Professional Documents
Culture Documents
ከምእራፍ 1-6
የኤፌሶን መጽሀፍ መግቢያ
የመልእክቱ ጸሀፊ እራሱ ጳውሎስ መሆኑ መልእክቱ ይገልጻል 1፣1 እና 3፣1 ይህ መልእክት ኤፌሶንን ጨምሮ
ወደ ሌሎች ከተሞች እንዲደርስ የተጻፈ ዘዋሪ ደብዳቤ ሳይሆን ቸአይቀርም 1፣1፣15 6፣21-23 ፓውሎስ
የቆላስያስን መጽሀፍ በጻፈበት ጊዜ በ60 አመተ አለም ግድም በሮም እስር ቤት እያለ ይህንን ደብዳቤ
ጽፎታል፤ 3፣1 እና 4፣1 6፤20
የኤፌሶን ከተማ በትንሹ እስያ በዛሬዋ ቱርክ ምእራፍ ክፍል ከሚገኙት ከተሞች እጅግ የታወቀች ከተማ
ነበረች። ከተማዋ ወደ ኤዥያን ባህር በሚፈሰው የካይስተር ወንዝ ላይ አንድ ወደብ ነበራት ታላላቅ የንግድ
መንገዶች አቋርጠው በሚያልፉበት ቦታ ላይ የተመሰረተች ስለሆነች የንግድ ማእከል ለመሆን በቅታለች።
ግሪኮች አርጤምስ ሮማውያን ዲያና የሚሏት ጣአኦት አምላክ ቤተመቅደስ በዚችው ከተማ ይገኝ ነበር።
ጳውሎስ በኤፌሶን ሶስት አመት ያህል ተቀምጦ የወንጌል ስርጭት ማእከል አድርጓት ነበር ሐዋርያት 19፤10
በዚያን ጊዜ የነበረችው ቤተክርስቲያን በአንድ ወቅት አድጋ ተስፋፍታ ነበር በኋላ ግን በራእይ 2፤1-7 ያለው
ማስጠንቀቂያ ተሰጣት
የመልእክቱ ይዘት እንደ ሌሎቹ የጳውሎስ መልእክቶቸ የስህተት ትምህርት ወይንም ነቀፌታን በተመለከተ
የሚያወሳው ነገር የለም። መልእክቱን ሲጽፍ የአንባቢዎችን አድማስ በማስፋት የእግዚአብሔርን
የዘላለም እቅድና የጸጋውን ጥልቀት ይበልጥ እንዲረዱና እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ያለውን ታላቅ ግብ
እንዲያደንቁና በዛ ውስጥ መኖር እንዲችሉ ነው ሲሆን ቅዱሳን በክርስቶስ ያላቸውን ህብረትና ማንነት
እንዲያውቁና እርስ በእርስም እንደ አካል አንድነትን በመጠበቅ እንዴት መገንባትና ማደግ እንዳለባቸው
ለማስተማር ነው።
የመወያያ ጥያቄዎች
2. እግዚአብሔር እኛን አማኞችን መቼ፣ በምን፤ ለማን እንደመረጠን የሚገልጹትን ሀሳቦች ዘርዝር
5. በተነበበልህ ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ልጆቹ እንድንሆን የጸጋው ክብር ተካፋዮች እንድንሆን የሚስጥሩና
የመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ተካፋዮች እንድንሆን ያደረገው በክርስቶስ በኩል እንደሆነ ተገልጿል፤ በክርስቶስ
ተብሎ በተደጋጋሚ ከተጻፈው ሀሳብ የምትማረው (የምትረዳው) ዋነኛውን ሀሳብ ግለጽ?
ማጠቃለያ ዛሬ ከክርስቶስ ጋር ህብረት በማድረግ የሚገኙትን ጥቅሞችና በረከቶች ተምረናል። ክርስቶስ የጁሉ ነገር
ቁልፍ እንደሆነ ካወክ ከክርስቶስ ጋር ፍጹም የሆነ ህብረት እለት እለት እንዲኖርህ ቃሉን በማጥናት፤ በጸሎት፤
ያወከውን እውቀት በተግባር በመተርጎም ትጋ
የእግዚአብሔር አብ ስራ፤ መምረጥ (ኤፌሶን 1፤3-6)
የእግዚአብሔር ወልድ ስራ፤ መዋጀት (ኤፌሶን 1፣7-12)
የመንፈስ ቅዱስ ስራ፤ ጥበቃ (ኤፌሶን 1፤13፣ 14
በረከት ቁጥር 3
መመረጥ ቁጥር 4
ልጅ መሆን ቁጥር 5
ተቀባይነትን ቁጥር 6
ይቅርታን ቁጥር 7
ኤፌሶን 1፣15-16
ማጠቃለየቅር
የመወያያ ጥያቄዎች
1. ከቁጥር 15_23 ጳውሎስ የጸለየላቸውን ሶስት የጸሎት ሀሳቦችን ዘርዝር
ማጠቃለያ
እግዚአብሔርነ በበለጠ ለማወቅ የሚረዳህን ጥበብና መገለጥ እንዲሰጥህ።
እንዲሁመ በእርሱ የተጠራህበትን ተስፋ ምን እንደሆነ ታውቅ ዘንድ የልቦናዎችህ
አይኖች እንዲበሩና ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነውን ሀይሉን እንድታውቅ እለት እለት
በዚህ ሀሳብ በመጸለይና ቃሉን በማሰላሰል ትጋ
ጥናት 4
ምእራፍ 1 22-23
በዛሬው እለት በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ስላለው ግንኙነት እንማራለን።
የመወያያ ጥያቄዎች
5. እርሱ አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የክርስቶስ ሙላቱ ናት ከሚለው ሀረግ አካሉና
የእርስ ሙላት የሚለውን ሀሳብ ተወያዩበት
ማጠቃለያ
በዘህ እለት የተማርነው ለክርስቶስ ሁሉም ነገር እንደተገዛለትና እግዚአብሔርም
ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ በመስጠት ቤተክርስቲያን ደግሞ የክርስቶስ
የሙላቱ መገለጫ መሆኗን ነው፤ ስለዚህም አንተም ደግሞ በክርስቶስ አካል ውስጥ
ስላለህ ጌታ ባስቀመጠህ ቦታ እሱን ለመግለጽ ድርሻህን ተወጣ
ጥናት 5
ምእራፍ 2፣1-10
በዛሬው ጥናታችን እግዚአብሔር እኛን ከምን እንዳዳነን፣ እንዴት እንዳዳነንና፤ ለምንስ
እንዳዳነን የምንማርበት ክፍል ነው።
የመወያያጥያቄ
1. ስለ ኤፌሶን አማኞች የቀድሞ ማንነታቸው ሐዋርያው ጳውሎስ የገለጸውን
በዝርዝር አስፍር?
መጠቃለያ
በዘሬው ትምህርት በክርስቶስ ስለሚገኝ አንድነት ተምረሀል። ክርስቶስ በአይሁዳውያንና
በአህዛብ መሀከል የነበረውን ልዩነትና ጥላቻ በሞቱ አስወግዶ እንዴት አንድነትን
(ቤተክርስቲያን) እንደመሰረተና በዚህች አዲስ በተፈጠረችው የክርስቶስ አካል ውስጥ
ሁላችንም አንድ እንደሆንና እኩል መብት እንዳለን አውቀሀል። ዛሬ ክርስቶስ በመስቀል ላይ
ሞቶ የፈጠራትን አንድነት ለመጠበቅ እንደቃሉ በመሰረቱ ላይ በመታነጽ የጌታ ቤተመቅደስ
በመሆን ተሰራ።
ጥናት 7
ምእራፍ 3፣1-13
መግቢያ በዚህ ጥናት ውስጥ ሀዋርያው ጳውሎስ ስለተሰጠው የወንጌል አገልግሎትና
ሰለተገለጠለት የአገልግሎት ሚስጥር እንወያያለን
የመወያያ ጥያቄዎች
1. ሐዋርያው ጳውሎስ ስለተሰጠው አገልግሎት የጠቀሰውነ ግለጽ
ማጠቃለያ
ጳውሎስ ይህንን ጸጋ ለአህዛብ ለማድረስ ህይወቱን እንደከፈለ፤ አንተም የተጠራህለት ዋነኛ
አላማ እንደሆነ አውቀህ ይህንን የእግዚአብሄርን የጸጋ ወንጌል ለሌሎች በቃልና በስራል ትጋ
ጥናት 8
ከምእራፍ 3፤14-21
በዚህ ክፍል የምንማረው ጸሎት የሐዋርያው ጳውሎስ የአገልግሎት አንዱ ክፍል እንደሆነና
እኛም ያለብንን ሀላፊነት ለመወጣት ለሌሎች መጸለይ እንደሚገባን ያስተምረናል።
የመወያያ ጥያቄዎች
ሐዋርያው ጳውሎስ የጸለየው የጸሎት ዋና ሀሳቦች በምንና በምን ላይ ያተኮረ ነው?
ማጠቃለያ
ዛሬ ከጳውሎስ ፀሎት በተማርከው መሰረት ያንተም ሆነ የሌሎች ውስጣዊ ሰውንት
እንዲጠነክር፤ክርስቶስ በእምነት በልባችሁ እንዲኖርና ፍቅሩም በሙላት በአንተና
በአመኑት ሁሉ እንዲኖር፤ በግል ህይወትህም ሆነ በሌሎች ህይወት ውስጥ የጎደሉትን
ነገሮች በማየት በእግዚአብሔር ፊት በፀሎተ ትጋ።
ክፍልሁለት
ከምእራፍ አራት እስከ ስድስት
የዛሬንውን ጥናታችንን ከመጀመራችን በፊት ስለዚህ ክፍለ ማለት ከምእራፍ አራት እስከ
ስድስት ውስጥ ሀዋርያው ጳውሎስ የስተማረውን ዋና ሀሳብ እንመልከት። በክፍል አንድ
ጥናታችን ከምእራፍ አንድ እስከ ሶስት እንደምታስታውሱት አማኞች ከክርስቶስ ጋር
ስላላቸው አንድነትና እንዴት ክርስቶስ ቤተክርስትያንን እንደመሰረተ ተምረናል።በዚህ ክፍል
ሁለት ከምእራፍ አራት እስከ ስድት ባለው ክፍል ደግሞ በቅዱሳን መሀከል በቤተክርስትያን
ሊኖር ስለሚችለው አንድነትመ እንዲሁም በባልና በሚስት፤ በወላጆችና በልጆች
በተጨማሪም በአሰሪና በሰራተኛ መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነትና ክርስቶስ
የመሰረተውን አንድነታችንን (ቤተክርስትያንን) እንዴት መገንባት ወይንም ማነፅ
እንደሚገባን የሚያስተምር ክፍል ሲሆን በመጨረሻም የእግዚአብሔርና የህዝቡ ጠላት
የሆነውን ሰይጣንን እንዴት መዋጋት እነደሚገባን ንማራለን።
ጥናት ዘጠኝ
ምእራፍ 4:1-6
መግቢያ: በዛሬው ጥናታችን በክርስቶስ ያለንን አንድነት ወይንም ቤተክርስትያንን
ለማነፅ(ለመገንባት) መሰረታዊና ዋነኛ ስለሆኑት ጠቃሚ ነገሮች እንማራለን።
የመወያያ ጥያቄዎች
1. በቁጥር አንድ እስከ ሶስት መሰረት ሀዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን አማኞች
እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ነገሮች ዘርዝር።
ማጠቃለያ
በክርስቶስ የተገኘኸውን አንድነት ለመጠበቅ ዛሬ በተማርከው መሰረት በትህትና፣
በየዋህነት፣በትእግስት፣እርስ በርስ በመፋቀር የተጠራህበትን መጠራት የሚያስመሰግን
ኑሮ በመኖር የሚቻልህን ሁሉ በታማኝነት ፈፅም።
ጥናት አስር
ምእራፍ 4 ፣ 7- 16
መግቢያ
በዛሬው ጥናታችን ክርስቶስ ለቤተክርስትያን ስለ ሰጣቸው ስጦታዎች እንዲሁም
የስጦታዎቹን አስፈላጊነትና ጥቅም እንማራለን።
የመወያያ ጥያቄዎች
1. በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ የሱስ ክርስቶስ ለቤተክርስትያ የሰጠውን ስጦታዎችንና
ጥቅማቸውን ዘርዝር።
ማጠቃለያ
በክርስቶስ ያገኘነውን አንድነት ተግቶ የመጠበቅ የሁላችን ድርሻና ሀላፊነት ነው።
ለዚህም ይረዳን ዘንድ ክርስቶ እየሱስ ይህቺ በደሙ የዋዧትን አካሉ የሆነችውን
ቤተክርስትያንን በሚገባ እንድትታነፅ የተለያዩ የፀጋ ስጦታዎችን ሰቷል።አንተም
የሚገባህ ለመፈፀም የተሰጠህ የፀጋ ስጦታ ምን እንደሆነ ለይተህ በማወቅ ድርሻህን
በታማኝነት እለት እለተ በመፈፀም ትጋ።ይህንንም ሀላፊነት በሚገባ መፈፀም
የምንችለው በትህትና፣በየዋህነት፣በትእግስት፣እርስ በርስ በመዋደድና በመንፈሳዊ
ህይወታችን ስናድግ ነውና ይህንን ሁሉ ለማድረግ ትጋ።
ጥናት 11
ከጥናት አስር የቀጠለ
መግቢያ በዛሬው ጥናታችን በክርስትና ህይወታችን እንዴት ማደግ እንዳለብንና
ማደጋች በቤተክርስቲያን ላይ የሚያስከትለውን ውጤት ምን እንደሆነ እንማራለን።
የመወያያ ጥያቄዎች
10. የእያንዳንዳችን መንፈሳዊ እድገት ቤተክስትያንን እንዴት ማነፅ ይችላል?
ማጠቃለያ
ለቤተክርስቲያን መታነፅ እንዲሁም ወደ ክርስቶስ ሙላት በማደግ የተሰጣትን ሀላፊነት
መፈፀም የምትችለው እያንዳንዱ የአካል ብልቶች የራሳቸውን ተግባር ተግተው በታማኝነት
ሲፈፅሙ ብቻ ነው። ይህም ሊሆን የሚችለው ብልቶች ሁሉ ወደ ክርስቶስ ሙላት ማደግ
ሲችሉ ነው።ስለዚህ የተሰጠንን ፀጋ በሚገባ ተጠቅመን ቤተክርስትያን ትታነፅ ዘንድ
ሁላችንም በክርስቶስ እርስበርስ ተገጣጥመን ሙላት ወደሆነው ወደ ክርስቶስ እንደግ።
ጥናት 12
ምእራፍ 4፤17-32
በዚህ ክፍለ ትምህርት ላይ አካልን ለማነጽና ለቤተ ክርስቲያን እድገት በክርስቶስ ስለሚገኝ
አዲስ ማንነት እንማራለን፤
ማጠቃለያ
1. በዚህ ክፍል ውስጥ እንደ እግዚአብሄር ልጆች ከእኛ የሚጠበቁብንን ነገሮች ዘርዝር።
ማጠቃለያ
ዛሬ በተማርነው መሰረት የጨለማንና ስራውን ክደን እለት በለት የብርሀንን ፍሬ
እያፈራን እንደ ተወደዱ ልጀች እግዚአብሄርን እንከተል።
ጥናት አስራ አምስት
ምእራፍ 5፣21- 6፣9
መግቢያ
በዛሬው ጥናታችን በቤተክርስቲያን፤ በባለና በሚስት፣በወላጆችና በልጆች እንዲሁም
በአሰሪና በሰራተኛ መሀከል ሊኖር ስለሚገባ ግንኙነት ይህም ቤተክርስቲያንን ለማነፅ
የሚያስከትለውን ጥቅም እንማራለን።
የመወያያ ጥያቄዎች
1. በዚህ ክፍል ውስጥ ግንኙነትን በተመለከተ የተገለጹትን ዋና ሀሳቦችን ዘርዝር።
ማጠቃለያ
ዛሬ በተማርከው በእግዛብሄር ቃል ህይወትህን እየመረመርክ እራስህን ለሌሎች
እያስገዛህ በቤትና በውጭ በቅርበት ካሉ ሰዎች ጋር ሁሉ መልካም ግኑኝነት እንዲኖርህ
የተቻለህን ሁሉ አድርግ። ይህንን ድርሻችንን ብንወጣ ቤተክርስቲያን ትታነጻለች
ቤተክርስቲያንም እንደሚገባ ታድጋለች።
ጥናት 16
ኤፌሶን 6፤10-13
በዛሬው ጥናታችን ጠላታችንን ስለማወቅና ውጊያችን ከማን ጋር እንደሆነ ለዚህም
ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልጉንን መንፈሳዊ የጦር እቃዎች ምን እንደሆኑ እናጠናለን።
1. የዲያብሎስን ስራ ይቃወሙ ዘንድ፤ ጳውሎስ የገለጸላቸውን ሀሳቦች ዘርዝር፥
2. ለዚህ መንፈሳዊ ውጊያ የሚያስፈልጉንን የጦር እቃዎች ምን ምንድናቸው?
የመወያያ ጥያቄዎች
1. በዚህ ክፍል ውስጥ ከተዘረዘሩት የመጀመሪያ የጦር እቃ እውነት ነው፤ ይህ እውነት
ምንድነው? ይህንን የጦር እቃ በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ እነዴት ነው
ልንጠቀምበት የምንችለው?
ማጠቃለያ
የጠላትህን ማንነትና ምንነት በደንብ ከተረዳህ በቂ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ
እንደ ክርስቶስ ወታደር አቋምህ በተስተካከለ ሁኔታ ላይ እንዲገኝ በማድረግ በውጊያው
ባለድል ለመሆን አስቀድመህ በመዘጋጀት የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ለብሰህ በጸሎት
መጋደልህን ቀጥል።