Professional Documents
Culture Documents
Untitled
Untitled
ትምህርት መንፈሳችሁን
እየገደለው ነው፡፡
በጣም ብዙ ሰዎች የለከፉዋቸውን
ቫይረሶች ሳያውቁ እንደሚሞቱ ሁሉ በዓለም
ሁሉ ያሉ ክርስቲያኖችም በንስሐ ጸሎቶች
ትምህርት ተለክፈው እየሞቱ ነው፡፡ የንስሐ
ጸሎቶች ትምህርት እንዲህ ያለ አደገኛ የተሳሳተ
ትምህርት መሆኑን ማወቅ የቻለ ማን ነው?
በርካታ ክርስቲያኖችን ወደ መንፈሳዊ
ውዥንብር ገደል ውስጥ የነዳቸው ማን
እንደሆነ ታውቃላችሁን? ዳግመኛ ሳይወለዱ
ቃሉን ያስተማሩ የክርስቲያን መሪዎች ናቸው፡፡
ስለዚህ አሁንም እንኳን እግዚአብሄር
በሰጠን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ቃል ማመንና
ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ መንጻት አለባችሁ፡፡
ይህ የተባረከ ዕድል እንዲባክን ልትፈቅዱ
አይገባችሁም፡፡ ሁላችሁም በውሃውና
በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከመንፈሳዊ ግራ
መጋባት ነጻ መውጣትና በእውነት ብርሃን
ውስጥ መኖር አለባችሁ፡፡
የንስሐ ጸሎቶችን ትምህርት ስህተት
እስከ አሁን ድረስ ሳታውቁ ቀርታችሁ ከሆነ
ከዚህ መጽሐፍ ልታውቁት፣ በውሃውና
በመንፈሱ ወንጌል ልታምኑና ወደ ጌታ
ልትመለሱ ይገባችኋል፡፡ ጌታ አዲስ ሕይወት
የሚገኝበትን እንጀራ አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ
ነው፡፡
-ፖል ሲ. ጆንግ-
ስላሴ አምላክ ለእኛ
ምን እንዳደረገልን
PAUL C. JONG
ISBN 978-89-282-1823-3
ዲዛይን፡ በሚን ሱ ኪም
ንድፍ፡ በዮንግ አይ ኪም
ትርጉም፡ በካሳሁን አየለ
የታተመው በኮርያ ነው፡፡
♠ Website: https://www.nlmission.com
https://www.bjnewlife.org
https://www.nlmbookcafe.com
♠ E-mail: newlife@bjnewlife.org
መቅድም ----------------------------------------------------------------- 9
ሐምሌ 7፤2008
ደራሲ ሬቨረ. ፖል ሲ. ጆንግ
ለውጠውታል፡፡
ብዙ ሰዎች እነዚህን ፍልስፍናዊ የሆኑ የክርስቲያን ትምህርቶች የሙጥኝ
ብለው በመያዝ ነፍሳቸውን እያጠፉ ነው፡፡ ምክንያቱም ፍልስፍናዊ እምነታቸው
ትክክለኛ እምነት እንደሆነ ያስባሉና፡፡ በራሳቸው አስተሳሰቦች መሠረት በኢየሱስ
ቢያምኑም ጥሩ ክርስቲያኖች ለመሆናቸው እርግጠኞች ናቸው፡፡ ስለ ኢየሱስ ደም
ሲያስቡ ስሜታቸው ይነካል፡፡ ይህንን በጥልቀት ባሰላሰሉ ቁጥርም ሌላው ሰው
ሁሉ ጥሩ ክርስቲያኖች መሆናቸውን እንዲደግፍላቸው አብዝተው ይሻሉ፡፡ ነገር
ግን በተጨባጭ ሰው ሰራሽ ትምህርቶችን እያሰራጩ ባሉት በእነዚህ ክርስቲያን
‹‹መሪዎች›› ተብዬዎች በተፈጠረው ግራ መጋባት ምክንያት ሐሰተኛና በስሜት ላይ
በተመሰረተ እምነት ውስጥ ጠልቀው እየገቡ ነው፡፡ እነዚህ በተሳሳቱ የክርስቲያን
ትምህርቶች የተጠመዱ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት አብዝተው
ይቃወማሉ፡፡ እነዚህ የታዋቂው ክርስትና ሐሰተኛ ትምህርቶች ፈላስፋ ቀመስ ከሆኑ
የቃለ እግዚአብሄር ምሁራን አስተሳሰቦች ውስጥ የፈለቁ ናቸው፡፡ እነርሱ የዘሩት
ሎጂክ ያፈራው ነገር ቢኖር ግራ የተጋቡ የክርስቲያን ትምህርቶችን ብቻ ነው፡፡
በአንጻሩ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምን ሁሉ የጠፋውን
የእግዚአብሄር መንጋ ከልቡ ይሻል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የሚሻው እውነተኛ ደህንነት
የሚገኘው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ሰው በዚህ
እውነተኛ ወንጌል በማመን ሐጢያቶቹን በሙሉ ማንጻት ይችላል፡፡ ስለዚህ
እያንዳንዱ ክርስቲያን ሐጢያተኛ በተቻለ ፍጥነት ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል
መመለስ አለበት፡፡
ይህንን ችግር እንዴት እንደምትፈቱት ሳታውቁ ቀርታችሁ በሐጢያቻችሁ
ተቸግራችኋልን? እንደዚያ ከሆነ በመጀመሪያ በኒው ላይፍ ሚሽን የተታተመውን
በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግመኛ ተወልዳችኋልን? የሚለውን የክርስቲያን
መጽሐፋችንን እንድታነብቡ እጠይቃችኋለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ ወደ ውሃውና
መንፈሱ ወንጌል እንደዚሁም ወደ እውነተኛው የደህንነት መንገድ ይመራችኋል፡፡
አሁን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አታውቁትምን? አሁንም ለራሳችሁ
‹‹እንደ ሐጢያት ችግር ያለውን ይህንን ትንሽ ችግር መፍታት ያልቻልሁት
ለምንድነው? እኔ ማድረግ የምፈልገው ነገር ቢኖር ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው
ደም ብቻ በማመን የአዳም ሐጢያቴን ስርየት መቀበልና ከዚያም በየቀኑ የንስሐ
ጸሎቶቼን በማቅረብ የግል ሐጢያቶቼን ማስወገድ ነው›› ትላላችሁን? ብዙ
ክርስቲያኖች በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶቻቸውን በማቅረብ የዘወትር ሐጢያቶቻቸውን
ማንጻት እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን እንደዚህ የምታስቡና የምታምኑ ከሆነ
ነው፡፡
ዛሬ በልቦቻቸው በውሃውና በመንፈሱ ወንገል የሚያምኑ ሰዎች በዚህ
እምነት የሐጢያቶችን ስርየት ተቀብለዋል፡፡ የእነርሱ ጉባኤም የእግዚአብሄር
ቤተክርስቲያን ነች፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን የተዋጁ ሰዎች እግዚአብሄርን
ለማመስገንና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመስበክ የሚሰበሰቡባት ነች፡፡
ይህንን እውነተኛ ወንጌል በጭንቅላቱ ብቻ የሚያውቅና በልቡ የማያምን ሰው ካለ
ይህ ሰው በእርግጠኝነት ሐጢያተኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ
ወንጌል ለማመን አሻፈረኝ የሚለውንና ልቡ አሁንም ሐጢያተኛ የሆነውን ሰው
ይጸየፈዋል፡፡ በልቦቻችን ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሄር ጽድቅ
በማያምን ሰው አይደሰትም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ማንኛውንም ሥራውን
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለማያምን ሰው በአደራ አይሰጥም፡፡
ሁሉም ሰው ወዲያውኑ የወሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንደማያስተውልና
እንደማያምን የታወቀ ነው፡፡ አንድ ሰው አንድ ቀን በዚህ ወንጌል ከማመኑና ቅዱስ
ከመሆኑ በፊት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሄር
ቃል ለተወሰነ ጊዜ ማድመጥ አለበት፡፡ ነገር ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል
እስከ መጨረሻው ድረስ የማይቀበሉ ሌሎች ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች
በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ቢገኙም የእግዚአብሄር ጽድቅ ጠላቶች
ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በመጨረሻ ከእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ይቆረጣሉ፡፡
ምክንያቱ ምንም ይሁን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምን ሁሉ የእግዚአብሄር
ቤተክርስቲያን አባል ሊሆን አይችልም፡፡ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በትክክል የማያምን ሰው ካለ የእግዚአብሄርን
ቤተክርስቲያን ይመራ ዘንድ ይህንን ሰው በጭራሽ ልንሾመው አይገባንም፡፡
የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ አካል ስለሆነች መሪዎችዋ
በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት አልባ መሆን አለባቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በልቦቻቸው
ውስጥ ሊሰራ የሚችለው የእግዚአብሄር አገልጋዮችና ቅዱሳኖች ሁሉ ሙሉ በሙሉ
ሐጢያት አልባ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የዳነ ሰው ተብሎ ሊገለጥ
የሚችለው ሐጢያት የሌለበት ሰው ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዳችን እምነቱ
በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ እንዲህ ያለ ቅዱስ ሰው ለመሆን ከፈለግን
ሁላችንም እግዚአብሄር በሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ማመን አለብን፡፡
የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ሁሌም በጎችን ከፍየሎች መለየትና ቤተክርስቲያንን
መንከባከብ የሚችል ሰው ያስፈልጋታል፡፡
እግዚአብሄር ራሱን በካደና በእግዚአብሄር ጽድቅ ባመነ ሰው ሁሉ
ነው፡፡
ቢሆንም ብዙ ክርስቲያኖች አሁንም በክርስቶስ ውስጥ እንደሞቱ ይናገራሉ፡፡
ብዙውን ጊዜ የትኩረት ነጥባቸው ይህ ነው፡፡ ቀድሞውኑም በእግዚአብሄር ጽድቅ
ላይ እምነት ያላቸው ይመስል ስለ ራሳቸው ስጋዊ ጽድቅ ይመጻደቃሉ፡፡ እነዚህ
ሰዎች ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም ብቻ እንደሚያምኑ ቢናገሩም
የራሳቸውን ጽድቅ ለማጽናት እየሞከሩ ነው፡፡ እዚህ ላይ በእግዚአብሄርም
ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደዚሁ በእግዚአብሄር ጽድቅ ከመታመን ይልቅ የገዛ ራሱን
ጽድቅ ለማጽናት የሚሞክር ማንኛውም ሰው የስጋውን መሻቶች ለማርካት የሚሻ
ሰው ነው፡፡ ይህ ሰብዓዊ ጽድቅ የስጋቸውን መሻቶች ብቻ ለማርካት በሚሹ
ሐይማኖተኞች የተፈጠሩ ከንቱ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችን እንጂ ያፈራው ሌላ
ምንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ግን በጭራሽ እንደማይታገሳቸው ተናግሮዋል፡፡
እነርሱ እነዚህን ሰዎች በመጨረሻው ቀን ሊቀጣቸው እንዳዘጋጃቸው ተናግሮዋል፡፡
ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ?›› (ዮናስ 1፡8) ያን ጊዜ ነቢዩ ዮናስ እንዲህ አላቸው፡-
‹‹እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሄርን
አመልካለሁ፡፡›› (ዮናስ 1፡9) ዮናስ በዚህ ክስተት አማካይነት ለራሱ ማንነቱን፣
ያለበትን ሁኔታዎችና ጥሪውን አስታወሰ፡፡ እኛም ደግሞ በየቀኑ ራሳችንን
መመርመር፣ ደህንነታችንን ማጽናት፣ የማን ወገን እንደሆንን መረዳት፣
የእግዚአብሄር ሕዝብ የመሆናችንን ማንነት ማመንና በዚያው መሰረትም መመላለስ
ይገባናል፡፡
ዛሬ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ላሉት አገልጋዮቻችንና
ቅዱሳኖቻችን ሁሉ የማስተላልፈው መልዕክቴ ይህ ነው፡፡ ሁሉን በሁሉ የሚሞላው
የእርሱ ሙላት የሚገኘው በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ማለትም የውሃውንና
የመንፈሱን ወንጌል በማወጅ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን በመላው ዓለም
ከሚገኝ ስፍራ ይልቅ እጅግ ብሩክ የሆነች ስፍራና የበረከቶች ሁሉ መጋዘን ነች፡፡
ይህች የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን የበረከቶች የሐብት መጋዘናችሁ እንደሆነች
ትገነዘቡ ዘንድ ሁላችሁንም እጠይቃችኋለሁ፡፡ እግዚአብሄር በቤተክርስቲያኑ
አማካይነት የደህንነት በረከቶቹን ለእናንተ፣ ለቤተሰባችሁና በዓለም ሁሉ
ለሚኖረው ለእያንዳንዱ ሰው እያካፈለ ነው፡፡ ይህንን ሁሌም እያስታወሳችሁ
በየቀኑ በእግዚአብሄር በረከቶች መካከል በእምነት እንድትኖሩ እመክራችኋለሁ፡፡
ይህች የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ የተወለዱ
ሰዎች የሚሰበሰቡባት፣ የእግዚአብሄርን ሥራ የሚሰሩባት፣ የሚያርፉባት፣ እርስ
በርሳቸው የሚሳሳቁባትና ሕብረት የሚያደርጉባት ስፍራ ነች፡፡ የእግዚአብሄር
ቤተክርስቲያን የእርሱ በረከቶች የሚጠራቀሙባት፣ በየቀኑ የሚታደሱበትና
ለሁሉም የሚካፈሉበት ስፍራ ነች፡፡ እኛ የዚህች የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን
አባሎች መሆናችንን በመረዳት ሁላችንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል
በመታመንና ጌታ እስከሚመለስበት ቀን ድረስ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ
በመቆየት የእርሱን ሥራ መስራት አለብን፡፡ እናንተም የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን
አባል ስለሆናችሁ ቃሉን ለማቅረብና ዳግመኛ ለመወለድ ለሚናፍቁ በእያንዳንዱ
የዓለም ማዕዘን ላሉ ሰዎች አዲስ ሕይወትን ለማምጣት የእርሱን ክቡር ሥራ
እየሰራችሁ ነው፡፡
እግዚአብሄር ኢየሱስ ክርስቶስን ለእናንተና ለእኔ የላከው የቤተክርስቲያኑ
አባሎች ሊያደርገን ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ስለተጠመቀና
በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ስለሞተ ለአንዴና ለመጨረሻ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ
ድነናል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ካዳነን በኋላ ቢተወን ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር?
ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ እምነት በአደገኛ ሁኔታ ከተሳሳተ እሳቤ የመነጨ ፈጽሞ
የተሳሳተ እምነት ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እግዚአብሄር የሰጣችሁ
ፍጹም የሆነ የደህንነት ስጦታ ነው፡፡ ይህንን ወንጌል ከልባችሁ ካመናችሁ
በእርግጠኝነት የእግዚአብሄርን ማለቂያ የሌለው ፍቅር ትቀበላላችሁ፡፡ ነገር ግን
ይህንን የሚያድነውን የውሃና የመንፈስ ጸጋ የማትቀበሉ ከሆነ የእግዚአብሄርን ቁጣ
ትቀበላላችሁ፡፡
የዘመኑ ሐሰተኛ ክርስቲያኖች እምነት ያረፈው ከመጀመሪያውም
ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ምንም ግንኙነት በሌለውና ከራሳቸው አስተሳሰቦች
በፈለቀው ነገር ላይ ነው፡፡ እነርሱ የራሳቸውን አምላኮች ከፈጠሩ በኋላ በራሳቸው
አስተሳሰቦች በተበጁ ትምህርቶች ያምናሉ፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ ማመኑ ከእንግዲህ
ወዲህ የማይጠቅማቸው ሲሆን በቀላሉ በአንድ ሌላ ነገር ይተኩታል፡፡ ስለዚህ
በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ ክርስቲያኖች ለእነርሱ በሚስማማቸው በማንኛውም
መንገድ ራሳቸው ባበጁዋቸው ትምህርቶች ያምናሉ፡፡
ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በትክክል የሚያምን ከሆነ አሁንም
ሐጢያተኛ እንደሆነ ሊናገር ይችላል? በመካከላችሁ ኢየሱስ የወሰደው የአዳምን
ሐጢያት ብቻ ነው፤ ሰው በየቀኑ የሚሰራቸው ሐጢያቶች በሚሰራው ጊዜ ሁሉ
መወገድ ያለባቸው በንስሐ ጸሎቶች አማካይነት ነው ብሎ በተሳሳተ መንገድ
የሚያስብ ሰው አለ? እንዲህ የሚል ማንኛውም ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል
የመጣውን የእግዚአብሄር ፍቅርና ምህረቱን የሚንቅ ሰው ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች
ብቻቸውን የራሳቸውን የደህንነት መንገድ አበጅተዋል፡፡
እግዚአብሄር በኢሳይያስ 1፡18 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሐጢአታችሁ እንደ አለላ
ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች፡፡››
በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሎናል፡- ‹‹ሐጢያቶቻችሁ እንደ ጭጋግ
ቢሆኑም እናንተ አሁንም የእኔ ናችሁ፤ ምክንያቱም አድኜአችኋለሁ፡፡ በሰማይ ላይ
እንዳለው ጭጋግ የበዙትን በርካታ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ አስወግጃለሁ፡፡
ስለዚህ እናንተ ሐጢያተኞች ሁሉ ወደ እኔ ተመለሱ፡፡›› በእርግጥ ሕያው በሆነው
አምላክ፣ በእርሱ እውነትና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው የእርሱ ጽድቅ
የምታምኑ ከሆነ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ትቀበላላችሁ፡፡ ነገር ግን
የእግዚአብሄርን ጽድቅ የምትንቁ ከሆነ ከአዳም ሐጢያታችሁ የነጻችሁ ብትሆኑም
በየቀኑ የምትሰሩዋቸውን ሐጢያቶችና የወደፊት ሐጢያቶቻችሁን ስርየት
እንዳልተቀበላችሁ ትናገራላችሁ፡፡
ጽድቅ እንከተላለንና፡፡
በዚህ ዓለም ላይ የሚኖር ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢቆጣጠርም እንኳን
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከሚያገለግሉት በላይ በጣም ደስተኛ ሊሆን አይችልም፡፡
ሰው በመላው ዓለም ላይ ሁሉም ነገር ቢኖረው እንኳን በእግዚአብሄር ጽድቅ
እስካላመነ ድረስ በመጨረሻ ይጠፋል፡፡ እነርሱ በሕይወታቸው ውስጥ
በእግዚአብሄር ፊት በርካታ ሐጢያቶችን ይሰራሉ፡፡ ሁሉም ሰው በእግዚአብሄር
ጽድቅ በመታመን እስካልኖረ ድረስ ከእግዚአብሄር ፈቃድ በተቃራኒ ለመኖር
ይገደዳል፡፡ ለጸጋው ምስጋና ይሁንለትና የእግዚአብሄርን ሥራ መስራት
የምንችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምነው አማኞች እናንተና እኔ
የሆንነው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ በስጋችን ደካሞች ብንሆንና በጣም ብዙ ጉድለቶች
ቢኖሩብንም እርሱን ለማስደሰት የእግዚአብሄርን ሥራ በእምነት መስራታችንን
መቀጠል አለብን፡፡ ያን ጊዜ እግዚአብሄርንና የእርሱን አገልጋዮች እናመሰግናለን፡፡
ምክንያቱም ሕይወታችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ታድሶና
ከብሮዋልና፡፡
ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ሳታውቁ በነበራችሁበት ጊዜ ሕይወታችሁ
እንዴት እንደነበር እንደምታውቁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ደግማችሁ አስቡ፡፡
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከማመናችሁ በፊት ምን ዓይነት ሕይወት ትኖሩ ነበር?
በቀድሞው ኑሮዋችሁ እጅግ አስጸያፊና እጅግ ክፉ የሆኑ ሐጢያቶችን ብቻ
ሰርታችኋል እያልሁ እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን በእነዚያ ዘመናት
ከእግዚአብሄር ሥራ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ብዙ ክፉ ነገሮችን
እንደሰራችሁ እረግጠኛ ነኝ፡፡
ሁላችንም የኢየሱስ ክርስቶስን ጽድቅ ከመረዳታችን በፊት ሳናውቅም ቢሆን
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ተቃውመናል፡፡ አሁን ግን በልቦቻችን በውሃውና በመንፈሱ
ወንጌል ስለምናምን በትክክል መልካምና ንጹህ የሆነውን በደስታ እናደርጋለን፡፡
እነዚህን የሰማይ መንፈሳዊ በረከቶች ለማሰራጨትም ሁላችንም የእግዚአብሄርን
የደህንነት ጸጋ ለብሰናል፡፡ ማንም ሐጢያተኛ በእግዚአብሄር ፊት አንዳች መልካም
ነገር ማድረግ ባይችልም አሁን እግዚአብሄር በሕይወታችን ውስጥ ትክክለኛውን
ጽድቅ ተግባራዊ ማድረግ የምንችልበትን ችሎታ ሰጥቶናል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ
ወንጌል በመታመን በሕይወታችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ መስበካችን ትልቅ በረከት
ነው፡፡
ይህ ሆኖ ሳለ የእግዚአብሄርን የጽድቅ ሥራ መስራት ተስኖን ቢሆን ኖሮ ምን
ይፈጠር ነበር? ለስጋችን በጣም አድካሚ በመሆኑ ምክንያት የእግዚአብሄርን ጽድቅ
ድህነታቸው ነው›› (ምሳሌ 10፡15) ይላል፡፡ ሰዎች ድሆች ምንም ያህል አንደበተ
ርቱዕ ሆነው ቢናገሩ እንኳን አይሰሙዋቸውም፡፡ ነገር ግን የሰው ቃሎች ተጨባጭ
በሆኑ ቁሳዊ ጥቅሞች ሲታጀቡ እነዚህ ቃሎች ይበልጥ በቀላሉ ተቀባይነትን
ያገኛሉ፡፡ ለእነርሱ ያለንን ፍቅር ለማጋራትና ወንጌልንም በመላው ዓለም ሁሉ
ለመስበክ መጽሐፎቻችንን በዓለም ሁሉ ለሚገኙ ሰዎች በነጻ የምንሰጠው ለዚህ
ነው፡፡ በመላው ዓለም የሚኖሩ እነዚህ ሰዎች ከወንጌል መጽሐፎች አንዱን
በማንበብ ብቻ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት መቀበል የሚችሉት እንዲህ ነው፡፡
ይህንን ወንጌልን የማስፋፋትን ሥራ መሥራታችንን መቀጠል ብቻ ሳይሆን
እስከ መጨረሻው ድረስም ይህንን እምነት መጠበቅ በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡ ይህንን
እምነት እስከ መጨረሻው ድረስ መጠበቅ የሚገባን የድል አክሊል የሚሰጠው
ይህንን ለሚያደርጉ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ወንጌልን በዓለም ሁሉ ብትሰብኩ ነገር ግን
እምነታችሁን ብታጡ ሰላማችሁንም ደግሞ ታጣላችሁ፡፡ ይህንን ሰላም ካጣችሁ
ደግሞ ሕይወታችሁንም ታጣላችሁ፡፡ ሕይወታችሁን ካጣችሁ ደግሞ ወደፊት
የሚጠብቁዋችሁ እርግማኖች ብቻ ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ እስከ መጨረሻው ድረስ
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያላችሁን እምነታችሁን መጠበቅ
ያስፈልጋችኋል፡፡ እናንተና እኔ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እንደምን ክቡርና ድንቅ
እንደሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ ሁላችንም በዚህ ወንጌል ላይ ያለንን እምነታችንን
መጠበቅ ይገባናል፡፡
እዚህ ላይ ሁላችሁንም እንደምወዳችሁ ልናገር፡፡ እኔ የማልወደው ማንም
ሰው የለም፡፡ የምወደው በዓይኖቼ ፊት የተሰበሰባችሁትን እናንተን ብቻ ሳይሆን
በመላው ዓለም ባለችው የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን
አገልጋዮቻችንንና ቅዱሳኖቻችንንም ሁሉ ነው፡፡ ከቤተክርስቲያን ውጪ ያሉትንም
እንኳን እወዳቸዋለሁ፡፡ ስለ እነርሱ በጥልቀት የምናስበውና አንዳንድ ጊዜም
በግትርነታቸው የምንረበሸው እነዚህን የጠፉ ነፍሳቶች ሁሉ ስለምንወዳቸው ነው፡፡
እስከ መጨረሻው ድረስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያለንን እምነታችንን
ለመከላከል እንዲህ ላሉት የማያምኑ ሰዎች ሁሉ ርህራሄ ሊኖረንና ወንጌልን
ልንሰብክላቸው የሚያስፈልጋቸው አሳዛኝ ነፍሳቶች እንደሆኑ ልናጤን ይገባናል፡፡
በተመሳሳይ ጊዜም ሐሰተኛ ወንጌል ይዞ ወደ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ሾልኮ
የሚገባውን ማንኛውንም ሰው መቃወም እንድንችል ሊረዳን የሚችል እምነትም
ደግሞ ያስፈልገናል፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ እዚህ በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ላይ
እንዳስተማረን አንድ ጌታ፣ አንድ እምነትና አንዲት ጥምቀት እንዳለ ሳታወላውሉ
ለብሰናልና፡፡
እያንዳንዱ ክርስቲያን ከላይ የሚመጡትን ትዕዛዛቶች ማለትም እግዚአብሄር
የተናገረውን ቃል መታዘዝ አለበት፡፡ እግዚአብሄር ራሱን ለእኛ ገልጦዋል ማለት
ቃሉን ከፍቶ በቃሉ አማካይነት ፈቃዱን አሳይቶናል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር
ፈቃዱን ያሳየውና የገለጠው በቃሉ አማካይነት ነው፡፡ የክርስቲያን እምነት ይህንን
ቃል ማድመጥ ከቃሉ ውስጥም የእግዚአብሄርን ፈቃድና የሚደሰትበትን ነገር
መረዳትና ቃሉን እየታዘዘ መመላለስ ነው፡፡ በአንጻሩ ዓለማዊ ሐይማኖቶች ሰው
የሰራውን አምላክ ስለ ማምለክ የሚናገሩ ናቸው፡፡
እናንተስ ታዲያ? እግዚአብሄርን የምትመስሉ ናችሁን? በእግዚአብሄር ፍቅር
እየተመላለሳችሁ ነውን? ሁላችንም በእግዚአብሄር ፍቅር መመላለስ አለብን፡፡ ቁሳዊ
ነገርን በሚመለከት የምንሰጠው ብዙ ነገር ባይኖርም በእውነተኛ ፍቅር
እየተመላለስን ነው ማለትም እርስ በርሳችን በመንፈሳዊ ሁኔታ እየተረዳዳን ነው፡፡
በተጨባጭ እየጎዱዋቸው እያሉ ሌሎችን እየረዱ እንደሆኑ የሚናገሩ በርካታ ሰዎች
አሉ፡፡ በአንጻሩ እኛ ሌሎችን ከልባችን እንወዳቸዋለን፡፡ ይህንን የምናደርገው
ለራሳችን ስንል ሳይሆን ለክርስቶስ ኢየሱስ ስንል ነው፡፡ ለእኛ በእግዚአብሄር ፍቅር
መመላለስ ማለት ሌሎች ክርስቶስን እንዲከተሉና የእግዚአብሄርን በረከቶች
እንዲቀበሉ መርዳት ነው፡፡
ፍቅርን የተናገረ ማነው? እግዚአብሄር ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ፍቅርን
መናገርና መተግበር የሚችል ሰው ካለ ይቅርብ፡፡ ሰው እንዴት እውነተኛ ፍቅርን
ማብራራት ይችላል? እውነተኛ ፍቅር የእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ የእግዚአብሄር
ፍቅር ስለ እኛ ሲል ራሱን መስዋዕት በማድረግ የተሰጠን እውነተኛ ፍቅር ነው፡፡
በእርግጥ በእግዚአብሄር ፍቅር እየተመላለስን ነውን? እርስ በርሳችን ሕብረት
የምንካፈለው እንዴት ነው? ከእናንተ ጋር ሕብረትን የሚካፈሉት ሰዎች ያንን
የሚያደርጉት ለክርስቶስ እንድትኖሩ ሊረዱዋችሁ ነው? እንዲህ ዓይነት ሕብረት
የሚጋሩ ሰዎች ካሉዋችሁ ምን ያህል ልታመሰግኑዋቸው እንደሚገባችሁ
ታውቃላችሁን? አብረዋችሁ ያሉ ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ቢሆኑ ወይም
የእግዚአብሄር አገልጋዮች ለእግዚአብሄር እንድትኖሩ ሊረዱዋችሁ ሕብረታቸውን
የሚጋሩትን ሁሉ ልታመሰግኑዋቸው ይገባችኋል፡፡
በሆኑት መካከል እንኳን እነዚህን ሐጢያቶች የሰሩ አንዳንድ ቅዱሳን ነበሩ፡፡ ስለዚህ
ጳውሎስ በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ላይ ቀድሞውኑም በውሃውና
በመንፈሱ ወንጌል ስለምናምን ማናችንም ገና ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች
በሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች ውስጥ ተካፋዮች መሆን እንደሌለብን ይመክረናል፡፡
እኛ ቅዱሳኖች የዓለም ሰዎች እንደሚኖሩት ላለመኖራችን በየትም ቦታ
የተሰጠ ዋስትና እንደሌለ የታወቀ ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ብናምንም
እንኳን ስጋዊ ተፈጥሮዋችን አሁንም አለ፡፡ ስለዚህ ልክ እንደ ዓለም ሰዎች መኖር
ይቻላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ለመኖር በምትፈተኑበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሄር በዛሬው
የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ውስጥ ምን እንዳላችሁ ልታስታውሱ ይገባል፡፡
‹‹ዝሙትና ርኩሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፡፡›› (ኤፌሶን
5፡3)
ይህ ምንባብ እነዚህን ሐጢያቶች አለመስራታችን ምን ያህል አስፈላጊ
እንደሆነ በግልጥ አሳይቶናል፡፡ በጣም የረከሱ በመሆናቸው እግዚአብሄር
በመካከላችን እንኳን እንዳይሰሙ ነግሮናል፡፡ ገና ከመጀመሪያው ጥንቃቄያችን
ፈጽሞ እንዲወድቅ መፍቀድ እንደሌለብን፣ ሁሌም ከእነዚህ ሐጢያቶች
እንድንጠነቀቅ፣ ራሳችንን ከእነርሱ እንድናርቅና ስማቸውንም እንኳን እንዳንጠራ
ይመክረናል፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር በቸልተኝነት በጥቂቱም እንኳን ወደ
እነዚህ ሐጢያቶች ለመሳብ ከፈቀድን መጨረሻችን እነርሱን መፈጸም እንደሚሆን
እያስጠነቀቀን ነው፡፡
ይህንን ምንባብ በመንፈሳዊ መልኩ ማጤንና መረዳት በጣሙን
ያስፈልገናል፡፡ አሁን ሁላችንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባናምንም አንዳንድ
ጊዜ ልቅ የጾታ ግንኙነቶችን ወደሚያሳዩ ምስሎችና ፊልሞች እንደዚሁም ወደ
ዝሙት ነገሮች እናሳባለን፡፡ ለእነዚህ ፍትወታዊ መሻቶችና ፈተናዎች በግድየለሽነት
ከተሸነፍን ጣዖት አምልኮን እንፈጽማለን፡፡
ወደ ብሉይ ኪዳን ስንመለስ ኢዮርብዓም የተባለ ንጉሥ እስራኤልን ጣዖት
አምላኪ ሕዝብ አድርጎ እንደለወጣቸው እናያለን፡፡ ይህ ሰው በሕይወቱ
የፈለጋቸው ሦስት ነገሮች ብቻ ነበሩ፡፡ እነርሱም ዝና፣ ሥልጣንና ጾታዊ ልቅነት
ነበሩ፡፡ የመሳሳቱ ውጤት ምን ነበር? በመጀመሪያ እግዚአብሄርን ራሱ በሰራቸው
የወርቅ ጥጆች ተካው፡፡ እነዚህንም የወርቅ ጥጆች በእግዚአብሄር መቅደስ ውስጥ
እስከማኖር፣ በፊታቸው እስከ መንበርከክና ለሕዝቡም ከግብጽ ባርነት ነጻ
ያወጡዋቸው እነዚህ የወርቅ ጥጆች እንደሆኑ እስከ ማስተማር ድረስ ርቆ ሄደ፡፡
ኢዮርብዓም የእግዚአብሄርን ሕግ ተወ፡፡ እንዲህ በማድረጉም ራሱ እግዚአብሄር
ቢበዛ 70-80 ዓመት ነው፡፡ (መዝሙረ ዳዊት 90፡10) በዚህ ዓለም ላይ ያለው
ሕይወታችን በጣም አጭር በመሆኑ የእግዚአብሄርን ሥራ ለመሥራት ምን ያህል
ጊዜ አለን? ከዕድሜያችን በጣም ያነሰ ጊዜ እንደሆነ ግልጥ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች
ለ30 ወይም ለ40 ዓመታት ይሠሩ ይሆናል፡፡ አብዛኞቹ ሰዎች ግን ለመሥራት
ያላቸው ጊዜ አነስተኛ ነው፡፡ ከረጅም ጊዜ በፊት በሌላ ትውልድ ውስጥ ተወልደን
ቢሆን ኖሮ አሁን ካለው በበለጠ ለረጅም ጊዜ የእግዚአብሄርን ሥራ ለመሥራት
በቻልን ነበር፡፡ ነገር ግን የጌታ ምጽዓት ያን ያህል ሩቅ ባልሆነበት ዘመን እየኖርን
በመሆናችን የእግዚአብሄርን ሥራ ለመሥራት ያለን ጊዜ አጭር ነው፡፡ ስለዚህ
አሁን ሁላችንም ሌሎችን ለማዳን የጽድቅ ጥሪያችንን በመፈጸም ረገድ በትጋት
መሥራት አለብን፡፡
በዓለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ ብዙ የሥነ ምህዳር ተቆርቋሪዎች የባህር ውስጥ ዓሣ
አንበሪን ማደን አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ ከእነርሱ አንዳንዶቹም ተቃውሞዋቸውን
የሚያሰሙት በቃላት ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን በራሳቸው መርከብ ወደ ባህሩ
በመዝለቅ የባህር ውስጥ ዓሣ አንበሪዎችን የሚያድኑ መርከቦችን ለመከልከል
እየሞከሩ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እምነታቸውን ለመደገፍ ሲሉ ሕይወታቸውን አደጋ
ላይ ጥለዋል፡፡ በሕይወት ውስጥ የእነርሱ እጅግ የላቀው ቅድሚያ ነገር የሥነ
ምህዳር ጥፋትን መከላከል ስለሆነ የሥነ ከባቢን ዝቅጠት ለማቆም የሚቻለውን
ነገር ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ በሒደቱ ውስጥ ሕይወታቸውንም እንኳን ለአደጋ
ያጋልጣሉ፡፡ ሁሉም ሰው ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጠው እጅግ ክቡር የሆነ ዕሴት
ብሎ ለሚቆጥረው ነገር ነው፡፡ ራሳቸውን የሰጡ የሥነ ምህዳር ተቆርቋሪዎች ወደ
ማንኛውም ስፍራ ለመሄድ ሳይፈሩና የሥነ ምህዳር ጥፋት ምክንያቶችን
ለመመርመርና የሥነ ከባቢን ዝቅጠት የውሃም ይሁን ወይም የአፈር ወይም
የተበከለ አየርን ለመከላከል መደረግ ያለበትን ሁሉ በማድረግ ተፈጥሮን ለመጠበቅ
የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ ብዙ ሰዎች እንዲህ ላለ ተገቢ ዓላማ ሳይታክቱ
በመሥራታቸው ያሞግሱዋቸዋል፡፡
በቅርቡ በኮርያ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ አጠገብ የፈሰሰ ከፍተኛ የዘይት ፍሳሽ
ኑሮዋቸውን በባህር ላይ የመሠረቱ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት አመሳቅሎዋል፡፡
በባህሩ ዳርቻ ላይ የተፈጠረው አጠቃላይ ጥፋት በጣም ከባድ ስለነበር ከእነርሱ
አንዳንዶቹ በተስፋ መቁረጥ ራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች
ለቤተሰቦቻቸው ዳቦ ለማግኘትና ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚደገፉት በባህሩ
ነበር፡፡ አሁን ግን ኑሮ መደጎሚያቸው በመውደሙ ምንም ነገር ማድረግ
አይችሉም፡፡ ዕጣ ፈንታቸው እጅግ አስከፊ በመሆኑ አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን
እግዚአብሄርን ማገልገል የቻልነው ጠንካራ ፈቃድ ወይም ብርቱ ማንነት ስላለን ሳይሆን
የጌታን ጽድቅ በያዘው የውሃና የመንፈስ ወንጌል በሚያምነው እምነታችን አማካይነት
የእግዚአብሄር ወታደሮች ስለሆንን ነው፡፡ ይህንንም እምነት እስከዚህች ቀን ድረስ
ጠብቀነዋል፡፡ በጌታ ጽድቅ በመታመንም መኖራችንን መቀጠል አለብን፡፡
ምን ያህል ሰዎች እንደሚቃወሙንና ጌታችንንና የእርሱን ጽድቅ ከመከተል
ሊያግዱን እንደሚሞክሩ ታውቃላችሁን? እነዚህ ጠላቶች ምን ያህል በጭካኔ
እንደሚቃወሙንና ሊያዋርዱን እንደሚሞክሩ ታውቃላችሁን? እንደዚያም ሆኖ ግን
እምነታችንን በጭራሽ ለእነርሱ አሳልፈን አልሰጠንም፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ
ያለንን እምነታችንን በሚመለከት በፍርሃት ለማንም አሳልፈን ሰጥተን አናውቅም፡፡ ነገር
ግን ሁሌም ጥብቀነዋል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ደግሞ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹በቀረውስ
በጌታና በሐይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ፡፡›› (ኤፌሶን 6፡10) ይህ ምንባብ በጌታ ጽድቅ
በመታመን ራሳችንን እድናበረታ በግልጥ ያስተምረናል፡፡
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ባላንጣዎች በሙሉ የምንቃወመው
እምነታችንን ለመከላከል ነው፡፡ ጠላቶቻችን ያለ ምህረት ሲያጠቁንና ሲያላግጡብን
ምንም ተቃውሞ ሳናደርግ ዝም ብለን መሳቅ ብቻ ይጠበቅብናልን? የለም፤ በእምነታችን
ልናሸንፋቸው ይገባናል፡፡ ልቦቻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ባላንጣዎች በሙሉ
ለመቋቋምና እምነታቸው የተሳሳተ መሆኑን በግልጥ ለመናገር ጠንካራ መሆን አለበት፡፡
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እያመናችሁ ልፍስፍሶች ትሆኑ ዘንድ የምትፈቅዱ
ከሆነ መጨረሻችሁ ለእግዚአብሄር ጽድቅ ጠላቶች መማረክ ነው፡፡ ብዙ ልፍስፍሰ
ቅዱሳኖች የደረሰባቸው ይህ ነው፡፡ ስለዚህ እምነታችን ደካማ ይሆን ዘንድ ፈጽሞ
መፍቀድ የለብንም፡፡ ልቦቻችን በእግዚአብሄር ፊት ደካሞች መሆናቸው አስከፊ
ሐጢያት ከመሆኑም በላይ የእርሱ ጠላቶችም ያደርገናል፡፡ እነዚህ ልፍስፍስ ሰዎች
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከማመስገን ርቀው መጨረሻቸው የእግዚአብሄር ጠላቶች
መሆን ይሆናል፡፡ ውለው አድረውም የእርሱን ጽድቅ ይቃወማሉ፡፡ ጌታ ፈሪሳውያንን
አስመልክቶ በሐዋርያው ጳውሎስ በኩል እንዲህ አለ፡- ‹‹የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሳያውቁ
የራሳቸውን ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ ለእግዚአብሄር ጽድቅ አልተገዙም፡፡›› (ሮሜ 10፡3)
ሁላችንም የእግዚአብሄርን ቃል በልቦቻችን ውስጥ ልንጽፍና እነዚህን ግብዝ ጠላቶች
በሙሉ በእምነት ደፍረን ልንቃወማቸው ይገባናል፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝብ ልፍስፍስ
መሆናቸው ከባድ ስህተት ነው፡፡
ዲያብሎስ በብሉይ ኪዳንም ይሁን በአዲስ ኪዳን በዚህ ዓለም ገዥዎች አማካይነት
እንደሰራ ማየት እንችላለን፡፡
በጥንቷ የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያቶች በሙሉ የውሃውንና የመንፈሱን
ወንጌል አምነው ሰብከዋል፡፡ በዚያን ዘመን በርካታ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን
ወንጌል ከሐዋርያቶች ሰምተዋል፡፡ ሐዋርያቶች በጥንቷ የቤተክርስቲያን ዘመን
እንዲህ በሐይል የሰበኩት ወንጌል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እንጂ ሌላ
አይደለም፡፡ ነገር ግን ሰይጣን በሐዋርያቶች የተሰበከውን እውነት ለመቅበር
ቆስጠንጢኖስ የተባለውን ሰው ሥልጣን ተጠቀመ፡፡ ይህ ሰው የሮም ንጉሠ ነገሥት
በሆነ ጊዜ ከርስትናን የመንግሥት ሐይማኖት አድርጎ አጸደቀ፡፡ ሕይወት
ለክርስቲያኖች በጣም ቀላል ስለነበር ቆስጠንጢኖስ ከዚህ ዓለም ስጋዊ
ሥልጣናቶች ጋር እንዲስማሙ በማጥመድ ልቦቻቸውን ማዳከም ችሎ ነበር፡፡
ጳውሎስ ‹‹የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች እንድናጠፋ›› (ኤፌሶን 6፡16)
መክሮናል፡፡ ይህ ማለት ጌታ በሰጠን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን
የሰይጣንን ጥቃቶች ማክሸፍ አለብን ማለት ነው፡፡ ሰይጣን በክፉ ሽንገላዎቹ
ትክክለኛውን እውነትና ትክክለኛውን እምነት ለማጥፋት እየሞከረ ነው፡፡ በየጊዜው
በልቦቻችን ውስጥ ስጋዊ መሻቶችን ያነሳሳል፡፡ ስጋዊ ስኬትን ብቻ እንሻ ዘንድ
እንደንፈተን በውስጣችን ስጋዊ ስስትን ይቀሰቅሳል፡፡ በሌላ አነጋገር ዲያብሎስ
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለጠፉ ነፍሳቶች ከመስበክ ይልቅ ትኩረታችንን
የጉባኤውን ቁጥር በመጨመር ላይ እንድናደርግ ያጠምደናል፡፡
የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያን በማገልገል ረገድ እጅግ ትልቁ ፈተና
አባላቶችን በማብዛት መታለል ነው፡፡ አገልጋዮቻችን ጠንቃቆች ካልሆኑ በቀላሉ
በዚህ ፈተና ውስጥ ሊወድቁና በእግዚአብሄር ትክክለኛ የእምነት ሕይወትን
ከመኖር ይልቅ የጉባኤውን መጠን በማሳደግ ላይ ብዙ ትኩረት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ሰይጣን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ይህንን ማታለያ ሲጠቀም ነበር፡፡ በዚህ ዕቅዱም
በተወሰነ ደረጃ ተሳክቶለታል፡፡ አሁንም እንኳን የእርሱ አገልጋዮች የዚህ ተመሳሳይ
ማታለያ ሱሰኞች ሆነዋል፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች በእነዚህ ክፉና ቆሻሻ የሰይጣን
ሽንገላዎች እየተታለሉ ነው፡፡
እኛ ግን ሕያው የሆነውን የእግዚአብሄር ቃል በእምነት መያዝ፣ የእምነትን
ጋሻ መጠቀምና በዚህም የዲያብሎስን ቆሻሻ ሽንገላዎች በሙሉ ማሸነፍ አለብን፡፡
ማናችንም እዚህ ስህተት ውስጥ መውደቅ የለብንም፡፡ የእግዚአብሄር አገልጋዮች
በጉባኤያቸው መጠን መወጠር የለባቸውም፡፡ እግዚአብሄር ተጨማሪ ነፍሳቶችን
ካመጣልን አመስጋኞች ልንሆን ይገባናል፡፡ እንደዚህ ካልሆነ ደግሞ ለጠፉት
መነሻ ገጽ
ኦድዮ መጽሐፎች
ኢ-መጽሐፍት
Rev. PAUL C. JONG
ደራሲው የውሃውንና የመንፈሱን
ወንጌል ለሁለት አስር አመታት ያህል
ለጠፉት የዓለም ነፍሳቶች ሲሰብኩ
ቆይተዋል፡፡
የኒው ላይፍ ሚሽን መስራች
በመሆናቸው በአሁኑ ጊዜ በኒው ላይ
ሚሽን ብዙ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶችን
እያፈሩ ነው፡፡
ሚሽን ተኮር ቤተክርስቲያኖችን
በመትከልም በጽሁፍ ሥራዎቻቸው
አማካይነት ወንጌልን እያሰራጩ ነው፡፡
መጽሐፎቻቸው በአሁኑ ጊዜ በ96
ዋና ዋና የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉመው
እየተነበቡ ነው፡፡
-- ሬቨረ.
ሬቨረ. ፖል
ፖል ሲ.
ሲ. ጆንግ
ጆንግ --