Professional Documents
Culture Documents
**************************************
በክርስትና ሁልጊዜ የማሸነፉ ጥበብ በሚገጥመን ማንኛውም ፈተና ማድረግ የምንችለውን አድርገን
ለእግዚአብሄር ፈንታ በመስጠቱ ላይ ነው፡፡ መንፈሳዊ ነገር የእግዚአብሄርና የሰው የአጋርነት ስራ ነው፡፡ እኛ
መስራት የማንችለው እግዚአብሄር የሚሰራልን ነገር አለ፡፡ እኛ ደግሞ የምንሰራው ነገር አለ፡፡ ታዲያ የእኛን ስራ
ሰርተን ለእግዚአብሄር ፈንታ መስጠት ብልህነት ነው፡፡ ከመጣባቸው ከታላቅ መከራ የተነሳ ወደ እግዚአብሄር
የጮሁና እግዚአብሄር በድንቅ የመለሰላቸው ሰዎች ምስክርነት የተሞላ መፅሃፍ ነው መፅሃፍ ቅዱስ፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ
እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ፊልጵስዩስ 4፡6
3. ምስጋናን አለመተው
በውጥረትም ጊዜ እግዚአብሄር ከእኛ ምስጋናን ይጠብቃል፡፡ እንዲያውም እውነተኛ ትህትናችን የሚለካው
በፈተና ጊዜ ስናመሰግነው ነው፡፡ እውነተኛ የምስጋና መስዋእት የሚባለው ላለማመስገን ብዙ ምክኒያቶች
ያገኘን ሲመሰለን ያንን የስንፍና ሃሳብ ሁሉ አልፈን የምናመሰግነው ምስጋና ለየት ያለ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ
የማጉረምረም ትምክታችንን ዋጥ አድርገን የምንሰጠው በቀላሉ ያልመጣ የምስጋና መስዋእት ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን
ስጥ፤ መዝሙር 50፡14
4. እምነትን አለመጣል - ፍርሃትንና ጥርጥርን አለማስተናገድ
እምነት ብቸኛው የማሸነፊያ መንገዳችን ሰለሆነ ውጥረቶች በህይወታችን የሚመጡት እምነታችንን
ሊያስጥሉ ነው፡፡ እምነታችንን ካላስጣሉን ውጥረት አይሳካለትም አላማውም ተጨናግፏል፡፡ የውጥረት
አላማው ፈተናውን ማግዘፍና እግዚአብሄርንም ማሳነስ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያሳስ ሃሳብ በልባችን
አለመፍቀድ ውጥረትን በአሸናፊነት እንድናልፈው ይረዳናል፡፡ ፈተና በፍርሃት ከምነሄደው ጉዞ ካስቆመን ብቻ
ነው ስኬታማ የሚሆነው፡፡ ጊዞዋችንን ከቀጠልን ወደፈተና ሳንገባ እናልፈዋለን፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥
አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳይያስ 40፡28
ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው። ማርቆስ 5፡36
6. ደስታን አለመተው
በውጥረት ጊዜ ደስታን መተው አይገባንም፡፡ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ያለውን የእግዚአብሄርን ቃል ትእዛዝ
መተው የለብንም፡፡ ደስ ይበላችሁ ብሎ ካዘዘ ይቻላል ማለት ነው፡፡ ደስታ የውሳኔ ጉዳይ እንጂ የስሜት ጉዳይ
አይደለም፡፡ ደስ እንዳይለን ምንም ምክኒያት የለንም፡፡ እግዚአብሄር እረኛችን ነው የሚያሳጣንም የለም፡፡
አባታችን እግዚአብሄር ከመሆኑ በፊት ሁሉን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስደንቀው ነገር የለም፡፡ ፈተናው
በእኛ ላይ የሚያራግፈው የማያስፈልገውን ነገር ብቻ እንጂ እኛን አያገኘንም፡፡ በፈተና ሙሉ የሚያደርገንና
ወደሚቀጥለው ደረጃ የሚያሸጋግረን እድገት ስለሚመጣ ደስ ይበለን፡፡