You are on page 1of 4

ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ›› (ኤር.

፲፰፥፲፩)
‹‹

ሥነ ምግባር ሰዎች በዕለት ተዕለት ኑሮችን ውስጥ የምናሳየው ጠባይ ወይም ድርጊት፣ አንድን ነገር ለመሥራትና ላለመሥራት
የሚወስኑበት ኅሊናዊ ሚዛን ነው፡፡ በጎ ሥነ ምግባር ክፉ የሆኑ ነገሮችን አስወግዶ ደግ የሆኑትን መምረጥ መሥራት ሲሆን
በተቃራኒው ክፉ ሥነ ምግባር ከበጎ ይልቅ ክፉ ነገሮችን መርጦ መሥራት ማለት ነው፡፡ ክፉ የሚለው ቃል የመልካም ነገር
ተቃራኒ፣ የበጎ ነገር መጥፋት፣ ሐሰት፣ ኃጢአት፣ በሰው ልጅ ላይ የሚደርስ የሥጋና የነፍስ መከራ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡
ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ክፉና በጎን መለየት እንዲችሉ አስቀድሞ በሕገ ልቡና ከዚያም በሕገ ኦሪት ከዚያም
በሥጋ ተገልጦ የሰው ልጅ ሊኖር የሚገባውን ኑሮ ምሳሌ አርአያ ሆኖ አሳይቶናል፡፡

ክፋት ምንድነው ?

ክፋት፡- ለሰው ጉዳት የሚሆን ሁሉ ክፋት ይባላል፡፡ ክፋት በኃጢአት ምክንያት ወደ ዓለም ገባ፤ ሰው ኃጢአት ስለሠራ
፥እግዚአብሔር በሰው ላይ ፈርዶ ቅጣት ወሰነ፡፡ (ዮና. ፫፥፲፣የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ ፻፺፭)

አምላካችን እግዚአብሔር ‹‹ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን
ትእዛዜንና ሥርዓቴን ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ›› ብሎ በነቢዩ ኤርሚያስ አድሮ በእስራኤልና በይሁዳ ተናገረ፡፡ በዚህ ኃይለ ቃል
ነቢዩ ኤርምያስ የሚስተላልፍልን መልእክት እስራኤላዊያን እንደ ቀደሙ አባቶቻቸው ለሕገ እግዚአብሔር የማይገዙ
፣የማይፈጽሙ ሁነው ስለተገኙ ከክፋታቸሁ ተመለሱ አላቸው፡፡ የእስራኤላውያን ክፋት የተባለው አምላካቸውን
እግዚአብሔር በድለው ሌሎች አማልክተ ጣዖት ሲያምልኩ ነበርና፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር በነቢዩ አድሮ እንዲመለሱ
የፈለገው የአንዲትን ነፍስ መጥፋት ስለሚፈልግ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጠረ የሰው ልጅ በምድር የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ገዣቸው ሆነ፡፡ እግዚአብሔር ፍጥረታት
ከፈጠረ በኋላ ‹‹መልካም እንደ ሆነ አየ›› ተብሎ በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ እንደተጻፈው የሰው ልጅ መልካም ሁኖ ተፈጥአል፤
ነገር ግን መልካም

ሁኖ አልተገኘም ፡፡ (ዘፍ. ምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፩ እስከ መጨረሻ፣ ዘፍ. ምዕራፍ ፲፱ ከቁጥር ፩ እስከ መጨረሻ)

ክፉ መንገዳችሁ የተባለው
ዘርኝነት፡- ዘርኝነት በሰው ልጅ ኅሊና ውስጥ እንዲኖር ማንም አይፈቅድም፡፡ ስለ ዘር ስናስብ ተሎ አእምሯችን የሚመጣልን
ሐሳብ የአዝርዕት ዘር እንጂ የሰው ዘር አይደለም፡፡ የሰው ልጅ መገኛው እና መሠረቱ አንድ የአዳም ልጅ እንጂ እኔ የዚህ ዘር ነኝ
እነ እገሌ የዚህ ዘር ናቸው ተብሎ አይነገርለትም፡፡ ዘር የሚያስቆጥር ሰይጣናዊ መንፈስ እንጂ መልአካዊ መንፈስ አይደለም፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ሰው ልጅ ዘር እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ ‹‹ሳትጠራጠሩ በፍጹም ልቡናችሁ ወንድሞቻችሁን
ትወዱ ዘንድ ፥ለእውነት በመታዘዝ ሰውነታችሁን የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም ፥በሕያውና ለዘለዓለም በሚኖር
በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ፡፡›› (፩ኛ ጴጥ. ፩፥፳፪‐፳፬)
በመጽሐፍ ‹‹የሰው ዘር የከበረ ዘር ነው፥ የከበረ ዘር ማን ነው ?እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች የእግዚአብሔር ትእዛዝ
የሚጠብቁ ሰዎች ዘር አይደለምን?›› በሁለቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ መሠረት የሰው ዘሮች ሳይሆን የሰው ዘር ማለቱ የሰው
ዘር አንድ መሆኑ ያሳየናል፡፡ ታዲያ ይህን ዘረኝነት ማን አስተማረን? ጠላት ዲያብሎስ ነጻ ፈቃዳችን በመጠቀም፤ የልቡናችን
ጭካኔ እንደ ዙፋን በመጠቀም እርስ በርሳችን እንድንጠፋፋ ክፉ መንገድ ተከተልን፡፡ ይህ የዘረኝነት ክፍፍል የምንከላከለው
ቆም ብለን ራሳችን ከዘረኝነት በመጽዳት እና እግዚአብሔርን በመጠየቅ ፤እያንዳንዱ ንስሓ በመግባት ነው፡፡ (ሲራ.፲ ፥፲፱-
፳፩)
ራስ ወዳድ፡-
በክርስትና ትምህርት ሰው ራሱን ወዶ ወንድሙንም እንደራሱ ይወዳል እንጂ ራሱን እንደወደደ ይሞታል የሚል ትምህርት
የለም፡፡ ብዙዎቻችንን ለራሳችን ከበላን ፣ ከጠጣን ናከለበስን ሌላው ወንድማችን የሚያስፈልገው አይመስለንም፡፡ ነገር
ግን ‹‹ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ›› ብሎ አምላካችን ሲሰጠን ልንሠራው የሚከብደንን ሥርዓት አልሠራልንም
እንዲያውም ቀላልና ቀና እንደሆነ ‹‹ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀላል ነውና›› በማለት ተናግሮአል፡፡ በሁሉም ነገር ራሳችንን ብቻ
ከመውደድ ልንመለስ ያስፈልገናል፡፡ አምላካችን ለሰው ልጅ ካለው ፍቅር የተነሣ ራሱ መሥዋዕት አድርጓል ታዲያ እኛ
ለወንድማችን መራራት ፣ማዛን አይገባንም፡፡ (ዘሌ. ፲፱፥፲፰፣ማቴ. ፲፩፥፴)
ባዕድ አምልኮ፡- እግዚአብሔር ለነቢዩ ሙሴ ‹‹ኢታምልክ ባዕደ አምላከ ዘእንበሌየ፤ ከእኔ በስተቀር ሌሎች አማልክትን
አታምልክ›› በማለት ሕግጋት አውጥቶ በጽላትም ጽፎ ቢያስነግርም እስራኤላዊያን በምርኮ ግዜ እንዲሁም ከምርኮ በኋላ
በባዕድ አምልኮ ውስጥ ሁነው እግዚአብሔርን ሲያዛኑ ኑረዋል፡፡ እኛም እስራኤል ዘነፍስ የተባልን ክርስቲያኖች ባዕድ አምልኮን
የምንከተል ስንቶቻችን ነን? ለግዑዝ ተገዢዎች ፣ጥቅም ፈላጊዎች እና ዐዋቂ ነን ባዮች ተከታይ አይደለምን? ከዚህ ክፉ
አምልኮ ራሳችን ማውጣት ያሰፈልጋል፡፡ (ዘፀ. ፳፥፫)
ከክፉ መንገድ ለመለየት/ለመውጣት / ምን ማድርግ አለብን ?
ስሜት ሕዋሳትን መግዛት፡- የስሜት ሕዋሳቶች መግዛት መቻል አለብን፡፡ ካልሆነ ግን በምኞትና በፍትወት ገመድ እየጎተቱ
ወደ ኃጢአት ይወስዱናል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ዓይን ክፉ ነገር ከማየት፣ አንደበታችን ክፉ ከመናገር፣ ጆሮአችንንም
ክፉ ከመስማት ልንከለከል እንደሚገባ የነገረን ለዚህም ነው፡፡
መልካም የሆነውን ማድረግ፡- ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ›› እንዳለው፡፡ ክርስትና የሚጠይቀው
መጥፎ የሆነውን መተው ብቻ ሳይሆን መልካም የሆነውን ማድረግም ጭምር ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ‹‹ሁሉ
ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን አይሰለጥንብኝም›› እንዳለው ሁሉ
ነገር መልካም እና መልካም ያልሆነውን በመለየት ራሳችንን በቀና መንገድ መጓዝ አለብን ፡፡ (መዝ.፴፫፥፲፬፣፩ኛቆሮ.፮፥፲፪)
እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ፡- ነቢዩ ዳዊት ‹‹አቤቱ ምሕረትህ በላያችን ትሁን ፥ በአንተ እንደ ታመንን›› እንዳለው ቅዱስ
ዳዊት እኛም ክፉ የሆኑት ሐሳቦችን ከልቡናችን እንዲያርቅልን ስምዓነ አምላክነ ወመድኃኒነ (አምላካችን መድኃኒታችን
ስማን) እያልን እንድንማጸናነው ያስፈልገናል፡፡ (መዝ.፴፫፥፳፪)
በንስሓ መመለስ፡- ከክፉ ሥራችን ተመልሰን ፣ አዲስ ዘመን በመጣ ቁጥር ዘመንን የሚያድለን ዕድሜንም የሚሰጠን የዘመናት
ባለቤት እግዚአብሔርን ረስተን ፈቃዱንም ሳንፈጽም የተፈጠርንበት ዓለማ ዘንግተን በቀድሞ የክፋት ሥራችንን በመፈጸም
የምንቀጥል ከሆን የምንድንበት መንገድ ስተናል ማለት ነው፡፡ ክፉ ሥራችንን በመተው በንስሓ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ
ከእርሱ ጋር እንድንኖር የአምላካችን ፈቃድ መሆኑን የምንረዳው በቅዱስ ቃሉ በነቢያቱ አንደበት አድሮ ‹‹ኃጢአተኛው
ከሠራው ኃጢአት ቢመለስ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ነፍሱን ይጠብቃል አስቦ ከሠራው በደል ሁሉ ተመልሷልና ፈጽሞ
በሕይወት ይኖራል እንጂ …የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና ይላል ጌታ እግዚአብሔር ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት
ኑሩ›› በማለት ከክፉ ሥራችን ሁሉ ተመልሰን ከእርሱ ጋር እንድንኖር ያስተምረናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ‹‹ወድቆ መነሳት
አዳማዊ ፤ ወድቆ አለመነሳት ዲያብሎሳዊ ነው›› በማለት እንደተናገረው ሁላችን ከወደቅንበት ኃጢአት እንድንነሣ በቸርነቱ
ይርዳን፡፡ (ሕዝ.፲፰፥፳፯-፴፪)
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በንስሓ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይቅርታ እንድናገኝ እንጂ ማናችንም ከነኃጢአታችን
እንድንጠፋ አይፈቅድምና አምላካችን እግዚአብሔር ወደ እርሱ እስክንቀርብ ዕድሜ ለንስሓ እየሰጠ ሁልጊዜ እንደሚታገሠን
ሲያስረዳ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ሳለ ስለ እናንተ
ይታገሣል፡፡›› የእግዚአብሔርን ትዕግሥት በዚሁ እንደምንረዳ የሐዋርያው ቃል ያስተምረናል፡፡ አያይዞም በንስሓ ወደ እርሱ
ለመቅረብ መፋጠን አንዳለብን ‹‹የጌታ ቀን ግን እንደሌባ ሆኖ ይመጣል›› በማለት ፈጥነን ወደ ንስሓ መቅረብ እንዳለብን
ይመክረናል፡፡ (፪ኛጴጥ.፫፥፱-፲)

የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት አይለየን፤ መልካሙን መንገድ ያስተካከልን፤ ዕድሜችን ለንስሓ፣ ዘመናችን ለፍሥሐ
ያድርግልን፤ አሜን፡

ባዕድ አምልኮን ድል መንሣት


ከሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን አራተኛዋ ናት። ለትያጥሮን
ቤተ ክርስቲያን ጌታ የተገለጸው፡- “እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ
የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል” በማለት ነው /ራእ. 3፡
18/። “እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት” ማለት ሁሉን መርማሪ ነው ማለት ነው።
በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚከናወነውን ክፉ ነገር ያያል፣ የሚቆጭ ቢጠፋ ይቆጫል፣ የሚታየው
መሪ አይቶ እንዳላየ ቢያልፍም የማይታየው ጌታ ግን ምክሩን ይልካል። ጌታ የሚደረገውን
መልካምም ሆነ ክፉ ያያል። ቤቱን ለማንም አይተውምና። እንዳየ መጠን ይመክራል እንጂ
አይፈርድም። ቢፈርድ እንኳ እየተበቀለ ሳይሆን እንደገና ለንስሐ እየጋበዘ ነው። መዓትም
ምሕረትም በእጁ ቢሆኑም እርሱ የሚሻው መማር ነው።
ሌላው መልኩ “በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት” የሚል ነው።
ይህ ጽኑነቱን የሚገልጥ ነው። ኃያላን የማያሸንፉት ኃያል፣ ጎበዞች የማይጥሉት ጎበዝ፣
አስፈሪዎች የማያስፈሩት ግርማዊ ነው። በዚህ መልኩ ለምን ተገለጠ? ስንል በቤተ
ክርስቲያኒቱ ውስጥ ውበትን፣ ሥልጣንን፣ ገንዘብን ታምና አማንያኑን የምታረክሰውን፣ በግብር
ስሟ ኤልዛቤል የተባለችውን ሴት ዝም በማለቱ ነው። እኔ ባስፈራህ ኖሮ ማንንም አትፈራም
እያለው ነው ለቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ። በመቀጠልም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ” ይላል።
የእግዚአብሔር ልጅ ማለት የባሕርይ አምላክነቱን የሚገልጥ ነው። ነገሥታት እያሉ ንጉሥ
ቢባልም አማልክት ስላሉ ግን አምላክ አልተባለም። እርሱ ከማንም ጋር የማይወዳደር አምላክ
ነው። ለማንም የአምላክነት እውቅና አይሰጥም። ስለዚህ የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን መሪ
ከበላዩ ያለው ትልቁ ጌታ መሆኑን ማወቅ አለበት።
የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን ፈተና የሆነችባት አንዲት በግብር ስሟ ኤልዛቤል የተሰኘች
ሴት ናት። የብሉይ ኪዳኗ ኤልዛቤል የእስራኤል ንጉሥ አክዓብን አግብታ ለጣዖት ያሰገደችው፣
ለእስራኤልም በጣዖት መውደቅ ምክንያት የሆነች ሴት ናት /1 ነገሥ. 16፡31/። በትያጥሮን ቤተ
ክርስቲያንም አማንያኑን ዝሙትን የምታደፋፍር ለጣኦት የታረደውን እንዲበሉ
የምታስተምር ሴት ነበረች። ዝሙትና ጣኦት አምልኮ ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው። ቃል
ኪዳንን መጣል የሚያመለክቱ ናቸው። በዝሙት ምክንያት በትዳሩ ላይ ሌላ ነገር ይደርባል፣
በጣኦት ምክንያትም በአምላኩ ላይ ሌላ ይደርባል። አመንዝራው ከቤቱ ላይወጣ ሚስቱን
በአዋጅ ላይፈታ ይችላል። ልቡ ደጅ ሆኖ አካሉ ብቻ እቤት ተቀምጧል። ጣኦት አምላኪም
በቤተ ክርስቲያን እየኖረ ልቡ ግን የሚገዛው ለሌላ ነገር ነው። በዚህች ሴት ድፍረት
አስተማሪነት የትያጥሮን አማንያን ከቤታቸው እስከ አምልኮአቸው የተፈቱ ሆነዋል።
የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን መሪ ሥራውን በትጋት የፈጸመ፣ ፍቅሩ ብዙዎችን የገዛ፣
እምነቱ የደከሙትን ያበረታ፣ አገልግሎቱ ብዙዎችን ያስመለጠ፣ ትዕግሥቱ ለብዙዎች
መመለስ የረዳ ነው /ራእ. 3፡19/። ይህ ሁሉ ያለው መሪ ግን አንዲትን ሴት መገሰጽ የማይችል
የይሉኝታ ሰው ሆኖ ነበር። በአንድ በጥባጭ ወይፈን በረት ሙሉ መንጋ እንደሚታመስ እንዲሁ
በዚህች ሴት ብዙዎች በዝሙትና በጣኦት አምልኮ ወድቀው ነበር። ስለዚህ አገልግሎቱ በቀዳዳ
ስልቻ እንደ መሙላት፣ በበር እያስቡ በጓሮ እንደ ማስወጣት ሆኖ ነበር።
ትልቁን ባለሥልጣን ኢየሱስ ክርስቶስን ተማምኖ መገሰጽ አለበት። በርግጥ የብሉይ
ኪዳኗን ኤልዛቤል በመገሰጽ ምክንያት ኤልያስ ለስደት ተዳርጓል /1 ኛ ነገሥ. 19፡1-3። ብዙ
ነቢያትም ለረሀብ ተጋልጠዋል። የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን መሪም ይህ ፈተና ቢገጥመውም
ለዓላማው መጽናት ያስፈልገዋል። እርሱ ሥጋዊ መከራ በመፍራቱ ሌሎች በነፍስ መከራ
ውስጥ እየወደቁ ነው። ለመምከርም ሥልጣን ያለው እርሱ ነው። ሳይናገር ባትሰማኝስ ማለት
አይገባውም። በፍቅር ምክር ይህችን ሴትና ያሳተቻቸውን መመለስ አለበት።
ይህንን ድርሻ ቢወጣ የተዘጋጀለት በረከት፣ የድል ነሺነት ክብር አለ፡- “ድል ለነሣውና
እስከ መጨረሻውም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብም ላይ
ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፣ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፣ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቅጣሉ፤
የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ” /ራእ. 3፡26/። ይህ ሽልማት ጌታ ራሱ የተቀዳጀው ነው /መዝ.
2፡8-9/። ድል መንሣት ማለት እስከ መጨረሻው ጌታ የሚሠራውን መጠበቅ ነው። ደክሞ
ከመንገድ አለመውጣት፣ ክፉ አሸነፈ ብሎ ለምርኮ እጅን አለመስጠት ነው። ለጊዜው
እግዚአብሔር ዝም ሲል ጠላት ያሸነፈ ይመስላል። ለጠበቁት ግን የማታው ድል የጌታ ነው።
ድል ለነሡ የተዘጋጀው ፍጹም የሆነ ገዢነት ነው። በአሕዛብ ላይ ማስፈራትን መጎናጸፍ ነው።
ሌላው የንጋት ኮከብ እሰጠዋለሁ ይላል። የጨለማን መሸነፍ የሚያረጋግጥ፣ ጎልቶ የሚታይ
ድምቀትና ምሳሌነት ነው።
ራስና እግር ቦታ ከተለዋወጡ መራመድ የለም። ሁሉም ቦታውን ሲይዝ ብቻ ሕይወት
ቀጣይነት አገልግሎትም ስምረት ይኖረዋል። በቤተ ክርስቲያን ስፍራን አለመያዝና ጸጋን
ያለመለየት ችግር ይታያል። ይህ ብቻ አይደለም ሰዎች በዓለም ትልቅ የሆኑበትን ነገር ይዘው
በመምጣት በቤተ ክርስቲያንም የበላይ መሆን ይፈልጋሉ። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የጸጋ
የበላይነት የሌለባት በሥጋ ክንድ ያሸነፈና ደፋር የሚሆንባት ስፍራ ሆናለች። በትያጥሮን ቤተ
ክርስቲያን ራሷን የቀባች ይህች ሴት ለብዙዎች የድፍረት ኃጢአት ምክንያት እንደሆነች
እንዲሁ ዛሬም ጳጳስ የሚያዋርዱ፣ የቤተ ክርስቲያንን ቁልፍ እየተቀበሉ ቄስ የሚያባርሩ
ደፋሮችን እያመረትን ይሆን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።
ባዕድ አምልኮን ድል መንሣት አለብን። ባዕድ አምልኮ የምንለው ከእግዚአብሔር ውጭ
ያለው ትምክሕታችን፣ የሚታየውና የማይታየው ጣኦት ነው። በዛሬው ዘመን ሰው የአንድ
ትምክሕት ባለቤት መሆን ይፈልጋል። በእውቀቱ ወይም በሀብቱ ለመኩራት ይከጅላል።
ትምክሕትን ድል መንሣት ወደ እግዚአብሔር ያስጠጋል። ይህን ድል የነሡ ከክርስቶስ ጋር
ይከብራሉ።

You might also like