You are on page 1of 55

ስነ አፈታት

Hermeneutics
አዘጋጅ
መጋቢ ይዲድያ ማሞ
2015 ዓ ም
መጸሃፍ ቅዱስና
የትርጉም ስልቱ
ሃዋ 8፡27 ሉቃ 10፡25
= ትርጎሜ ወይም ስነ አፈታት ምንድ ነው?
=Hermeneutics የሚለው የቃሉትርጉም (ሄርሜስ ከሚባል የግሪካውያን ጣዎት
ስም የተገኘ ነው )
ሄርሜስ መልክት ወደ ሰዎች ያመጣል ወይም ያደርሳል ተብሎ የሚታመን ጣወት ሲሆን
የፈጠራ የንግግር; የሳይንስ የስነ ጽሁፍ አምላክ በመባል ይ ታወቃል ሃዋ 14፡12
1, ስነ አፈታት የትርጎሜ መርሆችን የምናጠናበት ስልት ነው።
2; ስነ አፈታት በድሮ ዘመንና በድሮ ባህል ውስጥ ለነበሩ ሰዎች የተጻፈ ለአሁን ዘመን
አንባቢ ግልጽ የምናደርግበት ስልት ነው።
3; ስነ አፈታት የጸሃፊውን ወይም የጸሃፊዎቹን ሃሳብ ይህውም ለማለት የፈለጉትን ነገር
በምንባቦች ወይም በጽሁፎቹ አማካኝነት ለመረዳት የምንሞክርበት ነው።
4; ስነ አፈታት መጸሃፍ ቅዱስ እንዴት መተርጎምና እንዴት
መፍታት እንዳለብን የምንማርበት የትርጎሜ ስልት ወይም
ሳይንስ ነው።
ትርጎሜ ወይንም ስነ አፈታት የሚያስፈልገው
ለምንድነው?
1; የቋንቋ፣የባህል፣የታሪክና፣የስነ ጽሁፍ ልዩነቶች በመኖራቸው
2; የመጸሃፍ ቅዱስ ትርጉም ልዩነት ብሉይ ኪዳን በእብራይስጥ
አዲስ ኪዳን በግሪክ መጻፉ
3; ጠጣርና ጠንካራ ምንባቦች በመኖራቸው ምክንያት
ለምሳሌ= ዘፍ 6፡5; ዘጸ 9፡12 ኢያ 6፡2 ኢሳ 45፡7 ህዝ 21፡4
ናሆ 1፡2 ዮሃ 3፡5 ሮሜ 9፡12 18 ሮሜ 11፡26 1ጢሞ 2፡
151 ጼጥ3፡19 ራይ 12፡1፟ 2
4 መጸሃፍ ቅዱስ ሰባዊና መለኮታዊ በሃሪ ስላለው
መጸሃፍ ቅዱስ ሁለት ባህሪያት አሉት የእግዚአብሄ ቃል በሰው ቃል ወይም ቃለ
እግዚአብሄር ቃለ ሰብእ።
የመጸሃፍ ቅዱስን ባህሪ በተመለከተ ሁለት ባህሪያት አሉት መለኮታዊና ሰባዊ።መጸሃፍ
ቅዱስ የእግዚአብሄር ቃል ቢሆንም በሰዎች ቋንቋ ተጽፎል።
መጸሃፍ ቅዱስ አምላካዊ መገለጥ ቢሆንም በሰዎች ቋንቋ ተነግሮል።
የእግዚአብሄር እንደሆነ ሁሉ የሰው ቃል ወይም በሰዎች መንገድ የተነገረ ቃል
ነው።ይህን መንገድ ስነጽሁፍ ብለን እንጠራዋለን። መጸሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ቃል
እንደ ሆነ ሁሉ የሰውም ቃል ነው።
5; ቅድመ ልባዊ ወይም ቅድመ እሳቤ ( Presuposition/Preunderstanding)
ቅድመ ልባዊ ማለት ሰዎች በሂደት ውስጥ አካብተውትና አጎልብተው የራሳቸው
ያደረጉት አተያይ ወይም አመለካከት ማለት ነው።
6 መጸሃፍ ቅዱስ ምክንያቶች
ስነ አፈታት የሚያስፈልግበት ምናልባትም ትልቁ ምክንያት
እራሱ መጸሃፍ ቅዱስ ለትርጎሜ ወሳኝነት የሚሰጠው ስፍራ
ነው።
ማር 12፡24 ዮሃ 5፡39_46 ሉቃ 24፡13_32_45 ሃዋ 8፡
30_32 ሃዋ 9፡5_9 2ጢሞ 2፡15 2ጼጥ 1፡20
የምንከተለው የትርጉም ስልት
• የምንከተለውን የትርጉ ስልት ከማየታችን በፊት ካሉት የትርጉም አይነቶች የተወሰኑትን
እንመልከት
• የትርጉም አይነት ታሪካዊና ወቅታዊ አሰሳ
1 ሚስጥራዊ ትርጉም የመፈለግ ዘዴ(Allegorical interpreation)
= በትርጉም ሂደት ውስጥ ስውርና ሚስጥራዊ ፍችን መከተል ማለት ነው፡፡ አሊጎሪካል
ትርጉም በቀጥታና በግልጽ ከተቀመጡ ትርጉም ይልቅ በስውር ያለውን ፈልጎ ለማግኘት
የትርጉም አይነትነው።
አላጎሪካል ትርጉም ከምናነበው በስተጀርባ ድብቅ መልእክት አለ ይህም መልእክት በጾምና
በጸሎት እንዲሁም እረጅም ጊዜ በማሰላሰል እናገኘዋለን የሚል ሃሳብ ነው።
ታሪካዊ አመጣጡ ከግሪክ ፍልስፍና የመጣ ነው ይህ አስ ተሳሰብ በዋናነት እንዲስፋፋ
ያደረገው ከ20ዓ 、 ዓ _54 ዓ.ም ባለውጊዜ ፌሎ ተብሎ የሚጠራ ፈላስፋ ነው።
• መጸሃፍ ቅዱስን እና ፍልስፍናን ለማስማማት ሲሞክር ነው።
• የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ይህን ትርጉም የተጠቀሙ ነበሩ።
• ብሉይ ኪዳንን ለአዲስ ኪዳን አማኞች ጥቅም ላይ ለማዋል
በአሊጎሪዝም መንገድ ስንጠቀም ብቻ ነው የሚሉ ስለነበሩ
ከነዚህም ጁስቲን ማርቲን አንዱ ነበረ ከ100_164 ዓ.ም
ለሌሎችም ነበሩ።
• ለምሳሌ የተጠቀሞቸው ጸሃፎች
• አስቴር መጸሃፍ አስቴርን ቤተክርስቲያንን ስትወክል ሃማ
ዲያቢሎስን መርዶኪዎስ መነፈስ ቅዱስን ወክሎል
የአሊጎሪዝም ጉዳቱ
• ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል በትክክል እንዳያውቁ ወይም እንዳይረዱ
ያደርጋል።
• መጸሃፍ ቅዱስን የመተርጎም ስልጣን በተርጎሚው ግምት ላይ እንዲ
መሰረት ያደርጋል።
• ሚስጥራዊ ሃሳብ የመፈለጉ ተግባር ገደብ ስለማይኖረው ተርጎሚው
ያሻውን ሊል ይችላል።
• የእግዚአብሄርን ቃል ሃይል ያሳጣዋል።
• የሚደነቀው ሰባኪው ብቻ ይሆናል። ይህ ደግሞ መጸሃፉ የአገልጋይ ብቻ
ይሆናል። ሰዎች ከመጸሃፉ ይለያሉ፣የምንባቡ ትርጉም እንዲደበክ
ያደርገዋል፣እንደየግለሰቡ የተለያየና የአንባቢው ግምት ብቻ ሆኖ ይከራል።
ቀኖናዊ ትርጉም
Dogmatc Interpnetation
• ትርጉም በቤተክርስቲያን ወይም በማህበረሰብ ሲወሰን ማለት ነው።
• ከመጸሃፍ ቅዱስ ይልቅ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ከመጸሃፍ ቅዱስ ውጪ ላለስልጣን ነው።
• ይህ ትርጉም መሰረቱ ሰዎች፤የተወሰኑ ቡድኖች፤ወግና ቤተክርስቲያን ናቸው። ቤተክርስቲያን
ካስቀመጠችው ፍቺ ውጪ ማለፍ አይቻልም።
• ታሪካዊ አመጣጡ
• የጥንት ቤተክርስቲያንን ከስህተት ለመከላከል ስትል የጀመረችው ነው።
• ቤተክርስቲያን እና የቤተክርስቲያንን አገልጋይ ከፍ ለማድረግ።
• ያመጣው ችግር
• ቀኖናዊ ትርጉም ጉዳቱ
• የዶክትሪን ልዩነቶች እንዲፈጠሩ አድርጎል
• ሰዎችን ከመጸሃፍ ቅዱስ አርቆል
• ከመጸሃፍ ቅዱስ በላይ ሰነድን የስልታን ምንጭ አድርጎል
አመክኖዊ የትርጉም ዘዴ
Rationalistic Interpretation
• ምክንያታዊ ትርጉም መጸሃፍ ቅዱስን ለመተርጎም መሰረት
የሚያደርገው በሠዎች አመለካከት ላይ ነው።
• ማንኛውም የመጸሃፍ ክፍል በሰዎች ምክንያታዊ አስተሳሰብ
ካልተገለጸ በስተቀር እንደ ስህተት ወይም ሃሰት ይቆጠራል
ወይንም ሌላ ትርጉም እንዲሰጠ ይደረጋል።
• በአምሮ ተቀባይነት የሚያገኘው ትርጉም መረጃ ወይንም
ምክንያት ማቅረብ የሚችል ብቻ ነው።
• ለምሳሌ የባህር መከፈል እና የዮናስ በአሳ ነባሪ ውስጥ ለሶስት
ቀን መቆየትን አይቀበሉም።
ታሪካዊ አመጣጡ
• ምክንያታዊ አተረጓጎም እውቅና ያገኘው በአብርሆት ዘመን ነው።
(Enightement Periad Or Age of Enightement) 17_18
ክፍለ ዘመን የጀመረ ነው
• ይዘመን ለሰዎች አስተሳሰብ ከፍተኛ ስፍራ ይሰጥ ነበር።አመክኖአዊ
አተረጓጎም መሰረቱን የጣለው ሳይንስ ባመጣው ምርምር ዘዴላይ
ነው።
• የሰዎች ሳይንሳዊ መረጃ ለመለኮታዊ የእግዚአብሄር ቃል ትንታኔ
መስጠ ጀመረ።
• ምክንያታዊ አተረጓጎም ለዘብተኛ ( liberal) አመለካከት መሰረት
ነው።
ምክንያታዊ አተረጓጎም አደገኛነቱ
• የሠዎችን አመለካከት ከፍ በማድረግ መለኮትን አሳንሶ
ያሳያል።የሰውን አመለካከት የመጸሃፍ ቅዱስመለኪያ አድርጎ
ያቀርባል።
• የመጸሃፍ ቅዱስ ታምራቶችን አይቀበልም።
• የመጸሃፍ ቅዱስን ሉዋላዊነት ተፈጥሮ ወይም ስልጣን ይክዳል።
• ከሰው አእምሮ ተነስቶ ወደ መጸሃፍ ቅዱስ በመሄድ መጸሃፍ
ቅዱስን ይመክራል።
• ስለዚህ ይህ አተረጓጎም ተቀባይነት የለውም አደገኛ ነው።
ህሊናዊ አተረጓጎም
SUBJECTIVE INTERPRETATION
• በህሊናዊ አተረጓጎ የመጸሃፍ ቅዱስ ትርጉም የሚወሰነው
ወይም የሚታወቀው በተርጓሚው ስሜትና ልምድ አይ ነው።
• እያንዳንዱ ተርጓሚ የሚተረጉመው መጸሃፍ ቅዱስ ለግለሰብ
በተረዳው ወይም በገባው መጠን ነው።
• መጸሃፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ግለሰቡ ይወስናል ማለት ነው።
ይህ አተረጓጎም በአንድ የመጸሃፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ ብዙ
አይነት የተለያዩ ትርጉም ሊኖር ይችላል።

ታሪካዊ አመጣጡ
• ይህ አተረጓጎም የመጣው በዘመኑ ትልቅ ተጽኖ ካመጡ ሰዎች ነው።
• ኪርጋድ 1813—1976 ዓ.ም መጸሃፍ ቅዱስ መተርጎምና መረዳት
የግድ በተርጎሚው ልምምድ መሆን አለበት ብሏል።
• ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ካርል ባርዝና 1884__1968 ዓ ም
እና ሩዶልፍ ቡልትማን 1884_1976 ዓ ም የመጸሃፍ ቅዱስ
አተረጓጎም በሰዎች ህሊና ሲሆን መመስረት ያለበትም በተርጓሚው
ህይወት ነው።
• እነዚህ ሰዎች መጸሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ቃል አይደለም ነገር ግን
ከእግዚአብሄር ቃል ይዞል ይላሉ።
አደገኛነቱ
• መጸሃፍ ቅዱስን መተርጎም በሰዎች ማንነት ላይ ይወድቃል
ባለስልጣኑ ግለሰቦች ቡድኖች እንዲሁም ጳጳሳት እና
ፓስተሮች ይሆናሉ
• ምንም አይነት ገደብ መወሰንና የአተረጓጎም መመሪያ መከተል
አይችልም። ከተርጓሚው ውጪ የትርጉምን ትክክለኛነት
የሚወስን ተጨባጭ መለኪያ የለም ይላሉ።
• No Standard to interpret the biblical truthe
LEETRALL INTERPRETATION
ሊትራል አተረጓጎም
• መጸሃፉ የሚለውን በቀጥታ መቀበል ማለት ነው። ነገር ግን
ስራ ይፈልጋል ለምሳሌ;
• ጸሃፊው ለምን እንደጻፈ ማወቅ
• ለማ እንደጻፈ መረዳት ያስፈልጋል
• ለተቀባዮቹ ያለውን ዋና መልክት ምንድነው የሚለውን
መረዳት ያስፈልጋል። ጳውሎስ ለምን ስጋ አትብሉ አለ ምን
ማለቱ ነው የሚለው መታሰብ አለበት።
ሊብራል አተረጓጎም
LEABRAL INTERPRETATION
• ሊብራል አተረጓጎም በ19ኛው ክፍለ ዘመን የአተረጓጎም ዘዴ
ነው። ይህን ሃሳብ ያመጣው ቻርስ የተባለ ሰው ሲሆን
የአተረጓጎሙ ሲስተም መጸሃፍ ቅዱስን ለአእምሮ በሚመች
ሁኔታ መተርጎም ነው።
• ለምሳሌ; እግዚአብሄር ፍቅር ነው ስለዚህ ሲኦል የለም፤
• እግዚአብሄር ስሜትን ስለፈጠረ እንደፈለክ ተጠቀም ስሜትን
መጨቆን ሃጥያት ነው የሚሉ ናቸው።
ኒው ኦርቶዶክስ የትርጉም ዘዴ
• ኒው ኦርቶዶክስ የትርጉም ዘዴ
• መጸሃፍ ቅዱስ ብቻውን እግዚአብሄርን መግለጥ አይችልም ወይን በቂ
አይደለም ይላሉ።
• መጸሃፍ ቅዱስ የሰውን ውድቀትና መነሳት በመጨረሻም በክርስቶስ
በማመን የሚገኝን ድነት ነው የሚያወራው ስለዚህ ሌሎች መጸሃፍ
ማስገባት አለብ ብለው ያምናሉ።
• አዋልድ መጸሃፍ ወደ መጸሃፍ ወደ መጸሃፍ ቅዱስ እንዲገባ ይፈቅዳል፤
• ሰዎች የተለያዩ ፍልስፍናና የተለያዩ ሰዎች እንዲከተሉ ያደርጋል።
• መጸሃፍ ቅዱስ ግን ለሰዎች በቂ እውቀት አስተላልፎል።
ስርአታዊ ጥናትና የአተረጓጎም ዘዴ
• ታሪካዊ፤ ሰዋሰዋዊ፤ እና በቁም የመተርጎም ዘዴ ወይም
ታሪካዊ፤ ሰዋሰዋዊ፤ ቃል በቃል አውዳዊ እይታ አተረጓጎም።
• Historical Grammatical And Litral (Contextual)
Method
• ሁነኛ የትርጉ ስልቶች አብይ የሚባሉት ሶስት ናቸው።
• 1ኛ ታሪካዊ ሂሳዊ ወይም ሰዋሰዋዊ ትርጓሜ ሲሆን
• 2ኛ ስላሤአዊ ትርጓሜ ነው
• 3ኛ አመክሎተ ክርስቶሳአዊ ናቸው።
አመክሎት ክርስቶሳዊ ትርጓሜ
• አመክሎአት ክርስቶሳዊ ትርጓሜ ምንድነው ? ማለትም
ክርስቶስን መአከል ያደረገ ትርጓሜ ምን ማለት ነው ?
• አመክሎት ክርስቶስሳዊ ትርጓሜ በአጭሩ የክርስቶስን ሞትና
ትንሳኤ ወይም የክርስቶስን ህይወት አገልግሎትና ተልኮ
ማዕከል ያደረገ አተረጓጎም ወይም አፈታት ማለት ነው።
• የትርጉም ስልቱ ቅዱስ መጸሃፍትን ለመተርጎም የሚነሳው
ከክርስቶስ አንጻር ወይም ክርስቶስ በህይወቱና በአገልግሎቱ
ካከናወናቸው ተግባሮች አንጻር ነው።ዕብ 1፡3
ስላሴአዊ ትርጓሜ ለሶስት ነገሮች አጽኖት ይሰጣል
• 1ኛ ደራሲ ወይም ጸሃፊ ነው
• 2ኛ ድርሰቱ ወይም ጽሁፉ ነው
• 3ኛ ድርሰቱን ወይም ጽሁፉን ከሳች ወይም ገላጭ ነው።
• አብ ወጠነ ወልድ ውጥኑን ፈጸመ መንፈስ ቅዱስ ውጥኑን
በሰዎችና በፍጥረት አለሙ ህይወት ተገበረ።
• ይህን ወደቃሉ ወደትርጓሜው ስናመጣው አብ ተናጋሪው ወልድ
ንግግሩ ቢሆን መንፈስ ቅዱስ የተናጋሪውን ንግግር ከሳች ይሆናል።
• ድነት ከሶስቱም የስላሴ አካላት በእኩል የተሳተፉበት ስላሴአዊ
ተግባር ነው።
አመክሎት ክርስቶሳዊ ትርጓሜ ሁልጊዜ ከክርስቶስ
የሚጀምርበት ሶስት መሰረታዊ ምክንያቶች አሉ።
• 1ኛ ክርስቶስ የመላ አለም ወይም ፍጥረት ዓለም መአከል በመሆኑ ነው። ቆላ 1፡15 18 ዮሃ
14፡6 ራዕ 1፡18
• ክርስቶስ መአከል ብቻ ሳይሆን መሰረት እና ግብ ነው።
ዮሃ 5፡39 ሉቃ 10፡22 ዕብ 10፡1 12 ሉቃ 4፡17፟ 19
2ኛ ኢየሱስ የእምነት መሰረት በመሆኑ ነው። ዕብ 12፡1_2
= ክርስቶስ የእምነት ምንጭ ግብና ፍጻሜ ነው። ዕብ 6፡20 ዕብ 10፡19_20
= ክርስቶስ መነሻ ብቻ ሳይሆን መድረሻ ነው። ዮሃ 1፡18 2ቆሮ 5፡19_20
መጸሃፍ ቅዱስ ከክርስቶስ ውጪ ምንም ወይም አንዳች ትርጉም ወይም ፍቺ የለውም።
3ኛ ክርስቶስ የትንቢቶችና የተስፋዎች ፍጻሜ በረከት በመሆኑ ነው ሉቃ 24፡44 ሃዋ 26፡
22_23 1ጴጥ 1፡10_11 ሮሜ 5፡1_12
ይህን ወደ ትርጓሜ ስናመጣው አብ ደራሲ ሲሆን ወልድ ድርሰቱ ቢሆን መንፈስ ቅዱስ ድርሰቱን
ለተደራሲዎች ግብ አድራጊ ይሆናል። መልክትካለ የመልክቱደራሲና የመልክቱ ተቀባይ መኖር
አለባቸው።
• ጸሃፊ፤ ጽሁፍና፤አንባቢ ወይም ደራሲ ድርሰትና ተደራሲ አሉማለት
ነው።
• የስነ ሙሁራን ከሚያነሱት ወይም ካነሱት ጥያቀቌ ጋር ይዛመዳል።
• 1ኛ ወሳኙ ማን ነው? ደራሲው ድርሰቱ ወይም ተደራሲው
• 2ኛ ማነው ተርጓሚው ? ትርጉም ያለው ማጋነው ? አንባቢው ጋር
ነው ? ንባቡ ላይነው ? ወይስ ጸሃፊው ጋር ነው ?
• ንባብ አንባቢውን ይተረጉመዋል ወይስ አንባቢ ንባቡን
ይተረጉመዋል ? ይህ አዲሱ ትርጓሜ ሲባል አ ንዳንዶች የርጓሜ
ስልት ስነ አፈታታዊ ዑደት ( Hermeneutical spiral) ይሉታል
• ምንባብ ሁልጊዜ የመለወጥ ሃይል እንዳለው ሁሉ አንባቢውም ሁልጊዜ ምንባቡን
የመተርጎም ሃይል አለው።
• በንግግር ህግ ሶስት መሰረታዊ ነገሮች አሉ። እነርሱም
• 1ኛ የሚናገረው ሰው
• 2ኛ የሚነገረው ነገር
• 3ኛ ንግግሩን አድማጭ ናቸው።
• በስነ ጽሁፍ ህግ ልክ እንዲሁ ነው።
• 1ኛ ደራሲው ወይም መጸሃፉ
• 2ኛ ድርሰት ወይም ጽሁፍ እና
• 3ኛ ተደራሲው ወይ ም አንባቢው ነው።
• ሶስቱም ሁልጊዜ እንደ ተዛመዱ መቀናጀት አለባቸው።
• መጸሃፍ ቅዱስ በዘፈቀደ መተርጎም የለበትም እንደቋንቋው
ስርአትና ደንብ ወይም እንደ ስነጽሁፍ ህግ መተርጎም አለበት።
• መገለጡ በሰው ቋንቋ ተላልፎል በመሆኑም የሰው ቋንቋ
እንዴት እንደሚሰራ መገንዘብ አለብን።
• ስርዓታዊ ጥናትና አተረጓጎም ዘዴ
• ተርጓሚው በጥናታዊና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የጻፈውን
የደራሲውን ብቸኛና ቀጥተኛ ትርጉም ለማግኘት የሚደረግ
የአጠናን ስልት ነው።
• ለታሪካዊ
• ለሰዋሰዋዊና
• ለስነ ጽሁፋዊ አውዶች ትኩረት በመስጠት ዋናውን መልክት ይፈልጋል።
• ደራሲው ወይም ጸሃፊው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ያስተላለፈውን ብቸኛና
ቀጥተኛ ፍቺተርጓሚው ለታሪካዊው ሰዋሰውና ስነ ጽሁፋዊ አውዶችን
ትኩረት በመስጠት የሚፈልግበት ዘዴ ነው።
• ይህ ትርጉም ለመጸሃፍ ቅዱስ ስልጣን ከፍተኛ ስልጣን ይሰጣል።
• ብቸኛና ትክክለኛውን ቀጥተኛውን የመልክት የመልክት ሃሳብ ፈልጎ
ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።
• ቀጥተኛ ትኩረት የሚሰጠው የጸሃፊውን ዋና ሃሳብና ዓላማውን ነው።
የስርዓታዊ ጥናት የአተረጓጎም ዘዴ ጥቅም
ስርአታዊ የአተረጓጎም ዘዴን ይጠቀሙከነበሩት
ለምሳሌ; ሉተር፤ ኤሪክ ዚዊንግሊን፤ እንዲሁም ካልቪን ይህን ዘዴ ይጠቀሙ
ነበር።
= ኢራኒየስ የተባለው ( 130᎗202 ዓ/ም ) የነበረው የቤተክርስቲያን
አባት መጸሃፍ ቅዱስ በቀጥተኛና በግልጽ ትርጉም ልንረዳው ይገባል በማለት
አበክሮ ተናግሮል።
= ሌላው መታወቅ ያለበት ሁለት የመጸሃፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ነበሩ
በአሌክሳደርያ እና በአንጾኪያ ሁለቱ ትምህርት ቤቶች የተለያየ የአተረጓጎም
ስልት ይጠቀሙ ነበር በአሌክሳደሪያ ትምህርት ቤት የአሊጎሪካል አተረጓጎም
ሲከተሉ የአንጾኪያው ትምህርት ቤት ታሪካዊ፤ሰዋሰዋዊና ስነ ጽሁፋዊ
አተረጓጎም (HGL) ይከተሉ ነበር
• 1ኛ የመጸሃፍ ቅዱስ ስልጣን ይጠብቃል።
• ይህም ተርጓሚው ለመተርጐም የሚነሳው ከቃሉ ስለሚሆንና ከቃሉ
ውጭ ለሌላ ስፍራ ስለማይኖረው ነው።
• መጸሃፍ ቅዱስ ስለራሱ የሚናገረውን ለማወቅ ይጥራል።
• ተርጓሚው ከመጸሃፍ ቅዱስ ውጪ ትርጉም ከማምጣት ተቆጥቦ
የመጸሃፍ ቅዱስን ስልጣ እንዲያከብር ያደርገዋል።
• 2ኛ በመጀመርያው ጸሃፊ ያለውን እውነተኛ መልክት ለማግኘት
መጣር፤መጸሃፍ ቅዱስ እንዲጻፍ ምክንያት የሆነውን መንፈስ ቅዱስን
የእስትንፋሰ መለኮት ስራ ማመኑን ወይም የመንፈስ ቅዱ ስን ስራ
መቀበሉን ያሳያል።
• 3ኛ ታሪካዊ አውዱን በመረዳት መጸሃፍ ቅዱስን የሚያጠና መጸሃፍ ቅዱስ በሰዎች
ታሪክ ውስጥ የተሰጠ ዘላለማዊ የእግዚአብሄር ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።
• 4ኛ መጸሃፍ ቅዱስን በሰዋሰው አጻጻፍ ህግጋት መተርጐም ስልጣን ያለው
የእግዚአብሄር ቃል በሰዎች ቌንቌ መምጣቱን በቃላትና በሰዋሰው አጠናን ዘዴ
በመጠቀም እናሳያለን።
• 5ኛ መጸሃፍ ቅዱስን በቁም በመተርጐም ዘዴ ስናጠና የመጸሃፍ ቅዱስን የአጻጻፍ ዘይቤ
ከመቀበላችን በላይ የእግዚአብሄርን ቃል ስልጣን አሁንም በሰዎች ቌንቌ መገለጡን
እንቀበላለን
• በሰዎች ቌንቌ የተሰጠ መሆኑን
• ስልጣን ያለው የእግዚአብሄር ቃል መሆኑን
• በውስጡ ላሉ የስነ ጽሁፍ አይነቶች ትኩረት ይሰጣል ወይም ትኩረት በመስጠት
ማጥናት ይለማመዳል።
ስርዓታዊ ጥናትና የዓተረጓጐም መመሪያ
• ሶስት ዋና ዋና ነገሮች ላይ ትኩረት ያደርጋል።
• 1ኛ መመልከት(observeation)
• በጥንቃቄ ማየት እና መመርመር
• መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ,,ምን ይላል,, ? ሃዋ 17፥11
• 2ኛ መተርጎም(interpretation)
• ምን ማለት ነው ? ሃዋ 8፥30_35
• 3ኛ ማዛመድ ወይም መተግበር(application)
• ለተረዳነው ቃል ወይም እውነት መታዘዝ
• ,,ምን ላድርግ,, ? ሃዋ 22፥8_9
ምልከታ
• መጸሃፍ ቅዱስን ለማጥናት የመጀመርያው ደረጃ ምልከታ ነው።
• የመጸሃፍ ቅዱስ ጥናት የመጀመሪያው ደረጃ ነው።
• አንቀጹን በጥንቃቄ መመልከት ወይም መመርመር ነው።
• ምን ይላል ? ምንድ ነው የማየው ?
• ሶስት ቁልፍ ሃሳቦች አሉ።
• 1ኛ በምናነበውን ሃሳብ ላይ ትኩረት መስጠት
• 2ኛ ምንባቡላይ ያለውንና የሌለውን መለየት
• ለምሳሌ; ማቴ 2፥1_2 ስንት ሰብአሰገል አሉ?
• ኢየሱስን በየት አግኝተው ጎበኙት? ማቴ 2፥9_11
• በምንባቡውስጥ ያለውን እና የሌለውን ለመለየት
• በጥንቃቄ ማንበብ
• በተደጋጋሚ ማንበብ
• በትግስት ማንበብ፤ በመጸለይ ማንበብ፤በአላማ ማንበብ፤ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማንበብ ያስፈልጋል።
• 3ኛ ለምትመለከተው ነገር እርግጠኛ እና ጠንቃቃ ሁን
• ምልከታ ላይ የተለመዱ ስህተቶች
• ሙሉውን ክፍል አለማየት
• በምንባቡ የሌለውን ማየት
• በጥንቃቄ አለመመልከት
• የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ መድረስ
• ያነበብነውን እንዳወቅንው መቁጠር
• በማንበብ እና በጥናት መካከል ያለውን ልዩነት አለመረዳት
• በመመልከት ሂደት ውስጥ የሚረዱን የምናነሳቸው ጥያቄዎች
• ማን ? Who _ ተናጋሪው ፤ አድማጩ ማነው?
• ምን ? What _ ስለ ምን እየተወራ ነው ? ምን ይቀድማል? ምን ይከተላል ?
• የት ? Where _ ቦታው የት ነው ?
• መቼ?when_ ጊዜው መቼ ነው ?
• ለምን ? _አላማው ምንድነው ?
ቃላቶች
• እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ቁልፍ ቃሉን ወይም ሃረጉን ማወቅ
• ሀ) ምንባቡ ውስጥ ያለውን ቁልፍ ቃል መለየት
• ለምሳሌ; ሮሜ 8_9 የእግዚአብሄር መንፈስ
• ዕብ 11 እምነት
• ለ) ቃሉ በቀጥታ የሚወሰድ ነው ወይስ ስዕላዊ መግለጫ ነው።
• ዮሃ 10፥6_9፤ የበጎች በር ,, የወይን ግንድ,,
• ሐ) ሰዋሰዋዊ ይዘቱን ተመልከት ( ስም፤ ግስ፤ መስተዋድድ፤ አያያዥ)
• ግስ _ ዘጸ 2፥11_15 አየ ፤ ገደለ፤ ኮበለለ ወይም ድርጊት የተፈጸመበት ሁኔታ
• ማቴ 7፥21 _ አላውቃኋችሁም , አላቃችሁም ?
• ፊሊ 4፥13 _ በ, ከ, ለ, ( በእርሱ, ከእርሱ, ለእርሱ )( መስተዋደድ ) _ preposition
• በእናንተ (Through)
• አያያያዥ = እንግዲህ ሮሜ 12፥1 _ ማጠቃልያ ሃሳብን ይገልጣል
• ስም ዮሃ 1፥1 ዮሃ 1፥14 ቃል
• መ ) እነዚህን እናስተውል
• ጽዎታ _ ( ወንድ/ሴት ) ጽዎታ የሌለው _ እርሱም
• ቁጥር _ ( ነጠላ/ብዙ ) ገላ 3፥16
• ድርጊቱ የተፈጸመበት ጊዜ ( tense) ዕብ 1፥1_2
• ሠ) ቁልፍ ቃል በምንባቡ ውስጥ ምን ማለት እንደሆነ እወቅ
• ይሁዳ 3 “ እምነት” የሚለው ስም ሲሆን ትርጉሙ “ደህንነት”
ማለት ነው።
• ሮሜ 6፥1_12 የሚገኙትን ቁልፍ ወይም ሃረግ ጥቀስ
• በዕብ 11፥1_8 የሚገኙትን ቁልፍ ወይም ሃረግ ጥቀስ
አወቃቀር
• ምንባቡ እንዴት እንደተደራጀ ወይም እንደተመሰረተ ማወቅ መመልከት ነው።
• የምንከተለው መመሪያ
• 1 አንቀጽ በአንቀጽ ማጥናት
• አንቀጽ አንድን ወይም ከአንድ የበለጠን አረፍተ ነገር ሆኖ አንድን ሃሳብ የሚገልጥ ነው።
ቆላ 2፡6_12
• 2 አንቀጽ እንዴት እንደተዋቀረ መመልከት።
• በሰዎች ታሪክ _ለምሳሌ ; ዘፍ 12_ 50 አብርሃም፤ ይሳቅ፤ያቆብ፤ዮሴፍ _ ሃዋ 1_12
ጴጥሮስ _ ሃዋ 13_28 ጳውሎስ
• በቦታ አቀማመጥ_ ዘጸአት
• በታሪክ ክስተት_ ኢያሱ
• በስነ መለኮት ሃሳብ _ሮሜ
• በጊዜ ቅደም ተከተል_ 1እኛ 2ኛ ነገስት
አወቃቀር
• 3 ምንባቡ የተፈጸመበት መንፈስ ወይም በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ
እንደተጻፈ መርምር።
• የተጻፈበት መንፈስ; ማለት ምንባቡ የተጻፈበት መንፈስ ወይም ሁኔታ
ሆኖ በአንባቢው ላይ የሚፈጥረው ስሜት ነው።
• ለምሳሌ; ማር 16፡9_14 _ጥርጥር ወይም አለማመን
• 4 የስነ ጽሁፍ አይነት
• ቃሎችን መመልከትና አወቃቀሩን ማየትና የተጻፈበትን መንፈስ መረዳት
ብቻ በቂ አይ ደለም ሌላ የሚያስፈልግ ነገር አለ የአጻጻፍ ስልቱን ማወቅ
ለአተረጓጎም በጣም የሚጠቅም ሃሳብ ነው።

መጸሃፍ ቅዱስ ውስጥ አራት ዋና ዋና የስነ ጽሁፍ አይነቶች
አሉ።
• 1ኛ ትረካ ( narrative)_ አንድን ታሪክ እና እውነት በምሳሌ፣በእውነታ፣በሰዎች
ታሪክ ላይ በማስደገፍ መለኮታዊ እውነታን እንድንረዳ የሚያደርገን የስነ ጽሁፍ አይነት
ነው።
• የትረካ በሃሪ_ እውነትን የሚገልጠው በተዘዋዋሪ መንገድ ነው።
• በአእምሮ ውስጥ ጥልቅ ስሜትን ይፈጥራል።
• ብዙውን ጊዜ የባህሪን እድገት ወይም ውድቀት ይገልጣል
• ለምሳሌ, ዮሴፍና ሳምሶን
• በተግባር ላይ ልናውለው የምንችለውን መመሪያ ይሰጠናል።
• በአንድ ጊዜ ቀጥተኛ ትእዛዝ ሊይዙ ይችላሉ
• 2ኛ ትምህርታዊ ስብከት ( discousse)_ ህጋዊ እና ቅደምተከተሉን የጠበቀ ሆኖ
በደብዳቤ ወይም በትምህርት ወይም በስብከት መልክ አንድን ሃሳብ ወይም እውነት
ወይም አስተምሮ የሚያሳይ የስነ ጽሁፍ አይነት ነው።
= ባህርዩ _ እውነትን በቀጥታ ይገልጻል
= በአእምሮ ውስጥ እውቀትን ይሰታል
= ግሳጼን እና ትእዛዝን የያዘ ነው
= ወደ ውሳኔ ወይም ወደ ድምዳሜ ያደርሳል
ለምሳሌ ሮሜ, ኤፌሶን የተራራው ስብከት የመሳሰሉት
3ኛ ቅኔ ወይም የቅኔ መጸሃፍ
=በውስጣቸው ድብቅ መልክትን የያዙ ጽሁፎች አንድን እውነት ለማስረጽ የምንጠቀምባቸው
ገላጭና ተምሳሌታዊ አነጋገሮች ናቸው።
= በቀጥታ የማይወሰዱ ቃላቶች ሆነው መልክታቸውና ሊያስተላልፉት የሚፈልጉት መልክት ግልጽ
ነው
= ስሜትን ይቀሰቅሳሉ
= ትኩረት ለመስጠት _ ሃሳብን ለማጠናከር እና ለማነጻጸር ይጠ ቅማሉ
4ኛ ትንቢትዊ,_ አንድን ያልታወቀ እውነት ለመግለጽ የምንጠቀምበት
ምልክታዊ አነጋገር ነው።
= ባህሪው ወደ ፊት ያልታወቀን ነገር መግለጥ ነው;።
= በአብዛኛው ምልክትንና ስዕልን፤ ዘይቤን በመጠቀም እውነትን ይገልጣል
= ስለ ወደ ፊት ይተነብያል
= በጥንቃቄ መተርጎም ያለባቸው ራዕይ የያዙ ናቸው።
ኢሳያስ; ኤርሚያስ; ዳንኤል; ህዝቄል; ዘካርያስ
= አደጋው ያለመመሪያው መፍታትና ስእላዊ መግለጫዎችን አለማወቅ ነው።
= ትክክለኛ ትርጉሙን ለማወቅ የስነ ጽሁፉን አይነት ማየት ወሳኝ ነው።
መተርጎም
• መተርጎም ማለት ምን ማለት ነው ?
• መተርጎም የመጸሃፍ ቅዱስ ጥናት ሁለተኛ ደረጃ ነው
• አላማው_መጀመሪያ ሲጻፍ ሊባል የተፈለገውን እውነት ፈልጎ ማግኘት ነው
• እግዚአብሄር ሊል የፈለገውን ትርጉም ካላገኘን የእግዚአብሄርን ቃል አገኘን ወይም ተረዳን
ማለት አንችልም 1ጴጥ 1፡20_21 ም
• ምን እናድርግ ወደሚለው ተግባር ከመግባታችን በፊት መመልከትና በአግባቡ መተርጎም
ተገቢ ነው።
• መጠየቅ ያለብን ቁልፍ ጥያቄዎች ,
• = ምን ማለት ነው ? ሃዋ 8፡30_31
• = ጥቅሙ ምንድ ነው ? ሮሜ 9፡10_13
• = የዚህ ምንባብ አላማ ምንድ ነው ? መጀመሪያ የጻፈው ሰው ምን ሊል ፈልጎ ነው ?
• = ከሙሉ የመጸሃፉ ክፍል ጋር እንዴት ይስማማል ?
ወደ አተረጓጎም ከመሄዳችን በፊት ልንገነዘበው የሚገባ
ጉዳይ
• 1ኛ መጸሃፉ ሲጻፍ የነበበረበት ሁኔታ እኛ ካለንበት ሁኔታ ፍጹም የተለየ መሆኑን
• ታሪካዊነቱ ( ከብዙ መቶ አመት በፊት የተጻፈ መሆኑን )
• ቦታ መልካም ምድሩ
• ቋንቋው ( እብራይስጥ፤ ግሪክ፤ አረማይክ ) መሆን
• አጻጻፉ ( ጸሃፊውና አንባቢው የተለያዩ መሆናቸው )
• እነዚህ ሁኔታዎች መጸሃፉ ሲሳፍ የነበረውን ትርጉም እንድናውቅ ስለሚረዱን በጥንቃቄ መጠናት አለባቸው። ዘዳ
29፡19
• 2ኛ መጸሃፍ ቅዱስ የተለያዩ የስነ ጽሁፍ አይነቶች እንደያዘ ግምት ውስጥ ማስገባት።
• 3ኛ መጸሃፍ ቅዱስ አንድ የሆነ እና ተከታታይነት ያለው መለኮታዊ መገለጥ ነው።
• 4ኛ ብሉይ ኪዳን ያለ አዲስ ኪዳን ሙሉ አይደለም አዲስ ኪዳን ያለብሉ ኪዳን ብርሃን መረዳት አንችልም።
• 5ኛ የእግዚአብሄርን የቃሉን እውነት በመንፈስ የምንረዳው እና የምንቀበለው ነው። 1ኛቆሮ 2፡14
• የመጸሃፍ ቅዱስን እውንተኛ ትርጉም ለማግኘት
• ሀ በትጋት ማጥናት
• ለ በመንፈስ ቅዱስ ተደገፍ
• ሃ የመተርጎም መመሪያን ተከተል
የመተርጎም ዋነኛ መመሪያዎች
• 1ኛ በቀጥታ መተርጎም (እንዳለ እንደተጻፈ መተርጎም)
• ሀ ) በቀጥታ የተጸፈ ግን ስእላዊ ያልሆነ
• ለምሳሌ, ዘፍ 2፡7 ዮሃ 8፡24 ዕብ 9፡27
• ለ ) በቀጥታ የተጻፈ ዘይቤያዊ
• ምልክታዊ ወይም ዘይቤያዊ አነጋገር ሆነው ግልጽ የሆነ
ሃሳብን፤ትርጉምን፤እውነትን የያዙ ናቸው።
• ሉቃ 13፡31_32 ሄረደስ_ ቀበሮ ኤር 17፡1
• ቃልን ለመተርጎም የሚጠቅሙን
• = መዝገበ ቃላት
• = በሌላ ክፍል ምን ትርጉም አላቸው
• = አውዱላይ ያለው አግባብነት
የመተርጎም ዋነኛ መመሪያ
• 2ኛ በአውዱ መተርጎም
• የክፍሉን ሃሳብ በሙሉ በማየት መተርጎም ነው
• እያንዳንዱ ጥቅስም ሆነ ምንባብ የት እንዳለ፤ምን
እንደሚቀድም፤ምን እንደሚከተል፤ከሌላ የመጸሃፍ ቅዱስ
ክፍልም ጋር በማዛመድ አውዱን ጠብቀን መተርጎም
• አውድ ጥቅስ, አረፍተ ነገር, ምንባብ, አካባቢ ያሉ ምንባቦች
ወይም ምዕራፉን ሁሉ ማንበብ, ሙሉ መጸሃፉን ማንበብ
• አውድ ንጉስ ነው = ለአተረጓጎም ዋና እና አስፈላጊ ነው።
• ማቴ 19፡1_11 ዘፍ 9፡3 1ኛቆሮ 7፡1
አውዱን ለማወቅ የሚጠቅሙ ጠቃሚ ነጥቦች
• 1ኛ ሙሉውን መጸሃፍ ማንበብ ሃጌ 1_5
• 2ኛ ባነበብ ነው ምንባብ ላይ የሰላ አመለካከት ይኑርህ
• ለምን እዚጋር ተጻፈ?
• ከላይና ከታችኛው ጋር ምን ዝምድንና አለው ?
• ከሙሉ ምንባብ ጋር ከሙሉ ምዕራፉ ጋር ከሙሉ መጸሃፉ ጋር ምን ዝምድና አለው።
• 3ኛ እነዚህን በውስጡ ፈልግ
• ዋና አላማ
• የመጸሃፉን ዋና ዋና ክፍሎች ( ለስንት ተከፈለ )
• ዋና ዋና ሰዎች
• ጠቃሚው ክስተት የቱ ነው
• በመሃሉ ያለው ውድድር
• ንጽጽሩን
• መለኮታዊ ሃሳቡ
• ጡዘት ( የት ተጀመረ የት አለቀ )
• 4ኛ ወደፊትና ወደኋላ ያለውን አስብ
• 5ኛ በሰንጠረዥ መልክ አስቀምጠው
የመተርጎም ዋነኛ መመሪያ
• 3ኛ በታሪኩና በባህሉ መሰረት ተርጉም
• ባህ ላዊና ታሪካዊ መሰረቱን በማየት ተርጉም
• ለምሳሌ, ሃዋ 15፡1_35
• ባህል በተወሰነ ቦታና ጊዜ ህዝብ የሚያምነው = የሚለው= የሚያምነው=
የሚሰራው= የሚለብሰው= የሚበላው እና የሚለማመደው ነገር ነው። 1ኛቆሮ
11፡2_16፤መክ12፡11፤ሃዋ9፡15
• 4ኛ በስነ ጽሁፉ ይዘቱ መተርጎም
• ትምህርት፤ትረካ፤ትንቢት፤ቅኔአዊ ነው።
• ቅኔአዊ= ዘይቤአዊ አነጋገሮች እና ምልክታዊ ቆንቆዎች አሉት።
• ምሳሌ= መዝ 19፡1_4 ዘፍ 22፡1_2
• 5ኛ ከሌላ ጥቅስ ጋር በማዛአመድ መተርጎም።
አስቸጋሪ እና ከባድየሆኑ ምንባቦችን ለመፍታት
የሚጠቅም መመሪያዎች
• 1ኛ መጸሃፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ አይቃረንም።
• ዘጸ 20፡5_6፤ህዝ 18 1_4፤ህዝ 19፡20
• 2ኛ ከተወሳሰቡ ትርጉም ይልቅ ቀላልና ቀጥተኛ ትርጉምመምረጥ።
• 3ኛ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን አንዱ ሌላኛውን እንድንረዳ
ይረዳናል። ዘፍ 3፡1፤ ራዕ 12፡9
• 4ኛ አጠራጣሪ እና ግልጽ ያልሆኑ ምንባቦችን ግልጽ በሆኑ ምንባቦች
ተርጉም።
• ሃዋ 2፡38 ለጥምቀት ከዚህ ክፍል ይልቅ ግልጽ የሆኑ ክፍሎችን
መጠቀም
• ዮሃ 3፡16፤ ሮሜ 10፡12_13 ሃዋ 8፡12_13
• 5ኛ አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳንን ጥቅስ ሲጠቀም ቃል በቃል ላይሆን ይችላል
ወይም መጠነኛ ልዩነት አለው።
• 6ኛ ለእያንዳዱ የመጸሃፍ ክፍል ከሌላ ቦታ ማረጋገጫ ላናገኝ እንችላለን። ዘፍ
34፡13_31
• 7ኛ በተለያየ ቦታ የተጻፉ አንድ አይነት ታሪኮች ተቃራኒ ሳይሆኑ ተደጋጋፊ
ናቸው። ማቴ 20፡29_34፤ሉቃ 18፡35_43
• 8ኛ አንዳንድ የቁጥር ስህተቶች የጸሃፊው ስህተት ሊሆን ይችላል። 2ኛሳሙ
15፡7 ፤ 2ሳሙ 4፤ 2ሳሙ 40
• 9ኛ ለአንዳንድ ጥቅሶች ትርጉም መስጠት አለመቻላችን ጥቅሱ ስህተት ነው
አያስብለንም እውቀት አንሶን ሊሆን ይችላል።
• ሮሜ 11፡33_36
ልዩ የአተረጓጎም መመሪያ
• አንዳንድ የመጸሃፍ ቅዱስ ስነ ጽሁፎች የተለየ የአተረጓጎም ስልት ይፈልጋል።
• 1ኛ ተምሳሌታዊ አነገሮች ( parables)
• በማቴዎስ፤በማርቆስ፤በሉቃስ፤ እንዲሁም በሌሎች የመጸሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ይገናል።
• ተምሳሌት; ማለት; አንድ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ በየቀኑ ከሚገጥመን የህይወት ገጠመኝ የሚወሰድ ታሪክ ነው።
• ምሳሌ ማለት , መንፈሳዊትርጉም የሚሰጠን በምድር ላይ የሚሰራ ታሪክ ሆኖ
• አንድን ቁልፍ እውነት የሚያስረዳ፣አንድ ዋና ነጥብ ያለው፣አንድን እውነት የሚገልጥ ወይም የሚያብራራ
ነው። ማቲ 20፡1_16
• ተምሳሌትን ለመተርጎም የሚረዱን
• የታሪኩን ቀጥተኛ ትርጉም ምን እንደሆነ ለመረዳት መሞከር
• ምክንያቱ ተገልጦ ከሆነ ምሳሌው የተሰጠበትን ምክንያት ያስተውሉ
• ዋናውን ትምህርት ወይም መአከላዊ ነጥቡን ያግኙ
• ታሪኩን ለመረዳት ችግር ካጋጠመ ችግሩን ለመፍታት የሚረዱ ባህላዊና ታሪካዊ ሁኔታን ማገናዘብ ይረዳል።
• ትምህርቱን ከቅዱስ ቃሉ ቀጥተኛ ትምህርት ጋር ያገናዝቡ
• መቼና የት ተጻፈ ታሪኩንና ተዛምዶውን ልናውቅ ይገባል።
ልዩ መመሪያ
• 2ኛ ምሳሌ(proverb )
• ምሳሌ እንዴት በጥበብ መኖር እንደምንችል የሚያስተምሩንን እውነቶች ያሳየናል።
• ጥበብ የተሞላ አነጋገር ነው
• እንዴት መኖር እዳለብን የሚያሳይ የእግዚአብሄር ጥበብ ነው
• ቀላል እውነትን የያዘ አረፍተ ነገር ነው።
• መመሪያ ያስተምረናል እንጂ ተስፋ አይሰጠንም
• በአብዛኛው በህይወታችን የሚሰራ ዋና መመሪያ እናገኛለን
• በአብዛኛው በሞኝና በብልህ ሰው መካከል በማወዳደር እና በማነጻጸር ይገለጣል
• ብልህ ሰው እግዚአብሄርን እንደሚያውቅና ህይወቱን በስርአት እደሚመራ ያሳየናል
• ዘይቤአዊ አነጋገሮችን የያዘ ነው
• የመዝራትን እና የማጨድን ህግ ያብራራል
• ምሳሌ 5_7
• በእውቀትን (knowledge observation)
• በመረዳት(understanding interpretation)
• በጥበብ መኖር ( wisdom aplication) ያለውን ልዩ ነት ያሳያሉ ጠቃሚ ምክር ይሰጠናል።
ልዩ መመሪያ
• 3ኛ ቅኔ(poetry)
• የእብራውያን ቅኔ,,
• ቤትአይመታም፣
• በሁለቱ ግንዶች መሃል የሚስማማው ሃሳብ ነው( ሃሳብ ነው የሚመታው)
• ብዙ ዘይባዊ እና ምልክታዊ ቃላቶችን ይይዛል
• ብዙ ጊዜ የሁለተኛው መሥመር ስለ መጀመሪያው መስመር የሚለው አለው
• 1 ያንኑ እውነት ይደግማል ምሳ 9፡9
• 2 ያንኑ እውነት ያብራራዋል ምሳ 24፡1_2
• 3 የአንድን ነገር መነሻ እና ውጤት ይገልጣል ምሳ 16፡3 ምሳ 5፡22
• 4 ንጽጽርን ወይም ውድድርን ያሳያል ምሳ 9፡8
• መመሪያ
• 4ኛ ዘይቤያዊ አነጋገሮች
• ዘይቤያዊ አነጋገር , በአእምሮ ውስጥ ምስል የሚፈጥር ያልተሰወረ የቃል አገላለጽ ነው
• ዘይቤያዊ አነጋገር የምንጠቀመው
• 1 እውነትን ለማጠከር
• 2 ትኩረት ለመጨመር
• 3 ሃሳቡን ለማጉላት
• 4 ስሜትን ለመቀስቀስ
• 5 ጥልቀት ለመስጠት
• 6 የተደበቀን ሃሳብ ለመግለጥ
ልዩ መመሪ
• 5ኛ ምልክት ( smbol)
• ምልክት አንድን ነገር ግልጽ ለማድረግ ነገሩን ወክለን የምንጠቀምበት ቃል ነው።
• ምልክት ከአንድ የበለጠ ነገር ወክሎ ልናገኘው እንችላለን 1ኛ ጴጥ 5፡8 ራእ 5፡5
• መንፈስ ቅዱስ _ውሃ, ዘይት, ንፋስ, እርግብ
• የእግዚአብሄር መገኘት _ደመና, እሳት
• ሰይጣን _ ዘንዶ, እባብ
• ስልጣን _ ቁልፍ
• ልዩ መመሪያ
• 6ኛ አምሳያ ( type, typolgy)
• አምሳያ_ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉትን ሁኔታ የሚያመለክት የብሉይ ኪዳን ሁኔታ ነው
• ሮሜ 5፡12 1ኛ ቆሮ 15፡22 ፤15፡44_49 አዳም በክርስቶስ ተመስሎል
• ዘጸ 12፡21_23 1ኛቆሮ 5፡7
• ዘፍ 14፡17_20 ዕብ 5፡5_10 ፤ 7፡1_17
• ዘኁ 21፡4_9 ዮሀ 3፡14_15
ልዩ መመሪያ
• 7ኛ ትንቢት
• ትንቢትን ለመተርጎም የሚረዱን ነገሮች
• 1 ተመሳሳይና አንድ አይነት ምንባቦችን በማወዳደር ( ዳንኤል እና ራዕይ ) ራዕይ 13፡5 ዳን 7፡25
• 2 በተነገረበት እና በተፈጸመበት መሃከል ብዙ የጊዜ እርቀት እንዳለ አስብ
• 3 የተፈጸሙት እና ገና ሊፈጸሙ ያሉትን ለይ
• 4 ዘይቤያዊ አነጋገሮችን እና ምልክቶችን በጥንቃቄ መተርጎም
• 5 አተረጓጎሙ ከሌሌላ የመጸሃፍ ክፍል ጋር አለመጋጨቱን አረጋግጥ።
• በአዲስ ኪዳን ውስጥ የብሉይ ኪዳን አጠቃቀም
• አስፈላጊነቱ
• 1 ከ100 በላይ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይገኛሉ
• የአዲስ ኪዳን 10% የብሉይ ኪዳን ጥቅስ ነው።
• 2 ብሉይ ኪዳንም አዲስ ኪዳንም ደራሲያቸው መንፈስ ቅዱስ ነው
• 3 አዲስ ኪዳንን ለመረዳት ብሉይ ኪዳን እጅግ አስፈላጊ ነው
• አዲስ ኪዳን ብሉይ ኪዳንን እንዲት ይጠቀማል ?
• 1 መግቢያ ቃላቶችን በመጠቀም ማቲ 4፡6, ማቲ 1፡22, ሮሜ 4፡3
• 2 ከአንድ የበለጠ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች በመቀላቀል
• 3 በብሉይ ኪዳን ያለውን ቃል ለወጥ አድርገው ይጠቀማሉ ሮሜ 15 ከ ኢሳ 11፡12 ሀዋ 28፡6 ከ ኢሳ 6፡9_10
• ብሉይ ኪዳንን በአዲስ ኪዳን የመጥቀስ አላማ
• 1 የትንቢትን ፍጻሜ ለማሳየት 2 የብሉይ ኪዳንን የእውነት መመሪያ ለማረጋገጥ 3 ትኩረት ለመስጠት ሮሜ 10፡8 ከ ዘዳ 30፡14
የመተርጎም ዋነኛ ችግር
• መጸሃፍ ቅዱስ ስንተረጉም መወገድ ያለባቸው ሶስት ነገሮች
• 1 ያልተሟላ ትርጓሜ_ ይህ የሚከሰተው አንቀጹን ሙሉ ለሙሉ
ማየት ሲያቅተን ነው
• 2 የተጋነነ ትርጓሜ _ ይህ የሚከሰተው መጸሃፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ
ስናነብ ነው ወይም ከሃሳባችን ወደ መጸሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስንገባ
ነው።
• 3 ስህተት ያለበትትርጉም ትርጓሜ _ በትጋት ካለማጥናት በደንብ
ካለመመልከት እና በመንፈስ ቅዱስ ካለመደገፍ የተነሳ የሚከሰት
ነው።
• ሁል ጊዜ የተሳሳተ ትርጉም ውደተሳሳተ ተግባር ያመራል/
መተግበር፣ ማዛመድ፣ ለእግዚአብሄር ቃል መልስ
መስጠት
• የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት ሶስተኛው ደረጃ ነው
• ልንጠይቃቸው የሚገቡ ቁልፍ ጥያቄዎች
• ምን ላድርግ ?
• እዴት በህይወቴ ይሰራል?
• ወደ ተግባር እንዴት ልለውጠው ?
• ስንሰብክና ስናስተምር ትኩረት መስጠት ያለብን
• ወደ ውሳኔ የሚያደርስና ጉልህ የሆነ ( significant)
• ለመረዳት የቀለለ
• ለመከተል አጭር የሆነ
• ለመለወጥ መንፈሳዊ የሆነ መሆን አለበት
• በምንባቡ ውስጥ ያለውን ግዜ የማይሽረውን እውነት ወይም መመሪያ የሆነውን ነገር ማቅረብ ይገባል
• በተግባር ለማዋል በውስጥህ ያለውን ወይም የሚኖረውን መንፈስ ቅዱስን ተደገፍ
• ሌላው ማስተዋል የሚገባን የማዛመድ ግብ
• 1 ህይወትን ለመለወጥ ነው
• 2 ኢየሱስን እንድንመስል ነው 2ቆሮ 3፡18 1ዮሀ 3፡2
• “አንተም ከመጸሃፉ ጋር መጸሃፉ ከአንተ ጋር ተዛመዱ”
• “እየጸለያቹ አንብቡ እያነበባቹ ጸልዩ”

You might also like