ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ
የመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ስራ
ክፍል አንድ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮት
ስለ መንፈስ ቅዱስ
አንደኛ ሳምንት
የመንፈስ ቅዱስ ማንነት፥
የሥላሴ አንዱ አካል ነው፤ እግዚአብሔር ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ስራ፥
የእግዚአብሔርን ገቢራዊ ሐልዎት ወይም መገኘት በቤተ ክርስቲያን
ውስጥ እንዲሁም በዓለም ላይ መግለጽ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ይባላል።
የመንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሐልዎት መገለጥ ላይ ያለው ድርሻ፥
በብሉይ ኪዳን፥ እግዚአብሔር አብ - ክብር እና በልዩ ልዩ አካላዊ
መገለጦች፤ (ለምሳሌ፥ መላእክትን ወይንም ሰዎችን መስሎ) ተገልጥዋል፤
በወንጌላት፥ እግዚአብሔር ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ) - ተገልጥዋል፤
በቤተ ክርስቲያን (ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ)፥ እግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስ - ተገልጥዋል፤
አንደኛ ሳምንት
የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ከፍጥረት ጀምሮ፥
እግዚአብሔር አብ ያቀደውን፣ እግዚአብሔር ወልድ የጀመራውን፣
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በሚገባ በሕይወት ተጠብቆ
እንዲቀጥል ያደርጋል።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2, የሐዋርያት ሥራ 1:8, የሐዋርያት ሥራ
2:4,17,18, ወደ ሮሜ ሰዎች 8:23
የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ በእግዚአብሔር የማዳን ስራ ላይ፥
እግዚአብሔር አብ፥ ልጁን ሰጠ፣
እግዚአብሔር ወልድ፥ አባቱን ታዞ ኃጢአተያውን ወዶ ያማዳንን ስራ
ፈጸመ፣
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፥ በእግዚአብሔር የተሰጠውን ስጦታ፣
በልጁ የተሰራውን ስራ፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት እያመጣው ነው፤
አንደኛ ሳምንት
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን በረከቶች ወደ እኛ የሚያመጣበት መንገዶች፥
ኀይልን በመስጠት - መንፈስ ቅዱስ ኀይልን ይሰጣል፤
በመቀደስ - መንፈስ ቅዱስ ያነጻል፤
በመገለጥ - መንፈስ ቅዱስ ይገልጣል፤
በአንድነት - መንፈስ ቅዱስ አንድ ያደርጋል፤
የእግዚአብሔር ሐልዎትና በረከት በማረጋገጥ - መንፈስ ቅዱስ
የእግዚአብሔር ሐልዎትና በረከት ያረጋግጣል (የመጠኑ ልክ እና የእኛ
ምላሽ ያለው ቁርኝት)፤
አንደኛ ሳምንት
የአስተምህሮተ መንፈስ ቅዱስ አስፈላጊነት፣
1. መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን ስለተሰጠ፥ በአማኝ ውስጥ
ያደረ፣ የሚሰራ፣ የእግዚአብሔርን ህልውና የሚገልጽ ራሱ እግዚአብሔር
ስለሆነ፣
2. ይህ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ዘመን ስለሆነ፥ ለቤተ ክርስቲያን
እግዚአብሔርን ሊገልጥላት እና እግዚአብሔርን እንድትገልጥ የተሰጣት
መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ፣
3. መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰራ
ስለሆነ፥ በዚህ ዘመን መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርን በቅድስናው
እየገለጠው ስለሆነ፣ በአማኞች መካከል በረከቱን እየሰጠ ስላለ
አስተምህሮተ መንፈስ ቅዱስ መማር በጣም አስፈላጊ ነው።
አንደኛ ሳምንት
1. የመንፈስ ቅዱስ ስሞች እና ማንነት፤
1.1. የመንፈስ ቅዱስ ስሞች፣
1.1.1. መንፈስ ቅዱስ፥
የሉቃስ ወንጌል 11፥13, የዮሐንስ ወንጌል 20፥22,
የሐዋርያት ሥራ 1፥5, መዝሙረ ዳዊት 51፥11
1.1.2. የጸጋ መንፈስ፥
ወደ ዕብራውያን 10፥29
1.1.3. የእውነት መንፈስ፥
የዮሐንስ ወንጌል 14፥17, የዮሐንስ ወንጌል 15፥26,
የዮሐንስ ወንጌል 16፥13, 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፥7
1.1.4. የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥
ትንቢተ ኢሳይያስ 11፥2, ትንቢተ ኢሳይያስ 61:1-3, 1ኛ
ወደ ጢሞቴዎስ 1:17
1.1.5. የክብር መንፈስ፥
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፥14, ኦሪት ዘጸአት 15፥11, መዝሙረ
ዳዊት 145፥5
1.1.6. አጽናኝ፥
የዮሐንስ ወንጌል 14፥15-16, የዮሐንስ ወንጌል 16፥7
አንደኛ ሳምንት
1.2. የመንፈስ ቅዱስ ማንነት፣
1.2.1. መንፈስ ቅዱስ ከስላሴ አንዱ አካል ነው፥
የማቴዎስ ወንጌል 3፥16-17, የዮሐንስ ወንጌል 14፥15-16,
የሐዋርያት ሥራ 10፥38
1.2.2. መንፈስ ቅዱስ እውቀት አለው፥
ትንቢተ ኢሳይያስ 11፥2, ወደ ሮሜ ሰዎች 8፥27, 1ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች 2፥10-11
1.2.3. መንፈስ ቅዱስ ስሜት አለው፥
ትንቢተ ኢሳይያስ 63፥10, ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፥30,
የሐዋርያት ሥራ 7፥57, ወደ ሮሜ ሰዎች 15፥30
1.2.4. መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ አለው፥
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፥11