You are on page 1of 8

ልባችንን መጠበቅ

መግቢያ

 በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በጣም አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው?


 መልሱን በማቴዎስ 22፡34-40 ኢየሱስ ሰጥቶናል፡፡ (ጥቅሱ ይነበብ)
 እግዚአብሔርን መውደድና ሰውን መውደድ— እኔና እናንተ ማድረግ ያለብን በጣም አስፈላጊው
ነገር ይህንን ነው፡፡ የሁሉም ነገር መሠረት አድርጎ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን ይህንን ነው፡፡
 በምንናገረውና በምናደርገው ነገር ሁሉ ግድ የሚለን ወይም የሚገፋፋን ኀይል ቢኖር
እግዚአብሔርን መውደድና ሰውን መውደድ መኾን ይኖርበታል፡፡
 ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 13፣ በፍቅር ላይ ተመሥርተን የምናደርጋቸው ነገሮች
ብቻ ናቸው እውነተኛ ዋጋና ዘለቄታ የሚኖራቸው በማለት ያብራራል፡፡
 በሌላ አባባል በሰዎች ዘንድ ለመመስገንና ለመደነቅ በመሻት ብዙ መልካም ተግባራትን ልናከናውን
እንችላለን፤ ይሁን እንጂ ከፍቅር ተነሥተን የማናደርጋቸው ከኾነ አይጠቅሙንም፡፡ ከእግዚአብሔር
ዕይታ አኳያም እንዲሁ የማይቆጠሩ ናቸው፡፡

ልባችሁን ጠብቁ

 የፍቅራችን ምንጭ ከየት ነው? ፍቅር ተወልዶ የሚያድግበት የሰውነታችን ክፍልስ ማን ነው? ልብ
ነው፡፡
 ለዚህም ነው በምሳሌ 4፡23 እንዲህ ተብሎ የተጻፈው "አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት
መውጫ ከእርሱ ነውና።"
 ይህን ሰምታችኋልን?
 ከሁሉም አብልጣችሁ ልባችሁን ጠብቁ!
 ይህ ክፍለ ምንባብ(ጥቅስ) የሥጋ ልባችሁን የሚያመለክት አይደለም፡፡
 የሥጋ ልባችሁ ወደ ተለያዩ የሰውነታችሁ ክፍሎች ደምን የሚረጭ ጡንቻ ነው፤ ከሐሳብ፣
ምክንያትና ከስሜታችሁ ጋር እምባዛም ግንኑነት የለውም፡፡
ልባችን ምንን ይወክላል (ያመለክታል )

 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልብ ሲናገር፣ ብዙውን ጊዜ በሰብእናችን ውስጥ የማንኛውም ሐሳብ፣ ስሜት፣


ቃልና ተግባር መነሾ- ምንጭንና ማዕከል(መኻል)የሆነውን ልቡናን ነው የሚያመለክተው፡፡
 መላ ሰብእናችንን የሚገዛና የሚቈጣጠር የውስጥ ልቡናችን (ማንነታችን) ክፍል ነው፡፡
 ልባችን የፍቅራችን የመወለጃ ቦታና መኖሪያ ቤት ነው— እንዲሁም ፍቅር ባጽናፈ ዓለሙ ውስጥ
ከሁሉም በላይ ዓይነተኛውና አስፈላጊው ኀይል ነው፡፡
 ልባችሁ ምንኛ ለእግዚአብሔር ክቡር እንደሆነ አስተዋላችሁን?

ዋነኛው መሥፈርት

 እግዚአብሔር አዲስን ንጉሥ በእስራኤል እንዲሾም ነቢዩ ሳሙኤልን በላከው ጊዜ፣ ዋነኛው
መሥፈርት የፊት መልክ፣ ልምድ፣ አልፎ ተርፎም ተሰጥዖ አልነበረም፡፡
 ለተወሰነ ጊዜ ያህል፣ ሳሙኤል ለሥራው ትክክለኛውን ሰው እንዳገኘ ተሰምቶት ነበር፡፡
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ "ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር
አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።" (1ሳሙ 16፡7)፡፡
 ጌታን ማገልገል እና በሰዎች ላይ የሕይወት ለመውጥን ማምጣጥ የምትፈልጉ ከኾነ፣ በጣም አስፈላጊ
የሆነው ነገር ልባችሁ እንጂ የእናንተ ተሞክሮ ወይም ብቃት-ችሎታ አይደለም፡፡
 የእግዚአብሔር የልቡን ፈቃድና ሐሳብ የምታድርጉ ሰዎች ለመሆን ምረጡ!

ልባችንን መጠበቅ ለምን ያስፈልጋል?

 ምሳሌ 4፡23 ልባችንን እንድንጠብቅ ይነግረናል፡፡


 ልባችንን መጠበቅ ለምን ያስፈልገናል?
 ምክንያቱም በጥቃት ዒላማ ውስጥ ነው ያለው! እነኝህ ጥቃቶች የሚሰነዘሩትም ከውስጥም
ከውጭም ነው፡፡
 መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልብ በዓለም ቊጥር አንድ የጦርነት አውድማ እንደኾነ ይናገራል፡፡
 በሦስት ተቀኛቃኝ ወገኖች (ፓሪቲዎች) መካከል የማያቋርጥ ትግል እየተካሄደ ነው፡፡ አሸናፊውንም
የምትወስኑት እናንተዉ ናችሁ!
 ታዲያ በልባችሁ ጌታ እንዲሆን የምትፈቅዱለት ለየትኛው ነው?
 ሥጋን ይኾንን? ዲያብሎስን ይኾንን? ወይስ መንፈስ ቅዱስን?
ከሥጋ የሚሰነዘር ጥቃት

 ሥጋ የሚወክለው የወደቀው የሰውነት ጠባያችንን ነው፤ ለእግዚአብሔር ፈቃድ አልገዛ- አሻፈረኝ


ያለውን ክፍላችንን ነው፡፡
 የራሱ ጌታ መሆን የሚሻ፣ ትክክልና ስህተት የሆነውን በራሱ- ለራሱ የሚወስን፡፡ ድሎት፣ ራስ
ወዳድነት፣ እና የሥጋን ሕይወትን መምራት የሚመርጥ ነው፡፡
 " ለኔ! ድገሙኝ-ጨምሩልኝ! አሁንም! እንደሚል ልክ እንደተራበ ወጣት ወፍ
 የሥጋ ምኞቶች ለብዙ ታላላቅ ሰዎች የውድቀት ምክንያት ሆኖኣል፡፡
 በተለይ ወንዶች፣ በርግጥ ሴቶችም ቢሆን ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ ሦስት የታወቁ ፈተናዎች
አሉ፡-

1) ወሲብ
2) ገንዘብ
3) ሥልጣን

የዘራነውን ያንኑ እናጭዳለን

 እነዚህ ፈተናዎች አስተሳሰባችንን እንዲሞሉ እና አእምሮአችንን እንዲቈጣጠሩት ከፈቀድን ውሎ


አድሮ ልባችንን ይመርዙታል::
 አመለካከታችንንና ጠባያችንን ያበላሹታል፣ ብሎም ክብርና ማዕረጋችንን ሁሉ ይገፉታል፡፡
 መጽሐፍ ቅዱስ ሐሳባችንን እንደ ምንዘራው ዘር ልባችንን ደግሞ እንደ እርሻ አድርጎ ይመስለዋል፡፡
 ለዚህም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በገላ 6፡7-9 ይህን ጒዳይ በእንዲህ መልኩ የገለጠው (ጥቅሱ
ይነበብ)፡፡
 ይህ ክፍለ ምንባብ (ጥቅስ) "የመዝራትና የማጨድ ሕግ" ተብሎ ይታወቃል፡፡
 መልካም ይሁን ክፉ ሁሌም ቢሆን የዛራችሁትን ነው የምታጭዱት፡፡
 በልባችሁ እርሻ ውስጥ ምን ዓይነት አስተሳሰብ ዘርታችኋል?
ከዲያብሎስ የሚሰነዘር ጥቃት

 ትግል የምንግጥመው ከሥጋ ጋር ብቻ አይደለም፡፡


 መጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛ ዓለማው "መስረቅ፣ ማረድና ማጥፋት" አድርጎ የሚንቀሳቀስ ወደረኛ-ጠላት
እንዳለን ይነግረናል፡፡(ዮሐ 10፡10)፡፡
 ሰይጣን ወይም ዲያብሎስ ተብሎ የሚጠራው ጠላታችን - ልባችንን መቆጣጠር የቻለ እንደሆነ፣
መላ ሰብእናችንን መቆጣጠር እንደሚችልና ለጥፋት ተግባሩ ሊያውልው እንደሚችል ያውቃል፡፡
 ሰይጣን አስተሳሰባችንን እና ስሜታችንን ዒላማ በማድረግ፣ ልባችንን መውረርና መግዛት ነው
የሚፈልገው፡፡
ጠላት ሥጋን ይጠቀማል

 ሰይጣን በጣም ብልኅና የጦርነት ስልት ዐዋቂ መሪ እንደመሆኑ መጠን የወደቀውን የሥጋ
ጠባያችንን ይጠቀማል፡፡ እኛን አባብሎ ለማጥመድም በሥጋ መሻቶቻችን በኩል ይወተውተናል፡፡
 ደካማ የሆነውን ጎናችንን ያውቃል፤ በዚያም ገብቶ ጥቃቱን ይሰነዝርብናል፡፡
 ገንዘብ የምንወድ ከሆነ በሀብት ይፈትነናል፡፡
 ጒጒታችን ሥልጣንና ታዊቂነት የሆነ እንደሆነ ደግሞ ሹመትና ሽልማት እንደሚሰጠን አድርጎ ቃል
ይገባልናል፡፡
 በፍትወተ ሥጋ የምንቃጠል ከሆነ ደግሞ ምናባዊውንና በልጭልጩን ዓለም ያቀርብልናል፡፡
 እግዚአብሔር ለሕይወታችን ካለው ቅዱስ ዓላማ ለማጨናገፍ ጠላት አደንዛዥ ዕፆች፣ መጠጥ፣
ጥንቈላ/መተት/፣ ዓመጽ የሞላባቸው ፊልሞች፣ ወሲብ ነክ ድረ-ገጾች ብሎም ሁሉንም የማሰናከያ
ዘዴዎችን ሁሉ ያለእረፍትና ያለማቋርጥ ለመጠቀም ይጥራል፡፡
ጠላት የሚጠላውና የሚፈራው ነገር

 ዲያብሎስ እንደ ፍቅር አድርጎ የሚጠላው ነገር የለም፤ ምክንያቱም ፍቅር የሆነው ኢየሱስ ክርሰቶስ
የርሱ ዋነኛ ወደረኛው ነውና፡፡
 ስለዚህ ዲያብሎስ እንደ ፍቅር አድረጎ የሚፈራው አንዳች ነገር የለም፣ ምክንያቱም፡-
1) ልብን ሊፈውስና ሊያድስ የሚችል ብቸኛው ኃይል ፍቅር ነውና፡፡
2) የእግዚአብሔርን ሕዝብ ታላቁን ተልዕኮ እንዲያከናውኑና ሰዎችን ሁሉ ደቀመዛምርት እንዲያደርጉ
ማስከተት፣ አንድ ማድረግና ኀይልን ማስታጠቅ የሚቻለው ፍቅር ብቻ ነውና ነው፡፡
 ጠላት ፍቅራችንን ለማጥፋትና ለማቀዝቀዝ፣ የተሰበረና ድንዙዝ ልብ ለማኖር በጣም መጨነቁ
አያስደንቅም፡፡

ረዳታችን - መንፈስ ቅዱስ

 ሥጋና ዲያብሎስ አንድ ላይ አብረው ሰውን ለመደብደብ ጠንካሮች ናቸው፡፡


 አሳዛኙ ነገር ግን የኛ ጥንካሬና ኀይል እነዚህን ጣምራ ጠላቶቻችንን ገጥሞ ለማሸነፍ አይቻለውም፡፡
 የምሥራቹ ዜና በራሳችን ጥንካሬና ኀይል ላይ አለመተማመን ነው፣

ምክንያቱም:-

 እነዚህን ወደረኞቻችንን ኢየሱስ ክርስቶስ አሸንፎልናል፣


 ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ረዳታች እንዲኾን አድርጎ ሰጥቶናል፣
 በልባችን ውስጥ ለሚደረገው ጦርነት በመንፈስ ቅዱስ ላይ ልንታመን እንችላለን!
 የልባችን ሙሉ ፈቃድ ለእርሱ በስጠትና የአካል፣ የነፍስና መንፈሳችን ሙሉ ባለቤት እርሱ እንዲሆን
ከፈቀድን አሸናፊዎች እንሆናል፤ መሆንም እንችላለን፡፡

ልባችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?

 የልባችንን ገዥ መንፈስ ቅዱስን ስናደርግ፣ የጠፋብንን ፍቅር፣ ደስታ፣ እና ሰላም ማደስ ይጀምራል፡፡
 ነገር ግን ይህ ሂደት ጊዜን ሊወስድ ይችላል - የእኛንም ፈቃደኝነት ይጠይቃል፡፡
 እዚህ ላይ ጥያቄው፡-
 በእኛ ውስጥ ሥራውን እንዲያከናውን ለመንፈስ ቅዱስ ትክክልኛውን ሁኔታ እንዴት
ልናመቻችለት እንችላለን?
 ልባችን ጽኑና ጤናማ መሆኑን ማረጋገጥ የምንችለው እንዴት ነው?
 በሌላ አነጋገር ልባችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?

አድርግ አታድርግ

 ልባችንን መጠበቅ ስንል የምናደርጋቸውንና የማደርጋቸውን ነገሮችንም ለይቶ ማወቅንም


የሚያካትት ነው፡፡
 በአንድ በኩል፣ መልካም ልማዶችን ዕለት ተዕለት ማዳባር ያስፈልገናል፣ ይህም ሲባል፣ ልብ ለዋጭ
ለሆነው ለመንፈስ ቅዱስ በየዕለቱ ልባችንን ክፍት ማድረግ አለብን ማለት ነው፡፡
 በሌላ በኩል ደግሞ መጥፎ ከሆኑ ልማዶች ራሳችንን ማስወገድ ይኖርብናል፤ ይህም ሲባል ሥጋና
ዲያብሎስን ሊጋብዙና በዚህም ልባችንን ሊበክሉና ሊመርዙ ከሚችሉ ነገሮች መቆጠብ ማለት
ነው፡፡
 ልባችን ፈውስ እንዲያገኝ፣ እንዲያድግ እና ብዙ ፍሬን እንዲያፈራ ቀና ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ
አድርግና አታድርግ በጋራ ሆነው ይሠራሉ፡፡
መልካም ልማዶችን መገንባት

 መልካም ልማዶችን መገንባት ሲባል ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ መስጠት ማለት ነው፡፡
በጊዜ ሰሌዳችን ውስጥ በጣም ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ትኲረት ሰጥተን እንሠራለን፡፡
 ሮሜ 12፡2 "በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ
በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።" በማለት በጥብቅ ያሳስበናል፡፡
 እንዲህ ዓይነቱ መታደስ በየዕለቱ የሚያስፈልገን ነገር ነው፡፡ ይህም እውን ሊሆን የሚችለው፣ ጊዜ
ሰጥተን በጸሎትና መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ከሰማያዊው አባታችን ጋር ስንገናኝ ብቻ ነው፡፡
 የእግዚአብሔር ቃል እውነት እና ሕይወትን ለልባችን ይናገረናል፣ እንዲሁም ደግሞ የጠላትን ውሸት
ይገልጥልናል፡፡
 መንፈስ ቅዱስ የኛን ሐሳብ በርሱ ሐሳብ ሲተካቸው፣ ከጭነቀት ነጻ እንሆንና ርሱ ራሱ
የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናደርግ ኀይልን ያስታጥቀናል፡፡

የክርስቲያን ኅብረት አስፈላጊነት

 ከክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋርም ጊዜ ማሳለፍ ያስፈልገናል፡፡


 ብቻውን የቆመ ዛፍ በቀላሉ በኀይለኛ የነፋስ ማዕበል ተገንድሶ ይወድቃል፡፡ በአንጻሩ በሌሎች ዛፎች
ዙሪያ የተከበበ ዛፍ ግን በነፋስ ተገንድሶ ከመውደቅ ይተርፋል፡፡
 ሕይወት ማለት ብቻህን መኖር ማለት አይደለም፤ የሕይወትን ማዕበል ለመቋቋም እንድንችል ዘንድ
አንደኛችን በሌላኛችን ላይ ጥገኞች ነን፡፡
 በዚህ ትምህርት ጸንታችሁ መቆም እንድትችሉ በሚረዷችሁ ሰዎች ተከባችኋል፤ ስለሆነም
እርስበራሳችሁ እንድትመካከሩበትና አንደኛችሁ ለሌላኛችሁ ኀላፊነትን እንድትወስዱ አድርጋችሁም
ዕድሉን ተጠቀሙበት፡፡
 ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል መኾኗን አስታውሱ፣ በዚህ አካል ውስጥ መኖራችንም እምቅ
የሆነው አቅማችንን በማውጣት እርስበራሳችን ለመረዳዳት ነው፡፡

መጥፎ ልማዶችን ማስወገድ

 መጥፎ ልምዶችን ማስወገድ ማለት ጊዜያችንንና ትኲረታችንን ሰርቀው አደጋ ላይ ለሚጥሉን ነገሮች
እምቢ -አሻፈረኝ ማለት ነው፡፡
 መቼስ ሳምንቱን እንዴት እንደምታሳልፉት እናንተዉ ታውቃለችሁ፡፡

ምናልባትም፡-

- አንድዳንድ ፊልሞችንና ድረ-ገጾችን ከመመልከት መቆጠብ፣


- አንዳንድ ነገሮችን መጠቀም መተው ወይም አንዳንድ አልበሞችንና መጽሄቶችን ማስወገድ፣
- አንዳንድ ነገሮችን ከመናገር መቆጠብ፣ ወይም በዙሪያችሁ ካሉ ሰዎች ጋር ያላችሁን
አቀራረብ/ግንኙነት/ መቀየር ይኖርባችሁ ይሆናል፡፡
 እምቢተኛነታችሁን ከሚገባው በላይ አታድረጉት! መጽሐፍ ቅዱስ "ትቢያ" ናችሁ ይለናልና፡፡
 የሕይወትን እንጀራ መመገብ ስትችሉና ከሕይወት ወንዞችም ውሃን መጠታት ስትችሉ፣ ለምንድን
ነው ልባችሁን አሸር በሸር የሆነ መንፈሳዊ ምግብ መመገብ የምትፈልጉት?

ውሣኔዎች ሁሉ የሚያስከትሉት ውጤት አላቸው

 ውሣኔዎች ሁሉ የሚያስከትሉት የራሳቸው የሆነ ውጤት ስላላቸው፣ ጠቃሜታቸውን አስቀድሞ


በጥልቀት መረዳት ወሳኝ ነገር ነው፡፡
 በየዕለቱ የምታደርጓቸው ትናንሽ ውሣኔዎች ናቸው መጨረሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ መዘዝን
የሚያስከትሉባችሁ፡፡
 በፈታኝ ሁኔታ ኀይል ሥር ከመውደቃችሁ በፊት በተቻለ መጠንና ከሁሉም በተሻለ የጥበብ
አማራጭ ፈተናዎችን ልታሸንፉ በምትችሉባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ራሳችሁን ማስቀመጥና መጠበቅ
ያለባችሁም ለዚህ ነው፡፡

ኀጢአት በሐሳብ ውስጥ ይጀምራል

 ሁል ጊዜ ኀጢአት የሚጀምረው በሐሳባችን ውስጥ እንደሆነ ኢየሱስ ግልጽ አድርጎልናል፡፡ እነዚህን


ሐሳቦች ከሥራቸው መንግለን መጣል ካልቻልን፣ ውለው አድረው ኀጢአተኛ ጠባይና ባሕርይ
ማመንጨታቸው የማይቀር ነው፡፡
 በሥራ ገበታ "በቅን ልብ የተደረገ ማሽኮርመም" 'የቅን ልብ' አይደለም፤ ምክንያቱም፡-" ወደ ሴት
ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።" (ማቴ 5፡28)
 ለደንበኛው "ነጭ ውሸት" የዋሸም ውሸቱ 'ነጭ' አይደለም፡፡"ቃላችሁ 'አዎን' 'አዎን' ወይም
'አይደለም' 'አይደለም' ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው።" (ማቴ 5፡37)
 አንዴ መሥመሩን አቋርጣችሁ በሐሳብ ኀጢአት ከወደቃችሁ፣ ተንበርክካችሁ ንስሐ ግቡ፡፡
ወዲያውም ነጻ ትወጣላችሁ!
እኔና እናንተስ?

 ልባችሁን ጠብቁ ማለት የሚቀጣጠለውን የእግዚአብሔርን እሳት፣ የእምነትን፣ የተስፋንና የፍቅርን


እሳት መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ይህም እሳት በዙሪያችሁ ላሉ ሰዎች ስታካፍሉት ደግሞ እየበረታና
እየጨመረ ይሄዳል፡፡
 ሁሉንም የቀን ተግባሬን በፍቅር አደርገዋለሁኝ በማለት ማለዳ ከእንቅልፋችሁ ስትነሡ ወስናችሁ
ተነሡ!
 ተጨማሪ ጊዜ አይወስድባችሁም፣ የእናንተን ትኲረትና አመለካከታችሁን ብቻ ነው የሚቀይረው፡፡
በጣም ቀላልና ተራ (ትንሽ) በሆኑ ነገሮች ሳይቀር አዲስ ትርጒም እና ደስታን በማግኘታችሁ
ትደነቃላችሁ!
 በ1ኛ ተሰሎንቄ 5፡23-24 በሚገኘው የሐዋርያው ጳውሎስ ሰላምታ እንዝጋው (ጥቅሱ ይነበብ፡፡)
 እንጸልይ፡፡ (በጸሎት ይዘጋ)

ለቡድን ውይትት የቀረቡ ጥያቄዎች

 ከክፍለ ትምህርቱ ምን ገንቢና ጠቃሚ ሐሳቦችን አገኛችሁ?


 ልባችሁን ጠብቁ የሚለው ሐረግ ምን ትርጒም ይሰጣችኋል?
 እንዴት ባለ አኳኋን ነው ዛሬ ልባችሁን የምትጠብቁት? የመንፈስ ቅዱስ ሚናስ ምንድን ነው?
 "በመዝራትና በማጨድ ሕግ" ሂደት ውስጥ ያለፋችሁባቸው ተሞክሮዎች አሏችሁን?
 በዕለት ተዕለት የሕይወት ጒዟችሁ ውስጥ ጌታ ልታደርጉትና ልትሆኑት ከመደበላችሁ ነገሮች
እናንተን ለማስቀረትና ሐሳብ ለማዛባት ጠላት የተጠቀመባቸው ነገሮች አሉን? ምንስ ልታደርጉ
ትችላላችሁ?
 በቤተሰባችሁ ውስጥ፣ በሥራ ቦታችሁና ማኅበረሰባችሁ ውስጥ በግላችሁ ምን ዓይነት አዳዲስ
መልካም ልምዶችን ነው ማዳበር የምትፈልጉት?

ጸሎት (በትንንሽ ቡድኖች ውስጥ የሚከናወን)

 እንደ ረዳታችሁ አድርጋችሁ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፡፡


 ለልብ ንጽሕናና ሙሉዕነት ጸልዩ፡፡
 ጥፋት ከሚያደርሱ ልማዶችና ከሱሶች እንዲገላግላችሁ የእግዚአብሔርን ኀይል እና ተግሣጽ(ሥነ
ሥርዐት) ጠይቁ፡፡
 በግላችሁ መልካም ልማዶችን በቤተሰብ ውስጥ፣ በሥራ ቦታና በማኅበረሰባችሁ ውስጥ እንድታሳዩ
ጥበብ እንዲሰጣችሁ በጸሎት ጠይቁ፡፡

You might also like