You are on page 1of 10

ማውጫ ገጽ

ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ ቆዩ .........................................................................................2


የምንወደው ቅዱስ የምንጠላው ነው ...................................................................................3
በረቱ ለዓለም ይሸታል ......................................................................................................5
ያ... የከበደን ቦታ ............................................................................................................7
ያ... የከበደንን ቦታ እንዴት እናቅልለው? ............................................................................9
ሀ] በርእስ መዋጋት (የምንጭ ኃይሉን ለማፍረስ) ...............................................................9
ለ] ቅዱሳንን ማሰለፍ (ተጓዳኝ ፈተናዎቹን ለመቋቋም)........................................................9

1
ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ ቆዩ
ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ ቆዩ የሚለው የተስፋ ቃል በሉቃስ ወንጌል 24፥49 ላይ ተጽፎ የምናገኘው
እንዲህ የሚል የጌታ ድምፅ ነው፤ "እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል
እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።"

ሁልጊዜ በሕይወታችን ውስጥ ጌታ የምሰጣችሁ አለ የሚለው ስጦታ ይኖረዋል፡፡ እነዚህ ስጦታዎቹ ደግሞ
ከቸር እጆቹ ውስጥ በነጻ ተፈልቅቀው የሚወጡ የፍቅሩ መገለጫዎች የሚሆኑ በረከቶቹ ናቸው፡፡ ነገሮችን ባላቸው
የዋጋ ተመን ግምት የምንሰጣቸው እኛ፤ በነጻ የሚሰጡን ነገራት ላይ ትኩረት መስጠት ራሱን የቻለ የአመለካከት
ፈተና ሲሆንብን ይስተዋላል፡፡ የሚገርመው ደግሞ ዓለም ላይ ስንኖር፥ ከሁሉ ከተሰጡን ስጦታዎች ሁሉ እጅግ የሚልቁት
በነጻ የተሰጡን ስጦታዎች ናቸው፡፡ አሁን ለምሳሌ፤ አየርን በየቀኑ በነጻ ያለ ቆጣሪ እንተነፍሳለን፡፡ ለደቂቃዎች ግን
ይህን አየር ብናጣ በሕይወት የመቆየታችን ነገር ይቋረጣል፡፡ ከነዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ አምላካችን የሚሆን ኢየሱስ
ክርስቶስ ራሱን በነጻ አሳልፎ ሰጠን፡፡ መላእክት ለመዳሰስ የሚፈሩትን ቅዱስ እርሱነቱን ሥጋና ደም አድርጎ ያለዋጋ
እንበላው እንጠጣው ዘንድ ሰጠን፡፡

በነጻ ከተሰጡን ስጦታዎች መካከል ትልቁን ስፍራ የሚይይዘው ቅዱስ ቁርባን፤ ዛሬ ለኛ በሕይወታችን
ትኩረት ካልተሰጣቸው ጉዳዮችም ቀዳሚው ሆኗል፡፡ በውድ ዋጋ ለምንመገባቸው ምግቦች የምንሰጠውን የመሻት
ፈቃደኝነት ለዚህ ሰማያዊ ማዕድ ስንሰጥ አይታይም፡፡ ከብዙ ምክንያቶቹም ውስጥ አንዱ በነጻ ስለተሰጠን፥ ሰለ
አስፈላጊነቱ አረጋግጦ የሚስብ ዋጋ ስሌለውም ጭምር ነው፡፡ እዚህ አሁን ለሐዋሪያቱም በነጻ የምሰጣችሁ አለኝ
እያላቸው ነው፡፡ "እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤" ነው ያላቸው፡፡ ይህ ሰማያዊ ተስፋ ወደናንተ
እስኪመጣም ድረስ፥ "ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ "አለና ደግሞ ጨመረላቸው፡፡

ክርስቲያኖች ዛሬ የክርስቶስን ኃይል ረስተዋል፡፡ መለኮታዊ ኃይል፣ ሰማያዊ ኃይል፣ መንፈሳዊ ኃይል የሚባል
የእምነት ጉልበት እንዳለ ብዙዎቻችን አላወቅንም ወይንም ዘንግተናል፡፡ ስለዚህ የኑሮአችንን ድጋፍ በሌላ ምድራዊ
ኃይል ላይ ለማሳረፍ ብዙ ድካም እየደከምን፥ ባወጣነው ጉልበት ልክ ቀናቶቻችንን እንደምናሰምር ከሥጋዊ
ተሞክሮዎች ላይ ግንዛቤ ወስደን፥ ሕይወታችንን በምንፈልገው ጎዳና ለመምራት እንታገላለን፡፡ ነገር ግን ከላይ
ወደታች ይመጣ ዘንድ ፍቅር ያለውን የእግዚአብሔር ኃይል ከጊዜያችን እውቅና ውጪ ስላደረግን፤ በምድር ኃይል
ብቻ ወደላይ ከፍ ለማለት የምንጥረው ጥረት፤ ወዳልጠበቅነው ሸለቆ እየመራን፣ ወደማንፈልገው ቁልቁለት
እያንደረደረን፣ ወዳላሰበነው አቅጣጫ እየወሰደን ስንቸገር እንገኛለን፡፡

እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ሆናችሁ ቆዩት የተባሉት ኃይል ከየት የሚመጣ ነው? ከላይ የሚመጣ
ነው፡፡ ዘመናዊያኑ ትውልዶች፤ የላይኛውን ኃይል አንፈለገውም ብለን በአንድም በሌላም መንገድ በኑሮአችን
ስለተናገርን፥ ወደታች የሚያወርዱ አጋጣሚዎች የጊዜያችንን መስመር ተጋርተውት፤ ወደ ብዙ ቁልቁለታማ
ስፍራዎች ሲያደርሱን አላስተዋልናቸውም፡፡ ትልልቅ ፎቆች ላይ እየኖርን ልባችን ግን ታች ወርዶ ምቀኛ ነው፡፡
የትልቅ ደሞዝ ተከፋዮች ሆነን እጃችን ግን ታች ወርዶ ንፉግ ነው፡፡ ትልልቅ ላብራቶሪዎችን አቋቁመን ሳለ፥ ጤናችን
ግን በሽተኛ ነው፡፡ ትልልቅ ድልድዮችን ገንብተን፥ አንድነታችን ግን የተነጣጠለ ነው፡፡ ከላይ የሚመጣው ኃይል
ወደኛ እንዲደርስ መንገድ የሚሰጥ የእውነት ቦታ ስሌለን፥ ወደታች የመውረድ ገጽታዎችን በሕይወታችን ውስጥ
እያስተናገድን ሰማይን የረሣ ኑሮ ከጣራ በታች እንኖራለን፡፡

ከላይ የሚመጣው ኃይል ሕይወትን ከነፍስ ወደ ሥጋ የሚመራ ኃይል ነው፡፡ የከበበበን ወጥመድ ሁሉ ጥሰን
ለማለፍ የሚያስችል ኃይል ነው፡፡ በበረከት ጎዳና ላይ እንድንራመድ ውሳኔ የሚሰጥ ምሪት ነው፡፡ በሚገጥሙን

2
ሁኔታዎች መሠረት ላይ በመሆን ጊዜያችንን እንድንቆጣጠረው የሚያግዘን ሕሊናን በመንፈስ ቅዱስ ሹክሹክታ
የሚሞላ ኃይል ነው፡፡

ይሄን ምንም አይነት ምድራዊ ጥበብና ብልጠት የማይተካው ኃያል የሆነ ኃይል ለማግኘት ደግሞ
የሚያስፈልገን አንድ መስፈርት አለ፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም መቆየት ነው፡፡

ኢየሩ-ሳሌም ማለት የሰላም ስፍራ እንደማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኃይልን እስክትረከቡ በሰላም ስፍራ ቆዩ ሲል
ነገራቸው፡፡ እኛም ይሄ ኃይል የሕይወታችን አካል አንድ ክፍል እንዲሆንልን፤ በሰላም ስፍራ መቆየት አለብን፡፡
ይሄውም፥ በስግደት መቆየት፣ በጸሎት መቆየት፣ በመቀደስ (ቅዱስ ቁርባን) መቆየት፣ ክፋትን እየተቃወሙ መቆየት፣
ቃልኪዳኑን እየጠበቁ መቆየት፣ የወደቁትን እያነሡ መቆየት፣ የተራቡትን እያበሉ፥ የተጠሙትን እያጠጡ፥ የታረዙትን
እያለበሱ መቆየትን የያዘ ሰላማዊ ቆይታ ነው፡፡

ጥቂት የማንባል ሰዎች በዚህ በመንፈሳዊው ዓለም ላይ የማንገናዝበው ጉዳይ ቢኖር መቆየትን ነው፡፡ ኃይልን
መልበስ በጣም እንፈልጋለን፥ ነገር ግን 'ቆዩ' ያለውን ቃል እንዘለዋለን፡፡ በዚህም ሳቢያ ተንበርክከን የጸለይነው ጸሎት
ምላሽ ሳይቆይ እንዲመጣ እንወዳለን፡፡ ዛሬ የጀመርነው ስግደት ዛሬውኑ ኃይል እንዲሰጠን እንቸኩላለን፡፡ አሁን
ያለቀስነው እንባ ወዲያኑ እንዲታበስ እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን ሳይቆይ የሚመጣ ነገር ሳይቆይ ሊሄድ እንደሚገባው
አናስተውልም፡፡ በመቆየት እውነታ ውስጥ እግዚአብሔር አደራጅቶ በትክክለኛው ሰዓት የሚሰጠን ነገር እኛ ካስፈለገን
ሰዓት እንደሚበልጥ አናውቅም፡፡ በመሆኑም፤ ኃይልን እስክንለብስ በኢየሩሳሌም መቆየት አቅቶን፤ በቶሎ የሚተረጎም
መፍትሔ ፍለጋ ወጥተን ሄደን፤ "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው" የሚለውን ቃል ተሻግረን፥ "መሆን
ያለበት ሁሉ በኛ ጊዜ ውስጥ ይለፍ" ብለን የእግዚአብሔርን ሥራ ውብነት ከኑሮአችን አርቀን፤ ላንጨርሰው መንገዱን
እየጀመርን፥ የወከባ ሰዓትን የጊዜያችን መገለጫ እናደርጋለን፡፡

በመቆየት ጸጋ ውስጥ ቆይተው የቆየች አገራችንን ያቆዩልን አባቶቻችን ይህንን የመቆየት ኃይል በጣም
ያውቁታል፡፡ እንኪያስ፥ ቃሉን እየጠበቁ ይቆያሉ፡፡ ጸጋቸውን እያከበሩ ይጠብቃሉ፡፡ የእያንዳንዷ ቀን አካሄዳቸውን
ከኢየሩሳሌም ውስጥ ያረጉታል፡፡ አምልኮትን አያቆሙም፡፡ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ኃይላቸው እያደገ እያደገ ይመጣል፡፡
ጽድቃቸው መነበብ ይጀምራል፡፡ ክብሩን ይገልጡታል፡፡ ሞገሱ በገጻቸው ይታያል፡፡ ምክንያቱም ጌታ እንዲህ ያለውን
ቃል ኖረውበታል "ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ፡፡"

የምንወደው ቅዱስ የምንጠላው ነው


ሰዎች ከሰማያውያን ቅዱሳን ጋራ ልዩ የሆነ ፍቅር ይዞአቸው ይገኛሉ፡፡ ለምን እንደሆነ ሳያውቁት አንዳንዶች
ልባቸው እስኪጠፋ ድረስ ወላዲተ አምላክን ይወዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ቅዱስን ሚካኤልን ይወዳሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ቅዱስ
ገብርኤልን፡፡ አንዱ እግዚአብሔርን ራሱ በተለያየ ስሙ በኩል በልባቸው ይዘውት ዘወትር ከአፋቸው የማያርቁት
አሉ፡፡ ሲወጡ ሲገቡ አማኑኤል የሚሉ አሉ፣ መድኃኒዓለምን ደጋግመው የሚጠሩ አሉ፣ ሥላሴ እያሉ በአገኙት
አጋጣሚ የሚናገሩ አሉ፣ ክርስቶስ እያሉ ሁሌ የሚጠሩት አሉ፡፡ እንደኔ አባትየው የሚሉም ይኖራሉ፡፡ እመቤቲቱንም
እንዲሁ በተለያየ ስሞቿ በኩል ይዘዋት፤ ነጥለው በያዙት ስም በኩል ከልባቸውና ከሕይወታቸው ውስጥ በየቀኑ
የሚያሳታውሷት ሰዎች አሉ፡፡

ይሄ ነጥሎ ብዙ የመውደድ ነገር መነሻ ምክንያት ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል፡፡ አንዳንዱ ሰው በሥላሴ
ቀን ከከባድ አደጋ የተረፈ ሲሆን "ሥላሴ ሥላሴ" ይላል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ለምን የኪዳነ ምሕረት ስም አንደበቱ ላይ
እንደሚበዛበት ቢጠየቅ አያውቀውም፡፡ አንዳንዱ በቅዱስ ገብርኤል እርዳታ ትልቅ ነገር ተከናውኖለት ዘወትር
መልአኩን የሚያነሣ ይኖራል፡፡ ሌሎች ደግሞ ቅዱስ ሩፋኤል ለምን በልባቸው ለየት ያለ ስፍራ እንዳለው በውል

3
አያውቁትም፡፡ ብቻ ባለም በሌለም ምክንያት ይሁን፤ ብዙ ሰዎች ከአንድ ቅዱስ ጋር ኑሮአቸው የተቆራኘበት አንድ
የሆነ ገመድ አለ፡፡

በዚህ መካከል ታዲያ ይሄን የምእመናንን እና የሰማያዊ ቅዱሳንን መንፈሳዊ ትስስር አምርሮ የሚጠላ ሦስተኛ
ፍጡር አለ፡፡ ይኸውም የአዳም ዘር "ብቸኛ ጠላት" ዲያቢሎስ ነው፡፡

ዛሬ ላይ ሰዎች ቅዱሳን መልአክት እንጂ ርኩሳን መልአክት እንዳሉ ፍጹም በዘነጋ አካኋን ያለ ጥንቃቄ
ተዘናግተው ይኖራሉ፡፡ የአጥፊ መናፍስት ነገድ ግን በተቻለው አቅም የሰው ልጆችን ሁሉ ሰብስቦ ያጠፋ ዘንድ
እያንዳንዷን የሰኮንድ ስባሪ በሥራ ላይ ያውላታል፤ እያዋላትም ነው፡፡ ይሄ እኛ እስከመፈጠሩም የረሳነው ክፉ ባላንጣ፤
እርሱ የዘወትር ሥራው እንደሆንን አስታውሶን፤ ባሕሪያችን ውስጥ ገብቶና ጠባያችንን ተመሳስሎ፤ ውስጣዊ
ሰውነታችንን መኖሪያ ቦታው በማድረግ በእያንዳንዱ ቀናችን ውስጥ ውሎአችንን ተጋርቶ በመኖር፤ ብዙ ጥፋት
ያጠፋ ዘንድ ከኛ ስንፍና የተነሣ ዕድል ኖሮት ሳለ፤ ቢሆንም ግን እንዳሰበው ያህል ሮጦ ሊያወድም አልቻለም፡፡
ለምን?

ምክንያቱም... ያ ዝም ብለን የምንጠራው ቅዱስ፣ ትኩስ ሻይ ሲደፋብን ስሙን የምናነሣው ቅዱስ፣ ከእውነት
ስንናገር ማረጋገጫችን እናደርገው ዘንድ የምንጠራው ቅዱስ፣ ስዕሉን ባየን ጊዜ ሁሉ ፈጥነን የምንስመው ቅዱስ፣
ስለ እርሱ ለመናገር ስንጀምር የዓይን ውኃ የሚያመጣብን ቅዱስ፣ በተጨነቅን ጊዜ ስለተሸነፍንበት ጉዳይ የምናዋየው
ቅዱስ፣ በተደሰትንበት ጊዜ ለማመስገን የምንቸኩለው ቅዱስ፤ እርሱ አብዝቶ ይከተለናልና ነው፡፡

ሚካኤል ሚካኤል የምትሉ ሰዎች ሊቀ መልአኩን ፍለጋ ሩቅ አትባዝኑ፡፡ አብሯችሁ አለ፡፡ እመቤቴ እመቤቴ
የምትሉ ሰዎች ድንግል ማርያም የሆነ የማይደርስበት ቦታ ላይ ያለች አትምሰላችሁ፡፡ በአጠገባችሁ ናት፡፡ ዑራኤል
ዑራኤል የምትሉ ሰዎች ቅዱስ ዑራኤል እናንተ ሕይወት ውስጥ ስንት ጊዜ መጥቶ ከብዙ ከማታዩት የመናፍስት
አደጋ እንደጠበቃችሁ አላወቃችሁም፡፡ መድኃኒዓለም መድኃኒዓለም ማለታችሁ ሰንት ቦታ ከስንት ነገር እንደከለላችሁ
እንደምን አድርጌ ላሳያችሁ?

ስለዚህ "የምንወደው ቅዱስ የምንጠላው ነው"፡፡ ማለት፤ ከውስጥ በኩል አድፍጦ እኛነትን የተዳበለውን
ዲያቢሎስ፤ እኛ የምንወድው ቅዱስ እየተከታተለ ያጠቃዋልና፥ እየጠበቀ ሥራውን ያፈርስበታልና፥ ሊያሳካው ጫፍ
አድርሶት የነበረውን እቅድ ያከሽፍበታልና፥ መንፈሱ "ከኛ ውስጥ ሆኖ" ቅዱሱን አጥብቆ ይጠላዋል፡፡ ቅድስት አርሴማን
በጣም የምትወዱ ሰዎች፤ ተመሳስሎ ያደፈጠው ርኩስ መንፈስ በጣም የሚጠላው እርሷኑ ይሆናል፡፡ አቡነ
ተክለሃይማኖትን አጥብቃችሁ የምትወዱ ሰዎች ላይ ያለው መንፈስ እሳቸውን አጥብቆ የሚጠላ ነው፡፡ የኛ እና
የዲያብሎስ ድንበር በአምልኮተ እግዚአብሔር ልምምድና የዕለት ተዕለት መንፈሳዊ ውጊያ እስካልተሰጠነቀ ድረስ፤ እኛ
ውስጥ ያደፈጡ መናፍስት ከእኛ በምንም ሌላ ሥጋዊ ዘዴ አይለዩምና፤ የምንወደው ቅዱስ የምንጠላው ነው በማለት፤
የኛ መውደድ እና በእኛ ውስጥ ያለው ዲያቢሎስ መጥላት በአንድ ሐረግ ተያይዞ መገለጽ ይችላል፡፡ እጅግ ብዙ
ሰው፤ ርኩሳን መናፍስት በሰው ውስጥ ያድራሉ ሲባል፤ ሰውየውን ለመምሰል ሰው መሆን እስኪቀራቸው ድረስ
ተመሳስለው እንደሚደበቁ ገና አልተረዳም፡፡ ስለሆነ "የምንወደው ቅዱስ የምንጠላው ነው" የሚለው አባባል፤ የኛ
በሰብአዊ ባሕሪይ መውደድ እና እኛ ውስጥ ያለው መንፈስ በዲያቢሎሳዊ ባሕሪይ መጥላት በአንድ የ'እኛነት' ሥጋ
ውስጥ የተገኙ መሆናቸውን በመጠቆም፤ በአካላችን ተሸሽጎ ያለው መንፈስ ሕልውናችንን ተጣብቶ፥ ሥጋችንን
እንደ ልብስ ለብሶ፥ እንደሚገኝ ማስገንዘቢያ እንዲሆን የተጠቀምኩት አገላለጽ ነው፡፡

"ለመሆኑ አብዝተን የምንወደው ቅዱስ ለምን እኛን አጥብቆ ይከተለናል?"... ስለ ፍቅር ሲል ይከተለናል፡፡
"ፍቅር" የሰማይ ቅዱሳን ሁሉ የሚታዘዘሉት ድንቅ ኃይል ነው፡፡ ስለዚህ ለነርሱ ከልባችን ያሳየነውን እውነተኛ ፍቅር
ከሰማይ ዳርቻ አይተው ይከተሉናል፡፡

4
የአምልኮት ሕይወት ስትጀምሩ፤ መነሻ መሠረታችሁ መገንባት ያለበት በዚህ ፍቅር ላይ ነው፡፡ ከፍቅር
ያልጀመረ መስገድ ለማቋረጥ ብዙ የችግር ሰበቦች አሉለት፡፡ ከፍቅር ያልጀመረ ጸሎት የገጠመው እከል እስኪፈታለት
ድረሰ ብቻ የሚዘልቅ ነው፡፡ ከፍቅር ያልጀመረ ቅዱስ ቁርባን የጌታን ሥጋና ደም እንደተሰጠው ስጦታ ሳይሆን
እንደሚወጋ ጦር ፈርቶ ያየዋል፡፡ ከፍቅር ያልጀመረ ሃይማኖት፤ በልምድ አረም የተወረሰ ሥርዓትና ወግ ላይ "ብቻ"
ያተኮረ የፊሪሳዊያን ጥላ ይሆናል፡፡ ከፍቅር ያልጀመረ የክርስትና አካሄድ፤ የእምነት ክንውኖችን ለማድረግ ሁሌ
መጨቅጨቅ፣ መጎትጎት የሚፈልግ፤ ለገዛ ነፍሱ ሲባል ካልተለመነ የእምነት እውነት ላይ ፍቃድ የማያሳይ ነው፡፡

ሰዎች ከልብ የምንወደውን ነገር የማግኛ መንገዱ የቱን ያህል ከፍ ያለ ዳገት ቢሆንብን እንኳ፤ ተፍጨርጭረን
ለመውጣት እንደምንቧጥጥ ዓለማዊ ነገራት ላይ ካከናወንናቸው ነገሮች አንጻር አስረግጦ መናገር ይቻላል፡፡ ይሄ
ጥረታችን ግን መንፈሳዊ ቦታዎችና ጊዜዎች ላይ ጉልበት የለውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔርን ከልብ በሆነ ፍቅር
አንወደውም፡፡ ቀድሞውኑ ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋው ሲያመን፣ ሲዘጋብን፣ ሲፈርስብን፣ ሲጨንቀን፣ ስናጣ፣
መፍትሔ ሲርቀን ጠብቀን ነው፡፡ በሰላሙ ጊዜ፣ ሁሉ የተሟላ በሚመስልበት ጊዜ፣ አማራጭ ብዙ ባለበት ጊዜ
እግዚአብሔርን እንተወዋለን፡፡

አምልኮተ እግዚአብሔርን ከጠንካራ ፍቅር አንሡና ጀምሩ፡፡ መስገድ ያለባችሁ በመጀመሪያ ዲያቢሎስ
እንዲደክም አይደለም፤ ልባችሁ በአባትየው ፍቅር እንዲደክም ነው እንጂ፡፡ መጸለይ ያለባችሁ በመጀመሪያ ዲያቢሎስ
እንዲቃጠል አይደለም፤ ሰውነታችሁ በመደኃኒቱ ፍቅር እንዲቃጠል ነው እንጂ፡፡ መቁረብ ያለባችሁ ያደፈጠ መንፈስ
እንዲወጣላችሁ አይደለም፤ በእደ ስብእና ወደ ሰማያዊ ማንነት ከፍ እያላችሁ እንድትወጡ ነው እንጂ፡፡ በሃይማኖት
ጎዳና ላይ አስቀድማችሁ እግዚአብሔርንና ቅዱሳን ቤተሰቦቹን ከፍቅር ፈልጋችሁ ስትሄዱ፤ የዲያቢሎስ ፈተና ሁሉ
የሕይወት ማጣፈጫ እንጂ፤ እውቀት መጨመሪያ እንጂ፤ አቅም መፈተሻ እንጂ፤ ልምድ ማካበቻ እንጂ፤ ጥንካሬ
ማሳደጊያ እንጂ፤ መራር ትግል አይሆንባችሁም፡፡ ምክንያቱም ለምትወዱት መድረሻ ከመነሻ ጀምሮ መፋለም ራሱን
የቻለ ውብ የደስታ ጉዞ ነውና፡፡

በረቱ ለዓለም ይሸታል


"በረቱን እጅ እነሣው ዘንድ ማን በከፈለኝ? የሙታን ሕይወት፤ የኃጥአንም ንጽሕና፤ የቅቡጻን ተስፋ፤
የተጨነቁትንም የሚያድን ጌታ ወደተቀመጠበት" መጽሐፈ አርጋኖን ዘሱነይ (ምዕ. ፬፥፮)

በረት የእንሳስት (በተለይም የከብቶች) ማደሪያ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከብቶችን እያረቡና ለግብርና ሥራ
እየተጠቀሙ የሚተዳደሩ ሰዎች በረትን በዕለት ተዕለት ኑሮ የተሻለ ያውቁታል፡፡ በረት የእንስሳት ማደሪያ ከመሆኑ
ጋር ተያይዞ የራሱ የሆነ ደስ የሚልም፥ የማይልም መገለጫዎች አሉት፡፡ ለምሳሌ በእንስሳቱ መኖሪያ ጭቅጭቅ፣
ምቀኝነት፣ ኩርፊያና ራስ ወዳድነት የለም፡፡ የኔን ቦታ ወስድክ የሚል መገፋፋት የለም፡፡ ሰላም አለ፡፡ በሌላኛው ጎን
እንስሳት በሚያድሩበት ቦታ ላይ ሊጸዳዱ ይችላሉ፡፡ እንደ ሰው ልጅ መጸዳጃ ቤት ልግባ ብለው አይተካክዙም፥ እዛው
ግዳጃቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡

ከዚህ የተነሣ በረት ለሰው ይሸታል፡፡ ስለዚህ በበረት ውስጥ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች መቆየት የሚፈልግ ሰው
አይገኝም፡፡ አብሮ ከመቆየት የተላመዱት እረኞችም ከብቶቻቸውን እስከ ማደሪያቸው ይሸኛሉ እንጂ ተከትለዋቸው
አይዘልቁም፡፡ በጠቅላላው በረት ለሰው ልጆች "የማይመች" ስፍራ ነው፡፡

መድኃኒቱ በሥጋ ሲመጣ የተወለደው እንግዲህ በዚህ ለሰው በማይደላ ቦታ ላይ ነው፡፡ ይሄን ዝም ብሎ
ተቀምጦ በጥሞና ለሚያስብ አማኝ መንክር ነው፡፡ የመድኃኒቱ በከብቶች ማደሪያ መወለድ ብዙ ሚስጢራትንና
አንድምታዎችን የሚያስተምር መንፈሳዊ ሐተታ አለው፡፡ አንዱን እንይ፡፡

5
ጌታ በበረት እንዲወለድ የሆነው ለእንግዶች የተዘጋጀ ማረፊያ በማጣቱ የተነሣ እንደሆነ ወንጌል ጽፎአል፡፡
(የሉቃስ ወንጌል 2፥7) ነገሩ ከገንዘብ ጋር የሚያያዝበት ክር አለው፡፡ በሌላ አባባል የመድኃኒቱ ቤተሰቦች (እናቱ እና
ጻድቁ ዮሴፍ) የሆቴል ባለቤቶችን ቀልብ የሚያስደነግጥ ሐብት ቢያሳዩ ኖሮ፤ ምናልባትም ቀድሞ አልጋ የያዘን ድሃ
ምክንያት ሰጥተው በማስወጣት እነርሱ እንዲገቡ ይሆን ነበር፡፡

ዞሮ ዞሮ እናቱ በረከት ያሉ የቄሣር ሳንቲሞችን ብትከፍል ኖሮ ማደሪያ የሚሰጡ አከራዮችን ስለማግኘቷ


ነባራዊ የአኗኗራችንን ሰበዝ ወደኋላ በመምዘዝ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ስለዚህ ገንዘብ የማይጠይቀው፣ ሞልቷል የማይለው፣
አለባበስና የሥጋ አኳኋን የማይለካውን በረት ተጠግታ ወለደቺው፡፡ በግርግምም አስተኛቺው፡፡

የተወለደው ብላቴና ባደገ ጊዜ እጁን ዘርግቶ የተቀበለውን በረት አልዘነጋውም፡፡ ዓለም ወደናቀቻቸው፣
ይሸታሉ ብላ ወደገፋቻቸው፣ ገንዘብ ወደሌላቸው፣ ሐብታሞች ወደማያስጠጓቸው ድሆች እየሄደ፤ በረቱን ያስታውሰው
ነበር፡፡

በእርግጥም የድሆች ኑሮ በረትን የሚመስልበት መልክ እናገኝበታለን፡፡ ንዝንዝ፣ ውጥረት፣ ክሕደትና ወንጀል
ብዙ ጊዜ አይገኝበትም (አሁን አሁን እንጃ) ፡፡ ከመንገድ ዳር የሚያድሩ ሚስኪኖች መተኛቸውን ለሌላ ሚስኪን
ለማጋራት አይሰስቱም፡፡ አንዷን አንሶላ ለብዙ ለመልበስ አይጨቃጨቁም፡፡ ባለቤቱ የፈጠረውን ውኃ በብረት መስኖ
(ባንቧ) እየጠለፍን በየቤታችን ስላስገባነው፤ ምናልባት የፈለጉትን (በተለይ ከተማ ያሉት) ያህል ገላቸውንና ልብሳቸውን
በፍጥነት ሊያጥቡ ባለመቻላቸው ይቆሽሻሉ፡፡ እኛም እንደ በረቱ ሽታ እንጠየፋቸዋለን (መግቢያ ላይ የተጠቀሰውን
ጸሎት ግን ሰኞ ሰኞ እንጸልይው ይሆናል) ፡፡

መድኃኒቱ የሚገኘው በበረት ነው፡፡ በድሆች ውስጥ፡፡ እንደዚህ አምናለሁ እኔ፡፡ ስለማምንም ብቻ አይደለም፥
አባትየው ራሱ ይላል፦

"ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ


አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።" (የማቴዎስ ወንጌል 25፥35-36)

እውነት እላችኋለሁ፥ በእያንዳንዱ ስለ እርዳታችን ተማጽነው እጃቸው በዘረጉ ድሆች ውስጥ ክርስቶስ መዳፉን
አብሮ ዘርግቷል፡፡ ምክንያቱም "ተርቤ" እንጂ "ተርበው" ሲል አልተናገረም፡፡ እርሱ የበላበትን ሳህን አይሰብርም፥
የበረቱን ውለታ አያጥፍም፡፡ ጌታ በድሆች ውስጥ የመኖሩ እውነት ፍጹም የታመነ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በማለት ለሁለት የተከፈሉ ቃልኪዳኖችን ሲተረክ አንድ መሠረታዊ
ምክንያት አለው፡፡ ይኸውም በቀዳማዊው አዳምና በዳግማዊው አዳም መካከል ያለውን የሰው ልጆችን የባሕሪይ
ጽሑፍ ያስተነትናል፡፡ መድኃኒቱን ያልተቀበሉ ሰዎች የመጀመሪያዋ ሴት ዘር (ከእባብ የመከረቺው ሔዋን ልጆች)
እንደሆኑ ይቀጥላሉ፡፡ በመንፈስና በሕይወት (በቃል) ሳይወለዱ በሥጋ ብቻ ተወሰነው ያልፋሉ፡፡ ለተቀበሉት ግን፥
በስሙ ለሚያምኑት የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ተቀብለዋል፡፡ ከማይጠፋ ዘር ተወልደናልም
የሚያሰኘው ይህ ነው፡፡

አሁን እኛ ያለነው በሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም እንደግለሰብም (ደቡቡ በር) ፥ እንደ
ዓለምም ታሪክ (ሰሜኑ በር) በባሕሪያችን ላይ የሚነበቡት እውነቶች በመድኃኒቱ (በምሥራቁ በር) የተጻፉ ናቸው፡፡
ለዚህ ነው ተማሪዎቹን በአንድ ወቅት "እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው
እንደ ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ" ሲል የነገራቸው፡፡

ወደ ርእሳችን አሳብ ስናመጣው፤ መስቀል አሰርንም አላሰርንም ድሃን የሚገፋ ማንነት ካለን፤ በዚያን ዘመን
ክርስቶስን ከገፉት አይሁዳውያን መካከል አንዱ ነን፡፡ ይሄ ማነጻጸሪያ አይደለም፡፡ ለስብከት መድመቂያነት ያገለገለ

6
ማያያዣ አይደለም፡፡ ከመጀመሪያው አዳም የተወለድን ሁላችን በእርሱ የሆነው ሁሉ በባሕሪይ እየተተረተረ እስከ
ምፅዓት እንደሚቀጥል ሁሉ፤ በዳግማዊው አዳምም ታሪክ የተፈጠሩት ክስተቶች መልክና ትውልድ እየቀየሩ በባሕሪይ
መደገማቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ባይደገሙማ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ" የሚለው ቃል
አይቀመጥም ነበር፡፡ በአጭሩ ድሆችን የምንንቅ ሁላችን፥ "ይሄ የዮሴፍ ልጅ አይደል፥ አናውቀውም እንዴ?" ካሉት
የንቀት ድምፆች ጋር አንድ ነን (ይህን አንቀጽ የምታነብ ነፍስ "ልብ ይሰጠኝ" ስትል ራሷን አትሸንግል፥ ይልቅስ
የተሰጣትን ለባዊነት ተጠቅማ ስለ ንፍገት ደቂቃዎቿ ታልቅስ፥ ትታረምም) ፡፡ የእግዚአብሔር ልብ የተባለ ባለገናው
እንዲህ ይዘምራል፦

"ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል። እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥
ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም። እግዚአብሔር በደዌው አልጋ
ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።" (መዝሙረ ዳዊት 41፥1-3)

ዳዊት አምላክ "እንደ ልቤ" ያለው ታላቅ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ደግሞ መለኮታዊው አሳብ
አለ፡፡ ከላይ በዳዊት የተገለጸው ቃል በእግዚአብሔር ልብ (በአብ) ያለ ነው፡፡ አሳቡን ካወቅን ዘንዳ፥ ፈቃዱን የመፈጸምና
ያለመፈጸም መብቱ በእጃችን ሆነ ማለት ነው፡፡ አዎ... መንግሥተ ሰማያት "በመካከላችን" ናት!

በረቱን ለማጽዳት ባይቻል እንኳ፤ አለመጠየፍ በራሱ ራሱን የቻለ ክርስቲያናዊ ስብዕና ነው፡፡ ለወደቁት
የሚታመም ሰውነት፣ ለተራቡት የሚያዛጋ ሆድ፣ ለተጠሙት የሚደርቅ ጉሮሮ፣ ለተራቆቱት የሚበርደው አካል፣
ለደኸዩት የሚቸገር ቸርነት የሌለው ግለሰብ፤ የቱን ያህል ሃይማኖተኝነት ይኑረው የእግዚአብሔርን ቃልና እውነት
የሚገልጥ ልዕልና ላይ አይደርስም፡፡

ያ... የከበደን ቦታ
የመናፍስት ውጊያን በአምልኮተ እግዚአብሔር የዘወትር ልምምድ ውስጥ የጀመራችሁ ሁላችሁ፤
በእርግጠኝነት ለሰው የተናገራችሁት ወይንም ለፈጣሪ ብቻ ያካፈላችሁት፤ ለረጅም ጊዜ ሲታገላችሁ የቆየ፤ ለውጥ
ታመጡበት ዘንድ ፈተና የሆነባችሁ፤ መፍትሔ ብታገኙለት በጣም የሚያስደስታችሁ አንድ የከበዳችሁ ቦታ አለ፡፡
ስለዚህ ስለከበዳችሁ ቦታ እንነጋገራለን፡፡

በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እቅድ አድርገን ያስቀመጥነው አልሳካ ያለ፤ ወይንም የሰማያዊ ጉዞ መሰናክል
ሆኖ አልታለፍ ያለ የከበደን ቦታ ሁላችንም ጋር አለ፡፡ ይሄ ቦታ የስግደት ቁጥር መጨመር ፈልገን ያልቻልንበት፣
የጸሎት ሰዓት ማሳደግ ፈልገን እምቢ ያለን፣ ቅዱስ ቁርባን መውሰድ ተመኝተን ሩቅ የሆነብን፣ የቅርብ ሰውን
መንፈሳዊ ማድረግ ሽተን ያስቸገረን፣ የልምድ ኃጢአት አስሮን ለመተው የከበደን፣ ከሕይወታችን ለማውጣት ታግለን
አልወጣ ያለን አንድ ቦታ ነው፡፡

ይሄን የከበደንን ቦታ በመንፈሳዊ መነጽር ሰርስረን ስንመለከተው፤ የዲያብሎስ መናፍስት "የምንጭ


ኃይላቸውን" ያስቀመጡበት ቦታ እንደሆነ ሊታየን ይችላል፡፡ ምንድነው የምንጭ ኃይል ማለት?

ከምንጩ የሚወጣ የኤሌክትሪክ ኃይል በአንጻሩ በማስተላለፊያ አካል ተላልፎ ከሚመጣው ኃይል ጋር
ሲወዳደር ከፍተኛ ጉልበት የሚይይዝበት ሁኔታ ሰፊ ነው፡፡ እሳትንም ስንመለከት፤ ከምንጩ የሚነድድበት ቦታ
ከፍንጥርጣሪው የእሳት ነበልባል አንጻር እኩል አያቃጥልም፡፡ የድምፅ ጉልበትም ከምንጩ ሲወጣና በአንዳች ማሳለፊያ
(medium) ሲያልፍ ያለው አቅም የተለያየ ነው፡፡

7
እንዲሁ ርኩሳን መናፍስትም ልዩ ትኩረት ሰጥተው፣ የተጠናከረ ኃይል ተጠቅመው፣ ትልቅ ጉዳይና ዓላማ
አድርገው የሚንቀሳቀሱበት ቦታ የምንጭ ኃይላቸው የተከማቸበት ስፍራ ነው፡፡ ይሄንን በኛ ሕይወት ውስጥ
ስንመነዝረው፤ ብንገፋው ብንገፋው አልከፈት ካለን በር ጀርባ፤ ወደኛ ተቃራኒ አቅጣጫ የሚገፋ የመንፈስ ሠራዊት
በቁጥርም፣ በውጊያ ስልትም፣ በጥፋት ጉልበትም ተደራጅቶ እንደሚገኝ መረዳት ይገባናል፡፡

የዲያብሎስ መንፈስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዘንዶ ይመሰላል፡፡ (የዮሐንስ ራእይ 12፥9)

እንግዲያው ያ የከበደን ቦታ ማለት ይሄ ዘንዶ ተጠምጥሞ ያለበት ቦታ ማለት ነው፡፡ መቁረብ ፈልገህ እምቢ
የሚልህ አለመቁረብ ሆኖ የተጠመጠመብህ ዘንዶ ስላለ ነው፡፡ ብዙ መስገድ ፈልገህ የሚታገልህ የመበርታት መንገድህ
ላይ የተኛ ዘንዶ ስላለ ነው፡፡ በጣም የምትደክምለት ዕድል አልጨበጥ ብሎ ያስቸገረህ ዕድልህን የሚውጥ ዘንዶ ስላለ
ነው፡፡

ክፉው መንፈስ ጥፋትን ተልዕኮው ፈተናን ሂደቱ አድርጎ በሚጓዝበት አሠራሩ ውስጥ ለመዋጋት
የሚጠቀመውን ኃይል የሚከፍለው በሁለት መንገድ ነው፡፡ እነርሱም የምንጭ ኃይሉን የሚያሳርፍበት ቦታ እና ይሄን
የምንጭ ኃይል ላለማስነካት ሲል በዙሪያ የሚያሰልፈው ኃይል ነው፡፡

አንደኛው፥ የምንጭ ኃይሉን የሚያስቀምጥበት ቦታ ማለት፤ በከፍተኛ የሠራዊት ቁጥርና የጥፋት ስልት
ከጉልበት ጋር የሚሠራበት፤ አንተ ደግሞ ይከናወንልህ ዘንድ የምትፈልገው ጽድቅ አሊያም ይርቅልህ ዘንድ የምትሻው
ኃጢአት ያለበት ቦታ ነው፡፡ ያ የከበደህ ቦታ ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው፥ የምትፈልገውን ቦታ እንዳትደርስበት ወይንም
የማትፈልገውን ቦታ እንዳትርቀው ለማድረግ ትኩረት የመበተኛ ሥራዎችን የሚሠራበት፤ የሰበሰበውን ኃይል በነጠላ
እቅድ ለይተህ በመዋጋት እንዳታፈርሰበት ሲል ወከባ እንዲከብህ የሚያደርግበት፤ የማዘናጊያ ፈተና ማምጫ ቦታው
ማለት ነው፡፡ /ተደጋግሞ ይነበብ! /

ለምሳሌ፤ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል በጣም ፈልገህ፤ ነገር ግን እንዳትቀበል ለማድረግ ይሄንን የውጊያ ስምሪት
ለብቻ ለይተው ሌላ የጥፋት ሥራ ሳይሠሩ ይሄንን ጉዳይ የሚፈጽሙ መንፈሶች የመቀደስ ጉዞህ ላይ በጭፍራ
ብዛትና በጥብቅ ኃይል ሲከማቹ የዲያብሎስ የምንጭ ኃይል ያለበት ስፍራ ማለት ያ ቦታ ነው /ቦታ ሲባል በተጨባጭ
የተገለጸ ስፍራን ያይደለ መንፈሳዊ አቀማመጥን እንዲያስብ አንባቢ ይጠየቃል/፡፡ ይሄንን ቦታ ደግሞ አገናዝበኸውም
ሆነ ሳታውቀው በልዩ ትግል እንዳትፋለመው፤ ቅዱስ ቁርባንን የመውሰድ የውሳኔ አሳቦችን የሚያረሳሱ፣ ስለ ቅዱስ
ቁርባን በቂ ትምህርት የመውሰድን ጊዜን የሚረብሹ፣ ሥጋና ደሙን መቀበል አለብኝ ብለህ ኃይል አጠራቅመህ
እንዳትንቀሳቀስ የትኩረት አቅጣጫን የሚያስለውጡ የጎን ፈተናዎች፥ ማለትም፤ መታመም፣ በረከት ማጣት፣ የቤት
ሰላም መጥፋት፣ የትምህርትና የሥራ ዕድል መበላሸት፣ የቤተሰብ መታመምና ወዘተ... ችግሮችን የሚያስከትሉ ሌሎች
መናፍስት ደግሞ ይዋጋሉ፡፡ የከበደህን ቦታ ልዩ ትኩረት እንዳትሰጠው የሚዋጋበት ሁለተኛው የኃይል አሰላለፍ ይሄ
የጎንዮሽ የዕለት ተዕለት ፈተናዎቹ ላይ የሚገለጥ ነው፡፡

በደንብ ግልጽ የሚያደርግ ምሳሌ እንጨምር፡፡ እውቀትህን መጠቀም የሚፈልግ የሲዖል መንፈስ (እንደ
ሉሲፈር) ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በኃይል የሚመሽገው ከእውቀት ጋር የተያያዘ የኑሮና የአካል ክፍልህ (ጭንቅላት)
ላይ ይሆናል፡፡ መንፈሱ ታዲያ ተጓዳኝ ሥራ የሚሠሩለትን ጀሌ መንፈሶች (እንደ ቡዳ፣ መተት፣ ዓይነጥላ) ደግሞ
በተለያየ አቅጣጫ ያሰማራል፡፡ ማለትም መተቱ በጤናህ በኩል፣ ቡዳው በሰውነትህ ውበት ላይ፣ ዓይነጥላው በዕድልህ
ላይ ተሰልፈው፤ ለየብቻ ተልዕኮአቸውን ከግብ ለማድረስ ይሠራሉ፡፡ እነዚህ መናፍስት የሲዖሉ መንፈስ የሚሠራው
በጣም አስፈላጊ ሥራ እንዳይነካበት በሌሎች ችግሮች ወከባችንን በማብዛት እውቀታችን ላይ ያለውን ውጊያ ለብቻ
(በርእስ) እንዳንፋለም ትኩረት የሚበትኑ መናፍስት ናቸው፡፡

8
ያ... የከበደንን ቦታ እንዴት እናቅልለው?

ሀ] በርእስ መዋጋት (የምንጭ ኃይሉን ለማፍረስ)


በርእስ መዋጋት ማለት አንድ ችግር እየፈጠረብን ያለውን ውጊያ ለብቻው በመለየት፤ እርሱን ለማስተካከል
ስንል ችግሩን በተመለከተ የመፍትሔ ጸሎት መጸለይ፣ የችግሩን ባለቤት የሆነ መንፈስን ለብቻ አስሮ ማሰገድና
በመቁጠሪያ መቅጣት ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ የጸሎት ሰዓት መጨመር ፈልገን ነገር ግን ያቃተን ሲሆን፤ ይሄ ያዳገተንን ችግር ለመወጣት ጉዳዩን
ለብቻ ለይተን ሰፊ ጸሎት ስለ ጉዳዩ ማድረስ፤ ጸሎት ሰዓት እንዳንጨምር ያደረገውን መንፈስ መፍትሔ እስኪመጣ
ድረስ ሰማያዊ ስሞችን እየጠሩ ለብቻው በማሰር፤ ማሰገድ፣ በመቁጠሪያ መቀጥቀጥና ጸበል ማስጠመቅ፤ ቅዱስ ቁርባንን
ከመቀበላችን በፊት የከበደንን ጉዳይ ለብቻው በማስታወቅ ስለ መፍትሔው ስንል በተደጋጋሚ መቁረብ በርእስ
መዋጋት ይባላል፡፡

ለ] ቅዱሳንን ማሰለፍ (ተጓዳኝ ፈተናዎቹን ለመቋቋም)


ከላይ እንደተብራራው ዲያቢሎስ ልንደርስበት የምንፈልገው ጽድቅ ላይ አሊያ ልንላቀቀው የምንፈልገው
የኃጢአት እስራት ላይ ልዩ ኃይልና ሠራዊት በማደራጀት ይዋጋል፡፡ ይህንን የትኩረት ቦታ ደግሞ በርእስ እየለየን
እንዳናጠቃበት ተጓዳኝ ፈተናዎችን በማከታተል የውጊያ ርእሳችንን ለማብዛት አሊያም ትኩረታችንን ለመበተን ስልት
ይቀይሳል፡፡ በዚህ ጊዜ የቅዱሳንን እርዳታ እንጠይቃለን፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ምሳሌ መሠረት ስንቀጥል፤ በርእስ የምንዋጋለት ጉዳይ ጸሎት ሰዓትን ስለመጨመር ከሆነ፤
በዚህ ፍልሚያ ውስጥ እያለን በጎን ደግሞ የጤና መታወክ፣ የቤተሰብ ጤና መታወክ፣ የትምህርት መበላሸትና ሌላም
ተጓዳኝ ችግር እንዲገጥመን መንፈሶቹ የጀመርነውን የውጊያ ትኩረት የማዘናጊያ ሥራ ይሠራሉ፡፡ ይሄን ጊዜ ወደ
ምንወደው ቅዱስ በመሄድ፤ ያንን ተጓዳኝ ችግር እንዲዋጋልን ባለጉዳይ እናደርገዋለን፡፡ ለምሳሌ የርእስ ውጊያው
ውስጥ ሆነን፤ የሥራ ዕድል የመበላሸት ችግር ቢገጥመን ይሄ ዕድል እንዲስተካከል ወደ አንድ ቅዱስ በመጸለይና
በስግደት በመማጸን ጉዳያችንን (ፈተናውን) እንዲይዝልን ችግራችንን በእምነት ኃይል አሳልፈን እንሰጣለን ማለት
ነው፡፡

አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው

-------------------------------//-------------------------------

You might also like

  • ( )
    ( )
    Document11 pages
    ( )
    tadious yirdaw
    100% (3)
  • 2
    2
    Document88 pages
    2
    Belayneh Hailegeorgis
    No ratings yet
  • የመጽሐፍተ መነኮሳት መግቢያ
    የመጽሐፍተ መነኮሳት መግቢያ
    Document4 pages
    የመጽሐፍተ መነኮሳት መግቢያ
    Besufkad Getachew
    100% (1)
  • Ginbot 2004
    Ginbot 2004
    Document8 pages
    Ginbot 2004
    Sisay Tekle Gebremedhin
    No ratings yet
  • የፅዋ መመሪያ መጠነኛ ማብራሪያ
    የፅዋ መመሪያ መጠነኛ ማብራሪያ
    Document27 pages
    የፅዋ መመሪያ መጠነኛ ማብራሪያ
    Abraham Ayana
    0% (1)
  • ነገረ ድኅነት - www.dirzon.com
    ነገረ ድኅነት - www.dirzon.com
    Document22 pages
    ነገረ ድኅነት - www.dirzon.com
    mesfin
    100% (4)
  • Love 7
    Love 7
    Document5 pages
    Love 7
    የዓለምዘውድ መኮንን
    No ratings yet
  • ቅድስት
    ቅድስት
    Document8 pages
    ቅድስት
    dihirdigital
    No ratings yet
  • ተንበርክኮ መጸለይ
    ተንበርክኮ መጸለይ
    Document5 pages
    ተንበርክኮ መጸለይ
    fitsum
    No ratings yet
  • 27
    27
    Document77 pages
    27
    Daniel Ergicho
    100% (2)
  • Megbia
    Megbia
    Document22 pages
    Megbia
    Henok Z Glory
    No ratings yet
  • !
    !
    Document5 pages
    !
    Emmanuel Abebe
    No ratings yet
  • Misterekurbane
    Misterekurbane
    Document11 pages
    Misterekurbane
    eyoukassa08
    No ratings yet
  • Mister Ek Urbane
    Mister Ek Urbane
    Document11 pages
    Mister Ek Urbane
    Wedaje Alemayehu
    No ratings yet
  • Untitled
    Untitled
    Document28 pages
    Untitled
    Abeniezer Fentaw
    No ratings yet
  • የመናፍስት ውጊያ ስልቶች
    የመናፍስት ውጊያ ስልቶች
    Document28 pages
    የመናፍስት ውጊያ ስልቶች
    agegnehumola51
    No ratings yet
  • 2
    2
    Document54 pages
    2
    Daniel Ergicho
    100% (2)
  • እማሆይ
    እማሆይ
    Document6 pages
    እማሆይ
    abenezer
    No ratings yet
  • ንሰሐ.docx
    ንሰሐ.docx
    Document5 pages
    ንሰሐ.docx
    Anteneh Beshah Wasia
    100% (2)
  • .53÷5
    .53÷5
    Document521 pages
    .53÷5
    እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው(ጌታችን፣መድሐኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
    100% (1)
  • .53÷5
    .53÷5
    Document521 pages
    .53÷5
    እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው(ጌታችን፣መድሐኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
    No ratings yet
  • 53÷5 (By His Wound We Are Healed (The Grace of God and The Cure of Death) )
    53÷5 (By His Wound We Are Healed (The Grace of God and The Cure of Death) )
    Document521 pages
    53÷5 (By His Wound We Are Healed (The Grace of God and The Cure of Death) )
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • 1 53÷5 PDF
    1 53÷5 PDF
    Document521 pages
    1 53÷5 PDF
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • ( ) 53÷5 ( )
    ( ) 53÷5 ( )
    Document521 pages
    ( ) 53÷5 ( )
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • ( )
    ( )
    Document521 pages
    ( )
    እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው(ጌታችን፣መድሐኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
    No ratings yet
  • Ethiopia ( ) by His Wound We Are Healed (The Grace of God and The Cure of Death)
    Ethiopia ( ) by His Wound We Are Healed (The Grace of God and The Cure of Death)
    Document521 pages
    Ethiopia ( ) by His Wound We Are Healed (The Grace of God and The Cure of Death)
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • Song
    Song
    Document5 pages
    Song
    Markos Mathewos
    No ratings yet
  • Ethiopia ( )
    Ethiopia ( )
    Document520 pages
    Ethiopia ( )
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • .53÷5 ( )
    .53÷5 ( )
    Document520 pages
    .53÷5 ( )
    እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው(ጌታችን፣መድሐኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
    No ratings yet
  • ( )
    ( )
    Document520 pages
    ( )
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • Medan Final
    Medan Final
    Document7 pages
    Medan Final
    admasugedamu2
    No ratings yet
  • ጾም
    ጾም
    Document16 pages
    ጾም
    kidisttaye578
    No ratings yet
  • የእግዚአብሔር ጸጋ እና የሞት መድሐኒት
    የእግዚአብሔር ጸጋ እና የሞት መድሐኒት
    Document522 pages
    የእግዚአብሔር ጸጋ እና የሞት መድሐኒት
    እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው(ጌታችን፣መድሐኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
    No ratings yet
  • 5
    5
    Document8 pages
    5
    Dav Sugo
    No ratings yet
  • Lidetalemariam Ginbot 2009
    Lidetalemariam Ginbot 2009
    Document14 pages
    Lidetalemariam Ginbot 2009
    Sisay Tekle Gebremedhin
    No ratings yet
  • 29
    29
    Document7 pages
    29
    Chu Chu Simeon
    No ratings yet
  • አህጉሮች፡- ይህ ርእስ
    አህጉሮች፡- ይህ ርእስ
    Document26 pages
    አህጉሮች፡- ይህ ርእስ
    ephrem
    No ratings yet
  • Melkamune Gedil Tegadel
    Melkamune Gedil Tegadel
    Document2 pages
    Melkamune Gedil Tegadel
    Daniel Ergicho
    No ratings yet
  • ™
    Document3 pages
    Melaku Awgichew Mamo
    No ratings yet
  • ‹‹ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ››
    ‹‹ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ››
    Document4 pages
    ‹‹ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ››
    admasugedamu2
    No ratings yet
  • ነገረ ትንሣኤ
    ነገረ ትንሣኤ
    Document4 pages
    ነገረ ትንሣኤ
    Asheke Zinab
    No ratings yet
  • Ephesians 6-10-24 Armor of God For Postinga
    Ephesians 6-10-24 Armor of God For Postinga
    Document12 pages
    Ephesians 6-10-24 Armor of God For Postinga
    Hachalu Lenjisa
    No ratings yet
  • ቁጣ
    ቁጣ
    Document16 pages
    ቁጣ
    animaw abebe
    100% (1)
  • 12 2 14
    12 2 14
    Document4 pages
    12 2 14
    Yohannes Kifle
    No ratings yet
  • Yimtal Kirstos
    Yimtal Kirstos
    Document5 pages
    Yimtal Kirstos
    antehunegn tesfaw
    No ratings yet
  • ፍርሳውነት
    ፍርሳውነት
    Document13 pages
    ፍርሳውነት
    Daniel Ergicho
    100% (1)
  • ‹‹_በሰላም_ማሰሪያ_የመንፈስን_አንድነት_ለመጠበቅ_ትጉ፡፡_››
    ‹‹_በሰላም_ማሰሪያ_የመንፈስን_አንድነት_ለመጠበቅ_ትጉ፡፡_››
    Document1 page
    ‹‹_በሰላም_ማሰሪያ_የመንፈስን_አንድነት_ለመጠበቅ_ትጉ፡፡_››
    kahsu berihu
    No ratings yet
  • Lidetalemariam Miyazia 2004 PDF
    Lidetalemariam Miyazia 2004 PDF
    Document12 pages
    Lidetalemariam Miyazia 2004 PDF
    AbeyMulugeta
    No ratings yet
  • Servant Hood2 1
    Servant Hood2 1
    Document282 pages
    Servant Hood2 1
    ፋሲካችን ክርስቶስ ቤተክርስቲያን-ዲላ
    No ratings yet
  • Tselot
    Tselot
    Document7 pages
    Tselot
    Nati Ysl
    100% (1)
  • Lidetalemariam Yekatit 2004
    Lidetalemariam Yekatit 2004
    Document8 pages
    Lidetalemariam Yekatit 2004
    Sisay Tekle Gebremedhin
    No ratings yet
  • Miazia 2004
    Miazia 2004
    Document12 pages
    Miazia 2004
    sisaytekle
    No ratings yet
  • Ethiopia ( )
    Ethiopia ( )
    Document509 pages
    Ethiopia ( )
    እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው(ጌታችን፣መድሐኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
    No ratings yet
  • አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል
    አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል
    From Everand
    አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል
    Rating: 5 out of 5 stars
    5/5 (5)
  • በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን
    በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን
    Document530 pages
    በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    100% (2)
  • .53 ÷5 ( )
    .53 ÷5 ( )
    Document530 pages
    .53 ÷5 ( )
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • .53 ÷5 ( )
    .53 ÷5 ( )
    Document530 pages
    .53 ÷5 ( )
    እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው(ጌታችን፣መድሐኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
    100% (1)
  • The Grace of God and The Cure of Death (By His Wound We Are Healed)
    The Grace of God and The Cure of Death (By His Wound We Are Healed)
    Document530 pages
    The Grace of God and The Cure of Death (By His Wound We Are Healed)
    ክርስቶስ ኢየሱስ ያድናል(ጌታችን፣መድሐኒታችን እናአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡)
    No ratings yet
  • ወደኋላ ማፈግፈግ
    ወደኋላ ማፈግፈግ
    From Everand
    ወደኋላ ማፈግፈግ
    No ratings yet
  • ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች
    ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች
    From Everand
    ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች
    Rating: 4 out of 5 stars
    4/5 (1)