Professional Documents
Culture Documents
AY Bible Club Discipleship University +251 11 5 1 3202
AY Bible Club Discipleship University +251 11 5 1 3202
ጥናት
መንፈሳዊ ሥጦታዎችና
.1
አገልግሎቶች
የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር ደቀ መዝሙርነት ትምሕርት ቤት
AY Bible Club Discipleship University
እግዚአብሔር ይባርካችሁ
መግቢያ
እግዚአብሔር እያንዳንዱ አባል ለቤተ ክርስቲያኑና ለሰብዓዊ ዘር የጋራ ጥቅም ሥራ ላይ ሊያውላቸው
የሚገባውን መንፈሳዊ ሥጦታዎች በየዘመኑ ላሉ የእርሱ ቤተ ክርስቲያን አባላት ሁሉ ይሰጣል፡፡ ለእያንዳንዱ
ሰው እንደሚፈልገው በሚያካፍለው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጡት እነዚህ ሥጦታዎች ቤተ
ክርስቲያንዋ በመለኮት የተሰጧትን ተግባራት ለማሟላት እንድትችል የሚያስፈልጉ ችሎታዎችንና
አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልፀው እነዚህ ሥጦታዎች እንደ እምነት፣ መፈወስ፣
ትንቢት መናገር፣ መስበክ፣ ማስተማር፣ ማስተዳደር፣ ማስታረቅ፣ ርህራሄ፣ ራስን መስዋዕት የሚያደርግ
አገልግሎትና ሰዎችን ለመርዳትና ለማበረታታት የሚያስችሉ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ያጠቃልላል፡
፡ አንዳንድ አባላት በእግዚአብሔር ተጠርተው በተለየ ሁኔታ አባላትን ለአገልግሎት ለማስታጠቅ፣
ቤተክርስቲያንን ወደ መንፈሳዊ ብስለት ደረጃ ለማድረስና የእምነት አንድነትንና እግዚአብሔርን
ማወቅን ለማጎልበት በሚያስፈልጉ ቤተ ክርስቲያን በምታውቃቸው በእረኝነት፣ በወንጌላዊነት፣
በሐዋሪያነትና በማስተማር አገልግሎቶች ማገልገል እንዲችሉ መንፈስ ተሰጥቷቸዋል፡፡ አባላት እነዚህን
መንፈሳዊ ሥጦታዎች እንደ እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ፀጋ ታማኝ መጋቢዎች ሥራ ላይ በሚያውሉበት ጊዜ
ቤተ ክርስቲያን አጥፊ ከሆነው የሐሰት አስተምህሮ ተጽእኖ ነፃ ትሆናለች፣ ከእግዚአብሔር የሆነ እድገትን
ታድጋለች፣ በእምነትና በፍቅርም ትገነባለች፡፡ (ሮሜ 12፡4-8፤ 1ቆሮ፣12፡9-11፣27፣28፤ ኤፌ.4፡8፣11-16፤
የሐዋ.6፡1-7፤ 1ጢሞ.3፡1-13፤ 1ጴጥ.4፡10፣11)፡፡
መድኃኒታችን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት የተናገራቸው ቃላት ታሪክን የቀየሪ ነበሩ።
ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱና ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ›› (ማርቆስ 16፡15) ብሎ አዘዛቸው፡፡
ለዓለም ሁሉ? ለፍጥረት ሁሉ? ደቀ መዛሙርቱ የማይቻል ሥራ ነው ብለው አስበው ይሆናል፡፡ ጌታችን ረዳተ-
ቢስነታቸው ተሰምቶት በኢየሩሳሌም ሆነው ‹‹የአብን ተስፋ እንዲጠብቁ›› አዘዛቸው፡፡ ከዚያም ‹‹መንፈስ ቅዱስ
በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም፣ በይሁዳም ሁሉ፣ በሰማሪያም፣ እስከ ዓለም
ዳርቻም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ›› (የሐዋ.1፡4፣8) በማለት አረጋገጠላቸው፡፡
ከጌታችን ወደ ሰማይ ማረግ ቀጥሎ በነበረው ጊዜ ደቀ መዛሙርት አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያሳለፉት በፀሎት ነበር፡
፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው በነበሩ ጊዜ አብዛኛውን ጊዜያቸውን አበላሽተው የነበሩት አለመስማማትና ቅናት
በስምምነትና ራስን ዝቅ በማድረግ ተተኩ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ተለውጠው ነበር፡፡ ከክርስቶስ ጋር የነበራቸው የቅርብ
ግንኙነትና የዚያ ውጤት የነበረው አንድነት ለመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ ዝግጅት አስፈላጊ ዝግጅቶች ነበሩ፡፡
ኢየሱስ ለአገልግሎቱ ገጣሚ እንዲሆን በመንፈስ ቅዱስ የተለየ ቅባት እንደተቀበለ ሁሉ (የሐዋ. 10፡38) ደቀ
መዛሙርቱም ለመመስከር እንዲያስችላቸው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ተቀበሉ (የሐዋ. 1፡ 5)፡፡ ውጤቶቹም
የሰዎችን ስሜት የሚያነሳሱ ነበሩ፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ሥጦታ በተቀበሉበት ቀን ሦሥት ሺህ ሰዎችን አጠመቁ
(የሐዋ. 2፡41ን ይመልከቱ)፡፡
ወደ ሩቅ አገር ይሄድ የነበረው ሰው ወደ ሰማይ ሊሄድ የነበረውን ክርስቶስን ይወክላል፡፡ የሰውዬው ‹‹ባሪያዎች››
‹‹በዋጋ የተገዙት›› (1ቆሮ. 6፡20)፣ ‹‹በከበረው በክርስቶስ ደም የተገዙት›› (1ጴጥ.1፡ 19) የእርሱ ተከታዮች
ናቸው፡፡ ክርስቶስ የዋጃቸው ለአገልግሎት ስለሆነ ‹‹ከእንግዲህ የሚኖሩት ለራሳቸው ሳይሆን ለሞተላቸውና
ለተነሣው›› ነው (2ቆሮ. 5፡15)፡፡
ክርስቶስ ለእያንዳንዱ ባሪያ እንደ ችሎታው ገንዘቡንና ‹‹ለእያንዳንዱም ሥራውን›› (ማር.13፡34) ሰጠ፡፡ ከሌሎች
ሥጦታዎችና ችሎታዎች ጎን ለጎን (የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 21ን ይመልከቱ) ይህ ያከፋፈላቸው ንብረት
በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጡአቸውን ልዩ ሥጦታዎች የሚወክሉ ናቸው፡፡
በተለየ ሁኔታ ክርስቶስ እነዚህን መንፈሳዊ ሥጦታዎች የሰጠው በጴንጤ ቆስጤ ቀን ነበር፡፡ ጳውሎስ ‹‹እርሱ
ባረገ ጊዜ ለሰዎች ሥጦታዎችን ሰጠ›› ብሏል፡፡ ስለዚህ ‹‹እንደ ክርስቶስ ሥጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ፀጋ
ተሰጠን›› (ኤፌ 4፡7፣8)፡፡ ቤተ ክርስቲያን የተሰጣትን ሥራ እንድታከናውን የሚያስችሏትን እነዚህን ሥጦታዎች
‹‹ለእያንዳንዱ እንደሚፈቅድ›› (1ቆሮ.12፡11) የሚያከፋፍለው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
በቤተ ክርስቲያናቸው የነበረው መከፋፈል ስላሳሰበው ስለ እነዚህ ሥጦታዎች እውነተኛ ባሕርይና እንዴት
መሥራት እንዳለባቸው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ጻፈላቸው፡፡ መንፈሳዊ ሥጦታዎች የፀጋ ሥጦታዎች ናቸው
ብሎ አስረዳቸው፡፡ ከዚያው መንፈስ ወደ ‹‹የተለያዩ አገልግሎቶች›› እና ‹‹ልዩ ልዩ ተግባራት›› የሚመሩ ‹‹የተለያዩ
ሥጦታዎች›› ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን ‹‹ሁሉን በሁሉ የሚሰራ እግዚአብሔር አንድ›› (1ቆሮ. 12፡4-6) እንደሆነ
ጳውሎስ አጽንዖት ሰጥቷል፡፡
መንፈስ ቤተ ክርስቲያንን ለማስተካከልና ለማነጽ ለእያንዳንዱ አማኝ ሥጦታዎችን ያከፋፍላል፡፡ መንፈስ ምንና
ለማን እንደሚያከፋፍል የሚወስኑት የጌታ ሥራ የሚፈልጋቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ሁሉም አንድ ዓይነት ሥጦታዎች
አይቀበሉም፡፡ ጳውሎስ መንፈስ ለአንዱ ጥበብን፣ ለሌላው ማስተዋልን፣ ለሌላው እምነትን፣ ለሌላው ትንቢትን፣
ለሌላው መናፍስትን መለየትን፣ ለሌላው ልሳንንና ለሌላው ልሳንን የመተርጎም ሥጦታን ይሰጣል አለ፡፡ ‹‹ይህን
ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል›› (ቁጥር 11)፡፡ በቤተ
ክርስቲያን ውስጥ ለሚሠራው ሥራ ምሥጋና መሰጠት ያለበት ሥጦታውን ሥራ ላይ ለሚያውለው ግለሰብ
ሳይሆን ለሰጪው ነው፡፡ ሥጦታዎቹ የተሰጡት ለቤተ ክርስቲያን እንጅ ለግለሰብ ስላልሆነ ተቀባዮቹ ሥጦታዎቹን
እንደ ግል ንብረታቸው መቁጠር የለባቸውም፡፡
መንፈስ ሥጦታዎቹን የሚያከፋፍለው ገጣሚ ሆኖ እንዳየው ስለሆነ ማንኛውንም ሥጦታ መናቅ ወይም ዝቅ
አድርጎ መመልከት ተገቢ አይደለም፡፡ ማንኛውም አባል አንድ ኃላፊነት ወይም ተግባር ስለተሰጠው መኩራራት
ወይም ዝቅተኛ ደረጃ ያለው ኃላፊነት ስለተሰጠው የዝቅተኛነት ስሜት ሊሰማው አይገባም፡፡
የአሰራር ተምሳሌት
ጳውሎስ በተለያዩ ሥጦታዎች ውስጥ መኖር ያለበትን መስማማት ለመግለጽ የሰውን አካል ተጠቅሟል፡፡ አካል
እያንዳንዳቸው በተለየ ሁኔታ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ብዙ ክፍሎች አሉት፡፡ ‹‹አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ
ብልቶችን እያንዳንዳቸውን በአካል ውስጥ አድርጓል (ቁጥር 18)፡፡
ገጽ 2
ማንኛውም የአካል ክፍል ሌላኛውን ‹‹አልፈልግህም!›› ማለት የለበትም፡፡ ሁሉም አንዱ በአንዱ ላይ የሚደገፍ
ስለሆነ ‹‹ዓይን እጅን፡- አታስፈልገኝም ልትለው አትችልም፣ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን፡- አታስፈልጉኝም
ሊላቸው አይችልም፡፡ ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤ ከአካልም
ብልቶች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፣ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብር
ይጨመርላቸዋል፤ ክብር ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም፡፡ ነገር ግን ብልቶች እርስ በርሳቸው
በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን ለጎደለው ብልት የበለጠ ክብር እየሰጠ እግዚአብሔር
አካልን አገጣጠመው›› (ቁጥር 21-21)፡፡
አንዱ የአካል ክፍል በትክክል መስራቱን ካቆመ ችግሩ አካልን በሙሉ ይነካል፡፡ አካል አእምሮ ከሌለው ጨጓራ
ሥራውን መስራት አይችልም፤ ጨጓራ ከሌለም አእምሮ ዋጋ ቢስ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከአባላት አንዱ፣ የፈለገውን
ያህል ትንሽ ቢሆን፣ ከጎደለ ቤተ ክርስቲያን ትቸገራለች፡፡
በአሰራራቸው ደካማ የሆኑ አንዳንድ የአካል ክፍሎች የተለየ ጥበቃ ይሻሉ፡፡ አንድ ሰው ያለ እጅ ወይም ያለ
እግር መኖር ይችላል፣ ነገር ግን ያለ ጉበት ወይም ያለ ሳንባ ወይም ያለ ልብ መኖር አይችልም፡፡ በተለመደው
ሁኔታ እጆቻችንንና ፊታችንን ገልጠን እንሄዳለን፣ ነገር ግን ሌሎች የአካል ክፍሎቻችንን ጨዋነታችንን ወይም
ውበታችንን ለመጠበቅ ስንል በልብስ እንሸፍናለን፡፡ አነስተኛ ሥጦታዎችን አቅልለን ከመመልከት ይልቅ የቤተ
ክርስቲያን ጤንነት በእነርሱ ላይ የሚደገፍ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡
እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ሥጦታዎችን ለማከፋፈል ያሰበው ‹‹በአካል ውስጥ
መከፋፈል›› እንዳይኖር ለመከልከልና የመስማማትና በእርስ በርስ ላይ የመደጋገፍ መንፈስን ለመፍጠር ነበር፡
፡ ‹‹ነገር ግን ብልቶች እርስ በርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን ለጎደለው
ብልት የበለጠ ክብር እየሰጠ እግዚአብሔር አካልን አገጣጠመው፡፡ አንድም ብልት ቢሠቃይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ
ጋር ይሠቃያሉ፣ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል›› (ቁጥር 25-26)፡፡ ስለዚህ አንድ
አማኝ ሲሣቃይ ቤተ ክርስቲያንዋ እንድታውቅ መደረግ አለበት፤ ችግሩን ለመፍታትም መርዳት አለባት፡፡ የቤተ
ክርስቲያንዋ ጤንነት የሚጠበቀው ይህ ግለሰብ ከችግሩ መውጣት ሲችል ብቻ ነው፡፡
ከእነዚህ ሥጦታዎች መካከል የእያንዳንዱን ጥቅም ከተናገረ በኋላ ጳውሎስ የተወሰኑትን ዘረዘራቸው፡
- ‹‹እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመጀመሪያ ሐዋርያትን፣ ሁለተኛም ነቢያትን፣ ሦሥተኛም
አስተማሪዎችን፣ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፣ ቀጥሎም የመፈወስን ሥጦታ፣ እርዳታንም፣ አገዛዝንም፣
የልዩ ልዩ አይነት ልሳኖችንም አድርጓል›› (ቁጥር 28፤ ኤፌ.4፡11)፡፡ ማንም አባል ሁሉም ሥጦታዎች ስለሌሉት
ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን በማመልከት ሁሉንም አባላት ‹‹ነገር ግን የሚበልጠውን የፀጋ ሥጦታ
በብርቱ ፈልጉ›› (ቁጥር 31) ብሎ አበረታትቷል፡፡
ይህ እግዚአብሔር የሚሰጠው ፍቅር (በግሪክ ቋንቋ አጋፔ የተባለው) ራስን መስዋዕት የሚያደርግና አሳልፎ
የሚሰጥ ፍቅር ነው (1ቆሮ.13፡4-8)፡፡ ‹‹በአንድ በሚወደድ ሰው ወይም ነገር ውስጥ አንድ ዋጋ ያለውን ነገር
መገንዘብ የሚችል ከፍ ያለ የፍቅር ዓይነት ነው፤ በስሜት ላይ ሳይሆን በመርህ ላይ የተመሠረተ ፍቅር ነው፤
በሚወደው ነገር ውስጥ ላሉት አስደናቂ ባሕርያት ካለው አክብሮት ውስጥ የሚያድግ ፍቅር ነው፡፡›› ፍቅር
የሌላቸው ሥጦታዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ውዝግብንና መከፋፈልን ያስከትላሉ፡፡ ስለዚህ ከሁሉ የሚበልጠው
መንገድ እያንዳንዱ መንፈሳዊ ሥጦታ ያለው ግለሰብ የዚህ ሙሉ በሙሉ ከራስ ወዳድነት የፀዳ ፍቅር ባለቤት
መሆን ነው፡፡ ‹‹የፍቅርን መንገድ ተከተሉ፣ መንፈሳዊ ሥጦታዎችንም በብርቱ ፈልጉ›› (1ቆሮ.14፡1)፡፡
ጴጥሮስ የመንፈሳዊ ሥጦታዎችን ርዕስ የነገር ሁሉ ፍጻሜ በደጅ መሆኑን ከሚገልፀው አውድ ኋላ ነው የገለፀው
(1ጴጥ.4፡7)፡፡ የጊዜው አስቸኳይነት አማኞች ሥጦታዎቹን እንዲጠቀሙ ያስገድዳቸዋል፡፡ ‹‹ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር
ፀጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደመሆናችሁ እያንዳንዳችሁ የፀጋ ሥጦታን እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ፀጋ እርስ
በርሳችሁ አገልግሉ›› ብሏል (ቁጥር 10)፡፡ እንደ ጳውሎስ ጴጥሮስም እነዚህ ሥጦታዎች የሚሰጡት ራስን ከፍ ከፍ
ለማድረግ ሳይሆን ‹‹በሁሉም ነገር እግዚአብሔር እንዲከብር›› ነው ብሎ አስተምሯል (ቁጥር 11)፡፡ እርሱ ፍቅርን
ከሥጦታዎቹም ጋር አገናኝቷል (ቁጥር 8)፡፡
ክርስቶስ እራሱ ‹‹አንዳንዶችን ሐዋርያት፣ ሌሎችን ነቢያት፣ ሌሎችን ወንጌላውያን፣ ሌሎችን ደግሞ እረኞችና
መምህራን እንዲሆኑ ሰጠ፡፡›› እነዚህ ሥጦታዎች ‹‹ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅና በማመን ወደሚገኝ
አንድነት፣ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፣ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፣ ቅዱሳን
አገልግሎትን ለመስራትና ለክርስቶስ አካል ህንፃ ፍፁማን ይሆኑ ዘንድ›› (ቁጥር 11-13) ማገልገልን ያማከሉ
አገልግሎቶች ናቸው፡፡ እነዚያ መንፈሳዊ ሥጦታዎችን የሚቀበሉ ሰዎች በተለየ ሁኔታ አማኞችን ማገልገልና
ከሥጦታዎቻቸው ጋር አብሮ ለሚሄድ አገልግሎት ማሰልጠን አለባቸው፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ክርስቶስ
ሙላትና ሙሉ ሰው ወደ መሆን የብስለት ደረጃ ያደርሳታል፡፡
በመጨረሻም መንፈሳዊ ሥጦታዎች በክርስቶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ብልጽግና ያመጣሉ፡፡ ‹‹ከእርሱም
የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሰራ፣ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፣ ራሱን
በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል›› (ቁጥር 16)፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ዓይነት እድገት ቤተ ክርስቲያን
እንድትለማመድ እያንዳንዱ አባል እርሱ የሰጠውን የፀጋ ሥጦታዎች መጠቀም አለበት፡፡
ከዚህ የተነሣ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት እድገትን ትለማመዳለች፡፡ እርሱም በአባላት ቁጥር ማደግና በግል
መንፈሳዊ ሥጦታዎች ማደግ ናቸው፡፡ እንደገና ቤተ ክርስቲያን ይህን መታነጽና እድገት መገንዘብ የምትችለው
እነዚህን ሥጦታዎች በፍቅር ስትጠቀም ብቻ ስለሆነ ፍቅር የዚህ ጥሪ አካል ነው፡፡
የመንፈሳዊ ሥጦታዎች አንድምታ
የጋራ አገልግሎት
የተቀቡ አገልጋዮች ብቻ ማገልገል እንዳለባቸውና ተራ ምዕመናን ወንበር እያሞቁ ለመመገብ ብቻ መጠበቅ
እንዳለባቸው የሚያስብ አመለካከትን መጽሐፍ ቅዱስ አይደግፍም፡፡ ‹‹የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን››
(1ጴጥ.2፡9) የሚመሠርቱት ቀሳውስቱና ተራ ምዕመናን ናቸው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ደህንነትና ብልጽግና ሁለቱም
ተጠያቂ ናቸው፡፡ እያንዳንዳቸው ክርስቶስ እንደ ሰጠው ልዩ ሥጦታዎች መጠን እንዲያገለግሉ ተጠርተዋል፡፡
የሥጦታዎች ልዩነት የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋትና ዓለም አዳኝን ለመገናኘት እንድትዘጋጅ ለማድረግ
ሁሉም በምስክርነታቸው አንድ እንዲሆኑ የሚያግዙ የተለያዩ አይነት አገልግሎቶች እንዲኖሩ ያደርጋል (ማቴ.28፡
18-20፤ ራዕይ 14፡6-12)፡፡
ገጽ 4
የተቀቡ አገልጋዮች (ቀሳውስት) ሚና
የመንፈሳዊ ሥጦታዎች አስተምህሮ ጉባኤውን የማሰልጠን ኃላፊነትን በአገልጋዩ ጫንቃ ላይ ያስቀምጣል፡፡ እግዚአብሔር
ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ ወንጌላውያንን፣ እረኞችንና መምህራንን የሾመው የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለአገልግሎት
እንዲያስታጥቁ ነው፡፡ ‹‹አገልጋዮች ራሳቸውን እያደከሙና ሌሎች ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ እየከለከሉ ቤተ ክርስቲያን
መሥራት ያለባትን ሥራ መስራት የለባቸውም፡፡ አባላት በቤተ ክርስቲያን ውስጥና በማህበረሰቡ ውስጥ እንዴት መስራት
እንዳለባቸው ማስተማር አለባቸው፡፡››
የማሰልጠን ተስጥኦ የሌለው አገልጋይ በእረኝነት (ቅስና) አገልግሎት ውስጥ ሳይሆን በሌላ የእግዚአብሔር ሥራ ዘርፍ
መሰማራት አለበት፡፡ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ ያለው እቅድ ስኬታማነት የሚደገፈው አገልጋዮች አባላቱን
እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሥጦታዎች መጠቀም እንዲችሉ ለማሰልጠን ፈቃደኛ በመሆናቸውና ባላቸው ችሎታ ላይ
ነው፡፡
ሥጦታዎችና ተልዕኮ
እግዚአብሔር መንፈሳዊ ሥጦታዎችን የሚሰጠው ዝም ብሎ ተቀባዮቹን ግለሰቦች ለመጥቀም ሳይሆን ሙሉውን አካል
ለመጥቀም ነው፡፡ ተቀባዩ ሥጦታውን የሚቀበለው ለራሱ ብቻ እንዳልሆነ ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም አጠቃላይ ሥጦታዎችን
ለራስዋ ብቻ አትቀበልም፡፡ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ማህበረሰብ ሥጦታዎችን የሚሰጠው ቤተ ክርስቲያን ለዓለም
እንድታስተላልፍ እርሱ የሰጣትን ተልዕኮ ለመፈፀም ነው፡፡
መንፈሳዊ ሥጦታዎች በደንብ ለተሠሩ ሥራዎች የተሰጡ ሽልማቶች ሳይሆኑ ሥራውን በደንብ ለመስራት የሚረዱ
መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የተፈጥሮ ሥጦታዎች ብቻቸውን መንፈሳዊ ሥጦታዎች ባይሆኑም መንፈስ
አብዛኛውን ጊዜ ከግለሰቡ የተፈጥሮ ችሎታዎች ጋር የሚጣጣሙ ሥጦታዎችን ይሰጣል፡፡ አዲስ ልደት ግለሰቡን በመንፈስ
ኃይል ይሞላዋል፡፡ መንፈሳዊ ሥጦታዎችን ለመቀበል እንደገና መወለድ አለብን፡፡
መንፈሳዊ ዝግጅት
ሐዋርያት ኃጢአተኞችን ወደ ክርስቶስ ሊመሩ የሚችሉ ቃላትን መናገር እንዲችሉ ገጣሚዎች ለመሆን ተግተው
ፀልየዋል፡፡ በመካከላቸው ቆመው የነበሩ ልዩነቶችንና ከሌሎች የበላይ የመሆን ፍላጎቶችን አስወገዱ፡፡ የኃጢአት
ንስሐና ኑዛዜ ከክርስቶስ ጋር የቅርብ ህብረት እንዲፈጥሩ አደረጋቸው፡፡ ዛሬም ክርስቶስን የሚቀበሉ ሰዎች
ለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እየተዘጋጁ ሳለ ተመሳሳይ ልምምድ ያስፈልጋቸዋል፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የአንድ ጊዜ ክስተት አይደለም፤ በየቀኑ ልንለማመደው እንችላለን፡፡ ለቤተ ክርስቲያን
የመመስከርንና ወንጌልን የማወጅን ኃይል ስለሚሰጥ ጌታ ያን ጥምቀት እንዲሰጠን መለመን ያስፈልገናል፡
፡ ይህን ለማድረግ ያለማቋረጥ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር መስጠት፣ ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ መኖርና
ሥጦታዎቻችንን ለይተን ማወቅ እንድንችል ለጥበብ መጠየቅ አለብን (ያዕቆብ 1፡5)፡፡
ማረጋገጫ ከአካል
እነዚህን ሥጦታዎች እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የሚሰጥ ከሆነ የሥጦታዎቻችን የመጨረሻ
ማረጋገጫ ከራሳችን ስሜት ሳይሆን ከክርስቶስ አካል ውሳኔ እንዲነሣ ልንጠብቅ እንችላለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ
የሌሎች ሰዎችን ሥጦታ ከማወቅ ይልቅ የራሳችንን ሥጦታዎች መገንዘብ ይከብዳል፡፡ ስለ ሥጦታዎቻችን ሌሎች
የሚነግሩንን ለመስማት ዝግጁ መሆን ብቻ ሳይሆን እኛም በሌሎች ላይ ያሉትን የእግዚአብሔርን ሥጦታዎች
መገንዘብና ማረጋገጫ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡
የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለእኛ የሰጠንን ቦታ ወይም አገልግሎት ይዘን እንዳለን ከማወቅ የበለጠ
የሚያስደስትና የስኬት ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ምንም ነገር የለም፡፡ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት
የሰጠንን ልዩ ሥጦታ ለእርሱ አገልግሎት ማዋል እንዴት ያለ በረከት ነው፡፡ ክርስቶስ የእርሱን የፀጋ ሥጦታዎች
ለማካፈል ይናፍቃል፡፡ ዛሬ የእርሱን ግብዣ መቀበልና ሥጦታዎቹ በመንፈስ በተሞላ ሕይወት ውስጥ ምን
ማድረግ እንደሚችሉ ማወቅ እንችላለን!
ገጽ 6