You are on page 1of 135

አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ምዕራፌ አንዴ
ሰውና ኑሮው
1.1 የምንመገበው ምግብ
1.1.1 የምንመገበው ምግብ ጥቅም
ተማሪዎች! ከዚህ ቀዯም ስሇ ምግብ ተምራችሁ ነበር፡፡ ምግብ ከሶስቱ
መሰረታዊ ፌሊጎቶቻችን ውስጥ አንደ ነው፡፡ ምግብ ባሌተመገብን ጊዜ ምን
ይሰማናሌ? ተማሪዎች እስቲ ተነጋገሩበት፡፡

ሥዕሌ 1/1 የምግብ አስፇሊጊነት

1
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ተማሪዎች! ሰይዴ የሰጠው መሌስ ትክክሌ ነውን? ሰይዴ ከሰጠው መሌስ


ተጨማሪ ካሊችሁ ሇመምህራችሁ ተናገሩ፡፡
ምግብ ካሌተመገብን መኖር አንችሌም፡፡ ስሇዚህ ሰዓታችንን ጠብቀን ዘወትር
በቂ ምግብ መመገብ አሇብን፡፡ ምግብ ሇሰውነታችን ሶስት ዋና ዋና ጥቅሞች
አለት፡፡ እነርሱም፡-ሇሰውነታችን እዴገት፣ ሇጤንነትና ሀይሌ ሰጪ ናቸው፡፡

ሀ. ሇሰውነታችን እዴገት
ምግብ በበቂ መጠንና በየዓይነቱ ስናገኝ ሰውነታችን እዴገት እያሳየ ይሄዲሌ፡፡
ሌጆች እንዱያዴጉ ምግቦችን መመገብ አሇባቸው፡፡

ሥዕሌ 1/ 2 ሇሰውነታችን ዕዴገት ምግብ ያስፇሌገናሌ፡፡

ሕፃን ሌጅ ትሌቅ ሌጅ እንዱሆን ምግብ መመገብ አሇበት፡፡

2
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሇ. ሇጤንነት

ተማሪዎች! ምግብን በበቂ መጠንና በየዓይነቱ የምንመገብ ከሆነ ዯስተኞች


እንሆናሇን፣ በቀሊለ በበሽታም አንጠቃም፡፡

ዯስተኛና ተጫዋች ሕፃን ዯስተኛ ያሌሆነና የሚያሇቅስ ሕፃን

ሥዕሌ 1/3 ሇጤናችን ምግብ ያስፇሌጋሌ፡፡

3
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሏ. ሇሀይሌ
ሰዎች ሥራን ሇመስራትና ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ ሇማዴረግ ምን
ያስፇሌጋቸዋሌ? ምግብ ያስፇሌግቸዋሌ ካሊችሁ ትክክሌ ናችሁ፡፡ ሰዎች
ሀይሌ የሚሰጡ ምግቦችን በበቂ ሁኔታ መመገብ አሇባቸው፡፡ ካሌተመገቡ
በሚሠሩት ሥራ ውጤታማ አይሆኑም፡፡

ኳስ የሚጫወቱ ሌጆች የሚማሩ ሕፃናት


ሥዕሌ 1/4 ሐይል ሇማግኘት ምግብ ያስፈልገናል፡፡

1.1.2 ተዘውትረው የሚበለ ምግቦች


ተዘውትረው የሚበለ ምግቦች እንዯየአካባቢው መሌከዓ ምዴርና እንዯየ
ሕብረተሰቡ ባህሌ ከቦታ ቦታ ይሇያያለ፡፡ ተማሪዎች! በአካባቢያችሁ
ተዘውትረው የሚበለ ምግቦች ምን ምን ናቸው? እስቲ ጥንዴ ጥንዴ ሆናችሁ
ከጓዯኞቻችሁ ጋር ተወያዩ፡፡ በመቀጠሌም መሌሳችሁን ሇክፌሊችሁ አቅርቡ፡፡

4
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 1/5 የምግብ አይነቶች

5
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ተማሪዎች! እስቲ የምትወዶቸውን የምግብ አይነቶች ተናገሩ፡፡


የምትወዶቸው የምግብ አይነቶች ብቻ ሇጤንነታችሁና ሇእዴገታችሁ በቂ
ይመስሎችኋሌ? መሌሳችሁን ሇክፌሊችሁ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

ሥዕሌ 1/6 የምግብ ማዕዴ

አንዴ የምግብ ዓይነት ሇሰውነታችን አስፇሊጊ የሆኑ ነገሮችን ሁለ ይዞ


አይገኝም፡፡ ስሇዚህ ምግብን ከየዓይነቱ መመገብ ይጠበቅብናሌ፡፡

1.1.3 የምግብ ምንጮች

ተማሪዎች! ምግብን ከተሇያዩ ምንጮች እንዯምናገኝ ታውቃሊችሁ? አዎ!


ምግብን የምናገኘው ከእንስሳትና ከእፅዋት ነው፡፡
ተማሪዎች! በአካባቢያችሁ የሥጋ ምንጭ የሆኑ እንስሳት ምን ምን ናቸው?
እስቲ በአበበና በዘምዘም መካከሌ የተዯረገውን የሀሳብ ሌውውጥ ተከታተለ፡፡

6
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 1/7 ስሇ ምግብ ምንጮች ውይይት

ተማሪዎች! ከአበበና ከዘምዘም የሏሳብ ሌውውጥ ምን ተማራችሁ?

7
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ከእንስሳትና ከእፅዋት የተሇያዩ የምግብ ዓይነቶችን እናገኛሇን፡፡


እነዚህን የምግብ ዓይነቶች እስቲ ከጓዯኞቻችሁ ጋር ጎን ሇጎን
በመነጋገር ሇመምህራችሁ ንገሯቸው፡፡

ሥዕሌ 1/8 ከእንስሳት የሚገኙ የምግብ አይነቶች

ፌራፌሬዎች

8
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ጥራጥሬዎች

ሥዕሌ1/9 ከእፅዋት የሚገኙ ምግቦች

9
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ከእንስሳትና ከእፅዋት የበርካታ ምግብ አይነቶች ምንጭ የቱ ነው?


ከእፅዋት የሚገኙ ምግቦች በርካቶች ናቸው፡፡
1.1.4 የአመጋገብ ስርዓት
ተማሪዎች! የአመጋገብ ስርዓት ምንዴን ነው?

የአመጋገብ ስርዓት ማሇት በምግብ ገበታ ሊይ የምንከተሇው የአመጋገብ ዯንብ


ነው፡፡ እስቲ ዯንቦቹን አንዴ በአንዴ ሇመምህራችሁ ተናገሩ፡፡

ሥዕሌ 1/10 የአመጋገብ ስርዓት


10
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ተማሪዎች! ከዚህ ቀዯም የአመጋገብ ሥርዓት ባሇመጠበቃችሁ የዯረሰባችሁ


ችግር አሇን? ወሊጆቻችሁ እናንተን ጥሩ የሆነ የአመጋገብ ሥርዓት
እንዱኖራችሁ ምን መከሯችሁ?
ከመመገብ በፉት እጅን መታጠብ፣ ከምግብ ጋር የሚጠጣ ውሀ ማቅረብ፣
መጥኖ መጉረስ ፣ ረጋ ብል መመገብ፣ እየተመገቡ አሇመጫወት፣
እየተመገቡም ላሊ ነገር አሇማሰብ፣ ከመዋጥ በፉት በዯንብ ማኘክ ጥሩ
የአመጋገብ ስርዓት ይባሊሌ፡፡
1.2. ጤናችን
1.2.1. ጤንነት ምንዴን ነው?

መሌመጃ 1.1
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. ጤና ምንዴን ነው?
2. አንዴ ሰው ጤናማ ነው ሉባሌ የሚችሇው እንዳት ነው?
3. አንዴ ሰው ከጎረቤቱ፣ ከጓዯኞቹ፣ እና ከማህበረሰቡ ጋር ተግባብቶ መኖር
ካሌቻሇ ጤናው ታውኳሌ ማሇት ይቻሊሌን?

ጤንነት ማሇት የአንዴ ሰው አካሊዊ፣ አዕምሯዊ እና ማህበራዊ ዯህንነት ማሇት


ነው፡፡ ጤነኞች ሁሌጊዜ ዯስተኞች፣ ነፃ፣ ከሰው ጋር ተግባቢ፣ ጠንካራና ንቁ
በመሆን የዕሇት ከዕሇት ሥራቸውን በአግባቡ የሚያከናውኑ ናቸው፡፡
በሚሰሩትም ስራ ውጤታማ ይሆናለ፡፡

11
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 1.2
ሇሚከተለት ጥያቄዎች መሌስ ስጡ፡፡
1. ከጤነኛና ከታመመ ሰው በሥራው ይበሌጥ ውጤታማ የሚሆነው
የትኛው ይመስሊችኋሌ? ሇምን?
2. ከቤተሰቦቻችሁ አባሌ ታመው የሚያውቁ አለ? በምን ምክንያት
እንዯታመሙ ምክንያቶቹን መዘርዘር ትችሊሊችሁ?
3. የጤና መታወክ የሚመጣው እንዳት ነው?

ጤናማ እና ዯስተኛ ሌጆች ጤናው የታወከ ሌጅ

ሥዕሌ 1/11 ጤናማ ሌጆችና ጤናው የታወከ ሌጅ

12
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

1.2.2. ጤናማ የመሆን አስፇሊጊነት

መሌመጃ 1.3
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. ጤናማ መሆን ሇምን ያስፇሌጋሌ?
2. ጤናማ እና ዯስተኛ ሇመሆን ምን ምን ሁኔታዎች ያስፇሌጋለ?
3. ዯስተኛ መሆንና መከፊትን የሚያመጡ ነገሮችን በቡዴን በመወያየት
ዘርዝሩ፡፡

ሰዎች ጤነኛ እና ዯስተኛ እንዱሆኑ የተመጣጠነ ምግብ፣ ንፁህ ውሃ፣ አየርና


ንፅህናው የተጠበቀ ተስማሚ ሌብስ ማግኘት ይኖርባቸዋሌ፡፡ በተጨማሪም
የጤና አገሌግልት፣ በቂ እረፌት እና መዝናኛ ያስፇሌጋቸዋሌ፡፡ እነዚህ
ሁኔታዎች የተሟለሊቸው ሰዎች በእሇት ከእሇት ኑሯቸው ዯስተኛ እና ጤነኛ
ይሆናለ፡፡ ስራንም በንቃት ይሰራለ፡፡ ከሰዎች ጋር ተግባብተው ይሰራለ፡፡
በስራቸውም ውጤታማ ይሆናለ፡፡

መሌመጃ 1.4
በሚከተሇው ጥያቄ ሊይ ተወያዩ፡፡
በሽታ የሚመጣው በምን ምክንያት እንዯሆነ ታውቃሊችሁ? ምክንያቶቹን
ዘርዝሩ፡፡

13
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

በሽታ ሉመጣ የሚችሇው፡-


በግሌና በአካባቢ ንፅህና ጉዴሇት፣
በዴንገተኛ አዯጋ፣
በጎጂ ሌማዲዊ ዴርጊቶች፣
በጭንቀት፣ እረፌት በማጣት ወዘተ ሉሆን ይችሊሌ፡፡

1.2.3. የታመመ እና ጤነኛን ሰው ማነፃፀር


መሌመጃ 1.5
በሚከተሇው ጥያቄ ሊይ ተወያዩ፡፡
በቤተሰባችሁ ውስጥ የታመመ ሰው አሇ? ይህ ሰው በታመመ እና ጤነኛ
በሆነ ጊዜ የሚያሳየው ፀባይ ተመሳሳይ ነው ወይስ ይሇያያሌ? ሇምን?

የታመመ ሰው በአጠቃሊይ ስሜቱ የተረበሸ፣ ዯስተኛ ያሌሆነ፣ ከጤነኛ ሰው


ይሌቅ ሥራን በአግባቡ ሉሰራ የማይችሌ ነው፡፡

መሌመጃ 1.6
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ ፡፡
1. እስቲ አንዴ የታመመ ሰው እና ጤነኛ ሰውን ፀባይ አነፃፅሩ፡፡
2. ሇአቅመ ዯካሞች እና ሇታመሙ ሰዎች እንክብካቤ እና አክብሮት
መስጠት ያስፇሌጋሌ ብሊችሁ ታስባሊችሁ? ሇምን?
3. ሇአቅመ ዯካሞች እና ሇታመሙ ሰዎች አክብሮትና እንክብካቤ እንዳት
መስጠት ይቻሊሌ?

14
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

1.2.4. የሕመም ምሌክቶች


መሌመጃ 1.7
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. እናንተ ከአሁን በፉት ታማችሁ የምታውቁ ከሆነ ሲሰማችሁ የነበረውን
የሕመም ስሜት ግሇፁ፡፡
2. የሕመም ስሜቶች ወይም ምሌክቶች ሲሰሙን ምን ማዴረግ አሇብን?
3. በአካባቢያችሁ ሰዎች የሕመም ስሜት ሲሰማቸው ወዯ ሀኪም ቤት
እንዲይሄደ የሚያዯርጉ ጎጂ ሌማዲዊ ዴርጊቶች አለ? ካለ ዘርዝሩ፡፡

ሕመም ሲሰማን የተሇያዩ ምሌክቶች ይታዩብናሌ፡፡ እንዯ ሕመሙ ዓይነት


የሚሇያይ ቢሆንም በአጠቃሊይ ሕመም ሲሰማን የራስ ምታት፣ የስሜት
መረበሽ፣ ጠቅሊሊ የሰውነት መታወክ፣ የምግብ ፌሊጎት ማጣት፣ ዯስተኛ
አሇመሆን፣ ተቅማጥና ትውከት፣ የሰውነት መዛሌ የመሳሰለ ምሌክቶች
ሉታዩብን ይችሊለ፡፡

እነዚህ የሕመም ምሌክቶች ሲሰሙን ወዱያውኑ ሇቤተሰቦቻችን ወይም


በአቅራቢያችን ሇሚገኙ ሰዎች በግሌፅ መናገር እና ወዯ ጤና ተቋም በመሄዴ
መታከም ይኖርብናሌ፡፡

15
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 1/12 የታመመ ህፃን

መሌመጃ 1.8
በቡዴን ሆናችሁ የሚከተሇውን ተግባር ሥሩ፡፡
1. ከመካከሊችሁ አንደን ወይም አንዶን ተማሪ ሀኪም አዴርጉና ምረጡ፡፡
ከዚያም የተወሰኑ የቡዴን አባሊት እንዯታመሙ በማስመሰሌ
የሚሰማቸውን የሕመም ስሜት ሇሀኪሙ/ሟ/ በግሌፅ እንዱናገሩ ማዴረግ፡፡
ይህን ማዴረግ ሇምን እንዯሚጠቅም በቡዴናችሁ ተወያዩ፡፡
2. በሰው ሊይ የሚዯርስ ዴንገተኛ አዯጋ ሰምታችሁ ታውቃሊችሁ? እስቲ
የምታውቁትን ሇጓዯኞቻችሁ ተናገሩ፡፡

16
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

1.3. የግሌ ንፅህናችንን እንጠብቅ


1.3.1. ንፅህናችንን ሇምን እንጠብቃሇን?
መሌመጃ 1.9
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. እስቲ በአንዯኛ ክፌሌ የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ስሇ ሰውነት ክፌልች ንፅህና
አጠባበቅ የተማራችሁትን በማስታወስ ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ ተናገሩ፡፡
2. የሰውነት ክፌልቻችንን ንፅህና ሇመጠበቅ የሚረደ ቁሳቁሶች ምን ምን ናቸው?
3. የግሌ ንፅህናን መጠበቅ በተሇይም ዯግሞ በምግብ ዝግጅት ወቅት ሇምን
ይጠቅማሌ?
4. የግሌ ንፅህናችንን አሇመጠበቃችን ሇላልች ሰዎች ምን ችግር ሉያመጣባቸው

ይችሊሌ?

በሽታ ወይም ሕመም በአብዛኛው የሚይዘን ከግሌ ንፅህና ጉዴሇት ነው፡፡


የግሌ ንፅህናን በመጠበቅ በበሸታ የመያዝ አጋጣሚዎችን መቀነስና ጤነኛ
መሆን ይቻሊሌ፡፡ የግሌ ንፅህናን መጠበቅ የሚከተለትን ያካትታሌ፡፡

ሥዕሌ 1/13 የግሌ ንፅህና አጠባበቅ ዘዳዎች

17
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 1.10
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. የግሌ ንፅህናችሁን እንዳትና መቼ እንዯምትጠብቁ በቡዴን ተወያዩ
እና ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ አቅርቡ፡፡
2. የግሌ ንፅህናን የመጠበቅ ሏሊፉነት የማነው? የእናንተ ወይስ የላሊ
ሰው? ሇምን?

መዝሙር

እንዱጠበቅሌን ዘወትር ጤናችን፣

ሁሌጊዜ እናፅዲ ሰውነታችንን፣

እናፅዲ ዘወትር መሊ አካሊችንን፣

ፉታችን፣ ዓይናችን ጆሮና አፌንጫችን፡፡

ፀጉራችን ጥርሳችን እጅና እግሮቻችን

ይፅደ ከቆሻሻ ይጠበቅ ጤናችን፡፡ /2/

ሌብሳችንም ይፅዲ ይቆረጥ ጥፌራችን፣

ዯብቀው አይያዙ በውስጥ ቆሻሻን፣

ይፅደ ከቆሻሻ ይጠበቅ ጤናችን፡፡ /2/

ከቆሻሻ ይፅዲ መሊ አካሊችን፣

18
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ከቆሻሻ ይፅዲ ዙሪያ አካባቢያችን፣

ሕመምተኛ እንዲንሆን፣

በሽታ እንዲይዘን፣

እንዱጠበቅሌን ዘወትር ጤናችን፡፡ /2/

መሌመጃ 1.11
በሚከተሇው ጥያቄ ሊይ ተወያዩ ፡፡
ከሊይ የቀረበውን መዝሙር በጋራ ከዘመራችሁ በኋሊ ከመዝሙሩ ምን
እንዯተረዲችሁ በቡዴን በመወያየት ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ አቅርቡ፡፡

1.3.2. ንፅህናን ባሇመጠበቅ የሚመጡ በሽታዎች

የግሌ ንፅህናን ካሇመጠበቅ የተነሳ የሚከሰቱ በርካታ በሽታዎች አለ፡፡

መሌመጃ 1.12
በሚከተሇው ጥያቄ ሊይ ተወያዩ ፡፡
በአካባቢያችሁ የግሌ ንፅህናን ካሇመጠበቅ የተነሳ በቤተሰቦቻችሁ ወይም
በጎረቤቶቻችሁ የተከሰቱ በሽታዎችን ዘርዝሩ፡፡ እነዚህን በሽታዎች ሇመከሊከሌ
ምን መዯረግ አሇበት ትሊሊችሁ?

19
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

1.3.3. ኤች አይ ቪ/ኤዴስ

መሌመጃ 1.13
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. በአንዯኛ ክፌሌ የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ስሇ ኤዴስ ከተማራችሁት
ምን ታስታውሳሊችሁ?
2. የኤዴስ በሽታ ከሰው ወዯ ሰው እንዳት ይተሊሇፊሌ?
3. ከኤዴስ በሽታ መዲን ይቻሊሌን?

የኤዴስ በሽታ በዯም ንክኪ አማካኝነት ከሰው ወዯ ሰው የሚተሊሇፌ በሽታ


ነው፡፡ ኤዴስ ሰውነትን የሚያዯክም በሽታ ነው፡፡ በኤዴስ በሽታ የተያዘ ሰው
ላልች በሽታዎችን መቋቋም አይችሌም፡፡ ኤዴስ ገዲይ እና መዴሀኒት
የላሇው በሽታ ነው፡፡
መሌመጃ 1.14
ሇሚከተለት ጥያቄዎች መሌስ ስጡ፡፡
1. አንዴ መሬት ሊይ የወዯቀ ስሇታም ነገር ወይም ሹሌ ነገር ብታገኙ
ወይም ስትጫወቱ ወዴቆ ብታዩት ምን ታዯርጋሊችሁ?
2. ሌጆች መሬት ሊይ ሲጫወቱም ሆነ ስሇት ያሇው ነገር በመንካት
የመቆረጥና የመዴማት አዯጋ ቢያጋጥማቸው ምን ማዴረግ አሇባቸው?
3. ኤች አይ ቪ/ኤዴስ/ ባሇበት ሰው ዯም የተነካ ስሇት ያሇው ነገር
ቢቆርጣችሁ የኤዴስ በሽታ ሉተሊሇፌባችሁ ይችሊሌን?

20
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

1.3.4. የግሌ ንፅህናን በተግባር ማሳየት

መሌመጃ 1.15
የሚከተለትን ጥያቄዎች ስሩ፡፡
1. የግሌ ንፅህናን ተግባራዊ ሇማዴረግ በሚያስፇሌጉ ነገሮች ሊይ ተወያዩ፡፡
2. የላልች ሰዎችን ጤና ሇመጠበቅ የእናንተ ሏሊፉነት ምን ሉሆን
ይገባሌ?

ስሇ ንፅህና አጠባበቅና የግሌ ጤንነት በተግባር ሇማሳየት ዘወትር ሰውነትን


መታጠብ፣ ጥርስን መፊቅ፣ ንፁህ ሌብሶችን መሌበስ፣ መጸዲጃ ቤት መጠቀም፣
ንፁህ አካባቢ መፌጠር፣ ቆሻሻን በየቦታው አሇመጣሌ፣ የእንስሳትና የሰዎችን
መኖሪያ መሇየት ያስፇሌጋሌ፡፡

መሌመጃ 1.16
የሚከተለትን ጥያቄዎች መሌሱ፡፡
1. ንፁህ አካባቢና ተስማሚ የመኖሪያ ቦታ ሇምን ይጠቅማለ? እነዚህንስ
እንዳት መፌጠር ይቻሊሌ?
2. ስሇግሌ ንፅህና አጠባበቅ የእናንተ ዴርሻ ምን መሆን አሇበት?
3. በመኖሪያ ቤታችሁ፣ በአካባቢያችሁ እና በትምህርት ቤታችሁ ቅጥር ግቢ
ውስጥ በግሌ ጤንነት እና ንፅህና አጠባበቅ ሊይ ምን አስተዋፅኦ
የሚኖራችሁ ይመስሊችኋሌ?

21
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ምዕራፌ ሁሇት
ማህበራዊ አካባቢያችን
2.1 የማህበራዊ አካባቢያችን አባሊት
2.1.1 የማህበረሰባችን አባሊት
አንዴ ማህበረሰብ በውስጡ የተሇያዩ አባሊት ሉኖሩት ይችሊለ፡፡ እዴሜን
መሰረት በማዴረግ እነዚህን የማህበረሰብ አባሊት በአራት ከፌል ማየት
ይቻሊሌ፡፡ እነርሱም፡-
ሕፃናት፣
ወጣቶች፤
ጎሌማሶችና
አዛውንቶች ናቸው፡፡

ሥዕሌ 2/1 የማህበረሰብ አባሊት

22
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 2.1
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. እናንተ ከየትኛው የማህበረሰብ አባሊት ውስጥ ናችሁ?
2. በቡዴን በመሆን በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡-
ሕፃናት ወዯ ወጣትነት የሚሸጋገሩት በስንት ዓመት ሊይ ነው?
ወጣቶች ወዯ ጎሌማሳነት የሚሸጋገሩት በስንት ዓመት ሊይ ነው?
ጎሌማሶች ወዯ አዛውንትነት የሚሸጋገሩት በስንት ዓመት ሊይ ነው?

2.1.2. እኛ ሕፃናት ምን ምን መብቶች አለን?


ሀ. የሕፃናት መብቶች
ሕፃናት ማሇት ዕዴሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ሌጆችን ያካትታሌ፡፡
ሕፃናት የወዯፉት ሀገር ተረካቢና ገንቢ ናቸው፡፡ ሕፃናት ጥሩ ዜጋ ሆነው
የወዯፉት ሀገር ተረካቢ እንዱሆኑ ዯግሞ መብቶቻቸው ተከብሮ ማዯግ
አሇባቸው፡፡
እናንተ ሕፃናት በቤተሰብ አባሌነታችሁ ምን ምን መብቶች አሎችሁ?

23
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 2/2 የሕፃናት መብቶች

የሕፃናት መብትን ሁለም ሰው ማክበር አሇበት፡፡ሕፃናትም የራሳቸውንና


የላልችን መብቶች ማወቅ ይጠበቅባቸዋሌ፡፡ሕፃናትም በበኩሊቸው
ቤተሰቦቻቸውን ማክበርና በስራ ማገዝ ይገባቸዋሌ፡፡
ሕፃናት መብቶቻቸውን ማወቅ ሇምን ያስፇሌጋቸዋሌ?

ሇ. የሕፃናት መብቶች ጥሰት

ቀዯም ሲሌ ሕፃናት ምን ምን መብቶች እንዲሎችሁ አይተናሌ፡፡ አንዲንዴ


ወሊጆች ወይም ላልች ሰዎች የሕፃናትን መብቶች በምን በምን አይነት
መንገዴ ሉጥሱ ይችሊለ?

24
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 2/3 የሕፃናት መብት ጥሰት

25
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ውስን ጥናት
በአንዴ የገጠር መንዯር ውስጥ የሚኖሩ አቶ በሇጠና ወ/ሮ አሇሚቱ
የሚባለ ባሌና ሚስት ነበሩ፡፡ እነዚህ ወሊጆች ሁሇት ሌጆች አሎቸው፡፡
ሌጆቹም አበበና ጥሩወርቅ ይባሊለ፡፡ አበበ 11 አመት ሲሆነው ጥሩወርቅ
ዯግሞ 13 አመቷ ነው፡፡ ሁሇቱም ሌጆች መማር ቢፇሌጉም መማር
አሌቻለም፡፡ ወሊጆቻቸው ሌጆቹን በተሇያዩ ስራዎች ሊይ ስሊሰማሯቸው
እንዲይማሩ ይፇሌጋለ፡፡ አበበ ከቤት ውጪ ያለ ስራዎችን ይሰራሌ፡፡
ሇምሳላ እርሻ ያርሳሌ፣ ከብት ይጠብቃሌ፣ የተወቃ እህሌ ወዯ ቤት ጭኖ
ይወስዲሌ፡፡ ጥሩወርቅ በበኩሎ ሌዩ ሌዩ ስራዎችን እንዴታከናውን
ኃሊፉነት ተሰጥቷታሌ፡፡ ሇምሳላ እንጀራ መጋገር፣ በእንስራ ውኃ ከምንጭ
መቅዲት፣ ወጥ መስራት ቡና ማፌሊትና ቤት ማጽዲት ዋና ዋናዎቹ
ተግበሮቿ ናቸው፡፡ የአበበ እና የጥሩወርቅ ቤተሰቦች በቂ ሀብት ያሊቸው
አርሶ አዯሮች ቢሆኑም ሇሌጆቻቸው አዲዱስ ሌብስ አይገዙሊቸውም፡፡
ሁሇቱም ሌጆች አዘውትረው የሚሇብሱት የተቀዲዯና የተጣጣፇ ሌብስ
ነው፡፡

አበበና ጥሩወርቅ ያጧቸውን የሕፃናት መብቶች ሇክፌሌ ተማሪዎች ተራ


በተራ ተናገሩ፡፡
ሏ. የሕፃናት መብቶች ጥበቃ
ሕፃናት የወዯፉት ጥሩ ሀገር ተረካቢ ዜጋ እንዱሆኑ ከአሁን ጀምሮ
መብቶቻቸው ሉከበሩሊቸው ይገባሌ፡፡ ይሁን እንጂ አንዲንዴ ግሇሰቦች
በማወቅም ይሁን ባሇማወቅ የሕፃናትን መብት በተሇያዩ መንገድች እንዳት

26
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

እንዯሚጥሱ ቀዯም ሲሌ አይተናሌ፡፡ ስሇሆነም የሕፃናት መብቶች እንዲይጣሱ


ጥበቃ ያስፇሌጋቸዋሌ፡፡
የሕፃናት መብቶች በአግባቡ እንዱከበሩ ሇማዴረግ የሚመሇከታቸው አካሊት
እነማን ናቸው?

መብታቸው ያሌተከበረሊቸው ሕፃናት እንዳት ሉከበርሊቸው ይችሊሌ?


ወሊጆቻቸውን በተሇያየ ምክንያት ያጡ፣ በቂ ምግብና ሌብስ የማያገኙ እና
ትምህርት መማር ያሌቻለ ሕፃናትን ህብረተሰቡ፣ መንግስት እና
መንግስታዊ ያሌሆኑ አካሊት ሉንከባከቧቸውና መብታቸውን ሉያስጠብቁሊቸው
ይገባሌ፡፡ የሕፃናት ወሊጆችና አሳዲጊዎች የሕፃናትን መብቶች የሚጥሱ ከሆነ
የአካባቢው ሕብረተሰብ፣ መምህራን፣ የትምህርት ቤቱና የቀበላው አመራሮች
ወሊጆችንና አሳዲጊዎችን ሉመክሯቸው ይገባሌ፡፡ በዚህም መሻሻሌ ሉመጣ
ይችሊሌ፡፡

ወሊጆች በዴህነት ምክንያት ሇሌጆቻቸው ማዴረግ የሚገባቸውን ማዴረግ


ባይችለ የሌጆቻቸው መብት እንዳት ሉጠበቅ ይችሊሌ? ወሊጆች ባሊቸው
አቅም ሇሌጆቻቸው ማሟሊት ያሇባቸውን ነገሮች ሇምሳላ ምግብ፣ ሌብስ፣
ሕክምና፣ የመማሪያ ቁሳቁሶች ወዘተ ናቸው፡፡

በእናንተ ትምህርት ቤት የበጎ አዴራጎት ክበብ አሇን? ካሇ ስራው ምን


እንዯሆነ ጠይቁና ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ ሪፖርት አቅርቡ፡፡

27
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

2.2. በማህበራዊ አካባቢ ውስጥ መኖር


2.2.1. የእሇት ስራዎቻችንን ማቀዴ

ሰዎች ስራ ሲሰሩ እቅዴ ያወጣለ፡፡ ስራን ሇመስራት ሶስት ነገሮች


ያስፇሌጋለ፡፡ እነርሱም ጊዜ፣ ገንዘብና ጉሌበት ናቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች
ዯግሞ በአግባቡ ሇመጠቀም ዕቅዴ ያስፇሌገናሌ፡፡ እናንተ ጊዜያችሁን
ታቅዲሊችሁ? ሇምሳላ፡- የሉዱያን የጊዜ አጠቃቀም እንመሌከት፡፡

28
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 2/4 የጊዜ አጠቃቀም

ሉዱያ በየቀኑ የምትሰራውን ስራ በጊዜ ከፊፌሊ አውጥታሇች፡፡ እያንዲንደን


ቀን የመኝታ፣ የቁርስ መመገቢያ፣ የትምህርት ቤት መሄጃ፣ የመማሪያ፣ የምሳ
መመገቢያ፣ የመጫወቻ፣ የቤት ስራ መስሪያና ወሊጆቿን በስራ የማገዣ ጊዜ
ብሊ ከፊፌሊዋሇች፡፡

29
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሇዚህም የሚከተሇውን የጊዜ አጠቃቀም ተመሌከቱ፡፡


ስራዎች ጊዜ
የመኝታ ጊዜ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ተኩሌ
ቁርስ መመገቢያ ጊዜ ከጠዋት1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ከሩብ
ትምህርት ቤት የመሄጃ ጊዜ ከጠዋት1 ሰዓት ከሩብ እስከ 1 ሰዓት ተኩሌ
የመማሪያ ጊዜ ከጠዋት2 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ተኩሌ
ምሳ የመመገቢያ ጊዜ ከቀኑ 6 ሰዓት ተኩሌ እስከ ሇሰባት ሩብ ጉዲይ
የጥናት ጊዜ ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት
የመጫወቻ ጊዜ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት
የቤት ስራ የመስሪያ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት
ወሊጆቿን በስራ የማገዣ ጊዜ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት

እናንተም ከሉዱያ የበሇጠ ስራ ሉኖራችሁ ይችሊሌ፡፡ ስራዎቻችሁን ሁለ


ዘርዝራችሁ ጊዜ በመስጠት በፕሮግራም መስራት አሇባችሁ፡፡ ይህም ዕቅዴ
ይባሊሌ፡፡ እቅዴ ስታወጡ የቀን፣ የሳምንት፣ የወር፣ የዓመት እያሊችሁ
ማውጣት ትችሊሊችሁ፡፡ እናንተም እንዯ ሉዱያ የዕሇት የጊዜ አጠቃቀም
ዕቅዴ ሰርታችሁ ሇመምህራችሁና ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ አሳዩ፡፡
እቅዴ ሇምን ያስፇሌገናሌ?
ያሇ ዕቅዴ መስራት ምን ችግር ያመጣሌ?

30
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

2.2.2. ራስን ማስተዲዯር


ሌጆች አቅማቸው የሚችሇውን ሥራ መስራት አሇባቸው፡፡ አቅማቸው
የሚችሇውን ስራ ከሰሩ ራሳቸውን ማስተዲዯር እየተሇማመደ ነው ማሇት
ነው፡፡ ሌጆች መስራት ከሚችለት አንደ የግሌና የጋራ መገሌገያ እቃዎችን
በአግባቡ መጠቀም ነው፡፡
በግሌ የምንጠቀምባቸውን መፅሏፍቻችንን ፣ ዯብተሮቻችንን ፣ ቦርሳዎቻችንና
የትምህርት ቤት ዯንብ ሌብሶቻችንን እንዲይቀዯደና እንዲይቆሽሹ በንፅህና
በጥንቃቄ መያዝ አሇብን፡፡ በተጨማሪም የፀጉር ማበጠሪያችንን በንፅህና
መያዝና ላልች እንዲይጠቀሙበት መጠንቀቅ አሇብን፡፡

ከግሌ መገሌገያ ዕቃዎች በተጨማሪ በጋራ የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች አለ፡፡


ሇምሳላ የመኖሪያ ቤታችንን ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ የመመገቢያ ዕቃዎች
ወዘተ በንፅህና መጠበቅ አስፇሊጊ ነው፡፡ እንዲይሰበሩና እንዲይበሊሹ
መጠንቀቅ ይገባናሌ፡፡
በትምህርት ቤትም በጋራ የምጠንቀምባቸውን ሇምሳላ የመማሪያ ወንበሮች፣
ዳስኮች፣ ጥቁር ሰላዲ፣ የመማሪያ ክፌልችን በጥንቃቄና በንፅህና መያዝ
ይጠበቅብናሌ፡፡
መሌመጃ 2.2
1. ተማሪዎች! ራሳችሁን ችሊችሁ የምታከናውኗቸው ተግባራት ምን ምን
ናቸው?
2. ቀጥል የቀረቡትን ዕቃዎች የግሌና የጋራ መገሌገያ በማሇት መዴቡ፡፡
እርሳስ፣ የመስኮት መጋረጃ፣ መፀዲጃ ቤት፣ ጫማ፣ የመማሪያ ክፌሌ፣ በርና
መስኮቶች፡፡

31
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

2.2.3. በማህበረሰቡ ውስጥ በተሇያዩ ስራዎች ሊይ መሳተፌ

በእናንተ ትምህርት ቤት ውስጥ ምን ምን ክበባት አለ? በየትኞቹ


ክበባት ውስጥ ትሳተፊሊችሁ?
በክበባት ውስጥ መሳተፌ ሇምን ይጠቅማሌ?

32
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 2/5 ተማሪዎች በማህበረሰቡ ውስጥ በተሇያዩ ስራዎች በመሳተፌ ሊይ

ተማሪዎች በትምህርታቸው ጎበዝና ታታሪ መሆን አሇባቸው፡፡ በክፌሌ ውስጥ


ከመማር በተጨማሪ በተሇያዩ ክበቦች ሇምሳላ በአካባቢ እንክብካቤ ክበብ፣
በፀረ ኤዴስ ክበብ፣ በሌጃገረድች ክበብ ወዘተ በመሳተፌ የበኩሊቸውን
አስተዋፅኦ ሉያዯርጉ ይገባሌ፡፡ የትምህርት ቤት ክበቦች የትምህርት ቤቱንና
የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግሮች መፌቻ ስሇሆኑ ተማሪዎች በንቃት ተሳትፍ
ማዴረግ አሇባቸው፡፡ ሇምሳላ የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ፣ የትምህርት ቤትና
የአካባቢውን ንፅህና እንዱጠበቅ እና ዛፌ እንዱተከሌ ትምህርት ይሰጣለ፡፡
የፀረ ኤዴስ ክበብ የኤች አይ ቪ/ ኤዴስ በሽታን መተሊሇፉያ መንገድችና
መከሊከያ ዘዳዎችን ሇተማሪዎችና ሇአካባቢው ማህበረሰብ ያስተምራሌ፡፡

33
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

2.3. የማህበረሰቡ የጉሌበት ምንጮች


2.3.1. የጉሌበት አስፇሊጊነት
ጉሌበት በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ ምግብ ሇማብሰሌ፣ ቤታችንን ሇማሞቅ፣
እርጥብ ሌብሶችን ሇማዴረቅ፣ መኪናዎችን ሇማሽከርከርና መብራት ሇማግኘት
ያስችሇናሌ፡፡
በአካባቢያችን የተሇያዩ የጉሌበት ምንጮች አለ፡፡እነዚህን የጉሌበት
ምንጮች በሦስት ምዴቦች ከፌል ማየት ይቻሊሌ፡፡
ሀ. የማገድ እንጨትና ከሰሌ
የማገድ እንጨትና ከሰሌ ሇምን አገሌግልት ይውሊሌ?

ሥዕሌ 2/6 የማገድ እንጨትና የከሰሌ አገሌግልት

ሇ. የነዲጅ ዘይቶች

የነዲጅ ዘይቶች ሇምን ተግባር እንዯሚያገሇግለ ተናገሩ?


ምን ምን ዓይነት የነዲጅ ዘይቶችን ታውቃሊችሁ?

34
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 2/7 የነዲጅ ዘይት አይነቶች

የነዲጅ ዘይቶች መኪናን ሇማሽከርከር፣ ሇመብራት፣ ምግብ ሇማብሰሌና


ሇወፌጮ ያገሇግሊለ፡፡
ሏ. የታዲሽ ሀይሌ ምንጮች

የታዲሽ ጉሌበት ምንጮች የምንሊቸው ምን ምን ናቸው?

የታዲሽ ጉሌበት ምንጮች የምንሊቸው ሇምን ሇምን አገሌግልት ይውሊለ?

ታላቁ የህዳሴው ግድብ /የውሃ ግድብ/

35
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የፀሐይ ጨረር ጉልበት ሇመብራት የንፋስ ሀይል ሇኤሌክትሪክ ጉልበት


ሇአገሌግልት ሲውል ማመንጫነት ሲውል

ሥዕሌ 2/8 ታዲሽ የሀይሌ ምንጮች

2.4. የተሇያዩ ቁሳቁሶችን ከሸክሊና ከወረቀት መሥራት


2.4.1. የንዴፌ ስራ
የተሇያዩ ነገሮችን ሥዕሌ ሇመስራት በመጀመሪያ የንዴፌ ስራን መሇማመዴና
ማወቅ ጠቃሚ ነው:: የንዴፌ ስራን በወረቀት፣ በጥቁር ሰላዲ፣ በጨርቅና
ላልች አመቺ ነገሮች ሊይ በመስራት መሇማመዴ ይቻሊሌ:: ሇንዴፌ ስራ
መስመሮችን በማስመር መሇማመዴ የስዕሌ ችልታን ያዲብራሌ::

36
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

1. ተማሪዎች ቀÕታ መስመር በማስመሪያና ያሇማስመሪያ በመስራት


ተሇማመዱ::

ሥዕል 2/9 ቀጥታ መስመሮች

የማይገናኙ መስመሮችን በማስመሪያና ያሇማስመሪያ እየሰራን እናወዳድር::

ሥዕል 2/10 የማይገናኙ መስመሮች

መስመሮችን በማገናኘት አራት ማዕዘን ቅርጽ በመስራት እንሇማመድ::

ሥዕሌ 2/11 አራት ማዕዘን ቅርፆች

37
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መስመሮችን በማገናኘት ሶስት ማዕዘን እንስራ::

ስዕል 2/12 ባሇሶስት ማዕዘን ስዕሎች

የተሇያዩ ሥዕሎችን በመስራት እንሇማመድ::

ሥዕል 2/13 የተሇያዩ ስዕሎች

38
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መስመሮችን በመጠቀም የጎጆ ቤት እንስራ፡፡

ሥዕል 2/14 የጎጆ ቤት ስዕል

2.4.2. ማስጌጫ
ወረቀትን በተሇያዩ ቅርፆች በመተሌተሌ የሠርግ ቤትና የምርቃት
አዲራሾችን ውብ ሇማዴረግ በማስጌጫነት አገሌግልት ሊይ ማዋሌ
ይቻሊሌ፡፡ ከወረቀት ቢራቢሮ፣ አበባና ላልችን ጌጣጌጦች መስራት
ይቻሊሌ፡፡

ሥዕሌ 2/15 ከወረቀት የቤት ውስጥ ማስጌጫ የአሰራር ቅዯም ተከተሌ

39
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

እናንተም ከወረቀት የተሇያዩ ጌጣጌጦችን ስሩ፡፡


2.4.3. ቅርፅ

የተሇያዩ ቅርፆችን ከወረቀት መስራት


ወረቀትን በማጠፌ ወይም በመቆራረጥ የተሇያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት
ሇተሇያዩ ተግባራት መጠቀም ይቻሊሌ፡፡ የሚከተለትን ቅርፆች መመሪያውን
በመከተሌ ሰርታችሁ ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ እንዳት እንዯሰራችኋቸው አሳዩ፡፡
 ወረቀትን በማጣጠፌ ቅርፆችን መስራት
ሀ) ፈራፈሪት
የሚያስፇሌጉ ነገሮች:- እርሳስ፣ የማባዣ ወረቀት፣ መቀስና የወረቀት መርፋ
ናቸው፡፡
የአሰራር ቅዯም ተከተሌ
1. ወረቀት ማዘጋጀት 2. ነጠብጣብ በማዕዘናቱ አግድም መስራት

3. እስከ ክቡ ድረስ በነጠብጣቡ ላይ በመቀስ መቁረጥ

40
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

4. ቁጥር 2፣4፣6ና 8ን ወደ መሀል ማጠፍና በእጥፋቶችና በክቡ መሀል

በወረቀት መርፌ ወይም በእሾህ መብሳት፡

ሇ) ፖስታ
የሚያስፇሌጉ ነገሮች:- እርሳስ፣ የማባዣ ወረቀት፣ መቀስና ሙጫ ወይም
ሙቅ ናቸው፡፡
1. የማባዣ ወረቀት ማዘጋጀት 2. ዙሪያውን 2 ሳንቲ ሜትር ወደ ውስጥ
ገባ ብሎ ማስመር

41
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3. ወረቀቱን እኩሌ ቦታ ጫፍቹን በመያዝ በትክክሌማጠፌ

4. በስዕለ እንደሚታየው ማስመርና የጠቆሩትን ክፍሎች ቆርጦ ማውጣት

5. ማስመሪያ በመጠቀም በስዕለ እንደሚታየው ማጠፍ

42
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

6. በሙቅ ወይም በሌላ ማጣበቂያ በማጣበቅ ዙሪያውን በቀሇም ማስጌጥ

ተማሪዎች! በአካባቢያችሁ ከምታዩቸው ነገሮች ተጨማሪ ቅርፆችን ከወረቀት አዘጋጅታችሁ


ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁና ሇመምህራችሁ አሳዩ፡፡ምሳላ የኮፌያ ቅርፅ፣ የማስመሪያ ቅርፅ፣
የሰዓት ቅርፅ ወዘተ ስሩ፡፡

 ወረቀቶችን በመቆራረጥ ቅርፆችን መስራት

ከካርቶን የፌየሌ ቅርፅ የማዘጋጀት ፕሮጀክት


አስፇሊጊ ነገሮች፡- ካርቶን ወይም ክሊሰር፣ መቀስ(ምሊጭ)ና እርሳስ
የአሰራር ቅዯም ተከተሌ
1. ካርቶን ወይም ክሊሰር ማዘጋጀት

2.በካርቶኑ ወይም በክሊሰሩ ሊይ በእርሳስ የሚከተሇውን ንዴፌ መሳሌ

43
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3. በካርቶኑ ወይም በክሊሰሩ ሊይ በእርሳስ የተሳሇውን ንዴፌ እጃችንን


እንዲይቆርጠን ጥንቃቄ በማዴረግ በመቀስ ወይም በምሊጭ ቆርጦ
ማውጣት

4. ከወጣው ቅርፅ ላይ የፍየልን እግሮች፣ፊት፣ቀንድ፣አንገትና ጅራት ሇይቶ


ማስተካከል፡፡ በመጨረሻም ሁሇት ዓይኖችንና አፍንጫን በመቀስ ቀስ ብሎ
ሇየብቻቸው ቆርጦ ማውጣት፡፡

ተማሪዎች! የምታውቋቸውን የእንሰሳት ቅርፅ በተመሳሳይ መንገድ ከካርቶን


በማዘጋጀት ሇመምህራችሁ አሳዩ፡፡

44
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

2.4.4. የሸክላ ስራ
ተማሪዎች! ወላጆቻችሁ የሚጠቀሙባቸውን የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን
ስም ዘርዝሩ፡፡ ከምን ከምን የተሰሩ ናቸው? የምታውቋቸውን በሚከተሇው
ሰንጠረዥ መሰረት መድባችሁ ፃፉ፡፡
የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች
ተ.ቁ ከብረት ከእንጨት ከሸክላ የተሰሩ ከቆዳ የተሰሩ ከፕላስቲክ
የተሰሩ የተሰሩ የተሰሩ
1
2
3
4

45
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ምዕራፌ ሶስት
ተፇጥሯዊ አካባቢያችን
3.1. ተፇጥሯዊ ክስተቶች
3.1.1 ተፇጥሯዊ ክሰተቶችን መመሌከት

ሀ. ቀንና ላሉት

መሌመጃ 3.1
1. ቀን ማሇት ምን ማሇት ነው?
2. ላሉትስ ማሇት ምን ማሇት ነው?

መሬት ሇ12 ሰዓት ግማሽ አካሎ ፀሏይ ሲያገኝ ይህም የመሬት አካባቢ ቀን
ተብል ይጠራሌ፡፡ የተቀረው ግማሽ አካሎ ዯግሞ የፀሏይ ብርሃን አያገኝም፡፡
ይህም ላሉት ተብል ይጠራሌ፡፡ሇቀጣይ 12 ሰዓት ፀሏይ ሲያገኝ የነበረው
ላሉት ሲሆን ላሉት የነበረው ፀሏይ ማግኘት ይጀምራሌ፡፡

46
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/1 የመሬት ከፉሌ ገፅታ በጨሇማ ከፉሌ ገፅታ የፀሏይ ብርሃን አርፍበት
ሇ. ወቅቶች
መሌመጃ 3.2
የሚከተለትን ጥያቄዎች መሌሱ፡፡
1. በአካባቢያችሁ ስንት አይነት ወቅቶች ይፇራረቃለ?
2. የክረምት ወቅት ማሇት ምን ማሇት ነው?
3. በጋ ማሇትስ ምን ማሇት ነው?
4. በእናንተ አካባቢ የክረምት ወራት የትኞቹ ወራት እንዯሆኑ ተናገሩ፡፡

47
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/2 የወቅቶች መፇራረቅ


ትጉህ ገበሬ

አቶ ፇሇቀ ትጉህ ገበሬ ናቸው፡፡ በበጋ መሬቱን አሳምረው ያርሳለ፣


ሇበሌግና ክረምት ወቅት አዝመራ የሚሆነውን መሬት ይሇያለ፡፡ በበሌግ
የዘሩትን ይንከባከባለ፣ ሇክረምት አዝመራ መሬቱን አሇስሌሰው ዘርና
ማዲበሪያ ያዘጋጃለ፡፡ በክረምቱ ወቅት ዘሩን በመዝራት አዝርዕቱን
ይንከባከባለ፡፡ወቅቱ ፀዯይ ሲሆን ምርት መሰብሰብ ይጀምራለ፡፡

48
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

በአገራችን አራት ወቅቶች አለ፡፡ እነርሱም ክረምት፣ ፀዯይ ወይም ጥቢ፣


በጋና በሌግ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ሰኔ፣ ሀምላና ነሏሴ የክረምት ወራት
ሲሆኑ ፣ መስከረም፣ ጥቅምትና ህዲር የፀዯይ ወቅት ናችው፡፡ እንዱሁም
ታህሳስ፣ ጥርና የካቲት የበጋ ወራት ሲሆኑ መጋቢት፣ ሚያዝያና ግንቦት
የበሌግ ወራት ናቸው፡፡
 ክረምት ዝናባማና ቀዝቃዛ ወራት ነው፡፡
 በጋ ሞቃትና ዯረቅ ወራት ነው፡፡
 ፀዯይ የአበባ ወራት በመባሌ ሲታወቅ ነፊሻማና እርጥበት ያሇበት
ወቅት ነው፡፡
 በሌግ ሞቃትና እርጥበት የሚዘወተርበት ወቅት ነው፡፡
ሏ. ቀስተ ዯመና

መሌመጃ 3.3
1. ተማሪዎች! ቀስተ ዯመና አይታችሁ ታውቃሊችሁ? መሌሳችሁን
ሇመምህራችሁ ተናገሩ፡፡
2. የቀስተ ዯመና ቀሇማት ምን ምን ናቸው?
3. ቀስተ ዯመና በምን ወራት ይከሰታሌ?

ቀስተ ዯመና በክረምት ወቅት ዝናብ እየዘነበ ፀሏይ ስትወጣ የሚፇጠር


ክስተት ነው፡፡ ቀስተ ዲመና ሰባት ቀሇማት ያለት ሲሆን በአብዛኛው
ዯምቀው የሚታዩት አረንጓዳ፤ ቢጫና ቀይ ቀሇማት ናቸው፡፡

49
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መ. ጎርፌ

መሌመጃ 3.4
1. ጎርፌ ምንዴን ነው?
2. ጎርፌ መቼ ይከሰታሌ?

ጎርፌ ማሇት ከባዴ ዝናብ ያሇማቋረጥ በሚዘንብበት ወቅት ከከፌተኛ ቦታ


የዝናብ ውሃ በከፌተኛ ግፉት ወዯ ዝቅተኛ ቦታ ሲፇስ የሚታይ ክስተት
ነው፡፡ በሃገራችንም ጎርፌ የሚከሰተው በክረምት ወቅት ነው፡፡
ሠ. ዴርቅ

መሌመጃ 3.5
1. ዴርቅ ማሇት ምን ማሇት ነው?
2. የዴርቅ ተፅዕኖ ምንዴን ነው?
3. ዴርቅ የሚከሰተው በምን ምክንያት ነው?

ዴርቅ የሚከሰተው ከፌተኛ የሆነ ሙቀት በመሬት ገፅ ሊይ ሇረጅም ጊዜ


በሚቆይበት ወቅት ነው፡፡ ሇምሳላ፤ በረጅም የበጋ ወራት የፀሏይ ሙቀት
ሇረጅም ጊዜ ስሇሚቆይ የከርሰምዴር ውሃ በከፌተኛ ሁኔታ ይቀንሳሌ፡፡
የዝናብ መጠን ሲቀንስ እና የዝናብ ወቅት ሲያጥር ድርቅ ይከሰታል፡፡ ድርቅም
በአንድ አካባቢ ሲከሰት ዕፅዋት በመድረቅ ይመናመናለ፡፡ እንስሳትም
የሚመገቡትና የሚጠጡት ነገር ይጠፋል፡፡

50
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3.1.2 ዑዯተ ህይወት

መሌመጃ 3.6
1. ሕይወት ያሊቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?
2. ሕይወት ያሊቸውና የላሊቸው ነገሮች የሚሇያዩበት ባህርያት ምን
ምን ናቸው?

ሕይወት ያሊቸው ነገሮች ዕፅዋትና እንስሳት ናቸው፡፡ ሕይወት ያሊቸው ነገሮች


ይራባለ፣ ያዴጋለ፣ ይሞታለ፡፡ ይህ የተፇጥሮ ክስተት ነው፡፡
የእንስሳት የእዴገት ዯረጃዎች

ሥዕል 3/3 የቢራቢሮ ዑደተ ህይወት

51
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የዕፅዋት የዕዴገት ዯረጃዎች

ሥዕሌ 3/4 የአበባማ ዕፅዋት ዑዯተ ህይወት

3.1.3 መሇኪያዎች

መሌመጃ 3.7
1. ተማሪዎች የቁመታችሁን ሌክ ታውቃሊችሁ?
2. ክብዯታችሁ ምን ያህሌ ነው?
3. ከቤታችሁ እስከ ትምህርት ቤታችሁ ያሇው ርቀት ምን ያህሌ ነው?
4. ከቤታችሁ ወዯ ትምህርት ቤት ሇመዴረስ የሚወስዴባችሁ ጊዜ ስንት ነው?
5. የአካባቢ ሳይንስ መፅሏፊችሁ ርዝመት ስንት ነው?
6. በአካባቢያችሁ ሰዎች የሌዩ ሌዩ ነገሮች መጠን እንዳት ይገሌፃለ?

52
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

በአካባቢያችን የሚገኙ ሌዩ ሌዩ ነገሮችን ሌክና መጠን ሇማወቅ ሌዩ ሌዩ


የመሇኪያ ዓይነቶችን እንጠቀማሇን፡፡ በተሇያዩ አካባቢዎች ሰዎች የአካሌ
ክፌልቻቸውን በመጠቀም በአካባቢያቸው ያለ ነገሮችን ሌክና መጠን ሲገሌፁ
ይታያለ፡፡ ስሇዚህ በአካባቢያችን ያለትን ነገሮች ሌክና መጠን ሇመግሇፅ
ሌዩ ሌዩ የመሇኪያ መሳሪያዎች ያስፇሌጉናሌ፡፡ የአካባቢያችንን መሇኪያ
መሳሪያዎች ሌማዲዊና ዘመናዊ በማሇት መክፇሌ እንችሊሇን፡፡ እስቲ
በአካባቢያችሁ ያለ መሇኪያዎችን ስም ተራ በተራ ሇመምህራችሁ ተናገሩ፡፡

ሀ. ሌማዲዊ መሇኪያዎች

ከጥንት ጀምሮ እስካሁን በተሇይ በገጠሩ አካባቢ ሰዎች የነገሮችን ሌክ ወይም


መጠን ሇማወቅ የሚሇኩት በአካሌ ክፌልች በመጠቀም ሲሆን እነዚህንም
ሌማዲዊ መሇኪያዎች ብሇን እንጠራቸዋሇን፡፡

1. ሌማዲዊ የርዝመት መሇኪያ

መሌመጃ 3.8

1. ተማሪዎች በእናንተ አካባቢ በሌማዲዊ መንገዴ ርዝመት በምን ይሇካሌ?


2. እናንተ የሰውነት ክፌልቻችሁን በመጠቀም የሌዩ ሌዩ ርዝመትን
ሇክታችሁ ታውቃሊችሁ?
3. እስቲ የጠረጴዛችሁን ርዝመት በክንዲችሁ ሇኩ፡፡
4. የመፅሏፊችሁን ቁመት በስንዝር ሇኩ፡፡
5. የክፌሊችሁን ርዝመት በእርምጃ ሇኩና ከክፌሌ ጓዯኞቻችሁ ጋር

አነጻጽሩ፡፡

53
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/5 ሌማዲዊ የርዝመት መሇኪያዎች

መሌመጃ 3.9
በቡዴን በመሆን በሚከተለት ነጥቦች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. የሁለም ሰው ክንዴ እኩሌ ይሆናሌ ወይ? ርምጃስ? ስንዝርስ?
2. ሌማዲዊ የርዝመት መሇኪያ ጥቅሙ ምንዴን ነው? ጉዲቱስ?
ከውይይት በኋሊ ሪፖርቱን ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ አንብቡሊቸው፡፡

በአካባቢያችን የሚገኙ ሌማዲዊ የርዝመት መሇኪያዎች ክንዴ፣ ርምጃ፣ ጋት፣


ስንዝርና ጫማ ናቸው፡፡

54
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

2. ሌማዲዊ የግዝፇት መሇኪያ

መሌመጃ 3.10
1. በአካባቢያችን ግዝፇት እንዳት ይሇካሌ?
2. ከአካባቢያችሁ በሚገኙ ቁሳቁሶች የግዝፇት መሇኪያ መሳሪያ ስሩና
ሇመምህራችሁ አሳዩ፡፡
3. በሌማዲዊ የግዝፇት መሇኪያ ዘዳ የአንዴን ነገር ትክክሇኛ ግዝፇት

ሇማወቅ የማይቻሇው ሇምንዴን ነው?

ሥዕሌ 3/6 ሌማዲዊ የግዝፇት መሇኪያ

3. ሌማዲዊ የጊዜ መሇኪያ

መሌመጃ 3.11
1. ጊዜን እንዳት መሇካት ይቻሊሌ?
2. ጊዜ በእናንተ አካባቢ በምን ይሇካሌ?

55
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ጊዜን በሌማዲዊ ዘዳ ሰዎች የፀሏይ አቅጣጫን በመከተሌ፣ የዛፌ ወይም የሰው


ጥሊን በማየት፣ የድሮ ጩኸትን በመጠባበቅና ውሃን በማንጠባጠብ ይሇካለ፡፡

ሥዕሌ 3/7 ሌማዲዊ የጊዜ መሇኪያዎች

ሇ. ዘመናዊ መሇኪያዎች
ሳይንስ የሰው ሌጅ በአካባቢው ያለ ነገሮችን ሌክና መጠን በቀሊለና በትክክሌ
ሇመሇካት እንዱችሌ ከፌተኛ አስተዋጽኦ ሲያዯርግ ቆይቷሌ፡፡ እነዚህም
የሳይንስ ውጤት የሆኑት መሣሪያዎች ዘመናዊ መሇኪያዎች ይባሊለ፡፡

56
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

1. ዘመናዊ የርዝመት መሇኪያ

ሥዕሌ 3/8 ዘመናዊ የርዝመት መሇኪያዎች

ርዝመትን ወጥ በሆነና በትክክሌ ሇመሇካት


የፕሮጀክት ሥራየሚያስችሌ መሇኪያ መሳሪያ
ማስመሪያ ይባሊሌ፡
ርዝመትን መሇካት
የትምህርት ቤታችሁን አንዴ ሕንፃ በመውሰዴ ዙሪያውን በተጠቅሊይ
ማስመሪያ በመጠቀምና በመሇካት ምን ያህሌ እንዯሆነ ሇመምህራችሁ ሪፖርት
አዴርጉ፡፡
ርዝመትን የመሇካት ዘዳ ቅዯም ተከተሌ
1. ተጠቅሊይ ማስመሪያውን ከሚሇካው ነገር አጠገብ ማስጠጋት፣
2. የማስመሪያው ዜሮ ምሌክት ያሇበት ቦታ ሌክ የሚሇካው አካሌ የመነሻ
ነጥብ ሊይ መሆኑን ማረጋገጥ፣
3. ላሊው የማስመሪያው ጫፌ/ሌክ/ በዯረሰበት ነጥብ በትክክሌ አንብቦ
መመዝገብ፡፡

57
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የርዝመት መሇኪያ አሀዴ ሜትር ይባሊሌ ፡፡ ላልች አባዢዎችና ምንዝር


አሃድች አለት፡፡ እነርሱም ሚሉ ሜትር፣ ሣንቲ ሜትር፣ ዳሲ ሜትር፣ ኪል
ሜትር ወዘተ ናቸው፡፡
የርዝመት መሇኪያ አሃድች ዝምዴና
1ሜትር = 100 ሣንቲ ሜትር

1 ሣንቲ ሜትር = 10 ሚሉሜትር

1 ኪል ሜትር = 1000 ሜትር

የሚከተለትን አካልች በመሇካት ሠንጠረዡን ሙለ፡፡

ሠንጠረዥ 3/1

የሚሇካው አካሌ ርዝመት


የአካባቢ ሳይንስ መፅሏፌ
የክፌሊችሁ ጥቁር ሰላዲ
የማስታወሻ ዯብተራችሁ

የመማሪያ ክፌሊችሁ

ሙከራ 3/1
አንዴ ሜትር ርዝመት ያሇው ማስመሪያ መስራት
አስፇሊጊ ነገሮች
አንዴ ሜትር የሆነ ጠፌጣፊ እንጨት፣ ወረቀት፣ ማስመሪያ፣ መቀስ፣
የብርጭቆ ወረቀት

58
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የአሰራር ቅዯም ተከተሌ


1. ጠፌጣፊውን እንጨት/ጣውሊ/ ማሇስሇስ፣
2. ከሇሰሇሰው ጠፌጣፊ እንጨት /ጣውሊ/ ሊይ ወረቀቱን በሙጫ ማጣበቅ፣
3. ማስመሪያ በመጠቀምና በሚሉ ሜትር በመከፊፇሌ ቁጥሮችን በትክክሌ
በአንዴ ሳንቲ ሜትር ርዝመት ሊይ መፃፌ፣

2. ዘመናዊ የግዝፇት መሇኪያዎች

መሌመጃ 3.12
1. ስኳር ወይም ቡና ሲገዛ ወይም ሲሸጥ ግዝፇቱ በምን ይሇካሌ?
2. የግዝፇት መሇኪያ አሀዴ ምንዴን ነው?

የማንኛውም አካሌ ግዝፇት የመሇኪያ መሣሪያ ሚዛን ነው፡፡ሚዛን ሁሇት


ሣህኖች ያለት ሲሆን በአንዴ ወገን ባሇው ሣህን ሊይ ግዝፇቱ የሚታወቀውን
አካሌ /መዯበኛ ግዝፇት/ በማኖር በላሊ ወገን ዯግሞ መጠናቸው ያሌታወቁ
ግዝፇቶችን በማስቀመጥ የነገሮቹን መመጣጠን /እኩሌ መሆን/ በማረጋገጥ
መሇካት ይቻሊሌ፡፡

59
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የሚከተለትን ሥዕልች በትኩረት ተመሌከቱ፡፡

ሀ. የሚዛን ስዕሌ ሇ. የግራም ዴንጋዮች /መዯበኛ ግዝፇቶች/

ሥዕሌ 3/9 ዘመናዊ የግዝፇት መሇኪያ

የመጠነቁስ መሇኪያ አሃዴ ኪል ግራም ነው፡፡ ላልች የመጠነቁስ አሃድች


ሚሉግራም፣ ሳንቲግራም፣ ዳሲግራም፣ ኪልግራም ወዘተ ይባሊለ፡፡
የመጠነቁስ አሃድች ዝምዴና
1 ኪልግራም = 1000 ግራም
1 ግራም = 1000 ሚሉግራም

60
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሙከራ 3/2
የሚዛን አሰራር
አስፇሊጊ ዕቃዎች
ቀጭን የእንጨት ዘንግ፣ ክሮች ወይም ሲባጎ፣ ሁሇት የሊስቲክ ሳህኖች
/የጫማ ቀሇም ቆርቆሮዎች/
የአሰራር ቅዯም ተከተሌ
1. እያንዲንደን የሊስቲክ ሳህን /የጫማ ቀሇም ቆርቆሮዎች/ ጫፊቸው ሊይ
ሶስት/አራት/ ቦታ በምስማር ብሷቸው፣
2. የእንጨት ዘንጉን መሏሌ ቦታ ፇሌጋችሁ በአንዶ ብጣሽ ክር እሰሩ፣
3. የእንጨት ዘንጉ ሳያጋዴሌ በእኩሌ ርቀት በግራና ቀኝ ሁሇቱን ሳህኖች
ማንጠሌጠሌ፣
አስታውሱ! የተሇያዩ አካሊትን በሚዛኑ ሇክቶ ሇመጠቀም መዯበኛ የግራም
ዴንጋዮችን ማግኘት አስፇሇጊ ነው፡፡
4.ዘመናዊ የጊዜ መሇኪያዎች

መሌመጃ 3.13
1. ወዯ ትምህርት ቤት ሇመሄዴ የመነሻ ጊዜውን እንዳት ታውቂያሇሽ/ሇህ/?
2. የአካባቢ ሳይንስ ክፌሇጊዜ ርዝማኔ ምን ያህሌ ነው?
3. ከትምህርት ቤት እስከ ቤታችሁ ሇመዯረስ ምን ያህሌ ጊዜ ይወስዴባችኋሌ?
4. ጊዜን በትክክሌ እንዳትና በምን መሇካት ይቻሊሌ?

61
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ነገሮች ሁለ የሚከናወኑት በጊዜ ሂዯት ውስጥ ነው፡፡ የጊዜ መሇኪያ ሰዓት


ሲሆን የጊዜ መሇኪያ አሃዴ ሴኮንዴ ነው፡፡ ላልች የጊዜ መሇኪያ አሃድች
ዯቂቃ፣ ሰዓት፣ ቀን፣ ሳምንት፣ ወራት ናቸው፡፡

ሥዕሌ 3/10 ዘመናዊ የጊዜ መሇኪያ

መሌመጃ 3.14
1. በአንዴ ሰዓት ውስጥ ስንት ዯቂቃዎች አለ?
2. በአንዴ ዯቂቃ ውሰጥ ስንት ሴኮንድች አለ?
3. በአንዴ ቀን ውስጥ ስንት ሰዓቶች አለ?
4. አንዴ ሳምንት ስንት ቀናት አለት?
5. አንዴ ወር ስንት ቀናት አለት?

62
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የጊዜ መሇኪያ አሃድች ዝምዴና


1 ቀን = 24 ሰዓት
1 ሰዓት= 60 ዯቂቃ
1 ዯቂቃ = 60 ሴኮንዴ

ሥዕሌ3/11 ሰኞ፣ ማክሰኞ ጨዋታ

በአንዴ ሳምንት ሰባት ቀናት አለ፡፡

3.1.4 ቁሶችን መመዯብ

ቁሶች በተፇጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ የሚገኙ ነገሮች ናቸው፡፡ በተፇጥሮ


የሚገኙ ቁሶች ዴንጋይ፣ ፀጉር፣ ጥጥ፣ እንጨት፣ ገሇባ፣ አፇር ወዘተ ሲሆኑ ሰው
ሰራሽ የምንሊቸው ዯግሞ ጎማ፣ ብርጭቆ፣ ፕሊስቲክ፣ ጨርቅ፣ ወዘተ ናቸው::

63
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.15
1. በተሰጡት ምሳላዎች መሰረት በአካባቢያችሁ የሚገኙትን ሰው ሰራሽ
የሆኑና ተፇጥሮአዊ የሆኑ ቁሶችን ዘርዝሩ፡፡ እንዱሁም ሻካራና ሇስሊሳ
በማሇት ሇዩ፡፡
የቁስ ስም ሰው ሰራሽ ተፇጥሯዊ ሻካራ ሇስሊሳ
ብርጭቆ √ √
ዴንጋይ √ √

3.2 የተፇጥሮ ሀብቶች

የተፇጥሮ ሀብቶች በተፇጥሮ የሚገኙ ነገሮች ሆነው ሇሰው ሌጅ በቀጥታም ሆነ


በተዘዋዋሪ ጥቅም የሚሰጡ ናቸው፡፡

መሌመጃ 3.16

1. በአካባቢያችሁ የሚገኙ የተፇጥሮ ሃብቶችን ስም ዘርዝሩ፡፡


2. የዘረዘራችኋቸውን የተፇጥሮ ሀብቶች ሇሰው ሌጅ የሚሰጡትን ጠቀሜታ
ግሇጹ፡፡

64
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3.2.1 የተፇጥሮ ሀብቶች ዓይነት

ውሃ፣ አየር፣ አፇር፣ ዕፅዋት፣ እንስሳትና ማዕዴናት ዋና ዋናዎቹ የተፇጥሮ


ሀብቶች ናቸው፡፡

ሀ. ውኃ

መሌመጃ 3.17
1. ውኃ ምንዴን ነው?
2. ውኃ ከየት ይገኛሌ?
3. ውኃ ሇተክልችና ሇእንስሳት ምን ጥቅም ይሰጣሌ?

ውኃ ፇሳሽ ሲሆን በውስጡ በሙሙት መሌክ ማዕዴናትን ይዟሌ፡፡ አብዛኛው


የመሬት ክፌሌ የተሸፇነው በውኃ ነው፡፡ እነዚህም ውኃማ ቦታዎች
ውቅያኖሶች፤ ወንዞች፤ ሏይቆች፤ ኮሬዎች ወዘተ ይባሊለ፡፡ ውኃ ሇእንስሳትና
ሇዕፅዋት በጣም አስፇሊጊ የሆነ የተፇጥሮ ሃብት ነው፡፡
ሇ. አየር

መሌመጃ 3.18
1. አየር ምንዴን ነው?
2. ዕፅዋትና እንስሳት ያሇ አየር መኖር ይችሊለ ይመስሊችኋሌ?
ሇምን?
3. እኛስ ያሇ አየር መኖር እንችሊሇን?

65
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

አየር የመሬትን ዙሪያ ከቦ የሚገኝ የተፇጥሮ ሀብት ነው፡፡ አየር የብዙ ጋዞች፤
የውኃ ትነትና የዯቃቅ ነገሮች ቅይጥ ነው፡፡ አየር ሇእንስሳትና ሇዕፅዋት
ጠቃሚ ነው፡፡ ዕፅዋትና እንስሳት ያሇ አየር መኖር አይችለም፡፡
ሏ. አፇር
አፇር አብዛኛውን ምዴር ሸፌኖ የሚገኝ ሲሆን የሚፇጠረውም ከአሇቶች
ስብርባሪ፣ ከዕፅዋት ብስባሽና ከእንስሳት ቅሪተ አካሌ ነው፡፡ የአፇር
አይነቶች ሶስት ናቸው፡፡ እነርሱም አሸዋማ አፇር፣ ሸክሊ አፇርና ሇም አፇር
ናቸው፡፡
አፇር ሇዕፅዋት እዴገት ወሳኝ ነው፡፡ ዕፅዋት ከአፇር ውኃና ማዕዴናትን
ያገኛለ፡፡

መሌመጃ 3.19
1. አፇር ምንዴን ነው?
2. አፇር ሇምን ይጠቅማሌ?
3. ከአፇር ምን ምን ቁሶችን መስራት ይቻሊሌ? በቡዴን ሆናችሁ
ተወያዩ፡፡
4. ስንት አይነት አፇር ታውቃሊችሁ?
5. አርሶአዯሮች፣ የሕንፃ መሏንዱሶች፣ መንገዴ ሰራተኞች አፇርን
ሇምን ሇምን ይጠቀሙበታሌ? ተወያዩ፡፡

66
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መ. ዕፅዋት
መሌመጃ 3.20
1. በአካባቢያችሁ ምን ምን ዓይነት ዕፅዋት ይገኛለ?
2. ዕፅዋት ሇእንስሳትና ሇሰው ምን ጥቅም ይሰጣለ?
3. ቅጠልቻቸው የሚበለ ዕፅዋትን ዘርዝሩ፡፡
4. ስራቸው የሚበለ ዕፅዋትን ዘርዝሩ፡፡
5. ዘሮቻቸው የሚበለ ዕፅዋትን ዘርዝሩ፡፡

ዕፅዋት ሇምግብነት፣ ሇሌብስና ሇመጠሇያ መስሪያ ያገሇግሊለ፡፡ ዕፅዋት ሶስት


ዋና ዋና ክፌልች አሎቸው፡፡ እነርሱም ቅጠሌ፣ ግንዴና ሥር ናቸው፡፡
የዕፅዋት ባሕርያት
 ዕፅዋት ይመገባለ፡፡
 ዕፅዋት ይተነፌሳለ፡፡ የሚተነፌሱትም በቅጠልቻቸው ሊይ ባለ
ቀዲዲዎች ነው፡፡
 ዕፅዋት በዘርና ያሇ ዘር ይራባለ፡፡
በዘር የሚራቡ ዕፅዋት በቆል፣ ስንዳ፣ ባቄሊ፣ ጤፌ፣ ጎመን፣ ባህር ዛፌና ላልች
ሲሆኑ፣ ያሇዘር የሚራቡ ዯግሞ ሙዝ፣ ፅጌሬዲ፣ ሸንኮራ አገዲ ወዘተ ናቸው፡፡
ሠ. ማዕዴናት
መሌመጃ 3.21
1. ማዕዴናት የሚባለት ምን ምን ናቸው?
2. ማዕዴናት ከየት ይገኛለ?
3. በአካባቢያችሁ ምን ምን አይነት ማዕዴናት ይገኛለ?

ማዕዴናት በተፇጥሮ በገጸ ምዴርና በመሬት ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ሰዎች


መሬትን በመቆፇርና አሇቶችን በመፌጨት ማዕዴናት ያገኛለ፡፡

67
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሇምሳላ አለምኒየምንና መዲብ ከአሇቶች ወርቅና ብረት ዯግሞ ከአፇር


ይገኛለ፡፡ ከማዕዴናት ጌጣጌጥና የተሇያዩ መገሌገያ ዕቃዎችን ማምረት
ይቻሊሌ፡፡ ሇምሳላ የወርቅ ቀሇበት፣ ሳንቲሞች፣ ማንኪያ፣ ቢሊዋ፣ ምስማር
የሚሰሩት ከማዕዴናት ነው፡፡

ሥዕሌ 3/12 ከማዕዴናት የተሠሩ መገሌገያዎች

68
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3.2.2 የተፇጥሮ ሀብቶች ጥቅም


መሌመጃ 3.22
1. የተፇጥሮ ሀብቶች ሇምን ሇምን ያገሇግለናሌ?
2. ውኃ፣ የደር እንስሳት፣ ማዕዴናትና አየር ያሊቸውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
ተወያዩና ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ አቅርቡ፡፡
3. የተፇጥሮ ሀብትን እንዳት ሇመዝናኛነት ማዋሌ ይቻሊሌ?
4. የተፇጥሮ ሀብቶች ቱሪስቶችን እንዳት ሉስቡ ይችሊለ?

የተፇጥሮ ሀብቶችን ወዯ ገበያ በማቅረብ ገንዘብ ያስገኛለ፡፡ በገንዘቡ ዯግሞ


አስፇሊጊ የሆኑ ነገሮች ይገዛበታሌ፡፡ መሰረተ ሌማትም ይስፊፊበታሌ፡፡

3.2.3 የተፇጥሮ ሀብቶች ጥበቃ

ሀ. የውሃ መበከሌን መከሊከሌ

መሌመጃ 3.23
1. ውሃ እንዲይበከሌ ምን ማዴረግ አሇብን?
2. በአካባቢያችሁ ውሃ ከየት ታገኛሊችሁ? እንዳትስ
ትንከባከቡታሊችሁ?
3. ውሃ በተሇያዩ ነገሮች እንዲይበከሌ መጠንቀቅ ሇምን ያስፇሌጋሌ?

የምንጠቀምበት ውሃ በቆሻሻ፣ በመርዝና በበሽታ አምጪ ተህዋሲያን


እንዲይበከሌ መከሊከሌ አሇብን፡፡ የውሃ ጉዴጓድችና ምንጮች እንዲይበከለ፡-
 በአካባቢው ምንም ቆሻሻ እንዲይኖር ማፅዲት፣
 ዙሪያውን በአጥር ማጠር፣
69
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

 ከእንስሳት ንኪኪ ማራቅ፣


 የመፀዲጃ ቤትን ከውሃ አርቆ መቆፇር፣
 ሇእንስሳት መጠጫ መከሇሌ፣
 ሇሌብስ ማጠቢያ የሚሆን ቦታን መከሇሌ፣
 ከቤትና ፊብሪካዎች የሚወጡ ቆሻሻዎች ወዯ ወንዝ እና ኩሬ
እንዲይፇሱ ማዴረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ሇ. የአየር ብክሇትን መከሊከሌ

መሌመጃ 3.24
1. አየር እንዳት ይበከሊሌ?
2. ቆሻሻ በበዛበት አካባቢ ስታሌፈ ምን ይሰማችኋሌ?
3. እንጨት ሲቀጣጠሌ ወይም ጫካ ተቃጥል ሲጨስ ምን አይነት ሁኔታ
ያስከትሊሌ?

አየር በጭስና በተሇያዩ ቆሻሻዎች ሉበከሌ ይችሊሌ፡፡ ሇምሳላ የከሰሌ ጭስ


ሰውን በማፇን ሇሞት አዯጋ ያጋሌጣሌ፡፡ በቆሻሻ አካባቢ ያሇ አየር ሇተሇያዩ
በሽታዎች ያጋሌጣሌ፡፡ ስሇዚህ አየር እንዲይበከሌ አካባቢን ከቆሻሻና
ከተሇያዩ ጭሶች መከሊከሌ አሇብን፡፡

70
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሏ. የአፇር መሸርሸርን መከሊከሌ

ሥዕሌ 3/13 የተሸረሸረ መሬት

መሬት ተዲፊት ሲሆንና ሇወራጅ ውኃ ሲጋሇጥ አፇሩ ይጠረጋሌ፡፡


ሙከራ 3/3
የአፇር መሸርሸርን ሇማሳየት
አስፇሊጊ ቁሳቁሶች
ትንሽ ሇም አፇር፣ ውኃ፣ የውኃ ማንጠባጠቢያ
የአሰራር ቅዯም ተከተሌ
1. ትንሽ ሇም አፇር በጠረጴዛ ወይም በወረቀት ሊይ ቆሇሌ አዴርጎ
ማስቀመጥ፣
2. ውኃውን በውኃ ማንጠባጠቢያ ሊይ ማዴረግ፣
3. ውኃውን በአፇሩ ሊይ ቀስ በቀስ ማንጠባጠብና ውጤቱን መመሌከት፣
ከሙከራው ምን ተማራችሁ? እስቲ የሚከተለትን ጥያቄዎች መሌሱ፡፡

71
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.25
1. አፇር እንዲይሸረሸር ምን ምን ማዴረግ አሇብን?
2. በአካባቢያችሁ ያለ አርሶ አዯሮች አፇር ሇምነቱን ጠብቆ እንዱቆይ
ምን ምን ተግባራትን ያከናውናለ?
3. አፇር በውሃ የሚሸረሸረው በየትኛው አካባቢ ነው? በሜዲማ ወይስ
በተዲፊት ቦታ? ሇምን?

ሥዕሌ3/14 ጥበቃ የተዯረገሇት መሬት

የአፇር መሸርሸርን ሇመከሊከሌ የሚያስችለ ዘዳዎች


ሀ. መሬትን በዕፅዋት መሸፇን፣
ሇ. የዛፌ ችግኞችን መትከሌ፣
ሏ. የተሇያዩ እርከኖችን መስራት፣
መ. በተራሮች ሊይ ውሃ የሚሰርግበት ጉዴጓዴ መስራት፣ ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡፡
72
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3.3. በአካባቢያችን ያለ ዕፅዋት


መሌመጃ 3.26
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. እናንተ በምትኖሩበት አካባቢ ምን ምን አይነት ዕፅዋት አለ?
2. ዕፅዋትን ከእንስሳት በምን እንሇያቸዋሇን?
3. የዕፅዋት ዋና ዋና ክፌልች ምን ምን ናቸው?

3.3.1. የዕፅዋት ክፌልችና ተግባራቸው


ዕፅዋት ሇተሇያዩ አገሌግልት የሚውለ የተሇያዩ የአካሌ ክፌልች አሊቸው፡፡
መሌመጃ 3.27
የሚከተሇውን ጥያቄ በቡዴን ተወያዩበት፡፡
ቀጥል በተመሇከተው ስዕሌ ሊይ በፉዯሌ የተመሇከቱትን የተክሌ
ክፌልች ስማቸውን ተናገሩ፡፡

ሥዕሌ 3/15 የአበባማ የዕፅዋት አካሌ ክፌልች

73
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ስር፣ ግንዴ፣ ቅጠሌና አበባ የዕፅዋት ዋና ዋና ክፌልች ናቸው

መሌመጃ 3.28
ቀጥል በቀረበው ጥያቄ በቡዴን ተወያዩ፡፡
የዕፅዋት ወይም የተክልች ሥር፣ ግንዴ፣ ቅጠሌና አበባ ተግባራት ምን ምን
ናቸው?

ሀ. ሥርና ጥቅሙ
ሥር ከመሬት በታች ያሇው የተክልች ወይም የዕፅዋት ክፌሌ ነው፡፡

ሥዕሌ 3/16 ሌዩ ሌዩ የሳር አይነቶች

የስር ዋና ዋና ተግባራት
ዕፅዋትን ከመሬት ጋር አቆራኝቶ ሇማያያዝና ሇመዯገፌ፣
ውሃና ላልች ማዕዴናትን ከአፇር ወዯ ተክልቹ እንዱገባ ሇማዴረግ እና
ምግብን ሇማከማቸት ናቸው፡፡

74
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.29
1. የተሇያዩ ተክልች ሥሮችን በማየት ሌዩነታቸውን አስረደ፡፡
2. ሥሮቻቸው ሇምግብነት የሚያገሇግለ ተክልችን ተናገሩ፡፡
3. አንዴን ዛፌ ስንገፊው ወይም ስንዯገፇው የማይወዴቀው ሇምንዴን ነው?

የስኳር ዴንች ስር የቀይ ስር የካሮት ስር

ሥዕሌ 3/17 ስሮቻቸው ሇምግብነት የሚያገሇግለ ዕፅዋት

ሇ. ግንዴ እና ጥቅሙ

በአካባቢያችን ያለ ዕፅዋት ግንዴ አሊቸው፡፡ ግንዴ የዕፅዋትን ቅጠልችና


ቅርንጫፍች ዯግፍ የያዘ የዕፅዋት ክፌሌ ነው፡፡

75
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.30
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. ግንዴ ሇዕፅዋት ምን ጥቅም አሇው?
2. በአካባቢያችሁ የሚገኙ ዕፅዋት ግንዲቸው አንዴ አይነት ቅርፅ አሇው ወይስ
ይሇያያሌ?
3. በአካባቢያችሁ ግንዲቸው ሇምግብነት ከሚያገሇግለ ዕፅዋት ውስጥ ሁሇት
ምሳላዎችን ስጡ፡፡

ሥዕሌ 3/18 የግንዴ አይነቶች

76
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የዕፅዋት ግንዴ የሚከተለት ጠቀሜታዎች አለት


የዕፅዋትን ቅጠልችና ቅርንጫፍች ዯግፍ መያዝ
በቅጠልች የሚዘጋጀውን ምግብ ከቅጠልች ወዯ ታች /ወዯ ስር/
ማስተሊሇፌ
በስር የተመጠጠውን ውኃና ማዕዴናት ወዯ ቅጠልች ማስተሊሇፌ
ሏ. ቅጠሌና ጥቅሙ

መሌመጃ 3.31
ሇሚከተለት ጥያቄዎች መሌስ ስጡ፡፡
1. በአካባቢያችሁ የሚገኙ ዕፅዋት የቅጠልቻቸው ቀሇም ምን ምን አይነት
ነው?
2. በአካባቢያችሁ የሚገኙ ዕፅዋት የቅጠልቻቸው ቅርፅ ተመሳሳይ ነው
ወይስ ይሇያያለ?
3. የዕፅዋት ቅጠሌ ሇሰውና ሇዕፅዋቱ የሚሰጡት ጥቅም ምንዴነው?
4. ቅጠሊቸው ሇሰው ምግብነት የሚያገሇግለ ዕፅዋትን ዘርዝሩ፡፡

77
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/19 የተሇያዩ ቅጠልች

የአብዛኞቹ ዕፅዋት ቅጠልች አረንጓዳ ቀሇም አሊቸው፡፡ የዕፅዋት ቅጠልች


በቅርፅ ይሇያያለ፡፡ ቅጠልች ከፀሏይ የሚሇቀቀውን የፀሏይ ብርሃን ሏይሌ
ተጠቅመው ምግብ ያዘጋጃለ፡፡ በመሆኑም ቅጠልች ምግብ አዘጋጅ ተብሇው
ይጠራለ፡፡ ቅጠልች ሇትንፇሳ ወይም ሇአየር ሌውውጥ ያገሇግሊለ፡፡

መ. አበባና ጥቅሙ
አበባ በሁለም ዕፅዋት ሊይ አይገኝም፡፡ አንዴንዴ ዕፅዋት አበባ ሲኖራቸው
አንዲንድቹ ዯግሞ አበባ የሊቸውም፡፡

መሌመጃ 3.32
አበባ ያሊቸውና አበባ የላሊቸውን እፅዋት ሁሇት ሁሇት ምሳላ ስጡ፡፡

የዕፅዋት አበቦች በቀሇማቸው፣ በሽታቸው እና በሚኖራቸው ቅርፅ ይሇያያለ፡፡

78
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/20 የተሇያዩ አበቦች

መሌመጃ 3.33
ቀጥል ባለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. አበቦች ሇዕፅዋት እና ሇላልች እንሰሳት ምን ጥቅም አሊቸው?
2. የፅጌረዲ አበባ ከአዯይ አበባ በምን ይሇያሌ?

ዘርና ፌሬ የሚገኙት ከአበባ ነው፡፡ አበባ ሇንብ እርባታ ያገሇግሊሌ፡፡ አበባ


ሇገቢ ምንጭነት፣ ሇስጦታ ወዘተ ሁለ ይጠቅማሌ፡፡

መሌመጃ 3.34
ቀጥል ያሇውን ጥያቄ በግሊችሁ ስሩ፡፡
ሁለንም የእፅዋት ክፌልች የያዘ ስዕሌ ሳለና የዕፅዋቱን ክፌልች ሰይሙ፡፡

79
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3.3.2. እፅዋትን መሇየት እና መመዯብ

ዕፅዋት በመጠናቸው፣ በግንዲቸው ቅርፅ፣ በቅጠሊቸው ቅርፅና መጠን ወዘተ


ይሇያያለ፡፡ በአካባቢያችን የሚገኙ ዕፅዋትን የተሇያዩ መስፇርቶች በማውጣት
መመዯብ ይቻሊሌ፡፡
መሌመጃ 3.35
የሚከተለትን ጥያቄዎች በትምህርት ቤታችሁ ውስጥ የመስክ ጉብኝት
በማዴረግ ስሩ፡፡
በአካባቢ ሳይንስ ክፌሇ ጊዜ ከመምራችሁ ጋር በትምህርት ቤት አካባቢ
የሚገኙ ዕፅዋትን ስም ተዘዋውራችሁ በመመዝገብ የምዯባ መስፇርት አውጡ
እና ምዯባ አዴርጉ፡፡

መጠናቸውን መሰረት በማዴረግ ዕፅዋት በሶስት ይከፇሊለ፡፡ እነርሱም


ሀ. ትናንሽ ዕፅዋት
ሇ. መካከሇኛ ዕፅዋት /ቁጥቋጦ/
ሏ. ትሊሌቅ ዕፅዋት /ዛፌ/
ሀ. ትናንሽ ዕፅዋት፡- በዚህ ሥር የሚመዯቡ ዕፅዋት ሳሮችን እና ላልች
አነስተኛ እፅዋትን ያጠቃሌሊሌ፡፡

80
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/21 ትናንሽ ዕፅዋት

ሇ. መካከሇኛ ዕፅዋት፡- በእነዚህ ሥር የሚመዯቡት መካከሇኛ መጠን ያሊቸው


ናቸው፡፡ እነዚህ ዕፅዋት በብዛት በቆሊማ እና ሞቃታማ አካባቢ የሚበቅለ
ቁጥቋጦዎች ናቸው፡፡ ምሳላ ቀጋ፣ አጋም፣ ክትከታ፣ ወዘተ ናቸው፡፡

ሥዕሌ 3/22 ቁጥቋጦዎች

81
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሏ. ትሊሌቅ ዕፅዋት፡- እነዚህ ዕፅዋት ከላልቹ አንፃር ሲታዩ በጣም ትሌሌቅ


መጠን ያሊቸው ናቸው፡፡ ሇምሳላ ጥዴ፣ ዝግባ፣ ኮሶ፣ ባህር ዛፌ፣ ዋርካ፣ ሾሊ፣
የመሳሰለት ናቸው፡፡

ሥዕሌ 3/23 ትሊሌቅ ዛፍች

3.3.3. የዕፅዋት እዴገት


1. ሇዕፅዋት እዴገት አስፇሊጊ የሆኑ ነገሮች
በአንዯኛ ክፌሌ የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ሊይ ዕፅዋት ሕይወት ያሊቸው
ነገሮች መሆናቸውን፣ እንዯሚተነፌሱ፣ የራሳቸውን ምግብ እንዯሚያዘጋጁ፣
እንዯሚራቡ እና እንዯሚያዴጉ ተምራችኋሌ፡፡

82
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.36
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. ሇዕፅዋት ዕዴገት አስፇሊጊ ናቸው የተባለት ውሃ፣ አፇር፣ አየርና የፀሏይ
ብርሃን አስፇሊጊ የሆኑበትን ምክንያቶች ዘርዝሩ፡፡
2. ዕፅዋት ከሚከተለት ነገሮች ውስጥ አንደን ቢያጡ ምን ሉሆኑ እንዯሚችለ
በቡዴን ሆናችሁ ተወያዩ፡፡
ሀ. ውሃ
ሇ. አየር
ሏ. አፇር
መ. የፀሏይ ብርሃን

ሙከራ 3/3
ሇዕፅዋት እዴገት የሚያስፇሌጉትን ነገሮች በሙከራ ማረጋገጥ
ሀ. ውሃ ሇዕፅዋት ዕዴገት አስፇሊጊ መሆኑን በሙከራ ማረጋገጥ
ሙከራውን ሇመስራት የሚያስፇሌጉ ቁሳቁሶች
 ውሃ፣
 ሁሇት የተቆረጡ ተመሳሳይ የዕፅ ቅርንጫፍች ወይም አበባዎች፣
 ሁሇት የዘር ማብቀያ ሸክሊዎች ወይም ቆርቆሮዎች፣
የአሰራር ቅዯም ተከተሌ
 ሁሇት በተመሳሳይ ጊዜ የተቆራረጡ የዕፅዋት ቅርንጫፍችን
ወይም አበባዎችን ማዘጋጀት፣
 በአንዯኛው የዘር ማብቀያ ሸክሊ ውስጥ ውሃ መጨመር፣

83
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

 ሁሇተኛውን የዘር ማብቀያ ሸክሊ ውሃ ሳይጨመርበት ባድውን


መተው፣
 በሁሇቱም የዘር ማብቀያ ሸክሊዎች ውስጥ በተመሳሳይ ጊዜ
የተቆረጡትን ሁሇት የዕፅ ቅርንጫፍች ወይም አበባዎች
ማስቀመጥ፣
 ሁሇቱም ቅርንጫፍች ወይም አበባዎች ከአንዴ እስከ ሁሇት ቀን
ማቆየትና ሇውጣቸውን መመዝገብ

መሌመጃ 3.37.
1. ከአንዴ ቀን በኋሊ በሁሇቱ የዘር ማብቀያ ሸክሊዎች ውስጥ
በተቀመጡበት የዕፅ ቅርንጫፌ ወይም አበባዎች ሊይ ምን አይነት
ሇውጥ አያችሁ? ይህ የሆነው ሇምን ይመስሊችኋሌ?
2. እስቲ እናንተም በቤታችሁ በጣሳ ወይም ብርጭቆ ውስጥ ዘር ዘርታችሁ

በበቀለት ዘሮች ሊይ ውሃ በማጠጣትና ባሇማጠጣት ሇዕፅዋት ውሃ


ያሇውን ጠቀሜታ ሇዩ፡፡

ሙከራ 3/4
ሇ. አፇር ሇዕፅዋት ዕዴገት አስፇሊጊ መሆኑን በሙከራ ማረጋገጥ
የሚያስፇሌጉ ነገሮች ቁሳቁሶች
 ሶስት አይነት /ሇም አፇር፣ አሸዋማ አፇር፣ ከጥሌቀት ቦታ ተቆፌሮ
የተወሰዯ ጥሌቅ አፇር፣
 ሶስት የዘር ማብቀያ ሸክሊዎች፣
 ተመሳሳይ ዝርያ ያሊቸው ዕፅዋት ወይም ችግኞች፣
84
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የአሰራር ቅዯም ተከተሌ


1. በሶስቱም የዘር ማብቂያ ሸክሊዎች ውስጥ የተሇያየ ዓይነት አፇር
/ሳይቀሊቀለ/ ጨምሩ እና ሇዘር ማብቀያ ሸክሊዎቹ የተሇያየ ስያሜ
ስጡ፡፡ ከዚያም በሶስቱም የዘር ማብቀያ ሸክሊዎች ውስጥ ውሃ
ጨምሩ፡፡
2. በእያንዲንደ ሸክሊ ውስጥ ተመሳሳይ ዝርያ ያሊቸውን ችግኞች
ትከለ
3. በየዕሇቱ ውሃ እያጠጣችሁ ከሁሇት ሳምንት እስከ አንዴ ወር
ዴረስ የችግኞቹን እዴገት እየተከታተሊችሁ መዝግቡ፡፡

መሌመጃ 3.38
ከሰራችሁት የሙከራ ውጤት ተነስታችሁ የሚከተለትን ጥያቄዎች መሌሱ
1. ከሶስቱ ችግኞች ውስጥ የበሇጠ ወይም ፇጣን ዕዴገት ያሳየው
የትኛው ነው? ሇምን?
2. ከሶስቱ ችግኞች ውስጥ በዯንብ ያሊዯገውስ የትኛው ነው? ሇምን?

ሙከራ 3/5

ሏ. አየር ሇዕፅዋት ዕዴገት አስፇሊጊ መሆኑን በሙከራ ማረጋገጥ


መሌመጃ 3.39
በሚከተሇው ጥያቄ ሊይ ተወያዩ
ተማሪዎች! ዕፅዋት ምግባቸውን ከምን ከምን ያዘጋጃለ?

85
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የሚያስፇሌጉ ነገሮች
በሁሇት የዘር ማብቀያ ሸክሊዎች ወይም ቆርቆሮዎች ውስጥ የተተከለ
ዕፅዋት
ውሃ
አየር የማያሳሌፌ ትሌቅ ሊስቲክ ወይም መርዕይ ገንዲ ወይም ሰፉ
ጠርሙስ
የአሰራር ቅዯም ተከተሌ
1. በዘር ማብቀያ ሸክሊዎች ውስጥ የተተከለትን ዕፅዋት በተመሳሳይ ሁኔታ
ሇተወሰኑ ቀናት ውሃ ማጠጣት እና አየር እንዱያገኙ ማዴረግ፣
2. ከተወሰኑ ቀናት በኋሊ አንዯኛውን ተክሌ አየር እንዲይገባበት በሊስቲክ
ወይም ጠርሙስ ወይም በመርዕይ ገንዲ መሸፇን፣
3. ሁሇተኛውን ተክሌ እንዲሇ መተው፣
4. በየዕሇቱ የዕፅዋቱን ሁኔታ መከታተሌ እና የሚታየውን ሇውጥ
መመዝገብ፣

መሌመጃ 3.40
ከሰራችሁት የሙከራ ውጤት በመነሳት በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ
1. ከሁሇቱ የዘር ማብቂያ ሸክሊዎች ውስጥ ሇዕፅዋት ዕዴገት አስፇሊጊ
ከሆኑት ነገሮች ውስጥ ጉዴሇት ያሇበት የቱ ነው?
2. በሁሇቱ ዕፅዋት መካከሌ ምን ሇውጥ ተመሇከታችሁ?
3. ሇውጡ ከምን የመጣ ይመስሊችኋሌ?

86
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሙከራ 3/6
መ. የፀሏይ ብርሃን ሇተክልች ዕዴገት አስፇሊጊ መሆኑን በሙከራ ማረጋገጥ
መሌመጃ 3.41
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. የፀሏይ ብርሃን ሳያገኝ የቆየ ተክሌ አይታችሁ ታውቃሊችሁ?
2. የፀሏይ ብርሃን ያሊገኘ ተክሌ የቅጠልቹ ቀሇም ምን ዓይነት ይሆናሌ?

የሚያስፇሌጉ ነገሮች
በሶስት የዘር ማብቀያ ሸክሊዎች ውስጥ የተተከለ ሶስት ተመሳሳይ
ዕፅዋት፣
ውሃ፣
የፀሏይ ብርሃን የማያስገባ አንዴ ሳጥን ወይም ካርቶን፣
በአንዴ በኩሌ ቀዲዲ ያሇው እና የፀሏይ ጨረር /ብርሃን/ የሚያስገባ
ሳጥን ወይም ካርቶን
የአሰራር ቅዯም ተከተሌ
በሶስት የዘር ማብቂያ ሸክሊዎች ውስጥ የተተከለትን ሶስት ተመሳሳይ
ችግኞች መሇያ በመስጠት ውኃ ማጠጣት፣
አንዯኛውን ችግኝ ምንም የፀሏይ ጨረር /ብርሃን/ በማያስገባው ሳጥን
ሸፌኑና አስቀምጡ(ሥዕሌ 3/24-2 ተመሌከቱ)፡፡
ሁሇተኛውን ችግኝ በአንዴ በኩሌ ብቻ የፀሏይ ብርሃን ሉያስገባ
በሚችሇው ሳጥን ውስጥ አስቀምጡ (ሥዕሌ 3/24-3 ተመሌከቱ) ፡፡
ሶስተኛውን ችግኝ ምንም ነገር ሳትሸፌኑ በነበረበት ቦታ አስቀምጡ
(ሥዕሌ 3/24-1 ተመሌከቱ)፡፡

87
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሶስቱንም የፀሏይ ብርሃን በሚገኝበት ቦታ አስቀምጡ እና ውሃ


እያጠጣችሁ የእዴገታቸውን ሁኔታ በየጊዜው እየተከታተሊችሁ መዝግቡ
ከአምስት ቀናት ቆይታ በኋሊ ሳጥኖቹን ከፌታችሁ የሶስቱን ችግኞች
የዕዴገት ሁኔታ አወዲዴሩ፡፡

ሥዕሌ 3/24 የፀሏይ ብርሏን ሇተክልች ያሇው አስፇሊጊነት

መሌመጃ 3.42
ከሙከራችሁ ውጤት በመነሳት በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. በሶስቱ ችግኞች መካከሌ ምን ሇውጥ ተመሇከታችሁ? ይህ ሇምን የሆነ
ይመስሊችኋሌ?
2. በ ”ሇ” የዘር ማብቂያ ሸክሊ ውስጥ ያሇው ተክሌ ወዳት አቅጣጫ አዯገ? ይህ
ሇምን ሆነ?
3. እስከ አሁን ከሰራችኋቸው ሙከራዎች ምን ተገነዘባችሁ?

88
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

3.4 በአካባቢያችን ያለ እንስሳት

መሌመጃ 3.43
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. በአንዯኛ ክፌሌ የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ሊይ ከተማራችኋቸው
በአካባቢያችሁ ከሚገኙ እንስሳት አስታውሱና ስማቸውን ዘርዝሩ፡፡
2. ከሊይ ከዘረዘራችኋቸው እንስሳት ውስጥ የትኞቹ ሇማዲ እንስሳት
የትኞቹ ሇማዲ ያሌሆኑ እንስሳት እንዯሆኑ ሇዩ፡፡

3.4.1. የእንስሳት ምዯባ

በአንዯኛ ክፌሌ የአካባቢ ሳይንስ ትምህርታችሁ ሊይ እንስሳትን ከሰዎች ጋር


ከሚኖራቸው ቀረቤታ አንፃር የቤት ወይም ሇማዲ እንሰሳት እና የደር ወይም
ሇማዲ ያሌሆኑ እንሰሳት ተብሇው እንዯሚመዯቡ ተምራችኋሌ፡፡

መሌመጃ 3.44
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ ፡፡
1. ሇማዲ ወይም የቤት እንሰሳት የሚባለትን ዘርዝሩ፡፡
2. በአካባቢያችሁ የሚገኙ ሇማዲ ያሌሆኑ እንስሳትን ስም ጥቀሱ ፡፡
3. ሇማዲ እና ሇማዲ ያሌሆኑ እንሰሳት በምን ይሇያያለ?

89
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/25 ሇማዲ እንሰሳት

እንሰሳትን ከሰው ጋር በሚኖራቸው ቀረቤታ፣ በአረባባቸው፣


በእንቅስቃሴያቸው፣ በአመጋገባቸው፣ በአኗኗራቸው፣ በቆዲቸው ሽፊን ወዘተ
መሰረት ሉመዯቡ ይችሊለ፡፡
መሌመጃ 3.45
በሚቀጥለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. በመኖሪያ ቤታቸሁ ወይም በትምህርት ቤታችሁ አካባቢ ያለ እንስሳትን
ዘርዝሩ፡፡
2. በጥያቄ ቁጥር አንዴ ሊይ ያለትን እንስሳት ከሰው ጋር ባሊቸው ቀረቤታ፣
በአረባባቸው፣ በእንቅስቃሴያቸው፣ በአመጋገባቸው፣ በአኗኗራቸው እና
በቆዲቸው ሽፊን መዴቧቸው፡፡

90
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሀ. ከሰው ጋር ባሊቸው ቀረቤታ


እንስሳት ከሰው ጋር ባሊቸው ቀረቤታ ሇማዲና ሇማዲ ያሌሆኑ እንስሳት
ተብሇው ይመዯባለ፡፡

ሥዕሌ 3/26 የደር እና የቤት እንሰሳት

ሇ. በአረባብ
እንስሳት ባሊቸው የአረባብ ሂዯት እንቁሊሌ በመጣሌ የሚራቡ ወይም እንቁሊሌ
ጣይ እና መሰሊቸውን በመውሇዴ የሚራቡ ወይም አጥቢ ተብሇው በሁሇት
ይከፇሊለ፡፡

91
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/27 እንቁሊሌ ጣይ እንስሳት

ሥዕሌ 3/28 አጥቢ እንስሳት

92
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሏ. የእንስሳት እንቅስቃሴ

እንስሳት ከቦታ ቦታ እንዯሚንቀሳቀሱ በአንዯኛ ክፌሌ የአካባቢ ሳይንስ


ትምህርታችሁ ሊይ ተምራችኋሌ፡፡ እንስሳቱ ከቦታ ቦታ ሇመንቀሳቀስ የተሇያዩ
የአካሌ ክፌልቻቸውን ይጠቀማለ፡፡

መሌመጃ 3.46
በሚቀጥለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. በአካባቢያችሁ የሚገኙ እንስሳት ከቦታ ቦታ እንዳት ይንቀሳቀሳለ?
2. እነዚህን እንስሳት በእንቅስቃሴያቸው በስንት መክፇሌ ይቻሊሌ?
ሇእያንዲንደ ምሳላዎችን ስጡ ?

እንስሳት በሰማይ የሚበሩና በምዴር ሊይ የሚሳቡ እና በእግራቸው የሚራመደ


ተብሇው ይከፇሊለ፡፡

ሥዕሌ 3/29 በራሪ እንስሳት

93
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/30 ተሳቢ እንስሳት

ሥዕሌ 3/31 በእግራቸው የሚራመደ

94
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መ. በአመጋገብ

መሌመጃ 3.47
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. ተማሪዎች! በአካባቢያችሁ የሚገኙ እንስሳት ምን ይመገባለ?
2. እንስሳት በአመጋገባቸው ምን ምን በመባሌ ይመዯባለ?

እንስሳትን በሚመገቡት የምግብ አይነት ሥጋ በሌ፣ ዕፅ በሌ እና ሁሇበሌ


በማሇት በሶስት መመዯብ ይቻሊሌ፡፡

መሌመጃ 3.48
የሚከተለትን እንስሳት በአመጋገባቸው መሰረት በቡዴን ሆናችሁ ሥጋ በሌ፣ ዕፀ
በሌ እና ሁሇ በሌ በማሇት መዴቡ፡፡
ውሻ . ጅብ . በግ . ሰው . ፇረስ
ዴመት . በቅል . ፌየሌ . ዝንጀሮ . ጥንቸሌ
ነብር . አህያ . ዝሆን . ቀበሮ . ድሮ
አንበሳ . አይጥ . ግመሌ . በሬ . ቁራ

ሀ. የእንስሳት መኖሪያ ቦታ

እንስሳት ሇመራባት፣ ሇማዯግ፣ ሇመመገብ ወዘተ ምቹ በሚሆንሊቸው ቦታዎች


ይኖራለ፡፡

95
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.49
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. በአካባቢያችሁ የሚገኙ እንስሳት የሚኖሩባቸውን ቦታዎች ጥቀሱ፡፡
2. እስቲ! በአካባቢያችሁ የሚገኙትን እንስሳት በውሃ ውስጥ የሚኖሩ፣
በመሬት ሊይ የሚኖሩ እና በውሃና በመሬት የሚኖሩ በማሇት መዴቡ፡፡

እንስሳት በአኗኗራቸው ወይም በሚኖሩበት ቦታ መሰረት በመሬት ሊይ


የሚኖሩ፣ በውሃ ውስጥ የሚኖሩ እና በውሃና በመሬት የሚኖሩ ተብሇው በሶስት
ይመዯባለ፡፡

ሥዕሌ 3/32 በውኃ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት

96
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/33 በመሬት ሊይ የሚኖሩ እንስሳት

ሥዕሌ 3/34 በመሬት እና በውሃ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት

97
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.50
የሚከተሇውን ጥያቄ ተወያይታችሁ መሌሱ፡፡
ተማሪዎች! በአካባቢያችሁ የሚገኙ እንስሳት ቆዲቸው የተሸፇነው በምንዴን ነው?

የእንስሳት ቆዲ በሊባ፣ በፀጉር እና በቅርፉት የተሸፇነ ነው፡፡ በዚህም መሰረት


እንሰሳትን ቆዲቸውን በሚሸፌነው ነገር ሊይ ተመስርቶ መመዯብ ይቻሊሌ፡፡
እነዚህም ቆዲቸው በሊባ፣ በፀጉር እና በቅርፉት የተሸፇኑ በማሇት በሶስት
መመዯብ ይቻሊሌ፡፡

መሌመጃ 3.51
ተማሪዎች! በአካባቢያችሁ የሚገኙና የምታውቋቸውን እንስሳት ከሊይ
በተገሇፀው አመዲዯብ መሰረት ሇእያንዲንደ ምዴብ ሶስት ሶስት ምሳላዎችን
ስጡ፡፡

98
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 3/35 ቆዲቸው በተሇያየ ነገር የተሸፇኑ እንስሳት

3.4.2. ከእንስሳት የሚገኙ ውጤቶች

እንስሳት በተሇያየ መንገዴ ሇሰው ሌጅ አገሌግልት ይሰጣለ፡፡ ሇምሳላ፡-


እንስሳት ሇምግብነት ያገሇግሊለ፡፡

መሌመጃ 3.52
በሚከተሇው ጥያቄ ሊይ ተወያዩ፡፡
የእንስሳት ውጤቶች ከምግብነት በተጨማሪ ሇሰው ሌጆች የሚሰጡትን
ጥቅሞች ዘርዝሩ፡፡

99
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሀ. እንስሳት ሇምግብነት ያገሇግሊለ

ተማሪዎች! በአካባቢያችን ከሚገኙ እንስሳት ውስጥ ሥጋቸው የሚበለ


የትኞቹ እንዯሆኑ ዘርዝሩ፡፡

ሥዕሌ 3/36 ሇምግብነት የሚያገሇግለ እንስሳት

ሇ. እንስሳት ሇጉሌበት ሥራ ይጠቅማለ

በአካባቢያችን የሚገኙ አንዲንዴ እንስሳት የተሇያዩ የጉሌበት ሥራዎችን


ሇመሥራት ያገሇግሊለ፡፡

100
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.53
ሇጉሌበት ሥራ የሚያገሇግለ በአካባቢያችን የሚገኙ እንስሳትን ስም ጥሩ፡፡

ሥዕሌ 3/37 ሇጉሌበት ሥራ የሚያገሇግለ እንስሳት

ሏ. እንሰሳት ሇመጓጓዣነት ያገሇግሊለ


በአካባቢያችሁ ከሚገኙ እንስሳት ውስጥ ዕቃንና ሰውን ከቦታ ቦታ ሇማጓጓዝ
የሚያገሇግለ እንስሳትን ዘርዝሩ፡፡

ሥዕሌ 3/38 ሇመጓጓዣነት የሚያገሇግለ እንስሳት

101
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መ. የእንስሳት ፀጉርና ቆዲ ሇሌብስ መስሪያነት ያገሇግሊሌ፡፡

በአካባቢያችን ከሚገኙ እንስሳት የሚገኝ ፀጉርና ቆዲ ሇሰው ሌጆች ሌብስ


መስሪያነት ያገሇግሊሌ፡፡

መሌመጃ 3.54
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. በአካባቢያችሁ ከእንስሳት ፀጉር ወይም ቆዲ የተሰሩ ሰዎች
የሚጠቀሙባቸው የሌብስ አይነቶችን ዘርዝሩ፡፡
2. በአካባቢያችን ከሚገኙ እንስሳት መካከሌ ፀጉራቸው እና ቆዲቸው
ሇሌብስ መስሪያነት የሚያገሇግለትን ዘርዝሩ፡፡
3. ከእንስሳት ቆዲ ውጤቶች የሚሰሩ ሌብሶችን ዘርዝሩ፡፡

ሥዕሌ 3/39 ቆዲቸው እና ፀጉራቸው ሇሌብስ መስሪያነት የሚያገሇግለ እንሰሳት

ከእንስሳት ቆዲ ጫማ፣ ቀበቶ፣ ቦርሳ፣ የቆዲ ጃኬቶችን መስራት ይቻሊሌ


ከእንስሳት ፀጉር ዯግሞ ብርዴ ሌብስ፣ ኮፉያ ወይም ባርኔጣ ማዘጋጀት
ይቻሊሌ፡፡

102
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሠ. እንስሳት ሇጥበቃ ሥራም ያገሇግሊለ


አንዲንዴ ሇማዲ እንስሳት በቤት ውስጥ ሇጥበቃ ሥራ ያገሇግሊለ፡፡
መሌመጃ 3.55
በቤት ውስጥ ሇጥበቃ ስራ ከሚያገሇግለ እንስሳት ውስጥ ሁሇቱን ጥቀሱ፡፡

ሥዕሌ 3/40 ሇጥበቃ ስራ የሚያገሇግለ እንስሳት

ረ. እንስሳት ሇገቢ ምንጭነት ያገሇግሊለ

የሰው ሌጅ በአካባቢው የሚገኙ እንስሳትን በማሇማመዴ፣ በመንከባከብ፣


በማራባት እና በመሸጥ ሇገቢ ምንጭነት በሰፉው ይጠቀምባቸዋሌ፡፡

መሌመጃ 3.56.
የሰው ሌጅ እያረባ ሇገቢ ምንጭነት የሚጠቀምባቸውን እንስሳት ዘርዝሩ፡፡

103
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 3.57
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. እንስሳት ሇምን ሇምን አገሌግልት እንዯሚውለ አካባቢያችሁን
ካስተዋሊችሁ በኋሊ በቡዴን ሆናችሁ ቀጥል የተዘረዘሩትን እንስሳት
ሇምግብነት፣ ሇመጓጓዣ ፣ ሇጥበቃ እና ሇሌብስ መስሪያነት የሚያገሇግለ
መሆኑን ሇዩ፡፡
. ፇረስ . በቅል . ፌየሌ . ሊም . አሳ
. ውሻ . በሬ . ግመሌ . ድሮ . ዴመት
. በግ . አህያ
2. ከእንስሳት የምናገኛቸው ውጤቶች ምን ምን ናቸው?
እነዚህ ከእንስሳት የሚገኙ ውጤቶች ሇምን ሇምን እንዯሚያገሇግለ
አብራሩ፡፡

3.4.3. የእንስሳት እንክብካቤ


ሕይወት ያሊቸው ነገሮች እንክብካቤ ያስፇሌጋቸዋሌ፡፡ እንሰሳት ተገቢ
እንክብካቤ ከተዯረገሊቸው ጤናማና ምርታማ ይሆናለ፡፡
መሌመጃ 3.58
በሚከተለት ጥያቄዎች ሊይ ተወያዩ፡፡
1. እንስሳትን መንከባከብ ሇምን ያስፇሌጋሌ?
2. ሇእርሻ ተግባር የሚውለ እንስሳትን እንዳት መንከባከብ ይቻሊሌ?
3. እንስሳትን ሇመንከባከብ የሚረደ ነገሮችን እና መሳሪያዎችን ዘርዝሩ፡፡
4. ሇጭነት ተግባር የሚያገሇግለ እንስሳትን እንዳት መንከባከብ ይቻሊሌ?

104
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የተሇያየ አገሌግልት የሚሰጡ እንስሳት የተሇየ እንክብካቤ ይፇሌጋለ፡፡


እንስሳትን በእንክብካቤ ከያዝናቸው ተገቢውን ጥቅም ይሰጣለ፡፡ ብዙ
ውጤትም ያስገኛለ፡፡
ሇእርሻ ሥራ የሚያገሇግለ እንስሳትን ሇመንከባከብ የሚያስፇሌጉ ነገሮች
የሚከተለትን ሉያካትቱ ይችሊለ፡፡
ማፅጃ ብሩሽ፣ ንፁህ ውሃ፣ የውሃ ማጠጫ ገንዲ፣ የምግብ መስጫ ገንዲና
የእንስሳት መኖ

መሌመጃ 3.59

1. በቤታችሁ ወይም በአካባቢያችሁ ሰዎች ሌዩ ሌዩ እንስሳት


እንዳት እንዯሚንከባከቡ በመጠየቅ ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ ሪፖርት
አቅርቡ፡፡

2. ቤተሰቦቻሁችሁ ድሮ እንዴታረቡ ቢያዯርጉ እንዳት እናንተ


እንዯምትንከባከቧቸው ሇመምህራችሁ ተነገሩ፡፡

105
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ምዕራፌ አራት
ወረዲችን /ከተማ አስተዲዯራችን/
4.1 የወረዲችን /የከተማ አስተዲዯራችን/ አቀማመጥ

መልመጃ 4.1
1. ወረዲችሁ ወይም ከተማችሁ ማን ይባሊሌ?
2. ሁሊችሁም የምትኖሩበትን መንዯር፣ ቀበላና ወረዲ ተናገሩ?

የፀሏይና ውብነሽ ጭውውት


ፀሏይ፡- እንዯምን አዯርሽ ውብነሽ?
ውብነሽ፡- እንዯምን አዯርሽ ፀሏይ?
ፀሏይ፡- ቀበላሽ የት ነው?
ውብነሽ፡- ቀበላ 18
ፀሏይ፡- የመንዯርሽ ሌዩ ስም ማን ይባሊሌ?
ውብነሽ፡- ወይራ አምባ ይባሊሌ፡፡
ፀሏይ፡- ወረዲሽስ ማን ይባሊሌ?
ውብነሽ፡- ወረዲየማ ካንቺው ተመሳሳይ ነው፡፡
ወረዲ ማሇት ብዙ ቀበላዎችን በውስጡ የያዘ አካባቢ ነው፡፡ በወረዲ ውስጥ
የተሇያዩ የመሬት ገፅታዎች፣ ማህበራዊ ተቋማት ይገኛለ፡፡

106
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

4.1.1 አራቱ አቅጣጫዎች

የወረዲችንን አንፃራዊ መገኛ ሇማወቅ በቅዴሚያ አራቱን አብይ አቅጣጫዎች


መሇየት ያስፇሌጋሌ፡፡ አራቱ አብይ አቅጣጫዎችም ምስራቅ፣ ምዕራብ፣
ሰሜንና ዯቡብ ናቸው፡፡

ሥዕሌ 4/1 አራቱ አብይ አቅጣጫዎች

ተግባራዊ ክንውን

ከሊይ በስዕለ እንዯተመሇከተው ፉታችሁን ወዯ ፀሏይ መውጫ አዙራችሁ


በመቆም እጆቻችሁን ወዯ ጎንና ጎን ዘርጉ፡፡

107
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ግራ እጃችሁ ያመሇክታሌ፡፡
ቀኝ እጃችሁ ያመሇክታሌ፡፡
ፉታችሁ ያመሇክታሌ፡፡
ጀርባችሁ ያመሇክታሌ፡፡
በትምህርት ቤታችሁ ዙሪያ በቅርብ ርቀት ያለትን ዋና ዋና ነገሮች፣
ሇምሳላ ተራራ፣ መንገዴ፣ የቀበላ ጽህፇት ቤት ወዘተ ዘርዝሩና
ከትምህርት ቤታችሁ በየት በኩሌ እንዯሚገኙ ግሇፁ፡፡

4.1.2 የወረዲችን መገኛ ከላልች ወረዲዎች አንጻር

የወረዲው ከተማ እናንተ ከምትኖሩበት ቀበላ በየት አቅጣጫ ይገኛሌ?


ምስራቅ ፀሏይ የምትወጣበት አቅጣጫ ነው፡፡ ምዕራብ ፀሏይ
የምትጠሌቅበት አቅጣጫ ነው፡፡

ሥዕሌ 4/2 የወረዲችን አቀማመጥ

108
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

እኛ የምንገኝበት ወረዲ ነው፡፡ ወረዲችን፡-


በሰሜን በ ወረዲ ይዋሰናሌ፡፡
በዯቡብ በ ወረዲ ይዋሰናሌ፡፡
በምስራቅ በ ወረዲ ይዋሰናሌ፡፡
በምዕራብ በ ወረዲ ይዋሰናሌ፡፡
4.1.3. የወረዲችን ታሪካዊ ቦታዎችና ቅርሶች
በአንዴ ወረዲ ውስጥ የሚኖር ሕዝብ የራሱ ባህሌ፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ቅርስ
አሇው፡፡ የሚከተሇውን ስዕሌ ተመሌከቱና የወረዲችሁን ታሪካዊ ቦታዎችና
ቅርሶች ተናገሩ፡፡

ሥዕሌ 4/3 ታሪካዊ ቦታዎችና ቅርሶች

109
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 4.2.
የሚከተለትን ጥያቄዎች በግሌ ስሩ፡፡
1. በወረዲችሁ ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን ዘርዝሩ፡፡
2. በቀበላያችሁ የሚገኙ ቅርሶችን ቤተሰቦቻችሁን በመጠየቅ ፃፈ፡፡

3. ቅርሶችን መንከባከብና መጠበቅ ሇምን ያስፇሌጋሌ?

4.2. የወረዲችን የመሬት አቀማመጥ

ወረዲዎች የተሇያዩ የመሬት አቀማመጥ አሊቸው፡፡ አንዲንዴ ወረዲዎች


በዝቅተኛ ሥፌራ ይገኛለ፡፡ አንዲንዴ ወረዲዎች በከፌተኛ ሥፌራ ይገኛለ፡፡
ላልቹ ዯግሞ በዝቅተኛም በከፌተኛም ስፌራ ይገኛለ፡፡ እነዚህ የመሬት
አቀማመጥ ዓይነቶች መሌከዓምዴር ይባሊለ፡፡

110
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 4/4 የተሇያዩ የመሌከዓምዴር አይነቶች

ጉብኝት
ከክፌሌ ውጪ ከመምህራችሁ ጋር ጉብኝት በማዴረግ የተሇያዩ የመሌከዓምዴር
አይነቶችን አስተውሊችሁ የሚከተለትን ጥያቄዎች መሌሱ፡፡
የትምህርትቤታችሁን ግቢ የመሬትአቀማመጥ ግሇጹ፡፡
ዛፍችና ቁጥቋጦዎች ያለት በከፌተኛ ቦታ ነው ወይስ በዝቅተኛ ቦታ?
አፇሩ የተሸረሸረው በሜዲማ ቦታ ነው ወይስ በከፌተኛ ቦታ?

111
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

4.3. በወረዲ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት


ተማሪዎች! በቀበላያችሁ ወይም በወረዲችሁ ውስጥ ምን ምን ተቋማት
ይገኛለ? ተቋማት ብዙ አይነት ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የሌማት ተቋማት፣
ማህበራዊ ተቋማት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ባህሊዊ ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ተቋማት ሇህዝቡ ማህበራዊ አገሌግልት ይሰጣለ፡፡
ሀ. የሌማት ተቋማት

በአካባቢያችሁ የሚገኙ የሌማት ተቋማትን ተናገሩ፡፡


የሌማት ተቋማት የሚባለት የግብርና፣ የገንዘብ፣ የግንባታ፣ የኤላክትሪክ
ሏይሌ እና ላልች መሥሪያ ቤቶች ናቸው፡፡

ሥዕሌ- 4/5 የሌማት ተቋማት

ተማሪዎች! በአካባቢያችሁ የሚገኙ ማህበራዊ የሌማት ተቋማትን ስም


ዘርዝሩ፡፡

112
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሇ. ሀይማኖታዊ ተቋማት

ሥዕሌ 4/6 ኃይማኖታዊ ተቋማት

እናንተና ቤተሰቦቻችሁ የምትጠቀሙበት የሃይማኖት ተቋም የትኛው


ነው?
የሀይማኖት ተቋማት ሰዎች የእምነት አገሌግልቶችን የሚያገኙበት
ነው፡፡ ቤተክርስቲያኖችና መስጊድች ሃይማኖታዊ ተቋማት ይባሊለ፡፡
ሏ. ማህበራዊና ባህሊዊ ተቋማት
ባህሊዊ ተቋማት የሚባለት ሕዝቡ ግጭትን ሇመፌታት፣ ሇመረዲዲትና
ሇትምህርት የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡ ሇምሳላ ሽምግሌና የተጣለ ሰዎችን
ሇማስታረቅ ይረዲሌ፡፡ እቁብ ገንዘብ ሇመቆጠብ ይጠቅማሌ፡፡
ከሊይ እንዯተማራችሁት የተሇያዩ ተቋማት መኖራቸውን አይታችኋሌ፡፡ እስቲ
እነዚህ ተቋማት ሇሕዝቡ ምን ጥቅም እንዲሊቸው ተናገሩ፡፡

113
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕሌ 4/7 ማህበራዊ ባህሊዊ ተቋም /ባህሊዊ ሽምግሌና/


መሌመጃ 4.3 ከዚህ በታች የቀረቡትን ተቋማት ከሚሰጡት አገሌግልት ጋር
አዛምደ፡፡
የተቋም ስም የተቋሙ ጥቅም
1. የእንስሳት ማራቢያ ማዕከሌ ሀ. ምርጥ የእንስሳት ዘርን ማሰራጨት
2. ባንክ ሇ. ሕፃናትና ወጣቶችን ሇማስተማር
3. ትምህርት ቤት ሏ. በሽታን ሇመከሊከሌ
4. ክሉኒክ መ. መሌዕክትን ከአንዴ ቦታ ወዯ ላሊ ቦታ
5. ትራንስፖርት ሇማስተሊሇፌ
6. ፓስታ ቤት ሰ. ገንዘብን ሇመቆጠብ
7. መስጅዴ ረ. ፇጣሪን ሇማመስገን
8. እዴር ሠ. ሰዎችንና ዕቃን ከቦታ ቦታ ማዘዋወር
9. ሽምግሌና ሸ. ያዘነን ሇማፅናናት
በ. የተጣሊን ሇማስታረቅ

114
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ማስታወሻ፡- በወረዲችን ውስጥ ያለ ተቋማት ሌዩ ሌዩ ጥቅም አሊቸው፡፡ ባንክ


ገንዘብ ሇማስቀመጥ ይጠቅማሌ፡፡ ትምህርት ቤት ሕፃናትንና ወጣቶችን
ሇማስተማር ይጠቅማሌ፡፡ የጤና ተቋም የጤና ትምህርት ሇመስጠትና
ህመምተኞችን ሇማከም ይጠቅማሌ፡፡ እስቲ የላልቹን ተቋማት አገሌግልቶች
ተናገሩ፡፡
4.4. የወረዲ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ
ሰዎች መሰረታዊ ፌሊጎታቸውን ማሟሊት የሚችለት ሲሰሩ ነው፡፡ በወረዲችን
ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በተሇያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች የተሰማሩ
ናቸው፡፡
4.4.1. የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሲባሌ በወረዲው ውስጥ የሚካሄዯውን የግብርና፣
የንግዴ፣ የትራንስፖርት፣ የእዯ ጥበብና ኢንደስትሪ እንቅስቃሴ ማሇት ነው፡፡
ሀ. ግብርና
በአገራችን በተሇያዩ ወረዲዎች የሚኖረው ሕዝብ በአብዛኛው የሚተዲዯረው
በግብርና ነው፡፡ የግብርና ሥራ በሁሇት የሚከፇሌ ሲሆን እነርሱም እርሻና
የከብት እርባታ ናቸው፡፡

115
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሀ/ በበሬ ማረስ

ሇ/ በፇረስ ማረስ

ሥዕሌ 4/8 የእርሻ ሥራ

116
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 4.4. ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄዎች መሌሱ፡፡


1. በአካባቢያችሁ በእርሻ ሥራ የሚመረቱ እህሌ፣ አትክሌትና ፌራፌሬዎችን
ዘርዝሩ?
2. ሇምግብ አገሌግልት የሚውለት ሰብልች የትኞቹ ናቸው?
3. ሇፊብሪካ ጥሬ ዕቃነት የሚውለት ሰብልች የትኞቹ ናቸው?
4. የእርሻ ሥራ ውጤቶች በገጠርና በከተማ ሇሚኖረው ሕዝብ ያሊቸው
ጠቀሜታ ምንዴን ነው?
5. ሇምግብ ፌሊጎትና ሇፊብሪካ በጥሬ እቃነት የሚጠቅሙትን ሇዩ?

ሥዕሌ 4/9 የእንስሳት እርባታ

በአገራችን ኮረብታና ተራራ በሚበዛባቸው ወረዲዎች የሚኖሩ አርሶ


አዯሮች በአብዛኛው የሚተዲዯሩት በምን ሥራ ይመስሊችኋሌ?
የትኞቹ የእንስሳት ዓይነቶች በእናንተ አካባቢ ይገኛለ?

117
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሇ. ንግዴ

ሌዩ ሌዩ ሸቀጣሸቀጦችንና የግብርና ምርቶችን የመሸጥና የመሇወጥ ተግባር


ንግዴ ይባሊሌ፡፡ በንግዴ ሥራ የሚተዲዯሩ ሰዎችም ነጋዳዎች ይባሊለ፡፡
የንግዴ እንቅስቃሴ በከተሞች የሚመረቱ ሸቀጦችን ወዯ ገጠሩ ሇማቅረብ
ይጠቅማሌ፡፡ በገጠር የሚመረቱ የግብርና ምርቶችንም ዯግሞ ወዯ ከተሞች
ሇማቅረብ ያግዛሌ፡፡ የንግዴ ሥራ በሁሇት ዋና ዋና ክፌልች ይከፇሊሌ፡፡
እነርሱም፡-

የጅምሊ ንግዴ እና
የችርቻሮ ንግዴ ናቸው፡፡

ሥዕሌ 4/10 የጅምሊ ንግዴ

118
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

የጅምሊ ንግዴ ሸቀጦችንና የግብርና ምርቶችን በብዛት ከገበሬዎችና አምራች


ዴርጅቶች ገዝቶ ሇአነስተኛ ነጋዳዎች የማከፊፇሌ ተግባር ነው፡፡

ሥዕሌ- 4/11 የችርቻሮ ንግዴ

በአካባቢያችሁ ገበያ ወጥታችሁ ታውቃሊችሁ? ምን አስተዋሊችሁ?

የችርቻሮ ነጋዳዎች የተሇያዩ ሸቀጦችን በከተሞች ከሚገኙ ጅምሊ ነጋዳዎች


በመግዛት ሇገጠርና ሇከተማ ነዋሪዎች ያቀርባለ፡፡ አትክሌትና ፌራፌሬን
ከጅምሊ አከፊፊዮች ተረክበው ሇተጠቃሚው ህብረተሰብ ያቀርባለ፡፡

ሏ. ትራንስፖርት

ትራንስፖርት ምንዴን ነው? ትራንስፖርት ሰዎችንና ዕቃን ከአንዴ ሥፌራ


ወዯ ላሊ ሥፌራ የማጓጓዝ ተግባር ነው፡፡ ትራንስፖርት ሇኢኮኖሚ

119
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

እንቅስቃሴ አስፇሊጊ ነው፡፡ ሰራተኞች ወዯ ሥራ ቦታቸው በፌጥነት ሄዯው


መሥራት አሇባቸው፡፡ ሇዚህም ትራንስፖርት ያስፇሌጋቸዋሌ፡፡

ሥዕሌ- 4/12 ከከተማ ወዯ ገጠር የሚጓጓዙ ሸቀጣሸቀጦች

ሥዕሌ- 4/13 ከገጠር ወዯ ከተማ የሚጓጓዙ ምርቶች

120
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

በአካባቢያችሁ ሰዎች የግብርና ምርቶችን ወዯ ገበያ የሚያጓጓዙት በምን


ዓይነት የትራስፖርት ዘዳዎች ነው?
መ. ኢንደስትሪ
ኢንደስትሪ ምንዴን ነው? ኢንደስትሪ ሌዩ ሌዩ ምርቶችን በዘመናዊ ማሽን
በመታገዝ የማምረት ሂዯት ነው፡፡ ኢንደስትሪዎች ምርት ሇማምረት ጥሬ
ሀብት ያስፇሌጋቸዋሌ፡፡ ሇምሳላ ቆዲና ላጦ፣ ጥጥ፣ የቅባት እህልችና ጣውሊ
ወዘተ ናቸው፡፡
የኢንደስትሪ ጥሬ ዕቃዎች በዋናነት ከግብርና ምርቶችና ከተፇጥሮ ማዕዴናት
ይገኛለ፡፡ ኢንደስትሪዎች ምርትን ሇማምረት የኤላክትሪክ ሀይሌ
ይጠቀማለ፡፡

ሥዕሌ 4/14 ፊብሪካዎች

በላሊ በኩሌ ሇአካባቢ ፌጆታ የሚሆኑ ቀሊሌ ምርቶችን የሚያመርቱ የጎጆ


ኢንደስትሪዎች ዕዯ ጥበብ ይባሊለ፡፡

121
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሠ. እደ ጥበብ
ዕደ ጥበብ ትልቅ ጥቅም አሇው፡፡ በዕደ ጥበብ ሥራ የተሰማሩ ሰዎች የዕደ ጥበብ
ባሇሙያዎች ይባላለ፡፡ የዕደ ጥበብ ባሇሙያዎች የተሇያዩ ምርቶችን ያመርታለ፡፡
ከዕደ ጥበብ ሥራዎች ውስጥ ሽመና፣ የብረታ ብረት ሥራ፣ የቆዳ፣ የሸክላ፣
የእንጨት፣ የቀርከሃ ሥራዎችና ሌሎችም ይጠቀሳለ፡፡
የዕደጥበብ ሥራዎች ሇአካባቢው ህብረተሰብ የተሇያዩ ምርቶችን ያቀርባለ፡፡
-ከጥጥ የሚሰሩ አልባሳት ሇምሳሌ ጋቢ፣ ነጠላና ቀሚስ
-የእርሻ መሳሪያዎች ሇምሳሌ፡ ማረሻ፣ ማጭድ፣
-ልዩ ልዩ የእጅና የአንገት ጌጣጌጦች ሇምሳሌ አምባር፣ አልቦ፣ቀሇበት
-ልዩ ልዩ የቆዳ ውጤቶች ሇምሳሌ የእጅ ቦርሳዎች፣ መጫኛ፣ ቀበቶ
-ልዩ ልዩ የሸክላ ሥራ ውጤቶች ሇምሳሌ ጀበና፣ ድስት፣ እንሰራ፣ ምጣድና
ሌሎችም ይገኛለ፡፡
መልመጃ 4.5
1. በቤታችሁና በአካባቢያችሁ ሰዎች የሚገሇገለባቸውን የዕደ ጥበብ
ሥራ ውጤቶችን ፃፉ፡፡
2. በአካባቢያችሁ ሰዎች የሚገሇገለባቸውን የዕደ ጥበብ ውጤቶች
ዘርዝሩና ከጥጥ፣ ከብረታ ብረት፣ ከቆዳ፣ ከሸክላ፣ ከእንጨት የተሰሩ
በማሇት መድቡ፡፡

122
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕል 4/15 የሸክላ ሥራ

ሥዕል 4/16 ብረታ ብረት ሥራ


123
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሥዕል4/17 የሽመና ሥራና ምርቶቹ

የእደ ጥበብ ጥቅሞች

የዕደ ጥበብ ስራዎች ሇዘመናዊ ኢንዱስትሪ እድገት መሰረት ይጥላለ፡፡


እንደዚሁም የሥራ እድል በመፍጠር ገቢን ያሳድጋለ፡፡
መልመጃ 4.6
1. በቀበሌያችሁ የሚከናወኑ የዕደ ጥበብ ሥራዎችን በተመሇከተ
ቤተሰቦቻችሁን ጠይቃችሁ ፃፉ፡፡ በቤታችሁ የምትገሇገለባቸውን የዕደ ጥበብ
ሥራ ውጤቶችንም ፃፉ፡፡
2. በአካባቢያችሁ ሰዎች የሚገሇገለባቸውን የዕደ ጥበብ ውጤቶች የሽመና፣
የብረታ ብረት ሥራ፣ የቆዳ ወይም የሸክላ ውጤቶች በማሇት መድቡ፡፡

124
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

4.4.2 የቴክኖልጂ አገሌግልትና የምርት ውጤት

ቴክኖልጂ የሰው ሌጅ እውቀቱን ተጠቅሞ አዲዱስ የአሰራር ስሌት ቀይሶ


ምርቶችን በተሇያየ ዓይነትና መጠን ማምረት መቻሌ ነው፡፡ ቴክኖልጂ
የሰውን ሌጅ አኗኗር ቀሊሌና ምቹ ያዯርጋሌ፡፡ ሇምሳላ መኪናን ብንወስዴ
ረጅም ርቀትን በትንሽ ሰዓታት ውስጥ ሇመጓዝ ያስችሊሌ፡፡ ስሌክ ሩቅ ቦታ
ካለ ሰዎች ጋር በቀሊለ ሇመገናኘት ይረዲሌ፡፡

የቴክኖልጂ ውጤቶች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ የተወሰኑትን ሇማሳየት ያህሌ፡-


ሬዱዮ፣
ቴላቪዥን፣
የኤላክትሪክ ምዴጃ፣
ማቀዝቀዣ ማሽን /ፌሪጅ/፣
የሌብስ መተኮሻ ካውያ፣
ተንቀሳቃሽ ስሌክ /ሞባይሌ/ ወዘተ ይጠቅሳለ፡፡

ቴላቪዥን ኮምፒዩተር

125
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

ሞባይሌ ቴፕ ሪከርዯር

ፍቶግራፌ ካሜራ ካውያ

ጀነሬተር ኤላክትሪክ ምዴጃ

ሥዕሌ4/18 የመገናኛና ላልች የቴክኖልጂ ውጤቶች

126
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 4.7
ሇሚከተለት ጥያቄዎች መሌስ ስጡ፡፡
በመኖሪያ ቤታችሁ ውስጥ የሚገኙ የቴክኖልጂ ውጤቶችን ተናገሩ?
ከፌ ብል የቀረቡትን የቴክኖልጂ ውጤቶች አገሌግልት ተናገሩ?
በአካባቢያችሁ ከሚገኙ ነገሮች ሇምሳላ ካርቶን፣ ወረቀት፣ ጣውሊ፣
ፕሊስቲክ ወዘተ በመጠቀም አንዴ የቴክኖልጂ ውጤት አስመስሊችሁ
ስሩና ሇክፌሌ ጓዯኞቻችሁ አሣዩ፡፡

4.4.3. ሥራ ሇወረዲችን ሌማት


ስራ ምንዴን ነው?
ሰዎች ፌሊጎታቸውን ሇማሟሊት የተሇያዩ ሥራዎችን ያከናውናለ፡፡ሥራዎች
በተሇያዩ የሥራ መስክ ይከፇሊለ፡፡ ሇምሳላ እርሻ፣ድሮ እርባታ፣ አትክሌት
ሌማት፣ አናፂነት፣ ግንበኝነት፣ ሙዚቀኛ፣ ሰዓሉ፣ ንግዴና ሌብስ ስፋት
ይጠቀሳለ፡፡ ሰዎች በተሇያዩ የሥራ መስኮች ሲሰማሩ ባሊቸው ተሰጥኦ፣
የትምህርት መስክ፣ የሥሌጠና ዘርፌ፣ ሌምዴና ችልታ ነው፡፡

ሥዕሌ 4/19 ሌዩ ሌዩ የሥራ መስኮች

127
አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መፅሐፍ 2ኛ ክፍል

መሌመጃ 4.8

1. በስዕለ የተመሇከቱትን ሥራዎች ግሇፁ፡፡

2. በወረዲችሁ ወይም በአካባቢያችሁ የሚከናወኑ ሥራዎችን ዘርዝሩ፡፡

3. የምታዯንቁት የሥራ መስክ ምንዴን ነው?

4.4.4. የሥራ ክቡርነት

ማንኛውም ሥራ ክቡር ነው፡፡ የሰው ሌጅ ሇመኖር የሚችሇው ሰርቶ


መሰረታዊ ፌሊጎቱን ሲያሟሊ ነው፡፡ ሳይበሊና ሳይጠጣ የሚኖር ሰው የሇም፡፡
ስሇዚህ ሥራ የሰው ሌጅ ህሌውናውን የሚያረጋግጥበት ክቡር ተግባር ነው፡፡

መሌመጃ 4.9
የቡዴን ውይይት፡-
1. በቡዴን በመዯራጀት የሚከተለት ሙያዎች ሇህብረተሰቡ የሚሰጡትን
አገሌግልት አብራሩ፡፡
ሀ. መምህርነት
ሇ. ህክምና
ሏ. ፖሉስ
መ. ግብርና
ሠ. ዕዯ ጥበብ
2. ጥቁር ሰላዲ ሊይ እየወጣችሁ ወዯፉት መሆን የምትፇሌጉትን የሙያ
ዓይነት ፃፈ፡፡

128
አካባቢ ሳይንስ
መማሪያ መጽሐፍ
ሁለተኛ ክፍል

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ት/ቢሮ


በደብረ ብርሃን መምህራን ትምህርትና ሙያ
ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተዘጋጀ

አዘጋጆች፡- 1. በለጠ አየለ ዋና አርታኢዎች፡-

1. ሲሳይ ሀይሉ 2. በቀለ ደጉ 1. መልኬ ክፍሌ

2. በለጠ ከበደ 3. አሊ ሀሰን 2. ህብስቴ ካሴ

3. ነቅንቄ ዘውዴ 4. አብዱራህማን 3. ሙሉጌታ መሥፍን

4. አሰፋ ይሁኔ ይማም

5. ዘነበ ሽፈራው 5. ወሰን አያሌው

አርታኢዎች፡-

ሰዓሊ፡- በላይሁን ፀጋዬ


© አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ፣2004
ምስጋና

ይህንን የሁሇተኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ መማሪያ መጽሐፍ

እንድናዘጋጅ ሁኔታዎችን ላመቻቸልን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮና

እንዲሁም ሁልጊዜ ከጎናችን በመሆን ከፍተኛ እገዛ ላደረጉልን ሇአቶ

ማሙዬ ገብረሕይወት የደብረብርሃን መምህራን ትምህርትና ሙያ

ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን ከፍ ያሇ ምሥጋና እናቀርባሇን፡፡ በተጨማሪም

የኮምፒውተር ትየባውን በጥራትና በቅልጥፋና ላከናወኑልን ሇወ/ሮ

አይናሇም ሲሳይ እና ሇወ/ሮ ምስራቅ ግርማ ምሥጋና እናቀርባሇን፡፡


መግቢያ
ይህ የሁሇተኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት መማሪያ መፅሐፍ
በአዲሱ መርሀ ትምህርት ላይ ተመሥርቶ የተዘጋጀ ነው፡፡ መፅሐፉ
የአካባቢን ነባራዊ ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን
በውስጡ አራት ምዕራፎችን አካቷል ፡፡ እነዚህም ሰውና ኑሮው፣
ማህበራዊ አካባቢያችን፣ ተፈጥሯዊ አካባቢያችን እና ወረዳችን/ከተማ
አስተዳደራችን የሚለት ናቸው፡፡

በመሆኑም መምህራን የሕፃናቱን አካላዊና ሥነ-አዕምሮዊ ዕድገት


ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከትምህርቱ የሚጠበቁትን የባህርይ ሇውጦች
ሇማምጣት ጥረት ማድረግ ያጠበቅባቸዋል፡፡

አዘጋጆቹ
ማውጫ
ርዕስ
ገፅ
መግቢያ
ምዕራፍ አንድ፡- ሰውና ኑሮው
1.1. የምንመገበው ምግብ
1
1.2. ጤናችን
11
1.3. የግል ንፅህናችን እንጠብቅ
17
ምዕራፍ ሁለት፡- ማህበራዊ አካባቢያችን
2.1. የማህበራዊ አካባቢያችን አባላት
22
2.2. በማህበራዊ አካባቢ ውስጥ መኖር
28
2.3. የማህበረሰቡ የጉልበት ምንጮች
34
2.4. የተለያዩ ቁሳቁሶችን ከሸክላና ከወረቀት መሥራት
36
ምዕራፍ ሶስት፡-ተፈጥሯዊ አካባቢያችን
3.1. ተፈጥሯዊ ክስተቶች
46
3.2. የተፈጥሮ ሀብቶች
64
3.3. በአካባቢያችን ያሉ ዕፅዋት
73
3.4. በአካባቢያችን ያሉ እንስሳት
89
ምዕራፍ አራት፡-ወረዳችን /ከተማ አስተዳደራችን/
4.1 የወረዳችን /የከተማ አስተዳደራችን/ አቀማመጥ
106
4.2. የወረዳችን የመሬት አቀማመጥ
110
4.3. በወረዳ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት
112
4.4. የወረዳ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ
115

You might also like