Professional Documents
Culture Documents
PAUL C. JONG
♠ Website: https://www.nlmission.com
https://www.bjnewlife.org
https://www.nlmbookcafe.com
♠ E-mail: newlife@bjnewlife.org
መቅድም --------------------------------------------------------------- 9
ምዕራፍ 1
ምዕራፍ 2
ምዕራፍ 3
ምዕራፍ 4
ምዕራፍ 5
የተራራው ስብከት
(ማቴዎስ 5፡1-16) ------------------------------------------------ 107
ምዕራፍ 6
ምዕራፍ 8
‹‹ቃል ብቻ ተናገር››
(ማቴዎስ 8፡5-10) ---------------------------------------------- 265
ፖል ሲ. ጆንግ
አገር ላይ ጸሐይ ትወጣ ነበር፡፡ ስለዚህ ጸሐይ ፈጽሞ በብሪታንያ ቅኝ ግዛት ውስጥ
አትጠልቅም፡፡ ታላቋ ብሪታንያ በዓለም ላይ ብርቱ የነበረችው እንደዚህ ነበር፡፡
ዓለምን በሐይል አሸንፈው ነበር፡፡ በዚያን ዘመን በታላቋ ብሪታንያ ብዙ
ፑሪታውያን ነበሩ፡፡ ኢየሱስን ጌታቸውና አዳኛቸው አድርገው ያመኑ እነዚህ
ፑሪታውያን ከታላቋ ብሪታንያ ሸሽተው ወደ አሜሪካ ሄዱ፡፡ ስለ እምነታቸው
በምታሰድዳቸው አገር ውስጥ መኖር አልቻሉም፡፡ ፑሪታውያን ከታላቋ ብሪታንያ
ሲሸሹ ጸሐይ አትጠልቅም የሚለው ዝናም እንደዚሁ ደበዘዘ፡፡ እነርሱ በዓለም ላይ
የነበራቸው ሐብትና ሥልጣንም ሞተ፡፡ ዛሬ የቀረላቸው ብቸኛው ዝና የጨዋዎች
አገር መሆን ብቻ ነው፡፡
ወደ አሜሪካ የሸሹት ፑሪታውያን ትክክል ይሁን ወይም አይሁን ወንጌላቸውን
ለቀረው ዓለም አሰራጩ፡፡ ይህ ሲሆን አሜሪካ በዓለም ላይ አዲስ ልዕለ ሐይል ሆና
ተነሳች፡፡ ይህ ምስጢር ነው ብላችሁ አታስቡምን? አሜሪካኖች ወንጌልን በኮርያ
አስፋፉ፡፡ አሁን የኮርያ ኢኮኖሚ አደገ፡፡ እኛም አሁን ‹‹የእስያ ደራጎን›› ተብለን
እንጠራለን፡፡ የደራጎን (ዘንዶ) ምልክት በመንፈሳዊ ምልክት ጥሩ ምልክት አለመሆኑ
እርግጥ ነው፡፡ ነገር ግን ለማያምኑ ሰዎች ደራጎን አምላካቸው አድርገው
የሚሰግዱለት ጠንካራ ምልክት ነው፡፡ የኮርያ የኢኮኖሚ ዕድገት ‹‹የእስያ ደራጎን››
ወይም ‹‹የእስያ ነብር›› የተባለው ለዚህ ነው፡፡
የዓለምን ታሪክ ስንመለከት ኢየሱስን ያገለገሉና ወንጌልን ያስፋፉ አገሮች
የኢኮኖሚ ተሐድሶ እንደነበራቸው ማየት እንችላለን፡፡፡ አንድ አገር ከኢየሱስ
ሲያፈነግጥና ምዕመናኖችን ሲያሳድድ ኢኮኖሚው ይሞታል፡፡ የአንድ አገር ብልጥግና
የሚደገፈው ያ አገር በሚያስፋፋው ወንጌል ነው፡፡
ማየት እንደምንችለው ኢየሱስ የዓለም ታሪክ ማዕከል ነው፡፡ ኢየሱስ በሰው
ዘር ታሪክ ውስጥ እጅግ የተባረከ ጌታና አዳኝ ነው፡፡ ኢየሱስ አሁንም ሕያው ነው፡፡
ዩኒቨርስንና የእናንተንና የእኔን ሕይወት ይገዛል፡፡ በልባችን ውስጥም ሰላምን
ይሰጠናል፡፡ ወደ እርሱ መመልከት፣ እርሱን ማምለክ፣ ስለተትረፈረፈው ጸጋውም
እርሱን ማመስገን አለብን፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ሕይወታችንን ስንኖር ሁሉንም ነገር
በጌታ ውስጥ መመልከትና በጌታ ባለን እምነት መኖር አለብን፡፡ ያልኩት በጌታ
ውስጥ ነው! በዚህ ዓለም ላይ የሰውን ታሪክ ገጠመኞችና የኢኮኖሚ ለውጦችንም
በእምነት መነጽር መመልከት ያስፈልገናል፡፡ እያንዳንዱን ነገር በትክክል ማየት
የምንችለው ነገሮችን በኢየሱስ ክርስቶስ መነጽር ስናይ ብቻ ነው፡፡
ከሐጢያቶቻችንም ለመዳን ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ማነው? እርሱ የነገሥታት ንጉሥ ነው፡፡ ንጉሡ የራሱን
ከሌሎች ጻድቃን ሰዎች ጋር ያማረ የገና በዓል ይኖራችሁ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እግዚአብሄርን ስለ ደህንነታችንና በእኛ ላይ ስላለው ጥበቃው
እናመሰግነዋለን፡፡ በእያንዳንዱ የገና በዓል ወቅት ብዙ አደጋዎችን እናያለን፡፡
ከእነዚህ አደጋዎች እየጠበቀን ስላለ እግዚአብሄርን እናመሰግነዋለን፡፡ ሰክሮ
በመንዳት የሚከሰቱ ብዙ የመኪና አደጋዎች አሉ፡፡ ቅጥ ላጣው ተድላቸው ሲሉም
ገንዘብ ለማግኘት የሚፈልጉ ወጣቶች የሚፈጽሙዋቸው ወንጀሎችም አሉ፡፡ በገና
በዓል ወቅት ጠንቃቆች መሆን አለብን፡፡
ያለ ማቋረጥ የእርሱን ጥበቃ ለማግኘት፣ ወንጌልን ለማሰራጨት፣
ለመንግሥቱ፣ ለራሳችሁ ደህንነት፣ ለቤተክርስቲያኑ ደህንነት፣ አብረዋችሁ ላሉ
ክርስቲያኖች፣ እንደዚሁም ለብዙ ነፍሳቶች መዳን እንደምትጸልዩ ተስፋ
አደርጋለሁ፡፡
ትክክለኛ እምነት ባልሆነ ነበር፡፡ እኛም ደግሞ ለጌታ ሦስቱን ስጦታዎች መስጠት
የሚኖርብን መሆኑን ማጤን አለብን፡፡ ኢየሱስን መገናኘት የምንፈልግ ከሆነ
በመጀመሪያ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቀበል፣ የሐጢያቶችን ስርየት
መቀበልና እርሱን በእምነት ብቻ መከተል አለብን፡፡
ሰብዓ ሰገል የተጻፈውን ቃል ከተከተሉ በኋላ ኢየሱስን በቤተልሔም
ሲያገኙት ሕጻኑ ኢየሱስ በግርግም ውስጥ ተኝቶ ነበር፡፡ በሕጻኑ ኢየሱስ ፊት
ያጎነበሱት፣ ስጦታዎቻቸውን ያቀረቡትና እምነታቸውን የመሰከሩት ያን ጊዜ ብቻ
ነው፡፡ ጴጥሮስ ‹‹አንተ የሕያው እግዚአብሄር ልጅ ክርስቶስ ነህ›› ብሎ
እንደመሰከረ እነርሱም ምስክርነታቸውን መስጠት ቻሉ፡፡ ሰብዓ ሰገል በተጻፈው
ቃል ከመደገፍ ይልቅ በራሳቸው እሳቤዎች ላይ ተደግፈው ኢየሱስን ፍለጋ
በኢየሩሳሌም አውራጃ ቢዞሩ ኖሮ ከጌታ ጋር መገናኘት አይችሉም ነበር፡፡ ነገር
ግን ወደተጻፈለት ስፍራ በሄዱ ጊዜ ሕጻኑ ኢየሱስ እዚያ ነበር፡፡ በዚህ ዘመንም
ከልቡ ዳግመኛ መወለድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የተጻፈውን የእግዚአብሄር
ቃል መከተልና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግመኛ መወለድ
ያስፈልገዋል፡፡
ማንም ይሁን ሰው ዛሬም ኢየሱስን ለመገናኘት በተጻፈው ቃል ማመን
ያስፈልገዋል፡፡ በራሳችን እሳቤዎች የሚያምነውን የእምነት ዓይን ማስወገድ ነገር
ግን በተጻፈው ቃልና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ከሐጢያቶቻችን
ሁሉ ባዳነን ኢየሱስ በማመን ወደ አዳኙ መመለስ ያስፈልገናል፡፡ በዓለም ላይ
ያሉ ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማወቅ ወደ
እግዚአብሄር መመለስ አለባቸው፡፡ አዳኙን ኢየሱስን የምናገኘው እንደዚህ ነው፡፡
ትክክለኛ እምነታችንን ለእግዚአብሄር አቅርበን ድጋፍ የምናገኝበት ብቸኛው
መንገድ ይህ ነው፡፡
ገና ኢየሱስ ክርስቶስን ያልተገናኙት በዓለም ያሉ ሰዎች በውሃውና
በመንፈሱ ወንጌል በማመን ወደ እግዚአብሄር መመለስ አለባቸው፡፡ ወደ
እግዚአብሄር ቃል መመለስና በእውነቱም በኩል ኢየሱስን መገናኘት አለብን፡፡
የተጻፈውን ቃል እንዳለ ስናምነውና ስንከተለው በትክክለኛ እምነት የሚያምኑ
ምዕመናን እንሆናለን፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ ወደ ውሃውና መንፈሱ
ወንጌል መመለስ ይገባቸዋል፡፡ ኦርቶዶክስ የእምነት ድርጅቶች ተብዬዎችን ወይም
ታላላቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻዎችን ከመሻት ይልቅ ራሳችንን በማዋረድ
በተጻፈው ቃል በኩል የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቀበል አለብን፡፡
ኢየሱስ እንደሚመጣ መላው ዓለም ያወቀ ቢሆን አብዛኛው ሕዝብ ገናም
እነዚህ የሌዊ ዘሮች ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ የአዲስ ኪዳን ዘመን ይህንን ክህነት
በእግዚአብሄር ፊት በትክክል ለመፈጸም እኛ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል
አማኞች የብሉይ ኪዳንን የመስዋዕት ስርዓት መረዳትና የኢየሱስን ጥምቀትና
ስቅለቱን ይበልጥ በጥልቀት መረዳት አለብን፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ከተወለደ አሁን 2005 ዓመት
ሆኖታል፡፡ ይህ ኢየሱስ አዳኝ ሆኖ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በአጥማቂው ዮሐንስ
በመጠመቅና ደሙን አፍስሶ በመሰቀል ሐጢያቶቻችንን ለዘላለም አነጻ፡፡ ስለዚህ
ኢየሱስ የተወለደበት ዓመት የዓለም የዘመን ቅደም ተከተል ሰሌዳ ማጣቀሻ
መሆኑ ተገቢ ነው፡፡ ይህም የነገሮች ሁሉ ጅማሬ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን
ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም በእኛ እሳቤ ኢየሱስ ይህንንን ዩኒቨርስ የፈጠረ
አምላክና በውሃውና በደሙ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የደመሰሰ አዳኝ ነው፡፡
እርሱ የዩኒቨርስ ታሪክ ማዕከልም ነው፡፡
የመጀመሪያ ፈተና፡፡
ሁለተኛ ፈተና፡፡
ሦስተኛ ፈተና፡፡
ከተሞክሮ ይማራሉ፡፤
የእግዚአብሄርን የጽድቅ ሥራ ተርባችኋልን? እንደዚያ ከሆነ የውሃውንና
የመንፈሱን ወንጌል በማሰራጨትና የእግዚአብሄርን ሥራ በመስራት
የመንፈሳችሁን ሙላት ትቀበላላችሁ፡፡ ውጫዊው ማንነታችሁ ሥጋዊ ፍላጎቶችን
የመከተል ልብ ቢኖረውም በውስጣችሁ ያለው መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄርን
የጽድቅ ሥራ ይራባል፡፡ ሁልጊዜም የጽድቅን ሥራ መስራት ይሻል፡፡
ጌታችን በማቴዎስ ምዕራፍ 4 ላይ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ሰው ከእግዚአብሄር
አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም፡፡›› ኢየሱስ 40 ቀን
ከጦመ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ ‹‹የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንህስ እነዚህ
ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል›› አለው፡፡ ዲያብሎስ ኢየሱስንና ማንኛውንም
ሌላ ሰው ሁሉ ‹‹ለሥጋ የሚሆን እንጀራ ሕይወትን ይሰጣል›› በማለት
ይፈትናል፡፡ ነገር ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ‹‹ሰው ከእግዚአብሄር አፍ በሚወጣ
ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም፡፡›› ሰው ለሥጋ በሚሆን እንጀራ ብቻ
አይኖርም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች መንፈስ አላቸውና፡፡ ስለዚህ ሰዎች ለሥጋ
የሚሆን እንጀራ መብላት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ነገር ግን ደግሞ ከእግዚአብሄር አፍ
የሚወጣውንና የመንፈስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሄር ቃልም መመገብ
ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሥጋችንና መንፈሳችን በሕይወት ሊኖሩ የሚችሉበት ብቸኛው
መንገድ ይህ ነው፡፡
በመሰረቱ ይህ እውነት እግዚአብሄር የተናገረው የአምላክ ቃል መንፈሳችን
በሕይወት ይኖር ዘንድ እንደሚያደርገው ይነግረናል፡፡ እኛ ጻድቃኖች ለሥጋችን
የሚሆነውን እንጀራ በመመገብ ብቻ በሕይወት መኖር አንችልም፡፡ ነገር ግን
ከእግዚአብሄር የሚወጣውን የእግዚአብሄር ቃል በመስማትና በማመን በሕይወት
መኖር መቻል አለብን፡፡ ዳግመኛ የተወለደ ሰው ምንም ያህል ብዙ እንጀራ
ቢመገብ መራቡና መጠማቱ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በጻድቃን
ልብ ውስጥ ስለሚኖር የጽድቅ ምግባሮችን በማድረግ ልንኖር ይገባናል፡፡ ያም
ማለት ጻድቃን በሕይወት መኖር የሚችሉት ከእግዚአብሄር አፍ የሚወጣውን
ቃል ሁሉ በመስማትና በማመን ነው፡፡ ይህም እኛ በሕይወት መኖር የምንችለው
የእግዚአብሄርን ቃል ሁሉ በማመንና ጌታንም በእምነት በመከተል እንደሆነ
ያሳየናል፡፡
ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች መንፈስ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ይራባል፡፡ ሰዎች
በሕይወት የሚኖሩት ከእግዚአብሄር የሚወጣውን ቃል ሁሉ በመስማትና
በማመን እንጂ ለሥጋ በሚሆን እንጀራ አይኖሩም፡፡ የጻድቃን መንፈስ
ሰዓታት ያህል ይነጋገሩ ነበር፡፡ አንዱ ሲናገር ሌላው ያዳምጥና ‹አዎ› ይላል፡፡ ሌላው
ሲናገር የመጀመሪያው ሰው ‹አዎ› ይላል፡፡ እርስ በርሳቸው በመነጋገርና
በመደማመጥ ይደሰቱ ነበር፡፡ የውይይታቸው ይዘት ምንም ነገር ይሁን ለውይይት
ያላቸው ረሃብ በጣም ከልብ የመነጨ ይመስል ነበር፡፡
እኔ የዚህ ዓይነት ሰዎች ስመለከት ርህራሄ ይሰማኛል፡፡ እነርሱ ስለማይረቡ
የሥጋ ጉዳዮች ሲወያዩ ከልባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን የውሃውንና የመንፈሱን
ወንጌል ከእኛ መስማት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሊወያዩበት የሚገባቸው በጣም ወሳኙ
ርዕስም ይህ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ሰዎች ስመለከት ሐዘኔታ ይሰማኛል፡፡
ቢኩራሩም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስለማያውቁ ያሳዝናሉ፡፡
በእኛ የጻድቃኖች ልብ ውስጥ ለጠፉት ነፍሳቶች መብል ይሆኑ ዘንድ
መጽሐፎችን የማተምና ለእያንዳንዱ ግለሰብ የማሰራጨት ፍላጎት አለን፡፡
አገራችን ከሰለጠኑት ምዕራባውያን አገሮች ጋር ስትነጻጸር ብዙ ሐብትና ብሄራዊ
ጉልበት ባይኖራትም እኛ ጻድቃኖች በዚህ ዓለም ላይ ለሚኖር ለእያንዳንዱ ነፍስ
ሐዘኔታ አለን፡፡ ብዙ ሐብት ባላቸው አገሮች የሚኖሩ ሰዎች እንኳን በጻድቃን
ዓይን ሲታዩ የሚያሳዝኑ ናቸው፡፡
‹‹የሚምሩ ብጹዓን ናቸው፤ ይማራሉና፡፡›› ይህ ማለት ለሌሎች የሚራሩ
ሰዎች ምህረትን ይቀበላሉ ማለት ነው፡፡ ልንምራቸው የሚገቡን ሰዎች እንደምን
ብዙ ናቸው! ይህ በመላው ዓለም እውነት ነው፡፡
መጨረሻ ላይ አካተተው፡፡
ጸሎት አዳጋች ነው ወይስ አይደለም? አዳጋች አይደለም፡፡ የጸሎት መሰረት
እምነት እግዚአብሄር አምላኬ፣ አዳኜና አባቴ ነው የሚል እምነት ነው፡፡ እርሱ
ፈጠረን፡፡ ከሐጢያቶቻችንም ሁሉ አዳነን፡፡ እንደዚያ ከሆነ እኛ ዳግመኛ
የተወለድን ሰዎች የእርሱ ሕዝብ የእርሱ ቤተሰብ ስለሆንን አባት ብለን
ብንጠራው እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ በተጨማሪም እኛ የእርሱ ሕዝብ
በመሆናችን እርሱን ማመስገናችን ጽደቅ ነው፡፡
ወደ ክፋትና ፈተና እንዳንገባና በተሳሳተ መንገድ ላይ ቁልቁል እንዳንሮጥ
መጸለይ ይገባናል፡፡ ኢየሱስ መጀመሪያ ምን እንደምንጸልይ አስተምሮናል፡፡
‹‹አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፤ ይህም ሁሉ
ይጨመርላችኋል፡፡›› የሚያስፈልጋችሁ አንዳች ነገር አለን? እንግዲያውስ
አስቀድማችሁ ለእግዚአብሄር መንግሥት ጸልዩ፤ ኑሩም፡፡ አባታችሁ ሁሉን
ይሰጣችኋል፡፡ የእግዚአብሄር ተስፋ ይህ ነው፡፡
ስለዚህ ይህንን ማመን ይገባናል፡፡ ጉድለቶች ቢኖሩብንም እንኳን
አስቀድመን በእግዚአብሄር ፈቃድ ለመኖር በመሞከርና የእግዚአብሄርን እርዳታ
በመጠየቅ አስቀድመን የእግዚአብሄርን ሥራ መሻት አለብን፡፡ ሁልጊዜም በመንፈስ
የማደግና ጉድለቶች ቢኖሩብንም እንኳን የእርሱን ጸጋና እርዳታ በመጠየቅ
ለእግዚአብሄር ሥራዎች ታማኝ መሆን ይኖርብናል፡፡ ገባችሁ? --አዎ--፡፡
ታምናላችሁን? --አዎ--፡፡
ሁላችንም አብረን ስንጸልይ በጥንቃቄ ድምጻችንን ከፍ አድርገን ልንጸልይ
ይገባናል፡፡ ያንን ስታደርጉ አሳቦቻችሁ ስለሚቀናጁ ‹‹እንደዚህ ጸለይሁ፤ እንዲህም
አምናለሁ›› በማለት እምነታችሁ ይዳብራል፡፡ እግዚአብሄር መልስ ሲሰጥም
‹‹ከእግዚአብሄር ዘንድ መልስ የመጣው እንደዚህ ስለጸለይሁ ነው›› በማለት
ስለምናውቅ እምነታችን ያድጋል፡፡ በአንደበታችን ጥርት አድርገን መጸለይ ጥሩ
የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡
በተጨማሪም በምንጸልይበት ጊዜ ተመሳሳይ በሆኑ ነገሮች ላይ ደጋግመን
መጸለይ ይቻላል፡፡ ነገር ግን እንደ ስርዓተ ደንብ አድርገን ልንጸልይ አይገባንም፡፡
አንዳንድ የሚያስቆጡ ነገሮች ሊወጡ ይችላሉ፡፤ ያ በሚሆንበት ጊዜ በቃላት
ልናርመው ይገባል፡፡ እግዚአብሄር በልባችን ማዕከል ውስጥ ያለውን ያያል፤
ያውቃል፡፡ በዚያ ውስጥም ይሰራል፡፡ ነገር ግን በአንደበታችን በትክክል
መመስከርም እንደዚሁ አስፈላጊ ነው፡፡ ‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም
መስክሮ ይድናልናል፡፡››
ቁሳዊ ነገሮችስ ከጌታ የመጡ አይደሉምን? ከጌታ የመጡ ናቸው፡፡ እርሱ እንዲህ
ብሎዋል፡- ‹‹መዝገብ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡›› ስለዚህ
ልቦቻችሁን በእግዚአብሄር ላይ ካኖራችሁ ሁሉም ነገር ወደ እናንተ ይመጣል፡፡
ሁሉም ነገር በጽድቅ መንገድ ይቀርብላችኋል፡፡
ሆኖም አንዳንድ ሐሳዊ ሰባኪዎች ይህንን ቁጥር ‹‹ብዙ መባዎችን ብትሰጡ
ትልቅ እምነት አላችሁ ማለት ነው›› ‹‹መዝገቦቻችሁን በሰማይ እንጂ በምድር ላይ
አታኑሩ፡፡ በሌላ አነጋገር ብዙ አስራትና ስጦታዎችን ለቤተክርስቲያን ስጡ›› እያሉ
ያስተምራሉ፡፡ በስጦታ ፖስታው ላይም ‹‹መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ
ይሆናልና›› የሚለውን በመጻፍ ከውስጥ ይከቱታል፡፡
ይህ የሐሰት ትምህርት ነው፡፡ የዓለማዊ ቤተክርስቲያኖች ዓላማ በዚህ
ዓለም ላይ ለመበልጠግ ስለሆነ የሚጨነቁት ገንዘብን ለማከማቸት ነው፡፡ ለጽድቅ
ቢጠቀሙበት በማን ዕድላቸው! ነገር ግን የሚጠቀሙበት የስስታምነት
ፍላጎታቸውን ለመሙላት ነው፡፡ ገንዘብን በማከማቸት በጣም የተካኑ ስለሆኑ
ከክርስቲያኖች ገንዘብ ለመጠየቅ የዚህ ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥሮችን
ይጠቅሳሉ፡፡ በስሞቻቸው የቆጠቡትን ገንዘበቸውን ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን
እንዲያመጡ ያደርጉዋቸዋል፡፡
አንዳንድ ሰባኪዎች ከቤተክርስቲያን አባሎች ገንዘብ በመውሰድ አዳዲስ
ቤተክርስቲያኖችን ለመገንባት ግፊት ያደርጋሉ፡፡ ይህ ጽድቅ ነውን? ‹‹መዝገብህ
ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡›› እነርሱ የሚያስቡት ስለ ቤተክርስቲያን
ግንባታ ብቻ ስለሆነ መዝገባቸው ያ ነው፡፡ የቤተክርስቲያን አባሎች
$15,000,000 ስለፈጀው የቤተክርስቲያን ሕንጻ በመኩራራት እንደዚህ ባለ
ቤተክርስቲያን ውስጥ መገኘት በጣም የሚያስከብርና የሚያኮራ ነገር እንደሆነ
ያህል ጉራቸውን ይነዛሉ፡፡ አስተሳሰቦቻቸውን ጠልቀን ብንመለከት ምናልባትም
ባዶ ነው፡፡ በእርግጥም ልባቸው ባዶ ነው፡፡ ልቦቻቸውን ያኖሩት $15,000,000
በፈጀው የቤተክርስቲያን ሕንጻ ላይ ስለሆነ ኢየሱስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል
ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደ ጭጋግ የደመሰሰ መሆኑን ማየት አይችሉም፡፡
እግዚአብሄር ልጆቹ እንዳደረጋቸውና መንግሥተ ሰማይን እንደሰጠን ማየት
የማይችሉ ብዙ የሚያሳዝኑ ሰዎች አሉ፡፡
በተቃራኒው ለእኛ ዳግመኛ ለተወለድነው መዝገባችን ጌታችን ነው፡፡
ጌታችን የለገሰን የምህረት በረከቶች ሁሉ --የእርሱ ደህንነት፣ የእግዚአብሄር
ልጆች ያደረገን መሆኑ፣ መንግሥተ ሰማይን የሰጠን መሆኑ፣ ሐጢያቶቻችንን
ማስወገዱና ጻድቃን ያደረገን መሆኑ-- መዝገቦቻችን ናቸው፡፡ ከእነዚህ የበለጠ
እንደሌለ ይሰማናል፡፡
ዛሬ ይህ ትምህርት ባይኖረን ኖሮ ‹‹ኦ! አሁን ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡ ኦ አሁን
እሞታለሁ!›› እንደምንል የታወቀ ነው፡፡ የጌታ ምጽዓት ሲቃረብ እንዲህ ያሉ ብዙ
ሰዎችን እንደምናይ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የዚህ ዘመን ተስፋ ሰውን
ሁሉ ለጉድለቶች እንዲጋለጥ እያደረገው መሆኑ ነው፡፡ አለም እየተበጠበጠና
ለመኖርም አስቸጋሪ እየሆነ ስለመጣ ጭንቀቶቻችን ይጨመራሉ፡፡ ነገር ግን
የወደፊቱን ጭንቀት አስቀድማችሁ ዛሬ መጨነቅና ዛሬ መሞት የለባችሁም፡፡ ስለ
ነገዎቹ ችግሮች ነገ እንደሚጨነቁ ሰዎች እንደምትሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፤ ለቀኑ
ችግሩ የሚበቃው መሆኑን የምታምኑ ሰዎች እንደምትሆኑም ተስፋ አለኝ፡፡
ችግሮችና ጭንቀቶች ለዘላለም አይቆዩም፡፡ የሐጢያት ይቅርታን ለተቀበልን
ሰዎች ለዘላለም የሚዘልቁት ጌታ፣ ደህንነትና መንግሥተ ሰማይ ናቸው፡፡
ጭንቀቶች ጊዜያዊ ስለሆኑ አይዘልቁም፡፡ ቀኑ ብራ ወይም ደመናማ ወይም
ዝናባማ ወይም ጸሐያማ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ እኛም ሁልጊዜ ዓለማዊ ወይም
ሁልጊዜ መንፈሳዊ አንሆንም፡፡ ደካሞች ብንሆንም እኛ ጻድቃኖች ሁልጊዜም
ዓመጸኞች አይደለንም፡፡ ደካሞች ብንሆንም የጌታን ፈቃድ የምንከተል ነን፡፡
ኢየሱስ አስቀድሞ ጉድለቶቻችንን ሁሉ ወስዶዋል፡፡ ስለዚህ በጌታ ትምህርት ላይ
በእምነት እንደምትኖሩ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጭንቀቶች ውስጥ እንዳንወድቅ
እንዲህ ያለውን ትምህርት ስለሰጠን ጌታን እናመሰግነዋለን፡፡ ይህ ትምህርት ለእኛ
በመጨረሻዎቹ ቀኖች ውስጥ ለምንኖር እንዴት ታላቅ ነው! በእርግጥም
አመስጋኞች ነን፡፡
በየቀኑ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ነገር ግን የአንድ ቀን ችግር ለዚያ ቀን በቂ
ነው፡፡ እርሱ የወንጌልን ሥራ ለመስራት እንቅፋት የሚሆኑብንን ችግሮችና
መከራዎች ሁሉ ለማሸነፍ በየቀኑ አዲስ ጉልበት እንደሚሰጠን በማመን በየቀኑ
ለተባረከው የእግዚአብሄር ሥራ መኖር አለብን፡፡
ሐሌሉያ!
አትከስምም፡፡
ማቴዎስ 7፡22 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በዚያን ቀን ብዙዎች፡- ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ
በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ
ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል፡፡›› እግዚአብሄር በጻፈው ቃል
የማያምኑ ብዙዎቹ እምነት የለሽ ሰዎች የሚሉት ይህንን ነው፡፡ ይህንን
የተጻፈውን የእግዚአብሄር ቃል ሳያምኑ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ምን ያህል ናቸው?
በዚያ ቀን ከእነርሱ ብዙዎቹ ‹‹ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ›› ይላሉ፡፡ ነገር ግን በተጨባጭ
በእግዚአብሄር አላመኑም፡፡ ያመኑት ልክ እንደ ሎጥ በራሳቸው ሁኔታዎች ነው፡፡
ብዙ ክርስቲያኖች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃል እንደማያምኑ የታወቀ
ነው፡፡ የሚያምኑት ከንቱ በሆኑት አስተሳሰቦቻቸው ነው፡፡ ከእነርሱ ብዙዎቹ
የሚያምኑት በራሳቸው አስተሳሰቦች፣ በሐሰት ምልክቶችና በአጋንንቶች ሐይል
ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ተመስርተው ሳይሆን በሐሰተኛ
ትምህርቶችና በአጋንንቶች ሐይል ላይ ተመስርተው የሚያምኑ ብዙ ‹‹ዕውር
ክርስቲያን›› ተብዬዎች አሉ፡፡ ዳግመኛ ባልተወለዱት መካከል በአጋንንቶች
የተያዙ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ በተቀበሉት በዚህ አጋንንታዊ ሐይል ላይ
ተመስርተው በኢየሱስ እናምናለን ይላሉ፡፡ ይህ ለእናንተ የማይመስል መስሎ
ይታያችኋልን? የዛሬው ዋናው ምንባብ በትክክል የሚለው ይህንን አይደለምን?
በእርግጥም ከላይ በማቴዎስ 7፡22 ላይ የተጠቀሰው ምንባብ የሚለው ይህንኑ
ነው፡፡ ‹‹በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን?
በስምህስ ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን?››
አጋንንት የያዛቸው ሰዎች አጋንንቶችን በመለየትና እነርሱን በማስወጣት
የተካኑ ናቸው፡፡ ትንቢት በመናገርም የተካኑ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጠንቋዮች
አንዳንድ ጊዜ የወደፊቱን የመተንበይ ብልህ ችሎታ ያላቸው አይመስሉምን? በጌታ
ስም ትንቢት የሚናገሩ፣ በስሙ አጋንንቶችን የሚያወጡና በስሙ ብዙ ድንቆችን
የሚያደርጉ ሰዎች አጋንንት ከያዙዋቸው ከእነዚህ ጠንቋዮች አይለዩም፡፡ እነዚህ
ሰዎች በአጋንንት ተይዘው ለመረዳት የሚያዳግቱ፣ የማይጣጣሙና ፈጽመው ግራ
የሚያጋቡ አይረቤ ነገሮችን የሚናገሩባቸው ብዙ ስፍራዎች አሉ፡፡
‹‹ቫይንያርድ ፌሎውሺፕ›› ተብሎ ስለሚጠራ የመናፍቅ ቡድን ሰምታችሁ
ይሆናል፡፡ እነርሱ ‹‹መንፈስ ቅዱስ›› ሲወርድባቸው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሳቅ
እንደሚጠለቀለቁ፣ እንደ በግ፣ ፈረሶች ወይም እንደሚያገሱ አንበሶች የእንስሶችን
ድምጽ እንደሚያወጡና ሚዛናቸውን ስተው እንደ ወፈፌ በመሳቅ ‹‹መንፈሳዊ
ስካር›› ብለው የሚጠሩትን እንደሚለማመዱ አበክረው ይናገራሉ፡፡
ለመከተል ወሰንሁ፡፡
በዚህ ዓለም ላይ ኑሮዋችንን ስንኖር ብዙ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች
ይገጥሙናል፡፡ ዳግመኛ ከተወለድን በኋላ ‹‹አስቀድሜ አባቴን ልቅበር›› ያልነው
ስንት ጊዜ ነው? በኢየሱስ በማመን ዳግመኛ ብንወለድ ማድረግ የምንፈልጋቸው
ብዙ ሥጋዊ ነገሮች የሉምን? የእኛን እንክብካቤ የሚፈልጉ ምን ያህል ሰዎች
አሉን? በዛሬው ምንባብ ላይ የተጠቀሰው ደቀ መዝሙር ‹‹አስቀድሜ አባቴን
ለመቅበር ልሂድ›› አለ፡፡ ነር ግን እርሱ ሥጋዊ ጉዳዮቹን ሁሉም የሚፈጽም ከሆነ
የእግዚአብሄርን ሥራዎች ለመስራት ጊዜ የሚገኘው መቼ ነው? በቂ ጊዜስ
የሚኖረው መቼ ነው? ኢየሱስ ‹‹ተከተለኝ፤ ሙታኖቻቸውንም እንዲቀበሩ
ሙታንን ተዋቸው›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ እርሱ ይህንን ያለው እውነት ስለሆነ
ነው፡፡
ማንም ሰው በአንድ ጊዜ ሁለት ነገሮችን በሚገባ መስራት አይችልም፡፡
ሥጋዊ ጉዳዮቻችንንና መንፈሳዊ ሥራዎችን ለማከናወን ብንፈልግም እነዚህን
ሁለት ነገሮች በተመሳሳይ ጊዜ ማከናወን አንችልም፡፡ ሁለት ነገሮችን ጎን ለጎን
መፈጸም የሚችል ብቃት ያለው ሰው ቢኖርም እንኳን አንዱ ነገር ላይ
ሲንጠለጠል ሌላውን ሥራ ለመስራት ታማኝ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ምንም
ያህል የተካነ ቢሆንም አቅሙ ገደብ አለው፡፡ አንድ ምሳሌ ላሳያችሁ በቀድሞ ጊዜ
ገናም በትምህርት ቤት ሳለንና ፈተናዎችን ለማለፍ ስናጠና ብዙውን ጊዜ በተወሰኑ
ትምህርቶች ላይ እናተኩር ነበር፡፡ በአንድ ትምህርት ላይ ትልቅ ክብደት ሰጥተን
የጥናት ጊዜያችንን በአብዛኛው እዚያ ላይ ስናሳልፍ ሌሎቹን ትምህርቶች
በተመሳሳይ ግለት ማጥናት እንደማንችል የታወቀ ነው፡፡ ለእነርሱ የምናጠፋው
ጊዜና የምንሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ ውሱን ፍጡራኖች
ነንና፡፡
ስለዚህ በእግዚአብሄርም ፊት ቀጣዩን ምንባብ የእርግጠኝነት ጉዳይ
አድርገን ልንመለከተው ይገባናል፡፡ ‹‹ተከተለኝ፤ ሙታኖቻቸውንም እንዲቀርቡ
ሙታንን ተዋቸው፡፡›› የዚህን ምንባብ ትርጉም ማወቅና መከተል ያስፈልገናል፡፡
የራስን አባት መቅበር ትክክል ነው፡፡ ሁላችንም ልናደርገው የሚገባን ነገር ነው፡፡
በእኛ ዳግመኛ በተወለድነው መካከል በሞት ለተለየው የቤተሰብ አባል ለአንዱ
ተገቢውን ቀብር የማያደርግ አለ እንዴ? ሁሉም ሰው ይህንን ያደርጋል፡፡ ጌታ ግን
ዳግመኛ ለተወለዱት ደቀ መዛሙርቶቹ አስቀድመው ምን ማድረግ እንዳለባቸውና
እርሱን ከልባቸው የሚከተሉት ደቀ መዛሙርትም አስቀድመው ምን ማድረግ
እንደሚገባቸው ተናግሮዋል፡፡
መነሻ ገጽ
ኦድዮ መጽሐፎች
ኢ-መጽሐፍት
Rev. PAUL C. JONG
ደራሲው የውሃውንና የመንፈሱን
ወንጌል በዓለም ላሉ የጠፉ ነፍሳቶች ላለፉት
አስርተ ዓመታት ሲሰብኩ ቆይተዋል፡፡
የኒው ላይፍ ሚሽን መስራች
በመሆናቸውም በአሁኑ ጊዜ በኒው ላይ ሚሽን
ትምህርት ቤት ብዙ ደቀ መዛሙርቶችን
እያሳደጉ ነው፡፡
በሚሽን ላይ ያተኮሩ ቤተክርስቲያኖችን
ከመሰረቱ በኋላ በመጽሐፎቻቸው አማካይነት
ወንጌልን እያሰራጩ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ መጽሐፎቻቸው በዓለም
ላይ ባሉ 96 ዋና ዋና ቋንቋዎች ተተርጉመው
እየተነበቡ ነው፡፡
-ከመጽሐፉ የተወሰደ-