You are on page 1of 9

[Pick the date]

ርዕስ፡- መንፈሳዊ ዕድገት


መንፈሳዊ ዕድገት/ብስለት

ማውጫ

1. መንፈሳዊ ብስለት ወይም ዕድገት ማለት ምን ማለት?


2. እንዴት በመንፈስ ማደግ እንችላላን?
3. በመንፈስ ማደግ ያለብን መሰረታዊ የህይወት ዘርፎች ምንድናቸው?

መግቢያ

ብዙ ጊዜ ስለመንፈዊ ዕድገት የተለያዩ ብዥታ የሚፈጥሩ


አስተምህሮዎች በቤተ-ክርስቲያን ይሰጣሉ ይህም ቅዱሳን ግራ በመጋባት
ህይወት ውስጥ እንዲኖሩ እና በህይታቸው እድገትን አለማሳየታቸው ተጨባጭ
ማስረጃ ነው፡፡ የተለያዩ አስተምህሮዎች መብዛት ቅዱሳን እንደ ህጻናት
በትምህርት ነፋስ በመፍገምገም ወዲያና ወዲህ በማለት ለሰይጣን ሀሳብ
ታልፈው በመሰጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ብቻ ሣይሆን አገልጋዮችን
ማለትም ነብያት፤ሐዋሪያት ሌሎችም የመፍቴያቸው መንገድ እንደሆኑ
በማሰብ ሲጉላሉ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ይህም እውነትን በሚገባ
ባለመረዳት እና ሀሰተኞች ሰዎችን መተቀሚያ ለማድረግ በሚሰጡት የተሳሳተ
አስተምህሮ የተፈጠረ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ሰዎችን የመፍትሔ መንገድ
አድርጎ ማሰብ ለሀሰተኛው መሲህ መንገድ ከፋች ስራ እየተሰራ እንደሆነ
ያሳያል፡፡

ስለዚህ ነው መንፈሳዊ እድገት ወይንም ብስለት አስፈላጊ የሆነው፡፡

በመሰረቱ መፅሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ እድገት, የነፍስ መዳን እና የአዕምሮ


መታደስ ሶስቱም ስለ እንድ ነገር ነው የሚያወሩት፡፡

ክፍል አንድ፡ መንፈሳዊ ብስለት ወይም ዕድገት ማለት ምን ማለት?

ሰው ንስሃ ሲገባ እና በክረስቶስ ኢየሱስ ሲያምን ከእግዚአብሔር ዳግመኛ


ይወለዳል፡፡ ይህ የሚወለደው ማንነት መንፈሱ ነው፡፡ መንፈስ ዳግመኛ
ሲወለድ በእግዚአብሔር ሙላት ይሞላል፡፡

ይህንንም ለማብራራት የሚከተሉትን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እንመልከት


‹‹ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤
እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል፡፡›› 2ተኛ ቆሮንቶስ 5፡17

‹‹ የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁንም


ነፍሳችሁም ስጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ
ፈፅመው ይጠብቁ፡፡›› 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡23

‹‹የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን


አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል፡፡›› ቆላስያስ 3፡10

ከላይ የተዘሩትን ጥቅሶችን በደንብ ስናጠናቸው ዳግመኛ የተወለደው የውስጥ


ማንነታችን ይህም መንፈሳችን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፀጋ ምክንያት
እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ የልጁን መልክ በእኛ ውስጥ ለዘላለም
አድርጓል፡፡

‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች


ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው፡፡›› ዩሐንስ 1፡12

ስለዚህ እውነት በግልፅ የሚነገሩ ብዙ ክፍሎች አሉ፡፡ ስለዚህ ዳግም የተወለዳ


የማንነታችን ክፍል መንፈሳችን በእግዚብሔር የተሞላ ነው፡፡ ይህም ማለት
ቅዱስ ፤ ፃዲቅ፤ባለፀጋ ና በእግዚብሔር ብርሃን-እውቀት እና ጥበብ የተሞላ
ነው ለዚህ ነው እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን፡፡ ይህም በእግዚብሔር ፀጋና
ፍቅር የሆነው እንጂ በእኛ አቅም የሆነ አይደለም፡፡

ይህ ማንነት ከክርስቶስ ጋር ሞቶ የነበረ ከክርስቶስ ደግሞ ከሙታን የተነሳ


ደግሞ ከክርስቶስም ጋር በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተቀመጠ ነው፡፡

ኤፌሶን 2፡4-8 ተመልከቱ

1ኛ ቆሮንቶስ 1፡30-31 ተመልከቱ

ስለዚህ ዳግመኛ የተወለደው ማንነታችን ሙሉ ነው አያድግም፡፡


‹‹ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፡፡ ለአለቅነትና እና
ለስልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል፡፡›› ቆላ 2፡9-10

ዳግምኛ የተወለደው ማንነታችን የሚመስለው ክርስቶስ ኢየሱስን ነው፡፡


መንፈስ የእድገት ሂደት የለውም ስለዚህ መንፈሳችን ክርስቶስን ስለተሞላ
አሁን ሙሉ በፍቅር የተሞላ፣ ፤በሳል ፤ጠንካራ፤ፃዲቅ፤ቅዱስ፤ሀጢያትንም
ሊያደርግ አይችልም ወ.ዘ.ተ ነው፡፡

1ኛ የሐንስ 3፡1-2፣ 4፡13፣ ተመልከቱ

ታዲያ ይህ መንፈሳዊ ዕድገት ምንድነው?

መንፈሳዊ እድገት/ብስለት በእግዚአብሔር ቃል መገለጥና መረዳት የተለወጠ


አዕምሮ ወይም ነፍስ ማለት ነው፡፡

የአዕምሮ መታደስ፤የነፍስ መዳን እግዚአብሔርን መምሰል ና መንፈሳዊ


እድገት አራቱም ስለ አንድ ነገር ነው የሚናገሩት ይህም በእግዚአብሔር ቃል
መታደስ ወይም መለወጥ ስላለበት ስለ ሁለተኛው ማንነታችን መንፈሳችን
ነው የሚናገረው፡፡ ይህ ሁለተኛው ክፍላችን ብዙ አስተሳሰቦች፤ልምምዶችና
ምስለ አዕምሮን የያዘ የማንነታችን ክፍል ነው፡፡ ነፍስን ማዳን የሚችለው
የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡

ዳዊት፡ ነፍሴን መለሳት ስለ ስሙም በፅድቅ መንገድ መራኝ ያለው ለዚህ


ነው፡፡

ስለ ነፍስ የመዳን ወይም የመታደስን ሂደት በሚገባ የሚያስረዳው የመፅሐፍ


ቅዱስ ክፍል 2ተኛ ጴጥሮስ 1፡2-9 ያለው ክፍል ነው፡፡
ይህን ሂደት መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ቃል ነፍሳችን በእውቀት እና
ቃሉን በመረዳት እንዲታድግ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመተባበር
በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በመቆየት እግዚአብሔር በእኛ የሚሰራው ስራ
ነው፡፡ ይህም እዕምሮአችን ውስጥ ያለውን የክርስቶስ መልክ እንዳይገለጥ
የሚጋርደውን አስተሳሰብ፤እምነት እና ምስለ እዕምሮን እያስወገደ ዳግም
በተወለደው ማንነት ውስጥ ያለውን የክርስቶስን መልክ በእኛ ውስጥ እየሳለ
ከክብር ወደ ክብር ከእምነት ወደ እምነት እያደግን እንድንሄድ ይረዳንል፡፡

ለዚህ ነው ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ ወደ እውነት


መንገድ ይመራናል በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ዓለማም ይህ ነው፡፡

ኤፌሶን 4፡11-15፣ 20-24 ‹‹… ሙሉ ሰው ወደ መሆን….››

ሰዎች ሁል ጊዜ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ያለበት ሰው እየፈለጉ ከቤተ


ክርስቲያን ወደ ቤ ተክርስቲያን ከሀገር ወደ ሀገር እንዲከራተቱ
የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ የስጦታዎች ዓላማ በእውቀት እና
በእምነት አስክናድግ ድረስ ማገዝ ነው፡፡

ክፍል፡እንዴት በመንፈስ ማደግ እንችላለን?

መንፈሳዊ እድገት ሂደት ነው፡፡ በአንድ ቀን በአንድ ሳምንት የሚሆን


አይደለም፡፡ ሁሉን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በመንፈሳችን ውስጥ
አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ይህን ህይወት ለመኖር በእግዚአብሔር ቃል እውቀት
ማደግ ያስፈልጋል፡፡

ያዕቆብ 1፡21 ‹‹ … ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም


የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ፡፡››

1ኛ ጰጥርስ 2፡3-5 ተመልከቱ

ይህም ብቻ ሳይሆን ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን የእግዚአብሔር መንፈስ


መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ስላለ እውነትን እንዲገልጥልን መፀለይ
ይኖርብናል፡፡

በአዲስ ኪዳን ለቤተክርስቲያን ሐዋሪያት የፀለዩት ፀሎት አብዛኛዎቹ ስለ


እውቅትና ስለመረዳት ነው፡፡

ለምሳሌ፡

ዩሐንስ 17፡3 ‹‹…አንተንና ያላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ…›


ኤፌሶን 1፡19-24 ‹‹ አንተን በማውቅ የጥበብንና የመገለጥን(መረዳት) መንፈስ
እንድትሰጣቸው…..የልቦናቸው አይኖች እንዲበሩ….››

ቆላ 1፡9-12 ‹‹ …የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብና እዕምሮን (መረዳት)


ሁሉ እንዲሞላባችሁ…›

ፊሊጵስዩስ 1፡9-11 ‹‹… ፍቅራችሁ በእውቀት እና በማስተዋል ሁሉ ከፊት


ይልቅ እያደገ እንዲበዛ…››

ስለዚህ ይህን መፀለይ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

በመጨረሻ ትክክለኛ ህብረት ያስፈልገናል፡፡ ለመንፈሳዊ ዕድገት የወንጌልን


እውነት በሚገባ ከተሩዱና የመንፈስ ፍሬ ከሚታይባቸው ወንድሞችና እህቶች
ጋር ህብረት ማደረግ እኛም በእግዚአብሔር ቃል መረዳትና እምነት
እንድናድግ ያግዘናል፡፡ ይህ በስመ ሀይማኖት ወይም ጴንጠነት መደረግ
ያለበትም መጀመሪያ የህይወታቸውን ፍሬ በመመልከት የሚከተሉትን
የእግዚአብሔር ቃል ማጤን ያስፈልጋል በዚህ ሁሉ ግን መንፈስ ቅዱስ
ከማንም በላይ ከእኛ ጋር እንደሆነ ማወቅ ና መረዳት ያስፈልጋል፡፡

1ኛ ዩሐንስ 1፡3 ‹‹… ከእኛ ጋር ህብረት እንዲናራችሁ….››

ይህን ለመጥቀለል፡-

1. የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ፣መማር፣ ማጥናትና ማሰላሰል በኑሮአችን


እንደቃሉ በእምነት መኖር
2. ፀሎትና አምልኮ
3. ትክክለኛ ህብረት

ክፍል-3 መንፈሳዊ እድገት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ የህይወት ዘርፎች

1. እግዚአብሔርን በማወቅ ማደግ


በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ማንነትና ባህሪ በሚገባ
ማወቅ እና መረዳት በእግዚአብሔር ሕይወት ወደመኖር ያመጣናል፡፡

አብዘኛው ክርስቲያን ስለእግዚአብሔር ያለው እውቀትና መረዳት ሀይማኖት


እና የሰው ትምህርት ብቻ ነው፡፡ ማቴ 15፡9

2. ራስን በማወቅ ማደግ

በእግዚአብሔር ፊት ማን እንደሆንን እና እግዚአብሔር በልጁ ናችሁ ያለንን


እውነት ማወቅና መረዳት በዛ እውነት መኖር

3. ተልዕኮአችንን በማወቅና በመፈፀም ማደግ

እያንዳንዳችን እዚህ ምድር የመጣነው በእግዚአብሔር ዓላማ ነው፡፡ ይህም


እንድንናደረግ እግዚአብሔር የሰጠን ነገር አለ፡፡ እኛ ብቻ የምናደርገው እኛ
ካለሰራነው የሚቀር ተልዕኮ አለ፡፡ ይህን በማወቅና በማድረግ እግዚአብሔር
ማክበር ወደ ምንችልበት ዕድገት መምጣት አለብን፡፡

ዩሐንስ 17፡4፣ ሮሜ 12፡1-3 ፣

ዕብ 12፡1-2 ‹‹…በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ…››

4. በዙሪያችን ያለውን መንፈሳዊ ከባቢ በማወቅ ማደግ


4.1 ቅዱሳን መላዕክት ፡- ዕብ 12፡22-24

አላማቸው፣አቅማቸው ምን እና ምንያህል እንደሆነ መረዳት


4.2 የጨለማ ሀይላት፡ ቆላ 2፡13-15፣1ኛ ጴጥሮስ 5፡8፣ ኤፌ 6፡11-18
አላማቸው፣አቅማቸው ምን እንደሆነ እና ምንያህል እንደሆነ መረዳት

5. ቤተሰባዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሀላፊነትን በመረዳት ማደግ


5.1 ቤተሰባዊ ሀላፊነትን መረዳት ኤፌ 5፡21-6፡9
5.1.1 ባልና ሚስት
5.1.2 ልጆችና ወላጆች
5.1.3 እናት አባት
5.2 ማህበራዊ ሀላፊነትን መረዳት
በማህበረሰቡ ውስጥ የእኛ ሀላፊነት ምን እንደሆነ ማወቅ የሌሎችም ሀላፊነት
እሰከ ምን ደረስ እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡

5.3 አኮኖሚያዊ ሃላፊነትን መረዳት

በአጠቃለይ የማን ሀላፊነት ምንድነው የሚለውን መርህ መረዳት እና በምን


ልብ ወይም መረዳት ነው የመረዳዳት መንገዳችን መሆን ያለበት የሚለውን
ማወቅ አለብን እንጂ በማያገባን እየገባን ወይም ሰዎች ያለአግባብ በእኛ
ጉዳይ እንዲገቡ በመፍቀድ ህይወታችንን ውስብስብ ማድረግ የለብንም፡፡

በህይወታችን ውስጥ ከሰዎችን ምንም መጠበቅ የለብንም ሰዎች የራሳቸው


ሩጫ አላቸው ከቻሉ ያደርጋሉ ካልቻሉ ግን ሌላ መንገድ እንዳለ መረዳት
አለብን፡፡ ሰዎች ላይ በከንቱ ቂም መያዝ ትክክል አይደለም፡፡ የራሳችንን
ሸክም ለሌሎች ማሸከም ወይም የሌሎችን ሸክም ያለአግባብ መሸከም እና
ሌሎችን ለመቆጣጠር ወይም በሌሎች ቁጥጥር ስር መሆን የለብንም፡፡በፍቅር
እና በእውነት ማደግ አለብን፡፡

መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሰሩ፡፡

You might also like