ ምህላ ስለፈውሰ ሕሙማን ስለ ሀገርና ስለነገሥታት ስለ ጳጳሳት፣ ካህናት ዲያቆናት፣ ምዕመናን
ሕይወት ቸነፈር፣ ጦርነት፣ ረሀብ፣ ድርቅ ወይም ሌላ አስጊ ነገር በሆነ ጊዛ በብዚት፣ በማኅበር የሚጸለይ
ጸሎት ነው፡፡ የምህላ ጸሎት ሲጸለይ በእስራኤል ላይ ቸነፈር በተነሣ ጊዛ አሮን በሽተኞን ባንድ ወገን
ጤነኞችን ባንድ ወገን አድርጎ የክህነት ልብሱን ለብሶ ማዕጠንተ ወርቁን ይዝ በራስህ የማልክላቸውን
አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን አስበህ የወገኖችህን ኀጢአት ይቅር በል‛ እንደጸለየላቸው ነው፡፡ ኁ.16፥
46-50
ዚሬም ካህናት ከጠቀስናቸው አስጊ ነገሮች ማንኛውም በሀገር ላይ ቢመጣ ወደ ሀገር እንዳይገባ ገብቶ
ቢሆን ከፍ ያለ ጉዳት እንዳያመጣ የክህነት ልብስ ለብሰው ማዕጠንቱ ይው ሥዕለ ማርያም፣ መስቀል
አቅርበው ማኅበረ ክርስቲያንን ሰብስበው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ‚ስለእኛ ከድንግል ማርያም መወለድህን
ስለእኛ መሠቀል መሞትህን አስበህ የህዜብን ኀጢአት ይቅር በል ከመዓት ወደ ምሕረት ተመለሰ‛ እያሉ
በምህላ ይጸልያሉ፡፡
የምህላ ጸሎት መአትን መቅሰፍትን ይመልሳል ጦርን፣ ቸነፈርን ያስታግሳል መሠረቱም፡፡‚ጾም ለዩ ምህላ
ስበኩ‛ ያለው ቃል ነው፡፡ ይህ ጸሎት በሰላም ጊዛ ሰላሙ ላቂ እንዲሆን በጦርነት ጊዛ ለመከላከያነት ዋና
መሣሪያ ነው፡፡ ስለዙህ አጥብቀን ልንከተለው ይገባል፡፡
የምህላ ጸሎት ነገሠታት ከዘፋናቸው ወርደው ወንድ ሙሽራ ሴት ሙሽራ ከጫጉላቸው፣ ከመጋረጃቸው
ለምግብ የደረሱ ልጆች ከምግብ ለምግብ ያልደረሱ ከጡት ተከልክለው ሕዜብ ሁሉ ምንጣፍ ለብሰው
አመድ ነስንሰው የሚጸልዩት ከፍተኛ ጸሎት ነው ኢዩ.2፥12-18፣ ዮና.3፥5
ጸሎተ አስብቊዖት
ይህ ጸሎት አንድ ሰው ስለሚፈልገው ነገር ቦታ ለይቶ ሱባኤ ገብቶ የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ ይህ ጸሎት
በተለይ ጣዕመ ጸጋን በቀመሱ በተባሕትዎ፣ በምናኔ በገዳም በሚኖሩ አበው ንድ የተለመደና የሚደረግ
ጸሎት ነው፡፡ ወጣንያን እግዙአብሔርን ጠይቀው አድርግ አታድርግ የሚል መልስን አይጠብቁም፡፡ ፍጹማን
አባቶች ግን እግዙአብሔር ጠይቀው አድርግ ወይም አታድርግ የሚል ፈቃደ እግዙአብሔርን ሳይቀበሉ
የሚያደርጉት ነገር የለምና ቦታ፣ ጊዛ ወስነው ፈቃደ እግዙአብሔር ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ጸሎተ አስተብቊዖት
ይባላል፡፡ ይህም ማለት መላልሶ ደጋግሞ ያለ ዕረፍት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚደረግ ጸሎት ነው፡፡
ለምሳሌ ትልቁ መቃርስ ዓለምን ዝሮ ለመጎብኘት ለተከታታይ አምስት ዓመታት እግዙአብሔርን ከለመነ
በኋላ እየዝረ መካነ ቅዱሳንን እንዲጎበኝ ከእግዙአብሔር ፈቃድ አግኝቷል በዙህም ከእርሱ ከገድል በትሩፋት
የሚበልጡ መናንያን በማግኘቱ መነኮሳትማ እነርሱ እንጂ እኔ ምንድን ነኝ? እያለ ራሱን እየወቀሰ
እንደተመለሰ በመጽሐፈ መነኮሳት ተጽፎ እናገኛለን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ‚መስተበቊዕ‛ የሚባል የጸሎት
ክፍል፡፡ አለ ይህ ጸሎት በካህናት አባቶቻችን ስለሙታን፣ ስለሕያዋን፣ ስለነገሠታት፣ ስለ ጳጳሳት ስለ ንዑሰ
ክርስቲያን፣ ስለ ምእመናን መባዕ ስለሚያቀርቡ ስለነጋድያን፣ ስለዜናም ስለ ወንዝች የሚጸለይ ትልቅ ቦታ
የሚሰጠው የጸሎት ክፍል ነው፡፡
ጠቅላላውን በቤተ ክርስቲያን የሚጸልዩ ጸሎታት ጸሎተ ፍትሐት፣ ጸሎተ ተክሊል፣ ጸሎተ ህሙማን፣ ጸሎተ
ቅዳሴ፣ ጸሎተ ሰዓታት፣ የግል ጸሎት፣ የማኅበር ጸሎት በተጨማሪም ጸሎተ ንዋየ ቅዱሳት እነዙህ ሁሉ ከላይ
ከረርዓቸው ሦስቱ የጸሎት ክፍሎች አይወጡም፡፡ ከጸሎተ አኰቴት ከጸሎተ ምህላ፣ ከጸሎተ
አስተበቊዖት ይመደባሉ፡፡ እነዙህን ጸሎታት በሰቂለ ኅሊና በአንቃዕድዎ /ዐይንን ወደ እግዙአብሔር
በማንሳት/ መጸለይ ታላቅ ዋጋ የሚያሰጥ ከሰይጣን ወጥመድ የሚታደግ ሕይወትን የሚስተካከል
ከእግዙአብሔር ጋር የሚያስታርቅ አጋንንትን የሚያርቅ ኀይለ እግዙአብሔርን ለሚጸልየው የሚያስታጥቅ
መላእክትን የሚያስመስል ነው፡፡
ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት‛ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ ፣ስለ ጽድቅህ ፍርድ
በቀን ሰባት ጊዛ አመሰግንሃለው‛/መዜ 118-164/ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዛ
በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ሰባቱ የጸሎት ጊዛያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡
ቅዱስ ዳዊት ‚አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ‛ መዜ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ
ሲተካ፣ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡በዙህ ጊዛ የሚከተሉትን
ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡ ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ
በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን። የመጀመሪያው ሰው አዳም
የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ
መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና
ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዙህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ
ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን።
ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት) ጸሎት ይባላል፡፡ይህ የጸሎት ጊዛ
ሔዋን የተፈጠረችበት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆ ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት ነቢዩ ዳንኤል
ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ
ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዙአብሔር ንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ
የተቀበሉበት /ሰዓት ነው፡፡
አምስተኛው የጸሎት ጊዛ የሠርክ ጸሎት ነው፡፡ስለዙህ የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡‛ጸሎቴን
እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን‛ (መዜ 140 ÷2) ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር
የወረደበት ሰዓት ነው፡፡ (ማቴ. 27÷ 57)
ይህ ጊዛ ዕለቱን በሰላም አሳልፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንጋጅበት ነው፡፡በሰላም ላዋለን ፈጣሪ በሰላም
አሳድረን ብለን ራሳችንን በእምነት የምናስረክብበት ነው፡፡ እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን
የማያንቀላፋ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል።ስለዙህ ከመተኛታችን በፊት ሊሌሊቱን እንዲባርክልን እንጸልያለን።
በዙህ ጊዛ፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ዚሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡
ቀኑ አልፎ በሌሊቱ ይተካል ስለዙህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡
ሰላም አሳድረንም ብለን ለፈጣሪ ራሳችንን በእምነት አደራ እናስረክባለን፡፡
እኩለ ሌሊትም እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት ። ቅዱሰ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት
እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ‛‚ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ንድ
እነሳለሁ‛/መዜ 118-62/በማለት ይህ ሰዓት ከእግዙአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት ሰዓት ነው። ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ
ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም
ሰዓት ነው። ከዙህ የተነሳ ለእኛ ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም
ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን በማሰብ ሞትን ድል እንደተነሳልንም አስበን በማመስገን
ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዙህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡
በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት የታቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታናል፡፡እነዙህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ
መነኮሳት በየበረሃው የሚዝሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ ይጸልዩባቸዋልም፡፡በከተማ በሥራ ምክንያት
ሩጫ በዜቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና
ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል።ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና
ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡
ምን እንጸልይ?
በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት / በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ
የሚወተሩ እለታዊ ጸሎታት/ እነኚህ ናቸው፡፡
1.መዝሙረ ዳዊት
መዜሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ምእመናን በሁሉም
ንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው።አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዙህ ጊዛ ጀምረው
እየደገሙት፣እየጸለዩበት ይኖራሉ።ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም።መዜሙረ
ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው።ቀጥለን እንመልከት ሰኞ ከ 1 – 30
ማክሰኞ ከ 31 – 60፣ረቡዕ ከ 61 – 80፣ሐሙስ ከ 81 – 110፣አርብ ከ 111 – 130፣ቅዳሜ ከ 131 – 150
እሁድ- ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ሰሎሞን ይጸለያል፡፡
አንድ ንጉሥ መዜሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታውን ሃያ እና ሰላሳ መዜሙር ማድረስ ባንችል
እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል። አንድ ንጉሥ የሚባለው፡-አስር መዜሙር ነው፡፡ለምሳሌ ሰከኞ
አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ 1 – 10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ 30 -40 ያውን
የመጀመሪያውን አስር መዜሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ
መዜሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡
2. ውዳሴ ማርያም
ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው።የወትር ጸሎት ካደረስን
በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ
መሆን ተገቢ ነው፡፡ በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው
አያድሩም፡፡በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎች እና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ
ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ
ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡
3. ወንጌል ዮሐንስ
የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡አባቶች ይህንን ጸሎት
በየእለቱ እያደረሱ ብዘ ተጠቅመውበታል።
4.ሌሎች ጸሎታት
ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም ፣ በመዜገበ ጸሎት እንዲሁም በመዜሙረ
ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣እንዲሁም ገድላት፣ተአምራትን፣እንደ ችሎታችን በየዕለቱ
እናደርሳለን፡፡ ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዜሙረ ዳዊትና ፣ውዳሴ ማርያምን
ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡
9.ሥርዓተ ቀንዲል
ቅብዓ ቅዱስ /የተለየ የከበረ ይት (ቅባት) እየተባለ ይጠራል። ይህም ከወይራ ዚፍ በጸሎት በመታገዜ
በረድኤተ እግዙአብሔር የሚጋጅ /የሚወጣ /ይት ነው። በተጋጀለት የክብር ዕቃ /ብልቃጥ/
ተደርጎ በከርሰ መንበር ወይም በዕቃ ቤት በክብር ይቀመጣል።
በመቀጠልም ባቅሙ የሚችለውን ቀኖና እንዲፈጽም ያዋል:: ከዙያም ካህኑ /የንስሐ አባቱ/ ከሌሎች
ካህናት ጋር ሆኖ ምሥጢሩን ለታማሚው ለመፈጸም ይጋጃል፡፡ ከዙያም ቀንዲሉን /መብራቱን/
አብርቶ መጽሐፈ ቀንዲልን በመጠቀም የታውን ጸሎት ይጸልዩለታል።
በጸሎቱ ፍጻሜም የሕመምተኛውን ሕዋሳት በተለይ የታመመውን ክፍል በተጸለየበት ቅብዐ ቅዱስ
ሥርዓተ ቀንዲልን የሚፈጽሙት ሰባት ኤጲስ ቆጶሳት ወይም ቀሳውስት ሆነው ነው። እነዙህ ሰባት
መሆናቸው ሰባት ቁጥር በዕብራውያን ፍጹም ቁጥር እንደመሆኑ በምሥጢረ ቀንዲል ፍጹም
ሥርየትና ፈውስ መገኘቱን ለማጠየቅ ነው። እነሱም /ካህናቱ/ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ያያቸው የሰባቱ
የወርቅ መቅረዝችና መብራቶች ምሳሌ ናቸው። (ራእ፩፥፳፡፡) ከላይ እንደገለጽነው ኃጢአቱን ለተናው
ምእመን በቀረበው ንጹሕ ይት ላይ የታው ጸሎት ይደረሳል። ሰባቱም ካህናት በየተራ በታመመው ራስ
ላይ የታዘትን የወንጌል ክፍላት ያነባሉ ወንጌል ከተነበበ በኋላም ሰባቱም እጃቸውን በሕመምተኛው
ላይ ጭነው የታዘትን ጸሎታት ይጸልዩለታል፡፡
አእምሮ የሚገኝበት የአምስቱ የስሜት ሕዋሳት ማዕከልና የማስተዋል /የማሰብ/ ኃይል የሚገኝበት
ክፍል ነውና፤ በዋናነት ግንባርም ይቀባል፡፡ የልብ ማረፊያ ነውና ደረቱም ይቀባል፡፡ ሰውነቱን ሁሉ
ሊበክል የሚችል የርኩሰት ቁስል /ቁስለ ነፍስ/ የሚመነጭ ከሱ ነውና ፈጽሞ እንዲፈወስ እነዙህ ሁሉ
ይቀባሉ፡፡ ከቀሳውስት በታች ያሉ ዲያቆናት ግን ለካህናት ከመታዜና ከመራዳት በስተቀር ይህንን
ምሥጢር መፈጸም እንደማይችሉ የታወቀ ነው።
በምግባርና በሃይማኖት ይዚ የቆየች ወደፊትም የምትኖር ብቸኛዋ የክርስቶስ ሙሽራ ይህችው እናት
ቤተክርስቲያን ነች።
ሰንበት ትምርት ቤት ከሕጻንነት እድሜያችን ጀምሮ እስከ እርጅና መናችን የማንለያት የጥበብና የፍቅር
ቤታችን ናት የቅደስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት የሀይማኖታችንን ዶግማና ቀኖና ጠንቅቀን እድናውቅ
የምታደርገን የጥበብ ማሕደር የቅደስት ቤተ ክርስቲያን አንዷ የወንጌል ማደረሻ ክፍል ነች፡፡ስለዙህ ለንጸና
በእውነት ልንመላለስ ለነፍሳችንም ለስጋችንም የሚበቃ ጥበብን እድንቀስም አደራ እላለሁ!!!