You are on page 1of 80

ራፕሶዲ ኦፍ

ሪያሊቲስ
...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Chris Oyakhilome
u}K¾ G<’@ “M}Ökc ue}k` G<KU Øpf‹
ŸSÅu—¨< ¾SêNõ pÆe ¾}¨cÆ “†¨<::

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ


ISSN 1596-6984
መስከረም 2010 edition
Copyright © 2010 by LoveWorld Publishing

KuKÖ S[Í“ }ÚT] KT²´:

UNITED KINGDOM: SOUTH AFRICA:


Believers’ LoveWorld 303 Pretoria Avenue
Unit C2, Thames View Business Cnr. Harley and Braam Fischer,
Centre, Barlow Way Rainham-Essex, Randburg, Gauteng
RM13 8BT. South Africa.
Tel.: +44 (0)1708 556 604 Tel.:+27 11 326 0971
Fax.: +44(0)2081 816 290 +27 62 068 2821
USA: Fax.:+27 113260972
Believers’ LoveWorld
4237 Raleigh Street
Charlotte, NC 28213 USA:
Tel.: +1 980-219-5150 Christ Embassy Houston,
CANADA: 8623 Hemlock Hill Drive
Christ Embassy Int’l Office, Houston, Texas. 77083
50 Weybright Court, Unit 43B Tel.: +1-281-759-5111;
Toronto, ON MIS 5A8 +1-281-759-6218
Tel.:+1 647-341-9091
NIGERIA: CANADA:
Christ Embassy 600 Clayson Road North York Toronto
Plot 97, Durumi District, Abuja, Nigeria. M9M 2H2 Canada.
Tel/Fax:+1-416-746 5080
LoveWorld Conference Center
Kudirat Abiola Way, Oregun
P.O. Box 13563 Ikeja, Lagos
Tel.: +234-703-000-0927, +234-812-340-6791 www.rhapsodyofrealities.org
+234-812-340-6816, +234-01-462-5700 email: info@rhapsodyofrealities.org

All rights reserved under International Copyright Law. Contents and/or cover
may not be reproduced in whole or in part in any form without the express written
permission of Christ Embassy (LoveWorld Publishing).
መግቢያ
የ 2010 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ
እርምጃና እድገት ለማሳደግ በተለየና ባማረ ሁኔታ ለተሻለ ነገር በሚያነሳሳ
መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመረጃና በመገለጥ ከተሞሉ ፁሁፎች በተጨማሪ የዚህ
ወር ዕትም በየዕለቱ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ መገኘት ለማወቅ በምታደርገው
ጉዞ እምነትህን በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንድታሳድግ በተመቻቸ ሁኔታ ተዘጋጅቶ
ቀርቦልኃል፡፡ በየቀኑ ባጠናኽው፣ ባሰላሰልከውና በአፍህ በተናገርከው ወይም
ደግሞ ባወጅከው መጠን እየታደስክ ትሄዳለህ፡፡

- ይህንን መነቃቅያ እንዴት በበለጠ መጠቀም ይቻላል -

ይህን ጽሁፍ አንብብና በጥንቃቄ አሰላስል፡፡ ፀሎቶቹንና የአፍ ምስክርነት ቃሉን


በየቀኑ ለራስህ ድምጽህን ጎላ አድርገህ መናገርህ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወትህ
እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በአዲሱ የሁለት ዓመት የመጽሐፍ
ቅዱስ ጥናት በሚገባ አንብቡ

የዕለታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡን በጠዋትና በማታ ከፍለህ ማንበብ ትችላለህ

መነቃቅያውን በጸሎት ተጠቀሙበትና በእያንዳንዱ ወራት ያላችሁን ግብ ጻፉና


ከአንዱ ግብ ወደ ሌላው ግብ ያላችሁን ስኬት በሚገባ ለኩ

የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ በወሰድን ጊዜ የእግዚአብሔርን የክብር


መገኘትና ድል ዓመቱን በሙሉ እንዲደሰቱበት ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በጣም
እንወዳችኋለን፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

-ፓስተር ክሪስና ኦያኪሎሜ


¾ÓM S[Í

eU
݃^h

eM¡
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ
...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

www.rhapsodyofrealities.org
አርብ

1
ዛሬ እናንተ የእርሱ ምስክሮች ናችሁ

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥


በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ
ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ (የሐዋርያት ሥራ 1:8)።

በ ቀደመችው ቤተክርስቲያን የነበሩ ሐዋሪያት ወንጌልን ስያውጁ


እና ብዙዎችን ወደ ጽድቅ ሲመልሱ የመንፈስ ቅዱስን ታላቅ
ኃይል እና ልቀት አሳይተዋል:: ከተግባራቸው እና ከመንፈሳዊ ድላቸው በፊት
በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እንዳነበብነው ከኢየሱስ የተፈጸመ የተስፋ ቃል
ነበራቸው:: ሚስጥራቸው እና ወደር የሌለው ጥቅማቸው የመንፈስ ቅዱስ
በእነርሱ ውስጥ ለመኖር መምጣት ነበር:
ለምሳሌ ከፍርሀት የተነሳ ኢየሱስን በወጣት ሴት ልጅ ፊት የካደውን
ጴጥሮስን እነውሰድ፥ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ ይኸው ጴጥሮስ
ወንጌልን በድፍረት ብዙ ህዝብ በሞላበት ሰበከ፤ በአንድ ጊዜም ሦስት ሺህ
ነፍሳት ክርስቶስን ተቀበሉ (የሐዋርያት ሥራ 2:41)::
ሐዋርያው ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላም ተመሳሳይ
ነገር ሆኖአል:: በቀጥታ ወደ ምኩራቦች እየሄደ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ
መሆኑን መስበክ እንደጀመረ የሐዋርያት ሥራ 9:20 ይነግረናል:: 1ኛ ቆሮንቶስ
2:4 እንዲህ ይላል: - “. . . ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ
ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።” መላጥያ በምትባል
ደሴት ላይም የእግዚአብሔርን ኃይል ገለጠ፤ የአገሬው ተወላጆችም ይህስ
አምላክ ነው አሉ (ሉቃስ 28 1-6)::
ዛሬ ያው መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ይኖራል:: የእግዚአብሔር
ክብር፥ ኃይል እና መንግስት እውነታ ምስክሮች እንድትሆኑ ወደ እናንተ
መቶአል:: 2ኛ ቆሮንቶስ 3:6 (ኤ ኤም ፒ ትርጉም) እንዲህ ይላል “[እርሱ
ነው] ለአዲስ ኪዳን [በክርስቶስ ያለ ደህንነት] አገልጋዮች እና ምስክሮች
እንድንሆን ያበቃን [ችሎታ ያለን ፥ የሚገባን እና ብቁ እንድንሆን ያደረገን]
“:: ወንጌልን ያለ ፍርሃት ስበኩ፤ እየሰበካችሁ መንፈስ ቅዱስ ያስችላችኋል፥
amharic
ይመራችኋል እና ኃይል ይሰጣችኋል:: መንፈስ ቅዱስ በቃሎቻችሁ ላይ
ኃይልን ያደርጋል:: ልክ ከቀደሙት ሐዋርያት ጋር እንዳደረገው ሁሉ በሚታዩ
ምልክቶች፥ ድንቆች እና ተዓምራት ቃሉን ያጸናል (ማርቆስ 16:20)::
ይህ የእናንተ ቀን ነው:: ይህ የእናንተ ሰአት ነው:: ሐዋርያት ወደ ሰማይ
ሄደዋል:: አሁን የክርስቶስን ክብር፥ ልቀት፥ በጎነትን እና ፍፁምነትን ለዓለም
ለማሳየት የተመረጠነው እኛ ነን:: ሃሌሉያ!

ጸሎት
ውድ የሰማይ አባት ሆይ፥ የአንተን ኃይል፥
ክብር እና ጸጋ ለዓለም እንዳሳይ ውጤታማ
ምሥክር እንድሆን ስላደረግከኝ አመሰግናለሁ::
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ኃጢአተኞችን ከጨለማ ወደ ብርሃን ፥
ዱስ ጥናት
ከኃጢአት ወደ ጽድቅ በመምራት እንደ
ወጤታማ የወንጌል አገልጋይ ስፍራዬን 1 ኛ ቆሮንጦስ
እይዛለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን:: 15:35-58
መጽሀፈ ምሳሌ 8-9

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
20:9-18
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 20

ለተጨማሪ ጥናት:
የሐዋርያት ስራ 26:16-18; 2 ኛ ቆሮንጦስ 3:5-6; የማርቆስ ወንጌል 16:15
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ቅዳሜ

2
በክርስቶስ ያለን የድል ህይወት ንቃተ ህሊና

ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም


በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን
(2ኛ ቆሮንቶስ 2:14)::

መ ልእክቶችን በምታጠኑበት ጊዜ በቀደመችው ቤተክርስቲያን


የነበሩትን የሐዋሪያት አስተሳሰብ ከማድነቅ በስተቀር ሌላ
ነገር ሊሰማችሁ አትችሉም:: ይህ አስተሳሰባቸው የነበራቸውን የህይወት
ደረጃ አመጣ:: እነርሱ በእምነታቸው ደፋር እና ጀግና ነበሩ:: በክርስቶስ
ያለን ህይወት ይህ ነው:: ይህንን የከበረ ህይወት ለማጣጣም በዚህ ንቃተ
ህሊና ውስጥ ልትመላለሱ ይገባል::
ለምሳሌ የሐዋርያው ጳውሎስን አስተሳሰብ እንመልከት፤ በፊሊጵስዩስ
4:13 ላይ እንዲህ አለ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
ምን አይነት አስተሳሰብ ነው! ለህይወታችሁ የሚያስፈልጋችሁ ነገር
ክርስቶስ በውስጣችሁ መሆን ብቻ ነው:: ጳውሎስ “ ስለሁኔታው ስጸልይ
በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” እንዳላለ አስተውሉ፤ አይደለም! ይልቁኑ እርሱ
የተቀበለውን መለኮታዊ ህይወት እና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእርሱ ውስጥ
መሆኑን ያውቅ ነበር::
ሐዋሪያው ዮሐንስም በክርስቶስ ያገኘነውን የሁልጊዜ የአሸናፊነት እና
የድል አድራጊነት ህይወት ንቃተ ህሊና ነበረው:: በ1ኛ ዮሐንስ 4:4 እንዲህ አለ
“ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም
ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።” በ1ኛ ዮሐንስ 1:3 ላይም ከአብ
ጋር ያለንን ህብረት እና ከእርሱ ጋር አንድ እንደሆንን ይገልጻል:: ከባባድ
ፈተናዎች እና ስደቶች ቢያጋጥመውም ሐዋሪያው ዮሐንስ ግን በጣም ደፋር
እና የማይበገር መሆኑ አያስገርምም::
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ስደት በነበረበት
ጊዜ ሐዋሪያው ዮሐንስ በጋለ ዘይት ውስጥ እንደተጣለ እና እንዲሞት
እንደተተወ ነገር ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስበት እንደወጣ ያሳየናል:: እርሱ
amharic
“ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና” (1ኛ ዩሐንስ 5:4) እያለ
በሚያሳድዱት ላይ እየሳቀባቸው የነበረ ይመስለኛል:: ሃሌሉያ!
ይህ ብቻ አይደለም:: ስለ ጴጥሮስ አንብቡ፤ እኛን ከእግዚአብሔ
ዓይነቶች ጋር ተባባሪዎች በመለኮታዊ ልምምዶች ተካፋዮች ብሎ
ይጠራናል፡- “. . . ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥
በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።” ዛሬ
ምን አይነት ህይወት እየኖራችሁ ነው? የእግዚአብሔር ሕይወት እንዳላችሁ
በመረዳት ንቃተ ህሊና ልትኖሩ ይገባል:: ስለዚህ ፍጹም የማትበገሩ እና
ለዘላለም ድል አድራጊ ናችሁ!

የእምነት አዋጅ
ውድ አባት ሆይ፥ በእኔ ውስጥ ቃልህ
ስላስቀመጠው የድል፥ የስኬት እና የክብር
ንቃተ ህሊና አመሰግንሀለሁ:: ስኬታማ ነኝ::
በጤንነት እኖራለሁ:: እኔ ባለጸጋ ነኝ:: እኔ ንቁ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
፥ ጠንካራ እና ብርቱ ነኝ:: በእኔ ውስጥ ያለው
የክርስቶስ ህይወት ከሰው እንድልቅ፥ ለዘላለም 1 ኛ ቆሮንጦስ 16:1-24
ድል አድራጊ አድርጎኛል! እግዚአብሔር መጽሀፈ ምሳሌ 10-11
ይባረክ!

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
20:19-26
መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
21

ለተጨማሪ ጥናት:
1 የዮሐንስ ወንጌል 5:4; 1 ኛ ቆሮንጦስ 15:57
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
እሁድ

3
በእናንተ ውስጥ የሚሰራው ኃይል

እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም


ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥ ለእርሱ
በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም
እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን (ኤፌሶን 3፡20-21)።

እ ግዚአብሔር እንዲያደርግላችሁ የምትፈልጉት ነገር ካለ


ያንን የሚፈጽመው ኃይል በሰማይ ሳይሆን ያለው በእናንተ
ውስጥ ነው:: ብዙዎች ማንኛውንም ነገር ሲፈልጉ እግዚአብሔር ነገሮችን
ለማስተካከል ከሰማይ እጆቹን ይዘረጋል ብለው ያስባሉ:: አይደለም!
መንፈሳዊ ነገሮችን ገና የበለጠ መረዳት እንደሚገባው አንድ መንፈሳዊ
ሕፃን ከእግዚአብሔር ጋር እንደዚህ ልትነጋገሩ እና አንዳንድ ውጤቶችን
ልታገኙ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ የህጻንነት ባህርያትን
ማስወገድ ይኖርባችኋል::
ይህም በቀደመችው ቤተክርስቲያን የነበሩት ሐዋርያት ስደት
ሲደርስባቸው ካደረጉት ጋር ተመሳሳይ ነው:: እንዲህ ብለው ጸለዩ “አሁንም፥
ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ
ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም
ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው” (ሐዋርያት ሥራ 4: 29-30)። በዚህ
ጊዜ ወንጌልን በመረዳት ገና በእድገት ላይ ነበሩ:: ገና ሕፃን ቤተክርስቲያን
ነበር::
እግዚአብሔር እነርሱ እንደጠየቁት ተአምራትን ለማድረግ “ከሰማይ
እጆቹን እንደዘረጋ” አናነብም:: ይልቁኑ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል
“ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ
ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ” (ሐዋርያት ሥራ
4:31)። የእግዚአብሔር መልስ የተቀበሉት መንፈስ ቅዱስ ነበር::
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ኃይል ነው፥ ለማንኛውም ነገር ሁሉ

amharic
የሚያስፈልጋችሁ ኃይል ነው:: እርሱ በእናንተ ውስጥ ይኖራል:: አንድ ሁኔታ
እና ፍላጎት ሲኖር ቃሉን በማሰላሰል እና በልሳኖቻችሁ በመናገር በመንፈስ
ቅዱስ እራሳችሁን አነሳሱ:: ይህን ስታደርጉ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእናንተ
ውስጥ ይሠራል::

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፥ መልካም ፈቃድህን መሻትንም
ማድረግንም በእኔ ውስጥ የምትሰራው አንተ
ስለሆንክ አመስግንሃለሁ:: ዛሬ በረከቶችን እና
ተዓምራቶችን ለማምጣት የአንተ ኃይል በእኔ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ውስጥ ይሠራል:: እኔ በቃሉ ስለምኖር ህይወቴ
በበቂ ወሃ ያገኘ የአትክልት ሥፍራ እንደ ሆነ 2 ኛ ቆሮንጦስ
እና በወቅትም ያለ ወቅትም ፍሬ እንደማፈራ 1-2:1-4
አውጃለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን:: መጽሀፈ ምሳሌ 12-13

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል 20:27-
38
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 22

ለተጨማሪ ጥናት:
1 የዮሐንስ ወንጌል 4:4: ኤፌሶን 3:20-21 AMPC
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሰኞ

4
የምንጸልየው በኢየሱስ ስም ነው

በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥


አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል (ዮሐንስ 16 23)።

አ ንዳንድ ክርስቲያኖች በጸሎታቸው መደምደሚያ ላይ “በጌታችን


በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል” ይላሉ:: በኢየሱስ ክርስቶስ “በኩል”
እያሉ መጸለይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ እንደዚያ እንድንጸልይ
በፍጹም አልተነገረንም:: በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጸለይ ማለት እርሱን
አገናኝ (የሚያገናኝ) ማድረግ ነው:: ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር መገኘት
ገብቶአል፤ ስለዚህ የሚያገናኝ አያስፈልገውም:: የሚያገናኝ የሚያስፈልገው
ሀጢያተኛ ብቻ ነው፤ በመሆኑም ይድን ዘንድ ኢየሱስን ይጠራል:: በኢየሱስ
ክርስቶስ በኩል ሲድን በእግዚአብሔር ኃይል ወደ እግዚአብሔር መገኘት
ይመጣል እናም ከዚያ በኋላ የሚያገናኝ አያስፈልገውም::
በኢየሱስ በኩል በመጸለይ እና በኢየሱስ ስም በመጸለይ መካከል
ጠንካራ እና ሕጋዊ የሆነ ልዩነት አለ:: በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት በኢየሱስ
ምትክ መጸለይ ነው:: በስሙ አንድን ነገር መጠየቅ ማለት የሚጠይቀው እርሱ
ራሱ ነው ማለት ነው፤ እናም በአባቱ ዘንድ ሊከለከል አይችልም::
ኢየሱስ በ(ዮሐንስ 16:23-24) እንዲህ አለ “በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች
አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን
ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ
ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ”። ስለዚህ ልንጸልይበት የሚገባን
ትክክለኛ መንገድ በኢየሱስ ስም ወደ አብ መጸለይ ነው:: ወደ እራሱ ወደ
ኢየሱስ አንጸልይም ፤ምክንያቱም በኢየሱስ ስም ወደ ራሱ ወደ ኢየሱስ
መጸለይ አንችልም:: ይህ ምንም መንፈሳዊ ትርጉም አይሰጥም::
“ወደ አብ ስንጸልይ ኢየሱስ ይማልድልናል እናም ይለምንልናል”
ብለው የሚናገሩ ሰዎች አሉ:: አይደለም፤ እንደዚያ አያደርግም:: በዮሐንስ
16:26-27 እርሱ እንዲህ አለ “በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ
እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ
amharic
ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ
ይወዳችኋልና”። አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋል እንዳለ አስተውሉ፤ ማንም
ለእናንተ ወደ እርሱ እንዲጸልይ አይፈልግም:: ስለዚህ በኢየሱስ ስም ጸልዩ
እና መልስን ተቀበሉ:: ሀሌሉያ!

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፥ ስለሰጠኸኝ በኢየሱስ
ስም መጸለይና መልስን መቀበል ልዩ ጥቅም
አመሰግናለሁ:: በዛ ስም ውስጥ ስላለው ኃይል
አመሰግንሃለሁ:: በኢየሱስ ስም ስልጣን፥ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
የበላይነት እና ማንነት ስለምጸልይ ለእኔ
የማይቻል ነገር የለም ! ሁል ጊዜ ድል አድራጊ 2 ኛ ቆሮንጦስ
ነኝ፤ ለዘለአለማዊ ፍሬአማንነት እና ምርታማነት 2:5-3:1-6
መጽሀፈ ምሳሌ 14-15
ተሾሜያለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
20:39-47
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 23

ለተጨማሪ ጥናት:
የማርቆስ ወንጌል 16:17-18; የዮሐንስ ወንጌል 14:14; የዮሐንስ ወንጌል 15:16
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ማክሰኞ

5
አዲሱ ፍጥረት ‘ የተዋጀ’ አይደለም
የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤
(ሉቃስ 1:68)።

ከ ላይ ያለው ጥቅስ አይሁዳዊያንን እንደሚያመለክት ግልጽ ነው፤


ከህግ እርግማን ሥር ስለነበሩ መዋጀት ያስፈልጋቸው ነበር::
ገላትያ 3:13 እንዲህ ይላል: - “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው
ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን”::
አንዳንድ ክርስቲያኖች ይህን ጥቅስ ሲጠቅሱ ሁሉንም ሰው የሚመለከት
ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን የሚመለከተው አይሁዳዊያንን ብቻ ነው:: እንደ
አይሁዳዊ ጳውሎስ በጥቅሉ ይናገር የነበረው ለአይሁናውያን ነበር::
አሕዛብ ከህግ እርግማን አልተዋጁም፤ እነርሱ የተዋጁት ከህግ ኩነኔ
ነው:: ህግ መኖሩ በራሱ የአሕዛብን ኩነኔ ያመለክታል:: እግዚአብሔር
አይሁዶችን የእርሱ ህዝብ እንዲሆኑ ሲመርጥ እና ለመኖር የሚያስችሏቸውን
የጽድቅ ህጎች ሲሰጣቸው ያ ወዲያውኑ በአሕዛብ ላይ ኩነኔ አመጣ:: ለዚህ
ነው በኤፌሶን 4:17-18 አሕዛብ “ከእግዚአብሔርም ሕይወት የራቁ እና
ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዳ የሆኑ፥ ተስፋ የሌላቸው እና በዓለም ላይ ያለ
እግዚአብሔር የሆኑ” ተብለው የተገለጹት::
ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ አይሁድም ሆነ አሕዛብ ያልሆነ አንድ
አዲስን ሰው ለመፍጠር አይሁዳውያንንና አሕዛብን በአንድ አዋህዷል፤
አዲሱ ፍጥረት ማለትም ይህ ነው:: (ኤፌሶን 2:14) “እርሱ ሰላማችን ነውና፤
ሁለቱን (አይሁድ እና አሕዛብ) ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን
ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ”(ኤፌሶን 2፡
14)፡፡
ይህ አዲስ ፍጥረት ከህግ እርግማን የተዋጀ አይደለም፤ ምክንያቱም
እርሱ ቀድሞም በህግ እርግማን ሥር ያልነበረ ነው፤ እርሱ ከዚህ በፊት
ፈጽሞ ያልነበረ አዲስ ሰው ነው: “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ
ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል”(2ኛ
amharic
ቆሮንቶስ 5:17)።
ህይወታችሁ ከዚህ ምድራዊ ግዛት ያለፈ ነው፤ ህይወታችሁ የክርስቶስ
ህይወት ነው:: “ትዋጁበት” ዘንድ አርነት ትወጡበት ዘንድ የሚያስፈልጋችሁ
አሮጌ ማንነት የላችሁም፤ አሮጌው ተፈጥሮአችሁ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሏልና፤
እናም አሁን እተመላለሳችሁበት ያለው የአዲስ ህይወት ምዕራፍ ነው:: በዚህ
መረዳት ተመላለሱ::

የእምነት አዋጅ
እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር
ህይወት እና ተፈጥሮ የተወለድኩ አዲስ
ፍጥረት ነኝ! ከዚህ በፊት ፈጽሞ ያልነበረ
አዲስ ሰው ነኝ፤ ከተፈጥሮ በላይ በሆነ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ህይወት በሚገባ እየኖርኩ እና በመንፈሳዊ
ክንፎች በከፍታ እየበረርኩ ነው:: እኔ ባለጸጋ፥ 2 ኛ ቆሮንጦስ
ጤናማ እና ጠንካራ ነኝ፤ በመንፈስ ቅዱስ 3:7-4:1-18
መጽሀፈ ምሳሌ 16-17
በወንጌል ላይ ተፅዕኖ እያመጣሁ ነው:: ክብር
ለእግዚአብሔር ይሁን!
የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል 21:1-9
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 24

ለተጨማሪ ጥናት:
2 ኛ ቆሮንጦስ 5:17-21; ቆላስያስ 3:8-10; ሮሜ 6:4
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ረቡዕ

6
እርሱ ከመከራ ያወጣችኋል
በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ
ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት (ኤፌሶ ን 1:7)።

ል ክ በቆላስይስ 1:14 ላይ እንዳለው ከላይ የተጠቀሰው “ቤዛነት”


የሚለው ቃል በዋጋ ክፍያ ነጻ መውጣትን አያመለክትም::
ይልቁኑ “ጠርጎ ማውጣት” ለሚለው ቃል ሌላ ተመሳሳይ ቃል በመሆን
ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ይህ ቃል “አፖሎቱሮሲስ” ከሚለው የግሪክ ቃል
የተተረጎመ ነው፤ ይህም ከመከራ መውጣት ማለት ነው:: ስለዚህ “ክርስቶስ
ቤዛዬ ነው” ስትሉ እርሱ የእናንተ ነጻነት እና ነፃ አውጪአችሁ፤ የእናንተ
አዳኝ፤ ከመከራ ውስጥ የሚያወጣችሁ ማለት ነው::
ይህ በመዝሙር 50:15 ላይ ዘማሪው ከተናገረው ጋር ተመሳሳይነት
አለው:: “በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።”
የገባችሁብት መከራ ምንም አይነት ቢሆን ግድ አይልም፤ ክርስቶስ የእናንተ
ነፃ አውጪ ነው፤ ከዛ መከራ እናንተን ያወጣችኋል:: መከራውን ራሳችሁ
ያመጣችሁት ቢሆንም ምንም ለውጥ አያመጣም፤ እርሱ ያወጣችኋል::
እናንተን ከመከራ ማውጣት ወይም መከራን ከእናንተ ማውጣት ፣ የእርሱ
በምትክነት መሞት ውጤት አንድ ክፍል ነው::
መጽሐፍ ቅዱስ፥ ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል ይላል (ምሳሌ
12:13)፤ ይህ ማለት ጻድቅ መከራ ሊያጋጥመው ይችላል፤ ነገር ግን አንድ
ነገር እርግጥ ነው፤ ይህም እርሱ ከመከራ መውጣቱ አይቀርም:: ወደ መከራ
እንድትገቡ ያደረጋችሁ አዋጅ ምንም ቢሆን ግድ አይልም፤ ክርስቶስ
ነጻ አውጪያችሁ ነው:: ከመከራ እና ወንጌል ከሚሰጣችሁ ነገሮች ጋር
የማይጣጣሙ ማንኛውንም ነገሮች ያስወግድላችኋል:: እርሱ እናንተን
የማዳንና ከማንኛውም ረግረግ የማውጣት ኃላፊነት አለበት::
ዘማሪው በ(መዝሙር 40:2-3) እንዲህ ብሎ መመስከሩ አይስገርምም፤
“ከጥፋት ጕድጓድ [ከተረበሸ አእምሮ እና ከውድመት] ከረግረግም ጭቃ
አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
amharic
አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ ብዙዎች ያያሉ
ይፈሩማል፥ በእግዚአብሔርም ይታመናሉ።”ሀሌሉያ!
ይህ ከሚሰጣችሁ ደስታ እና መጽናናት ባሻገር በየቀኑ ህይወትን
ለመጋፈጥ እና ለማሸነፍ አንድ ዓይነት መረዳት እና በራስ መተማመንን
ሊሰጣችሁ ይገባል::

ጸሎት
ደግ የሰማይ አባት ሆይ፤- በክርስቶስ ስላለኝ
እጅግ የላቀ ሕይወት አመሰግንሃለሁ! ከእኔ
በላይ በሆነው ዐለት ማለትም ክርስቶስ
ኢየሱስ ላይ ተተክያለሁ! ስለዚህ በሁኔታዎች የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
አልናወጥም:: ሁል ጊዜ አሸናፊ ነኝ ምክንያቱም
ክርስቶስ ነፃ አውጪዩ ነው:: ከማንኛውም 2 ኛ ቆሮንጦስ
መከራ ያወጣኛል እናም ከክብር ወደ ክብር 5:1-6:1-2
መጽሀፈ ምሳሌ 18-19
በድል ይመራኛል፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
21:10-19
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 25

ለተጨማሪ ጥናት:
መዝሙረ ዳዊት 27:1-2 & 5; መጽሀፈ ምሳሌ 12:13; 1 ኛ ቆሮንጦስ 1:30;
መጽሀፈ ምሳሌ 11:8
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሐሙስ

7
የእናንተን ድርሻ ተወጡ
ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል
ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ
ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ
(ፊልጵስዩስ 1:27)።

እ ንደ ክርስቲያን መንፈሳዊ እድገትን የምታመጡበት አንዱ መንገድ


ለክርስቶስ ወንጌል እምነት በመትጋት ነው:: ጸንታችሁ ለመቆም
ወስኑ እናም በቤተክርስቲያን ካሉ ሌሎች አማኞች ጋር የወንጌልን ዓላማ
ለመፈጸም ፤ የእግዚአብሔርን ጽድቅ በአለማችሁ እና ከክልሎች ባሻገር
ለማስፋፋት ሥሩ:: ለዚህ የተሰጣችሁ ሁኑ፥ ከዳር ሆናችሁ ተመልካች
መሆንን እምቢ በሉ:: ኢየሱስ በ(ማቴዎስ 24:14) እንዲህ አለ “ለአሕዛብም
ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥
. . . ።”
የአንድ አጥቢያ ቤተክርቲያን አባል በመሆናችሁ ብቻ አትርኩ::
በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋፋት ከእርሱ ጋር እንደ
አጋር፥ አብሮ ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ አድረጉ:: ኢየሱስ በ(1ኛ ቆሮንቶስ 3:9)
እንዲህ አለ፡- “የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤
ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።” ነብሳትን በማዳን ከእርሱ ጋር አብሮ
ሰራተኞች ነን:: በአባል እና በአብሮ ሰራተኛ መካካል ልዩነት አለ:: አባል
ከእናንተ ጋር በጀልባ ውስጥ ያለ ሰው ሲሆን አብሮ ሰራተኛ ግን ከእናንተ ጋር
እየቀዘፈ ያለ ሰው ማለት ነው:: አብሮ ሰራተኛ በሥራ ውስጥ ይሳተፋል::
መጽሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እያንዳንዱ ጅማት በሚያቀርበው
እንደምታድግ እና እንደምትሰፋ ይናገራል (ኤፌሶን 4:16):: በመንግስቱ
መስፋት፥ በዓለም የወንጌል ስርጭት የእናንተ ሚና ወሳኝ ነው:: ወንጌልን
ለማስፋት ኃላፊነት የተቀበላችሁ ብቸኛው ሰው እንደሆናችሁ አድርጋችሁ
ወንጌልን አስፉ:: ባላችሁ ብቃት ሁሉ ይህን አድርጉ::
በ2ኛ ቆሮንቶስ 12:15 ጳውሎስ ለወንጌል በብዙ ደስታ ገንዘቤን እና
amharic
ራሴን እንኳ እከፍላለሁ አለ:: በ1ኛ ቆሮንቶስ 9:16 በጥልቀት ይህንኑ አረጋገጠ
“. . . ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።”
ዛሬ እኛ ለዓለማችን ለመውሰድ እድል ያገኘነው ኢየሱስ ራሱ ማድረግ
እና ማስተማር የጀመረውን፥ ጳውሎስና ሌሎች ሐዋርያት የሰበኩትን
ተመሳሳይ መልእክት ነው:: በትውልዳችን የተባረከውን የጌታ ኢየሱስ
ክርስቶስን ታላቅ ወንጌል ተሸካሚዎች መሆን እንዴት ያለ ክብር ነው!
ነፍሳትን አዳኝ ከመሆን የበለጠ ለመኖር የተሻለ ምክንያት የለም::

ጸሎት
እኔ ውጤታማ ነፍሳትን አዳኝ ነኝ፤ ሌሎችን
በጽድቅ በመማረክ፥ በመገንባት እና በማሳደግ
፤ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መንግስት
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
በማስፋፋት እና ብዙዎችን ከጨለማ ወደ
ዱስ ጥናት
እግዚአብሔር ልጅ ነፃነት ለማምጣት ከመንፈስ
ቅዱስ ጋር አብሮ ሰራተኛ ነኝ፤ በኢየሱስ ስም:: 2 ኛ ቆሮንጦስ
6:3-7:1
አሜን:: መጽሀፈ ምሳሌ 20-21

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
21:20-28
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 26

ለተጨማሪ ጥናት:
1 ኛ ቆሮንጦስ 15:58; 1 ኛ ቆሮንጦስ 3:6-9
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
Te ¨h

Te ¨h

amharic
Te ¨h

Te ¨h
አርብ

8
መከራዎች ቦታ የላቸውም

[ለአፍታ እንኳን] በተቃዋሚዎች እና በጠላት አትደንግጡ ወይም አትሸበሩ፤


ይህ [እርጋታችሁ እና አለመፍራታችሁ] ለእነርሱ ውድቀታቸው [የማይቀር
ለመሆኑ] ግልጽ ምልክት (ማረጋገጫ እና መዝጊያ) ይሆናል፥ ለእናንተ ግን
ከእግዚአብሔር የሆነ [ምልክት እና ማስረጃ] ነፃ የመውጣት እና የመዳን
ነው (ፊልጵስዩስ 1:28 ኤ አም ፒ ትርጉም)::

እ ንደ ክርስቲያን ለዘላለም ድል አድራጊ ናችሁ፤ ስለዚህ ማንም


ቢቃወማችሁ ወይም በሚያጋጥማችሁ ፈታኝ ችግሮች ፈጽሞ
አትጨነቁ:: ለምሳሌ ማንኛውም እራሱን ከእናንተ ጋር ባላጋራ ያደረገ ሰው
የግድ ይሰናከልና ይወድቃል:: ለዚህ መጸለይ አያስፈልጋችሁም፤ ቃሉ
እንዲህ ይላልና “. . . ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ
ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ” (መዝሙር 27:1-2)። ስለዚህ
ተመልከቱ የሚያጋጥማችሁ ጠላቶች እና መከራዎች ቦታ የላቸውም::
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር
ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ
ነውና”(1ኛ ዮሐንስ 4:4)። እናንተ የማትወድቁ ናችሁ:: ያዕቆብ 1:2 እንዲህ
ይላል “. . .ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት”::
በትምህርታችሁ ችግር አጋጥሟችሁ ይሆናል፥ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፤
ምክንያቱም ምንም ቢሆን ምስክርነትን ይዛችሁ ትወጣላችሁ:: በችግር
ቀን መዛልን ወይም መፍራትን እንቢ በሉ፤ እግዚአብሔር በእናንተ
ይተማመናል! እርሱ ችግሮችን እንድትጋፈጡ እና እንድታሸንፉ በበቂ ሁኔታ
እንዳሰለጠናችሁ ይተማመናል::
ጸልያችሁም እንኳን ችግሩ የተወገደ ባይመስልም ተስፋ አትቁረጡ::
በችግር ስር ፈጽሞ አንወድቅም! ተግዳሮቶች ሲያጋጥሙን ፈጽሞ
አናለቅስም:: ሰይጣን ላይ አፍጡበትና እንዲህ በሉ “ሰይጣን፣ ምንም
ብታደርግ እኔ ከአሸናፊዎች በላይ ነኝ ፤ምክንያቱም በዓለም ካለው ይልቅ
በእኔ ያለው ታላቅ ነውና::”
amharic
ፈጽሞ ልንሸነፍ እንደማንችል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መጽናኛ
እና በህይወታችን የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫ አለን:: በማንኛውም ነገር
መሸበርን እምቢ በሉ:: በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እየሰራችሁ እስካለ
ድረስ በምድርም ሆነ በሰማይ ውስጥ እናንተን ሊያሸንፏችሁ የሚችሉ
ተቃዋሚዎች ወይም መከራዎች የሉም:: ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

ጸሎት
በዓለም ካለው ይልቅ በእኔ ያለው ታላቅ ነው::
ሁልጊዜ ጌታ በእኔ ውስጥ እና ከእኔ ጋር ስለሆነ
መጨነቅን ወይም መረበሽን እንቢ እላለሁ::
በእኔ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም:: የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
በታላቅ ልዑል እግዚአብሔር ምሥጢራዊ ቦታ
ውስጥ እኖራለሁ ፤እናም ሁልጊዜ በመንፈስ 2 ኛ ቆሮንጦስ 7:2-16
ቅዱስ ብቃት እሰራለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: መጽሀፈ ምሳሌ 22-23
አሜን::

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
21:29-38
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 27

ለተጨማሪ ጥናት:
መዝሙረ ዳዊት 91:3-7; ትንቢተ ኢሳያስ 54:17; መጽሀፈ ምሳሌ 24:10
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ቅዳሜ

9
በጽድቅ ፍሬዎች ተሞልታችኋል

ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና [ክብሩ እንዲታይ እና እውቅና


እንዲያገኝ] ከኢየሱስ ክርስቶስ(የተቀባው) የሚገኝ የጽድቅ
(በእግዚአብሔር ፊት የመቆም መብት እና ትክክል የማድረግ) ፍሬ
ሞልቶባችሁ፥ (ፊልጵስዩስ 1:11 አምፕሊፋይድ ትርጉም)።

ሮ ሜ 5:1 (አምፕሊፋይድ ትርጉም) እንዲህ ይላል፡- “እንግዲህ


በእምነት ከጸደቅን (በነፃ መለቀቅ፥ ጻዲቅ መባል እና
በእግዚአብሔር ፊት የመቆም መብት ማግኘት) በእግዚአብሔር ዘንድ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ (በመሲሁ በተቀባው) ሰላምን [እርቅን ማግኘት
እና ማጣጣም] እንያዝ፤”:: መጽደቅ ማለት ያላጠፋ ተብሎ የታወጀለት
ማለት ነው:: ክርስቲያን ማለት ያ ነው፤ ጻዲቅ ተብሎ የታወጀለት እና
በእግዚአብሔር ፊት የመቆም መብት ያለው ነው:: እርሱ እንዲሁ “በጸጋ
ከኃጢያት የዳነ” ብቻ ማለት አይደለም::
አዎን፤ በጸጋ ድነናል፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ጽድቅ
እንድንሆን በጸጋ ድነናል:: ህይወታችን በጽድቅ ፍሬዎች ማለትም የጽድቅ
ሥራዎች መሞላት ያለበት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ኢየሱስ በ(ዮሐንስ 15:5)
ላይ እንዲህ አለ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ . .
.”። እኛ ፍሬ የምናፈራ የግንዱ አካል ነን እናም የጽድቅ ፍሬ እናፈራለን::
በምንሄድበት በየትኛውም ስፍራ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍሬ እንገልጣለን፤
ጽድቅ በእኛ ውስጥ እየሰራ ነው::
ተመልከቱ፥ በከባድ ተፅእኖ ጊዜ ወጥቶ የሚታየው የተሞላችሁትን
ነገር ነው:: በሌላ አባባል መስጠት የምትችሉት በውስጣችሁ ያለውን ነገር
ነው:: በጽድቅ ፍሬ ተሞልተናልና ጽድቅን እናሳያለን፥ በጽድቅ እንመላለሳለን
እናም የጽድቅን ሥራ እንሰራለን::
ኢየሱስ የዓይነ ስውር ሲያበራ፥ ደንቆሮውን ነፃ ሲያወጣ፥ መራመድ
ለማይችል አዲስ እግሮችን ሲሰጥ፥ የሞተን ሲያስነሳ፥ የተራበን ሲመግብ፥
የተጎዱትን ሲያጽናና፥ ስዎችን ለማበረታታተና ለመባረክ መለኮታዊ ቃላትን
amharic
ሲናገር እርሱ የጽድቅን ፍሬ እያሳየ ነበር:: እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ
በዚህ ዓለም ነንና (1ኛ ዮሐንስ 4:17)።
እናንተ የጽድቅ ዛፍ ናችሁ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ እንድታፈሩ እና ውጤታማ
እንድትሆኑ ተሹማችኋል፤ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታሳዩ ተሾማችኋል::
እኛ የእርሱ ፍጥረት ነን፤ መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ
ተፈጠርን (ኤፌሶን 2:10)።

ጸሎት
ውድ የሰማይ አባት ሆይ፥ ለእኔ ስለተገለጠው
ቃልህ እና በመንፈሴ ውስጥ ቃልህ እየሰራ ስለሆነ
አመሰግንሃለሁ:: በጽድቅ ፈሬ ተሞልቻለሁ፤
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ስለዚህ ልክ ኢየሱስ እንዳደርገው እንዲሁ
ዱስ ጥናት
ለአለሜ ጽድቅን እገልጣለሁ፤ ምክንያቱም
እርሱ እንዳለ እኔ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም 2 ኛ ቆሮንጦስ 8-9
ነኝና:: ሀሌሉያ! መጽሀፈ ምሳሌ 24-26

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
22:1-13
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 28

ለተጨማሪ ጥናት:
2 ኛ ቆሮንጦስ 5:21; ፈልጵሱዮስ 2:13; 2 ኛ ቆሮንጦስ 9:10
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
እሁድ

10
በእግዚአብሔር የጦር ዕቃ ሁሉ ያጌጠ

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት


ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት
መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ (ኤፌሶን 6:12)።

የ መክፈቻ ጥቅሳችን መጋደላችን ከሰብአዊ አካል ካላቸው ጠላቶች


ሳይሆን ከመንፈሳዊ ኃይሎች ጋር እንደሆነ በግልጽ ያሳየናል::
ሰዎች ጠላቶቻችሁ አይደሉም:: በሰዎች ውስጥ ያያችሁት የትኛውም የክፋት
ድርጊት ቢሆን በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እንደተገለጸው ያ በእርግጥ የሆነው
ከጨለማ መንፈሳውያን ሠራዊት: ከአለቆች፥ ከሥልጣናት፥ ከጨለማ
ዓለም ገዦች፥ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት የተነሳ ነው:: በአካባቢያችን
ለምናየው እና ለሚያጋጥመን የተለያ ደረጃ ያለው ክፋት እና ሰይጣናዊ ስራ
ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው::
እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክና አምሳል በመፍጠሩ
እንደምትመለከቱት ሰው በራሱ ክፉ አይደለም:: እርሱን እንዲመስል እና
እንደ እርሱ እንዲያደርግ እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ (ዘፍጥረት 1:26) ነገር
ግን ዳግም ያልተወለደን ሰው ከርቀት የሚቆጣጠር እና ክፉ እንዲያስብ፥
እንዲናገር እና እንዲያደርግ የሚያደርገው አንድ ነገር አለ (ኤፌሶን 2:2)::
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛ ግን አንደናቀፍም:: ከእነዚህ ክፉ
መናፍስት ጫና በሚመጣባችሁ ጊዜ አትረበሹ! የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ
ሙሉ በሙሉ እስከታጠቃችሁ ድረስ ከክፉው በድንገት የሚላኩ ድንገተኛ
ጭካኔ የተሞላባቸውና አረመኔያዊ ከባድ ጥቃቶችን እና ተቃውሞዎችን
ለማጥፋትና ለመቃወም ትችላላችሁ፤እንዲሁም በክፉው ቀን ጸንታችሁ
ትቆማላችሁ::
ሰይጣን እና አጋንንቱ ለክርስቲያኖች ምንም ስጋት አይደሉም::
በስልጣናት፥ በኃያላን፥ በዚህ ዓለም ባሉ የጨለማ ገዦች እና በሰማያዊም
ስፍራ ባሉ በክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ላይ የበላይነት እና ሥልጣን
አላችሁ:: እነርሱን ለማቆም እንድትችሉ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር
መሳሪያ ሰጥቷችኋል (ኤፌሶን 6:13-19አንብቡ)::
amharic
ቃሉን በተግባር ላይ አውሉ:: የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ አንዳንዴ
ሳይሆን ሁል ጊዜ በመልበስ በጠላት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጁ፤
ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም
ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁን ተጫምታችሁ ጸንታችሁ ቁሙ፥
የማትናወጡ ሁኑ:: የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም
የእግዚአብሔር ቃል ነው። የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ
እንድትለዩ የእምነትን ጋሻ አንሡ:: በሁሉም ጊዜና ሁኔታ እና በሁሉም
ዓይነት ጸሎቶች እና ጥያቄዎች በመንፈስ ጸልዩ:: ሀሌሉያ!

የእምነት አዋጅ
የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ በሙሉ
ታጥቄያለሁ፤ በጌታ እና በኃይሉ ችሎት
ጠንክሬያለሁ:: እምነቴ ከክፉ የሚወረወርን
ፍላጻ የምከላከልበት ፣ በጠላትና በመከራዎች የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ላይ ተቃውሞ የማደርግበት እና አሸናፊ
የሚያደርገኝ መሣሪያ ነው:: በክርስቶስ ለዘላለም 2 ኛ ቆሮንጦስ 10:1-18
አሸናፊ ነኝ:: እግዚአብሔር ይባረክ! መጽሀፈ ምሳሌ 27-28

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
22:14-23
መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
29

ለተጨማሪ ጥናት:
ኤፌሶን 6:13-17
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሰኞ

11
በየቀኑ አምልኩት
“የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል
ነውና። ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ። መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም
ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤” (ዕብራውያን10:4-5)።

የ ዘጸአት መጽሐፍን ምዕራፍ ሀያ ዘጠኝ እሰከ ሰላሳ ስታጠኑ


ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች የተወሰኑ ትእዛዛትን
እንደሰጣቸውና የሐጢያት መስዋዕትንና የሚቃጠል መስዋዕትን እንዲሁም
እጣንን ያቀርቡ ዘንድ እንደ ጠየቃቸው ትመለከታላችሁ ፡፡ እነኚህም ዕለት
ዕለት እንዲደረጉ ነበር፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር በሚቀርቡት የእንስሳት መስዋዕትና መባ
አልተደሰተም፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ መስዋዕትን ማለትም ክርስቶስ
ኢየሱስን ፈልገ፡፡
በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ የሐጢያታችን መስዕዋት ሆነልን፡፡ ኢየሱስ
ለዘላለም እንደ አንድ መስዋዕት ስለእኛ ቀረበ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ እኛ
ለእግዚአብሔር የእንስሳት መስዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገንም፡፡ ዕብ 10፡
14 እንዲህ ይላል “አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን
አድርጎአቸዋልና።” እርሱ ፍጹም መስዋዕት ብቻ አልነበረም፣ መስዋዕትነቱ
እኛንም ፍፁማን አደረገን፡፡
መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙር 141፡2 ይህንን ለመረዳት የሚጠቅም
አንድ ድንቅ ነገር ይነግረናል፡፡ እንዲህ አለ “ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን
ተቀበልልኝ፥ እጅ መንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።” እንደ ነብይ
ስለ ወደፊቱና ከክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በኋላ ስለሚመጣው አዲስ
ቃል ኪዳን መገለጥ ነበረው፡፡
አሮጌው ቃል ኪዳን ሊነሳና ሊለወጥ ነበር፡፡ ታድያ ለእግዚአብሔር
ሳይቋረጥ ይሰዋ የነበረውን እጣንና ለካህናት በጠዋትና በማታ እንዲሰዉ
ያዘዛቸውን መስዋዕት ምን ሊተካው ነው?
ምላሹም የአምልኮ ጸሎታችንና እጃችንን ማንሳት ነው! እግዚአብሔር
ይሄ የሚቀጥልና የማያቋርጥ መሆን እንዳለበት ይነግረናል፡፡ እጃችንን
amharic
አንስተን ሁል ጊዜ የምናመልከው ለዚህ ነው፡፡ ሁልጊዜ ጌታችሁን በተለይ
በመንፈስ ሆናችሁ ማለትም በልሳኖቻችሁ ስታመልኩት ፀሎታችሁ እንደ
እጣን ወደ እርሱ ይሄዳል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “የዕጣኑም ጢስ
ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ። (ራእይ
8:4)
እጆቻችሁን ወደ እርሱ አንስታችሁ እየባረካችሁት በስሙ አዋጆችን
ስታውጁ ይህ እንደ ምሽት መስዋዕት ነው፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ
መልካም መዓዛ ያለው መባና መስዋዕት ነው፡፡

ጸሎት
ወድ አባት ሆይ፣ አንተ ብቻ አምላክ ነህ
ግርማዊነትሀን እባርካለሁ አምግስማለሁ፡፡
አምልኮ፣ ክብር፣ አድናቆት፣ ታላቅነት፣ ውበትና
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ፀጋን ሁሉ ላንተ ይገባሃል፡፡ባርኮት፣ ክብር፣
ዱስ ጥናት
ጥበብ፣ ምስጋና፣አክብሮት ኃይልና ብቃት
ለአንተ ከዘላለም እስከዘላለም ይሁን አሜን ፡፡ 2 ኛ ቆሮንጦስ
11:1-15
መጽሀፈ ምሳሌ 29-31

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል 22:24-
34
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 30

ለተጨማሪ ጥናት:
መዝሙረ ዳዊት 134:1-2; የዮሐንስ ራዕይ 7:11-12; ዕብራውያን 13:15
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ማክሰኞ

12
ጽኑ መሰረት የሆነው ቃሉ

ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥


እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
(1ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:11)።

መ ጽሐፍ ቅዱስ ጴጥሮስ መልካም በሚሏት መቅደስ ደጅ


አንድ አንካሳ ሰው እንደ ፈወሰ ይነግረናል፡፡ ምንም እንኳን
ከመወለዱ ጀምሮ በዛ ሁኔታ ውሰጥ ቢሆንም ጴጥሮስ ቃሉ እንደሚለውጠው
ያውቅ ነበር፤ በኢየሱስ ስምም ሲያዘው ሰውዬው ሙሉ በሙሉ ተፈወሰ
(ሐዋ 3፡1-8)፡፡ ቃሉ ከልጅነት ጀምሮ አንካሳ የነበረን ሰው ሕይወት ከለወጠ
ማንኛዉንም ሰው ይለውጣል፡፡
የ እግዚአብሔር ቃል የታመመን የሚፈውስ፣ ሐጢያተኛውን
የሚቀድስ፣ እንዲሁም በውድቀት ውስጥ ያለን ስኬታማ የማድረግ ብቃት
አለው፣ ቃሉን እመኑት፡፡ ቃሉን በሕይወችሁ ተግብሩት፡፡ በቃሉ መሠረት
ስትኖሩ ሕይወታችሁን በጽኑ መሠረት ላይ እየገነባችሁ ነው፡፡
ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ ምዕራፍ ሰባት ስለዚህ ነገር አንስቶ ይናገራል፡
፡ ስለ አንድ ቃሉን ሰምቶ ስላመነና እንዲሁም በሕይወቱ ቃሉን ተግባር ላይ
ስላዋለ ሰው ይናገራል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ይህንን ሰው ቤቱን በጠንካራ ዐለት
ማለትም በጽኑ መሠረት ላይ ከሰራ ሰው ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በሕይወት
ውስጥ የሚመጣ ቀውስ መከራና ጫና በቤቱ ላይ በኃይል ቢመጣበትም
ቤቱ ግን አልወደቀም፡፡
በሁለተኛ ደረጃ፣ ቃሉን ሰምተው በስራ ላይ የማያውሉትን ደግሞ ጌታ
ኢየሱስ ቤቱን በአሸዋ ላይ ከሰራ ሰው ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡ ንፋሱ ነፈሰ፣
ማዕበሉም ነፈሰ ያንን ቤት መታው ወደቀም፡፡ (የማቴዎስ 7:26-27)
ብዙ ሰዎች በቃሉ መርህ ስለማይመሩ እምነታቸው ይፈተናል::
ብዙዎች ሕይወታቸውን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሳይሆን በሰዎች ግምትና
ጽነሰ-ሃሳቦች ላይ መስርተዋል፡፡ መሰረታችሁ የእግዚአብሔር ቃል መሆን
አለበት፡፡ (ማር 13፡31)
amharic
እንደዚህች አለምና በውስጧ እንደያዘችው ሳይሆን በእግዚአብሔር
ቃል ላይ መታመን ትችላላችሁ፡፡ ቃሉ የማይሻርና፣ የማይለወጥና ዘላለማዊ
ነው፡፡ ሕይወታችሁን በየጊዜው በሚቀያይረው በሰው ፍልስፍና ላይ ሳይሆን
በእግዚአብሔር ቃል ላይ ገንቡ፡፡

ጸሎት
ወደ አባት ሆይ አስተማማኝና ጽኑ ስለሆነው
ቃልህ አመሰግነሃለሁ፡፡ በቃልህ ላይ ተተክዬ
ሳልናወጥ በጥንካሬ ተማምኜ እደገፋለሁ፡
፡ ፍጹም ታማኝ አስተማማኝና እውነተኛ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ስለሆነ፣ ቃልህ የተደገፍኩበት አለቴ ነው፡፡
2 ኛ ቆሮንጦስ
በቃልህ ውስጥና በቃልህ በኩል ስላለኝ የድል
11:16-33
ሕይወት ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ ፤በኢየሱስ
መጽሀፈ መክብብ 1-2
ስም፡፡ አሜን፡፡

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
22:35-43
መጽሀፈ ሳሙኤል
ቀዳማዊ 31

ለተጨማሪ ጥናት:
የሐዋርያት ስራ 20:32; የማቴዎስ ወንጌል 7:24-27
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ረቡዕ

13
ከተፈጥሮ በላይ የሆነው በውስጣችሁ ያለ ሕይወት

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ


ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ
(ዮሐንስ ወንጌል 10:10)።

በ እርግጥ የመግቢያ ጥቅሳችን የሚመለከተው ስለስጋዊ ሕይወት


ሊሆን እንደማይችል እንረዳለን፤ምክንያቱም ኢየሱስ እነኛን
የሚያነቃቁ ቃላትን ይናግራቸው የነበሩት ሰዎች ቀድሞውኑም በስጋ
በሕይወት ነበሩ፡፡ ይልቁንም እርሱ ስለ መለኮታዊ ሕይወት ማለትም ስለ
እግዚአብሔር አይነት ሕይወት እየተናገረ ነበር ፡፡ በኪንግ ጀምስ የመጽሐፍ
ቅዱስ ትርጉም “እንዲበዛላችሁ” የሚለው ቃል ብዙም ግልጽ አይደለም፤
ትክክለኛው የግሪክ ትርጓሜ “በሙላት” የሚለው ቃል ነው፡፡ እንደዚህ
ነው እርሱ ያለው “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው በሙላት እንዲኖራቸው
መጣሁ”፡፡
ኢየሱስ በምድር ሲመላለስ ከእግዚአብሔር ሕይወት አላስፈለገውም
ነበር፤ እርሱ እራሱ የሕይወት ምልዐት ነበር!፡ ዮሐ 1፡4 እንዲህ ይላል
“በእርሱ ሕይወት ነበረች…”፡፡ በዮሐንስ መልዕክት 1፡2 ሐዋሪያው ዮሐንስ
እርሱ የሕይወት መገለጥና ሁለንተና እንደሆነ ያስረዳል፡፡(”ሕይወትም
ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም
የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤” ) :: በዮሐንስ 5፡26
ላይ ኢየሱስ እራሱ እንዲህ ሲል አረጋግጧል “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው
እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።”
አሁን ለምን ኢየሱስ ያንን ሕይወት በሙላት ወደ እርሱ ለሚመጣ
ማንም ሰው መስጠት እንደቻለ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ
በዮሐ 5፡12 ልጁ ያለው ይህ ሕይወት አለው፤ ይላል፡፡ ዳግም ከተወለዳችሁ
ከመጀመሪያው አዳም ሳይሆን ከሁለተኛውና ከመጨረሻው አዳም ማለትም
ከኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዳችኋል፡፡ መለኮታዊው ማለትም ዘላለማዊ
ሕይወት በመንፈሳችሁ ውስጥ አለ፡፡ ይህ ሕይወት ኖሯችሁ በኤች አይ
amharic
ቪ ልትያዙ ወይም በካንሰር ሰውነታችሁ ሊጠቃ አይችልም! ይህ ሕይወት
ከ “ስትሮክና” ከስኳር በሽታ ጋር አብሮ ሊኖር አይችልም፡፡ ጨለማን
ይቃወማል፤እናም በሽታንና ህመምን ያጠፋል፡፡
የብዙዎች ችግር የእግዚአብሔርን ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ሕይወት
እንዳላቸው አለማወቃቸው ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በዮሐንስ ውስጥ
ሆኖ ሲጽፍ መለኮታዊነታችሁን እወቁ ብሎ ያስጠነቀቀው በዚህ ምክንያት
ነው፤ዘላለማዊ ህይወት ማለትም የእግዚአብሔር ሕይወት በእናንተ ውስጥ
እንዳለ እወቁ:: “የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር
ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።” (1ኛ ዮሐ 5፡13)
እናንተ ተራ አይደላችሁም፡፡ በእናንተ ያለው ሕይወት ከሕመም፣
ከበሽታ ወይም ከአሉታዊ የሕይወት ኃይላት በላይና የማይጠፋ ነው፡፡
በየቀኑ በዚህ መረዳት ኑሩ፡፡

ጸሎት
ወድ አባት ሆይ የላቀ የክብር፣ የጽድቅ፣ የድል፣
የስኬት፣ የብልጽግና እና የጤና ሕይወት
በክርስቶስ ኢየሱስ ስላለኝ አመሰግናለሁ፡፡ ይህ
ሕይወት የበላይነትና የመግዛት ነው፡፡ በዚህ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ዓለም ካሉ ገደቦች በላይ እየበረርኩ፣ በክርስቶስ
ያለኝን መለኮታዊ ምንጭና ሕይወት በመረዳት 2 ኛ ቆሮንጦስ 12:1-21
አመላለሳለሁ፤በኢየሱስ ስም ፡፡ አሜን፡፡ መጽሀፈ መክብብ 3-5

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
22:44-53
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
1

ለተጨማሪ ጥናት:
1 የዮሐንስ ወንጌል 5:11-12; ሮሜ 8:11; 1 የዮሐንስ ወንጌል 4:4
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሐሙስ

14
የላቀ ሕይወት
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና
እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥
በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
(2ኛ የጴጥሮስ 1:3)።

እ ግዚአብሔር ወደ ከበረና የላቀ ሕይወት ጠርቷችኋል፡፡ ገና


ሊያደርገው እየሞከረ ሳይሆን አስቀድሞ አድርጎታል፡፡ ይህ
የተስፋ ቃል አይደለም፡፡ ከላይ ባለው ጥቅስ ላይ “በጎነት” ማለት ልቀት
ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ወደ ሐፍረት፣ ሕመም፣ በሽታ፣ ዘለፋ፣ጥፋት
ወይም ፍርድ አልጠራንም፡፡ እርሱ የጠራን ወደ ክብርና ልቀት ነው፡፡ ስለዚህ
ምላሻችሁ መሆን የሚገባው “የተባረክህ አባት ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔ
በክብር የተሞላሁና የላቅሁኝ ነኝ! የላቁ ነገሮችን እሰራለሁ፡፡”
ምናልባት ወደ ሐፍረት ጎዳና እየተጓዛችሁ ይሆናል፤ አሁን
በመንፈሳችሁ ውስጥ የአሰራር ለውጥ እየተካሄደ ነው፡፡ ቃሉ ከሐፍረት
ወደ ክብርና ልቀት ያከንፋችኋል፡፡ ማንነታችሁን በማወቅ ተመላለሱ፡
፡ በውስጣችሁ የላቁ ነገሮችን ለማድረግ የመነሳት፣ የማደግና የመበልጸግ
መለኮታዊ ችሎታ ማለትም የእግዚአብሔር ኃይል አላችሁ፡፡ እርሱ ልቀትን
እንድታንቆረቁሩ ሾሟችኋል፣ስፍራ አስይዟችኋል ፤ ለመላቅ ከዚህ በኋላ
መፍጨርጨር አያስፈልጋችሁም፡፡
ሕይወታችሁን ከክብር ወደ ክብር የመለወጥ እና አእምሯችሁ ልቀትን
እንዲያፈራ የመምራት ግዴታ አለባችሁ፡፡ የአእምሯችሁ መታደስ ማለት ይህ
ነው፡፡ (ሮሜ 12፡1-2) እግዚአብሔር ይህንን ከእናንተ ይጠብቃል፤ምክንያቱም
በውስጣችሁ ችሎታውን አስቀምጧል፡፡ በእናንተ ስኬትና መሻሻል እንዲሁም
በስብእናችሁ ልቀት እርሱ ሊከብር ይፈልጋል፡፡

amharic
ጸሎት
ወድ አባት ሆይ ሕይወቴን የተዋበና በሁሉም
ነገር የላቀ ስላደረግከው አመሰግንሃለሁ፡፡
በውስጤ ከሚሰራው ቃልህ የተነሳ ባገኘሁት
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ስኬትና መሻሻል አንተ ዛሬ በእኔ ውስጥና
ዱስ ጥናት
በእኔ በኩል ከብረሃል፡፡ የፅድቅህ ተምሳሌትና
2 ኛ ቆሮንጦስ
የክብርህ መገለጫ ስላደረግከኝ አመሰግንሃለሁ፤
13:1-14
በኢየሱስ ስም ፡፡ አሜን፡፡ መጽሀፈ መክብብ 6-8

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
22:54-62
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
2

ለተጨማሪ ጥናት:
መጽሀፈ ምሳሌ 4:18; 2 ኛ ጴጥሮስ 1:3 AMPC; የዮሐንስ ወንጌል 15:8
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
Te ¨h

Te ¨h

amharic
Te ¨h

Te ¨h
አርብ

15
የድል ሕይወት

ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን


ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። (1ኛ ቆሮንቶስ 15:57)፡፡

እ ግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት ሲያስነሳው እናንተም አብራችሁ


ተነስታችኋል፡፡ አሁን እናንተ ከእርሱ ጋር አብራችሁ
ተቀምጣችኋል “ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ
በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ…”
(ኤፌ 1፡ 21) ፡፡
በዚህ አለም ላይ እየሆኑ ያሉት ነገሮች ምንም ቢሆኑ ለውጥ
አያመጣም፤ እናንተ ስኬታማና ከአሸናፊዎች በላይ ናችሁ፡፡ እግዚአብሄር
ከበሽታ፣ ከህመም፣ ከውድቀትና ከሞት የበለጠ የድል ህይወት ማለትም
የሰላም፣ የብርታት፣ የጤናና የብልጽግና ሕይወት ሰጥቷችኋል፡፡
የእነዚህ እውነታዎች እውቀት ንግግራችሁን አረማመዳችሁንና
ድርጊቶቻችሁን በተጨባጭ ሊቀይረው ይገባል፡፡ እግዚአብሔርን ሰላም፣
አቅም፣ ጤናና ብልጽግና እንዲሰጣችሁ ወይም ስኬታማ አድርገኝ ብላችሁ
አትጠይቁት፡፡ እነኝህና ብዙ ሌሎችም ክርስቶስ በሰጣችሁ የከበረ ሕይወት
ውስጥ ተጠቃለዋል፡፡ ምሳሌዎችን እሰጣችኋለሁ፡፡
በመጀመሪያ፣ ጌታ ኢየሱስ በዮሐ 14፡27 ላይ እንዲህ አለ “ስላምን
እተውላችኋለሁ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ...”፤ ይህ ማለት እርሱ ራሱ
ሰላማችሁ ሆኗል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ፣ መዝሙር 27፡1 እንዲህ ይላል “…
እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው…” ሶስተኛ፣ እርሱ ጠንካራና
ጤናማ አድርጓችኋል:: ኢሳ 33፡24 እንዲህ ይላል “በጽዮን የሚቀመጥ
ታምሜያለሁ አይልም፡፡”
በተጨማሪም እርሱ ብልጽግናን ሰጥቷችኋል፡፡ 1ቆሮ3፡21 እንዲህ
ይላል “ስለዚህ ማንም በሰው አይመካ፡፡ ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና ፡፡” ከዚያ
ደግሞ ፊሊጲ 4፡19 እንዲህ ይነግረናል “አምላኬ እንደ ባለጠግነቱ መጠን
በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል፡፡” ይህም
amharic
ማለት ጌታ የሚያስፈልጋችሁን ስለሚያቀርብላችሁ በእናንተ ሕይወት ውስጥ
ማጣት አይኖርም፡፡ መዝ 1፡3 እናንተ በውሃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች
ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ ዛፍ ገልጿችኋል፡፡ የምትሰሩትን ሁሉ
ይከናወንላችኋል፡፡ እንዴት ያለ በረከት ነው!
አሁን ዳግም ተወልዳችኋልና የስኬት ቋጠሮ ናችሁ፡፡ ቦታችሁ
በእግዚአብሄር መንግስት፣ ከክርስቶስ ጋር በህይወት ውስጥ የምትገዙበት
የእግዚአብሄር ህይወት ግዛት ውስጥ ነው፡፡

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ በክርስቶስ ስላለኝ የከበረ
ሕይወት አመሰግናለሁ፤ በጽድቅ እየተመላለስኩ
በህመም፣በዳያቢሎስና በሕይወት አሉታዊ
ተጽእኖች ላይ በበላይነት ዛሬና ሁሌም የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
እራመዳለሁ፤በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን ፡፡
ገላትያ 1:1-24
መጽሀፈ መክብብ 9-12

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል 22:63-
71
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
3-4

ለተጨማሪ ጥናት:
ሮሜ 5:17; 2 ኛ ቆሮንጦስ 2:14
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ቅዳሜ

16
የእርሱ መስዋዕትነት ክብር

በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም


በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት
ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር፡፡ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ
በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር
እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር
መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ። (1ኛ ጴጥሮስ 1፡10-11)፡፡

የ ክርስቶስ ኢየሱስ መከራ መቀበል የእግዚአብሔር ትዕዛዝ


ሲሆን መከራን የመቀበሉ ውጤት ደግሞ ለእኛ ክብርን፣ድልንና
ስኬትንና ብልጽግናን ማምጣቱ ነዉ፡፡ ስለሆነም ኢየሱስ ያደረገላችሁን ነገር
ልታከብሩት ይገባል፤ የሞተው በከንቱ አይደለምና የእርሱ የምትክነት ሞት
ለሰው ልጅ በሐጢያትና በውጤቶቹ ላይ ድልን አጎናጽፎታል፡፡
በመስቀል ላይ በእናንተ ምትክ እንደ እግዚአብሔር መስዋዕት
ሆኖ ለሐጢያት ድልን ሰጥቷችኋዋል፡፡ አሁን እግዚአብሔር ያንን ድል
እንደታውጁት ብቻ ሳይሆን ዕለት ዕለት የእርሱ ሞት መከራና በክብር
ማረግ በሰጣችሁ ድል እንድትመላለሱ ይፈልጋል፡፡ ይህም ማለት የአልጋ
ቁራኛ ሆናችሁ ቢሆን አሁን ሰዓቱ የመነሳት ነው፤ ምክንያቱም የክርስቶስን
ሕይወት ተቀብላችኋልና፡፡
ድህነትንም በተመለከተ እንዲሁ ተመሳሳይ ነው፤ በእናንተ ላይ
ሊሰለጥን አይገባም ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ድህነትን በእናንተ ምትክ ወስዶ
ብልጽግናን ለእናንተ ሰጥቷችኋል፡፡ “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር
ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች
ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።” (2ቆሮ 8፡9) ከእዳ ፍጹም ነጻ ሆናችሁ
መኖር ትችላላችሁ፤ ምክንያቱም ጌታ እንደ ባለጸግነቱ መጠን በክርስቶስ
ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል፡፡
በ ዚህ መረዳት ተመላለሱ፤ ከዚህ አለም ተመርጣችሁ ለከበረ
ሕይወት ተለይታችኋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል እናንተ “ ከጨለማ
amharic
ወደ ሚደነቅ ብርሃን የጣራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ
ትውልድ የንጉስ ካህናት ቅዱስ ሕዝብ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ” (1ኛ
ጴጥ 2፡9)
የእግዚአብሔር ሕይወት እና ተፈጥሮ ያላችሁ ምርጥ ዘር ናችሁ::
መንገዳችሁ የድልና የስኬት ብቻ ይሆን ዘንድ እርሱ መድቦታል፡፡

ጸሎት
በክርስቶስ ለእኔ የሰጠኸኝን
የጤና፣የሰላም፣የብልጽግና፣የለውጥ፣የድልና
የስኬት ሕይወት እያያጣጣምኩኝ እንደ
ንጉስ ወደ ምነግስበትና የምገዛበት ህይወት የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ስላወጣኸኝ
ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ ገላትያ 2:1-21
አሜን፡፡ መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን
1-2

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
23:1-12
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
5-6

ለተጨማሪ ጥናት:
2 ኛ ቆሮንጦስ 5:21; ኤፌሶን 2:4-7; ሮሜ 6:4
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
እሁድ

17
በቃሉ አማካኝነት መንገሥ

በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና


የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል
በሕይወት ይነግሣሉ። (ሮሜ 5፤17)፡፡

ዛ ሬ ማድረግ የሚገባችሁ አንድ ጠቃሚ ነገር ቢኖር የመክፈቻ


ጥቅሳችንን የማንነታችሁ አካል እስከሚሆን ድረስ ማሰላሰል ነው፡
፡ የአምሊፋይድ ትርጉም የጥቅሱን የመጨረሻ ክፍል ውብ በሆነ መንገድ
አስቀምጦታል፡፡ ይህንን የጽድቅ ስጦታ የተቀበሉት ፣ እነርሱ በህይወት እንደ
ንጉሦች ይነግሳሉ፤ ይላል፡፡ ይህ የሚናገረው በምድር ላይ ስለ መንገሥ ማለትም
በምድር ላይ ንጉሣዊ ህይወትን ስለመኖር ነው፡፡
ራዕይ 5፡10 እንዲህ ይላል፡- “…ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና
ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ…” በመክብብ 8፤4
ላይ የተጠቀሰ አንድ ደማቅ የሆነ የንጉሥ ችሎታን እንመልከት፡፡ እንዲህ ይላል፡
-“የንጉሥ ቃል ኃይለኛ ነውና…” ፡፡ ንጉሦች በቃላት ይገዛሉ፡፡ እናንተ ንጉሦች
ስለሆናችሁ በቃል ግዙ፡፡ ፍርሃት እንዲሄድ ስታዙት፣ ይሄዳል! በማንኛውም
የበሽታ ዓይነት ተጠቅታችሁ ቢሆን፣ በስሙ ጠርታችሁ እንዲሄድ ብታዙት፣
ማቋረጥ ይገባዋል! በህይወት ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ነገር የመረዳት ችሎታ
አለው፤ እያንዳንዱ ነገር ንጉሡ ቃልን ሲያወጣ ለመለየት የሚያስችል በቂ ችሎታ
አለው፤እና ያ ንጉሥ እናንተ ናችሁ!
እናንተ ለምን በትክክል መናገር እንደሚገባችሁ እና እምነታችሁን
መቼም ቢሆን ሽባ ማድረግ እንደሌለባችሁ ማየት ቻላችሁ? በአካላችሁ
ውስጥ የማንኛውም ዓይነት ህመም ወይንም በሽታ ምልክቶች ቢሰማችሁ፣እጅ
አትስጡ! ቃሉን ብቻ ተናገሩና ለውጥን አምጡ! እያንዳንዱ የምትናገሩት ቃል
በመንፈሳዊው ግዛት ውስጥ ለውጦችን ለማምጣት ወጥቶ ይሄዳል፡፡
በ ዮሐንስ 6፡63 ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- “ሕይወትን የሚሰጥ
መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው
ሕይወትም ነው።” ፣ እናም እናንተ እንደ እርሱ ናችሁ(1ኛ ዮሐንስ 4፤17)፡፡ ባዶ
amharic
፣ከንቱ፣ውጤት አልባ እና የማይሰሩ ቃላትን መናገር እምቢ በሉ፡፡ ተራ ሰዎች
እንዳመጣላቸው ሊያወሩ ይችላሉ፤እናንተ ግን እንደዚያ አይደላችሁም! እናንተ
መንፈሳዊ ሰዎች ናችሁ፤ቃላቶቻችሁ የመፍጠር ኃይል አላቸው፡፡
የበላይነት ሥፍራችሁን ያዙና፣ በቃላቶች አማካይነት በሁኔታዎች ላይ
በኢየሱስ ስም ንገሡ፡፡ በኢየሱስ ስም እያንዳንዱ ማዕበል ጸጥ እንዲል እዘዙት፡
፡ ዝቅተኛ ህይወትን እምቢ በሉ፡፡ ንጉሥ እንደ መሆናችሁ መጠን በቃሎች
አማካይነት በህይወት ውስጥ ንገሡና ግዙ፡፡

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፡- በመገኘትህ ውስጥ ድፍረትን
ስለሚሰጠኝ እና በህይወት እንደ ንጉሥ እንድገዛ
ስለሚያስችለኝ የጽድቅ ስጦታህ አመሰግናለሁ፡፡
እኔ በቤተሰቤ፣በጤናዬ፣በንግዴና በአገልግሎቴ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ለውጦችን የሚያመጡ ትክክለኛ ቃላቶችን
ብቻ እናገራለሁ፡፡ እኔ በጽድቅ እየተመላለስኩ፣ ገላትያ 3:1-14
የጽድቅ ስራዎችን አፈራለሁ፤በኢየሱስ ስም፡ መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን
3-5
፡ አሜን፡፡

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
23:13-25
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
7-8

ለተጨማሪ ጥናት:
የዮሐንስ ራዕይ 1:6; የማርቆስ ወንጌል 11:23; የማቴዎስ ወንጌል 12:37
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሰኞ

18
እናንተ የእግዚአብሄር ሕጋዊና ህያው ልጆች ናችሁ

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ


ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው
እኛን አያውቀንም። (1 ዮሃ 3፤1)፡፡

አ ንድ ክርስቲያን ህያውና ሕጋዊ የሆነ ማለትም እውነተኛ


የእግዚአብሄር ልጅ ነው፡፡ በ1ኛ ቆሮ 6፡20 ሐዋርያው ጳውሎስ
እንዲህ ሲል ገልጾታል፡- “በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤
ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” ይህ የመዳን ሕጋዊ ሁኔታ
ነው፤እናንተ በዋጋ ተገዝታችኋል፡፡ እናም አሁን እግዚአብሄር እኛን ወደ
እርሱ የማንነት ምድብ ውስጥ እንድንኖር በማምጣት፤እና እርሱ እራሱን
በእኛ ውስጥ በማፍሰስ፤ የእኛን ስጋዊ አካል የእርሱ የምስክርነት መኖርያ
እንዲሆን አድርጎታል፣ ማለትም የእርሱ ህያው ቤተ መቅደስ አድርጎታል፡
- “…ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው
የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?።” (1ኛ ቆሮ 6፡20)፡
፡ ይህ የመዳን ሕያው አሰራር ነው፡፡ ሕጋዊ የሆነው ሁኔታ የእግዚአብሄር-
ሕይወት የሆነውን ህያው ልምምድ የሚቻል አድርጎታል!
ይህ ከእኛ ጽድቅ ጋር የሚመሳሰል ነው፣አንዳንዶች አሁንም እኛ ሕጋዊ
ጽድቅ ብቻ እንዳለን አድርገው ያስባሉ፤አይደለም፣ እኛ ህያው የሆነም ጽድቅ
አለን፡፡ እግዚአብሄር የእርሱን ጽድቅ ሰጥቶናል፤እናም አሁን፣ እናንተ ካለ
ምንም የጥፋተንነት ፣የክስና የዝቅተኝነት ስሜት በእርሱ መገኘት ውስጥ
የመቆም ችሎታ አላችሁ፡፡ በ1ኛ ዮሐ 3፡1-2 ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ ሲል
ጮዃል፡- “የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን
ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥…” ይህ የተስፋም ሆነ የትንቢት ቃል አይደለም፡፡
ይህ እውን የሆነ፣የአሁኑ ሰዓት እውነት ነው፡፡
ህያው የሆነው የልጅነታችን ሁኔታ ማለት እናንተ ዳግም በተወለዳችሁ
ጊዜ፣እናንተ የተወለዳችሁት ከእግዚአብሄር መንፈስ በመሆኑ ነው፡፡ 1ኛ
ጴጥሮስ 1፤23 እንዲህ ይላል፡- “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር
አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ
amharic
ዘር ነው እንጂ።” አሁን እናንተ የእግዚአብሄር ሕይወት በውስጣችሁ
አለ፤ተራ ሰው መሆናችሁ አብቅቷል፤ከተፈጥሮ በላይ የሆነን ሕይወት
ትኖራላችሁ፡፡
ሐዋርያው ዮሐንስ፣ ጉዲ ፈቻን ወይንም የልጅነትን ደረጃ ማለትም
ስልጣንን እንዴት መያዝ እንደሚቻል የሠለጠነን አንድ ሰው ከሚያስረዳው
“ሁዮቴዝያ” ከሚለው የግሪክ ቃል ይልቅ፣ እኛ የእግዚአብሄር ህያው ልጆች
እንደሆንን ለማስረዳት ሲል ቃሉን በጥንቃቄ መርጦ “ቴክኖን” የሚለውን
ቃል ተጠቅሟል፤እኛ ከእግዚአብሄር ተወልደናል፡፡ እኛ አሁን የእግዚአብሄር
ልጆች ነን፤ነገ ወይም አንድ ባልታወቀ ቀን ፣ ወይም መንግስተ ሰማያት ስንገባ
ሳይሆን አሁን ልጆች ነን፤ይህ እናንተ ዳግም በተወለዳችሁ ጊዜ ወድያውኑ
ሆኗል፡፡ ገላትያ 4፤6 እንዲህ ይላል፡-“ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር
አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።”

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፡- የዘላለም ህይወትን ህያው
ልምምድ እውን እንዲሆን ስላደረገው የመዳን
ሕጋዊ አሰራር እኔ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ እኔን
የመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋይ፣ ከእግዚአብሄር የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ዓይነቶች ጋር ተባባሪ አድርገኸኛል፡፡
እኔ በህይወት የተሞላሁ ነኝ፤ እናም እኔ ገላትያ 3:15-25
ለአንተ ክብርና ምስጋና በድል አድራጊነት መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን
እኖራለሁ፤በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡ 6-8

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
23:26-33
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
9-10

ለተጨማሪ ጥናት:
1 የዮሐንስ ወንጌል 3:1-2 CEV; የዮሐንስ ወንጌል 1:12-13
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ማክሰኞ

19
እራሳችሁን በከፍተኛው የእምነት ደረጃችሁ ላይ
ማጽናት
እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ
ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
(ይሁዳ 1፡20)፡፡

ሐ ዋርያው ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 14፤4 ላይ “በልሳን የሚናገር


ራሱን ያንጻል፤…” ብሎ በተናገረው እና ከላይ በተጠቀሰው
ጥቅስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ በ1ኛ ቆሮ 1፡14 ላይ
የተጻፈው “ያንጻል” የሚለው ቃል ትርጉሙ ራሳችሁን ማነጽ ማለት ሲሆን
በተጨማሪም ራሳችሁን በኃይል መሙላት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ይሁዳ
“ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ
በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥” ሲል እየተናገረ ያለው ከመሰረት በላይ
ያለውን የህንጻ አካል ከማነጽ ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡
“ማነጽ” ተብሎ የተተረጎመው “ኢፒዪኮዶሚዮ” የሚለው የግሪክ
ቃል ነው፤ትርጉሙም በአንድ ቀድሞ በነበረ ነገር ላይ ማነጽ ማለት ነው፡
፡ ስለዚህ ይሁዳ በመንፈስ ቅዱስ እየተናገረ ያለው በአንድ ቀድሞ በነበረ
ነገር ላይ ማነጽን ነው፡፡ ስለዚህ እርሱ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን
እንድታንጹ ብሎ መናገሩ የተቀደሰው ሃይማኖታችሁ ብሎ የጠቀሰው
ቀድሞውንም የነበረ ነገር መሆኑን ነው፡፡
ያ “የተቀደሰ ሃይማኖታችሁ” የተባለው የሚመለከተው የእናንተን
ከፍተኛውን እምነት፣ የእናንተን የተቀደሰ እምነት፣በማንኛውም ጊዜ እናንተ
የደረሳችሁበት ከፍተኛው የእምነት ደረጃ ማለት ነው፡፡ ይሁዳ በልሳን
በመናገር በዛ በደረሳችሁበት ከፍተኛ የእምነት ደረጃ ላይ እንድታንጹ
ይናገራል፤ከዚያ ደረጃችሁ በታች አትሁኑ፡፡ እንደምታውቁት ከጊዜ ወደ
ጊዜ የተለያዩ የእምነት ደረጃዎችን እንለማመዳለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ እጅግ
ከፍተኛ ደረጃ ያለውን እምነት እንለማመዳለን፤በሌላ ጊዜ ደግሞ እምነታችን
ከተለመደው በጥቂቱ ያነሰ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

amharic
ነገር ግን በተደጋጋሚ በልሳን በመናገር በደረሳችሁበት ከፍተኛ
የእምነት ደረጃ ላይ ራሳችሁን ታንጻላችሁ፤ ከዚያም፣ ያ ደረጃ የማጣቀሻ
ምልክታችሁ ይሆናል፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ያ ከፍተኛው የእምነት ደረጃችሁ
ዝቅተኛው የእምነት ደረጃችሁ ይሆናል፡፡ ከዚያም ከደረሳችሁበት ደረጃ ላይ
ሆናችሁ ወደ ሌላ ከፍተኛ የእምነት ደረጃ ለመድረስ ትሰራላችሁ፤እናም
እንዲያ እያደረጋችሁ ማነጻችሁን ትቀጥላላችሁ፡፡
በልሳን መናገር ላይ የምናተኩርበት አንደኛው ምክንያት ይህ ነው፡
፡ እናንተ የእግዚአብሄርን ቃል ስትቀበሉ፣እምነታችሁ ወደ ከፍተኛ ደረጃ
ይደርሳል፤ነገር ግን በዚያም ላይ ማነጽ አለባችሁ፤በልሳን በመጸለይ በዛ
በደረሳችሁበት ከፍተኛ የእምነት ደረጃ ላይ ጸንታችሁ ትቆማላችሁ፡፡ በዚያ
ደረጃ ላይ ሆናችሁ ምንም ዓይነት መከራ፣ተግዳሮቶች እና ችግሮች እናንተን
አያስፈራችሁም፤ምክንያቱም ከእነርሱ በላይ ሆናችኋል፡፡ ይህንን አድርጉና
ህይወታችሁ ባልተለመደ አኳኋን ሲያድግ ተመልከቱ፡፡

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፡- ከፍተኛ በሆነው የእምነት
ደረጃዬ ላይ ራሴን ለማነጽ የሚያስለኝን ሰማያዊ
ቃላት የመጠቀም ልዩ መብት ስለሰጠኸኝ
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
አመሰግንሃለሁ፡፡ዓለም ን የሚያሸ ንፈው
ዱስ ጥናት
እምነቴ ነው! እናም በልሳን በመጸለይ
እንደሚበር ንሥር ወደ ከፍታ እወጣለሁ፤ ገላትያ
3:26-4:1-20
ከተግዳሮቶችና ከመከራዎች በላይ በድል ትንቢተ ኢሳያስ 1-2
እመጥቃለሁ፤በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
23:34-43
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
11-12

ለተጨማሪ ጥናት:
1 ኛ ቆሮንጦስ 14:2 & 4 AMPC; ሮሜ 10:17
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ረቡዕ

20
በከንፈራችሁ ላይ አኑሩት

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ


ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው የዚያን ጊዜም
መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። (ኢያሱ 1፡8)፡፡

የ ስኬትና የብልጽግና ዋነኛው መርሆ በመክፈቻ ጥቅሳችን ውስጥ


በግልጽ ተቀምጧል፡፡ይኸውም ቃሉን በከንፈራችሁ ላይ አኑሩት!
ይህም ማለት እናንተ ልትናገሩት ይገባል ማለት ነው፡፡ ቃሉ በልባችሁ መኖሩ
በቂ አይደለም፤ቃሉ ከአፋችሁ ሊወጣ ይገባዋል፡፡ በሉቃስ 6፡45 ጌታ ኢየሱስ
እንዲህ አለ፡-“በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ
መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ …” ፡፡ ቃሉ በልባችሁ ስለመኖሩ
ማስረጃ የሚሆነው ከአፋችሁ ሲወጣ ነው፡፡
በ ህይወት የሚያሸንፉት የሚናገሩ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው፡
፡ ይህንንም ስል ለፍላፊ ክርስቲያኖች ማለቴ ሳይሆን እነኛን ቃሉን
የሚናገሩትን ማለቴ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ሳታቋርጡ እየተናገራችሁ
ደካማ፣ድሃ፣ባዶ ኪሱን የሆነ፣በሽተኛ ወይንም ተሸናፊ ልትሆኑ አትችሉም፡
፡ ነገር ግን ጥንካሬን፣ድልን እና ጤናን ከተናገራችሁ እናንተ ሁልጊዜም ድል
አድራጊ ትሆናላችሁ፡፡ በማርቆስ 11፡23 ኢየሱስ የምትናገሩትን ታገኛላችሁ
ብሏል፡፡ የስኬት መንገድ ይህ ነው፡፡
እግዚአብሄር ስለስኬታችሁ ግድ ይለዋል፤ወደ ምድር ያመጣችሁም
ለስኬት ነው፡፡ ለስኬታማ፣ምንጊዜም አሸናፊ ለሆነ፣ንቁ ለሆነ እና ለተሻለ
ህይወት የእርሱን የአሰራር ዘዴ በድጋሚ አስተውሉ፤ “የዚህ ሕግ መጽሐፍ
ከአፍህ አይለይ፥ …”:: ቁልፉ አፋችሁ ነው፡፡
አፋችሁን በትክክለኛ መንገድ መጠቀም ማለትም የእግዚአብሄርን ቃል
መናገር ብትማሩ፣ ለእናንተ የማይቻል ነገር የለም፡፡ አንድ ሁኔታ ምንም ያህል
ተስፋ የሌለው መስሎ ቢታይም፣ በቃሉ ለውጥን ማምጣት ትችላላችሁ፡
፡ የእግዚአብሄር ቃል በከንፈራችሁ ላይ አኖራችሁ ማለት እግዚአብሄር
እየተናገረ ነው ማለት ነው፤የሚናገረውን እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፤
amharic
በውስጣችሁ ያለውን ፍርሃት እንዳይሰራ ሽባ ያደርገዋል፤ እናም ከስኬት
ወደ ስኬት እንድትዘሉ ያስችላችኋል፡፡

የእምነት አዋጅ
አንደበቴ ጤናማ በመሆኑ የሕይወት ዛፍ ነው!
በመንፈስ የተነሳሱ ጠንካራና ሕይወት ሰጪ
ቃላትን እናገራለሁ፡፡ እኔ በቃሉ ስለምኖር
በህይወት ስኬታማ ነኝ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
በልቤና በአፌ ውስጥ አለ፤ እናም ለዘላለም
አሸናፊ አድርጎኛል፡፡ ክብር ለእግዚአብሄር ገላትያ 4:21-5:1-15
ይሁን! ትንቢተ ኢሳያስ 3-5

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
23:44-56
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
13-14

ለተጨማሪ ጥናት:
1 ኛ ጢሞቴዎስ 4:15; መዝሙረ ዳዊት 1:1-3; የማርቆስ ወንጌል 11:23
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሐሙስ

21
የስሙ ስጦታ

እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ


የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ፡፡ ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ
እኔ አደርገዋለሁ፡፡ (ዮሐንስ 14:13-14)፡፡

ጌ ታ ኢየሱስ የስሙን ሀይል የመጠቀም ስልጣን ሰጥቶናል፡፡ ዛሬ ያ


ስም የእናንተ ነው፤ እናንተ የጌታ ኢየሱስን ስም የመጠቀም ህጋዊ
ስልጣን ተሰጥቷችኋል፡፡ በስሙ ማንኛውንም ነገር ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
ልክ ከማረጉ በፊት ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “. . . ሥልጣን ሁሉ
በሰማይና በምድር ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና
በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ
እያስተማራችኋቸው . . . “(ማቴዎስ 28፡18-19) በሰማይና በምድር ያለው
ስልጣን ሁሉ ለኢየሱስ ተሰጥቶታል፡፡ እያንዳንዱ በዚህ ዓለምና ከዚህ ዓለም
ባሻገር ያለ ነገር ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይገዛል፡፡
ዳግም ከተወለዳችሁበት ቀን አንስቶ በስማችሁ መኖር አቁማችኋል፤
የኢየሱስን ስም ወርሳችኋል፡፡ ስለዚህም በእርሱ ስልጣንና በእርሱ ባህሪይ
መንቀሳቀስ ይጠበቅባችኋል፡፡ ቃላቶቻችሁ ልክ እንደ ኢየሱስ ተመሳሳይ
ኃይልና ስልጣን አላቸው፡፡ ስሙ በሁሉም ቦታ ጉልበት አለው፡፡ ስሙ
በየትኛውም ቦታ ኃይል አለው፡፡ በመንግስታት፣ በአጋንንቶች፣ በስልጣናት
እና በኃይላት ላይ ኃይልት አለው፡፡ ይህንን ስም ተጠቀሙበት፡፡
ብዙ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ስም እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው
አያውቁም፤ በፀሎት መጨረሻ ላይ እንዲሁ የሚቀመጥ ስም ይመስላቸዋል፤
ከዚያ እጅግ የሚበልጥ ነገር ነው፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “. .
.አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ፡
፡ ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ፡፡” ( ዮሐንስ 14፡
13-14) ይህንን እየተናገረ ያለው ኢየሱስ ሲሆን እየተናገረ ያለው ስለ ፀሎት
አይደለም፤ ምክንያቱም ለኢየሱስ በኢየሱስ ስም መፀለይ አትችሉም፡፡ እርሱ
እየተናገረ ያለው ስሙን እንደ መሣሪያ በመጠቀም በስሙ ስለማዘዝ ነው፡፡
ጴጥሮስ መልካም በሚሉአት መቅደስ ደጅ ለሽባው ሰውዬ ያደረገው
ያንን ነው፤ “በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ” አለው፡
amharic
፡ ከዚያም ሽባውን ሰውዬ በቀኝ እጁ ይዞ አስነሣው፤ ቁርጭምጭሚቱም
ጸና፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም
ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር
ወደ መቅደስ ገባ።” (የሐዋርያት ሥራ 3፤8) ይህ አስደናቂ ነው! በሐዋርያት
ሥራ 3፤16 እና 4፡9-10፣ ጴጥሮስ ተአምሩ የተሰራው የኢየሱስን ስም እንደ
መሳሪያነት በመጠቀም እንደሆነ ገልጿል፡፡ እግዚአብሔር ይባረክ!
በማንኛውም ጊዜ ሊኖራችሁ ከሚችለው ዓይነት ስጦታ የበለጠ
ስጦታ ማለትም የኢየሱስ ስም ስጦታ አላችሁ፤ ፡፡ በየቀኑና በሁሉም ቦታ
ተጠቀሙበት፡፡ በስሙ አንድ ነገር እንዲሆን ስታዙ እርሱ ጉዳዩን ይዞታል፤
ያላችሁት ነገር መፈፀሙን ያረጋግጣል፤ ምክንያቱም እርሱ ኃይል አለው፡፡
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

ጸሎት
የተባረክህ የሰማይ አባት ሆይ፡ ስለ ኢየሱስ
ስም ስጦታና እንድጠቀምበትም ስለሰጠኸኝ
የውክልና ስልጣን አመሰግንሃለሁ፡፡ እጅግ ከፍ
አድርገህ ባከበርከውና ከስሞች ሁሉ በላይ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ባደረግከው ይህ ስም፡ በድል አድራጊነት
እየኖርኩ ከሕይወት ሁኔታዎችና ክስተቶች ገላትያ 5:16-26
በላይ ሆኜ እገዛለሁ፡፡ አሜን፡፡ ትንቢተ ኢሳያስ 6-8

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል 24:1-12
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
15-16

ለተጨማሪ ጥናት:
የሐዋርያት ስራ 4:12; ፈልጵሱዮስ 2:8-11; የማርቆስ ወንጌል 16:17
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
Te ¨h

Te ¨h

amharic
Te ¨h

Te ¨h
አርብ

22
የእግዚአብሔር ሕይወትና ተፈጥሮ

የኃጥያት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን


በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡ (ሮሜ 6፡23)፡፡

የ እግዚአብሔር ሕይወትና ተፈጥሮ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡


በክርስቶስ ኢየሱስ ያለን ከፍ ያለ ሕይወት ነው፡፡ በእርሱ ፅድቅ፣
ክብር እና ፀጋ እንኖርና እንመላለስ ዘንድ ፣ ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ ሰጠ፡
፡ ነገር ግን ሰው ምንም ያህል ቢጥር ዳግም ካልተወለደ በስተቀር የዘላለም
ሕይወት ሊኖረው አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚታገሉ ሰዎች
አሉ፤ በትክክል ለመኖር እየታገሉ ነው፥ ነገር ግን ያን ለማድረግ ምን
እውነተኛ ክርስትና ከመለኮት ጋር የሚደረግ ህብረት ነው፤ ሰብዓዊው
ሕይወታችሁን በእግዚአብሔር ሕይወትና ተፈጥሮ በመተካት ነው፡፡ የእርሱ
ሕይወት በውስጣችሁ እስካልኖረ ድረስ ልትኖሩት አትችሉም፡፡ ጌታ ኢየሱስ
የአይሁድ አለቃ የሆነውን ኒቆዲሞስን እንዲህ አለው፦ “. . . ሰው ከውኃና
ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም፡
፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡ ዳግመኛ
ልትወለዱ ያስፈልጋችኃል ስለልሁህ አታድንቅ፡፡” (ዮሐንስ 5፡ 3-7)፡፡ ዳግም
መወለድ ማለት ለእግዚአብሄር ህያው እንድትሆኑ፣ የክርስቶስን ሕይወት
በመንፈሳችሁ ውስጥ መካፈል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት የእግዚአብሔርን
አባትነት ወደምትቀበሉበት ንቃት መጥታችኋል፥ እርሱም በልባችሁ ውስጥ
መኖርያውን ያደርጋል፡፡
ይህ ታግላችሁ የምትደርሱበት ነገር አይደለም፤ ይህ የሚሆነው
ዳግም በተወለዳችሁበት ቅጽበት ነው፤ በዚያን ጊዜ በትክክል እንድትኖሩና
የፅድቅ ፍሬዎችን ማፍራት እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ሕይወትና
ተፈጥሮ በመንፈሳችሁ ተካፍላችኋል፡፡ የእርሱ ሕይወትና ተፈጥሮ
በውስጣችሁ ሲኖርና ስለመኖሩም መረዳት ሲኖራችሁ ፣ ሕይወታችሁ
የእግዚአብሔር መልካምነት፣ ክብር፣ ፀጋ እና ፍቅር መግለጫ ይሆናል፡፡

amharic
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለእኔ
እንዲሞት በመላክ ስለገለጽከው ለእኔ ያለህ
ታላቅ ፍቅር አመሰግናለሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ
የሕይወቴ ጌታ መሆኑን አውጃለሁ፤ ሕይወቱንና የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ተፈጥሮውን በመንፈሴ ተካፍያለሁ፡፡
የእግዚአብሔርን አባትነት ወደ መረዳት ገላትያ 6:1-18
ደርሻለሁ፤ በዓለሜም የእግዚአብሔርን ፅድቅ ትንቢተ ኢሳያስ 9-10
አሳያለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
24:13-27
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
17-18

ለተጨማሪ ጥናት:
1 የዮሐንስ ወንጌል 5:11-13; 2 ኛ ቆሮንጦስ 5:21
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ቅዳሜ

23
በውስጣችሁ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ሕይወት

ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጥያት ምክንያት የሞተ


ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው፡፡ (ሮሜ 8፡10)፡፡

ሐ ዋሪያው ጳውሎስ ከላይ በተጠቀሰው ጥቅስ ላይ ሮም ባሉ


ወንድሞች ውስጥ ክርስቶስ መኖር አለመኖሩን እየጠየቀ
አይደለም፤ ይልቁኑ አስፈላጊ ወደሆነ እውነታ አእምሮአቸውን እያነቃቃ
ነበር፡፡ ክርስቶስ በእነርሱ ውስጥ ህያው እውነታና፥ የጤናማና የተነቃቃ
ሕይወት ማስተማመኛ መሆኑን እንዲያውቁ ስለፈለገ ነው፡፡ ምንም እንኳን
አካላችሁ ደካማና ሕመምተኛ ቢሆን ፣ ክርስቶስ በውስጣችሁ ካለ እርሱ
ብርታትን ይሰጣችኋል ማለቱ ነው፡፡
የጳውሎስ ድምዳሜ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ካለ መታመም
የለባችሁም ፤ ምክንያቱም በዚያው ተመሳሳይ መንፈስ አካላችሁ ይበረታል
የሚለው ነው፡፡ “ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ
በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ
በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን
ይሰጠዋል፡፡” (ሮሜ 8፡11) ለሰውነታችሁ ሕይወትን መስጠት የሆነው
የመንፈስ ቅዱስ ስራ አሁን የሚሆን እንጂ የወደፊት ሁኔታ አይደለም፤
እኛ መንግሰተ ሰማያት ስንገባ የሚሆን ሳይሆን እርሱ አሁን በውስጣችሁ
ይሰራል! ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን!
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሀይል ነው፤ በውስጣችሁ የእርሱ
መገኘት ለዘላለም የሕመምንና የድካምን ነገር አስወግዷል፤ ምክንያቱም
በሰውነታችሁ ውስጥ ያለን ማንኛውንም ትክክል ያልሆነ ነገር ሁሉ
“ለማስተካከል” በእናንተ ውስጥ ይሰራል፤ ይመላለሳልም፡፡ የእርሱ
ሕይወት በውስጣችሁ መኖሩ የማትሸነፉ ያደርጋችኋል፡፡ ሞቶ የነበረውን
የኢየሱስን ሰውነት መልሶ ሕይወት የሰጠው እርሱ ነው፤ እና አሁንም
እርሱ በሙሉ ክብሩ፣ ሀይሉና ግርማው በእናንተ ውስጥ ይኖራል፡፡

amharic
ዛሬ ሰውነታችሁ በሕመምና በበሽታ ምንም ያህል የተጎዳና የተጎሳቀለ መሆኑ
ለውጥ አያመጣም፤ ለእናንተ የሚያስፈልጋችሁ ፈውስ ሰጪው ማለትም
መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ እንዳለ ማወቅ ነው፡፡ እርሱ በውስጣችሁ
መኖር ማለት ፥ እንደገና ተነስታችሁ የመራመዳችሁ ተስፋ እና በመለኮታዊ
ጤንነት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ መኖር ማለት ነው፡፡

የእምነት አዋጅ
ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው ያ መንፈስ በውስጤ
ይኖራል፥ ለሰውነቴ ሕይወትን፣ ጥንካሬንና
ጉልበትን ሰጥቶታል፡፡ እኔን በጤንነት፣
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
በፅድቅና በእግዚአብሔር ክብር ለማቆየት ዱስ ጥናት
በውስጤ በሚንሸራሸረው መንፈስ ቅዱስ ፣ እኔ
በየዕለቱ እመገባለሁ፣ እታደሳለሁ እናም እንገና ኤፌሶን 1:1-14
ወጣት እሆናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይባረክ! ትንቢተ ኢሳያስ 11-12

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
24:28-39
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
19-20

ለተጨማሪ ጥናት:
1 ኛ ጴጥሮስ 2:24; ሮሜ 8:10 AMPC
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
እሁድ

24
ለማዕበሉ ንገሩት

ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፥ ባህሩንም፦ ዝም በል፤ ፀጥ በል አለው፡፡


ነፋሱም ተወ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ፡፡
(ማርቆስ 4፡39)፡፡

እ ግዚአብሔር በሕይወት ጉዞ ፣ ረዳት አልባና ስንኩል እንደሆነ ሰው


እንድትመለለሱ አይፈልግም፡፡ ይልቁኑ ኃላፊነትን በመውሰድ
ስለ ሕይወታችሁና ስላላችሁበት ሁኔታ አንድ ነገር እንድታደርጉ ይፈልጋል፡
፡ በሕይወታችሁ ውስጥ ነገሮች እንዲከሰቱ ማድረግ ይገባችኋል፡፡
“ጌታ ሆይ፥ ያለሁበትን ሁኔታ አታይምን? አንድ ነገር አድርግ!”
እያላችሁ ትጮሁ ይሆናል፡፡ እንደዚህ አይደለም፥ አንድ ነገር ማድረግ
ያለባችሁ እናንተ ናችሁ፤ ምክንያቱም ኃይሉን ሰጥቷችኋል፡፡ ልክ እንደ
ኢየሱስ አድርጉ፡፡ እርሱ በቃላቶች ማዕበሉን ፀጥ አደረገ፡፡ እርሱ በሀይል
ይናወጥ የነበረውን ማዕበል፥ “ዝም በል፤ ፀጥ በል” አለው፤ ከዚያም ታላቅ
ፀጥታም ሆነ፡፡
ምናልባትም በአንድ ምክንያት ስለ አንድ ሁኔታ ተረብሻችሁና
ፈርታችሁ ሊሆን ይችላል፤ ማድረግ ያለባችሁ ነገር ቀላል ነው፡፡ ቀኝ
እጃችሁን ደረታችሁ ላይ አድርጋችሁ “በጌታ በኢየሱስ ስም ጸጥ በል” በሉ፤
ከዚያም የእርሱ ሰላም ነፍሳችሁን ያጥለቀልቃችኋል፡፡
ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ሲነሣና ውኃ በታንኳይቱ ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ
በጣም ፈርተው ነበር፡፡ ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “ስንጠፋ አይገድህምን?”
አሉት፡፡ ኢየሱስም መልሶ “እምነታችሁ ወዴት ነው?” አላቸው ፡፡ በሌላ
አነጋገር፥ “ለምንድን ነው እንዲህ የፈራችሁት? እኔ በዚህ አለሁ፤ እኔ
ሰላማችሁ ነኝ፡፡” አላቸው፡፡ እርሱ የእስራኤል ሰላም ስለሆነ እነርሱ
በጀልባቸው ውስጥ ሰላም ነበራቸው፤ ዛሬ ደግሞ እርሱ የእኛ ሰላም ነው፡

መፍራትን እምቢ በሉ፡፡ ሰላማችሁ ክርስቶስ ነው፤ እርሱም
በውስጣችሁ ይኖራል፡፡ እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ እርሱ
amharic
“የተገለጠው” የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ እናንተ ስትናገሩ፥ ኢየሱስ፥
ማለትም ቃሉ፥ ይገለጣል፡፡ ስለዚህ ምንም ዓይነት ማዕበል ፀጥ ማድረግ
ስትፈልጉ ደቀ መዛሙርቱ እንዳደረጉት “እርሱን ለመቀስቀስ” አትሞክሩ፤
ቃሉን ተናገሩ፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ “የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፡፡” ቢለን
የሚገርም አይደለም ፡፡ (ቆላስይስ 3፡16) ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “በእኔ
ብትኖሩ ቃላቶቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ …” (ዮሐንስ
15፡7)፡፡ የምትፈልጉት ምንድን ነው? አታጉረምርሙ፤ አትለምኑ፤ ቃሉን
ተናገሩ፡፡ ጠይቁና ተቀበሉ፡፡ ሀሌሉያ!

የእምነት አዋጅ
ውድ አባት ሆይ፦ በኢየሱስ ስላለኝ በረከትና
ስልጣን አመሰግንሃለሁ፡፡ ክርስቶስ የእኔ ሰላም
ነው፤ አሁን በሕይወቴ ላይ፣ በንግዴ ላይ፣
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
በቤተሰቤ ላይና እኔን በሚመለከቱ ነገሮች
ዱስ ጥናት
ሁሉ ላይ ሰላምን አውጃለሁ፡፡ እኔ በመንፈስ
ቅዱስ ክብርና ጸጥታ ተጥለቅልቅያለሁ፡፡ ኤፌሶን 1:15-2:1-10
መንገዴ ለዘላለም የስኬት፣ የደስታና የድል ትንቢተ ኢሳያስ 13-14
ነው፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የሉቃስ ወንጌል
24:40-53
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
21-22

ለተጨማሪ ጥናት:
የማርቆስ ወንጌል 9:23; መጽሀፈ ኢዮብ 22:28; መጽሀፈ መክብብ 8:4
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሰኞ

25
መኸርን ማጨዳችሁ እርግጥ ነው

በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን


ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ፡፡
(መዝሙረ ዳዊት126፡6)፡፡

አ ብዛኛውን ጊዜ ጌታን ለማገልገል ብዙ ጥረት እና ሀብትን


የሚሰጡ ሰዎች ያጋጥሙናል፤ ነገር ግን ከተወሠነ ጊዜ በኋላ
“ለዚህ ሁሌ ጥረቴ እኔ የማገኘው ጥቅም ምንድን ነው?” በማለት ራሳቸውን
ይጠይቃሉ፡፡
እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ቃል ግልፅ ነው፤ ሁልጊዜም እግዚአብሔር
የመጨረሻው ሰጪ ነው፡፡ ማንም ሰው ከእርሱ በበለጠ ሊሰጥ አይችልም፡
፡ ስለዚህ ተበረታቱ ፤ተስፋ አትቁረጡ ፤ ምክንያቱም መፅሐፍ ቅዱስ
እንዲህ ይላል፦ “. . . እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም
ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር
ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና፡፡” (ዕብራውያን 6፡10)
የመክፈቻ ጥቅሳችን ባጭሩ አስቀምጦታል፡- “በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን
ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው
ደስ እያላቸው ይመጣሉ፡፡” ይህ ማለት መኸራችሁ እርግጥ ነው፤
ማለትም ያለ ምንም ውድቀት እውን ይሆናል፡፡ ነዶ ማለት ከተቆረጠ
በኋላ የታሰረ የአገዳ ወይም የእህል ዛላ እሥር ማለት ነው፡፡ ለማጓጓዝና
ለማከማቸት አንድ ላይ ይታሰራል፡፡ ይህ ቃል አንዳንድ ጊዜ በበአንድ ላይ
የተቀመጡ የብዙ ነገሮች እሽግን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ነገር
ግን በእኛ ርዕስ ጥቅስ ላይ ፥ ቃሉ እናንተ ለሰጣችሁት ነገር የምታጭዱትን
አንድ ዓይነት መኸር ይመለከታል፤ ይህ ደግሞ የሚመለከተው ገንዘብን ብቻ
አይደለም፡፡
የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን መኸራችሁን
በማንኛውም በመረጣችሁት ጊዜ ማግኘት እንደምትችሉ ማወቅ አስፈላጊ
ነው፤ በማንኛውም በፈለጋችሁበት ጊዜ እውን እንዲሆን ማድረግ
amharic
ትችላላችሁ፡፡ ዘፍጥረት 8፡22 እንዲህ ይላል፦”በምድር ዘመን ሁሉ
መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት
አያቋርጡም፡፡” ይህ ማለት መኸሩ የሚታጨድበት የተወሰነ ቀን የለም
ማለት ነው፡፡ “መዝራትና ማጨድ” የሚያመለክተው፥ የሚታጨደው
በማንኛውም ጊዜ መሆኑን ነው፡፡ ምንም እንኳን የመዝራት ዘመን(ዘር
መዝሪያ ጊዜ) ቢኖርም መኸሩን በማንኛውም ጊዜ መጥራት ትችላላችሁ!
መኸር የማጭድበት ቀን፣ የምባረክበትም ቀን ዛሬ ነው ብላችሁ መውሰድ
ትችላላችሁ! እግዚአብሔር ይመስገን!
መኸራችሁ መምጣት ያለበት በመለኮታዊ መንገዶች ነው፡፡ ለምሳሌ
፣ይስሐቅ በረሃብ ጊዜ ማለትም ተፈጥሮ መኸርን ለማጨድ በፍጹም
በማያስችልበት ጊዜ እንደዘራ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል፣ ነገር ግን በዚያው
ዓመት መቶ እጥፍ ተቀበለ፡፡ (ዘፍጥረት 26፡12-13)፡፡
መኸራችንን ለማጨድ መወሰንና በምንፈልግበት ጊዜ እንዲሆንም
ማድረግ እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው የምንሰራው በኢየሱስ ስም
ስለሆነ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ትዕግስት አስፈላጊ ነው፤ (ዕብራውያን 10፡36)
ምክንያቱም የሚያምን ሰው አያፍርም፡፡ (ኢሳያስ 28፡16)፡፡

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፡-ዘርቼና ሰጥቼ በረከት የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
የመሆንንና፥ መኸሬን ጠርቼ የማጨድን ልዩ ዱስ ጥናት
ጥቅም ማግኛ ዕድሎችን ስለሰጠኸኝ እወድሃለሁ፡
፡ በአገልግሎቴ፣ በገንዘቤ፣በቤተሰቤ እና ኤፌሶን 2:11-22
በሕይወት ባሉ ማንኛውም ነገሮች ብዙ ትንቢተ ኢሳያስ 15-18
እጥፍ የበረከቶች መኸር ለማፍራት፣ ዘሮቼና
የፍቅር አገልግሎቶቼ በመንፈስህ ተቀድሰዋል፤
የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ
በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡ ዱስ ጥናት
የዮሐንስ ወንጌል 1:1-13
መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ
23-24

ለተጨማሪ ጥናት:
2 ኛ ቆሮንጦስ 9:7-11; ገላትያ 6:9; የሉቃስ ወንጌል 6:38
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ማክሰኞ

26
መላእክት ስለኛ ይታዘዛሉ

ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ


ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል፡፡ (ዕብራዊያን 1፡4) ፡፡

በ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሄር ሕይወትና አሰራር በአዲስ


ኪዳን ካለው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡ ለምሳሌ፣
በብሉይ ኪዳን ጊዜ መላእክት የእግዚአብሄር ሰዎች ሲያጠፉ ፍርድና ቅጣት
እስከ ማስተላለፍ የሚደርስ ሥልጣን ነበራቸው፡፡
ቀላል ምሳሌ የሚሆነው ዘካሪያስ የመላእኩ ገብርኤልን ቃል
ባለማመኑ የሆነው ነገር ነው፡፡ መልአኩ አልራራለትም፡፡ እንደዚህ አለ፡
- “እኔ በእግዚሃብሄር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ እነሆም በጊዜው
የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንክ ይህ ነገር እስኪሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ
መናገርም አትችልም አለው ” (ሉቃስ 1፡19-22 አንብቡ) እንዳለውም ሆነ፡፡
ይህንን ማሰብ ትችላላችሁ ? ዘካሪያስን ባለማመኑ ምክንያት ቀጣው፡፡
ነገር ግን በአዲሱ ኪዳን መላእክት የእኛ አገልጋዮች ናቸው፤
እኛን ያገለግሉናል፡፡ ዕብራውያን 1፡13-14 እንዲህ ይላል፡- “ከመላእክት
ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፡፡ ከቶ
ለማን ብሎአል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ
የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” እኛ የመዳን ወራሾች ነን፤ መላእክት
በእኛ ላይ ሳይሆን እኛን ሊያገለግሉ የተላኩ የአገልግሎት መናፍስት ናቸው ፡
፡ በብሉይ ኪዳን ለነበሩ ሰዎች ላይ ይላኩ ነበር፤ በአዲሱ ኪዳን ግን ስለእኛና
ለእኛ ያገለግላሉ፡፡ ይህ አስደናቂ ነው!
ፊልጵስዮስ 9፡2-11 ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፡- “በዚህ
ምክንያት ደግሞ እግዚአብሄር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ
በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች
ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ…” ይህ የሚያሳየው የኢየሱስ
ስም ምን ያህል እውነትና ኃያል እንደሆነ ነው፡፡
እኛ ከመላእክት እንበልጣለን ምክንያቱም የተወለድነው ከእግዚአብሄር
amharic
ተወልደናል ከኢየሱስም ጋር ደግሞ አብሮ ወራሾች ነን፡፡ እኛ ከእግዚአብሄር
ዓይነቶች ጋር ተባባሪዎች ነን፡፡ እግዚአብሄር ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነውን
የኢየሱስን ስም ሰጠን፤ በዚህም ስምና በውስጡ እንኖራለን፡፡ ስለሆነም
ለመላእክት ትእዛዝን እንሰጣለን፤ እነርሱም ይታዘዙናል፡፡ ምክንያቱም
እነኛን ትእዛዛት የምንሰጠው በኢየሱስ ስም ነው፡፡ ሃሌሉያ!

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ! የእኔ በሆነው በክርስቶስ
ኢየሱስ ያለኝ ስልጣን አመሰግንሃለው፡፡ እኔ
በሁሉም ነገሮች ላይ ከእርሱ ጋር እነግሳለሁና
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
እገዛለሁ፡፡ እኔን ስለሚያገለግሉኝ ቅዱስ
ዱስ ጥናት
መላእክቶችህ አመሰግናለሁ፤ ዛሬ ስለ እነርሱ
ከእኔ ጋር መገኘት እወቅና እሰጣለሁ፡፡ ኤፌሶን 3:1-21
እነዲሁም አሁን እነርሱ ያለ ምንም ገደብ ትንቢተ ኢሳያስ 19-22
የእግዚአብሄርን በረከቶች እና አቅርቦቶች ዛሬ
ለእኔ በነጻነት ያመጡ ዘንድ በኢየሱስ ስም
እልካቸዋለሁ፤በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡ የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
የዮሐንስ ወንጌል
1:14-23
መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ
1

ለተጨማሪ ጥናት:
ዕብራውያን 1:7; ዕብራውያን 1:13-14
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ረቡዕ

27
በጸጋው ላይ ተጣበቁ
ነገር ግን በእግዚሃብሄር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው
ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፤ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር
ያለው የእግዚሃብሄር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡
(1ኛ ቆሮ 15፡10)፡፡

ከ ላይ የተገለጸውን ጥቅስ የሐዋርያው ጳውሎስ ዋነኛ የስኬት


ምስጢሮቹ መካከል አንዱ እንደሆነ አድርገን ልንወስደው
እንችላለን፡፡ እርሱ እግዚአብሄር በኃይል የተጠቀመበት ሰው ነበር፤ምክንቱም
እርሱ በእግዚአብሄር ጸጋ ላይ ሙሉ በሙሉ የተደገፈ ስለነበረ ነው፡፡
እርሱ የሰራቸው እና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነበት ነገሮች በሙሉ፣
በእርሱ ሰብአዊ ወይንም የተፈጥሮ ችሎታ ሳይሆን፤ በህይወቱ ላይ ያረፈው
የእግዚአብሄር ጸጋ ውጤቶች ናቸው፡፡ የሰው የተፈጥሮ ችሎታዎች እና ቁሳዊ
ስኬቶች ፤ በእግዚአብሄር ዘንድ ምንም ቦታ እንደሌላቸው ተረድቶ ነበር፡፡
የራሱ የተፈጥሮ ችሎታዎች ስላመጡት ውጤቶች ሲናገር እንዲህ
ብሎ ጽፏል፡- “ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለክርስቶስ እንደ ጉዳት
ቆጥሬዋለሁ፡፡ አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ
ኢየሱስ ስለጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ፤ ስለ እርሱ
ሁሉን ተጎዳሁ፤ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ” (ፊልጵስዮስ 3፡7-8)፡፡
ምንም እንኳን መልካም ነገር ቢሆንም፣እግዚአብሄር የትምህርት
ደረጃችሁን አይመለከትም፡፡ ምንም እንኳን መልካም ነገር ቢሆንም፣
እርሱ የእናንተን የሃብት ደረጃ አይመለከትም፡፡ እርሱ በአለም ውስጥ
የተማራችሁትን ነገሮች አይመለከትም፡፡ እንዲያውም እርሱን ለመከተልና፤
ከእርሱ ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ መራመድ እንድትችሉ ፤ በእምነት
መመላለስ አለባችሁ፡፡ እናንተ የሚያስፈልጋችሁ ብቸኛ ነገር ጸጋው ነው፡
፡ በ 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9 ላይ ጳውሎስ ይህንን እንዴት እንደሚያረጋግጠው
ተመልከቱ፡- “እርሱም ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ሀይሌም በድካም ይፈጸማል አለኝ፡
፡ እንግዲህ የክርስቶስ ሃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ
እወዳለሁ፡፡”
amharic
የእግዚአብሄር ጥንካሬ የሚገለጠው በእናንተ ድክመት ውስጥ
ነው፡፡ አሁን ወጣቱ ዳዊት አለምንም የሚታይ የተፈጥሮ ስጦታ በተክለ-
ሰውነታቸው የተሻሉትን ታላላቅ ወንድሞቹን በልጦ ለንግስና እንደተመረጠ
የበለጠ ትረዳላችሁ፡፡ ተክለ-ሰውነትን በተመለከተ ዳዊትን ለንግስና
ሊያስመርጠው የሚያስችል ምንም ነገር አልነበረውም፤ ከነበረው የልብ
ሁኔታ ጋር ተዳምሮ፣ ሙሉ በሙሉ ምርጫው በጸጋ ብቻ ነበር፡፡
እግዚአብሄር ሁልጊዜ ለመጠቀም የሚፈልገው በተፈጥሮ ወይንም
በራሱ ምንም የሚያኮራ ነገር የሌለውን ወንድ ወይም የሌላትን ሴት
ነው፡፡ ይህ ካልሆነማ የእርሱ ክብር አይገለጥም፡፡ እግዚአብሄር በሃይል
እንዲጠቀምባችሁ ከፈለጋችሁ፤ በራሳችሁ ወይንም ባላችሁ የተፈጥሮ
ስጦታዎች ላይ አትደገፍ፡፡ ይልቁኑ ፣ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ሙሉ
በሙሉ በእግዚአብሄር ጸጋ ላይ ተማመን፡፡

ጸሎት
ው ድ አ ባ ት ሆይ ፡ - በ ታ ላቁ ፍ ቅ ር ህ
ስለወደድከኝና በህይወቴ ላይ ስላለው የአንተ
እጅግ የተትረፈረፈ ጸጋህ፤ ስምህ ለዘላለም
ይባረክ፡፡ በነገሮች ሁሉ ለእኔ በቂ መሆኑን የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
በማወቅ፤ በጸጋህ እጠቀማለሁ፡፡ በጸጋህ፣
በህይወት በአሸናፊነት እነግሳለሁና እገዛለሁ፤ ኤፌሶን 4:1-16
በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡ ትንቢተ ኢሳያስ 23-24

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የዮሐንስ ወንጌል
1:24-34
መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ
2

ለተጨማሪ ጥናት:
ያዕቆብ 4:6; መጽሀፈ ምሳሌ 3:5; ፈልጵሱዮስ 4:13; ኤፌሶን 2:8
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ሐሙስ

28
የእናንተ የሆነውን ውሰዱ

የመለኮቱ ኃይል፤ በበዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፤ ለህይወትና


እግዚሃብሄርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለሰጠን፤
በእግዚሃብሄርና በጌታችን በእየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፡፡
(2ኛ ጴጥሮስ 1፡3)፡፡

ዳ ግም የተወለዳችሁ በመሆኑ፣ የክብርና የስኬት ህይወት


ተሰጥቷችኋል፡፡ አንዳንድ ክርስቲያኖች ይህንን ባለመገንዘብ፤
እግዚአብሄር ሁኔታቸውን ለማሻሻል አንድ የበለጠ ነገር እንደሚያደርግ
ተስፋ እያደረጉ ይጸልያሉ፡፡ በክርስቶስ አስቀድሞ ካደረገላችሁ የበለጠ ጌታ
ሊያደርላችሁ የሚያስፈልገው ምንም ሌላ ነገር የለም፡፡ ለእናንተ አጠቃላይ
ደህንነትና ብልጽግና የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አስቀድሞ አድርጓል፡፡ እናንተ
በጽድቅ፤ በበላይነት እና በኃይል እንድትኖሩ ሁሉን ነገር አድርጎላችኋል፡፡
ለምሳሌ “ጌታ ሆይ ሰላም ስጠኝ” እያላችሁ እየጸለያችሁ ከነበረ፤
አቁሙ! አስቀድሞ ሰላም ሰጥቷችኋል፡፡ በዮሐንስ 14፡27 ላይ እንዲህ ብሏል
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ…” በእውነት በተጨማሪ
ልትጠይቁት የሚገባችሁ ምንም ነገር የለም፤ የመግቢያ ጥቅሱን በድጋሚ
አንብቡት፡፡
ዛሬ ማድረግ የሚገባችሁ ነገር አስቀድሞ ለእናንተ ያዘጋጀላችሁን
በረከቶች መውሰድ ብቻ ነው፡፡ እርሱ አስቀድሞ የሰራውን ነገር ተጠቀሙበት፡
፡ 1ኛ ቆሮንጦስ 3፡21 እንዲህ ይላል፡- “…ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና…” ፡፡ ነገር
ግን 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2 እንዴት እነዚህን ነገሮች እንደምትጠቀሙባቸው
ፍንጭ ይሰጠናል፡- “…በእግዚአብሄር እና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት፡፡”
በእግዚአብሄር እና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት አማካኝነት ሞገስ፤ ሰላም፤
እድገት፤ በረከቶች እና ብልጽግና በህይወታችሁ ላይ ይበዛሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በቃሉ (በግሪክ- ኤፒግኖሲስ) አማካኝነት
ትኩረታችሁን ወደ የመገለጥ እውቀት እንደመራችሁ አስተውሉ! ለእናንተ
የሚያስፈልጋችሁ ቃሉን በማጥናትና በማሰላሰል ወደ እናንተ የሚመጣው
amharic
ልዩ እውቀት ነው፡፡ ሃሳባችሁን የሚያስፈልጋችሁ ይሄ ነው፡፡ ቃሉን
በማሰላሰልና በማጥናት የሚመጣ የተለየ እውቀት፡፡
በዚህ ልዩ የሆነ የእግዚአብሄር እና የጌታችን ኢየሱስ እውቀት፣
በክርስቶስ እናንተ ያላችሁን መብቶች፤ ጥቅሞች፤ በረከቶች እና ውርስ ማወቅ
ብቻ ሳይሆን፣ እናንተን በወንጌል አጠቃላይ በረከቶች ህያው እውነታ ውስጥ
ወደ የምትመላለሱበት ግዛት ያመጥቃችኋል፡፡ እግዚአብሄር ይባረክ፡፡

የእምነት አዋጅ
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ሁሉ
በመንፈሳዊ በረከቶች ለባረከኝ ለእግዚአብሄር
ምስጋና ይሁን፡፡ እኔ የክብርና የስኬት ህይወት
አለኝ፤እናም በየዕለቱ አሸንፋለሁ፡፡ በውስጤ የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዱስ ጥናት
ያለውን የእግዚአብሄርን ታላቅ የክብር ውርስ
ለመለየት እና ለመውሰድ መንፈሳዊ አይኖቼ ኤፌሶን
4:17-5:1-2
የበሩ ናቸው፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡ ትንቢተ ኢሳያስ 25-26

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት
የዮሐንስ ወንጌል
1:35-42
መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 3

ለተጨማሪ ጥናት:
2 ኛ ጴጥሮስ 1:2-3; 2 ኛ ጢሞቴዎስ 2:15; ዕብራውያን 4:16
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
Te ¨h

Te ¨h

amharic
Te ¨h

Te ¨h
አርብ

29
የአማላጅነት ስፍራችሁን ያዙ

እጁን በሁለታችን ላይ የሚያኖር ዳኛ በመካከላችን ምነው በተገኘ !


(ኢዮብ 9፡33)፡፡

የ መክፈቻ ጥቅሳችን የሰው ልጅ “ዳኛ” ማለትም አስታራቂ የፈለገበት


ጊዜና ወቅት እንደነበርና እንዳልተገኘም ያሳያል፡፡ ኢዮብ ይህንን
ፈልጎ ነበር፤ ግን አላገኘም፡፡
ስለ አሰቃቂ ስራቸው ሲገስጻቸው፤ ኤሊ ለልጆቹ የተናገራቸውን
ቃላትም ያስታውሰናል፡፡ እንዲህ አለ፡- “ሰውስ ሰውን ቢበድል እግዚአብሄር
ይፈርድበታል፤ ሰው ግን እግዚአብሄርን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምነው ማን
ነው? ” (1ኛ ሳሙኤል 2፡25)፡፡
ነገር ግን እግዚአብሄር ይመስግን ኢየሱስ መጣ! ኢሳያስ 59፡16 እንዲህ
ይላል፡- “ሰውም እንደሌለ አየ፤ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ
ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድሃኒት አመጣለት፤ ጽድቁም አገዘው፡፡”
እግዚአብሄር ሰው እንደሌለ፤ አማላጅ እንደሌለ አየ፤ እናም ጌታ ኢየሱስን
ላከው፤ እርሱ ደግሞ ዛሬ አባቱ እንደላከው እኛን ላከን (ዮሐንስ 20፡21)፡፡
ዛሬ የሰው ልጅ ረዳት-አልባ እና ተስፋ የሌለው አይደለም፤ አማላጅ
የሌለው አይደለም ፡፡ በምድር ላይ እና በሰዎች ህይወት ላይ ለመማለድ እና
የእግዚአብሄር ፍጹም የሆነ ፍቃድ እንዲፈጸም ለማድረግ የተጠራነው እኛ
ነን፡፡ ኃይልን፤ ችሎታንና ሃላፊነትን ሰጥቶናል፡፡
በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1 ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ሲል ጻፈለት፡-
“ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለሰዎች ሁሉ… እንዲደረግ ከሁሉ በፊት
እመክራለሁ፡፡” በተጨማሪም በኤፌሶን 6፡18 ላይ ይህንን ገለጸ፡- “በጸሎትና
በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም ሃሳብ ስለቅዱሳን ሁሉ
እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ…”፡፡
እኛ የምልጃ ጸሎት ስንጸልይ፤ መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር አንድ ላይ
በመሆን የጨለማ ኃይላትን ለመግታት፤ የኛ የሆነውን ነገር እንድናገኝ
ለማድረግና፤ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በሁሉም ሥፍራ ለመመስረት ይሰራል፡፡
ይህንን አገልግሎት የምናደርገው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነትና በእርሱ በኩል
ነው፡፡ የአማላጅነት ስፍራችንን ስንይዝ፤ እኛ እግዚአብሄርን በመምሰልና
amharic
በሀቀኝነት ሁሉ የጸጥታና የሰላም ህይወት እንደምንኖር ጌታ ተናግሯል፡፡
(1ኛ ጢሞቲዎስ 2፡4)፤ ህብረተሰባችን በጽድቅ ይመሰረታል፡፡
ምልጃ ሁልጊዜም ስለ ሌሎች ነው፤ ትኩረታችሁ ሌሎች መልካም
እንዲሆንላቸው የእግዚአብሄር ኃይል ተጽእኖ እንዲያመጣ ነው፤ ይህን
ማድረግ ደግሞ ያለማቋረጥ መጸለይን ይጠይቃል፡፡ አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ
በካንሰር ወይንም በአንድ በሚገድል በሽታ ተይዟል ብለን እናስብ፤ ስለራሱ
ፈውስ እና ጤና የክርስቶስን በረከቶች ለማግኘት አይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን
በእናንተ ምልጃ ፤ ማለትም በእርሱ ምትክ ስትጸልዩ እና ጠላትን ስትገስጹ፤
እርሱ ተአምር ሊቀበል ይችላል፡፡

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ በስቃይ ላይ ስላሉ ሁሉ
እ ጸ ል ያ ለሁ፤ በ ተ ለ ይ ም ለ ታ መ ሙ ት ፤
ለተሰደዱት፤ ለተጎዱ ወይም በማንናውም
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ዓይነት ሥቃይ ውስጥ ላሉ የእግዚአብሄር
ዱስ ጥናት
ልጆች፤ ፤ በአንተ መንፈስና በመላእክት
አገልግሎ ት በኩል፤ እርዳታ፣ ድጋፍና ኤፌሶን 5:3-21
መጽናናት እንዲሆንላቸው እጸልያለሁ፡ ትንቢተ ኢሳያስ 27-28
፡ በድል አድራጊነት ካሉበት ለመውጣት
የሚያስፈልጋቸውን እምነት፤ ድፍረትና
ጥንካሬ እንዲያገኙ እጸልያለሁ፡፡ በኢየሱስ የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ስም አሜን፡፡ ዱስ ጥናት
የዮሐንስ ወንጌል
1:43-51
መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 4

ለተጨማሪ ጥናት:
ሮሜ 8:34; ገላትያ 4:19; ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:7
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
ቅዳሜ

30
አብዝታችሁ ጸልዩ
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሱ፤ በጸሎት ጽኑ
(ሮሜ 12፡12)፡፡

ከ ላይ ያለው ጥቅስ የእግዚአብሄር መንፈስ ያለማቋረጥ በክርስቶስ


የአሸናፊነት ህይወት ለመኖር የሚያስፈልገንን አንድ ነገር
ያሳየናል፡፡ ምንም እንኳን በዙሪያችን መናወጥ ቢኖርም ፤ እኛ ግን ሳንናወጥ
በጸሎት መጽናት እንደሚኖርብን መንፈስ ቅዱስ ገልጾልናል፡፡
አንዳንዶች ጸሎት ማለት እግዚአብሄር አንድ ነገር እንደሚያደርግ
ተስፋ በማድረግ፣ ችግሮቻችሁን ለእርሱ መንገር ብቻ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ይህ
ጸሎትን በተመለከተ የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ የጸሎት አላማ በቀዳሚነት
ከአብ ጋር ህብረት ማድረግ ነው፡፡ ይህ ህብረት ፍቅርን ለመገንባትና
ለማጠንከር ይረዳል፡፡
ስለዚህ ጸሎት ከሰማያዊ አባታችሁ ጋር ያላችሁን ህብረት እና ግንኙነት
የሚገነባ ነው፡፡ ይህም ማለት እናንተ ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እንዲያድግና
እንዲጠነክር ፤ አብዝታችሁ መጸለይን መማር አለባችሁ፡፡
አንዳንድ ሰዎች የሚጸልዩት የሆነ ነገር ሲፈልጉ ብቻ ነው ፤ የጸሎት
ጊዜ ግን ነገሮችን ለማገኘት እግዚአብሄርን የመጠየቂያ ጊዜ ብቻ አይደለም፤
ከእርሱ ጋር ህብረት ማድረጊያ ወይም ግንኙነት መፍጠሪያ ጊዜ ነው፡፡ ይህ
ጊዜ መንፈስ ምን እንደሚላችሁ የምትሰሙበትና ለእያንዳንዱ ቀን ከእርሱ
የሚያስፈልጋችሁን አቅጣጫና ምሪት የምትቀበሉበት ጊዜ ነው፡፡
ኢየሱስን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ማለዳም
ተነስቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ” (ማርቆስ
1፡35)፡፡ ኢየሱሰ በምድር ላይ ሳለ ለጸሎት ያለው ትኩረት ከፍተኛ ነበር፤
ምክንያቱም ከአብ ጋር ስለሚደረግ ህብረት አስፈላጊነት ተረድቶ ነበር፡
፡ ስለ ጸሎት ያላችሁ መረዳት እንዲህ በሆነ ቅጽበት፣ የበለጸገ ህይወት
ይኖራችኋል፤ እና በምትሰሩት ስራም ፍሬያማ ትሆናላችሁ፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራን ለመስራት ፣ከመንፈስ ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት
amharic
እና ፍሰት ያስፈልጋችኋል፤ አለበለዚያ የምትሰሩት ስራ ምንም አይነት
መንፈሳዊ ተጽእኖ አይኖረውም፡፡ ከጌታ ጋር በተደጋጋሚ ህብረት ማድረግን
ተማሩና፤ ህይወታችሁ በአስገራሚ ሁኔታ ሲያድግ እዩ፡፡

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ በጸሎት ስለምለማመደው
መለኮታዊ መቀየርና መለወጥ አመሰግንሃለው፤
ክብርህ ህይወቴን ይሞላዋል፤ ፍቅርህ ነፍሴን
የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅ
ያነቃቃታል፤ በመገኘትህ ውስጥ ማምለክ
ዱስ ጥናት
ምንኛ እወዳለሁ! በጸሎት ካንተ ጋር ህብረት
ለማድረግ ስላለኝ በረከቶችና ልዩ ጥቅም ኤፌሶን 5:22-6:1-9
አመሰግናለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ትንቢተ ኢሳያስ 29-30

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅ


ዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 2:1-11


መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 5

ለተጨማሪ ጥናት:
መዝሙረ ዳዊት 55:17; የሉቃስ ወንጌል 21:36; 1 ኛ ተሰሎንቄ 5:17
Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org
የደህንነት ጸሎት

በ ዚህ መጸሐፍ እንደተባረካችሁ እናምናለን፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን በሕይወ


ታችሁ ጌታ እንድታደርጉ እንጋብዛችኋለን፡፡

ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ኢሱስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፤


በሙሉ ልቤ አምነለሁ ፡፡ ለእኔ ሲል እንደሞተ እና እግዚአብሔርም ከሞት
እንዳስነሳው አምናለሁ፡፡ ዛሬ ሕው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ
ኢየሲስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ እንደሆነ በአፌ አውጃለሁ፡፡ በእርሱ በኩል
እና በስሙ ዘላለማዊ ሕይወት አለኝ፡፡ዳግም ተወልጃለሁ፡፡ ጌታሆይ ነብሴን
ስላዳንካት አመሰግንሀለሁ! አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡፡ ሀሌሉያ!

እንኳን ደስ ያልዎት፤ አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ኖት፡፡ እንደክርስቲያን በመንፈሳዊ


ሕይወትዎ እንዲያድጉ ከኋላ በተጻፈውን ስልክ ቁጥር ይደውሉ፡፡

united kindom: south africa:


Tel.:+44 (0)1708 556 604 Tel.:+27 11 326 0971
+27 62 068 2821
nigeria:
Tel.:+234-703-000-0927
+234-812-340-6791 usa:
+234-812-340-6816
Tel.:+1 (0) 980 219 5150
+234-01-462-5700
+1-281-759-5111;
canada: +1-281-759-6218
Tel.:1 647-341-9091;
Tel/Fax:+1-416-746 5080

amharic
ስለ ፀሐፊው

የቢሊቨርስ ላቭ ወርልድ ፕሬዘዳንት የሆነው ሬቨረንድ


ክሪስ ኦያኪሎሜ የተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ
ሲሆን ወደ ብዙ ሰዎች ልብ የመለኮታዊውን ሕይወት
እውነታ አምጥቷል፡፡

በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በቴሌቪዥን


አ ገ ልግ ሎ ቱ “ የ ተ አ ምራ ት ከ ባ ቢ ” በ ሚባ ለው
አገልግሎቱ፤ኮንፍረንሶቹ ፣መጽሔቶቹ እንዲሁም
የተለያዩ መሐፎቹ እና የድምጽ እና ምስል ካሴቶቹ
ተጽእኖ ተደርገዋል፡፡ እነዚህም ሁሉ አገልግሎቶች
የእግዚአብሔርን ቃል እውነት እና ሀይል ያገለግላሉ፡፡

Learn more about


Christ Embassy a.k.a.
Believers’ LoveWorld Inc.
on
www.rhapsodyofrealities.org
www.christembassy.org
Te ¨h

Te ¨h

amharic
Te ¨h

Te ¨h
Te ¨h

Te ¨h

amharic
Te ¨h

Te ¨h
Te ¨h

Te ¨h

amharic

You might also like