You are on page 1of 27

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት


(የመምህሩ መምሪያ)

በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት

የህጻናትና ማዕከላውያን ክፍል ለክረምት የማጠናከሪያ ት/ት ተማሪዎች የተዘጋጀ

ሰኔ 2014 ዓ.ም
ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ማውጫ
መግቢያ ............................................................................................................................................................ 4

የትምህርቱ ጥቅል መረጃ ........................................................................................................................................ 5

ምዕራፍ 1 - ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት ................................................................................................................ 6

1.1 ሕይወት ምንድነው? ............................................................................................................................ 6

1.2 የሕይወት ክህሎት ምን ማለት ነው? .......................................................................................................... 6

1.4 ኦርቶዶክሳዊ ስብዕና ምንድነው?..................................................................................................................... 6

1.4.1 ሰው ኦርቶዶክሳዊ ሰብእናን እንዴት ያዳብራል?............................................................................................ 7

1.4.2 ኦርቶዶክሳዊ ጠባያት ............................................................................................................................ 7

1.4.3 የኦርቶዶክሳዊት ግብ ............................................................................................................................ 8

1 ምድራዊ ግብ (Earthly Goals)................................................................................................................... 8

2 ሠማያዊ ግብ (Eternal Goals) ................................................................................................................... 8

1.5 ተግባራዊ ኦርቶዶክሳዊነት ............................................................................................................................. 9

ምዕራፍ 2 - ራስን መገንዘብ .................................................................................................................................. 11

21 ራስን ማወቅ ............................................................................................................................................ 11

2.2 ራስን ማክበር .......................................................................................................................................... 12

2.3 ራስን መግዛት......................................................................................................................................... 14

2.3.1 ስሜቶችን እንዴት መግዛት እችላለሁ? .................................................................................................... 14

2.4 በራስ መተማመን ..................................................................................................................................... 16

ምዕራፍ 3 – አወንታዊ ግንኙነት............................................................................................................................. 17

3.1 የተግባቦት ክሂሎት /ነባቢት ባህርይን የማሳደግ ጥበብ /communication skill ...................................................... 17

3.2 የአቻ ግፊት ............................................................................................................................................ 20

ምዕራፍ 4- በጥልቀት ማሰብ ................................................................................................................................. 21

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 2


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

4.1 በጥልቀት ማሰብ ...................................................................................................................................... 21

4.2 ውሳኔ ሰጪነት......................................................................................................................................... 22

4.3 የአቋም ሰው መሆን................................................................................................................................... 23

4.4 የጊዜ አጠቃቀም....................................................................................................................................... 24

ዋቢ መጽሐፍት ................................................................................................................................................. 27

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 3


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

መግቢያ
የሕይወት ክህሎት ስልጠናዎች ታዳጊዎችንና ወጣቶችን ትኩረት በማድረግ ብቻውን ወይም
ከሌሎች ትምህርቶች ጋር በመቀናጀት በመደበኛ ትምህርት ወይም ስልጠና መልክ የሚሰጥ
የስብዕና ግንባታ አንዱ አካል ነው፡፡ ስለልጠናው ታዳጊዎችና ወጣቶች ወደፊት ለሚገጥማቸው
የሕይወት ውጣ ውረዶች ራሳቸውን እነዲያዘጋጁ፣ ውጤታማ የሆነ ግንኙነቶችን
ከአቻዎቻቸውና ከማህበረሰቡ ጋር እንዲፈጥሩ፣ ራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ የሚረዳ
በመሆኑ በአሑን ሰአት በበርካታ ሀገራት የተስፋፋ ሲሆን በዋናነትም እንደ ዩኒሴፍና የአለም
የጤና ድርጅት ባሉ አለማቀፋዊ ተቋማት ማኑዋል ተዘጋጅቶለት እየተተገበረ ይገኛል፡፡
በሐገራችን ኢትዮጵያም እነዚህ ክህሎቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት
ተማሪዎች ድረስ ላሉ ተማሪዎች በተለያዩ መንገዶች በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ
ድርጅቶች መሰጠት ከተጀመረ ከሁለት አስርት አመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡

ስልጠናው ከአለማዊ ዕይታ አንጻር በርካታ ጠቀሜታዎች ቢኖሩትም የታዳጊዎችን መንፈሳዊ


አቅም ከመገንባት አንጻር ደካማ በመሆኑ በሕይወት ክህሎት ሥልጠናው መንፈሳዊ
ህይወታቸውን ማጠንከር ካለመቻሉ ባሻገር በተለይ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አንጻር ተገቢ
ያልሆኑ ሐሳቦችን ለአብነት ያህል ወጣቶች በራስ አቅም መመካትን፣ የትውፊትና የሥርዓት
አላስፈላጊነትን፣ ቅድመ ትዳር የሚጀመሩ ግንኙነቶችና የመሳሰሉት ታቅዶበትም ሆነ ሳይታሰብ
ስለሚተላለፍበት በቀላሉ ታዳጊ ወጣቶችን የመበከልና አለማዊ ብቻ አድርጎ የመቅረጽ ዕድል
ይሰጠዋል፡፡

በመሆኑም ይህን ስልጠና አወንታዊ ጎኖቹን በመውሰድና በኦርቶዶክሳዊ እይታዎች፣


ማሳያዎችና እሴቶች በማጥመቅ ኦርቶዶክሳዊ መልክና ጣዕም በመስጠት ሰልጣኞችን
በቤተክርስቲያን ህብረት ውስጥ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያሻግር መንፈሳዊ ስንቅ ከነገረ
ሃይማኖት፣ ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ከነገረ ቅዱሳን እንዲቋጥሩበት ለማስቻል ይሄ ማስተማሪያ
ተዘጋጅቷል፡፡

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 4


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

የትምህርቱ ጥቅል መረጃ


የትምህርቱ ርዕስ: ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

የትምህርቱ አይነት: ተከታታይ

ታሳቢ ተጠቃሚዎች: የ7ኛና 8ኛ ክፍል የክረምት የማጠናከርያ ት/ት ተማሪዎች

የትምህርቱ አላማ

• ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው ባሻገር ተጨማሪ ክህሎቶችን እንዲያገኙ ማስቻል

• በመንፈሳዊም ሆነ በማህበራዊ ህይወታቸው ውስጥ ክርስትናን እንዲገልጡ ማነሳሳት

• በአለማዊ የሕይወት ክህሎት ስልጠናዎች የሚዘነጉና በተሳሳተ መልኩ የሚገለጹ


ኦርቶዶክሳዊ እሴቶችን ማሳየት

የትምህርቱ ይዘት

• ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

• ኦርቶዶክሳዊ ስብዕና

• የተግባቦት ክህሎት

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 5


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ምዕራፍ 1 - ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

1.1 ሕይወት ምንድነው?


ሕይወት ማለት በማህፀን ውስጥ የሚጀመርና በሞት ሳይቋረጥ ከዚህ አለምም ተሻግሮ በወዲያኛውም
አለም የሚቀጥል ሂደት ነው፡፡ ይሔ ሕይወት በምድር ያለው ቆይታ በመወለድ ጀምሮ በሞት የሚዘጋ
ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ጊዜያትን ሲይዝ በዋናነት ዘመነ ነፋስ፣ ዘመነ እሳት፣ ዘመነ ማይና ዘመነ
መሬት ተብሎ ይከፈላል፡፡

1.2 የሕይወት ክህሎት ምን ማለት ነው?


የሕይወት ክህሎት ማለት ሰዎች በሕይወት ባሉ ዘመን ሁሉ ገንዘብ ሊያደርጓቸው የሚገቡ
መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን የሚያቀሉ ክህሎቶች ሲሆኑ
በዋነኝነት በታዳጊነት ላይ ለሚገኙ ወጣቶች የሚሰጥ ሲሆን በተሻለ መልኩ አመስጋኝ፣ ንቁና
መልካም ትውልድ ሆነው እንዲያድጉ የሚረዳ ጥበብ ነው፡፡

1.4 ኦርቶዶክሳዊ ስብዕና ምንድነው?


ሰው በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረ ክቡር ፍጡር ነው፡፡ ሰው ፈጣሪውን የሚመስል ብቸኛ
ፍጡር ነው፡፡ ሰው ሥጋና ነፍስ ሲሆን፤ የሚናገርና የሚያስብ ነጻ አእምሮ ያለው ፍጡር ነው፡፡
የፍጥረታት ሁሉ ዘውድ ነው፡፡ እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረታት ላይ የሾመው ባለሥልጣን
(ገዥ) ነው፡፡ እርሱ ደግሞ የገዥዎች ሁሉ ገዥ ለሆነው ለእግዚአብሔር ይገዛል፡፡ መዝ.
2÷01፡፡ ሰው ነጻነት፣ ነጻ ፍቃድ፣ አሳቢ አእምሮና ሐሳቡን መግለጫ አንደበት አለው፡፡
አምላኩን የሚመስለው በነፍስ ባሕሪው ነው፡፡ ሰው ኑሮውን በአምላኩ ፍቃድ የሚመራ መሆን
አለበት፡፡ ሰው በሥጋም በነፍስም ሙሉ ሲሆን፣ በመንፈሳዊ ሕይወቱና በሥጋዊ ኑሮው በጥበብ
ሲመላለስ እንዲሁም በመንፈስ ፍሬዎች ያጌጠ ማንነት ሲኖረው ጠንካራ ሰብእና አለው
ይባላል፡፡ የጠንካራ ሰብእና መገለጫዎች ትዕግሥት፣ ይቅር ባይነት፣ ልበ ሰፊነት፣ ጽንዓት፣
ራስን መግዛትና የዋህነት ናቸው፡፡ ሰው ዕውቀቱን፣ ጉልበቱንና ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 6


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ሲችል፤ በጎነትን ሲያበዛ፤ በክፉዎች ላይ የመልካምነት ተፅዕኖ ሲያደርግ፤ ጠንካራ ሰብእናን


አዳብሯል እንላለን፡፡

1.4.1 ሰው ኦርቶዶክሳዊ ሰብእናን እንዴት ያዳብራል?


ሰው በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጠንካራ ለመሆን ሙሉ ሰው ወደ መሆን ማደግ
አለበት፡፡ በሥጋዊ ሕይወቱ ሥጋዊ ዕውቀት መጨመር፣ ማኅበራዊ ሕይወትን በጥበብ
መምራት፣ በጥንቃቄና በማስተዋል መጓዝ፣ በልባምነትና በየዋህነት መመላለስ ጊዜና ኃይሉን
በአግባቡ መጠቀም አለበት፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወቱ በክርስቶስ ማመን፤ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
ኅብረት ማድረግ፣ በመንፈስ ፍሬዎች ማንነቱን ማስጌጥ፣ ከክብር ወደ ክብር መሻገር አለበት፡፡
ለሌሎች ያለውን ፍቅር ማሳደግ በመልካም ሥራው መግለጽ አለበት፡፡ ጠላታችንን እስከ
መውደድ ፍቅራችን ሊያድግ ይገባል፡፡ ሥጋዊ ፍላጎቶችን ድል መንሣት፣ በትሕትና ዝቅ ብሎ
ማገልገል፣ ችግሮችን መቋቋም፣ ልበ ሰፊ (ብልህ)ና የዋህ መሆን፣ ዕውቀትን መጨመርና
የመልካምነት ተፅዕኖ መፍጠር የመንፈሳዊ ሰው ጠንካራ ሰብእና መገለጫዎች ናቸው፡፡ ጠንካራ
ሰብእናን ለማዳበር ጥበብን መፈለግ፣ ዕውቀትን መጨመር፣ በጽድቅ ፍሬ ለማደግ መበርታትና
የእግዚአብሔርን ፈቃድና ርዳታ በጸሎት በመጠየቅ በእምነት ወደ ሙሉነት መገስገስ
ያስፈልጋል፡፡

1.4.2 ኦርቶዶክሳዊ ጠባያት


❖ ተማሕሏዊነት (Mystical Experience): ጸሎትና ልመናና፣ መማለድ በኦርቶዶክሳዊነት ውስጥ
ትልቁ ተግባር ነው፡፡ የትኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክዋኔያት ያለ ጸሎት አይከወንም፡፡
የቤተክርስቲያናችን ትልቁ የጸሎት ክፍል የሆነውን ቅዳሴን እንኳን ብንመለከት ዋና ዋና
የሚባሉ የአንድ ምዕመንን ሕይወትም ሆነ ቤተክርስቲያናዊ ተግባራትን ጠቅልሎ የያዘ የነገረ
ሃይማኖትና ሥርዓተ አምልኮ ማዕከል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

❖ አንድነት (Unity)፡ ክርስትና በአይነቷ ህብረታዊት ናት በመሆኑም በእዚህች ህብረት ውስጥ ያሉ


ክርስቲያኖች እርስ በእርስ የማይጣሉ፣ የሚስማሙ፣ የሚረዳዱና አንዳቸው ለአንዳቸው ድጋፍ
የሚሆኑ ናቸው።

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 7


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

❖ ቤተክርስቲያናዊነት (Ecclesiastic)፡ ቤተክርስቲያን የሚለው ትርጉም ለምዕመናን ህብረት


እንደሚሰጠው ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለሆንን ለኛም ለእያንዳንዳችንም የሚያገለግል ነው
ዶግማዋ፣ ቀኖናዋና ትውፊቷ በሕይወት የምንኖራቸው የየራሳችን የሕይወት አንዱ አካል
አድርጎ መኖርን ይጠይቃል፡፡

❖ ሥርዐታዊነት፡ ኦርቶዶክሳዊነት ከክርስቶስና ከምዕመናን ጋር የሚኖር ያልተቋረጠ ህብረት


እንደመሆኑ መጠን ግንኙነቶቹ የሚሰምሩባቸው ሥርዐተ አምልኳዊና ማሕበራዊ ሥርአቶችና
ሥነ ምግባራት አሏት

❖ ክርስቶሳዊነት / ሱታፌ አምላክ (Theosis)፡ ኦርቶዶክሳዊነት ቀስበቀስ ወደ አምላክ ዘበጸጋነት


የሚታደግበት ሕይወት ነው፡፡ ይህ ሂደት በመጥፎ ተግባራት ከመሸሽ ጀምሮ፣ መልካም ሥነ
ምግባርን መላበስ ምሥጢራትን በመካፈል የሚከወን ነው፡፡

1.4.3 የኦርቶዶክሳዊት ግብ

1 ምድራዊ ግብ (Earthly Goals)


• ምድራዊ ግቦች የምንላቸው

• የመንፈስ ፍሬዎችን ማፍራት

• ተፈጥሮን ለመግዛትና ለመንከባበከብ

• ለዓለም ብርሐንና ጨው ለመሆን

• ነፍሳትን ወደ እግዚአብሔር መንግስት መሳብ (ሌሎችን መዳን)

2 ሠማያዊ ግብ (Eternal Goals)


መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ ማቴ 5:48 እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ
እናንተ ፍጹማን ሁኑ። በማለት እንደተናገረው የኦርቶዶክሳዊ ወጣት ግቡ በንስሃና በሚስጥራት
በኩል ፍጽምናን ገንዘብ ማድረግ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ ወጣት የፍጽምና ከፍታ ላይ ለመድረስ እነዚህን ነገሮች ሊከተል ይገባል፡

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 8


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

❇ከእግዚአብሔርና ከሰዎች በሚያገኛቸው ምክሮችና ድጋፎች መሰረት የራሱን ውሳኔ መወሰንና


ለራሱ ሓላፊነትን መውሰድ

❇ደስታ በትክክለኛው ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ስሜታዊ ፍላጎቶችን ማዘግየት;

❇ወዳጅነትን በትእግስትና በይቅርታ አድርግ

❇ግልጽ የሆነ የሕይወት መርህና ግብ ይኑርህ

❇በዙሪያህ ሁሉ የእግዚአብሔርን መኖርን አስታውስ. ለህጉም ተገዛ.

1.5 ተግባራዊ ኦርቶዶክሳዊነት


ተግባራዊ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና እውነትን በሥራ የምንገልጽበት
መንገድ ነው። ተግባራዊ ኦርቶዶክሳዊነት በቤተክርስቲያን ውስጥና በማሕበራዊ ሕይወት ተብሎ
ለሁለት የሚከፈል ሲሆን አእምሮንና የስሜት ህዋሳትን ለፈቃደ እግዚአብሔር ማስገዛት ማለት
ነው።

ተግባራዊ ኦርቶዶክሳዊነት በሂደት የሚያድግና ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም እርምጃዎች ግን በቶሎ


የሚጀመሩና በእምነት ላይ የተመሰረቱ መሆን ይኖርባቸዋል። ተግባራዊ ኦርቶዶክሳዊነት ከክፉ
ቦታዎች መሸሽን፣ ሐሳቦችን መቆጣጠር፣ የስሜት ህዋሳትን ከሐጢያት መጠበቅና በምትኩ
መልካም ነገርን መለማመድን ያጠቃልላል።

የኦርቶዶክሳውያን መመሪያ

✅ ከእግዚአብሔር የሚያርቅ ሃጥያትን በመተግበር የእግዚአብሔርን አርአያ አለማጣት

✅ በከንቱ ምኞት በባዶነት ስሜት ውስጥ አለመዘፈቅ

 የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው


እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። (ኤፌ 4:28).

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 9


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

✅ ለምድራዊ ደስታ ወርቃማ ክርስቲያናዊ እሴቶችን ዝቅ አያደርግም

✅ እውነተኛውን የፍቅርን ትርጉም አያረክስም (1 ቆሮ 13).

✅ ክርስቲያናዊ መርሆች ከአካባቢያዊ ጫናዎች በላይ መሆናቸውን አይዘነጋም

✅ የክርስቶስ አካሉ ከሆነች ቤ/ክ አገልግሎትና ምግባረ ሰናያት አይርቅም

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 10


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ምዕራፍ 2 - ራስን መገንዘብ

21 ራስን ማወቅ
እስከዚህ ያደረስከኝ እኔ ማን ነኝ 1ኛ ዜና 17፡16

በህይወታችን ውስጥ ሊኖረን ከሚገቡ ነገሮች ቁልፉ እራስን ማወቅ ነው፡፡ ራሱን የማያውቅ
ሰው በየትኛውም መንገድ ውጤታማ መሆን አይችልም፡፡

ራስን ማወቅ ማለት የራስን ሁኔታ፣ጠባይ፣ማንነት፣ድካም፣ጥንካሬ፣ ምቹ እድሎችና


መሰናክሎችን ለይቶ ማወቅና ማሰብ ነው፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እግዚአብሔር በፈርኦን ፊት
ሲልከው በዘጸ 3፡11 የጠየቀውም ሆነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የተደረገለትን አስቦ በ1ኛ ዜና
17፡16 እኔ ማነኝ ብለው የጠየቁት ጥያቄ ራስን የማወቅ መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡

ራስን ለማወቅ ሌሎች ተጨማሪ ጥያቄዎች

❖ አላማዩ ምንድነው

❖ ምን ሞክሬ ምን አልተሳካልኝም

❖ እኔ ምን አለኝ

❖ ምን ማድረግ እችላለሁ

❖ ምን ማድረግ እፈልጋለሁ

❖ ምን ለማድረግ የሚያሰችል ምን አቅም አለኝ

❖ ምን ባደርግ ምን እንቅፋት ይገጥመኛል

ክርስቲያኖች ራሳቸውን ለማወቅ በሚሄዱበት መንገድ ውስጥ በራሳቸው ደካማና ሐጢያተኛ


መሆናቸውንና በእግዚአብሔር በኩል ሁሉን ማድረግ የሚችሉና በዙሪያቸው እንደ ደመና

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 11


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

የከበቡ ቅዱሳንና በዙሪያቸው እንደሚያገሳ አንበሳ የሚዞር የዲያቢሎስ ፈተና እንዳለባቸው


መዘንጋት አይኖርባቸውም፡፡

የራስን ማወቅ ሰንጠረዥ

ዓላማ ጠንካራ ጎን ደካማ ጎን ምቹ ፈተናዎች መፍትሔዎች


ሁኔታዎች

2.2 ራስን ማክበር


መጽሐፍ ቅዱስ ሰው በእግዚአብሔር አርአያ እና አምሳል የተፈጠረ ክቡር እንደሆነ
ይመሰክራል፡፡ ሰው ግን ብዙ ጊዜ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እንዲሁም በተለያዩ ተጽእኖዎች
ይህን ክብሩን ሲዘነጋ እና የማይገባውን ሥራ ሲሠራ ይታያል፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት ይህን
ሲገልጽ በመዝሙሩ፤ “ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም፤ እንደሚጠፋ እንስሶች መሰለ፡፡” ብሏል፡፡
/መዝ. 8/9/÷02/ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳከበረን ተገንዝበን ስለራሳችን በጎ Aመለካከት
ሊኖረን ይገባል፡፡ ሰው የእግዚAብሔር ፍጡር እንደሆነ የሚናገረው መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ
ነው፡፡ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ስለተፈጠረ እግዚአብሔር የሰጠውን ክብርና
ማዕረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ተዘርዝሮ እናነባለን፡፡ “እግዚአብሔርም አለ፡- ሰውን በመልካችን
እንደምሳሌያችን እንፍጠር…እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ ወንድና ሴት አድርጎ
ፈጠራቸው፡፡” (ዘፍ. 1.!6) በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል መፈጠራችንን አምነንና ተቀብለን
ራሳችንን ማክበር የሁላችንም ሓላፊነት ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ውብ ሆኖ
እንደተፈጠረ ሲመሰክር፡- “እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ” ብሏል፡፡ /መኃልየ መኃልይ

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 12


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

1÷5/ መዝሙረኛው ዳዊትም ክብሩን ስላወቀ ስለ ተፈጥሮው እግዚAብሔርን “ግሩምና ድንቅ


ሆኜ ተፈጥሬያለሁና አመሰግንሃለሁ፤ሥራህ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች”
(መዝ.)"8()"9)÷04) በማለት አመሰግኗል፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ሰው ሆኖ በመምጣቱና የኛን ሥጋ በመልበሱ፤
ሰው የከበረ ፍጡር መሆኑን በሥጋዌው አስተማረን፡፡ ፈሪሳውያንም ለሰው የተዛባ Aመለካከት
ስለነበራቸውና ሰውን ከሰንበት አሳንሰው ያዩ ስለነበር የሰው ልጅ የሰንበት ጌታዋ እንደሆነም
አስተማረ፡፡ (ማቴ. 02.1-04) ባልንጀራችንን እንደራሳችን እንድንወድ ታዘናል፡፡ ራሱን
ያልወደደ፣ ያላከበረ፣ ጤንነቱን፣ ንጽሕናውን የማይንከባከብ፣ ለሕይወቱ ዋጋ የማይሰጥና ራሱን
ያልተቀበለ ሰው ሌላውን ሊያፈቅር፣ ሊንከባከብ፣ ስለሌላው ጤንነት ለማሰብ ለመጨነቅ
ስለማይችል ጌታችን፤ ‹‹ባልንጀራችሁን እንደራሳችሁ ውደዱ›› አለ፡፡ ሰውነቱን ያከበረ ሰው
ሌላውን ሰው ያከብራል፡፡ ራሱን የተቀበለ ሰው ሌላውን ለመቀበል አይከብደውም፤ በራሱ
የሚተማመን ሰው ሌላውን ለማመን በሌላው ላይ እምነት ለመጣል አይከብደውም፡፡

1. ለራሳችን ጥሩ የሆነ አመለካከት ካለን፡-


• ለሕይወት ትርጉም እንሰጣለን፤
• በተፈጥሯችን ደስተኞች እንሆናለን፤
• ለሌሎች ተፈላጊዎች እንደሆንና እኛም ሌሎች እንደሚያስፈልጉን እናምናለን፤
• በሚገጥሙን ችግሮች ሳንማረርና ተስፋ ሳንቆርጥ ነገ የተሻለ እንደሚሆን እናስባለን፤
• በጎ ነገሮችን የማሰብና ደስተኛ የመሆን እድላችን ሰፊ ነው…ወ.ዘ.ተ፡፡
2. ለራሳችን ጥሩ የሆነ አመለካከት ከሌለን፡-
• ሕይወታችን ትርጉም ስለሚያጣ ተስፋ እንቆርጣለን፤ መኖርን እንጠላለን፤
• ራሳችንን የማንጠቅምና የማናስፈልግ አድርገን እናያለን፤
• ራሳችንን አስቀያሚ አድርገን ስለምንመለከት ራሳችንን እንጠላለን፤
• በሌሎች ተወዳጆች እንዳልሆንና ፈላጊ እንደሌለን እናስባለን፤
• በራሳችን ውበትና ተፈጥሮ ስለማንረካ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ማረጋገጫ ለማግኘትና፤
ራሳችንን

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 13


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

• ከሌሎች ጋር በማነጻጸር እንጠመዳለን… ወ.ዘ.ተ፡፡

2.3 ራስን መግዛት


ሰው ነጻ ፈቃድና ነጻ አእምሮ አለው፡፡ በውስጣችን ባለው መሻት ላይ ባለሥልጣን ሆነን ነጻ
ፈቃዳችን ለኃጢአት ተገዥነት አይዳረግም፡፡ሰው ስሜት ያለው ፍጡር ነው፡፡ ራሳችንን ስንገዛ
ስሜታችንን መቆጣጠር እንችላለን፡፡ በሰው ውስጥ ብዙ ሐሳብ፣ የጋለ ስሜት፣ ክፉና ደግን
የመምረጥ ነጻ ፈቃድና ወሳኝ ነጻ አእምሮ አለ፡፡ እነዚህ ነገሮች የሥጋ ወይም የመንፈስ ፈቃድ
መገልገያ ክፉ ወይም ደግ መሥሪያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስሜት በራሱ ኃጢአት አይደለም፡፡
ስሜትን ያለቦታው አለአግባብ ስንጠቀም፣ ለሥጋ ፍላጎትና ለዓይን አምሮት ስንገዛ ኃጢአት
እንሠራለን፡፡ 1ዮሐ. 2÷06፡፡
ስሜታችንን ለበጎ ሥራ ማዋል እንችላለን፡፡ ውስጣችን ለነገሮች ሁሉ የሚሰጠው ምላሽ ስሜት
ነው፡፡ ለምናየውና ለምንሰማው ነገር ስሜታችን መልስ አለው፡፡ ባየነውና በሰማነው ነገር
ስሜታችን ክፉ ወይም መልካም መነሣሣት ይፈጥራል፡፡ ውጫዊ እንቅስቃሴያችን ወይም
ድርጊታችን የሚመነጨው ከውስጣዊ ስሜት ነው፡፡ ስሜታችንን በድርጊት እንገልጻለን፡፡
ውስጣዊ ስሜታችን በውጫዊው ነገር ይቀሰቅሳል፡፡ ስለዚህ የክፉው ዓለም የኃጢአት ሥርዓት
ስሜታችንን ተጠቅሞ ከጽድቅ ጎዳና እንዳያወጣን ራሳችንን መግዛት አለብን፡፡ ከውስጥ
የሚመነጩ ክፉ መሻቶችን በአግባቡ ማሸነፍ ይጠበቅብናል፡፡በአግባብ ሲባል፣ከግብታዊነት ወይም
ከደመ ነፍስ ድርጊት በራቀ መልኩ ይህም ማለት ትዕግስተኛ በመሆን፣ ምክንያታዊ በመሆን፣
ትክክለኛ ቦታንና ጊዜን በመምረጥ መሆን ይኖርበታል፡፡

2.3.1 ስሜቶችን እንዴት መግዛት እችላለሁ?


✓ ሳያቋርጡ በመጸለይ፡፡ 1ተሰ. 5÷07፡፡
✓ ራስን በቅድስና በመጠበቅ፡፡ 1ጢሞ. 5÷!2፡፡
✓ ጠላትን በመውደድ፤ ክፉን በመልካም በማሸነፍ፡፡ ማቴ. 5÷#4፡፡
✓ የባልንጀራን ጥቅም በማስቀደም፡፡ 1ቆሮ. 0÷!4፡፡
✓ በልበ ሰፊነት ከጥፋት ለመዳን በማሰብ፡፡ 1ጴጥ. 3÷0-03፡፡
✓ ለራስ በመጠንቀቅና ራስን በመፈተን፡፡ 1ቆሮ. 01÷!8፣ 1ጢሞ. 4÷06፡፡
በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 14
ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

✓ ንዴት የተፈጠረበትን ቦታ ትቶ መሄድ፡፡


✓ መዝሙር ማዳመጥ
✓ ለሌሎች ማውራት፡፡
✓ መጽሐፍ ማንበብ፡፡
✓ አንዳንድ ሥራዎችን መሥራት፡፡
2.3.2 ራሳቸውን የሚገዙ ሰዎች

✓ ግብታዊ አይሆኑም/በደም ነፍስ/ በነሲብ አይነዱም፣ ምክንያታዊ ናቸው፡፡


✓ ለአደጋ ተጋላጭ አይደሉም /ከአደጋ ተጋላጭነት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፡፡
✓ ራስ ወዳድ አይደሉም፡፡
✓ ከጥፋተኝነት ይርቃሉ፡፡
✓ ስሜታቸውን ይቆጣጠራሉ፡፡
✓ ከድርጊት በፊት ያስባሉ፣ ከንግግር በፊት ያስባሉ፡፡
✓ ለነገ ደስታ ዛሬን ይሠራሉ፣ ሥራን ከመዝናናት ያስቀድማሉ፡፡
✓ ከውሸታምነት፣ ከአጭበርባሪ፤ ከከዳተኛነት፣ ከሌብነት፣ ከዘረፋ---ወዘተ የተቆጠቡ
ናቸው፡፡
✓ ለራሳቸው የሚሰጡት ግምት ከፍተኛ ነው፡፡
✓ ውጤታማ የሆነ ውሰኔ ለመወሰን አይቸገሩም፡፡
✓ ውጤታማ የሆነ የችግር አፈታት ዘዴን ለመከተል አይቸገሩም፡፡
✓ ከሌሎች ጋር በመተባበር ሥራዎችን ማከናወን ይወዳሉ፡፡
✓ በትምህርት ውጤታማ ለመሆን/ስኬታማ ለመሆን ይጥራሉ፡፡
✓ የሌሎችን መብት ሳይነኩ የራስን መብት ለማስከበር ይጥራሉ፡፡
ስሜት ጤናማ እንደሆነ እንዲቀጥል በመንፈሳዊ ሕይወት መጠንከር አስፈላጊ ነው፡፡ ዘወትር
በጸሎት ስንተጋ መንፈስ ቅዱስ ራስን የመግዛት ጸጋን ያጎናጽፈናል፡፡ ራሳችንን መግዛት ከቻልን
ከክፉ ተጠብቀን ዓይኖቻችን መልካሙን ቀን ያያሉ፡፡ ሰው ለስሜቱ ከተገዛ እንስሳ ይሆናል፡፡ ዛሬ
የስሜቱን ጥያቄ ሲያሟላ ለነገ ሕይወቱ ፀፀትና መከራ ያተርፋል፡፡ ስሜትን መግዛት ግን ከብዙ

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 15


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ርኩሰትና ጥፋት ያድናል፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት ስንኖር የዘወትር ልምምዳችን ስሜትን


ለመንፈስ ፈቃድ ለማስገዛት መትጋትና ራስን በጾምና በጸሎት በመጎሰም በመልካም ሥርዓት
መመራት አለብን፡፡

2.4 በራስ መተማመን


ሰዎች ብዙ አቅምና ችሎታ እያላቸው ነገር ግን በራሳቸው መተማመንን ገንዘብ ባለማድረጋቸው
ምክንያት ነገሮችን ማሳካት ሳይችሉ ይቀራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ከመጠን በላይ በሆነ የራስ
መተማመን ምክኒያት የወረደ ውጤታማነትና መልካም ያልሆነ ጸባይን ይይዛሉ፡፡ ነገር ግን
ለአንድ ክርስቲያን በራስ መተማመን ከበራስ መመካት ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ካለ ፍጹም
ዕምነት የሚመነጭ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የራስ መተማመን መነሻው በማርቆስ ወንጌል ላይ ጌታችንና


አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ለሚያምን ሁሉ ይቻላል የሚለው ቃል ሲሆን (ማር
9፡23) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ሐይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ሲል በራስ
መተማመናችን የሚመነጨው የሐይል ሁሉ ባለቤት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ነው፡፡
(ፊሊ 4፡13)

በራስ መተማመን ማለት

የምንችለውንና ማድረግ የሚገባንን ነገር ያለምንም ፍርሐትና ጭንቀት በሙሉ ልብ በማድረግ


መቻል ነው፡፡ ይሔ መተማመን የሚመጣው ራስን ከጭንቀት ነጻ በማድረግና እስከአለም ፍጻሜ
ድረስ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ የሚለውን አምላካዊ ቃል በመታመን ነው፡፡

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 16


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ምዕራፍ 3 – አወንታዊ ግንኙነት

3.1 የተግባቦት ክሂሎት /ነባቢት ባህርይን የማሳደግ ጥበብ


/communication skill
ተግባቦት ምንድነው

ተግባቦት በሁለትና ከዛ በላይ በሆኑ አካላት መካከል የሚደረግ የመልዕክት ልውውጥ ነው፡፡ ተግባቦት
መረጃን ወደ ቃላዊ፣ ጽሁፋዊ፣ ወይም ምስላዊ ወደሆነ መንገድ በመቀየር ለተቀባይ የሚደርስበትና
ከተቀባይም ቃላዊ፣ ጽሁፋዊ፣ ወይም ምስላዊ ግብረ መልስ /አጸፋ/ምላሽ/ የሚገኝበት ሂደት ነው፡፡

የተግባቦት አይነት

1. ከተሳታፊዎች ብዛት አንጻር

❖ ግላዊ ተግባቦት /intera communication

❖ የሁለትዮሽ ተግባቦት / inter communication

❖ የብዙኃን ተግባቦት/ mass communication ተብሎ ይከፈላል

2. ከተሳታፊዎች ማንነት አንጻር ተግባቦት

❖ መንፈሳዊ ተግባቦት spiritual communication

❖ ከሰው ጋር የሚደረግ /inter personal communication

❖ ከራሰ ጋር የሚደረግ /self-communication

❖ ከግዑዛን ጋር የሚደረግ ተግባቦት /inter things communication

3. ከመንገዱ አንጻር

❖ ባለ አንድ መንገድ /one way communication

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 17


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

❖ ባለ ሁለት መንገድ /two way communication

4. በሁኔታው

❖ ቃላዊ/ልሳናዊ / verbal ፡

❖ ኢ-ቃላዊ / non verbal፡

ተግባቦት ለምን

▪ መልእክት ለመቀባበል

▪ አውቀትን ለመቅሰም

▪ ትዕዛዝ ለመቀበል

▪ ሃሳብን ለማዋጣት

▪ መፍትሔ ለመስጠት ወይም ለመቀበል

3.1.1 የተሳካ ተግባቦት መለያዎች

▪ ሃሳቡ ላይ እንጂ ግለሰቡ ላይ አያተኩርም

“አለባበስህን አልወደድኩትም.” - ሃሳቡ ላይ ሲያተኩር

“ዝርክርክ.” - ገለሰቡ ላይ ሲያተኩር

▪ ተስማሚ ሁኔታዎችን ይጠቀማል ▪ ገላጭ ነው፡፡

▪ በሚታሰበውና በሚነገረው መካከል ▪ አይኮንንም አይፈርድም


መጣጣም ይፈጠራል

እንዴት:

1. ኣላማዎቹ ላይትኩረት ያረጋል;

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 18


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

2. ትኩረቱን የተቀባይ ጠባይና ግብረ መልስ ላይ ብቻ ያደርጋል

3. መፍትሔን መሰረቱ ያደርጋል

3.1.2 ለንግግር የሚረዱ ነጥቦች

1. አስተያየትህ ተናጋሪውን የሚጠቅም መሆኑን እርግጠኛ መሆን፡፡

2. ስሜትን በቀጥታ መግለጽ.

3. ቀጥታ የግለሰቡን ድርጊትና የሚያሰከትለውን ችግር መግለጽ.

4. ፈራጅም አዛኝም አለመሆን.

5. አለመደፋፈን፣ አለመጠቅለል.

6. ተቀባዩ ዝግጁ ሲሆን ብቻ አስተያየትን መስጠት.

7. የመልእክቱን አቀራረብ ልክነት ማረጋገጥ.

8. ማድረግ የሚችለውን፤ በዓቅሙ ልክ ሃሳብን ማቅረብ

3.1.3 ለመስማት የሚረዱ ነጥቦች

1. ለመከላከል አለመሞከር 5. ግልጽ ላልሆኑ ጉዳዮች ማብራሪያና


ትርጉሞችን መጠየቅ.
2. ምሳሌዎችን መረዳት.
6. ለአስተያየት ሰጪው አካላዊና
3. ለዋናውን ሃሳብ መረዳታችን
እንቅስቃሴያዊ መልእክት ትኩረት
እርግጠኛ መሆን
ስጥ
4. ሥለ አስተያየቱ ያለን ሃሳብ ማካፈል.

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 19


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

3.2 የአቻ ግፊት


በታዳጊነት ዘመን ኃጥያትን ከጓደኞቻችን ልንማር እንችላለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ ዳዊት
ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ ያለው ክፉ ባልንጀርነት የሚያመጣውን ክፉ ችግር
ሲያሳይ ነው፡፡ መዝ 17፡26 ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክቱ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል
ያጠፋዋል ብሏል 1ኛ ቆሮ 15፡33

መንፈሳዊ ወጣት ከማንም ጋር የሚኖረው ጓደኝነት ሃይማኖቱና መለልካሙን ማንነቱን


እስካልነካበት ድረስ መሆን ይገባዋል በሌላ በኩል እርሱም ጓደኛውን ወደማይሆን ተግባር
ሊገፋፋው አይገባም፡፡

የአቻ ግፊትን ለመቋቋም ምን እናድርግ

1. ጓደኛን መምረጥ

2. የአቋም ሰው መሆን

3. ጓደኝነታችሁን የጋራ ማድረግ

4. ለአብሮነት ትከክለኛ ቦታዎችን መምረጥ

5. ለራስ ዕቅድ ማውጣት

6. ልክ ላልሆኑ ነገሮች እምቢ ማለትን መልመድ

7. የተሳሳተ ጓደኛን መምከር

8. የማይስተካከል ከሆነ መለየት

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 20


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ምዕራፍ 4- በጥልቀት ማሰብ

4.1 በጥልቀት ማሰብ

የማሰብ ሂደቶች

 ማወቅ:

 እምቅ መረዳት: እውቀትን መረዳት

 መተግበር: የተረዱትን መተግበር

 መተንተን: ድምር እውቀትን ወደ ንኡሳን እውቀቶች መከፋፈል

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 21


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

 መጭመቅ: ትንትን እውቀቶችን ወደ አንድ ትልቅ እውቀት ማዋሃድ

 መገምገም: የእውቀቱን አስፈላጊነትና ተዓማኒነት ማገናዘብ

በጥልቅ ማሰብ ያልሆኑት

• በጣም ፈጣን ናቸው.

• ከማይመለከታቸው ሰዎች ጋ የተመከሩ ናቸው.

• በስሜታዊነት ውስጥ የተወሰኑ ናቸው.

• አግባብ ካልሆኑ የትናንት ልምዶች ጋ የተገናዘቡ ናቸው.

• ፍጹም እውናዊ ያልሆኑና ከኛጋር የማይሄዱ ናቸው.

4.2 ውሳኔ ሰጪነት


የሰው ሕይወት በእያንዳንዱ እርምጃዎቹ በውሳኔ የተሞላ ነው፡፡ ለምሳሌ, ጠዋት ከእንቅልፋችን
ስንነቃ ቢያንስ የሚከተሉት ጥያቄዎች ከኛ ውሳኔ ይፈልጋሉ:

• ምን አይነት ልብስ ልልበስ;

• ምን አይነት ጫማ ልጫማ;

• ቤ/ክ ልሂድ ወይስ አልሂድ

• ቁርስ ምን ልብላ /ወይስ ልጹም

እንዴት እንወስን

• ፈቃደ እግዚአብሔርን መጠየቅ

• ራስን ማወቅ፣ ዋጋን መረዳት፣ የአቅማችንን መጠን መገንዘብ

• አካባቢን /እድሎችን፣ ተጽዕኖችን፣ አማራጮችን/ መረዳት

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 22


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

• በስሜትና በእውነት መካከል ያለውን ልዩነት መለየት

• በተወጠርንበት ወቅት እራስን ውሳኔ ከማሳለፍ መጠበቅ .

ሁሌም ለመወሰን ማሰብ ያለብን ነገሮች

• ፍቃዳችንን ለእግዚአብሔር መስጠት ነገሮችን እንደሚያቀል

• ቅዱሳኑ ሁሌም ለእርዳታ ከኛ ጋር መሆናቸውን መረዳት

• ያለፉ የተሳሳቱ ውሳኔዎችን የመሻር መብት እንዳለን መረዳት.

• Remember that there are alternative decisions.

• አማራጭ ውሳኔዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገንዘብ

• ውሳኔ መስጠት ሂደታዊ መሆኑን ማስታወስ

• ውሳኔና ውጤት የተለያዩ መሆናቸውን መገንዘብ.

የውሳኔ ሒደት

ችግሩን ማወቅ > መረጃና ግብአት መሰብሰብ > ያሉ አማራጮችን መዘርዘር > አማራጮችን
ማወዳደር > ከግብ ለመድረስ ማቀድ > መወሰን > ውሳኔያችንን መገምገም > መከለስ

4.3 የአቋም ሰው መሆን


• የአቋም ሰው መሆን ማለት የራስን ሃሳብ፣ ፍላጎት፣ አመለካከትና፣ መብት
ያለመፍራትና የሌሎችን መብት ባለመጫን በግልጽ ማስረዳት መቻል ነው፡

ብዙዎቻችን ለሌሎች ብለን ፍላጎታችን እናፍናለን

ሌሎቻችን ደግሞ የሌሎችን ሃሳብ በመርገጥ የራሳችን ፍላጎት አሽከር እናደርጋቸዋለን፡፡

• ሰለወዳጆቻችን ስንል ከአገልግሎት እንርቃለን

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 23


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

• በጾም እንበላለን

• ከጸሎት እንታጎላለን

• ለሌሎች መሰናክል እንሆናለን

የአቋም ሰው አለመሆን ለሚከተሉት ችግሮች ያጋልጣል

• ጭንቀት -- ህይወታችንን መቆጣጠር እነዳልቻልን ስንረዳ እንረበሻለን.

• ቁጣ-- ሰዎች በኛ ሲጠቀሙ እንናደዳለን.

• መሳቀቅ -- ለምን ይህ እንዲሆን ፈቀድኩ?

• ግልፍተኝነት -- ቶሎ ስሜታዊ መሆንነነ መጋጨት

የአቋም ሰው መሆን እንዴት ይቻላል

▪ ራስን በማወቅ

▪ ራስን በማክበር

▪ ለሌሎች ግልጽ በመሆን

▪ የሌሎችን ፍላጎት ማክበር

4.4 የጊዜ አጠቃቀም


ጊዜ የሕይወት ጠቃሚ ሳይሆን ወሳኝ ሃብት ነው፡፡

የጊዜ አጠቃቀም

• ግብ አስቀምጥ

• አቅድ

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 24


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

• እቅድህን ቅደም ተከተል አሲዝ

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 25


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

• እቅድ: ምን፣ መቼ፣እንዴት፣ ጥቅሙ


• ድርጊቶች : ግባችንን የሚያሳካውን እቅድ የሚረዳ ድርጊቶችን መተለም
• ወዳጅ: ግቦችህን የሚደግፉ ወዳጆችን ለይ
• ለራስ ተዝናኖት መፍጠር /ራስን ነጻ አድርግ
• ልኬት/ግምገማ: ራስን መመዘን
ቀታልያነ ጊዜ
• ስራን ማሳደር/መዘግየት
• ትርጉም አልባ ስራዎች
• “እምቢ“ን አለመቻል
• ለራስ ክብር አለመስጠት
• ቅደም ተከተል የማሲያዝ ችግር

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 26


ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት

ዋቢ መጽሐፍት
ለእግዚአብሔር ጊዜ ማጣትና ሌሎቹም፣ ተስፋዬ ቢሆነኝ
መሠረተ ሕይወት፣ ሰምንተኛ ክፍል፣ ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
መሠረተ ሕይወት፣ ሰባተኛ ክፍል፣ ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
መሠረተ ሕይወት፣ አስረኛ ክፍል፣ ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
መሠረተ ሕይወት፣ አስራ ሁለተኛ ክፍል፣ ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
መሠረተ ሕይወት፣ አስራ አንደኛ ክፍል፣ ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
መሠረተ ሕይወት፣ ዘጠነኛ ክፍል፣ ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
ማስያስ ዲ/ን ሚኪያስ አስረስ
ኦርቶዶክሳዊ ወጣት፣ ምንተስኖት ደስታ
ኦርቶዶክሳዊ የሕይወት ክህሎት፣ምንተስኖት ደስታ
ኦርቶዶክሳዊ የወጣቶች ሕይወት፣ መ/ር ህሩይ ባዬ
የሕይወት ክህሎት ስልጠና፣ ክፍል አንድ፣ አዲስ ሶሊዩሽን ኤጀንሲ
የተግባቦት ክህሎት፣ ምንተስኖት ደስታ
የወጣቶች ክርስቲያናዊ ሕይወት
ያለጭንቀት የመኖር ሚስጥር፣ ዲ/ን የሺጥላ ሞገስ
Basic life skills course facilitator’s manual, MYS of Azerbaijan and UNICEF
Christian life skills, Ersin Civanlar and Barbara Rogers
Facing today’s challenges, Yousry Armanios (MD)
Knowledge brief; Basic life skill curriculum, MYS of Azerbaijan and UNICEF
Programs of orthodox religion in primary school, EU-ScholaEuropaea joint teaching Committee
Strengthing life skills for youth, world bank and international youth foundation
The orthodox home: the little church, V.Rev. Fr.Philip Tolbert

በደ/ገ/ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና ማዕከላውያን ክፍል 27

You might also like