Professional Documents
Culture Documents
PA00T7JG
PA00T7JG
ማውጫ
መግቢያ
የሥልጠና መመሪያው ለማን እና እንዴት ተዘጋጀ
ርዕስ 1. ስርዓተ-ፆታና ሀይል
1.1. የትውውቅ ክፍለ- ጊዜ 1
1.2. የራስን አመለካከት መፈተሽ 3
1.3. ስለ ስርዓተ-ፆታ እንወቅ 6
1.4. እንደ ወንድ ሁን እንጂ 10
ርዕስ 2. ወንዶችና ጤና
2.1 ወንዶችና ጤና 15
ርዕስ 3. ዕጽ መጠቀም
3.1 ዕፆች ምንድናቸው? 20
3.2 አልኮልን አብዝቶ መውሰድ አደጋውና ኤች አይ ቪ 23
3.3 ውሳኔ ሰጪነት እና አደንዛዥ እጽን መጠቀም 28
ርዕስ 4. ጥቃት
4.1 ጥቃት ምንድነው? 30
4.2 በዕለት ተዕለት ኑሮ ሊያጋጥም የሚችል ወሲባዊ ጥቃት 35
4.3 በማህበረሰባችን ውስጥ ጥቃት የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ 37
ርዕስ 5. እርምጃዎችን መውሰድና ለውጥን ማምጣት
5.1 በዝምታ አትመልከቱ፤ የመፍትሄ እርምጃ ውሰዱ 39
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ምሥጋና
ፖፑሌሸን ሰርቪስ ኢንተርናሸናል (ኢትዮጵያ) ይህን የአቻ ለአቻ መመሪያ ኢንጄንደር ሔልዝ
ኢትዮጵያ፡ የወንዶች አጋርነት መመሪያ መሠረት በማድረግ አዘጋጅቷል
ፖፑሌሸን ሰርቪስ ኢንተርናሸናል ኢትዮጵያ ይህን የአቻ ለአቻ መመሪያ ሙያዊ አስታያየት በመስጠት
እና እርማት በማድረግ ለአዘጋጆች ፍሬህይወት ታከለ ፡ መኩሪያ ይልማ፡ ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል፡
ይህ የአቻ ለአቻ የመወያያ መመሪያ ዝግጅት ስራ የተሳካው የአሜሪካን ህዝብ እና መንግስት በአሜሪካን
ፕሬዝዳንት አስቸኳይ የኤድስ እርዳታ እቅድ (ፔፕፋር) ቀና እገዛ ነው፡፡ ይህ የስልጠና መመሪያ
የተዘጋጀው ፒኤስአይ/ ኢትዮጵያ በሚተገብረውና ኤች አይ ቪን በመከላከል ሥራ ይበልጥ ትኩረት
ለሚሹ ህብረተሰብ ክፍሎች ላይ እየሰራ በሚገኝ በዩ ኤስ አይ ዲ የሙሉ ኤች አይ ቪን የመከላከል
ፕሮጀክት በኩል ነው፡፡ የስልጠና መወያያው የተዘጋጀው ኢንጀንደር ሄልዝ በወንዶች አጋርነት
ፕሮግራም ያዘጋጀውን ማኑዋል ሙሉ በሙሉ መሰረት በማድረግ እና የተወሰነ ለውጥ በማድረግ
ነው፡፡ የስራው ይዘት እና በውስጡ የተካተቱት ሀሳቦች የፒኤስአይ/ኢትዮጵያ ሀላፊነት ሲሆኑ፤
የአሜሪካን መንግስትንም ሆነ የ ዩ ኤስ አይ ዲን አቋም ወይም አመለካከት አያንፀባርቅም፡፡
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
መግቢያ
ለበርካታ ጊዜያት ወጣትና ጎልማሳ ወንዶች ከልጃገረዶችና ከእናቶች ይልቅ ጤናቸው እንደተሟላላቸው እና
አነስተኛ የስነተዋልዶ ጤና ችግር እንዳላቸው ተደርጎ ሲታሰብ ቆይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጎልማሳ እና
ወጣት ወንዶች ከሴቶች ይልቅ በባህሪያቸው ቁጡ፣ ለጤናቸው ብዙም ደንታ የሌላቸውና ከነሱም ጋር አብሮ
መስራት አስቸጋሪ እንደሆነ ተደርጎ ሲወሰድ ቆይቷል፡፡ ማህበረሰቡ በወንዶች አስተዳደግና ባህሪ ላይ
ያሳረፈውን አሉታዊ ተጽዕኖ በውል ሳንረዳ ባጠቃላይ ወንዶች በወንዶች ላይ እንዲሁም በሴቶች ላይ ጥቃት
ፈፃሚ እንደሆኑ ሲወሰድ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት
የወንዶችን የጤና ሁኔታ ለማማሻሻል ማህበረሰቡ በአስተዳደጋቸውና በባህሪያቸው ላይ ያሳረፈውን ተጽእኖ፤
የሚገኙበትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፤ የሚኖራቸውን የተለየ የጤና ፍላጎት በመስኩ የተሰማሩ
የጤናው ዘርፍ ባለሞያዎች ትኩረት ሰጥተው መረዳት እንደሚገባቸው ያመለክታሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
ላለፉት 20 ዓመታት በሴቶች መብት ጥበቃ ዙሪያ ሲካሄዱ የነበሩ እንቅስቃሴዎች የልጃገረዶችንና የእናቶችን
ማህበራዊ ደህንነት እና ጤንነት ለማረጋገጥ፤ ሴቶች እራሳቸውን የቻሉ ዜጎች እንዲሆኑ የሚደረገውን ጥረት
ከዳር ለማድረስና በሁለቱ ፆታዎች መካከል እኩልነትን ለማስፈን ወንዶችን ማሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ
አስምሮበታል፡፡
ወንዶች ከዕድገታቸው ጋር ተያይዞ በወረሱት አስቸጋሪ ወንዳወንድነት ባህሪ ምክንያት ባለፉት ጥቂት አመታት
ጊዜ ውስጥ ከሴቶች ይልቅ በትራፊክ አደጋ፣ የራስን ህይወት ማጥፋት፣ ጥቃት በመፈፀም እንዲሁም በከፍተኛ
ደረጃ አልኮልና የአደንዛዥ እፅ ተጠቂ እየሆኑ እንደመጡ ይታወቃል፡፡ ወንዶች ባላቸው የወንዳወንድነት ባህሪ
ምክንያት ከሴቶች ይልቅ ለእንደነዚህ እና መሰል ችግሮች ተጋላጭ ናቸው፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች ለመለወጥና
የወንዶችና ሴቶችን ለችግር ተጋላጭነት ለማስወገድ በሥርዓተ-ፆታ አመለካከት የተቃኘ ፕሮግራም ነድፎ
ሥራ ላይ ማዋልን ይጠይቃል፡፡
ወንዶችና ኤችአይቪ/ኤድስ
በአብዛኛው የአለማችን ክፍል የሚገኙ ጎልማሳና ወጣት ወንዶች በባህሪያቸው ምክንያት ራሳቸውንና የፍቅር
ጓደኛቸውን ለኤችአይቪ ያጋልጣሉ፡፡ በአማካይ ሲታይ ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ከአንድ በላይ የሆኑ የወሲብ ጓዳኛ
አላቸው፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ኤች አይቪ ከሴቶች ወደ ወንዶች ይልቅ ከወንዶች ወደ ሴቶች በቀላሉ
ይተላለፋል፡፡ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኝ ወንድ ቫይረሱ በደሟ ውስጥ ከሚገኝ ሴት ይልቅ ቫይረሱን በቀላሉ
ወደ ሌሎች የማስተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ወንዶችን የግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም ወንድነታቸው
ማረጋገጫ አይነተኛ መንገድ እንደሆነ አድርገው ይወስዱታል፡፡
ወንዶቸ ከአቻዎቻቸው የሚደርስባቸውን ግፊት ለመቋቋምና ወንድነታቸውን ያስመስከሩ ከአንድ በላይ የወሲብ
ጓደኛ ስለሚኖራቸው ለኤችአይቪ የሚኖራቸው ተጋላጭነትም የዛኑ ያህል ይጨምራል፡፡ ጥናቶች በተጨማሪ
እንደሚያመለክቱት በገጠርና በከተማ አካባቢዎች መታቀብን የመረጡ ወንዶች በአቻዎቻቸው ወይም ቅርብ
ጓደኞቻቸው እንደ ደካማ ወይም ግንኙነት መፈፀም እንደማይችሉ ሰነፎች ተደርገው ስለሚቆጠሩ ከአንድ በላይ የፍቅር
ግንኙነት እንዲመሰርቱ ይገደዳሉ፡፡ በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙ ወንዶች በኮንዶም አጠቃቀም ላይ ባላቸው
አነስተኛ እውቀት፣ የኮንዶም ስርጭት መዛባት፣ እንዲሁም ያለኮንዶም ግንኙነት መፈፀም የበለጠ ርካታን ይሰጣል
የሚል የተሳሳተ ግንዛቤና ማስረገዝን እንደወንድነትና ወጣትነት ማረጋገጫ አድርጎ ከመመልከት የተዛባ አመለካከት ጋር
ተዳምሮ በኤችአይቪ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ የመጠቃት እድላቸውን ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የወንዶች ጥቃት ፈፃሚነት እና በወሲብ ጓደኛቸው ላይ የሚያደርሱት በደል በተፈጥሮ ያገኙት ሳይሆን በማህበረሰቡ
ውስጥ ካለው የስርዓተ ፆታ ደንቦችና ባህሪያት የመነጨ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት
አንዳንድ ወንዶች በሴቶች ላይ የሚፈፅሙት ጥቃት ትክክለኛና በወንድነታቸው ምክንያት ይህንኑ ለመፈፀም ስልጣን
ያላቸው፣ ትዳርንም አጽንቶ ለማቆየት ተገቢ የሆነ የዲሲፕሊን እርምጃ አድርገው ሊወስዱት እንደሚችሉ እንገነዘባለን፡፡
የትውውቅ ክፍለ-ጊዜ
ደረጃ 1፡
ትውውቅ
ራስን ማስተዋወቅ
• ተሳታፊዎቹን እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት አመቻቹ/አሳታፊው እራሱን
ያስተዋውቅ
1 7
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ደረጃ 2
እርስ በእርስ መተዋወቅ /የጥንድ ትውውቅ
• ይህኛው ትውውቅ አንድ ለ አንድ ምክክር /ጥንድ (ሁለት ሁለት) በመሆን ትውውቅ
ማድረግ::
2
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የስልጠናው አላማ ፡-
በስርዓት ፃታ ዙሪያ ያሉ አመለካከቶችን መዳሰስ
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡-
አራት ምልክትና ‘በጣም እስማማለሁ’፣ ‘በጭራሽ አልስማማም’ ፣ ‘እስማማለሁ’ ፣
‘አልስማማም’ የሚሉ ካርዶች፡፡
ለተሳታፊዎች ከታች የተዘረዘሩትን ዐ/ነገሮች በማንበብ በጣም እስማማለሁ፣
በጭራሽ አልስማማም፣
እስማማለሁ፣ አልስማማም በማለት እና በሰጡትም ሀሳብ ላይ እንዲወያዩ
አድርግ፡፡
ሃሳቦች፡-
99 ኑሮ (ህይወት) ከሴቶች ይልቅ ለወንዶች ይቀላል፡፡
3 9
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ደረጃ 2.
ሁሉንም አባባሎች ካነበባችሁ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ ውይይቱን መምራት
4
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ደረጃ3.
የተግባር እንቅስቃሴውን ስታጠናቅቅ ተሳታፊዎችን ስለ ስርዓተ-ፃታ ያላቸው
የራሳቸውን አመለካከት ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን እንዲያጤኑትና እንዲሁም በዚህ
ስልጠና ሂደትና ከስልጠናው በኋላ ተሳታፊዎች ስርዓተ-ፆታን በተመለከተ በጥንቃቄ
እንዲገመግሙትና እንዲያሻሽሉት ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡
ማጠቃለያ
ማንኛውም ሰው በስርዓተ-ፆታ ዙሪያ የራሱ የሆነ አመለካከት አለው፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ
አመለካከታችን ከሌላው ሰው አመለካከት ጋር ሊጋጭ ይችላል፡፡ ስለሆነም በስርዓተ-ፆታ
ዙሪያ የሌሎችን ሃሳብ ማክበር አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ አመለካከታቸውና ግዴታቸው
ለራሳቸውና ለሌሎች ሰዎች ጐጂ ከሆነ አመለካከታቸው ትክክል እንዳልሆነ ማሣመን
አለብን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በስርዓት ፆታ ዙሪያ እየሰራችሁ እስከሆነ ድረስ በስርዓት
ፆታ ዙሪያ ያላችሁን እሴቶችና አመለካከት መገምገም ጠቃሚነት አለው፡፡
5 11
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የርዕሱ ዋና አላማ
• የስልጠና ተሳታፊዎች ስለ ፆታና ስርአተ ፆታ ፅንሰ-ሃሳብ ምንነትና ልዩነት
እንዲያውቁ ለማድረግ፡፡
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡-
• ለተሳታፊዎች በቂ የስርዓተ ፆታ ጨዋታ የማስተማሪያ ፅሁፍ ቅጂ፡፡
ስርዓተ-ፆታ፡-
ማለት በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያገኘ ሴቶች እንደ ሴትነታቸው ወንዶችም እንደ ወንድነታቸው
በተለያዩ ሁኔታዎች እና ጊዜያት ማሳየት የሚገባቸው በቃላትና በድርጊት ባህሪያት የሚገልፅ
ነው፡፡
ደረጃ 2.
ለተሳታፊዎች የተዘጋጀውን የማስተማሪያ ፅሁፍ በማንበብና በማስተማሪያ ፅሁፉ ውስጥ
ያሉትን አረፍተ ነገሮች በመመልከት ፆታ ወይም ስርዓተ-ፆታን የሚገልፁ መሆናቸውን
ጠይቅ/ቂ፡፡
ደረጃ 3.
ተሳታፊዎች የራሳቸውን ግንዛቤ ካቀረቡ በኋላ የሚቀጥለውን ትርጉም እንዲገነዘቡ አድርግ/ጊ፡፡
ደረጃ 4.
ተሳታፊዎችን ከላይ የተገለፀው የስርአተ ፆታ ትርጉም ምን ስሜት እንዳሳደረባቸው ጠይቅ/ቂ፡፡
ደረጃ 5.
በመቀጠልም ተሳታፊዎች በሚኖሩበት አካባቢ የሰርዓተ ፆታ እኩልነት መኖሩንና አለመኖሩን
ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቅ/ቂ፡፡ የሚከተሉት ሃሳቦች በተሳታፊዎቹ ካልተጠቆሙ መካተታቸውን
እርግጠኛ ሁን/ሁኝ፡፡
7 13
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
99 በስራ መስክ ወይም በሃላፊነት ቦታዎች ላይ ከሴቶች ይልቅ አብዛኛውን ስልጣን የያዙት
ወንዶች ናቸው፡፡
ደረጃ 6.
የስልጠና ተሳታፊዎች ስለ ስርዓተ-ፆታ ፍትሃዊነት ሰምተው ያውቁ እንደሆነ ጠይቅ፡፡
በተጨማሪም ስለ ስርዓተ-ፆታ ፍትሃዊነት ትርጉም የራሳቸውን ግንዛቤ እንዲሰነዝሩ እንዲሁም
የስርዓተ- ፆታ ፍትሃዊነት ከስርዓተ-ፆታ እኩልነት የሚለይበትን ሁኔታ እንዲያብራሩ ጠይቅ፡፡
የተሳታፊዎችን ምላሽ ካደመጥክ በኋላ የሚከተለውን ትርጉም እንዲገነዘቡ አድርግ፡፡
8
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ማጠቃለያ
የወንዶች ንቁ ተሳትፎ ላይ የሚያተኩር ማንኛውም ፕሮግራም ዋነኛ አላማ ህብረተሰቡ ስርዓተ-
ፆታን አስመልክቶ ትኩረት እንዲኖረው ድጋፍ ለማድረግ ሲሆን፣ ይህም ሁኔታ ወንዶችና ሴቶች
ጤናማና ደስተኛ ህይወት እንዲኖራቸውና የኤችአይቪን ወረርሽኝ ለመከላከል በሚደረገው
እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና የሚያንፀባርቁ ባህሪያት እንዲኖራቸው ማበረታታት ይገባል፡፡ ይህም
ማለት፡- ወንዶችና ሴቶች ጤናቸውን አስመልክቶ የጋራ ውሳኔ እንዲኖራቸው፤ ግብረ-ስጋ
ግንኙነትን አስመልክቶ የሴቶችን ወሲብ ለመፈፀም አለመፈለግ መብትን ወንዶች እንዲያከብሩ
ማድረግ፤ በወንዶችና ሴቶች መሃከል የሚፈጠረውን ያለመግባባት ያለ ሃይል ጥቃት በውይይት
መፍታት፤ እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች በቤተሰብ ውስጥ የጋራ ኃላፊነት እንዳላቸው እንዲያውቁ
ማስገንዘብን ያጠቃልላል፡፡
9 15
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ስልጠናው የሚወስደው
ጊዜ:
hh 45 ደቂቃ
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች
• ዝርግ ወረቀት (ፊሊፕ ቻርት)
• ማርከር
ደረጃ በደረጃ
የሚከናወኑ ተግባራት
10
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ደረጃ 1:
ተሳታፊዎች እንደወንድ ሁን እንጂ! ተብለው ተጠይቀው ያውቁ እንደሆነ ጠይቅ:: ቀጥሎም
የማገናዘቢያ ጽሁፍ በመመልከት ሰዎች ለምን ይሄንን መሰል ጥያቄ እንደሚሰነዝሩ ፤
በውስጣቸው የሚያካሂደውን ስሜት ጠይቅ::
ደረጃ 2:
ተሳታፊዎችን ከላይ የተጠቀሱትን አባባሎች በቅርበት እንዲያጤኗቸው ንገሯቸው:: ህብረተሰቡ
ወንዶችና ሴቶች ምን አይነት ባህርያት መላበስ እንዳለባቸው የተለያዩ ደንቦችን እንደሚያወጣ
አብራራ:: እነዚህ ደንቦች “የስርዓተ ጾታ ደንቦች“ በመባል እንደሚታወቁ ግለጽ:: ይህ የሆነበት
ምክንያት ህብረተሰቡ ለወንዶችም ለሴቶችም ትክክል ነው ብሎ የሚያስበው አስተሳሰብ፣
ስሜትና ድርጊት ስላለና እነዚህን ደንቦች የወንዶችንና የሴቶችን ህይወት እንደሚገድቡ ወይም
ውስን እንዲሆን ሊያደርጉ እንደሚችሉ አብራራ::
ደረጃ 3:
እንደ ወንድ ሁን እንጂ የሚለውን አባባል በማስታወስ ተሳታፊዎችን በማህበረሰባቸው ውስጥ
ወንዶች ማሳየት የሚገባቸውን ባህርያትን በተመለከተ ከማህበረሰቡ የሚነገሩ አባባሎችን
እንዲጠቅሱ በመጠየቅ ውይይት እንዲደረግባቸው አድርግ::
ደረጃ 4:
ተሳታፊዎች ተጨማሪ የሚሰነዝሩት ነጥብ ከሌላቸው ከታች ወንዶችን አስመልክቶ ለቀረቡት
ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቅ::
• የትኞቹ አባባሎች በቀጣይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ? ለምን?
• የትኞቹ አባባሎች እንዴት በወንዶች እና በሌሎች ጤና ላይ ኤችአይቪን ጨምሮ ጉዳት
ያስከትላል?
• ከተለመደው የማህበረሰብ አስተሳሰብ ወይም ባህርያት ወጣ ባሉ ወንዶች ላይ ምን
አይነት ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ? የማህበረሰቡ አካላትስ እንዴት ይመለከታቸዋል?
11 17
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ደረጃ 5.
በመቀጠልም ከተለመደውና ጎጂ ከሆነው የስርዓተ- ፆታ ሳጥን የተላቀቁ ወንዶች የሚያሳያቸውን
ባህሪያት የሚገልፁ አባባሎችን እንዲጠቅሱ በመጠየቅ ምላሾችን ከአገኝህ በኃላ በተመሳሳይ መንገድ
ከተለመደው አስተሳሰብ ሳጥን ውጭ ያሉ ሴቶች የሚያሳዋቸውን ባህሪያት የሚገልፁ አባባሎች
እንዲጠቅሱ ጠይቅ/ቂ፡፡ በመጨረሻም ተሳታፊዎች የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን የተቀበሉ ወንዶችና
ሴቶች ባህርያት ተመሳሳይ መሆኑን እንዲገነዘቡ ተገቢውን ድጋፍ አድርግ፡፡
ደረጃ 6.
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለተሳታፊዎች ጠይቅ፡፡
• የወንዶችንና የሴቶችን ሚና በተመለከተ ያለን ግንዛቤ፣ ለቤተሰብና ለጓደኛችን ያለን
አስተሳሰብ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድርብን ይችላልን? እንዴት?
• በኑሮአችን የሚያጋጥመንን ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ ወንዶች እንዲያሳዩ የሚጠበቅባቸውን
ባህሪያት እንዴት መታገል እንችላለን? ሴቶችስ? የሴቶችን ባህሪ (የሴቶችን
የበታችነትን የሚያሳይ አመለካከት፣ ልማድ፣ ባህልን) እንዴት መለወጥ ይቻላል?
ማጠቃለያ
ከላይ መገንዘብ እንደቻልነው እነዚህ ልዩነቶች የተመሰረቱት በአብዛኛው በማህበረሰቡ አማካኝነት
ሲሆን ተፈጥሮአዊና ስነ-ፍጥረታዊ ገፅታዎች እንደሌላቸው ማወቅ ይገባል፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ
የሕብረተሰብ መልዕክቶች አብዛኞቹ ጤናማ ሲሆኑ፣ የወንድ ወይም የሴት ባህሪያትን ተቀብለን
እንድንኖር የሚያደርጉን ናቸው፡፡ ይሁንና ማንኛውም ሰው ጤናማ ያልሆኑ መልዕክቶችን የመለየት
ብቃት አለው፡፡ እነዚህ ጤናማ ያልሆኑ መልእክቶች ሰብአዊ መብታችንን እንዳይገደቡ የመከላከል
መብት ያለን መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
ስለ ስርአተ-ፆታ የተነገሩ አባባሎች እንዴት በእኛ እንዲሁም በማህበረሰቡ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ
እንደሚፈጥሩ ግንዛቤ ባገኝን ቁጥር እነዚህ ሁኔታዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎችን ገንቢ
በሆነ መንገድ በመዋጋትና በአንድ ሰው ህይወትም ሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ ጤናማ የሆነ የስርዓተ-
ፆታ ሚናና ግንኙነት እንዲመሰረት አስተዋፆኦ ማድረግ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ሁላችንም የየራሳችንን
የስርዓተ-ፆታ የአስተሳሰብ ሳጥን ለመመስረት ነፃ መሆናችንና እንዲሁም እንዴት እንደ ወንዶችና እንደ
ሴቶች መኖር እንደምንችል ለመምረጥ ነፃነት ያለን መሆናችን መታወቅ ይኖርበታል፡፡
12
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
13 19
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
14
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ርዕስ 2: ወንዶችና ጤና
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች
• ዝርግ ወረቀት
• ማርከር
• የማገናዘቢያ ጽሁፍ፣ 1 የስርዓተ-ጾታ እና ጤና መጠይቅና የተሰጡ መልሶች
15 21
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
በአገራችን ደረጃ ካለው ሁኔታ ጋር በማገናዘብ መግለፅ አስፈላጊ ነው፡፡ በማገናዘቢያ ፅሁፍ የሥርዓተ-
ፆታና ጤና መጠይቅ እና የተሰጡ መልሶችን መሰረት በማድረግ የስልጠናው አሳታፊ ይህን ክፍል
መምራት ይኖርበታል፡፡
ደረጃ 2.
የተሰጡትን መልሶች በመዳሰስ
መልሱ ለምን እንደተሰጠ በዝርዝር
እንዲያደርሱ አድርግ፡፡
ደረጃ 3.
ተሳታፊዎች መልሳቸውን ካቀረቡ
በኋላ ለሁሉም ጥያቄዎች ትክክለኛው
መልስ “ወንዶች” የሚለው መሆኑን አስረዳ፡፡
16
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ደረጃ 4.
እያንዳንዱን ጥያቄ በተመለከተ በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማቅረብ
አወያይ፡፡
99 የወንዶችን ጤና ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ በአካባቢያችን የተለመደ ነውን?
99 ወንዶችን ከሴቶች የበለጠ ለአደገኛ የጤና ችግር የሚያጋልጧቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው ?
99 ወንዶች ለእነዚህ አደገኛ የጤና ጠንቆች የሚጋለጡበት የዕድሜ እርከን የትኛው ነው?
99 ወንዶች ለምንድን ነው ለእነዚህ የጤና ጠንቆችና አደጋዎች በይበልጥ የሚያጋልጡት?
ወንዶች የሚያጋጥማቸው የጤና ችግር
99 ከአስተዳደጋቸው ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
99 እነዚህ የጤና ጠንቆች በራስህ ህይወትና በሌላ ሰው ህይወት ላይ የሚከሰቱበትን ሁኔታ
ለመቀነስ ወይም ለመከላከል ምን ማድረግ ትችላለህ/ሽ?
ማጠቃለያ
በዚህ የትምህርት ክፍልና ቀደም ባሉት የትምህርት ክፍሎች እንደተረዳነው የወንዶች አስተዳደግ
ለጤናቸው በሚያደርጉት ጥንቃቄ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያደርጋል፡፡ በአብዛኛው ወንዶችን
ለሞት አደጋ የሚያጋልጧቸው ሁኔታዎች መንስኤ በአኗኗር ዘይቤአቸው እራሳቸውን ከሚጎዱና
ከሚያጠፋ ሁኔታዎች አለመቆጠባቸው ነው፡፡ በአለም ዙሪያ ወንዶች በህብረተሰቡ ዘንድ
ተቀባይነት ባለው ሁኔታ ነገር ግን ጤናቸውን ሊጎዳ በሚችል መንገድ እንዲኖሩ ይገደዳሉ/
ይገፋፋሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች የፍቅር ጓደኞቻቸውና እራሳቸውን አደጋ ላይ እንዲወድቁ
ያደርጓቸዋል ፡፡ ወንዶች የአኗኗር ዘይቤአቸውን መገምገምና አደጋ ላይ የሚጥሏቸውን ነገሮች
መገንዘብ አለባቸው፡፡ ስለ አደገኛ ሁኔታዎች (ለምሳሌ እፅን መጠቀም፤ ልቅ የሆነ የግብረ-ስጋ
ግንኙነት ባህሪ ማሳየትና በፆታዊ ጥቃት ላይ መሳተፍ፣ ወዘተ… ) መነጋገር፣ መከራከርና መፍትሄና
ድጋፍ መሻት፣ ወንዶች በተለያዩ አደገኛ የጤና ጠንቆች እንዳይጎዱ ይረዳል፡፡ ትኩረት ልንሰጠው
የሚገባው ነገር ይህ የጤና ጉዳይ የወንዶች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሴቶችንም የሚመለከት መሆኑን
ነው፡፡
17 23
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
18
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
19 25
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ስልጠናው የሚወስደው
ጊዜ፡-
hh 30 ደቂቃ
የሚያስፈልጉ ቁሶች
• 4 ዝርግ ወረቀት፤ ማርከር
• የማገናዘቢያ ጽሑፍ-2፡-
ዕፆች ምንድን ናቸው?
20
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ማጠቃለያ
አደንዛዥ ዕፆች የብዙ ሴቶችና ወንዶችን ኑሮን ይነካሉ፡፡ ብዙ አይነት አደንዛዥ ዕፆች ያሉ
ሲሆን አንዳንዶቹ ሕጋዊ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ ሕገ-ወጥ ናቸው፡፡ ሰዎች አደንዛዥ ዕፆችን
እነዲጠቀሙ የሚገፋፋቸው የግለሰብና የሕብረተሰብ ጫናዎችን/ ግፊቶችንና እነዚህ ዕፆች
በአንድ ሰው ኑሮ፣ በሰዎች ግንኙነትና በማህረሰብ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ ማስተዋል ጠቃሚ
ነው፡፡
21 27
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
22
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ትምህርቱ
የሚወስደው
ጊዜ፡
1 ሰዓት
23 29
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች
• የማገናዘቢያ ጽሑፍ -፡-
‹‹አልኮልን የመጠጣት ዝንባሌና ልምድ››
24
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
25 31
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ማጠቃለያ
በአልኮል መጠጥና በኤች አይ ቪ መካከል ያለው ቁርኝት ከተረጋገጠ ረዥም ጊዜን አስቆጥሯል፡፡
በአጠቃላይ አደንዛዥ እፆች ከልቅ የግብረ-ሥጋ ግንኙነትና ከአባላዘር በሽታዎች ኤች አይ ቪ ኤድስን
ጨምሮ ተዛማጅነት አላቸው፡፡ ይህም ማለት እነዚህን አደንዛዥ ዕፆች የሚጠቀሙ ግለሰቦች
በከፍተኛ ደረጃ ሊልቅ የግብረ-ሥጋ ግንኙነትና ለአባላዘር በሽታዎች ኤች አይ ቪን ጨምሮ በቀላሉ
ለመጋለጥ ይችላ፡፡ በመርፌ አማካኝነት አደንዛዥ እፆችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች በአለም ላይ 10%
በኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎችን ይወክላሉ፡፡ በተጨማሪ በቀጣይነት አደንዛዥ ዕፆችን መጠቀም
በሱስ እንድንጠመድና ለተለያዩ የጤና ችግሮች (ለሞት እስከመዳርግ ድረስ) እንድንጠቃ እና በግል
ሕይወታችን ላይ የተለያዩ ችግሮች እንዲከሰቱ ያደርጋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ከሴቶች ይልቅ
በብዛት አልኮል ይወስዳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የሚሆነው አብዛኛውን ጊዜ የአልኮል መጠጥ
መጠጣት የወንድነት መገለጫ እንደሆነ በመቁጠርና ከአቻ ጓደኞቻቸው ለመስተካከልና ለመመሳሰል
ነው፡፡
በመሆኑም በአልኮል መጠጥ ዙሪያ ያሉትን ልማዶች መመርመርና ይህንን ድርጊት የሚያስወግድና
የአልኮል መጠጥን ማዕከል ያደረገ ትርፍ ጊዜን የማሳለፊያና የመዝናኛ ሁኔታን መፍጠር
እንደሚገባን ማሰብ ይኖርብናል፡፡
26
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የማስተማሪያ ፅሑፍ 3
አዎ አይደለም
አንድ ሰው አልኮል ሳይጠጣ ደስተኛ ማህበራዊ ሕይወት
መምራት የሚችል ይመስለኛል
በአንድ ድግስ ላይ ጓደኞቼ መጠጥ እንድጠጣ ጋብዘውኝ እምቢ ብል
ድግሱ ላይ የተካፈልኩ አይመስለኝም
ድግስ ላይ መጠጥ ባይኖር መደሰት አልችልም
እኔ ጠጥቼ ጓደኞች ጠጥተው ባይሆን ኖሮ እንዲጠጡ እንገፋፋቸው ነበር
የማስብላቸው ሰዎች በአልኮል ምክንያት ሲጎዱ አይቻለሁ
ሌሎች መጠጥ በመጠጣታቸው እኔ ተጎድቼ አውቃለሁ
አልኮል በመጠጣቴ የምፀፀትባቸውን ድርጊቶች ፈፅሜአለሁ
27 33
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የስልጠናው ዓላማዎች
የስልጠናው ተሳታፊዎች
h h ፆታ፡- ወንዶች
ትምህርቱ የሚወስደው ጊዜ ፡-
hh 1 ሰዓት
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡-
hh አያስፈልግም
28
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
29 35
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ርዕስ 4- ጥቃት
የትምህርቱ ዓላማ
ተሳታፊዎች በሚቀራረቡ ሰዎችና
በሕብረተሰብ ውስጥ የሚከሰቱ
የተለያዩ የጥቃት አይነቶች
መለየት እንዲችሉ ነው፡፡
ስልጠናው የሚወስደው
ጊዜ፡-
h60
h ደቂቃ
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡-
hአያስፈልግም
h
30
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የጥቃት አይነቶች
• አካላዊ ጥቃት ይህ ማለት የሀይልን ጥቃትን መጠቀም ነው፤ ለምሳሌ መደብደብ፣
መገፍተር፣ በጥፊመምታት ወዘተ.
• ሥነ- ልቦናዊ ጥቃት ማለት ከሌሎች ጥቃቶች ለይቶ ለማስረዳት የሚያስቸግር
ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ ማዋረድ፣ ማስፈራራት፣ መሳደብ፣ ማስጨነቅ፣
ከልክያለፈ ቁጥጥር፣ አላስፈላጊ ቅናት ወዘተ.
• ወሲባዊ ጥቃት አስገድዶ ግብረ-ሥጋ ግንኙነትን መፈፀም ወሲባዊ ትንኮሳን
በማድረግ ማዋረድና ማሳፈርን ያካትታል፡፡
በመቀጠል ከታች የተጠቀሱትን ጥቃት ላይ ያተኮሩ ጽሁፎች በማንበብ ከሳታፊዎች ጋር
ውይይት አድርግ
31 37
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ጽሁፍ 1.
የሙላቱና የለምለም ታሪክ
ሙላቱና ለምለም ባለትዳሮች ሲሆኑ የሙላቱ ቤተሰቦች ዛሬ እነርሱ ቤት ለእራት ግብዣ ይመጣሉ፡
፡ ሙላቱም የቤተሰቦቹን መምጣትና ከእነርሱ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ጓጉቷል፡፡ በመሆኑም ሚስቱ
ባለሙያ እንደሆነችና ጥሩ ምግብ እንደምታዘጋጅ ለማሳየት አስቧል፡፡ ሆኖም ግን ወደ ቤት ሲመለስ
ለምለም አሟት ስለ ነበር ምንም ምግብ አልተዘጋጀም፡፡ በዚህ የተነሳ መላቱ በጣም ተናደደ፡
፡ ቤተሰቡም እርሱ ሚስቱን እንደማይቆጣጠራት እንዲያስቡ ስላአልፈለገ፤ በተፈጠረው ሁኔታ
ለምለምና ሙላቱ ብዙ ተጨቃጨቁ፣ ተጋጩ፣ በመጨረሻም ሙላቱ ለምለምን ደበደባት፡፡
• ሙላቱ ለምለምን መደብደቡ ትክክል ነውን?
• ለምለም ምን ማድረግ ነበረባት?
• በዚህ ገጠመኝ ላይ ሙላቱ ጉዳዩን ለማስተካከል ከዚህ የተለየ ነገር ማድረግ ነበረበትን?
ጽሁፍ 2.
በአንድ የምሽት ዳንስ ቤት ከጓደኞችህ ጋር ስትደንስ ከቆየህ በኃላ ልክ ልትወጣ ስትል ሁለት ጥንዶች
መውጫ በር ላይ ሲጨቃጨቁ አየህ፡፡ ወንዱ አንቺ ውሻ ብሎ ይሰድባታል፤ ከእርሱ ጋር ሆኖ
ከሌላ ወንድ ጋር ለምን እንደማገጠች ይጠይቃታል፤ በፍጹም እንዳልማገጠችና ጭራሽ ሌላ ሰው
እንዳላየችና ከእርሱ ጋር እንደሆነች ነገረችው፡፡ ርሱም አንቺ ዋጋ የሌለሽ ከንቱ ሴት በይ ከዓይኔ
ጥፊ፤ ፈጽሞ ላይሽ አልፈልግም፤ በማለት በሀይል መታት፡፡ እሷም ጮክ ብላ ይህን የማድረግ መብት
እንደሌለው እየነገረችው ወለሉ ላይ ወደቀች፡፡
• ከዚህ ሁኔታ ላይ ምን ተረዳህ?
• በዚህ ሁኔታ ላይ ምን ማድረግ ነበረብህ? ጥለህ መሄድ? ሰውየውን ማነጋገር? ምንም
ካላደረግህ ለምን?
• እኛ ጥቃትን በመከላከል ሂደት ያለብን ኃላፊነት ምንድነው?
32
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ጽሁፍ 3.
ሞገስ ከሐብታም ቤተሰብ የተወለደ በዕድሜው ከፍያለ ወጣት ወንድ ልጅ ነው፡፡ ስህን የተባለችውን
ወጣት አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲመለስ ያገኛትና ሰላምታ ተለዋውጠውና አውርተው ይለያያሉ፡
፡ በማግስቱም እንዲሁ ያገኛታል፡፡ ይህ መገናኘት በተደጋጋሚ ይሆንና አንድ ቀን እንደተለመደው
ሲያገኛት ምን ያህል እንደሚወዳት ይነግራታል፡፡ የዚህ ግንኙነት የተጠናከረ ስለመጣ ሲገናኙ
ይስማታል፤ ጡቷን ይዳብሳል፤ በዚህ ሂደት ስህን ቆም ትልና በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማትፈልግ
ትነግራዋለች፡፡ ሞገስ በጣም ይናደድና ከአንቺ ጋር ብዙ ጊዜ አባክኛለሁ ጓደኞቼ ምን ይሉኛል
ይላታል፡፡ ሀሳቧንም እንድትቀይር ለማግባባት ይሞክራል፡፡ አቋሟን ላለመቀየር መወሰኗን ሲያውቅ
በብስጭት ይጮህባታል፤ በሀይል ይሰድባትና ወደ መሬት በመጣል አስገድዶ ይደፍራታል፡፡ ርሷም
እስከ መጨረሻው አይሆንም ድርጊትህን አቁም እያለች ብትጮኸም አልሰማትም፡፡
• ይህ ከላይ ያነበብነው ታሪክ የሀይል ጥቃት ነውን? ከሆነ ለምን? ካልሆነስ ለም ጥቃት
አልሆነም?
• ሞገስ ምን ማድረግ ነበረበት?
• ስህን ምን ማድረግ ነበረባት?
33 39
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ማጠቃለያ
ጥቃት ማለት አንድ ሰው በሌላው ሰው ላይ ሀይልን መጠቀምና የሚፈልጉትን ለማስፈፀም የሚደረግ
እንቅስቃሴ ነው፡፡ ጥቃት ሌላውን ሰው ለመቆጣጠርና ስልጣንን ለማስከበር የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡
፡ ጥቃት በብዙ አገሮች ይካሄዳል፡፡ መንስኤዎቹ በሰዎች አስተዳደግ ላይ ያተኩራሉ፡፡ በተለይም ወንዶች
ንዴትንና ግጭትን የሚገልጹት የሀይል ጥቃት በመፈፀም ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ጥቃት ተፈጥሮአዊና ጤናማ
የሆነ የሰዎች ግንኙነት መግለጫ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ሆኖም ግን ጥቃት መፈፀምን የምንማረው
ከቤተሰብና በሕብረተሰብ ውስጥ በሚታየው አስተሳሰብ ልምድ ላይ ተመርኩዞ ነው፡፡ በመሆኑም
ጥቃት የመፈፀም ባህሪ በህይወታችን እንቅስቃሴ የምንማረው ስለሆነ ልንተወውና ልንከላከለው
የምንችለው ባህርይ ነው፡፡ ባለፉት የትምህርት ጊዜ እንዳየነው ብዙ ጊዜ ወንዶች የሚያስቡትን ስሜት
በግልጽ ስለማይናገሩትና ስለማይወያዩ፤ ጥቃት መፈፀም እንደአንድ አንድ የስሜት መገለጫ እንደሆነ
አድርገው ይወስዱበታል፡፡ በተጨማሪም ወንዶች ሲያድጉ በሴቶች ሕይወት ላይ የማዘዝ፣ የመወሰንና
የመቆጣጠር መብት እንዳላቸው ስለሚያምኑ ይህንን የበላይነት ስሜት ለመግለጽ ሀይልን ይጠቀማሉ፡
፡ (በተለይም የቤት ውስጥ ሥራን፤ የግብረ-ሥጋ ግንኙነትን በተመለከተ አገልግሎት የማግኘት መብት
እንዳላቸው ያምናሉ፡፡) ይህን አገልግሎት ካላገኙ ጥቃት የመፈፀም (አካላዊም ሆነ የሥነ-ልቦና ጥቃት
(ድብደባና ስድብ ጨምሮ) መፈፀምን እንደመብት ይቆጥሩታል፡፡ እንዲሁም ወንዶች ያሰቡትንና
የወሰኑትን ለማስፈፀም የሀይል ጥቃትን ይጠቀማሉ፡፡ በእነዚህ በህብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው
የወንዶችና የሴቶች ሚና የተነሳ ወንዶች የወንድነታቸው መገለጫ በቁጣና በሀይል በመሆኑ ከሴቶች
ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ስሜታቸውን በሀይል ጥቃት ይገልጻሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ ከሴቶች ጋር
የሚኖራቸውን ግንኙነትና መግባባት ጤናማ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ወንዶች እራሳቸው
ከጥቃት ፈፀሚነት በመታቀብ ሌሎች ወንዶች የሚያደርሱትን የሀይል ጥቃት ለመከላከልና ለማስቀረት
ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
34
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የትምህርቱ ዓላማ
ይህ የትምህርት ጊዜ የሴቶች ኑሮና ሕይወት ነፃና ስኬታማ እዳይሆን ከሚያደርጉት
ምክንያቶች አንዱ ፆታዊ ጥቃት መሆኑን የትምህርቱ ተሳታፊዎች እንዲረዱ ለማስቻል
ነው፡፡
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡-
h h አያስፈልግም
35 41
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ማጠቃለያ
የወሲባዊ ጥቃት መከሰትና ጥቃትን በመፍራት መኖር በብዙ ሴቶች የተለመደ ገጠመኝ ነው፡
፡ ወንዶች ወሲባዊ ጥቃት የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ስለሚያደርጉት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን
ጉዳት ሲገነዘቡት አያስተውሉም፡፡ ሆኖም ግን በወሲባዊ ጥቃት የተነሳ የወንዶችም ሕይወት
ለጥቃት የተጋለጠ መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ለጥቃት የተጋለጡት ሴቶች ማለት ለወንዶች
እህቶች፣ እናቶች፣ ልጆች፣ የአክስትና፣ የአጎት ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ ጓደኞች ወዘተ. ስለሚሆኑ፤ ወንዶች
የሚያሳስባቸው እኒህ ሴቶች በየእለቱ ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ
የሚታየውን ፆታዊ ጥቃት ትክክል ነው ብሎ መቀበል ወንዶች በሴቶች ላይ ጥቃትን እንዲፈጽሙ
ያደርጋል፡፡ ወሲባዊ ጥቃት ሴቶች በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ወቅት ፈቃደኝነታቸውን የማግኘትና ኮንዶም
ለመጠቀም የመደራደር መብት እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡ ሴቶች ተገደው እንዲደፈሩ በዚህም
ምክንያት የመቁሰል ሁኔታና ለኤች አይ ቪ የመጋለጥ አጋጣሚ ይከሰታል፡፡ በመሆኑም ወሲባዊ
ጥቃትን መከላከል የኤች አይ ቪ/ ኤድስን መስፋፋትን ለመከላከል ይረዳል፡፡
36
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የሥልጠናው ዓላማ
በአካባቢያችን የሚገኙ የጥቃት ሰለባዎችን ለመርዳት የሚያስችል ሐብትን
በማፈላለግ ተሳታፊዎች ተጠቂዎችን የሚረዱበትን መንገድ ማፈላለግ፡፡
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡-
hh አያስፈልግም
37 43
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ማጠቃለያ
ብዙ ጊዜ የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ስለደረሰባቸው ጥቃት ለሌሎች ችግራቸውን በመግለጽ
እርዳታ አይጠይቁም፡፡ በተለይ ሴቶች ወንድ ጓደኞቻቸው ወይም ባሎቻቸው ስለአደረሱባቸው
ጥቃት ቢናገሩ ሰምተው ወይም አውቀው ተጨማሪ ጥቃት በበቀል መልክ ያደርሱብናል ብለው
ስለሚፈሩ ችግራቸውን አውጥተው አይናገሩም፡፡ ሌሎች ሴቶች ደግሞ በተለይ በትዳር ውስጥ
ከሆኑ ወይም ልጆች ካሏቸው ጥቃቱን ተቀብለው ጥቃቱን ከፈጸመባቸው ሰው ጋር አብረው
ይኖራሉ፡፡ ትዳራቸውን ቢፈቱ ወይም ከወንድ ጓደኛቸው ጋር ቢለያዩ የሚደርስብን የኢኮኖሚ
ወይም የስነ -ልቦና ችግር ከሚደርስብን ጥቃት ይብሳል ብለው ስለሚያስቡ ጥቃቱን ተቀብለው
ይኖራሉ፡፡ ሴቶች ለጥቃት በሚሰጡት ምላሽ ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ብዙ ሁኔታዎች አሉ
በመሆኑም ከጥቃት ጋር በተያያዙ ሰዎች ላይ መፍረድ ከባድ ይሆናል፡፡ እነዚህ ሰዎች እንዴት
አድርገው ከጥቃት ሊድኑና መፍትሄ የሚያገኙበትን መንገድ እነዲፈልጉ መርዳት አስፈላጊ
ነው፡፡ በተጨማሪም በሕብረተሰቡ ውስጥ ሰዎች ከጥቃት ነፃ የሆነ ሕይወት የሚመሩበትን ሁኔታ
ማመቻቸት አስፈላጊ ነው፡፡
38
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
39 45
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
የሥልጠናው ዓላማ
1. ወንዶች ጥቃትን በመከላከል ዙሪያ ቀዳሚ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉበትን
ሁኔታ ለይቶ ለማወቅ፣
2. ወንዶች ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል እዲችሉና ብቃት እንዲኖራቸው
የሚያስፈልጓቸውን ድጋፍ ለይቶ ለማወቅ እንዲያስችል ነው፡፡
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ፡-
h h አያስፈልግም
40
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
41 47
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ማጠቃለያ
ጥቃት በተለይ ደግሞ ወንዶች ሴቶች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት በየዕለቱ ከዕለት ኑሮአችን
የሚከሰት ጉዳይ ሆኖ ሳለ ብዙ ሰዎች እንደሌላ ጉዳይ አድርገው ይመለከቱታል፡፡ ንቁ የጥቃት
ተከላከይ ግን ጥቃትን እንደሌለ አይቆጥርም፤ ጥቃት እንዳይቀጥል የበኩሉን አስተዋጽኦ
ያደርጋል፤ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ የሚከሰትን ጥቃት ለመከላከልና ለማስቆም የብዙ
ወንዶችን ነንቁ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡ ብዙ ጊዜ ፆታዊ ጥቃት የሚፈፀመው በወንዶች ስለሆነ
ብዙ ወንዶች ጥቃትን ለመከላከልና ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ከሴቶች ይልቅ ወንዶችን
ይሰማሉ፤ በመሆኑም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ሁኔታዎች ብዙ ወንዶች በጥቃት
መከላከል ሂደት እንዲሳተፉ ቅስቀሳ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ በመሆኑም ጥቃት
መከላከል ላይ የተለያዩ ተሰሚነት ያላቸውን ወንዶች ማሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ በእነዚህም
ተሰሚነት ያላቸው፡፡
ወንዶች የመንግስት ባለሥልጣናት የሕብረተሰብ መሪዎች ወዘተ. ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ንቁ ጥቃት
ተከላካይ ሰው በመሆን እርምጃዎችን በመውሰድ ወንዶች ሌሎች ወንዶችን ጥቃት እንዳፈጽሙ
ማሳመንና መከላከል ቀላል ስለማይሆን ወንዶች እርስ በርስ ተደጋግፈው የጥቃት ተከላከይ ሚና
ሊኖራቸው ይገባል፡፡
በወንዶች የበላይነት ላይ የተመረኮዘ የስርአተ -ፆታ ወንዶች የሴቶች ጠባቂዎች ወይም የችግር
ተከላካዮች እንደሆኑ ይገለፃል፡፡ ሆኖም ግን የአንድ ንቁ ፆታዊ ጥቃት ተከላካይ ሰው ሚና
ሴቶችን እንደደካማና ወንዶች በወንድነት ጠንካራ ስለሆኑ ሴቶችን የመጠበቅ ሚና እንዳለበት
በማስብ ሳይሆን ፍትሃዊ ግንኙነትን ለመፍጠርና በሴቶች ላይ የሚከሰተውን ጥቃት ወይም
ወንጀል ለማስወገድ በማሰብ መሆን አለበት፡፡ ይህ ከሆነ ሴቷን በባህል እንደተለመደው ደካማ
አድርገው እንዳይመለከቱ ይረዳቸዋል፡፡ በመሆኑም የወንዶች ተሳትፎ ጥቃትን በመከላከል
ሂደት የተጠቂዎችን ጥንካሬ በማጎልበትና ከጥቃት ነፃ ሆነው እንዲኖሩ በማስቻል ላይ ያተኮረ
መሆን አለበት፡፡
42
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
ለእዚህ መጠይቅ የሚሰጡት ምላሽ በሚስጥር የሚያዝ ነው፡፡ የዚህ ጥናት ውጤት የስልጠናውን
ይዘት ለማሻሻልና የስልጠናውን አጠቃላይ ውጤታማነት ለመመዘን ይረዳል ተብሎ ይታመናል፡
፡ የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች በማንበብ በዓረፍተ ነገሮቹ በከፊል መስማማትዎን ወይም
ያለመስማማትዎን ይግለጹ፡፡
1. የልጅ ሽንት ጨርቅ መለወጥ፣ ገላን ማጠብ እና መመገብ የሴቶች የስራ ድርሻ ብቻ ነው፡፡
ሀ/ እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
2. አንድ ወንድ ከማግባቱ በፊት ብዙ የፍቅር ጓደኞች ሊኖሩት ይገባል
ሀ/ እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
3. ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ብዙ ወሲብ ያስፈልጋቸዋል፡፡
ሀ/እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
4. ኮንዶም የማይለያቸው ሴቶች ለወሲብ ጥያቄ በቀላሉ አውንታዊ ምላሽ የሚሰጡ ናቸው፡፡
ሀ/ እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
5. እውነተኛ ወንዶች በሚታመሙበት ወቅት ወደ ዶክተር መሄድ አያስፈልጋቸውም፡፡
ሀ/ እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
6. አንድ ሰው ከዘለፈኝ ሀይልን በመጠቀም ጭምር ክብሬን አስጠብቃለሁ፡፡
ሀ/ እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
7. ወሲብ ለመፈፀም ፍቃደኛ ካልሆነች አንድ ሰው ሚስቱን ቢደበድብ ምንም ማለት
አይደለም፡፡
ሀ/ እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
8. ርግዝናን መስወገድ /መከላከል የአንድ ሴት ሀላፊነት ነው፡፡
ሀ/ እስማማለሁ ለ/ አልስማማም ሐ/ በከፊል እስማማለሁ
43 49
የወንዶች አጋርነት የአቻ ለአቻ መመሪያ
44
HIV Prevention Project