Professional Documents
Culture Documents
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩት ጥንታውያን የገዳም አባቶች አንዱ የሚኾን አባ ሰራፊም አንድ ቀን ከግብፅ ወደ
ሮም ኼደ፡፡ እዚያ እንደ ደረሰም አንዲት የተከበረችና ወደ ውጭ ሳትወጣ ዘወትር በበዓትዋ ተከትታ የምትኖር መነኰሲት
እንዳለች ይሰማል፡፡ እርሱ ራሱ በየበረኻው እየተጓዘ የሚኖር ነበርና ይህን የመነኰሲትዋ አኗኗር ደንቆት፡- “ለምን እዚህ
ተከትተሽ ትቀመጫለሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ እርስዋም፡- “ቁጭ አላልኩም፤ እየተጓዝኩ ነው” ብላ መለሰችለት፡፡
ይህ የመነኰሲቱ አነጋገር የኦርቶዶክሳዊነትን ባሕርይ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አገላለፅ ነው - ኦርቶዶክሳዊነት ጉዞ ነውና፡፡
ልክ በሲና በረኻ ይጓዙ እንደ ነበሩት እስራኤላውያን የሚደረግ የሕይወት ዘመን ጉዞ! በሰዓታት፣ በመዓልታት፣ በዓመታት
ከሚለካው ጊዜ ወደ ዘለዓለማዊነት የሚደረግ ጉዞ! ከግብፅ ወደ ከንዓን የሚደረግ ጉዞ! ሽንኩርትና ዱባ ከሚበሉበት
ከግብፅ፥ ማርና ወተት ወደምታፈልቅ ምድር የሚደረግ ጉዞ! ኀዘን - ደስታ፣ መከራ - ዕረፍት፣ ማጣት - ማግኘት
ከሚፈራረቁበት ዓለም፥ ደስታ፣ ዕረፍት፣ ምስጋና ጸንተው ወደሚኖሩበት ዓለም የሚደረግ ጉዞ! ክርስትና ቀድሞ
ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ “መንገድ” የሚል መኾኑም ይህን ይበልጥ ግልፅ የሚያደርግልን ነው (ሐዋ.19፡23፣ 24፡22)፡፡
በወልድ ውሉድ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልነው እኛም ይህን ጉዞ ከተጠመቅንበት ጊዜ አንሥቶ የምንጓዘው ጉዞ ነው፡፡
በእምነታችን ካልታመምን በስተቀር ይህን ጉዞ እንጓዛለን፡፡ አንድ ሰው ጤናማ እስከ ኾነ ድረስ ከተለመደው ጊዜ በላይ
መተኛት እንደማይቻለውና መንቀሳቀስ እንደሚፈልግ ኹሉ፥ እኛም ክርስትናችን ጤናማ እስከ ኾነ ድረስ በእኛ ዘንድ
ያደረው መንፈስ ቅዱስ ጉዞውን እንጓዝ ዘንድ ዘወትር በማይነገር ምሥጢር እየቀሰቀሰንና እየረዳን የምንጓዘው ጉዞ ነው፡፡
አንድ ሰው ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ስለሚኼድበት መንገድ ጠባይና ስለ መዳረሻው አገሩ ማወቅ አለበት፡፡ የሚኼድትን አገር
ካወቀ “የእገሌ አገር በየት በኩል ነው? ወደዚያ የሚወስደው መንገድስ የቱ ነው?” ብሎ እየጠየቀ ይኼዳል፡፡ የሚኼድበትን
አገር ካላወቀ ግን የመንገዱን ጠባይ ብቻ ሳይኾን መንገዱን ራሱ ማወቅ አይቻለውም፡፡
የኦርቶዶክሳዊ ጉዞ መንገዱና መዳረሻው የት እንደ ኾነም ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ይህን ጥያቄ ለጠየቀው
ለቅዱስ ቶማስ፥ በቅዱስ ቶማስ አንጻርም ለኹላችንም ነግሮናል፤ እንዲህ ሲል፡- “የእውነት መንገድ እኔ ነኝ” (ዮሐ.14፡6)፡፡
መንገድ የሚመስል የሐሰት መንገድ፣ መዳረሻ የሚመስል የውሸት መዳረሻም አለና ጌታችን “የእውነት መንገድ እኔ ነኝ”
አለ፡፡ ወደ እሳተ ገሃነም የሚያደርስ ሰፊ መንገድ አለና ክብር ይግባውና አምላካችን ወደ ባሕርይ አባቱ ወደ አብ፣ ወደ
ባሕርይ ሕይወቱ ወደ መንፈስ ቅዱስ፣ ወደ ራሱ፥ እንደዚሁም ከእርሱ የተነሣ ወደምትሰጠው ወደ መንግሥተ ሰማያት
የሚያደርሰው “የእውነት መንገድ እኔ ነኝ” አለ፡፡ መኼጃው መንገዱ፣ አብነት መምህሩም እርሱ ራሱ ነውና “እኔ ነኝ” አለ፡፡
ስለዚህም ይህ እውነተኛው መንገድ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ፡- “ክቡር ዳዊት ‘ከኃይል ወደ ኃይል [ከምግባር ወደ ትሩፋት]
ይኼዳሉ’ እንዳለው፥ ክርስቲያኖች ዕለት ዕለት ሊጓዙበት የሚገባቸው ሐሰት የሌለበት ደገኛው ፍኖት ይህ ነው”
እንዳለው፥ መዳረሻ ወደ ኾነው ክርስቶስ በክርስቶስ አብነትነት በክርስቶስ መንገድነት የምንጓዘው ጉዞ ነው፡፡ በጌታችን
ክርስቶስ አርአያነትና አጋዥነት ወደ አምላካችን ክርስቶስ የምናደርገው ጉዞ ነው፡፡
ተመልከቱ! ጌታችን ክርስቶስ ማደሪያ አጥቶ በበረት እንደ ተወለደ፥ ሰዎች ለሥጋችን ማደሪያ ሊያሳጡን ይችላሉ
(ሉቃ.2፡7)፡፡ ጌታችን ክርስቶስ ወደ ግብፅ እንደ ተሰደደ፥ እኛንም ሊገድሉን ሽተው ከተወለድንበት አገር ሊያሳድዱን
ይችላሉ (ማቴ.2፡13)፡፡ ጌታችን ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ በገዳመ ቆሮንቶስ ከዲያብሎስ እንደ ተፈተነ፥ እኛም በወልድ
ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳውያን ስለ ተሰኘን ዲያብሎስ እርሱን መካዳችንን ቆጭቶት እኛን
ለመጣል ብሎ በተለያየ መንገድ ሊፈትነን ይችላል (ማቴ.4፡3)፡፡ ጌታችን ክርስቶስን “ከአገራቸው እንዲኼድላቸው” እንደ
ለመኑት፥ እኛንም የክርስቶስ በመኾናችን “ከአገራቸው” እንድንወጣላቸው ግድ ሊሉን ይችላሉ (ማቴ.8፡34)፡፡ ጌታችን
ክርስቶስን “ጋኔን አለበት” እንዳሉት፥ እኛንም የተለያየ ስም እየሰጡ ሊሰድቡን ይችላሉ (ዮሐ.10፡20)፡፡ ጌታችን
ክርስቶስን በቅንአት ተነሣሥተው “ይሰቀል ይሰቀል” እንዳሉት፥ እኛንም እንደዚሁ በተለያየ መንገድ አመካኝተው ግርግር
አንሥተው የግርግሩ መነሻ እኛ እንደ ኾንን ዋሽተው “ይወገር፣ ይቀጥቀጥ” ብለው ሊፈርዱብን ይችላሉ (ማቴ.27፡22-
23)፡፡ ጌታችን ክርስቶስን ስፍር ቊጥር የሌለውን ግርፋት ገርፈው መከራ አድርሰው በመስቀል ላይ ዕራቁቱን እንደ
ሰቀሉት፥ እኛንም የክርስቶስ በመኾናችን ቊጥር የሌለው መከራ አድርሰው ሊገድሉን ይችላሉ፡፡ ይህ ኹሉ ሲኾን
መንገዳችንን ልንጠራጠር አይገባም፡፡ ይህ ኹሉ ሲኾን “ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ የቀጠነ” መኾኑን እርሱ ራሱ
ነግሮናልና ልንጠራጠር አይገባንም (ማቴ.7፡14)፡፡ መንገዳችንን ብቻ ሳይኾን መዳረሻችንም ልንጠራጠር አይገባንም፡፡ የዚህ
አብነቱ፣ የዚህ መምህሩ የእምነታችን ራስ ክርስቶስ ፈርሶ በስብሶ እንዳልቀረ፥ ይልቁንም በክብር እንደ ተነሣና እንዳረገ፥
እኛም በእርሱ መንገድነት ስንኼድ መዳረሻችን ከእርሱ ጋር በክብር መነሣትና ማረግ ነውና ልንጠራጠር አይገባንም፡፡
ልዑለ ቃል ኢሳይያስ እንዳለ ይህ መንገድ “ንጹህ መንገድ” ነውና ልንጠራጠር አይገባም፡፡ ይህ መንገድ “የተቀደሰ መንገድ
ይባላልና” ልንጠራጠር አይገባም፡፡ በዚህ መንገድ “ንጹሃን ያልኾኑ አያልፉበትምና” ልንጠራጠር አይገባም፡፡ በዚህ መንገድ
የሚኼዱት ድኅነታቸውን የሚፈጽሙ ተጓዦች ናቸውና ፈጽመን ልንጠራጠር አይገባም፡፡ ይህ መንገድ ወደ ዘለዓለም
ደስታ የሚያደርስ ነውና ልንጠራጠር አይገባም (ኢሳ.35፡8-10)፡፡
ይህ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት ምንኛ ድንቅ ነው፡- “በኹሉም ረገድ ራሳችንን እናበርታ፡፡ የሀብት ማጣትም
ቢኾን፣ ሞት ራሱም ቢኾን ሃይማኖታችንን ካልቀማን ከሰዎች ኹሉ ይልቅ ደስተኞቹ እኛ ነን፡፡ ጌታችን ክርስቶስም ይህን
በማስመልከት እንዲህ ብሎ አዝዞናል፡- ‘እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ’ (ማቴ.10፡16)፡፡ እባብ ራሱን [ጭንቅላቱን] ለማዳን ሲል
ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን፣
ሰውነትህን፣ የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን!
አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትኼድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉንም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ
ይመልስልሃልና፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃልና፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ
ነገሮችን ይሰጥሃልና” (በእንተ ሐውልታት፣ ድር.4፡10)፡፡
ይልቅስ ተወዳጆች ሆይ! የእግዚአብሔርን ጥበብ እያደነቅን እንጓዝ፡፡ እርሱስ ምንድን ነው ያላችሁኝ እንደ ኾነ፥ አዳም
በመሳሳቱ ምክንያት መከራና ሞት ወደ ሕይወቱ ዘልቀው ገቡ፡፡ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም እነዚህን ኹሉ በመከራና
በሞት ነው ያራቀልን፡፡ መከራችንን የራቀው ስለ እኛ በተቀበለው መከራ ነው፡፡ ሞታችንን ያራቀው ስለ እኛ በሞተው
ሞት ነው፡፡ ምን ይደንቅ? ምንስ ይረቅ? ስለዚህ እነዚህ ነገሮች በውሸትና ኦርቶዶክሳውያን ከመኾናችን የተነሣ
የሚደርሱብን ከኾነ በሥጋ የምንቀበለው መከራ፥ የነፍሳችን መከራ የሚያርቅና የሚያድን መከራ ነው፡፡ እንዲህ ኾኖ አሁን
በሥጋችን ብንሞት የዘለዓለም ሞታችንን የምናርቅበት ክቡር ሞት ነው፡፡ ዳግመኛም ብፁዕ ጳውሎስ እንደ ተናገረ ፈራሽ
በስባሽ በሚኾን በዚህ ሥጋችን ላይ የክርስቶስ ሕይወትነቱ ይታወቅ ዘንድ ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ ኹልጊዜ
በሥጋችን ተሸክመን የምንዞር ነንና (2 ኛ ቆሮ.4፡10)፡፡
ትራጃን የተባለ ንጉሥ “የተሰቀለውን ክርስቶስን እንደ ተሸከመና በውስጡ እንዳለ አረጋግጦአል፡፡ ስለዚህ ለሕዝቡ
መቀጣጫ እንዲኾን በወታደሮች ታስሮ ወደ ታላቅዋ ከተማ ወደ ሮም ሔዶ ለተራቡ አንበሶች ይሰጥ፡፡ ሕዝቡን
ለማስደሰትና ለማርካት ሲባል ይህ እንዲኾን አዘናል” በማለት በቅዱስ አግናጥዮስ ላይ በፈረደ ጊዜ ሊቀ ጳጳሱ ይህን
ሰምቶ እጅግ ነበር የተደሰተው፡፡ እንዲያውም ተንበርክኮ፡- “አምላክ ሆይ! የፍቅርህን ብዛት ለግሰኸኛልና ስለ ሰጠኸኝ
ክብር አመሰግንሃለሁ፡፡ ሐዋርያህ እንደ ኾነው እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በብረት ሰንሰለት እንድታሰር ፈቅደህልኛልና
አመሰግንሃለሁ” ብሎ ነበር ያስሩት ዘንድ ያመጡለትን የብረት ሰንሰለት የሳማቸው፤ መንገዱ የጽድቅ መንገድ ነውና፡፡
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር፣ ጌትነት፣ ኃይል
የባሕርይ ገንዘቡ የሚኾን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ በአባቱ ቤት ወዳለው ብዙ መኖሪያ
እንደርስ ዘንድ የጽድቅ መንገዱን ይምራን (መዝ.85፡11)፤ አሜን፡፡
* #ማርያም *
ርግብ ማለት ነው። #ያ - ያንቃዐዱ ኀቤኪ ፣ በአንቺ አማላጅነት ያመኑ ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልን እያሉ ወዳንቺ
ይለምናሉ ማለት ነው። #ም - ምስአል ወምስጋድ ወመስተስረዬ
መርታ ወደ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስርየተ ኃጢያትን በረከተ ስጋንና በረከተ ነፍስን ከልጇ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ
ክርስቶስ እየለመነችና እያማለደች የምታሰጥ ማለት ነው ። #ማርያም ፦ ማለት ፍፅምት ማለት ነው ። ለጊዜው መልክን
ከደምግባት ጋር አስተባብራ ተገኝታለችና ፍፃሜው ግን ንፅሀ ስጋን ንፅሀ ልቡናን ንፅሀ ነፍስን አስተባብራ ተገኝታለችና።
ፍፅምት ትባላለች። #ማርያም ፦ ማለት ፀጋ
ታዝዋል
ምክንያት (ሚስጥር)
ታዘዋል