Professional Documents
Culture Documents
ነጻ ፍቃድ
የመጀመሪያ እትም
Copyright ©2001
የሁለተኛ እትም
REVISED 2015
FOUNDER OF
THE LION S CALL FOR ALL NATION INTERNATIONAL MINISTRY
www.tlcfan.org 1
ነጻ ፍቃድ 2015
ማውጫ
ርዕስ ገጽ
Copyright © 2001
All rights Reserved to Leon
www.tlcfan.org 2
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 3
ነጻ ፍቃድ 2015
draw
www.tlcfan.org 4
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 5
ነጻ ፍቃድ 2015
ሁለተኛው ደግሞ የአዳም በግል ወይም በነጻ ፍቃድ የመኖር ምኞት በስው ውስጥ
ስላለ ነው። (Adamic self-life) ይህ የእኔነት ሕይወት ከድሮ አባታችን ከአዳም ጀምሮ በደም
ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በእኛም የሚኖር ስፍራውን ለእግዚአብሔር መልቀቅ እንቢ አልፈልግም
የሚል ያለመታዘዝ ማንነት ነው። ከዚህም የተነሳ ለእግዚአብሔር ነጻ ፍቃድና ፍላጎት ወይም
ትዕዛዛት መገዛዝ ወይም መታዘዝ አንፈልግሞ። ይህም ሥጋዊ አዕምሮ ‘ego’ ነው።
www.tlcfan.org 6
ነጻ ፍቃድ 2015
“18 ኤፍሬም። ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና
መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ። 19 ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤
የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም ብሎ ሲያለቅስ ሰማሁ።” ኤር.31፥18-19
was chastised, as a bullock unaccustomed to the yoke: turn thou me, and I shall be turned;
for thou art the LORD my God. 19 Surely after that I was turned, I repented; and after that I
was instructed, I smote upon my thigh: I was ashamed, yea, even confounded, because I
Jeremiah 31:18-19
በመንፈስ ኤፍሬም ራሱን እንደ ወይፈን መስሎ ሲጸልይ ኤርሚያስ ሰማ። ይህም
በእርሻ ላይ ሳለ ጌታ ሲመልሰው እንደሚመለስ ተናገረ። መመለስ ማለት ንስሃ መግባት ማለት
ነው። ኤርሚያስ እንደ ሚያሳየው ወይፈኑ ተመልሶ ትክክል መስመሩን እንዲይዝ ማድረግ
የገበሬው ድርሻ እንደ ሆነ ያሳያል። ወይፈን የኤፍሬም ነገድ አርማና ሰንደቃላማ ነው። ዘሁ.2
ኤፍሬም ወደ እግዚአብሔር መመለስና ለጌታ መገዛትን አላወቀም ነበር። ኤፍሬም ግን ወደ ጌታ
እግዚአብሔር ጸሎቱን አላቆመም። እግዚአብሔርን መልስኝ እመለሳለሁ ይለዋል።
www.tlcfan.org 7
ነጻ ፍቃድ 2015
“አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና።” ኤር.17፥14
ትልቁ እግዚአብሔር የሚሰጠን ከሰማይ የሚወርድ መልካም ስጦታ ደግሞ ወደ እርሱ መመለስ
ወይም ንስሃ ነው። ሮሜ.2፥4
the goodness of God leadeth thee to repentance
www.tlcfan.org 8
ነጻ ፍቃድ 2015
Which were born, not of blood, nor of the will of the flesh, nor of
the will of man, but of God 1 John 1:13
የሥጋ ፍቃድ ሰውን ዳግም ሊወለድ ፈጽሞ አይችልም። የሰውም ፍቃድ በሰው ፍቃድ
ላይ በመጫን ሰው ዳግም እንዲ ወልድ ማድረግ አይችልም። ሁሉ ሊሆን የሚችለው
በእግዚአብሔር ፍቃድ ብቻ ነው። ዮሐንስ ይህን ሃሳብ የእግዚአብሔርን ሁሉን ገዢነትና ጀማሪነት
ደግሞም የሁሉን ተቆጣጣሪነት በግልጽ እየደጋገመ በወንጌሉ ያስቀምጠዋል። ዮሐንስ ስለ ነጻ
ፍቃድ ክርክር ሳያውቅ ይህን ጻፈውን? አይደለም። በእኛ ዘመን ስለዚህ ጉዳይ ጥያቄና ክርክር
እንዳለ ሁሉ በዚያን እርሱ በነበረበት ዘመን ክርክር እንደሚኖር ግልጽ ነው።
ዮሐንስ ወንጌሉን በጻፈበት ዘመን በይሁዳ ሦስት ታላላቅ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች
ነበሩ። የሰዱቃውያን፣ የጻፎችና የፈሪሳዊያን ትምህርት ቤት ናቸው። ሰዱቃዊያን በእግዚአብሔር
ሁሉ ገዥነትና ተቆጣጣሪነት ያምናሉ። ጻፎች ደግሞ ሰው ነጻ ፍቃድ አለው ብለው ያምኑ ነበር።
ፈሪሳዊያን ደግሞ እግዚአብሔር የሚረዳቸውን ይረዳል ብለው ያምኑ ነበር። ይህ አንድ በልጅነቴ
የምስማውን አባባል ያስታውሰኛል “እርዱኝ እረዳችኃለሁ” የሚለው ቃል ነው። ይህን አባባል
የሚያምኑ አሁንም አሉ። ይህ ሁሉ የእነዚህ በይሁዳ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ቲዮሎጂያን እውቀት
አሁን እስካለንበት ቀን ድረስ ሲወርድ ሲዋረድ መጥቷል። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገር
ሁሉን ነገር በፍቃዱ እንደ ሚያደርግ ያሳየናል። ኤፌ.1፥11
“እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን
በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።”
www.tlcfan.org 9
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 10
ነጻ ፍቃድ 2015
እንግዲህ ሰዎች እንደ ሚሉት እግዚአብሔር የነጻ ፍቃድን መብት ስጥቶን ከሆነ
እንግዲህ ጳውሎስን ሲያድን እግዚአብሔር ይህን የነጻ ፍቃድ መብት ጳውሎስን ገፎታል ማለት
ነው። ይህ ደግሞ እግዚአብሔርን ፍጹም አያደርገውም። የሰው ልጆች እግዚአብሔር ሁሉን
አያድንም ብለው ያምናሉ። እንዴትስ እግዚአብሔር ሰው ለይቶ ለጥቂቶች ብቻ ይገለጣል?
እግዚአብሔር የሰው ልጆን ሁሉ የሚወድድ ከሆነ ለሰው ልጆች ሁሉ እንደ ጳውሎስ ለምን
አያደርግላቸውምን? የሚሉም አይታጡም። እግዚአብሔር የሰው ልጆች ሁሉ አሁን በአንድ ጊዜ
ማዳን ከፈለገ ሊያድን ይችላል። ማድረግ ያለበት አንድ ነገር ቢኖር ለጳውሎስ እንዳደረገ ለሰው
ልጆች ሁሉ ማድረግ ነው። ሁሉንም በመሬት ላይ እየጣለ እኔ ኢየሱስ ነኝ ካለ ሁሉ ያምናል።
ያኔ ማን ይቃወመዋል ማንስ አልክተልህም ይለዋል?
www.tlcfan.org 11
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 12
ነጻ ፍቃድ 2015
ሃጢያት እንደ እዳ
ሃጢያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ዕዳ የሚቆጠር ነው። ሃጢያትን በምንሰራበት
ወቅት ለሕጉ ባለ እዳዎች እንሆናለን። ሕጉ አንድ ሰው ጎረቤቱን ቢበድል ሕጉ እንደሚበይንበት
ለጎረቤቱ እዳውን ይመልሳል። ይህም የሚመልሰው ለበዳዮ እንደ እዳ ሰለሚቆጠርበት ነው።
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በጠየቁት መሰረት ጸሎትን ሲያስተምራቸው እንዲህ አለ፦
Forgive us our debts, as we forgive our debtors (Matthew 6:12).
“23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች። 24 መቈጣጠርም
በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። 25 የሚከፍለውም
ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ፣”
ይህን አስቡ አዳም በእግዚአብሔር ሚስት ተሰጥቶት ነበር። ልጆችም ነበሩት። ደግሞም
በምድር ላይ ይገዛ ዘንድ ግዛትም ተሰጥቶት ነበር። አዳም ያለው ሁሉ ሚስት፣ ልጅና በምድር
ያለው ሁሉ ነው። አዳም ሃጢያትን ሲሰራ ይህ ያለው ሁሉ ለሃጢያት ተሸጠ። ሰው ሁሉ የሃጢያት
ባሪያ ሆነ። ኢየሱስም የሃጢያትን እዳ እስከ ሚከፍልበት ቀን ድረስ ምድር የአዳምን ሃጢያት እዳ
መዝገብ ይዛው ነበር። ኢየሱስ የእዳ መዝገባችንን ከፈለና ከሃጢያት ነጻ አወጣን። ኢየሱስ የሰሙ
ትርጉም ራሱ አለሙን ከያጢያት የሚያድን ማለት ነው። ስሙን ስንጠራ ምን እያልን እንደሆነ
መገንዘብ ይገባናል። ከሃጢያት ባርነት ደግሞ ነፃ ስንወጣ የኢየሱስ ባሪያዎች የጽድቅ ባሪያዎች
እንሆናለን። ይህም ጳውሎስ በሮሜ.1፥1, ላይ ራሱን እንደገለጸ ማለት ነው። ሮሜ. 6፥15-19
ያንብቡ።
www.tlcfan.org 13
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 14
ነጻ ፍቃድ 2015
የምድር ሕግ
ፈጣሪያችን እግዚአብሔር የምድር ሕግ አለው። ይህን የነጻ ፈቃድ ሃሳብ በጥቂቱ
ከተረዳን ከዚህ ያለፈ በጣም ልንረዳው የምንፈልገውን ነገር አለ። ይህም ስለ ነጻ ፍቃድ ሳይሆን
ሰለ ባለቤትነት “ownership” ነው። ይህን በደንብ ለመመልከት የእግዚአብሔር ሕግና ቃል ውስጥ
የተለያዮ ጥቅሶችን እንመልከታለን። ይህም ከምድር ሕግ ጋር የተያያዘ ነው።
መቼም ቢሆን አንድ ነገር ለመጀመር ከዘፍጥረት መነሳት መልካም ነገር ነው። ሁላችን
እግዚአብሔር ፈጣሪ እንደ ሆነ እናምናለን? አንዳንድ የሃይማኖት ድርጅቶች ምድርን ዲያቢሎስ
እንደ ፈጠረው ያምናሉ። የጥንት ግሪኮች የሚታየውና የሚጨበጠው ግዑዙ ዓለምና በውስጡ
ያለው ክፋት በዲያቢሎስ የተፈጠረ ለሰው ልጆች የተዋወቀ ርኩስ ነገር ነው ብለው ያምናሉ።
ይህ በእግዚአብሔር ቃል ሰናየው መሰረት የሌለው ውሸት ነው።
አንዳንድ ሰዎች የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔር በጣም የሚቆጣ ጨካኝ ነገር ግን የአዲስ
ኪዳኑ ደግሞ መልካም የሚወደድ አምላክ ነው ብለው ያምናሉ። እንግዲህ እነዚህ ሰዎች እርስ
በእርሱ የሚቃረን ባሕሪ ያለው አምላክ ያመልካሉ ማለት ነው። ለእኔ ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው።
እግዚአብሔር ሰውን ጨምሮ ሁሉን ፈጥሯል። ዘፍ.2፥7
www.tlcfan.org 15
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 16
ነጻ ፍቃድ 2015
ባለቤትነትና ነጻ ፍቃድ
www.tlcfan.org 17
ነጻ ፍቃድ 2015
ass fall therein; 34 the owner of the pit shall make it good, and give money unto the owner of
Exodus 21:33-34
www.tlcfan.org 18
ነጻ ፍቃድ 2015
“14 ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ
ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።
www.tlcfan.org 19
ነጻ ፍቃድ 2015
15 ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ
ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ
ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ። 16 አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን
እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ
በደል ለማጽደቅ መጣ። 17 በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና
የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። 18
እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ
ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። 19 በአንዱ ሰው
አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን
ይሆናሉ።” ሮሜ.5
www.tlcfan.org 20
ነጻ ፍቃድ 2015
house, then thou shalt make a battlement for thy roof, that
Deuteronomy 22:8
www.tlcfan.org 21
ነጻ ፍቃድ 2015
shall feed in another man's field; of the best of his own field, and of the best of
Exodus 22:5
የበሬው ባለቤት ነው። የአስገዳጁ ባለቤት ደግሞም አስገዳጁ ነው። እዚህ ላይ ባለቤቱ
አውቆ አጥሩን አስጥሶታልና ሕጉ እጥፍ ቅጣትን ይጠይቃል። የበሬው ባለቤት ለእሻው ባለቤት
ዋጋውን ለባለ እርሻው ይመልሳል። በሬው ግን ማንም ሳይገፋው በራሱ ፍቃድ ቢኔድና ቢበላ
አሁንም ተጠያቂው የበሬው ባለቤት ነው። ነገር ግን አንድ ጊዜ ይከፍላል እንጅ እጥፍ
አይጠየቅም።
www.tlcfan.org 22
ነጻ ፍቃድ 2015
ስለዚህ ባለቤትነት ከነጻ ፍቃድ ለሚባለውና ከሁሉ ነገር የበለጠ ሁሉን ጠቅልሎ የያዘ
ታልቅ ሚስጥርን የያዘ የእውነት ቃል ነው። ባለቤትነትና የባለቤትነትን ተጠያቂነት መመልከት
እንችላለን። ከዚህ እውነት በመነሳት ነው እኔ የነጻ ፍቃድ ክርክር ምንም ጥቅም እንደ ሌለው
የማምነው። ነጻ ፍቃድን እግዚአብሔር ያልሰጠውን ለሰውም ሆነ ለዲያቢሎስ ብንስጥ ለነገሩ ምንም
አይነት መፍትሄ አናመጣም። እግዚአብሔር ምን ጊዜም ቢሆን ራሱ ካስቀመጠው ከማይሻረው
ሕጉ የተነሳ ተጠያቂ ነው። ከተጠያቂው ከእግዚአብሔር ወገን ሆነን ከእርሱ እይታ ኃላ ሆነን
ብንመለከት ነጻ ፍቃድ ሰጠን አልሰጠን ምንም ለውጥ አያመጣም።
www.tlcfan.org 23
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 24
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 25
ነጻ ፍቃድ 2015
ማጠቃለያ
ሰው ለምን እንዲወድቅ እንደ ተደረገ ክፋትም ምድር ለምን እንደ ወረረ በቀላሉ
መመልከት የምንጀምረው የአምላካችንን ማንነትና ሕጉን በደንብ ጠንቅቀን ስንማር ነው።
እግዚአብሔር ሳያወቁ ምንም ዓይነት የእውነት እውቀት ማወቅ ከቶ አይቻልም። የእግዚአብሔር
ሚስጥር ጥልቅ ነው። ይህም እግዚአብሔር ራሱን በማወቅ ውስጥ ጥቂት በቂት እርሱ በመንፈሱ
በረዳን መጠንና፣ እይታችንን እንደከፈተልንና አይበታችን የሆነውን ልባችንን የሞላልን መጠን
ያህል ከእርሱ የምንቀበለው ነው።
ምንም እንኳን ሁሉን ባናውቅ እኛ የምናምን አሁን በምድር ያለው ክፋትና መከራ
ልንቀበለው ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን ምንም እንዳል ሆነ እንቆጥራለን። ይህም በእግዚአብሔር
ላይ ባለን እምነት ነው። ሮሜ.8፥18 በምድር ላይ ስላለው ስለ እያንዳንዱ ክፋት ማብራሪያ የለኝም
በምድር ላይ ስላለው ክፋት እርሱ የገለጠልኝን ያህል አውቃለሁ። አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት
አውቃለሁ እምነቴ በእርሱና በቃሉ በሕጉ ላይ ነው።
www.tlcfan.org 26
ነጻ ፍቃድ 2015
www.tlcfan.org 27
ነጻ ፍቃድ 2015
……………………………………ተፈጸመ……………………………………….
www.tlcfan.org 28