You are on page 1of 2

ለሁሉም ጤና ኬላዎቻችን።

ጉዳዩ ፥የቤተሰብ እቅድ ግንዛቤዎች ማሻሻልን ይመለከታል::

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እደተሞከረው የኩታበር ጤና ጣቢያ መጋቢ የሆናችሁ ቀበሌዎች በል

የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ስንመለከተው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ወይንም እየተለመደ ቢመጣም

በተለያየ ምክንያት ማህበረሰባችንን ግንዛቤውን ልንረዳው ሞክረናል ይሁን እንጅ ሁሉም ክላስተሮቻችን ላይ

በሚባል ደረጃ ስለ ቤተሰብ ምጣኔ የሚአስተምርም ወይም ስለ እያንዳንዱ ቤተሰብ እቅድ የሚአስረዳ ወይንም

ግንዛቤ የሚሰጥ ባለሙያ የለም ይልቁንም ማህበረሰቡ በስተትም ይሁን በትክክል ከጎረቤት ወይንም ከቤት ባለችው

እውቀት ብቻ እየተጠቀመ ይገኛል ።ስለዚህ ይህን ደግሞ መረጃ ከጤና ኤክስቴንሽን ወይንም ከጤና ባለሙያ
ማህበረሰባችን ትክክለኛ እና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ማስረዳት ይጠበቃል። ስለሆነም

መታረም ያለብን

0, የቤተሰብ ምጣኔ ሳይሆን የቤተሰብ እቅድ ማለትና እዲባል ማስለመድ

1; የማህበረሰባችንን ግንዛቤ መረዳትና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ማስረዳት

2, ሙሉ ግብዓት በጤና ተቋማት ማሟላት

3, ሙሉ መረጃ መያዝና መላክ

4 , ብልህ ጅምርን ማበረታታት

5,የረጅም ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድን ዝርዝር በየወሩ መላክ ከ 25 በፊት

6, ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ግንዛቤዎች መፍጠር

7,የጎንዮሽ ጉዳቶችን መያዝና መፍትሔዎችን ማመቻቸት እና ማስረዳት

8,እደመጡ በቁም መስጠትን ማስቀረትና ቁጭ አድርጎ ስለ እያንዳንዱ ቤተሰብ እቅድ ዘዴ

ማስተማርና ግንዛቤዎች ማስጨበጥና የመረጡትን ማስጠቀም።

"የማህበረሰባችንን ጤና መጠበቅ ግዴታችን ነው"። ከሰላምታ ጋር

አቶ ናሁሰናይ ልንገርህ

You might also like