You are on page 1of 40

ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች

በጤና ዙሪያ የማህበረሰብ ንቅናቄ ለመፍጠር


አጋዥ መረጃዎችን የያዘ መመሪያ
የማህበረሰብ ንቅናቄ መፍጠር ለምን ያስፈልጋል?
በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ብዙ የጤና ችግሮችን ለመፍታት
አብዛኞቹ የማህበረሰቡ አባላት የባህርይ ለውጥ ማምጣት አለባቸው።
ለምሳሌ ተቅማጥና ሌሎች በንፅህና ጉድለት የሚተላለፉ በሽታዎችን
ለመቀነስ ሁሉም የማህበረሰብ አካላት የመፀዳጃ ቤት ሊኖራቸውና
በአግባቡ ሊጠቀሙ ይገባል፣ የወባ በሽታን ለማስወገድ የማህበረሰቡ
አባላት በሙሉ በአጎበር ውስጥ መተኛትና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ
ይኖርባቸዋል፣ ወንዶች በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ አዎንታዊ ተሳትፎ
እንዲኖራቸው። እንዲህ ዓይነት የባህርይ ለውጦችን ለማምጣት
ተሰሚነት ያላቸው የማህበረሰብ አካላትን እገዛ ማግኘት ተገቢ ነው።

1
የመመሪያው አጠቃቀም
በዚህ መመሪያ ውስጥ የሚገኙ ነጥቦች የተዘጋጁት ለጤና ኤክስቴንሽን
ባለሙያዎች ጤናን በተመለከተ ማህበረሰባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር
እንዲያስችሉ ነው። ይህ ማዕቀፍ አራት አጠር ያሉ ነጥቦችን ይዟል።
እነዚህም፦
• ወንዶችን በቤተሰብ ጤና ላይ ማሳተፍ
• የሃይማኖት መሪዎችንና ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች በጤና
ጉዳዮች ላይ ማሳተፍ
• ከግብርና ሴክተር ጋር በጤና ጉዳዮች ላይ አብሮ መሥራት
• ከት/ቤቶች ጋር በጤና ጉዳዮች ላይ አብሮ መሥራት

የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ጤናን


አስመልክቶ በሚሠሩት ሥራዎች ዙሪያ ማህበረሰባዊና ግላዊ ባለቤትነትን
ለማዳበር የሚያግዙ ስልቶችን ከእነዚህ መመሪያዎች ላይ ሊያገኙ
ይችላሉ።

2
ማውጫ
ወንዶችን በቤተሰብ ጤና ማሳተፍ 4
አላማዎች 6
ወንዶችን በቤተሰብ ጤና የማሳተፍ ጥቅሞች 7
ወንዶች ሊሳተፉባቸው የሚችሉባቸው የጤና ጉዳዮች 8
ወንዶችን የማሳተፊያ መንገዶች 10
ቅድመ ጥንቃቄ 11
ጠቃሚ ምክሮች 12

ከት/ቤቶች ጋር በጤና ዙሪያ አብሮ መስራት 14


ከት/ቤቶች ጋር አብሮ መስራት ለምን ያስፈልጋል? 16
ተማሪዎችና ት/ቤቶች ሊሳተፉባቸው የሚችሉ የጤና ጉዳዮች 17
ት/ቤቶችን ለባህሪ ለውጥ ተግባቦት ማሳተፊያ መንገዶች 19

የሀይማኖት መሪዎችንና ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦችን በጤና ጉዳዮች ማሳተፍ 22


የሃይማኖት መሪዎች እና ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች የጤና ባለሞያዎችን
እንዴት ማገዝ ይችላሉ? 24
የሀይማኖት መሪዎችንና ተሰሚነት ያላቸው ጋር ለመወያት የተመረጡ
የጤና ርእሰ ጉዳዮችና ዋና ዋና ነጥቦች 25
ለሃይማኖት መሪዎችና ተሰሚነት ላላቸው ግለሰቦች መደረግ የሚገባቸው
ድጋፎች 27

ከግብርና ሴክተር ጋር በአጋርነት መሥራት 30


የግብርና ባለሞያዎች ለጤና ባለሞያዎች እንዴት ድጋፍ መስጠት ይችላሉ? 32
የግብርና ባለሞያዎች ሊያግዙ የሚችሏቸው የጤና ጉዳዮች 33
ለግብርና ባለሙያዎች መደረግ የሚገባቸው ድጋፎች 35

3
ወንዶችን በቤተሰብ ጤና ማሳተፍ

4
ወንዶች በቤተሰብ ጤና ጉዳዮች ለመሳተፍ ያሏቸው አመለካከቶቸና
ድርጊቶች ማህበረሰቡ ከሚጠብቅባቸው ወይም ከሚሰጣቸው የሀላፊነት
ሚናዎች ይመነጫሉ። ይህም የገዛ ልጆቻቸው እና ቤተሰባቸው ጤና
ለማሻሻል የሚኖራቸውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲቆጥቡ ወይም የሴቶች
ሀላፊነት ናቸው በሚል እንዲተዉ ያደርጋቸዋል። ወንዶችን በስነተዋልዶ
ጤና፣ በእናቶች እና ህፃናት ጤና፣ በኤችአይቪ፣ በስርአተ ምግብ፣ ፆታን
መሰረት ባደረገ ጥቃት እና ሌሎች ጤና ነክ ጉዳዮች ላይ ቀጥታ ተሳታፊ
ማድረግ በጤና ጉዳዮች ላይ ለውጥ ከማምጣቱ ባሻገር ወንዶችና ሴቶች
እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበት ፍትሀዊ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣
ባህላዊ እና ፖለቲካዊ አካባቢ እንዲፈጠር ያግዛል።

5
አላማዎች
• የጤና መልእክቶችን ለወንዶች ማሰራጨት
• ወንዶች በትዳር አጋሮቻቸውና በልጆቻቸው ጤና ላይ በቀጥታ
አለመሳተፋቸው በቤተሰባቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለውን የጤና
ችግር እንዲገነዘቡ ማገዝ
• ወንዶች የቤተሰባቸው ጤና በእጃቸው እንዳለ አመዛዝነው በቤት
ውስጥ ገንቢ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማገዝ
• የቤተሰብን ጤና በማሻሻል ረገድ ወንዶች ሀላፊነት እንዲወስዱ
ንቅናቄ መፍጠር
• በማህበረሰቡ ውስጥ ወንዶች በቤተሰብ ጤና ዙሪያ ለሚያደርጉት
ተሳትፎ ተቀባይነት እንዲኖር ማድረግ

6
ወንዶችን በቤተሰብ ጤና የማሳተፍ ጥቅሞች
• በወሲባዊና ስነተዋልዶ ጤና፣ በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ በኤችአይቪ፣
ስርአተምግብ፣ ፆታን መሰረት ባደረገ ጥቃትና እና ሌሎች ጉዳዮች
ላይ ገንቢ ተፅዕኖ ፈጥረው ለውጥ እንዲመጣ ያግዛሉ።

• ወንዶች የቤተሰብ ሃላፊነታቸውንና የሃብት አጠቃቀም ውሳኔን


ከሚስቶቻቸው ጋር በመጋራት የቤተሰባቸውን ጤና እንዲጠብቁ
ያበረታታል።

• ወንዶች በቤታቸው ሚዛናዊ የሀይል ግንኙነት እንዲፈጥሩ፣


ስርአተፆታ ፍትሀዊነት እንዲላበሱ ያግዛል።

• ወንዶችም ሴቶችም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች


እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን ሁኔታዎች ለማመቻቸት ይረዳል።

• በቤተሰባቸው ጤና ላይ ከሚስታቸው እኩል መቆርቆርና መሳተፍን


እንደ ባህል እንዲወስዱና በተለይ በጤና ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ጎጂ
ባህሪዎችን እንዲቀይሩ ያደርጋል።

7
ወንዶች ሊሳተፉ የሚችሉባቸው የጤና ጉዳዮች
• ልጅ መቼና ስንት መውለድ እንዳለባቸው ከአጋራቸው ጋር
መወያየትና መወሰን፤ ብሎም የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶችን
መጠቀም

• በቤተሰብ ጤና ጉዳዮች ላይ ከትዳር አጋርና ከሌሎች የቤተሰብ


አባላት ጋር በግልፅ መወያየትና አብሮ መወሰን

• የጤና ባለሙያን ምክር በመስማት ለሚስቶቻቸውና ለልጆቻቸው


ጤንነት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ፥ እንዲሁም ለራሳቸው
የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለመጠቀም እንዲችሉ ከባለቤቶቻቸው ጋር
ለቤተሰብ ምጣኔ የምክክር አገልግሎት፣ ለቅድመ-ወሊድ እና ድህረ
ወሊድ ምርመራ እና ኤችአይቪ ከእናት ወደ ፅንስ እንዳይተላለፍ
የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት አብሮ ወደ ጤና ተቋም መሄድ

8
• ለጤና እንክብካቤ የሚያስፈልግ ገንዘብ መቆጠብና መጠቀም (ለምሳሌ
ቤተሰባቸው በአፋጣኝ ህክምናዎችን እንዲያገኝ የትራንስፖርት ክፍያና
ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎችን መሸፈን፣ ለቤተሰባቸው የተመጣጠኑ
ምግቦችን ማቅረብ፣ ወዘተ)

• የቤት ውስጥ ስራዎችንና ልጆችን የመንከባከብ ሀላፊነቶችን መጋራት

• ስርአተ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ማለትም ድብደባ፣ ስድብና


ማንቋሸሽ፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ ያለእድሜ ጋብቻን፥ የሴቶችን ግርዛትና
የመሳሰሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አለመፈፀምና መከላከል

• ወንድና ሴት ልጆቻቸውን በእኩል ደረጃ መንከባከብ፣ እንዲሁም እኩል


የትምህርት እና ሌሎች ዕድሎችን ለወንድና ለሴት ልጆቻቸው መፍጠር

9
ወንዶችን የማሳተፊያ መንገዶች

• አንዳንድ ወሲባዊ እና ስርአተ ፆታዊ የጤና ጉዳዮችን


በተናጠል ከመጀመር ይልቅ በማህበረሰብ ውይይቶች
እንዲነሱ ማመቻቸት

• በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የቤት ለቤት ጉብኝት ወቅት


ወንዶችን ማሳተፍ

• በወንዶች ላይ በጎ ተፅዕኖ ያላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች


ለይቶ ከእነርሱ እገዛ ማግኘት

• እንደ ባሎች ኮንፍረንስ የመሳሰሉ የወንዶች የውይይት ቡድን


ማደራጀት

• ወንዶች ሰብሰብ ብለው የሚገኙባቸውን ከጤና ውጪ ያሉ


ማህበራዊ መስተጋብሮች ተጠቅሞ ማስተማር (እንደእርሻ፣
ት/ቤቶች፣ የወጣት ክበቦች፣ ስፖርታዊ ክንውኖች፣
ሀይማኖታዊ ስብሰባዎች፣ የገበያ ቦታዎች፣ እድሮች/እቁቦች፣
የግብርና ልማት ሰራዊት፣ ወዘተ)

10
ቅድመ ጥንቃቄ
ወንዶችን በጤና ጉዳይ ከማወያየት በፊት ሊነሱ በሚችሉ የተለመዱ
የተቃውሞ ሀሳቦችን መገመትና መዘጋጀት ያስፈልጋል። ከተሳሳተ ግንዛቤ
የተነሳ ከታች የተዘረዘሩትና መሰል ሃሳቦች ሊነሱ ስለሚችሉ አግባብነት
ያላቸው መልሶችን አስባችሁበት ሂዱ።

• አርግዞ መውለድና ልጅ መንከባከብ የሴት ስራ ነው። መፅሀፍ


ቅዱስ /ቁርኣን እንደሚያዘው የቤት አስተዳዳሪነት ሀላፊነቴን
ከተወጣሁ አይበቃም?

• እሷ ያረገዘችው ሀኪም ጋር ከሄደቸ አይበቃም? እኔ ምን


እፈጥራለሁ?

• የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ማግኘት የሴቶች ሀላፊነት ነው። እኔ


አረግዛለሁ?

• ወንድ በገንዘቡ ሴት በጓዳዋ ማዘዟ ወግ ነው። ባህላችሁን ተዉ


ነው የምትሉን?

• ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ ሲያስፈልገኝ ሚስቴ ፍላጎቴን


መሙላት አለባት። ታዲያ ለምን አገባኋት?

• ጥረታችሁ ወንዱን ሴታሴት ማድረግ ነው? ወንድ ያለተፈጥሮው


ጓዳ ጓዳ እንዲል እና ሴቷን ተከትሎ በየጤና ጣቢያው እንዲዞር
ነው ፍላጎታችሁ?

11
ጠቃሚ ምክሮች

• ወንዶችን እንደ ትዳር አጋሮች እና አባቶች የቤተሰባቸው


ጋሻ እና መከታ እንጂ ለጤና ለውጦች እንቅፋት እንደሆኑ
አድርጎ መውሰድ ተገቢ አይደለም። የወንዶቹ ተሳትፎ
ጥቅሙ ለራሳቸው እና ለሚወዷቸው ቤተሰባቸው እንደሆነ
ያስረዷቸው።

• ወንዶችን ለማሳመን ያልተጠበቀ ተቃውሞ ቢያጋጥም


በአካባቢው ተሰሚነት ያላቸውን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እገዛ
ማግኘት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

• ወንዶች ጫና ሳይደረግባቸው እርስበርስ ተወያይተው


የሚማማሩባቸውን መንገዶች ማመቻቸት ጠቃሚ ነው።

12
ከት/ቤቶች ጋር በጤና ጉዳዮች ዙሪያ
አብሮ መሥራት

14
የትምህርት ቤት ማህበረሰብን ጤና ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች
በቀጥታ የተማሪዎች እና የመምህራንን ግንዛቤ ከመጨመር ባለፈ
ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ጤና ለማሻሻል ይጠቅማል። ተማሪዎች
የማህበረሰብ ንቅናቄ በመፍጠርና የተለያዩ የጤና ዘመቻዎች ለማከናወን
ከፍተኛ እገዛ ማድረግ ይችላሉ።

በትምህርት ቤቶች ለጤና ስራ በርካታ የተመቻቹ ሁኔታዎች አሉ።


ከእነዚህም መካከል የክበባት እና የሚሳተፉ አባላቶቻችው መኖር፥
ለጤና እና ተዛማጅ ስራዎች በጎ ፈቃደኝነትና ተነሳሽነት በመምህራን እና
በተማሪዎች ዘንድ መኖሩ እና የመሳሰሉት ናቸው።

15
ከት/ቤቶች ጋር መስራት ለምን ያስፈልጋል?
• ተማሪዎች ስለተማሩት ጉዳይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ስለሚወያዩ

• ተማሪዎች ተፈላጊውን የባህርይ ለውጥ በቀላሉ ለማምጣት የተሻለ


ዕድሜ ላይ በመሆናቸው

• ታናናሾቻቸውን የሚንከባከቡ ተማሪዎች የቤተሰባቸውን ጤና


ለመጠበቅ ከፍተኛ ድርሻ ስላላቸው

• እነሱንም ጤናማ ማህበረሰብ የመፍጠር ጥረት ውስጥ ያሳትፋቸዋል

• ተማሪዎች በመምህራኖቻቸውና በአቻዎቻቸው ተፅእኖ ስር


የመውደቅ እና እነሱን የመስማት ዝንባሌ ስላላቸው

• የማህበረሰብ ጤና ንቅናቄዎችን በማቀጣጠል ረገድ ከፍተኛ ሚና


ስላላቸው

16
ተማሪዎችና ት/ቤቶች ሊሳተፉባቸው
የሚችሉ የጤና ጉዳዮች
ስርዐተ ምግብ
• የፀረ አንጀት ትላትል የማስወገድ ዘመቻ

የውሃ አያያዝ፣ የግልና የአካባቢ ንፅህና


• ውሃን በንፅህና መያዝ
• ምግብ ከማዘጋጀት፣ ከመመገብ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ
እጅን በውሃና በሳሙና በደንብ መታጠብ
• የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅና የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም

ወባ
• አጎበር አጠቃቀም
• የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን መድፈንና ማጥፋት
• ለወባ በሽታ ቶሎ ህክምና ማግኘት

17
የወጣቶችና የስነ ተዋልዶ ጤና (የተማሪዎቹን እድሜ ባገናዘበ ሁኔታ)
• ኤችአይቪ፣ የሌሎች አባላዘር በሽታዎች እና የቲቢን መከላከያ መንገዶች
ማወቅ
• የኤችአይቪ፣ የሌሎች አባላዘር በሽታዎች እና የቲቢ ምርመራ ማድረግ
• የጤናማ ወሲብ ግንኙነት
• የተሻለ የስርዕተ ፆታ ግንኙነትና ፍትሃዊነት እንዲኖር አስተዋፅዖ
ማድረግ

በሌሎች የቤተሰብ ጤና ጉዳዮች ቤተሰቦቻቸውንና ማህበረሰቡን


እንዲያስተምሩ ማገዝ
• በእናቶችና ህፃናት ጤና ዙሪያ
• በወባ መከላከልና ህክምና ዙሪያ
• በስርዓተ ምግብ ዙሪያ
• በውሃ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ
• በግልና አካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ

18
ት/ቤቶችን ለባህሪ ለዉጥ
ተግባቦት ማሳተፊያ መንገዶች

• የተማሪዎችን እድሜ ያገናዘበ የጤና መልዕክቶችን በተለያዩ


አጋጣሚዎች ማሰራጨት
• የስነ ተዋልዶ ጉዳዮችን የተማሪዎቹን እድሜ ባገናዘበ
ሁኔታና ወንዶችንና ሴቶችን ለያይቶ ማወያየት
• በት/ቤት ውስጥ ዓመታዊ የጤና ቀናትን አስመልክቶ
የመዝናኛና የማስተማሪያ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት
• በክፍል ውስጥ ሊከናወኑ የሚችሉ የማስተማሪያ አሳታፊ
ተግባራትን መለየትና ማከናወን
• በት/ቤት ክበባትና በሚኒ ሚዲያዎች የጤና ሥራዎችን
ማጠናከርና የተማሪዎችን ተሳትፎ መደገፍ

19
• በአካባቢው የሚከናወኑ እንደ ያለዕድሜ ጋብቻ፣ የሴት ልጆች
ግርዛትና ሌሎች ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችን በመለየት ትምህርት
መስጠት
• ከመምህራን ጋር በመመካከር ተማሪዎች ማህበረሰቡን
ሊያስተምሩ የሚችሉባቸውንና በተለያዩ የጤና ንቅናቄዎች
የሚሳተፉበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት (ለምሳሌ: - የቤት ለቤት
ጉብኝት፣ የመስክ ስራ፣ ወዘተ)
• ለመምህራን መሠረታዊ የሆነ የጤና ስልጠና በመስጠት በተዋረድ
ተማሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት
• ማንኛውንም የት/ቤት የጤና ስራዎችን ለማስቀጠል የት/ቤቶችን
ባለቤትነት ማጠናከር
• ጥሩ ለሰሩ ት/ቤቶች እውቅና መስጠትና ሌሎች ት/ቤቶች ልምድ
እንዲቀስሙ እድሎችን ማመቻቸት

20
የሀይማኖት መሪዎችንና
ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦችን
በጤና ጉዳዮች ማሳተፍ

22
የሀይማኖት መሪዎችንና ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች የህብረተሰቡን ጤና
ለማሻሻል በሚከተሉት ምክንያቶች ከሌላ ሰው የተለየ አቅም አላቸው።
• በአብዛኛው ማህበረሰብ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው በአርዓያነት
የሚታዩ በመሆናቸው
• በማህበረሰብ ውስጥ ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነትና ትስስር
ስላላቸው
• በማህበረሰብ ዘንድ እምነት ስለሚጣልባቸው
• ጥሩ የመግባባት እና ተናግረው የማሳመን ጥበብ ስላላቸው
• ለውጥ ለማምጣት የሚያሰችል በጎ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉ
በመሆናቸው

23
የሃይማኖት መሪዎች እና ተሰሚነት
ያላቸው ግለሰቦች የጤና ባለሞያዎችን
እንዴት ማገዝ ይችላሉ?
• ከእምነት፣ ከባህል፣ ከወግና ልማድ ትውፊቶች በጎ የጤና
መልእክቶችን ለይተው በማውጣት

• መሰል አቻ መሪዎችን በማሳመንና በማስተባባር

• በንግስ፣ በበዓላት እና በማህበራዊ ስብሰባዎች ላይ የጤና


መልእክቶችን በማስተላለፍ

• በንግስ፣ በጸሎት አገልግሎት፣ በክብረ በዓላት፣ በማህበራዊ


ስብስቦሽ ጊዜ የጤና ባለሞያዎች መልእክት እንዲያስተላልፉና
ትምህርት እንዲሰጡ መድረክ በማመቻቸት

• አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ጋር የቤት


ለቤት ጉብኝት በማድረግ

• በማህበረሰቡ ውስጥ በጎ የጤና አጣባበቅ ባህሪያት እንዲተገበሩ


እና ማህበራዊ ለውጥ እንዲፈጠር መረጃ በመስጠት፣
በማስተማርና በማበረታታት

24
የሀይማኖት መሪዎችንና ተሰሚነት
ያላቸው ጋር ለመወያት የተመረጡ የጤና
ርእሰ ጉዳዮችና ዋና ዋና ነጥቦች
ስለ ውሃ አያያዝ፣ የአካባቢና የግል ንጽህና አጠባበቅ
• በበዓላት እና በክብረበዓላት አከባባር ወቅት ትክክለኛ የአካባቢ ንጽህና
አጠባበቅ እንዲኖር ማድረግ
• በሃይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ ንጽህና መጠበቂያ ቦታዎች እና መጸዳጃ
ቤቶች ተሰርተው ለአገልግሎት እንዲውሉ ጥሪት እንዲሰበሰብ
ማስተባበር
• የአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ መርሆዎችን ማስተማር የእምነቱ ተከታዮች
እጃቸውን በሳሙና/በአመድ እንዲታጠቡ መምከር
• ትክክለኛ የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀምን ማበረታታት

የተመጣጠነ ምግብ ተገቢነት


• ጸረ-ኤች አይ ቪ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎች አመጋገባቸው
ለጤናቸው ወሳኝ መሆኑን ማስተማር
• ህጻናት መፆም እንደሌለባቸው ማስተማር
• እናቶች በእርግዝናና ጡት በሚያጠቡበት ወቅት አመጋገባቸው
ለራሳቸውም ሆነ ለልጃቸው ጤና ወሳኝ መሆኑን ማስተማር

25
ስለ እናቶች ጤና አጠባበቅ
• በእርግዝና ወቅት ነፍሰጡር ሴቶች ቢያንስ አራት ጊዜ የጤና
ተቋም እንዲሄዱ ማበረታታት
• የነፍሰጡር ሴቶች ባለቤቶች ከሚስቶቻቸው ጋር ጤና ተቋም
አብረው እንዲሄዱ ማበረታታት
• ነፍሰጡር እናቶች በህክምና ተቋም እንዲወልዱ ማበረታታት
• ከወሊድ በኋላ እናቶች ከቤተሰብ የሚገለሉበት ሁኔታ እንዳይኖር
ማስተማር
• እናቶች የድህረ ወሊድ እንክብካቤና የክትባት አገልግሎት
እንዲጠቀሙ ማበረታታት

ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ሥለ መከላከል


• ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ወገኖች ላይ አድልዎና
መገለል እንዳይኖር ማስተማር
• ነፍሰጡር ሴቶች ከባሎቻቸው ጋር የኤች አይ ቪ ደም ምርመራ
እንዲያካሂዱ ማበረታታት
• ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሴቶች ፀረ-ኤችአይቪ
መድሃኒት በአግባቡ እንዲወስዱ ማበረታታት

26
ለሃይማኖት መሪዎችና
ተሰሚነት ላላቸው ግለሰቦች
መደረግ የሚገባቸው ድጋፎች

ትክክለኛ የጤና መልእክቶችን እንዲያውቁ የቤተሰብ ጤና


መመሪያን ተጠቅሞ ማስተማር
የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ተሰሚነት
ያላቸው ግለሰቦች በጎ እና አዎንታዊ የጤና ባህሪያትን
በተመለከተ ህብረተሰቡን ለማስተማርና ለመለወጥ
የሚደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው
ያስፈልጋል። ስለዚህም ከላይ በተጠቀሱት የጤና ርዕሰ ጉዳዮች
ዙሪያ የቤተሰብ ጤና መመሪያን ተጠቅሞ ማወያየት ይገባል።

የትምህርት መርሀግብር ማዘጋጀት


የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ተሰሚነት
ያላቸው ግለሰቦች የማህበረሰብ ውይይቶችን እንዲመሩ፣
በተለያዩ ማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች ላይ መልእክት
እንዲያስተላልፉና እንዲያስተምሩ የሚያስችላቸውን የጤና
ርእሰ ጉዳዮችን እና ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት።

27
የትምህርት አሰጣጡን መከታተል እና ድጋፍ መስጠት
የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች
ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች የሚያደርጓቸውን ንግግሮች፣
የሚያስተላልፏቸውን መልእክቶችና የሚሰጧቸውን የጤና
ትምህርቶች አግባብነታቸውን በመከታተል ድጋፍ መስጠት፣
የጎደሉ መረጃዎች ካሉ እንዲሟሉ ማድረግ እና ማበረታት።

28
ከግብርና ሴክተር ጋር በአጋርነት
መሥራት

30
የግብርና ስራዎች በስርአተ ምግብና በጤና ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ
ስላላቸው ከግብርና ሴክተር ጋር መስራት አስፈላጊ ነው። የግብርና
ሴክተሩ የሚከተሉትን ምቹ እድሎች መፍጠር ይችላል።
• ማህበረሰቡ የተመጣጠነ፣ በርካታ መጠን ያለውና ዋጋው
ያልተወደደ ምግብ እንዲያመርት፣ እንዲገዛና እንዲመገብ
ማበረታታት
• አርሶ አደሮች ገቢያቸውን ሊያሳድጉ የሚችሉባቸውን ዘዴዎች
አብሮ መምከር
• የማህበረሰባቸው አባላት አመጋገባቸውን እንዲያሻሽሉ ማስተማር
• አባወራዎችን በጤና መልዕክቶች ለመድረስና ለማሳመን
የሚያስችል መልካም አጋጣሚ መፍጠር
• የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በአርሶአደሮች ሰርቶ ማሳያ
ማእከላት ተገኝተው እንዲያስተምሩ ዕድል መፍጠር

31
የግብርና ባለሞያዎች ለጤና
ባለሞያዎች እንዴት ድጋፍ
መስጠት ይችላሉ?
• አርሶ አደሮች የተመጣጠነ የምግብ ፍልጎቶችን ሊያሟሉ
የሚያስችሉ ቀለል ያሉ የግብርና ስራዎችን እንዲሠሩ በማበረታታት
(ለምሳሌ የጓሮ አትክልት፣ የዶሮ እርባታ፣ እህልና ጥራጥሬ፣ ስጋ፣
ወተት፣ ወዘተ)
• አርሶ አደሮችን ሰብስቦ በጤና ጉዳዮች ላይ በማወያየትና ለችግሮች
የጋራ መፍትሔ በመፈለግ፤ እንዳስፈላጊነቱም የጤና ባለሙያዎችን
በውይይቱ እንዲሳተፉ በመጋበዝ
• ቤተሰቦች የምግብ እጥረትን ለመቅረፍ ያላቸውን ሀብት እንዲለዩ
በማገዝ
• እውቀት፣ ክህሎት፣ በራስ የመተማመንና በጋራ የመስራት አቅምን
እንዲጠናከር በማገዝ
• በማህበረሰቡ አባላት መካከል ያሉትን ግንኙነቶች በማጠናከር
• የቤት ለቤትና የማህበረሰብ የመስክ ጉብኝቶችን ከጤና ኤክስቴንሽን
ሰራተኞች ጋር በማካሄድ

232
የግብርና ባለሞያዎች ሊያግዙ
የሚችሏቸው የጤና ጉዳዮች
የውሀ አያያዝ፣ የግልና የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅን በተመለከተ
• ምግብ ከማዘጋጀት፣ ከመመገብ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን
በውሃና በሳሙና በደንብ መታጠብን ማስተማር
• የእንስሳት ማደርያ ከሰዎች ማደርያ ተለይቶ እንዲሰራ መምከርና
ስለቤት ንፅሕና ማስተማር
• ስለአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ማስተማርና የመፀዳጃ ቤትን መጠቀምን
ማበረታታት

ስርአተ ምግብን በተመለከተ


• ቅይጥ ግብርናን ስለማካሄድ (ለምሳሌ የእንስሳት እርባታ፣ የጥራጥሬና
አዝርእት እርሻ እንዲሁም የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬዎችን አሰባጥሮ
ስለማምረት) ማስተማር
• ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ስለመመገብ ጠቀሜታ ማስተማር
• በአንድ ማሳ ላይ አሰባጥሮ በመዝራት የተስተካከለ የስርአተ ምግብ
አቅርቦት እንዲኖር ማገዝ

33
የእናቶችና ህፃናት ጤናን በተመለከተ
• የነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶችን የአመጋገብ ስርአት እንዲሻሻል
ማበረታታት
• እድሜያቸው ከስድስት ወራት በላይ የሆኑ ህፃናት ያሏቸው
ቤተሰቦች ተጨማሪ ምግብ እንዲመግቧቸው ማበረታታት
• ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ከሁሉም የምግብ ምድቦች የተሰባጠረ
ምግብ (ለምሳሌ የእንስሳት ተዋፅኦ፣ ፍራፍሬዎች፣ ጥራጥሬ፣
አትክልት፣ ወዘተ) እንዲመግቡ ማበረታታት
• ወንዶች የሚስቶቻቸውንና የልጆቻቸውን ጤንነት ቅርብ ሆነው
እንዲከታተሉና እንዲሳተፉ ማበረታታት

34
ለግብርና ባለሞያዎች
ለግብርና መደረግ
ባለሙያዎች መደረግ
የሚገባቸው
የሚገባቸውድጋፎች
ድጋፎች

የግብርና ኮሚቴ ካለ ከኮሚቴው ጋር አብሮ መሥራት


• የተመጣጠነ ምግብንና (ስርአተ-ምግብን) ግብርናን
በተመለከተ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ተጨባጭ
ችግሮችን ለመለየትና መፍትሄ ለመፈለግ ኮሚቴውን
መሰብሰብና ማወያየት

የማህበረሰብ ስብሰባዎችን ማዘጋጀት


• ከስርአተ ምግብ ጋር የተገናኙ የጤና ችግሮችንና
የተመጣጠነና የበለፀገ ምግብን ጠቀሜታ የተመለከተ
ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ መግለጫ ማሰራጨት
• ግብርናና ስርአተ-ምግብ ነክ ችግሮች ላይ ውሳኔ
ለመስጠት የማህበረሰብ ውይይቶችን ማካሄድ 1 1
• ለችግሮች መፍትሄ ለማፈላለግ ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን
የትግበራ እቅድ ማዘጋጀት፤ ይሄዉም ፍራፍሬዎችንና
አትክልቶችን ማምረት፣ አመቱን ሙሉ በሁሉም የግብርና
መስኮች መሳተፍ፣ ቅይጥ ግብርናን መጠቀም እና
የተለያዩ ሰብሎችን በአንድ ማሳ መዝራትን ያጠቃልላል።

35
Photo Credits
© 2005 Virginia Lamprecht, Courtesy of Photoshare
© 2014 Nicole M. Melancon, Courtesy of Photoshare
© 2009 Quique Bassat/CRESIB, Courtesy of Photoshare
© 2013 SC4CCM/JSI, Courtesy of Photoshare
© 2005 Virginia Lamprecht, Courtesy of Photoshare
© 2005 Virginia Lamprecht, Courtesy of Photoshare
© 2009 Alemneh Tadele, Courtesy of Photoshare
© 2007 Mengistu Asnake, Courtesy of Photoshare
© 2013 Jasper Wilkins, Courtesy of Photoshare
© 2005 Abebual Zerihun, Courtesy of Photoshare
© 2013 SC4CCM/JSI, Courtesy of Photoshare
© 2006 Peter Roberts, Courtesy of Photoshare
© 2006 Mengistu Asnake, Courtesy of Photoshare
© 2006 Greg Allgood, Courtesy of Photoshare
© 2005 Abebual Zerihun, Courtesy of Photoshare
© 2006 Virginia Lamprecht, Courtesy of Photoshare
This booklet is made possible by the generous support of the American people through the
United States Agency for International Development (USAID). The contents are the responsibility
of Johns Hopkins Center for Communication Programs Ethiopia and do not necessarily reflect
the views of USAID or the United States Government.

You might also like