You are on page 1of 8

2

ጥናት

እግዚአብሔር
.4
መንፈስ ቅዱስ
የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር ደቀ መዝሙርነት ትምሕርት ቤት
AY Bible Club Discipleship University

የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር


ስልክ ቁጥር፡ +251 11 551 3202
ኢሜይል፡ aybibleclub@gmail.com
ከጋንዲ ሆስፒታል ፊት ለፊት ፍልውህ አድቬንቲስት ቤተከርስቲያን
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
በኃጥያት መውደቃችን የመለኮትን ንግግር በቀጥታ እንዳንሰማ አድርጎናል። እግዚአብሔር
አምላክ በቀጥታ ሊናገረን ስላልቻለ በጸጋው በተለያዩ መንገዶች የፍቅር ቃሉን ላከልን።
መ ግቢያ
በበዙ ዘመናት በተለያዩ መንገዶች ከተናገረን በኋላ ልጁን በመላክ በመጨረሻው ዘመን
በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ተናገረን። ቃሉ ሥጋ በመሆነ ጸጋንና እውነትን ተመልቶ
በመካከላችን ተመላለሰ። ሙት የሆነው መንፈሳዊ ጆሮአችን ሊሰማው ስላልቻለ እንደጠላት
ቆጠርነው። ሥጋዊው ጆሮ የሥጋን እንጂ የመንፈስን ድምጽ ሰለማይሰማ በፍቅር ሲቀርበን
አልተቀበልነውም። “የምናገራችሁን ሁሉ አሁን ልታስተዉሉት አትቸሉም” በማለት በመንፈሳዊ
ጎዳና የጀመርነውን እድገት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታው እንድንቀጥል አደረገ።

የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት በሰው ሁለንተዊ የሕይወት ግንኙነትና ብልፅግና ላይ ወሳኝ


ተፅዕኖ አለው። ለማህበረሰብ ደህንነት መሰረታዊ የሆኑ፤ የቤተሰብን ጥምረት ጠብቆ ለማኖር
የሚጠቅሙ፤ ለአንድ አገር ብልፅግና የመሰረት ድንጋይ የሆኑ፤ ለግለሰብ የአላማ ጥንካሬ፤
ደስታ፤ ሞገስና የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ማረጋገጫ የሚሆኑ መሰረታዊ መመሪያዎችን
ይገልጣል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወሳኝ መዘጋጃ የማይሆንበት ምንም አይነት የሕይወት
ደረጃና ልምምድ የለም። የእግዚአብሔር ቃል ሲጠና እና ሲነብብ የሰው ፍልስፍና ከሚሰጠው
ጠቅላላ እውቀት በላይ ጠንካራ እና ሕያው የሆነ የአዕምሮ ጥንካሬን ይሰጣል። ለሰዎችም
የባህርይ ጥንካሬ፤ አስተማማኝነትን፤ ማስተዋልን እና መልካም ፍርድን እየሰጠ ለእግዚአብሔር
ክብርና ለአለም በረከት ያሳድጋቸዋል።

የእግዚአብሔር ቃል ሕይወታችንን በሙሉ የሚቆጣጠር፤ የኑሮ መመሪያችን፣ የሕሊና ሕጋችን


ሊሆን ይገባዋል። የንግግራችን መለኪያ፤ የቃላችን መሰረት፤ የፍርዳችን መነሻ፤ የእምነታችን
ምክንያት፤ የዝማሪያችን ምንጭ፤ የመነሳትና የመቀመጣችን እንዲሁም ሁለንተናችን ነው።
የትምህርት፤ የቤተሰብን፤ የስራ፤ የእረፍት፤ የማንነት፤ የኢኮኖሚ መሰረታችን የእግዚአብሔር
ቃል ይሁን። ወደ ከነዓን ከመግባታቸው ትንሽ ቀደም ብሎ እግዚአብሔር ለእስራኤላዉያን
ያስታወሳቸው ይህንኑ ነበር። “እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ።
ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥
ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል
እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው”። ኦሪት
ዘዳግም 6:6-9

ይህ ትምህርት እርስዎንና ቤተሰብዎን በእግዚአብሔር ቃል ለማነጽ፤ እንዲሁም የኢየሱስ ደቀ


መዝሙር በመሆን ለሌሎች ይህን የከበረ ቃል ያሰሙ ዘንደ ለማስታጠቅ የተዘጋጀ ነው። በጸሎትና
በትጋት ሲጠና መንፍስ ቅዱስ ሕይወትን በቃሉ ይለውጣል። በሁሉም ቦታ የክርስቶስን መንፈስ
ለማንጸባረቅ ያግዛል።

የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር


ደቀ መዝሙርነት ትምሕርት ቤት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
 ማንም መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ተወዶ፣
ተጠልቶ፣ ተከብሮ፣ ተረግሞ አያውቅም። ብዙ ሰዎች
ለመጽሐፍ ቅዱስ ሲሉ ሞተዋል። ሌሎች ደግሞ ስለ
እርሱ ሲሉ ገድለዋል።

የትምህርቱ መመሪያ

1. ይህ ትምህርት በግል፤ በቤተሰብ ወይም በቡድን መጠናት ይችላል

2. ይህን ጥናት ለመጨረስ የአንድ ሳምንት ጊዜ አለዎት

3. በሳምንት መጨረሻ ላይ ጥያቄዎችን በኢሜይላችን ወይም


በቴሌግራም ልኮ መጠየቅ ይቻላል

4. በግል ማብራሪያ ካስፈለግ በታች በተጠቀሰው እድራሻ ቢሮአችን ብቅ


ቢሉ የሚፈልጉትን እርዳታ ያገኛሉ

5. ይህን ትምህርት ሲጨርሱ ቀለል ያሉና ለማስታወስ የሚያግዙ


ጥያቄዎችን እንልክልወታለን

እግዚአብሔር ይባርካችሁ
መግቢያ
ዘላለማዊው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፍጥረት፣ መለኮት ሥጋ በመልበሰና በድነት ሥራ ከአብና ከወልድ
ጋር አብሮ ሰርቷል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎችን አነሳስቶአቸዋል፡፡ የክርስቶስን ሕይወት በኃይል ሞልቶአል፡፡
ሰብዓዊ ፍጡራንን በመዝለፍ ወደ እግዚአብሔር ይመልሳል፤ ምላሽ የሚሰጡትንም በማደስ ወደ እግዚአብሔር
አምሳል ይለውጣቸዋል፡፡ ሁልጊዜ ከልጆቹ ጋር እንዲሆን በአብና በወልድ ስለተላከ ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ
ሥጦታዎችን ይሰጣል፣ ለክርስቶስ ምስክር እንድትሆን ኃይል ይሰጣታል፣ ከቅዱሳት መጽሐፍት ጋር በተጣጠመ
ሁኔታ ወደ እውነት ሁሉ ይመራታል (ዘፍ.1፡1፣2፤ ሉቃስ 1፡35፤ 4፡18፤ የሐዋ.10፡38፤ 2ጴጥ.1፡21፤ 2ቆሮ.3፡18፤ ኤፌ.4፡
11፣12፤ የሐዋ.1፡8፤ ዮሐ.14፡16-18፣26፤ 15፡26፣27፤ 16፡7-13)፡፡

ምንም እንኳን ስቅለቱ የክርስቶስን ተከታዮች ግራ ቢያጋባቸውም፣ ቢያሳዝናቸውም፣ ቢያስፈራቸውም፣ ትንሣኤው


ለሕይወታቸው ንጋትን አመጣላቸው፡፡ ክርስቶስ የሞትን ሰንሰለት በበጠሰ ጊዜ የእግዚአብሔር መንግሥት በልባቸው
ነጋ፡፡ አሁን ሊጠፋ የማይችል እሳት በሕይወታቸው ውስጥ ተቀጣጠለ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አስቀያሚ ግርዶሽ
አስቀምጠው የነበሩ ልዩነቶች ቀለጡ፡፡ ስህተታቸውን ለእርስ በርስ ተናዘው ያረገውን ንጉሣቸውን ኢየሱስን ለመቀበል
ራሳቸውን የበለጠ ክፍት አደረጉ፡፡

አንድ ወቅት ተበታትኖ የነበረው የዚህ መንጋ አንድነት በየቀኑ በፀሎት በቆዩ ቁጥር እያደገ ሄደ፡፡ በአንድ ሊረሳ በማይችል
እለት እየፀለዩ ሳሉ እንደ ባህር ሞገድ ያለ ድምጽ በመካከላቸው ሰነጠቀ፡፡ በልባቸው ውስጥ ያለው መቃጠል እንደሚታይ
ነገር በእያንዳንዳቸው ራስ ላይ የእሳት ነበልባሎች ወረዱባቸው፡፡ እንደ ሰደድ እሳት መንፈስ ቅዱስ በላያቸው ወረደ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ከተሞሉ በኋላ ደቀ መዛሙርት በኢየሱስ ያገኙትን አዲሱን ኃይለኛ ፍቅርና ደስታ መቆጣጠር አልቻሉም፡
፡ የድነትን የምሥራች በሕዝብ ፊት በግለት መስበክ ጀመሩ፡፡ በሰሙት ድምፅ ተቀስቅሰው የአገሩ ነዋሪዎችና ከብዙ አገሮች
ለመንፈሳዊ ክብረ በዓል የመጡ ተጓዦች ወደ ሕንጻው ጎረፉ፡፡ በመደነቅ ተሞልተውና ግራ ተጋብተው በእነዚህ ባልተማሩ
ገሊላውያን አንደበት ይነገር የነበረውን አስደናቂ ምስክርነት በራሳቸው ቋንቋ ሰሙ፡፡

አንዳንዶች “ላስተውለው አልችልም፣ ይህ ምንድነው?” አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ “ሰክረዋል” በማለት ችላ ብለው ለማለፍ
ሞከሩ፡፡ ከሕዝቡ ጩኸት ከፍ ባለ ድምጽ ጴጥሮስ “እነዚህ የሰከሩ አይደሉም” ብሎ ጮኸ፡፡ “አሁን ከጧቱ ሦሥት ሰዓት
ነው፡፡ እናንተ ያያችሁትና የሰማችሁት እየሆነ ያለው ከሙታን የተነሣው ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ
ስላለ አሁን መንፈሱን እየሰጠን ስለሆነ ነው” አላቸው (የሐዋሪያት ሥራ ምዕራፍ 2)፡፡

መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?


መንፈስ ቅዱስ አካል የሌለው ኃይል አለመሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል፡፡ ‹‹እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና›› (የሐዋ.15፡
28) የሚለው አረፍተ ነገር የጥንቱ አማኞች መንፈስ ቅዱስን እንደ አካል አድርገው እንደ ተመለከቱ ያሳያል፡፡ ክርስቶስም
መንፈስ ልዩ አካል እንደሆነ ተናግሮአል፡፡ ‹‹እርሱ ያከብረኛል፣ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና›› (የሐዋ.16፡14)፡፡ ሦስት
አካል ስላለው አምላክ የሚናገሩ ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ አካል እንደሆነ ይገልጻሉ (ማቴ.28፡19፤ 2ቆሮ.13፡14)፡፡

መንፈስ ቅዱስ ማንነት አለው፡፡ እርሱ ይኖራል (ዘፍ.6፡3)፣ ያስተምራል (ሉቃስ 12፡12)፣ ይወቅሳል (ዮሐ.16፡8)፣ የቤተ
ክርስቲያንን ጉዳዮች ይመራል (የሐዋ.13፡2)፣ ይረዳል፣ ያማልዳልም (ሮሜ 8፡26)፣ ያነሳሳል (2ጴጥ.1፡21)፣ ይቀድሳልም
(1ጴጥ.1፡2)፡፡ እነዚህን ተግባራት ዝም ብሎ ኃይል፣ ተጽእኖ ወይም የእግዚአብሔር ባህርያት መፈጸም አይችሉም፡፡ እነዚህን
ሊያከናውን የሚችለው አካል ብቻ ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ በእውነት አምላክ ነው፡፡


መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን የሚመለከተው እንደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ጴጥሮስ ለአናንያ መንፈስ ቅዱስን በመዋሸት
‹‹እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም›› ብሎ ነገረው (የሐዋ.5፡3፣4)፡፡ ኢየሱስ ‹‹መንፈስ ቅዱስን መሳደብ›› ምህረት
የሌለው ኃጢአት መሆኑን የገለጸው ‹‹በሰው ልጅ ላይ ቃልን የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ላይ
የሚናገር ግን በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም›› በማለት ነበር (ማቴ.12፡31፣32)፡፡ ይህ እውነት
መሆን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ከሆነ ብቻ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ባሕርያትን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያገናኛቸዋል፡፡ እርሱ ሕይወት ነው፡፡ ጳውሎስ እርሱን ‹‹የሕይወት
መንፈስ›› ብሎ ይጠራዋል (ሮሜ 8፡2)፡፡ እርሱ እውነት ነው፡፡ ክርስቶስ ‹‹የእውነት መንፈስ›› ብሎ ጠርቶታል (ዮሐ.16፡
13)፡፡ ‹‹የመንፈስ ፍቅር›› (ሮሜ15፡30) እና ‹‹የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ›› (ኤፌ.4፡30) የሚሉ መግለጫዎች ፍቅርና
ቅድስና የእርሱ ተፈጥሮ አካል መሆናቸውን ያሳያል፡፡
መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ቻይ ነው፡፡ መንፈሳዊ ሥጦታዎችን ‹‹ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ›› ያከፋፍላል

ጥናት 2.4 | እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገጽ 1


(1ቆሮ.12፡11)፡፡ እርሱ በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡ ከሕዝቡ ጋር ‹‹ለዘላለም ይኖራል›› (ዮሐ.14፡16)፡፡ ከእርሱ ተጽእኖ ማንም
ማምለጥ አይችልም (መዝ.139፡7-10)፡፡ እርሱ ሁሉን ያውቃል፡፡ ‹‹መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳን ሳይቀር
ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው፡፡ በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው
ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም
አያውቅም›› (1ቆሮ.2፡10፣11)፡፡

የእግዚአብሔር ሥራዎችም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ በፍጥረትና ትንሳኤ ውስጥ ድርሻ ነበረው፡፡ ኢዮብ
‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፣ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ›› (ኢዮብ 33፡4) ብሎአል፡፡
ባለ መዝሙሩም እንዲህ ብሎአል፡- ‹‹መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠሩማል፣ የምድርንም ፊት ታድሳለህ (መዝ.104፡30)፡፡
ጳውሎስ ‹‹ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ
ሕይወትን ይሰጠዋል›› ብሏል (ሮሜ 8፡11)፡፡

መለኮታዊ የሆነውን ክርስቶስን ወደ አንዲት ግለሰብ፣ ወደ ማርያም የማምጣትን ተአምር መሥራት የሚችል በሁሉም
ቦታ መገኘት የሚችል ግላዊ የሆነ አምላክ ብቻ እንጂ ማንነት የሌለው ተጽእኖ ወይም ፍጡር አይደለም፡፡ በጴንጤቆስጤ
ቀን አንድ የሆነውን አምላክ-ሰው፣ ኢየሱስን፣ ለመቀበል ፈቃደኛ ለሆኑ ሁሉ በሁሉም ቦታ እንዲገኝ አደረገው፡፡

መንፈስ ቅዱስ በጥምቀት ቀመር (ማቴ.28፡19)፣ በሐዋርያት ቡራኬ (2ቆሮ.13፡14) እና ስለ መንፈሳዊ ሥጦታዎች
በተሰጠው ገለጻ (1ቆሮ.12፡4-6) ውስጥ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል እንደሆነ ተገልፆአል፡፡

መንፈስ ቅዱስና ሥላሴ


ከዘላላም ጀምሮ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሥላሴ ጋር ሦስተኛው አባል ሆኖ ኖሮአል፡፡ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ
እኩል በራሳቸው የሚኖሩ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ከሌላው ጋር እኩል ቢሆንም በሥላሤ ውስጥ የሥራ ድርሻ አለ (ጥናት
ሁለትን ይመልከቱ)፡፡

ስለ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እውነቱን በደንብ መረዳት የሚቻለው በኢየሱስ አማካይነት ሲታይ ነው፡፡ መንፈስ ወደ
አማኞች የሚመጣው እንደ ‹‹የክርስቶስ መንፈስ›› ነው፡፡ የራሱን ፈቃድ በመያዝ በራሱ ሥልጣን አይመጣም፡፡ በታሪክ
ውስጥ የእርሱ ሥራ የሚያተኩረው በክርስቶስ የድነት ተልዕኮ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ልደት በንቃት ተሳትፎአል
(ሉቃስ 1፡35)፣ እርሱ አገልግሎቱን በሕዝብ ፊት መጀመሩን በጥምቀቱ ጊዜ አረጋግጦአል (ማቴ.3፡16፣17)፣ ለሰብዓዊ ዘር
የክርስቶስን የሥርየት መስዋዕትንና የትንሣኤውን ጥቅሞች አምጥቶላቸዋል (ሮሜ 8፡11)፡፡

በሥላሤ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የፈጻሚነትን ሚና የሚያሟላ ይመስላል፡፡ አብ ልጁን ለዓለም አሳልፎ በሰጠ ጊዜ (ዮሐ.3፡
16) የተፀነሰው በመንፈስ ቅዱስ ነበር (ማቴ.1፡18-20)፡፡ መንፈስ ቅዱስ እቅዱን ለመፈጸምና እውነት ሊያደርግ መጣ፡፡

መንፈስ ቅዱስ በፍጥረት ሥራ በቅርበት መሳተፉ በፍጥረት ጊዜ አብሮ በመኖሩ ይታያል (ዘፍ.1፡2)፡፡ የሕይወት ጅምርና
መቆየት በእርሱ ሥራ ይደገፋል፡፡ እርሱ ተለየ ማለት ግለሰቡ ሞተ ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ‹‹መንፈሱንና
እስትንፋሱን ወደ ራሱ ከሰበሰበ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፣ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል›› ይላል (ኢዮብ 34፡
14፣15፤ 33፡4)፡፡ ለእግዚአብሔር ክፍት በሆነ በእያንዳንዱ ግለሰብ ውስጥ፣ በእርሱ እንደ ገና በመፍጠር ሥራ፣ የመንፈስ
ቅዱስን የመፍጠር ሥራ ነጻብራቆችን እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር በግለሰቦች ውስጥ የሚሰራውን ሥራ በፈጣሪው
መንፈስ አማካይነት ያከናውናል፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ ሥጋ መልበስ፣ በፍጥረትና በእንደገና መፍጠር ሂደት ውስጥ መንፈስ
የእግዚአብሔርን እቅድ ለመፈጸም ይመጣል፡፡

ቃል የተገባው መንፈስ
እኛ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንድንሆን ነበር የታቀደው (1ቆሮ.3፡16ን ይመልከቱ)፡፡ የአዳምና ሔዋን ኃጢአት ከኤድን
ገነትና በውስጣቸው ከሚኖረው መንፈስ ለያቸው፡፡ ይህ መለየት ይቀጥልና ከውኃ ጥፋት በፊት የነበረው ክፋት እጅግ
መብዛት እግዚአብሔር ‹‹መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም›› ብሎ እንዲያውጅ መራው (ዘፍ.6፡3)፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን መንፈስ አንዳንድ ሰዎችን የተለየ ሥራ እንዲሰሩ አስታጠቃቸው (ዘሁ.24፡2፤ መሳፍንት 6፡34፤
1ሳሙ.10፡6)፡፡ እውነተኛ አማኞች ያለ ጥርጥር የእርሱን መገኘት ያውቁ ነበር፣ ነገር ግን ትንቢት የመንፈስ ቅዱስ ታላቅ
መገለጥ አዲሱን ዘመን የሚጀምርበትን ለመግለጽ ‹‹ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ›› መንፈስን ስለ ማፍሰስ ተንብዩአል (ኢዮኤል
2፡28)፡፡
ዓለም በአታላዩ እጅ እንዳለ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት መፍሰስ መቆየት ነበረበት፡፡ መንፈስ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመፍሰሱ
በፊት ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎቱን መፈጸምና የስርየት መስዋዕት ማቅረብ ነበረበት፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ የክርስቶስን
አገልግሎት እንደ መንፈስ አገልግሎት አድርጎ በማመልከት ‹‹እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፣ ነገር ግን እርሱ በመንፈስ
ቅዱስ ያጠምቃችኋል›› (ማቴ.3፡11) ብሏል፡፡ ነገር ግን ወንጌሎች ኢየሱስ በመንፈስ ሲያጠምቅ አያሳዩም፡፡ ከመሞቱ
ሰዓታትን ቀደም ብሎ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ‹‹እኔም አብን እለምናለሁ፣ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ

ገጽ 2
አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው››
ብሏል (ዮሐ.14፡16፣17)፡፡ ቃል የተገባው የመንፈስ ጥምቀት በመስቀል ላይ ተቀባይነትን አግኝቷልን? በስቅለት አርብ ቀን
ከጨለማና ከነጎድጓድ ድምጽ በቀር ምንም እርግብ አልታየም፡፡

ኢየሱስ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ በደቀ መዛሙርቱ ላይ መንፈስን እፍ ማለት አልቻለም ነበር (ዮሐ.20፡22)፡፡ እንዲህ አለ፡
- ‹‹እነሆም አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፣ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ
ቆዩ›› (ሉቃስ 26፡49)፡፡ ይህን ኃይል መቀበል የሚችሉት አማኞችን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ የእርሱ ምስክሮች ለማድረግ
‹‹መንፈስ ቅዱስ በላያቸው በመጣ ጊዜ›› ነበር (የሐዋ.1፡8)፡፡

ዮሐንስ እንዲህ ጽፎአል፡- ‹‹ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፣ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ
መንፈሱ ገና አልወረደም ነበርና›› (ዮሐ.7፡39)፡፡ አብ የክርስቶስን መስዋዕት መቀበል መንፈስ ቅዱስን ለማፍሰስ ቅድመ
ሁኔታ ነበር፡፡

አዲስ ዘመን የጀመረው ድል የነሣው ጌታችን በሰማይ ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስን በእርሱ ሙላት
መላክ የሚችለው ያኔ ብቻ ነበር፡፡ ጴጥሮስ ‹‹በአባቱ ቀኝ ከፍ ከፍ›› (የሐዋ.2፡33) ካለ በኋላ ክስተቱን በታላቅ ጉጉት
ይጠባበቁ በነበሩትና ‹‹በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ›› (የሐዋ.1፡5፣14) በነበሩት በደቀ መዛሙርቱ ላይ መንፈሱን
‹‹አፈሰሰ›› ብሏል፡፡ ከቀራንዮ አምሳ ቀን በኋላ በጴንጤቆስጤ ቀን በመንፈስ ቅዱስ መገኘት ኃይል አዲስ ዘመን ብቅ አለ፡፡
‹‹ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ፣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው (የሐዋ.2፡2-4)፡፡

የኢየሱስና የመንፈስ ቅዱስ ተልዕኮዎች ሙሉ በሙሉ ተደጋጋፊ ነበሩ፡፡ ክርስቶስ ተልዕኮውን እስኪጨርስ ድረስ የመንፈስ
ቅዱስ ሙላት ሊሰጥ አልቻለም ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ የተፀነሰው በመንፈስ ቅዱስ ነበር (ማቴ.1፡8-21)፣
በመንፈስ ተጠምቆ ነበር (ማር.1፡9፣10)፣ በመንፈስ ተመርቶ ነበር (ሉቃስ 4፡1)፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ተአምራቶችን
ሰርቶአል (ማቴ.12፡24-32)፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በቀራንዮ ራሱን ሰጥቶአል (እብ.9፡14፣15)፣ እንዲሁም በመንፈስ
ከሙታን ተነስቶአል (ሮሜ 8፡11)፡፡

የተልዕኮው መነሻ
አዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስን በተለየ ሁኔታ ይገልጻል፡፡ ‹‹የኢየሱስ መንፈስ›› (የሐዋ.16፡7)፣ ‹‹የልጁ መንፈስ›› (ገላ.4፡
6)፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ›› (ሮሜ 8፡9)፣ ‹‹የክርስቶስ መንፈስ›› (ሮሜ 8፡9፤ 1ጴጥ.1፡11) እና ‹‹የኢየሱስ ክርስቶስ
መንፈስ›› (ፊል.1፡19) ተብሎ ተጠርቶአል፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ተልዕኮ የጀመረው ማን ነበር? ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር ወይስ
እግዚአብሔር አብ?

ክርስቶስ ለጠፋው ዓለም የመንፈስ ቅዱስ ተልዕኮን መነሻ በገለጠ ጊዜ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶአል፡፡ በመጀመሪያ አብን
ነበር የጠቀሰው፡- ‹‹እኔም አብን እለምናለሁ፣ ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል›› (ዮሐ.14፡16፤
15፡26፣ ‹‹ከአብ››)፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅን ‹‹የአብ ተስፋ›› ብሎታል (የሐዋ. 1፡4)፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ክርስቶስ ወደ
ራሱ አመልክቶአል፡- ‹‹እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ›› (ዮሐ.16፡7)፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው ከአብና
ከወልድ ነው፡፡

የእርሱ ተልዕኮ ለዓለም


የክርስቶስን ጌትነት መቀበል የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ብቻ ነው፡፡ ጳውሎስ ‹‹በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በስተቀር
ማንም ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት አይችልም›› ብሏል (1ቆሮ.12፡3)፡፡

‹‹እውነተኛ ብርሐን›› የሆነው ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ‹‹ወደ ዓለም የሚመጣውን ሰው ሁሉ›› (ዮሐ.1፡
19) እንደሚያበራ መተማመኛ ተሰጥቶናል ፡፡ ተልዕኮው ‹‹ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ መዝለፍ›› ነው
(ዮሐ.16፡8)፡፡

በመጀመሪያ መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ የሆነ የኃጢአተኛነት ስሜት፣ በተለይም ክርስቶስን ያለመቀበል ኃጢአት ስሜት
እንዲሰማን ያደርጋል (ዮሐ.16፡9)፡፡ ሁለተኛ ሁሉም የክርስቶስን ጽድቅ እንዲቀበሉ መንፈስ ያደፋፍራል፡፡ ሦሥተኛ መንፈስ
ስለ ፍርድ ያስጠነቅቀናል፣ ይህም በኃጢአት የጨለማውን አእምሮ ንስሐና መለወጥ እንደሚያስፈልግ እንዲገነዘብ
የሚያነሳሳ ኃይለኛ መሳሪያ ነው፡፡

ንስሐ ስንገባ በውኃና በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት እንደገና እንወለዳለን (ዮሐ.3፡5)፡፡ ከዚያ በኋላ የክርስቶስ
መንፈስ ማደሪያ ሥፍራ ስለሆንን የእኛ ሕይወት አዲስ ሕይወት ነው፡፡

የእርሱ ተልእኮ ለአማኞች


ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚናገሩት አብዛኞቹ ጥቅሶች እርሱ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ስላለው ግንኙነት የሚገልጹ ናቸው፡
፡ የእርሱ የመቀደስ ተጽእኖ ወደ መታዘዝ ይመራል (1ጴጥ.1፡2)፣ ነገር ግን ማንም ሰው አንዳንድ ሁኔታዎችን ካላሟላ

ጥናት 2.4 | እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገጽ 3


በስተቀር የእርሱን በውስጥ መገኘት በቀጣይነት መለማመድ አይችልም፡፡ ጴጥሮስ እግዚአብሔር ያለማቋረጥ ለሚታዘዙት
መንፈሱን ሰጥቶአል ብሎአል (የሐዋ.5፡32)፡፡1 ስለዚህ አማኞች መንፈስን እንዳይቋቋሙ፣ እንዳያሳዝኑና እንዳያጠፉ
ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአቸዋል (የሐዋ.7፡51፤ኤፌ.4፡30፤ 1ተሰ.5፡19)፡፡ መንፈስ ለአማኞች ምን ያደርጋል?

1. አማኞችን ይረዳል፡፡
ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ሲያስተዋውቅ ‹‹ሌላ ጳራቅላጦስ›› ብሎ ጠርቶታል (ዮሐ.14፡16)፡፡ ይህ የግሪክ ቃል ‹‹ረዳት፣››
በድሮው ኪንግ ጄምስ እትም ‹‹አጽናኝ፣›› በሪቫይዝድ ስታንዳርድ እትም ደግሞ ‹‹መካር›› ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን
‹‹አስታራቂ፣›› ‹‹አማላጅ፣›› ወይም ‹‹ጠበቃ›› ማለትም ሊሆን ይችላል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ ሌላኛው ብቸኛ ጳራቅላጦስ ራሱ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ በአብ ፊት ጠበቃ ወይም
አማላጅ ነው፡፡ ‹‹ልጆች ሆይ፣ ኃጢአት እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ፡፡ ማንም ኃጢአት ቢሰራ በአብ ዘንድ ጠበቃ
አለን፣ እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (1ዮሐ.2፡1)፡፡

እንደ አማላጅ፣ አስታራቂ፣ እና ረዳት ክርስቶስ እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበንና ለእኛ እግዚአብሔርን ያሳየናል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ መንፈስ ወደ ክርስቶስ ይመራናል፣ የክርስቶስን ፀጋም ለእኛ ይገልጽልናል፡፡ መንፈስ ‹‹የፀጋ መንፈስ››
(እብ.10፡29) ተብሎ ለምን እንደተጠራ ይህ ያብራራልናል፡፡ ከእርሱ ታላላቅ አስተዋጽኦዎች አንዱ የሚያድነውን የክርስቶስን
ፀጋ በሰዎች ሕይወት መተግበር ነው (1ቆሮ.15፡10፤ 2ቆሮ.9፡4፤ ዮሐ.4፡5፣6ን ይመልከቱ)፡፡

2. የክርስቶስን እውነት ያመጣል


ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ‹‹የእውነት መንፈስ›› ብሎታል (ዮሐ.14፡17፤ 15፡26፤ 16፡13)፡፡ የእርሱ ሥራዎች ‹‹እኔ
የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል›› (ዮሐ.14፡26) የሚለውንና ‹‹ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል›› (ዮሐ.16፡13) የሚለውን
ያጠቃልላል፡፡ የእርሱ መልእክት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል (ዮሐ.15፡26) የተባለው ነው፡፡ ክርስቶስ እንዲህ ብሎአል፡
- ‹‹የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል፡፡ እርሱ ያከብረኛል፣ ለእኔ ካለኝ
ወስዶ ይነግራችኋልና›› (ዮሐ. 16፡13፣14)፡፡

3. የክርስቶስን መገኘት ያመጣል


መንፈስ ቅዱስ ስለ ክርስቶስ መልእክት የሚያመጣልን ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን የራሱን መገኘት ያመጣልናል፡፡ ኢየሱስ
እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል፡፡ እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን
እልክላችኋለሁ›› (ዮሐ.16፡7)፡፡

ሰብዓዊነትን ተሸክሞ የነበረው ሰው ኢየሱስ ቢሄድ ይሻል የነበረው እርሱ በሁሉም ቦታ መገኘት ስለማይችል ነበር፡፡
በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በሁሉም ቦታ ሁልጊዜ መገኘት ይችላል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔም አብን እለምናለሁ፣
ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አፅናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው
የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፣ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፣ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ፡
፡›› መንፈስ በውስጣቸው እንደሚያድር ‹‹በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፣ በውስጣችሁ ስለሚሆን ወላጆች እንደ ሌላቸው
ልጆች አልተዋችሁም፣ ወደ እናንተ እመጣለሁ›› በማለት ማረጋገጫ ሰጥቶአቸዋል (ዮሐ.14፡17፣18)፡፡ ‹‹መንፈስ ቅዱስ
የክርስቶስ ተወካይ ነው፣ ነገር ግን ከሰብዓዊ ማንነት የተለየና የእርሱም ጥገኝነት የሌለበት ነው፡፡››2

ክርስቶስ ሥጋ በለበሰ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን መገኘት ማርያም ወደ ተባለች ግለሰብ አመጣ፡፡ መንፈስ ቅዱስ
በጴንጤቆስጤ አሸናፊውን ክርስቶስ ወደ ዓለም አመጣ፡፡ ክርስቶስ ‹‹ከቶ አልተዋችሁም፣ አልጥላችሁምም›› (እብ.13፡5)
ያለውና ‹‹እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እኔ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ›› (ማቴ.28፡20) ያላቸውን ተስፋዎች ልንረዳ የምንችለው
በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አዲስ ኪዳን ለመንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በፍፁም ተሰጥቶት
የማያውቀውን ‹‹የኢየሱስ መንፈስ›› የሚለውን ማዕረግ ይሰጠዋል (ፊል.1፡9)፡፡

አብና ወልድ አማኞችን ማደሪያቸው የሚያደርጉት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደ ሆነ ሁሉ (ዮሐ.14፡23) አማኞችም
በክርስቶስ መኖር የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው፡፡

4. የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ይመራል፡፡


መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን መገኘት የሚያመጣ እስከ ሆነ ድረስ በምድር ላይ የክርስቶስ እውነተኛው ተወካይ ነው፡፡ እምነትንና
አስተምህሮን በተመለከተ ሥልጣን ያለበት ማዕከል እንደ መሆኑ መጠን እርሱ ቤተ ክርስቲያንን የሚመራባቸው መንገዶች
ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማሉ፡፡ ‹‹ያለ እርሱ ፕሮቴስታንትነት ሊኖር የማይችለው የፕሮቴስታንታዊነት
መለያ ባህርይ መንፈስ ቅዱስ በምድር ላይ የክርስቶስ እውነተኛ ወኪል ወይም ምትክ መሆኑ ነው፡፡ በድርጅት ወይም
በመሪዎች ወይም በሰዎች ጥበብ መደገፍ ማለት ሰብዓዊን በመለኮታዊ ቦታ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡››3

መንፈስ ቅዱስ የሐዋርያትን ቤተ ክርስቲያን በማስተዳደር ሂደት ውስጥ በቅርበት ተሳትፎአል፡፡ ቤተ ክርስቲያን
ሚስዮናውያንን ስትመርጥ በፆምና በፀሎት የእርሱን አመራር ተቀብላለች፡፡ (የሐዋ.13፡1-4)፡፡ የተመረጡት ግለሰቦች

ገጽ 4
ለመንፈስ ቅዱስ አመራር ክፍት በመሆናቸው የታወቁ ነበሩ፡፡ የሐዋርያት መጽሐፍ ‹‹በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ›› ብሎ
ይገልጻቸዋል (የሐዋ.13፡9፣52)፡፡ እንቅስቃሴዎቻቸው በእርሱ ቁጥጥር ሥር ነበሩ (የሐዋ.16፡6፣7)፡፡ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን
ሽማግሌዎችን ሥልጣን የሰጣቸው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አስታወሳቸው (የሐዋ.20፡28)፡፡

መንፈስ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ክፉኛ አደጋ ላይ የጣሉትን ችግሮች በመፍታት ረገድ ጠቃሚ ሚና ተጫውቶአል፡
፡ እንዲያውም የመጀመሪያውን የቤተ ክርስቲያን መማክርት ጉባኤ ውሳኔዎች መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹….እኛና መንፈስ ቅዱስ
ፈቅደናል›› (የሐዋ.15፡28) በሚሉ ቃላት ያስተዋውቀናል፡፡

5. ቤተ ክርስቲያንን ልዩ በሆኑ ሥጦታዎች ያስታጥቃል፡፡


መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ሕዝብ የተለዩ ሥጦታዎችን ሰጥቶአል፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ››
በግለሰቦች ላይ በመምጣት እሥራኤልን እንዲመሩና ነፃ እንዲያወጡ (መሳ.3፡10፤ 6፡34፤ 11፡29፤ ወዘተ)፣ እንዲሁም
ትንቢት መናገር እንዲችሉ (ዘሁ.11፡17፣25፣26፤ 2ሳሙ.23፡2) ከተለመደው ውጭ የሆነ ኃይል ይሰጣቸው ነበር፡፡ ሳኦልና
ዳዊት የእግዚአብሔር ሕዝብ ገዦች ሆነው በተመረጡ ጊዜ መንፈስ በላያቸው መጥቶ ነበር (1ሳሙ.10፡6፣10፤ 16፡3)፡፡
ለአንዳንድ ሰዎች በመንፈስ መሞላት ልዩ የሆኑ የእደ ጥበብ ችሎታዎችን አምጥቶላቸዋል (ዘፀ.28፡3፤ 31፡3፤ 35፡30-35)፡፡

በጥንቷ ቤተ ክርስቲያንም በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቶስ ሥጦታዎቹን ለቤተ ክርስቲያን የሰጠው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት
ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ አጠቃላዩን ቤተ ክርስቲያን ለመጥቀም ገጣሚ ሆኖ እንዳየው እነዚህን ሥጦታዎች ለአማኞች አከፋፈለ
(የሐዋ.2፡38፤ 1ቆሮ.12፡7-11)፡፡ ወንጌልን እስከ ምድር ዳርቻ ለመስበክ የሚያስፈልገውን ልዩ ኃይል ሰጠ (የሐዋ.1፡8፤ የዚህን
መጽሐፍ 17ኛውን ምዕራፍ ይመልከቱ)፡፡

6. የአማኞችን ልብ ይሞላል፡፡
ጳውሎስ በኤፌሶን ያሉትን ደቀ መዛሙርት ‹‹ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን?›› (የሐዋ.19፡2) ብሎ የጠየቀው
ጥያቄ ለእያንዳንዱ አማኝ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

ጳውሎስ አፍራሽ የሆነ መልስ ከተሰጠው በኋላ በደቀ መዛሙርቱ ላይ እጁን ጫነባቸውና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ተቀበሉ
(የሐዋ.19፡6)፡፡

ይህ ክስተት እንደሚያሳየው መንፈስ ቅዱስ የሚያመጣው ኃጢአተኛነትን ማመንና በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ሁለት
የተለያዩ ልምምዶች ናቸው፡፡

ኢየሱስ ከውኃና ከመንፈስ የመወለድን አስፈላጊነት ጠቆመ (ዮሐ.3፡5)፡፡ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት አዲስ አማኞችን ‹‹በአብ፣
በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም›› እንዲጠመቁ አዘዛቸው (ማቴ.28፡19)፡፡ ከዚህ ትዕዛዝ ጋር በተጣጠመ ሁኔታ ጴጥሮስ
‹‹የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታን›› መቀበል የሚቻለው በጥምቀት እንደሆነ ሰበከ (የሐዋ.2፡38)፡፡ ጳውሎስም አማኞችን ‹‹መንፈስ
ይሙላባችሁ›› (ኤፌ.5፡18) የሚል አስቸኳይ ተማጽኖን በማቅረብ በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅን አስፈላጊነት አጠናከረ
(የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 15ን ይመልከቱ)፡፡

በመንፈስ ቅዱስ መሞላት እኛ የእግዚአብሔርን መልክ እንድንመስል በመለወጥ በአዲስ ልደት የተጀመረውን የቅድስና ሥራ
ይቀጥላል፡፡ እግዚአብሔር እኛን ‹‹እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ
አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ
ወራሾች እንድንሆን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትረፍርፎ አፈሰሰው›› (ቲቶ.3፡5፣6)፡፡

‹‹የወንጌልን አገልግሎት ኃይል የለሽ የሚያደርገው የመንፈስ ቅዱስ አለመገኘት ነው፡፡ ትምህርት፣ መክሊት፣ አንደበተ
ርቱዕነት፣ እያንዳንዱ በተፈጥሮ ወይም በትምህርት የተገኘ ችሎታ ሊኖር ይችላል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ከሌለ
በስተቀር አንድም ልብ አይነካም፣ አንድም ኃጢአተኛ ወደ ክርስቶስ አይመለስም፡፡ በተቃራኒው ከክርስቶስ ጋር ከተገናኙ፣
የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች የእነርሱ ከሆኑ እጅግ ምስኪንና ያልተማሩ ደቀ መዛሙርት ልብን መንካት የሚችል ኃይል
ይኖራቸዋል፡፡ እግዚአብሔር በዓለማት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ የሚፈስባቸው መተላለፊያ ቦዮች ያደርጋቸዋል፡፡››

መንፈስ ንቁ ነው፡፡ ክርስቶስ በእኛ ውስጥ የሚፈጽማቸው ለውጦች በሙሉ የሚመጡት በመንፈስ አገልግሎት ነው፡፡ እንደ
አማኞች፣ ያለ መንፈስ ቅዱስ ምንም ነገር ማድረግ እንደማንችል ሁልጊዜ ማወቅ አለብን (ዮሐ.15፡5)፡፡

ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ትኩረታችንን እግዚአብሔር በልጁ አማካይነት ወደሚሰጠን ወደ ታላቁ የፍቅር ሥጦታ ይመልሳል፡
፡ ተማጽኖውን እንዳንቃወም ግን አፍቃሪና በፀጋ ከተሞላው አባት ጋር የምንታረቅበትን ብቸኛ መንገድ እንድንቀበል
ይለምናል፡፡

ጥናት 2.4 | እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገጽ 5

You might also like