You are on page 1of 22

አቦጊዳ ሪከቨሪ ቡድን

Zoom Meetings Sat & Sun 6 pm Ethiopian Time

Meeting ID: 81479756061

Passcode: 445355

https://www.facebook.com/groups/44610726693439
የአልኮሆሊክስ አኖኒመስ 12 ደረጃዎች
1. አልኮልን በተመለከተ አቅመ ቢስ መሆናችንን፣ ሕይወታችንንም ለመቆጣጠር የተቸገርን መሆኑን አምነን ተቀበልን።

2. ከእኛ በላይ የሆነው ኃይል የአእምሮ ጤንነታችንን መልሶ ሊሰጠን እንደሚችል አመንን።

3. ፈጣሪን እኛ በተረዳነው መጠን እንዲንከባከበን፣ ፈቃዳችንና ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለመስጠት ወሰንን።

4. ያለምንም ፍርሃት በራሳችን ላይ የሥነ ምግባር ፍተሻ አደረግን።

5. ለፈጣሪ፣ ለራሳችንና ለሌሎችም ሰዎች ያደረግነውን ጥፋት ሁሉ በትክክል ተናዘዝን።

6. ፈጣሪ እነዚህን ብልሹ ባሕሪዎቻችንን ያስወግድልን ዘንድ ፍጹም ዝግጁ ሆንን።

7. በደላችንን ሁሉ ይቅር እንዲለን ፈጣሪን በተሰበረ ልብ ለመነው።

8. የበደልናቸውን ሰዎች በማሰብ ዝርዝራቸውን ይዘን ይቅርታ በመጠየቅ ከእነሱ ጋር የነበረንን ግንኙነት ለማደስ

ተዘጋጀን።

9. ይህንን ስናደርግ የበለጠ የምንበድላቸው መስሎ እስካልታየን ድረስ በሚቻለን ሁሉ የበደልናቸውን ሰዎች እየፈለግን

ታረቅን።

10. ዕለት ዕለት ራሳችንን እየመረመርን ንሰሐ ገባን፣ ጥፋት እንዳጠፋንም ጥፋታችንን አምነን ወዲያውኑ ተቀበልን።

11. በተረዳነው መጠን ከፈጣሪ ጋር ያለንን ግንኙነት የተሻለ ለማድረግ፣ በእኛ ላይ ስላለው በጎ ፈቃድና ይህንንም

ለመፈፀም ስለሚያሻን ኃይል ለመለመን በፀሎትና በተመስጦ አዘወትረን ተጋን።

12. እነኚህን እርምጃዎች ከወሰድን በኃላ የደረስንበትን መንፈሳዊ ንቃት ከተላበስን በኋላ እኛ ያገኘነውን መልዕክት

ለአልኮል ሱሰኞች የማድረስና እንዲሁም ከላይ የዘረዘርናቸው ሁሉ በሕይወት ጉዞአችን መርሕ በማድረግ

ልንለማመዳቸው ወሰንን።

1
1ኛ ደረጃ
“አልኮልን በተመለከተ አቅመ ቢስ መሆናችንን፣ ሕይወታችንንም ለመቆጣጠር የተቸገርን መሆኑን አምነን ተቀበልን።”

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የሚጠጡበት ዋናው ምክንያት አልኮል የሚፈጥርባቸውን ስሜት ስለሚወዱት ነው። ይህ ስሜት
የማይጨበጥ ከመሆኑ የተነሳ የሚጐዳ መሆኑን ቢያምኑም፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እውነቱን ከሐሰት መለየት ይሳናቸዋል።
ለእነርሱ የመጠጥ ሕይወታቸው ብቸኛው መደበኛ ኑሮ መስሎ ይታያቸውል። ታዲያ እነሱም ሌሎች ጉዳትና ቅጣት
ሳይደርስባቸው ሲጠጡ የሚያዩትን፣ ሦስት አራት መለኪያ ጨልጠው ወዲያው የመዝናናትና የምቾት ስሜት እስካላገኙ ድረስ
ቁንጥንጥ፣ ግልፍተኛና ርካታ የለሽ ናቸው። ከዚያም ያው ብዙዎቹ እንደሚያደርጉት እጃቸውን ለመጠጥ አምሮት ዳግም ከሰጡ
በኋላ፣ ለመጠጥ መጓጓታቸው ይዳብራል፤ ተለይተው ከታወቁት የስካር ፈንጠዝያ ደረጃዎች ያልፋሉ። ከዚያም ከስካር
ማግሥት ፀፀትና ቅሬታ ሲሰማቸው ደግመው ወደ መጠጥ ላለመመለስ ይወስናሉ። ስካርና ፀፀት መፈራረቃቸውን ይቀጥላሉ፤
እናም ጠጪው ሙሉ የሥነ ልቦና ለውጥ ማምጣት ካልቻለ የማገገሙ ተስፋ የመነመነ ይሆናል።
በመጠጥ ሱስ ያልተያዙ ጠጪዎች በቂ ምከንያት ካላቸው መጠጥን ሙሉ በሙሉ ለመተው አይቸገሩም። እርግፍ
አድርገው ሊተዉት ወይም በዚያው ሊቀጥሉ ይቸላሉ። ታዲያ በሌላ በኩል አዘውትሮ የሚጠጣ፣ የሚያበዛው ሰው አለ።
ይህም ሰው መጠጣትን ልማዱ አድርጎ ስለወሰደው ቀስ በቀስ የአካልና የአእምሮ ጉዳት ይደርስበታል። ከእድሜው ዳርቻ
ጥቂት ዓመታት አስቀድሞም ሊገለው ይችላል። ግን ደግሞ የጤና መታወክ፣ በፍቅር መውደቅ፣ የአካባቢ ለውጥ፣ አልያም
የሐኪም ማስጠንቀቂያን የመሳሰሉ ጠንካራና በቂ ምክንያቶች ካጋጠሙት ይህ ሰው መጠጣቱን ሊተው ወይም ሊቀንስ
ይችላል። እዚህ ላይ ግን መተው ወይም መቀነሱ ከባድና የሚያስጨንቅ ሊሆንበት ይችላል፣ ምናልባትም የሐኪም እርዳታ
እንዲጠይቅ ያደርገዋል። የለየለት የአልኮል ሱሰኛውስ? መነሻው ላይ መጠነኛ ጠጪ ሆኖ ሊጀምር ይችላል፣ በቀጣይም ኃይለኛ
ጠጪ ሊሆንም፣ ላይሆንም ይችላል። ሆኖም ግን በተያያዘው የመጠጣት ሂደት ውስጥ አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ መጠጣት
ከጀመረ በኋላ የሚጠጣውን የመጠጥ መጠን የመቆጣጠር አቅሙን እያጣ ይሄዳል።
እንደ እውነቱ ከሆነ አብዛኞቹ የአልኮል ሱሰኞች ግልጽ ባልሆነ ምክንያት መጠጥን በተመለከተ የምርጫ ኃይላቸውን
አጥተዋል። የፈቃደኝነት ኃይላችን የምንለው በተጨባጭ እንዳልነበር ይሆናል። በአንዳንድ ወቅቶች ከአንድ ሳምንት ወይም
ከአንድ ወር በፊት እንኳ የደረሰውን ስቃይና ውርደት ማስታወስ ይሳነናል። የመጀመሪያውን መለኪያ መጠጥ ለመከላከልም
አቅም የለንም። አብዛኞቻችን የአልኮል ሱሰኞች የነበርን መሆናችንን ለማመን ፈቃደኞች አልነበርንም። ማንም ቢሆን በአካልና
በአእምሮ ከመሰሎቼ እለያለሁ ብሎ ማሰቡን አይወደውም። ስለሆነም መጠጣትን እንደ ሙያ ይዘነው በነበሩባቸው ዘመናት
እንደሌሎች ሰዎች መጠጣት እንደምንችል ለማሣየት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ያልተሳኩ ሙከራዎች ማድረጋችን አያሰደንቅም።
ማንኛውም ከመጠን ያለፈ ጠጪ እንደምንም ብሎ አንድ ቀን መጠጡን እንደሚቆጣጠረውና መዝናኛ ሊያደርገው
እንደሚችል ሁሌም ከማሰብ አልፎ የሚያሰላስለው ዋና ጉዳይ ነው። የዚህ የማይለቅ ራስን የማታለል ሀሳብ ከአስገራሚነቱም
አልፎ ብዙዎች ራሳቸውን እንዲስቱ ያደረገ አልያም ለሞት የዳረገ ነው።
የአልኮል ሱሰኞች የሆንን ወንዶችና ሴቶች መጠጥን የመቋቋም አቅም ያጣን ነን። የወጣለት የአልኮል ሱሰኛ መቼም
መች ቢሆን የመቆጣጠር አቅሙን መልሶ እንደማያገኝ እናውቃለን። ይህም ሆኖ ሁላችንም አልፎ አልፎ ራሳችንን የመቆጣጠር
አቅም ያገኘን ያህል ይሰማናል። ይሁን እንጂ ስሜቱ ሄድ መለስ የሚል፣ ለረጅም ጊዜም የማይቆይ ነው። ግን ደግሞ
በተጨባጭ የመቋቋም አቅምን የሚያዳክም አልፎም ለአሳዛኝና ለማይቋቋሙት የሞራል ውድቀት የሚዳርግ ነው። እኛን
የመሰሉ የአልኮል ሱሰኞች እየበረታ በሚሄድ ሕመም የተያዝን መሆናችንን አምነናል። ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ ደግሞ ይብስብናል

2
እንጂ አይሻለንም ። መጠጥ ለማቆም በእርግጥ ፈልገው እያሉ ግን ሙሉ በሙሉ መተው ካዳገተዎ፣ ወይም እየጠጡ እያሉ የሚጠጡትን
መጠን መቆጣጠር ከተሳነዎ፣ ምናልባት እርስዎ የአልኮል ሱሰኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ጉዳዩ እንደዚህ ከሆነ ደግሞ በመንፈሳዊ ተሞከሮ ብቻ
ሊፈወስ በሚችል ሕመም የሚሰቃዩ ነዎት ለማለት ይቻላል። የእያንዳንዳችን ባሕሪይ የተለያየ በመሆኑ ያቀረብነው የአልኮል ሱሰኛ
ገጽታ፣ ሁሉንም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አይደለም። ሆኖም ግን አገላለጹ በደፈናው የአልኮል ሱሰኛን ገጽታ የሚጠቁም ነው።
የተማርነው ዋና ነገር የአልኮል ሱሰኞች የነበርን መሆናችንን ለውስጥ እኛነታችን ሙሉ በሙሉ ማሳመን ያለብን መሆኑን ነው። ይህም
ለማገገም የመጀመሪያው እርምጃ ነው። እንደሌሎች ሰዎች ነን ወይም እንሆናለን እያልን ራሳችንን መደለሉን እርግፍ አድርገን መተው
አለብን። (አአ ገጽ 30)

1ኛ ደረጃ የሥራ ሉህ
አልኮልን በተመለከተ አቅመ ቢስ መሆናችንን፣
1. መጠጥ መጠጣት ለማቆም ሞክራችሁ ነበር? ውጤቱ እንዴት ነበር?
2. የምትጠጡትን መጠን ለመቆጣጠር ሞክራችሁ ነበር? ውጤቱ እንዴት ነበር? ለምሳሌ፥ ዛሬ ሁለት ብቻ ነው የምጠጣው
ብላችሁ፣ ስትጠጡ ማደር።
3. አንዴ መጠጣት ከጀመራችሁ መሀል ላይ ማቆም ትችላላችሁ? ለምሳሌ፥ የሦተኛውን ጠላ ግማሹን ትታችሁ መሔድ።
4. ጠጥታችሁ አድራችሁ ጠዋት ስትነሱ ከበፊቱ ምሽት ምንእንደሆነ የማታስተዉሱት ጊዜ ነበር?
ሕይወታችንንም ለመቆጣጠር የተቸገርን መሆኑን አምነን ተቀበልን።
1. ሕይወታችን ውስጥ ምን ለውጦች ናቸው ወደ አአ ያመጡን?
2. መጠጥ ስንጠጣ ምንድነው የምናደርገው እኛም ሌሎቾም የማንቀበሉት?
3. መጠጥ በመጠጣታችን ማድረግ የተሳኑን ነገሮች ምንድን ናቸው?
ማጠቃለያ ሐሳቦች
1. ምንድነው ያሳመናችሁ ከዚህ በኃላ መጠጥ ወይም ድራግን ያለችግር መውሰድ እንደማትችሉ?
2. ምክንያቶቻችሁ ምንድንናቸው በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ለመቀጠል?

2ኛ ደረጃ
ከእኛ በላይ የሆነው ኃይል የአእምሮ ጤንነታችንን መልሶ ሊሰጠን እንደሚችል አመንን።

ለራሳችን አንድ አጭር ጥያቄ ማቀረብ አስፈልጎንም ነበር። ጥያቄው «ከእኔ በላይ የሆነ አንድ ኃይል መኖሩን
አሁን አምናለሁ፣ ካልሆነስ ለማመን እንኳ ፈቃደኛ ነኝን? የሚለው ነው። አንድ ሰው ወዲያው እንደሚያምን መናገር ከቻለ፣
ወይም ደግሞ ለማመን ፈቃደኛ ከሆነውን መንገድ መጀመሩን በቃል አጋኖ እናረጋግጥለታለን። በተደጋጋሚ በመካከላችን
ያረጋገጥነው ነገር ቢኖር በዚች አነስተኛ የመዓዘን ድንጋይ ላይ ተመስርቶ አስደናቂና ወጤታማ የሆነ መንፈሳዊ መዋቅር
መገንባት የሚቻል መሆኑን ነው። መልሣችሁ ከእኔ በላይ የሆነ አንድ ኃይል መኖሩን አሁን አምናለሁ፣ ወይም ደግሞ
ለማመን ፈቃደኛ ነኝ ከሆነ ሁለተኛዉን ደረጃ ጨርሳችሖል።

2ኛ ደረጃ ጥያቄዎች
ጤናማ ያልሆነ አስተሳሰብ (Insanity) - ድርጊቶቻችን ሳንለውጥ የተለየ ውጤት መጠበቅ።

3
1. የአልኮሆሊክስ አኖኒመስ የእንግሊዝኛ መዽሐፍ በሱስ ላይ ሆነን የአእምሮ ጉድለታችንን ጤናማ ያልሆኑ ድርጊቶች
ብሎ ያስረዳቸዋል። ይህንን ድርጊት በምሳሌ ያስረዱ በሱስ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ካደጉት በመነሳት፡፡
2. ትክክል ያልነበሩት ውሳኔዎችዎ በሱስዎ የተነሳ ነው ብለው ያምናሉ?
3. ከእኛ በላይ ያለአንድ ኃይል መኖሩን ማመን ይቸገራሉ?
4. በአሁኑ ሰዓት አዲስ ነገር ለመቀበል ዝግጁ ያልሆነ አእምሮ ካለዎት እንዴት ሊጎዳዎት ይችላል?
5. ግልፅ አስተሳሰብን በፕሮግራሙና በሕይወቶ ዉስጥ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ከሆነ በምን መልኩ ?

3ኛ ደረጃ
ፈጣሪያችን እኛ በተረዳነው መጠን እንዲንከባከበን፣ ፈቃዳችንና ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለመስጠት ወሰንን።

ስለአልኮል ሱሰኞች በሰጠነው መግለጫ፣ ስለ ተጠራጣሪዎች በተጻፈው ምዕራፍና በፊትና በኋላ ላይ ስለነበረው
የግል ጀብዳችን ስናቀርብ ሦስት ዋነኛ ሃሳቦች ግልጽ ሆነዋል። እነሱም፣

ሀ. የአልኮል ሱሰኞች የነበርን መሆኑንና የራሳችንን ኑሮ መምራት አቅቶን እንደነበርን፣

ለ. ከተያዝንበት የአልኮል ሱሰኝነት ሊያድነን የሚችል ምንም ዓይነት የሰው ኃይል ሊኖር አለመቻሉን፣

ሐ. ሊያድነን ከፈለገ፣ ሊያድነን የሚችለውና የሚያደርገው ፈጣሪ መሆኑን የሚሉት ናቸው።

በዚህ ከተስማማን፣ ከሦሥተኛው እርምጃ ላይ ደርሰናል፣ ይህ ማለት ደግሞ ፈጣሪያችን በተረዳነው መጠን
ሕይወታችንንና ፈቃዳችንን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እንክብካቤ አሳልፈን ለመስጠት ወስነናል ማለት ነው። ግን እንዲህ ስንል
ምን ማለታችን ነው? ምንስ አደረግን? ራስ ወዳድነት − ለራስ ብቻ ማሰብ! በእኛ አመለካከት የችግሮቻችን ሁሉ መነሻ ሥር
መሠረት ነው፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ አገላለጾች ባሉት ራስ ወዳድነት፣ ለራስ ብቻ ማዘን፣ ራስን መጠራጠር፣ ለራስ ፍላጎት
መቆም ወዘተ፣ በሚለው ተገፋፍተን ባልደረቦቻችንን ስንጫናቸው፣ እነሱም በተራቸው አጸፋውን ለመመለስ ይገደዳሉ፡፡ በዚህ
ጊዜም ሊጎዱን አስበው በመነሳት ሳይሆን በአጸፋ ምላሻቸው ይጎዱናል፡፡ እናም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የተጎዳንበትን ምክንያት
ወደኋላ መለስ ብለን ስንፈትሽ ራሳችን የፈጠርነው ነገር ለጉዳት እንደዳረገን እንገነዘባለን፡፡
ስለዚህ የችግሮቻችን መንስኤው የእኛው የራሳችን ተግባር ነው፡፡ የችግሮቻችን መንስኤዎች እኛው ራሳችን ነን፡፡
የአልኮል ሱሰኛ ደግሞ፣ ምንም እንኳ እሱ እንደዚያ ባያስብም ለረብሻ መቀስቀስ ምክንያት ይሆናል፡፡ ከዚህ የተነሳም እኛ
የአልኮል ሱሰኞች ከራስ ወዳድነት ነፃ ልንሆን ግድ ይለናል፡፡ ስለሆነም ራስ ወዳድነታችን ሳይገድለን ልንቀድመው ይገባል፡፡
በእርግጥ ራስ ወዳድነትን ለማሸነፍ የፈጣሪ ዕርዳታ ወሳኝ ነው፡፡ የፈጣሪ ዕርዳታ ካልታከለበት በስተቀር ብዙውን ጊዜ ከራስ
ወዳድነት ሙሉ በሙሉ ለመዳን መንገዱ ጠባብ ነው፡፡ ብዙዎቻችን በርካታ የሞራልና የፍልስፍና እምነቶች አሉን፤ ይሁን
እንጂ የፈለግነውን ያህል ብንሞክርም የአመንባቸው ሞራልና ፍልስፍናዎች እንደሚጠይቁን ለመሆንም፣ ለመኖርም አንችልም፡
በሌላ በኩል በራሳችን አቅም፣ ጥረትና ፍላጎት በራሳችን ዙሪያ ብቻ ማተኮራችንን ልንቀንስ አንችልም፡፡ የ ፈጣሪ ዕርዳታ
ሊታከልበት ግድ ይሆናልና፡፡
እንዴትና ለምን የሚለው የጉዳዩ ጭብጥ የሚከተለው ነው፡፡ በመጀመሪያ በፈጣሪ ጉዳይ ላይ መቀለድ ስለማያዋጣ
ቀልዱን አቆምን፡፡ በመቀጠል በሕይወት መድረክ የሚቀርበው ተውኔት፣ የተውኔታችን አዘጋጅ፣ ፈጣሪ መሆን ይገባዋል ብለን
ወሰንን፡፡ እሱ ዋና አዛዥ እኛ ደግሞ ታዛዦቹ፡፡ እሱ አባታችን እኛ ደግሞ ልጆቹ ነን፡፡ ብዙዎች ጥሩ አስተሳሰቦች ቀላልና ቀና

4
ናቸው፡፡ ይህም ሃሳብ፣ ባለድል ሆነን ወደ ነጻነት ለተጓዝንበት መንገድ የመሠረት ድንጋይ ሆነ፡፡ ፈጣሪያችን እኛ በተረዳነው
መጠን እንዲንከባከበን፣ ፈቃዳችንና ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለመስጠት ከወሰንን። የሚቀጥለውን ፀሎት እንፀልይ፥
3ኛ ደረጃ ጸሎት
ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት ይህንን እንዸልይ
«ፈጣሪ ሆይ! አንተ እንደፈቀድክ ታቋቁመኝ፣ በእኔም ላይ ትሠራ ዘንድ ራሴን ለአንተ አቀርባለሁ፡፡ የአንተን ፈቃድ
በተሻለ አኳኋን እፈጽም ዘንድም ከራስ ወዳድነት-ባርነት ነፃ አውጣኝ፡፡ ችግሮቼን ሁሉ አስወግድልኝ በእነሱ ላይ የምቀዳጀው
ድልም በአንተ ኃይል ልረዳቸው ለምፈልግ ምሥክር ይሆነኝ ዘንድ አንተ ፍቅርና የሕይወት መንገድ ነህ፡፡ ሁልጊዜም ፈቃድህን
እፈጽም ዘንድ ዕርዳኝ!´ እንለዋለን፡፡
3ኛ ደረጃ ተስፋዎች
እኛም ልባዊ በሆነ ስሜት በአቋማችን በጸናን ጊዜ በርካታ አስደናቂ ነገሮች እውን ሆኑ፡፡ አዲስ አለቃ አገኘን፡፡ የኃያላን
ኃያል በመሆኑም፣ ወደ እሱ በቀረብን ቁጥርና የሚጠበቅብንንም ምግባር በአግባቡ በአከናወንን መጠን የሚያስፈልገንን ሁሉ
አደረገልን፡፡ በእንዲህ ዓይነት አካሄድ ደረጃችን ከፍ ባለ ቁጥርም በራሳችን ጥቃቅን እቅዶች መመራትና በራስ ወዳድነት
መጠመዳችን እየመነመነ፣ እየቀነሰ ሄደ፡፡ አልፈንም በሕይወት ዘመናችን ልናበረክተው ስለሚገባን መልካም ነገር አብዝተን
ማሰብ ጀመርን፡፡ ውስጣችን በአዲስ ኃይል እየተሞላ መሄዱን ተገነዘብን፣ በአገኘነው የመንፈስ ሰላም ተደሰትን፣ ሕይወትን
ልንቋቋምና ውጤታማ ልንሆን መቻላችንን አወቅን፣ የፈጣሪ ከእኛ ጋር አብሮ መሆን በተረዳን ቁጥር፣ ስለ ዛሬ፣ ስለነገና ከዚያም
በኋላ ስለሚኖረው ሁሉ አድሮብን ከነበረው ፍራቻ ተላቀቅን፡፡ እንደገናም፣ ዳግም ተወለድን፡፡
3ኛ ደረጃ የሥራ ሉህ
ፈጣሪያችን እኛ በተረዳነው መጠን እንዲንከባከበን፣ ፈቃዳችንና ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለመስጠት ወሰንን።

“እምነት ያለ ሥራ የሞተ ነው።” “አስተሳሰባችንን እና ተግባራችንን ለፈጣሪ ለመስጠት ወሰንን።”

1. በአሁን ሰአት በምን ነገሮች ላይነው ጥገኛነታችን? ለምሳሌ በጭለማ ሰአት በመብራት ላይ ጥገኛነን
2. ሕይወታችን ውሥጥ እኛ የምንቆጣጠራቸውና የማንቆጣጠራቸ ነገሮች ምንድንናቸው? ለምሳሌ የምቆጣጠረው
ጠዋት ስነሳ ጥርሴን መፋቅ፣ የማልቆጣጠረው አንዴ መጠጣት ከጀመርኩኝ ምንያህል እንደምጠጣ፣ ፀሐይ በስንት
ሰዐት እንደምትወጣና መቼ እንደምትጠልቅ
3. የእኛፈቃዶች በአሑን ሰአት ምንድን ናቸው? በምሣሌ አስረዱ። ለምሳሌ አስተሳሰቤ መጠጥን በሚመለከት በየጠዋቱ
ለፈጣሪዪ ከመጠጥ እንዲያርቀኝ መፀለይ ነው።
4. ፈቃዳችንን ሙሉ በሙሉ ለፈጣሪ ሰጠን ስንል ምን ማለታችን ነው? በምሣሌ አስረዱ።
5. ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለፈጣሪ ሰጠን ስንል ምን ማለታችን ነው? በምሣሌ አስረዱ
6. ይሄንን ደረጃ በተግባር የምናሳየው እንዴት ነዉ?

5
4ኛ ደረጃ
“ያለምንም ፍርሃት በራሳችን ላይ የሥነ ምግባር ፍተሻ አደረግን።”

ተከታዩ ጠንካራ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድን የሚጠይቅ ይሆናል፡፡ ይህ የመጀመሪያ እርምጃም ማናችንም
ሞክረነው የማናውቀው ግን ቢሆንም አስፈላጊ የሆነ የራስን ቤት ማፅዳት ስራ ነው፡፡ የወሰድነው እርምጃ ጠቃሚ ቢሆንም
እንኳ፣ ገድበው የያዙንን ነገሮች ሁሉ ፊት ለፊት ካልተጋፈጥናቸውና በተጠናከረ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲወገዱ
ካላደረግናቸው፣ የተደረገው ጥረት ሊያስከትል የሚችለው ዘላቂነት ያለው ውጤት ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ መጠጥ ያለብን ችግር
ምልክት ነው፡፡ ስለሆነም ከመጠጥ ጋር እንድንቆራኝ ያደረጉንን ምክንያቶችና ሁኔታዎች ከመሠረቱ መፈለግ ይኖርብናል፡፡
ይህን ስናደርግም የግል ሕይወታችንን በዝርዝር መፈተሽ ጀመርን ማለት ነው፡፡ በየጊዜው የኦዲት ቆጠራ
የማይደረግለት ማንኛውም የቢዝነስ ሥራ ይከስራል፡፡ በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚደረግ የኦዲት ምርመራ፣ ዓላማ
እውነታውን ማግኘትና የተገኘውንም እውነታ መጋፈጥ ነው፡፡ ጥረት የሚደረገውም ስላለው የሸቀጦች ይዞታ እውነታውን
ለማወቅ ነው፡፡ ከዓላማዎቹ አንዱ የተበላሹና የማይሸጡ ሸቀጦችን ለይቶ ለማወቅ፣ ወዲያውኑ ያለምንም ማቅማማትና ቅሬታ
አውጥቶ መጣል ነው፡፡ የንግዱ ባለቤት በደንብ አትራፊ ለመሆን የተነሳ ነጋዴ ከሆነ ስለተበላሸው እቃ ዋጋ መጨነቅ የለበትም፡
እኛም በሕይወታችን ያደረግነው ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ ፍተሻውን ያደረግነው በሀቀኝነት ነበር፡፡ መጀመሪያ ያደረግነው
ለውድቀታችን ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በደንብ መፈተሽ ነበር፡፡ በአጠቃላይ የውድቀታችን ምክንያት በተለያየ መልኩ
የተገለጸው እኔነት (ራስ ወዳድነት) መሆኑን ተረዳን፣ ከዚያም እኔነት በሚገለጥባቸው በተለመዱት ችግሮች ላይ አተኮርን፡፡
ቂምን "ቁጥር አንዱ˝ አጥፊ ሆኖ አገኘነው፡፡ ቂም ከምንም በላይ የመጠጥ ሱሰኞችን ያጠፋል፡፡ ቂም የብዙ መንፈሳዊ
ሕመሞች ምንጭ ነው፡፡ እኛ ደግሞ የአእምሮና የአካል ብቻ ሳይሆን የመንፈሳዊ ሕመም ተጠቂዎች ነበርን፡፡ የመንፈሳዊ ሕመም
ሲፈወስም የአእምሮአዊና የሥጋዊ ሕመማችንም መፍትሔ ያገኛል፡፡ ስለ ቂም ማሰብ በጀመርን ጊዜም፣ ቁጭ ብለን
የተቆጣናቸውን ሰዎች፣ ድርጅቶችንና አልፎም ቅር የተሰኘንባቸውን መርሆች በወረቀት ላይ በዝርዝር አሰፈርን፡፡ ከዚያም
ለምን ተቆጥተን እንደነበር ራሳችንን ጠየቅን፡፡ በአብዛኛው ምክንያት ሆኖ የተገኘው ለራሳችን ያለን ከበሬታ፣ ገንዘባችን፣
ፍላጎታችን፣ እንዲሁም የግል ግንኙነታችን (የጾታ ግንኙነትን) ጨምሮ የተጎዳ ወይም የተነቀፈብን መሰሎን መቆጣታችን ነበር፡
በዚህም ምክንያት "ተቃጥለናል˝፡፡ የያዝናቸውን ቂሞች ስንዘረዝር በየቂሙ ትይዩ የተጎዳው ምናችን መሆኑን አሰፈርን፡፡

ቂም የያዝኩባቸው ምክንያቱ እኔን የጎዳኝ

አቶ አበበ በባለቤቴ ላይ የነበረው ትኩረት የፆታ ግንኙነት፣ ለራስ-ያለ ከበሬታ መነካት(ፍራቻ)


ለባለቤቴ(ለሚስቴ) ስለውሽማዬ መንገሩ የፆታ ግንኙነት፣ ለራስ-ያለ ከበሬታ መነካት(ፍራቻ)
አበበ የቢሮ ሥራዬን ይቀማኝ ይሆናል ዋስትና የማጣት ስጋት፣ ለራስ-ያለ ከበሬታ መነካት(ፍራቻ)

የዩሐንስ ባለቤት እብድ ነች፣ ትንቀኛለች ባለቤቷን የግል ግንኙነት፣ ለራስ-ያለ ከበሬታ መነካት(ፍራቻ)
ለመጠጥ የዳረገችው እርሷ ናት፣
ባለቤቷ ጓደኛዬ ነው፣ ሐሜተኛ ናት

ቀጣሪዬ ምክንያታዊ ባልሆነና ትክክል ባልሆነ ለራስ-ያለን ከበሬታ መንካት(ፍራቻ)፣ ዋስትና የማጣት ስጋት
ነገር በበላይነት ይጫነኛል፣
ስለምትጠጣና ወጪ ስለምታበዛ ለራስ ያለ ክብር መነካት
ከሥራ አባርርሃለሁ በማለት አስፈራራኝ

ባለቤት አንግባባም፣ ትጨቀጭቀኛለች፣ የግል ክብር መነካት


አበበን ትወደዋለች የፆታ ግንኙነት
ቤታችንን በሷ ስም ማዞር ትፈልጋለች የዋስትና ማጣት ፍራቻ

6
የተጎዳው ለራሳችን ያለን ከበሬታ፣ ደህንነታችን(ዋስትናችን)፣ ፍላጎታችን፣ የግል ወይም የፆታ ግንኙነታችን የቱ ነው የሚለውን
ዝርዝሩ ላይ አመለከትን፡፡
ወደ ኋላ መለስ ብለን ሕይወታችንን በጥልቀት ሙሉ በሙሉ መረመርን፡፡ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠነውም በጥልቀትና
በታማኝነት ስለመፈተሻችን ነበር፡፡ ከዚያም በራሳችን ላይ ያገኘነውን ነገር ሁሉ በጥንቃቄ ትኩረት ሰጥተን አጤነው፡፡
በመጀመሪያ የታየን ነገር ይህ ዓለምና ሕዝቡ ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ መሆኑን ነው፡፡ ስህተቱ የሌሎች ነው ለማለት የበቃነው
ብዙዎቻችን ልንደርስ የምንችለው እስከዚህ ድረስ ብቻ ስለነበር ነው፡፡ የሚደረገው ነገር ጥፋትና ስህተት ሆኖ አገኘነው፡፡
የደረስንበት የተለመደው መደምደሚያ ሰዎች እኛን ማሳሳታቸውን ቀጠሉ እኛም በነገሩ ቆሰልን፣ ሻከርንና ተቀየምን፡፡ አንዳንዴ
ደግሞ በጥፋታችን እንፀፀትና ራሳችንን እንቀየማለን፡፡ በጦርነት ጊዜ ለአሸናፊው ድል ማለት ማሸነፍ ብቻ እንደሚመስለው፣
ነገሮችን በተጋፋንና የራሳችን የሆነ የማሸነፊያ መንገድ ለማግኘት በታገልን ቁጥር ሁኔታዎች እየከፉና እየተበላሹ ይሄዳሉ፡፡ ድል
አድርገን የነበረ ቢሆንም እንኳ ድሉ የቆየው ለቅጽበት ያህል ብቻ ነበር፡፡
በቂም የተሞላ ሕይወት ከንቱና ደስታ የራቀው ሕይወት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ነገሩን በትክክል ለማስቀመጥ ለቂም
ቦታ መስጠት ማለት እጅግ በጣም ውድ የሆነ ጊዜን ማባከን ነው፡፡ ከችግሩ ለማገገም ተስፋው መንፈሳዊ እውቀቱን መጠበቅና
ማሳደግ ለሆነ የመጠጥ ሱሰኛ ግን ቂም ማለት ማለቂያ የሌለው መከራ ማለት ነው፡፡ ቂም የመጠጥ ሱሰኛ ገዳይ ነው፡፡ እኛ
ቂም ስንይዝ ራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ዝግ እናደርገዋለን፡፡ በዚህ ጊዜ የአልኮል እብደታችን ስለሚመለስብን መጠጣት
መጀመራችን አይቀሬ ይሆናል፡፡ ለእኛ ደግሞ መጠጣት ማለት መሞት ማለት እንደሆነ እርግጠኞች ነን፡፡ መኖር ከፈለግን፣
ከቁጣና ንዴት ነፃ መሆን አለብን። መነጫነጭና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ መረበሽ ለእኛ አይበጀንም። ምናልባት ለጤናማ ሰው
የምቾት ጥርጣሬ ሊሆኑ ይችላሉ። ለአልኮል ሱሰኞች ግን እነዚህ ነገሮች መርዞች ናቸው።
የወደፊት ተስፋችን ቁልፍ ያለበት በመሆኑ የጻፍነውን የቂሞች ዝርዝር ተመልሰን አነበብነው። ዝርዝሩንም በጣሙን
ለየት ካለ አቅጣጫ አመዛዝነን ልንመለከት ፍፁም ዝግጁ ነበርን። ስናጤነውም ዓለምና ውስጧ ያሉ ሰዎች ከበላያችን የተጫኑን
መሆኑን መገንዘብ ጀመርን። በዚህም ሁኔታ የሌሎች የክፋት ድርጊት፣ የፈጠራም ይሁን እውነታ በተጨባጭ የመግደል አቅም
እንዳለው ተረዳን። ከዚህ ለማምለጥ የምንችለው እንዴት ነው? ቂመኝነት ሙሉ በሙሉ መሸነፍ እንዳለበት ተስማምተናል
ግን እንዴት? ቂመኝነትም እንደ አልኮል ከሕይወታችን መወገድ አለበት ።
ያገኘነው ትምህርት መጥፎ እንድናደርግ ወይም ቂመኛ እንድንሆን ያደረጉን ሰዎች መንፈሳዊ ሕመም ያለባቸው
መሆኑን አንድንገነዘብ አደረገን። የሚታዩባቸውን የሕመም ምልክቶች አልወደዱአቸውም፤ በዚህ እኛም ተረበሽን። እነሱም
ልክ እንደኛው ታመው ነበርና። ፈጣሪንም ለታመሙ ጓደኞቻችን የምናሳየውን የመሰለ መቻልን፣ ሐዘኔታንና ትዕግሥትን
እንዲሰጠንና እኛም ደስ ብሎን እናደርግላቸው ዘንድ እንዲረዳን ለመነው። ማንም ሰው ሲሰድበንና ሲቆጣን ሁሉ በውስጣችን
«ይህ ሰው ሕመምተኛ ነው እንዴት ልንረዳው እንችላለን? ፈጣሪ ሆይ እንዳልቆጣ መንፈሴንና ስሜቴን አንተ ተቆጣጠር፣
ፈቃድህ ብቻ ይፈጸም።´ እንል ነበር።
ጭቅጭቅና በቀልን እስካላስወገድን ድረስ በሕመም ላይ ያሉን መንከባከብ አንችልም። የምንጨቃጨቅና የምንበቀል
ከሆንን ሰዎችን ለመረዳት ያለንን ዕድል እናበላሸዋለን። በእርግጥ የሁሉም ሰው ረዳቶች ለመሆን አንችልም፣ ነገር ግን ፈጣሪ
የእያንዳንዱን ሰው ሁኔታ እንዴት በቻይነት ስሜት ልንመለከተውና ልንረዳው እንደምንችል ያመላክተናል።
ደግመን የያዝነውን ዝርዝር ተመለከትን። በእኛ ላይ ደርሶብናል የምንለውን በደል ሁሉ ከሀሳባችን አወጣንና ራሳችን
በሠራናቸው ስህተቶች ላይ በቆራጥነት አተኮርን። ግን እኛ የትና መቼ ነው ራስ ወዳድ፣ እምነት አጉዳይ፣ የግል ጥቅም አሳዳጅ
የሆነውና የፈራነው? ምንም እንኳ እኛ ለተፈጠረው አጉል ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂዎች ልንሆን ባንችልም፣ የሌሎች

7
ሰዎችን ተሳትፎ ሙሉ በሙሉ ቸል ብለን በራሳችን ላይ አተኮርን። እናም እኛ የት ነበርንና ነው የምንወቀሰው በማለት ጠየቅን።
ፍተሻው የራሳችንን ማንነት የምናይበት እንጂ የሌሎችን የምናይበት አይደለም። በፍተሻው ሂደት ስህተቶቻችንን በአገኘን ቁጥር
መዘገብናቸው። አጎልተን ጽፈንም ከፊት ለፊታችን በሚታዩበት ሁኔታ እንዲሆኑ አደረግን።
ስህተቶቻችንንም በሐቀኝነት አምነን ከመቀበላችንም በላይ ያለምንም ማንገራገር ለማስተካከል ከራሳችን ጋር
ተስማማን። ከአቶ አበበ፣ ከዩሐንስ ባለቤት ከአሠሪዬና ከባለቤቱ ጋር ከነበረን ችግር አኳያ (ፍራቻ) የሚለው ቃል የሠፈረው
በቅንፍ ውስጥ ነበር። ይህ አጭር ቃል ከሞላ ጎደል የሕይወታችንን ዘርፎች ሁሉ የሚነካ ነው። ቃሉ የኃጢያት በትርና
ኑሮአችንን የሚያኮላሽ የክፉ ሀሳብ መግለጫ ነው። ልናልፍበት በማይገባና ጠማማ በሆነ መንገድ እንድናልፍ በሰባራ የሕይወት
ባቡር ላይ ያስቀመጠን ክፉ ጠላታችን ራሱ ፍራቻ ነው። ለነገሩ የሕይወታችን አቅጣጫ አሽከርካሪዎች እኛው ራሳችን
አልነበርንም? አንዳንዴ ፍራቻን ከስርቆት ጋር እንመድበዋለን ምክንያቱም የብዙ ሁከትና ችግር ፈጣሪ በመሆኑ።
ከፍራቻ ጋር በተያያዘ በማንም ላይ ቂም አልያዝንም፣ ይሁን እንጂ ፍራቻዎቻችንና ምክንያቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ
በመመራመር በወረቀት ላይ አሰፈርናቸው። በምን ምክንያት ፈርተን እንደነበር ራሳችንን ጠየቅን። በራስ መተማመን አቅቶን
ስለነበር ይሆን? በራስ መተማመን በትክክል ከተያዘ መልካም ነገር ነው ይሁንና ከተገቢው ያለፈ ወይም ያነሰ ከሆነ ግን ችግር
አያጣውም። በአንድ ወቅት አንዳንዶቻችን ለፍራቻም ሆነ ለሌላ ችግራችን መፍትሔ ያላስገኘ ጠንካራ በራስ መተማመን
ነበረን። በራስ መተማመናችን ትምክህተኞች ሲያደርገን ውጤቱ የከፋ ነው።
አሁን እኛ እንደምናምነው በጣም ጥሩ የሆነ (የነፃነትና የሰላም) መንገድ አለን። አሁን ያለንበት ጠንካራ መሠረት
በፈጣሪ በመተማመንና በእሱም በመመካት ነው። ጥቂት ዘመን ባለው እኔነት (በራስ) ከመታመን ይልቅ ዘለዓለማዊ በሆነው
ፈጣሪ ላይ ማመን እጅጉን ይበልጣል። እኛ በዚች ዓለም ላይ የተገኘነው የእሱን ፈቃድ ለመፈጸም ነው። እሱ ሁለንተናችንን
እንደተቆጣጠረ ስለምናስብ የምናደርገውን ነገር ሁሉ የፈጣሪ ፍቃድን በመደገፍ እናደርጋለን። በቅንነትና በጭምትነት በእሱ
እንታመናለን፣ ፈቃዳችንን እንሰጠዋለን፣ ለእሱም እንገዛለን፣ እሱም ሰቆቃችን ሁሉ በእርጋታ ለማለፍና መቅሰፍቶችንም
ለማብረድ ያስችለናል።
መንፈሳዊነት ደካማነት ነው ብለው በሚያስቡ ሰዎች ላይ ከመሳቅ አልፈን በፈጣሪያችን በመተማመናችን ማንንም
ይቅርታ አንጠይቅም ጠይቀንም አናውቅም። መንፈሳዊነትም ደካማነት ሳይሆን በተቃራኒው ጥንካሬ ነው። እምነት ማለት
ብርታት እንደሆነ ዘመናት ሁሉ ፍርዳቸውን ሰጥተውበታል፣ የእምነት ሰዎች የሆኑ ሁሉም ፈጣሪ የሚያምኑ በመሆናቸው
ደፋሮች ነበሩ። በፈጣሪ ስለመተማመናችን ምንጊዜም ይቅርታ አንጠይቅም። ይልቁንም ፈጣሪ ሊያደርግ የሚፈልገውን ሁሉ
በእኛ እንዲያደርግ እንፈቅድለታለን። እኛም ከፍራቻ አላቆን፣ አቅጣጫና ትኩረታችን እሱ፣ እኛ እንድንሆን ወደ ሚፈልገው
ያደርግልን ዘንድ ፈጣሪን ጠየቀነው። ወዲያም ከፍራቻ መላቀቅ ጀመርን።
አሁን ደግሞ ስለ ወሲብ እናውሳ። ብዙዎቻችን የወሲብን ጉዳይ መመርመር ያስፈልገናል። ከሁሉ በላይ ግን ይህን
ጥያቄ በተመለከተ አስተዋዮች ለመሆን ሞክረናል። በቀላሉም ከትክክለኛው አካሄድ መውጣት ይቻላል። እዚህ ላይ የሰዎች
አስተያየት በፅንፈኝነት መካከል ያለ ሆኖ አግኝተነዋል - ምናልባትም በማይመሳሰሉ ፅንፎች። አንዱ ወገን ወሲብ የፍጥረታት
መገኛ ስለሆነ እጅግ አስፈላጊ ነገር ሆኖ ሳለ ነገር ግን የክፉ ተፈጥሮአችን፣ የዘማዊነት መግለጫ ሆኖአል የሚል ነው። በሌላ
በኩል ደግሞ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሁሉም እንደፈለገ ወሲብ ይፈፅም፤ በጋብቻ ለምን ይወሰናል ከማለትም አልፎ የሰው ልጆች
ችግሮች ሁሉ ምክንያት ከወሲብ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ለማመልከት የሚሞክር አለ። እነዚህም ወገኖች እስከአሁን በነበረው
ወሲብ የሰው ልጅ የሚበቃውን ያህል አላገኘም ወይም ደግሞ ትክክለኛው ዓይነት አይደለም ብለው የሚያስቡ ናቸው።
በየትኛውም ቦታ አስፈላጊነት አለው ይላሉ። አንዱ ክፍል ይህንን ነገር ለምንም ነገር ማጣፈጫ አይደለም ሲለን ሌላኛው ክፍል

8
ደግሞ የሁሉም ነገር ማጣፈጫ ቅመማችን እንደሆነ ያሳስበናል። ያም ሆነ ይህ እኛ ከየትኛውም ወገን ሆነን ስለ ማንም የወሲብ
ጉዳይ ለመዳኘት አንፈልግም። የገባን ነገር ቢኖር ወሲብን በተመለከተ ችግሮች ያሉብን መሆኑ ነው። የተባሉት ችግሮች
ከሌሉብን ሰው መሆናችን አነጋጋሪ ይሆናል። ታዲያ ግን እነዚህን ችግሮች እንዴት እናድርጋቸው?
እንደገና ባለፉት ዓመታት የነበረንን ፀባይ መመርመር ጀመርን። የትና መቼ ነው ራስ ወዳድ ፣ እምነት አጉዳይ፣ ወይም
ደግሞ ነገሮችን በደንብ ያላጤነው? በእነዚህ ነገሮች ምክንያትስ ማንን ጎዳን? በቂ ምክንያት ሊቀርብ በማይችልበት ሁኔታ
ቅናትን፣ ጥርጣሬንና መራርነትን ቀስቅሰን ነበር ይሆን? የተሳሳትነው የት ጋ ነው? በዚያ ምትክ ምን ማድረግ እንችል ነበር?
ይህን ሁሉ ዘርዝረን በመፃፍ እያንዳንዱን ጥቃቅን የሚመስል ነገር ሁሉ ወደኋላ ዞር ብለን ለማየት ደፍረናል።
በዚህ አይነት ለወደፊት የወሲብ ሕይወታችን ጤነኛና ተገቢ ነው ብለን ያመንንበትን ነገር ነደፍን። ቀድሞ የነበረንን
የወሲብ ታሪካችንን አዲስ ከነደፍነው መመሪያ አኳያ በመመዘን «ምን ይመስል ነበር?´ ብለን ገመገምነው። ሁሌም
የምናስታውሰው የወሲብ ኃይልንና የማድረግ አቅምን የሰጠን ፈጣሪ ስለሆነ ጥሩ ነገር ነው። ስለሆነም በራስ ወዳድነት ወይም
ደግሞ እንደፈለግን የምንጠቀመው አለበለዚያም በጥላቻ የምንጥለው ነገር እንዳልሆነ በደንብ ገብቶናል። ወሲብንም
በተመለከተ የነደፍነው መመሪያችን እንደ ፈጣሪ ፈቃድ እንዲሆንና በመመሪያው መሠረትም እንኖር ዘንድ ፈጣሪ እንዲረዳን
መፀለይ ነው።
አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት የመረጥናቸው መመሪያዎች ለመፈጸም አቅደን የሆነ ቦታ ላይ ብንደናቀፍ ወደ
መጠጣት እንመላሳለን ማለት ነው? ከሆነስ እስክንሰክር ድረስ እንጠጣለን ማለት ነው? ወደ መጠጥ የመመለሱና የአለመመለሱ
ጉዳይ እንደየሰውና እንደ ምክንያቱ ይለያያል። ስለዚህ ወደ መጠጣት ትመለሳላችሁ የሚሉ ሰዎች በከፊል ትክክል ናቸው
ለማለት ይቻላል። ስለ ተደናቀፍን አዝነን በሰራነው ሥራ ተፀፅተን ፈጣሪን በንሰሐ ይቅር እንዲለንና ወደተሻለውም መንገድ
እንዲመራን ብንጠይቅ ይቅር እንደሚለን እናምናለን፣ እኛም ከደረሰብን ዕክል ትምህርት እንቀስማለን። በሌላ በኩል ደግሞ
በሥራችን ባንፀፀትና ሰዎችን ማጥቃታችንን ብንቀጥል በንድፈሀሳብ ደረጃ ሳይሆን በሕይወት ልምዳችን እንደተማርነው ከሆነ
ወደ መጠጣትና እብደታችን እንደምንመለስ እርግጠኞች ነን።
የራሳችንን የእኔነት ጓዳ በፈተሽን ጊዜ እጅግ ብዙ ነገሮች በዝርዝር ወረቀት ላይ አስፍረናል። በውስጣችን
የያዝናቸውን ቂሞች በደንብ አብላልተን አይተናቸዋል። በዚህም ጊዜ የሚያስከትሉትን አደጋና ሞት በመመርመር
አጥፊነታቸውን በደንብ ማየት ጀምረናል። ሁሉንም ሰው በተመለከተ መልካም፣ ታጋሽና ቻይ መሆን እንዳለብን ተምረናል።
ጠላቶቻችንን እንኳ ሳይቀር፣ ምክንያቱም እነሱ በእኛ ላይ ክፉ የሚያደርጉብን ታምመው ነው ብለን ሰለምናምን። ባለፈው
ዘመናችን የበደልናቸውን ሰዎች በዝርዝር ይዘናቸዋል፣ በሚቻለን ሁሉም ይቅርታ በመጠየቅ ግንኙነታችንን ለማስተካከል
ፍቃደኞች ነን።
መዘንጋት የሌለበት ነገር በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ደግመን ደጋግመን ያወሳነው ማድረግ ያልቻልነውን ነገር ሁሉ
እንድናደርግ ያስቻለን እምነታችን መሆኑን ነው። እርስዎም ከዚህ በፊት የነበርዎትን መጥፎ ብለው የሚያስቡትን ልምድ ሁሉ
በማሰብ በዝርዝር በመፃፍ ራስን ለመፈተሽ ወስነው ከሆነ ትክክለኛ ውሳኔና በጎ ጅማሮ አድርገዋል። ይህንን ሲያደርጉ ስለ
እርስዎ መራራውንና ጠንካራውን እውነታ ተቀብለዋል ማለት ነው። ይህንን ሊያደርጉ እንደተዘጋጁ በማሰብ ፈጣሪ በእርስዎና
በእሱ መካከል በመግባት የለያያችሁን ኃጢያት ሊያስወግድልዎት እንደሚቻለውና እርስዎንም ከችግርዎ ነፃ በማውጣት
ከመንፈሳዊ ዕድገት ወደ በለጠ ዕድገት፣ ከእሥራት ወደ መፈታት፣ ከሞትና ፍርሃትም ወደ ሕይወትና ነፃነት እንደሚያሻግርዎ
በማመን ወደ እሱ እንዲጠጉ የሰጠነውን ምክር እንደተቀበሉ እናምናለን።

9
የ4ኛ ደረጃ ዝርዝር
ቂም የያዝኩባቸው ምክንያቱ ምኔን ነው የጎዳኝ? የት ጋ ነው የኔ ጥፋት? በምትኩ ምን ማድረግ እችል ነበር?
ራስ ወዳድነት፣ ሐቀኛ ያለመሆን፣ ራስን
የተናደዱባቸውን ሰዎች፥ ተቋማትና መርሆዎች በራስ መተማመን፣ ኩራት፣ ስሜታዊ ደህንነት፣ ፋይናንስ (የገንዘብ
ለምንድነው የተናደድኩት? ማገልገል፣ ፈርሐት፣ ሌሎችን ከግምት
ዘርዝሩ ጉዳይ፣ ምኞቶች፣ የግል ግንኙነቶች፣ ወሲባዊ ግንኙነቶች
አለማግባት

በወሲብ ባህሪዬ ማንን ነው የጎዳሁት? እንዴት ጎዳኃቸው? የት ጋ ነው የኔ ጥፋት? በምትኩ ምን ማድረግ እችል ነበር?
ራስ ወዳድነት፣ ሐቀኛ ያመሆን፣ ራስን ማገልገል፣ ሌሎችን ከግምት
አለማግባት

ምንድነው የምፈራው? የዚህ ፍራቻ ተጽዕኖዎች

የምትፈሩአቸውን ሰዎች፥ ተቋማትና መርሆዎች በራስ መተማመን፣ ኩራት፣ ስሜታዊ ደህንነት፣ ፋይናንስ (የገንዘብ ጉዳይ፣ ምኞቶች፣ የግል ግንኙነቶች፣ ወሲባዊ
ዘርዝሩ ግንኙነቶች

5ኛ ደረጃ
ለፈጣሪ፣ ለራሳችንና ለሌሎችም ሰዎች ያደረግነውን ጥፋት ሁሉ በትክክል ተናዘዝን።

በግል የአካሄድነውን ʿየእኔነትʾ ፍተሻ ተከትሎ ምን ማድረግ አለብን? ብለን ራሳችንን ጠየቅን። ከፈጣሪያችን ጋር
አዲስ አመለካከትና አዲስ ዓይነት ግንኙነት ለመመስረትና በመንገዳችን ላይ ያጋጠሙንን እንቅፋቶች ለይቶ ለማወቅ ሞከርን፡
፡ በአደረግነው ፍተሻም በአገኘናቸው ደካማ ጎኖች ላይ በማተኮር ያሉብንን አንዳንድ ጉድለቶች አምነን ተቀበልን፣ ከሞላ
ጎደልም የችግሩን ምንነት አረጋግጠን፡፡ እነሱንም ለማስወገድ ተቃርበናል፡፡ ይህ ደግሞ በእኛ በኩል ተግባራዊ እንቅስቃሴን
የሚጠይቅ ይሆናል። ይህም ሲጠናቀቅ ለፈጣሪ፣ ለራሳችንና ለሌሎቸ ሰዎችም የጉድለቶቻችንን እውነተኛ ባሕርይና ምንነት
አመንን ማለት ይሆናል፡፡ ይህም ቀደም ባለው ምዕራፍ ወደተገለጸው የማገገሚያ ፕሮግራም አምስተኛ እርምጃ ይወስደናል፡፡

10
ምናልባትም፣ በተለይ ስለ ጉድለቶቻችን ከሌላ ሰው ጋር መወያየት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ስለ ችግሮቻችን ምንነት
ከአወቅንና አምነን ከተቀበልን ለራሳችን የሚበቃንን ያህል አድርገናል ብለን እናስባለን፡፡ እዚህ ላይ ግን አጠራጣሪ ነገር አለበት፡
፡ በተግባር ሲታይ ለብቻ ሆኖ ራስን በራስ መገምገም/መፈተሽ በቂ አይደለም። ብዙዎቻችን ከዚህም አልፎ መሄድ አስፈላጊ
ነው እንላለን፡፡ ስለችግሮቻችን ከሌላ ሰው ጋር ለምን መወያየት እንዳለብን የሚያሳምን ጥሩ ምክንያት መኖሩን ከተረዳን
ስለራሳችን ከሌሎች ጋር ለመወያየት በእጅጉ እንስማማለን፡፡ በመጀመሪያ ከሁሉም የሚበልጠውን ምክንያት እናንሳ፣ ይህን
ወሳኝ እርምጃ ከዘለልነው የመጠጥ ሱስን ማሸነፍ ያዳግተን ይሆናል፡፡ በየጊዜው እንዳየነው አዳዲስ መጤዎች፣
ስለሕይወታቸው አንዳንድ ሀቆችን ለመደበቅ ሞክረዋል፡፡ ይህን ራስን ዝቅ የሚያስደርግ ተሞክሮ ለመሸሽ ሲሉም ቀለል
ወደሚሉ ሌሎች ዘዴዎች ፊታቸውን አዙረዋል፡፡ ታዲያ አብዛኞቹ ወደዚያው ወደ ተለመደው ስካር ተመለሱ፡፡ ይሁን እንጂ
በፕሮግራሙ በሚያደርጉት ተሳትፎ ፀንቶ በመቀጠል ለምን እንደወደቁ ራሳቸውን ጠይቀዋል፡፡ እንደመሰለን ለዚህ ምክንያቱ
ʿየእኔነትʾ ፍተሻቸውን (የቤት ማጽዳት ተግባራቸውን) በአግባቡ ሳያጠናቅቁ በመቅረታቸው ነው፡፡ እርግጥ ፍተሻውን
አካሂደዋል፤ ግን ከተከማቹት ችግሮቻቸው መካከል እጅግ መጥፎ ናቸው ያሏቸውን ለራሳቸው ይዘው ቆይተዋል፡፡ ከራስ
ወዳድነትና ከፍርሃት የተላቀቁ መስሏቸዋል፣ በዚያውም ልክ ራሳቸውንም ዝቅ ያደረጉ መስሏቸዋል፡፡ እዚህ ላይ ለሌላ ሰው
የሕይወት ታሪካቸውን በሙሉ እስካልተናገሩ ድረስ ራስን ዝቅ ስለማድረግ፣ ከፍርሃት ስለመላቀቅ አልባነትና ስለሀቀኝነት
በሚገባ ተገንዘበዋል ለማለት አይቻልም፡፡
የአልኮል ሱሰኛ ከአብዛኛው ሰው በተለየ የመምሰል (የማታለል) ሕይወት ነው የሚመራው፡፡ በሕይወቱ ከመድረክ
ተዋናይ ጋር የተመሳሰለ ነው፡፡ ለውጭው ዓለም፤ ሌሎች እንዲያዩለት የሚሻውን የመድረክ ባሕሪውን ያሳያል፡፡ ስሙ በጥሩነት
እንዲነሳለትም ይፈልጋል ይሁን እንጂ በልቦናው የማይገባው መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የሚያሳየው ተለዋዋጭነትም
በሚሰክርበት ጊዜ በሚሠራቸው ነገሮች ይባባሳል፡፡ ከስካር በኋላ ራሱን ሲያውቅና የፈጸማቸው አንዳንድ ተግባሮቹ በጥቂቱ
ትዝ ሲሉት ራሱን ይወቅሳል፡፡ ትውስታዎቹ የቅዠት ያህል ናቸው፡፡ ሆኖም ታዲያ በዚያ ሁኔታ እያለ ሰው አስተውሎኝ ይሆናል
ብሎ ማሰብ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ ድርጊቶቹንም በሚቻለው ሁሉ እንዳይታወሱት አድርጎ በውስጡ ደብቆ ለመያዝ ይጣጣራል፡፡
መቼም ቢሆን ከተደበቁበት ወጥተው ብርሃንን እንደማያዩ ሰውም እንደማያስተውላቸው ተስፋ ያደርጋል። ይህን ሲያደርግም
በማያቋርጥ ፍርሃትና ጭንቀት ይወጠራል፡፡ ይህም ወደ ተጨማሪ መጠጥ ይገፋፋዋል፡፡
በዚህች አለም ላይ ረዥም እድሜ አግኝተን በደስታ ለመኖር ተስፋ የምናደርግ ከሆነ፣ ሌላው ቢቀር ለአንድ ሰው
ሙሉ ለሙሉ እውነተኞች መሆን አለብን፡፡ እርግጥ ነው ይህን ግላዊና ሚስጢራዊ እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ከማን ወይም
ከእነማን ጋር ማድረግ እንደሚገባን አስቀድመን ማሰቡ ትክክለኛና መሆን የሚገባው ተግባር ነው፡፡ ከመካከላችን ንስሐ
የመግባትን አስፈላጊነት የሚያስተምር ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑ፣ በአግባቡ ወደተመደበው፣ ተግባሩ ንስሐ መቀበል ወደ
ሆነውና ሥልጣኑ ወደተሰጠው መሄድ መፈለጋቸው አያጠያይቅም፡፡ ሃይማኖታዊ ቁርኝት የሌለን ደግሞ፣ በሃይማኖታዊ ተቋም
ስልጣኑ ለተሰጠው ሰው ብንናዘዝ መልካምና የሚደገፍ ይሆናል፡፡ እንዲያውም እንደዚህ ያለ ሰው ችግራችንን ፈጥኖ የሚያይና
የሚገባው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አንዳንዴም የአልኮል ሱሰኞች ችግር የማይገባቸው ሰዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡
ይህን ማድረግ ካልቻልን ወይም ማድረግ ካልፈለግን ከጓደኞቻችን መካከል ምስጢር መያዝ ይችላል፣ ችግራችንንም
ይረዳልናል የምንለውን መፈለግ ይኖርብናል፡፡ ምናልባት ይህ ሰው የእኛን ጉዳይ የሚከታተለው ሐኪም ወይም የስነ ልቦና
ባለሙያ ሊሆን ይችላል። ምናልባትም አንዱ የቤተሰባችን አባል ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ለሚስቶቻችንም ሆነ ለወላጆቻችን
ሊያስቀይማቸውና ሊያስከፋቸው የሚችልን ማንኛውንም ነገር መንገር የለብንም፡፡ ራሳችንን ለማዳን ሸክማችንን በሌላው ላይ

11
የመጫን መብት የለንም፡፡ እነኚህን የታሪካችንን ክፍሎች መንገር የሚገባን በጥሞና ለሚያዳምጠንና በሁኔታው ለማይጎዳ ሰው
ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሕጉ በራሳችን ላይ ጠንካሮች ለሌሎች ግን አሳቢዎች መሆን ነው፡፡
ስለራሳችን ጉዳይ ከሰው ጋር ለመወያየት በከፍተኛ ደረጃ እየፈለግንም እንኳ፣ ከችግራችን አንጻር የምናዋየው
ተስማሚ ሰው ላናገኝ እንችላለን፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም የምንወስደውን እርምጃ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፍ
እንችላለን፣ ይህ የምናደርገውም በሚያጋጥመን የመጀመሪያ አመች አጋጣሚ ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ዝግጁ ሆነን የምንጠብቅ
ከሆነ ነው፡፡ ይህን የምንለው የውስጣችንን ለመንገር የሚገባን ለትክክለኛው ሰው እንዲሆን ስለምንጓጓ ነው። የተባለው ሰው
ሚስጥር መጠብቅ የሚችል፣ ልናደርግ በምንፈልገው የሚረዳንና የሚደግፈን እንዲሁም ዕቅዳችንን ለመለወጥ የማይሞክር
መሆን ይገባዋል፡፡ ነገር ግን ይህን ብቻ ምክንያት በማድረግ የምናዋየው ሰው እስክናገኝ በማለት ጊዜውን ማራዘም የለብንም፡
ታሪካችንን ከማን ጋር እንደምንወያይ ከወሰንን በኋላ ጊዜ አናባክንም፡፡ በጽሑፍ የቀረበ ʿየእኔነትʾ ፍተሻ ይዘን በጉዳዩ
ላይ በሰፊው ለመወያየት ተዘጋጅተናል፡፡ ለምናወያየው አጋራችን ምን ለማድረግ እንደምንፈልግና ለምንስ ማድረግ እንዳለብን
ማስረዳት ይኖርብናል። እሱም የያዝነው ጉዳይ የሞት የሽረት መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ በእንዲህ ያለ ሁኔታ የምንቀርበው
ሰው በአብዛኛው ጊዜ ደስ ብሎት የሚረዳን ከመሆኑም በላይ እምነታችንን ስለጣልንበት ክብር ይሰማዋል፡፡
ይህንንም የምናደርገው ኩራታችንን ዋጥ አድርገን፣ ለምናሳየው ለእያንዳንዱ የባሕሪ ለውጥና ለቀድሞ ድብቅ
ሕይወታችን ማብራሪያ እየሰጠን መሆን አለበት፡፡
5ኛ ደረጃ ተስፋዎች
እንደምንም ብለን አንድ ጊዜይ ህንን እርምጃ ምንም ነገር ሳንደብቅ ከወሰድን በጣም ደስተኞች እንሆናለን፡፡ ዓለምንም
ፊት ለፊት ማየት እንችላለን፡፡ ሙሉ ሰላም አግኝተን ውስጣችንን ቀለል ብሎን ብቻችንን መሆን እንችላለን፡፡ ፍርሃታችን
ጥሎን ሄዷልና። ይህ ሲሆንም ፈጣሪያችን ለእኛ ቅርብ መሆኑን የምናውቅበት ጊዜ መጣ ማለት ነው፡፡ አንዳንድ መንፈሳዊ
እምነቶች ኖረውን ይሆናል፤ አሁን ግን መንፈሳዊ ተሞክሮ ማድረግ ጀምረናል፡፡ ከውስጣችን የመጠጡ ችግር የጠፋ
የሚያስመስል ስሜት አልፎ አልፎ ጎልቶ ይሰማናል፡፡ በሰፊው አውራ ጎዳና ላይ ከፍጥረተ ዓለም ገዥ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን
እየሄድን መሆናችንም ይሰማናል፡፡

6ኛ ደረጃ
ፈጣሪ እነዚህን ብልሹ ባሕሪዎቻችንን ያስወግድልን ዘንድ ፍጹም ዝግጁ ሆንን።

ወደ ቤታችን ከተመለስን በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ፀጥ ብለን ለመቆየት የምንችልበት ጥግ ይዘን ያደረግነውን ሁሉ
በጥንቃቄ መለስ ብለን ማየት ይኖርብናል፡፡ ፈጣሪን ከቀድሞው በተሻለ ለማወቅ በመቻላችን ከልባችን እናመሰግነዋለን፡፡
በመጀመሪያ የቀረቡትን አምስት የእርምጃ ሀሳቦች በጥንቃቄ አንብበን ያልፈጸምነው ነገር እንዳለ ራሳችንን እንጠይቃለን፡፡

1. አልኮልን በተመለከተ አቅመ ቢስ መሆናችንን፣ ሕይወታችንንም ለመቆጣጠር የተቸገርን መሆኑን አምነን ተቀበልን።
2. ከእኛ በላይ የሆነው ኃይል የአእምሮ ጤንነታችንን መልሶ ሊሰጠን እንደሚችል አመንን።
3. ፈጣሪን እኛ በተረዳነው መጠን እንዲንከባከበን፣ ፈቃዳችንና ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለመስጠት ወሰንን።
4. ያለምንም ፍርሃት በራሳችን ላይ የሥነ ምግባር ፍተሻ አደረግን።
5. ለፈጣሪ፣ ለራሳችንና ለሌሎችም ሰዎች ያደረግነውን ጥፋት ሁሉ በትክክል ተናዘዝን።

12
ይህንን የምናደርገው የምንገነባውን ቅስት የምንሻገረው ነጻ ሆነን መሆን ስላለበት ነው፡፡ እስከአሁን ያከናወነው
ተግባር አስተማማኝ ነውን? ድንጊያዎቹ ተገቢ ቦታቸውን ይዘዋል? ለመሠረቱ የዋለውን ሲሚንቶ አሳንሰን ይሆን? አሸዋ
ሳንጨምር ለመለሰን ሞክረን ይሆን?
ለጥያቄዎቹ የሰጠነው መልስ አርክቶን ከሆነ ወደ ስድስተኛው እርምጃ መሻገር እንችላለን፡፡ እዚህ ላይ ፈቃደኝነት
እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስምረንበታል፡፡ በሕይወታችን የፈጸምናቸው የማይገቡና የሚነቀፉ ነገሮች ናቸው ብለን
የማናምናቸውን ሁሉ እግዚአብሔር ከላያችን ገፎ እንዲጥልልን ለማድረግ ተዘጋጅተናልን? እሱስ፤ እያንዳንዱን በአጠቃላይ
ሁሉንም ከላያችን ገፎ ሊወስዳቸው ይችላልን? ምናልባት የሙጥኝ ብለን የያዝነውና መልቀቅ የማንፈልገው አንድ ነገር እንኳ
ካለ እግዚአብሔር ይረዳን ዘንድ በጸሎት እንጠይቀው፡፡

7ኛ ደረጃ
በደላችንን ሁሉ ይቅር እንዲለን እግዚአብሔርን በተሰበረ ልብ ለመነው።

ዝግጁ ስንሆን፣ የሚከተለውን የመሰለ ቃል ከአንደበታችን ይወጣል "ፈጣሪዬ ሆይ! በውስጤ ያለውን ሁሉ ጥሩም
ሆነ መጥፎ ያንተ እንድታደርግልኝ ፈቃደኛ ሆኜ ቀርቤአለሁ፣ ለአንተና ለጓደኞቼ ጠቃሚ እንዳልሆን በመንገዴ ላይ
የተጋረጠውን እያንዳንዱን ብልሹ ባሕሪዬን ከእኔ እንድታስወግድልኝ እለምንሀለሁ፡፡ ከዚህ ስወጣም ትዕዛዝህን ለመፈጸም
እበቃ ዘንድ ብርታቱን እንድታድለኝ እማጸንሀለሁ። አሜን!" በዚህም ሰባተኛውን እርምጃ አጠናቀናል፡፡

8ኛ ደረጃ
የበደልናቸውን ሰዎች በማሰብ ዝርዝራቸውን ይዘን ይቅርታ በመጠየቅ ከእነሱ ጋር የነበረንን ግንኙነት ለማደስ ተዘጋጀን።

አሁን የሚያስፈልገን ተጨማሪ ተግባር ነው፣ አለበለዚያ ግን "እምነት ያለ ተግባር ዋጋ የለውም"፡፡ እስቲ ስምንተኛና
ዘጠነኛ እርምጃዎችን እንመልከት፡፡ ያስቀየምናቸውና ልንክሳቸው የምንፈልገውን ሰዎችን ዝርዝር ይዘናል፡፡ ሊስቱን
ያዘጋጀነውም የ "እኔነት" ፍተሻ ባደረግንበት ጊዜ ነበር። በወቅቱም ራሳችን ላይ ስር ነቀል የሆነ የግል ግምገማ አድርገናል፡፡ አሁን
ደግሞ ወደ ጓደኞቻችን በማምራት ቀድሞ ላደረስንባቸው ጉዳት እንክሳለን፡፡ በራሳችን ፈቃድ ለመኖርና እኛነታችንን አጉልተን
ለማሳየት ባደረግነው ጥረት፣ ባጠፋነው ጥፋት የተከማቸውን ፍርስራሽ ለመጥረግ እንሞክራለን፡፡ ይህን ለማድረግ ፈቃደኝነቱን
ካጣን፤ ፈቃደኛ እስከምንሆን ድረስ በጸሎት እንጠይቃለን፡፡ አስታውሱ፤ ገና ከመነሻው የተስማማነው በአልኮል ላይ ድልን
እስከምንቀዳጅ ድረስ ማንኛውንም እርምጃ ከመውሰድ ላንገታ ነው

የ8ኛ ደረጃ ዝርዝር


ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁነኝ
ጉዳት የደረሰበት ሰው የጉዳቱ ዝርዝር
አዎ አይ ምን አልባት በጭራሽ

13
9ኛ ደረጃ
ይህንን ስናደርግ የበለጠ የምንበድላቸው መስሎ እስካልታየን ድረስ በሚቻለን ሁሉ የበደልናቸውን ሰዎች እየፈለግን
ታረቅን።

በጥቂቱም ቢሆን በውስጣችን ተጠራጣሪነቱ አይጠፋ ይሆናል፡፡ አስቀይመናቸው የነበረውን በሥራው ዓለም
ያወቅናቸውንም ሆነ የሌሎች ጓደኞቻችንን ዝርዝር ስናይና መንፈሳዊነትን መሠረት አድርገን ወደ እነርሱ መሄድን ስናስብ በራስ
ያለመተማመን ስሜት ይሰማን ይሆናል፡፡ እንረጋጋ፡፡ አንዳንዶቹን በተመለከተ መጀመሪያ ላይ ስንቀርባቸው መንፈሳዊ ገጽታን
ማጉላት ላያስፈልገን እንደውም ላይኖርብን ይችላል። አግባብ የሌለው ጥላቻ ልንፈጥር እንችላለን፡፡ ለጊዜው የምናደርገው
ሕይወታችንን መስመር ለማስያዝ መሞከር ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህ በራሱ መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ እውነተኛው
ግባችን ራሳችንን ብቁ በማድረግ እግዚአብሔርንና በአካባቢያችን የሚገኙን ሁሉ አቅማችን በፈቀደ መጠን ለማገልገል መቻል
ነው፡፡ ቀደም ሲል ባደረስንባቸው በደል ከደረሰባቸው ጉዳት ወዳላገገሙ ሰዎች በመቅረብ ሃይማኖተኞች ሆነናል ብሎ ማወጁ
ብልህነት አይሆንም፡፡ ስለምንስ ራሳችንን አክራሪዎች ወይም አታካች ሃይማኖተኞች ለመባል አሳልፈን እንሰጣለን። በዚህን
መሳዩ ድርጊት ወደፊት ጠቀሜታ ያለውን መልዕክት ለማስተላለፍ የሚያስችለንን አጋጣሚ በአጭሩ ልንቀጨው እንችላለን።
የተባለውን ሰው ግን ያደረስንበትን ጥፋትን ለማረም ባደረብን ጽኑ ፍላጎት መገረሙ አጠያያቂ አይሆንም፡፡ በይበልጥ
የሚያተኩረውም በምናወሳቸው መንፈሳዊ ግኝቶች ሳይሆን በምናሳየው በጎ ፈቃደኝነታችን ላይ ይሆናል፡፡
ይህን ግን የምንጠቀምበት እግዚአብሔርን አስመልክቶ ከምንነጋገርበት ርዕሰ ጉዳይ ለመሸሽ መሆን የለበትም፡፡
ሁኔታው ለመልካም ዓላማ ግብ መምታት አመቺ በሚሆንበት ጊዜ እምነታችንን በብልሃትና በሚዛናዊ አንደበት ለመግለጽ
ፈቃደኞች እንሆናለን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንጠላው የነበረውን ሰው በምን ዓይነት ዘዴ ልንቀርበው ይገባል የሚል ጥያቄ
ይነሳል፡፡ ምናልባት ይህ ሰው እኛ ካደረስንበት በደል ይልቅ እሱ በእኛ ላይ ያደረሰብን ይበልጥ ይሆናል፤ ይህም ሆኖ እኛ እሱን
በተመለከተ በውስጣችን የተሻለ አመለካከት አሳድረናል፡፡ ይሁን እንጂ ጥፋታችንን አምነን ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም፡፡
የምንጠላው ሰው ስለሆነም ጥርሳችንን መንከስ ይኖርበናል፡፡ ወደ ጠላት መሄድ ወደ ጓደኛ ከመሄድ የበለጠ ይከብዳል፤ ግን
የበለጠ ጠቃሚ ሆኖ ያገኘነው ወደ ጠላት መሄዱን ነው፡፡ ወደ እርሱ የምንሄደው በረዳትነትና በይቅር ባይ መንፈስ የቀድሞ
እኩይ ስሜታችንን ለመናዘዝና መጸጸታችንን ለመግለጽ ነው፡፡
በምንም ሁኔታ እንዲህ ያለውን ሰው መንቀፍ ወይም ከእሱ ጋር መከራከር የለብንም፡፡ የሚጠበቅብን ያለፈ
ታሪካችንን ለማስተካከል የተቻለንን ሁሉ ከማድረግ በስተቀር መቼም ቢሆን መጠጥን ለማሸነፍ እንደማንችል መንገር ብቻ
ነው። እኛ ከእሱ ዘንድ የተገኘነው በእኛ በኩል ያለውን መንገድ ለመጥረግ ነው፤ ይህን እስካላደረግን ድረስ ደግሞ ምንም
ዓይነት ቁም ነገር እንደማንፈጽም እናውቀዋለን፡፡ ማድረግ ያለብንን ከመፈጸም አልፈንም እሱ ምን ማድረግ እንደሚገባው
ለመንገር ፈጽሞ አንሞክርም፡፡ የእርሱ ጥፋቶች ውይይቱ ውስጥ አይገቡም፡፡ በራሳችን ጥፋቶች ላይ ብቻ እናተኩራለን፡፡
አቀራረባችን የረጋ፣ እውነተኛና ግልጽ ከሆነ በውጤቱ እንረካለን፡፡
ከእንደዚህ ዓይነቶቹ አስር አጋጣሚዎች በዘጠኙ ያልተጠበቀ ሁኔታ ይከሰታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ልናየው የሄድነው
ሰው የግል ጥፋቱን ያምንና ለዓመታት ከሮ የቆየው ቂም በቀል በአንድ ሰዓት ውስጥ ይሟሟል፡፡ እርምጃችን ስኬታማ ሳይሆን
የሚቀረው አልፎ አልፎ ነው። አንዳንዴ የቀድሞ ጠላቶቻችን የምንሰራውን ሥራ አድንቀው ደጉን ይመኙልናል፡፡ በአንዳንድ
አጋጣሚ ደግሞ እንርዳችሁ የሚሉም ይኖራሉ፡፡ ሌላው ደግሞ ከቢሮው ገፍትሮ ሊያስወጣን ይችላል፡፡ ይህም ምንም ማለት
አይደለም፡፡ በእኛ በኩል የሚፈለግብንን አድርገናል፣ ሁኔታዎችን አስረድተናል።

14
አብዛኞቹ የአልኮል ሱሰኞች ዕዳ አለብን፡፡ አበዳሪዎቻችንን አንሸሻቸውም፡፡ ስለ ጠጪነታችን ብንነግራቸውም
ባንነግራቸውም የሚያውቁት ጉዳይ ስለሆነ ጭብጡን ሳንደብቅ ምን እየሰራን እንደሆነ ልንነግራቸው ይገባል፡፡ ስለ አልኮል
ሱሰኝነታችን ማውሳቱ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ የፋይናንስ ችግር ያስከትልብናል በሚል ፍራቻ ልንደብቃቸው አይገባም፡፡ በዚህ
ዘዴ ከቀረባችሁት ርህራሄን የማያውቅ አበዳሪም እንኳ ቢሆን እንዳንድ ጊዜ የሚያስገርም ተግባር ይፈጸማል፡፡ ከእነዚህ ሰዎች
ጋር ብድራችንን ለመክፈል በሚያስችለን ሁኔታ ላይ ከስምምነት ለመድረስ መቻላችን በራሱ በነገሩ ያዘንን መሆናችንን
ያሳውቃቸዋል፡፡ በመጠጥ ሱስ መያዛችን፣ የተበደርነውን ፈጥነን እንዳንከፍል አድርጎናል፡፡ የተበደርነው ገንዘብ የቱን ያህል
የበዛ ቢሆንም አበዳሪዎችን መፍራቱ ሊለቀን ይገባል፡፡ ይህ ሳይሆን! ቀርቶ እነርሱን ማየት ከፈራን ግን ወደ መጠጥ ማዘንበላችን
አይቀርም፡፡
ምናልባት ቀደም ባለው ጊዜ ባለስልጣኖች አውቀውት ቢሆን ኖሮ ለእስር ሊዳርገን የሚችል የወንጀል ድርጊት ፈጽመን
ይሆናል፡፡ ተቀማጭ ሂሳብ አጉድለን ለማሟላት ሳንችል ቀርተን ይሆናል፡፡ ይህንን ደግሞ ገና ድሮ በሚስጥር ለሌላ ሰው
ነግረናል፡፡ ነገሩ ታውቆ ቢሆን እንደምንታሰር ወይም ሥራችንን እንደምናጣ እርግጠኞች ነን፡፡ ምናልባትም ጥፋታችን ቀለል
ያለ ወጪን አበርክቶ የማሳየት ድርጊት ብቻ ይሆናል፡፡ አብዛኞቻችን ይህን መሳይ ነገር ፈጽመናል፡፡ ምናልባትም ከትዳር
ጓደኛችን ተለያይተን ተፋተን ሌላ ያገባን ግን ለመጀመሪያዋ ባለቤታችን ማድረግ ያለብን ተቆራጭ አንዴ ብቻ ሰጥተን መቀጠል
አቅቶን ይሆናል፡፡ እርሷም በጉዳዩ በመናደዷ ተይዞ ይቅረብ የሚል ማዘዣ አውጥታለች፡፡ ይህም በየጊዜው የሚታይ የተለመደ
ችግር ነው፡፡
ያደረግናቸውን ጥፋቶች በበጎ ለመመለስ የምንወስዳቸው ማካካሻዎች እጅግ የተለያዩ ገጽታዎች ቢኖራቸውም
ለሁሉም መመሪያ ይሆናሉ የምንላቸው አንዳንድ አጠቃላይ መርሆች አሉ፡፡ መንፈሳዊ ተሞክሮን ለማግኘት የቱን ያህል ርቀትም
ቢሆን ለመጓዝ መወሰናችን ይታወሳል፣ ስንወስንም በራሳችን ላይ ሊከተል የሚችለው ምንም ይሁን ምን መልካሙን ነገር
ለማድረግ አቅምና አመራር እንዲሰጠን ጠይቀናል። ምናልባትም ሥራችንን ወይም መልካም ስማችንን ልናጣ ወይም ደግሞ
ልንታሰር እንችላለን ይሀንንም ለመቀበል ፈቃደኞች ነን። መሆን ያለብንን እንሆናለን በሆነ ባልሆነው ነገር ደግሞ መሸማቀቅ
የለብንም፡፡
ሆኖም ግን አብዛኛውን ጊዜ እንደሚታወቀው ሁሉ የአኛ በምንለው ጉዳይ ሌሎች ሰዎችም አሉበት፡፡ ስለሆነም
ራሳችንን ከአልኮል አዘቅት ለማዳን ስንል ሌሎችን ለማያስፈልግ መስዋእትነት የምንዳርግ ችኩሎችና ደደቦች አንሁን፡፡ አንድ
የምናውቀው ሰው እንደገና አግብቷል ታዲያ ሰውየው በቅያሜና በመጠጥ ሳቢያ ለመጀመሪያ ሚስቱ እንዲከፍል የተጣለበት
ተቆራጭ ገንዘብ ሳይሰጥ ይቀራል። እርሷም በሁኔታው ተቆጥታ ወደ ፍርድ ቤትም በመሄድ የእስር ማዘዣ ታወጣለች።
ሰውየው በበኩሉ ከችግሩ ለመውጣት የኛን ዓይነት ኑሮ መምራት ጀምሮ በውጤቱም ሥራ አግኝቶ ራሱን ከገባበት ከአዘቅት
በማውጣት ላይ ነው። እና ይህ ሰው ዳኛው ፊት በመቅረብ "ክቡር ዳኛ ይኸው መጥቻለሁ" ብሎ ቢል ጀግንነቱ ባስደነቀ
ነበር'፡፡
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እሱም ቢሆን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ሆኖ መገኘት አለበት ብለን እናስባለን። ይህ ሳይሆን
ቀርቶ እስር ቤት ቢገባ ለዚችም ሆነ ለዚያች መስጠት የሚችለው ነገር አይኖረውም። በእኛ በኩል፣ ለቀድሞ ሚስቱ
እንዲጽፍላት፣ በሚጽፈውም ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ ይጠይቅ የሚል ሀሳብ አቀረብን፡፡ እሱም መጻፍ ብቻ ሳይሆን አነስተኛ
መጠን ያለው ገንዘብም ላከላት፡፡ ለወደፊቱ ምን ለማድረግ እንደሚሞክርም ነገራት፡፡ አያይዞም የለም አይሆንም የምትል ከሆነ
ወደ እስር ቤት ለመግባት ሙሉ ፈቃደኛ መሆኑን ገለጸላት። እሷም ብትሆን የለም አይሆንም አላለችም፤ እናም ሁኔታው
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወዲህ የተስተካከለ ሆነ።

15
በአጠቃላይ ሌሎች ሰዎችን ሊያስጠይቅ የሚችል ከባድ እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት የእነሱን ስምምነት ማግኘት
አለብን። ፈቃዳቸውን ካገኘን፤ ሌሎችን ካማከርን፤ እግዚአብሔርንም እንዲረዳን ከጠየቅን በኋላ አስፈላጊ ነው ብለን
ያመንበትን ከባድ እርምጃ እንወስዳለን። በዚህም መሸማቀቅ የለብንም፡፡
ይህ ደግሞ የአንድ ጓደኛችንን ታሪክ ያስታውሰናል፡፡ ጓደኛችን እየጠጣ ሳለ፤ ከአንድ በጣም ከተጠላ የቢዝነስ
ተፎካካሪው ደረሰኝ ሳይሰጠው ገንዘብ ይቀበላል። የኋላ ኋላም ገንዘቡን መቀበሉን ይክደዋል፣ አልፎም አጋጣሚውን
የሰውዬውን ስም ለማጥፋት ይጠቀምበታል፡፡ በእንዲህ ዓይነትም ራሱ ያጠፋውን ጥፋት የሌላን ሰው መልካም ዝና ለማጉደፍ
ተጠቀመበት፡፡ ከዚህ የተነሳ ተፎካካሪው ለውድቀት ተዳረገ፡፡
ዘግይቶ መልሶ ሊጠግነው የማይችለውን ጥፋት መፈፀሙ ተሰማው። ይህን ያለፈ ታሪክ እንደገና ቢቀሰቅሰው የቢዝነስ
አጋሩን መልካም ዝና እንዳያንኮታኩት፤ ቤተሰቡን እንዳያዋርድና መተዳደሪያውን እንዳያጣ ፈራ። የእሱ ጥገኞች የሆኑትን
በጉዳዩ ውስጥ ለማስገባት ምን መብት አለው? እንዴትስ አድርጐ ይሆን የቀድሞ ተፎካካሪውን ስም ባላንጣውን በአደባባይ
ለማደስ የሚችለው?
ጓደኞቹን፣ ባለቤቱንና የቢዝነስ አጋሩን ካማከረ በኋላ የተፎካካሪውን መልካም ዝና በማጉደፉና ለውድቀት
በመዳረጉ ጥፋተኛ ሆኖ ከፈጣሪው ፊትከመቅረብ ይልቅ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ መጋፈጡ የተሻለ ነው ከሚል ውሳኔ ላይ
ደረሰ። እሱም አጠቃላይ ሁኔታውንና ሊሆን የማችለውን ሁሉ ለእግዚአብሔር መተው እንዳለበት፣ አለበለዚያ ግን እንደገና
መጠጣት እንደሚጀምርና ዳግም ለውድቀት እንደሚዳረግ ተረዳ። ከብዙ ዓመታት በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ
ቤተክርስቲያን ሄዶ ሥርዓቱን ተካፈለ። ከስብከት በኋላም ብድግ ብሎ ችግሩን አስረዳ። ተግባሩም ከፍተኛ ድጋፍ አገኘ፣ እናም
ይህ ሰው ዛሬ እጅግ ከታመኑት የከተማው ነዋሪዎች አንዱ ሆኗል። ይህ ሁሉ የሆነው ከዓመታት በፊት ነበር።
በቤት ውስጥ ችግር መኖሩ የማይቀር ነው። ምንአልባት መታወቁ በማያስጨንቀን ሁኔታ ከተለያዩ ሴቶች ጋር እንወጣ
ይሆናል። በዚህ ረገድ የአልኮል ሱሰኞች ከሌሎች ሰዎች የባሱ መሆናቸው ያጠራጥራል። ነገር ግን መጠጥ፣ በቤት ውስጥ
ያለውን የወሲብ ግንኙነት ውስብስብ ያደርገዋል። ከአልኮል ሱሰኛ ጋር ለጥቂት ዓመታት የኖረች ሚስት በነገሮች ትደክማለች፣
በሁኔታዎች ትቆጫለች፣ ብላም ጋግርታም ትሆናለች። ሌላ ምን ልትሆን ትችላለች? ባለቤቷ ደግሞ ብቸኝነት ይሰማውና በራሱ
ማዘን ይጀምራል። ከዚያም በየዳንስ ቤቱ ወይም በተመሳሳይ ቦታዎች ከመጠጥ የተለየ ነገር መፈለግ ይጀምራል። ምንአልባት
«ሁኔታው ከሚገባት ሴት ጋር´ አስደሳች የሚስጥር ግንኙነት ጀምሮ ይሆናል። ሚዛናዊ ሆኖ ለመናገር፤ ችግሩን ስለተረዳችለት
ነው እንል ይሆናል፣ ግን እንዲህ ያለ ጉዳይ ሲያጋጥመን ማድረግ ያለብን ምንድነው? እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው፣ በተለይም
ያገባት ሴት ለእርሱ ስትል ብዙ ችግር ያሳለፈች ታማኝና ብርቱ ከሆነች ብዙውን ጊዜ በእጅጉ ይፀፀታል።
ሁኔታው ምንም ይሁን ምን፤ እኛ ግን አንድ ነገር ማድረግ አለብን። ይህን መሳይ ችግር ያለብን ከሆነና፣ ባለቤታችንም
ችግር መኖሩን እንዳማታውቅ እርግጠኞች ከሆንን ልንነግራት ይገባን ይሆን? እንደሚመስለን ሁሌም መናገር አይገባም። በሌላ
በኩል ደግሞ ችግር መኖሩን ከአጠቃላይ ሁኔታው ተገንዝባ ከሆነ በዝርዝር መናገር አለብን? ይህ ከሆነ ያለምንም ጥርጥር
ማጥፋታችንን ማመን አለብን። በዚህን ጊዜ እሷ በበኩሏ ዝርዝር ሁኔታውን ማወቅ አለብኝ ልትለን ትችላለች። ምንአልባትም
ሴትየዋ ማን እንደሆነችና የት እንዳለች ማወቅ አለብኝ ትል ይሆናል። እዚህ ላይ በእኛ በኩል ሌላን ሰው እዚህ ጉዳይ ውስጥ
የማስገባት መብት እንደሌለን ልንነግራት ይገባል። በፈጸምነው ጥፋት ማዘናችንን በመግለጽ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ቢሆን
ወደፊት የማይደገም መሆኑን መናገር ይኖርብናል። ከዚህ በላይ የምናደርገው ነገር የለም፣ ከዚህም አልፈን የመሄድ መብት
የለንም። እርግጥ ሌሎች በቂ ምክንያት ያላቸው ሊኖሩ ቢችሉም፣ ማንኛውንም ዓይነት ደንብ ለማስቀመጥ ባንሻም፣
ከተሞክሮአችን እንዳየነው አዋጩና የተሻለው መንገድ ይህ እንደሆነ ተረድተናል።

16
የመኖር ዕቅዳችን ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ አይደለም። ያቀረብነው የመፍትሔ ሀሳብ ጥሩነቱ ለባልም ለሚስትም
ነው። እኛ መርሳት ከቻልን እርሷም መርሳት ትችላለች። የሚሻለውም የሰው ስም አለመጥራቱና ቅናቷን ልትወጣበት
የምትችለውን ሰው ማንነት አለመንገሩ ነው።
ምንአልባት እውነቱን ዘክዝኮ ማውጣት የሚያስፈልግባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎች ይኖራሉ። ባለትዳሮችን ብቻ
በሚመለከተው በዚህን መሳይ ሁኔታ የውጭ ሰው ሊሆን የሚችለውን መገመት አይችልም። ሁለቱም የመልካም አስተሳሰብንና
የፍቅርን መንገድ መርጠው ያለፈው አልፏል እንተወው ብለው ይወስኑ ይሆናል። ምንአልባትም እያንዳንዳቸው የትዳር
ጓደኛቸውን ደስታ ከሁሉም በማስቀደም ለዚሁ ይጸልዩ ይሆናል። ምንጊዜም ቢሆን መዘንጋት የሌለብን የምንደራደረው አስፈሪ
ከሆነው ሰብአዊ ስሜት፣ ከቅናት ጋር መሆኑን ነው። ጥሩ የጦር አመራር ብቃት ያለው አዋጊ ችግሩን በፊት ለፊት ውጊያ
ከመግጠም ይልቅ ከጎኑ ለማጥቃት ይወስን ይሆናል።
ይህ መሳይ የተወሳሰበ ነገር ከሌለብን፤ በቤታችን ልናደርግ የሚገባን ብዙ ነገር አለ። አንዳንድ ጊዜ የአልኮል ሱሰኛ
ማድረግ የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ከመጠጣት መታቀብ ብቻ እንደሆነ ሲናገር እንሰማለን። በእርግጥም መታቀብ አለበት፣
ካልታቀበማ ቤት የለውም ማለት ነው። ይህም ሆኖ ለዓመታት ፍዳቸውን ሲያስቆጥራቸው የነበሩትን ሚስቱን ወይም ወላጆቹን
ለመካስ ገና ብዙ ይቀረዋል። ምንም ሊገባን ያልቻው ደግሞ እናቶችና ሚስቶች የአልኮል ሱሰኞችን በተመለከተ የነበራቸው
ትዕግሥት ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ ብዙዎቻችን ዛሬ ቤት አይኖረንም ነበር፣ ከዚያም በባሰ መልኩ በሞት ተለይተን ነበር።
የአልኮል ሱሰኛ እንደ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እያጉረመረመ በሌሎች ሕይወት ውስጥ የሚያልፍ ነው። በዚህን ጊዜም
ልብ ይቆስላል፣ ጣፋጭ የፍቅር ግንኙነት እንዳልነበር ይሆናል፣ መውደድም ከስሩ ይነቀላል። ራስ ወዳድነትና ለሌሎች ደንታ
ቢስ መሆን ቤት ያምሳሉ። ከመጠጥ መታቀቤ ብቻ በቂ ነው የሚል ሰው የማያስብ እንደሆነ ይሰማናል። እሱም ወዥብ
የተቀላቀለበት አውሎነፋስ ከአለፈ በኋላ ተደብቆበት ከነበረው የምድር ቤቱ ሲወጣ የቤቱን እንዳልነበር ሆኖ እንዳገኘው ገበሬ
ያህል ነው። ገበሬውም ለሚስቱ አንችዬ ምንም አይደል፣ ዋናው ነገር አውሎ ነፋስ መቆሙ አይደል? ይላታል።
አዎን ወደፊት ረጅም የመልሶ ግንባታ ጊዜ ይጠብቀናል። የመሪነቱን ቦታ መያዝ አለብን። አዝናለሁ እያሉ በመፀፀትና
በማጉረምረም ብቻ የሚወራረድ ዕዳ የለም። ከቤተሰባችን ጋር ቁጭ ብለን ያለፈውን ዛሬ በምናይበት ሁኔታ በግልፅ መተንተን
ይኖርብናል፣ ይህን ስናደርግም የቤተሰብ አባሎቻችንን ላለመንቀፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል። ምናልባት የእነሱ ጥፋት
ጎልቶ ይታይ ይሆናል፤ ለዚህ ደግሞ በከፊል ራሳችን የፈጸምናቸው ድርጊቶች አስጠያቂ ናቸው። ታዲያ ከቤተሰብ ጋር ሆነን
ቤት የምናፀዳው፤ በጧት በጸሎታችን ፈጣሪያችን የትዕግስትን፤ የመቻቻልን፤ የደግነትንና የፍቅርን መንገድ እንዲያሳየን
በመለመን ነው።
መንፈሳዊ ሕይወት ንድፈ ሃሳብ አይደለም። የምንኖረው መሆን አለበት። ይህም ሆኖ ቤተሰቡ በመንፈሳዊ መርሆዎች
መሠረት መኖር እንደሚሻ ካልገለጸ በቀር እኛ መገፋፋት አይገባንም ብለን እናስባለን። ለቤተሰቡም ስለ መንፈሳዊ ጉዳዮች
በሚያታክት ሁኔታ ማውሳት የለብንም። ሁሉም በጊዜያቸውን ይለወጣሉ። የምናሳያቸው የጠባይ ለውጥ ከቃላቶቻችን የበለጠ
ያሳምኗቸዋል። አስር ወይም ሃያ ዓመታት ሙሉ ሲሰክር የነበረ ሰው በማንም ዘንድ ቢሆን እምነት ሊያጣ እንደሚችል
ማስታወስ ይኖርብናል።
አንዳንድ መቼም ልናስተካክላቸው የማንችለው ጥፋቶች ይኖራሉ። እነሱንም በተመለከተ የሚቻለን ቢሆን ኖሮ
እናስተካክላቸው ነበር፣ ብለን በእውነተኛነት ከተናገርን፤ ሊያስጨንቁን አይገባም። አንዳንድ የማይታዩ ሰዎች አሉ–ለእነሱ፤
ቁም ነገር የያዘ ደብዳቤ እንላክላቸው። በአንዳንድ አጋጣሚዎች ደግሞ ጊዜው ለማስተላለፍ በቂ ምክንያት ይኖራል። የሚቻል
ከሆነ ግን አለመዘግየት ይመረጣል፣ በማናቸውም ሁኔታ ግን እግር ላይ መውደቅ ሳንደርስ፤ አስተዋይ፣ ዘዴኛ፣ ለሰው አሳቢና

17
ትሁት መሆን አለብን። የእግዚአብሔር ፍጡሮች እንደመሆናችን መጠን በሁለት እግሮቻችን እንቁም፣ በማንም ፊት ቢሆን
አንዳህ።
9ኛ ደረጃ ተስፋዎች
ዕድገታችን በሚገኝበት በዚህ ምዕራፍ ላይ ጠንክረን ከተጋን፣ ገና ከአጋማሹ ሳንደርስ በውጤቱ እንገረማለን። አዲስ
ነፃነትና አዲስ ደስታ ይሰማናል። ባለፈው ሕይወታችን አናዝንም፣ በላዩም ላይ በር አንዘጋበትም። የመንፈስ እርካታ ስንል ምን
ማለታችን መሆኑ ይገባናል፣ እናም ሰላም እናገኛለን። የቱን ያህል ወደ አዘቅት ወርደን የነበርን ቢሆንም፣ በተመክሮአችን ሌሎች
ምን ያህል ሊጠቀሙ እንደሚችሉ መገመት አያዳግተንም። የከንቱነትና በራስ የማዘን ስሜትም ይጠፋል። ከራስ ወዳድነት
ስሜት ተላቀን በጓደኞቻችን ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ለራስ ፍላጐት መቆም ይቀራል። በሕይወት ላይ ያለን አቋምና
አስተያየት ይለወጣል። ሰዎችን የመፍራትና የኢኮኖሚ ዋስትና የማጣት ስጋት ጥለውን ይሄዳሉ። ግር ይሉን የነበሩ ሁኔታዎችን
በዘዴ መፍታት እንጀምራለን። በድንገትም ለእኛ ለራሳችን ማድረግ ያልቻልነውን እግዚአብሔር እንደሚያደርግልን
እንገነዘባለን። እነኝህ የተገቡት ቃልኪዳኖች የተጋነኑ ናቸውን? አይመስለንም። በእኛው መካከል አንዳንዴ ፈጥነው አንዳንዴ
ደግሞ በዝግታ እየተፈፀሙ ነው። ዓላማ አድርገን ለተግባራዊነታቸው ከሰራን ሁልጊዜም እውን ይሆናሉ።

10ኛ ደረጃ
ዕለት ዕለት ራሳችንን እየመረመርን ንሰሐ ገባን፣ ጥፋት እንዳጠፋንም ጥፋታችንን አምነን ወዲያውኑ ተቀበልን።

ይህ ሀሳብ ወደ አስረኛው እርምጃ ያሸጋግረናል፤ እርሱም በእኔነታችን ፍተሻ እንድንገፋበትና በመንገዳችን ላይ


የሚፈፀሙ አዳዲስ ስህተቶች ቢኖሩ እንድናስተካክላቸው ይመክረናል። ያለፈውን ሕይወታችንን ካፀዳን በኋላ ይህን መሳዩን
የአኗኗር ዘይቤ ተጠናክረን ጀምረነዋል። ከመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ገብተናል። የሚቀጥለው ተግባራችን ሁኔታዎችን ለመረዳትና
ውጤታማ ለመሆን መስራት ነው። ይህ ደግሞ በአንድ ሌሊት ተፈጽሞ የሚያድር ሳይሆን ዕድሜ ልካችንን መቀጠል ያለበት
ነው። ራሳችንን ከራስ ወዳድነት፤ ከሸፍጠኝነት፤ ከቁጭትና ከፍርሃት በመከላከሉ እንግፋበት፤ ብቅ ባሉ ቁጥርም ወዲያው
እንዲያስወግድልን እግዚአብሔርን እንለምነው። የእነዚህን ስሜቶች መከሰት እንደተገነዘብን ወዲያውኑ ከሰው ጋር መወያየት፤
ያስቀየምነው ሰው ካለ በፍጥነት እርምት ማድረግ ይኖርብናል። ከዚህ በኋላ ሀሳባችንን በቁርጠኝነት ልንረዳው ወደምንችል
ሰው እናዞራለን ። መመሪያችን ሌሎችን መውደድና መቻል ይሆናል።

10ኛ ደረጃ ተስፋዎች


እናም እኛ ከዚህ በኋላ ከምንም፣ ከማንም ጋር፤ከአልኮልም ጋር መታገላችንን አቁመናል። ምክንያቱም አሁን
የምንገኝበት ሁኔታ የአእምሮ ጤንነታችን የሚመለስበት ስለሆነ ነው። የአልኮል ናፍቆት አያስጨንቀንም። ቢያሰኘንም እንኳ
የእሳት ወላፈንን እንደምንሸሽ ከአጠገቡ እንሸሻለን። ለዚህም ምላሽ የምንሰጠው ጤናማና ፈር በያዘ አኳኋን ነው፤ ይህ ደግሞ
ሳናውቀው ወዲያውኑ የተከሰተ ሆኖ እናገኘዋለን። እንዲሁም ስለ አልኮል መጠጥ የያዝነው አዲስ አቋም የተሰጠን በእኛ በኩል
ሳናስብ ወይም ጥረት ሳናደርግ መሆኑ ይገባናል። በቃ እንዲሁ ይመጣል፤ ተአምሩ ደግሞ እዚህ ላይ ነው። አንታገለውም፤
ፈተናውንም አንሸሸው። በገለልተኛ ስፍራ ጥበቃና ከለላ ተደርጐልን የተቀመጥን ያህል ይሰማናል። ቃለ መሃላ መፈጸም
ሳያስፈልገን ችግራችን ተወግዷል። በእኛ በኩል ችግር የለብንም። ድፍረትም ሆነ ፍርሃት አይሰማንም። በመንፈሳዊ ሁኔታ ብቁ
ሆነን እስከተገኘን ድረስ ምላሻችን የሚሆነው ይህ ነው።

18
11ኛ ደረጃ
በተረዳነው መጠን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት የተሻለ ለማድረግ፣ በእኛ ላይ ስላለው በጎ ፈቃድና ይህንንም
ለመፈፀም ስለሚያሻን ኃይል ለመለመን በፀሎትና በተመስጦ አዘወትረን ተጋን።

አሥራ አንደኛው እርምጃ ፀሎትና ተመስጦ ማድረግን ይመክራል። ፀሎትን በተመለከተ አይናፋሮች መሆን የለብንም፣
ከኛ የተሻሉ ሰዎች አዘወትረው ይጠቀሙበታል። አግባብ ያለው አቋም ከያዝንና የምንሰራበት ከሆነ ውጤት ይኖረዋል። ይህን
ጉዳይ አደብዝዘን ማለፍ ቀላላ ነው፣ ይህም ሆኖ ግን እርግጠኛ የሆኑና ዋጋ ያላቸው አስተያየቶችን ማቅረብ እንችላለን ብለን
እናምናለን። ማታ ወደመኝታችን ስንሄድ ያለፈውን ቀን ውሎአች ገንቢ በሆነ መልኩ መቃኘት ይኖርብናል።ውሎአችን ቁጭት፣
ራስ ወዳድነት ፣ ሸፍጥ ወይም ፍርሃት ነበረበት? ይቅርታ መጠየቅ ያሻን ነበር ይሆን? ከሌላ ሰው ጋር ወዲያውኑ መነጋገር
ይገባን የነበረብንን ጉዳይ ለራሳችን ይዘን አቆይተናል? ያገኘነውን ሁሉ በደግነትና በፍቅር ስሜት ቀርበናልን? የተሻለ ማድረግ
የምንችለው ነገር ነበር ይሆን? አብዛኛውን ጊዜ ያሰብነው ስለኛው ስለራሳችን ነበርን? ወይስ ደግሞ ለሌሎች ማድረግ
ስለምንችለው ወይም በሕይወት ጉዞአችን መያዝ ስለአብን ስንቅ አስበን ነበር? ይህን ስናደርግ ግን ላለመጨነቅ፣ ላለመፀፀትና
ከመጠን በላይ ላለማሰብ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፣ በሌሎች ዘንድ ያለንን ጠቃሚነት ይቀንሰዋልና። የዕለት ውሏችንን
ቃኝተን ስናበቃ፤ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በመለመን፤ ምን ዓይነት የእርማት እርምጃዎች መወሰድ እንዳለብን
እንጠይቀዋለን።
በማግስቱ ጠዋት ስንነቃ ስለመጭዎቹ ሃያ አራት ሰዓታት እናስብ። ለዕለቱ ያሉንን ዕቅዶች እናጥናቸው፣
ለተግባራዊነታቸው ከመነሳታችን በፊትም እግዚአብሔር አስተሳሰባችንን እንዲመራልን፤ በተለይም በራስ ከማዘን፤ ከሸፍጥ
ወይም ራስን ከማስቀደም እንከኖች ነፃ እንዲያደርገን እንጠይቀው። በዚህ ሁኔታም እግዚአብሔር እንድንጠቀምበት የሰጠንን
አዕምሮ አቅማችን በፈቀደ መጠንና በልበ ሙሉነት ለመጠቀም የሚያስችለንን ዋስትና እናገኛለን። አስተሳሰባችን ከአሳሳች
ምክንያቶች በፀዳ መጠን ስለሕይወት የሚኖረን አስተሳሰብ ከፍ እያለ ይሄዳል።
ስለ ዕለት ውሎአችን ስናስብ በሁኔታዎች ላይ መወሰን ያዳግተን ይሆናል። የትኛውን መንገድ መያዝ እንዳለብን
ለመወሰን እንቸገር ይሆናል። እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚያነሳሳ መንፈስ፤ አስተዋይነት ያልተለየው አስተሳሰብ ወይም ለውሳኔ
የሚያበቃ አቋም እንዲሰጠን እንጠይቀዋለን። ከዚያም እንዝናና፤ ነገሩንም በቀላሉ እንየው። ትግል አንገጥምም። ይህን ለአንድ
አፍታ ከሞከርን በኋላ መነሻው ላይ በምናገኛቸው በትክክለኛ መልሶች እንገረማለን። ቀደም ሲል የትንቢት ስሜት ወይም
በአጋጣሚ የሚሰማ የመንፈስ መነሳሳት ይመስለን የነበረው ደረጃ በደረጃ ወደ አእምሮአችን የሥራ ድርሻነት ይሸጋገራል። ገና
በቂ ልምድ ያላዳበርንና ከእግዚአብሔር ጋርም በሕሊናችን የተገናኘነው ገና በቅርቡ ስለሆነ፤ ሁልጊዜ ሁኔታዎቹ ሊገለጹልን
አይችሉም። በዚህ ላይ የችኩልነት መታከል ለተለያዩ አጓጉል ድርጊቶችና ሀሳቦች ሊዳርገን ይችላል። ሆኖም ጊዜው እያለፈ
ሲሔድ አስተሳሰባችንም በይበልጥ ወደ መገለፅ ደረጃ እንደሚደርስ እንረዳለን። በእርሱም ለመተማመን እንበቃለን።
ለተመስጦ የመደብነውን ጊዜ የምናጠናቅቀው፤ በቀኑ ውሎአችን ተከታዩ እርምጃችን ምን መሆን እንዲታየንና
የሚገጥሙንን ተመሳሳይ ችግሮች ለመቋቋም የሚያስፈልገንን ማንኛውንም ነገር እንዲሰጠን በመጸለይ ነው። በፀሎታችንም
ለራሳችን ብቻ የምናቀርበው ጥያቄ እንዳይኖር በመጠንቀቅ በተለይ ከራስ ፈቃድ ነፃ ስለመሆን እንጠይቅ። ሆኖም ሌሎችንም
የሚረዳ ከሆነ ለራሳችን መጠየቅ እንችላልን። መቼም ቢሆን ግን ፀሎታችን ለግል የራስ ወዳድነት ግባችን እንዳይሆን
እንጠንቀቅ። ብዙዎቻችን ይህን በማድረግ ብዙ ጊዜ አባክነናል፣ ውጤት ግን አልተገኘበትም። ለምን እንደሆነ ይህም በቀላሉ
ይገባችኋል።

19
ሁኔታዎች አመች ሆነው ከተገኙ የትዳር ጓደኛችንን ወይም ጓደኞቻችንን በጧቱ የተመስጦ ኘሮግራማችን ከጐናችን
እንዲሆኑ እንጠይቃቸው። ጧት ጧት የሕሊና ፀሎት የሚያዝ እምነት ተከታዬች ከሆንን፣ ይህንንም እንፈፅም። የሃይማኖት
ተቋማት አባልነት ከሌለን፤ የተወያየንባቸውን መርሆዎች ጎልተው የሚያሳዩ ጥቂት የፀሎት ስንኖችን መርጠን እናስታውስ።
በዚህ ጉዳይ ሊረዱን የሚችሉ በርካታ መጽሐፍትም አሉ። እነኝህንም በሚመለከት ጥቆማ ከቄስ፣ከፓስተር ወይም ራቢ
ማግኘት ይቻላል። ሃይማኖተኞች ምኑ ላይ እውነት እንዳላቸው ለማየት ፍጠኑ። የሚለግሱትንም ጥቅም ላይ አውሉት።
በዕለት ውሎአችን እየገፋን ስንሄድ ካልተረጋጋን ወይም ጥርጣሬ ከገባን ቆም እንበልና ልክ ስለሚሆነው ሀሳብ ወይም
እርምጃ እንጠይቅ። እኛ የዕለቱ ትርኢት መሪ አለመሆናችንን ሳናቋርጥ በማስታወስ በየቀኑ ደጋግመን ደጋግመን ራሳችንን ዝቅ
በማድረግ «አንተ ያልከው ይፈጸማል» እንበል። ከዚህ በኋላ ለመቅበጥበጥ፤ ለፍርሀት፤ ለጭንቀት፤ ለንዴት፤ ለራስ ማዘን
ወይም ላልተጠና ውሳኔ የመጋለጣችን አደጋ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል። የበለጠ ውጤታማ እንሆናለን። በቀላሉ አይደክመንም፤
ምክንያቱም እንደ ቀድሞው ሕይወትን ለእኛ እንድትስማማ ለማድረግ በሚደረግ ጥረት የኃይላችንን ማገዶ በከንቱ
አናቃጥልምና ነው። ይህም ውጤት አለው በእውነትም ውጤት ያስገኛል።

12ኛ ደረጃ
እነኚህን እርምጃዎች ከወሰድን በኃላ የደረስንበትን መንፈሳዊ ንቃት ከተላበስን በኋላ እኛ ያገኘነውን መልዕክት ለአልኮል
ሱሰኞች የማድረስና እንዲሁም ከላይ የዘረዘርናቸው ሁሉ በሕይወት ጉዞአችን መርሕ በማድረግ ልንለማመዳቸው ወሰንን።

ተግባራዊ ተሞክሮ እንደሚያረጋግጠው ከሌሎች የአልኮል ሱሰኞች ጋር በርትቶ የመሥራትን ያህል ከመጠጣት ነፃ
ለመውጣት ዋስትና የሚሰጥ ነገር የለም። ሌሎች ሙከራዎች ባልተሳኩበት ይህ ውጤታማ ሆኗል። ይህ አሥራ ሁለተኛው
ምክር ነው፤ ይህን መልዕክት ለሌሎች የአልኮል ሱሰኞች አድርስ! ሌላ ማንም ያላደረገውን በማድረግ አንተ እነሱን መርዳት
ትችላለህ። ሌሎች ያልተሳካላቸውን የአልኮል ሱሰኛን በራስ መተማመን የምታረጋግጠው አንተ ነህ፤ ይህም ሆኖ በጣም
የታመሙ መሆናቸውንም አትርሳ። ይህም የአልኮል ሱሰኛ ካልሆነው ይልቅ የአልኮል ሱሰኛው በሌላው የአልኮል ሱሰኛ ላይ
ተፅዕኖ የማሳደር አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ይመስላል። ከዚህም በተጨማሪ ለዘለቄታው መጠጥ ለመተው የአልኮል
ሱሰኛው፣ ከሌላው አልኮል ሱሰኛ ጋር ጠንክሮ መሥራቱ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ይጠቁማል።
የቢል ታሪክ- ጓደኛዬ እነዚህን መርሆች በማናቸውም ተግባሮች የማስመስከር ግዴታ እንደተጣለብኝ አስምሮበት
ነበር። በተለይም እርሱ ከእኔ ጋር እንዳደረገው ሁሉ እኔም ከሌሎች ጋር እንድሠራ አጥብቆ አሳሰበኝ። እምነት ያለ ምግባር
የሞተ ነገር ነው ነበር ያለኝ። ይህ አባባል በመጠጥ ሱሰኞች ዘንድ በእጅጉ አስፈሪ እውነታ ነው! ለምን ቢሉ አንድ የአልኮል
ሱሰኛ መንፈሳዊ ሕይወቱን በሥራና ራሱን ለሌሎች አሳለፎ በመስጠት ካላሟላውና ካላሳደገው፣ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎችና
እንቅፋቶች መቋቋም አይታየውም። ካልሰራ ደግሞ ያለምንም ጥርጥር ወደ መጠጥ ይመለሳል፣ ከጠጣ ደግሞ መሞቱ የማይቀር
ነው። ያኔ ታድያ እምነትም ይሞታል። በእኛ በኩል ያለው ይህን ይመስላል። ባለቤቴና እኔ ሌሎች የአልኮል ሱሰኞችን መርዳትና
ችግሮቻቸውን መፍታት የሚለውን ሀሳብ በደስታ ተቀበልነው። የቀድሞ የቢዝነስ ሸሪኮቼ ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ያህል የእኔን
መለወጥ ለማመን ተስኗቸው ስለነበር ይህ ነው የሚባል ሥራ ያልነበረኝ በመሆኑ አጋጣሚው መልካም ሆነልኝ። በወቅቱም
ገና በማገገም ላይ የነበርኩ ከመሆኑም በላይ በራስ የኃዘን እና ቁጭት ሞገድ እንገላታ ነበር። ይህ ደግሞ አንዳንዴ ወደ መጠጥ
እንድመለስ የሚገፋፋኝ የነበረ ቢሆንም በእኔ በኩል ግን ሌሎቹ የመከላከያ ሙከራዎች ሲከሽፉብኝ ከአንዱ የአልኮል ሱሰኛ
ጋር በመሥራት ቀኑን ማሳለፍ መቻሌን ብዙም ሳልቆይ ተረዳሁ። ከተስፋ መቁረጥ ጋር በተያያዘ ወደ ቀድሞ ሆስፒታሌ ብዙ

20
ጊዜ ሄጃለሁ። እዚያም አንድ ሰው በማናገር ብቻ በሚያስገርም ሁኔታ መረጋጋት በውስጤ ይፈጠራል። ለመኖር የሚደረግ
ዕቅድና ጥረት ችግርን ለመቋቋም ያስችላል።
ማጠቃለያ
ግን ደግሞ መንፈሳዊውን መርሃ ግብር ተወት አድርገን በተቀናጀነው ድል መዝናናትን ቀላል ሆኖ እናገኘዋለን። ይህን
ካደረግን ለችግር መጋለጣችን አይቀርም፤ አልኮል የረቀቀ ባለጋራ ነውና። ከአልኮል ሱስ ገና አልዳንም። እንደ እውነቱ ከሆነ
ያገኘነው መንፈሳዊ ሁኔታዎችን ለመጠበቅ የሚረዳን ዕለታዊ ፋታ ነው። እያንዳንዱ ቀን የፈጣሪን ራዕይና ፈቃድ
በእንቅስቃሴዎቻችን ውስጥ ሁሉ ተግባራዊ የምናደርግበት ነው። «እንዴት ይሆን በይበልጥ ላገለግልህ የምችለው? ፈቃድህ
(የኔ ሳይሆን) ይፈጸማል»። እነዚህ ሀሳቦች ምንጊዜም ከእኛ ሊለዩ አይገባም። በዚህ ዓይነት የምንመኘውን ሁሉ በፈቃደኝነት
ኃይል ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን። ስናጤነውም ሁኔታው ፈቃደኝነትን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው።
በዚህ ሁኔታ አደግን፡፡ እርስዎም ይህን መፅሀፍ በእጅዎ የያዙ እርስዎ ብቻ ቢሆኑም እንኳ ማደግ ይችላሉ፡፡
መጽሐፍም ለጅማሮ የሚያስፈልጉዎትን ነገሮች ሁሉ ይዟል ብለን እናምናለን፣ ተስፋም እናደርጋለን፡፡ ምን እያሰቡ እንደሆነ
እናውቃለን፡፡ በራስዎ ለራስዎም የሚነግሩት ‹‹ርብትብትና ብቸኛ ነኝ፡፡ ያን ማድረግ አልችልም፡፡›› እያሉ ነው፡፡ ሆኖም ማድረግ
ይችላሉ፣ ከራስዎ እጅጉን የሚልቅ የኃይል ምንጭ ማግኘትዎን ረስተዋል፡፡ እገዛ እየተደረገልን ያገኘነውን ስኬት የማባዛቱ
ተግባር በፈቃደኝነት፣ በትዕግሥትና በጥረት ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡

12ኛ ደረጃ ተስፋዎች


ሕይወት አዲስ ትርጉም ያገኛል። ይህም የሚሆነው ሰዎች ከሕመማቸው ሲያገግሙ ለማየት ስትበቃ፣ ከራሳቸው
አልፈው ሌሎችን ሲረዱ ስታይ፣ ብቸኝነት በኖ ሲጠፋ፣ በአንተ ዙርያ ማህበር ተጠናከሮ ስታይ፣ ጋባዥ ጓደኞች ሲኖሩህ -
በመሆኑ ሊቀርብህ ወይም ሊያመልጥህ የማይገባ ተሞክሮ ነው። አንተም ብትሆን እንዲቀርብህ የማትፈልግ መሆኑን
እናውቃለን። በተቻለ ሁሉ ከአዲስ መጦች ጋር ቶሎ ቶሎ ግንኙነት ፍጠር፣ እናም አብሮነታችን የሕይወታችን ብሩህ ፍንጣቂ
ይሆናል።

21

You might also like