Professional Documents
Culture Documents
የእግዚአብሔር_ፈቃድ_እንዴት_ይታወቃል
የእግዚአብሔር_ፈቃድ_እንዴት_ይታወቃል
እንዳልተፈጠረ ማድረግ ይችላል፡፡ ነገር ግን ማድረግ ስለሚችል ብቻ (ይህን ለማድረግ ክሂል ስላለው
ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን? ከሰማይ ይልቅ ከፍ
1|Page
፪. የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምናውቀው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር ፈቃዱን ለእኛ መግለጥ ፍላጎቱ ነው፡፡ ሥነ ፍጥረትን የፈጠረው፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን
የሰጠው፣ በኋላም የባሕርይ ልጁን በሥጋ የላከው ፈቃዱን በግልጥ እንድናውቅ እንዲሁም በዚያ
መሠረት እንድንመራና እንድንኖር ጽኑ ፍላጎቱና ፈቃዱ ስለሆነ ነው፡፡ ሐዋርያው “….እንደ አሳቡ ፥
እንደሆነ? አጠቃላይ የእግዚአብሔር ፈቃድና ለሰው ልጆች ያለው ዓላማ ምን መሆኑን ለእኛ
ለመንገርና ለማሳውቅ ነው፡፡ ይኽን በተመለከተ ቅዱሳት መጻሕፍት ብዙ ይናገራሉ፡፡
ነቢዩ ዳዊት “እግዚአብሔር ይነግሮሙ ለሕዝቡ በመጽሐፍ ወለመላእክቲሁኒ እለ ተወልዱ
በውስቴታ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ፥ በውስጧም ለተወለዱት አለቆቿ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል”
ይላል። /መዝ፹=፮፥፮/ እንዲሁም “ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፣ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ፡፡
ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው” ይላል፡፡ /መዝ ፻=፲=፰፥፻=፭/ የእግዚአብሔር ትእዛዝ
አእምሯችንንና ልቡናችንን ፈቃዱን ለማወቅ ብሩህ የሚያደርግ ስለ መሆኑ ሲናገር ደግሞ “ትእዛዙ
ለእግዚአብሔር ብሩህ ወያበርህ አዕይንተ- የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ዓይንንም ያበራል”
ይላል፡፡ /መዝ፲=፰፥፰/
ቅዱስ ጳውሎስም ደቀ መዝሙሩን ጢሞቴዎስን “ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን
2|Page
ስለሆነም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ምን እንደ ሆነና እንዳልሆነ በቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ የተነገረ
ነው “የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት አድርጌ ላውቅ እችላለሁ? ከየትስ አገኘዋለሁ? የሚል ጭንቀት
ሊኖር አይገባም በቅዱሳት መጻሕፍት በዓዋጅ የተነገረ ነውና። ለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር
እስትንፋስ የሆኑትን የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መብላትና በውስጣቸው ባለው በትምህርታቸው
መጥገብ ግድ ይላል። ለነቢዩ ሕዝቅኤል እንዲህ ተብሎ እንደ ተነገረ- “እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ
ያገኘኸውን ብላ፣ ይህን መጽሐፍ ብላ፥ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር አለኝ። አፌንም
ከፈትሁ፣መጽሐፉንም አጐረሰኝ። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ አፍህ ይብላ በምሰጥህም በዚህ
መጽሐፍ ሆድህን ሙላ አለኝ። እኔም በላሁት በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ።” /ሕዝ ፫፥፩-፫/
ቅዱሳት መጻሕፍትን ያልተማረ ሰው ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ በእጅጉ ይቸገራል።
በአኗኗራችን፣ በአነጋገራችን፣ በምርጫዎቻችን፣ ወዘተ የምናያቸው ምስቅልቅሎችና ከፈቃደ
እግዚአብሔር ጋር የማይስማሙ ድርጊቶቻችን አብዛኛዎቹ በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠውን
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠንቅቆ ካለመረዳት የሚመነጩ ናቸው። ስለዚህ የእግዚአብሔርን
ፈቃድ ለማወቅ ቅዱሳት መጻሕፍትን መማርና ለተማርነውም መታዘዝና ታማኝ መሆን ይገባል።
በትንሹ ስንታመን፣ ላወቅነው ቃለ እግዚአብሔር አክብሮት ስንሰጥና በሕይወታችን መተግበር
ስንጀምር ሌላውንም በቸርነቱ እየገለጠልንና እየረዳን ይሄዳል። ፈቃዱን ለማድረግ የሚጥርን
ሰው እግዚአብሔር የበለጠውን የጥበቡን በር እየከፈተለት ይሄዳል። ጌታችንና መድኃታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ “ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን
ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል" ያለው ለዚህ ነው። /ዮሐ 7፥07/
መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነታ አዲስ በሚገጥሙ የተለያዩ ሁኔታዎች ላይ መተግበር
መጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ አቅጣጫ የሚያሳይና ዋና ዋና የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን የሚነግረን ነው
እንጂ በእያንዳንዱ ዝርዝርና ተራ ጉዳይ ውስጥ ገብቶ እኛ በአእምሯችን እያብሰሰለልነው ያለውን
ጉዳይ ሁሉ በቀጥታ “እንዲህ አድርግ'' ወይም “አታድርግ” እያለ የሚነግረን አይደለም። መጽሐፍ
3|Page
ቅዱስ ሀገራት “ሕገ መንግሥት'' እንደሚሉት ያለ ነው። የሀገራት ሕገ መንግሥት የዚያን ሀገር ሕዝብ
በተመለከተ አጠቃላይ መሠረቱን የሚጥልና ወሰኑንና ዳርቻውን የሚወስን ነው። ስለ እያንዳንዱ
ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ፣ ፍትሐ ብሔራዊ፤ ወንጀል ነክ፣ ወዘተ ጉዳይ ገብቶ
አንቀጽ የሚያትት አይደለም፡፡ ነገር ግን በዚያ በሕገ መንግሥቱ መሠረትነት የተለያዩ የማስፈጸሚያ
ሕጎችና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ በየዓይነቱ ይወጣሉ።
መጽሐፍ ቅዱስንም በዚህ ዓይነት ሁኔታ ልናየው እንችላለን። ስለ መዳናችንና ዘለዓለማዊ ሕይወትን
ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ ተነግሮናል። ከዚያ ውጭ ስላሉ
ሌሎች ጉዳዮች ግን አጠቃላይ አቅጣጫና መመሪያ በመስጠት ዳሩንና ድንበሩን ያሳየናል እንጂ
ዝርዝር ነገር ላይነግረን ይችላል። ለምሳሌም እያንዳንዱ ሰው በምን ዓይነት የሥራ መስክ
መሰማራት እንዳለበት፣ ማንን ማግባት እንዳለበት፣ ምን ዓይነት ቤት እንደሚሠራ ወዘተ
አይነግረውም፡፡ ስለዚህም የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በሚገባ በመማርና በማስተዋል መጽሐፍ ቅዱስ
ላይ በግልጥ ያልተነገሩ ወይም በግልጽ ያልተናገረባቸው ጉዳዮች ሲገጥሙን ቃሉን በሚገባ
የተረዳን ከሆነ ጥሩ መሠረትና መነሻ እናገኛለን፡፡ አጠቃላዩን የቅዱስ መጽሐፍ አቅጣጫና
መመሪያ በዚያ በገጠመን ዝርዝር ጉዳይ ላይ በመተግበርና ከቃሉ አንጻር በመመዘን ምን ማድረግ
እንደሚኖርብንና እንደማይኖርብን ፍንጭ እናገኛለን፡፡
ከሌሎች ሕይወት መማር
ከእኛ በፊት ኖረው ካለፉትም ሆነ በዘመናችን ካሉት ከሌሎች ወገኖቻችንም ለእኛ ጠቃሚ የሆኑ ብዙ
ትምህርቶችን ማግኘት እንችላለን፡፡ እነ ማን ምን አድርገው ከእግዚእብሔር ፈቃድ አፈነገጡ? ምንስ
4|Page
ነው፡፡ ታላቁ አባታችን ቅዱስ ጳውሎስ እሥራኤላውያን ከግብጽ ሲወጡና ከዚያም ኋላ በመንገድ
ላይ እያሉ ያደረጉትንና የደረሰባቸውን ካስታወሰ በኋላ “ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥
እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ” ያለው ለዚህ ነው፡፡ /፩ቆሮ ፲፥ ፩-፲=፩/
5|Page
“ኢያሱም፡ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ? አላቸው፡፡… እነርሱም አሉት፡- ከአምላክህ
ከእግዚአብሔር ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር ባሪያዎችህ መጥተናል፡፡ ዝናውንም፥ በግብጽም
ያደረገውን ሁሉ፥ በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፣ በሐሴቦን ንጉሥ
በሴዎን፣ በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።
ሽማግሌዎቻችንም በምድራችንም የሚኖሩት ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ፥
ልትገናኟቸውም ሂዱ፣ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፣ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሏቸው አሉን፡፡
ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩሱን ለስንቅ ከቤታችን ወሰድነው፣
አሁንም እነሆ ደርቋል ሻግቷልም፡፡ እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች አዲስ ሳሉ ሞላንባቸው፣ እነሆም
ተቀድደዋል፤ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።
ሰዎቹም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ እግዚአብሔርንም አልጠየቁም፡፡ ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ሰላም አደረገ
/ኢያ ፱፥ ፫—፳/
ምንም እንኳ ኢያሱ እግዚአብሔር እንደማይለየውና ከእርሱ ጋር እንደሚሆን የነገረው ቢሆንም
እነዚህ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁት እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ነበረበት:: ነገር ግን ያን
6|Page
ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው::'' /፪ ሳሙ
::” /፪ ሳሙ፪፥ ፩/
ምክር መጠየቅ
እግዚአብሔር በሰዎች አማካይነት የሚያስፈልገንን ነገር ሊነግረንና ሊመክረን ይችላል፡፡ በእርግጥ
የምክር ጉዳይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ጥሩ መካር እንዳለ ሁሉ መጥፎ መካርም አለና፡፡
ሰዎች የሚሰጡንን ምክር ከቅዱሳት መጻሕፍት፣ ከአባቶቻችን ሕይወትና ትምህርት ጋር
የሚቃረን መሆን አለመሆኑን መመዘን የሁል ጊዜም ተግባራችን መሆን አለበት። ይኽ እንዳለ ሆኖ
በውስጣችን ከብዶ፤ መያዣና መጨበጫው ጥፍት ብሎ የሚያስጨንቀንን ነገር ለሰዎች
ስናካፍለው፤ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው አባታዊ ደግነት የተነሣ በዚያ ሰው አማይነት ውስጣችንን
ሊነግረንና የፈቃዱን አቅጣጫ ሊያመለከተን ይችላል፡፡
እግዚአብሔርን መውደድ
ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር እየጨመረ በሄደ መጠን፣ እርሱን አምላካችንን የበለጠ በወደድነው
መጠን እርሱ የሚወድደውን የበለጠ እያወቅን እንሄዳለን፡፡
እናት ልጇ የሚፈልገውን ነገር ፍላጎቱን በቃላት መግለጽ ከመቻሉ በፊት ታውቀዋለች፡፡ እኛም
እንዲሁ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በወደድነው መጠን እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር የበሰጠ እያወቅን
እንመጣለን፡፡ በአንጻሩም ደግሞ ለእርሱ ያለን ፍቅር እየደከመ በሄደ መጠን ፈቃዱን ማወቅና
7|Page
መለየት እየተሳነን ይሄዳል፡፡ ፍቅረ እግዚአብሔር የሕግጋቱ ሁሉ መጀመሪያና መጠቅለያ የሆነው
ለዚህ ነው፡፡
የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ ማዳመጥ
ምናልባት እያደረግነው ያለው ነገር ወይም ልናደርገው በሒደት ላይ ያለው ጉዳይ የእግዚአብሔር
ፈቃድ ያልሆነ ነገር ከሆነ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይናገራልና ያን ማዳመጥ ይገባል፡፡
ከውስጣችን በጸጥታ ውስጥ ሲናገረን እንሰማዋለን፡፡ ውስጣችን ዕረፍት እንዲያጣ ምቾት
ሕሊናን ማዳመጥም ተገቢ ነው፡፡ / ሮ ሜ ፲ ፫= ፥፭/ ሕሊናችን አንድ ነገ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆን
አለመሆኑን የምንለካበት ሚዛን ነው፡፡ ስለዚህ ሕሊናችንን ለፍላጎታችን ሳናስገዛና ለስሜታችን
እንዲያደላ ሳናደርግ እንደ እውነተኛ ዳኛ አድርገን በፊታችን ያለውን ጉዳይ ከእግዚአብሔር ፈቃድ
አንጻር እንመዝንበት፡፡ ጉዳዩ በሕሊናችን ሚዛን የማይደፋ ሆኖ ከታየን ወይም ደግሞ ሕሊናችን
ዕረፍት ካጣ፣ ከተረበሸ ... በዚያ ጉዳይ ወይም ድርጊት ላይ ጥያቄ ምልክት አለ ማለት ሊሆን
ይችላል፡፡ ሆኖም የራስን ስሜትና ሐሳብ ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ማደባለቅ አይገባም፡፡
አንድ ሐሳብ ደጋግሞ በሕሊናችን ስለተመላለሰ ብቻ እውነትና የእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሊመስል
ስለሚችል ከሥጋ ስሜትና ፍላጎት የመነጨ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ጊዜ
መስጠት ወሳኝ ነው፡፡ ከሥጋና ከደም የሆነ ነገር ጊዜ ሲያልፍ እየጠፋና እየደበዘዘ ሲመጣ
ከእግዚአብሔር የሆነ ነገር ደግሞ እየጎላና እየጠነከረ ይሄዳል፡፡
እግዚአብሔርን በትዕግሥትና በትሕትና ሆኖ መጠበቅ
8|Page
እግዚአብሔር ፈቃዱን ለእኛ የሚገልጥበትን ጊዜና ሁኔታ (መንገድ)እርሱ በሚወድደውና
በሚፈቅደው መንገድ እንዲያደርገው ለእርሱ ልንተውለት ይገባል እንጂ እኛ መወሰንና መምረጥ
የለብንም፡፡ እኛ እንዲህ ቢሆን የምንለው መንገድ መኖሩ ስሕተት ነው ማለት ሳይሆን፤ የግድ
በዚያ መንገድ ካልሆነ ማለት ግን ተገቢ አለመሆኑን መዘንጋት አይገባም፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ
የሚገልጥልን ሕሊናችንና ዐቅማችን ያን ለመቀበል ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሕልም
ወይም በራእይ ወይም እንዲህ ባለ ሁኔታ ፈቃድህን ግለጥልኝ ብሎ አስቀድሞ መወሰን አይገባም፡፡
በምን ዓይነት መንገድ ቢገልጥልን እንደሚጠቅመን እርሱ ስለሚያውቅ ለእርሱ ልንተውለት
ይገባል፡፡
ሕልምና ራእይም አስተማማኝ መንገዶች አይደሉም፡፡ ይልቁንም እነዚህ ነገሮች ሰይጣን ብዙዎችን
በምትሐት ያሳሳተባቸውና ወደ ጥፋት ጎዳና የመራባቸው ነገሮች ናቸው፡፡ አብርሃም አባታችንን
ባለጠጋው ለራሱ የለመነው ልመና እንደማይሆንለት ካወቀ በኋላ ገና በሕይወተ ሥጋ ያሉትን
ወገኖቹን ያስተምራቸው ዘንድ አልዓዛር ከሞት ተነሥቶ ሄዶ እንዲያስተምራቸው በጠየቀ ጊዜ
አብርሃም መልሶ “ሙሴና ነቢያት አሏቸው እነርሱን ይስሙ” አለው፡፡ ባለጠጋውም መልሶ
“አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ” ባለው ጊዜ፤
አብርሃም እንደ ገና “ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ
አያምኑም” ያለው ለዚህም ነበር፡፡ /ሉቃ ፲=፮ ፳=፯-፴=፩/ “ከሞት ተነሥቼ መጣሁ፣ በራእይ ታዘዝሁ፣
ሕልም አለምሁ ... ” እያሉ ለሚያሳስቱ ለርኩሳን መናፍስት መሣሪያዎችና ተንኮሎች መግቢያ በር
እንዳይከፈትላቸው ለማድረግ ነው፡፡ እናደርገው ዘንድ የሚያስፈልገን የእግዚአብሔር ፈቃድ
በቅዱሳት መጻሕፍት በጥቁርና በነጭ የተጻፈልን ስለሆነ ሌላ መገለጥና ከሙታን የተነሣ ሰው
መምህርነት አያስፈልገንም፡፡
ለነገሮች ጊዜ መስጠት አጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ በጊዜ ሒደት ውስጥ የእግዚአብሔር ፈቃድ
የሆነውንና ያልሆነውን ፍንትው አድርጎ መለየት ይቻላል፡፡ አንድ ጉዳይ የሚያስጨንቀን ወይም
ፈቃደ እግዚአብሔር መሆን አለመሆኑ ግራ አጋብቶን ሊሆን ይችላል ፡፡በዚህ ሁኔታ ላይ ስንሆን
ከስሜታዊነትና ወደፊት በጊዜ የሚገለጠውን ነገር አስቀድመን ማወቅ ካለመቻላችን የተነሣ
እንጨነቃለን፡፡ እየቆየ ሲሄድ ግን አእምሯችን የተሻለ እየተገነዘበው፣ እውነታው ፍንትው ብሎ
9|Page
እየተገለጠ ስለሚሄድ ጉዳዩን በአግባቡ መረዳትና መለየት በእጅጉ ቀላል እየሆነልን ይመጣል፡፡
እንዲሁም እግዚአብሔር ወዲያውኑ እውነቱን ቢነግረን አአምሯችን ሊቀበለው የሚከብደውን ነገር
ቀስበቀስ ሲገልጥልን ለመቀበል የነበረው ክብደት ይቀንሳል፡፡ ውስጣችን እየተረዳውና
እየተገነዘበው ይሔዳል፡፡ በዚህም መጀመሪያውኑ ብናውቀው ሊደርስብን ይችል ከነበረው ድንጋጤና
የሕሊና መታወክ ያድነናል፡፡ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ በሒደት የሚገጥሙንን ነገሮች
በአንድ ጊዜ የማይገልጥልን አንዱ ምክንያት ይኽ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ ባልነው ጊዜ ሳይሆን ለእኛ
በሚጠቅመን ሁኔታና ጊዜ ፈቃዱን እንዲያስታውቀን እግዚአብሔርን በትዕግሥትና በትሕትና ሆኖ
መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡
፫. በፈቃደ እግዚአብሔር ውስጥ የእግዚአብሔርንና የእኛን ድርሻ እንዴት መለየት
እንችላለን?
ይኽን መለየት የሚቻለው እኛ የራሳችንን ድርሻ ከተወጣን በኋላ ነው፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍትና በቤተ
ክርስቲያን ሕይወት በተገለጠው ፈቃዱ መሠረት ሁኔታውና ጊዜው የፈቀደልንን ያህል እስከ
መጨረሻው ድረስ ዓቅማችንን አሟጠን ከተጠቀምንና ማድረግ ያለብንን ካደረግን በኋላ ያ ነገር
ካልሆነ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም ማለት ይቻል ይሆናል፡፡ አለዚያ ግን በአኛ ስንፍና ወይም
ፈቃድ ስላልሆነ ነው” ማለት አግባብ አይደለም፡፡ የእኛን ስሕተትና ስንፍና ሁሉ እንዲሁ
በእግዚአብሔር ላይ ማሳበብም ከታላላቅ ስሕተቶችና ኃጢአቶች ወገን ስለሆነ መጠንቀቅ
ያስፈልጋል፡፡
ልበ አምላክ የተባለ ዳዊት የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመሥራት አጥብቆ ተመኘ፡፡
በጸሎትም፣ በቁሳዊ ዝግጅትም የሚቻለውን ሁሉ አደረገ፡፡ በመጨረሻ ግን ቤተ መቅደሱን
የሚሠራው እርሱ ሳይሆን ልጁ ሰሎሞን እንደ ሆነ ተነገረው፡፡ በነቢዩ በናታን አማካይነት
ፈቃደ እግዚአብሔር ከነምክንያቱ
10 | P a g e
እንዲህ ተብሎ ተነገረው - “... የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ እጅግ ደም
አፍስሰሃል ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፣ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት
አትሠራም፡፡''
ዘጌዴዎን - ኃይልን ሰጥቶ ድል ማድረግ የእግዚአብሔር ነው፣ ሠይፍ ታጥቆ መዝመት ደግሞ
የጌዴዎን ድርሻ ነው” አለ፡፡ /መሣ ፯፥፳/ እንዳለውም ብዙ ዘመን ባስጨነቋቸው በምድያማውያን
ላይ እግዚአብሔር ድልን ሰጣቸው፡፡ የራሳችንን ድርሻ ባለመወጣታችን ምክንያት ሳይሆን
የሚቀረውን ነገር ሁሉ “አይ፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይሆን ነው'' እያሉ በእግዚአብሔር ላይ
ማሳበብ ድርብ በደል ነውና ማስተዋልና መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
ታላቁ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ወገኖቹን ከግብጻውያን ጭቆናና መከራ ነጻ ለማውጣት
ምኞቱና ጉጉቱ ከልጅነቱ ጀምሮ በውስጡ ይመላለስ ነበር፡፡ ሆኖም ግን አርባ ዓመት ሲሆነው
ወገኖቹን ሊጎበኝ በወጣ ጊዜ በግብጻዊው ሲገፋና ሲበደል ላየው ለዕብራዊው በማበር ያደረገው
ድርጊት ግን የተሳሳተ አካሄድ ነበር፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ፈቃድና አሠራር እንዲማርና
ለዚያም ዝግጁ እስኪሆን ድረስ ለአርባ ዓመታት ያህል ወደ ምድያም በረሐ በስደት እንዲሄድ
አደረው፡፡ ጊዜው
11 | P a g e
ሲደርስ እግዚአብሔር ሕዝቡን በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚያወጣቸው ገለጠለት፤ የሙሴ ምኞትም
ተፈጸመ፡፡ ከውስጣችን ጥልቅ ፍላጎትና ውሳኔ ሳይኖር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማየትና መለየት
አንችልም፡፡ ይኽ ካለ ግን ምናልባት እንደ ሙሴ ከአካሄዳችን የተሳሳተውንና መስተካከል ያለበትን
ያርመዋል እንጂ ፈቃዱን ከማድረግ አይከለክለንም፤ ወይም ደግሞ እንደ ዳዊት በግልጥ
ያስታውቀናል እንጂ እንዲሁ በብዥታ ውስጥ ወዲያና ወዲህ እየዋዠቅን እንድንኖር
አይተወንም፡፡
የሚሆነውን ሲሆን ተግባራዊ ፈቃዱ (Subsequent Will) የሚባለው ደግሞ ከእኛ የተነሣ
የሚሆነውን ነው፡፡ ፍጥረቱን እግዚአሔር ሲፈጥረው ያዘጋጀለት ነገር በእርሱ በቅድምና የታሰበ
(የተዘጋጀ፣ የተፈቀደ) ነው ተብሎ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ነገር ግን ያ ፍጥረት በራሱ ውድቀት
ምክንያት ከዚያ እግዚአብሔር ካዘጋጀለት ፍጻሜና ግብ ሳይደርስ ከቀረ ይህ የመጀመሪያው
እግዚአብሔር ለዚያ ፍጥረት ያዘጋጀለት ፍጻሜ ባይሆንም ከመሆን ግን በግድ አያስቀረውም፡፡
ተግባራዊ ፈቃዱ የሚባለው ይኸኛው ነው፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ የፈጠረው
በደስታና በመልካም ሁኔታ እንዲኖር ነው፡፡ እንዲሁም ከወደቀ በኋላም ስው በሥጋዌው
የሚድንበትን መንገድ ሁሉ አዘጋጅቶለታል፡፡ ይኽ ቀዳማዊ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ነገር ግን
አንዳንዶች ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወትና ወደ ድኅነት ከሚወስዳቸው መንገድና ድርጊት በተቃራኒ
ስለሚጓዙና ስለሚያደርጉ እንዲያ በማድረጋቸው ምክን
12 | P a g e
ምርጫቸው ከሚያስከትለው ነገር አይከለክላቸውም፡፡ ይኽም ሆኖ የእግዚአብሔር ፈቃድ
ከመፈጸም አይስተጓጎልም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉትም በራሳቸው ፈቃድና ምርጫ እንደማይድኑ
መለኮታዊ እውቀቱ ጥንቱንም ያውቀዋልና ያ እውቀቱ ነው የሚፈጸመው፡፡ እግዚአብሔር
ሁሉንም ነገር ከጥንቱ (ከጊዜ እሳቤ ውጭ በሆነ ዘለዓለማዊነቱ) ያውቀዋል፡፡ ነጻ ፈቃድ ያላቸውን
ፍጥረታት ምርጫና ውሳኔ ግን አስቀድሞ አይወስንም፡፡
እግዚአብሔር ከሰውና ከመላእክት ውጭ ባሉት ፍጥረታት ላይ ፈቃዱ ያለ አንዳች ማወላወል
ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል፡፡ መላእክትንና ሰውን በተመለከተ ግን ነጻ ፈቃድ ስላላቸው እነዚህ
ፍጥረታት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ተቃራኒ የሆነ ነገር የማድረግ ነጻነት አላቸው፡፡ ተፈትነው
ባለፉት በቅዱሳን መላእክት ዘንድም ፈቃዱ ያለ አንዳች መዛነፍ ይፈጸማል፡፡ “ፈቃድህ በሰማይ
እንደ ሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን” ብላችሁ ጸልዩ ያለንም ለዚህ ነው፡፡ በሰማውያን መላእክት
ዘንድ ፈቃዱ ያለ አንዳች መሰናክልና ተቃውሞ ይፈጸማል፣ ይገለጣልና። በዓለመ መላእክት ዘንድ
ሳጥናኤል በራሱ ፈቃድ ተነሳሥቶ ባደረገው ዓመጽና ክሀደት ከእግዚአብሔር ክብር ተለይቶ፣
ብርሃናዊነቱን አጥቶ፣ ከጸጋና ከቅድስና ተራቁቶ፣ የወደቀ ውዱቅና ጽልመታዊ ሆኗል፡፡ ይህ
የእግዚአብሔር ፈቃዱ አልነበረም፡፡ ማለትም እግዚአብሔር ሳጥናኤልን ሲፈጥረው እንደ ሌሎቹ
መላክእት በክብርና በቅድስና እንዲኖር ነበር እንጂ ራሱ መርጦ እንደ ሆነው እንዲሆን አልነበረም፡፡
ሆኖም ግን እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ስለሆነ ሳጥናኤል የመረጠውን ዲያብሎስ የመሆን
ምርጫ አልከለከለውም፡፡
በሰውም እንዲሁ ነው፡፡ ሰውን በአርአያውና በምሳሌው የፈጠረው የክብሩ ወራሾች የቅድስናው
ተሳታፊዎች እንድንሆን ነው፡፡ ሆኖም ግን ሰዎች እንደየ ፍላጎታቸውና እንደየ ውሳኔያቸው
እግዚአብሔርን መተውና ከእርሱ መለየት፣ ሌላ የፈለጉትን መምረጥና መሆን ይችላሉ፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ያለው የሰው ውሳኔና ምርጫ እንዲሆን ቀዳማዊ ፈቃዱ አይደለም፡፡ ነገር
ግን እርሱ ስላልፈለገው ብቻ ሰውን አስገድዶ ወይም አእምሮውን ጠምዝዞ እንዳይሆን
አይከለከልውም፡፡ እግዚአብሔር ነጻነትን ሲሰጥ ያለ መሸራረፍ ሙሉውን ነውና፡፡ ከዚህም የተነሣ
መሆናቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆኑ፣ ነገር ግን በሰዎች የነጻነት ምርጫ አላግባብ መጠቀም
13 | P a g e
ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሞልተዋልም፡፡ ለአብነትም እግዚአብሔር እንዲሆን የሚያዝዘው
ነገር ሌላ፧ የተነገራቸው ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ደግሞ ከፈቃደ እግዚአብሔር ተቃራኒ እንደሆነ
የሚያሳዩን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፡፡ እንደሚከተለው እንመለከተቸዋልን፡፡
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥
ዶሮ ጫጨቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ
ወደድሁ! አልወደዳችሁምም፡፡ እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል፡፡ እላችኋለሁና፥
፳=፫ ፴=፯-፴=፱/
አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና:: ዓለም በልጁ እንዲድን ነው
እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና፡፡ በእርሱ በሚያምን
አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን
ተፈርዶበታል፡፡ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን
ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው፡፡” / ዮ ሐ ፫ ፥፲፮= -፲=፱/
“ኑና አንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፣ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ
ትነጻለች እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች፡፡ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥
የምድርን በረከት ትበላላችሁ፣ እምቢ ብትሉ ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፣የእግዚአብሔር
14 | P a g e
“አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ቤት፡- እናንተ በደላችንና ኃጢአታችን በላያችን አሉ
አሽዋ፣ በውሃ ጥም፣ በእባብና በጊንጥ፣ ... እንዲሰቃዩ አደረጋቸው። ከዚያም ከግብጽ ከወጡት
ሕዝብ መካከል ከሁለቱ ከኢያሱና ከካሌብ፤ በስተቀር ሙሴና አሮንም ጭምር አንዳቸውም ምድረ
ርስትን ሳያዩ በበረሓ ወድቀው እንዲቀሩ አደረጋቸው። ይኽን ሁሉ ያደረገው የእግዚአብሔር ፈቃድ
ሳይሆን የራሳቸው ጠማማ ልብና አካሄድ ነበር።
15 | P a g e
ያን ጊዜ የነበሩት እሥራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ በየዘመኑ የነበሩና የሚኖሩ የሰው ልጆች ብዙዎቹ
ፈቃደ እግዚአብሔርን በተለያየ መንገድ ተቃውመዋል። እግዚአብሔር ባዘጋጀው የዕረፍት ውኃና
የለምለም መስክ ሳይሆን መከራና ቃጠሎ በበዛበት ሕይወት የዳከሩና የኳተኑ ብዙዎች ነበሩ፣ ዛሬም
አለን። ሰው ፈቃደ እግዚአብሔርን በተለያየ ሁኔታ ይቃወማል። አንዳንዱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ
በግልጽ በይፋ ይቃወማል። ቅዱስ እስጢፋኖስ አይሁድን “እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና
ጆሯችሁም ያልተገረዘ ፥እናንተ ሁል ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ
ተቃወሙት እናንተ ደግሞ” በማለት እንደ ተናገራቸው። /የሐዋ፯፥፶=፩/ ሌላው ደግሞ በግልጽ
ባይቃወምም እንደ ፈቃዱ የሆነ ምንም ነገር ባለማድረግ፣ ፈቃዱን ባለመፈጸም ይቃወማል።
“አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ
ባለማመን ስላደረ ግሁት ምሕረትን አገኘሁ” እንዳለ፡፡ /፩ጢሞ.፩፥ ፲=፫/ በእነዚህ ብቻ ሳይሆን ሰው
ፈቃደ እግዚአብሔርን የራሱን መንገድና ፈቃድ በመከተልም ይቃወማል፡፡ አይሁድን ከእግዚአብሔር
የለያቸውና በኢየሱስ ክርስቶስ ከተገኘው ጸጋ ሁሉ ያራቃቸው እግዚአብሔር በአምላካዊ ፈቃዱ
ባጋጀውና በሰጠው መንገድ ሳይሆን ራሳቸው የጽድቅ መንገድ ብለው ባዘጋጁት በመሄዳቸው ነበር፡፡
ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም” ተብሎ እንደ
ተነገረ፡፡ /ሮሜ.፲፥፩-፫
16 | P a g e
ዋናውና መሠረታዊው የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰው ሁሉ መዳንና ዘለዓለማዊ የሆነውን ሕይወት
ማግኘት ነው፡፡ “ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር
በድፍረት ተነሥተን “አይ እግዚአብሔር፣ ለምን እንዲህ ያደርጋል? ወይም ለምን እንዲህ
17 | P a g e
ይህን ያመለክታል። /ኢሳ. ፵=፭ ፥፯/ ይኽም ማለት እግዚአብሔር ክፋትን የሚፈጥር አምላክ ሆኖ
ሳይሆን በኃጢአታቸው ምክንያት የሚያመጣባቸውን አባታዊ ተግሣጽ እነርሱ እንደ ክፉ ነገር አድርገው
ይመለክቱት ስለ ነበር በዚያ በእነርሱ አረዳድ መንገድ ለመግለጽ ነው። ስለሆነም ድርጊቱ ለእኛ ስለ
ጎረበጠን ወይም እኛ እንዳሰብነውና እንደምንፈልገው ስላልሆነ ብቻ፣ በዚያውም ላይ እንደ ፈቃዱ
ሳንሄድ የሚደርስብንንና በዓለሙ ላይ የሚሆነውን ነገር በማየት ካለማወቅና ካለማስተዋል የመነጨ
አስተያየትና ትንታኔ መስጠት አግባብ አይደለም፤ ከባድ ድፍረትና ጽርፈትም ነው። እግዚአብሔር
ሰዎች ከክፋታቸው የተነሣ የሚደርጓቸውን ነገሮች ከአምላካዊ ድንቅና ረቂቅ ጥበቡ የተነሣ የራሱን
ሥራ ለመሥራትና ሐሳቡን ዳር ለማድረስ ሊጠቀምባቸው ይችላል። ሆኖም እንዲያ ሲያደርግ እርሱ
ከክፉዎቹ ከክፋታቸው አይሳተፍም። ክፋትን እንዲያደርጉም ምክንያታቸው እርሱ አይደለም። ክፉውን
የሚያደርጉት(ያደረጉት) ሰዎችም በዚህ ምክንያት ከክፉ አድራጊነትና ከተጠያቂነት ነጻ ሊሆኑ
አይችሉም፡፡
ይኽን ሐሳብ በምሳሌ ማየቱ የበለጠ ይረዳ ይሆናል፡፡ እሥራኤል የተባለ ያዕቆብ ብኩርናን ማግኘቱ
የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፡፡ ምክንያቱም ዔሣው ምድራዊና ቁሳዊ ሀብትንና ተድላ ደስታን እንጂ
መንፈሳዊ በረከትን የሚሻ ሰው አልነበረምና በረከቱ ይኽን ሲሻ ለነበረው ለያዕቆብ መሆኑ ፈቃደ
እግዚአብሔር ነበር፡፡ ሆኖም ግን ያዕቆብ በረከትን የወሰደበት የማታለል መንገድ ግን እግዚአብሔር
ዘንድ የተወደደ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ምን ጊዜም ሐስትንና ተንኮልን ይጸየፋልና፡፡ ሆኖም በእናቱ
በርብቃ ምክርና በያዕቆብ ፈጻሚነት በተንኮልም ቢሆን በረከቱ ከዔሣው ቀርቶ ለያዕቆብ እንዲሆን
ሆነ፡፡ እግዚአብሔር ይኽን ዓላማውን በያዕቆብ አካሄድም ቢሆን ፈጽሟል፡፡
ሆኖም ግን ያዕቆብ በረከትን ለማግኘት የሄደበት የማታለል አካሄድ ስሕተት ስለ ነበረ እግዚአብሔር
ያዕቆብን በዚያው ባታለለበት መንገድ እንዲታለል አሳልፎ ስጥቶታል፡፡ ከዚህም የተነሣ ያዕቆብን
የራሱ ልጆች ዮሴፍን ሽጠው ልብሱን ገፍፈው የአውራ ፍየል ደም ነክረው “ይህን አገኘን፣ ይህ
የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው'' አሉት። እርሱም “የልጄ ቀሚስ ነው፣ ክፉ
ውሬ በልቶታል፣ ዮሴፍ በርግጥ ተበጫጭቋል አለ:: ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ በወገቡም ማቅ ታጥቆ
18 | P a g e
ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ::'' /ዘፍ ፴=፯፥፴=፩-፴=፬/ ያዕቆብ ወንድሙን በልብስ እንዳታለለውና
እንዳስለቀሰው እርሱን ደግሞ የራሱ ልጆች በዚያው መንገድ አታለሉት፣ አስለቀሱት:: ከዚያም ራሔልን
አገባለሁ ብሎ ሰባት ዓመት ከተገዛ በኋላ አባቷ ላባ ሌሊት እኅቷን ልያን በመስጠት አታለለው፤
ራሔልን ለማግኘት ሲል እንደገና ሌላ ሰባት ዓመት ተገዛ፡፡ እንዲሁም አጎቱ ላባ ደመወዙን ብዙ ጊዜ
እየለዋወጠ ሲያታልለው ኖረ፡፡
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍን መሸጣቸው እነርሱ በዚያው ይጠፋል፣ የነገረን ሕልም በእኛ ላይ
ከመፈጸም ይቀራል፣ እኛም ይነግሥብናል ከሚል ስጋት ነጻ እንሆናለን ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን ያ
የፈሩትን ነገር ያስቀርልናል ብለው ያደረጉት ድርጊታቸው በተቃራኒው ዮሴፍን በሕልም ያየው ነገር
ወደሚፈጸምበት አገርና ሁኔታ እንዲሄድ መንገድ ከፋችና መሰላል ሆነው፡፡ ኋላም በረኃብ ምክንያት
ግብጽ ሲሄዱ ወንድማቸው ዮሴፍ በግብጽ ላይ ነግሦ አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ አገኙት፣ ሰገዱለት፡፡
እግዚአብሔር የወንድሞቹን ክፉ ሐሳብና ድርጊት ያዘጋጀውን ሐሳብ ለመፈጸም መጋቢ(አገልጋይ)
አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ ሆኖም በእነርሱ ክፋት ውስጥ ፈጽሞ የለም፣ ይኽ ከእርሱ ይራቅ፡፡ የዮሴፍ
ወንድሞችም ወንድማቸውን የመሸጣቸው ክፋትና ወንጀል በዚህ ምክንያት (ዮሴፍን
አለቆች በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብጽ ሸጡት'' በማለት በደለኛነታቸውን የገለጸው ለዚህ ነው፡፡/
የሐዋ፯፥፱/
እነዚሁ ወንድሞቹ አባታቸው ያዕቆብ ከሞተ በኋላ “ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል
19 | P a g e
ይላል፦ “ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው እነሆ እኛ
ለእንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት። ዮሴፍም አላቸው ፦ አትፍሩ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን? እናንተ
ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
20 | P a g e