You are on page 1of 20

መሠረታዊ ትምህርት

ክፍል አንድ
Level One
1

ይህ ትምህርት የቤተ-ክርስቲያን ራዕይን፤ተልዕኮን እና ዓላማዎችን ለማሳካት በትምህርት እና


ስልጠና ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህም ቤተ-ክርስቲያ ቅዱሳን በሙሉ ባለ ራዕይ ሆነው
እግዚአብሔር የሰጣቸውን ራዕይና ህይወት በሙላት መፈፀምና መኖር እንዲችሉ ካላት ራዕይ
የተነሳ የተዘጋጀ ትምህርት ነው፡፡

የቤተ-ክርስቲያን ራዕይ

 ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሲፈፅሙ ማየት

የእግዚአብሔር ከዋክብት ቤተ-ክርስቲያን ተልዕኮ

 ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈፅሙ መርዳት

የቤተ-ክርስቲያን ዓላማዎች ከትምህርትና ስልጠና ክፍል አንፃር

 ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል እውቀት እንዲበለፀጉ መመገብ


 በበጎ ስራ ሁሉ ፍሬ እንዲያፈሩ በእግዚአብሔር ዕውቀት እንዲያድጉ ማገዝ

የትምህርት እና ስልጠና ክፍል ዓላማዎች


 ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት ፤ ሙሉ
ሰውም ወደመሆን፤ወደሙላቱ ልክ እንዲደርሱ ማስተማር
 በቤተ-ክርስቲያን ያለውን ቅዱሳን አገልግሎቶችን በዕወቀት እና ቅድስና እንዲያገለግሉ
ማገዝ
 ቅዱሳን በሙሉ የቤተ-ክርስቲያንን ራዕይ፤ተልዕኮናዓላማዎችን እንዲያዉቁና አብሮ ባለ
ራዕይ ሰራተኛ እንዲሆኑ ማገዝና አብሮ መስራት
 በየወቅቱ ከሚነሱ የሐሰት ትምህርቶች ቅዱሳንን መጠበቅ

ማውጫ ገፅ

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


2

1. ትምህርት አንድ ሰው----------------------------------------------3


2. ትምህርት ሁለት ክርስቲያናዊ እድገት----------------------------6
3. ትምህርት ሶስት እምነት-----------------------------------------12
4. ትምህርት አራት ክርስቲያናዊ ባህሪ ና ብልጥግና--------------15
5. ትምህርት አምስት የክርስቶስ ደም--------------------------------19
6. ትምህርት ስድስት ራዕይ እና አገልግሎት ----------------------21

ትምህርት አንድ
ሰው

ሰው በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረ መንፈሳዊ ፍጡር ነው፡፡

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


3

ዘፍ 1 26-27 እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር

 የሰው በእግዚአብሔርም መልክናምሳሌ የተፈጠረው የእግዚአብሔር መልስ ያለበት ክፍሉ

መንፈሱ ሲሆን ሰው ሶስት ሁለንተና አለው፡፡ እነርሱም መንፈስ፤ነፍስና ስጋ በመባል


ይታወቃል

 በዘፍ 2;16-17 እግዚአብሔር ለአዳም የሰጠው ተዕዛዝ በበላክ ጊዜ ሞትን ትሞታለክ


የሚል ሲሆን የመጀመሪያ ተዕዛዝ መንፈስን የሚነካ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም
አዳም ትዕዛዙን በተላለፈ ጊዜ የሞተው መንፈሱ እንጂ ስጋው አልነበረም፡፡
 መንፈሱ ሞተ ማለት ከዛ በኋላ አዳም መንፈስ የለውም ማለት ሳይሆን ከእ/ር መለየቱና
በጨለማው ገዢ ሰር መውደቁን ለብርሃን አለም ሞቶ ለጨለማው አለም መንቃቱን
የሚያስረዳ ቃል ነው ምክንያቱም በምድር ላይ ያለ ሰው ሁሉ መንፈስ አለው ልዩነት
የሚፈጥረው አንዱ የሰው መንፈስ በጨለማ ስር ሌላው ደግሞ በብርሃን ስር መሆናቸው
ሲሆን ሁለቱም ለ ተወለዱበተ አልም ንቁዎች ናቸው፡፡ይህም ለጨለማ ወይም ለብርሃን
አለም ማለት ነው፡፡

1.1 ስጋ
ሰው ሶስት ሁለንተና አለው ሲባል ሶስት አካል አለው ማለት አይደለም፡፡ ሰው ሁለት
ተጨባጭ አካላት አሉት እነርሱም ስጋ እና መንፈስ ሲሆኑ ነፍስ በሁለቱም የምትገለጥ ስሜት
ዕውቀት ፈቃድ ናት፡፡

 ስለዚህ ስጋ የመንፈስ ቤት ይለዋል መጽሐፍ ቅዱስ


ኢዩ 4፤19 2ኛ ቆሮ 5፤1-4
 ስጋ ከግዑዙ አለም ጋር የምንገናኝበት በዚህ በፍጥረታዊ አለም መኖር እንድንችል
ተደርገን የተሠራንበት ስሪታችን ሲሆን ሰው ያለስጋ በዚህ ምድር መኖር አይችልም፡፡
 ስጋ አዳም ሀጢያትን በሰራ ጊዜ በሀጢያት ስለተበከለ ለእግዚአብሔር የመገዛት
ተፈጥሮውን አጥተዋል ምክንያቱም በስጋ ውስጥ ደም አለ በደም ውስጥ ደግሞ ህይወት
አለ በ ደም ውስጥ ያለው ህይወት ሀጢያተኛ ተፈጥሮ ስለተካፈለ ነው፡፡ዘሌ 17፡11-17
 ስጋ ለእግዚአብሔር እናስገዘዋለን አንጂ ፍፁም ነፃነቱን በምድር አይቀበልም ምክንያቱም
የመንፈስ በኩራት የለን የዳንን ማለት ነው የሰውነታችን(የስጋችንን) ቤዛነት
እንጠባበቃለን፡፡ ሮሜ 8፡23 ሮሜ 8፡8
 በስጋ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አንችልም ያ ማለት ስጋ መልካም አይደለም ማለት
ሳይሆን በስጋ የመንፈስ ፍሬ እስካልገለጥን ድረስ ስጋ የራሱ ምኞት ና ፍላጎት ስላለው
ሮሜ 8፡5 ፤ 1ኛ ቆሮ 3፡1 ገላ 5፡16-20 ቆላ 3፡5 የመንፈስ ፍሬ እንድገለጥብን
ማድረግና ለክርስቶስ ማዋል አለብን፡፡1ኛ ቆሮ 6፡13

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


4

 ስለዚህ ስጋ በትንሳኤ ቤዛነቱን ይጠብቃል አልያም በቅጽበት አይን በመለወጥ በአፀደ


ስጋ እያለን ኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ይጠብቃል፡፡
 በአፀደ ስጋ እያለን ኢየሱስ ክርስቶስን ቢገለጥ በቅጽበት አይን በመለወጥ ይህ
የሚበሰብሰው ስጋችን በቅፅበት የማይበሰብሰውን ይለብሳል፡ ይለወጣል፡፡
1ኛ ቆሮ 15፡51-52
 በትንሳኤ ቀን የስጋችን ቤዛነት የምንቀበለው የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሙታን
የማይበሰብሱ ሆነው ይነሳሉ በማንኛውም አይነት አማማት በሞቱ እንደ ገዛ አሰራሩ
ያስነሳቸዋል፡፡ ራዕ 20፡13 ፤ ዳን 12፡2
1.2. ነፍስ
 ነፍስ፡- ስሜት ዕውቀት ፈቃድ ነው፡፡
 ነፍስ የራሱ የሆነ አካል የለውም ነገር ግን በስጋ ወይም በመንፈስ የሚገለጥ የሰው
ክፍል ሲሆን ስጋ በመንፈስ ለይ ሲያይል የስጋ ባህሪያት መታየት አልያም መንፈስ
በስጋ ላይ ሲያይል የመንፈስ ፍሬ መታያ ነው፡፡
ለምሳሌ ፡- አንድ ሰው ሲሞት የዛ ሰው ህይወት እዛጋ አበቃ ማለት እንዳልሆነ
ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም መንፈሱ ከስጋው በተለየ ቅጽበት ስጋ እዚሁ ሲቀር የመንፈስ
ህይወት ይቀጥላል፡፡ስጋ በዛ ሰዓት ስሜት ዕውቀት ፈቃድ የሌለው ይሆናል ያ ማለት
በሌላ አለም መኖር የቀጠለው መንፈስ ነፍስን የራሱ አድርጓል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ
ነፍስ የራሱ የሆነ አካል የለውም፡፡
 ነፍስን በእውቀት መሙላት መልካም ነው፡፡ ምሳ 19፡2
 ነፍስ፡- ስሜት ዕውቀት ፈቃድ ነው ብለናል የትኛውንም ነገር ለማድረግ ከ እውቀት
ብንጀምር ና በስሜት አነሳሽነት ወይም ጉልበት ፈቃዳችን ጋር ብንደርስ መልካም ነው፡፡

1.3. መንፈስ
 እግዚአብሔርን የሚመስለው እኛነታችን መንፈሳችን ነው፡፡ ሠው ወደ ሃይማኖት ቤት
በመመላለስ ወይም አዘውተሮ በማገልገል እግዚአብሔርን መምሰል አይችልም፡፡
 እግዚአብሔር በባህሪው መንፈስ ነው ስለዚህ ሊወልደው የሚችለው ልጅ መንፈስ አንጂ
ስጋ ሊሆን አይችልም፡፡ ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው ፤ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው፡፡
ዩሐ 1፡1-12-13
 መንፈስ የተወለደ ሲሆን ስጋ ግን የተበጀ ወይም የተሰራ ነው፡፡ ዘፍ 2፡7

ዳግም መወለድ
 ክርስትና ከሌሎች ሃይማኖቶች የሚለየው በመወለድ የሚጀመር መሆኑ ነው፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት የዝምድና ግንኙነት ነው ማለትም የእግዚአብሔር
ዘር በእኛ ውስጥ አለ፡፡ 1ኛ ዩሐ 3፡9 ፤ ዩሐ 1፡12-13

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


5

 ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም፡፡ በስጋ


ያልተወለደ ሰው ወደዚህ ምድር እንደማይገባ ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደም ወደ
መንፈስ አለም አይገባም፡፡
 ሰው በቃሉ አማካኝነት ከመንፈስ ቅዱስ ይወለዳል፡፡ 1ኛ ጴጥ 1፡23
 ዳግመኛ የተወለደው ሰው እግዚአብሔርን በመምሰል የሚያድግ ነገር ግን የማይሞት
ማንነት ያለው የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ ቆላ 3፡10 ፤ 1ኛ ጢሞ 3፡16 ፤4፡7፤6፡3
፤2ኛ ጴጥ 1፡2-3 ፤1ኛ ዩሐ 3፡1
 እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው፡፡ ዕብ 12፡9
ማጠቃለያ
1. የሰው ትክክለኛ እሱነቱ ወይም ከእግዚአብሔር የሚወለደው ማንነቱ መንፈስ ነው፡፡
ዩሐ 3፡6 ፤ ዩሐ 1፡12-13
2. ስጋን በመፅሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ቤት፤ድንካን፤ማደሪያ እያለ ይጠራዋል፡፡ ስጋ
ከእግዚአብሔር ያልተወለደ ነገር ግን የእጁ ስራ የሆነ አካላችን ነው፡፡
ስጋን ለመንፈስ በማስገዛት ለእግዚአብሔር ክብር ልናውለው ይገባል፡፡
1 ኛ ቆሮ 9፡27፤ ገላ 5፡17
ነፍሳችን እለት እለት በእግዚአብሔር ቃል በመንፃት የነፍሳችንን መዳን ልንፈፅም
ይገባል፡፡ ነፍስ ትድናለች ስንል ከዘላለም ፍርድ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ባህሪ ውጪ
ከሆነ ተቃራኒ እውቀት ድና እግዚአብሔርን ለመምሰል ወደሚጠቅማት እውቀት
ታድጋለች ማለት ነው፡፡ፊሊ 2፡12 ፤ ያዕ 1፡21 ፤1ኛ ጴጥ 1፡8-9፤1ኛ ጴጥ 1፡22

ተፈፀመ

ትምህርት ሁለት

ክርስትያናዊ እድገት (spiritual growth)

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


6

2.1 መግቢያ
እድገት ሂደት ነው፡፡ ይህ ክርስትያናዊ እድገት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ከእግዚአብሔር
የተቀበልነውን መለኮታዊ ህይወት የመግለጥ ሂደት ነው፡፡ በዚህ ትምህርት አንድ በክርስቶስ
ሞትና ትንሳኤ ያመነ አማኝ በምን አይነት መንገድ ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን መለኮታዊ
ህይወት መግለጥና መኖር እንደሚችል እናያለን፡፡ በዚህ የእድገት ሂደት ውስጥ እንደ ፍጥረታዊ
ማንነታችን ሶስት ደረጃዎች አሉ፡፡

1. ህፃንነት (Babyhood) 1 ጴጥ 2፡2

በዚህ ክርስትያናዊ ህጻንት ወቅት የሚታዩብንን ሶስት ዋና ዋና ባህሪያት እንመልከት

ሀ. ንፅህና (innocence)

ህፃናት ከምንም ወንጀል ንፁ ናቸው ምክንያቱም ምንም ያለፈ ታሪክ የላቸውምና፡፡

ለ. ቸልተኝነት (Ignorance)

ህፃናት ምን እንደሚጎዳቸው ስለማያውቁ ያገኙትን ሁሉ ወደ አፋቸው ያስገባሉ፡፡ በዚህ ደረጃ


ላይ ያሉ ክርስትያኖችም እነደዚሁ ናቸው፡፡ ከማን ጋር መዋል፤ምን መስራት፤ምን መንፈሳዊ
ነገሩን እንደሚጎዳ ና እንደሚጠቅመው ስለማያውቅ ያገኘውን ሁሉ ወደ ስጋው፤ነፍሱና መንፈሱ
ያስገባል፡፡ ህፃናቱ በካይ ነገር ሲበሉ እንደሚታመሙ ሁሉ እሱም ክርስትያናዊ ብክለት ውስጥ
ይሆናል ማለት ነው፡፡

ሐ. በቀላሉ መረበሽ (Irritability)

ህፃናት በቀላሉ የሚደነግጡና የሚረበሹ ናቸው፡፡ እንደዚሁ ደግሞ መንፈሳዊ ህጻናትም አላፊ
አግዳሚው ሁሉ የሚያስፈራቸውና የሚያስደነግጣቸው ናቸው፡፡

2. ልጅነት ( Childhood) ኤፌ 4፡14

በዚህ ክርስትያናዊ ልጅነት ወቅት የሚታዩብንን ሶስት ዋና ዋና ባህሪያት እንመልከት

ሀ. መወላወል (unsteadiness)

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


7

አንድ የተሰጠንን ስራ ተረጋግተን አንጨርስም ቤት አፅዳ ተብለን ፊልም እያየን እንጠብቃለን፡፡


በምንም ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ሚዛናዊ አቁአም አለመያዝ፡፡

ለ. ጉጉት (Curiosity)

በልጅነት ወቅት ብዙ ነገር ያምረናል፡፡ ሁሉንም ነገር የማወቅ ፍላጎታችን እጅግ ከፍተኛ
ከመሆኑ የተነሳ ለብዙ መጥፎ ነገሮች የመጋለጥ እድላችን የሰፋ ነው፡፡ ይህ ባህሪ መንፈሳዊ
ልጅነት ላይ በጣም የጎላ ነው፡፡

ሐ ብዙ ማውራት (Talkativeness)

ልጆች የዝምታን ዋጋ አያስተውሉም፡፡ ዝምታ ማለት አለማውራት ማለት አይደለም፡፡

ዝምታ ማለት፡- አንድን ጉዳይ መች፤በምን አይነት ሁኔታ፤ መንገድ ና አላማ እና ለምን
አይነት ሰው ማውራት ወይም መናገር እንዳለብን ማወቅ ነው፡፡ ብዙ የሰዎችን እና የቤተ-
ክርስትያንን ምስጢር በተሳሳተ መንገድ ለተሳሳቱ ሰዎች በተሳሳተ አላማ የሚያወሩት መንፈሳዊ
ልጅነት ላይ ያሉ ክርስትያን ወንድሞችና እህቶች ናቸው፡፡

3. አዋቂነት ( Manhood)

አዋቂነት እጅግ በጣም የሚናፈቅ ና ደስ የሚል የእድገት ደረጃ ነው፡፡ በዚህ የእድገት ደረጃ
ሁለንተናዊ ዕድገት በብዛት ይስተዋላል፡፡

በዚህ ክርስትያናዊ ብስለት ልክ ስንደርስ የሚታዩብንን ሶስት ዋና ባህሪያትን እንመልከት

ሀ. ለቁሳዊ ነገሮችን ሚዛናዊ ዋጋ መስጠት ዕብ 11፡24-26

ከምድራዊ ነገሮች ይልቅ ለመንፈሳዊ ነገሮች ና ለመንፈሳዊ እድገት ትልቅ ዋጋ መስጠት


ይታይባቸዋል፡፡ ብርቱ ሰራተኞች ናቸው ደግሞም ብርቱ አገልጋዮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን
የብልጥግና መርህ(መንፈሳዊ፤ቁሳዊ፤አካላዊ፤ማህበራዊ ና አዕምሮአዊ ብልጥግና) በሚገባ
ያስተዋሉ ናቸው፡፡

ለ. ለወቀሳ እና ለምስጋና የሞቱ ናቸው 1 ቆሮ 4፡3-4

ከሰዎች የሚሰነዘርባቸውን ወቀሳ ልባቸውን አያወርድም፤የሚሰጣቸውም የምስጋና እና


የአድናቆት ብዛት ልባቸውን ከፍ አያደርግም ምክንያቱም ሁሉን በሚያውቅ ና በሚችል አምላክ
ፊት ራሳቸውን ማስቀመጥን ተምረዋልና፡፡ በተጨማሪም ሰዎችን ከመውቀስ ይልቅ በእምነት
የደከመውን መቀበልንና እውነትን በፍቅር መያዝንና ማስተማርን ከራሱ ከክርስቶስ ተምረዋል፡፡

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


8

ሐ. እግዚአብሔር የሚሰራበትን ሰዓት ያውቃሉ

የእግዚአብሔርን ፈቃድና የስራ ጊዜውን ያውቃሉ፡፡ዘፍ 45፡5-7

ከእግዚአብሔርም ጋር መራመድን የሚያውቁ ና የሚያስተውሉ ናቸው፡፡

ስለዚህ የዚህ ትምህርት ዋና ግብ የአማኞችን የእድገት ደረጃ መግለፅ ሳይሆን አማኞች ወደ


መንፈሳዊ ብስለት እንዲደርሱ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መርሆችን ማስተማር ነው፡፡

2.2 ለክርስትያናዊ እድገት ወሳኝ ነገሮች

ለክርስትያናዊ እድገት መንፈሱና ቃሉ እጅግ በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ


የምናድግ አድርጎ ፈጥሮናል፡፡ኤፌ 4፡11-16

እድገት የምናፈራውን ውጤት ከመጨመር በላይ የበለጠ ፍሬያማ እንድንሆን ያደርገናል፡፡


2ኛ ጴጥ 1፡2-3

ክርስትያን በእግዚአብሔር ፊት ሊያድግ ይገባል፡፡1ኛ ሳሙ

ክርስትያን በእግዚአብሔር እና በሰው ፊት ሊያድግ ይገባል፡፡ ሉቃ 2፡52

2.3 ማደግ አስፈላጊ እንደሆነ ያመነ አንድ አማኝ የሚከተሉትን አስፈላጊ ነገሮችን ማድረግ
አለበት

1. ቃሉን ማንበብናማጥናት
ክርስትያን በምድር ላይ ለመኖር ከምግብናውሃ በተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል
ያስፈልገዋል፡፡መዝ 1፡2 ኢያ 1፡8
ቃሉ፡-
 ለእድገታችን ወሳኝ ነው፡፡
 ጠላትን የምናሸንፍበት መሳሪያ ነው፡፡
 እርስታችንን የምንወርስበት ማስረጃ ነው፡፡
 የእግዚአብሔርን ባህሪ የምንካፈልበት መንገድ ነው፡፡ 2ኛ ጴጥ 1፡4
 ፍሬ የምናፈራበት መንገድ ነው፡፡
ቃሉን በየቀኑ ማጥናት፡-
ቃሉን በየቀኑ በማጥናት የህይወታችን አንዱ ክፍል ማድረግ ይኖርብናል፡፡
ሐዋ 17፡11 ፤ ሐዋ 2፡26
ቃሉን በየቀኑ በማሰላሰል የነፍሳችንን መዳን መፈፀም 1ኛ ዩሐ 2፡5 ፤ ያዕ 1፡22

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


9

2. የጥሞና ጊዜ

የጥሞና ጊዜ ለክርስትያናዊ እድገት ሰፊ ጥቅም አለው፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ እንደመሆኑ


ከዚህ ፍጥረታዊ ዓለም ፍፁም የተለየ ባህሪ አለው፡፡ የጥሞና ጊዜ ማለት እራስን
ለእግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ ማቅረብ ማለት ነው፡፡

ካለንበት ሁኔታ በመውጣት ፀጥ ባለ ስፍራ እግዚአብሔርን መገናኘት ዘፀ 33፡7

2.1 በፀጥታ በእግዚአብሔር ፍት መቀመጥ ዘፍ 24፡63


ይህ አይነቱ የጥሞና ጊዜ እኛ በእግዚአብሔር ፍት ዝም የምንልበት
እግዚአብሔር እንደፈቀደ የሚናገርበት ጥልቅ መረዳት ወይም ሚስጥር
የሚገለጥበት የጥሞና ጊዜ አይነት ነው፡፡ ማር 6፡31
2.2 አንድ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ይዘን በጽሞና የምናሰላስላበት ጊዜ
ኢያ 1፡8 ፤ ሉቃ 9፡10 መዝ 40፡8 መዝ 119፡29 መዝ 119፡97

2.3 ሕብረት(የቤተ-ክርስትያን ስብሰባዎች)

ሀ. የሕብረት አስፈላጊነት ሐዋ 2፡42-47

በሐዋሪያዊ ትምህርትና ፀሎት ፀጋን ለመካፈል

ለ. በስብሰባዎች ሳይቀሩ መገኘት ዕብ 10፡24-25

ፍቅራችንን ለቅዱሳን ለመግለፅና የቅዱሳንን ፍቅር ለመካፈል

እርስበርሳችን ለመነቃቃትናለመበረታት፤ለመመካከር

ለመተያየትና አንዳችን የአንዳችንን ጉድለት ለመሙላት

ሐ. ነፍሳትን ለመማረክ(ወንጌል ለማሰራጨት)

ይህ የአንድ ክርስትያን እድገት አመላካች ነው፡፡ ለቅዱሳን ሁሉ የተሰጠ አገልግሎት


የማስታረቅ አገልግሎት ነው፡፡ 2ኛ ቆሮ 5፡18

ሀ. ነፍሳትን ለመማረክ ብቁ ማን ነው

በቃሉና በመንፈሱ የተሞላ ክርስትያን ነፍሳትን ለመማረክ ብቁ ነው፡፡

ሐዋ 1፡8 ሐዋ 4፡18-19

ለ. ነፍሳትን የመማረክ አስፈላጊነት

አብዝተን በማፍራት አብን ለማክበር፡፡ ዩሐ 15፡8

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


10

ያልሰሙትን የምስራች ለማሰማት፡፡ ሮሜ 10፡13-15

ሐ. ነፍሳትን ለሚማርኩ ዋጋቸው ምንድነው

ዳን 12፡3 ፤ 1ኛ ቆሮ 9፡16-18

የፅድቅ አክሊል 2ኛ ጢሞ 4፡8

የሕይወት አክሊል ያዕ 1፡12 ፤ ራዕ 2፡10

የክብር አክሊል 1ኛ ጴጥ 5፡4

ማስታወሻ፡- እነዚህ አክሊሎች ቅዱሳን በፅድቅ ሲኖሩና እስከሞት የታመኑ ሲሆኑ


የሚሰጣቸው አክሊሎች ናቸው፡፡

ማጠቃለያ

ሁል ጊዜ ህፃናት መሆን የለብንም፡፡

በበጎ ስራ ሁሉ ፍሬ እያፈራን በእግዚአብሔርም እውቀት እያደግን


በኑሮአችን፤በስራችን፤በትዳራችን፤በትምህርታችን፤በአገልግሎታችንና በማህበራዊ
ህይወታችን ደስተኛ እና ስኬታማ የምድር ላይ ቆይታ እንድኖረን ፅኑ መጋደልን
ለመጋደል በፅናት እንበርታ፡፡ እድገት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ በማመን ሙሉ
ሰው ወደ መሆን በማደግ ለራሳችን፤ለእግዚአብሔር፤ለእግዚአብሔር መንግስትና
ለምድራችን ጠቃሚና እጅግ አስፈላጊ ሰው ለመሆን እንስራ፡፡

ትምህርት-ሦስት

እምነት
3.1 መግቢያ

ክርስትና በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት የምንጀምረው አዲስ


የህይወት ጅማሬ ነው፡፡ ይህ አዲስ ህይወት ሲጀመር በእምነት፤ ሲኖርም በእምነት
፤ሲፈፀምም በእምነት ነው፡፡ አንድ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ ሲቀበል
የሚሰጠው ወይም የሚናዘዘው የእምነት ቃል አለ፡፡ ይህም አለምን፤ስጋን፤ዲያብሎስን
ክጃለው ኢየሱስ ክርስቶስን የህይወቴ ጌታ እድርጌአለው ይላል፡፡ ከዚህ የተነሳ ሰው በዚህ
አለም ዕውቀት፤በራሱ ወይም በስጋ ዕውቀት ና በዲያብሎስ ዕውቀት ከመኖር

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


11

በእግዚአብሔር ዕውቀት ለመኖር የእምነት ውሳኔ ያደርጋል፡፡ ይህም የአዲስ ህይወት


ጅማሬ ነው፡፡ ስለዚህ አዲሱ ህይወት በእምነት የሚጀመር፤በእምነት የሚኖርና በእምነት
የሚፈፀም ነው፡፡ ስለዚህ አዲሱ ህይወት ስንል የማንነት ለውጥ እንጅ የአስተሳሰብ
ለውጥ ብቻ አይደለም፡፡ ይህም ማለት ለአዳም ማንነት ሞተን ክርስቶስ ማንነት
ተወልደናል ማለት ነው፡፡ በትምህርት አንድ እነደተመለከትነው መንፈሳችን የክርስቶስ
መልክ እንጅ የአዳም መልክ የለውም፡፡

3.2 የትምህርት ሶስት ዋና ዓላማ


እምነት መነሻ አለው፡፡ ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ የተለያየ እምነት አላቸው፡፡ ይህ
የሆነበት ምክንያት ስለዚያ ጉዳይ ያላቸው ዕውቀት የተለያየ ስለሆነ ነው፡፡ የዚህ
ትምህርት ዋና አላማ ቅዱሳን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ
የተመሰረተ እምነትን እንዴት ማሳደግ የሚችሉበትን መርሆች በማሳየት ትክክለኛ
የክርስቶስ ደቀ-መዝሙር እንዲሆኑና የእግዚአብሔር ልጅነትን ህይወት በሚገባ
ወደመኖር እንዲደርሱ ማገዝ ነው፡፡
3.3 እምነት ማለት ምን ማለት ነው?
 እምነት የማናየውን የሚያስረዳ ተጨባጭ ማስረጃ ነው፡፡ዕብ 11፡1
 እምነት ተስፋ የምናደርጋቸው ነገሮች ተጨባጭ ማስረጃ ነው፡፡
 እምነት ነገሮች የሚፈጠሩበት ኃይል ነው፡፡
 እምነት በእግዚአብሔር ባህሪና በተስፋ ቃሉ መደገፍ ማለት ነው፡፡

3.4 እምነት በሰዎች ውስጥ እንዴት ይፈጠራል?


 እምነት ከምንሰማው የእውቀት ቃል የተነሳ በልባችን ውስጥ ይፈጠራል፡፡
 የእግዚአብሔርን ቃል ስንሰማ መልካም መልክ(image) ልባችን ውስጥ
ይፈጠራል፡፡
 የክፉውን ቃል ስንሰማ መጥፎ መልክ(image) በልባችን ውስጥ ይፈጠራል፡፡
 በልባችን ውስጥ የተፈጠረውን መልካምም ሆነ መጥፎ መልክ ስንቀበለው
እምነት ይሆናል፡፡ ከዚያም የእምነት ኃይል ደግሞ ያመነውን ነገር ቅርፅ
ሰጥቶ ወደዚህ ፍጥረታዊ አለም ያስገባዋል ማለት ነው፡፡
ሎጎስ፡-የእግዚአብሔር ልብ ውስጥ መልክ፤ቅርፅናፍሬ አለ፡፡
ሬማ፡-እግዚአብሔር ሬማን ወይም መገለጥን ይናገራል፡፡
እኛ ደግሞ እምነትን እንናገራለን፡፡
Faith is the substance (ዕምነት ተጨባጭ ነገር ነው፡፡)
እምነት፡- በልባችን ውስጥ እምነት አለ፡፡
ማመን፡-ማመን ድርጊት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-ምግብ ተጨባጭ (substance) ነገር ነው፡፡ መመገብ ደግሞ
ድርጊት ነው፡፡

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


12

3.5 እምነት የሚሰራባቸው መንገዶች


እምነት ድፍረት ማለት አይደለም ነገርግን በእምነት ውስጥ ድፍረት አለ፡፡
ፍርሃት የእምነት ተቃራኒ ኃይል ነው፡፡ ስለዚህ በእምነት ውስጥ ድፍረት
ያስፈልገናል፡፡ ነገር ግን እምነት በሌለበት ድፍረት ከንቱ ነው፡፡
1. እምነት ከፍቅር ጋር ይሰራል
ገላ 5፡6 በክርስቶስ ሆኖ በፍቅር የሚሰራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም
አለመገረዝ አይጠቅምም፡፡
1ኛ ጢሞ 2፡15 ቲቶ 2፡2
2. እምነት ከትዕግስት ጋር ይሰራል

በምናልፍባቸው የህይወት መንገዶች ሁሉ በአስችጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ


ከእኛ ፈቃድ ይልቅ የእግዚአብሔር ፈቃድ፤በእኛ ጊዜ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጊዜ ነገሮች
እንዲሆኑ እግዚአብሔርን ፍፁም በመታመን ምንም አይነት ማጉረምረም ሳይኖር
በእግዚአብሔርና በተስፋ ቃሉ ላይ ባለን እምነት ወደፍት በመሄድ እምነት ይሰራል፡፡

ሮሜ 4፡3 ፤ ዕብ 6፡11-12 ፤ ሮሜ 8፡25 ፤ዕብ 12፡1-2

3. እምነት ከተስፋ ጋር ይሰራል

ሮሜ 4፡18 ፤ ሐዋ 2፡39 ፤ ሮሜ 4፡13 ፤ ገላ 3፡22 ፤ ዕብ 11፡9

4. እምነት ከቅድስና ጋር ይሰራል

2ኛ ቆሮ 7፡1 ፤ 1ኛ ተሰ 4፡7 ፤1ኛ ጢሞ 2፡15 ፤ ዕብ 12፡10

5. እምነት በእኛ እንዲሰራ ሕያው የሆነ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር


ያስፈልገናል፡፡
6. እምነት እራሱን በፀሎት ያንቀሳቅሳል
የምታምነውን ነገር ካልተናገርከው አይሰራም፡፡
ያዕ 5፡15 ፤ 2ኛ ተሰ 1፡12 ፤ ሮሜ 10፡8
7. እምነት ከበጎ ሕሊና ጋር ይሰራል

1ኛ ጢሞ 1፡19 ፤ ዕብ 10፡22 ፤ 1ኛ ጢሞ 1፡5

ማጠቃለያ

እግዚአብሔርን ማመን ማለት ቃሉን ማመን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሐርን ቃል


መሰረት ያደረገ እምነትን በማሳደግ በቃሉ ውስጥ ያሉትን ለእግዚአብሔር ልጆች በዚህ ምድር
ና በሚመጣው አለም የተወሰነውን በረከት ለመካፈል ከፊት ይልቅ እለት እለት እየበረታን
መኖር ይኖርብናል፡፡ ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ቃል ና ፈቃድ የሆነን ነገር በህይወታችን ላይ

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


13

መናገር፤ የተናገርነውን ለማድረግ ክርስቲያናዊ መንገድ መራመድ፤ መቀበልና የተደረገልንን


መመስከርና ማመስገንን ሁልጊዜ መለማማድ ይኖርብናል፡፡

ተፈፀመ

ትምህርት-አራት

ክርስትያናዊ ባህሪ እና ብልፅግና


4.1 መግቢያ

ገላ 3፡13 ላይ ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን ይላል፡፡ ምን ማለት ነው


ይህ የህግ እርግማን ማለት? ይህ የህግ እርግማን መንፈሳዊ ሞትን፤በሽታን፤ደህነትንና
ጉስቁልናን ያካትታል፡፡ ይህ የጀመረው ዘፍ 3፡22-24 ላይ አዳም እግዚአብሔርን ባልታዘዘ ጊዜ
ነው፡፡ ከዚህ በበላህ ጊዜ ሞትን ትሞታለህ እንዳለው እንደዚሁ ሞት በሰው ልጆች ላይ ነገሠ፡፡
ይህ ሞት መንፈሳዊ ሞት ነው፤ይህም ሞት አካላዊ ሞትንና መበስበስን በሰው ልጆች ላይ
አመጣ፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች በጌታችንና በመድሐኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ፀጋ
በእግዚአብሔር አብ ፍቅር፤ በመንፈስ ቅዱስ ከዚህ መንፈሳዊ ሞት ለዘለዓለም ነፃ ወጥተናል፡፡
ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሐር ለዘለዓለሙ ይሁን፡፡ አሜን!!!!

ስለዚህ በዚህ ትምህርት የአዲሱ ሰው ባህሪ እና የብልፅግና መርሆችን እንመለከታን፡፡

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


14

4.2 የዚህ ትምህርት አላማ

 የእግዚአብሔር ልጆች የስራ መርህን በሚገባ ማስተዋል


 የእግዚአብሔር ልጆች የብልፅግና ልክ ማወቅ
 የእግዚአብሔር ልጆች የብልፅግና አላማ መገንዘብ

4.3 ክርስቲያናዊ ባህሪ ወይም ስብዕና


የእግዚአብሔር ልጆች የባህሪያቸው መነሻ ከተወለዱበት ማንነታቸው ነው፡፡ ይህም
በዩሐንስ ወንጌል 1፡13 ላይ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም
ከስጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም፡፡ ይላል፡፡ ስለዘህ የክርስቲያን
የባህሪው ምንጭ ከእግዚአብሔር በተወለደበት እሱነቱ ላይ ነው፡፡
እግዚአብሔር ባህሪያቶች አሉት፡፡ እንዱና ዋንኛው ፍቅር ነው፡፡
1. ዳግመኛ የተወለድን በሙሉ ለፍቅር ተፈጥረናል
ዩሐ 13፡34 ፤ ዩሐ 15፡12 ፤ 1ኛ ዩሐ 4፡21 ፤ ፊሊ 5፡1-5
ፍቅር የደቀ-መዝሙርነት መለያ ነው፡፡
ፍቅር እግዚአብሔርን የማወቃችን ምልክት ነው፡፡ 1ኛ ዩሐ 4፡8
ፍቅር የእግዚአብሔር ልጅነት መለያ ነው፡፡ 1ኛ ዩሐ 3፡1
ፍቅር የመዳናችን ምልክት ነው፡፡ 1ኛ ዩሐ 3፡4
2. ያመነውን ማወጅ (መናገር)
ሞትናህይወት በምላስ እጅ ናቸው፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ
የተናገረውን መልካሙን ቃል ደጋግመን ማወጅ ይኖርበታል፡፡
እግዚአብሔር በሚሰራበት መንገድ መስራት ያማለት እግዚአብሔር
በቃሉ ነው የሚሰራው እኛም በቃላችን ወደ መስራት ማደግ
ይኖርብናል፡፡ ያዕ 3፡2-6 ፤ ምሳ 18፡21 ፤ ምሳ 14፡3
3. አለመግባባትንናግጭትን መፍታት
ከክርስቲያናዊ ባህሪ አንዱ ቂም አለመያዝ ነው፡፡ ቂም መያዝ
ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ያበላሻል፡፡ስለዚህ ግጭቶች ሲፈጠሩ
በክርስቲያናዊ መንገድ መፍታት ያስፈልጋል ይህም እውነትን በፍቅር
በመያዝ፤በእምነት የደከመውን እንደ እግዚአብሔር ምህረት በመቀበል
፤በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን እንድነት በመጠበቅ ፤ ከሰው ሁሉ
ጋር(ከማያምኑ ና ከሚያምኑ) በሰላምና በፍቅር መርህ መኖር ማለት
ነው፡፡ ማቴ 18፡15-19 ፤ 1ኛ ቆሮ 6፡1-8
4. የስራ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መርህ
ስራ የሀጢያት ውጤት አይደልም ፤ ስራን የጀመሩት የሰው ልጆች
አይደሉም፡፡ ስራን የጀመረው ራሱ አባታችንና አምላካችን እግዚአብሔር

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


15

ነው፡፡ ሥራ የበረከታችን መንገድ ነው፡፡ ስራ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ትዕዛዝ


ነው፡፡ ዘፍ 1፡28 ፤ 2ኛ ተሰ 3፡10 ፤
ለሌሎች ለማካፈል ኤፌ 4፡28

5. ተፅዕኖ ፈጣሪ ህይወት (Dominion in life)


ሀ. በአለም ላይ (Over the world)
አለም ማለት ይህ የምናየው ሰማይ እና ምድር ማለት አይደልም፡፡
አለም ማለት ከእግዚአብሔር ህይወት፤እውቀትና ፈቃድ ፍፁም የተቃረነ
የአስተሳሰብ፤ የህይወትና የእውቀት ምህዳር ማለት ናት፡፡ አለም
በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የራሱ የሆነ አሰተምህሮ አለው፡፡ስለ ሰው፤ስለ
ፍቅር፤ስለ ትዳር፤ስለእግዚሰብሔር፤ስለ ሀይማኖት፤ስለ
ኢየሱስ፤ስለስራ፤ስለ ወንድ፤ስለ ሴት፤ስለ ገንዘብ፤ስለ ሰይጣን…ወዘተ
ከእግዚአብሔር ፍፁም የተለየ አስተምህሮ አላት፡፡1ኛ ዩሐ 5፡4

ለ. በህይወት በሚሆኑ ነገሮች (over life circumstance)

ሮሜ 5፡17

ሐ. ሐጢያት የበላይነቱን አጥተል (Sin has lost its Dominion)

እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የህይወት መንፈስ ሕግ ከሀጢያትና

ሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛል፡፡ ሮሜ 8፡1-2 ፤ ሮሜ 6፡14

መ. ስህተትን መፍታት (Handling mistakes)

በህይወት ወስጥ ስህተቶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ መረዳትና ስህተቶችን

በወቅቱ መፍታትና የኃላን እየተዉ ወደ ፍት መዘርጋት ለክርስቲያነዊ

ባህሪ ወሳኝ ነው ፡፡

4.4 የብልፅግና መርህ

ሀ. ብልፅግና ምንዲነው?

መፅሐፍ ቅዱስ ስለ ብልፅግና ምን ይላል?

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


16

ብልፅግና እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው መልካም ፈቃዱ ነው፡፡

ብልፅግና እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ለእኛ በያዘልን ልክ መኖር ማለት ነው፡፡

ለ. የብልፅግና አላማ

እግዚአብሔር ለእኛ የተናገረውን ኪዳን ለማስፈፀም፡፡ ዘዳ 8፡17-18

የሌሎችን ጉድለት እንድንሞላ፡፡

በምድር የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሰዎች ለመግለጥ፡፡

ማጠቃለያ

እግዚአብሔር የሰውን ልጆች ከፈጠረ በኃላ ወስዶ ያስቀመጠው በገነት ነው፡፡ አሁንም
እግዚአብሔር ለእኛ ለልጆቹ ያለው አላማ ልጆቹ በራሱ መልክ እንዲንኖር ነው፡፡ ስለዚህ
ራሳችንን ከእግዚአብሔር ፍቅር በታች ራሳችንን ዝቅ በማደረግ በፈቃዱ ጥላ ስር ራሳችንን
ማስቀመጥንን እና በአባታችን ባህሪ ላይ ፍፁም መደገፍን ራሳችንን እናስተምር፡፡ የፍጥረት እና
የህይወት ጀማሪዎች እኛ አይደለንም፡፡ ፍጥረትና ህይወት የተፈጠሩት በእግዚአብሔር እውቀት
ነው፡፡ በአንድ ወቅት እኛ ራሳችን የእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርን፡፡ ስለዚህ ሁሉም በእሱ እውቀት
ከተፈጠሩ ሁሉም እንደእሱ እውቀት ይኖራሉ ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሔር እውቀት ከተፈጠርን
በእርሱ እውቀት፤መርህ እና ፈቃድ መኖርን ራሳችንን አያስለመድን በእግዚአብሔር ፍቅር
ወስጥ ለእኛ ያለዉን መንፈሳዊ ና ስጋዊ በረከትን ለመቀበል ከክርስቶስ ፀጋ በታች ራሳችንን
እየጣልን ከመንፈስቅዱስ ጋር ህበረት በማደረግ እንደእግዚአብሔር ባለጠግነት የተበረክንበትን
መባረክ እናጣጥም፡፡

ተፈፀመ

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


17

ትምህርት-አምስት

የክርስቶስ ደም (Blood of Christ)

5.1 መግቢያ

ስለ ክርስቶስ ደም ና ስጋ ማውራት ለምን አስፈለገ ? በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ እነዚህ ጉዳዮች


በተደጋጋሚ ለምን ተገለፁ? በቤተ ክርስቲያን ላለፉት ብዙ ዘመናት ስለዚህ ጉዳይ ሲነገር
ቆይተዋል አሁንም በተደጋጋሚ ትምህርት ና ስልጠና ይሰጣል፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች
የክርስቶስን ደም አላማና በክርስቶስ ደም በኩል የተገጠዉን የእግዚአብሔር ፍቅርናፀጋ ምን
ያህል እንደሁነ በዚህም ውስጥ ለእኛ የተሰጠንን ህይወት ካላስተዋልን የተገለጠዉን
የእግዚአብሔርን ህይወት በሙላት መኖር ይሳነናል፡፡

5.2 የትምህርት አምስት አላማ


 የእግዚአብሔር ልጆች በክርስቶስ ደም በኩል የተካፈልነዉን ህይወት
ማወቅ
 የእግዚአብሔር ልጆች በክርስቶስ ደም በኩል የተቀበልነዉን ህይወት
እንዴት መኖር እንዳለብን ማወቅ

ዘሌ 17፡11 የስጋ ህይወት በደም ውስጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕይወት ከአካል ጋር የተዋሀደ
መንገድ ደም ነው፡፡ ከሰው ልጆች በሰይጣን የተወሰደው ነገር ሁሉ የሚመለሰው በክርስቶስ
ኢየሱስ ደም ብቻ ና ብቻ ነው፡፡ በ ራዕይ 5፡9-10 ላይ እንደተገለፀው የክርስትና ሕይወት
ጅማሬ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ነው፡፡

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


18

1. ደሙ ለእኛ ያመጣልን ትርፍ


1. በደሙ የኃጢያት ይቅርት አግኝተናል(ሥርየት እግኝተናል) ኤፌ 1፡7
ሌዋ 16፡1 ፤ ሕዝ 18፡20 ፤ ሮሜ 6፡23 ፤ ዕብ 2፡10 ፤ ሮሜ 5፡9
2. በጠላት ላይ ድል ሰጥቶናል
የክርስቶስ ደም እግዚአብሔርን ከእኛ ጋር ያስታረቀና የዲያብሎስን መብት ያሳጣ ነው፡፡
ዘፀ 12፡13 ፤ ቆላ 2፡15
3. የክርስቶስ ደም የኪዳን ደም ነው
እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠውን የተስፋ ቃል ያዳነው በኢየሱስ ደም ነው፤ ደሙ የኪዳን
ደም ነው፡፡
4. ኪዳን የሁለት ወገኖች ስምምነት ሲሆን እግዚአብሔር ለእኛ ለሰጠው ቃል ያቀረበው
ማስረገጫ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ነው፡፡ ዕብ 9፡1 ፤ ማቴ 26፡26-27 ፤ ዩሐ 1፡29
5. የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ህጋዊ ዋጆ ነው
ዋጆ ማለት የአንተ የነበረን ማንኛውም ነገር በተለያየ ምክንያት ወደ ሌላ ወገን የገባን
ነገር ዋጋ ከፍለክ ስታስመልስ ዋጆ ይባላል፡፡ ኤፌ 1፡7

የኢየሱስ ደም ወደ ሕልውናው መግቢያችን ነው


ሰው ያለ ኢየሱስ ደም ወደ መለኮት መቅረብ አይችልም ፡፡ ዕብ 9፡12 ፤ ዕብ 13፡12
የኢየሱስ ደም የእግዚአብሔርን ሕይወት የተካፈልንበት መንገድ ነው
የስጋ ሁሉ ህይወት በደም ውስጥ ነው ፤ በኢየሱስ ስጋ ውስጥ ደም አለ ፤ በደም
ውስጥ ሕይወት አለ፡፡ ኢየሱስ ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም አለው ሲል የአኔ
ሕይወት ወይም የመለኮት ሕይወት አለው ማለቱ ነው ምክንያቱም በኢየሱስ ደም
ውስጥ ያለው የመለኮት ሕይወት ነው፡፡
ዩሐ 6፡53-56
6. ደሙ ለአማኞች መልካም ምስክርነት ይሰጥላቸዋል
ደም ውስጥ ሕይወት ስላለ መልካምም ሆነ የክስን ቃል ሊናገር ይችላል፡፡የአቤል የደሙ
ድምፅ በወንድሙ ላይ ክስን እንደተናገረ ሁሉ የኢየሱስ የደሙ ድምፅ ለአማኞች ድልንና
ነፃነትን ይናገራል፡፡
የደሙን ኃይል እንዴት መጠቀም እንችላለን
በቃሉ መንፈስ ደሙን በመንፈስ በመረጨት(ቃሉን ስንካፈል)
የእግዚአብሔር ቃል ፊደል አይደልም መንፈስ እንጂ ፤ ፍደል ይገድላል መንፈስ ግን
ህይወትን ይሰጣል፡፡ ዕብ 10፡22 ፤ ራዕ 1፡5 ፤ ሮሜ 5፡9 ፤ ዘፀ 12 ፤ ዩሐ 6፡63
በእምነት በደሙ በመረጨት
1ኛ ጴጥ 1፡1-2 ፤ ዕብ 12፡24 ፤ ዕብ 10፡19
የጌታን እራት( ስጋውን ና ደሙን ስንወስድ)
በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ አማካኝነት ለእኛ የሆነውን ትርፍ እያሰብን በሙሉ
እውቀት ስንወስድ፡፡ 1ኛ ቆሮ 10፡16-18 ፤ 1ኛ ቆሮ 11፡22-30

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ


19

ማጠቃለያ
የክርስቶስ ደምና ስጋ እኛን ወደ ቀደመው የእግዚአብሔር ፈቃድ ማለትም ገና ሰማይ ና ምድር
እንዱሁም አኛን ጨምሮ ፍጥረት ሁሉ ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር ያሰበውን ሰው የተባለውን
ሰው ወደ መሆን ዳግም እግዚአብሔር ሰው ወደሚለው ሰው ዳግም የተፈጠርንበት መሆኑን
አውቀንና አስተውለን በደሙ ውስጥ ባለው የሕይወት ልክ ለመኖር እንበርታ፡፡ በደሙ ወስጥ
ያለው የክርስቶስ ሕይወት ነው፡፡ የተቀበልነው የክርስቶስን ሕይወት ነው ይህም ማለት
የክርስቶስን ማንነት ነው የእኛ ማንነት የሆነው ስለዚህ ይህንን እያሰብን ሁሌ በምስጋና እና
ዝማሬ በእግዚአብሔር ፍት እንሁን፡፡

ትምህርት ስድስት

ራዕይ እና አገልግሎት

6.1 መግቢያ

Foundation class level-one የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ

You might also like